Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

አረማሞ (ሥርጉተ ሥላሴ )

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 19.09.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

እንዴት ናችሁ ቤቶች? ደህና ናችሁን? እኔ  እህታችሁ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ዛሬ በጋዜጠኛ ደምስ በለጠ  ዙሪያ የሚሰጡ አስተያዬቶችን ለመግራት አባ ቅንይ ጸሐፊ አቶ ይገርም አለሙ „መፈራረጅ አይገባም“ ሲሉ ላቀረቡት የመከላከያ ጹሁፍ – መልስ መስጠት ግድ አለኝ። የማከብረወት እንደ ሃሳበወት ቢሆን መልካም ነበረ። ዘመቻው ገንቢ ቢሆን ኖሮ፣ አቅማቸው ብቁ ነው ዬሚቃወማቸው ተቋማት። ጠረባውን ለማስተናገድ። ነገር ግን የነጠረው የሂደት መስታውት ዬጉዞው ምርጫ አረማሞነት ክትር እንዲሰራለት – አላደረገውም። ሃቅን አላይህም ቢሉት፣ ህሊና ማንዘርዘሪያውን ይዞ – ያፋጥጣል። ተወደደም – ተጠላም፣ ተፈቀደም – አልተፈቀደም። የአቋም ልዩነትንና ዬአሰተሳሰብ ልዩነት ለሳይንሳዊ ተፈጥሯቸው ዕውቅና ለመስጠት – ከፈቀድን።

በቅድሚያ አረማሞ የነገር ሥምን ነው የሚወክለው። የዕሳቤ አረማሞ ለማለት ነው። አረማሞ ማለት እንደ ዘር ተዘርቶ በቅሎ – አስብሎ – በቁመናው – ያድጋል። ይጎለምሳል። ሸበላ ሆኖ ነው – ዬሚበቅለው። ውስጡ የሚገኘው እድገቱን ከጨረሰ በኋላ ነው። ለዚህም ነው እንደ አረም እድገቱን ሳይጨርስ ተነቅሎ – የማይጣለው። የመዳህኒተዓለም አስተምህሮ ተምሳሌን እንድናስተውለው ነው፤ የአምላካችን ረቂቅ ጥበቡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በትርጉም ነው – የተፈጠረው። አረማሞ በሽፉኑ ምንም ልዩነት ሳይኖር፣ ሽፋኑ ሲሸለቀቅ – እንደ ሌሎቹ  አፍርቷል ተብሎ ሲገለጥ የተቃጠለ የአፈር ዱቄት፣ የጭስ አቧራ፣ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ጠረኑ ሆነ አጠቋቈሩ ሥም የለሽ ነው። አረማሞ ከየትኛውም የእህል ዘር ብቻ ሳይሆን፣ ከወገነ – ፅጽዋትም ለምሳሌ፣ ከእሳር ሆነ ከእንዶድ ሊፈጠር – ይችላል። አንድ የሚያደርጋቸው የአረማሞ ፍሬ የተቃጠለ፣ የተፈጬ የአፈር ጭስ፣ አቧራ መሆኑ ነው። እርእሱ ብቻውን pilar ሆኖ ዬብሄራዊ ነፃነታችን ቀበኛ ሆነ ተቀናቃኝ ቂመኛ ዕሳቤዎች ውስጣዊ ጭብጥ፤ ተፈጥሯዊ ባህሪ ዙሪያ – ገብ ቀልቡን ግልጥ አድርጎ ያሳዬናል። ከአረማሞ ተፈጥሮ ጋር መደማመጥ – ከቻልን፤

በተረፈ ዬኔዎች – መቅደም የነበረባቸው ጹሁፍ ስለነበሩብኝ፣ ትንሽ የዘገየሁ ቢመስልም፣ ቁስሉ አሁንም ንፍርቅርቅ ብሎ ስለ ቀጠለ፣ በቅንነት ተነሳስተው በዚህ እርዕስ የማከብራቸው  ጸሐፊ አቶ ይገርም አለሙ የጻፋትን ግርም እያለኝ ነበር – ያነበብኩት፤ ከሥርም በአጭሩ የምለውን – ብያለሁ። በዝርዝር ግን ማህበራዊ ድህረ ገጽ ለይ ስለ ተለቀቀ፣ የግድ መታረቅ አለበት ሥራዬ ነው – ዘበኝነት። ዬፀሐፊ አቶ ይገርም አሉሙ ዬተነሱባቸው ጹሑፍ ….

  1. „ፐ!ፐ!ፐ! ኢትዮጵያ እንዴት ያለ ትንታግ ጋዜጠኛ አላት በል!“ August 31, 2015 ፀሐፊ ነፃነት ዘለቀ
  2. „ጽሁፍህ ወያኔ፣ ወያኔ ይሸታል” ይድረስ ለደምስ በለጠ September 2, 2015 ፀሐፊ ቢላል አበጋዝ፣ ዋሽግቶን ዲሲ
  3. ለእነኝህ ጹሑፎች መልስ ለመስጠት ነበር ፀሐፊ አቶ ይገርም አለሙ „መፈራረጅ ለምንም አይበጅ“  September 2, 2015 ዬፃፉት

