Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የራስን እድል በራስ መወሰን፣ እርስ በርስ እስከማጣላት…ሌላው ኢትዮጵያዊ የተዋረደበት፤ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን –በኦጋዴን!

$
0
0

የራስን እድል በራስ መወሰን፣ እርስ በርስ እስከማጣላት…

ሌላው ኢትዮጵያዊ የተዋረደበት፤ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን – በኦጋዴን!

ዘንድሮ በኢትዮጵያ ተከበረ የተባለውን የብሄሮች  ቀን ምን ያህሎቻችሁ እንደተከታተላቹህ አላቅም። ላላያችሁት ግንዛቤ ለመፍጠር ያህል… ዘንድሮ በአሉ የተከበረው ሱማሌ ክልል፣ በኦጋዴን ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን በመንገር ወጋችንን እንጀምራለን። ይህ ዝግጅት እስከዛሬ በትግራይም፣ በአማራውም ክልል ተደርጓል… ሆኖም በአሉ ላይ ሁሉም የየብሄሩን ባህል ለማሳየት ሲጥር እንጂ፤ አንደኛው ብሄር ሌላውን ሲሰድብ ያየንበት አጋጣሚ አልነበረም። የዚህ አመቱ የብሄር ብሄረሰቦች ወይም የብሄረተኞች ቀን ሌላውን ኢትዮጵያዊ በመውቀስ ላይ የተመሰረተ ነበር።

“አማራው፣ ደገኛው፣ የመሃል አገር ሰው…” እያሉ ቀጠሉ አስተያየት ሰጪዎቹ። በአሉን ምክንያት በማድረግ በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት ታዳሚዎች ወቀሳቸውን ቀጠሉ፤ “የመሃል አገር ሰዎች ‘ሽርጣም ሱማሌ’ እያሉ ይጠሩን ነበር” አለ። እኛንም በሃሳብ ወደኋላ መለሰን። የመሃል አገር ሰው ይህንን ቃል አይጠቀምበትም ለማለት አይደለም። ነገር ግን “ሽርጣም ሱማሌ” የሚለውን ቃል መስማት የጀመርነው፤ በኢትዮጵያ እና ሱማሌ ጦርነት ወቅት ነው። “ሽርጣም ሱማሌ” የሚለውን አባባል ሁሉም የመሃል አገር ሰው እንደማይጠቀምበት ሁሉ፤ በቴሌቭዥን መስኮት ላይ ብቅ ብለው ሌላውን ኢትዮጵያ የሰደቡት እና ያሰደቡትም መላውን የኢትዮጵያ ሱማሌ እንደማይወክሉ እናውቃልን። በመሆኑም ይህ ጽሁፍ በሁሉም የኢትዮጵያ ሱማሌዎች ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን፤ የማያውቁትን ታሪክ ለማሳወቅ ያህል የተዘጋጀ መሆኑን ልብ ይበሉ።

 (በዳዊት ከበደ ወየሳ –  ጋዜጠኛ)

ethiopia somalia
በ1969 ዓ.ም. ሱማሌ ኢትዮጵያን ስትወር፤ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አፈናቅለዋል፤ ገድለዋል፤ በሺህ የሚቆጠሩትን ማርከው ወስደው አገራቸው ውስጥ አስረዋል። ሱማሌዎች ይህንን በሚያደርጉበት ወቅት ታዲያ ሽርጥ እንጂ ሱሪ ታጥቀው አይደለም። በዚያን ወቅት ታዲያ የኢትዮጵያ ልጆች ዳር ከዳር “ሆ” ብለው ሲነሱ፤ በወገናቸው ላይ የደረሰው በደል ቢያንገበግባቸው፤ “ይሄ ሽርጣም ሱማሌ” ብለው ቢሳደቡ ሊገርመን አይገባም። ከዚያ በፊት በነበሩት ጦርነቶች ፈረንጆች ኢትዮጵያን ሲወሩ፤ “ይሄ ሶላቶ” ብለው እንደሚጠሯቸው ጠላት የነበረውን የሱማሌ ታጣቂ “ይሄ ሽርጣም” እያሉ በመፎከር፤ የገባበት ገብተው ደምሠውታል፤ ዳግመኛም የኢትዮጵያን ድንበር እንዳይሻገር አድርገውታል።

በ1970 የሱማሌ ጦር ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያውያን ብርቱ ክንድ ተደመሰሰ። ከጅጅጋ እና አካባቢው ተፈናቅለው የነበሩት የኢትዮጵያ ሱማሌዎች ወደ ድሮ መንደራቸው ተመልሰው፤ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ሰላማዊ ኑሯቸውን ቀጠሉ። “ሽርጣም ሱማሌ” የሚለውም አባባል እየቀረና እየተረሳ መጣ። ዘንድሮ በሱማሌ ክልል፣ በአሉ ሲከበር…  ሌላው ኢትዮጵያዊ ለሱማሌ ኢትዮጵያ የሰራው ውለታ ተረስቶ፤ የመሃል አገር ሰዎች “ሽርጣም ሱማሌ እያሉ ይሰድቡን ነበር” የሚል የጥላቻ መልዕክት ሲተላለፍ ሰማን።

ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ቀጠለ።  “ድሮ ያስተማሩኝ ሰዎች ስማቸው ‘በቀለ፣ መኮንን፣ በየነ’ ነበር። አሁን ግን ጊዜው ተቀይሯል። አስተማሪዎቻችን ስማቸው መሃመድ እና አብዱል ሆኗል።” በማለት ለኢህአዴግን መንግስት ምስጋና ሲያቀርብ ስንሰማ፤ ጆሯችንን ማመን አቅቶን ተገረምነ። ኢትዮጵያ ውስጥ ትምህርት ሲጀመር፤ የዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት የመጀመሪያ መምህራን የመጡት ከግብጽ አገር ነበር። በኋላም ላይ ከህንድ ድረስ መምህራን እየመጡ አስተምረዋል፤ ወይም አስተምረውናል። በውጭ ሰው ስለተማርን… “ለምን የውጭ ሰው አስተማረን?” ብለን አንቆጭም፤ ይልቁንም ለእነዚህ መምህራን አክብሮት እና ምስጋናችንን እናቀርባለን እንጂ። በሱማሌ የተመለከትነው ግን ከዚህ የተለየ ነበር… እቺም እድሜ ሆና… እነበቀለ፣ መኮንን እና በየነ የሚባል ስም የነበራቸው ኢትዮጵያውያን ስላስተማሯቸው የሚናደዱ ሰዎችን ለማየት በቃን።

ደግሞም አንድ ሌላ እያሳቀ የሚያናድድ ነገር ሰማን። ሌላው አስተያየት ሰጪ እንዲህ አለ። “አካባቢያችን ልጅ ምግብ አልበላም ብሎ ሲያስቸግር፤ ‘አማራ መጥቶ እንዳይበላብህ’ በማለት ልጁ አማራ ሳይመጣበት ቶሎ እንዲበላ እናደርግ ነበር።” አለ።

“ጉድ እኮ ነው የሱማሌ ኢትዮጵያ ህዝብ አማራውን ይህን ያህል ይጠሉት ነበር? ማስፈራሪያስ አድርገውት ነበር?” እያልን ተገርመን ሳናበቃ ይኸው ሰውዬ ንግግሩን ቀጠለ።

“በሌላ በኩል ደግሞ የመሃል አገር ሰዎች (አዲሳባ ያለው ሌላው ኢትዮጵያዊ መሆኑ ነው) ልጆቻቸው ምግብ አልበላም ብለው ሲያስቸግሯቸው፤ “ሱማሌ እንዳልጠራብህ!” ብለው ሲያስፈሯቸው፤ ምግቡን ጥርግ አርገው ይበሉ ነበር።” ሲል ሰማን። አብረውኝ ኢቲቪን ይመለከቱ የነበሩ “የመሃል አገር” ሰዎችን በጣም አሳቃቸው። እርስ በርስ ተያየንና “ሱማሌ እንዳይመጣብህ!” ተብሎ ምግብ ሲበላ የነበረ ከመሃላችን ነበር?” ብሎ ጠየቀ አንዱ…

ሌላኛው “እኛ አያጅቦን ነው የምናውቀው” ሲል ትንሽ አሳቀን።

“ሱማሌ ሳይመጣብህ!” ተብሎ እያስፈራሩ ምግብ ያስበሉት ይፍረደን” በማለት በጉዳዩ ላይ ስቀን ልናልፍ እንችል ይሆናል። ነገር ግን … ለአማራው ድርጅት ‘ቆሜያለሁ’ የሚለው ብአዴን/ኢህአዴግ ነገሩን እንዴት አይቶት ይሆን?

የብሄር በሄረሰቦችን ቀን ምክንያት በማድረግ የሚተላለፈው የጥላቻ አስተያየት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ኢቲቪን ከመዝጋታችን በፊት ሌላ አስተያየትም አደመጥን። ሰውየው እንባ እየተናነቃቸው፤ “መናገሻ ከተማችንን አዲሳባን ለማየት እንኳን አይፈቀድልንም ነበር።” ብለው ሲሉ፤ በራስ ተፈሪ መኮንን ዘመን የነበሩ የሱማሌ ፖሊሶች ታወሱን። በወቅቱ በአዲስ አበባ፤ በፖሊስነት ተቀጥረው ሰአት እላፊ እና ጸጥታ የሚያስከብሩት የመጀመሪያ ባለደሞዝ የአዲስ አበባ ፖሊሶች የሱማሌ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። እናም “አዲስ አበባን ለማየት እንኳን አይፈቀድልንም ነበር” እያሉ የሚያለቅሱትን አዛውንት አይተን፤  “ወደ አዲስ አበባ መሳፈሪያ ካላጡ በቀር የባቡር መስመር ከተዘረጋ ራሱ፤ መቶ አመት አልፎታል”። በማለት ታዝበናቸው ዝም አልን።

