Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ማንዴላ ለኢትዮጵያዊነት –ቤዛ ነበሩ! መራራ ስንብት –ከመብራታችን ጋር ….

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ – 07.12.2013

የእኔ የዕይታዬ ጎራ ከሌሎች ወገኖች ትንሽ ለዬት የሚል ይመስለኛል። የሆነ ሆኖ ውስጤ የሚለኝን ልል ነው … እንዲህ

Nelson Mandelaበዘመነ ወያኔ የተከበሩ ማንዴላ የተስፋዬ ሀገር የሚሏትን ሀገርና ህዝብ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵውያንን ሳያዩ አረፉ። ስለ ምን? ለጥቁሮች የተፈሪነት ፍጹም ልዩ ዓርማ የሆነችውን የሀገራችን ቀደምትነት፤ ያን የአፍሪካዊ የጥቁር ገድል፤ የቅኝ ግዛትን ቀንበር በምኞት ያስቀረ የፈካ ታሪክ በዕብሪትና በበቀል የጣሰው የወያኔ ኃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አልተመቻቸውም ነበርና።

የፍቅር አባት የሆኑት የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ የወያኔ ድርጅት የወሰደውን ኢትዮጵያዊነትን  የማፍረስ ዘመቻ ጠንቅቀው ያወቁ፤ የተገነዘቡ ስለነበር እዬተቃጠሉ አምቀውና መስጥረው በማያዝ ለወያኔ ማንፌስቶ ፊት ሳይሰጡት፤ ጀርባቸውን እንደሰጡት ላይመለሱ አለፉ።

ለማዬት አብዝተው የሚናፍቋት፤ የሚጓጉላት፤ የሚሳሱላት ሀገር ኢትዮጵያ ሆና፤ ግን ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድነቷን አጥታ፤ የኢትዮጵያዊነት መግለጫ እንብርት የነበሩት ተቋማት ሁሉ በጠላትንት ተፈርጀው ሲፈርሱ፤ ሲናዱ፤ ዋጋ ሲያጡ እያዩና እዬሰሙ ናፍቆታቸው ፈርሳ ከማዬት እንደናፈቀቻቸው ማሸለብ ነበር ምርጫቸውና ጸጸታቸውን ይኸው በቃል ኪዳናቸው አጸንተው ቋሚ ዓምድ አደረጉት – ልዩ  ባለውለታችን። በቀጥታም ኢትዮጵያዊነትን ለማሰንበት ሆነ ለማቆዬት ያቀረቡት ጥያቄ ነበር። ምላሹ ሬት – ኮሶ ነበረና ውስጣቸው አምርሮ እንደ አዘነ፤ እንደ ተከዘ ለኢትዮጵያዊነት ሰግደው እንደ ተርመጠመጡ መራራ ስንብት እንሆ ሆነ፤

እንደ እኔ የተከበሩት የሰላም መምህር ኔልሰን ማንዴላ በዘመናችን ከማንኛችም በላይ ለኢትዮጵያዊነት የከፈሉት መስዋዕትንት፤ ለሀገራቸው ከከፈሉት መስዋዕትንት ቢዘል አንጂ አያንስም። የአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች መሪዎችና የኢትዮጵያን ፍርሰት ምኞታቸው የነበሩ ዬአደጉ ሀገሮች መሪዎች ሁሉ አዲስ ዴሞክራሲያዊ ወጣት መሪ እያሉ ሀገር አፍራሹን ሄሮድስ መለስን ሲያንቆለባብሱ፤ ለሸሩና ለደባው ሲያሸበሸቡ፤ የምህረት ቀንዲል የሆኑት የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ግን ለኢትዮጵያ አንድነትና ልዑላዊነት በፅናት እንደቆሞ እነሆ አለፉ። ለኢትዮጵያዊነትም በ21ኛው ምዕተ – ዓመት የፓን እፍሪካኒስትንትን ልዑቅነት በተግባር አቅልመው …. ቤዛ ሆኑ። የተከበሩት የነፃነት አርበኛ ኔልሰን ማንዴላ የታሪካችን ጠበቂ፤ ሁነኛ ባለሟል፤ ትንፋሽና ማህደርም ነበሩ … አቅማቸው ኃይል ነበረው። ንጉሥ ዳዊት በምስባኩ „የቤትህ ቅናት በላኝ“ እንዳለው ሁሉ ለነፃነት ዓርማቸው – ለክብራችን፤ ለእናት ሀገራችን ለኢትዮጵያ የወጣላቸው ቀናተኛ ነበሩ ማለት እችላለሁ … ምልክታቸው ነበረችና …

እጅግ የማከብራችሁ የጹሑፌ አንባቢዎች የሀገሬ ልጆች … ውለታው … ሸቀጥ አልነበረም። ውለታው የሚሸጥ የሚለወጥ የከንቱንት ክምር አልነበርም። የእኛነታች ጠንካራ ሚስጢር በውስጣቸው በአጽህኖት የጸነሱ፤ ያረገዙ ግን ሳያገላገሉ ከነህምሙ ያሸለቡ የፍቅር አባት አካላችን ናቸው ኔልሰን ማንዴላ። በዚህ በከፋን ጠቀራማ ዘመን በህማማታችን ሳይለዩን በመንፈስ አብረውን የሆኑ፤ – ሰንደቅዓላማችን የመንፈሳቸው ማህተም ያደረጉ አርማችን ናቸው ኔልሰን።  ክቡርነታቸው … በኢትዮጵያዊነት በተፃራሪነት የቆመ ኃይል ሁሉ መስጥረው በጥርሳቸው እንደነከሱት አረፉ። የነፃነት አርበኛው … ለኢትዮጵያዊነት ተንገበገቡ። የቅኔው ልዑል ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህ በእሳት ወይ አባባ መድብሉ  „የወንድ ልጅ እንባው በሆዱ“ ነው ያለው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ….

እርግጥ ይህ ለተዋህዶ አማንያን የሚስጢረ ሥላሴ ያህል ጥልቅ ሲሆን፤ ኔልሰን በመንፈሳቸው መስጥረው በተግባር ያሳዩና ያሰመሰከሩ ድንቅ የእኛነታችንና የማንነታችን ጠበቃ አባታችን ነበሩ። የተከበሩ ክቡር ኔልሰን ማንዴላ ለእኔ  ትርጉም ነበሩ። ቅኔ ነበሩ። ውስጣቸው የምህረት ልዩ ሰፊ አንባ ነበረው፤ ለወልዮሽ የእኩልነት ማዕድ የማዬት ህልምና ዕውንነት ትግላቸው ለሰው ልጆች ሁሉ ነበር። እርግጥ ነው ይቅርታቸው ንዑድ ሆኖ፤ ግን በውስጣቸው የመሰጠሩትን የሰው ልጆች የእኩልነት፤ የነፃነት፤ የወንድማማችንት መብታዊ ጉላላት የሚያጎላ፤ እንዲያፈራ፤ እንዲለመለምልም በትህትና የሚያደርግ እንጂ የሚያከስም በፍጹም አለነበረም። ለግል ህይወታቸው ያልተጨነቁ አበው ብዙኃን፤ አበው ግፉዓን ነበሩ … ዕንባ አባሽ።

 

በድርጊት የበለጸጉት ክቡር ኔልሰን ማንዴላ ሆነው – መሆንን ለፅናት ሸለሙ። ሀገር መውደድ ምን ማለት እንደሆነ ተንትነውና በትነው እራሳቸውን አሳለፈው በመስጠት አተረፉ። ድንቁ ነገር የትርፉ ዕሴት ርትህን ወልዶ ትውልዱን ከጥፋት በማዳን አዲስ መርህና መንገድ በነፃነት ዜማ ቀይሶ እኩልነትን አበቅለ። ዘረኝነትንም ነቀለ – ከሥሩ። የክብር ምንጩ ሀገርን ከማፍቀር፤ የህይወት ዋጋ ተሽቀዳድሞ ከመክፈል የሚነሳው ከራስ ነውና እንሆ እሳቸው በተግባር ስለ አማረባቸው፤ ፍቅር ካለገደብ ስለተሸለሙ አርያንታቸው ዛሬ ዓለምን በተደሞ አስለቀሰ። የኃያሉ መንግሥት የአሜሪካ ሰንደቅዓለም ዝቅ ብሎ ለበርካታ ቀናት ተውለበለበ። ዓለም በሙሉ በአኃቲ ድምጽ ሀዘኑን ተጋራ ….። ስኬቱ ውጤትን አዝምሮ የጥቁርነትን አንገት አቀና። የኔልሰን  የአርነት እንቅስቃሴ የመከራ ዘመን ያመረተው ፍሬ፤ ብሄራዊነትን ብቻ ሳይሆን ዓለምዓቀፋዊነትን ያጸደቀ – ድንቅ ሐዋርያነት ነበር። ሁለመናው ቆሞ እንሆ ይመሰክራል። ተቋምነቱ ሳይደክመው ይሰብካል በቋሚነት – ለዘለዓለም።

 

በተከበሩ የኔልሰን ማንዴላ ዘመን ምንም የባከነ ጊዜ አልነበረም። ታሪካቸው መከራን አስመችቶ በመቀበል ትእግስትን አበራ፤ የእኩልነት የተጋድሎ ጊዜያቸው በሆደ ሰፊነት ሁሉንም የአሳር ቁልል ያስተናገደ ልዩ ትዕይንት ነበር። ስለሆነም ትርፉ መንፈስ ሆነ። በመሆኑም ጥቁርነት የቀፈፈውን … ሥር የሰደደው ዘረኝነትን አልደፈረም ቢልም አለሰለሰ፤ የከረረውን ትዕቢት አረገበ፤ የዘረንነት በሽተኞችን ፈቅፍቆ ፈወሰ – ልዩ መዳህኒት ነበርውና፤ ተጋድሎውም ትውልዱን በፍቅር አጋባ። ስለሆነም ያ ሁሉ ግፍ ተቀብሮ ብሄራዊ ክብርን ወለደ። መገለሉ ከስሞ ብሄራዊ መገለጫን አዘከረ። ስለሆነም የምልዓቱ ግራሞት ያሰበለ እንዲሆን አደረገ። ማዬት ማማን ነውና መስዋዕትነቱ ጭብጥ ሆነ። ስለሆነም የሀዘኑ ታዳሚዎች ሁሉ ከውስጣቸን አዘን። ብዙም አትኩሮትን የማይለግሱ ሀገሮች እንኳን በሚዲያ የሚሰጡት አስተያዬት ሳዳምጥ ተግባር ምን ያህል የቅዱስ መንፈስ ኃይልና መስህብም እንዳለው ተረዳሁ። ተገነዘብኩ። የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ የላቀ የተግባር ቅዱስ መንፈስ ነበሩ። ስለዚህም ኔልሰን ማንዴላ አለሞቱም አረፉ እንጂ።

 

እኔ እንደማስበው የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ቅንም ነበሩ ብዬ አስባለሁ። አምላካችን ቅኖችን ይወዳልና መስዋዕትነታቸውን በድል ቋጭቶ የዓለምን ልብ በፍቅር እንዲሰግድ እንሆ አደረገ። ደቡብ አፍሪካም ዕድለኛ ነው። ይህን መሰል እግዚአብሄርና የሰው ልጆች የሚወዱት የእርቅ ልዩ የወርቅ ድልድይ፤ የተመረቀ ሙሴ ሰጣቸው። እርግጥነው የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ከእኛዎቹ ቀደምት አርበኞቻችን ጋር የትውፊት ቅብብል አድርገዋል እላለሁ፤ ከዓፄ ቴወድሮሰ፤ ከአፄ የኋንስ ሆነ ከአፄ ሚኒሊክ እንዲሁም ከአፄ ኃይለሥላሴ፤ በተጨማሪም ከመጀመሪያው አፍሪካዊ የሽምቅ ውጊያ „ከጥቁር አንበሳ“ ጋራ የአደራ ውርስ እንደ አደረጉ ይሰማኛል። ያነሳሳቸው፤ የቀሰቀሳቸው ውስጣቸውን ለነፃነት ትግል ተክል እንዲያቆጠቁጥ፤ በጸጋ ያበረከተው ይህ አፍሪካዊ የአርበኝነት፤ የተፈሪነት፤ የመቻል ቅምጥ ጥሪትና ቅርስ ነው ብዬም አምናለሁ። የዛሬን አያድርገውና የነፃነት ትርጉም በኽረ እናት ኢትዮጵያ ክብርት ሀገራችን ነበረችና።

 

እኔ እንደሚሰማኝ የመጀመሪያ የነፃነት ፍለጋ ጽንሰት በኔልሰን ማንዴላ የወጣትነት ዘመን ህሊና የተጠነሰሰው፤ ፊደል የቆተረው ኢትዮጵያ ቅኝ ካለመሆኗ የሚነሳ ይመሰለኛል። ያ … ለእንግሊዞች፤ ለዱርቡሽቶች፤ ለፋሽስቶች ያልተነበረከከ ኢትዮጵያዊነት በመላ አካላታቸውና ደማቸው ውስጥ ቦታ ሰጥቶ ትርጉም መሆኑን ነጥሮ እነሆ ለዓለም አስነበበ …. እላለሁ እኔ ሥርጉተ ….

 

ሄሮድ መለስ ዜናዊ በማንአለብኝንት የገፉት፤ በእብሪት የጠቀጠቁት፤ በግፍ የጨፈለቁት፤ በትዕቢታቸው የደፈጠጡት፤ በበቀል የጨቀጨቁት፤ የናቁትና ያዋርዱት የኢትዮጵያዊነት ቅዱስ መንፈስ ሰንደቅነቱ ወይንም መንበርነቱ በብሄራዊነት ብቻ የተወሰነ አልነበረም።  … ለአህጉራችን ለአፍሪካ ሆነ ለዓለም ፋና ወጊና መሪ እጬጌም ነውና። ይህ ዘመን የሰጣቸው ያደጉ ሀገሮች የሚፈሩት ቢሆንም፤ አሁንም እንደ ሥርጉተ ዕይታ የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ግን ለኢትዩጵያውያን የተለዬ ፍቅርና አክብሮት ነበራቸው እላለሁ። እርግጥ ቀደም ባላው ጊዜ ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵውያን በመኖሪያ ፈቃድ ዙሪያ የሚያነሱት ነገር ነበር። ነገር ግን ይህ በሌላ ቢሮክራሲያዊ ምክንያት የተበተበ እንጂ ኔልሰን ከልጆቻቸው ለይተው እኛን እንደማያዩን አስባለሁ። እንዲያውም አሁን ከእረፍታቸው በኋላ ደቡብ አፍሪካን ኑሯቸው ያደረጉ ወገኖቻችን ላይ ችግር ይገጥማቸው ይሆን በማለት ታላቅ ስጋት አለበኝ።

 

መቋጫ

 

ሰማዕቱ፤ መምህሩ፤ ሐዋርያውና ሰባኪው ቅዱስ ጳውሎስ …….. ወደ ቆላስያስ በላከው በአንደኛቱ መልዕክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር  ከ11 እስከ 12 „ .. ይህንን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል፡ ማለትን ተምሬያለሁና። መዋረድንም፡ አውቃለሁ፡ መብዛትንም፡ አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ፡ ነገር በነገረም፡ ሁሉ መጥገብንና መራብንም፡ መብዛትንና መጉደልን ተምሬያለሁና“ ይላል …

 

ሥልጣን ትወደዳላች፤ ክብርም ከሁሉ በላይ ትፈቀራለች ፤  የሥልጣን ዘመናቸውን ሊደግሙ ቢፈልጉ የሚያግዳቸው አልነበርም። እሳቸው ግን አላደረጉትም። ከዚህም አንጻር ኔልሰን ማዴላ ዬይበቃኛልም ልዑል ነበሩ እንደ መምህሩ ቅዱስ ጳውሎስ ….። በሌላ በኩል የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ፤ በቀልን ያሸነፉና የረቱ የአንደበተ – እግዚአብሄር ሰማዕትም ናቸው። የፈጣሪያቸውን ፈለግም የተከተሉ ማህሪ። ዓለምን የሚካልለው ዝቀሽ ተምክሮና ብቃታቸው ደግሞ ከመከራቸው ፈቅደው የተቀለቡ ስለሆኑ የነፃነት ብርቅዬ ትምህርት ቤት ነበሩ።

 

ኔልሰን በዬትኛውም አጋጣሚ በሚዲያ ሲመጡልኝ ሁሉ ፊታቸው ፈክቶ ውስጣቸውን ፈቅደው በፍቅር እንደ አስጎበኙን …. ተሰናበትን።  ገፃቸው አዘውትሮ በትጋት አስተማረን፤ በጽናት ባትለው ዘመኑን በሥልት በፍቅር ገሩት። ምህንድስናቸው  ሰባኪ … ትንግርትን መስካሪ ነበር፤ ዕውነትንም …. አፍላቂ።  የምዕተ – ዓመቱ የነፃነት ሊቅ፤ ትውልድ

ሊተካቸው የማይችሉ ዕንቋችን ነበሩ። ፅናትን በልጅነት ሸምተው ጽናትን ለሁላችን በቅንነት አቅንተው፤ ፅናትን አንግሠው ከፅናታቸው ጋር በጽናት – ድንግልና  …ትምህርት ቤት ሆነው አረፉ። በወጣትንት በዕድሜ መጥ የሆኑትን ፈተናዎች ሁሉ አንበርክከው ከወርቅ በተሰራ ብርታታቸው የነፃነት ወተት በድንበር አልቦሽ ቀለቡ።

 

የዘመናችን … የኢትዮጵያዊነት መሪዎች ትምርት ቤቱን በመሆን ካዘመሩት ማሳው ለፍሬ ይበቃል። ውዳሴ መልካም ቢሆንም፤ በመሆን ካልቀለመ … መዘክር ብቻ ሆኖ ይቀራል። …. እራሳቸውን ሳይዋሱ፤ ሳይበደሩ፤ እንደ ተፈጥሯቸው ሆነው ከተለዩን የአፍሪካ ብርኃን የኛዎቹም ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነትን በመስዋዕትንት ይሸመቱ ዘንድ በርከክ ብዬ እለምናቸዋለሁ …. አምላካችንም ይርዳን። …. ካለጠበቂ፤  ካለአጃቢ የሚሄድ የጓደኛ መሪ …. መከፋቱ – መካፋታችን፤ ህምሙ – ህመማችን፤ ሞቱ – ሞታችን የሚሆን እረኛ አምላካችን እዬሱስ ክርስቶስ መርቆ ይሰጠን። አሜን! የናፈቀኝ እሱ ነውና ….

 

ጌጣችና ውዳችን የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ መከራዎትን በምድር ጨርሰውታል። ጽድቅ ለዕልፎች መቃጠል ነበርና አድርገውታል። …. መልካም የጽድቅ ጉዞና የእረፍትም  ጊዜ። ለነፃነት ቤተኞች ሁሉ መጽናነትን እመኛለሁ። ከድርጊት ለተማርነው መልካም የኔልሰን ተመክሮ ውስጣችነን ሳንሸፍን ወይንም ሳንከናንብ ገልጠን በንጽህና እንፍቀድለት – እላለሁ።

 

 

አራት ዓይናማው መንገዳችን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 


ይድረስ ለክቡር አቶ ዘውዴ ረታ እና ኢትዮጵያውያን በያላችሁበት ቦታ ሁሉ ።

$
0
0

በ ታደለ ብጡል ክብረት (ኢ/ር)

“የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት” በሚል ርዕስ  አቶ ዘውዴ ረታ ያሳተሙትን መጽሐፍ በጥሞና አንብቤዋለሁ። መጽሐፉ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የተፈጸሙትን እውነተኛ ታሪክ በሙሉ የካተተ ነው ባልልም፤በውስጡ ያሉት በርካታ ዘገባዎች ከዚህ በፊት በሌሎች መጽሐፎች ውስጥ ተጽፈው ያልነበሩ ናቸው። በተለይም ክቡር ጸሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስን፤ ክቡር አቶ ይልማ ደሬሳን፤ ክቡራን አቶ አክሊሉ እና አቶ መኮንን ሀብተወልድን በተመለከተ የተጻፈው፤እነዚህን የኢትዮጵያ ብርቅ ልጆች ስም ህያው የሚያደርግ ስለሆነ ለደራሲው ያለኝን አድናቆት በከፍተኛ አክብሮት እገልጻለሁ፡፡

ይሁን እንጂ “ይድረስ ለአንባቢዎቼ” በሚለው ርእስ ስር ደራሲው በአቀረቡት ዘገባ ውስጥ “ይህ ጎድሏል፤ ይህ ቀርቷል የሚባሉ ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ እና እንደሚኖሩ አውቃለሁ” ብለው አስተያየት እንድንሰጥ በር ከፍተዋል። እኔ ደግሞ “ጎድሏል፤ ቀርቷል” ከሚለው በተጨማሪ አቶ ዘውዴ ረታ የተሳሳቱትን ለማረም ይጠቅማቸዋል ብዬ ያሰብኩትን እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።

በመጀመሪያ የማነሳው “የቫቲካን አቋም በኢትዮጵያ ጉዳይ” ብለው ስለአቀረቡት ዘገባ ነው። በዚህ ርእስ ስር፤ እሳቸው የጻፉትን እዚህ ላይ ለመድገም አልፈልግም። ዋናው ቁም ነገር፤ “የቫቲካን አቋም በኢትዮጵያ ጉዳይ” የሚል ርእስ ሰጥተው ከጻፉ ዘንዳ፤ የቫቲካንን አቋም ይገልጻሉ ብዬ ስጠብቅ፤እሳቸው ሸወድ አድርገው ወደ ፒዮስ 11ኛ አሉባልታ ገብተዋል። ለምን ይህን ለማድረግ አንደፈለጉ ስላልገባኝ፤የእኔን እይታ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

አንድ የበላይ የሆነ የሃይማኖት አባት ወይም የአገር መሪ፤ከበታቹ ያሉት ሰዎች ለሚፈጽሙት ተግባራት ሁሉ ተወዳሽም፤ተወቃሽም እደንደሚሀን እሳቸው ሳያውቁ ይቀራሉ የሚል እምነት የለኝም። ይህ ሐቅ ተቀባይነት ያለው የአስተዳደር ጽንፈ ሐሳብ በመሆኑ፤የቫቲካን ካርዲናሎች (ጳጳሶች) በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸሙት በደል ዋና ተጠያቂ፡ የቫቲካን የበላይ መሪ ፒዩስ 11ኛ ናቸው፡፡ ይህን ሐቅ አቶ ዘውዴ ረታ መካድ አልነበረባቸውም። በፒዩስ 11ኛ ስር ያሉት ካርዲናሎች የፈጸሟቸውን ተግባራት አቶ ዘውዴ እንዲያስታውሱት፤ከዚህ ቀጥሎ በዝርዝር አቀርባለሁ፡፡

አቶ ዘውዴ ረታ “የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት” በሚል ረእስ በጻፉት መጽሐፍ ገጽ  301 ላይ “የሚላኖው ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ኢደልፎንስ ሹስተር፤የፋሸስት መንግሥት ደጋፊነታቸውን በግልጽ አስረድተዋል” ብለዋል። በመቀጠልም “- – - – የጣሊያን መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር  የባርነትን አገዛዝ ሰንሰለት በመጣስ፤የካቶሊክን ተልዕኮ የተቀበለ ነው – - ” ብለው ከጻፉ  በኋላ፤ፒዩስ 11ኛን ለመደገፍ የተነሱበትን ዓላማ ለማሳካት ሲሉ “የሚላኖ ሊቀ ጳጳስ በተናገሩት፤ፒዩስ 11ኛ እጅግ ማዘናቸውን ገልጠዋል” በማለት ነገሩን ለማርገብ ሞክረዋል። በትልቅ ሥልጣን ላይ ያለው ካርዲናል ኢደልፎንስ ሹስተር፤የኢትዮጵያን ነፃነት የሚያሳጣ እና  ክብሯን የሚነካ ድርጊት በመፈፀሙ፤ቢያንስ አሰተዳደራዊ እርምጃ አለመውሰዳቸው ፒዩስ 11ኛ የድርጊቱ ተባባሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንጂ፤እሳቸውን ከበደሉ ነፃ የሚያደርግ አይደለም።

ከዚህ ዝቅ ብሎ የሚታየው ፎተግራፍ የሚያሳየው “የሚላኖው ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ኢደልፎንስ”    ሕዝብ በተሰበሰበበት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በር ላይ ቆሞ፤በልበ ሙሉነት የፋሸስትን መንግሥት የሚደግፍ ንግግር ሲያደርግ ነው። በዚህ ፎተግራፍ ላይ ያሉት አብዛኛዎቹ ሰዎች ካርዲናል ሹስተር የሚናገረውን የሚያዳምጡ ቢሆኑም፡አንድ ግርምት የፈጠረበት ሰው አፉን ይዞ እናያለን።

andinet11111

ካርዲናል ሹስተር የፋሽስት ደጋፊነቱን ሲናገር

ፒዩስ 11ኛ “ፍትሐዊ ባልሆነ ጦርነት አናምንም” ከማለት ውጭ የኢትዮጵያን መብት ለማስጠበቅ ምን የተናገሩት ወይም የፈፀሙት ተግባር አለ

የጣሊያን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ በሚሳፈርበት ወቅት፤ መድፎቹንና ሌሎች አውዳሚ መሣሪያዎቹን የባረከው፣ የቫቲካን ካርዲናል ፎቶግራፍ ከዚህ በታች ያለው ነው።

andinet111111

የኒው ዮርክ ታይምስ እ.አ.አ. የካቲት 13 ቀን 1937 ባወጣው ህትመት “ዛሬ ማለዳ ላይ ጳጳሱ ለጣሊያን ንጉሥ እና ለኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት፣ ለቪክቶር ኢማኑኤል፣ ብለው ቅዱስ ቡራኪያቸውን በመስጠት፣ ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ላይ ስላላት ሉዓላዊነት እውቅናቸውን ገልጸዋል” ብሏል።  የእንግሊዝኛውን ጽሁፍ ከዚህ በታች አቀርባለሁ።

(Earlier today the Pontiff had given his recognition of Italian sovereignty over Ethiopia by bestowing benediction upon Victor Emmanuel as King of Italy and Emperor of Ethiopia)

  1. የፋሽስት ኢጣሊያ ወታደሮች መረብን ተሻግረው፣ ወደ መሐል አገር ለመገስገስ ሲሰለፉ ቡራኬ ሲሰጥ በፊልም የተቀዳው በእጄ ይገኛል።
  2. እምነተ ቢስና የቀኖና አፈንጋጭ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ማካሄዴ፤የካቶሊክን እምነት ለማስፋፋት በር ስለሚከፍት፤ የተቀደሰ ጦርነት ነው በማለት የቶራኖ ሊቀ ጳጳስ ተናግሯል፡፡ “The war against Ethiopia should be considered as a holy war, a crusade to open Ethiopia, a country of infidels  and Schismatics to the Expansion of the Catholic Faith.”  (By OCP on Mach 12, 2010)
  3. የሚላኖው ሊቀ ጳጳስ ሹስተር ከተናገሩት ቀደም ሲል ከገለጽሁት በተጨማሪ “የጣሊያን ፋሽስት ባንዲራ፤በአሁኑ ጊዜ የክርስቶስን መስቀል በኢትዮጵያ ውስጥ በድል አድራጊነት  ባሮችን ነፃ ለማውጣትና ለእኛም የሚስዮን ፕሮፓጋንዳ  መንገድ እየከፈተ ነው” ብለዋል።

The Archbishop of Milan, cardinal Schuster, went farther and did all he could to bestow upon the Abyssinian War, the nature of a Holy Crusade. “The Italian (Fascist Flag) is at the moment bringing in triumph the Cross of Christ in Ethiopia to free the road for the emancipation of the slaves, opening it at the same time to our missionary propaganda.” (By T.L. Gardini, Towards New Italy.)

ከዚያ በኋላ የሚላኖው ራሱ ሊቀጳጳሱ አንድ ታንክ ላይ ዘልሎ ወጣና ረጋ ብሎ እዚያ የተሰበሰቡትን የፋሽስት ጀሌዎች ባረከ።  የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ሳለቬሚኒ እንደገለጸው፣ ቢያንስ ሰባት ካርዲናሎች፣ 29 ሊቀ ጳጳሶች፣ 61 ጳጳሶች ወዲያውኑ ጦርነቱን ደግፈዋል።  የቫቲካን ድጋፍ በዚህ ብቻ ሳያበቃ፣ በውጭ አገርም ጦርነቱን ደግፈዋል። በየአገሩ ያሉት የካቶሊክ ጋዜጦች በሙሉ እንደ እንግሊዝ አገርና አሜሪካም ያሉት ሳይቀሩ ኢጣሊያን ደግፈዋል።

እ.አ.አ. በ1949 አቭሮ ማንሃታን በጻፈው መጽሀፍ እንደገለጸው “ፓዮስ 11ኛ ለሙሶሊኒ ትልቅ ክብር የሚሰጡ መሆናቸው ይታወቃል።  በአጠቃላይ፣ የጣሊያን ቀሳውስት በሙሉ፣ የፋሽስቶቹ ወገን መሆናቸውን በቀላሉ ለመረዳት የሚቻለው፣ የፋሽዝም መርሆ፣ ብሄርተኛነት፣ ፈላጭ ቆራጭና ሕዝባዊነትን የሚቃወም አስተዳደር መሆኑ ነው” ይላል።  በእንግሊዝኛው የተጻፈው እንዲህ ይላል።

(Pope Pius XI is credited with much admiration for Mussolini that the Italian Clergy as a whole are pro-Fascist is easy to understand, seing that Fascism is a nationalist, authoritarian, anti-Socialist Force”.) Avro Manhattan 1949.

ሀቁ ይህ ሆኖ እያለ አቶ ዘውዴ ረታ ደግሞ “- – - የዓለም የካቶሊኮች አባት (ፓዮስ 11ኛ ማለታቸው ነው) ከፋሽስቱ ዲሬክተር መሪ ተጣልተው ከባድ ችግር ላይ ከመውደቅ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ዓይነት ፍትሕን የተመረኮዘ አስተያየት ከመስጠት ታግደው መኖር የሚሻል መሆኑ ታያቸው” ሲሉ መስክረዋል።   ይሄ እንግዲህ አቶ ዘውዴ ረታ ሽንጣቸውን ገትረው የሚሟገቱላቸው የካቶሊኮች አባት፣ ፓዮስ 11ኛ፣ ለፍትሕ አለመቆማቸው በራሳቸው አንደበት ገለጹት።  ሌላው የፒዩስ 11ኛ ጥፋት፣ የራሳቸው ካርዲናሎች ከፋሽስቱ መሪ ሙሶሊኒ ጎን ቁመው ወረራውን ከፍ ብዬ በማስረጃ እንዳቀረብኩት፣ የጦር መሣሪያዎች ሲባርኩና ፋሽስቶችንም ሲያወድሱ፣ እነዚህን የቫቲካን ባለሥልጣናት ላይ የመገሰጽም ይሁን የማገድ እርምጃ አለመውሰዳቸው ነው።

 

ክቡራን አንባቢያን

ሌላም ላክልበት።  ሙሶሊኒ እና ጭፍራዎቹ ኢትዮጵያን በመውረር የፈጸሙት በደል እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ለማስታወስ ያህል፣ ጥቂቶቹን ከዚህ በታች አቀርባለሁ።

  1. የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር

2,000

  1. የተቃጠሉ ቤቶች ቁጥር

525,000

  1. በጦርነት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር

275,000

  1. በአምስት ዓመት የተገደሉ አርበኞች ቁጥር-

78,500

  1. ተማርከው የተገደሉ አርበኞች ቁጥር `

24,000

  1. በአምስት ዓመት ውስጥ የተገደሉ ሴቶችና ሕፃናት ቁጥር

17,800

  1. ታስረው የሞቱ ሰዎች ቁጥር`

35,000

  1. በስደትና በረሀብ የሞቱ ሰዎች ቁጥር

300,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ የቀንድ ከብቶች ቁጥር

5,000,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ በጎችና ፍየሎች ቁጥር

7,000,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ ፈረስና በቅሎዎች ቁጥር

1,000,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ ግመሎች ቁጥር `

700,000

 

ከላይ ከተዘረዘረው በተጨማሪ፤ለዚህ ሁሉ እልቂት መሪና ኃላፊ የሆነውን ጀነራል ግራዚያኒን ለመግደል ሞገስ አስገዶምና አብረሃ ደቦጭ ባደረጉት ሙከራ ሰበብ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ እ.አ.አ. ከየካቲት 12 እስከ 15 1937 ድረስ ባሉት ሦስት ቀናት ውስጥ 30,000 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ በእነዚሁ ቀናት ውስጥ ሞገስ አስገዶምንና አብርሀም ደቦጭን ደብቀዋል በሚል ሰበብ ደብረሊባኖስ የነበሩትን ከ300 እስከ 500 የሚደርሱ መነኩሴዎችና ካሕናት ተረሽነዋል።  አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤል፣ ሕዝቡ ለፋሽስት መንግሥት እንዲገዛ ስበኩ ሲባሉ አሻፈረኝ በማለታቸው በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል።

ይህን ሁሉ የሰው እልቂት፣ እንዲሁም የንብረት መውደም የሚያውቁት የቫቲካኑ መሪ ፓዩስ 11ኛ በዝምታ ማለፋቸው ይታወቃል።  አቶ ዘውዴ ረታ ይህን ሐቅ ወደ ጎን ትተው ፓዩስ 11ኛ የዓለም ነርሶችን ሲቀበሉ “በመንግሥታት ግንኙነት መሀከል የሚፈጠር ማናቸውም አለመግባባት – - – በሰላም መንገድ መፈታት ያለበት መሆኑን በጥብቅ ካሳሰቡ በኋላ – - -” በሚል ቃል ለማስረጃነት ለማቅረብ ሞክረዋል። ይህን መሰል አነጋገር፣ እንኳን በከፍተኛ ሥልጣን ያለ ሰው ይቅርና ማንም ተራ ሰው ሊናገረው የሚችል አባባል አለመሆኑን አቶ ዘውዴ ረታ የሚገነዘቡት ይመስለኛል።  በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሥር ያሉት ጳጳሶች እና ካርዲናሎች ተጠሪነታቸው ለፓዩስ 11ኛ በመሆኑ እሳቸውን ከተወቃሽነት ሊያድናቸው አይችልም።

የዓለምን ሰላም ፈላጊ የሆኑ ሁሉ፣ የፋሽስቶች መሪና ጭፍሮቹ በኢትዮጵያ የተፈጸመውን ግፍ አውግዘዋል። ሐቁ ይህ ሆኖ እያለ፣ አቶ ዘውዴ ረታ የቫቲካኑን መሪ ፓዩስ 11ኛ ከደሙ ንጹህ ናቸው ብለው ለመደገፍ መነሳሳታቸው እጅግ የሚያሳዝን ጉዳይ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

የናዚ መሪ የነበረው ሂትለር፣ አይሁዳውያንን በጨፈጨፈ ጊዜ ዝምታን መርጣ የነበረችው ቫቲካን፣ ጦርነቱ ካለቀ በኋላ፣ ከአንዴም ሁለት ጊዜ፣ አይሁዳውያንን ይቅርታ ጠይቃለች። ፋሽስቶች በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸሙት ግፍ ግን ቫቲካን እስከ ዛሬ ምንም ዓይነት የመጸጸት እርምጃ አልወሰደችም።  ስለዚህ፣ ዛሬ በሥልጣን ላይ ያሉት ፓፓ ኢትዮጵያን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው የምንል ብዙ ኢትዮጵያውያን አለን።

ውድ አንባቢያን

ከዚህ ከፍ ብሎ የተጻፈው ቫቲካንን በተመለከተ ያለው ጉዳይ ብቻ ነው። “የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት” በሚለው መጽሀፍ ውስጥ ያሉትን አንዳንድ ግድፈቶች ልጠቁማችሁ። አቶ ዘውዴ ረታ ስለ ሙሶሊኒ አስተዳደግ፣ ጠባይ እና ተግባራት ብዙ ብለዋል።  ግን ይህ ትረካ እሳቸው ከሰጡት ርእስ አኳያ ሲታይ ምን ጠቀሜታ አለው? ይልቁንስ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ አቤት በማለት ከአገር ቢወጡም፣ ለረጅም ጊዜ እንግሊዝ አገር እንዲቆዩ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ስላደረጉት አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሼቱ ጠባይና ተግባራት ቢጽፉ ጥሩ ነበር።  ከሁሉም የሚገርመው የሲልቪያ ፓንክረስት በጥቂቱም ቢሆን መጻፋቸው ነው።

ሲልቪያ ፓንክረስት ስለ ኢትዮጵያ ልትጽፍ የቻለችው ከ1927 እስከ 1931 ዓ.ም. ድረስ በሎንዶን የኢትዮጵያ ሙሉ ባለ ሥልጣን ሚንስቴር በነበሩት አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ ድጋፍና ቡራኬ መሆኑን “የአዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሼቱ የሕይወት ታሪክ፣ ከታደለ ብጡል ክብረት” የሚባለውን መጽሐፍ ቢያነቡ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎች ያገኙ ነበር።

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንግሊዝ አገር ሲደርሱ፤ አንድም የእንግሊዝ መንግሥት ባለሥልጣን የክብር አቀባበል አላደረገላቸውም። ከመርከብ ከወረዱ በኋላ የተቀበሏቸው የአዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሸቱ የግል ወዳጆች ናቸው።  ይህንን ሁኔታ የሚያሳየው ፎተግራፍ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል።

andinet1111

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መርከብ ውሰጥ ገብተው የተቀበላቸው አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሸቱ መሆናቸውን የሚያሳየው ፎቶ

ከ1927 እስከ 1931 ዓ.ም. ድረስ በአወሮፓ፤ በአሜሪካ እና በሕንድ የብዙሃን መገናኛዎች፤ በጽሑፍ እና በአካል ተገኝተው፤ፋሽስት ሙሶሊኒ ኢትዮጵያን በግፍ እንደወረረ፤ ሕዝቡን እንዳሰቃየና ንብረትን እንዳወደመ በሰፊው ገልፀዋል። እንኳን እሳቸው፤ ሕፃናት ልጆቸቸው ዳዊትና ዮሐንስ ሳይቀሩ በአደባባይ ላይ ቆመው ስለ ወረራው ያላቸውን ኀዘኔታ ገልጸዋል። አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እንደ ዴል ቫዩ ያሉ ሰዎች በጦር ሜዳ ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መልምለው ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል።

andinet11

የአዛዥ ሐኪም ወርቅነህ ወዳጆች ወደቡ ድረስ ሄደው ንጉሠ ነገሥቱን ሲቀበሉ

 

andinet111

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ ስለ ሥራ ጉዳይ ሲወያዩ

አቶ ዘውዴ ረታ ይህን ሁሉ ታሪክ አያውቁም ነበር ለማለት አልደፍርም። ሆን ብለው የሸሹት ጉዳይ ነውም አልልም። ግርምት እንደፈጠረብኝ ግን አልክድም

ጽሁፌን ከማጠቃለሌ በፊት አንዳንድ ነገር ላክልበት፡፡

  1. በቅርቡ ከመገናኛ አውታሮች እንደ ተረዳነው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጸመው ግፍ እና አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ከሰላሳ ሺህ በላይ ሰዎች ላስገደለው ለጀነራል ግራዚያኒ፣ አፊሌ በሚባል ትንሽ ከተማ ውስጥ አንድ የመታሰቢያ ሙዚየምና ሐውልት ጭምር ተሠርቷል። ሐውልቱ በተመረቀ ዕለት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካርዲናል በሥፍራው ተገኝተው ቡራኬ መስጠታቸውም ተነግሯል። ይህ ተግባር የሚጠቁመው፣ ዛሬም ቢሆን ቫቲካን ለፋሽስቶች እንጂ ለተበዳይዋ ኢትዮጵያ መብት አለመቆማቸውን ነው።  ስለዚህ የአሁኑ የሮማ ጳጳስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ ነው።
  2. ለፋሽስቱ ጨፍጫፊ ጀነራል ግራዚያኒ አፊሌ ከተማ የቆመው ሐውልት እንዲፈርስ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪ የሆኑት ጳጳስ የጣሊያንን መንግሥት መጠየቅ አለባቸው የሚል ጥያቄ ማቅረብ ተገቢ ነው።
  3. ኢጣልያ ሊቢያ ውስጥ ለፈጸመችው ግፍ ካሳ የከፈለች መሆኗ ይታወቃል። ፋሺስት ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ውስጥ የፈጸመችው ሊቢያ ውስጥ ከፈጸመችው የማይተናነስ በመሆኑ፣ ለኢትዮጵያ ካሳ እንድትከፍል መጠየቅም ትክክል ነው።
  4. አቶ ዘውዴ ረታ የቀዳማዊ  ኃይለ ሥላሴ መንግሥት በሚለው መጽሀፍ ውስጥ ፒዩስ 11ኛን በመደገፍ ከጻፉት በተጨማሪ፣ ታኅሳሥ 7 ቀን 2005 በሪፖርተር ጋዜጣም አውጥተውታል።  ይህን ለማድረግ የተነሱበት ዓላማ ባይገባኝም አካሄዳቸው፣ በስተጀርባው አንድ ድብቅ ዓላማ ያለው አስመስሎባቸዋል።

እንደ እኔ አስተሳሰብ፣ ይህ ድርጊታቸው ትክክል እንዳልነበረ አምነው በመቀበል፣ አቋማቸውን እንዲያስተካክሉና የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ቢጠይቁ ጥሩ ነው እላለሁ።

ታደለ ብጡል ክብረት (ኢ/ር)

ሞባይል፡  00911 23 24 43

ፖ.ሣ. ቁጥር 5510

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ከወያኔ ምን አተረፍን?