በዚህ አጋጣሚ በድካም ዕውቅና ያገኙ የትምህርት ደረጃዎች ጥሰት በግራ ቀኙ ግድፈት – አያለሁ። ይህም ሁላችነን ዬሚያስገምት ይመስለኛል። ብናርመው መልካም ነው። ስለዚህም ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ጋዜጠኝነቱን በሥልጠና ነው ያገኘው። በጋዜጠኛ ደምስ በለጠ በኩልም የመጨረሻው እርከን ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፕሮፌሰር መሆናቸውን ሆን ብሎ በተደጋጋሚ ዶር. እያለ ነበር የገለጠው። ይህ ዓለምዓቀፍ ዕውቅና ያገኘ የዕውቀት የክብር ልዕቅና ሥያሜ ያልተገዛ ስለሆነ ተሞልቶ መገለጽ አለበት።

ማያያዣ

እህ – እጅግ በርካታ ግራሞቶች በሰንበት መታደሚያ ቤቴ ኢትዮ ሚዲያ በልኮንዳ ቤት ተግባር ቅርጥምጣሚዎችን፣ ቅንጥብጣቢዎችን በያይዶ በሚቀርበው በአቶ አንለይ ከበደ (ቤኒ) ደመ ነፍስ የቢዲዮ ቅንብር መማረኩበፍቅር  እብድ ማለቱ ለካንስ የፋሽስቱ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቱባ ቱባ ባለስልጣኖች ዝክረ – ጀግንነት ሽሽት መሆኑ – አስተውዬበታለሁ። እንደ ነበረኝ አክብሮትም እግዚአብሄር ይማራችሁ እላለሁ። አያያዛችሁ – አላማረኝም፣ ዬተቀናላችሁ ሕዝባዊ ፍቅር እንዲህ በግፍ ከገፋችሁት፣ አንቴና ወደ ጠረን ብቻ እንዲያደርግ – ይገደዳል። እንደ ጣዖት ዬምታመልኩትን ቤተ – ነገዳችሁን የማዳን ጸጋችሁም ፉርሽ ሆነ። በሰሞናቱ ደስታችሁን የመቆጠብ አለመቻላችሁ አቅምም አቅልም ስስ መሆኑ፣ በእናንተ ላይ የነበረኝን ጽኑ እምነቴን ለዳጥ – ገበራችሁት። እግዚአብሄር – ይይላችሁ። መጠራጠርን ዘውድ ደፋችሁለት። ዬታሪክ አሻሮ እሮ – አሮ።

 http://www.ethiomedia.com/1000parts/7253.html “Now hailed as hero by Ethiopia, TPDM leader Molla Asgedom has been a TPLF implant for over one year, an official source said on Sunday.” የማከብራችሁ የኢትዮ ሚዲያ ቦርድ አባላት – የነፍስ ወከፍ ዬጥበብ ፍቅረኛ ሜዳ ላይ ዬሚታፈስ – መስሏችኋል። ቀረባችሁ። ልብ ያለው ሽብ። ቀን ጥሩ ነው የታጬቀ ገመና – ተዘክዝኳል። አቶ ሞላ አስገዶም ገለበጥኩ ብለው ተገልብጠዋል። እንዲህ ሲሉ „ህወሃትን አርጅታችኋል፣ ተተኪዎችን ወጣቶች አለን፣ በሙስናም በክታችኋል ሲሉ በአሽሙር ሾጥ አድርጓቸዋል። ስለ ልማታቸውም ኤርትራን ትራስ አድርገው ጎሸም” በማድረግ ቀዳዳ – በቀዳዳ። ከእንግዲህ በኋላ አቶ ሞላ አስገዶምን በሚዲያ ለማየት – ይቸግራል።

ውዴ አብርሽ ዬተመረጠ ለዚህ – ነበር። እንኳንም ዬአሉላ ዬአደራ ልጅ – ታሰረ። አሁን ነው ዬአዳኜ ሚስጢር – ዬታዬኝ።

በተረፈ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ “ዬደምህቱ መሪ ሞላ አስገዶም ከትናንት በስትያ እስከ ዛሬ“ ሲል ለአዲስ አመት ውስጡን አሳይቶናል። እኔ እንደማስበው ብዕሩና ብራናው ብቻ ሳይሆን ከውጊያ ወረዳ ላይ ዬነበረው ዬልብ ማዳመጫ ይዞ ስለ ነበረ የተዋጊዎች ልብ ድም … ድም ሲል ልባቸውን – አስደምጦናል። ወንዳታ¡ የላስቤጋሳው ሰው አልባ ምርጥ ትራፊክ (navigation) „ … በዚህም የነፃነታቸውን  ብስራትና  የአዲሱን አመት ችቦ ኤርትራና ሱዳን ደንበር ላይ ተዋጊዎች በጥይት ለኮሱ።“  ነፃነት ኢትዮዽያ ስላለ ነው ዬሙያ አጋሮቹ እስር ቤት ዬወጣትነት ዘመናቸውን – የሚገብሩት። ማለፊያ ነው¡ ሚሊዎኖች በስጋት -በፍርሃት በባእታቸው የታፈኑት – ለጋዜጠኛው እንደ ዜጋ ለመታየት ማመልከቻ ማስገባት – አለባቸው። በህወሃት ፉሽስታዊ ሥርዓት ወይንም ፖለቲካ የምትመራው ኢትዮጵያ በእርሱ ግምት ነፃነት በገፍ የሰፈነባት መሆኑን በተደጋጋሚ አስረግጦ ነግሮናል። ይህው ነው የጉዳዩ – አስኳል።

