Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ክፍል አንድ/2፡ የዝንጀሮዎቹ ጌታ ሞተ –ለምን እና እንዴት? ከግርማ ሞገስ

$
0
0

ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
ሰኞ መስከረም 6 ቀን 2006 ዓ.ም. (September 16, 2013)

Girma Moges

አቶ ግርማ ሞገስ

የዝንጀሮዎቹ ጌታ አጭር ታሪክ የተወሰደው ቻይናዊው ሊዩ ጂ/ Liu-Ji (1311-1375) ከጻፈው የሞራል ማስተማሪያ መጽሐፍ ነው። ይኽ አጭር ታሪክ የአምባገነን ገዢዎች የፖለቲካ ኃይል ከየት እንደሚፈስላቸው (ምንጩ ምን እንደሆነ) እና እንዴት ምንጩን በመቆጣጠር የአምባገነኖችን አቅም መቆጣጠር አልፎም ምንጩን በማድረቅ አምባገነኖችን ማስራብ እንደሚቻል በምሳሌ አድርጎ ግልጽ ያደርጋል። ሰለዚኽ የሰላማዊ ትግል ተመራማሪው እና ዘመናዊ የፖለቲካ ሳይንስ ጠበብቱ ሲድኒ ታይ (Sidney Tai) ከቻይንኛ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ተረጎመው። የእንግሊዘኛ ትርጉሙን “በማጭበርበር መግዛት” (“Rule by Tricks”) የሚል ርዕስ ሰጠው እና ሰላማዊ ቅጣቶች (Nonviolent Sanctions) በሚል ርዕስ የአልበርት አነስታይን ሰላማዊ ትግል ምርምር ተቋም በሚያትማት ጋዜጣ ላይ አሳተመው ሲድኒ ታይ (Sidney Tai)። የዝንጀሮዎቹ ቅጣት ሰላማዊ ቅጣት እንደነበር እና የዝንጀሮዎቹ ጌታ ቅጣት ግን የኃይል ቅጣት (Violent Sanction) እንደነበር ወደፊት ከቦታው ስንደርስ እናስተውላለን። በቅርብ ደግሞ ጂን ሻርፕ (Gene Sharp) የተባለው ሌላው የዘመናችን የሰላማዊ ትግል ተመራማሪ እና በካምብሪጅ ዩንቨርስቲ መምህር ይኽን አጭር ታሪክ ከአምባገነን ወደ ዲሞክራሲ በሚለው መጽሐፉ ገጽ 17-18 ላይ ሰላማዊ ትብብር የመንፈግ ትግል (Nonviolent Non-cooperation Struggle) የሚለውን የሰላማዊ ትግል ጽንሰ አሳብ ለማብራራት ተጠቅሞበታል። የዚህ ጽሑፍ ግብ በዚህ አጭር ታሪክ አንባቢዎች እየተዝናኑ እንዲመራመሩ ማድረግ ነው። ይኽ ምርምር በቅርብ ለንባብ ለማቀርበው ጽሑፍ መሰረት ይጥላል የሚል እምነት አለኝ።   ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ  

 


የምስራች ለኢህአዴግ የምጡቅ ጭንቅላት ባለቤትነት ምልክቶች በአንድ ካድሬ ተገኘ

$
0
0

ከዳዊት ሰለሞን (ጋዜጠኛ)

ኢህአዴግ መለስን በተፈጥሮ ሞት እንደተነጠቀ የድርጅቱ አመራሮች የሙሉ ጊዜ አገልግሎቱን ለለቅሶው ባበረከተው ቴሌቪዥን በመቅረብ ሟቹ መለስ የምጡቅ ጭንቅላት ባለቤት እንደነበሩ ይናገሩ ነበር፡፡የኢህአዴግን አቅጣጫ የሚቀይሱ፣የትግራይን ስትራቴጂክ እቅድ የሚነድፉ፣የድርጅቱን የንድፈ ሃሳብ መጽሄት በዋና አዘጋጅነት የሚያገለግሉ፣የአገሪቱን የጦር ሃይል በ1997 ጠቅልለው ወደ ራሳቸው ዕዝ ያስገቡ፣ዶክተሩን፣መምህሩን፣ተማሪውን፣አርቲስቱን፣ወጣቱን፣በንግራቸው የሚያማልሉ፣የአፍሪካ አዲስ ተስፋ ተሰኝተው በእነ ቶኒ ብሌር የተመረጡ፣የአገር ውስጡን ተቃዋሚ ጣት እቆርጣለሁ በማለት የሚያስፈራሩ፣እነዚህና ሌሎች ስንክሳሮች ተመዝዘው መለስ‹‹የምጡቅ ጭንቅላት ባለቤት ናቸው ››ተባሉ፡፡ከመለስ በኋላ ይህን ጭንቅላት ስለ ማግኘቱ የተነገረለት ወይም አለኝ ያለ እስከ ዛሬ ማለዳ አላጋጠመኝም ነበር፡፡
በመለስ እግር የገቡት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የመለስ ጫማ እንዳልበቃቸው በመታመኑ በክላስተሮች የተከፋፈሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተመደቡላቸው ወይም ተመደቡባቸው፡፡(ሂደቱን አንዳንዶች በጠቅላይ ሚኒስትሮች ብዛት አገራችን እመርታ አስመዘገበች በማለት መቀለዳቸውን አስታውሳለሁ)ነገር ግን ለእኔ ሹመቱ የእመርታ ጉዳይ ሳይሆን ያን ምጡቅ ጭንቅላት በአንድ ሰው መተካት አለመቻሉን ኢህአዴግ ማመኗን የሚያሳብቅ ነው፡፡

(የፎቶ ምንጭ አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ)

(የፎቶ ምንጭ አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ)


ኢህአዴግ አንዱን መለስ በብዙ ለመተካት እየወሰደ ከሚገኘው እርምጃ በተቃርኖ ዳንኤል ብርሃነ የሚባል ግለሰብ የምጡቅ ጭንቅላት ባለቤት ነኝ››በማለት ራሱን አስተዋውቋል፡፡ይህ ምጡቅ ጭንቅላት በመፈለግ ከመለስ ሞት በኋላ በቀን ብርሃን ባትሪ እያበራ ሲፈልግ ለከረመው ኢህአዴግ ትልቅ የምስራች ነው፡፡
ወዳጄ እርስዎ ‹‹ምጡቅ ጭንቅላት››የሚል ቃል ሲያደምጡ ወደ አይነ ህሊናዎ የሚመጡት እነ አልበርት አነስታይን፣ሊዮ ቶሎስቶይ፣አጼ ምኒልክ፣ማዘር ቴሬዛ፣ኔልሰን ማንዴላና ሌሎች ይሆናሉ ፡፡በኢህአዴግ ማውጫ የምጡቅ ጭንቅላት ባለቤትነት ሁሉን በጠላትነት አይን ማየት፣ዘረኝነት፣ፍረጃ፣አማራጭ የሚባል ሃሳብ ጠረጴዛው ላይ እንዳይቀርብ የተለየ ሃሳብ አመንጪን መምታት ነው፡፡በዚህ ረገድ የፌስ ቡኩ ዳንኤል ብርሃነ ‹‹የምጡቅ ጭንቅላት ባለቤት ስለ መሆኑ መከራከር ጉንጭን ማልፋት ነው፡፡የህግ ባለ ሞያና የምጡቅ ጭንቅላት ባለቤት ነኝ የሚለን ግለሰቡ በቅርቡ ፖስት ያደረጋቸውን ወይም አስተያየት የሰጠባቸውን አንዳንድ ጹሁፎች በመመልከት ምጡቅ ጭንቅላት እኛ በምናውቀውና እነርሱ በሚሉት መካከል የሰማይና የምድር ያህል ልዮነት እንዳለው እንገነዘባለን፡፡
Wossi Zebdewos:- ”There was a defection news/ Rumor at the first place??”

Daniel Berhane:- ”Yes, there is such a news from the enemies of Tigrai.”
ዘብዴዎስ የተሰኙ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ለዳንኤል እነ አርከበን በተመለከተ የኩብለላ የጭምጭምታ ዜና ከመነሻው ስለ መኖሩ ይጠይቁታል፡፡ዳኒ በመልሱ ‹‹አዎን ከትግራይ ጠላቶች እንዲህ አይነት ወሬ ነበር››ብሎ ቁጭ፡፡በቃ በእርሱ ምጡቅ ጭንቅላት ውስጥ እነ አርከበ ኮበለሉ ማለት የትግራይ ጠላት መሆን ነው፡፡ የባለስልጣኑን ኩብለላ ከትግራይ ጠላትነት ጋር ሊያቆራኝ የሚችል የዳንኤል ምጡቅ ጭንቅላት ካልሆነ በቀር እንዲህ አይነት ጭንቅላት ማግኘት ያስቸግራል፡፡እንቀጥል
Daniel Berhane:- #Ethiopia: History repeats itself. Now Arena-Tigray is the enemy with-in.
አረና በቀድሞ የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች የተመሰረተ ፓርቲ ነው፡፡ዳንኤል ይህንን ፓርቲ እንዴት እንደሚመለከተው ሲጠቅስ በውስጥ ያለ ጠላት ብሎታል፡፡በቃ ለዚህ ምጡቅ ጭንቅላት ህወሃትን መቃወም ጠላትነት ነው፡፡አረና በትግራይ ምድር ሆኖ ህወሃትን መቃወሙን ደግሞ በውስጥ ያለ ጠላት በማለት እንዲፈርጅ አድርጎታል፡፡ምን ይደረግ የምጡቅ ጭንቅላት ባለቤት ነዋ፡፡አሁንም ከዳንኤል ይቅርታ ከምጡቅ ጭንቅላት ጋር ነን፡፡
Daniel Berhane:- በትግራዮች እና በኢሕአዴግ አባላት ላይ ማህበራዊ መገለልን ያወጃቹሁ ሰዎች(ጨዋው የኢትዮጲያ ሕዝብ አሳፈራችሁ እንጂ)፣ በተግባርም የትግራዮች ቤት ሲቃጠል እና ‹‹የሚቃጠል›› ተብሎ ሲፃፍበት ግድ ያልሰጣችሁ ሰዎች፣ የበድሩ አደምን ዘረኛ መፈክር ከማውገዝ ይልቅ የቃላት ጨዋታ የመረጣችሁ ሰዎች፣ በእናንተ አመራርና ቅስቀሳ ስለተደበደቡና ስለተገደሉ ትግራዮች ከመቆጨት ይልቅ መከራከር የመረጣችሁ ሰዎች፣ እንኳን በፈቃዳችሁ መራብ ቀርቶ ምግብ አጥታችሁ ብትራቡ ግድ የሚሰጠው የሚኖር ይመስላችላኋል
ደረጄ ሀብተወልድ የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን የርሃብ አድማ በማስመልከት የዳንኤል ወንድሞች የሰጡት ምላሽ አበሳጭቶት እነርሱ እኮ ለቅንጅት አመራሮች የርሃብ አድማ የሰጡት መልስ ተመሳሳይ ነበር እናም ርዕዮት የርሃብ አድማ በመጀመሯ ያዝናሉ ብለን መጠበቅ አይገባም፡፡ይላል ዳኒ ለደረጀ መልስ በመጻፍ‹‹እንኳን በፈቃዳችሁ መራብ ቀርቶ ምግብ አጥታችሁ ብትራቡ ግድ የሚሰጠው የሚኖር ይመስላችላኋል››ምጡቅነቱን አሳየን፡፡አዎን በዳንኤል ዙሪያ ግድ የሚለው ላይኖር ይችላል፡፡እናንተ ግድ እንዲላችሁ ነፍስ መበላለጥ አለበት፡፡ደግሞስ ይህን ዘረኛ ከፋፋይ የፖለቲካ እሳት እንዲዛመት ያደረጋችሁት እናንተው መሆናችሁን መዘንጋት አይኖርብህም፡፡በጣም ግራ ያጋባኝ ነገር ድሬዳዋ ያደገ ሰው በድሬ የተማረ ከየት ነው ይህንን ዘረኛ አመለካከት የያዘው?
Daniel Berhane:- It is boring to see such a long collection of stupid comments. If you don’t like the info, go hang yourselves.
ዳንኤል ለለጠፈው ጽሁፍ በዛ ያሉ ሰዎች ተቃራኒ አስተያየት መሰንዘር በመጀመራቸው ባለ ምጡቅ ጭንቅላቱ ‹‹እኔ የሰጠሁት መረጃ ያልተመቸው ራሱን ማጥፋት ይችላል ብሎ አረፈው፡፡ጠላትነት፣ራስን ማጥፋት፣ማንም ስለ እናንተ ግድ የለውም፣የትግራይ ጠላቶች ››የሚሉ ቃላትን በዳኒ እያንዳንዱ ጽሁፍ ውስጥ ተሰግስገው ያገኛሉ፡፡እነዚህን ቃላትም መለስ በህይወት ዘመናቸው የተካኑባቸው እንደነበሩ ካስታወሱ ቃላቶቹ ምጡቅ በመሆን የሚገኙ ወይም የምጡቅነት መለኪያ መሆናቸውን ይረዳሉ፡፡

Daniel Berhane:- ርዐዮት ሐኪም ተከለከለች በለኝ – ምንም ማድረግ ባልችል አብሬ እታመማለሁ፡፡
ፍቅረኛዋን በዚህ ቅዳሜና/እሁድ ሳታገኝ ቀረች በለች አዝናለሁ፡፡
ሌላው የሚዲያ ሰርከስ አይመለከተኝም፡፡
ወዳጄ ስላቁን ተመልከቱ፡፡የርእዮትን የርሃብ አድማ ፍቅረኛዋን ከማግኘት ጋር በማቆራኘት እቃቃ ሊያደርገው ይሞክራል፡፡አስረኛዋ በማንም የመጎብኘት ፍቅረኛዋን ጨምሮ መብት አላት፣ህክምና ማግኘትም የታሳሪ መብት ነው፡፡ወደ ጡት ካንሰርነት ሊያደግ የሚችል እጢ እንዳለባት የተነገራት ሴት የህመሙን እድገት ለመቀነስ የተመረጠ ምግብ መብላት፣ጭንቀት ከሚፈጥር ሁኔታ መራቅ ይገባታል፡፡የጀመረችው የርሃብ አድማ ደግሞ በተቃራኒው ለህመሙ መፋጠን የራሱን አስተዋእጾ ያበረክታል፡፡ምጡቅ ሆይ ሰብዓዊነት ግድ ሊለን አይገባም ይሉን ይሆን?አብረው የሚታመሙ ከሆነ ምነው አብረዋት ባይራቡ የመራቧን መንስኤ ባያወላግዱት?ረስቼው ምጡቅነት ለካ ለሰብዓዊነት ቦታ የለውም፡፡

የኛ ነገር፤ ከኔ ማእዘን፤ ክፍል 14 (ከተክለሚካኤል አበበ)

$
0
0

ከተክለሚካኤል አበበ

የግንቦት ሰባት ርእሰ-አንቀጽ
1. ከግንቦት ሰባትና የግንቦት ሰባት አመራር አባላት የማደንቅላቸው ድንቅ ነገር ቢኖር ሌሎችን ያለመተናኮስ ባህርያቸው ነው። ሌሎች ቢተነኩሷቸውም እንኳን፤ ምንም ምላሽ ያለመስጠት አቋማቸውን አደንቅላቸዋለሁ። እስካለፈው ሁለት ሳምንት ድረስ። ባለፈው ሁለት ሳምንት ግን፤ በራሳቸው አነሳሽነት አገር ቤት ያሉትን ድርጅቶች ወደመተንኮስ ያዘነበሉ ይመስላል። በተለይም ሰማያዊ ፓርቲን። ስለዚህም ጥያቄ ተነሳብኝ።
2. ግንቦት ሰባት፤ ነሀሴ መጨረሻ ላይ፤ http://www.ginbot7.org/2013/09/02/በሰማያዊ-ፓርቲ-አባላት-በደረሰው-ወያኔያ/ አንድ ርእሰ አንቀጽ ጽፏል። ርእሰ አንቀጹ የሚቆጣም የሚያላግጥም ይመስላል። ድሮ ልጆች ሆነን አባቶቻችን የሚሉንን አይነት ለዛ አለው። “ሀሳብህ ጥሩ ነው፤ ጥረትህንም እናደንቃለን፤ ነገር ግን ልጅ ስለሆንክ ነው” አይነት ነገር።
3. የኢህአዴግ አገዛዝ የሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰልፍ ሲዘጋጁ በነበሩ አባላት ላይ ያደረሰውን ድብደባ ያወገዘው ግማሽ ገጽ ርእሰ አንቀጽ፤ በግማሽ ገጽ ላይ ሰባት ግዜ “ወጣቶች ወጣቶች” እያለ ወርዶ (ትንሽ አጋንኜ ነው እንጂ አምስት ግዜ ብቻ ነው)፤ ወጣቶቹን ተስፋ ለማስቆረጥ የታለም የሚመስል መልእክት ይሰነቅራል። እንዲህ ይላል።

ginbot 7
“ወጣቶች ምን ትላላችሁ? ጥንካሬያችሁን እናደንቃለን፤ ሆኖም የያዛችሁት መንገድ የባላንጣችንን ባህሪይ እግምት ውስጥ ያስገባ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አለን። … ባርነትን ትቀበላላችሁ ወይስ አማራጭ የትግል ስልቶችን ለመመርመር ትደፍራላችሁ? ባዶ እጆቻችሁን እያሳያችሁት እየረገጠና እያዋረደ “መንግሥት” ነኝ ብሎ የሚኮፈስ እኩይ ጋጠወጥ ጋር ሰላማዊ ትግል ያዋጣል ትላላችሁ?”
4. ርእሰ አንቀጹ ሀቀኛ አይደለም። ርእሰ አንቀጹ፤ መልሱን ለናንተ እንተወዋለን ቢልም፤ መልሱን ግን ዝቅ ብሎ ይመልሰዋል። መልሱ፤ ባንድ በኩል “የሰላም ትግል ከእኛ ወዲያ አልቆለታል” የሚል መልእክት ያለው ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ “ሁለቱም ተያይዘው ይሄዳሉ” የሚልም ለዛ አለው። አንዱ ያላንዱ፤ ሰላማዊው ከአመጽ፤ የአመጹም ከሰላማዊው ተለይተው ህይወት ይላቸውም ይላል። አንዱ መንገድ ያለሌላው ህይወት ከሌላቸው የራሳቸውን ጠበቅ አድርገው ሌሎቹም የራሳቸውን ጠበቅ እንዲያደርጉ መምከር ሲገባ፤ ወያኔ ከዚህም የከፋ ድብደባና ውርደት ስለሚያከናንባችሁ፤ መንገዳችሁን መርምሩና፤ ዛሬውኑ ወስኑና እኛን ተቀላቀሉ ምን የሚል ግብዣ ነው ያቀረቡት።
Tekele5. እነሱማ ወስነዋል። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወስነው፤ የለም ጠብመንጃ መሸከም አንችልም፤ ዳገት ቁልቁለቱን መውረድ፤ እሾህና ጋሬጣውን መቋቋም፤ አውሬውንና መከራውን እንደምን መሸከም አይቻለንም፤ መሸከም ብንችልም፤ የትጥቅ ትግል ተገቢ አይደለም ብለው በሰላም፤ ነገር ግን በመጋፈጥ እዚያው አገር ቤት ሊፋለሙ ወስነዋል። ግንቦት ሰባት አንዳቸው ያላንዳቸው ህይወት የላቸውም ካለና፤ የራሱ የመለመላቸው ጫካ የገቡ ሀይሎች ካሉት፤ ለሰላሙ የቆሙትን ደግሞ ባላችሁበት በርቱ ማለት ሲገባው፤ እንደገና ደግሞ ከወያኔ ጋር የሰላማዊ ትግል አያዋጣምና እኛን ተቀላቀሉ ምን የሚሉት ጅልኛ አነጋገር ነው።
6. የዚህ ርእሰ አንቀጽ መንሸዋረሩ ብቻ ሳይሆን የታሪክ ድግግሞሹም የሚገርም ነው። የዛሬ ዘጠኝ አስር አመት ሰላማዊ ትግል ብቸኛው ምርጥ መንገድ ነው የሚሉት የግንቦት ሰባት መሪዎች ነበሩ። እነ ኢህአፓ አገር ቤት በሰላም የሚታገሉትን ድርጅቶች ወያኔዎች ናቸው ወይም ለወያኔ ህጋዊነት ያሰጡታል እያሉ ሲከሱ ሁሉ ብርሀኑ ነጋ (ዲባቶ) አውሮፓና አሜሪካ መጥቶ በፍጹም ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ መንገድ ነው እያለ ይሰብክ ነበር። የዛሬው ርእሰ አንቀጽ ግን ልክ እነሱ ከአገር ሲወጡ የሰላማዊ ትግል ከነሱ አብሮ እንደተሰደደ ነው የሚነግረን። የሰላማዊ ትግል ከነሱ መሰደድ ጋር እንዳበቃለት ይሰብካሉ።
7. እንደኔ እንደኔ አስተያየት፤ የግንቦት ሰባት ርእሰአንቀጽ፤ በሰላም እንታገላለን የሚሉትን ሁሉ እነሱን እንደሚያሳጡ አድርገው ከማሰብ የመነጨ ይመስላል ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ፤ የዛሬው የግንቦት ሰባት አቋም፤ ትናንት እነሱ ቅንጅት በነበሩበት ግዜ፤ ኢህአፓና ወዳጆቹ ሲያራምዱት የነበረውና እነሱ የግንቦት ሰባት ሰዎች ሲዋጉት የነበረው አቋም ነው። ርእሰ አንቀጹ፤ “ያለን ምርጫ ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው ሲል የደነገገልን ማነው?” ብሎ ይጠይቅና፤ ሰላማዊ ትግል ከትጥቅ ትግል በላይ መስዋእትነት ሊያስከፍል እንደሚችል፤ እንደውም ሰላማዊ ትግል ብቻውን ድል ማቀዳጀት እንደሚችል ማረጋገጫ እንደሌላ ይናገራል። እንዲህ ያለው ያልጠራና የተደባለቅ አካሄድ ነው ቀደም ሲልም በቅንጅት ዘመን ድል ያሳጣን።
8. ግንቦት ሰባት የሚያዋጣውን መንገድ መርጦ ከገባ በሁዋላ፤ የሌሎችን መንገድ ባደባባይ መተቸትና መጠየቁ አግባብነቱ አይታየኝም። የራስን የትጥቅ መንገድ መተንተን አንድ ነገር ነው፤ የሌሎችን የሰላም መንገድ ማጣጣል ደግሞ ሌላ ነገር ነው። ይሄ ርእሰ አንቀጽ፤ ቀደም ሲል ግንቦት ሰባት የተናገረውን፤ በምንም መልኩ ሌሎችን አንነካም የሚል መርህ የሚጣረስም ነው። በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የደረሰውን መከራ ማውገዝ አንድ ነገር ነው። ከዚያ አልፎ ግን ይሄ የደረሰባችሁ ሰላማዊ ትግል የሚባል የፖለቲካ ደዌ ስለአዛችሁ ነው ብሎ በሌሎች መንገድ ላይ መፈትፈትና ማላገጥ ፋይዳው አይታኝም። ስለዚህ ግንቦት ሰባት ርእሰ አንቀጹንም፤ ርእሰ ነገሩንም ይመርምር።
9. በመጨው አርብ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቃለምልልስ ላይና፤ ብርሀኑ ነጋ (ዲባቶ) ጎበዝ የዴሞክራሲ ጊዜ መሪ ስለመሆኑ፤ በምንም መልኩ ግን ውጤታማ የትጥቅ ትግል መሪ ሊሆን ስላለመቻሉ እጽፋለሁ። የማደንቀውና የማከብረው የግንቦት ሰባት ዋና ጸሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ እኔ አምስት ስድስት አመት በተደጋጋሚ የጻፍኩበትን ከኤርትራ በቅርበት የመስራት ነገር ደግፎ መናገሩ ቢያስደስተኝም፤ ያቀረበት መንገድና ትንተናው በጣም የሚዘለዘል ነው። ባለፉት አራት ቀናት በቶሮንቶና ኦታዋ ስለከረመው አቶ ግርማ ሰይፉም ትንሽ እቀዳለሁ። ከአቶ ግርማ ጋር ያደረግነው ይፋ ህዝባዊ ስብሰባ በቪዲዮ ስለተቀዳ፤ ለኢሳት እንልከውና ኢሳት ካልገገመና መልካም ፈቃዱ ከሆነ በኢሳት ትመለከቱታላችሁ። በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ በግልና በቡድን ከአቶ ግርማ ጋር ስለተጫወትናቸው አንኳር ጨዋታዎች እጽፋለሁ። ኢንሽ አላህ አለ ሀሰን ኡመር አብደላ። እግዚአብሄር ያውቃል እንደማለት ነው።
እኛው ነን፤ ከቶሮንቶ፤ ካናዳ፤ መስከረም፤ 2006/2013

በቻድ አንድ የስነ አእምሮ ሐኪም ብቻ በኢትዮጲያስ? (ክፍሉ ሁሴን)

$
0
0

ቢቢሲ የ12 ሚሊዮን ሕዝብ ባለቤት በሆነችውና የተጠናወታት ድህነት ሳያንሳት በጦርነት ስትናወጥ በከረመችው ቻድ ያለው የስነ አእምሮ (psychiatrist) ሐኪም አንድ ብቻ ነው ይለናል።

ቻድስ ሰብ ሰሃራ አፍሪካ ተብሎ በሚታወቀው ቀጠና ከሚገኙት አገሮች ሁሉ በባሰ ሁኔታ የድሆች ድሆች መሆኗ ታውቆላታልና ዜናው አያስገርምም።ለመሆኑ ገዳይና አካል አሰናካይ የሆነው የልጅነት ልምሻ (polio ) ተመልሶ ተዛመተባት ከተባለ በኋላ በማግስቱ ደግሞ የሕጻናትን ሞት ቀነሰች በተባለችው “ልማታዊዋ” ኢትዮጲያስ ያሉት የስነ አእምሮ ሃኪሞች ስንት እንደሆኑ እናውቃለን?ትክክለኛው መረጃ እጄ ላይ ባይኖርም ከ86 ሚሊዮን በላይ ለሆነው የኢትዮጲያ ሕዝብ ያሉት የስነ አእምሮም ይሁን የሌላ ሐኪሞች ብዛት ከቻድ እምብዛም እንደማይለይ ፍርጥም ብዬ እወራረዳለሁ።mental

እስካሁንም ድረስ በአፄ ሃይለስላሴ ጊዜ ከተሰራው የአእምሮ ሕሙማን ሆስፒታል—አማኑኤልን ማለቴ ነው—-ሌላ እንደተጨመረ የሚያሳይ ምንም መረጃ አላገኘሁም።ይልቁንም በጥቅምት 1998 እስከ ጥቅምት 1999 በቃሊቲ ማጎሪያ ካምፕ ተቀፍድጄ በነበረ ጊዜ በነፍስ መግደል ወንጀል ተከሰው የታሰሩትንና የአእምሮ ሁኔታቸው አጠራጣሪ የሆኑትን ባለሙያ እንዲመረምራቸውና የተከሰሱበትን ወንጀል እንዲፈጽሙ ያደረጋቸው ይኸው የአእምሯቸው ሁኔታ መሆን አለመሆኑን እንዲመሰክር “ፍ/ቤት” በሚያዝበት ጊዜ በዚያ ለአገሪቱ አንድ ለናቱ በሆነው አማኑኤል ሆስፒታል ያሉት ባለሙያዎች ሊያዳርሷቸው ስለማይችሉ ረጅም ቀጠሮ እየተሰጠ እነዚህ አደገኛ ዝንባሌ ያላቸው ተጠርጣሪዎች በልዩ ልዩ ሰበብ ከታጎረው ሌላው ምስኪን ሕዝብ ጋር አብረው እንዲከርሙ ይደረጋል። የአእምሮ ሁኔታቸውም እየተባባሰበት መሄድ ብቻ ሳይሆን በሌሎች እስረኞች ላይ ከፍተኛ አደጋ ሲያደርሱ በአይን ምስክርነት ከማየት ባሻገር ካንዱ አደጋ በደቂቃዎች ልዩነት የተረፍኩበትንም አጋጣሚ አስታውሳለሁ።

ለማንኛውም የዛሬዎቹ ገዢዎች እድሜ ለሟቹ ባለ”ራዕይ መሪያቸው” በ”ልማት”የሚያህለን የለም ተመንድገናል ስለሚሉና ይህንኑም እንዲያስተጋቡላቸው የፈረንጅ ቱልቱላዎች (lobbyists ) ቀጥረው ራሳቸውን በመቀባባት ላይ ስለሆኑ ከኢትዮጲያ የሚወጣው ዜና እንደቻድ ሳይሆን በመልማታችን የተነሳ ሕዝቡ ደስተኛ ስለሆነ የአእምሮ ሕሙማን የሉም የሚል ሊሆን ይችላል፤ይሆናልም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአእምሮ ሕመምተኞች ሁሉ ምንም የማያውቁ ፉዞዎች አድርገን ለምንገምት ይልቁንም ብሩህ አእምሮ ያላቸው ሰዎች በፉዞዎች ምድር ለአእምሮ ሕመም እንደሚጋለጡ ለማናውቅ ቀጥሎ ያለው ታሪክ እያዋዛ ያስተምረናል።

አንድ ዘመናይ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ጉዳዩ ሲከንፍ አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ ሲደርስ ጎማ ይተነፍስበትና ወደጥግ አቁሞ ለመቀየር ይገደዳል።እናም ኮፈኑን ይከፍትና የጎማውን ሳህን አውልቆ ብሎኖቹን ከፈታ በኋላ ሳህኑ ላይ አስቀምጦ ክሪኩንና ተቀያሪ ጎማውን ለማውጣት ወደኋላ ዞሮ ወደኮፈኑ ይመለሳል።ጎማውንም ክሪኩንም ካወጣ በኋላ ወደሚቀየረው ጎማ ሲመለስ ሳህኑ ላይ አስቀምጧቸው የነበሩት ብሎኖች ከነሳህኑ ተሰርቀዋል።በሴኮንዶች ልዩነት ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ከተደመመ በኋላ ወደመለዋወጫ ሱቅ ሄዶ ብሎኖች ለመግዛት አሰበና መልሶ ደግሞ “እዚችው ሆኜ በሴኮንዶች ውስጥ ብሎኖቼን ከሞጨለፉኝ መኪናውን ትቼ ዞር ካልኩማ ቅርጫ ያደርጉታል”በማለት እየተገረመም እየተከዘም ሲያስብ በዘመዶቹ እየተጠበቀ አማኑኤል ሆስፒታል ለመታከም ተራ በመጠባበቅ ላይ ያለ የ”አእምሮ ህምመተኛ”ያስተውለው ኖሮ “ወንድም! ለምን ትጨነቃለህ?ከሌሎቹ ደህነኛ ጎማዎች አንዳንድ ብሎን ፍታና ግጠምለት፤ሁሉም አንዳንድ ብሎን ቢጎድላቸውም እየነዳህ ከመሄድ ስለማያግደህ ረጋ ብለህ ገዝተህ ታሟላችዋለህ” ይለዋል።

ሲጨነቅ የነበረውም አሽከርካሪ በመፍትሄ ሃሳቡ ተደስቶ ማመስገን ከጀመረ በኋላ አንድ ነገር በድንገት ብልጭ አለለትና “ግን አንተ–!”ብሎ ሊጠይቅ ያሰበውን አንጠልጥሎ ሲተወው የ”አእምሮ ሕምመተኛው” ገብቶኛል ልትል ያሰብከው “ዳሩ እኔ እብድ እንጂ እንዳንተ ደደብ አይደለሁም።”ብሎ በአእምሮ ህመምና በደደብነት መካከል ያለውን ገደል አሳየው።

ቻድንም በውሸት ተቁዝረው እንድንቆዘር ለሚያስገድዱን የዘመኑ ገዢዎቻችንም ለኢትዮጲያ ሲባል ከዚህ አይነቱ ደዌ ይሰውርልን።

እ.ኤ አ መስከረም ወር 2013 ካምፓላ፤ዩጋንዳ ተጻፈ
ኢሜይል፤kiflukam@yahoo.c

ገንዳው –በእውቀቱ ሥዩም (አሜሪካ እንደመጣ የፃፈው)

$
0
0

beweketuእዚህ አሜሪካ – በሀገረ ማርያም – በጊዚያዊ ቤቴ – ጊዚያዊ በረንዳ
ቆሜ ሳነጣጥር
አየሁኝ መንገድ ዳር – ተገትሮ ያለ የቆሻሻ ገንዳ
ዳቦው እንደ ጉድፍ
ወተቱም እንደ እድፍ
ልብሱም እንደ ቅጠል
በገንዳው ከርስ ውስጥ ይረግፋል እንደ ጠል ::
ያሜሪካ መልኳ
አይደለም ህንፃዋ ሰማይ የሚነድለው
አይደለም መንገዷ – እንደ ቆለኛ ቅል የተወለወለው
አይደለም ፖሊስዋ – ዝሆን የሚያህለው
ያሜሪካ መልኳ ጎልቶ የተሳለው
በገንዳዋ ላይ ነው እመንገድ ዳር ባለው
ባገሬ ሰማይ ስር
ሰው ጠኔ ገፍትሮት ሲውድቅ በመደዳ
ያሜሪካ ንስር
ላንዲት ስኒ ሆዱ በጋን እያስቀዳ
እዚያ ማጣት እዳ
እዚህ ማትረፍ እዳ
እዚያ ባዶ መሶብ
እዚህ ሙሉ ገንዳ
ከእለታት አንድ ቀን
በሰማያት እና በምድሪቱ ድንበር
ከእኛ ጎታ አጠገብ የቆሻሻ ገንዳ ተቀምጦ ነበር
የሰማይ አማልክት አላጋጭ ቀልደኛ
“ራበን መግቡን” ስንላቸው እኛ
ብዙ መና ጋግረው ሲያዘንሙ ከሰማይ
የእኛን ጎታ ስተው ከተቱት ገንዳው ላይ::
ከቶ ለምን ይሆን
ያፍሪቃ ህፃናት በደቦ ሚያልቅሱ
የወተቶች አዋሽ – የርጎ ሚሲሲፒ – በበዛበት ዓለም – ጤዛ የሚልሱ
የሹራብ ተራራ – የቡልኮ ጋራ – በበዛብት ዓለም – ጭጋግ የሚለብሱ
የምድር ጠቢባን
ለዚህ ግዙፍ ምስጢር – መልስ አገኝ ብላችሁ – ጠፈር አታስሱ
አሜሪካ ያለው – የቆሻሻ ገንዳ – ግጣሙ ሲከፈት – ወለል ይላል መልሱ::
- በእውቀቱ ሥዩም (September 16, 2013. Maryland | USA)

መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ ……

$
0
0

ከይድነቃቸው ከበደ

(የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኋላፊ)

Yidnakachewየዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በየትኛውም አገር እንደ አገሩ ወግና ልማድ በድቅመት የሚከበር በዓል ነው፤በእኛ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ደግሞ ልማድና ወጋቻን እጅግ ከመጠንከሩ የተነሳ ለአዲስ ዓመት ወይም ለዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ዝግጅታችንም ሆነ አከባበራችን እጅግ በጣም ጠንካራና ደስ የሚል ነው፡፡

አዲስ ዓመት የሁሉ ነገር መጀመሪያ ነው ለዚህም ነው ብዙ እቅዶቻችን ከመስከረም ወር የሚጀምረው፤ያቀድነው ነገር በዓመቱ መጨረሻ ሊሳካ ወይም ላይሳካ ይችል ይሆናል ቁም ነገሩ ግን በዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ለማሳካት የታሰበ እቅድ መኖሩ ነው፤ለእቅዱ አለመሳካት ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ እነዚህን እንቃፋት የሆኑ ምክንያቶች ለይቶ ማወቅ በራሱ የእቀዱ አንድ አካል በማደረግ እንደገና ለመጪው አዲስ ዓመት ለተሸለ እቅድ ግባት ይሆናል፡፡

የዘንድሮ አዲስ ዓመት ከግለሰባዊ ፋይዳ በላይ አገራዊና ህዝባዊ የለውጥ ፋይዳ የበዛ እንደሚሆን ምልክቶቹ አብዝተው ይታያሉ፤እነዚህ ምልክቶች ከባለፈው ዓመት ለዘንድሮዎ የተሸጋገሩ የለውጥ ምልክቶች ናቸው፤በመሆኑም ለለውጥ የተነሳሳው ለወጥ ፈላጊ ለውጡኑ የሚያከሽፍበት አንዳችም ምክንያት ስለመኖሩ እጠራጠራለው ክሽፈት ቢያጋጥም እንኳን ወድቆ ለመነሳት ብዙ ጊዜ የሚባክን አይመስለኝም ፡፡

መውደቅ መነሳት ከሚንቀሳቀስ ነገር የሚጠበቅ ክስት ነው መንቀሳቀስ ደግሞ በሀገር ውስጥና በውጪ በሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ ፖለቲከኞች፣ በአይማኖት ተቋመት፣በሲቪክ ማህበራት እና በመሳሰሉት እንቅስቃሴው መሰልቸትና ድካም የማይታይበት ጠንካራ እንቅስቃሴ ነው፤ይህ እንቅስቃሴ ከባለፉት ወድቆ መነሳት እንቅስቃሴ ት/ት የተቀሰመበት ስለመሆኑ ከምልክቶቹ መካከል አንዱ ነው፡፡

በአገራችን ለለውጥ የሚገፋፉ ብዙ ምክንያቶች መኖራቸው የሚታወቅ ቢሆንም ከብዙ ምክንያቶች በዋንኝነት ትኩረትን የሚስቡት የለውጡን አይቀሪነት አሳበቂ ምክንያቶች ከሆኑት ውስጥ፡-

1ኛ. በዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ እምነቶች መካከል ክርስትና እና እስልምና ዋንኞቹ ናቸው፤እነዚህን እምነቶች በመቀበል እኛ ኢትዮጵያዊያን ከቀዳሚዎቹ መካከል እንገኛለን ክርስትናን እና እስልምና እምነትን መቀበላችን ብቻ ሣይሆን የተቀበልነው እምነት ህግና ሥርዓት አክብሮ በማስከበር ወደር አይገኝልንም፡፡ይሁን እንጂ መንግስት በልማት ስም  የአምልኩ ቦታዎችን በመጋፋት ቤተ ክርስቲያንን ተዳፍሯል፤ይህ ነገር ተገቢ አይደለም ያሉ የሃይማኖት አባቶች ተደብድበዋል፣ተገለዋል እንዲሁም ከአገር ተሰደዋል፡፡

መንግስት በሃይማኖት ሃይመኖት በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌ መንግስት በመጣስ በሙስሊም እምነት ዘው ብሎ በመግባት የእመንቱን መሪዎች እስከመምረጥ ደረጃ ተደርሷል፤ ይህን አይቶ ዝም አለማለት እስላማዊ ግዴታ እንደመወጠት የቆጠሩ እንቢ ለእምነቴ ያሉ በእስር እና በስቃይ ላይ ይገኛሉ፡፡    በእነዚህ ታላላቅ እምነቶች መንግስት እጁን በማስገባት የፖለቲካ ዓላማ ማስፈፀሚያ ለማድረግ ያልፈነቀለው ድንጋይ ምን አለ? በተለይ በሙስሊሞች ላይ እተየፈፀመ ያለው በደል እና በእምነቱ ተከተዮች የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ ያለጥፋታቸው በሐሰት በመወንጀል አሸባሪ ብሎ በእስር ማሰቃየቱ እጅን ጨብጦ ጥርሱን ነክሶ ያልተቆጨ ማነው ?

2ኛ. ኢትዮጵያ አገራችን የብዙ ሺህ ዓመት አኩሪ ታሪክ ያላት እና የተለያዩ –ን–ዎች የሚነገርባት ህዝቧ የቋንቋ ልዩነት ሣይገድበው አንዱ ከሌላው የተዋለደባት እጅግ ውብ እና ማራኪ –ን–፣ብህል ፣ልምድ ፣ወግ ፣አለባበስ እና አመጋገብ ወዘተ….. የሚታይባት ድንቅ አገራችን ናት፡፡ ይሁን እንጂ የኢህአዴግ መንግስት ይህ ቦታ የናተ አይደለም በማለት ዜጎችን በማፈናቀል ሀብትና ንብረት በማውደም ጎጠኝነትና ዘረኝነት በማስፋፋት ላይ ይገኛል፤እንዲህ አይነቱ አሳፋሪ ተግባር በአገራችን በአራቱም አቅጣጫ በዘመቻና በእቅድ በመንግስት የተፈፀመ ህገወጥ ተግባር ነው፡፡በመሆኑም ከኢትዮጵያዊነት በላይ መንደረኝነት እንዲነግስ በመንግስት እየተደረገ ያለው ዘመቻ ያላስቆጨው፣ ያላንገበገበው ማነው ? ይህን ቁጭቱን እና በደሉን ለመግለፅ ጊዜና አጋጣሚውን እየጠበቀ ያለው ስንቱ ነው ?

እኛ ኢትዮጵያዊያን በእድሜና በውቀታቸው ከፍ ላሉ ሰዎች ያለን ከበሬታ እጅግ የላቀ ነው ፤ለዚህም ነው ለሽምግልና ጉዳይ ቶሎ እጅ የምንሰጠው በሽምግልና ካጣነው ነገር በላይ ያተረፍነው የበዛ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ የቆየውና ጠቃሚ የሽምግልና ወገና ሥርዓት በመጠበቅ የአፋር ፣ የኦሮሚያ ፣ የጋምጎፋ (ቆጫ ወረዳ) እና የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች በአካባቢያቸው ለታየው አስተዳዳሪያዊ ችግር መፍትሔ ለመሻት ከታችኛው የአስተዳደር አካል እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጉት ጥረት ውጤት አልባ ነበር፤ ከምንምንም በላይ የሽምግልና ክብር በመጋፋት መንግስት ጠቃሚ የሆነውን ወግና ሥርዓት ለመናድ የሄደበት መንገድ ሽማግሌዎችንና የተወከሉበትን ማህበረሰብ ምን ያህል ነው ያስከፋው ?

3ኛ. ‹‹ በኑሮ ውድነት የጎበጠው ትከሻችን እረፍት ይሻል ›› ኑራችን አላምር ሲል መፈክራችን ማማሩ የሚገርም ነው ! ይህ መፈክር ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ባካሄደው የተቃውሞ ሠልፍ ከፍ ብሎ የተሰማ ጥያቄ ነወ፤ እውነትም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የኑሮ ውድነት ትከሻውን ከማስጉበጥ አልፎ ህይወቱን እየነጠቀወ ነው፡፡ ባለ ሁለት ሃአዝ እድገት በመንግስት ተደጋግሞ የሚነገር አስማታዊ እድገት ምግብም መጠጥም አልሆን ብሎ በመንግስት የሚነገረው እድገትና የምንኖረው ሕይወት ሆድና ጀርባ ሆኖ አልገጥም እያለ ተቸግረናል፡፡

የስራ አጥነት ቁጥሩ በጣም የበዛ ነው፣ሰራተኛም ሰርቶ የሚከፈለው ወራዊ ደሞዝ ወሩን ሙሉ የሚያቆይ አይደልም፣ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት 2.5 ሚሊዩን ዜጎች ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸው የመንግስት መስሪያ ቤት የሆነው የማህበራዊ ዋስትና ድርጅት ባስጠናው ጥናት መሰረት ይፋ አድረጎኃል፤ጎዳና ያልወጡ እቤታቸው ጎዳና የሆነባቸው ዜጎች ቤት ይቁጠራቸው፡፡

በመሆኑም እንዲህ አይነቱ ምስቅልቅል የበዛበት የኑሮ ውድነት ዋንኛው መንስሄ ብልሹ የመንግስት አስተዳደር ስለመሆኑ የእኛ መንገስትና ኑራችን ዋንኛ ማስረጃ ነው፤ስለሆነም እንዲህ አይነቱ ብልሹ የመንግስት አስተዳደር አቅፎና ደግፎ ይዞ የሚሄድ ጉልበትም ሆነ አንጀት ከወዴት ይምጣ ?

4ኛ. አሁን ያለው የአባገነን ሥርዓት የተረጋጋና ጉልበት አልባ መሆኑ ሌላኛው የለውጡን አይቀሪነት አሳበቂ ምክንያት ነው፡፡ ከእሳቸው ሞት በፊት ይታይ የነበረው የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭነት ከእሳቸው ሞት በኃላ የስርዓቱ ፊት አውራሪዎች ከመብዛታቸውም በላይ በቡድን የተከፈሉና እኛ እናተ መባባላቸው ከጥጋባቸው በላይ የስልጣን ጥማታቸውን የሚያሳይ ነው፤ ግን በሁለት ሆዳሞች መሃል እህል ይደፋል እንጂ ማንም አይበላውም፡፡

ሌላው የስርዓቱ የፊት ሰዎች ከውስጣዊ ሹኩቻ ባለፍ በአደባባይ አንዱ ለሌላው በሙስና እና በስልጣን መባለግ ስም ማሰርና መክሰስ ሌላኛው አገር ጥሎ መሄድ መሳ ለመሳ እየተካሄደ ያለ ውስጣዊ ሹኩቻ ነው፤በእንዲ መልኩ በውስጥ የተወጠረው የአባገነን ስርዓት በተጠናከረ እና ሠላማዊ በሆነ ህዝባዊ ግፊት ፈንድቶ ውስጣዊ ሰንኮፉ የማይነቀልበት ምክንያት ምንድነው ?

5ኛ. ሐሳብን በነጻ የመያዝና የመግለጽ እንዲሁም የመደራጀት መብት ዓለም አቀፍ  እንዲሁም ሕገ መንግስታዊ መብት ነው፡፡በመሆኑም አንዱአለም አራጌ፣ ናትናሄል መኳንን፣ በቀለ ገራባ፣ ኦልባና ለሊሳ እና ሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች እንደማንም ኢትዮጵያዊ የራሰቸው ኑሮ እና ህይወት ያላቸው ናቸው፤ ይሁን እንጂ ነፃነት እና ፍትህ ለነሱ ሁለተኛ ጉዳይ አይደለም የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ነው ! ከራስ ወዳድነት አልፈው ይህ ጥያቄ የኛ ብቻ ሣይሆን የኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው በማለት በአደባባይ ስለነፃነት እና ፍትህ የዘመሩ በዚህም አኩሪ ተግባራቸው በእኛ የኢትዮጵያዊያን ዘንድ ልዩ ቦታ የምንሰጣቸው ነን፡፡የታሰሩበት እና የሚሰቃዩበት ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው የሚሉ ቁጥራቸው መብዛቱ ሠላማዊ ትግሉ አባገነን ስርዓቱን የሚበላ እሳት መሆኑ ማሳያ ነው፡፡

ይህ በእንዲ እንዳለ  በአገር እና በህዝብ ላይ የሚፈፀም በደል ማቆም አለበት መንግስት እየወሰዳቸው ያለው እርምጃ የዜጎች ሰብአዊ እና ዲሞክራሳዊ መብቶችን የጣሱ ናቸው፤ በማለት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው ከምንም በላይ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር ጠብቀው ሚዛናዊ መረጃ ለእዝብ ያደረሱ ዓለም ዓቀፍ ተሸላሚ የሆኑ ጋዜጠኖች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ እርዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ በስራቸው ዓለም ያደነቃቸው አድናቆቱም በሽልማት የታጀበ መሆኑ ለማናችንም ግልፅነው፡፡ይሁን እንጂ እነዚህ የዓለም ህዝብ ቆሞ ያጨበጨበላቸው ጋዜጠኞች አባገነኑ መንግስት በሽብርተኝነት ወንጅሎ በማሰር እያሰቃያቸው ይገኛል ፡፡ ይህ ስቃያቸው ያልተሰማው ማነው ? ከዚህ ስቃይ እንዲወጡ ምን ባደርግ ይሻላል እያልን እራሳችንን ያልጠየቅን ስንቶቻችን ነን ? በሆነውስ ነገር ያልተቆጨ ማነው ?

6ኛ. በውጪ የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተፅኖ ሌላው ለአባገነኑ ሥርዓት የእግር እስታ መሆን ነው፤ በውጪ የሚገኙ ዜጎች በአገር ውስጥ ለታየው ብሉሹ አስተዳደር ፊት ከመንሳት ባለፈ በተደራጀና በሚያስደንቅ ሁኔታ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው፡፡ እንቅስቃሴውም ከሌላው ጊዜ በተሸለ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካው ስኬታማ መሆኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተለያየ ወቅት በሰጡት ቃለ ምልልስ እና መንግስት በሰጠው መግለጫ በውጪ በሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን መንግስት መሸነፉን የሚያሳብቅ ነው፡፡

በመሆኑም ከላይ በማሳያነት የቀረቡ የለውጡ ግፊት ሃይል ከሆኑ ምክንያቶች ውስጥ የተጨለፈ ቢሆንም  በመንግስት የአስተዳደር ብሉሹነት ምክንያት ይህ አስተዳደር በቃኝ ለማለት ምክንያቱ ብዙ ነው፡፡ ስለሆነም መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈናድ ለውጥ ፈላጊ የፈለገውን ለውጥ ላለማጣት ከባለፈው ዓመታት ት/ት በመውሰድ በዘንድሩ አዲስ ዓመት ከግለሰባዊ ፋይዳ በላይ አገራዊና ህዝባዊ ለውጦች የምናይበት ዓመት ይሆናል፡፡

 

ለአርቲስት ታማኝ በየነና ለሻምበል በላይነህ በእስራኤል የተደረገላቸው የጀግና አቀባበል ቪድዮ

ወፍር ትታማለህ፤ ክሳ ትታማለህ፤ አትወፍር አትክሳ ያኔም ትታማለህ!

$
0
0

aheyawa
ከዳግማዊ ጉዱ ካሣ

 

እንዲህ ዓይነት ርዕስ እንኳን በኔ ጽሑፍ በሌላም የቅርብ ጊዜ ጽሑፍ ገጥሞኝ የሚያውቅ ስለመሆኑ ትዝ አይለኝም፡፡ ይህ ርዕስ በትንሹ ሦስት ነገሮችን ያስታውሰኛል – ዘና እያላችሁ እንድታነቡ ነውና እምፈልግ በቁም ነገሮች ብቻ የታጨቀ መጣጥፍ ልጀባችሁ አልፈልግም፡፡ ከሚታወሱኝ አንዱና ዋናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አያቸው የነበሩና አሁንም ድረስ በስፋት የማያቸው የጥናት ርዕሶች ናቸው – ለምሳሌ እንዲህ ሊገጥማችሁ ይችላል፡- The Vulgarism of Some National and International Article Contributors to the Ethiopian Opposition Websites that Claim to Play a Positive Role in the Emancipation of Ethiopia from the Roguish Ethnocentric Tyranny of Tigray People’s Liberation Front (TPLF): With Specific Reference to the Malignant and Insulting Articles Contributed by so Called Dagmawi Gudu Kassa who is Currently Working at MoFA in Addis Ababa, the Capital of Ethiopia . … ልብ አድርጉ ይህ ዓይነቱ ርዕስ ከ‹አጫጭር› ርዕሶች አንዱ መሆኑ ነው – ሁለተኛው የዱሮ ቤሣ ልቦለዶችን ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ርዕስ ልታገኙ ትችላላሁ፡- “ ‹ድሃ ስለሆንኩኝ ጥጋበኛ ሀብታም እኔን በሽመል ነርቶ በማባረር እጮኛየን ቀማኝ አጭር ልቦለድ› – የስም መመሳሰል ቢኖር በአጋጣሚ እንጂ ሆን ብዬ አለመሆኔን በታላቅ ትህትናና አክብሮት እገልጻለሁ፡፡”  እነዚህን ዓይነት ርዕሶች በራሳቸው ነጋሪ በመሆናቸው ማን ወደ ውስጥ ገብቶ እንደሚያነባቸው አንድዬና አላህ ይወቁት፡፡ ሦስተኛው ስም አወጣጥ ላይ ነው፡፡ በ‹ቤቶች› ድራማ በምናውቀው  ስም ልጀምርላችሁና እውነተኛ ገጠመኜን ላስከትል፡፡ ‹እከደከን ማንችሎት በብልጠት ሆነ በጉልበት ሁሌም ከወንዶች በላይ አበጀ! አበጀ የአባት ስም ነው እንግዲህ፡፡ ሌላውና በቅርብ የማውቀው እውነተኛ የሰው ስም፡- ሺህ ማጫሽ ሺህ መገመቻሽ፣ አባይ በደጅሽ ተከዜ በጅሽ አበጀ – የሚል ነው፤ አሁንም እንደአጋጣሚ ሆኖ አበጀ የአባቷ ስም መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ጊዜ ያላችሁ በርዕስና ስም አወጣጥ ላይ እስኪ ተጨማሪ ጥናት አድርጉና አስነብቡን እባካችሁን፡፡ ለመግቢያ ያህል ይህችን ካልኩ ወደሌላ አንቀጾች ልውረድ፡፡
[ሰበር ወሬ! የዚህ የቅንፍ ወሬ ከምሽት የአምስት ሰዓት የኢሳት ዜና በኋላ የተጨመረ ነው ፤ ቅድም እየጻፍኩ ሳለ እንደሁልጊዜው ሁሉ መብራት ድርግም አለ፡፡ ተናድጄ ወደምሄድበት ሄድኩ፡፡ አሁን ስመለስ ደግሞ መብራት መጥቶ አገኘሁ፡፡ ተመስገን ነው፡፡ በቀን ዘጠኝና አሥር ሰዓት መብራት ማግኘት በራሱ እሰዬው ነው፡፡ በየደቂቃው እኮ ነው ድርግም የሚልብን - እሚጠየቅ አካል የለ፤ ጠያቂ የለ፤ እንዲያው ባጭሩ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የለዬለት ዳፍንት ውስጥ ገብተንላችኋል፡፡ ሥራው በኮረንቲ ላይ የተመረኮዘ ሰው ሁሉ ጉድ ፈልቶበታል፡፡ ለሚደርስበት ኪሣራ ማንን ይጠይቃል? ማንንም! በዚህ ችግር ብቻ ስንቱ ባለድርጅት ሥራውን እየቀነሰ ወይ እየዘጋ ብዙዎች ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው እንደሚሰናበቱ ይነገራል፡፡ ጉዳችን እየተንተከተከ ነው ጎበዝ! እናማላችሁ በአሁኑ ዜና የርዕዮት ዓለሙን የርሀብ አድማ በድጋሚ ከሰማሁ በኋላ ይቺን ቅንፍ መጨመር አሰኘኝ፤ አሰኝቶኝም እንዲቀር አልፈለግሁም፡፡ ያበጠው ይፈንዳ - ኢትዮጵያ በሰላማዊ ትግል ነጻ አትወጣም - እህል ብትተው መኖ ቀነስክላቸው እንጂ ምናቸውም አይጎዳም፡፡ ይህ ዓይነቱን ትግል የምታደርገው አእምሮ ባላቸው በሰለጠኑ መንግሥታትና ሕዝቦች መካከል ነው - እንደኛ ባለው ግዑዛን የመንግሥት ‹ሰዎች› ዘንድ አይደለም፡፡ ምድር ከፍ ሰማይ ዝቅ ቢሉ ኢትዮጵያ በወያኔ ፈቃድ ነጻ ወጣች ማለት በትንሹ አዜብ ጎላ ሰው ሆነች የማለት ያህል ነው - አዜብ ሰው አይደለችማ! የርሷን የባህር ዳር የድህነት ንግግር ያደመጠ መቼም እሷን ሰው ነች ብሎ የሚቀበል ከሆነ ራሱም ሰው ስለመሆኑ የሀኪም ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል - ይህች ዮዲት ጉዲት ያለችበት ድርጅት አመራር እንዴት ሰው ሆኖ እንደሰውም አስቦ ለሕዝብ ሰቆቃ ቅድሚያ ሊሰጥ ይችላል? እንግባባ - ዋናው ነገር ወያኔ በድርድርና በሰላማዊ ትግል ሥልጣኑን አይለቅም - አራት ነጥብ፡፡ በሙስና በተካበተ የሀብት ባህር የሚዋኙ ሰዎች፣ በሚሊዮኖች የደም ውቅያኖስ ውስጥ የተዘፈቁ ሰዎች፣ በጥላቻና በፀረ-ኢትዮጵያ ልክፍት የተመቱ ሰዎች እንዲህ በቀላሉ ለሰላማዊ ትግል ይንበረከካሉ ብሎ ማሰብ ከጅልነትም በላይ ዕብደት ነው፡፡ ወያኔ ማለት ባልጩት ራስ የማፊያዎች ቡድን ማለት ነው፡፡ ማፊያ እንዲያውም ከወያኔ ይሻላል፡፡ ማፊያ በተወሰነ ደረጃ መደማመጥና መግባባት ያውቃል፡፡ ወያኔ ግን ደነዝና በዘረኝነት የሰከረ የወሮበሎች ጥርቅም ነው፡፡ ወያኔን የማያውቅ ብቻ ነው በሰላማዊ ትግል ታግዬ ዴሞክራሲን አሰፍናለሁ የሚል፡፡ ለመሆኑ ከአንበሣ መንጋጋ ሥጋን መንጠቅ የሚችል ማን ነው? ዮሤፍ መርሻ ከግብጽ ለምን ተመለሰ? ያኔ በ84 እነየማነና ገነት ግርማ ለምን ከርቸሌ ወረዱ? ፕሮፌሰር አሥራት፣ አሰፋ ማሩ፣ ተስፋሁን ወርቁ፣… ለምን ተገደሉ? ከ22 ዓመታት በላይ የተሞከረው “ሰላማዊ” ትግል የውኃ ሽታ ሆኖ በህልም ደረጃ የቀረውና የነጻነታችን ጥያቄ እየፈጩ ጥሬ እሚሆነው ለምን ሆነና? በሰላማዊ ትግል ለምን ይቀለዳል? ሰላማዊ ትግል ቢሠራ ኖሮ ዳግማዊ ጉዱ ካሣ ሣሪስ በሚገኝ የኪራይ ቤቱ ተደብቆ እንዲህ ይንጨረጨር ነበር ወይ? ለምን ይዋሻል ነው ያለው ያ ራሱ ዋሽቶ ሰውን ውሸታም የሚል ቀልማዳ ባለመድረክ መላ-ያጣ ሰውዬ? ጎበዝ አንወሻሽ! ወያኔ በምንም መንገድ በሰላማዊ ሰልፍ ወደሚሄድበት አይሄድም፡፡ ጊዜያችሁን አታባክኑ፡፡ ዓለም የማን ሆነችና! ዓለም የውሸታሞችና የአስመሳዮች ናት፡፡ ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ቢወርድ ኖሮ ከግንቦት 97 ወዲህ የወያኔ ታሪክ ልክ እንደቀዳማዊ ወያኔ ታሪክ በታሪክ መዘክር ብቻ በተወሳ ነበር፡፡ አይ፣ የለም፣ ቀልድ በልክ ሲሆን ያምራል፡፡ እንኳንስ በተበጣጠቀ የከበደና የአምባቸው የተለያዩ ቀናት ሰላማዊ ሰልፎች ይቅርና በተባበረ የሚሊዮኖች ሰልፍም ወያኔ ሥልጣኑን ለድርድር አያቀርብም፡፡ ታዲያ መፍትሔው ምን ሊሆን ነው ብሎ መጠየቅ አግባብ ነው፡፡ እንደኔ መፍትሔውም ቢሆን ቀላል ነው - ልክ እንደ አሁኑ በዘርና በጎሣ፣ በብሔርና በአገር ልጅነት ተደራጅተው ሲያበቁ ወታደራዊ ሥልጠና በመውሰድ ጎጣዊና ዘውጋዊ ጦር መዝዞ ወያኔን ‹በሚገባው ቋንቋ ማናገር›፣ በሃይማኖትና በንዑሳን የሃይማኖት ክፍሎች(sectarian divisions) እየተዋቀሩ ወያኔን በየዱር ገደሉ ማርበድበድ፣ በፖለቲካ ፓርቲ ረገድም በ33 ቦታ፣ በ66 ቦታ፣ በ99 ቦታ እንዳስፈላጊነቱም ከነዚህም በላይ እየተቧደኑ በሣምንታዊና በወርኃዊ ፕረስ ኮንፈረንሶችና በራሪ ወረቀቶች አማካይነት ወያኔን በዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ለቀጣዮቹ 1000 ዓመታት እርቃኑን ማውጣት፣ የት አባቱንስና! ስበሳጭ የመፍትሔ ሃሳብ እንዴት እንደሚዥጎደጎድልኝ አትጠይቁኝ… የቅንፍ ሰበር ወሬ እዚህ ላይ አበቃ፡፡ ቀድሞ ወደተጻፈው እንውረድ፡፡]

