አሁን እጅግ በላቀ የዕድገት ደረጃ ሆኖው የሚናያቸው የአለም አገራት መሰረታቸው እውቀት ነው::ያለ እውቀት ፈጠራና ምርምር÷ጥበብና ክህሎት÷ዕድገትና ልማት ሊኖሩ አይችሉም::
ትምህርት የእውቀት ቤት ነው:: እውቀት ካለ ደግሞ ምክንያትነት አለ:: ምክንያትነት ካለ ደግሞ ምርምርና ጥናት አለ::ምርምር ካለ ደግሞ መጠየቅ አለ:: መጠየቅ ካለ ደግሞ መከራከርና መወያየት አለ:: መከራከር ካለ ደግሞ የለውጥ መንገድ አለ:: የለውጥ መንገድ ካለ ደግሞ ዕድገት አለ!!!!
ህወሓት ገና በረኻ ደደቢት እያለች 1973 “የወደፊት የኔ ጠላት ሙሁሩ ክፍል ነው” ማለቷም “የኔ ጠላት ዕውቀት ነው” ከሚል ሐሳብ ጥልቅ የሆነ ግንኙነት አለው::በአሁኑ ዘመን ትምህርት ምላሷ እንጂ ተክለ ሰውነቷ(ቁመናዋ) የለም ማለት ይቻላል:: ይህ ማለት ደግሞ የዕውቀት ግንብ ፈርሷል ማለት ነው::ይህ ማለት ደግሞ የጥበብና የምርምር ቤት ተንዷል ማለት ነው::ይህ ማለትም ምክንያታዊ አስተሳሰብና ግንዛቤ ቀብሮ አገርን ያለ ጠያቂና ተጠያቂ በማስቀረት የለውጥ ድልድይ እንዳይሰራ ያደርጋል::አሁን እያየነው ያለነውም ይህ ነው::
በህወሓት ዘመነ ስልጣን ብዙ ሙሁራን ደብዛቸውን ጠፍቷል::ወህኒ ቤት(ጓንታናሞ) ወርዷል::አገራቸውን ለቀው በባዕድ አገር ሰፍሯል::ይህ ማለት ደግሞ የህወሓት/ኢህአዴግ የዕቀት ጠላትነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መስታዎት ነው::
ህወሓት በእውነት ለኢትዮጵያ ዕድገት ከልብ የሚቆረቆር ቢሆን ኖሮ አሁን ያለው እጅግ የሞተ የትምህርት ጥራት አስተካክሎ ትውልድን የዕውቀት ባለቤት አድርጎ የምርምር ማዕበል በመክፈት ለውጣዊ የዕድገት መንገድ መስራት በቻለ ነበር:: ዳሩ ግን ይህ አይደለም::
የህወሓት ዋና አለማ ከጅምሩ የትምህርት ጥራትን በማበላሸት የትውልድ የእውቀት ጥይትን በመቅበር አገር ያለ ምንም ጠያቂና ተጠያቂ በማስቀረት ዘላለማዊ አምባገነናዊ ስልጣን መቆናጠጥ ነው::ይህ እባባዊ ጥቁር ሴራ “ለህዝብ ኑሮ ለህዝብ የሞተ አገራዊ÷አህጉራዊና አለማዊ ምጡቅ መሪ”እየተባሉ የተሞካሹ የአቶ መለስ ዜናዊ ነው:: አቶ መለስ ዜናዊ የትውልድ የእውቀት ጥይት ለመቅበር የእውቀት አባት የሆኖውን ‘መምህር’ ክብሩን ዝቅ አድርገው በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማያቅ አኳሃን አድቅቀውና አመንምነው አረከሱት::የእኝህ ሰው ታላቁ ጥቁር አስተሳሰብም መነሻው ይህ ነው::ትውልድ ገዳይ ስውር መርዝም ይህ የእውቀት ጠላትነት ነው!!
በአሁኑ ዘመን መምህርና ትውልድ ላይገናኙ አብረው እየተራመዱ ነው::እውቀትና ትውልድም በጣም ተራርቋል::የዕውቀት ድልድይ ተንዳለች::የትውልድ አስተሳሰብም በእጅጉ ወርዷል::የለውጥ ሻማም ጠፍታለች::
ኢትዮጵያ የትምህርት አብዮት ያስፈልጋታል::የዕውቀት አብዮት ያስፈልጋታል::የጥበብና የምርምር አብዮት ያስፈልጋታል::የባህል አብዮት ያስፈልጋታል::ይህን ሳታደርግ ዕድገት ልታመጣ አትችልም::ኢትዮጵያ በድንጋይ ሳይሆን በእውቀት መገንባት አለባት::በምላስ ሳይሆን በተግባር መገንባት አለባት::በዘፈቀደ ሳይሆን በምርምርና በጥበብ መገንባት አለባት::
ህወሓት በአሁኑ ጊዜ የት እንደነበረ÷አሁን የት እንዳለ÷ለወደፊት ወዴት እየሄደ እንዳለ በእውን ለይቶ የማያቅ የምክንያታዊ አስተሳሰብ መኸን ትውልድ እያፈራ ይገኛል:: ይህም ዛሬ ኢትዮጵያ በካድሬው÷ ነገ ደግሞ በካድሬው ልጆች መመራቷ የማይቀር ነው ማለት ነው::
ይህ የህወሓት ጥቁርና የማይረባ አጉል አስተሳሰብ(የእውቀት ጠላትነት) እስካልተወገደ ድረስ “ኢትዮጵያ መካክለኛ ዕድገት ካላቸው አገራት ትቀላቀላለች” ማለትም ከንቱ ምኞት(ቅዠት) ከመሆን የሚያልፍ አይደለም::………..