“ወይን ለኑሮ” ተቀባይነት ያለው የኑሮ ዘይቤ እየተባለች የምትጠራዋ ኮሎራዶ በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚኖሩባት ከተማ ብትሆንም ቅሉ ሁሉም ግን የህወሃት ደጋፊዎች ናቸው ማለት በጣም አስቸጋሪ ነው። ለዚህ ዋቢ ማስረጃ ከትግራይ የወጡ ጠንካራ የአረና ፓርቲ የኮሎራዶ ቻፕተር ተጠቃሽ ነው። አረና በኮሎራዶ ከአንድነት ሃይሎች ጋር ብዙ ጊዜ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ይታያል።
ስለዚህ የጽሁፌ መነሻ በህወሃትና በተቃዋሚዎች መካከል መፈራረቅ የበዛባት ኮሎራዶ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ እንቅስቃሴዎችን በተቃዋሚው ጎራ እየታየባት ነው። ኮሎራዶ እንኳን ለአበሾቹ፣ ለነጮቹም በዴሞክራቶችና በሪፐብሊካን ያለች ስዊንግ ስቴት(swing state) ነች። ልዩነቱ ለሆዳቸው ባደሩ፣ ለስምና ለዝና ሲሉ ለሃገራቸው ውድቀት ሌት ተቀን በሚሰሩና ሃይሎችና፤ ለእውነተኛ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ በሚታገሉ ነው።
ኮሎራዶ የወያኔ መሪዎች በሰላም ገብተው የሚወጡባት ከተማ ነች። በኮሎራዶ ያለው የህወሃት ስልት በተቃዋሚ ጎራ ያሉትን በ 40/60 እና በሌሎች ጥቅማ ጥቅም በመደለል የገለልተኛ ካርድ በመስጠት ቢያንስ እንቅፋት ለህወሃት እንዳይሆኑ ከፍተኛ መዋእለ ነዋይ በማፍሰስ ቢያንስ (undecided voters) እንዲሆኑ ይሰራል።
ከእነዚህ ውስጥ ተጠቃሾች የእምነት ተቋማትን እርስ በርስ ማጋጨት፣ የኮሚውኒቲ ማህበራትን በየጎራው በመክፈል ለምሳሌ በብሄር የተደራጁ፣ የትግራይ ተወላጆች ኮሚውኒቲ፣ የአፍሪካ ኮሚውኒቲ ሴንተር እና ዋነኛውና ሌላው የገለልተኛ ካርድ በመምዘዝ ደግሞ የኢትዮጵያ ኮሚውኒቲ በኮሎራዶ በሚል ተቋማትን ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በዝርዝር እመለስበታለሁ።
ኮሎራዶ በርካታ ኢትዮጵያኖች የሚገኙባት ተራራማ ከተማ ስትሆን፣ ህወሃት ወያኔ የተመሰረተባት ከተማ በመባልም ትጠቀሳለች፡፡ ከተማዋም አክሱም ሲስተር ሲቲ በሚል የህወሃት ባለስልጣኖች በአክሱም ስም ፓርክ እንዲሰየምላቸውም አድርገዋል። ምንም እንኮን አክሱም የሁላችን ቢሆንም ትልቅ መዋእለ ነዋይ አፍሰዋል። እንግዲህ ይህ በሚሆንባት ከተማ የተቃዋሚ ሃይሉ በጋራ በመሆን ለኢትዮጵያ አንድነት ልዩነትን በማቻቻል እየሰራ ቢሆንም ቅሉ ገና በርካታ ስራዎችን በመስራት ኮሎራዶ እንደ ተቀረው የአሜሪካን ስቴት ወያኔዎች የሚዋረዱባት እና የሚሰቀቁባት ከተማ ለመሆን ግን ሰፊ ስራዎች ያስፈልጋሉ። ኮሚውኒቶችን ማጠናከር፣ እድሮችንና፣ ማህበራዊ ስብሰባዎችን ማደራጀት ያስፈልጋል። በቤተክርሰቲያን ያሉ ልዩነቶችን በሰከነ መፍታትም ተገቢ ነው።
