ዳኛቸው ቢያድግልኝ
‘የመለስ ትሩፋቶች ባለቤት አልባ ከተማ’ን አነበብኩት ግሩም ሥራ ነው ብዬ አድናቆቴን ቸርኩ። ቀላል አቀራረብና ብዙ የትየባ ግድፈትም የሌለው በመሆኑ ለማንበብ አይታክትም። ያነበብኩት ውስጥ ሊነሱ የሚገቡ ቁርጥራጭ ሃሳቦችን በማንሳት የሰዎችን ትኩረት መሳብና በጉዳዩ ዙርያም ተጨማሪ መረጃዎች ካሉ በሚል አንዳንድ ነገሮችን መነካካት ፈለኩኝ። ይህ የመጽሃፍ ግምገማም ቅኝትም አይደለም በዚያ ጉዳይ አንዳንድ ወገኖች የሚሉትን ብለዋል። የኔ ሳር እንደ መምዘዝ ተብሎ ይወሰድና ለዛሬ አንዷን ሳር አብረን እንምዘዝ። ኤርምያስ ገና ብትንትናቸውን እያወጣ የሚነግረን አለና ይህ ምናልባትም ሰልፍ ላስያዛቸው ድርሳኖቹ ያግዘውም ይሆናል። የበርካቶቻችን ልምድ የነበረን ስህተት ለመሸፈን ደጋግሞ መሳሳት ነውና ሰዎች ለምን ተሳሳቱ ሳይሆን ስህተታቸውን ተገንዝበው ወደ እውነቱ ጎዳና መምጣት መቻላቸውን በማድነቅ ኤርምያስን እንኳንም ወደ ህሊናህ ተመለስክ እንደ በደልህ መጠን ሳይሆን ከዚያም በላይ ሀገርህ ካንተ የምትሻው አለና በሙሉ ልብና በቆራጥነት የድርሻህን አበርክት እስካሁን ላደረከውም እያደረግህ ላለውም አክብሮት አለኝ ብለው እወዳለሁ። ይህንን የሚጋሩም በርካቶች ናቸው።
↧
በመለስ “ትሩፋቶች” ዙርያ የሕዳሴው ግድብ የማን ፕሮጀክት ነው?
↧