Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ከአቶ ገብሩ አስራት አዲስ መጽሐፍ የተገኙ 9 ነጥቦች

$
0
0

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕ/ት አይተ ገብሩ አስራት “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” የሚል አዲስ መጽሐፍ ማሳተማቸውና በዋሽንግተን ዲሲ ሴፕቴምበር 1 ቀን 2014 እንዳስመረቁ ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል። በዚህም መሥረት ከመጽሐፉ ውስጥ የተገኙ 9 ነጥቦችን ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ አስነብቦናል፤ ሙሉ መጽሐፉን እስክታነቡት ድረስ ነጥቦቹን እነሆ፦
ከመጽሐፉ የተወሰዱ
gebru asrat
1ኛ. ህወሃት በ17ቱ የትግል ዓመታቱ 54ሺ ሰዎች መሞታቸውንና ከነዚህ 90 ከመቶ የሚሆኑት የገጠር ወጣቶች ናቸው። በገጽ 165 ።
2ኛ. “የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች በሚሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ እያፈሰሱ ህዝቡ ትግላቸውን እንደገድለ ሰማዕታት እንዲቀበለው አድርገው በሥልጣን ለመቆየትና ከሞቱም በኋላ ዘለዓላማዊ ክብርና ዝና ለማግኘት መሞክሩን ተያዘውታል። ይህን የህዝብና የሰማዕታት የተጋድሎ ታሪክ ጠቅልለው ለአንድ ሰው ለማሸከም ይሞክራሉ። ሰውየው ከሰውነት አልፎ እንዲመለክ ለማድረግ ይሞክራሉ። ይህን ሁሉ የሚያደርጉትም በአሁኑና በወደፊቱ ተግባሮቻቸው ከመኖር ይልቅ ባለፈው ታሪክ መኖሩ ለሥልጣናቸው ህልውና ጠቃሚ ሆኖ ስላገኙት ነው።(ገጽ 4)
3ኛ. እጅግ የሚያናድደኝ ይህ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የዘመነ ምኒልክ የጎፌሬዎች ቀረቶና ሸለላ ነው።- ስብሀት ነጋ ገጽ 303
4ኛ. የደርግ ሠራዊት አባላት በግለሰብ ደረጃ እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በጥቅም ላይ የሚያውሉበትና አዲስ በተደራጀው ሠራዊት ውስጥ በአባልነት የሚቀጥሉበት ሁኔታ ቢመቻች ኖሮ ከፖለቲካው አንጻር ይፈለግ የነበረውን የብሔር ብሄረሰብ ስብጥር ከማሟላትም ሌላ የረጅም ጊዜ ልምዳቸውንና እውቀታቸውን አገራዊ ሠራዊት ለመገንባት ባዋሉት ነበር።222
5ኛ. አሁን ሳጤነው በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እምነታችን ምክንያት የመረጃ ፍሰትን ገድበን የአገራችንን የአስተሳሰብ እድገት በመጎተታችንና በማጫጨታችን እጸጸታለሁ። ገጽ 249
6ኛ .. ኢህ አዴግ ተቃዋሚዎችን ለመድፈቅና ለማጥፋት ከሚጠቀምባቸው ስልቶች የአመራር አባላቱንና ከፍተኛ ኃላፊዎችን መቆጣጠር። በጥቅም መግዛትና መደለለል ነው። በክፍያ መዝገብ ስማቸው የሠፈረ አሁን ድረስ ተቃዋሚዎች ነን እያሉ የሚንቀሳቀሱ የማውቃቸው አሉ። የነዚህ ሰዎች ተቀጣሪነት ያወቅኹት በኢሕአዴግ አመራር አባልነቴ ሳይሆን ቅርበት ከነበረኝ የደሐኀንነት አባላት ነውና አሁንም የነዚህን የማውቃቸውን ሰዎች ስም ላለመጥቀስ መርጫለሁ። 251
7ኛ. ኢሕአዴግ አማራው ክልል ውስጥ ሲንቀሳቀስ ጠባቦች መጥተው ሊውጡህ ስለሆነ ከ እነርሱ የሚያድንህ ከኢህ አዴግ ጎን ተሰለፍ ብሎ ይቀሰቅሳል። በኦሮሚያ በትግራይና በሌሎች ክልሎች ደግሞ ትምክህተኞች ዳግም አንሰራርተው ሊውጡህ ነው ኢሕ አዴግን ካልተቀበልክና ካልደገፍክ መቀመቅ ትገባለህ እያለ በማስፈራራት ይቀሰቅሳል። ገጽ 199
8ኛ. የሓየሎም ሞት ገዳዩ ኤርትራዊ መሆኑን እያወሱ ከኤርትራ ከነበረው አለመግባባት ጋር ያያዙታል። ይህ ፍጹም ሊሆን አይችልም ብሎ ለማለትም ያዳግታል። 265
9ኛ. (ስለተባረሩ ኤርትራውያን) ጉቦ እየተሰጣቸው መባረር ያለባቸውን እያስቀሩና መባረር የሌለባቸውን ያባርሩ እንደነበር የሚባረሩት ንብረታቸውን ሲሸጡ ተደራጅተው ንብረቱን በርካሽ ይገዙ እንደነበር ኋላ ላይ ተጋልጧል።…እኛን ፀረ- ኤርትራውያንና ፀረ- ዴሞክራሲያዊ ናቸው እያሉ ሲከሱን የነበሩ ቱባ ባለሥልጣኖች ሳይቀሩ ኤርትራውያን ሲባረሩ ቪላዎቻቸውንና የንግድ ድርጅቶቻቸውን ገዝተው እንደነበር ተራው ዜጋ ሳይቀር ያውቀዋል። ሆኖም የህወሃት/ኢህአዴግ አመራር በአንዱ ወይም በሌላው ከኤርትራውያን ጋር በተያያዘ ወንጀል ተዘፍቀው ስለነበር “በመስተዋት በተሠራ ቤት የሚኖር ሰው በድንጋይ አይጫወትም” እንዲሉ ምንም ማድረግ አልቻሉም። 281

ምንጭ፡ ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles