በደረጀ በጋሻው ከምስራቅ አፍሪቃ
አንባገነኖች ባህሪያቸው ተመሳሳይ በመሆኑ በማምን ላይ ሲሞዳሞዱ ህሊናቸውን አይቆረቁራቸውም።
የመን የምትባል ከቀይ ባህር ማዶ ያለች የአረቦች ምድር ሰሞኑን የፈጸመችው የልወደድ ባይነት ፖለቲካዊ “ግልሙትና”ታሪክና ትውልድ በመሪር ትዝታው ሲያስታውሱት የሚኖር ወራዳ ተግባር ነው። ሀገሪቱን ድሮም አትጥመኝም። አሁን ጨርሶ ጠላኋት።
ወገኔ አንዳርጋቸው በምርጫ 97 ማግስት ከወዳጄ ያሬድ ጋር ዝዋይ ማጎርያ ካምፕ መከራ የቀመሰና ወያኔን አብጠርጥሮ የሚያውቅ ፥”ነጻነትን የማያውቅ ነጻ አውጪ”በተሰኘው ምርጥ መጸሐፉ ገዢውን ሃይል በጥልቀት እንድናውቅ የበኩሉን ድርሻ የተወጣና የአውሮፓ ዮሮም ሆነ የንግስት ኤልሳቤጥ ባውንድን በጡረታ እየተቀበለ እንደማንኛውም ዲያስፖራ ፖለቲካን የቢራ ላይ ጨዋታ ማድመቅያ ያላደረገ የነጻነት ፋኖ ነው።
ዛሬ በግፍ አንበሶች ጉድጓድ እንደተጣለው ዳንኤል ከአንድዬ በቀር ምንም ሊታደገው የማይችል ምስኪን መሆኑን ስሰማ ውስጤ ይደማል። ያቺ ሐገር ሊታደጓት የሚባዝኑ ልጆቿን ለነጣቂ አውሬ የምትገብር ምድር በመሆኗ መጨረሻዋ የናፍቀኛል። የኔን ዕድሜ ሙሉ መከራ ስትዝቅና እኔንም ለ18 ዘመናት ስታዝቀኝ መኗሯ ዕድሏና ዕድሌ መጣመሩ በውስጤ እንድብሰከሰክ አድርጎኛል።
ዩጋንዳ ሸራቶን ሆቴል ሚሊኒየሙን ድል ባለ ድግስ የወያኔን ቆንስላ ሳንጨምር ያከበርንበትን ምክንያት አንድ ከካናዳ መጥቶ የነበረ ዲያስፖራ ጠይቆኝ በወቅቱ የጣልነው ዕገዳ ወያኔን “ኢትዮጲያዊ አይደልህም ማለታችን ሳይሆን አላግባብ ያሰራቸውን ጋዜጠኞች፥የሰባዊ መብት ተሟጋቾችና የቅንጅት አመራሮችን ሳይፈታና በሩን ለብሔራዊ ዕርቅ አስካልከፈተ ድረስ” ቢፈልግ የሚቀጥለውን ሚሊኒየም ያክበር ብለን አልነበረም። ዲያስፖራው ወዳጄ ቀደም ሲል እንደኔ ዲያስቁራ በነበረ ጊዜ የንበረው ሐገራዊ ወኔ ኮንዶሚኒየም ቤት ለማግኘት ከተመዘገበበት ጊዜ ወዲህ ሸርተት ያለና ተለጣፊ የሚመስል ማንነት ካነገበ ወዲህ በምናደርጋቸው የሃሳብ ልውውጦች ውስጡ መቦርቦሩን ቆሌዬ ነግሮኛል።ምንም ሆነ ምንግን እውነቱን መንገር የኔ ዐቢይ ተግባሬ ነበርና ጋትኩት።ካስመለሰውም ጉዳዩ የርሱ ይሆናል።
ዛሬም ካለንበት ብሔራዊ ቀውስ ለመው