አስኳል

የማከብረወት ጸሐፊ አቶ ይገርም ሃሳብን ለማስታረቅ የፈቀዱትን የአሸማጋይነት ተግባር – አከብራለሁ። ይህ ማለት ግን የእርሰዎን ዕይታ እሸምታለሁ ወይንም እሸከማለሁ ማለት አይደለም። እኔም በቅንነት መንገዱን “ውስጤ” በሚል ሂጀበት ነበር። ለማንኛውም መረጃ አቅርቡና ተሟገቱ ስላሉ፣ ፍላጎተዎት ተንጠልጥሎ እንዳይቀር – ትንሽ ልል ፈለግሁኝ። አውራንባ ታይምስ አዘጋጅ ቤተ – ትግራይ ስለሆነ ነው የተወገዘው ወይንስ ወጣት ጆዋር ቤተ – ኦሮሞ? ድፍረት ይኑረን፣ የምናከብራቸው ወንድሞቻችን ሆነ እህቶቻችን ለግድፈታቸው ጥብቅና መቆሙ መጠን ሊኖረው – ይገባል። ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ሰብዕናውን ሳንነካ ከእኛ ጠረን በፍጹም ሁኔታ እዬራቀ ዬሄደውን የሃሳብ ጉዞውን ልንጸዬፈው – ይገባል። የእኔ ስለሆነ ብቻ ይህን ያህል በሙሉ ትጥቅ ተስፋን ሲያደቅ ታከብረው ከነበረ እህቱ የብዕር ጦር – ይታዘዛል። ይህ ዬነሲብ ትረካው ለአቶ ወንድም ከነበረኝ ግንዛቤ ጋር – ተጣላ።

የማከብረወት – ለመሆኑ በጠላት ወረዳ ተገኝቶ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ የሰጣቸውን ሦስት ቃለ ምልልሶችን – አዳምጠዋል? ትጥቁን የፈታው ከማን ጋር? የትኛው ቤት? አለማለቱ ብቻ ሳይሆን፣ ከ95 ሚሊዮን ሕዝብ ስቃይ በእጅጉ እርቆ ነው ያዬሁት። መማሩ እራሱ አሳዘነኝ፣ በህዝብ ስቃይ ዘመቻ ነው ዬተያያዘው። ሰፋ – አላለም። ለእኔ ዕንባ የማበስ አቅም የላቸውም – ጹሁፎቹ። ለዕንባዬ  እርቅ ያላደረገ – ጥንቃቄ የጎደለው የቂም ኩትኩት። ጠብታ ለዕንባዬ ማስታገሻ ዬለውም። ይዘረገፋል ያለው ገመና ዬትረካ ባህሬ ከማያዙ በሰተቀር ካሴቱ ገልብጦ – ተገልብጦ – ተገለባብጦም ጭብጡ ከሌሎች ከሰማናቸው ውጪ፣ የመረጃ ጥማትን ረጠብ የማድረግ፣ ተጽእኖ ዬመፍጠር፣ መንፈስን ዬመግዛት አቅሙ ጥግ ስላላገኜ ስደት ጠይቋል።

ሁለት ዘለላዎችን ላንሳ፣ አደኛው „ገመና እዘረግፋለሁ“ አለ፣ ቁምጥ አሉ የህወሃት ደጋፊዎች፣  እውነቱን ለማወቅ የሚሹም ቅኖች ጠበቁ። እንደ የሰለጠነ  (professional )ጋዜጠኛ በቪዲዮዎ፣ በቃል መቅጃ፣ በተደራጀ የፎቶ ቅንብር፣ ሲጠበቅ ክፍል አንድ ተጀምሮ ክፍል ሁለት ተዘሎ ክፍል ሦስት ቀረበ። ከዛ በኋላ በክፍል መጀመሩን መዝለሉ ብቻ ሳይሆን የጹሁፍን ተካታይ ባህሪ ውልብሊቢቱን በመያዝ በጭብጡ ማእከል ዙሪያ ለመከተም – አልተቻለም። የሆነ ሆኖ የጀግና አንዳርጋቸው ጽጌ ጠለፉ የሀገር ጥቃት ነበር። በህወሃት ዬተቆራረጡ ቪዲዎች ዬወገኖቻችን ዬሰቆቃ ድምጽ እንኳንስ ለእኛ፣ ሰውን ለመተረጎመ ፍጡር መራር ነበር። ያን ጊዜ ዬት ነበር? እኛ የማናውቀው መረጃ 2014 በስቃያችን ውስጥ ሳይኖር ዬምናውቀውን ለእኛ መልሶ ይነግረናል። እምንጠብቀው የተመላለሰትን ወደ ኤርትራ „ገመና“ ያለውን ነበር። ማጣፊያ አጠረ …

ሁለተኛው በመጨረሻ ምን ትላለህ? ተብሎ ሲጠዬቅ እዬተሳለቀ መሪያችሁን ሂድ ወደ ወንዶቹ በሉት። ወኔ ከኖረው „ ነበር ያለው። በዚህ ፈጣሪ አምላካችን የመጀመሪያ ሰው አድርጎ የፈጠረው አዳምን ነው ያላገጠበት። አዳምን ሲፈጥረው አሳስቶ – አልነበረም። አዳም ወንድ ሆኖ ነው – የተፈጠረው። ተባእት ሁናችሁ የተፈጠራችሁት እራሳችሁን ፈትሹ – በአክብሮት፤ ህመሙን ልቡን ታገኙታላችሁ። ይህ ሽቅብታ የፈላስማውን ማስተር ፒስ የሊወናርዶ ዳቬንች የአዳምና የፈጣሪው መንፈስ እስኪ ጉግል አድርጉና ተመልከቱት – በትህትና። ፍጹም አምላክ በፍጽምና ስልጣኑ የፈጠረውን የወንድነት ረቂቅ ተፈጥሮ የደፈረ ነበር የቃለ ምልልሱ  – እድምታ።። በስማ በለው ሳይሆን ቁጭ ብዬ ነው – ያዳመጥኩት። ወንድም ላለው፣ አጎት ላለው፣ የትዳር አጋር ላላት አንስት ሁሉ ዬምጥ ቀን ነበር። ከዚህም ሌላም ማንሳት ይቻላል። ጫካ ጥርሱን የነቀለበት ስለመሆኑ – ያላገናዘበ ነበር። ፕሮፌሰር ዶር. ብርሃኑ ነጋ (ሥህነ – ቤዛ) በቅጡ 17 ዓመት አልሞላው ዱር ቤቴ ሲል። እንዲሁም ፕሮፌሰር ዶር ብርሃኑ ነጋ ዓለምዓቀፋዊ ትንፋሽ፣ አኽጉራዊ የሩህ መናህሪያ ቀለማም መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያው በህዝብ ፈቃድ የተመረጠን „ቀበቶ የለውም“ ብሎ መሳለቅ ያን የህዝብ ድምጽ መናቅም – መጠቅጠቅም ነው።

ሌላው አንድ ዬፖለቲካ ድርጅት ሆነ ንቅናቄ ከፕሮግራምና ከደንቡ ተነስቶ መረህ – ግብር አለው። ጊዜውን የሚተምነው፣ ዬሰው ኃይል እንደ ወቅቱ የሚያሰማራው በመርኻ ግብሩ ነው። ይህ ማለት ትጥቅን የመረጠው ፕሮግራሙን ያጸደቀ ዕለት ነው። ያልተገባ ዘለፋው ለዛውም ለመሥራቹ – ለቀባሪው አረዱት ነበር። የንቅናቄው መሪ ጋዜጠኛ ደምስ ስላባጨለው አልነበረም „የሚታዩ ነገሮች ለማምጣት የማይታዩ ነገሮችን መሥራትን ይጠይቃል“ „ ከእንግዲህ ሰው ሰብስቤ ማነጋገር ላቆም ነው“ ዬአርበኝነቱ መንገድ ጠራጊ መርህ ነበር። ይሄን እንደ አንድ ከፍተኛ ሙሁር አቶ ወንድም ለመተንተን ሆነ አስቀድሞም ለመተንበይ አቅም – አልነበረው። ይህ ቅላፄ የማን ትንፋሽ እንደሆነ ከህሊናው ጋር ለሚኖረው ነፃነት ፈላጊ አሳምሮ ያውቀዋል። ስለዚህም ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ዬማን አምሳያ ነው? በማን ቁስል ነው የሚረማመደው? ዕንባን እዬረገጠ ወይንስ እዬጠረገ? ለዚህም ነው የግንዛቤ ወለምታው ራቁቱን የሆነው።

ስለዬትኛው ዬህግ እረገጣ ነው ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ዬፃፈው? ዛሬ እስር ቤት ውስጥ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንዲገለል ብቻ ሳይሆን አንድ ጆሮው ተደፍኖ ዬዱካ ማስቀመጫ – ተክልክሏል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በጽንሱ እስር ቤት ከነበረው አንድያ ልጁ ትዳሩ መለየት አልበቃ ብሎ፣ መጽናኛውን ቅዱሱን መጸሐፍ – ተነጥቋል። ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ በእንኩላሊት በሽታ እዬተሰቃዬ ከአንድያ ልጁ ከትዳሩ ተለይቶ ለዛውም ቤተሰቦቹ የረባ መተዳደሪያ – የላቸውም። መምህርና ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ በምን ስቃይ ሁኔታ እንደ ነበረች – ይታወቃል። ሲፈቷት በቁም እስር ስለመሆኑ የአፓርታይድ አግናባት ጨለማዊ የአያያዝ ሁኔታ ሰሞኑን እሷንና የነገን ተስፋ በሰነቅኩበት ጹሑፏ – ተረድቻለሁ። መምህርና ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ስንቅ አቀባይ አልባ ከቤተሰቦቹ ተነጥሎ – በሥነ ልቦናው ሳይቀር ልዮ ደባ እየተደረገበት ነው።። ዬዞን ዘጠኝ ቤተሰቦች ወጣትነታቸውን ሲነጠቁ ምን አለ? ምን ተናገረ? ምን ፃፈ? ሊያስረዱኝ ይችላሉ ጸሐፊ ይገርም አለሙ – በትህትና?

የእስልምና እምነት አቨው አስታራቂ ሽማግሌዎች መፍትሄ አመንጭዎች በግፍ ሲታሰሩ፣ ፍፁም ልዩ የሆነ የሰላማዊ ትግል ለእኛ ዬማርቲን ሉተር የትግል ተመክሮ – ሰልጥኖና ደምቆ ትዕይንቱ – ሲታይ፣ ዬት ነበሩ የአቶ ወንድም ብዕርና ብራና? ማገዶዎች የአንድነት፣ የሰማያዊ፣ የመኢህድ መሪዎች ሲታሰሩ (አቶ አንዱአለም፣ አቶ ናትናኤል መኮነን፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ) እንዲሁም ሺዎች ሁሉንም የመስዋእትነት መፈተኛ ዬሆኑለት አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ብሄራዊ ፓርቲ በትእቢት በህወሃት ሲፈርስ የብዕሩ ትንፋሽ ለመሆኑ የት ነበረች? የሰላማዊ ትግል ደቀ መዝሙር እንደሆነ እየነገረን ነው፣ አራባና ቆቦ የሆነ ነገር፣

