Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

በባህር ዳርቻ ደፋ ብሎ የተገኘው ሶርያዊ ብላቴና

$
0
0

nebyu
የማለዳ ወግ … ለጥቅም አንጅ ለሰብዕና ያልቆመው ፖለቲካ ድምር ውጤት !
=================================
* በባህር ዳርቻ ደፋ ብሎ የተገኘው ሶርያዊ ብላቴና
* “KiyiyaVuranInsanlik”

በቱርክኛ “KiyiyaVuranInsanlik” በተጻፈ አጭር ቃላት የዚህ ልብን ሰባሪ ሶርያዊ ህጻን የተናኘው ከትናንት መለዳ ጀምሮ ነበር ፣ ከስዕሉ ጋር በቱርክኛ የተያያዘውን ይህን ጽሁፍ ወደ እንግሊዝኛ ቀይሬ ተዛማጅ ትርጉም ሰጠሁት ፣ ” ሰብዕና በባህር ዳርቻ ሲረክስ ፣ ሲታጠብ “ በሚል ፣ ይህ አጭር ቃላት በቱርክኛ የተሰታጨው ወደ አረንግሊዝኛ የተቀየረውኛ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ለመተርጎም የሞከርኩት ሁሉም ተደምሮ የተሰራጨውም ሶርያዊ ብላና የሰብዕናን ዳራ አልገልጽልህ አለኝ ! መግለጫ ቃላት የማጣቴ የውስጥ የተጎዳ ስሜቴን ስላላረካው መሆኑን ግን የገባኝ ቆይቶ ነበር …
የዚህ ህጻንና ደፋ ብሎ መቅረትን ሳስበው ብዙ ክፉ ደግ በውስጤ ተመላለሰ ፣ በሜዲትራንያን በተሰረጎደው መርከብና አለያም ጀልባ የተጫኑት የተፈናቃይ አረቦችና አፍሪካውያን በጨቋኝ መሪዎቻቸውና በአለም አቀፉ ፖለቲካ የተከላ ሰብዕና ዘልቆ ሰውነቴን አስቆጣው !… ለጥቅም አንጅ ለሰብዕና ያልቆመው ፖለቲካ ድምር ውጤት ብየ መጻፊን አቆምኩት …

በቱርክ የባህር ዳርቻ በግንባሩ ደፋ ብሎ የቀረው ወላጆችስ የት ገቡ ? ይህ አንድ ፍሬ ልጅ ከእጃቸው አንዴት አመለጣቸው ? ነው ወይስ ሁሉም ሲሰጥሙ ተለያዩ ? ቴሌታቢስ ፣ ባርኒስ እያለች አላስነብብ አላስጸደፍ ያለችኝን ማህሌት ልጀን እያየሁ በጥልቅ የሀዘን ስሜት አሰላሰልኩት … ብዙ አሰቃቂ ምስሎችን አይቻለሁ ፣ ይህኛው ደግሞ አንጀት ይበላል ! በስዕሉ ላይ የተጻፈው ሁሉም በዘመናችን የደረስንበትን አሳፋሪ የሰብዕና መርከስ ቅሌት በትክክል አልገልጽልህ አለኝ ። ደግሜ ደጋግሜ አንብቤው አልገባህ አለኝ ! ብላቴናውን ከወደቀበት ያነሳውን ፖሊስ የተከፋ ፣ ተስፋ የቆረጠ አሳዛኝ ስሜትን ነበር ፣ የበሁለት እጆቹ የብላቴናውን ሬሳ አቅፎ ሲወስደው የሚያሳየው ን ተንቀሳቃሸረ የቪዲዮ ምስል እያየሁ ክችም ብያለሁ ፣ የፖሊሱ መከፋት ከወደቀው ህጻን ምስል እኩል አመመኝ …ቱርክኛው “KiyiyaVuranInsanlik” ይላል ” ሰብዕና ረክሶ ክቡሩ የሰው ልጅ ረክሶ በባህር ውሃ ታጥቦ ሲጣል ” ብየ ራሴው አሻሽየ ልተረጉም ብሞክርም አሁንም ስዕሉን የሚገልጽልኝ ቃላት አጥቻለሁ … ይህ ሁሉ መከራ ለጥቅም አንጅ ለሰብዕና ያልቆመው ፖለቲካ ድምር ውጤት ነው! ስል ተነፈስኩት …

23 ስደተኞች በሁለት ትናንሽ ጀልባዎች ከአንካሪላር Akyarlar ጠረፍ ተጭነው ወደ ቡርዱም Bodrum የቱርክ ባህረ ሰላጤ ሲያመሩ አደጋ አጋጠማቸው …ከተጫኑት 23 ሶርያውያን ስደተኞች መካከል አምስት ህጻናትና አንዲት አዋቂ ሴት ሞተው መገኘታቸው ተረጋግጧል ፣ ሰባት ያህል ተርፈዋል ። ሁለት ያህልም ተጨማሪም ተገኝተዋል ። የቱርክ ባህር ኃይል አባላት ብዙዎች ያሉበት ፣ የገቡበት አለመታወቁንና የመገኘት ተስፋ እንደሌላቸው ተናግረዋል !

በህይዎት የሌለ አንድ ቀይ ቲ ሸርትና ሰማያዊ ሱሪ የለበሰ ህጻን በቱርክ ታዋቂ ከሆኑት የቱሪስት መዳረሻ ቡርዱም Bodrum የባህር ዳርቻ ፊቱ ባህር ማዕበል ዘወትር በሚያጥበው አሽዋ ፊቱን ደፍቶ እስከ ወዲያኛው አንቀላፍቷል ! ይህ ማሙየ ሀገራቸው በጦርነት ታምሳ ወደ ቱርክ ከተሰደዱትና ቀን ከከፋባቸው ፣ ብቻውን ውሃ በልቶት የቀረ ያንዱና ያንዷ ልጅ ነው … በያዝነው ዓመት ብቻ የቀይ ባህሩ ሳይጨመር በሜዲትራንያን ባህር ብቻ 2,500 ያህል ስደተኞችም ህይዎት ተቀጥፏል … ጭቆናና ግፍ ቀጥሎ አለም ዝምታን መርጧልና ሰብዕና ረክሷል ፣ ባህሩ ደግሞ አፉን ከፈወቶ ይጠብቀናል … በአፍሪካና የአረብ አንባገነን መሪዎች ያልረጋ ፖለቲካ እየታመሱ ያሉ ዜጎችን አልጠገበም … በልቶ ፣ አጥፍቶ እንደማሙየ ከባህር ሆዱ አውጥቶ ለአውሬ ምግብነት ይጥለናል: (አነሆ ዘመን ስለመክፋቱ አለም ምስሉን እየተቀባበለ ክንፈሩን ይመጣል ፣ ለጥቅም አንጅ ለሰብዕና ያልቆመው ፖለቲካ ድምር ውጤት ስደት ለመሆኑ ገዥዎቻችን ጨምሮ የአለም ኃያላን መንግስታት በሚያውቁት እውነት ሰብዕና ረክሷል !
አቤቱ የዚህን ብላቴና የተገፊዎችን ነፍስ ማር !
ነቢዩ ሲራክ
ነሀሴ 28 ቀን 2007 ዓም


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>