ከምኒልክ ሳልሳዊ
ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የግለሰቦች ጥርቅም እስከሆኑ ድረስ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ጽንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ተላላኪ፣ ኒዮ ሌንራል፣…….የሚባሉት መለጠፊያዎች እየተሰጧቸው አሳራቸውን የሚበሉት ‹‹ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ናቸው፡፡
ምንም ያህል ልዩነት ቢኖረው የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ህዝቦች ይልቅ የሚያመሳስሉን፣ የምንጋራቸው በርካታ እሴቶች አሉን፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያውይነታችን (ዜግነታች) የጋራችን ነው፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ ተብሎ በጅምላ ዜግነት ሊሰጠው አይችልም፡፡ አንድ ሰው ኢትዮጵያዊ ለመሆን መደራጀት አይጠበቅበትም፡፡
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰብ ኦሮምኛ ተናጋሪዎችን ‹‹ኦሮሞ››፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ግለሰብ አማርኛ ተናጋሪዎች ‹‹አማራ››፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰብ ሶማልኛ ተናጋሪዎን ‹‹ሶማሊ››…….እያሉ ነው ኢትዮጵያውያንን ‹‹ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› በሚል አዲስ ማምነት የሚደረድሩን፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ የሚባለው ከግለሰቦች እንጅ ከምንም የመጣ አይደለም፡፡ የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር ካለበት መጀመሪያ መቅደም የሚገባው የስሪታቸው የግለሰቡ መብት ነው፡፡
‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ትግሬ….› እየተባሉ የተቦደኑት ህዝቦች አንድ አይነት አይደሉም፡፡ እንዲያውም ኦሮምኛ ተናጋሪው ‹‹ኦሮሞ›› ከሚባለው ውጭ ከአማርኛ ተናጋሪው ጋር የሚጋራው በርካታ ማንነቶች ይኖሩታል፡፡ አማርኛ ተናጋሪው ‹‹አማራ›› ከተባለው ይልቅ ከኦሮምኛ ተናጋሪው ጋር የሚያመሳስሉት በርካታ ማንነቶች ይኖሩታል፡፡ ለአብነት ያህል ትግርኛ፣ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማሊኛ፣ ….ተናጋሪው ህዝብ ከቋንቋውም በላይ አንዱ የሌላውን ድንበር ተሸግሮ ከሌላኛው ቋንቋ ተናጋሪ ጋር በእምነት፣ በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች ገመዶች ይገናኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአንድ ብሄር ሰዎች አይደሉም፡፡ የሙስሊሙ እንቅስቃሴ እንዲህ እስካሁን በጥንካሬ የዘለቀው በድንበር ተሸጋሪው ማንነቱ እንጅ በጠባብ ‹‹የብሄር›› ማንነት ታጥሮ አይደለም፡፡ ኦርቶዶክሶቹ፣ ፕሮቴስታንቶቹ፣ ካቶሊኮቹ በ‹‹ብሄር›› የታጠሩ አይደሉም፡፡
የአንድ ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› የእምነት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ…መብቱ በግለሰብ ደረጃ ካልተጠበቀለት በስተቀር የ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› መብት ሊጠበቅ አይችልም፡፡ ችግሩ የ‹‹ብሄርና›› ሌሎች ማንነቶችን የሚጠቀሙ የፖለቲካ ቡድኖች ከግለሰብ ማንነት ይልቅ ጥቅል ማንነትን የሚያስቀድሙት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ መሆኑ ነው፡፡ በ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ሶማሊ…….›› ስም በጅምላ ከመነገድ ያለፈ ስለ እያንዳንዱ ህዝብ አያስጨንቀቃቸውም፡፡ 30 ወይንም 40 ሚሊዮን የአንድ ‹‹ብሄር›› ህዝብ በአንድ ጉዳይ ሊከፋ አይችልም፡፡ ቢያንስ ከገዥዎች ጋር ሆኖ የሚጠቀም አይጠፋም፡፡
ከፊሉን በእምነቱ፣ ከፊሉን በኢኮኖሚው፣ ከፊሉን እናከብርልሃለን በሚሉት ቋንቋው፣ ከፊሉን በነጻነቱ…. እያሉ ግን ሁሉንም ይጨቁኑታል፡፡ ሁሉንም ይጎዱታል፡፡ መስፈርቱ በብሄር ሳይሆን በግለሰብ ቢሆን ግን የሚድበሰበስ ነገር አይኖርም፡፡ ሁሉም የግለሰብ መብቶች እስከተከበሩ ድረስ የአገሪቱ ህዝብ መብት ይከበራል፡፡ የግለሰብ መብት ካልተከበረ ግን የማንም መብት ሊከበር አይችልም፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የግለሰቦች ጥርቅም እስከሆኑ ድረስ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ጽንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ተላላኪ፣ ኒዮ ሌንራል፣…….የሚባሉት መለጠፊያዎች እየተሰጧቸው አሳራቸውን የሚበሉት ‹‹ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ናቸው፡፡
የግለሰብ መብት ካልተከበረ የማንም መብት ሊከበር አይችልም የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው
የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ (ተመስገን ደሳለኝ)
(ተመስገን ደሳለኝ)
…አውሮፕላኑ ቅዳሜ ጠዋት ሶስት ሰዓት ላይ ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ደርሶ ከተርሚናሉ ስወጣ፣ ተጠራጥሬ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ የድሬ የጠዋት ፀሐይ ከተለመደው ንዳዷ ጋር የአዲስ አበባን የቀትር መራራ ፀሀይን ታስከነዳለች፤ እናም አጥበርባሪ ጨረሯን ያለምህረት ስትለቅብኝ፣ ጓደኛዬ መኪና ይዞ እቦታው እስኪደርስ መጠበቁ በገዛ ፍቃድ መለብለብ ስለመሰለኝ፣ በቀጥታ ከተደረደሩት ታክሲዎች አንዱን ይዤ ወደ ከዚራ አመራሁ፤ ድሬ የሄድኩት በዋናነት ከማህበራዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምክንያት በመሆኑ ሊቀበለኝ የተዘጋጀውን
ጓደኛዬን ደውዬ ከማውቃቸው የአንዱን ሆቴል ስም ጠቅሼ እዚያ እንድንገናኝ ነገርኩት፡፡
የሆቴሉ ፍተሻ ከወትሮው ጠንከር፣ ጠጠር ያለ በመሆኑ ትዕግስትን ይፈትናል፡፡ እንዲህም ሆኖ ወደ ውስጥ ስንዘልቅ ማረፊያ ክፍሎች በሙሉ መያዛቸው ተነግሮን ቀኝ ኋላ ለመዞር ተገደድን፤ ይሄኔም ነው የጓደኛዬ ፊት ልውጥውጥ ሲል ያስተዋልኩት፤ ጭንቅላቴን በማነቃነቅ በምልክት ምን እንደተፈጠረ ጠየኩት፤ ለአፍታ አመንትቶ ከፊት ለፊታችን በግምት አስር ሜትር ርቀት ላይ ወደቆሙ ሁለት ሰዎች ጠቆመኝ፤ ልብ ብዬ አየኋቸው፤ ሁለቱንም ከዚህ ቀደም አይቻቸው አላውቅም፤ ደግሞም በዙሪያችን ከሚርመሰመሱ ሰዎች የተለየ ምንም አይነት ሁኔታ ላስተውልባቸው አልቻልኩም፤ እናም ወደ ጓደኛዬ ዞሬ በግርታ ግንባሬን ቋጥሬ ጥያቄ በተሞላ ዓይን አተኮርኩበት፤ ጓደኛዬም ከሁኔታዬ እንዳልገባኝ ተረድቶ ከሹክሹክታም ዝቅ ባለ ድምፅ ‹‹ደህንነቶች ናቸው፣ እየተከታተሉህ ነው›› አለኝ፤ ቢሆኑስ ታዲያ!? በግዴለሽነት ትከሻዬን እየሰበቅሁ ‹‹ለራሳቸው ጉዳይ መጥተው ሊሆን ይችላል›› ብዬው ወደ ሌላ ሆቴል አቀናን፤ እዛም የተለቀቀ ክፍል አለመኖሩ ተነግሮን ፊታችንን ከእንግዳ መቀበያው ‹‹ዴስክ›› ዘወር ስናደርግ እነዛ ‹ደህንንቶች› ቆመው ተመለከትኳቸው፡፡ አሁን ከልምዴ በመነሳት ክትትል ሊሆን እንደሚችል ለማመን በተቃረበ ጥርጣሬ ተውጬ ሌላ ሆቴል ደርሰን ክፍል ጠየቅን፤ በለስ ቀናንና የሆቴሉን መስፈርት አሟልቼ ሳበቃ ጓደኛዬን ቡና ቤቱ ውስጥ እንዲጠብቀኝ አድርጌ፣ ክፍሉን ከተረከብኩ በኋላ ሻንጣዬን አስቀምጬ፣ ገላዬን ተለቃልቄ፣ ልብስ ቀይሬ ደረጃውን መውረድ እንደጀመርኩ ከሰዎቹ ጋር ፊት ለፊት ተገጣጠምኩ፡፡ የጭንቅላት ሰላምታ ሰጥቼ አለፍኳቸው፤ ምላሽ የለም፤ ፈገግ አልኩ፡፡ ከወዲሁ የሰሞኑ ምስራቅ ኢትዮጵያ አክራሞቴ ምን ሊመስል እንደሚችል አሰብኩና፣ በልጅነቴ ከሰፈር ማቲዎች ጋር የምንጫወተውን የአኩኩሉ ድብብቆሽ አስታውሼ፣ በድጋሚ ለራሴ ፈገግኩ፡፡
ገና ከአዲስ አበባ ስነሳ ማህበራዊ ጉዳዬን ስጨርስ የድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሶማሌ ክልልን ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳት ለማዳመጥ ለተጨማሪ ስድስት ቀናት የሚያቆይ ፕሮግራም አስቀድሜ ይዤ ነበር፤ ከአራት ቀን ቆይታ በኋላም ቀጥታ ወደዚሁ ስራዬ ነበር የገባሁት፡፡ ለጉዳዩ ትኩረት እንድሰጥ ያደረገኝ በቅርቡ ሐረር ከተማ ውስጥ በተከበረው ‹‹የዓለም የመቻቻል ቀን›› ላይ በክልሉ የተንሰራፋው መድልዎና የሐብሊ ተፅዕኖ ተደብቆ፣ ፍትሐዊ አስተዳደር የሰፈነ ለማስመሰል መሞከሩ፤ እንዲሁም ህዳር 29 ቀን በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ (ጅግጅጋ) የሚከበረውን ‹ስምንተኛው የብሔር ብሔረሰብ ቀን›ን አስመልክቶ አካባቢውን ከዋጠው ስጋት በተቃራኒው መንግስት እየነዛ ያለው የሀሰት ፕሮፓጋንዳን ከተጨባጩ እውነታ ጋር ለመፈተሽ ፍላጎት አድሮብኝ ነው፡፡
ፊታችሁን ወደ ምስራቅ…
ምስራቅ ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ የ3ሺ ዓመት ታሪክ ዕኩሌታውን ሰላምና መረጋጋት የተሳነው ከመሆኑም በላይ፣ ለማዕከላዊ መንግስት የስጋት ምንጭ ሆኖ ነው ዛሬ ድረስ የቀጠለው፡፡ ከአቶማን ተርኪሽ ወታደሮች እስከ አል-ሸባብ ሰርጎ ገቦች ድረስ መተላለፊያ ‹‹ኮሪደር›› ሆኖ አገልግሏል፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ ሶማሊያውያን የዘር ግንድ ከጐረቤት ሀገራት ሶማሊያና ጅቡቲ ጋር የሚተሳሰር መሆኑና የሃይማኖትና የኢኮኖሚ ምንጭም ተመሳሳይነት አካባቢውን በበቂ ደረጃ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንዳደረገው የፖለቲካ ተንታኞች ያምናሉ፤ ነዋሪዎቹ በቀላሉ ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው እየተዘዋወሩ የሚኖሩ መሆናቸውም ሌላው ችግር እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ ቅኝ ገዥዎቹ የአውሮፓ ሀገራት በበኩላቸው አካባቢውን ‹ፍሬንች ሶማሌ ላንድ›፣ ‹ብሪታኒያ ሶማሌ ላንድ› እና ‹ኢታሊያ ሶማሌ ላንድ› በሚል ከፋፍለው ማስተዳደራቸው፣ ከሶማሊያ ነፃነትም በኋላ የሞቃዲሾን ቤተ-መንግስት የተቆጣጠሩ ገዢዎች ‹ታላቋን ሶማሊያ እንመሰርታለን› በሚል ቀቢፀ ተስፋ ከአንድም ሶስቴ የኢትዮጵያን ወሰን ተሻግረው የኃይል ወረራ መፈፀማቸው የአካባቢውን ውጥረት ይበልጥ አባብሶት ነበር፤ ከዚያም ባሻገር የዚያድባሬ ሶማሊያ መፈራረስም የቀጠናውን ሠላምና ፀጥታ ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎታል፡፡
በዚህ ሁሉ ከባቢያዊ ውጥረት እየታመሰ እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ በአንድነት በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ስር ሲተዳደር የቆየው የምስራቁ የሀገራችን ክፍል፣ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ ባነበረው ‹‹ፌደራሊዝም›› በሶስት ሊከፈል ችሏል፤ ‹‹የሶማሌ እና ሐረር ክልል›› እንዲሁም ‹‹የድሬዳዋ አስተዳደር›› በሚል፡፡ ይህ ሁኔታም ከዚህ ቀደም በውጭ ተፅዕኖ ይተራመስ የነበረውን ‹ጂኦ-ፖለቲክስ› ብሔር ተኮር ለሆነ ተጨማሪ አዲስ ቁርቁስ አጋለጠው፡፡ በአናቱም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ኦጋዴን፣ ጎዴ፣ ደጋሀቡር፣ ቀለፎን የመሳሰሉ ከተሞች ክልሉን ‹እንገነጥላለን› የሚሉት የኦጋዴን ብሔራዊ ግንባር ታጣቂዎች መርመስመሻ መሆናቸው አካባቢውን የስጋት ቀጠና አድርጎታል፤ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ድሬዳዋ ላይ ያነጋገርኳቸውና በሽግግር መንግስቱ ወቅት የአስተዳደሩ አባል የነበሩ አቶ ኡስማን (ለዚህ ፅሁፍ ስማቸው የተቀየረ) ‹‹የዚህ ሁሉ ተጠያቂ ለጣልቃ ገብነቱ ያልተመቹትን የአካባቢው ልሂቃን ‹ለወረራ የመጡ የዚያድባሬ መኮንኖች› እያለ አሸማቅቆ ከፖለቲካው ገፍቶ በማስወጣት ክልሉን ዛሬ ላለው ደካማ አስተዳደር የዳረገው ኢህአዴግ ነው›› ይላሉ፡፡ በግልባጩ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ካሳ ተክለብርሃን የተገፉት ሰዎች ኢትዮጵያዊ አለመሆናቸውን ለ‹‹ዘመን›› መፅሄት የገለፀው እንዲህ በማለት ነበር፡-
‹‹ሶማሊያ የፈራረሰበት ወቅት ስለነበር በጣም ትላልቅ የሶማሊያ ተፈናቃዮች የሰፈሩባቸው ካምፖች ነበሩ፡፡ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ አንዱ የስደተኞች ካምፕ የነበረባት አገር ነበረች፡፡ በተለይ አርትሼክ አካባቢና ሌሎች አካባቢዎችም ትልልቅ ካምፖች ነበሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የመጡ የዚያኛው ሶማሊያ መኮንኖች፣ ሲቪል ሰራተኞች ኢንጂነሮችና ፓይለቶች ነበሩ፤ በአካል ያገኘናቸው የምናውቃቸው እነዚህ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ጋር የሚለያቸው ነገር ስላልነበረ በአብዛኛው በስደተኛነት ከመጡ በኋላ የአካባቢውን የፖለቲካ ስልጣኑንም ያደራጁት እነሱ ነበሩ፡፡ አንዱ ትዝ የሚለኝ ይሄ ነው፡፡ ይሄንን የኢህአዴግ ሰራዊትና ከላይ የሄደው የኢትዮጵያ ሰራዊት ሊለየው አይችልም ብቻ ሳይሆን ያ የመጣውን እንዳለ የሚያቅፍ ሁኔታ ነው የነበረው በአካባቢው፡፡ ስለዚህ ለረጅም ጊዜ ያ ኃይል ነው እንግዲህ አዲስ በተፈጠረው አጋጣሚ የታላቋ ሶማሊያን አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሶማሊያ ላይ ለመዝራት ትልቅ ጥረት ያደረገው››
ይህ ክርክር በራሱ ኢህአዴግ ‹‹ፊታችሁን ወደተረጋጋችው ምስራቅ ኢትዮጵያ (ሶማሊ ክልል) መልሱ›› ያለበት አውድ የተለመደው የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ እንጂ አካባቢው የጦርነት ወረዳን ያህል የሚያሰጋ መሆኑን ያመላክታል ፡፡ እናም ከአርቲስቶች እና ጋዜጠኞች እስከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፊት-አውራሪነት የተካሄደው የጉብኝት ፕሮግራም፣ መንግስት ምንም እንኳ የህዝቦችን አንድነት ‹የማጥበቅ ዕቅድ› የሚል የዳቦ ስም ቢሰጠውም፣ ‹ሶማሌ ክልል ፍፁም ሰላም ነው› የሚል የሀሰት ፕሮፓጋንዳን ለመንዛት መሆኑን ለመረዳት በአካባቢው ያለውን የፀጥታ አጠባበቅ ብቻ መመልከቱ በቂ ይመስለኛል፡፡
የቦምባስ ዕገታ
ዘንድሮ ለስምንተኛ ጊዜ ‹‹ሕገ-መንግስታችን ለህዳሴያችን›› በሚል መሪ ቃል የሚከበረው ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች ቀን›› በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ በመሆኑ በአካባቢው ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት ለመለካት ረቡዕ ህዳር 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ወፍ ጭጭ ሳይል ነበር ድሬዳዋን ለቅቄ ወደ ሐረር ጉዞዬን የተያያዝኩት፡፡ ይህንን ሰዓት የመረጥኩት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዲስ አበባ ላይ እንኳ ጋብ እየለ የመጣውን የደህንነት ሰራተኞች ክትትል ድሬዳዋ ላይ በየደረስኩበት ሲያንዣብብብኝ፣ በማስተዋሌ፣ ምናልባት ከዕይታ ውጪ መንቀሳቀስ ብችል በሚል እሳቤ ነበር፡፡ መኪናው ከአንድ ቀን በፊት የተከራየሁትና ድሬ ውስጥ ያልተጠቀምኩበት በመሆኑ፣ በስጋት የሚንጠውን የደንገጎ አቀበትም ሆነ ጥንታዊቷን ሐረር ከተማ አቋርጠን እስክናልፍ አንዳች ችግር አላጋጠመንም፡፡ ይሁንና ከሐረር በግምት 80 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በሶማሊያ ክልል የምትገኘው ቦምባስ ከተማ ደርሰን ጥቂት እንደተጓዝን፣ መኪናውን ዳር አስይዞ እንዲያቆም አንድ የትራፊክ ፖሊስ ለሹፌሩ የእጅ ምልክት አሳየው፤ ይሄኔም ነው ድሬ ላይ እንደ ተሰወርኩባቸው እርግጠኛ ሆኜ በልቤ ከሳቅኩባቸው ሁለቱ ሰላዮቼ ጋር ፊት ለፊት የተፋጠጥነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ስሜን ጠርተው አነጋገሩኝ፤ እኔም ከምንም ነገር በፊት መታወቂያቸውን እንዲያሳዩኝ ጠየቅኩ፤ ሳያቅማሙ አሳዩኝ፤ ወዲያውኑም የአፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛ እንዳልሆነ የአነጋገር ዘዬው በግልፅ የሚያስታውቀው አንደኛው የደህንነት አባል፣ ከዚህ በላይ ጉዞውን መቀጠል እንደማልችልና በቀጥታ ወደ ድሬዳዋ መመለሱ እንደሚጠቅመኝ ሊነግረኝ ሞከረ፡፡ ከመገረሜ ብዛት ንግግሩን ለመረዳት ጥቂት ሰከንዶች ፈጅተውብኝ ነበር፡፡ መቼም ይህ ሰው ቀልደኛ መሆን አለበት! አለዛ በገዛ ሀገሬ የት ድረስ መሄድ ወይንም የት ቦታ ጉዞዬን መግታት እንዳለብኝ ሊወስንልኝ ባልደፈረ ነበር፤ ሆኖም ንዴቴን ዋጥ አድርጌ ምን ማለት እንደፈለገ እንዲያስረዳኝ በትህትና ጠየኩት… ይኼኔ ጓደኛው ጣልቃ ገባና ወደ ጅግጅጋ ለመሄድ ማሰቤን እንደደረሱበትና ወደ ከተማው እንድገባ እንደማይፈቅዱልኝ ቆጣና ኮስተር ብሎ አሳወቀኝ፡፡ እኔም ፈርጠም ብዬ እዚህ ድረስ መጥቼ ጅጅጋ ሳልደርስ እንደማልመለስ ቁርጡን ነገርኳቸው፡፡ ቃለ-ምልልሱ እየከረረ ሲሄድ ማስፈራራቱን ወደ ሹፌሩ አዞሩትና በብርቱ ያዋክቡት ያዙ፤ ይህ ድርጊታቸው ያልጠበቅኩት በመሆኑና የሹፌሩንም ምላሽ አለማወቄ መጠነኛ ድንጋጤ አጫረብኝ፡፡ እንደገመትኩትም ሁኔታውን በፍርሃት ተውጦ ይከታተል የነበረው ሹፌር ትንሽ እንኳ ሳያንገራግር መኪናውን ቆስቁሶ ወደ ሐረር አዞረው፡፡
‹‹ምን ሆነሃል?›› አልኩት በንዴት ጮኽ ብዬ፡፡
‹‹ወንድሜ እኔ ቤተሰብ የማስተዳድር ሰው ነኝ፡፡››
ፈይሳ ጃታ… ብሄራዊ ውርደትን ያልተቀበለ ጀግና
ተራኪ – ተስፋ ጥ ዑመ-ልሣን
ጸሃፊ – ዳዊት ከበደ ወየሳ
ሰሞኑን ስለብሄራዊ ውርደት ብዙ ይባላል። ብዙ ስለሚባለው ነገር መልሼ ከማውራት ይልቅ፤ አንድ ሰው ላስተዋውቃቹሁ። ፈይሳ ጃታ ይባላሉ። ሀረር ውስጥ ለብዙ አመታት የኖሩ ናቸው። ጣልያን የጫነብንን ብሄራዊ ውርደት ያልተቀበሉ፤ የሱማሌ ወረራን ተከትሎ የመጣውን ሽንፈት፤ “እምቢኝ” ያሉ ጀግና ነበሩ።
የሀረሩን ፈይሳ ጃታ ያለ ምክንያት አላነሳሁዋቸውም። “ብሄራዊ ውርደት” ብለን በምንጠራቸው ዘመኖች፤ እንደሳቸው አይነት ያለተዘመረላቸውና ምንም ያልተባለላቸው ሰዎች መኖራቸውን ለማስታወስ፤ ከዚያም አልፎ ሁሌ ብሄራዊ ውርደትን ያሸነፉ፤ ጀግኖች መኖራቸውን ማውሳት አስፈላጊ ስለሆነ ነው።
ለነገሩ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በበርካታ የታሪክ ምዕራፎች ብሄራዊ ውርደትን አስተናግደናል። አንደኛውና ሁላችንም የምናውቀው በጣልያን ወረራ ወቅት፤ በራሳችን ባንዳዎች የተፈጸመብን ውርደት ነው። ሁለተኛውን ውርደት የተከናነብነው በቀይ ሽብር ዘመን ወንድም ወንድሙን ገድሎ የፎከረበት ወቅት ሲሆን፤ ሶስተኛው ብሄራዊ ውርደት ደግሞ፤ አሁን በአገራችን ያለው ስርአት ያከናነበን የቅሌት ቡሉኮ ነው። በመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኩት ስለያንዳንዱ ዘመን ብሄራዊ ውርደት ለመተንተን አይደለም – የዛሬ መነሻዬ። ይልቁንም በእንደዚህ አይነት የውርደት ዘመናት አንገታቸውን ቀና አድርገው፤ ሰንደቅ አላማችንን ከፍ ስላደረጉ አንድ ግለሰብ ጥቂት ለማለት ፈልጌ ነው።
እንደገና ላስተዋውቃቹህ። ፈይሳ ጃታ ይባላሉ። ፊታቸው ሁሌም ሙሉ ጺም ያለው፣ ቀጭን፣ ቁመታም፣ ሁሌ ቁምጣ የሚያደርጉ ቆፍጣና ሰው ናቸው። በጣልያን ዘመን ገና ወጣት ልጅ ነበሩ። የተወለዱት ሰላሌ አውራጃ ሲሆን፤ ኩሩ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ናቸው። በወቅቱ የአርበኝነት ዘመን የአካባቢው ወጣቶች ይሰለፉበት በነበረው የጃጋማ ኬሎ ጦር ስር ሆነው ለአገራቸው ክብር ከቆሙት መካከል አንዱ ነበሩ።
በዚህ የአርበኝነት ዘመን እሳቸው የነበሩበት ጦር፤ ጣልያንን ለመምታት እና ግዳጁን ለመወጣት ወደ ሰላሌ ያመራል። እዚያ ሲደርሱ ግን፤ የሰላሌ አካባቢ ዋና ሃላፊ ወይም ባንዳ ሆነው ለጣልያን አገልግሎት ይሰጡ የነበሩት የእናታቸው ወንድም፤ አጎታቸው መሆኑን ይሰማሉ። ቀጥሎም ወደ ከተማ ገብተው ይህንኑ በአይናቸው አይተው ያረጋግጣሉ። የአካባቢው ኦሮሞዎች ከጣልያን ጦር ባልተናነሰ፤ የፈይሳ አጎት ይፈጽሙባቸው የነበረው በደል ከባድ መሆኑን ተመለከቱ። በሁኔታው አዝነው፤ ከአጎታቸው ጋር ጦርነት ላለመግጠም ብለው፤ እንዳዘኑ ያቺን መንደር ለቀው ወጡና በሌላ መስመር በአርበኝነት አገለገሉ።
ጣልያን ድል ከተመታ በኋላ አርበኞች ወደ አገራቸው ሲመለሱ፤ አጎታቸው የባንዳነት ቡሽ ኮፍያቸውን አውልቀው፤ ጃንሆይ የሰጧቸውን አዲስ የስልጣን ካባ ደርበው… አሁንም ከድል በኋላ ህዝቡን ሲያተራምሱት ተመለከቱ። በጣልያን ጊዜ የነበረው ብሄራዊ ውርደት ሳያንስ፤ ከድል በኋላም ተጨማሪ ውርደትን ለመሸከም ትከሻቸው አልቻለም፤ ከህሊናቸው ጋር ሙግት ገጠሙ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ አንድ ቀን፤ አጎታቸው እንደተለመደው በቅሎ ላይ ሆነው ገበያተኛውን ሲያምሱት፤ የሚታሰረውን ሲያስሩና ሲያሳስሩ አይተው አዘኑ። በዚህን ጊዜ “ሁለት ጊዜ አንዋረድም! ሞትም አንዴ ነው!” ብለው፤ የራሳቸውን አጎት በጥይት መትተው ገደሏቸው።
ከዚህ በኋላ ፈይሳ ጃታ ሰላሌን ለመጨረሻ ጊዜ ለቀው ወጡ። የሰላሌው የታሪክ ምዕራፍ ተዘጋና ሌላኛው የታሪካቸው ምዕራፍ ሀረር እና ጅጅጋ ላይ ተጀመረ። በኋላ ላይ ብሄራዊ እርቀ ሰላም ለማውረድ ሲባል መንግስት የምህረት አዋጅ አወጀ። “ነፍስ ያጠፋህ በሙሉ፤ እጅህን ሰጥተህ ታርቀህ በሰላም ኑር።” ተባለ። ፈይሳ ጃታም አዋጁን ተከትለው፤ ምህረት ተደርጎላቸው እንደማንኛውም ሰው ከጅጅጋ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው ፋፈም ላይ መሬት ተመርተው መኖር ጀመሩ።
ከጊዜ በኋላ ግን… ፈይሳ ጃታ የተመሩበት መሬትት ውስጥ ለውስጥ የፋፈም ወንዝ ይሄድበት ኖሮ፤ ሚስጥሩ ሲታወቅ የወቅቱ ባለስልጣናት ይዞታው ላይ አይናቸውን ጣሉ። ከነዚያ ባለስልጣናት መካከል አሁን ስማቸውን መጥቀስ የማልፈልጋቸው፤ ፖሊስን ማዘዝ የሚችሉ ጄነራል ነበሩ። ጄነራሉ ፈይሳ ጃታ መሬቱን እንዲለቁ ቢያስጠይቋቸው “አሻፈረኝ” አሉ። ሽማግሌዎች ቢላኩም፤ “ሬሳዬን ተሻግሮ ይውሰድ” ብለው መለሷቸው። በኋላ ላይ እንዲያዙ ፖሊስ ተላከ።
ፈይሳ ጃታም፤ “በህግ አምላክ፤ ይዞታዬ ውስጥ አትግቡ!” ብለው አስጠነቀቁ። ፖሊሶቹ ግን የሚሰሙ አልሆነም። በመጨረሻ ሁለቱን ፖሊሶች ገደሉ። ፈይሳ ጃታ ፖሊሶቹን ገድለው፤ ለተወሰነ ግዜ ከፖሊስ ጋር ድብብቆሽ ይጫወቱ ጀመር። የአጋጣሚ ነገር ሆነና፤ በ1953 ዓ.ም. ጄነራሉ በጃንሆይ ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በማድረግ ጥፋት ተወንጅለው ተገደሉ። ከጄነራሉ ሞት በኋላ… ለፈይሳ ጃታ ለሁለተኛ ጊዜ ምህረት ተደረገላቸው።
በዚህ መሃል ያለውን ታሪክ እንለፈውና ወደ ሱማሊያ ወረራ ዘመን ልውሰዳቹህ። በየካቲት ወር 1969 ዓ.ም. የሱማሊያ ወረራ ወቅት፤ ሱማሌዎች ጎዴ፣ ቀላፎ፣ ቀብሪዳሃር፣ ደገሃቡር፣ ዋርዴር የሚባሉት ከተሞችን ያዙ። ሃምሌ ላይ ደግሞ ጅጅጋን ለመያዝ ትልቅ ጦርነት ተከፈተ። በወቅቱ ፈይሳ ጃታ እድሜያቸው ወደ እርጅናው ተጠግቶ ነበር። እንደዚያም ሆኖ ህዝቡን ለማስተባበር ጉልበታቸው አልደከመም፤ አንደበታቸው አልታሰረም።
ሃምሌ 8 ቀን፣ “ከሱማሌ ጋር ተባብራችኋል” የተባሉ ሰዎች ተገደሉና በጅጅጋ ትልቅ ፍጅት ሆነ። በሳምንቱ የሱማሌ ጦር እየገፋ ሲመጣ፤ ህዝቡ ተስፋውን በኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት ላይ ጥሎ ነበር። ሆኖም የጅጅጋ ከተማ ከመያዟ አንድ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ከየወረዳው አፈግፍጎ የመጣው የጦር ሰራዊት አባላት፤ ለሊቱን ቤተሰባቸውን ይዘው አካባቢውን ለቀው፤ ጉዟቸውን በመኪና እና በእግር ወደ ሃረር አደረጉ።
በንጋታው ጠዋት የጅጅጋ ህዝብ ከእንቅልፉ ሲነሳ፤ ከተማው ዙሪያውን በሱማሌ ታንክ ተከቦ ተመለከተ። በየጋራው ላይ በርካታ የሱማሌ ታንክ አፈ ሙዙን ወደ ከተማው አድርጎ ቆሟል። የጅጅጋ ህዝብ በሁኔታው ተደናገረ። ለሊቱን ሲከናወን ስለነበረው ሁኔታ ብዙም የሚያውቀው ነገር አልነበረም። የኢትዮጵያ ጦር አካባቢውን ለቅቆ ስለመሄዱም የሚያውቁት ነገር አልነበረም። ከነዋሪው በቀር ጅጅጋ ባዶዋን ናት። ማንም የሚጠብቃት ሰው አልነበረም።
የሱማሌ ታንከኛ ጦርም በኢትዮጵያ አየር ኃይል እንዳይመታ በመስጋት በቀን ወደ ከተማው ለመግባት አልደፈረም። ከአምላኳ በቀር ሌላ ጠባቂ ያልተረፈላት የጅጅጋ ከተማ እስከ ምሽት ድረስ፤ አጭር እድሜ አላት። የመንግስት ባለስልጣና እና ወታደሩ አካባቢውን ለቅቆ ወጥቷል።
ጀንበር ስትጠልቅ፤ የሱማሌ ጦር ወደ ጅጅጋ ገብቶ የነበረው እንዳልነበረ ይሆናል። በዚህ የመጨረሻ የጭንቅ ሰዓት አንዳንድ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ጦር ሰፈር ገብተው የቻሉትን ያህል መሳሪያ ወስደው ራሳቸውን ለመከላከል ታጠቁ። የኢትዮጵያ ጦር የሚለብሰውን የወታደር ልብስ ለብሰው፤ ጠመንጃቸውን አንግተው… በታንክ የመጣውን የሱማሌ ጦር ለመዋጋት ተዘጋጁ። ፈይሳ ጃታ በዚህ ሁኔታ የጅጅጋን ህዝብ የሚያስተባብሩ ብቻ ሳይሆን፤ ለዚያን ቀን ከመንግስት ያልተሾሙ፤ የጅጅጋ ህዝብ መሪ ሆኑ።
ፈይሳ ጃታ… በዚያች ቀውጢ ወቅት መሪነታቸውን አስመሰከሩ። በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከሰው ባልተናነሰ መልክ፤ ሰንደቅ አላማ ትልቅ ክብር ስለሚሰጠው “ሰንደቅ አላማ በጠላት እጅ መውደቅ የለበትም።” በማለት፤ በቅድሚያ በጅጅጋ አስረኛው ሜካናይዝድ ብርጌድ ግቢ ውስጥ የተሰቀለውን የኢትዮጵያ ባንዲራ አወረዱ። ለአገራቸው ክብር የኢትዮጵያ ወታደር ልብስ የለበሱት ፈይሳ ጃታ ይህችን ሰንደቅ አላማ ይዘው፤ ህዝቡን እያረጋጉ፣ ወጣቱን እያስተባበሩ ወደ ሃረር ጉዞ ጀመሩ። ሆኖም የሃረር መንገድ ተዘግቷል። ከሃረር አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ… ከመቶ ሺህ ህዝብ በላይ ከካራማራ ተራራ ጀርባ፤ ሀደው ከተማ ላይ ሰፍሯል።
ከሃደው ከተማ የተነሳው ህዝብ ቀስ በቀስ ወደ ሃረር መሄድ ቢጀምርም፤ የሚደረገው ጉዞ አስቸጋሪ ነበር። በየጋራው ላይ የመሸገውን የሱማሌ ጦር እየተዋጉ መሄድ ግድ ይላል። ፈይሳ ጃታ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ጦር መትረየሳቸውን ደግነው፤ እየተኮሱና እየተዋጉ ጉዞ ወደ ሀረር ሆነ። ከጅጅጋ ወደ ሃረር የነበረው ጉዞ ከ25 ቀናት በላይ ፈጀ። የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰማይ ሲያንዣብብ፤ የሱማሌ ጦር የሚገባበት ስለሚጠፋው… በዚያች አጋጣሚ ህዝቡ ከየመሸገበት እየወጣ ወደ ሃረር የሚያደርገውን ጉዞ በፍጥነት ይቀጥል ነበር።
የሃረር ህዝብ እንዳይደነግጥ ስለተሰጋ፤ ከጅጅጋ እና ከኦጋዴን ከተሞች የፈለሰው ህዝብ ወደከተማው እንዲገባ የተደረገው ለሊት ላይ ነበር። የሃረር ህዝብ ግን ቀደም ብሎ መስማቱ አልቀረም። ፈይሳ ጃታ ሃረር ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሲሄዱ፤ ልጆቻቸው የደርግ ተቃዋሚ ተብለው ቀበሌ እንዳሰራቸው ይሰማሉ። በሱማሌ ወረራ ጅጅጋ ላይ የተመለከቱት ውርደት ሳያንስ፤ ሃረር ውስጥ ልጆቻቸው መታሰራቸውን ሲሰሙ በቀጥታ ወደ ቀበሌ ሄደው አብዮት ጠባቂውና ሊቀመንበሩ ላይ አነጣጥረው፤ “ሱማሌ 45 ኪሎ ሜትር ላይ ቁጭ ብሏል። እናንተ መንደር ለመንደር ትበጠብጣላቹህ። ፍቷቸው!” ብለው ሲጮሁ ሚስታቸው፤ “አረ ይተዉ። የታሰሩት የርስዎ ብቻ አይደሉም፤ የሁሉም ልጆች ናቸው እኮ” ቢሏቸው… “አሁን የአገር ጉዳይ ነው። አገር እየተገደለች እና እየተዋረደች ልጆቻችን እንደገና በእስር አይንገላቱም። ፍቷቸው!” በማለት ሁሉም ታሳሪ እንዲፈቱ አደረጉ። (በወቅቱ ከታሰሩት ልጆቻቸው መካከል አንዳንዶቹ አውሮፓ ውስጥ ናቸው)
ፈይሳ ጃታ በዚህ አይነት ሃረር ላይ ከቆዩ በኋላ፤ አንድ ቀን ሌላ ችግር ገጠማቸው። የወታደር ልብስ፣ ጫማ ወይም መለዮ መልበስ በአዋጅ ተከልክሏል። ሆኖም ፈይሳ ጃታ አላግባብ የወታደሩን ልብስ በመልበሳቸው ታሰሩ።፡ ታስረም የሃረር ክፍለ አገር አስተዳዳሪ ከነበረው ኮሎኔል ዘለቀ በየነ ዘንድ ቀረቡ። እዚያም ቀርበው፤ የወታደሩን ልብስ መልበሳቸው ትክክል እንዳልሆነ እና ወንጀል የፈጸሙ መሆኑ ተነገራቸው።
ፈይሳ ጃታም የባለስልጣናቱን ውንጀላ ከሰሙ በኋላ፤ “ይህን የወታደር ልብስ እኔ ብቻ አይደለም የለበስኩት። ይህንን መለዮ እና ልብስ ትታችሁ የሸሻችሁት እናንተ ናቹህ፤ ይህን ልብስ በየቦታው በመተዋቹህ የሱማሌ ጦር ጭምር ለብሶታል። እኔ እናንተ ትታችሁ የሄዳችሁትን ልብስ በመልበሴ እወነጀል ይሆናል። እናንተ ደግሞ ልብስ እና መሳሪያዎችን ትታችሁ ሱማሌ እንዲወስደው በማድረጋቹህ፤ አንድ ቀን ትጠየቃላቹህ።” አሏቸው።
በዚህ ጉዳይ አንድ ሁለት እያሉ ሲከራከሩ፤ ፈይሳ ጃታ በመጨረሻ የሰንደቅ አላማውንም ጉዳይ ነገሯቸው። “እናንተ የልብሱ ጉዳይ ለምን ይገርማችኋል? ከ10ኛ ሜካናይዝድ ብርጌድ ግቢ የተዋችሁትን ሰንደቅ አላማ ጭምር፤ በስርአት አውርጄ ይዤው መትቻለሁ።” አሏቸው። ይህ አባባል ሁሉንም ዝም አሰኘ። ማንም መልስ ለመስጠት አልሞከረም። ኮሎኔል ዘለቀ በየነም፤ የፈይሳ ጃታን ጀግንነት አድንቀው እንዲፈቱ ትዕዛዝ ከመስጠት ውጪ ምንም አላሉም።
ጊዜው በግርግር እና በጦርነት እሳት ተወጥሯል። የኢትዮጵያ ጦር ተጠናክሮ እንደገና ማጥቃት ጀመረ። ከአስር ወራት በኋላ፤ የሱማሌ ጦር ከአካባቢው ሙሉ ለሙሉ ተደምስሶ ጅጅጋ እንደገና በኢትዮጵያ አስተዳደር ስር ወደቀች። ሀረር ላይ ሰፍሮ የነበረው ህዝብ እንደገና ወደ ጅጅጋ ከተማ ተመለሰ። እነሆ የድል ምስራች ከዳር እስከ ዳር አስተጋባ።
ፈይሳ ጃታ እና ተከታዮቻቸው ወደ ጅጅጋ ከተማ ሲመለሱ፤ ህዝቡ እንዳጀባቸው በቀጥታ ያመሩት ወደ ቤታቸው አልነበረም። ከአስር ወራት በፊት በክብር ያወረዱትን ሰንደቅ አላማ በክብር መልሰው ለመስቀል ወደ 10ኛው ሜካናይዝድ ብርጌድ ግቢ አመሩ። ወታደሩም አስተዳደሩም፣ ህዝቡም አጀባቸው። የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን በታላቅ ክብር፤ በደስታና በሆታ መልሰው ሰቀሉ።
ከዚህ በኋላ ፈይሳ ጃታ ወደ ቤታቸው ተመልሰው የወታደር ልብሳቸውን አወለቁ። የዚህ ታሪክ ተራኪም ከጥቂት ቀናት በኋላ ኢትዮጵያን ለቅቆ ስለወጣ፤ ስለፈይሳ ጃታ በወሬ በወሬ ከሚሰማው በቀር፤ ቀሪ ታሪካቸውን አያውቅም። ሆኖም በታሪክ ስማቸውን ከፍ የሚያደርግ ብሄራዊ ውርደትን አልቀበል ብለው እንደተፋለሙ ጠንቅቆ ያውቃል። በመጨረሻም በእርጅና ቆይተው አስከሬናቸው ሃረር ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በክብር ማረፉን ሲያወራ፤ ለሱም ክብር ይሰማዋል።
ዛሬ የምንሰማው “ብሄራዊ ውርደት” በየትኛውም ዘመን እና ወቅት፤ በየትኛውም መንደር እና አገር ሊያጋጥም ይቻላል። ዋናው ቁም ነገር… ይህንን ውርደት የሚሸከም ህሊና የሌለን መሆኑን ማረጋገጡ ላይ ነው። ይህንን የምናረጋግጠው ደግሞ በወሬ ብቻ ሳይሆን፤ እንደ ፈይሳ ጃታ ለኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እና ለህዝብ ክብር በመቆም ነው!!
የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት) በዳዊት ተሾመ
በዳዊት ተሾመ (dawit-teshome@hotmail.com)
4. የብሔራዊ ዕርቅ ፈተናዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች
በኢትዮጵያ የብሔራዊ ዕርቅ ፈተናዎች የሚመነጩት ስለ ብሔራዊ ዕርቅ ባለን ግንዛቤና እኛ ከለንበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ለመቃኘት በምናደረገው ጥረት ውስጥ ነው:: በኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ብሔራዊ ዕርቅ ሲነሳ እንድ ዋነኛ መነጻጸሪያ ሁኖ የሚቀርበው በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተካሄደውን ብሔራዊ ዕርቅን ነው:: በአብዛኛው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች የሚታሰበው የደቡብ አፍሪካ ዕርቅ ምንም እንከን እንደሌለውና በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታም አንጻር ሊደገም እንደሚችል ነው:: ነገር ግን፣ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ዕርቅ ሂደት የራሱ የሆኑ ጉድለቶች ያሉበት ከመሆኑም በላይ ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ አንጻርም ብዙ ልዩነቶች አሉት:: ስለዚህም፣ በኢትዮጵያ የሚያስፈልገው ብሔራዊ ዕርቅ ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ የሚመጥን መሆን አለበት:: ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ የብሔራዊ ዕርቅ ፈተናዎችንና የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንደሚከተለው ቀርቧል::
ሀ) እውቅና ስለመስጠትና የብሔራዊ ዕርቁ አካሄድ ላይ ያሉ ፈተናዎችና የመፍትሄ ሃሳቦች
ላለፉት ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነቶችና በደሎች እውቅና መስጠት ላይ የሚታዩት ችግሮች ሁለት አይነት ናቸው:: አንደኛው ችግር ያለፉትን በደሎች እውቅና መስጠት በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ መሆኑ ነው:: ይኸ ማለት ላለፉት በደሎች እውቅና መስጠት ማለት በደሎችን የፈጸሙ ኃይሎች ለፈጸሙት በደሎች ተጠያቂነት ስለሚያመጠና በደሉን ፈጽመዋል የሚባሉት ደግም እንደ <ሀገር-መስራች፣ ስልጣኔ አስተዋዋቂና ሰለምና ብልጽግና አምጪ> በሚል በተለምዷዊው የኢትዮጵያ ታሪክ (meanistream Ethiopian history) ተክለ-ሰውነታቸው ስለተሳለ ነው:: ሁለተኛው ችግር ያለፉት በደሎች ዕውቅና ቢሰጥ ቀጥሎ ሊመጣ የሚችለው ነገር ላይ ብዥታ መኖሩ ነው:: ይህም ማለት ዕውቅና ቢሰጥ ተበድለናል የሚሉ የፖለቲካ ኃይሎች ለራሳቸው ፖለቲካዊ ጥቅም ሊያውሉት ይችላሉ የሚል ፍራቻ መኖሩ ነው:: እነዚህ ዕውቅና በመስጠት ላይ ያሉ ተግዳሮቶች በምንም መልኩ በደሎችን በመካድ ሊፈቱ አይችሉም:: እንደ አቅጣጫ መወሰድ ያለበት አካሄድ ያለፉትን በደሎች አለመካድና በድጋሚ እንዳይፈጸሙ ማድረግን ነው::
በሌላ በኩል ደግሞ፣ በደሎቹ የተፈጸሙበት ወቅት ያለውን የአስተሳሰብ ደረጃና የአገዛዛ ባህሪ ከጭፍን ስሜታዊነት ውጭ መመልከት ተገቢ ነው:: ታሪክ ለፖለቲካዊ ግብ መምቻ ብቻ ከመጠቀም ወጥተን ታሪክን ለታሪክ ተመራማሪዎች መተውን መልመድ መቻል አለብን:: በሀገራችን ሊኖረን የሚገባው ፖለቲካ ትላንትን መሰረት ያደረገ ሳይሆን በነገው ብሩህ ቀንና አብሮነታችን ላይ የተመሰረተ መሆን ይገባዋል:: ይህ ማለት፣ ሙሉ ለሙሉ ታሪክን ከፖለቲካ መነጥል ይቻላል ማለት አይደለም:: ይልቁኑም ፖለቲካችን በባለፈው ታሪካችንና በነገው አብሮነታችን እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነታችን ላይ ያለውን ሚዛን ማስተካከል ቁልፍ መሳሪያ መሆን ይገባዋል::
በአገራችን የነበሩ አገዛዞች ምንም እንኳን ማህበረሰባዊ መሰረታቸውን በስነ-ልቦና ደረጃ ተጠቃሚ ያደረጉ ቢመስልም፣ በሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ህዝቦች በባለፉት አገዛዞች ተበዳዮች ናቸው፤ የበደላቸው መጠንና የበደላቸው አይነት ምንም እንኳን ቢለያዩም:: ያለፉት አገዛዞችም ሆነ አሁን በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ የጠቀሙት ጥቂት ከስርአቱ ጋር ቅርበት ያላቸው ልሂቃንን እንጂ በአጠቃላይ ልሂቃኑ የወጡበትን ወይም እንወክለዋለን የሚሉትን ማህበረሰብ አይደለም:: ስዚህም፣ ያለፉትን በደሎች ዕውቅና መስጠት ማለት ይህ ህዝብ በዚህ ህዝብ ተበድሏል፤ እከሌ የሚባል ህዝብ በዳይ እከሌ የሚባል ህዝብ ተጎጂ በሚል መንፈስ መሆን የለበትም:: ሁሉም ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነቶችም ሆነ በደሎች መታየት ያለባቸው በደሎቹን የፈጸሙት አገዛዞች ከተመሰረቱበት ፓለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረቶች የመነጩ መሆናቸውን ነው::
ይህ አካሄድ አንድ በኩል በህዝቦች መካከል ሊፈጠር የሚችለውን በቂም በቀል የታጀለ ማህበረሰባዊ ግንኙነት መሰረት እንዳይዝ ሲያረግ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከባለፈው ታሪካችን ተምረን የተሻለ ነገን ለመፍጠር ለምናደርገው ሂደት ማህበረሰባዊ መነቃቃትን ይፈጥርልናል:: ስለዚህም፣ በዚህ አካሄድ ላለፉት በደሎች ዕውቅና በመስጠት ሊከሰት የሚችለው የፖለቲካ ኃይሎች ያለፉትን በደሎች ፖለቲካዊ ትርጉም በመስጠት ለፖለቲካ ጥቅም የሚያውሉበትን እድል ማጥበብ ይቻላል:: በመሆኑም፣ የብሄራዊ እርቅ ጉዳይ መታየት ያለበት የባለፈውን ጠበሳ በመነካከት ቅራኔን በማባባስ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማስገኘት ሳይሆን ከባለፈው ታሪክ በመማርና ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነትን በማረም የተሻለ ነገንና ብሩህ-ተስፋን ከመፍጠር አንጻር መሆን ይገባዋል::
ለ) የተፈጸሙትን በደሎች ያስከተሉት ውጤቶች ላይ፣ ተጎጂዎች የከፈሉት መስዋትነት እና እንድምታ ላይ ስምምነት መድረስን (Consensus building) በተመለከተ ያሉ ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር <ብሔራዊ ዕርቅ የሚያስፈልገው ለየትኛው ታሪካዊ በደል ነው> የሚለው ጥያቄ በተፈጸሙ በደሎች ላይ ስምምነት ለመድረስ ወሳኝ ጥያቄ ነው:: ኢትዮጵያ የአሁኗን ቅርጽ እንድትይዝ ካደረጋት የሀገር ግንባታ ሂደት አንስቶ አሁን እስከምንገኝበት ዘመን ውስጥ የተፈጠሩትን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነትና በደሎችን ማካተት አለበት:: እነዚህን ሁሉ በደሎች አንድ ሰው ወይም አንድ አገዛዝ ሳይሆነ የፈጸመው፣ በየወቅቱ በሀገራችን የሰፈኑት አገዛዛችና አገዛዛቹን የመሰረቱት እና ተጠቃሚ በሆኑት ለአገዛዛቹ ቅርበት ባላቸው ጥቂት ልሂቃን ነው:: ስለዚህም፣ ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት የጎደላቸው ነገሮች ተደግረዋል፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአገዛዛቹ ተበድለዋል፤ የበደሉ አይነትና መጠን ቢለያይም:: ስለዚህም የተፈጸሙት በደሎች ያስከተሏቸው ውጤቶች በደንብ ተመርምረው ለታሪክ መማሪያነት መቀመጥ አለባቸው:: እንደ ሁሉም ሀገር፣ ሀገራችን ኢትዮጵያም ያላት ታሪክ <ጥሩም መጥፎ> ነው:: ከ<ጥሩ> ታሪካችን አንድነታችንን የበለጠ በማጠናከር <ከመጥፎው> ታሪካችን ደግሞ በመማር ማህበራዊ ግንኙነታችንን ይበልጥ በመተማመንና በመከባበር ላይ የተመሰረት ማድረግ እንችላለን:: ስለዚህም፣ የተፈጸሙት በደሎች ያስከተሉት ውጤቶችና ተጎጂዎች የከፈሉት መስዋትነትና እንድምታ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ ተመዝግቦ መያዝ ይገባዋል::
ለዚህም አላማ ሲባል ሊደረጉ የሚችሉ ተግባራት የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ:: አንደኛ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ የነበሩና ያሉ ግንኙነቶች፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በአግባቡ ሳይንሳዊ መሆነ መንገድ ተጠንተው እንዲቀመጡ በየዩኒቨርስቲዎቻችንና መንግስታዊ በሆኑ የምርምር ተቋማት ውስጥ እንደ አንድ ፕሮግራም ተቀርጾ ሊዘረጋ ይችላል:: በዚህም ሂደት የብሔራዊ ዕርቁን ተቋማዊ ገጽታ ማላበስ ይቻላል:: ሁለተኛ፣ ብሄራዊ ዕርቁን የሚመለከት መታሰቢያ ብሄራዊ ቀን ቢመረጥና በየዓመቱ የምርምር ስራዎች የሚቀርቡበት፣ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር፣ በመከባበርና ፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት በማህበረሰባችን ውስጥ ሊመጡ በሚችሉ ተግባራት ታስቢ እንዲውል ማድረግ ይቻላል:: ሶስተኛ፣ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በታሪካዊ በደሎች ምክንያት ውድ ህይወታቸውን ላጡ፣ ከመኖሪያቸውና ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ እና የተለያዩ መሰዋትነት የከፈሉትን ሰዎች ለማስታወስ ሃውልት እንዲቆም ማድረግ የሚቻል ነው::
ሐ) የተፈጸሙት በደሎች በድጋሚ እንዳይፈጸሙና የተገለሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ፍላጎትና ደህንነት የሚያረግገጥ ስርአት ለመፍጠር መዋቅራዊ ለውጦችን ማምጣትና የፖለቲካ ውህደትን ማሳለጥን (Structural changes and institutionalization of the process of political integration)፣ ብሔራዊ ዕርቅ ማህበራዊ ለውጥን ለማማጣትና ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት እንደ ወሳኝ ግብአት የምንጠቀምበት ከሆነ፤ ብሔራዊ ዕርቅ ሂደት በራሱ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ነው:: ይህ ማለት የተፈጸሙት በደሎች በድጋሚ እንዳይፈጸሙና የተገለሉ የማህበረሰቦች ክፍሎች ፍላጎትና ደህንነት የሚያረጋግጥ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መፈጠር አለበት:: ይህን ለማድረግም፣ የፖለቲካ ስርአቱ የሚመራበትን የጨዋታ ህግ ማውጣትና የጨዋታውን ህግ የሚመሩ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት ይጠይቃል:: ይህም ማለት በማህበረሰባችን ውስጥ መዋቅራዊ ለውጦችን ማምጣትን የሚጠይቅ ነው:: የሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ፍላጎቶችና ደህንነት ለማስከበር የፖለቲካዊ ስርአቱ ውስጥ ሁሉንም ተሳታፊ ማድረግ ግድ ነው::
ከዴሞክራሲያዊ ስርአት ውጪ በሀገራችን ያለውን ብዝሃነት ሊያስተናግድ የሚችል ስርአት የለም:: ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በመሰረቱ ሁለት ግቦች ላይ ማነጣጠር አለበት:: አንደኛ፣ በዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ሂደት ውስጥ ተቋማት የሚወክሉት ግለሰቦችን አሊያም የተወሰኑ የልሂቃን ቡድኖችን አይሆንም:: ተቋማት የሚወክሉት ስምምነት የተደረሰባቸውን የጨዋታ ህጎችን ሲሆን እነዚህም ህጎች በልሂቃን ውስጥ የሚፈጠሩ የጥቅምና የፍላጎት ግጭቶችን ለመዳኘት ዋና መሳሪያ ይሆናሉ:: ስለዚህም፣ የብሔራዊ ዕርቅ ሂደት ዴሞክራሲያዊ ተቋማትንና የጨዋታ ህጎችንና ደንቦችን ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች በሚስማሙበት መልኩ ለመቅረጽ የሚያስችል ሂደትን ይፈጥራል:: ይኸም ማለት ብሄራዊ ዕርቅ ከሚመጣባቸው ዋነኛ ሂደቶች መካከል የጨዋታ ህጎቹ የሚወጡበት አግባብና ሂደት ወሳኝ ነው:: ኢህአዴግ ብሔራዊ ዕርቅን የሚመለከትበት አግባብ ማለትም << ብሔራዊ ዕርቅ ማለት አሁን በለው ህገመንግስና ህገመንግስታዊ ስርአቱ ላይ መግባባት መፍጠር ነው::>> የራሱን ፖለቲካዊ የበላይነት ለማስጠበቅ ያለፈ ትርጉም አይኖረውም:: ምክንያትቱም የጨዋታ ህጎቹ የወጡበት አግባብና ሂደት ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎችን ያገለለ ከመሆኑም በላይ ዋነኛ ተገዳዳሪ የሚባሉትን በተለይ ደግሞ ሀገር-አቀፍ ፖለቲካ የሚያራምዱትን ያላካተተ ነው::
ሁለተኛ ደግሞ በዴሞክራሲያዊ ስርአት የስልጣን ክፍፍልን ስለሚያመጣ፣ ተጠያቂነትን ስለሚያሰፍንና ፖለቲካዊ ስልጣን በጉልበት ሳይሆን በህዝብ ፍላጎት ላይ በተመሰረተ አካሄድ ስለሚያዝ አዲስ ፖለቲካዊ ባህልን በሃገራችን ውስጥ እንዲሰፍን ያደርጋል:: ስለዚህም፣ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ የስልጣን ክፍፍሎሽ ስለሚኖር በልሂቃኖች መካከል ሊኖር የሚችለው የስትራተጂና የታክቲክ ጉዳይ እንጂ ጫፍ የወጣ ፖለቲካዊ ልዩነት አይሆንም:: በመሆኑም የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ መዋቅራዊ ለውጥ ከማምጣትና ፖለቲካዊ ውህደትን ከማሳለጥ አንጻር መታየት ያለበት ነው:: ይኸም፣ ፖለቲካዊ ውህደት የጋራ ነገን ከመፍጠርና የጋራ ራዕይ እንዲኖረን እና አዲስ ሲቪክ ፖለቲካዊ ባህል እንዲገነባ ከማስቻሉም በላይ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ መሰረት ይሆናል::
መ) ፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት በማምጣት ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ማረጋገጥ (enhancing socio-economic development and economic integration)
በታሪካችን እንደምንመለከተው ከሆነ በአብዛኛው በልሂቆቻችን መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች በፖለቲካ ሃሳቦች ልዩነት ላይ የተመሰረቱ ሳይሆን አንዱ አንዱን ጥሎ በማለፍ የፖለቲካ ስልጣን ለመቆጣጠር በሚደረጉ ግብግቦች ላይ የተመሰረቱ ናቸው:: የፖለቲካ ስልጣን ጥያቄ በዋናነት የሚያያዘው ደግሞ የሀገሪቱን ሀብት ከመቆጣጠር ጋር ነው:: በግልጽ ለማስቀመጥ ያክል የዘመናዊት ኢትዮጵያ ሀገር ምስረታ ሂደት ፖለቲካዊው እንድምታው ያልተማከለና በጣም ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት መመስረት ሲሆን፣ ኢኮኖሚያዊው እንድምታው ደግሞ በጦር አሸናፊ ሆነው የማዕከላዊ መንግስት ምስረታን ሂደት የተቆጣጠሩትን ኃይሎች የኢኮኖሚ ጥቅሞችን የማስከበር ሂደት ነበር:: ይህ ሂደት በደርግ አገዛዛም ሆነ በኢህአዴግ አገዛዝ የተደገመ ነው:: በዘውዳዊው፣ በደርግም ሆነ በኢህአዴግ አገዛዞች የተዘረጉት ኢኮኖሚያዊ ስርአቶች የሰፊውን ህዝብ ተጠቃሚነት ያላረጋገጡና የአገዛዞቹን ቀጣይነት ብቻ ለማረጋገጥ ያለሙ ናቸው:: ይህም በመሆኑ የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ ኢኮኖሚያዊ ፍትሃዊነትንና የህዝብ ተጠቄሚነት ላይ ያነጣጠረ መሆን ይገባዋል::
እንደ ደቡብ አፍሪካ ፖለቲካዊ ስልጣን ላይ ብቻ የተመሰረት የብሄራዊ ዕርቅ ሂደት በኢትዮጵያ ውስጥ ረጅም ርቀት የማይወስድ ብቻ ሳይሆን ወደ በለጠ ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ችግሮች የሚያጋልጥ ነው:: ስለዚህም የኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አንዱ የብሔራዊ ዕርቅ ዋና አላማ መሆን ይገባዋል:: በሌላ በኩል ደግሞ፣ የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ማረጋገጥ እና በክልሎች መካከል ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው:: ድህነት በራሱ ሰዎች በወደፊት ሕይወታቸው ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ፣ ጨለምተኛ እንዲሆኑ ከማድረጉም በላይ ለዚህ ሁሉ ቀውስ ተጠያቂ የሚያረጉት አንድ ነገር ይፈልጋሉ፤እራስን ከጥፋተኝነት ነጻ ለማውጣት:: ስለዚህም ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነቶችን ለዛሬው ውድቀት ብቸኛ ተጠያቂ እንደሆኑ ሲታሰብ፣ በተወሰኑ ልሂቃን ደግም ይህን ስሜት ለራሳቸው ፖለቲካዊ ጥቅም እንዲውል ያደርጋሉ፣ እያደረጉም ነው:: ስለዚህም፣ ፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ማስፋን የብሔራዊ ዕርቅ ውጤታማነትንና ዘላቂነትን ከማረጋገጥ አንጻር ወሳኝ ነው::
ከዚህ ጎን ለጎን፣ ሙስናን ማስወገድ የሚያስችሉ ተቋማዊ፣ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ ሪፎርሞችን ማካሄድ ግድ የሚል ነው:: በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በቁጥጥር ስር ያዋሉት ሶስት ኢኮኖሚያዊ ሃይላት ናቸው:: እነርሱም፣ መንግስት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚቆጣጠራቸው ድርጅቶች፣ የሚድሮክ ድርጅቶች እና በኢፈርት ድርጅቶች ናቸው:: ይህም፣ የአሁን ኢኮኖሚ ስርአት በዋናነት የፖለቲካ ስልጣን የተቆጣጠሩት ጥቂት ልሂቃን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በቀጥታ የሚቆጣጠሩበትን አግባብ ተቋማዊ ገጽታ የሚያላብስ ነው:: ስለዚህም፣ ፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትና ከዚህ ልማት እኩል ተጠቃሚነትን ከማስፈን አንጻር ሙስናን ማስወገድና ተወዳዳሪነትን የተላበሰ ኢኮኖሚያዊ ስርአት መዘርጋትን ግድ የሚል ነው:: በሌላም በኩል፣ በባለፉት የአገዛዝ ስርአቶች ከኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ትሩፋት የተገለሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል:: ይኸም፣ በባለፉት አገዛዞች ተበድለናል የሚሉ የፖለቲካ ልሂቃን ጫፍ የወጣ የፖለቲካ አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ የሚስገድዳቸው፣ የማያስተካክሉ ከሆነ የማህበረሰባዊ መሰረታቸው እንዲያጡ የሚያደርግ፣ ከተናጥል ጉዞ የአብሮነት ጉዞ እንደሚበልጥ ሰፊው ህዝብ እንዲረዳ የሚደርግ ነው:: በመሆኑም፣ ይህ ሁኔታ የብሄራዊ ዕርቅ ዘላቂነትን ከማረጋገጡም በላይ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ወሳኝ ነው::
ሠ) ለብሔራዊ ዕርቅ ምቹ ሁኔታን ስለመፍጠርና አማራጭ መፍትሄዎች
እስካሁን ድረስ ብሔራዊ ዕርቅን ለማሳካት ምቹ ሁኔታን አልተፈጠረም:: ይህ ምቹ ሁኔታ አለመኖር የሚመነጨው ከገዢው ፓርቲ ከፋፍሎ የመገዛዝ ባህል እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጣዊ ደካማነትና የጋራ አላማ መፍጠር አለመቻላቸው ነው:: ብሔራዊ ዕርቅ እንዲሳካ ስልጣን ላይ ያሉ ገዢዎችን የሚያስገድድና የሚገዳደር ተቃዋሚ ኃይል መኖርን ግድ የሚል ነው:: ካለ ጠንካራ ተቃዋሚ ኃይል የሚገኝ ብሔራዊ ዕርቅ፣ ዕርቅ ሊባል የሚቻል አይደለም:: ምክንያቱም የዕርቅ ሂደቱ ስልጣን ላይ ያሉ ልሂቃንን ጥቅም የሚያስጠብቅ ነው፤ ሁሉን የፖለቲካና ማህበረሰባዊ ኃይላትን የሚያካትት አይደለም:: ከዚህ ቀደም በወጡ ጹሁፎቼ እንዳመለከትኩት፣ የኢትዮጵያ የተቃውሞ ኃይሎች በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉት በብዙ ችግሮች የተተበተቡ ናቸው:: የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ ግማሹ ምላሽ በተቃውሞ ኃይላት ጥንካሬ ላይ የሚመሰረት ነው:: አንድነት ጥንካሬ፣ መከፋፈል ድክመትን እንደሚያመጣ ከባለፈው ታሪካችን በተሻለ ሁኔታ ልንማርበት የምንችልበት መድረክ የለም:: ስለዚህም፣ በተቋማዊ ብቃት፣ በስትራተጂ፣ በታክቲክ እና አባላትን በማፍራት ተቃዋሚ ሃይላት ከገዢው ፓርቲ ጋር ተገዳዳሪ መሆን አለባቸው::
አብዛኞቹ የሀገራችን የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነታቸው ርዕዮተ አለማዊ፣ ስትራተጂያዊ ወይም ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በግለሰቦች ቁርሾ ላይ የተመሰረተ ነው:: ስለዚህም፣ ግለሰባዊ ቁርሾዎችን ከብሔራዊ ፖለቲካ ጥያቄ መለየት መቻል አለብን:: በሌላም በኩል፣ አሁን የሚታየው የፖለቲካ ኃይሎች መሰባሰብ ይበል የሚያስብል ሲሆን፣ እዚያው ሳለም ሁሉን ማህበረሰብ የሚያቅፍና የሚያንቀሳቅስ አጀንዳ መቅረጽ ይጠበቅባቸዋል:: ተቃዋሚ ኃይላት ማህበረሰባዊ መሰረታቸውን መስፋትና ሁሉን የማህበረሰብ ክፍል (cross-cutting social cleavages) ማቀፍና ማንቀሳቀስ መቻል አለባቸው:: ይህን በማድረጋቸው፣ ገዢው ፓርቲ ስልጣን ላይ ብቻውን ለመቀመጥ የሚከፍለው መሰዋትነት በዕርቅ ሂደት ውስጥ በመሳተፍና ፖለቲካዊ ስርአት ለውጥ በመምጣቱ ከሚያጣው ጥቅም ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ እንዲሆን ያደርገዋል:: ይኸም፣ ለዘብተኛ የአገዛዙን ልሂቃን ወደ ብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄን እንዲያራምዱ ሲያስችላቸው፣ አክራሪ ልሂቃንን ደግሞ የበለጠ ደካማ ያረጋቸዋል::
በሌላ በኩል ደግሞ፣ የብሔራዊ ዕርቅ ስትራተጂያዊ ውጤቶችና ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባት ሂደት ተጠቃሚዎች ጥቂት ልሂቃን መሆን የለባቸውም:: በብሔራዊ ዕርቁ ሂደት ማንም የፖለቲካ ኃይል ሳይሆን አሸናፊ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት፣ አንድነት እና ሉአላዊነት ነው:: ስለሆነም፣ የብሔራዊ ዕርቅ ሂደት ማነጣጠር ያለበት ማን ስልጣን ላይ ወጣ የሚለው ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ የጨዋታ ህጎች ማውጣት እና ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት ላይ ነው:: ይኸም፣ የብሄራዊ ዕርቁ ስተራተጂያዊ ውጤቶች (ዴሞክራሲያዊ ስርአት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና ሀገራዊ መግባባት) እና ታክቲካዊ ግቦች መካከል አንድነትንና ሚዛንን የሚያስጠብቅ ይሆናል:: በመሆኑም፣ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ለብሔራዊ ዕርቅ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩም በላይ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ወሳኝ ግብአት ነው::
5. ማጠቃለያ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በብዙ ውስብስብ ታሪካዊ ሂደት ያለፈች ሀገር እንደመሆኗ መጠን፣ ያሉብን ችግሮች መጠነ ሰፊና ውስብስብ ናቸው:: እስካሁን ድርስ ጉልበት ላይ የተመሰረተ ልዩነቶችን የመፍታት ሂደቶች የበለጥ ልዩነቶችን ውስብስብ እንዲያደርግና ጥላቻ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ስር እንዲሰድ ሆኗል:: ምንም እንኳን ከደርግ ወታደራዊ አገዛዝ ውድቀት በኋላ የተለያዩ የብሔራዊ ዕርቅ አስተሳሰቦች በሙሁሯንና በፖለቲካ ኃይላት ቢራመዱም፣ የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄን የፖለቲካ ኃይላት የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ማሳኪያ መሳሪያ ያደረጉበት አረዳድ እንደሰፈነ መረዳት አያዳግትም:: የብሔራዊ ዕርቅ ሂደት ውስብስብ ችግሮችን የምንፈታበት ሂደት እንደመሆኑ መጠን በእንዳንዱ ጥቃቅን በደሎች ላይ የምናተኩርበት፣ ፖለቲካዊ ትርፍ የምናሰላበት፣ አግላይ ስርአት የሚመሰረትበት ሂደት ሳይሆን የተሻለች ኢትዮጵያንና ብሩህ ቀን የመፍጠር ሂደት አካል መሆን ይገባዋል::
ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወዳገራቸው የመመለስ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው! ግልጽ ደብዳቤ ለሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/የሱስ
ኅዳር 23፣ 2006 ዓም
ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወዳገራቸው የመመለስ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው!
ግልጽ ደብዳቤ ለሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/የሱስ
ለዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም፤
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ኢትዮጵያውያንን በቀለም፣ በዘር፣ በጎሣ፣ በቋንቋ፣ በጾታ፣ በክልል፣ ወዘተ ሳይከፋፍል በየትኛውም የዓለም ክፍል (ኢትዮጵያንም) ጨምሮ የሚደርስባቸውን ማንኛውም ዓይነት ማኅበራዊ ኢፍትሃዊነት ለመከላከል፣ ለማስቆም፣ ለማጋለጥ፣ ወዘተ እና ባሉበትም ቦታ ሁሉ ከፈጣሪ የተሰጣቸውን መብት ለማስጠበቅ የቆመ ድርጅት ነው፡፡ ሆኖም ግን እኔ ኦባንግ ሜቶ ይህንን ደብዳቤ የምጽፍልዎ የዚህ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር እንደመሆኔ ብቻ ሳይሆን የውቢቷ ኢትዮጵያ የደም ውጤት በመሆኔ እንደ አንድ ወንድም በመሆንም ጭምር ነው፡፡
ይህንን ደብዳቤ የምጽፍልዎ እርስዎንም ሆነ እርስዎ አባል የሆኑለትን የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና ኢህአዴግን ለመለመን ወይም ለማስደሰት ሳይሆን በሳዑዲ አረቢያና በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ውስጥ በኢትዮጵያዊ ሕዝቤ ላይ እየደረሰ ያለውን ከሰብዓዊነት ውጪ የሆነ አሰቃቂ ተግባር የማስቆምና አስቸኳይ መፍትሔ የማምጣት ግዴታ ህወሓት/ኢህአዴግ እንዳለበት ለማስታወቅ ነው፡፡
በመሆኑም እኔና እርስዎ የፖለቲካም ሆነ የአስተሳሰብ ልዩነት እንዳለን ግልጽ ቢሆንም አገር “እየመራሁ ነኝ” የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ የኃላፊነት ቦታ ላይ ያስቀመጥዎት እርስዎን በመሆኑ ይህ ጉዳይ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ሰዎች አንዱ ነዎት፡፡ ከሥልጣኑም ጋር አብሮ ከፍተኛ የሆነ ኃላፊነት ይመጣል፤ ይህም በሁሉም ዘንድ ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግም የሕዝብ ውክልና ባይኖረውም እንኳን ለእያንዳንዱ ነገር በቀጥታ ተጠያቂ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ደብዳቤ ላይ የማሰፍራቸው ነጥቦች እርስዎንም ሆነ ህወሃት/ኢህአዴግን የሚያስደስት ላይሆን ይችላል፡፡ በተለይ በሳዑዲና በሌሎች የመካከለኛ ምስራቅ አገራት በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍ በዓለም ዙሪያ ተበትነው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ያሳረፈው ተጽዕኖና ኃፍረት እንዲሁም ቁጭት ይህ ነው ተብሎ የሚነገር እንዳልሆነ ህወሃት/ኢህአዴግ በሚከተለው የመረጃ ማፈን ፖሊሲ የኢትዮጵያ ሕዝብ መመልከት ባይችልም እርስዎና አብሮዎት ያሉት ሳታዩት ያለፋችሁት ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህንን ደብዳቤ የምጽፍልዎ መረጃን በመመርኮዝ በመሆኑ ለምጽፈው እያንዳንዱ ነገር ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ መሆኑን አስቀድሜ ላስገነዝብዎት እወዳለሁ፡፡
ባለፉት ሳምንታት በ30 አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በ80 ከተሞች ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በአንድ ድምጽ በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ይቁም በማለት ቁጣችንን ስናሰማ ቆይተናል፤ አሁንም ቀጥሏል፡፡ ይህ እየተደረገ ያለበት ምክንያትም በሳዑዲ ያሉት ኢትዮጵያውያን ከአንድ የተወሰነ ክልል ወይም የአንድ ጎሣ ቋንቋ ተናጋሪ ወይም የተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍል ወዘተ ስለሆኑ ሳይሆን በቅድሚያ ሰብዓዊ ፍጡራን ስለሆኑ ከዚያም በላይ የእኛንም ኢትዮጵያዊነት ማንነትና ክብር የሚነካ በመሆኑ ነው፡፡ ታዲያ ለዚህ ቀውስ መፍትሔው ለመንገድ ሥራ እንደሚገኝ ድጎማ ከዓለም ባንክ ወይም ከተባበሩት መንግሥታት ወይም ከሌሎች ለጋስ አገራት ወይም ደግሞ እንደ “ህዳሴ ግድብ ቦንድ” ከዳያስፖራ የሚገኝ አይደለም፡፡ በተጻጻሪው ለዚህ ቀውስ ዋንኛውን ኃላፊነት የሚወስደውና በሳዑዲ የሚሰቃዩትን ኢትዮጵያውያንን የመታደግ ግዴታው የህወሃት/ኢህአዴግ ነው!
ይህ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ የሁላችንንም ህልውና የነካ በመሆኑ “በእርግጥ ኢትዮጵያዊን አገር አላቸው ወይ?” ብለን እንድንጠይቅ ያደረገን ሆኗል፡፡ በተጻጻሪው ግን በህወሃት/ኢህአዴግ በኩል የሚታየው የውሳኔ አሰጣጥ እና እርምጃ አወሳሰድ አናሳነት እንዲሁም ዝግተኝት በአመራር ላይ ያሉትን ሁሉ ስለ ችግሩ ያላቸው የግንዛቤና የአመራር ደካማነት ያለአንዳች ጥያቄ በጉልህ ያሳየ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ፈርጀ ብዙ ለሆነው የኢትዮጵያ ችግር ዋንኛ ተጠያቂ ህወሃት/ኢህአዴግ ቢሆንም የችግሩ አፈታት ግን ለሥራ ባልደረቦች ጊታር የመጫወት ያህል ወይም በጥቂት ቃላት ትዊተር ላይ መልዕክት የመላክ ያህል የቀለለ እንዳልሆነ እሙን ሆኗል፡፡
በዚህ ደብዳቤ ላይ የማነሳቸው በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩኝም በቅድሚያ መጠየቅ የምፈልገው ጥያቄ ቢኖር ለመሆኑ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ የት ነው ያሉት? ህወሃት/ኢህአዴግም ሆነ አቶ ሃይለማርያም የህዝብ ውክልና ያላቸው ባይሆኑም የሥራ አስፈጻሚው ሥልጣን የተሰጠው ለእርሳቸው በመሆኑ በዚህ ቀውስ ጊዜ በውክልና ሳይሆን በግልጽ በመታየት የሥራ አስፈጻሚነት ተግባራቸውን መወጣት ይገባቸው እንደነበር የእኔ ብቻ ሳይሆን የበርካታ ኢትዮጵያውያን በተለይም በሳዑዲ ያሉቱ ጥያቄ ሆኗል፡፡ ወይስ ሁኔታው ከዚህ በፊት ሲነገር የነበረውን እና ህወሃት/ኢህአዴግ እርስዎን ወደ ጠ/ሚ/ር መንበር ላይ ለማስቀመጥ ያለውን ውጥን እውን የማድረጊያ መንገድ በመሆኑ ይሆን? ይህ ከሆነስ የእነዚህ ወገኖቻችንን ስቃይ ለራሱ የፖለቲካ ዓላማ እየተጠቀመበት ያለው ማነው?
