እመቤት በሳዑዲ አረቢያ የሪያድ ከተማ ነዋሪ ነች። እስካሁን እጇን ለፖሊስ አትስጥ እንጂ ሰሞኑን በተፈጠረው ችግር ከቤት መውጣት አቁማለች። “ካለሥራ እቤት ከተቀመጥኩ 2 ሳምንት ሊሆነኝ ነው፤ ወደ ውጭ መውጣት ያስፈራል” ትላለች። “እስካሁን በእንደዚህ ያለው ፍራቻ ውስጥ ባለንበት ሁኔታ መረጋጋት ሊባል አይችልም” የምትለው እመቤት “በሳዑዲ አረቢያ ሰሞኑን በጣለው ከባድ ዝናብና ጎርፍ ላይ ትኲረታቸውን በማድረጋቸው፤ የኢትዮጵያውያን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደረጉት ባለው ሰልፍ የተነሳ የሚደርስብን ድብደባ ጋብ ይበል እንጂ ተረጋግቶ ሥራ ለመሥራት አስቸጋሪ ነው” ትላለች። እመቤት በሳዑዲ አረቢያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በስልክ ለዘ-ሐበሻ አጫውታለች፤ ያድምጡት።
[jwplayer mediaid="9658"]
“በሳዑዲ ተረጋጋ የሚባለው በጎርፍ በደረሰባቸው አደጋ ላይ ስላተኮሩ ነው፤ አሁንም ሰው እየተሰቃየ ነው”–ቃለ ምልልስ ከሳዑዲ (Audio)
ዶ/ር ቴዎድሮስና ሌሎቹ !
ግርማ ጌታቸዉ ካሳ
Muziky68@yahoo.com
ኅዳር 11 ቀን 2006 ዓ.ም
ኢሕአዴግን እንደ አንድ የሚመለከቱ፣ ሁሉን አባላቶቹን በጅምላ የሚፈርጁ ጥቂቶች አይደሉም። ነገር ግን ኢሕአዴግ ዉስጥ የተለያዩ ቡድኖች አሉ። አንዱ የገነባዉን አንዱ ያፈርሳል። አንዱ ሲያነሳ አንዱ ይጥላል። አንዱ ሰላማዊ ሰልፍ ሲፈቅድ፣ አንዱ በጎን የዜጎችን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ይጋፋል። አንዱ የታሰሩ የሕሊና እስረኖች እንዲፈቱ ሲፈልግ፣ ሌላዉ «እዚያዉ ቃሊቲ ይበስብሱ» ይላል። አንዱ በጎና ቀና ሕሊና ሲኖረዉ፣ ሌላዉ ደግሞ የጠመመና የጫካ አስተሳሰብ ያለው ሆኖ ይገኛል።
በኢሕአዴግ ዉስጥ ያለው ተቃርኖ ሰሞኑን በጉልህ ለማየት ችያለሁ። ነገሩ እንዲህ ነዉ። በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን አሳዛኝ ግፍ ለመቃወም፣ በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያዉያን ወደ ሳዉዲ ኤምባሲ ያመራሉ። ወዲያዉ የደህንነት ሰራተኞች ባዙቃቸዉንና እና ዱላቸውን ይዘው፣ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከማድረግ ይልቅ፣ ሰልፈኞችን መደብደብ ጀመሩ። ብዙዎች ታሰሩ።
ሰልፉ፣ የደህንነት ሰራተኞችና ፖሊሶች ሳይቀሩ ሊቀላቀሉት የሚገባ ሰልፍ ነበር። በሰልፉ የተነሳዉ ጉዳይ፣ ኢትዮጵያዉያንን በሙሉ ያዋረደ ጉዳይ ነዉ። ነገር ግን ፣ የዜጎቻችን መብት ተረግጦ በሳዉዲ የተፈጸመዉን ድብደባ ለመቃወም፣ በአገሩ የወጣዉ ሕዝባችን ተደብድቦ ተመለሰ።
በዚህ ጉዳይ ላይ ፣ አልጃዚራ እንደዘገበው፣ የኢሕአዴግ መንግስት ቃለ አቀባይ፣ አቶ ሽመለስ ከማል፣ አስተያየት ሰጥተዉበታል። «ሰላማዊ ሰልፉ ሕገ ወጥ ነዉ። ፍቃድ አልተሰጣቸውም። በኢትዮጵያዊያን መካከል ፀረ-አረብ ስሜት (anti-Arab sentiments) እንዲኖር ለማድረግ እየሞከሩ ነዉ። ስለዚህ ፖሊስ እርምጃ ወስዷል» ነበር ያሉት።
አቶ ሽመልስ እንዲህ ማለታቸውን ከአልጃዚራ ዘገባ ሳነብ፣ ልክ ወላፈን በፊት ያለፈ ይመስል በጣም ደነገጥኩኝ። ለማመን አልቻልኩም። ደቂቃዎች እያለፉ፣ ፍም ላይ እንደተጣደ ምጣድ፣ ዉስጤ መንደድ ጀመረ። የኢትዮጵያዉያን ስሜት ተጎድቶ ባለበት ወቅት፣ ቆስለን ባለንብት ወቅት፣ ግፍ ለፈጸሙብን አረቦች ስሜት የምንቆረቆርበት ጊዜ ነዉን ? ይህ አይነቱ የኢትዮያዉያንን ስሜት ክፉኛ የሚጎዳ አስተያየት ከአንድ ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚል፣ ያዉም የመንግስት ባለስልጣን፣ ይጠበቃልን ? በእዉኑ እንዲህ አይነት፣ ለሕዝብ ስሜትና ክብር ፍጹም ደንታ የሌላቸው ሰዎች ናቸዉን የሚገዙን ?
«በቂ የጥበቃ ኃይል እንዲኖር ዝግጅት ስላላደረግን፣ ሕዝቡም በንዴት ዉስጥ ስለሆነ ፣ የሳዉዲ ኤምባሲን የማቃጠል ተግባር ሊፈጸም ይችላል» የሚል ስጋት ኖሯቸው ሊሆን ይችላል፣ ሰልፉን በኃይል ያስቆሙት። ነገር ግን አንድ የዘነጉት ጉዳይ ቢኖር የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋ ሕዝብ መሆኑን ነዉ። ላለፉት 5 ወራት በተለያዩ የአገራችን ግዛቶች በርካታ ሰልፎች መደረጋቸውን ማስታወስ እፈልጋለሁ። አንድም ድንጋይ አልተወረወረም። አንዲትም ንብረት አልጠፋችም። እንደዉም በደሴ ሰልፈኞቹ ለፖሊስ አበባ ያድሉ ነበር። በርግጥ ሕዝባችን የተከበረ፣ የሚያኮራ፣ ጨዋ ህዝብ ነዉ።
አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ሰልፍ ለማድረግ፣ በሕጉ መሰረት ባለስልጣናት ቢያሳዉቁም፣ አሁንም ሕገ መንግስቱ ተንዶ፣ ሰልፍ ማድረግ እንደማይችሉ ነዉ በደብዳቤ የተነገራቸው። እንኳን ሌሎች ድርጅቶች ሰልፍ ሲጠሩ መከልከል ቀርቶ፣ በዚህ አንገብጋቢ አገራዊ ጉዳይ፣ እራሱ ኢሕአዴግ ሰልፍ መጥራት ነበረበት። የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲክ ሳይንስ መምህር የሁኑት አቶ ሰይፉ ኃይሉ፣ በቅርቡ በለቀቁት ጽሁፍ « why not the government has arranged even public demonstration at least in our major cities to condemn the event and send message to the world?» ሲሉ ነበር የጠየቁት።
አሁን ደግሞ ወደ ሌላ የኢሕአዴግ ባለስልጣን ልዉሰዳችሁ። የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶር ቴዎድርስ አዳኖም። ኅዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም ዶር ቴዎድሮስ፣ ከሳዉዲ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ጊዜያዊ ማረፊያ ድረስ በመሄድ እንዳጽናኑና እንዳበረታቱ ፋና ዘግቧል። በርግጠኘንት ማረጋገጥ አልቻልኩም፣ ግን ዶክተሩ፣ ስደተኞች፣ የአገራቸውን መሬት በአይሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው እንደተቀበሏቸው የሚገልጹ አንዳንድ አስተያየቶች ፌስቡክ ላይ አንብቢያለሁ። ከአጥር አልፎ ሕዝብ ጋር መቀላቀል ማለት ይሄ ነዉ !!
ቅዳሜ ኅዳር 7 ቀን ዶር ቴዎድሮስ ፣ አዲስ አበበ በተደረገ ሶስተኛዉ የአለም ቀፍ ፋሚሊ ፕላኒንግ ኮንፍራንስ ላይ ያደረጉትን ንግግርም ማንሳት እፈልጋለሁ። «ዜጎቻችን ወደ አገር ሲመለሱ፣ ነገሮች በተስተካከለ ሁኔት እንዲሄዱ ለማድረግ እንሞክራለን። ሳዉዲዎች ሕገ ወጥ ናቸው (ከአገር ዉጡልን) ቢሏቸው፣ ግድ የለም፤ የሚሄዱበት አገር አላቸው። አጠንክሬ ላረጋግጥላችሁ ፣ ዜጎቻችን በአክብሮት እንቀበላቸዋለን» ነበር ያሉት። ከአንድ ጨዋ፣ የተማረ፣ በሳል መሪ የሚጠበቅ ግሩም ንግግር ! በአቶ ሽመልስ ከማል አይነቶቹ የደማዉ ልቤ ትንሽ ታደሰ።
ምን አለ ኢሕአዴግ እራሱን ከሽመልስ ከማሎች አጽድቶ ቴዎድሮስ አዳኖሞችን ቢያበዛ ? ምን አለ ባለስልጣናቱ የሚሰብርና ለሕዝብ ንቀት የሞላበት ንግግር ከሚናገሩ፣ የሚያሰባብስ፣ የሚያነጽ፣ የሚገነባ ንግግር ቢናገሩ ? ምን አለ ዜጎችን በማሰቃየት፣ በመደብደብ ፣ ሽብርተኞች እያሉ በማሰር፣ በማንገላታት ከሚደሰቱ፣ ዜጎች ሲጠቁ ማዘን ቢጀመሩ ? ምን አለ እንደ እንስሳ ከሚሆኑ እንደ ሰዉ ቢሆኑ ?
እንግዲህ እነቴዎዶሮስ አዳኖም የሚያረጉትን እያበረታታን፣ የተለየ ትእዛዝ እየላኩ፣ ዜጎችን የሚያስደበድቡ ፣ የዜጎችን መብት የሚረግጡና በዜጎችን መቆሳቆል የሚደሰቱ፣ የአገዛዙ ባለስልጣናትን ለማጥራት ሁላችንም ተባብረን መስራት ይኖርበናል። እነዚህ ግለሰቦች ለኢሕአዴግም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እርግማን ናቸው!!!! አገራችንን እንዲያምሱና እንዲያወኩ ሊፈቀድላቸው አይገባም።በተለይም የኢሕአዴግ ደጋፊዎች እነዚህ ሰዎች የድርጅታቸው ጠንቅ፣ ድርጅታቸው የበለጠ እንዲጠላ የሚያደርጉ መሆናቸውን አዉቀቁ፣ እነርሱ ላይ ዘመቻ እንዲጀምሩ አሳስባለሁ።
በመጨረሻ አንድ ነገር ጣል ላድርግና ላቁም። በዚህ ወቅት የ«ጠቅላይ ሚኒስቴራችን» ኃይለማሪያም ደስ አለኝ መሰወር ነዉ። እኝህ ሰው ዝምታን ለምን መረጡ ? ጋዜጠኛ ወሰን ሰገድ፣ «አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ “እስረኛ” ናቸዉ» በሚል አዉራምባ ታይምስ ላይ ባወጣዉ ጽሁፉ፣ ጠቅላይ ሚኒስተሩ የሕዝብን ትረታ እንዲያዳምጡ፣ ከአማካሪዎቻቸው አጥር እንዲወጡ፣ እንደመሪ አገር መምራት እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርቧል። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያም በ3ኛዉ የአፍሮ-አረብ ስብሰባ ላይ ለመገኘት (ሳዉዲዎችም ያሉበት) ወደ ኮዌት ትላንት ኅዳር 10 2006 ዓ.ም ቀን አመርተዋል። ከዚያ በኋላ ደግሞ በቀጥታ የተባበሩት መንግስት ክላይሜት ቼንጅ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ዋርሶዉ ፖላንድ ያመራሉ።(የአለማችን የአየር ሁኔታ በወገኖቻችን ላይ ከደረሰዉ ግፍ በልጦ ማለት ነዉ)
አቶ ኃይለማሪያም የተማሩ ሰው ናቸው። በዚህ ወቅት ከአገር ምንም አይነት መግለጫ ሳይሰጡ፣ ሕዝቡን ሳያበረታቱ፣ ከአገር ዉጭ መዉጣታቸው፣ ምን ያህል ተሰሚነታቸውን እንደሚጎዳ ያጡታል ብዬ አላስብም። ታዲያ ምን ነክቷቸው ነዉ እራሳቸዉን እንደዚህ የሚያገምቱት? ወደፊት በስፋት የምንነጋገርበት ይሆናል።
“አንድ አንዳርጋቸውን መግደል የነፃነቱን ትግል ማስቆም አይቻልም”–ግንቦት 7
ህወሃቶች የንጹሃን ዜጎችን ደም በከንቱ ሲያፈሱ የኖሩ ነብሰ ገዳዮች እንደሆኑ የሚታወቅ ነው። አሁንም ክብሬንና ነፃነቴን የሚሉ ዜጎችን ይዘው ደብዛቸውን ለማጥፋት ብዙ ዓይንና ብዙ ጆሮዎችን በየቦታው አቁመናል እያሉ ያቅራራሉ። ይሄን ሁሉ ዓይንና ጆሮ ይዘንስ የሚያሸንፈን ማን ነው ? ሲሉም ይደመጣሉ። እነርሱ እንደሚሉት ዓይኖቻቸው ማየት፤ጆሮዎቻቸውም መስማት የሚችሉ አይደሉም። የህወሃት ዓይኖች ማየት የተሳናቸው እውራን፤ ጆሮዎቻቸውም ማድመጥ የማያውቁ ደናቁርት እንደሆኑ የታወቀ ነው። ህወሃቶች ይህን የማይሰማ ጆሮና ፤ማየት የተሳነውን ዓይን ይዘው እየተደናበሩ፤ ይህን ለመደበቅ ህይዎት ያላቸው መስለው ይታያሉ። አዎን ህወሃቶች ጭው ባለ በርሃ ላይ ብቻችሁን እንደቆማችሁ እወቁ። የሚነገረው እና የሚሆነው በሙሉ ስለተሰወረባችሁ በብዙ ሚሊየኖች መሃከል ብቻችሁን እርቃናችሁን ቀርታችኋል። ብዙ ሚሊዮን ዓይኖች እና ጆሮዎች በእናንተ ላይ መተከላቸውን ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።
ግንቦት ሰባት የፍትህ፤የነፃነት እና የእኩልነት ንቅናቄ እንደ ህወሃት-ኢህአዴግ ጆሮዉ የተደፈነና አይኑ የታወረ ድርጅት አይደለም። ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የሚያይ ዓይን፤ የሚሰማ ጆሮና የሚያስተዉል ልቦና ያለው ህያው ንቅናቄ ነው። የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጥያቄ ግልፅ ነው። ነፃነት ! ፍትህ ! እና ዲሞክራሲ ! ናቸው። እነዚህ ጥያቄዎች በአግባቡ መልስ እንዲያገኙ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ተነስተናል ጉዞ ጀምረናል፤ ሺ አንድአርጋቸውን ፈጥረናል። ልብ ይበሉ ነፃነት ፍትህ እና ዴሞክራሲ ለሰው ልጆች የተሰጡ ክቡር ስጦታዎች ናቸው። ህወሃት እነዚህን ክቡር ስጦታዎች ከዜጎች ላይ ነጥቆና ህዝብን ረግጦ መቀጠል የለበትም። ህወሃት የዜጎችን ነፃነት ነጥቆ ፤ ፍትህን አጓድሎና ህዝብን ረግጦ እንደከዚህ በፊቱ በሠላም እኖራለሁ ብሎ የሚያስብ ከሆነ ተሳስቷል። በህወሃት ቅዥት አገራችን ተጎድታለች። ህዝቧም ለማያባራ ጉስቁልናና ውርደት ተዳርጓል። ብዙዎችም አገር አልባ ሁነው በየሰው አገሩ መፃተኛ ሁነው እንዲኖሩ ተገደዋል። በእኛ እምነት በአገራችን ላይ እየደረሰ ላለው ውርደት በዋናነት ተጠያቂው ህወሃት ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ ዋነኛው ጠላት ነው የምንለውም ዜጎቻችንን ለጉስቁልናና ለውርደት ስላደረገም ጭምር ነው። እኛ ይህን አገር በቀል ጠላት ከሥሩ ነቅለን ለመጣል ተነስተናል። ከዚህ ትግል የሚያቆመን ምንም ዓይነት ምዳራዊ ኃይል እንደሌለ ህወሃቶች እንዲያውቁት እንፈልጋለን። ህወሃቶች አንገታችንን አስደፍተው አይገዙንም። ጥቁር ደም ያፈራቻቸው የቁርጥ ቀን ውድ ልጆቿ የነጻነት ታሪክ በጥቁር ቀለም ይጻፍ ዘንድ የሚያደርጉትን ሀገርን የማዳን ጥሪ እንዲህ በቀላሉ መግታት ከቶ አይቻልም። ወያኔዎች አትደናበሩ! ጋሬጣውን መለየትን ለእኛ ተውሉን።
ታዲያ ይህን ንቅናቄ አንድ አንዳርጋቸውን በመግደል ማስቆም የሚቻል የሚመስለው ጅላ ጅል ቡድን አገሪቷን እየገዛ በመሆኑ ተቆጭተናል። አንዳርጋቸውን መግደል ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊ አንዳርጋቸውን መፍጠርና ትግሉንም የሚያጠናክር እና የሚያፋፍም መሆኑን አልተረዱም። የኢትዮጵያ ህዝብ የእምቢተኝነት፣ የአልገዛም፣ የነጻነት ታሪክን ለማስከበር መሰዋእትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆንን ከአንዳርጋቸው ከተማረ ቆይቷል። መቆጨታችን ግን እንዲሁ በቁጭት ብቻ የሚቀር የሚመስለው ካለም ድግሞ ተሳስቷል። ይሄ ቁጭት በየደረሱበት የንፁሃንን ደም በከንቱ ማፍሰስ አገር መምራት የሚመስላቸውን ህውሃቶች ከተንጠለጠሉበት ዙፋን አውርደን በልካቸውና በአቅማቸው እንዲኖሩ ለማድረግ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን እንድንቀጥል ያደርገናል። ህወሃት ውስጥ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ግለሰብ ካለ አሁን ቆም ብሎ እንዲያስብ እናሳስበዋለን። ጀንበር ሳትጠፋባችሁ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚደረገውን ትግል ተቀላቀሉ። እርግጥ ነው ለነፃነት የሚደረገው ትግል በየመስኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ህወሃትም የእጁን እንደሚያገኝ ምንም ዓይነት ብዥታ እንዳይኖራችሁ ልንነግራችሁ እንወዳለን።
ግንቦት ሰባት የቆመበት መሠረት ፅኑ፤ ዓላማውም ህዝባዊ ነው። በዚህ በፀና መሠረት ላይ ህዝባዊውን ዓላማ አንግበው የተነሱ ሚሊዮኖች አሉ። እነዚህ ሚሊየኖች የሌሉበት ሥፍራ የለም። ከቤተ-መንግስት እስከ እርሻ ማሳ፤ ከስለላ ተቋማት እስከ አገሪቷ መከላከያ ኃይል፤ ከሃይማኖት ተቋማት እስከ መንግስት መሥሪያ ቤቶች፤ ከዘመናዊ ትምህር ተቋማት እስከ ተከበሩ ገዳማት ድርስ ለክብራቸው ዘብ የቆሙ ሚሊየኖች አሉ። እነዚህ ሚሊኖች የቆሙት መረቅ የበዛበትን ወጥ ዓላማ አድርገው ሳይሆን በፀናው መሠረት ላይ ለተተከለው ክቡር ዓላማ ነው። ይህ ክቡር ዓላማ ነፃነት፤ ፍትህ ፤እኩልነት እና የህግ የበላይነት እንጂ ሌላ አይደለም። እነዚህ ሚሊየኖች አትኩረው ማየት የሚችሉ ድንቅ ዓይኖች ያሏቸው፤ አጥርተው ማድመጥ የሚችሉ ክቡራን ጆሮዎች ያሏቸው መሆናቸውን ህወሃቶች እንዲያውቁት እንወዳለን።
ግንቦት ሰባት ማንንም ፍርሃት እና ድንጋጤ ውስጥ መክተት አይፈልግም።እንዲያውም ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የሚታገለው ዜጎች ሁሉ ከፍርሃት ነፃ ሁነው በደስታ እንዲኖሩ ለማስቻል ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ካሁን ወዲያ ከግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዓይንና ጆሮ የሚያመልጥ አንዳችም ነገር እንደማይኖር የሚያሳድደን ቡድን እንዲያውቀው እንፈልጋለን። ዓይንና ጆሯችን በሁሉም ሥፍራ በንቃትና በጥንቃቄ ነገሮችን እየተከታተሉ ይገኛሉ።
ህወሃቶች ከትዕቢታችሁ ብዛት የተነሳ የህዝቡን ምክር መናቃችሁን እናውቃለን።የወገኖቻችንንም ድምፅ ጫጫታ እያላችሁ እንደምትሳለቁም እናውቃለን። ይሄ እንደማይጠቅማችሁ ብዙ ግዜ ነግረናችኋል። የህዝቡን ምክር ስሙ፤ የወገኖቻችሁንም ድምፅ አድምጡ ብንላችሁ በእምቢታችሁ ፀንታችኋል። ልቦናችሁ እንደ ፈርዖን ልብ ደንድኗል።ልብ ማደንደን እንኳን እናንተን ለመሠለ ደካማ ፍጡር ይቅርና በዘመኑ እኔ “እምላክ” ነኝ እሰከ ማለት ለደረሰው ለፈርዖንም አልበጀም። እንዲህ ዓይነት የልብ ድንዛዜ እናንተ በዚያ ጠባብ ዓላማችሁ ጣልነው ለምትሉት ለመንግስቱ ኃ/ማሪያምም አልረባውም። አሁንም የእኛ ምክር አጭርና ግልፅ ነው። የመዘዛችሁትን የበቀል ሰይፍ ወደ ሰገባው መልሱ። የዘጋችሁትን በር ክፈቱ። የነጠቃችሁትን የዜጎች ነፃነት መልሱ። በህዝቡ ላይ ያወረዳችሁትን የፍርሃት ድባብ አስወግዱ። የተከላችሁትን የዘረኝነት እሾህ ንቀሉ። ከእውነት ጋርም ታረቁ። እንዲህ ብታደርጉ የዚያችን አገር በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን የሚበላችሁን እሳት ማጥፋት አይቻላችሁም። መጥተናል!!
እኛም ከምን ግዜውም በላይ ተጠናክረናል። የትግል ዘርፋችን ሰፍቷል። በሁሉም አቅጣጫ መረባችን ተዘርግቷል። ከዚህ መረብ የትም አታመልጡም። ማምለጫ መንገዳችሁ አንድ ብቻ ነው። እርሱም የህዝቡን ድምፅ መስማት፤ እውነተኛ መልስ መስጠት እና ለህግ ተገዢ መሆን። አበቃን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
የማለዳ ወግ . . .በግጭት መካከል የሚሰራ ጋዜጠኛና ለመረጃ ፍቅር ያለው ዜጋ ህይዎት . .
በ ነቢዩ ሲራክ
ሳውዲ አረቢያ በተለይም በመንፉሃ ሪያድ የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ መረጃዎችን ስንለዋዎጥ ባጅተናል ። አሰቃቂውን የወገን ጉዳት አብረን አውግዘን ፣ ወገኖቻችን ደራሽ ያገኙ ዘንድ ኢትዮጵያውያን ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ በመላ አለም ያሰማነው ድምጽ ፍሬ አፍርቷል ! ደስ ሲል … በሁከቱ የተፈጠረውን ችግር ፣ የፈሰሰውን እንባና ደም የአይን ምስክሮችን በአካል ላነጋገረና ህመሙን ሲታመም ለከረመ የእኔ ቢጤ ዛሬ የተገፊው ወገን ችግሮች ተቀርፈው ማየትና መስማት ቢችል ከምንም በላይ እንደሚያስደስት ቃላት የሚገልጹት አይሆንም! ከሁከቱ ዋዜማ ጀምሮ በሁከቱና ከሁከቱ በኋላ ባሉት ቀጣይ ቀናት የእለቱን ክንዋኔ በቅርብ ተከታትየዋለሁ ። ሁከቱ ሲግም “ጋመ !” በማለትና ወገን ግፍ ሲበዛበት የዋይታ ድረሱልኝ ድምጹን የማሰማቴን ያህል ሃገር ሰላም ሲሆን መረጃ አጣቅሸ ” ሃገሩ አማን ነው! ጸጥ ረጭ ብሎ ረግቷል ” አላለሁ … ይህን ሳደርግ ተቃውሞና ድጋፉ በሁሉም አቅጣጫ እንደ ጎርፍ ይወርድኛል ! ይህን መሰሉን ኑሮ ከወጣትነት እስከ ጎልማሳነት የጋዜጠኝነት እድሜየ የገጠመኝ መሰናክል፣ የኖርኩበትና የማውቀው በመሆኑ አልደነቀኝም!
ይህን ሁለት ሶስት ቀን በሳውዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ ውስጥ በምትገኘውንና ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩባት የነበረችውን የመንፉሃን መንደር ጨምሮ በመላ ሪያድ የሚገኙትን ከስልሳ በላይ መጠለያዎች ሁኔታ በቅር እከታተላለሁ ። በጅዳ መካና በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍ ስላለው እንቅስቃሴ ከተለያዩ የማህበረሰቡ አካላትና በተለይም በጊዜያዊ እስር ቤት ያለውን ጭብጥ መረጃዎችን አገኛለሁ ። ነባራዊ የዜጎቻችን አያያዝና እየሆነ ያለውን ከክስተቶች ጋር ገምግሜ ተደጋጋሚ መረጃዎች ማቅረቤ ያልተመቻቸው ” ይህን ሶስት ወን የምታቀርበው ተረጋግቷል የሚል መረጃ አይመችም ፣ ይህም ከታች ያሉት እንዳይረዱ አንቅስቃሴውን አበረድከውሳ? ! ” በሚል የሰላ ወቀሳ አቅርበውልኛል ። የመንግስት ደጋፊዎች ደግሞ በአንጻሩ በአንጻሩ “መንግስት እየወሰደው ያለውን እንቅስቃሴ አትዘግብም !” በማለት ይቃወሙኛል። አንዳንዴማ ሙግታቸውን ያወርዱታል። በሳውዲ ሪያድ መንፉሃ የቤት ለቤት አሰሳ ዝርፊያ ፣ማሳደድ ፣ድብደባ፣ ሴቶችን የመድፈር እና የግድያው ጥቃት በእኛ ላይ ህግና መመሪያ ተጥሶ መሆኑ ግንዛቤ ሳይኖራቸው ቀርቶ ይሁን አውቀው ” በሳውዲ በእኛ ላይ የተለየ የተወሰደ እርምጃ የለም! ” ብለው ቅር ያሰኙኝን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ብቻ “አወድስ !” ለማለት ይከጅላቸዋል። በትዊተር ጠቃሚ መረጃን የሚሰጡን ዶር ቴዎድሮስ አደሃኖም ድምጻቸውን እስካሁን ካልሰማነው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለ ማርያም ደሳለኝ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገዋል ብልም ለአሁኑ ችግር መንስኤ መስሪያ ቤታቸው ድርሻ አለው ለምለው እማኝ ሚኒስትሩ ጥሩ ሰሩ እንኳ ቢባል ብቻቸውን ስራውን እየሰሩት እንዳለ ተደርጎ አድሃኖምን በመለስ ቦታ ለማስቀመጥና ” ለማምለክ !” እየተኬደ ያለው ፕሮፖጋንዳ በስራየ ላይ ተጽዕኖ እንዲያደርግ ይሞክራሉ። ከሁሉም የሚደንቀው በስልጡኑ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ የሚመሩት የሳውዲ አረቢያ ዲፕሎማቶች መረጃን አልቀበል አልሰጥ እያሉ ፍዳችን እያሳዩን ነው!
አዎ ! ዛሬም ነገም በግጭት መካከል የሚሰራ ጋዜጠኛ ኑሮ ከዚህ ያለፈ አይደለም ! … ትናንት ምሽት ካንድ ብርቱ ወዳጀ ለስለስ ብሎም ቢሆን የተሰነዘረብኝ ወቀሳ ግን ከዚህ በፊት ሞነጫጭሬያት የነበረችን የማለዳ ወጋወግ ሳብ አድርጌ ይህን መግቢያ ሰርቸ ወደ እናንተ እንዳደርሰው ምክንያት ሆነኝ … በግጭት መካከል የሚሰራ ጋዜጠኝነት ህይወት እንዲህ ነው!
መረጃ ስላለው ጠቀሜታ ያለኝ እምነት ጽኑ ነው፡፡ ይህ በመሆኑም የግል ፍላጎቴ ሆኖ በአረቡ አለም በሀገሬንና በዜጎቻችን ዙሪያ የሚለቀቁ መረጃዎችን በቅርበት እከታተላለሁ ! የማገኘው መረጃ ትክክለኛ ለመሆኑ አስቀድሜ እጠነቀቃለሁ ፡፡ ተገቢ መረጃዎችን አሰባስባለሁ ፡፡ የዜናውን ክብደትና አስፈላጊነት አውጥቸ አወርዳለሁ ! ከዚያም እውነታው እንዲህ ነው ብየ መረጃን በትክክል ማግኘት ላለበት ወገኔ አቀርባለሁ፡፡ ዋናው ቁምነገር የያዝኩት መረጃ እስከሆነ ድረስ የሚያሳስበኝ ነገር የለም ! ሁሉንም መረጃዎች ማቅረብ ባልችልም ይጠቅማሉ የምላቸውን መረጃዎች ለማካፈል ጥረት አደርጋለሁ፡፡ በአረብ ሃገር እንደ ሌላው ሃገር መረጃን ለማድረግ ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ድካም አለው ፡፡ ያም ሆኖ አስቸጋሪ የሆነው ውስብስብና አደገኛ የመረጃ ስብሰባ እኔን አያደክመኝም ! አይታክተኝምም !
መረጃውን ከወዲያ ወዲህ ቧጥጨና ፈልፍየ “እውነቱ ይህ ነው !” ስል የሚሰማኝ የደስታ ስሜት ከምንም በላይ ነው ! አዎ መረጃዎችን ሳቀርብ ከፊትና ከኋላ የሚሰነዘርበኝ በጎና በጎ ያልሆኑ አስተያየቶች መጠነ ሰፊ ናቸው፡፡ ባንድ ወቅት የማቀርበውን የሚወዱት በሌላ ጊዜ ይቃዎሙታል ! እኔኑ እንደ ግለሰብም ይጠሉኛል ብቻ ሳይሆን ድምጥማጤን ለማጥፋት ምለው ይገዘታሉ ! አንዳንዴ ደግሞ ይቃወሙኝ የነበሩት ያቀረብኩት መረጃ እንዳስደሰታቸው መጠን ይደግፉኛል ! ያሞካሹኛልም ! ይህ ሁሉ መረጃውን በአየር ላይ ባቀረብኩ ቅጽበት የሚስተዋል እውነታ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን እኔ የማንም ድርጂት አባልና ተቀጽላ ሆኘ ከማንም እንቅስቃሴ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ለመቸለስና የማንንም ትግል ለማኮሸት አይደለም፡፡ የሚሰማኝ እንደ ዜጋና እንደ ባለሙያ መረጃ ማቀበሌ ብቻ ነው የማውቀው ! ብዙዎች የሚደሰቱበትን መረጃ አቀብየ ሁሉንም ደስ ላሰኝ አልልም ፣ ብዙዎች ሲደሰቱ በእርኩስ መንፈስ ደስታቸውን ለማደፍረስና አንገታቸውን እንዲደፉ አስደናጋጭ መረጃ ማቀበሉንም ነፍሴ ፍጹም አይፈቅደውም !
በመረጃ ቅበላው ዙሪያ አንዱን ወገን በማደሰትና ሌላውን በማስከፋት የመረጃ ፍሰቱን ላዛባው ህሊናየ አይፈቅድም ! የምወደው ሙያ ነውና ላረክሰውም አልሻም ! ይህ እስከሆነ ድረስ የማቀርበው መረጃ እውነተኛ ድርጊቱን እስከ ሆነ ድረስ ሁሉንም የሁሉንም ስሜት በአንድነት መግዛት አይቻለውምና የተቃውሞም ሆነ የድጋፍ አስተያየቶች ማስተናገድ ግድ ይላል ፡፡ ሁሉም በአግባቡና በጨዋ መንፈስ በየፈርጁ ሲቀርቡ ያስደስቱኛል ! ግርታን ይፈጥራሉ ለምላቸውና መልስ ለሚያስፈልጋቸው መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ ! እንዲህ እየሆነ የጎልማሳነት እድሜየን ገፍቻለሁና ለምጀዋለሁ ! በግጭት መካከል የሚሰራ ነጻ ጋዜጠኛና ለመረጃ ፍቅር ያለው ዜጋ ህይዎት ደግሞ ከዚህ ያለፍ ሊሆን አይጠበቅም ! አይችልምም !
እስኪ ቸር ያሰማን !
ማስታወሻ በቸግራችን ለደረሳችሁልን ኢትዮጵያውያን በሙሉ
በሣዑዲ ዓረቢያ የምንኖር ወገኖቻችሁ
በሳዑዲ ዓረቢያ ከግማሽ ሚለዮን በላይ የምንቆጠር ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተን እንገኛለን፡፡ ከሃገር ያስወጣንን ድህነት ለማሸነፍ ብዙውን ግዜ ከአቅም በላይ የሆኑ የጉልበት ስራዎችን እና ስነልቦና የሚጎዱ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ በሆኑ የስራ መስኮች ተሰማርተን እስከአሁኑ ግዜ ደርሰናል፡፡ በሺዎች የምንቆጠር ደግሞ ባለንበት ሃገር ቤተሰብ መስርተን እና ሃብት ንብረት አፍርተንና ለአመታት በአንፃራዊ ሰላም ስንኖር ቆይተናል፡፡ የሃገሪቱ መንግስት ህገ ወጦች ናችሁ በሚል ሰብአዊ መብትን በጣሰ መንገድ በዜጎቻችን ላይ የሚፈፅመው አሳዛኝ ድርጊት እስከተፈጠረበት ግዜ ድረስም በሃገራችን ያጣነውን የስራ ዕድል ሳዑዲ ዓረቢያ ላይ ተፈጥሮልን በሃበሻነታችን ተፈልገን የምንሰራ እንጂ ሃበሻ በመሆናችን እንድንሸማቀቅ የተደረግንበት አጋጣሚ የጎላ አልነበረም፡፡ አሁን ባለው ወቅታዊ አሳሳቢ ችግር በአስር የሚቆጠሩ ትናንት አብረውን የነበሩ ወንድምና እህቶቸችንን የመቅበር እድል እንኳን ሳናገኝ ተሰናብተናቸዋል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩት ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በጤና ጥለዋት የወጧትን ሃገራችንን በበሽታ ሊመለሱባት እየናፈቁ ነው፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ይዞታው ከግዜ ወደግዜ እየተባባሰ በሚመጣ ማቆያ ክፍል እና እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡
ውድ ወገኖቻችን፡ በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ በሌላቸው ኢትዮጵያውያን ላይ እየተወሰደ ባለው ኢ-ሰብአዊ እርምጃ መነሻ በመላው ዓለም የምትገኙ ወገኖቻችን ልብ ምን ያህል እንደተነካ እና ለችግራችን ደራሽ መሆናችሁን ማሳየታችሁ እዚህ ያለንበትን ስቃይ እንድንረሳ የሚያደርግ ትልቅ ማፅናኛ ነው፡፡ ይህ የወገን መተባበር ካለንበት ችግር ተላቀን ሁላችንም ከስደት ተመልሰን ሃገራችንን ለማልማትም ትልቅ አቅም እንደሚሆን አንጠራጠርም፡፡
ውድ ኢትጵያውያን፡ በመላው ዓለም በምታደርጓቸው የተቃውሞ ሰልፎች እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች ብሶታችንን ለአለም ማሰማታችሁ የማይተካ ሚና አለው፡፡ ይህ አጋርነታችሁ እንዲጠናከር እየጠየቅን ጥቂት ነጥቦችን ለማስታወስ ወደድን፡፡ ቀዳሚው ነጥብ ኢ ሰብአዊ ድርጊቶቹ የሚፈፀሙት በውል በሚታወቁ ጥቂት አካባቢዎች እና ግለሰቦች በመሆኑ ሃገርን እና ህዝብን አጠቃላይ በጅምላ የመፈረጁ አካሄድ ችግራችንን ከመቅረፍ ይልቅ በቀጣይነት ያልታሰበ ጉዳት እንዳያስከትል ሊታሰብ ይገባል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የምንሆን ኢትዮጵያውያን የምንገኝ ስንሆን ሃገርን እና ህዝብን በጅምላ የመፈረጁ አካሄድ ከገፋ ህጋዊ ሁነው በሚኖሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ላይ የሚኖረው አሉታዊ ተፅእኖ እጅግ ከባድ ነው፡፡ በተለይ ምንጫቸው ባልተረጋገጡ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች በዚያ የሚኖሩ ህጋዊ ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ የሆነ የመጠላት እና የመገለል አደጋ እያመጣ ይገኛል፡፡ ሌላው ትኩረት የሚሻ ጉዳይ የጎላ ባይሆንም አገርን በአገር ላይ ህዝብን በህዝብ ላይ የማነሳሳት አዝማማያ ያላቸው አካሄዶች የሃገራቱን እና የዜጎች ለዜጎች ግንኙነት ታሪካዊ እና ቀጣይ ግንኙነትን ታሳቢ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ የአንድን ሃገር ሉአላዊነት ማክበርም እኛ ከሌሎች የምንጠብቀው በመሆኑ ለሌሎችም ልንሰጠው ግድ ይለናል፡፡ በተጨማሪም የችግሩን መነሻ እና ለዚያ የሚመጥን አፀፋም እኛኑ ሚዛናዊ የሚያስብለን የብስለት አካሄድ ነው፡፡ ምክንያቱም ሚዛናዊነት በድጋፍም ሆነ በተቃውሞ በሁሉም ጉዳይ ከኛ ይጠበቃል፡፡
በስተመጨረሻም ለማስተላለፍ የምንፈልገው መልእክት በመላው ዓለም የምትገኙ ወገኖቻችን እያደረጋችሁ ያላችሁት ድጋፍ እና ጫና የሃገራችን መንግስት ዘግይቶም ቢሆን የማዳን ጥረት እንዲጀምር አስገድዶታል፡፡ በሳዑዲ መንግስትም ይደርሱ የነበሩ የመብት ጥሰቶች ጥቂትም ቢሆን ጋብ እንዲል አድርጎታል፡፡ በቀጣይ የምታደርጓቸው የአጋርነት ድጋፎች ለችግር የተጋለጡ ሁሉም ዜጎቻችን በሰላም ወደ ሃገራቸው ገብተው የስነልቦና ስብራታቸው ተጥግኖ አምራች ዜጎች እስኪሆኑ እንዲቀጥል እንጠይቃለን፡፡ በሃገራችን ፍትህ እና ልማት መጥቶ በሰው ሃገር የሚፈሰው ላብ እና እውቀት ለሃገራችን የሚውልበት ቀን እንዲመጣም በፀሎትም በሰላማዊ ትግሉም እንድትጠነክሩ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
በሣዑዲ ዓረቢያ የምንኖር ወገኖቻችሁ
የሳምንቱ የአብርሃ ደስታ በፌስቡክ ላይ የተለቀቁ ምርጥ ጽህፎች
የነቀዘው የሙስና ትግል!
————————-
ስለ “የነቀዙ ህሊናዎች” አንድ የነቀዘ ፅሑፍ አዘጋጅቼ ስጨርስ መብራት ሃይል ነቀዘብኝና መብራት ሲጠፋ ፅሑፌን አብሮ ጠፋ። የፅሑፉ መሰረተ ሐሳብ ባጭሩ እነሆ።
የኢህአዴግ መንግስት የነቀዘውን ዘጋቢ ድራማ (ዘጋቢ ፊልም አላልኩም) በማቀናበር “ሙስናን ከልቤ እየታገልኩ ነው። እየታሰሩ ያሉ ባለስልጣናት በስርቅ እንጂ በፖለቲካ አለመሆኑ ይታወቅልኝ፣ ሰው ግን አያምነኝም” አለን። መንግስት ለሚናገረውና ለሚያደርገው ነገር ህዝብ እንደማያምነው ማመኑ አንድ ትልቅ ነገር ነው። ችግሩ ግን አሁንም በድራማው ማመን አለመቻለ ነው።
እኔ “የነቀዙ ህሊናዎች”ን ድራማ መንግስት በፈለገው መጠን አልተቀበልኩትም። በኔ እምነት በሙስና ሰበብ የታሰሩ ሰዎች በትክክል በስርቅ (ሙስና) የተያዙ አይመስለኝም። የታሰሩት በፖለቲካ ሊሆን ይችላል። ይህን የምልበት ምክንያት የታሰሩት (ወይ የተያዙት) ባለስልጣናት ሙስና አለመስራታቸው (አለመስረቃቸው) ወይ አለመስራታቸው (አለመስረቃቸው) ማስረጃ ስላለኝ ወይ ስለሌለኝ አይደለም። የኔ መከራከርያ ሐሳብ ‘በኢህአዴግ መንደር ሙስና የሰራ (የሰረቀ) ይታሰራል ወይ?’ የሚል ነው። ሙስና የሰራ የሚታሰር ቢሆን ኑሮ አብዛኞቹ ባለስልጣናት ይታሰሩ ነበር። አሳሪዎቹም ጭምር ይታሰሩ ነበር። የኢህአዴግ ሙሰኞች የታሰሩት ሰዎች ብቻ ናቸው? ከነሱ በባሰ ሁኔታ በሙስና የተዘፈቁ ግን ያልታሰሩ የሉም?
ኢህአዴግ ልናምነው ከፈለገ ሙስና የሰሩ ባለስልጣናት ሁሉንም መታሰር አለባቸው። የተወሰኑ እያሰረ ሙስና መስራታቸው ቢነግረን የታሰሩት በሙስና ነው ብለን ለማመን ይከብደናል። ምክንያቱም የሰረቀ ሁሉ እንደማይታሰር እያየን ነው። ብዙ ግዜ ኢህአዴግ የራሱ ልጆች የሚያስረው የፖለቲካ ልዩነት ሲፈጥሩ ነው። ለምሳሌ አቶ ስየ አብርሃ በሙስና ሰበብ የታሰረው ከመለስ ጋር አለመግባባት ከፈጠረ በኃላ ነበር። ስየ በትክክል ሙስና ሰርቶ ከሆነ የሰረቀው ከክፍፍሉ በኋላ ነው? ሊሆን አይችልም። ስየ ሰርቆ ከሆነ ከክፍፍሉ በፊት ነው መሆን ያለበት። ከክፍፍሉ በፊት ግን አልታሰረም። ስለዚህ ስየ ከመለስ ዜናዊ ጋር ባይጣላ ኑሮ ያለመታሰር ዕድል ነበረው ማለት ነው። ባይታሰር ኑሮ ሙስና መስራቱ አንሰማም ነበር።
ስለዚህ በኢህአዴግ የሚታሰር ሁሉ ሙስና የሰራ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። እናም ኢቲቪን አላመንኩትም። ለመታመን ከፈለገ የሰረቁት ሁሉ ይታሰሩ።
“ከህወሓት የባስክ ትሆናለህ” አሉኝ
——————————
“ጨቋኝ ስርዓት አልፈልግም” ብዬ በፃፍኩት ላይ አንድ የፌስቡክ ወዳጄ “አንተ ራስህ ስልጣን ብትይዝ ከህወሓት የባስክ አምባገነን ትሆናለህ” አለኝ።
እኔም እላለሁ፣
ከህወሓት የተሻልኩ እንደምሆን እርግጠኛ አይደለሁም (ራሴ ለግዜው እንደ ፓርቲ ልቁጠር)። ስለ አንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ። እኔ ሰለማዊ ታጋይ ነኝ። ስልጣን የምይዘው በህዝባዊ ምርጫ እንጂ በጠመንጃ አይደለም። የምወዳደረው በሐሳብ እንጂ በሃይል አይደለም።
ስለዚህ ስልጣን ስይዝ የራሴ ወታደር፣ ፖሊስ፣ ዳኛ ወዘተ ይዤ አልመጣም። ስልጣን የምይዘው በሕገመንግስት መሰረት እስከሆነ ድረስ በኔና በወታደሮቹ ያለ ግንኙት ሕገመንግስታዊ ይሆናል። ስለዚህ ወታደሮቹ እንደፈለኩ የግሌ የስልጣን ጥም ለማርካት አላዝዛቸውም። ዳኞችም ነፃ ይሆናሉ።
ስለዚህ እኔ ስልጣን ከያዝኩ በኃላ ከህወሓት ካልተሻልኩ በህዝብ ምርጫ እንደወጣሁ ሁሉ በሚቀጥለው በህዝብ ምርጫ ከስልጣን እወርዳለሁ። ከስልጣን ላለመውረድ ምንም ዓቅም የለኝም፤ ምክንያቱም በምርጫ ስልጣን የያዘ አካል የግሉ ወታደርና ፖሊስ የለውም። የስልጣን መሰረቴ የህዝብ ድምፅ ከሆነ በስልጣን ለመቆየት ስል ህዝብን አልጨቁንም። ከጨቆንኩ ደግሞ ህዝቡ ያወርደኛል።
የኢህአዴግ መንግስት ሰለማዊ ትግልን አጨልሞብኝ በትጥቅ ትግል ስልጣን ከያዝኩ ግን አምባገነን የመሆን ዕድል አለኝ። ምክንያቱም የስልጣን ምንጬ ጠመንጃ እንጂ ህዝብ አይደለም። ለህዝብ ታማኝና አገልጋይ የምሆንበት ዕድል ይጠባል። ስለዚህ በምርጫ ስልጣን የያዘ መንግስት ቢያበላሽ እንኳ በምርጫ ይወርዳል። አሁን የቸገረን በጠመንጃ የመጣ መንግስት ነው።
ዓላማችን ስልጣን መያዝ ብቻ ሳይሆን ስልጣን በጠመንጃ ከመያዝ በምርጫ የምያዝበት ስርዓት መገንባት ጭምር ነው።
(ስልጣን የመያዝ ዕቅድም ፍላጎትም የለኝም። የኔ ፍላጎት በነፃነት የፈለኩትን ማድረግ ነው። እኔ የሌሎችን መብት ሳልዳፈር የፈለኩትን የማድረግ ነፃነት እንዲኖረኝ የህዝብ መንግስት ወይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት አለበት። ስልጣን መያዝ ነፃነትን ይገድባል)።
‘ኢትዮዽያዊነት’ ምንድነው?
——————————
የህወሓት በስልጣን የመቆየት ስትራተጂ መከፋፈል ነው። ለመከፋፈል ወዳጆችና ጠላቶች መለየት ነው። ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት “ሸዋ አማራ” ጠላቱ እንደሆነ ይሰብካል (‘ዓረና ከጠላቶቻችን ጋር እያበረ ነው’ የሚል ፕሮፓጋንዳ መሰረት እናድርግ)።
እንዴት ነው አንድ ህዝብ ለሌላ ህዝብ ጠላት የሚሆነው? የህዝብ ጠላት ሊሆን የሚችለው ገዢ መደብ ነው። ህዝብን የሚጨቁን ገዢ የህዝብ ጠላት ነው። ስለዚህ መወገድ ይኖርበታል። ህዝብ ግን የሌላ ህዝብ ጠላት ሊሆን አይችልም።
‘የሸዋ አማራ’ የትግራይ ጠላት መሆኑ የሚነግሩን ደርግ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀመውን ግፍ በማጣቀስ ነው። ደርግ ጨካኝ የነበረው ለትግራይ ህዝብ ብቻ አይደለም፤ አማራውም፣ ኦሮሞውም ሌላውም ተጨቁኗል። የአማራ ህዝብም “ደርግ አማራ ነው፣ የኛ ነው” ብሎ ከሌሎች ህዝቦች የተለየ ድጋፍ ለደርግ አልሰጠም። ደርግም “ለአማራ ህዝብ የቆምኩ ነኝ” አላለም። ደርግ “ለኢትዮዽያ የቆምኩ ነኝ” እያለ ሁሉም ኢትዮዽያውያንን በደለ።
ህወሓት ከስልጣን የሚወርድ ከሆነ ትግራይ ኢትዮዽያ እንዲሆን የሚፈልግ አይመስልም። ህወሓትና የትግራይ ህዝብ በተመሳሳይ ዕድሜ መመዘን ግን ስህተት ነው። ምክንያቱም የህወሓት የስልጣን ዕድሜ አጭር ነው። የትግራይ ህዝብ ግን ለዘላለም ይኖራል። በሌላ ስርዓት ሌላ ታሪክ ያስመዘግባል። ህወሓት ግን በምርጫ ወይ በጠመንጃ በቅርብ ግዜ መውደቁ አይቀርም፤ የተፈጥሮ ሕግ ነውና።
“ኢትዮዽያዊ ነኝ” ካልክ “የሸዋ ልሂቃን ደጋፊ ነህ” ይሉሃል። ኢትዮዽያ የሸዋ ፖለቲከኞች ብቻ የግል ንብረት ነች እንዴ? ኢትዮዽያኮ የሁላችን ነች። የትግራዮች፣ የአማራዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ሶማሌዎች፣ ቤኑሻንጉሎች፣ ጋምቤላዎች፣ ዓፋሮች፣ ደቡቦች … የሁሉም ናት።
ኢትዮዽያዊ ማንነት ለተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ከሰጠነው ተሳስተናል። የፖለቲካ ተፎካካሪዎቻችን “ኢትዮዽያውያን ነን” ስላሉ እነሱን ለመቃወም “ኢትዮዽያውያን አይደለንም” ካልን ችግሩ የኛ ነው። ምክንያቱም ኢትዮዽያዊነታችን በራሳችን ፍቃድ ለሌሎች አሳልፈን ሰጥተናል ማለት ነው። ኢትዮዽያዊነት ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ ማን ሰጠው? ኢትዮዽያውነት’ኮ የጋራ ማንነታችን ነው።
እያንዳንዱ ሰው የራሱ (የግሉ) የሆነ ማንነት አለው። በወረዳ፣ ዞን፣ ብሄር ወዘተም ቡድናዊ የግል ማንነት አለው። በኢትዮዽያ ደረጃ ደግሞ የሁላችን የጋራ የሆነ ኢትዮዽያዊ ማንነት አለን።
ፖለቲከኞች “እነዚህ ሰዎች ኢትዮዽያዊ ስሜት የላቸውም፣ በዘር ያስባሉ፣ ትክክለኛ ኢትዮዽያውያን እኛ ነን ወዘተ …” ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል። ምክንያቱም ኢትዮዽያ የየተወሰኑ ግለሰቦች አይደለችም። ኢትዮዽያ የሁሉም ነች። ኢትዮዽያዊነት የተወሰነ ብሄር ወይ ክልል ወይ አውራጃ የሚወክል አይደለም። ሁሉም የኢትዮዽያ ህዝቦች የሚወክል ነው።
የኢትዮዽያ ህዝቦች እንደ አንድ ሰው አንድ ዓይነት ሃይማኖት፣ ባህልና ማንነት ሊኖራቸው አይችልም። በአንድ ሀገር የተለያዩ ሰዎች እስካሉ ድረስ የተለያየ ማንነት አለ (በብሄር፣ ወረዳ ወዘተም የተለያየ ማንነት ነው ያለው)። ስለዚህ ኢትዮዽያዊነት የአንድ ሰው ማንነት ሳይሆን የብዙ ሰዎች ማንነት ድምር ዉጤት ነው።
ስለዚህ ኢትዮዽያዊነት የጋራ ማንነት ነው። ኢትዮዽያዊነት አብሮነት ነው። እናም አንድ ግለሰብ ወይ የፖለቲካ ድርጅት “እኔ ነኝ ትክክለኛ ኢትዮድያዊ” ካለ ኢትዮዽያዊነት ወደ አንድ አከባቢ (ብሄር ወይ ክልል ወይ መንደር) አውርዷታል ማለት ነው። ይህም ስህተት ነው።
ኢትዮዽያዊ መሆን ከደበረን ችግር አለ ማለት ነው። ችግሩ ጭቆና ሊሆን ይችላል። ጭቆና (ለምሳሌ የብሄር ጭቆና) ካለ ጭቆናውን ለማስወገድ ሁሉም ኢትዮዽያውን ህዝቦች ተባብረው መፍታት ይኖርባቸዋል። ሁላችን ከተባበርን ችግሮችን (ብሄራዊ ጭቆናን) ማስወገድ እንችላለን።
ጭቆና ስለበዛብን ከኢትዮዽያ መገንጠል (አብሮነትን መቃወም) መፍትሔ ሊሆን አይችልም። እንበልና በትግራይ ህዝብ ወይ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ብሄራዊ ጭቆና ተፈፅሟል። አሁን መታገል ያለብን በነዚህ ህዝቦች ላይ የነበረውን ብሄራዊ ጭቆና በማስወገድ ነፃነትና እኩልነት ማረጋገጥ ነው። ለዚህ ጉዳይ ሁሉም ዜጎች መተባበር ይኖርባቸዋል።
“ብሄራዊ ጭቆና ስለነበረ (ስላለ) መገንጠል እንፈልጋለን” የሚለው ሐሳብ አይመቸኝም። ምክንያቱም ጭቆናው ከነበረ አሁንስ ቢሆን እንዴት በመለየት መቅረፍ ይቻላል? ትግራዮችና ኦሮሞዎች ጭቆና የደረሰባቸው ባለፉ ስርዓቶች ከሆነ ላለፈው በደል አሁን በመገንጠል እንዴት መቅረፍ ይቻላል? ብሄራዊ ጭቆናው ያለው አሁን ድረስ ከሆነም ለመለየት ከመምረጥ አብሮ ታግሎ ጨቋኝ ስርዓቱ በመጣል እኩልነትን ማስፈን እየተቻለ ለመገንጠል ማሰብ ምን አመጣው?
ጨቋኝ ስርዓቱ ለማስወገድ አቅሙ ከሌለን ለመገንጠልም አቅሙ አይኖረንም። ምክንያቱም ከመገንጠል ስርዓቱን መቀየር ይቀላል። ምክንያቱም ለመገንጠል ብቻህን ነው የምትታገለው፤ ስርዓት ለመቀየር ግን ከኢትዮዽያውያን ወገኖችህ ጋር ነው የምትታገለው። ደግሞ በመገንጠል ጭቆና አይወገድም። ለእኩልነት ጠንክረው በመታገል እንጂ በመገንጠል ጭቆናን ያስወገዱ ህዝቦች የሉም።
ኢትዮዽያዊነቴ ለማንም አሳልፌ አልሰጥም። ኢትዮዽያዊነት ለ”ሸዋ አማራ” ብቻ የተሰጠ ማንነት አይደለም። ኢትዮዽያዊነት የሁላችን ነው።
ስም የማጥፋት ዘመቻ!???
—————————–
ህወሓቶች በኔ መጨነቅ የጀመሩ መሰለኝ (ስም የማጥፋት ዘመቻ መጀመራቸው ሳስብ ነው)። እርግጥ ነው የኔ ስም ማጥፋት / ማፍረስ አይችሉም። ምክንያቱም የኔ ስም አልተገነባም። ያልተገነባ አይፈርስም። እኔን አጀንዳ ማድረጋቸው (በዚህ ሳምንት በተለይ) ግን ለምን ይሆን?
መልሱ ቀላል ነው። ያሁን የህወሓት መሪዎችና የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች መለየት በመቻሌና ለይቼ በመምታቴ ይመስለኛል። ህወሓቶች ከትግራይ ህዝብ ተለይተው እንዲታዩ አይፈልጉም። ምክንያቱም ተቃዋሚዎች የትግራይን ህዝብ ከህወሓት ጋር ደርበው ዒላማ ሲያደርጉት ህወሓት ከትግራይ ህዝብ ድጋፍ ያገኛል።
ስም ለማጥፋት አንዴ “አብርሃ የሚፅፈው ዉሸት ነው” ይላሉ፤ ሌላ ግዜ “የትግራይን ማንነት ትቶ ኢትዮዽያዊ ለመሆን ጥረት ያደርጋል” ይላሉ። የምፅፈው “ዉሸት” ከሆነ ለምን ት ሸበራላቹ? ዉሸት ከሚፅፍ ሰው በዉሸት የሚሸበር ሰው የባሰ ከንቱ ነው (እኔ የምፅፈው ዉሸት ነው ብላቹ ካመናቹ)። አዎ! አሁንም ኢትዮዽያዊ ነኝ። ምክንያቱም ትግራይ ነኝ። ትግራይ ደግሞ ኢትዮዽያ ነው።
ህወሓትን ከትግራይ ህዝብ ነጠልነው። አሁንም ከቀድሞ ታጋዮች ስንነጥለው ተሸበረ። አዎ! ለይተን አነጣጥረን መምታት አለብን።
ስም የማጥፋት ስትራተጂ የውድቀት መንገድ ነው።
የፕሬዝደንት ኢሳያስ ከዕይታ መሰወር ምክንያት ምን ይሆን?