ሌላዋ ሴት ደግሞ ቀጠለች። ሴትዮዋ መናገር ስላለባት ብቻ የምትናገር ነው የምትመስለው… “የድሮ እና የአሁኑን ሳስተያየው በጣም ብዙ ልዩነት አለው” ብላ ጀመረች። ልጅቷ እንኳንስ ስለቀዳማዊ ሃአይለስላሴ ዘመን ቀርቶ ስለደርግ ለማውራት እድሜዋ የሚፈቅድላት አይደለችም። ወሬዋን ግን በድፍረት ቀጠለች። “የድሮና የአሁኑ በጣም ልዩነት አለው… ዑውውውው።” በማለት የአሁኑን አዳነቀች። አድናቆቷን ሳታቋርጥ “የድሮ እና የአሁኑን ልዩነት ለመግለጽ ቃላቶች ያጥሩኛል” ብላ በቃላት እጥረት ምክንያት ልዩነቱን ሳትነግረን ቀረች።

ሌላው ደግሞ እንዲህ አለ። “ይሄ አካባቢ ለወታደራዊ ጦር ካምፕ ይጠቀሙበት ነበር እንጂ፤ ለህዝቡ ግድ አልነበራቸውም።” አለን። እውነት ነው። ፈረንሳይ ከጅቡቲ አልፋ ወደ ኢትዮጵያ የመስፋፋት ብዙም ህልም አልነበራትም። እንግሊዝ እና ጣልያን ግን… ሁለቱም ከሱማልያ ግዛቶቻቸው ተነስተው፤ ኦጋዴን እና አካባቢውን ጨምረው እስከ ሃረር ድረስ ለመግዛት፤ ግልጽ የሆነ እቅድ እና ሙከራ አድርገው ነበር። ሱማሊያ ነጻ ከወጣች በኋላ ደግሞ ከራሽያ ባገኘችው የጦር መሳርያ በመታገዝ እጅግ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ አድርጋለች። በዚህ ጊዜ ሁሉ ሰራዊቱ ከመሃል አገር እየተነሳ፤ ኦጋዴን እና አካባቢው በውጭ ሃይሎች ስር እንዳይወድቅ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል። ይህ ሌላውን አገር በወታደራዊ ኃይል የመከላከል ስራ… ዛሬ ስሙ እና ውለታው ተረስቶ “አካባቢውን የወታደር ካምፕ አደርገውብን ነበር” በሚል ወቀሳ መቀየሩ ይገርማል።

አብረውን የነበሩት ጓደኞቼ በኢቲቪ ተናደዋል።  ቴሌቪዥኑን ከመስበራቸው በፊት በሰላም ዘጋነውና ሰላማዊ ጨዋታችንን ጀመርን። “ለመሆኑ ሌላው ኢትዮጵያዊ ደገኛ፣ የመሃል አገር፣ ክርስቲያን፣ አማራ…” እየተባለ ቅጽል እየወጣለት መሰደብ አለበት ወይ? ይህ ደገኛም ሆነ ነፍጠኛ ያሉት ኢትዮጵያዊ ለዚያ ህዝብ ውለታ አላደረገምን? ዝርዝር ውስጥ አንገባም። ሆኖም በታሪክ ቅኝት ወደኋላ መለስ ብለን የእውነትን ማህደር በማገላበጥ ታሪክን እስኪ እንመርምር። እንዲህ ነው።

ወደ አጼ ምኒልክ ዘመን እንሂድ… በፊት በቱርኮች፤ በኋላ ደግሞ በግብጾች ሲተዳደር የነበረው ህዝብ የጠመንጃውን አፈሙዝ በኢትዮጵያውያን ላይ አነጣጥሮ እንደነበር ይታወቃል። በ1524 ዓ.ም. ግራኝ አህመድ እና አሊ ኑር እንደገነኑት ሁሉ፤ በ1876 ዓ.ም. ደግሞ አሚር አብዱላሂን ጨምሮ ሌሎች የአካባቢው ገዢዎች ጉልበታቸው የደረጀበት ወቅት ነበር። በወቅቱ ነዋሪውን በቁጥጥራቸው ስር አውለው፤ “በክርስቲያን መንግስት አንገዛም” ማለታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ከዚያ እምነት ውጪ የነበሩትን የገደሉበትና ያጠፉበት ታሪክ ነው ያለን። (ይህም በአረብኛ ተጽፎ የሚገኝ ሰፊ ታሪክ ያለው ጉዳይ ነው) አሚር አብዱላሂም ቢሆን፤ ለአጼ ምኒልክ “አልገብርም” ማለት ብቻ ሳይሆን፤ “አንተም እንደኛ ካልሰለምክ በስተቀር፤ በክርስቲያን ንጉሥ አንገዛም” በማለት ለአጼ ምኒልክ፣ ሽርጥ፣ መቁጠርያ እና መስገጃ ምንጣፍ ነበር የላከላቸው።

አጼ ምኒልክ የተላከላቸውን ሽርጥ፣ መቁጠሪያ እና መስገጃ አብረዋቸው ለነበሩ ሙስሊሞች ሰጥተው፤ ፊታቸውን ወደምስራቅ ኢትዮጵያ አዙረው፤ በአሚር አብዱላሂ የሚመራውን ጦር፤ ጨለንቆ ላይ ገጠሙት። በዚያ የጨለንቆ ጦርነት በርካታ ኢትዮጵያውያን አለቁ። ከሚንልክ ጋር የነበሩ የአማራ ተኳሾች እና የኦሮሞ ፈረሰኞች፤ የአሚር አብዱላሂን ጦር አሸነፉት። ጥር 18 ቀን፣ 1879 አካባቢው በምኒልክ ጦር ነጻ ወጣ። አሚር አብዱላሂም በጅጅጋ አድርጎ አገር ጥሎ ጠፋ።

በኋላ ላይ የአሚር አብዱላሂ ዘመዶች ወደምኒልክ ዘንድ መጥተው፤ “እባክዎን አገሩን እንዳያጠፉት” ቢሏቸው፤ “እኔ አገር አቀናለሁ እንጂ አላጠፋም። እዚህ ድረስ የመጣሁትም ሃይማኖት ለማጥፋት አይደለም። ሁሉም ሰው እንደየ እምነቱ ያድራል።” ብለው ወደጀጎል በሰላም ሲሸኙዋቸው፤ ከነሱም ጋር እነበጅሮንድ አጥናፌ እና እነሻቃ ተክሌ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይዘው ሀረር ገቡ። ከዚያ በኋላ አካባቢው በርግጠኝነት የኢትዮጵያ ግዛትነቱ ታውቆ፤ በአምስቱም የጀጎል በሮች ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንዲሰቀል ሆነ። 3ሺህ ወታደሮችም ከራስ መኮንን እንዲቀሩ አድርገው፤ ክልሉ እንደገና በኢትዮጵያ መንግስት ስር ይተዳደር ጀመር።

አጼ ምኒልክ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ፤ የማረኩትን የግብጽ ወታደሮች አልገደሏቸውም። ይልቁንም ግብጾቹ የአሚር አብዱላሂን ጦር ለማበረታት ወታደራዊ ማርሽ ያሰሙ ነበር። አሁንም የምኒልክ ጦር በድል አድራጊነት ወደ አዲስ አበባ ሲገባ፤ አጼ ምኒልክ እነዚህኑ የጦር ሙዚቀኞች ታምቡር እያስመቱና ጥሩንባ እያስነፉ በወታደራዊ ስነ ስርአት አዲስ አበባ ሲገቡ ህዝቡ ግራና ቀኝ ተሰልፎ በታላቅ ደስታ እና እልልታ ተቀበላቸው። ያንጊዜ ታዲያ ማርከው ያመጡት ግብጾቹን ብቻ ሳይሆን፤ ለማዳ እርግቦች በሽቦ ቤት ያሉ እርግቦች እና ትላልቅ ሰሎግ ውሻዎች ጭምር ነበር። ያኔ ታዲያ እንዲህ ተባለ…

የምኒልክ ነገር፣ ይመስለኛል ተረት፤

አሞራው በቀፎ፣ ውሻው በሰንሰለት።

ይህ የሆነው የካቲት 28፣ 1879 ዓ.ም. ነው። እንግዲህ ሌላው ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው እውነት ይህ ሆኖ ሳለ፤ የአካባቢው ሰዎች “ክልላችንን የጦር ካምፕ አደረጉብን” በማለት ምኒልክን እንደጨፍጫፊ እና ተስፋፊ ሲያዩ “እንቁላል ለመጥበስ መጀመሪያ ቅርፊቱን መስበር ያስፈልጋል” ከማለት ሌላ ብዙም የምንለው አይኖርም። ይልቁንስ ከአስር አመታት በፊት ይመስለናል… በዚሁ ኢቲቪ የተመከትነው አንድ ለቅሶ ነበር። ስለኢትዮጵያ አንድነት ሲባል፤ ምኒልክ እና አሚር አብዱላሂ ጦርነት ያካሄዱበት ጨለንቆ ድረስ ሄደው፤ መሬቱን ቆፍረው የሟቾችን አጽም ከመቶ አመት በኋላ በማውጣት፤ “ምኒልክ የጨፈጨፏቸው…” ብለው ደረት እየመቱ ሲያለቅሱና ሲያስለቅሱ አይተን፤ “ወይ ታሪክ!?” ብለን ያለፍንበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር።

በሱማሌ ክልል የተከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እና በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ የደረሰው ውርደት ምን ያህሉን ሰው እንዳበሳጨው ለማወቅ ያስቸግራል። እኛ ግን እንላለን… “የአካባቢው ሰዎች ታሪካቸውንና ማንነታቸውን ወይም ታሪካችንን እና ማንነታችንን አያውቁም ማለት ነው። ሰው ሱማሌ፣ ኦሮሞ ወይም አማራ ስለሆነ አዋቂ አይሆንም። አገር እና ብሄር ሰውን አይለውጥም፤ ትምህርት ግን ሰውን ይለውጣል” ስለዚህ አሁንም ትንሽ ወደኋላ መለስ ብለን የጋራ ታሪካችንን እንጨዋወት፤ በዚያው እንማማር፤ እንለወጥ።

እንደ እውነቱ ከሆነ፤ ይህ አካባቢ ከጥንት ጀምሮ በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ተይዞ የነበረ ክፍለ ግዛት ነው። በ10ኛው ክፍለዘመን የሱማሌ ነገድ ከታጁራ ቤይ ተነስቶ መስፋፋት ሲጀምር የኦሮሞን ህዝብ እየተገፋ፤ በዋቢ ሸበሌ እና ጁባ ወንዝ መሃል በሚገኘው ቤናዲር በሚባለው ቦታ ላይ እንዲቆይ አድርጎት ነበር። በኋላም ኦሮሞዎቹን… ከታች የባንቱ ህዝብ ከላይ ሱማሌ ሲያስቸግራቸው ወደ ወላቡ፣ አበያ፣ ባሌ ድረስ ዘልቆ ራሱን በገዳ ስርአት እያደራጀ ቆይቶ፤ የግራኝ አህመድ ልጅ ወራሽ የሆነውን አሊ ኑርን ሐዘሎ ላይ ገጥሞ በ1551 ዓ.ም. እስከሚደመስሰው ድረስ በመሃል ብዙ ታሪኮች አልፈዋል። ከ10ኛው እስከ20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ አካባቢው በዚህ አይነት ምስቅልቅል ውስጥ ነው የቆየው።

በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የነበረው ምስቅልቅል እንዳለ ሆኖ፤ በተለያዩ ጊዜያት ከሱማልያ ግዛት የጦር መሳርያ ይዘው በመግባት፤ የኦሮሞውን ህዝብ በመግደል እና ከብቱን በመዝረፍ፤ ህዝቡን በማፈናቀል ብዙ ግፍ ተሰርቷል። እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ ክልል፤ በሌሎች ላብ እና ደም የተገነባ ክልል ነው። ይህን በማለት ወደኋላ ተመልሰን የምንቀይረው ነገር የለም። ሆኖም የማያውቁትን ወይም እያወቁ ሊያውቁ የማይፈልጉትን አንዳንድ ነገሮች ብናስታውሳቸው ክፋት የለውም።

በምኒልክ ዘመን ከተፈጠሩት አኩሪ ገድሎች መካከል የአድዋ ጦርነት አንደኛው ነው። ይህ ጦርነት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. በድል ከተጠናቀቀ በኋላ፤ በጦር ተማራኪዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ምኒልክ ዘንድ ምርኮኞችን አቀረቧቸው። ምኒልክ ምርኮኞች እንዲገደሉ አላደረጉም። ፈረንጅ ተማራኪዎችን ወደ አዲስ አበባ ይዘው ሲመለሱ፤ በኤርትራ እና በሱማሌ ተወላጆች ላይ ለየት ያለ ፍርድ ሰጡ። “ከአውሮፓ ወራሪ ጋር ሆነው የገዛ ወገናቸው ላይ ጥይት መተኮሳቸው ያሳዝናል። አሁንም ቀሪው ህዝብ እነሱን እያየ እንዲማር፤ ተንበርክከው የተኮሱበት ግራ እግራቸው እና ቃታ የሳቡበት ቀኝ እጃቸው ይቆረጥ።” ብለው ፈረዱ እንጂ አልገደሏቸውም።

ወደ አሁኑ የሱማሌ ክልል ልውሰዳቹህ። አካባቢው በ1879 ነጻ ከወጣ በኋላ ህዝቡ በሰላም መኖር ቢጀምርም፤ ኦሮሞዎቹ መሬት እና ከብታቸውን መነጠቃቸው ሊቆም አልቻለም። በወቅቱ የነበሩት የአካባቢው ኦሮሞዎች በተደጋጋሚ በሚደረግባቸው የድንበር ውጊያ ምክንያት ከብቶቻቸውን እየተዘረፉ፤ መሬታቸውን እየተነጠቁ፤ የሞቱት ሞተው፤ የቀሩት አካባቢውን እየለቀቁ ወጡ።  ባለንበት ዘመን ደግሞ ሰዎቹን ብቻ ሳይሆን የሰጡትን ስያሜ ጭምር ሊቀይሩት ሲጥሩ ተመለከትን። ለምሳሌ “ጅጅጋ” ማለት በኦሮምኛ “ዝቅ ዝቅ” እንደማለት ነው (የአካባቢው ከፍታ ዝቅ ያለ በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው)። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን “ጅጅጋ” ማለታችውን ትተው “ጅግጅጋ” በሚል መጤ ስያሜ ለመቀየር እና አዲስ ስም ለመስጠት የሚሯሯጡ ሰዎችን ታዝበናል።

የቅርቡን ታሪክ ትተን… እንደገና ወደኋላ እንመለስ። ይህ ሁሉ ግፍ በኦሮሞዎቹ ላይ ሲሰራባቸው፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ዝም አላሉም። ይልቁንም በራስ መኮንን አስተዳደር ወቅት… የሱማሌ እና የኦሮሞ ህዝቦችን በሚያጣሉት የድንበር ቦታዎች ላይ በሙሉ፤ ነፍጥ የያዙ ወታደሮች ተመደቡ። በኋላ ክልሉን ለቀው ሊሄዱ ሲሉ፤ ህዝቡ እንቢ ብሎ መሬት እየሰጠ፤ ልጆቻቸውን እየዳሩላቸው ኑሯቸውንም እዚያው አደረጉ። እነዚህ ነፍጥ አንጋቾች ወይም ነፍጠኞች…. አብዛኛዎቹ ከሰሜን ሸዋ የተውጣጡ ጎበዝ አልሞ ተኳሾች ነበሩ። ሱማሌው እንደለመደው የኦሮሞውን ከብት እና እርሻ ለመዝረፍ ድንበር እያለፈ ሲመጣ፤ በጥይት እየለቀሙ ስርአት አስያዙት። የ85 አመት አዛውንት የሆኑት  አቶ ሉልሰገድ ጎበና የሚነግሩን ቁም ነገር አለ… ቀደም ሲል በ1879 ምኒልክ ድል ሲያደርጉ እነሻቃ ተክሌን ሰንደቅ አላማ አስይዘው ወደሃረር መላካቸውን ተጨዋውተን ነበር። (የሻቃ ተክሌ ልጆች ደግሞ ፊታውራሪ ዝቅ አድርጌ እና ግራዝማች መኩሪያ ብዙ ታሪክ ያላቸው ጀግኖች ናቸው።) የሻቃ ተክሌ የልጅ፣ ልጅ፣ ልጅ ናቸው - አቶ ሉልሰገድ። በወቅቱ ልጅ ነበሩ። በአያታቸው ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሳሉ። የነገሩኝን ዝርዝር ታሪክ ሰብሰብ አድርጌ ላስነብባችሁ። እንዲህ አሉኝ… “በኋላ ላይ አያቴ ግራዝማች መኩርያ ተክሌ ወደ ጅቡቲ ድንበር አስተዳዳሪ ሆነው ተመደቡ። ከአፋሮች ጋር ጥሩ ወዳጅ ሆነው ነበር። ሱማሌዎቹ ተደራጅተው ወደ ኢትዮጵያ ሲዘልቁ፤ አፋሮቹ መጥተው ይነግሯቸዋል። ከዚያም ግራዝማች ሱማሌዎቹን እየተከታተሉ ይቀጧቸው ነበር…” እኚህ እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ኑሯቸውን እዚሁ አድርገው፤ እስከ2ኛ የጣልያን ወረራ ድረስ ዘልቀዋል። ከጣልያን ጦርነት በኋላ ኤጄርሳ ጎሩን አስተዳድረዋል። በዚህ አይነት ወልደው እና ከብደው የኖሩትን ሰዎች ነው ታድያ… ዛሬ በብሄር ብሄረሰቦች ሽፋን የሚሰድቧቸው።

“ክልላችንን የጦር ካምፕ አደረጉት” አልነበር የተባለው? እንግዲያው ሌላም ታሪክ እንጨምር። በ1953 ዓ.ም. በዋርዴር እና በገላዲን አካባቢ የሱማሌ ጦር በወገናችን ላይ ጉዳት ሲያደርስ፤ በመልሶ ማጥቃት ዘመቻ የ3ኛ ክፍለ ጦር አንድ ሻምበል ተንቀሳቅሶ ድል ተጎናጽፎ ነበር። በዚያው አመት ጄነራል አማን አምዶም ቡርበርዴን እና ቡክሲን አልፎ ሲመጣ… በጥቂት እግረኛ፣ መድፈኛ እና ፓራ ኮማንዶ ወታደሮች ወሰን አልፈው የመጡ የሱማሌ ወራሪዎችን ደምስሠዋል። ኢትዮጵያውያን በዚህ የኦጋዴን በርሃ የተሰዉት አካባቢውን የጦር ካምፕ ለማድረግ ሳይሆን ህዝቡን ከወራሪ ለመጠበቅ መሆኑን ለማወቅ ዲግሪ መጫን አይኖርብንም። በዚህ የምስራቁን ድንበር በማስከበር ላይ ከተሰማሩት ጀግኖች መካከል፤ በኦጋዴን በርሃ የእድሜውን ማምሻ የጨረሰውን ጀግናው አብዲሳ አጋን መጥቀስ ያስፈልጋል። የሱማሌ ባህል እና ብሄራዊ ማንነቱ እንደተከበረ ሆኖ፤ የኢትዮጵያውያን የህይወት መስዋዕትነት ሊዘነጋ አይገባም።

ዘንድሮ በሱማሌ ክልል የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሲከበር፤ ሌላውን ብሄር በመሳደብ ከሚከበር ይልቅ… ሌላው ብሄረሰብ ለዚህ ክልል ያደረገውን መልካም ነገር በማስታወስ፤ ታሪካቸውን በማወደስ… ሌላውን ኢትዮጵያዊ የሚያከብሩበትና የሚያመሰግኑበት ጥሩ አጋጣሚ ይሆን ነበር። ይህ ግን ሳይሆን ቀረና፤ የትላንቱ ታሪክ ተረስቶ… ጆሯችን የስድብ ውርጅብኝ ለማዳመጥ በቃ።

እሩቅ ባልሆነው በትላንት ታሪካችን… አካባቢው በሱማሌ ወራሪ ሃይል ሲያዝ የነበረውን ሁኔታ በማስታወስ ስንብት እናደርጋለን። በወቅቱ የሱማሌ ጦር ከራሽያ ያገኘው የጦር መሳሪያ ከኢትዮጵያ በአምስት እጥፍ የሚበልጥ ነበር። ይህን ሃይል በመያዝ በምስራቅ በኩል እስከ አዋሽ ያለውን የኢትዮጵያ መሬት ለመያዝ በቅተው ነበር። በገላዲን፣ በጅጅጋ፣ በደገሃቡር፣ በቀብሪደሃር፣ በጎዴ… እስከ ድሬዳዋ ድረስ የሱማሌ ጦር በምድር እና በአየር እየታገዘ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ወርሯል። ይህ ሁሉ ወረራ ሲደረግ ታዲያ… የሱማልያ ጦር ዝም ብሎ… መንገዱ አልጋ ባልጋ ሆኖለት አይደለም የገባው። በያንዳንዱ ግንባር የኢትዮጵያ ወታደሮችን እየገደለ፤ ሰላማዊ የሆነውን የአካባቢውን ነዋሪ እየጨፈጨፈ ነበር – ድሬዳዋ ድረስ የዘለቀው።

እነዚህን ሁሉ አካባቢዎች መልሶ በማጥቃት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የተከፈለው መስዋዕትነት ቀላል አልነበረም። በአካባቢው የነበረው 3ኛ ክፍለ ጦር እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል የፈጸሙት ታላቅ ጀብዱ ምንግዜም በታሪክ የሚወደስ ነው። F-5 ተዋጊ ጀቶች ከደብረዘይት እየተነሱ የሱማሌን እግረኛ በመትረየስ ሲረመርሙት፤ እግረኛው የኢትዮጵያ ጦር ደግሞ ሱማሌውን እግር በ’ግር እየተከተለ መግቢያ ያሳጣው ነበር። ከአየር ኃይል አብራሪዎች መካከል እነሜ/ጄነራል አምሃ ደስታ፣ ሜ/ጄነራል ፋንታ በላይ፣ ኮ/ል አስማረ ጌታሁን የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ደምሴ ቡልቶ እና ሌሎች… ከምንም በላይ ደግሞ በዚህ ጦርነት ላይ ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን፤ ለኢትዮጵያ ሲሉ ከየመን የመጡ መድፈኞች እና የኩባ ወታደሮች ጭምር፤ የከፈሉትን መስዋዕትነት ለአንድ አፍታም ቢሆን ልንዘነጋው አይገባም – ክብር ለነሱ ይሁን።

ኦጋዴን እና አካባቢው “ራሴን አስተዳድራለሁ” ብሎ ስራ መጀመሩ ደስ ያሰኛል እንጂ፤ ማንንም አያስቆጣም። ነገር ግን አሁን ያለው አይነት ጥላቻ፤ የአንድ መጥፎ ነገር አመላካች ነው። ሌላው ኢትዮጵያ ለዚያ አካባቢ ህዝብ የከፈለውን መስዋዕትነት ዋጋ የማንሰጠው ከሆነ፤ በርግጥም ችግር አለ ማለት ነው። አንዳንድ የሱማሌ ኢትዮጵያ ሰዎች ሌላውን ብሄር እንዲህ የሚጠሉት ከሆነ፤ “ምናለበት ታላቂቱ ሶማልያ በገዛችን ኖሮ?” የሚል አንደምታን ይፈጥራል።

በኦጋዴን ወይም በሱማሌ ኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ሲከበር፤ በአካባቢው ያሉትን የኦሮሞ ተወላጆች በማቀፍ በልዩነት ውስጥ አብረው መኖራቸው እንደጥሩ ምሳሌ ማሳየት ይቻል ነበር። በብሄር ብሄረሰቦች በአል ሰበብ… ሌላውን ህዝብ ከመሳደብ ይልቅ፤ ስለመስዋዕትነቱ ማመስግን ምንም ክፋት የለውም። ህዝብን ማመስገን ባንችል እንኳን፤ ምናል አምላካችንን ብናመሰግን? አምላክን በትንሹ ማመስገን ካልቻልን ያለንን ያሳጣናልና ተመስገን ማለትን እንወቅበት።

የማመስገን ነገር ከተነሳ አንድ የስንብት ታሪክ እናውጋ።

እኚህ ሰው… በኢትዮ-ሶማልያ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪ ነበሩ። በአየር ላይ ሆነው፤ የሱማሌ ተዋጊ ጀቶች ከፊት እና ከኋላ ሲመጡባቸው፤ በአየር ላይ እየተታኮሱ ቆይተው እሳቸው አቅጣጫቸውን ቀይረው ሲምዘገዘጉ፤ ሁለቱ የሱማሌ የጦር ጀቶች እርስ በርስ እንዲጋጩ አድርገው… ጸጥ አሰኝተዋቸዋል። እኚህ የአየር ኃይል አብራሪ በኋላ ላይ የሚያበሩት ጀት ተመትቶ እሳቸው በፓራሹት ወርደው ህይወታቸው ተረፈ። ሆኖም በሱማሌዎች መማረካቸው አልቀረም። ከሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በሱማሊያ እስር ቤት ለአስራ አንድ ከታሰሩ በኋላ ተፈቱ። በእስር ህይወታቸው ያጋጠማቸውን ነገር ሲያጫውቱን እንዲህ አሉ።

“የታሰርኩት በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ነው። እጅ እና እግሬ በካቴና ታስሯል። ከላይ ጣርያው ስለተሸፈነ የጸሃይ ሙቀትን እንጂ ብርሃኗን አይቼ አላውቅም። ወደውጭ የሚያወጡኝ ከጨለመ በኋላ በመሆኑ፤ ቀስ በቀስ የአይኔ ብርሃን ደከመ። እንዳልሞት ያህል ጥቂት ምግብ እና ውሃ ይሰጠኝ ነበር። በዚህ አይነት ለብዙ አመታት ስቆይ አምላኬን አማርሬው አላውቅም። አንድ ቀን ግን አምላኬን አማረርኩት። ‘ለምን እንዲህ ታሰቃየኛለህ?’ ብዬ በአምላኬ ላይ አዘንኩበት። የዚያኑ ቀን የነበርኩበትን እስር ቤት ለመጎብኘት አንድ የሱማሌ ወታደራዊ መኮንን መጣ። መኮንኑ እንደመጣ… እኔ ከጨለማው እስር ቤት እንድወጣ አዘዘ። ከዚያም እጅ እና እግሬ እንደታሰረ እሱ ፊት ቀረብኩ። የሱማሌው መኮንን እጅ እና እግሬ የታሰረበትን ሰንሰለት አይቶ ተቆጣ።”

“እንደዚህ አይነት ከፍተኛ እስረኛ እንዲህ ነው የሚታሰረው?” ብሎ አፈጠጠባቸው። አሳሪ ወታደሮች ግራ በመጋባት ዝም አሉ። እኔም አምላኬ ለቅሶዬን ሰማ። በእጆቼ እና በእግሬ ላይ የታሰረው ሰንሰለት ሊፈታልኝ ነው።” ብዬ ደስ አለኝ።

“የጦር መኮንኑ ቁጣውን ሳይቀንስ ሰንሰለቱን ፍቱ።” አላቸው። ከብዙ አመታት በኋላ ሰንሰለቱ ተፈታልኝ። የሱማሌው መኮንን አሁንም እየተቆጣ… “እንዲህ አይነት ከፍተኛ እስረኛ የሚታሰረው እንደዚህ ነው።” ብሎ… ቀኝ እጄን፣ ከቀኝ እግሬ ጋር፤ ግራ እጄን ደግሞ ከግራ እግሬ ጋር እንዲታሰር አዘዘ፤ እንደትእዛዙም ሆነ። በዚህ አይነቱ አዲስ አስተሳሰር… ቢያንስ ቆሜ እሄድ የነበርኩት ሰው አጎንብሼ ቀረሁ። በፊት እጅና እግር ለየብቻ በታሰሩበት ወቅት እንደልቤ እተኛ ነበር። አሁን ግን ለመተኛትም ተቸገርኩ። በፊት የነበረው አስተሳሰር ናፈቀኝ። ያንን ሁሉ አመት ስታሰር አንድም ቀን አምላኬን አማርሬው የማላውቀው ሰው፤ አሁን እርሜን አንድ ቀን ባማርር የባሰ ነገር መጣብኝ።” በማለት… ሰው ባለው ነገር ማመስገን እንዳለበት አስተምረውናል።

እኚህ በሱማሌ ጦርነት ወቅት ለአገራቸው ትልቅ ውለታ የሰሩ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪ ታደለ ይባላሉ። (የአየር ኃይል ማዕረጋቸውን አላውቀውም) ከ11 አመታት እስር በኋላ ከሱማሊያ እስር ቤት ተፈትተው አገራቸው ከገቡት ኢትዮጵያዊ አንዱ ናቸው። ለ11 አመታት ብርሃን ባለማየታቸው የአይናቸውን ብርሃን ሊያጡ ተቃርበው፤ በህክምና ነገሮች ወደነበሩበት ተመልሰውላቸዋል።

እኚህ አብራሪ ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ አንድ ልጅ ወለዱ፤ ስሙንም “በፀጋው” አሉት። ሃያ ምናምን አመታት ተቆጠረ። በፀጋው ታደለ ኢትዮጵያ አድጎ ለትምህርት ወደ አትላንታ መጥቶ፤ በታዋቂው ሞርሃውስ ዩኒቨርስቲ ሲመረቅ፤ ከትምህርት ቤቱ በሙሉ ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገቡ፤ ድንቅ ተማሪ ተብሎ… ሁሉንም ተማሪ በመወከል ንግግር ያደረገው እሱ ነበር። በእለቱ እንግዳ ሆነው የተገኙት የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ንግግራቸውን ከመጀመራቸው በፊት፤ መምህራኑን አመሰገኑ። ለዚህ ኢትዮጵያዊ ወጣት አድናቆታቸውን ለገሱት።

ስለሱማሌ እስር ቤት አስከፊነት እና ስለጭካኔያቸው አቶ ታደለ ከማንም የበለጠ አደባባይ ወጥተው መናገር ይችላሉ። እሳቸው ግን ያለፈውን እንዳለፈ ትተው፤ አዲስ ህይወት በመጀመራቸው ራሳቸው ተከብረው፤ ሌላውን ኢትዮጵያዊ የሚያስከብር ልጅ ለትውልድ አስረከቡ።