ሰሞኑን በቤተሰብ ምጣኔ ጉዳይ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር ባጠቃላይ ያተኮረው በሳዑዲ ስላሉት ኢትዮጵያውያን ብቻ ላይ ማተኮሩ በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅና በዓለም ዙሪያ በመከራና በስቃይ ውስጥ ስላሉት ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ ስላለው ችግር ያለዎን የግንዛቤ ማነስን ወይም ግዴለሽነት የሚያሳይ ነው ከማለት ሌላ ምን ሊባል ይችላል? ምክንያቱም በመላው አረቢያ ምድር ኢትዮጵያውያን ምን ያህል እየተሰቃዩ እንደሆነ ዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ለዓመታት ሲዘግቡት የኖረ፣ እኛም በየጊዜው የምናሳውቀውና ህወሃት/ኢህአዴግ በውል የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ቀውሱ ይፋ በሆነበት ሰሞን ስሜትዎ ምን ያህል እንደተረበሸና ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ በሚደርስባቸው ሰቆቃ እንዴት እንዳዘኑ ለሚዲያ ሲገልጹ የነበረው ከፖለቲካና ሚዲያ ፍጆታ ውጪ ልባዊ ስሜት ነው ብለን ለመቀበል ችግር ውስጥ ከትቶናል፡፡
በሳዑዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰው ሰቆቃ በድንገት እንዳልሆነ ማንም መካድ የሚችለው ጉዳይ አይደለም፡፡ ሳዑዲ የምትከተለው የከፋላ አሠራር መሠረት የአንድ ጉዞ ቲኬት ቆርጠው ወደዚያ የሚሄዱ ሁሉ ሳዑዲ አየር ማረፊ እንደደረሱ ፓስፖርታቸውን እና ሌሎች የመታወቂያ ሰነዶቻቸውን እንዲያስረክቡ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ግን ከሳዑዲ ለመውጣት የሚፈልጉት እንኳን የመውጫ ቪዛ ለማግኘት በሚፈልጉበት ጊዜ ፓስፖርታቸውንም ሆነ ማንኛውንም መታወቂያቸውን መልሰው የማግኘት ዕድል የላቸውም፡፡ በዚህ ዓይነት አሠራር ውስጥ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በድንበር የገቡትን ሳይጨምር ሌሎቹ ግን በተሠጣቸው የሰባት ወር ምህረት ጊዜ የመጓጓዣ ሰነዶቻቸው እጃቸው ላይ ሳይኖር በተፈቀደው ጊዜ ለመጠቀም የሚችሉበት ሁኔታ ሊከሰት አልቻለም፡፡ ሰነዱ በእጆቻቸው ያሉትም እንኳን ቢሆኑ ቀውሱ በተፈጠረ ጊዜ ለመውጣት እንዳይችሉ በሳዑዲ ወሮበሎችና ፖሊሶች የደረሰባቸው ሰቆቃ በሁኔታው ላይ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዳያመጣ አድርጓል፡፡ ከዚህ ሌላም ሳዑዲ አረቢያ ሰጠች በተባለው የምህረት ጊዜ የተለያዩ አገራት ዜጎቻቸውን በቻሉት ሁኔታ ሁሉ እያስወጡ ባሉበት ጊዜ ኢትዮጵያውያኑን የሚታደግ መታጣቱ መልስ የሚያሻውና በኃላፊነት የሚያስጠይቅ ነው፡፡ (ይህንን ጉዳይ ከዚህ በፊት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ባወጣው ደብዳቤ ላይ ተዘርዝሯል)
ችግሩን ወደኋላ መለስ ብለን ስንቃኘው ሰቆቃው የጀመረው ከጥቂት ሳምንታት ወይም ከጥቂት ወራት ወይም ጊዜያት በፊት ሳይሆን ለዓመታት የቆየና በተለይም ከስድስት ዓመታት ጀምሮ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ አረቢያ ምድር መፍለስ በጀመሩበት ጊዜ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ዋንኛው ምክንያት ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለውና ጥቂቶችን በመጥቀም ሌሎችን የሚያገልለውና አገር አልባ የሚደርገው ፖሊሲ በርካታ ዜጎችን አገራቸውን እንደ አገር እንዲቆጥሯት ስላላደረጋቸው ነው፡፡ በመሆኑም በአገሩ ሁለተኛና ከዚያ በታች ዜግነት ተሰጥቶት በተወለደባት አገር ስደተኛ የሆነ ሁሉ በሌላ አገር ሄዶ እውነተኛ ስደተኛ ለመሆን ለምን ይፈልጋል ብሎ የሚጠይቅ አእምሮ ቢስ ነው ቢባል ማስረጃ የሚያስፈልገው አይመስለኝም፡፡ እነዚህ ወገኖቻችን እንደዚህ ዓይነት ውሳኔው ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ ሁሉ በአረብ ምድር እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ እየሰሙ መሆኑ የሚካድ ባይሆንም የኢኮኖሚ ስደተኞች እንደመሆናቸውና ባገራቸው እንደዜጋ ተቆረው ኢኮኖሚያዊ ችግራቸውን ማቃለል አለመቻላቸው ኢሰብዓዊነት በተጠናወታቸውና ጨካኝ የአራዊት ባህርይ ባላቸው አረቦች እጅ እያወቁ እንዲወድቁ አስገድዷቸዋል፡፡
ይህ ብቻ አይደለም፤ በአረብ ምድር ያለው ሁኔታ ችግር አልባ የሆነ ይመስል ህወሃት/ኢህአዴግ ዝም ባለበትና በግልጽም ይሁን በእጅ አዙር ተጠቃሚ በሆነበት በዚህ የሰው ማዘዋወርና ኢትዮጵያውያንን የመሸጥ ድርጊት እንደ መልካም ንግድ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ውስጥ (የገጠር ቦታዎችም ጭምር) ትልልቅ ማስታወቂያዎች (ቢልቦርድ) እየተሰራላቸው ንግዱ ሲጧጧፍ ቆይቷል፡፡ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚሄዱ በተለይ ሴቶች እህቶቻችን የሚደርስባቸው ሰቆቃ በሰው አእምሮ የሚታሰብ አለመሆኑ በሚነገርበትና ከበቂ በላይ ማስረጃዎች በሚቀርቡበት ጊዜያት ሁሉ ምንም ዓይነት የቀረበ መፍትሔ የለም፡፡ ለመሆኑ በቅርቡ በአረቢያ በሚገኙ የአእምሮ ተቋማት ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ በሽተኞች ኢትዮጵያውያን ሴቶች መሆናቸው ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ምን የተወሰደ እርምጃ ይኖር? እርስዎስ የውጭ ጉዳይ መንበር ላይ እንደመቀመጥዎ ይህንን ሁሉ ሰቆቃ እየሰሙ እስካሁን ትልልቅ ማስታወቂያ የተሰራላቸውን ወደ አረቢያ ኢትዮጵያውያንን የሚያግዙትን ድርጅቶች እንዲዘጉ ያላደረጉት ለምን ይሆን? ይህንን ከማድረግ ይልቅ ራስዎ የሚመሩት መ/ቤት ድረገጽ ባለፈው ዓመት ብቻ 160ሺህ ኢትዮጵያውያን ለቤት ሠራተኛነት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለማቅናት መፈለጋቸውን መዘገቡ በምን ቋንቋ የሚገለጽ ይሆን? እነዚህ ወገኖች ለሰቆቃ፣ ለመከራ፣ አስገድዶ ለመደፈር፣ ያለዋጋ ለመሥራት እንዲሁም ለመሞት እየተጋዙ መሆናቸው እየታወቀ ዝም መባሉ ምን ዓይነት አስረጅ የሚቀርብበት ይሆን? ለመሆኑ ከዚህ የደም ገንዘብ እያተረፈ ያለው ማነው? እኔ አላውቅም የሚለው በቂ ምላሽ ሊሆን ፈጽሞ አይችልም፤ እንደ ምላሽ እንቀበለውም ከተባለ እንኳን የዛሬ 30ዓመት አካባቢ እርስዎ አሁን የተቀመጡበት ወንበር ላይ የነበሩትና ደርግ የሚከተውን ፖሊሲ በመቃወም ሥልጣናቸውን የለቀቁትን የኮ/ሎ ጎሹ ወልዴን ፈለግ መከተል አንድ አማራጭ የሚጠቀስ ብቻ ሳይሆን በታሪክም የሚታወስ ተግባር ነው፡፡ ከልቡ ያዘነ ሆኖም ፓርቲው የሚከተለው ፖሊሲ ከራሱ ኅሊና ጋር የተጋጨበት የሚወስደው ውሳኔ በመሆን ለትውልድ የሚያልፍ አኩሪ ተግባር ነው፡፡
ሚ/ር ቴድሮስ፤
እርስዎ አባል የሆኑበት ህወሃት/ኢህአዴግ የደርግ አገዛዝን “ሰው በላ” እያለ ይክሰሰው እንጂ ህወሃት/ኢህአዴግ በአሁኑ ጊዜ እየፈጸመ ያለው ተግባር “ሰው በላ” ብቻ የሚያስብለው ሳይሆን “ሰው አስበዪ” የሚያስብለውም ጭምር ነው፡፡ እንደ ማስረጃም፡- እርስዎ በሳዑዲ በሚገኙ ኢትዮጵያውያ ሰቆቃ ዕንቅልፍ ነስቶኛል ባሉበት ሰሞን እንዲሁ ሰቆቃው ከዕንቅልፍ በላይ የነሳቸው ወገኖች በአዲስ አበባ በሚገኘው የሳዑዲ ኤምባሲ ፊት የተቃውሞ ሃሳባቸውን ለመናገር በተሰበሰቡበት በፌዴራል ፖሊስና በደኅንነት ኃይሎች መደብደባቸውና ሰልፉ መበተኑ የዓለም ህዝብ ተመልክቶታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የእኔም ጥያቄ እርስዎ በሳዑዲ ለሚሰቃዩት ዕንቅልፍ እስኪያጡ ካዘኑላቸው ምነው ያው እንቅልፍ ማጣት በፌዴራል ፖሊስ ለተደበደቡት ተግባራዊ ሳይሆን ቀረ? ወይስ በሳዑዲ የደኅንነት ኃይላት የሚደርሰው ሰቆቃ በፌዴራል ፖሊስ ከሚደርሰው ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ሆኖ ይሆን? ወይስ ከኢትዮጵያ ውስጥና ውጭ ያሉ የህመም አሸካከማቸው የተለያየ ይሆን? እንደ እውነቱ ከሆነ አዲስ አበባ ላይ የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት ከወጡት ጋር እርስዎም እንደ ዜጋ እና የጉዳዩ ቀጥተኛ ባለቤትነት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ አብረው በሰልፉ ሊገኙና ተቃውሞዎን ሊያሰሙ በተገባ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ተነሳሽነት በሌለበት እና ለወገኖቻቸው መብት የሚቆሙት ሁሉ በሚረገጡበትና አገር አልባ መሆናቸው እንዲሰማቸው በሚደረግበት ጊዜ ሳዑዲዎች ለምን ኢትዮጵያውያንን እንዲህ እንደሚሰቃዩ ለተጠየቀው አንዱ የሳዑዲ ተወላጅ “እኛን ከምትረግሙና ከምትኮንኑን በመጀመሪያ የራሳችሀ መንግሥት እንደ ሰው እንዲቆጥራችሁ አድርጉ” በማለት የመለሰው ሁኔታውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡
እንደ እኔ እምነት የሰው ዘር በሙሉ ከፈጣሪ የተሰጠው በማንም የማይገሰስ መብት ስላለው ሁሉም ሰው በእኩል ዓይን ሊታይ ይገባዋል፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ይህ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል፡፡ ከንፈር መምጠጥ ከሚመስል የታይታ ዕርዳታም ሆነ ሥራ ይልቅ እውነተኛ ሥራ በተግባር ሊታይ ይገባል፡፡ እውነተኛ “ዕድገትና እና ትራንስፎርሜሽን” የሚያስፈልገው በዚህ ሰብዓዊ በሆነ ጉዳይ ላይ ነው፡፡ ከዚህ የሚቀድም ነገር ሁሉ ከሰብዓዊነት ተራ የወጣ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለውና ዘላቂ ለውጥ የማያመጣ ነው፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በስቃይ ላይ በሚገኙት ኢትዮጵያውያን ስም እና ከስደተኛ ኢትዮጵያውያን ጋር ለዓመታት በመሥራት ባለኝ ኃላፊነት ሁሉን ዓቀፍና አጠቃላይ የሆነ ፈጣን እርምጃ በመውሰድ ሰብዓዊ ፍጡርን የማዳኑ ሥራ ባስቸኳይ መካሄድና መጠናቀቅ እንዳለበት ላሳስብዎ እወዳለሁ፡፡ ይህንን ማድረግ ደግሞ ህወሃት/ኢህአዴግ ለኢትዮጵያውያን የሚውለው ውለታ ወይም የሚፈጽመው መልካም ነገር ሳይሆን በቅድሚያ የችግሩ ፈጣሪ በመሆኑ ኃላፊነቱ የራሱ ነው፡፡ ሲቀጥልም እንደ እርስዎ በኃላፊነት የተቀመጣችሁ ሁሉ ይህንን ማስፈጸም በቦታው ላይ ስትቀመጡ የገባችሁበት ግዴታና በኃላፊነት የምትጠየቁበትም ጉዳይ በመሆኑ ነው፡፡
ይህ ቀውስ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በሳዑዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያሳየው ግዴለሽነትና ተግባርን በሥርዓት ያለመወጣት ችግር በደረሰው ችግር ላይ ተጨማሪ ሰቆቃ በመፍጠር በወገኖቻችንን ስቃይ ላይ አስከፊ ጠባሳ ጥሏል፡፡ ከዚያም አልፎ በእንዲህ ዓይት የቀውስ ወቅት ያለውን ኃይል ሁሉ በማስተባበር 24ሰዓት ሊሰራ የሚገባው ኤምባሲ አንዴ ሥራውን ሲያቋርጥ አልፎም ለሦስት ቀናት በሩን በመዝጋት “አገልግሎት አንሠጥም” በማለት ማስታወቂያ መለጠፉ በኤምባሲው ውስጥ ያሉትን ኃላፊዎች አምባሳደሩንም ጨምሮ በሥነምግባርና በሕግ የሚያስጠይቅ ነው፡፡ ይህ ክስተት የኤምባሲው ከፍተኛ ኃላፊዎችና አምባሳደሩ ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ በማስመጣት ህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የትርፉ ተጠቃሚዎች ናቸው እየተባለ ለጋራ ንቅናቄያችን ሲደርስ የነበረውን መረጃ እውነትነት ወደ ማመኑ እንድንደርስ ያደረገን ነው፡፡ እርስዎም የአምባሳደሮች አለቃ እንደመሆንዎ ባለው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ሲገባዎ ዝምታን መምረጥዎ የጥፋቱ ተባባሪ ያደርግዎታል፡፡
ሌላው በዚህ ደብዳቤ ላይ ላነሳው የምፈልገው ጉዳይ ከሳዑዲ አረቢያ የሚመለሱትን ወገኖቻችን በተመለከተ ነው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በትዊተር ላይ የሚልኩት መልዕክት ብዙዎቻችንን ግራ ያጋባ ስለመሆኑ ነው፡፡ እስከ ህዳር 19፤ 2006 ቀን ድረስ 55392 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢ መመለሳቸውን ጽፈዋል፡፡ በአማካይ ኤርባስ ወይም ቦይንግ አውሮፕላን በአንድ በረራ 400 ሰው ይጭናሉ፤ እርስዎ ተመለሱ ያሉትን ያህል ሰዎች ለማመላለስ ወደ 140 ከሳዑዲ አዲስ አበባ በረራ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ ይህንን ያህል በረራ ለመካሄዱ ግን የሰጡት ምንም ዓይነት ፍንጭ ሆነ መረጃ የለም፡፡ በቀን ስንት በረራ እንደሚደረግ፣ በእያንዳንዱ በረራ ውስጥ ምን ያህል ወገኖቻችን እንደሚሳፈሩ፣ ተመላሾች ቦሌ ከደረሱ በኋላ ወደ የት እንደሚገኙ፣ ወዘተ ዝርዝር መረጃ ከእርስዎም ሆነ ከሌሎች ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ማግኘት አልተቻለም፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ባሉት መረጃ አቀባዮችና እኔም በቀጥታ ጉዳዩን ስንከታተል የተረዳነው ነገር ቢኖር እስካሁን እጅግ ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ የማጎሪያ ጣቢያዎች ውስጥ ያለ በቂ ምግብ፣ ውሃና መሠረታዊ ፍላጎት ማሟያዎች እየተሰቃዩ እንዳሉ ነው፡፡ ቦሌ ደርሰዋል የተባሉትም ይህንን ያህል ቁጥር ያላቸው ሳይሆኑ በጥቂት መቶዎች የሚቆጠሩ መሆናቸውን ነው፡፡ ይህ የእርስዎ የትዊተር መረጃ ትንታኔ ሊሰጥበት የሚያሻው ነው፡፡ ይህንንም የመስጠቱ ኃላፊነት የማንም ሳይሆን የመረጃ አቀባዩ የራስዎ ነው፡፡ አለበለዚያ ህወሃት/ኢህአዴግ ቁጥር ነክ በሆኑ ጉዳዮች የሚያደርገውንና የኢትዮጵያን “የኢኮኖሚ ዕድገት ድርብ አኻዝ ነው” በማለት ለዓመታት ሲፈጽም እንደነበረው የቁጥር ጨዋታ ተዓማኒነት የሌለው አድርገን የምንወስደው ይሆናል፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ለዓመታት በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ እኔም የጋራ ንቅናቄው ዋና ዳይሬክተር በመሆን እነዚህን ወገኖች እንደ መንግሥት የሚታደጋቸው ባጡበት ሁኔታ እጅግ በርካታ የሆኑ ወገኖቼን ስቃይ በቅርብ የመመልከትና የመካፈል አጋጣሚዎች ላይ ተገኝቻለሁ፡፡ በእስር ቤት ሲንገላቱ የነበሩትን፣ ሰብዓዊ ፍጡር ሊያልፍበት በማይችልበት ስቃይ ውስጥ የነበሩትን በዓለም ዙሪያ እየሄድኩ የማነጋገር እና ከእስር የማስፈታት ተግባራትን በመፈጸም ካካበኩት ልምድ አንጻር አሁን በሳዑዲ አረቢያ በተከሰተው ቀውስና በአጠቃላይ በመካከለኛው ምስራቅ ስለሚገኙት ወገኖቻችን ጉዳይ የሚከተሉት የመፍትሔ ሃሳቦች ተግባራዊ እንዲሆኑ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
የመፍትሔሃሳቦች፡-
- ህወሃት/ኢህአዴግ ህዝብና ሚዲያ ሊመሰክር በሚችልበት መልክ የመጓጓዣ አውሮፕላኖችንና መርከቦችን በማዘጋጀት በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን በአስቸኳይ በብዛትና በፍጥነት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ይገባዋል፡፡ ይህንን ለማከናወን የኢትዮጵያ አየር መንገድንም የመደጎም፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጓዦችን የሚጭኑ መርከቦችን የማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት፡፡ መርከቦች ጅቡቲ ዜጎቻችንን ጭነው ወደብ በሚደርሱበት ጊዜ ባስቸኳይ በርካታ የመጓጓዣ አውቶቡሶችን በማዘጋጀት ወደ አዲስ አበባና ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች እንዲደርሱ ማድረግ ይገባል፡፡ ይህንን ወጪ የመሸፈን ኃላፊነት ከአገዛዙ ጀምሮ እስከ ኤፈርትና ሌሎች የህወሃት/ኢህአዴግ የንግድ ሸሪኮች እንዲፈጽሙ ማድረግ በአደጋ እና ቀውስ ወቅት የሚጠበቅ ከመሆን ባሻገር አንድ ኃላፊ ለተሰጠው ቦታ መመጠኑን የማሳያና ብቃቱም መለኪያም ነው፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ መሠረት ግን ስደተኞቹን በማጓጓዝ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እየወሰደ ያለው የሳዑዲ መንግሥት ስለሆነ ህወሃት/ኢህአዴግ ግን በ“ይህንን አደረኩኝ” ስም የወገኖቻችንን ስቃይ ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሙ መቆም አለበት፡፡
- የሳዑዲ አረቢያ በአሁኑ ጊዜ በተግባር ላይ ያዋለችውን የከፋላ አሠራር በተመለከተ ግልጽ ውይይት በማድረግ ወደ ስምምነት ውሳኔ መደረስ አለበት፡፡ በአሠራሩ ውስጥ ያለውን የተበላሸና ለሙስና የተጋለጠውን አካሄድ እንዲሁም ወደ ሳዑዲ የሚመጡ ሁሉ ለችግር እንዲያጋልጣቸው የሚያደርገውን አሠራር በውይይትና በስምምነት አንድ ደረጃ ላይ እንዲደርስ በማድረግ በስቃይ ላይ የሚገኙት ወገኖቻችን በፍጥነት ወደ አገራቸው የሚመለሱበት ሁኔታ መፈጸም አለበት፡፡ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ባልሆነ ጥፋት ፓስፖርታቸውና ሌሎች መታወቂያ ወረቀቶቻቸው ከእነርሱ ጋር ባለመሆኑ ለዚህ ዓይነት ስቃይና መከራ መጋለጣቸው በችግራቸው ላይ ተጨማሪ ችግር መፍጠሩ እየታየ እስካሁን ዝም መባሉ ተገቢ ስላልሆነ ይህ አሰቃቂ ሁኔታ ወደ መጨረሻ ውሳኔ መምጣት ይገባዋል፡፡
- ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የገንዘብ ወጪ ጉዳይ አንዱ አሳሳቢ እንደሆነ ይሰማ፡፡ በሳዑዲም ይሁን በሌሎች አገራት ያሉትን ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራችን ለመመለስ ህወሃት/ኢህአዴግ የኤፈርትን በተለይ ደግሞ የሳዑዲውን ባለሃብትና የኢህአዴግ “ወዳጅ” አላሙዲን ሳይጠይቅ መቅረቱ እርሳቸውም እስካሁን በጉዳዩ ላይ እንደማያገባው ሰው ዝምታን መምረጣቸው የሚያስጠይቅ ነው፡፡ የአባታቸው አገር ተወላጆች በእናታቸው አገር ወገኖች ላይ ይህንን ዓይነት ሰቆቃ ሲያደርሱ በማየት ሼክ መሐመድ አላሙዲ ራሳቸውን የኦፐሬሽኑ አካል በማድረግ የዜግነት ድርሻቸውን እንዲወጡ መጠየቅ የህወሃት/ኢህአዴግ ኃላፊነት ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ እኚህ ሰው በኢትዮጵያን አንጡራ ሃብት አሁን ለደረሱበት ብልጽግና እንዳበቃቸው የሚታወቅ ነው፤ ወደፊት በኢትዮጵያ ያላቸውን የንግድ ኢንቨስትመንት እንዲቀጥል ከፈለጉ በጉዳዩ ላይ የባለአእምሮ ውሳኔ መስጠት የሚጠቅመው ራሳቸውን ነው፡፡ የዛሬውን አያድርገውና በአሁኑ ወቅት በሳዑዲ ወሮበሎች ስቃይና መከራ ከደረሰባቸው ሴቶች አንዷ እናታቸው ወይም እህታቸው ልትሆን ትችል ነበር፡፡
- ህወሃት/ኢህአዴግ በተደጋጋሚ “ባስቆጠረው” ያለመታመን ሬኮርድ ምክንያት አሁን እያደረኩ ነኝ የሚለው ነገር ሁሉ ተዓማኒነት የሌለው ሆኗል፡፡ እርስዎም መግለጫ ሲሰጡ መንግሥት 24 ሰዓት እየሠራ እንደሆነ ገልጸው ነበር፤ በትዊተርም ላይ የሚያቀርቡት ቁጥር ለመታመኑ ራሱን የቻለ አጠያያቂ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም አሠራሩ በሙሉ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው ፍትሐዊ አሠራር እየተካሄደ መሆኑን ለማሳመን እንዲቻል ስደተኛ ወገኖቻችንን ወደአገራቸው የመመለሱን አጠቃላይ ሂደት ዓለምአቀፉን የስደተኛ ድርጅት (IOM) ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና ሌሎች ተዓማኒነት ያላቸው ድርጅቶች በሚሳተፉበትና በሚታዘቡበት መልኩ ግልጽ ሊሆን ይገባዋል፡፡ አሠራሩ ግልጽ ሆኖ ሕዝብ ይታዘብ፣ መልስም ይስጥበት፡፡
- በአሁኑ ጊዜ ሰቆቃው በሳዑዲ ያለ ቢመስልም በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አገራትም ያሉት ወገኖቻችን በከፍተኛ ስቃይ ላይ ስለሚገኙ በተለይ በየመን፣ በእስራኤል፣ በሊባኖስ፣ በዱባይ፣ በሊቢያ፣ በአረብ ኤሜሬት፣ ወዘተ እነዚህ ሁሉ ወደ አገራቸው የመመለሱ ግዴታ የህወሃት/ኢህአዴግ በመሆኑ በተለይ የከፋላ ስርዓት ተግባራዊ በሆነባቸው አገራት ለሚገኙት ልዩ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል፡፡
- በተደጋጋሚ በህገወጥ መንገድ ኢትዮጵያውያንን ሥራ እናስቀጥራለን በማለት በሰው ማዘዋወር ንግድ ውስጥ የሚገኙ ግለሰቦችና የህወሃት/ኢህአዴግ ሸሪክ ድርጅቶች መኖራቸው ሲሰማ የቆየ ነው፡፡ በተለይ በሳዑዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዚህ ንግድ ውስጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለውና ወገኖቻችንን ለባርነት አሳልፎ በመስጠት ሥራ ላይ መጠመዱ ሲነገር የቆየ ነው፡፡ ይህንን የተቀናጀ የወንጀል ተግባር የእርስዎ መ/ቤትም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ነገሩ እንዳልተፈጠረ አድርገው ሲቆጥሩና ሲያድፈነፍኑት ቆይተዋል፡፡ አሁን ያለንበት ሁኔታ ከፍተኛ ምርመራ የሚያስፈልገውና ወንጀለኞች ለፍርድ መቅረብ የሚገባቸው ጊዜ ላይ በመሆኑ ከአገር ውስጥ ጀምሮ እስከ ውጭ አገር ኤምባሲዎች ድረስ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ምርመራ መካሄድ አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር በቀጥታ ተጠያቂው እርስዎና በተዋረድ ያሉ ኃላፊዎች መሆናቸውን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
- በአገር ውስጥ በተለያዩ ከተሞች በየመንገዱ ላይ ወደ አረቢያ ምድር ሥራ እናስቀጥራለን በማለት የተለጠፉት ማስታወቂያዎች በሙሉ ባስቸኳይ መነሳት አለባቸው፡፡ በዚህ “ሥራ” ላይ የተሰማሩት በሙሉ ምርመራ እየተካሄደ ጉዳዩ ይፋ መሆን አለበት፡፡
- ሳዑዲዎች በወገናችን ላይ የሚያደርሱት ግፍ እየታየ አጸፋዊ እርምጃ የመውሰድ አካሄድ አለመተግበሩ አሳሳቢ ነው፡፡ የሰው መብት እየተገፈፈና እየተዋረደ፤ ወገኖቻችን እየተገደሉ ሳዑዲዎች ንግዳቸውን በአገራችን ላይ እያካሄዱ ትርፍ ሲያጋብሱ ዝም መባሉ የህወሃት/ኢህአዴግን ለወገናችን ያለውን ግዴለሽነት የሚያሳይ ከመሆን አልፎ ከዜጎቹ ይልቅ የራሱን ጥቅም የሚሳድድ ለመሆኑ በተደጋጋሚ ያሳየበት ማስረጃ ነው፡፡ ስለሆነም ጉዳዩ ወደከፋ ደረጃ በመሄድ ዜጎች የራሳቸውን እርምጃ መውሰድ ከመጀመራቸው በፊት በሳዑዲ አረቢ በነበሩት በወገኖቻችን ላይ ለደረሰው ተመጣጣኝ ባይሆንም እስካሁን የሳዑዲ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ መቆየታቸው በድጋሚ ሊጠናና ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ንብረታቸውን እያጡ እንደተባረሩ ተመሳሳይ አጸፋዊ እርምጃ በሳዑዲ ድርጅቶች ላይ ባስቸኳይ ሊወሰድ ይገባል፡፡
ለሳዑዲአረቢያመንግሥት፣ሕዝብእናአጎራባቾችበሙሉ፡
በየአገሮቻችሁ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ሠራተኞችን ላይ የምታደርሱትን ስቃይና መከራ ልታቆሙ ይገባል፡፡ ሕዝባችሁንም በዚህ ዓይነቱ ሕገወጥ ተግባር ከመሰማራት እንዲታቀብ ማስጠንቀቂያ ልትሰጡ ይገባል፡፡ በተለይ የጋራ ንቅናቄያችን ለሳዑዲ አረቢ መንግሥት የሚያስተላልፈው መልዕክት ቢኖር በአሁኑ ወቅት በአገራችሁ ላይ እየተካሄደ የሚገኘው የሰብዓዊ መብት ገፈፋ እስልምና ከሚያስተምረውም ሆነ ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ከሰጡት መመሪያ ውጪ የሆነና ለእርሳቸው ተከታዮች በአንድ ወቅት ከለላ በመሆን ላስተናገዷቸው የሰጡትን መልካም ተግባርና ውለታ መዘንጋት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ይህ ዓይነት ምላሽ አይገባቸውም፤ እምነቱም አይፈቅድም፤ ባስቸኳይ ሊቆም ይገባዋል፡፡
ለሳዑዲአረቢያውያን፡
በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ የሆነው ህግ ያስከተለውም ሆነ ወሮበሎች በዜጎቻችን ላይ የፈጸሙት የወንጀል ተግባር የአብዛኛውን ሳዑዲዎች የሚወክልና ሁሉንም በአንድ ሳጥን ውስጥ የሚያስገባቸው እንዳልሆነ የጋራ ንቅናቄያችን ያምናል፡፡ በተፈጸመው ተግባር ያዘኑና ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ የሚያደርጉ ሳዑዲዎች እንዳሉ እገነዘባለን፡፡ በዚህ መልካም ሥራችሁ እንድትቀጥሉ እናሳስባለን፤ እኛም ባለን መልካም ግንኙነት የምንቀጥልና ይህ የደረሰው ሰቆቃ ወደበለጠ የተቀራረበ ግንኙነት ሊያደርሰን የሚችል እንዲሆን እንጥራለን፡፡
ሚኒስትርቴድሮስአድሃኖም፡
በአገራችን ላይ ከሚደርሰው ስፍር ቁጥር ከሌለው ወንጀልና ሰቆቃ በተጨማሪ አሁን በአረቢያ ምድር እየደረሰ ያለው ችግር የጋራ ንቅናቄያችንንም ሆነ እኔን በቀጥታ በጉዳዩ ላይ እንድንቀሳቀስ አድርጎናል፡፡ ይህ የሆነው ግን እርስዎን በዚህ ሥልጣን መንበር ላይ ያስቀመጥዎና አባል የሆኑለት ህወሃት/ኢህአዴግ ለኢትዮጵያውያን ፈጽሞ ግድ የሌለውና በዘር ፖለቲካ ላይ ተጠምዶ ሁሉንም በዘር መነጽር የሚመለከት በመሆኑ ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ከመክሰር አልፎ ከጥቅም ውጭ በሆነበት ባሁኑ ወቅት እርስዎ የሚመሩት የሚ/ር መ/ቤትም ሌላ ኪሣራ ታይቶበታል፡፡ ከአገራችን ሕዝብ በታች የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች አፍሪካውያን ይህንን ዓይነት ሰቆቃ በየትኛውም አገር ሲደርስባቸው አንሰማም፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊ ይህ ልባችንን የሚያደማና “ለመሆኑ ኢትዮጵያውያን አገር አላቸው?” ብለን እንድንጠይቅ ያስገደደን ነው፡፡
ፈጣሪ አሁንም ለአገራችን የምንሠራበት ሌላ ጊዜ እና አጋጣሚ እየሰጠን ያለው፡፡ ለሌሎች ልባችንን እንድናዘጋጅና በአገራችን ላይ ፍትህ፣ ይቅርታ እና ዕርቅ የሚሰፍንበትን ሁኔታዎች በሙሉ እንድናመቻችና ለተግባራዊነቱ ተግተን ልንሠራ የሚገባን ጊዜ አሁን ነው፡፡ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ዜጎች በዘራቸው ወይም በቀለማቸው ወይም በቋንቋቸው፣ ወዘተ ልዩነት ሳይደረግባቸው በቅድሚያ ሰው ሆነው በመፈጠራቸው፤ ከዚያም ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው በአንድነትና በመተሳሰብ የሚኖሩባት እንድትሆን የጋራ ንቅናቄያችን ይተጋል፡፡ ፈጣሪም ይርዳን!
በዚህ ደብዳቤ ላይ ያነሳኋቸውን ነጥቦች በጥንቃቄ ተመልክተው ምላሽ መስጠት እንደሚገባዎት ላሳስብዎት ባልተገባኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም ጉዳዩ የሕዝብ ጉዳይ ስለሆነ ምላሽ መስጠቱም ለሕዝብ ጉዳይ የሚሰጡትን ትኩረት በገሃድ ስለሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ስላልሆነ ማሳሰብ እንዳለብኝ አምኛለሁ፡፡ ስለዚህ መልስዎን እጠብቃለሁ፡፡
በሳዑዲ አረቢና በመላው ዓለም በስደት በሚሰቃዩት ኢትዮጵያውያን ስም፤
ኦባንግ ሜቶ
ዋና ዳይሬክተር
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ
አድራሻ፤
910- 17th St. NW, Suite 419
Washington, DC 20006 USA
ኢሜይል:Obang@solidaritymovement.org.
ድረገጽ:www.solidaritymovement.org
ማሳሰቢያ፤ አቶ ኦባንግ ሜቶ ይህንን ደብዳቤ የጻፉትና የላኩት አስቀድመው በመሆኑና ተዛማጅ ትርጉሙ ዘግይቶ በመውጣቱ ከጊዜ ማለፍ አኳያ አንዳንድ ነጥቦች አሁን እየተከሰተ ካለው ሁኔታ ጋር ላይጣጣሙ ይችላሉ፡፡ አንባቢያ ይህንን የጊዜ ልዩነት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ደብዳቤውን እንዲያነቡት ይሁን፡፡
_______________________________
ይህደብዳቤለሚከተሉትበግልባጭተልኳል፡
Hailemariam Desalegn, Prime Minister of the Federal Republic of Ethiopia
P.O.Box 1031 Addis Ababa, Ethiopia. Fax: 2511-55-20-20
Crown Prince Salman bin Abdulaziz Al-Saud, Deputy Prime Minister and Ministry of Defence
Airport Road, Riyadh 11165, Tel: 1-478-5900/1-477-7313 Fax: 1-401-1336
Jeddah Office TEL: 2-665-2400. Web site: http://www.moda.gov.sa
SAUD al-Faysal bin Abd al-Aziz Al Saud, Ministry of Foreign Affairs
Nasseriya Street, Riyadh 11124 TEL: 1-406-7777/1-441-6836 Fax: 1-403-0159 Jeddah Office Tel: 2-669-0900. Web site http://www.mofa.gov.sa
AHMAD bin Abd al-Aziz Al Saud, Ministry of Interior
PO Box 2933, Riyadh 11134 Tel: 1-401-1944 Fax: 1-403-1185 Jeddah Office
Tel: 2-687-232. Web site: http://www.moi.gov.sa
Muhammad bin Abd al-Karim bin Abd al-Aziz al-ISA, Ministry of Justice
University Street, Riyadh 11137 Tel: 1-405-7777/1-405-5399 Jeddah Office TEL: 2-665-0857. Web site: http://www.moj.gov.sa
Prince Mohammed bin Nawaf Al Saud Ambassador of The Kingdom of Saudi Arabia to the United Kingdom and Ireland
Ambassador of The Kingdom of Saudi Arabia to Ethiopia
Ambassador of The Kingdom of Saudi Arabia to United States
Ambassador of The Kingdom of Saudi Arabia to Canada
Ambassador of The Kingdom of Saudi Arabia to German
Ambassador of The Kingdom of Saudi Arabia to Norway
Ambassador of The Kingdom of Saudi Arabia to Sweden
Ambassador of The Kingdom of Saudi Arabia to Switzerland
Ambassador of The Kingdom of Saudi Arabia to Netherlands
Ambassador of The Kingdom of Saudi Arabia to Australia
Her Majesty Foreign and Common Wealth Office Billy Benet, League of Arab States Headquarters
His Excellency Dr. Nabil El Araby, Secretary General
Egypt Cairo – Secretariat –Tahrir Square Tel: 5752966 – 5750511, Fax: 5740331 – 5761017
PO. Box: 11642
Office of the High Commissioner for Human Rights
United Nations Office at Geneva 1211 Geneva 10, Switzerland
Fax: + 41 22 917 9022 (particularly for urgent matters) E-mail: tb-petitions@ohchr.org
United Nations High Commissioner for Refugees (UNHCR)
International Labor Organization (ILO)
International Organization for Migration (IOM)
African Commission on Human and Peoples’ Rights (ACHPR)
Mr. Donald Yamamoto, Acting U.S. Assistant Secretary of African Affairs
Patricia M. Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia, Addis Ababa, Ethiopia
Mr. Christopher Smith, House of Representatives, Chairman of the Subcommittee on Africa
Human Rights Watch
Amnesty International
ከዚህ በተጨማሪ ደብዳቤው ለሚከተሉት የዜና አውታሮችና የሚዲያ ተቋማት ተልኳል
BBC, the Guardian, New York Times,
A24MEDIA
All Africa
Bloomberg News
NCNB Africa
CNN
REUTERS AFRICA
The East Africa
African Review
VOA Ameharic
VOA-English
እንደራደር —–ተደናግሮ ለማደናገር (ሙሉጌታ አሻግሬ)
ሙሉጌታ አሻግሬ / mulugetaashagre@yahoo.com
የሕዝብ ትግል ማለት ለሕዝብ ጥያቄ እና ብሶት ምላሽ ለመስጠት ብሎም ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት የሚደረግ የመስዋዕትነት ሂደት ማለት ነው። ከቅርብ ግዜ ወዲህ በኢትዮጵያ አገር ወዳዶችና የፍትህ ናፋቂ ዜጎች ህልውናው የተረጋገጠው የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በሁለገብ የትግል ስልት ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ግንቦት ሰባት ከአፈጣጠሩ ህዝባዊ ጥያቄዎችን ማንሳቱ ያልተዋጠለት ወያኔ የግንቦት ሰባት አመራሮችን በሞት ፍርድ ፣ ንቅናቄውን ደግሞ በአሸባሪነት በመፈረጅ የትግሉን እንቅስቃሴ ከጥንስሱ ለማዳፈን ተፍጨርጭሯል።
በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያ እንደሰማነው ደግሞ የንቅናቄውን አካሄድ ለማኮላሸት እችልበታለሁ ብሎ ባመነው የአሸባሪነት ስራ በመሰማራት ቅጥር ነፍሰ ገዳዮችን እስከ መግዛት ደርሷል። አፈጣጠሩ አሸባሪ የሆነው ወያኔ ይህንን መፈፀሙ የለመደው ተግባርና ያደገበት ባህሪው ቢሆንም መንግስት ነኝ እያለ በእነደዚህ ያለ የተልከሰከሰ ተግባር በመሰማራት አገር እያዋረደ ይገኛል።
ቦግንቦት ሰባት መሪዎች እና አባላቱ ላይ የሞት ፍርድ መፍረድ፣ ንቅናቄውን በአሸባሪነት መፈረጅ አልፎ ተርፎም የግድያ ሙከራ ማድረግ የተፈለገውን ውጤት ያላመጣለት ወያኔ እንደራደር በሚል ግዜው ያለፈበት ብልጣብልጥነት ትግሉን ለመበረዝ መሞከሩ የእነዚህ ጎጠኞች አስተሳሰብ በምን ደረጃ ላይ እንዳለና ምን ያህል ወደ ኋላ እንደቀሩ የሚያሳይ ነው።
የግንቦት ሰባት ዓላማ በግልፅ የተቀመጠ የህዝቦች ጥያቄ ነው። በኢትዮጵያ ፍትሃዊና በእኩልነት የሚያምን አስተዳደር ያስፈልጋል። ዜጎች በእውቀታቸውና ችሎታቸው ሰርተው የሚኖሩባት ኢትዮጵያ ፤ ዜጎች በአገራቸው በየትኛውም ስፍራ ተንቀሳቅሰው መኖር የሚችሉባት ኢትዮጵያ ፤ ዜጎች ሃሳባቸውን በሰለጠነ መንገድ የሚገልፁባት ኢትዮጵያ ፤ ዜጎች የተለየ አመለካከት ሲኖራቸው የማይሳደዱባት፣ የማይጋዙባት፣ የማይታሰሩባት ኢትዮጵያ ፤ ለሕግ ተገዥ የሆነ መንግስት የሚመራት ኢትዮጵያ ፤ ግለሰቦች ሳይሆኑ ሕግ የሚመራቸው ተቋማት የሚገኙባት ኢትዮጵያ። ይህ ነው የግንቦት ሰባት ራዕይ። አዎ እነዚህ ህዝቦችን በአንድ ልብ እንደ አንድ ሕዝብ ተባብሮ ለመኖር የሚያስችሉ ቁልፍ የሆኑ ጥያቄዎች ምላሽ እስካላገኙ ድረስ የሚፈለገው ዲሞክራሲና እድገት ይመጣል ብሎ መጠበቅ የቀን ቅዠት ነው።
ወያኔ የሽብርተኛ ሕግ በማለት ባወጣው ዜጎችን አሳቃቂ ሕግ መሠረት “ ግንቦት ሰባትን ጨምሮ ከተወሰኑ ድርጅቶች ጋር በማንኛውም መልኩ ግንኙነት ያደረገ፣ሐሳብ የተለዋወጠ ግለሰብ ይሁን ድርጅት በሙሉ በሽብርተኛነት ይፈረጃል። ለፍርድም ይቀርባል።” ይላል። ይህ ህግ እንደ ህግ በተቀመጠበት ሁኔታ ወያኔ እንደራደር ብሎ በጓዳ በር መምጣቱ ስርዓቱ ምን ያህል የተምታታበትና የሚያደርገውን የማያውቅ፤ የተደናገሩና አዙሮ ማሰብ የተሳናቸው ግለሰቦች ስብስብ መሆኑን ያሳያል። ለእነርሱ ሕዝብ ማስተዳደር ማለት አንዱን ሕዝብ በጥላቻ ሰቅዞ በመያዝ ሌላኛው ከወንዝና ከቀበሌ በላይ እንዳያስብ በማድረግ አገራዊ ወኔን መስለብ ነው።
በማንኛውም መልኩ ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት መፍጠር አሸባሪ የሚያደርግ ሕግ ያወጣ የከፋፋይ ቡድን ይህን ‘የእንደራደር’ (እናደናግር) ጥያቄ ሲያቀርብ (ከልብ እንኳን ቢሆን) ወዲያውኑ እራሱኑ በሽብርተኝነት ያስፈርጀዋል። ይህ ካልሆነ ግን ከዚህ በፊት በስፋት እንደሚታወቀው ሕግ የሚወጣው የተወሰኑ የአገሪቱን ዜጎች ስቃይ ለማባባስና ለእንግልት ለመዳረግ እንደሆነና ከዚህ በተለየ መልኩ ሕግ የማይመለከታቸው ዜጎች እና ቡድኖች እንዳሉ የሚያሳይ ጥሩ ማስረጃ ነው።
ወያኔ ግንቦት ሰባትን ወንጀለኛ እና ሽብርተኛ ብሎ ለመፈረጅ ፓርላማ ሰብስቦ በሚድያ አደባባይ ላይ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ለያዥ ለገናዥ አስቸግሮ እየጮኽ እንደሆነ ሁሉ፤ የእንደራደር ጥያቄውንም ፓርላማ አቅርቦ በሚድያ ሕዝብ እንዲያውቀው ማድረግ አለበት። ይህንን ካደረገ ETVም በሃያ ምናምን ዓመቱ አንድ ቁምነገር እንደሰራ ይቆጠርለት ነበር። ወያኔ አሁን የተያያዘው የልጆች ጨዋታ አኩኩሉ ከአንድ መንግስት ነኝ ባይ ቡድን እንደማይጠበቅ ተገንዝቦ ለህዝቦች እኩልነትና ሰላም የሚበጁ ስራዎችን መስራት ያስፈልገዋል። አዎ ንቅናቄው እንዳለው ወያኔ ከድርድሩ በፊት እዚያው መሬት ላይ ያሉትን ያፈጠጡ የዲሞክራሲና የሕዝቦች እኩልነት እጦት ጥያቄዎችን በመመለስ ከእንቅልፉ እንደነቃ ማሳየት መቻል አለበት።
ወያኔ አይኔን ግንባር ያርገው የተለመደ ክህደቱን እንዳይደረድር በአሁኑ ግዜ ያለውን የአገሪቱ ሁኔታ በጥቂቱ ማስታወስ ግድ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔ ማጎሪያ ስፍራዎች አሁንም በነጻነት ሲቃ በሚቃትቱ ሕዝቦች ተሞልተዋል። ኢትዮጵያ ዜጎች ተወልደው ባደጉበት አካባቢ የመኖር ዋስትና በማጣት ነገን በጥርጣሬ የሚኖሩባት አገር ሆናለች። ኢትዮጵያ ከአንድ ህዝብ (ዘውግ)መወለድ ሃጥያት የሆነባት አገር ሆናለች። ኢትዮጵያ ዜጎች ሃሳባቸውን መግለፅ አይደለም ማሰብ አትችሉም የተባለባት አገር ሆናለች።በአጠቃላይ ኢትዮጵያ እንደ አገር የዜግነት ዋስትና ወደ መቃብር ተወርውሮ ግለሰቦችና ቡድኖች ፈላጭ ቆራጭ የሆኑባት አገር ሆናለች። የአገሪቱ ሉዓላዊነት ተሸጦ የዓለም መሳለቂያ ሆናለች። ከዚህ በከፋ መልኩ ወያኔ ዜጎች በስደት የሚደርስባቸውን ስቃይ ‘ሕገወጦች’ በማለት ለባሰ ስቃይ በማጋለጥ የረከሰና የደነቆረ መግለጫ የሰጠ ቡድን ነው።
ስለዚህ ‘እንደራደር’ ብሎ አዲስ ድራማ በህዝቦች ስቃይ ላይ መተወን ትግሉን ወደ ጠነከረ ደረጃ ሊያሳድገው ካልሆነ በስተቀር ወያኔ ያሰበውን የማዘናጋት ህልም እውን አያደርገውም።
የዜጎች ድምፅ ይሰማ። መከፋፈል ይቁም። ጎጠኝነት ይቁም። አድልዎ ይቁም። መፈናቀል ይቁም። እስራት ፣ ግርፋት፣ እንግልት ይቁም። ሁሉም ዜጎች የዜግነታቸው ዋስትና ይረጋገጥ። ህዝቦች ከታሰሩበት ትናንሽ ‘የክልል’ እስር ቤት ይፈቱ። ማንኛውም ዜጋ ባመነበት እና በፈቀደው አስተዳደር ይተዳደር።
አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
የኢህአዴግ የድርድር ጥያቄና የግል እይታዬ –ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)
አንድ፣ ኢሳት ፣ ኢህአዴግን እና ግንቦት7ትን የተመለከተ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ አንዳንዶች ዜናውን ሲጠራጠሩት ተመልክቻለሁ፣ ያሽሟጠጡም አልታጡም። መጠራጠርም፣ ማሽሟጠጥም የሰውልጅ ባህሪ በመሆኑ አልገረመኝም። ትንሽ የገረመኝ አንዳንድ “ጋዜጠኞች” መረጃውን ካገኙ በሁዋላ በራሳቸው መንገድ አጣርተው ሀቁን ማውጣት ሲችሉ እነሱም እንደሌላው መልሱን በማንኪያ እንዲቀርብላቸው መፈለጋቸው ነው። ጋዜጠኛ “ጥቆማ” ከተሰጠው ተመራምሮ፣ የምርምር ስራውን ይጽፋል እንጅ እንደ አንባቢ መልሱ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብለት አይጠብቅም፣ ጥያቄ መጠየቅማ ማንም ይጠይቃል፣ ጋዜጠኛን ጋዜጠኛ ወይም ተመራማሪ የሚያደርገው ለጠየቀው ጥያቄ ላይ ታች ብሎ መልስ ማቅረብ ወይም በአሰባሰባቸው መረጃዎች ላይ ተንተርሶ ትንተና መስጠት ሲችል ነው ( በሁለተኛው መስፈርት መሰረት ተመስገን ደሳለኝን እና በእስር ላይ የሚገኘው ውብሸት ታየን አደንቃለሁ)።
ሁለት፣ ዜናውን እንደሰማሁ መጀመሪያ የመጣልኝ ጥያቄ “እና ምን ያስገርማል?” የሚለው እንጅ፣ “ድርድሩ የተጠየቀው መቼና በእነማን በኩል ነው?” የሚለው አልነበረም። የአለም የፖለቲካ ታሪክ በግጭትና በድርድር የተሞላ ነው። “ድርጅቶች ይጋጫሉ፣ ይደራደራሉ፣ ምን ያስገርማል?”፣ በፖለቲካ ትግል” በመቃብሬ ላይ ..” የሚባል ነገር የለም። “ለምን ሰበር ዜና ሆነ ታዲያ?’ እንዳትሉኝ፣ ሰበር ዜና ማለት አስገራሚ የሆነ ዜና ማለት አይደለም ።
ሶስት፣ ቀጥሎ የመጣልኝ ጥያቄ “ኢህአዴግ ከግንቦት7 ጋር መደራደር ለምን ፈለገ?” የሚለው ነው። ይህን ጥያቄ ለመመለስ ” የፖለቲካ ድርጅቶች የእንደራደር ጥያቄ የሚያቀርቡት መቼ ነው?” የሚለውን ማየት ነበረብኝ። የፖለቲካ ድርጅቶች በአብዛኛው ለድርድር የሚቀመጡት ህልውናቸውን ለማቆየት ወይም ተደራድሮ የሚገኝ ጥቅም ሳይደራደሩ ከሚገኝ ጥቅም ( ጉዳት) የተሻለ ሆኖ ሲያገኙት ነው። በዚህ ንድፈሀሳብ ላይ ተመስርቶ ኢህአዴግ እና ግንቦት7 አሁን ያሉበትን ቁመና መፈተሽ ይገባል። ኢህአዴግ ከመለስ በሁዋላ ኢህአዴግ አለመሆኑ ይታወቃል።ሊቀመንበሩ ድርጅቱን ይዞ ለመቀጠል ተቸግሯል፣ (ምናልባትም በቅርቡ ይፋ የሚሆኑ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከፍተኛ የገንዘብ ችግር አጋጥሞታል)፣ የ ህዝቡ ልብ እንደሸፈተ አውቋል፣ ወጣቱ ለውጥ እንደሚፈለግ ተረድቷል፣ ሰራዊቱ የሚተማመንበት ሀይል እስኪያገኝ እንጅ እንደሚከዳው ተገንዝቧል። በአጠቃላይ መጪው ጊዜ ለኢህአዴግ ብሩህ አለመሆኑን ግንባሩ ጠንቅቆ ያውቃል። በዚህ አደጋ ውስጥ ሆኖ ጊዜ ለመግዛትና ድርጅቱን ለማጠናከር የድርድር ጥያቄ ቢያቀርብ አይገርምም።
ግንቦት7 ለኢህዴግ “አጣዳፊ ጠላት” (immediate threat) ሆኗል እያልኩ አይደለም፣ ነገር ግን እምቅ ጠላት ( potential threat) መሆኑን አልጠራጠርም ። አንድ ድርጅት ለሌላው ድርጅት አጣዳፊ ጠላት የሚሆነው ፣ አሁን ባለበት ሁኔታ፣ ከተቃራኒው ድርጅት የበለጠ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ የሀይል ሚዛን ሲኖረው ነው። ግንቦት7 ኢህአዴግን ዛሬውኑ ለማስወገድ አይችልም ምክንያቱም ከኢህአዴግ የሚበልጥ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ ሀይል የለውምና ፤ ነገር ግን በጊዜ ሂደት እንደሚያስወግደው መገመት ይቻላል፣ ከመለስ በሁዋላ ያለውን ሁኔታ ብታጠኑ የኢህአዴግ የሀይል ሚዛን ወደ ታች እየወረደ፣ በአንጻራዊ መልኩ የግንቦት 7 የሃይል ሚዛን ደግሞ ወደ ላይ እየወጣ ነው፣ የ ግንቦት7 መሪዎች በዚህ አመት የሀይል ጥቃት እንደሚጀመሩ አስታውቀዋል፣ በዚህ አመት ቀርቶ በሚቀጥሉት 3 አመታት ጥቃት ከፈጸሙ እያደጉ መሆኑን የሚያሳይ ነው ( 4 ፓይለቶች መክዳታቸውንም አንዘንጋ)። የፖለቲካ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ሁለት አይነት ሀይል አለ። አንዱ መቺው ሀይል ( hard power) ሲሆን ሌላው ደግሞ መለስተኛው ሀይል ( soft power) ነው። መቺው ሀይል የሚባለው ወታደራዊው ሀይል ነው። በዚህ በኩል ኢህአዴግ ከግንቦት7 በብዙ እጅ የሚልቅ ጉልበት አለው። ነገር ግን ግንቦት7ትም በዚያው ጎዳና እየተጓዘ መሆኑን መርሳት የለብንም።
መለስተኛ ሀይል (soft power) የሚባለው ደግሞ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎችን፣ ጥራት ያለው የሰው ሀይልን ( መሪም ተከታይም)፣ ህዝባዊ ድጋፍ ፣ የካፒታል አቅም ፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት የመሳሰሉትን ያካትታል። ግንቦት7 በዚህ በኩል ከፍተኛ ጉልበት መገንባቱን መመስከር ይችላል። ከኢህአዴግ ተመጣጣኝ የሆነ ካፒታል ባይኖረውም፣ ከሌሎች ድርጅቶች የተሻለ ካፒታል( ገንዘብ)እንደሚኖረው ከስራዎቹ መገመት ይቻላል ። የተማሩ ሰዎችን በመያዝ በኩልም፣ ከኢህአዴግ ቢበልጥ እንጅ አያንስም። በፕሮጋንዳውና በህዝብ ድጋፍ በኩልም እንዲሁ። እንዲያውም የግንቦት7 የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች ከኢህአዴግ የተሻሉ ለመሆናቸው ብዙ አስረጅ አይጠይቅም፣ የግንቦት7 ራዲዮና ዌብሳይት እስከዛሬ ሳያቋርጥ እየሰራ ነው፣ ጠንካራ የፓልቶክ ደጋፊዎችም አሉት። ኢህአዴግ ራሱ የሚሰራላቸው ፕሮፓጋንዳም ቀላል አይደለም። ኢህአዴግ ቢያንስ በውጭ ያለውን ድጋፉን፣ በተለይም ለጀመራቸው የአባይ እና ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ገንዘብ ለመለመን ሲል ግንቦት7ን ለድርድር ቢጠይቀው አይገርምም። ኢሳት የግንቦት7 ነው ብሎ ስለሚያስብም፣ ኢሳትን እንዲያስቆምለት ልደራደርህ ቢል አሁንም አይገርምም። (በኢሳት ላይ እንኳ ቀልድ የለም፣ መደራደር ከፈለገ ከኢሳት ጋር እንጅ ከግንቦት7 ጋር ሊሆን አይችልም፣ ምክንያቱም ግንቦት7 ስለኢሳት ምንም የሚያገባው ነገር የለምና፣ ከኢሳት ጋር ድርድር ከተጀመረም ለኢሳት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ዙሪያ እንጅ፣ ከስራው ጋር የተያያዘ እንደማይሆን መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ)
አራት፣ ኢህአዴግ ከግንቦት7 ጋር ብቻ ነው ወይ ድርድር የመረጠው? እኔ ባለኝ መረጃ ኢህአዴግ በእነ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሀቅ በኩል ላለፉት 4 ወራት ከእነ አቶ ሌንጮ ለታ ድርጅት ጋር ሲነጋገር ነበር። ይህን ጠንቅቄ አውቃለሁ። ከኦብነግ ጋርም እንዲሁ ተደጋጋሚ የድርድር ጥያቄዎች ቀርበዋል። እነዚህ ድርጅቶች በፓርላማ “አሸባሪ” የተባሉ ናቸው። እና ለግንቦት7 ጥያቄ ቢያቀርብ ምን ይደንቃል? ፖለቲካ እኮ ፊት ለፊት የምትናገርውና በውስጥ የምታደርገው የተለየ ነው። That is politics. በነገራችን ላይ ” አንደኛው የአለም ጦርነት የተጀመረው በድብቅ በሚካሄድ ፖለቲካ የተነሳ ነው” ተባለና ፖለቲካ ግልጽነት እንዲኖረው ተብሎ አዲስ አስተሳሰብ ለረጅም ጊዜ ተራመደ። ፖለቲካ ግን ዛሬም ፊትና ጀርባ እንደያዘ ቀጥሎአል።
አምስት፣ “ጥያቄው በእነማን በኩል ቀረበ?’ የሚለውንም ለራሴ አንስቻለሁ። የድርጅቱ መሪዎች መልሱን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፣ ነገር ግን የራሴን ግምቶች አስፍሬአለሁ። አንድ፣ በቅርቡ በእነአቦይ ስብሀት የተመራ ቡድን አሜሪካ ከርሞ ሄዷል። ሁለት፣ ፕ/ር ኤፍሬም አሜሪካ ከርመዋል፣ ኦነጎችን ለማስታረቅም ላይ ታች ሲሉ ከርመዋል። ሶስት፣ በቅርቡ የአውሮፓ እና የካረቢያን አገሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፣ ብዙ ዲፐሎማቶችም አዲስ አበባ ነበሩ። አራት፣ ኖርዌይና ሆላንድ ሁሌም ተቃዋሚዎችን ለማቀራረብ ይሰራሉ። ይዋል ይደር እንጅ ትክክለኛውን መልስ እናገኛለን። መልሱ ግን ከጠቀስኳቸው ሰዎች ወይም አገሮች በአንዱ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። የእንደራደሩ ጥያቄ ለመቅረቡ ግን መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ። እስከዛው እንደ ጋዜጠኛ መላ ምት በማስቀመጥ ምርምራችን መቀጠሉ ተገቢ ነው።
ስድስት፣ ግንቦት7 ለምን ይህን ድርድር ይፋ ማድረግ ፈለገ? ኢህአዴግ አስቀድሞ በኢቲቪ ” ከግንቦት7 ጋር ሲያደርግ የነበረው ድርድር ከሸፈ” ብሎ መግለጫ ቢሰጥ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት? የግንቦት7 ደጋፊዎች የድርጅቱን መሪዎች በጥሩ አይን የሚያዩዋቸው አይመስለኝም፤ ግንቦት7ትም ውስጥ አለመተማመን ይፈጠርና ድርጅቱን ከሁለት ሊከፍለው ይችል እንደነበር መገመት ይቻላል፣ ዲሞክራሲያዊ ነኝ የሚል ድርጅት ከአባሎቹና ከህዝቡ የሚደብቀው ነገር መኖር የለበትም። ግንቦት7 በመግለጫው “ድርድር መደረግ ካለበት ከሁሉም ድርጅቶች ጋር ነው፣ ሁሉንም ነገር ግልጽ እናደርጋለን የምንደብቀው የለንም” ብሎአል። ትክክል ነው። እውነተኛ ድርድር ሲጀመር ለጊዜው ይፋ የማይወጡ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ድርድር ተጠየቅሁ ብሎ መግለጫ መስጠቱ ግን የሚገርም አይመስለኝም። ግንቦት7 መረጃውን ከኢህአዴግ ቀድሞ ይፋ ማድረጉ ድርጅቱን ከመከፋፈል ማዳን ብቻ ሳይሆን ንቅናቄው ከኢህአዴግን አንድ እርምጃ ቀድሞ የ ሚያስብ መሆኑን ለማሳየትም ጠቅሞታል።
በአገር ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች በኢህአዴግ በኩል ያለውን መልስ ይዘውልን እንደሚቀርቡ ተስፋ እናድርግ።
“ትግራይ በመወለዴ ልዩ ነገር ይገባኛል የሚል አመለካከት የለኝም” –ዶ/ር ኃይሉ አረአያ (ቃለ-ምልልስ)
“ትግራይ በመወለዴ ልዩ ነገር ይገባኛል የሚል አመለካከት የለኝም”
“እነ አቶ ልደቱ የፖለቲካ መጠቀሚያ ነው ያደረጉን”
ዶ/ር ኃይሉ አርአያ
ዶ/ር ኃይሉ አርአያ በኢዴፓ በኋላም በቅንጅት አመራርነት አገልግለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአንድነት ፓርቲ ምክር ቤት አባል ናቸው፡፡ የ”ሎሚ” አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ከዶ/ር ኃይሉ አርአያ ጋር ሰፊ ቃለመጠይቅ አድርጓል፡፡ በሃገር ቤት የሚታተመውን ሎሚ መጽሄት በውጭ ሃገር ለማታገኙት ወገኖች ቃለምልልሱን ዘ-ሐበሻ ትካፈሉት ዘንድ አስተናግዳዋለች።
ሎሚ፡- እርስዎ ያዘጋጁዋት የነበረችው “ፕሬስ ዳይጀስት” ለዲፕሎማቲኩ ማህበረሰብ ኢትዮጵያን በተመለከት መረጃ የሚሰጥ “ታብሎይድ” ነበር፡፡ የትንሿን ጋዜጣ ዝግጅት ለምን አቋረጡት?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ጋዜጣዋ አሁንም እየተዘጋጀች ነው፡፡ እኔ ግን ያቋረጥኩት ጋዜጣዋ የምትፈልገውን ጊዜ እና ጥረት ማበርከት ባለመቻሌ ነው፡፡ በአጭሩ ብዙ ጊዜ ይጠይቃል፡፡ ዝግጅቱ ብዙ ጊዜ የመጠየቁን ያህል ደግሞ ብዙ ጥቅምም አያስገኝም፡፡ ከዚያም ባሻገር ስራው የሦስት ሰዎች ስራ ነበር፡፡ ግን የሦስት ሰዎችን ጥረት የሚጠይቅ ስራ አልነበረም፡፡ በዚያን ጊዜ ሌላ የምሰራው ስራ ስላልነበረ ሁላችንም ትንሽ ትንሽ እየሰራን ነበር የምናሣልፈው፡፡ የአንድ ሰው ስራ ነው፡፡ የአንድ ሰውም የሙሉ ጊዜ ስራ አልነበረም፡፡ ስለዚህ ጊዜ ከማባከን ያንን ለአንድ ሰው ትቶ ሌሎቻችን ሌላ ስራ ብንሰራ ይሻላል በሚል ነው የተውነው፡፡
ሎሚ፡- በደርግ ዘመን “የብሔረሰብ ጥናት ኢንስቲቲዩት” ኃላፊ እርስዎ እንደነበሩ ይታወሳል፤ ኢንስቲቲዩቱ ምን አስተዋጽኦ አበረከተ? አሁን የብሔረሰብ መብት ተከብሯል ከሚባለው ጋር ሲያነጻጽሩት “የብሔረሰብ ጥናት ኢንስቲቲዩት” ሰርቶታል የሚሉትን አብይ ጉዳይ ሊገልፁልን ይችላሉ?
ዶ/ር ኃይሉ፡- በመጀመሪያ የኢንስቲቲዩቱ ኃላፊ አልነበርኩም፡፡ ኢንስቲቲዩቱ ራሱ ኃላፊ ነበረው፡፡ እንደውም ኃላፊው የሚኒስትር ማዕረግ ነበረው፡፡ በኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የብሔረሰቦች ጉዳይ መምሪያ በሚባለው ቦታ በምክትል ኃላፊነት ነበር የምሰራው፡፡ ያ መምሪያ ነው ተቋሙን ያቋቋመው፡፡ ብዙ የሚሰሩ ስራዎች ነበሩ፤ ጥናቶች ነበሩ፤ ሕገ መንግስቱን ለማዘጋጀት ብዙ ጥናቶች መደረግ ነበረባቸው፡፡ የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የነበረው የኛ መምሪያ ብዙ ስራ ሊሰራ ስለማይችል የግዴታ ራሱን ችሎ ለመንቀሣቀስ “ኢንስቲቲዩቱን” መመስረት አስፈላጊ ነበር፡፡ ስለዚህ “የብሔረሰቦች ጥናት” ኢንስቲቲዩት ተቋቋመ፡፡ ነገር ግን በመምሪያችን ስር ነበር፡፡
የእኛ መምሪያና ኢንስቲቲዩቱ አብረው ነበር የሚሰሩት፡፡ ጥናቶች ሲካሄዱ አብረን ሁላችንም እንሳተፋለን፤ አመራር የሚሰጠው ግን ከመምሪያው ነበር፡፡ በሁሉም ዘርፍ ለአምስት ዓመት ያህል ነው ኢንስቲቲዩቱ ጥናት ያካሄደው፡፡ በዛን ጊዜ የተሰሩ ስራዎች ኢህአዴግም ከመጣ በኋላ ብዙ ጠቅሞታል ብዬ ነው የምገምተው፡፡ ያኔ የህግ መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ሰው አሁን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሉ ይመስለኛል፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህግ አማካሪ ናቸው፡፡ ሌሎችም በሀገሪቱ አሉ የተባሉ ምሁራን ተሰባስበው ከፍተኛ ጥናት አካሂደዋል፡፡ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ጥናቶች ናቸው የተካሄዱት፡፡ ጥናቶቹ አልባከኑም ብዬ አምናለሁ፡፡ በርግጥ የተፈለገው ሕገ መንግስት በተደረጉት ጥናቶች መሠረት ተቀርጿል፡፡ መቅረፅ ብቻም አይደለም፤ ስራ ላይም ውሏል፡፡ በተለይ በብሔረሰቦች ላይ የተደረገው ጥናት በዝርዝር ነው የተካሄደው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የብሔረሰቦች መብት ምን ያህል ተከብሯል የሚለው የትኩረት መጠን ካልሆነ በስተቀር ያኔ የተደረገው የብሔረሰቦች ጥናት እና የተሰጠው የብሔረሰቦች ትኩረት በጣም ከፍተኛ ነበር፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ስለ ብሔረሰቦች መብት መከበር እንደ አዲስ የጀመረ በማስመሰል ሲናገር ስሰማ በጣም አዝናለሁ፡፡ በዛን ጊዜ የነበረውን ነገር አልተከታተለውም፤ ውጊያ ላይ ስለነበር ሊከታተልም አይችልም፡፡ ውጊያ ላይ እያለ ባይከታተልም ስልጣኑን እና ኢንስቲቲዩሹኑን ከተረከበ በኋላ በዛን ጊዜ የነበሩ ሰነዶችን መመርመር ይችል ነበር፡፡ ሰነዶቹ አሁንም ይኖራሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ ኢህአዴግም ተጠቅሞባቸዋል ብዬ ነው የምገምተው፡፡
“የብሔረሰቦች መብት” ኢህአዴግ እንደ አዲስ የጀመረው ጉዳይ አይደለም፡፡ በባህላቸው፣ በቋንቋቸው…በሌላውም አቅጣጫ ኢህአዴግ እንደ አዲስ እንደጀመረ አድርጐ ነው የሚያወራው፡፡ ይህንን ትዝብት መቼም ለታሪክ እንተወዋለን፡፡ የደርግ ስርዓት ሌሎች ድክመቶች ሊኖሩበት ይችላል፡፡ የብሔረሰቦችን ጉዳይ በተመለከት ግን መሠረቱን ያስቀመጠው የደርግ ስርዓት ነው፡፡ ኢህአዴግ ምናልባት አጠናክሮታል፣ አስፋፍቶታል ማለት ይቻላል፡፡ አንደ አዲስ ጀመርኩት የሚለው ነገር ግን ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ይህ ሊስተካከል ይገባል፤ ምክንያቱም ታሪክ ራሱ ቁጭ ብሎ የሚመሰክርበት ጉዳይ ስለሆነ በዝምታ ማለፍ ነው የሚሻለው፡፡ የብሔረሰቦችን ጉዳይ በተመለከተ እንዲሁ ለይስሙላ ከሚደረግ በስተቀር ነፃ የሆነ ለውጥ ተደርጓል ብዬ አልገምትም፡፡ ምናልባት በጥቅም፣ በሀብት አከፋፈል በጀትን በተመለከተ ለብሔረሰቦች የሚመደበው ገንዘብ አሁን በከፍተኛ መጠን ጨምሯል፡፡ ሌላው የቅርፅ ጉዳይ ነው፡፡ ብሔረሰቦች የሕገ-መንግስት ባለቤት ሆነዋል፡፡ ህገመንግስትን መስርተዋል፤ ሕገ መንግስት አላቸው፤ ሰንደቅ አላማም ያውለበልባሉ…እነዚህ ከቅርፅ አኳያ ለውጦች ናቸው፡፡ እነዚህ የቅርፅ ለውጦች በተግባር ቢደገፉ ጥሩ ይሆኑ ነበር፡፡ ነገር ግን አልተደገፈም፡፡ ምክንያቱም ብሔረሰቦች አሁንም መሠረታዊ የሆኑ ችግሮች አሉባቸው፡፡ መሠረታዊ የምላቸው በኔ በኩል የህግ መከበር ነው፡፡
ህጐች ይጣሳሉ፤ መብቶች ይደፈራሉ፤ ምን ያህል ነፃነት እንዳላቸውም እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ምንም እንኳን ስርዓቱ ፌዴራል ቢሆንም ቅርፁ ፌደራላዊ ቢሆንም በተግባር ግን “አሃዳዊ” ነው፤ ምክንያቱም በደርግ ጊዜ መንግስት “አሃዳዊ” ነበር፡፡ ክልሎች የአስተዳደር መብት ነበራቸው፡፡ ያም ቢሆን በሚገባ ተግባራዊ አልሆነም፡፡ ከይዘት አኳያ በደርግ አሃዳዊ መንግስትና በኢህአዴግ ፌደራላዊ መንግስት መካከል ልዩነት አለ፡፡ “ደርግ” የነበረው የውስጥ አስተዳደር ነው፤ የኢህአዴግ ግን ፌዴራል ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ብሔረሰቦች ሕገ መንግስት አላቸው፣ የራሣቸው መንግስትና ባንዲራ….አላቸው፡፡ በዛን ጊዜ የነበረው ኢሠፓ መዋቅሩን ታች ድረስ አውርዶ ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው ኃይል እርሱ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ምንም እንኳን በቅርፅ “ፌደራላዊ” ቢባልም ሀገሪቱን ጠርንፎ በአሃዳዊ መልክ ነው የሚያስተዳድረው፡፡ በሁለቱ መካከል የይዘት ልዩነት የለም፡፡ ለውጡ ምንድነው? ብትለኝ ጥቂት ነው፡፡ እምቢልታና መለከት የሚያስነፉ አይደሉም፡፡ አሁንም ብሔረሰቦች ይጨቆናሉ፡፡
የሚጨቁኗቸው ደግሞ የራሣቸውን ቋንቋ የሚናገሩ የራሣቸው ወገኖች ናቸው፡፡ ስለዚህ አሁንም ከጭቆና እና ከችግር አልወጡም፡፡ ፌደራላዊ ስርዓት ጥሩ ሆኖ ከአሃዳዊ ሲለይ አልታየም፡፡ ሕዝቡ ቢጨቁነኝም ይጨቁነኝ፣ ቢረግጠኝም ይርገጠኝ፣ የኔን ቋንቋ እስከተናገረ ድረስ የሚል ከሆነ ሌላ ነገር ውስጥ ነው የሚገባው፡፡ ለኔ ቋንቋ አይደለም ትልቁ ነገር:: ከዛ ባለፈ ሕግ መከበር አለበት፤ ፍትህ መከበር አለበት፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር አለበት፡፡ እውነተኛ ነፃነት መኖር አለበት፡፡ አሁን የብሔረሰቦች ቀን ተብሎ “በዓል” ይከበራል፡፡ ሰባት ዓመት ሙሉ ተከብሯል መሰለኝ፡፡ ስምንተኛው በዓል በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ነው የሚከበረው፡፡ በአንድ በኩል ይህ ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም በብሔረሰቦች መካከል ያለውን ስሜት በማጠናከር እና በራስ መተማመንን ለማምጣት የሚረዳ ነገር ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንዲሁ ዘፈንና ጫጫታ ሆኖ መሠረታዊ ጉዳዮች ሣይደረጉ ሲቀሩና እዛው በቦታው ሲመለስና እንደ ድሮው የሚጨቆን ከሆነ ምንድነው ትርጉሙ? የሰው ልጅ ፍላጐት ከዛ ያለፈ ነው፡፡ ይሄ ግን እየተመለሰ አይደለምና ከዳንሱና ከጭፈራው ጐን ለጐን የብሔረሰብ ነፃነት ሊከበር ይገባል፡፡ ሊሰሩ የሚችሉበት ነፃነት ይኑራቸው፡፡ ትምህርትን፣ የጤና አገልግሎትን ያየን እንደሆነ ተስፋፍቷል፡፡ “በቁጥር” ተስፋፍቷል፤ “በጥራት” ግን ገና ነው፡፡ መስፋፋቱ ጥሩ ነው፤ ግን ቁጥር ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ይሄ መንግስት አሁን እየጠቀሰልን ያለው ቁጥር ነው፡፡ ይህን ገንብቻለሁ እያለ በሁሉም ዘርፍ ይገልፃል፡፡ ያ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ በጥራት መሻሻል አለበት፡፡ ቁሣዊና ሰብአዊ ልማት አለ፡፡
መንግስት እየተገበረ ያለው ቁሣዊ ልማትን ነው፡፡ ሰብዓዊ ልማት የለም፡፡ ሰብዓዊ ልማት ያለ ነፃነት፣ ያለፍትህ፣ ያለ ዴሞክራሲ ይሄን ያህል ጠቃሚ አይደለም፡፡
ሎሚ፡- በሚያዝያ 1983 ዓ.ም. ደርግ ባቋቋመው ሸንጐ የመጨረሻ ስብሰባ ላይ አባል እንደመሆንዎ ተገኝተው ለኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም የተናገሩትን ለዚህ ትውልድ መረጃ እንዲሆን ቢያስታውሱን?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ጊዜው በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ ሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ነበረች፡፡ ሀገሪቱን እመራለሁ፣ ግንባር ቀደም ነኝ የሚለው የፖለቲካ ድርጅት (ኢሠፓ) በየጊዜው እየተሰባሰበ የሀገሪቱን ሁኔታ እየገመገመ ሕዝቡ ምን እንደሚልና በሚለው መሠረት ምን መደረግ እንዳለባቸው ማወቅ ነበረበት፡፡ ግን ሳያደርግ ቀረ፡፡ ስብሰባዎች እንዲካሄዱ ነበር ብዙ ጊዜ የምንጐተጉተው፡፡ ከዛ ከፓርላማ ስብሰባው በፊት ኢሠፓ ተሰብስቦ የዚህችን ሀገር ሁኔታ እንዲገመግም፣ መፍትሄ እንዲፈልግና ተግባራዊ እንዲያደርግ በየጊዜው በሚደረጉ የመሠረታዊ ድርጅት ስብሰባዎች እንከራከር ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት ውጤት አልተገኘም፡፡ ነገሮች እየተባባሱ ሄዱ፡፡
በመጨረሻ የተደረገው ተስፋ የመቁረጥ ዓይነት ሙከራ ነው፡፡ ሙከራው ቢዘገይም ከሚቀር ይሻላል፡፡ ምንም ካለማድረግ የተወሰነ ነገር ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ይሄ የግል ስሜቴ ነው፤ የግል ስሜቴን ለመግለፅ ነው የሞከርኩት፡፡ ግን አሁን መለስ ብዬ ያለንበትን ሁኔታ ሳይ ደግሞ ያን ያህል ጊዜ መዘግየት አልነበረብንም እላለሁ፡፡ ጊዜ መስጠት አልነበረብንም የሚል እምነት አለኝ፡፡ አሁን ደግሞ ለዚህ ስርዓት አላግባብ ተገቢ ያልሆነ ጊዜ እየሰጠን ነው፡፡ በስልጣን በቆየ ቁጥር እየበሰበሰ ነው የሚሄደው፡፡ በተፈጥሮው ስልጣን ያሞስናል፤ ያበሰብሳል፡፡ አንድ ወገን፣ አንድ ኃይል ስልጣን ላይ ከሚፈለገው በላይ በቆየ ቁጥር እየበሰበሰ ይሄዳል፡፡ ይሄ እኮ የተፈጥሮ ሂደት ነው፡፡ ሌሎች ሀገሮች የፕሬዚዳንትና የጠ/ሚኒስትር (በተለይ “የፕሬዚዳንት”ን) የስልጣን ቆይታ የቱንም ያህል ጥሩ ቢሆን ከስምንት አመት በላይ አያልፍም፡፡ ስለዚህ ሀገሪቱን ትጐዳለህና ቦታ ልቀቅ ነው የምትባለው፡፡ የኛ መንግስት እስካሁን ድረስ ብዙ ቆይቷል፡፡ 22 ዓመት ብዙ ነው፡፡ በኔ እምነት መበስበስ ከጀመረ ቆይቷል፡፡ የመበስበሱ ምክንያቶች በየጊዜው እየታዩ ናቸው፡፡ መቀጠል የለበትም ብለን መናገር አለብን እንጂ ዝም ማለት የለብንም፡፡ ከዚህ በፊት ዘግይተን ከነበረ እናዝናለን፡፡ በስንፍናችን እናዝናለን፤ እንቆጫለን፡፡ ነገር ግን ከዚያ ተምረን ያ መደገም የለበትም እንላለን፡፡ የሀገራችን ጉዳይ መፍትሄ ማግኘት አለበት፡፡ ገደብ የሌለው ስልጣን መፍትሄ ማግኘት አለበት፡፡ እነሱ ሥልጣን ላይ የተቀመጡት ሕዝብ ስለፈለጋቸው አይደለም፡፡ በእንዴት ዓይነት ሁኔታ ስልጣን ላይ እንደወጡ የኢትዮጵያ ሕዝብም እነሱ ራሣቸውም ያውቁታል፡፡ አዲሱ ትውልድ በተለይ ወጣቱ ትውልድ መናገር መቻል አለበት፡፡ ለመብቱ ለነፃነቱ መቆም መቻል አለበት፡፡ አስፈላጊ ከሆነም ደግሞ መስዋዕትነት መክፈል አለበት፡፡
ሎሚ፡- በዚያ ወቅት በትግራይ ተወላጆች ላይ ግድያ ሲፈጸም የድፍረት ንግግር ለመናገር የገፋፋዎት የተለየ ምክንያት ምን ነበር?
ዶ/ር ኃይሉ፡- በወቅቱ ካለፈው ታሪኬ የተነሣ እንደ አደገኛ ሰው የታየሁ አልመሰለኝም፡፡ ፍራቻም አልነበረኝም፡፡ እንዲያውም የትግራይ ተወላጅ መሆኔን
ያስታወስኩት እኮ ዘግይቼ ነው፡፡ ጐሣ፣ ጐጥ… እየተነሣ ሲመጣ ነው ይሄ ነገር
መጉላት የጀመረው፡፡ እንጂ በፊት እኔ የዚህ ተወላጅ ነኝ፣ የዛ ተወላጅ ነኝ የሚል
ነገር አልነበረም፡፡ ስሜቱም አልነበረኝም፤ ትግራይ ነው የተወለድኩትና በተወለድኩበት አካባቢ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነው ያደግኩት፡፡ በአጋጣሚ ትግራይ ማይጨው ራያ ተወለድሁ፡፡ የተወለድኩበትን አካባቢ እቀበላለሁ፡፡ ግን እዚያ ትግራይ በመወለዴ ልዩ ነገር ይገባኛል የሚል አመለካከት የለኝም፡፡ እዚያ መወለዴም ስጋት አላሳደረብኝም፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ሰው ነኝ፤ ከዛ በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ በዛ ምክንያት እንዲህ እሆን ወይ ጉዳት ይደርስብኝ ይሆን ወይ ብዬ አላስብም፡፡ እንደውም በዛን ጊዜ ኮ/ል መንግስቱ ፊት እንደዛ ስናገር ሰዎች በጣም ደንግጠው ከአካባቢው ለመራቅ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ በኋላ ደግሞ ታስታውስ እንደሆነ ኮ/ል መንግስቱ በፃፉት ጽሁፍ /እኔ እንኳን መፅሐፉን ሣይሆን በቴፕ ነው የሰማሁት/ “ዶ/ር ኃይሉ እንደዛ የተናገረው ምናልባት ዘመዶቹ አምቦ ስለደረሱ ይሆናል፤ /ሣቅ/ ነው፤ ለኔ እንዲህ ዓይነት ስሜት ነው የፈጠረብኝ” ብለው ነበር፡፡ በጣም አሣዘነኝ፤ ምናቸው ነው ለኔ ዘመድ የሚያደርጋቸው?… በጣም አዘንኩ፤ የማንነት ጉዳይ አንዳንዴ ብወድም ባልወድም ብልጭ ማለቱ አይቀርም፡፡ ትኩረት የምሰጠው ነገር ግን አይደለም፡፡ ፍርሃት አልነበረብኝም፡፡ ያኔ የትግራይ ተወላጆች ብቻ አይደለም የሚገደሉት፤ ማንም ያንን መስመር የሚቃወም ሁሉ ነበር የሚገደለው፡፡
ሎሚ፡- ኮ/ል መንግስቱ እንደዛ ከተናገሩ በኋላ ቤትዎ ገብተው በሰላም አደሩ?… ሌሊቱን የት አሣለፉ? የኮ/ል መንግስቱ የደህንነት ሰዎች ምላሽስ ምን ነበር?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ምንም ችግር አልደረሰብኝም፡፡ ሰዎች ወስደው የት እንዳሳደሩኝ አላስታውስም፡፡ ብቻ የሆነ ቦታ ነው የወሰዱኝ፡፡ የተለየ ነገር አልገጠመኝም፡፡ አስታውሳለሁ፤ ኮ/ል ተስፋዬ ወ/ስላሴ /የደህንነት ኃላፊው/ “ጐሽ ጥሩ ነው ያደረግከው” ብሎ መለስ ቀለስ እያለ እየፈራ እየቸረ ነው ያናገረኝ፡፡… /ረዥም ሳቅ/፡፡… በኋላ ጡረታ እንድወጣ ደብዳቤ ተፃፈ፡፡ በነገራችን ላይ ቀደም ብዬ ነበር ጡረታ እንድወጣ የጠየቅኩት፡፡ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ጥያቄዬ ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቶ ነበር፡፡ ወዲያው የተወሰደውን እርምጃ ሰዎች ነግረውኛል፡፡ …ኮ/ል መንግስቱ በጣም ተቆጥተው ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ ለምነን አባብለን ነው ያስታገስናቸው ብለውኛል፡፡ አንደኛው የማውቀው ወዳጄ “እንዲያውም እግራቸው ላይም እስከመውደቅ ደርሰናል“” ሲል ነበር የነገረኝ፡፡ ይህ ምን ያህል እውነት እንደሆነ አላውቅም፡፡ መናደዳቸው አያከራክርም፤ እግዚአብሔር ይመስገን የከፋ ነገር ግን አልደረሰብኝም፡፡ በእሣቸው የደህንነት ሰዎችም የደረሰብኝ ነገር የለም፡፡
ሎሚ፡- እንግዲህ ውይይታችን ሰፊ ነውና ወደኋላም ወደፊትም እያልን ጥያቄ እናንሳ፤ ወደ ቅርብ ጊዜው እንመለስና ወደ ቅንጅት (ምርጫ 97) ግርግር እንምጣ፡፡ በወቅቱ አቶ ልደቱ የነበረው አቋም በእርግጥም የኢዴፓ ውሣኔ ነበር? በቅርቡ አቶ ልደቱ ከመፅሔታችን ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ “የስልጣን ጥያቄ ስላልነበረን የበሰሉ ሰዎች ቢመሩት ይሻላል ብለን ነው ዶ/ር ኃይሉ አርአያን እና ዶ/ር አድማሱን ከቤታቸው አምጥተን ስልጣን እንዲይዙ ያደረግነው” ብሏል፡፡ ይሄን እንዴት ይመለከቱታል?
ዶ/ር ኃይሉ፡- በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብዙ መናገር አልፈልግም፡፡ ይሄ በእኔና በአንተ ቃለ መጠይቅ ላይ ብቻ ተገልፆ የሚያልቅ አይደለም፡፡ በጣም ሰፊ የሆነ ታሪክ ነው፡፡ ግን መናገር ካለብኝ አንድ ወጣት (ታምራት ታረቀኝ) የሚባል መፅሐፍ ፅፎ ነበር፡፡ ምናልባት እዚያ ላይ ያለውን ብደግመው በቂ ይሆናል፡፡ ተጠቅመውብናል ማለት እችላለሁ፡፡ በዛን ጊዜ የነበሩ የኢዴፓ አመራር /እነ አቶ
ልደቱ/ ተጠቅመውብናል፡፡ ከተጠቀሙብን በኋላ ጊዜው ሲመጣ እኛን ወደ ጐን ለማግለል ሞክረዋል፡፡ አቶ ልደቱ ብዙ ውይይት የሚከፍት ሰው ነው፡፡ መጠቀሚያ አደረገን እንጂ በምሁርነቴ ጠርቶ ይሄ ቦታ ይገባሀል ብሎ አይደለም ቦታ የሰጠኝ፡፡ በኔ ውስጥም የሚሰማኝ ይሄ ነው፡፡
ሎሚ፡- አቶ ልደቱ “ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከቅንጅት ጋር የትም አንደርስም” ብሎ
ይከራከር ነበር ሲልም ገልጿል፤ ይሄስ እውነት ነው?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በተቃራኒው ነው እሱ የገለፀው፡፡ ከቅንጅት ጋር አብሮ ስለመስራት ነበር የኔ ክርክር የነበረው፡፡ አቶ ልደቱ በወቅቱ ብዙ ነገር የተወሳሰበና የተተበተበ ነገር ነበር የሚያነሣው፡፡ እንዲያውም “ቅድመ ሁኔታዎች” በሚል ይከራከር ነበር፡፡ በኔ በኩል በቅንጅት ዙሪያ መግባባት አለብን የሚል አቋም ነው የነበረኝ፡፡ በአቶ ልደቱ የተገለፀው የተገላቢጦሽ ነው፡፡
ሎሚ፡- ኢዴፓ ያንን አጋጣሚ አክሽፏል ብለው ያምናሉ?
ዶ/ር ኃይሉ፡- አዎ! አምናለሁ! በሁለት ምክንያት፡፡ አንደኛ ከምርጫ በኋላ የቅንጅት አመራር የአራቱ ፓርቲ አመራር ከልደቱ በስተቀር ለመዋሃድ ውሣኔ ሲያሳልፍ እና መሪዎቹ ፊርማቸውን ሲያሳርፉ በስምምነቱ ላይ አቶ ልደቱ በኢዴፓ ሰነድ ላይ ማህተም ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማህተሙ ሳያርፍ ቀረ፡፡ ይሄ የሆነው ማህተሙን የሙጥኝ ብሎ በመያዙ ነው፡፡ ሁለተኛ ለምርጫ ቦርድ በቅንጅት የተጠየቀው የውህደት ጥያቄ ተግባራዊ እንዳይሆን የሚል ደብዳቤ በማስገባቱ ያለጥርጥር ያንን ዕድል አክሽፎታል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይሄን ስል ግን ሌሎችም ችግሮች አልነበሩም ማለቴ አይደለም፡፡ ሌሎችም ችግሮች ነበሩ፡፡ ቀሪዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶች ራሣቸው አስፈላጊውን ጉባኤ አካሂደው ማሟላት ያለባቸውን ነገሮች አሟልተው አንድ መሆን ሲገባቸው ሣይችሉ ቀርተዋል፡፡ ያ ብቻም ሣይሆን ያከሸፈው ሌሎች የውስጥ ችግሮችም ነበሩ፡፡
ሎሚ፡- በወቅቱ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ሲመረጡ በአቶ ልደቱ ላይ ምን ዓይነት ስሜት ነበር የታየው?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ብርቱካን በተመረጠችበት ጊዜ አቶ ልደቱ መበሣጨቱ ምንም የሚያከራክርና አንድና ሁለት የሚባል ነገር አይደለም፡፡ በጣም በጣም ተበሣጭቷል፡፡ በግል የተመለከትነው ነገርም ነው፡፡
ሎሚ፡- ከእርስዎ ጋር በኢዴፓም ሆነ በቅንጅት ውስጥ ሲሰሩ የነበሩት ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ ከፖለቲካ የራቁበት ምክንያት ምንድን ነው?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ይህንን ጥያቄ መመለስ የሚገባው እሱ ዶ/ር አድማሱ ነው፡፡ እንደው ስገምተው ግን አንደኛ የትምህርትና የስራ ዕድልም ስላገኘ ይመስለኛል፡፡ ለባለቤቱም ጭምር ነው ይህ ዕድል የመጣው፡፡ ምክንያቱም የኛን ሃገር የመሰለ ፖለቲካ በሩቅ የሚከናወን አይደለም፡፡ ምናልባት አንድ ቀን ይመለስና የጀመረውን ትግል ይቀጥልበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ የዚህ ሀገር ተቃዋሚዎች ሁኔታ ደግሞ የሚያበረታታና ተስፋ የሚያጭርም አይደለም፡፡ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ አሁን አንዳንድ መሻሻሎችና መስተካከሎች የሚኖሩ ይመስላሉ፡፡ ምናልባት እነዚህ የ33ቱ ፓርቲዎች የመሰባሰብና አንድ ላይ ለመስራት የመወሰን ጉዳይ የሚያበረታታ ነው፡፡ ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራችን በፊትም ቢሆን እንኳን ሩቅ ላለና እዚህ ሀገር ውስጥ ላለም የሚያበረታታ ተስፋ የሚሰጥ አይደለምና አልፈርድበትም፡፡ እንዲህ እግዚአብሔር ሲፈቅድ ወደሀገሩ ጠቅልሎ መጥቶ እገባበታለሁ ካለ መልካም ነው፡፡ ውስጡ ግን ማሰቡና መጨነቁ አይቀርም፡፡
ሎሚ፡- አቶ ልደቱ በሕይወትህ ምን የሚፀፅትህ ነገር አለ ለሚለው ጥያቄጠይቄው ነበር፡፡ ሲመልስም “በሕይወቴ ከሚፀፅተኝ ነገር አንዱ ምሁራንን ማመኔ ነው፡፡ ለምሁራን የነበረኝ ግምትና አስተሳሰብ ነው የሚጸጽተኝ” ብሏል፤ አባባሉን እንዴት አዩት?
ዶ/ር ኃይሉ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ማንን አመነና ነው፡፡ ምንስ ተጓደለበት ነው የኔ ጥያቄ፡፡ ሣልፈልግ ወደዚህ የማልወደው ነገር ውስጥ እያስገባኸኝ ነው፡፡ የሚፀፅተኝ ሊል አይገባም፤ ምንም የሚፀፅት የተፈጠረበት ነገር የለም፡፡ የእሱን ተወውና በራሴ ግን በምሁራን ዙሪያ ከተባለ “ምሁራን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ንቁ ተሣታፊ አለመሆናቸው ነው የሚያሣዝነኝ፡፡ የማመንና ያለማመን ጉዳይ አይደለም፡፡ አምነናቸው ጉድ አደረጉን፤ አሳልፈው ሰጡን የሚል መንፈስ ያለው
ይመስላል አባባሉ፡፡ በምን ጉዳይ ምንድን ነበር የጠበቀው? ምንስ ቀረበት?
አዲሱ ነጠላ ዜማ፣ ድርድር –ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)
በሳውዲ የተነሳው የወገን ሰቆቃ ገና አልበረደም። ስቃዩ የበለጠ ሲከፋ እንጂ ሲቀንስ አላየንም። ለውጭ ምንዛሪ ማግኛ ሲባል ልክ እንደ ባርያ ንግድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ በኩል የተላኩት ምስኪን ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በገዥው ፓርቲ እንደታሰበው አልሆነም። እንዲያውም ሌሎች መዘዞችን አስከትሎ መጥቷል። ዲያስፖራው እንደገና ተነሳ። ለቦንድ ግዢና ለግንቦት ሃያ በዓላት የሚሰባሰቡትም ጭምር ገዢው ፓርቲን ማውገዝ ጀመሩ። የስደተኛው ጎርፍም እንደሱናሚ ማእበል ያንን ጎራ ማጨናነቁ ግልጽ ነው። ወቅት እየጠበቀ የሚነሳው የክረምቱ ነቀርሳ አሁን በነበረከት ስምዖን ላይ ጠና ያለ ይመስላል። ይህ ህመም ማስታገሻ ያስፈልገዋል። ዘላቂ ሳይሆን ግዚያዊ ማስታገሻ። መቼም ለነቀርሳ ዘላቂ መፍትሄ የለውም። ለግዜው ግን እድሜ ማራዘሚያ … የድርድር ጥያቄ።
የኢሕአደግና የግንቦት ስባት ድርድር ? ግርማ ካሳ
የኢሕአደግና የግንቦት ስባት ድርድር ? ግርማ ካሳ
Muziky68@yahoo.com
ዲሴምበር 3 ቀን 2013 ዓ.ም
«የኢሕአዴግ መራሹ መንግስት ለግንቦት ሰባት የእንደራደር ጥያቄ አቀረበ» ሲል ኢሳት ሰበር ዜና አሰማን። ዶር ብርሃኑ ነጋንም በማቅረብ በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንዲሰጡም አድርጓል። ምንም እንኳን የቀረበዉን ዘገባ ከሌላ ምንጭ ማጣራት ባይቻልም፣ ዜናዉ እዉነት ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ግን ይሰማኛል። አገዛዙ ከኦብነግ፣ ኦነግ ከመሳሰሉ ጋር ድርድር እየጀመረ፣ የማቋረጥ ልማድ እንዳለው ታሳቢ በማድረግ። የግንቦት ሰባት «እንደራደር» ጥያቄም ከዚያ የተለየ አይሆንም። በሳዊዲ
የድርድር ጥያቄዉን ይዘው የመጡ መልእክተኖች እነማን እንደሆኑ የተገለጸ ነገር የለም። ዶር ብርሃኑም «ጥያቄዉ የመጣዉ ከብዙ አቅጣጫዎች ነው» ከማለት ዉጭ ትንፍሽ ያሉት ነገር የለም። ከአንዳንድ የግንቦት ስባት አመራር አባላት ጋር የቅርብ የስራ ትውውቅ ባላቸውና፣ በቅርቡ ኢትዮጵያን በጉበኙት ፣ በተከበሩ አና ጎምዜ ይሆን መልእክቱ የመጣዉ ? ወይንስ ብዙ ጊዜ በሽምግልና ተግባር በመሰማራት በሚታወቁት በተከበሩ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳእቅ ? ወይስ በሃይማኖት አባቶች ? ወደፊት የምናውቀዉ ይሆናል።
ድርድር መቼም ቢሆን የሚደገፍ እንጂ የሚጠላ አይደለም። እርቅና ሰላም እንዲሰፍን፣ ኢትዮጵያዊያን ልዩነቶቻችንን በዉይይት እንድንፈታ የሚገልጹ በርካታ ጽሁፎችን አስነብቢያልሁ። ነገር ግን በኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር ለማስፈንና የዲሞክራሲ ተቋማትን ለመገንባት ያስችል ዘንድ፣ ያለ አንዳች ቅደም ሁኔታ ለመነጋገር ፍቃደኛ ከሆኑ፣ አገር ዉጥ ካሉ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር፣ ኢሕአዴግ «በፍጹም አልደራደርም» እያለ፣ በሌላ በኩል «ጠመንጃ አንስተን እንታገላለን» ለሚሉ የድርድር ጥያቄ ማቅረቡ ግን ምን ይባላል ? በአንድ በኩል ብእር አንስተዉ በመጻፋቸው፣ «ከግንቦት ሰባት ጋር ተነጋግራቹሃል። ከሽብርተኞች ጋር አብራቹሃል» እየተባሉ፣ በዉሸት ክስ ዜጎች ለእድሜ ልክ እስራት እየተደረጉ፣ በሌላ በኩል ከ«ሽብርተኞቹ» ግንቦት ሰባቶች ጋር መነጋገር፣ ግብዝነትን አያሳይምን? አገዛዙ ሌላ አላማ ኖርት እንጂ በርግጥ ሰላም ፈልጎ ነዉ ማለት እንችላለን ?
በነገራችን ላይ ኢሕአዴግ ድርድር የጠየቀው ግንቦት ሰባትን ፈርቶ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት። በዚህ ላይ ብዙ አንሳሳት። ግንቦት ሰባትን ኢሕአዴግ አይፈራም። እስቲ ንገሩኝ ለምንድን ነዉ ኢሕአዴግ ግንቦት ሰባትን የሚፈራዉ? የድርድር ጥሪ መቅረቡ በምንም መስፈርትና መለኪያ የግንቦት ሰባት ጥንካሬንም አያሳይም። ጥንካሬ የሚለካው በፍሬና በዉጤት ነዉ። ጥንካሬ የሚለካው በሜዳ ነዉ። ጥንካሬ ኢሕአዴግ በሚያወራዉ አይለካም። በመሆኑም ግንቦት ሰባቶች «ኢሕአዴግ ድርድር ከኛ ጋር የፈለገዉ ፈርቶ ነዉ፤ ስላሰጋነው ነዉ፤ ጥንካሬያችንን አይቶ ነዉ፤ ወዘተረፈ» እያሉ ብዙ ዳንኪራ ባይመቱ ይሻላል። ሰዉ ይታዘባቸዋል። ይልቅስ እራሳቸዉን ቢመረምሩ ዉጤት በሚያመጡ እንቅስቃሴዎች ላይ ቢሰማሩ ይበጃል ባይ ነኝ። (በዚህ አርእስት ላይ፣ ይረዳቸው ዘንድ ፣ ለግንቦት ስባቶች የተጻፈ ምክር አዘልና አቅጣጫ ጠቋሚ ግልጽ ደብዳቤ በቅርብ ጊዜ አቀርባለሁ)
እንደሚመስለኝ ኢሕአዴጎች ለመደራደር ጥያቄ ያቀረቡት፣ የአለም አቀፍ ማህበረሰብን ግፊት ለመቀነስ ነዉ። አራት ነጥብ። ግንቦት ሰባት ከሻእቢያ ፍቃድ ዉጭ ሊደራደር እንደማይችል፣ ጥያቂያቸዉን ዉድቅ እንደሚያደርገዉ ከወዲሁ ያዉቃሉ። ነገር ግን «ይኸው እናንተ ከተቃዋሚዎች ጋር ተደራደሩ ስትሉን፣ እሺ ብለን፣ በራሳችን አነሳሽነት፣ ለግንቦት ሰባት፣ ኦብነግ ጥያቄ አቀረብን። እነርሱ ግን ፍቃደኛ አልሆኑም። ከኦብነግ ጋር ተደራደርን ፣ ግማሾቹ እሺህ ብለው የተወሰኑት ግን እምቢ አሉ። ታዲያ ምን አድርጉ ነዉ የምትሉን ? » ለማለት ነዉ።
አገር ቤት ያሉ ፓርቲዎችን «እንደራደር» ቢሉ እሺ እንደሚሉ፣ በዚያም ድርድር የፖለቲካ ምህዳሩን በትንሹም ቢሆን መክፈት ኢሕአዴጎች እንደሚኖርባቸው፣ የፖለቲካ ምህዳሩን በትንሹ ከከፈቱና በአንጻራዊነት ዴሞክራቲክ ምርጫ ከተደረገ፣ እንደሚሸነፉ ያውቃሉ። በመሆኑም ባለ አቅምና ጉልበት፣ ጠንካራ ፓርቲዎችን እያዳከሙ፣ ዋጋ ቢስና ምናምንቴ ዘጠና፣ መቶ የሚቆጠሩ ፓርቲዎችን አየለቃቀሙ፣ ዲሞክራሲ እንዳለ ለማስመሰል ይሞክራሉ። አገር ቤት ያሉት ጠንካራ መሪዎችን በአንድ በኩል እያሰሩና እያወኩ፣ ዉጭ ካሉ፣ ሊስማሙ ከማይችሉ ጋር እንደራደር በማለትም፣ የ«ሰላም አርበኞች» መስሎ ለመታየት ይጥራሉ። አሳዛኝ !!!!!
ድርድርና ሰላም የሚጠላ የለም። ኢሕአዴግ በቅንነት ለእርቅ ተዘጋጅቶ፣ እራሱን አሻሽሎ፣ የሕዝብን ጥያቄ ሰምቶ ፣ የዜጎችን መብትና ነጻነት አክብሮ፣ ለአገራችን ልማትና ብልጽግና ከሁላችንም ጋር በጋራ ለመስራት ቢዘጋጅ፣ ደስታዬ ገደብ አይኖረዉም። ያም እንዲሆን የድርሻዬን ከመወጣት ወደ ኋላ አልልም። ጸሎቴም ነዉ።
ነገር ግን ፣ ያ አልሆነም። ኢሕአዴግ ዉስጥ ያሉ ጥሩ ሰዎች እየተዋጡ፣ ከመጋረጃ ጀርባ የተቀመጡ፣ ጥቂት ፈላጭ ቆራጭ የሆኑ፣ አክራሪዎች ድርጅቱን ወደ ገደል እየከተቱት ነዉ። ምንም እንኳን በአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የሚመራ የመንግስት መዋቅር ቢኖርም፣ አክራሪዎቹ የሚመሩት ሁለተኛና ሚስጥራዊ የመንግስት መዋቅር ያለ ይመስለኛል። በዚህ መዋቀር ያሉቱ የፈለጉትን ይገድላሉ። የፈለጉትን ለፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጥተዉ ያሳስራሉ። የፈለጉትን መሬት ለዉጭ አገር ዜጎች (ለእንደነ ሳዉዲዎች) በርካሽ ይሸጣሉ። የፈለጉትን እቃ ያለ ቀረጥ ያስገባሉ። የፈለጉትን ከአገር ያስወጣሉ ። ለዘመዶቻቸው ቢዝነስ ስለተፈለገ፣ ዜጎችን በግፍ አፈናቅለው ፣ የዜጎችን ቤት አፍርሰው በቦታዉ የነርሱን ሕንጻ ያሰራሉ። የፈለገ ወንጀል ሲሰሩ አይጠየቁም። እነርሱ በዊስኩ እጃቸዉን እየታጠቡ፣ ሌላዉ ወገናችን ግን ለስደት፣ ለጠኔ የተጋለጠ ሆኗል።
ምንም እንኳን ከኢሕአዴግ ዘንድ ሊታዩ የሚችሉ ጥቂት መልካም አዝማሚያዎች ላይ በር መዝጋት ባያስፈልግም፣ ምንም እንኳን ኢሕአዴግ ዉስጥ ያሉ ጥሩ ኃይላትን ማበረታቱ ጠቃሚ ቢሆንም፣ እንቁላሎቻችንን በኢሕአዴግ ቅርጫት ዉስጥ ብቻ ማድረጉ ግን ጉዳት አለው። የአገዛዙንም ርካሽ ፕሮፖጋንዳም ሆነ የድርድር ወሬ ከቁም ነገር መዉሰድ ያለብንም አይመስለኝም። ኢትዮጵያዉያን አንድ ዜና በመጣ ቁጥር፣ ወደዚህና ወዲዚያ እየነፈስን፣ ከዋናዉ ነገር ላይ ትኩረታችንን ማንሳት ማቆም ይኖርብናል። ዉጤት ከማያመጣና በስሜት ላይ ብቻ ከተመረኮዘ እንቅስቃሴዎች አልፈን መሄድ ይጠበቅብናል። በተለይም ደግሞ፣ አጠንክሬ የማሰምረበት፣ ሻእቢያ ወይንም ሻእቢያ ጋር ያሉ ቡድኖች ነጻ እንዲያወጡን አንጠብቅ። አሜሪካና አዉሮፓውያንም ጥቅማቸውን እንጂ ለኢትዮጵያ አያስቡም። «እናንተ ለመብታችሁ ካልታገላችሁ እኛ ምን አገባን ነዉ ?» ነዉ የሚሉት።
እግዚአብሄር በጸጋዉ የቸረንን፣ ጥቂቶች የሰረቁንን መብታችንን፣ ነጻነታችንና እኩልነታችንን የምናስጠብቀዉ እኛዉ እራሳችን ነን። በአሥር ሚሊዮኖች እንቆጣራለን። እያንዳንዳች ከልባችን «በቃ» ብንል፣ ለመብታችን ብንነሳ፣ ብንቆርጥ፣ ብንጨክን፣ የለበስነዉን ፍርሃት አዉልቀን ብንጥል፣ ለውጥ የማናመጣበት ምንም ምክንያት የለም። እኛን ማስፈራራትና መከፋፈል በመቻሉ እንጂ፣ ኢሕአዴግ እፍ ቢባል በቀላሉ የሚበን፣ የሞተና የበሰበስ ድርጅት ነዉ። እራሳችንን አሳንሰን አንመልከት። በዘር በሃይማኖት አንከፋፈል። ከአዲግራት፣ እስከ ሞያሌ፣ ከወልወል እሰከ አሶሳ፣ በቆላዉና በደጋዉ የአገራችን መሬት የምንኖር፣ በስደት በአለም ዙሪያ የተበተንን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንነሳ። ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ ጥይት ሳይተኮስ፣ በሰለጠነ የፍቅር ፖለቲካ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ማወጅ እንችላለን። ሰላማዊ በሆነ የእምቢተኝነት ዘመቻ የአገዛዙን ቀንበር መስበር እንችላለን። እየገደልን ሳይሆን እየሞትን አናሸንፋለን።
ልብን የሚነካዉ የኢትዮጵያዉያን ጉዞ በሳዑዲ አረቢያ
ከሳዲቅ አህመድ
የሳውዲ አረቢያው ቀውስ መከሰት ለኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)
የሳውዲ አረቢያው ቀውስ መከሰት ለኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ
ፍቅርና አንድነት ትምህርት ሰጥቶ ይሆን?
በፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ
በአረብ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሠራተኞች ላይ የሚደረገው ህገወጥ የማሰቃየት እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም! በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በሪያድና በአዲስ አበባ ከተሞች ባሉ ገዥ አካሎች እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት እረገጣ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ ለጉዳዩ ልዩ የሆነ ትኩረት እንዲሰጡትና ለወገኖቻቸው የማያቋርጥ ድጋፍ እንዲያደርጉ ምቹ አጋጣሚን ፈጥሯል፡፡ ባለፉት በርካታ ሳምንታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየተፈጸመ ባለው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት እረገጣ የቪዲዮ ምስል መታየት መጀመሩን ተከትሎከአውስትራሊያ እስከ አሜሪካ ባሉ በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ቁጣ እና የልብ ስብራት በማስከተሉ ምክንያት በየአካባቢያቸው ባሉ የሳውዲ አረቢያ ቆንስላዎችና የዲፕሎማሲ ማዕከላት በሮች ላይ ፊት ለፊት በመሰለፍ በግንባር በመግጠም ባሳዩት ቆራጥ ኢትዮጵያዊ የተቃውሞ ወኔ የመብት ረጋጮችን የሳውዲ አረቢያ ገዥ ባለስልጣኖች በማሸማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ6 – 7 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን/ት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ከሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት የሳውዲ አረቢያ ገዥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየፈጸመ ያለውን ህገወጥ እርምጃና የሰብአዊ መብት እረገጣ በአስቸኳይ እንዲያቆም በመጠየቅ በሳውዲ አረቢያ ከሚገኙ ወገኖቻቸው ጋር የማያቋርጥ ትብብርና ወገናዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በአደባባይ በግልጽ አሳይተዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ከአትላንታ እስከ ሲያትል ከተሞች በመሰለፍ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች በመውጣት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡ የሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች በየደረሱባቸው ቦታዎች ሁሉ ባነሮችን በመያዝ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ “ሳውዲ አረቢያ ሃፍረተኛ! ሃፍረተኛ! ሃፍረተኛ! “ሳውዲ አረቢያ ሃፍረተኛ!” በማለት ተቃዎሟቸውን አሰምተዋል፡፡
በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ እየተደረገ ያለው የሰብአዊ መብት እረገጣና ህገወጥ አያያዝ በአስተማማኝ መረጃ ላይ ተደግፎ የቀረበ በመሆኑ ሊካድ የሚችል ጉዳይ አይሆንም፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch እ.ኤ.አ ዴሴምበር 1/2013 ባወጣው ዘገባ መሰረት “የሳውዲ አረቢያ መንግስት በግዛት ክልሉ ውስጥ በሚኖሩ የውጭ አገር ሠራተኞች ላይ የኃይል እርምጃን በመውሰድ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞችን የአካል ጉዳት ሰለባ እንዲሆኑ አደርጓል፣አንዳንዶችንም ገድሏል፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉትን ኢትዮጵያውያን/ት ደግሞ ያለበቂ ምግብና መጠለያ አቅርቦት በጊዚያዊ የእስር ቤት ማዕከሎች አጉሮ ይገኛል“ በማለት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ ማህበረሰብ በወገኖቹ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በመመልከት በተግባር እያሳየ ያለውን ንዴትና ቁጣ ሶስት ዋና ዋና ነገሮች በትክክል ይገልጹታል፡፡ 1ኛ) የሳውዲ አረቢያ የመንገድ ላይ ዘራፊዎች እና የፖሊስ ሌቦች እንዲሁም ህገወጦች ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሠራተኛ ዜጎችን ከየቤታቸው በማስወጣት በየመንገዱ በመጎተት በቃላት ለመግለጽ በሚያስቸግር መልኩ ጭካኔና አረመኔነት በተመላበት ሁኔታ ሲደበድቡ፣ ሲዘርፉና ሲያስሩ በመታየታቸው፣ 2ኛ) የሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል የእራሱ ፖሊሶችና ሁከት ፈጣሪዎች በእብሪት ተነሳስተው በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ ያለምንም ማቋረጥ ጥቃት ሲሰነዝሩ እያየ ምንም ነገር ሳያደርግ በማንአለብኝነት መመልከቱ፣ 3ኛ) በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ከመሰሉ ገዥ የሳወዲ አረቢያ አካል ጋር በመሞዳሞድ የገንዘብ እርዳታ ስለሚያገኝ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ደካማነትና የእግር ላሽነት ባህሪ በግልጽና በዓለም የአደባባይ መድረክ ላይ በማሳየት ላይ በመገኘቱ የሚሉት ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ እና በአትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል እየደረሰ ባለው የሰብአዊ መብት እረገጣና ህገወጥ አያያዝ ሁለት የማይገናኙና ተጻራሪ የሆኑ ምላሾን ሲያንጸባርቁ ይታያሉ፡፡ በአንድ በኩል በውጭ አገር ያለው የዲያስፖራ ማህበረሰብ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ስደተኛ ሠራተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየደረሰ ባለው መከራ እና ስቃይ ከወገኖቹ ጎን በጽናት ሲቆም በተጻራሪው ገዥው በአዲስ አበባ የሚገኘው አካል ደግሞ ጠንከር ያለ መግለጫ ከማውጣት ወደኋላ ያፈገፍጋል፣ እንደ አሉሚኒየም ብረት ወደኋላ ይለመጣል፣ የሳውዲን ገዥ አካልን ጫማ ለመላስ ወደ ተረከዙ ያጎነብሳል፣ እንዲሁም አምባገነኑን አረብ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ በአጭሩ ሎሌነቱን በይፋ አሳይቷል!፡፡
ከወባ ትንኝ ተመራማሪነት በፍጥነት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተሸሙትና እ.ኤ.አ ከ2015 አገራዊ “ምርጫ” በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ይጠቀልላሉ ተብለው የሚጠበቁት ቴዎድሮስ አድሃኖም የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣኖችን ውሳኔ እና ህገወጥ ስደተኞችን የማባረር ፖሊሲያቸውን ኢትዮጵያ እንደምታከብር በድፍረት ለብዙሃን መገናኛ ይፋ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ በተደረገው የዜጎች ህገወጥ አያያዝ ስሜታቸው የተጎዳ መሆኑን ለሳውዲ አረቢያው አምባሳደር በቀልድ መልክ ገልጸው ይደልዎ ብለዋል፡፡ በዲፕሎማሲያዊ በእራስ መተማመን መልክ አድሃኖም “ይህ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል፡፡ እርሳቸውና ገዥው አካል ነገሮችን ሁሉ በቁጥጥራቸው ስር እንዳደረጉ በሚመስል መልኩ አድሃኖም “ዜጎቻችንን ለመቀበል ሙሉ በሙሉ ዝግጅታችንን ያጠናቀቅን መሆናችንን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ“ በማለት የምጸት ጩኸት አሰምተዋል፡፡
ማዘናቸውን የገለጹበት ሁኔታ ከልብ ያልሆነ፣ ለታይታ እና ለይስሙላ የተደረገ፣ የባለስልጣንነት ሞገስ የሌለውና እርባናየለሽ ነበር፡፡ እንዴት አንድ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጠ ባለስልጣን የእራሱን ዜጎች ለሚያዋርድ የሌላ አገር ፖሊሲ “ክብር” ይሰጣል? እንዴት አንድ ሰው የአንድን በባዕድ አገር የሚኖሩ ወንድሞችና እህቶች አስገድዶ የሚድፍር፣ የሚገድል፣ ሰውነትን የሚበጣጥስ፣ የሚያሰቃይና ተጠርጣሪ ነው በማለት ያለፍርድ የሚገድል ኃይል በእራሱ አስተሳሰብ በመመራት “ተቀባይነት የለውም” የሚለውን ትርጉምየለሽ የዲፖሎማሲ ቃል ይመርጣል? እንዴት አንድ ሰው በትክክለኛው የዲፕሎማሲያዊ ንዴትና ቁጣ ኖሮት በህጋዊ መንገድ ጉዳዩን ለመከታተል ሳይሞክር “ስሜቴ ተጎድቷል” እንዲሁም “አዝኛለሁ” ሊል ይችላል?
ስዕል የአንድ ሺ ቃላትን ያህል የመናገር ኃይል ያለው መሆኑ ሀቅ ነው፡፡ የሳውዲ አረቢያዎች የሰብአዊ መብት እረገጣ የቪዲዮ ምስሎች የዲያስፖራውን ቁጣ የመቀስቀስ ኃይል ነበራቸው፡፡ በቀላሉ ሊታይ የማይገባው እውነታ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የተፈጸመው አሳንሶ የማየት፣ የማዋረድ፣ ማሰቃየትና ሰብአዊ መብትን መርገጥ በተመሳሳይ መልኩ በተራው ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በኢትዮጵያው ገዥ አካል ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሲፈጸም ቆይቷል፡፡ የአድሃኖም ገዥው አካል ነጻውን ፕሬስ በማሽመድመድ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የሰብአዊ መብት እረገጣ ከህዝብ ዕይታ ለመደበቅ ያደረገው ጥረት በአብዛኛው ስኬታማ ቢሆንም ሁሉንም ደብቆ ለማስቀረት ግን አልተቻለውም፡፡
ብዙ አስደንጋጭ የፎቶግራፍ ምስሎች በማስረጃነት ቀርበዋል፣ እነዚህም የፎቶግራፍ ምስሎች የሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ከፈጸመው የሰብአዊ መብት እረገጣ የበለጠ የኢትዮጵያ ገዥ አካል በተራ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የፈጸመው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት እረገጣ ፎቶግራፍ የበለጠ አስደንጋጭ ነው፡፡ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በኖቬምበር 2013 የተፈጸመው የሰብአዊ መብት እረገጣ በኢትዮጵያ ገዥው አካል በተራ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በኦክቶበር 2013፣ በኖቬምበር 2012፣ በዴሴምበር 2011፣ ወዘተ በተመሳሳይ መልኩ ተፈጽሟል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ገዥው አካል እስረኞችን ከህግ አግባብ ውጭ አስገድዶ የእምነት ቃል እንዲሰጡ ያደረገውን ሂዩማን ራይትስ ዎች በዘገባው “በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ማዕከላዊ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት እስረኞች በማያቋርጥ ሁኔታ በጥፊ ይጠናገራሉ፣ በእርግጫ ይደበደባሉ፣ በቦክስ ይነረታሉ፣ በዱላና በጠብመንጃ ሰደፍ ይደበደባሉ፡፡ ጥቂቶቹ በሚያሰቃይ ሁኔታ እጆቻቸውን ከኩማዎቻቸው ላይ በማንጠልጠል፣ ወይም ደግሞ እጆቻቸውን ከጭንቅላታቸው በላይ ከፍ አድርገው በማቆም ማሰርና ለብዙ ጊዜ እየተደበደቡ እንዲቆዩ ማድረግ“ አካቶ አቅርቦታል፡፡
ዋናው ከክስተቱ የተማርኩበት አጋጣሚ፣ የነቃና የተበሳጨ ህዝብን መመልከት፣ እውነት ለመናገር ለእኔ አሁን ባለው የሳውዲ አረቢያ ሁኔታ ዋናው “የተማርኩበት አጋጣሚ” ብዬ የምወስደው አብዛኛው የዲያስፖራ ማህበረሰብ በዚህች አጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰባስቦ ተቃውሞውን በመግለጽ እረገድ ውጤታማ መሆኑ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ በዚህ አይነት ቀልጣፋ በሆነ መልክ፣ ኃይልና አስደናቂ ፍላጎት ስልታዊ በሆነ መልክ ዓለም አቀፍ የቁጣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አይችልም የሚለውን የቀድሞ እምነቴን እንድሰርዝ አድርጎኛል፡፡ በእርግጠኝነት ለመናገር ይህ ድርጊት ለእኔ “ይበል” የሚያሰኝ ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አይቻለሁ፣ ከተለመዱት የመብት ተሟጋቾች በስተቀር አብዛኛው ለእኔ ዝምተኛ ብቻ ሳይሆን የተኛም ጭምር መስሎ ይታየኝ ነበር፡፡ ነገር ግን እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2013 በሚያስደንቅ ሁኔታ ግዙፉን የኢትዮጵያን ዲያስፖራ በንቃት ሲሳተፍ ተመልክቻለሁ፡፡ ወንዶች ሴቶች፣ ወጣቶችና አዛውንቶች በሳውዲ አረቢያ በወንድሞቻቸውና በእህቶቻቸው ላይ የሚፈጸመውን ስቃይና የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም በመቶዎችና በሺዎች በመሆን እየወጡ ከጎናቸው ተሰልፈዋል፡፡
ይህን ግዙፍ ዲያስፖራ እንዲነቃ ያደረገው ምንድን ነው? እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ትልቁ ስጋቴ በሳውዲ ያለው ቀውስ ካበቃ በኋላ ይህ ግዙፍ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ተመልሶ ይተኛ ይሆን የሚለው ነው፡፡
የሁላችንም ትምህርታዊ አጋጣሚዎች፣
የኢትዮጵያ ስደተኛ ሰራተኛ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በደርሰባቸው የሰብአዊ መብት እረገጣና ማሰቃየት የኢትዮጵያ ገዥው አካል ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ ልዩ የሆኑ ትምህርታዊ አጋጣሚዎችን በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ሰጥቷል የሚል እምነት አለኝ፡፡ “ትምህርታዊ አጋጣሚ” የሚለውን ሀረግ ለብዙሀን ትምህርት፣ ለህዝቦች መነሳሳትና ለግለሰቦች በንቃት መሳተፍን ሊያመጣ የሚያስችል በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ልዩ ድርጊት በማለት ተርጉሜዋለሁ፡፡ ከዚህ በመቀጠል የሚቀርቡትን ጥቂት የማስተማሪያ እና የመማሪያ ትምህርቶች የትርጉም ቅርጽ ከግንዛቤ በማስገባት ማስተላለፍ የምፈልገው ዋናው መልዕክት ቀውስ በደረሰ ጊዜ ብቻ የሚወረወር ምላሽ ነጻነትን፣ ዴሞክራሲን ለመጎናፀፍ እና በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትን ለማስከበር ስኬታማ እና ለድል የሚያበቃ ስሌት አይደለም፡፡
በሳውዲ አረቢያ እንደደረሰው ቀውስ ሁሉ በሌሎችም ትክክል ናቸው ብለን በምናምንባቸው ጉዳዮች ሁሉ ልዩ የሆነ ዓለምአቃፋዊ ትብብር፣ ወንድማማችነት፣ እህትማማችነት እና መነሳሳትን በተረጋጋ ሁኔታ ማንጸባረቅ ይጠበቅብናል፡፡ በሳወዲ አረቢያ ቀውስ ምክንያት የታየውን የመነሳሳት “አዚም” ደግመንና ደጋግመን ማሳየት ይኖርብናል፡፡ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን/ት በቋሚነት ለሰብአዊ መብት መከበር መሟገትና መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡
በኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ መነጽር መመልከት፣ ተራ ንግግር እራሳችንን ከስሜታዊነት፣ ግንፍልተኝነት እና ከቀውስ ለመውጣትና የእራሳችንን እጣ ፈንታ እራሳችን ወሳኝ እንድንሆን ሰላማዊ ሽግግር ለማድረግ “የኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት” ምናባዊ ቅርጽ የሚል ላስተዋውቅ፡፡ የነቃውን ግዙፍ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ለዘለቄታው እንደነቃ ለዘላለሙ ጠንቃቃ ተመልካች ሆኖ አንዲቀጥል ልዩ ስትራቴጂ መንደፍ ያስፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ያሉ ችግሮችና ጉዳዮች ምን ምን እንደሆኑ እናውቃለን፣ ጥቂቶች በጣም ቀላል ነገሮች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ መፍትሄ ለማግኘት የበለጠ አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ በግልጽ በመተማመን እና በመወያየት ችግሮችን ካልፈታናቸው በስተቀር ታላቁን የነቃ የዲያስፖራ እንቅስቃሴ ወደኋላ በመመለስ እንዲተኛ ማድረግ ያስችላሉ፡፡ ከአንድ ቀውስ ወደሌላ ቀውስ መሸጋገር እኔ በበኩሌ ያመኛል፣ ይደክመኛልም፡፡
የዲያስፖራው ማህበረሰብ እርስ በእርስ እንዲዋደድ፣እንዲደራጅ፣ እንዲታደስ እና ለውጤት እንዲንቀሳቀስ ማድረግ አለብን፡፡ ከእራሳችን እና ከእያንዳንዳችን ጋር ንግግሮች ያስፈልጉናል፡፡ “በኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት” እመለከታለሁ፡፡ ንግግር ለማድረግ መስታወቱን ከግድግዳው ጋር እሰቅለዋለሁ፡፡ እኔን ወደኋል ይመለከተኝ እና እንዲህ ይላል፣
ሁላችሁም ማድረግ ትጀምራላችሁ ነገር ግን አትጨርሱትም፡፡ መስታወቱ እንዲህ በማለት ያስታውሰናል፣ “በቅርቡ በህይወት የተለዩት የኢትዮጵያ ገዥ አካል መሪ እንዲህ ብለው ነበር ’የአትዮጵያ ዲያስፖራዎች ብዙ ነገሮችን ይጀምራሉ፣ የጀመሩትን ግን በፍጹም አይጨርሱትም፣ ታዲያ ስህተት ተናግረዋልን?’”
ጥያቄውን ላለመመለስ ቃላትን ለመፈለግ እሞክራለሁ፡፡ “እውነት ለመናገር ብዙ ብዙ ነገሮችን እንጀምራለን፣ ነገር ግን በጣም ጥቂቶችን ብቻ ለውጤት እናበቃለን፣ ከእኔ የግል ተሞክሮ ማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ፣ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አጠባበቅ ትግል በንቃት ስቀላቀል ያየኋቸው፣ የሰማኋቸው፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የተሳተፍኩባቸው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ወይም የአድቮኬሲ ቡድኖች፣ ግብረ ኃይሎች፣ ኮንፈረንሶች፣ ፎረሞች፣ የምክክርና የውይይት ቡድኖች፣ ቴሌኮንፈረንሶችና የግል ስብሰባዎች፣ ወርክሾፖች፣ ስምምነቶች፣ የአካዳሚክ ሴሚናሮች እና ሲምፖዜሞች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ አንዱም ፍሬ አፍርቷል ብየ ለመናገር አልደፍርም“:: ወዲያዉኑ እራሴን በፍጥነት አርማለሁ፡፡ “አንድን ነገር በግማሽ አሳክተናል፣
በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ኤችአር/HR 23ን ማን ይረሳዋል (ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እና ተጠያቂነት ድንጋጌ)፣ አዎ! ያ ታላቅ ትምህርታዊ አጋጣሚ ነበር፡፡ ያ የህግ ሰነድ በቅርቡ በህይወት ለተለዩት ጠቅላይ ሚኒስትር የእራስ ምታት፣ የልብ ስብራት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጀርባ ውጋት፣ የጥርስ ቁርጥማት እና የጆሮ ህመም ሆኖባቸው ነበር! ኤችአር 2003 የተለያየ አመለካከት የነበራቸውን የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ወደ አንድ እንዲመጡና ተቀራርበው ዓላማቸውን በጋራ እንዲያሳኩ ለማድረግ አስችሎ ነበር::
መስታወቱ አቁአረጠኝ፡ “እንዲህ ነው እንጂ! ሁላችሁም አንድ ሁሉን አቀፍ የሆነ ጠንካራ መሰረት ያለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች የዲያስፖራ ማህበረሰብ ድርጅት ማቋቋም ትችላላችሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ለማሰቃየት፣ ከህግ ውጭ ለሚፈጸም ግድያ፣ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ማዋል እና እስራቶች፣ ድብደባዎች እና ለምርጫ ድምጽ ስርቆት የተለየ ትኩረት በመስጠት የማያምን ማን አለ?” ግልጽ የሆነውን መልስ ላለመስጠት ወሰንኩ፡፡ አንድ ነገር ስንጀምር ወደ ስኬታማነት ልናመጣው ይገባል ወይም ደግሞ የፈለገውን ጊዜ ቢውስድም እየሞከርነው መቀጠል ይኖርብናል፡፡
ሁልጊዜ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሁላችሁም አንድን ነገር ለመቃወም በንዴት በስሜታዊነት ትነሳላችሁ፡፡ መስታወቱ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፣ “በኢትየጵያ ያለው ታማኝነት የጎደለው ገዥው አካል አንድ ነገር ሲያደርግ ወይም ሳያደርግ ሲቀር ሁላችሁም ሁልጊዜ በንዴትና በስሜታዊነት ምላሽ ለመስጠት የምትሞክሩት ለምንድን ነው?“ በፍጥነት የሳውዲ አረቢያን ሁኔታ ሃሳብ መጣብኝ፡፡ “ስሜታዊነት መሆን ምንም ስህተት የለበትም፡፡ ሰው መሆንና ስሜታዊ አለመሆን ማለት ሮቦት መሆን ማለት ነው፡፡
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሳውዲ አረቢያ ከሰው በወረደ መልክ ግፍ ሲፈጸምባቸው እያየን እና እየሰማን ለምንድን ነው የማንናደደውና ከቁጥጥር ውጭ የማንሆነው?“ መስታወቱ በጥንቃቄ መጠየቁን ይቀጥላል፣ “ከተነፈስክ በሁላ ንዴት ሲበርድልህ የሚተርፍህ ምንድን ነው? ተስፋ መቁረጥ፣ በጣም ስሜታዊ መሆን፣ ማዘን? ኃይል የለሽነት፣ ተስፋቢስነት፣ ምንም ነገር ያለማድረግ ሁኔታ ውስጥ ልትገባ ትችላለህን? ወይም ደግሞ እንደገና ለመደራጀትና ወሳኝ እርምጃ ለመውሰድ ያለ የሌለ የፈጠራ ኃይልህን ትጠቀማለህ? እራሴን በመነቅነቅ ሀሳቤን አንጸባርቃለሁ፡፡ “ምንጊዜም ቢሆን ንዴት በመጨረሻው ተፈጻሚነት እንዳይኖርና ሽባ ሆኖ ያስቀራል፡፡ በምንናደድበት ጊዜ የምናባክነው ኃይል ወደ ረዥሙና ቀጣይነት ስላለው የአድቮኬሲ እና ድርጊት በአወንታዊነት ማዋል አለብን::” ንዴታችን ለምክንያታዊነት፣ በስሌትና በጥቅል ታስቦበት ለሚሰራ ተግባር መንገድ መስጠት አለበት፡፡
ሁልጊዜ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሁላችሁም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ቀውሶችን የመቃወም ዝንባሌ ታሳያላችሁ፣ ነገር ግን ከእነዚህ ያላነሰ ጠቀሜታ ላላቸው ሆኖም ግን ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትን ችላ ትላላችሁ:: መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “ባለፈው ዓመት በርካታ አስደንጋጭ ቀውሶች በግልጽ ለመውጣታቸው ምስክር ናችሁ፡፡ በኢትዮጵያ ገዥ አካል በሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት ላይ ሰብአዊ መብት መርገጥና ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲፈጸምባቸው ነበር፡፡ ጥንታዊውንና የተከበረውን የኢትዮጵያን የኃይማኖት መሬት የዋልድባን ገዳም ዓይን ባወጣ መልኩ ገዥው አካል ለውጭ የሸንኮራ አገዳ አልሚዎች ማስረከቡ ይታወሳል:: በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ከሚኖሩበት አካባቢ በኃይል በማፈናቀል የዘር ማጽዳት ዘመቻ መፈጸሙ ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው::” መስታወቱ ቀጥሏል፣ “በርካታ ዝቅተኛ ገጽታ ያላቸው ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ የአውዳሚነት ባህሪ ያላቸው እየተከናወኑ ያሉ ቀውሶች አሉ፣ የገዥው አካል “የሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት” ማስመዝገብ ፕሮፓጋንዳ ቢኖርም በአሁኑ ጊዜ ወደ አስር ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን/ት በረሀብና ቸነፈር የህይወት አጣብቂኝ መካከል ወድቀዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ1970ዎቹና በመጀመሪያዎቹ 1980ዎቹ እንደነበሩት ዓመታት ዓይነት ረሀብ የማይታየው በዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ ምክንያት ነው፡፡ በጎረቤት አገሮች እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮያውያን/ት ቁጥር በየዓመቱ በመቶዎችና በሺዎች እየጨመር በመሄድ ላይ ይገኛል፣ በትምህርትና በጤናው ዘርፍ ቀውሶች ይታያሉ፡፡ የሙስና ቀውስ እና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጥራት ደካማ መሆን እና የአገልግሎቱ እጥረትም ይታያል፣ ይህም በወጣቶች ስብዕና ላይ ትልቅ የሰብአዊ መብት እረገጣ ተብሎ ሊመደብ ይችላል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች በተሳሳተ አስተዳደር እየተመሩ ነው፣ የፖለቲካ ተቋማት እየሆኑና የገዥው ፓርቲ ታማኞች የሙስና ስልጠና አካባቢዎች እየተደረጉ ነው::” በገፍ መቃወም ያለብን ትልቅ ገጽታ ያላቸውን ቀውሶች ብቻ ሳይሆን ትንሽ ገጽታ ያላቸውን ጭምርም መሆን አለበት፡፡
የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ሁላችሁም በሚባል መልኩ ሁልጊዜ ደካማ የመከላከል ጨዋታ ታደርጋላችሁ:: መስታወቱ እንዲህ ይገልጻል፣ “በዲያስፖራው ያላችሁ ሁላችሁም መንግስት የሚሰራውን ሁልጊዜ ትቃወማላችሁ፣ የማይሰራውን ግን በጣም ጥቂት ብቻ ትይዛላችሁ:: በቅርቡ በህይወት የተለዩት የገዥው አካል መሪ ይህንን ደካማ ጎን እንደ በሰይፍነት የመጠቀም ጉብዝና ነበራቸው::
እና እናንተ በሙሉ ለአገራችሁ እርባና ያለው ነገር ስትሰሩ አትታዩም፣ እሳቸው የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ሲሉ አንድ አስደንጋጭ የሆነ ነገር ሲያደርጉ ወይም ሲናገሩ እናንተ ለዚያ ምላሽ ለመስጠት ስትሽከረከሩ ትወጡ ትወርዱ ነበር፣ ይህንም አይተው በዚያ ጭራቃዊ ፈገግታቸው ይመለከቱ ነበር::”
ለመስታወቱ እንዲህ በማለት ለመግለጽ እሞክራለሁ፣ “እኒያ ሰው ጨካኝ በመሆናቸው ጎበዝ ነበሩ፣ እሳቸው ዋና የነገር አጧዥ፣ የተንኮል ንድፍ አውጭ፣ ታማኝነት የሚጎድላቸው እና የብልጥነት ሴራ የሚሰሩ ነበሩ፡፡ ምርጫ አልነበረንም::” መስታወቱ ይሄን አስተያየት ችላ አለው:: “አሁንም የእርሳቸው ጋሻጃግሬዎች በእርሳቸው ፈለግ እንደዚያው እንደተለመደው የማይረባ ድርጊታቸውን እንዲቀጥሉ ትፈቅዳለህ?“ እኔ መልስ የለኝም፣ ጥያቄው እንዳልሰማ ለማስመሰል እሞክራለሁ፣ ለእራሴ ቀስ ብየ እናገራለሁ፣ “ምንም ዓይነት ቡድን ጠንካራ የመከላከያ መስመር ሳይኖረው ለድል አይበቃም“:: ጠንካራ የዲያስፖራ ቡድኖችን መፍጠርና ጠንካራ የመከላከል ጨዋዎችን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ሁላችሁም ትኩረት ይጎድላችኋል፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣”ሁላችሁም ከአንድ ጉዳይ ወደ ሌላ ዝውውር ለማድረግ ትኩረትና ተስፋ ይጎድላችኋል፣ የቀውስ ሁኔታዎችን በንዴት ምላሽ ለመስጠት ስትሞክሩ ይህ ሁኔታ ደግሞ በጣም ረዥም በሆነ ምንም ነገር ያለመስራት ወሰንተኛ የሆነ ቸልተኝነት ያስከተላል::” እራሴን እጠይቃለሁ፣ “ያ የሚሆነው ለምንድን ነው?“ ድርጅትና አመራር ሳይኖር አንድ ጉዳይ ላይ ትኩረት ማድረግ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላልን? ለምንድን ነው ግልጽና ጠንካራ የአድቮኬሲና የድርጊት አጀንዳ የማይኖረን?” ለመስታወቱ እነግረዋለሁ፣ “ትኩረት ያጥረናል ምክንያቱም ግልጽ ራዕይ የለንም፣ ራዕይ ያጥረናል ምክንያቱም ቁርጠኝነት ያጥረናል፣ ቁርጠኝነት ያጥረናል ምክንያቱም በእራሳችን በራስ መተማመን እና በክርክር ጭብጦቻችን ላይ እምነት ያጥረናል፡፡“ እዚህ ላይ የአፍሪካን የጥንት አባባል በመዋስ፣ “ወደየት እንደምትሄድ ካላወቅህ ማንኛውም መንገድ እዚያ ያደርስሀል፡፡“
አብዛኞቻችሁ ቆሞ ተመልካች ናችሁ፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “አብዛኞቻችሁ ከጎዳና ዳር ቆሞ ማየትን ትመርጣላችሁ፣ ሌሎቹ ደግሞ ከጎን ሆነው ትችት መሰንዘርን ይመርጣሉ፡፡“ አቋረጥኩ፡፡ “ዋናው ዘዴ የተመልካቾችን ምዕናብ ለማጎልበት፣ ለእነሱ ተስፋ ለመስጠትና ለማጠናከር፣ እውቀት እና በሰብአዊ መብት ጥበቃ ላይ በእራስ የመተማመን ጠቀሜታ ለማጎልበት ነው፣ በዚህም መሰረት ከተመልካችነት ወደ ሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ይቀየራሉ፡፡“ መስታወቱ ስሜትን እንዲህ በማለት ያነሳሳል፣ “ሰብአዊ መብት የተመልካች እስፖርት አይደለም፣ ሰብአዊ መብት የቡድን ስራ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በሜዳው ውስጥ ነው፣ እያንዳንዱ ሰው የሚጫወተው ድርሻ ይኖረዋል እና ትልቅ ግብ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡“ ከታች ጀምረን ማነሳሳትና ማንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡
እናንተ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በሙሉ የሲቪክ ማህበረሰብ የድርጊት ዘመቻ መመስረት አለባችሁ፣ መስታወቱ እንዲህ በአንክሮ ያስጠነቅቃል፣ “እናንተ ሁላችሁም ለድል የሚያበቃችሁን መንገድ በመከተል በተለየ ሁኔታ ለመስራት፣ ቅድሚያ ዝግጅት በማድረግ ለመስራት፣ ከስሜታዊነት ነጻ ሆኖ ለመስራት መብቃት አለባችሁ፡፡“ እናንተ ሁላችሁንም ማስተማር፣ ማንቀሳቀስ፣ ማደራጀትና ማጠናከር የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ለጋራ ጥረት ማብቃት አለባችሁ፡፡ እናንተ ሁላችሁም የሰቪክ ማህበረሰቡ ጋር በመሆን ዘመቻውን በቀልጣፋነት ማካሄድ አለባችሁ፣ ለሲቪክ ማህበረሰቡ እንቅስቃሴ ህበረተሰቡን በኮሚቴ፣ በጎ ፈቃደኞችን በመመልመል፣ ለወርክሾፖች አመራር በመስጠት፣ ከታች ጀምሮ ያለውን እያንዳንዱን ዜጋ ለማጠናከር እና በንቃት ለማሳተፍ በቴሌቪዥንና ሬዲ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት በመስጠት መስራት ያስፈልጋል፡፡ የሲቪክ ማህበረሰቡ ከታች ጀምሮ በሙሉ እንዲሳተፍ!
