Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ገደል (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ 24.07.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ይድረስ ለአቶ አለማዬሁ አንበሴ ካሉበት።

እርእሱን የፈቀዳችሁት እናንተ ስለሆናችሁ እኔ ተጠያቄ አይደለሁም። ከርቤም ዝቅንቅም ይሁንላችሁ ብያለሁ የሰማዕቱ የዬኔ ሰው ገብሬ ሥጋ ጪስ …. ወይ ጠቅጥቁት ወይ ወደ ውስጣችሁ ይመልስላችሁ። ታሪክን ጥላሸት ማቅ አታልብሱት!

Gedel

ሰዉ ታሟል ወይ አዚም ተደርጎበታል – አላውቅም። ታዲያ ምን ልበል እንዲህ አራባና ቆቦ የሚያስረግጠው የጤናው ነውን? ወይስ ይህ አካል የሚባላው ነገር ሁሉ በወያኔ ተዘርፏልን? አሁን አሁንማ በጣም ጥርጣሬ የሚያስገቡኝ ብዙ ዕድምታዎች እዬተበራከቱ ነው። እኔ ነኝ ከእኔ ወዲያ ለነፃነት የሚለው የመጸሐፍ ቅዱስ ታሪክ የጦርነት ታሪክ መሆኑን ዘንግቶ „በጸሎት ብቻ ወያኔ ይወገዳል“ እያለ ትጥቅ ሲያስፈታ ታዩታላችሁ …. በሌላ በኩል ደግሞ ቢያንስ ልጆችን እናገናኝ አዋቂዎች በፖለቲካ ቢለያዩም ተብሎ መርህ የጣሰ በሳቢዮዎች ላይ አሸሼ ገዳሜ የሚል ብክነት ታያላችሁ፤ የዬኔ ሰው የገላው ጥብስ ሽታ ጠረን መንፈስ ውስጥ ተቀምጦ ሊነስት ሲጋባ እራስን በማሰናዳት በዕንባ ጥሪ ታድሞ ምን ተባላ ወይንም ኢሳት ምን አለ ከማለት እራስን ማሸነፍ ተስኖን – ሻታ!

ያቺ አንስት ባላቤትሽ መሳሪያ ደብቋል ተብላ ተወልዳ ባደገችበት – በኖረቸውበት ነፍሰጡሯ የባላቤቷን የመለያነት አካል በጥርሷ እንድትጎት መደረጓ እንደ ሰው እህል ቀምሶ ለማደር የሚያነገፈግፍ ግፍ መፈጸሙ የሰርግ ድንኳን ሆኖልን ይሆን? ያ ዓለም ሳያውቅ የመኖር መብቱን ተነፍጎ በግፈኞች ጽንሱ ህልፈት የተፈረደበት ደምና ሥጋ ተፈጥሯዊ  ዕንባም እንደ የምቾት ሽርሽር እያጣጣምነው ይሆን?  የጀግና የወ/አልጋነሽ ገብሩ ልጆች ወላጅ አልባ ሆነው ጎዳና ላይ መውጣታቸው ለእኛ ሞቅ ያለ 50 ክንድ ጋቢያችን ሆኖ ይሆን? የምወዳት ወይኔ ተቀጥቅጣ ጭንቅላቷ ተፍንክታ ስትሰፋ ካለመደንዘዣ ነበር ይህም ለእኛ ገነታችን ሆነን? በጡት ህመም በሽታ የምትሰቃዬው የርዕዮት የዬሰከንዱ ህመም ሞዝቦልድ አልጋችን ሆነልን? የውብሸት የኩላሊት ህመም ንጹህ አዬራችን ሆነን? የጀግናው አቶ አንዳርጋቸው ሁለተኛ ዬETV ጀርባ ያለው ያ መራር ያ ጥቁር ያ ሃሞት ያ ጎምዛዛ ያዳመጥነው የጣር ኡኡታ የወገኖቻችን የቀራኒዮ ድምጽ ሐሴታችን ሆኖ ይሆን እንዲህ የምናላግጠው? እንዲህ ዝምንምን የምንለው? እንዲህ ቅብጥብጥ የሚያደርገን? አላውቅም ብቻ … እም!