ለመሆኑ የብዕሩ ባዕት ዬትኛው ፕላኔት ነው – ያለችው? የወያኔ ሃርነት ትግራይ ዞጋዊ አስተዳደር የ2007 ምርጫ በደም ተለውሶ ሲያላግጥ፣ የደም ዋጋ ሥጋና ደሞቻችን ሲከፍሉ፤ በህዝብ ዕንባ ሲጬፈር፣ ከቶ ለአቶ ወንድም የሰርግ ቅልቅል ሆኖለት ይሆን? የሰማያዊ መሪ ኢንጂነር ይልቃል ስንት ጊዜ ታሰሩ – ተፈቱ? የአንቦ ወጣቶች የነገ የኢትዮዽያ ተስፋዎች ባሩድ ሲበላቸ – ሺዎች የውቅያኖስ ስንቅ ሲሆኑ – ሳውዲ ላይ እህቱ በሰባት እንሰሳ ተደፍራ ሰንደቋን እንደ ለበሰች ድፍት ስትል – ደቡብ አፍሪካ ላይ ወንድሞቹ ሲቃጠሉ – ሲነዱ – የሥጋቸው ጥብስ ሽታ ለብዕሩ ለምን ራቀ? የእርሱ ብዕር ዬአርበኞች ትግል ለመፍለጥ ብቻ ነው የተፈጠረችውን? ይንገሩኝ አቶ ይገርም …

ከነማተባቸው ሊቢያ ላይ ሰማዕትነት በኢትዮጵያዊ – ዜግነት ሲደምቅ ሃዘንተኛ በጠገበ አጋዚ – ሲወቃ፤ የዘመናት ዬትውፊት – ታሪክ ዬማተብ አውደ ምህረት ቅዱስ ዋልድባ አብረንታንት – ስቋር ገዳማት ሲደፈሩ፣ ቅዱሳኑ ሲደበደቡ፣ ሲገፈተሩ፣ ከአርምሞ ቤታቸው ሲነቀሉ፣ የሰለጠነው ጋዜጠኛ  (professional journalist ) የወንድም ደምስ በለጠ ብራና ሃኪም ቤት ወይንስ ጫጉላ ቤት? ወይንስ ኮማ ላይ ነበረችን?

ዬኮፐን ሃገኑ ዬድል ጎመራ ዕለቱ 2014 በዓለም ዙሪያ በፍሰሃ – ሲናኝ፣ ዬሴቶች ቀንዲል ዬንግስት ጣይቱ፣ ምንቴ፣ ዘውዴ ልጆች  በአጋዚ ቆመጥ ተቀጥቅጠው ወደ እስር ሲጋዙ፣  እስር ቤት ለሴቶች ካቴና ብቻ – አይጠብቃቸውም፣ ብዕር ሊያው ዬማይችለው፣  ዓለምም ዬማያውቀው፣ የዘለዓለም የመንፈስ ግዞት ይጠብቃቸዋል። ከእስር ሲለቀቁ ኢትዮዽያን ቢለቁ እንኳን ተልጦ መጣል – አይቻልም። እነኝህን መከረኞች በሆነ ባልሆነው ቁሙ ተቀመጡ ሲባሉ፣ ሳስብ ምነው አምላኬ በህልማቸው እንኳን ብትነግራቸው እላለሁ። እንደ ሰው መቆማቸው በእሱ በባለቤቱ ታምር ብቻ ነው። ወላጆቻቸው እራሱ ሊያውቁት አይችሉም፣ ታዲያ በዚህ ዙሪያ ቂም አምራች ብዕሩ ምነው እስከዛሬ ለፋሽስት መሞከሪያ ፆታዊ ማንነት በሚመለከት ዝምታን መረጠ? ረመጥ …

ቁስሌና ውስጤ ዬዬኔሰው ገብሬ ሰማእትነት – ተረሳ፣ ዬትዳር አጋርሽ መሳሪያ ደብቋል ተብላ ዬባለቤቷን ዬዘር ማፍርያ ባደገችበት ባዕት በጥርሷ እንድትጎትት – ሲደረግ፣ ዓለምን የማያውቀው ዕንቡጥ ሞት – ሲፈረድበት፣ ከእህል ጋር ለመገናኘት ቅኖችን ወገኖቿ ሁሉ በተሳነን አሳንጋላ ወቅት ምን ሲል – ተደመጠ? ጋዜጠኛው ለምን ገለልተኛ ሆነ? ነፍሰጡሯ ታጋይ ወይንሸት ሞላ መርዝ – ስትወጋ፣ በነጋ በመሼ ቁጥር ካቴና ስንቋ ሲሆን፣ እሱ ለደላዉ የህወሓት ካድሬ ለአቶ ሄኖክ ሰማእግዚር ጥብቅና ቆሞ አዬነው፣ ያ አልበቃው ብሎ ለአንድ ካህዲ የትግራይ ህዝብን ክብር ዬቀነሰ የአቶ ሞላ አስገዶም ፈን ሆኖ – ተገኘ፣

