የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ትናንት መግለጫ አውጥቶ ነበር ….እናም በመግለጫው ኤርትራ ‹‹በኢትዮጲያ እየተደረገባት ያለው ዛቻና ወታደራዊ ትንኮሳ እየጨመረ ነው …ማስፈራሪያውም በርክቷል ›› መባሉን ዘ ገልፍ ቱዴይ ዘግቦታል ፡፡ የኤርትራው መግለጫ ጨምሮ እንደገለፀው ‹‹ኢትዮጲያ አይነውሃዋ አላማረንም ወረራ ማሰቧንና ለዚሁ መዘጋጀቷን የሚያመላክቱ መረጃዎች አሉ ….ለዚህም የልብ ልብ የሚሰጧት እንደአሜሪካ አይነት የኢትዮጲያ አጋሮች ናቸው›› ሲል ክሱን አስፍቶታል !
በኢትዮጲያ በኩል እስካሁን ለዚህ ክስ የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለኢትዮጲያ ፓርላማ ኤርትራ እጇን ካልሰበሰበች እና እያሰረገች የምታስገባቸውን ‹ሽብርተኞች› ሃይ ካላለች ‹‹ህዝባችንን አስፈቅደን›› እርምጃ ልንወስድባት እንጅላለን ›› ማለታቸው የሚታወስ ነው …አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በወቅቱ ‹‹ህዝብ ለግድቡ ሳንቲም ከማዋጣት ጎን ለጎን እንዲህ ለጦርነት ሃሳብ እና ፈቃድ ማዋጣት መጀመሩ የአገራችንን ባለሁለት አሃዝ እድገት የሚያመላክት ነው ›› ማለታቸው ይታወሳል፡) ….በነገራችንላይ ሁለቱም አገራት አንዱ አንዱን ‹‹ውስጥ ችግራቸውን መፍታት ሲያቅታቸው የህዝቡን ትኩረት ወደውጭ ለመመለስ ነው ጦርነት ሽብር የሚያስቡት›› እየተባባሉ ይወነጃጀላሉ እነፕሬዝደንት ኦባማም ዝምታን መርጠዋል ምናልባት ዘና ብለው ተቀምጠው ‹‹አስተናጋጅ ቡጥቡጡ ከመጀመሩ በፊት አንድ ቢራ›› እያሉ ይሆናል !….
ለማንኛውም አገራችን በዚህ ወቅት እንደገና ወደጦርነት ባትገባብን ምርጫችን ነው !! ‹‹አይ ሳንዋጋ አስር አመት አለፈንኮ እጃችንን እናፍታታ …ወንድነታችንም ትንሽ ይፈተሸ እንጅ ›› ከተባለ . . .፡)ማነሽ አልጣሽ ምንሽሬን አቀብይኝ…ወደሰማይም ቢሆን እተኩሳለሁ …እግዜርን በምንሽር ካልቀሰቀስነው ፆለታችንን አልሰማ ብሏል፡)፡) እናተ ልጆች ዝሆኖች እንደገና ሊጣሉ ነው ሳሩን ወደጥግ ወደጥግ አድርጉት እስቲ !