ለመሆኑ እንዴት አሉ አቶ አንበሴ ካሉበት። ጫታ ሰፍኗል በሃገሩን? ጫታ ነዎትን? እጅ ነሳን ለእርሰዎ – ለአካለዎት ብቻ። ለመንፈስዎ ግን አይደለም። ምክንያቱም መንፈሰዎት የገማ እንቁላልን ተዛመደኝ እያለ ጉዞ መጀመሩን ከጹሁፎዎት መንፈስ ስለ ተረዳን እኔና ብዕሬ – ያው ለነገርኩወት ለነገ አፈር ገላ ብቻ ለጥ ብለን መስገዱን መረጠን።

በአንድ ወቅትም እንዲህ ዓይነት ጠቃራ ነገር ነበር። ወራቱን አላስተውሰውም ብቻ ተዛነፍ መርዝን ያነገበ ጹሑፍ እርእሱን ብቻ አይቼ ለማንበብ አቅም አነሰኝ። እውነት ለመናገር ጤነኛው መንፈሴ አብዝቶ ተጸዬፈው። ከሩቁ ጠረኑ አይስቀርብም ነበር ይሸታል።  ለጎንደር ዘመን ዘለቅ የማንነት ንዑድ ብቃት ጥያቄ ይህ ዲዲት በቀል ጥንዙል አስተሳሰብ የማይምጥነው ስለነበረ። ዛሬም ገባ ብዬ ዘልቄ አላነበብኩትም። የማንበብ ግዴታም የለብኝም። ታሪክን አጋድሞ ያረደው እርእሱና መግቢያው በቂ ነበር።

እንዴት ነው „የቅማንትን“ ዓርማ ጋሼ ነጋ ፈርማሴው ላይ አላንጠለጠለ ሆኖ ይሆን ታላቁን የማንነት ዓርማ ከዚህ ከሚያቁስል የማንነት ክብር ገዳይ ፍላጎት ጋር ወስዳችሁ የቀረቀራችሁት? እናንተ አልማችሁ ለተነሳችሁበት የወያኔ የባንዳነት ፈል ሰንድቅዓላማችን አራንጓዴ ቢጫ ቀዩ ፈጽሞ አይመጥንም። በቃ እኮ ተሽንፋችኋል። በዜግነታችሁ ሳይሆን ሳንባችሁ የሚተነፍሰው በጎጥ መሽረፊት ነው – እፍረት! አፈርኩላችሁ!

ኢትዮጵያን ያህል ታላቅ ሐገር ያለው አንድ ህዝብ፤ ኢትዮጵያን ያህል ገናና ታሪክ ያለው ታላቅ ህዝብ፤ ኢትዮጵያን ያህል በወርቅ የተባ ትውፊት ያለው አንድ ታላቅ ህዝብ፤ ኢትዮጵያን ያህል ባላብዙ ህብረ ቀለም ባህል ያለው አንድ ታላቅ ህዝብ እያለ ከዚህ ማዕቀፍ ወጥቶ ጣሊያኖች፣ ቱርኮች፣ ፖርቹጊዞች፤ እንግሊዞች ባጠቃላይም የምዕራቡ ዓለም በሚፈልገው የውድቀት ረግረግ ውስጥ ገብቶ መዛገጥ ሳልፈጠር ከእናቴ ማህጸን ውሃ ሆኜ ቀርቼ በሆነ ያስብላል።

አሁን ቢዘህ ዘመን ያቺ ኩርማን የምታክለው – ከምክትል ወረዳ ያነሰቸው ጎንደር ዳር ድንበሯ ተጥሶ ለሱዳን ተሰጥቶ፤ በታላቋ ትግራይ ቅዠት እሰኪበቃው ወያኔ አንጡራ ሃብቷን ዘርፎ ትግራይ ለናሙና የተግባር የእድገት ት/ቤት ሆና በልማት አደገች ተብሎ የምንሰማው ዲስኩር ከዬት የተገኘ ይመስላችኋል? ከሰሊጥ – ከጥጥ ምርት ውጤት መሆኑን እያወቃችሁ፤ በመተማ በኩልም ተጎርዶ ለቤንሻጉል ተሰጥቶ በዘነዘናዋ ሆና በምታነባ ባዕት ይህም ተቀንቶባት ዛሬ እናንተ ደግሞ ሊቆረቁራችሁ – ሊያርመጠምጣችሁ – ሊያንገበግባችሁ – ሊያቃጥላችሁ የሚገባውን መሰረታዊ የሀገር ዳር  የሉዕላዊነት ድፍረት፣ የትውልድ ክስምት መሆን ሲገባው ሌላ ትውልድ ከቶውንም ይቅር የማይለው ነቀርሳ ለመትክል ከፍና ዝቅ ትላላችሁ። እፍረት!