በሌላ በኩል ደግሞ ኦጋዴን ወይም የኢትዮጵያ ሱማሌ ከሽግግር መንግስቱ ግዜ ጀምሮ እስካሁን አስር የክልል ፕሬዘዳንቶች ተፈራርቀውባታል። ከነዚህ ፕሬዘዳንቶች መካከል አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማልያ ጦርነት ወቅት የሶማልያ አየር ኃይል ባልደረባ የነበረና ኢትዮጵያን በአየር ሲደበድብ የነበረ ሰው ነው። አንበሳው የኢትዮጵያ ጦር ተጠናክሮ በመጣበት ወቅት… በፋፈም ሸለቆ በኩል አድርገው ወደ ሃርጌሳ ይሮጡ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው፤ በብሄር ብሄረሰቦች በአል ሽፋን ሌላውን እየሰደቡት ነው። እንዲህ አይነቱ አሳፋሪ ተግባር የማይደገም ስለመሆኑ ምንም ዋስትና የለንም። እነሱ ሌላውን ደገኛ፣ የመሃል እና የዳር አገር ሰዎች እያሉ የጥላቻ መርዝ ሲነሰንሱ፤ የኛ ጉልበታችን እውነትን መናገር ነው፤ ታሪክን ማስተማር ነው።

በመሆኑም በኦጋዴን ወይም በሱማሌኢትዮጵያ ክልል ውስጥ… ለአንደኛው ብሄር ወይም ለሌላው ሃይማኖት ሳይሉ… ለኢትዮጵያ ድንበር መከበር እና ለህዝቡ አንድነት ብለው የህይወት መስዋዕት ለከፈሉት ጀግኖች ሁሉ ኢትዮጵያዊ አክብሮት አለን። ስለነሱ ክብር… በጨዋ ኢትዮጵያዊነት ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን… እንደየእምነታችንም በህሊናችን እናስታውሳቸዋለን። እናም ክብር እና ማዕረግ ለነሱ ይሁን።


ዛሬም አንደ ጥንቱ ባርነትና የሰው ንግድ

$
0
0

Ethiopians in Saudi
(ተፈራ ድንበሩ)

በሰዎች መካከል በጥቅም ላይ በሚደረግ ግጭት ጦርነት ከተደረገበት ጊዜ አንሥቶ ተሸናፊዎች በባርነት እንደተገዙ የታወቀ ሲሆን ሰውን እንደ ዕቃ የመሸጥ-መለወጥ ሥራ የተጀመረው በአረብ ነጋዴዎች ነበር። “Hugh Thomas” የሚባል መጽሐፍ ፀሐፊ “The Slave Trade and Robin Blackburn’s The Making of the New slavery“ በሚል ርዕስ በጻፈው መጽሐፍ ላይ እንዳስቀመጠው ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እሰከ 869 (ኢኤአ) አረቦች ሸቀጥ ይዘው ወደ አፍሪካ ሲወስዱ የአፍሪካ መሪዎች በገዛ ሕዝባቸው ሸቀጣቸውን ይለውጧቸው ነበር ብሏል። ከዚህ በታች ከመጽሐፉ በቀጥታ የተጠቀሰውን ይመለከቷል፦
“…it [slave trade] was pioneered by Arabs, its economic mechanism was invented by the Italian and Portuguese, it mostly run by Western Europeans, and it was conducted with the full cooperation of many African kings.” 1
ጎርዶን ሙሬይ ስለባሪያ ንግድ ከሬጂናልድ ኮፕላንድ ሥራ ጋር በማገናዘብ ያጠናቀረውን ጥናት እንደሚከተለው ገልጾታል፦

Read full Story in PDF/በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስለምኒሊክና ስለኢትዮጵያ

$
0
0

ጎልጉል ጋዘጣ

Ato Bulcha

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

Emperor Menelik II s

እምዬ ምኒልክ፡ የጥቁር ሕዝብ ኩራት

የአጼ ምኒሊክን መቶኛ የሙት አመት መከበር ምክንያት በማድረግ በ DW ሬድዮ በተደረገው ጥያቄና መልስ አቶ ቡልቻ

ደመቅሳ፣ ዶ/ር ሓይሌ ላሬቦና ዶ/ር ሹመት ሲሳይ (የታሪክ ተመራማሪዎች) ቃለ መጠይቅ ተደርጎ በሚሰጠው መልስ ላይ ስለ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በተናገሩት ላይ አስተያየቴን አቀርባለሁ።

አንባቢያንን ቃለመጠይቁን ቢያዳምጡ ጥሩ ነው ባይ ነኝ፤ ሁለቱ የታሪክ ምሁራን ትምህርታዊ ትንተና ይሰጣሉና፡፡

ውሸት ሲደጋገም እውነት ሊመስል ይችላል፤ በተለይም የአገራችንን የኢትዮጵያን ታሪክ ለማያውቁ እውነታው ምን እንደሚመስል መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ።

አቶ ቡልቻ ኦሮሞ ከባሌ እየተስፋፋ ሲመጣ ልብነ ድንግል እንዳይስፋፋ አቆሙት ይላሉ፡፡ ለምን ይህን ምሳሌ እንዳቀረቡም ግልጽ አይደለም ለሳቸው ትንታኔ የማይመች በመሆኑ፤ ለዛውም በአጼ ልብነ ድንግልና በኦሮሞች መሀከል ስለነበረው ግኑኝነት በከፊል ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ሊያስረድዋቸው ሞክረዋል፤ ስለመስፋፋቱና እንዲያውም አማራውን እንደገፋው ለአቶ ቡልቻ መረጃ ላቅርብ፡፡

ጥንት ሌላ ስም የነበራቸው በኦሮሞ ከተያዙ ማግስት ስማቸው የተቀየረ፤ ደዋሮ-ጨርጨር፣ ጋፋት-ሆሮ፣ ገራሪያ-ሰላሌ፣ ዳሞት-ወለጋ፣ አበቤ-በቾ፣ ሽምብራ ኩሬ-ሞጆ … (የሃያኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያ ገጽ 50 በጥላሁን ገ/ስላሴ) በቅኝ ተገዛ የሚሉት ኦሮሞ ተጨማሪ ቦታ እንደያዘ እንጂ እንደተወሰደበት አይደለም ታሪኩ የሚመሰክረው፡፡

BULCHADEMEKSAአቶ ባልቻ የኦሮሞን ታሪክ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ሊያዛምዱት ይሞክራሉ፤ ኦሮሞም እንደ ደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ሲረገጥ የኖረ ሕዝብ አድርገው ያቀርቡታል። መፍትሄውንም ሲጠይቁ reconciliation እርቅ ኦሮሞ ይቅርታ ተጠያቂ የተቀረው ይቅርታ ጠያቂ በተለይም የፈረደበት አማራ ለዚህ ወንጀል ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ባለፉት አስተዳደሮች ስህተቶች አልተሰሩም ብሎ የሚከራከር የለም፤ ጥያቄው እንዴት አብረን ወደፊት መሄድ እንችላለን ነው?

እንደቅኝ ተገዛን የሚሉት ቡልቻ ደመቅሳ አገሪቱን በእርሻ ሚኒስቴርነትና በምክትል ገንዘብ ሚኒስቴርነት አስተዳድረዋል – ቸር ቅኝ ገዢ ነበር የነበራቸው፤ እኛ ቅኝ እየተገዛን ስለሆንን በሚኒስቴርነት ቅኝ ገዢዬን አላገለግልም ብለው አላንገራገሩም፡፡

ኦሮሞ በሲቪሉም ሆነ በወታደራዊው ክንፉ ታላቅ የሚባሉትን ስልጣኖች ይዞ የኖረና ያለ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ አገሪቱ ውስጥ ለነበሩትና ላሉትም ደግ ነገሮችም ሆነ ክፉ ነገሮች ተጠያቂነቱ እኩል ነው፡፡ አቶ ቡልቻ ቅኝ ገዢ የሚሉትን የአማራውን ክፍለሀገር ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ ያስተዳድሩት ነበር፡፡ (ምሳሌ የሚያቀርቡበት ደቡብ አፍሪካ የማስተዳደር ቅንጦት ይቅርና ነጭ በሚዝናናበት ቦታ ጥቁር መግባት አይፈቀድለትም ነበር)፡፡

ስለኦሮሞ ባለስልጣናት እስቲ እንመልከት

ምኒሊክ በሸዋ ሲነግሱ የረዷቸው አብሮ አደግ ባልንጀራቸው ጎበና ዳጬ ናቸው፡፡ የወለጋውም አስተዳዳሪ ኩምሳ ምኒሊክን በደጃዝማችነት አግልግለዋል፤ እነ ባልቻ አባ ነፍሶም የማይረሱ ታላቅ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡

የአጼ ሃይለስላሴ አባት ራስ መኮንን ወልደሚካኤል (ጉዲሳ) አባታቸው ኦሮሞ ነበሩ፤ እናታቸውም ወ/ሮ እመቤት እናታቸው ኦሮሞ ነበሩ፡፡

ራስ ዳርጌ የሸዋው ንጉስ ሳህለስላሴ ከወለዷቸው አራት ወንዶች መሃከል አንዱ ሲሆኑ ጥናታቸው አርሲ ውስጥ የአንድ አካባቢ ኦሮሞ ባላባት ልጅ ነበሩ (አባ ቦራ በታቦር ዋሚ፤ ገጽ 9)

ራስ አበበ አረጋይ መከላከያ ሚኒስትር

አቶ ይልማ ዴሬሳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ የገንዘብ ሚኒስትር

ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ የጎንደር አስተዳደር

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የእርሻ ሚኒስትርን ምክትል የገንዘብ ሚኒስትር

ሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ የክብር ዘበኛ አዛዥና የባህል ሚኒስትር

ደጀዝማች ገረሱ ዱኪ የኢሊባቡርና የጎሙገፋ አስተዳዳሪ

ሜጀር ጀኔራል ደምሴ ቡልቲ የሁለተኛው ክፍለ ጦር አዛዥ

ሌተና ጀኔራል ጃጌማ ኬሎ የአራተኛው ክፍለጦር አዛዥና የባሌ አስተዳደር

ፊታውራሪ ለማ ወልደጻድቅ የሲዳሞ ምክትል አስተዳደር

ሜ/ጀኔራል አበራ ወልደማርያም የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ

ደጃዝማች በቀለ ወያ የጨቦና ጉራጌ አስተዳደር ከዚያም የጨርጨር አስተዳደር

ደጃዝማች ካሳ ወልደማርያም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና የእርሻ ሚኒስትር