$
0
0

ከተስፋየ ታደሰ (ኖርዌ)

ኢትዮጵያ ሃገራችን 3000 ሺህ ዘመን ታሪክ ባለቤት ብትሆንም ያለመታደል ሆነና ዛሬ ድርስ ጥሩ መሪ አላገኘችም። ወያኔ የደርግን ስረዓት ጥሎ የስልጣን ኮርቻዉ ላይ ሲቀመጥ ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ አሜን ብሎ ተቀብሎት ነበር። አበው ሲተርቱ እዉነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንደሚሉት የወያኔ ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ እያደር ፍንትው ብሎ መታየት ጀመረ። ዘር ከዘር መለያየትና ማጋጨት ለከፋፍሎ መግዛት ፖሊሲው ይመች ዘንድ፣ በእምነት ላይ ጣልቃ መግባት እንዲሁም ለዘመናት በመቻቻል የሚታወቁትን ሁለቱን ታላላቅ ሃይማኖቶች ክርስቲያኑን ከሙስሊሙ ጋር ማጋጨት እንዲሁም በምርጫ የህዝብ ድማፅ መስረቅ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ማፈን፣ ማሰር፣ ማሳደድ እንዲሁም መግደል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በወያኔ ስረዓት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘዉ ከመቼዉም ጊዜ በላይ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ድህነት፣ ጉስቁልናና ስራ-አጥነት ናቸዉ።
tplf-rotten-apple-245x300
ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፍትህ በሌለበት በአጠቃላይ ፍትህ ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር በተነፈገበት ሃገር ህዝብን ማእከል ያላደረገ ልማትና እድገት ይኖራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ በስልጣን ላይ ያለው ቡድን የራሱን ጉድ ለመሸፈን ሲል ኢትዮጵያ አድጋለች፣ ሁለት አሃዝ እድገት አስመዝግባለች፣ ረሃብ የለም ወዘተ….እያለ ነጋ ጠባ በአሸብራቂ ቃላት የአለም ማህበረሰብን ቀልብ በመሳብና ለማደናበር ይሞክር እንጂ በመሬት ላይ የሚታየው ሃቅ ግን በተቃራኒው ነው፡፡ በተለመደው መሰሪ ፕሮፓጋንዳው አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ ይበለን እንጂ የኑሮን ውድነት፣ መልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት በረሃብ እየተቀጣ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብን ማታለል ግን በፍጹም አይችልም፡፡ በተለይም ያልበላውን በልቷል፣ ያልሰማውን ሰምቷል ነጻ ወጥቷል የስርአቱ ልዩ ተጠቃሚ ሆኗል ወዘተ…እየተባለ ለአመታት በስሙ ሲነገድበት የኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮው በጣም ከባድ እንደሆነ ላይ የተገለጹ እውነታዎች ይመሰክራሉ።

ዛሬ በዚህ አስከፊ ስርአት ሳቢያ ከአንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተመርቆ የወጣ በእዉቀቱ ሳይሆን የኢህአዴግ አባል ካልሆነ የመንግስት ስራ አያገኝም ። ገበሬው ሰፊ የእርሻ ቦታውን እየተነጠቀ ለባዕድ ኢንቨስተሮች በሊዝ እየቸበቸበ ገበሬዉን ለድህነት ለጉስቁልና እየዳረገው ይገኛል። ወያኔ የዛሬ አስራ አምስት ዓመት ገደማ በመጪዉ አስርት አመታት የኢትዮጵያ ህዝብ በቀን ሶስት ጊዜ ይመገባል እንዲሁም የምግብ ዋስትና ይጠበቃል ብሎ ነበር ፤ ነገር ግን በየዓመቱ ከሰባት ሚሊዮን ህዝብ በላይ በረሃብ አለንጋ እየተጠበሰ ይገኛል። ሰብአዊነት ያልተላበሰ መንግስት ቢኖር እንደ ወያኔ ያለ መርዝ መንግስት ይኖራል ብሎ መናገር በጣም ያዳግታል። በአለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና መንግስታቶች ምክንያት ለተረጂዉ የመጣዉን እህል አረመኔው የወያኔ መንግስት በምስኪኑ ተረጂ ወገን ጉሮሮ ላይ ቆሞ ለስግብግብ ነጋዴዎች አየር በአየር እየቸበቸበ የግል ኪሱን እያደለበ ይገኛል።

ሀገራችን ነፃ ጋዜጠኞችን በማሰርና በማፈን ከአፍሪካ ቀዳሚ ደረጃን ከያዙ ሃገሮች ተርታ መሰለፏ ይታወቃል ። ይህ ደግሞ የመናገር የመፃፍ መብትን የሚጋፋና የሚፃረር ተግባር መሆኑ ግልፅ ነዉ፤ በሌላ አለም ባልታየ መልኩ በኤሌትሮኒክስ መገናኛዎች መረጃ ተለዋዉጣችኋል፣ መንግስት የሚተች ፅሁፍ ጽፋችኋልና ለኔ አልተመቻችሁኝም የሚል ቅኝት ያለዉ ዉንጀላ በማቀነባበር ሽብርተኛ የሚለዉን ፀያፍ ስያሜ በማሸከም ዜጎችን ለእስርና ለስደት እንዲሁም የቀረዉን ለፍረሀት የሚዳርግ ሽብርተኛ ስረአት ነዉ ተሸክመን ያለነው። በተጨማሪም በነፃነት መደራጀት እና መንግስትን መቃወም አንድም ለእስራት አልያም ለስደት እየዳረገ ይገኛል፡፡ በርካታ ጋዜጠኞች፣ ወጣት ፖለቲከኞች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ነጋዴዎች በነጻነት የመኖር፣ በነፃነት የመናገር እና የመፃፍ መብታቸው እየተገፈፈ በየእስር ቤቱ እየተሰቃዩ ይገኛለ፡፡ አሁን በሃገራችን በደልና ጭቆና በዝቷል ድህነትና ጉስቁልና ከመቸዉም በባሰ ተንሰራፍቷል እስርና ሰቆቃ ተራ ነገሮች ሆነዋል በአሸባሪዎች ስም እራሳቸዉ ቦንቦች አጥምደው ህዝቦች እየፈጁ ሰላማዊ ዜጎች በአሸባሪነት እየተፈረጁ ለስቃይ እየተዳረጉ ነዉ። ዛሬ በሃገራችን አርሶም ሆነ ነግዶ መኖር አይቻልም። መኖር የሚቻለዉ ኢሕአዴግ ልማት ነዉ የሚለዉን መዝሙር በመዘመር ብቻ ነዉ።

ባጠቃላይ ስረዓቱ ፀረ- ዲሞክራሲና ፀረ- ፍትህ አቋም የሚያራምድ ነዉ። በመሳሪያ የያዘዉን ስልጣን በዲሞክራሲና በፍትህ ለሚያምን ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንዲያስረክብ እና የነፃነት አየር እንዲተነፍስ ስለ ሀገራቸዉ በመቆርቆር በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሳይሸማቀቁ ጊዜና ሰአት እንዲሁም ቦታ ሳይገድባቸዉ የመናገር፣ የመፃፍ ጥያቄ ፣የመጠየቅ መብታቸዉ ተከብሮ አለም ከደረሰበት የእድገት ደረጃ ላይ ለማድረስና ከቂም በቀል የፀዳች አገር ለመጭዉ ትዉልድ ለማቆየት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ስልጣን ላይ ያለዉን ጨቋኝና ኢ-ዲሞክራሲያዊ የሆነና አንባገነናዊ ገዥ ፓርቲ አዉርዶ በምትኩ ዲሞክራሲያዊ የሆነ እና በበለጠ መልኩ የሁላችንን ነፃነት እና እኩልነት የሚያከብር መንግስት ለመተካት በሚደረገዉ ትግል ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የአገሪቷን እድገት ጎዳና በአንድ ላይ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ጥሪዬን አቀርባለሁ። አገራችንን ከወያኔ ዘረኝነት አገዛዝ ነፃ ለማዉጣት ትግላችንን በማንኛዉም መልኩ ልናጠናክር እንደሚገባን በኢትዮጵያ ስም በድጋሚ አሳስባለሁ።

ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ኢሜል አድራሻየ፡ tesfayetadesse20@gmail.com

ሚሚ ስብሃቱ ጠረጴዛ ምን ያደርግላታል?

$
0
0

ከዳዊት ሰለሞን

mimi sibehatuጠረጴዛ ከመመገቢያነት፣ለመጻፊያ ማስደገፊያነትና ከቁሳቁስ ማስቀመጫነት በተጨማሪ በዙሪያው በሚኮለኮሉት ወንበሮች የተነሳ ሰዎችን በአንድነት መሰብሰብ በመቻሉ የሐሳብ መንሸራሸሪያ መድረክ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡በጠረጴዛ ዙሪያ የሚቀመጡ ግለሰቦችና ቡድኖች በፊት ለፊታቸው በተዘረጋው ጠረጴዛ ላይ ሐሳባቸውን፣አመለካከታቸውንና አይዶሎጂያቸውን ያቀርባሉ፡፡የተጣሉ፣ልዩነት ያለባቸው ወገኖችም በጠረጴዛ ዙሪያ ቅራኔያቸውን ለማጥበብ ይደራደራሉ፡፡
ሚሚ ስብሃቱ ከቪኦኤ መልስ በታደለችው ዛሚ ራዲዩ ጣቢያ አማካኝነት ‹‹የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ››የተባለ መርሃ ግብር ታዘጋጃለች፡፡በሚሚ ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲታደሙ የሚፈቀድላቸው ወይም በቋሚነት በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ጋዜጠኝነታቸው‹‹በጠረጴዛው››የተወሰነ መሆኑም ድንቅ ይለኛል፡፡
ጋዜጠኞቹ ሚሚ ስታሽካካ አብረዋት የሚያሽካኩ የራሳቸው ሳቅ ወይም ለቅሶ የሌላቸው ‹‹እንገላበጥ››በማለት የሚጠይቁ ሁሌም ባለችው ላይ የሚጨምሩ መሆናቸውም ‹‹ጠረጴዛው››እውነት ከብበውታልን በማለት እንድጠይቅ ያደርገኛል፡፡
ሚሚ ዳዊት ከበደ መታሰር ይገባዋል ካለች ቀሪዎቹ የጠረጴዛው ታዳሚዎች‹‹እስካሁን አለመታሰሩ እንደሚገርማቸው ያክላሉ፣አንድነት ፓርቲ የግንቦት 7 ትርፍራፊን ለማግኘት ይሰራል ካለች አጃቢዎቿ ‹‹ለዚህ እኮ ነው የጸረ ሽብር አዋጁ ይሰረዝ የሚለው ይላሉ፡፡
ዛሬ አንድ ወዳጄ ደውሎ ሚሚን ስማት አለኝ፡፡ወሪያቸው ሚስ አና ጎሜዝን የተመለከተ ነበር ፡፡ሚሚ የስድብ መዝገበ ቃላቷን ጠረጴዛዋ ላይ ከፍታ ፖርቹጋላዊቷን የሰብዓዊ መብት ታጋይና የአውሮፓ ፓርላማ አባል ታወርድባታለች፡፡አና ሚሚን ባትሰማትም ሚሚ በተሳደበች ቁጥር ማንነቷን የምትገኝበትን ስብዕና የበለጠ እመለከት ነበር፡፡ማን ነበር ሰው አፉን ሲከፍት ሆዱ ይታያል ያለው፡፡
ሚሚ አና ጎሜዝ ወደ አገራችን እንድትገባ በመደረጓ ብዙ ኢትዮጵያዊያን አዝነዋል፡፡ብላለች የእርሷ ብዙ ስንት እንደሆነ ባይገባኝም፡፡አና ለሚዲያዎች በሰጧቸው ቃለ ምልልሶች መለስን መረር ባሉ ቃላቶች መግለጻቸው ሚሚን አንጨርጭሯታል፡፡እንዲህ በመናገሯ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ተቆጥተዋል ከማለትም አልተመለሰችም ‹‹መለስ መላጣ ብሎ ማንም ሊሰድበኝ ይችላል መላጣዬን ግን እንዲነካ አልፈቅድለትም››ማለታቸውን ሚሚ እንዴት እንደረሳቸው አልገባኝም፡፡አና መለስን ‹‹አጭበርባሪ ነበር››በማለት ገልጸውታል፡፡አያጭበረብርም የሚል ካለ አናን መሞገት እንጂ‹‹እንዴት ብሎ በጠረጴዛ ዙሪያ የስድብ መዓት ማዝነብ የሚቻል አይመስለኝም ፡፡
አና መለስን እንዲህ ያሉት ከመሬት ተነስተው አልነበረም፡፡ያው ምርጫ 2005ን ማስታወስ ብቻ ይበቃል፡፡እነ ሚሚ የመለስን የቲና ተርነር ዘፈን በማስታወስም ወይዘሮዋ ብርሃኑ ነጋ ጋር ስለነበራቸው ግኑኝነት ለመሳለቅ ሞክረዋል፡፡እንግዲህ አና በዘንድሮው የአዲስ አበባ አመጣጣቸው ደመቅ ያሉ ፎቶ ግራፎችን ከአባ ዱላ ገመደና ከተሾመ ቶጋ ጋር ተነስተው ተመልክተናል፡፡አና አባዱላን ወይም ተሾመን አፈቀሩ ወይስ ሁለቱ ሰዎች አናን ከብርሃኑ ነጠቁ?
እነሚሚ ይህንን ሊያነሱ አልቻሉም፡፡ከዚህ ይልቅ ተዘባዝበው አድማጮቻቸውን ተሰናበቱ፡፡እኔ ልጠይቅ በዛሚ ጠረጴዛ የሚሰባሰቡ ሰዎች አንድ አይነት ዘፈን የሚዘፍኑ ሚሚ ያለችውን እንደ በቀቀን የሚደግሙ እንደ ገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡ ናቸው፡፡ታዲያ ጠረጴዛ ምን ያደርግላቸዋል፡፡ባዶ ቤት አይሻልም፡፡ለእስክስታውም ይመቻል ብዬ እኮ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምን ይዋሻሉ?

$
0
0

ከዳዊት ሰለሞን

የአውሮፓ፣ የፓስፊክ፣የካሪቢያንና የአፍሪካ ፓርላማ አባላት ስብስባን ከሰሞኑ አዲስ አበባ ማስተናገዷ አይዘነጋም፡፡ በስብሰባው ለመካፈል በዛ ያሉ እንግዶች በከተማይቱ የሶስት ቀናት ቆይታ በማድረግ በአገሪቱ የፓለቲካ፣ የሰብአዊ መብት አያያዝና የሚዲያ ነጻነት ዙሪያ ከመንግስት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ ዳዊት ሰለሞን ከእንግዶቹ ለኢትዮጵያ መንግስት ቀርበው ከነበሩ ጥያቄዎች መካከል አንዱን በመምዘዝ የተሰጣቸውን ምላሽ ያጠይቃል፡፡

205178_229995677134311_714646790_n የየአህጉራቱ የፓርላማ ተወካዮች በአዲስ አበባ ካደረጉት ስብሰባ በተለይ ትኩረት ስቦ የከረመው ፖርቹጋላዊቷ የአውሮፓ ፓርላማ ተወካይ ሚስ አና ጎሜዝ ከዘጠኝ አመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ነው፡፡ አና በ1997 የተካሄደውን አገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ የመጣው የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ነበሩ፡፡ በኢትዮጵያ በነበራቸው ኃላፊነት ጠንከር ያሉ መግለጫዎችን በማውጣት ምርጫው መጭበርበሩን ማጋለጣቸው በመንግስት ጥርስ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል፡፡ በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ አና ጎሜዝን የተመለከተ ሰፊ ሃተታ በማቅረብ ወይዘሮዋ የቅንጅቱ አመራር ከነበሩት ብርሃኑ ነጋ ጋር በፍቅር መውደቃቸውን ጭምር መፃፋቸው አይዘነጋም፡፡ መለስ የቲና ተርነርን ተወዳጅ የሙዚቃ ስራ ‹‹What’s love got to do with it›› በመጥቀስ የአና ተቃውሞን ከዶክተሩ ጋር ነበራቸው ካሉት ግላዊ ግኑኝነት ጋር ለማቆራኘት ሞክረዋል፡፡

የፓርላማ አባሏ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ወደ አውሮፓ ከተመለሱ በኋላም ሪፓርታቸውን በማጠናከር በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጠንከር ያሉ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ወትውተዋል፡፡ ውትወታቸው በተወሰነ መልኩ ተቀባይነት በማግኘቱም መንግስት የቀጥታ የበጀት ድገማውን እስከማጣት ደርሷል፡፡ አና ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት በአውሮፓ ፓርላማ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዙ የሰብአዊ መብት ሪፓርቶችን ከማቅረብ አልተቆጠቡም፡፡ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ስለተጣሉ ፓለቲከኞችና ጋዜጠኞች ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ በማሰማትም የአውሮፓ ፓርላማ ስለ ኢትዮጵያ ግድ እንዲለው ተማጽነዋል፡፡

ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙና እስክንድር ነጋ የሳካሮቫን ሽልማት ለማግኘት በዕጩነት እንዲያዙ ጥቆማ የሰጡት አና ስለመሆናቸውም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ህልፈተ ህይወት በመንግስት ሆን ተብሎ መደበቁንም በመግለጽ መለስ ይህችን አለም የተሰናበቱት በመንግስት በይፋ ከመነገሩ አንድ ወር ቀደም ብሎ እንደነበር መናገራቸውም ከገዥው ፓርቲ ጋር የነበራቸውን የተበላሸ ግኑኙነት የበለጠ እንዳከፋው ለመገመት አያዳግትም፡፡ ወይዘሮዋ የአውሮፓ ፓርላማን በመወከል በስብሰባው ለመካፈል የቪዛ ጥያቄ ማቅረባቸው ከተደመጠ ጀምሮ የሚዲያውን ትኩረት አግኝተዋል፡፡ መንግስት አምርረው ለሚተቹት አና ወደ አገር የሚገቡበትን ቪዛ ይፈቅዳል? የማይፈቅድ ከሆነስ ምን ይፈጠራል? ፡፡

ሁሉን በጥርጣሬ የሚመመለከቱ ወገኖችም ‹‹አና ወደ አገር የሚገቡ ከሆነ ከመንግስት ጋር ተደራድረዋል›› ማለት ነው የሚሉ ቅድመ ግምቶችን ያሰፍሩ ነበር፡፡ በመጨረሻም አና ቪዛውን አገኙ፡፡ ‹‹ቪዛ እንደማገኝ እርግጠኛ ነበርኩ›› የሚሉት የሰብአዊ መብት ተሟጋቿ ‹‹ከዚህ በፊት በብራሰልስ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩ ዲፕሎማት የ2ዐዐ2 ምርጫን ለመታዘብ የምፈልግ ከሆነ ቪዛ እንደሚሰጡኝ ነግረውኝ ነበር፡፡ ነገር ግን በግዜው ሌሎች የምርጫ ታዛቢ ቡድን አባላት በአገሪቱ ያለውን ሁኔታ እንዲመለከቱ ስለፈለግኩ የቪዛ ጥያቄ አላቀረብኩም፡፡ ደግሞም መለስ ባለመኖራቸው ቪዛውን እንደሚሰጡኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡

ወደ አገሪቱ የመጣሁት የአውሮፓ ፓርላማን በመወከል ነው፡፡ እኔን መከልከል የአውሮፓ ፓርላማን አለመቀበል ስለሚሆን እንደተቀበሉኝ ይሰማኛል›› ማለታቸው ተደምጧል፡፡

አና የተገኙበትን የስብሰባ መድረክ በንግግር የከፈቱት በተፈጥሮ ሞት ስልጣናቸውን የተሰናበቱትን መለስ ዜናዊን የተኩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ነበሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የኢትዮጵያን መንግስት ዴሞክራትነት የሚያሳዩ ዐረፍተ ነገሮችን ተጠቅመዋል፡፡ የፓለቲካ ምህዳሩን ለተቃዋሚዎች የበለጠ ክፍት ለማድረግ በቁርጠኝነት መነሳታቸውን፣ ሙሰኝነትን መዋጋታቸውንና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ጭምር ዘብጥያ መውረዳቸውን አስታወቁ፡፡
Hailemariam-PM1-300x282
የቀድሞው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ዲን በንግግራቸው ማሳረጊያ የጠቀሱት ዐረፍተ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያን በቅርብ ሲከታተሉ የቆዮትን ሚስ አና ጎሜዝን አላስደሰተም፡፡ ‹‹ዛሬ ኢትዮጵያ ለብዙዎች አርአያ መሆን በምትችልበት ደረጃ ላይ ትገኛለች›› ያሉት ኃይለማርያም ‹‹በእስር ቤቶች ውስጥ በፖለቲካ አመለካከታቸው የተነሳ የታሰሩ ፖለቲከኞች የሉም፡፡ ጋዜጠኞች በጻፉት ነገር የተነሳ ለእስር አልተዳረጉም፡፡››

አና ወደ ጉባዔው የመጡት ነገሮችን በዝምታ በመከታተል ሌሎች ባልደረቦቻቸው ስለ ኢትዮጵያ በቅርበት ማወቅ የሚችሉበትን ነገር ለማመቻቸት ቢሆንም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር በቸልታ ሊያልፉት አልወደዱም፡፡ የዚህ ዘገባ ፀሐፊ ከአና ጎሜዝ ጋር ከመጡት የፖርላማ አባላት መካከል ኦሌ ስክሚደትን በማግኘት እንደተገነዘበው ወይዘሮዋ መረርና ከረር ባሉ ቃላት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ውስጥ በመማቀቅ ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች መኖራቸውን በማስረዳት ያልተጠበቀ ጥያቄ ለፓርላማ አባላቱ አቅርበዋል፡፡ ‹‹በእስር ቤቶች ውስጥ ፖለቲከኞች ጋዜጠኞች መኖር አለመኖራቸውን ለመረዳት ለምን ቃሊቲን እንድንጎበኝ አንጠይቅም?›› በአና ጥያቄ የተስማሙት የስብሰባው ተካፋዮች አንድ ቡድን በማቋቋም በስፍራው ለነበሩ የመንግስት ባለስልጣናት የጉብኝት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ባይሳካም፡፡ መንግስት ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን በሚከተሉት አስተሳሰብ ይሁን በሚያራምዱት ፍልስፍና የተነሳ ለእስር አልዳረግኩም በማለት ሲናገር የመጀመሪያ ግዜው አይደለም፡፡

አና እንደመሰክሩት በ1997 ምርጫ ገዥውን ፓርቲ በመገዳደር ከፍተኛ ድምፅ አግኝተው የነበሩት ቅንጅቶች ተጠራርገው ቃሊቲ ሲወርዱ አቃቤ ህግ ‹‹አገር በመክዳትና ህገ መንግስታዊውን ስርዓት በኃይል ለመናድ›› በሚል ክሶች ፍርድ ቤት ገተራቸው፡፡ መንግስትም ሰዎቹ የተከሰሱት አገር በመክዳት ወንጀል እንጂ ኢህአዴግን በመቃወማቸው አይደለም አለን፡፡ አቃቤ ህግ በፍርድ ቤት ቅንጅቶች ላይ ያቀረበው ማስረጃ ግን በምርጫ ክርክር ወቅት ያደረጓቸውን ንግግሮች ጭምር ያካተተ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ የፍርድ ውሳኔውን ካስተላለፈ በኋላ ታሳሪዎቹ ‹‹በፖለቲካ ውሳኔ›› የተቆለፈባቸውን የብረት ፍርግርግ አልፈው ነጻነታቸውን ተቀዳጁ፡፡ የፖለቲካ እስረኛ የለም›› በማለት ሽንጡን ገትሮ ይከራከር የበረው መንግስት‹‹ በፖለቲካ ውሳኔ›› እስረኞቹን ለቀቀ፡፡

የፖለቲካ እስረኛ ከሌለ እንዴት የፖለቲካ ውሳኔ እስረኛን ነፃ ሊያወጣ ይቻለዋል?፡፡ መኢአድ ከገዥው ፓርቲ ጋር አንድ ስምምነት የተፈራረመባትን ገጠመኝ ማስታወስም ተገቢ ይሆናል፡፡ የምርጫ ስነ ምግባር ኮድን መኢአድ የተፈራረመበት ቀለም ሳይደርቅ መንግስት ከ2ዐዐ የሚልቁ የፓርቲውን አባላት ከእስር ፈትቷል፡፡ እነዚህ ሰዎች የታሰሩበት ምክንያት ከደረቅ ወንጀል ጋር የሚያያዝ መሆኑን መንግስት ሲገልጽ ቢቆይም በመጨረሻ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ተለቅቀዋል፡፡

እንዴት ነው በደረቅ ወንጀል ተከስሶ የታሰረ ሰው በአንድ የስልክ ጥሪ ሊለቀቅ የሚችለው? መኢአድ አባላቶቼ ታሰሩ በማለት ወቀሳ ሲያቀርብ በመክረሙ የሰዎቹ መፈታት የሚያሳየው ወቀሳው እውነተኛ እንደነበር ነው፡፡ ዛሬም በእስር ቤቶች ውስጥ አንዷለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሄር፣ በቀለ ገርባ፣ አበበ ቀስቶ፣ ኦልባና ሌሊሳን የመሳሰሉ ፖለቲከኞችና አምስት ጋዜጠኞች በእስር ቤት ይገኛሉ፡፡ ሁሉም በ2ዐዐ1 በወጣው የፀረ ሽብረተኛነት አዋጅ የተወነጀሉ ናቸው፡፡ መንግስት የእነዚህ ሰዎች የእስራት ምክንያት ‹‹ከሽብርተኝነት›› የተጋመደ መሆኑን ቢናገርም የሚያምነው አካል አላገኘም፡፡ የሚበዙት እስረኞች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ሲያደርሱ፣ የማስተማር ስራቸውን ሲከውኑ፣ በቢሯቸው የአዘቦት ስራቸውን ሲፈጽሙ የተያዙ ናቸው፡፡ በፍርድ ቤት የቀረቡባቸው ማስረጃዎችም አለም ሽብርተኝነትን በሚያውቀው ደረጃ የተሰናዱ አልነበሩም፡፡

አና ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች በፖለቲካ አሰተሳሰባቸውና በሚጽፉት ጽሁፍ የተነሳ አልታሰሩም የሚለውን ንግግር ካዳመጡ በኋላ ‹‹እንግዲያውስ የታሰሩት ምንድን ናቸው?›› በማለት ጠይቀዋል፡፡ እነ ውብሸት ታዬ በታሰሩበት ምሽት የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ባስደመጡት ዜና ‹‹የመንግስትን የመሰረተ ልማት ለማፍረስ ሲዘጋጅ ተያዙ›› ያሉ ቢሆንም ተያዙበት የተባለው የማሰሪያ ምክንያት በፍርድ ቤት በማስረጃነት አልቀረበባቸውም፡፡ እስክንድር ነጋ በአንድነት ፓርቲ ቅጥር ግቢ ተገኝቶ ስለ አረብ አብዮትና ኢትዮጵያ ያደረገው ንግግር አስረጂ ተደርጎ ቀርቦበታል፡፡

ርዕዮት አለሙ አውቶብስ ተራ አካባቢ ‹‹በቃ›› ተብሎ የተለጠፈን ፅሁፍ ፎቶ ግራፍ አንስታለች ተብላ መከሰሷ አይዘነጋም፡፡ አንዷለም አራጌ ከወንድሙ ጋር ያደረገው የስልክ ልውውጥ በማስረጃነት ቀርቦበታል፡፡ ጋዜጠኛ ውብሽት ታዬ የቅርብ ዘመዱ ያደረጉትን የአይን ቀዶ ህክምና መሳካት አሜሪካን አገር ለሚገኝ የሰውዬው ልጅ ‹‹ኦፕሬሽኑ ተሳክቷል›› በማለት ኢሜይል ማድረጉ ሌላ ትርጉም ተሰጥቶት ቀርቦበታል፡፡ ታሳሪዎቹ ለፈረደባቸው ፍርድ ቤት የሞራል ጥያቄ በማቅረብ ፍርዱን በደስታ እንደሚቀበሉት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡እነዚህን ሂደቶች በጥንቃቄና በቅርበት ሲከታተሉ የቆዩት አና ጎሜዝ በአገሪቱ የፖለቲካ እስረኞች የሉም መባሉ አልተዋጠላቸውም፡፡እኔም፡፡እርግጥ ነው በየትም አለም የሚገኝ መንግስት ተቃዋሚዎቹን ለእስር ሲዳርግ ‹‹በፖለቲካ አመለካከታቸው አሰርኳቸው አይልም››እንዲህ ብሎ እንዲናገር መጠበቅም የዋህነት ሊሆን ይችላል፡፡

ሃይለማርያም ግን ፖለቲከኛ ብቻ አይመስሉኝም ለእግዜር ያደሩ ሃይማኖተኛ ናቸው፡፡ለመንፈሳዊው አለም ያደረ ሰው ደግሞ ከእውነት መወለዱን ይሰብካልና እውነትን በተመለከተ መደራደር አይፈልግም፡፡በዚህ ላይ ሀይማኖተኞች ለህሊና ቅርብ ናቸው፣ህሊና ስላላቸው ስራዎቻቸውን ይመዝናሉ፣አንደበታቸውን ስለሚከፍቱበት ነገር እርግጠኛ መሆንን ያስቀድማሉ፡፡ፖለቲካው የእግዜር ሰዎች እንደሚያስፈልጉት አምነው ወደ መድረኩ የመጡት ኃይለማርያም በጨዋታው ህግ ተገደው ሲዋሹ ማየት ህመም ይፈጥራል፡፡ግን ለምን ይዋሹናል?

ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግስት…… ከይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ ጉዳይ ሃላፊ)

$
0
0

ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ሕገ-መንግስቱ የፀደቀበት ቀን ነው፡፡ይህንንም ተከትሎ በመንግስት አሳሳቢነት እልፍ ሲልም አስገዳጅነት ህዳር 29 በየዓመቱ ከተለያዩ ጎሳ የተወጣጡ ሰዎች ተሰባስበው በመንግሰት ሹማምንቶች ፊት በአደባባይ ከበሮ የሚደለቅበት ቀን ነው፡፡ይሁን እንጂ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን መልካም ፍቃድና ተሳትፎ ባልታየበት የፀደቀው ህገ መንግስት በብዙሃን ዘንድ ተቀባይነቱ ጥያቄ ውስጥ የገባ ነው፡፡በዚህም መሠረት ከቃሉ አጠቃቀም ጀምሮ እስከ አከባበሩ ክብረ በዓል አብዛኛዉ ሰው እኔንም ጨምሮ ግድ አይሰጠንም፡፡
‹‹ይህ ህገ-መንግስቱን የመነዳ ተግባር ነው!!!›› ከገዢው መንግስት ተደጋግሞ የሚሰማ ለመፈረጅ ወይም ለመከሰስ የሚጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ አንድ ወዳጄ እንዲህ አለኝ ‹‹ ይህ ህገ መንግሰት ዝም ብሎ የተደረደረ ብሎኬት ነው እንዴ የሚናደው ?›› በማለት ሲተች ሰምቸዋለው፡፡በመናድ እና ደግፎ በማቆየት ላይ የተመሠረተሁን ህገ መንግስት እጅግ በጣም ብዙ ነገር ተብሎለታል፡፡

(ይድነቃቸው)

(ይድነቃቸው)


እየተንገዳገደ ያለው ህገ መንግስት ከአፀዳደቁ ጀምሮ የሚቀሩት ድንጋጌዎች መኖራቸው ለማንም ግልፅነው፡፡ ቢሆንም ፀድቆ በተግባር ላይ የሚገኘው ህገ መንግስት ዋጋ እንዳይኖረው እያደረገ ያለው የገዢው መንግስት አካሄድና ተግባር መሆኑ በአጭሩ ለማሳየት እሞክራለው፡፡
1ኛ. መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚለው በሕገ መንግስት አንቀጽ 11 ንዕሱ አንቀፅ 3 ተደንግጎ የሚገኝ ነው፡፡ይሁን እንጂ ገዢው መንግስት በሃይማኖት ላይ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት እየፈፀመ ይገኛል፤ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው በእስልምና አይማኖታ እየተፈፀመ ያለው በደል ነው፡፡በደሉ በይፋ የወጣ ሲሆን በተለይ ለእምነታችን እንቢኝ ያሉ ለሞት፣ለእስርና ለእንግልት ተዳርገው ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪ በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥም ጣልቃ ገብነቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡ገዳማትና አድባራት በልማት ስም ፈርሰዋል የተቀሩት ቦታቸው ተጎምዶ ተወስዶል በዚህም ምክንያት የሀይማኖት አባቶችና ጥቂት የማይባሉ የእምነቱ ተከታዮች ለእስርና ለእንግልት ተዳርገዋል፡፡
ከምንም በላይ ደግሞ በሁሉም በተለይ በኦርቶዶክስና በእስልምና የሀይማኖቱ መሪዎች (አባቶች) ሹመታቸው ከሚያመልኩት አምላክ እና ከምዕመናኖ የመነጨ ሳይሆን በመንግስት ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት የተፈፀመ ነው፡፡
2ኛ. የመንግስት አሠራር ለሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት፡፤ በሕገ መንግስት አንቀጽ 12 ንዕሱ አንቀፅ 1 ተደንግጎ የሚገኝ ነው፡፡ቢሆንም ከታችኛው የስልጣን እርከን ከሆነው ከቀበሌ ጀምሮ እስከላይኛው የመንግስት ባለስልጣናት አማከኝነት የሚከናወኑ የመንግስት አሰራሮች ግልፅነት እጅግ በጣም ጠባብ ነው፡፡በመሆኑም ህብረተሰብ በአገሩ ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን በመንገስት አሠራር ላይ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አልተደረገም፡፡
በዚህም ምክንያት የመንግስት አሠራር ለሙሱና የተጋለጠ ነው፤ሙሱና በአሁን ወቅት በአገራችን ህጋዊ እስከመሆን ደርሷል፡፡በመሆኑም ማናኛውም የመንግስት ኃላፊ ኃላፊነቱን ወይም ስልጣኑን መሠረት አድርጎ ሲበድል እንጂ ለበደሉ ተጠያቂ ሲሆን አልታየም፡፡ስለዚህም የመንግስት አሠራር በየትኛውም ደረጃ ለህዝብ ግልፅ አይደለም ይህ ደግሞ የህገመንግስቱ ድንጋጌ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
parlama
3ኛ. ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት አለው፡፡ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 14 ተፅፎ ይገኛል፡፡ነገር ግን የሰው ደህንነትን ለመጠበቅ የተቋቋመው የደህንነት መስሪያ ቤት በየደኑና በየጫካው የስንቱን ሰው ህይወት እንዳጠፋና የአካል ጉዳት እንዳደረስ የሚያውቀው ያውቀዋል፡፡ በተጨማሪ ይህ የነፃነት መብት ገዢው መንግስት በችሮታ ወይም በፍቃዱ የሰጠን እንጂ ሰው በመሆናችን ያገኘነው መብት እንዳልሆነ በሚያሳብቅ መልኩ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት በገዢው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረተ እስከሚመስል ደረስ ተደርሷል፡፡
4ኛ. ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት ፣ኢሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 18 ላይ ይገኛል፤ ይህ የህገመንግስት ድንጋጌ መሸራረፍ ሳይሆን መገርሰስ የሚጀምረው በህገመንግስቱ በተቋቋመው በህግ አስፈጻሚው አካል ነው፡፡
በመሆኑም ክብርን ለማወረድና ጭካኔን ለማሳየት የሰለጠኑ አሰቃዮችና ማሰቃያ ቦታዎች መኖራቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ነገሩን ለማነፃፀር እንዲረዳ ፖለቲከኛ ወይም በህግ ጥላ ስር ያለ ሰውን ይቅርና ስታዲዮም እግር ኳስ ለመመልከት ወራፋ የሚጠብቅ በወረፋ ምክንያት ለተነሳ አለመግባባት ፖሊስ እንዴት አድርጎ እንደሚቀጠቅጥ ዱላውን የቀመሰ ያውቃል፡፡
5ኛ. በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ መልኩ የመያዝ እና ከሰዎች ወይም ከጠያቂዎቻቸው የመገናኘት መብት አላቸው፡፡ በማለት በህገመንግስቱ አንቀፅ 21/1እና2 ተፅፎ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ ነፃ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች አያያዛቸው ክብርን ከመንካት አልፎ በህይወታቸው ላይ አደጋ የሚያስከትል ነው፡፡በተጨማሪ ከቤተሰብ፣ከወዳጅ መጠየቅ የማይሞከር ነገር ነው፤ የመጠየቅ እድል ያላቸው እስረኞች እድላቸው በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
6ኛ. ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገ መንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብ ላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ነው፡፡ነፃ አሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል አሉ ? እርግጥ ነው ገብያውኑ መሰረት ያደረጉ መዝናኛ ላይ ያተኮሩ መፅሔትና ጋዜጣ ለቁጥር በዝተው ይሆናል፡፡ ግን ሁሉ ነገር በአገር ነው የሚያምረው! ታዲያ ስለ አገር በነፃ አሳብ የሚንሸራሸርበት መፅሔትና ጋዜጣ ምን ያኸል ነው ? ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ መጥፎ ሪከረድ አስመዝግባለች፡፡መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ተጠራርጎ ቃሊቲ የሚገባበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡
7ኛ. ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ ሠላማዊ ሠልፍ እና ስብሰባ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 30/1 ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆን የቅርብ ጊዜ አይን ያወጣ የህገመንግስት ጥሰት ማቀረብ ይቻላል፡፡በሳውዑዲ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍና በደል ይቁም፣ይህንንም የፈፀሙ ለፍርድ ይቅረብ በማለት አቤቱታ ለማቅረብ የተጀመረው ሠላማዊ ሠልፍ በፖሊስ ዱላ እና እስራት ነው የተጠናቀቀው፡፡ በተጨማሪ በመንግስት እየታየ ያለው የአስተዳደር ብሉሹነት ለማመልከት እና ምላሽ ለማገኘት የተጠሩ የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎች እና ስብሰባዎች በመንግስት ቀጥተኛ ትእዛዝ ተከልክሏአል፡፡ሠላማዊ ሰልፍ ማድረግ እና አቤቱታ ማቅረብ መብት ነው! በማለት ክልከላውን ወደ ጎን በመተው አደባባይ ለመውጣት የሞከሩ ለእስርና ለድብደባ ተዳርገዋል፡፡በመሆኑም የተቃውሞ ሠልፍና ስብሰባ በማድረግ አቤቱታ በኢትዮጵያ ማድረግ የሞት ሽረት ትግልና ጥያቄ ከሆነ ሰንብቷል፡፡
8ኛ. የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን ሆነ አካል ተፅዕኖ ነጻ በመሆን በሙሉ ነፃነት ከህግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም፡፡በማለት በህገመንግስቱ አንቀፅ 79 እና በተከታዮቹ ንዑስ አንቀፅ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ዳኞች የመንግስት አስፈፃሚ አካል ከሆነው ነው ሹመታቸውን የሚያገኙት፡፡በመሆኑም ከመንግስት ጋር ቀጥተኛ ግኝኙነት ያላቸው የፍርድ ውሳኔዎች ምንያኽሉ በህግ እና በህሊና ላይ የተመሠረቱ ናቸው ? በተለይ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች የፍርድ ሂደታቸው ምን ይመስል ነበር ? እነዚህን እና መሰል ዳኝነቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በህገመንግስቱ የሰፈረው ነጻ ዳኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
millitery ethiopian9ኛ. የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የጎሳዎች ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ይሆናል፡፡ ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 87/1 ተደንግጎ ይታያል፡፡ነገር ግን በየድንበር እና በተልኮ ጭዳ ከሚሆነው ውጪ አብዛኛው የሠራዊቴ አባል እና አዛዥ የአንድ ጎሳ ስብስብ ነው፡፡ ስለዚህም ሠራዊቱ የማነው የኢትዮጵያ ወይስ ወደሚል ጥያቄ እያመራ ይገኛል፡፡
10ኛ. በየደረጃው ትክክለኛ ምርጫ እንዲካሄድ ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 102 ላይ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ሹመታቸው ከመንግስት መልካም ፍቃድ የመነጨ ሲሆን አሰራራቸውም ለገዥው መንግስ በእጅጉ በጣም ያደላ ነው፡፡ስለዚህም ምርጫ ቦርድ ህገመንግስቱን መሠረት አድርጎ ነጻ እና ገለልተኛ ነው ለማለት ከበድ ድፍረትን የሚጠይቅ ነው፡፡

በመሆኑም እነዚህ እና መሰል የህገመንግስቱ ድንጋጌዎች ጥሰት ወይም በእነሱ ቋንቋ የመንድ ተግባር እየተፈፀመ ያለው በህገመንግስቱ በየወንዙ ዳር የሚማማለው ገዥው መንገስት ነው፡፡ ህገመንግስት የበላይ ህግ ነው፡፡ማንኛውም ህግ፣ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣን አሰራር ከህገመንግስቱ የሚቃረነረ ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም ፡፡ የሚለው አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 1 የገዥው መንግስት ደራሽ ዉሃ ጠራርጎ ወስዶታል፡፡ ስለዚህም የብሔሮ፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የሚለውን መጠሪያ ስም በመስጠት ከበሮ ተይዞ የሚደለቅለት እና የሚከበረው ህገመንገስት መልሶ ካላስከበረ ፌሽታው እና ቀረርቶው ከምን የመነጨ ነው ?