አቬቶ ነጋ ፈርማሲ ለዚህ መርዝ ቡቃያ እኔ ነኝ ብሎ በግንባር መሰለፉ ያቺ ደግና ሩህሩህ ባለቤቱ አበጠርዬ ምን ልትል እንደምትችል አላወቅም። ምክንያቱ „ኢንተርናስዮናል የሰውዘር ይሆናል“ ብላ ከእኔ ጋር ዘምራለችና፤ እንዲህ ከዛቀጠ -ከሚያረግርግ መጠራቅቅ ገብታ ትቀረቀራለች ብዬ አላስብም። ብልህ መሆኗን ስለማውቅ አሁንም ጥረቷን ቀጥላ አቬቶ ነጋን ብታድነው እመርጣለሁ። ስለምን እኔ በግሌ ከባንዳነት ለይቼ አላዬውምና። እስከ መጨረሻውም ፊት ለፊት ወጥቼ እጋፈጠዋለሁ። እንዲህ በቀደምት አርበኞቻችን ታሪክ ላይ ተቀለዶ መኖር ሆነ ተከብሮ መኖር አይታሰብም።

የኢትዮጵያዊነት ፍረሰት የኢትዮጵያ ንደት፤ የትውልዱ ጥፋት መሰረቱ የወያኔ የጎሳ ማንፌስቶ ነውና። ይህን የሚደግፍ ይህን የሚያንቆለባብስ ሁሉ ለእኔ ባንዳ ነው። ወያኔ የሠራው የፈጠረው መርዝ እኮ ጊዜውን እዬጠበቀ እያዬነው ነው። የቀረ ምን ተቋም አለና? የፈራው አንድነታችን – ጥንካሬያችን  - ጉልበታችን ነው። የጥንካሬያችን የጉልበታችን የሃይላችን መሠረቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። ከዚህ ማዕቀፍ እስከአለን ድረስ ሁሉም አለን። ከዚህ ማዕቀፍ በትንሹ ፈቅ ስንል ደግሞ በራሳችን በውስጣችን ንደትን እናውጃለን። እንዲያውም ለወያኔ የኢትዮጵያዊነት አፍራሽ ዘመቻው እንደእናንተ ያሉ አጋፋሪዎች ናቸው የመጀመሪያ ረድፍ ተጠያቄዎች። ተግባባን? እሱ ብቻ አይደለም እጅግ በጣም ታሪክ ዘለቀ ትውፊት በሞዶሻ እዬከተከታችሁት ነው።

ጎንደር ሲፍረስ ጎጃም፤ ጎጃም ሲፍረስ ሽዋ፤ ሽዋ ሲፈርስ ወለጋ፤ ወለጋ ሲፈርስ ሐረር ወዘተ ነው …. የፍርስት ድምሩ ደግሞ እራስን ማጣት ነው። ካለአፈር ካለመኩሪያ ካላ መመኪያ። ካለ እናት … በረንዳ አዳሪነት።

እንዲህ የጫካ አራዊት በመንፈሳችሁ ላይ ሲጋልብ ፈቅዳችሁ ማስጋለባችሁ መንፈሳችሁ ከዬት ሊመደብ እንደሚችል ልባችሁን ለአራዊቱ አካልሸለማችሁት „ልብ ያለው ሸብን“ አዋህዱት።

እኛ ኢትዮጵውያን የወያኔ ማናቸውም ህጉ – ፖሊሲው – መርሁ – ፍላጎቱ – ህልሙን – ንክኪውን ሁሉ  በጣም ነው የምንጸዬፈው። የትግራይ ወያኔ ሃርነት ስርክራኪ ይቀርበናል ካላችሁ ቀጥሉበት። የቀደሙትን አያት ቅድማያታችሁን አጥንት በብረት ጫማ ቀጥቅጡት፤ ልጅ ያወጣላችሁ ከሆነ። ትውልድ ይተካላችሁ ከሆነ። ሀገር ቃሬዛ ላይ ሆና እናንተ „በ2007 የቅማንት ብሄረሰብ እራሱን ያስተዳድራል ብለን እናምናለን“  ትሉናላችሁ። ያሳፍራል። መጀመሪያ ሀገር ይኑራችሁ። ሀገራችሁ ተዋርዳ ሞቷን የምትጠብቅ፤ ሰኔልና ቹቻ የተዘጋጀላት፤ ክብርና ኩራቷ የተገፈፈ እርቃኗን ያለች ሀገር ናት። የመን ሀገር ሆና ነው የደፈረቻት። ሳዊዲ ሀገር ሆኖ የልጆቿን ደም አስፓልት ላይ አፍሶ የረገጠው። ሰንደቋን የተፋበት፤ ይህ  ለእናንት የሽርሽርሽር ጉዞ ሊሆን ይችላል።  ለእኔ ግን ደም የማምጥበት ዘመኔ ነው። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/32804

