Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የኢትዮጵያ የቀድሞ ዘመናዊ የጦር ሰራዊትን ታሪክ ሳንዘክር ስለ ኢትዮጵያ ማውራት አንችልም

$
0
0

የኢትዮጵያ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት መሰረቱ በዳግማዊ ምንሊክ ዘመን ይጣል እንጂ በተደራጀ መልክ የተመሰረተው ከፋሽሽት ኢጣልያ መባረር በኃላ መሆኑን በርካታ ድርሳናት ያስረዱናል።ዛሬ ቀና ብለን ስለ ኢትዮጵያ መናገር የቻልነው በጥንት አባቶቻችን ተጋድሎ ብቻ አይደለም።የቀድሞ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት ገድልም ትልቅ አስተዋፆ አለበት።ሱማልያ ”ቁርስ ድሬዳዋ ምሳ አዲስ አበባ” በሚል መፈክር በ1969 ዓም በከፈተችብን ጦርነት ከሞቃዲሾ በምታስተላልፈው የአማርኛ ራድዮ ፕሮግራም ፎክራብን ነበር።ምስራቃዊውን የሀገራችንን ክፍል ይዛ ነበር።
በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሚሊሻ ከመደበኛ ሰራዊት ጋር እልህ አስጨራሽ ውግያ አድርጎ ነፃነታችንን እና የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ያስከበረው የቀድሞ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት ነው።ኢትዮጵያውያን ብዙ ያልገቡን፣ክብር መስጠት ሲገባን ክብር ያልሰጠናቸው ክቡራን አሉን።
ክብር ለቀድሞ ዘመናዊ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት! የኢትዮጵያ የቀድሞ ዘመናዊ የ ጦር ሰራዊትን ታሪክ ሳንዘክር ስለ ኢትዮጵያ ማውራት አንችልም።

Source: ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>