ኢትዮጵያዊነት የታላቁን የሰላም አባት የኔልሰን ማንዴላ ህይወት የታደገ ታላቅ ሚስጢር …. አነጠረ

$
0
0

ኢትዮጵያዊነት የታላቁን የሰላም አባት የኔልሰን ማንዴላ ህይወት የታደገ ታላቅ ሚስጢር …. አነጠረ።

ወርቁ ፈለቀ፤ ገድሉ – ተገለጠ፤ እውነት -ሳቀ፤ የሙያ ሥነ – ምግባር
ከበረ፤ በዘውዳችን በሻንበል ጉታ ዲንቃ ….
„የተከበሩ ረቂቅ ሰው ናቸው“ ይሏቸዋልም።

ታሪክ ይዋባል። ኢትዮጵያ የኔልሰን፤ ኔልሰንም የኢትዮጵያ … ፍቅር – ድህነት።

ከሥርጉተ ሥላሴ

(ስርጉት)

(ስርጉት)

ወደ አራት ወራት ሆነኝ የሲቢሊቲ ሩም ታዳሚ ከሆንኩኝ። ወረፋው አይጣል ነው። ሌሊት ላይ ተነስቼ ድንጋይ አስቀምጥና ድምጹን ቀንሼ እተኛለሁ። አሁን አሁን ሰንበት ይናፍቀኛ ጀምሯል። ያው እዬተዝናኑ ቁምነገር መልቀም መልካም ነውና ተመቸኝ። የአባ መላን ሞደሬተርነትም እወደዋለሁ። ይስቃል … ቀልድ ጣል … ጣል ያደርጋል …. ይችላልም። እርግጥ ስጀምረው ትንሽ የሚታመሱ የመንደር ጉዳዮች በተለይም እስከ አባ መላ የመጀመሪያ ቡና ድረስ ነበሩ። ከዛ በኋላ ሁሉም ነገር መልክ ይይዝና መኮምኮም ነው። … የዛሬው ሰንበት ግን ወርቅን ያነጠረ ዕንቁ ነበር …. ዋው! እግዚአብሄር የኢትዮጵያዊነትን ሚስጢር ከኔልሰን ማንዴላ የህይወት ዘመን ጋር እርስ በእርሳቸው እንደ ሊማሊሞ መንገድ አያይዞ ፍትኃት የሰጠበት ታላቅ ቀን ነበር። ሳንተኛ ተግተን ከሰራንበት ኢትዮጵያዊነትን የክብር ካባ በ21ኛው ምዕተ ዓመት የሚያጎናጽፍ ፍጹም አዲስ የወርቅ እንክብል በእጃችን ሰተት ብሎ እንሆ ገባ። ተመስገን አልኩ ማለት ነበረብኝና። እኔ እንደማስበው የኢትዮጵያዊነት ሚስጢር ገና የሚፈልቅ ልዩ የሰማይ ሥነ – ጥብብ ብዬ ነበር። ዛሬም እላሁ – በድፍረትና በእርግጠኝነት።

Click here to view the embedded video.

እንደሰማን …. በተደሞና በግራሞት ሁላችንም ተደመምን … አባ መላ / አቶ ብርኃኑ ዳምጤ/ የሩሙ ባለቤት ዛሬውኑ አድራሻውን ፈልጌ ቃለ ምልልስ አድርጋለሁ በማለት በጸጸት ቃል ገባ … እየተቁነጠነጥን ሰዓቱን ጠበቀን። ሰዓቱ በጣም ራቀ … አይደረስ የለም ደረሰ …. በቀጥታ ከጀግናው ጋር ቃለ ምልልሱ ተጀመረ … በባተሌው ጠቅለል ሲል … እንዲህ ነው ….

የ78 ዓመት አዛውንት ናቸው። ምዕራብ ሽዋ አንቦ አካባቢ ነው የተወለዱት። የቄስ ትምርት ቤት ትምህርታቸውን እዛው አካባቢ አጠናቀው የአንደኛ ደራጃ ትምህርታቸውን እስከ 6ኛ ክፍል ተምረው፤ ከዚህ በኋላ ወደ ተመረጡበት ወደ ውትድርና ሙያ ተሰማሩ – በኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ። ከህግ ባለቤታቸው ከወ/ሮ አስቴር ፈንታ ጋር በሥርዓተ ጋብቻ የሁለት ሴት ልጆችና የስድስት ወንድ ልጆች እንዲሁም የአራት የልጅ ልጆች አባት ባለ ጸጋ ናቸው። በአዲስ አበባ ከተማ ላፎቴ ካልተሳሳትኩ በ450.00 የኢትዮጵያ ብር በጡረታ ይኖራሉ። የታሪካችን አንብርት የተከበሩ ሻንበል ጉታ ልጆቻቸው የተሟላ ድጋፍና እንክብካቤ እንደሚያድረጉላቸው አባ መላ ካደረገላቸው ቃለ ምልለስ ለማወቅ ችያለሁ።

የኢትዮጵያዊነታችን ሚስጢር የሆኑት እኒህ ታላቅ ሰው እንደ ቀደምቶች ወርቆቻችን እንደ አብዲሳ አጋ፤ እንደ አብርኃም ደቦጭ፤ አንድ ሞገስ አስገዶም እንደ ዘርዓይ ደረስ ታሪክን የፈጠሩ የነፃነታችን ቀንድ ናቸው። ለእኛ ብቻ አይደለም የዓለም የነፃነት ትግል ጠባቂና አዲስ ፊኖሚና እንዲሁም አምክንዮም ናቸው ብል ማገነን ተብዬ እንደማልከሰስ ነው። ዘውዳችን የሆኑት እኒህ እንቁ የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ለተለዬ ተልዕኮ ለሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ በስውር፤ በረቂቅና በርቀት እንዲጠብቋቸው ከተመደቡት ወገኖቻችን አንዱ ነበሩ። የሰላም ሐዋርያውን ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ ይገልፆቸዋል“ ስልጡን ….የተከበሩ ረቂቅ ሰው ናቸው። ቀልጣፋና አንባቢ፤ ሰውነታቸውን በማፍታት በተለይም በቦክስ ስፖርት ላይ የሚተኩሩና መዝናናትም የሚወዱ ነበሩ“

ብሄራዊ ኃላፊነታቸውን በጀግንነት የተወጡት እኒህ ታላቅ ሰው ሳንበል ጉታ፤ ኔልሰን ማንዴላ ለስልጠና በመጡ በወራቸው በአንድ የስልጠና ጓደኛቸው ኔልሰን ማንዴላ ህይወት በአጭሩ ለመቅጨት ከአሴረው ድርጅት ጋር አብረው እንዲሰሩ ተጠዬቁ። እዬፈሩ ፈቃዱን ተቀበሉ። ምሳ እቴጌ ሆቴል ተጋባዙ፤ ተልዕኮው ተነገራቸው፤ የ2000.00 ፓውንድ ብርና ካሜራም ተሰጣቸው። ሂደቱን በፎቶ እንዲያነሱ ተገለጸላቸው። የግድያው እቅድ መራራ ነበር። በገመድ አንቀው እንዲገድሉ ነበር የተነገራቸው። ከግድያው በኋላ ከኮልፌ የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማሰልጠኛ ጣቢያ 500 ሜትር ላይ በርቀት በመኪና እንደሚጠብቃቸውና ከዚህ በኋላ ውጭ ሀገር እንደሚኖሩ፤ ከድህነት ጋርም ለአንዴና መጨረሻ ጊዜ እንደሚፈቱ ተነገራቸው። ውሉ በጳውሎስ ቤተክርስትያን ቃል እንዲታሰርም ተሰማሙ። ሁሉን ከከወኑ በኋላ ታማኙ ወታደር በቀጥታ ወደ አዛዣቸው በመሄድ ዝርዝር ሪፖርቱን ገለጹ ለጄ/ ታደሰ ብሩ። ዕለተ ሰንበት ልክ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት የነፃነትን ነፍስ የታደገ ሕይወት፤ የዘርኝነትን ቅስም የሰበረ፤ የአፍሪካ መብራታ እንዲጠፋ ነበር ብይኑተ። ለዛውም በፍጹም ሁኔታ ታምና አፍሪካ ልጇን ለላካችባት የነፃነት ዓርማ ሀገር ኢትዮጵያ መሬት ላይ። ለተልእኮው አንድ ነጭና ሌላ ጥቁር ሰው እንደነበረ ባለ ታሪኩ ይናገራሉ …. ድርድሩ ቅዳሜ ነበር።

ክቡር ሻንበል ጉታ በበነገታው ሰንበት ተራኛ ነበሩ። ቅደመ መሰናዶውን ያሟለው ወታደራዊ የደህንት ክፍል ወንጀሉን ቀድሞ ስለደረሰበት አከሸፈው። … ቅጣቱም ለስም የለሽ ተሰጠ። …. እሩቅ ቦታ ተመደበ …. ሁለቱ የውጭ ሀገር የሴራው መሪዎች በ24 ሰዓት ኢትዮጵያን እንዲለቁ ተደረገ። የኛው ክብር፤ ተክሊላችን ሻንበል ጉታም ዲንቃም ኃላፊነታቸውን በድልና በብቃት አጠናቀቁ። ታማኝታቸው ለኢትዮጵአዊነት ክብር ሸለሙ። የተሰጣቸውን የ2000.00 ፓውንድና ካሜራም አስረከቡ ለክፍሉ። ሚስጢሩ በሚስጢርነት ቀጥሎ ለሌሎች የሙያው ባልደረቦች ሹመት ሲሰጥ በሚስጢር የዛሬው ሻንበል ጉታ የ10 አለቃነት ለደበበ የ50 አለቃነት ማዕረግ ተሰጠ ይላሉ። ድንቁ …. ይህም ሚስጢር ነበር። የሚገርመው ሂደቱም ድርጊቱም ሚስጢርነቱ እጅግ ጥብቅ መሆኑ ነው።

የታወቁት የተከበሩት ኔልሰን ማንዴላ በስውርና በርቀት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ሆነ የግድያ ሙከራው ታስቦ እንደከሸፈ ሳያውቁ ነበር ያለፉት። ዛሬ …. ለነገም ሌላ ከመቃብር በላይ ሌላ አዲስ ትዕይታዊ የታሪክ ምዕራፍ ኪኖ ልበለው ገድል …. የመረጣችሁትን ብያለሁ። ያን ጊዜ በሴራው ውስጥ ስለነበረው ዛሬ 08.12.2013 አባ መላ ሲጠይቃቸውም ስሙን ለመስጠትና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም። ይህ በራሱ ከወርቅ የነጠረ ወታደራዊ ሥርዓት …. ያኮራል። ግን ዛሬ …. ቅንቅን የበላው ይመስለኛል በወያኔ …

ህልም ነባራቸው የሀገራቸውን ባህላዊ ልብስና ጃኖ የተግባር አዛውንቱን፤ የጽናት አብነቱን፤ የምህረት ድርጊተኛውን አጎናጽፈው ከኔልሰን ጋር ፎቶ ለመነሳት …. ለ2 ዓመታት ቢጥሩም አልተሳካላቸውም። የመንፈስ ሚስጢራቸውን እንደ ቋጠሩ ዛሬ ሀዘናቸው መራር ቢሆንም በቀብሩ ላይ ለመገኘት ፈልገዋል። እንኒህ ታላቅ ሰው የዓለምን ተስፋ የታደጉ በመሆናቸው በርካታ ዓለም ዓቀፍ ሽልማት ማግኘት አለባቸው እላለሁ። ቢያንስ ዛሬ ለቀበር ሥርዓቱ በክበር እንዲገኙ በደስታ ምኞታቸውን ለማሳካት ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ወገኖቻችን ሥጦታቸውን በደስታ አክበረው በማሰተናገድ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ በወገኖቼ እዬተማመንኩ ቢዛ ካገኙም መሄድ በቀብር ሥርዓቱ ላይ መገኘት ስለ አለባቸው የሎቢ ተግባራትን ከመከወን በተጨማሪ ጠቅላላ ወጪያቸውን እንሸፍን ዘንድ ቆሜ እለምናችኋለሁ።

አዎን …. የመጨረሻው የተከበሩ የኔልሰን ማንዴላ ጉዞ ድንገተኛ ነበር። የምሽት እራት ግብዣ ነበር። ዝግጅቱም በክበቡ ነበር። ከሌሎች አርቲስቶች ጋር ቀደምቷ አርቲስ ሂሩት በቀለ ተገኝታለች። በመጨረሻዋ ሰዓት የፈጥኖ ደራሽ የማዕከሉ አዛዥ ጄ / ታደሰ ብሩና የሰላሙ አባት ኒልሰን ማንዴላ አብረው አሳለፉ። የነበራቸውን ልዩ አድናቆት፤ ክብርና ፍቅራቸውንም የተከበሩ ጄ/ ታደሰ ብሩ የወገባቸውን ኮልት 38 ሽጉጥ ፈተው ለኔልሰን ሸለሙ። ልጅን፤ ክብርን የመስጠት ያህል ነበር። ጌታችን መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ለወዳጁ ለቅዱስ ዮኋንስ ቀበቶውን እንደ ሰጠው ሁሉ። ዕንቁው አባታችን ከ ኢትዮጵያ እንደተመለሱም ነበር የካቴና ስንቅ የሆኑት።

የላቀ ሜዳሊይ፤ ዓለም አቀፍ ሽልማትና ተደማጭነትን ሊአተርፍ የሚችለው ይህን ታላቅ ተልዕኮ የእፍሪካ እናት ምድር፤ የዓለም እናት እምዬ ኢትዮጵያ ስታስተናግድ በዛን ወቅት በአጠቃላይ በካንፑ ውስጥ የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ስልጠና የሚያውቁ 5 ሰዎች ብቻ ነበሩ። ጠባቂዎቹ ከጄኒራላቸው ጋር በቀጥታ የመገናኘት መብት ነበራቸው። ተፈልፍሎ … ተዝቆ የማያልቅ ብቃትና መክሊት …. ከድንቅነሽ አንባ ….

ኮንታክት ኢሜል ለእርዳታ bdamte56@gmail.com

ኢትዮጵያዊነት የነጠረ ወርቅነት!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ግርማ ካሣ ቀልድ ጨምሯል!

$
0
0

ነጻነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ

የግርማ ካሣን ጽሑፎች አልፎ አልፎ አነባቸዋለሁ፡፡ ሀገር ወዳድ መሆኑን ይጠቁማሉ – ጽሑፎቹ፡፡ ታታሪ ሰው ይመስለኛል፤ በጥረቱና በሀገር ፍቅር ስሜቱ እወደዋለሁ፡፡ ሁልጊዜ ሳይታክት ይጽፋል፡፡ ሳይታክቱ የሚጽፉ ብፁዓንነት የሚበዛባቸው ቢሆን ዕድለኞች ግን ናቸው፡፡ ብዙዎቻችን እየደከመን መጻፍ ቀርቶ ማንበባችንንም እያቆምን በምንገኝበት ሰዓት አዘውትሮ መጻፍ መታደል ነው፡፡


አያ ግርማ ሰሞኑን የጻፋቸውን ሁለት ያህል መጣጥፎች አንብቤያለሁ፡፡ ሁለቱም ግንቦት ሰባትን ለመንቀፍ ብዕራዊ አንደበታቸውን ያሾሉ ናቸው፡፡ መነቃቀፍ በራሱ መጥፎ አይደለም፡፡ አግባብነትና እውነት ያለው መነቃቀፍ ወይም መወቃቀስ የዕድገት መሠረት በመሆኑ ሊጠላ አይገባውም፡፡ ነቀፌታንና ትችትን መፍራት ብልህነት አይደለም፡፡ ብሂሉ “ያልተቀጣ ሕጻን ሲቆጡት ያለቅሳል” እንደሚል አንድ በግለሰብም ይሁን በቡድን ደረጃ የሚገኝ አካል ጥፋት ካለው ያን ጥፋት በተጨባጭ መረጃና ከተገኘም ማስረጃ ነቅሰው ቢመክሩት መካሪውን “አንተን ብሎ መካሪ፤ ለራስህ ምን ታውቅና” በማለት ምክሩን ላለመቀበል መሞከር አስተዋይነት የሚጎድለው ጠያፍ ነገር ነው፡፡ አንድ ሰው ሌላው ቀርቶ ዕብድና ማይም ቢሆን እንኳን፣ ለሰው የሚያስላልፈው ገምቢ ሃሳብ አያጣም፡፡ ችግሩ መናናቅ ካልሆነ በስተቀር ወይም ጭፍን ጥላቻ ካላወረን አንዳችን ለአንዳችን ጥሩ መስተዋት ነን፡፡ ስንተቻች ግን የተደበቀ ሌላ አጀንዳ የምናራምድ ለመሆናችን ፍንጭ የሚሰጡ በቀጥታ ወይም በዐይነ ውሃችን የሚታወቁ ስስ ስሜቶች ከታዩብን ሚዛናዊነታችን ጥያቄ ውስጥ ይገባና ትዝብት ላይ ልንወድቅ እንችላለን፡፡ ጭፍን ፍቅርና ጭፍን ጥላቻ ሁለቱም በእኩል መንገድ ጎጂዎችና ጥቁር ጥላ የሚጥሉ ናቸው፡፡ መግባባት ሳይሆን መናቆርና ከንቱ መተቻቸት እንዲስፋፋ ያደርጋሉና ከነዚህ መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ ለገምቢ ምክርና አስተያየት ልቦቻችንን ቀና አድርገን ብንሳሳብ ተጠቃሚዎች እንሆናለን፡፡ አለበለዚያ የዱሮው ጥፋት በአዲስ መንፈስ ወደአዲስ ሰውነት ውስጥ እየተዛነቀ መስማማት ሳይኖር እንደስከዛሬው እየተቋሰልንና እየተዳማን እንኖራለን፡፡ ለማንኛውም በዚህ ረገድ ልቦናችንን ክፍት ብናደርግ ጥሩ ነው፡፡ መገፈታተር ይብቃንና ስሜት ለስሜት ለመናበብ እንጣር፤ አንጎዳበትም፡፡
ginbot 7የግርማን መጣጥፎች የምመለከተው እንግዲህ ከዚህ በላይ ከጠቆምኳቸው ሃሳቦች በመነሳት ነው፡፡ ግርማ ግንቦት ሰባትን ለመንቀፍ የተጠቀመባቸውን አንዳንድ ቃላት አልወደድኳቸውም፡፡ በቀዳሚው ጽሑፉ ላይ የኢሕአዴግን ግንቦት ሰባትን አለመፍራት ለመግለጽ የተጠቀመባቸው ቃላትና ድምፀቱ ራሱ (ቶን) ለትችት የሚዳርገው ነው፡፡ በመጀመሪያ “ኢሕአዴግ ግንቦት ሰባትን አይፈራም” የሚለው ነገር ከግርማ ሣይሆን ከራሱ ከኢሕአዴግ ቢወጣ የተሻለ ነው – ግርማ የኢሕአዴግ ቃል አቀባይ እስካልሆነ ድረስ ማት ነው፤ በርግጥም በማግሥቱ ኢሕአዴግ ከምልክት ቋንቋና ከተግባራዊ እንቅስቃሴው ባለፈ በግልጽ “ግንቦት ሰባት ያሰጋኛል” ቢል ግርማን ማጣፊያው ያጥረዋል፡፡ ግርማ ቢያንስ በለዘበ አማርኛ “ግንቦት ሰባት አሁን ባለው (ወታደራዊ) አቋሙ ኢሕአዴግን የሚያስፈራው አይመስለኝም፡፡ ጊዜው ገና ነውና ኢሕአዴግ በጦር ማንንም የሚፈራበት ሁኔታ በግልጽ አይታየኝም፡፡…” ቢል የእኔንም ብዕር ባላናገረ ነበር፡፡ ግና አንዳች ነገር በሚያስጠረጥር ሁኔታ ግርማ የኢሕአዲግን የሕዝብ ግንኙነት ሥፍራ መውሰዱን መገመት ችያለሁ – ባለማወቅ ሊሆን እንደሚችልም አስባለሁ፡፡ ይህንን ስል ደግሞ ከጽሑፎቹ አጠቃላይ ይዘት በመነሣት ግርማን በወያኔነት ለመክሰስ ወይም ከነጭራሹም ለመጠርጠር በቂ ምክንያት አለኝ ለማለት እንዳልሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡
በበኩሌ ኢሕአዴግ እንደግንቦት ሰባት የሚፈራው ነገር እንደሌለ በሙሉ ልብ እመሰክራለሁ፡፡ ይህን ስል ግንቦት ሰባት አንዳንድ “ወዳጆቹ” እንደሚሉት ከ30 የማይበልጡ ተዋዎች ኖሩትም ዜሮ የተዋጊ ኃይል ኑረውም ያ ከጉዳይ ሳይጣፍ ነው፡፡ ግንቦት ሰባት መጠሪያው ብቻ ወያኔን የሚገባት እንደሚያሳጣው በስድስተኛው ሕዋሴ እረዳዋለሁ – ስሙ ብቻውን ያምጰረጵረዋል፡፡ ጠላት በሁለት ይከፈላል – ተጨባጭና እምቅ ተብሎ፡፡ እንደማንኛውም ጠላትና ወዳጅ አፍሪ አካል የወያኔ ጠላቶች ሁለቱም ናቸው፡፡ ይበልጥ ወያኔን የሚያሰጋው ጠላት ግን ከተጨባጩ ይልቅ እምቁ ነው፡፡ እምቁ ወደተጨባጭነት የሚለወጥበትን ሰዓት ደግሞ ወያኔ ቀርቶ ሰይጣንም ላያውቀው ይችላል፤ ግርማም እኔም አናውቀውም – ግን ያስፈራል፡፡ መፍራ ደግሞ ተፈጥሯዊ ነው፤ በአለመፍራት ጮቤ አይረገጥም፡፡ አልፈራም የሚል ጀብደኛና ጉረኛ ብቻ ነው፡፡ ግንቦት ሰባት ያነገበው ዓላማ በመላው ጭቁን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚደገፍ ዓላማ ነው፡፡ ግንቦት ሰባት ሲጠራ ወያኔ የሚርበተበተውና ይይዘውንና ይጨብጠውን የሚያጣው እንግዲህ ንቅናቄው በኒኩሌር መሣሪያ ትጥቅ ታምቶ ሳይሆን በዚህ ንቅናቄ የትግል መቅደስ ውስጥ በክብር ታቅፋ የተቀመጠችው የወይዘሪት ነጻነት ፅላት ባልታሰበ ቅጽበት አፈትልካ ወደሕዝቡ መሀል የገባች እንደሆነ በወያኔና ጭፍሮቹ ላይ ሊደርስ የሚችለው አደጋ ከወዲሁ ቁልጭ ብሎ እየታየው ነው፤ ሌላ አይደለም፡፡ ለአቶ ግርማ ግልጽ ሆኜ ከሆነ ወያኔ ግንቦት ሰባትን አሳምሮ ይፈራዋል፡፡ ይህን ተጨባጭ የሚመስል ነገር በመናገሬ በግንቦት ሰባትነት ልፈረጅ አይገባም፡፡ ግርማን በወያኔነት መፈረጅ እንደማይገባን መከራከሬ እኔንም ነጻ ለማውጣት ነውና እኔንም ባለመፈረጅ እባካችሁን ተባበሩኝ፡፡
በዛሬው መጣጥፉ አቶ ግርማ ለዚሁ ንቅናቄ አንድ ግልጽ ደብዳቤ ጽፎ በዘሃበሻ ላይ አስነብቦናል፡፡ ብዙዎች የመንጫጫት ያህል ብዙ ነገር ጽፈዋል፡፡ ለወደፊቱ እንደዚህ መሆን የለበትም – “የአህያ ‹ጓዝ› በሆድ ይያዛል ነው”ና ለአንዳንድ ንግግሮችና ትችቶች ብዙ ክብደት መስጠት ቢያንስ ጊዜን ይሻማል፤ የትኩረት አቅጣጫንም ያዛባል፡፡ አንድ ሰው የመሰለውን ሲጽፍ በመጣበት መንገድ ተጉዞ በጽሑፍ ተገቢውን መልስ መስጠት እንጂ መሳደብና ሌላ ሌላ ታሪክ መቸክቸክ አስፈላጊም ተገቢም አይመስለኝም፡፡ ሥራ ፈት ወያኔዎች እንደዚያ ቢያደርጉ ሥራቸው ነውና ምንዳም ያገኙበታልና ምንም አይደል ሊባል ይችላል፡፡ በትግል ላይ ከሚገኙ ወገኖች ውስጥ በዚህ ዓይነት የአንድን ታዋቂ ጸሐፊ ስም ለማጉደፍ በመሞከር ሙያ ላይ የተሠማራ ሰው ካለ ግን ስህተት ነውና ለወደስተፊት ይታረም፡፡ እውነት እንደሆነች በብዕር ቱማታ ይቅርና በመትረየስና በታንክም ቢሆን ከላችበት ቦታ ንቅንቅ አትልም፡፡ ግንቦት ሰባት ከሻዕቢያ ሥር መወተፉ በርግጥም ሀገርን የሚጎዳ ነገር ካለውና ድርጅቱ ከዚህ ተግባሩ እንዲታቀብ ሃሳብ መሰንዘር የዜግነት ግዴታ እንጂ እንደባይተዋር ሊያስወቅስና ምን አገባህ ሊያስብል አይገባም፡፡ ቅስምን ለመስበር የሚደረገው ጥረት በብልህነትና በአስተዋይነት ቢቀየር መልካም ነው፡፡ ስለጋራ ሀገራችን መጨነቅ የሁላችንም ኃላፊነትና ግዴታም ነው፡፡
በበኩሌ ግንቦት ሰባት ከሻዕቢያ ጋር ብቻ ሳይሆን በዓለም አሉ ከሚባሉ አምባገነኖች ጋር ተባብሮና ዕርዳታም አግኝቶ ኢትዮጵያን ነጻ ቢያወጣ ደስተኛ ነኝ፡፡ ዝንጀሮዋ “ቀድሞ የመቀመጫየን” ነው ያለችው፡፡ ተደጋግሞ በብዙዎች እንደተነገረውም የአንድን ድርጅት የመታገያ መስመር የሚመርጥለት ራሱ ድርጅቱ እንጂ ሌላ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህን ስል ኤርትራ ለኢትዮጵያ ነጻነት የምትቆም ሀገር ስለመሆንዋ መጣጥፋዊ ዋስትና ዋስትና እየሰጠሁ እንዳልሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን ወያኔ በምንም መንገድ ከሻዕቢያ የተሻለ እንዳልሆነ በመሃላ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ፡፡ ትልቁ ዕንቆቅልሽ…
ትልቁ ዕንቆቅልሽ አቶ ግርማ ግንቦት ሰባትን ከኤርትራ አውጥቶ ወደሀገር በማስገባት ከነሸንጎና ከነአንድነት ጋር በመተባር ወያኔን በ“ሰላማዊ ትግል ድባቅ እንዲመታ” ያደረገው ፌዘኛ ጥሪ እጅግ አስገርሞኛል፡፡ አቶ ግርማ አንዳንድ ነገሮችን ለማሰብ ሲፈልግ እንቅልፍ ይይዘዋል፡፡ አንዳንድ ነገሮችን ለማሰብ ሲፈልግ ደግሞ ይነቃል፡፡ ግንቦት ሰባት ምርጫ አጥቶ ወይም ካሉት ምርጫዎች ውስጥ የመረጠውን መርጦ ወደ ትግል ሜዳ እንደገባ ነግሮናል፡፡ እሱ በዚያው ይቅናው ብለን ከመጸለይ ይልቅ ሳቢውን ግረፈው እንዲሉ ወደማይሠራ የትግል ሥልት በመጋበዝ ቃሊቲ እንዲወረወሩ ወይም ቀድሞ በተፈረደባቸው ፍርድ እንደነመንግሥቱ ንዋይ ተክለ ሃይማኖት አካባቢ እንዲንጠለጠሉ ለማድረግ የተሸረበ ሤራ ያለ ይመስለኛል፤ ለምን? ትግሉ ቢኮላሽ ማን ይጠቀማል? እነብርሃኑ እኛን ምን አምጡ አሉና አስቸገሩን? ለምንድነው አንድ መሆን ካተቻለ፣ መስማማት ካልተፈለገ ሁሉም በመሰለው መንገድ ታግሎ ሁላችን የምንፈልጋት ነጻነት እንድትገኝ ዕድል የማንሰጠው? ማደፍረስ የሚቀናን ለምንድነው?
eprdfትግሉን ለማወክ ካልሆነ ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ – ሰላምን በማያውቅ የወያኔ መንደር ውስጥ ሰላማዊ ትግል ፍለጋ እንዴት ኑና እጃችሁን ስጡ ተብሎ ይጻፋል? ችግሩ መጻፉ አይደለም – የተጻፈው ነገር ተግባራዊነት ግን አልተጤነበትም ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ ግርማ ዐይቹን ጨፍኖ የጻፈውን ነገር እንደገና እንደሚያጤን እገምታለሁ፡፡ በአሁኒቷ ቅጽበት ማን ነው ለኢትዮጵያ አደገኛ? ግንቦት ሰባት ወይንስ ወያኔ ወይንስ ሻዕቢያ? ልብ ይደረግልኝ – ወደ “ጥንት” ታሪክ አልገባሁም፡፡
አቶ ግርማ ካሣ፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? እውን ወያኔ ለሰላማዊ ትግል በሩን ከፍቷል? በዓለም ዙሪያ ያሉ ወገኖቻችን ስለሳዑዲዎች አረመኔነት ለመግለጽ ለወገናቸው ሲሉ በየሚኖሩባቸው ሀገራት ዋና ዋና ከተሞች ሲሰለፉ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ በሰማያዊ ፓርቲ ሰልፎኞች ላይ የተደረገውን ሰምተሃል ወይንስ ያኔ በሀገር ውስጥ አልነበርክም? ከዚህ የነሰ ትንሽ መብት የት አለ? ለዚህች ሚጢጢዬ መብት – በሌሎች ሀገራት የተፈቀደ – በኛዎቹ ናቡከደነፆሮች ግን በኃይል እርምጃ የተደፈጠጠ ሰልፍ ምን ያመለክታል? እርግጠኛ ነኝ ግርማ እዚህ ቦታ ስትደርስ በጻፍከው ነገር ልትፀፀት ትችላለህ፡፡ እነእስክንድር ነጋ ለምን ዘብጥያ ወረዱ? … ወያኔን በሰላማዊ ትግል ፈቃጅነት መፈረጅ ራሱ እንደኔ ከሆነ ወንጀል ነው – በኢትዮጵያውያን ደም መቀለድም ነው፡፡ ስዚህ አንተ ግንቦት ሰባትን እንደፈለግህ ጥላው ነገር ግን በነሱ ሰበብ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰላማዊ ትግል ሁሉም ነገር የተመቻቸ ነው በሚል ቃና የምታስተላልፍላቸውን የኑ ታረዱ ጥሪ በፍጹም አልተቀበልኩትም፤ እነሱን መጉዳት ከተፈለገ ሌላ መንገድ መፈለግ ይቀላል፤ ለወያ ግን አይስጣቸው፤ የወያኔን ቅጣትና የበቀል እርምጃ “ለጠላትም አይስጥ”፡፡ “የደላው ሙቅ ያኝካል” አሉ፡፡ ለኔ አደገኛ ሆኖ ያገኘሁት ግንቦቶች ለወደፊቱ ሊያስከትሉ ይችላሉ ተብሎ ከሚሰጋ አደጋ ይልቅ አሁን በመጣጥፍህ ውስጥ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ትግል መንግሥትን እንታገለው የሚለው የደናቁርት አስተሳሰብና የወያኔ ጭራቅነት ናቸው፡፡ ወያኔ ከጦጣና ዝንጅሮ የሰውነትና የአእምሮ የዕድገት ደረጃ ባልወጣበት ሁኔታ፣ ዘረኝነት ከአጥናፍ አጥናፍ ሀገሪቱን ሰቅዞ ይዞ መግቢያ መውጫ ባሳጣን ሁኔታ፣ የኑሮ ውድነቱ ገድሎ ሊጨርሰን ባሰፈሰፈበት ሁኔታ፣ የትግሬዎች የበላይነት ነግሦ ሁሉም ነገር በነሱ ቁጥጥር ሥር ሆኖ እኛ የበይ ተመልካች በሆንበት ሁኔታ፣ … ምን ዓይነት ጥሪ ነው ለግንቦት ሰባት የምታስተላልፍላቸው? አሁን እነዚህ ሰዎች ከወያኔ ይበልጥ ለኢትዮጵያና ሕዝቧ አደጋ ሆነው ነውን? ለምን አንዳንዴ፣ እንዲያው ሲያመቸን አንዳንዴ እንደጤናማ ኢትዮጵያዊ ሆነን አናስብም? እስኪ እነዚህ ሰዎች የት ይሂዱና ትግላቸውን ይጀምሩ? አይ፣ እያሰብን እንጻፍ፤ እንናገርም፡፡ ለኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ከሰይጣንም በባሰ ሁኔታ ታላቁ ጠላት ወያኔና እርሱ የዘረጋው የዘረኞች የቢዝነስ ኢምፓየር ነው፡፡ ከአፓርታይድ የሚበልጥ የጭራቆች ንጉሠ ነገሥት ወያኔን አራት ኪሎ አስቀምጦ ስለሻዕቢያ ማውራት፣ ታላቁን የመለስ ሙት መንፈስ ቤተ መንግሥት አስቀምጦ ስለግንቦት ሰባት “አደገኛነት” ማውራት የበቅሎዋን ተረት መተረት ነው፤ “በቅሎ አባትሽ ማን ነው?” መልስ፡- “እናቴ ፈረስ ነች!” አስፈላጊ ከሆነ ሌላ ጊዜ እመለሳለሁ፡፡


ሰርኬ እንደ ዊኒ –እስክንድር እንደ ማንዴላ –ደፍሬ ልናገረው። ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

የቀጥታው መንገድ ቅጣቱ ማዬሉ ።
ከሥርጉተ ሥላሴ 10.12.2013

sekeፎለቄዋ ደማሟ እና ሳቢዋ እማማ ዊኒ የአፓርታይድ ሴራ ከነፃነት በፊትም ሆነ በኋላም ግቡን ያሳካባት ድንቅ የነፃነት አርበኛ ሴት ናት። ዕውቅናዋን ግን በስውር ያለው አፓርታይድም ሆነ የዓለም ሚዲያ  እንደ ተጫነው ነው – ዛሬም። ድንቋ የነፃነት እናት ዊኒ ጥንካሬዋ ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ነው። የፍቅርት ዊኒ የአርበኝነት የተጋድሎ ታሪክ ብሄራዊ ብቻ አልነበረም። የዓለምን ህዝብ ጥንካሬና ብርታት በፍጹም እናታዊ ሰማያዊ መክሊት በልግስና የመገበ ነበር፤

ወርቋ ዊኒ ለፓርቲዋ ተልዕኮ መሳካት ዘወትር ጥራላች – ባትላላች፤ ዊኒ ለአካሏ ለተከበሩ የሰላም መሪ ለኔልሰን ማንዴላ የጽናት ማህጸን ሆና ጽናትን በልዩ ሁኔታ ሸልማላች፤ እማማ እያሉ በንጹህ ልባቸው እናትነትነቷን ላፃደቁ የደቡብ እፍሪካ ግፉዓን ህዝቦችም በፍ ሳትሰስት ፍቅሯን አጥብታለች- ዛሬም። ከማህጸኗ የፈለቁትን ልጇቿን በመከራዋ ዘመን ሁሉ እንደ አባትም እንደ እናትም ሆና በአንድ ክንዷ እንደ ወታደር ዘባኛም ሆና በታታሪነት አገልግላቸዋለች። ከጥቃትም ታድጋቸዋላች። በማናቸውም ዙሪያ ትንፋሿን ከትንፋሻቸው ጋር አጋባታ ጠረናቸውን አጣጥማ፤ ገረድና ሎሌ በመሆን በትጋት በፍቅር ተገዝታላቸዋለች። መንፈሳቸው ላይ ይፈታታናቸው የነበረውን ያን ጥቁር ጥላት የበታችንት ስሜት ታግላ አሸንፋለች። ዕንቋዋ ዊኒ የድል አንባ ናት። ከመከራ የፈለቀች የምትጥም ነፍስ ናት – የመንፈስም ቅዱስ ቋንቋ።

ክብርት ዊኒ ቤበተሰብ ኃላፊነቷ የጓዷውን ገመና ሁሉ ብቻዋን በጸጋ አስተናግዳለች። ሴቶች የማህበራዊ ኑሮ መስራቾች ናቸውና በዘርፉም መሪ ሁና አደረጃታለች። የማህበራዊ ኑሮ እውነተኛ እረኛም ሆናለች። በግፍ ይጨፈጨፉ፤ ወደ እስር ይጋዙ የነበሩ ወገኖቿን ከጎናቸው በመሆን ዕንባቸውን ተጋርታላች። አጽናንታቸዋላች። ትዳራቸው ለተፈታ፤ ለተበተነ እንቁዋ ዊኒ ቅርብም ነበረች – ሚስጢር! በእዬአንዳንዱ ቀንና ሰከንድ በፈተና በተከዘነው ህይወቷ ሁሉ የነፃነት ሰንደቅን ተሸክማ ተጋድላላች። ሁለቱ ከነትዳራቸው ቀጥለው ቢሆን … ትንግርትን ዓለም ያይ ነበር። በአዲስ ርዕዮት ዓለም ብዙኃን ይታዳም በነበረ … አዲስ ምዕራፍ ለዘመኑ በአናገረም  ነበር ….

የጥቁር አልማዝዋ ዊኒ ቀጥታ ናት። ቀጠታ – ቀጥታ ነው። በቀጥታው መንገድ ተጉዛላች። ይህ የቀጥታ መንገድ ያሰጋው አፓርታይድ የሴራ መረብ አዘጋጅቶ ብዙ ተፈታትኗታል። በግድያ ሙከራ እጇ አለበት ብሎ ጥላሸት ከመቀባት ባሻጋር የትዳር፤ የመንፈስ፤ የትንፋሽ፤ የራዕይ አጋሯን የመጀመሪያ የጥምር ንዑድ ፍቅር ቀምቷታል። ይህ አሳንጋላ እንቆቆ ነው። በእያንዳንዱ የዊኒ ህይወት ውስጥ የአፓርታይድ የስላላ ድርጅት የሸርና የተንኮል መርዝ አለበት – በረቂቅ።

ዓለም – ዓቀፉ የሴቶች ድርጅትም ዝምታ በመምርጡ የዊኒ የጥንካሬ፤ ሕይወት የዘራ ሙሉዑና እኩል ተሳትፎ ታፍኖ መቅረቱ፤ ተቆርቋሪ አጥቶ ነጥፎ መቅረቱ ለእኔ እሳት ነው ረመጥ። ይህም በመሆኑ ውቧ ዊኒ  ከዓለም ዓቀፉ የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ ውስጥ ምዕራፍ ከፋች ሆና ግን ተዘላ ዕውቅናዋ … ባክኖና ከስቶ ቀረ። ነገር ግን እናቴ ዊኒ እንኳንስ በደቡብ አፍሪካውያን የነፃነት ቤተሰቦች በእኛ ውስጥ ያለውን የፍቅር ፏፏቴና ማንም ሰው ሊወስደው ወይንም ሊቀማው ወይንም ሊፍቀው አይችልም። እኛ ምሳሌያችነን ዊኒን የማይነጥፍ ፍቅር ሸልመናታል። የክብርትነቷ የተጋድሎ ሞገድ ከሰላሙ መሪ፤ ከጽናቱ አውሯ፤ ከማሃሪው ከኔልሰን እረፍት በኋላ አቅጣጫው ወደ ዬት የሚለው ሁላችንም የምናዬው ይሆናል …. የታፈና፤ የታመቀ ነገር ባንቧ መተንፈሻ ካላተሰራላት በማናቸውም ጊዜና ሁኔታ ሊፈነዳ ይችላል። አቅጣጫውን ከሳተ ደግሞ አደጋው ከአደጋ ባላይ ነው – እሳተ ጎመራ … ኢትዮጵያዊነት የሚመሩ ሁሉ ልብ ሊሉት የሚገባ ቁምነገር ነው … ሁሉ ነገር የመተንፈሻ ጥግ አብዝቶ ይናፍቀዋልና ….

ከዚህ አንፃር በዊኒ እና በማንዴላ የተፈጸመው ሴራ በልዑል ቻርልስና በልዕልት ዲያናም ተፍጽሟል ብዬ እኔ አስባለሁ። የልዕልት ዲያና ዕውቅና መሬትን ማነቃነቅ ሲጀመር የልዕሉ የቻርልስ ልብ ከትዳር አጋሩ እንዲሸፍት ተደረገ። ለልዕልት ዲያናም ሌላ ድራማ ተዘጋጀ …. ክብሯን ዝቅ አድርጎ ለህልፈት የሚያበቃ የበቀል ፍቅራዊ መንገድ … ሁሉም ሆነ። ነገር ግን ዛሬም ነገም የልዕልት ዲያና ታሪክና ፍቅር ማንም ፈልቅቆ ሊሸጠው ሊለውጠው የማይችል በጽኑ አግናባት በደማችን ውስጥ የተገናባ ሆነ። ለዚህ ማካካሻ የእንግሊዙ ቤተመንግሥት ዛሬ በልዑል ዊሊያም ጋብቻ ላይ ያለው የቅነንት ዕይታ ያን … የጠቆረ ታሪክ እንዲያጥብ የታለመ ነው። በአጭር ጊዜ የከሰመውን የልዕልት ደያና ራዕይና የሰብዕዊነት …. ጉዞ መጫናገፍ …. የሚሰውር አዲስ ትዕይንት ነው …. ለእኔ። ልዕልት ዲያና ዕድሉን አግኝተው ቀጥለው ቢሆን የተተበተበውን ሴራና ሸር፤ በሌሎች ሀገሮች ጣልቃ በመግባት ማማስና ማተራመስ  …. መሰል ጎምዛዛ ገጠመኞች ተግ ይሉ በነበረ …..