 

ለመሆኑ እንዴትና እንዴት አድርጋችሁ ነው ልታካልሉት የምትችሉት። ወገራ መግቢያ ጫፍ ላይ ያለውን ኮሶዬን፤ ጎንደር ድንበር ያለውን ወለቃን በምንና በምን ስሌት ነው ጭልጋ ካላው ጋር አካላችሁ ልትመሠርቱ ያሳባችሁት። ዕብን ናችሁ ልብል ከቶ? ተኝታችሁ ነው የምትሄዱትን? እንኳንም አለፉ እነዛ በዘመናቸው ተከብረው – ተወደው – ተጋብተው – አበልጅ ተናሰተው በአንዲት ኢትዮጵያ መንፈስ የኖሩት ግንዱ – ዋርካው ክቡር ካሰኝ አለማዬሁ። እንኳንም ይህን ጉዳችሁን ይህን ገመናችሁን ይህን ጃርት ያሰናዳላችሁን ጉዞ ሳያዩ አለፉ። ለነገሩ ቅኖች ስለሆኑ እንደ እኛው ዘመን ያሻከረው ልቦና ስላልነበራቸው ዕትብታቸው ከተቀበረው ማህበረሰብ ጋር ተመራርቀው ነው በሥጋ የተለዩት። አሁንም ነፍሳቸውን የሚወዱት ጥዋት ማታ ከደጁ የማይለዩት መዳህኒዓለም አባቴ አርያመ – ገነት ያስገባልን! አሜን።

አቬቶ ነጋን ደግሞ የነቀዘ ዘመኑን ተሸከሞ በቁሙ እያለ ፍርዱን አምላክ ይስጠው። ቀፎውን ያስቀረው። ድንቄም ሽልማት። እናውቀዋለን እኮ —- እጅግ የተከለከለውን ዬሙያውን ሥነምግባር ጥሶ ስንት ገመና ሲከዘን። „ጅብ ከማያውቁት ሀገር ሄዶ ቆርበት አንጥፉልኝ“ ይላል።

ዛሬ አቬቶ ነጋ ባልተፈጠራችሁበት፤ ባልኖራችሁበት፤ ገደል ላይ አንጠልጥሎ ታላቁን ክብራችሁን እንድታጡ የእኩይ ሙሴ ሆኗልና የእጁን ይስጠው። ለነገሩ እራሱን ለመግለጽ እንኳን አቅም ያልነበረው ሰው ነበር፤ እኔ ሳውቀው። ልጅ ሆኜም ወጣት ሆኜም ሳውቀው አንድ የረባ ቃል ሲተንፈስ ተስምቶ አያውቅም።

እርግጥ የሰጠ ቁመና እና ልዩ ግርማ ቢኖረውም የአደባባይ ሰውነቱ ከእሱ ይልቅ ባለቤቱ ወ/ሮ አበጠሩ አንቱ ነበረች። ሥነ ምግባሩ ግን እእ! የሚጎድለው ትልቅ ነገር ነበር። አንቱ ተብሎ የኖረውም በትዳሩ ነበር። ለማንኛውም በፃፋችሁት ላይ ከታች የጻፍኩት አስተያዬት እራህቤን ሊያስታግሰው ስላልቻለ፤ ሾልካችሁ ከምትቀሩ ወደ ራሳችሁ ትመለሱ ዘንድ ለመጻፍ ተገደድኩኝ። ምን ልትሆኑ እንደሚገባችሁ ደግሞ እኔ ሳልሆን  ያልባለቀው ደማችሁ ከእናንተ ጋር መሆኑን ካረጋገጣችሁ  ጠይቁት። ይነግራችኋል። እኔን የሚመራኝ ድንግሉ ደሜ ነው – እንደራሴ እንድሆንም ልዩ ጥበቃ ዘብ የሚያቆምልኝ – እሱ ነውና።