አንባቢያን መረዳት ያለብን ሁላችንም በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያውያን መሆናችን ነው፡፡ ሕዝባችን በጋብቻ፣ በእምነት፣ በባሕል፣… የተሳሰረ በመሆኑ መሰረት የሌለው ታሪክ እያነበነቡ ሊበታትኑን የሚያስቡትን ታሪካዊ መረጃ እያቀረብን ወግዱ ልንላቸው ይገባል፡፡ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ነው፤ ምኒሊክም ያስተማሩን መቻቻልን አንድነትንና ፍቅርን ነው፡፡

ዶ/ር ካሳሁን በጋሻው

 

ኃያሉ አፄ ሚኒሊክ ለሴቶች እኩልነት ተግባራዊነት ዓለምን የቀደሙ ንጉሥ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 

ስርጉተሥላሴ

ስርጉተሥላሴ

ያን ዘመን ሳስበው ዛሬን መስለችን ያስለቅሰኛል። ያን ፈርጣማ ዘመን ሳስታውሰው ዛሬ ውስጣችነን መሳሳቱ ያቃጥለኛል። ያን ገድላማ ብቁ፣ ሥልጡን፣ ልዑቅ የአመራር ጥብብ ሳናግረው ግን መጽናናትን፣ ሙላትን ያጎናጽፍልኛል። ክብራቻን፤ ማንነታችን፤ ተፈሪነታችን፤ መሪነታችን፤ ብልህነታችን፤ እርግጠኛ ያደረጋል፤ የቀደምቶቹ ብቃት የሰማይ ገደል ለዛሬ ፍንጣቂ ማስተዋል ቢልክልን አምላኬ ምን አለበትም እላለሁ። የባዕዳን ግራሞት ጭብጥ፤ የእርስ በርስ ችግራችውን ዋጥ አድርገው በጋራ ቆመው ትንግርትን ሰማዕታት ማዘከራቸው የህሊናችን ዳኛ ሆኖ እኛን ሊገራን ባለመቻሉ ግን የልቤ ክናድ ይላል። ነገ ሌላ ቀን ነውና ነገን እንዲመርቅልን ህይወቱ ያላቸው አበው ሱባዬ ቢይዙበት ምኞቴና ናፍቆቴ ነው … አንደ ዕምነታቸው።

ዓለም ስለ ሴቶች ብቃት ብጣቂ እውቀት ባልነበረበት ጊዜ የኛው አፄ ኃያሉ ንጉሥ ሚኒሊክ ደማቸው – መንፈሳቸው – ሙሉዕ ፈቃድ ሰጥቶ ተግባር ላይ የዋለ በኽረ ጉዳይ ነበር የሴቶች እኩልነት። ኢትዮጵያ ሚስጢር ናት። ኢትዮጵያ ገድል ናት። ኢትዮጵያ ዓለም – ዓቀፍ ህግ ናት።  ኢትዮጵያ የቀደመች ሥልጡን መምህርት ናት። በዘመኑ የጣሊያን ተጋነት፤  የኢትዮጵያ ጥበበኛው መሪ የአፄ ሚኒሊክ አመራር ደግሞ ዕርቅና ሰላም ፈላጊነት ዓለምን ያሰደመመ መረቅ ትውፊት ነበር። ምርኮኛን ተንከባክቦና መርቶ ወደ ሀገሩ መሸኘትም አብነታዊ የአፄ ሚኒልክ ልዑቅ በኽረ ተግባር ነበር። ዛሬ ያሉት ሰበነካዊ ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች መሰረተ ጥንስስ ብቻ ሳይሆን ዓላማው ቀድሞ ኢትዮጵያ መሬት ላይ በድርጊታ ላይ የዋለው በድንቅነሽ አንባ ነበር – በብጡሎቹ።

ሀ. የእኩል ተሳትፎ ፈቃድ … ለሴቶች።

የጣሊያን ከመቀሌ አልፎ መስፋፋትን መመረጡ ያልተማቻቸው ንጉሥ ሚኒሊክ አልጋቸውን ለአጎታቸው ለራስ ዳርጌ አደራ ሰጥተው፤ ረዳትም ደጃዝማች ኃይለማርያምንና የወህኒ አዛዡን ወልደ ጻድቅን ጨምረው ሊነሱ ሲያስቡ ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ አልለይም ሲሉ ሙሉ እምነትና ፈቃድ ሰጡና እቴጌ ጣይቱ አብረው ዘመቱ። „ … ከጃንሆይ ጋር እቴጌ ጣይቱ አልለይም ብለው ጦራቸውን ይዘው ተጓዙ“ (ገጽ 100*)  „ „ወንድ ያለ ዕለት – በዕለት፤ ሴት ባለ በዓመት“ የሚለውን የሴቶችን መብት ደፍጣጭና ተጫኝ ኮስሳ ብሂል ቅስሙን እንኩት አድርገው የአካላቸውን ክፋይ የማይገሰስ ክብር ሰጥተው፤ ፈቃዳቸውንም ተንከባባክበውና አልምተው የታሪክ ዐይነታ ታዳሚ አደረጉት። ዘመናቸውንም ሙሉና ጌጣማ አደረጉት። የቀደመና የሰለጠነ መክሊት ባላጸጋው የንጉሦች ንጉሥ አፄ ሚኒሊክ የተግባር ምሰሶና ዋልታ ነበሩ ለሁለመናችን።

minilikለ. የጦር ጄኒራልነት፣ የአዋጊነት፣ የመሪነት፣ የአዝማችነት ጥንድ የእኩልነት ዕውቅና እና ዕሴቱ – ለሴቶች።

 ዓለምዓቀፉ የቅኝ ግዛትን ቅስም የሰበሩት ክቡር አፄ ሚኒሊክ „ሴትና አህያ በዱላ“ የሚለውንም ሥነ – ቃል ጨፍልቀው ከጠላት ጋር ለጦርነት ዐዲማህለያ ላይ በ10 ግንባር ካሰለፉት 30 ሺህ ጦር ውስጥ የልዕልታችን፤ የንግሥታችን  የእመቤት ጣይቱ ግንባር ከ3ሺህ ጦር ጋር አንዱ ግንባር ነበር። ይህ በዬትኛው የዓለም ታሪክና መዘክር የሚገኝ ጣዝማዊ ገቢር ነው። ማንም ሀገር እንዲህ በዚያ ዘመን የተግባር ዲታ የሆነ የሴቶች የእኩልነት ታሪክ የለውም። አባታችን፤ መሪያችን፤ መኩሪያችንና ንጉሣችን አፄ ሚኒሊክ ግን እኩልነትን የተቀበለ፤ እኩልነት በድርጊት ያዋለ፤ እኩልነትን ያከበረ – ያስከበረ – ያደመጠ፤ እኩልነትን በጥንግ ድርብ ካባ ያንቆጠቆጠ የመኖራችን ልዩ የታሪክ ጉልላት እንዲያብብ ፈቀዱ።

ስለዚህ አፄ ሚኒሊክ ለእኛ ለኢትዮጵያ ሴቶች ብቻም ሳይሆን ዓለምን በድርጊት ያስተማሩ ድንቅ የኢትዮጵያዊነት አንዱ ታላቅ ሚስጢር ናቸው። ንጉሥ ሚኒሊክ ለሴቶች እንደ አደራጅነተቻው የክብር አባላችን ሰንደቃችን ናቸው።

ኃያሉ የአፍሪካ ቀንዲል ንጉሥ ሚኒሊክ የሴቶችን የብቃት ሚስጢር መንፈስ ቅዱስ ስላቀበላቸው ውጤቱ አዲስ የጥቁር  የማይደፈር የድል ፕላኔት ሆነ። በውጊያውም ሳይደክሙ እቴጌ ጣይቱ ከአካላቸው ጎን ሆኑ በፋመው ውጊያ ላይ “ …  በዚህ ጊዜ ዐፄ ሚኒሊክ የጦር ወታደራቸውን በሚያበራታታ ቃል ሲያደፋፍሩ፤ እንዲሁም እቴጌ ጣይቱ እንደ ወንድ በጦርነቱ መካካል እዬተላላፉ የቆሰለውን ሲያነሱ፤ ለተጠማው መጠጥ፤ ለተራበው ምግብ ሲሰጡ ዋሉ“* ይሉናል ሊቁ ጸሐፊ (ገጽ 110 )የተደራጀ የቀይ መስቀል ተግባር በእናትነት ተፈጥሯዊ ክህሎት በቅሎ፤ በአጋርነት ጸድቆ፤ እንሆ … ሚስጢር ይቀዳል ከድንቅነሽ አንባ …. ከእግዚአብሄር በታች እኩልነታችን ያፀደቁ ብቸኛ መሪ፤ የእኩልነታችን መሸሸጊያ የልብ አድርስ እረኛ ፤ አስተዋሽ ጌታ ንጉሥ ሙሴ አፄ ሚኒሊክ።

ሐ. የእቴጌ ጣይቱ ብርሃነ ዘ ኢትዮጵያ በፖለቲካ እኩል የመወሰን አቀም ይለፍ በሀሴት ያረገበት ዕውነት፤

  “ሴት ቢያውቅ በወንድ ያልቅ“ ተረት ሆኖ ቀራንዮ የዋለበት ሌላው ትርጉም እቴጌ በባለቤታቸው የነበራቸው የላቀ ተደማጭነትና ተቀባይነት ነበር። ሴትነት ሰማይ ያረገበት ልበለው ከቶ? የአማካሪነት ልዩ ፈቃድ በገፍ ማግኘትና የመደመጥ እርግጠኝነት በልበ ሙሉነት መለገስ … አፄ ሚኒሊክ ለእቴጌ ጣይቱ ወደው ሰጡ። በጠባያቸው፣ በብልህነታቸው፣ በጣም ይወዷቸውና ያከብሯቸው ስለነበረ አብዛኛውን ጊዜ ውሳኔው የሚፀናው በእቴጌ ጣይቴ እንደ ነበረ ሊቁ ተክለጻድቅ መኩሪያ እንዲህ ይገልጡታል“ … አቴጌ የጠሉት ይነቀፋል ከሹመትም ይሻራል፤ የወደዱትም በንጉሰ ነገሠቱ ዘንድ ክብርና ሹመትም ያገኛል። ስለዚህ መሳፍንቱንና መኳንነቱ ንጉሡ ነገሥቱን እንደሚፈሩና ደጅ እንደሚጠኑ ሁሉ እንዲሁም እቴጌዪቱንም ደጅ ይጠኑ ነበር።  ዋው! ቅቤ የሚያጠጣ አንጀት የሚያረሰርስ ተመክሮ ነው። እንዴት ድንቅ ፈለፈል የሆነ ውብ ጥልፋማ ዘመን ነበር።