- መሰወራቸው አነጋጋሪ ሆኗል
- የአሜሪካ መንግስት ለዜጎቹ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል
- በአስመራ ጀኔራሎች መካከል የስልጣን ሽኩቻ ይጠበቃል
በሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር
በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም አጋማሽ በኤርትራ ጎዳና መታየታቸው የተነገረላቸው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአደባባይ እና ከኤርትራ ቴሌቪዥን ዕይታ ውጪ መሆናቸው በአስመራ ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ የሆነ መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል።
የሰንደቅ ጋዜጣ ዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደገለፁት “ከዚህ በፊት ፕሬዝደንቱ ከሚሰቃዩበት የጉበት በሽታ ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ ሕመም ተዳርገዋል። በአሁን ሰዓት በኳታር ሆስፒታል ሕክምና እየወሰዱ ይገኛሉ” ብለዋል።
በአስመራ ከተማ ውስጥ እየተናፈሰ ያለው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከበሽታቸው አገግመው ሀገር ሊያስተዳድሩ ይችላሉ የሚሉ በአንድ ወገን በሌላ ወገን ያሉት ከዚህ በኋላ ፕሬዝደንቱ ሀገር በሚያስተዳድሩበት ቁመና ውስጥ ሊገኙ አይችሉም የሚሉት ይገኙበታል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ መንግስት እ.ኤ.አ. በግንቦት 10 ቀን 2013 ወደ ኤርትራ የሚጓዙ የአሜሪካ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያርጉ የሚያሳስብና ከተቻለ ወደ ኤርትራ ጉዞ እንዳያደርጉ የሚመክር የማሳሰቢያ መልዕክት በዚሁ ሳምንት በድጋሚ ለዜጎቹ አስተላልፏል።
“የኤርትራና የአሜሪካ ጥምር ዜግነት ያላቸው ዜጎች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ያስራቸዋል። ስለታሰሩ ዜጎች ከአሜሪካ መንግስት ማብራሪያ ሲጠየቅም ምላሽ አይሰጥም። አስመራ የሚገኘውም የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ መታሰራቸውን ሰምቶ ማብራሪያ ለአስመራ መንግስት ቢያቀርብም ምላሽ አይሠጥም” ሲል መግለጫው ተቃውሞውን አሰምቷል።
በተለይ እ.ኤ.አ. ከ2012 ጀምሮ የኤርትራ መንግስት በግለሰብ ደረጃ ዜጎቹን አውቶማቲክ መሳሪያ በማስታጠቁ በቀላሉ የአሜሪካ ዜጎች ለአደጋ ተጋላጭ ይሆናሉ ከሚል ስጋት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ታጣቂዎች በአስመራ ከተማ ሚሊሽያ በሚል ስለሚታወቁ ማንኛውንም ሰው በፈለጉት ቦታና ሰዓት መፈተሽ ይችላሉ። በዚህም የተነሳ በአስመራ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻና የሃይማኖት ቦታዎች ለመጎብኘት የሚመጡ የአሜሪካ ዜጎች በእነዚህ ታጣቂዎች ላይ ሊደርስባቸው ከሚችለው ስጋት ለመዳን ከአሜሪካ መንግስት ዕውቅና ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ መግለጫው አሳስቧል።
በኦክቶበር 3 ቀን 2013 በላምባዱሳ ለተሰውት 350 ኤርትራዊያን ማስታወሻ በተደረገ ስነ-ስርዓት በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አካባቢ ኤርትራዊያን በመንግስታቸው ላይ ባሰሙት ቅሬታ ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱ የሚታወቅ ነው።፡
የኢሳያስ አፈወርቂ ጤና መሻሻል ካላመጣ በአስመራ ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል የስልጣን ሹኩቻ መነሳቱ አይቀርም ሲሉ የዲፕሎማቲክ ምንጮቻችን ለሰንደቅ ጋዜጣ አስተያየታቸውን ገልፀዋል። አያይዘውም፤ ለምስራቅ አፍሪካ ሰላምም የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት እ.ኤ.አ. 2009 የአስመራ መንግስት በሚከተለው የትርምስ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መነሻነት በኤርትራ መንግስት ላይ ባስተላለፈው ማዕቀብ የተነሳ እስከ ዛሬ ድረስ የአስመራ መገናኛ ብዙሃን በአሜሪካ መንግስት ላይ ከፍተኛ የስም የማጥፋት ፕሮፖጋንዳ እየፈጸመ መሆኑ ይታወቃል።¾
ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!! ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እንዲያውም በግል በሚኖሩበት ቤት እምነታቸውን በማራመዳቸው ብቻ ኢትዮጵያውያኑ/ቱ ዜጎች ላይ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲጋዙም ተደርጓል፡፡
እ.ኤ.አ 2011 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ (Human Rights Watch) ዘገባ የሳውዲ አረቢያ ፖሊስ “ህገወጥ ስብሰባ በሚል ሰበብ 35 የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያወያንን/ትን“ “በአንድ ኢትዮጵያዊ የክርስትና እምነት ተከታይ የግል መኖሪያ ቤት በእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዋዜማ ተሰባስበው ጸሎት በማድረግ ላይ እንዳሉ” በፖሊስ ቀጥጥር ስር ውለዋል” ይላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ ጥገኝነት በሚፈልጉ እና ሌሎች ስደተኛ ኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኖች ላይ በሚደረገው ሰብአዊ መብት ረገጣ ምክንያት ምንጊዜም የማያቋርጥ ትችት እየተደረገ መሆኑን መግለጽ ማጋነን አይሆንም፡፡ በዚህ ወር በዕየለቱ በሚባል መልኩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ የደህንነት ኃላፊዎችና ተራ የሳውዲ ዜጎች በየመንገዱ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ያድናሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አንዳንድ ጊዜም ይገድላሉ፡፡ የሳውዲ ፖሊሶች ኢትዮጵያውያንን ሲያሰቃዩ የሚያሳየው የቪዲዮ ቅርፅ ለህሊና የሚሰቀጥጥ ነው፡፡ የሳውዲዎች ኢትዮጵያውያንን በየመንገዱ የማባረር ሁከት፣ ጥቃት የመሰንዘርና የመግደል ድርጊት ምንም ዓይነት ማብራሪያ አያስፈልገውም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚያሳየው የፎቶግራፍ ምስል አስደንጋጭና ከሰለጠነ የሰው ልጅ አስተሳሰብ በእጅጉ የዘለለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አስተዳደር 200 ሺ እና ከዚያ በላይ የሚሆኑትን በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን/ት ለማገዝ ምን እያደረገ ነው? ምንም!!! እራሱ አምኖ በተቀበለው መሰረት ገዥው አስተዳደር ምን ያህል ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ እንደሚኖሩ እንኩዋን አያውቅም፣ ሆኖም ግን ተጨባጭነት በሌለው መልኩ ኢትዮጵያውያንን/ትን ከሳውዲ አረቢያ ሙሉ በሙሉ በተቻለ መጠን ወደ ኢትዮጵያ እመልሳለለሁ የሚል ቃል ገብቷል፡፡
የወባ ተመራማሪው “የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር”፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም የሳውዲ መንግስት በግዛቱ በሚገኙት ስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ሰራተኞች ላይ የፈጸመውን አረመኒያዊ የኃይል እርምጃ “መንግስቱ አውግዘዋል፡፡ ይኸ በፍጹም ተቀባይነት የለውም፡፡ ይህን ጉዳዩ የሳውዲ መንግስት እንዲያጣራ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ እዚያ በነበሩበት ጊዜ በክብር መያዝ የነበረባቸውን ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስም ደስተኞች ነን፡፡ ተቀባይነት የለውም” የሚለውን አባባል ገዥው አስተዳደር እንደ አስፈሪ የጭካኔ ድርጊቶች፣ ያለመሰልጠንነትና ዘግናኝ ጨካኝነትና ወንጀለኛነት የሚሉትን ቃላት ለመግለጽ የሚጠቀምበት የውግዘት ቃል ነው፡፡ አልጄዚራ እንደዘገበው ከሆነ በተፈጸመው ድርጊት ተበሳጭተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን/ት አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ለማሰማት በሄዱበት ጊዜ የገዥው አስተዳደር ፖሊስ በቁጥጥር በማዋል ድብደባ ፍጽሞባቸዋል፡፡ “ፖሊሶች ከመጡ በኋላ ደብድበውናል፣ እና በአሁኑ ጊዜ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በእስር ቤት ይገኛሉ” በማለት የተቃዋሚው የሰማያዊ ፓርቲ ነባር አባል ጌትነት ባልቻ ገልጿል፡፡ ጌትነት በመቀጠልም “የፓርቲው ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከታሰሩት ውስጥ ይገኙበታል” በማለት ሀሳቡን አጠቃሏል፡፡
ሆኖም ግን ኢትዮጵያውያን/ት በሀዳር ወር መጎዳትና መጎሳቀል ለምን ይደንቀን? እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 ያለው የገዢ አስተዳደር ለመናገር በሚዘገንን መልኩ የጭካኔ ድርጊት በአትዮጵያኖች ላይ ፈፅሞአል:: በዚያው ዓመት የፓርላማውን ምርጫ ተከትሎ በግንቦት ወር በጠራራ ፀሐይ የተዘረፈውን የህዝብ ድምጽ በመቀወም ድምጻቸውን ባሰሙ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች እራሱ መለስ ዜናዊ ያቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን 193 ያልታጠቁ ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች በአዲስ አበባ መንገዶች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በመግለጻቸውና እና ሌሎች በከፍተኛ ደህንነት በእስር ቤት የሚገኙ እስረኞችን ሆን ተብሎ በጥይት ደብድበዋል፣ ሌሎች 763 የሚሆኑት በጽኑ ቆስለዋል፡፡
እ.ኤ.አ ከ2007 ጀምሮ በየጊዜው በህዳር ወር እ.ኤ.አ የ2005 ምርጫን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጨዋና ያልታጠቁ ሰልፈኞች ተኩስ በመክፈት ገደሏቸው፣ አካለ ጎደሎ አደረጓቸው፡፡ እኔም ያንን ጊዜ ለማስታወሰ ስል መጻፌን ቀጥየ ነበር፡፡
በመጀመሪያው የማሰታወስ ጽሁፌ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 እና በጁን 2005 የተከፈለው መስዕዋትነት ለዘላለም ይታወሳል! ለአንባቢ ዎቼም ሳስታዉስ በህይወት ላሉትና ለሞቱት ምስክርነት መስጠት እንዳለባችሁ የሞራል ግዴታ ተጥሎባችኋል ብዬ ነበር፡፡ ኤሊ ዌይሰል የዕልቂቱ ተራፊና የኖቬል ተሸላሚ በክብር እንዳስቀመጠው “ማስታዋስ አለብን ምክንያቱም የጋራ ትውስታችን የሆኑትን ያለፉ ድርጊቶች የወደፊቱን ትውልድ መብት መከልከል ስለማንችል ነው መርሳት መጥፎ ነገር ብቻ አይደለም ነገር ግን ስድብም ነው፡፡ የሞቱትን መርሳት ሁለተኛ ከመግደል እኩል ነው፡፡”
በ2005 ያለቁትን መርሳት ማለት በእነርሱ ላይ የተፈጸሙትን ግፎች መርሳት እንዲህም ያሉትን አረመኔአዊ ወንጀል መርሳትማለት ነው፡፡ እልቂቱን መርሳት ማለት ወንጀለኞች ተጠያቂ እንዳይሆኑ የልብ ልብ መስጠት ማለት ነው፣ ምክንያቱም ወንጀሎቹ ተረስተዋል፡፡ በመጨረሻም መርሳት ማለት በስልጣን ላይ ያሉ ወንጀለኞች እንደገና እና እንደገና የወንጀል ደረጃውን ከፍ በማድረግና ተጠያቂነት የሌለበትን ሁኔታ በመፍጠር ወንጀል እንዲሰሩ ማበረታታት ማለት ነው፡፡
አስታውሳለሁ! በምንም አይነት አልረሳምም፣ በፍጹም!!!
አስታውሳለሁ ምክንያቱም እኔ ካላስታወስኩ ማን ያስታዉሳል? አስታውሳለሁ ምክንያቱም የምረሳ ከሆነ ወንጀሎችና ወንጀለኞች ይረሳሉ፡፡ የምረሳ ከሆነ ታሪክ እንዴት ሊያስታውስ ይችላል? ታሪክ ሊያስታውስ የሚችለው ሌላ ሊያስታውስ የሚችል ሰው ሲኖር ነው:: በህዳር፣ በታህሳስ፣ በጥር፣ በየካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዝያ… ዛሬ ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ነገ ለሚወለዱ ህጻናት አስታውሳለሁ፡፡
የእኔን ስራ በማድነቅና ለበርካታ ዓመታት ሲደግፉ ሲቆዩ ሌሎች ደግሞ ሲተቹ ሲቃወሙ የሚኖሩ አሉ። እኔ በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ ነው ይሉኛል:: በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ መሆን ለኔ ታላቅ ክበር ነው::
የ2005 ዕልቂትን አስታውሳሁ፡፡ እያንዳንዱን በግፍ የተገደሉትን አስታዉሳለሁ፡፡ አስታውሳለሁ ወጣት ሴቶች ወደፊት እናት ላይሆኑ፣ ወጣት ወንዶችን የአራዊቱን ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም ወደፊት አባት ላይሆኑ፣ ወላጅ የሌላቸውን ወላጆቻቸው የተገደሉባቸውን አስታውሳለሁ፡፡ ልጆቻቸው የተገደሉባቸውን እናቶችንና አባቶችን አስታውሳለሁ::
ወንጀለኞችን አልረሳም፣ ተንኮል የሰሩትን 237ቱን የፖሊስ አባላት አስታውሳለሁ፣ የወንጀለኞችን ቁንጮና መሪ የነበረዉን አራዊትን አልረሳም:: የአራዊቱን ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም::
አስታውሳሁ፣ መቼ ረሳለሁ: ሁልጊዜ ህዳርን፣ ታህሳስን፣ ጥርን፣ የካቲትን፣ መጋቢትን፣ ሚያዝያን…. አልረሳም፡፡
ተ.ቁ |
ስም |
ጾታ |
እድሜ |
ስራ
|
መግለጫ |
1 |
ሬቡማ ኢርጋታ |
ወ |
34 |
ግንበኛ |
|
2 |
መለሳቸው አለምነው |
ወ |
16 |
ተማሪ |
|
3 |
ሀድራ ኦስማን |
ወ |
22 |
አይታወቅም
|
|
4 |
ጃፋር ኢብራሂመ |
ወ |
28 |
ቢዝነስ |
|
5 |
መኮንን |
ወ |
17 |
አይታወቅም |
|
6 |
ወልደሰማያት |
ወ |
17 |
||
7 |
ባህሩ ደምለው |
ወ |
አይታወቅም |
||
8 |
ፈቀደ ነጋሽ |
ወ |
25 |
መካኒክ |
|
9 |
አብርሀምይልማ |
ወ |
17 |
ታከሲ ነጂ |
|
10 |
ያሬድ እሸቴ |
ወ |
23 |
ቢዝነስ |
|
11 |
ከበደ ገ/ህይወት |
ወ |
17 |
ተማሪ |
|
12 |
ማቴዎስ ፍልፍሉ |
ወ |
14 |
ተማሪ |
|
13 |
ጌትንት ወዳጆ |
ወ |
48 |
ቢዝነስ |
|
14 |
ቃሰም ራሽድ |
ወ |
21 |
መካኒክ |
|
15 |
ሸውሞሊ |
ወ |
22 |
ቢዝነስ |
|
16 |
አሊየ ኢሳ |
ወ |
20 |
የቀን ስራ |
|
17 |
ሣምሶን ያዕቆብ |
ወ |
23 |
የህዝብ ማመላ |
|
18 |
አለባለው አበበ |
ወ |
18 |
ተማሪ |
|
19 |
በልዩ ዛ |
ወ |
18 |
ትራንስ. ረዳት |
|
20 |
ዩሱፍ ጀማል |
ወ |
23 |
ተማሪ |
|
21 |
አብርሃም አገኘሁ |
ወ |
23 |
ትራንስ.ረዳት |
|
22 |
መሀመድ በቃ |
ወ |
45 |
አርሶ አደር |
|
23 |
ረዴላ አወል |
ወ |
19 |
የታክሲ ረዳት |
|
24 |
ሀብታሙ ኡርጋ |
ወ |
30 |
ቢዝነስ |
|
25 |
ዳዊት ፀጋዬ |
ወ |
19 |
መካኒክ |
|
26 |
ገዛኸኝ ገረመው |
ወ |
15 |
ተማሪ |
|
27 |
ዮናስ አበራ |
ወ |
24 |
አይታወቅም |
|
28 |
ግርማ ወልዴ |
ወ |
38 |
ሾፌር |
|
29 |
ደስታ ብሩ |
ሴ |
37 |
ቢዝነስ |
|
30 |
ለገሰ ፈይሳ |
ወ |
60 |
ቢዝነስ |
|
31 |
ተስፋዬ ቡሽራ |
ወ |
19 |
ጫማ ጠጋኝ |
|
32 |
ቢንያም ደገፋ |
ወ |
18 |
ስራ አጥ |
|
33 |
ሚሊዮን ሮቢ |
ወ |
32 |
ትራንስ.ረዳት |
|
34 |
ደረጀ ደኔ |
ወ |
24 |
ተማሪ |
|
35 |
ነብዩ ሃይሌ |
ወ |
16 |
ተማሪ |
|
36 |
ምትኩ ምዋለንዳ |
ወ |
24 |
ዶመስቲክ ሰራተኛ |
|
37 |
አንዋር ሱሩር |
ወ |
22 |
ቢዝነስ |
|
38 |
ንጉሴ ዋብግነ |
ወ |
36 |
ዶመስቲክ ሰራተኛ |
|
39 |
ዙልፋ ሀሰን |
ወ |
50 |
የቤት እመቤት |
|
40 |
ዋስይሁን ከበደ |
ወ |
16 |
ተማሪ |
|
41 |
ኤርሚያስ ከበደ |
ወ |
20 |
ተማሪ |
|
42 |
00428 |
ወ |
25 |
አይታወቅም |
|
43 |
00429 |
26 |
አይታወቅም |
||
44 |
00430 |
30 |
አይታወቅም |
||
45 |
አዲሱ በላቸው |
ወ |
25 |
አይታወቅም |
|
46 |
ደመቀ አበበ |
ወ |
አይታወቅም |
||
47 |
00432 |
22 |
አይታወቅም |
||
48 |
00450 |
20 |
አይታወቅም |
||
49 |
13903 |
25 |
አይታወቅም |
||
50 |
00435 |
30 |
አይታወቅም |
||
51 |
13906 |
25 |
አይታወቅም |
||
52 |
ተማም ሙክታር |
ወ |
25 |
||
53 |
በየነ በዛ |
ወ |
25 |
አይታወቅም |
|
54 |
ወሰን አሰፋ |
ወ |
25 |
አይታወቅም |
|
55 |
አበበ አንተነህ |
ወ |
30 |
አይታወቅም |
|
56 |
ፈቃዱ ኃይሌ |
ወ |
25 |
አይታወቅም |
|
57 |
ኤሊያስ ጎልቴ |
ወ |
አይታወቅም |
||
58 |
ብርሃኑ ዋርካ |
ወ |
|||
59 |
አሸብር መኩሪያ |
ወ |
አይታወቅም |
||
60 |
ዳዊት ሰማ |
ወ |
አይታወቅም |
||
61 |
መርሀጽድቅ ሲራክ |
ወ |
አይታወቅም |
||
62 |
በለጠ ጋሻውጠና |
ወ |
አይታወቅም |
||
63 |
ብኃይሉ ተስፋዬ |
ወ |
20 |
አይታወቅም |