እናንተ ሁላችሁም በሌሎች ላይ ስድቦችን በመወርወር ጊዜ ማባከን፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “እናንተ ሁላችሁም ገዥውን አካል በማውገዝ እና ዘለፋዎችን በመወርወር ብዙውን ጊዚያችሁን በከንቱ ታባክናላችሁ፣ ሁላችሁም አታገኙትም፣ የዱሮ አባባል በመዋስ፣ ’ከአሳማ ጋር (ወይም ከሌባ) ከጭቃ ውስጥ ትግል አትግጠም‘ አሳማው (ወይም ሌባው) ሲደሰት አንተ ቆሻሻ ትሆናለህ::
ወሮ በላን በጭቃ ጅራፍ በዝልፍያ መስተካከል አይቻልም::” ምላሽ ለመስጠት ፈጠንኩ፡፡ “አንድ ሰው አካፋን አካፋ ማለት አለበት፡፡“ መስታወቱ እንዲህ በማለት ምክር ይለግሳል፣ “ስለዚህ አንዴ ጥራው እና ተንቀሳቀሱ፣ አስታውስ! ወደ ዴሞክራሲ ወይም ወደ ነጻነት በስድብ አትደርስም፡፡”” መስማማቴን ለመገልጽ እራሴን ነቀነቅሁ፡፡ “የእውነት ወንጭፎችን እና ቀስቶችን ታጥቀን መዋጋት አለብን፣ በእውነት ጋሻዎች መመከት አለብን፣ ከመብት እረጋጭ ኃይሎች ነጻ ሆነን በነጻነት ለመናገር፣ ለመዘመር፣ ትልቁን ጉዞ መጓዝ አለብን፡፡“ እውነትን ተናገር እንጅ የሰብአዊ መብት እረጋጭ ኃይሎችን አትሳደብ፡፡
እናንተ ሁላችሁም በክፍል ውስጥ ላለው ዝሆን ትኩረት ስጡ፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “እነሱን ለመረዳት ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ጫማዎች ለመጓዝ ሞክር (ምክንያቱም“እነሱን ለመረዳት መሞከር ጊዜ ማጥፋት ነው) ነገር ግን የእነርሱን ፍርሃት ለመረዳት እና የድብቅ እንባ ማፍሰስ ለመገንዘብ ሞክር፣ እነሱ አደጋዎች ጭካኔ የተሞላባቸው እና ህሊና የሌላቸው ናቸው፣ ነገር ግን ፍርሃት አልባዎች አይደሉም፡፡ በፍርሃት ይኖራሉ፣ ነገር ግን መሰረተቢስ ፍርሃቶች አይደሉም፣ የእነርሱ ፍርሃት በጫካው ውስጥ በማታ አያነደደ እንደሚያበራው ነብር ሁሉ ተመሳሳይ ናቸው፡፡” ይላል ዊሊያም ብሌክ፡፡ “የቸርቺል ኬኔዲ የፍርሃት ተቃርኖ’ በሚሉት ወጥመድ ተይዘዋል፣ አምባገነኖች ደፍረው ወጥተውው በማይጋልቧቸው ነብሮች ከወዲያ ወዲህ ይላሉ፣ እና ነብሮቹ ተርበዋል”፣
ቸርችል ያስጠነቅቃሉ፡፡ ፕሬዚዳንት ጆን ኬኔዲ ለማስታወስ “በጥንት ጊዜ በሞኝነት በነብሮች ጀርባ ላይ በመቀመጥ ኃይልን ለማግኘት ይፈልጉ የነበሩ አምባገነኖች በነብሮቹ ሆድ ውስጥ ገብተዋል፣ በሌላ አባባል “በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ የሚከለክሉ እነሱ በአመጽ መወገዳቸው የማይቀር ነው፡፡“ መስታወቱ ቀጠለ፣ “አምባገነኖች እርግጠኛ እና እብሪተኛ ይመስላሉ፣ ነገር ግን ይህ ሁሉን አቀፍ የሆነ ፍርሃታቸውን ለመሸፈን ሲሉ የሚያደርጉትና ከዕለታት በአንዱ ቀን እነርሱ ከታች ለወደቁ ጭቁኖች እነርሱ በፈጠሩት ገሀነም አነርሱ ስልጣናቸውን በኃይል ተነጥቀው ወደ መቀመቅ መውረዳቸው የማይቀር ነው፡፡“ መስታወቱን እጠይቀዋለሁ፣ “አምባገነኖች ቀን በቀን ይኖራሉ ብለህ መናገር ትችላለህ? ነገ ድረስ ለመቆየት አምባገነኖች ዛሬ ሁሉን ነገር ያደርጋሉ፣ ነገ ከነገ ወዲያም እና ከዚያ ወዲያም ቀን በቀን ነው የሚኖሩት?“ መስታወቱ እንዲህ ያስተካክለዋል፣ “በፍጹም፡፡
አምባገነኖች ሰዓት በሰዓት፣ ደቂቃ በደቂቃ፣ ሰከንድ በሰከንድ በፍርሃት ተውጠው ነው የሚኖሩት፣“ የተራቡ ነብሮች? የነቁ ግዙፎች ነብሮች! እናንተ ሁላችሁም ብቻችሁን ልትሰሩት አትችሉም፣ ከመሄድህ በፊት የመጨረሻዋን ቃል መስታወቱ እንዲህ ይናገራል፣ “እናንተ ሁላችሁም ብቻችሁን ልትሰሩት አትችሉም፣ እናንተ ሁላችሁም ጓደኞች መፈለግና ከእነርሱ ጋር ተባብራችሁ በጋራ ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡”
ማሰብ ጀመርኩ፣ “ስንቶቻችን ነን ለእኛ ምርጥ ጓደኞች ጓደኞች የሆን? ስንቶቻችን ነን የሂዩማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ዘላለማዊ መጠበቂያ አባል የሆንነው? ስንቶቻችን ነን የሲ ፒ ጄ የጋዜጠኞች ተከራካሪ ድርጅት መብራቱን በቃሊቲ እስር ቤት ላይ በማነጣጠር እነ አስክንድር ነጋ፣ ውብእሸት ታየ እና ሌሎች በህገወጥ መንገድ ታስረው ለሚገኙት አባል የሆንነው?
ስንቶቻችን ነን ባህላዊውን የህብረተሰብ ቡድኖች እና የኢትዮጵያን የአካባቢ ጥፋት ለመከላከል ብለው ልዩ ስራዎችን ዓለም አቀፍ ወንዞች በፍትሀዊነት እንዲያገለግሉ የሚታገሉትን ዜጎች የምናደንቅ? በዓለም አቀፍ እና በአገር ውስጥ ከሚሰሩ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች ጓደኛ አለን? በድንገት በአምሮዬ ጥያቄ መጣ፡፡ ለምንድን ነው እነ ሲኤን ኤን፣ቢቢሲ፣ ኤቢሲ፣ ሲቢኤስ፣ አልጃዚራ፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ኤልኤ ታይምስ፣… የእኛን ሰላማዊ ተቃውሞዎች ለህዝብ ይፋ የሚያደርጉት?“ ከእነርሱ ጋር ጓደኝነት ስላልመሰረትን ነው? ብቻችንን ልንሰራው የምንችለው ጉዳይ አይደለም፡፡ አብረን ለምንሰራው ሁሉ ሰማይ ወሰናችን ሊሆን አይችልም!
መስታወት፣ መስታወት በ….
“የኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት” እውነቱን ወይም ደግሞ ውሸቱን ሊነግረን ይችላል፡፡ ምናልባት በመስታወቱ ውስጥ ማየት የምፈልገውን አይቼ ይሆናል፣ ምናልባት መስተዋቱም እኔ በመስታወቱ ላይ እንዲታይ ያስቀመጥኩትን አንጸባርቆ ይሆናል፣ ምናልባት መስታወቱ ሁሉም መልሶች ያሉት ወይም የሌሉት ይሆናል፣ ምናልባት መስተዋቱ የእኔ ህሊና ይሆናል፣ በእርግጥ በበየእለቱ በመስታወቱ ስመለከት የምጠይቀው፣ “በግድግዳው ላይ ያለህው መስታወት የነቃው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ከዚህ በኋላ ምን ማድረግ ይኖርበታል?
ወደፊት ይቀጥላ …
ለአንባቢዎች ማስታወሻ፣ “ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት ንግግሮች“ ልዩ በተከታታይነት የሚወጡ ትችቶች ናቸው፣ ወደፊት በየጊዜው
በሚስቡ ክስተቶችና ድርጊቶች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደምጽፍ እገምታለሁ፡፡ ማስተማሪያና መማሪያ በሚሆኑ ድርጊቶች ለመምህር ፈልጎ
ማውጣት መቻሉ በአጣቃላይ የሚያስደንቅ አይሆንም፡፡
12/4/2013
የመለስ ጎጂ ሃሳቦችና ድርጊቶች (የኢትዮጵያ ሲቪክ ንቅናቄ)
Email: ethiocivic@gmail.com
የመለስ ጎጂ ሃሳቦችና ድርጊቶች
ሕዳር 2006
የኢትዮጵያ አንድነትንና የመንግስት ስርዓቱን የሚመለከቱት የመለስ ሃሳቦችና ድርጊቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ ከባድና አሳሳቢ ትርጉም አላቸው፡፡ የአንድነቱ ጥያቄ የኢትዮጵያ እንደ አገር የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ሲሆን፣ ስርአቱ ደግሞ በኢትዮጵያ ህዝብ መብቶች ላይ ማን መወሰን እንደሚችል ያመለክታል፡፡ የአገር ህልውና እና የህዝብ መብትን ያህል ትልቅ ጉዳይ ሊኖር ስለማይችል ክብደቱና አሳሳቢነቱ አያጠያይቅም፡፡
መለስ አንድነትን በሚመለከተው ሃሳቡ ትግራይን ከመገንጠል ኣላማ ጀምሮ ሳይተገብረው ቢቀርም፤ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ አድርጓል፤ ህዝብን በቋንቋ ክልሎች ከፋፍሎ በጉራ ፈርዳና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ለተከሰቱት አማሮችን የማፈናቀል ግፍ መሰረት ጥሏል፤ የመገንጠል “ህገ መንግስታዊ” አንቀፅ አዘጋጅቷል፤ ለሱዳን መሬት አድሏል፤ ዜጎችን አፈናቅሎ ለም መሬት ለውጭ ድርጅቶች በርካሽ ለረዥም ጊዜ አከራይቷል፡፡
የመንግስት ስርዓቱ በቃላት መድብለ ፓርቲ በተግባር ያንድ ፓርቲ አፋኝ ስርዓት ነው፡ስለዚህም ስርዓቱ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ወሳኙ መለስ እንደነበረ ለ21 ዓመታት ደጋግሞ አረጋግጧል፡፡ ሰውየው በኢትዮጵያ በነበሩ መንግስታት በተለመደ መሳሪያ ማለትም የፈላጭ ቆራጭነት ስልጣንን በመጠቀም፣ በኢትዮጵያ ግን ያልተለመደና በውጭ ሃይሎችም ያልተሳካ፣ ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማ ለመተግበር ሞክሯል፤ በከፊልም ተሳክቶለታል፡፡
አሁን ጥያቄው ከመለስ ህልፈተ-ህይወት በሁዋላ የኢትዮጵያ ህዝብን አፍኖ አንድነቱን የሚሸረሽረው ስርዓት ምን ይሁን? ነው፡፡ መልሱም የመለስ ስርዓት መፍረስ፣ አስተሳሰቡም መወገዝ አለበት እንደሆነ ለኢትዮጵያውን አሻሚ መሆን የለበትም፡፡
በዚህ መሰረት ካልታረሙ ለወደፊቱም ሊቀጥሉ የሚችሉ፣ ህወሓት የትጥቅ ትግል ከጀመረበት ጀምሮ እሰካሁን ያሉ በዋናነት ከመለስ የፈለቁ ጎጂ አስተሳሰቦችና አሰራሮች ባጭሩ መቃኘት ያስፈልጋል፡፡
ያልተፃፈ የጥንት ታሪክ አሁን ሲፃፍ ያልተረጋገጡ ወሬዎችና ግምቶች እንደ እውነተኛ ታሪክ የመፃፈቸው አደጋ ከፍተኛ ቢሆን የሚጠበቅ ነው፡፡ ታሪኩ ሲፈፀም የነበሩ ሰዎች በህይወት እያሉና የፅሁፍ ማስረጃዎች ሳይታጡ ያልተፈፀመ ታሪክ ብቻ ሳይሆን የእውነቱ ተፃራሪ የሆነ ታሪክ ሲፃፍና ሲነገር ግን በጣም ያሰገርማል፡፡ ጠንቁም ብዙ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ውሸት የሚያሰራጩ ሰዎችን እንዴት ማመን ይቻላል? ለምንስ በዚህ መልክ ይቀጥላሉ? |ብለን መልስ-አዘል ጥያቄን በማቅረብ ጉዳዩን ላንባቢዎች ፍርድ መተው እንችል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በመለስ ትእዛዝ ውሸቱን የሚያሰራጩት ሰዎች ደግሞ በበኩላቸው በውሸቱ የሚያምኑ ሰዎችን መፍጠር ችለዋል፤ ምክንያቱም በጉልበት መገናኛ ብዙሃንን ለሁለት አሰርት ዓመታት በብችኝነት በመቆጣጠር የተወሰነ ህዝብ ጀሮን አይንና አእምሮን ተቆጣጥረው ህዝቡ መስማት፣ ማየትና መግለፅ ያለበትን ሲወስኑ ቆይተዋል፡፡ ስለዚህ ውሸቱ እውነት መስሎ ህዝብን ማወናበዱ እንዳይቀጥል የሚያመዛዝን አእምሮ ያላቸው ዜጎች እውነቱን ለማወቅና ለማሳወቅ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ ባንድ በኩል በውሸት ላይ በተመሰረተ ቅስቀሳ የተስፋፋውን ድንቁርና ማጋለጥና ማስወገድ፤ በሌላ በኩል ለዘለቄታዊ የህዝብ ደህንነት ጥፋት የሚያስከትሉትን ሃሳቦችና አሰራሮች እንደ አደገኛ ቆሻሻ ላንዴና ለሁሌ መቅበር ያስፈልጋል፡፡
መለስና ግብረ-አበሮቹ በ1968 ባወጡት የህወሓት (የዚያን ጊዜ ተሓህት) መግለጫ (ማኒፌስቶ) ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠል ዓላማ እንደነበራቸው በይፋ ስለገለፁ፣ መለስ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ እንጂ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ራእይ ይዞ ለትግል አልተሰለፈም፡፡ ሰውየው የፈለገው ራእይ ቢኖረው ኢትዮጵያን የሚመለከት በጎ ነገር ሊሆን አይችልም፡፡ ሃቁ ይህ ነው፤ በቃ፡፡
የመለስ ፍጡራን ማኒፌስቶው መታረሙን በመጥቀስ ቁም ነገር የተናገሩ ሊመስላቸው ይችላል፡፡ ቁምነገሩን ጭራሽ የሳቱት ቢሆኑም፣ ማኒፌስቶው እንደታረመ የሚገልፁት ሰዎች ቢያንስ የእርማቱን አስፈላጊነት ስለሚገነዘቡ ይህንን ግንዛቤ ከሌላቸው ሰዎች ይሻላሉ፡፡ ሆኖም፡
1ኛ ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠል ዓላማ ማንሳቱ ራሱ በኢትዮጵያዊነቱ በሚያምን ሰው ሊነሳ እንደማይችል ሊያስተባብሉ አይችሉም፡፡
2ኛ እርማቱ (በ1971 የህወሓት ጉባኤ) በመገንጠል ፈንታ የትግራይ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ እንዲወስን መታገል እንደ ድርጅታዊ ዓላማ ማስቀመጥ ስለነበረ ከማጭበርበር የተለየ ትርጉም የለውም፡፡ ምክንያቱም በአንድነትና በመገንጠል አማራጮች አንድ ህዝብ ድምፁን በመስጠት መወሰን የሚያስፈልገው የአንድነትና የመገንጠል ሃይሎች ሲኖሩ ነው፡፡ ደርግ ፀረ ዴሞክራሲ ቢሆንም አቋሙ ላንድነት ነበር፤ የትግራይ ህዝብም የመገንጠል ጥያቄ አላነሳም፡፡ ስለዚህ የመገንጠል ፍላጎቱ የመለስና ግብረ-አበሮቹ አቋም ነበር፡፡ መለስና ግብረ-አበሮቹ በመገንጠል ፍላጎታቸው ያልቀጠሉበት አንዱ ምክንያት በተለይ ህዝብን አፍነው ከመቆጣጠራቸው በፊት ለዓላማቸው የህዝብ ሰፊ ድጋፍና ያንዳንድ ታጋዮች ትብብር እንደማያገኙ ስለተገነዘቡ ነው፡፡ በዛም ምክንያት በድርጅታቸው ውስጥ በ68 የፃፉትን ማኒፌስቶ ለድርጅቱ አባሎች ሳያሰራጩ ቀርተዋል፡ ሁለተኛው ምክንያት የህወሓት ሰራዊት በኢትዮጵያ ደረጃ ስልጣን ለመያዝ የሚያስችል ጥንካሬ ስላካበተና እነ መለስ ራሳቸው በጠፈጠፏቸው አሻንጉሊት ድርጅቶች መሳሪያነት ኢትዮጵያውያንን እየከፋፈሉና እጨፈጨፉ መግዛትና መዝረፍ ስለቻሉ ነው፡፡ ትግራይን የመገንጠል ቅሰቃሳ ከቆመ በሁዋላም የመለስ ነገድ-ተኮር ፖለቲካ በመገንጠል መብት ስም ህጋዊ ልባስ እንዲያገኝ በህገ መንግስት ተካትቷል፡፡
እውነቱ ከላይ እንደተገለፀው የማሻማ እያለ መለስ የተቆጣጠረው ህወሓት ከመጀመሪያ ጀምሮ ለኢትዮጵያ አንድነት እንደታገለ፣ ያ ቡድን ዓላማው ኢትዮጵያን ለመታደግ እንደነበረ አሁን የሚወራው የፈጠራ ታሪክ ከየት መጣ? በኢህአዴግ የረቀቀው ህገ መንግስት ኢትዮጵያን ከመገነጣጠል እንዳዳነ የሚሰራጨው ቅስቀሳ በታሪክ ውሸት፣ በአመክንዮ የተዛባ ነው፡፡ ሻዕብያ በራሱ አቅምና በመለስ ጥረት ኤርትራን መገንጠል ችሏል፤ በኢትዮጵያ የመገንጠል ጥያቄ ካነሱት በቂ ወታደራዊ አቅም ያልገነቡ ድርጅቶች ከማስገንጠል የተገቱት በኢህአዴግ ጉልበት እንጂ በህገ መንግስቱ አይደለም፡፡ ስለሆነም የመለስ ነገድ-ተኮር ፖለቲካ አንድነትን የሚያጠናክር ሳይሆን በአገራችን በመታየት ላይ እንዳለው ህዝብን የሚያጋጭና የሚያፈነቅል መርዝ በመሆኑ መወገድ አለበት፡፡
መለስ በህወሓት ውስጥ በ1968 ተጠባባቂ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ከሆነ ጀምሮ እሰከ 2004 ህልፈተ ህይወቱ ድረስ ለ36 ዓመታት በሰው ህይወት ላይ ለመወሰን የሚያስችለው ስልጣን ይዞ የዜጎች ህይወት እየቀጨ ቆይቷል፡፡ የመለስን አገዛዝ መገለጫዎች በሚከተሉት አርእስት ስር ማየትና የያንዳነዱ ባህርይ፣ አቋምና ድርጊት እውነታ በማስረጃ እያረጋገጥን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ ክብሩ እንዲጠበቅ የመለስ እኩይ ስርኣት ተወግዞ ካገራችን እንዲወገድ ከፍተኛ ጥረት እንደሚያስፈልግ እናሳስባለን፡፡
የህወሓት/ኢህአዴግ ማለትም የመለስ የስልጣን መሰረት ጉልበት ነው፡፡ ውሸትና ሙስና የተንሰራፉትም ከጀርባቸው ጉልበት ስላለ እንጂ በቀላሉ ተጋልጠው ሊወገዱ ይችሉ ነበር፡፡ ስለዚህ ህወሓት/ኢህአዴግ የመለስ ፈር መከተሉን ከቀጠለ በሰላማዊ ህዝብ ላይ ጉልበት ስለሚጠቀም ብዙ ዓይነት ወንጀሎች መፈፀም ይችላል፡፡ ሌሎች ፀረ ህዝብ ድርጊቶቹም ህዝብን በማሸማቀቅ ስለሚፈፅማቸው ጉልበት ሰውን እንደመጉጃና እንደማስፈራሪያ ለፖሊሲዎቹ ተፈፃሚነት የሚፈጥረው አመቺ ሁኔታ መገንዘብ ይቻላል፡፡
1. ፈላጭ ቆራጭነት
በኢትዮጵያ ያንድ ግለ-ሰብ ፈላጭ-ቆራጭ አምባገነንነት አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ቢሆንም ከተካሄደው ረዥም ትግልና፣ ከተከፈለው እጅግ ከባድ መሰዋእት አንፃር ሲታይ ትውልዱን በበላ ትግል ፈላጭ-ቆራጭ ግለ-ሰብ መንገሱ ባንድ በኩል የሰውየው ኢሰብአዊነት አረገግጧል፡፡ የመለስ ፈላጭ ቆራጭነት በህወሓት ውስጥ ከማሌሊት ምስረታ ጋር የሚፈልጋቸውን ካድሬዎች መልምሎ፣ የማይፈልጋቸውን አባላት ካጠቃ በሁዋላ የጀመረ ነው፡፡ በሌላ በኩልም ታጥቆ ከታገለው ሃይል ጥቂቱ ባለው ሙስና ጎልቶ እንደሚታየው ለዝርፊያ የቆመ እንደሆነ፣ አብዛኛው የድርጅቱ አባል ደግሞ ታግሎ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የመገንባት ብቃት እንደሌለውና የአምባገነን መሳሪያ ሆኖ የግለ-ሰብ አምባገነንነት በመመስረቱ፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በመረገጣቸው፣ ፍትሕና የህግ የበላይነት ባለመኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ ስለዚህ የመለስ ፈላጭ ቆራጭነትና የህወሓት/ኢህአዴግ አባላት አድርባይነትና መሰሪያነት ህዝብን የሚያሸማቅቅ ገዳይና አፋኝ ስርኣት ፈጥሯል፡፡
2. ተከታታይ የጅምላና የተናጠል ግድያዎች
ቀደም ብሎ የደርግ ግፎች የታዛቢዎችን ቀልብ በሳቡበት የትጥቅ ትግል ጊዜ ግልፅነትና ተጠያቂነት ባልነበረበት ሁኔታ የህወሓት አመራር በድርጅቱ አባላት እና በሰላማዊ ህዝቡ ላይ በምስጢር ብዙ ግድያዎች ይፈፀሙ ነበር፡፡ ብዙ የትግራይ ህዝብና የህወሓት ተራ አባሎች በዝምድና፣ በጐረቤትነትና በጓደኝነት የሚያውቃቸው የህወሓት ሰለባዎች መኖራቸውን ቢያውቁም ባገዛዙ ስለታፈኑ፣ ከስርዓቱ ጋር በጥቅም ስለተሳሰሩ፣ ወይም የህወሓት ወታደራዊ ድል እንደ ጀብድ ስለሚያዩና ጀብዱን በመጋራት ዝና የሚያገኙ ስለሚመስላቸው በህወሓት ስለተፈፀሙት ወንጀሎች በይፋ አይናገሩም፡፡
በትጥቅ ትግሉ ጊዜ በተለይ በሲቪሎች በድብቅ የተፈፀሙት ግድያዎች ተደብቀው አይቀሩም፤ በግድያው ጊዜ ህፃናት የነበሩና ባገር ቤትና በስደት ያደጉም በቤተሰብ መረጃው ስለተላለፈላቸው ያውቁታል፡፡ ስለዚህ የድብቅ ግድያዎቹ፣ በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ (1985፣ 1993፣ 1997፣ 1998) እና በሌሎች ከተሞች በይፋ እንደተፈፀሙት ጭፍጨፋዎች በታሪክ ይመዘገባሉ፡፡ ስለዚህም ግፍ ከፈፀመው ሃይል ጋር የወገኑት ዜጎች ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው፡፡
3. የፖለቲካ ሙስና እና ጎጠኝነት
ብዙ ጊዜ ስለ ሙስና ሲወራ ከጉቦና ስልጣንን ካለአግባብ ከመጠቀምና ሃብት ከማካበት ጋር ይያያዛል፡፡ ባለስልጣኖች የሚፈፅሟቸውን የሙስና ድርጊቶች ለመፈፀም የሚያስችላቸው መሰረት ግን ስልጣኑን ለመያዝ የሚፈፅሙት በጉልበት የታጀበ ቅጥፈት ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በውሸት ምርጫ ስልጣኑን በህዝብ ፍላጎት እንዳገኘ የሚገልፀው በጉልበት የሚፈልገውን ማድረግ ስለሚችል እንጂ ማጭበርበሩ፣ ህዝብን ማስገደዱና ድምፅን መዝረፉ ህዝብ ስለማይነቃበት አይደለም፡፡ በውሸት ምርጫ ከፍተኛውን የስልጣን እርከን የመያዝ አሰራር የስርዓቱ መገለጫ እስከሆነ ድረስ ለሙስና ድርጊቶች አመቺ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ከላይ ከፈተኛውን መንግስታዊ ስልጣን በጉልበትና ቅጥፈት የሚቆጣጠሩና ስልጣኑን ለዝርፊያና ለግል ምቾት የሚጠቀሙ ሰዎች አስካሉና ለዚህ ድርጊት በውስጣቸው መተማመን እንዲኖራቸው በነገድ፣ በጎጥና በዝምድና የተሳሰሩ ሰዎች እስከገዙ ድረስ፣ ከታች የገዢዎቹን አርአያ እየተከተለ ሙሰኛ የሚሆን መብዛቱ የሚገርም አይደለም፡፡
መለስ ሙስናን በቅንነት የሚቃወም ቢሆን ኖሮ በነበረው ፍፁም ስልጣን ሊገታው እየቻለ ከሱ በፊት ከነበሩት አገዛዞች ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለከት የሌለው ሙስና አይስፋፋም ነበር፡፡ በተፃራሪው ግን መለስ ገና ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ ለተራበ ህዝብ የመጣውን እርዳታ ለምሳሌ ተጋይ የነበረውን ገብረመድህን አርአያን እህል የሚሸጥ ነጋዴ መስሎ ገንዘብ ከእርዳታ ሰጪዎች እንዲቀበል ያደርግ ነበር (Tigray, Ethiopia’s untold story, by Max Peberdy)፡፡ ትእምትን (ኢፈርት) ለመመስረት የተጠቀመበት ገንዘብ ከእርዳታ ተጭበርብሮ የተወሰደ ነው፡፡ የመለስ ሚስት የትእምት ከፍተኛ ስልጣን የያዘችው በቤተሰባዊ የሙስና አሰራር ነው፡፡ መለስ ያገዛዙ አካል ሆነው የተፈጠሩት ሙሰኞች ለስርዓቱ የቆሙ የሱ ደጋፊዎች እንደሆኑና እንደሚያስፈልጉት አያውቅም ማለት የዋህነት ነው፡፡
ሰውየው ግን ደርጊቶቹን በቃላቱ፣ ቃላቱን በድርጊቶቹ የማፍረስ አመል ነበረው፡፡ ዴሞክራሲን የማይፈልገው ወንጀሎቹ እንዳይጋለጡ ስለሚሰጋ መሆኑ እየታወቀ፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን እንዳይገነባ ሙስና እንዳደናቅፈው ለውጭ ዜጎች እንደሚከተለው ይገልፅ ነበር፡፡ ለምሳሌ አሌከስ ዴ ዋል (Alex de Waal) መለስ በተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበራት ላይ በሚወስዳቸው እርምጃዎች ምክንያት ለሚያወግዙት ሰዎች መልሱ ምን እንደሆነ ጠይቆት መለስ ሲመልስ „የአባታዊነትና የሙስና የበላይነት ባለበት የፖለቲካ ኢኮኖሚ (በሚወስዳቸው እርምጃዎች ምክንያት እሱን) የሚያወግዙት ሰዎች ዴሞክራሲን እንዴት እንደሚገልፁትና ወደ ዴሞክራሲ የሚወስደው አዋጪ መንገድ እንዴት እንደሚፈልጉ ያውቃሉ ወይ?“ ብሎ በመጠየቅ ዴሞክራሲ እንደሌለ ከማመን አልፎ ጥያቄውን ማንሳቱን ስህተት ሊያስመስለው ይሞክራል፡፡ (Alex de Waal ፣ Dec. 06, 2012፣ ጉግል) የዜጎች መብቶችን ያፈነው ራሱ፣ ሙስና ያንሰራፋውም ራሱ መሆኑ ቢታወቅም መለስ ለኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደገነባ ከመግለፅ ቦዝኖ አያቅም፡፡
4. ህዝቡን በአንድ ሰው ሃሳብ እንዲመራ ማስገደድ
የተለያዩ ሃሳቦች ሲገለፁ እየተፋተጉ ስህተቶች ይታረማሉ፤ ከተለያዩ ሃሳቦች የተሻሉ ሃሳቦች ሊፈልቁ እና በተግባር እየተፈተኑ ሲጎለብቱ እውቀት በሂደት ያድጋል፡፡ መለስ የራሱ ሃሳብ ቢይዝና በፍላጎት ለሚቀበሉት ሃሳቡን ለማስፋፋት ቢሞክር ችግር አይሆንም ነበር፡፡ ችግሩ የፖሊቲካ ስልጣኑን፣ መገናኛ ብዙሃንን፣ የሚቆጣጠረው አስተዳደርንና ከተነገራቸው ውጪ የራሳቸውን ሃሳብ መግለፅ የማይፈቀድላቸው አሻንጉሊት ካድሬዎችን እየተጠቀመ የዜጎች ሃሳብ የሚቆጣጠርበት ስርዓት መመስረቱ ነበር፡፡
የመለስ ሃሳብ በጉልበት ከሚሰራጭ የሃይማኖት ስብከት የማይለይ፤ አማራጭ ስለሚከለክል ሚዛናዊ አስተሳሰብ ከነፃነት ጋር የሚያፍን፤ በማስረፅ (indoctrination) መልክ የሚሰራጭ፣ ካለ ደራሲው ፍላጎት አዲስ ግብአት ስለማይቀበል የማያድግና፤ የተለየ ሃሳብ የሚያቀርቡ ዜጎችን በጠላትነት በመፈረጅ በዜጎች መካከል የጠላትነት መንፈስ የሚፈጠር ቀኖና ነበር፡፡ ሰውየው ዜጎች በሱ ትእዛዝ እንዲተዳደሩ ብቻ ሳይሆን እሱ ራሱ ቢያምነበትም ባያምነበትም ላጭር ጊዜም ቢሆን ዜጎች በሱ ሃሳብ እንዲመሩ ያደርግ ነበር፡፡ በዚህ አሰራሩም ማመዛዘን የማይችሉ አምላኪዎችና አምላኪዎች በመምሰል የግል ጥቅማቸውን የሚያሳድዱ አድርባዮች ፈጥሯል፡፡ መለስ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ የማሌሊትን እምነት ያልተቀበሉ እንደ ጠላት ያሳድዳቸውና የጋንግሪን ስም አውጥተላቸው በጋንግሪን እንደተለከፈ አካል እዲቆረጡ ይቀሰቅስና በተግባር የተለየ ሃሳብን ለማጥፋት የተለየ ሃሳብ ባላቸው አባላት ላይ ግፍ ይፈፅም ነበር፡፡
መለስ ማሌሊትን በህወሓት ውስጥ ፍፁም ስልጣን ለመጠቅለል ከተጠቀመባት በሁዋላ ስለ ነጭ ካፒታሊዝም ማውራት ጀመረ፡፡ ስለዚህ ሰውየው የተወሰነ ሃሳብ ሲያሰራጭ በመርህ ደረጃ አምኖበት ሳይሆን ሃሳቡን ለስልጣን መሳሪያ ለመጠቀም ነበር፡፡ እሱ ራሱ ሃሳቡን መቀየር ስለሚችል፣ ይዞት ቆይቶ የሚጥለው ሃሳብ ትክክል እንዳልነበረ ማመኑን ያመለክታል፡፡ መሳሳቱን የሚገነዘብ ሰው ደግሞ ሌሎች ሰዎችም ትክክል ሊሆኑም ሊሳሳቱም እንደሚችሉ መገንዘብ መቻል አለበት፡፡ መለስ ሁሉንም የሱ ተከታዮች ያልሆኑትን በራሳቸው ፖለቲካዊ ሃሳብ የሚመሩትን ዜጎች በራሱ ብቻ ሳይሆን በህዝብ ጠላትነት እየፈረጀ አልፏል፡፡ ስለዚህ ማመዛዘን የሚችሉና ቅንነት ያላቸው የኢህአዴግ አባሎች ካሉ የመለስን መንገድ መከተል የለባቸውም፡፡
5. የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መርገጥ
የኢህአዴግ ህገ መንግስት ብዙ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ቢያካትትም የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ህገ መንግስቱን ባያከብሩ አያስገርምም፡፡ ህገ መንግስቱ የተዘጋጀው በወንጀለኞች ማለትም በመለስና ግብረ-አበሮቹ ይሁንታ ስለሆነ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ወንጀል ሲፈፅሙ የቆዩ ሰዎች መንግስታዊ ስልጣን ከያዙም በሁዋላ በተራ ቁጥር 1 እንደጠቀስነው ወንጀል መፈፀማቸውን ቀጥለዋል፡፡ ግፈኛ ገዳዮች “እያንዳንዱ ዜጋ በህይወት የመኖር መብት” እንዳለው ቢገልፁ ምን ትርጉም አለው?