ያ … ብቁ ጀግና ካፒቴን ሃይለመድህን አበራ ሁለት መቶ ሁለት ነፍስን የታደገ፣ ዬሀገሩን ክብር ደም – ሳያጋባ፣ በሙሉ ጀግንነት ሲዊዘርላንድ ጄኔባ በድል ሲገባ፣ ሰው አልባው ትራፊኩ ለእሱ ለምን አልሰራም? ልክ እንደ አቶ ሞላ አስገዶም ስለምን መልካም አልተመኘም? በርካታ ጋዜጠኞች የዓለሞቹ ሳይቀር የእውነት አርበኛ ጋዜጠኞች ያደነቁት የሁሉ ነገር አብነትና ሞዴል ታናሹ ጀግንነትን ሲያደምቅ ለምን ድፍረቱ የእንቧይ ካብ ሆነ? ከዛ በኋላ ስንት የአውሮፕላን አደጋ ገጠመ? በእነ አንድርያስ ሉቢስ Andreas Lubitz በ2015 የጀርመን ዊንግ ረዳት አብራሪ ሆነ የማላዢያውን ጀርመን ለተሳፋሪዎች ለያንዳዳቸው ካሳውን እስከ 50.000 ሃምሳ ሺህ ኢሮ ለተጎዱ ቤተሰቦች ከፈለች  – የሦስት ሳምንት የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ የስፔን የወል የሌትና ቀን ዘመቻ ጠቅላላ ወጪ – ሳይጨምር። ሰቀቀኑ እጅግ መራራ ነበር፣ የእኛ ብልህ ግን ከሁሉም ነገር ያዳነ የጀግኖች ቁንጮ ሆኖ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ  „ወንድሜ ሞላ አስገዶም አንተም ሆንክ አብረውህ ያሉ ተዋጊዎች፣ እንኳን ከሻብያ ገሃነም ወጣችሁ። ለነፃነት በቃችሁ። አዲሱ አመት የሰላም እንዲሆንላችሁ ምኞቴ ነው። እግዚአብሄር የምታስቡትን ሁሉ ያሟላላችሁ ዘንድ እፀልያለሁ“ ሲል በተማህጽኖ ደጅ ጥናቱን – አሳየን። ኢትዮጵያ ገነት ሆናለች ይለናል – ተረበኛው አቶ ወንድም — ሎቱ ስብሃት ነው።

ከቶ ዬት ነበር ይህ ሰው? ዬእኛ ነው ወይንስ ዬሌላ? ለማን ነው ዬቆመው? ሊለምኑ ያፈሩ ሚሊዎኖች ናቸው። ትራፊ እንዲኖር ዬሚማጸኑት ሚሊዎን ልጆቻችን ድልድዬ – ጉድጓድ ውስጥ የሚኖሩ ሺዎች ናቸው። ትምህርት – ህክምና – መጠለያ ያጡ ሚሊዎኖች ናቸው። መሬታቸው ተሽጦ – አልቋል። ዕዳው ለዘመነኞች-  መዳነሻ፣ የነገ የፈተና ዳገት ነው። ይህ ሥም ዬለሽ ህመም ለጋዜጠኛ ደምስ በለጠ የህሊና ሰሌዳ ባዕድ ነው።  እኛ አይደለነም እራሱ የመረጠው መንገድ ነው። —- ተግባቶ? አቶ ይገርም።

እንደ ጦር ልክ እንደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚፈራው ደግሞ ኢሳትን ሲሆን፣ ይህ ከሚሊዮኖች መንፈስ ጋር መጣላት ነው። የኢሳት ቲ ሸርት የለበሰ ያንገበግበዋል – ለምን? የሚገርመው በአሁኑ ፁሁፍ „ለመጀመሪያ ጊዜ ኢሳት ሰበር ዜና እውነቱን ሲናገር“ አለ። ጠቅላላ ሁኔታው – ሆድ እቃው – አሮጌ ቆረንጮ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ኢሳት እኮ የመጀመሪያው አፍሪካዊ – ኢትዮጵያዊ – ዓለማቀፋዊ ሚዲያ ነው። ለአፍሪካ ሀገሮች ዬሚዲያ ታሪክ በስደት ሀገር ዬአብነት አዲስ መዲና ነው። ኢሳት ዬሚሊዎኖች ነው። በታሪካችን ወላዊ ተስፋችን ያበራ ህሊናች ነው። ከስድስት ኮሮች በላይ የፀሐይ ጉልበት ያለው ዬጥራት የጥረት ዓውዳችን። ኢሳት ዬእሱን ሃላፊነት መከራውን ሁሉ ታግሶ ስለተወጣ በቅናት ተጠምዶ ምን – ያሳብደዋል? ሲሆን በሙያው ሊረዳ የሚችልበትን ትብብር ማሰናዳት ሲገባው፣ ዬታላቋ ትግራይ አረማሞ ቡቃያ ዕሳቤ ማዳበሪያ መሆን ምን – ይሉታል? ከቻለም አማራጮችን ዘርግቶ ክፍተት ነው በሚለው ቦታ ላይ መትጋት – ይችላል። ከሁሉ በላይ ሲያከብሩት ለነበሩት መንፈሶች ሁሉ ዬማይጠነቀቀው ለምንድን ነው? ስለምንስ አስተውሎ – አይራመድም? የትምህርት ጸጋ – ዕድሜ ዬሚለግሱትን ሥነ – ምግባሮች ለማዳመጥ ስለምን ቀና አይሆንም?