የወያኔው ሄሮድስ መልስ ሴራ – ተንኮል – በቀል – ጥላቻ – የማግለል ፓሊሲ ጠብተው ያደጉት ከአፓርታይድ ምንጭ ነው። ልዩነቱ የአፓርታይዱ አመራር እንደ ማርክሲስቶቹ ሳይንሳዊ ትንተና በማህረሰብ እድገት ከፒታሊዚም ላይ ሲተገበር የሄሮድሱ መለስ ዘረኛነት ደግሞ ከቤተሰብ ቀጥሎ ካላው ጎሳ ላይ መተከዙ ነው፤ ወይንም በሌላ አገላላጽ በሰለጠናና ባልሰለጠነ፤ በአደገ ህሊናና ባላደገ መንፈስ የሚታዳደር ወይንም የሚመራ ከመሆኑ ላይ ነው እንጂ ….  ወያኔ ሃውዚን ሲያሰደበደብ ቅንጣትም ስለነዛ ንፁኃን ዜጎች አላሳበም – ፈጽሞ። የእሱ የቋሳ ተልዕኮ በኮሶ ተጥቅልሎ መሳካቱ ብቻ ነበር ያደናበረው። የደቡብ አፍሪካውያኑን የክብርት ዊኒ እጅ አለበት ተብሎ በሚጠረጠረው የብዙ ሰዎች ህልፈትም እኔ የማዬው ከዚህ አንጻር ነው። የዊኒና የኔልሰን ትዳር፤ የቻርልስና የዲያናንም ትዳር መፍረስንም የማዬው ከዚህ ዕይታ ነው። ጭራ ሳይሆን ሥር መፈለግ የመፍትሄ መዳረሻ ነውና። ልንገመግመው የሚገባ …. ከዚህ አንፃር ነው የሚል እድምታ ነው ያለኝ። በእውነቱ ቁጭ ብሎ ማሰብ ነገሮችን በትኖ በማጥናት ዘሩን መፈለግ የትውልዱ ታሪክ ጸሐፊዎች ወሳኝ ተግባር ይመስለኛል።

ስለዚህ ለተከበሩ የጽናት አርበኛው ድል፤ ክብር፤ ዓለምዓቀፋዊ ተወዳጅነት ዊኒ እንብርትና አንጎል ናት። ኔልሰን እስር ቤት በነበሩ ጊዜ የዊኒ ደብዳቤዎች ጨላማውን ተዳፈረው ሌትና ቀን ጽናትን ተግተው የሚያጠቡ ብርኃናት ነበሩ። ወደ ቀዝቃዛው ክፍል ተጉዘው ሳይታክቱ በታታሪነት ትእግስትን የሰነቁ ሙቀቶች ነበሩ። በዛች ጠበቃ ክፍል ዘምተው የማይደክሙ የተስፋ ሰፊ እልፍኞች ነበሩ። በራህብና በጥማት ኩርምት ላላው አንጀት ሙሉዑ ተበልቶ የማይልቅ የሰማይ መና ነበሩ፤ ተጥጥተው የማይነጥፉ የኤዶም ፏፋቴዎች ነበሩ። በእሾህ የታጠረው አካባቢ የነፃነት ጎህ የሚዘንብበት የማግሥት ራዕይ ርችት ነበረው። ማንም በሌለበት የጣሪያና ግድግድጋ ጋብቻ ኑሮ ብቸኝነትን ያለ ይግባኝ የረታ ዳኛነት ነበረው። የልጅ እቅፍ ስስት ሲመጠምጥ፤ የደህንነተቻውና የዕድገታቸው ብሥራት በእርግጠኝነት ያበስሩ ዕለታዊ ሰበር ዜናዎች ነበሩ ለኔልሰን። ዊኒ ለማንዴላ ሁሉንም ነበረች። በዛ ጠቀራማ ጉዘው ባለዬው የነፃነት ጥብቆ እስር ቤት ዊኒ ለማንዴላ የመንፈስ ሀገሩ ነበረች።

ጅሎች ብዬ ልጀምር። የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ሰው ናቸው። አንዳንድ ሰዎች ኔልሰንና የኛዋቹን አርበኞች አታመሳስሉ ይላሉ። ምን ያንሳቸዋል። „ በእጅ የያዙት ወርቅ“ እንዲሉት ካልሆነ በሰተቀር መስዋዕትነትን በጸጋ ተቀብሎ በማስተናገድ እረግድ እኩል ነው። በጠላት ወረዳ የተነሰረዘው ጥላቻ ጥቃት እኩል ነው – በቀሉም በቀል ነው። በፈተና መፈተሉም እኩል። የሞቋቋም ትክሻ ጽናቱም ጽናት ነው። ተጋድሎውም ዓለምን ያስደመመ ተጋድሎ ነው። መከራን ፈቅዶ የመቀበል አቅሙም መሳ ለመሳ ነው።

ዘረኛው ወያኔ „ሀ“ ብሎ የነፃ ፕሬሱን ሲያውጅ ለመበቀያ ነበር። ከተጠቂዎች በኽሩ የኛው ማንዴላ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነው። ሁሉ እያለው ሁሉም እዬተቻለው ግን ለነፃነት ራህቡ ሁሉንም የመከራ ዓይነት ፈቅዶና ወዶ ሰጠ። ሁልጊዜ ፎቶግራፎችን ሳያቸው ጸሐይ ናቸው ለእኔ ይሞቁኛል። የሚያስተላልፋቸው መልዕክቶች ሁሉ ነገን የሚያበሩ ዛሬን የሚያጽናኑ ናቸው። እስክንድር ፍቅር ነው። እስክንድር እስር ቤት ሆኖ ሳቂተኛ – ማህሪ ነው። በጮርቃው በእናቱ ማህጸን የቃሊቲ ታዳሚ የነበረው ታምሩ ናፍቆት እስክንድር ከበቀል የጸዳ አዕምሮ እንዲኖረው መልእክቱን ሁልጊዜ በአፅኽኖት ይልካል። አደራውን ለእኛዋ ዊኒ ለጋዜጠኛ ሰርካለም ሰጥቷል። እኛም ብንታደምበት ምንኛ ዕድለኞች በሆን ነበር። ሥጋውን ተውት፤ ለረቂቁ ዓለም … የጻድቃን ጉዞ በሆነ — በነበረ።

የጣይቱ ልዩ ዓርማ ሰርኪ እንደ ዊኒ በዛ ድቅድቅ ጨላማ አይዞህ ትላላች። በርታ ጠንክር ትላላች። ታውጃላች የኛ ጌጥ ሆናለች። መራራውን የመጨረሻ መለያዬት የባሰ ቢመጣ እንኳን ቆርጣላች። ጨክና ወስናላች። ፈቀቅ ሳትል ሁሉንም ተቀበል ብላ ቃሏን ለኪዳኗ፤ ብርታትን ከጽናት አጋባታ ልካላች። የሰርክዬ ዱካ ጽናት ለነፃነት ግብር መሆን አለበት ብላ አስተምራናለች። የሰርክዬ ብርታት ምንጩ ከትናቶቹ አርበኞቻችን ከእነ – ንግሥት ጣይቱ -  ከዊኒ ጋር ያበረ ነው።

eskinderጋዜጠኛ ሰርካላም ፋሲል የጫጉላ ጊዜዋን በእብሪተኛች የተነጠቀች፤ ቅብጥብ የሚያደርገውን የበኽር ልጅ የእርግዝና ወራቶቿን ከቤተሰብ ቁልምጥ ተለይታ በሳጥናኤላዊ መለስ አስተዳደር በግፍ የተቀማች፤ የአራስነት ወጓን ደግሞ ለአረመኔዎች ቋሳ ሰላባ የሆነ ነው። ከድንቅ በላይ የተግባር ጻድቅ ናት – ሰርኬ። ዊኒና ኔልሰን ሰርኬና እስክንድር ራዕያቸው አንድ ነው። ነፃነት በቃ …. ለዚህ ደግሞ ዋጋውን እኩል ከፍለዋል። አሁንም እዬከፈሉ ነው። ሰርኬ ለእኔ ሚስጥር ናት። ሰርኬ ለእኔ አብነቴ ናት። ሰርኬ  ለእኔ ትምህርት ቤቴ ናት። ሰርኬ ለእኔ የጽናቴ ድሪ ናት። ሰርኬ ለእኔ የነገ የተስፋ ሃዲዲ ናት … ሰርኬ ለሁላችን ተቋማችን ናት። የጽናቱ አርበኛ የእስክንድር የጽናት ውበት ጋዜጠኛ ሰርካለም ናት። ጋዜጠና ሰርኬ ኪዳንም ናት – የመንፈስ ውል። የአደራ የዓይን ማረፊያ – ብርቅ።

አዳራ! እላለሁ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ  የዓለም የሚዲያ ተቋማት የኔልሰን ክብር ከዊኒ እንደነጠለው ሳይሆን ከነፃነት በኋላም ሆነ በፊት ሰርኬንና እስክድርን እኩል በክብር ፍቅርን አጎልምሰን እንሸልማቸው። ዓይነታ ናቸውና። ዛሬም እስክንድርን ስናስታውስ ሰርኬን „ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ“ እንዲሉ መታደላችን እባካችሁ የሀገሬ ልጆች እናክበረው ትርጉምንም እንወቅበት። ትውልዱ ዓርማውም ማህተሙም ይህ እንዲሆን እሻለሁ። ኔልሰን ይህን ሁሉ ጸጋ የተጎናጸፉት፤ የተማሩት፤ ዝቀሹን ተመክሮ የተካኑበት ብቃትን ለዓለም የመሩበት፤ እንደ እናታቸው ጡት የጠቡት እኮ የክብሮቻችን የጄ/ ታደሰ ብሩ፤ የሻንበል ጉታ ዲንቃ፤  የኮ/ ፈቃዱ ወንድሙ ፤ የመቶ አለቃ ፈቃዱና የ50 አለቃ  ደበበ ተማሪ ከማሆን የተገኘ ሚስጢር ነው። ዛሬም፤ ነገም የኢትዮጵያዊነት ሚስጢር ገቢራዊ ማድረጉን ካለመታከት ተግተን ልንፈጽመው ይጋባል። ከዚህ ሚስጢር ጋር እዬተላላፍን እኮ ነው የምናጠፈውም … ለድልም የማንበቃው። እኛ መሪ ነን። መሪነታችን ግን እንግራው በተፈጥሮችን ሚስጢራዊ ዲስፕሊን …

በጋዜጠኛ እስክንድር የብቃት፤ የብርታት ጥናካሬ፤ የጽናትም አቅም ደም ውስጥ ቅሙሙ ከፈርጣችን ከጋዜጠኛ ሰርካለም ነው የሚቀዳው። ይህን ማማሳጠር፤ መተርጎም ለዓለምም ማስተማር አለብን። ይህ ትውልዳዊ ድርሻችን ነው … ይህን የነጻነት ድርሳን ፈልፍሉና ረቂቁን የጽናት ጎለጎታ ድረሱበት … /የቤት ሥራ/ ጽላትም እናድርገው።

http://www.ethiotube.net/video/28543/A-must-watch-The-deception-exposedEskendirs-wife-speak  እስኪ እዩት። አዳምጡትም …

http://www.zehabesha.com/2013/10/serkalem-fasil-send-a-voice-message-to-her-husband-eskinder-nega/

ከጥቁሯ አልማዝ ከዊኒ ይልቅ አሜሪካዊቷ የተከበሩ ሄነሪ ክሊንትን ዕድለኛ ናቸው እላለሁ። የቀድሞው ክቡር ፕሬዚዳንት ቪል ክሊንተን በጥንካሬያቸው ሁሉ አካላቸው ወ/ሮ ሄነሪ ክሊንትን ነበሩ። መደማመጣቸው፤ መከባባራቸው፤ መተሳሰባቸው ሁለቱም በአገኙት የከፍተኛ ሥልጣን አጋጣሚ  ዓለምን አስተምረውበታል። በአንድ ወቅት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሄነሪ ክሊንትን ባለቤታቸው በፆታዊ ግድፈት ተከሰው በነበረ ጊዜ ከአካላቸው ወገን ምንም ዓይነት ለግድፈቱ እውቅና በመስጠት ሆነም የአጋፋሪነት እርምጃ አለመወሰዱ የገረመው አንድ ጋዜጠኛ እንዲህ ሲል ክብርት ሄነሪ ክሊንትን ጠይቋቸው ነበር „ አለሰማሽም ስለ ፕሬዚዳን ክሊንተን የሚወራውን ሆነ ያዬሽውስ የለምን?“  ሲል … መልሳቸው እንዲህ ነበር“ እናቴ ስታሳደገኝ ሰው የሚለውን ከሰማሁ የምሰራው የሰዎችን እንደምሰራ፤ ካልሰማሁ ግን የራሴን ሥር ለመስራት እንደምችል አስተምራኛለችና፤ የሰማውትም ዬያዬሁትም የለም“ በማለት እጹብ የሆነውን የተግባር ሰውነት ነበር ያሳዩት። ይህ የበሰለና የሰለጠነ ግንዛቤ … እስከ መሪነት አሳጫቸው። …. ትዳራቸውንም ከፍርሰት ታደጉት … ታሪካቸውንም ሙሉዑ አደረጉት። ክቡር ኔልሰን ፈተናውን አሸንፈው ቢሆን … ደስታዬ ሐሴት በሆነ …

„ልብ ያለው ሸብ“ ይላል ጎንደሬ … የአሜሪካን ህዝብ መስጥሮ የሰነቀውን ተግባር ለፕሬዚዳንትት ተፎካካሪነት አበቃቸው። የተከበሩ ብልኋ ሄነሪ ክሊንትን ከ2008 አስከ 20012 የታላቋ አሜራካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በመሆን ዕውቅና ክብር ማግኘታቸው ብቻ ሳይሆን የሴቶችን የእኩልነት ብቃትና አቅምን በድርጊት ሰብከዋል። ዕድለኝነታቸው ከዚህ አንጻር ነው …. እውነት ለመናገር ተመሳሳይ ፍላጎት፤ ሙያ ዓላማና ራዕይ ያላቸው ጋብቻዎች የሎተሪያ ያህል ዕጣታቸው ጠባብ ነው … ከተሳካላቸው ግን ሀገርን ከምንም በላይ ሊጠቅም የሚችል ልዩ ሥጦታ ነው …. ። ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ሚሻዬል ኦባም ጥንካሪያቸው ነገን የሚያሰውብ ይመስለኛል። ልዕልት ካትሪንም መንገዱን ትከተላላች ብዬ አስባለሁ ….

እጅግ የምትናፍቁኝ የሀገሬ ልጆች … በዘለቄታ ሃብታችን ማድነቅ፤ ሃብታችን ማክበር፤ ሃብታችን ታሪካችን ማደረግ፤ ለሃብታችን እኛን መስጠት እግዚአብሄርን ከመፍራት ጋር አቡነ ዘሰማያታችን ወይንም ሰላዳችን ሊሆን ይገባል። ድንቆችን ማፍቅር፤ ምቀኝትን ገድለን ቅንነትን ካነገስን ታሪካችን በዘመኑ ማድመቅ ማስዋብ ይቻላል። አይከፈልበት። ዳጋት አያስወጣ ቁልቁላት አያሰውርድ። በእጅ ያለ እኮ ነው … ለድንቆቻችን ውስጣችን መሰጠት።

 

እርገት

እማማ … ዊኒ አንቺ እልኳት እንደ እናቴ ስለማያት … ዓለምዓቀፍ የሴቶች የእኩልነት፤ የአርነት መሪ ብትሆንልኝ ፈቃዴ ነው አቅም የለኝም እንጂ። ለሴቶች ታዳያለሽ ተብዬ እታማለሁ። እስከ አሻችሁ ድረስ እሙኝ ውቁኝ … ውስጤን በቀጣዩ  ጹሑፌ አሳያችኋለሁ። የሰማዕቷ ሺብሬ ደስአለኝ ወጣትነቷ አፈር መሆኑ ይቆጠቁጠኛል፤ የክብርት ዳኛ ብርቱካን ፍቅርና ችሎታ ይንፍቀኛል – የሀገሬን ያህል። ያንሰፈስፈኛል። የእስረኛዋ የአበራሽ ሰቆቃም ያርመጠምጠኛል። የወጣቷ እስረኛ የጋዜጠኛ ርዕዮት ናፍቆት ሰቀቀን ስጋትን ሰንቆ ይነስተኛል። ሻማችን ርዕዮት በጡት ህምም እዬተሰቃዬች ነው። በእስር ቤቱ እንኳን ይህም ተቀንቶባት በወንበዴ ትራፊ ሴቶች ግልምጫ  የዕለት ጉርሷ መሆኑ ያቃጥለኛል። የአብዛኞቹ ብቃታቸው የእህቶቼ ተዝቆ አያልቅም። የአብዛኞቹ ብልህነታቸው ተመርቶ አያልቅም። አብዛኞቹ ጥበባብ ናቸው …. መሆን ናቸው። ቆራጥ ናቸው – ሴቶች። የእማማ ዊኒ ቆራጣነት ነፃነትን የፈጠረ ቅምጥ ሀብት ነው። ጽናት መልኩን እምታውቁት ከሆነ ሴቶችን ይመስላል። የብርኃን ብሥራትን የገለጸቸው ቅድስት መግዳላዊት ነበረች። የዓለም የድህነት ድርሳንም ድንግል – ለተዋህዶ አማንያን …  አምላካችን ከዲያብሎስ ጋር ተደራድሮ ሃጢያት ከምድር እንዲደረቅ በድፍረት የጠየቀችም ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ናት። … ዋ!  እመለሰላሁ በዚህ ዙሪያ  ክብሮቼ በጥቂት ቀናት ውስጥ እሰከዛው ግን ለሰጣችሁኝ የማይጠገብ ትእግስት … ዝቅ ብዬ ኢትዮጵያዊ ጀርጋዳ ምስጋዬን እነሆ …. መልካም ጊዜ።

ሴቶች የመሆን ሸማ ሰሪዎች ናቸው!

ሰርኬ ለእስክንድር የመንፍስ ልዩ ሀገሩ ናት!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ናፍቆት።

ለምን ሕወሃት/ኢሕአዴግ ያሸንፋል ? –አማኑኤል ዘሰላም

$
0
0

አማኑኤል ዘሰላም
amanuelzeselam@gmail.com

tplfበምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት የነበረዉን ሁላችንም የምናስታወሰው ነዉ። ያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምጹን ለቅንጅት ቢሰጥም፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ የሕዝቡን ድምጽ ነጥቆ እስከአሁን ድረስ በኃይልና በጡንቻ እየገዛ ነዉ። በስልጣን ላይ ለመቆየት በቀዳሚነት አገዛዙ የወሰዳቸው አምስት  እርምጃዎች ነበሩ። እነርሱም የቅንጅት አመራሮችን ማስወገድ(እንዲታሰሩ፣ እንዲሰደዱ በማድረግ)፤ ቅንጅትን መከፋፈል፣ ሕዝቡን ተስፋ ማስቆረጥ፣ ሌላ ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳያንሰራራ ማፈን እና እኮኖሚዉን እንደመቆጣጠራቸዉ በጥቅም በጉያቸው የሚያስገቧቸዉን ማብዛት።

አገዛዙ እነዚህን የክፋት ስትራቴጂዎች ይዞ ሲንቀሳቀስ፣ በተቃዋሚ ወገን ያሉት ግን ፣ የአገዛዙን ተንኮል ለማምከን ፣ ተመጣጣኝ ሥራ ሰርተዋል ማለት አይቻልም።

«ተባበሩ ወይንም ተሰባበሩ» የሚባል አባባል አለ። ትብብር መልካምና ወሳኝ ነዉ። «መተባበር ያስፈልጋል»  ተብሎ ግን የማይሆንና የማይሰራ ትብብር ዉስጥ መግባት ግን ችግር አለዉ። ገዢውን  ፓርቲ በተለያዩ ምክንያቶች ስለሚቃወሙ ብቻ፣  ደርጅቶች አንድ ላይ መሰባሰብና መቀናጀት የለባቸውም። የቅንጅቱ ወይም ትብብሩ መስፈርት «ኢሕአዴግን መቃወም» ከሆነ ትልቅ ስህተት ነዉ የሚሰራዉ። ነገር ግን ትብብር/ቅንጅት የሚፈጥሩ ድርጅቶች፣ በፖለቲካ አቋሞቻቸውና ፕሮግራሞቻቸው  የተቀራረቡ፣ አብረዉ ሊሰሩ የሚችሉ መሆን አለባቸው።በፖለቲካ ፕሮግራሞቻቸው መሰረታዊ ልዩነቶች እያሉ፣  የሚደረግ ትብብር፣  በሂደት መፍረሱ አይቀርም።

ኢትዮጵያ ዉስጥ በርካታ ደርጅቶች አሉ። አብዛኞቹ አገር አቀፍ ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ አንድን ጎሳ ብቻ ያቀፉ ናቸው። በጎሳ ድርጅቶችና በአገር አቀፍ ደርጅቶች መካከል በጋራ ሊሰሩ የሚችሉ ስራዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህ ድርጅቶች ሊቀናጁ አይችሉም። ለምን መሰረታዊ የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነቶች አሏቸዉና። (የጎሳ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ደረጃ መደራጅት ጥቅሙ ገብቷቸው፣ የአቋም መሸጋሸግ እስካላደረጉ ድረስ)

ከጎስ  ድርጅቶች ዉጭ፣  በርካታ ተመሳሳይነት ያላቸው አገር አቀፍ ደርጅቶች እንዳሉ ይታወቃል። ለምሳሌ መኢአድ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ እና ኢዴፓ ፣ አራቱም ቅንጅት የነበሩ፣ ተመሳሳይ የፖለቲካ ፕሮግራም ያላቸው ድርጅቶች ናቸው። አራቱም አሁን ያለዉ በዘር ላይ የተመሰረተ ከፋፋይና ዘረኛ ፌዴራል አወቃቀር መቀየር አለበት ብለው ያምናሉ። አራቱም ለሁሉም ዜጎቿና ብሄረሰቦቿ እኩል የሆነች አንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትመሰረት ይፈልጋሉ። አራቱም ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት እንደሚገባ በማስረገጥ፣  የአልጀርሱን ስምምነት ይቃወማሉ። አራቱም አሁን ባለዉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችና የመሬት ጥያቄ ዙሪያም ተመሳሳይ አቋም አላቸው። በአጭሩ አራቱም ቀድሞ በሕዝብ ትልቅ ድጋፍ አግኝቶ የነበረዉን  የቅንጅት ማኒፌስቶን  ይቀበላሉ።

እንደዚያም ሆኖ ግን እነዚህ ድርጅቶች፣ አብረዉ እንደገና መቀናጀት እስከአሁን አልቻሉም። ይሄ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ዴሞክራሲን ለተጠማው ወገናችን በጣም አሳዛኝ ሲሆን፣ ለአገዛዙና ለአምባገነኖች ደግሞ በጣም ያስደሰተ ዜና። ይሄ በአስቸኳይ መቀየር ያለበት ይመስለኛል።

በአቶ ልደቱ አያሌው ይመራ የነበረው ኢዴፓ፣  ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ ብዙም አላውቅም። በምርጫ 2002 ኤዴፓዎች፣ በአንዳንድ ጉዳዮች ከኢሕአዴግ ጎን በመሰለፍ ፣ ከሌሎች ተቃዋሚዎች የተለዩ እንደሆኑ ለማሳየት ሞክረው ነበር። ነገር ግን ያ አካሄዳቸው ብዙ ዉጤት ያመጣላቸው አይመስለኝም። ይሄን በሚገባ እነርሱ እራሳቸው የተረዱ ይመስለኛል።

አንዳንዶቻችን ደግሞ መረጃ ሳንይዝ፣  በኢዴፓ አመራሮች ላይ ስንዘነዝራቸው የነበሩ በርካታ ክሶችም ጠቃሚ አልነበሩም። ይህ፣ ከኢሕአዴግ ጋር ደምሮ ፣ ኤዴፓዎችን የማጥቃት ዘመቻ፣  ኤዴፓ ወደ ኢሕአዴግ እንዲጠጋ በማድረጉ አንጻር አስተዋጾ ያደረገ ይመስለኛል። እኛ ነን ወደዚያ የገፋናቸው። ሕወሃት/ኢሕአዴጎች ብልጥ ናቸዉና ፣ ሆን ብለው ለ ኤዴፓ ነገሮችን በማመቻቸት፣ በደስታ አስተናገዷቸው። በዚህም መልክ ኤዴፓን ኒዉትራላይዝድ የማድረግ አላማቸው ከሞላ ጎደል ተሳካ።

እንግዲህ ኤዴፓዎችና እኛ ብዙ ተባብለናል። ብዙ ስህተቶች ሰርተናል። ነገር ግን ወቅቱ ትብብርን ይጠይቃል። «ያለፉትን ቁርሾዎች ወደ ጎን በመተዉ፣ በፖለቲካ ፕሮግራም ከሚመሳሰሏቸው ጋር ኤዴፓ አብሮ መስራት መጀመር ይገባዋል» እያልኩ ሌሎቻችን ደግሞ ኤዴፓን  ለመቀበል እንድንዘጋጅ እጠይቃለሁ። ለምን ሕወሃት/ኢሕአዴግ ያሸንፋል ?

ወደ ሰማያዊ ፓርቲ ስንመጣ ይሄን እላለሁ። የሰማያዊ ፓርቲ፣ አዲስ ፓርቲ ቢሆንም በአጭር ጊዜ ውስጥ የገነነ ፓርቲ ለመሆን ችሏል። በተለይም የአመራር አባላቱ ድፍረትና  ቆራጥነት  በዉጭ አገር ብዙ ደጋፊዎችን አፍርቶላቸዋል። ለዚህ በወጣቶች ለሚመራ ድርጅት፣ እኔም በግለሰብ ደረጃ ትልቅ አድናቆት አለኝ።

ነገር ግን  ሰማያዊዎች አንድ ማስተካከል ያላባቸው ጉዳይ አለ።  ከሌሎች ድርጅቶ ጋር የመስራት ፍላጎት ብዙም ያላቸው አይመስልም። በትብብርና በአንድነት ማመን ይኖርባቸዋል። ለጊዜው ትልቅ የሆኑ ቢመስላቸው፣  አይሳሳቱ፣  ለብቻቸው ብዙ ርቀዉ እንደማይሄዱ ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ። ይህ የ«ብቻህን ተጓዝ» አቋማቸዉን ትተው፣ ከሌሎች፣  በፖለቲካ ፕሮግራም ከሚመሳሰሏቸው ጋር አብሮ መስራት መጀመር ይጠበቅባቸዋል። በተለይም ደግሞ በዉጭ ካሉ ጽንፈኛ ፖለቲከኞች መጠበቅ አለባቸው። በአገር ቤት ካሉ ወንድሞቻቸው ጋር በበጋራ በመሆን ትግሉን ከአገር ቤት መምራት አለባቸው እንጂ ዉጭ ባሉ መመራት የለባቸዉም።

ወደ መኢአድና የአንድነት ፓርቲ ስመጣ ደግሞ፣ ተስፋ ሰጪ ምልክቶችን እያየው መሆኔን መግለጽ እወዳለሁ። ለዚህም አንድ ምሳሌ ልጥቀስ። አቶ አበባዉ መሃሪ ጌታነህ ይባላሉ። የአንጋፋዉ የመኢአድ ሊቀመንበር ናቸው። በቅርቡ ኤስ.ቢ.ሲ ከተባለ ራዲዮ ጣቢያ ጋር አጭር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር። «ከአንድነት ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ በንግግር ላይ መሆናችሁ ይነገራል። ይህ ምን ያህል እዉነት ነዉ። ከሆነስ ከዉህደቱ ምን ፋይዳ ይገኛል ይላሉ ?» ተብለው ሲጠየቁ፣ አቶ መሃሪ የሚከተለዉን ነበር የመለሱት።

«ሂደቱ እዉነት ነዉ። ተጀምሯል። የሁለቱ ፓርቲዎች ፍላጎት ያሳዩበት ሁኔታ ነዉ ያለው። በእዉነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሚያመች ሁኔታ ይሄ ድርድር ይጠናቀቃል። የኢትዮጵያን ሕዝብ የድል ባለቤት ወይንም የመብቱ ባለቤት ያደርጋል ብለን እናስባለን።  ይሄ ዉህደት የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ ነዉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ “ወይ ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ” የሚል ነዉ። ሕዝቡ የትብብርን ግፊት እያደረገ ነዉ። “አንድ ላይ ሆናችሁ ይሄን ክፉ መንግስት መገርሰስ አለባችሁ። አንድ ላይ ካልሆናችሁ ለዉጥ ማምጣት ያስቸግራል”  እያለ ሕዝቡ ግፊት እያደረገ ነዉ ያለዉ። ይሄንን የሕዝቡን ፍላጎት ምክንያት በማድረግ እየተደራደርን ነዉ» [1]

መኢአድ በአገሪቷ ክልሎች ሁሉ መረብ ያለዉ ፣ ከአንጋፋዉና ተወዳጁ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጊዜ ጀመሮ፣  ለኢትዮጵያ አንድነትና ለዜጎቿ መብት የታገለ አንጋፋ ድርጅት ነዉ። እልም ያለ የአገራችን ገጠሪቷ ክፍል ብትሄዱ በዚያ መኢአድ አለ።

የአንድነት ፓርቲ  በበኩሉ፣ በቅርቡ በደሴ፣ ጎንደር፣ መቀሌ፣ አርባ ምንጭ ፣ ባህር ዳር፣ ፍቼ፣ ባሌ ሮቢ፣ ጂንካ፣ አዳማ፣ ወላይታ ሶዳ ..በመሳሰሉ የአገሪቷ ክፍሎች፣ ባደረገዉ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴ በግልጽ እንዳሳየው፣ በጣም ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር ያለው፣ አገር ዉስጥ ሆነ በዉጭ አገር በስፋትና በብዛት ደጋፊዎችን ያፈራ፣ በሳል ደርጅት ነዉ።

የመኢአድና አንድነት መቀራረብ ወቅታዊ፣  ትግሉን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ፣ በማያሻማ መልኩ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚቀየር መልካም ዜና ነዉ። ይሄ፣  ሕዝቡ እነርሱ የሚሉትን ብቻ በፍርሃት አሜን ብሎ እንዲቀበልና አማራጭ እንዳይኖረዉ የሚፈልጉ ሕወሃት/ኢሕአዴጎችን የሚያስከፋ ነዉ። እንግዲህ የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ ከተፈለገ፣  ይህ አይነቱ፣ አገዛዙን ከመስደብና ከመርገም ያለፈ፣ ነገር ድርጅታዊ ጥንካሬን በሕዝቡ ዘንድ የሚያጎለብት፣ የሕዝቡን አመኔታና ድፍረት የሚያሳድግ፣  በሳል የፖለቲካ ሥራ መሰራት አለበት።

መኢአድ ከጥቂት ወራት በፊት አዲስ አመራር አባላትን መርጧል። የአንድነት ፓርቲም፣ በቅርቡ በሚያደርገዉ ጠቅላላ ጉባኤ፣  አዳዲስ ወጣቶችን በብዛት ያካተተ አመርሮችን ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከአዳዲስ አመራሮች ጋር፣ የመኢአድና የአንድነት መቀናጀት እዉን ይሆናል የሚል ትልቅ ተስፋ አለኝ። እድነ አንድ ኢትዮጵያዊም የመኢአድ እና የአንድነት አመራር አባላትን እያደረጉት ባለው ዉይይት «በርቱበት፣ ቀጥሉበት፤ ለሕዝቡም መልካም ዜና አሰሙት» እላለሁ።

እግዚአብሄር ያክብርልኝ !



[1] http://www.sbs.com.au/yourlanguage/amharic/highlight/page/id/303599/t/Interview-with-Abebaw-Mehari/

ማንዴላ፣ ኦባማና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ –ከሳዲቅ አህመድ (ያድምጡ)

የብሄር እኩልነት!

$
0
0

Abrham Destaየብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን’ ማክበር ጥሩ ነው። ምክንያቱም ባህሎቻችን ስናቀርብ እርስበርሳችን በደንብ እንተዋወቃለን፤ ከተዋወቅን እንከባበራለን። ከተከባበርን አንድነታችን ይጠነክራል።

ግን …
ቀን ጠብቆ፣ አብሮ መጨፈር፣ ስለ ብሄር ብሄረሰቦች መዘመር በራሱ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ማረጋገጫና ዋስትና ሊሆን አይችልም። የሁሉም ህዝቦች እኩልነት ለማረጋገጥ አብሮ ከመጨፈር ያለፈ ተግብራዊ ዉሳኔ ይሻል።

‘ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩል ናቸው’ ብለን ከተነሳን ሁሉም ብሄራቸው ግምት ዉስጥ ሳናስገባ (ምክንያቱም ሁሉም እኩል ናቸው ብለናል) በኢትዮጵያውነታቸው እንመዝናቸው። ለማንኛውም ጉዳይ (ለስራ፣ ለስልጣን …) በትምህርት ደረጃቸው ወይ ብቃታቸው ወይ ሌላ ለሁሉም በእኩል ሊያገለግል በሚችል መስፈርት እንመዝናቸው።

ሁላችን እኩል ከሆንን አንድ ሰው ለመመዘን ጉራጌነቱ፣ ኦሮሞነቱ፣ ትግራዋይነቱ፣ አማራነቱ፣ ዓፋርነቱ፣ ሶማሌነቱ፣ ጋምቤላነቱ … ማስታወስ አያስፈልገንም። ማንነቱ የራሱ ነው። በኢትዮጵያዊነቱ መመዘን መቻል በቂ ነው።

ሰው ለመመዘን ብሄሩ ግምት ዉስጥ ካስገባን ግን ሁሉም ብሄር፣ ብሄረሰቦች እኩል መሆናቸው አናምንም ማለት ነው። ሺ ግዜ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብናከብርም ሰው እንደሰው መመዘን ካልቻልን በቃ የብሄር፣ ብሄረሰቦች እኩልነት አላረጋገጥንም ማለት ነው።

ይሄ የመለየየት ችግር በብሄር፣ ብሄረሰቦች ብቻ አይደለም የሚስተዋለው፤ በአንድ ብሄር ዉስጥም አለ። ለምሳሌ በትግራይ ክልል አንድ ሰው ለስራ ወይ ለሌላ ሐላፊነት ሲፈለግ የመጣበት አከባቢ ግምት ዉስጥ ይገባል። ስራ ከመሰጠቱ በፊት ከዓድዋ፣ ተምቤን፣ ዓጋመ፣ እንደርታ፣ ራያ ወዘተ እየተባለ በትምህርት ደረጃውና ብቃቱ መሰረት ሳይሆን በትውልድ አከባቢው ነው የሚመደበው (የሚመዘነው)።

ሰው በመጣበት አከባቢ መሰረት ከተመዘነ እኩልነት የለም ማለት ነው። ስለዚህ እኩልነት የሚረጋገጠው በጭፈራ ሳይሆን በተግባር ነው። የሰው መብት በሕገመንግስት ስለተፃፈ ብቻ መብቱ ተከበረ፣ ተፈፀመ ማለት አይደለም። በተግባር መታየት አለበት።

አዎ! ሰው በብሄሩ ሳይሆን በተግባሩ መመዘን አለበት።

ማንዴላና የማንዴላ የማይመስሉ እዉነቶች

$
0
0

ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

ባለፈዉ ዓመት ደግሞ ሳይንቲስቶች አንድ ግንደ ቆርቁር መሰል የጥንት ወፍ ዝርያ አገኙ። «ኔልሰንማንዴላ» ብለዉ ሰየሙት።ማንዴላ ጀርመናዊዉ ፖለቲከኛ እንዳሉት ታሪክን የዘወሩ ታላቅ ሰዉ ነበሩ።በዚያ ዘመን ግን ሰዉ መሆናቸዉን እንኳ ያወቁት ካንዲት የጥቁሮች ነፃ ሐገር ሲደርሱ ነበር።1962።

0,,17279004_303,00

ማንዴላ እና ማንዴላን የማይመስሉ ማንዴላዎች።ሰዉዬዉ ሞቱ።ሐሙስ።ዕሁድ ይቀበራሉ።ሥራ ምግባራቸዉን እየጠቃቀስን፥ የማንዴላ የማይመስሉ ድርጊቶችን ባጭሩ እንቃኛለን።አብራችሁኝ ቆዩ።
ማንዴላ፥ አንዴ እንዲሕ ብለዉ ነበር አሉ።«እንዲያዉ ሁሌም የሚሞክርን ሐጢያተኛ እንደ ቅዱስ ካለሰብክ በስተቀር እኔ ቅዱስ አይደለሑም።» ይበሉ እንጂ በተለይ ከእስር ቤት ከተፈቱ በኋላ አብዛኛዉ ዓለም እንደ ከከሰዉ በላይ ሰዉ ይመለከታቸዉ ነበር።ሚሊዮኖች ሊያዩ፥ የተሳካላቸዉ ሊያነግሩ፥ ሊጨብጡ፥ ሊያቅፏቸዉ በሚመኙበት ወቅት ግን በቴሌቪዥን መስኮትም አልታይም አሉ።ግን በተቃራኒዉ እኔ እደዉልላችኋለሁ።

«የአደባባይ እንቅስቃሴዬ ከዛሬ ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።እንዳትደዉሉሉኝ። እኔ እደዉልላችኋለሁ።»

የመጨረሻቸዉ መጀመሪያ ነበር።ባንድ ወቅት ግን «ትምሕርት» አሉ «ዓለምን የምትለዉጥበት መሳሪያ ነዉ።» የሌላዉን አናዉቅም ወይም አያገባንም።እሳቸዉ ግን ያሉትን ከማለታቸዉ ከብዙ ዘመን በፊት ተማሩ።በሕዋላም ዓለምን በርግጥ ለወጡ።ዓለምን የለወጡበትን ትምሕርት በ1925 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ኤ ከማለታቸዉ በፊት ግን ወላጆቻቸዉ እንደ አፍሪቃዊ ባሕል-ወግ ያወጡላቸዉ ሥም ለአዉሮጳዉያን ቅኝ ገዢዎች እንዲመች፥ በአዉሮጳዉያን ቅኝ ገዢዎች ሲለወጥ መቀበል ግድ ነበረ ባቸዉ።

መምሕርት ምዲንጋነ፥ ሆሊሻሻ የሚለዉን የዚያን ሕፃን አፍሪቃዊ ሥም «ኔልሰን» በሚለዉ አዉሮጳዊ ሥም የለወጡት እንደ ቅኝ ገዢዎቹ መርሕ፥ ፈሊጥ የቅኝ ገዢዎቹን ባሕል፣ ቋንቋ፣ ሐይማኖት በቅኝ ተገዢ አፍሪቃዉያን ላይ ለመጫን፥ ለአጠራርም እንዲመቻቸዉ አስበዉ እንጂ አፍሪቃዊዉ ሥም በአፍሪቃዊዉ ሕፃን ሥነ-ልቡና ላይ ተፅኖ እንዳያሳድር አስበዉ አይደለም።

ብቻ ያ ሕፃን አፍሪቃዊ ስሙን ጥሎ፣ ነጭ ቅኝ ገዢዎች የለወጡለትን ሥም ተቀብሎ ተማረ፣ ጎበዘ፣ አደገም።ትምሕርቱን አጋምሶ፣ ቀሪ እድሜዉን የኖረበትን ፖለቲካ ማነፍነፍ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ግን አላማ፣ ምግባሩ ሁሉ ወላጆቹ እንደሰጡት ስም ሆነ።ሆሊሻሻ።የዛፍ ቅርንጫፍ ገርሳሽ፣ወይም አብጤ እንደ ማለት ነዉ-በአገሬዉ ቋንቋ።ስሙን ነጭ ቅኝ ገዢዎች በሰጡት ለዉጦ፣ የነጭ ዘረኞችን እኩይ ዛፍ ለመገንደስ ቅርንጫፎቹን ይዘነጥል፥ ጭካኙን ሥርዓታቸዉን ለመጣል ያብጥ ገባ።

ከእንግዲሕ አንቱ ናቸዉ።ዓላማቸዉ በ1960 እንዳሉት በርግጥ ግልፅ ነዉ።«አንድ ሰዉ አንድ ድምፅ።»«አፍሪቃዉያን የሚጠይቁት አንድ ሰዉ አንድ ድምፅ በሚለዉ መርሕ መሠረት መብታቸዉ እንዲከበር ነዉ።የፖለቲካ ነፃነት።»

ይሕ ቀላል፥ ሰብአዊ ዲሞክራሲያዊ፥ ግን የነጭ ዘረኞችን አገዛዝ ከፍፃሜዉ የሚያደርስ ዓላማ ጥያቄቸዉ አስወነጀላቸዉ።።እድሜ ልክ አስበየነባቸዉ።ተጋዙም።ግን አልተበገሩም።

ታገሉ፥ ተወነጀሉ፥ ታሰሩ።ከቻርልስ ሮበርትስ ብላኪ ስዋርት እስከ ፒተር ቪሌም ቦታ፥ ደቡብ አፍሪቃን ለገዙት የነጭ ዘረኛ መሪዎችና ለየመንግሥቶቻቸዉ ማንዴላ እና የማንዴላ የፖለቲካ ፓርቲ የደቡብ አፍሪቃ አፍሪቃዉያን ብሔራዊ ምክር ቤት (ኤ.ኤ.ሲ) ሲያንስ ሰላምን አባጭ፥ ሲበዛ አሸባሪ ነበሩ።በ1989 የደቡብ አፍሪቃን የፕሬዝዳትነት ሥልጣን የያዙት ፍሬድሪክ ቪለን ደ ክላርክ ከእሳቸዉ በፊት እንተፈራረቁት ስድስት ብጤዎቻቸዉ ሁሉ የነጭ ዘረኞቹ መንግሥት መሪ ነበሩ።

ማንዴላ ግን ለዴክላርክ ከእስር መለቀቅ የሚገባቸዉ ነፃ ሰዉ፣ኤ ኤን ሲም መታገድ የሌለበት ሰላማዊ ፓርቲ ሆኑ።ዴክላክ የአባት፣ አያቶቻቸዉን፣ አስተሳሰብ ለዉጠዉ፣ የቀዳሚዎቻቸዉን ዉሳኔ ሽረዉ፥ የማንዴላን ፓርቲ ሕጋዊነት አፀደቁ።ማንዴላን ለቀቁ።

