Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ተጠያቂው ማን ነው?

$
0
0

ከደብረጊዮርጊስ
ኢትዮጵያ ዳግም ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እየሔደች መሆኗ እጅግ ያሳዝናል። የደርግ መንግሥት የሰላምና የለውጥ በሮችን ሁሉ ዘግቶ ሁሉንም በኃይልና በጉልበት በመግደል እና በማሰር ጨርሶ ሰላም የሚያገኝ መስሎት ነበር። ግን አልሆነም። የሰላምና የለውጥ አማራጭ በሮች ሁሉ የተዘጋባቸው ኃይሎች ምንም ምርጫ ስላልነበራቸው ወደ ጦርነት አማራጭ ለመሄድ ተገዋል። አሁን ሥልጣን ላይ ያለውን ኃይል ጨምሮ። በዚህ ለረጅም ዓመታት በተካሔደ የእርስ በርስ ጦርነትም ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ኢትዮጵያዊ በሁሉም ወገን ተሰውቷል የአካል ጉዳተኛ ሆኗል። ብዙ የኢኮኖሚ መሻሻል ልታሳይ ትችል የነበረች ሃገራችንም ሕዝቧ በሚያሳዝን የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲገኝ አድርጎታል።
clash
ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ዛሬም በኢትዮጵያ ላይ ሊደገም አንዣቧል። ልክ እንደ ደርግ በሥልጣን ላይ ያለው ኃይል በሮችን ሁሉ ዘግቶ የአገዛዙን ስህተት የተቹትን ሁሉ በማሰር በመግደልና ስደተኛ በማድረጉ ምክንያት ዳግም ወደ ጦርነት እየገሰገስን መሆናችን እጅግ ያሳዝናል። ለዚህም አሁን ሥልጣን ላይ ያሉት ደርግን ተጠያቂ እንደሚያደርጉት ዛሬም ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው ኃይል ነው። ይህ ጦርነት ከቀድሞው ጦርነትም በበለጠ መሠረቱ ሰፋ ያለ ጅማሬ ያለው የጦርነት ክተት ውጤቱም እንዲሁ ሰፊና አስከፊ እንደሚሆን ስልጣን ላይ ያሉት ብቻ ሳይሆኑ በተለያየ ምክንያት መንግስት የሆነውን ኃይል የሚደግፉ ሁሉ ሊያጤኑት ይገባል። ለምን? ለምን? ለምን? በጥቂቶች እምቢ ባይነትና ትእቢት ለምን ሃገር ወደ ጦርነት ትገባለች? ይህ ደም የመፋሰስ እና የሃገር ጥፋት ወደማይመለስበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት ሁላችሁም ምከሩ ዝከሩ!!!

100% አሸንፈናል እያሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ማላገጥ ዋጋ እንደሚያስከፍል እና ዘላቂ የሃገርና የሕዝብ ጥቅምና ሰላም እንደሚያሳጣ ደጋፊና ወዳጅ ነን ያላችሁ ምከሩ ዝከሩ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በባህሉ ተዋጊ ነው። ጀግናም ነው። የህዝብ ቁጣ ከገነፈለም የተከማቸ መሳርያ ወይንም ገዢ መሬት አያድኑም። ባሳለፋችሁት የጦርነት ልምድ ይህን እውነታ እናንተ ይበልጥ ታውቁታላችሁ። ደርግ በሰው ኃይል በመሳርያና ገዢ ቦታዎችን ይዞ ይበልጣችሁ ነበር። ግን ያ በቁጣ የተነሳውን ህዝብ ሊያቆመው አልቻለም። በህዝቡ ውስጥ ያለውን ብሶትና ስሜትም በሚገባ ታውቁታላችሁ። ነገር ግን ልክ እንደ ደርግ አሁን በመሳሪያ ተማምናችኋል። ነገር ግን ልክ እንደደርግ ጠባችሁ ከፈጣሪም ጋር ነውና አወዳደቃችሁም እንደዛው እንደሚሆን አትርሱ። ወደልቦናችሁ ከተመለሳችሁ ግን አሁንም ግዜ አላችሁና ተመከሩ።

በተለይም በሃይማኖት አባትነት ቦታ ላይ የተቀመጣችሁ በፍርሃትና በአድርባይነት ተሸብባችሁ የሃገራችሁ ህዝብ በጥቂቶች እምቢ ባይነትና እብሪት ዳግም ወደ ጦርነት ሲገባ እያያችሁ ሊገሰጽ የሚገባውን ክፍል ባለመገሰጻችሁ እግዚአብሔር በነፍስ ብቻ ሳይሆን በሥጋም የከበደ መከራ እንደሚያመጣባችሁ አትርሱ። እግዚአብሔር ይህ መጪው አዲስ አመት እብሪተኞች ወደልቦናቸው ተመልሰው በኢትዮጵያ ላይ የለውጥ ሂደት የሚታይበት እንዲሆን እና የሰላምን ወሬ የምንሰማበት እንዲሆን ያድርግልን።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles