Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

በሽብርተኝነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!

$
0
0

ከቅዱስ ዬሃንስ

ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ሁለት ጥቅም ያስገኝላቸዋል፡፡ አንደኛ በፀረ- ሽብርተኝነት ስም ከምዕራባውያን ኃያላን ጎን በአጋርነት በመቆማቸው በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት (ለምሳሌ በመሣሪያ፣ በፖለቲካ ድጋፍ) ዳጎስ ያለ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ ሁለተኛ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም የሚያወጡት ሕግ የውስጥ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቃት የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ሽፋን ይሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ነው ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ከሰማይ የወረደ የተቀናቃኝ ማጥቂያ መሣሪያ ነው የሚባለው፡፡ ይህንን ያልኩበት አብይ ጉዳይ ዛሬ ሃገራችንንና ህዝቧን እያስጨነቀ ያለው የወያኔ አገዛዝ የፀረ ሽብርተኝነት ህግን ከለላ በማድረግ በሰላማዊ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣ፤ እጅግ የከፋ ደረጃ በመድረሱ ነው።

በሰላማዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ የመንግስት ለዉጥ ለማምጣት የሚታገሉ ሰላማዊ ዜጎችን አግባብ ባልሆነና ባልተጨበጠ ክስና ዉንጀላ ማሰር፣ አፍኖ መሰወር፣ ንብረትን ማዉደምና መዉረስ እንዲሁም የአደባባይ ግድያ ባለፉት 22 የወያኔ የአገዛዝ ዘመናት የተለመዱ ተግባሮች ሆነዉ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ ይህ አምባገነናዊና ኢፍትሀዊ ተግባር በህግ ሽፋን ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለገዥዉ ስርአት የአፈናና የጥርነፋ መዋቅር ተባባሪ ያልሆኑና ለመብታቸዉ መከበር የሚታገሉ ዜጎች በአሸባሪነት ስም በጅምላ እየታፈሱና እየታሰሩ ይገኛሉ። ታፍነዉ የተወሰዱና ያሉበት ቦታ የማይታወቀዉም ጥቂቶች አይደሉም። ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሽብርተኝነት ተወንጅለዉ ታስረዋል። ሰብአዊ መብታቸዉም በማንአለብኝነት እየተረገጠ ይገኛል። ከነዚህ ንፁሀን ዜጎች ዉስጥ ብዙዎቹ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላቶች፤ የእምነት መሪዎችና ለሞያቸዉ ታማኝ የሆኑ ጋዜጠኞች መሆናቸዉን ስናይ ደግሞ ዘመቻዉ በሀገራችን ተጠናክሮ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል ለመጨፍለቅና ህዝብን ከትክክለኛ መረጃ አርቆና አፍኖ ለመግዛት ታስቦበትና ሆነ ተብሎ የተያዘ ስልት መሆኑን ግልፅ ነው።
Addis abab Demo
በሽብርትኝነት ያለመከሰስ መብቱን በጠመንጃ ያስከበረው ወያኔ ግን ሰላማዊውን ህዝቡ በተለያዩ መንገዶች እያሸበረ የስልጣን ቆይታውን ለማርዘም ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ዜጐችን በማፈናቀል፤ በእምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባትና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በመከፋፈል እያፋጀ የሽብር ሴራውን እየፈፀመ ይገኛል። ሰላማዊ ዜጋውን ፣አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን በልማት ስም ተወልዶ ባደገበት እትብቱ ከተቀበረበት ሃገር እያፈናቀለ ለስደት እየዳረገው ይገኛል፡፡ ለዚህም የሽብር ሴራው ሰለባ የሆኑት፤ የሚበሉት፤ የሚጠጡት እና በመጠለያ እጦት በየአደባባዩ ሰፍረው የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ የሚገኙት የአማራ ብሔረሰብ ወገኖቻችን ናቸው፤ እነዚህ ወገኖቻችን በሃገሪቱ አራቱም ማዕዘናት እየተፈናቀሉና እየተዋከቡ ይገኛሉ። ማፈናቀለ አልበቃ ያለው የወያኔ የሽብር መረብ ወደ እምነት ቦታዎችም በመዛመት ዋልድባን እና የተለያዩ የሃይማኖት ቦታዎችን በማፈራረስ በአለም ደረጃ እውቅና እና አድናቆት የተሰጣቸውን የሃገሪቱን የሃይማኖት፤ የታሪክ ቅርሶች በማውደም፤ ኢትዮጵያውያን በቀደምትነት በምንታወቅበት እምነታችን ላይ አደጋ በመፍጠር፤ አዋራጅ ድርጊቶችን በንቀት እና በጥላቻ እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ ከእምነት ቦታዎች ባሻገር በአለም ደረጃ እውቅናን ካገኙት ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ ተጠቃሹ የታችኛው አዋሽ እና ኦሞ ሸለቆዎች አንዱ ነው፡፡ ይህ ታሪካዊ ቦታ ያራዊቶች እና የተለያዩ የደኖች ስብስብ ያለበት ሰፊ የሃገራችን ቅርስ የነበረው ሲሆን ዛሬ ላይ ግን ወያኔዎች በልማት ስም ለውጭ ባለሃብቶች አስረክበውት ድብዛው እየጠፋ ነው፡፡ አምባገነኑ ወያኔ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ያነሱትን የመብት ጥያቄ ወደ ጎን በመተው በእኔ አውቅላችኋለሁ እብሪት የተሞላ አስተሳሰብ በማፈን ንፁሃኑን ሙስሊም እየገደሉ ብሎም በሽብርተኝነት በመወንጀል እያሰቃዩት ይገኛሉ። ሙስሊሙ ህብረተሰብ የተቃውሞ ድምፁን ያሰማበትን አላማ ምንድነው? ችግሩስ ከምን የመነጨ ነው? ብሎ እልባት ከመስጠት ይልቅ ጥያቄአቸውን በማንቋሸሽ እና በማጥላላት በጠመንጃ አፈ ሙዝ የሚመልሱት ይመስል ህዝበሙስሊሙን ለከፋ መከራና ስቃይ ዳርገውታል። ለዚህ ድርጊታቸው ደግሞ ሚስጥሩ ንፁሃኑ ህዝበ ሙስሊም ላይ የሃሰት ታርጋ በመለጠፍ አሸባሪነትንና አክራሪነትን እየተዋጋው ነው በሚል የማስመሰልና የማታለል ስራው የምዕራባውያን ሃገራትንና የአሜሪካ ቀልብ ለመሳብና እርዳታ ለማጋበስ ነው። ቢያውቁት ግን ይህ ድርጊታቸው አውሬ እንጅ ሰው አለመሆናቸውን ቁልጭ አድርጐ ያሳያል። ለገንዘብ ሲባል ሰውን ያክል ፍጡር መግደል፤ ማሰርና ማሰቃየት ከአንድ ሰው የሆነ ሰብአዊ ፍጡር አይጠበቅምና።

ሌላው ወያኔዎች 22 ዓመታት በጠመንጃ ስልጣን ላይ ከወጡበት ጊዜ አንስቶ ሲጠነስሱት የነበረው ሽብር የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በመከፋፈልና በማፋጀት የኢትዮጵያን ህልውና አንድነትን፣ ማንነትን በማናወጥ፤ የስልጣን እድሜያቸውን ማርዘም ነው። ይህ ስራቸው ከምን ጊዜውም በላይ በአሁኑ ሰአት እያፋፋሙትና፤ ሰላማዊውን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በማጋጨት የሽብር ሴራቸውን እያስፋፉ ይገኛሉ። ዳሩ ግን ለወያኔዎች ህዝብን መከፋፈል የሚበጅ ቢመስላቸውም የዚህ የሽብር ድራማቸው ተጠቂዎች ግን በፍፁም ልንሆን አልቻልንም፤ ወደፊትም ልንሆን አንችልምም። ምክንያቱም መቻቻል እና በፍቅር አብሮ መኖር መለዬ ባህላችንን በፍፁም ይህ ሰይጣናዊ ድርጊታቸው ሊያመክነው ስለማይችል ነው። ይህንን አንድነታችንን፤ ፍቅራችንን የመቻቻል ባህላችንን የበለጠ በማጎልበት፤ ባህላችንን፣ አንድነታችንን፣ ሃይማኖታችንን እየተፈታተነ ያለው የወያኔን የሽብር ስልት በማክሸፍ፤ ለበለጠ ድል እስክንበቃ ትግላችንን ማጠናከር ይኖርብናል።

በመጨረሻም የወያኔ ባለስልጣናት በፈረጠመ አምባገነናዊ ክንድ ህዝብን በማሸበርና በማፈን የስልጣን ዘመንን ለማራዘም መሞከር አወዳደቅን ማክፋት መሆኑን ካለፉት አምባገነናዊ ስርአቶች ሊማሩ ይገባል! አሁንም በድጋሚ ወያኔዎች ጠንቅቀው ሊያውቁት የሚገባ እውነት የኢትዮጵያ ህዝብ ሽብኝነትን በጽናትና በቁርጠኝነት ይቃወማል፤ ያወግዛልም፡፡ በፀረ -ሽብርተኝነት ሽፋን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን እየጣሰ ያለውን የወያኔ አገዛዝንም በተመሳሳይ ጽናትና ቁርጠኝነት ይቃወማል፤ ይታገላልም!!!

ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!

ያለዎትን አስተያየት በፀሃፊው አድራሻ: kiduszethiopia@gmail.com ይላኩ።


ኢትዮጵያዊ ዋጋው ስንት ነው? (ተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

ኢትዮጵያዊ ዋጋው ስንት ነው?
(ተመስገን ደሳለኝ)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

የዚህ ፅሁፍ ማጠንጠኛ የፖለቲካ አመለካከትን መተቸት አይደለም፤ ከዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ወረድ ያሉ የጉልበታሙን ስርዓት የሥራ አፈፃፀሞችን ማብጠልጠልም አይደለም፤ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ስንክሳር መንቀስም… አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ (አል-ሀበሽ) መሆን ለፈተና፣ ለመከራ፣ ለሰቆቃ… መዳረጉ የወለደው ብሶት እንጂ፤ መመረር-ማምረር ነው፡፡ …ይህ የእኛ ዕጣ ፈንታ የሆነበትን ምስጢር መመርመር ነው፡  -

ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ታጣቂዎች እና በድጎማ የሚያድሩ የሀገሬው ተወላጆች በመሰረቱት የጥፋት  ግንባር ጉልበታቸውን ገብረው፣ በላብ በወዛቸው በሚያድሩ ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው አረመኔያዊ  ወንጀል፣ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልብ በከባድ ሀዘን የሰበረ፣ በቁጭት ያንገበገበ አሳዛኝ ፍፃሜ ሆኗል፡፡  ጭፍጨፋው ሃይማኖታዊው ጀሀድ ያወጀው አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት ባመጣው ዕዳ በድሃ ወንድም-እህቶቻችን ጀርባ ላይ ያረፈ ምህረት  የለሽ ብትር እንጂ፡፡..;;;ይህ ግን ለምን ሆነ? ጥያቄ ነው፡፡

ርግጥ ነው፣ እንዲህ አይነቱ የእልቂት ነጋሪት መጎሰም ከጀመረ ዓመታት ነጉደዋል፤ መነሻ ሀገሩ ግን ሳውዲ አረቢያ ወይም ሊቢያ አይደለም፤ እዚሁ ኢትዮጵያችን ምድር ላይ እንጂ…

ዘ-ፍጥረት…
የየካቲቱ አብዮት ድንብዥታ (ሀንግኦቭር) ዛሬም ድረስ ዘመን ተጋሪዎቼን እያሳደደና እያሰደደ ይገኛል፡፡ ያኔ ያ ትውልድ ‹ኑ እንነሳ፣ ከተማውን እንውረር፤ አሮጌውንም ቅፅር በጩኸት አፍርሰን፣ አዲሱን እንፍጠር!› የሚል መለከት መንፋቱ ሙሉ ለሙሉ ስህተት ባይሆንም ‹የተጠሩ ብዙዎች፣ የተመረጡ ጥቂቶች› እንዲል መፅሀፉ፣ እፍኝ ለማይሞሉ ‹ምርጥ ወታደራዊ መኮንኖች› የተናጠል አሸናፊነት፣ የወል ተጠያቂ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ስለምን ቢሉ? ስለተከሰተው ታሪክ ይሆናል መልሱ፡፡ በርግጥም ‹ፓርቲ› የሚባል የ‹ጦስ ዶሮ› ባነበረው ልዩነት በጥይት ደብድበው ሲያበቁ፣ አፈር ፈጭቶ፣ ውሃ ተራጭቶ ባደገበት መንደር እንደ መናኛ በየመንገዱ አስጥቶ ማዋል፣ ለግብዓተ መሬቱ የጥይት ዋጋ ማስከፈል፣ ወላጆችን እርም መከልከል… ከዚህ የከፋ ምን ሊያመጣ ኖሯል? …ከተኛበት አልጋ እያነቁ መስቀል፣ ከገሀነም በከፋው ቅጣት ‹ወፌ-ላላ› ገልብጦ ማሰቃየት፣ በአንድ ጉድጓድ ስልሳውን አነባብሮ መቅበር… ከዚህ ሌላ ምን ሊያስገኝ ኖሯል? …የሆነውም ይህ ነበር፡፡ እነሆም ያ ትውልድ የፀነሰው የተገነባውን መናድ፣ የተሰራውን ማፍረስ፣ በራስ ወገን ላይ መከራ ማዝነብን የሚመክረው የዘ-ፍጥረት መፅሀፍ ምዕራፍ እዚህ ጋ ነበረ የጀመረው፡፡
አዲስ ታሪክ አልተሰራም!

 

‹አዲስ ንጉስ እንጂ፣ ለውጥ መቼ መጣ!› እንዳለው ከያኒው፣ ታጋዮቹ በወታደሮቹ ቦታ ከተቀመጡ በኋላ የነበረው-እንደነበረው ነው የቀጠለው፤ ‹ባለሙያ› ገራፊዎች በአሸናፊዎቹ ከመተካታቸው በቀር፣ ማሰቃያ ጎሮኖቹ ዛሬም ወደ ሙዚየምነት አልተቀየሩም፣ መገረፊያው፣ መገልበጫው፣ መግደያው፣ መጋዣው… አሁንም የቀድሞውን ግልጋሎታቸውን እየሰጡ ነው፡፡ ማን ያውቃል? ነገም በዚሁ ይቀጥሉ ይሆናል፤ ለአጎራባች መንደሮች መቀጣጫ በሚል የጭካኔ ፈሊጥ፣ የአማፅያን ኮሽታ የተሰማበትን መንደር ሁሉ ዶግ አመድ ማድረግም፣ የጄነራሎቻችን የጦር ‹ጠበብ›ነት መገለጫ ሆኖ ቀጥሏል፤ በሀውዜን፣ አርባ ጉጉ፣ አርሲ፣ ሐረር፣ ጋምቤላ፣ አዋሳ፣ ኦጋዴን፣ ቀብሪ-ደሀር፣ ደገ-ሀቡር… የፈሰሰው የግፉአን ደም፣ የተከሰከሰው የንፁሀን አጥንት ታሪክ ነጋሪ ጥቁር ሀውልት መሆኑን ማን ይክዳል? ይህንን ሁሉ ምድራዊ ፍዳ፣ ዓለም እንደ ማንኛውም አሳዛኝ ዜና ሰማው እንጂ፣ ሰለባዎቹን ለመታደግ ያደረገው እዚህ ግባ የሚባል እንቅስቃሴ አልነበረም፤ በራስ መንግስት፣ በራስ ወገን መናቅ፣ ክብር መነፈግ፣ ለ‹ምርኮኛ ሕግ› ማደር… ክፋቱ እዚህ ላይ ነው፡፡ የዛሬዎቹ አረቦቹም በወገኖቻችን ላይ የጭካኔ እጃቸውን እንዲያነሱ የልብ ልብ የሰጣቸው፣ ይኸው የእኛው የእርስ በእርስ አለመደጋገፍና አለመከባበር ነው፡፡ ትላንትና በጉራ ፈርዳና ቤንች ማጂ ዞን ጎሳ መመዘኛ ሆኖ ‹ውጡ የክልሉ ተወላጅ አይደላችሁም› በሚል በገዛ ወገኖቻቸው እንደጠላት ሀገር ሰው በጦር መሳሪያ ተከበው፣ ንብረታቸውን ሜዳ በትነው ስለተባረሩ ኢትዮጵውያኖች፣ የሰሙ አረቦች ‹ሳወዲያ አረቢያን ልቀቁና ውጡ› ብለው ይህ አይነቱን መዓት ቢያወርዱ ምን ይደንቃል? የባዕድ ሀገር ሰው የትንኝ ነፍስ ያህል እንኳ ሳይጨነቅ እንደዘበት ህይወታችንን ቢነጥቀን በእርሱ ላይ መፍረድ እንዴት ይቻለናል? አሳልፈው የሰጡን እነማን ሊሆኑ ነው?

እመነኝ፣ በሳውዲ አረቢያ ጎዳናዎች የሰው ራስ ቅል እንደ በግ በመጥረቢያ ሲከሰከስ፣ እንደ ጦስ ዶሮ ተጋድሞ ሲታረድ፣ በቁሙ እሳት ሲለቀቅበት፣ ህፃናት የወታደር መለዮ በለበሱ አረመኔዎች ሲረገጡ… ልብህ እያለቀሰ፣ ፊትህ በእንባ እየታጠበ ያየኸው አይነት ጭካኔ ምንጩ ይህ ነው፤ ይህም ነው የኢትዮጵያን ሰው በአልባሌ ምክንያት መግደል፣ እያፏጩ ጉዞን የመቀጠል ያህል ያቀለለው፤ ለዚህም ነው በሙስሊሞች ቅድስቲቷ መዲና ላይ በድንጋጤ የጨው አምድ የሆነ አካለ-ቁመና፣ በሽብር ተውጣ አቅሏን የሳተች እህት፣ ስጋት ያናጠበው ወንድም ተመልክተህ በሀዘን የተቆራመድከው፤ ‹‹ወይኔ ወገኔ!›› ብለህ ደም እንባ የተራጨኸው፡፡ …እናስ! ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተመጣጣኝ ዋጋ መክፈል ያለበት ማን ነው? ንጉሥ አብደላና ዕኩይ ተከታዮቹ ብቻ? ወይስ እንዲህ የፊጥኝ አስሮ ለአረብ ሀገራት መቀለጃ የዳረገህ መንግስትህም ጭምር?

 
ከችጋርና ጭቆና ያልተፋታ ሕዝብ ዳቦና ነፃነት ፍለጋ እግሩ ወዳደረሰው ሀገር ተሰዶ መኖሩ በእኛ የተጀመረ አይደለም፤ እንዲያውም ስደተኞችን ካስተናገዱ ከመጀመሪያዎቹ ጥቂት የዓለም ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምነት የምትጠቀሰው የእኛዋ የአቢሲኒያ ምድር ኢትዮጵያ ነች፡፡ የሩቁን ትተን እስከ የኃ/ስላሴ ስርዓት ፍፃሜ ድረስ የነበረውን ተጨባጭ ሁነት ብንመለከት እንኳ፣ ‹አረብ ቤት› በሚል ተቀፅላ የሚታወቁት ብዙዎቹ ሱቆችና የንግድ መደብሮች፣ በስደት መጥተው እኩል እንደ ዜጋ ሀገራችን መኖር በቻሉ አረቦች የተያዙ ነበሩ፡፡ የዛሬን አያድርገውና ይህች ገናና ሀገር ለሌሎች ሀገራት ሕዝቦች የነፃነትና የክብር ተምሳሌትም ነበረች፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስም ሆነ በቅዱስ ቁርአን ውስጥ በፈሪሐ እግዚአብሔርነቷ፣ በፍትሐዊነቷና በርትዓዊነቷ ስሟ ተደጋግሞ የተወሳና የተመሰከረላት፣ የታላቅ ሕዝብ ታላቅ ሀገር ነበረች፡፡ ዛሬ በተፈጥሮ ማዕድን በልፅጋ የሀበሻ ስደተኞች መናኸሪያ ለመሆን በበቃችው ሳውዲ አረቢያ የተወለዱት ነብዩ መሀመድ የዛሬ 1400 ዓመታት ገደማ በስደት መጠለያነት የመረጧት፣ ሀገሪቷም ተከታዮቻቸውን እጇን ዘርግታ በመቀበል ከራሷ ዜጋ እኩል ተንከባክባ ያኖረቻቸው ስልጡን ሀገር ነበረች፡፡ ማን ነበረ ‹ወርቅ ላበደረ…› ያለው? እነሆም ዘመኑ ተቀያየረና ‹‹የኋላኞቹ ፊተኞች፣ የፊተኞቹ ኋለኞች›› ይሆኑ ዘንድ ግድ በማለቱ ዛሬ አብዛኞቹ የአረብ ሀገራ ኢኮኖሚያዊ ልዕልና እየተጎነፀፉ ሲመጡ፣ እኛ የኋሊት ተንሸራተን ቁልቁል ለመውረድ በቃን፡፡

 
ምንም እንኳ እነዛ ሁሉ መልካም መገለጫዎቻችን ዛሬም ድረስ ባናጣቸውም፣ በብሔር ክፍፍልና በእርስ በእርስ ሹኩቻ የተነሳ ግን በደህነት ማጥ ውስጥ ተዘፍቀን፣ እኛም በተራችን መሰደድ ዕጣ ክፍላችን ሆኖ ቀረ፡፡ ዛሬ አብዛኛው ወጣት በሀገሩ የመኖር ተስፋው በመሟጠጡ፣ በስደት ወጀብ የሚንገላታ፣ ማረፊያ እንዳጣች ወፍ ሲናወዝ መሽቶ የሚነጋለት ብኩን ሆኗል፡፡ በሀገሩ እጅግ ከመመረሩም የተነሳ ራሱን ለሻርክ ጥርስ፣ ለእንግልት፣ ለግርፊያና ለበልዓ-ሰቦች አሳልፎ እስከ መስጠት በሚያደርሰው የስደት ጉዞ ለማለፍ የማያመነታ ትውልድ ለመሆን ተገዷል፡፡ ይህ ከድህነት ወለል ስር ያሳደረን የዘመን ግርሻ፣ ይህ ከመንግስት ጋር አይንና ናጫ ያደረገን አምባገነናዊ አገዛዝ፣ ለዚህ ሁሉ አሳረ-መከራ ዳርጎን፣ ከሀፍረት ጋር አንገታችንን እስደፋን… ውለታን ከማስረሳቱም በላይ ለከፋ በደል አጋልጦ ቁጭት አስታቀፈን፡፡

 
ሰሞኑን ‹‹የበላችበትን ወጪት…›› ከሰበረችው ሳውዲ አረቢያ የተሰማው አሰቃቂ ዜናም የእዚህ የኢትዮጵያን ስደተኞች ተከታታይ ፍዳ ጉትያ ነው፡፡ እርግጥ አብዛኛው የአረብ ሀገራት መሬቱ ሰለጠነ እንጂ ሕዝቡ ገና ጨለማ ዘመን ውስጥ ነው፤ ሌላ ሌላውን ወደጎን ብለን የሰሞኑን አውሬአዊ ባህሪያቸው እንኳን እንደ አይነተኛ ማሳያ ልንወስደው እንችላለን፤ ይህ ድርጊትም እንሰሳዊ ባህሪያቸው የስነ-ዝግመት ለውጥን ገና አለማገባደዱን ያመለከተ ነው፡፡ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒሊክ አድዋ ላይ፣ ያውም ሀገራቸውንና ዙፋናቸውን በጦር ኃይል ለመንጠቅ የጎመዠችው ሮም ያዘመተቻቸው ወታደሮች፣ እልፍ አእላፍ ሠራዊታቸውን ፈጅተው፣ የቅርብ ወዳጆቻቸው የሆኑ የጦር አበጋዞቻቸውን ገድለው የማታ ማታ የሽንፈትን ፅዋ አስጎንጭተው ከማረኳቸው በኋላ በርህራሄ ተንከባክበው እንደያዟቸው የዓለም ታሪክ ያውቀዋል፡፡

 
በሀገሩ ኑሮ አልቃና ብሎት፣ በሰው ምድር የሰው አደፋ አፅድቶ፣ ቆሻሻ ለቅሞ… ፋታ የማይሰጠውን የእህል ውሃ ጥያቄ ለመሙላት በማሰነ፣ ሆድቃን በሳንጃ መዘርገፍና የዱር አውሬ እንኳ የማይፈፅመው የጋርዮሽ ሴት ደፈራ መፈፀም… ምን አይነት ‹ኢብሊሳዊ› (ሠይጣናዊ) ተግባር ነው? የተቸነፈን መልሶ ማቸነፍ፣ የወደቀን መርገጥስ ‹ከመክፈር› (ፈጣሪን ከመካድ) በምን ይለያል?
አሁንም እደግመዋለሁ፡- ይህ ፖለቲካ አይደለም፤ እየፈሰሰ ስላለ የንፁሀን ደም፣ የወላድ መሀን ስለሆኑ እናቶች፣ ጧሪ ቀባሪ ስላጡ የተራቡ አባቶች፣ አሳዳጊ አልባ ስለሆኑ ህፃናት፣ ያለሚስት ስለቀሩ አባወራዎች፣ ባላቸውን ስለተነጠቁ የቤት እመቤቶች … የሰቆቃ እሪታ ነው፡፡ በወጡበት ሰው ሀገር ላይ ወድቀው ስለሚቀሩ ወገኖቻችን ዋጋ ስለመጠየቅ ነው፤ ለነጋዴው መንግስታችን ኢትዮጵያዊው ዜጋ ዋጋው ስንት እንደሆነ የመሞገት ጉዳይ ነው፡፡

 
ሀገር ማለት…

ሀገር ምን ማለት ነው? ‹ሀገር› የሚለውን ቃል የኢህአዴግ መራሹ-መንግስት መዝገበ ቃላት ምን ፍቺ ሰጥቶት ይሆን? ሉዓላዊነትስ በ‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ› ቀዩ መፅሀፍ አንደምታው ምን ይሆን? …ቀለብ ሰፍረን የምናሳድረውን ሠራዊት ሞቋዶሾ ድረስ ልኮ፣ የባራክ ኦባማን ስጋት ማቃለል? በ‹ተባበሩት መንግስታት› ስም የሲ.አይ.ኤ ቅጥረኛ ሆኖ በሱዳናዊያን የውስጥ ችግር ላይ-ታች እንዲማስን ማድረግ? የሕዝብ ደህንነት መ/ቤትስ ኃላፊነቱ የእናንተንና የቅምጦቻችሁን ደህንነትና ምቾት መጠበቅ ነውን? የአምባሳደሮቻችን የሥራ ድርሻ ፓስፖርት ማደስና የመግቢያ ፍቃድ መስጠት ብቻ ነው? በስደተኛ ወገኖቻችን ላይ ‹ጊንጥ ሰላይ› መሆን? ቦንድ መሸጥ? ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው› እያሉ መስበክ? …ወይስ የዜጎችንም ደህንነት መከታተልና መጠበቅንም ጭምር? …ይህ ነው የወቅቱ ዓብይ ጥያቄ፡፡
የዲፕሎማሲ ግንኙነትስ ምን ማለት ነው? አገዛዙ በአንድ ወቅት ተቀማጭነቱ ኳታር-ዶሀ የሆነው ‹አልጄዚራ› ቴሌቪዥን ‹ስሜን አጠፋ› በሚል የኳታርን ኢምባሲ እንደ ዘጋው አይነት ስራን ብቻ የሚመለከት ይሆን? ከዋነኞቹ ለጋሽ ሀገራት በግንባር ቀደምነት የምትመደበው ኖርዌይስ ኢምባሲዋ የተዘጋው ለማን ትርፍ ነበር? ለብሔራዊ ጥቅም መቆርቆርስ ‹ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አልተከበረም› ብለው ዘገባ ባወጡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ያንን ሁሉ አቧራ ማስነሳት ይሆን?

 
ሌላው ቢቀር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለምን እንደ ተመሰረተ ይዘነጋል? አባቶቻችን ኮሪያና ኮንጎ ድረስ የዘመቱት ለዓለም ዜጎች ሰላም መሆኑስ እንዴት ይረሳል? የድርጅቱ አባል ሀገራት የፈረሙት ስምምነትስ የሳውዲ አረቢያን ሽፍትነት እንኳ ለመከላከል አቅም አይኖረውም? በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት እልፍ አእላፍ ወታደሮቻችን ካለቁብን በኋላ ከባረንቱ የተመለስነው፣ ባድሜ ላይ የቆምነው፣ በዛላንበሳ የታገድነው… የማንን ሕግ አክብረን ነበር? ያውም ‹በስለላ ስራ ሊሰማሩ ይችላሉ› ተብለው የተጠረጠሩ ኤርትራውያን እንዲያ በክብርና በእንክብካቤ ወደ ትውልድ ሀገራቸው የተሸኙት፣ በጦር ሜዳ የተሸነፈው ሻዕቢያ ተፈርቶ ነበር እንዴ? …ይህ ነው እንቆቅልሹ፡፡

 
ዛሬስ መንግስታችን የስደተኛ ዜጎችን ደህንነት በምልዓት የማይከታተለውና የድረሱልኝ ጩኸታቸውን ሰምቶ ፈጥኖ እጁን የማይዘረጋላቸው ለምን ይሆን? ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ ሆኖበት? ወይስ በለመደው የንቀት መነፅር አይቶ እንዳላየ በቸልተኛነት አልፎት ነውን? በርግጥ ይህንን የበደል ማማ ካለፈው ታሪኩ አንፃር ከገመገምነው ምክንያቱ ሀገራዊ ስሜቱ ደካማና ከሥልጣኑ ሌላ ምንም የሚያሳስበው ነገር ባለመኖሩ ብቻ እንደሆነ ይገባናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ሠማያዊ ፓርቲ የአረቦቹን ወደር የለሽ ጭካኔ ለማውገዝ በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ በር አጠገብ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ያገደው ‹ይህ አይነቱ ሀገራዊ መቆርቆር ነገ ደግሞ መስቀል አደባባይን በሕዝብ ሱናሚ ለማጥለቅለቅ መነቃቃት የሚፈጥር ገፊ ምክንያት ሊሆን ይችላል› ብሎ በስጋት ስለተጠፈነገ ይመስለኛል፡፡

 
የሆነው ሆኖ የመንግስት ህልውናም ሆነ አቅም በእንዲህ አይነቱ ወቅት ነውና የሚፈተነው ኢህአዴግም በዚህ ተግባሩ ዜጎቹን የመታደግ ገት እንዳሌለው አስመስክሯል፡፡ መቼም በሲ.አይ.ኤ ተላላኪነቱ በ‹ዋይት ሀውስ› ማህደረ-መዝገብ ውስጥ ከጊዜ ጊዜ እየዳጎሰ የመጣው የ‹ውለታ›ው ዶሴ ለእንዲህ አይነቱ ፈታኝ ወቅት መሆን ይሳነዋል ማለት ይከብዳል፡፡ ሼክ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ የሳውዲ ነጋዴዎች፣ ሀገራችን ውስጥ በበርካታ የንግድ ዘርፎች ተሰማርተው አትርፈው ማደራቸው፣ በሰፋፊ እርሻዎች ዘርተው ማጨዳቸውስ እንደምን ተዘነጋ? ይህ ቢያንስ በነፍስ-ውጪ ነፍስ-ግቢ ለተያዙ ወገኖቻችን እንዴት የመደራደሪያ ጉልበት መፍጠር ሳይችል ቀረ? …በርግጥ መለስ ዜናዊ በ2004 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ከጎራ ፈርዳ ስላፈናቀላቸው አማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን በተጠየቀበት ጊዜ ‹‹ደን ጨፍጫፊዎች ናቸው›› ሲል የስላቅ መልስ እንደሰጠው ሁሉ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኀኖምም የሳውዲውን እልቂት በተመለከተ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርቦ ‹‹የማባረር ሥራው በኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልነበረ ተረድተናል›› በማለት መቀለዱ፣ ስርዓቱ ‹አስተዳድረዋለሁ› ከሚለው ሕዝብ ይልቅ ሥልጣኑንና ተያይዘው የሚመጡ ጥቅሞቹን በዜጎች ሕይወት ጭምር ተደራድሮ ከማስከበር እንደማይመለስ የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ እንደ መንግስት በሀገር ሀብት እንደአሻው እየተምነሸነሸ፣ ‹ግዴታዬ የባቡር መንገድና ኮንዶሚንየም ቤት መስራት ብቻ ነው› ማለቱ ይህንኑ ይመሰክራል፡፡ አሊያማ ፋሺስቱ ጣሊያን እንዲያ በርካታ ድልድዮች፣ መንገዶች፣ ቤቶች… ገንብቶ ሲያበቃ፣ ‹ሀገር› ማለት ሕዝብ የሰፈረበት ሉዓላዊ ግዛት ማለት ነው ተብሎ ያ ሁሉ መስዕዋትነት ተከፍሎ በኃይል እንዲባረር ባልተደረገ ነበር፡፡

 
‹ሕዝቤን ልቀቅ!

 
በዘመነ-ኦሪት በግብፅ ዙፋን ላይ በተፈራረቁ ፈርኦኖች፣ ለባርነት የተዳረጉ ዕብራዊያንን ነፃ ያወጣ ዘንድ በፈጣሪ ተመርጦ የተላከው ሙሴ ‹‹እግዚአብሄር ‹ያመልከኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ!› ብሎሀል›› ማለቱ በቅዱሳት መፃህፍት መገለፁ እውነት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ ራሱን ‹ኢህአዴግ› ሲል በሚጠራው ‹አምሳለ-ፈርኦን› ለመከራና ለሀፍረት የተዳረጉ ሕዝቦች አርነት ይጎናፀፉ ዘንድ ‹የሙሴ ያለህ!› የሚለው ጩኸታቸው ከተራራ ተራራ እያስተጋባ መሆኑ ሌላ እውነታ ነው፡፡ በሳውዲ አረቢያ የግፍ ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵውያን ደምም ዋይታ እየተበራከተ ነው፤ ስርዓቱ እንዲህ አይነቱ ሰቆቃን ለፖለቲካ ትርፍ እየተጠቀመበት መሆኑንም ሰሞኑን የመንግስት እና ደጋፊዎቹ ሚዲያዎች የሚያሰራጩትን ዘገባ መመልከት በቂ ነው፡፡ መቼም መሬት ልሰው፣ አፈር ቅመው ያፈሩትን ንብረት ተነጥቀው፣ ባዶአቸውን እየተመለሱ ያሉ ስደተኞችን ‹በሀገራችን መስራት ይሻለን ነበር› እንዲሉ ማስገደድ ለርካሽ ፖለቲካዊ ትርፍ ካልሆነ በቀር ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ አስከፊው ድህነታችን ጉርሻ እስከ መግዛት፣ ከቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ቅልጥም እስከ መምጠጥ፣ የወደቀ ምግብ ከውሻ ጋር ተጋፍቶ እስከ መመገብ… በደረሰበት በዚህ የችጋር ዘመናችን ላይ በምን አመክንዮ፣ ከየትኛው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ተመዝኖ ሊታመን ይችላል ተብሎ ነው ‹ሀገር ውስጥ ሰርቶ በሰላም መኖር ይቻላል› የሚለው ተራ ፕሮፓጋንዳ ነጋ-ጠባ የሚደሰኮረው? ምንድር ነውስ የሚሰራው? እዚህ እኛ ሀገር የማንን መፀዳጃ ቤት ንጽህና መጠበቅ ይሆን የአረቦቹን ያህል ዳጎስ ያለ ክፍያ ማስገኘት ቀርቶ፣ በቀን ሁለቴ ለመብላት የሚያግደረድረው? ቅጥ አንባሩን ያጣው የግብር ፖሊሲያችን፣ እንጀራ ቸርቻሪዎችን ሳይቀር አሳድዶ የእለት ጉርሻቸውን እየነጠቀና በተንሰራፈው ድህነት ላይ ተጨማሪ እልቂት አውጆ ድሆችን ለማጥፋት ሰይፉን በሚያወናጭፍበት በዚህ ወቅት፣ ወጣቱ እንዴት ብሎ ነው በሀገሩ ሰርቶ መኖር ይችላል የሚባለው? ገና ጀንበር ከማዘቅዘቋ ጎዳናውን የሚያጥለቀልቁት ህፃናት ሴተኛ አዳሪዎችንስ ምን እንበላቸው? የትኛው ተቀጣሪስ ነው በደሞዙ የወር ቀለቡን ሳይሳቀቅ መሸመት የቻለው? …ሁላችንም የመዳፋችንን ያህል አብጠርጥረን የምናውቀው በመሬት ያለው ተጨባጭ እውነታ ይህ ነው፡፡

 
እነሆም በመጨረሻ እንዲህ ማለት ወደድኩ፡- ስርዓቱ ሰባኪው እንዳለው ‹የከንቱ ከንቱ፣ ከንቱ› ቢሆንም፣ አቶ መለስ ዜናዊ በኤርትራ የመጀመሪያው የነፃነት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ተገኝቶ በአስመራ ሳባ ስታዲዮም ለተሰበሰበው ህዝብ በደርግ የደረሰባቸውን በደል በማስታወስ ‹‹በእናንተ ጀርባ ላይ ያለው ጠባሳ በእኛም ላይ አለ›› ሲል ሀዘኑንና መቆርቆሩን እንደገፀላቸው ሁሉ፣ በሳውዲ አረቢያ የግፍ ሰለባ የሆናችሁ ወንድም-እህቶቼ ሆይ! የእናንተ ሰቆቃና በደል፣ በእኛም ግንባር ላይ ተቸክችኮ ሀፍረታችችንና ውድቀታችንን የጋራ እንዳደረገው የታሪክ ፍርድን መጠበቁ አይቀሬ ነው፡፡ እመኑኝ ያች ዕለትም አብረን የምንነሳበት፣ ከፍ ብለን የምንበርበት ትሆናለች፡፡›

 
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

 
ኢት

 

 

የሳዑዲ ጉዳይ –ከረመጥ ወደ ረመጥ (ከፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም)

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

ባለፉት አስርት ዓመታት በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች በአገራቸው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አህጉር በተለየ መልኩ ተንሰራፍቶ እየተፈጸመ ካለው ጭካኔና ርህራሄ የጎደለው አምባገነናዊ ስርዓት ለማምለጥ ሲሉ እግራቸው ወዳመራቸው አገር በመሰደድ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ “ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር” እንደዘገበው ከሆነ እ.ኤ.አ በ2012 በግምት 200,000 ኢትዮጵያውያት ሴቶች በውጭ አገር በአብዛኛውም በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የውጭ የስራ ዕድል ለመፈለግ ተገደዋል፡፡ ከእነዚህ ኢትዮጵያውያት ሰራተኞች አብዛኞቹ በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ከሚገኘው አምባገነናዊ የእሳት ነበልባል አመለጥኩ የሚል እምነት ነበራቸው፣ ሆኖም ግን ወደ ሳውዲ አረቢያው የእሳት እረመጥ ተወርውረው እራሳቸውን አገኙት፡፡    

በኢትዮጵያውያን ስደተኛ ሰራተኞችና በሌሎች በሳውዲ አረቢያ ጥገኝነት በጠየቁ ዜጎች ላይ ገደብ የለሽ አደን እየተካሄደ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በዚህ ወር በየዕለቱ በሚባል መልኩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ የደህንነት ኃላፊዎች፣ ወሮበሎች እና ህገወጦች ኢትዮጵያውያንን/ትን ሁሉ በየመንገዱ እያደኑ ይደበድባሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አንዳንድ ጊዜም ይገድላሉ፡፡ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ሲደበድቡ የሚያሳየውን የዩቱቤ የቪዲዮ ምስል መመልከት ለህሊና የሚሰቀጥጥ ነገር ነው፡፡ የሳውዲ አረቢያ ወሮበሎችና ህገወጦች ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን በየመንገዶች ሲያሳድዱ፣ ሲያጠቁና ሲገድሉ የሚያሳየው የቪዲዮ ምስል ለኩነቶቹ እውንነት ምንም ዓይነት ማብራሪያ አላስፈለገውም፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሳውዲ አረቢያ ወሮበሎችና ጋጠወጦች በኢዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ እየፈጸሙት ያለው በቪዲዮ ማስረጃነት ተደግፎ የቀረበው የሰብአዊነት መብት ረገጣ ወንጀል በጣም የሚዘገንንና በሰለጠነ የሰው ልጅ ህሊና ሊታሰብ የማይችል ነገር ነው፡፡ 

ze ethiopiaኢትዮጵያና ሳውዲ አረቢያ፡ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች፣ 

ኢትዮጵያና ሳውዲ አረቢያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ የሳውዲ አረቢያና የኢትዮጵያ ገዥዎች ከአንድ ጥለት የተቆረጡ ናቸው፡፡ የሳውዲ አረቢያ መንግስት በሰብአዊ መብት አያያዝ መዝገቡ በመጥፎ ተምሳሌነቱ ይታወቃል:: በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብአዊ መብት አያያዝ እንደ ሳውዲ አረቢያ ሁሉ ያስጠይፋል፡፡ የሳውዲ አረቢያው ገዥ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን በጣም ሰብአዊነት በጎደለው መንገድ ከግዛቱ በኃይል እንዲጋዙ/እንዲባረሩ የሚያደርግ መርህን ተከትሏል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ መደብም በተመሳሳይ መልኩ በሀገሩ ግዛት ውስጥ ኢትዮጵያውያንን/ትን ከሚኖሩበት ቀያቸው በግዳጅ ወደሌላ አካባቢ በማጋዝ አስደንጋጭ የሆነ የሀገር ውስጥ የማጋዝ (ሰፈራ) መርህን ተከትሏል፡፡ የሳውዲ ገዥ አናሳ የእምነት ተከታዮችን አሰቃይቷል፣ የኢትዮጵያ ገዥ መደብም እንደዚሁ አድርጓል፡፡ በሳውዲ ያለው ገዥ መደብ ዜጎችን በስፋት በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ያውላል፣ በእስር ቤት ያጉራል፣ ያሰቃያል፣ እንዲሁም በህግ ከለላ ጥላ ስር በሚገኙት ዜጎች ላይ ህገወጥ የእስር ቤት አያያዝን ያራምዳል፡፡ የኢትዮጵያ ገዥ መደብም በተመሳሳይ መልኩ የሳውዲ ገዥ የሚፈጽማቸውን የአፈና ድርጊቶች ሙሉ በሙሉ ይፈጽማል፡፡ የሳውዲ ገዥ የባሪያ ንግድን እ.ኤ.አ በ1962 በአዋጅ ካስቆመ በኋላ “ከፋላ” “kafala” (ተያዥ ያላቸው ስደተኛ ሰራተኞች፣ ሆኖም ግን በባሪያ ንግድ የአሰራር ሁኔታ የሚሰሩ) የሚል ቅጥያ በመስጠት ብዝበዛውን ቀጥሎበታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 የባህሬን የሰራተኛ ሚኒስትር ማጅድ አል አላዊ ሲናገር ከፋላ የሚለውን የማደናገሪያ ቅጥያ ከባሪያ ንግድ ጋር አመሳስሎታል፡፡ እ.ኤ.አ የ2013 ዓለም አቀፍ የባርነት አመላካች አሀዝ/Index እንዳመለከተው 651,000 የሚሆኑ በባርነት ተይዘው ህይወትን በመግፋት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዜጎች ሲኖሩ ከእነዚህም የዓለምን ሶስት አራተኛ ከሚይዙት ከመጀመሪያዎቹ አስር አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን በግልጽ አስቀምጧል፡፡ 

ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch እ.ኤ.አ በ2013 ባቀረበው ዓለም አቀፋዊ ዘገባው የኢትዮጵያንና የሳውዲ አረቢያን የሰብአዊ መብት አያያዝ ሬከርድ በሚመሳሰል መልኩ እንደሚከተለው አቅርቦታል፤

በ2012… የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ሀሳብን በነጻ የመግለጽ፣ የመደራጀትና የመሰብሰብ መሰረታዊ መብቶችን መገደብን በስፋት ቀጥለውበታል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባውን በመቀጠል በአዲስ አበባ ማዕከላዊ እየተባለ በሚጠራው የፌዴራል ፖሊስ የምርመራ ማዕከል ፣ እንዲሁም በሶማሊ፣ በኦሮሚያ እና በጋምቤላ ክልሎች እስር ቤቶችና በወታደራዊ ማዕከሎች የሚፈጸሙትን የማሰቃየት ድርጊቶች ዝርዝር ዘገባ አቅርቧል፡፡

የሙስሊሙን ህብረተሰብ አመጽ ተከትሎ በኦሮሚያና የአገሪቱ መናገሻ በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ አመጹን ለመግታት በሚል ሰበብ የደህንነት ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎችን ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስር በማዋል፣ እስራትና ድብደባዎችን ፈጽመዋል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ድብደባን ጨምሮ በአገሪቱ ከፍተኛ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ላይ መንግስት ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም የሚጠይቀውን የሙስሊሙን ህብረተሰብ ሰላማዊ ተቃውሞ ለመግታት ሲል መንግስት ከልክ ያለፈ ኃይልን ተጠቅሟል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ለማድረስ በሚል ሰበብ የመንደር ማሰባሰብ ተግባሩን እውን ለማድረግ በአምስት የአገሪቱ ክልሎች 1.5 ሚሊዮን የገጠር ሰፋሪዎችን የማሰባሰብ ስራ ቀጥሏል፡፡ በጋምቤላ ክልል ብዙ ሰፋሪዎች ከሚኖሩበት ቀዬ በኃይል ተፈናቅለው ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል… በመንግስት ጥረት የሚከናወን የሸንኮራ አገዳ ልማትን ለማፋጠን ሲባል በኢትዮጵያ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ የሚኖሩትን ኗሪ የፓስቶራል ህዝቦች መንግስት በኃይል አፈናቅሏል:: በደቡብ ኦሞ ዞን ወደ 200 ሺ የሚሆኑ የአካባቢው ኗሪ ህዝቦች መሬታቸውን ለሸንኮራ አገዳ ልማት ይፈለጋል በሚል ሰበብ መንግስት መሬታቸውን በመንጠቅ ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰደዱ አድርጓል፡፡   

ሳውዲ አረቢያን በሚመለከት ሂዩማን ራይትስ ዎች የሚከተለውን ዘገባ አቅርቧል፣

እ.ኤ.አ በ2012 ከህግ አግባብ ውጭ የሚከናወኑትን እስራቶችና ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን የማዋከቡ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው ምክንያት የሳውዲ አረቢያ መንግስት የኃይል እርምጃን ተጠቅሟል… እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ፍትሀዊ ያልሆነ ፍርድን ተቀብለዋል፣ ወይም ደግሞ ከህግ አግባብ ውጭ ለእስራት ተዳርገዋል… እስረኞች ህጻናትን ጨምሮ ስልታዊ የህግ የበላይነት ጥሰት እና ፍትሃዊ ህግ የማግኘት መብት የመነፈግ፣ ከህግ አግባብ ውጭ እስራትና ማሰቃየት እንዲሁም ህገወጥ የእስር ቤት አያያዝ ደባ ይፈጸምባቸዋል… ባለስልጣኖች የ9 ሚሊዮን የውጭ ሰራተኞችንና የ9 ሚሊዮን የሳውዲ ሴቶችና ልጃገረዶች መብት ማስከበር አልቻሉም ወይም ጭቆናውን ቀጥለውበታል…

ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑ የአገር ውስጥ ስደተኛ ሰራተኞች ከ2005 የሰራተኞች ህግ ውጭ ተደርገዋል… ባለፉት ዓመታት የኤሲያ ኤምባሲዎች ዘገባ እንደሚያመለክተው ከሀገር ውስጥ ሰራተኞች ቅሬታ እንደሚያሳየው በቀን ከ15 እስከ 20 ሰዓታት፣ በሳምንት ደግሞ 7 ቀናት እንዲሰሩ ከመገደዳቸውም በላይ ደመወዛቸውን ያለመክፈል ሁኔታም ተንጸባርቋል፡፡ የሀገር ውስጥ ሰራተኞች በአብዛኛውም ሴቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ተገደው እንዲወልዱ ይደረጋል፣ ምግብ የማግኘት መብታቸውን ያጣሉ፣ እንዲሁም የጾታ ትንኮሳ፣ የአካልና የስነልቦና ጫናዎች ይደረጉባቸዋል፡፡ 

ሳውዲ አረቢያ ከእስልምና አስተህምሮ ውጭ የሌሎችን እምነቶች አስተምህሮዎችን ለመቀበል ትዕግስቱ የላትም፡፡ ባለፈው መጋቢት ወር ልዩ ልብስ ለባሹ ሸክ በአረቢያ ፔንሱላ የሚገኙ ማናቸውም ቤተክርስቲያኖች በሙሉ እንዲወድሙ ጥሪ አስተላልፎ ነበር… 

“የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር” ቴዎድሮስ አድሃኖም ምን እንዳሉና ያሉትንም እንዳላወቁ፣ 

tewedros adhanom with returneesበኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በአሁኑ ጊዜ እየደረሰ ያለውን አስፈሪ ሁኔታ በማስመልከት የሚሰጠው ምላሽ ጭንቅላትን ይበጠብጣል፡፡ የወባ ትንኝ ተመራማሪውና ከመቅጽበት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተቀየሩት ቴዎድሮስ አድሃኖም እንዲሁም እ.ኤ.አ ከ2015 ሀገራዊ ምርጫ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ይረከባሉ ተብለው የሚጠበቁት ባለስልጣን ስለሳውዲ አረቢያው የኢትዮጵያውያን/ት ሁኔታ አስመልክቶ በኖቬምበር አጋማሽ በአዲስ አበባ ላይ በተካሄደው በ3ኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ዕቅድ ምጣኔ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ ግራ ተጋብተዋል፣ እዚህና እዚያ የሚዋዥቅ ንግግርም አሰምተዋል፡፡ ቅንነት የጎደለው እርግጠኝነትና በባዶ ተስፋ የተሞሉ ቃልኪዳኖችን አነብንበዋል፡፡ ወገኖቻችን ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመጡ በደስታ ለመቀበልና ዓለም ቀፋዊ ተብብርን ማጠናከር አስፈላጊ እንደሆነ በየኋህነት/ሞኝነት አገላለጽ አስቀምጠውታል፡፡ 

እንደምታውቁት፣ ከሳውዲ አረቢያ እንደምታውቁት ኢትዮጵያውያንን ብቻ ቢያግዙም/ቢያባርሩም ቅሉ ሌሎችን ዜጎችም እንዳባረሩ እንረዳለን… ባለፉት አስርት ቀናት እንዳየሁትም፣ ምክንያቱም በቤተሰብ ምጣኔ ዕቅድ እንደምንለው ለልጃገረዶችና ለሴቶች ክብካቤ እናደርጋለን፣ ከጣቢያዎች እርዳታ በመፈለግ ከሚጮሁ ሴቶች በቀጥታ ጥሪዎች ደርሰውኛል… በመቶዎቸ የሚቆጠሩትን በእርግጠኝነት ተቀብለናል፣ በሺዎችና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን እንቀበላለን ብለን እንጠብቃለን፣ በእርግጠኝነት ለመናገር የምፈልገው ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው እንዲመጡ ለመቀበል ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነን፡፡

በጣም አዝኛለሁ፣ ስሜቴም ተጎድቷል፡፡ ለዚህም ነው ይህ ሁኔታ ከተጀመረ ወዲህ ባለው የጊዜ መደበላለቅ ምክንያት ወደዚህ ላለመምጣት ዶ/ር ተከስተን ጠይቄ የነበረው፡፡ ሆኖም ግን በዓለምአቀፋዊነት ትብብር መሰረት ህገወጦችን ማባረር/ከአገር ማስወጣት የምንችል ቢሆንም ይህንን ጉዳይ በሰከነና በሰለጠነ መልክ እናደርገዋለን፣ ምክንያቱም ይህ ድርጊት የጦርነት ሁኔታ አይደለምና፡፡ እንደዚህ ያለው ሁኔታ ተቀባይነት ሊኖረው የሚችለው አገሮች በጦርነት  ላይ ሲሆኑ ብቻ ነው፣ ህዝብም በፈጠነ መልኩ ነገሩን ሊረዳው ይችላል፣ ነገር ግን በሰላማዊ ሁኔታ ሊሆን አይችልም፡፡ 

…በመሆኑም በዚህ መልክ በመጀመሬ አዝናለሁ፣ ይህ ሁኔታ እስከ አሁን ድረስ እየቆጠቆጠኝ የቆየ ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡

በእርግጥ በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ የአጭርና የረዥም ጊዜ መፍትሄ በማስቀመጥ ችግሮቹን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት ጥረት ስናደርግ ቆይተናል፣ ምክንያቱም ችግሮቹ ስር የሰደዱና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መወገድ ያለባቸው በመሆናቸው ነው፡፡ እንደምታውቁት ኢትዮጵያ እያደገችና ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት ምጣኔ እያስመዘገበች ነው፣ በዚህም አካሄድ ከጨለማው ዋሻ የውስጥ ጉዞ በኋላ ከጫፍ ላይ ብርሀን ይታየኛል፣ እና ይህንን ያለጥርጥር ተግባራዊ እናደርገዋለን፣ በዚህም ጥረታችን ድህነትን ተረት እናደርጋለን፡፡ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነን፣ ሆኖም ግን ዓለም አቀፋዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ እምነቴ የጸና ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ይሳካል ብለን አንጠብቅም፡፡ 

ነገሩን ለማታውቁት አንድ ነገር ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ፡፡ ነብዩ መሀመድ ታላቁን የእስልምና እምነት አስተምህሮቱን ሀ ብሎ ሲጀምር በደረሰበት መሳደድ ምክንያት ደቀመዝሙሮቹን/ተከታዮቹን ወደ ኢትዮጵያ ነበር የላከው… ስለዚህ አዝናለሁ፣ ንግግሬንም እዚህ ላይ አቆማለሁ…ሆኖም ግን የሚሰማኝን ስሜት ሁሉ በዝርዝር በመግለጼ፣ ያለፉት 10 ቀናት በህይወቴ ካየኋቸው ነገሮች ሁሉ እንዴት መራር እንደነበሩና ይከሰታሉ ብለን የማንጠብቃቸው አስገራሚ ነገሮች እየሆኑ በማየቴ እዚህ በመካከላችሁ በመገኘት ለእናንተ ሀሳቤን በማካፈሌ ደስታ ይሰማኛል…:: 

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ በሳውዲ አረቢያ መንግስት አየተፈጸመ ያለውን አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀል በማስመልከት የኢትዮጵያ “ቁንጮ የዲፕሎማት ሰው” እንደዚህ ያለ ተያያዥነት የሌለው፣ የተበታተነ፣ ዝብርቅርቅ ያለ እና እጅ እግር የሌለው ትንታኔ እና ገለጻ ሲያቀርቡ ስሰማ እጅጉን ነው ያዘንኩት፡፡ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከወባ ትንኝ ተመራማሪነትና ከመቅጽበት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት በተቀየሩ ግለሰብ የአፍ ካራቴ ዥዋዥዌ ልምምድ መቀለጃ ሆነ! ማንም ሊያደርገው እንደሚችለው የአድሃኖምን ቅጥ አምባሩ የጠፋ ንግግር መሰረት በማድረግ የሚከተሉትን ጭብጦች መመርመር ተገቢ ይሆናል፡፡

1. አድሃኖም እንዲህ አሉ “…በቃላት ሊገለጽ በማይችል መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያደረሰውን ሰቆቃ ሲያስታውሱ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጣቸው“ እና አሁንም ድረስ “እንዳዘኑ“ እና የሳውዲ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያት ሴቶች ላይ በሚፈጽመው ደባ ምክንያት ሰብአዊ መብታቸው እየተረገጠ ያሉ ሴቶች እገዛ ለማግኘት በሚያሰሙት ጩኸት “ስሜታቸው እንደተጎዳ“ ተናግረዋል፡፡ ይኸ “ታላቁ የዘመኑ ውሸት!“ ሊባል ይችላል፡፡

ምናልባትም አድሃኖም በእንግሊዝኛ ቃላት መካከል ያለውን ጥቃቅን ልዩነት ማስተዋል ባለመቻላቸው በተለይም ቀጥተኛ ያልሆነውን የአነጋገር ዘየ/colloquialism ተከትለው ይሆናል በማለት አስተያየት መስጠት ይቻል ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን እንደ ቁንጮ የዲፕሎማት ሰውነታቸው ለአላዋቂነት የቃላት አጠቃቀሞቻቸው ይቅርታ ሊደረግላቸው አይገባም (በእርግጥ የቃላት እና የሀረጎች አመራረጣቸው አመለካከታቸውንና ስሜታቸውን የሚገልጹ ቢሆንም)፡፡ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ በሳውዲ አረቢያ መንግስት እየተደረገ ያለው ግፍ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጣቸው“ እንደሆነ የሚገልጸው አባባል ተጎጂ ኢትዮጵያውያን/ት በሳውዲ አረቢያ ያሉበት ሁኔታ የንዴት ምንጭ እንደሆናቸውና ጥቂት እንዳሳሰባቸውም ጠቋሚ ነው፡፡ ይህ ትልቅ ጉዳይ አይደለም እንደማለት አነጋገር ነው ፡፡ በዓለም ላይ የየትኛውም አገር የዲፕሎማሲ ቁንጮ የሆነ ሰው በዜጎቹ ላይ ኢሰብአዊና ኃላፊነት የጎደለው አያያዝ መደረጉን አስመልከቶ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጠው” መሆኑን ለሌላ አገር ሰው ሲናገር አልተሰማም፣ አልታየምም፡፡ 

አድሃኖም በውል ያላጤኑት ቢሆንም ቃላት በዓለም አቀፍ የዲፖሎማሲው ቋንቋ ትልቅ ትርጉም አላቸው፣ ቃላት የዲፕሎማቶች ዓላማ ማስፈጸሚያ መሰረታዊ ሀብቶች ናቸው፡፡ የዲፕሎማቲክ ሰዎች እነርሱ በመረጧቸው ቃላትና የቃላት አጠቃቀም ዓለም እንዲቆምና እንዲሄድ የማድረግ ወይም አንዳንድ ጊዜም ሆን ብለው ለትርጉም ልቅ የሆኑ ወይም ደግሞ ውሱን የሆኑ ቃላትን በመጠቀም ዓላማቸውን ለማሳካት የሚሄዱበት ዘዴ ነው፡፡ የዲፕሎማቶች ቃላት ግልጽና ድብቅ ትርጉም ባላቸው መልዕክቶች የተሽሞነሞኑ እና ድብቅ ዓላማን ለማሳካት የተዘየዱ ማስፈጸሚያ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ በሰዋስዋዊው የቃላት አመሰራረትና በሚሰጡት ትርጉም ጥንቁቅነት በዲፕሎማሲው ቋንቋ ቃላት ሰላምን ያሰፍናሉ፣ ጦርነትን ያውጃሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የዲፕሎማቶች ቃላት የዲፕሎማቶችን ግላዊ የሀዘን ስሜትና የስሜታቸውን መጎዳት ብቻ የሚገልጹ ሳይሆን ከዚህ በተጨማሪ የዲፕሎማቶቹን የሞራል ስብእና፣ የስቅይቱን ጥልቀትና የሀገራቸውን ህዝቦች ስሜት ሊያንጸባርቅ ይገባል፡፡ 

አድሃኖም በሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ሁኔታ “እስከ አሁን ድረስ ነገሩ እየቆጠቆጣቸው“ እንደሆነ ሲገልጹ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት አደገኛ የሆነ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ እንዲህም ብለው እየነገሯቸው ነው፣ አዲሱ የይስሙላው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለማውገዝ በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተው የተናገሩትን በመዋስ “የዘር አደን“ በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎች ላይ በሳውዲ አረቢያ ፖሊሶችና ጋጠወጦች በየመንገዱ እየተደረገ ያለውን ሁከትና ትርምስ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ተገቢ የዲፕሎማሲ ንግግር ከተደረገ ይህንን አደገኛ ሁኔታ  እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ እየተካሄደ ያለው ኢትዮጵያውያንን/ትን የማዋረድና ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት የመፈጸም ሁኔታ ትልቅና በጣም ትልቅ የሆነ አገራዊ ጉዳይ ነው፡፡ በግሌ ለምሳሌ በዋና የስራ ሰዓት ጊዜ የሚይዝ የትራፊክ መኪና መጨናነቅ የንዴት ደረጃየን ከፍ ያደርገዋል፣ የተሰጣቸውን የቤት ስራ ሳይሰሩ በሚመጡ ተማሪዎቼ ላይ የሚኖረኝ ንዴት ከልኩ ያለፈ ነው:: ሳውዲዎች በኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየፈጸሙት ያለው ግፍ ግን እንድናደድ ብቻ አላደረገኝም፣ ደሜ እንዲፈላ ጭምር አደረገኝ እንጅ፡፡ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች በኢትዮጵየውያን/ት ላይ ሲፈጽሙት የነበረውን አረመኒያዊና ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት ስመለከት እሳት ነበልባል ሆኛለሁ፡፡ የሳውዲ አረቢያ ወሮበሎችና ጋጠወጦች በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ ሲፈጽሙት የነበረውን አረመኒያዊና ጭካኔ የተሞላበት የሰብአዊ መብት ረገጣ ስመለከት በንዴት ድብን ብዬ አራሴን አስከ መሳት ደርሼ ነበር፡፡ በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በሳውዲ አረቢያ ወሮብሎችና ጋጠወጦች እየተደረገ ያለውን ኢሰብአዊና ከህግ አግባብ ውጭ እየተደረገ ያለውን ጀብደኝነት የሳውዲ ገዥው አካል እያየ ጆሮዳባ ማለቱ የበለጠ እንድበሳጭና እራሴን እንድስት አድርጎኛል፡፡ የሳውዲ መንግስት ዓለም አቀፍ ሕግን በጠበቀ መልኩ በኢትዮጵያውያን ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎች መብት አያያዝ ላይ ምንም ነገር ባለማድረጉ በጣም ተበሳጭቻለሁ፣ አማርሪያለሁም፡፡ ኢትዮጵያውያን/ት በሳውዲ አረቢያ እየተፈጸመባቸው ያለው ግፍና መከራ አድሃኖምን ብዙም ያሳሰባቸውና ያስጨነቃቸው አይመስልም፡፡ 

በዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ቋንቋ መርህ መሰረት ጠንካራና ፊትለፊት በመግጠም የሚደረግ እና አስታራቂና ዲፕሎማሲያዊ በሆነ ለስለስ ባለ ቋንቋ ለመጠቀም የራሱ ጊዜ አለው፡፡ በእውነቱ ይህ ታላቅ ሀገራዊ ውድቀት ነው፣ አድሃኖም በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት በውል የተገነዘቡት አይመስለኝም፡፡

1463694_604158499630460_178987358_n2. ሳውዲ አረቢያዎች በኢትዮጵያውያን/ት ላይ እንዲህ በፈጣን መልኩ እየፈጸሙ ያሉት ከአገር የማባረርና የማስወጣት ሁኔታ “አንድ አገር በጦርነት በወደቀችበት ጊዜ የተደረገ ቢሆን ኖር ተቀባይነት ሊኖረው ህዝብም ሊረዳው ይችል ነበር” ብለዋል አድሃኖም፡፡ ከዚህ አንጻር አድሃኖም ያልተገነዘቧቸው በርካታ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ በጣም መሰረታዊ የሆኑ መርሆዎችና ህጎች መኖራቸውን ያሳያል፡፡ ከጦርነት ጋር በተያያዘ መልኩ ዜጎችን ከሀገር የማባረሩ ሁኔታን አስመልክቶ ያሉትን ህጎችና ልምዶች አንዳንድ ጊዜም የዘር ማጽዳት ድርጊቶች እንደሚፈጸሙ አድሃኖም የተገነዘቡ አለመሆኑን ይህ ሁኔታ በግልጽ ያመላክታል፡፡ እ.ኤ.አ 1990ዎቹ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ገደማ በሄርዞጎቪና እና ቦሲኒያ መካከል በተደረገው ጦርነት በርካታ የቦሲኒያ እስልምና እምነት ተከታዮች፣ ክሮሽያዎች፣ ሰርቦችና ቦሲኒያዎች ከትውልድ ቦታቸው የተቀነባበረ የማባረር/የማስወጣት ስልት በመጠቀም ተግባራዊ ተደርጎባቸዋል፡፡ ያ የጦር ወንጀለኝነት ነው፡፡ ይኸ እንዲሁ “ህዝብ በቀላሉ ሊረዳው የሚችል” ጉዳይ አይደለም አድሃኖም አንዳሉት፡፡ በጦርነት ጊዜ በኃይልና በማስገድደ ከአገር የማስወጣት አስፈላጊነት ለህዝቡ ደህንነት ሲባል በሚጠበቁ ሰዎች ወይም በጦር መሪዎች ላይ የሚፈጸም መሆኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ1949 የጸደቀው ስምምነት (IV) በጦርነት ጊዜ የሲቪል ሰዎችን ለመከላከል የተዘጋጀው ሰነድ በግልጽ ያሳያል፡፡ የስደተኞችን ጉዳይ አስመልክቶ በ1951 ስምምነት መሰረት በ1967 የስደተኞችን ሁኔታ አስመልክቶ የተዘጋጀው ፕሮቶከል እንዲሁም በአንቀጽ 3 በ1984 ማሰቃየትን በተመለከተ የተዘጋጀውን ስምምነት መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኞች ከማንኛውም ህገወጥ ማባረር/ማስወጣት ድርጊት መጠበቅ እንዳለባቸው በግልጽ ያሳያሉ፡፡ በጣም መሰረታዊ በሚባሉ የዓለም አቀፍ ህጎች፣ ደንቦችና መርሆዎች አንጻር አድሃኖም ያላቸው ግንዛቤ ሲመዘን በጣም አናሳ ሆኖ መገኘቱን ስናጤን እንደ ሀገር አሳሳቢ ሀገራዊ ኪሳራ መሆኑን ያሳያል፡፡ 

3. በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ለሚፈጸመው ሰቆቃና አንገብጋቢ ችግር መፍትሄው ዜጎቹ ከዚያ ሀገር የሚወጡበትን ስራ ማፋጠን እንደሆነ አድሃኖም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኞች ላይ የሚፈጸመውን የኃይል እርምጃ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ግድያና ማሰቃየት ማስቆም ጊዜ የማይሰጠው አጣዳፊ፣ ወሳኝ፣ አንገብጋቢ እና ክብደት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥ አድሃኖም ይህንን ጉዳይ በሚመለከት እንደሚከተለው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ “በእርግጥ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት የረዥምና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎችን በመንደፍ ጥረት ስናደርግ ቆይተናል፣ ምክንያቱም እነዚህ ችግሮች ለብዙ ጊዜ የቆዩና ስር የሰደዱ በመሆናቸው ነው“ በማለት አስተያየታቸውን ቋጭተዋል፡፡ እርግጥ ነው የረዥምና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎች ሊቆዩ ወይም ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ ወሮበሎች እና ህገወጦች በየዕለቱ እየተፈጸሙ ያሉ የውርደት ሰራዎች፣ ህገወጥ አያያዞች፣ ፍትህአልባነት እና ወንጀሎች በእንዲህ ያለ ሁኔታ ሊቆዩ በፍፁም አይችሉም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየተፈጸመ ያለው መጠነሰፊ ኪሳራ ነው፡፡ ስቅይቱን በፍጥነት ለማስቆም አድሃኖም ምንም ዓይነት ሀሳብ የሌላቸው እና መፍትሄዎችን ያላመላከቱ በመሆኑ ይህ አንገብጋቢ አገራዊ ኪሳራ ነው፡፡ 

አድሃኖም እንዲህ ይላሉ፣ በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ትዮጵያውያን/ት ስደተኞች ላይ “እንዲህ ያለ ድርጊት ይፈጸማል ብለን በምንም ታምር አልጠበቅንም“፣ እንዲህም ይላሉ ለእራሳቸው፣ “ሁሉም ነገር የሚያስደንቅ ነው“፣ በመቀጠልም እንዲህ ይላሉ፣ “የረዥምና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎችን ለማምጣት ለብዙ ጊዜ ጥረት አድርገናል“፡፡ ይህ የተምታታ እና የተዘበራረቀ አባባል እርስ በእራሱ የሚጣረስ ብቻ አይደለም፣  ሊታመን በማይችል መልኩ አሳሳች መግለጫ እና የአድሃኖምን የዋህነትና የዲፕሎማሲ  እውቀት እጥረትና ችሎታ ማጣት የሚያሳይ መገለጫ እንጅ፣ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮያውያንን/ትን ሁኔታ በሚመለከት “ሁሉም ነገር የሚያስደንቅ ነው“ የሚለው የአድሃኖም አባባል ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2013 አድሃኖምና የእርሳቸው ገዥው አካል  የሳውዲ አረቢያ ገዥ በሀገሩ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ገብተው ምንም ዓይነት ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው በሀገሩ የግዛት ክልል ውስጥ የሚገኙ የውጭ አገር ሰራተኞችን ህጋዊ ለማድረግ ወይም ደግሞ ወደየመጡባቸው አገሮች እንዲመለሱ እና ህገወጥ ማባረር፣ እስራትና ስቅይትን ለማስቀረት በማለት ያስተላለፈውን ትዕዛዝ በሚገባ ያውቃሉ፡፡ የአድሃኖም ገዥው አካልም በተመሳሳይ መልኩ በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ምንም ዓይነት ህጋዊነት  ሳይኖራቸው የሚሰሩና የሚኖሩ በርካታ ህገወጥ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት እንዳሉ ከማመናቸውም በላይ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሳውዲ ገዥ እ.ኤ.አ በጁላይ 2013 በሀገሩ ውስጥ የሚገኙትን ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸውና ምንም ሰነድ የሌላቸውን የውጭ አገር ዜጎች በማስመልከት ህጋዊ እንዲሆኑ ወይም ሀገር ለቀው እንዲወጡ አጽንኦ በመስጠት እ.ኤ.አ እስከ ኖቬምበር 2013 ድረስ ቀነ ገደብ መስጠቱን አድሃኖምና ገዥው አካላቸው በሚገባ ያውቁታል፡፡ ግና የአድሃኖም ገዥ አካል ከመስማት ባለፈ የአዋጁን እንደምታና ወደፊት በስደተኛ ዜጎቹ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ ጉኑ ሊያየው ስላልፈለገ የወደፊቱን ማቀድም አልቻለም፣ በቀጣይነት በገፍ ወደ ሳውዲ አረቢያ በሚጓዙ ዜጎች ላይ እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ ፖሊስና ወሮበሎች በቀጣይነት ስለሚደረገው ጥቃት የሚሉት ነገር አልነበራቸውም፡፡ በአጭሩ ምንም ነገር ሳያደርጉ እጃቸውን አጣጥፈው በመቀመጥ ሲመለከቱ በከንቱ ሳይጠቀሙበት ጊዚያቸውን አባክነዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2013 በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ዜጎች ላይ ማህበራዊ ቀውስ ይደርሳል የሚለውን ሁኔታ እንዴት አድሃኖም በእርግጠኝነት መተንበይ አልቻሉም ይቻላል? 

Police-Addisአድሃኖም ፈጣን የፖሊሲ እርምጃ ለመውሰድ ብቃት የሌላቸው ሰው መሆናቸውን የድርጊቶች ኩነት በተጨባጭ ያሳያል፡፡ እንደ “ቁንጮ የዲፕሎማሲ ሰው” ብዙ መማር ይጠበቅባቸዋል፣ እንዲሁም ወደፊት ሊከሰቱ በሚችሉ ነገሮች ላይ ትኩረት በመስጠት የነገሮችን የአመጣጥ ሁኔታና ችግሮችን አስቀድሞ በማየት ተጨባጭ መፍትሄ ለማምጣትና ወደተግባር ለመፈጸም የሚያስችል ብቃትን ሊጎናጸፉ ይገባል፡፡ ፈላስፋው ጎቴ የሚከተለውን ሲል እውነትም ትክክል ነበር፣ “ምንም  ድንቁርናን በተግባር ከማየት የበለጠ አስደንጋጭ ነገር የለም ብሏል:” 

አድሃኖም ያልተናገሩት ወይም ያላደረጉት፤ 

በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የኃይል እርምጃ ለማስቆም የኢትዮጵያ ገዥው አካል ስላደረገው ሁኔታ አድሃኖም አንድም ያሉት ነገር የለም፣ ሆኖም ግን አገዛዙ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ዘለቄታዊ መፍትሄ ለመስጠት የረዥም እና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎችን ለማምጣት ብዙ ርቀት የተጓዘ መሆኑን ከመግለጽ ውጭ ተጨባጭነት ያለው እርምጃ አልታየም፡፡ በተጨባጭ እየሆነ ያለው ግን አድሃኖም እና ገዥው አካላቸው አትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ዜጎቻቸው በሳውዲ አረቢያ መንገዶች እንደ አውሬ እየታደኑ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጸምባቸው ከዳር ቆመው ጣቶቻቸውን በመቀሰር፣ ጭንቅላቶቻቸውን በመነቅነቅ ከመታዘብ ውጭ ሌላ መገለጫ የለውም፡፡ አድሃኖም በዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የኃይል እርምጃ ለማስቆም ምንም  ጥረት አለማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን ትንሿን ነገር ለዓም አቀፉ ማህብረሰብ በማሳወቅ በሳወዲ አረቢያ መንግስት ላይ ጫና እንዲደረግ እንኳን ሙከራ አላደረጉም፡፡ አድሃኖም ካልተናገሯቸው ወይም ካልፈጸሟቸው ጉዳዮች ውስጥ ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ 

በጠንካራ ቃላት የተዘጋጀ የውግዘት መግለጫ፤ አድሃኖም እንዲህ ብለዋል፣ “ገዥው አካል የሳውዲ አረቢያ መንግስት በግዛት ክልሉ ውስጥ ባሉ ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎቻችን ላይ ያደረሰውን ጭካኔ የተሞላበት የኃይል እርምጃ እናወግዛለን፣ ይህ በምንም ዓይነት መልኩ ተቀባይነት የለውም፣ የሳውዲ መንግስት ለጉዳዩ አጽንኦ በመስጠት ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ እናደርጋለን፣ ዜጎቻችን ባሉበት በክብርና በመልካም ሁኔታ እንዲያዙ ሆኖ ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን“ የሚል ነበር፡፡ “ተቀባይነት የለውም“ የሚለው ቋንቋ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል፣ በፖሊስ ኃይሉ እና በወሮበሎች እየተፈጸመ ያለውን ዘገናኝ ጭካኔ፣ ለመናገር የሚዘገንን አረመኔነት፣ አስደንጋጭ ስቅይትና ወንጀለኝነት ለመግለጽ የሚጠቀሙበት የውግዘት ቃል ነው፡፡ እንደ አድሃኖም ግንዛቤ “ምርመራ“ ማለት የሳውዲ ገዥ ክፍል ከዚህ ከተፈጸመው ዘግናኝ ወንጀል አንጻር ጠንካራ እርምጃ ተወስዶ ማየት ነው፡፡ 

አድሃኖም “ተቀባይነት የለውም“ የሚለውን ቋንቋ በውል የተገነዘቡት አይመስልም፡፡ ይህ አባባል በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ የዲፕሎማሲ ሰዎች ምንም ነገር ሳይሉ አንድ ነገር እንዳሉ በማስመሰል የሚጠቀሙበት ባዶና መሰረት የለሽ ቃል ነው፡፡ ሁሉንም ነገር የሚል ትርጉም የያዘ ቃልም ነው…”ምንም ዓይነት ጠንቅ የለዉም አይኖረዉም ማለትም  ነው”:: እንደዚህ ነው እንግዲህ የዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ  ባህሪያት፡፡ አንድ መስመር ዓረፍተ ነገር ሁለት የማይገናኙ ዓላማዎችን ሊያስተላልፍ የሚችል መልዕክት ሊኖረው ይችላል፡፡ በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ አትዮጵያውያን/ት ላይ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት “ተቀባይነት የለውም” የሚል መልዕክት ለሳውዲ አረቢያ አምባሳደር በማስተላለፍ አድሃኖም በጉዳዩ ላይ የይስሙላ ስራን በመስራት ጉዳዩ አስኪረጋጋ ድረስ መጠቀሚያ ያደርጉታል፣ ከዚያ በኋላ ግን ሁሉቱም ወገኖች ወደነበሩበት ግንኙነት ተመልሰው የመሞዳሞ ስራቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ቃሉን በትክክል ለመግለጽ “ተቀባይነት የለውም” የሚለው ቃል ብልህነት የጎዳላቸው ፉከራና ባዶ ኳኳታ በሚያሰሙ ምንም ነገር እና አንድም ነገር የማያደርጉ ሰዎች መገለጫ ነው፡፡ 

የጥገኛውን ሀገር አምባሳደር በመክሰስ የብጥብጡን ሁኔታ እንዲረዳና በፖሊስና በህገወጦች የሚፈጸመውን ህገወጥ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲያስቆም ማድረግ፡ አድሃኖም የሳውዲ አረቢያ አምባሳደርን በመክሰስ እንዲህ ብለዋቸዋል፣ “የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህገወጥ ስደተኞችን ለማስወጣት የተከተለውን መርህና የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣኖች በህገወጥ ስደተኞች ላይ የወሰዷቸውን እርምጃዎች በተመለከተ ኢትዮጵያ ታላቅ አክብሮት አላት፡፡ እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ የተወሰደውን ህገወጥ አያያዝና ግድያ ታወግዛለች“ ይላል፡፡ ግን ሰው  ምን ዓይነት አሽከርነትና ጫማ ላሽነት ውሰጥ ይዘፈቃል?! ለዜጎቹ የሚቆረቆር በምድር ላይ የሚኖር ማንም አገር ቢሆን የራሱን ዜጎች የስቃይ ሰለባ ላደረገ ሌላ አገር በምንም ዓይነት መልኩ ቢሆን “ክብር አለው” የሚል ቃል አይተነፍስም፡፡ አድሃኖም በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ ያላቸው አይመስልም፣ ምክንቱም ጉዳዩ ስለሳውዲ አረቢያ የግዛት ሉዓላዊነት ወይም ስለስደተኞች ፖሊሲ ጉዳይ አይደለም፣ ጉዳዩ የሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኛ ዜጎች ላይ እየፈጸመ ስላለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ተገቢውን እርምጃ የመውሰድና ያለመውሰድ ጉዳይ ነው፡፡ 

ከዚህም በላይ አደሃኖምም ሆነ ወይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ከሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር የሚኖርን ተቃውሞ በይፋ ለህዝብ አላሳወቁም፡፡ “የተቃውሞ ደብዳቤ” ወይም “የዲፕሎማቲክ ማስታወሻ” የአንድ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሌላው ጥፋት ለፈጸመው መንግስት ይቅርታ የማይደረግለትን የማይናወጥ አቋም በመግለጽ በይፋ ያሳውቃል፡፡ የተቃውሞ ደብዳቤው በምንም ዓይነት መልኩ ቢሆን “ተቀባይነት የለውም” የሚል ቃል አይጠቀምም፡፡ በጥቂቱም ቢሆን ስለ “”አሳሳቢ ጉዳዮች” እና ነገሮች መሻሻል ካላሳዩ ወደፊት “ጉዳት ሊያመጡ” የሚችሉ ጉዳዮችን በመጥቀስ ሊያሳውቅ ይችላል፡፡ አድሃኖም እንዳደረጉት እንቁጠረውና የተቃውሞ ደብዳቤ ለሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጻፉ መሆኑን ለህዝብ ይፋ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ 

በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በሚመለከት የአፍሪካ ህብረት የውግዘት መግለጫ እንዲያወጣ ማድረግ፤ እ.ኤ.አ በ2015 አስከሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ ድረስ የአድሃኖምን ወንበር እያሟሟቁ የሚገኙት የይስሙላው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያ ደሳለኝ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት የዝውውር ሊቀመንበር ናቸው፡፡ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአፍሪካ መሪዎች ላይ የዘር አደን ይፈጽማል በማለት የዘር አደናውን ለማስቆም የአፍሪካ መሪዎችን በማሰባሰብና በማስተባበር ቆላ ደጋ በማለት ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ እና እንዲያውም የህብረቱ አባል አገራት የሮማ ስምምነተን በመጣስ ከአይሲሲ አባልነት እንዲወጡ በመሃንዲስነት ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸወ የሚታወስ ነው፡፡ ነገር ግን በመቶዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ የአገራቸው ዜጎች በሳውዲ አረቢያ መንገዶች በፖሊሶች፣ በወሮበሎችና በህገወጦች “የዘር አደና” ጥቃት ሲፈጸምባቸው ትንፍሽ አላሉም፣ የጎመንዘር ቅንጣት የምታክል ድርጊት አልፈጸሙም፡፡ (በነገራችን ላይ ይህ ሁሉ ስቃይ በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ ሲፈጸም የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአገር ውስጥ ነበሩን? ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ “የዘር አደን” እየተፈጸመባቸው መሆኑን አስመልክቶ ቃል ትንፍሽ ሲሉ የሰማ ይኖራልን?) 

አስቸኳይ ምርመር እንዲካሄድ ለተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ኮሚሽነር ማሳወቅ፣ ዩኤንኤችሲአር/UNHCR በተባበሩት መንግስታት በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት “ዓለም አቀፍ የስደተኞችን ጥበቃ ማድረግና በስደተኞች ችግር ላይ ውሳኔ የመስጠት እንዲሁም ስደተኞችን የመምራትና የማስተባበር ስራ” ያከናውናል፡፡ ስደተኞች አግባብ ባልሆነ መልክ ሲያዙና የሰብአዊ መብት ጥሰት ካለ የመመርመር ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ አድሃኖም UNHCR ጉዳዩን እንዲመረምረው መጠየቃቸውን የገለጹበት ሁኔታ የለም፡፡ ምናልባትም ጥያቄ አቅርበው ከሆነ መጠየቃቸውን የሚገልጽ መረጃ አልቀረበም፡፡ 

እንዲህም ሆኖ UNHCR ስደተኛ ሰራተኞችን ግጭት ከተከሰተበት ቦታ ወደ ሌላ ለማዘዋወር የሎጅሰቲክስ እርዳታ ብቃት አለው፡፡ ለምሳሌ ያህል እ.ኤ.አ በ2011 በሊቢያ ጸረ መንግስት አመጽ በተቀሰቀሰ ጊዜ UNHCR በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኛ ሰራተኞችን ከሊቢያ ወደ ጎረቤት አገሮች በማመላለስ የተቀላጠፈ ስራ ሰርቷል፡፡ 

ጉዳዩ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር/UNHCR እና በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ጽ/ቤት/OHCHR ቀርቦ እንዲጣራ ቅሬታን ማስመዝገብ፤ ከOHCHR ዋና ዋና ተግባራት መካከል “የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ማጣራት” እና “የሰብአዊ መብት ጥበቃ ስራዎችን ማከናወን” ናቸው፡፡ የማጣራት ስራውን እንዲሰራ የሳውዲ ገዥ አካልን ከመጠየቅ ይልቅ አድሃኖም እንዲያጣሩትና ጣልቃ እንዲገቡ UNHCR እና OHCHRን መጠየቅ ነበረባቸው፡፡ 

የኢትዮጵያ ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ መፍቀድ፤ ኢትዮጵያውያን/ት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ላይ በተፈጸሙባቸው እና እየተፈጸሙባቸው ባሉት የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ምክንያት ተዋርደዋል፣ ሀፍረትም ደርሶባቸዋል፡፡ አድሃኖም በኢትዮጵያ ጥገኝነት እንዲጠይቁ ነብዩ መሀመድ ተከታዮቹን ወደ ኢትዮጵያ ልኮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአንድ ወቅት ጥገኘነት የሚጠየቅባት ምቾትና እርዳታ የሚደረግባት ቅዱስ ቦታ ነበረች፡፡ ኒልሰን ማንዴላና ሌሎች የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ አመራሮች እ.ኤ.አ በ1962 ስልጠና ለመውሰድ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፡፡ በአጼ ኃይለ ስላሴ ልዩ ትዕዛዝ መሰረት ኒልሰን ማንዴላ የኢትዮጵያ ፓስፖርት እንዲሰጣቸው ተደርጎ ያለምንም ችግር ዓለምን ሲዞሩ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ኢትዮጵያውያን/ት በዓለም ላይ የሚከበሩና የሚሞገሱ ነበሩ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደካሞችና በባርነት የሚገዙ ሆነዋል፡፡ ያሰቡትን በመናገራቸው ይደበደባሉ፣ ይታሰራሉ፡፡ አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት ሲሞክሩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊስ በሀገሩ ኢትዮጵያውያንን/ትን ባስተናገደበት መጥፎ አያያዝ ሞዴልነት በተመሳሳይ መልኩም በአዲስ አበባ እንዲደረግ ሆኗል፡፡ ተዋርደዋል፣ ርህራሄ በጎደለው መልኩ ተደብድበዋል፣ በቁጥጥር ስርም ውለዋል፡፡ የገዥው አካል አፈቀላጤ የሆነው ሽመልስ ከማል ገዥው አካል በሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል ብሏል፣ ምክንያቱም ይላል፣ “አብዛኞቹ ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች በኢትዮጵያና በሳውዲ አረቢያ መካከል ጸንቶ የቆየውን ጠንካራ ግንኙነት የሚያበላሽና ጸረ አረብ የሆኑ መልዕክቶችን የያዙ በመሀናቸው ነው::”

ማንም ቢሆን ከሚቀርበው ጓደኛው ጋር የመስታወት ላይ ጠብ ያደርጋል የሚል ግምት የለኝም፡፡ አድሃኖምና ገዥው አካል እንዲያስታውሱት የምፈልገው ነገር…”ለመበሳጨት ዘገምተኛ የሆነውን እሱን ተጠንቀቁ፣ ለመምጣት ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ፣ ከመጣ ደግሞ ኃይለኛው እርሱ እንደሆነ እና ለብዙ ጊዜ የሚቆይ ነው፡፡ የተዋረደ ትዕግስተኝነት ወደ ቁጣ ይቀየራል::” 

የአጣዳፊ ሁኔታውን ለመስራት ልዩ ግብረ ኃይል አያስፈልግምን? ኢትዮጵያ በሳውዲ አረቢያው እንደደረሰባት ዓይነት ኪሳራ በሚደርስባት ጊዜ ለዜጎቹ የሚያስብ ገዥ አካል ተገቢውን ምላሽ ለመስጠትና ለማስተባበር የአስቸኳይ ጊዜ ማስፈጸሚያ ግብረ ኃይል ያቋቁማል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች ተመላሽ ስደተኛ ወገናቸውን ለማገዝ  እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እገዛ እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ፡፡ አነዚህ አልተደረጉም:: በሳውዲ አረቢያ ያለው የኢትዮጵያውያን/ት ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያልፋል፣ ስለዚህም ብዙ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለሳውዲ አረቢያ ኢንቨስተሮች በመስጠት የተለመደው ቢዝነስ በተለመደው ሁኔታ ይቀጥላል የሚል ስሌት በአድሃኖምና በገዥው አካል አቅዋም የተያዘ መሆኑም ይገልጣል፡፡ 

አድሃኖም ወደፊት አንደሚሉ ፤

አድሃኖምና ገዥው አካል ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱትና ለሚቋቋሙበት የተመደበውን 50 ሚሊዮን ብር ተመድቧል ብለዋል:: ይህ ከባልዲ ውኃ አንዷ ጠብታ ናት፡፡ ይህም ገንዘብ ወደ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይሆናል፡፡ በዚህች በጣም ትንሽ በሆነች 2 ሚሊዮን ዶላር 200 ሺ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ ከስደት ተመላሾችን ለማስፈር፣ ለማዘዋወርና ለማጓጓዝ የሚያስችል አይደለም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ገዥው አካል ይህን ያህል ገንዘብ ለእነዚህ ተግባራት ተብሎ የተያዘ ለመሆኑ ማረጋገጫ የለም፡፡ እ.ኤ.አ ጁላይ 2013 የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎች ተልዕኮ መግለጫ መሰረት ኢትዮጵያ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ለምታስገባቸው ሸቀጦችና አገልግሎቶች ለሶስት ወራት ብቻ ሊያቆይ የሚያስችል የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዳላት ይፋ አድርጓል፡፡ 

አድሃኖምና ገዥው አካል ብዙም ሳይቆዩ ተመላሽ ዜጎቸን ለማጓጓዝና ለማቋቋም የልመና ኮሮጃቸዉን አንጠልጥለው ወደ ዓለም አቀፉ የመንገድ ልመና መውጣቸው የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥ የሚገኘውን እርዳታ ለመቀራመት የሚችሉ የራሳቸውን አትራፊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አስቀድመው ያቋቁማሉ፡፡ አድሃኖም ይለምናሉ፣ እንዲህ በማለት፣ “ከሳውዲ አረቢያ ለሚመለሱ ስደተኛ ዜጎች ገንዘብ በጣም ብዙ ገንዘብ እንፈልጋለን፡፡“ ጋሻጃግሪዎቻቸው በህዳሴው ግድብ ወይም በሌላ መልክ እንደሚጠሩት እንዳደረጉት ሁሉ በዓለም ዙሪያ በመሰማራት ኑስ ሳንቲም ሳይቀር ልመናቸውን ያጧጡፋሉ፡፡ ለገዥው አካል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶች ይህ ሁኔታ ንፋስ አመጣሽ ዘረፋ ነው፡፡ በልመናው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደሚገኝ በመገመት እነዚህ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እጃቸውን በማሻሸት እና ለሀጫቸዉን በማንጠባጠብ ሰፍ ብለው ይጠባበቃሉ፡፡ ግን በልመና ብዙ ዕርዳታ ላያገኙ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ነው በሳውዲ አረቢያ መንገዶች ላይ እጃቸውን በመዘርጋት ምጽዋት፣ ቢለምኑ አልደነቅም ያልኩት፡፡ 

ለኢትዮያችን አለቅሳለሁ፣ ለውዲቷ አገሬ! ግን “ከዋሻው መጨረሻ ብርሃን አለ“ 

አድሃኖም እንዲህ አሉ፣ “ከዋሻው መጨረሻ ብርሃን አለ፣ እና ይህን እውን እንደምናደርገው እናውቃለን፣ እና ድህነትን ተረት እንደምናደርገው ጥርጥር የለንም”፡፡ እኔ ደግሞ እላለሁ በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ከዘውዳዊነትና ከአምባገነንነት ዋሻ መጨረሻ ብርሃን አለ፡፡ ከአድማስ ባሻገር አዲስ ቀን አለ፡፡ መደጋገፍ አለብን፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን ሁለት አስርት ዓመታት እና ከዚያ በላይ ከዘለቀው የጭቆና እና የመሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች እጦት ዋሻ ውስጥ ተጉዘን በድል አድራጊነት መውጣት አለብን፡፡

በሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን/ት ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ አስመልክቶ የተዘጋጁትን የእኔን ትንታኔዎች ያነበበ ሁሉ እኔ በጣም ህግ አጥባቂና ሲበዛ ትንታኔ ሰጭ እንደሆንኩ ሊናገር ይችላል፡፡ እንዲያውም ታላቁን የሰው ልጅ ሰቆቃ “ለመፈላሰፊያ ትምህርታዊ ክህሎት” አውሎታል ብለው ሊከሱኝ ይችላሉ፡፡ ይህን ሊሉ ይችላሉ ምክንያቱም ለዚህች ተወዳጅ አገሬ ምን ያህል እንዳለቀስኩና ምን ያህል ተስፋ እንደቆረጥኩ ስለማያውቁ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1948 በዚሁ ዓመት አፓርታይድ በአፍሪካ ህግ ሆነ፣ አላን ፓቶን እንዲህ ሲል ጻፈ…”ውዷ ሀገሬ አልቅሽ“… እና በደቡብ አፍሪካ ዕጣ ፈንታ ላይ ያለውን የታሟጠጠ ተስፋ ገለጸ፡፡ የእኔም በኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ላይ ያለኝ ተስፋ ፓቶን ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ፓቶን ሲጽፍ፣

ለተገነጣጠለው ጎሳ፣ ለወደቀው ባህልና ህግ አልቅስ! አዎ! ለሞተው ሰውዬ ድምጽህን ከፍ በማድረግ አልቅስ፣ ፍቅሩን ላጣችው ሴትና ለልጆቹ አልቅስ፡፡ ለውድ ሀገርህ አልቅስ፣ እነዚህ ነገሮች በእራሳቸው የመጨረሻ አይደሉም፡፡ ፀሐይ በመሬት ላይ ብርሀኗን ትፈነጥቃለች፣ በተወዳጁ መሬት ሰው ባልተደሰተበት ላይ፡፡ የልቡን ፍርሃት ብቻ ያውቃል፡፡ 

አኔም በኢትዮጵያ “ለተበጣጠሰው ጎሳ” አለቅሳለሁ፡፡ ከሰውነት በታች ሆነው በሳውዲ አረቢያ ለሚሰቃዩት ወንድሞቸና እህቶቸ በዝምታ አለቅሳለሁ፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚደፈሩት፣ ለሚደበደቡት እና በመስኮት ለሚወረወሩት፣ ከጣራ እና ከዛፍ ላይ ተሰቅለው ለሚሞቱትና በፈላ ውኃ ሰውነታቸውን ለሚጠበሱት እህቶቸ አለቅሳለሁ፡፡ በሳውዲ ሌባ ጭንቅላቱን ለሚበረቅሰው ወጣት አለቅሳለሁ፡፡ ነጻነት በማጣታቸው እና በሀገራቸው መብት እንደሌላቸው በመቆጠራቸው ምክንያት ሀገር ጥለው ለመሰደድ ለሚገደዱት ወጣት ወንዶች እና ሴቶች አለቅሳለሁ፡፡ ህይወታቸውን ለማሻሻል በማሰብ የየመንንና የሳውዲ አረቢያን በረሀዎች ሲያቋርጡ በሞት ለተለዩ ኢትዮጵያውያን አለቅሳለሁ፡፡ በየዕለቱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሲኦሉ ሳውዲ አረቢያ ለሚበሩ ወጣት ኢትዮጵያውያት ቆነጃጅት አለቅሳለሁ፡፡

የ2005 ሀገራዊ ምርጫን ተከትሎ በኢትዮጵያ በየጎዳናው በግፍ ለተገደሉት ወጣት ወንዶችና ሴቶች፣ እንዲሁም አባቶች እና እናቶች አለቅሳለሁ፡፡ ለእህቴ ለርዕዮት ዓለሙ እና ለወንድሞች ለእስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ፣ አቡበከር አህመድ፣ እና በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች አለቅሳለሁ፡፡ መሪ በመምሰል በባዶ ልብስ ለተጀቦኑትና በሙሰኛ ሌቦች መዳፍ ስር ለወደቁት ኢትዮጵያውያን/ት አለቅሳለሁ፡፡

አዎ አለቅሳለሁ እናም አለቅሳለሁ፣ “ልቅሶዎቸ ያልተሳኩ ቢሆንም“ ለውዲቷ አገራችን አለቅሳለሁ፣ ግን እኮ ጩኸታችን ይሰማል፣ ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ የአምባገነንነት ዋሻ ወጥቷል፣ ኒልሰን ማንዴላም ቃል ገብተዋል…”በፍጹም በፍጹም እና በፍጹም ይህች የተዋበች መሬት ተመልሳ የአንዱ በአንዱ ላይ መጨቆኛ አትሆንም፣ ክብር የታጣባት የተዋረደች ዓለም አትሆንም“::

ኢትዮጵያውያን/ት እንደገና ክብራቸውን ይቀዳጃሉ፣ እና በአገር ውሰጥም ሆነ በውጭ የተከበሩ ይሆናሉ፡፡ “የዓለም ተዋራጂ” ሆነው አይቀጥሉም፡፡ እና በጥልቅ ከልብ አምናለሁ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች፣ እንደገና አናለቅስም፣ ሀሴትንም እናደርጋለን፡፡

የወያኔ በዲሞክራሲ ቁማር እስከመቼ? -በአሸናፊ ንጋቱ

$
0
0

በአሸናፊ ንጋቱ

በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግስት የዛሬ 22 ዓመት አንግቦት የነበረውን የዲሞክራሲ መፈክር በማየት ዲሞክራሲ የጠማው የኢትዮጵያ ህዝብ የደስታ ጮቤ በመርገጥ ነበር የተቀበለው፡፡ ነገር ግን ይህ መፈክር ድራማ መሆኑ እየዋል እያደረ ነበር እየተጋለጠ የመጣው። ጮቤ እየረገጠ፤ ትግሉን ተቀላቅሎ መስዋት የከፈለውን ህዝብ የቁልቁል ወደ ባሰ የመከራ ማጥ ከቶታል።
Woyanes shoud face justiceወያኔ እራሱ ህግ አውጥቶ እራሱ የማፍረስና በህጉ ያለመገዛት አባዜ የተጠናዎተው አንባገነን ስርአት መሆኑ በሃያ ሁለት አመታት የስልጣን ጉዞው አስመስክሯል፡፡ በትክክል እንደ ህገ-መንግስቱ ቢሆን ኖሮ ህገ-መንግስት የህጎች ሁለ የበላይ ህግ ነው፡፡ነግር ግን ወያኔ ያለምንም ከልካይ እንዳሻው ያለ ህዝብ ተሳትፎ ለስልጣናቸው እርዝማኔ ይመች ዘንድ ሲዘርዙትና ሲደልዙት ይስተዋላል፡፡ ሲፈልግ ስልጣን መብት ሲሰጥህ/ሽ ሳይፈልግ ደግሞ ሲከለክልህ/ሽ በስመ ዲሞክራሲ እየነገደ የሚኖር የማፍያ ስርአት ነው፡፡ የአምባገነን መንግስታት መለዬ በሆነው ሃይልን እየተጠቀመ በመግደል፤ በእስር፣ በመሳርያ እና በዱላ እያስጨነቀ የህዝቡን ስነ ልቦና በማድከም የስልጣን ቆይታውን ማርዘምም የስርአቱ ዋና አላማ፡፡ እንዲህ አይነቱ አምባገነንና በዲሞክራሲ ስም ህዝባችን ላይ ቁማር የሚጫዎት ስርአት ለኢትዮጵያውያችን አያስፈልግም፡፡ ስለዚህ ይህንን በጨካኝኔ የተሞላ ስርአት ከሃገራችንና ከህዝባችን ጫንቃ የምናስወግድበት ሰአት አሁንና አሁን ብቻ ነው።

በዲሞክራሲ ቸነፈር መመታታችን ሳያንሰን አገር አልባ ለመሆን በተቃረብንበት እና ማንነታችን ጥያቄ ውስጥ በገባበት በዚህ ጊዜ ዲሞክራሲን መናፈቃችን ብቻ ተፈጥሮአዊ አያደርገንም፡፡ በተፈጥሮ ያገኘነውን ነፃነት በተግባር ስናስጠብቅ ብቻ ነው፡፡ ይህ ሁሌ ፍዳና መከራ የሆነው በሃገራችን ላይ በጣም ገኖ ከእኔ በላይ ላሳር በማለት በሃይል በጉልበት በስልጣን ላይ በተቀመጠው የወያኔ ስርአት ነው፡፡ የወያኔ ስርአት ስልጣን ከያዘ ቀን ቀንን እየተካ፤ ሳምንት ሳምንታትን እየተካ፤ ወር ወራትን እየተካ፤ አመት አመታትን እየተካ ይኸው እነሆ 22 አመታችንን አስቆጠርን፡፡ በዚህ 22 ዓመት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ለዲሞክራሲ፤ ፍትና ነፃነት የዘመሩ ዜጎች አልቀዋል፤ ለስደትም ተዳርገው የድራማው ሰለባ ሆነዋል፡፡ አሁንም ዝም ካልነው ሌላ ብዙ አስርት የመከራ አመታትን መጋፈጥ ሊኖርብን ነው፡፡ እስከመቼ ዝም እንደ ምንለው ግን ወገን አይገባኝም፡፡ አሁንም ህፃን፤ ወጣት፤ ጐለምሳና አዛውንት ወገኖቻችን ሲረግፍ፤ ሲሰደዱ ማየት ከሆነ ህልማችን መልካም! ግን ይህንን የሚያልምም ሆነ የሚመኝ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፤ ከራሳቸው ከወያኔ ሆዳደር ካድሬዎች በስተቀር፡፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ ይህንን መንግስት ዝም ብለን ልናየው አይገባም፡፡ ወይም እንደ ፈለገ ሊፈነጭብን ቦታ መስጠት የለብንም፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰው ጭቆናና በደል ይበቃል ልንለው የግድ ነው፡፡

በዲሞክራሲ እጦት ሃገራችንን ማስጨነቁ አልበቃው ያለው ይህ ክፉ ስርአት በአሁኑ ጊዜ የህዝባችንን ኑሮ ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎት ይገኛል፡፡ ህዝባችን በኑሮ ውጣ ውረድ ህይወቱ ሰላም አጥቷል። ወያኔ ስርአቱን የሚቃወሙትን ብሎም የዲሞክራሲ ጥያቄን ያነሱ ንፁሃን ዜጐችን መግደል፤ ማሰርና ማሰቃየት መለዬው ነው። ወያኔ ይህን ስትራቴጂ የሚጠቀመው ለሃገራቸው መልካም የሚመኙትን እና ለሃገር ይሰራሉ ተብለው የሚገመቱትን ሃገር ወዳድ ዜጐች ማጥፋት ከመፈለጉ የተነሳ ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ሁሌም ለሃገራቸው ደህንነት ለህዝባቸው ኑሮ የሚጨነቁ ስለሆኑ ስርአቱን የመደገፍ ፍላጎት ስለማይኖራቸውና እየፈፀመ ያለውን አረመኔ ተግባር ለህዝብ ሊያጋልጡብኝ ይችላሉ ብሎ ስለሚፈራም ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ሁኔታ የሚቀጠለው እንዴት ነው? ውድ ኢትጵያውያን በአሁኑ ጊዜ ህዝባችን ስቃይ ላይ ነው፡፡ ልንደርስለትና ከህዝባችን ጐን ተሰልፈን ነፃነታችን ማፋጠን ይገባናል፡፡

በስተመጨረሻም መጠየቅ የምፈልገው በዲሞክራሲ እየነገደ ያለው ይህ የወያኔ ስርአት በሃገራችን ገነባሁት፤ እያበበም ነው የሚለው የዲሞክራሲ ስርአት የቱ ይሆን?

በየትኛው ዲሞክራሲ፡ ነፃነትና ፍትህ ያለበት ሃገር ላይ ነው አንድ መንግስት ለ22 አመታት ሲገዛ ያየነው? ዲሞክራሲ፡ ነፃነት እና ፍትህ አሰፍናለሁ ብሎ ቃል የገባላትን እናት ሃገር ዛሬ ግን ድንበሯን በመሸራረፍ እየሸጧት፣ እየለወጧት ብሎም ህዝባችንን በኑሮ እሳት ረመጥ እያቃጠሉት፤ ነፃነቱ ቀርቶ የሃገራችንን ህዝቧን እየከፋፈሉ የብሄር ብሄረሰብ መብትን አስከብራለሁ እያሉ እርስ በእርስ ህዝቡን ማጋጨትና ማጨፋጨፉ ይሆን የሃገራችን ዲሞክራሲ መገለጫው?

ነው ወይስ ዲሞክራሲ ለወያኔ ህዝቡን መከፋፈል፣ እንደልብ እንዳይናገር ማፈን፣ መሬትን ያለባለቤቱ ፈቃድ እየነጠቁ መሸጥ፣ ሙስናን ተዋጋሁ እያሉ በሙስና ተጨማልቆ መገኘት፡፡ ይሄ ነው የወያኔ ዲሞክራሲና እና ፍትህ? የቆሰለችውን ኢትዮጵያ አድንሻለሁ ብሎ ለባሰ ህመም መዳረግስ ለምን!? እውነት ግን በተቃራኒው በቁስሉ ላይ እየሸነቆሩ ማድማት ነበር እንዴ አላማቸው? የተራባችሁትን ሰላም እና ዲሞክራሲ እሰጣችኋለሁ ብሎ ቃል የገቡለትን ህዝብ እልል ብሎ ሲቀበል፣ በታሪኩ አይቶት የማያውቀው የመከራ ጦስ መክተት ነበር እንዴ የወያኔ አላማ!? ስራቸውና ተንኮላቸው የገባው/ት ለምን ብሎ ሲጠይቅ/ ስትጠይቅ ወደ ወህኒ እና ወደ ሞት መጣል መሆን አለበት እንዴ የዚያ የምስኪን ህዝብ ለሰራው ውለታ መልሱ? ታዲያ የወያኔ ዲሞክራሲያዊ ግዛት ይኼ ነው?

ዛሬ ህዝባችን የተወለደበትን ምድርና ቀየ በሃይል በማስለቀቅ መሬቱን በኢንቨስትመንት ስም እየተሸነሸነ እየተሸጠ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ታዲያ ይሄ ጭቁን ህዝብ ምድሩን ለቆ ወዴት ይሂድ የትስ ይድረስ? ነው ወይስ ስርአቱ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ነው ቆርጦ የተነሳው? ወገኔ ሆይ ሃገር አለን ብለን የምንኮራው መቼ ይሆን? እስኪ መልሱልኝ፤ የቀን ከሌት ጥያቄየና በራሴ መልስም ለማግኘት ባለመቻሌ አንድ ብትሉኝና ለአምሮየና ለመንፈሰይ ሰላምን ባገኝ ነው ለዘመናት የሚመላለስብኝን ጥያቄዎች መሰንዘሬ፡፡ በእኔ በኩል ይህንን አፋኝና አምባገነን ስርአት ያለምንም ልዩነት በአንድ ልብ በቃ ልንለውና፤ በቁርጠኝነት ልንታገለው ይገባል ባይ ነኝ።

ድል ለጭቁኑ ኢትዮጵያ ህዝብ!!!

በአሸናፊ ንጋቱ

ለአስተያየትዎ: andethiopia16@gmail.com የኢሜል አድራሻየ ነው።

 

 

 

 

ስንቶች ሳይኖሩ ሞቱ ስንቶቻችንስ ነን ሳንኖር የምንሞተው? -ጌታቸው ከሰ

$
0
0

ጌታቸው ከሰ/አሜሪካ

(መሪ ቃሉን ፋሲል ተካልኝ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየን ከያኔ አብርሃም አስመላሽ ካቀረበው የግጥም መድብል አንዷን ስንኝ ወስጄ ነው የዛሬውን ጹሑፌ ያቀረብኩት ። ግጥሙን በሙሉ ለማንበብ የዘ-ሐበሻን ድሕረ-ገጽ ከፍተው ያንብቡ።)

እኔ የዚህ ጹሁፍ አቅራቢ በደርግ ዘመነ መንግሥት በአንድ ጊዜ በአራት የወንጀል ዓይነቶች ተጠርጥሬ ታስሬ በልዩ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ 214 ሀ እና ለ ወይም ንኡስ አንቀጽ 23 ተብለው በተጠቀሱ ድንጋጌዎች ይመስለኛል የሞት ፍርድና የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል ተከስሼ ነበር።ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል እንዲሉ በነዚህ ባለጊዜዎችም እንዲሁ ታስሬ በዋስ ተፈትቼ ጉዳዩ በተንጠልጠል ላይ እያለ ወደዚህ አገር ለመምጣት ችያለሁ። አፍላው የወጣትነት ዘመንና የጉርምስናውን ወቅት እናት አባት ባሉበት ከቤተሰብ ሳይለዩ ከአብሮ አደግና ከሰፈር ጓደኛ ጋር ጊዜን በደስታ ማሳለፈና ለአካለ መጠን ሲደርሱም ዲል ባለ አዳራሽ ወዳጅ ዘመዱ ተጠርቶ ጋብቻ መፈጸም አቅም በሚመጥነው ደረጃ ተመድቦ በመሥራት ወላጅን መጦር ቤተሰብን ማስተዳደር ሀገርን ማገልገል የሚባል ወዘባው ጠፍቶ ይህችን ጥቂት ጊዜ የምንቆይባትን አጭር እድሜም  በትግል ማሳለፍ አንድ አዲስ ትውልድ ተወልዶ ባደገበት አገር በትውልድ ቀየው ለሙያ ሳይበቃ በትምህርት ቤት ሕይወቱን በውል ሳያገናዝብ ጧት ወጥቶ ማታ ለመመለስ ዋስትና በሌለበት የባንዳ ልጆችና ብረት አምላኪዎች ተደራጅተው ሀገር በሚያውኩበት መፈጠርና የተንጠለጠለች ሕይወት ይዞ መኖር መኖር ሊባል ይችላልን? እኔ በሕይወት አለሁ ቢያንስ ያሳለፍኩትን የጨለማ ሕይወት አሁንም ያለሁበትን የባርነት ዘመን ኑሮ መናገር እችላለሁ ሳይኖሩ የሞቱ ሴት እህቶቼንና ወንድሞቼን ሳስብ እጅጉን ልቤ በሀዘን ቀስት ይወጋል።ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ- ሀገሬ ኢትዮጵያ-የኢትዮጵያን ሕዝብ የምወድ -ለሀገሬ እድገትና ብልጽግናን የምመኝና የምሠራ -እንዴት በትውልድ ሀገሬ መማር፤መሥራት ፤ንብረት ማፍራት ፤ ቤተሰብ መመሥረትና ቤተሰቤን ማስተዳደር፤ መጦር ያለባቸውን ወላጆቼ መጦርና በነጻነት መኖር ይነፈገኛል?እንደኔ የዜግነት መብታቸው ተገፎ የትውልድ ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ የተገደዱ ፤በሀገራቸውም ሌሊት ከመኖሪያ ቤታቸው እየታፈኑ ቀን ከሚሠሩበት የሥራ ገብታ  እየተዘረፉና በየጎዳናው እየታፈሱ እስር ቤት አጨናንቀው የሚገኙ እህትና ወንድሞቼ እውን በቁማቸው አልሞቱም? ሳይኖሩ መሞት ቢባል ስህተት ሊሆን ይችላልን? ወይንስ ይኸም ኑሮ ነው ሊባል ነው። ? ሕይወትን ለማትረፍ በሚደረግ ጥድፊያ የሰሃራን በርሃ ለማቋረጥ ሲሉ ስንቶቹ  ሕይወታቸውን አጡ ።ስንቶች ኢትዮጵያውያንን የዱር አውሬ በላቸው፤ስንቶችስ ውሃ እንደጠማቸውና መብላት እንደፈለጉ ሞቱ፤ስንቶቹስ በሞት አፋፍ ላይ ይገኛሉ?የወገንን ሕይወት ለማትረፍ እነማን ናቸው ግንባር ቀደም የቆሙት?እውነት ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ጠልተው ወይም ጠግበው የሚሰድዱ ይመስላችኋል?በፈላ ዘይትና ውሃ የሚቀቀሉት? በየዐረቡ መዲና ጎዳና ላይ በጥይት የሚገደሉትና ፎቅ ላይ ተጥለው ተከስክሰው የሚሞቱት ጠግበው ? ህጻናቶቹ የ15ና የ16 ዓመት ወጣቶች ሀገር ጥለው ሲወጡ በሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ ሴተኛ አዳሪነት እንኳን አልሆን ብሏቸው ሲሰደዱ ማንም የዐረብ ውርጋጥ ተቀብሎ ሲማግጥባቸው የሚሰማ ጀሮ የሚያስብ ሕሊና ላለው ይዘገንናል።«ኧረ ጎበዝ እኛን ኢትዮጵያውያንን ምን ነካን? ምን አይነቶቹ  ትውልዶች ነው የተፈጠርን»? ጠግበው እንደወጡ የሚፈርጅባቸው ማን ነው ምን አግኝተው ማን አብልቷቸው ጠገቡና ነው እንዴትስ ጠግበው የተሰደዱ የሚባሉት ኢትዮጵያን የመሰለች ሀገር ያለው ሰው ሀገሩን ይጠላል እንዴ? በጭራሽ ይህ የማይታሰብ ነገር ነው። ይልቅስ ጥሬ ሀቁን እንነጋገርበት ካልን እናንተም እኔም ምሥጢሩን በሚገባ እናውቀዋለን።ምናልባት ይህንም እንደሚሥጥር  ቆጥረነው ከእኛ ለተወለዱት በግልጽ ባለማሳወቃችን ጉዳዩ እንቆቅልሽ  ሊሆንባቸው ይችል ይሆናል ። አሁንም ሌላ ስህተት ፈጸምን ማለት ነው።መረገም ይሉታል ይህ ነው።

ዋናው የችግሩ መንስኤና ተጠያቂው ህወሃትና የህወሃትን ደም የተጣቡ አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት ኃይሎች ሲሆኑ ሌሎች ለዚህ ችግር መምጣት የመጀመሪያውን በር የከፈቱ ያደቆኑ ፤ያካኑ ዛሬም ያን ጮማ ምላሳቸውን እንዲያርፍ ያለደረጉ የትውልድ ማለቅ ያጀገናቸው ኤርትራን ያስገነጠሉ፤ህወሃትን እዚህ ያደረሱና በርጅና በህወሃት በር ደጅ እየጠኑ ህወሃትን የሚያበረታቱ የቀደምት የድርጅት አመራሮችና አባላትም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየቀለዱ ያሉ መሆናቸው ግልጽ ሊደረግና ሕዝቡ ሊያውቃቸው ይገባል።« በተለይም አማራውንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን» የኢትዮጵያ ኋላቀርነት፤ ድህነት፤ማይምነት፤የዴሞክርሲ መታፈን፤የዜጎች እኩልነት አለመከበር ምክንያት አድርገው የተነሱና ለኢትዮጵያ አንድነትና በነጻነት ተከብራ እንድትኖር ሳይታክቱ የታገሉትን እየታገሉም እያሉ በሽምግልናቸው እንኳ ርህራሄ ማድረግ ያልቻሉና የገደሉ (ክቡር ቢትዎደድ አዳነ መኮነንን ይመለከታል)፤የካቲት 1966ቱን የሕዝብ እንቅስቃሴ ያስማረኩና ህወሃትን ያነገሱ በስም ሕብረ-ብሔር በተግባር ግን የአማራን ዘር ለማምከን ከጧቱ የተነሱና የዘመሩ የመጡበትን መንገድ መመርመር አሁን ደግሞ መንገዳቸውን አስተካክለው ካልተጓዙ ያችን የጥፋት ካርዳቸውን ማሳየት ብቻ ሳይሆን እንዳለ የድርጅቶችን ተግባር እየመዘዝን መረጃውን እያወጣን ታቀቡ ልንላቸው ዝግጁ ነን።ምክንያቱም አሁን ላለው ትግል ተመክሮውም ሆነ አጠቃላይ መርሁ እጅግ የሚጎዳ በመሆኑ እንጅ ወደ ኋላ ተመልሶ የነገር ቋንጣ ለማመንዥክ ወይም ታግየበት ሳይጠቅመኝ ጉድ አድርጎኝ ቀረ በሚል ስሜት በመገፋትና ፀፀት አይደለም።

ችግርን አለማወቅ አንድ ችግር ሲሆን ችግሩን እያወቅን ችግሩን ማስወገድ አለመቻል ግን የጎርፍ  ውሃ እያሳሳቀ እንደሚወስደው ሰው እየሳቁ እንደመሄድ ነው የሚቆጠረው።

መተማመን ከሌለ እውነት አይኖርም” እውነት ከሌለ ፍቅር አይኖርም” ፍቅር ከሌለ ደግሞ ሰላምና አንድነት አይኖርም” ሰላምና አንድነት ሳይኖር ደግሞ የሚፈለገውን ዓላማ ከግቡ አደርሳለሁ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው።

መተማመን ፦ በአባትና ልጅ ፤ በባልና ሚስት ፤ በወንድማማች ፤ በእህትማማች ፤ በወንድምና እህት ፤ በአክስት አጎት ፤ በቤተዘመድ ፤ በአብሮ አደግ ጓደኛሞች ፤ በቤተክህነት በሚያገለግሉ የሃይማኖት አባቶች ፤ በመስጊድ በሚያገለግሉ ሸኮች ፤ በአንድ ዓላማ በተሰለፉ የድርጅት ሰዎች ፤ በመንግሥት ሥራ ተሠማርተው በሚሰሩ ሰራተኞች ፤ በስቪክ ማህበራት ፤ በንግድ ድርጅቶች ፤ በወታደሩ ፤ በደህንነቱ ፤ በፖሊሱ ፤በግብረ-ሰናይ ድርጅቶች(ኤንጅኦ) ፤ በሙያ ማህበራት ፤ በገበሬው…ወዘተ ከጠፋና የውሃ ሽታ ከሆነ ረጅም ዓመታት አለፉ።

እውነት፦ በአባትና ልጅ ፤ በባልና ሚስት ፤ በወንድማማች ፤ በእህትማማች ፤ በወንድምና እህት ፤ በአክስት አጎት ፤ በቤተዘመድ ፤ በአብሮ አደግ ጓደኛሞች ፤ በቤተክህነት በሚያገለግሉ የሃይማኖት አባቶች ፤ በመስጊድ በሚያገለግሉ ሸኮች ፤ በአንድ ዓላማ በተሰለፉ የድርጅት ሰዎች ፤ በመንግሥት ሥራ ተሠማርተው በሚሰሩ ሰራተኞች ፤ በስቪክ ማህበራት ፤ በንግድ ድርጅቶች ፤ በወታደሩ ፤ በደህንነቱ ፤ በፖሊሱ ፤በግብረ-ሰናይ ድርጅቶች(ኤንጅኦ) ፤በሙያ ማህበራት ፤ በገበሬው…ወዘተ በዓለማችን ከጠፋ ረጅም ዓመታት አለፉ።

ፍቅር፦ በአባትና ልጅ ፤ ባልና ሚስት ፤ ወንድማማች ፤ እህትማማች ፤ ወንድምና እህት ፤ በአክስት አጎት ፤ በቤተዘመድ ፤ በአብሮ አደግ ጓደኛሞች ፤ በቤተክህነት በሚያገለግሉ የሃይማኖት አባቶች ፤ በመስጊድ በሚያገለግሉ ሸኮች ፤ በአንድ ዓላማ በተሰለፉ የድርጅት ሰዎች ፤ በመንግሥት ሥራ ተሠማርተው በሚሰሩ ሰራተኞች ፤ በስቪክ ማህበራት ፤ በንግድ ድርጅቶች ፤ በወታደሩ ፤ በደህንነቱ ፤ በፖሊሱ ፤በግብረ-ሰናይ ድርጅቶች(ኤንጅኦ) ፤በሙያ ማህበራት ፤ በገበሬው …ወዘተ ከተወገደ  ረጅም ዓመታት አለፉ።

ሰላምና አንድነት፦ በአባትና ልጅ ፤ በባልና ሚስት ፤ በወንድማማች ፤ በእህትማማች ፤ በወንድምና እህት ፤ በአክስት አጎት ፤ በቤተዘመድ ፤ በአብሮ አደግ ጓደኛሞች ፤ በቤተክህነት በሚያገለግሉ የሃይማኖት አባቶች ፤ በመስጊድ በሚያገለግሉ ሸኮች ፤ በአንድ ዓላማ በተሰለፉ የድርጅት ሰዎች ፤ በመንግሥት ሥራ ተሠማርተው በሚሰሩ ሰራተኞች ፤ በስቪክ ማህበራት ፤ በንግድ ድርጅቶች ፤ በወታደሩ ፤ በደህንነቱ ፤ በፖሊሱ ፤በግብረ-ሰናይ ድርጅቶች(ኤንጅኦ) ፤በሙያ ማህበራት ፤ በገበሬው…ወዘተ  ከደፈረሰ ረጅም ዓመታት አለፉ።

በነዚህ ምክንያቶች የአገራችን ሉዓላዊነት ማስከበር ሳንችል ቀረን ፤ በእኩልነትና በመፈቃቀር ፤ በመተማመን ላይ የተገነባ አንድነት ለመፍጠር አልችል አልን ፤ ራሳቸውን ከሕግ በላይ ያደረጉ አምባገነን ወራሪዎችን ታግሎ መጣል ሲገባ እጅ መንሳትና አጎንብሶ መሄድን መረጥን ፤ በብዕራቸው ህወሃትን በሚያስጨንቁት ላይ ተሳለቅን ፤ ከህወሃት አፍንጫ ሥር ተደራጅተው እየታገሉ ያሉትን ህወሃት መጠነ ሰፊ ግፍ ሲፈጽምባቸውና ግፉ በዝቶ ሲፈስ ከሚገባው በላይ ሲሄድ እዚህ በላይ ማለፍ አትችልም ቁም ማለት ተሳነን። ይህ ሁሉ የህወሃት ጌቶች በደደቢት ህወሃትን ያደቆኑበት እኩይ መርህ መሆኑን እናውቃለን(ምዕራባውያንና ዐረቦች)። ዳሩ ግን ባርነትን መርጠናልና  በባርነት መኖርን የመረጠው በፈለገው መንገድ መሄድ መብቱ ነው። ጣልቃ መግባትና ማደናቀፍ ግን አይችልም መብቱ የለውም ጉዳዩ የሀገር የኢትዮጵያ ጉዳይ ነውና።ባርነትን አልቀበልም እታገለዋለሁ ያለ ደግሞ ባርነትን ሊያስወግድ የሚችለውን የትግል ስልት አንድነትን ሰንቆ መነሳት የግድ ይለዋል።በውጭ የሚገኘው ስደተኛ ኢትዮጵያዊ በአብዛኛው የመጣበትን ወይም ለስደት ያበቃውን ምክንያት ጠንቅቆ የሚያውቅ ይመስለኛል።በመሆኑም ነው ህወሃት በውጭ ድጋፍ እንዲያጣ ያደረገውና በዓለም ዙሪያ በየመድረኩ እየተሸነፈ የሚወጣው።ይህን ከዕለት ዕለት እንደ ሰደድ እሳት የሚቀጣጠል የሕዝብ እንቅስቃሴ የህወሃት ግብረ በላዎች ወይም በትናንሽ ንግድ ወይም በኮንዶኒየም ጎጆ ተደልለው ለስለላ የተሰለፉ ሊገቱት አለመቻላቸውና የህወሃት ሥርዓት ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን የሚያመለክት ነው።ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው ግን እላይ የጠቆምኳቸውን ችግሮች ተሸክሞ እየተጓዘ ነው። እንግዲህ እነዚያን የሰላም የአንድነትና የአብሮነትን መሠረታዊ እንቅፋቶች አስወግደን ብንቀሳቀስ ኖሮ ኢትዮጵያ የትና የት ትደርስ እንደ ነበር መገመት ያዳግትም።እዚህ ላይ የህወሃት ደጋፊዎችን ካነሳሁ ዘንዳ በውጭ ምን እንደሚሠሩ አንዳንድ ግልጽ መሆን ያለባቸውን ነገሮች ማስመር ካለብን ቀደም ብለው በደርግ ዘመነ መንግሥት በሱዳንና ኬኒያ እንዲሁም በሌሎች አገሮች የወጡ፤ በዲቪ የወጡ፤በኢትዮጵያ ኤምባሲ በፓስፖርት የወጡ፤በሀገር ሀብት ለትምህርት የተላኩ ሲሆን በኤምባሲው አማካኝነት በተለያዩ የስቪክ ማህበራት የተደራጁና በየትኛውም የሥራ መስክ በመግባት ለህወሃት መዋጮ በማዋጣት የሚረዱ፤የህወሃትን የውሸት እድገትና ጸረ-ሕዝብ ፖለቲካ የሚያናፍሱ፤በስለላ ተግባር የተሰማሩ፤ጠንክሮ የታገላቸውን በገንዘብ የተለያየ አይነት ጥቃት እንዲደርስበት ማድረግ፤ከሥራ ቦታም ችግሮችን በመፍጠር ሠርቶ እንዳይበላ በማድረግ የተሰማሩ…ወዘተ ሲሆን ሀገር ቤት የሚገኘውን ጥቅምና ጠቀሜታም የሚጋሩ ናቸው።ከባለ ሥልጣናት ጋር የቅርብ ዝምድና ያላቸው የግል ድርጅቶችን በአጭር ጊዜ ከፍተው የከበሩና አሰሪ ከመሆናቸውም በላይ ሀገር ቤት ባለሥልጣናቱ የሚዘርፉትን የሀገር ሀብት የሚያሸሹና በባንክ የሚያስቀምጡ እነዚሁ እኛ መሀል የተሰገሰጉ ትግርኛ ተናጋሪዎችና የሌላው ነገድ አባል የሆኑ ሆዳሞችንም ያካትታል።ስለዚህ እነዚህን ለይቶ ማውጣትና ህዝብ እንዲያውቃቸው ማድረግ ያስፈልጋል።

መቀበል አለመቀበል የእያንዳንዱ የግለሰብ ባሕርይ የሚወስነው ቢሆንም ከ40 ዓመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ክልል ውስጥ ያለን(የምንገኝ) ኢትዮጵያውያን የታሪክ ግርዶች፤ሀገራዊ ኃላፊነት የጎደለን፤ግዴታችን የማንወጣ፤ፈሪና ስግብግቦች፤የሌላው ኢትዮጵያዊ ችግርና እንግልት የማይሰማን፤እኛ ላይ ትንሽ ነገር ጎድላ ስናይ ግን ከጋለ ምጣድ ላይ እንደፈሰሰ ዘይት የምንጨረጨር፤ሆዳሞችና የማንጠግብ፤ብልጣ ብልጦች ፤ አስምሳዮችና ውሸታሞች መሆናችን ሳናቅማማ መራሩን በሀገር የማዳንና የመጥፋት ጉዳይ የሚቀርብ ነቀፌታ ወይም ሂስ በፀጋ ልንቀበል ግድ ይለናል።የትግሉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ሊቀመጥ የሚገባው »መፈክርም« ይህ ሊሆን ይገባዋል ብየ አምናለሁ። የቆሸሸ ልብስን ለማጠብ ዝም ብሎ ውሃ ውስጥ መጨመር  የቆሸሸውን ልብስ ሊያጸዳው አይችልም ሳሙና መጨመርና በእጅ ማሸት ወይም ማሽን ውስጥ አስገብቶ እድፉን ማስለቀቅ ያስፈልጋል። እኛም በውስጣችን ያለውን ቆሻሻ ሳናጸዳ ለማስመሰል የምናደርገው የማታለል ስልት መታረም አለበት።የትግሉ እንቅፋት ከመሆን ዝምታም እኮ አንዱ እርዳታ ሊሆን ይችላል።

ከዋናው ጠላት ለመድረስ በመንገድ የሚገጥሙንን እንቅፋቶች ለመጠቆም ብዙ ሀተታ ስለአበዛሁ ይቅርታ እየጠየቅሁ የሀገርና የሕዝብ ጠላት የሆነው ህወሃት የቆመለት ዓላማ መጀመሪያ የተከተለውን መንገድ ኪሱ ውስጥ አስገብቶ ሳያስብ የገጠመውን እድል ማለትም ተገንጥሎ ታላቋን ትግራይ ሪፐብሊክ መቀየስ ሳይሆን እነአዲሱን ኩማና በረከት ተፈራ ዋልዋን እያስመሩ ሀገርን ከጫፍ እስከ ጫፍ መመረሽና መክበር ነበር።ከመክበርም አልፎ አገር መግዛት ተቻለ አገር መግዛት ደግሞ ብዙ ጊዜ ላይሆን ይችላል የሚል ስጋት ነበር 22 ዓመት አሁንም «አብዮታዊ ዴሞክራሲ»የምድር አምላክ ስለሆነ በያንዳንዳችሁ አእምሮ እስኪሰርጥ ሌላ 40እና 50 ዓመት ስጡን ይህን ካልፈለጋችሁ ሰላም አታገኙም እንደ እባብ እራስ እራሳችሁን እያልኩ እፈጃለሁ አለ።እያደረገም ነው።ሌላ-ሌላም ይደረጋል።ምን ይደረግ ዓላማቸው ነውና እነሱ ለቆሙለት ዓላማ ቆመዋል።አልሳካ ሲል ደግሞ የሚበትኑትን በትነው ትግራይ ላይ ለመተከልና የተረፍነውን ለማድማት ያቀዱ ስለመሆናቸው ስጋት ሊኖረን አይገባም።ከዚያ ሁሉ በፊት ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምንና የሚይኮራ የስልጣን ጥማት በሽታ ያልወረረው ኢትዮጵያዊ ወገን ህወሃት ለጥፋት ይህን ያህል ተግቶ ሲሰራ ራሱን በምን ደረጃ ሊመድብ ሊገምት እንደሚችል ሊጠይቅ ይገባዋል።እኛ ታሪክ ልንሰራ አልቻልንም ፤አልሠራንም ቀደምት ወላጆቻችን የሠሩትን ታሪክም መጠበቅና ማስከበር አልቻልንም ለምን?እስኪ ሁላችንም ሊያግባባ የሚችል አንድ ዋናው የችግራችን መንስኤ ይህ ነው የሚል የፖለቲካ ይሁን የታሪክ ተመራማሪ የችግሩ መንስኤ ይህ ነው ይበለን።የፖለቲካ ሥልጣን ፍላጎት፤ዘረኝነት፤ጥቅም ፈላጊነት፤ክብር ፈላጊነት፤ውሸታምነት፤ማናክሎኝነት፤ፍርሃት…ወዘተ ከመሆን አያልፍም ብየ በግሌ አስባለሁ።ህወሃት ግን አንድ ነገር ብቻ ዓይወድም ይፈራል። እሱም አንድነትን ነው።ህወሃትን አንድነት የሚያስበረግገው ጉዳይ ከሆነ ለምን አንድነት አንፈጥርምና ህወሃት ገደል እንዲገባ አናደርግም? ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ያነሳው አንገብጋቢ ጥያቄም ይኸው የአንድነት ጥያቄ ነው።ዳሩ ግን የተቃዋሚ ኃይሎች፤የእምነት ተከታዮችና የሃይማኖት መሪዎች፤የስቪክ ማህበራት የባሰውን ሕዝቡን በመከፋፈል የጎላ ሚና ተጫወቱ እንጅ አንድነትን ሊያመጣ የሚችል ለም የሆነ ንጣፍ ሲመሰርቱ አልታዩም። ችግርን በውይይት የመፍታት ባህላችን ኋላ ቀር በመሆኑ ምክንያት ህወሃት 22ኛውን አንገት አስደፊ አገዛዝ አገባዶ ወደ ሌላኛው ዓመት እያኮበኮበ ይገኛል።የሚገርመው ግን በህዝብ አንቅሮ የተተፋና ውስጡ በችግር የተወጠረን ድርጅት መታገልና ማስወገድ አለመቻላችን ነው።ሕዝብ በያለበት ሆኖ ይጮኻል ግድያው አፈናው፤እሥራቱ ቀጥሏል ከአንድ አካባቢ በመጡ ጥቂት ጠባቦችና ጎጠኞች።ተቃውሞውም በተናጠል ቀጥሏል።ወደ ተግባር ሊለወጥ ግን አልቻለም።ህወሃት የተቃዋሚውን ሆነ የሕዝቡን የልብ ትርታ በማዳመጥ ዝምታ እንዲሰፍን ተራ በተራ በነገር እየተነኮሰ ማስተንፈሱን አላቆመም።የሚፈራው አንድነት እንዳይመጣ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ሲገኝ እኛ ግን ህወሃትን ማስፈራራት እንኳን አልቻልንም።ዋናው ችግርም ፍላጎታችን የሥልጣን እንጅ የሕዝብን ጩኸት መሠረት ያላደረገ ከመሆን አይዘልም።ለወር ያህል የቀጠለውና አሁንም መፍትሄ ያላገኘው በሳውዲ አረቢያና አካባቢ የዐረብ አገሮች በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ዘግናኝ አስገድዶ መድፈር፤ጎዳና ላይ ገድሎ መጎተት፤በሰይፍ መታረድ፤በርሃብና ውሃ ጥማት በበሽታ ማሰቃየት በጅምላ እስር ቤት መታጎር ምክንያት በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን በተለያየ መንገድ ማሰማት ሲችሉ በሀገር ቤት በሰማያዊ ፓርቲና አንድነት የሞከሩትን ተቃውሞ ማሰማት ህወሃት አያገባችሁም ብሏል።ሌሎች ድርጅቶች ደግሞ ትርፍ ፍለጋ ሲራወጡ ይስተዋላል።ወከባውን ለማርገብ ህወሃት ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው ይበል እንጅ እውነታው ሌላ ነው።ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ አገራቸው ብትሆንም አዲስ አበባም ሆነ ሳውዲ ዐረቢያ በተመሳሳይ መንገድ እንደተያዙ መዘንጋት አይኖርብንም።ሀገርን ጥሎ ለመሰደድ ተቋም አደራጅቶ የሸጠ ህወሃት ነው።ከሳውዲ መንግሥት ጋር ተባብሮ እልቂት ያወጀውም ህወሃት ነው።ስለዚህ ንግዱን ትተን መጀመሪያ አስከፊውን ስአርት ማስወገድና ከዚያ በኋላ ደግሞ ንግድ ያሰበውም ሆነ ወንበር የፈለገው እንደፍላጎቱ ለመሆን ሊንቀሳቀስ ይችላል።አሁን የነብስ አድን ጉዳይ ስለሆነ ሁላችንም አቅሙ በፈቀደልን መጠን ለወገን እንድረስለት።በመጨረሻም ይህችን መጣጥፌን ስሞነጫጭር አንድ ዜና ሰማሁና ብዙ ነገሮች ወደ ኋላ ውስደውኝ ትዝ አሉኝ።በሽግግር ወቅት እንበለው ጠቅላይ ሚንስትር የነበረው ታምራት ላይኔ በሲቢየስ ራዲዮ ኢንተርቪው ሲደረግ አዳምጨ የተዳፈነው ሁሉ ሊጎለጎል ነው ብየ አስብኩና ይህን ሰው ቀረብ ብሎ ማነጋገር ከተቻለ ኢትዮጵያን ከዚህ ያደረሰው ጉዞ ምን እንደሆነ ፍንትው አድርጎ ሊያሳየን ስለሚችል ከተቻለም ሌላውን ያሬድ ጥበቡንም ጨምሮ አፍነው የያዙትን ምሥጢር እንዲተነፍሱ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ሆኖ ይታየኛል በተለይ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ኢህዴንን አንቀበልም ብለው ህወሃትን የመረጡበትና ህወሃት የኢህዴንን ዶክመንት የጠለፈበት ታሪክ አሁን ለደረስንበት የሀገር ጥፋት ምንጩ እዛ ላይ ስለሚነሳ።

በቸር ይግጠመን

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!

ጌታቸው ከሰ/አሜሪካ

 

 

 

       

                    1/ወንጀለኛው ዳኛ ፦

 

ዳኛ የለም እንጅ ቢኖርማ ዳኛ

እጁን አስሮ እግሩን በመጫኛ?

ዳሩ ዳኛ የለም

ቢተውት ግድ የለም።

—ወንጀለኛው ዳኛን የጻፉት ክቡር ሐዲስ ዓለመየሁ ሲሆኑ እነዚህን ስንኞች ሁልጊዜ የተዛባ ነገር ስመለከትና ውስጤ ሲከፋ የማጉረመርምበት በመሆኑ አገራችን ዳኛ እስከምታገኝና የሕግ የበላይነት እስከሚከበር ድረስ ይህን የወሮ በላና የወራሪ ሥርዓት እስከምናስወግድ ድረስ እንዲህ እያጉረመረምኩ ትግሌን እቀጥላለሁ እንጅ ዳኛ የለምና ህወሃትን ታግሎ መጣል መተው አለበት አላልኩም። ወንጀለኛው ዳኛ ብለው የጻፉት ክቡር አቶ ሐዲስ ዓለመየሁም ዳኛ የለም ብለው ተስፋ አልቆረጡም ነበር። መሪና አታጋይ የሆኑ መጽሐፍትን በመጻፍ በወቅቱ የነበረውን ሥርዓት አስከፊነት ፍንትው አድርጎ በማሳየት አስነበቡ አሳወቁን እንጅ።

እህህ! ሀገሬ እህህ! ሀገሬ ሀገሬ ኢትዮጵያ

ሳልኖርብሽ ብሞት ጥፋቱ የማን ነው መቼ ኖርኩብሽና መቼ አይቸሻለሁ

አንች እየናፈቅሽኝ ሀገር እንደሌለው በየባዕዳው አገር እንከራተታለሁ

አራቱን ማእዘን ጓዳ-ጉድጉዳሽን ዘልቄ ሳላየው

የኔውስ እድሌ ተሰዶ መኖር ነው

አወይ ስደት ክፉው ሁሉ ይመኘዋል

እንደኔ ቢቀምሰው መቼ ያስበዋል

አንች ሀገር ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ

የደማልሽ ሲጋዝ ያደማሽ ሲበላ

አወይ ጊዜ ሞኙ ስንቱን አጃጃልከው

አንዱን ከፍ አንዱን ዝቅ ማለቱ ሳያንሰው

እንዴት ባገሩ ላይ መኖሪያ ያጣል ሰው

ተው እናንተ ሰዎች እሱ ነው ድንበሩ

ሁሉ ዘራፍ ካለ ይጠፋል ሀገሩ

ስማኝ አንተም እንደሌላው አፈር ትለብሳለህ አፈር ትሆናለህ

ድንጋይ ተንተርሰህ ትቢያም ትሆናለህ

እመነኝ ካንተጋር ተጣልተህ

በፍርሃት ተውጠህ

ቅዥቱ በዝቶብህ

በሀሰት መስክረህ ይገደሉ ያልከው

»           »     ይታሰሩ ያልከው

በሐሰት መስክረህ ይሰደዱ ያልከው

»            »      ይራባቸው ያልከው

ሀገሬን ለመሸጥ ፊርማ ያሰፈርከው

ሕዝቤን ለመጨረስ ምክር የመከርከው

ጥቁር ካባ ለብሰህ ሐሰት የፈረድከው

ፍትሕን አዛብተህ ሕጉን ያፈረስከው

ወንጀለኛው ዳኛ ለሆድህ ያደርከው

የኮተቤው ዳኛ ለሆድህ ያደርከው (ኮቴቤ የህወሃት ዳኞች መፈልፈያ ፋብሪካን ይመለከታል)

ፍርድ እየገመደልክ ስንቴ ልትኖር ነው?

እምነቴን እንዳጣ ነገድ እንዳይኖረኝ

ትውልድ እንዳልተካ ዘርም እንዳይኖረኝ

ሀብት እንዳላፈራ ድኻ ልታደርገኝ

ዜግነቴ ጠፍቶ ሰንደቄን እንዳላይ

የሀገሬ የጥንት አባቶቼ ታሪክ እንዳይታይ

ባህል ወግ ልማዴ ቅርሴ እንዳይታወቅ በዚህች ምድር ላይ

አብረን እንዳንወግን እኛን ልትለያይ

ነገር ስታሻኩት ጥላቻን ስታምጥ

አገር ልታጠፋ ሕዝቤን ልትበጠብጥ

ቆላ ደጋ ስትል በየአገሩ ስትሮጥ

ክፉ ቀን ተጣራ ወዴት ልትገባ ነው

ምላስህ ሊታሰር ልሳንህ ሊዘጋ እየተጠራህ ነው

ጦሩ ሲመክትህ ገንዘቡ ሲያወጣህ ደህንነት ሲያድንህ

እኮ እናይሃለን እብሪቱ ትቢቱ ከመሞት ሲያድንህ

Pen

ዶክተር ቴወድሮስ አድህኖም በእውነት አዝነው ወይስ መስታወቂያ እየሰሩ !!

$
0
0

Gebregziabher Lema /Kitzingen/

tewedros adhanom with returneesየኢትዮጽያ ህዝብ  የሞተበት፤ ያዘነበት፤ ፍትህ ያጣበት ፤የተራበበትና የተሰደደበት ግዜአቶች ቢኖሩም   አሁን ግን እራሳቸው ከሚያደርሱብን ግፍና በደል  በተጨማሪ በባእዳን ሀገራት    ተደፍሮና ተነክቶ የማያውቀው ህዝብ   አሁን ባለው  ስርአት  ታሪካችንንና መንነታችንን  ለመጥፋት መጠነ ሰፊ ዘመቻ እየተካካሄደብን ነው። ይህ የማንነታችን መደፈር ዛሬ በገሀድ ወጥቶ ሁላችንም እንስማው እንጅ  ቀደም ሲል ከእኛ በታች በነበሩ የጎረቤት ሀገራት በነጂቡቲ ፤ሱዳን ና ኬንያ ተዋርደንና ተጠቅተን  እንድንኖር ከተደረገ  ውሎ አድሮአል  ። ዛሬ በኢትዮጽያ ህዝብ ጀርባ  ህልውናዋ የቆመው በጂቡቲ እንኮ ኢተዮጺያዊነት ተወርዶ  በነሱ ስንገደል ፤ስንታሰር፤ ሴት እህቶቻችን የነሱ መጫወቻ ሲሆኑ፤ ሹፌር ወንድሞቻችን በራሳቸው ላይ በደል ተፈጽሞባቸው እራሳቸው ተቀጭ ፤በንብረቶቻቸው ላይ አደጋ ተፈጽሞባቸው እራሳቸው ከፋይ ፤ግመሎቻቸውና ፍየሎቻቸው ላይ አደጋ ቢደርስ  ገና ውደፊት እሰከምትወልደው የልጅ ልጅ እዲከፍሉ በማድረግ  ለሚደረገው ህገወጥ ስራወች ሁሉ ለወያኔ አቤት ያልተባለበት ግዜ የለም  የገንዘብ ኪሳቸውን  ለመሙላት ሲሉ ህዝብን  ለባርነት ዳርገውት ይገኛሉ።

ታዲያ ዛሬ ቴወድሮስ አድህኖም ያዞ እንባውን ከየት አመጡት  ምን አልበት በሳውዲ መንግስት ከወገኖቻችን  አላግባብ የፈሰሰው ደም ፤  በቃየል ላይ እንደ መሰከረበት የአቤል ደም ሆኖባቸው ይሆን ? ወይስ  ለሚቀጥለው  ምርጫ  የቢል ቦርድ  ማስታወቂያ  ፎቶ  እያዘጋጁ ? አዎ ይህ ነው እንጂ ካልሆነማ  በስደት  በመንገድ ላይ በየኮንተቴይነሩ ለሚያልቁት ፤በሱዳን፤በጂቡቲ፤በየምን ና ኬንያ በባርነት ያሉ ወገኖች ፤ በሀገራቸው በክልላችሁ ሂዱ ተብለው   ሀብት ንብረት ካፈሩበትና ወልደው ከዳሩበት አያት ቅድምአያቶቻቸው  ለነጻነት አጥትና ደማቸውን ከገበሩበት ሀገርና ቀየ ያንተ አይደለም ተብሎ ሲፈናቀሉ ሌሎች ዘመዶቻቸው እንደጀብድ ሲያወሩት እንደነበር አያውቁም ? ስለዚህ ይህ የውሸት እንባ የኛን አንጀት ያጠነክራል እንጂ የሚያለሰልሰው ፈጽሞ አይሆንም።

ወደ ሳኡዲ አደንዛዥ እጽንና መጠጥን ለማስገባት የሞከሩ ሰዎች ተያዙ ከመካከላቸዉም አንዱ ታጣቂ ተገደለ ተባለና በሰዎቹ ማንንነት ላይ ኢትዮጵያዊ የሚል ታፔላ ተለፈጠበት ለምን?

$
0
0

ምኒልክ ሳልሳዊ

Sadityህወሃት የራሱን ሰዎች በጣም ይፈራል፤ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸዉ እንዳይገኛኙም በጣም ይጥራል፤ህወሃት ስልጣኑንን ከለቀቀም ከሰሜን የኤርትራ ህዝብና ከትግራይ ዉጪ ያለዉ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ተወላጆችን እንደሚያጠቃም ይስፈራራል።

ህወሃት የለዉጥ ብስራትን የሚሹ የትግራይ ልጆች ኤርትራ ካለዉ የተቃዋዊ ሐይል ጋር ያብሩብኛል የሚልም ስጋት ስላለዉ የትግራይ ወጣት ይሰደድ ዘንድም ሁናቴዎችን ሲያመቻች ቆይቷል። ስለዚህ ብዙ የትግራይ ወጣቶች በየመን አድርገዉ በሳዉዲዋ የጀዛን ግዛት ወደ ሳኡዲ በመግባት ወደ ተለያዩ ከተሞች ተበታትነዋል።ለሳኡዲ ባህልና ሐይማኖታዊ ህግ በቂ የስነልቦና ግንዛቤ የሌላቸዉ ወጣቶችም ያገሪቱን ህግ በመጣስ በኢትዮጵያዊነት መለዮ ላይ ቀዉስን ፈጥረዋል የሚል ቅሬታ ይደመጣል።

በተለይ በሪያዷ የመንፉሃ ክፍለ ከተማ በመጠጥና በአደንዛዥ እጽ ህገወጥ ስራ ላይ የተሰማሩት ወጣቶች በህወሃት ፖለቲካዊ እኩይ ተግባር ሰለባ የሆኑ ለመሆናቸዉ መረጃዎች መዉጣት ከጀመሩ አመታት ቢቆጠሩም ችግሩ ገንፍሎ አንባገነናዊዉ የሳኡዲ መንግስት ዜጎቹ ያነጣጠሩበትን የለዉጥ ኢላምን አቅጣጫ ለማስቀየር እስኪጠቀምበት ድረስ ሃይ ባይ አልነበረም።ይህ ጥቂት ኢትዮጵያዉያን የተሰማሩበት ህገወጥ ተግባር ያለ ሳኡዲ የደህንነትና የህግ አስከባሪ ሐይላት ትብብር እዉን ያልሆነ በመሆኑ የሳኡዲ መንግስትም ከተጠያቂነት አይድንም። ሳኡዲ ዉስጥ ካለዉ ኢትዮጵያዊ ቢያንስ ዘጠና ስምንት ከመቶዉ ለፍቶ አዳሪ ሲሆን በጣም ጥቂት የሆነዉ ኢትዮጵያዊ ባቋራጭ እድገትን ፈላጊ የሚሆንበት አጋጣሚ ይታያል።

ስደተኛ ወይም ስራ ፈላጊ የሆኑ ኢትዮጵያዉያን በነቂስ በሳኡዲ ዜጎች  ጥርስ መግባታቸዉ፣መደብደባቸዉ፣መገደላቸዉ፣የአስገድዶ መድፈር ሰለባ መሆናቸዉ የሳኡዲ መንግስት እራሱ ላወጣዉ ያገሩ ህግ  ወይም አለማቀፋዊ ህግ ደንታ የሌለዉ መሆኑን ፍንትዉ አርጎ ያሳያል። የሳኡዲ መንግስት ለፈጸማቸዉ ኢሰብዓዊ ተግባራት ተጠያቂ ከመሆኑም ባሻገር የደም፣የሞራል፣የጉዳትና የሰራተኞችን የልፋት ዋጋ በካሳ መልኩ እንዲከፍል ኢትዮጵያዉያኑ በጋራ ሊሰሩበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ ነዉ።

ኢትዮጵያዉያኑ በሳኡዲ የደረሰዉን ግፍ ለመታደግ በመላዉ አለም ያሳዩት እምርታዊ ተቃዉሞ እሰየዉ የሚያስብል ቢሆንም፤በየሰልፎቹ መሃከል በጥቂት የጥላቻ አቀንቃኞች የታየዉ ጸረ-ኢስላምና ጸረ-አረብ አቋም የኢትዮጵያን ህዝብ በቢሊዮን ከሚቆጠሩ የአላማችን ዜጎች ጋር የሚያጣላ ሃላፊነት የጎደለዉ ተግባር በመሆኑ ከፋፍሎ የሚገዛዉን ህወሃትን ከመጥቀም ባሻገር ፋይዳ አይኖረዉምና ካማረዉ  የአንድነት ማሳ ላይ የጥላቻዉን አረም ማረሙ ተገቢም ነዉ።

ኢራን ከሳኡዲ አረቢያ ጋር ስር የሰደደ ፖለቲካዊና መልከ-አምድራዊ የሆነ ታሪካዊ  ባላንጣነት አላት። እንደ አንዳንድ የሳኡዲ የመገኛና አዉታሮች አገላለጽ በኢራን የተመለመሉ ኢትዮጵያዉያን ደህነቶች በሳኡዲ አረቢያ ዉስጥ ይገኛሉ የሚል ስጋት አለ። ስጋቱን የሳኡዲ መንግስት ሆን ብሎ የፈጠረዉ ሊሆን ቢችልም፤ የራሱን የዉስጥ  ቅዋሜ ለማርገብ የሚኳትነዉ ህወሃት የለዉጥን ብስራት ፈላጊ የሆኑ  ወጣቶችን ለመሰል ተልእኮ አሳልፎ አይሰጥም ለማትም አዳጋች ይሆናል።

ሁለት አንባገነናዊ ስርዓቶች በጥምረት አንባገነናዊ ተዉሳክን ለማስረጽ ሲዳክሩ፤ በመሃል የሚጠቁትን ኢትዮጵያዉያን ለመታደግ ፍቅር፣አንድነት፣ትብብር ያሻልና በሳኡዲ የሚንቆረቀረዉን የወገን እንባ አባሽ እንሁን። ልብ ያለዉ ልብ ይበል!

 

 

 

ቴዎድሮስ አድሃኖም ቢያጥቡት የማይጠራ ወያኔ ነዉ (ኤፍሬም ማዴቦ)

$
0
0

ኤፍሬም ማዴቦ

tewedros adhanom with returneesየኢትዮጵያ ህዝብና እናስተዳድረዋለን የሚሉት አምባገነን ገዢዎቹ ተስማምተዉና አንዱ ሌላዉን አክብሮ የኖረበት አንድም የታሪክ አጋጣሚ የለም። የእስከዛሬዉ ታሪካችን ምዕራፍ በጥቅሉ ሲታይ ታሪካችን የሚቋጨዉ ህዝብ ተረገጠ፤ ተጋዘ፤ ገዢዎች ደግሞ ረገጡ፤ገዙ፤ አሰሩ፤ አጋዙ እየተባለ ነዉ። አዎ! የኢትዮጵያ ህዝብ እስከዛሬ ባለዉ ታሪኩ ተግዟል፤ ተረግጧል፤ ተንቋል፤ ተንቋሿል። የዘንድሮዉ በተለይ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት እየደረሰብን ያለዉ ብሄራዊ ዉርደትና ንቀት ግን ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ልዩ ከልዩም ልዩ ነዉ። በቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብ ልክ እንደዛሬዉ ሰብዓዊ መብቱ ተረግጧል፤ ፍትህ ተነፍጓል፤ ነጻነቱን ተገፍፏል፤ ሆኖም አገር ዉስጥም ከአገር ዉጭም ፈላጊና ባለቤት አንደሌለዉ የቤት ዉስጥ እንስሳ የወገንም የባዳም እጅ አልተረባረበበትም። አንገፍግፎን አንፈልግም በቃ ብለን ያስወገድነዉ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ስርዐት በስልጣን ላይ በነበረበት ግዜ “ኢትዮጵያ” የሚለዉ ስምና “ኢትዮጵያዊነት” አገር ዉስጥም ሆነ አዉሮፓ፤ አሜሪካና አፍሪካ ዉስጥ እጅግ በጣም የተወደደና የተከበረ ስም ነበር። ዛሬ ወያኔ ነጻ አወጣኋችሁ፤ እኩልነት አመጣሁላችሁ እያለ በሚሰብክበት ዘመን ግን የኢትዮጵያ ሀዝብ አገር ዉስጥም በዉጭ አገሮችም ባለቤት አንደሌለዉ ፈረስ ማንም የሚጋልብበት ፈላጊ እንደሌለዉ  ዕቃ ያገኘ ሁሉ እንዳሰኘዉ እጁን የሚያሳርፍበት የተናቀ ሀዝብ ሆኗል። ለመሆኑ ለምንድነዉ ኢትዮጵያዊነት እንደዚህ  እንደ ተራ ዕቃ የቀለለዉ? ኢትዮጵያዉያንስ ለምንድነዉ በየሄዱበት እንዲህ አይነት ዉርደትና ስቃይ የሚደርስባቸዉ? መልሱ ቀላል ነዉ። “ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ” ወይም  “ባለቤቱ ያቀለለዉን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለዉም” ነዉ።

የወያኔ አገዛዝ እኛ ኢትዮጵያዉያን “ኢትዮጵያዊነት” እያልን ስለምንሳሳለትና ስለምንከባከብለት ትልቅና ክቡር ሀሳብ በፍጹም ግድ የለዉም። እንዲያዉም ወያኔ ሽንጡን ገትሮ ከሚታገላቸዉ ዋና ዋና ብሄራዊ እሴቶቻችን ዉስጥ “ኢትዮጵያዊነት” የመጀመሪያዉ ነዉ። ስለዚህም ነዉ ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት በግልጽ እንደተመለከትነዉ “ኢትዮጵያዊነት”  ብለዉ የተጣሩ፤የጮሁ፤ ህዝብን ያስተማሩና የታገሉ ግለሰቦች በወያኔ እየተለቀሙ የታሰሩትና የተገደሉት። ከአገር ዉጭም ቢሆን በየዉጭ አገሩ የሚገኙት የወያኔ ኤምባሲዎች ኢትዮጵያዉያን ከአገራቸዉ ዉጭ ማግኘት የሚገባቸዉን የዜግነት አገልግሎት የሚሰጡት ዜግነታቸዉን እያዩ ሳይሆን ቦንድ የገዛ ያልገዛ፤ “ልማታዊዉን መንግስት” የደገፈ ያልደገፈ እያሉ ወይም “የወርቃማዉ ዘር” አባልነቱን እያጣሩ ነዉ። እነዚህንና ሌሎችም እነዚህን የመሳሰሉ ሰንካላ የወያኔ መስፈርቶች ያላሟሉ ኢትዮጵያዉያን አገር ዉስጥም ከአገር ዉጭም ወያኔ በዜግነት ሳይሆነ በጠላትነት የሚመለከታቸዉ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ዜጎች ናቸዉ። ዛሬ ከአፍሪካ፤ ከኢሲያና ከላቲን አሜሪካ አገሮች ስራ ፍለጋ ሳዑዲ አረቢያ ከሄዱ ዜጎች ዉስጥ እንደ ኢትዮጵዉያን እጁንና እግሩን ታስሮ የተገረፈ፤ እንደሴቶቻችን በሳዑዲ ጎረምሶች የተደፈረና እንደ ኢትዮጵዉያን በየአደባባዩ የተገደለ የሌላ አገር ዜጋ የለም። ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የሚገኙ የሌሎች አገሮች ኤምባሲዎች የዜጎቻቸዉ መብት በሳዑዲ መንግስትና ህዝብ ሲደፈር ለምን ብለዉ ይጠይቃሉ ወይም ለዜጎቻቸዉ ግዜያዊ መጠለያ፤ የህክምና እርዳታና የህግ ሽፋን ይሰጣሉ እንጂ ኤምባሲያቸዉ በራፍ ላይ “ዝግ ነዉ” የሚል ጽሁፍ አይለጥፉም።

የወያኔ ኤምባሲ ግን ከስረ መሠረቱ የተቋቋመዉ የወያኔን የራሱን እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ስላልሆነ ይህንን የሌሎች አገሮች ኤምባሲዎች ለዜጎቻቸዉ የሚያደርጉትን ጥበቃና እንክብካቤ ለወገኖቹ ለማድረግ አልታደለም፤ ፍላጎቱም የለዉም።  ይህንን ቅሌትና ዉርደት ደግሞ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት በግልጽ ተመልክተናል። ጂዳና ሪያድ ዉስጥ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰዉን መከራና በደል ተቃዉመዉ ሠልፍ የወጡ ኢትዮጵያዉያን በሳዑዲ ፖሊሶች ታድነዉ እንደታሰሩ ሁሉ አዲስ አበባ ዉስጥም በወንድሞቻችንና እህቶቻች ላይ እንዴት እንዲህ አይነት በደል ይፈፀማል ብለዉ ሳዑዲ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሠላማዊ ሠልፍ የወጡ ኢትዮጵያዉያን በአረመኔዎቹ የወያኔ ፖሊሶች ታድነዉ ታስረዋል፤ተደብድበዋል። አዎ! ኢትዮጵያዉያን ሳዑዲ ዉስጥም ኢትዮጵያ ዉስጥም ለምን የሳዑዲን መንግስት ተቃወማችሁ ተብለዉ በሁለቱም አገር ፖሊሶች እየታደኑ ታስረዋል ተደብድበዋል።

ከወያኔና ከጥቂት ሆድ አምላኪ ደጋፊዎቹ ዉጭ በአገር ዉስጥና በመላዉ ዓለም የሚገኘዉ ኢትዮጵያዊ በአንድ አላማ ዙሪያ የተሰባሰበበትና አንድ ሳምንት ሙሉ አንድ ቃል በአንድ ትንፋሽ የተነፈሰበት ግዜ ቢኖር ወርሃ ህዳር 2006 የመጀመረያዉ ነዉ ማለት ይቻላል። የአንድ አገር ህዝብ በአንድ አላማ ስር ሲሰባሰብና በአንድነት ሲቆም ከማንም ከምንም በላይ በዚህ አንድነት መጠቀምም መደሰትም ያለበት መንግስት ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ የወያኔ አገዛዝ ግን ዕቅዱና ስራዉ ሁሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ማስጨነቅና ማበሳጨት ነዉ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በሚሰራዉ ስራ ተደስቶ አያዉቅም፤ ለወደፊትም የሚደሰት አይመስልም። ከሰሞኑ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰዉ ልክ የሌለዉ ስቃይና መከራ መላዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀፎዉ እንደተነካ ንብ ከዳር ዳር ሲያስቆጣ ወያኔና ሞራለ ብልሹ ሹማምንቶቹ ግን ከዚህ ወገኖቻችንን በባዕድ አገር ለከፍተኛ ጥቃት ካጋለጠና ብሄራዊ ዉርደት ካከናነበን ክስተት ትርፍ ለማግኘት የፖለቲካ ቁማር እየተጫወቱ ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ሳዑዲ ዉስጥ በአሰሪዎቻቸዉ፤ በመንደር ዉስጥ ጎረምሶችና በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ፤ እንግልትና ዉርደት ሲደርስባቸዉ ኤምባሲዉ በራፍ ላይ “ኤምባሲዉ ዝግ ነዉ” የሚል ጽሁፍ በመለጠፍ ይበላችሁ እያለ አፉን ዘግቶ የተመለከተዉ የወያኔ አገዛዝ ዛሬ የወገን አሳቢና ተቆርቋሪ ለመመሰል የጭቃ ዉስጥ እሾኩን ቴዎድሮስ አድሀኖምንና የአገዛዙን የዉሸትና የቅጥፈት ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲን በግምባር ቀደምትነት በማሰለፍ የፖለቲካዉን ገደል ቁልቁል ተያይዞታል።

ቴዎድሮስ አድሃኖም ቢከፋም ቢለማም የአገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነዉ፤ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የስራ ሀላፊነት ደግሞ አገሪቱንና ዜጎቿን ከዉጭ አገሮች ጋር በሚያገኛኙ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ነዉ እንጂ በአገር ዉስጥ የሚሰራዉ ይህ ነዉ ተብሎ የሚነገር ስራም ሀላፊነትም የለዉም። አንዴ ወዳጅ አንዴ ጠላት እየመሰለ እንደ እስስት መልኩን የሚቀያይረዉ ቴዎድሮስ አድሀኖም ግን ሳዑዲ ዉስጥ ድረስልን ብለዉ ሲጣሩት ፊቱን ያዞረባቸዉ ኢትዮጵያዉያን አዲስ አበባ ሲመለሱ ያሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት ሲሞክር ይታያል።  ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ቅርቅር አድርጎ ዘግቶ የወገን ያለህ ብለዉ የመጡትን ኢትዮጵያዉያን እንጃላችሁ ብሎ ፊቱን ያዞረባቸዉ የአዛኝ ቅቤ አንጓቹ ቴዎድሮስ አድሃኖም እነዚሁኑ እንደ ባዳ ፊቱን ያዞረባቸዉን ኢትዮጵያዉያን አገር ቤት ሲመጡ “እንኳን ደህና መጣችሁ” ማለቱ የገደለዉን ወታደር ለማከም ከሞከረዉ የናዚ ጀርመን ወታደር ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ቴዎድሮስ አድሀኖም እንደ ፈረስ ገርተዉ ለዚህ ባደረሱት በነመለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ ጭቅላት ሳይሆን በራሱ ጭንቅላት የሚያስብ ሰዉ ቢሆን ኖሮ የሱ የስራ ድርሻና ሀላፊነት ዜጎቻችን አገር ቤት ከገቡ በኋላ ሳይሆን ሳዑዲ ዉስጥ እያሉ ነበር።

ዛሬ ቴዎድሮስ አድሃኖምም ሆነ ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች ከሳዑዲ በሚመለሱት ወገኖቻችን ዙሪያ የሚያደርጉት ልታይ ልታይ የፎቶ እሽቅድምድም ወገኖቻችንን ለመርዳት ሳይሆን ዘረኛ መሪያቸዉ መለስ ዜናዊ ሲሞት ሳያስቡት በድንገት ከእጃቸዉ የወጣዉን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ መልሰዉ እጃቸዉ ለማስገባት ወይም በሚቀጥለዉ አመት በሚደረገዉና ወያኔ ከወያኔ ጋር በሚወዳደርበት ትርጉም የለሽ ምርጫ የፈረደበት ኃ/ማሪያም ደሳለኝን በቴዎድሮስ አድሃኖም ለመተካት ነዉ። አዎ! ለመተካት  . . . ለመተካካት። ወያኔ መተካካት እያለ አንዱን ጌኛ በሌላ ጌኛ በልቶ የጠገበዉን አህያ በተራበ አህያ መተካት ከጀመረ ዉሎ አድሯል። የአሁኑም ሩጫቸዉ ቢጭኑት አልሸከም ቢቀመጡበት አልመች ያላቸዉን ኃ/ማረሪያም ደሳለኝን የራሳችን ሰዉ ብለዉ በሚጠሩት በቴዎድሮስ አድሃኖም ለመተካት ነዉ (ኃይለማሪያምማ አሁንስ ቢሆን በቁሙ አልተተካም ብላችሁ ነዉ . . . ድፍን አበሻ ዉጭ አገርም አገር ዉስጥም ሲተራመስ ኃ/ማሪያም አንዲት ቃል አልተነፈሰምኮ)  ሳዑዲ ዉስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቻችን ፓስፖርታቸዉን ሲቀሙ፤ ሲደበደቡ፤ሲታሰሩና ሲገደሉ ቴዎድሮስ አድሀኖም የሰጠዉ ምላሽ ቢኖር  የኤምባሲዉንና የቆንስላ ጽ/ቤቶችን በር መዝጋት ነበር።  አዎ መዝጋት። ልክ ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ከመለስ ዜናዊና ከአግዓዚ ነብሰ ገዳዮች የጥይት እሩምታ ለማምለጥ ወደ ቤተክህነት ጽ/ቤት ግቢ ሸሽተዉ ለመግባት በሞከሩ ወጣቶችና ህፃናት ላይ አባ ጳዉሎስ በሩን እንደዘጉባቸዉ ዛሬም የአባ ጳዉሎስ ታናሽ ወንድም የሆነዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም በባዕድ አገር ዉስጥ አድነን ብለዉ በተጠጉት ወገኖቻችን ላይ የኤምባሲን በር ቀርቅሮባቸዋል።

ለመሆኑ ቴዎድሮስ አድሃኖም በየአመቱ ከ40ሺ በላይ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በለጋ ዕድሜያቸዉ ከወላጆቻቸዉ ተለይተዉና ትምህርታቸዉን ትተዉ ስራ ፍለጋ ወደ አረቡ አለም የሚጎርፉት እሱ ሊነግረን እንደሚፈልገዉ  በአትራፊ ደላላዎች ተታልለዉ ወይም የአረብ አገር ኑሮ ጥሟቸዉ ሳይሆን ወያኔ በሚከተለዉ የዘረኝነት ፖሊሲና የተበላሸ የኤኮኖሚ ስርዐት የተነሳ መሆኑን ያዉቅ ይሆን? በተለይ ወጣት ሴቶቻችን በአረቡ አለም የሚደርስባቸዉን ዉርደትና መከራ እያወቁ በነጋ በጠባ አረብ አገር የሚሄዱት አገራቸዉ ዉስጥ ሰርተዉ መኖር ስላልቻሉ ከወያኔ ጋር ከመኖር አረብ አገር ሄዶ መሰንበት ይሻላል ብለዉ ነዉ አይናቸዉ እያየ የሞት ወጥመድ ዉስጥ የሚገቡት። ወያኔ በእጥፍ ድርብ አሳደግኩት የሚለዉ የአለማችን ፈጣኑ ታዳጊ ኤኮኖሚ ለእነዚህ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሮ ቢሆንና ዜጎች ስራ የሚያገኙት ችሎታቸዉ ብቻ እየታየ ቢሆን ኖሮ ይህ ዛሬ የምናየዉ ብሄራዊ ችግርና ዉርደት አይኖርም ነበር። ይሉኝታና እፍረት የሚባል ነገር አብሮት ያልተፈጠረዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም የዜጎቻችንን ወደ አረብ አገር መጉረፍ በደላሎችም ሊያሳብብ ሞክሯል። አሱ ለሚከስሳቸዉ ደላሎች የስራና የንግድ ፈቃድ ሰጥቶ በዜጎች ንግድ እንዲከብሩ መንገዱን ያመቻቸዉና የከፈተዉ የራሱ የቴዎድሮስ ፓረቲ ነዉ፤ ብዙዎቹ አትራፊ ደላላዎችም የራሱ የቴዎድሮስ ጓደኞች ናቸዉ። የቴዎድሮስ አድሃኖም ጉድ ብዙ ነዉ፤ ተዘርዝሮ አያልቅም።

ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ሳዑዲ ዉስጥ ሲጋዙና ሲገደሉ ቁጥሩ ተገኗል እያለ በወገኖቻችን ላይ ያፌዝ የነበረዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም ነበር፤ ኢትዮጵያዉያን ወገንና ረዳት አለን ብለዉ ወደ ኤምባሲዉ በብዛት ሲመጡ ኤምባሲዉና ቆስንላ ጽ/ቤቶች በራፍ ላይ “ዝግ ነዉ” የሚል ጽሁፍ ለጥፎ ወገኖቻችንን ለባዕዳን ጥቃት አሳልፎ የሰጠዉ ቴዎድሮስ አድሀኖም ነዉ፤የሳዑዲ መንግስት በአገሩ ዉስጥ ወንጀል ሲፈጸም ህጋዊ እርምጃ መዉስድ መብቱ ነዉ ብሎ የወገኖቻችንን መገደልና የሴቶች እህቶቻችንን መደፈር ህጋዊ ለማድረግ የሞከረዉም ቴዎድሮስ አድሃኖም ነዉ። የሚገርመዉ ይህ ወገኖቻችንን በባዕድ አገር “አይናችሁን ለአፈር” ብሎ በሩን የዘገባቸዉ ከሃዲ ሰዉ ነዉ ዛሬ የወገን አሳቢና ደራሽ መስሎ ቀልዱ እንዳማረለት የመድረክ ላይ ኮሜዲያን እዚህም እዚያም ሽርጉድ የሚለዉ። ሳዑዲ ዉስጥ በወገኖቻችን ላይ ለደረሰዉ ይህ ነዉ የማይባል ትልቅ በደልና ጥፋት የኢትዮጵያ ህዝብ በዋናነት ተጠያቂ ከሚያደርጋቸዉ የወያኔ ባለስልጣኖች ዉስጥ ቴዎድሮስ አድሃኖምና ተላላኪዉ ዲና ሙፍቲ የመጀመሪያዎቹ ናቸዉ።

ከሰሞኑ ፊቱን እያሳመረ በየደቂቃዉ ኢቲቪ ላይ መቅረብ የጀመረዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም  “ሳዑዲ ዉስጥ ለደረሰዉ ጥፋት መንግስት ተመጣጣኝ እርምጃ ይወስዳል” እያለ ሲዘለብድ ተሰምቷል፤ የሱ ተላላኪ የሆነዉ ዲና ሙፍቲ ደግሞ “በዜጎች ላይ ምን ግዜም ድርድር የለም” ብሎ ሲናገር ተደምጧል። ይህንን በሁለት ባዶዎች የተነገረ ባዶ ንግግር ያዳመጠ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን “ጽድቁ ቀርቶበኝ በወጉ በኮነንከኝ” እያለ የቴዎድሮስንና የዲና ሙፍቲን “ጅብ ከሄደ ዉሻ ጮኸ” ንግግር ሰምቶ እንዳልሰማ አልፎታል። የሚገርመዉ ይህ ወገኖቻችንን በክፉ ቀን ወግዱ ብሎ ፊቱን ያዞረባቸዉ ቴዎድሮስ አድሀኖም ነዉ ዛሬ የሳዑዲ መንግስት በራሱ ወጪ አዲስ አበባ የሚልካቸዉን ዜጎች ዘመድ መስሎ ለመጠየቅ የሚሄደዉ። ደግሞኮ እስከዛሬ ድረስ አዲሰ አበባ ገብተዋል የሚባሉት በጣት የሚቆጠሩ ሰዎችም ቢሆኑ በተለመደዉ የወያኔ የዘመድ አሰራር እየተመረጡ የመጡ እንጂ ዜግነታቸዉ፤ ዕድሜያቸዉና የጤንነት ሁኔታቸዉ እየታየ የተመረጡ ሰዎች አይደሉም። ባጠቃላይ የተጣለበትን አገራዊ አደራና የተሰጠዉን ህዝባዊ ሀላፊነት መወጣት የተሳነዉን ቴዎድሮስ አድሀኖምን በየሜድያዉና በተገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ እያሽሞነሞኑ ለማቅረብ የሚደረገዉ ጥረት እንደ ህፃን ልጅ ሽንት መቀበያ የቆሸሸዉን የወያኔ ፊት በቆሻሻ ዉኃ ከማጠብ ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ወያኔ ከአሳማ አሳማ እየመረጠ ለማሳመርና ለማሽቀርቀር የሚያደርገዉ ጥረት አሳማዉን ወደ ለመደዉ ወደ ጭቃዉ ዉስጥ ይበልጥ ይስበዋል እንጂ በፍጹም አያሳምረዉም፤ ምክንያቱም አሳማ አጌጥነዉ አላጌጥነዉ ምን ግዜም አሳማ ነዉ። የቴዎድሮስ አድሃኖም ነገርም እንደዚሁ ነዉ ፤ ወያኔ ያሻዉን ያክል ቢቀባዉና ቢያሳምረዉ ቴዎድሮስ አድሃኖም ወያኔነቱን አይለቅም! ወያኔ ደግሞ በልቶ የማይጠግብ ታጥቦ የማይነጻ አሳማ ነዉ።

ebini23@yahoo.com


መፍትሔው (አበራ ሽፈራው ከጀርመን)

$
0
0

አበራ ሽፈራው ከጀርመን

TPlFበተለይም ባለፉት 22 ዓመታት በሀገራችን ለተከናውኑት አበይት ችግሮች ሁላችንም እጆቻችንን ወደ ህወሓት እየቀሰርን ለችግሮቻችን መፍትሔ መስጠት አቅቶን ይባሱኑ ለከፍተኛ ስቃይና መከራ መዳረጋችንና፤ መፍትሔውን ከህወሓት እየጠበቅን ለችግራችን መባባስ አስተዋጽኦ በማድረጋችን ችግራችን እየተባባሰ ቀጥሏል። በምን መልኩ ነው አስተዋጽኦ አደረግነው?

በምን መልኩ አስተዋጽኦ አደረግን? ለምንል ደግሞ በተደጋጋሚ የህወሓትን ማንነት አይናችን እያየና እየተመለከት መስዋዕትነት ለመክፈል መወሰን ባለመቻላችንና የሀገራችንን እጣፋንታና የወደፊት እድላችንንም ጭምር በህወሓት እጅ አስቀምጠን አሁንም ለህወሓት ባርነት እራሳችንንና ሀገራችንን አሳልፈን መስጠታችን መቀጠሉ አስገራሚ ጉዳይ መሆኑና እኛም ለዚህ ውርደታችን መባባስ ለህወሓት ከፍተኛ እድል በመስጠታችንም ጭምር ነው።

ለችግራችን መፍትሔ ፈጣሪ ለመሆን እስካልቻልንና መፍትሔ የመፈለጉ ጉዳይ በራሱ በኢትዮጵያ ህዝብ እጅ እስካልገባ ድረስ አሁንም የህወሓት ጥቂት ጨቋኝ ቡድን የባርነት ቀንበር ተጭኖብን ለመኖር በመፍቀዳችን መፍትሔ አልባ ህዝቦች ሆነን ለመኖር መፍቀዳችንን ልንገነዘብ ይገባናል።

ባለፉት ዓመታት ህወሓት በሀገርቷና በህዝቧ ላይ መጠነ ሰፊ ግፍን ሲፈጽም ዝም ተብሎ ዛሬ እዚህ ደርሰናል። ሀገር እየተቆረሰ ለሌላ ሀገር ሲሰጥ፣ ህዝብ በጅምላ ሲገደል፣ ህዝብ እያፈናቀሉ ወደመጣህበት ዘር ሂድ ሲሉና የሰውን ልጅ ከደን ውድመት ጋር እያዛመዱ ሲሳለቁብን፣ በታጋይነት ሰበብ የአገሪቷን ጠቅላላ ወታደራዊ ሥልጣንን በቁጥጥር ውስጥ አስገብተው ጥቂቶች በህዝብ ሃብትና ንብረት ሲሳለቁ ፣ ጠቅላላውን የአገሪቷን የንግድ እንቅስቃሴ በመቆጣጠር የራሳቸውን የፓርቲ ንግድ ሲያስፋፉና ሌላውን የንግድ እንቅስቃሴ ሲያቀጭጩ እየተመለከትን፣ የአገሪቷ ህዝቦች በስደትና በመከራ ላይ ሆነው እነሱ የአገሪቷን መሬትች በመኖሪያ ቤት፣ በንግድ ቦታና በእርሻ ቦታነት እየተከፋፈሉ የራሳቸውን መስፋፋት ሲያጠናክሩ እየተመለከትን፣ በተለይም ላለፉት 22 ዓመታት የአገሪቷን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉትን ጠቅልለው ይዘው የንግድና የራሳቸው የኑሮና የመስፋፋት ዓላማን ለማስፈጸም ከፍተኛ እድልን ፈጠረው ሲቀልዱብን አይናችን እያየ እየተመለከትን ለመሆኑ እኛ ማን ነን? ምንስ እንጠብቃለን?

ስለሆነም ህወሓት አሁን ካለበት ሁኔታ አንጻር በምን አይነት ሁኔታ እንዳለና ምን መፍትሔ መፍጠር እንደሚቻል ትንሽ ነገር ልበል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ህወሓት/ ኢህአዴግ አሁን ያለበት ሁኔታ በእኔ እይታ

ህወሓት ለአለፉት 22 ዓመታት ህዝቡን ሲረግጥ፣ ሲጨቁንና ሲከፋፍል የኖረ ከመሆኑ አንጻርና በህዝቡ ላይ ከመቼውም ጊዜያት ባልታየ ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብን ለመከራ፣ለረሃብ፣ ለስደትና ለብዝበዛ ከበዳረጉም በላይ ጥቂቶች ባልተጠበቀ ሁኔታ በሃብት ጣራ የነኩበት ሀገር ከመሆኗ አንጻርና ከሌሎችም ተያያዝ ጉዳዮች ጋር ሲታይ ህወሓት ኢትዮጵያን ለመምራት ሃላፊነት በህዝቡ ሊሰጠው የማይችል መሆኑን ህዝቡና እራሱ ህወሓትና ባለሟሎቹ ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ይሁንና በጉልበትና በአንባገነነነት፣ እንዲሁም ህዝብን በማሸበር የመንግስትን ስልጣን ተቆጣጥረው ለመቀጠል ቆርጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን እየደረሰበት ካለበት መከራ አኳያ ሲታይ ህወሓት ሁኔታዎች እንደከዚህ በፊቱ ሁሉም አልጋ ባልጋ ይሆኑለታል ማለት ግን አይደለም። ምክንያቱም ህወሓት እኩይ የሆነው ተግባሩ ሰፊ ጠላትን አፍርቶለታልና ነው። ስለሆነም ህወሓትን ከዚህ አንጻር ልንገመግመው እንችላለን።

1. ህወሓት በራሱ በህወሓት ውስጥ ሲታይ

በነገራችን ላይ ህወሓት ህዝባዊ መሰረት እንዳለው የሚነገረው ትክክለኛ አለመሆኑን የተለያዩ ማስረጃዎች ማሳየት ይቻላል። ህወሓት በመሰሪነትና በገዳይነት የሚታውቅ ድርጅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በትግራይ ውስጥም ሆነ በራሱ በታጋዮች መካከልም ለዓመታት ታጋዮችን ጭምር በመግደል፣ በማሰቃየት፣ በማሰር፣ በማጥፋት እና መሰል የሽብር ተግባርን በመፍጠር ፍርሃትን በማንገሱ ፣እንዲፈራ በማድረግ በፍርሃት የተፈጠረ ድጋፍ እንጅ ሰው አምኖበት የደገፈው ድርጅት አልነበረም አሁንም አይደለምም። ህወሓት አሁንም በትግራይ ህዝብም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ እየፈጠረ ያለው አንባገነናዊ ሥርዓት በህዝቡ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ህዝብን በመንግስታዊ ሽብርተነት በማስገደድ እንዲሰገድለት ማድረግ ትልቁ አላማ አድርጎ ያለ ድርጅት እንጂ በፍጹም በዲሞክራሲያዊ ግባቶች እንደማያምን የራሱ የፓርቲው አፈጣጠርና አመጣጥ በግልጽ ያሳየናል።

እነዚህ ሁኔታዎች ህወሓት በራሱ ፓርቲ ውስጥ ሰፊ የሆነን ጥላቻን ይዞና፤ ቂም በቀልን የያዞ መሆኑና ብዙዎቹ ሁኔታዎችንና ጊዜዎች እየተጠባበቁ ያሉ መሆናቸውንም ጭምር ሊገባን ይገባል። በተወሰነ አጋጣሚ ሁኔታዎች ቢለወጡ ብዙዎቹ ለመበቃቀል የሚፈላለጉ መሆናቸውን በግልጽ እናያለን፤ ከዚህም በላይ አሁንም ቢሆን በመሃከላቸው ትልልቅ ልዩነቶች ያሉባቸው ከመሆናቸው አንጻር ለአደጋ የተጋለጡም መሆናቸውንም በቀላሉ መረዳት እንችላለን።

2. ህወሓት በኢህአዴግ ውስጥ ካለው ቦታ አንጻር ሲታይ

  • ህወሓት ሌሎችን የኢህአዴግን ፓርቲዎች በማስፈራራትና የሚፈልገውን እየሾመባቸው ለመኖር የሚሻ መሆኑ
  • ሁሌም የበላይነትን ይዞ ለመቆየት ሲል ሌሎችን በማሰር፣ በመግደል፣ በማስፈራራትና የመብትና የዲሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎችን እንዳያነሱ በማድረግ ጥቂቶች በበላይነት እንዲቀጥሉ በማድረግ
  • ዋና ዋና የአገሪቷን ሥልጣኖች በሙሉ በራሱ ቁጥጥር ውስጥ ከማስገባቱ ጋር ተያይዞ በሌሎች ፓርቲዎች ውስጥ ተቀባይነቱ እየተሸረሸረ መሆኑና፤ በተለይም ከ1997 ምርጫ በኋላ አይን ያወጣ አንባገነንነቱን ይዞ መቀጠሉ ችግሩን በይበልጥ እየጎላ መምጣቱና በፓርቲዎቹ መካከል አለመተማመን እየተፈጠረ መምጣቱ
  • ጥቂቶች በመቀያየር እየተሽከረከሩ የሚያስተዳድሩት መሆኑና ለዘለቄታ የሚሆን መሰረት የሌለው መሆኑ
  • በራሱ አባላት ጭምር የተጠላ አንባገነን ፓርቲ መሆኑ

3. ህወሓት በኢትዮጵያ ህዝብ አንጻር

  • ጥቂቶች ይባስም ብለው በቤተሰብ ደረጃ የተሰባሰቡበት ቡድን መሆኑ መታወቁ
  • ኢትዮጵያን የማይወክል ቡድን መሆኑ መታወቁ
  • ጥቂቶች እስከ እድሜ ልካቸው ድረስ በዚህ ቡድን ውስጥ ተሸሽገው የኢትዮጵያ ህዝብ ደም እስከ ጡረታቸው ድረስ የሚፈልጉትን ለማደረግ እንዲችሉ የተዋቀረ የማፍያ ቡድን መሆኑ መታወቁ
  • ወታደራዊ ሃይሉን የሚያስተዳድሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ ሳይሆኑ ጥቂቶች አንድን አካባቢ ብቻ የሚወክሉ ተሰባስበው አገሪቷንና ህዝቧን እያስፈራሩ ለመኖር የተዋቀሩ የማፍያ ቡድን አባላት መሆናቸው መታወቁ
  • በሙስና የተጨማለቁ መሆናቸው ህዝቡ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑ
  • ለህይማኖት ነጻነት ክብር የማይሰጥ መሆኑና የነጻነት አምልኮ መገደቡ መታወቁ
  • በአጠቃላይ በየትኛውም መለኪያ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የተጠላ ቡድን መሆኑ

4. ህወሓት በመከላከያ፣ በፖሊስና በልዩ ልዩ ወታደራዊና የደህንነት መስሪያ ቤት ሲታይ

  • ኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊቷና ሌሎች ወታደራዊ አደረጃጀቶቿ እጅግ በሚገርም መልኩ የአገሪቷ ሳይሆኑ የጥቂት ይልቁንም የአንድ አካባቢ ሰዎች ተሰባስበው የሚያስተዳድሩት መስሪያ ቤት ከመሆኑም በላይ በየትኛውም የአገሪቷ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አገሪቷ ለትልቅ የብዝበዛ መዋቅርነት እንዲያገለግል ተደርጎ የተደራጀ መሆኑ፤ ይህ ተቋም የአገሪቷ ተቋም ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ለወደፊቱም ቢሆን ለአገሪቷም ሆነ ለህዝቦቿ ነጻነት ትልቅ አደጋ መሆኑ
  • ብዙዎች የመከላከያ ሰራዊት አባላትም የአገሪቷ የመከላከያ አወቃቀር መስተካከል እንዳለበት በመጠየቅ ላይ መሆናቸው
  • ወታደሩ ለኢትዮጵያ ከማገልገል ይልቅ የእነዚህን ጥቂት ዘረኞች የብዝበዛ መዋቅር እያስጠበቁ መሆናቸውን እያወቁ መምጣታቸው።
  • በአጠቃላይ ወታደሩ በልዩ ልዩ ጭቆና ውስጥ ያለ መሆኑና ጥቂት ነገር የሚፈልግ መሆኑ

ከላይ እንደተመለከትነው ህወሓት በአጠቃላይ ባለፉት ዓመታት ህዝቡን ባስመረረ መልኩ መጠነ ሰፊ ግፍን በህዝቡ ላይ ፈጽሟል ከዚህ በላይ ምን እስከምንሆን እንደምንጠብቅ አላውቅምም ወይም አልገባኝም። አንድ ነገር ግን ይገባኛል፤ እሱም እያንዳንዳችን ለራሳችን፣ ለህዝባችንና፤ ለሀገራችን የሚጠቅመውን ባለማድረግ፣ በመፍራት፣ እራስን በመውደድ፣ ለግል ጥቅም በመራራጥ፣ በግድየለሽነት፣ ነግበዕኔ ባለማለት፣ ህወሓት ለአቀረበልን ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች እየተገዛን በመንበርከካችንና በጋራ ባለመታገላችን፣ ከጋራ ጠላታችን ከህወሓት ይልቅ ሌሎች ተቃዋሚዎችን ለመተቸት በመሽቀዳደማችንና በሌሎችም ምክንያቶች አሁን እየደረሰብን ላሉ ሀገራዊ ውርደቶች እንድንዳረግ ሆነናል። እነዚህን ነገሮች ለመቀየር እንችል ዘንድ ቆም ብለን ማሰብ መቻል ያለብን ጊዜ ግን አሁን መሆኑ ግልጽ እየሆነ መጥቶልናልና እስኪ እናስብ።

ህወሓት አሁን ለምናየው እኩይ ተግባሩ ታግሎ መጥቶ በምስጊን ህዝብ ደም በነጻነትና በእኩልነት ሰበብ ይህንን ተግባሩን ሲፈጽም እንዴት እኛ ለእውነተኛው እኩልነት መነሳትና የራሳችንን መብት ለማስጠበቅ እንዴት ያቅተናል? ለዚህስ መስዋዕት ለመሆን ለምን ተቸገርን? ማን መስዋዕት እንዲሆን እንጠብቃለን? ግንቦት ሰባት ታግሎ ነጻ እዲያወጣን፣ አርበኞች ነጻ እንዲያወጣን፣ ኦነግ ነጻ እንዲያወጣን ወይስ ሌሎች ነጻ እንዲያወጡን እንደኔ ድርጅት ነጻ አያወጣንም። መጀመሪያ እራሳችን በግል እራስን ነጻ ለማውጣት መቁረጣችንን ማረጋገጥ አለብን። ከዚያ በኋላ ነው ድርጅቶችን መፈለግ ያለብን፣ከዚያ በኋላ ነው በመረጥነው የትግል መንገድ ከጠላታችን ጋር መፋለም የምንችለው፣ በመጀመሪያ ነጻነት ያስፈልገናል ወይስ አያስፈልገንም የሚለው ጉዳይ ሊያግባባን ይገባል፤ ከዚያም ነጻነትን እንዴት እናገኛለን ካልን የመጀመርያው መልስ ድርጅትን መምረጥ ሳይሆን ለመታገልና መስዋዕትነት ለመክፈል መነሳትና መቁረጥ ያስፈልጋል፤ ከዚያም ከቆረጡ ታጋዮች ጋር መደራጀት ይጠብቅብናል። መስዋዕትነት ለመክፈል መቁረጥ ይኖርብናል ሲባል ግን መስዋዕትነት የህይወት መሰዋዕትነት ብቻ አይደለም የጊዜ፣ የገንዘብ፣የእውቀት ማካፈል፣ የመረጃ መስጠት፣ ሌሎችም እንዳሉ ማመንና በአንደኛው ወይም በሌላኛው የትግል መስክ ተሰማርቶና የትግሉ አካል በመሆን ወደትግሉ በመቀላቀል የጋራ ጠላታችንን ዓላማ መቀልበስ ጊዜ የሚሰጠው አይደለምና እሁን እናስብበት! ግዜው አሁን ነው! ያለንም መፍትሔም ይኸው ብቻ ነው።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ሀገራዊ ውርደት ይብቃን!

አበራ ሽፈራው ከጀርመን
aberay12@googlemail.com  

የሚኒሶታዉ ደብረ ሰላም መድሃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን የወያኔ እጅ መንሻ አይሆንም

$
0
0

ከወንድሙ በላይነህ (ሚኒሶታ)

ሰሞኑን ከማቀርባት እህቴ ጋራ ጨዋታ ጀምረን ሳዉዲ አረቢ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ሥላለዉ ስቃይና መከራ ስናወራ እህቴ ቆጣ ብላ፦ አይ እኛ ስለነሱ መከራ ልባችን እዬደማ ተጨናንቀናል፤ ሌሎች በቤተክርስቲያናችን ላይ ከሚዶልቱ ሰይጣኖች ጋር ዛሬ ተጋጭቸ መጣሁ አለችኝ፦ የምን ግጭት ስላት አባወች እኮ ቤተክርሲቲያን ወዳገርቤት ሲኖዶስ አስተዳደር ኢንዲገባ ቅስቀሳ አድርጊ ብለዉኝ በጣም ተናደድኩ ብላ ስትነግረኝ ከርሷ በባሰ ድንጋጤዉ እኔንም በቁሜ አፈዘዘኝ። ኢትዮጵያዉያን ባዓለማት ተበትነዉ እያለቀሱ፦ በአገራቸዉ መኖሪያ አተዉ በሰዉ አገር እየተደበደቡ፦ እዬተደፈሩ፦ እየሞቱ እንዴት ዛሬ ወደወያኔ ለመግባት ቅስቀሳ አካህጅ ይሉኛል ብላ አለቀሰች። ጀሮ ከተማ ነዉ ሁሉ ይሰማበታል፦ በእርግጥም ከሃያ ሶስት የግፍ ስርዓት ዓመታት በሗላ ይህንን መስማት ያስደነግጣል፦ እንዲያዉም በዉጭ ያለን ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በሳዉዲ አረቢያ እዬተጎዱ ላሉ ወገኖቻችን ተባብረን በአንድ ላይ በምናለቅስበት ሰዓት ይህን አፍራሽ ስራ ከጀመሩ መድሃኒዓለም ስራዉን ይሰራል አልኳት እና ጨዋታየን አቋረጥኩ።
deb
ደሙ የዋጀበትን መስቀል ተሸክመዉ ግን የዕምነት ይህይዎታቸዉ በመዋዕለ ንዋይ ህሊናቸዉ የተሰዎረ የወያኔ ምልምል ቄሶችና ዘማሪዎች ለጥቅማቸዉና ለወደፊት ሹመታቸዉ የባዘኑ ተስፈኞች ቤተ ክርስቲያናችን ለወያነዉ ፓትራሪክ ለማስረከብ ሃያ አራት ሰዓት በሴራ ተጠምደዉ ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛሉ። እኩይ ስራቸዉን ተግባራዊ ለማድረግም በመድሃኒአለም በራፍ የታየ ምዕመናንን ሁሉ በጌቤታቸዉ እዬጋበዙ ወደ አገርቤቱ ሲነዶስ ለማስገባት ቀስቅሱ እያሉ መሃላ የሚያስገቡት ቁጥር ጥቂት አይደሉም። በወያኔ ዉስጣዊ ሎሌነት ታማኝ የሁኑት ቀንደኛወች ከአሁኑ ጀምሮ የሚቸራቸዉ (የሚሰጣቸዉ),ሹመት ምን እንደሆነ፦ በኢትዮጵያ ዉስጥ የከፈቱት ቢዝነስ ለነሱ ብቻ ሳይሆን ለአገሪቱ ተስፋ እንደሚሆን ተረጋግጦላቸዉ፦ ተማሪ የሆኑ ዘማሪያን ም ለ SCHOLAR እንደሚከፈላቸዉ ቃል እዬተገባ መሆኑ አንዳዶችን ነገሩ አስደንግጧቸዉ ለመቃወም በመነሳሳት ላይ ናቸዉ።

የሚገርመዉ ነገር አብዛኛወቹ በቤተ ክርስቲያኑ ምስረታና ግንባታ ያልነበሩ፦ እዳ ከተከፈለ ለስዉር ዓላማ በወያኔ የዘር መስመር አምነዉ ለመጥፎ ተግባር የተሰገሰጉ፤ ነገር ግን እራሳቸዉን መስራች ነን ብለዉ የመዘገቡ፦ በድምጽ ለማሸነፍ የአብዛኛ አባላት ድጋፍ ለማግኘት በየሰፈሩ እየተዘዋወሩ መልካም ዘመድ መስለዉ ለማሳመን የቆጡን የባጡን እያሉ ነዉ። ለመሆኑ ወያኔ ምን አዲስ ነገር ይዟል ብለዉ ሊያሳምኑን ፈለጉ? የህዝቦቻችን ድምጽ ለሃያ ሶስት ዓመታት በወያኔ ሙሉ በሙሉ ታፍኖ፤ ሃይማኖታችን በዘር ስርዓት ተቦርቡሩ፤ በወያኔ የበላይነት በየአድባራቱ ተመዝብሮl፦ የዕምነት ነጻነት ተነፍጎ። አሁን በያዝነዉ ወር እንkኳን በሳዉዲ አረቢያ ጥቃት ለደረሰባቸዉ ኢትዮጵያዊያን በአዲሳበባ ድምጻቸዉን እንዳያሰሙ ወገኖቻችን ተከልክለዉ መንግስት አጣን እያሉ ከሰባት ወራት ጩኸት በሗላ ለሞት ሲዳረጉ፦ አገራዊ ዉርደት ሲደርስብን እንዴትስ የወያኔ አጋርነት አሁን ይሞከራል? ወይስ አባ ማትያስ የወያኔ የዘር ምልምል ካድሬ ጳጳስ አደሉም ብለዉ ለማሳመን እየተጃጃሉ ነዉ። እኛማ አዉቀናል……:አያጅቦ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ።

በሚኒሶታ ኢትዮጵያዉያን በህይወት እያለን ደብረ ሰላም መድሃኒአልምን ወያኔ አይረከበዉም። አወ ሰሞኑን እኛን እዉነተኛ አማኞችን ለማዋረድና በወያኔ ቃል የተገባዉን ለማሳካት፤ ግድያ ለመጣል፤ የነጻነቱን ትግል እንደበረዶ ለማቀዝቀዝ፦ በአህዝበ ክርስቲያን ላይ የመርዝ ሴራ የምትረጩ ሁሉ መድሃኒአለም በሩን ዘግቷል። ከወደቃችሁ በሗላ ወያኔ እንደማያነሳችሁ ካሁኑ እወቁት፤የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች እንዳይሆንባችሁ ወዮላችሁ። ይልቅስ እናተዉ የሃጣን ሎሌ ሁናችሁ ንጹ ጻድቃንን ግራ አታጋቡ፤ሰላም አታችሁ ህዝበ ክርስቲያን አታስቆጡ። እዉነት ልበላችሁ እሚመቻችሁ ከሆነ ከዚህ አሜሪካ ካሉ የወያኔ ቤተክርስቲያናት መጀመሪ ጠቅላችሁ ግቡና የወያኔን አስተዳደር ሞክሩት በቤተ ክርስቲያን እንኳ ምርጫ ማካሄድም አትችሉም። እኛ የምንለዉ መድሃኒአለምን ተዉት ወይም ሃብታችሁን ይዛችሁ ልቀቁት። ከእንግዲህ ይህ የተቀደሰ ቦታ የንግድም ሆነ የስልጣን ቦታም አይሆንም። እናንተ እጃችሁን ስጡ የዕምነት ቦታችን ግን እጅ መንሻ ለማድረግ ፍጹም አትሞክሩ። ህዝበ ክርስቲያን ሆይ የእግዚአብሔር ቤትህን ጠብቅ።

ከወንድሙ በላይነህ

ወስብሃት ለእግዚአብሔር

በቃን ሊባል የሚገባው ሥርዓት (ዮናስ አዲሱ ቱፋ)

$
0
0

ዮናስ አዲሱ ቱፋ / ከጀርመን

Bekaበየትኛውም ታሪካችን በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን ኢትዮጵያውያን እንደተዋረድን መቼም ተዋርደን አናውቅም ።  ሊያውም በዚህ ዓለም በሰለጠነችበት ዘመን የአገሬ ህዝቦች ለስደት የተዳረግንበት፣ በልዩ ልዩ አገራት ለችግር የተዳረግንበት፣ ጥቂቶች አይን ባወጣ ብዝበዛ ውስጥ የተሳተፉበት፣ የህዝቦች የመሬት ባለቤትነት ተነጥቆ የአገሪቷ መሬትና የተፈጥሮ ኋብቶች በጥቂቶች በቁጥጥር ስር የሆነበት ዘመን ፣ የተወሰኑ ኋይሎች አገሪቷን በቁጥጥር ስር አስገብተው ህዝቡን በሚፈልጉት መንገድ የሚመሩበት ፣ ህዝቡና አገሪቷ በግዳጅ የምትመራበት ዘመን ሊያውም በሰለጠነ ዘመን፣ አገራችንና ህዝቦቿ በእፍረት ውስጥ የወደቅንበት ዘመን፣ የህዝባችን መከራ ከሃገራችን አልፎ በውጭው አገራት በመከራ ላይ ያለንበት ዘመን ፡፡

ይበልጥኑም የአገራችን ወጣቶችና ሴቶች በአገሪቷ ውስጥ የስራ እድል የሚሰጠው ለኢህአዲግ አባላትና ደጋፊውች ብቻ እንደሆነ   አውቀው የሰው አገርን እንደተሻለ የስራ እድል ስፍራ የመረጡ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በየአረብ አገራት ለዓመታት ሊያውም በከፍተኛ ችግርና መከራ ውስጥ ሆነው፣ ያለባቸውን ጭቆናንና መከራ ተቋቁመው በኖሩና በአገር ቤት ለሚገኙ ዘመዶቻቸው በተለይም በድህነት ያሳደጓቸውን  አባትና እናቶቻቸውን ለመደጎም ቁምስቅላቸውን እየዩ በሚኖሩባት ሳውዲአረቢያ ይባስ ብሎ ወገንና አገር እንደሌላቸው ፤ ይልቁንም ሊከላከልላቸው የሚችል መንግስት እንደሌላቸው የተረዱት ሳውዲ አረቢያዎች፤ በሌሎች  አገራት ዜጎች ላይ ባልፈጸሙት መልኩ ኢትዮጵያውያኑን ዓለም ሁሉ እያየ ሲግድሏቸው፣ ሲገርፏቸው፣ ሲደፍሯቸው፣ እየገደሉ ስጋቸውን ሲቆራርሱና እንደውሻ በመንገድ ላይ ሲታዩ ማየት ምን ያህል ያደማል፣ ያቆስላል፣ ያማል፣ ያስለቅሳል።

የሳውዲ አረቢያው በዚህ መልኩ ታየ እንጂ በሌሎችም የአረቡ ዓለም በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ችግርና መከራ ምን ያህል አስቸጋሪና የከፋ መሆኑን በቀላሉ መገመት ይቻላል። በአረቡ አለም የታየው ስቃይ ምን አልባትም ኢትዮጵያውያን በአገራችንም ከምናየው መከራና ስቃይ በምንም መልኩ እንደማይተናነስ ከማንም  የተሰወረ አይደለም። በአረቡ አለም የተፈጸመው በባዕዳን የተፈጸመ ከመሆኑ ውጭ በመንገድ ላይ ተገደሉ አገር ቤትም ውስጥ ግድያ አለ፣ እስራትና ድብደባም በአገር ቤትም አለ፣ ችግርና ድህነት በአገር ቤት በዝቶ አይደለም እንዴ እህቶቻችን ለመሰደድ የተዳረጉት ፣ ሳዊዲአረቢያ ሁሉም  በህግ ወጥ መንገድ በሌላ አገር ዞረው ወጡ እንዴ? አይመስለኝም! ብዙዎች የህወሃት ባለማዋሎች  በደላላነት በተሰማሩበት የሰዎች  ማዟዟር አማካኝነት ይህ እንደተከናወነ እየታወቀ  እንዳላወቁ እየሆኑ ህወሃቶች በህዝቡ ላይ ሲያላግጡ ያሳዝናል። ለመሆኑ ከአገር ተደብቆ የወጣው ምን ያህሉ ነው? አብዛኛው ወጣት መሆኑና ይልቁንም በዚሁ በአገራችን ዘረኛ ቡድን አመራር ዘመን  የተወለዱና ያደጉ መሆናቸውን ማንም ምንም መረጃ ሳያገላብጥ በመገናኛ ብዙሃን ላይ ያሉትን ፎትግራፎች አይቶ በቀላሉ መገመት ይችላል።

ዛሬ አገራችን ለራሳቸው ጥቅም በተደራጁ ሃይሎች እየተመራች መሆኑ፣ ለአገር ሳይሆን ለቡድናዊ ጥቅሞቻቸው ቆርጠው በተነሱ፣ ለአገሪቷ ህዝቦችና ለአገሪቷ ምንም የማይቆረቆሩ ተሰብስበው አገሪቷን የሚመሩ በመሆኑ ፤ ምንም የህዝብ ውክልና ሳይኖራቸው በግድና ህዝብን በማስገደድ ለሁሌም አገሪቷን ለመበዝበዝ በቆረጡ ኋይሎች እጅ ወድቃ ያለች አገር በመሆኗ ፤ የተፈጠሩ ችግሮች እንጂ በህዝብና በመንግስት መካከል ልዩነቶች ባይኖሩና ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው በጋራ ሰርተን መኖር አቅቶን አይደለም፣ ማደግም አቅቶን አይደለም፣ ተሳስበን ለሃገራችን መስራትም አቅቶንም አይደለም ፣ 22 ዓመታት አሁን ካለንበት ውድቀት ለመዳንበቂ ጊዜ ሳይሆን ቀርቶም አይደለም።

በኢትዮጵያውያን  ስም ከውጭ አገራት  በብድር፣ በእርዳታና በንግድ የተሰበሰቡ ገንዘቦችን በውጭ ባንኮች እያሸሹ የሚያስቀምጡት እነማን ሆኑና ህወሓቶች አይደሉምን? በአገሪቷ ሃብት ላይ የብዝበዛ ስራን የሚፈጽም ማን ሆነና ህወሓቶች አይደሉምን ? ለዚህስ የህዝብ ድህነት ላይ መውደቅና ለችግር መዳረግ ምክንያቱ ማን ሆነና ህወሓቶች አይደሉምን ? ዛሬ ሀብታሞቹና በአገሪቷ ውስጥ እንደፈለጉ በአገሪቷ ሃብት የሚባልጉት እነማን ሆኑና ህወሓቶች አይደሉምን ? ዛሬ የአገሪቷ ህዝብ መከራ የሚያየው በማን ሆነና ነው ዛሬ ህወሃት/ኢህአዲግ አሳቢ ሆኖ ለመታየት የሚፈልገው ?

የችግሮቻችን ምክንያቶች የህዝባችን ስንፍና፣ አልሰራ ባይነት እና ተመሳሳይ ጉዳዮች ሳይሆኑ ህወሃት የፈጠረው የማህበራዊ፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ምስቅልቅል እንጂ ህዝቡ በራሱ ላይ የፈጠረው ችግር እንዳልሆነ ማንንም ለማስረዳት መሞከር አያስፈልግም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሁሉ የችግሩ ምክንያትንም ሆነ የአገሪቷንና የህዝቧን መከራ ምክንያቶች ህወሃቶች እንደሆኑ በግልጽ ያውቃል  ። ይህንንም አፍረት ለመቋቋም ህዝቡ የሚችለውን ለማድረግ የቆረጠበት ሰዓት ነው።

እንግዲህ ህወሃቶች የአገሪቷና የህዝቧ እፍረቶች ስፍራችሁን አዘጋጅታችኋል፣ የምትፈልጉትን በዝብዛችኋል፣ አይን ያወጧ ዝርፊያን ፈጽማችኋል፣ ዘረኝነትን አንግሳችሁ ህዝቡን በመለያየት ለጋራ አላማ እንዳይሰራ አድርጋችኋል፣ ለእናንተ የብዝበዛ ዘመናችሁን ለማርዘም ጠቅሟችኋል ለህዝቡና ለአገሪቷ ግን ትልቅ ፈተናና መከራ ሆናችኋላና ይበቃችኋል ።  እናንተ የማትሸከሙትን ሁሉ አሸክማችሁ አሰቃይታችሁታል፣ በእናንተና በልጆቻችሁ ወይም በቤተሰቦቻችሁ ላይ ሊደርስ የማትፈልጉትን ፈጽማችሁበታል። አሁን ለራሳችሁ ስትሉ የምታስቡበት መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛላችሁ።

ይህ ካልሆነ ግን ህዝቡ ብዙ ታግሷል፤ አሁን ግን የእፍረታችን ምክንያቶች የሆናችሁ ህወሃቶች ካልሆነ ግን ይህ የፈጸማችሁትን ግፍ ለፍርድ የሚያቀርብን ትግል እያፋጠናችሁ እንደሆነ ልመክራችሁ እፈልጋለሁ። አገራችን የናንተ ብቻ ሳትሆን የሁላችንም ናት። ወደዳችሁም  ጠላችሁም የአገሪቷ መጻኢ ፋንታን የመወሰን መብት የአገሪቷ ህዝብ እንጂ የጥቂት በዝባዥ ህወሃቶች እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል።

የአገሬ ህዝቦች ዛሬ የችግራችንን ጥልቀት ከዚህ በኋላ በጽሁፍ በማስረዳት መሞከር የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ አይደለንም  ማንም ኢትዮጵያዊ ሁሉ የህወሓት/ኢህአዴግ ችግር እቤቱ ያልገባ የለም፣ በህወሃት ያልተገደለ የለም፣ በህወሃት/ኢህአዴግ ክብሩ ያልተነካ የለም፣ በህወሃት/ኢህአዴግ ያልተሰደደ የለም፣ በህወሓት/ኢህአዴግ ቤት ንብረቱ ያልተነጠቀ የለም፣  በህወሓት/ኢህአዴግ ያላለቀሰ የለም ዛሬ ግን በአንድ ጉዳይ ላይ ልንስማማ ይገባናል። ይህም የዚህ ሁሉ ችግር ምክንያትና የመከራችን ሁሉ፣ የአፍረታችንም ሁሉ ምክንያት በሆነው በህወሓት/ኢህአዴግ መቃብ ላይ የተስፋችንን ችቦ ማውለብለብ ይገባል። ለዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ለትግል ሊቆርጥ ይገባል። በህወሓት/ኢህአዴግ መቃብር ላይ የተስፋችንን ችቦ እናቀጣጥል! በዚህም የአገራችን ህዝቦች መከራ ያብቃ!   አት ባለሓት ሕሕሕ

 

ድል ለኢትዮጵያ ህዝቦች !

ማን ነው የተዋረደው? (ይሄይስ አእምሮ)

$
0
0

ይሄይስ አእምሮ

ከጥቂት ሣምንታት ወዲህ በተለይ የኢትዮጵያን የወያኔ መንግሥት በሚቃወሙ የሚዲያ ማዕከላት ዘንድ ዋና መነጋገሪያ ሆኖ የሚገኘው በሳዑዲ የኢትዮጵያውያን መንገላታትና መሰቃየት እንዲሁም ከኢሰብኣዊነትም በወረደ ሁኔታ በግፍ መጨፍጨፍ ነው፡፡ ዜጎቻችን በአካፑልኮ ቤይ የመዝናኛ ሥፍራ ሲንሸራሸሩ ከርመው የመጡ ይመስል ይህ ምስል በኢትዮጵያው የወያኔ ሚዲያ በአስደሳች መልክ እየቀረበ ቢሆንም ትክክለኛውን መረጃ ከአማራጭ የዜና ምንጮች እንደወረደ እንደምንከታተለው ከሆነ ግን ከሀገርና ከሕዝብ ኅልውና አኳያ ነገሩ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ከአንድ ጨለማ ውስጥ ብርሃን እንደሚጸነስ ሁሉ ከዚህ አስከፊ ገጠመኝ ውስጥ የፈነጠቀው የሕዝብ አንድነት ግን በሌላ ወገን ተስፋችን እንዲያንሠራራ አድርጓል፡፡ ፈረንጆቹ “blessing in disguise” ወይም “mixed blessing” እንደሚሉት ይህ መጥፎ አጋጣሚ ሊረሳ የተቃረበውን የሕዝብ አንድነት በማደስ በመላው ዓለም የተበተነው ኢትዮጵያዊ በአንድነት ቆሞ ድምፁን እንዲያሰማና ለጋራ ኅለውናው እንዲያለቅስ አስችሎታል፡፡ በተመሳሳይም የሕዝቡ ስሜትና እውነተኛ ፍላጎት በየስብሰባዎቹና ሰላማዊ ሰልፎቹ ሲንጸባረቅ እንደተመለከትነው ወያኔን ከመሰሉ በርካታ ከፋፋይ የዘር ፖለቲከኞችና የሃይማኖት ቡድኖች ሸረኛ ሤራ ባፈነገጠ መልኩ በአንድ ሉዓላዊ መንግሥትና በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ሥር የመኖር የቆዬ ኢትዮጵያዊ አብሮነቱን የታዘብንበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በሌላ አቅጣጫ ደግሞ በዚህ ስቃይ ለማትረፍ የሚፈልጉ በተለይም ወያኔዎችና መሰል ልበ ደንዳናዎች ለምርጫ ዝግጅት በፕሮፓጋንዳነት ሲጠቀሙበት፣ ለገቢ ማግበስበሻም ከማዋል እንደማይመለሱ እየተነገረ ነው፡፡

ከጓደኞች ጋር ስንወያይ አንዳንዶቻችን ይህ ነገር በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ የተነጣጠረ ሣይሆን በአጠቃላይ በሰው ልጅ ኅልውና ላይ የተቃጣ ታላቅ የክፍለ ዘመኑ ወንጀል መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ስለዚህ ማፈር ያለበት ነጭ ጥቁር ሳይል የሰው ልጅ በአጠቃላይ እንጂ ኢትዮጵያውያን ብቻ አይደሉም ወደሚለው እሳቤ አዘንብለናል፡፡ አንድ የዓለም ዜጋ በመጥቆር በመንጣቱ ወይም በመክበር በመደኽየቱ፣ በዚህ ወይ በዚያ ዘውግ አባልነቱ፣ በዚያ ወይ በዚህ ቋንቋ ተናጋሪነቱ፣ ወይም በመስለምና ባለመስለሙ፣ በክርስትና እምነትም በመጠመቁ ወይ ባለመጠመቁ ሣይሆን በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ እንዲህ ዓይነት ዘግናኝ ግፍ የሚደርስበት ከሆነ ነግ ከነግ ወዲያ ታሪክ ሲለወጥ ይህ ዓይነቱ ውርጅብኝ በማንም ሌላ ወገን ላይ እንደማይደርስ ማንም ዋስትና ሊሰጥ አይችልም፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ዕልቂት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአይሁዶች ላይ ከደረሰው ቢበልጥ እንጂ አይተናነስም፤ አሁን በኢትዮጵያውያን ላይ በሀገራቸው ውስጥም ሆነ ከሀገራቸው ውጭ እየደረሰባቸው የሚገኘው ዕልቂት ሩዋንዳና ዩጎዝላቪያ ወይም ኢራቅና አርመን ውስጥ ከደረሰው ጭፍጨፋ ቢብስ እንጂ አያንስም፡፡ መነሻ ምክንያታቸው የሚለያዩ ግን ይበልጡን ከኢኮኖሚ ጥቅምና ከዓላማ ቁርኝት ጋር የሚያያዙ የሰው ዘር ፍጅቶች በየዘመናቱ በብዙ ሀገራት ተፈጽመዋል፤ አሁንም ድረስ በመፈጸም ላይ ናቸው፡፡ ነገር ግን ግንዛቤ ያላገኘው ነገር በአንዱ ላይ የሚፈጸመው ነገር በለሌላው ላይ እንደተፈጸመ ያለመቁጠር ነው፡፡ ይህ ትልቅ ዓለም አቀፍ ችግር ነው፡፡ በአንድ የየትኛውም ሀገር ዜጋ ላይ የሚደርስ ችግር በማንኛውም የሰው ልጅ ላይ እንደደረስ ችግር ካልተቆጠረ በሰው ልጆች አጠቃላይ አስተሳሰብ ላይ የተዛባ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ይህ የተቃወሰ አስተሳሰብና አመለካከት መፍትሔ ካላገኘ የሰው ልጅ በውድቀት መንገድ እንደነጎደ ይቀጥላል ምፅዓቱንም ያቃርባል እንጂ ዓለማችን ወደተሻለ ኅሊናዊና ቁሣዊ የዕድገት ጫፍ አትደርስም፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለው መከራና ውርደት ወቅቱን ጠብቆ ነገ በሌላ ሕዝብና መንግሥት ላይ ይደርሳል – እንደእስካሁኑ ሁሉ፡፡ ይህ አነጋገር የትንቢት ጉዳይ ሣይሆን ማንም አእምሮ አለኝ የሚል የዓለም ዜጋ ሁሉ ሊረዳው የሚችል ነባራዊ እውነታና የማይሸሹት ወረፋ ነው – ወረፋ እስኪደርስ ያለው የጊዜ እርዝማኔ እያነሆለላቸው ብዙዎች ይሞኛሉ፡፡ ያዋጣ የነበረው አካሄድ ግን በምንም ዓይነት የልዩነት አጥር ራስን ሳያካልሉ በሰው ልጅነት ብቻ አንዱ የአንዱን ችግር ለማስወገድ መጣር ነበር፡፡ በሆነ አጋጣሚ አንድኛችን ከሌላኛችን በተለዬ ሁኔታ ወደአውሬነት በምንለወጥበትና እንደሳዑዲዎች አንድ ምሥኪን ወገን ላይ ቀን የሰጠንን ኃይልና ጉልበት በምናሳይበት ጊዜ በዝምታና በአግራሞት ማለፍ ሣይሆን ሃይ ብንልና ብናስቆም ተጠቃሚዎቹ ሁላችንም የሰው ዘሮች በሆንን ነበር፡፡ ሰዎች ግን ለዚያ አልታደልንምና የዘራነውን እንዳጨድን ዝንታለማችንን በየተራ ስናለቅስ እንኖራለን፡፡ ወደኋላው ላይና ቋቱ ሲሞላ ግን ሁላችንም በኅብረት የምናለቅስበት ዘመን መምጣቱ አይቀርም – ያኔ ታዲያ አልቃሽም አስለቃሽም፣ ፊሽካ ነፊም አስተኳሽም … ሁሉም ተያይዞ የደም ዕንባ እንደጎርፍ ያወርዳል፡፡ የምናስቀምጠው ነገር ሁሉ የኛው ነው – ማንም አይወስድብንም፡፡ በባንክ የምናኖረውን ገንዘብ ሲያስፈልገን አውጥተን እንደምንጠቀምበት ሁሉ በሰዎች ላይ የምንሠራውን የግፍ መዝገብም ሁሉ የምናወራርድበት ጊዜ ሲመጣ በእጃችን የገቡ ሌሎች ምሥኪኖችን ባስለቀስነው መጠንና ከዚያም በላይ እኛም እናለቅሳለን፡፡ አሁን ግን በብረት አጥር ውስጥ የምንኖርና መቼም ቢሆን ምንም ችግር እንደማይደርስብን የምንቆጥር ወገኖች አንዳችን በአንዳችን ችግር እየተዝናናን መኖርን መርጠናል፡፡ የምንመርጠው መንገድ ሁሉ ግን አዋጭ ሊሆን እንደማይችል ከታላቁ መምህር ከታሪክ መማር በተገባን ነበር፡፡ ያለቀሱ ይደሰታሉ፤ ያስለቀሱም ያለቅሳሉ፡፡

ዐረቦች በእኔ ዕድሜ ኢትዮጵያ ውስጥ በርሜል ገፊ ነበሩ፡፡ የሚገፉት በርሜልም የነዳጅ ሣይሆን የውሃ ነው፡፡ ከአምስትና ከአሥር ኪሎ ሜትሮች ከሚገኙ የወንዝና የጉድጓድ ውሃዎች በሽክናና በቅል እየቀዱ ሃዲድ በተገጠመላቸው በርሜሎች በመግፋት ለሀብታም ኢትዮጵያውያን እየሸጡ በሚያገኙት የላብ ፍሬ ይተዳደሩ ነበር – የዛሬውን አያድርገውና፡፡ ዛሬና አሁን ግን ያን መገፋታቸውን ፈጣሪ ተመልክቶ ይሄውና በየሥፍራው እንደምንጭ እየቆፈሩ በሚያወጡት ነዳጅ ጠግበው ይሠሩትን አጥተዋል፡፡ ለዚህም ያበቃቻቸው ባለብዙ ካርድ ሀገር የሆነችው አሜሪካ ናት፡፡ ገንዘብ በፍጥነት የሚገባለት ጭንቅላት ውስጥ ደግሞ የሚያስብ አንጎል አይኖርም፤ ገንዘቡ ወደ ኪስ ሲንዶለዶል አንጎል ከጭንቅላት እየወጣ ወደከርስ ወርዶ ይደበቃል፡፡ ዐረብ ደግሞ ስናየው አብዛኛው ሃይማኖት የለሽ ጥጋበኛ ነው፡፡ እንደዐረብ አስመሳይና መረን የለም፡፡ ዕውቀቱ ሣይኖር ፔትሮዶላሩ ተትረፈረፈላቸውና የሚሆኑትን አጡ፡፡ ዕድሜ ለአሜሪካ ሥልጣኔን በገንዘባቸው ከአሜሪካና አውሮፓ አመጡላቸው – ዐረቦች የዛሬ ስንት ዓመት ከተማቸውን በፍየልና በዓሣሞች ያስጸዱ እንዳልነበር ዛሬ የሀበሻ ጉልበትና የአሜሪካን ቴክኖሎጂ አጠገባቸው፡፡ እነዚህ ለይስሙላ “አላሁኣክበር” እያሉ ሃይማኖት ያላቸው የሚመስሉ ስድ ሰዎች በተለይ ሀብታሞቹና የቤተ መንግሥት ልዑላኑ የሚሠሩትንና በኪታቦቻቸው የሠፈሩትን ቀኖና ሃይማኖት ብናስተያይ ከሞላ ጎደል ሁላቸውም የሰይጣን አምላኪዎች መሆናቸውን መረዳት አይከብደንም፡፡ እነዚህ የለዬለትን ጥቁር ሰይጣን አምላኪ ዐረቦች በግልጽ ባይሆንም ብዙዎቹ በኅቡዕ ሉሲፈርን ከሚያመልኩ የሩቅ አጋዦቻቸውና የሀብት ተጋሪዎቻቸው ነጫጭባዎች ጋር እየተመሣጠሩ ዓለምን ከሃይማኖት፣ ከሞራልና ከባህላዊ ትውፊቶች አንጻር እያላሸቋት ይገኛሉ፡፡ የሁለቱም እምነት አንድ ነው፤ በገራምነት ሉሲፈር የተሻለ ቢሆንም ሲመጣበት ከሰይጣን ባልተናነሰ ቁጡ ነው፤ ለአንድ ክፋት ተመጣጣኝ ደግነት እንዳለው የሚያምኑት ሉሲፈራውያን ለጥቅማቸው ሲሉ ከሰይጣናውን በማይተናነስ ሁኔታ ዓለምን እስከመሸጥና መለወጥ ይደርሳሉ፡፡ የሁለቱም የእምነት መሠረት ገንዘብ ነው፡፡ ገንዘብ ሁሉን ያደርጋልና ሥልጣንንና ገንዘብን የተቆጣጠረ ወገን ሁሉ ያሻውን መሆንና ማድረግም ይችላል፡፡ ዴሞክራሲ፣ ፍትህና ነጻነት ጭምብሎች ናቸው – ለሁሉም እኩል የማይሠሩ የሚጠሉትን የማንበርከኪያ ካርዶችም ጭምር፡፡ ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ የተባለው ለጊዜውና በአሁኑ የዓለማችን ቅርጽ እውነት ነው፡፡

ገንዘብ ካለህ ዴሞክራሲን ከአሜሪካም ሆነ ከእንግሊዝ ትገዛለህ፤ ገዝተህም ለሕዝብህ ታድላለህ፤ አድለህም “ዴሞክራሲን ለሕዝቤ አደልኩ!” ብለህ ብትናገር ትታመናለህ፡፡ ባትታመንም በዴሞክራሲያዊነትህ ተቀባይነትን አታጣም፡፡ ዕድሜ ለገንዘብህ፡፡ ድሃ ከሆንክ ግን በኢዴሞክራሲያዊነት፣ በአሸባሪነት፣ በሰብኣዊ መብት ጣሸነት፣ በምርጫ አጭበርባሪነት፣ … ትወቀሳለህ፤ ወደ ጓንታናሞ ልትላክና ልትበሰብስ ዕድል ከቀናህም ወደዘሄግ የነሱው መሣሪያ ልትቀርብ ትችላለህ፡፡ በአይኤም ኤፍና በዓለም ባንክ ልምጮችም ልትሸነቆጥ ትችላለህ፤ በልዩ ልዩ ማዕቀቦችና ጠና ሲልም በኔቶ ጦርና በተናጠል የኃያላን ብትርም ልትኮረኮም ትችላለህ፡፡ ዓለማችን እንዲህ ዐይናቸውን በጨው ባጠቡና ባፈጠጡ መድሎዎች የተሞላች ናት፡፡ አንበሣ ምን ይበላል ተበድሮ ምን ይከፍላል ማን ጠይቆ  ነው ነገሩ – ግን አይምሰልህ – የቀንም ቀን አለው ፤ የጀግናም ጀግና አለው፤ ፍርድ ቢዘገይ አይቀርም፡፡ እናም ወዮ እንላለን – ወዮ ለቀኑ፡፡ ከሳዑዲና ከመሰል ጭራቅና ሰይጣን መንግሥታት አንሶላ ለምትጋፈፈዋ የሉሲፈር ሀገር ወዮላት! የ”ወዮላት!” መንስኤውም ፍርደ ገምድልነቷና ያንን ተከትሎ ቢሊዮኖች መከራና ስቃይ ውስጥ መግባታቸው ነው – ሚዛናዊ ፍርድን የማያውቅ እንዲያውቅ የሚገደድበት አጋጣሚ ይመጣለታል – ወደደም ጠላም፡፡ ይህች ሀገር የምትለውንና የምትሠራውን አጥኑ፡፡ ያለባትንም ወዮታ ልብ በሉ፡፡ የአሁኑንም ብቻ አትመልከቱ፡፡ ለዚህ ለዚህማ ኢትዮጵያም በዓለም ከነበሩ አራት ኃያላን መንግሥታት አንዷና እስከየመንና ከዚያም ባለፈ  የምታስገብር ታላቅ ሀገር ነበረች፡፡ ብዙ የአሁን ነገሮች ታሪክ የሚሆኑበት፣ ብዙ የወደፊት ነገሮችም የአሁን የሚሆኑበት ዕፁብ ድንቅ ሁኔታዎች ይከሰታሉና እንዳለ የሚቀር፣ እንደቀረም የሚኖር ነገር አለመኖሩን ማስታወስ ይገባል፡፡ ይህች ቀን በቅርብ ታልፋለች፡፡…

በልጅነቴ ቤተሰብ ወደሱቅ ሄጄ ዕቃ እንደገዛ ይልኩኝ የነበረው “ዐረብ ቤት ሄደህ ይህን ዕቃ ገዝተህ ና!” እንጂ ወደሱቅ ሂደህ ይህን ወይ ያን ግዛ አይሉኝም ነበር፡፡ በ”ሰይቼንቶ ሄድኩ” ይባል የነበረውና አሁንም ድረስ በአንጋፋ ዜጎች የሚባለው የመጀመሪያዋን የጣሊያን ታክሲ መኪና እንደሚያስታውሰን ሁሉ ዐረብ ቤትም የሚያስታውሰን የሱቅ ሸቀጦች ይበልጡን በዐረቦች መጀመራቸውን ወይም በነሱ ይካሄዱ የነበረ መሆኑን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከእኛም በላይ የነሱ ቤት ነበረች፡፡ “ፈረስት ሂጅራ”ን ትተነው ትናንትናና ከትናንት ወዲያ በነገሥታቱ ዘመን የአሁኗ ኢትዮጵያ በልጽገውና ከብረው ከእኛው ባልተናነሰ እንዲያውም በበለጠ እየተዘባነኑ የሚኖሩባት የእኩል ሀገር ነበረች – ለነገሩ ኢትዮጵያ ለውጪዎች እንጂ ለራሷ ልጆች ሆና አታውቅም – ሀገራችን ብዙውን ጊዜ የሚጠቅማትን ከማይጠቅማት ያለመለየት ችግር አለባት፡፡ ዛሬ ወያኔ የሚባል ሀገር አጥፊ አንበጣና ተምች መላዋ ሀገራችንን ቀስፎ ስለያዛት የተለዬ ውርደት ገጠመንና ለዚህ ውርደት ተዳረግን እንጂ ዐረቦች ልብ ኖሯቸው እንዲህ ሊጫወቱብን የሚቃጡ አልነበሩም፡፡ ጊዜ ነው፡፡ ጊዜ ሁሉም ነገር ነው፡፡ ‹ጊዜ ባለውሉ› ሁሉንም ያሳያል፡፡ … ዕድሜ ከሰጠን ደግሞ ወደፊት ይህን ሂሳባቸውን ሲያወራርዱ እናይ ይሆናል፡፡ አንድዬን ለበቀልና ለአጸፋዊ ምላሽ ማን ብሎት? አሁን አሁንስ ፈጣሪ ለዚህ ተግባር ብቻ ያለ ይመስለኛል – ለቅጣትና የኃጢኣት ዋጋን ለመስጠት፡፡

የሆኖ ሆኖ ግን ኢትዮጵያዊ መንግሥት ስለሌለን እየደረሰብን ያለው ይህ ግፍና ቅጣት በኛ ላይ ብቻ የወረድ የውርደትና ቅሌት መዓት ሣይሆን በሰው ልጆች ላይ እየደረሰ ያለ መቅሰፍት መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ በሳዑዲ አንድ ዜጋ አለኃጢኣትና አለወንጀል ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ብቻ በጠራራ ፀሐይ ታረደ ማለት የታረደው ሰው በሃይማኖትና በፆታ ወይም በመልክዓ ምድር ሳይወሰን ነጭም ነው፤ ጥቁርም ነው፤ ቢጫም ነው፡፡ አለፍርድና አለአበሳው የታረደው ሰው ሁሉንም የሰው ዘር የሚወክል እንጂ አንድን ሀገር ብቻ ለይቶ፣ የአንዲትን ሀር ዜጎች ብቻ አጣቅሶ በውርደት የሚያስጠራ ክልላዊ ወይም ብሔራዊ ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ ይህን ማድረግ ድፍረት እንጂ ሌላ ባለማስፈለጉ በማንም ላይ እንዲህ ማድረግ ቀላል ነው፡፡ በአሳቻ ቦታ አንድን ነጭ አሜሪካዊ ማረድ ወይም ጠቃሚ የሰውነት ብልቶቹን እያወጡ ለሀብታም መሸጥ ቀላል ነው፡፡ በአሳቻ ቦታ አንድን ነጭ እንግሊዛዊ ወይ ሞስኮባዊ ማረድ ቀላል ነው፡፡ በተመቸ ሥፍራ አንድን ነጭ እስራኤላዊ አንቆ በከንቱዎች ዘንድ መዘባበቻ ማድረግ ቀላል ነው – በአልቃኢዳዎች ሲደረግ የነበረም ነው፡፡ አደጉ ከተባሉ ሀገራት የተመለመሉና አንቱ በተባለ ዘመናዊ የጦር ሥልት ሠልጥነው ለግዳጅ የተሠማሩ “የሰለጠነው ሀገር” ወታደሮች ኢራቅ ውስጥ ሬሣ ላይ ሲሸኑ አይተናል፤ ያኔም በዓለም የሥልጣኔ ደረጃ “ምጥቀት” ተደንቀናል – ከዚህች ሰዎች ሰዎችን ከምድረ ገጽ ሊያጠፉ አሰፍስፈው ከሚታዩባት፣ የሞተ ሰውን ሳይቀር በ”ማሰቃየት” ሰይጣናዊ እርካታ ለማግኘት ከሚማስኑባት ከዚህች ድውይ ዓለም፣ ሳዑዲዎች እየፈጸሙት ከሚገኘውና ከመሳሰለው አረመኔነት ሌላ ምን ይጠበቃል? ዕውር ዕውርን እየመራው ገደል እንጂ ገነት አይጠበቅም፡፡

በመሠረቱና በእውነትም ብዙ ክፉ ነገሮችን ማድረግ በጣም ቀላል ነው፡፡ ዋናው ነገር ልክ እንደጥጋበኞቹ ዐረቦችና ተባባሪዎቻቸው ወያኔዎች ኅሊናን የመሳትና ወደአውሬነት የመለወጥ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ተዋራጁ ጨካኙ አውሬና ሰብኣዊነት በአጠቃላይ እንጂ የሚታረደውማ ዋናውን የዕልቂት በርኖስ ተከናንቦት እያለ የምን ውርደትን መደረብ ነው? እውነትን መነጋገር ከተፈለገ እንግዲያውስ የታረደ ከበረ፡፡ የታረደ በፈጣሪ ዘንድ የሰማዕትነትን ካባ ተጎናጸፈ፡፡ በከንቱ ጭዳ የሆነ የዘላለም ክብርን አገኘ፡፡ ተጠየቁ እንደዚህ ነው፡፡ የተዋረደው እዳር ቆሞ “አይዞህ ወንድሜ እረዳቸው፤ ቀብጠዋልና ጉልበትህን አሳያቸው፤ እኛን ጠልተው ከሀገር ስለወጡ ቀኝ እጃችንን አውሰንሃልና እንደፈለግህ አድርጋቸው” እያለ በስቃይ የሚደስት ወገን ነው፡፡ ጊዜው ሲደርስ ወዮ ለዚህ ዓይነቱ ፍጡር! እናም ውድ ኢትዮጵያውያን ለቅስቀሳ ፍጆታው ያህል ልክ ነው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ተዋርደናል፤ ተንቀናል፤ ከዚያም በላይ፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ ግን የተዋረደው ዓለም ነው፤ የተናቀው የሰው ልጅ ዘር በአጠቃላይ ነው፤ የታረደው በትዕቢትና በዕብሪት አንገታችንን እየቆለመመ በሠይፍና በጎራዴ እየቀነጠሰን ያለው በሌላኛ ጠርዝ የሚገኘው የሰይጣን አሽከርና ሎሌ የሆነው የሰው ልጅ ነው፡፡ እንጂ ኢትዮጵያማ በአሁኑ ሰዓት በጽርሓ አርያም ከሁሉም በበለጠ ክብርና ሞገስ እየተሸሞነሞነች ናት፡፡ የዚህን አያዎኣዊ(paradoxical) አነጋገር አንድምታዊ ፍቺ ወደፊት ምናልባትም በቅርብ የምናየው ይሆናል፡፡ … የተዋረድን የመሰልነው ደግሞ በውጭ ብቻ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ ወያኔ እስካለ ክብር የለንም፤ ከነአካቴውም እንደሰው አንቆጠርም፡፡ የሁሉም መጫወቻ ነን፡፡

እንደብዙዎች ዜጎች ኢቲቪን አልመለከትም፡፡ ስመለከት በሽታየን የሚቀሰቅስ አንዳች ነገር ስለማገኝ አላይም – ስህተት ነው – ግን ምን ላድርግ፤ ከጤና የሚበልጥ ነገር ደግሞ የለም፡፡ ዛሬ ለምሳሌ ትልቅ በሽታ ነው የተቀሰቀሰብኝ፡፡ ወደሌላ ጣቢያ ላልፍ ስል ድንገት ኢቲቪን ስከፍት ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚባለው ዳግማዊው መቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርስ በወቅቱ የወገኖቻችን አሰቃቂ ጉዳይ በ”ጋዜጠኛ” እየተጠየቀ አየሁ፤ ኃይለማርያም ደንቆሮና በልጆች ቋንቋ ጀዝባ መሆኑን ዛሬ ከእስከዛሬው  በበለጠ ልብ አልኩ፡፡ ራሴን እንደምንም አሳምኜ ትንሽ ልከታተል ወሰንኩና ማየቴን ቀጠልኩ፡፡ ግን የጋዜጠኛ ተብዬውና የሰውዬው የአቀማመጥ ሁኔታ ራሱ ትልቅ የፕሮቶኮል ችግር ስላለበት መከታተል አትበሉት – እየቀፈፈኝ እንደምንም ለጥቂት ደቂቃዎች ታገስኩና ተከታተልኩ፡፡

ጋዜጠኛው ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብዬው ደግሞ ጋዜጠኛ መስለዋል፡፡ ጋዜጠኛው እግሮቹን አጣምሮ ተንቀባርሮና እጅግ ተዝናንቶ ‹ሲጠይቅ›፣ ኃ/ማርያም እግሮቹን በሥርዓቱ ዘርግቶ ሽቁጥቁጥ እያለ ሲመልስ አንጀትን ይበላል – በ”ሥርዓቱ” ባልኩበት መንገድ መቀመጡ ጥሩ ሆኖ የ“ጋዜጠኛው” “ጠቅላይ ሚኒስትራችን”ን በማንጓጠጥ መልክ እግሮቹን አጣምሮ መጠየቁ ነው የቆጨኝ – በጠቅላይ አሽከሩ አማካይነት የናቁን ግብጾችና ሳዑዲዎች ብቻ ሣይሆኑ ጋዜጠኞቻችንም ናቸው ማለት ችያለሁ፤ ወያ በሚያገኘው አጋጣሚ ሁሉ ኢትዮጵያን ለማዋረድ የማይፈነቅለው ድንጋይ አለመኖሩን ስረዳ የወያኔን ሥነ ልቦናዊ ደዌ የክብደት ደረጃና የኛን የምሕረት ዘመን መንቀራፈፍ አስታውሳለሁ፡፡ ይህ ነገር መለስን እንዳንረሳ ሲባል በወያኔዎች ሆን ተብሎ የተቀናበረም ይመስላል፡፡ የሚናገረውን ብቻም ሣይሆን እንዴት መቀመጥ እንዳለበትም መመሪያ ቢጤ ሳይሰጡት አልቀረም፡፡ ቤተሰቤ በሙሉ ነው በዚህ ነገር የተሸማቀቀው፡፡ በርግጥም አቶ መለስን አስታወስነው – ተሳክቶላቸዋል፡፡ አቶ መለስ ‹ጋዜጠኞቹን› እንዴት እንደሚገላምጣቸውና አጥንተው ከመጡት ይጠይቁትን ያሳጣቸው እንደነበር ትዝ አለኝ፡፡ ከመሞቱ አጎደለን ማት ነው? በርግጥም እኮ መለስ ቢኖር ኖሮ ሳዑዲዎችም ይህን ያህል አይማግጡም ነበር ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ በርግጥም እኮ መለስ ቢኖር ኖሮ ግብፆች በኃ/ማርያም ላይ እንዳፌዙበት በርሱ ላይ አያፌዙበትም ነበር፡፡ ስለዚህ ወያኔ የቀረው ጊዜ አንድ ወርም ይሁን አንድ ዓመት ለምን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዱ ወያኔ አይሆንልንም? እውነቴን ነው – እንደለመድነው አንዱ ትግሬ ቁጭ ይበልበትና ይህን ኮንዶም ሰውዬ ወደማስተማር ሙያው ይመልሱት፡፡  “ውርደታችን” እኮ ለከት አጣ፡፡ በንነው እስኪጠፉ ድረስ  በዚህች እንኳን አንዋረድ፡፡ በአሁኑ ሰዓት እኮ ኢትዮጵያውያንን እንደውዳቂ ዕቃ የማይቆጥርና እንደጠፍ አህያ ልቡ እስኪጠፋ የማይጭን የለም፡፡ እስኪያልፍ ያለፋልና አይዞን!!!

በቅድሚያ ይህ ሰውዬ ብዙዎች እንደሚሉትና በብዙዎች እንደሚታመነው ከአንድ ሀብታም ሰው የቤት ጠባቂ ያነሰ የስብዕና ደረጃና የሥራ አፈጻጸም ሥልጣን ያለው መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ነገር ነው፡፡ የዚህ ሰውዬ ጭንቅላት ሥሪት ምን እንደሆነ ግራ የሚያጋባ በመሆኑ እንጂ እኔ እሱን ብሆን እንደዚህ መሣቂያና መሣለቂያ ሆኜ መኖርን አልመርጥም ነበር – የሰው ተፈጥሮ ግን በውነቱ አስገራሚ ነው፡፡ ከኃይለማርያም ደሳለኝ ይልቁንስ የፍቅር እስከመቃብሩ ፈረጃ ይሻላል፤ “ፈረጃ በሚለው የባሪያ ስሜ የሚያውቀኝ ሰው ምን ይለኛል?” በሚል መዘባበቻ ያደርገኛል ብሎ የፈራውን ዕዝራ የሚለውን አዲሱን ስሙን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም – ባህሉንና ማኅበረሰብኣዊ አወቃቀሩን ተረድቶታልና የሰው የሃሜት ግርፋት አስቀድሞ የታዬው ይመስላል፡፡ (ይህን ስል ነገሮችን ለንጽጽር አስቀመጥኩ እንጂ ፍርድ ውስጥ እንዳልገባሁ ማስታወስ እፈልጋለሁ)፡፡ በዚህ መልክ እየተሸቆጠቆጠ አንድም የራሱ ቃል ሳይኖረው (with out any say in ‘his’ government) የሰጡትን የሚያስተላልፍ አሸንዳ ሆኖ መኖሩ ምን ዓይነት እርካታና ደስታ እንደሚያገኝበት አይገባኝም፡፡ አለኝ ከሚለው ሃይማኖትም ሆነ ከራሱ ኅሊና ጋር እንደተጣላ እስከመቼ በሌሎች ሰዎች ጭንቅላት እየተመራ – ለቃሉ አጠራር ይቅርታ ይደረግልኝና – ኮንዶም ሆኖ እንደሚኖር አላውቅም፡፡ ራሱ ነጻ ቢወጣ ይሻለዋል፡፡ ኃይለማርያም ራሱን ቢሆንና በነጻይቱ ኢትዮጵያ ባሰኘው የሥልጣን እርከን ተወዳድሮ በራሱ አእምሮ የሚንቀሳቀስበትን መድረክ ቢጠብቅ፣ ለዚሁ መድረክ እውንነትም የበኩሉን ትግል ቢያደርግ እንደሚሻለው በዚህ አጋጣሚ ብጠቁም ብዙ የዘገየሁ አይመስለኝም፡፡ ካሰበበት ይችላል፡፡ አሁን ካለበት የጥፋት መንገድ ግን በአፋጣኝ ይውጣ፡፡ ክፉኛ መሽቷል፡፡ ወያኔ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚዳክር፣ በራሱ ኃይልና ጥበብ ሳይሆን በአጋጣሚዎች መወሳሰብ ብቻ እስትንፋሱ ብን ብን እያለች የሚኖር ድርጅት ነው፡፡ እንደሚመስለኝ ወያኔ እንዳይወድቅ እያገዘው ያለው የጥቂቶች ብፁዓን አባቶች ጸሎት ነው፤  መውደቁን የምንመኘው ዜጎች ራሳችንን ሳናስተካክል እንዲሁ በባዶ ሜዳ ርስ በርስ እየተናቆርን በምንገንበት ሁኔታ ወያኔ አሁን ቢወድቅ ጦሱ ብዙ፣ መዘዙም በቀላሉ የማይወገድ ነው፡፡ በመቶዎች የተከፋፈለ ፖለቲከኛ፣ ለሥልጣን የቋመጠ ጎጠኛ፣ በዘር የተቧደነ ጦረኛ፣ ለበቀል ያሰፈሰፈ ሸፍጠኛ፣ ለሀብት የተስገበገበ ሆዳም፣ … በየጉራንጉሩ አንዳች ዕድል በሚጠባበቅበት ሁኔታ ይህ በቁሙ ሞቱን ጨርሶ ጣር ላይ ያለ የማፊያ ቡድን ለይቶለት እንዳይወድቅ እኔም ብጸልይ የሚኮንነኝ እንዳይኖር እማጠናለሁ፡፡ መውደቅ ያለበትን ጊዜ በበኩሌ አውቃለሁ፡፡ ያም ቀን አሁንና ዛሬም ሊሆን በቻለ፡፡ ግን ፈጣሪ የታከለበትና ሌላ አደጋ የማያስከትል እንዲሆን የምንመኝ ብቻ ሣይሆን በርትተን የምንጸልይ ወገኖች አንጠፋምና ጌታ ይሰማናል፡፡ ችግሩ የመንግሥት ለውጥ አይደለም፡፡ መንግሥት መቼም ሊለወጥ ይችላል፡፡ ዋናው ነገር ‹አሮጌው ወይን በአዲሱ አቅማዳ እንዳይገባ› የመጠንቀቅ ጉዳይ ነው – ለኢትዮጵያ ደግሞ ከሰው በላይ የሚጠነቀቅላትና የሚጨነቅላት አምላክ አላት፤ እንደሰው ቢሆንማ እስካሁን ድረስም ቢያንስ በሕይወት መቆት ባልተቻለን ነበር – ወርቁ ጠፍቶ ሚዛኑ ያለው በአንድዬ ተራዳኢነት ብቻ ነው – ይህን አንተ ላታምን ብትችል አልፈርድብህም – ምክንያቱም የሰቆቃው ዘመን በእጅጉ በመራዘሙ ሳቢያ ከአምላካችን ጋር የተጣላን ዜጎች ቁጥር ብዙ መሆኑን መገንዘብ አያስቸግርምና፡፡ እንጂ በመሪና በመንግሥት መለወጥማ መንግሥቱስ በመለስ ተተክቶ አልነበረምን? እናም በዚህ አምናለሁ – ወያኔን መጣል የሴከንዶች ጉዳይ ነው፡፡ እንዲያውም ሴከንዶችንም ላይፈጅ ይችላል፡፡ ዱሮውን የወደቀ ነውና – የታመመ ሰው ሲሞት እኮ ሳይተጣጠብ፣ ሳይከፈንና ሳይበጃጅ መሞቱ ለቤተሰብ ተነግሮ እንዲለቀስ አይደረግም፤ የወያኔም ነገር እንደዚሁ ነው – ከሞተ ቢቆይም ገናዥ እስኪገኝ – ገናዦች እስኪስማሙና ወደሬሣ ክፍል ደፍረው እስኪገቡ ድረስ ኅልፈቱ አይነገርም፤ “እባብ ልቡን ዐይቶ እግሩን ነሣው” – ወያኔም እንደ እባብ አናቱን ተቀጥቅጦ እንደድመት በዘጠኝ ነፍስ፣ ከዘጠኙም በመጨረሻዋ ይኖራል – “የተበዮች አለመስማማት ለበዮች ይመቻል”፡፡ አሁን የሚታየው ትልቁ ነገር ወያኔን ሥልጣን የሚረከበው አጥቶ ራሱንም በሚገርመው አኳኋን ሀገሪቱ ሰው አልባ ሆና መቅረቷ ነው – ይህ ካልሆነ በስተቀር ወያኔ አልሞተም ተብሎ ሊዋሽ የሚችልበት አንድም ሀገራዊ ሁኔታ የለም፡፡ ይህም ሥራ የተሠራው በደርግ፣ በወያኔ በራሱና የኢትዮጵያን ኅልውና በማይፈልጉ የውጭ ኃይሎች ነው – ኢትዮጵያ ከአናት ተመታች – ለጊዜው እስትንፋሷ ፀጥ አለና የሞተች መሰለች፤ “hibernate” ባደረገው ሕይወት ያለው በድኗም ላይ ወያኔ እንደልቡ ተንጎማለለባት – የማይቀር ፍርድ ነበረና እንደምንም ተወጣነውና ይህም ክፉ ቀን ሊያልፍ የምሥራቹ ደረሰ፡፡ ፈጣሪ እሾህ አሜከላውን ሲገፍላት፣ ይህን የ80 ሚሊዮኖች የአስተዳደር ወንበር ሊረከቡ የሚችሉ የበቁ ዜጎች ፈጣሪ ፈልጎ ሲያገኝና ከያሉበት ሲያሰባስብ ኢትዮጵያ ምን በመሰለ ክብርና ሞገስ እንደምትነሣ ለማየት ያብቃን፡፡ እንዲህ በል አለኝ እንዲህ አልኩ፡፡ በትንሣኤዋ የሚፈራ ይፍራና ይውጣለት፡፡ የማይቀርን መናገር ነውር አይደለም፡፡ ሞቶ መነሳት በግለሰብ እንጂ በሀገር ደረጃ በጣም ቀላል ነው፡፡ ሞቶ ያልተነሳ ሀገር የለም፡፡

ኃ/ማርያም ከተናገረው ፍሬፈርስኪ አንዱ አስገርሞኛል፡፡ በዚህ በወቅቱ የዜጎቻችን በ‹ቅጡ አለመያዝ› ምክንያት ስለሳዑዲና ኢትዮጵያ ወዳጅነት መጠልሸት መቻል አለመቻል ሲጠየቅ “በዚች ክስተት፣ በዚህች ትንሽ ነገር” በማለት ይህን በሙሉጌታ ሉሌ አነጋገር – ቃል በቃልም ባይሆን ጭብጡን ልጥቀሰው – “ይህ ሳዑዲ ዐረቢያ ውስጥ በሀገራችን ዜጎች ላይ የተከሰተው ዕልቂትና ስቃይ መንግሥት ቢኖረን ኖሮ ጦርነት የሚያሳውጅ ታላቅ ሀገራዊ ጉዳይ ነው፤ ብዙ የዓለም ጦርነቶች የተቀሰቀሱት ከዚህ በሚያንሱ ትናንሽ አጋጣሚዎች ነው፡፡ ይህ የኛው ጉዳይማ ወዲያውኑ ክተት የሚያስብል ነው፡፡…” ተብሎ የተመሰከረለትን ሀገራዊ ታላቅ ጉዳይ እንደተራ የጎረቤት ጠብ ቆጥሮት ዐረፈው፡፡ ያኔ የዚህን ሰውዬ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን አእምሮኣዊ ጤንነቱንም ተጠራጠርኩ፡፡ አቶ መለስ  እንደዚህ ያሉ ጀዝባ ሆዳሞችን፣ እንደደመቀ ያሉ ደናቁርት ጌኛዎችን መርጦ አጠገቡ ማስቀመጡ ለወያኔው ሥርዓት ዕድሜ መራዘም በርግጥም ጠቅሞታል፡፡ እናላችሁ ይህን ላንቃችን እስኪበጠስ እያስጮኸን የሚገኘውን ታላቅ ጉዳይ፣ ደም እስክናነባ እያስለቀሰን የሚገኘውን የሚሌንየም ሰቆቃ እንደቀላል ነገር ቆጥሮ “በዚች ክስተት ወዳጅነታችን አይሻክርም…” ብሎን ዕርፍ፡፡ ይህ – በነሱው ቃል – ወደር የማይገኝለት ተንበርካኪነት ወያኔዎች ከሕዝብ ስለተጣሉ ከዐረቦቹም ጋር ላለመቀያየምና  በል ልዩ ሰበብ አስባቦች ከነዳጁ ዶላር ለመመጽወት ካላቸው ጽኑ ፍላጎት የሚመነጭ እንጂ ኢትዮጵያዊ መንግሥት ቢኖረን ኖሮ ሰው አይደለም አንዲት ጥንቸልም ብትገደልብን ብሔራዊ ጦርነት ያሳውጃል፡፡ አንደኛውን ይሁን ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት የቀሰቀሰችው እኮ አንዲት ዓሣማ ናት አሉ፡፡ እንዲያው ለነገሩ ግን በወገን ደም ለመቀለድ ይህን ያህል ድንቁርናና የገረረ ቆዳ ከየት አመጡት? በዘርና በቋንቋ ተመሥርተው በስቃይ ላይ ከሚገኙ ወገኖች የራሴ ናቸው የሚሏቸውን ዜጎች እየመረጡ ወደ ሀገር መመለስንስ እንዴትና ከየትስ ተማሩት? የበረሃው ወያኔ ከ23 ዓመታት በኋላ እንዴት ይህን ዓይነቱን የጫካ የመድሎ አሠራር አይረሳም? ቂም በቀልንና የነገር ቁርሾን ለአፍታም እንዳይዘነጉ ምን ዓይነት ሶፍትዌር ይሆን በየጭንቅላታቸው ያስገጠሙት? ለነሱም ሆነ ለኛ  ምን ዓይነት መረገም ይሆን? የሚመለሱትን ብዙዎቹን ስትመለከቱ እኮ የሕወሓት የጦር ባታሊዮን ይመስል ቋንቋቸው … ምንም ይሁን … ያው ግን ወገኖቻችን ናቸውና ምን ይደረጋል፤ ሀዘናችንና ልቅሶኣችን ቅጥ አጣ – ሟቹም ገዳዩም እቤቷ መሽገውባት አትስቀው አታለቅሰው  ነገር ሆነባትና ግራ ገብቷት እንደተቸገረችው ያቺ ምሥኪን ወይዘሮ ሆነናል፡፡ ብቻ ግን ከዚህ ሁሉ የመንግሥትነት ዘመን በኋላ እንደዚህ ያለ አድልዖ ሲታይ ክፉኛ ያምማል፡፡ በዚህ የግሎባላይዜሽን ዘመን የሰው ዘር ስለሰው ዘር መጨነቅ ሲገባው ሊያውም የሁላችን የምንለው  መንግሥት የኤምባሲዎቻችንን ሥራና ባጀት ለራሱ ሰዎች ብቻ ማዋሉ ከማሳዘን ያለፈ የሀገር ሸክምና ዕዳ ነው፡፡   ሌላው ኢትዮጵያዊ በዐረቦች እንዲጨፈጨፍ ተትቶ የራስ የሚሉትንና መዋጮና ድጋፍ ያደርግ የነበረን እየመረጡ ከእሥር ማስፈታት፣ ቅድሚያም ሰጥቶ ወደሀገር ማስገባት … ነገ የሚያመጣውን የዞረ ድምር ካለማየት የሚመጣ ድንቁርና ነው፡፡ አቤት የዚህ ዘመን ትንግርት! እግዚአብሔር ሆይ ቶሎ ናልን!!

 

yiheyisaemro@gmail.com

Pen

 

የኛ ነገር፡ ክፍል 20፤ ሰይፋችንን አጥተነው፤ ሰልፋችንንም ልንቀማ ?? (ከተክለሚካኤል አበበ )

$
0
0

ከ ተክለሚካኤል አበበ

የሳኡዲ ግፍና የኛ ሰልፍ፤

እንደመግቢያ፤ የፋና ነገር

  1. ፋና፤ ኢትዮጵያዊ ካናዳዊት ነች፡፡ ቆንጆ ነች፡፡ እሱዋ እንደምትለው ከሆነ ፖለቲካ አትወድም፡፡ በአባይ ቦንድ ሽያጭና በመሰል የመንግስት መርሀ ግብር ዝግጅቶች ላይ ግን ቀድማ የምትገኝ ጎበዝ ነች፡፡ በውጭ አገር የሚገኙ ተቃዋሚዎች መፈክር ይዘው በኢህአዴግ ላይ ሲሰለፉ ስትመለከት ግን ደምዋ ይፈላል፡፡ ሰሞኑን በዚህ በሳኡዲአረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ግፍ ስላሳዘናት፤ ሳውዲዎችን ልክ ልካቸውን ልትነግራቸው ቆርጣ ተነስታለች፡፡ ስለዚህም በመጪው አርብ መሰል ጉዋደኞችዋን ይዛ ሰልፍ ልትወጣ ተፍ ተፍ ትላለች፡፡ በፋና እምነት በሳኡዲ በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ሰቆቃ፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም፡፡ ስለዚህ የሰልፉ እንዱ ደንብ በምንም አይነት መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት ስም በክፉ አይነሳም የሚለው ነው፡፡ ሰናይም ወንዱ ፋና ነው፡፡ እንደፋና ያምናል፡፡ ከፋና ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር፤ ኢትዮጵያውኑን በግዜ ባለመርዳቱ የኢትዮጵያን መንግስት የሚመለከተው ቢሆንም፤ የኢትዮጵያን መንግስት የሚያወግዙ መፈክሮች ማንገብ ይከፈፍለናል ባይ ነው፡፡ በተወሰነ በሰሞኑ ሰልፎች የገረመኝ፤ ያሳሰበኝ፤ ያቃጠለኝም ነገር ይሄ ነው፡፡
  1. የሳኡዲን ግፍ ተከትሎ፤ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ቁጣቸውን ገልጸዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ሰዎች ይሄንን የሳኡዲን ግፍ ተከትሎ በየከተማው የሚገኘውን ተቃውሞ በመገናኛ ብዙሀን በመመልከት በኢትዮጵያዊን አንድነትና መደጋገፍ የረኩ፤ በተቃውሞው ግዝፈትም የተደሰቱ ይመስላል፡፡ እኔ ደግሞ በየስፍራው ከሚታዩት ተቃውሞዎች ጀርባ የተደበቀውን ፍርሀት፤ ጥርጣሬና ድንቁርና ስመለከት፤ እጅግ አዝኜ ልጽፍ ነው፡፡ ስለተደፈሩና ስለተገደሉ፤ ስለተዘረፉና ስለተገረፉ ኢትዮጵያውን በበቂ ስለተዘገበ ስለነሱ አልጽፍም፡፡ በነሱ ላይ በደረሰውና በኛ በውች በምንገኝ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵዊ ድርጅቶች በኩል ስለታየው ምላሽ እንጂ፡፡ ከኒው ዮርክ እስከ ሲያትል፤ ከኦታዋ፤ እስከ ከቶሮንቶ እስከ ቺካጎ … ያለውን የተቃውሞ ሰልፎችናና የተቃውሞዎቹን አፈጣጠር እንዲሁም አካሄድ በጥልቀት የተመለከትን እንደሆን፤ ከቁጣው ጀርባ የሚያሳስብና ርምጃ ሊወሰድበት የሚገባ ነገር አለ፡፡ አንዳንዶቹ ሰልፎች የኛ አልነበሩም፡፡ የነሱ እንጂ፡፡ ኮሚቴ ለማቁዋቁዋም ላይ ታች ስንል ተመለከተም፤ ከ23 አመታት በሁዋላም ይሄንን መሰል ግፍ ለመቃወም የሚያስተባብር ቁዋሚ ተቁዋም አለመኖሩም አሳዛኝ ነው፡፡

ቶሮንቶ፡

  1. በቶሮንቶ በዚህ በሳኡዲ ግፍ ጉዳይ ላይ፤ እስካሁን አራት ሰልፎች፤ አንድ ሕዝባዊ ስብሰባ ተደርገዋል፡፡ የመጀመሪያው የተቃውሞ ሰልፍ የተጠራው የአካባቢውን የሙዚቃ ባለሙያዎች ተገን ባደረጉ፤ ሰልፍና ፖለቲካ መደባለቅ የለባቸውም በሚሉ ግለሰቦች ነበር፡፡ ተቃውሞው ሙሉ በሙሉ በሳኡዲ ላይ ነው፡፡ ሁለተኛው ሰልፍ የተጠራው ደግሞ ሕወሀትን በሚቃወመው ወገን ነበር፡፡ ሁለቱም ሰልፎች የተጠሩት ባንድ ቀን ነው፡፡ በሰልፉ እለት፤ የሁለተኛው ሰልፍ ጠሪዎች ሰልፋቸውን አስቀድመው ጨርሰው ወደአንደኛው ሰልፍ ወርደው ሰልፉን በተቃውሞ መፈክሮች ባያጥለቀልቁት ኖሮ፤ መጀመሪያ የተጠራው ሰልፍ ኢትዮጵያዊያን ከአገራቸው ስለሚፈነቅላቸው ስርአትም የሚቃወም ሳይሆን፤ የሳኡዲን ግፍ ብቻ አውግዞ የሚለያይ ይሆን ነበር፡፡ ምክንያት፤ ከላይ በአንቀጽ አንድ የጠቀስኩትና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶችም፡፡ ግፍ ግፍ ነው፡፡ በሳኡዲም ይፈጸም በጋንዲ፤ በመለስም ይፈጸም በዳዲ፤ ግፍ ግፍ ነው፡፡ ፖለቲካ አንወድም ወይንም ፖለቲካ እንፈራለን በሚሉ ወገኖች ዘንድ ግን ይሄ ግንዛቤ ያለ አይመስልም፡፡ ቢኖርም፤ እነዚህ ሰዎች፤ የራስ-መንግስት ግፍ ተቀባይነት አለው አይነት የሞራል አስተሳሰብ አላቸው፡፡ ፖለቲካና ሰብአዊ መብት የተለያዩ ናቸው አይነት ነገር፡፡
  1. የቶሮንቶውን በተመለከተ፤ በሰልፉ ላይ ትንታግ ሆና የዋለች እህት፤ ይሄንን ፖለቲካና ሰብአዊ መብት አትደባልቁ ስልት በተመለከተ እንዲህ ስትል ጽፋለች፡፡ Just to let you know all, this is the new trend TPLF has started now, they organize protests before activists do … Please, also spread this word and warn innocent Ethiopians not to be used in every media outlet available. Jiraf erasu gerfo, erasu yichohal, sad. አዲሱ የህወሀት ስልት፤ የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ አይነት ነገር፡፡ ወይም ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል፡፡ የዋህ ኢትዮጵያዊያን እንይሸወዱና መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ለመገናኛ ብዙሀን አሳስቡ፤ ስትል ተናግራለች፡፡

 

ኒውዮርክ፤ ሺካጎ፤ ኦታዋ

  1. አንድ የኒው ዮርክ ሰው እንደጻፈው፤ ሌላ የቺካጎ ሰውም እንደዘገበው፤ የኦታዋ ጋደኞቼ እንደነገሩኝ ከሆነ፤ በኦታዋ፤ በሺካጎና በኒው ዮርክም የሆነው ተመሳሳይ ነው፡፡ ለምሳሌ፤ አቶ አለማየሁ በሁሉ ከኒው ዮርክ እንዲህ ብሎ ጽፎዋል፡ The demonstration was organized by pro-Woyanne, but overtaken and led by anti-Woyanne group which included loud verbal disagreement and some shoving, pushing between the 2 groups for few minutes:: ሰልፉ የተዘጋጀው በአፍቃሬ መንግስቶች ነበር፤ ነገር ግን ከጥቂት አተካሮ በሁዋላ አፍቃሬ ዴሞክራሲዎቹ ቀሙት እንደማለት ነው በግርድፉ፡፡ ሺካጎዎች ለጊዜው የተረቱ ይመስላል፡፡ የረዥም ግዜ የሺካጎ አካባቢ ተሙዋጋች አቶ አበራ ሲሳይ ስለሺካጎ ተሞክራቸው እንዲህ ብለው ጽፈዋል፡፡ We in Chicago tried to do the same but overtaken by a group named “hand to hand” .We proposed that we collectively denounce the woyane government along with the Saudi officals in our slogans and petition. The group rejected our proposed idea. They said they will not allow woyane to be denounced. በሺካጎም እንደኒውዮርኩ ወይም ቶሮንቶው ቡድን ከሳውዲ ጎን ለጎን የወያኔ ስርአትንም ማውገዝ አለብን ብለን ጠየቅን፡፡ ነገር ግን ወያኔ አይነካም በሚል እጅ በእጅ በተሰኘ ቡድን ተዋጥን እንደማለት ነው በጥሬው፡፡

 

ትንታኔ፤ ትችትና ጥቆማ፤

  1. በሳኡዲ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ግፍ አሰቃቂ ነው፡፡ በርግጥ መጠኑና ቅርጹ ለየት አለ እንጂ፤ የሴቶቻችን መደፈር፤ የኢትዮጵያዊያን በአረብ አገር መገደልና መንገላታት ያለና የነበረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ቅርጽ እስካለችም ወደፊትም የሚኖር ይመስላል፡፡ ከግፉ ይልቅ ግን፤ ስለግፉ በኢትዮጵያውያን መካከል የታየው ግዙፍ የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት በጣም አሳሳቢ ነው፡፡ ጎን ለጎንም፤ ይሄ ወቅት፤ መንግስት ዜጎቹን ለመሰብሰብና ለመጠበቅ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ሲሰንፍ፤ በተቃዋሚው በኩል ለዜጎች እንደተለዋጭ መንግስት የሚያስብና የሚሙዋገት ፖለቲካዊ ተቁዋም አለመኖሩ የትግላችንን ሰንካላነትና የተቃወወሞዋችንን ጉዶሎነት ቁልጭ አድርጎ አሳይቶዋል፡፡ ከሀያ ሶስት አመት በሁዋላም፤ ይሄ ነው የምንለው እኛን የሚያሰባስብ አስተማማኝ ተቁዋም ባለመገንባታችን፤ እንደገና ኮሚቴ ወደማቁዋቁዋም ስንራወጥ መመልከት እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ ትግላችን የአድ ሆክ ኮሚቴ ግንባታ ሆነ፡፡
  1. የበለጠ የሚያሳስበው ደግሞ፤ ከዚህ ከሳኡዲ ችግር ጋር በተያያዘ ያቁዋቁዋምነው አለማቀፍ ኮሚቴም፤ አስር ሀያ አመት ከምናደርግበት የትግል ስልት ብዙ ፈቀቅ ያለ አይመስልም፡፡ የኮሚቴው ሙሉ ዝርዝር ባይኖረኝም፤ የሶስቱ ሰዎች ስም እንደሚያሳየው ከሆነ፤ ኮሚቴው ዘመኑን ያልዋጀ፤ የአንድ ብሄር ስብስብ ነው የሚመስለው፡፡ ስብስቡ አለማቀፍም አገርአቀፍም ደረጃውን እንዲጠብቅ አልተደረገም፡፡ ወዳጆቼ ታማኝና አበበን በቅርበት አውቃቸዋለሁ፡፡ በኢትዮጵያዊነት ስሜታቸው ከነሱ የተሣለም የተሻለም አለ ለማለት ይከብዳል፡፡ አቶ ብርሀኑ ዳምጤም እንደሰማሁት ከሆነ ሌሎች የግል ህጸጾች ቢኖሩትም፤ በኢትዮጵያዊነቱ ጥያቄ የሚነሳ አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን፤ ቢያንስ ሴቶችና የእስልምና እምነት ተከታዮች መታከል፤ ካሉበትም ደግሞ ግንባር ላይ መቀመጥ ነበረባቸው፡፡  ከታላቁ የኦሮሞ ብሄረሰብም በግልጽ ሚታይ ሰው አለመወከሉ ስህተት ነው፡፡ እንዲህ ያለው እነሱን ያላካተተ ኮሚቴና አካሄድ መብዛቱ ነው ብዙ የኦሮሞ ተቆርቃሪዎችን ሌላ መፈክርና መለያ ይዘው እንዲወጡ የሚጋብዛቸው፡፡ በዚህ ሌሎችን ብሄሮች በማስተናገዱ ረገድ፤ ኢህአዴግ/ሕወሀት ከኛ ብልጥ ነው፡፡
  1. ብዙ በተለምዶ የአንድነት ሀይል ተብሎ በሚጠራው ስብስብ የሚገኙ ሰዎች ይሄንን ብሄርና ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ትችቴ እንደሚጎመዝዛቸው አውቃለሁ፡፡ ጎበዝ፤ ባይሆን ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን ሆነ፤ ወደድንም ጠላንም ያላፉት 23 አመታት እንደሚያሳዩን፤ ብዜ ግዜ ብሄርን፤ አንዳንዴ ሀይማኖትን መሰረት ያደረገው የኢህአዴግ ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም  ገዢ ሆኖ ቆይታል፡፡ ሰዎች በብሄር ነቅተዋል፡፡ ሰዎች በሀይማኖትም ነቅተዋል፡፡ ስለዚህ ብንቀበለውም ባንቀበለውም፤ በአደባባይ እንደዚያ ብለን ባናውጅም፤ ይሄንን የሳኡዲን ግፍ ለማለስለስና ለማስቀልበስ የምናቃቁማቸው ተቁዋማትና ስብስቦችም ሁኑ ሌሎች መሰል ፖለቲካዊና ሲቪክ ማህበራቶቻችን፤ በተዘዋዋሪ ይሄንን የሀይማኖትና የብሄር ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገቡ መሆን አለባቸው፡፡ እስከአሁን እንደታዘብኩት ከሆነ፤ በኛ በአንድነቱ በኩል ያለምንም ማሻሻያ የድሮውን ኢህአዴግ ከመግባቱ በፊት የነበረውን አሰላለፍ እየደጋገምን ከማንንጸባረቅ ውጪ፤ የኢህአዴግን ርእዮተዓለም የሚያንፉዋቅቅም ይሁን የሚተካ አስተሳብ ማምጣት አልቻልንም፡፡ በዚህ በሰሞኑ ክስተት ውስጥ፤ በትንሹ፤ ለሳኡዲ፤ ከታማኝ ልቁ ሀጂ ነጂብ፤ ከአበበ ይልቅ አባስ አይነ-ግቡ ናቸው፡፡ እንዲህ ያለው ነገር ከፍተኛ አለማቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ስራም ስለሚፈልግ፤ ኮሚቴው በቀድሞ ጎምቱ ዲፕሎማቶች ቢጠናከር መልካም ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያንን ለማስተባበርና ሳኡዲዎችን ለመጀንጀን የምናቁዋቁመውን ኮሚቴ መለየት ያለብን ይመስለኛል፡፡

ሰልፎቹን ግን ተቀምተናል፡፡

  1. ከዚያ በተረፈ፤ በዚህ በሳኡዲ ግፍ ማግስት በሚደረጉ ሰልፎች ላይ የተወሰኑትን ሰልፎች ተቀምተናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የካናዳ ዋና ከተማ፤ ኦታዋ ነች፡፡ የዛሬ ሶስት አመት ለድህረ ምረቃ ትምህርት ኦታዋ ስገባ፤ የአንጋፋው ፖለቲካ ድርጅት፤ ኢህአፓ አባላት፤ ይሄማ የኛ ግዛት ነው እያሉ እያንዳንዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በነሱ ፈቃድና ቡራኬ እንዲያልፍ ለማድረግ ይንጎማለሉ ነበር፡፡ ባይሳካላቸውም፡፡ እነሆ የሳኡዲውን ክስተት ተከትሎ በኦታዋ ሰልፍ ሲጠራ ግን፤ የቶሮንቶ ሰልፈኞች በአውቶብስ ተጉዘው ብርታት እስኪሰጡዋቸው ድረስ፤ እነዚያ እኛ ጋር ዘራፍ ይሉ የነበሩት የኢህአፓ ቀናተኞች፤ አንገታቸወንም ይሁን የያዙትን የተቃውሞ መፈክር እንኩዋን ቀና አድርገው ለመሄድ አልደፈሩም፡፡ ኢህአፓዎች ልጆቻቸውን እንኩዋን ሳይተኩ ማርጀታቸው እንዴት እነደማያሳስባቸው ይገርመኛል፡፡ ጎበዝ እያረጀን ነው፡፤ ተተኪ አባላት ሳንወልድ ልናልፍ ነው ብሎ ማን እንደሚነግራቸው እንጃ፡፡ በንጽጽር ግንቦት ሰባት ለወጣቱ የተሻለ መስህብ ቢኖረውም፤ ይሄንን አጋጣሚ እንዋን ተጠቅሞ በኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ከማውገዝ ባሻገር፤ መደረግ ስለሚገባቸውም ነገሮች ተጨባጭ ነገር መጠቆም አልቻለም፡፡ በውጭ አገር መሪ አጣን፡፡ በዚህ ረገድ በአገር ቤት ያሉት፤ ሰማያዊና አንድነት ፓርቲዎች ይሻላሉ፡፡

እንደ ማጠቃለያ

  1. ጎበዝ ባንዲራውን ተቀምተናል፡፡ አገራችንን ተቀምተናል፡፡ ነጻነታችንን ተቀምተናል፡፡ ሰልፋችን ነበር የቀረን እሱንም ልንቀማ ነው፡፡ ለጊዜው ድነናል፡፡ በዘላቂነት ግን እንጃ፡፡ የኒው ዮርኩ አቶ አለማየሁ እንደጻፈው፤ እነሱ፤ ኢህአዲጎች  መተካካታቸው የምር ነው፡፡ I was hoping that the Woyanne and its supporter’s children grew up in melting pot cities such as, Addis and free of hatred. It appears they are here to make us shut our mouth and take their parent’s torch:: ወያኔና ደጋገፊዎቹ እንደአዲስ አበባ ባሉ ሰፊ ከተሞች በማደጋቸው ከጥላቻ ነጻ ናቸው ብዬ አስብ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ፤ የወላጆቻቸውን ችቦ ተቀብለው፤ እዚህም አፋችንን ሊያዘጉን ይፈልጋሉ፡፡ የህወሀት ልጆች ዘመናዊ ትምህርት በአውሮፓና አሜሪካ ቢማሩም፤ ባህላዊውን ፖለቲካም በሚገባ እየሸመደዱት ነው፡፡ በርግጥም በተወሰነ መልኩ የመፈክሮቻችንን ቅኝቶች ለውጠዋቸዋል፡፡ በዚህ ሳምንት የቶሮንቶ የኢትዮጵያ ማህበር ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ፤ አመራሩ መፈክሮቹና ንግግሮቹ ፖለቲካዊ እንዳሆይኑ ለማድረግ ያደርግ የነበረውን ጥንቃቄ ለተመለከተ፤ በርግጥም ኢህአዴግ/ሕወሀት አካሄዳችንን ምን ያህል እንደሸበው ያሳያል፡፡
  1. በዚህ የሳኡዲ ክስተት የተረዳሁት ነገር ቢኖር ከዚህ ቀደም በተካንበት ነገር ስንኩዋን መቀደማችንን ነው፡፡ በአንዳንዶቹ እኔ በቅርበት በታዘብካቸው ሰልፎች ያየሁት ነገር ቢኖር፤ ሰልፎቹ የተዘጋጁት ወይንም የመጀመሪያውን ተነሳሽነት የወሰዱት፤ አንድም የመንግስት ደጋፊዎች ናቸው፤ ወይንም ከጀርባቸው የመንግስት ደጋፊዎች የተደበቁባቸው ፖለቲካን እንደእሳት የሚፈሩ ገለልተኛ የተሰኙ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ ክስተት ድክመታችን የተጋለጠበት፤ ገመናችን የታየበት፤ እኛ እያረጅን ልጆቻችንን ሳንተካ፤ ኢህአዴግ/ሕወሀቶች ግን ልጆቻቸውን ሲተኩ የተመለከትንበት ክስተት ነው፡፡ ኢህአዴግ የደንቆሮዎች ስብስብ መሆኑ እንጂ፤ ይሄ እንኩዋን እርቅ ለመፍጠር መልካም አጋጣሚ ነበር፡፡ ይሄ አንድነት አንድነት የሚባል ነገር ባይመቸንም፤ በተቃዋሚውም ዘንድ የኢህአዴግን ድንቁርና ትንሽ ስለምንጋራ እንጂ፤ ለአንድነት መልካም አጋጣሚ ነበር፡፡ አልሆነም፡፡ ልዩነታችን ግን፤ ቢያንስ አነሱ አውራ-ፓርቲ አላቸው፡፡ እኛ ግን አውራም፤ አውራ ፓርቲም የለንም፡፡ ጎበዝ፤ 23ኛ ፓርቲ አያስፈልገንም፡፡ አንድ አሸናፊ እነጂ፡፡

 

ተክለሚካኤል አበበ ሳኅለማሪም፤ ቶሮንቶ፤ ካናዳ፤ የህዳር ሚካኤል ሳምንት፡ 2006/2013

Pen

የሳምንቱ የአብርሃ ደስታ በፌስቡክ ላይ የተለቀቁ ምርጥ ጽህፎች

$
0
0

ትናንትና ዛሬ!
——————–

Abrham Destaበሑመራ ከተማ ከሚገኘው አንድ ባንክ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለማጭበርበር ወይ ለመዝረፍ ሞክረዋል ወይ ወስደዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች ለማእከላዊ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸው ሰማሁ። የሑመራና አከባቢው ፖሊስ እንደሚለው ባንክ የዘረፉ ወይ ለመዝረፍ የሞከሩ ግለሰቦች የዴ.ም.ህ.ት ታጋዮች ናቸው (ይህ በመንግስት አካላት ለአከባቢው ህዝብ የተነገረ ነው)።

ከሑመራው ጉዳይ የተያያዘ ነው መሰለኝ እዚሁ መቐለም ባንኮችና የመንግስት መስራቤቶች (በተለይ የህወሓት ቢሮዎች) ሃያ አራት ሰዓት በፀጥታ አካላት እየተጠበቁ ነው። ከመከላከያ፣ ፖሊስና ደህንነት የተውጣጣ አንድ ግብረሃይል (Command Post) የመንግስት ተቋማትን (በተለይ ባንኮች) በተለየ ሁኔታ ጥበቃና ክትትል እያደረገ ይገኛል። ግብረሃይሉ የሚያግዙ አዲስ አበባ የሰለጠኑ ወደ አምስት መቶ የሚሆኑ ወጣት ሲቪል ፖሊሶች (ጀሮ ጠቢ) በዚሁ ወር በመቐለ ከተማ ተሰማርተዋል።

ፀጥታ ማስከበር መሞከራቸው ጥሩ ነው። ስለ ባንክ ዘረፋ ጉዳይ ስሰማ ግን አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ድሮ በደርግ ግዜ የህወሓት ታጋዮች በአክሱም ባንክ ሲዘርፉ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸው ነበር። ህወሓቶች ስልጣን ከያዙ በኋላም ባንክን የዘረፉ ግለሰቦች ጀግኖች ተብለው እነሱን ለማወደስ ፊልም ተሰርቶላቸዋል። ላከናወኑት የዝርፍያ ተግባር ለማሞካሸት ቁልፍ ስልጣን ተሰጣቸው። እስካሁንም የኢትዮጵያ ገዢዎች ሁነው እያገለገሉ ነው።

ድሮ ባንክ የዘረፈ ተሸለመ፤ አሁን ባንክ የዘረፈ ወንጀለኛ ነው። ባንክ መዝረፍ አንድ ተግባር ነው፤ አንድም ወንጀል ነው አልያም ደግሞ ጀግንነት ነው። አሁን በሑመራ ባንክ ለመዝረፍ ሞክረዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች (አድርገውት ከሆነ) ወንጀለኞች (ጥፋተኞች) ተብለው እንደሚፈረዱ ሳይታለም የተፈታ ነው።

በሕግ መሰረት ባንክ መዝረፍ ወንጀል ነው። ድሮ ህወሓቶች ባንክ ሲዘርፉም ተግባሩ ወንጀል ነበር። ግን ህወሓቶች ለዘረፉት ነገር ተጠያቂ አልሆኑም። እንዳውም ለነሱ ባንክ መዝረፋቸው የጀግንነት ተግባር ነበር። ራሳቸው ባንክ ዘርፈው የተሸለሙ ሰዎች አሁን ተመሳሳይ ተግባር ለፈፀሙ (ባንክ ለዘረፉ) ግለሰቦች የጥፋተኝነት ዉሳኔ ይሰጣሉ። ራሳቸው ባንክ ሲዘርፉ ጀግንነት ነው፤ ሌሎች ባንክ ሲዘርፉ ግን ወንጀል ነው።

ግን እንዴት ሆነ? በደርግ ግዜ ባንክ መዝረፍ ወንጀል ነበር። ግን ወንጀለኛ የሚኮነው ስትሸነፍ ነው። ህወሓቶች ባንክ ሲዘርፉ በደርግ ወታደሮች ቢያዙ ኖሮ ወንጀሎች ተብለው በህዝብ ፊት ይረሸኑ ነበር። ዉምብድና በራሱ ሕገወጥ ነበር። ለህወሓቶች ግን ዉምብድና ጀግንነት ነበር። አሁን ውንብድና ይሁን ባንክ መዝረፍ ወንጀል ነው። ህወሓቶች ግን ራሳቸው እንደ ጥሩ ነገር ቆጥረው ሲያደርጉት የነበረውን ተግባር እንዴት አሁን ሕገወጥ አደረጉት?

አዎ! ህወሓቶች ዉምብድና ሲሰሩ (ለምሳሌ ባንክ ሲዘርፉ) ወንጀለኞች ተብለው ከመያዝ ይልቅ ጀግኖች ተብለው የተሸለሙበት ምክንያት ስላሸነፉ ብቻ ነው። ህወሓቶች አሸንፈው ስልጣኑ ስለተቆጣጠሩት የሰሩት ጥፋት ሁሉ ወንጀል ሳይሆን ጀግንነት ሆነ። ህወሓቶች ቢሸነፉ ኖሮ ግን ተግባራቸው ጀግነንት ሳይሆን ዉርዴት ይሆን ነበር። ስለዚህ ወንጀለኝነት/ጀግንነት ከመሸነፍ/ማሸነፍ ግንኙነት አለው።

በቃ ከተሸነፍክ ወንጀለኛ ትሆናለህ። ካሸነክፍ ደግሞ ጥፋትህ ሁሉ እንደ ጀብድነት ይቆጠርልሃል። በሰው አገዛዝ ትልቁ ወንጀል መሸነፍ ነው። አንድ ወጣት እንውሰድ። ተርቧልና ከባንክ አንድ ሺ ብር ሰርቆ ጠፍቷል። በፖሊስ ከተያዘ በስርቅ ወንጀል ተከሶ ወህኒ ይወርዳል። ያ ልጅ አቅም አግኝቶ፣ የራሱ ፖሊስና ወታደር ይዞ ገዢውን ፓርቲ አሸንፎ ስልጣን ቢቆጣጠር ኖሮ ግን አንድ ሺ ብር ቀርቶ አንድ ሚልዮን ብር ቢያጭበረብር የማይጠየቅበት ሰፊ ዕድል አለው።

በመቐለ ከተማ አንድ በካድሬዎች የሚናፈስ ወሬ አለ። ከወራት በፊት በፊትዋ አስገራሚ ፅሑፍ የነበራት አንድ ዕብድ መሳይ ለማኝ ነበረች። አሁን አትታይም። አሁን እንደምንሰማው ከሆነ (ትክክል ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም፣ ግን ‘ግርማይ ገብሩ’ የተባለ ጋዜጠኛም ስለሷ መፃፉ አስታውሳለሁ) ለማኟ በፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ዉላለች። ምክንያት: የዴምህት ሰላይ ሆና በመገኘቷ የሚል ነው።

ይህ የለማኟ ወሬ የድሮ የህወሓት ታሪክ ያስታውሰኛል። ህወሓቶች አንድ ጓዳቸው በውምብድና ወንጅል ተጠርጥሮ በደርጎች ተይዞ ይታሰራል። ጓዳቸውን ለማስፈታት የታሰረበት ቦታና ሌላ ተያያዥ መረጃዎች ማግኘት አስፈላጊ ነበርና ሰላይ ወደ ቦታው ላኩ። የተላከው ሰላይ ስዩም መስፍን ነበር። ስዩም ዕብድ ሁኖ ነበር የሚሰልለው። ዕብድ መስሎ ለመሰለል የተፈለገው የመንግስት የፀጥታ ሃይሎችን ለመሸወድ ነበር።

ይህን ጉዳይ (ዕብድ መስሎ መሰለይ) በህወሓቶች እንደ ጥሩ ስትራተጂ ተወስዶ ፊልም ተሰርቶበታል (‘ሙሴ’ ፊልም ይመለከቱ)። ብዙ ነገር ተብሎለታል። ስዩም ዕብድ መስሎ መሰለይ በመቻሉ ቆራጥና ጀግና ተብሏል። ምክንያቱም ህወሓቶች አሸንፈዋል። እንዳሁኗ ስዩም መስፍን በመንግስት (በደርግ) ፀጥታ ሃይሎች ቢያዝ ኖሮስ? ወንጀለኛ ተብሎ ይሰቃይ ነበር። ቶርቸር ይደረግ ነበር።

ያሁኗስ (አሁን የተያዘች ለማኝ)? በጠላት እጅ ወድቃለች። ስለዚህ ትሰቃያለች። ምክንያቱም ወንጀለኛ ናት። ምክንያቱም ለግዜው አላሸነፈችም። ምናልባት (እንደሚባለው የዴምህት ሰላይ ናት ብለን እናስብና) ዴምህቶች አሸንፈው ስልጣን ከተቆጣጠሩ ልጅቷ ‘ጀግና’ ተብላ ፊልምና ሐውልት ይሰራላት ይሆናል። አሁን በህወሓቶች ከተገደለችም ልክ እንደነ ‘አሞራ’ና ‘ቀሺ ገብሩ’ ዘጋቢ ፊልም ተዘጋጅቶላት ታሪኳ ይተረክልን ይሆናል። ዴምህቶች ከተሸነፉ ግን ወንጀለኛ እንደተባለች ትቀራለች። ስሟም አይነሳም። ህወሓቶች ባያሸንፉ ኖሮ ስለ አሞራና ቀሺ ገብሩ ምንም ነገር አንሰማም ነበር። ተራ ወንበዴዎች እንደሆኑ ይቀሩ ነበር። ልጅቷ ሰላይ ናት የሚል ግምት የለኝም ምክንያቱም ሰላይ ብትሆን ኖሮ ቀልብ (ትኩረት) የሚስብ ነገር (የፊትዋ ፅሑፍ) አታረግም ነገር። ሰላይ ቀልብ የሚስብ ነገር ማድረግ የለበትም።

ህወሓቶች ‘ስዩም መስፍን ዕብድ መስሎ ለመሰለል የፈለገው ለዓላማ ነበር’ ይሉን ይሆናል። ዴምህቶችም ‘ለማኟ ዕብድ መስላ ለመሰለል የሞከረችው ዓላማ ስለሆነ ነው’ ሳይሉን አይቀሩም። ነጥቡ ግን ‘እርስበርሳችን መሰለል፣ መገዳደል ለምን አስፈለገ?’ የሚል ነው።

ጀግኖችን እናደንቃለን። ጀግና መሆን ግን ያስፈራናል። ጀግና ለመሆን ፈተናን ፊትለፊት መጋፈጥ ይኖርብናል። ከፈተና በመሸሽ ጀግንነት አይገኝም። ፈተና የጀግንነት መንገድ ነው። ጀግናን ማድነቅ ጀግና አያደርግም። ጀግና የሚያደርገን ፈተና ነው። ላብዛኛው አስፈሪ የሆነ ፈተና ለኛ የጀግንነት መለኪያችን ነው። ጀግኖችን የምናደንቅ ከሆነ ለምን ራሳችን ጀግና ለመሆን አንጥርም?

ዞሮዞሮ በሰው አገዛዝ ስርዓት ሕግ የሚወጣው ገዢው እንዲገለገልበት እንጂ ፍትሕ ለማስፈን አይደለም። ገዢዎች ህዝብን ለመጨቆን እንዲያገለግላቸው የራሳቸው ሕግ ያወጣሉ። ሕጉ እነሱን አይመለከትም። ገዢዎቹ ከሕግ በላይ ናቸውና። ገዢዎች ሕግ የሚያወጡት ተፎካካሪዎቻቸውን ለመቅጣት ነው።

አሁን የምንፈለገው የገዢዎች የራስ ሕግ ሳይሆን የህዝብ ሕግ ነው። በህዝብ ሕግ ሁሉም ሰው (ገዢም ተገዢም) እኩል ነው። የሕግ የበላይነት ይኖራል። ሰው በወንጀል የሚጠየቀው ጥፋት ሲሰራ እንጂ ሲሸነፍ ብቻ አይደለም። የሕግ የበላይነት ሲኖር ሁሉም (አሸናፊውም ተሸናፊውም) ከሕግ በታች ይሆናል፣ በሕግ ይጠየቃል። ገዢው ሰው ሳይሆን ሕጉ ይሆናል።

አሁን የስርዓት ለውጥ ያስፈልጋል። ሰዎች ሳይገድሉና ሳይገደሉ የፖለቲካ ስርዓት ለውጥ የምናመጣበት መንገድ ማመቻቸት ይኖርብናል። ያሁኑ ባለስልጣናትም የማይሰደዱበት (የማይገደሉበት)፣ ከሀገር ዉጭ ያሉ (የሃይል መንገድ የመረጡ ሃይሎችም) በሰላም ወደ ሀገራቸው የሚገቡበት ሁኔታ የሚፈጠርበት ሀገራዊ መግባባትና ዕርቅ እንፈልጋለን። ስልጣን ለመያዝ ይሁን ስልጣን ለመልቀቅ የሞት ስጋት መኖር የለበትም።

ሰው ሳይሰደድና ሳያሳድድ፣ ሳይገድልና ሳይገደል የስልጣን ሽግግር የሚደረግበት የፖለቲካ መድረክ እንጠብቃለን። ስልጣን ለመያዝ ወይ በስልጣን ለመቆየት ደም መፋሰስ ይቁም።

 

 

አንዱአለም አራጌና አስተያየቶች!
———————————–

ትናንት እንዲህ ፅፌ ነበር:

“ከትግራይ ሰዎች ባሰባሰብኩት መረጃ መሰረት ባሁኑ ሰዓት ክብርና አድናቆት የተቸረው የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪ አንዱአለም አራጌ ነው። (በትግራይ ሰዎች የሚወደድ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ: አንዱአለም)!”

ከተሰጡኝ አስተያየቶች በመነሳት አንድ ነገር ተገነዘብኩ፤ አንድም እኔ አማርኛ አልችልም (የፈለኩትን አልገለፅኩም) አልያም ደግሞ የትግራይ አንባቢዎቼ የአማርኛ ቋንቋ ችግር አለባቸው።

እኔ የፃፍኩት “ከትግራይ ሰዎች” የሚል ነው። እኔ እንደሚገባኝ “ከትግራይ ሰዎች” ማለት ትግርኛ የሚናገሩ ግለሰቦች ማለት እንጂ የትግራይ ህዝብ ወይም የመቀሌ ወይ የሌላ አከባቢ ኗሪዎች ማለት አይደለም። አንድ ሰውም ትግርኛ ተናጋሪ ከሆነ የትግራይ ሰው ነው፤ የትግራይ ህዝብ ግን አይወክልም። ስለዚህ “ከትግራይ ሰዎች” ብዬ ስል ያናገርኳቸው ሰዎች የትግራይ (ትግርኛ ተናጋሪ) ናቸው ለማለት ነው።

ሌላው ችግር የፈጠረው ሐረግ “ባሰባሰብኩት መረጃ” የሚል ነው። እዚህ ላይ መረጃ መሰብሰብና ጥናት ማካሄድ ይለያያሉ። መረጃ ሰበሰብኩ እንጂ ጥናት አላካሄድኩም። መረጃ ያሰባሰብኩት Informal በሆነ መንገድ ነው። ስለዚህ ለትግራይ ህዝብ ኮሽኔር (questionnaire) በመበተን የተሰበሰበ መረጃ አይደለም።

ሌላው ደግሞ “ከተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች ነው” እንጂ ከአጠቃላይ ፖለቲከኞች አይደለም። አሁንም የትግራይ ሰዎች (ትግርኛ ተናጋሪ) እንደነገሩኝ ከሆነ ከተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች ተወዳጁ አንዱኣለም ነው።

መረጃ የሰጡኝ ሰዎች (አንደኛ) የትግራይ ሰዎች ናቸው፣ የሌሎች ክልሎች ግምት ዉስጥ አላስገባሁም። (ሁለተኛ) መረጃ የተቀበልኳቸው ሰዎች አንዱኣለምን በቅርበት የሚያውቁ ወይም በቂ መረጃ ያላቸው ናቸው። (ሦስተኛ) መረጃው የተሰበሰበው ስርዓት ባለው መደበኛ አሰራር አይደለም (Informal ነው)። በስተመጨረሻ አከባቢ ግን ሆን ብዬ ስለሱ መረጃ እያሰባሰብኩ ነበረ። (አራተኛ) መረጃ የሰጡ ሰዎች በፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸው ብቻ ናቸው (ከአምስት ሰዎች ዉጭ)።

በዚሁ መሰረት ከአርባ ሦስት ሰዎች (እኔ አርባ አራተኛ ነኝ) የሰበሰብኩት መረጃ ነው። እነኚህ ሁሉ ትግርኛ ተናጋሪ (የትግራይ ሰዎች) ብቻ ናቸው። አስራዘጠኙ የዓረና ትግራይ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች፣ አስራአንድ የህወሓት አባላት (አብዛኞቹ የደህንነት ሰዎች)፣ ሦስት የአንድነት ፓርቲ አባላት፣ አምስት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ያልሆኑ፣ ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የነበሩ (አሁን ግን ያልሆኑ)፣ ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ የፖለቲካ አቋማቸው በግልፅ ማወቅ አልቻልኩም።

ከነዚህ ሰዎች አብዛኞቹ አንዱኣለም አራጌን ያደነቁበት ምክንያት (አንድ) በሚሰጠው በሳል ሓሳብ፣ (ሁለት) የጥላቻ ፖለቲካ ስለማያራምድ። በብዙዎቹ አገላለፅ አንዱአለም ምንም ዓይነት የብሄር (የጥላቻ) ፖለቲካ አያራምድም። በኢህአዴግ የታሰረውም በፖለቲካ ብቃቱ ምክንያት ገዢውን ፓርቲ ስላሰጋ ነው ሊሆን የሚችለው ብለዋል። ከሰዎቹ ስድስቱ ግን ስለ አንዱኣለም መጥፎም ጥሩም አልተናገሩም።

በዚህ መሰረት ነው አንዱኣለም አራጌ በትግራይ ሰዎች (ትግርኛ ተናጋሪ ግለሰቦች) ተወዳጁ የተቃውሞ ፖለቲካ መሪ ነው ብዬ ለመፃፍ የተገደድኩት። አሁንም ልብ በሉ ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ነው።

እኔም ስለ አንዱኣለም አራጌ መረጃ ያገኘሁት ከነዚህ ሰዎች ነው።

 

 

 

‹‹ድኅረ ምርጫ 97 በኢትዮጵያ ያለው ዲሞክራሲያዊ ምህዳር ጠቧል›› አና ጐሜዝ፣ የአውሮፓ ኅብረት የፓርላማ አባል

$
0
0

reporter amharic

Ana Gomez

Ana Gomez

ምርጫ 97ን ተከትሎ የአውሮፓ ኅብረትን የምርጫ ታዛቢ ቡድንን የመሩት አና ጐሜዝ ምርጫውን ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ በኢትዮጵያ መንግሥትና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላይ የሰላ ትችትና ወቀሳ በመሰንዘር ይታወቃሉ፡፡

ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ በ26ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያን፣ ፓስፊክ እና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ የመጡትን አና ጐሜዝን በዴሞክራሲ፣ በእስረኞች አያያዝ፣ በሰብአዊ መብት አጠባበቅ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ነአምን አሸናፊ አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ምርጫ 97ን ተከትሎ በእርስዎና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት ጥሩ የማይባል ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ያቀረቡት የቪዛ ጥያቄ እንዴት ነበር? ቪዛ መስጠት ያለመፈለግ አልያም ሌላ ነገር አጋጥሞዎታል?

አና ጐሜዝ፡- በፍጹም፡፡ ምንም ዓይነት ክልከላ ወይም እምቢታ አላስተናገድኩም፡፡ ለነገሩ የአውሮፓ ኅብረት የሰብአዊ መብተት ንኡስ ኮሚቴ ባለፈው ሐምሌ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት በአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ አምባሳደር እኔም መሄድ እፈልግ እንደሆን ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ እኔም መሄድ ብፈልግም ባልፈልግም ቪዛ አትሰጡኝ ምን ያደርጋል አልኩት፡፡ እርሱ ግን የለም እንሰጥሻለን አለኝ፡፡ እሺ ለአሁን የሥራ ባልደረቦቼ ይጓዙ የእኔ ጊዜው ሲደርስ አመለክታለሁ አልኩ፡፡ ስለዚህ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የአፍሪካ ፓስፊክ ካሪቢያንና የአውሮፓ ኅብረት ጥምር ስብሰባ ላይ ለመካፈል የቪዛ ጥያቄ አቀረብኩ፤ እነርሱም ያለምንም ቅድመ ሁኔታና ያለምንም ችግር ቪዛውን ሰጥተውኛል፡፡ በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በማለፋቸው የተለየ የፖለቲካ አተያይ እየተፈጠረ እንደሆነ የሚያሳይ ነገር ነው፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ለማምጣት ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ተረድቻለሁ፡፡ በተለይ ሙስናን በመዋጋት የጀመሩት ዕርምጃ ከፍተኛ የሥርዓቱን ባለሥልጣናት ሳይቀር ወደ እስር ቤት አስገብዋል፡፡ ይህም መልካም ጅምር ነው፡፡

ነገር ግን በኢትዮጵያ ከፍ ያለ ለውጥ ማየት እሻለሁ፡፡ ይህ የእኔ ብቻ ፍላጐት አይደለም፣ የኢትዮጵያውያንም ጭምር እንጂ፡፡ እዚህ በመምጣቴ ከስብሰባው ጐን ለጐን ሌሎች ሰዎችን በማናገር ለውጡ በእንዴት ያለ ሒደት ላይ እንዳለ ለመመልከትም እሞክራለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን በመምራት በ1997 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ውስጥ ስለነበሩ የአገሪቱን የምርጫ የዲሞክራሲና ሰብአዊ መብትንና የመሳሰሉ ጉዳዮችን ያውቋቸዋል፡፡ አገሪቱ አሁን ያለችበትን ሁኔታ እንዴት ይገመግሙታል?

አና ጐሜዝ፡- እንደሚመስለኝ ድኅረ ምርጫ 97 በኢትዮጵያ ያለው ዲሞክራሲያዊ ምህዳር ጠቧል፡፡ ከምርጫ 97 በፊት ከነበረበት ገጽታ አንፃር ብሶበታል፡፡ ምርጫውን ተከትሎ እልቂቶችን አይተናል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሲታሠሩ አይተናል፣ ለሲቪል ማኅበራት ምህዳሩ ሲጠብ አይተናል፡፡ እንደሚመስለኝ በበጐ አድራጐት ማኅበራት ላይ የወጣው ሕግ አሉታዊ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ አላግባብ ጥቅም ላይ ሲውል አስተውለናል፡፡ ሕጉ እጅግ የተለጠጠ ትርጓሜ እየተሰጠው የተለየ ሐሳብ ያላቸውንና የሚቃወሙ ግለሰቦችን ለማጥቃት አገልግሎት ላይ ለማዋል እየሞከረ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ የተነሳ ሁኔታው የባሰበት ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ምርጫ 2002 በቀዘቀዘ ሁኔታ ተከናውኖ አልፏል፡፡ የሥራ ባልደረባዬ ቴስ በርማን ምርጫውን ለመታዘብ በአውሮፓ ኅብረት ተወክሎ ነበር፡፡ ምርጫው መቀዛቀዙን ገልጿል፡፡ ምክንያቱም በምርጫ 97 ኅብረተሰቡ በስፋት ከመሳተፉ በተጨማሪ በምርጫው ለውጥ ይመጣል የሚል ተስፋ ነበረው፡፡ ይህ ተስፋውም እስከ ድምፅ ቆጠራው ድረስ የዘለቀ ነበር፡፡ ነገር ግን ሕዝቡም ሆነ እኔ ምርጫው መጭበርበሩን ተረድተናል፡፡ ስለዚህ በምርጫ 2002 ኅብረተሰቡ በአብዛኛው ወደ ምርጫ አልሄደም፡፡ እኩለ ቀን ላይ ሁሉም ነገር የተጠናቀቀበት የምርጫ ጣቢያዎች ነበሩ፡፡

የአውሮፓ ኅብረትን የወከለው ቴስ በርማን የምርጫውን ሪፖርት ለማቅረብ እንኳን ወደ አዲስ አበባ መመለስ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ሪፖርቱ ሒስን የያዘ ስለሚሆን ነው፡፡ ሒሱ ግን ገንቢ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ይህን ከልብ የመነጨና ቀና ሒስ መቀበል አልፈለጉም፡፡

እንደሚመስለኝ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ካለፉ በኋላ ነገሮች በሚገርም ሁኔታ ተለውጠዋል፤ የሚለወጡም ይመስለኛል፡፡ ይህም የመነጨው አመራሩ በመለወጡ ነው፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ለማምጣት እየሠሩ ይመስለኛል፡፡ ነገሮች ተጠናክረው እንዲጓዙ እንፈልጋለን፡፡ በፀረ ሙስና ላይ የተጀመረው ትግል፣ የዲሞክራሲያዊ ምህዳሮች መስፋፋት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶች እንዲስፋፉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲጠናከሩ፣ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ማየትን እንሻለን፡፡

እርግጥ ነው በተደጋጋሚ በመንግሥት በኩል የሚነገር መከራከሪያ አለ፡፡ ይህም እነዚህ ግለሰቦች የታሰሩት ጋዜጠኞች በመሆናቸው ሳይሆን በሽብርተኝነት ወንጀል ነው ይላል፡፡ እኔ ግን ይህን አልቀበለውም፡፡ ምክንያቱም አሁን አሁን ሽብርተኝነት የሚለው ሐሳብ የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ዝም ለማሰኘት እያዋሉት ነው፡፡

ከአሁን በፊት በአገሬ የነበረው አምባገነን መንግሥት ይጠቀምበት የነበረው ቃል አመፀኛ የሚል ነበር፤ አሁን ግን ቃሉ ሽብርተኛ ሆኗል፡፡ እንደሰማሁት እነዚህ ሽብርተኛ የተባሉ ግለሰቦች ያለፉበት የፍትሕ ሥርዓቱ ፍትሐዊ አልነበረም፡፡ ግለሰቦቹ የሽብር እንቅስቃሴን ማድረጋቸው የሚያስረዳ በቂ መረጃ አልቀረበም፡፡ ለኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ ጥሪ ማስተላለፍ ፈጽሞ የሽብር ተግባር ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የትኛውም ዲሞክራሲ ሊጠብቀው የሚገባ እውነተኛ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ድኅረ ምርጫ 97 ኢትዮጵያን አሁን ካለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር እንዴት ያነጻጽሩታል?

አና ጐሜዝ፡- አዲስ አበባ የቆየሁት ከመጋቢት ጀምሮ እስከ ምርጫው ድረስ እንደሆነ ማስታወስ ጥሩ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ጥቂት ተስፋ ሰጪ ነገሮች ነበሩ፡፡ መንግሥት በተወሰነ መልኩ የፖለቲካ ምህዳሩን ክፍት ለማድረግ ይሞክር ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ ግን የብዙኃኑን ሐሳብ ተቆጣጥሮት የነበረው ለአምስት ጊዜያት በቀጥታ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈው የፓርቲዎችን ክርክር ነው፡፡ ይህ ክርክር የሕዝቡን ሐሳብ ተቆጣጥሮት የነበረ ሲሆን፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ያንን በመፍቀዳቸው እንደ ተጸጸቱ እገምታለሁ፡፡ ምክንያቱም ኅብረተሰቡ አማራጮችን በአግባቡ የተረዳበት ክርክር ነበርና፡፡

ድኅረ ምርጫ የተፈጠረውን ሁኔታም አስታውሳለሁ፣ በምርጫው ዕለት ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለምንም በቂ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ፡፡ ይህም ምን ያህል እንደ ተሸበሩ የሚያሳይ ነበር፡፡ ምርጫው በአጠቃላይ በሰላምና በሥርዓት ተካሂዷል ብሎ የሚያምን ከሆነ እንዲህ ያለ ውሳኔ ለምን አስፈለገ? ለምን ሕዝቡን አያማክሩም ነበር፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነው፣ ምርጫውን ለማጭበርበር በመታሰቡ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ መሠረት አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ሁኔታ የማወዳድረው ከቅድመ 97 ሁኔታ ጋር ነው፡፡ በዚያን ወቅት ቢያንስ በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በፓርላማ ውስጥ መቀመጫ ነበራቸው፡፡ አሁን ግን በፓርላማው መቀመጫ ያለው ተቃዋሚ አንድ ብቻ ነው፡፡

እርግጥ ነው አንዳንድ የማውቃቸው ግለሰቦች የሚዲያው ዘርፍ በትንሹም ቢሆን እየተከፈተ እንደሆነ ገልጸውልኛል፡፡ ነገር ግን እየተከፈተ ያለው የሚዲያው ዘርፍ ዋናው ሳይሆን አማራጭ የሆኑት ማኅበራዊ ሚዲያዎች ናቸው፡፡ እርሱም የሚመነጨው ደግሞ ሕዝቦች ከቴክኖሎጂ ጋር ባላቸው ቅርርብም ጭምር ነው፡፡ በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ የቴክኖሎጂ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ አሁን ያለውን ቴክኖሎጂ ለማገድ ከአውሮፓም ይሁን ከእስራኤል የምታመጣው ባለሙያ ለመቆጣጠር የሚሆንለት አይሆንም፡፡ በምትቀጥራቸው ባለሙያዎች ፌስቡክንም ሆነ ትዊተርን መቆጣጠር እጅግ አዳጋች ነው የሚሆነው፡፡ በዚህ የተነሳ ባለሥልጣናቱም ወደ እዚያው ለመቅረብ እየሠሩ ይመስለኛል ምክንያቱም መንግሥት ሚዲያውን በሥነ ሥርዓት ካልከፈተው ሕዝቡ የራሱን መንገድ ይፈልጋል፡፡

ሪፖርተር፡- ዲሞክራሲን፣ የሰብአዊ መብት አያያዝን እንዲሁም ስለ እስረኞች ጉዳይ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል?

አና ጐሜዝ፡- አዎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት አባዱላ ገመዳ ምሳ ጋብዘውኝ ነበር፡፡ ከእርሳቸውም ጋር አቶ ተሾመ ቶጋ ነበሩ [የቀድሞው የሕዝብ ተወካዮች አፈ ጉባኤ፣ በአሁን ሰዓት በብራሰልስ የኢትዮጵያ አምባሳደር] ከእነዚህ ባለሥልጣናት ጋር በጣም ግልጽ የሆነ ውይይት ከማድረጋችን በተጨማሪ በግልጽ ያሉኝን ጥያቄዎች፣ ቅሬታዎችና ሒሶች ሰንዝሬያለሁ፡፡ ምንም ግለሰባዊ ችግር እንደ ሌለብኝም አስረድቻለሁ፡፡ በግሌ የማገኘው ምንም ዓይነት ኢኮኖሚያዊም ሆነ ሌላ ጥቅም የለኝም፤ ሥራዬን ግን በቁርጠኝነትና በትጋት እሠራለሁ፡፡ ስለዚህም ያየሁትንና የሰማሁትን የመናገር ግዴታ አለብኝ፡፡ በዚህም መሠረት ውይይታችን እጅግ በጣም ግልጽና ገንቢ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

ሪፖርተር፡- ከባለሥልጣናቱ ያገኙት መልስ ምን ይመስላል?

አና ጐሜዝ፡- ይህን እንኳን በዝርዝር አልነግርህም፡፡ የውይይታችን አንዱ ጠቀሜታም በግል መያዙ ነው፤ ምክንያቱም ውይይታችን የተካሄደው በግል ስለነበር፡፡ ነገር ግን ላረጋግጥልህ የምፈልገው ነገር ቢኖር ውይይታችን የፖለቲካ ምህዳሩን ስለማስፋት፣ የታሠሩ የፖለቲካ እስረኞችን ስለማስፈታት፣ ለበጐ አድራጐት ማኅበራት ምቹ ሁኔታን ስለመስጠትና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማጠናከርና መሰል ጉዳዮች የተዳሰሱበት ከመሆኑም በተጨማሪ ግልጽና ገንቢ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

ሪፖርተር፡- ከባለሥልጣናቱ ባገኙት መልስ ረክተዋል?

አና ጐሜዝ፡- እንደሚመስለኝ እኔን ለመስማት መፍቀዳቸውና መወያየታችን አንድ ጥሩ ምልክት አድርጌ እመለከተዋለሁ፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች በሙሉ የኢትዮጵያ ጉዳዮችና ሒደቶች ናቸው፡፡ የትኛውም አካል ምንም ዓይነት ተፅዕኖ ማሳደር አይችልም፡፡ ነገር ግን ከእኔ ጋር ለመወያየትና እኔን ለመስማት መፍቀዳቸው እንደ ጥሩ ጐን አድርጌ እመለከተዋለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ መንግሥትን ከሚወቅሱበት ጉዳይ አንዱና ዋነኛው የእስረኞች ሁኔታ ነው፡፡ እዚህ በመጡበት ወቅት ወደ ቃሊቲ ተጉዘው እስረኞችን ለመጠየቅ ጥያቄ አቅርበዋል?

አና ጐሜዝ፡- ጥያቄ አቅርቤያለሁ፡፡ ጥያቄዬ ግን በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን የጋራ ስብሰባው የፖለቲካ ኮሚቴ ወደ ስፍራው ተጉዞ እስረኞችን እንዲጐበኝ ባለፈው ቅዳሜ ጥያቄ አቅርቤያለሁ፡፡ (ይህ ኢንተርቪው የተካሄደው ሰኞ ዕለት የነበረ ሲሆን ረቡዕ ዕለት በሌዊ ሚሽል የተመራ ቡድን እስረኞችን ጐብኝቷል)

ከእስረኞች ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የሚደመጥ ነገር አለ፡፡ እነዚህ ግለሰቦች የታሰሩት ጋዜጠኛ ወይም ሌላ ስለሆኑ አይደለም፡፡ ይልቅስ አሸባሪ በመሆናቸው ነው የሚለውን አስተሳሰብ የሚጋሩ የአውሮፓ ተወካዮችም እንዳሉ ለመታዘብ ችያለሁ፡፡ እኔ ግን በዚህ አስተያየት ፈጸሞ አልስማማም፡፡ ምክንያቱም የስዊድን ዜግነት ያላቸው ሁለት ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ተከሰው መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በበርካታ ወንጀሎች ክስ ተመሥርቶባትና ተፈርዶባት መፈታቷ ይታወሳል፡፡ የእነዚህ ሰዎች ጉዳይም የተለየ አይደለም፡፡ የታሰሩት ግለሰቦች የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምልክቶች ናቸው፡፡ የወጣቱ ትውልድ ምልክቶች ናቸው፤ ምናልባትም ያቋቋሙት የፖለቲካ ሥርዓትም የላቸውም፡፡

ሪፖርተር፡- መንግሥት በሽብርተኝነት ነው ያሰርኳቸው የሚለውን የሚያምኑ ከሆነና እነዚህ ሰዎች አሸባሪ አይደሉም ብለው የሚያስቡ ከሆነ የእርስዎን ሐሳብ የሚያጠናክር ምን መረጃ አለዎት?

አና ጐሜዝ፡- ኢትዮጵያ ከሽብርተኝነት ጥቃት ሥጋት ነፃ ነች እያልኩ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያና የአውሮፓ አገሮች ከሽብርተኝነት ጥቃት ሥጋት እንዳለባቸው አምናለሁ፡፡ ነገር ግን በስመ ሽብርተኝነት የዲሞክራሲ ምህዳሩን ማጥበብ፣ የተለየ ሐሳብ ያላቸውንና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን የሚጠይቁ ግለሰቦችን ፀጥ ማሰኘት፣ ሽብርተኝነትን መታገል አይደለም፡፡ ይህ እንዲያውም ግለሰቦችን በይበልጥ ወደ ሽብር ተግባር እንዲሰማሩ መመልመል ነው፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን የሽብር ሥጋት ደረጃ ለማሳነስ እየሞከርኩኝ አይደለም፤ ነገር ግን የታሳሪዎቹን የፍርድ ሒደት የታዘቡ ግለሰቦች እንደነገሩኝ የፍርድ ሒደቱ ፍትሐዊ ካለመሆኑም በተጨማሪ የቀረቡት ማስረጃዎች የግለሰቦቹን የሽብርተኝነት ተግባር የሚያሳዩ አልነበሩም፡፡ ለዚህ ነው እነዚህ ሰዎችን አሸባሪ ብሎ መጥራትን የማልቀበለው፡፡

ሪፖርተር፡- ይህ የሰጡኝ ማብራሪያ ትክክል እንደሆነ የሚያረጋግጥ ሁነኛ ትንታኔ ሊሰጡኝ ይችላሉ?

አና ጐሜዝ፡- አላውቅም፡፡ እኔ እኮ ታሳሪዎቹን በግል አላውቃቸውም፡፡ ለምሳሌ የብርቱካን ሚደቅሳ ጉዳይን ያነሳህ እንደሆነ በግል እንተዋወቃለን፡፡ እንዲሁም ከብርሃኑ ነጋ ጋር የግል ትውውቅ አለን፡፡ እነዚህ እስረኞች ግን በግሌ አላውቃቸውም፡፡

ሪፖርተር፡- በቅርበት እንደሚያውቋቸው ከገለጹት ግለሰቦች መካከል አንዱ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው፤ እርሳቸው ያቋቋሙት የፖለቲካ ድርጅት በኢትዮጵያ መንግሥት እንደ አሸባሪ ይቆጠራል፡፡ እሳቸውም ሥርዓቱን ለመለወጥ ከምርጫ የተለየ መንገድ ያስፈልጋል እያሉ ነው፡፡ እርሳቸው አቅጣጫቸውን ይቀይራሉ ብለው አስበው ያውቃሉ?

አና ጐሜዝ፡- ብርሃኑ ነጋን የማውቀው በምርጫ 97 ወቅት ነው፡፡ ቅድም የገለጽኩት በቀጥታ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈው የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር የተነሳ በአገር አቀፍ ደረጃ ተቃዋሚ ጐራ ወኪል እንዲሆን አስችሎታል፡፡ በክርክሩ የተነሳ በአገር አቀፍ ደረጃ ተቃዋሚ ጐራውን በመወከል ስሙ የሚነሳ ግለሰብ ቢኖር ብርሃኑ ነጋ ነበር፡፡ እርግጥ ነው በየምርጫ ወረዳቸው የታወቁ ግለሰቦች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ አቶ ቡልቻ ደመቅሳና ወዘተ፡፡ በነገራችን ላይ ብርሃኑ ነጋ በምርጫ 97 ወቅት ባይታሰር ኖሮ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ይሆን ነበር፡፡ ከእስር እንደተፈታም ወደ ስደት አመራ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች አቅጣጫውን እንዲቀይር ያደረጉት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በአገሪቷ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ ሊኖረው የሚችለው ሚና በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓት በመበላሸቱ የተለወጠ ይመስለኛል፡፡

ሪፖርተር፡- እርስዎ በስፋት የሚታወቁት የኢትዮጵያ መንግሥትንና የአውሮፓ ኅብረትን ከዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፋፋት ጋር ባለባቸው ችግር በተደጋጋሚ ሲወቅሱ ነው፡፡ አሁን በእርስዎ ላይ የተፈጠረ የአቋም ለውጥ አለ?

አና ጐሜዝ፡- ኢትዮጵያን በተመለከተ ከፍተኛ ትችትና ሒስ እሰነዝራለሁ፡፡ አውሮፓ ኅብረት ላይ የምሰነዝረው ሒስ ደግሞ የባሰ ነው፡፡ የአውሮፓ ኅብረትን በተለያዩ ጉዳዮች እተቻለሁ፡፡ በተለይ በኅብረቱና በኢትዮጵያ ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ትችት እሰነዝራለሁ፡፡ ምክንያቱም የአውሮፓ ከፍተኛና ጠንካራ ተፅዕኖ ማሳረፍ ሲችልና በኢትዮጵያ ጉዳይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ሲችል ዝምታን ይመርጣል፡፡ ይህን አይቻለሁ፡፡

አንዳንድ ሰዎች የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲ የተሻለ እንደሆነ ይገልጹልኛል፡፡ እርሱን እጠቀምበታለሁ፤ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውልም አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ከፍተኛ ጫና የማሳደር ዲፕሎማሲ (ሜጋፎን) መጠቀም ይኖርብናል፡፡

ባልደረባዬ ሊዊ ሚሸል ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ሁለት የስዊድን ዜግነት ያላቸውን ጋዜጠኞችን አስፈትቶ ስለ ኢትዮጵያውያን እስረኞች ጉዳይ አንዳች ሳይሠራ ወደ አውሮፓ በመመለሱ በጣም ተናድጄ ነበር፡፡ በተለይ ለኢትዮጵያውያንና በአጠቃላይ ለአፍሪካውያን የምናስተላልፈው መልዕክት ምንድነው? እኛ የምንጨነቀው ለዜጐቻችን ብቻ ነው፡፡ ይህ ተግባር ተራና ማዳላት ያለበት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ በነበሩበት ወቅት ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት እንደነበሮት ይታወሳል፤ እዚህ ከመጡ ያገኟቸው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች አሉ?

አና ጐሜዝ፡- እስከ አሁን ያገኘሁት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የለም፡፡ ነገር ግን እንደማገኛቸውም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ከዚህ በላይ ግን በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የትውልድ ችግር አለ፡፡ በግሌ በተቃዋሚ ፓርቲና በውጪ አገሮች ባሉ ኃይላት መካከል ግንኙነት ቢፈጠር መልካም ይመስለኛል፡፡ ይህም ለፖለቲካው ምህዳር መከፈትና ለውይይት መዳበር ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ ይህ ደግሞ እውነተኛ ለሆነ የዲሞክራሲ ግንባታ እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ መጠላላትን አስወግዶ ወደ ፊት ለመጓዝ ይረዳል፡፡

ሪፖርተር፡- ምርጫ 97ን ተከትሎ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በተደጋጋሚ ውዝግብ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዴት ይገልጿቸዋል?

አና ጐሜዝ፡- ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እስከ ምርጫው ድረስ የነበረኝ ግንኙነት መልካም የሚባል ነበር፡፡ ከእርሳቸው ጋር ግልጽ የሆኑ ብዙ ውይይቶች አካሂደናል፡፡ ተለዋዋጭ ባሕሪ እንዳላቸው ለመታዘብ ችዬ ነበር፡፡ በግንኙነታችን መጀመሪያ አካባቢ አምናቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ቀስ በቀስ ሊያሞኙኝ እየሞከሩ እንደሆነ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ እርሳቸው በጣም ክፉ ነበሩ፡፡ በጣም ክፉ የሆነ አእምሮ የነበራቸው ናቸው፡፡ ብልህ ናቸው ግን ክፉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያን ሔራልድ ጋዜጣ ላይ የጻፉትን የምንጊዜውም ረዥሙን ርእሰ አንቀጽ አልረሳውም፡፡ መጨረሻ ላይ ግለሰባዊ ጥቃት በመሰንዘር ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ገንዘብ ተቀብላለች የሚል ዘመቻ ጀመሩ፡፡ ፈጽሞ ተራ የፈጠራ ውሸት ነው፡፡

እኔ በግሌ ከእርሳቸው ጋር ምንም ዓይነት ችግርም፣ ጸብም ባይኖረኝም እኔን በመክሰስና በመዝለፍ ጉዳዩን ግለሰባዊ አደረጉት፡፡ እርግጥ ነው ያኔ በጣም በጣም ብናደድባቸውም አሁን ግን የሉም፤ ሄደዋል፡፡


የትምህርት ተቌማት የእውቀት ወይስ የፖለቲካ ሜዳ!?

$
0
0

ከቅዱስ ዮሃንስ

 

higher educationትምህርት ዜጎችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ በመቅረጽ ለራሳቸው፣ ለማህበረሰባቸውና ለሃገራቸው ጠቃሚ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያግዝ የእውቀት ማሸጋገርያ ስልት ነው፡፡ ዛሬ በስልጣኔ የገሰገሱ የአለም ሀገራት የዕድገታቸው ዋነኛ መነሻ ትምህርት ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ነው። ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ የአገልግሎት ፓኬጅም ሆነ ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች በዘመናዊ አኳሃን እንዲመነደጉ ከተፈለገ በተግባር የታገዘ፣ ፈጠራና ክህሎትን የሚያዳብር ጥራት ያለው ትምህርት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡

የትምህርት መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ መጣል ከጀመረ ከመቶ ዓመታት በላይ የተቆጠረ ሲሆን ከሁለተኛው አለም ጦርነት በፊት ትምህርት የሚሰጠው በመንግስትና በሃይማኖት ተቋማት ዙርያ ለአስተዳደራዊ ክህሎት፣ ለቀኖናና ለሃይማኖት እውቀት ሲባል እንደነበረ ጥናቶች ይገልጻሉ፡፡ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የአፄ ሃይለ ስላሴ ስርዓት ዘመናዊ ትምህርትን በተደራጀ መልኩ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲሰጡ ሁኔታዎችን ያመቻቸ ቢሆንም የትምህርት ቤቶች እድገት ከማህበረሰቡም ሆነ ከሃይማኖት ተቋማት በገጠመው ተጽእኖ ምክንያት የመስፋፋቱ እድል አዝጋሚ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በደርግ ወቅቱም ቢሆን የነበረው አጣዳፊ ጉዳይ አብዮቱ በመሆኑ በመማርና ማስተማር ላይ የነበሩትን መምህራንና ተማሪዎች በነቂስ አሰልፎ አብዮቱን ለማስተዋወቅ በሚል ሰበብ ወደ እድገት በሕብረት የዕውቅትና የስራ ዘመቻ አዘመተ፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ እራሱን በጥቂቱም ቢሆን ማጎልበት የጀመረው የትምህርት ስርዓት ከባድ ፈተና ውስጥ ወደቀ፡፡ በማያባራ ዘመቻ፣ ግድያ፣ አፈናና ጦርነት ተተብትቦ እራሱን ፋታ የተነሳው ደርግ፤ በቂ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባትና መምህራንን ለማብቃት ጊዜ አልነበረውም፡፡ በዚህም ምክንያት መምህር አልነበሩም፡፡ ትምህርት ቤቶችና ለመማር ማስተማር ሂደቱ በሚያስፈልጉ ግብአቶችና ቁሳቁሶች አልተሟሉም፡፡ የትምህርት ስርዓቱ በአጠቃላይ እርቃኑን እንደቀረ ነበር፡፡ ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓተ ውድቀት አንድ ተብሎ ተጀመረ፡፡

 

የኢትዮጵያን የትምህርት ስርዓት ተብትበውና ቀስፈው የያዙት ችግሮች ከደርግ ጋር ተዳብለው ስር እየሰደዱ ቆይተው፣ ዛሬም በኢህአዴግ ውስጥ በመሸጋገር ማጣፊያ እንዳጠራቸው ቀጥለዋል ፡፡ የመማር ማስተማር ሂደቱ በደርግ ስርዓት የለከፈው የማጥራት ሳይሆን በማብዛት፣ በማዳረስ ላይ የመተማመን በሽታ ዛሬም ወያኔን ቀስፎ እንደያዘው ይገኛል፡፡ ትምህርትን ለሁሉም ዜጐች በስፋት የማድረስ ተልዕኮን እንደያዘ የሚያስበው ወያኔ፤ የትምህርቱን የጥራት ደረጃ ለዚህ ግቡ ሲል እየጨፈለቀው ስለመሆኑ ብዙ ጥናቶች አረጋግጠዋል። ሀገሪቱ ካስቀመጠችው አነስተኛ ማለፊያ ነጥብ እጅግ ያነሰ ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎች ከመጀመሪያ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ባሉት የትምህርት እርከኖች ቁጥራቸው እየበዛ መምጣቱ ሳያንስ፤ ወደ መሰናዶ ትምህርት የገቡት በሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡበት አሳፋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል። ለየትምህርት ክፍሎቹ በማይመጥኑ መምህራን መማር፣ በአነስተኛ ደረጃ መሟላት ይገባቸው የነበሩት የትምህርት መሳሪያዎች እጦት አልፎም የአካዳሚያዊ ነፃነት በፖለቲካዊው ስርዓት በጥልቁ መጣስ፤ የኢትዮጵያ ትምህርት ተቋማት መሰረታዊ መለዮ ሆኗል። የዚህ ፅሁፍ ዋና ትኩረት የትምህርት ስርአቱን ቀስፈው የያዙት ችግሮችን አንድ በአንድ ነቅሶ ማሳየትና መዳሰስ ሳይሆን፤ ለስርአቱ ውድቀት በተለይም ለጥራቱ ዝቅጠት ግንባር ቀደም መንስኤዏች ተብለው ከሚፈረጁት መካከል ትምህርትን ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ላይ ትኩረት ያደርጋል።

 

የወያኔ መንግስት ትምህርትና የትምህርት ተቋማትን ለፖለቲካ ፍጆታ በመጠቀሙ ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት የመምህራን አመራረጥ በተለይም ለከፍተኛ ትምህርት አስተማሪነት የሚታጩ መምህራን የመለኪያው ዋና መስፈርት የፖለቲካ አቋም መሆኑን መመልከት ይቻላል። ወያኔ በዘረጋው የትምህርት ዘርፍ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ተቋማት ድረስ መምህራን የሚመለመሉት በፖለቲካ መስፈርት ነው። በነዚህ የትምህርት ደረጃዎች ችግሮች በቀጥታ ከትምህርት ጋር የተያያዙ መሆናቸው እየቀረ ፖለቲካዊ ይዘት እየተጎናፀፉ መጥተዋል፡፡ የወያኔ የካድሬ እንቁላል መጣል እና የረጅም ጊዜ አሕዳዊ አገዛዝ ፍላጎት የራስ መከላከል ሥራዎች በይፋ ይጀመራሉ፡፡ ባለፈው በደርግ ስርዓት ውስጥም ትምህርቱ ከሶሻሊዝም ርዕዩተ ዓለም ውጪ አልነበረም። አሁንም ቢሆን ትምህርትና ተቋማት በፖለቲካውና በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዮተ -ዓለም የተቃኙ ናቸው። ከዚህም በላይ መንግስት ዩኒቨርስቲ መክፈትን እንደ ፖለቲካዊ አፍ የማዘጊያ ስልት ተጠቅሞ የፖለቲካ ድጋፍና ታማኝነትን እንደማግኛ መሳሪያ እየተገለገለበት ነው፡፡ ዛሬ በሃገራችን ቁጥራቸው በርከት ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ መገኘታቸው እሰይ የሚያስብል ቢሆንም እጅግ አሳዛኙ ነገር ግን ሁሉም ተቋማት በፖለቲካ ተተብትበው የእውቀት አምባ መሆናቸው ቀርቶ የካድሬ መፈልፈያ ተቋማት መሆናቸው ነው። ይህም የትምህርት ጥራቱን እንዲያሽቆለቁል አድርጐታል።

 

ወያኔ በዩኒቨርስቲዎች እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በነጻነት እንዲያስቡ አይፈለግም፤ አይፈቀድምም፡፡ እንኳን ተማሪዎቹ ይቅርና መምህራኑ ጭምር በነጻነት የሚያስተምሩትን ለመምረጥ አይደፍሩም፡፡ በንድፈ-ሐሳብ ደረጃ ለተማሪዎቻቸው የሚያስተላልፉትን እውቀት ሀገሪቷ ላይ ካለ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ተንትኖ ለማስረዳት የሚደፍሩት ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ ክፍል ውስጥ ለሚያስተምሩትም

ሆነ ለሚናገሩት ነገር ልክ በቤተ ክህነት ውስጥ የአምላክን ቃል እንደሚሰብክ ሰባኪ ጥንቃቄን ማድረግ ግድ ይላቸዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው የተዘረጋውን አስጨናቂ የአምባገነን ስርአት ከመፍራት፤ የተናገሩት ነገር ገዥው ፓርቲን የሚነቅፍ (የማይደግፍ) ከሆነ ያለአግባብ ስም ተለጥፎባቸው የእንጅራ ገመዳቸውን ስለሚበጠስ ነው። በለፈለፉ ባፍ ይጠፉ ይባል የለ። ከክፍል ውጪም በተቋማቱ አመራሮች ለሚፈፀሙ የአሰራር ስህተቶች እና በደሎች ለመተቸት እምብዛም ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ ምክንያቱም አመራር ተብለው የሚሾሙት የትምህርት ተቌማት ባስልጣናት የተሻለ እውቀትና ልምድ ያላቸው ሰዎች ሳይሆኑ የመንግስት ቀኝ እጅ በመሆን የሚያገለግሉት የወያኔ ግልገል ካድሬ ናቸው። እነዚህ አካላት በሚያስተዳድሩት መምህራን ላይ ኢፍትሃዊ እርምጃ ቢወስዱም ማንም ሃይ ባይ የላቸውም።

 

ተማሪዎች በአብዛኛው ለትምህርታቸው የሚሰጡት ትኩረት እና ውጤታቸው ምንም አያስጨንቃቸው፤ ደንታቸውም አደለምም ለማለት ያስደፍራል። ከዚህ ይልቅ የወጣቶች ሊግ እና ማንኛውንም የመሪው ፓርቲ ተደራሽነት የሚያሳድጉ/የሚያጠናክሩ ሥራዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ታትረው ይሰራሉ። ይህም በጓደኞቻቸው ላይ የበላይነትን እንዲያገኙ ከማድረጉም በላይ ተሰሚነትን በትምህርት ቤት ኃላፊዎች ያስገኝላቸዋል፤ ከበድ ሲልም የንግድ እና የፖለቲካ ሥራ እንዲያገኙ ይመቻችላቸዋል፡፡ ይህ በትምህርት ዘርፍ ላይ የተዘረጋው ስርዓት ለተማሪዎች የሚያስተላልፈው መልእክት ግልፅ ነው፡፡ በትምህርት ተግቶ እውቀት ሸምቶ ሀገሪቷን ለመጥቀም ከመታተር ይልቅ ርካሽ የፖለቲካ ተወዳጅነት ማግኘት የስኬት መንገድ አቋራጭ መሆኑን ነው፡፡ ለትምህርት ትኩረት መስጠት ያለውን ጥቅም ተረድተው ይሻለኛል ብለው የሕይወት መስመራቸውን የሚያስተካክሉት ተማሪዎች ቁጥር እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ አሽቆልቁሏል።

 

በአሁኑ ወቅት ወያኔ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚማሩት ውስጥ 85% የሚሆኑ አባላት እንዳሉት እና በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍሎች ውስጥ ህዋስ እንደዘረጋ ይገልፃል፡፡ እንግዲህ ይህ ፐርሰንት በመመልከት አብዛኞቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የስርዓቱ አካል እና አስፈጻሚ እንደሆኑ መናገር ይቻላል፡፡ እጅግ አሳዛኙ እውነታው ግን እነዚህ ሁሉ አባላት ወደ ድርጅቱ የተቀላቀሉት በፍላጐት ሳይሆን በግዳጅ ብሎም በሃገሪቱ የተዘረጋው አላፈናፍን ያለው አስጨናቂው ስርአት የሚያስከትልባቸውን የከፋ መዘዝ ለመሸሽ ከመፈለግ መሆኑ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ በዩንቨርስቲዎች ውስጥ እየታየ ያለው አዲስ ገፅታ፤ የተማሪዎች ጊዜያቸውን በህዋስ ውይይት እና ግምገማ ማዋላቸው፣ ከአባላት ሁሉ ልቆ ለመታየት የሚደረግ ጥረት፣ ከትምህርት ውጤታቸው ይልቅ፤ በአባልነታቸው ወደሚሰጣቸውን ነጥብ መጨነቅና አብዝቶ ማተኮር፣ ሲብስም የትምህርት ጊዜያቸውን መሉ በሙሉ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ለፓርቲ ተግባራት በማዋል የመጡበትን ዋነኛ የትምህርት አላማ በመሸሽ፤ ብቁ የካድሬ ምሩቃን ሆነው ለመውጣት ወ.ዘ.ተ መሽቀዳደም የተማሪዎች መገለጫዎች ናቸው፡፡ ይህም የተሻለ ስራ እንዲያገኙ ያግዛቸዋል፤ በተቃራኒው ይህንን የሚሸሹ ምሩቃን ለስራ ማጣት እና ለከፋ ችግር እየተጋለጡ ይገኛሉ።

 

በመጨረሻም መንግስት ትምህርትና ተቋማቱን የፖለቲካ ሜዳ ከማድረግ መታቀብ አለበት፤ ከካድሬዎችም ነፃ ማድረግና የእውቀት አምባ ብቻ ሆነው መቀጠል ይኖርባቸዋል። በዘርፉ ያለው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መስተካከል እንደሚገባው፣ ተማሪዎችና መምህራኖች አካዳሚክ ነፃነት ማግኘት እንዳለባቸው፣ ተቋማቱ ዕውቀት የሚገበይባቸው እንጂ የፖለቲካ ማራመጃ ሜዳ መሆን እንደሌለባቸው፣ የትምህርት ሥራ ሙያ እንጂ ፖለቲካ አለመሆኑ፣ እንዲሁም በመልካም ተምሳሌትነት ሊጠቀሱ የሚገቡ የልሂቃን /Elite/ ት/ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች ሊፈጠሩ ይገባል። ትምህርት በዋናነት መፍትሄ ሰጪ ዕውቀት ካላስጨበጠና ችግር ፈቺ መሳሪያ ካልሆነ ለብዙሃኑ እንደሚታደል መሰረታዊ ሸቀጥ ካየነው አደጋው የከፋ የሀገር እድገት እንቅፋት ከመሆን የዘለለ ሚና እንደማይጫወት ይታወቃል፡፡ ስለዚህ የትምህርት ስርአታችን ከተደቀነበት ከፖለቲካ ተፅዕኖ ማላቀቅ ግድ ነው። ይህ ብቻ ሲሆን አምራችና በእውቀት የዳበረ ዜጋ ማፍራት ይቻላል። ትምህርት ቤቶች (ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ) በግልፅም ሆነ በስውር የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ገዥ አካል ፖለቲካዊ አጀንዳ ማስፈፀሚያ መሆን የለባቸውም፡፡ ይህ ከሆነ ግን አሁን በሃገራችን እየተስተዋለ እንዳለው ውድቀቱ የከፋ ነው።

 

ኢትዮጵያችን በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

 

ለአስተያየትዎ: kiduszethiopia@gmail.com ይጠቀሙ።

ይድረስ ለሳኡዲው ባለሃብት ሼክ መሃመድ ሁሴን አላሙዲ “ዝምታን” ለምን መረጡ?