በቃችሁን! ጎጥ ላይ ተቀርቅራችሁ በኢትዮጵያ የነፃነት አርማ በሰንደቅዓላማችን አትነገዱ! ይህ ሰንደቅ የእናንተ ሊሆን ከቶም አይችልም። ዜግነታችን ኢትዮጵያዊ – ሀገራችን ኢትዮጵያ  ለሚሉት ብቻ የተሰጠ የሰማይ ሥጦታ ነው። መጀመሪያ ሥራ ላይ ያዋሉትም እቴጌ ምንትዋብ ነበሩ። ይህን ነው እናንተ ቤንዚን አርከፍክፋችሁ እያቃጠላችሁት ያላችሁት። ይህ ሰንደቅዓላማ የክብር መለያቸው ሊሆን እንዲገባ አሁንም ተኝታችሁ እሰቡት!

እንደመሸ አይቀርም። ብቻችሁን እንደምትቀሩ ደግሞ እርግተኛ ነኝ። የጭልጋን ገበሬ አሳምሬ አውቀዋለሁ። አንድ ቀን ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ጮንጮቅ በወያኔ ጥቃት ደረሰባት ብሎ ዘገባ ሲያቀርብ ለአካባቢው ህዝብ የምትቆረቆሩ ከሆነ ስለምን ዝምታን መረጣችሁ? እዬተለጉ እንለጋለን የሚሉት ጨዋታ እራስን ለግቶ ከጫወታ ውጭ ያደርጋል። የቀደመው ቀለማሙ ማንነት ይብልጥ ውበት አላው ከዛሬው የጎጥ ባንዳ በሽተኝነት። እኔም ለጮጮንቅ ገበሬ ስል ነበር አባቴን የገበርኩት። አዎን ….. ቁስሌን ህመሜን ዛሬ ልናገረው። ዛሬም እናንተ ሽህ ካድሬ ብታሰልፉ ክልትምት ብላ ከዛች ደሳሳ ጎጆው ኑሮውና ኑራ ያደራጀቻቸው እሙሃይ በአንድ መስምር ንግግር አፈር ታስግጠው ነበር የሰነቃችሁትን ቁርሾችሁን። አለመገናኘታችን ብቻ ነው እንዲህ ሠርግና መልስ የሆነላችሁ። እያንዳንዷን አጥቢያ፤ እያንዳንዷ ዳገትና ቁልቁለት፤ እያንዳንዷ ጋራና ሸንተረር ሥርጉተ ታውቃታለች። የመጀመሪያው የገጠር ሴቶች ማህበር የተደራጀበት ጭልጋ ላይ ነበር። ለጭልጋ ህዝብ ኩራቱ – ኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ነው።

 

ወገኖቼ የጹሑፌ ታዳሚዎች አንድ የማውቀውን ታሪክ ላጫውታችሁ። ጎንደር ከቤተ መንግሥቱ ጀርባ ጡረታ ሰፍር የሚባል አለ። በውትድርና ቆይተው በጥሮታ ከሥራ ሲገለሉ ከዬትኛውም የሀገራችን ክልል የመጡ አባቶች ቤት ሰርተው ጎጆ ፈጥረው ልጆች ወልደው የሚያሳድጉበት ማህበራዊ ኑሮ ቁሞ በእግሩ የሚሄድበት ድንቅ ቦታ። በከፍተኛ አንድ በቀበሌ ሶስት ይገኛል። አንዲት ደህና ኑሮ የነበራት የቴሌ ኮምኒኬሽን ባልደረባ ወ/ሮ እልፏ ትባላላች ቢነኳት የምታድፍ የምትመስል አበባ የሆነች ሴት አንድ የአውራጎዳን ባልስልጣን ካልተሳሳትኩኝ ደጉን አቶ ካሳን አግብታ በአጥር በተከለለ ትልቅ ቢላ ጡሮታ ሰፈር ትኖር ነበር፤