የኢህአዴግ አባሎችና ደጋፊዎች ህገ መንግስቱን በታጋዮች ደም እንደተፃፈ ተኩራርተው ሲገልፁ ታጋዮቹ ራሳቸው የራሳቸውን መብት አስከብረው እንደማያውቁ የተገንዘቡ አይመስሉም፤ ወይም እውነቱ እንዲገለፅ አይፈልጉም፡፡ በትግሉ ጊዜ ድርጅቱን መለስና ጥቂት ግብረ-አበሮቹ ታጋዮችን ሲያስገድሉ፣ አስረው ሲያሰቃዩና ሲያባርሩ እንኳንና ተቃውሞ ማቅረብ መጠየቅም በአመራሩ የተወሰዱ እርምጃዎችን ትክክለኛነት እንደ መጠራጠር፣ በአመራሩ እምነት ማጣትና ሌሎችም እምነት እንዲያጡ በማድረግ ድርጅቱን ለማፈረስ እንደመሞከር እየተተረጐመ ያስወነጅል ነበር፡፡ ሁሉም እንደ በቀቀን የተባለውን እንዲደግም ስለሚፈለግም ዝምታም ያስጠረጥር ነበር፡፡ የድርጅቱን ማለትም የኢህአዴግን በተለይም የህወሓትን ታሪክ የማያውቁ አንባቢዎች ታሪኩን ማጥናት ሳያስፈልገቸው ከኢህአዴግ መንግስት ባህሪ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንደሚረግጡ ያውቃሉ፤ የተለየ ሃሳብ ያላቸውና መብታቸው እንዲከበር የሚጠይቁ ሰዎች እንዴት በቅጥፈት እየተወንጀሉ እንደሚጠቁ ማንም በቅን ህሊና የሚያስተውል ኢትዮጵያዊ ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡
6. በግድ ማደራጀትና ነፃ ድርጅቶች እንዳይኖሩ/እንዲዳከሙ ማድረግ
የተማሩና በከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ራሳቸውን ማደራጀት ይችላሉ፤ በገጠር የሚኖረው ህዝብ ግን የመደራጀት ልምድ ስለሚያንሰው፣ እንደፈለገው በዘመናዊ መጓጓዣ መጠቀም ይሁን በስልክ መገናኘት ስለማይችል፣ ከማሃይምነት ስላልተላቀቀና፣ የኑሮረው ሁኔታ ፋታ ስለማይሰጠው ራሱን የማደራጀት አቅሙ የተወሰነ ነው፡፡
የተማሩና በከተሞች የሚኖሩ ዜጎች የገጠሩን ህዝብ እንዲደራጅ ሊያግዙት ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ኢህአዴግ የመንግስት ስልጣን፣ ጉልበት፣ አስተዳደርና የመንግስት ንብረት እየተጠቀመ ስጋት በማስፈን ህዝቡን እንደመሳሪያ ለማሽከርከርና ትእዛዙን ለማስፈፀም በመለሳዊ ነገድ-ተኮር ስልትና እስከ ቤተሰብ ድረስ ለመቆጣጠር በሚያመች መልክ በራሱ ሹመኞች ስር ያደራጃል፡፡ ይህ ኣይነት ስልት አፋኝና አማራጭን የሚነፍግ የሁሉም ጠርናፊ (totalitarian) ስርዓቶች አደረጃጀት ነው፡፡ ከኢህአዴግ ነፃ ሆነው በሙያ፣ እንደ ሲቪክ ማህበራትና እንደ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመደራጀት የሚሞክሩ ዜጎች በአገዛዙ ይዋከባሉ፤ እንቅስቃሴያቸው ይገታል፤ ፍርሃት በማስፈን አባላትና ደጋፊዎች እንዳይጠጓቸው፣ ለህይወታቸውና ነፃነታቸው ዋስትና እንዲያጡ ይደረጋሉ፤ ህይወታቸው የተቀጨም አሉ፡፡ በዚህ አሰራር አገዛዙ በቃላት ስለ መድብለ ፓርቲ እያወራ በተግባር የአንድ ፓርቲ ስርዓት አስፍኗል፡፡
7. ህዝብን በቋንቋ መከፋፈል
የአገራችን ክፍለ ሀገሮች በቋንቋ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑና የነገድ ድርጅቶች በብዛት እንዲመሰረቱ መደረጋቸው በተወሰኑ ምሁራን መካከል የነበረውን ነገዳዊ ቅራኔ ተቋማዊ በሆነ መልክ፣ ማለትም በቋንቋ ክልሎች፣ በነገድ ድርጅቶችና ባስተዳደራዊ መዋቅር ለሁሉም ህዝብ እንዲዳረስ ተድርጓል፡፡
የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር የሚደገፍ መሠረታዊ የዴሞክራሲ ጥያቄ ቢሆንም፣ የመለስ ነገድ-ተኮር ፖለቲካ ግን በዋናነት የኢትዮጵያ ህዝብን ከፋፍሎ ለመግዛት የተጠቀመበት ስልት ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት እየተሸረሸረ ይገኛል፡፡ የሱማሌ ክልል ፕረዚደንት ትግሬዎች አማሮች ወደ ስልጣን እንዲመለሱ እንደማይፈልጉ መናገሩ፣ አማሮች በአገራቸው ውስጥ ከጉራ ፈርዳና ከቤኒ ሻንወጉል-ገሙዝ በግፍ እንዲባረሩ መደረጉ፣ ባገሪቱ እስር ቤቶች የኦሮሞዎች ቁጥር መብዛቱ እና ባንዳንድ ወገኖች መለስና ተከታዮቹ ለፈፀሟቸው ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ተጠያቂና እንዲሁም በልማት ተጠቃሚ ተደርጎ መታየቱ መለስ በመሃንዲስነት የመሰረተው መርዘኛ ስርአት ውጤት ነው፡፡
8. የተቋሞች ወገንተኝነት
መለስ ስልጣን ከመያዙ በፊት የነበሩ የተማሩና ልምድ ያካበቱ ኢትዮጵያውያን የሲቪልና የሰራዊት አባሎችን እንደ ባእድ አባርሮ ከነበቴሰባቸው ለስራ አጥነትና ለችግር እንዲጋለጡ አድርጓል፡፡ ቀጥሎ ሁሉም ታጣቂ ሃይሎች፣ ህግ አውጪው፣ ያስተዳደርና የፍርድ ቤት ተቋሞች፣ የሙያና የሃይማኖት ድርጅቶች ሳይቀሩ ያንድ ፖሊቲካ ድርጅት(መለስ በህይወት እስከነበረበት ጊዜም ያንድ ግለ-ሰብ) መሳሪያ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ እነዚህ ተቋሞች ለራሳቸው ተነፃፃሪ ነፃነት እንዲኖራቸውና ህዝብን በእኩልነት እንዲያገለግሉ ያንድ ፓርቲ ስርዓቱ ፈርሶ፤ በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር የመድብለ ፓርቲ ስርዓት መገንባት አለበት፡፡
9. መርዘኛ የጥላቻ ቅስቀሳ
በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ማንም ዜጋ ኢትዮጵያውያንን እንደ ወገኑ ማየትና ለራሱ የሚፈልገው የዜግንት ክብር ለማንም ኢትዮጵያዊም እንደሚገባ መቀበል አለበት፡፡ ፖለቲካው ነገድ-ተኮር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዋናነት በቅንጅት ላይ ተመስርቶ የነበረው የዘር ማጥፋት ክስ የጥፋት ዒላማ ተደርጎ የተገለፀው የህዝብ ወገን (የትግራይ ህዝብ) አጥፊ ተደርጎ በተወነጀለው ወገን ላይ (በዋናነት በአማራው) የጥላቻ ስሜት ለመቀስቀስ ነው፡፡
ተከሳሹ ኢንተርሃምዌን መስሎ እንዲታይ ቅስቀሳ ተደርጓል፡፡ ኢንተርሃምዌ በሩዋንዳ በ1994 እ.አ.አ. እስከ 800 000 የሚደርሱ ሰላማዊ ሰዎችን (በዋናነት ቱትሲዎችንና እንዲሁም ለዘብተኛ ሁቱዎችን) የገደለ የመንግስት አካል የሆነ የሁቱ ሚሊሽያ ነበር፡፡ በቅንጅት አባላትና ሌሎች ዜጎች ላይ የተመሰረተው የፈጠራ የዘር ማጥፋት ክስ ውድቅ ቢሆንም የቅስቀሳ መልእክቱ ተላልፏል፤ በህዝብ አለመተማመን አሰራጭቷል፡፡ ኢንተርሃምዌ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ ጥግተኛ፣ ቅንጅት ወዘተ ተመሳሳይ ትርጉም እንዲኖራቸውና በተወሰነ የህዝብ ክፍል ላይ የኢትዮጵያ አንድነትን በሚፈልጉ ዜጎች ላይ የጥላቻ መቀስቀሻና ማስፈራሪያ ተደርገዋል፡፡
10. አስፀያፊ ባህል
አገዛዙ ህዝቡን እያሸበረ አሸማቅቆና አፍኖ ስለሚገዛ ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጤኞችና የህዝብን መብቶች ለማስከበር የሚሞክሩ ህዝባዊ (ሲቪክ) ድርጅቶች ሊያድጉ አልቻሉም፡፡ በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንደሚባለው ግን መለስ አገዛዙን አሰፀያፊ የሆነ ዜጎችን የማዋረድና የማሰቃየት አመል አስለምዶታል፡፡
መለስ ሁሉንም ስለተቆጣጠረ ተቃዋሚዎቹም በቁጥጥሩ ስር እንዳሉና ምንም እንደማያሰጉት እያወቀ የሚፈፅማቸው ድርጊቶችና የሚረጫቸው ቃላት የቆሰለ ምርኮኛን ረግጦ እንደሚደበድብ፣ በላዩ ላይ እንደሚተፋና እንደሚቅራራ ሰው ነበር፡፡ ለምሳሌ በ2002ቱ የህወሓት 37ኛ ዓመት ሲያከብር ለውሸት ምርጫም ይቀሰቅስ ስለነበረ፤ በህዝብ ድምፅ ላይ እሱ ራሱ ወሳኝ መሆኑ እያወቀ አስነዋሪ ንግግር ከማድረግ አልተቆጠበም፡፡ የድሮ ጓደኞቹን በይፋ ገለባ፣ እንጉብላይ፣ ለህዝብ ጠላቶች ሽፋን የሆኑ እያለ ሰደባቸው፡፡ ህዝባችን ጨዋነትን እንደ ትልቅ እሴት ያያል፡፡ መለስ ግን ባህላችንን የሚበክልና ለነበረው የራሱ ስልጣንም ክብር የማይሰጥ አመሉ አስፀያፊ ነበር፡፡ መለስ የተለየ ሃሳብ የገለፁ ሰዎችን አመክንዮ ባለው አቀራረብ ስህተት የሚለውን ሃሳባቸው በመግለፅ ፈንታ የሰዎቹ ጭንቅላት እንደበሰበሰ ይሰድብ ነበር፡ ሰው በፅኑ ካልታመመ ጭንቅላቱ አይበሰብስም፤ ጭንቅላቱ እስኪበሰብስ ከታመመም ተቃዋሚ አይሆንም፡፡ ስለዚህ በመለስ የሚሰደቡት ጤኔኛ ሰዎች ናቸው፡፡
አገዛዙ ራሱ ሊያስከበረው የሚገባውን ህግ በመጣስ ሊያጠቃው የሚፈልገውን ሰው (ለምሳሌ ስየን) ካሰረ በሁዋላ ያሰረውን ሰው የሚጎዳ አዲስ ህግ በማውጣት፣ ህግ ወደ ሁዋላ ተመልሶ ተፈፃሚነት እንዲኖረው ማድረጉ አሰፀያፊና ፍርደ ገምደላዊ የበቀል ድርጊት ነው፡፡ በውሸት ተከሰው ታስረው የሚሰቃዩ ዜጎችን በሽምግልና ስም እርቅ ፈላጊ መስሎ በመታየት ህዝብን ለማወናበድ የሚደረግ ቅስቀሳ፣ ነፃነታቸው የተነፈጉ እስረኞች በስነ-ልቡና በማሰቃየት ራሳቸውን እንዲወነጅሉ (ቅንጅት ወዘተ.. ብርቱካን ሚደቅሳ ለሁለተኛ ጊዜ) ማድረግ መለስ ምን ያህል የሰውን ሰብአዊ ክብር የማንቋሸሽ አመል እንደነበረው ያመለክታሉ፡፡ መለስ በአንድ በኩል ለሰብአዊና ዴሞክራሲአዊ መብቶች በሚታገሉ ዜጎች ላይ የጭካኔና አስፀያፊ ድርጊቶች ሲፈፅም በሌላ በኩል ጤንነትን ለሚጎዱና የስነ ምግባር ብልሹነት ለሚያስከትሉ የጫትና አደንዥ እፆች ሱስ መስፋፋት ሊበራል ዴሞክራሲያዊ ሆኖ አልፎአል፡፡
የውሸት ምርጫ ማካሄዱ ራሱ ብዙ አሰፀያፊ ድርጊቶችን ያጠቃልላል፤ ህዝቡንና ተቃዋሚዎችን ያሸማቅቃል፣ የምርጫ ቦርዱን፣ ዳኞቹን፣ የመንግስት ሰራተኞቹንና ካድሬዎቹን ለቅጥፈት፣ ታጣቂዎቹን ለጉልበት ተግባሮች ያሰማራል፤ ማጭበርበር፣ ጉልበት መጠቀምና፣ መዋሸት ስልጣንን ለመያዝ፣ በስልጣን ተጠቅሞም የህዝብና የእርዳታ ሃብት መዝረፍ መጥፎ አርአያ የሆኑ የአገዛኡ መገለጫዎች ሆነዋል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ዘርፈ-ብዙ ጎጂ ድርጊቶችና ጠባዮች ስንገልፅ ባገዛዙ የተጀመሩ ጠቃሚ ድርጊቶች የሉም ለማለት አይደለም፡፡ በተለይ የመሰረተ ልማት ጥሩ ጀማሮዎች አሉ፡፡ ያሉትም በጥራት እንዲያድጉ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
ጥሩ ስራዎች እንዳሉ በመጥቀስ ጎጂዎቹን ለመደበቅ መሞከር ግን ጉዳቶቹ እንዲቀጥሉ ከማድረግ አይለይም፤ ስታሊን ከኢንዱስትሪ እድገት፣ ጋዳፊ ከውሃ አቅርቦት ጋር መንግስቱ ሃይለማርያምም ማሃይምነትን በማጥፋት ሙከራ በአዎንታዊ ሚናቸው ይጠቀሳሉ፤ በዚህ ምክንያት ግን አረሜኔያዊ ድርጊቶቻቸው እየተወገዙ እንዳይደገሙ የሚደረገው ጥረት አልተገታም፡፡ ስለዚህ ባገራችንም በዋናነት መለስ ያመጣቸው የአረሜኔው ስርአት መገለጫዎች እንዲወገዱ ጥረታችን መጧጧፍ አለበት፡፡
ከላይ እንደተገለፀው መለስ በአገርና በህዝብ ዘርፈ-ብዙ ወንጀሎች የፈፀመ፣ በወንጀሎቹ ህዝባዊ ፍርድ ሳያገኝ ያለፈ ሰው ነው፡፡ ቢሆንም እሱ ያሳደጋቸው ደጋፊዎቹና ተከታዮቹ የስልጣን እድሜቸውን ለማራዘም ታላቅ አገራዊ ራእይ የነበረው መሪ ነበር እያሉ በሚቆጣጠሩት የመገናኛ ብዙሃን ህዝብን ሲያደነቁሩ ከርመዋል፤ አሁንም ይቀጥላሉ፡፡
በተለይም መለስ „ዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስት“ እንደተመሰረተና ኢትዮጵያም በኢኪኖሚ በጣም እንዳደገች ያልተቆጠበ የውሸት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለዚህ የውሸት ፕሮፓጋንዳ መሠረት ደግሞ በመለስ አገዛዝ ተሰሩ የተባሉትን ወይም እሱ ያቀዳቸው ናቸው የተባሉትን የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በመጥቀስ ነው፡፡ ሃቁ ግን ከዚህ ነጭ ውሸት የተለየ ነው፡፡
በመሠረቱ ማንኛውም ስርዓት ወይም መንግስት፣ ዴሞክራሲያዊ የሆነም ያልሆነም፣ የተወሰኑ የመሠረተ ልማት ስራዎች መስራቱ የሚጠበቅ ነው፡፡ እጅና እግሩን አጣጥፎ የሚቀመጥ ስርኣት የለም፡፡ በተለይም ዴሞክራሲያዊ ተቀባይነት (legitimacy) የሌላቸው ስርአቶች በልማት ለውጥ አምጥተናል እያሉ አገዛዛቸውን ለማራዘም እንደሚጠቀሙ በታሪክ የታየ አሁንም በተለያዩ አገሮች የሚታይ ክስተት ነው፡፡ መለስ ባጭበረበራቸው ምርጫዎችና በፈፀማቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዴሞክራሲያዊ እንዳልነበረ እንኳን የኢትዮጵያ ህዝበ ይቅርና የሚደግፉት የውጭ መንግስታትና እንዲሁም አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የሚመሰክሩት ሃቅ ነው፡፡ ስለሆነም መለስ „ልማታዊ መንግስት“ የአገዛዙን እድሜ ለማራዘምና እሱና ተከታዮቹ የህዝብ ሃብትን ለመዝረፍ የተጠቀሙበት ስልት ነው፡፡
በመለስ አገዛዝ የተሰሩ የመሰረተ ልማት አውታሮች በአብዛኛው አገሪቱ ከውጭ ባገኘችው በብዙ ሚልዮን ዶላር የሚቆጠር ብድርና እርዳታ ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በሚፈፅመው ሙስናና ዘረፋ አይጠየቅምና በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በአብዛኛው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ህወሓት/ኢህአዴግ ተጠቃሚ መሆኑ የሚካድ አይደለም፡፡ ለአብነት የአባይ ወንዝ ግድብ ስሚንቶና ብረታ ብረት የሚያቀርበው የህወሓት ትእምት (EFFORT) መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
ባጠቃላይ በመለስ አምባገነናዊ አገዛዝ በዘረፋ የበለፀጉት የሱ ተከታዮችና ደጋፊዎች ሲሆኑ፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ተጠቃሚ አይደለም፡፡ የኢኮኖሚ እድገት ቢኖር አብዛኛው የከተማ ህዝብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በሚሄደው የኑሮ ውድነት አይሰቃይም ነበር፡፡ አርሶ አደሩም የማዳበሪያ ዕዳ መክፈል አቅቶት ሳይቸገር የምርቱ ተጠቃሚ በሆነ ነበር፡፡ በብዙ ሺ የሚቆጠር የአገሪቱ የተማረ ሃይልና ወጣት ለስደት ተጋልጦ በሳወዲ አረብያ የግፍና ውርዴት ሰለባ አይሆንም ነበር፡፡
በመጨረሻምው ኢትዮጵያውያን መለስ የፈፀማቸው ወንጀሎች አደገኛነት በመገንዘብ፣ በተለይም የቀበራቸው የአገር አንድነትን የሚሸረሽሩ ፈንጂዎችን ለማፅዳትና የአገራችን አንድነትን ለማጠናከር ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በአንድነት መታገል ታሪካዊ ግዴታችን ነው፡፡
«ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» ምንድን ነው?
ከመ/ጥ መንገሻ መልኬ
«በሰላም ተሳስራችሁ ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኘውን ለመጠበቅ ትጉ። በተጠራችሁ ጊዜ ለአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ ሁሉ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ። እንዲሁም አንድ ጌታ አንድ እምነት እና አንድ ጥምቀት አለ። ደግሞም ከሁሉ በላይ የሆነ በሁሉም የሚሠራ፤ በሁሉም የሚኖር የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ።» ኤፌ4፤3-7
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በዘመናችን የደረሰባት የመለያየት እና የመከፋፈል ዘመን፤ አንዱ ሌላውን ለማጥቃት ቀን ቆርጦ፣ቦታ መርጦ፣ ዘገር ነቅንቆ፣ ጦር ሰብቆ፣ ዝናር ታጥቆ፤ነፍጥ ቀስሮ ወረድ እንውረድ ተባብሎ በጦር መሳሪያ መዋጋት እና በሀገር፣ በሰው ኃይል፣ በማህበራዊ ግኑኝነትና ማህበራዊ ኑሮ፣በኢኮኖሚ ጥፋት ሀገሪቱን ከአንድነት ወደ መበታተን፣ ከማዕከላዊ የንጉሳዊ አስተዳደር የክፍፍሎሽ ሰለባ በማደረግ እድገትዋን እና ሥልጣኔዋን አንቆ ይዞ ለሰባ ስምንት ዓመታት ሲያንገላታት የቆየውን የዘመነ መሳፍንት ታሪካዊ የጥፋት ክስተት ወይም አገዛዝ ጋር የሚዛመድ ነው።
ቤተ ክርስቲያን የሀገራችን ኢትዩጵያን አብላጫ ቁጥር ያለውን ሕዝብ በሃይማኖት የምትመራ በመሆንዋ ሕዝቡን በቀላሉ ለመቆጣጠር ወይም ከአንድነት አስወጥቶ ከፋፍሎ ለማስተዳደር ያመች ዘንድ በተለይም ከዘውዳዊ ሥርዎ በመንግሥት ለውጥ በኃላ እራሳቸውን መንግሥት ያደረጉት ያለፉት አርባ ዓመታት የኢትዮጵያ መንግስታት፤ መንግሥት ሆነው ከዙፋናቸው በወጡ ማግስት ሕገወጥ ጥቃታቸውን እና ጣልቃ ገብነታቸውን የሚፈጽሙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ነው።
ቀደም ብሎም ቢሆን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሰ ነገሥት መፈንቅለ ዘውዳዊ መንግስት አደርጎ እራሱን ጊዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር መንግስት ብሎ የጠራው ደርግ፤ ንጉሰ ነገሥቱን በግፍ ከገደለ በኃላ ፊቱን ወደ ቤተ ክርስቲያኗ በማዞር ውስጥ ውስጡን እጅግ ተናጋሪ ደፋር የሆኑትን እነ ባህታዊ ቀለመወርቅ ካሣሁን እና ሌሎችንም ካህናት መልምሎ በለውጡ ማዕበል በማጥመቅ በቤተ ክርስቲያን ጉልላትን ዘመቻ ጀመረ፤ አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳትም የፓትርያርክነት ስልጣን ፈላጊ በመሆን በደፈጣ የለውጥ አራማጆችን ደጋፊ በመሆን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በደርግ በግፍ ነዲገደሉ አስተዋጽዖ አድርገዋል።
በድጋሜ ከደርግ መንግሥት ላይ ከኤርትራው የገንጣይ ፓርቲ ጋር በመተጋገዘና በመረዳዳት ለአስራ ሰባት ዓመታት የትጥቅ ትግል ያደርገው የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር (ሕወሀት) በግንቦታ 20 ቀ 1983ዓ.ም ደርግን ተክቶ አዲስ መንግሥት ሆኖ ሥልጣኑን በተቆጣጠረበት ማግስት በኢትዮጵያ አርቶኦክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያደረገው ጣልቃገብነት በዋናነት የሚጠቀስ ቢሆንም፤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ በአራት ኪሎ እና በአካባቢው የሚገኙ መሀል ሰፋሪዎች ጥቂት አደባርት ካህናት ጣልቃ ገብነቱን በማጠናክር ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ችግሩን ማባባሳቸው የሚዘነጋ አይደለም።ከዚያም በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በልዩ ልዩ ምክንያት ግራ በማጋባታ እና በማዋከብ ከመንበራቸው ወርደው በግዞት እንዲቀመጡ አስገዳጂ ትዕዛዝ ደረሰባቸው፤ ከዚያም ቀጥሎ የሚጠብቃቸው የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ እጣ ፋንታ መሆኑን ተረድተው የሚወዷትን ሀገራቸውን ጥለው ለስደት ሕይወት ተዳረጉ።
ታሪኩን ለማሳጠር መንግሥት በተለወጠ ቁጥር በቤተ ክርስትያኗ ላይ የሚታየው ጣልቃ ገብነት ተደጋግሞ የታየ ሲሆን በዚህ ሃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት ምክንያት በቤተ ክርስቲአቲያን የአንደነት አስተዳደር ያስከተለው ችግር እጂግ በጣም መጠነ ሰፊ ነው።ከዚህም አንጻር «ፓትርያርክ በሕይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ አይመረጥም» ከሚለው ሃይማኖታዊ ሕግጋት እና ትችት አልፎም ቤተ መግሥቱና ቤተ ክህነቱ በአንድ ክፍለ ሀገር በተለይም በአንድ የአድዋ ተወላጆች ቁጥጥር ሥር በመዋሉ መንግሥትን ይበልጥ በጠባብ ጎሰኝነት ላይ የተመሠረተ አስተዳደር እጂግ በጣም ክፍተኛ በሆነ ደረጃ እያስተቸው መጣ። የቤተ ክርስቲያኗም አስተዳደር ከመንፈሳዊነት ይልቅ ሥጋዊነትና የጎሳ ልዩነት ጎልቶ የሚታይበት ነው! የሚለው ሐሜታና ትችት የአደባባይ ምስጢር ሆነ። ይህ በዚህ ላይ እንዳለ አሁን በዋናነት የሚታየው የቤተ ክርስትያን መከፋፈል ጎልቶ ወጣ፤ ይኸውም፦
2ኛ. በብጽዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ኒውዬርክ፤ አሜሪካ
3ኛ. «ገለልተኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን» በማለት እራሳቸውን የሰየሙ አዲስ ባለታሪኮች በአሜሪካ ና በአውሮፓ የሚገኙ ናቸው።
በዚህ የመከፋፈል ዘመን ከሰባት ሚሊዮን በላይ የቤተ ክርስትያኗ ተክታዮች የጠፉ ስለመሆናቸው አንዳንድ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ጥናት ያደረጉ አባቶች ምስክርነታቸውን እየሰጡ ነው። ይህን ያክል ቁጥር ያለው የቤተ ክርስቲኒቱ አንጡራ ሀብቶች ሲጠፉ ተጠያቂው ማን ነው? የሚለውን ምላሽ በኃላፊነት መልስ የሰጠ የቤተ ክርስትያኗ አካል ባይኖርም፤ በዚህ ጽሑፍ አቅራቢ እምነት ለአንድ መንጋ አንድ እረኛ አለመኖሩ፤ ለአንዲት አማናዊት ቤተ ክርስቲያን አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ አለምኖሩ፣የሃይማኖቱ ባለአደራዎች ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች የተፈጠረውን መክፋፈል ለመመለስ በቂ ጥረት አለማድረጋቸውና ከዚያም አልፎ አዲሱ የመለያየት አርበኛ «የገለልተኛው»ክፍል የውጭውን የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ደጀን አድርጎ በግለሰባዊ የጥቅም ተገዥነት የቤተ ክርስትያኗን የመከራ ዘመን እንዲራዘም አቀንቃኝ እና አራጋቢ ሆኖ በመገኘቱ ጭምር ነው።
በተለይ አሜሪካን ሀገር በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ስም ለገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን መፈልፈል የተመቻቸች ሰገነት ሁናለች። ዛሬ በአሜሪካን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሚለው ስያሜ እየተዘነጋ፤ ከሀገር ውስጥ ነው ወይስ ከወጭው ሲኖዶስ፤ ከገለልተኛ የሸዋ ፤ የጎንደር፤ የጎጃ፤ የወሎ፤ የጉራጌ፣ የኦሮሞ… ቤተ ክርስቲያን በሚል ቤተ ክርስቲያንን የመከፋፈል የዘመነ መሳፍንት አስተዳደር በቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ያነጣጠረ የጥፋት «ገለልተኛ» ዘመን እያንሰራራ መጥቷል።
ይህ አስከፊ ተግባር እና መድኅኒት የጠፋለት የጥፋት በሽታ ከአሜሪካም አልፎ ወደ አውርፓ ዘለቆ በመግባት በርዕሰ አድባራት ሎንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን «ሲኖዶስን እንቀብላለን ፓትርያርኩን አንቀበልም» በሚለው ሰንካላ ምክንያት በር ከፋችነት የንብረት አስተዳደር በምዕምናን ብቻ በሌላ መልኩ የመንፈሳዊ አገልግሎት አስተዳደር በካህናት ብቻ ፤ የሰብካ ጉባዔ አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ እና ሥራ አስፈጻሚ ያለሆነ ተብሎ በአንዲት አጥቢያ ቤተ ክርስትያን የመክፋፈል ጥያቄ አስነስቶ ቤተ ክርስቲያንን ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ኩባንያ በማስመዝገብ፣ በመጭረሻም ሕንጻውን በግል ባለቤትነት ይገባኛል ጥያቄ የተነሳ የተፈጠረው አስቀያሚ ውዝግብ ቤተ ክርስቲያንን አስገደዶ እስከማዘጋት እና ምዕመናኑን በመከፋፈል ያደረሰው አደጋ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም።
«ነገር ግን ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልቦና በአንድ ሐሳብ የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኃለሁ።» 1ኛ ቆሮንቶስ 1፤10
ከላይ በተራ ቁጥር 1ኛ እና 2ኛ የተጠቀሱት ቤተ ክርስቲያን እና በተክታዩ ምዕመናን የተፈጠረው መከፋፈል እጅግ የሚያሳዘን ሲሆን፤ ቅዱስ ሲኖዶሳቱ በአጠራሩ ሕጋዊ ቢሆንም ባይሆንም እራሱን የቻለ ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የየራሳቸው ምክንያት ያላቸው እንደመሆኑ መጠን፤ ግራቀኙ ችግራቸውን በማወቅ በመረዳት ለእርቅ የመደራደርና የመቀራረብ ሙከራ በማድረግ ላይ ቆይተዋል። የዚህን ዝርዝር ሐተታ በሌላ ጊዜ የምንመለስበት ሲሆን ለዛሬው በተነሳሁበት «ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» ምንድን ነው? በሚለው ብቻ በማተኮሩ መልካም ነው ።
«ገለልተኛ» የሚለው የአማርኛ ቃል በእንግዚዘኛው «Independent» የሚለውን ተመጣጣኝ (አቻ) ቃል ያገኛል። ትርጉሙም ከሌላ ውጫዊ ኃይል ተጽኖ ነጻ መሆን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሙሉ ለሞሉም በማንም በምንም አለመታዘዝ እና አለመመራት፤ በሌሎች ላይ ጥገኛ እና ግኑኝነት ወይም ውህደት እና አንድነት አለመፍጠር፤ እራስን ችሎ በነጻነት መንቀሳቀስ የሚሉትን ትርጉሞች ይይዛል።
ከዚህም አንጻር ኢትዮጵያ በአፍሪካ ገኖ ከነበረ የምራብ ሀግሮች (የኮሎኒአይዜሽን) የእጂ አዙር ቅኝ አገዛዝ «ገለልተኛ» «Independent» ነጻ የሆነች አንድ ሀገር ናት ሲባል፤ የተለያዩ ብሔሮች ቋንቋወች ባህሎች ሳይነጣጠሉ ሳይለያዩ በአንድነት ተቻችለው እና ግንባር ፈጥረው በወቅቱ የነብረውን የምራብ ሀገሮች የኢኮኖሚ፣ የቋንቋ፣ የአስተዳደር፣ የባህል፣የፓለቲካ እና የተገዥነት(ባርነትን)፣ማንነትን አሳልፎ መስጠት .. ከመሳሰሉት ተጽኖዎች ገለልተኛ (ነጻ) መሆንኗን በራስ መመራትን ብቃትን እና ተከላካይነትን ያመለክታል። ይህም ከላይ እንደተጠቀሰው፣ ለዘመናት እንደምናውቀውና እንደተማርነው Indepandant Nation ክቀኝተገዥነት ገለልተኛ ወይም ነጻ መሆን የሚለውን የእንግሊዘኛ አቻ ቃል የሚይዝ መሆኑን ያስረዳናል ማለት ነው።
በመሆኑም «ገለልተኛ» የሚለውን ቃል ለመጠቀም ፓለቲካዊ ይዘት እና ሌሎችም በገሀዱ ዓለም በሥጋዊ ፍላጎት እና ተምኔት ዕራይና ተልዕኮ ለሚከናወኑ አንድነት እና ውህደት የሌላቸው ግለሰባዊ እና ቡደናዊ ድርጂቶች መሥሪያቤቶች
እንዲሁም የሳይንሳዊ ጠባይ ያላቸው ነገሮች እና የመሳሰሉት ሰዋዊ የምርምር ግኝቶች መገለጫ መሆኑን ይበልጥ ያስተምረናል እንጅ በክርስቲያናዊ ሕይወት እና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ገብቶ የሚሰራ ቃል አይሆንም።
ይሁን እንጂ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት በክርስቲናዊ ሃይማኖታዊ ትውፊት እና ቤተ ክርስቲያናዊ አወቃቀር ቀኖና እና ስያሜ አንጻር «ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» የሚለው መጠሪያነት ግለሰባዊ ጠቀሜታ እና ፍላጎትን የማስከበር ዓላማ ያለው በሌላ በኩል ደግሞ ተዋህዶና እንድነት ፈጥሮ ከመኖር ይልቅ የመለያየት፣ የመበታተን የመከፋፈልና ብሎም የነበረን ማንነትን (መጠሪያን) የማጣት እና ከአንድነት ጉባኤ የመለየት የመጥፋት አመሠራረት ነው። «ሐዋርያት በሰሯት በአንዲት ቅደስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን» ከሚለው ሁሉም ካናትና እና ምዕመና በሁሉም አብያተ ከርስቲያናት በየቀኑ ከሚጸለየው የአንደነት የሃይማኖት ጽሎት እና የሊቃውንት ሃይማኖታዊ ድንጋጌ የመወጣት ነው።
ለቤተ ክርስትያናችን አንድነት የእምነታችን ሥራዓት፣ቀኖና እና ሕግጋት፣ ትውፊትና አፈጻጸም፣ አስተዳደርና የስተዳደር መዋቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው ነው። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግኑኝነት ጥገኝነት፣ መሠረትነት፣ ተጠቃሽነት አስረጂነት የሌለው ሃይማኖታዊ ክዋኔ ሁሉ ተቀባይነት የለውም። በቤተ ክርስትያን ውስጥ የሚገኙት አገልጋዮች እና ተገልጋዮች በአንድነት ክርስቲያኖች፣ የሚደርጉት አገልግሎቶች መንፈሳዊ እና መገልገያዎች ሁሉ ንዋየ ቅሳት ተብለው የሚጠሩት በዚሁ ምክንያት ነው። ስለሆነም እነዚህ ቃላት ተደጋጋፊ ወይም ጥርስና ከንፈር ሆነው አንድ ሆነው የሚኖሩ እንጂ ምክንያት እየፈጠሩ አንዱ ከአንዱ የማይነካካ «ገለልተኛ» ተብሎ የሚጠራ አይደለም ።
መጽሐፍ ቅዱስ በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነሱም የብሉ ኪዳን መጽሐፍ ነቢያት በዘመን፣ በጊዜ፣ በቦታ፣ በቀን በሳዓታት፣ አመላክተው ወደፊት የሚፈጸመውን የተናገሩትን የትንቢትና የሕግ መጻሕፍትን የሚያጠቃልል ሲሆን ሁልተኛው የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ክፍል ፈጣሪ በተነገረለት ትንቢት፣ በተቆጠረለት ዘመን፣ በታወጀለት ቦታ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ከተወለደበት ከቤተልሔም፣ በተሰደደበት ግብጽ፣ ተዘዋውሮ ባስተማረባት በከንአን/ኢስራኤል፣ በጸለየበት ገዳመ ቆረንቶስ፣ ከተሰቀለበት ቀራንዮ፣ ከተቀበረበት ጎልጎታ በአምላክነቱ ሞትን ድል አድርጎ እስከተናሳበት ድረስ ያሰተማረውን፣ ያደረገውን ገቢረ ታምራት፣የሙታን ማስነሳት እና ለእኛ የሰጠውን ተስፋ መንግስተ ሰማያት የሚያስተምረውን ነው። የሁለቱ ክፍል ጥምረት፣ አስረጂነት፣ ገላጭነትና ተወራራሽነት፣ ተግባቢነትና ተደጋጋፊነት በአንድነት መጽሐፍ ቅዱስ ተብሎ ይጠራል።በመሆኑም በውስጡ ባሉት የመጽሐፍት አንድነት መካከል «ገለልተኛ» የሚለው ስያሜ፤ አወቃቀርና አመሠራረት ቦታ የለውም።
በመጽሐፍ ቅዱስ የአንድነት መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት መጽሐፍት ነጻ፣ ግኑኝነት የሌለው፣ እራሱን የቻለ፣ ለየብቻው የሆነ፣ የተከፋፈለ፣ የተለየ ግንዛቤ የሚሰጥ «ገለልተኛ» መጽሐፍ የለም፤ ይልቁንም አንዱ በአንዱ ላይ ጥገኝነት አንድነት፣ ተግባቢነትና አንድ አይነት መልዕክት የሚያስተላልፍ አንድ ቅዱስ መጽሐፍ ተብሎ የሚጠራ ዘመን የማይሽረው፣ ጥቅም የማይለያየው፣ ተነጣጥሎና ተለያይቶ የማይታይ ሁሉም በአንድነት ሕያው የአንድ የአምላክ ቃል ብለን የምንቀበለው እና የምናምነው ነው። ስለሆነም «ገለልተኛ» ብለን የምንሰይመው አንድም ነገር የለም ሊኖርም አይችልም።
«ይህንንም ያደረገው የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እንድትታነጽ ምእመናን ለክርስቲያናዊ አገለግሎት ለማዘጋጀት ነው። እንዲሁም በእምነት የእግዚአብሔርን ልጅ በማወቅ ወድሚገኘው አንድነት ደርሰን ክርስቶስ ፍጹምና ሙሉ እንደሆነው እኛም ሙሉ ሰው እንድንሆን ነው።» ኤፌ 4፤12-13 እንግዲህ ከላይ በዝርዘር እንደተመለከትናው ከወንጌልና ከሀገራችን ታሪክ ጋር እንዳገንዘብነው በማስረጃ ይዘን እንደተከታተልነው «ገለልተኛ ቤተ ክርስትያን» የሚለው አስተሳሰብ ግለሰባዊ ጥቅም፣ ፍላጎትና እና ግብዝነት የተፈጠረ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን እንረዳለን።
«ገለልተኛ ቤተ ክርስትያን» የሚለው ከኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ አንዲት ቤተ ክርስቲያን የወጣ፣ የብልጣብልጦች የንግድ መርከብ በሌላ አቅጣጫ ደግሞ የአኩራፊዎች ወይም እንቢተኞች በራሳቸው ፈቃድ የመሠረቱት መደበቂያ ዋሻ መሆኑ በሁሉም ዘንድ ይታወቃል። ይሁን እንጂ «ወልድ ሲነካ አብ ይነካል» በማለት ወንጌል የጠገቡ ምስጢር የመረምሩ አባቶቻችን እንደሚተርቱት ሁሉ ቤተ ክርስቲያኗን በሚበታትን ደካማ «የገለልተኝነት» ግለሰባዊ የመክፋፈል አስተሳሰብ ብዙዎቹ ታታላቅ የሚባሉ ዛሬ ለቤተ ክርስቲያንዋ ተቆርቋሪ ነን የሚሉ አባቶች ጭምር የዚህ አሳፋሪ እና የአንድነት አደራ ጠባቂነት ጉድለት ተግባር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተባባሪ እና ተሳታፊ ሆነው ቆይተዋል ፤ ለሃይማኖቱ
ተቆርቋሪ ነን የሚሉ አንዳንድ ማህበራትም እንደዚህ ያለውን ሕገወጥ «የገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» የሚለውን የአንድነት አፍራሽ ተውሳክ ለማጋለጥ አልደፈሩም።
ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚታየው «የገለልተኝነት» ጥቃት አዲስ የሚመሠረቱትን አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ሳይሆን ከላይ እንደተ ገለጸው ወደ አውሮፓም ዘለቆ በመግባት በተለይም የዛሬ አርባ ዓመት በቅድስ ሲኖዶስ ውሳኔ እና በብጹ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የተመሠረተችውን መንፈሳዊ መዋቅሩን ጠብቃ ስትመራና ስትገለግል የቆየችውን የርዕሰ አደባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድሥት ማርያም ነባር ቤተ ክርስቲያንን የተደራጁ ግለሰቦች የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ የግል ባለቤት ለመሆን በገለልተኝነት ለማደራጀት ባስነሱት ከፍተኛ አመጽ ምክንያት መንፈሳዊ አገለግሎቱ በኃይል ተቋርጦ ምዕመናን ተከፋፍለው ከአንድ ዓመት በላይ የቆየ ውዘግብ ፈጥሮ በመጨረሻ በዚሁ ምክንያት እጅግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ መንፈሳዊ አገልግሎቱ በግፍ ተቋርጦ ቤተ ክርስትያኑ ከተዘጋ ስምንት ወራት ተቆጠሩ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሲመሠረተው ቢያንስ ክአራት መቶ ያላነሱ ምዕመናን የሚገለገሉበት ቤተ ክርስቲያን የሚያገለግላቸው ካህን እንደሚያስፈልጋቸው እና ለመንፈሳዊ አገልግሎቱ የሚሆነውን መባውን፣ ማስቀደሻውን እና ማወደሻውን ሁሉ እንደሚችሉ ተፈራርመው ሲያቀርቡና አስፈላጊነቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ሲታመንበት ይመሠረታል። ነገር ግን «ገለልተኛ ቤተክርስትያን» የሚለው ይህን መመዘኛ ሳያሟላ በአስተዳደር በደል ደረሰብኝ ብለው ያኮረፉ ሊቃነ ጳጳሳት፣ በግል ጥቅመኝነት ግለስባዊ ፍላጎት ያላቸው ካህናትና መነኮሳት ወዳጂነት ካላቸው ጳጳሳት በግል ጽላት እያስባረኩ እንደ ሱቅ በደረቴ በተመቻቸው አጋጣሚ «ገለልተኛ» አድርገው ይሰይሙታል። መነገጃ ታርጋው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሚል ነው። እውነታው ግን የወቅቱን ግርግር ተጠግቶ በግለሰቦች ፈቃድ ብቻ የተመሠረተ ከአንድነት ጉባዔ የተለየ አስመሳይ «ገለልተኝነት» ነው። ምክንያቱም ግለሶቹ ያለፈቀዱለት ሊቀ ጳጳስ ገብቶ ያማይባርክበት፣ ግለሰቦቹ ያልፈቀዱለት ካህን የማያገለግልበት፣ ምዕመናን ቢሆን እንደ መጻተኛ ለጎሪጥ የሚታዩበት የሚገላመጡበት እና «መጤዎች» ተብለው የሚሰደቡበት የተበሻቀጠ ግንዛቤ የጎደለው ስሪት ነው። በመሆኑም አሁን በሎንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረው ችግር የዚህ በሽታ አዛማቾች ወይም ተላላኪወች «ገለልተኛ» እና የቤተ ክርስቲያንን ሕንጻ በግለሰብ ለመያዝ የሚደረግ እጅግ በሚቀፍ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስተዳደር መዋቅር ላይ የተደረገ በመለያየት የተሞላው የጥቅም ያደነዘዘው አሳዛኝ ዘመቻ ነው።
«ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» ማለት በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠውን የአባቶች መለያየት ክፍተት እንዲቀጥል የተሳሳተ መገድ የሚጠርግ ነው። ቤተ ክርስቲያን ሁሉም የክርስትያኖች ማምለኪያ፣ የመንፈስ ቅዱስ ሀብት መሆንዋ ቀርቶ ጊዜ የፈቀደላቸው፣ኃይለ የተሰማቸው፣ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው የተመኩ ግለሰቦች በቡድን ተደራጅተው በቤተ ክርስትያኗ ውስጥ ግንዛቤ የጎደላቸው ግብረ በላተኞችን እና ገንዘብ አምላኪ መሰል ካህናትን በማስተባበር፤ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት የወጣ፣በጠባብ ጎሰኝነትን መሠረት ያደረገ፣ በግለሰቦች የግል ባለቤትነት የተያዘ፣ አስታራቂም ታራቂም ያልሆነ፣ የቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ መንፈሳዊ መዋቅር የተለየው፣ ተቆጣጣሪና የበላይ ጠባቂ የማይታወቅበት፣ መለያየትና መበታተን የሚጠናከርበት ከሀገራችን ኢትዩጵያ እና ከኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአንድነት ታሪክ ውስጥ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ጸረ አንድነት አስተሳሰብ እኩይ ተግባር ነው።
ስለዚህ ሁሉም ኢትዩጵያዊ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተክታዩች ሁላችን «እርስ በርስሷ የተለያየች መንግሥት አትጸናም» ብሎ መጽሐፍ እንደሚያስተምረን እምነትን በፍቅር በሰላም ለማከናወን የሀገር አንድነትን ለማስጠበቅ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ለውጥ ለማምጣት የሚቻለው የእምነትና የታሪክ በለአደራ የሆነችውን ቅደስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን በሐዋርያት ትዕዛዝ መሠረት በአንድነት ስንጠብቅ እምነታችን የጸና መሆኑን አወቀን «ገለልተኛ» በማለት እየተቋቋሙ የቤተ ክርስቲያንን የመከራ ጊዜ የሚያረዘሙ ትርጉም የጠፋለትን የጸረ አንድነት ግለሰባዊ የጥቅመኞች ጎዞ እንዲገታ ማድረግ የአዲሱ ትውልድ ታሪካዊ ግዴታ ነው።
እንዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችን በአንድነት ይጠብቅልን!
