ፈላስፋ እንዲ አለ ብዬ ፅሁፌን ልጃምር ”የማሰብ ደግነቱ ነገርን ከልብ መረዳት ነው ፤መጥፎነቱም ነገርን ከልብ አለመረዳትና አለማወቅ ነው’::የማስተዋል ቁም ነገሩ ትግስትና ዝግታ ነው።መጥፎነቱም መቸኮልና መቅበዝበዝ ነው። ይህን ከአንጋረ ፈላስፋ (ከፈላስፋዎች አባባል ከጠቀስኩ ዛሬ ብዕሬን እንዳነሳ ወደገፋፋኝ አንዳች ነገር ነጥብ በነጥብ ለመጋዋዝ ልሞክር ።
ሰሞኑን አንዳች የሚያስገርም ከመባል ያለፈ ነገር በእኛ ዘንድ ተሰማ ።መቼስ መንግስታችን ልበል ከተባለ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን(የግንቦት7 ዋና ፀሃፊ) ከየመን መንግስት ላይ በዶላር መግዛቱን እውን ሆነ። ህሊናውን እንደ መጫሚያው በሚረግጥ እና የሐገር ክብር በማይሰማው ብሎም ነገን ባላገናዘበ ሁኔታ አሳልፎ ሰጣቸው ።ግድ የለም ነገ እሩቅ አደለም ።እናት ሐገር ኢትዮጲያ የትላንት ትውልድ ካላት ብድሩ ብዙ ግዜ አይወስድም።ይሁንና አሁን የገዛ ሐገሩን በሽፍትነት ስለሚያስተዳድረው የኢትዮጲያ ቅኝ ገዢ ጥያቄ ይኑረኝና ወደ ዛው ልጓዝ። በተለምዶም ሆነ ስለጥሩ መጠቃቃም የሰው ልጅ ውሃ ሊቀዳ ወደ ውሃው ይሄዳል ። ቢህ ምክንያት የሰው ልጅ በውሃው ተጠቃሚ ሆኖ(ለፈለገው ተግባር እየተጠቀመበት) ይሄው አስከዛሬ አለ። በተቃራኒው ግን ውሃው እዛው የሰው ልጅ ያለበት ድረስ ከሄደ በሰውና በንብረት ላይ የሚያደርሰው አደጋ መጠኑ ሰፊ ነው ።ለዚህ አለም በሙሉ ያለነጋሪ የሚያውቀው ህገ ልቦና የተረጎመለት አንድምታ ነው ። ስለ እርእሴ ለትርጓሜ ያህል ያህል ካልኩ እስቲ ለምን ይህን እንዳልኩ ከላይ ከተንደርደርኩበት ሃሳብ ጋር ሁኜ ወደ ታችኛው ልዝለቅ።
ሰሞኑን አንዲት ወያኔዎቹና ሽፍቶቹ የምትል አጠር ያለች መድብል በማነብበት ግዜ፤ወየነ’ማለት ሐራ(ነፃ) ለማውጣት ታገለ አደመ እንደማለት ሲሆን ወያነ ማለት ደግሞ አብዮት፤ወያናይ ማለት ደግሞ አብየተኛ ማለት እንደሆነ ባስረጂ የሚናገር ፅሁፍ አጋጠመኝ። (ትርጓሜው በትግርኛ ቋንቓ) ማለት እነደሆነ(ዶ/ር ካሳ ገ/ሂይወት እና ዳንኤል ተኸሉ ረዳ ያጤኑታል) ሲል ይገልፀዋል።በዚህም ይመስላል ማለትና ድርጊት አልተገናኘም ሲል በሽፍቶቹ እየተጠቀመ አንድ 7 የሚሆኑ የሽፍትነት ስራ የጀመሩትን እያነጋገረ ይነጉዳል አልጨረስኩትም ። ስለመፃሃፉም ልገልፅ አደለምና ጅማሬዬ፤ወደ እራሴ ከመመለሴ በፊት ወያኔ የሚለው ስም እንኳን አይገልፃችሁም ከትርጓሜ አኳያ ብሎ ሽፍቶችን ስለወሰደ አሱን ተጋርቼው ወደ ጉዞዬ ልቀጥል።
ኢትዮጲያ ደርግን የ መሰለ በቁም ሰው የሚበላ መንግስት እጅግ ውድና በአለም ዘንድ ታላቅ ነገር በመስራት ሐገራቸውንና አለምን ሊያገለግሉ የሚችሉ ልጆቿን ባደባባይ እያረደ ጥሎ እርሱ ግን በመሰሪያ ተከልሎ 17 አመት ከከረመ በሗላ ዳግም ላይመለስ ሊያሸንፋቸው በሚችለው ግን ባለሸነፋቸው ሽፍቶቶች ተከቦ ኢትዮጲያን ዳግም ለሚበላት አዲስ አውሬ አስረክቦ ከሔደ ይሄው 23 አመት ዘለቀ።በዚህ በ23 አመት የፍዳ ዘመናት ውስጥ ከነበረችበት ሳትራመድ ይሁን አልያም ከፍና ዝቅ እያለች ዛሬ በ አለም 2ኛ ደሃ ሐገር ሆና እነ ኤርትራና ሱማሌ ብሎም ጅቡቲ ብቻ በጦርነት የሚታመሱትም ይሁን በሰላም ያሉት ሳይቀድሟት ተስልፋ ይሄው አለች ።