«መንግሥት ሚስተር ማንዴላን ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመፍታት ወስኗል።»
1990።ለቄስ ዴዝሞንድ ቱት፥ ማንዴላ «ፕሬዝዳት» ለመባል በድምፅ እስኪመረጡ መጠበቅ አያስፈልግም። ለቱቱና እንደ ቱቱ ሁሉ የማንዴላን መርሕ ዓላማ ለሚጋሩት ሚሊዮኖች የማንዴላ መፈታት ራሱ ታላቅ ድል ነበርም።

«አዲሱን ፕሬዝዳታችንን ከሳጥን (ከእስር ቤት) በመዉጣታቸዉ እንድትቀበሏቸዉ እጠይቃለሁ።ኔልሰን ማንዴላን።»

ድል አደረጉ። ነፃ ወጡ።ሰዉዬዉ ግን አስፈላጊዉ ነገር ሌላ ነዉ-አሉ።

«አስፈላጊዉ ነገር የአንድ ግለሰብ ወይም የአንድ ድርጅት ድል አይደለም።የደቡብ አፍሪቃ ሕዝብ ድል እንጂ።»

እና ነፃዉ ማንዴላ፥ ደቡብ አፍሪቃዉያንን ነፃ ለማዉጣት ከዴክላርክ ጋር ተደራዳሪያቸዉ ሆኑ።፣ ከምርጫ በሕዋላ ፕሬዝዳቱ ማንዴላ፥ ከእስር ነፃ የለቀቋቸዉ የፕሬዝዳት ዴክላርክ አለቃ ሆኑ። ኋላ ደግሞ ዴክላክ በቀደም እንዳሉት ከማንዴላ ጋር በመስራታቸዉ «መኩሪያ፥ መከበሪያቸዉ።» ሆኑ።

የታላቅዋ ብሪታንያ ትላልቅ ጠቅላይ ሚንስትሮች በጣሙን የወግ አጥባቂዉ ፓርቲ ጠንካራ መሪዎች ስም ሲጠራ ዊንስተን ቸርችር ብሎ ማርጋሬት ታቻርን ማስከተል ግድ ነዉ።ታቸር በደጋፊዎቻቸዉ ዘንድ «ብረቷ እመቤት» በሚል ቅፅል በሚንቆለጳጰሱበት ዘመን ወሕኒ ቤት ይማቅቁ የነበሩትን ማንዴላን «የአሸባሪዎች መሪ» አሏቸዉ።ኤ ኤን ሲ ደግሞ «የለየለየለት አሸባሪ ድርጅት።» 1987 ነበር-ዘመኑ።

ኔልሰን ማንዴላ የዓላማቸዉ ፅናት፣ የብልጠት፣ ብስለታቸዉ ጥልቀት፣ የድል-እድላቸዉ ትልቅነት በአንዳዶች ዘንድ ከሰዉ በላይ ሰዉ አይነት ስሜት ማሳደራቸዉን ሲቃወሙ «በድሎቼ ብዛት አትመዝኑኝ። ብለዉ ነበር። «ወድቄ በተነሳሁበት ብዛት እንጂ።»

የሰማቸዉ እንጂ የተቀበላቸዉ መኖሩ አጠራጣሪ ነዉ።የማንዴላ ገድል-ድል በዓለም በናኘበት ዘመን የነታቸርን ፓርቲ መርተዉ እንደነታቸር የታላቂቱን ሐገር ትልቅ ሥልጣን የያዙት ዴቪድ ካሜሩን በማንዴላ ምግባር፣ ሥም ዝና ተማርከዉ የሥልጣን መርሕ አዉራሾቻቸዉን የነታቸርን እምነት ብሒል ተቃረኑ።ማንዴላን አከበሩ።በቀደም ደግሞ ቃላት ሊገልፀዉ በሚችለዉ አገላለፅ አወደሷቸዉ።

«ዛሬ ከዓለማችን ደማቅ ብርሐኖች አንዱ ጠፋ።ኔልሰን ማንዴላ የዘመናችን ጀግና ብቻ አልነበሩም። የሁሉም ዘመን ጀግና ጭምር እንጂ።የነፃዋ ደቡብ አፍሪቃ የመጀመሪያ ፕሬዝዳት፥ለነፃነት እና ለፍትሕ ከሚገባዉ በላይ የተሰቃዩ፥ በታሰሩበት ዘመን ባሳዩት ፅናትና ድፍረት የሚሊዮኖችን ቀልብ የሳቡ ሰዉ ነበሩ።እሳቸዉን ባገኛችሁ ቁጥር የሚያድርባችሁ ስሜት ለሌሎች ያላቸዉን ልዩ ፍቅር፥ ደግነትና ይቅር ባይነታቸዉን ነዉ።»

«የሁሉም ዘመን ጀግና።» ከሁሉም ዘመን ባንዱ ዘመን ግን ለለንደን-ዋሽግተን መሪዎች አሸባሪ ነበሩ።ማንዴላና ኤ.ኤን.ሲን በአሸባሪነት ለመወንጀል ማርጋሬት ታቸርና ባለሥልጣኖቻቸዉ የመጀመሪያ፥ የመጨረሻዎቹም አልነበሩም።የፕሪቶሪያ የጥቂት ነጭ ዘረኛ ሥርዓት ገዢዎች ቀደሙ።ያን ዘረኛ ሥርዓት የሚደግፉት የዋሽግተን መሪዎች ተከተሉ።ፕሬዝዳንቱ ዝነኛዉ የሪብሊካኖቹ ፓርቲ ፖለቲከኛ ሮናልድ ሬጋን ነበሩ።

የሬጋን መስተዳድር በ1980ዎቹ ማንዴላን እና ኤ.ኤ.ንሲን በአሸባሪነት ሲወነጅል ጆርጅ ሐዋርድ ደብሊዉ ቡሽ ምክትል ፕሬዝዳንት ነበሩ።ቡሽ የፕሬዝዳንቱን ሥልጣን በያዙበት ዓመት ማንዴላ ከዕስር ሲፈቱ እንደ ምክትል ፕሬዝዳት የደገፉ፣ ያፀደቁ፣ ያስፈፀሙትን ደንብ ሽረዉ ማንዴላን እንደ ጀግና መሪ ዋይትሐዉስ ጋበዟቸዉ።1990።«የፅናት እና፣ የድፍረት አብነት» አሏቸዉም።

በቀደም ማንዴላ ሲሞቱ ደግሞ «ፕሬዝዳንት በነበርኩበት ወቅት ማንዴላ ያለ ጥፋታቸዉ ለሃያ-ስድስት ዓመታት ያሰሯቸዉን ሰዎች ይቅር ሲሉ፥ ያላቸዉን ልዩ ችሎታና መሐሪነት በአድናቆት አይቻለሁ» አሉ።ጆርጅ ሐዋርድ ቡሽ።

ማንዴላ ነብይ አይደሉም። እራሳቸዉ እንዳሉት ቅዱስ አይደሉም-ይሆናልም።ብዙዎች እንደሚመኙ፥ እንደሚያስቡላቸዉ ከሰዉ በላይ ሰዉ አይደሉምም።የጀርመኗ መራሒተ-መንግሥት የአንጌላ ሜርክል የአፍሪቃ ጉዳይ ልዩ መልዕክተኛ ግንተር ኖከ እንዳሉት የማንዴላ ምግባር፥ ፅናት፥ ብልሐት አንድ ሰዉ ብቻዉን ሊያከናዉነዉ ከሚገባዉ በላይ ነዉ።

«እንደሚመስለኝ ታሪካቸዉን በትክክል የሚያዉቅ፥ ማንዴላ ለደቡብ አፍሪቃ እና ለመላዉ አፍሪቃ ያደረጉትና ሚናቸዉን የሚረዳ አንድ ሰዉ ብቻዉን ያደረገዉ ነዉ ብሎ ለመገመት ይከብዳል። እሳቸዉ እንደ አንድ ሰዉ በታሪክ ላይ ታላቅ አወንታዊ ተፅኖ አሳርፈዋል።አፓርታይድን ማስወገድ፥ ሃያ-ሰባት ዓመት ሲታሰሩ ያሳዩት ፅናት፥ ከዚያ በሕዋላ ደግሞ ሐገሪቱን በሚመሩበት ዘመን ሕዝቡ በእኩልነት፥ በሰላም እንዲኖር ማድረጋቸዉ በአንድ ሰዉ አቅም የማይታሰብ ነዉ።»

ማንዴላ የተሸለሙትን በትክክል የቆጠረዉ የለም።እንደሚገመተዉ ግን ከስፖርተኞች ቲሸርት እስከ ኖቤል ድረስ ሁለት መቶ ሐምሳ ሽልማቶች አግኝተዋል። ከዩኒቨርስቲ እስከ አደባባይ፥ ከመንደር እስከ መንገድ በብዙ ሐገር ብዙ ሺሕ አካባቢ በስማቸዉ ተሰይመዋል።በ1973 የሊድስ-ብሪታንያ ዩኒቨርስቲ ሳይንቲስቶች አንድ የኑክሌር ቅንጣት ያገኛሉ።ስሟን «ማንዴላ-ቅንጣት» አሏት።

ባለፈዉ ዓመት ደግሞ ሳይንቲስቶች አንድ ግንደ ቆርቁር መሰል የጥንት ወፍ ዝርያ አገኙ። «ኔልሰንማንዴላ» ብለዉ ሰየሙት።ማንዴላ እስከ ዛሬና ከዛሬም በሕዋላ ጀርመናዊዉ ፖለቲከኛ እንዳሉት ታሪክን የዘወሩ ታላቅ ሰዉ ነበሩ።ናቸዉም።በዚያ ዘመን ግን ሰዉ መሆናቸዉን እንኳ ያወቁት ጥቁር እንደ እንሳስ ከሚረገጥበት ሐገራቸዉ ወጥተዉ ካንዲት የጥቁሮች ነፃ ሐገር ሲደርሱ ነበር።1962። በ1990 ከሰዉም ሰዉ ሆነዉ ያቺን ሐገር ዳግም ሲጎበኙ ይሕንን መሰከሩ።

«ሰዉ እንደነበርኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅሁት እዚሕ ነበር።»

ያቺ ሐገር ማን ትሆን? ይገምቱ።

«ማንዴላን ያሰለጠነዉ ማነዉ? አድሐሪዉ ንጉስ ሐይለ ስላሴ፥ አብዮታዊዉን ማንዴላን አሠልጥነዋል።»

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ናቸዉ።አሁንስ ማንዴላ ሰዉ መሆናቸዉን ያወቁበትን ያወቁባትን ሐገር እርስዎ አወቋት።ካለወቁ እንደገና ይገምቱ።እኔ ለዛሬ ይብቃኝ።ሥለ ማሕደረ ዜና ያላችሁን አስተያየት፥ ማሕደረ ዜና ቢቃኘዉ ጥሩ ነዉ የምትሉትን ሐሳብ እንደ ተለመደዉ በደብዳቤ፥ በፌስ ቡክ፥ በስልክ፥ በኤስ ኤም ኤስ ላኩልን።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

የተከበሩ አፍሪካዊ ኔልሰን ማንዴላ ስንብት! ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

ኔልሰን ሮሺስላሽላ ማንዴላ ለነጻነት የሚያደርጉትን ረዥሙን ጉዞ እ.ኤ.አ በ2013 መገባደጃ ወር ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ደመደሙ፡፡

Nelson Mandela

ኔልሰን ማንዴላ 1918-2013

ፀሐይ የደቡብ አፍሪካን ሕዝብ ከአፓርታይድ የጭቆና አገዛዝ ነጻ ባወጡት ኔልሰን ማንዴላ ላይ የመጨረሻ ማህለቋን ጣለች፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ፈለግ አቸዉን ትተውልን አልፈዋል፡፡ በጥላቻ በተዘፈቀው ዓለም፣ በማያቋርጥ ሁኔታ በፍርሃት ተሸብቦ በሚገኘው ህዝብ፣ በአምባገነኖች በሃይል ተይዞ በሚሰቃየው ብዙሀን ህዝብ እና ስሜት አልባ ተደርጎ በተያዘው ህዘብ ላይ የፀሐይን ማህለቅ ለመጣል የኔልሰን ማንዴላን ፈለግ መከተል አለብን፡፡ በምንም ዓይነት መልኩ አንፈራም፣ የኔልሰን ማንዴላ መንፈስ ከአጠገባችን ናትና!

ኔልሰን ማንዴላን በፍጹም አግኝቻቸው አላውቅም፣ ባገኛቸው እንዴት ደስ ባለኝ! ለማግኘት የምፈልገው ደግሞ በዓለም ላይ እጅግ ከተከበሩት ሰው ጋር ተገናኝቸ ነበር በማለት ለስሜቴ ክብር ለመስጠት አይደለም፣ ነገር ግን ለአፍሪካውያን ክብርን፣ ኩራትን እና ሞገስን ላጎናጸፉት እኒያን ጀግና ኔልሰን ማንዴላን በዚህ አጋጣሚ አመሰግናለሁ የምትለዋን ቃል በትሕትና  ለማቅረብ እንጅ፡፡

ኔልሰን ማንዴላ ድልድይ ቀያሽ ነበሩ፡፡ ዘርን፣ ጎሳን እና የህብረተሰብ መደብን የሚያገናኙ ድልድዮችን ገንብተዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እሳት አጥፊ ነበሩ፡፡ በዘር እና በጎሳ ጥላቻ ተቀጣጥሎ የነበረውን ቤት እሳት በማጥፋት በደቡብ አፍሪካውያን ዘንድ እውነት እና ዕርቅ እንዲሰፍን አድርገዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ መንገድ ቀያሽ ነበሩ፡፡ በረዥሙ ጉዞ ወደ ነጻነት የሚያደርሱ በስም “ደግነት“ እና  “ዕርቅ“ የሚባሉ ሁለት መንገዶችን በመገንባት የተናገሩትን በተግባር አሳይተዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ የህንጻ ንድፍ ነዳፊ/architect ነበሩ፡፡ በአፓርታይድ አመድ ላይ በብዙሃን ዘር ዴሞክራሲ የተዋበውን ማማ ገንብተዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ የልዩ ተሰጥኦ ባለቤት ነበሩ፡፡ ጥቁር እና ነጭ እርግቦችን በአንድ ጊዜ በመልቀቅ በነጻነታቸው ተንፈላስሰው እንዲበሩ አድርገዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ለዘላለም የሚኖር የለውጥ ሐዋርያ ነበሩ፡፡ ጥላቻን በፍቅር፣ ፍርሃትን በወኔ፣ ጥርጣሬን በእምነት፣ ታጋሽየለሽነትን በሩህሩህነት፣ ቁጣን በመግባባት፣ ጥላቻን በስምምነት፣ እና ቅሌትን በክብር የሚለውጡ ነበሩ፡፡

ኔልሰን ማንዴላ በዘመናዊው የህብረተሰብ ታሪክ ሂደት ውስጥ እንከን ባለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ እንከንየለሽ በመሆን እንከን ያላቸው ሰው ነበሩ፡፡ ሙሉ በሙሉ በዘር፣ በጎሳ እና በመደብ በተከፋፈሉ ወገኖቻቸው ላይ አንከንየለሽ ማህበርን ለማምጣት ጥረት አድርገዋል፡፡ ነጭ ደቡብ አፍሪካውያንን በልቦቻቸው ውስጥ ዘልቀው ከገቡት ከአፓርታይድ መጥፎ ገጽታ እና ከአስቀያሚ ዘረኝነት አድነዋቸዋል፡፡ በጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ልቦች እና ነፍሶች ውስጥ ይንከባለሉ የነበሩትን የበቀል ጥላቻዎች  ወደ ፍቅር እና ወንድማዊነት ስሜት ቀይረዋቸዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ በእራሳቸው ልብ ውስጥ የፍቅር፣ የስምምነት እና የዕርቅ ጓሮን አልምተዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እጅግ በጣም እንከን ለበዛባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ምክራዊ መልዕክት እንዲህ በማለት አስተላልፈዋል፣ “ሰው ከጠላቱ ጋር ሰላም ለማውረድ ከጠላቱ ጋር አብሮ መስራት አለበት፣ እና ያ ጠላት የነበረው ወዳጅ ይሆናል“፡፡ ሌሎቻችን ግን ጠላትን በመግደል ሰላም እናመጣለን ብለን እናምናለን!

ማንዴላ መጥፎ ነገር ለማድረግ ጥሩ ጊዜ የለም በማለት ዓለምን አስተምረዋል፣ ሆኖም ግን “የሚመጣው ጊዜ ሁሉ ጥሩ ነገር ለማድረግ መሆኑን ማመን አለብን“፡፡  ለደቡብ አፍሪካውያን እና ለመላው አፍሪካውያን እንዲህ በማለት አስተምረዋል፣ “ለቆንጆዋ ደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ለመላዋ አፍሪካ ህልሞች ካሉ እነዚህ ህልሞች ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ የሚያስችሉ መንገዶችም አሉ“፡፡ ከእነዚህ መንገዶች ሁለቱ “ደግነት” እና “ይቅርታ አድራጊነት” በመባል ሊሰየሙ ችለዋል፡፡ እነዚህን የማንዴላን ቃላት ለዘላለም ስናስታውሳቸው እንኖራለን፡፡ የሮበርት ፍሮስትን አባባል በመዋስ፣

እኛ …ይህንን በጥልቅ ተንፍሰን እንናገራለን፣
የትም በጊዜዎች እና በጊዜዎች ቢሆንም፣
ሁለት መንገዶች ሁለት መንታ መንገዶች በደን ጫካ ዉስጥ ነበሩ
ማንዴላ ጥቂትሰዎች የተጉአዙበትን መንገድ ወሰዱ፣
እና ሁሉንም ልዩነት ያመጣው ይኸ ነው፡፡

በደቡብ አፍሪካ ሁሉንም የመልካም ስራ ልዩነት ያመጡት ደግነት እና ይቅርታ አድራጊነት ናቸው፡፡

ሃያ ሰባት እና ከዚያም በላይ በትንሽ እስር ቤት አድሚያቸውን ያሳለፉ ሰው ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ትክክለኛ ትርጉም እንዲህ በማለት አስተምረውናል፣ “ነጻ መሆን እግረሙቅን ከእጅ ወይም ከእግር ማስወገድ አይደለም፣ ነገር ግን ሌሎችን በማክበር እና ነጻነታቸውን በማራመድ የመኖር መንገድ ነው“ ፕሬዚዳንት ክሊንተን “በተሻለው ቀን ሁሉ ሁላችንም ኔልሰን ማንዴላን መሆን አለብን“ ሲሉ እውነትም ልክ ናቸው፡፡ ነገር ግን ዛሬ መጥፎው ቀናችን ነው፣ ምክንያቱም ኔልሰን ሮሺስላሽላ ማንዴላ አብረውን የሉምና! ዛሬ ማንዴላን ለዘላለም ተነጥቀናል!

ኔልሰን ማንዴላን በፍጹም አላገኘኋቸውም፣ ነገር ግን ብዙ ንግግሮችን ከእርሳቸው ጋ አግኝቻለሁ፡፡ በእርግጥ ሁሉም ምዕናባዊ ነበሩ፡፡ ማንዴላ ግድየላቸውም፣ እንዲህ ብለዋል፣ “በእውኑ ዓለም በእርግጠኝነት ከማየው ይልቅ ራዕይዬ የበለጠ በመጓዝ ምዕናባዊ ኃይሌ ስሜትን/አዕምሮን የሚፈታተን ሀሳብን ይፈጥራል“፡፡ ነገር ግን የኔልሰን ማንዴላን ራዕይ በአዕምሯችን ዓይን ከተመለከትነው የሀሰት ምዕናባዊ ሀሳብ አይደለም፡፡ ከኮሎኒያሊዝም፣ ከኢምፔሪያሊዝም እና ከአፓራታይድ አመድ ነጻ የወጣችውን ጀግና፣ በእራስ የምትተማመን አዲሲቷን የፍቅር አፍሪካ ራዕያቸውን እናያለን፡፡ በኔልሰን ማንዴላ ራዕይ የምትመራዋን አዲሲቷን አፍሪካ ለመገንባት ምዕናባዊ ሀሳባችንን አሁኑኑ መጠቀም አለብን፡፡

አንዳንድ ሰዎች ትልቅ ሆነው ይወለዳሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ የትልቅነት እምነትን ይላበሳሉ እየተባለ ይነገራል፡፡ ምንልባትም አንዳንዶቹ ታላቅነትን በአጋጣሚ ይጎናጸፋሉ፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ታላቅ ነበሩ ምክንያቱም ይሞክሩ ነበር፣ ይሞክሩ ነበር እና ይሞክሩ ነበር፡፡ ማንዴላ እንዲህ በማለት አስተባብለዋል፣ “እኔ ነብይ አይደለሁም፣ ነብይን ሁልጊዜ እንደሚሞክር ሃጢያተኛ ካልቆጠራችሁት በስተቀር“፡፡ ሁላችንም ሃጢያተኞች ሁልጊዜ እስከሞከርን እና እጃችንን እስካልሰጠን ድረስ የሚሞክር ሃጢያተኛ ነብዮች ብንባል ኔልሰን ማንዴላ ሞተውም ቢሆን ህያው ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡

ለኔልሰን ማንዴላ ከፍተኛ የሆነ ሃዘን እና አድናቆት የሚደረግላቸው ናቸው፡፡ በከፍተኛ የስልጣን እርካብ ላይ ያሉ በዓለም ታላላቅ ከተሞች የሚገኙ መሪዎች ስለ ኔልሰን ማንዴላ የነጻነት ታጋይነት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ያወሳሉ፡፡ የደቡብ አፍሪካ መሪዎች ስለኔልሰን ማንዴላ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ አመራር ሰጭነት እና የማያቋርጠውን እና ኢሰባዊ የነበረውን የአፓርታይድ ገዥ አካል በሰላማዊ እና በትጥቅ ትግል ለመጣል የተጫወቱትን ሚና በማድነቅ ይናገሩላቸዋል፡፡ ተራው የደቡብ አፍሪካ ህዝብ ኔልሰን ማንዴላን በኩራት የሀገራቸው አባት እንደሆኑ አድርገው ይናገራሉ፡፡ ስለኔልሰን ማንዴላ የኖቤል ተሸላሚነት፣ ስለዓለማቀፋዊ የሰብአዊ መብት እና ስልሰው ልጅ ሰብዕና ተከራካሪነት፣ ስለማህበራዊ ፍትህ እና ሰላም ለማስፈን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስላደረጉት ያልተቋረጠ ትግል የዓለም ህዝብ አድናቆቱን ይገልጻል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የማንዴላ ተችዎች ጭቃ ጅራፍ ይዘው ይላሉ፡፡ ለዕርቅና ለሰላም ያላቸው የማይታጠፍ አቋም ለደቡብ አፍሪካ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሃይል ሚዛን የሚያስፈልገውን አብዮት እንዳይመጣ ይከላከላሉ በማለት ይተቿቸዋል፡፡ ማንዴላ ለአፓርታይድ ጨቋኖች ብዙ ትኩረት በመስጠት ከእነርሱ ግን በመልሱ የወሰዱት ነገር አናሳ ነው በማለት ይታቻሉ፡፡ ከአፓርታይድ አለቆች ጋር በእርቀሰላሙ ጉዳይ ላይ ጥረት በማድረግ የመለሳለስ እና ሃይለኛ ሆነው ያለመውጣት ሁኔታ እንዳለባቸው ይተቻሉ፡፡ ተቺዎቻቸው በመቀጠልም አፓርታይድ አሁንም ቢሆን በኢኮኖሚው በኩል ሃያልነቱን እንደያዘ እና ሙስና በአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ የፖለቲካ ህይወት ውሰጥ እየተስፋፋ የመጣ ነቀርሳ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የማንዴላን ውድቀት በተጨባጭ ሁኔታ ለመተቸት አልቻሉም፣ ነገር ግን እነርሱ በምዕናባቸው ሆኖ የሚታያቸውን በማቅረብ ይተቻሉ፡፡ እንዲህም ይላሉ፣ አፓርታይድ ከሞተ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ በደቡብ አፍሪካ በከተሞች እና በገጠሮች የሚኖረው ህብረተሰብ ኑሮ ልዩነቱ በጣም ጠባብ ነው፡፡ ማንዴላ ስለዕርቅ ጉዳይ በትጋት የሰሩት ብዙም ለውጥ አላምጣም ይላሉ፣ እንዲያውም ደቡብ አፍሪካ ቀደም ሲል እንደነበረው በዘር ተከፋፍላ ትገኛለች ይላሉ፡፡ ሌሎቹ ተቺዎች ደግሞ ማንዴላ ስህተት ሰርተዋል፣ የገቧቸውን ቃልኪዳኖች አላከበሩም ይሏቸዋል፡፡ በከተሞች የሚገኙት ያጡት እና የነጡት በዕየለቱ የዕለት ዳቦ እየለመኑ የሚተዳደሩት ስለማንዴላ መልካም ነገር አይናገሩም፣ ምክንያቱም ማንዴላ አዲስ በፈጠሯት ደቡብ አፍሪካ እራሳቸውን እንደተቆለፈባቸው አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ በገጠሩ የሚኖሩት እና በመገለል ብዛት እየተሰቃዩ ያሉት ህዝቦች ህይወታቸው ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ለውጥ ያላመጣ መሆኑን ይከስሳሉ፡፡

የማንዴላን “የሃጢያት ነብይነት” የተጋነነ ትችት አንድ ነገር ልነግራቸው እፈልጋሉ፣ “እራሳችሁን እረገብ አድርጉ! በማንዴላ ላይ ከባድ ትችት ከመሰንዘራችሁ በፊት 27 ዓመታት ሙሉ በእግር ብረት ታስረው የቆዩትበን የጫማ ጉዞ በመከተል እስቲ አንድ ማይል እንኳ ለመጓዝ ሞክሩ፡፡ በከተማ እና በገጠር ለነጻነታችሁ ስትታገሉ ለቆያችሁት ልጠይቃችሁ የምፈልገው ነገር ማንዴላን ልዩ ኃይል እንዳለው መልዓክ አድርጋችሁ አትቁጠሩ ነገር ግን ማንዴላ እንደማኝኛችሁም ሁሉ ሰው ናቸው፡፡ ማንዴላ ነጻነትን ማጣት ምን ማለት እንደሆነ ብቻ ሳይሆን ክብርን እና ማንኛውንም ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በሚገባ የሚያውቁ ሰው ናቸው፡፡ ለማናቸውም ባዶ ተስፋዎች እና ተስፋቢስነቶች እንዲሁም ተፈጻሚነትን ላላገኙ ቃልኪዳኖች ኔልሰን ማንዴላን ይቅርታ እንዲያደርጉላቸው እጠይቃለሁ፡፡ ሰዎች ማንዴላን እንደ መላዕክ መቁጥር የለባቸውም፣ ነገር ግን ለሰው ልጅ ጥሩ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ለማድረግ የሚሞክሩ ሆኖም ግን ከፍተኛ ጥረትን ቢያደርጉም ሁሉም ነገር ያልተሳካላቸው ሃጢያተኛ ነብይ ነበሩ፡፡

ማንዴላ ተራ ሰው የነበሩ መሆናቸውን እናገራለሁ፣ ተራ ሰው አስገራሚ ከፍታ ላይ የወጡ፡፡ ማንዴላ የህግ ሰው የነበሩ መሆናቸውን እናገራለሁ፣ የሰብአዊ መብት የህግ ሊቅ፡፡ ማንዴላ ያልተከለሱ እና እውነተኛ አብዮታዊ የነበሩ መሆናቸውን እናገራለሁ፣ ደቡብ አፍሪካውያንን እና አፍሪካውያንን በሙሉ ነጻ ማውጣታቸው ብቻ ሳይሆን በጭቆና ቀንበር ስር ወድቆ የሚማቅቀውን የሰው ልጅ ዘር ሁሉ ነጻነት በማውጣታቸው ጭምር እንጅ፡፡ ማንዴላ ታላቁ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የነበሩ ለመሆናቸው እናገራለሁ፣ ለኤች አይቪ በሽታ ሰለባ ለሀኑት፣ ለህጻናት ሰብአዊ መብት ጥበቃ፣ ጥራት ላለው ትምህርት መስፋፋት እና ለገጠር ልማት ስኬታማነት ግንባራቸውን ሳያጥፉ ይታገሉ ነበርና፡፡

የህግ ባለሙያ ለመሆን መረጥኩ ምክንያቱም ማንዴላ ለእኔ ተምሳሌት/ሞዴል አንዱ ነበሩና፡፡ እ.ኤ.አ በኤፕሪል 1964 የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንዴላ በሪቮኒያ የህግ ሂደት ያሰሙትን ንግግር ከሰማሁ ጀምሬ ንግግራቸው አእ ምሮዬ ዉስጥ ተቀርፅዋል፡፡ እንደ ማርቲን ሉተር ኪንግ “ደብዳቤ ከቢርሚንግሀም እስር ቤት“ ሁሉ የማንዴላ ንግግር በአዕምሮየ ተሰንቅሮ እያቃጨለ እንዲህ በማለት ያሳስበኝ ነበር፣ “በህይወት ዘመኔ ሁሉ ለዚህ ለአፍሪካ ህዝብ ትግል ነጻነት እራሴን መስዕዋት አደርጋለሁ፡፡ የነጮችን የበላይነት ለማስወገድ እታገላለሁ፣ እንዲሁም የጥቁሮችን የበላይነት ለማስወገድ እታገላለሁ፣ ሁሉም ህዝቦች በፍቅር እና በእኩልነት፣ ዴሞክሪያሴያዊ እና ነጻ ህዝቦች ሆነው በጋራ የሚኖሩባትን ዓለም እመኛለሁ፣ ለመኖር ቃልኪዳኔ እና እውን ሆኖ ማየት የምፈልገው ፍልስፍና ይኸ ነው፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ይህ ፍልስፍና እውን እንዲሆን ህይወቴን ለመስጠት ያለማመንታት የተዘጋጀሁበት ጉዳይ ትልቅ ጉዳይ ነው“፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ይህንን ሲሉ በትክክል ምን ማለታቸው እንደሆነ ለመረዳት አስርት ዓመታትን ወስዶብኛል፡፡

ማንዴላ በሪቭኦኒያ የሕግ ሂደት ጥፋተኛ ተብለው የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸዋል፡፡ ማንዴላ በቁጥር 46664 የአፓርታይድ እስረኛ ተደርገዋል፡፡ የ27 ዓመታት ቁጥር 46664 እስረኛው ማንዴላ የዕለት ከዕለት ውርደት፣ ኢሰብአዊነት፣ ከባድ እና ጭካኔ የተሞላበት የጉልበት ስራ እንዲሰሩ በማስገደድ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል፣ ከቤተሰቦቻቸው እና ከጓደኞቻቸው እንዲለያዩ ተደርጓል፡፡ የልጃቸውን የቀብር ስነስርዓት እንኳ ለመገኘት  አልተፈቀደላቸውም፣ የባለ 46664 ቁጥሩ እስረኛ በአፓርታይድ ጌቶች በሁሉም እይታ እና ተግባር እንዲሞቱ የተወሰነ ነበር፡፡ እስረኛ ቁጥር 46664 ግን አልሞቱም፣ በዚያች እግዚአብሄር በረገማት ደሴት እንዳይታዩ ሆነው ተወረወሩ፡፡ የኔልሰን ማንዴላ የ27 ዓመታት የግዞት እስራት ማንዴላን የሮብን ደሴት ተመላኪ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡ በጊዜ ሂደት በግለሰብ ደረጃ የማይታወቁት ቁጥር 46664 እስረኛ ተስፋ ለሌላቸው ህዝቦች የተስፋ፣ መጠጊያ እና ኃይል ለሌላቸው ለደቡብ አፍሪካ እና ለሌሎች ዓለም ህዝቦች ደግሞ የነጻነት ቀንዲል ለመሆን በቅተዋል፡፡

ቁጥር 46664 እስረኛ በአብዛኛው የ27 ዓመታት የእስር ሂደት በሚያቃጥለው ፀሐያማ ሀሩር የኖራ ድንጋይ ቁፋሮ እንዲቆፍሩ ይገደዱ ነበር፣ ማታ በእስር ቤታቸው ተቀምጠው ሰለወደፊቱ ዕቅዳቸው እና የአሰራር ስልታቸው ንድፍ ያወጡ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በእራሳቸው፣ በቤተሰቦቻቸው እና በሌሎች ወገኖቻቸው ዘንድ ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ ስቃይ እና መከራ ሲያደርሱባቸው በነበሩት ጠላቶቻቸው ላይ በቀል እና ቅጣት ለመውሰድ አያስቡም ነበር፡፡ ቁጥር 46664 እስረኛ የአፓርታይድ ጨቋኞቻቸው መጥፎ አካሄዳቸውን እና ሰይጣናዊ ድርጊታቸውን እንዲተው ስትራቴጂ ይነድፉ ነበር፡፡ ቁጥር 46664 ህዝቦቻቸውን ከባስቱንታንስ የአፓርታይድ ደሴት ነጻ ለማውጣት ሌሊት ተጋድመው የወረቀት ላይ ንድፋቸውን በመስራት አርቺቴክት መሆን ጀመሩ፡፡ በደቡብ አፍሪካውያን የፖለቲካ ሰውነት ላይ ተንሰራፍቶ የቆየውን የዘረኝነት ቁስል ለማዳን እና ለመጠገን እዕምሯቸውን ክፍት በማድረግ ጥረት ማድረግ ጀመሩ፡፡ ቁጥር 46664 እስረኛ ከህዝቦች ነቢያትን እና ሃጢያተኞችን ለማውጣት ሌሊቱን በብቸኝነት በያዟት በጠባቧ እስር ቤታቸው ማስፈጸሚያ ዘዴዎችን ማውጠንጠን ጀመሩ፡፡

እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 1 1990 እስረኛ ቁጥር 46664 ከሮበን ደሴት እስር ቤት ኔልሰን ማንዴላ ሲወጡ አየን፡፡ በክብር እና ተስፋን በሰነቀ አቀራረብ በጣም ፈገግ የሚሉ ሰው ተመለከትን፡፡ ለሶስት አስርት ተከታታይ ዓመታት ያህል በእስር ቤት ውስጥ የቆየ ሰው ከእራሱ ጋር በሰላም ለመኖር እና እንዲህ በክብር ለመቆየት እንዴት ይችላል? ወዲያውኑም ግልጽ ሆነ፣ የእስረኛ ቁጥር 46664ን እዚያው እስር ቤቱ ውስጥ በመራራው እና በተሰባበረው የእስር ቤት ጓደኝነት የሲኦል በር በሮበን ደሴት ላይ ተውት፡፡ እንዲህም ብለዋል፣ “የእስር ቤቷን በር አልፌ ወደ እስር ቤቱ አጥር ግቢ በር ስራመድ ወደ ነጻነት እየሄድኩ መሆኑን ተረዳሁ፡፡ ጥላቻየን እና ሰቆቃውን እዚያው እስር ቤት ትቸው ካልወጣሁ አሁንም እዚያው እስር ቤት እንዳለሁ አውቃለሁ“፡፡ ማንዴላ እስረኛ አልነበሩም!  እስር ቤቱ አፓርታይድ እራሱ ብቻ ነበር፣ እስረኞቹም የእስር ቤቱ ኃላፊዎች እና የአፓርታይድ ጌቶች ነበሩ፡፡ ኔልሰን ማንዴላ በአፓርታይድ የግንብ አጥር ተከልለው በእውን የሚገኙትን ጥላቻ፣ ፍርሀት እና በቀል በማስወገድ ነጻነትን ለማምጣት ሮቤን ደሴትን ለቀው ወጡ፡፡ ማንዴላ ዊኒ ማንዴላን ከጎናቸው በማድረግ በፊታቸው ታላቅ ፈገግታ እና ፍቅርን እንዲሁም ዕርቅ እና ልባዊ እውነትን  በማሳየት ከሮቤን ደሴት እስር ቤት ወጡ፡፡ “ኃጢያተኛውን ነብይን ተመለከትን! ሲራመዱ ሲናገሩ!  በዚያን ዕለት በአይኖቸ አልቅሻለሁ፡፡ ሌላ ያላለቀሰ ማን ነው?

ማንዴላ ሀሳባዊ አልነበሩም፣ ነገሮችን ሁሉ በአንክሮ የሚመለከቱ ጭምር እንጅ፡፡ የዕርቅን እና የዕውነትን መንገድ መረጡ፣ ምክንያቱም እነዚህ ወደ ፍትህ እና ሰላም ይመራሉና፡፡ ጥላቻ እና በቀል ወደ ሲኦል እንደሚወስዱ ማንዴላ ያውቃሉና፡፡ “ሰው የመሆናችን ተፈጥሯዊ ባህሪ አንዳችን ካአንዳችን እንድንተሳሰር ያደርገናል፣ በማዘን እና በጓደኝነት አይደለም፣ ነገር ግን ሰው እንደመሆናችን መጠን አሁን የሚያሰቃዩንን ነገሮች ለወደፊት ተስፋ ባለው ነገር መለወጥ የሚያስችል ችሎታም ስላለን ነው“፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ ሲያደርጉት እንደነበረው ሁሉ ኔልሰን ማንዴላም በተመሳሳይ መልኩ ስልፍቅር… በተለይም ስለሰው ልጅ ያልተገደበ ፍቅር “አፋቸውን ከፈት” አድርገው በማስተማር ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ ከአፓርታይድ ጨቋኞች ጋር ዕርቅ ማድረግ የማይቻል ነው ሚሉትን ወገኖች ማንዴላ እንዲህ በማለት አስተምረዋል፣ “ተፈጽሞ አስከሚታይ ድረስ አንድ ነገር የሚሆን አይመስለንም“፣ እንዲህ ሲሉም መክረዋቸዋል፣ “በዚህች ዓለም ላይ ቅጣትን ከመፈጸም ይልቅ ምህረትን በማድረግ ብዙ ነገሮችን ማሳካት ትችላለህ“፡፡ ማንዴላ ትክክል ናቸው፡፡

ማንዴላ “በጎነት እና ይቅርታ አድራጊነት” በሚባሉ ሁለት አውራ ጎዳናዎች ረዥሙን የነጻነት ጉዞ ተጉዘዋል፡፡ ረዥም ጉዞ ነበር ምክንያቱም፣ ብዙ ተለዋጭ መንገዶችን መጓዝ ስለነበረባቸው፡፡ ሰፊውን የጓደኝነት ጎዳና እና ትልቁን የመቻቻል መንገድ መጓዝ ነበረባቸው፡፡ ትንሿን የፍርሀት እና ያለመግባባት መንገድ መጓዝ ነበረባቸው፡፡ በረዥሙ የጉዞ መንገድ ድፍረት፣ ታጋሽነት፣ ፍቅር፣ ጽናት እና ሩህሩህነት በማሳየት ብዙ ቆይታ ማድረግ ነበረባቸው፡፡

ማንዴላ በእስር ቤታቸው ክልል ተወስነው በጊዜ ብዛት ለመለካት በማይቻል መልኩ ታማኝነትን አዳብረዋል፡፡ “ሰዎች በውጭ በሚያከናውኑት መጠን እራሳቸውን ይለካሉ፣ ነገር ግን እስር ቤት ሰውን በውስጥ ጉዳዩች ማለትም ታማኝነት፣ ቅንነት፣ ግልጽነት፣ ሰብአዊነት፣ ለጋሽነት እና የማይለዋወጥ ባህሪ ላይ እንዲያተኩር ያደርገዋል“፡፡ ማንዴላ ወደ እስር ቤት ሲገቡም ሆነ ሲወጡ ቋሚ ጓደኞች ነበሯቸው፡፡ ሮናልድ ሬጋን እና ማጂ ታቸር የአፓርታይድን መንግስት መርዳት ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ማዕቀብም እንዲጣልበት አድርገዋል፡፡ በማንዴላ እና በኤኤንሲ ላይ “የአክራሪነት ባህሪ ዝርዝር ውስጥ“ በማስገባት እ.ኤ.አ እስከ 2008 ድረስ በዘለቀው ሁኔታ ማዕቀብ መጣል አልቸገራቸውም ነበር፡፡ እነዚህ የጊዜው ጥሩ ጓደኞች እና ተመሳሳዮቻቸው ማንዴላ ከፊደል ካስትሮ እና ከሙአማር ጋዳፊ ጋር ጓደኝነት መመስረታቸውን ለመተቸት ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ ማንዴላ በፍጹም መንገዳቸውን የማይቀያይሩ እና ከአመኑበት ነገር ላይ በቀላሉ የሚያፈገፍጉ አልነበሩም፡፡ ማንዴላ እንዲህም ይሉ ነበር፣ “ጓደኛ ማለት የደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በጭንቅ ጊዜም የሚገኝ ነው“፡፡ ወዲያው እንዳዩ ይጣሩ ነበር፡፡ በጊዜ ሂደት አሜሪካ “በዓለም ላይ በቃላት ሊገለጽ በማይችል መልኩ ትፈጽም በነበረው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ“ ላይ ጠንከር ያለ ትችት ያቀርቡ ነበር፡፡ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ወደ ኢራቅ ጦር ባዘመቱ ጊዜ ማንዴላ በዝምታ አልተመለከቱም ነበር፣ እንዲህ አሉ እንጅ፣”ኢራቅን ለነዳጅ ዘይቷ ሲል“ የወረረ እንዲሁም “በትክክል ማሰብ የተሳነው እና አርቆ ማየት የማይችል ፕሬዚዳንት“ በማለት በትችት ወርፈዋቸዋል፡፡

ማንዴላ የአስታራቂነት ጌታ እና የሰይጣን ነብይነት ከመሆናቸው በፊት አማጺ ነበሩ፣ ነገር ግን አማጺነታቸው በጸረ ዘር መድልኦነት ላይ ነበር፡፡ “አሸባሪ“ ነበሩ ነገር ግን የአፓርታይድን ስርዓት በመቃወም ላይ ብቻ፡፡ ለደቡብ አፍሪካውያን በሙሉ የነጻነት ታጋይ ነበሩ፡፡ ለህግ የበላይነት መከበር ቀናኢ ነበሩ፡፡ አሜሪካ ከህግ አግባብ ውጭ በኦሳማ ቢን ላደን ላይ የፈጸመችውን ግድያ ተችተዋል፡፡ ማንዴላ “የኮሙኒስት” ሽምቅ ተዋጊ እና የቀዝቃዛው ጦርነት አብዮታዊ ስለነበሩ አገራቸው የልዕለ ኃያላኑ የጦርነት መፎካከሪያ ሆና ነበር፡፡ ማንዴላ ለሰራተኛው መደብ መብት ተከራካሪ እና በዓላማቸው የጸኑ ታጋይ ነበሩ፡፡ ለዚህም እ.ኤ.አ በ1990 በዴትሮይት የሚገኙትን የአውቶ ሰራተኞች እንዲህ በማለት ነግረዋቸዋል፣ “እህቶች እና ወንድሞች፣ ጓደኞች እና የትግል አጋሮች፣ አሁን ከእናንተ ጋር ንግግር የሚያደርገው ሰው እንግዳ አይደለም፡፡ አሁን ነግግር እያደረገ ያለው ሰው የዩኤደብልዩ/UAW አባል ነው፡፡ እኔ ስጋችሁ እና ደማችሁ ነኝ፡፡“ በሮቤን ደሴት የኖራ ድንጋይ ቁፋሮ ተገደው ሲሰሩባቸው የነበሩትን ዓመታትን  አልረሱም፡፡ ማንዴላ ቡጢያቸውን የሚጠቀሙ ቦክሰኛ ብቻ አልነበሩም፣ ግን በብሩህ አዕምሯቸው በመመራት ጥብብ በተመላበት ዘዴ በመዋጋት ትጥቅ የሚያስፈቱ ጀግና ነበሩ፡፡  ማንዴላ በጣም ተጫዋች ሰው ነበሩ: በራሳቸዉም ላይ ይሰቁ ነበር፡፡ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸውን በቢሯቸው ካጠናቀቁ በኋላ የነጮች የንግድ ማህበረሰብ ስብሰባ ላይ በመገኘት እንዲህ ሲሉ ነግረዋቸዋል፣ “እኔ በአሁኑ ጊዜ ደኃ ጡረተኛ ነኝ፡፡ ስራ አጥ ነኝ፡፡ ልትቀጥሩኝ ትችላላችሁን?“

ማንዴላ እስከፈለጉበት ጊዜ በስልጣን መንበራቸው ላይ መቆየት ይችሉ ነበር፡፡ እንደሌላው የአፍሪካ አምባገነን ገዥ ሁሉ በስልጣን ላይ ተጣብቀው መቆየት ይችሉ ነበር፡፡ ከአራት ዓመታት በኋላ ስልጣናቸውን ማስረከብ ነው የመረጡት፡፡ በፍላጎታቸው ስልጣን በሚለቁበት ጊዜ ለደቡብ አፍሪካውያን እና ለአፍሪካውያን በሙሉ ሊተመን የማይችል ቅርስ ነው የሰጡት፣ የፖለቲካ ስልጣን የውልደት መብት እርስት አለመሆኑን ነገር ግን በህዝቦች ፍላጎት የሚሰጥ እና ሲያስፈልግም የሚቀማ ኃላፊነት መሆኑን በተግባር አሳይተዋል፡፡ በዚያ ድርጊት መሰረት ማንዴላ የህግ የበላይነትን በህገመንግስቱ እንዲካተት እና የደቡብ አፍሪካ ሉዓላዊነት እንዲጠበቅ በማድረግ ለሁሉም አፍሪካውያን አርአያ ለመሆን በቅተዋል፡፡

ማንዴላ ስልጣንን የህዝቦች ፈቃደኝነት፣ ፍላጎት ማስፈጸሚያ፣ የዓላማዎች ማሳኪያ ስልት እንጅ በእራሱ የመጨረሻ ግብ እንዳልሆነ አድርገው ነበር የሚመለከቱት፡፡ ጥሩ ነገር ለመስራት ስልጣንን መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ያምናሉ፣ ኃይል የሌላቸውን ኃይል ካላቸው ለመጠበቅ፣ ስልጣንን አላግባብ መጠቀምን ለመከላከል፣ ስልጣንን በመጠቀም ኃይል የሌላቸውን ኃይለኞች ለማድረግ፣ ኃይልን በመጠቀም ወጣቶችን ኃይል እንዲኖራቸው ለማድረግ የኃይል መጠቀምን አስፈላጊነት ይናገሩ ነበር፡፡ ህዝብ ተስፋ እንዲኖረው የኃይል መጠቀምን አስፈላጊነት ያምኑ ነበር፡፡ ኃይልን መጠቀም ለመግደል ወይም ለመስረቅ ሳይሆን ህዘቦችን ለማዳን መሆን እንዳለበት ያምኑ ነበር፡፡ በሰላም ኃያልነት ያምኑ ነበር፡፡ ከባንቱስታንስ የዘረኝነት ደሴት በማላቀቅ ብሩህ የህዝቦችን ህይወት መመስረት እንዲቻል በደግ ስራ እና በዕርቅ ኃያልነት ያምኑ ነበር፡፡

ማንዴላ የዕርቅ ዋጋው እውነት ነው፡ ብለዋል፡፡  አንድ ሰው ለሰራው ስራ ወይም ላጠፋው ጥፋት በህዘብ ፊት ኃላፊነትን መውሰድ ዕርቅ የሚፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ የአፓርታይድ ሰብአዊ መብት ደፍጣጮች አስከ አሁን ድረስ ለፈጸሙት ወንጀል ኃላፊነት በመውስድ ለፈጸሙት ለጥፋታቸው በህዝብ ፊት አምነው ይቅርታ መጠየቅ ይኖረባቸዋል፡፡ የጥፋት ሰለባዎቻቸው እና ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች የእነዚህን እኩይ ተግባር ፈጻሚዎች እውነተኛ ባህሪ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ እውነት እና እውነት ብቻ እርምጃ ከመውሰድ እና የጥላቻ በቀል ከመውሰድ ያድናል፡፡ ማንዴላ አገራቸውን ከአፓርታይድ የሞራል ዝቅጠት ለማጽዳት እና ህዝቡን ከአፓርታይድ የጨለማ መንገድ ለማውጣት እንዲሁም የብዙሀን ፓርቲ ስርዓት እንዲጎለብት በማሰብ የእውነት እና የዕርቅ ኮሚሽን አቋቁመዋል፡፡

ለሶስት አስርት ሩብ ዓመታት ለነጻነት ረዥሙን ጉዞ የተጓዙት ሰው አሁን ማረፍ አለባቸው፡፡ ረዥሙን ጉዞ ተጉዘዋል፣ ምክንያቱም ነጻነትን የመጠበቅ ቃልኪዳን ነበራቸውና፡፡ አሁን አሸልበዋል፡፡ ለዘላለም በሰላም ይረፉ፡፡

ሆኖም ግን ወደ ነጻነት የሚደረገውን ረዥሙን ጉዞ ለማጠናቀቅ ገና ብዙ ማይሎች እና ብዙ ያልተሳኩ ቃልኪዳኖች ይቀራሉ፡፡ የማንዴላን ረዥሙን ጉዞ አሁን የሚጓዘው ማን ነው? የማንዴላን ቃልኪዳኖች የሚፈጽማቸው ማን ነው? ማንዴላ የአፍሪካ ወጣቶች ቀንዲል…

የማንዴላ ስንብት ለአፍሪካ ወጣቶች፡ “ትግላችሁን ቀጥሉ፣ በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ…!”

ለአፍሪካ ወጣቶች ባስተላለፉት የስንብት መልዕክት ላይ እንድደነቅ እና በጉዳዩም ላይ የበለጠ እንዳስብ ያደርገኛል፡፡ ብልሁ የአፍሪካ አንበሳ እረፍት ስለሌላቸው ወጣት የአቦሸማኔ የአፍሪካ ነብሮች ምን ይላሉ?

ትልቅ ለመሆን ድፍረት ይኑራችሁ ፣ ማንዴላ የፍሪካን ወጣቶች ታሪካዊ መጻኢ ዕድል ያስታውሳሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ታላቅ እንዲሆኑ መክረዋል፡፡ “አንዳንድ ጊዜ ታላቅነት በትውልድ ላይ ይወድቃል፡፡ ያንን ታላቅ ትውልድ ልትሆን ትችላላቸሁ፡፡ ታላቅነትህ ያብብ፡፡“

ማህበረሰቡን ከመለወጥህ በፊት መጀመሪያ እራሳችሁን ለዉጡ፣ አሮጌው የጥላቻ እና የፍርሃት መንገድ ለአዲሱ የመግባባት እና የዕርቅ መንገድ ቦታ መስጠት እንዳለበት ማንዴላ ለወጣቶቹ መክረዋል፡፡ መዘጋጀት አለባቸው፡፡ “ድርድር ሳደርግ ከተማርኳቸው ነገሮች አንዱ እራሴን እስክለውጥ ድረስ ሌሎችን መለወጥ አልችልም“፡፡ በፍጹም መጥላት የለባቸውም ምክንያቱም “ጥላቻ መርዝን እንደመጠጣት ያህል ነው፣ ጠላቴን ይገድልልኛል በሚል ተስፋ“፡፡ ጥላቻ ከውልደት በኋላ የሚመጣ ባህሪ ነው፡፡ “ባለው የቆዳ ቀለም ልዩነት፣ ባለው የአስተዳደግ ሁኔታ፣ ወይም ደግሞ በሚከተለው እምነት ምክንያት ማንም ማንንም ሊጠላ አልተወለደም፡፡ ሰዎች ጥላቻን መማር አለባቸው፣ እና ጥላቻን መማር ከቻሉ ፍቅር እንዲኖራቸው ሊማሩ ይገባል፣ ፍቅር በተፈጥሮ ወደ ሰው ልጅ ልብ ውስጥ ከተቃራኒው የበለጠ ለመግባት ስለሚችል::“

ሙከራቹህን ቀጥሉበት፣ ማንዴላ የአፍሪካ ወጣቶች ምንጊዜም እንዲሞክሩ እና በፍጹም በፍጹም እጅ እንዳይሰጡ በመምከር አዲሲቷን ጀግና አፍሪካ የመመስረት ቃልኪዳን ለመጠበቅ አንድ ሰው በቆዳው፣ በጎሳው እና በእምነቱ ጠቃሚነት ከጸጉሩ/ሯ ቀለም ልዩነት በስተቀር ጠቃሚነቱ  እርባና እንደሌለው አጽንኦ ሰጥተው አስተምረዋል፡፡ በአፍሪካ “ፍትህ እንደ ውኃ እንዲንቆረቆር እና እውነት እንደማያቋርጥ የጅረት ምንጭ እንዲፈስ” ወጣቱ መቀጠል እና ሙከራውን ማቆም እንደሌለበት ማንዴላ ምክር ለግሰዋል፡፡  በውድቀት ላይ ተመስርቶ የስኬት አዝመራ እንደሚታጨድ በመገንዘብ ወጣቶች ውድቀትን ሳይፈሩ ትግላቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ማንዴላ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ “እኔን በማስገኘው ስኬት አትገምግሙኝ፣ ይልቅስ ምን ያህል ጊዜ እንደወደቅሁ እና ለስኬት ምን ያህል ጥረት በማድረግ እንደተነሳሁ እንጅ“ ውድቀት ኃጢአት አይደለም፡፡ ለመሞከር አለመቻል ነው ውድቀት ማለት፡፡ በህይወት ስንክሳር “ታላቁ ዝና ፍጹም አለመውደቅ አይደለም፣ ነገር ግን ትልቁ ነገር በወደቅን ቁጥር ለመነሳት የምናደርገው ጥረት ነው፡፡” ማንዴላ ለወጣቶቹ ሲመክሩ ወጣቶች በስኬት ማማ ላይ ፊጥ ለማለት ጥረት ማድረግ ብቻ ሳይሆን ትከሻቸውን በማጠንከር ሊመጡ የሚችሉትን ችግሮቸ ሁሉ በመጋፈጥ በድል አድራጊነት ለመውጣት ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ምክንያቱም “ትላቁን ተራራ ከወጣህ በኋላ ሌሎች ብዙ ሊወጡ የሚችሉ ተራሮች እንዳሉ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡“ በማለት አስተምረዋል፡፡

በአንድነት ሁኑ፣ የአፍሪካ ወጣቶች እንደወጣት ኃይል በአንድነት መምጣት እንዳለባቸው ማንዴላ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ እንዲህ ሲሉም መክረዋል፣ “አንድ ነጠላ ሰው ሀገሩን ነጻ ሊያወጣ አይችልም፡፡ አገራችሁን ነጻ ልታደርጉ የምትችሉት በአጠቃላይ በጋራ ስትንቀሳቀሱ ነው፡፡“

ጥሩ ሞራል ያለው/ላት ሰው ሁኑ፣ ደግነት የሞራል ቆንጆነት ነው፡፡ ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ጥረት የማድረግ ጉዳይ ነው እና ማንም አዬ አላዬ ጥሩውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አለማለት ነው፡፡ “ከዚህ ቀደም እንደተናገርኩት ሁሉ ለእራስ ታማኝ መሆን ነው፡፡ በቅድሚያ እራስህን ካልለወጥክ በህዝብ ላይ ውጤት ሊያመጣ የሚያስችል ተጽእኖ ልታመጣ አትችልም…ታላላቅ የሰላም መሪዎች በሙሉ ሀቀኞች ናቸው፣ ታማኞች ናቸው፣ ነገር ግን ከብር ፈላጊ አይደሉም::“

አገር ወዳድ አርበኛ ሁኑ፣ ማንዴላ በአገር ወዳድ አርበኝነት ላይ እምነት ነበራቸው፣ እናም የአፍሪካ ወጣቶች ለህዝቦቻቸው እና ለአህጉራቸው አርበኛ መሆን እንዳለባቸው መክረዋል፡፡ ማንዴላ እንዲህ አሉ፣ “በመጀመሪያ ደረጃ እኔ እራሴን ሁሌም የአፍሪካ አህጉር ወዳድ አርበኛ አድርጌ እቆጥራሉ፡፡“ የአፍሪካ አርበኞች የቅኝ ገዥ ጌቶቻቸውን ከአሁጉሩ አባረዋል፡፡ የአፍሪካ አርበኞች አፓርታይድን ያለደም መፋሰስ አስወግደዋል፡፡ የአፍሪካ ወጣቶች በአሁኑ ጊዜ በጋራ በመሆን ድህነትን፣ ድንቁርናን እና አምባገነንነትን ማስወገድ ይኖርባቸዋል፡፡

ደፋር ሁኑ፣ ወጣቶቹ ደፋር እንዲሆኑ ማንዴላ መክረዋል፡፡ “ድፍረት የፍርሃት አለመኖር ብቻ አለመሆኑን ተረድቻለሁ፣ ነገር ግን በፍርሃት ላይ ድል መቀዳጀት ማለት ነው፡፡ ጀግና ሰው ማለት ፍርሃት የማይሰማው ማለት አይደለም፣ ነግረ ግን ፍርሃትን የሚያሸንፍ እንጅ::“

ትልቅ ነገር አልሙ፣ ማንዴላ የአፍሪካ ወጣቶች ትልቅ ነገር እንዲያልሙ መክረዋል፡፡ ትልቅ እንዳይሆኑ እና ሀብታም ወንድ እና ሴት እንዳይሆኑ፣ ነገር ግን ሰላሟ የተጠበቀ እና የበለጸገች አፍሪካ እንድትሆን ማለም፡፡ “በእራሷ ሰላሟ የተረጋገጠ አፍሪካን አልማለሁ፡፡ ለቆንጆዋ ደቡብ አፍሪካ ህልሞች ካሉ ወደ ግቧ የሚያደርሱ መንገዶችም አሉ፡፡ እነዚህ ሁለቱ መንገዶች ደግነት እና ይቅርታ አድራጊነት በመባል ተሰይመዋል፡፡“

ከኋላ ሆናችሁ ምሩ፣ ማንዴላ በጅግናዋ አዲሲቱ አፍሪካ በአሮጌው የአስተዳደር ስልት አንዴ ስልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ እስከሞት ድረስ ስልጣን አልለቅም ማለት ቦታ እንደሌለው ለአፍሪካ ወጣቶች ምክር ለግሰዋል፡፡ ማንዴላ ወጣቶቹን እንዲህ በማለት ተማጽነዋል፣ “ከመንጋዎቹ በኋላ እንደሚሆን እረኛ በጣም ፈጣኑን ከፊት እንዲሆን መፍቀድ፣ሌሎቹ ግን እንዲከተሉ ማድረግ፣ ሁሉም ከኋላ ባለ እንደሚታዘዙ እና እንደሚመሩ እንዲያውቁት ሳይደረግ ጉዞውን ማስኬድ“፡፡ ማንዴላ እንዲህ ይላሉ፣ “ከኋላ ምራ እና ሌሎችን ከፊት አድርግ፣ በተለይም ጥሩ ነገር በሚኖርበት ጊዜ እና ድልን በምታከብሩበት ጊዜ“፡፡ አደጋ በሚኖርበት ጊዜ የፊተኛውን ረድፍ ትይዛላቸሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ህዝብ የናንተን አመራር ሰጭነት ያደንቃል… ከኋላ ሆነህ ምራ ሌሎቹ ከፊት ነኝ የሚል እምነት እንዲኖራቸው አድርጉ፡፡ “መሪነትን ማቆምም መምራት ነው“ በማለት ማንዴላ ወጣቶቹ በአንክሮ አንዲመለከቱት መክረዋል፡፡

ችግርና መከራ በትግል ላይ አንዳለ እወቁ ፣ ለነጻነት በሚደረገው ረዥሙ ጉዞ  ብዙ የህግ ሂደቶች እና ቅጣቶች እንደሚገጥሟቸው ማንዴላ ለአፍሪካ ወጣቶች ምክር ለግሰዋል፡፡ እንደሚሰቃዩ እንደ እንደሚፈረድባቸው፣ እንደሚዋረዱ፣ ኢሰብአዊነት ድርጊት እንደሚፈጸምባቸው ለአፍሪካውያን ወጣቶች ግልጽ አድርገውላቸዋል፡፡ በመጨረሻም ነጻነት እንደሚመጣ እርግጠኞች ሆነዋል፡፡ “ትናንት አክራሪ ተብየ ነበር፣ ከእስር ቤት ስወጣ ግን ብዙ ህዝቦች ጠላቶቸ ሳይቀሩ በእቅፋቸው አስገቡኝ፣ እናም ይኸንን ነው እንግዲህ  ለሌሎች ሰዎች መናገር ያለብኝ በሀገራቸው ለነጻነት የሚታገሉ ሰዎች አሸባሪዎች ናቸው“ የሚለውም መታወቅ አለበት፡፡

ከጠላቶቻችሁ ጋር ሰላም ሁኑ፣ ለሰላም ሲባል ከእነርሱ ጋር መገናኘት፣ እጅ መጨባበጥ እና ጠላቶቻቸውን እቅፍ አድርገው መሳም አንዳለባቸው ማንዴላ መክረዋል፡፡ “ከጠላትህ ጋር ሰላም እንዲመጣ ከፈለግህ ከእርሱ ጋር አብረህ መስራት አለብህ፣ ከዚያም ጓደኛ ታደርገዋለህ፡፡“

ድህነትን ተዋጉ፣ ማንዴላ የአፍሪካ ወጣቶች በአፍሪካ ቀንድ በጣም አንገብጋቢ የሆነ ችግር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ከመጨረሻው የድህነት ቋት ውስጥ ተዘፍቃ የምትገኘውን አፍሪካን የአፍሪካ ታላቁ ትውልድ እና የወደፊቱ ብሩህ ተስፋ መንጥቆ እንደሚያወጣት ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ ድህነትን ማስወገድ የልገሳ ስራ አይደለም፣ የፍትህ ጉዳይ እንጅ፡፡ እንደ ባርነት እና አፓርታይድ ድህነት ተፈጥሯዊ አይደለም፡፡ ሰው ሰራሽ ነው፣ እናም በሰዎች ጥረት ሊጠፋ እና ድል ሊደረግ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትልቅ በሚሆነው ትውልድ ላይ ይወድቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የማንዴላ ታላቅነት በአፍሪካ ወጣቶች ላይ ወድቋል፡፡

በመርሆዎች ላይ በፍጹም አትደራደሩ፣ የአፍሪካ ወጣቶች በመርሆዎች መደራደር እንደሌለባቸው ማንዴላ አጽንኦ በመስጠት ለአፍሪካ ወጣቶች ምክር ለግሰዋል፡፡ ማንዴላ ለወጣቶቹ ሲያስተምሩ እድሜልካቸውን ከአፓርታይድ እና ከዘረኝነት ጋር ስዋጋ ስታግል ኖሪያለሁ ምክንያቱም እነዚህ ጭራቆች ለሰው ልጅ ሟች ጠላቶች ናቸው፡፡ “የዘር መድልዎን እና መገለጫዎቹን ሁሉ በጣም እጠላለሁ “ በህይወት ዘመኔ ሁሉ ስታገል ቆይቻለሁ፣ አሁንም እየታገልኩ ነው እና ቀኖቸ እስኪያልቁ ድረስ መታገሉን እቀጥላለሁ…፡፡”  ይህንን በሚገባ አድረገውታል፣ ፈጽመውታልም፡፡ የአፍሪካ ወጣቶች በጥላቻ እና በሁሉም መገለጫዎቹ ላይ ማለትም በጎሰኝነት፣ በፖለቲካ ማንነት፣ በማህበረሰባዊነት፣ በጎሳ ክፍፍል፣ በጾታ ጭቆና፣ በኢኮኖሚ ብዝበዛ እና በህብረተሰብ አድልኦ ላይ በመርህ ላይ የተመሰረተ እና ድርድር የማያስገባ አቋም መያዝ እንዳለባቸው ማንዴላ በአጽንኦ ጠይቀዋል፡፡

ብሩህ አላሚ እና ጽናት ይኑራችሁ፣ የአፍሪካ ወጣቶች ብሩህ አላሚዎች መሆን እንዳለባቸው ማንዴላ መክረዋል፣ ምክንያቱም የአፍሪካውያን ምርጥ ቀኖች ገና እየመጡ ነውና፡፡ “እኔ በመሰረቱ ብሩህ አላሚ ነኝ፡፡ ከተፈጥሮም መጣ ከእራስ ጥንካሬ የምለው ነገር የለም፡፡ በከፊል ብሩህ አላሚ መሆን ማለት የአንድን ሰው እራስ ወደ ጸሐይ ቀጥ ብሎ እንዲያመለክት እንዲሁም የአንድ ሰው እግሮች ወደፊት እንዲራመዱ የማድረግ ያህል ነው፡፡ በሰው ላይ ያለኝ እምነት በሚገባ በሚፈተሽበት ጊዜ ብዙ የጨለማ አጋጣሚዎች ነበሩ፡፡ ነግር ግን ተስፋ ቢስ ለመሆን አጅ አልሰጥም፣ አላደርገውምም አልሞክረውምም፡፡ ያ መንገድ የሽንፈት እና የሞት ነው፡፡“ የአፍሪካ ወጣቶች ያን ረዥሙን ጉዞ መጓዙን መቀጠል አለባቸው፡፡ የማንዴላ ጠንካሮች መሆን አለባቸው፡፡ “ጥንካሬው እና አስፈላጊው ጥበብ ቢኖርህም በዓለም ላይ ወደ ግለሰባዊ ድልነት ልትቀይራቸው የማትችላቸው ጥቂት መጥፎ አጋጣሚዎች አሉ፡፡“  

ተማሩ፣ ህዝብንም አስተምሩ፣ ማንዴላ ትምህርት ለአፍሪካ ወጣቶች ለእራሳቸው ስኬታማነት እና ለወደፊቷ አፍሪካ ቁልፍ ነገር እንደሆነ አስተምረዋል፡፡ “ዓለምን ለመለወጥ ትምህርት ትልቁ መሳሪያ ነው፡፡ ዜጎቹ ካልተማሩ በስተቀር ማንም ሀገር ቢሆን እድገት ሊያስመዘግብ አይችልም፡፡“

ዝምተኛ አትሁኑ፣ በጭራቅነት እና በፍትህ እጦት ጊዜ የምን አገባኝነት ባህሪ መኖር እንደሌለበት ማንዴላ ለአፍሪካ ወጣቶች አስተምረዋል፡፡ ጭራቃዊ ድርጊቶች ሲፈጸሙ እየተመለከቱ ዝም ከማለት የበለጠ ጭራቅነት የለም፡፡ ጭራቃዊ ድርጊት በየትኛውም መልኩ ሲፈጸም ስናይ ልንዋጋው ይገባል፣ ወጣቶች ጭንቅላታቸውን ክፍት ካደረጉ እውነት በእራሱ ይገለጽላቸዋል፡፡ “ምንም ዓይነት ድንገት ያገኘሁት ግንዛቤ የለኝም፣ ምንም ዓይነት መረጃም የለኝም፣ እውነት የተገለጸበት አጋጣሚም የለም፣ ነገር ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ጨዋነት የጎደላቸው ድርጊቶች፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ውርደቶች፣ እና እንድናደድ፣ እንዳምጽ እና ህዝቤን አፍኖ የያዘውን ስርዓት እንድዋጋ በሺዎች የሚቀጠሩ ላስታውሳቸው የማልችላቸው አጋጣሚዎች ያሉ መሆኑን“ በማለት ማንዴላ ለአፍሪካ ወጣቶች አስተምረዋል፡፡ በተነገርኩት ላይ የተወሰነ ቀን የለም፣ ስለሆነም እራሴን ለህዝቤ ነጻነት መስዋዕት አደርጋለሁ፣ ይልቁንም በተግባር እያዋልኩት መሆኑን እራሴን አዚያው ውስጥ አገኘሁት፣ እንደዚያ ካልሆነ ወደ ተግባር መተርጎም የሚቻል አይሆንም፡፡”

ወደ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት ጥበቃ የሚደረገው ረዥሙ ጉዞ ቀላል አይደለም…፣ ማንዴላ ለነጻነት፣ ለክብር፣ ለዴሞክራሲ እና ለሰብአዊ መብት ጥበቃ የሚደረገው ትግል ረዥም፣ አስቸጋሪ እና አደገኛ መሆኑን ለአፍሪካ ወጣቶች መክረዋል፡፡ እንዲህም ብለዋል፣ “ወደ ነጻነት የሚያስኬድ ቀላል ጎዞ የትም ቦታ አይገኝም፣ እናም አብዛኞቻችን ከምንመኘው የተራራ ጫፍ ላይ ከመድረሳችን በፊት ደግመን እና ደጋግመን በሸለቆው የሞት ጥላ ስር ማለፍ አለብን፡፡“

ገና ብዙ የሚወጡ ተራሮች ይቀሩኛል፣ ወደ ነጻነት የሚደረገው ታላቁ ጉዞ በኮረብታዎች እና በተራሮች የሚያቋርጥ እና በሸለቆዎች የሚዘረጋ ነው፡፡ በጉዞው ላይ ያልተጠበቁ አደጋዎች ያጋጥማሉ፡፡ ለማረፍ ትንሽ ጊዜ ነው ያለው፡፡ ማንዴላ እንዲህ ብለዋል፣ “ለነጻነት የሚያስኬደውን ያንን እረዥሙን ጉዞ ተጉዠዋለሁ፡፡ በእራስ መተማመንን እንዳላጣ ጥረት አድርጊያለሁ፡፡ በጉዞው መንገድ ላይ የተሳሳቱ ቅደምተከተሎችን ፈጽሚያለሁ፡፡ ነገር ግን ከትልቁ ተራራ ጭፍ ላይ ለመውጣት ገና ብዙ ኮረብታዎችን መውጣት አንደሚኖርብኝ አረጋግጫለሁ፡፡ ለማረፍ ትንሽ ጊዜ ወስጃለሁ፣ ሰረቅ አድርጌም የከበበኝን አስደናቂውን አካባቢያዊ ሁኔታ ተመልክቻለሁ፣ የተጓዝኩትን ርቀት መለስ ብዬ ተመልክቻለሁ፣ ግን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው ለማረፍ የቻልኩት፣ ነጻነትን ለማግኘት ኃላፊነት መምጣት አለበት፣ እና በምንም ዓይነት መልኩ ከወዲያ ወዲህ እያልኩ አልንገዋለልም፣ ረዥሙ ጉዞዬ አልተጠናቀቀምና፡፡“

ሁልጊዜ ደግ ለመስራት ሞክሩ ፣ ይቅርታ ለማድረግ፣ ዕርቅ ለማውረድ…. ጥሩ ነገር ለማድረግ፣ ይቅርታ ለማድረግ እና ዕርቀ ሰላም ለማውረድ ጥረት አድርጉ፡፡ የስኬት ቃልኪዳን ባይኖርም ሞክሩ፣ ውድቀት እንዳለ ብታውቁም ሞክር፣ ጥርጣሬ ያለ እና እርግጠኝነት የጎደለ መሆኑን ብታውቅም ሞክር፡፡ ደክመህ እና መቀጠል የማትችል መሆኑን ባታውቁም እንኳ ሞክሩ፡፡ ተስፋ በማይኖርበት ጊዜም ሞክሩ፡፡ ዓላማህን ካሳካህ በኋላም ቢሆን ሞክሩ፡፡ ለመሞከር አስቸጋሪ እና ትርጉምየለሽ በሆነበት ጊዜ እንኳ ቢሆን ሞክሩ፡፡ ምርጫ በሌለበት ግን ሙከራ ብቻ ባለበት ሁኔታም ቢሆን ሞክሩ፡፡ ጭራቅነት በመልካም ተግባር ላይ ድልን እንዳይቀዳጅ ሞክሩ፣ ማንዴላ እንደሞከሩት ሁሉ ሞክሩ፡፡

ስንብት፣ ለእኔ አፍሪካዊ ክቡር! ለእኛ አፍሪካዊ ክቡር!

ብዙ ምናባዊ ንግግሮችን ላደረግሁላቸው ለኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ የሚወዱትን እና የሚደሰቱበትን “የሸክስፒርን” ቃላትን በመዋስ የመጨረሻ ስንብቴን ላቅርብ፡፡ ማንዴላ በእስር ቤት ውሰጥ ሳሉ የሸክስፒር ጁሊየስ ቄሳር የቄሳር ቃላት ይስሟሟቸው ነበር፡፡

እስከአሁን ከሰማኋቸው አስደናቂ ነገሮች መካከል ለእኔ እንግዳ የሚሆነው ወንዶች ሞት የሚመጣ የመጨረሻ መሆኑን አይተው መፍራት አለባቸው የሚለው ነው፡፡ አለመፍራት አስደናቂ አይሆንምና፡፡ ለኔልሰን ሮሺስላሽላ ማንዴላ የሆራሽዎ የሀዘን ቃላትን በመጠቀም የመጨረሻ ስንበት አደርጋለሁ፡፡

አሁን የተከበረ ሰው ልብ ተሰብሯል፡፡
የተከበሩ ደህና ይደሩ፣
ነብስዎ በሰላም እንድታርፍ መላዕክት ይዘምራሉ፣

እና በዚህ አሳዛኝ ህልፈት የጆህን ዶኔን ቃላት በመጠቀም እጮሃለሁ፡፡

ሞት ኩራት አይደርብህ፣ አንዳንዶች ኃይለኛ እና አስፈሪ ብለው ቢጠሩህም፣ አትፈራም
ሞት ማዲባን አትገድልም አትችልም!

ዘላለማዊ ክብር ለማንዴላ፣ ዘላለማዊ ክብር ለኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ!

ታህሳስ 2 ቀን 2006 ዓ.ም

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ፪ –ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

harar
ባለፈው ሳምንት የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካን ተጨባጭ እውነታዎችን ቃኝቼ ተከታዩን ክፍል በይደር አቆይቼው እንደነበረ ይታወሳል፤ እነሆም ዛሬ እንዲህ እቀጥላለሁ፡-

ሐረር እንደ ማሳያ

(መቼም ኢህአዴግ በብቸኝነት የሚኩራራበት የፖለቲካ ‹ስኬት›፣ ለዘመናት አንድ ሆኖ የኖረ ሕዝብን ‹ብሔር ብሔረሰቦች› በሚል ከፋፋይ የ‹ክርስትና ስም› እጥምቆ በአደባባይ ማስጨፈር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ርግጥ ነው በአንድ ወቅት በፍትህ ጋዜጣ ላይ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መጨፈር›› በሚል ርዕስ የታተመ መጣጥፍን ተከትሎ ‹ፀረ-ብሔር ብሔረሰቦች› ተደርጌ በተመሰረተብኝ ክስ ፍርድ ቤት መመላለሴ ዛሬም ድረስ መቋጫ አላገኘም፤ ርግጥ ነው ኢትዮጵያውያን ወንድም እህቶቼ በስታዲዮሞች እየተሰባሰቡ የራስ ፀጉራቸው ላይ ላባ ሰክተው፣ ቆዳ አገልድመው እየዘለሉ ትርኢት ከማሳየት ባለፈ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ መብቶቻቸው ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም፡፡ …እውነታው ይህ ቢሆንም ወደ አጀንዳችን /የከሸፈው ፌደራሊዝምን/ ወደ መፈተሹ በአዲስ መስመር እንመለስ፡፡

ቋንቋን መሰረት ያደረገው ኢህአዴግ ሰራሹ ‹ፌደራሊዝም› አወቃቀር የሀገሪቱ መፃኢ ዕድል የተቋጠረበት ‹የሰዓት ቦንብ› መሆኑን ለመረዳት የምስራቅ ኢትዮጵያዋን ሐረር እንደ መሳያ መውሰዱን ግድ የሚያደርጉ በርካታ ገፊ ምክንያቶች አሉ፡፡ እንደሚታወቀው የሐረር ከተማ አመሰራረት ብዙሃኑ ህዝብ ከሚኖርበት ‹ጀጎል› ከተሰኘው በግንብ የተከለለ ቅፅር ጋር ይያያዛል፡፡ በ16ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ራሳቸውን ከብሔር ወረራ ለመከላከል በአካባቢው ነዋሪዎች እንደታነፀ በርካታ ድርሳናቶች የሚናገሩለት ጥንታዊውና ታሪካዊው የጀጎል ግንብ በአምስት (ሐረር፣ ኤረር፣ ሠንጋ፣ ቡዳ እና በርበሬ በር በሚባሉ) በሮች የተከፋፈለ ነው፡፡

ጀጎል ከ40ሺ ለማያንሱ የክልሉ ነዋሪዎች መጠለያ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ ከዘጠኝ ሺህ በላይ የሕዝብ ቁጥር ያላቸው የሐረሪ ተወላጆች እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህም ሆኖ መስከረም 30 ቀን 1997 ዓ.ም. ‹‹የሐረሪ ሕዝብ ክልል መንግስት ሕገ-መንግስት›› በሚል ርዕስ ተሻሽሎ የፀደቀው አዋጅ፣ ስርዓቱ በአደባባይ ከሚመፃደቅበት ቋንቋን መሰረት ያደረገ ‹ፌደራሊዝም› የሚቃረኑ እና ከዴሞክራሲ ባህሪያት ጋር የሚጋጩ በርካታ አንቀፆች የታጨቁበት መሆኑ ለጠቀስኩት ሀገራዊ ስጋት መነሻ ነው፡፡ ለማሳያም ያህል የክልሉ ምክር ቤት ይቋቋምበታል ተብሎ በሕገ-መንግስቱ ውስጥ የተካተተውን የምርጫ ሕግ መመልከት የሚችል ይመስለኛል፡፡ ይህ ሕገ-መንግስት ተሻሽሎ ከመፅደቁ ሶስት ዓመት ቀደም ብሎ በስታስቲክ ባለሥልጣን ይፋ የተደረገው መረጃ የክልሉ ነዋሪ ህዝብ ብዛት በጥቅሉ 131,139 እንደሆነ ይገልፅና በየብሔሩ ሲከፋፈል ደግሞ ኦሮሞ 41%፣ አማራ 22.77%፣ ሐረሪ 8.65%፣ ጉራጌ 4.34% ሶማሌ 3.87%፣ ትግራይ 1.53%፣
አርጎባ 1.26% መሆኑን ይዘረዝራል፤ በስፋት የሚነገሩ ቋንቋዎችም ኦሮምኛ 56%፣ አማርኛ 27.53%፣ ሐረሪ 7.33%፣ ሶማሊኛ 3.70%፣ ጉራጌኛ 2.91%… ነው ይለናል፡፡

በመሬት ያለው እውነታ ይህ ቢሆንም የክልሉ ሕገ-መንግስት ደግሞ በአንቀፅ 49 ‹‹የሐረሪ ሕዝብ ክልል ምክር ቤት›› በሁለት ጉባዔዎች እንደሚመሰረት ከገለፀ በኋላ፣ እነርሱም ‹‹የህዝብ ተወካዮች ጉባኤ›› እና ‹‹የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ›› እንደሆኑ ይነግረናል፤ ይኸው አንቀፅ በቁጥር 2 እና 3 ላይ ‹የሕዝብ ተወካዮች› ሃያ ሁለት፣ የሐረሪው በብሔሩ ተወላጆች ብቻ የሚወከሉ 14 አባላት ይኖሩታል ይላል፡፡ ይህ ሁኔታ በምርጫ ወቅት እንዴት እንደሚተገበር ደግሞ በአንቀፅ 50 ላይ ‹‹የጉባዔዎች አከፋፈል፣ አወካከልና አመራረጥ›› በሚል ርዕስ ስር እንደሚከተለው ተብራርቷል ‹የሕዝብ ተወካዮች› ለተሰኘው ጉባኤ ከጀጎል ነዋሪዎች አራት፣ ከጀጎል ውጪ ከሚገኙ የከተማና የገጠር ቀበሌ ገበሬ ማህበራት 18 አባላት ይመረጡበታል፡፡ ለሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ደግሞ በክልሉና ከክልሉ ውጪ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ከሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ ውስጥ 14 አባላት ይመረጡበታል፡፡ ይሁንና ሕጉ ብዙሃኑን የአካባቢው ነዋሪዎች የፖለቲካ ውክልና ከመንፈጉ በተጨማሪ ከክልሉ ተቋማትም ሆነ መብቶች እንዲገለሉ አድርጓቸዋል፡፡ በተለይም በራሱ በመንግስት መረጃ ሳይቀር በተወላጅነትም ሆነ ቋንቋውን በመናገር ከኦሮሞ ብሔር ቀጥሎ በሁለተኛነት የሚገኙት፣ እንዲሁም አብላጫውን የፖለቲካ ስልጣን ከያዘው ከሐረሪ ብሔረሰብ አባላት ከእጥፍ በላይ ቁጥር እንዳላቸው የተረጋገጠው አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በዞን ደረጃ እንኳ እንዲዋቀሩ አለመደረጉ ‹ፌደራሊዝሙ› ከአፋዊነት አለማለፉን ያመላክታል (በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በዞን ደረጃ እንዲዋቀሩ የተደረጉ ጥቂት የማይባሉ ብሔሮች እንዳሉ ልብ ይሏል) እንዲህ አይነቱ አደረጃጀት ሌላው ቢቀር እንኳ በዚህ ዘመን ፋሽን ከሆነው ‹‹ውጡ፣ ክልላችሁ አይደለም!›› ከሚለው ነውረኛ
ፖለቲካ የመታደግ ጉልበት ሊኖረው የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ በርግጥ ይህ ሁናቴ ዛሬም ድረስ መፅናቱ ‹ብሔረሰቡን እወክላለሁ› የሚለው የእነ አዲሱ ለገሰ ብአዴን ከተላላኪነት ያለፈ ሚና እንደሌለው የሚያመላክት ይመስለኛል፡፡

የሆነው ሆኖ የሙግቱ ዋነኛ መግፍኤ የጀጎል ነዋሪ ከሆኑት ውስጥ ከሶስት እጅ ለሚልቁት አራት፣ ለተቀሩት ጥቂት ሐረሪዎች ደግሞ አስራአራት የምክር ቤት ወንበር ከመስጠቱ ጋር ይያያዛል፡፡ በዚህ ሕግ መሰረት በጀጎል የምርጫ ክልል ከአራቱ ወንበሮች ውጪ ሐረሪ ያልሆነ የትኛውም ፓርቲም ሆነ ግለሰብ ለውድድር መቅረብ እንደማይችል በግልፅ ተደንግጓል፡፡ እንዲህ አይነቱ አናሳዎችን በብዙሃኑ ላይ የሚሾም ኢ-ፍትሃዊ የሥልጣን ክፍፍል አብዛኛውን የክልሉ ነዋሪ በገሃድ እየተንፀባረቀ ላለው ባይተዋር አገዛዝ ከማጋለጡም በላይ፣ ከመልካም አስተዳደር ጋር በአዋጅ የተፋታ እስኪመስል ድረስ በሙስናና በአድሎአዊነት ለተተበተበ ስርዓት ዳርጎታል፤ ይህ ሁኔታም በህዝቦች መካከል መከፋፈል እንዲፈጠርና በጥላቻ ምሽግ ውስጥ እንዲያደፍጡ ማስገደዱ አይቀርም፡፡
በጥቅሉ የብዙዎችን መብት ጨፍልቆና አንዱን ነጥሎ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስርዓት ማንበር የማታ ማታ ጊዜውን ጠብቆ ከሚፈነዳ አደጋ ጋር ማላተሙና የብሔር ግጭት የመቀስቀስ መዘዝ ማስከተሉን አስቀድሞ ለማወቅ ነብይ መሆን አይጠበቅም፤ የኢህአዴግ ‹‹እኔ ከሌለሁ ኢትዮጵያ ትበታተናለች›› ፉከራም ይህን መሰል ተንኮል ከገመደው የክልል አወቃቀር ቀመር ጋር የተያያዘ ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ወደ እንዲህ አይነቱ ድምዳሜ የሚገፋን የሃሳቡ አመንጪዎችም ሆኑ መበታተናችን አይቀሬ እንደሆነ የሚያረዱን ራሳቸው የኢህአዴግ መስራቾች መሆናቸው ነው፡፡ በተቀረ ‹የምንከተለው የፌደራል ስርዓት ቋንቋን መስፈርት ያደረገ ነው› እስከተባለ ድረስ በሐረሪ ያለው አስተዳደር በራሱ በኢህአዴግ አጋፋሪነት በፀደቀው ህገ-መንግስትም ጭምር ተቀባይነት እንደሌለው ከገዥዎቻችን የተሰወረ አለመሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ ከፈለገ በክልሉ ምክር ቤት ሰላሳ ስድስቱም ወንበሮች ላይ የመወዳደር መብት ተሰጥቶታል፡፡ በግልባጩ ኦህዴድን ጨምሮ በሐረሪ ብሔረሰብ አባላት ያልተመሰረተ ማንኛውም የተቃዋሚ ፓርቲ ከሃያ ሁለቱ ወንበር ውጭ በአስራ አራቱ ላይ እጩ ማቅረብ እንደማይችል በሕግ ታውጇል፤ የስራ ቋንቋንም በተመለከተ በክልሉ ነዋሪዎች ከአማርኛ ቋንቋ በሁለት እጅ ያነሰ ተናጋሪ ያለው ሐረሪ እና በስፋት የሚነገረው ኦሮምኛ ብቻ እንዲሆኑ መደረጉም ራሱ አገዛዙ ከሚያቀነቅንለት የቋንቋ ‹ፌደራሊዝም› ጋር ይጣረሳል፡፡ በርግጥም የስርዓቱ ‹ኤጲስ ቆጶሳት› ደጋግመው ‹ለአስራ ሰባት ዓመታት የታገልነው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአፍ መፍጫ ቋንቋው እንዲማር፣ እንዲዳኝ፣ እንዲተዳደር… ነው› የሚሉት ሀቲት ማደናገሪያ መሆኑን ለመረዳት ከዚህ የበለጠ ክስተት ሊኖር አይችልም፡፡