„ሴትና አይህያ … „ ቀርቶ … ውሳኔ የማመንጨት፤ የማሻሻል፤ የመሰረዝ የብቃት ልኬታን ይለፍ የሰጠው፤ እንዲሁም  የእቴጌ በራስ የመተማማን ስኬታማ ጉዞ  … ሲፈተሽ ደግሞ  „ይልቁንም የውጫሌ ውል የ17ኛው አንቀጽ ንግግር እንዲለወጥ በዐፄ ሚኒሊክና በኮንቱ አንቶኔሊ መካካል ክርክር ሲደረግ እቴጌይቱ በክርክሩ እዬገቡ ይነጋገሩበት ነበር። በኋለም በ 17ኘው አንቀጽ ንግግር ፈንታ የኢትዮጵያ ንጉሠ – ነገሥት ከመሬቱ አንድ ክፍል ወይንም በ17ኛው አንቀጽ የተባለውን ጥገኝነት ለሌላ ለውጭ አገር መንግሥት እንዳይሰጥ  ግዴታ ይግባና ይለወጥ ብሎ ሲያቀርብ …  ንጉሠ ነገሥቱ ይህንን ሃሳብ ከራስ መኮነን ጋር ሲመካካሩ እቴጌይቱ የፈቀድነውን ብናደርግ የኛ የግል ሥልጣናችን ነው እንጂ እሱን በፍጹም የሚያገባው ነገር የለም ብለው ውሉ እንዲቀር አደረጉ“ (ገጽ 131 እና 132)*

Emperor Menelik II sይህን ያህል ክብራችን ንጉሥ ሚኒሊክ ፍጹም የሆነ ሙሉ እምነት በሴቶች ብቃትና የመወሰን አቅም ነበራቸው። የሴቶችን ማንም ሊጋረው የማይችለውን የእናትነት ሰማያዊ ጸጋ ሥራ ላይ የዋሉ ብቸኛ ንጉሥ። ስለሆነም ሀገራቸውን፤ ሰንደቃቸውን ዳር ደንባራቸውን አስከበረው ተከበሩ። ምክር ስለ አዳመጡ ፍላጎታቸውን እውን አድርገው በሥልጣኔ ጎዳና እናት ኢትዮጵያን መሩ። ነፃነታችን በድል ስላቀለሙት አንገታችን ደፍተን ከመኖር ታደጉን። ተፈሪ፤ በራስ ቋንቋ የምትናገር፤ በቅኝ ያልተገዛች ብቸኛ አፍሪካዊት ሀገር፤ በራሷ ፊደል የምትጽፍ ሀገር፤ የጥቁር መመኪያና መጠጊያ፤ የእኔ የምትለው ህግ – ባህል – ወግ – እምነትና ልማድ ያላት ውብ ሀገር በደማቸው ሸለሙን። ቅይጥና የትውስት ነገር አልነበረንም። ሁለመናችን ጠረኑ እኛን ይመስል ነበር። የዛሬን አያድርገው አረሙ ወያኔ ለባዕድ እስከ ሸጠው እስከለወጠው ዱድማ ዘመን ድረስ ….። ክብራችን እናመሰግነዎታለን። ጌታችን እንወደወታለን ጸሐያችን፤  እመቤታችን ብርሃነ ዘ ኢትዮጵያ …. እቴጌ ጣይቱም የድርጊት ጀግንነተወት የተስፋችን ማህደር ነውና እናፈቅረወታለን። አላሰፈሩንም። ይልቁንም ድፈርትን አዋጡን እንጂ ….

ይቋጭ መሰል … ደግመን ያለገኘው እድል ነው ኃያሉ ሚኒሊክ በዛ ዘመን ሰጥተውን የነበረው። የእኩልነት ዕውቅና፤ የመኖር ነፃነት ኪናዊ ቃና። አፄ ሚኒሊክ ለሴቶች ተቀድቶ የማያልቅ ባለውለታ፣ ክንድና ደጅን ነበሩ።ይህ ዝቀሽ ታሪክ የሀገርን ዳር ደንበር በማስከበር ብቻ የተወሰነ አልነበረም። ለሰው ልጆች መብት ማስከበሪያ የዲሞክራሲ ሂደት ልዕል ጉልትም ነው ትምሀርት ቤት።

በዘመኑ በነበሩ ሌሎች መንግሥታዊ አስተዳደሮችና መዋቅሮች አመሰራረት ሆነ አመራር፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሥልጣኔ ጉዞ እርምጃ በተሰጣቸው የእኩልነት መብት እቴጌ ጣይቱ መጠነ ሰፊ ተግባራትን በመከወን የሴቶች ኮከብ፤ እመ ብዙኃን መሆን ችለዋል። ስለሆነም እቴጌ የናሙና የተግባር ተቋም ነበሩ። ያገኙትም ዕድል ባክኖ አልቀረም።  በአግባቡ በብልህነት ተጠቅመው ጸጋቸውን ዓለም እራሱ እንዲመሰክርበት አድርገዋል። የሰከነው ተሳትፏቸው በተግባር ከብሮ ሀገርን ያህል ዕንቁ ነገር አተረፈ። ትውልድን ገነባ። በነገራችን ላይ የቀደመው የእናት ሀገራችን ምስላዊ ካርታ እኮ እንደ ሌሎች ሀገሮች ቅኝ ለማደረግ ባሰበት ተሰመሮ የተሰጠን አልነበረም። በፍጹም! በደምና በአጥንት የጸደቀ አልማዝ እንጂ …. ። ይህ አዲሱ ዜማ „ጣይቱ የኛቱ“ ትንቢት ዕውን ከሆነ ኢትዮጵያዊነት እንደ ገና ያበራል። ተስፋ አያልቅ … ም። በመጨረሻ — አብሮነት ደስ ይላል – ያሳምራል … በመንፈስ ሃዲድ ለነበረን ቆይታ ትህትና ከአክበሮታዊ ምስጋና ጋር ሸለምኳችሁ።

ማሳሰቢያ  በትምህርተ ጥቅስ ባሉት ሥንኞች ውስጥ በጉልህ የተጻፉትና የተሰመረባቸው ኃይለ ቃላት፤ የበለጠ ለማሰረገጥ ብዬ እኔ እንጂ መጸሐፉ ላይ የለውም። በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ የሚገኙት ኮከብ ያለባቸው አገላለፆች ሁሉ ገፃቸው ከላይ ተጽፏል፤ የደራሲው ሥምና የመጸሐፉ እርእስ ሲደጋጋም እንዳትሰለቹ በማለት ከላይ አልጻፍኩትም።

( በ1936 ዓ.ም የኢትዮጵያ ታሪክ – ከዐፄ ቴወድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከሊቀ ሊቃውነቱ ክቡር ተክለ ጻድቅ መኩሪያ መጸሐፍ የተወሰደ ነው) ከትህትና ጋር ..

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘለዓለም ያዘራሉ!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ::

ይቁረጥ –በዳዊት ዳባ

$
0
0

ዳዊት ዳባ
Friday, December 06, 2013
denfo.dd46.gmail.com

1998 በቅድስት ባይልልኝ ተደርሶና  ተዘጋጅቶ ለእይታ የቀረበው ህይወት እንደዋዛ ድራማ ላእይታ ከቀረበ ሀያ አንድ አመት ሆነው። ቅድስት በዚህ ስራዋ በየአረብ አገሩ ለስራ የሚላኩ ዜጎች በይበልጥም የሴት እህቶቻችን ሂወት ምን ያህል በመከራና ስቃይ የተሞላ እንደሆነ እንደወረደና መታየት በሚገባው መንግድ አሳይታናለች። ይህንን ፊልም በጊዜው ሁላችንም ተመልክተን ጉድ ብለናል። ለረጅም ጊዜ ዋና መወያያችንም ነበር።  መንግስት ነን ያሉት ለቀጣይ ሀያ ምናምን አመታት በየአረብ አገራቱ ወንድምና እህቶቻችንን በገፍ ሲልኩ በነዚህ አገራት የሚጠብቃቸውን ፍዳ አናውቅም ነበር ሊሉ አይችሉም። ይህ ፊልም የችግሩን መነሻ ጊዜ አመላካችም ነው።

በቀጠሉት አመታት በመከራ ብዛት አይምሯቸው ታውኮ ወይ ያካል ጉዳተኛ ሆነው ያለረፍት ከመስራትና በተለያዩ መንገዶች ክብር የሆነ ሂወታቸውን አጥተው   እሬሳቸው ወደ አገር  የተመለሱ ወገኖቻችን ከመብዛታቸው ብዛት አሁን አሁን በትናንሿ መንደር ደረጃ ብዙም ማሰብ ሳይፈልግ ሁሉም ዜጋ በስም እየጠራ በቁጥር የሚያስቀምጠው ሆኗል። እረ እንደውም በዘምድ አዝማድ መሀል። አንድ ወይ ከዛም በላይ ሉሁላችንም ተዳርሷል።  እንትና እኮ አረብ ሀገር ሄዳ ከዛ ያሳዝናል ብለን የምናወራው አንጀት የሚያኮማትር ሀዘናችን ከሆነ ውሎ አደረ ። ዛሬ የእንባሲ ሰዎቻችው አይምሯቸው ታውኮና ለዘላለሙ እንዳይድኑ በሽተኛ ሆነው የሚመለሱትን ሳይጨምሩ በሳምንት ከስድስት እስከአስር እሬሳ ወደ አገር እንልክ ነበር እያሉን ነው። በእርግጥ ይህን መነገርም አያሻንም እናውቅ ነበር።

ከአገር ቤት ወደ አደጉት አገራት የሚበሩ አይሮፕላኖች የኛዎቹን ጨምሮ በማደጎ ስም የሚቸበቸቡ ኢትዬጵያዊ ህጻናት ወና ደንበኞቻቸው ናቸው።  በተመሳሳይ ጦርነት ላይ ያለች አገር እስክትመስል ከየአረቡ አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ በረራዎች እሬሳና ህሙማምን  በገፍ ማመላለስ ከጀመሩ ሀያዎቹን አመታት አስቆጥረዋል። በየአረብ አገራቱ ተጎጂ ስለሆኑ ዜጎቻችን ስናወራ የምናወራው ስለ አምስት ሞቶ ሺ ተጎጂዎች ወይ ስለ አንድ ሚሎዮን ተጎጂ ዜጎች አይደለም። ስለ ብዙ ሚሊዮን ተጎጂ ዜጎች ነው?። በተመሳሳይ  የምናወራው ዛሬ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ እየሆነ ስላለው ብቻ አይደለም ሀያ ሶስት አመት ስላስቆጠረ የዜጎቻችን መከራና አገራዊ ችግር ነው።