  1. በተለይ በተረገመችዋ ሀገራችን ኢትዮጵያ የሚሠራ ሰው ሁልጊዜ ይታማል፡፡ ከሞትክና ካልሠራህ አትታማም፡፡ ሥራህ የሚያሳማ ሆኖ ብትታማ፣ የሚያስወቅስ ሆኖ ብትወቀስ መልካም ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ግን ልትወቀስበት በሚገባህ ትሞገስበታለህ፤ ልትሞገስበት በሚገባህ ደግሞ ትወቀስበታለህ፡፡ የሀገራችን ነገር ግራ አጋቢ ነው፡፡ ለዚህ ነው በርዕሴ ላይ የጠቀስኩትን ነገር የጠቀስኩት፡፡ ብትወፍር ዕዳ ነው፡፡ ብትከሳም ዕዳ ነው፡፡ ባትወፍርም ባትከሳም እንዲሁ ዕዳ ነው፡፡ ዝቅ ብለህ፣ ወደታችኛው የማኅረሰብ ክፍል ወርደህም ይሁን ወጥተህ ሁኔታዎችን ስትታዘብ የምታየው አብዛኛው ያሳዝንሃል፡፡ ብዙ ከመማርና ከማወቅም ይሁን ከተቃራኒው የተነሣ ብዙውን ጊዜ የምትታዘበው ነገር ወዴት እየሄድን ነው ያስብልሃል፡፡ መተማማት – ሲለዩ ቡጭቅ ይባላል – መጨቃጨቅ፣ በረባ ባልረባው መጣላት፣ መከዳዳት፣ በማያገባ እየገቡ በሃሜትና በአሉቧልታ ‹ወርቃማ ጊዜ›ን ማባከን … በጣም የተዘወተረ መሆኑን ትረዳለህ፡፡ ብትወፍር ‹ከየት አባቱ አምጥቶ በላና ተመቸው› ትባላለህ፤ ብትከሳ ‹ያ ነገር ገዝግዞ አሰለሰለው› ትባላለህ፤ ባለህ አቋም ብትገኝ ‹ይሄ ሰው እየበላ እየጠጣ ለውጥ የማያመጣው የገደሉ አይቶት ይሆን ?› ትባላለህ፡፡ በሥራህም አለሥራህም የምትታማበት ሀገር ቢኖር የአፍሪካ ቀንድ ነው – ሊያውም ኢትዮጵያ፡፡ ሰው የተጠመደው በሥራ ሳይሆን በወሬ ነው ብለህ እስክታምን ብዙዎቻችን በዚህ አጥፊ መንገድ እየተመምን እንገኛለን፡፡ ጥቂቶች እየሠሩ ሚሊዮኖችን የሚያኖሩባት ሀገር – ኢትዮጵያ፡፡ ሁላችን ብንሠራ የት እንደርስ ነበር?
  2. ዛሬ ጧት ኢሳትን የተመለከትኩት በልቅሶ እየተነፋረቅሁ ነው፡፡ ፕሮግራሙ ተወልደ በየነ የሚያቀርበው የመዝናኛና የማስተማሪያ ‹የጥበብ ቃና› እሚባለው ዝግጅት ነው፡፡ በዛሬው ዝግጅቱ የቀረበው ታማኝ በየነ በጥላሁን ገሠሠ የህመምና የጥበብ ሕይወት ዙሪያ ያሰናዳው በትዝታ ማዕበል የሚያላጋ ግሩም ዝግጅት ነው፡፡ ይህን ፕሮግራም ስመለከት ሰሞኑን ያነበብኳቸው የድረ ገጽ ጽሑፎች ትዝ አሉኝና በተለይ በኢሳት ላይ የሚደረጉ ዓላማቸው ያልገባኝ ዘመቻዎች ላይ እኔም አንዳች ነገር መናገር አለብኝ ብዬ ተነሳሁ፡፡ በዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ ሆኖ አለመፈጠር ምን ያህል ፀጋ ነው ጎበዝ! ‹ያውጡብሽ እምቢ፣ ያግቡብሽ እምቢ› ዓይነት ጉራማይሌ ዘመን፡፡ ይህን ብቻ ብዬ አላበቃም፡፡
  3. ኢሳትን ሰዎች ለምን ጠምደው ያዙት? ይህን ብርቅዬ የሀገር ልጅ ታማኝ በየነን ለምንድን ነው ሰዎች እንደወገብ ቅማል ሰቅዘው የያዙት? ግራ እሚያጋባ ነው ነገሩ፤ ለእኔ ግራ ገባኝ፡፡ ለነገሩ ግራ አያጋባም፡፡ በበኩሌ ቀናሁ፡፡ ምነው እኔም እንደታማኝ አንዳች ነገር ሠርቼ ሰዎች ትኩር ጥምድ አድርገው በያዙኝ አልኩና እውነቴን ነው ለመግለጽ ቃል እስኪጠፋኝ ድረስ በጣም ስቅስቅ ብዬ ቀናሁ፡፡ በኢትዮጵያ ከሠራህ ትወነጀላለህ ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሕዝብን የሚያነቃቃ (የሚያነቃንቅ?) ነገር ከሠራህ ትጠመዳለህ ማለት ነው፡፡ ‹በእግርዎ ገብቼ በራስጌ ብወጣ፤ ከትርንጎ በቀር የለብሁም ጣጣ› ያሉት ሼህ ማን ነበሩ? አዎ፤ በኢሳትና በታማኝ እግር ገብቼ በጭንቅላታቸው በኩል ብወጣ ሰዎችን እንዲህ ሊያንጨረጭር የሚችል አናዳጅ ነገር አጣሁ – መቼስ ኢቲቪን ትቼ እዚያው ተጎልቼ ነው እምውልና ስተኛ ወይም ሥራ ላይ ስሆን ካላመለጠኝ በስተቀር ኢሳትና ታማኝ ይህን ያህል ሀገርን የሚያናውጥ መጥፎ ድርጊት ፈጽመዋል ወይም ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጨራርስ ዐዋጅ አስነግረዋል ለማለት የሚያስችል አጋጣሚ አጣሁ – ባገኝባቸው ከኔም በላይ ተሳዳቢ ላሳር ነው ብዬ የምታበይ ነኝና በወረድኩባቸው – በዚህችስ ማንም አይስተካከለኝ – ዱሮውንስ ሰው በስንቱ ይበደላል – ከሥልጣን ሥልጣን የለኝ – ከሀገር ሀገር የለኝ – ከሀብት ሀብት የለኝ – በድራቦሹ ታዲያ የመሳደብ ችሎታም ልጣ? … ነገር ግን በሌላ አቅጣጫ ስናይ አናዳጅ ነገር ምን ማለት ነው? አናዳጅ ነገር ሲባል በወርድና በቁመት ተለይቶ ሊታወቅ ይችላል ወይ? በሚሉት ጥያቄዎች ዙሪያ ሁሉንም የሚያስማማ የወል መደላድል ላይ መድረስ የሚገባ ይመስለኛል፡፡ አለበለዚያ ለኔ የሚያስደስትኝ ነገር አንተን ሊያናድድ ከቻለ የተለያየንበት ነገር ተፈጥሯል ማለት ነውና ቁጭ ብለን መነጋገር ይኖርብናል ማለት ነው – መነጋገራችን ጥቅም ካለው – ከሌለው ግን እልህን፣ ጊዜንና እንዳስፈላጊነቱም ስድብንና ዘለፋን በማይሆን ዒላማ ላይ በከንቱ ማባከን ነው ትርፉ፡፡ ከዘመድህ ጋር ብትወቃቀስ ተገቢ ነው – በማከያው ትታረቅና ትስማማለህ፡፡ ልትግባባው ከማትችለውና ዐይንና ናጫ ከሆንከው ሰው ጋር መናቆር ግን ኪሣራ እንጂ ትርፍ የለውምና አይመከርም – በግዕዝ ‹ኢይጥዕም መዓር ለአድግ ዘእንበለ እንጉስታር› ይባላል፡፡ አንድ ሰው የሚጥመውን ነገር ቀድሞ ከወሰነና ከውሳኔው ውጪ ምንም ነገር ላይጥመው ምሎ ከተገዘተ ያ ሰው እጅግ አስቸጋሪ ነው፤ ከዚያ ዓይነቱ ሰው ጋር በፍጹም መግባባት ቀርቶ በቅጡ አለመግባባትም እንኳን ላትችል ትችላለህ – በአለመግባባታቸው የሚግባቡ ብፁዓን ናቸውና፤ ሊያጠፋህስ ቢችል ምን ይውጥሃል? በመሠረቱ ዓለማችን የተሞላችው በዚህ ዓይነቱ የተቃርኖዎች ተቃርኖ ነው – አንዳንዱ የተቃርኖ ተቃርኖ ግን የጅል ፍቅር ሆድ ይገትር ዓይነት ከተፈጥሯዊ የግጭቶች ሂደት ወጣ ያለ ነው – እምልክ – ለምሳሌ ሴትና ወንድ አብሮ ቢተኛ ተፈጥሯዊ መሳሳብና ያን መሳሳብም ተከትሎ የሚከሰት ብዙ ነገር  አለ፤ ሴትና ሴት ወይም ወንድና ወንድ ቢተኙስ? ዝርዝር ውስጥ መግባት አይገባም፤ ከግትርና መንቻካ ሰው ጋር የመከራከር ሂደት እንግዲህ ከሁለተኛው የምሳሌየ ነጥብ ጋር የሚገናኝ ትርጉም የለሽ ልፋት ነው ማለት ነው፡፡ በመሠረቱ ይህች ዓለም በ‹binary opposition and polarization› ከአፍ እስከ ገደፏ ጢም ብላ ሞልታ በምትገኝበት በአሁኑ ሁኔታዋ እኔ የምወደውን ሌላው ሰው ሁሉ በግድ ይውደድልኝ ብሎ መሟገት ወይ መጠበቅ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ እንዲያማ ባይሆን ኖሮ የአንዲት ሀገር የሦርያ ዜጎች እንዲህ ዓለምን ጉድ ባሰኘ አሣፋሪ ሁኔታ በኬሚካል መሣሪያ ሳይቀር ሊጨራረሱ ባልቆረጡና ባልተገባቸውም ነበር፡፡ እዚህ እኛው ጋ መለስን በክፉ ስታነሳበት እሚያለቅስና ጦር እሚመዝብህ አለ፤ መንግሥቱን በበጎ ስታነሳበት ጩቤ ሊሰካብህ የሚያሯሩጥህ አለ – በደስታ ጮቤ እሚረግጥም ሞልቷል፤ አፄ ቴዎድሮስን በጥሩ ስታነሳ ገደል ግባ የሚልህ አለ፤ አፄ ዮሐንስን ካማህበት በቴስታ የሚያጋጭህ አለ፡፡ የዚህ ሁሉ መሠረት የዓላማና የጥቅም መለያየት መሆኑ ባይካድም መነሻው እውነትነት አለው ማለት ግን የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ለምን ቢባል እውነት ከጥቅምና ከቡድናዊ የጋራ ዓላማ በእጅጉ ትለያለችና፡፡…
  4. ባለፈው ሰሞን ሰይጣን አነሳስቶ ባስጀመረኝና እኔው በጨረስኩት አንድ መጣጥፍ ብዙ ሰው አስከፍቻለሁ፡፡ እኔ የምጽፈው በመሠረቱ ሰውን ለማስከፋትም ሆነ ለማስደሰት አይደለም፤ ስትጽፍ የሆነ መንፈስ ይመጣብሃል ወይም ይመጣልሃል፤ ያ መንፈስ ሳትወድ በግድህ በምትዘባርቀው ነገር አንዱን ልታስከፋ ሌላውን ልታስደስት ትችላለህ – ይህ ደግሞ የሚጠበቅ ነው፤ ሰዎች ዘንድ ልዩነት አይጠፋምና ልዩነቶችን በቀናነትና በገራምነት ለማቻቻል ወይንም ለመረዳዳት መሞከር ብልህነት ነው – ተስፋ መቁረጥ ደግሞ ጥሩ አይደለም፤ ዛሬን የሚሳሳት ሁሌ እንደተሳሳተ አይኖርምና አንድ ቀን ወደፊት ወይም በቅርብ እንደሚመለስ ማመን ይኖርብናል – ጠላ እምትጠምቅ ሴት ሁልጊዜ ለሁሉም እኩል የሚጥም ጠላ መጥመቅ አይቻላትም፤ ያኔ ታዲያ ብዙም ሳይከፉና ሳይቆጡ እንደ አለቃ ገ/ሃና ‹አይ አንቺ ሴት፣ ዛሬስ ምነው አይጥም ጠላሽ!› ብሎ ቀልዶ ማለፍ ነው፡፡ እኔ እውነት የመሰለኝን እጽፋለሁ፡፡ የምጽፈው ደግሞ ከስሜት እንጂ ከእውነት ብቻ እንዲሆን አይጠበቅም – መጣጥፍ እንጂ የጥናትና ምርምር ዘገባ አይደለምና፡፡ የሀገር ጉዳይ ደግሞ ይበልጡን የሚቆራኘው ከስሜት እንጂ ከእውነት ብቻ አይመስለኝም፡፡ ስሜትና እውነት ደግሞ ለየቅል ናቸው፡፡ በዚያ ልጅ ላይ የጻፍኩት ተናድጄበት እንጂ ግንቦት ሰባትን ወድጄው አይደለም፡፡ ግንቦት ሰባትንም ብወደው የግሌ ጉዳይ ነው፡፡ ማንም ሊከለክለኝ ወይም ሊፈቅድልኝ የማይችል ነገር ነው፡፡ አንዳንዶች በመጣጥፉ አስተያየት መስጫ ላይ እንዳሉኝ ግንቦት ሰባትን አዝየው ብዞር የኔ የግል ጉዳይ ነው – ዋናው ነገር ግን እንዳዝለው የሚያሳምነኝ በቂ ምክንያት የመገኘቱና የት አግኝቼም ላዝለው እንደምችል ማወቁ ነው፡፡ በተረፈ ግንቦት ሰባት ይሁን ጳጉሜ ስምንት የሚያስወድዳቸው ነገር ካለና ቢወደዱ ምን አለበት? የብዔልዘቡል መለያ ከሆኑት ቁጥሮች መካከል 11 ቁጥርን በማፍቀር የሚከንፉለት አሉ አይደለምን? ቀልዱ በቀልድነት ይቀመጥና የሀገራችን ጉዳይ ግን እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ተገንዝቤያለሁ፡፡ … ሆዳችንን ግን ሰፋ እናድርግ ጎበዝ!
  5. ግንቦት ሰባት ለምን ይጠላል? እንዲህ በአንዳንዶች ክፉኛ እንዲጠላ ያደረገውና እኔንም በደራሽ ወንዝ አስተኔ አጣልፎ የግንቦት ሰባት ፍቅረኛ እንደሆንኩ ያስመሰለብኝ ምክንያት ምን ይሆን? ይህ ድርጅት እየሠራው ያለው አንዳች ጠቃሚ ነገር ይኖር ይሆን ወይንስ ሌላ ይህን ታዳጊ ድርጅት እንደማይወዱት በሚነገርላቸው ወገኖች አካባቢ የተደበቀና ለእንደኔ ዓይነቱ ሞኝ ዜጋ ያልተገለጠ አንዳች አጀንዳ ይኖር ይሆን? አንዱ የማውቀው ጸሐፊማ ትናንት ባወጣው አንድ ጽሑፉ ታማኝን በትልቅዬ ውሃ እማያሰኝ ብዕር ሲወግረው ሳይ ‹እንዴ! እንታይ ኢዩ ጉዱ?› አልኩና በጣም ተረበሽኩ፡፡ እነዚህን ሰዎች(እነታማኝን) አላውቃቸውም ማለት ነው? አልኩ፡፡ ታማኝ በርግጥም የትግራይን ሕዝብ በነቂስ ወይ በጅምላ በዕንቁላል ሻጭነት ፈርጆ ከሆነ እኔም በግማሽ ትግሬ በመሆኔ በቁማችን ገድሎናል ማለት ነውና የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ግን አይመስለኝም፡፡ ልጁ ትሁት መሆኑን እረዳለሁና ይቺ ከዐረፍተ ነገር እንደደሮ ብልት እየተገነጠለች የምትወሰድ ነገር ተቃጥታበታለች ማለት ነው – ሰዎች ስንባል የምንጠላውን ሰው በቃላት እሩምታ ድባቅ ለመምታት በማቀድ ምን ያህል ወንጀል ልንሠራ እንደምንችል ሳስበው ይገርመኛል – እንዲህ ስል እኔንም ጨምሮ ነው ታዲያ፤ ከዚያች ቆረጥ እዚያች ላይ ወስደን ለጠፍ እናደርግና ሰውዬው ማለት ያልፈለገውን ወይም ጭራሽ ያላሰበውን እንደተናገረ አስመስለን በሰዎች ዘንድ እናሳጣዋለን – ክፋት ነው፤ ሰይጣናዊነትና ወንጀልም ነው፡፡ Dearest fellow Ethiopians [who are soaked in such nasty game of distortion], please let us begin to be genuine and let us stop harassing words and phrases by detaching them from their context and applying them for the enhancement of an insincere intention to harm innocent people; let us resort to other plausible mechanisms and deploy them to our offensive side if we are overzealously keen to smear the names on our black list. Misusing the meanings of words out of their original context is an abuse of moral principles and it is satanic as well. በዚህ ቃልን በመገነጣጠልና ለሸረኛ ዓላማ ሲባል ከዐውዳቸው ውጪ በማዋል ረገድ ብዙዎች ለጥቃት ዒላማ ሲዳረጉ ይስተዋላል – ፕሮፌሰር መስፍን በዚያ የፋብሪካ ዕቃ ነው ምርት ብለው በተናገሩት ስንትና ስንት ተብለዋል፤ በ97 የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት አቶ በድሩ አደም እንዲሁ ተቦጫጭቀዋል፡፡ ይህ የተንኮል አካሄድ ይቅርብን please!
  6. እውነቴን ነው የምለው አንዱ የምር ወዳጄ በኔ የግንቦት ሰባትና መሪው ዶር. ብርሃኑ ‹ጠበቃነት› ምክንያት ግራ መጋባቱን፣ ከእንግዲህ ማንን ማመን እንደሚቻልም ውዥንብር ውስጥ መግባቱን በአንድ ወዳጄ አማካይነት ስረዳ እኔም ለተወሰነ ጊዜ ግራ ተጋባሁ፤ ዓላማየ ያ ወጣት ብዕሩን እንዲገራ ሆኖ ሳለ ለካንስ ሰዎች ባላሰብኩት መንገድ ተረድተውኛል ማለት ነው፡፡ እኔ በመሠረቱ ተክሌን የተቃወምኩት አካሄዱን እንጂ ተቃውሞውን አልነበረም – እዚያም ላይ ገልጫለሁ – ‹መቃወምን እኔ ቀርቼ ማንም ምድራዊ ኃይል አይከለክለውም› ብያለሁ፡፡ ምናልባት በአነጋገሬ ከራርነት ተክሌን አስቀይሜው ከሆነ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ የግንቦት ሰባትን ገመና ለመሸፈን ወይም ከአግባብ ውጪ ለመደገፍ ያደረግሁት ጥረት ግን በጭራሽ የለም እላለሁ፡፡ በተቃዋሚዎች ጎራ በትግል ሥልት ረገድ ልዩነት መኖሩን አውቃለሁ፡፡ አንድ ሰው ወደሂልተን ለመሄድ ፈልጎ ወደዚያ ከሚወስዱ መንገዶች መምረጥ ቢፈልግ የምርጫው ጉዳይ የራሱ የግሉ ብቻ ይመስለኛል፡፡ በአየር ዘልዬ እደርሳለሁ፤ በመሬት ውስጥ ለውስጥ ቆፍሬ በዋሻ ውስጥ ተጉዤ እደርሳለሁ፤ በሌላ ረጂም አቋራጭ ተሹለክልኬ  እደርሳለሁ… ብሎ ራሱ ይመርጣል እንጂ እኔ በፈቀድኩልህ መንገድ ብቻ ወደሂልተን ተጉዘህ ካልደረስክ መንገድህም የመንገድህ ውጤትም ዜሮ ነው ቢባል እንደ አካሄድ ትክክል አይመስለኝም፡፡ ይህ ሲባል ደግሞ የ‹የትም ፍቺው ዱቄቱን አምጪው› ይትባሃላዊ የመፍትሄ ፍለጋ መንገድ ጭፍን ተከታይ እንዳይደለሁ በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ I would rather prefer the means to justify the end instead of the end to justify the means. ይሁንና ለወጣት ድርጅት ጊዜ መስጠት የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ እኔ ደግሞ ብዙ የማውቀው ነገር የለኝም – አውቃለሁ ብዬ ብገምትም እንኳን በደምባራ ብዕር ብዙ የማይገባኝን (የማያገባኝን አላልኩም!) የፖለቲካ አካሄድ እየዘነኮርኩ አንባቢን የማደናበር ፍላጎት እንዲኖረኝ አልሻም፡፡ ዘመን እየተለወጠ ነው – ታሪካዊ ጠባሳዎችና ጨፍጋጋ ሥነ ልቦናዊ ዳራዎች በዘመኑ ፖለቲካ ላይ ምን ያህል አሉታዊ ጥላቸውን እንደሚያጠሉ ለመረዳት በትንሹ ዝምታንና ትዕግስትን እንደሚጠይቁ እንዲሁ በመንፈስ ይገባኛል፡፡ ለነገሩ ማንም ጮኸ አልጮኸ ሁሉም በመሰለው እየታገለ ባለበት ሁኔታ ትርፉ ትዝብት ማትረፍ እንጂ በዚህ ሂድ በዚያ አትሂድ ብሎ ምክርም ሆነ ተግሣፅ መስጠቱ የሚያዛልቅና ትርጉም ያለውም አይመስለኝም፡፡ ከዚህ ነጥብ አንጻር ስለእንትና ይህን መናገርህ ወይ አለመናገርህ ጥሩ ነው ወይ ጥሩ አይደለም ማለቱና በፍሬፈርስኪ ነገር መበሳጨቱ ያንኑ ያህል ብዙ ዋጋ ያለው አይመስለኝም፡፡ በበኩሌ ስለሚባለው ሁሉ ተጨባጭ ነገር ባውቅ ኖሮ ብዙ በጮሁ – በዚያ ላይ በመታገያ ሰነዱ ላይ ‹ማንኛውንም ዘዴ ተጠቅሜ አምባገነኑን የወያኔ ሥርዓት እጥላለሁ› ብሎ የተነሣን ድርጅት ባይሆን እሱም በለስ ቀንቶት ሥልጣን ሲይዝ ልቡን ያራራልንና የምንናፍቀውን ዴሞክራሲ ያጎናጽፈን ብሎ ከመጸለይ ውጪ የትግል ሥልት ምርጫህ ተሞክሮ የከሸፈ ነው እያሉ ከወዲሁ ማጣጣል ከሁሉም ሳይሆኑ የመቅረት ያህል ተስፋ አስቆራጭ ይመስለኛል – የግንቦት ሰባት መንገድ መጥፎ ሊሆን ይችላል – ግን በማን ዐይን? ከሰሜን የመጣ ዝናብ ሁሉ አጥፊ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ የደረሱ ወገኖች እንደሚኖሩ ባውቅም ገሣ ቢጤ ለመግዛት መጣር እንጂ በአድማስ ክልል ውስጥ ባልታዬ ችግር ያን ያህል መሸበርም ለጊዜው የሚገባን አይመስለኝም – ቢያንስ እኔ ልሸበር አልፈልግም፡፡ …  ብዙዎች ሲጮሁ ግንቦት ሰባት ዝም ማለቱ ግን ብዙም እንዳላስደሰተኝ በዚች አጋጣሚ መጠቆም እወዳለሁ፡፡ ያቺ የኢሕአፓ የብረት ዲስፕሊን ወይም የእባብን ያዬ በልጥ በረዬ ዓይነቷ ነገር ለፀጥታው መስፈንና ለምሥጢሮች መጠንከር አስተዋፅዖ ሳያደርጉ እንዳልቀሩ እገምታለሁ – ዝምታ ደግሞ ሰውን ይረብሻል፤ ያኔ መጯጯህ ቢበዛ አይገርምም፤ እንደኔ ችግሩ ያ ይመስለኛል፡፡ ለማንኛውም ሁሉም ከልኩ አይዘልም፡፡ ግንቦት ሰባት ምን ያህል ለጦርነት ቢሰናዳና ወያኔን በ‹ሚያውቀው ቋንቋ ለማነጋገር ቢዘጋጅ›፣ ፀረ-ግንቦት ሰባቶችም የፈለጉትን ያህል ቢያብጠለጥሉትና በቃላት እሩምታ ቢዋጉትም የታሪክ ሂደት እንደሆነ ከላይ በተወሰነለት ጊዜና ከታች በተመደበለት የሰውና የማቴሪያል ኃይል መጓዙ፣ የመጨረሻውን የወያኔ ግብአተ መሬትም በቅርቡ ማየታችን የማይቀር ነው፡፡ ትዝብት እንዳናተርፍ ግን ሁላችንም ብዙ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ከዚህ በላይ ባላልፍ ደስ ስለሚለኝ ነው እንዲህና እንደሚከተለው የምለው፡፡
  7. አንድ ገበሬ እርሻ ውሎ ሲመጣ ዛፍ ላይ የነበረች አንዲት ጦጣ ‹ገበሬ፣ ምን ዘርተህ መጣህ?› ብላ ትጠይቀዋለች፡፡ ገበሬውም ምኑ ሞኝ የዘራው ባቄላ መሆኑን ልቡ እያወቀ ‹ ተልባ!› ይላታል – እሷ የማትለቅመውን የሰብል ዓይነት መርጦ ማለት ነው፡፡ እርሷስ ብልጥ አይደለች? – ‹ ወርደን እናየዋለና!› ትለዋለች፡፡ እንግዲህ ‹ቂጣም ከሆነ ይጠፋል፤ ሽልም ከሆነ ይገፋል› ነውና ሰሞኑን እየሰማነው ያለነው ነገር የምር ከሆነ ‹ወርደን የምናየው› ይሆናል፡፡ እንደኔ እንደኔ ግን ሁላችንም የአንዲት ሀገር ልጆች እንጂ ባዕዳን ስላልሆንን – አሁንም ልድገመውና – በከንቱ አንጠላላ፤ በከንቱ አንጠላለፍ፡፡ ዘርን መሠረት ያደረገ ወይም ሌላ ሥልጣንንና ጥቅምን መነሻ ያደረገ ጥላቻ ወይ ሥጋት ካለብን ያን በምክክር ለማስወገድ እንሞክር፡፡ መረጃን በመሸቀብ የምንታወቅ ድርጅቶችም ሆንን ግለሰቦች በወቅቱ ተገቢውንና በሕዝብ ዘንድ ቢደርስ ለክፉ የማይሰጥ መረጃን እንስጥ – እርግጥ ነው – ሁሉም መረጃ አይዘከዘክም – ይህንንም በጨዋነት ማስረዳት ይቻላል፡፡ በፍርሃትና በሥጋት የተቀነበበ እጅግ የጠነነ ምሥጢራዊነት ለምሥጢራውያን ዓለም አቀፋዊ የጥፋት ድርጅቶቸም አልበጀም፡፡ ይሄውና ከ500 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ያከማቹት ሀብትና ንብረት የዓለምን ቅርጽ እነሱ በፈለጉት መጠን ሊያስገኝ አልቻለም፡፡ ጥፋት ላይ ጥፋት እየተደረበ፣ ምሥጢር ላይ ምሥጢር እየተደረበ፣ ገብጋባነት ላይ ገብጋባነት እየተደረበ በተደረገው የምዕተ ዓመታት ጉዞ … የዓለም ምጽዓት ቀረበ እንጂ … የዓለም አንጡራ ሀብት በጥቂቶች እየተግበሰበሰ በባንኮቻቸውና ጎተራዎቻቸው ውስጥ አላግባብ ሲከማች በሌላ ወገን ግን ቢሊዮኖች እጅግ ለሚያማቅቅ ድህነት ተዳረጉ እንጂ…  ዓለማችን የጅምላ ጨራሽ ጦር መሣሪያ መሞከሪያ ሆነች እንጂ፣ … ምንም እንኳ የሰው ልጅ ጨረቃንና ሕዋን ቢዳስስም ጉንፋንን እንኳ ማሸነፍ አቅቶት ይሄውና አጠቃላይ ዕልቂቱን እየተጠባበቀ ነው፡፡ ሰው በወደደው ይቆርባልና በሠራነው ልንጠፋ የቀረን በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፡፡ እመኑኝ፡፡ የምታውቁትን ስነግራችሁ አትዘባበቱ፡፡ የኛ ቀን ግን ይመጣል፡፡ ከንፍሮ ጥሬ የሚያወጣ አምላክ ሀገረ ኢትዮጵያን የሰው ዘር መሸሻ ሳያደርጋት አይቀርምና ይልቁንስ ከእስካሁኑ ስህተታችን እንማር፡፡
  8. እናም ምቀኝነታችንን አሁኑኑ እንተው – በአንዴ ልንተው ባይቻለን እየቀነስነው እንሂድ፤ መተሳሰባችንን እንመልስ – የሚሻለን እርሱ ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ገንዘብ ለማግኘት ሲል በተለይ ወጣቱ ትውልድ አቅሉን ስቶ እየተራወጠ ነው – በህጋዊ መንገድ ሠርቶ እንዲያልፍለት ቢተጋ እሰዬው ነው፡፡ ግን ብዙው ዜጋ የሰው ሥጋ የመጋጥ ያህል በህገወጥ ንግዶችና በስንጥቅ ትርፍ የድሃውን ገንዘብ እየቀማ ኢትዮጵያ ለአንዱ ገነት ለሌላው ሲዖል እየሆነች ነው፡፡ መተያየትና መተሳሰብ ቀርቷል፡፡ ኑሮው በየቀኑ እያሻቀበ አብዛኛው ዜጋ በመኖርና ባለመኖር የሕይወት ውጣ ውረድ ተወጥሮ ይገኛል፡፡ ዱሮ ለበዓል በግና ዶሮ ይገዛ እንዲሁም ቅርጫ ይገባ የነበረ ዜጋ ዛሬ የዶሮና የዕንቁላል ስዕልም መግዛት የሚያስችል ገንዘብ የለውም፡፡ የገንዘቡ የመግዛት አቅምም ላሽቆ አንድ መቶ ብር እንደክፍልፋይ ሣንቲም የሚቆጠርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፤ አንዳንድ ዜጎች ግን ብሩን ከጓሮ ባህር ዛፍ ይሸመጥጡት ወይም ከቻይና በኮንቴነር ያስመጡት እስኪመስል ድረስ ሲመነዝሩት ሲታዩ ለጉድ ነው፡፡ የስሙኒ ዶሮ 200 ብር፣ የስሙኒ ቤንዚን ሃያ ብር፣ የስሙኒ ቢራ ሃያና ሠላሳ ብር፣ የስሙኒ ቲማቲም 30 ብር፣ የስሙኒ የሉካንዳ ቤት ሥጋ 150 ብር፣ የስሙኒ ዕንቁላል 100 ብር፤ የስሙኒ የምግብ ቅቤ 200 ብር፣ የስሙኒ ጋዝ 15 ብር፣ የስሙኒ ክትፎ 100 ብር፣ የስሙኒ ቀይ ወጥ 70 ብር፣ የስሙኒ የምግብ ዘይት 80 ብር(ሃቱም የሚሉት)፣ የስሙኒ ታክሲ አሥር ብር፣ የስሙኒ ባለ18 ካራት ወርቅ 300 ብር(ማነጻጸሪያየ ግራም ሳይሆን ስሙኒ መሆኑን ልብ አድርጉልኝ) …. ይህ ሁሉ ውርጅብኝ በሀገር የታወጀው በእኛ ስግብግብነትና ከፈጣሪ ትዕዛዛት መውጣት እንጂ ሀገራችን የጎደላት ነገር የለም፡፡ ፈጣሪ ፊቱን ቢመልስልን የአንድ ላም ወተት ለሀገር የሚበቃበትን ጊዜ ለማየት የማንችልበት ምክንያት የለም፡፡ …
  9. ወያኔን ለማስወገድ ከመነሳታችን በፊት ከላያችን ላይ ገፍፈን መጣል ያለብን ብዙ ደካማ ጎኖች አሉብን – በግለሰብም በማኅበረሰብም ደረጃ፡፡ አንድ ሕዝብ ከሚገባው በታችም ሆነ በላይ መንግሥት አያገኝም የሚባለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አባባል እውነት መሆኑን የምናረጋግጥባቸው በርካታ ምልክቶች በሀገራችን በስፋት ይታያሉና እነሱን ከሁሉም በፊት ማስተካከል ይኖርብናል፡፡ መጽሐፉ እንዲህ ይላል፡- ‹በራስህ ዐይን ውስጥ የሚገኘውን ዕርፍ እሚያህል ጉድፍ ሳታወጣ በጓደኛህ ዐይን ውስጥ የሚገኘውን ስንጥር እሚያህል ጉድፍ ለማውጣት አትሞክር›፡፡ ከመጠን ባለፈ ጥላቻ የተጠማመድን ዜጎች ሞልተናል፤ የምንጠላው ሰው ምንም ዓይነት መልካም ነገር ቢያደርግ የማይጥመን ዜጎች በሚሊዮን እንቆጠራለን፡፡ ጥላቻን በፍቅር ካልለወጥነው ባለንበት እየረገጥን አንዱን ወያኔ ሸኝተን ሌላውን ወያኔ እንቀበላለን እንጂ የምንመኘውን መልካም አስተዳደር አናገኝም፡፡ ጥላቻ ለብዙ ነገሮች እንቅፋት ነው፡፡ ጥላቻ በፈረንጅኛው arrogance, ignorance, bias, prejudice … ከምንላቸው የኔጌቲቭ ኢነርጂ ምድብ የሚወለድ የዕድገት ፀር ነው፡፡ የሰው ልጅ ከአካላዊ የሦስተኛ ዳይሜንሽን ኑባሬው ወደመንፈሣዊ ልዕልናው እንዳያቀና የዕድገቱ ፀር የሆኑትን እነዚህን ደንቃራዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ያሸነፈ አንድ ሰው ነበር – በ33 ዓመቱ ገደሉት፡፡ ገዳዮቹም አልተጠቀሙም ፤ እኛም በተጨናገፈው ዕድገታችን ምክንያት ተጎዳን፡፡ ከዚያ ሰው ኅልፈት በኋላ በተለያዬ ጊዜና ዘመን የመጡ ጥቂት ብፁዓንና ንዑዳን ሰዎች ቢኖሩም የፖለቲካ ሥልጣንና የሀብት ጉጉት በማረካቸው የሰው ልጆች አሰናካይነት ምክንያት መልካም ምኞታቸው ሳይሳካና ወደሚገባቸው የአመራር ደረጃም ሳይወጡ በአጭር ተቀጭተዋል ወይም ሃሳባቸው ተቀባይነት ሳያገኝና ዳር ሳይደርስ ወደሌላው ዓለም አልፈዋል፡፡ እነ ማኅተመ ጋንዲ፣ እማሆይ ተሬዛና ኔልሰን ማንዴላ በዚህ የብርቅዬ ዜጎች ማዕቀፍ ውስጥ ይካተታሉ፡፡

ወያኔን ለማስወገድ በቅደሚያ ከወያኔ በኋላ እንዲመጣ ለሚፈለገው ማኅበራዊ ሥርዓት ዝግጁ የሆነ ስብዕናን መላበስ ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ አሮጌውን ወይን በአዲስ አቅማዳ እንደመጨመር ዓይነት ይሆንና አዲሱ አቅማዳ በአሮጌው ወይን ተቦጫጭቆ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ወጡ ሳይወጠወጥ በስደትም ሆነ በሀገር ቤት ውስጥ በሚገኙ ተቃዋሚዎች ዘንድ ይህን ያህል ፉክቻና የጥላቻና የንትርክ አባዜ የሠፈነው እንግዲህ አሮጌው አስተሳሰባችን ወደአዲሱ አስተሳሰባችን ለመስረግ ያለውን ቆራጥ አዝማሚያ ያሳያል፡፡ እንደዚያ ካልሆነ ግንቦት ሰባትና ኢሕአፓ ወይም አርበኞች ግምባርና ሌሎች የተቃዋሚ ኃይላት ለምን አብረው አይሠሩም? ይሄ ሁሉ መቶና መቶ ሃምሳ የፖለቲካ ስብስብ ለምን አስፈለገ? በሬው ባልተገዛበት ሁኔታ በረቱ በሌቦች መወረሩ ምንን ያመለክታል? የሥልጣን ጉዳይ ነው ወይንስ የዓላማ? የዓላማ ልዩነት አለ ከተባለ እስኪ ይነገረንና እንወቀው? ሀገር በመዥገር ተወርራ በስደት ላይ ይህን ያህል የተቃዋሚዎች መወራከብ ምን ይባላል? እንበልና ወያኔ በራሱ ፈቃድ ሥልጣኑን ቢያስረክብ የአሁን ተቃዋሚዎች የነገ ሥልጣን ተረካቢዎች አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ሳይደርሱ መስቀል አደባባይ አካባቢ እርስ በርስ ይጨራረሳሉ ማለት ነው? ምን ዓይነት መርገምት ነው? ይህን የብልጥነት ይሁን የሞኝነት ፈሊጥ ምን እንበለው? … እጅግ ብዙ ተቃዋሚዎች፣ እጅግ ብዙ የሲቪክ ማኅበረሰብ ማኅበራት፣ እጅግ ብዙ ታዋቂ ግለሰቦች፣ እጅግ ብዙ ፎረሞች፣ እጅግ ብዙ እንትኖችና እገሌዎች በየቀኑ እየከረረ ከሚሄድ ጭቆናና የሀገር ውድመት መች ነጻ አውጡን? የምን በሀገር መቀለድ ነው? ለመሆኑ ተቃዋሚዎች ሕዝቡን ያውቁት ይሆን? እርግጠኛ ነኝ – ከእኛ ችግር ይልቅ የነሱን መናቆር ነው በሚገባ የሚያውቁትና ዋናውን ትኩረታቸውንም የሚሰጡት፡፡ ስለዚህ ለውጥ ከመሻታችን በፊት አስቀድመን እኛ ሰው ለመሆን እንሞክር የምለው ለዚህ ነው፡፡ አንድ ሰው፣ ሰው ከሆነ በኋላ – ማለትም እንደሰው ማሰብ ከጀመረ በኋላ የሚያጣው ነገር የለም፡፡ አሁን ግን እኛ ተጨቋኝ የምንባለውም እነሱ ጨቋኝና በዝባዥ የሚባሉትም ሁላችንም ሰው መሆን ስላቃተን ይሄውና ድንበር ለሌለው መሪር አገዛዝና ሥነ ልቦናዊ ቀውስ ተዳርገን እንገኛለን፡፡ ወያኔዎችም ተመችቷቸው የሚኖሩ እንዳይመስለን፡፡ ከእኛ የበለጠ በጭንቀትና በፍርሀት እንዲሁም በሰቀቀን እየተሰቃዩ የሚኖሩት እነሱው ናቸው፡፡ የመጨረሻውን የታሪክና የፈጣሪ ፍርድ ያውቃሉና፡፡

አሁን ሕዝቡ እንዴት ነው እየኖረ ያለው? በብዙ ነገሮች አፍራለሁ፡፡ ብዙዎቻችን ከሰውነት ተራ ወጥተናል፡፡ ከሞራልና ከእምነት ወይም ከሃይማኖት መርሆዎች ወጥቶ እንደልቡ እየፈነጨ የሚኖረው ዜጋ ቁጥር የትዬለሌ ነው፡፡ አብዛኛው ወጣት ለሱሶች ተዳርጎ የነገይቷ ኢትዮጵያ አየር ላይ ተንሳፍፋ እንዳትቀር ያሰጋል – በሁሉም ረገድ ተረካቢ የሚሆን ጤናማ ዜጋ እየጠፋ ነው፡፡ ማይምነቱ አናታችን ላይ ወጥቶ እየፈነጨብን ነው፡፡ ስግብግብነትና ሆዳምነት የጊዜያችን ፋሽን ሆነው በሀገር ሲወረር አብረህ ውረር ፈሊጥ የምትበላ ነገር ስትገኝ ሁሉም እየተረባረበ የሀገር ሀብት እየተመናመነ ነው፡፡ መሬት ተቸብችቦ ሊያልቅ ምንም አልቀረው፡፡ ባለሥልጣናት ብቸኛ ዘመዳቸው ሆዳቸው ሆኗል፡፡ ያለ ጉቦ የሚፈጸም አንድም ነገር የለም፡፡ የሀብት ምንጩ ምን እንደሆነ ባላወቅኸው ሁኔታ የማይናቅ ቁጥር ያለው የኅብረተሰብ ክፍል በአንድ አዳር እንደሮኬት ሲወነጨፍ ታያለህ፡፡ የመኪናውን ብዛት ስታይ፣ የንግዱን እንቅስቃሴ ስትመለከት፣ የጮማ ቆራጩን የውስኪ ጨላጩን የዳንኪራ ረጋጩን ምዕመን ዕለታዊ የአሥረሽ ምቺው ሕይወት ስትታዘብ በ‹የት ነው ያለሁት?› ክፉኛ ልትጨነቅ ትችላለህ፤ አዲስ አበባ እየኖርክ ፓሪስ ላይ ያለህ ሊመስልህ ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ የዕንቆቅልሽ ሀገር ሆናለች፡፡ በሌላ ወገን በየአደባባዩ የሚርመሰመሰውን ድሃና ቁርስ በልቶ ምሣና እራት የማይደግም ምሥኪን ዜጋ ስታይ ጭንቅላትህ በጭንቀት ሊፈነዳ ይደርሳል፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህ ህልም-እውናዊ ዕንቆቅልሽ ልትወጣ የምትችለው ታዲያ ዜጎች ቁጭ ብለው ‹በርግጥ እኔ ሰው ነኝን? በእውነቱ የቀድሞዎቹ ትሁታንና እርስ በርስ በመተዛዘን የሚታወቁ ኢትዮጵያውያን ትውልድስ ነኝን? ብለው ማሰብ ሲጀምሩ ነው፡፡ ልክ እንደ እስካሁኑ በራስህን አድን የአህያ ፍልስፍና ከተመራን በሰውኛ አስተሳሰብ ሀገሪቱ መቅኖ አጥታ እንደምትቀር መገንዘብ አይቸግርም፡፡ ስለዚህ ሀገራዊ ነጻነትን ከማሰባችን በፊት እያንዳንዳችን ነጻ መውጣት አለብን፤ ነጻ ያልወጣ ስብዕናና አስተሳሰብ ተይዞ ስለነጻነት ማሰብ አይቻልም፡፡ የምቾቱ ባሪያ የሆነ ሰው ነጻነትን አያውቅም፤ ነጻነት ሊኖረውም አይችልም፡፡ በጥቅም የተከፋፈለን ሕዝብ፣ በአመለካከት የተወነዣበረን ሕዝብ፣ በማይምነት ጥቁር መጋረጃ የተሸበበን ሕዝብ ነጻ የምታወጣው ከምንድን ነው? ነጻ አውጪውስ ማን ነው? ነፍስንና ኅሊናን በሚያቆሽሹ ተግባራት የበሰበሰና ሰውነቱ በሙስና የጨቀዬ ሰው – ተጸጽቶ ከልቡ ንስሃ ካልገባ በስተቀር – ራሱ የክፋት ባሪያ ሆኖ ሳለ ሌላን ሰው ነጻ ሊያወጣ አይቻለውምና በዚህ ረገድ መጠንቀቅ የሚገባን ወገኖች ጊዜ ሳናባክን ወደዬኅሊናችን እንመለስና ለኛም ለሀገርም የሚበጀውን እናድርግ፡፡ ለማንኛውም ከከሃዲነት፣ ከሀሰተኝነት፣ ከሌብነት፣ ከመረንነት፣ከዋልፈሰስነት፣ከሸፍጠኝነት፣ ከጨካኝነት፣ ከመተተኝነት፣ ከጠንቋይና አስጠንቋይነት፣ ከፍቅረ ንዋይ፣ ከጥላቻ፣ ከሃይማኖት የለሽነት፣ ከዘረኝነት፣ ከኋላቀር አስተሳሰብ፣ ከሆዳምነት፣ ከሙሰኝነት፣ ከማይምነትና ከአላዋቂነት፣ ከግብዝነት፣ ከግልብነት፣ ከሸረኝነት፣ ከራስ ወዳድነት፣ ከአስመሳይነት፣ከአድርባይነት፣ ከምቀኝነት፣ከአጭበርባሪነት፣ ከቅናት፣ ከህገ-ወጥነት፣ ከህግ-አልባነት፣ ከወንዘኝነት፣ ከጎጠኝነት፣ ከሥርዓት አልበኝነት፣ ከትምክህት፣ ከትዕቢት፣ ከዕብሪት፣ ከጉረኝነት፣ከዝምድና አሠራር፣፣ ከንፉግነት፣ ከስግብግብነት፣ ከሞራለቢስነት፣ ከአመፀኝነት፣ ከሴሰኝነት፣ ከአመንዝራነት፣ ከሰካራምነት፣ ከቃሚነት፣ ከዕፀኝነት፣ ከስንፍና፣ ከግዴለሽነት፣ ከባዶነት ስሜት፣ ከግልፍተኝነት፣ ከተሳዳቢነት፣ ከአሽሙረኝነት፣ … ከነዚህ እሥር ቤቶች ባፋጣኝ ራሳችንን ነጻ ካላወጣን አይደለም ወያኔ አፄ ቦካሣና ኢዲያሚን ዳዳም ሲበዙብን ነው – ለወያኔ ሌባ ጣታችንን ስንቀስር ሦስቱ ጣቶቻችን ወደኛ ማመልከታቸውን ልብ እንበልና ከአርቲፊሻል ሕይወት ወጥተን እውነተኛ ሰውኛ ሕይወት ለመኖር የፈጣሪን ረድኤት እንጠይቅ፤ አለበለዚያስ አልጠፋንም ብለን ልንዋሽ አይገባንምና ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን በሚገባ ጠፍተናል፤ ተለያይተንማል፡፡ ተለያይቶና ጠፍቶ ደግሞ ነጻነትን መመኘት የሚቻል አይደለም፤ ህልምና ቅዠት ነው፡፡ የሚመጣው መሪ ሁሉ የኛ ነጸብራቅና የማንነታችን ቅጂ መሆኑን አንርሳ፡፡ ያልዘሩት አለመብቀሉ የታወቀ ነው፤ እናም ወያኔን ማማረራችንን ወደጎን ትተን ራሳችንን እንፈትሽና የንጹሕ ኅሊና ባለቤቶች ለመሆን እንትጋ፡፡ ‹ቤታቸውን ከፍተው ሰው ሌባ ይላሉ› አለ አሉ አንዱ ሣተና ሌባ፡፡ ቸር ያሰንብተን፡፡

 

የሚከተለውን ቆንጆ አባባል ያገኘሁት አንድ ጽሑፍ ሳነብ ነው፡፡ ደስ አለኝና ከነአማርኛ ትርጉሙ ከዚህ በታች አስቀመጥኩት፡፡ ተመልከቱትና አንዳች ግንዛቤ ጨብጡበት፡፡ ማንበብ ሙሉና ጎደሎ ሰው ያደርጋል – እንዳንባቢውና እንደተነባቢው ጽሑፍ፡፡

Here is to the crazy ones, the misfits, the rebels, the trouble makers, the round-pegs in the square holes… the ones who see things differently – they are not fond of rules… you can quote them, disagree with them, glorify or vilify them, but the only thing you can’t do is ignore them because they change things … they push the human race forward, and while some may see them as the crazy ones, we see genius, because the ones who are crazy enough to think that they can change the world, are the ones who do.

Steve Jobs, US Computer Engineer and industrialist

 

በማኅበረሰባችን ውስጥ ዕብዶች የምንላቸውን፣ በጋጠወጥነት የምንፈርጃቸውን፣ በአማጊዶነት(ወሮበልነት) የምንኮንናቸውን፣ በችግር ፈጣሪነታቸው ምክንያት የምንታወክባቸውን፣ ነጭን ጥቁር ጥቁርን ነጭ ብለው ድርቅ ካሉ የሚመለልሳቸው አንዳችም ምድራዊ አመክንዮ የማናገኝላቸውን መንቻካና ልበ ሥውራን ወገኖቻችንን፣ … እኚህን መሰል ነገሮችን በተለዬና በራሳቸው አቅጣጫ ብቻ ማየት የሚፈልጉ አፈንጋጭ ዜጎችን በሚመለከት መናገር የሚቻለው የሚከተለውን ነው፡- ሕግና ደንብ አያከብሩም – የሕግጋት መኖር አለመኖርም ደንታቸው አይደለም፡፡ … ብዙ ዋቢዎችን እየጠቀስክ ልትከራከራቸው ትችላለህ፤ በዚህ ጥረትህም ላትግባባቸው ትችላለህ፤ ይህን ጥረትህን በተመረኮዘም ልታከብራቸው ወይም ልታንቋሽሻቸው ትችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ልታደርገው የማትችለው ነገር ቢኖር እነሱን ችላ ብለህ ማለፍ ወይም በተራ አነጋገር ‹መዝጋት› ነው፤ ምክንያቱም የነገሮችን ሂደት በመለወጥ ረገድ ያላቸው ተፅዕኖ የወሳኝነት ያህል የሚሆንበት አጋጣሚ ብዙ ነውና፡፡ (የናቁት ‹ወንድ› ያስረግዛል ዓይነት መሆኑ ነው፡፡) … ከነዚህ አፈንጋጭና ወፈፌ መሰል የማኅበረሰብ አባላት መካከል የተወሰኑት የሰውን ዘር በክፉም ይሁን በበጎ ነገር ከነበረበት ሁኔታ ወደተለዬ አቅጣጫ የመግፋት አቅምና ችሎታ አላቸው፤ ምንም እንኳን አንዳንዶች እነዚህን ዜጎች እንደዕብድና ወፈፌ ቢቆጥሯቸውም ከነሱው ውስጥ ዓለምን መለወጥ እንደሚችሉ የሚያምኑና በርግጥም መለወጥ የሚችሉ የታላቅ አእምሮ ባለቤቶችንም ማግኘት ይቻላል፡፡


የሳውዲ መንግስት በኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ላይ እየፈፀመ ያለውን ኢሰብኣዊነት አጥብቀን እናወግዛለን!!!

$
0
0

መድረኩ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ህዝቡ በነቂስ እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን!

ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) የተሰጠ መግለጫ

         ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ድብደባ፣ ግድያና በጅምላ ማጎር ከኢሰብአዊነቱም በላይ የሳውዲ መንግስት ለዜጎች ያለው ክብር በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የሚያሳፍር ድርጊት  ነው፡፡ በኢትዮጵያዊነት ክብር ላይ የተሰነዘረ ጥቃትም ነው፡፡ በኢትዮጵያውያን ሉአላዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል ሲሆን ዜጎቻችን በጭካኔ ሲገደሉ፣ ሲፈነከቱ ሲታጎሩና ሲገረፉ ማየት አንገት ያስደፋል፡፡ በአንድ አፋኝ ስርዓት ውስጥ የምንገኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በላይ ምን እንላለን?