በርግጥ ነው ኢትዮጵያን የገጠማት ፈተና አድረባይነትና “ወይን ለኑሮ” ተቀባይነት የሌለው የዘመኑ የኑሮ ዘይቤ ሲሆን፣ ኮሎራዶም የተቃዋሚ ሃይል ደጋፊ ነው የሚባለው ከህወሃት አባላት ይልቅ የሌላው ብሄር ተወላጅ እራሱን አናሳ በማድረግ ተላላኪነትን ወይም አዲስ አበባ ስገባ በሚል ወያኔዎች ያዘጋጁትን የገለልተኛ መታወቂያ በመውሰድ ከደሙ ንጹህ ለመምሰል ሙከራዎች ሲያደርግ ይታያል። በኮሎራዶ የህወሃት አስተባባሪ የሆኑት ወርቁ፣ ፈጸመ፣ ሰመረ፣ ወንዶሰን፣ ይሳቅ የጎንደር እና የደቡብ ልጆች ናቸው፤ ማለትም ታማኝ የህወሃት አገልጋዮች ሲሆኑ በየጊዜው በይፋ የህወሃት ስብሰባዎችን የሚያዘጋጁ ሲሆኑ እነዚህን ከበስተጀርባ ሆኖ የሚነዳቸው ግን የህወሃት አባል የትግራይ ተወላጆች ናቸው።
ይህ በንዲህ እንዳለ ነው ኮሎራዶ በተቃዋሚዎች ከፍተኛ ጥረት እና ትብብር የኮሎራዶ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ለሃገርና ለሕዝብ የቆሙ ግለሰቦችና ኢትዮጵያውያን ድርጅትና፤ ተቋማት የሚያደርጉት ያላሳለሰ የአንድነት ጥረት ይበረታታል። ይሁን እንጂ ከላይ እንደገለጽኩት በባንዳ ተላላኪ እና ለሆዳቸው ባደሩ ለማን እንደሚሰሩ በማያውቁ ሰዎች በመደገፍ ህወሃት/ወያኔ አሰልጥኖ ያሰማራቸው ቅጥረኞች ሕዝብን ሳይፈሩና ሳያፍሩ የባንዳነት ተግባራቸውን ቀጥለውበት ይገኛሉ።
ጥሩ ምሳሌ፡- በኮሚውኒቲ ደረጃ ሁለት አይነት ኮሚውኒቲ አለ። አንደኛው በግልጽ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰበአዊ መብት የሚከራከር ከ20 አመት በላይ ያስቆጠረ በኢትዮጵያኖች እጅ ተይዞ የሚገኝ ሁሌም በሀገራዊ ጉዳዮች ያገባኛል የሚል ኮሚውኒቲ በአቶ ሽፈራው የሚመራ ሲሆን፤
ሌላኛው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባለመስማማት የተፈጠረ ነገር ግን የወያኔ ሰዎች የወረሩት እና ተቃዋሚዎችም የነበሩትና ግለሰቦች በጥቅማ ጥቅምና በፍርሃት አገልጋይ የሆኑበት በአቶ መለሰ ወርቅነህ የሚመራው ኮሚውኒቲ ነው።
የሁለቱ ኮሚውኒቲ ልዩነቶችና የሚመራው አካል፡-