በአናቱም የክልሉ ፕሬዝዳንት እና ም/አፈ ጉባዔ ከሐረሪ ብቻ የሚመረጡ ሲሆን፣ ዋናውን አፈ-ጉባዔ ደግሞ በጋራ ሁለቱ ጉባኤዎች እንደሚመርጧቸው በአዋጅ ተደንግጓል፡፡ እንዲሁም በፌደራሉ ህገ-መንግስት ላይ የተካተተውና አጨቃጫቂው ‹‹የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት›› የተሰጠው በተናጠል ለሐረሪ ብሔረሰብ ብቻ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ልዩ ችሎታም ሆነ ከላይ የተጠቀሰው ልጓም አልባ ሥልጣን በሌሎች ክልሎች በተመሳሳይ መልኩ ለሚገኙ ብሔሮች አልተሰጠም፤ ለምሳሌ በደቡብ ሲዳማ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ…፤ በአማራ ክልልም የአገው ብሔረሰብ ከሐረሪ የበለጠ ቁጥር ቢኖራቸውም በዞን ደረጃ እንዲዋቀሩ ከመፍቀድ ያለፈ ያገኙት ልዩ መብት የለም፡፡
በነገራችን ላይ ሐረሪ እንዲህ ለሀገር አንድነት አስጊ በሆነ መልኩ እንዲደራጅ የተደረገው በተወላጆቹ ፍላጎት እና ጥያቄ ነው የሚል እምነት የለኝም፤ ምክንያቱም የብሔረሰቡ አባላት እንደማንኛውም ዜጋ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑና የሚኮሩ መሆናቸውን ከታሪክ መረዳቱ አያዳግትም፡፡ እናም በግሌ የዚህ ሁሉ መግፍኤ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ኤርትራን እና አሰብን የመሰለ የሀገር ጉሮሮ (ወደብ) ኃላፊነት በማይሰማው መልኩ አሳልፎ የሰጠው ኢህአዴግ እንደ መጠባበቂያ አስልቶ ያጠነጠነው የተንኮል ድር ይመስለኛል፡፡ የክልሉ ህገ-መንግስትም ሆን ተብሎ ወደ አንድ ወገን እንዲያጋድል መደረጉ (በአንዳች ክፉ ቀን ሊመዘዝ የሚችል አደገኛ የፖለቲካ አጀንዳ ማቀፉ) ከላይ የጠቀስኳቸውን ማሳያዎች ያስረግጥልናል፡፡

የኃይማኖት መቻቻል…
muslim and christian
የሐረሪ ክልል ሌላኛው ችግር የኃይማኖት ልዩነት ያነበረው ውጥረት ለነዋሪው ሕዝብ ተጨማሪ ስጋት መፍጠሩ ነው፡፡ ከዓመታት በፊት በእንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን አልቃይዳ እንዳቀነባበረው የታመነውን የቦንብ አደጋ አድርሷል ተብሎ ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ ዘግይቶ በነፃ የተለቀቀው ሐምዲ ኢስሐቅ የሐረሪ ተወላጅና የጀጎል ልጅ መሆኑ ክልሉ በማዕከላዊ መንግስቱ በአይነ ቁራኛ እንዲታይ አድርጎት እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ሐምዲ በአደጋው ተጠርጥሮ ጣሊያን ሮም ውስጥ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ለዜናው ከፍተኛ ሽፋን መስጠታቸውን ተከትሎ፣ በወቅቱ አንድ ጊዜ ብቻ ታትማ የጠፋችው ‹‹መዝናኛ›› መፅሔት ባቀረበችው ሰፊ ዘገባ እንዲህ በማለት ማስነበቧ አይዘነጋም፡- ‹‹በሐረር ጥብቅ የእስልምና ሃይማኖት ትምህርት ስር እየሰደደ ነው፡፡ አንዳንድ ሃይማኖተኞች እስከ ፓኪስታንና አፍጋኒስታን በመዝለቅ የእስላማዊ ትምህርትና ትግል ስልጠናን በመቅሰም እንደሚመለሱ ተረድቻለሁ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በቁጣና በቁጭት የሚመለከቱት ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ‹እውነት ከእኛ መካከል የተፈጠረው ሐምዲ ይህንን ሰርቶ ከሆነ አደንቀዋለሁ› ብሎኛል አንድ ወጣት፡፡››

በ2004 ዓ.ም. አፈንዲ ሙተቂ በተባለ ፀሐፊ ተዘጋጅቶ፣ የቅጂ መብቱን በመጋራት የሐረሪ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ወጪውን በመሸፈን ‹‹ሐረር ጌይ›› በሚል ርዕስ ባሳተመው መጽሐፍ ላይም ሐረር ‹‹እስላማዊ ከተማ ናት›› ተብሎ መገለፁ በራሱ የሚያመለክተው ጉዳይ አለ፤ መቼም ዓለማዊቷን ከተማ ‹እስላማዊት›› እያለ የሚጠራን መጽሐፍ መንግስታዊው ተቋም አሳትሞ ማሰራጨቱ፣ ሃይማኖትና መንግስት የተነጣጠሉ ናቸው ብሎ በአዋጅ ለሚለፍፈው ኢህአዴግ መራሹ ስርዓት ምፀት ይመስለኛል፡፡ በርግጥም ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት›› የሚሉትንም ሆነ፣ ሐረርን እስላማዊ ለማድረግ የሚያሴሩትን እንዲህ አቅፎና ደግፎ ‹በኃይማኖታችን መንግስት ጣልቃ አይግባ› ያሉ መዕምናን ተወካዮችን (መንፈሳዊ መሪዎችን) ሰብስቦ ማሰሩ አገዛዙ የመጨረሻው አፈና ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው፤ የፖለቲካ ተንታኞችም ‹መንግስታዊ ሽብርተኝነት› የሚሉት ይህ አይነቱን ተግባር ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
ድሬዳዋ
ሌላኛው የምስራቅ ኢትዮጵያ ውጥንቅጥ የፖለቲካ መገለጫ የድሬዳዋ አስተዳደር ነው፡፡ ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን በመጣባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታትና በቀድሞዎቹ ስርዓታት ድሬ በሀገሪቱ ግንባር ቀደም የንግድ እንቅስቃሴ ከሚደረግባቸው ጥቂት ከተሞች አንዷ እንደነበረች ነዋሪዎቿ ዛሬም ድረስ በትዝታ ያስታውሳሉ፡፡ ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቀሰው በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ከአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና ጁቡቲ ድረስ ተዘርግቶ የነበረው የባቡር መስመር ነው፡፡ ይሁንና ኢህአዴግ ትግል ላይ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ያሰሙበት ከነበሩ የሀገሪቷ ከተሞች ድሬዳዋ አንዷ መሆኗ ቂም እንዲይዝባት ከመግፋቱም በላይ ‹የነፍጠኛ መከማቻ› ተብላ በ‹ጥቁሩ› መዝገብ መስፈሯ ባለፉት ሃያ ሁለት የስልጣን ዓመታት ባለችበት ትረግጥ ዘንድ በማይታየው የስርዓቱ ‹ክፉ እጅ› ለመዳመጥ ዳርጓታል፡፡

የሆነው ሆኖ ድሬ በተጧጧፈ የንግድ ሂደት ደምቃ የምትታይበት ያ የመኸር ዘመኗ እንደ ጉም በንኖ፣ ለአስከፊ ድህነትና ሥራ እጥነት እጅ መስጠቷን ለማስተዋል ከተማዋን ለጥቂት ሰዓታት ብቻ ተዟዙሮ መቃኘቱ በቂ ይመስለኛል፡፡ ርግጥ ነው የኢኮኖሚዋ ዋልታ ከምድር ባቡርና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪክ (ኮተን) በተጨማሪ ሕጋዊም ባይሆን የኮንትሮባንድ ንግድ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ዛሬ ከሞላ ጎደል ሶስቱም የሥራ ዘርፎች በጥልቅ እንቅልፍ የተወሰዱ መስለዋል (ምንም እንኳ ከታማኝ ምንጭ ባላረጋግጥም ኮንትሮባንዱ ‹ፖለቲካዊ ቡራኬ› ማግኘት በቻሉ የስርዓቱ የጥቅም ተጋሪዎች በድብቅ እንደሚሰራ ይነገራል) ምድር ባቡርን በተመለከተ ግን በህይወት ለመኖሩ ደፍሮ የሚከራክር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በርግጥ ለድርጅቱ መፍዘዝ ብሎም መክሰም እንደምክንያት የሚቀርበው ‹ኪሳራ› ቢሆንም ስማቸውን መናገር ያልፈለጉ፣ የተቋሙ የሒሳብ ሠራተኛ የነበሩ አንድ የድሬዳዋ ነዋሪ በዚህ አይስማሙም፤ እንደእርሳቸው አገላለፅ መስሪያ ቤቱ ለኪሳራ የተዳረገው የህወሓት ሰዎች ከጀርባ ባሴሩበት ደባ ነው፤ ‹‹በኤፈርት ስር ከተቋቋሙ ድርጅቶች አንዱ የሆነው የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ላይ የተሰማራው ‹ትራንስ› ከጅቡቲ የሚጫኑ እንደ የዕርዳታ ስንዴና ማዳበሪያ መሰል ምርቶችን በጨረታ እንዲያሸንፍ ይደረግና በጣም እርካሽ በሆነ ዋጋ ለምደር ባቡር የኮንትራት-ኮንትራት ይሰጠዋል፤ ይህ ሁኔታም እየተደጋገመ ሲሄድ ድርጅቱን ለኪሳራ ዳረገው፤ በዚህ ላይ ማነጅመንቱ በተቋሙ ንብረትና ጥቅም ላይ ሙስና ሲፈፅም፣ የስርዓቱ መሪዎች አይተው እንዳላየ ያልፉ ነበር፤ ሠራተኛ ማህበሩ ሳይቀር በግልፅ ለፀረ-ሙስና ሪፖርት ያቀረበባቸው፣ ነገር ግን በሕግ ያልተጠየቁ የአስተዳደር ኃላፊዎች አሉ›› ሲሉ ገደል አፋፍ ስለቆመው የቀድሞ የድሬ ‹ደም-ስር› ምድር ባቡር በቁጭት ይናገራሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት የድርጅቱ ንብረት በሙሉ በመከላከያ ቴክኖሎጂ (መቴክ) ለሚመራው የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ከሰራተኞቹም አብላጫው ተባርረው አምስት መቶ ለሚሆኑት ኢንዱስትሪው ከጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ደሞዝ እየከፋላቸው እንደሚገኝና ከነበሩት 19 ሞተሮች (ባቡር) መካከልም አገልግሎት የሚሰጡት አራት ብቻ እንደሆኑ የድርጅቱ ቅርብ ሰው አረጋግጠውልኛል፡፡ ከአዲስ አበባ-መተሀራ እና ከካሳራት-ኤረር በጠቅላላ 114 ኪ.ሜ. ለሚሸፍን የድልድይ (ሀዲድ) ዕድሳት ይውል ዘንድ የአውሮፓ ህብረት የለገሰውን 60 ሚሊዮን
ዩሮንም (ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ የወሰደው የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ የረባ ስራ ሳይሰራ ‹‹ቄሱም ዝም…›› መሆኑ ብዙዎችን ግራ ከማጋባቱም በላይ በሀገሪቷ ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት ያለመኖሩ ማሳያ ነው፡፡

በአናቱም መንግስት ሕገ-ወጡን የኮንትሮባንድ ንግድ በኃይል ሲያስቀር፣ ካለበት ኃላፊነት አኳያ አማራጭ የስራ ዘርፎችን አለመፍጠሩ ለችግሩ መባባስ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ይቀርባል፡፡ በተለይም በከፍተኛ ባለስልጣናት አንደበት ሳይቀር የ‹ደረቅ ወደብ› አገልግሎት መስጫ በድሬዳዋ እንደሚመሰረትና ለአካባቢው ነዋሪ አማራጭ የሥራ ዕድል እንደሚሆን ተደጋግሞ ከተነገረ በኋላ፣ ሃሳብ ተቀይሮ ሞጆ ላይ እንዲመሰረት መደረጉ ከተማዋ ‹አልቦ ተቆርቋሪ› መሆኗን እንደሚያሳይ በአንድ ወቅት የመስተዳደሩ ምክር ቤት አባል የነበሩ ግለሰብ ይናገራሉ፡፡ የግለሰቡ መከራከሪያ ‹‹ድሬዳዋ ለጁቡቲ ካላት ቅርበት አኳያ የከባድ መኪናዎችን ምልልስ ያፈጥነዋል፤ ይህ ደግሞ በወደብ ላይ ለሚከማቹ ጭነቶች የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል›› የሚል ነው፡፡ በርግጥም ከአዲስ አበባ እምብዛም ከማትርቀው ሞጆ ይልቅ፣ ለእንዲህ አይነቱ አገልግሎት ድሬዳዋ የተሻለች መሆኗን ለመረዳት ጥናትና ምርምር የሚጠይቅ አይመስለኝም፡፡

diredawa
የድሬ ፖለቲካ…

የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በተመለከተ በ1998 ዓ.ም (በፈረንጆች 2007 ዓ.ም) በስታስቲክ ባለስልጣን የተደረገው ቆጠራ እንደሚያሳየው አጠቃላይ የሕዝብ ብዛቷ 341 ሺህ 834 ሲሆን፤ ኦሮሞ 45%፣ ሶማሌ 24.3%፣ አማራ 20.7%፣ ጉራጌ 4.5%፣ ትግራይ 1.2%፣ ሐረሪ 1.01% ቁጥር አላቸው፡፡ በስፋት የሚነገሩ ቋንቋዎች ደግሞ ኦሮምኛ 46.1%፣ አማርኛ 33.2%፣ ሶማሊኛ 13.4%… መሆናቸውን ይዘረዝራል፡፡ ይሁንና ድሬ በተፃፈው ሕግ እንደ ሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ በፌደራል መንግስት ስር መዋቀሯ ቢደነገግም፣ በገሃድ ያለው እውነታ የሚያሳየው (በተለይም ከምርጫ 97 በኋላ) ኦህዴድና ሶሕዴፓ (የሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) ባልተፃፈ ሕግ በሚፈራረቁበት አድሎአዊና ብልሹ መስተዳደር ውላ-ማደሯን ነው፤ በርግጥም ዛሬ በሥልጣን ላይ ካለው የኦህዴዱ አሳድ ዚያድ በፊት፣ የከንቲባነትና የምክትሉን ወንበር አንድ የምርጫ ዘመንን ዕኩል በመክፈል ሁለቱ ድርጅቶች በየሁለት ዓመት ተመንፈቁ ሲቀያየሩበት መቆየታቸው የሚያመላክተው ዓብይ ጉዳይ ፌደራሊዝሙ በሕይወት ለመኖሩ በ‹ሳይንስ›ም ቢሆን ሊረጋገጥ አለመቻሉን ነው፡፡
በድሬዳዋ የሚታየው ሌላኛው ‹ፌደራሊዝማዊ› ፌዝ፣ ከነዋሪው ሕዝብ ቁጥር ኦሮምኛ ተናጋሪው 46.1% ሆኖ ሳለ የሥራ ቋንቋ አማርኛ መሆኑ ነው፤ ማንነትን በ‹ቋንቋ› የሚወስነው ኢህአዴግ ድሬዳዋ ላይ ተመሳሳይ መንገድ አለመከተሉ (…መቀነቱ ማደናቀፉ) በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚደረገውን ተቋማዊ ጫና የሚያመላክት ይመስለኛል፡፡ መቼም ሌላው ቢቀር እንኳ ቢያንስ ራሱ የቀረፀው ‹ፌደራሊዝም› ሁለቱንም የሥራ ቋንቋ ማድረግ የሚቻልበት በቂ መፍትሄ እንደማያጣ ግልፅ ነው፡፡ ይህ ኩነት ኦህዴድም ልክ እንደ ብአዴን ከተላላኪነትና ቱርጁማንነት ያለፈ የፖለቲካ ቁመና የለውም ወደሚል ጠርዝ ይገፋል (በነገራችን ላይ የአጀንዳው ተጠየቅ በዚህ መልኩ የቀረበው ከራሱ ከኢህአዴግ ርዕዮተ-ዓለም አንፃር እውነታውን ለመፈተሽ ሲባል ነው እንጂ በግሌ የብሔር ፖለቲካ ለኢትዮጵያችን ይበጃታል ብዬ ስለማምን አይደለም)

እንደ መውጫ

ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝሙ ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ እንደ አዲስ ሀገር ማዋቀሪያ አማርጭ ፖሊሲ ተደርጎ ሲጠነሰስ የፌደራሊዝሙ ቅርፅ አገሪቱን ይበታትናል ከሚለው ድምፅ ባላነሰ፣ ደርዝ ያለው ሙግት ሆኖ ቀርቦ የነበረው በሀገሪቱ የረዥም ጊዜ የሕዝብ ለሕዝብ ፖለቲካዊ ግንኙነት በአንድ ቋንቋ ብቻ የሚወሰን ማህበረሰባዊ ቡድን (ብሔር) ካለመገኘቱ ባለፈ፣ ያንን የተወሰነ ቋንቋ የሚናገረው ስብስብ በአንድ በተወሰነ መልክዐ-ምድራዊ ቅፅር ውስጥ አይገኝም የሚል ነበር፡፡ ይህንን ክርክር ከዚህ ፅሁፍ አውድ አንፃር ተጨባጭ የሚያደርገው የጠቀስኳቸው ሁለቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ናቸው፡፡ በሁለቱም ክልል ውስጥ ከኦሮሞ እስከ ትግሬ፣ ከአማራ እስከ ሶማሌ… ከጠንካራ ኢኮኖሚያዊ አደረጃጀትና የየራስ ወጥ መለዮ ጋር መገኘታቸው መልክዐ-ምድራዊውን የፌደራሊዝም ቅርፅ ትክክለኛ አማራጭነት ለማስረገጥ በቂ ማሳያዎች ይመስሉኛል፡፡

ከዚህ ባሻገር የኢህአዴግ ‹ፌደራሊዝም› እንኳን ድርጅቱ ሥልጣን ላይ ባለበት ወቅት ቀርቶ፣ በሕዝባዊ ማዕበል በሚወድቅበት ጊዜም ቢሆን በአንድ ጀንበር መቀየር እንደማይቻል ቢታወቅም ሂደታዊ የእርምት አካሄድ ብቸኛው ፖለቲካዊ ትክክለኝነት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ይህ ፌደራሊዝም የብሔር ግጭትን ከመከላከል በላይ ተራምዶ፣ ሰሞኑን እንዲያ ‹አሸሼ-ገዳሜ› የሚባልለትን በሕዝቦች መካከል አንድነት ሊያጠብቅ ቀርቶ በአግባቡ ባለመተግበሩ (ለምሳሌ በሐረሪና ድሬዳዋ የሚገኙ፣ ነገር ግን በክልሎቹ ስልጣን ውስጥ ያልተወከሉ ብሄሮች) የተፈጠሩት ኩነቶች ወደሰዓት ቦንብነት እየተቀየሩ የመጡትን የተለያዩ ቋንቋ ተናገሪዎች የእርስ በእርስ ትንቅንቆች
መግራት ከማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ ይህ ኩነት “ደግሞ የእዚህች አገር ህልውናን ለመፈታተን ጥቂት ጊዜያቶችን ብቻ መጠበቅ የማይቀር ዕጣ ፈንታ ያደረገው ይመስለኛል፡፡


የተከለከለ ~~ ፍቅር –ሲፈቀር –ይገርም … እኮ! ምን ልበል ታዲያ -. ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 11.12.2013

ፍቅር የትውልድ ዋዜማ ነው።

የመንፈስ ማዕቀብ ሲነሳ የነፃነት ፈል ችግኝ ይበቅላል በዚህ ልጀምረው ….

4568ፍቅር ምንድን ነው? ማድመጥ። ፍቅር ዜማ – ጹዑም! ፍቅር የመንፈስ ጥንግ ሽብሻባ። ፍቅር የስሜት ቃናዊ መዝሙር። ፍቅር የአኃቲነት ብርቅ ወረብ። ፍቅር የመስጠት ለጋስ ፏፏቴ። ፍቅር የታሪክ ማውጫ ፍትኃ – ነገሥት። ፍቅር የውስጥነት ፍውሰት – ድህነት! ፍቅር ጣዕም ንጥር – መረቅ! ፍቅር ብጡል* ክብረት። ፍቅር ምህረት። ፍቅር ይቅርታ። ፍቅር ረቂቅ። ፍቅር ቀጥታ። ፍቅር መሆን። ፍቅር ኃብታም ነው ዲታ። ፍቅር ምህረት ነው ዘንባባ! ፍቅር ወድ ነው ስጦታ። ፍቅር ሩህሩህ ነው ርግብ። ፍቅር ፈውስ የራህብ። ፍቅር ጻድቅ የመስቀል ወተት። ፍቅር የመስዋዕትነት ጤና አዳም። ፍቅርን ሲሰጡ ሊፈቀሩ የሚችሉ ፍጡራን ፍቅርን ሲከለከሉ ደግሞ ማመጻቸው አይቀሬ ነው!  ይፈነዳል።

ዋ!

እናት ከሁሉም በላይ ትውደዳለች። እናት የመጀመሪያዋ የህይወት ትምህርት ቤት ናት። እናት መቅድመ የቤተሰብ አሰተዳዳሪ፤ የተፈጥሮ ሙሁራ ሊቀ-ሊቃውንት የርህርህና መግቢያም።  እናት ደግሞ ሴት ናት። እኔ በዓለም ደረጃ የፍቅር ምልክት ወይንም ዓርማ ሊሆን የሚጋባው ልብ ሳይሆን እናት ነው መሆን ያለበት። ስለምን? እናት ልልጇ የምትሰጠው ፍቅር የማያብል ነውና። እውነተኛ የፍቅር ተፈጥሮ የሚገኘው ከስፖርት ማልያና ከእናት ብቻ ነው። እናት የሥነ ፍጥረት ሙሉዑ አጀንዳ ናት! እናት የመንፈስ ቋንቋ ናት!  ዬዓለም ተወዳጁ ሥም እማማ!

 

እስኪ ወፍ ካወጣን አብረን … ወደ ተለምኩት ብያለሁ፤ ቀልቤን ወደ ገዛው፤ ሩኼን ወደ ዳኘው። ጉዞ በጋራ መልካም ነው። ኑሮም በወል ጣዕሜ ነው። … ሴት እህት ስትሆን ትፈቀራለች። ሴት አክት ስትሆን ትጠጋላች። ሴት ሚስት ስትሆን እንደ ነፍስ ትታያለች። ሴት ጓደኛ ስትሆን ትታመናለች። ሴት እናት ስትሆን የጸጋ ስግደት ይሰገድላታል። ሴት ይሁን ይሁን … አሜን አሜን … ስትል ….. ሰጥ ለበጥ ብላ ስትገዛና ስትረገጥ …. ስትመች ትመረቃለች ….

 

እኔ እንደማስበው በእምነቴ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አምስቱ አዕማደ ሚስጢራት ላይ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልዑቅ ነገረ ሳይመር መቅረቱ በጣም ይጎረብጠኛል። እንደሚገባኝ ከሆነ ግን የተዋህዶ ልጆች ለቅድስት እናታችን ባለን ፍጹም ልዩ ፍቅርና ስስት ከጸጋ ስግደት ይልቅ የአምልኮ ስግደት ይገባታል ብለን እንዳንሟገት ብልሆቹ አቨው አስበውበት፤ ምንአልባትም መንፈስ ቅዱስም አቀብሏቸው ወይንም ሚስጢር ገልጦላቸው ሊሆን ይችላል። ለማንኛውም ከመንፈሳዊ ዓለም ወጥተን ወደ ገኃዱ ዓለም ስንመጣ … በፖለቲካ አስተሳሰብ ሴት ላቅ ስትል ግን „ጉልበታምንት“ ይለጠፍላታል። በጠራ ቋንቋ „ጉልበታም“ ትባላለች። ገና ሳትታወቅ እፍታ መስመር ላይ እኮ ነው …. ልደቷን ሳታከብር የምትገፋው – ገምድልንት* የተከለከለ ፍቅር ይሏችኋል ይህ ነው። ቁስለት!

 

ሴት ረድ ስትሆን ትወደዳላች። ሴት ሎሌ ስትሆን ትደነቃለች። ሴት የቤት ውስጥ ሰራተኛ ስትሆን ስንዱ ትባላለች። ሴት ጠቅልል ጠቅለል አድርጋ ስታጎርስ የራህብ ደራሽ ትባላለች። ሴት ጓዳ ጉድ … ጉድ ስትል ዓይን አብሮ ይዞራል። መንፈስም አብሮ ይንከራተታል። ልብም ዳንኪራውን ያስነካዋል ስሜትም አብሮ ይከትማል። ፍቅሬ ወ/ሮዬ ትባላለች። ዓለም የፈጠረው ቄንጠኛ የዘነጠ ሥያሜ ሁሉ ይሰጣታል። ሴት እንግዳ ስታስተናግድ ትመሰገናለች። ሴት ልጅ ስትሰጥ በዓይኔ ላይ ፍሰሺ ትባላላች። ሴት ስልጣን ልትጋራ ብቅ ስትል ግን „ኃይለኛ“ ተብላ ትኮረኮማለች ወይንም ትባረራለች። ሌላ ድልዝ ይፈልግላታል። ሌላ የሰብዕናዋ ድክምት ቁፋሮ ይጀመራል።  የተከለከለ ፍቅር … ጎባጣ

 

ሴት ገንዘብ ያዥ ስትሆን ትመረጣለች። ሴት ገንዘብ ስትሰበስብ ታማኝነቷ ይሰበክላታል። ሴት እልፍኝ ስታሰናዳ ትሞካሻለች። ሴት ስነጥፍ ወይንም ስነጠፍ እንደ ብርቅ ትታያለች። ሴት ቅራኔ ውስጥ ገብታ ስተቀረቀር ይጨበጨብላታል። ሴት መድረክ ላይ ወጥታ አቅም ባላው ብቃት በፍፁም ታማኝነትና ግልጽነት እኩል ስትመጥን አቅሟን ለአደባባይ ስታበቃ ግን በግሳፄ ትባረራለች ….. ድገም ሳትል ከቢጫው ቀዩ ካርድ ቀድሞ ያለ ማስጠንቀቂያ ከጨዋታ ውጪ ትሆናለች። ነዳላ ገጠመኝ። የአንተ ያለህ ….

 

ሴት ስትለብስ ትፈቀራለች። ሴት ስተሸቀረቀር እንጉርጉሮው ላቅ – መጠቅ ይላላታል። ሴት የተፈጥሮን ፍቅር ስትመግብ ንቢት ተብላ ትሞገሳለች – ትመገባለች – ትጎረሳለችም። ሴት ሽክ ብላ ከጎን ስትጓዝና ግብዣ ላይ እኩል ስትቀመጥ አጃችን* ይሞላል ልጎዝጎዝልሽ ነው። ሴት ገብያ ወጥታ ቀጨር መጨሬውን ስትሸማምት አበጀሽ ትባላለች። ሴት ኮስሜቲክስ ስትገዛዛ ውዳሴ ይነጠፍላታል።  ሴት ወንበርን ልትጋራ ጥንካሬዋን ስታስመከር ግን ትገፈተራለች …. ቆመጥ ይዘጋጅላታል ….. የተከለከለ ፍቅርነቀዝ!

 

ሴት ቤት ስትውል፤ እንደ እመቤት ትታያለች፤ ጨዋ የተረጋጋ መንፈስ የረበባት እዬተባለ ይሰበክላታል። – ደስታ ነዋ ስታፎከፉክ። ሴት አንገቷን ደፍታ መከራን ስትቀበል ቅኔ ይዘረፍላታል። ሴት የልጆች አሳዳጊ ብቻ ስትሆን ትበረታታለች – ትሸለማለች። ሴት በማይታዩ ሩትን /ጥቃቅን/ ተግባራት ስትሰማራ ማን እንደ አንቺ ትባላለች። ሴት አንደበቷ ታስሮ የሳሎን ጌጥ ብቻ ስትሆን ማለፊያ ይባልላታል። ሴት ግን ኃላፊነትን እኩል ለመጋራት ጠበቅ ጠንከር ብላ ብቅ ስትል ጦር ይሰበቅባታል።  ያደገ ወይንም ያልተነካ ድንግል ወጥ ሃሳብ ወይንም ግኝት ወይንም ላቅ ያለነ የቀደመ ግንዛቤ  ስታፈልቅማ እሷንማ በሽታሽቶሽ* መውቃት።የተከለከለ ፍቅር …. ምግለት!

 

ሴት ስትጋግር … ስትሰራ …. ስታጥብ … ልብስ ስትተኩስ፤ ስታረግዝ …. ስታጠባ …. ከሚፈለገው ቦታ ላይ ተገኝታለችና ይዘፈንላታል። ከዚህ አለፍ ብላ የመብትና የእኩልነት ጥያቄ ስታነሳ ግን ትወረወራለች …. እውነት ለመናገር በዘመናችን ያሉ ሴቶች እንኳን ጥቃ ሊቆምላቸው፤ እንክብካቤ ሊያገኙ ቀርቶ ገፍተው የሚወጡት በጣም ጥቂቶች ለምነው ለመታገል እንኳን ፈቃድ አያገኙም በወንድ ትምክህተኞች …. ዛሬም ከዛሬ 100 ዓመት በፊት ካላው ኮረብታ ላይ እንዳሉ አሉ እነ ተባዕት …. ከእነ- የወንድ የበላይነት ተጫኝ ስሜታቸው ጋር ተጋብተው። ስለ ሴቶች ብዕራቸው በተቆርቋሪነት የሚቃኙት ከአንድ ለእናቱ  ሙሁር ከፕ/ አለማዬሁ ገ/ማርያም በስተቀር …. ፕሮፌሰሩ ከክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ጋር በመገናኘታቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐሴትም አድምጠናል። ረስተውንም አያውቁም – ቅርባችን። ስለ ሴቶችን በሚያጠቃው የካንሰር በሽታ በተቆርቆሪነት የጻፉት ልብን የሚነካ ነበር። እውነት ልዩ አብነት ናቸው – ለእኔ። ድህነቴ እንጅ ለእሳቸው የምስጋና ቀን ባዘጋጅ ዕድለኛ በሆንኩ ነበር።

 

በፍጹም ሁኔታ የነፃነት ትግሉ ሆነ፤ ነገ የሚታሰበው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሰረቱና እርገቱ ከሴቶች ውጪ ሊታሰብም ሊሳካም እንደማይችል በጣም በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። የነፃነት ትግሉ የሴቶችን ሙሉዑ ተዋፆ በአጽህኖት፤ በተደሞና በአርምሞ ይጠይቃል። መደመጥ አለበት። አጥበቆ! አኔም የጥቃቱ ማዕደኛ በመሆኔ …. በልበ ሙለነት እጥፋለሁ … እንዲህና እንዲያ … ትርፉ ትራፊና ፍርፋሪ ካልሆነ ….

 

ይህቺ ለመላሾ እነ ተባዕት „ ቦታ አካፍለናል“ የሚሏት …. ልጥፍ ሽፋን ልግጫ ለማንም አይበጅም - ነገንም አያበጅ። የዶደመ …. መንገድ ነው። የነፃነት ትግሉ ሙሉዑነት ሊረጋገጥ የሚችለው የሴቶችን የመጠነ፤ ያስተዋለ፤ ያደመጠ፤ ያከበረ ተሳትፎ በቅንነት ተግባር ላይ ዛሬውኑ ሲያውል ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን ካላት ያልተነካ ቅምጥ ዕምቅ ኃይል በላይ የሴቶች ሃብት እስከ ዛሬ ድረስ ሥራ ላይ አልዋለም። … ነገም ከፍቶት ይታዬኛል።

 

እርግጥ ማሳሳቻ አስፓልት አለ። „የሴቶች መምሪያ ከፍተናል … ጉዳያቸውን የሚከታተል መዋቅር ዘርግተናል“ … ይህ የሴቶችን ብቃት የሚያቀጭጭ አፋኝ የማስመሰያ ጅራፍ ነው። በአንድ ወቅት ፕ/ መራራ ጉዴናን አበክሬ እጠይቃቸው ስለ ነበር ንገሩልኝ የሴቶች መምሪያ በድርጅቴ መጀመሬን አሉ። የዛሬ 14 ዓመት መሆኑ ነው። አሁንም እሳቸው ከያዟት ቁልፍ ቦታ ግን ፈቀቅ አላሉም። ጨምድደው ጉብ ብለው ይለፉንም ዘግተው አሉ እንደ አገዱ። ይህ ትልቅ ግድፈት ነው። የእኔ ሙግት የነበረው በ2ኛው  የኢተፖድህ ጉባዔ ከዬትኛውም አባል ድርጅት አንድም የአንስት ውክል አካል ልትገኝ ደረጃዋ ባለመፍቀዱ ነበር – አበክሬ እናገር የነበረው።

 

ዘግይቶ የዛሬ ዓራት ዓመት ገደማ መደረክ ሲቋቋም አዬነው በመላጣ – ጎብጦ የሴቶችን እኩልነት በባዶ ቃላት ተለብጦ። ያው ቢገላበጡም ጃኬቱም ቢቀያዬር የተባዕት ክምር። የድርጀታቸውም አቅም … የወንዶች ብቻ – ቁልቁል። ይህ ለናሙና እንጂ በሽታው ሁሉንም ያካልላል። ከእከሌ ድርጀት እከሌ ይሻላል ብዬ ውዳሴ ባቀርብ የሴትነቴ ክብር ይዘቅጣል። ሴትነቴ ካለይግባኝ ዘቅዝቆ ይሰቅለኛል። ተፈጥሮም ፊቷን ታዞርብኛለች። አምላኬም ከልቡ ያዝንብኛል። ሃቁን ለከንቱ ውዳሴ ብሸብብ።*

 

በማናቸውም ዘርፈ እኔ ነኝ ባለ ወሳኝ ኃላፊነት ሁሉ ሴቶች ጉልበታም አቅም አላቸው። ለዛ የሚመጥን ቦታቸውን አትጋፉ ነው መሰረታዊ ትግሉ። አጽህኖታዊ መጠዬቁም። እድሉን ያገኙ ሴቶች ተዝርክርኮ ሳይሆን አምሮና ሰምሮ፤ በጥራትና በጥንቃቄ እንዲሁም በስልትና በብልኃት ሁለመናው ያምርበታል። ሴቶች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚተጉት …. በእናትነታቸው ፍጹም የማይታይ ሰማያዊ ጸጋ አስውበው ነው። ምቹ ሁኔታ  ካገኙ፤ በቂ እንክብካቤና ጥበቃ ለመክሊታቸው ከተደረገ …. ማን ችሏቸው። ያኮራሉ! ተወዳዳሪም የላቸውም። ሚስጢር ይመሰጠራል። ትርጉምም ይነበባል። ተፈጥሮም ይዘክራል። የሰብዕዊ መብት አከባበርም ጽኑ ባለሟል ሲገኝ በደስታ ይፍለቀለቃል። እኔ እላለሁ ሴቶች የተፈጥሮ ድንጋጌ ናቸውና።

 

አውሮፓ ያላችሁ ሁሉ እንደምትከታተሉት አውሮፓ በኢኮኖሚ ውጣ ውረድ ተሰቅዞ ሲባትልና ሲብተለተል የመፍትሄው ጭንቅላት የተገኘው አንፃራዊ በሆነ ሁኔታ ማለቴ ነው ከጀርመን ነበር። የጀርመኗ መሪ ጠ/ሚ ወ/ሮ አንጅላ ሜርክል ቀጥ አድርገው በማያዝ ማገር ሆነው አውሮፓን ከውርዴት ዘመኑንም ከጥፋት ታድገውታል። ጠ/ሚር ሜርክል ፓን አውሮፓኒስት ናቸው። በተግባር የከበሩ የመጀመሪያዋ የጀርመን ተወዳጅ ሴት መሪ ናቸው። እርግጥ ከዚህ ጋር ያሉ ከፈረንሳይ ጋር የተሳሰረ ትብትብ ቢሮክራሲን  ዘልዬ …

 

ለናሙና …. የእንግሊዟ ታችር፤ ንግስት ኤልሳቢጥም፤ ተፍርተው በአጭሩ ተቀጩ እንጂ ልዕልት ዲያናም አሳይተዋል አስመስክረዋል … ያን ጉልበታም ተዝቆ የማያልቅ ብቃት …. ከብልህነት ጋር። ይህ በኒውዘላንድ፤ በአውስትራልያ፤ በፊላንድና በብራዚልም ተመሳጥሯል። ሲዊዘርላንድ በሰባት ሰዎች ትመራለች። አራቱ ሴቶች ናቸው። ያውም ቁልፍ ቁልፍ ቦታ የያዙ … በጀርመን ካለፈው ወራት ሀገራዊ ምርጫ በኋላ ያለውን ሽግሽግ አልተከታተልኩትም እንጂ ቀደም ባለው ጊዜ በርካታ ሴት ሚ/ራት ነበሩ …. የእውነት አባዛኞቹ ሴቶች በማለት ብቻ የሰከሩ አይደሉም። እናታዊ ሥነ -ምግባራቸው አይፈቅድላቸውምና! ይልቁንም በመሆን የበለጸጉ እንጂ …..

 

በዓለም በፈጠራ፤ በሳይንስና ምርምር፤ በሰብዕዊ ተግባር፤ እንዲሁም በሥነ – ጥበብ የበርካታ ምርጥ ዕንቁ ሴቶችንመዋዕለ ተጋድሎ፤ የያዘው የኖቤል ተሸላሚ ሴቶችን አስኪ ገድሉን ጎብኘት አድርጉት ….  እኔ በመንፈሴ እማማ ዊኒን፤ ሜርክልን እያጨሁ ነው። ብቁ ናቸዋ። በዬዓመቱ ከሲኤንኤን ጀግኖች ሴቶችም እኩላዊ ብቃታቸውን ለአደባባይ አብቅተዋል። እርግጥ እዬታፈኑ፤ ሳይታዩ እንዲጠፉ እዬታደመባቸው፤ እንዲከስሙ የተዘመተባቸው፤ እንዲሁም አስታዋሽና ጠበቃ ያጡት ሚሊዮኖች የነጻነት ሴት አርበኛ፤ የሥነ ተፈጥሮ ሁነኛ፤ የሥነ ጥበብ እማ ወራ … የፈጣራ ቀንዲል ዕልፍ ናቸው። የዓለም ብቁ ዜጎች ሴቶች መሆናቸው ምንም ለድርድር የሚቀርብ አይደለም። በአግባቡ ተከታታይና ባለቤት ቢኖረውማ …. በቁጥር ይበልጡም ነበር – በሁሉም ዘርፍ።

 

ለሁላችንም የሚጠቅም ስለሆነ ደግሜ በመፃፌ እንደማላሰላችሁ በማሰብ በዘመነ ክሊንተን ያን የዓለም ስሜትን የሳበ የፕ/ ቢል ክሊንተን ተብዕታዊ ቅብጠት ብልኋ ባለቤታቸው እመቤት ሄነሪ ክሊንተን የሆነውን እንዳልሆነ አድርገው ትቢያ አልበሰውታል። በወቅቱ አንድ የፕሬስ ሰው እንዲህ ሲል ጠይቋቸው ነበር … „የሚባለውን አልሰማሽንም? … አላነበብሽውንም?“ ሲል ብልኋ እመቤት ግን መንፈሱ እንዲህ ነበር „ እናቴ ከልጅነቴ ጀምሮ ያስተማረችኝ ሰው የሚለኝን ከሰማሁ የምሰራው የሰወችን እንጂ የእኔን እንዳልሆን ነግራኛለች፤ አስተምራኛለች። መርሄ ይህ ነው። እኔ የኔን ሥራ እሰራለሁ ሌሎች ደግሞ የራሳቸውን ይሰሩ“ ነበር ያሉት። ሰማዬ ሰማዬት የዘለቅ ዕጹብ መልስ ነበር። በዚህም ትዳራቸውን ከነዙፋኑ ሀገራቸውን ከነአልማዙ እስከብረዋል። አንስትን የወከለ ማለፊያ ብቃት!

 

ከዚህም በኋላ በዘመነ ፕ/ባራክ ኦባማ የውጭ ጉዳይ ሚር/ ሆነው እጅግ ውስብሰብና ፈታኝ በሆኑ መሰናክሎች ሁሉ በማለፍ የሴቶችን የመወስን አቅም በተግባር አሳብበውታል አሁንም የፕ/ ባራክ ኦባማ ባለቤት ቀዳማይ እመቤት ሚሻዬል ኦባማ ሁለገብ ንብ በመሆን ባለቤታቸውን ለሁለተኛ ጊዜ የሥልጣን ባለቤትነት አብቅተዋል … ለዚህም ደረጃ ያበቋቸው ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ሚሻዬል ናቸው። ነገም ለፕሪዚዳንትንት እራሳቸውን ችለው ሊወዳደሩ ይችላሉ። ተወዳጅም ናቸው – ወ/ሮ ሚሻዬል። ወንድሞቼ ሆይ! የነፃነት ትግሉ መሪ አባ ወራዎች ሆይ! ዓይን ካላችሁ ከዚህ ሀቅ ጋር የመንፈሳችሁ ብሌን ይታረቅ ዘንድ ብዕሬ በጽሞና ያሳስባችኋል … በአክብሮት – በትሁት መንፈስ።

 

በአፍሪካ ታሪክ ጉልበታሙ የፕ/ ማንዴላ ተገዳሎ የምዕተ ዓመቱ ታላቅ መዘክር ነው። ሚሊዮን ሰማዕት ሴቶች ታድመውበታል። በፆታዊ ችግር አፓርታይድ ያሴረውን መረብ ዝለሉትና ክብርት የነፃነት ብቁ አርበኛ እማማ ዊኒ ማንዴላ ባላቤቷ እስር ቤት በነበሩበት ጊዜ የነፃነት ትግሉን በግንባር በመምራት፤ ልጆቿን በማሳደግ፤ ለትዳር አጋራ አጥር ቅጥር በመሆን የጽናት ወተት ነበረች። ይህን ከባለቤቷ ጋር ትጻጻፍ ከነበረው የነፃነት ትግሉ ዋነኛ ትምህርት ቤት ዝክረ ደብዳቤዎች ማገናዘብ ይቻላል። ህያው ምስክር ነውና። ሁሉም ፍጡር እናቱን የሚወድበት ሚስጢር በሀገር ጉዳይ ላይ ቢውለው ምንያህል ፈውስ በነበረ – ለመለውዓለም። የ ዓለም ዝበርቅ አስፈሪ ውጣ ውረድ ፍቺ ያለው ከሴቶች ነበር … ባሊህ አጣ እንጂ …

 

በእኛዋ እናት ሀገርም … በቀደመው በዘመን ንግስት ዘውዲቱ የመቻልን ተፈጥሮ፤  ከእቴጌ ምንትዋብ የተግባር ሚስትነትና አርበኝነትን፤  ከከዕቴጌ ጣይቱ ብልህነት – ፖለቲካ መሪነትና አማካሪነት – ጠበብትነትና ጀግንነትን ጠብተን አድገናል። በዘመናችንም … ሳራ ግዛውና ሺብሬ በሰማዕትንተ፤  አያልነሽ – አለምዘውድ፤  ብርቱካን ሜዲቄሳ፤ ሰርካለም ፋሲል፤  ርዕዮት ዓለሙ፤ በላይነሽን ስንቶቹን የነፃነት አርበኞች እናት ሀገራችን አፍርታለች። መሬታች መሃን አይደለም። ተሳትፎውን በጉልበት ያነጠፈው* ያንጠፈጠፈውም የወንድ በላይነት ብቻ  ነው። አሁንም  በአንድነት ወ/ት ወይንሸት የምትሰጠውን ቃለ ምልልስ አኑትና አጣጥሙት …. ያው ታች ስለሆነች ቅጥቀጣው ያልፋታል ብዬም አስባለሁ … ቀና ካላች ግን ቅንጧን ነው … በለመደ እጅ … እህህህህህ!

 

እኔ … በአጽህኖት እናገራለሁ። የፖለቲካ መሪዎቻችን የውስጥ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል። በፍጥነት። በንግግራቸው ውስጥ እንኳን ብጣቂ እርስት አልተሰጠነም። እንኳንስ በፍላጎታቸው ልብ። በራዕያቸው አንጎልም የለንም። አብሰንት ነን።  ምንአልባት ትዝ የምንላቸው የራባቸው ጊዜ ይሆናል። ለነገሩ ነጭ ሀገር ፋስት ፉድም አለ … ዘመኑ ተለውጦ እራስም ይጋገራል … ሀገር ቤትም ተለምዷል አሉ … የጓዳ ነገር። እንዲሁም በዬአጋጣሚው የሚሾሟቸው አብዛኞቹ የበታች ገዢዎቻችንም ለውጡ ገፍቶ እንዲያነጥራቸው እንሻለን። አቅም በመበተንም አንቱ ናቸውና! ይደግም። የበታቾቻቸው አቅም በመበተን አንቱ ናቸውና!

 

የበላዮች የበታቾቸውን የሚከታተሉበት መስመር ቢኖር መልካም ነው። የጉሮሮ አጥንቶች እነሱ ናቸው። የፓለቲካ አመራር ልም ነው። ጣጣውን የጨረሰ ለስምሪት የበቃ ንጥር ቅቤም፤ ለስምሪትም ስንዱ። እኔ የማዬው ዘመንተኛው ፖለቲካ ግን ሽርክትና ግርድፍ ሆኖ ነው። አብሶ አጋርን በመገፍተር እረገድ ከንፍሮ የወጣ አንድም መሪ አልገጠመኝም። ቆሞ ስለ አርበኛ አንስት የሚመሰክር ዓይናችን አላዬም …. እንደናፈቃቸው ይቅር ዓይነት ነው ነገሩ …

 

እርግጥ ነው ሥር ላይ ያለው ተግባርን የሚያደምጡት፤ ከበታቾቻቸው ለዛውም ስታስቲክሱን በሩቁ ነው። ያው ወያኔ ባላው የተዛነፈ ዳታ ይወነጀላል። የኛም እኮ ያው ነው። ከታች ወደ ላይ የሚተላለፈው ቁጥር ተብዬ። የበቃ ፍጽምና ያለው ተሳትፎ …  ለማዬት ወረድ ይበሉ። ሰፊ መድረክ ይክፈቱ። የትችት አንባ ይወጁ። እንዲያድጉ እንዲመነደጉ ከፈለጉ። … በራስ አነሳሽነት የሚደረገው የፈጠራ ተሳትፎም እምብዛም ነው። ሁልጊዜ ከላይ የተንጠለጠለ መና ይጠበቃል። የማኒፌስቶውን ጭብጥ ይዞ ጭብጥን በጭብጥ አፋጭቶና አታግሎ የነጠረውን የፓርቲያቸውን አቋም አሸናፊ ለማድረግ ፈጠራ ከአቅም ጋር ይጠይቃል። ማረር!

 

ያው ቁንጮቹ የሚሉትን በተገኘው አጋጣሚ የጎረሱትን እዬፈቱ ሲደግሙና ሲሰልሱ ዓመት ይዞ እስከ ዓመት ከዛው ለዛው ሲዳክሩ ነው የሚታዩት። ተመስገን ነው ዛሬ እድሜ ለኢሳት በተለያዬ መድረኮች መሰናዶ ከሊቃኖች አዳዲስ ነገር ስንቅ ስለሚገኝ ተሽሎ ሊሆን ይችላል። ግን የራስ ጌታ ለመሆን ማንበብ መልካም ነገር ነው። የዬትም ሀገር ነፃነት ትግሎች ለድል እርከን ያደረሱት አጋራቸውን በበሰለ ህሊና ባሊህ ብለው ነው።  … እርግጥ ላይኞቹ ሴቶች ማለት ሲጀመሩ የታችኞች ቅጂውን እንደ ገደል ማሚቶ ያስተጋቡታልና እባካችሁ ላይኖቹ ጀመሩት …. ግን በተለበጠ መልኩ ሳይሆን ቁምነገር ባለው ዕውነት – ከልብም። ዝም ብሎ ከሆነ ልጥፍ ይሆንና የተላመጠ አገዳ ይሆናል ምኖታችን።

እኛ እንላላን። እኔና ትዳሬ ብዕሬ …. ተከታታይ የሆነ አቅም ያለው የመንፈስ ጥሪት ለመገንባት ይሞክሩ ፖለቲከኞቻችን ….፤ ሙሁሮቻችን። የሴቶችንም ነገረ ሚስጢር አክለው …. የሃይማኖት አባቶቻችን ሲያሰተምሩን „ነገረ መለኮትን“ ነጥለው ሳይሆን „ከነገረ ማርያም“ ተነስተውአስቀድመው እነሱ በቅድሰት ድንግል ፍቅር ቅጥል እያሉ ነው። የእናታቸው ፍቅር ግብግብ እያደረጋቸው ነው። እኛም እንደ እነሱ ሆነን እናታችን የማናሰነካው – ተከተል አባትህን ሆኖ ነው። የድንግል ነገር የሁለመናችን ገዢ የሆነውም በዚህው ቅኝት ተቀረጽን ስለሆን። ማለት ለተዋህዶ አማንያን። አሳምረው ጠረቡን። መንፈሳችን በቅዱስ መንፈስ ገሩት ነው። ያኑርልን ሊቀ – ሊቃውንቱን። የቅድስትን የመንፈስ ድንግልና ፍቅር በማያልቅ ወተት አጥብተው አሳድገውናልና። በሥጋዊ ፍቅርም ቢሆን ፍቅር ድብን አድርጎት እያለቀሰ ከልቡ የሚያዜም ከልብ ጠብ ይላል … በስተቀር ድው የለ ትም  ….

 

ይህ ትግል የሚባለው ጀግና … አርበኛና ሰማዕት …. ድሆኖው* ጉድሎበታል፤ ጎታው* ተራቁቶበታል ታላቅ ነገር ቅናዊ ዕይታ፤ ሥልጣንን የማጋራት ግልጽነት፤ ኃላፊነትን በቅመም የመመጠን ሥልጡን ዕይታ። ትርጉም ያለው ተግባራዊ እርምጃ ከኢትዮጵያዊነት መሪዎች በአጽህኖት ይጠበቃል።  እኩላዊ መስመር ሳይፈጠር አሯል። አይታይም። የመከነ ጉድ ነው …. በዬትኛውም ሁኔታ በቦታው የሌለ ነገር ቢኖር ሴቶችን  በአክብሮት እኩል ለማሳተፍ ያለው ፈቃደኝነት ልሙጥ መሆኑ ነው ድርቅ የተጫወተበት፤ ዝናብ ሲሄድበት የከረመ አለት የመሰለ ለዛ የለሽ ጉድ። በጣም በረቂቅ ሁኔታ በሴቶች ላይ የተጣለው ማዕቀብ ዘመንና ጊዜ ይፈታዋል የሚል ግምት የለኝም። የተሳሳረ ድንቡልቡል ነገር ነው። በሩ ተቀርቀሯል። ጭላንጭል መተንፈሿ ቧንቧው የታነቀ ነው ….  ለዛውም እኮ ቆርጠው የሚወጡት ጥቂት ሆነው እነሱን እንኳን በአግባቡ ለመያዝ ምንም …. ታውቃላችሁ?! ምንም ነው 00000 በቅናሴ ያለ … ተቋም ቢኖር …. የሴቶች የእኩልነት የተሳትፎ መድረክ ድርሻ ምክነት።

 

ህይወት ካለሴቶች ኮረኮንች — አመዳም — ቡላ —- የፋደሰ —- ቀዝቃዛ — የነፈዘ —– ነው የተፈቀፈቀ። …. የትግሉም ዕጣ ፈንታው ይህ እንዲሆን ተገምድሎበታል። ይፍታህ በሉት! ነይልኝ — ነይልኝ — „የህይወቴ ህይወት“ ለዚህ ብቻ  … ። ትውልድን በአዲስ የተሳትፎ ፖለቲካዊ ባህል ለመገንባት ዳገት። ታሪካዊ ድርሻን ለመወጣት ክትከታ። የምንፈለገው ለአጃቢነት ወይንም ጥላ ለመያዝ ወይንም ለዘበኝነት ብቻ። ደንበር ሰበር ለሆነ ለሚመጥን የሥልጣን ክፍፍል ወይንም ተደማጭነት ማነቆ – እገዳ – ክልከላ … ሰባራ ጉድ፤ …. ጨምዳዳ ….. ዕጣ። የተሸበሸበ … ራዕይ። ሽራፊ …. ህልም። ያመለ … ነገ። የሻገተ … ተስፋ። ያልተጠረገው መንገድ ረቂቅ ሚስጢር ይህን ይመስላል። መፍትሄው ለዛሬ አዲስ መኃንዲሶች፤ እራሳቸውን የዘለሉ ሙሴዎች ያስፈልጉታል … ይመስለኛል።

 

እናሳርገው። ….. የምቀኝነት በሽታ ያለባቸው ድውያን በዬአጋጣሚው ያፈኑት ነገር መተንፈሻ ከሌለው አጉል ቦታ ይፈስና ብዙ መስመሮችን ይበርዛል። „ልብ ያለው ሸብ“ ብለናል … ከብሂሉ ጋር እርገት ይሁን። እኔ ምን እንደሚናፍቀኝ ታውቃላችሁ ዓይነታ የወጣለት መሪ … ደፈር ብሎ ስለ ሴቶች …. ጥብቅና አጋፋሪ የሚሆን ሊጋባ። የነፃነት እልፍኝ አስከልካይ ሀቀኛ ዓራት ዓይናማ። ሴቶች ብዙ አላቸዋ። ያጡት ያላቸውን የሚያቀኑበት ገብያ ብቻ ነው ….. ግጥም ታውቃላችሁ … ቅኔዊ። እንደ ግጥም የልብን ድርስ የሚያደርጉ ምርጥ ፉጡራን ናቸው አብዛኞቹ ሴቶች። እርዳታቸው – ፈጣን፤ ምክራቸው የልብ አድርስ፤ ጽናታቸው ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ፤ ፍቅራቸው የትውልድ ዋዜማ፤ ሥልታቸው ሥልጡን፤ ብልህነታቸው ተጨባጭን የዋጠ። ጉዟቸው ደፋር።

 

ሳልሄድበት የማልፈልገው ጥምዝ መንገድ ደግሞ ሌላው አጋር ለአጋር መገፋፋቱ ነው። ይህ ደግሞ ለአንስት የእኩልነት አንባ የከፋው ዕጣ ነውና ለአጋራችን እኛው አጋር በመሆን ጥጓ እንሁን። ብቃቷን ለመመስከር አንደበታችን እንፍታው፤ ለሴት እህታችን ብቃት ዋቢ እንሁንላት። ለሴት እህታችን ተጋድሎ ቀድመን እንገኝላት – ከጎኗ።  ለዘንካታ ትዕግስት ሞንሟና ምስጋና እንሆ!

 

ሴቶች የነፃነት ትግሉ ዓርማ ናቸው!

ሴቶች ለነጻነት ቅኔ ናቸው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

መፍቻ

 

  • አጃ የልብ መደረስ፤ ከጠበቁት በላይ መርካት።
  • ቅንጧን … ቅንድቧን …
  • ብጡል የተለዬ … የተመረጥ …
  • መገምደል … ፍትህን የጣሰ ፍርድ።
  • ያነጠፈው …. ያደረቀው … ምደረበዳ ያደረገው …. ድርቅ ያስመታው … ለዘር ያላበቃው ….
  • ሽታሽቶ  …. እያረፉ፤ በፈረቃ በድርብ …. ማድቀቅ …. ማጥቃት ….
  • መሸበብ … መሸፈን … መጋረድ … እንዳይታይ ማገድ …
  • ድሆኖ … ከጭቃ የሚሰራ መሰል ግጣም ያለው የእንጀራ መያዣ … ሌማት፤ ወይንም ጥራር እንደማለት
  • ጎታ … ከጭቃ የሚሳራ ትልቅ የ እህል መያዣ … እንደ በርሚል ….

 

 

«ድምጽ አልባው አሳዛኝ የወገኖቻችን ለቅሶ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ!»

$
0
0

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መዝናኛ ክበብ ሰራተኞች ሰንደቃላማችን በተሰቀለበት ግቢ ግፍ እና በደል እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ

በኢትዮጵያን ሃገሬ ከጅዳ ዋዲ

በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ሁለት የጸጥታ ጥበቃዎችን ጨምሮ ከ13 በላይ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በስሩ እንደሚገኙ የሚነገርለት ይህ የመዝናኛ ማዕከል ከተቆርቆረ ሁለት አስርተ አመታትን ቢያስቆጥርም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶች ከትርፋማነት ይልቅ ኪሳራ፤ ከእድገት ይልቅ ውደቀትን እያቀነቀነ አሁን ላለበት ደረጃ መድረሱን የሚናገሩ እማኞች በሰራተኞቹ ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል ከመቸውም ግዜ በላይ እየከፋ መምጣቱን ገልጸዋል።
saudi 1
ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ካፍቴሪያ ማዕከል ዛሬ ላለበት አሳፋሪ ደረጃ ምክንያት መሆኑ የሚነገረው በተለያዩ ወቅቶች በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጀርባ ታዝለው ያለችሎታቸው አመራር የሚሆኑ ግለሰቦች ከኮሚኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች ጋር በቅርበት ተነጋግረው የካፍቴሪያውን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ከማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ እና ስርአት ውጭ በብሄር ተከፋፍለው እርስ በእርስ በመጋጨት በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ተላላኪ እና አፋሽ አጎንባሽ በመሆናቸው መሆኑንን ይጠቅሳሉ። የኮሚቲው አመራር አባላቶች ዲፕሎማቱ በሚሰጧቸው ትዕዛዝ እንደሚንቀሳቀሱ የሚናገሩ ምንጮች ከ10 አመት በላይ ያለ ደሞዝ ጭማሪ ደፋ ቀና የሚሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን መብት በመደፍጠጥ ፍሬ ፈርስኪ በሆኑ ጉዳዩች ተጠምደው «ሲሻም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል እንዲሉ» በተለያየ አቅጣጫ የወጪ ቀዳዳዎችን በማበጀት ወደ ማህበሩ ካዝና ዲፕሎማቱ እጃቸውን እንዲሰነዝሩ በመጋበዝ በሚፈጸም አስነዋሪ ተግባር ለኮሚኒቲው ውድቀት ግንባር ቀደም ምክንያት መሆናቸውን አክለው ይገልጻሉ። በዚህም ምክንያት የኮሚኒቲው ካፍቴሪያ በየአመቱ ኪሳራ አሳይቷል እየተባሉ አንገታቸውን እስከዛሬ አንገታቸውን ለመድፋት የተገደደዱት የኮምኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ተከትሎ ከዛሬ 10 አመት በፊት በተቀጠሩበት ደሞዝ የስደት አለሙን ህይወት መግፋት ተስኗቸው ለከፍተኛ ችግር በመዳረግ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሳውዲ አረቢያ ምድር በባዕዳን የሚፈጸምብን ግፍ እና ስቃይ ሳያንሰን ባዲራችን ከፍ ብሎ በሚውለብለበት የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በገዛ ወገኖቻችን መገፋታችን ያሳዝናል ያሉ አንድ የካፍቴሪያው ሰራተኛ ባለተዳር እና የሶስት ልጆች አባት መሆናቸውን ገልጸው ዛሬ በየአመቱ የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ እስከ 10 ሺህ ሪያል ለማውጣት እንደሚገደዱ አውስተው ለምኖርበት መኖሪያ ቤቴ በየስድስት ወሩ ከምከፍለው የቤት ኪራይ ጋር ተዳምሮ በ 2 ሺህ ሪያል ደሞዝ አይን ካልገለጹ ልጆቼ ጋር ኑሮን ማሸነፍ ተስኖኝ አቤት ለምለው አጥቼ በነዚህ ጨካኞች የሚፈጸምብኝን በደል ሳልወድ በግድ ለመቀበል ተገድጃለሁ ብለዋል። በተጠቅሰው ካፍቴሪያ ከ 8 ሰአት በላይ ያለ ተጨማሪ ክፍያ « ኦቨር ታይም» ሃይማኖታዊ በአላትን ጨምሮ ደስታ ምን እንደሆነ ሳያውቁ ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን ኑሮቸውን ለማሸነፍ ደፋቀና እያሉ መሆናቸውን የሚናገሩ እነዚህ ወገኖች ተጨማሪ ስራ ሰርተው እራሳቸውን መደጎም የሚችሉበት ግዜ እንደሌላቸው እና አቅማቸው እንደማይችል ጠቁመው ጉዳዩ ያችን እልባት እስኪያገኝ ለወግን ተቆርቋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጸሎት ከጎናቸው ይቆም ዘንድ ተማጽነዋል።
sudi
ይህ የኮሚኒቲ ማህበር እንደ ማህበር ህጋዊ ህልውና አጊቶ ስራ ከጀመረ ሁለት አስርት አመታትን ማስቋጠሩን የሚያወጉ አንዳንድ እድሜ ጠገብ አባላቱ በተጠቀሱት አመታት የአንባሳደሩን መኖሪያ ቤት ጨምሮ በሪያድ የኢትዮጵያን ኤንባሲን በ20 ሚልዮን ሪያል ወጪ አስገንብቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስረከበ ታላቅ እና ስመጥር ማዕከል እንደ ነበር በማስታወስ ዛሬ ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ግቢ ጥቂቶች እንዳሻቸው የሚያዙበት የአይንህ ቀለም አላማረኝም እያሉ የገዛ ወግናቸውን በቡጢ እይነረቱ ከግቢ የሚያባርሩበት ከሰሪዎቻቸው አምልጠው ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ቅጥር ግቢው በሚመጡ እህቶቻችን ላይ ጾታዊ ጥቃት የሚፈጸምበት እና የወገኖቻችን ሬሳ የሚቆጠርበት የጥቂት ወሮበሎች መሸሸጊያ መሆኑ አሳዛኝ እና ሳፋሪ ነው ብለዋል። በአጠቃላይ ከቅርብ ግዜ ውዲህ ይህ በሪያድ የኢትዮጵያ የኮሚኒት መዝናኛ ማዕከል በወገኖቻችን ላይ ኢሰባአዊ ድርጊት የሚፈጸምበት መዕከል ለመሆኑ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ምንጮች የመዝናኛው መዕከል ሰራተኞች አብዛኛዎቹ የወጣትነት እድሜያቸውን እዛው የኮሚቲ ማእከል ውስጥ የጨረሱ እና በብስጨት ለስኳር በሽታ ለድም ግፊት እና መስል ተዛማጅ በሽታዎች ተዳርገው የተጎሳቆሉ በመሆናቸው ሌላ ስራ ፈልገው የማግኘት እድል እንደሌላቸው በማውሳት የሚመከተው አካል አሁን የሳውዲ አረቢያ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ያወጣውን ህግ መስረት በማድረግ የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግላቸው እንደሚገባ እና የሳውዲ አረቢያ መንግስት አሁን ባወጣው ህግ መስረት የተጠቀሱትን ወገኖቻችንን ከህገወጥነት ለመታደግ የመኖሪያ ፈቃዶቻቸው በኤንባሲው ስር ሊሆን የሚቻልበትን መፍትሄ ማፈላለግ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሃላፊነት መሆኑንን ይገልጻሉ።

ይህን ተከትሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አክሳሪ ነው በሚል ለአያሌ አመታት ሲመዘበር መቆየቱን የሚናገሩ የሪያድ ነዋሪዎች በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አንባሳደር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘምድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የኮሚኒትው ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ምንጩ የማይታወቅ 2 ሚልዮን ሪያል «25 ሚልዮን ብር » ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሶስተኛ ሃገር ሊያሻግሩ ሲሞክሩ በሳውዲ አረቢያ መንግስት ደህነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ውለው እስካሁንም እስር ቤት እንደሚገኙ ይገልጻሉ።

አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ ነውረኞች !

$
0
0

አበራ ሽፈራው
ከጀርመን

እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጥር ጥቅምት መጨረሽና  ህዳር ወር 2006 እጅግ አሳዛኝና በህይወት እስከአለን ድረስ የማንረሳው ክፉ አጋጣሚ በእህቶቻችንና በወንድሞቻችን ላይ ግድያን፣ መድፈርን፣ እስርን፣ መታረድንም፣ በመኪና እየተገጩም ጭምር መሞትንም መጀመሩን ያየንበትና የሰማንበት:: ክፉ ወር:: ብዙዎቻችን በውስጣችን ከራሳችን ጋር የተሟገትንበት፣ ምን እናድርግ? ብለን ከቅርብ ጓደኞቻችን ጋር የተነጋገርንበት:: ሌሎቻችንም ተሰባስበን በውስጣችን ያለውን ሃዘን በግልጽና በአደባባይ ዓለም ሁሉ እየሰማ የተነፈስንበት::  ሳውዲ አረቢያዎች ለዘመናት አብሮአቸው የነበረውን ጭካኔ በአይናችን የተመለከትንበት ምን አልባትም እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ከዚህ በላይ ሲጨቆኑና ሲረገጡ መኖራቸውንም ለማየት የቻልንበት ጊዜ ይህ ይፋ ወጣ እንጂ::

በእርግጥም ሳውዲዎች ጨካኞች ናቸው ስራቸውም እጅግ አሳፋሪ ነው:: ጊዜ ይለወጣል ሀብትም ይጠፋል  ነገር ግን ታሪካቸው በተለይም በወንድሞቻችን ላይ የተፈጸመው ግፍ ግን ለታሪክ ሲታወስ ይኖራል :: በሳውዲዎች ድርጊት ያላዘነ ኢትዮጵያዊ የለም እኔ እስካየሁትና እስከሰማሁት ድረስ:: ታሪክ የእኛን እንግዳ ተቀባይነትን እንደመዘገበ ሁሉ የእነሱንም ውለታ መላሽነት በእኛ ዘመን ለማየት ችለናል ይህንንም ታሪክ መዝግቦታል:: በክፉ ዘመናቸው በአገራችን ተሰደው እንደ እናት ቤት ኢትዮጵያ እንዳልተቀበለቻቸው ሁሉ ዘሬ ሰርተው ሳይሆን አምላክ በተፈጥሮ በሰጣቸው ተመክተው  የጥጋብ ዱላ በወገኞቻችን ላይ አዘነቡ የብዙ የኢትዮጵያውያን እንባ በአለም ሁሉ ፈሰሰ፣ የአምላክንም እጅ ተማጸነ፣ ብዙዎች የአምላክንም ምህረት በእንባ ለመኑ በእርግጥም አምላክ ሰምቷል መልሱም አንድ ቀን ለአገሬም ይሠጣል::

ላለፉት 50 ዓመታት አረቦች ለኢትዮጵያ ያላቸውን ጥላቻ በተለያየ መልኩ ለመፈጸም ሞክረዋል ዋናው መነሻቸውም በሁሉም መልኩ ለመስፋፋት ያደረጉትን እንቅስቃሴ ሁሉ እሽ ብሎ የተቀበላቸው ያለመኖሩና በአፍሪካ ቀንድ የአረቦች አስተሳሰብ ተግባራዊ ሊሆን ያለመቻሉ ሲሆን ይሁንና ሃሳቦቻቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ግን አርፈው ተኝተዋል ማለት ግን አይደለም:: ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ ኢትዮጵያን ለመበታተን የተጠቀሙት አንደኛው መንገድ የዛሬዎችን ዘረኛ የህወሓት/ ወያኔ ቡድን እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁሉ አንደኛው መሳሪያ ሆኖ ያገለገላቸው እኩይ ቡድን መሆኑ ጭምር ነው::

በእርግጥም ኢትዮጵያና ልጆቿ ለአገራችው ሳይሆን የሌሎች ህዝቦችንና አገራትን ሰላም ለማስከበር ለመስወአት የቀረቡ የህወሃት ጀነራሎች የገቢ ምንጭ ሆነዋል፣ የአረቦችን ቆሻሻ ለመጥረግና በዚህ ዘመን የሌለን ባርነት ርካሽ ጉልበታቸውን ለመሸጥ ተገደዋል ይኸም ብሶ ለአስከፊ ችግር መጋለጣቸውም ቢሆን ከኢትዮጵያው የህወሓት ሥርዓት ማንነት ጋር የተያያዙ ችግሮች ውጤቶች ናቸውና መሰደድና የህወሃት ደላሎች መጠቀሚያ መሆንና ለመከራ መዳረግም ቢሆን የሥርዓቱ መዋቅሮች ለዚህ አስከፊ ችግር መፍትሄ መፈለግ አቅቷቸው ሳይሆን እራሳቸውን እስከጠቀማቸው ድረስ በዝምታ ቆይተው ችግሩ ተባብሶ  አስከፊ ደረጃ ሲደርስ ደግሞ “ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል“ እንዲሉ አሳቢ መስለው  መነሳታቸው ደግሞ ያሳዝናል::

ለአሁኑ የአረቦችም ሆነ የሌሎች አገሮች ማጥቃት መነሻው በአገራችን ያለው የፖለቲካ ችግር ሲሆን የኢኮኖሚ ችግሩም ቢሆን የዚሁ የፖለቲካው ችግር ውጤት መሆኑ ማንም ይስማማበታል:: ለመነሻም እንዲሆነን የአገሪቷን ፖለቲካ ለ22 ዓመታት የተቆጣጠረው ህወሃት/ወያኔ  በግልጽና በአደባባይ የኢትዮጵያ ህዝብ አይኑ እያየ የአዋቀረው የንግድ ብዝበዛ፣ የአገሪቷ የንግድ እንቅስቃሴ ከፓርቲ ንግድ ወይም ከEFFORT በተጨማሪ ትልልቅ የንግድ ተቋማት በህወሃት ሰዎች መያዛቸው፣ ጠቅላላ የንግድ መድሎ መኖሩ፣ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቶች በሙሉ በሚያስብል መልኩና በተጠና መልኩ በህወሃት ሰዎች መያዛቸው፣ ለንግድ ስራ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ልዩልዩ የሚንስትር መስሪያ ቤቶች በነዚሁ ሰዎች መያዛቸውና ልዩ ልዩ የአገሪቷን ንግድ በሙሉ በማክሮ ኢኮኖሚ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጭምር ለእነሱ የሚጥቅሟቸውን ሁኔታዎች እስከማመቻቸት ድረስ መድረሳቸውን ቀዳሚ እድሎችን የሚያገኙት እነሱ መሆናቸው ጭምር ናቸው::

ለአሁኑ ጥቃጣችን ምክንያት ከላይ የተጠቀሰው ጉዳይና ሌሎች ጉዳዮች ሲሆኑ በተጨማሪም አረቦች በተለይም ሳውዲ አረቢያ ለህወሃት ቅርበት ባለው ሼህ መሃመድ አላሙዲንና በሌሎች የንግድ ሸሪኮቻቸው አማካኝነት ባላቸው የቆየ ቅርርብ ማንነታቸውን በጥልቀት ያወቁ በመሆናቸው ወገኖቻችን ደራሽና ወገን ወይም የሚከላከልላቸው እንደሌላቸው ሰው ሆነው በአሳዛኝ መልኩ እንዲባረሩ መደረጉ ለህዝቡና ለተጎጂ ቤተሰቦች እንጅ ለህወሃት ሰዎች ቅንጣት ያህል እንደማይሰማቸው እርግጠኛ ነኝ:: ለዚህም ደግሞ የህወሃት የጭካኔ መጠንን ለመለካት የኢትዮጵያን ህዝብ ለህወሃት ያለውን አመለካከት በመለካት ማወቅ ቀላል ነው:: ይልቁንም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለህወሓት የማፍያ መዋቅር ሌላ የገቢ ምንጭ እንደፈጠረለት በቀላሉ መገመት ይቻላል:: ይህንን በቀላሉ ለመረዳት በተመላሽ ወገኞቻችን ንብረት ላይ የሚደርሰው የንብረት ንጥቂያ ብዙዎች በሳውዲ አረቢያ ከደረሰባቸው ስቃይ  ይልቅ በአገራችን በህወሃቶች የጉምሩክና በኤርፖርት አካባቢ የተደረጉት የፍተሻ ዝርፊያዎችና የንብረት ቅሚያ ቀላል ሊባሉ እንደማይችሉ እየተነገረ ይገኛል:: ይህም ችግር በአገር ውስጥ ተባብሶ ብዙዎችን ለተጨማሪ የስነልቦና ችግር ላይ መውደቅ ምክንያት እየደሆነ ይሰማል:: ታዲያ ይህንን የህወሃትን ሥርዓት ምን ልንለው እንችላለን?

ከላይ እንደገለጽኩት የህወሃት የማፍያ መዋቅር የትኛውንም አጋጣሚዎች እንደ አንድ ጥሩ አጋጣሚ የሚቆጥሩ መሆናቸውን ለማየት ከላይ ከጠቀስኩት ተግባራቸው በቀላሉ ለማየት ይቻላል:: አባይ ግድብ ብለው ይነሳሉ ከህዝቡ  ከልጆቹ ማሳደጊያ እየነጠቁ ሰብስበው ባልተጠና መልኩ የተጀመረን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በሚል የተሰበሰበውን በጀትና ገንዘብ ለህወሃት የንግድ ተቋማት ትልቅ የብዝበዛ ምንጭነት እንዲያገለግል ሲደረግ እያየን እንገኛለን፣ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ከስደት በግድ ሲመለሱ በላብና በደማቸው የሰበሰቡትንና ከሳውዲዎች እጅ አምልጦ በእጃቸው ይዘው የመጡትንም በጥሬ ገንዘብና በአይነት መበዝበዛቸው፣ በዚሁ አስከፊ ጊዜ ለእነዚህ መከረኞች መድረስ ሲቻልና የተሰደዱት ከማቋቋም ይልቅና የኢትዮጵያ ህዝቦች ሆነው ሳሉ በመቶ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠርን ብር በብሔር ብሄረሰቦች ስም አውጥተው ሲደንሱበት ከማየት በላይና አሁንም የህወሃት የንግድ ተቋማት የኪስ ማደለቢያ ማድረጋቸውን ስናይ እጅግ የሚዘገንን ተግባር ነው ለማለት ያስችላል::

ትላንት ደርግ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1977 ዓ.ም የወሎና የትግራይ ወገኖቻችን በድርቅ ሲጠቁ የደርግ 10ኛ ዓመትና የኢሠፓን ምስረታን በከፍተኛ ወጭ አከበረ እያሉ ሲሳለቁበትና የትግላቸው መቀስቀሻ አድርገው ሲዘምሩበት እንዳልነበረ ዛሬ የትላንት ነጻ አውጭዎች ነን ባዮች የዛሬዎቹ በዝባዦች በአደባባይ ስራቸውን፣ምግባራቸውንና አላማቸውን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድናያቸው አድርጎናል:: ደግሞም የኢትዮጵያ ህዝብ ከመቼውም ግዜ በላይ ለራሱ እያሰበ መምጣቱና እየነቃ የትኛውንም የክፋት መዋቅራቸውንም ይዘርጉ ይህንን ሁሉ በጣጥሶ እነዚህን ጎጠኞች አይናችሁ ለአፈር ያለበት ግዜ ላይ ደርሰናል:: በአገር ውስጥ መቃወም ባይችልም ዝምታን መርጠው የነበሩ ሳይቀሩ ዛሬ በአደባባይ ህወሃትን ለመጋፈጥ ቆርጠው ታይተዋል:: ትግሉንም ለመደገፍ ግልጽና ስውር ትግሉን መቀላቀል ተያይዞታል፣ ለህወሃት አስደንጋጭ በሚሆን መልኩ ትግሉን ወደከፍተኛ ምዕራፍ ለማሸጋገር ግልጽና የህቡ የትግል መስመሮችን እየተቀላቀለ ይገኛል::

ከዚህ በላይ የእህቶቻችንንና የወንድሞቻችንን ደምና እንባ ሳይደርቅ ለእነዚህ የሳውዲአረቢያ ጨካኞች የአገራችንን መሬቶችንና ሌሎች የንግድ ፍቃዶችን ለመስጠት ከ300 በላይ የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን መስማማታቸውን ስመለከት ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆንንና እነሱን እስከጠቀመ ድረስ ኢትዮጵያዊነት በህወሃቶች ፊት ምንም እንዳልሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል:: እንግዲህ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባይሆንም እና በሌላ ርዕስ የምመጣበት ቢሆንም ከኢትዮጵያ ድንበርን ወደሱዳን ለማካለል መነሳታቸውንም ስመለከት በጣም የሚያሳዝን መጥፎ አጋጣሚ ላይ መኖራችንንና የማንን መሬት ለሱዳን ለመስጠት እንደፈለጉም በደንብ አልገባኝም:: ስለሆነም ህወሃቶች ምን አይነት ትምህርት እንደተማሩ ምን አልባትም ብዙዎቹ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑና በአጋጣሚዎች ኢትዮጵያ በሌሎች እኩይ ተግባርን በሰነቁ የኢትዮጵያ ጠላቶች እጅ መውደቋን ለመረዳት እንችላለን::

ዛሬ አስቸጋሪ እንዲያውም ለአገራችን ህልውና አስጊ የሆነ ጉዳይ ቢኖር ህወሃትን ለመጋፈጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ  መሆናችንን ማስብ ካልቻልን ነው :: ስለሆነም እነዚህ የታሪክ ጥቁር መዝገቦች፣የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች፣ የህዝብና የትውልዱ ጠንቆችንና አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው የብዝባዛ መሳሪያነት የሚጠቀሙትን ጠላቶቻችንን ለመጋፈጥ አሁንም ያልቆረጥን እንቁረጥ::

ይህ አስከፊ የህወሃት ሥርዓት የሚፈልገውን ሳይሆን እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ የሚመኙትን ነጻነትና ፍትህ፣ ሁሉም ብሔረሰቦችና የኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ በእኩልነትና ያለመድሎ የምንኖርባት፣ ፍትህ የሰፈነባትን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በሁሉም ኢትዮጵያውያን ፍቃድ የምንመሰርትበት፣ የህግ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከህወሃት የዘር ጭቆና መላቀቅ ያለብን ሰዓት ላይ ደርሰናል:: አጋጣሚዎችን ሁሉ እየተጠቀሙ ለብዝበዛና ለእልቂት ከሚዳርጉን ነውረኞች እራሳችንን እናድን::

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

aberashiferaw.wordpress.com

comment_stage_5

                                                              

በራሳሽን ላይ የምንሰለፍበት ቀን ናፈቀኝ? ራሳሽንን

ይድረስ ለሚኒሶታ መድኃኔዓለም ምዕመናን፡ የተከፋፈሉት አባቶች 1 አስኪሆኑ ድረስ በአስተዳደር ገለልተኝነት ለመቆየት 7 ምክንያቶች

$
0
0

ቀን፡ 12-12-13
በሥላሴ ስም አንድ አምላክ አሜን።
ይድረስ ለሚኒሶታ መድኃኔዓለም ምዕመናን
ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተከፋፈሉት አባቶች አንድ አስኪሆኑ ድረስ በአስተዳደር ገለልተኝነት መቆየት ይገባታል!

deb
ምክንያቶች፦
1. የደብራችንን ሰላምና አንድነት ለመጠበቅ ያስችላል።
2. የተከፋፈሉትን አባቶቻችንን ለማቀራረብ በሚካሔደው ጥረት ውስጥ ተሳታፊ ለመሆንና የክርስቲያኖችን ድርሻን ለመወጣት ይጠቅማል።
3. የክርስትና ጠባይ ያልሆኑትን የፖለቲካና የዘረኝነትን ነገር በደብራችን እንዳይኖር ይረዳል።
(ስለአገርና ስለኅዝብ መበደል፣ ስለቤተክርስቲያን ጥቃትና መብት ገፈፋ መናገር ግን ፖለቲካ አይደለም።)
4. በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ በማንኛውም አካል በቤተክርስቲያን ላይ አንዲሁም በአገርና በህዝብ ላይ የሚደርሱ በደሎችን ተቃውሞ ድምጽን በነጻነት ለማሰማት ይረዳል።
5. ከሌሎች ቤተክርስቲያናት ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖርና በሕብረት ለማገልገል ያስችላል።
6. የምእመናንን ቁጥር ለማብዛትና የቤተክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ እድገት ለማምጣት ያስችላል።
7. ወገናዊነት ሳይኖርና ያለህሊና ወቀሳ እምነትን በነጻነት ለመፈጸም ይጠቅማል።

ከዚህ አንፃር በአሁኑ ሰዓት ዘረኝነት፣ አድሎ፣ሙስና፣ወዘተ ወዳለበትና በቀጥታ በመንግስት በሚታዘዝ አስተዳደር ስር እንሁን የሚሉ ክፍሎች ተሳስተዋል። በደብረ ሰላም ዘረኝነት የለም! ለማንም የፖለቲካ ድጋፍ መስጠት የለም!
ስለሆነም ቤተክርስቲያንህን በመንግስት አመራር ስር ለማድረግ የሚሮጡትን ልትቀድማቸው ይገባል!
ለብዙ አመታት ገንዘብህን ፣ጉልበትህን ፣እውቀትህን ፣ጊዜህንና ላብህን አፍስሰህ እዚህ ያደረስከውን የአምልኮ ቤትህን እንዳትቀማ ተነስ።
የችግሩን መንሰኤና መፍትሄ ልቦናቸው እያወቀ አሳልፈው ሊሰጡህ ባሴሩትንም ‘ካህናት’ ላይ ርምጃ ልትወስድ ይገባል።

ለቤተክርስቲያን አንድነት እና ሰላም ከቆሙ ምዕመናን።

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>