Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የአቶ ሞላ አስገዶም ክህደትና ህወሀትና የግንቦት ሰባት ጠላቶች ጉሮ ወሸባዬ

$
0
0

በበላይ አካሉ: belayakalu@yahoo.com

አቶ ሞላ አስገዶም ጥቂት ተከታዮቹን ይዞ ተመልሶ ወደ ህወሃቶች ካምፕ መቀላቀሉን በኢሳት ሰበር ዜና ከተነገረበት እለት ጀምሮ በጣም አሳዛኝና አሲቂኝ አስተያየቶችን ሰምተናል:: የገበያ ግርግር ለሌባ ሰርጉ ነው::
mola
ህወሀት/ወያኔ በጣም አሲቂኝ በሆነ መልኩ እንዲህ ብሎናል: “ለበርካታ አመታት በኤርትራ መንግስት አማካይነት ሲደራጅ የነበረ የጥፋት ሀይል ብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አገልግሎት በዚህ ሀይል ውስጥ ከነበሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር ምስጢራዊ የሆነ የግንኙነት ስርዓት በመመስረት በተሰራው የተቀናጀ የኦፐሬሽን ስራ አማካይነት በተደራጀ መልኩ ከነሙሉ ትጥቁና የሰው ሀይሉ ጋር መስከረም 1 ቀን 2008 ዓ. ም. ወደ ሃገሩ እንደገባ የጋራ ፀረ ሽብር ሀይሉ አስታውቋል፡፡”
እንደ ህወሀት አባባል እነሞላ 10 ዓመት በላይ ወደ ኤርትራ የተላኩት ተዝናንተው እንዲመጡ ነበር ማለት ነው? ለነገሩ የህወሀትን አሲቂኝ መግለጫ ወደ ጎን እናድርገውና፡ ከህወሀት መግለጫ በስተጀርባ ያለውን በጥቂቱ በአጭሩ እናስቀምጠው::

ህወሀት ይሄንን የተለመደ ቀዳዳ ዲስኩሩን ያስተላለፈልን አንደኛ የስለላ ድርጅቴ አቅም ከፍተኛ ነው ማንኛውም አይነት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ እጄ አለበት ብሎ ኢትዮጵያዊያን ላይ የስነ ልቦና ሽብራዊ ተጽእኖ ለማድረግ: ሁለተኛ ነገር አሁንም የትግራይ ህዝብን በሙሉ የህወሀት ደጋፊ በማስመሰል ከዚህ ቀደም የነበረውን የከፋፍለህ ግዛ ፓለቲካ ይበልጥ በማስፋት ሌላው ኢትዮጵያዊ በትግራይ ህዝብ ላይ ያለውን ጥላቻ ለማስፋትና: በአንፃሩ ደግሞ የትግራይ ህዝብን ከህወሀት ውጪ ምንም አማራጭ እንዳይኖረው ማድረግ: በሶስተኛ ደረጃ በራሱ በህወሀትና በአንዳንድ የምቀኛ የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር ሲጮህበት የከረመውን የቁራ ጩሀት ደረቅ ተራ ፕሮፓጋንዳ “ሻኧቢያ የኢትዮጵያ ጠላት ስለሆነ በሻኧቢያ በኩል የሚደረገው ትግል አያዋጣም” የሚለውን ለማስተላለፍ ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ እውነታው አሁን ህወሀት እንደሚቀባጥረው ሳይሆን እውነት እነ የአቶ ሞላ አስገዶም የተላኩት ከ10 አመት በላይ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ወቅታዊ መረጃ እንዲደርስ ለማድረግ ሳይሆን የህወሀትን አስከፊ የገዳይ ስርዓት ለመታገል ስለመሆኑ ለማወቅ የፓለቲካ ጠቢብ መሆን ወይንም የግድ እንደነ ኤልያስ ክፍሌ: ክንፉ አሰፋ: አበበ በለውና ሌሎችም “ድሮም ብዪ ነበር” ባዮች የምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባል መሆንን አይጠይቅም::

ምክንያቱም እነ አቶ ሞላ አስገዶም ከህወሀት ጋር በውስጥ ቢሰሩ ኖሮ ቢያንስ ቢያንስ እንዴት ፕሬዝደነት ኢሳያስ አፍወርቂንና ሌሎች ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት ላይ 10 ዓመት ሲቀመጡ አንድ ጊዜ እንኳን የመግደል ሙከራ አላደረጉም? እሺ እሱም ይቅር ለካስ በምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር መዝገበ ቃላት መሰረት ወያኔና ሻእቢያ አንድ ናቸው:: እሺ ቢያንስ ቢያንስ እነ ዶ/ር ብርሀኑና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ላይ የመግደል ሙከራ አላደረጉም? ወይስ አዝነውላቸው ነው?

ሀሰትና ስንቅ እያደር ያልቅ እንደሚባለው ከሰሞኑ ጉሮሮዋቸው ደርቆባቸውና ብእራቸው ዶልድሞባቸው የከረሙት የምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች አዲስ ስራ አግኝተዋል:: ስለዚሁም በተለያየ ቀለማቶች የያዝዋቸውን አዲስ የማደንቆሪያ የጭቃ ጅራፋቸውን ይዘው የፈረደበትን ግንቦት 7ትን ለመውቀጥ እንደ ጀት ተተኩሰው “ድሮም ብዪ ነበር” የሚባለውን ቦንብ እያዥጎደጎዱት ይገኛሉ። እንደሚታወቀው አባላቱ ሻእቢያን በመቃወም ስም ለረጅም ጊዜ ሲያራምዱት የነበረው ፀረ_ግንቦት 7 ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በቅርብ ጊዜያት በተደረጉ የአርበኞች ግንቦት7 የድጋፍ ማሰባሰቢያ ስብሰባዎች ላይ ኢትዮጵያዊያን በነቂስ ወተው ስብሰባዎችን መካፈል ብቻ ሳይሆን ገንዘባቸውንና አንጡራ ሀብታቸውን ለትግሉ በማዋጣት ደጀንነታቸውንና ለሚደረገው ትግል ቁርጠኝነታቸውን በማሳየት እንኳን የጥቂት የዲያስፓራ የተልባ ቢንጫጫ ህልመኞች የምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች ተራ የአሉባልታ ጋጋታ ብቻ ሳይሆን እራሱን የህወሀት/ወያኔን የወንጀለኛ ቡድን አንገት አስደፍትዎል::