$
0
0

ከዘላለም ገብሬ (ጋዜጠኛ)

የተከበሩ ሼክ መሃመድ ሁሤን አላህሙዲ ክብረቴ ይድረስዎት እያልኩኝ በአሁን ወቅት ባለው አንገብጋቢ እና አሰቃቂ በሆነው ጉዳይ ላይ ምላሽዎን ቢሰጡኝ ብዬ ይህችን አጭር ደብዳቤ ለእርስዎ እና እንዲሁም ለወኪሎችዎ እንዲደርስዎ በማለት ከልቤ ያለውን ሃሳብ ልጠይቅዎት ወደድኩኝ ፣ እኔን በውል የሚያውቁኝ ሰው አይደለሁም ተራ ሰው እና ሳገኝ የውስጤን የምሞነጫጭር የእስኪርቢቶ ጓደኛ ስሆን እርስዎን የማግኘት እድል ከአንድም ሁለት ጊዜ ቢገጥመኝም የእጅ ሰላምታ ሰጥቶ የእግዜር ሰላምታ ከመስጠት ያለፈ ሂደት አላከናወንኩም ፣ ይሄ ማለት ደግሞ ትልቅ ነገር ሆኖ ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም ግን ማነው ብለው የሚሉ ከሆነ አንድ
ተራ ብእርተኛ ብለው እንዲያስቡን እሻለሁ፣ እንዲህ ስልዎት ደግሞ ከሳቅዎ ጋር እየገነፈለ የሚወጣው ቁጣዎ መጥቶ እንዴት እኔን ይደፍረኛል ብለው እንዲሉ ሳይሆን እንዲያው ሃሳብን በሃሳብ ይረዱልኝ ዘንድ ቤዬ ችግሬን ላካፍልዎት ብዬ ወደድኩ ፤ ይሄውም በጣም በሚወዷቸው እና ዜግነትዎን ሁሉ ተናግረውለት በማይጠግቡት ሳኡዲዎች ፣በሌላ ወገንዎት (በትውልደ ኢትዮጵያውነትዎን በሚናገሩበት ዜጋዎት ላይ ፣)ደግሞ ከምንም በማይቆጥሩት እና ከመንግስት ጋር ባለዎት መልካም እና ጥብቅ ግንኙነት የሚጠቀሙበትን ህዝብ ፣ መንግስት እና እንዲሁም ሃገር ላይ ያለዎትን አስተያየት እና እንዲሁም አመለካከት እንዲነግሩኝ ሲሆን በአሁን ሰአት በዜጎችዎ የኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እንዴት እንዳዩት ልብ ሊሉልኝ ይገባል ።
alamoudi-dmeke
በአሁን ሰአት ባሉበት ስውዲን ሆነው ይህችን ብጣሽ ደብዳቤዬን ሊያነቡልኝ እንደሚችሉ እርግጠኛ ነኝ እርስዎ ማንበብ ባይችሉ እና ጊዜ ቢያጡም አማካሪዎችዎ ከመናገር ወደ ኋላ አይሉምና ሊያገኝውት እደሚችሉ እርግጠኛ ነኝ ። እንደ ኢትዮጵያውያን የኑሮ ሁኔታ 85 በመቶ የሚኖረው ህዝብ ከገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል፣ከፍተኛው አርሶ አደር ነው ጥቂቱ ደግሞ አርብቶ አደር ፣የአርሶ አደሩ እና የአርብቶ አደሩን የገቢ ምንጭ ቁጥር ስናነጻጽረው የአርሶ አደሩ የተሻለ ህይወት አለው ሆኖም ግን 75 በመቶ የሚሆነው ህብረተሰብ በድህነት አለም ላይ ያለ ህብረተሰብ በመሆኑም የብዙ ቤተሰብ ጫንቃ በአንድ ሰው ትከሻ ላይ የሚጫንበት አገር እንደሆነች ብጠቅስልዎት ለእርስዎ ተረት ተረት ሊመስልዎት ይችላል ግን አይደለም ግልጽ ነው ።
ይህንን ስናገር እርስዎ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመሩ እረጅም ጊዜ እንዳስቆጠሩ በአንድ ወቅት ላይ በተናገሩት በራስዎት አንደበት ለመረዳት ችያለሁ ታዲያ በደሃ አገር በደሃ ህዝብ ላይ ሃብታም የሆነ አንድ ባለሃብት የደሃውን ጉሮሮ ለመድፈን ሳይሆን የራስን ጥቅም ለማሽከርከር ሲል ከአለው መንግስት ጋር ተጣብቶ የግል ፍላጎትን ለማሟላት የሚደረገው ጥረት ከእርስዎ ብቻ የመጣ ሳይሆን ታላላቅ ሃገሮች የሚባሉት አውሮጳ እና አሜሪካውያኖች በአፍሪካ ሪሶርስ ላይ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን እጃቸውን አስገብተው እንደፈለጋቸው ለማሽከርከር በሚያመቹበት መልኩ እራሳቸውን አደላድለው ተቀምጠዋል ። ታዲያ እርስዎም በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና የንግድ ተቋም ላይ ለምን ገቡ ብዬ ልጠይቅዎት አልፈልግም በአንድ በኩል ትልቅ አስተዋጾ እያደረጉ መሆኑን ይገባኛል ይሄውም የዜግነት ግዴታዎን እየተወጡ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የደሃ ቤተሰቦችን ጉሮሮ እየደፈኑ እንደሆነ የሚታወቅ ስለሆነ ፣እንደዚያም ቢሆንም ከኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ይልቅ እርስዎ የሚያገኙት ጥቅም 90% በላይ ሲሆን ሃገሪቱንም ጎድተው አንጡራ ሃብቶቿንም ተጠቅመው ሃብትዎንም አካብተው ዛሬ ላይ ደርሰዋል ፣ይሄን ሁሉ ለሆነልዎት ባለውለታ ለከፈለልዎት ህዝብ እና አገር ምላሽዎ ዝምታ ሆኖአል ።
ለምን ዝምታን መረጡ ? እንደዜግነትዎ የሁለት አገር ዜግነት እንዳለዎት እየተናገሩ ባለበት ወቅት ፣በሃገራችን ላይ የመጀመሪያውን ዘርዎን ለማስጠራት ሲሉ ሳኡዲ ስታር የሚለውን ኩባንያ ተክለው ፣ምርቶቹን ወደ ሳኡዲ እንዲሄድ እያደረጉ የሳኡዲ ዜግነት ያላቸውን ወገኖችዎን እየረዱ ባለበት በዚህ ሁኔታ ለምንስ ይሄን ያህል ዋጋ ለከፈለልዎት ህዝብ ደግሞ የውለታው ምላሽ አልሆኑለትም ? ከላይ እንደጠቀስኩልዎት ሃሳብ መሰረት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የገጠሩ ህዝብ እንደሆነ እና የገጠሩ ህብረተሰብ ደግሞ በድህነት አረንቋ የሚኖር እነመሆኑ መጠን እራሱን ለማሻሻል ቤተሰቡን ለመርዳት ብሎም ሃገሩንም ከችግር ለማውጣት ሲል በሌላ ዜግነት ባለዎት የሳኡዲ ምድር ላይ ስራ ሰርቶ እንዲኖር ያስችለው ዘንድ አገሩን ፣ ወገኑን ፣የትውልድ ቀዬውን እንዲሁም የልጅነት ናፍቆቱን ያሳለፈባቸው ጓደኛ ዘመድ አዝማዶቹን በእዝነ ህሊናው እየዳሰሰ በረሃን አቋርጦ ኑሮው ሲያሸንፈው ኑሮን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ሲል “የሰው አገር ሰው ቢረግጡት አህያ ቢለጉሙት ፈረስ “ሆኖበት መከራ እና ስቃዩን ማየት ከጀመረ ከራርሞአል።
bereket alamudi demeke
ታዲያ አገር እየገዛሁ ነው ያለው መንግስትም ምንም እርዳታውን በተገቢው መልኩ ሊያደርግ አልቻለም ፣የሳኡዲ ዜግነት እያለዎት በሳኡዲ መንግስት ላይ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ ሳይቻልዎ ቢቀር በደሃ አገሮች ላይ ክርንዎን ለማሳየት የሞከሩበት ዋነና ሁኔታ በማንቂያ ገንዘብ እያሳዩ በአካፋ መዛቅ የለመዱበት አገር ላይ ህዝቡ ዝምታን ስለመረጠልዎ ይመስለኛል ታዲያ እርስዎ ለዚያ ደሃ ገበሬ ፣ያፈራውን ምርት ነጥቀው ለሳኡዲዎች የሚሰጡበት ገበሬ ያ ደሃው ህዝብ ዛሬ የድረሱልኝ ጥሪ ሲያሰማ እርስዎስ የት ገቡ ።
ንጉስ አብደላንስ ለምን ለማማከር አልሞከሩም ። ነው ወይስ እንደ አቶ አይለማርያም ደሳለኝ ቅጥፈትዎን በአደባባይ ሊያሳዩን ፈለጉ?
በኢትዮጵያ ምድር እና ህዝብ ላይ ከ20 በላይ ትላልቅ የሆኑ ኩባንያዎችን መመስረትዎ የሚታወቅ ነው ጥቂቶቹን ብናነሳ ኤልፎራ ፣ኒያላ ኢንሱራንስ ፣ኒያላ ባንክ፣ሸራተን አዲስ፣ሳኡዲ ስታር ፣ሰን ላይት የኤሌትሪክ ኩባንያ ፥እንዲሁም የወርቅ ማእድን ቁፋሮ የሚያመርተው ትልቁ ኩባንያዎት
Managed under the parent MIDROC Group is MIDROC Ethiopia Technology Group with several further
companies under its management:
- MIDROC Gold Mine
- ELFORA Agro-Industries
- Huda Real Estate
- Kombolcha Steel Products Industry
- Modern Building Industries
- Trust Protection and Personnel Services
- Addis Home Depot
- Trans Nation Airways
- Addis Gas & Plastics Factory
- Wanza Furnishings Industry
- Daylight Applied Technologies
- Blue Nile P.P & Craft Paper Bags Manufacturing
- United Auto Maintenance Services
- Unity University
- Rainbow Exclusive Car Rental and Tour Services
- Summit Engineered Plastics
alamudi የሃገሪቱን አመታዊ በጀት በአንድ ቀን የሚያገኙበት ዋነኛው የንግድዎ ምንጭ እና እንዲሁም ሌሎች የአበባ ፣ሰሊጥ ፣እህል እና ትራጥሬ ምርት የሚሰበስቡበት ኩባንያዎት ትልቁን የሃገሬን ገበሬ ጉሮሮ እየነጠቀ ምንም የሚበላ ነገር ለማያመርቱት እና በግብርናው አለም ህይወታቸው አልፎ የማያወቀው ፣ በነዳጅ ምርት ብቻ እምሮአቸው ለተደፈነው ጥጋበኛ ባለ ሃብቶች ዝርያዎችዎ ምርታችንን በማከፋፈል ስራዎ መጠመድዎን አውቃለሁ ፣ታዲያ ለምንስ በእናትዎ ወገን ያሉትንስ ለማዳን አይጥሩም ?ሴት እህቶቻችን ሲደፈሩ ሲገደሉ ፣ወንዶችም ሲደፈሩ ፣ሲገደሉ ፣በርሃብ እና ውሃ ትም ሲሰቃዩ እናት ከእንጭጭ ልጆችዋ ጋር በሜዳ ላይ ያለ መጠለያ ስትወድቅ ሰው ያለ ሃገሩ በደል እና ስቃይ ሲደርስበት አስትዋሽ ሲያጣ መንግስትም ጉዳየ አይደለም ብሎ ህዝቡን በንቀት ሲመለከት እርስዎስ እንዴት አዩት ? ከ63 % በላይ መሬቱን ነጥቀው ምርት የሚያመርቱት የእርስዎ ዝርያ ያላቸው የሳኡዲ አረቦች መሆናቸውን ዘንግተውታልን ? በሃገራችን ገብተው እንደሚሰሩት ሁሉ ለምን የሌሎቹንም ዜጎች ክብር ሊጠብቁ እንዳልቻሉ ለምን አንደበትዎን ከፍተው አልተናገሩልንም ? ኢትዮጵያን እወዳለሁ እያሉ የሚደነፉት የግላዊ ጥቅምዎ እስኪከናወን ብቻ እንደሆነ ያየንበት እና የታዘብንበት ወቅት ዛሬ መሆኑን ገብቶናል እንጂ የንብ ቲሸርት ለብሰው እኔ ወያኔ ነኝ ባሉበት ወቅት አልነበረም ምክንያቱም ለኢትዮጵያ ህዝብ
ፖለቲካ ሳይሆን የቸገረው ዳቦ ፣ሰላም እና መልካም አስተዳደራዊ መንግስት ብቻ ነው ስለዚህ ያንን ሰላሙን በሃገሩ የነጠቀው መንግስት በሰው አገር እንዲሰደድ አደረገው በሰው አገርም ስደቱ አልበቃ ሲለው ስቃዩ እና መከራው በዛበት እንደርስዎ በገንዘብ የጠገበ ዲታ ሰው ማንንስ ደሃ ያስታውሳል ብቻ ድከም ብሎኝ እና የደሃ እህት እና ወንድሞቼ ደም ቢከሰኝ ጥያቄዬን ልጠይቅ ብዬ እንጂ መልስዎን ሊመልሱ እንደማይችሉ አውቃለሁ ፣ስለዚህ ምላሽ ካለዎት ምላሹን በዝግጅት ክፍላችን ልናስተናግድ ዝግጁዎች ነን ስለዚህ በኢሜል አድራሻችን ቢያቀርቡልን ለህዝብ ከማድረስ ወደ ኋላ አንልም ።ለዚህ ደግሞ ውድ ጊዜዎን ተሻምቼ ይህችን ስላነበቡልኝ ሳላመሰግን አላልፍም ፣ታዲያ እንዲህ ስልዎት ስም ያለውን ሰው እየፈለጉ ወይን ባለስልጣን እያሰሱ ብርዎን ከሚረጩ የድረሱልኝ ጩኸታቸውን እያሰሙ ያሉትን ዜጎቻችንን መፍትሄ ቢሰጡልኝ ደስታዬ እጅግ የላቀ ነው ።ከዚያም አልፎ ከስደት መልሳቸው በሃገራቸው ኮርተው ይኖሩ ዘንድ ስራንም ፈጥረው የስራ አጡን ቁጥር ቢቀንሱት የስደተኛው ቁጥር ሊቀንስ ይችላል እናልብ ሊሉት ይገባል በማለት የዛሬውን ሃሳቤን እቋጭልዎታልሁ ላደረጉት ነገሮች ሁሉ በድጋሚ እያመሰገንኩ በኢሜል አድራሻችን አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ቢልኩልን እንወዳለን እናስተናግዳለን zelalem@maledatimes.com ወይንም
editor@maledatimes.com አሁንም ለጊዜዎ ክብረትን ይስጥልኝ !

መንግስት ነን ብላችሁ፤ አገር እያስተዳደራችሁ እንደሆነ ለምትቆጥሩ ግን ሞራል ለሌላችሁና ሀላፊነት ለማይሰማችሁ የሀገራችን ገዥዎች

$
0
0

ከመልካም ብሥራት

ማርም ሲበዛ ይመራል ይላሉ አበው፡፡ ውሸታችሁ፤አስመሳይነታችሁ፤ ወሰን ያጣው በቀለኝነታችሁ፤ አቅመቢስነታችሁ፤ ዘረኝነታችሁ፤ ሙሰኝነታችሁ….ኧረ ስንቱ የናንተ ነገር ተዘርዝሮ ያልቃል? በዛ፤ መረረንም፡፡ መንግስት ህዝብን ወክሎ የአንድን ሀገር ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚመራ ተቋም ሆኖ በእንቅስቃሴዎቹ ሁሉ ታሳቢና ተቀዳሚ የሚያደርገው የህዝብን ተጠቃሚነትና የሀገርን ልማት፤ እድገት፤ ብልፅግናና ሉዓላዊነት ነው፡፡

sa12 በዚህች መናኛ መለኪያ ስትለኩ የናንተ ቦታ የት ነው? ህዝብን የልማት ተጠቃሚ እያደረጋችሁት ነው? የትኛውን ህዝብ? ሀገሪቱን አለማችኋት? የግብርናው፤ የኢንዱስትሪው፤ የአገልግሎቱ ዘርፍ በናንተ የአገዛዝ ዘመን የት ደረሰ? ስራ አጥነቱ፤ መሰረተ ልማቱ የት ናቸው? የተፈጥሮ ሐብቶች ምን ላይ ናቸው? የዜጎች የፖለቲካ ተሳትፎ፤ መልካም አስተዳደሩ፤ ሰብኣዊና ፖለቲካዊ መብቶች እስከ ምን ድረስ ተከበሩ?

እናንተ መንበረ ስልጣኑን ከአምሳያችሁ ደርግ በጠመንጃ ነጥቃችሁ ከያዛችሁበት ጊዜ ጀምሮ በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና መከራ በናንተ የመጣ ሳይሆን ህዝቡ ራሱ በራሱ ላይ ያመጣው እያደረጋችሁ በህዝብ ሰቆቃና ችግር እየቀለዳችሁና እያሾፋችሁ በሞቱና ውርደቱ እየተዝናናችሁ እስከአሁን አላችሁ፤፤ በጣም የሚገርመውና የሚያንገበግበው በቅርቡ በራሳችሁ ሸር የተነሳውን የሳውዲ አረቢያ ቀውስ ሲመቻችሁ ኮረጆ በመገልበጥ አልሆን ሲል በጠመንጃ ለምታጭበረብሩት ምርጫ ተብዬ ቁማራችሁ የምርጫ ፖለቲካ ስትጠቀሙበት እጅጉን ገረማችሁኝ::

ይህንን ዓይን ያወጣ አረመኔ አመለካከታችሁን አምርሬ ጠላሁት፤ መቼም በምንም ሁኔታ ለሀገርና ለህዝብ የማትጠቅሙ ከንቱዎች እነደሆናችሁና ከስህተቶቻችሁ ለመማር ያልተዘጋጃችሁ አድሮ ጥጆች፤ ጥፋትን በልማት ከመመለስ ይልቅ ለጥፋቶቻችሁ ሽፋን ሌሎች ጥፋቶችን ከመስራት የማትቆጠቡ ሞራለ ቢሶች ሆናችሁ አገኘኋችሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ከእናንተ መልካም ነገር የሚጠብቅ የዋህ ማን ነው? ከእባብ የርግብ እቁላል መጠበቅ አይቀልምን?

ከእናንተ አዕምሮና ከሬዲዮና ቴሌቪዥናችሁ ከንቱ ልፈፋ ያላለፈው የኢኮኖሚ ፖሊሲያችሁ እድገትን እያቀጨጨ፤ ስራ አጥነትን እየፈለፈለ፤ የኑሮ ውድነትን ጣራ እያስነካ፤ ሰላምን አያናጋ፤ አንድነትንና አብሮ መኖርን እያፈረሰና መሰረቱን እየናደ፤ በምትኩ ጥላቻን፤በቀልን፤አለመተማመንን እያነገሰ ለመጭው ትውልድ ስቃይና መከራን ልታወርሱት ቀን ከሌት እየዳከራችሁ መሆናችሁን ከቶ መቼ ይሆን ልብ ልትሉት የምትችሉት? የስኬቶቻችሁ መገለጫዎችና ውርሶቻችሁስ ዘረኝነት፤ አለመተማመን፤ ጥላቻ፤ በቀል፤ድህነት፤ሞራለቢስነት መሆናቸውን ለመረዳት ማን እስኪነግራችሁ ነው የምትጠብቁት?

እግርና እጅ የሌለውና የተጨማለቀው፤ ለኢትዮጵያ የማይመጥነው፤ ከእንቅልፋችሁ በባነናችሁ ቁጥር የምትለዋውጡት የተደበላለቀ የነፃ ገበያ የኢኮኖሚ ፖሊሲያችሁ፤በየትኛውም የዓለም ክፍል የሌለ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማደናገሪያችሁ፤ የህዝብን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ ባልቻለና ይልቅስ ውስንና ሰንካላ፤ የጥቂት ቡድን አባላትን፤ ሌቦች ባለስልጣናትን፤ የስርዓቱ ታማኝ ጀሌዎችን ተጠቃሚነት የሚያሳይ ልማት ተብዬ የሀብት ቅርምታችሁ ከእናንተ አልፎ ለህዝብ ጠብ የሚል ነገር ስላላመጣ ውጤት አልባው ከንቱ ጥረታችሁ ጠብ ሲል ስደፍን እንዲሉ ውሃ በወንፊት መቋጠር እንደሆነባችሁና ውል የሌለው ክር መሆናችሁን ለመረዳት የሚያስፈልጋችሁ የጊዜ ርዝመት ምን ያህል ነው?

የአስተዳደራችሁ ድምር ውጤት በሆኑት ስራ አጥነት፤ ስደት፤ ርሀብ፤ እስር፤ እንግልት፤ ውርደት፤ አለመተማመን ወዘተ ምክንያት በሁሉም የዓለም ማዕዘናት በሚኖሩ ስደተኞች ላይ ለሚደርሰው የኢትዮጵያውያን መከራ ተጠያቂው ከእናንተ ውጭ ማን ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ? አስተዳደራችሁስ የበጀውና እሰየው ያስባለው የትኛውን የህብረተሰብ ክፍል ነው? ሙስሊሙን? ክርሰቲያኑን? አማራውን? ትግሬውን? ኦሮሞውን? ሲዳማውን? ጉራጌውን? ሃድያዉን? አኙዋኩን? ሶማሌውን? አፋሩን? ወጣቱን? አዛውንቱን? ሴቶችን? ወታደሩን? ገበሬውን? ሙሁሩን? የትኛውን የህብረተሰብ ክፍል ነው የበጃችሁት? ጥቃት ያላደረሳችሁበት ማን ይሆን? የበግ ለምዳችሁ ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ተቀዳዶ እርቃናችሁን ስለቀራችሁ ለምዳችሁ ኣያታልለንም፡፡ተጨማሪ በደል እንድትፈፅሙ እድልም አንሰጣችሁምና ለለውጡ ከመተባበር ያለፈ ተስፋ እንደሌላችሁ እወቁት ልላችሁ እፈልጋለሁ፡፡ በሴራዎቻችሁ እና በወጥመዶቻችሁ ያተረፍነው መከራና ስቃይን ብቻ መሆኑን ከተረዳን ውለን አደርን፡፡ ተስፋ ቁረጡ፡፡ መዝሙራችን ሠላም፤ ፍቅር፤ አንድነት፤ ህብረት፤ ብልፅግና ሁኗል፡፡
ቸር ይግጠመን

አረሙ ወያኔ በዬትኛውም መስፈርት ኢትዮጵያዊነትን የመቀማት ሞራሉም ሆነ አቅሙም የለውም ~~~ በጣም በእርግጠኝነት።

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 01.12.2013

 

(ሲርጉት)

(ሲርጉት)

ጥሪው የማህጸን ነበር። ምላሹም የዕትብት ሃዲድነት ነበር።

ጤና ይስጥልኝ ሞገደኛው ተክሌ እንደምን ሰነበትክ? ደህና ነህ ወይ? የብዕር አጣጣልህ እንደ አቤ ቶኬቻው ውብ ስለሆነ ለረጅም ጊዜ እያደንኩ አነባለሁ። ጠረባህንም አክሎ። በጠረባህ ዙሪያ አንድ ቀን የምለው ይኖረኛል …. ዛሬ ግን ልታገሰው ስላልቻልኩት ማለት ፈለግኩ ….. በሦስት ነገሮች ዙሪያ …. እንዲህም እላለሁ …. እኔው ….

ሳውዲ አረብያ ላይ ለደረሰው ውርደት ተጠያቂው አረሙ ወያኔ ነው። የወያኔ ፖሊሲ ነው ለዚህ የትውልድ ፍልሰት በይፋ  የፈቀደው። ሙጃው ወያኔ የተመሰረተበት ይህ ነውና። እኛ ጊዜ እዬጠበቀ ወያኔ በሚያፈነዳው ፈንጅ ዙሪያ ጥቃቱን ለመመከት ዕለታዊ ሰልፍ ስለምነደርግ ነው እንጂ የወያኔ መሰረታዊ ፍጥረት ትውልድን ከማፍለስ ላይ በመሆኑ መርዙ የማይነካውና የማያካተው አንዳችም ነገር የለም። ይህ የጥፋት አዟሪት የሚነሳው ኢትዮን ቅኝ ለማደረግ ህልማቸው ካልተሳከ ሀገሮች ምኞት ነው። ስለሆነም ዒላማችን ሊነሳ የሚገባው ከጥንስሱ መሰረት ላይ መሆን አለበት እላለሁ እኔ። ይህን መሰረት ያያዘ የኢትዮጵያዊነት የጥላቻ ፖሊሲ ከሥሩ ለመንቀል ደግሞ ከበቀለበት ማንፌስቶ ነው የትግሉ ወላፈን መነሳት ያለበት የሚል ጠንካራ አድምታ ነው ያለኝ በግሌ። መዳህኒቱም የወያኔ ማንፌስቶ ግብዕተ – መሬት ሲፈጸም ብቻ ነው። የፈውሱ ፍሬ ነገር ከሃርነት ትግራይ ህልፈት ላይ ነው። እያንዳንዱን የወያኔ የጥፋት ሆነ የቅጣት የበቀል  እርምጃ በሥርዓት በተጠና ሁኔታ ቢመረመር ቢተነተን – ቢነበብ – ቢፈታታሽ ድርጀቱ ከተፈጠረበት እንቁላል አስኳል ውስጥ ይመነጫል።

neb 7

ለማንኛውም በሳውዲ ላይ የተሰነዘረብን የጥቃት እርምጃ ለመቃወም እልፎችን ያስቆጣው ሰላማዊ ሰልፎች ወያኔ ኢትዮጵዊነትን የቀማበት ወይንም የነጠቀበት አልነበረም። በጭራሽ።“ኢትዮጵያዊያንን ለማስተባበርና ሳኡዲዎችን ለመጀንጀን የምናቁዋቁመውን ኮሚቴ መለየት ያለብን ይመስለኛልሰልፎቹንግንተቀምተናል፡፡  ከልጅ ተክሌ ጹሑፍ የተወሰደ”

ልጅ ተክሌ …. ምን አልባት አንተ በላህበት ሀገር ሆኖ ከሆነ ከተጠያቂዎቹ ውስጡ አንዱ ትሆናለህ። ከማንም በተሻለ ተደማጭነቱም፤ ተቀባይነቱም አለህና! ሁልጊዜ አንተ ታንከባላለህ ድክመቶችን ወደ ሌሎች። …. አንተ እኮ ምርጥ፤ ልዑቅ ከሚባሉ ኢትዮጵውያን ውስጥ አንዱ ነህ። የፖለቲካ ተንታኝ …. በታኝ፤ ጋዜጠኛ፤ አክቲቢስት፤ ሃያሲ፤ የምትፈልገውን ጽፈህ ተከብረህ የሚወጣለህ፤ ያልታገድክ፤ ገድብ ያልተሰረባህ፤ አንቱ የተባልክ ሚሊዮኖች በምታገኘው መድረክ ሁሉ በአክብሮት የሚያዳምጡህ ዕድለኛ ወጣት ነህ …. እና ካናዳ ላይ ወያኔ ኢትዮጵያዊነት ለመቀማት መድረክ ሲያገኝ አንተ የት ነበርክ? ምንስ ትሰራለህ? ….. እራስህን ጠይቅ

እኔ ሲዊዘርላንድ ነው የምኖረው። ሰላማዊ ሰልፉን ማን እንደጠራው አላወቅም። ከኢሳት ሰምቼ ነበር የሄድኩት። እንዲህ ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ ሲዊዘርላንድ ውስጥ አላዬሁም። እጅግ በጣም ብዙ ሰው ነበር። ቁጭቱ፤ እልሁ፤ እንባው፤ መቃጠሉና መንደዱ … የነጠረው ሰንደቅዓላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ካለምንም ቅይጥ በነፍስ ወከፍ ተይዞ ነበር …. እኔ  በሰዓቱ እጠረት ነድጃለሁ። ምክንያቱም እዛው ባድርም አልጠግብኩትም ነበርና። ወንድምዓለም ጊዜው ከኖረህ እንዲህ ሰርቸዋለሁ አዳምጠው www.lora.ch.tsegaye ዬ 21.11.2013 ወይንም … በዚህኛው ሊንክም ይቻላል ….

…. ይገርማል። ለመሆኑ ለዛውም ውጭ ሀገር ወያኔ በምን ሞራሉና አቅሙ ነው እኛነታችን፤ ማንነታችን፤ ውስጣችን የመቀማት አቅሙስ ሞራሉስ የሚኖረው። ወንድሜ ሆይ! በአባይ ቦንድ ምን ያህል አረሙ ወያኔ እንዴት እንደ ተራገፈ አላዬህንም? አይታሰብም! ተዎው እኛን ወያኔ ከመጠበት ዘመን ጀምሮ የተወለዱት አዲስ ፈርጦች እኮ ናቸው  የኢትዮጵያዊነት መሪና አደራጅ የሆኑት። ይህ ከድንቅ በላይ ነው። ኢትዮጵያዊነት እኮ ገና በሥነ – ምርምር ብዙ የፈካ ተግባር ከፊት ለፊቱ የሚጠብቀው የሰማይ ጥበብ ነው። ተቀማን? አፈርኩልህ ስለቃሉ ….. አኔ የብዕርህ ፍቅረኛ። ጥሎብኝ ደግሞ ድምጽህንም እወደዋለሁ።

 

ሳውዲ ላይ ለዛውም የውጭ ዜጋ በሳውዲ መሬት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሲደርግ እኮ ሰማዕት ኢትዮጵያውያኑ የመጀመርያ ናቸው። በማይቻልበት ቦታ ችለው ግን የተሰውበት የተጋድሎ ልዩ ታሪክ …..። የበቀል አምላክ እንደሚበቀለው የሳውዲን መንግስት ቀን ይናገራል …. አምላካችን እንደ ቻይነቱ ቁጡ ነውና።

 

ሰላማዊ ሰልፉ በመላ ዓለም የኢትዮጵውያን የአትንኩን አኅታዊ ድምጽ … ደመ – ነፍሱን ወያኔን ያራጋፈ፤ ያደናበረ፤ ከእንቅልፉ የቀሰቀሰው፤ ያተራመሰው፤ ከእንሰሳነት፤ ከአራዊትንት አስተሳሰቡ ተግ ብሎ ሰው ስለመሆኑ እራሱን እንዲጠይቅ ያፋጠጠበት፤ ወያኔ ከዛቀጠበት አርንቋ ለመውጣት እፍ ግብ ያለበት በፍጹም ሁኔታ የተዋረደበትና ማንነቱ ያጋለጠበት ነበር ማለት ይቻላል። እውነቱን ልንገረህ ትናንት የተቋቋመው ሰማያዊ ፓርቲ ከወያኔ አስተዳደራዊ ተቋም በላቀ ሁኔታ ዕውቅና ያገኘበት። ኢትዮጵያዊነት የወያኔን የ40 ዓመት ሴራ አክሽፎ የተሞሸረበት – የተመሳጠረበት ታላቅ አብነታዊ የኢትዮጵውያን የወል የጥሪት ውጤት ነበር። ካፒታላችን ቅርሳችን ነው ለዛሬ። ለነገ ደግሞ ትውፊታችን …..

 

 

ሌላው አንተ እንትቀማ በራስህ ላይ ማተኮር እንዳለብህ የሚያመለክት ነገርም ከጹሑፍ አዬሁ …. እንዳላዬሁ ሆኜ ላላፈው አልፈለግሁም። ምን? ምን አልክ ወንድምዓለም …. „„…የበለጠ የሚያሳስበው ደግሞ፤ ከዚህ ከሳኡዲ ችግር ጋር በተያያዘ ያቁዋቁዋምነው አለማቀፍ ኮሚቴም፤ አስር ሀያ አመት ከምናደርግበት የትግል ስልት ብዙ ፈቀቅ ያለ አይመስልም፡፡ የኮሚቴው ሙሉ ዝርዝር ባይኖረኝም፤ የሶስቱ ሰዎች ስም እንደሚያሳየው ከሆነ፤ ኮሚቴው ዘመኑን ያልዋጀ፤ የአንድ ብሄር ስብስብ ነው የሚመስለው፡፡ ስብስቡ አለማቀፍም አገርአቀፍም ደረጃውን እንዲጠብቅ አልተደረገም፡፡ “ ….  „ብንቀበለውም ባንቀበለውም፤ በአደባባይ እንደዚያ ብለን ባናውጅም፤ ይሄንን የሳኡዲን ግፍ ለማለስለስና ለማስቀልበስ የምናቋቁማቸው ተቁዋማትና ስብስቦችም ሁኑ ሌሎች መሰል ፖለቲካዊና ሲቪክ ማህበራቶቻችን፤ በተዘዋዋሪ ይሄንን የሀይማኖትና የብሄር ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገቡ መሆን አለባቸው፡፡ ከልጅ ተክሌ ጹሑፍ የተወሰደ” ዬት የት እዬተጓዝክ ነው እናትዬ …. አዬህው በወያኔ የጎጥ ፖሊሲ ምን ያህል እንደ ሰመጥክ፤ እዬተጠቃህም እንደሆነ …. እጅም እንደ ሰጠህ።  „እናስተውል“ ይላሉ አባቶቻችን …. እኔ ስለተደራጀው ግብረኃይል እራሱ በነፍሱ ስላለ የሚለውን ይበል ….

 

ነገር ግን እንደ አንተ ዓይነት ወንድም ግን በብሄረሰብ ስብጥር ላይ ማተኮሩ በጣም መውረድ ነው።  ይህ የሚመችህና የሚደላህ ከሆነ ከቶ ስለምን ተሰደደክ? አልገባኝም። የእኔ እናት ጎሰኝነት፤ መንደርተኝነት እኮ ኋላቀርነት ነው። ኋላቀርንት በኢኮኖሚያዊ ስሌቱ ያልተመጣጠነ እድገት ማለት ነው። በአስተሳሰብ ስሌት ስንሄድም ያው ያልተመጣጠነ እድገት ነው …. በ21ኛው ምዕተ ዓመት ከቤተሰብ ቀጥሎ ካላው ጎሳ ላይ መቆም ምን ሊሉት ይቻላል ከኋላቀርነት ውጪ

 

እባክህ እያንዳንዱን ነገር በዚህ ዝርዝርና ምንዛሬ አታሰባጠረው …. ከዚህ መጠራቅቅ መውጣት አለብህ። አዎና!  በአንድ ወቅት አንድ ቅዱስ አባታችን ከዚህዓለም ስደት ላይ እንዳሉ ሲያርፉ ዬእምነት ልዩነት ሳይኖር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቀብር ሥርዓቱ ላይ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን ስሜቱን አድንቀህ ተከታታይ ጹሑፎች በኢትዮ ዛሬ ላይ አስነብበህን ነበር። ያን ጊዜ ስትጽፍ ጎሰም አድርገህ የጻፍካት ነበረች። ሊቀ ሊቃውንቱን ብታገኛቸውና ልምዳቸውን ቢያካፍሉህ ግን ሸንቆጥ አድርገህ ያለፍካት ነገር „ላም ባለወለበት መሆኑን ትረዳ በነበረ“ ለማንኛውም ሁላችንም ….. በዚህ ስሌት ከተጓዝን …. ምን አልባት ያን የፍቅር ቤት ደርመሾቹ እኛው ሆነን እናርፋለን። የወያኔን የተጠያቂነት ጠቀረማ ዘመንም የመሸከም ግዴታ ሊኖርብን ነው። በዚህ የፋደሰ መንገድ ከተጓዝን። ከወያኔም እንሻል ቢያንስ እኛ …. በስተቀር ግን ዛሬም ጭቃ ነገም ረግረግ …. መዛገጥ … መዝገጥም – ኪሳራ መከዘን ይሆናል ዕጣ ፈንታችን።

 

ሌላው ያነሳህው …. እንዲህ ላሉ ድንገተኛ ችግሮች ቋሚ አካላት አለመኖራቸው …. እንዳሳዘንህም ጽፈኃል። አንተ እንዲህ ያለ የቀደመ ሃሳብ ከነበርህ ባለህበት ሀገር ማቋቋም ትችል ነበር አኮ። ማን ጌታ አለብህ። አቅሙ እንዳለህም አስባለሁ። በሌላው ድርጅት ላይ ካለይሉኝታ የምትሰንዝራቸው ወቀሳዎች እዳይደገሙ ጥርት ያለ ብቁ ተቋም። ከስህተት የጸዳ፤ ምርጥ ዘር የሚያፈራ፤ ፍጽምና ሸማው የሆነ ድርጀት የማቋቋም ሙሉ መብት ነበረህ። አለህም። እንዲህ በዬጊዜው እርር ድብን ከምትል …. ልጅ ተክሌ የአንተ ጹሑፍ አምልጦኝ አያውቅም፤ ቃለ ምልልሶችህም ከሌላ ድርጀቶች ጋር አንተ የደረካቸውም ሆነ አንተም በኢሳት ባለህ ቦታ …. ከሌሎች ጋር ያደረከውም …..

 

እኔ እንደማስበው ወያኔ ብዙ ቢፈታታነውም የኢትዮጵያ ሰብዕዊ መብት አስከባሪ ጉባኤ በፕሮፌሰር መስፍን ይመራ የነበረው፤ እስረኞችን ለመታደግ ውጭ ሀገር የተቋቋመው፤ የአዲሱቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ፤ ሌሎቹም … በተጨማሪም በኢሳትም ሰብዕዊ መብት በሚመለከት ራሱን ያቻለ መመሪያ መኖሩ …. ጅምሩ መልካም ነው። በዬጊዜው እስር ቤት የሚማቅቁት ጋዜጠኞች፤ ከዚህም ባለፍ ሥምና ዝና የማይፈልጉ፤ ድምጻቸውን አጥፈተው ከዬሀገሮችም ሆነ በድንበር ዘለልም ከዓለም ዓቀፍ የሰብዕዊ መብት ድርጅቶች ጋር የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን እንዳሉም አውቃለሁ። ይደክማሉ። ይሰራሉ።

 

እኔ በምኖርበት ሲዊዘርላንድ የሰብዕዊ መብት ረገጣ በኢትዮጵያ የቆረቆራቸው ወጣቶች ሶሎቶርን በሚባል ከተማ በ2010 የመሰረቱት አንድ ግብረኃይል አለ። ጥቅምት 12/2012 አቶ ኦባንግ ሜቶ ከአዲሲቱ ኢትዮጵያ የክብር እንግዳ የነበሩበት፤ ከግንቦት 7 ዶር. ታደሰ ብሩ፤ አቶ ወንድምአገኝ ጋሹ ከኢሳት በተገኙበት በዙሪክ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ

አካሄዶም አይቻለሁ። ስብሰባው ጥሩ መንፈስ ነበረው። ሃሳቦች በሚገባ ተንሸራሽረዋል። ከጀርመን ሙንሽን የመጡ ወገኖችም ነበሩ። …

 

…. እኔ እንደ አንተ ሃያሲ ስለሆንኩ ከልብ የተደሰትኩበት ስብሰባ ነበር … ማለት እችላለሁ። ያው አልጻፍኩትም። ልመናው ሆነ ድጅ ጥናቱ ገደለኝ። በዬድህረ ገፆች አውጡልኝ በማለት መንከራተት እንጂ  …. ያን የመሰለ የወጣቶች ጥረት ወሼኔ ተብሎ በተፃፈለት ነበር። በሌላ የሚዲያ ሽፋን ማግኘቱን ባላውቅም …. እኔ ግን በጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራሜ  በዜና ሰርቸዋለሁ ….. ከዚህ ጋር በተያዬዘ መልኩ በሰብዕዊ መብት ዙሪያ ጠንከር ያሉ ተግባራት በሲዊዲንም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዳለ  ይሰማኛል።

 

…. በተጨማሪ በዬሀገሩ የሚስማሙ፤ የሚግባቡ፤ የሚደማመጡ ሰዎች የራሳቸውን የግልና የወል ጥረት እንደሚያደርጉም አስባለሁ። ሌላው ቀደም ባላው ጊዜ አዲስ ድምጽና የሲዊዲን እንዲሁም ሌሎች የነፃነት ትግሉ ቤተኛ የሆኑ የኮሚኒቲ ራዲዮኖች ሆነ ማህበራዊ ድሀረ ገፆች በርካታ ተግባራትን ከውነዋል በዚህ ዙሪያ ። እንዲሁም የኢትዮጵውያን የመወያያ ሩሞች የራሳቸውን ሁለገብ ተግባር ሲከውኑ ቆይተዋል።  የትኛው የአፍሪካ ሀገር ነው እንደ ኢትዮጵውያን በሀገሩ ጉዳይ ትርጉም ያለው ተግባር ውጭ ሀገር የሚከውነው። እውነት ለመናገር ተጽፎ አያልቅም ….

 

ልጅ ተክሌ … ችግራችን ከቁጥር በላይ ነው። በሁሉም ቦታ ሁሉም ሊሆን ስላማይቻል ክፍት ቦታ እዬፈለጉ ቀዳዳ መሸፈን የእኔም የአንተም ግዴታ ነው። ሲናሪዮ ሆነ ፕሮቶኮል የማይጠይቁ ብዙ የተግባር መስኮች አሉና። ሌላው ግን እኛም ስደተኞች ነን። ብዙ መከራና ፈተና በግል ህይወታችን እዬፈተለን ነው። ይህም ሆኖ ውጪ ያለነው ኢትዮጵውያን ሁሉንም ሆነናል በአቅማችን ልክ። ከነድክመቶቻችን ለበርካታ ነገሮች በባለቤትነት ስሜት የምንችለውንም አድርገናል እያደረግነም ነው።

 

ስለሆነም በማናቸው ጊዜ በድንገተኛ የእናት ሀገር የእማ ጥሪ፤ ጠሪም ተጠሪም ወቃሽም ተወቃሽም የለም። ሊኖርም አይገባም። መወቀስ ካለብን ሁላችን። መመስገን ካለብን ደግሞ ሁላችን። ቁስሉም ህምሙም ስቃዩም እኩል ነው። በእናት ሀገር የችግር ቀን የድረሱልኝ ጥሪ አንዱ የክት ሌላው የዘወትር፤ አንዱ ልጅ ሌላው የእንጀራ ልጅ ሊሆን አይችልም …. ከወያኔ በስተቀር …. ወያኔ ይህን ለማጥፋታ 40 ዓመት ቢሰራበትም ንጉሥ ዳዊት በወጣትነቱ ማህልዬን፤ በጎልማሰነቱ ምሳሌን በእርጅና ዘመኑ ደግሞ ሁሉም ኖሮት ዓለምን ፈትሾና አይቶና መርምሮ ከመንፈስ ቅዱስ በተሰጠው መክሊት  ከንቱነትን አመሳጠረ …. በሳውዲ የኢትዮጵያዊነት መከራ የወያኔን ከንቱነት ያነበበ፤ የተረጎመና ያመሳጠረ ነበር ዓይንም ህሊናም የለውም እንጂ …. ሙጃው ወያኔ።

 

እናሳርገው …. በወሳኝ ጉዳይ። ….  አንድ ነገር ኢህድግ …. የሚባል ኑሮ ያውቃልን? ከዚህ የወያኔ ሸንኮፍ ተጠቂነትም መውጣት ያለብን ይመስለኛል። የልጅ ተክሌ ጹሑፍ ለወያኔ የጥፋት ሴራ ዕውቅና የሰጠ መሰለኝ። ሀገር ትውልድ ታሪክ ባህል እምነት ያጠፋ ወያኔ ነው። መነሻው መድረሻውም ተልዕኮውም በመሆኑ …. ቅርጽ ነው ኢህድግ ይዘቱ TPLF ነው ትናንትም ዛሬም …. በሌለ ነገር ላይ ምስክርነት …. መስጠት —- ትዝብት ነው … ይበቃኝ። ጨረስኩ።

 

እኔ እኔ ነኝ የምለው፤ እኔ በእኔ ውስጥ ሳይሾልክ እኔን ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው።

እኔ እኔ ነኝ የምለውም የጠላቴ ዒላማ ተጠቂ አለመሆኔን በፍጹም ሁኔታ በእኔ ውስጥ ሳረጋግጥ ብቻ ይሆናል።

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

አበሻ እና ሆድ –ክፍል 2 (ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

$
0
0

አበሻ ድግስ ይወዳል፤ ድግስ የሚወደው መብላትና ማብላት ስለሚወድ ነው፤ ለመብላት የአበሻ ምክንያቱ ብዙ ነው፤ ልጅ ተወለደ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ክርስትና ተነሣ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ አገባ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ሞተ ብሎ መብላት ነው፤ አበሻ ሰው ቀብሮ ሲመለስ በንፍሮ ይጀምርና ቀስ በቀስ ወደሌላው ይተላለፋል።
Pro Mesfin
ሃይማኖትም ቢሆን ለመብላት ካልሆነ የነፍሱ ጉዳይማ በጣም ሩቅ ነው፤ ሕያዋን ለነገሥታት፣ ሙታን ለካህናት ይገብራሉ፤ በሚለው መመሪያ መሠረት

ግብር መቀበል ያለ ነው፤ ክርስቶስ ተወለደ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ተጠመቀ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ሞተና ተቀበረ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ተነሣ መብላት ነው፤ ማርያም አረገች መብላት ነው።

ማኅበርም የሚጠጣው (የሚበላው ለማለት ነው፤) ለመብላት ነው፤ አምላክ በተለያዩ ስሞቹ፣ ቅድስት ማርያም በተለያዩ ስሞችዋ፣ መላእክት፣ ቅዱሳን፣ ሰማዕታት ሁሉ ለመብላትና ለማብላት ያገለግላሉ፤ ወደመንግሥተ ሰማያት ለመግባት አማላጅ ሊሆኑ የሚችሉ ሁሉ ማኅበር ለመብላት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፤ የሌሎች አገሮች ክርስቲያኖች በመብል አይመለሱም፤ ገበያቸው በጠገራ ብር ነው፤ ስለዚህም አብሮ መብላት ብሎ ነገር የለም።

አበሻ የሚበላው የመጣውን ሲቀበል ብቻ አይደለም፤ የሚሄደውን ሲሰናበትም መብላት ይወዳል፤ ሞትም ቢሆን ለመብላት ምክንያት ነው፤ ቀብር ብሎ እዝን እያቀረቡ መብላት ነው፤ ሠልስት ብሎ መብላት ነው፤ ለሰባት መብላት ነው፤ ለዓርባው መብላት ነው፤ የሙት-ዓመት ደግሶ መብላት ነው፤ በቀብር ላይም ቢሆን ለቅሶውም ‹‹ሆዴ! ሆዴ!›› ነው።

ለአበሻ ጾምም ቢሆን ለመብላት ነው፤ የጾም ትልቁ ምሥጢሩ ምግብ እንዲናፍቅ ለማድረግ ነው፤ የፍስኩ የተትረፈረፈ ምግብና ጥጋብ ባይኖር ማን ይጾማል? የለየላቸው ጠጪዎች በሁዳዴ መለኪያውንና ብርጭቆውን አርግፍ አድርገው የሚተውት ሲፈሰክ በናፍቆት ዊስኪውንና ቢራውን ለመጋት ነውኮ! ይህ ባይሆን አንድ ጊዜ ሞጣ ያየሁትየበግ ሌባ ለምን ይጦም ነበር? ታሪኩ እንዲህ ነው፤ በሞጣ አውሮጵላን ማረፊያ አንድ የበግ ቆዳ የያዘ ሰውዬ በፖሊሶች ይጠበቃል፤ እንደሰማሁት በግ ሰርቆ ጫካ ይወስድና ቆዳውን ገፎ ለመሸጥ ወደገበያ ሲሄድ ተይዞ ነው፤ የሁዳዴ ጾም ስለነበረ ሥጋውን ለማይጾሙ አውሬዎች ጫካ ውስጥ ጥሎ ነው! አሁን ይህ ሰውዬ የሚጾመው ሲፈሰክ ደህና አድርጎ በናፍቆት ለመብላት ካልሆነ ለሌላ ለምንድን ነው ሊባል ነው?

ሥራም ቢሆን ለመብል ነው፤ ከመኝታው ሲነሣ ጀምሮ እስኪተኛ ቢበላ ደስታውን አይችለውም፤ለገና፣ ለፋሲካ፣ ለእንቁጣጣሽና ለመስቀል ለገናና ለፋሲካ፣ ለእንቁጣጣሽና ለመስቀልም ከሌሊት ጀምሮ ከአንዱ ቤት አንዱ ቤት እየተዘዋወሩ በመብላት ቀኑ ያልፍ የለም እንዴ! በእውነት አበሻ መብላት የሚወደውን ያህል ማብላትም ይወዳል፤ ስሞት! ስቀበር! አፈር ስገባ! … ወዘተ. እየተባባለ የጠገበውን ሰው በቁንጣን እንዲሰቃይ ማድረግ የአበሻ ልዩ የፍቅር መግለጫ ነው! መጎራረስም አለ፤ ፍቅርና ጉርሻ ሲያስጨንቅ ነው እየተባለ ፍቅርና ሆድን ያያይዛል፤ አነጋገሩ አበሻ ለመብላት ያለውን እንጂ ፍቅርን አይገልጽም፤ ማሰጨነቅንና ፍቅርን ምን አገናኛቸው! አበሻ ሌላም ተረት አለው፤ የወለዱትን ካልሳሙለትና የሠሩትን ካልበሉለት ደስ አይለውም ይባላል፤ የልጅ ፍቅር ከምግብ ፍቅር ጋር ተስተካክሎ የቀረበ ይመስላል፤ ደሞም ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል፤ ይላል፤ ጉድ ነው! ሲሞትም ተከተሉኝ የሚል ይመስላል!! ለነገሩማ ፍቅርምኮ አበሻ ዘንድ ምግብ ነው፤ ሆዴ! አንጀቴ! ጎንደሬዎች ሲያሳምሩት ደግሞ ራቴዋ! ይሉታል።

ዛሬ ዛሬ አበሻ ከማብላት ይልቅ ማጠጣት ይወዳል፤ እስቲ ሰዎች ሰብሰብ ብለው በሚጠጡበት ቦታ ብቅ በሉ፤ ያቺን የፈረደባትን ጉበት ለማቃጠል በአቦ፣ በሥላሴ የማይል የለም፤ ቸገረኝ ብሎ ገንዘብ የሚጠይቅ አይምጣ እንጂ ለማብላትና ለማጠጣት፣ ለአንድ ጥሪኝ ፈሳሽ አበሻ ቸር ነው፤ በላኤ ሰብስ በማርያም ስም አንድ ጥሪኝ ውሀ ሰጥቶ አይደለም እንዴ የበላው ሰው ሁሉ የተሰረዘለት? አበሻ በሆድ አይጨክንም።

ለአበሻ ምግብ ክቡር ነው፤ ስለዚህም ምንም ነገር ሲበላ ተቀምጦ ነው፤ ፈረንጅ ቂሉ በየመንገዱ እንደመጋዣ ያመነዥካል፤ በየመንገዱ ማመንዠክ ምግቡን ማዋረድ ነው፤ ከዚያም በላይ ቆመው ሲበሉ ወደጉልበት ይወርዳል ይላል፤ ለአበሻ ጨጉዋራና ጉልበት በቀጥታ የተገናኙ ናቸው፤ ሳይንሱ የሚለው ሌላ ቢሆንም አበሻ አበሻ ምን ቸገረው?

ለመሆኑ ከሆድ ጋር ያልተያያዘ ነገር አበሻ ምን አለው? ነገርን በሆድህ ያዘው ምን ማለት ነው? ነገርን ማብላላት የማሰብ ምትክ መሆኑ ነው፤ ልጆች ሆነን አይጥ አበላሁት እንል ነበር፤ አሸነፍሁት ለማለት ነው፤ ዛሬም ቢሆን ቁማርተኞች በላሁ-ተበላሁ ይባላሉ፤ አይጥ ከማብላት ገንዘብ ወደማብላት ተለወጠ እንጂ ከሆድ አልወጣም፤

አበሻ በሆዱ የማይዘው ምን ነገር አለ? ፍቅርም፣ ጥላቻም በሆድ ነው፤ ቂምም በሆድ ነው፤ ምኞትም ፍላጎትም በሆድ ነው፤ ተስፋም በሆድ ነው፤ መጥኔ ይስጠው የአበሻ ሆድ! ሁሉን ከተናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል፤ አይ የአበሻ ሆድ! የነገር ስልቻ ከመሆኑ በላይ ነገር አልቆበት ‹‹ነገር እንዳይርበው(!)›› ጥንቃቄ ማድረግ አለበት! የአበሻ ሆድ እህል ቢያጣና ከእህል ባዶ ቢሆንም ከነገር ባዶ መሆን የለበትም፤ እህል ቢጠፋም ነገር አይጥፋ!

የአበሻና የሆድ ነገር በዚህ አያበቃም፤ አበሻ ሲያመው ቡዳ በልቶት ነው፤ ቆንጆውን ሁሉ ቡዳ ይበላዋል፤ ልብ በሉ ለአበሻ በዓይንም ይበላል ማለት ነው! አንዳንዴም ሲያመው መድኃኒቱ ምግብ ነው፤ ለሆድ ቁርጠት ብላበት፤ አበሻ ሲሞትም ለቅሶው ሁሉ ስለሆድ ነው፤ ‹‹የኔ ሆድ፣ ሆዴ እንዴት ይቻለው! ፋሲካን የት ልፈስክ?››

እስከናካቴው ‹‹ሆድ›› የሚባል ቃል ከአበሻ ቋንቋ ፈጽሞ ቢሰረዝ ቋንቋው ብቻ ሳይሆን አበሻም ጉድ ይፈላበታል፤ አእምሮ፣ ኅሊና የሚባሉትን ቃላት አበሻ አያውቃቸውም፤ ተግባራቸውንም ሁሉ ለሆድ ሰጥቶታል።

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>