Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ኢትዮጵያ የአረብ ሠራተኛ አምራች ሃገር መሆኗ መቅረት አለበት

$
0
0

ከምኒልክ ሳልሳዊ

ኢትዮጵያውያን በመካከለኛው ምስራቅ በስፋት መሰደድ የጀመሩት ባለፈው 20 አመታት የወያኔው ጁንታ መንግስት ስልጣኑን ተቆጣጥሮ በህዝቦች ላይ በተለየ መልኩ የፈጠረውን አደገኛ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ መሆኑ እሙን ነው::ይህ ቀውስ የደረሰባቸው ወገኖቻችን ከተሰደዱባት ሃገር አንዷ ሳኡዲ አረቢያ ተጠቃሽ ናት::ሳኡዲ አረቢያ ከሃብቷ ብዛት የመጣ የስራ ፍቅር ባሌለው ወጣት ዜጋ የተሞላች እና ፔትሮ ዶላር ባሰከራቸው ቱጃሮች የምትተዳደር አገር መሆኗ እና የዜጎቿ የስራ አለመስራት የስራ እድሎችን ስላሰፋ የወያኔ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተጠቂዎች ወደዚሁ መሰደድን መርጠዋል:: ይህንን ተከትሎም ይህን ሰሞን የአለም ዋና አጀንዳ የሆነው የኢትዮጵያውያን በሳኡዲ አረቢያ እየደረሰባቸው ያለ ስቃይ ነው::

maid2
ሰቆቃው ያደረሰው የሰብኣዊ መብት ጥያቄ ከሳኡዲ መንግስት ላይ ይልቅ ወደ ወያኔው ጁንታ ላይ እንዲተኮር ያደረገ ሲሆን የወያኔው ጁንታ ለከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ተዳርጓል::በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው አስደንጋጭ እና ሰብኣዊነትን ያለፈ ድርጊት በመንግስት ባለስልጣናት መሃከል የፈጠረው መረበሽ እስከአለመግባባት አድርሷቸዋል::ይህንን የወያኔን አቋም የተመለከተችው ሳኡድ አረቢያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ የበላይነት ተቀናጅታለች::የወያኔ ተቃዋሚ በሆኑት እና በአገር ውስጥ በውጪ በሚኖሩት ድርጅቶች እንዲሁን በከፍተኛ ደረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ ባሉ ኢትዮጵያውያን እና እርትራውያን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ አትኩሮት አግኝቶ የአለም ጎዳናዎች ሳኡዲን እና ወያኔን በሚቃወሙ በሰላማዊ ሰልፍ እየተጥለቀለቁ ነው::

ከወያኔው መንግስት የሚንጸባረቁ አጀንዳዎች ለዘብተኛ አቋሞች በስህተት እንደተፈጠሩ ወቅታዊ ሁኔታኦች እያሳዩ ሲሆን ስርኣቱ አጣብቂኝ ውስጥ እና የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ እንደገባ ተረጋግጧል:: የሌላ ሃገር እምባሲዎች ዜጎቻቸውን በመጠበቅ ላይ ሲያተኩሩ የወያኔው ዲፕሎማቶች የዜጎች ንብረት የሆነውን ኤምባሲ በመዝጋት አገልግሎት አቁመዋል::
የደረሰውን ሰቆቃ ተከትሎ ስርኣቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመተባበር ለሉአላዊ የዜግነት ክብር መነሳሳት ሲኖርበት እና ህዝብን ማቀፍ ሲኖርበት ለብሄራዊ ውርደት ዜጎችን ዳርጓል::የፖለቲካ ፓርቲዎች የጠሩትን ሰልፍ በሃይል እና በደብዳቤ በትኗል::የወያኔው ስርኣት የህዝቡን ቁጣ ባለማንበቡ በችኮላ ያልበሰለ ሃሳብ በማራመዱ የፖለቲካ ኪሳራውን አስፍቶታል::ህገመንግስታዊ መብቶችን አለመከበሩን እና ለዜጎች አለመቆርቆርን በማሳየቱ በአለማቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል::ሚዲያዎች ከዜጎች የሳኡዲ ሰቆቃ ይልቅ የወያኔን ስርኣት ጋጥወጥነት አትኩሮት ሰተውታል::

(ፎቶ ፋይል ኢትዮጵያዊው በሪያድ ከተማ በፖሊስ ተይዞ)