ጥላቻ ዬጎረሰ ዘመቻው በአርበኞች ግንቦት፣  ዬሚያወርደው ናዳ የፖለቲካ ድርጅቶችን የመመስረት ሙሉ ዓለምዓቀፍ ነፃነትን ይጋፋል። ህልውናቸውን እንዲህ መፈታተን ዬፍልስፍናው – ዬዶክትሪን እጥረት ያለበትም – ይመስለኛል። አሁንም አቅሙ ካለ ማን ከለከለ? መብት ነው -ነፃነት ነው። ጀምሮ ማዬት – ማሳዬት። ደጋፊ – አይገዛም። የዓላማ ብቃትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ነው ፍቅርን  ዬሚያሳፍስ። ለተደማጭነት በጥላቻ የበከተ ዘመቻ ሳይሆን – ተግባርን ጨበጥ ያደረገ ዬትእግስት ሰጋር በቅሎ። መጀመር አይደለም ቁም ነገሩ መጨረስ – ተጽዕኖ ከማሳደር አቅም ጋር መቀባትንም  – ይጠይቃል። ሌላው ደግሞ እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ ነው ዬሚወለደው፣ መክሊትን ያለማወቅ ችግርም ካለቦታ  – ይቀረቅራል። በሥነ – ምግባርም በሰብዕናም ዳጥ ያባዛል። ፖለቲካ የተርቲም ጉዳይ አይደለም። ፖለቲካ – ሳይንስ ፍልስፍና እና ጥበብ ነው። ንጹህ አዬሩ ማስተዋልና ሆደ ሰፊነት ይጠይቃል። የህዝብን ስሜት ውስጡ ነው።

የአዲሱን ትውልድ ብቃት – ፈሪነት።

ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ አዲሱን ትውልድ ብቃት እንደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ፈርቶታል። አጋጣሚ ቢኖረው ሃብትሽን ለካቴና  እንደ ዳረገው ፋሽስቱ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የአርበኞች ግንቦት የውጭ ሀገር ከፍተኛ መሪ አካሉ ወጣት አቶ እዮኤል ሙሉነህን እስር ቤት ነበረ – የሚከተው። ለእኔ ለዘመኑ የምርጥ – ምርጥ ንግግር ነበር። እጅግ ብቁ ነበር። የንግግር ህገ-ሥርዓት የአድማጭን ቀልብ ድንበር አልባ ገዝቶ፤ በውጤታማ አኃታዊ መንፈስ ማስከን አንድን ተናጋሪ ብቁ ያደርገዋል፤ ይህን ደግሞ ትንታጉ – ከውኖታል። አይደለም አዳራሽ ውስጥ ያለውን ኦዲየንስ ውጭ ያለውን ታዳሚ በፍቅር – በወኔ – በእውነት ዙሪያ የማሰባሰብ አቅሙ ዓፄ ነበር። የተነሳበት የጭብጥ አናት በሙሉ የተደማጭነት አቅም – ቋጭቶታል። እውነት ለመናገር ዕልፍ የነገ ተስፋዎች እሱን ባደረገኝ ስለሚሉ የመልካም ምሳሌ ለመሆን ያስቻለ ታሪካዊ ድንቅ ንግግር ነበር። ሰውን በድንበር አልቦሽ የፍጥረት አብይነት የተረጎመ መምህር ንግግር ነበር። „ሰው“ ማለት ኢትዮዽያዊ ብቻ አይደለም። ድንበር አልቦሽ ዓለም አቀፍ የፍጥረት ጠበቃዎች የተደራጁበት አመክንዮ ይሄው ሆኖ ለጋዜጠኛ ባእድ ሲሆን ሪህ ነው።

በነሲብ አይደለም የምናገረው – የንግግር ሥነ ጥበብን ንድፈ- ሃሳቡን ተምሬዋለሁ። በተጨማሪም የድምጽ ቃናን ውጪ ሀገር ኮርስ ወስጃለሁ። ጋዜጠኛ ደምስ ባለበት ከተማ በነፃነት ግብር ልቆ መታዬት ህመሙ – ሆኗል። እውነት ለመናገር ለዛውም ለጋዜጠኛ የሚበልጥ በቅሎ ማየት አለመፍቀድ የበሽታ ነው። ለምን ከእስር ተፈተህ? ለምን ተደማጭ ሆንክ ነው ቁጭ አድርጎ – ሲኮልም ያሳደረው። አስተማሪ ሊያስተምር፣ ሃኪም ሊያክም፣ ጋዜጠኛ ደግሞ ሊዘግብ – የህዝብን ስሜት ለመለካት ከማህበረሰቡ የተሳትፎ ዓውዶች መገኘት የተሰለጠነበት ሙያ ባህሪም – ተፈጥሮም ነው። አበባ ያዙልኝ ሆኖም – አያውቅ። እንዲህ የሚጸጽተው ከሆነ ማመልከቻ ያስገባለት – የለም። በወቅቱ መቅረት ይችል ነበር። በጸጸት ቁርሾ – ከአስር አመት በኋላ – ከሚባክን።

አቶ ወንድም በፋሽስት ወያኔ ሃርነት ትግራይ የታሰሩት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችም ይሁን ግፉ ያሰደዳቸው ወጣት መሪዎቻችን አንደባታቸው አንገት አያስደፋነም „በምንም ተጀምሮ በምንም የተጠናቀቀው“ የአንተ መንፈስ የረበበት አቶ ሞላ አስገዶም ደጋግመህ ተመልከታቸው አንገት ያስደፋል – ሙጃ። የገረፍታ ምችን የሙጥኝ የምትለው ብዕርህ እራሷን ለመግለጥ – አሳፋሪውን ጋዜጣዊ መግለጫ የተለመደውን ልበ ወለድ ለመስራት ሙሽሽ አለች። ይልቅ ለአቶ ሞላ አስገዶም ትንሽ የጣት ጥፍር ቀለም ብትልክላቸው የአዲስ አመት ስጦታ ማሟሻ በሆነልህ ነበር። ለማንኛውም መልካም አዲስ ፍቅር ….