|
64 |
21760 |
18 |
አይታወቅም |
||
65 |
21523 |
25 |
አይታወቅም |
||
66 |
11657 |
24 |
አይታወቅም |
||
67 |
21520 |
21 |
አይታወቅም |
||
68 |
21781 |
60 |
አይታወቅም |
||
69 |
ጌታቸው አዘዘ |
ወ |
45 |
አይታወቅም |
|
70 |
21762 |
75 |
አይታወቅም |
||
71 |
11662 |
45 |
አይታወቅም |
||
72 |
21763 |
25 |
አይታወቅም |
||
73 |
13087 |
30 |
አይታወቅም |
||
74 |
21571 |
25 |
አይታወቅም |
||
75 |
21761 |
21 |
አይታወቅም |
||
76 |
21569 |
25 |
አይታወቅም |
||
77 |
13088 |
30 |
አይታወቅም |
||
78 |
እንዳልካቸው ገብርኤል |
ወ |
27 |
አይታወቅም |
|
79 |
ኃይለማርያም አምባዬ |
ወ |
20 |
አይታወቅም |
|
80 |
መብራቱ ዘውዱ |
ወ |
27 |
አይታወቅም |
|
81 |
ስንታየሁ በየነ |
ወ |
14 |
አይታወቅም |
|
82 |
ታምሩ ኃይለሚካኤል |
ወ |
አይታወቅም |
||
83 |
አድማሱ አበበ |
ወ |
45 |
አይታወቅም |
|
84 |
እቴነሽ ይማም |
ወ |
50 |
አይታወቅም |
|
85 |
ወርቄ አበበ |
ወ |
19 |
አይታወቅም |
|
86 |
ፈቃዱ ደግፌ |
ወ |
27 |
አይታወቅም |
|
87 |
ሸምሱ ካሊድ |
ወ |
25 |
አይታወቅም |
|
88 |
አብዱዋሂደ አህመዲን |
ወ |
30 |
አይታወቅም |
|
89 |
ታከለ ደበሌ |
ወ |
20 |
አይታወቅም |
|
90 |
ታደሰ ፌይሳ |
ወ |
38 |
አይታወቅም |
|
91 |
ሶሎሞን ተስፋዬ |
ወ |
25 |
አይታወቅም |
|
92 |
ቅጣው ወርቁ |
ወ |
25 |
አይታወቅም |
|
93 |
ደስታ ነጋሽ |
ወ |
30 |
አይታወቅም |
|
94 |
ይለፍ ነጋ |
ወ |
15 |
አይታወቅም |
|
95 |
ዮሀንስ ኃይሌ |
ወ |
20 |
አይታወቅም |
|
96 |
በኃይሉ ብርሀኑ |
ወ |
30 |
አይታወቅም |
|
97 |
ሙሉ ሶሬሳ |
ወ |
50 |
አይታወቅም |
|
98 |
የቤት እመቤት |
አይታወቅም |
|||
99 |
ቴዎድሮስ |
ወ |
23 |
አይታወቅም |
|
100 |
ጫማ ሰሪ |
ወ |
ጫማ ሰሪ |
||
101 |
በኃይሉ ብርሃኔ |
ወ |
30 |
አይታወቅም |
|
102 |
ሙሉ ሶሬሳ |
ወ |
50 |
የቤት እመቤት |
|
103 |
ቴዎድሮስ ኃይሌ |
ወ |
23 |
ጫማ ሻጭ |
|
104 |
ደጄኔ ይልማ |
ወ |
18 |
መጋዝን ጠባቂ |
|
105 |
ኡጋሁን ወልደገብርኤል |
ወ |
18 |
ተማሪ |
|
106 |
ደረጀ ማሞ |
ወ |
27 |
አናጺ |
|
107 |
ረጋሳ ፈይሳ |
ወ |
55 |
ላውንድሪ ሰራተኛ |
|
108 |
ቴዎድሮስ ገብረዎልድ |
ወ |
28 |
የግል ንግድ |
|
109 |
መኮንን ገ/እግዚአብሄር |
ወ |
20 |
መካኒክ |
|
110 |
ኤሊያስ ገ/ጊዮርጊስ |
ወ |
23 |
ተማሪ |
|
110 |
አብርሀም መኮንን |
ወ |
21 |
የቀን ሰራተኛ |
|
111 |
ጥሩወርቅ ገ/ጻድቅ |
ሴ |
41 |
የቤት እመቤት |
|
112 |
ሄኖክ መኮንን |
ወ |
28 |
አይታወቅም |
|
113 |
ጌቱ ምሀትተ |
ወ |
24 |
አይታወቅም |
|
114 |
ክብነሽ ታደሰ |
ሴ |
52 |
አይታወቅም |
|
115 |
መሳይ ስጦታው |
ወ |
29 |
የግል ንግድ |
|
116 |
ሙሉአለም ወይሳ |
ሴ |
15 |
አይታወቅም |
|
117 |
አያልሰው ማሞ |
ወ |
23 |
አይታወቅም |
|
118 |
ስንታየሁ መለሰ |
ወ |
24 |
የቀን ሰራተኛ |
|
119 |
ጸዳለ ቢራ |
ሴ |
50 |
የቤት እመቤት |
|
120 |
አባይነህ ሰራሴድ |
ወ |
35 |
ልብስ ሰፊ |
|
121 |
ፍቅረማርያም ተሊላ |
ወ |
18 |
ሾፌር |
|
122 |
አለማየሁ ገርባ |
ወ |
26 |
አይታወቅም |
|
124 |
ጆርጅ አበበ |
ወ |
36 |
የግል ትራንስፖርት |
|
125 |
ሀብታሙ ዘገየ |
ወ |
16 |
ተማሪ |
|
126 |
ምትኩ ገ/ስላሴ |
ወ |
24 |
ተማሪ |
|
127 |
ትዕዛዙ መኩሪያ |
ወ |
24 |
የግል ንግድ |
|
128 |
ፈቃዱ ዳልጌ |
ወ |
36 |
ልብስ ሰፊ |
|
129 |
ሸዋጋ ወ/ጊዮርጊስ |
ወ |
38 |
የቀን ሰራተኛ |
|
130 |
አለማየሁ ዘውዴ |
ወ |
32 |
የቴክስታይል ሰራተኛ |
|
131 |
ዘላለም ገ/ጻድቅ |
ወ |
31 |
የታክሲ ሾፌር |
|
132 |
መቆያ ታደሰ |
ሴ |
19 |
ተማሪ |
|
133 |
ሀይልየ ሁሴን |
ወ |
19 |
ተማሪ |
|
134 |
ፍስሀ ገ/ጻድቅ |
ሴ |
23 |
የፖሊስ ተቀጣሪ |
|
135 |
ወጋየሁ አርጋው |
ወ |
26 |
ስራ ፈላጊ |
|
136 |
መላኩ ከበደ |
ወ |
19 |
አይታወቅም |
|
137 |
አባይነህ ኦራ |
ወ |
25 |
ልብስ ሰፊ |
|
138 |
አበበች ሆለቱ |
ሴ |
50 |
የቤት እመቤት |
|
139 |
ደመቀ ጀንበሬ |
ወ |
30 |
አርሶ አደር |
|
140 |
ክንዴ ወረሱ |
ወ |
22 |
ስራ ፈላጊ 141 |
|
141 |
እንዳለ ገ/መድህን |
ወ |
23 |
የግል ንግድ |
|
142 |
አለማየሁ ወልዴ |
ወ |
24 |
መምህር |
|
143 |
ብስራት ደምሴ |
ወ |
24 |
መኪና አስመጭ |
|
144 |
መስፍን ጊዮርጊስ |
ወ |
23 |
የግል ንግድ |
|
145 |
ወሎ ዳሪ |
ወ |
18 |
የግል ንግድ |
|
146 |
በሀይሉ ገ/መድህን |
ወ |
20 |
የግል ንግድ |
|
147 |
ሲራጂ ኑሩ ሰይድ |
ወ |
18 |
ተማሪ |
|
148 |
እዮብ ገ/መድህን |
ወ |
25 |
ተማሪ |
|
149 |
ዳንኤል ሙሉጌታ |
ወ |
25 |
የቀን ሰራተኛ |
|
150 |
ቴዎድሮስ ደገፋ |
ወ |
25 |
የጫማ ፋብሪካ ሰራተኛ |
|
151 |
ጋሻው ሙሉጌታ |
ወ |
24 |
ተማሪ |
|
152 |
ከበደ ኦርቄ |
ወ |
22 |
ተማሪ |
|
153 |
ለሊሳ ፋጤሳ |
ወ |
21 |
ተማሪ |
|
154 |
ጃገማ ባሻ |
ወ |
20 |
ተማሪ |
|
155 |
ደበላ ጉታ |
ወ |
15 |
ተማሪ |
|
156 |
መላኩ ፈይሳ |
ወ |
16 |
ተማሪ |
|
157 |
እልፍነሽ ተክሌ |
ሰ |
45 |
አይታወቅም |
|
158 |
ሀሰን ዱላ |
ወ |
64 |
አይታወቅም |
|
159 |
ሁሴን ሀሰን ዱላ |
ወ |
25 |
አይታወቅም |
|
160 |
ደጀኔ ደምሴ |
ወ |
15 |
አይታወቅም |
|
161 |
ዘመድኩን አግደው |
ወ |
18 |
አይታወቅም |
|
162 |
ጌታቸው ተረፈ |
ወ |
16 |
አይታወቅም |
|
163 |
ደለለኝ አለሙ |
ወ |
20 |
አይታወቅም |
|
164 |
ዩሱፍ ኡመር |
ወ |
20 |
አይታወቅም |
|
165 |
መኩሪያ ተበጀ |
ወ |
22 |
አይታወቅም |
|
166 |
ባድሜ ተሻማሁ |
ወ |
20 |
አይታወቅም |
|
167 |
አምባው ጌታሁን |
ወ |
38 |
አይታወቅም |
|
168 |
ተሾመ ኪዳኔ |
ወ |
65 |
የጤና ባለሙያ |
|
169 |
ዮሴፍ ረጋሳ |
ወ |
አይታወቅም |
||
170 |
አብዩ ንጉሴ |
ወ |
አይታወቅም |
||
171 |
ታደለ በሀጋ |
ወ |
አይታወቅም |
||
172 |
ኤፍሬም ሻፊ |
ወ |
አይታወቅም |
||
173 |
አበበ ሀማ |
ወ |
አይታወቅም |
||
174 |
ገብሬ ሞላ |
ወ |
አይታወቅም |
||
175 |
ሰይዴ ኑረዲን |
ወ |
አይታወቅም |
||
176 |
እንየው ጸጋዬ |
ወ |
32 |
እረዳት ትራንስፖርት |
|
177 |
አብዱራህማን ፈረጅ |
ወ |
32 |
የእንጨት ስራ ባለሙያ |
|
178 |
አምባው ብጡል |
ወ |
60 |
የቆዳ ፋብሪካ ሰራተኛ |
|
179 |
አብዱልመናን ሁሴን |
ወ |
28 |
የግል ንግድ |
|
180 |
ጅግሳ ሰጠኝ |
ወ |
18 |
ተማሪ |
|
181 |
አሰፋ ነጋሳ |
ወ |
33 |
አናጺ |
|
182 |
ከተማ ኡንኮ |
ወ |
23 |
ልብስ ሰፊ |
|
183 |
ክብረት እልፍነህ |
ወ |
48 |
የጥበቃ ሰራተኛ |
|
184 |
እዮብ ዘመድኩን |
ወ |
24 |
የግል ንግድ |
|
185 |
ተስፋዬ መንገሻ |
ወ |
15 |
የግል ንግድ |
|
186 |
ካፒቴን ደበሳ ቶሎሳ |
ወ |
58 |
የግል ንግድ |
|
187 |
ትንሳኤ ዘገየ |
ወ |
14 |
ልብስ ሰፊ |
|
188 |
ኪዳና ሹክሩ |
ወ |
25 |
የቀን ሰራተኛ |
|
189 |
አንዷለም ሺበለው |
ወ |
16 |
ተማሪ |
|
190 |
አዲሱ ተስፋሁን |
ወ |
19 |
የግል ንግድ |
|
191 |
ካሳ በየነ |
ወ |
28 |
ልብስ ሽያጭ |
|
192 |
ይታገሱ ሲሳይ |
ወ |
22 |
አይታወቅም |
|
የጸጥታ ኃይሎች እርስ በእርስ ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ በጥይት የተገደሉ ሰዎች፣
|
|||||
193 |
ነጋ ገብሬ |
ወ |
|||
194 |
ጀበና ደሳለኝ |
ወ |
|||
195 |
ሙሊታ ኢርኮ |
ወ |
|||
196 |
የሃንስ ሶሎሞን |
ወ |
|||
197 | አሸናፊ ደሳለኝ |
ወ |
|||
198 |
ፈይሳ ገ/መንፈስ |
ወ |
|||
በመቶዎቹ የሚቆጠሩትን የግድያ ሰለባዎች፣ አካለ ጎደሎዎች፣ ቁስለኞች፣ በኃይል የተመቱትንና ሰውነታቸው በጥይት የተበሳሱትን ሁሉ አስታውሳለሁ፡፡ |
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2/2005 ከቃሊቲ እስር ቤት ለማምለጥ ሲሞክሩ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በጥይት ተደብድበው ያለቁ ሰዎች ስም ዝርዝር፣
ተ.ቁ |
ስም |
ጾታ |
የተከሰሱበት ጥፋት፣ |
1 |
ጠይብ ሸምሱ መሀመድ |
ወ |
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት |
2 |
ሳሊ ከበደ |
ወ |
ምንም ዓይነት ክስ አልተጠቀሰም |
3 |
ሰፊው እንድሪስ ታፈሰ |
ወ |
በአስገድዶ መድፈር |
4 |
ዘገዬ ተንኮሉ በላይ |
ወ |
በዝርፊያ ወንጀል |
5 |
ቢያድግልኝ ታመነ |
ወ |
የተወነጀሉበት ያልታወቀ |
6 |
ገብሬ መስፍን ዳኘ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
7 |
በቀለ አብርሃም ታዬ |
ወ |
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር |
8 |
ጉታ ሞላ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
9 |
ኩርፋ መልካ ተሊላ |
ወ |
በማስፈራራት ወንጀል |
10 |
በጋሻው ተረፈ ጉደታ |
ወ |
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ ወንጀል |
12 |
አብደልወሃብ አህመዲን |
ወ |
በዘርፊያ ወንጀል |
13 |
ተስፋዬ አብይ ሙሉጌታ |
ወ |
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት |
14 |
አዳነ ቢረዳ |
ወ |
በነፍስ ማጥፋት ወንጀል |
15 |
ይርዳው ከርሴማ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
16 |
ባልቻ አለሙ ረጋሳ |
ወ |
በዝርፊያ ወንጀል |
17 |
አቡሽ በለው ወዳጆ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
18 |
ዋለልኝ ታምሬ በላይ |
ወ |
በአስገድዶ መድፈር |
19 |
ቸርነት ኃይሌ ቶላ |
ወ |
በዝርፊያ ወንጀል |
20 |
ተማም ሸምሱ ጎሌ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
21 |
ገብየሁ በቀለ አለነ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
22 |
ዳንኤል ታዬ ለኩ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
23 |
መሀመድ ቱጂ ቀኔ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
24 |
አብዱ ነጂብ ኑር |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
25 |
የማታው ሰርቤሎ |
ወ |
በአስገድዶ መድፈር |
26 |
ፍቅሩ ናትናኤል ሰውነህ |
ወ |
በማስፈራራት ወንጀል |
27 |
ሙኒር ከሊል አደም |
ወ |
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር |
28 |
ኃይማኖት በድሉ ተሸመ |
ወ |
ጽንፈኝትን በማራመድ |
29 |
ተስፋዬ ክብሮም ተኬ |
ወ |
በዥርፊያ ወንጀል |
30 |
ወርቅነህ ተፈራ ሁንዴ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
31 |
ሲሳይ ምትኩ ሁነኛ |
ወ |
በማጭበርበር ወንጀል |
32 |
ሙሉነህ አይናለም ማሞ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
33 |
ታደሰ ሩፌ የኔነህ |
ወ |
በማስፈራራት ወንጀል |
34 |
አንተነህ በየቻ ቁበታ |
ወ |
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት |
35 |
ዘሪሁን መርሳ |
ወ |
በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ወንወጀል |
36 |
ወጋየሁ ዘሪሁን አስፋው |
ወ |
በዝርፊያ ወንጀል |
37 |
በከልካይ ታምሩ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
38 |
የራስወርቅ አንተነህ |
ወ |
በማጭበርበር ወንጀል |
39 |
ባዝዘው ብርሀኑ |
ወ |
ግብረሰዶም በመፈጸም ድርጊት |
40 |
ሶሎሞን እዮብ ጉታ |
ወ |
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል |
41 |
አሳዩ ምትኩ አራጌ |
ወ |
በማስፈራራት ወንወጀል |
42 |
ጋሜ ኃይሉ ዘገዬ |
ወ |
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር |
43 |
ማሩ እናውጋው ድንበሬ |
ወ |
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል |
44 |
እጂጉ ምናለ |
ወ |
በግድያ ሙከራ ወንጀል |
45 |
ኃይሉ ቦስኔ ሀቢብ |
ወ |
የተቀደሰን ቦታ በማራከስ |
46 |
ጥላሁን መሰረት |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
47 |
ንጉሴ በላይነህ |
ወ |
በዝርፊያ ወንጀል |
48 |
አሸናፊ አበባው |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
49 |
ፈለቀ ድንቄ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
50 |
ጀንበሬ ድንቅነህ ቢለው |
ወ |
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር |
51 |
ቶሎሳ ወርቁ ደበበ |
ወ |
የዝርፊያ ወንጀል |
52 |
መካሻ በላይነህ ታምሩ |
ወ |
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ |
53 |
ይፍሩ አደራው |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
54 |
ፋንታሁን ዳኘ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
55 |
ጥበቤ ዋቀኔ ቱፋ |
ወ |
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት |
56 |
ሶሎሞን ገብረአምላክ |
ወ |
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ |
57 |
ባንጃው ቹቹ ካሳሁን |
ወ |
በዝርፊያ ወንጀል |
58 |
ደመቀ አበጀ |
ወ |
በግድያ ሙከራ ወንጀል |
59 |
እንዳለ እውነቴ መንግስቴ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
60 |
አለማየሁ ጋርባ |
ወ |
እ.ኤ.አ በ2004 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመጽ ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር የዋሉ |
61 |
ሞርቆታ ኢዶሳ |
ወ |
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ |
ለምዘገባ፣ በዚህ እልቂት ላይ ተዋንያን የነበሩ 237 የተረጋገጠ የፖሊስ እና የደህንነት አባላት ዝርዝርን የያዘ ሰነድ ተቀምጧል፡፡
የኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ!
እ.ኤ.አ በ11/11/11 የኔሰው ገብሬ የተባለ የ29 ዓመት መምህር እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች በደቡብ ኢትዮጵያ በዳውሮ ዞን በተርጫ ከተማ ከህዝብ መሰብሰቢያ ዳራሽ ፊት ለፊት እሳት በመለኮስ እራሱን በእሳት አያይዟል፡፡ ለሶስት ቀናት ቆስሎ ከቆየ በኋላ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ እራሱን በእሳት ከማያያዙ በፊት የኔሰው ከህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውጭ ለተሰበሰበ ህዝብ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምቶ ነበር፣ “በእኩልነት ላይ ባልተመሰረተ አስተዳደር እና ፍትህ በሌለበት እንዲሁም የሰብአዊ መብት በማይከበርበት አገር ውስጥ እራሴን ለመስዋዕትነት አቀርባለሁ፣ ይህንንም በማድረጌ ወጣቱ ትውልድ ነጻ ይወጣል፡፡” የአትዮጵያ ጀግናዉ የእኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ…
“ገዳዮችን አስታውሳለሁ፣ የግድያ ሰለባዎችንም አስታውሳለሁ፣ ለትግሌ የሚያግዙ አንድ ሺ እና ከዚያ በላይ ያሉ አሳማኝ ምክንያቶች እና ተስፋ ቢኖረኝም፡፡ ባስታወስኩ ቁጥር ተስፋየ ይሟጠጣል፣ ያንን ድርጊት ባስታውስኩ ቁጥር ደግሞ ተስፋቢስነቴን የማስወገድ ኃላፊነት እንዳለብኝ እገነዘበላሁ፣ ተስፋ ከተስፋቢስነት በላይ ነው፡፡“ ይላል ኤሊ ዊሴል!