(ፎቶ ፋይል ኢትዮጵያዊው በሪያድ ከተማ በፖሊስ ተይዞ)


ለዚህ ሁላ ችግር መንስኤው ስርኣቱ በልማት ሽፋን የሚከተለው የፖለቲካ እና እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ችግሮች እንደሆኑ አግጥጦ ገሃድ ከመውጣቱም በላይ የአደባባይ ሃቅ ሆኖ ለለውጥ እንትጋ የሚሉ ድምጾች በመላው ሃገሪቱ ተንጸባርቀዋል:; የወያኔ ስርኣት ህዝብን የሚያሳትፍ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ እስካልተከተለ ድረስ እና አሁን ባለው ሂደት ላይ ለውጥ እስካላደረገ ድረስ የስደት ችግሩ በስፋት እየቀጠል ይሄዳል:;ዛሬ ሳኡዲ ላይ የደረሰው ሰቆቃ ነገ በሌሎች ሃገራትም ይቀጥላል::ይህ ብሄራዊ ውርደት በታሪካችን አይተነው የማናውቅ ነው:;ኢትዮጵያውያን ከቀድሞው ጀምሮ በፖለቲካ ቢሰደዱም እንደዚህ አይነት ውርደትን አስተናግደው አያውቁም::የአሁኑ ውርደት ያለው ስርኣት ለዜጎቹ ደንታ ቢስ በመሆኑ የተወለደ ችግር ነው::በሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ተመዘገበ ከመባል ውጭ የተባለው እድገት ምንም አይነት ህዝባዊ ጠቀሜታ እንዳላሳየ በይፋ አስመስክሯል::የተማረው እና የሚሰራው ሃይል መሰደዱ ኢኮኖሚው እንደኮላሸ እንጂ እንዳደገ አያሳይም::የዚህ ሁላ መንስኤው ስርኣቱ የሚከተለው አፋኝ የፖለቲካ እና የእኮኖሚ ፖሊሲ ስለሆን ድጋሚ ሊከለስ እና ሊፈተሽ ይገባዋል::

የነቃ እና የተደራጀ አዲስ ፖሊሲ አስፈላጊ መሆኑ እሙን የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል::ስርኣቱ የሚከተለውን ፖሊሲ በአስቸኳይ ካልቀየረው የሚመጣው አደጋ ከፍተኛ ነው::በሃገሪቱ በልማት ስም እና በፖለቲካ ባላንጣነት በዜጎች ላይ የሚደርሰው ችግር የሙስና መንሰራፋት ሚዛናዊነት የጎደለው የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ የግሉን ሴክተር የማዳከም ውስጣዊ ሴራ ዘር ተኮር የሆነ ፖለቲካ እና አድሎኣዊ አሰራር የትምህርት ጥራት መውረድ እና የስራ አጡ ቁጥር እንዲስፋፋ የሚደረጉ ደባዎች ዜጎች ምንም አይነት ጥያቄ እንዳያነሱ የሚደረጉ የፖለቲካ ዱላዎች ለድህነት መፈጠር እና የስደት መስፋፋት ምክንያት ሆነዋል::የህዝብ ቁጥርን ተከትሎ የሚደረግ የእድገት ፖሊሲ አለመመጣተን የሃገሪቱ ዜጎች ተዘዋውረው እንዳይሰሩ የተደረገ የጎሳ ፖለቲካ የተማሩ ዜጎችን የስራ እድል አጥብቦታል::አለ ተብሎ የሚወራለት የኢኮኖሚ እድገት ጥቂት የስርኣቱን ካድሬዎች ተጠቃሚ ያደረገ በመሆኑ ማንኛውም ነገር በካድሬዎች ዙሪያ እና በፓርቲ ስራዎች ዙሪያ ያተኮረ በመሆኑ ዜጎች በሃገራቸው ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል::