መ/ጥ መንገሻ መልኬ
ኅዳር 2006 ዓመተ ምረት ዘመነ ማርቆስ ወንጌላዊ፤
ኔልሰን ማንዴላ እና ኢትዮጵያ!! –በዳዊት ከበደ ወየሳ (ጋዜጠኛ)
ኑዛዜ ማንዴላ
ከገለታው ዘለቀ
geletawzeleke@gmail.com
መቼም ሰው ሥጋ ነኝና ታከተኝ
እረፍት ለጎኔ ናፈቀኝ
ሩጫዬን ግን ጨርሻለሁ
እምነቴንም ጠብቂያለሁ
እነሆ ከፊቴ ……….
ከሰማዩ ከላይ ኣባቴ
የድል ኣክሊል ተዘጋጅቶልኛል
የሰላም የፍትህና የ’ኩልነት
ደግሞ የህግ በላይነት
ዋንጫዎች ይጠብቁኛል
እስትንፋሴ ሳይለይ ግን ኣንድ ነገር ልበል……..
ኣንቺ ኣፍሪካ………
እትብቴ ስወለድ የተቀበረብሽ
ዘመኔን ሁሉ የሰጠሁሽ
እናት ዓለም ኣዳምጪኝማ
ኑዛዜ ቃሌን ጻፊልኝማ
ኣዳምጪኝማ ልንገርሽ
ምክር ተግሳጼን ልስጥሽ
ብዙህ ተፈጥሮሽን
ቀስተ ደመናነትሽን
ውበትሽ ኣርጊው ድሪሽ
ክብርና ልዕልናሽ
ኣትለይው ካንገትሽ ላይ
ዘመን ሲመጣ በዘመን ላይ
ኣንቺ ደቡባዊት ኣፍሪቃዬ
አትብቴ የተቀበረብሽ እመዬ
እንደገና ኣንድ ነገር ላስተንክርሽ
ኣዳምጪኝ እማ ሆይ እባክሽ
ያኔ በለቅሶ ዘርን ስትዘሪ
የነጻነትን፣ የፍትህን ኣባት ስትጣሪ
ጩኸትሽ ከጸባኦት ገብቶ
ቅንፈረጁን ኣምላክ ኣትግቶ
የኢያሪኮን ግንብ ኣፈረሰው
የግዞት ቤቱን ደረመሰው
የብረት በሩን ኣባተው
እግረ ሙቁንም ኣቀለጠው
ት ዝ ይለኛል……
ስወጣ እስራቴ ተፈቶልኝ
ምናቤ ተከፍቶ እንዲህ ኣሳየኝ
አነሆ ጸሃይ ህጉዋን ሰብራ
የተፈጥሮ ልማዱዋን ሽራ
በደቡብ በኩል ስትወጣ
የዘንባባ ዝንጣፊ ኣምጥታ
ኣየኋትና ደስ ኣለኝ
ተሰፋና ሃሴት ወሰደኝ
ኣይኔ በሮቶልኝ ኣሻግሬ ሳይ
ከጸሃይ መውጪያ ወዲያ ማዶ ላይ
ከኒያ ካሳለፍናቸው ክፉ ዘመናት በላይ
ክምር የመልካም ነዶ ዘመን ተቆልሎ ባይ
የኣሁኑ ዘመን ስቃይ
ሊመጣ ካለው ክብር ጋር ሲተያይ
እንደ ኢምንት ሆኖ ኣየሁትና
የዘንባባ ዝንጣፊ ኣነሳሁኝ
ሰላምና ፍትህን ኣወጅኩኝ
በቀልና ዘረኝነትን ኮነንኩኝ
የኩልነትን እጀታ ኣጥብቄ ኣጥብቄ ያዝኩኝ
ያ ነበር በውነት ያስደሰተኝ
በርጅና ዘመኔ ሁሉ እንደ ንስር የሚያድሰኝ
ኣንቺ ደቡባዊት ኣፍሪካዬ
አትብቴ የተቀበረብሽ እናትዬ
ከምድርሽ ፍሬ በልቼ
ከሖድሽ ጠበል ጠጥቼ
ኣድጊያለሁኝና
ምስጋናዬ ይሄውና
ያ የክረምቱ ጊዜ ኣልፎ
ዶፍ ዝናሙ ደመናው ሁሉ ተገፎ
እሰይ እሰይ ኣጨዳሽን ጀምረሻል
የመኸር ጊዜ መጥቶልሻል
ኣጨዳሽን እጨጂ
በርቺ ሂጂ ተራመጂ
ግን ደሞ ….
ኣንድ ነገር ኣትርሺ
ያን ያፓርታይድ ዘረኝነት እንዲያ አንደጠላሽው
ኣንገፍግፎሽ ኣንዘፍዝፎሽ ወዲያ እንዳልሺው
እንደዚያው እንደጠላሽው ኑሪ
በፍቅር ባቡር ብረሪ
አንዳትመለሽበት ኣደረሽን
ከነፍስሽ ጥይው እባክሽን
በራስሽ ላይ አንደጠላሸው
በሌላውም ላይ አታድርጊው
እነሆ አግዚኣብሄር በሰጠኝ ኣገልግሎት
የፍቅርና የሰላም ክህነት
ውጉዝ ውጉዝ ከመ ኣርዮስ
ውጉዝ ከኣፍሪካ ብያለሁ ዘረኝነትን
ኣምባገነንነትና ኢፍታዊነትን
ኣትብቀሉ በምድሪቱ
ኣትለምልሙ ኣታኩርቱ
ባለም ሁሉ በምድሪቱ
ያለም ህዝቦች ሁላችሁ
የሰው ዘር ሁሉ የሆናችሁ
ከሰላምና ከእኩልነት ገበታ ብሉና ጠጥታችሁ ርኩ
ሰላም በሰላም ላይ ፍቅር በፍቅር ላይ ተኩ
የናቴ ያባቴ ልጅ ኣፍሪካ…………
ኣሁን ስጋዬ ረፍት ብጤ ናፈቀው
መቼም ሰው ነውና ስጋ ነውና ታከተው
ሄዶ ሄዶ ከዚህ ኣይቀርምና
የተፈጥሮ ህግ ኣይሻርምና
እኔ እንግዲህ ሄጃለሁ
ፍቅር ሰላም አኩልነት ላለም ሁሉ አመኛለሁ
ኣበቃሁ ቃሌ ይሄው ነው ኑዛዜየን ኣድርሻለሁ
ሃብቴ ቅርሴ ያለኝ ይሄው
ኑዛዜየ ስጦታዬ እምነቴ ነው
ለእምነት፣ ለእውነትና ለሕሊና የሚስማማ ሥራ እንስራ
ከእውነት መስካሪ
የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በዘመናት ካጋጠሟት ፈተናዎችና ችግሮች ሁሉ ምናልባትም በአይነቱ ብቻ ሳይሆን በስፋቱም ለየት ያለው ይህ አሁን በእኛ ዘመን የተከሰተው የአባቶች መከፋፈል ወይንም በፖለቲካ ጣልቃገብነት የተፈጠረው የቤተክርስቲያኗ አመራር ክፍፍል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በአጠቃላይ በክርስትና ላይ የደረሰውን ፈተና ትተን በእኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ብቻ የደረሰውን እንኳን ብናይ በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዮዲት ጉዲት፣በ15ኛው መ/ክ/ዘ በግራኝ መሐመድ፣በ18ኛው መ/ክ/ዘ በእንግሊዝ፣ በ19ኛውና በ20ኛው መ/ክ/ዘ በፋሺሰት ኢጣልያ ወረራ በቅርቡም በደርግና አሁን ደግሞ በወያኔ ኢህአዴግ መንግሥታት በቤተክርስቲያናችን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለው ጉዳት እጅግ ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን በቀደመው ዘመን የነበሩት አባቶቻችን በእምነትና በእውነት እየተመሩ ለህሊናቸው ብቻ ሳይሆን ለትውልድም የሚያኮራ ስራ ትተውልን አልፈዋል፡፡
በዮዲት ጉዲት 40 ዓመት የመከራ ዘመን መከራው ስለበዛባቸው 10ኛው ወይንም 20 ኛው አመት ላይ እንግዲህ በቃን እስከመቼ እንዲህ ሞተንና ተሰደን እንዘልቃለን ልጆቻችንስ እስከመቼ እንዲህ ሆነው ያድጋሉ በማለት እጃቸውን ለጨፍጫፊዋ ዮዲት አልሰጡም። 40 የመከራ አመታትን በሰማእትነት፣በስደትና በመከራ አሳልፈው ተዋሕዶ እምነታችንን እስከነምልክቷ አስተላልፈውልናል። በዘመነ ግራኝም እምዲሁ ሰማእትነትን ከፍለው ታቦታቱን በዋሻ ደብቀው ከአገር አገር ተንከራተው ኃይማኖታችንን ከነክብሯ አስተላልፈውልናል።
ፋሺት ኢጣልያንም በርካታ ገዳማትንና አድባራትን አቃጥሏል። በተለይም ታላቁን የደብረሊባኖስ ገዳም ከማቃጠሉ በተጨማሪ ቁጥራቸው ከ500 በላይ የሆኑ ገዳማዊያንን በግፍ ጨፍጭፏል። ይሁን እንጂ የቀደሙት አባቶቻችን በእምነታቸው ጽናት ለጨፍጫፊዎችና ወራሪዎች ሳይንበረከኩ ኃይማኖትን ከነምልክቱ አገርን ከነነጻነቱ አቆይተውልናል። በጣልያን የኋለኛው ወረራ ወቅት የቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊ አባት የነበሩትን ፃድቁ ሰማእትና አርበኛ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስን ጣሊያን በአደባባይ ከገደለ በኋላ ለጣሊያን መንግሥት ያደሩ አንዳንድ ባንዳ ‘አባቶች’ ከጣሊያን ጎን ተሰልፈው ሕዝቡ ለጣሊያን እንዲገዛ ሲያደርጉ የነበሩ መኖራቸው በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ በተለይም በሰማእቱ አቡነ ጵጥሮስ ወንበር አቡነ አብርሃም የተባሉ አባት ለጣሊያን አድረው በአቡነ ጵጥሮስ ቦታ ተሾመው ነበር። ጀግኖች አባቶቻችን ግን ይህን አይነቱን ክህደት አንቀበልም በማለት በዱር በገደሉ ለአገራቸውና ለኃይማኖታቸው ነጻነት ተጋድለዋል።
በተጋድሎአቸውም ተዋሕዶ እምነታችንን ከካቶሊክነት ኢትዮጵያንም ከቅኝ ግዛት ታድገዋታል። እንግዲህ እኛ አባቶቻችን የምንላቸው ሰማእታት ሆነው፣ተሰደውና በእምነታቸው ጸንተው እምነታችንን ከጠላቶቻችን ታድገው ያቆዩልንን እንጂ በክህድት፣በፍርሐት፣በወገኝተኛነት፣በዘርና በመሳሰሉት ምክንያት ከጠላት ጎን ሆነው ኃይማኖታቸውንና አገራቸውን የከዱትን አይደለም።
በዚህ በእኛም ዘመን ያለን የተዋሕዶ አማኞች አባቶቻችን የምንላቸው እነማንን ይሆን?
የኢትዮጵያ ክብር ሲዋረድና ሕዝቦቿ ሲሰደዱ ይህን ከሚያደርገው አካል ጋር የቆሙትን?
ወይንስ የአገር ዳር ድንበር መፋለስና የህዝቦቿ አንድነት መሸርሸር የለበትም ብለው ከተሰውና ከተሰደዱትን ጋር?
በቤተክርስቲያን ላይ በመጠን ሊገለጽ የሚከብድ ጥፋትን እያደረሰ ካለ ኃይል ጋር የቆሙትን? ወይንስ ይህን የቤተክርስቲያንን መጠቃት የሚቃወሙትን ነው አባቶቻችን የምንል?
ምናልባተ በዘመናችን በእውነት ስለኃይማኖትና ስለአገር ብቻ ሳይሆን የራስንም ክብርና ምኞት ለማሳካት የሚደረግ ነገር በሁሉም ዘንድ አንዳለ ቢታየን አምላካችን በእውነት እስኪገለጥልን በያለንበት እንጽና እንዳለው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከአጥፊዎችና ከጥፋቱ ተባባሪዎች ጋር ከመቆጠር ራሳችንን ልናቅብ ይገባናል። እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ መንገድ አለው፤በኃይለኛ ውኃ ውስጥ መተላለፊያ ያደርጋል እንዳለ ነብዩ ኢሳ.43፥13 ሁሉ በእግዚአብሔር ጊዜ ስለሚፈጸም፤ የቤተክርስቲያን ልዕልናና የኢትዮጵያ ትንሳዔ መምጣቱ ስለማይቀር ያለነው ትውልዶች ለእምነት፣ለእውነትና ለሕሊና የሚስማማ ሥራ ሰርተን እንድንገኝ እግዚአብሔር ይርዳን። አሜን!
ወያኔ የካደው = ግንቦት ሰባት የተነፈሰው = አና ጎሜዝ ያልሸሸጉት አዲስ ነፋስ (“ድርድር”)
ከምኒልክ ሳልሳዊ
ይህን ሰሞን በሃገር ውስጥ እና በውጪው ሃገር ኢትዮጵያውያን ዘንድ የመወያያ ርእስ የሆነው እና ይየወያኔ ካድሬዎችን ቀልብ የገፈፈው እና ከሰል ያለበሳቸው ወያኔ ለግንቦት ሰባት ያቀረበው የድርድር ጥያቄ ነው::በስፋት አሁንም እየተከራከሩበት ያለው ይህ ጉዳይ አገሩን በጡዘት አምሶት የሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት አንድ ተስፋ የሰጠ ሁኔታ እንደሚታይ እየተተነበየ ነው::
ወያኔ በእርግጥ በማይጥም የፖለቲካ እሰጥ አገባ የተጠመደ ቢሆንም የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ለላውን ከማዘናጋት ውጪ ምንም አይነት ፋይዳ እንዳሌለው እና ራሱን እየፈተሸ እንደሆነ ያጋለጠ ጉዳይ ነው:: የድርድር ጥያቄ አላቀረብኩም ያለው ወያኔ እንደለመደው ከኦነግ ከኦብነግ ከሻእቢያ ጋርም እየተደራደረ ጥያቄውን እራሱ እያቀረበው ሲክድ የቆየ ሲሆን በቅርቡ እንኳን በኬንያ ከኦብነግ በጀርመን ከሻእቢያ ጋይ ያደረጋቸውን ድርድሮች እየታከካቸው አልፏል::
ወያኔ የካደው እና ግንቦት ሰባት የተነፈሰው የእንደራደር ጥያቄ የአናጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ ተከትሎ የወጣ ጉዳይ ነው:: በእርግጥ በተለያዩ ጊዜያት ለወያኔ እና ለግንቦት ሰባት የቅርብ ርቀት የሆኑ ሰዎች ይህንን ጉዳይ በግል አንስተውት የሆነ ቢሆንም ባይሆንም ግን የአና ጎሜዝ የአዲስ አበባ ምላስ ተከትሎ ግንቦት ሰባት ለህዝብ ይፋ ያደረገው ጉዳይ አሁንም ሚዛኑ ወደ ግንቦት ሰባት እንዲሆን አድርጎታል::
እንቅልፍ የነሳቸው የወያኔ ባለስልታናት የቀን ተቀን የስብሰባ መቀመጫቸው ግንቦት ሰባት ነው:; በወታደሩ በደህንነቱ እና በታማኝ ካድሬው ዙሪያ ውይይቱ ምስጢሩ ግንቦት ሰባት ነው:: እነዚህ የሚስጥር ተወያዮች እንደሚጠቁሙት ሲሰበሰቡ በውይይት ወቅት ግንቦት ሰባትን አሸባሪ ብለው አይጠሩትም:; አሸባሪ የሚለውን ቃል የሚጠቀሙት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታቸው አደባባይ ላይ መሆኑን በይፋ የተረጋገጠ መረጃ ይጠቁማል::
በቅርቡ ከአባቱ ሻእቢያ ጋር ጀርመን ላይ የተወያየው ወያኔ ግንቦት ሰባት የራስ ምታት ስለሆነበት እንዲያደራድረው አሊያም እንዲገላግለው ተማጽኖ ቢሆንስ??? ወይኔ ሻእቢያ የሚፈልጋቸውን ተቃዋሚ ኤርትራውያንን እያፈነ እንደሚሰጥ የህን ሰሞን ሃተታዎች እየጠቆሙ ነው እንዲሁም በሱዳን በኩል እያሽከረከረም እንደሚያስረክብ::ነገሩ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል አይነት ነው ….
የአቶ ታምራት ላይኔም ወደ ፖለቲካው ለመቀላቀል ማቆብቆብ እኮ የዚሁ የድርድር አንዱ አካል ነው:; ብኣዴን ታምራት ላይኔን ይፈልገዋል:: አገሬ በፈለገችኝ ሰአት ለማገልገል ተዘጋጂቻለሁ የሚለው ታምራት ጠጋ በል እየተባል መሆኑስ የወያኔ አንድ የጭንቀት ምልክት አይደል?! … ወደ ሚዲያዎች አያሰገገ መምጣቱ ሌላ ምስጢር የለውም::
አና ጎሜዝ ከአዲስ አበባው ቆይታቸው ሁለት ንግግሮችን ከአንደበታቸው ሰምተናል:: አንዱ “ከባለስልጣናት ጋር ያደረኩት ውይይት በጎ እና ገንቢ ነው መልካም ምላሽ እንዳገኙም በእርካታ ተናግረዋል:; በመተማመን ስሜት ደሞ “አዲስ ንፋስ አለ” ሲሉ ተስፋቸውን አብርተዋል:: ይህንን የፖለቲካ ስሜታቸውን ያልተረዱ የደፈናው ጋዜጠኞች የወያኔን የሞተ እስትንፋስ ሊያበረቱ ቢሞክሩም የሚሳካ ካለመሆኑም ሌላ ወያኔም …ጌታ….ተላላኪ…;;እያለ ቢዘላብድም ታምኝነት ሊያገኝ አልቻለም:: አና ጎሜዝ ይህንን ሲናገሩ ከባለስልጣናት አንደበት የሰሙት እና የተላኩት መልእክት እንዳለ ይጠቁማል:: አና ጎሜዝ ወደ ግንቦት ሰባት ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የለውጥ ጠያቂዎችም የብሄራዊ ድርድርን ጉዳይ አስረግጠው አዋይተዋል:;በእርግጥ ስለግንንቦት ሰባት ባያነሱም ይህ የእንደራደር ጥያቄ የመልስ ምቱን ወያኔ ለማወቅ ፈልጎ ያደረገው ሊሆን የሚችል የማጭበርበሪያ የፖለቲካ ስልት ቢሆንም የድርድሩ ጥያቄ ግን የአና ጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ እና የአዲስ ነፋስ ምልክታን ተከትሎ መነገሩ እውነታውን ያጎላዋል:; ይህ የሚያሳፍረው ወያኔን ቢሆንም ወያኔ ግን ምንተእፍረቱን አይኑን በጨው አጥቦ ቢክድም አሁንም ግንቦት ሰባትን እንዲያደራድሩት ከትን እንዲያደበጀርባ እየተለማመጠ እንደሚገኝ ለማስገንዘብ እወዳለሁ
ስለሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ፦«የዋህነት ጸባይ እንጂ እምነት አይደለም» –መጽሀፈ ምሳሌ ምዕ 3 ቁ 1
ከጦመልሳን ወንድራስ
«የዋህነት ጸባይ እንጂ እምነት አይደለም»
መጽሀፈ ምሳሌ ምዕ 3 ቁ 1
«ልጄ ሆይ ሕጌን አትርሳ ልብህ ትዛንዜን ይጠብቅ»
ለእዚህ ጽሁፌ መነሻ ያደረኩት June 2, 2013 በሚኒሶታው ደብረሰላም መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን ውስጥ በተደረገው ስብሰባ ላይ ያየሁትን እኔም እምነቴ የሚስማኝን ለመጽፍ ወደድኩ።
ይህ ሀሳብ የእኔ ብቻ እንደሆነ አንባቢያን እንዲረዱልን በማክበር እጠይቃለሁን።
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእድሜ አንጋፋ ከሆኑ ሀይማኖቶች አንዱ ብል ማጋነን አይሆንብንም፤ ይህ ሀይማኖት ሳይከለስና ሳይበረዝ የራሱን ህግጋቶችና ደንቦች እየጠበቀ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ሲሸጋገር እነሆ ዛሬ ያለንበት ጌዜ ላይ ደርሰናል። ሂደቱም ቀላል አልነበረም። ስንት አበው አባቶች አንገታቸውን ሰተውበታል፣ ተሰደውበታል፤ ታሰረውበታል።
ላለፉት 22 አመታት ግን የምናየው የተለየ ሆኖ አግቸዋለሁን ለዚህም እንደማስረጀ ላቅርብ፦
1 የጸሎት አባቶች ከመንፈስ ስራ ይልቅ ጉቦ መዘፈቃቸው
2 ቤተክርስቲያኖቾ ለአልባሌ ንግድ መግባትና መሰማራት (ገብርኤል፤ኡራኤል፤ልደታ) ለምሳሌ መጠጥ ቤት፤ ቻት ቤት፤ ሙዚቃ ቤት ወዘተ።
3 በዋልድባ የሚኖሩ አባቶች ሲደበደቡ የሲኖዶስ አመራር አባሎች ዝም ብለው መመልከታቸው (አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ)
4 ጳጳሱ ሳይ ሞቱ ሃውልት አቁመዋል እንዲፍርስ ታዞ ድፍረቱ ያለው ነፍስ አባት ማየት ተቸግረናል
5 ጳጳሱ በአለ ሲመታቸውን በሸራተን አስረሽ ምችው ሲሉ ሌሎች ቤተክርስቲኖች የጣፍና የሻማ መግዥ አተው እናያለን
6 ጳጳሱ አቀንቃኖች አምጥትው ጉያቸው ስር እስከማስቀመጥ አዋርደዉታል
7 የስላሴ ኮሌጅ መዘጋት
8 የኦርቶዶክስ ምጽመን በጸሎት አባቶች እንዲያፍርና እንዲሸማቀቅ አድርግውታል
9 ከዚህ በፊት የተያዘው ሽምግልና ፈርሶ ገዥው መንግስት የራሱን ስው ሾሟል
ታዲያ በሂደት ያየናቸው ጳጳስ እንደ ብጽጹ አቡነ ተክለሀማኖትና በቅርቡ ህወታቸውን ያለፈውን ጵዉሎስን እንመልከት ማነው ለነፍሱ ያደር ማነው መንጋውን የጠበቀ ፍርዱን ለናንተ እተዋለሁኝ
ይህ በእንዲህ እንዳለ June 2, 2013 በቤተክስቲያን በተደረገዉ ጉባኤ የቤተክርስቲያኑ ቆሞስና አንዳንድ ሰንበት ተማሪዎች ተሰብስበው ይችን ቤተክርስቲያን ወደ አገር ቤት ካለው ሲኖዶስ እንቀላቀል ይሉናል እንግባ ይሉናል ፀሐይ ላይ ያሰጡት ኩታ ይመስል ይሞጉቱናል ይህ ማለት ከላይ የጠቀስዄቸውን ሁሉ አባሳ መደገፍ አይሆንም። ይቺ ቤተክርስቲያን ላለፉት 21 አመት ሕግና ደንብዋን አስጠብቃ የኖረች በአሜርካን ውስጥ ካሉት ቤተክርቲያን ለምሳሌ የምትቀርብ ብል ማጋነን አይሆንም በእዚህም ምንጊዜም እኮራለሁ።
ከሁሉም በላይ የሚገርመኝ የሰንበት ተማሪዎች ነን ባዮች ከላይ የጠቀስኩትን እውነታ እያወቁ ከቆሞሱ ጋር መወገናቸው ብዙ አይገርመኝም በየትኛውም ኦርቶዶስ ቤተክርስቲያን መዘምራን ቄሱ ፊሽካ ናቸው። ቄሱ በፈለገው ጌዜና ቦታ የሚነፋቸው ጡሩንባ ናቸው ቅዱስ ስራውን እየጣሱ ቅዱስ ማሕበር አባል ነኝ ማለት አይገባኝም ቁሞሱ ይህን ቤተክርስቲያን ወደ ሲኖዶስ ከቀላቀሉ ጳጳስ ይሆናሉ ተብለዋል ታዲያ መዘምራን ለእናንተ ምን ቃል ተገባላችሁ ንገሩን ትላንትና ቤተክርስቲያኑን ባለው ሕግና ደንብ መሰረት ስትመሩ የነበራችሁ ዛሬ ወደ እዛ እንግባ የምትሉን ቆሞሱ ቢሆን ለጳጳስነት የሚያበቃ ዕውቀት ልምድ አላቸውን እኔ እስከማቀው ድረስ በውነት፤ዛሬ፤በውነት፤ዛሬ ከማለት በስተቀር በትክክለኛው ወንጌል ሲያስተምሩ አይችሉም።
ለእዚህ ማስረጃ ሆኖ የማቀርበው ወደ ቆሮንጦስ ስዎች ምዕ 12, አንቀጽ 7-10 ምን ይላል
ቆሞሱ እግዜአብሔር በሰጣቸው ሊቅነት ቢያገለግሉ ምናለ የማታ ማታ የነፍስ አባት የሚሆኑት እርሳቸው አልነበሩምን ታዲያ የዚህን ምስኪና የዋሕነት ተጠቅመው መቼ ነው የምትቆርቡት ከማለት በስተቀር እስቲ አስራት በኩራት ስጡ አይሉም ምክኒያቱም አስራቱን ከሰጠ ቤተክርስቲን ሁሉ ለልመና አደባባይ ባልወጣች ነበር።
አሁን በቤተክርስቲናቺን ውስጥ 20% አስራቱን የሰጣል 80% አልገባውም ወይም የፀሎት አባቶች የሚነግሩት አፈታሪክ ነው የስንበት ተማሪዎች ተብየዎቹ ስንቶቻችሁ ናችሁ አስራት የምትከፍሉ ስንቶቻችሁ ናችሁ ለአዲሱ ሕንጻ መዎጮችሁን የከፈላችሁ ስም አልጠራም ሰም ማየት ይቻላል መዝገቡ ይናገራል ዳሩ አልፈርድባችሁም አንዳንዶቻችሁ ቄስ ጭን ስር ስላደጋችሁ የእግዚአብሔርን ክብር ለቄሱ ስታችሀል፤ አንዳዶቻችሁ መዋለንዋይ አማልሎችሀል ይህን እውነት ማንም ሊደፈጥጠው አይችልም። አንዳዶቻችሁ የዕውቀት ማነስ ይታይባቸዋል
ለእዚህም እንደ ምክኒያት የማቀርበው ሲኖዶስ ማለት ምን ማለት ነው(ሕግ ወይም መተዳደሪያ ደንብ)ማለት ሲሆን አስፈፃሜው አካል ደግሞ ቤተክህነት ይባላል ይህ የእኛ ቤተክርስቲያን በአንድ ኢትዮጵያ በአንድ ሲኖዶስ እናምናለን
ይህ ለእኔም ፤ለቆሞሱም፤ ለመዘምራንም፤ ለቦርዱም፤ እናም ለምመኑም ግልጽ መሆን አለበት ከዚህ ውጭ ስለ ህጉ የነገራችሁ ካለ ስህተት ነው።
ከሁሉም በላይ መናገር የምፈልፈው ማንም ሰው ኢየሱስ አላየም ሥራው፤ተአምሩ፤ ሰብስቦናል የምንጠየቀው በምግባራች ነው እንጅ በያዝነው ሀይማኖት አይደለም ይህ ቢሆንማ ኦርቶዶክስ ተለይቶ ሰማያዌ መንግስትን በወረስን ነበር ይህ አፈ ታሪክ ነው።
አንዳንድ የዋህ ምዕመን እዛ ገብተን መታገል አለብን ይላሉ።
«እግር እራስን አያክም« ትግል መሰዋትነትን ይጠይቀል የፀሎት አባቶች የያዙት ልፊያ ነዉ 22 አመት ተላፍተናል ደክሞናል፣ ለእዚህም «የዮሀንስ ወንጌል ምዕ 11 አንቀጵ 40 ማየት በቂ ነው። ወድ የቤተክርስቲያኑ አባላት ይህ የተጋረጠብን አበሳ አስወግደን ቤተክርስቲያናቺን እንጠብቅ« እምነት ሁሌም አልጋ በአልጋ ሆኖ አያቅም» ከእዚህ ትልቅ ጋሬጣ ካላስወገድን ወ ደፊት ለምናስበውና ለተለምነው የቤተክርስቲያኑ ግንባታ አንደርስም። ለእዚህም አንድ ቃል ልጥቀስና ጹሑፌን ላጠቃል።
«የያቆብ መልክት 2 ምዕ2 አንቀጵ 11 እንዲህ ይላል «ወንድሞቼ ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን ሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቀመዋል እምነቱ ሊያድነው ይችላልን»
ታዲያ ኦርቶዶክስ ነን የምንል ሁሉ ቤተክርስቲያናቺንን ማዳን ይኖርብናል ይህ ቡና ረከቦት ስር የሚወራ ወሬ አይደለም የልጆቻችሁ የወደፊት ተስፋ የሚያጠፋ ነው
ዠንጀሮ የመቀመጫዋ መላጣ አይታያትም ይህ ካልታየን በእንግሊዚ ያለውን ቤተክርስቲያን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ፣ በስላሴው ኮሌጅ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ማየት ይቻላል በዚህ ዓለም ስንኖር የምዳኘው በሕግ ነው ለነፍሳችን ግን የምንዳኘው በፈጣሪያችን ብቻ ነው።
አሁንም ቤተክርስቲናችንን ይጠብቃት መሪዎቻን ማስተዋል የስጥ ያልተከለሰና ያልተበረዘ ወንጌል ማስተማር ይጠብቅባቹኃል
እግዚአብሔር አገራችንን ይባርካት
ጦመልሳን ወንድራስ
ሚኒሶታ መድኃኔዓለም ደብረሰላማችን ፣ ትንሿ ኢትዮጵያ ምትክ አገራችን –ለሰላምና አንድነት የቆሙ ምእመናን ያስተላለፉት ጥሪ
Dec.7, 2013
በሥላሴ ስም አንድ አምላክ። አሜን!
ለሰላምና አንድነት የቆሙ ምእመናን
ኢትዮጵያዊነት የሚንጸባረቅበትንና መቻቻልና አንድነት የሰፈነበትን ማኅበር ወይንም ስብስብ ሁሉ የኃይማኖት ይሁን የሌላ የማፍረስና ሰላም የመንሳት አባዜ የተጠናወተው በትልቋ ኢትዮጵያችን ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የህዝቧን ደም እየመጠጠ የሚገኘው ወያኔ ኢሕአዴግ ነው። አስቀድሞ ገና ከጫካ ወደ ከተማ ሲመጣ እንደ አብይ መፈክር ይዞ የነበረው የታላቋን አገር ታሪክ ማንኳሰስ፣ ባንዲራዋን ማዋረድና ሕዝቧን በዘር መከፋፈል ነበር። አሁንም ነው፡፡ ይህች የረዥም ዘመን ታሪክ ያላት ታላቅ አገር በዘመናት ለተቀዳጀቻቸው አኩሪ ድሎችና ገድሎች ደግሞ ሁሉም እምነት፣ ተቋማትና ብሔረሰቦች አስተዋጽኦ ነበራቸው። በተለይ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከኢትዮያ ታሪክና ሁለንተናዊ ማንነት ጋር የነበራት ትስስር የጎላ መሆኑ ለሁሉም የተገለጸ ነው። በዚህም ምክንያት ይህ መሰሪና ዘረኛ ቡድን ገና ወደ ስልጣን ሲመጣ በቅድሚያ ካደረጋቸው እኩይ ተግባራት መካከል የቤተክርስቲያኗን ቀኖና በመጣስ ሉአላዊነቷን በመግሠሥ በወቅቱ ፓትርያርክ የነበሩትን አባት እንደ ምድራዊ ባለስልጣናት ከመንበራቸው ማባረር ነበር። ይህም አስነዋሪ ተግባር የተፈጸመው የራሱን እኩይ የፖለቲካ አላማ ያለተቃውሞ ለማስፈጸምና የቤተክርስቲያኗንም ሐብትና ንብረት በቀላሉ ለመዝረፍ ያመቸው ዘንድ ነው። ይሀንንም በቅርቡ ራሱ በስልጣን ያስቀመጣቸው አባት በአደባባይ የቤተክርስቲያኗ አሰራር ምን ያሕል ብልሹ እንደሆነ ተናግረውታል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገርን የሚያጠፋና ኃይማኖትን የሚያስቀይር ወራሪ ሲመጣ በግንባር ቀደምትነት ሕዝቡን ለአገሩና ለእምነቱ እንዲቆም የምትቀሰቅስ ባላደራ ነበረች። አሁን በእኛ ዘመን ግን ይህ ሁሉ ቀርቶ የራሷ ገዳማትና ቤተክርስቲያናት እንኳን ሳይቀሩ ሲደፈሩ፣ሲታረሱና ሲፈርሱ ለምን ብሎ ለመጠየቅ እንኳን የማትችል ሆና ተገኘች። ያቺ ቅድስት አገርም በእነ ጻድቁ ተክለኃይማኖት፣በእነ አባ ኢየሱስ ሞዓ፣በእነ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ፣በእነ አባ ሳሙኤል ዘወገግ፣በእነ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወዘተ የተባረከችና የቀናች አገር ለአረብ፣ለቻይናና ለሕንድ ተቸበቸበች። ይህ እጅግ የሚያሳዝን ኢትዮጰያዊነት ብቻ ሳይሆን ክርስትናም ፈጽሞ የጠፋበት ዘመን በመሆኑ የሚያስደምም ነው። ይህም ሁሉ በአገር ውስጥ ሲከናወን ሕዝብ ዝም ያለው በጠብ መንዣ ተይዞ ወይንም ጊዜና ቦታ እስኪገጥምለት ነው እንል ይሆናል። በነጻነት አገር ውስጥ የምንኖር ሰዎች ግን እንዴትና በምን ሕሊና ይሆን ባርነትን መርጠን አገርና ኃይማኖትን እያጠፋ ካለ ቡድን ጋር እንቀላቀል በእርሱም እንመራ እያልን ያበድነው? ? ? ሲሆን ሲሆን በጠመንጃ አፈሙዝ የተያዘውን ወገን ከእስራቱ እንዲፈታ፣ በወያኔ አመራር ስር የወደቀችውን ቤተክርስቲያናችንን ነጻነቷን እንድታገኝ ለማድረግ መነሳት ሲገባን እንዴት ወዶ ዘማች ሆነን እንገኛለን?
ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በዓለም ላይ ታዋቂ ከሆኑት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያናት አንዷ በመሆኗ በውጪው ዓለም ያለውን ኢትዮጵያዊ እንደ አገር ቤቱ በመቆጣጠር የእኩይ አላማው ፈጻሚና አስፈጻሚ ለማድረግ የሚንቀሳቀሰው ወያኔ ኢሕአዴግ ኢላማ ውስጥ ከገባች ቆየት ብላለች። ሁሉም በግልጽ እንደሚያውቀው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በወያኔ ቀጥተኛና የእጅ አዙር አመራር ሰጪነት የሚንቀሳቀስ ነው። ለዛውም መናፍቃን እና አላውያን በሆኑ ሹማምንት መሪዎች! የቤተክርስቲያናችን የሕግ ምንጭ የሆነው ፍትህ መንፈሳዊ /ፍትሐ- ነገሥት/ እንደሚደነግገው ከሆነ እንኳንስ በጵጵስና ደረጃ ያሉ ክርስቲያኖች ይቅርና አንድ ተራ ምእመን እንኳን በመናፍቃን ጉባኤ ላይ ቢገኝ የተወገዘና የተለየ ይሁን ይላል። ዛሬ ግን በተከበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ የኃይማኖቶች ጉዳይ ኃላፊ ተብለው የተሰየሙት ሰው /የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር// መናፍቅና በተለያየ ጊዜ ከጳጳሳት ጋር የሚሰበሰብ ሆኖ ስናየውና ስንሰማው ውስጣችን እጅጉን ያዝናል። ይህም ሁሉ ቀርቶ በፖለቲካው ጣልቃገብነት የተከሰተውን የጳጳሳቱን መለያየትና መወጋገዝ በአንድም ይሁን በሌላም መንገድ ፈትቶ እንደኃይማኖቷ ድንጋጌ በአንድ ዘመን አንድ ፓትርያርክ የሚለው የቤተክርስቲያን ሥርዓት ለማምጣት የተደረገው ውጣ ውረድ መምከን ስናይ በርግጥም የተመረጡትን እስኪያሰት ታአምራትን ያደርጋል የተባለው
ትንቢት እየተፈጸመ እንደሆነ እንረዳለን። የተመረጡ የተባሉ ዛሬ በአባትነት ተሹመው ብጹአን፣ንኡዳን፣ ቅዱሳን እየተባሉ የሚጠሩት ጳጳሳት ናቸውና። እንግዲህ እነኝህ አባቶች በምንኩስና ዘመናቸው አርባቸው ወጥቶ ለቤትክርስቲያንና ለክርስቶስ ወንጌል ሞተናል ብለው ቃል ከገቡ በኋላ ይህ ሁሉ ግፍ በቤተክርስቲያን ላይ ሲፈጸም ግማሾቹ አባሪ ተባባሪ፣ግማሾቹ ለሕይታቸውና ለደሞዛቸው ፈርተውና ሳስተው ግማሾቹ ደግሞ አላማ አድርገውት ቅድስት አገር ኢትዮጵያንና ንጽሕት ተዋሕዶ እምነትን ሊያጠፋ ከመጣ ኃይል ጋር መሰለፋቸው በርግጥም የትውልድ እርግማን እንዳለ ያሳያል። ራሳቸው ተጣልተው ሳይታረቁ ያሉ አባቶችም እንደምን ሌላውን ሊያስታርቁ ይችላሉ? ለራሱ ሰላም የሌለው ለሌላው ሰላም ሊያስገኝ አይችልም ይለናል ፍትህ መንፈሳዊ የማቴዎስንና የሉቃስን ወንጌል ጠቅሶ። አንቀጽ 5 ቁ. 12 ማቴ.12፥ 30 ሉቃ. 11፥ 23
ስለዚህ ነብዩ በመዝሙሩ ‘ከራስ ጥቅም ይልቅ ልቤን ወደ ምስክርነትህ አዘንብል።’ መዝ.119፥2 እንዳለው በዘመናችን የተፈጠረውን የአገርም ሆነ የቤተክርስቲያን ችግር ለራሳችን ጥቅም ቆመን ሳይሆን በእውነትና በኃይማኖት ሆነን በዘመናችን እንፍታ!! ! ይህም ማለት የተፈጠረው ችግር እንዲስተካከል ይህም በቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን የቀኖና ጥሰት እንዲስተካከል ማድረግ ማለት ነው እንጂ ከተበላሸው አሰራር ወይንም ከተጣሰው ቀኖና ጋር እንተባበር ማለት አይደለም። አሁን የተበላሸው ከተስተካከለ ወደፊትም ይህ አይነት ሕግ የመጣስ ነገር ቢከሰት ተቀባይነት ስለማይኖው ትውልዱም እንደዚሁ ሕገ ወጥነትን እምቢ ማለትን ይማራል፡፡ አባቶቻችን ቅኝ ገዥዎችን እምቢ ብለው፣ ሚሲዮናዊያንን እምቢ ብለው፣ መናፍቃንን እምቢ ብለው፣ አላውያን ነገሥታትን እምቢ ብለው አገርንና ኃይማኖትን እንዳቆዩልን ዛሬም እምቢ ልንል ይገባናል።
በአሁኑ ወቅት በደብራችን በሚኖሶታ ደብረሰላም ቤተክርስቲያን ውስጥ በአንድም በሌላም መንገድ ገብተው ቤተክርስቲያናችንን አገርና ኃይማኖትን ላጠፉ ኃይል አሳልፎ ለመስጠት የሚደረገውን ሽር ጉድ የሚኔሶታ ምእመናን በአንድ ድምጽ ሆነን ልካችሁን እወቁ ወያኔንም እዛው እለመድክበት ልንል ይገባናል። ቤተክርስቲያናችን ትንሿ ኢትዮጵያችን ምትክ አገራችን ናትና።
የሰላም አምላክ ሰላማችንን ይጠብቅልን! ልቦናቸውንና አዕምሯቸውን ላጡም አስተዋይ ልቦናና አዕምሮ ይስትልን።