**ለጥቃቱ ሰለባዎች ተጨማሪ መረጃ ይሆን ዘንድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ያሬድ ኃ/ማርያም እ.ኤ.አ ሜይ 15/2006 “በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ ወንጀል በኢትዮጵያ፣ የጁንና ኖቬምበር 2005 የአዲስ አበባው ዕልቂት“ በሚል ርዕስ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላሜንት ለልማትና ውጭ ጉዳዮች እና ለሰብአዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ አስቸኳይ ጥምር ጉባኤ የቃረቡትን ምስክርነት ይመለከቷል፡፡
***የመርማሪ ኮሚሽኑ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ የጥቃቱ ሰለባዎችን ነጻ ሲያወጣ አጠቃላይ ኃላፊነቱን ግን በፖሊስና ታጣቂ ኃይሎች ላይ ደፍድፎታል፡፡ መርማሪ ኮሚሽኑ አስተያየቱን በመቀጠል እንደሚከተለው አጠቃሎታል፣ “በተቃዋሚዎቹ የተጎዳ ንብረት የለም፣ በመንግስት በሞኖፖል በተያዘው መገናኛ ብዙሀን እንደተለፈፈው ጥቂት ተቃዋሚዎች የእጅ ቦንቦችንና ጠመንጃዎችን ታጥቀዋል እንደሚለው ሳይሆን በተቃራኒው የእጅ ቦንብ እና ጠብመንጃ የታጠቀ አንድም የተቀዋሚ አባል የለም፣ በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች የተከፈተው ተኩስ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለመበተን ሳይሆን በተቃራኒው የሰልፈኞችን ጭንቅላትና ደረት ለመበርቀስ ዒላማ ያደረገ ነበር፡፡” የመርማሪ ኮሚሽኑ የ193 የእልቂቱ ሰለባዎችን ስም ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚያካትተው እ.ኤ.አ ከጁን 6 – 8 እና ከኖቬምበር 1- 4/2005 በዚህ ጊዜ ብቻ ያለውን ድርጊት እንዲያጣራ ለአጣሪ ኮሚሽኑ የተሰጠው ስልጣን ነበር፡፡ አጣሪ ኮሚሽኑ ግን በፓርላማው ከተሰጠው የጊዜ ገደብ ውጭ ከህግ ውጭ በመንግስት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን ስም ዝዝዝር ያገኘ ቢሆንም እነዚህ ግድያዎች ኮሚሽኑ እንዲያጣራ ተለይቶ ከተሰጠው ጊዜ ውጭ በመሆናቸ ለህዝብ ይፋ ሳያደርገው ቀርቷል፡፡
ኢትዮጵያ የአረብ ሠራተኛ አምራች ሃገር መሆኗ መቅረት አለበት
ከምኒልክ ሳልሳዊ
ኢትዮጵያውያን በመካከለኛው ምስራቅ በስፋት መሰደድ የጀመሩት ባለፈው 20 አመታት የወያኔው ጁንታ መንግስት ስልጣኑን ተቆጣጥሮ በህዝቦች ላይ በተለየ መልኩ የፈጠረውን አደገኛ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ መሆኑ እሙን ነው::ይህ ቀውስ የደረሰባቸው ወገኖቻችን ከተሰደዱባት ሃገር አንዷ ሳኡዲ አረቢያ ተጠቃሽ ናት::ሳኡዲ አረቢያ ከሃብቷ ብዛት የመጣ የስራ ፍቅር ባሌለው ወጣት ዜጋ የተሞላች እና ፔትሮ ዶላር ባሰከራቸው ቱጃሮች የምትተዳደር አገር መሆኗ እና የዜጎቿ የስራ አለመስራት የስራ እድሎችን ስላሰፋ የወያኔ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተጠቂዎች ወደዚሁ መሰደድን መርጠዋል:: ይህንን ተከትሎም ይህን ሰሞን የአለም ዋና አጀንዳ የሆነው የኢትዮጵያውያን በሳኡዲ አረቢያ እየደረሰባቸው ያለ ስቃይ ነው::
ሰቆቃው ያደረሰው የሰብኣዊ መብት ጥያቄ ከሳኡዲ መንግስት ላይ ይልቅ ወደ ወያኔው ጁንታ ላይ እንዲተኮር ያደረገ ሲሆን የወያኔው ጁንታ ለከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ተዳርጓል::በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው አስደንጋጭ እና ሰብኣዊነትን ያለፈ ድርጊት በመንግስት ባለስልጣናት መሃከል የፈጠረው መረበሽ እስከአለመግባባት አድርሷቸዋል::ይህንን የወያኔን አቋም የተመለከተችው ሳኡድ አረቢያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ የበላይነት ተቀናጅታለች::የወያኔ ተቃዋሚ በሆኑት እና በአገር ውስጥ በውጪ በሚኖሩት ድርጅቶች እንዲሁን በከፍተኛ ደረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ ባሉ ኢትዮጵያውያን እና እርትራውያን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ አትኩሮት አግኝቶ የአለም ጎዳናዎች ሳኡዲን እና ወያኔን በሚቃወሙ በሰላማዊ ሰልፍ እየተጥለቀለቁ ነው::
ከወያኔው መንግስት የሚንጸባረቁ አጀንዳዎች ለዘብተኛ አቋሞች በስህተት እንደተፈጠሩ ወቅታዊ ሁኔታኦች እያሳዩ ሲሆን ስርኣቱ አጣብቂኝ ውስጥ እና የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ እንደገባ ተረጋግጧል:: የሌላ ሃገር እምባሲዎች ዜጎቻቸውን በመጠበቅ ላይ ሲያተኩሩ የወያኔው ዲፕሎማቶች የዜጎች ንብረት የሆነውን ኤምባሲ በመዝጋት አገልግሎት አቁመዋል::
የደረሰውን ሰቆቃ ተከትሎ ስርኣቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመተባበር ለሉአላዊ የዜግነት ክብር መነሳሳት ሲኖርበት እና ህዝብን ማቀፍ ሲኖርበት ለብሄራዊ ውርደት ዜጎችን ዳርጓል::የፖለቲካ ፓርቲዎች የጠሩትን ሰልፍ በሃይል እና በደብዳቤ በትኗል::የወያኔው ስርኣት የህዝቡን ቁጣ ባለማንበቡ በችኮላ ያልበሰለ ሃሳብ በማራመዱ የፖለቲካ ኪሳራውን አስፍቶታል::ህገመንግስታዊ መብቶችን አለመከበሩን እና ለዜጎች አለመቆርቆርን በማሳየቱ በአለማቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል::ሚዲያዎች ከዜጎች የሳኡዲ ሰቆቃ ይልቅ የወያኔን ስርኣት ጋጥወጥነት አትኩሮት ሰተውታል::
ለዚህ ሁላ ችግር መንስኤው ስርኣቱ በልማት ሽፋን የሚከተለው የፖለቲካ እና እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ችግሮች እንደሆኑ አግጥጦ ገሃድ ከመውጣቱም በላይ የአደባባይ ሃቅ ሆኖ ለለውጥ እንትጋ የሚሉ ድምጾች በመላው ሃገሪቱ ተንጸባርቀዋል:; የወያኔ ስርኣት ህዝብን የሚያሳትፍ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ እስካልተከተለ ድረስ እና አሁን ባለው ሂደት ላይ ለውጥ እስካላደረገ ድረስ የስደት ችግሩ በስፋት እየቀጠል ይሄዳል:;ዛሬ ሳኡዲ ላይ የደረሰው ሰቆቃ ነገ በሌሎች ሃገራትም ይቀጥላል::ይህ ብሄራዊ ውርደት በታሪካችን አይተነው የማናውቅ ነው:;ኢትዮጵያውያን ከቀድሞው ጀምሮ በፖለቲካ ቢሰደዱም እንደዚህ አይነት ውርደትን አስተናግደው አያውቁም::የአሁኑ ውርደት ያለው ስርኣት ለዜጎቹ ደንታ ቢስ በመሆኑ የተወለደ ችግር ነው::በሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ተመዘገበ ከመባል ውጭ የተባለው እድገት ምንም አይነት ህዝባዊ ጠቀሜታ እንዳላሳየ በይፋ አስመስክሯል::የተማረው እና የሚሰራው ሃይል መሰደዱ ኢኮኖሚው እንደኮላሸ እንጂ እንዳደገ አያሳይም::የዚህ ሁላ መንስኤው ስርኣቱ የሚከተለው አፋኝ የፖለቲካ እና የእኮኖሚ ፖሊሲ ስለሆን ድጋሚ ሊከለስ እና ሊፈተሽ ይገባዋል::
የነቃ እና የተደራጀ አዲስ ፖሊሲ አስፈላጊ መሆኑ እሙን የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል::ስርኣቱ የሚከተለውን ፖሊሲ በአስቸኳይ ካልቀየረው የሚመጣው አደጋ ከፍተኛ ነው::በሃገሪቱ በልማት ስም እና በፖለቲካ ባላንጣነት በዜጎች ላይ የሚደርሰው ችግር የሙስና መንሰራፋት ሚዛናዊነት የጎደለው የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ የግሉን ሴክተር የማዳከም ውስጣዊ ሴራ ዘር ተኮር የሆነ ፖለቲካ እና አድሎኣዊ አሰራር የትምህርት ጥራት መውረድ እና የስራ አጡ ቁጥር እንዲስፋፋ የሚደረጉ ደባዎች ዜጎች ምንም አይነት ጥያቄ እንዳያነሱ የሚደረጉ የፖለቲካ ዱላዎች ለድህነት መፈጠር እና የስደት መስፋፋት ምክንያት ሆነዋል::የህዝብ ቁጥርን ተከትሎ የሚደረግ የእድገት ፖሊሲ አለመመጣተን የሃገሪቱ ዜጎች ተዘዋውረው እንዳይሰሩ የተደረገ የጎሳ ፖለቲካ የተማሩ ዜጎችን የስራ እድል አጥብቦታል::አለ ተብሎ የሚወራለት የኢኮኖሚ እድገት ጥቂት የስርኣቱን ካድሬዎች ተጠቃሚ ያደረገ በመሆኑ ማንኛውም ነገር በካድሬዎች ዙሪያ እና በፓርቲ ስራዎች ዙሪያ ያተኮረ በመሆኑ ዜጎች በሃገራቸው ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል::
ያለው ስርኣት ስርነቀል ለውጥ ለማምጣት ፖሊሲዎቹን እና የደረሱ የዜጎችን ችግር ከስሩ መሰረቱ መመርመር አለበት:: በፓርቲው አመራር ደረጃ ያሉ የስርኣቱ ባለስልጣናት ለስርነቀል ለውጥ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው::በግል የንግድ ተቋማት ላይ ስርኣቱ ያለው አቋም ከመጀመሪያ ለውጦች አንዱ ነው የግል የንግድ ተቋማት መዳከም ምክንያቱ የስርኣቱ መራሽ የንግድ ድርጅቶች እና አድሏዊነት የፈጠረው የኢኮኖሚ ችግር ሲሆን መፍትሄውም የተዳከመውን የግሉን የንግድ እንቅስቃሴ እንዲያንሰራራ ማድረግ እና ለዜጎች በርካታ የስራ እድሎች እንዲከፍት ማበረታታን አንዱ ሲሆን የተለየ የፖለቲካ አቋም ያለው ዲያስፖራው በሃገሩ ጉዳይ እንዲሳተፍ እድሎችን ማመቻቸት እንዲሁ ለፖሊሲ ለውጥ ጅማሮ ሊሆን ስለሚችል ስደትን በስፋት ለመቀነስ እና ዜጎች ከሃገራቸው እንዳይወጡ ለማድረግ ይችላል::
በአሁን ሰአት ስርኣቱ እየተተቀመበት ያለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባ ከመሆኑም ባሻገር ባልተማሩ እና ባልሰለጠኑ የፖለቲካ ታማኞች ስለሚተገበር በአግባቡ እየተተረጎመ ባለመሆኑ ውድቀትን አምጥቷል::የሃገሪቱ አጠቃላይ ሃብት እና የኢኮኖሚ ምሶሶ በጥቂት የፓርቲ ድርጅቶች እና ባለስልጣናት እጅ በቁጥጥር ስር ስለሆነ የግሉ ኢንቨስትመት በመዳከሙ እና ስርኣቱ ከዚህ አይነት የንግድ እንቅስቃሴ ካልወጣ በቀር ምንም አይነት ለውጥ መምጣት እንደማይቻል እሙን ሲሆን መፍትሄው የተቆጣጠረውን እና በግል መያዝ ያለባቸውን የንግድት ተቋማት እና የአገልግሎት ዘርፎች መልቀቅ ካልቻለ ችግሩ እየከፋ ዜጎችን ምንም ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ያደርጋል::በአለም አቀፍ ደረጃ እንደሚታየው መንግስታት ህግ የማውጣት እና የማስፈጸም አቅም እንጂ ከትልቅ እንስከተራ ንግድ ድረስ እጃቸውን አስገብተው ሲሰሩ አይታይም::ያለው ስርኣት ወደ ቸርቻሪ ነጋዴነት በመቀየሩ ለዜጎች የስራ እድሉን አጥብቦታል::
ኢኮኖሚውን ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች እና የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች በሞኖፖል ስለተቆጣጠሩት ዜጎች በስርኣቱ ፖለቲካ ካልተጠመቁ ድረስ ስራ የማግኘት እድል የላቸውም::ይህ ኢኮኖሚውን የመቆጣጠር የፖለቲካ ጭብርብሮሽ የኢንቨስትመት ሂደቱን ከማዳከሙም በላይ ዜጎች በሃገራቸው እና በስርኣቱ ላይ እምነት እንዲያጡ አድርጓል::ስርኣቱ ከነጋዴነት መውጣት ሰፊ የስራ እድሎች እንዲፈጠሩ እና ስደት እንዲቀንስ የሚረዳ ሲሆን ዜጎች በሃገራቸው ተሳፋ እንዳይቆርጡ ያደርጋል:: እንዲሁም የመንግስት የመገናኛ ቡዙሃን በሃሰት የተሞሉ መሆናቸው እና አስፈላጊውን መረጃ መስጠት አለመቻላቸው ሌላኛው የኢኮኖሚ ድቀት እና የስደት መንስኤ ናቸው:: በነጻነት የማይሰሩት እና ለፖለቲካው የእድሜ ማስረዘሚያ የሆኑት የመገናኛ ብዙሃን ቀረጥ የሚከፍላቸውን ህዝን እንዳያገለግሉ ከመደረጉም በላይ በሃሰት የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ወንጀሎችን በመፈብረክ የታወቁ ሆነዋል::
ሕዝቡ ስርኣቱ እስካልተመቸው ድረስ ስደትን ማቆም አይቻልም ጊዜአዊ እገዳውም ውጤታማ አይሆንም:: ሀገሪቱ ብዙ ሴቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሊሰደዱባት የቻለውም ከሴቶች እኩልነት ጋር በተያያዘም ችግር በመኖሩና ብዙ ስራ አለመሰራቱን የሚያሳይ ነው::በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶችም በነፃነት አለመቋቕውማቸው ሴቶችም እንደሰው አለመታየታቸው ነው::የፓርቲ ፖለቲካ መስበክ ሳይሆን በሴቶች እኩልነት እና ተሳትፎ ዙሪአ ኢኮኖሚው መዳበር ሲኖርበት አስፈላጊውን ኦረንቴሽንም መስጠን የስርኣቱ ግዴታ ነው::አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ስራ የሚገባውን ወጣት የሚሸከም ኢኮኖሚ አልተፈጠረ:: የግል ሴክተሩም በርካታ ዜጎች እንዳይፈጥር ሆኖ እየሞተ መሆኑን ከዓለም ባንክ ሪፖርቶች ማየት ይቻላል::በዓለም ደረጃ በመንግስት ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያ በዓለም ሦስተኛ ስትሆን፤ በግል ኢንቨስትመንት ከመጨረሻዎቹ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ነን። ስለዚህ የግል ሴክተሩ ካልተስፋፋና ካላደገ ስራ ሊፈጠር አይችልም። በየዓመቱ ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቀው ወጣት በዓመት ወደ መቶ ሺህ ሊጠጋ ነው። ይሄንን ኃይል መጦ የሚያስቀር የሚያደርግ ኢኮኖሚ መፈጠር የሚቻለው የግል ሴክተሩ ሲነቃቃ ነው። አሁን የግል ሴክተሩ በኮንስትሪክሽን ዘርፍ ላይ ውር ውር እያለ ነው። ይሄም ሴክተር ቢሆን፤ የቀን ሰራተኛ ከመሳብ ባለፈ ሙያተኛውን መቅጠር አልቻለም። ለዚያውም ትንሽ ሲሚንቶ መለሰን ሲጀምሩ ወደ መካከለኛው መስራቅ በተከበረ ወርሃዊ ደመወዝ ሲቀጠሩ ይታያል። ሀገሪቱ የተማረ የሰው ኃይል የላትም። ያሉዋትም ለባዕድ አገር እያገለገሉ ነው። በአንፃሩ የአገሪቱን የባቡር መንገድ እና ግድብ የሚሰሩት ቻይናና ሕንድ ናቸው። ስኳር ፋብሪካውንም የሚሰሩት ሕንዶች ናቸው። በሚያሳዝን መልኩ ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የተማሩም ሆነ ያልተማሩ ችሎታቸውን እየሸጡ ያሉት ለባዕድ ሀገር ነው። ከአፍሪካ እስከ ደቡብ ሱዳን፣ ቦትስዋና እና ደቡብ አፍሪካ ሳይቀር በርካታ ኢትዮጵያውያን ችሎታቸውን በጥሩ ዋጋ እየሸጡ ነው። ይሄን አሳዛኝ ታሪክ ለመቀየር የግል ሴክተሩ ማደግ ወሳኝ ነው ።
የግል ዘርፉ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ይረከብ ማለት ግድብ ይገንባ፣ የባቡር መንገድ ይዘርጋ ማለት አይደለም ነገር ግን የግል ዘርፉ ሊሰራቸው የሚችሉ ስራዎች ተለይተውና ተጠንተው መሰራት አለባቸው። የኅብረተሰብ ችግርም እየተበራከተ ስለሆነ ችግሩን መመርመር ያስፈልጋል ። የግል ዘርፉ ከካፌና ሆቴል ላይ ብቻ የሚሯሯጠው ለምንድነው? የቀጥታ የውጪ ኢንቨስትመንት ችግር በገፍ የማይመጣው ለምንድነው፣ አነስተኛና ጥቃቅን አደረጃጀት ምን ያህል ውጤት አምጥቷል? የተደራጀ ጠንካራ የግል ዘርፍ መፍጠር ነው ወይስ አነስተኛ ጥቃቅን ድርጅቶች የሚለው መታየት አለበት። የትኛው ነው ብዙ ኀሳብ የሚያመነጩት፣ የገበያ ሁኔታስ? ባንኮች አካባቢ ያለው ችግር ምንድነው? ለምን አያበድሩም ይሄ ሁሉ መፈተሽ አለበት ።ኢትዮጵያ የአረብ ሠራተኛ አምራች ሃገር መሆኗ መቅረት አለበት ።
ለሕዝቡ ግደ የለሹ የኢህአዲግ መንግስት መወገድ አለበት
November 21/2013
ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ
በሳውዲ የሚገኙ ዜጐቻችን የወገን እና የሀገርን እርዳታን በሚሹበት በአሁኑ ሰአት የወገን እና የሀገር ህልውና እየተረገጠበት ባለበት ሰአት የኢህአዲግ መንግሰት ግን ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ለህዝባቸን ምንም ያክል እርዳታን አለማድረጉ በብዙዎች ዘንድ በርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት አለ ወይ እያስባለ ነው የሚገኛው :: ይህም ብቻ አይደለም በሳውዲ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን በማሰማት ላይ በሚገኙበት በአሁኑ ሰአት ሰአት በሀገር ቤት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ግን በገዛ ሀገራቸው በዜጐቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለመቃወም አልታደሉም :: በርግጥም እራሱን ትዝብት ላይ የሚጥለውን ተግባር በመፈጸም ድምጻቸውን ለማሰማት የወጡትን ዜጐች በመደብደብ በመግረፍ እና በማሰር ከሳውዲ አረቢያ መንግሥት ጐን በመቆም ዋና ተባባሪ መሆኑን አስመስክሯል አልፏል:: ይህ ሁሉ ሲሆን በራሱ በወያኔ ደገፊዎች ሳይቀር የወያኔ መንግስት እየተወገዘ እና እየተብጠለጠለ ይገኛል ምክንያቱም ነገሩ የፖለቲካ ነገር ጥያቄውም የፖለቲካ ጥያቄ እንዳልሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚገባ ጠነቅቆ ያውቀዋል እና:: በሳውድ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል በጣም ያላስቋጨው እና ያላንገበገበው ኢትዮጵያዊ የለም አንድ የወያኔ የኢህአዲግ መንግስት እንደሆነች በሚገባ የማውቃት ከሀገር ውጭ የምትኖሩር በዜጓቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ የሳዘናት እና የመንግስት ግድ የለሽነት ያናደዳት ወጣት አትንኩብኝ እያለች በፊስ ቡክገጽ ሳይቀር ስትክበው የነበረችውን መንግስት በመቃውም በፊስ ቡከ ገጾ ላይ እንዲህ አለች የኢትዮጵያ መንግስት ሆድ እንጅ ጭንቅላት የለውም :: እውነቷን ነው ይህች ወጣት እህታችን ለሆድ ሳይሆን በሚገባ ህዝቡን ለመመራት እና ለማስተዳደር የተቀመጠ መንግስት ቢሆን ኖሮ በሳውዲ በዜጐቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ ግድ ብሎት የወገን አጋርነቱን ያሳይ ነበር ይህንን ግን የወያኔ መንግስት ሊያደርገው አልቻለም::ስለዚህም ለዜጕቹ ግድ የሌለው መንግስት ለህዝብ ጥቅም የቍመ መንግስት ስለሆነ መወገድ አለበት ::አምላክ በስቃይ ውስጥ ያሉትን ወገኖች ይጠብቃቸው
የሳዑዲ ጉዳይ፡ ወደ ተግባር
ከአንተነህ መርዕድ እምሩ
ኖቬምበር 20 ቀን 2013
ኢትዮጵያውያን እንደ አሁኑ ተገፍተን ገደል ጠርዝ የቆምንበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። እስከ አሁን ትንንሽ መሸሻ ስለነበረን ፍርሃታችንን እንኳን ከሰው ከራሳችንም ደብቀን ስናፈገፍግ ኖረናል። ፈሪነታችንን ባባቶቻችን ጀግንነት፣ ውርደታችንን ባባቶቻችን ኩራት እያለበስነው መጓዝ የማያዛልቅ ለመሆኑ ከሰሞኑ የበለጠ ምስክር ምን አለና።
ያጋጠመን ብሄራዊ ውርደት ከፊሎቻችንን ከእንቅልፋችን ገና ሲያባንነን ብዙዎቻችንን አጥንታችን ድረስ ገብቶ ተሰምቶናል። አባቶቻችን “ሞት ሲዘገይ የቀረ ይመስላል” እንዳሉት ባንዳንዶች ላይ የደረሰው ውድቀት እኛን ስላልነካን የሚቀር መስሎን ነበር። በገዥዎቻችን በየለቱ በምትወረወረዋ ከፋፋይ የቤት ስራ ተጠምደን ግዙፉ ህልውናችን አዳጋ ላይ መሆኑን እንኳ ማየት ተስኖን ነበር።
የአገርን አንድነት የሚያስጠብቅ እድሜ ልኩን ቀበሮ ጉድጓድ የኖረ ሰራዊት ሲበተን፣ የጥርሱ ወርቅ በመዶሻ ሲወልቅ፣ መሳርያውን አስረክቦ ቤተሰቡ ዘንድ መድረሻ ትራንስፖርት ሲለምን ምን አድረረግን?