ይህ በሳውዲ መንግስት ደፋርና ኋላ ቀር የሆነ ድርጊት የኢህአዴግን መንግስት የዲፕሎማሲ ተፅዕኖ መፍጠር ድክመት ከመግለፁም በላይ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ያለውን ደንታቢስነት ይመሰክራል፡፡ ድሮስ በመልካም አስተዳደር እጦት ፍትህን ከተነፈገ፣ በሙስና ከተጨማለቀና በፖለቲካ ስልጣን ለመቆየት ቆርጦ ከተነሳ የስልጣን ኃይል ምን ይጠበቃል? ዜጎችንና ሃገሪቱን ያስደፍደራል፣ የሉኣላዊነትን ክብር ያስነካል፡፡

        የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ የኢህአዴግ መራሹ መንግስት የተሳሳተ ፖሊሲ እየፈጠሩ ካሉት ችግሮች አንዱ ማህበራዊ ቀውስ መሆኑን ገጠዋል፡፡ ዜጎች ተስፋቸው ጨልሞ እየታያቸው ነው፡፡ ተስፋ ያጣ ዜጋ ተስፋ ይቆርጣል፡፡ በተወለደበት ቀየና ሃገር የኑሮ እምነትና ዋስትና የሌለው ዜጋ ሞት እየሸተተውም ይሰደዳል፡፡ በአገራችን ስራ አጥተው ስራ ፍለጋ ሲንከራተቱ በሰው ሃገር በረሃ ሰብአዊ ክብራቸው ተዋርዶ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎችን ዜና መስማት በኢህአዴግ  አገዛዝ የተለመደ ሆኖአል፡፡ በጣም የሚያሳፍረው ኢህአዴግ እነዚህን ዜጎች “ህገ  ወጥ ስደተኞች “ በሚል ፍረጃ ለመብታቸው ለመቆም ቁርጠኝነት የሚጎድለው መሆኑም ጭምር ነው፡፡

መድረክ ዜጎቻችን የሚሰደዱበት የተሻለ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ፍትህ  ፍለጋ እንዲሁም አሰቃቂ የሆነውን የአንድ ፈላጭ ቆራጭ አምባገነናዊ ፓርቲ የፖለቲካ አስተዳደር ሽሽት መሆኑን ይገነዘባል፡፡

በተደጋጋሚ እንደገለፅነው ዜጎቻችን ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅና አውሮፓ ለመሰደድ በባህር፣ በበረሃና በጫካ ውስጥ ተቀጥፈው ቀርተዋል፡፡ የዚህ አንገት አስደፊ ዜና ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ እንጂ ሲቀንስ አይታይም፡፡ በለስ ቀንቷቸው ባህሩን፣ በረሃውንና የዱር አውሬውን አልፈው ማረፊያዬ ብለው ያሰቡበት አገር የሚደርሱትም ሌላ ግፍና በደል ይጠብቃቸዋል፡፡ ሃገራዊ ውርደትና ሞት ከተበላሸ ስርዓትና ፖሊሲው የሚፈጠር እንደመሆኑ የችግሩ ምንጭ ኢህአዴግ መሆኑን እናምናለን፡፡

መድረክ ይህ ሁሉ ውርደት የሚደርቀው የችግሩ ምንጭ ሲነጥፍ ነው ብሎ ያምናል፡፡ የችግሩ ምንጭ ደግሞ ኢህአዴግ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ፓርቲና መንግስት ላይ ህገ – መንግስታዊና ሰላማዊ የሆነ ተፅኖ በመፍጠር ስርአቱን መቀየር ወሳኝ መሆኑን ያምናል፡፡ ህዝቡ አንድነቱን በማጠናከር በጋራ እንዲንቀሳቀስ ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል፡፡

በሳውዲ አረቢያ የመንግስት ኃይሎች በዜጎቻችን ላይ በተፈፀመው ሰብአዊነት የጎደለው ድርጊት ላይ የመድረክ አቋም፡-

  1. በዜጎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት በአስቸኳይ እንዲቆም፤
  2. ለተፈፀመው አስነዋሪ ወንጀል ተጠያቂው አካል ተለይቶ ለህግ እንዲቀርብ፣ ለተጎጂዎችም ካሳ እንዲከፈል፤
  3. ለተፈናቀሉ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታና መስራት የማይችሉት ተለይተው በክብር ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ፡፡ መስራት የሚችሉና ፈቃድ የሚያገኙቱ ሰብአዊ ክብራቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ እንዲረግ፤
  4. የኢህአዴግ መንግስት በጉዳዩ ላይ ለሕዝብ ሰፊ ማብራሪያ እንዲሰጥና ከሳውዲ መንግስት ጋር ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት በመፈተሽ ጠበቅ ያለ አቋም እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡ በዚህ ድርጊት መባባስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና በሳውዲ የኢትዮጵያ አምባሳደር /ቆንስላ  ጽ/ቤት ተጠያቂዎች ሲሆኑ ይህም ስልጣን የሚሰጠው በችሎታና ለወገን ባለው ተቆርቋሪነት ሳይሆን በፓርቲ ታማኝነት እንደሆነ እየመሰከረ ያለ ጉዳይ መሆኑን ነው፡፡
  5. አለምአቀፍ የሰብአዊና የዲሞክራሲ ተቋማትም ይህን አሳፋሪ ተግባር ህግና መንግስት ባለበት አገር እየተፈጠረ መሆኑን እንዲያስተጋቡ፡፡ ጉዳዩን ለአለም እያደረሱ ያሉትን ታላላቅ ሚዲያዎችን በዚሁ አጋጣሚ ለማመስገን እንወዳለን፡፡
  6. መድረክ ድርጊቱን ለመኮነን በቅርቡ አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግና ለማስተባበር ወስኗል፡፡ ቀኑን በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚያሳውቅ ሲሆን አጠቃላይ ሕዝቡ፣ ደጋፊዎችንና አባላት፣ በአገር ውስጥ የምትገኙ የተቃውሞ ጎራው የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ነፃ ነን የምትሉ የሲቪክ ማህበራትና የኢህአዴግ አባላት ሁሉ በሚገለጸው ዕለት፣ ቦታና ሰዓት በመገኘት ድርጊቱን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ለማውገዝ ትገኙልን ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

                             ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)

                                       ኅዳር 04 ቀን 2006 ዓ.ም

medrek

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ! (የመጨረሻ ‹መጣጥፍ›)

$
0
0

ይነጋል በላቸው (yinegal3@gmail.com)

የመጽሐፉ ርዕስ፤   “የካድሬው ማስታወሻ”

“በደርግና በኢሕአዴግ አገዛዝ ውስጥ ከተራ ወታደርነት እስከ የጦር መኮንንነትና የፖለቲካ ካድሬነት የተደረገ ትግል …”

ደራሲ፤                   አስረስ ገላነህ ብዙነህ (ሻምበል)
የኅትመት ዘመን፤    ሐምሌ 2005ዓ.ም
የገጽ ብዛት፤            271
አርታዒ፤                በስም ያልተጠቀሰ (ግን እጅግ በጣም ጎበዝ ሰውዬ!)

 
የካድሬው ማስታወሻበሀገራችን የወቅቱ የፖለቲካ ትኩሣትና የትኩሣቱ መንስኤዎች ላይ በርካታ መጻሕፍት ረዘም ካለ ጊዜ ጀምሮ ለኅትመት እየበቁ ናቸው፡፡ ጊዜ ያለን ሰዎችም እንደየፍላጎታችንና እንዳለን ጊዜ ማንበብ የምንችለውን ያህል እያነበብን በ‹ጉድ ነው!› አጃኢበትም እየተደመምን አለን፡፡ ከመሳጭነቱ የተነሣ በዛሬዋ ዕለት በግማሽ ቀን ብቻ አንብቤ የጨረስኩት ከፍ ሲል የተገለጸው መጽሐፍ ከቅርብ ዓመታት የመጻሕፍት ንባቤ በስሜት ቆንጣጭነት ወደር አላገኘሁለትም፡፡ ጸሐፊውም አርታዒውም ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፤ ዘራቸው ይለምልም፡፡ የዘመናችን ወያኔ-ወለድ ፖለቲካ ያመጣብንን መርገምት አብዛኛውን የሚያጋልጥ በመሆኑ በታሪካዊ መዝገብነት መጪው ትውልድ ሊዘክረው የሚገባው ድንቅ ሥራ ነው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ነን የሚሉ አማርኛ ቋንቋን ማንበብ የሚችሉ የሀገሬ ዜጎች ሁሉ ባሉበት ይህን መጽሐፍ እንዲያነቡት ወገናዊ ጥቆማየን በታላቅ አክብሮትና ትህትና አቀርባለሁ፡፡ ብዙዎቻችን በአነስተኛ መጣጥፎችና ጦማሮች ስናትተው የከረምነውን ፀሐይ የሞቀው እውነታ በመጽሐፍ መልክ – ሊያውም ፈረንጆቹ “from the horse’s mouth” እንደሚሉት ከራሱ ገጠመኝ ጨልፎ ከሚያቀርብልን ተንከራታች ዜጋ በሚጥም አቀራረብ ታገኙታላችሁና በጥቆማየ እንደምትደሰቱ አልጠራጠርም፡፡ ብዙ የተደከመበት የአእምሮ ውጤት በመሆኑ መነበብ የሚገባው ነው፡፡ (ይህ ጽሑፍ የይነበብ ጥቆማ እንጂ የመጽሐፍ ቅኝት ወይም ትችት አይደለም!)

 

የምንገኝበት የእርግማን ዘመን እያበቃ እንደሆነ በበኩሌ ይሰማኛል – በዚያውም ላይ ‹ስድስተኛውን የስሜት ሕዋስ› በከንቱ ተሸክሜ የምዞር ገልቱ እንዳልመስላቸሁ!! አቅል አጥተን እንዲህ  በሀብትና በሥልጣን ራሳችን ያበድንበትና ሌሎችን ያሳበድንበት ዘመን ሊያከትም የቀረን ጊዜ በጣም ጥቂት ይመስለኛል፡፡ ሊነጋ ሲል መጨላለሙን በገሃድ እየተመለከትን ነው – በአሁኑ ወቅት ጨለማው ከፍቷል፤ ዐይንን ቢወጉ ጭራሽ የማይታይ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ነን፡፡ አቅጣጫውን በውል ለይቼ አላውቅም፤ ነገር ግን እየነጋና የብርሃን ብልጭታ እየታየኝ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ በታትኖ በዓለም ሕዝብ ዘንድ መሣቂያና መሣለቂያ ያደረገውን የወሮበሎች መንጋ ፈጣሪ ከአናት ጀምሮ ቀስ በቀስ ግን በፍጹም ሊጨናገፍ ወይ ሊስተጓጎል በማይችል ሁኔታ ብትንትኑን እያወጣው የሚገኝ መሆኑን መረዳት የሚከብደው ሰው ቢኖር ዐይነኅሊናው የታወረና ዕዝነልቦናው የደነቆረ ዓሣማ ወያኔ ወይም አጋሰስ ጥገኛ መሆን አለበት፡፡

ሮም በአንድ ቀን አዳር አልተገነባችም፤ ባግዳድና ደማስቆም በአንድ ቀን ጀምበር አልወደሙም፤ የቀን ጉዳይ እንጂ ወያኔዎች በሚያሣዝን ሁለንተናዊ አገባብ እየጠፉ ነው – በሥነ ልቦናም፣ በኅሊናና አእምሮም፣ በአካላዊ ጤንነትም፣ በቤተሰባዊ የጤናማ ትውልድ አለመቀጠልም … ብቻ በሁሉም ዘርፍ የተሣካ ውድቀት ውስጥ ተዘፍቀው እየተንፈላሰሱ እንደሚገኙ መገንዘብ ከጀመርን ውለን አድረናል , እንዳባታቸው ቃለ ቡራኬም “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችው” ብለን መርቀናቸዋል፡፡ ይህን እያደረገ ላለው የኢትዮጵያ አምላክ ምሥጋና ይድረሰው፡፡ አንድ ጥይት ሳይተኮስባቸው በትንቢቱ መሠረት እንደጉም እየተበታተኑና እንደጪስ እየበነኑ ነው – በዚህ ነባር አባባል አላፍርበትም ልድገምላችሁ – በትንቢቱ መሠረት ወያኔዎች እስከወዲያኛው ብትንትናቸው ሊወጣ ጊዜው ቀርቧል – ሃሌ ሉያ፤ በሰው ስቃይ መደሰት አግባብ ባይሆንም የፈጣሪን ፍርድ ማጣጣል ተገቢ ባለመሆኑ የውሻን ደም በከንቱ የማያስቀረው ፈጣሪ ለሚሰነዝረው ለዚህ ፍትሃዊ ብያኔ አኮቴት ማቅረብ ይገባል – እንደጥፋታቸው ከባድነት ደግሞ በሰው አምሳል የሚንቀሳቀሱ አጋንንት እንጂ እንደሰው ሊቆጠሩ የማይገባቸው ነገሮች በመሆናቸው በነሱ ላይ በሚወርድ ፍርድ ማዘን ጌታን ማስቀየም ነው፡፡ “ወይ ፍረድ ወይ ውረድ” ካልን በኋላ “እንዳይፈርድም እንዳይወርድ”ም ደንቃራ ልንሆን አይገባምና በርሱና ከርሱ ለሚመጣ የመጨረሻ ፍርድ እንቅፋት መሆን የሚዳዳን ዜጎች ብንጠነቀቅ አይከፋም፡፡ ማንም ደግሞ ሊያድናቸው አይችልም፤ የተፈረደን ፍርድ ዝምብሎ እንዳመጣጡ መቀበልና መኮምኮም እንጂ እኔ ነኝ ያለ ምድራዊ ኃይል ከዚህ ከተደገሰላቸው የመከራ ድግስ አያስጥላቸውም – “አንቺም ጨካኝ ነበርሽ ጨካኝ አዘዘብሽ፤ እንደገና ዳቦ እሳት ነደደብሽ” እንደተባለው እነሱም በሠፈሩት ቁና እየተሠፈረላቸው ነው፡፡ አስቡት፡- ከመለስና ገብረ መድኅን ሞት በኋላ ማን ይመስላችኋል እንዲህ ምንቅርቅራቸውን እያወጣ የሚገኘው? ለመሆኑ ማን ጻዲቅ ማንስ ኃጥዕ ሆኖ ነው እንዲህ እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ማጎሪያ ቤቶቻቸውን ሊሞሉ የደረሱት? ሥርቆትና ሙስና የሁላቸውም የሕይወት እስትንፋስ ያልሆነ ያህል አንዳቸው አንዳቸውን ካለምንም ሀፍረት እንደጅብ የሚዘረጥጡት እንደባቢሎንያውያን በክፋት ለክፋት እንዳይግባቡ እግዜር ስለፈረደባቸው አይደለምን? ይህን የማያውቅ ማን አለ? ጭካኔያቸው ወደር የሌለው እንደመሆኑ የግብ ዕዳ ክፍያቸውም ያንኑ ያህል ተወዳዳሪ የማይገኝለት እየሆነ ነው፡፡

ይህን ሂደት እነሱ ዐወቁት አላወቁት ምንም ለውጥ ስለማያመጣ ምሥጢር አይደለምና አጠፋፋቸውን ደግመው ደጋግመው ይስሙት – ይህንን ነባራዊና መለኮታዊ ፍርድ ኅሊናቸውም ቀድሞ ያውቀዋል፡፡ ፈጣሪ ሥራውን ዘንግቶ አያውቅም፤ ወደፊትም ሆነ አሁን አይዘነጋም፡፡ የሰውና የእግዜር የጊዜ አለካክ ለዬቅል በመሆኑ ግን ብዙዎቻችን ተስፋ እየቆረጥን ወዳልሆነ አቅጣጫ እንዞርና ከሁለት ያጣ ጎመን ወደመሆን ደረጃ እናጋድላለን፤ ያኔ በሁለት ጌቶች መካከል ስንመላለስ ወይ ከሥጋችን ወይ ከነፍሳችን ሣንሆን እንዲሁ በመሀል ቤት እንደተቅበዘበዝን እንቀራለን፡፡ በአቋማቸው የሚጸኑ ግን መጨረሻቸው ያማረ ይሆናል፡፡ “ንቁም በበኅላዌነ እስከንረክብ አምላክነ” አልነበር ቅዱስ ገብርኤል የተናገረው – ሰይጣን “አምላካችሁና ፈጣሪያችሁ እኔ ነኝና ለኔ ስገዱ” ብሎ የእግዚአብሔርን ኅልውና በተገዳደረበት ፈታኝ ወቅት? አዎ፣ እኛም በዚያ ዓይነት ከባድ ፈተና ውስጥ ነው የምንገኘው፡፡ እውነተኛ እናታችንን እስከምናገኝ ድረስ ታዲያ መረታት የለብንም፡፡

ለማሣጠር … በበኩሌ ከ2007ዓ.ም መጠናቀቅ በፊት ብዙ እናያለን የሚል ታላቅ የተስፋ ስንቅ ቋጥሬያለሁ፡፡ … ያልተነገረ የተፈጸመ፣ የተፈጸመ ያልተነገረ ነገር ፈጽሞውን አላስታውስም፡፡ ሁሉም ተነገረ፤ ሁሉም ተፈጸመ፡፡ ዘመነ መንሱት ወደታሪክ ሰገባ ገብቶ በብረት ክፈፍ ሊጠረቀም፣ በምትኩ ደግሞ ወርቃማው ዘመነ ፍስሐ ወሃሤት ሊብትና እምዬ ኢትዮጵያ ከሞት ልትነሣ የተሰደዱ ልጆቿም በ‹ጉሮ ወሸባየ› የድል ብሥራት ዘፈን ታጅበው ሊመለሱ፣ የሚሊዮኖች የዘመናት ሰቆቃም በፈጣሪ ዕልባት ሊያገኝ ተቃርበናል፤ ዕድሜ ለዕንባችን አሁን ዕፁብ ቅንቅ ተዓምራትን እያየን እንዳለን ሁሉ የመጨረሻውን ልዩ ትንግርት ልናይ ተቃርበናል፡፡ እነሱ ለእራት ሲያመቻቹን አንድዬ በብዙ አቅጣጫ ቀስፎ ይዟቸዋልና የነጻነታችን ቀን መቅረቡን መጠራጠር አይገባም፡፡ መተማመኛችንን እርሱን ያደረግን አናፍርም፡፡

ግን ለፈጣሪያችን ማድረስ ከሚገባን ልባዊ ጸሎትና ምህላ በተጓዳኝ ከቂም በቀለኝነትና ከክፋት መራቅ አለብን፤ እንደወያኔ በተመሳሳይ የክፋት ቅኝት የምንነጉድ ከሆነ ነጻነታችን የማይቀር መሆኑ በታሳቢነት ተይዞ ፈረሰኛው ጎርፍ እንዳይጠራርገን ያሰጋል፡፡ ልብ እንበል፡- እንደወያኔ እያሰቡ፣ እንደወያኔ እየሆኑ፣ እንደወያኔ እያደረጉ፣ እንደወያኔ እየሞሰኑ ወያኔን ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት አንድ ስንዝር ማባረር አይቻልም፡፡ ይህን ስል ወያኔን በሚገባው ቋንቋ ማነጋገር መጥፎ ነው ወይም ‹ኃጢኣት› ነው ለማለት ፈልጌ እንዳልሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን ጥፋተኛን ከንፁሕ የማይለይ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በባህል ተመሳስሎ መገኘትን እንደወንጀል የሚቆጥር፣ በብዕር የመጣን ወገን በታንክ የሚጨፈልቅ፣ ዳቦና የንግግር ነጻነትን የጠየቀ በአሸባሪነት ፈርጆ ዘብጥያ የሚወረውር፣ አማላይና ማራኪ የመንግሥትን ሕግና የፈጣሪን ትዕዛዝ የማይከተል ወያኔዊ አሠራር ማስወገድ ለዘለቄታዊ ድል እንደሚበጅ መረዳት ይገባል – እውነትን በመደፍጠጥ የሚገኝ አብረቅራቂ ድል የውሸትና ለተወሰነ ጊዜ ብቻ በጎመን ጥጋብ የሚያስፏልል መሆኑን ከዚህ ዘመን በላይ አስረጅ የለም፡፡

የሐጎስን ስህተት አምባቸው ቢደግመው፣ የስንሻውን ግድፈት ፈይሣ ቢሰልሰው ታጥቦ ጭቃ እንጂ የምንፈልጋቸውና የምናልማቸው ፍትህና ርትዕ እንዲሁም በዜጎች ሃቀኛ እኩልነት ላይ እንዲመሠረት የምንጠብቀው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሕልምና ቅዠት እንደሆኑ ይቀራሉ፡፡ ለታደለና አንጎል ላለው ሰው ያለፈ ስህተት ከዩኒቨርስቲ በሚበልጥ ሁኔታ ከፍተኛ ትምህርት የሚቀሰምበት ነው፡፡ እንደኛ ላልታደለ ሕዝብ ግን ያንዱን ስህተት ሌላው እያዘመነና በተንኮል እያጠናከረ የሚቀጥልበት የመሠሪዎች የጭቆና አገዛዝ አዙሪት ነው፡፡ ከእንስሳት ያነሱ ሰዎች ስለራሳቸው ብቻ ይጨነቃሉ፤ ሌሎችን መቅ ይከታሉ፡፡ ለሆዱ የሚያድር ጅብና ዓሣማ ነው፡፡ ወያኔዎች መነሻቸው ምንም ይሁን ምን ከዓሣማና ከጅብ ያልተሻሉ እንዲያውም የባሱ ሆዳሞችና በአንጎል ሣይሆን በከርሳቸው የሚያስቡ አውሬዎች ናቸው፡፡ ከባድ ዋጋ እያስከፈላቸው የሚገኘውና ገና አንዲትም ጥይት ሳትተኮስ እንዲህ ፍርጠጣና ሽሽት ውስጥ የገቡት ከሰውነት ተራ ባወጣቸው ሆዳቸው አማካይነት የሠሩት ወንጀል ከአሁኑ እያቃዣቸው ነው – የሰው ዋና ጠላቱ ሆዱ ነውና በዚህ በቀዳዳ በርሜል በሚመሰል ሆዳቸው ጦስ ወያኔዎች ገና ብዙ አሣር ይገጥማቸዋል፤ ሱቅ ውስጥ እንደገባ ሕጻን ሁሉንም ለራሳቸው የማድረግ አባዜ የተጠናወታቸው እነዚህ በጎደሎ ቀን የተፀነሱ ይሉኝታቢስ ዜጎች አወራርደው የማይጨርሱት ውዝፍ ሒሳብ አለባቸው፡፡ ከአሁኑ በነሱው ቋንቋ መላቅጡ በጠፋበት ውስጣዊ “ህንፍሽፍሽ” ገብተው እንዲህ የተራወጡ ዋናው የፈጣሪ ማዕበል ሲነሣማ ዕድሜውን ይስጠን እንጂ እንዴት እንደሚሆኑ የምናየው ይሆናል፡፡ አለ ነገር!

የአዲስ አበባን ነገረ ሥራ ብታዩ ከ‹አለ ነገር› በላይም ትላላችሁ፡፡ የምፅዓት ማወጃ ፊሽካው ብቻ የቀረ ይመስላል፡፡ ርሀቡ፣ የኑሮ ውድነቱ፣ ሙስናው፣ የፍትህ ዐይን መጥፋት፣ የነጋዴውና ባለሥልጣኑ እምብርት ማጣት፣ የዘረኝነቱና ጎጠኝነቱ መንሠራፋት፣ የድህነቱ አለቅጥ መስፋፋት፣የወንጀሉና ወንጀለኛው አበዛዝ፣ የኃጢኣቱ ከላይ እስከታች መዛመት … የጥቂቶች አለልክ መንደላቀቅና መዘባነን፣ የተያዘው አሥረሽ ምቺው፣ የተወሰኑ ዜጎች ገንዘባቸውን እምን እንጣለው በሚል በእሳት የማቃጠል ያህል አልባሌ መርጨት፣ የለፋና የደከመ እየደኸዬ አጭበርባሪውና የአየር ባየር ደላላና መልቲ ዜጋ በደቂቃዎች መክበር  … በአንዲት ጠባብ ከተማ ሲዖልና ገነት፣ ገሃነምና መንግሥተ ሰማይ ባልተፈረመበት ውል እየተጎሻመጡ ይኖራሉ – ጎን ለጎን እየተያዩ፡፡ ሊቀ ጳጳሱ በድብቅ ሚስቶቹን አግብቶ እየወለደ እያስተማረ አሳድጎም ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን ለወግ ለማዕረግ ሲያደርስ ብታዩ ልትደነቁ አይገባም – “አንተን በዚህ ምን አገባህ – እነሱው ይኮነኑበት” የማለት መብታችሁን አከብራለሁ – እየተገረፍንበት ስለምንገኘው የሀሰተኛ ነቢያት ዘመን ተጨባጭ ሁኔታ የመናገር መብት እንዳለኝ ደግሞ በግልጥ ማሳወቅ እወዳለሁ ፡፡ እኔ ይህን መሰል ታሪክ በጣም በቅርብ አውቃለሁ፡፡ ካህናት የነፍስ ልጆቻቸውን ሚስቶች ‹እየቀሙ› ቢያባልጉ አትገረሙ፤ ብዙ ወንጀሎችና ኃጢኣቶች ይሠራሉ፡፡ መንግሥተ እግዚአብሔርና መንግሥተ ሕዝብ የዱርዬዎችና የወሮበሎች መናኸሪያ ሆነው መልካም ዘመንን መጠበቅ ታዲያ የዋህነት ነውና በሚደርስብን ዕኩይ ነገር ሁሉ በቀላሉ መደናገጥ አይኖርብንም፡፡ እንደሥራችን ይህም ሲያንሰን ነውና፡፡ የእንግልታችን ሁሉ መንስኤ ይሄው ለመንግሥትና ለእግዚአብሔር ሕግጋት አለመታዘዝ ነው – ከጫፍ እስከ ሥር ድረስ – ከፓትርያርክ እስከ ዲያቆንና ከጠ/ሚኒስትር እስከተራው ዜጋ፡፡ ካልተወሻሸን በስተቀር ከሞላ ጎደል ሁላችንም ጠፍተናል፡፡

አሁንና ዛሬ ለምን አይፈርድ? ለምን ሶዶም ወገሞራዊ ብያኔውን አይደግም? ሚሊዮኖች በርሀብ አለንጋ እየተገረፉ በጠኔ ጣር ሲሞቱ ጥቂቶች በዘረፉት ወይም አግባብ በሌለው የንግድና የሙስና ተራክቦ ባገኙት ገንዘብ ዳንኪራና ጮቤ ሲረግጡ እያዬ እስከወዲያኛው የሚያስችለው ፈጣሪ ምን ዓይነት ፈጣሪ ነው? ንጉሥ ዳዊት ቢጨንቀው፤ “እስከማዕዜኑ ትረስዓኒ ሊተ” በማለት ጌታን ወቅሷል፡፡ እኛንስ እስከመቼ የረሳን እንደመሰለ ሊቆይ ይችላል? ሁሉም መጠን አለው፤ እሺ? እናም የኛ ነገር አሁን አሁን ያለቀ ይመስላል፡፡ ማለቁን ለማወቅ አዲስ አበባን ኑና ጎብኙ፡፡ አዲስ አበባ ብቻ ሣትሆን ሀገራችን ባጠቃላይ ከካምሱሩ የተላቀቀ ቦምብ ሆናለች፡፡ “የጨው ተራራ ሲናድ ብልኅ ያለቅስ፤ ሞኝ ይስቅ” እንዲሉ ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያ አንድ ሐሙስ ከሚቀራት የማስፈራሪያና የማስጠንቀቂያ ደረጃ ወጥታ መጥፋት ከተገባት ጊዜ ብዙ ሐሙሶችን እንዳለፈች ልብ ልንል ይገባል – እንደእግዚአብሔር ፈቃድና ጥበቃ ግን ይሄውና ጠላቶቿ ሊያጠፏት ከውጪም ከውስጥም በተቀናጀ ሁኔታ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም እስካሁን አለች፡፡ ነገም ትኖራለች፤ ለጊዜው ልጆቿ ተንገላታንባት እንጂ እርሷማ ሳለ ፈጣሪ ተመልሳ ታሪካዊ የክብር ሥፍራዋን እንደምትይዝ ጥርጥር የለውም – ሁሉም ነገር የሚፈራረቅባት ሁሉንም እንድታየው ነው፡፡ እነዚህን የታሪክ ወበሎዎችና አስካሪ እንክርዳዶች አቧራ ላይ ጥሎ የሚያንደባልልላት አምላክ አላትና በቅርብ የምናየው ልዩ ታሪካዊ ክስተት አለ፡፡ “stay tuned!” የሚሏት የጋዜጠኞች አባባል እንዴት ደስ እንደምትለኝ! አዎ፣ ተርፎ ከሚቀር ዕድሜና ጤናው አይንፈገን እንጂ ብዙ ድንቅ ነገሮችን በግምባር ማየታችን አይቀርም፡፡ ይህ የቅዠት ዘመን ሲያልፍ የሚጠሉን ይወዱናል፤ የሚንቁን ያከብሩናል፤ ያዋረዱን እግራችን ሥር ይወድቃሉ፤ … ለማንኛውም “stay tuned!”…

 

በደርግ ዘመን አንድ እንግሊዝኛ የማይችል የቀበሌ ለፋፊ “ነገ ሜይ ዴይ ስለሆነ በአብዮት አደባባይ ለሠልፍ እንድትወጡ!” የሚለውን ትዕዛዝ “ነገ መሄዴ ስለሆነ በአብዮት አደባባይ ለሠልፍ እንድትወጡ ” በማለት ጡሩንባውን እየነፋ ሲያውጅ “የቀበሌው ነዋሪ እመት ጠንፌ “እንዴ! አሁኑኑ ጥርግ ለምን አትልም፤ ላንተ ደግሞ የምን ሠልፍ ነው” አሉት አሉ፡፡ ይህንን ቀልድ አለነገር አላስታወስኩትም – የስንብት ሰላምታዬን ለማቅረብ ዳር ዳር እያልኩ ስለሆነ አንዳንድ ወዳጆቼ “ጥንቅር በላ!” ሲሉኝ እየታየኝ ነው ከወዲሁ ለፈገግታ ያህል ወደአብዮቱ ዘመን የኋሊት በመጓዝ ያቺን ጨዋታ የመዘዝኩት፡፡ እናም ማንንም የማትጠቅም ወይም የማትጎዳ አንዲት የግል መልእክት ቢጤ አለችኝ፤ ከ‹ጨዋ› መጣጥፈኛ ልንጠብቃት የሚገባን መሰነባበቻ ናት – ሌሎች ስለማይሉ እኔም አልልም አልልም፡፡ እናም ፈጣሪ ጨርሶ ፊቱን እስኪያዞርልንና የነጻነትን ብርሃን እስኪፈነጥቅልን ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ ‹ያመት ፈቃድ ሞልቼ› ማረፍን ወድጃለሁ፡፡  እግር ኳስ ተጫዋች ጫማ ይሰቅላል፤ አጫዋቹ ወይም ሪፌሪው ደግሞ ምናልባት ፊሽካውን ሊጨምርበት ይችላል፡፡ እኔም ስለቴ እስኪሰምርና በጉጉት የምጠብቀው የነጻነት ቀን እስኪብት በዚያውም እውነተኛ የመደማመጥ ቀን እውን እስኪሆን ድረስ ብዕሬን ሰቀልኩ፡፡ ምክንያቶቼ ብዙ ናቸው፡፡ በጣም ጥቂቱን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እንደገዳም መቁነን በቀን ለጥቂት ሰዓታት ብቻ የሚለቀቅልንና የሚንቀራፈፈው በኢንሳ አሰለጦችም እንደሚጠለፍና እንደሚፈተሸ የሚነገርለት የወያኔ ኢንተርኔት እንዳለ ስለማይቆጠር ያበሳጫል፤ የመብራቱ በቀን ሠላሣ ጊዜ መቆራረጥም ያበሳጫል፤ ኑሮውም ያበሳጫል፤ የሰው ‹ትግስት› ገደብ ማጣትም ያበሳጫል፤ የራሴው ፍርሀትም ያበሳጫል፤ ተናግረህ አለመደመጥም ያናድዳል፤ የማይቀረው የፈጣሪ ፍርድ መጓተትም እንደሰው ሆነው ሲታዘቡት ያናድዳል፤ የሃይማኖት መጥፋት ያናድዳል፤ የሞራል መላሸቅ ያቃጥላል፤ የትውልድ በትምህርትና በዕውቀት መምከን ያቃጥላል፤ የራሴ የምትለው ሰንደቅ ዓላማና ብሔራዊ መዝሙር አጥተህ የማታምንበት የነተበና የተቀዳደደ ባንዴራ ተመልካች አጥቶ 24 ሰዓት እንደተሰቀለ ሲውለበለብ ማየት ራሱ ያቃጥላል፤ የምታየው ወታደር ያንተን ጥቅምና ፍላጎት የማያስጠብቅ መሆኑን ስትረዳና ባንተ ገንዘብ በተገዛ የጦር መሣሪያና አንተው በምትከፍለው ደሞዝ ፀረ-አንተና ፀረ-ሀገርህ በሆነ መንግሥታዊ ተቋም እየታዘዘ አንተን ሊገድል መሠማራቱን ስታይ አንጀትን ያሳርራል፤ ሃይማኖት የለሽ የመንግሥት ሹመኛ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን አብዝቶ የሚጠላ፣ ሥልጣንንና ገንዘብን ግን በእጅጉ የሚያፈቅር ሆኖ ስታይ ያናድዳል፤ ሀገርህ ውስጥ ሆነህ ሀገርህ ስትናፍቅህ በብስጭት ኮረንቲ ያስይዛል፤ በየምትሄድበት ቢሮ ካለገንዘብ መብትህ የማይጠበቅ ሆኖ ስታገኘው ያናድዳል፤ … ባጭሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የማያበሳጭና የማያናድድ ነገር የማግኘት ዕድልህ በጣም አናሳ ነው፡፡ ስለዚህ … ለነገሩ ምን ስለዚህ አለው፡፡ ያው ለጊዜው ዝምብሎ መናደድና መበሳጨት ነው፡፡

እስካሁን በድረገፆችና በሌሎች የመገናኛ መንገዶች የምሰዳቸውን መጣጥፎችና የብሶት ጦማሮች በማስተናገድና በማንበብ ከ24 ለማይበልጡ ጥቂት ዓመታት አብረን የዘለቅን ወገኖቼን ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ ምናልባት – እንዲያው ጠባብ ዕድል አግኝቼ ከጎርፉ በማምለጥ በነጻነት ቀን በአካል የምከሰት ከሆነ እንደስካሁኑ በብሶት ሣይሆን በወያኔና በጋራ ‹ጥረቶቻችን›ም ጭምር የጠፋውን ትውልድ ለማነፅ በሚደረግ ርብርብ ዘልዛላው ዕድሜየና ሙያዬ በሚፈቅዱልኝ ለመሣተፍ ከወዲሁ ቃል እገባለሁ፡፡ እስከዚያው ወኔው ላላችሁ መልካም የጭቅጭቅና የንትርክ ዘመን ይሁንላችሁ፤ ለሀገራችን ደግሞ ፈጣን የነጻነት መባቻ ይሁንልን!(መለያየት ሞት ነው … የሚለውን የጥላሁን ገሠሠን ጣዕመ ዜማ ከዚችው ጊዜያዊ ስቱዲዮ ልጋብዝና ልለያችሁ፡፡ እናንተዬ … ከአሁኑ ሆዴን ባር ባር አለኝሳ! ውይ እውነትም መለያየት ለካንስ ክፉ ሰው ነው፡፡ … )

“ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር”

ዋና ጠላታችን የትግሬ ነፃ አውጪ ወያኔ ነው! ከቴዎደሮስ ሐይሌ

$
0
0
(ፎቶ ፋይል ኢትዮጵያዊው በሪያድ ከተማ በፖሊስ ተይዞ)

(ፎቶ ፋይል ኢትዮጵያዊው በሪያድ ከተማ በፖሊስ ተይዞ)

ከቴዎደሮስ ሐይሌ ‘’ ወዴት ነው የምንሄደው ለማን ነው የምንነግረው መንግስት ረስቶናል ኤንባሲው አላቃችሁም …ብሏል ነገ እኔ እህትህን ወይ ተደፍሬ ወይ ሞቼ ወይ አብጄ ነው የምታገኘኝ’’ አንዲት በሳውዲ ተደብቃ ያለች እህታችን ያስተላለፈችው መልዕክት አቦይ ስብሃት ከጉልምስና እስክ ሽምግልና የታገልክለት ኢትዮጽያና ኢትዮጽያዊነት የማዋረድ አላማህ ከሃገር አልፎ በአለም ሁሉ ሆኖዓልና እንኳን ደስ ያለህ አዜብ መስፍን የባልሽ እረፍት የለሹ እስከ መቃብር ያለመታከት የቆመለት አላማ ትቶት ያለፈው ራዕይ የአገዛዝ ውጤቱ ይህው ኢትዮጽያውያንን አንገት የማስደፋት ተሳክቶ እዚህ በመድረሱ የሃዘንሽ መጽናኛ ከሆነልኝ እንኳን ደስ አለሽ፤ በረከት ስምዖን የውሸት ጋጋታህ የክፋት ፕሮፓጋንዳህ ኢትዮጽያዊነት የማወረዱ አላማህ ግቡን መቷልና ከነሳውዲው ቱጃር ወዳጅህ እንኳን ደስ አለህ፤ ደብረጽዮን ገብረሚካዔልና ጌታቸው አሰፋ የገደላው መሃንዲሶች የአፈናው ሊቃውንቶች እንኳን ደስ አላችሁ ስታሳድዱት ያመለጣችሁን ሁን ብላችሁ....ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

ከዚህ መከራ እና ስቃይ እንዴት እንላቀቅስ?በይበልጣል ጋሹ

$
0
0

በይበልጣል ጋሹ

Saudicryዛሬ ላይ ስለ ስቃይ፣ መከራ፣ችግር እና እንግልት በቃላት መግለጽ አስፈላጊ አይመስለኝም። ምክንያቱም በእራሳችን ላይ ቀን በቀን በተግባር እየተፈጸመብን ነውና። ከተግባር በላይ አድን ነገር ሊገልጸው የሚችል ነገር የለም አይኖርምም። ምን አልባት አንዳንድ ሰዎች ችግሩ በቀጥታ ከእኔ አልደረሰም ልንል እንችል ይሆናል “አንተ በሰላም እንድተኛ ከፈለክ ጎረቤትህ ሰላም ይሁን” ይባል የለ በአገራችን ብሂል፤ ምናልባት ለጥቂት የዘመኑ እድለኞች ችግሩ በቀጥታ ባይደርሳቸውም ጎረቤት፣ ወገን ዘመድ ስቃይና እንግልት በዝቶበት ከሚችለው በላይ ሲሆን ሕይወትን በችግር ሲገፉ ማየት ለሰብአዊ ፍጡር እንቅልፍ የማያስተኛ ትልቅ በሽታ ነው። ይህን እያየ  አንድ ሰው ራስ ደና ካለ እሱ ከሰባዊ መደብ ወጥቷል ማለት ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን ትናት እና ከትናት በስተያ የነበረን ልዩ  መለያ ጠባያችን መተሳሰብ፣ መረዳዳት፣ የጎረቤት ችግር  ችግሬ፣ ጭንቀቱ ጭንቀቴ፣ አገሬ ህይዎቴ እያልን የኖርን ህዝቦች ነበርን። በተለይ ደግሞ  የአገርና የዜግነት ክብር ምን እንደሆነ በተግባር ያየን፣ ለአለምም ያሳየን ህዝቦች ነበርን።

በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት አንድ አገር አገር ለመባል ሦስት መሰረታዊ ነገሮች ያስፈልጓታል። ከእነዚህ መሰረታዊ ነገሮች መካከል አንዱ ከተነካ ሉዐላዊት አገር የሚለው ይቀርና ሌላ ስም ይሰጣታል። እነዚህ ሦስቱም ተደጋግፈውና አንዱ የአንዱን ሉዐላዊነት መጠበቅ፣ ማስጠበቅ ይኖርበታል። አንዱ አንዱን ካጣ ምዕሉ ሊሆን አይችልምና። የአንድ አገር ሦስቱ መሰረታዊ ነገሮች የሚባሉት ግዛት፣ ህዝብና መንግስት ናቸው።

1. ግዛት፦ የአንድ አገር ግዛት ማለት ወሰኗ፣ ድንበሯ፣ የቆዷ ስፋቷ፣ በውስጧ የየያዘዛቸው ወንዝ፣ ተራራ፣ሸለቆ፣ ባጠቃላይ ሙሉ ካርታዋ ማለት ነው። የኢትዮጵያ ግዛት ስንል በምስራቅ፣ በሰሜን፣ በደቡብና በምዕራብ ከሚያዋስኗት ግዛቶች የምትለይበት ቦታ፣ ድንበር ወይም ክልል ጀምሮ  በውስጧ የየያዘዛቸው ወንዝ፣ ተራራ፣ሸለቆ ወዘተ ሙሉ የቆዳ ስፋቷን ያዋስናል። ከዚህ የቆዷ ስፋቷ ትንሽ ከተነካ ግን የነበራት ሙሉ ግዛት አይኖራትም። ይህን ግዛቷን ለማስጠበቅ መንግሥት በማስተባበር ህዝብ በመተባበርና በመጠበቅ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት። ዛሬ ላይ የምናያቸው ነገሮች ግን ከዚህ የራቁ ናቸው። መንግሥት ለግዛቷ ሲጨነቅ አናይም፣ ህዝብም በተመሳሳይ። እንደ ጥሬ እቃ ግዛቷን ሲሸጥም፣ ሲደራደርባትም እናያለን። የጽሕፌ ዓላማ ይህን ማንሳት ስላልሆነ እዚህ ውስጥ መግባት አልፈልግም።

2. ሕዝብ፦ ከሁሉም በላይ ክብርና ሥልጣን ሊሰጠው የሚገባ ነው። ሕዝብ ከሌለ የምንላቸው ነገሮች የሉም። ህዝብ ከሌለ ለግዛት ስም ጠርቶ፣ ወሰን ወስኖ ሊያስቀምጥ የሚችል አካል የለም። ስለዚህ ሕዝም ውድ ዋጋ ያለው ነው። በሌላም በኩል ፈጣሪ አክብሮና ባለ አዕይምሮ አድርጎ የፈጠረው መተኪያ የለለው ፍጡር ነው። ስለዚህ ግዛት በሕዝም ይከበራል፤ መንግሥት ደግሞ  በሕዝብ ይከብራል/ይነግሣል። ላከበረው፣ ላነገሠው ሕዝብ መንግሥት ዋጋ ሊከፍልለት ይገባል። ከዚያ ውጭ ግን(የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ፣ ታየ ህዝባዊነት ዳር እስከዳር በርቶ)እያልን የአገር መለያ፣ የማንነታችን መገለጫ የሆነውን ባንዲራ እያውለበለብን የምንዘምረው የህዝብ መዝሙር ከንቱና ዋጋ አልባ ሆኗል ማለት ነው። ባንዲራ ደግሞ ጨርቅ አይደለም ልዩ መለያ ማንነታችን ነው። ይህን የማንነት ጉዳይ ሊያስከብረው የሚችል ደግሞ  ህዝብ ነው። ሕዝብ ማለት ደግሞ እያንዳንዳችን ስብስብ/ድምር ውጤት ነው።                                                                      ዛሬ ላይ እየተፈጸመ ያለው ችግር፣ ስቃይና እንግልት እንዲሁም ሞት የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የሕዝብን ክብርና የማንነታችንን መገለጫ ባዲራን ክብር የሚነካና ለዘላለም የማይጠፋ ጥቁር ጠባሳ ነው። ይህ ሲፈጸም ዝም ብሎ  ማየት ግን ከውርደትም በላይ ውርደት ከአረመኔነትም በላይ አረመኔነት ነው። የአረብ ሃገራት እኮ በሕዝባችን ላይ በደልና ግፍ የሚፈጽሙት አረመኔነት ቢሆንም ቅሉ አገራቸውንና የሕዝባቸውን የኑሮ ሁኔታ እንዳይነካባቸው ስለሚፈልጉ ጭምርም ነው።  ታዲያ እኛ ወገናችን የዜግነታችንን መገለጫ የሆነውን ባንዲራ ከራሱ ላይ ጠምጥሞ ሲሞት ስናይ እንዴት አስቻለን? አዎ እውነት ነው በስሜት ብዙዎቻችን በእጅጉ ተጎድተናል፣ ተረብሸናልም፣ ምግብ መመገብ አቅቶናል። ፊታችን በእንባ ታጥቧል። ግን መፍትሔ ሊሆን አልቻለም። ይህ አዲስ ክስተትም አይደለም፤ አስር፣ አስራ ዓመታትን አስቆጥሯል። ችግሩ፣ ስቃዩ  እየባሰ፣ እየጎላ መጣ እንጂ። በአገር ውስጥም በውጭም ችግሩ ያው ነው ልይነቱ የውጭው በመገናኛ ብዙኃን ጎልቶ  መታየቱ እንጂ ብዙዎች አገር ውስጥም እየተሰቃዩ፣ መከራ በዝቶባቸው የሚኖሩት በርካታ ናቸው። ወደ ሦስተኛው መሰረታዊ ነገር ልግባ መፍትሔውን በኋላ እንመለስበታለን።

3. መንግሥት፦ መንግሥት ማለት በጥሬ ትርጉሙ በአንድ አገር  ውስጥ ሕጎችን ለማውጣትና ለማስፈጸም፣ ሕዝብን ለማስተባበርና ደኅንነቱን ለማስጠበቅ፣ አገርን ለማስከበር  ስልጣንና ኃላፊነት ያለው አካል ማለት ነው። እንዲሁም በምርጫም ይሁን በሌላ መንገድ በሕዝብ ድጋፍ ስልጣን ላይ የወጣ አካል ነው። ስለዚህ ይህ በሕዝብ ድጋፍ ሥልጣንን የያዘ አካል ከስሙና ከትክክለኛ ትርጉሙ አንፃር ለህዝብና ለአገሪቱ ግዛት ከማንም በላይ የሚጨነቅ፣ የሚያስብና የሚቆረቆር አካል ነው ማለት ነው። ምክንያቱም ሕዝብ ከሌለ መንግሥት የለም፤ ግዛትም ከሌለ እንዲሁ። ከምንም በላይ ለመንግሥት መኖር ሁለቱም ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው። የየትኛም አገር መንግሥት ይህን ተገንዝቦ ለሁለቱም የሚገባውን እንክብካቤና ክብር መስጠት ካልቻለ የመኖር ዋስትናው ጥያቄ ውስጥ ይገባል። አወዳደቁም በእጅጉ የከፋ ይሆናል።

ከዚህ አንፃር የአገራችን መንግሥት የቱ ጋር ነው ያለው ብሎ መጠየቁ መሰረታዊና አስፈላጊ ጥያቄ ነው። ያለበትን ደረጃም በተገቢው መንገድ ማሳየት ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል። ስንተቻች/ስንነታረክ ብዙ ዓመታትን አሳልፈናል። አሁን ጊዜው የተግባር ነው። ተግባራዊ ሥራ ለመስራት ወኔ ሰንቀን መነሳት ይኖርብናል። የጦርነት ወኔ አይደም የሰላም፣ የአገር ፍቅር፣ የዜግነት ክብር ወኔ፣ የማንነት ወኔ እንጂ።

ሰሞኑን የዓለምን ዓይንና ጀሮ የሳበ ትልቁ ክስተት በሳዑዲ አረቢያ ለማየትም ሆነ ለመስማት ዘግናኝና አሰቃቂ በሰው ልጆች ላይ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት ነው። በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያውያን እህት ወንድሞቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ ነው። የክብራችን መገለጫ ባንዲራችን ሳይቀር በደም ታጠበ። ወንድሞቻችንም ሰማዕትነትን ተቀበሉ፤ ባንዲራችንም ተጨምራ በድንጋይ ተወገረች። አሁን ችግሩን ማዉራት መደጋገም መፍትሔ አይሆንም። ስለመከራው፣ ስቃዩ፣ እንግልቱና ችግሩ የመገናኛ ብዙኃኖች አወሩልን፣ እኛም ብዙ አወራን፣እያወራንም ነው።

የሁላችንም ውሳጣዊ ጥያቄ ከዚህ አስከፊ መከራና ስቃይ እንዴት እንላቀቅ?እንዴት ነጻነታችንን እንጎናፀፍ?እንዴት ወደነበርንበት ክብር እንመለስ?የሚለው ስለሆነ በዚህ ዙርያ ለመደርደርያ ያክል ጥቂት ነጥቦችን ላንሳ።

  • አንድነት መፍጠር፦ ችግር ለመፍታትም ሆነ መፍትሔ ለመፈለግ እኛ አንድ መሆን ይኖርብናል። መግባባት፣ መነጋገር፣ መወያየት በምንችልባቸው ነገሮች ላይ አንድ መሆን አለብን። እኛ በሃሳብ በአመለካከት ከተለያየን እንዴት ችግር ልንፈታ  እንችላለን። ከላይ ባነሳናቸው መሰረታዊ ነገሮች ላይ የጋራ መግባባት ሊኖረን ይገባል። ለአንድ አገር ግዛት፣ ሕዝብና መንግሥት እንደማስፈልግ መግባባት አለብን። በአንድ አገር ውስጥ የተለያየ ቋንቋ፣ ባህል፣እምነት ያለው ህዝብ በአገሪቱ ግዛት አንድ መሆን መቻል አለብን። ይህንን ሊያስተባብርና ሊመራ እንዲሁም አንድ ሊያደርገን የሚችል መንግሥት ሊኖረን ይገባል። ከዚያ ውጭ በቋንቋ፣ በባህል፣ በእምነት እንደተለያየን ሁሉ አንድ ሊያደርገን የሚችል የጋራ የሆነ ነገር ከለሌን ችግሩን በህብረት መቅረፍም ሆነ መቀነስ አንችልም። ስለዚህ መንግሥትም ይህን ተረድቶ ለመለያየት ምክንያት የሆኑ ነገሮችን፣ አንድነታችንን ሊያከስም የሚችሉ ነገሮችን ሊያስወግድልን ይገባል። ብሔር፣ ጎሳ፣ ቋንቋ፣ እምነት እያለ ሊከፋፍለን፣ ሊለያየን አይገባም። ይህን ድርጊት የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ የግል/ሰባዊ መብት ድርጅቶችና ሕዝብ ሁላችንም አግባብ ባለው መልኩ ማውገዝና ማስቆም ይኖርብናል። አንድነት፣ ህብረት ከሌለ ምንም ማድረግ የማንችል ባዶዎች ነንና። የቀደሙት አባቶቻችን በአንድነታቸው ያስመዘገቧቸውን ድል መመልከት እኛ ዛሬ አንድነት እንድንፈጥር ትልቅ ትምህርት ይሆኑናልና። ስለዚህ ዛሬ ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ድርጊት ለማስቆም  አንድነት ፈጥረን መወያየት፣ መነጋገርና መፍትሔ መፈለግ ትልቁ ሥራችን ሊሆን ይገባል።
  • አገራዊ ስሜት መፍጠር፦ ሁላችንም በእየአለንበት አንድነት መፍጠር ስላልቻልን አገራዊ ስሜታችንም በእጅጉ ወርዶብናል ማለት ይቻላል። ወጣቱ ስለአካባቢው እንጂ እንደ አገር ማውራት አቁመናል። ስለ ኢትዮጵያ ሲወራ እንደ ሁለተኛ ሦስተኛ ዜጋ ሁነን ቁመን የምንሰማ በርካቶች ሁነናል። ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉሙም ስሜቱም ጠፍቶብናል። ወጣቱም ብሔርን፣ ቋንቋን ይሰብካል። የፖለቲካ ድርጅቶችም ይህንኑ ያስተጋባሉ። ለአገር ሳይሆን ለብሔር ብቻ የቆሙ ናቸው። መንግሥትም ለስልጣን ማራዘሚያ ሲል አገራዊ ስሜት እንዲጠፋ ምክንያት ሁኗል። ይህን ከባድ ችግር አሶግደን አገራዊ ስሜት ሰንቀን ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳን አሁን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ችግር ማስቆም እንችላለን። አገር ወዳዶች ከሆን በቀላሉ ከአገር አንወጣም። አገራዊ ስሜት በውስጣችን ከነገሰ ለአገር፣ ለወገንና ለክብራችን ዘብ እንሆናለን።  በዚህ መልኩ ችግሩን ከአምላክ ጋር ማስዎገድ ይቻላል።
  • ዜጎች ሕጋዊና አግባብ ባለው መንገድ እንዲወጡ ማድረግ፦ እኛ ሁላችንም ማለት ይቻላል አገራዊ ስሜት ስለሌለንና ዜጋ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስለማይገባን ከመንግሥት ጀምሮ ሰዎችን ወደ ውጭ ማስወጣት እንደ አንድ የገቢ ማስገኛ መንገድ አድርገነዋል። ዜጎች ሕጋዊ ሁነው እንዲወጡ ሳይሆን ገንዘብ ከፍለው በተሳሳተ መንገድ ሲሄዱ ይመለከተኛል የሚል አካል ባለመኖሩ ችግሩ እንዲባባስ አድርጎቷል። ኤጄንሲ ነን ባዮች ለሚያገኟት ሽርፍራፊ ሳንቲም እንጂ የዜጎች መከራና ስቃይ አይገዳቸውም። ይህን ችግር ለመቅረፍ ማንኛውም ሰው ከአገር ሲወጣ በሕጋዊ መንገድ እንዲወጣ ቢደረግ አማራጭ መፍትሄ ነው። ይሁን እንጂ በሕጋዊም ሆነ በሌላ መንገድ ከአገር የወጣን ሰው እንደ ዜጋ ሰባዊ መብቱ ሊከበርለት የሚችልበትን መንገድ ማመቻቸት ይኖርብናል። ኤጄንሲዎችም ገንዘብ ላይ ብቻ ሳይሆን ለሚልኳቸው ሰዎች ደኅንነትና ክብር እንዲያስቡ ማድረግ። ይህን ጉዳይ የሚመለከተው ሁሉ በኃላፊነት ይዞ ቢቀሳቀስ ችግሩን በመጠኑም ቢሆን መቀነስ ይቻላል።
  • ኤምባሲዎች/ቁንስላዎች የዜጎችን መብት እንዲያስከብሩ ማድረግ፦ መቼም በየአገራቱ የተሰየሙት ኤምባሲዎች/ቁንሰላዎች ፓስፖርትና መታወቂ ለማደስና መሰል ጉዳዮችን ለማስተናገድ ብቻ አይመስለኝም። ይልቁንም በቅርበት ሁነው የዜጎችን መብት ማስከበር እንደ አንድ ትልቅ ኃላፊነት ይወስዱም ዘንድ እንጂ። ስለዚህ እነዚህ አካላት በዋናነት በሕጋዊም ሆነ በሌላ መንገድ የገቡትን ዜጎች መብት ከሚኖሩበት ሕግ አንጻር ማስከበር ተቀዳሚ ተግባር ማድረግ አለባቸው። የአሰሪና ሰራተኛ የስምምነት ውሉንም በሚገባ ማየትና ማስፈጸም ይኖርባቸዋል። ከክፍያ መጠን ጀምሮ ማየትና ከመግሥት ጋር ወጥ የሆነ የውል ስምምነት እንዲኖር መወያየት አለበት። አንድም ሰው ቢሆን ዜጋ ነውና መብቱ ሊከበርለት ይገባል። ይህን ማድረግ የሚችሉ የኢምባሲ/ቁንስላና ዲፕሎማት ሰራተኞ ያስፈልጋሉ። ይህን ማድረግ ከተቻለ ችግሩን በቀላሉ መቅረፍ ይቻላል። ሌሎች የሲቪክ ማህበራትም ሆነ የፖለቲካ ድርጅቶችም ይህን ይፈጽሙ ዘንድ ትችት ብቻም ሳይሆን እገዛ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብየ አምናለሁ። ከዚያ ውጪ ግን ልቅሶ፣ዋይታ፣ መከራና እንግልት የዘወትር ተግባራችን እንደሆነ ይቀጥላል ማለት ነው።
  • በዜጎቻችን ላይ ኢ_ሰባዊ ድርጊት ፈጻሚዎችን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መጠየቅ፦ ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን እንዲሉ…አገሪቱንና መንግሥትን ቢንቁ እንጂ በዚህ በ21ኛ ክፍለ ዘመን ማን የማነን ዜጋ ከሕግ ውጭ ይነካል። ሕጋዊ ባይሆንና ወንጀል እንኳ ቢሰራ በሕግ አግባብ ይቀጡታል እንጂ እንደ አሸባሪ በአገኙበት ቦታ ደሙን አያፈሱም፣ አካልን አያጎሉም። ምክንያቱም የሰባዊ መብት፣ የዓለም አቀፍ ሕግ አይፈቅድላቸውምና። እኛን ግን ተቆርቋሪና መንገሥት እንደሌለን ካለ ሕግ በአደባባይ ገደሉን፣ ወገሩን፣ ደፈሩን። እንደ እንስሳ ውሻ እየተባልን ክብራችን ይዋረዳል። የማንነታችን መገለጫ የሆነው ባንዲራችን በደም ታጠበ። በዚህ በሰለጠነ ዘመን ሴት እህቶቻችን በየመንገዱ እንዲወልዱ ተደረገ፤ ተደፈሩም። ስለዚህ ይህን ዘግናኝና አሰቃቂ ድርጊት ፈጻሚዎችንና የአገሪቱ መንግሥትን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መጠየቅና ለተባበሩት መንግሥታት አቤት ማለት። ይህን ደግሞ ከአገራችን መንግሥት ስለማንጠብቅ ሙያዊና ተሰሚነት እንዲሁም አቅሙ ያላቸውን ሰዎች በጊዛዊ ኮሚቴ አቋቁሞ ክስ መመስረትና ጉዳዩን መከታተል ከተቻለ ለዘላቂም መፍትሔ ትልቅ አስትዋጾ ያደርጋል፤ ለተጎዱ ወገኖቻችንም በዚህ መልኩ አለን ልንላቸው ይገባል።
  • ጸሎት ወደ ፈጣሪያችን ማቅረብ እና በሰላማዊ መንገድ ድምጻችንን ለዓለም ሁሉ ማሰማቱ እንደተጠበቀ ሁኖ……..

የማለዳ ወግ …ጭንቁን ቀን እንዴት እንለፍ ! ?

$
0
0

ከነብዩ ሲራክ (ጋዜጠኛ)

* የመረጃው ክፍተት የለያየን ግፉአን ዜጎችና ዲፕሎማቶች

    ጥላቻው እያደገ ሔዷል ፣ ሳውዲ አሰሪዎች ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞቻቸውን ድሮ ድሮ በአረቦች ዘንድ የተከበርን ፣ የታፈርን የእኛን የሃበሻ ልጆች “ጨካኞች ፣ የማይታመኑ !” እያሉ ጥላቻቸውን መገልጽ ጀምረዋል።  November 14,2013 የወጣው አረብ ኑውስ  Recent clashes make Saudis wary of Ethiopian maids በሚል ርዕስ ስር ሳውዲ አሰሪዎች  ኢትዮጵያን ሰራተኞችን ለማባረር  እየዛቱ ነው ! ይህ የአረብ ኒውስ ዘገባ በሹክሹክታ የምንሰማው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

illegals_web_0

     የሪያድ መንፉሃን ግጭት ተከትሎ ደም እድገብሮም ለኢትዮጵያን ተሰጠው ወደ ሃገር ቤት የመግባትን እድል ለመጠቀም ከሃያ ሽህ በላይ ኢትዮጵያውያን የሪያድ መጠለያወችን አጨናንቀዋል። እንዳውም በሪያድ የኢትዮጵያ አንባሳደር ቁጥሩን ወደ ሃያ ሶስት ሽህ እንደሆነ ረቡዕ November 14,2013 ለወጣው አረብ ኒውስ አስታውቀዋል። አሁንም በሽዎች የሚቆጠሩ ወደ መጠለያ ለመግባት እየጎረፉ ነው ። በመጠለያው የምግብና የሚጠጣ ውሃ እጥረቱ ደግሞ ኢትዮጰያውያኑ አጥር ሰብረው እንዲወጡ እያስገደደ ነው ተብሏል።

   
   በጅዳ  እና በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች ያሉ ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያንም የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተው  በቋፍ ላይ ናቸው ። በሪያድ እና በተለያዩ ከተሞቸ ባሳለፍነው ቅዳሜ በመንፉሃው ሁከት ጭካኔ የተቀላቀለበት በሃገሩ ነዋሪዎች ተወሰደ በተባለው እርምጃ ገና በመሰራጨት ላይ ያለው መረጃ ምስል ህጋዊ ሆነ ህገ ወጥ የሆነውን ሁሉንም እያስጨነቀ ነው ። እኔም እዚያው መንፉሃ ሆነውን የአይን እማኝ ከሰማሁ ወዲህ ከ16 አመታት በላይ የማውቃቸው ሳውዲዎች ይህን ፈጸሙ ለማለት ብቻ ሳይሆን በዚህች ሃገር  ይህ መሰል ግፍ በሰው ልጅ ይፈጸማል ለማለት ተቸግሬያለሁ። እውነት መሆኑን ደጋግሜ ሳሰላስለው ደግሞ የሳውዲ ኑሮ እየጎረበጠኝና ተስፋየን እየሟጠጠው ሄዷል። ብዙዎች በዚህና በመሳሰለው የማሳደድ ችግር ምክንያት ወደ ሃገር መግባት  ይፈልጋሉ ፣ በሪያድ ከመንፉሃ በተጨማሪ በኮንትራት ስራ የመጡና ለበርካታ አመታት በሳውዲ ነዋሪ የሆኑት ሳይቀሩ እንደ መንፉሃ ግፉአን በውድ የገዙትን እቃ በርካሽ እየሸጡና መኖሪያ ፍቃዳቸውን አሽቀንጥረው በመጣል  ወደ መጠለያው እየገቡ ነው ።

   9403551539675771-1    “በመንፉሃ ቁጥራቸው የማይታወቅ ኢትዮጵያውያን ሞተዋል … “  በሚል ነዋሪው በሚሞግተውና መንግስት ” ሶስት ብቻ ነው የሞተው! ” ያላቸው ኢትዮጵያውያን ደም ፈስሶ በድርድርም ቢሆን ሳውዲዎች  የጣሉትን ቅጣት አንስተው ህገ ወጥ ነዋሪዎች በፍላጎት እንዲገቡ ተፈቅዷል። ይህ ለሪያድ ነዋሪዎች የተሰጠው እድል በሁሉም ከተማ ላሉት ዜጎች ስለመስራቱ ማወቅ ባለመቻሉ ነዋሪው ተጨናንቋል።  በመካ ያለው ከበድ እያለ መጥቷል። በጅዳ ከንደራ የሚፈራውን ያህልም ባይሆን በእለተ ሃሙስ November  14,2013 እኩለ ቀን ለግማሽ ሰአት የዘለቀ ፍጥጫ እንደ ነበር እለታዊው አረብ ኒውስ ጋዜጣ ከቀትር በኋላ ዘግቦታል። በጣይፍ ፣ በጀዛንና በአቅራቢያ የተለያዩ አካባቢዎችም ጉዳይ  አሳሳቢ ነው ። ቢያንስ የመንግስት ሀላፊዎች መረጀ በመስጠት ሰውን ማረጋጋት ካልቻሉ ያየን የሰማነው የመንፉሃ አደጋ በከፋ መልኩ እንዳይጫር ስጋት አለኝ።

     በጅዳ ቆንስል ምን እየተሰራ እንዳለ የሚታወቅ ነገር የለም ። እርግጥ ነው ስራ እየተሰራ ነው ። ፖስፖርት ይታደሳል ፣አዲስ ይሰጣል፣ ከአስር ሽህ በላይ ይሆናሉ ለሚባሉ በእስር ቤት ላሉት ሊሴ ፖሴ ይሰጣል፣ ሌላም ሌላ ስራ ይሰራል። ከዚህ አልፎ ከግቢው በመታመስ ላይ ላሉ ወደ አስር የሚጠጉ ያበዱትን ፣ ከሰላሳ በላይ የነሆለሉና የታመሙትን ጨምሮ ሁለት መቶ የሚጠጉ ዜጎች ጉዳይ መቋጫ አልተገኘለትም። ለወራት ሲንከባለል የቆየ ወደ ሃገር የማሳፈር ክትትል ምን ምን ላይ እንደ ደረሰ የሚታወቅ ነገር የለም። የቻለው ምግብ እና ውሃ ብሎም አንዳንድ አስፈላጊ ቁሳቁስ እያቀረበላቸው ይገኛል ። ከዚህ ባለፈ ሁኔታውን አይቶ እንባውን እየረጨ ከመሄድ ባለፈ ምንም መስራት አልቻለም ፣ አቅሙም የለውም! በርካታ ወገኖች  እየሆነ ያለውን ለማወቅ ጉጉት አላቸው ። ያም ሆኖ የጅዳ ቆንስል የበላይ መረጃ መስጠትም ሆነ መቀበል አልፈለጉም። ወጌን በማስረጃ በአንዲት ማስረጃ ብቻ ላስረግጥ … !

     90439_91585ኢትዮጵያውያን እንደጨው ተበትነናል። ከቀናት በፊት ባሳለፍነው እሁድ  ሰባት ኢትዮጵያውያን ታሳሪዎች ይዞ ከጀዛን ክልል ወደ ሽሜሲ አዲሱ እስር ቤት ሲጓዝ የነበረ አንድ የፖሊስ መኪና እኩለቀን ሊዝ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰበት አደጋ አራት ኢትዮጵያውያን መሞታቸውና ሶስት ያህሉ መቁሰላቸውን በሰማሁ ማግስት መረጃውን በትኩሱ ለማድረስ ተወካዮቻችን በስልክ ደውየ ሳጣቸው ከጭንቀቱ ጋር ውስጤ የተሰማውን ለመግለጽ እቸገራለሁ ። ነገሩ እንዲህ ነው …እሁድ ለሰኞ አጥቢያ በጅዳ መኮሮና አካባቢ እኩለ ሌሊት ላይ አንድ መረጃ ደረሰኝ “ኢትዮጵያውያንና እዚህ አገር ተወልደው ባደጉ የውጭ  ዜጎች መካከል ሁከት ተቀስቅሷል! “የሚል ነበር።  መረጃ ለማቀበል ለብቸኛ ተጠሪዎቻችን ስልክ ደወልኩ ። አይመልሱም። መረጃ አቀባዮቸን መልሸ ስደውል አካባቢው በጩኸትና ረብሻ ሲታመስ ሰማሁ። ደግሜ ወደ ለሃላፊዎች ደወልኩ ። ዋና ሃላፊው አቶ ዘነበ ከበደም ሆነ ምክትላቸው አቶ ሸሪፍ ኸይሩ ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን አያነሱም ።  ፖሊስ ደርሶ ረብሻው ተበተነ። አካባቢው መረጋጋት ያዘ ። መንፉሃን እያስታወስኩ በደረቁ ሌሊት በአይኔ እንቅልፍ ሳይዞር ነጋ … !

       አይነጋ የለም ነግቶ ፣ ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት ተይዘው የቀሩት ቤታቸው ተዘርፎ ድልድይ ስር ማደራቸውን በቦታው ሔጀ ተመልክቻለሁ። በግጭቱ የቅርብ ርቀት ተሸብረው ያገኘኋቸው የግጭቱ ተጎጅዎች ህክምና ያገኙ እንደሁ እና ጉዳዩንም ስልክ የማያነሱት የቆንሰሉ ሃላፊዎች ጉዳታቸውን እንዲያውቁላቸው አሁንም ወደ ሃላፊዎች ደወልኩ። አያነሱም ። ተጎጅዎችም ሌሊት ለእኔ እንደ ደወሉ ወደ ቆንስሉ ከሃያ ጊዜ በላይ ደውለው ስልኩን የሚያነሳ ስላጡ ወደ እኔ መደወላቸውን አጫወቱኝ ። ግራ ብጋባም ቢያንስ የሆነውን ሁሉ ለማስረዳት ተጎጅዎችን ወደ ቆንስሉ ለመውሰድ ወስኘ ሳማክራቸው ” አድርገህው ነው! ” አሉኝ ከነፍሰ ጡሯ እህት ተጎጅና ሁለት በግጭቱ የቆሰሉ የተደበደቡትን እና ወደ ስምንት የሚደርሱ እማኞችን ይዠ ወደ ጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት አመራሁ። በሙግት ወደ ግቢው ብንገባም ሃላፊውን እኔን ለማነጋገር እንደማይችሉ እና ስብሰባ ላይ መሆናቸው እንደ ምክንያት ተሰጠኝ። ሰውነቴ ተቆጣ ፣ “የእነሱን ስራ ስሰራ ለምን አይተባበሩኝም!” ራሴን ጠየቅኩ ፣ መልስ ግን የለኝም! ከማይጋነን መጉላላቱ በኋላ ዋና ሃላፊው አቶ ዘነበ ከበደ አማካኝነት በወረደ ትዕዛዝ የዲያስፖራዋ ሃላፊ ቆንስል ሙንትሃ እንዲያነጋግሩኝ ተደርጎ ቆንስሏን አግኝቸ አነጋገርኳቸው ። ለመኮረና ግጭት መረጃ አዲስ እንደሆኑ ገልጸው ለመረጃው አመስግናውኝ  ቁስለኛና ተጎጅዎችን አስተዋውቄያቸው ወደ ስራየ ከመውጣቴ በፊት ማለት የፈለግኩትን በስጨት እንዳለኩ ተናገርኳቸው ! ቆንስል ሙንትሃ ባዩትና በሰሙት ተደናግጠው እዚያው እያለሁ በውስጥ መስመር ደውለው ለአቶ ዘነበ የጉዳዩን አሳሳቢነት አሰረዷቸው። ወደ ቆንስሉና ወደ ሃላፊዎች ስልክ ስደውል የማይነሳበትን እንቆቅልሽ ከማስረዳት ባለፈ በዚህ ሰአት በአንድ የስልክ ጥሪ በሚታጣ መረጃ ብዙ ጥሩም መጥፎም ሁኔታ ስለሚያስከትል የዜጎችን መብት ለማስከበር የተቀመጠ የመንግስት አካል ለመረጃ የራቀ መሆኑን አደገኛ አካሔድ ገለጽኩላቸው ። ብዙም ሳልቆይ ባለጉዳዮችን እዚያው ትቸ ወደ ስራየ አቀናሁ …

    ከቀትር በኋላ የቆንስሉ ሃላፊ አቶ ዘነበን ጨምሮ ሶስቱም ዲፕሎማቶች የመኮረናው ግጭት ወደ ሚመለከታቸው የሽማልያ ፖሊስ ጣቢያ ማቅናታቸውን ሰምቻለሁ። በመኮረና ሆነ ተብሎ በወሰድኳቸው ተጎጅወች የሰማነውን በዜጎች ላይ የመቁሰልና የሞት አደጋ መከሰቱን ጠይቀው ከጀኔራል አዛዡ መልስ እንደተሰጣቸው ቆንስል ሙንትሃ ስልክ ደውለው ገልጸውልኛል። የፖሊስ አዛዡም ረብሻው በኢትዮጵያውያንና በቻድ ዜጎች መካከል ከሶስት ቀብ በፊት በተጀመረ መጠነኛ ጸብ ምክንያት እንደነበር መረጃ እንደነበራቸው ፣እሁድ ለሰኞ አጥቢያ ደግሞ ሁከቱ መከሰቱን እና ፖሊስ እንዳበረደው ማስረዳታቸውን ፣ በእለቱ ግጭት ተኩስ እንደ ነበር ነገር ግን በተኩሱ የቆሰለ እንደ ሌለ  እንዳሰረዷቸው ፣ አምስት ያህል በድብድቡ የቆሰሉ እንጅ የሞተ ሰው እንደ ሌለ አስረግጠው ሲነግሯቸው በግርግሩ የታሰሩትን ኢትዮጵያውያን እንዳስጎበኟቸው ቆንስል ሙንትሃ ገልጸውልኛል። ሳውዲ ጋዜት በቀጣዩ ቀን Tuesday 12 November 2013 የመኮሮናውን ግጭት እንዲህ ብሎ አሽሞንሙኖ አቀረበው 57 held after Chadian-Ethiopian clash  http://www.arabnews.com/news/475786 . እንግዲህ ከላይ ለማሳየት የሞከርኳቸው የመረጃ ግብአቶች በዲፕሎማቶች ዙሪያና በጭንቀት ላይ ስላለው ነዋሪ መጠነኛ መረጃ በመስጠት እየሆነ እና እየተሰራ ያለውን በትክክል ካሳየ መልካም ነው ።

      መሬት ላይ በአይናችን የምናየውን እንዲህ ሆኖ እያለ እውነት የሚጣረስ ፕሮፖጋንዳ መሰል መረጃ ደግሞ ከመንግስት ቴሌቪዥንና ራዲዮ ሲነገር እየሰማን ነው። መንፉሃ ላይ ፍጅቱ ሊጀመር ሲዳዳው ፍጥጫውን ማርገብ ያልቻሉት ዲፕሎማቶች መንፉሃ በደም ከተበከለች በኋላ ዜጎች ያለ መቀጮና እስራት ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ስምምነት ማድረጋቸው እውነት ነው። ያም ሆኖ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደሚነግሩን ስራውን በቅንጅትና በማቀላጠፍ እየሰሩ አይደለም  የሚል መረጃ ከተጨባጭ ምንጮች ይደርሰኛል።

ከቀናት በፊት አንድ ጽነፈኛ የምለው የፊስ ቡክ አፍቃሬ ኢህአዲግ ወዳጀ Ramatohara Dertogada ችግሩ ሲከሰት የሰጣቸው ለወገን ተቆርቋሪነት የታየበት አስተያየት ተቀይሮ ተመለከትኩት ። “… ሳውዲን ጨምሮ በሁሉም ዓረብ ሀገራት በዜጎቻችን የሚያደርሱት በደልና ግድያ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ የጥላቻ ሴራ ነው። … መንግስት በዜጎቹ የሚደርሰው በደል እንዲቆም ህጋዊ የሆነ አቋም ለዓለም ማህበረሰብ ያቀርባል። በአሁኑ ስዓት ለዜጎቹ ግዝያዊ የሆኑ የነብስ አድን ስራዎችና የዲፕሎማሲ ማግባባቶች እየሰራ ነው። ” ይላል! ይህን ሃሳብ ወዳጀ አለመጻፉን ብረዳም በሃሳቡ መስማማት መደገፉን ጠረጠርኩና የተዛባ መረጃ እየሰጠ ያየሁትን የኢትዮጵያ ቲቪን ረገምኩ! እንደተባለው ስራው እየተሰራ መሆኑ እውነት ቢሆን ምንኛ ደስ ይል ነበር! ግን በመንግስተ  መገናኛ ብዙሃን ” በሳውዲ የሚገኙ ዲፕሎማቶች 24 ሰአት እየሰሩ ነው! ” የተባለው መረጃን ተሰራ ከተባለው ስራ ጋር ስናነጻጽረው እውነት አይደለም! ባሳለፍናቸው ቀናት መረጃን ለማግኘት በየቀኑ ወደ ሪያድ እደውላለሁ። በርካታ መረጃዎችን ለመስብሰብ ሞክሬያለሁ ፣  በመጠለያ ያሉት በርሃብና በውሃ ጥም እየተቸገሩ ነው። ማረጋገጥ አልተቻለም እንጅ አዲስ የሞት ዜናም አለ!