አሁን ወደ ቀደመው የአቶ ይገርም የማጠቃለያ ሙግቴ፣ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ እንዲህ ትክን እያለ ኢሳት – አርበኛ ግንቦት ከሚል ወራሪው የህወሃት ጠ/ሚር ለኃይለማርያም ደስአለኝ በሚያደርሱት በደል ዙሪያ ሆነ የትልልፍ ተራጋጭ አንደበት ለመግራት  አይተጋም? ትንፋሽ ለማሰማት – ተሳነው? ባለሟልነቱን እያየን ስለሆን ጆሮ ዘንበል – ይባልለታል። ቢያንስ በደንበራችን ጉዳይ ብዕሩ ኮተት ብትል ምን አለ?

ቃል ሲተረትር የሚውሉት ለፌስ ቡኩ ጄኒራሉ ለዶር ቴወድሮስ አዳህኖም ለምን  – አይሰራበትም? ለልብ ወለድ የነሲብ ትረካ የአፃፃፍ ዘይቤው ለህወሃት የለበጣ ጉዞ ብጡል ነው¡። ኮከብ – ለኮከብም ግጥምጥም ብሎ እየታየ ነው። ፍቅር እስከ መቃብሩ – ከዘለቀ? አቀራረቡ በትረካም ይሁን ሆነ በተረት ትርትር ለመነካካት ምን – አስፈራው? አርበኞች ግንቦት፤ ኢሳት ስለምን ዬስጋቱ ምንጭ ሆኑ? ይሄ መፈተሽ – አለበት። በቅንነትና በንፁህ ህሊና ሆድ እቃው ዝርግፍግፍ ብሎ ላንመለስበት እልባት ማግኘት – አለበት። በነሲብና በግምት ሳይሆን ከፍሬ ነገሩ ጋር ፊት ለፊት በእውነት (fact ) መድረክ መጋጠም አለብን።

ክወና።

ብልሁ ኢሳት ልጆቹን ቀድሞ ወደ ኤርትራ መላኩ ብቻ ሳይሆን፤ ያገኘውን መረጃ በቁጠባ መያዙ፤ ለበስ አድርገው ቁስል ሲረግጡ ሃዘን ካልፈጠረላቸው ከዶር. አረጋይ በርኽ ጋር ያደረገው ቃለ- ምልልስ የስጋቱን ቂመኛ ትልም መፈናፈኛ እንዲያሳጣ – አድርጎታል። ይህ እውነትን ለማግኘት ለሚተጉ ሰዎች የመፍትሄ መንገድ ይመስለኛል። ቀደም ብሉ ከVOA ጋር የተደረገው ቃለ – ምልልስ ወገንተኝነቱ የአደባባይ ሲሳይ አድርጎልናል። በአጃቢነት የተሰለፋችሁ የመከረኛው ቤተሰቦች ልብ ይስጣችሁ – ፈጣሪዬ። እነሱም እንደ ካቦ ነው የሚያዮችሁ።

ወቅትን በማቅለል፣ በማዛል፤ በማግነን ወይንም በማሳጠር ሳይሆን፤ በብልህነት ዬምትገኘውን ብጣቂ መረጃ ዋጋ እንዲኖራት በማድረግ፤ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ እረገድ ዬፀበል ያህል መዳህኒት ነው። ብዙ ስጋቶችን ጥበቡ መልክ – አስይዞታል። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ – አያከስርም። ብዙ ዬሚዲያ ተግባራት በአቶ ሞላ አስገዶም የተደረገው ቃለ ምልልስ ለለውጥ ፈላጊው ዬፖለቲክ ዬሥነ ልቦና ዬበላይነት ለእኛ – አትርፏል። አረማሞ ሆድ እቃዎች ካለ ሽፋን አደባባይ ስለዋሉ ዘመኑ የእኛ ነው፤ „አለ ነገር“ አቮላችን ከሆነ። አርበኛው ሻንበል በላይነህ „እንቢበል“ ሽልሞናል፤ እኔም የማከብረው መሪዬ የኢትዮዽያ አገር አድኑ ብሄራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (ሥህነ – ቤዛ) በግንቦት 2009 ፍራንክፈርት አማይን ለገላጭነት መጥቶ በነበረበት ጊዜ እርእሱ „እንቢበል“ የሚል ሥነ -ግጥም አቅርቤ ነበር። ለህትምት ከበቁትም መጸሐፍቶቼ በአንዱ አለ። መከረኛውም እንቢበል።  የአሻሮ መጠቅለያ – አትሁን። እንደ ክብርህ ዘመኑን – አንብበው። ውርደት ውርዴ – ለጉርድነት ነው። አንተ ግን የውርሰ – ጽናትን ጥቁር አንበሳን – ተከተል። ድሪቶ – ክፍልህ አይደለም። ሰንደቅን ለሚመራው ብቻ ልብህን ስጥ። ሙቀትህን “ለፍትህ” አርበኛ።

ክብሬ ዘሃበሻን አመስግኜ – ለናፍቆቶቼ የጹሑፌ ታዳሚዎች መሸቢያ ሳምንትን ተመኘሁ።

*ፎቶው ላይ ያለው ግጥም ዬእኔ ሃብት አይደለም።

ምንጭ http://ecadforum.com/Amharic/archives/15560/

http://ecadforum.com/Amharic/archives/15559/

http://ecadforum.com/Amharic/archives/15555/

 

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ኑሩልኝ።

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>