በዚህ ሁነት እና መተላለፍ ውስጥ 23 አመት መቆየት ፤ብሎም መከፋፈልና አንድ መሆን መግደልና መሞት ውስጥ የማስተዋል እጁን ሳይነኩ መቆየታቸው ትላንት ከወደቁት ከመማር ይልቅ ወዳቂዎች ከተንጠለጠሉ በሗላ ያደርጉ የነበሩትን እኩይ ተግባር በመፈፀም የትንፋሽ የበላይነትን ለማግኘት በመሯሯጥ አለቃ እኛ ነን ሲሉ ላስተዋለ” ”የማሰብ ደግነቱ ነገርን ከልብ መረዳት ነበር ” ሲል የሚመጥናቸውን ባይሆን እንኳ ለተናጋሪው የሚስማማውን በማለት ጉዳዩን ያስረዳል።
አሮጌ አመለካከትና የበላይነት ስሜት ለማንም ቢሆን የማስተዋል ነፃነትን ስለሚገፍ በመግደል፤በመግረፍ ፤በማሰር እና በመሳሰሉት እራሱን ለመግለፅ በሞመከር ማንነት ከምንግዜውም በላይ ያወርዳል ብሎም ለነገ የሚፈራው እና የሚሰጋው ነገር እንዳለ የዛሬ ቅዠቱ ያሳያል።
እስቲ እንጋገር አቶ አንዳርጋቸው(ግ7.ዋ.ፀ) በእናንተ እጅ ሲታሰሩ ሲያዙ ሲገደሉም ሆነ ሲገረፉ የመጀመሪያው አደሉም ።በዚህ ማንም አይደነቅም። ይእልቅስ የሚደንቀው አንድን ውሃ የያዘ እንስራ ካፉ ላይ ስለተሸረፈ ውሃ ይፈሳል ወይም ይጎላል ብላችሁ ስለምታስቡት ስለ እናተ መደነቅ ግድ ይላል። እንበል፤ አንዳች ነገር ግን አዲስ ያልሆነ ይኖራል በማለት መለስ ብላችሁ አስቡ።ከእናንተ ጋር ለትግል የወጡ ስንቶች ነበሩ ፤ ስንቶቹስ ተገደሉባችሁ ?ድርጅታችሁን ከመሰረቱት ጀምሮ ለዚ እስካበቁት? (ማውሳት የፈለኩት የትግሉ ሂደት በምን ሁኔታ ላይ እንደደረሰ ስለማላውቀው ግንቦት 7 አደለም)፤ በአግባቡ ማስተዳደር ሲያቅታችሁ ለድክመታችሁ ሽፋን የሚሆን ረጅም መንገድ ስለምትጓዙት ስለ እናንተ ነው።
ታዲያ የቀደሙት ሁሉ የትግል ጓዶቻችሁ ከእናንተ መለየት ሳያቋርጣችሁ ትግላችሁን ፈፅማችሁ እዚ ከደረሳችሁ ስለምን አንድ አንዳርጋቸውን ማሰርና መግደል ትግሉን እንደሚያቐርጠው አመናችሁ? እነሆኝ ማስተዋል ማጣታችሁ መቸኮልና መቅበዝበዛችሁ አለም በግርድፉ ሲያመችሁ ነበር አሁን ግን እያለጠ ማንነታችሁን እንዲያውቅ እድል ሰጣችሁት ።ይሄ ከሰው አደለም ከእግዚያብሔር ነው።አዳርጋቸው ያለው እኮ ትላንት ከትላንት ወዲያ እናንተ ተናግራችሁ ጫካ የገባችሁበትን ቃል ነው።ታዲያ ምኑ ላይ ጥፋቱ? ፍትህ እኩልነት የዲሞክራሲ የበላይነት ስለማይታየኝ ከእናንተ ጋር አልሰራም አለ፤ ወደ የሚመቸውና የተመኘውን ፍትህና እኩልነት አመጣበታለሁ ወዳለው መስመር ተጓዘ።በእናንተ ሲሆን ደግ ነገር ነበር ። ዛሬ ደግሞ አፈሙዙ ወደ እናንተ ሲዞር አንድን ታጋይ በመያዝ የተሻለ ነገር እንደሰራቸሁ ስትናገሩ አልዘገነናችሁም።ለአብነት ያህል አቶ ስብሐት ነጋ ከላይ ከጠቀስኩት መፅሃፍ አዘጋጅ ጋር ባንድ ወቅት ያወጉትን ላስነብባችሁ።
ጠያቂ፤-…….. መሰረታዊ ልዩነት እንዳለችሁ እያወቃችሁ ነው ለንግግር የጋበዛችኃቸው?