    አሁን አሁን በመላ ሃገሪቱ በተለይም በሪያድ የሚሰማው ደስ አይልም። ረቡዕ ከቀትር በኋላ ሪያድ መንፉሃ የከፋ ችግር ተከስቶ ነበር ። ለጊዜው በረድ ቢልም የተጎዳ ሰው አለ ….መካ ውስጥ ወደ ሃገራችን ስደዱን ባሉ ዜጎቻችን መካከል ሁከት ሊቀሰቀስ እንደ ነበር ተጨባጭ መረጃዎች ደርሰውኛል። የሳውዲ ጋዜጦችም ይህንን አረጋግጠዋል።  የሪያድ ዲፕሎማቶች ነዋሪውን በማቀናጀት ማስተባበሩ ላይ ዳተኛ መሆናቸው ሲያስተዛዝብ ፣ በጅዳ ዲፕሎማቶች ሌላው ቢቀር ነዋሪውን ሰብሰበው መረጃ ሊሰጡት አልፈቀዱም።  በቆንስሉ መጠለያው እየተርመሰመሱ አንጀት ስለሚበሉት ተፈናቃይ ሰራተኞችም ሆነ “ከሃገር ይውጣ !” በተባለው ህጋዊነመኖሪያ ፈቃዱን ማስተካከል ባልቻለው ዜጋ ዙሪያ እንዲመክር እንዲዘክር የሚሰሩት ስራ የለም! ይህን ለማጣራት ከቀናት በፊት ወደ ጅዳ ቆንስል ጎራ ብየ ነበር ። ጠባቂው ወንደሜ  የቀድሞው የህዝባዊ ሃርነት ግንባር መድፍ አገላባጭ ታጋይ “ገሬ! ” አትገባም አለኝ ። ምክንያቱን ስጠይቀው ” አቶ ዘነበ እኔ ሳልፈቅድ አታስገባው ብለውኛል !” ሲል መለሰልኝ ። ከብዙ ሙግት በኋለ በአማላጅ ገባሁ ። በጅዳና አካባቢው ያለ ነዋሪ መረጃ ተጠምቷል ፣ ሃላፊዎች መረጃ መስጠት ቀርቶ መረጃ ለነዋሪው ለመስጠት የምንሞክረውን ክብራችን እየነኩ እያሳዘኑን ነው! እውነቱ ይህ ነው! ብዙ አልልም  ! ብቻ በሳውዲ አረቢያ ሪያድና ጅዳ የሚገኙት የኢትዮጵያ  መንግስት ኢንባሲና ቆንስል መስሪያ ቤቶች እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ መረጃ በመስጠት እንኳ ለህዝብ ማስረዳት ፣ማረጋጋት እንዳይቻል በራቸው በብረት ሰረገላ ተከርችሟል። በሩን ለማስከፈት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም አልተቻለም!

     የሳውዲ በርካታ ክልሎች የተለያዩ መረጃዎችን አገኛለሁ። መረጃዎችን በተገቢ መንገድ ለመጠቀም እሞክራለሁ።  ከሪያድ መንፉሃ ከተሰደው እርምጃ ውጭ በቀሩት የሃገሪቱ ክፍሎች በኢትዮጵያውያን ላይ ማንኛውም ህገ ወጥ እንደሚያዘው ይያዛሉ እንጅ  የተለየ ተጽዕኖ ወይም ማሳደድ ተፈጠረ ሲባል አልሰማሁም።  ከምህረት አዋጁ ማለቂያ ከፍተሻው የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በሪያድ መንፉሃ እየሆነ ስላለው የአይን እማኞችን በአካል ከማግኘት ጀምሮ በስልክ እና በተንቀሳቃሽ ምስል ሳይቀር መረጃዎች ይደርሱኛል።  አሁን አሁን ቁጥራቸው ወደ ሃምሳ ሽህ ይዘልቃሉ የሚባሉት ዜጎች ኢትዮጵያውያን በመላ ሳውዲ ይገኛሉ ተብሎ እየተገመተ ነው ። ይህ ቁጥር ቀላል አይደለም ። ጉዳዩ የሃገር የህዝብ ጉዳይ በመሆኑ ዜጎችና የመንግስት ተወካዮች ዘር ፣ ሃይማኖት እና ፖለቲካ ሳይለያየን በጋራ መረጃን ከመለዋወጥ ባለፈ ብዙ መንገድ ሂደን በአደጋ፣ በስጋትና በጭንቀት ላይ ያሉ ወገኖቻችን ብንታደጋቸው መልካም ነበር ። ባሳለፍነው ሳምንት በዘር በሃይማኖትና በፖለቲካ ለየቅል የሚያነጉደው በመላ ሳውዲ አረቢያ ብቻ ሳይሆን በመላ አለም በሚገኙ  ወገኖች መሆናቸውን እንደኔ የታዘበ ካለ አላውቅም። ያም ሆኖ መንግስት በአዋጁ ማብቂያ የመጨረሻ ቀን በሰጠው መግለጫ “የቤት ለቤት ሰበራ አይኖርም!”  ብሎ ነበር ። ይህ የወጣው መመሪያ ግን በእኛ ላይ አልሰራም። መመሪያው በመንግስት ፈታሾች ለመጣሱ እና በመንፉሃ ለተወሰደው እርምጃ በመንፉሃ በዜጎቻችን ከዚህ ቀደም የተሰሩ ወንጀሎች እንደ ምክንያት ቢቀርቡም ተንቀን ለተወሰደብን ከሰብዕና የወጣ ነውረኛ ወንጀል ግን ብዙዎች አብረን በህብረት ደወርጊቱን በማውገዝ  የተሳካ ድምጽ መሰማቱን ተመልክቻለሁ !

      በመንፉሃ ዳግም ሁከት ተቀስቅሶ ከበረደ ወዲህ በሪያድ መጠለያ አና በአካባቢው የመረጃ ክፍተት የፈጠረው ከባድ ጭንቀት ነግሷል። ይህ ጭንቀት በሪያድ ከሴቶች እና ከወንዶች ጊዜያዊ መጠለያ ቤት ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም አገር ቤትን ባካለለ መልኩ እየተስፋፋ መሆኑን ከሚደርሱኝ መረጃዎች ለመረዳትና ለማወቅ ችያለሁ። በተለይም ከመጠለያ ፣ ከእስር ቤት እና ከነዋሪው ከሚበተኑትና ከሚደርሱት መረጃዎች አንጻር ነዋሪው ችግሩን እየለጠጠው ፣ ችግሮች በራሳቸው እያደጉ የሚያዝ የሚጨበጥ እንዳይጠፋ ስጋቴ ከብዷል !  የከበደውን አደጋ በመረጃ ልውውጥ የተደፋብንን የጭንቀት ደመና ለመግፈፍ መጠቀም ከቻልን እድሉ አላለቀም! በአሁኑ ሰአትም የመረጃው ክፍተት የሚታይበት የመንግስት ዲፕሎማቶችና የነዋሪው ግንኙነት መጠገን የማይቻል አይደለም ። ይቻላል! እናም የመፍትሄ ሃሳብ ልጠቁም …

    እኔም እንደ መፍትሔ ሃሳብ በጅዳና ሪያድ የምትገኙ መንግስት ተወካዮች እንደ ከዚህ ቀደሙ በድርጅታዊ አወቃቀር ሳይሆን ሁሉም አትዮጵያዊ እንደ ዜጋ የሚሳተፍና የሚመክርበት ስብሰባ በአስቸኳይ መጥራት ! ሌላው በዙሪያው የምንገኝ ወገኖች በማህበራዊ ገጾች አምድ ላይ የመጻፍ መብታችን የተጠበቀ ቢሆንም በየስርቻው እየተነዛ የስነ ልቦና ጭንቀት እየለቀቀ ያለው ያልተጨበጠና ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት መቆጠብ ይኖርብናል ! ጠቃሚ መረጃዎች ካሉ ከላይ ይቋቋም ዘንድ ሃሳብ ላቀረብኩት ኮሚቴ በመላክ የመረጃ ክምችት ከመፍጠር ባለፈ ትክክለኛውን መረጃ ለህዝብ አንዲደርስና በጥንቃቄ እና በተረጋጋ ሁኔታ እንድንመራ ይረዳናል።
ሌላውና ዋንኛው ስራ መሰራት አለበት ብየ የማምነው ወደ ሃገር ለማሳፈር የሚደረገው መንገድ እስኪስተካከል ድረስ ማንኛውም ስደተኛ ሰልፍ ማድረግና ወደ ንብረት ሰበራ አመጽ እንዳይሸጋገር ነዋሪውን የማረጋጋት ስራ መስራቱ ግድ ይላል !

     መላ ካልተባለ አጠቃላይ ሁኔታው ጥሩ አይደለም  ፣ ልዩንትን አስወግደን በህብረት የማንሔድ ከሆነና አሁንም በተቃራኒ ጥላቻ የምንሔደው አካሔድ ፍጹም አዋጣም! ይህ አደጋም ከዜጎች አልፎ በሳውዲና በኢትዮጵያ የቆየ ግንኙነት ታሪክ ትልቁን ስህተት ወደ መስራቱ እንዳያስኬደን ስጋት አለኝ  ! ችግሩ ሳያንሰን በግፉአን ዜጎችና በዲፕሎማቶች የሰመረ ግንኙንት እጦት ከሚኮላሸው የነፍስ አድን ህብረት ክፍተት ጣጣ አንድየ ይሰውረን !

የግርጌ ማስታዎሻ :
በመላ አሜሪካና አውሮፖ ብሎም በተለያዩ አለማት የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ ላለው ወገን ድጋፍ ስታደርጉ ማየት ለወገን ያላችሁን ፍቅር ያሳያልና ደስታየ ወሰን አጥቷል። የሳውዲ አረቢያን ባንዴራ ነገር ግን አደራ ! ይህ በአረንጓዴ መደብ ላይ በነጭ ቀለም የቁርአን ቃል የሰፈረበት ባንዴራ በመሆኑ በክብር ልንይዘው ይገባል! በስህተት አለያም በጥላቻ ስሜት ተገፋፍተን ለማቃጠልና ለመቅደድ ብንሞክር መላ የአለምን ሙስሊም አስከፍቶ ወገኖቻችን ወደ ሃገራቸው እንዳይሄዱ ከሚፈጥረው ጫና በተጨማሪ በዜጎቻችን መብት ይከበርልን ጥያቄ ዙሪያ ልናጣ የምንቸለው ድጋፍ ማስተዋል ግድ ይለናል!  ይህን አልፈን ከሔድን ተጠቃሚ ካለመሆናችን በተጨማሪ ጸብ ቅያሞታችን ከሳውዲ ጋር ብቻ ሳይሆን ከመላ የሙሰሊም እምነት ተከታዮች ጋር ስለሚሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል! በፍጹም ጨዋነት የሚካሔደው ሰላማዊ ሰልፍ ለማየት ጓጉቻለሁ!

ከምንም በላይ ደግሞ ከመጣብንን መከራ አንድ አምላክ ይጠብቀን!

ነቢዩ ሲራክ

 

በሰሞነኛ ጉዳዮች ትንሽ እንቆዝም –ግንቦቶች ከጥቅምት ንፋስ ተረፉ አሉ!

$
0
0

ይሄይስ አእምሮ

“አንበሣን ፍርቼ ዛፍ ላይ ብወጣ ነብር ጠበቀኝ፡፡”
Penእትብቱ በተቀበረበት የገዛ ሀገሩ መኖር ያቃተው ከርታታ ወገናችን የወያኔን ጭቆናና የኢኮኖሚ መድሎ ሸሽቶ ወደዐረቡ ዓለም ቢሰደድ የባሰ መከራና ጭፍጨፋ እየደረሰበት መሆኑን በሚዲያዎች እየሰማን ነው፤ እሰኪያልፍ ያለፋል፡፡ በዚህ በሰሞኑ ውርጅብኝ ሕይወታቸውን ያጡ ዜጎቻችንን ነፍስ ፈጣሪ በጽድቁ ቦታ ያኑርልን፡፡ ሀዘኑ እንደወገንና እንደሀገር ውርደት የወልም የግልም ነውና ለመላው ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያንና በተለይም ለሟቾች ቤተሰቦች እግዚአብሔር መጽናኛውን ይላክልን፡፡ ዕዳችሁ ይለቅ ብሎም ከአሁን በኋላ  ከተመሳሳይ ክፉ ዕጣ እንዲሠውረን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ ይህን ሽል መንጣሪ የሽፍቶች መንግሥትም ዕድሜውን እንዲያሣጥርልን በየምንከተለው የእምነት ፈለግ ለፈጣሪያችን እንጸልይ፡፡ ከልብ ማዘንና መጸለይ የብዙ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ ነው፡፡

 

“በራበህ ጊዜ የምታገኘው ምግብ ከምግቦች ሁሉ የበለጠ ጣፋጭ ነው!”

ከአትሌቲክስ ውጪ ሀገራችን በዓለም የክብር መድረክ የምትታወቅበት ዘመነኛ ክንዋኔ እምብዝም የለም፡፡ በጦርነት፣ በርሀብ፣ በግፈኛ አገዛዝ፣ በግድያና እሥራት፣ በደናቁርት መሪዎችና በሙስና … የምትታወቀው ኢትዮጵያችን በእግር ኳስ ስሟ መነሣት ከጀመረ ጥቂት ጊዜያት ተቆጠሩ፡፡ በዚህ ከድሆች አምባ ብዙም በማይስተዋል የስፖርት ዓይነት ብርቅየዎቹ ዋሊያዎች እያስመዘገቧቸው የሚገኙት አፍሪካዊና ዓለም አቀፋዊ ድሎች እሰዬው የሚያሰኙና ወያኔዎች ካስከተሉብን አጠቃላይ ውርደታችን በተቃራኒ ስማችን ጨርሶውን እንዳይጠፋ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ዘረኝነት ላይ የተመሠረተ መድሎንና አስተዳደራዊ በደልን የመሳሰሉ በርካታ ውስጣዊ ችግሮችን ተቋቁመው ለዚህ ሀገራዊ ድል ላበቁን ዕንቁ ልጆቻችን ከፍ ያለ ምሥጋና ይድረሳቸው፡፡

ወያኔው በሃይማኖትና በዘር የቆረጣ ሥልት ገብቶ ሊበታትነውና ሊያጨራርሰው የሚዳክርበቱ ሕዝብ በተለያዩ ዜማዎችና የአንድነት መግለጫ እንቅስቃሴዎች አማካይነት በካምቦሎጆና ከዚያም ዉጪ በየሠፈሩ ቁጭቱን የሚወጣበት ይህ የእግር ኳስ ጨዋታ ይበልጥ እያበበ እንዲሄድ ያለኝን ምኞት ከመግለጽ በተጓዳኝ የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ኅዳር 7 ቀን 2006ዓ.ም ለዓለም ዋንጫ የመጨረሻ አህጉራዊ ማጣሪያ ከናይጄሪያ ጋር ፍልሚያ የሚያደርገው ብሔራዊ ቡድናችን እንዲቀናው በተለያዩ አንገብጋቢ ምክንያቶች የተነሣ እግዚአብሔርን ማስቸገር እፈልጋለሁ፡፡ ተደጋጋሚ ድል የማይጠገብ ቢሆንም ለናይጄሪያውያን  አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የጨዋታ ድል አምሮታቸውን የተወጡ በመሆናቸውና እኛ ለዚህ ዓይነቱ መድረክ እንግዳና ባይተዋር በመሆናችን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና አጠቃላይ ኅልውና በወሮበሎች የከፋፍለህ ግዛ ማኪያቬላዊ ሥልት በተለይ ባለፉት ሃያና ሠላሣ ዓመታት ክፉኛ ስለተጎዳ ይህ አጋጣሚ ከናይጄሪያ ይልቅ ለዚህ ክፉኛ የተጎሣቆለ ሕዝብ ይበልጥ ስለሚጠቅም፣ በአሉታዊ ነገሮች ከናይጄሪያ ይልቅ ኢትዮጵያ ይበልጥ ስለምትታወቅ ይህ ዕድል የሀገሪቱን ምሥል በማፍገግ አኳያ የበኩልን ሚና ስለሚጫወትና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች የተነሣ  በዚህ ጨዋታ ፈጣሪ ፊቱን ወደዋሊያዎች ቢያዞር በልጆቹ መሀል አድልዖን እንደፈጸመ አልቆጥርም፡፡ እናት እንኳን ይበልጥ ለከሳውና ለተራበው ልጇ ከሳሳው ሞሰቧ ከዚያችው ካለችው ቆረስ አድርጋ ትጨምርለታለች፡፡  እናም ከዚህ ተጠየቃዊ አመክንዮ በመነሣት ፈጣሪ ለኢትዮጵያ “እንዲያዳላ” ብናስቸግረው በኃጢኣተኝነትና በይሉኝታቢስነት የምንፈረጅ አይመስለኝምና ለአንዲት አቡነ ዘበሰማያትና ለአንድ ቶባቶብቱልላህ የሶላት ዱኣ ባንጓደድ መልካም ነው እላለሁ፡፡

 

“ሰው በወደደው ይቆርባል”

ባለፈው ሰሞን የወያኔዎች ሦስት የድህነት አባላት በአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባል ላይ ፈጸሙት በተባለውና በሚዲያ በተገለጸው አሳዛኝ ገጠመኝ ላይ በመመርኮዝ አንድ መሠረታዊ የአቋም ለውጥ እንዳደረግሁና ግንቦት ሰባትን እንደደገፍኩ መግለጼ ይታወሳል፡፡ ያ አቋሜ እስካሁኒቷ ቅጽበት ትክክል ነው፤ ትክክል እንደሆነ እንዲቆይልኝም እየጸለይኩበት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ መደገፍም ሆነ መንቀፍ ወይም ድምፃዊት በዛወርቅ አስፋው በአንደኛው ቀደምት የቅንቀና ሥራዎች “መኖር አይቻልም ወይ የማንም ሣይሆኑ…” እንዳለችው ዐርፎ መቀመጥም ያስወነጅላል፤ በቃላት በትረ-ዲያብሎስም ያስጎንፋል፡፡ ይህ ዘመን አመጣሽ በሽታ ወረቱን ጠብቆ እስኪያልፍ ከመታገስ በስተቀር በጠብ ያለሽ በዳቦ ቅራኔንና አምባጓሮን እየፈበረከ ከሚወነጭፍ ሥራ-ፈት ሁሉ መወዛገብ አግባብ አይደለም፡፡ ጣልቃ መግባት ያለባት ብሂል ትዝ አለችኝ፡፡ እንደአቤቶኪቻው አባባል በቅንፍ ላስቀምጣት፡፡

(ባል ይሞታል፡፡ ጋለሞታ ሚስት ቆየት ብላ የባልን አንድ ወንድም ‹አግባኝና ባዕድ ሳይገባብን እኔና አንተው የወንድምህን ልጆች እናሳድግ› ትለዋለች፡፡ እሱ የሰውን ሃሜት በመፍራ እምቢዬው ይላታል፡፡ ደጋግማ ልታስረዳው ሞከረች – አልሆነላትም፡፡ ነባር ባህልን መጣስ አስቸጋሪ ነውና አንጎሉን ቀፍድዶ አላላውስ ስላለው በእምቢታው ይጸናል፡፡ ሴት መለኛ ናትናበምሳሌ ልታስረዳው እንዲህ አለችው፤ ‹ በል፣ ይህን በሬ ሳታርድ ቆዳውን በቁሙ ግፈፈውና ወደገበያ ወስደህ አዙረህ አምጣልኝ›፡፡ እንዳለችው አደረገ፡፡ ቆዳው የተገፈፈውን በሬ ለጥቂት የገበያ ቀናት እያመላለሰ አዞረው፡፡ ከተመልካች ገበያተኞች ያገጠመውን ግብረ-መልስም(ፊድባክ) በየጊዜው ይነግራታል፡፡ በመጀመሪያው ቀን ሁሉም ተከሩንና ገበያውን ትቶ ግር ብሎ እንደሞኝ እየተከተለ ሣይቀር በሬውን እንደተመለከተው፣ በቀጣዩ ቀን ባለፈው ያላየውና ቢያየውም ያልጠገበው ሰው እንደነገሩ እንዳየው፣ በሦስተኛው ‹ያ በሬ ዛሬም መጣ› በሚል የተወሰነ ገበያተኛ ከመቀመጫው ሳይነሳ መልከት እንዳደረገው፣ በአራተኛው የገበያ ቀን ማንም ከጉዳዩ ሳይጥፍ ቢያይም እንዳላዬ እንዳለፈው አብራርቶ ይገልጥላታል፡፡ ይሄኔ ‹አየህ፣ እኔና አንተም ብንጋባ ልክ እንደዚሁ ነው፡፡ በመጀመሪያው አካባቢ እንደወረት ቆጥረው ይንሾካሾካሉ፤ ያማሉ፤ የቡና ቁርስም ሊያደርጉን ይችላሉ፡፡ እየቆዬ ግን ከነመፈጠራችንም ይረሱናል፡፡ ስለዚህ ይህ ዕድል  ሁለታችንንም አያምልጠን› ትለዋለች፡፡ … ይስማሙ አይስማሙ የራሳቸው ጉዳይ፡፡ ለነገሩ በሰው ጉዳይ ምን አገባን? ማነው – ንዋይ ሳይሆን አይቀርም- ‹ሰው በሰው ጉዳይ ምን ኮነሰረው› ብሎ ያኔ ጥንት ሲያዜም አድምጨዋለሁ፡፡) በእውነቱ ከወሬ ባጀታችን ትንሽ ጊዜ ቀነስ አድርገን ለሥራ ብናውለው ኖሮ ይሄኔ እኛ ኢትዮጵያውያን የት በደረስን?)

ስለዚህ እኔ በአባልነት ባልመዘገብም በአሁኑ ወቅት ከፉልቶክና ከፓልቶክ የወሬ ጋጋታ ባለፈ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደገባ በይፋ የገለጸልኝን ድርጅት እንደምደግፍ በድጋሚ መግለጽ እፈልጋለሁ፤ ቁንጅና ደግሞ እንደተመልካቹ እንጂ የኔን ቆንጆ ማንም ሊመርጥልኝ አይችልም፤ አይገባምም – ያልተለመደ ነውና፤ የዚያ ዓይነት ቂልነት ካለ ህመሙ ሳይብስ በቶሎ ሃኪምን ማማከር ይበጃል፡፡ ይህን ስል ከወሬ ቱሪናፋ በስተቀር ሌላ አማራጭ የሚሰጠኝ ኃይል በማጣቴ እንጂ ግንቦት ሰባት ምንም ችግር የሌለበትና ምሉዕ በኩልሄ የሆነ ያህል እንደቀኖና የምቀበለው እንዳልሆነ ያለማመንታት መግለጽ እፈልጋለሁ – ግና ልጅን ሲወዱ ደግሞ ከነልሃጩና ከነንፍጡ መሆኑን ቢያንስ ለራሴ መረዳት እፈልጋለሁ – ሲያድግ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ሜዳ ፊልድ ማርሻል እሚሆነው እኮ እንዲያ ተዝረክርኮ አድጎ ነው፤ ደግሞስ ለአካለ መጠን ደርሶ የተወለደ ሰው ወይ ድርጅት ማንን ታውቃላችሁ? ጂ – ሰቨን ከተሳሳተም ይሳሳት – ሳይሳሳት እንዴት ሊማር ይችላል – ንዴት ቢጤ ወረር ሊያደርገኝ ሲፈልግኝ እንደመራቀቅም ያደርገኛልና ይቅርታ፡፡ እናም የኔን ግንቦት ሰባት መደገፍ የምትቃወሙ ፕሊዝ ለቀቅ አድርጉኝና የራሳችሁን ወገብ ጠበቅ አድርጉ፡፡ ፍቅርና ድንኳን የትም ይተከላል ሲባል አልሰማችሁ እንደሆነ አሁን ልንገራችሁ፡፡ አንድ ምቹ ቦታ ላይ ተቀምጦ ማውራት ማንም አያቅተውም፡፡ ከዚህ ሁሉ የወሬ ክምር ጥቂትም ቢሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያየሁት በዚህ ድርጅት ነውና እንዲቀናው፣ ጠላቶቹንም እንደሰሞኑ ሁሉ እግሩ ሥር እንዲያውልለት አንድዬን እለምናለሁ፡፡ መነሻው ምንም ይሁን ምን በከንቱ መጎነታተሉን ትተን ይልቁናስ ተጨባጭ ነገር ለመሥራት እንሞክር፡፡ መቶ ዓመት ቢያወሩትና መቶ ዓመት እርስ በርስ ቢወጋገዙ ጊዜ እንደሆነ እንደጋሪ ቆሞ አይጠብቅምና ጠብ የሚል ነገር የለም፡፡ አድሮ ቃሪና መሆን የለውጥ ማዕበልን ለመጋፈጥ በግትርነት እንደመቆም ይቆጠራል፡፡

ሌላ አማራጭ ቢመጣና ለምሳሌ ‹ሸንጎ› የሚባለው ስብስብ ወይም ከአንድ ሺህ ምናምን ክቡራንና ንዑዳን ኢትዮጵያውያን ፖለቲካዊ ኩይሣዎች ውስጥ አንድኛው በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ደጀንንና ጎሐ ጽዮንን በወያኔዊ አገላለጽ በመብረቃዊ የማጥቃት እርምጃ መቆጣጠሩን ቢያውጅና እኔ የምደግፈው ድርጅት እዚያው ኤርትራ በረሃ ውስጥ እንደተጎለተ ቢቆይ የመታገያየን ግምባርም በሉት ንቅናቄ ለመለወጥ አፍታ እንደማይፈጅብኝ ከአሁኑ ልገልጽላችሁ እፈልጋለሁ፡፡ ዘመኑ የለውጥ ዘመን ነው፡፡ ለውጥ ደግሞ የሕይወት ቅመም ነው ይባላል፡፡ ለውጡ አወንታዊና ከራስ ጥቅምና ፍላጎት ብቻ የተዋቀረ አይሁን እንጂ ዛሬ የኔ ግንቦት ሰባትን መደገፍና ማበረታታት በዚህ ድርጅት የቆረብኩ ያህል አስቆጥሮ ሌሎች እመርታ የሚያሳዩ የነጻነት እንቅስቃሴዎችን አልደግፍም ወይም ከዚያም በባሰ እቃወማለሁ ማለት አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር የሚከሰተው ለሕዝብ ነጻነት ሣይሆን ተዘውትሮ እንደሚባለው ትናንሽ ዘውዶችን በየጭንቅላቱ ሰንቅሮ ለሥልጣን ፍቅር ሲል ቀን ከሌት በሚበዛን ዜጋ የዘቀጠ ስብዕና ውስጥ ነው፡፡ እኔ ደግሞ ሥልጣን አልወድም፤ አልፈልግምም፡፡ ይህን ብልም የሀገራችንን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በሚመለከት ከኔ በላይ የሚያውቅ ዜጋ በጭራሽ ስለሌለ ሰው እስኪገኝ ድረስ ግፋ ቢል ለአንድ ሠላሳና ዐርባ ዓመታት ያህል ብቻ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ሊያውም ከፈቃዴ ውጪ በማስገደድ ጭምር ታስይዙኝ እንደሆነ እንጂ እኔ በፍጹም ሥልጣን አልሻም፡፡ ወደዚህ ዝቅተኛ የሥልጣን እርከን ራሴን ያጨሁትም የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ያዝ ብላችሁ በሎቢስቶች እንዳታስቸግሩኝ ከወዲሁ በመፍራና ያን በመሸሽ ነው …፡፡ አዎ፣ ፈጣሪ ይመስገን – እንደኔ ዓይነቶች ሥፍር ቁጥር የለንም፤ ሞልተናል፡፡ ማን ነበር እያረረ የሚስቅ? ማሽላ አይደለም – ኢትዮጵያዊ እንጂ፡፡

ግንቦት ሰባትን እደግፋለሁ ስል በተለይ ከአሁን በኋላ – እስካሁንም ያደረግሁት አይመስለኝም – የኔን በዋናነት ጨምሮ የብዙዎቻችን ንቃተ ኅሊና ገና እታች እመነሻው አካባቢ የሚርመጠመጥ በመሆኑ ቅን ዜጎችን ላለማሳሳት ሲባል በነገር አማረልኝ የሆነ ያልሆነና ያልተረጋገጠ አሉቧልታ ላለመጻፍ ለራሴ ቃል እገባለሁ፡፡ “አንድ ወሬኛ ያባረረውን ሺህ ጦረኛ አይመልሰውም” እንዲሉ በተለይ የሀሰት ወሬና የጥላቻ ቡጨቃ እግር አውጥቶ እንደልቡ በሚረማመድባትና በሚርመሰመስባት ሀገራችን ተስፋ የሚጣልባቸው ታዳጊ ድርጅቶችን ከመነሻቸው በነገር ቁድራ ቀንድ ቀንዳቸውን በመነረት ዕድገታቸውን ማቀጨጭ ወይም ከናካቴው ድራሻቸውን ማጥፋት በከንቱ የምንኮፈስበት የምዕተ ዓመቱ የጀብድ ተግባራችን በመሆኑ ከዚህ ወረርሽኝ ለመጠንቀቅ ሙከራየ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ለሥራየቤታዊ አሽሙርና አግቦ መልስ የማልሰጥ መሆኔን ደግሞ ከወዲሁ በ‹ታላቅ ኩራት› መግለጽ እወዳለሁ፡፡

ለድረገፆች መልእክቴን ስሰድ ስለግንቦት ሰባት አንዳች አወንታዊ ነገር የምገልጽ ከሆነ “ግንቦት ሰባት አለበትና ተጠንቀቁ” የሚል ማሳሰቢያ በ‹ሰብጀክት› መጻፊያው ላይ አስቀምጣለሁ፡፡ ከየተሸጎጥንባቸው የራሳችን ዓለሞች ወጥተን እውነተኛ መግባባት ላይ እስክንደርስ አንዳችን የአንዳችንን ስሜት መጠበቁ አይከፋም – እገሌ አወጣልኝ – እገሌ ደበቀብኝ ብየ አላላዝንባችሁም፤ ለኔ ብሎ የሚያወጣ ለኔም ብሎ የሚደብቅ እንደሌለ ደግሞ አውቃለሁ፤ አወጣም ደበቀም ለተነሣለት ዓላማ ነው – ማን ምን እንደሚፈልግም ጠንቅቄ ከተረዳሁ ቆይቻለሁ – “መጽሐፍ በሽፋኑ አይፈረድም/ የሚያብለጨልጭም ሁሉ ወርቅ አይደለም”፡፡ ብዙ የሚገርሙ ትዝብቶች አሉ፡፡ አሁን አላሰኘኝም አነሳሴም ውስጥ አልተካተተም እንጂ በተነፈስኩ፡፡ ፈቃደኛ የሆኑ ድረገፆች ግን ግንቦት ሰባትን በአወንታዊነት መልኩ ሣላነሳ የምጽፋቸውን መጣጥፎች ሊያትሙ ወይም በማንኛውም መንገድ ሊያሠራጩ ይችላሉ፡፡ ሆ …ሆ…ሆ… የዛሬው እኔ ለየት አለብኝ! አሰፋ ይርጉን ነው ያስታወሰኝ፡፡ መጣጥፌን ዐዋጅ በዐዋጅ አድርጌው ዐረፍኩ እኮ! አሁን እምን ቤት ነኝና ነው “ስታትሙ – ስታሰራጩ – ቅብጥሶ ጂኒጃንካ” እያልኩ በባዶ ሜዳ እምውረገረግ? ይገርማል! “ማን ሊስምሽ …” አሉ?

 

“ወርቅ ላበደረ ጠጠር፡፡”/ “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም፡፡”

አንድ ደንቆሮ አማራ፣ የአማራን ሕዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከቆመ የወያኔ ማፊያ ጋር በመመሣጠር የግንቦት ሰባትን ሕዝባዊ ኃይል አመራሮች ለመግደል ተሠማርቶ ያልተሣካለ ሙከራ ማድረጉን በኢሳት ሰማሁ፡፡ የሚገርም ጉድ ነው፡፡ ለነገሩ አይገርምም፡፡ የአስቆረቱ ይሁዳ ክርስቶስን በሠላሣ አላድ ጉንጩን በመሣም ለስቅላት ሞት አሣልፎ ሰጥቶት የለም? ይህን ታሪክ ስሰማ እንደጅል እየሣቅሁም፣ እየተከዝኩም … ምን አለፋችሁ ለኔውም ባልገባኝና ባልተጨበጠኝ የተዘበራረቀ ስሜት ነው ፈዝዤ ዜና-መርዶውን የጨረስኩት – ይቅርታ ‹እንደጅል› ማለቴ ለወግ ጥረቃ ያህል እንጂ ጅል መሆን/አለመሆኔን አላረጋገጥሁም፡፡

ጎበዝ! ወንደሞችና እህቶች እንዲሁም ጓዶች! አደገኛ ዘመን ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ማን ይታመናል ከእንግዲህ? ከአነጋገሩ እንደተረዳሁት ይህ ሰው – ራሱን በራሱ ለመግደል የሞከረ ጅላንፎ ልበለው – በቄንጠኛ የዘመኑ ቋንቋ የአማራው ብሔር አባል ይመስለኛል – እርግጥ ነው ኢትዮጵያውያንን በመልክና በቋንቋ እንዲህ ናቸው እንዲያ ናቸው ብሎ መፈረጅ እጅግ አስቸጋሪ መሆኑ ይገባኛል፡፡ ሆኖም ቢሆን ግን ይህ ሰውዬ አማራ መሆን አለበት ብዬ በበኩሌ አምኛለሁ – አሳማኝ ነገር ካገኘሁ ግን አሁንም በአንድ ሃሳብም ሆነ እምነት የመቁረብ ልምድ አላካበትኩምና ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡ በመሠረቱ ምንም ይሁን፤ ግዴለም፡፡ ያቺ ዮዲት ጉዲት ገነት ዘውዴስ ከነገሚስ ቤተሰቧ ስንትና ስንት ሚና ተጫውታብን የለም? ይች ጊንጥ – ደግሞ እሷን ብሎ አማራ! ገብረ መድኅን አርአያና ሌሎች ስንትና ስንት ትግራዮች ሕይወታቸውን በመገበር ሣይቀር ዘሩ እንዳይጠፋ የሚዋደቁለትን አማራ፣ ራሱ አማራው ተነስቶ ‹ባርነቴ ይሻለኛል› ሲል ለሰሚ ግራ ነው፡፡ ማዲንጎ አፈወርቅ ለፍቅረኛ ነበር ‹ስያሜ አጣሁላት› ብሎ የዘፈነው፤ የዚህን ጅል ሰውዬ ድርጊትስ ምን ስም እንስጠው? ወገኖች ሆይ – ጥናት በጤ ይደረግበትና ይገለጥልን – an action research is needed to be carried on such odd circumstances!

ወንድሞቼ! ለዚህ ሁሉ ያበቃን ድህነታችን ነው፡፡ ድህነት መጥፎ ነው፡፡ አፈር ያስባላል፤ ድንጋይ ያስግጣል፤ ሀገርንና ወገንን ያስክዳል፡፡ የገዛ ልጅንና ጓደኛን ሣይቀር ያስበላል – ጠኔ ሲነግሥ፡፡ በ1912ዓ.ም ይህ ዓይነቱ ሰውን በቁሙ የመብላት ነገር በሀገራችን ተከስቶ እንደነበር ይነገራል፡፡ በደምባራ ፈረስ ቃጭል ተጨምሮ ነውና በድህነት ላይ ማይምነት ተጨምሮበት የሚፈጠረውን አስቡት፡፡ እኔ አንዳርጋቸውን ግደልልንና ስምንት ልጆችህን ቻይና ልከን እናስተምርልሃለን፤ ላንተም የተደላደለ ኑሮ በፈለግኸው ሀገር እናመቻችልሃለን ቢሉኝ ዐይኔን አላሽም ነበር፤ ግን ይቺ የሀገር ፍቅር ልክፍት በጠማማው ቀን አሳውራኝ ይሄውና በከባድ የኑሮ ሸክም ውስጥ እየኖርኩ በድህነት እማቅቃለሁ፡፡ አጅሬ  – ማን ነው እቴ – ስሙም ጠፋኝ – አጅሬ ግን መግደል የሶደሬ ሽርሽር መስሎት፣ መግደልን ከጥንግ ጨዋታ ቆጥሮት የገዛ ወንድሙን – እርሱንና መላ ወገኑን ከዚህ አስከፊ አገዛዝ ነጻ በማውጣት ሌላ የተሻለ ቀን እንዲመጣ ቀና ደፋ የሚሉ ወገኖቹን ከጠላት በተላከ መሣሪያና ስንቅ ባጭር ሊቀጫቸው ዐቀደ፡፡ በዕቅዱም ለወራት ገፋበት፡፡ አሠማሪዎቹም በስልክ ቀባጠሩ፡፡ “የምትሠራው ሥራ በኢትዮጵያ ታሪክ ወደር የሌለውና ለአንተና ለቤተሰቦችህም ልዩ ጥቅም – አንተ ልትጠይቀን ከምትችለውም በላይ የሆነ እርዚቅ የሚያስገኝ…” ብለው ተመጻደቁ – በወንድሞቹ ላይ እንዲጨክን፡፡ ሰውዬውም በዚህ ሽንገላ ልቡ አበጠ፡፡ ወደዚህ ታሪካዊ ወንጀልም እንደኦስዋልድ ከነወንድሙ ዥው ብሎ ገባበት፡፡ ግን የደረሰ ደረሰበትና ከሸፈበት፡፡

ይህን ድርጊት ያከሸፉ በርግጥም ወንዶች ናቸው – እንዲሁም ሴቶች ብልም ችግር የለውም – ሴቶች እንዳይቀየሙኝ ነው ታዲያ እንጂ ለሌላ እንዳይመስልብኝ – ዘመኑ እኮ ነገረኛ እንደአሸን የሚፈለፈልበት ሆኗል እናንተዬ፤ ቀናነት ጠፋች፤ ሸረኝነት ነግሣ ባገር ምድሩ ተሞላቀቀችብን፡፡ እናም በርግጥም ይህን ዕኩይ ድርጊት ያከሸፉ ከሁሉም አቅጣጫ የሚገኙ ወገኖች የተባረኩ ናቸው፡፡ ግን ተጀመረ እንጂ አላለቀም፡፡ ጥሩ ትምህርት ይሰጣልና በራበሮችን፣ ስልካስልኮችን፣ ኢሜላኢሜሎችን መቆጣጠር አይከፋም፡፡ ሲአይኤና ሞሳድ እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩት ለካንስ ወደው አይደለምና? ውይ… ውይ .. ውይ … ሰው ግን እንዴት ክፉ ነው?