በእነ አቶ ሽፈራው የሚመራው፡- የኢትዮጵያ ባንዲራ አርንጎዴ ቢጫ ቀይ ነው፣ የሰበአዊ መብት ጥሰቶች ካሉ በኮሚውኒቲያችን ላይ የደረሰ በደል ስለሆነ ማውገዝ ግዴታችን መሆን አለበት፣ ከመንግስት የሚደረጉ ድጋፎችን አንቀበልም፣ ለዝና ብለን አንሰራም የሚል ነው። እነ አቶ አስቻለው ከእኛ ተገንጥለው የወጡ ናቸው ህጋዊ ኮሚውኒቲ አይደሉም የአንድ መንግስት ደጋፊ ናቸው። ኢትዮጵያውያን በአርብ ሀገራት ለደረሰባቸው እንግልትና ሞት ተጠያቂው መንግስት አይደለም፣ መንግስትን አትቃወሙብን በማለት በአደባባይ በጠሩት ሰልፍ የወያኔን ባንዲራ ይዘው ማንነታቸውን ያስመሰከሩ ናቸው ይሁን እንጂ በአማካሪ ቦርድ ስም ደግሞ ‘ተቃዋሚ” ቢኖሩም ንጹህ በሚል ሽፋን ለወያኔ ጥቃት ተጋልጠናል የሚባሉ ግለሰቦች አሉበት የሚሉ ናቸው።
በአቶ መለሰ (የህወሃት አባል እና የትግራያን ኮሚውኒቲ መስራች) ኦፊሻል ባንዲራችን በዩናይትድ ኔሽን የጸደቀው የኮኮብ ምልክት ያለበት ነው፣ (ይህ በዚህ ቡደን አማካሪ ቦርድ በሆኑት በእነ ፕ/ር ሚንጋ ተቃውሞ ውድቅ ተደርጎል) በኢትዮጵያ ሰበአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ አያገባንም እኛ ውጪ ነን ያለነው፣ መንግስት የሚያወጣቸውን እንደ 40/60 ጥቅማጥቅሞች ለህዝብ ማድረስ ይገባናል፣ ያኛው ኮሚውኒቲ በኢሃፓ እና በግንቦት 7 የሚመራ ነው፣ እነ አቶ ሽፈራው ግትሮች ናቸው፣ ኮሚውኒቲውን እየከፋፈሉብን ነው የሚሉ የክስ መላምቶች አሉበት።
ድህረ ገጽ http://ethiopiancommunityofcolorado.org/announcment
በህወሃት ይመራል የሚባለውን ኮሚውኒቲ አመራሮችና እና ጀርባ ያሉ ግለሰቦችን ዝርዝር በሚቀጥለው ጽሁፌ ይዤ እወጣለሁ።
እንግዲህ በዚህ ፍትጊያ ህወሃት የሚሰራውን የውስጥ ስራ አጠናክሮ እየሰራ ነው። ተቃዋሚውን በመክፈል ተቃዋሚ የነበሩትን ገለልተኛ በማድረግ ከትግሉ እንዲወጡ እያደረገ ነው። ለዚህ ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ በወያኔነት የማይጠረጠሩትን ግለሰቦች በመያዝ ክፍፍልን መፍጠር ሁነኛ ስራው አድርጎታል። ለዚህ ደግሞ ኮሎራዶ ምቹ ነች! የወያኔን ሞፈር መሸከም የሚችሉ ያሉባት፣ ዝና ፈላጊዎች የሚታዩባት፣ የኔ ሃሳብ ብቻ የሚል ያለባት፣ የህወሃት እህት ከተማ የሆነች ስትሆን በቀላሉ ባንዳዎችን በብልጭልጭ መፍጠር የሚቻልባት ውጣ ውረድ ያለባት ተራራማ ከተማ።
የኢሳት ኮሎራዶ ቻፕተር የዛሬ አመት ይህንኑ ኮሚውኒቲ እንዲረዳው በድበዳቤ ሲጠይቅ በእነ አቶ አስቻለው አማካኝነት ይህ የተቃዋሚ ድርጅት ሚዲያ ስለሆነ አንረዳም መተዳደሪያ ደንባችን ፓለቲካ ውስጥ እንደንገባ አይፈቅድም ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በአንጻሩ ደግሞ በእነ አቶ ሽፈራው የሚመራው ኮሚውኒቲ ለኢሳት በላከው ደብዳቤ ኢሳት የኢትዮጵያኖች CNN እንዲሆን ተመኝተው ነጻ የሚዲያ አውታር ሆኖ እንዲቀጥል መደገፍ አለበት በሚል ከገንዘብ እስከ ጊዜ መሰዋእት አደርገዋል። እዚህ ላይ ሳይጠቀሱ የማይታለፉ ጉዳይ ቢኖር የኢሳት ኮሎራዶ አስተባባሪ በወቅቱ ከፍተኛ በሆነ ሀገራዊ ሞራልና ብርታት ደከመኝ ሳይሉ ሁሉንም ወገኖች እንዲሳተፉ ያደረጉት ጥረት ይደነቃል።