ስብሃት ነጋ፤-…………..”እንደኛ ሁኑ አንልም።እንደኛ አልሆንክም ብለን የመታንም አንድም ድርጅት የለም…….” እያሉ በትግሉ ግዜ ከሌሎች ተወጊ ድርጅቶች ጋር ያሰለፉትን የትግል ታሪክ ሲመላለሱ ይነበባል።እሺ ይህ ከነበረ ሐሳባችሁ ዛሬስ አንዳርጋቸውን ለመያዝ ከሌላ ሐገር በእርጥባን የተገኘውን ብር ተጠቅማችሁ ስትወጡና ስትወርዱ መታየታችሁ ከማለታችሁ ጋር አይጋጭም ወይ?በቃ እንደ እናንተ አንሆንም ነው ያለው።እንደ እናንተ አልሆንም ያለሆነውን ካልመታችሁ፡ ባኢስር ላይ ያሉት ትልልቆቹና ትንንሾች ወንዶችና ሴቶች ፤ምን በሰሩ በያስርቤት ታጎሩ? አቦይ ስብሃት?ይህ ብዙ ብርቅ አደለም በእናንተ ዘንድ ። “የማስተዋል ቁም ነገሩ ትግስትና ዝግታ ነው።መጥፎነቱም መቸኮልና መቅበዝበዝ ነው”ይህ አባባል በትንሹ ይገልፃችኃልና።ግና በውኑ አንዳርጋቸውን ስትይዙ በውጭ ስለሚኖሩት ልጆቻችሁና አንባሰደሮቻችሁ ብቻ ስለሁሉም ፤ብሎም ለዲፕሎማሲ ስራ ስለመመላለሳችሁ አስባችኋል? እሱ የሚወክለው ድርጅት የቱንም ያህል መስዋትነት ከፍሎ ተመጣጣኝ ከሚባል በላይ ሊያደርስባችሁ እንደማይችል ስለምን አላወቃችሁም?እሰቲ ቆም ብላችሁ አስቡ።ሲጀመር ወደ ውሃው ትመጡ ወይስ ውሃው ወደ እናንተ ይምጣ ? ብያችሁ ነበር ።ይህ ጥያቄ በዱርና በከተማ በሰላምና በጦርነት የሚታገሉትን ይወክላል። ሕዝቡ ወደ እናንተ ጥያቄና ሓሳብ ከሚመጣ እናንተ ወደ ህዝቡ ሐሳብ ብትሔዱ ለመኖር ባትችሉ እንኳን ለማኗኗር አድሉ ይገጥማችሁ ነበር።በሐገር ውስጥ በሰላም የሚንቀሳቀሰውን ፓርቲ ሁሉ ወነጀላችሁ።ወጣት የተባለ አግዛችሁ አሰራችሁ፤ ገረፋችሁ፤ ገደላችሁ።ግን ትግሉን ማስቆም ግን አልቻላችሁም።ለዚህ ነው ውሃው ወደ እናንተ ከሚመጣ እናተ ወደ ውሃው ሒዱ የምንላችሁ።ይህ ማለት በሰላም ታጥባችሁ በሰላም ጠትታችሁ በሰላም ለመኖር የሚያበቃችሁን ንፁህ አየር እንድትነፍሱ ያደርጋችኋል።ነገር ግን በተቃራኒው ውሃው ወደ እናንተ ከመጣ ፤ከዚህ በፊት እና በቅርብ በውሃ መጥለቅለቅ ምክንያት ብዙ ሕዝባቸውን ብሎም ንብረታቸውን ያጡት ለማግኘት አንዳርጋቸውን የፈለጋችሁበትን ያህል ግዜና እሱን ልትገዙበት ያወጣችሀትን ያህል ገንዘብ ሳታወጡ ታገኛለችሁ።ባጋጣሚ ጋዳፊን (ሊቢያ)ሳዳም ሁሴን(ኢራቅ) ወዘተን እያሰባችሁ ቆዩ።ውሃው ወደ እነሱ እንዳይመጣ በኬሚካል መርዝ ሳይቀር የተጠቀሙ ነበር ግን …….