በአገሪቷ አንጡራ ሃብት የተማሩ ምሁራን ከብቸኛው ዩኒበርስቲ አርባዎቹ ሲመነጠሩ፤
አማራው እንደዋና ጠላት ተቆጥሮ ገደል ሲጣል፣ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የጮሁት ፕሮፌሰር አስራት እስር ቤት ሲበሰብሱ፣ ብሎም በግፍ እንዲሞቱ ሲደረግ፤
ኦሮሞው የተለያየ ስም እየተሰጠው ሲገደል፣ እስር ቤቱን ሲያጣብብ፤
አኝዋኩ ከገዛ መሬቱ ተነቅሎ ለሳውዲና ለህንድ ሃብታሞች እንዲለቅ ለማድረግ እንዳውሬ ሲታደን፤
መምህሩ ስርዓተ ትምህርቱ እንዲሻሻልና መብቱን በመጠየቁ ማህበሩ ሲበተን መሪዎቹ ሲታሰሩና አሰፋ ማሩ በጠራራ ፀሃይ ሲገደል፤
ነጋዴው ከሙያው ተፈናቅሎ በወያኔ ኩባንያዎች በሞኖፖል ሲታፈን፤
ህዝቡ በነጻ የመረጣቸው ወኪሎቹ ሲታሰሩና የምርጫ ኮሮጆ ሲገለበጥ፤
በሰላም ተቃውመው የወጡት የአጋዚ ኢላማ ሲሆኑ፤
ጋዜጠኞች እውነትን በመዘገባቸው ሲገደሉ፣ ሲታሰሩ፣ ሲታገዱና ሲሰደዱ፤
የኦርቶዶክስ አማኞች ሆኑ ገዳማት ሲደፈሩ ፤
ሁለት ዓመት ሊሞላው ያለ የእስልምና ተከታዮች እንቅስቃሴ ሲቀጠቀጥ፤
ተቃዋሚዎች መሪዎችቸው ባሸባሪነት ክስ ወህኒ ወርደው ሲማቅቁና ያሉትም ከእስር ባልተናነሰ እንዲኖሩ ሲገደዱ፤
የት ነበርን?? ይህ ሁሉ ሲፈጸም የት ነበርን?? እያልን መጠየቁ ጅል የሚያስመስል ቢሆንም፤ ምን ያህል እንደተኛንና ለዚህ ሁሉ ውድቀት ከአገሪቱ ጠላቶች ያላነሰ ስህተት መፈጽማችንን ያስገነዝበናልና። ዛሬ በእህቶቻችን ጩኸት ምክንያት እንባ ባረጠበው ዐይናችን ትናንትን አሻግረን ማየት ግድ ይለናል። የጠላቱን ምንነት ብቻ የሚያውቅና የራሱን ድክመትና ጥንካሬ ያልተገነዘበ ለድል አይበቃምና።
ይህ ሁሉ ተራ በተራ በስልት ሲፈጸም አንድ ሆነን መነሳት አቅቶን ዛሬ ጽዋው ሞልቶ መፍሰስ ሲጀምር የነቃን ይመስላል።
ዛሬም መንቃታችን አልዘገየም። ንቃታችን በቅጡ ሊያዝ ግን ይገባዋል። የብሄራዊ ውድቀታችን ጥልቀቱ ጎልቶ የወጣው በሳውዲ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ግፍና ይባስ ብሎ የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት ያሳየው እብሪተኝነት ነው። ወያኔ ባስቀመጠልን ትንንሽነት ተወስነን ስንባላና ስንነታረክ ብዙ ወርቅማ ጊዜ አሳልፈናል። የሚቆጨው ግን ካሁን በኋላ የምናሳልፈው ከንቱ ጊዜ ካለ ነው።
በሳውዲ አሸዋ ላይ የፈሰሰው የወገኖቻችን ደም የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ የሶማሌ፣ የክርስቲያን፣ የእስላም፣ የኦነግ፣ የግንቦት ሰባት፣ የኢህአፓ ወዘተ..ብለን የምንለየው አይደለም። ሬሳቸው የተጎተተው፣ የተደፈሩት፣ የታጎሩት ከውሻ ያነሱ ሆነው የታዩት በኢትዮጵያዊነታቸው ነው። ዛሬ በሲቃ “አድኑን” እያሉ የሚጮሁት ወገኖቻችን “ኢትዮጵያውያን ድረሱልን” እያሉ ነው። “የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ መንግስት የለንም” ብለዋል በድምጻቸው።
ለሳውዲዎች ስጋና ፍራፍሬ፣ አበባና ማዕድናት፣ ገረድና እቁባት የሚሆኑ ህጻናት እየመለመሉ በማቅረብ በሃብት የደለቡ የወያኔ ባለስልጣናት ይደርሱልናል የሚል ብዥታ የላቸውም። ህገወጦች ላይ እርምጃ የመውሰድ መብት አላቸው የሚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ወንድም እህቶቻችን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ይቁም ያሉ የሰማያዊ ፓርቲ ሰዎችን ለምን ሳውዲዎችን አወገዛችሁ ብሎ የሚቀጠቅጥ መንግስት የኛ ነው ብለው አይቀበሉትም።
አድኑን ብለው የጠየቁት እኛን ነው።
ማዳን ያለብን ዛሬ ባደባባይ የሚጮሁትን ወገኖቻችንን ብቻ አይደለም። ማዳን ያለብን አገራችንንና እራሳችንን ካለንበት ውርደት ነው።
መታገል ያለብን ለዚህ ያበቃንን ስርዓት ብቻ ሳይሆን፣ ይህንን ጨቋኝ ስርዓት በጸጋ ለመሸከም ያበቃንን ድክመታችንንም ነው። ያ ደግሞ ያንድ ሰሞን ሰላማዊ ሰልፍና ግርግር የሚመልሰው አይደለም። ደጋግሞ ከሚያጠቃን ስሜታዊነት መላቀቁ የትግሉ ቅድመ ሁኔታ መሆን አለበት።
ወያኔዎች የለመዱንና አሁንም ተስፋ የሚያደርጉት ያንድ ሰሞን ጫጫታችን እንደጉም ተኖ ወደነበርንብት የየግል ቁዘውማ እንድንገባና እነሱ ባቀዱልን ክፍፍል ስንፋጅ የዘረፋና ዘረኛ አገዛዛቸውን በሰፊው ለበቀጠል ነው። አቦ ፀሃይ የሞቀውን እውነት በመደጋገም ላሰለቻችሁ አልፈልግም። “ወሬ ቢበዛ በአህያ አይጫንም” ተብሏልና ምን እናድርግ ወደሚለው እንሻገር።
በዚች አገር ለውጥ ለማምጣትና ካለንበት ብሄራዊ ውድቀት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመውጣት የተወሰነ ቡድን፣ ድርጅት ሆነ ግለሰብ ሃላፊነት አይደለም። ሁላችንም የራሳችንን ሃቅምና ችሎታ እየመረመርን በየት ብሰለፍ የበለጠ አስተዋጾ አደርጋለሁ የሚለውን ካወቅን በኋላ የማንንም ጎትጓችነት ሳንጠብቅ መንቀሳቀስ ነው። ሁሉም ለዚች አገር ማድረግ የሚችለው ትንሽ ነገር አለው። ያም ትንሽ ነገር ሲጠራቀም ነው ትልቅ ብሄራዊ ሃቅም የሚሆነው። እስቲ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንጀምር።
ምሁራን፡ አገሪቷ በሌላት አቅም አስተምራን በአገር ውስጥና በዓለም ተበትነን እንገኛለን። ለዚይች ድሃና ኋላ ቀር ለምንላት አገር ምን ያህል እንደሰራንላት ራሳችንን እንጠይቅ። እስካሁን ለውጥ ለማምጣት እየተማገዱ ያሉትንና ከባዱን መስዋዕት የከፈሉትን ዋጋቸውን ሳንረሳ ሌሎቻችን አንድም ምን ማድረግ እንደምንችል ባለመገንዘብ ሌላም በመማራችን ያገኘነው መልካም እድል እንዳይደናቀፍና እንዳይጓደል እያየን እንዳላየን ተኝተን ቆይተናል። ምኝታው ይብቃን። የያዝነው ሳይጓደል ጭምር ብዙ አስተዋጾ ማድረግ ስለሚቻለን ከልብ የበኩላችንን እናድርግ። በዩኒቨርስቲ ምኩራቦች፣ በትላልቅ ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ድርጅቶች፣ በልዩ ልዩ ዘርፍ ተደላድለን ሌሎችን በሽሙጥ ብንወርፍ ወይም እንደሰጎኗ ራሳችንን ብንቀብር ምን ጥቅም አለው። ቢያንስ ቢያንስ ምናችሁም ሳይነካ ህዝቡን በማሳወቅ ለመስራት እንዳሁን የተመቸ የቴክኖሎጂ ጊዜ የለም። ያወቀ ህዝብ ሃያል ይሆናል። በዚህ ዙርያ ተሳትፎውን ቀድማችሁ የጀመራችሁም ለማን እንደምትጽፉ አስተውሉ። ለአሜሪካኖች፣ ለፈረንሳዮች አይደለም ለኢትዮጵያውያን መሆን አለበት። በቀላል ኢትዮጵያዊ ቋንቋ ጻፉ ካልሆነም ስራችሁ ተተርጉሞ እንዲደርሰው አድርጉ። ለተማረውና የነገር መላላጫ ሲያወጣ ለሚውለው ክፍል ከሆነ ስራችሁ ኢላማውን ስቷል።
ፖለቲከኞች፡ ጊዜአችሁንና ሃቅማችሁን የራሳችሁን ዓላማ በማስረዳትና ደጋፊ በማጠናከር እንጂ ሌላውን ጥላሸት በመቀባት አትዋትቱ። እስካሁን ጠንክሮ ያለመውጣታችሁ ትልቁ ችግር የወያኔ ዱላ ወይንም የህዝቡ ቸልተኝነት ብቻ አይደለም። የዓላማ ጥራትና ጽናት ጉድለት ነው። ዓላማችሁ ጠርቶ ከታወቀ፣ በዚያም ጸንታችሁ የምትታገሉ ከሆነ ከምትፈልጉት በላይ ኃይል ይከተላችኋል። እንደሰርገኛ ላንድ ሰሞን ግርግርና ሞቅ ሞቅ አድርጓችሁ የሚሸሸው ከናንተ የሚያገኘውን ስላጣ ነው። አርቲፊሻል አበባ ላይ ማር አገኛለሁ ብሎ የሚሰፍር ንብ የለም። በቀለምና በጊዜያዊ መአዛ ሳይሆን በይዘታችሁ ማር የሚቆረጥባችሁ ሆናችሁ እስካልተገኛችሁ ድረስ መጠውለግ የራሳችሁ ውጤት ነው።
ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፡ እስካሁን በየቦታው የሚደረገውን ሰባዊ መብት ጥሰት በማጋለጥ የተጫወታችሁት ሚና ቀላል ባይሆንም ከመሰል ግርጅቶችና ግለሰቦች ስራችሁን በማቀናጀት ሚዛናዊ የሆነውን ሪፖርት ለህዝቡና ለሚመለከተው ክፍል ሁሉ በማቅረን ትጉ። መረጃዎችም የሚሰባሰቡበት የዳታ ማዕከል ፍጠሩ። ተመራማሪዎች፣ የታሪክ ሰዎች፣ ፍርድ ሰጪ አካላት፣ አጠቃላይ ህዝቡ በቀላሉ የሚያገኛቸው ይሁኑ።
የሃይማኖት አባቶች፡ የሃይማኖት መሰረታዊ ተልዕኮ ለፍትህ መቆም ነው። ፍትህን የማይሰብክና ለፍትህ የማይቆም እምነት ፈጣሪ ከሰጠው ተልዕኮ ውጭ ነው። ፖለቲካን አይደለም ፍትህን ስበኩ። በደልን ማንም ይፈጽመውማን ማውገዝ አለባችሁ። ከዚያ የዘለለ ከናንተ አይጠበቅም። የታላላቅ ሃይማኖቶች ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ ፍትህ ሳይኖራት ሃይማኖቷ ምን ፋይዳ ይኖረዋል።
ጋዜጠኞች፡ ሃሳብን በነፃነት መግለጽ ባልተለመደባት አገራችን ባለፉት ጥቂት ዓመታት የህዝብ ድምጽ ለመሆን የታገሉት በርካታ ቢሆኑም፣ ብዙዎቹ በእስር ቢማቅቁም፣ ከፊሎቹ ቢሰደዱም ትግሉ አልሞተም። መስዋዕቱ የከፋ ቢሆንም አሁን ካለንበት በበለጠ እንድንታገል እንጂ እንድንዘናጋ የሚያደርግ ሁኔታ ስለሌለ ትግላችን በእጥፍ እንዲጎለብት እንነሳ። በተለያየ መንገድ ትክክለኛ መረጃ ለህዝቡ እንዲደርስ መሻትና መታገል የጊዜው አብይ ጥያቄ ነው። የዘመኑ ቴክኖሎጂ በፈቀደልን ሁሉ መንገድ መጠቀምና ሃቅምን አስተባብሮ መስራት ውጤቱ ትልቅ መሆኑን አይተናልና እንቀጥልበት።
ዲያስፖራ፡ ይህንን ክፍል ለይቼ ያነሳሁን ያለምክንያት አይደለም። ለትግሉ ወሳኝነት ባይኖረውም ተጽዕኖው ከባድ ስለሆነ ነው። በግድም በውድም አገሩል ለቆ የሄደው ኢትዮጵያዊ ቁጥር ቀላል አይደለም። የማይገኝበት የዓለም ክፍልም የለም። የኤኮኖሚ ሃቅሙና ዕውቀቱ ደግሞ በሚገባ ከተያዘ አገሪቱን ካለችበት የድህነት አዘቅት ከሚያወጧት ሰፊ ሃብቶች ትልቁ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ነው። እስከ አሁን የገንዘብ አቅሙን ወያኔ ለድሜው ማራዘምያ በስልት ተጠቅሞበታል። ይህ ሊያበቃ ይገባል። ዲያስፖራ በነጻነት ከወያኔ ተፅዕኖ ውጭ ስለሚኖር ምንም ጉዳት ሳያገኘው ህዝቡን ለነፃነት የሚያበቃ ትግል ውስጥ መሳተፍ ይችላል። በድህነት የሚማቅቁ ቤተሰቦችን መቶና ሁለት መቶ ዶላር በየጊዜ በመወርወር ከችግር ማላቀቅ አይቻልም። ስርዓቱን በመለወጥ በነፃነት ሰርተው የሚኖሩባት አገር መፍጠሩ ዘላቂነት አለው። ሳይዘገይ ፈጥኖ መድረሻው አሁን ነው።
ሌላው ኢትዮጵያዊ፡ ቀሪው ኢትዮጵያዊ ዳር ቆሞ ከሌሎች ተአምር ከመጠበቅ ራሱን ባመነበት አቅጣጫ አሰልፎ መንቀሳቀስ ያስፈልገዋል። ከላይ የተጠቀሱትን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሰባዊመብት ተሟጋች ተቋማት፣ የሃይማኖት ድርጅቶች፣ ማስሚድያዎች፣ የሲቢክ ተቋማት እንዲጠናከሩ አባል ሆኖ እውቀት፣ ጉልበትና ገንዘብን ማበርከት የመከራውን ጊዜ ያሳጥራል። በሳውዲና በሌሎችም የአረብ አገሮች የሞቱና የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያን ድምፅ ገንፍለን እንድንወጣ ያደረገን ሁሉ ተመልሰን ወደወትሮው ምሽጋችን አንግባ። ተጋድሎአችን በተግባር ነፃነት እስኪገኝ መቀጠል አለበት። ጽዋው ሞልቶ ፈስሷል። ብሄራዊ ወርደታችን ገደል ጫፍ አድርሶናል። ከዚህ በላይ መገፋት የሚያመጣው ውጤት ማንነታችንን ማጣት ነው የሚሆነው።
ሰልፉ፣ ጩኸቱ፣ ለቅሶው ይቁም ባይባልም ተጨባጭ ወደሆነ ተግባር ይቀየር።
ኢትዮጵያ ወደ እውነተኛ ክብሯ ትመለስ!
ዜጎቿ ከብሄራዊ ውርደት ይዳኑ!
በደልን የመታገል እንጂ የመሸከም ጽናት አይኑረን!
ፍቅርና መተባበር በሁሉም ኢትዮጵያዊ ይስፈን!!
ጸሃፊውን በ amerid2000@gmail.com ማግኘት ይችላሉ
አበበ በለው በኢትዮጵያ ኢምባሲ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ያደረገው ንግግር (Video)
[የሳዑዲ ጉዳይ] ይሄ ነው ወገኔ
ከጃ ዘ-ኢትዮጵያ
ይሄ ነው ወንድሜ ይሄ ነው ወገኔ
በመከራ ግዜ ያልሸሸው ከጎኔ
ከንፈር ሳይሆን ትከሻውን ያበደረ
ፊቱን ያላዞረ እጅን የሰደረ
እግሩ እግሬን ሆኖ ክፉ ቀኔን ያሻገረ
እሱ ነው ወገኔ ይሄነው መከታ
ምንም ቀን ቢጨልም ከጎኔ ያልሸሸ የማታ የማታ
ሀበሻ ምቀኛ ሀበሻ ክፉ ነው እያልኩኝ ስናገር
እንደኖህም መርከብ እንደሙሴ በትር
እግሩን ላጣ ወገን እግሩን በማበደር
በስደት በረሀ ወገን የሚያሻግር
ይሄ ነው ሀበሻ እውነት የሰውልጅ ዘር
በችግር ጉዳት ቆሞ ያልገለፈጠ
አይቶ እንዳላየ ዞሮ ያልፈረጠጠ
ይሄ ነው ወገኔ እርዳታውን ስሻ በኔ ያልተለወጠ።
ቅድሚያ ወያኔን ነው!! በ አንተነህ ሽፈራው
ቅድሚያ ወያኔን ነው!!
ደላላው ወያኔ ለዐረብ አሸሻጩ፣
ገጠር ድረስ ሄዶ ትዳር እያፋቱ – እርስ በርስ እያጋጩ፣
አዲስ ጎጆ አፍርሶ “ሀ” ብሎ ከንጭጩ::
በቀቢጠ ተስፋ ልብን አንጠልጥሎ፣
የራበውን አንጀት በመና ደልሎ፣
ለዐረብ ዳረጋቸው ጉቦ ተቀብሎ::
በዐረብ ሰላጤ ብሎም በቀይ-ባሕር፣
በሲና በረሃ በጭካኔ ምድር፣
የገጠር ሙሽራ ሴት ወንድ አልቀረ፣
ተማሪው ምሩቁ የተመራመረ፣
ያልፍልኛል ብሎ ስንቱ ወጦ የቀረ::
ዐረብ ግፍ አይፈራ ስብዕና የለው – - – ጭራሽ አረመኔ፣
ስንቱን ከፎቅ ጥለው ገሎ በጭካኔ፣
ስንቱን እህል ነፍገው ገደሉ በጠኔ፣
እግዜር ይክተታቸው ከሲዖል ኩነኔ::
ተልዕኮው ቀላል ነው ብዙም ሚስጢር የለው፣
ይህም ዘዴ ሆኖ ያው እንደልማዱ ትውልድ/ዘር ማጥፋቱ ነው፣
ለዚህ እርኩስ ስራው ጥማድ በሬ አይበቃው – - – ተመኑ ብዙ ነው፣
ከዚህም ለመላኪያ ከዚያም ለአባይ ግድብ የሚሞጨልፈው፣
ወገኔ ተረዳ መንታ መንገዱን ተው፣
የዐረብ ጠላትነት (በሶማሌ ወጉን) ከጥንትም ያለ ነው፣
ከአገር ነቅሎ መጣል የባንዳን ጥርቅም ቅድሚያ ወያኔን ነው (2)!!
አንተነህ ሽፈራው/23 Nov 2013
መታሰቢያነቷ በዐረብ አገር በግፍ ለተገደሉ፣
ክብራቸው በተለያዩ መንገዶች ለተደፈሩና
አሁንም ለሚንገላቱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ
ትሁንልኝ!!
እስቲ የነበርነው እንፃፍ፡- የኢሕአፓ ረጅም ትግል –ከኢያሱ ዓለማየሁ
የኢሕአፓ የ41 ዓመት መራራና ረጅም ትግል ረጅም ትዕግስትን ጠይቋል። አያሌ ፈተናዎችን ተቋቁሞና አልፎ ዛሬም ሕልውናውን ጠብቆ በትግሉ ሜዳ ላይ መገኘቱ በቅድሚያ የአባላቱ – ታሪክን ገርተውና ጽፈዋት ያለፏትም ሆነ በሕይወት ያሉትን ጽናትና ቆርጥነት – የሚመለከት ነው፦
ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
// ]]>
“የአሲምባ ፍቅር” ደራሲ፡ ካሕሳይ አብርሃ
ደራሲ፡ ካሕሳይ አብርሃ
በቅርብ ጊዜ “የአሲምባ ፍቅር” በሚል ርዕስ ባጠቃላይ የዛን ትውልድ ገድል፣ በተለይ ግን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊትን (ኢሕአሠ) ታሪክ በጊዜው በነበረ ተሳታፊ እይታ የተፃፈ እውነተኛ ታሪክ ምንባብ በመጽሐፍ መልክ ለገበያ ወጥቷል። ደራሲ ካሕሳይ አብርሃ፣ በሜዳ ስሙ አማኑኤል፣ ጊዜውን ከልጆቹና ከባለቤቱ ተቀራምቶ ይህን መጽሐፍ ስላቀረበልን በቅድሚያ ላመሰግነው እፈልጋለሁ።
።“የአሲምባ ፍቅር”
ሲያልቅ አያምር …..አለና
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በነሐሴ 27 ቀን 1967 ዓ.ም. እራሱን ለሕዝብ ይፋ ያደረገበትን የልደት በዓለ በትሊንትናው ዕለት በዲሲ ተከብሮለታል ….ሲያልቅ አያምር …..አለና…
// ]]>
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ምን እያሉን ነው?
ከዳዊት ሰለሞን
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም‹‹የኢትዮጵያ መንግስት በሳውዲ መንግስት ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ ገለጹ››
አሪፍ ሀሳብ ይመስላል፡፡ግን ምንድን ነው ተመጣጣኝ እርምጃ?እወስዳለሁ የሚሉንን እርምጃ ተመጣጣኝነት የሚለኩት በደረሰብን ውርደት ከሆነ ሳውዲዎች የሚከፍሉት ዋጋ ከዚሁ ጋር የሚስተካከል መሆን ይኖርበታል፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ግን መንግስት በሳውዲ ኢትዮጵያዊያኑ ስለደረሰባቸው ወይም እየደረሰባቸው ስለሚገኘው ሰቆቃ እንኳን ትክክለኛ መረጃ የለውም፡፡የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሶስት ብቻ ነው በማለትም ቴድሮስ ለሚዲያ ሰዎች ተናግረዋል፡፡ለዚህ ምስቅልቅል መፈጠር የቀድሞው የጤና ባለሞያ ጣታቸውን በደላሎችና በኤጀንሲዎች ላይ መቀሰራቸውም ለጉዳዮ የቀረበ ምልከታ እንደሌላቸው አስረጂ ነው፡፡
አስቂኙ ነገር ቴድሮስ ስለሚወስዱት ተመጣጣኝ እርምጃ ተጠይቀው ‹‹ወደፊት ምን እንደሚሆን እናጠናለን›› ብለዋል፡፡እስኪ በዚህ ጉዳይ ኢህአዴጎች/በማህበረሰብ ገጾች ደጋፊነታቸውን ያወጁ/ ሁሉ ምላሻቸውን ይስጡን፡፡
በሳውዲ ወገኖቻችን ኢህአዴግ፣ተቃዋሚ፣ትግሬ፣አማራ፣ኦሮሞ፣ክርስቲያን ሙስሊም ሳይባሉ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል፡፡አሁን ቴዲ ተመጣጣኝ እርምጃ እወስዳለሁ ሲሉ በሳውዲ ዜጎች ላይ ምን መዓት ሊያወርዱ ይሆን ?