በአሁኑ ሰአት ደግሞ ይሔው ኮሚውኒቲ በመከፋፈል ላይ ነው ቢባልም በእነ አቶ አስቻለው አማካኝነት ኮሚውኒቲውን ከፖለቲካ አናሰገባም፣ ይሁን እንጂ መንግስትን ግን እንደ አንድ ሀገር መንግስት በመንግስትነቱ እንቀበለዋለን። ተቃዋሚው እኮ ራሱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፎ የሰጠው ግንቦት 7 ነው። ስለዚህ እኛን ለምን ፖለቲከኛ ሁኑ ትሉናላችሁ በሚል የካድሬ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ። እንግዲህ የሚባሉትን የሚናገሩ እንጂ ከእራሳቸው ጋር ኖረው የማያውቁ ጥርቅም ጉጅሌዎች ያሉበት ቡድን መሆኑን ለማየት ይህ በቂ ነው።
ዞሮ ዞሮ ኮሎራዶ ተቃዋሚው ሲጠነክር ወደ ተቃዋሚው የምታጋድል፤ ህወሃት ሲጠነክር ደግሞ ወደ ህወሃት የምትሄድ ከተማ ነችና የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ ተኩላዎች በመጠንቀቅ ኮሚውኒቲው ለወያኔ አገልጋይና አደርባይ እንዳይሆን እነሱ በሚጠሩት ማናቸውም ስብሰባ ባለመገኘት ነዋሪው አንድነታችንን ማሳየትና መጠበቅ አለበት። በአለም አቀፍ ደረጃ የወያኔ ሰዎችን የሚተባበሩ፣ የጥቅሙ አገልጋዮች የሆኑትን ግለሰቦች፣ ድርጅቶች በየከተማችን በማውጣት ህወሃትን በተመባበራቸው የታሪክ ተጠያቂ እንደሆኑ መንገር ተገቢ ነው። በገለልተኛ ስም “ወይን ለኑሮ” ተቀባይነት የሌለው የኑሮ ዘይቤ መሆኑን በግልጽ ማሳየት ይኖርብናል። ዛሬ በወያኔ ወህኒ ቤቶች ተወርውረው የሚገኙት ሰመአታት ኮሚውኒቲው እንደሚለው ሳይሆን ለእናት ሀገራቸው ከበርሃ በርሃ ሲንከራተቱ መሰዋእት የሆኑ የቁርጥ ልጆች እንጂ፤ አእምሮ የሌላቸው ትንንሽ ሽፍን ሆዳሞች እንደሚሉት እንዳልሆነ የሚረዱበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።
ለዚህ ተምሳሌት ኦገስት 9 በኮሎራዶ እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል የተዘጋጀው ስብሰባ ማህበረሰቡ ያሳየው ድጋፍ የሚበረታታ ነው። ምናልባትም አንዳርጋቸው እሱ መሰዋእት ሆኖ ያስተሳሰረን ይመስላል።
በመጨረሻም የህወሃት አባላት የሆናችሁ በተለይም በኮሚውኒቲው ስም የምትገኙ ፡- አሁንም በኮሎራዶ የምታደርጉትን የድርጅት ድጋፍ እስከአላቆማችሁ ድረስ የምታደርጉትን እየተከታተልን ለህዝብ የምናሳወቅ መሆኑን እንገልጻለን።
ጨረስኩ
ያላችሁን አስተያየት በ loveethio777@gmail.com ይላኩልኝ