ማይምነትና ድህነት እየተዛነቁ እንዴቱን ያህል ጢባጢቤ እየተጫወቱብን እንደሆነ ገባችሁ አይደል? አዎ፣ የአጉራሽህን እጅ ቆርጠህ ለመነሳት አንድም አላዋቂ ደንቆሮ መሆን አለብህ፣ አንድም ከኅሊና ቁጥጥር በወጣ የርሀብና ድህነት ማነቆ ተወጥረሃል ማለት ነው፡፡ እንዲያ ካልሆነ በዚህ ዘመን ለዚያውም አንድ አማራ ከመሬትም ይሁን ከሰማይ ተነስቶ ኢትዮጵያን ከመዥገሮችና ከሲዖል ትላትሎች ነጻ ለማውጣት ጥረት ሲያደርግ ቢቻል መደገፍ ያ ባይሆን ከጠላት ጋር ባለመተባበር ዐርፎ መቀመጥ ሲገባ የገዛ አንገትን ቆርጦ ለመጣል እስከዚህ ርቀት መጓዝ በውነቱ እንደሀገርም ሆነ እንደሰብኣዊ ፍጡርነትም እጅጉን ያስጨንቃል፡፡ ስንቱንስ ተጠንቅቀህ ትዘልቃለህ? “አደጋ አለው!” አለች ወይዘሮ አዘሉ! እኔም አሁን “አማራ ቀለጠ!” ልበላ በዘሩ ቀለጠ ምትክ፡፡ (በማይሞት ቃላቸው ፕሮ. አሥራትን እናስባቸው፡፡ ‹አማራ መሣሪያውን መቼ እንደሚጠቀምበት አሣምሮ ያውቃል› ከሚለው ጠንቀኛ ንግግራው በተጓዳኝ ‹አንዳንድ ሆዳም አማራ …› ብለውም አልነበር?)

በወያኔዎች አልፈርድም፡፡ ማድረግ የሚገባቸውን ነው እያደረጉ ያሉት፡፡ ሰርቀህ እያለብካት የምትገኘውን ጥገት ላም ባለቤቶቹ ነቅተውብህ ሊወስዱብህ መምጣታቸውን ስትሰማ በተቻለህ መጠን መንገዶቹን ሁሉ መዝጋት አለብህ፡፡ ቀድሞውን ስትሰርቃት ለመግሥተ ሰማይ መግቢያ የጽድቅ በር ቁልፍ እንድትሆንህ ሳይሆን አንጎልህን ቦርጭህ ውስጥ ወሽቀህ በስባሹን ሥጋህን ለማወፈርና ተንደላቀህ ለመኖር ፈልገህ ነው፡፡ ስለዚህ መጠንቀቅ ነው እንጂ በወያኔ ከይሲ ተግባር አቅልን ስቶ መናደድ አይገባም፡፡ እነሱን መሰሎች ሁሉ በየዘመናቱ የሚያደርጉት  የእስትንፋስ መግዢያ ዘዴ ነው፡፡

በተመሣሣይ ሁኔታ በሰውዬውም አልፈርድም፡፡ ከፍ ሲል እንደገለጽኩት ምንም እንኳን የነአንዳርጋቸው ጽጌ በዚያ ቦታ የመገኘት ምሥጢር የዚህ ሰውዬ ችግር አንዱና ትልቁ መሆኑ ለማንም የተሠወረ ባይሆንም ሰውዬው በማይምነቱና ባልተገራ የሀብት ጉጉቱ እንዲሁም አሁን ለይቼ ላውቀው ባልቻልኩለት የተመሰቃቀለ ሥነ ሕይወታዊና ሥነ ልቦናዊ ተፈጥሮው የተነሣ የገዛ ወንድምና እህቶቹን ሊገድል ተነስቷል፡፡ ነገሩ እሱ ብቻና በዚያ ብቻም የሚያቆም አይደለም፡፡ ሰውዬው ያነገበው ዓላማ ከሰዎቹ ሞት በፊት ያለው ወያኔ የሰጠው የሀብት ተስፋ ከግዳይ ጥሎሹ በኋላ አብቦ ማየት እንጂ ከሰዎቹ ሞት ቀጥሎ የሚከሰተው የነጻነታችን ጅማሮ የፈነጠቀልን ተስፋ መጠውለግ አልታሰበውም፤ እንዳየሁት ይህ ዓይነቱ ረቀቅ ያለ ነገር ሊታየውም የሚችል አይመስልም – ፍጹም ማይምና  ተፈጥሮ በዘገምተኝነት ልምጭ የገረፈችው ምሥኪን ዜጋ ነው፡፡ ወያኔዎች ደግሞ ብልጦች ናቸው፡፡ የትሮይን ፈረስ የሚገፉላቸውንና በውስጡም መሽገው ተልእኳቸውን የሚፈጽሙላቸውን ዜጎች እንዴትና በምን መሥፈርት እንደሚመርጡ ጠንቅቄ አውቃለሁ – እናንተም ታውቃላችሁ፡፡ የወንጀለኝነት ባሕርይና የወንጀል ሪከርድ ያለባቸውን፣ እንደክፍሌ ወዳጆ ከደረታቸው በታች በተለጣጭነቱ ወደር የማይገኝለት ላስቲክ ያንጠለጠሉ ሆዳሞችን፣ እንደዮዲት ጉዲት (ገነት ዘውዴ) በቂም በቀልና በሥልጣን አራራ ልዩ በሆነ ሥነ ልቦናዊ ዋግ የተመቱ እርጉማንን፣ ለገንዘብና ለሥልጣን ሲሉ ልክ እንደዙሉዎች ንጉሥ (ሻካ ዘ ዙሉ) የገዛ ቤተሰቦቻቸውን ሣይቀር ለሰይጣናዊ የደም ግብር የሚያቀርቡ ራስ ወዳዶችን፣ … መርጠው ዓላማቸውን እንዴት ማራመድ እንደሚችሉ ወያኔዎች ከዱሮው ተክነውበታል፤ የዕድሜያቸው ማራዘሚያ ዓይነተኛ መፍትሔ ሥራያቸው ይህች ነች – ከውጪ ጠላቶቻችን ሤራ ቀጥሎ ነው ታዲያ፡፡ የትግላችን ፈርጀ ብዙነት እንግዲህ ይህን ይመስላል፡፡ ቀኝ እጅህ ሲታገል – ግራ እጅህ ሊቆርጣት ያሤራል፡፡ አንዳንዴ ምሥጢርህን ከማን ጋር እንደምትጋራም ስታስበው ይጨንቅሃል፡፡ ዕዳ እኮ ነው፡፡

እንደመፍትሔ፡- በበኩሌ ክፉን በክፉ መቃወምን እጠላለሁ፡፡ በዚህ “የተምታታ” አቋሜ ግንቦት ሰባትን ለምን እንደምደግፍ ሰዎች ግር ሊሰኙ ይችላሉ፡፡ ይሁንና አምርሮ የመጣን ጠላትና ለኅልውናህ መጥፋት አጥብቆ የሚታገልን ፀላኤ ሠናይ ሲቻል በጠበል ካልሆነም በጥብጣብ ለመከላከልና ለማስወገድም መጣር አግባብ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በዲያብሎስ ዘመነ መንግሥት ሥር ተቀምጦ ክርስቶሳዊ በመሆን ዝንተ ዓለም በሠይፍ መቀላት ሞኝነት ነው፡፡ አሁን ክርስቶስ ቢመጣ እንደጥንቱ በየዋህነት ይሰቀላል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ያ ሌላ ነገር ነውና እንተወው፡፡ ግን እንደመፍትሔ ይሆናል የምለው አንደኛ ዜጎችን በትክክለኛው መንገድ ስለሀገርና ሕዝብ ምንነት እናስተምር፡፡ አሁን እኮ ሀገር ምን እንደሆነ፣ ጭቆና ምን ማለት እንደሆነ፣ ባንዴራ ምን እንደሆነ፣ የሀር ፍቅር ስሜት ምን ማለት እንደሆነ … በጣም ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ብዙው ዜጋ ወዳለማወቅ ውዥንብር ውስጥ እየገባ ነው፡፡ በተለይ ወጣቱ በሚያየውና በሚደርስበት ነገር ተስፋ በመቁረጥ ራሱን ወደሚደብቅበት ልዩ ልዩ ሱስና ወሲብ ውስጥ በመዘፈቅ ሀገሩን እየረሳ ነው፡፡ ጥቂቶች ናቸው ስለሀገር የሚጨነቁ፡፡ የወያኔን ዕድሜ  – የአህያን ምን ያድረገው ነበር እሚባለው ፣ ጠፋኝ – የወያኔን ዕድሜ ያሣጥረውና በሀገራችን የወረደው መዓት እንኳንስ ሀገርን ራስንም ያስረሳል፡፡ እናም ማስተማር፣ ማንቃት፣ ሚዲያዎችን በመጠቀም ፍቅርንና መተዛዘንን – አብሮነትንና መግባባትን ማስረጽ ይገባል፡፡ በየድረገጹና በየጸሑፉ የሚደረገው ዱላቀረሽ እንካስላትያና የመጠላለፍ አባዜ ጋብ ብሎ እየጠፋ ያለውን ትውልድ ለመታደግ ጥረት መደረግ አለበት፡፡ የማይምነታችንና የድህነታችን ደረጃ ደግሞ ወሰን የሌለው መሆኑን ለዘመናዊ የመገናኛ አውታር ያለን ቀረቤታ ራሱ አመላካች ነው፡፡ ኢንተርኔቱ ይቅርና ጋዜጣና መጽሔት የሚያገኘውና ሊያነብም የሚችለው ዜጋ ቁጥር እጅግ ጥቂት ነው፡፡ የዜብራ ማቋረጫ ላይ በኩራት ቆሞ በመሳሳምና በማውራት ቤተሰባዊ ናፍቆቱን የሚወጣ ማኅበረሰብ እኮ ነው ያለን፤ የቀጠሮው ሰዓት አልፎበት ከቤቱ እየሮጠ ከወጣና ባቡር መንገድ ከደረሰ በኋላ ‹ፈርቶ መንገዱን በፍጥነት ተሻገረ› እንዳይባል አውራ ጎዳናውን እየተጀነነ የሚሻገረው ዜጋ ቁጥር እኮ ቀላል እንዳይመስላችሁ – እውነቴን ነው፤ የወቅቱን ባለሥልጣናት ያስደሰተና አንዳንድ ጥቅማቅሞችን የሚያስገኝለት መስሎት ጆሮውን ቢቆርጡት የማያውቀውን ቋንቋ “ቧይ…!” እያለ የሚጃጃል፣ የስልክ መጥሪያውን በማይወደው ሙዚቃ ሣይቀር የሚያስተካክል (በቅርብ የማውቃቸው ‹ኬዞች› ስላሉ እንጂ ለሌላ ነገር አይደለም) አድርባይ ዜጋ የበዛባት ሀገር እኮ እየተፈጠረች ናት፤ … ንግግራችን እቅጭ እቅጯን – እውነት እውነቷን ነው፡፡ ምኑ ሲቀርብን? ሞትን  እንደሆነ በቁማችን ተለማምደናታል – ባይሆን የሥጋና ነፍስ መለያያ ስቃይዋ ታስጨንቃለች እንጂ ዘጠኝ ቀርቶ ዘጠና ሞት ቢመጣ ብዙዎቻችን ከመላመዳችን የተነሣ መናፈቅም ጀምረናል፡፡ በዚህ ሁኔታ በ”እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል”ና ”ዛሬ ከምሞት ነገ ልሙት” የአህያና የሆዳም ሰው ተረት እየተመራ የገዛ ወዳጁን ለሞትና ለእንግልት የሚዳርግ ምሥኪን ዜጋ ቢኖር ብዙም አይፈረድበትም፡፡ ልንፈርድ የሚገባን በተሰነካከለው ማኅበረሰብኣዊ የኢኮኖሚና የፖለቲካ መዋቅራችን ነው፡፡

እናም በዐላዋቂዎች በሚደርስብን ጥቃትና የጥቃት ሙከራ ብዙም ሳንሸበርና ሳንደናገጥ ሥልቶችን በመቀያየር ትግላችንን ከግብ ማድረስ ነው፡፡ ለምሳሌ ያን ቂል ሰውዬ በምንም መንገድ ለመጉዳትና ለመበቀል አለማሰብ ተገቢ ነው፡፡ በምንም መንገድ ዝምቡን እሽ ማለት እንኳን አይገባም፡፡ አክብሮ፣ በቅጡ አስተናግዶ፣ ሥነ ልቦናዊ ችግሩን በሳይኪያትሪስት አሳክሞ ቢቻል ሳይኮአናሊስስ ተደርጎለት ሲያበቃ የህመሙ መነሾ ታውቆለት አእምሮው ወደትክክለኛ ሥፍራው መመለሱን ካረጋገጡ በኋላ እንደምርጫው አንድም የበደለውን ሕዝብ መካስ እንዲችል ሕዝባዊ ትግሉን እንዲቀላቀል መርዳት፣ አለዚያም ወደሚመርጠው አንዱ ሀገር በሰላም ሄዶ የስደት ሕይወቱን ‹እንዲዝናናበት› ማድረግ ነው፡፡ በቃ፡፡ ከርሱ ጋር “ማን ላከህ? ለምን ላከህ? ዓላማህ ምን ነበር? …” እያሉ መነዛነዝ አይገባም፡፡  ሕይወት ወደፊት ናት፡፡ ለመነታረክ ቀርቶ ለመፈቃቀርም በጣም ቅጽበታዊ ናት፡፡ ቢበቃኝስ ጃል! ምን እንዲያው … ሆሆሆ … ግን ግን አማራውን ለዚህ ግድያ ይጩት? ደፋሮች ናቸው! ዱሮ ‹ሴትን በሴት› ‹መጠጥ የገደለውን መጠጥ ያነሳዋል› ‹እሾህን በእሾህ› ይባል ነበር፡፡ እነወያኔ ደግሞ ለነጻነት የሚታገልን ዜጋ ነጻነት በሚያስፈልገውና በባርነት ቀምበር ሥር በሚማቅቅ ዜጋ ለማስገደል ተነሱ፡፡  ወይ የታሪክ ምፀት!!

ማን ይሆን ይህችን ይህችን ግሩም ጥቅስ የተናገረ? “If you want peace, prepare f

አሳዳጅና የሃገር ጠላት መንግስት –ሪያድ ኢብራሂም/

$
0
0

ሪያድ ኢብራሂም/ከኖርዌይ

security

ዛሬ ማምሻውን ወያኔ እንደለመደው ያው “ሰልፉ ሌላ አላማ ነበረው!!” ብሎ ይወነጅላል በሽመልስ ከማል አንደበት:: ፖሊስ አሁንም ህዝቡን በማስፈራራት ላይ ነው ::ወሎ ሰፈር በሚገኘው ሳኡድኣረቢያ ኤምባሲ የተቃውሞ ድምጾች ለማሰማት የወጡ ዜጎች በፖሊስ ተደብድበዋል:: በርካቶች ታስረዋል:: ሰልፉም በፖሊስ ቆመጥ እና አላስፈላጊ እርምጃ ተበትኗል::

ከሰሞኑ የሳዑዲ  አረቢያ መንግስት ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ የማንኛውም ሀገር ዜጎች ወደ ሃገራቸው በሃይል የመመለስ ስራ ተጠምዶዋል ። በመሆኑም ይህ ጉዳይ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ቤት በር የሚቆረቁር ዜና ሆኗል ። ወገኖቻችን እያዩት ያለውንም ፍዳ በአጫጭር ቪዲዮ ምስል ተቀርጸው በየማህበራዊ ድረገጾች የተለቀቁትን ተመልክተናል ። የምናየው ትእይንት አክሽን አሊያም ሆረር ፊልም አይደለም:: የወገኖቻችን የዕለት ተዕለት ትክክለኛ ስቃይ ነው ። ይህንንም ስቃይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደራሱ ስቃይ ሊሰማው፥ ሊቆረቆረው ና ሊያንገበግበንው ይገባል::ይህ ሁሉ ስቃይ፣ መከራ፣ ውርደት መቼም ቢሆን ደርሶም ፥ታይቶም አይታወቅም::  ከሁሉ በላይ የሚያስጨንቀው  ስቃይና መከራ ለደረሰው  ወገን እኔ አለሁ የሚል የመንግስት አካል ውይም ድርጅት አለመኖሩ ነው። አሁንም ቢሆን የወያኔ የጭቆና አገዛዝ መቋጫ እስካልተገኘለት ድረስ ይህ የወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የስደት ስቃይ ያበቃል ብሎ መገመትም ሆና ማሰብ አይቻልም። ስደት በሀገራችንም ከተጀመረ ትንሽ ቆየት ያለ ቢሆንም ግን ያሁኑ በወያኔ አገዛዝ ግን ከሁሉም በላይ መሰደድ ጣራ ላይ ደርሶዋል::  ወያኔ መንግስት መስሎ ሃገራችን ለማጥፋት፣ህዝባችንም ለማሳሰድ ሆን ብሎ አስቦበት እየሰራ፣ታሪክ ያለንን ፥ታሪክ አልባ ያደረገ፥የተከበርንን ያረከሰ፥ያልተሰደድንን ያሳደደ፥ለውጭ ሃገር ያልተገዛንን፥ እኛን መስሎ ወሮን የሚገዛ፥ አረመኔ የሃገር ጠላት የሆነ መንግስት ነው::

ግን እስኪ ቆም ብለንእኛ እናስብ  ምክንያቱ ምን ይሆን ? ኢትዮጵያ ባላት አንጡራ ሃብት ከአጎራባች ሃገሮችዋ አንሳ ነው? አረ በፍጹም ! እኛ እኮ የቡና ፣ የወርቅ  እንዲሁም  የተለያዩ አዝርእቶች ያሉባት ሀገር ባለቤቶች ነን ። ህዘቦችዋ ከመጠን  በላይ ሆነው እራሳቸውን በሃገራቸው ማኖር አቅቶአችው?  አረ በፍጹም ! ኢትዮጵያ እኮ ከአፍሪካ  በቆዳ  ስፋቷ 10ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገር ናት ይህም ማለት ከኛ በቆዳ ስፋት እጅጉን ያነሱ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የኛን ያህል አይሰደዱም ።

በአንደኛ  ደረጃ  የሚያሰድደን  ፦ የመልካም አስተዳደር እጦት ፣የሃገር ፍቅር ስሜትን በግድ መነጠቅ ፣ዜጋው በሀገሩ ላይ በፍርሃት እና በስጋት መኖሩ፣ በሃገሩ ላይ አንደሁለተኛ ዜጋ መታየቱ ፣ በሰው ሰራሽ የኢኮኖሚ ድቀት ምክንያት ህዝቡ እራሱን በአግባቡ ማሰተዳደር ባለመቻሉ ፣ ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬኣቸው በሀይል በመፈናቀላቸው፣ የእምነት ነጻነትን ማጣት እነዚህ ከዚህም አልፎ ወያኔ ሃገራችንን እያፈረሰ ሰለሚገኝ እና ለሃገረም ሆነ ለህዝብ የሚያስብ መንግስት ባለ መኖሩ ከዋናዎቹ በጥቂቱ ናቸው

security 2

ዛሬ ማምሻውን ወያኔ እንደለመደው ያው “ሰልፉ ሌላ አላማ ነበረው!!” ብሎ ይወነጅላል በሽመልስ ከማል አንደበት:: ፖሊስ አሁንም ህዝቡን በማስፈራራት ላይ ነው ::ወሎ ሰፈር በሚገኘው ሳኡድኣረቢያ ኤምባሲ የተቃውሞ ድምጾች ለማሰማት የወጡ ዜጎች በፖሊስ ተደብድበዋል:: በርካቶች ታስረዋል:: ሰልፉም በፖሊስ ቆመጥ እና አላስፈላጊ እርምጃ ተበትኗል::

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ፦ የወያኔ ስርዓቱ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ደባ በጥንቃቄ በመከታተል የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል ብለው ለሀገር እና ለህዝብ የሚታገሉ ኢትዮጵያውያ ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ና አባላት፣  ታዋቂ ና ሃገራዊ ስሜት ያላቸው ገለሰቦች ብሎም የሃይማኖት መሪዎች ና አባላት በሙሉ እስር፣ እንግልት፣ ድብደባ እና ሃገራቸውን ትተው እንዲወጡ እያደረገ፣ ህዝባችንን ሃገር አልባ እየሆነ ይገኛል::
ወያኔ ና የወያኔ አጃቢ ኣካላት የተለያየ ድርጅታዊ ፖሊሲ ይኑራቸው እንጂ ሃገርን ለማፍረስ ና የራሳቸውን ጥቅም  ብቻ ከማስከበር ውጭ ሌላ ምንም የህዝብ ና የሃገር ፍቅር የሌላቸውም ግዑዛን የማያስቡ ከእንስሳት ምንም የማይለዩ የሃገር ና የህዝብ ሸክም ሰለሆኑ በእነዚህ ግዑዛን አካላት ላይ አስተያት መስጠት በራሱ ለማይናገር ና ለማያስብ እንስሳ እንደ ሰው ቆጥሮ እውቅና መስጥት በመሆኑ ግዑዙን አካል ፈንቅሎ መጣል እንዳለብ ምንም ጥርጥር የለለው መንገድ ነው::

ስለዚህ የውያኔን መንግስት መጣል አለብን ብሎ ከመታግል ሌላ አማራጭ የለም :: መሰደድ መፍትሄ አደለም:: ተሰደንም ባደባባይ ለአዓለም ህዝብ መዋረዳችን እየታየ  ይገኛል:: ከዚህ በላይ ሌላ የምንሰደድበት ቦታ፣ ሃገር ፣ጊዜ ና ሰዓት የለንም:: አሁን ለሁሉም ግልጽ መሆን ያለበት ነገር ቢኖር እንደ ሚከተለው ይሆናል::

  • Ø ወያኔን ማስወገድ አለብኝ ብሎ እያንዳንዱ ግለሰብም ሆና ድርጅት ማሰብ መጀመር ብሎም ከሃገር ውስጥም ፣ ውጭም ያለ ማነኛውም ዜጋ ወደ ማስወገድ ተግባራዊ ስራ መግባት አለብን::
  • ሁሉ ተቃዋሚ ፓርቲ እርስ በርስ ከመቃወም ወያኔን ማሰወገድ እና ሃገራችንን ከማጥ ወጥመድ ውስጥ ማዳን ፣ እንደ ሃገር እንድትቀጥል ማደረግ  መቻል::
  • ወያኔን ለማስወገድ በጦር መሳርያ የሚፋለሙ  ድርጅቶችን ማበረታታት ከማነኛውም ዜጋ ብሎም በወያኔ ስር ላሉ የጉዑዙ አካል የድጋፍ ድርጅቶችም  ከወያኔ ጋር ሃገርን ለማጥፋት ከመስራት ሃገርን ወደ ማዳን መሸጋገር አለባቸው::
  • Ø ማነኛውም የሜድያ አወታር ለህዝብ ና ለሃገር፥ ኢትዮጵያኖች መከራ ፣ስቃይ ና ሞት ሲደርስባቸው ካልሆነ ለ 22 አመታት ለ85 ሚልዮን ህዝብ ውሸት ከማውራትን ማቆም ፥ከህዝብ ጎን መቆም ሜድያ ለወያኔ ሳይሆን ለ85 ሚልዮን መሆን አለበት::
  • ከመሰደድ ና ከመሞት እንድሰደድ እና እንድሞት፥ እንድስቃይ፥ ለአለም ውርድት ከመሆን ወያኔን ታግሎ መጣል፥ ያሃገርን ክብር ማስከበር አለብኝ የሚል ወጣት ና ዜጋ መፈጠር፥ መወለድ አለበት::

እስካሁን በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው የስደት እንግልት የእለት ተእለት ዜና ከሆነ ሰነባብቶኣል ከየዜና አውታሮች እንደምንሰማው ገሚሱ በበረሃ እንደቅጠል ሲረግፍ፣ገሚሱ ባህር ሲውጠው፣ ገሚሱ የሰውነት ክፍሉን በየበረሃው ሲነጠቅ፣ ገሚሱ በየአረብ ሀገሩ የአሰሪዎቻቸው ተጠቂ ሲሆኑ እያየነው ያለ እውነት ነው። መንግስትን በአንድ በቤተሰብ ብንመስለው  ፦አንድ ቤተሰብ ልጆቹን የሚበትነው የቤተሰቡ ሃላፊዎች ቤተሰቡን በአግባቡ ማስተዳደር ሲያቅታቸው ነው ።ስለሆነም ትልቁ በሀገራችንም ችግር የአስተዳዳሪ ማጣት ነው ። ስለዚህም የሚበጀንን አስተዳዳሪ ማበጀት እያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነት ነው ።ሃገሪቱዋ የሁላችንም እንደመሆኑዋ መጠን ሁሉም ዜጋ የራሱን ሃላፊነት መወጣት እንዳለበት ግልጽ ነው ። አንዱ ነጻ አውጭ  ሌላው ነጻ ወጭ  መሆኑ የትም የማያደርስ የትግል ስልት ነው ። ምክንያቱም የያዝነው ትግል የሁላችንም የጋራ ርብርብ ይፈልጋል ። ካልሆነ ግን ሁሌም የግፍ ቀንበር እንደተሸከምን ለቀጣዩ ትውልድ ስርዓቱን ማስረከባችን አይቀሬ ነው።

የሃገርን ና የህዝባችንን መከራ መጋራት፥ ሃገር እና ህዝብን ማዳን የሁሉም ዜጋ የግዲታ ውዴታ ነው!!!

 

 


ጨክነው እንዳስጨከኑብን እንጨክን!

$
0
0

በአበራ ሽፈራው /ጀርመን/

 

security 2

ዛሬ ማምሻውን ወያኔ እንደለመደው ያው “ሰልፉ ሌላ አላማ ነበረው!!” ብሎ ይወነጅላል በሽመልስ ከማል አንደበት:: ፖሊስ አሁንም ህዝቡን በማስፈራራት ላይ ነው ::ወሎ ሰፈር በሚገኘው ሳኡድኣረቢያ ኤምባሲ የተቃውሞ ድምጾች ለማሰማት የወጡ ዜጎች በፖሊስ ተደብድበዋል:: በርካቶች ታስረዋል:: ሰልፉም በፖሊስ ቆመጥ እና አላስፈላጊ እርምጃ ተበትኗል::

የሰው ልጅ ከተወለደበት አገር እንኳን ለመሰደድ ለአንድ ቀንም ለመሄድ አይፈልግም፡፡ በተለይም የተፈጥሮ ህግጋት ፣የኑሮ ቦታ ለውጥ ፣ለንግድ፣ለጉብኝት፣ እራሱን ለማዝናናት፣ለትምህርት፣ ቤተሠቡንና ጓደኛን ለመጠየቅ ወይም በአስገዳጅ ሁኒታ ካልሆነ በስተቀር ከሀገሩ ተለይቶ ለመኖር እንደማይፈልግ የአብዛኛው የሰው ልጅ ባህሪ መሆኑ ይታወቃል፡፡ አለመታደል ሆነና በሀገራችንና በህዝቧ ላይ በተለይም በዚህ ትውልድ ላይ ትልቅ የመከራ ተራራ ወድቆበታል፡ ፡ዛሬ በህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት የፖለቲካና የማህበራዊ ኑሮ ምስቅልቅልነት የተነሳ በሀገራችን በህዝብ ላይ ከሚደርሰው መከራ አልፎ በስደት ምክንያት ያለው መከራ ፣በየበረሐው የሚደርሰው ሞት፣ የአካል መጉደልና እንግልት በየሀገራቱ እስር ቤቶች የሚደርሰው ሰቆቃ እንዲህ ቀላል አይደለም፡፡

 

ዛሬ ብዙዎቻችን ኢትዮጵያውያን በአረቡ አለም በተለይም በሳውዲ አረብያ እየደረሰብን ያለውን መከራ ስናይ የአገራችንና የህዝባችን ጉዳይ እጅግ ወደመረረና ወደለየለት ሁኔታ መድረሱን ፤ ከህዝባችን ለቅሶና ዋይታ እንዲሁም የመንግስታችንን ዝምታና ግዴለሽነት ስንመለከት ምን ያህል ኑሮአችንና ህይወታችን ጭምር ለአደጋ መጋለጡን እናያለን ።

 

ዓለም በደረሰችበት የዕድገት ደረጃ አንጻር ሲለካ ዛሬ በኢትዮጵያዊያን ላይ የተፈጠረው ውርደት፣ስደት፣ የእህቶቻችን መደፈር፣ እስራት፣ አንገታችን በስለት መቀላት ፣ ንብረትና ሃብት መነጥቀ ፣ እንደ እንስሣ መታየታችን ያሳዝናልም፣ ያስቆጫልም ፤ በውጭ ሃገራትም እንዲሁ በአገር ቤትም እንዲሁ እስከመቼ ይቀጥላል? እኛስ እስከመቼ ድረስ ውጊያችን በሰላማዊ ሰልፍ ብቻ ይሆናል? እስከመቼ የሃይል ሚዛንን መፈጠርን ሳንችል፣ አስገዳጅ ሁኔታን መፍጠር እያቃተን እንጠቃለን ? በሃገር ቤት ጥቃት! በውጭ አገር ጥቃት!

 

እንደኔ ግን ይህ ትውልድ የለውጥ ራዕይ ይዞ እነዚህን የህዝብና የሀገርን ጠላቶች ከህዝቡና ከሀገሪቱ ላይ ለማንሳት በፍጥነት ወደ ትግል መግባት ካልቻለና የራሱንና የአገሪቷን አቅጣጫ ለመቀየር ካልተነሳ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ኢትዮጵያዊነት ውርደት እየሆነ እየቀጠለ መሆኑን አሁን ያለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ያሳየናል ። አሁን ያለንበት እውነታ የአገራችንና የህዝቦቻችን ሁኔታና የኑሮ ሰቆቃ ከማሳየቱም በላይ ዛሬ ጨክነው ያስጨከኑብን ላይ ልንጨክን መነሳት ያለብን ጊዜ አሁን መሆኑን  ከሁኔታው መረዳት ይኖርብናል።

 

የእኛዎቹ ዘረኞች ህወሃቶች ለ22 ዓመታት በለየለጥ ስቃይ መርተውናል።  አገሪቷን በብቃት ለመምራት የሚችሉ ሳይሆኑ የራሳቸውን ስውርና ቡድናዊ ጥቅም በሚያስጠብቁ ጥቂት ዘረኞች ጭካኔ ተሰደናል፣ ተንገላተናል፣ ተዋረደናል። የሆነው ሆኖ ግን የተሰደደው ህዝብ በሚልከው ገንዘብና ገቢ የራሳቸውን ሃብትና ምንዛሬ እየአጋበሱ የሚኖሩት ግን እነዚሁ አሳዳጆቻችን መሆናቸውና እነሱ ምናቸውም እንዳልተነካ ስመለከት በጣም አዝናለሁ ። ዛሬ ወያኔዎችና ግብረ አበሮቻቸው በኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ ላይ የወሰዱትን ጥቃት ለመቀልበስ አሁን በፍጹም ጭካኔ ልንነሳ ይገባናል ።

 

ዛሬ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን የማይሰማ እንደሌለ ግልጽ ነው፤ በጣም ያስቆጫል ፣ያቃጥላል፣ ያናድዳል። ይኽንን ነገር ለመቀየር በፍጹም ቁጭት መነሳት ያለብን ጊዜ ደግሞ አሁን ነውና ወጣቱ፣ የተማረውም ሆነ በልዩ ልዩ ሁኔታ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያለን በሙሉ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ልንነጋገር መቻል ይኖርብናል ፤መፍትሄም ማስቀመጥ ያለብን ጊዜ አሁን ነው። ዛሬ በሰልፍ ብቻ የምናስቆመው ችግር አይደለም ለዘለቄታውም ልንሰራ ያለብን ጊዜ አሁን ነው።

 

ዛሬ በአረቡ አለም እየደረሰብን ያለው ግፍ መነሻዎቹ በአገራችን ያለው የፖለቲካና የማህበራዊ ችግሮችና በኢትዮጵያዊነት ስም የህወሓቶች ጥርቅሞች በመላው ዓለም  የኢትዮጵያ ኢንባሲዎችና ቆንስላዎች በተለይም በአረቡ ዓለም ባሉ ኢንባሲዎችና ቆንስላዎች ውስጥ በህወሓት ዘረኝነት በተበከሉና በንግድ በተሰማሩ የህወሃት ባለማሎች ስብስብ የተያዙ መሆኑ ደግሞ በእንደዚህ አስቸጋሪ ወቅቶች እንኳን ለወገኖቻችን መድረስ ሳይችሉ ቀርተው የህዝቡን ጥቃት በዝምታ ማየታቸውና ኢትዮጵያዊነት በመላው ዓረብና በመላው የዓለም ሚዲያዎች እጅግ በሚያስቆጭ መልኩ  በውርደትና ወገንና ደራሽ እንደሌለው መታየቱ ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን ብዙ የኢትዮጵያን ወገኖችና ደጋፊዎች አሳዝኗል፣ አስደንግጧል።

 

ዛሬ ኢትዮጵያን የሚመሩ ዘረኞች አስቀድሞም ቢሆን ኢትዮጵያዊነትን የካዱና አሁንም ለኢትዮጵያዊነት ዴንታ የሌላቸው በመሆኑ ይህ  ችግር ተፈጠረ አልተፈጠረ ምናቸውም አይደለምና፤ ዛሬ ከምናየው የአገራችንና የህዝባችን ውርደት በላይ ገና ብዙ መከራዎች ከፊታችን ተደቅነዋል፤ አሁን በምንችለው አቅም ከምናደረገው ትግል በላይና ለህዝቦቻችን ከምንታገለው በላይ ሁላችንም ቆም ብለን የምናስብበትና  በአረቦች ባስጨከኑብን ጨካኞች ህወሃቶች ላይ መጨከን እንዳለብን ይታየኛል።

 

 

የዛሬዎቹ ችግሮች መስፋፋት ምክንያቶቹ በሀገር ውስጥ የሚደርሰው ግርፋት ፣እንግልት፣ እስራት፣ ሞትና ሌሎች የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እንዲሁም በመንግስት በተደራጁ ሀይሎች በሀገርና በህዝብ ላይ የሚደርሰው የሙስና ተግባር  ፣የዘር ጥቃት፣ ህዝብን ማፈናቀል፣ ሀብትና ንብረት መዝረፍ፣ የመሬት ቅሚያ፣ ሚዛናዊነት የሌለው የንግድ መድሎ  መሆናቸውን የማያውቀው ኢትዮጵያዊ የለም፡፡

 

አሜሪካና ሌሎች ምዕራባውያን ሀገሮች በአገራችን ውስጥ ያሉትን  ችግሮች እያወቁ እንዳላወቁ እየሆኑ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸውና ለነዚህ ለተደራጁ ሀገርንና ህዝብን ለሚያሸብሩ ዘረኞች በገንዘብና በቁሳቁስ በማጠናከርና በመርዳት የዚህን ትውልድ መከራ መጨመራቸው የሚያሳዝን ቢሆንም ትግላችን ከራሳችን የሀገርንና የህዝብን ስብዓዊና ቁሳዊ መብቶችን እየነጠቁ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ መሪዎች ጋር መሆኑና የትግሉም ውጤት ተጠቃሚዎች ኢትዮጵያውያን በመሆናችን በነዚሁ የሀገራችን አንባገነኖች፣ ዘረኞችና የህዝብንና የሀገርን ጥቅም በሚሸጡ ህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት አባላትና ደጋፊዎች ላይ ሠፊና ልዩ ልዩ የትግል ስልቶችን ተጠቅሞ ትግሉን ማቀጣጠል ከኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን ይጠበቃል፡፡

 

በየትኛውም የትግል መስመር እየታገሉ ያሉ ሁሉ ትግሉን በማፋፋም ከግብ ለማድረስ አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ የዚህ ትውልድ መከራ እንዲያበቃ እመክራለሁ፡፡ ካልሆነ ግን በሃገር ውስጥ ያለውም ችግር አሁን ካለው በላይ እንደሚባባስ፣ በውጭ ያለውም በስደት እንዲኖር እንደሚገደድና  ንሮውም ከዚህ አሁን ከምናየው በላይ የከፋ እንደሚሆንና ትውልዱም የመከራ ትውልድ ሆነን እንደምንቀር ማውቅ ይገባናል ፡፡

 

በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ የሀገራችን ህዝቦች ሁሉ አሁን በትግል ላይ ያሉ እውነተኛ ፓርቲዎችንና ትግሎችን መደገፍና የትግሉ አካል መሆን  ይጠበቅብናል ፡፡

 

የአሜሪካና የምዕራብ ሀገራትም ለተወሰኑ የዲፕሎማሲና ወታደራዊ ትብብር ብለው ህዝብ ከጠላው፣ የህዝብና የሀገር ጠላት ከሆነና ህዝብን ከሚያሸብር ጋር መወገናቸውን ትተው የኢትዮጵያውያንን ትግል እንዲያግዙና በታሪክም ከተወቃሽነት እንዲያመልጡ እጠይቃለሁ፡፡

 

ዛሬ አረቦች ይህንን ለመፈጸም ምክንያት የሆናቸው የመሪዎቻችንን ወይም የህወሃቶች ሙሰኝነት፣ ግደለሽነት፣ ባንዳነትን፣ ቅጥረኝነትን የሚያገለግሉ መሆናቸውን ባይረዱ ኖሮና ለአገርና ለህዝብ የሚቆረቆሩ አለመሆናቸውን ባያውቁ ኖሮ ዛሬ ባልተደፈርን ነበረ። አረቦች በኢትዮጵያ ምድር ተከብረው እንዳልኖሩ ዛሬ ሬሳችንን ሳይቀር ለመቆራረስ መድፈራቸው ያስቆጫል ያስለቅሳል።

 

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤትና ባለስልጣኑም ለኬንታው ኬንያታ እና ለሱዳኑ አልበሽር በአይሲሲ /ICC / ለሚጠብቅባቸው የፍርድ ሂደት ፍርድ እንዳይቀርቡ የተሟገተውን ያህል እንኳን  በአረቡ ዓለም በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃና ህይወትን ለመታደግ ቅድሚያ ሊሰራ የሚገባውን ሁሉ ባለመስራቱና ለሙግት ባለመነሳቱ አዝናለሁ ።

 

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትም ምንም ኢትዮጵያዊነት ስሜትም ሆነ ፈቃድ በሌላቸው የህወሓት ባለሟሎች ለ22 ዓመታት መመራቱም ሌላ ተጨማሪ መከራን አምጥቶብናልና ይህንን ለመቀየርና ለማስተካከል ሁሉም ኢትዮጵያውያን መነሳትና ባስጨከኑብን ላይ መጨከን አሁን ይኖርብናል። ትልቅ መሰዋትነትን የሚጠይቅ ትግል ከፊታችን ተደቅኖብናል። አረቦች ህወሃትን ደግፈው እዚህ ሲያደርሱት ዛሬ ይህንን ለመፈጸም እንደሚያስችላቸው ጭምር ተረድተው ነው። ከዚህ በኃላ ግን ኢትዮጵያና ህዝቦቿ የአረቦች መጫወቻ እንዳንሆንና አላማቸውንም ለማስፈጸም ተግቶ የሚሰራውን ህወሃትን ከላያችን ላይ ለማንሳት አሁን እንጨክን። ቸር ይግጠመን።

 

እግዚአብሐር ኢትዮጵያን ይባርክ!