እንበልና ከሳውዲ ጋር መንግስት ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነት አቋረጠ፡፡ይህ እንዴት ተመጣጣኝ እርምጃ ሊሆን ይችላል፡፡ግኑኝነቱ በመቋረጡስ ተጎጂ የሚሆነው ማን ነው?
ሳውዲ ስታር የተባለው በሼህ አላሙዲን ስር የሚገኝ ኩባንያ ቤልጂየምን የሚያክል መሬት በአንድ የሲጋራ ፓኮ መግዣ ዋጋ ተከራይቶ ከሳውዲ መንግስት በሚደረግለት የገንዘብ ድጋፍ ሩዝ እያመረተ ለሳውዲ ይልካል፡፡ይህንን መንግስት አቋርጣለሁ ቢልም የሚጎዱት ሼሁ ብቻ ናቸው ፡፡ሳውዲዎቹ ሌላ መሬት ፍለጋ ገንዘባቸውን ይዘው እብስ ይላሉ፡፡እናስ ቴድሮስ ምን አይነት ተመጣጣኝ እርምጃ ሊወስዱ ይሆን?
የ1997ዓ.ም ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው ሁከት ከ200 ሰው በላይ መገደሉ አይዘነጋም፡፡አጣሪ ኮሚሽኑ ለፓርላማው ባቀረበው ሪፖርት ወታደሮች በተሰላፊዎቹ ላይ ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ መውሰዱን ተናግሮ ነበር፡፡ወዳጄ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ወታደሩ ምን ተረደገ?ምንም፡፡ቴድሮስ ተመጣጣኝ እርምጃ እንወስዳለን ብለው የሳውዲን ኢምባሲ ቢዘጉ ምን እንላቸዋለን?ምንም፡፡
ሞት፣ ወያኔና “እኛ”–ከፊሊጶስ
ሞት፣ ወያኔና ‘’እኛ’’
የግፍ ጽዋው ሞልቶ፣ ……
ሞልቶ፣….. ሞልቶ ፈሶ
ሰው መባል በሰው፣ ስዕብናችን አሶ
ከ’ጥናፍ- እስከ-አጥናፍ፣ ደማችን “’ረክሶ’’፤
ውቅያኖስ፣ ባህሩን፣ ወንዙን አደፍርሶ
እዩት ይ’ጣለላል፣ አስፋልቱን አልብሶ።
ግን እኮ፣ …….. እንኳ’ ደም
ውኃ ፈሶ፣ አይቀርም
ይዘገያል እንጂ፣ በሰፈሩት ቁና፣ መሰፈር አይቀርም::
” ዓለም የም’ጠፋው፣ ሰይጣናዊ ምግባር በሚፈጽሙ ሳይሆን፤ ምንም ሳያደርጉ ቀጭ ብለው በሚመለከቷቸው ሰዎች ነው።” /አልበርት አነስታየን/
እናም የምድርን የሰቆቃና የሞት አይነት ሁሉ እያስከፈሉን፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን እያጠፉ ያሉት፣ ወያኔ/ሻአቢያ፣ ሳውዲ አረቢያ/ አረቦች፣ ምእራቡ ዓለም፣ ወይም ሌላ ሳይሆን፣ እኛ እራሳችን ቁጭ ብለን የምንመለከተው ወይም ለታይታ የምንታይው፣ ኢትዮጵያዊያኖች ነን። እኛ ነን….. በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ላይ ተቀምጠን፤ ለወገኖቻችን መሆን ያልቻልነው። እኛ ነን….. ለጠባብ መንደርተኞች ሀገራችን አሳልፈን የሰጠን። ትላ’ትናም ይሁን ዛሬ እውነቱ ይኸው ነው። ይኸን እውነታ ተቀብለን፣ በተለይም በዚች ወቅት ለህልውናችን ስንል የሚጠይቀውን መሰዋእትነት እስከ አልከፈልን ድረስ፣ ስቃይና ሰቆቃ፤ እንደትላ’ቱና እንደዛሬው ሁሉ፣ ነገም ተባብሶ ይደገማል። አሁን በያዝነው ከቀጠልን፤ ትውልድ ‘እየመከነ’፣ እኛም ‘ርስ-በርስ ስንጠላለፍ፣ የሚያለፍው ወያኔ፣ የማታልፈውን ኢትዮጵያን ”ለህልፈት” ያበቃታል። ይህ እንዲሆን ደግሞ እንዴት እንፈቅዳለን? ቅደመ-ህዝበ ኢትዮጵያዊያን አልዳረጉትም። እኛም አናደርገውም!
ለመሆኑ ከዚህ የበለጠ አሰቃቂና ዘግናኝ ሞት የበለጠ ምን ይሆን የም’ጠብቀው? ወይስ ገዥውቻችንም ከዚህ የባሰ በገዛ ሀገራችን ስለሚፈጽሙብን? ወይስ የሚሞቱትና የምድርን ፍዳ የሚከፍሉት ስደተኞች ስለሆኑ? የሞቱትስ ምን አንጅት ቢቆርጥና እንደግር እሳት ቢያንገበግብ፤ ወደ ‘ማይቀሩበት ሄዱ። እኛ ግን ቀሪዎቹ፣ ሀገራችን በወያኔ መዳፍ ወስጥ እስከ አለች ድረስ ወርቅ ብንጫመት፣ እንቁ ብንላበስ፣ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ብንገነባና ሜዳ ሙሉ የእምነበረድ ቤት ሰርተን ብንኖር በየደቂቃው፣ በየሰአቱና በየቀኑ እንሞታለን! እንቀበራለን!
ከሀገር ቤት ጀምሮ እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ በ’ስር ቤት የሚማቅቁት፣ የአቅመ-ደካሞች እምባ፣ የወላጆች ዋይታ፣ በየአውራ ጎዳናው ያሉት ምንዱባኖች፣ በየአስፍልቱ የሚፈሰው ደም፣ በጉዴፈቻ ስም የተሸጡት የህጻናት ለቅሶ፣ በየባህሩና በየውቅያኖሱ የዓሳ ነባሪ ቀለብ የሆኑትና የሚሆኑት ወገኖቻችን፣ በየበርሀው አሸዋ ለብሶ የቀረው አጽማቸው፣ እትብቱ ሳይቆረጥ፣ ጣሊያን ጠረፍ ላይ የተገኘው የህጻን ልጅ ሬሳ፣ ይጮሀል! ይጣራል! “ማራ ናታ!” ይላል:: ይህ ጩህትና ጥሪ ደግሞ እየበላን ያስርበናል፣ እየጠጣን ያስጠማናል፣ እየለበስን ያሳርዘናል፣ እየትኛን ያቃዥናል፣ ሳንሞት ይገለናል። ከዚህ የከፋ ደግሞ ለሰው ልጅ ምንም ነገር የለም። ‘ርግጥ ነው፤
ኑሮማ ይኖራል ኑሮ ከትባለ
ኅሊና ተሽጦ ለስጋ እየዋለ።
ለወያኔ አሳልፈን የሰጠነውን መብታችንና ነጻነታችንን፤ በዚህም ሳቢያ የሚደርስብንን ድህነት፣ እስራት፣ ውርደትና ንቀት በመሸሽ ፤ በባእድ ሀገር እናገኘዋለን ማለት የህልም እንጀራ ነው። ሁሉንም የሰቆቅቅ እይነት አልፈን፣ ከሞት ብ’ተርፍና ቁሳዊው ነገር ቢሳካ እንኳ’፣ የመንፈስ ድህነቱና የህሊና ህመሙ እሰከ መቅብራችን ይከተለናል። ታዲያ እጅግ የሚያሳዝነውና የሚዘገንነው ግፉና ሞቱ የሚደርስባቸው ፣ታግሎ የሚያታግላቸው ያጡና ከሀዲወችና ስግብግቦች በስማቸው የሚነግዱባቸው፣ የዚህ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸው ነው። ትውልድ የማጥፋቱም አንደኛው ዘዴም ይኸው ነው።
በዚች ሰዓት እንኳ’ አረቦችና ሌሎቹም በሀገራችን ምድር ደርታቸውን ነፈተው ሲራመዱና በመኪናቸው ገፍተውን ሲያልፍ፤ በፍርሀት አንገታችን ደፍተን ወይም እየትልጎመጎምን እንጂ የምናልፈው፤ ቀና ብለንም አናያቸውም። ‘የጥቂቶች” በሆነችው፣ ነገር ግን እትብታችን በተቀበረባት ምድራችን ”ባ’ዳነት” ይሰማናል።
ሀገሬ ላይ ሁኘ፣ እጅግ አ’ርጎ ከፋኝ፣ ሀገሬ ናፈቀኝ
በሰው ሀገር ሁኘም፣ እጅግ አ’ርጎ ከፋኝ፣ ሀገሬ ናፈቀኝ
እሬ በይ ሀገሬ! እሬ በይ ኢትዮጵያ! ሀገሬን ንገሪኝ።
ወያኔም ሆኑ የሌሎቹ፣ የሌት-ተቀን ምግባራቸውና ምኞታቸው፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ከምድረ ገጽ ጠፍተው ማየት ነው። ይህ ደግሞ በተለይም ወያኔ/ሻአቢያ ገና ሲፈጠሩ ጀምሮ፣ በተግባርም አሳይተውናል። አረቦች አይደሉምን ከምዕራቡ ዓለም ጋር በመተባበር ፤ ወያኔ/ሻአቢያዎችን ”ጡጦ እያጠቡ” ከዚህ ያደረሷቸው ? ወይስ መጽሐፍ እንደሚለው፤
” ….. አይናችን እያየ፣ አናስታውልም፤ ጆሮ’ችን እየሰማ፣ እናዳምጥም?………”
ወይስ “….. ህሊናችን በጋለ ብረት እንደተተኮሰ ሆኖ ደንዝዞ?…….’’ ወይስ
ፍርሀት? ማን ነበር “ፈራን ለማለት እንኳ ፈራን” ያለው::
በተለመደው ‘ቱልቱላቸው’ ”በሳአውዲ አረቢያ የሚገኙ ሕገ-ወጥ ስደተኞች ….” እኮ ነው ያሉን። እነሱ በኢትዮጵያ ምድር ”ሕጋዊ” ሆነው፣ ከርታታ ወገኖቻችንን ግን ” ሕገ-ወጥ ስደተኞች…” እያሉ በሚፈሰው ደማቸው ተሳለቁ፤ በሚዘምበው እ’ምባቸው ላይ ገለፈጡ ። ግን እነሱ ምን ያደርጉ? እኛ እንጂ! እነሱማ ትግላቸውን ታግለው፣ አላማቸውን እየተገበሩ ነው።
ለመሆኑ በየትኛው መመዘኛና ሀገራዊ ፍቅራቸው ነው፣ ለኢትዮጵያዊያን እንዲቆሙና እንዲቆረቆሩ የምንጠይቃቸው? የኢትዮጵያ መንግስት ነን ስላሉ? ታዲያ ማን ብለው ኢትዮጵያን ያፍርሱ? ማን ብለው ኢትዮጵያዊያንን እንደ አውሬ ያሳድኑ፣ ያድኑ? ማን ብለው ኢትዮጵያዊያንን ያዋርዱ?…
- የኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አይደለም እንዴ፣ ከኤርትራ ወገኖቻችን የለያዩን?
- የኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አይደለም እንዴ፣ ያለ ወደብ ያስቀሩን?
- የኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አይደለም እንዴ፣ ሱዳንን ለምነው ሀገራችን ቆርሰው ያስረከቡልን?
- የኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አይደለም እንዴ፣ በመቶ ሺ የሚቆጠረውን ወገናችን በባድሜ ስም ይስረሸኑልን?
- ኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አይደለም እንዴ፣ ወገኖቻችንን ከገደል የወረወሩልን?
- የኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አይደለም እንዴ፣ እኛ ቁራሽ መሬት የጎጆ መቀለሻና ጥማድ በሬ የምናውልበት ነፍገው፣ ለአረቡና እግር ላደረሰው ሁሉ የማእድን ሀብታችንን ሳይቀር የሚቸበችቡት?
- የኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አይደለም እንዴ፣ የሚገሉን፣ የሚያስገድሉን?
- የኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አይደለም እንዴ፣ እነሱ የሚዘርፉን አልበቃቸው ብሎ፣ እኛ ጠኔ እየጣለንና እያተሳደዱን፣ ለጥላቶቻችን አሳልፈው የሚሰጡንና ያሚያዘርፉን?
- የኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አይደለም እንዴ፣ በእስር ቤት ኢትዮጵያዊያንን የሚያማቅቁትና የሚገርፉት?
- የኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አይደለም እንዴ፣ በቋንቋና በሀይምኖት ከፋፍለው፣ስ’ብናችን ገፈው የሚጫወቱብን?
- የኢትዮጵያ መንግስት ነን እያሉ አይደለም እንዴ፣ በጣሊያን ሀገር የግራዚያን ሀውልት መሰራቱን ለመቃወም የወጡትን ያሰሩ? አሁንስ የሳአውዲን ግፍ ለመቃወም የወጡትን ምን እያደረጉ ነው? እነዚህን ሰላምዊ ሰልፎች እንኳ’ ቢፈቅዱ፤ ከሞኞቹ ላይ የለመዱትን ቦለቲካ ይቸረችርላቸው ነበር። ነገር ግን ባንዳነታቸውና ቅጥረኛነታቸው ስለማይፈቅድላቸውና ምንነታቸው ስለሆነ አላደረጉትም።
- ኧረ ስንቱ…….ኧረ ለመሆኑ ያለተነገር እንጅ ያልሆነው ነገር አለን?
ግን የትላ’ትናውንም ሆነ የየቀኑን ግፋቸውንና የሀገር ክህደታቸውን እየረሳን፣ አሁንም እንደ ሞት ሁሉ እነ’ሱም አዲስ ይሆኑብናል። ግን ለምን? ወይስ ከታሪክና ከትላንቱ ያለመማርና የመርሳት አባዜ?
ሞት ሁሌም አዲስ ይመስለናል ወይም ይሆንብናል፤ ይህ ‘ራሱን የቻለ ለሰው ልጅ ያለተፈታ ምስጢርና እንቆቅልሽ ነው። ይሁን እንጂ እንዲህ ተቀኝተውለታል፤
“እግዚ’ር በአንድ ነገር፣ አይጠረጠርም
የከፋው ሰው ሞቶ፣ ደስ ያለው አይቀርም” / የህዝብ /
ሌላው ቢቀር ወያኔ ግን ምስጢር ፣ አዲስና እንደ ሞት እንቆቅልሽ ሊሆንብን ፈጽሞ ባልተገባ ነበር:: አንድ ትውልድ ሙሉ የማንነቱንና የእኩይ ምግባሩን መከር እየሰበሰብን ነውና ያለነው።
ጥረታችን፣ ድካማችን፣ ጌዚያችን፣ ተግባራችንና ሁለንተናችን፤ ህዝቦችን ከውድቀት አትርፎ፤ ኢትዮጵያ የዜጎች ሀገር ማድረግ መሆኑ ቀርቶ፤ እኛ ግን እንደ ሞት ሁሉ የወያኔን ምግባሩንና ማንነቱን ትላንትናም ሆነ ዛሬ እንደ አዲስ እናወራለታለ፣ እናስወራለታለን፣ እናራግብለታለን፣ እንገረምለታለን፣ እናስገርምለታለን። እነሱ እንደሚሉን ”ውሻወቹ ይንጫጫሉ፤ ግመሎቹ ግን……… ትውልድንና ሀገርን የማጥፋቱን አላማችን እንተገብራለን፤ የ’ናንተም ስቃይና ሞት ከሀገር አልፎ በዓለምና በየደርሳችሁበት ሁሉ ይሆናል።”አንድ አዛውንት፤ ” ‘ርሀቡንና ንቀታቸውን ችለነው ነበር፤ እነ’ሱ ግን ጥጋቡን አልችለው አሉ።” የሚል ፈስቡክ ላይ አይቻለሁ። ግን እነ’ሱ እንዲያስርቡናን እንዲንቁን ማን ፈቀደላቸው?
መሞቱ የማይቀረው ወያኔ፣ እስከዚች ሰዓት ድረስ በሆድ – አደር ሎሌዎቹና በሀገሪቱ ጥላቶች እታገዘ፤ አላማውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይፈጽማል፣ ያስፈጽማል። ወያኔ ትላንት ሆነ ዛሬ፤
ወያኔ + ወያኔ – ወያኔ x ወያኔ ÷ ወያኔ = ወያኔ ነው።
ወያኔ ይህን አደረገብን፣ ለምን ይህን አደረገ ፣ ሀገር ሸጠ፣ ለዜጎቹ አይቆረቆርም፣ ትውልድን አጠፋ፣ ወዘተ እያልን ዓመታት ሙሉ ማላዘናችንና በጠላቶቻችን በር ድጅ መጥናቱ፣ የበለጠ ለግዥወቻችን የልብ- ልብ በመስጠት፣”ከእሳት ወደ ‘ረመጡ፣ ቁስሉ ወደ ማይሽር ውርደት ከተትን እንጂ ያስገኘው ተጨባጭ ውጤት የለም። አስገኘም ከተባለ አንድ እስረኛ አስፈትቶ፣ አምስት ማሳሰር ነው::
ከዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን፤ የግዥዎቻችንን ማንነትና እሥስታዊነት ማጋለጥና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በሰላማዊ ሰልፍም ተቃውሞው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህ ግን የትግሉ አንድ መቶኛ እንደ ማለት ነው። ስለዚህም ያለትቋረጠ ህዝባዊ አመጽና እምቢተኝነት የግድ ይላል። ተደጋግሞ እንደተነገረው ይህ ደግሞ ሊሆንና ሊፈጸም የሚገባው ከባህር ማዶ በሚበራ ሻማ ወይም በሚውለበለብ ሰንደቅ ዓላማ ሳይሆን በሀገር ቤት ወስጥ ብቻ ነው።
በተለይም በአሁኑ ሰዓት፣ ወያኔ ገፊ ኀይል አ’ቶ እንጂ፤ ‘ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ እየተሸራተተ ነው። ተቃዋሚ ነን ባዮች በዚህ የመከራችን ዘመን ወደ ተባበረ ኃይል መምጣት የማያስችላችሁ ነገር ካለ ወያኔያዊነት ወይም ሆድ-አደር ሎሌነት ወጭ ሌላ ምክንያት ሊኖር አይችልም። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በተለመደው ምርጥ ብዕሩ ባለፈው ሳምንት፤ ”አደባብዩ ምን ያህል ይርቃል?” በሚል ርዕስ አንድ ጦማር አስነብቦናል። እኔ ግን እላለሁ፤
አደባብዩ ምንም ያህል አይርቅም፤ ለ’ኛማ እንዲያውም እጅግ በጣም ቅርብ ነው። አደባብዩ ያለው ልባችን ውስጥ ነውና! እናም የአደባብይ ሰው ያድርገን!
—————//————
ፊልጶስ / 2006
አስተያየት ለመስጠት ለምትፈልጉ: philiposmw@gmail.com
[የሳዑዲው ጉዳይ] ተዋርደን አንቀርም –ከኢንጂነር ይልቃል ጌትነት
ከኢንጂነር ይልቃል ጌትነት
ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡
ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡
አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው“ብለዋል፡፡መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡
ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡በቃለ-መጠይቁ ሰላማው ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን?ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?
ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ሽማግሌወችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ከፖለቲካ ልዩነትም፣ከአምባገነንነትም በላይ ሰወቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሸለ ልገልጸው አልችልም፡፡
አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋነው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡
ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡
ለምሳሌ ኢቲቪ ስጉዳዩ ሲያወራ ህገ ውጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው?ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡
ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው?ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል? እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ኢምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣የድፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣አፈነን፡፡በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡
ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::
እንዴት!በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ሳውዲወችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡በዚህ ክፉ ጊዜ ስለስብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡
መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡
እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ጩኸቱ ግን ይቀጥላል……ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡
አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡
ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡
ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ቸልታንም አስበለጡ፡፡በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡
(ይህ ጽሁፍ በፋክት መጽሄት ተስተናግዷል፣ነገር ግን መጽሄቱ ላልደረሳቸው ሰዎች ይደርስ ዘንድ እዚህ ለማስተናገድ ወደድኩ፡፡)