ሌላው አሳዛኝ ሁኔታ አንዳንድ ፅንፈኛ ኢትዮጵያዊያኖች ህወሀት/ወያኔ በቀደደው የዘረኝነት ቀዳዳ ውስጥ ወድቀው የተከበረውን የትግራይ ህዝብን ከአንድ ግለሰብ ጋር በማገናኘት ዘርን ሲሳደቡና ልዩነቶችን ከወያኔ በላይ እያሰፉ የራሳቸውን ጠባብነትና ባዶ ጭንቅላት አሳይተዋል:: ለመሆኑ ልደቱ አያሌው በጠራራ ፀሀይ ህዝብን ሲከዳ ጠቅላላ የአማራ ህዝብ ባንዳ ነው መባል ነበረበትን? እንዴ ስንት ኦሮሞ: ጉራጌ: ወላይታ: አማራ: ከንባታ: አፋር: አደሬ: ሶማሌ: ወዘተ በየጊዜው እየከዳ የህወሀት/ወያኔ አገልጋይ ሲሆን አይተን የለ እንዴ? ታዲያ የትኛው ግለሰብ ነው ዘሩ ተጠቅሶ የተረገመው? ለማንኛውም እነዚህን ጥቂት በዘረኝነት ልክፍት ያበዱ በሽተኞችን የአቶ ሞላ አስገዶምን ክህደት ከጠቅላላው የትግራይ ህዝብ ጋር እያገናኙ የዘረኝነት አጀንዳቸውን የሚነዙትን ከህወሀት/ወያኔና ከምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች እኩል መታገል አለብን:: ምክንያቱም እንደዚህ አይነት ፍጹም ጥላቻ ላይ የተመሰረተ አንድን ማህበረሰብ በአንድ ከረጢት ዉስጥ አሰስገብቶ መፈረጅ በጣም ከዘቀጠ አስተሳሰብ የሚመጣ ድርጊት ነው ::

እንደሚታወቀው በእውነተኛ ትግል ውስጥ መውደቅ: መነሳት: መታሰር: መቁሰል: መክዳት: መሞትና ወዘተ ይኖሩበታል:: ስለዚህም ዛሬ ብቻ ሳይሆን ትናንትም ዛሬም ነገም ሌሎች ሞላ ይኖራሉ:: ይሄንን የማያውቅ ካለና በነ የምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች ተራ የአሉባልታ ፕርፓጋንዳ የሚታለል አለ ብዬ አላስብም:: ዋናው ነገር እንጨት ካልነፈጉት እሳት አይጠፋም እንደሚባለው: የዘረኛው የወያኔ አስከፊ አገዛዝ ጭቆናውን እስካላቆመ ድረስ በዛች አገር ላይ የነፃነት ትግል አይቆምም::

ስለዚህም አሁንም ቢሆን ደጋግመን ለህወሀት/ወያኔና ለምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች የምንነግራቸው አህያ ሞተች ተብሎ ጉዞ አይቀርም:: ኢትዮጵያዊያኖች የምንታገለው አቶ ሞላ ስለገባ ወይም ስላልገባ ሳይሆን ወይንም ዶ/ር ብርሀኑ ስለገባ ወይም ስላልገባ ሳይሆን ወይንም ጀነራል ከማል ገልቹ ስለገባ ወይም ስላልገባ ሳይሆን በአገራችን ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሰላም: ፍትህና ዲሞክራሲ በነውጠኛውና በዘረኛው የወያኔ የጉጅሌ ስርዓት ስለተነፈግንና በሀገራችን ላይ እንደ ማርያም ጠላት እየተደበደቡ: እየታረዙ: እየታሰሩና እየተገደሉ መኖር ስላንገሸገሸን ነው::

የሰካራም ግጥም ሁል ጊዜ ቅዳ ቅዳ: ስለዚህም ዛሬ የህወሀት/ወያኔና የምቀኛው የተቃዎሚ ሀይሎች ግንባር አባሎች ባዶ ጉሮ ወሸባዬ እና አሁንም ላንቃቸው እሲኪላቀቅ የሻእቢያን ጠላትነን ሊነግሩን አፍንጫችሁን ቆርጠን ለአፋችሁ እናጉርሳችሁ አይነት ፓለቲካ ቢጫወቱ ማንም አይሰማቸውም:: ምክንያቱም እንደ ተረቱ “ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ ነው:” ዛሬ ለየትኛውም ኢትዮጵያዊ ከህወሀት/ወያኔ የገለማ አገዛዝ ውጪ ማንም ጠላት የለውም፡ ስለዚህም ይሄንን አስከፊ ስርዓት ለመታገል ኢትዮጵያዊያን ከኤርትራ ብቻ ጋር ሳይሆን ገና ከሰይጣንም ጋር ቢሆን ያብራሉ::

ድል ለኢትዮጵያዊያን::


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>