የተባበሩ ክንዶች ከሳውዲ ባሻገር! (በተክሉ አባተ)

$
0
0

ተክሉ አባተ

8356492605412287ሰሞኑን ቅስም ሰባሪ በሆነ ክስተት ውስጥ ራሳችንን አግኝተናል:: ውድ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ ዘግናኝ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተካሄደባቸው ነው:: የችግሮቹን አይነትና መጠን የኢትዮጵያውያን የመገናኛ ብዙኃን በሚገባ እየዘገቡት ነው:: በአጠቃላይ ሲታይ ግን የሳውዲዎችን ርምጃ እንደሰው ለመረዳት የሚከብድ ነው:: በዚህ ዘመንና መንግስት ባለበት አገር እንዴት የሰው ልጅ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ካገር እንዲወጣ ይታሰባል? ህግን ለመጠበቅ ወይም ለማስከበር ሲባል በምንም ዋጋ የማይገኘውን ውድ የሰው ልጅ ህይወትን ማጥፋትና ማጎሳቆል እንዴት ሚዛን ይደፋል?—– የተባበሩ ክንዶች

Download (PDF, 145KB)

 

 

ሰላማዊ ሰልፍ በባዕድ ሀገራት እና “አስራ አንደኛው ቀን”በሳውዲ አረቢያ (በውቤ አለማየሁ)

$
0
0

በውቤ አለማየሁ

ከጀርመን

Saudicryበሳውዲ አረቢያ በወንድምና እህቶቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ ግፍና መከራ ለመቃወም በትላንትናው እለት ህዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም በጀርመን ፈራንክበርት ሳውዲ አረቢያ ቆንስላ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገኝቼ ነበረ።በሰልፉ ለይ ለመሳተፍ በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከለሊቱ አስራ አንድ ሰዓት ነበር ወደ ባቡር ጣቢያው ያመራነው።በለሊት የተነሳንበት ዋነኛ ምክንያት ሰልፉን በጠዋት ለመጀመር ዕቅድ በመያዙ ነው። እኔ ካለሁበት አካባቢ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወንድምና እህቶቼም ተሳታፊዎች ነበሩ።እለቱ በሳውዲ አረቢያ በምስኪኑ ህዝባችን ላይ መፈፀም የጀመረው ግፍና መከራ “አስረኛውን ቀን” ያስቆጠረበት ነበር።በእነኚህ አስር ቀናት የሰው ልጅ ደም  በየሜዳው እንደ ጎርፍ ሲወርድ ፤አካሉ ደግሞ እንደ እንጨት ሲፈለጥና ሲቆረጥ አይተናል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል ከስፍራው የሚወጡ የቪዲዮና የፎቶ ምስሎች እንደሚያመለክቱት የሳውዲ አረቢያ ደህንነቶችና ወጣቶች እንዲሁም አሰሪዎች እህትና ወንድሞቻችን ላይ እጅግ ዘግናኝና አሳዛኝ ድርጊት ፈፅመዋል።አንዳንዶቹ “የድርሱልን ጥሪ” ሲያሰሙ ከልብ የሚያስለቅሱ ናቸው።እንኳን አይደለም አስር ቀናት በመከራና በጭንቀት የሆነች አንዲት ደቂቃ ከዓመት ትስተካከላለች።

ሰላማዊ ሰልፋችን በፍራንክፈርት ሳውዲ አራቢያ ቆንስላ ልክ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከጠዋጡ አራት ሰዓት ነበር የተጀመረው።በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ህፃናትን በመሸከሚያ ጋሪ የያዙ እናቶች፣ ወጣቶች ፣አዛውንቶችና የሀይማኖት አባቶች ሳይቀሩ በተለያዩ የጀርመን ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ነበር።በጀርመን ሀገር የሚገኙ ኤርትራውያን ወንድሞቻችን በሰልፉ ላይ የኢትዮጵያና የኤርትራን ባንድራ በመያዝ “እኛ ኤርትራውያን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርገውን በደል እንቃወማለን ” የሚል መፈክር አሰምተዋል።

ዘር፣ሀይማኖት፣ ብሔርና የፖለቲካ አስተሳሰብን ሳንለይ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ወንድሞቻችን ኤርትራውያን በሳዉዲ አራቢያ ቆንስላ የተገኘንበት ዋነኛ ዓላማ የሳውዲ አራቢያ መንግስትና ህዝብ በንፁሀን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ እየፈፀሙት የሚገኘውን አሰቃቂና ዘግናኝ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በፍጥነት እንዲያቆሙ ለመጠየቅ ነው። ከዚህ ባለፈ መስማት የተሳነውንና ዝምታን የመረጠውን አንባገነኑን መንግስት “በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ህዝባችንን ከመጨፍጨፍ እንዲያድንልን” ለመጠየቅ ነው። የሰላማዊ ሰልፍ ሁነቱን ለመዘገብ በስፍራዉ ለሚገኙ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍና  መገናኛ ብዙሃን ኢ-ሰብአዊ ድርጊቱ ሲፈፀም  በዝምታ  መመልከት ለመረጡት  ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ባጠቃላይ ለዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እንዲያሳዉቁልን ለማድረግ በማሰብ ነው ።

ለሰላማዊ ሰልፉ ከተሰባሰብንበት መንገድ ፊት ለፊት አንድ ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ይታያል። የህንፃው እያንዳንዱ ፎቅ ለተለያዩ አማካሪና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተከራየ መሆኑን ህንፃው መግቢያ ላይ የተዘረዘሩት ፅሁፎች ያስረዳሉ። የሳውዲ አረቢያ ቆንስላ በዚህ ሰማይ ጠቀስ በሆነው ህንፃ ሀያ አራተኛ ፎቅ ላይ ነው የሚገኘው።

ሰላማዊ ሰልፋችን ከዚህ ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ትይዩ ቢበዛ በአስር ሜትር ርቀት ላይ ተጀመረ። ሰላማዊ ሰልፉችን “ሰብአዊነትንና የሀገር ክብርን”  መሰረት ያደረገ በመሆኑ የሰላማዊ ሰልፉ ስሜት እየጋለ መጣ። ሁላችንም የሰልፉ ተሳታፊዎች ያች የሶስት ሺህ ዓመታት ታሪክ ባለቤት የሆነችው ሀገራችን  ኢትዮጵያ በሳዉዲ አረቢያ “ንጉሶች” ስትደፈር ታየችን።የህዝባችን ሰቆቃና ጩሀት፣ መከራና እንግልት እያንዳንዳችን ላይ የተፈፀመ አድርገን አሰብነው። በእውነት ኢሰብአዊ ድርጊቱን ለመሸከም ይከብዳል።በአስር ሜትሮች ርቀነው የነበርነውን የሳውዲ አረቢያ ቆንስላ የሚገኝበትን ህንፃ መግቢያ ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠርነው። የህንፃው መግቢያና መውጫ  በሰልፉ ሙሉ ለሙሉ ተዘጋ።

የህንፃው መግቢያ ላይ ደህንነት የሚያስጠብቁ ፖሊሶች ቢኖሩም ፖሊሶቹ ወደ ህንፃው ውስጥ እንዳንገባ ከመከልከል ውጭ ሰላማዊ ሰልፋችንን በሰላማዊ መንገድ እንድናደርግ ሙያዊ ሃላፊነታቸውን ከመወጣት ውጭ  ሰላማዊ ሰልፉን በትዝብት ይመለከቱ ነበር።ሰላማዊ ሰልፉ ቢያንስ ለሶስት ሰዓታት ተደርጓል። በዚህ እለት በተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፎች በመላው አውሮፓ በእንግሊዝ ሎንዶን፣በሲውዲን ስቶኮልምና በሌሎች የአውሮፓ ዋና ዋና ከተሞች እንዲሁም በአሜሪካን ዋሽንግተን ዲሲ ይደረግ ነበር።በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዓለማችን ዋና ዋና ከተሞች ሰላማዊ ሰልፉ ሲደርግ በኢትዮጵያ የሚገኙ ወገኖናችን ግን በመንግስት ክልከላ ምክንያት በሀገር ቤት የሳውዲ አረቢያ መንግስትን ድርጊት ማውገዝ አልቻሉም።

አስራ አንደኛዉ ቀን

ይህ እለት በሳውዲ አረቢያ ያለው ሰቆቃና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት አስራ አንደኛ ቀኑን የያዘበት ነው።ይህ እለት ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራበት እለት ነው ።ሰላማዊ ሰልፉ ከሚደረግበት ሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግን በአምባገነኑ መንግስት የሚታዘዘው የደህንነት ክፍሉና ፖሊሶች በሰልፊ ተሳታፊዎች ላይ ከባድ ድብደባና እስራት በመፈፀም ሰልፉ እንዲበተን አድርገዋል።አሶሺየትድ ፕሬስ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዴታን ሽመልስ ከማልን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰልፉ የተበተነው “ሰልፈኞቹ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ ስላልተፈቀደላቸው ነው” ።ሽመልስ እንዳለው “ሰልፈኞቹ ሳውዲ አረቢያ ላይ ጥላቻ የሚፈጥሩ መልዕክቶችን በመያዛቸውና እነኚህ መልዕክቶችም ኢትዮጵያ ከሳውዲ አረቢያ ጋር ያላትን የጠበቀ ግንኙነት የሚያሻክር በመሆኑ ነው” ብሏል። ሰማያዊ ፓርቲ “የኢትዮጵያ መንግስት ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ጎን በመቆም ዋና ተባባሪ መሆኑን አስመስክሯል” ሲል ባውጣው መግለጨ የአምናገነኑን ኢህአዴግ መንግስት ድርፊት አውግዟል።

በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን የሰቆቃና የመከራ ድምፃቸውን ማሰማት ከጀመሩ ቀናቶች ቢቆጠሩም የሀገሪቱ ጠላት የሆነው አምባገነኑ መንግስታችን ግን ህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ ግፍና መከራ ቢያንስ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንኳን ለመፍታት አልቻለም።

በሀገር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሳውዲ አረቢያ ኢ-ሰብአዊ ድርጊትን በሰላማዊ ሰልፎች መቃወምና ሰላማዊ ሰልፎችንም በሀገራችን ማድረግ አልቻሉም። ወገናችን ለተፈፀመበት ግፍና ሰቆቃ ህዝባችን በሀገሩ መጮህ ተልክሏል። አምባገነኑ መንግስታችን ሰላማዊ ሰልፍ “በባዕድ ሀገራት ከተሞች እንጂ በኢትዮጵያ አታደርጉም፤አትችሉምም ” ብሎናል።መንግስት ተብዬው ኢህአዴግ በሀገራችን ባዳ አድርጎናል።መንግስታችን በሀገራችን ባዳ ሲያደርገን በሌሎች የዓለማችን ዋና ዋና ከተሞች የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ግን  በትውልድ ሀገራችን ማድረግ ያልቻለውን ሰላማዊ ሰልፍ በባዕድ ሀገራት ማድረግ ችለናል። በዚህም ምክንያት እኛ ኢትዮጵያውያን “ሰላማዊ ሰልፎችን በባዕድ ሀገራት ብቻ እንድናደርግ ነው እንዴ የተፈርደብን? ” ብዬ እንድንጠይቅ ተገደድኩ። ቢፈረድብንስ …..ግን ፍርዱ እስከመቼ?

 


// ]]>

የሳዑዲ ጉዳይ፡ ካስጨነቀ፣ ካስጠበበን የመንፉሃ ሁከት መልስ! –ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

YeMaleda Weg

ትናንት እንደ ቀልድ  …

        በያዝነው የፈረንጆች 2013 ዓም በወርሃ መጋቢት አጋማሽ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ” ህጋዊ ሰነድ ያልያዙትን አስወጣለሁ !” ብላ አወጀች ። ቀጠለና አፈሳ አሰሳው ተከተለ! አስፈሪው ያ ክፉ የጭንቅ ቀን በሳውዲው ንጉስ ሌላ የምህረት አዋጅ ተተክቶ ህገ ወጥ  የተባሉትን ህጋዊ በሚያደርግ ህግ ተተካና የምህረቱ አዋጅ በያዝነው ህዳር መባቻ እንደሚያልቅ በተጠቆመው አዲስ የምህረት አዋጅ ተተካ ! በሂደቱ የታደሉት የተበላሸ መኖሪያ ፍቃድን ከማደስ ጀምሮ አዲስ ፈቃድን አገኙ ። ያላለላቸው ከፖስፖር እድሳት መዘግየት ጀምሮ አዲስ ለማውጣት ባለው ውስብስብ የኢንባሲና የቆንስል አሰራሮች ህልማቸው ሳይሰምር እዚህ ደረሱ …ወደ ሃገር ለመግባት ፈልገው ከሃገራቸው ተወካዮች ህጋዊ ሰነድ ለማግኘት ሳይችሉ ቀሩና ተሰነካክለው ቀሩ  !  በላይ በታች ብለው የመውጫ ሰነዱን ያገኙት ጥቂቶች በሰላም ወደ ሃገራቸው በሰላም ሲሸኙ የቀሩት ብዙዎች ደግሞ ሳውዲዎች እንደለመዱት ይለሳለሳሉ ብለው ከፉውን ጥቂት ቀን እቤታቸው መሽገው ሊያሳልፉ ተዘናጉ …

 የእህታችን አሳዛኝ የቪድዮ መልዕክት ከሳዑዲ አረቢያ   አደጋውን በቅርብ የሚያዩት የመንግስታችን ተወካዮች ዜጎቻቸውን ሰብስበው መምከር ሳይችሉ ቀሩ! እንዲህ እያለ ቀን ቀንን ወልዶት የምህረቱ አዋጁ ህዳር ላይ ባባተ ማግስት ግን ዜጎች አደጋ ላይ ወደቁ … ይህ በሁሉም ሃገር ዜጎች የመጣ ነበርና በጸጋ መቀበል የግድ ነበር ። ፍተሻ አሰሳው በመላ ሳውዲ ተጠናክሮ ሲቀጥል ቤት ” ለበቤት ፍተሻ አይደረግም !” የሚል መመሪያ ወጣ ። ይህ መመሪያ ብዙዎችን አስደሰተ! ሪያድ መንፉሃ ላይ ግን መመሪያው በእኛ ዜጎች ላይ ብቻ ተጣሰ  … ህጋዊ የመንፉሃ ነዋሪዎች ሳይቀር የጥቃቱ ዳፋ ቀማሽ ሆኑ ። መንፉሃ ተሸበረች ! የሃበሻ ልጅ ቤቱ እየተሰበረ ያለ ገላጋይ በወሮበላ አረብ ወጣቶች ተቀጠቀጠ  ፣ ንብረቱ ተዘረፈ ፣ ተደፈረ ! የጸጥታ ሃይሎች ቤት እየሰበሩ በመፈተሽ ወንዶችን ወደ እስር ቤት እየተለዩ ሲልኩ “ጅብ በቀደደው ውሻ …!”  እንዲሉ በፈታሾች እግር”ሸባብ ” የሚባሉት ወጣት አረቦች ንብረት ከመዝረፍ ጀምሮ አቅመ ደካማ ሴት እህቶችን አጠቁ!  ቁጣ ተቀሰቀሰ!

       ይህን ግፍ  የተመለከቱ ደራሽ ገልጋይ አጥተው ተስፋ የቆረጡት ወጣት ኢትዮጵያውን ወንድሞች በአካባቢው ሳውዲዎች ዝር እንዳይሉ በማድረግ መኪናዎችን መሰባበር ያዙ! ሁከቱ ግሞ የበቀል እርምጃው በነጭ ላባሾች ተካሄደ! ጥቃቱን የአካባቢውን ነዋሪ እርምጃ ያስከፋው ነዋሪ ሻንጣውንና ቤተሰቦቹን ይዞ አደባበይ በመውጣት “ሴቶቻችን አይደፈሩ ፣ ከነቤተሰቦቻችን ወደ ሃገራችን መልሱን! ” የሚል ድምጹን በአደባባይ ሲያሰማ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ወደ አላስፈላጊ ግጭት አመሩ ! ተነግሯቸው መስማት ያልቻሉት የመንግስት ተወካዮች ጣልቃ ገብተው መብት ማስከበሩ ቢቀር  መሸምገል ሳይችሉ ቀረና የተፈራው ደረሰ  !

ዛሬ …በተስፋ 
ዛሬ ሌላ ቀን ነው! መንፉሃ ላይ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የወገን ደም ተገብሮ የሳውዲ መንግስት ህገ ወጥ ባላቸው ዜጎች ላይ የጣለው የመቶ ሽህ ብር ቅጣትና የሁለት አመት እስራት ተነሳ  ! እስካሁን ባለው መረጃ 50 ሺህ የሚገመት ወገን ወደ ሃገሩ ለመግባት በማቆያ እስር ቤት እና በመጠለያ ከትሟል! የእኛ ነገር “ሰርገኛ መጠሰ በርበሬ ቀንጥሱ !” ሆነና  የመንግስት ተወካዮች በስደተኛው መብት መከበር የማይተጉ ሃላፊዎችን በቅርብ መልምሎ እርምጃ በመውሰድ የስደተኛውን ህይወት ያልደገፈው መንግስታችን ዜጎች በከፋ ችግር ማጥ ስንወድቅ አለሁላችሁ እያለን ነው ። ” የምትኮሩበት ሃገር አላችሁ!  ኑ በእቅፍ እንቀበላችኋለን! ” ማለትም ጀምሯል!  አዎ!  ደስ ይላል!

8356492605412287ዛሬ የሰሞኑ ሮሮ በረድ ብሎ ብሏል! በውጭ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም የሳውዲ መንግስት በወገኖቻቸው የደረሰውን አሰቃቂ በደል ተመልክቷልና ሰብአዊ መብት ረገጣውን ከማውገዝ ባለፈ እርዳታ እያሰባሰቡ መሆኑን መስማት ያሰደስታል!  ለዚህ መሰሉ አለም አቀፍ እንቅስቃሴ  ታላቅ አክብሮት አለኝ !  በሳውዲ የከተምን ከአራት መቶ ሺህ በላይ የምንገመት የዚያች ሃገር ዜጎች አለንና ተቃውሞው በቀልን እንዳያጭር ያሳስበናል ።

ሳውዲና የእኛ ስደት   …

     ሰማችን ማንቴስ ብለንና እድሜያችን ቆልለን ከደላንና ከቀናን በጠያራ ፣ አልሆን አልመች ሲል የባህር የበርሃውን ሰቆቃ ተፋጥጠን እዚህ ለደረስነው ኢትዮጵያውያን ሳውዲ አረቢያ ባለውለታችን ናት !  በአብዛኛው በሳውዲ አሰሪዎችና በአንዳንድ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች የሚደርስብንን የመብት ጥሰት ችለን ላለፍን ሰላማዊ ነዋሪዎች “በሰብአዊ መብት ጥሰት የምትወነጀለው አረባዊቷ ሀገር ከሀገራችን የተሻለች ናት! ” እስከ ማለት መድረሳችን እውነት ነው ። ስለ እውነት እንነጋገር ከተባለና የሰብአዊ መብቱን ነገር ችላ ብለን ራስን መደገፉ ካመራን ሳውዲ አረቢያ  ራሳችን ጠቅመን ቤተሰቦቻችን መጥቀም የቻልንባት ሁለተኛ ሃገራችንናት ብል ማጋነን አይቦንም ። ይሁንና ይህች የምናመሰግናት ሃገር አልፎ አልፎ  ከምታወጣው ህግ ጋር በተገናኘ  የእኛን መብት የሚያስከብርልን ጠንካራ ተወካይ  አጥተን ህግ እየተጣሰ ተጎድተናል። ይህ ብቻ አይደለም በግርድፉ እናውራው ካልን ህግና ስርአትን ተከትለው የማይኖሩ ወገኖች በሚሰሩት ህገነወጥ ስራ በሚሰጠን ስም ገጽታችን ከመጉደፉ አልፎ ተርፎን “ለሃጥአን የመጣው ለጻድቃን !” እንደሚባለው  የሃጥአኑ ጥቃት ለቀረው ሰላማዊ ነዋሪ ሲተርፈው የመንግስት ተወካዮቻችን ዋቢ አልቆምልን እያሉ ኑሯችን ከፍቷል ። ካለን የገቢ ምንጭ አንጻር አኗኗራችን በህብረት መሆኑም ጎድቶናል። ይህ ከጥቂቱ ጉዳት መካካል ጥቂቱ ቢሆንም ኑሯችን ካከፋው ምክንያትነት ቀዳሚ ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም!  ከዚህ አንጻር በሰሞኑ አሰሳና ፍተሻ በላቡ ከሚያድረው ጎልማሳ እና ጉብሏ ጀምሮ አባወራው ሆነ የቤት እመቤቷ ህገ ወጥ ተብለን እንደወጣን ልንቀር የምንችልበት አደጋ ተደቅኖብናል። ዜጎች በከባድ ውጣ ወረድ ለአመታት ያፈራነው  ሀብት ቀርቶ የአብራክ ከፋይ ልጆች ቤተሰቦቻቸውን ሳይሰናበቱ ከሀገር ለሚባረሩበት አካሄድ በምክክር መላ ካልተበጀለት  አሰፈሪና አስደንጋጭ ነው !

የወገን ቁጭትና ቁጣ እና ቁጣው የደረሰው የሳውዲ መንግስት …

    በመንፉሃን የተፈጸመብንን ቅጥ ያጣ ጥቃት ተከትሎ ግፍ በደል መከራውን በዘመንኛው የመረጃ መረብ ሲናኝ ሃዘናችን የተጋራው ከሃገር ቤት ጀምሮ በመላ አለም ከጫፍ እስከ ጫፍ በቁጣ የተነሳው የኢትዮጵያን ቁጣ መልዕክት ለሳውዲዎች ደርሷቸዋል። ወደ ቀጠለው አለም አቀፍ  ከጅምሩ ሳውዲን ከአልቃኢዳ ጋር በመወንጀል የተጀመረው አስፈሪ የነበረ ቢሆንም  በቀጣይ ሰልፎች ጥያቄው ሰብአዊ መብትን አክብሩ በሚል መሻሻሉ ለሳውዲ ንጉሳዊ ቤተሰቦች እያስተላለፈ ያለው መልዕክት ቀላል አይደለም ባይ ነኝ ።  በዋሽንግተኑ የመጀመሪያ ተቃውሞ የተሰማው ሳውዲን ከአልቃኢዳ ጋር አጎዳኝቶ የመወንጅል እና ከበቂ ማነስ የተነሳ የብዙሃን ሙስሊማንን መመሪያ የቁርአን መልዕክት በነጭ ቀለም የተጻፈበትን ደማቅ አረንጓው የሳውዲ አረቢያ ባንዴራን ወደ ማንቋሸሽ  እንዳያመረ የነበረን ስጋት መወገዱ ያስደስታል ። ይህም ብዙ የሳውዲ ነዋሪዎችን አስደስቶናል!
ለተፈጸመው ግፍ ማካካሻ ባይሆንም በመጠለያዎች የምንሰማው የሰቆቃ ጩኸት ረገብ ብሏል። የሳውዲ መንግስት በመጠለያ ያሉትን ዜጎች መጠለያ ሲታይ የሰነበተውን የምግብ ፣ የውሃ እና የህክምና አቅርቦት እያስተካከለው መገኘቱን ከመጠለያው ከሚገኙ ግፉአን ማረጋገጥ ችያለሁ ። በቀን አንድ ሚሊዮን ብር የሚደርስ ወጭን የሳውዲ መንግስት ፣ ከማውጣት ጀምሮ ወደ ሃገር ቤት መግባት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውንን ለማሰባሰብ 300 ያህል አውቶቡሶች በሪያድ በመካ ተመድበው የማጓጓዙን ሂደት ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል።  ወጭውን ይሸፍነዋል ተብሎ ከተነገረኝ ከኢትዮጵያ አየር መንገዳችን ወደ ሃገር ቤት የማጓጓዙ ዘመቻ ጎን ለጎን የሳውዲ መንግስት በሳውዲ አየር መንገድ በኩል ነጻ የማጓጓዝ ስራ  በመካሄድ ላይ መሆኑን መረጃዎች ደርሰውኛል ።

መልካሙ ጅምር ፣ ሰው ሃይልና የመረጃው እጥረት…

    jida embassay   ከላይ ለመጠቆም እንደሞከርኩት በሪያድና በመካ ስደተኛን የመቀበሉ ስራ እየተሰራ ቢሆንም በማቆያው ባለው የስደተኛ ብዛት አንጻር በጅዳ ወደ ሃገር መግባት የሚፈልጉትን  ወደ ማረፊያ የማጓጓዙም ሆነ ባሉበት የመመዝገቡ እንቅቃሴ በጅዳ ገና አልተጀመረም ። በጅዳ የሽሜሲማረፊያ እስር ቤትና በሪያድ መጠለያ ያለውን ምዝገባ እና የመጓጓዣ ሰነድ አቅርቦት ለማሳለጥ የኢትዮጵያ መንግስት ልዑክ እና ድጋፍ የሚሰጡ ሃላፊዎችን አሰማርቶ ስራው እየተሰራ ቢሆንም ከፍተኛ ቁጥር ላለው ዜጋ ግልጋሎት ለመስጠት የሰው ሃይል እጥረት መስተዋሉ አልቀረም። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን በቅርቡ ለቀናት ዝግ የነበረውን የጅዳ ቆንስል አመዘጋት መጥቀስ ይቻላል። ምንም እንኳን ቆንስል መስሪያ ቤቱ ስራውን ለቀናት የዘጋበትን ምክንያት በግልጽ ባወጣው ማስታወቂያ አልተገለጸም ። ምክንያቱ ባልተገለጸው የጅዳ ቆንስል መዘጋት ብዙዎችን አስቆጥቷል ” የታመመ ቢሞት እንዴት እንቅበር? ፖስፖር ለማሳደስ ፣ የታደስ ለመቀበል ፣ ሰነድ ማስተካከል ቢያስፈልግ ፣ የጋብቻ ወረቀት ማረጋገጫና እና ተመሳሳይ ግልጋሎት ስንፈልግ የት እንሂድ? ” ሲሉ በማጠየቅ በአስቸኳይ ቆንስሉ እንዲከፈት ነዋሪዎች መንግስትን ተማጽነዋል። የቆንስሉን መዘጋት ምክንያት ሃላፊዎችን ጠይቀን መላሽ ብናጣም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ቴዎድሮስ አድሃኖም “የጅዳ ቆንስል አገልግሎት እንዳይሰጥ የተዘጋው የቆንስላው ሰራተኞች ስደተኞቹን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንዲያግዙ ስለተፈለገ ነው ” ብለው በትዊተር መረጃ አቀብለውናል። ይህ የሚያሳየው የሰው ሃይል እና የመረጃ ልውውጥ እጥረት መሆኑን ለመረዳት መማር መመራመርን አይጠይቅም። ይህ እውነታ ፈጦ እያለ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ግልጋሎት ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑትን የኮሚኒቱ መስሪያ ቤትና ችግሩ ችግራችን ነው በሚል መክረውና ዘክረው አቤቱታ ያቀረቡ ወገኖችን ለመቀበል አልደፈሩም። ምክንያቱን የሚያውቁት ሃላፊው ቢሆኑም ሲሆን ነዋሪውን አስቸኳይ ሰብሰባ ጠርተው ፣ ያ ቢገድ የድጋፍ ጥያቄውን በበጎ ተመልክተው አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለመቻላቸው ሂደቱን ከመሳለጥ እንዳይገታው ስጋት አለ። ሌላው በሪያድና በጅዳ ሃላፊዎች ዙሪያ የሚታየው የመረጃ ክፍተት የግልጋሎት አሰጣጡን አልፎ አልፎ የሚስተዋለውን የመብት ገሰሳ ከቁጥጥር ውጭ እንዳያወጣው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ለዚህም በሪያድ መንፉሃና በተለያዩ አካባቢዎች ፣ በጅዳና በመካ “ወደ ሃገራችን ውሰዱን ?” በሚሉ ዜጎች እና በመንግስት ጸጥታ አስከባሪዎች መካከል የሚፈጠሩ  ፍጥጫና ግጭቶችን በመንፉሃ የታየውን አደጋ እንዳይደግመው ለመከላከል ይረዳል። በመንፉሃ ባየነው የተንቀሳቃሽ ምስል ባየነው ድብደባና ውክቢያ አድራሻቸው የጠፋ ወገኖች በፖሊስ ጣቢያዎች፣ በሆስፒታልና በመጠለያው ፈልገው ያጧቸውን ወገኖቻቸውን በሚመለከት መረጃ ለመስጠት ፈልገው ወደ መንግስት ሃላፊዎች ቢደውሉም ምላሽ  እንዳላገኙ በምሬት የገለጹልኝ በርካታ ናቸው ። በውክበቱ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች የትየለሌ የመሆናቸውን ያህል የደረሱበት የማይታወቅ ዜጉች ጉዳይ ከሚሰራው የማጓጓዝ ስራ በተጓዳኝ በመረጃ ልውውጥ ተደግፎ መሰራት ያለበት ስራ ነው ። ይህንና ይህን መሰል ጉዳዮችን ስንመለከት በመንግስት ሃላፊዎች የመረጃ ተቀባይ አለመኖር ነገ  ቢያንስ ለህሊናችን ተወቃሽ እንዳያደርገን ዛሬ መሰራት ያለበት ስራ ነው ባይ ነኝ።  ከዚህ አንጻር መረጃ ትልቅ አስተዋጽጾ እንዳለው በቦታው የሚገኙ የመንግስት ተወካዮች ሊያጤኑት ይገባል። ይህን ክፍተት ለመዝጋትም  የአደጋ ጊዜ ተጠሪና መረጃ ተቀብሎ የሚያጣራ ኮሚቴ በአፋጣኝ ሊቋቋም ይገባል። የኮሚቴው አባላትም ነዋሪውን ሃያ አራት ሰአት ክፍት የሆነ ነዋሪውን የሚያስተናግዱበት ስልክ ሳይውል ሳያድር መሰራት ካለበት ስራ አንዱ መሆኑን ማጤን ብልህነት መሆኑን ጠቁሜ የማለዳ ወጌን ልቋጨው ወደድኩ ..

እስኪ ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ

አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ አንድ –ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0

Pro Mesfinጥቅምት 2006

ወያኔና የነፖሊቲካ አጋሮቹ የሚያደርጉትን ለእነሱ የሚመች አከፋፈል ትተን አበሻን ለሁለት እንክፈለው፤ ሆድ ያለውና ሆድ የሌለው፤ ወይም የሚበላና የማይበላ፤ ዛሬ የምናገረው ሆድ ስላለው ወይም ስለሚበላው አበሻ ነው፤ አታውቁት እንደሆነ ተዋወቁት፤ በአጠቃላይ ስንመለከተው ግን የአበሻ ፍቅርም ሆነ ጠብ ለሆድ ነው፤ አበሻን የሚያጣላው፣ የሚያነታርከው፣ የሚያቧጭቀው የሆድ ነገር ነው፤ ለመብላት ነው፤ አንዳንዴም ሎሌውን ለማብላት ነው፤ ግብር ለማግባት ነው።

አዳም አበሻ ሳይሆን አይቀርም፤ ሁሉንም ነገር ብላ ከተከለከለው በቀር ብሎ ያስቀመጠው ይመስላል፤በላባችሁ ወዝ ብሉ ተብለው አዳምና ሔዋን መረገማቸውን አበሻ ገና አልሰማም፤ አበሻ የተፈጠረው ገነት ውስጥ ቁጭ ብለህ ያለውን ሁሉ ብላ በተባለበት ጊዜ ነው፤ እግዚአብሔር አበሻን ሁሉንም ብላ ሲለው ምናልባትም በጆሮው ጭራሽ አታስብ ብሎት ይሆናል፤ እስቲ በመጀመሪያ ስለምግብ እንነጋገር።

በሌላው ነገር ሁሉ ኋላ-ቀር ቢሆንም በምግብ ጉዳይ አበሻን የመበልጠው ያለ አይመስለኝም፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምግብ ውድድር ቢያደርጉ በምግብ ዓይነት፣ በጣዕም፣ በአሠራሩ ጥበብ አበሻ በቀላሉ እንደሚያሸንፍ በፍጹም አልጠራጠርም፤ የቱ አገር ነው ወዝ ያለውና ለስላሳ እንጀራ ያለው? በነጭ ጤፍ በሠርገኛው፣ በጥቁር ጤፍ፣ በስንዴውና በገብሱ፣ በማሽላውና በዘንጋዳው፣ በበቆሎው በእጅ ለመጠቅለል፣ በጉሮሮ ለማውረድ እንደአበሻ አመቻችቶ የሚሠራ የቱ ሕዝብ ነው? እንጀራው ሲፈለግ ቃተኛ፣ ሲፈለግ አነባበሮ እየሆነ በቅቤና በአዋዜ ርሶ ሆድ የሚያርስ ምግብ ማን ይሠራል፣ ከአበሻ በቀር?

የዳቦው ዓይነትስ ቢሆን ብዛቱና ጣዕሙ! ድፎው፣ የዶሮ ዳቦው፣ አምባሻው፣ ሙልሙሉ፣ ቂጣውስ ቢሆን ስንት ዓይነት ነው?

አበሻ ከጥንትም ጀምሮ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ ስለዚህም ይጾማል፤ ለእግዚአብሔር ሲል፣ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ሲል ከወዳጁ ከምግብ፣ በተለይም ከሥጋና ከቅቤ ይለያል፤ መጾም ዓላማው ለነፍስ ቢሆንም ለሥጋም ትልቅ ጠቀሜታ አለው፤ በአካል ውስጥ የተጠራቀመውን ጮማና ሞራ ለማራገፍ ይረዳል፤ አበሻ ግን ምኑ ሞኝ ነው፤ በሆድ ቀልድ የለም! የጾም ምግብ የሚባል ነገር ፈጥሮ ሆዱን ያስደስተዋል፤ ሥጋና ቅቤ ቀረብኝ ብሎ እንዳይጠወልግ ተቆጥሮ ብዛቱ የማይታወቅ ዓይነት የጾም ወጥ አለው፤ ስንት ዓይነት የአትክልት ምግብ፣ በዚያ ላይ ሹሮው፣ ክኩ፣ ስልጆው፣ ተልባው፣ ሱፉ፣ የሽምብራ ዓሣው፣ አዚፋው፣ ስንቱ ይቆጠራል!

ጾሙ ያልፍና ፍስኩ ሲመጣ አበሻ ፊቱን ከአትክልት ዓለም ወደእንስሳት ዓለም ያዞራል፤ ከዶሮ ጀምሮ እስከበሬው ኡኡ እያለ ለእርድ ይሰለፋል፤ የዶሮው ወጥ፣ የበጉ ወጥና አልጫው፣ ቅቅሉ፣ ምንቸት አብሹ፣ ክትፎው፣ ጥብሱ፣ ዱለቱ፣ ጥሬ ሥጋው፣ ምኑ ቅጡ!

የአበሻ ምግብ በዚህ ብቻ አይቆምም፤ አንዳንድ አበሻን የማያውቁ ሰዎች አበሻ ፍቅር አያውቅም ይላሉ፤ አበሻ ሌላ ቀርቶ በምግብም ፍቅሩን ይገልጻል፤ የመዝናኛና የፍቅር ምግብም አለ፤ እነቅንጬ፣ እነጨጨብሳ፣ እነግፍልፍል እዚህ ውስጥ የሚመደቡ ናቸው።

አበሻ የመንገድ ምግብም አለው፤ አገልግሉ፣ ቋንጣው፣ በሶው፣ ጭኮው፣ ጭኮው፣ የቡና ቁርስ እያለ ቆሎውን፣ ንፍሮውን፣ በቅቤና በአዋዜ የራሰ ቂጣውን፣ አነባበሮውን፣ አሹቁን ይከሰክሳል፤ አበሻ ከተመቸው መቼ ነው ከመብላት የሚያርፈው? የቱ አገር ነው በዚህ ሁሉ ምግብ ተወዳድሮ አበሻን ማሸነፍ የሚችለው?

አበሻ ምግብ ስለሚወድ የሚያስበላው ነገርም ይወዳል፤ ቃሪያን መብላት ልዩ ጥበብ ያደረገው ለዚህ ነው፤ ቂሉ ፈረንጅ አፐረቲቭ እያለ (ከሣቴ ከርስ መሆኑ ነው፤) አንጀቱን የሚጠብሰውን አረቄ ይጠጣል፤ በቅመማቅመምና በድልህ የተቁላላውን ወጥ በእንጀራ እየጠቀለለ ቢጎርስ እያላበው ይበላ ነበር!

የአበሻ ምግብ የሚበላው ወገን በፈረንጅ አገር ሲኖር አገሬ የሚለውና የሚናፍቀው የአበሻ ምግብ ነው! ስለዚህም በሄደበት የአበሻ ምግብ አይለየውም! አበሻ ሆዱን ትቶ አይሰደድም! እንዴት ብሎ!

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>