ጎንደር ሰው ሲሞት ወይንም መርዶ ሲኖር ባህሉ እሰከ ሰባት ቀን ሁሉም እያዋጣ በእድር ሆነ በተደራጃ ቡድን  ነገር በሃዘንኑ አብሮ ሁሉ ይታደማል። ታዲያ እመቤቲቱ ሃዘን ሲኖር እንጀራዋንና ወጡን እያሳያዘች ለቤት ሠራተኛ ትልክ ነበር። ሁሉን እኩል የሚያደርገው አቶ ሞት ከቤቷ መጣ። ደህና ሰው የነበሩት ባለቤቷ አለፉ። በቀብሩ ሁሉ ተገኝቶ እንደ አባት አደሩ ቀበረ። ማታ ግን ሠራተኛ ያለው በሠራተኛ፤ የሌለው በልጁ፤ ልጅም የሌላው የጎረቤት ልጅ እዬለመነ እማ ወራዋ ያሰናዳችውን እንጀራውና ወጡ ብቻ እዬተላከ ድንኳኑን ብቻዋን አስታቀፏት። ማን ያስተናብረው ያ በዬቤቱ ለሰባት ቀን የሚላከውን እንጀራና ወጥ፤ ማንስ ይታደምበት? አምሮ የተሰራው ድንኳኑ እርቃኑን ውሎ ያድራል። ከዛ በኋላ እሜቴ እልፏ እዬወጣች ሃዘን ላይ መገኘቱን ማን ቀድሟት።

ይህን ያነሳሁት ያለምክንያት አይደለም ነጋ ፋርማሲ ይኖር የነበረው የዛሬን አላውቅም ጡሮታ ሰፈር ሲያልቅ ዳገቱ ላይ ነው። በላሊበላ መንገድ አፋፉ ላይ ነበር ቢላው፤ ስለዚህ የእኔ ጀግኖች ሰላምታ ንፈጉት። መላ የጎንደር ከተማ ነዋሪም ፈርማሲው አንዲት መዳህኒት አትግዙት።

ውዶቼ የጹሑፌ ታዳሚዎች ይህችን ፌስ ቡካችሁ ላይ ለጠፍ አድርጉና ቁጣችሁንና ኩርፊያችሁን አሳዩት። አበጠርዬ ማለትም ባለቤቱ ከእኛ ጋር ከሆነች አሷም አቋሟን አስተካክላ ከእናነተ ጋር ከሆነች እንደ አባት አደሩ እግሯን ተሰብራ ለረጅም ጊዜ ሆስፒታል ተኝታ በነበረች ጊዜ እናደርግ እንደነበረው አድርጉላት። ከነጋ ፈርማሲ ጋር ከሆነች እሷንም እከሉ። በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞን በተግባር መግለጽ። ከማህበራዊ ኑሮ ማግለል ነው ታሪክን ሊያድን የሚችለው መንገዱ። ከኢትዮጵያዊነት ከሉዕላዊነታችን የሚበልጥ የለምና። የጥንት የጥዋቱ የአርበኛው መንደር ጡረታ ሠፈር ይህንን ያደርገዋል። ልኩን አሳውቁት የጋሼ ነጋን እሺ – ክብረቶቼ!

በተረፈ ለድውያን ወገኖቼ ደግሞ እግዚአብሄር ይማራችሁ። ጸበል የሚያስፈልግ ከሆነም ተጠመቁ። ያችን በአንኮላ „ስላህ“ የምታስፈልግ ከሆነችም በአንኮላዋ  ጎንጨት እያደረጋችሁ መላልሳችሁ ምከሩ።  ገደሉን ስትወዱ ተድርምሶ እንዳይውጣችሁ ገደሉን ሩጡና ቅደሙት። ታታሪ መሆናችሁን፤ ብልህ መሆናችሁን፤ ሥልጡን መሆናችሁን በሚገባ አውቃለሁ ታዲያ ለገደል ከሆነ ግን ግደለት ይሆናል ወፋችሁ! ወፏን አድማጭ አይደላችሁ? ጠይቋት። ጉዟችሁ ወፍ አላወጣውም። በመላ ዓለም ተበትኖ ያለው ወገናችሁ ሁሉ ይህቺን የሃቅ ፈለፈል ካነበበ በኋላ ለባንዳ ትብብር መንፈሱን እንማይሸልም ልብ ልክ ነው። ተዛነፋችሁ ….. በጣም …. ምነው ጋድም መንገድ አሰኛችሁ //// የጤና!!!!?

 

ክውና ምን ነበር አሁን ራዲዮ ፕሮግራሜ እረፈት የበጋ ብለው ከርችመውታል። የሆነ ሆኖ የቆዩትን ገባ እያላችሁ ማደመጥ ካሰኛችሁ www.tsegaye.ethio.info or www.lora.ch.tsegaye or Radio Tsegaye በዚህ እንገኛለን። ውድድ – ክብር – ፍቅር አድርጌ ውስጤን ሸልሜ ስንብት። ቸር እንገናኝ!

 

ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረው ምስጥር ኢትዮጵያዊነት።

 

  • ስላህ በቅማንትኛ ጠላ ማለት ነው።

 

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>