ያለው ስርኣት ስርነቀል ለውጥ ለማምጣት ፖሊሲዎቹን እና የደረሱ የዜጎችን ችግር ከስሩ መሰረቱ መመርመር አለበት:: በፓርቲው አመራር ደረጃ ያሉ የስርኣቱ ባለስልጣናት ለስርነቀል ለውጥ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው::በግል የንግድ ተቋማት ላይ ስርኣቱ ያለው አቋም ከመጀመሪያ ለውጦች አንዱ ነው የግል የንግድ ተቋማት መዳከም ምክንያቱ የስርኣቱ መራሽ የንግድ ድርጅቶች እና አድሏዊነት የፈጠረው የኢኮኖሚ ችግር ሲሆን መፍትሄውም የተዳከመውን የግሉን የንግድ እንቅስቃሴ እንዲያንሰራራ ማድረግ እና ለዜጎች በርካታ የስራ እድሎች እንዲከፍት ማበረታታን አንዱ ሲሆን የተለየ የፖለቲካ አቋም ያለው ዲያስፖራው በሃገሩ ጉዳይ እንዲሳተፍ እድሎችን ማመቻቸት እንዲሁ ለፖሊሲ ለውጥ ጅማሮ ሊሆን ስለሚችል ስደትን በስፋት ለመቀነስ እና ዜጎች ከሃገራቸው እንዳይወጡ ለማድረግ ይችላል::

በአሁን ሰአት ስርኣቱ እየተተቀመበት ያለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባ ከመሆኑም ባሻገር ባልተማሩ እና ባልሰለጠኑ የፖለቲካ ታማኞች ስለሚተገበር በአግባቡ እየተተረጎመ ባለመሆኑ ውድቀትን አምጥቷል::የሃገሪቱ አጠቃላይ ሃብት እና የኢኮኖሚ ምሶሶ በጥቂት የፓርቲ ድርጅቶች እና ባለስልጣናት እጅ በቁጥጥር ስር ስለሆነ የግሉ ኢንቨስትመት በመዳከሙ እና ስርኣቱ ከዚህ አይነት የንግድ እንቅስቃሴ ካልወጣ በቀር ምንም አይነት ለውጥ መምጣት እንደማይቻል እሙን ሲሆን መፍትሄው የተቆጣጠረውን እና በግል መያዝ ያለባቸውን የንግድት ተቋማት እና የአገልግሎት ዘርፎች መልቀቅ ካልቻለ ችግሩ እየከፋ ዜጎችን ምንም ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ያደርጋል::በአለም አቀፍ ደረጃ እንደሚታየው መንግስታት ህግ የማውጣት እና የማስፈጸም አቅም እንጂ ከትልቅ እንስከተራ ንግድ ድረስ እጃቸውን አስገብተው ሲሰሩ አይታይም::ያለው ስርኣት ወደ ቸርቻሪ ነጋዴነት በመቀየሩ ለዜጎች የስራ እድሉን አጥብቦታል::

ኢኮኖሚውን ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች እና የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች በሞኖፖል ስለተቆጣጠሩት ዜጎች በስርኣቱ ፖለቲካ ካልተጠመቁ ድረስ ስራ የማግኘት እድል የላቸውም::ይህ ኢኮኖሚውን የመቆጣጠር የፖለቲካ ጭብርብሮሽ የኢንቨስትመት ሂደቱን ከማዳከሙም በላይ ዜጎች በሃገራቸው እና በስርኣቱ ላይ እምነት እንዲያጡ አድርጓል::ስርኣቱ ከነጋዴነት መውጣት ሰፊ የስራ እድሎች እንዲፈጠሩ እና ስደት እንዲቀንስ የሚረዳ ሲሆን ዜጎች በሃገራቸው ተሳፋ እንዳይቆርጡ ያደርጋል:: እንዲሁም የመንግስት የመገናኛ ቡዙሃን በሃሰት የተሞሉ መሆናቸው እና አስፈላጊውን መረጃ መስጠት አለመቻላቸው ሌላኛው የኢኮኖሚ ድቀት እና የስደት መንስኤ ናቸው:: በነጻነት የማይሰሩት እና ለፖለቲካው የእድሜ ማስረዘሚያ የሆኑት የመገናኛ ብዙሃን ቀረጥ የሚከፍላቸውን ህዝን እንዳያገለግሉ ከመደረጉም በላይ በሃሰት የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ወንጀሎችን በመፈብረክ የታወቁ ሆነዋል::

