November 21/2013
ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ
በሳውዲ የሚገኙ ዜጐቻችን የወገን እና የሀገርን እርዳታን በሚሹበት በአሁኑ ሰአት የወገን እና የሀገር ህልውና እየተረገጠበት ባለበት ሰአት የኢህአዲግ መንግሰት ግን ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ለህዝባቸን ምንም ያክል እርዳታን አለማድረጉ በብዙዎች ዘንድ በርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት አለ ወይ እያስባለ ነው የሚገኛው :: ይህም ብቻ አይደለም በሳውዲ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን በማሰማት ላይ በሚገኙበት በአሁኑ ሰአት ሰአት በሀገር ቤት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ግን በገዛ ሀገራቸው በዜጐቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለመቃወም አልታደሉም :: በርግጥም እራሱን ትዝብት ላይ የሚጥለውን ተግባር በመፈጸም ድምጻቸውን ለማሰማት የወጡትን ዜጐች በመደብደብ በመግረፍ እና በማሰር ከሳውዲ አረቢያ መንግሥት ጐን በመቆም ዋና ተባባሪ መሆኑን አስመስክሯል አልፏል:: ይህ ሁሉ ሲሆን በራሱ በወያኔ ደገፊዎች ሳይቀር የወያኔ መንግስት እየተወገዘ እና እየተብጠለጠለ ይገኛል ምክንያቱም ነገሩ የፖለቲካ ነገር ጥያቄውም የፖለቲካ ጥያቄ እንዳልሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚገባ ጠነቅቆ ያውቀዋል እና:: በሳውድ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል በጣም ያላስቋጨው እና ያላንገበገበው ኢትዮጵያዊ የለም አንድ የወያኔ የኢህአዲግ መንግስት እንደሆነች በሚገባ የማውቃት ከሀገር ውጭ የምትኖሩር በዜጓቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ የሳዘናት እና የመንግስት ግድ የለሽነት ያናደዳት ወጣት አትንኩብኝ እያለች በፊስ ቡክገጽ ሳይቀር ስትክበው የነበረችውን መንግስት በመቃውም በፊስ ቡከ ገጾ ላይ እንዲህ አለች የኢትዮጵያ መንግስት ሆድ እንጅ ጭንቅላት የለውም :: እውነቷን ነው ይህች ወጣት እህታችን ለሆድ ሳይሆን በሚገባ ህዝቡን ለመመራት እና ለማስተዳደር የተቀመጠ መንግስት ቢሆን ኖሮ በሳውዲ በዜጐቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ ግድ ብሎት የወገን አጋርነቱን ያሳይ ነበር ይህንን ግን የወያኔ መንግስት ሊያደርገው አልቻለም::ስለዚህም ለዜጕቹ ግድ የሌለው መንግስት ለህዝብ ጥቅም የቍመ መንግስት ስለሆነ መወገድ አለበት ::አምላክ በስቃይ ውስጥ ያሉትን ወገኖች ይጠብቃቸው