ተክሉ አባተ
ሰሞኑን ቅስም ሰባሪ በሆነ ክስተት ውስጥ ራሳችንን አግኝተናል:: ውድ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ ዘግናኝ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተካሄደባቸው ነው:: የችግሮቹን አይነትና መጠን የኢትዮጵያውያን የመገናኛ ብዙኃን በሚገባ እየዘገቡት ነው:: በአጠቃላይ ሲታይ ግን የሳውዲዎችን ርምጃ እንደሰው ለመረዳት የሚከብድ ነው:: በዚህ ዘመንና መንግስት ባለበት አገር እንዴት የሰው ልጅ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ካገር እንዲወጣ ይታሰባል? ህግን ለመጠበቅ ወይም ለማስከበር ሲባል በምንም ዋጋ የማይገኘውን ውድ የሰው ልጅ ህይወትን ማጥፋትና ማጎሳቆል እንዴት ሚዛን ይደፋል?—– የተባበሩ ክንዶች