ጫጩት ፊት ፈንግል አይወራም።በርግጥ አስተዳደር ያለማወቅ በራስ መተማን እዳይኖር ከሚያመጣው ጭንቀት በበመነጨ ይህ እንደሚሆን ለማንም ግልፅ ነው ።ግን እኮ አቃተን በቃን ብሎ በሰላም ማስረከቡ በክብር በላይ ክብር እንጂ ውርደት አይሆንም። ጋዳፊም ይሁን ሳዳም ወይም ሁስኒ ሙባረክ ሌሎችም ዛሬ እናንተ የምትመርበትን አብዮት ገንዘብ ስለማድረጋቸው የመጣ የመጨረሻ ጣጣ ነው ።ከሌላው አለም ገንዘብ ብቻ መሰብሰብ ሳይሆን በመምራትና በመመራት ሂደት ውስጥ ላለው ቁም ነገር የሚረዳውን እውቀት መሰብሰብም ብልህነት ነው ።ሰውንም ከመግደል እራስም ከመሞት ያድናልና።
ስለ ሐገር በጥቂቱ ፤-በዚህ ግንዘቤ ውስጥ ለህዝባችሁ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ግራ በሚያጋበ ሁኔታ እየሰራችሁ እንደሆነ ለእናንተ ግልጸፅ ባይሆንም አለምና የኢትዮጲያ ህዝብ ይገነዘባችኋል።እናንተን እንደማይመለከት ለመግለፅ የወደድኩት ፤ያወጣችሁትን የፀረ ሽብር ሕግ አለም እየተቸበትና እየተቀለደበት እንደሆነ ብሎም በሰባአዊ መብት ተከራካሪዎች ዘንድ የአውሬነት መደብ ተሰጥቶአችሁ ስትገለፁ መቼስ አንዳርጋቸውን በያዘችሁበት(በተለይ)ሰሞን ሚዲያዎችን ተከታትላችሁ ከሆነ የደረሳችሁበትን ደረጃ ያስረግጣል።ታዲያ በዚህ ሁነት ማንን እየመራችሁ ነው?የኢትዮጲያ ህዝብስ ስንት ሚሊዮን ነው?በስልጣን ለመቆየት ትውልድን ማጥፋትን ጨምሮ ሐገርን ቆርሶ አስከመቸብቸብ ድረስ ሁሉንም አደረጋችሁ።ከላይ በተገለፀው መሰረት ሽፍትነትም ላይገልፃችሁ እየተሰናበተ ነው ።አሺ ማን ይሁን ስማችሁ?የኢትዮጲያ መንግስት? ቅኝ ገዢ?ወንበዴ ቡድን? እንደው ማን ?አስቲ ለአፍታ ያህል ተወያዩ።እናንተ ብታረጁም ቢበቃችሁም ገና ያልበቃቸው ልጆቻችሁ አሉ?የትም ይሁኑ የትም የሚኖሩት ማርስ ላይ አደለም ምድር ላይ ነው።ስለዚህ ግፍ ለእነሱ አታቆዩ።በተረፈው ከመለስ ዜናዊ በፊትና በኋላ ብዙ ከእናንተ በህይወትና በሞት የተለዩአችሁ አሉ። ያ ሆኖ እናንተ ማድረግ የምትፈልጉትን እንዳላ አገዳችሁ ሁሉ፤ አንዳርጋቸውንና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎችን በማሰርና በመግደል ነገ የተሻለ እንደሚሆን የምታስቡ ከሆነ ከትላንትና ጀምሮ የተኛችሁ ደካሞች ናችሁ።
ቸር እንሰንብት