የህወሓት ደጋፊ አለ የተባለዉ
የፓርቲዎች ጉባኤ በኢትዮጵያቸን አስጨናቂ እየሆነ መጥቷል፡፡በተቃዉሞ ጎራዉም በገዢ ፓርቲዎችም ዉስጥ ማለት ነዉ፡፡በተቃዉሞዉም እጁ ስላለበት ተረጋግቶ ጉባኤ ማካሄድ አልተቻላቸዉም(አንዳንዶቹ በተፈጥሮኣቸዉ ያዉ ቢሆኑም)፡፡በገዥዉ ፓርቲ አባልና አጋር ፓርቲዎች መካከል ፉክክሩ ድብቅ ነዉ፡፡ጸረ ዲሞክራሲያዊና በጥቅም ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ይህ የታፈነ ዉድድር የት ቦታ እንደሚበጠስና የአሸናፊና ተሸናፊ ወገን እንደሚፈጥር አይታወቅም፡፡ፍጻሜዉ ግን ይህ ሃቅ ይመስለኛል፡፡ የኢህኣዴግ አባል ፓርቲዎች ወደላይም ወደ ጎንም ማደግ አይችሉም፡፡ካደጉ ዉድቀት ይከተላል፡፡እድገታቸዉ ቀድሞዉኑ የተወሰነባቸዉ ናቸዉ፡፡ታድያ እዚህ ከተደረሰ መጪዉን ማሰብ ነዉ፡፡ማእበሉም ይበሉት ናዳዉ ሲነሳ የሚጠርገዉን በዋንኝነት ቢለይም ቅድሚያ የሚጎዳዉ ግን የአሁኑን ጎጅዎችን ነዉ፡፡ታሪክ እያሳየን ያለፈዉ ይህንን ነዉ፡፡በዚህ ማእበልና ናዳ የሚጠቀም ያለ አይመስለኝም፡፡በበኩላችን የሚጠቅመዉን ልናሳይ ባቅማችን ስንቀሳቀስ መንገዱን ዘግተዉ በደል ላይ በደል ጨምረዉ ቀብረዉም ቁመዉብናል፡፡
የብአዴንና ኦህዴድ ከፍተኛ የአመራር አባላት ጭምር እንወክለዋለን ስለሚሉት ሀዝብና ምድር የሚያቀርቡት እሮሮ የታመቀ በደል እንዳለ ያመኑ መሆኑን ይጠቁመናል፡፡ጉዳየ ተከድኖ ይብሰል አይነት ነዉና በሂደት እናየዋለን፡፡ድሮ ድሮ ህወኃት ለሁሉም የሚያለብሳቸዉ የረዕዮተ አለም ልባስ ነበረዉ፡፡ልባሱን አዉልቆ ከጣለዉ ሰንብቷል፡፡በኣንዳድንድ ልምድና ቀለም ቀመስ አመራር አባላቱ ለምኞት የሚሆን የተለጋገበ ርእዮት አለም ያላቸዉ ለማስመሰል ለአባሉና ህዝቡ በማይሰርጽበት ሁኔታ በሚድያዎቻቸዉ ሲግቱት ታዝበናል፡፡ኣባሉ ወድያዉ ይተፋወል፤ህዝቡ መስሚያ የለዉም፡፡መርህም የለም፤ለነገሩ ድሮም አልነበረም፡፡ተገፍተን ወጥተን ነበር ያሉትም የሚተካ አጥተዉ፤ተኩን ባዮችም ጠፍተዉ ወደ እርካቡ መጥተዋል፡፡ምንም አዲስ ነገር የለም!
“እኛ ውጪ ሆነን ተጨንቀናል፤ እነርሱ ውስጥ ሆነው ያልቀላፋሉ!” የህወሓት ደጋፊ የሆነ ሰዉ ተናገረዉ የተባለዉ ነዉ(የዋህ መሆኑ እንጂ የሚያንቀላፉትና ፖለቲካዉን የሚጫወቱት፤እዚያ አምሽተዉም ቤታቸዉ ገብተዉ የማይተኙትን ማየት ነበረበት)፡፡ዉስጡን ስለሚያዉቅ የጨነቀዉ አባል ነዉ፡፡ከቲፎዞነት ተነስቶ ለጥቅሙ ተጨንቆ ከማለት ይልቅ እንደ አባልና ዜጋ ጉዳዩ አሳስቦት ነዉ ብሎ ማሰብ ይሻላል፡፡ግን ይህ አባልና ሌሎች የህወሓት/ኢህኣዴግ ደጋፊዎች ደም የተገበረበትን ትግል ዲሞክራሲን በመግደል እንደተባበሩ በቅዲሚያ ሊረዱት ይገባል፡፡አገሪቱ የጋራ እንደመሆንዋ ተጸጽቶም ቀናዉን መንገድ መያዝ እንደህዝብ ለቀጣዩ ጉዞኣችን ይጠቅማል የሚል እምነት አለኝ፡፡እናንተ የለዉጥ ሃይሎች ሆይ ለዉጥን ፓርቲ እንደማይገድበዉ ልተረዱ ይገባል፡፡ከፓርቲ በላይ ሃገርና ህዝብ ነዉ፡፡ለዉጥ ፈላጊ የድርጅቱ አባላት ለዉጡ እንዳማራችሁ እንደቀረ ብናስተዉልም፤ለዉድቀታችሁ ተጠያቅዎች ግን ራሳችሁ መሆናችሁን ልትክዱት አይገባም፡፡ የህዝብ ድምጽን ደፍጥጦ በስልጣን ለመኖር ላሰበዉ ድርጅታቸችሁ በጭካኔ ሙሉ ድጋፍ ሰጥታችኃል፤በኛ በኩል የምንጠየቅበት ካለ የድርሻችንን ለመዉሰድ ዝግጁ ነን!የህዝባችንን መስዋእትነት አክብረን፤ህገ ምንግስቱን ተቀብለን ልናድግ ስንጥር ባለበሌለ አቅማችሁ ደፍጥታችሁን እዚህ ደርሳችኋል፤መልካም ጉዞ!!!!!!