ሕዝቡ ስርኣቱ እስካልተመቸው ድረስ ስደትን ማቆም አይቻልም ጊዜአዊ እገዳውም ውጤታማ አይሆንም:: ሀገሪቱ ብዙ ሴቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሊሰደዱባት የቻለውም ከሴቶች እኩልነት ጋር በተያያዘም ችግር በመኖሩና ብዙ ስራ አለመሰራቱን የሚያሳይ ነው::በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶችም በነፃነት አለመቋቕውማቸው ሴቶችም እንደሰው አለመታየታቸው ነው::የፓርቲ ፖለቲካ መስበክ ሳይሆን በሴቶች እኩልነት እና ተሳትፎ ዙሪአ ኢኮኖሚው መዳበር ሲኖርበት አስፈላጊውን ኦረንቴሽንም መስጠን የስርኣቱ ግዴታ ነው::አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ስራ የሚገባውን ወጣት የሚሸከም ኢኮኖሚ አልተፈጠረ:: የግል ሴክተሩም በርካታ ዜጎች እንዳይፈጥር ሆኖ እየሞተ መሆኑን ከዓለም ባንክ ሪፖርቶች ማየት ይቻላል::በዓለም ደረጃ በመንግስት ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያ በዓለም ሦስተኛ ስትሆን፤ በግል ኢንቨስትመንት ከመጨረሻዎቹ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ነን። ስለዚህ የግል ሴክተሩ ካልተስፋፋና ካላደገ ስራ ሊፈጠር አይችልም። በየዓመቱ ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቀው ወጣት በዓመት ወደ መቶ ሺህ ሊጠጋ ነው። ይሄንን ኃይል መጦ የሚያስቀር የሚያደርግ ኢኮኖሚ መፈጠር የሚቻለው የግል ሴክተሩ ሲነቃቃ ነው። አሁን የግል ሴክተሩ በኮንስትሪክሽን ዘርፍ ላይ ውር ውር እያለ ነው። ይሄም ሴክተር ቢሆን፤ የቀን ሰራተኛ ከመሳብ ባለፈ ሙያተኛውን መቅጠር አልቻለም። ለዚያውም ትንሽ ሲሚንቶ መለሰን ሲጀምሩ ወደ መካከለኛው መስራቅ በተከበረ ወርሃዊ ደመወዝ ሲቀጠሩ ይታያል። ሀገሪቱ የተማረ የሰው ኃይል የላትም። ያሉዋትም ለባዕድ አገር እያገለገሉ ነው። በአንፃሩ የአገሪቱን የባቡር መንገድ እና ግድብ የሚሰሩት ቻይናና ሕንድ ናቸው። ስኳር ፋብሪካውንም የሚሰሩት ሕንዶች ናቸው። በሚያሳዝን መልኩ ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የተማሩም ሆነ ያልተማሩ ችሎታቸውን እየሸጡ ያሉት ለባዕድ ሀገር ነው። ከአፍሪካ እስከ ደቡብ ሱዳን፣ ቦትስዋና እና ደቡብ አፍሪካ ሳይቀር በርካታ ኢትዮጵያውያን ችሎታቸውን በጥሩ ዋጋ እየሸጡ ነው። ይሄን አሳዛኝ ታሪክ ለመቀየር የግል ሴክተሩ ማደግ ወሳኝ ነው ።

የግል ዘርፉ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ይረከብ ማለት ግድብ ይገንባ፣ የባቡር መንገድ ይዘርጋ ማለት አይደለም ነገር ግን የግል ዘርፉ ሊሰራቸው የሚችሉ ስራዎች ተለይተውና ተጠንተው መሰራት አለባቸው። የኅብረተሰብ ችግርም እየተበራከተ ስለሆነ ችግሩን መመርመር ያስፈልጋል ። የግል ዘርፉ ከካፌና ሆቴል ላይ ብቻ የሚሯሯጠው ለምንድነው? የቀጥታ የውጪ ኢንቨስትመንት ችግር በገፍ የማይመጣው ለምንድነው፣ አነስተኛና ጥቃቅን አደረጃጀት ምን ያህል ውጤት አምጥቷል? የተደራጀ ጠንካራ የግል ዘርፍ መፍጠር ነው ወይስ አነስተኛ ጥቃቅን ድርጅቶች የሚለው መታየት አለበት። የትኛው ነው ብዙ ኀሳብ የሚያመነጩት፣ የገበያ ሁኔታስ? ባንኮች አካባቢ ያለው ችግር ምንድነው? ለምን አያበድሩም ይሄ ሁሉ መፈተሽ አለበት ።ኢትዮጵያ የአረብ ሠራተኛ አምራች ሃገር መሆኗ መቅረት አለበት ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>