እነዚህ ብዙ ሚሊዮን ሰቆቃ የተፈፀመባቸው ዜጎች የበዙት ህጋዊ በሚባለው መንገድ ወደየ አረብ አገራቱ የተላኩ ናቸው። ህጋዊ የሚባለው መንገድ የትኞቹንም ተጎጂዎች እስከዛሬ አልታደገም። ህጋዊ መሆን አለመሆን  ምንም አይነት ልዩነትም አልነበረውም።  ልዩነቱ ፍዳውን ጉዞ ላይ መጀመር ወይ በሚመች አይሮፕላን ቶሎ ቦታው ደርሶ  የመከራውን ሂወት መጀመር ብቻ ነው። ወገኖቻችን እዛ ሲደርሱ ህጋዊ የሚያሰኛቸው ወረቀታቸው ባሰሪዎቻቸው እጅ ስለሚሆን ህገወጥ ብቻ ሳይሆን ያሰሪዎቻቸው ባርያ ነበር የሚሆኑት።  ላለመገደል፤ ላለመደፈር ሰቆቃ እንዳይፈፀምባቸው፤ ጉልበታቸው ያለአግባብ እንዳይበዘበዝ፤ የለፉበትን ሀቃቸውን እንዲይከለከሉ ህጋዊ ወረቀቱም ሆነ ወያኔዎች ተዋዋልን ወይ ስምምነት አደረግን ሲሉት የነበረው ቅራቅንቦ ምንም አልፈየደም።

ይህንን መካድም አይቻልም። አለም ሁሉ ያየውን ያለማቀፋ ሜድያዎችን ሽፋን ካገኙት ውስጥ የጋዳፊ ልጅ ሚስት ወ/ሮ ሀኒባል እህታችን ሸዋዬ ሞላ ላይ ያን ሁሉ ሰቆቃ የፈፀመችባት  ወረቀት ስለሌላት አይደለም። ወይስ ቤሩት ውስጥ ባደባባይ እየደበደቡና ኡ ኡ አድኑኝ፤ የወገን ያለህ እያለች አፍነው የወሰዷትና ጩህቷን አለም ስላየው ወስደው ከገደሏት በሗላ እሯሳን ገደለች ብለው የተፈፀማባትን ግፍ ያዳፈኑት አለም ደቻሳስ እሷም ህገወጥ ስደተኛ ስለነበረች ነበር ወይ?። በጭራሽ። እንዲሁ በየበረሀው የሰውነት ክፍሎቻቸውን የተሰረቁት ወገኖቻችን ህገ ወጥ ስለሆኑ ወይስ ተቆርቋሪ ስለሌላቸውና ውድ የሆነ የሰውነት ክፍላቸውን ስለተፈለገ።

አለም ባልሰለጠነበት ዘመን ሰዎች ያለፍላጎታቸው ባርያ ተደርገው ያድሩ ነበር። እጅግ ዘግናኝ ኢሰባዊ ድርጊት ይፈፀምባቸው እንደነበር አውቃለው። በጊዜው ባሮቹ ሲሸጡ ዋጋ ስላላቸውም ይሆናል  ዋና አላማው በሂወት እንዲኖሩና ስራ በነፃ እንዲሰሩ ነበር። ወያኔዎች  በየአረብ አገራቱ የምትልኳቸው ወገኖቼ ጉዳይ የሚመስለው “እስኪያብዱ ወይ እስኪሞቱ ባሰኛችሁ መንገድ አሟጣችሁ ተጠቀሙባቸው ነው።  ሰቆቃ ፈፅሙባቸው ነው። ሌላ ሙሉ ጉልበት ያለው ይላካል ትቀይሯቸዋላችሁ ነው።”   ይህን እንድል ያደረገኝ በየትኛውም ባርያ ማሳደር ህጋዊ በነበረበት ዘመን  ወይ በየትኛው የባርያ ስርአት የነበረበት አገር  ባርያ የተደረጉ የሰው ልጆች ሰቆቃና ስቃይ ስጋቸው መቋቋም እያቃተው በዚህ ብዛት(ሬሾ) ይሞቱ እንደነበር ወይ  ሰቆቃውን መሸከም እያቃተቸው ያብዱ እንደነበር ስለማላውቅ ነው። “ምን እያደረጓቸው ነው?” “ምን አይነት ማሰቃያ ነው የሚጠቀሙት?” የሚለው ጥያቄ ሁሌም የብዙ ተቆረቀቋሪ  ዜጎችና የኔም መልስ ያላገኘ እንቆቅልሽ ከሆነ ከረመ።

የሚያሳዝነው ግን የበዛው ኢትዮጵያዊ ሀዘኑና መጠቃቱ በየቤቱ እየገባ እያለም ባገር የመጣ(አገራዊ ችግር) አድርጎ በቶሎ አላየውም።  ችግር የሆነው በአገሪቷ ውስጥ ባለው አፈና ግዙፍነት  (አፈናውን በጭራሽ በጭራሽ አሳንሰን አንዳናየው)    ተጎጂዎቹ የሱ እህት፤ የነሱ ሰፈር ልጅ፤ ያአክስቷ ልጅ እንደሆነች እንጂ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በተመሳሳይ ስለባ እየሆኑ ያሉበት ስር የሰደደ አገራዊ ችግር አድርጎ አለማየቱ ነው።

ሁለተኛው ምክንያት ወደየአረብ አገራቱ የተገፉው ህዝብ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ነው። ስለ አረብ አገራት ስናወራ የምናወራው ስለህዝብ ነው። ክፉ ሰዎች ያሉትን ያህል ደግና ጥሩ ሰዎች ደግሞ አሉበት። በአገሮቹ መሀከልም የሰማይና የምድር ያህል ልዩነትም አለ። እድለኛ ሆነው እነዚህ ደጋጎች ጋር ተቀጥረው መስራት የቻሉት ወይ ሰቆቃ የማይበዛበት  አገራት ውስጥ የሄዱት ጉዳተኛ የመሆን እድላቸው ያነሰ ስለሆነ የተወሰኑት አምሮባቸው ገንዘብም ይዘው ወደአገር ቤት ይመጣሉ። ጎጆ ይቀይሳሉ፤ ቆርቆሮም ይቀይራሉ። ህዝብ ይህንንም አይቷል ሰምቷልም ስለዚህም ይህንንም አዳምሮ ነው ችግሩን ሲያይ የነበረው።

ሶስተኛው ምክንያት ሰቆቃውን መሸከም አቅቷት እስከመጨረሻው ያንቀላፋችው  ወይ አይምሮውን የሳተውን ጨምር ሁሉም በሂወት እስከነበሩና እስከቻሉበት ጊዜ የገኟትን ወደቤተሰቦቻቸው መወርወራቸውን አላቆሙም። ብዙዎቹ በደም፤ በላባቸው፤ በሰውነታችውና በሂወታቸው ዋጋ ይከፍሉ ነበር እንጂ አኗኗራቸው የገንዘብ ወጪ አልነበረበትም። እጃቸው የገባችውን ሁሉ ነው ሲልኩ የነበሩት። መንግስትን ያፀናው የበዛው ከውጪ ይገባል የሚባለው ገንዘብ በዚህ መንገድ ወደ ወደ አገር ሲፈስ የነበረ ነው። በተጨማሪ መናገር ምንም ላይፈይዱ ቤተሰብ ማሳሰብ ነው ብሎ በደላቸውን መደበቅም አለበት። ድቅድቅ ባለ አፈና ውስጥ ለምንኖር ህዝቦች በነዚህና ይህን በመሰሉ ሊሎች ምክንያቶች ተጨማምረውበት ህዝብ የችግሩን ስፋት፤ የጉዳቱን ደረጃና አገራዊ ውርደት መሆኑን ለማወቅ ጊዜ ቢወስድበት አያስገርምም።

በአግባቡ ያልተረዳነው ግን የችግሩን ደረጃና ስፋት ብቻም አልነበረም ። ከዛሬ ሀያ ሁለት አመት በፊት የመጀመርያዋ አይምሮ ህመምተኛ፤ የመጀመርያው እሬሳ  ሲገባ ጀምሮ መንግስት ያውቅ  እንደነበረም ነው።  የምናወራው የውስጥ ሱሪያችንን ቀለም ለማወቅ ስለሚሰሩ ዘረኛ ውላጆች ነው። በአሀዝ ማስቀመጥ በሚችሉበት ደረጃ አንድ ብሎ ሲጀምር ጀምሮ ያውቁ ነበር ። እኛ ግን ችግሩን በየግሉ ወስደን የልጆቻችን እሬሳ ሲልኩልን ተቀብለን አልቅሰን እንቀብራለን። አብደው ሲመጡ ዜጋው ተቀብሎ በግሉ ለማዳን መከራውን ያያል።

ሌላው አይደለም የበዛው ህዝብ ስር የሰደደ ችግር መሆኑን የሚያውቀውና ተቆርቋሪነቱን ሲያሳይ የነበረውም ወገን ውስጥም ብዙ ቁጥር ያለው  ዋና መሆን ይገባው የነበረውን መንግስት ተብዬው እዚህ አገራዊ ውርደት ውስጥ ያለውን ድርሻና ሀላፊነት  አውጥቶ ነው ችግሩን ሲያይ የነበረው። ዛሬም ድረስ ይህ ዳተኛ አመለካከት አለ።  ዛሬም በሳውዲ በወገኖቹ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ሰቆቃ እያየም ይሄ ፖለቲካ  አይደለም  ወይ መንግስትን አታስገቡበት የሚሉ ተላላዎች ብዙ ናቸው። ይህንን አይነት አመለካከት ህዝብ ውስጥ እንዲቀጥል የስራ ድርሻቸው የሆኑ ጊንጦችም አሉ። ወዲያም አደረግነው ወዲህ ግን መሪዎቻችን ዘረኛ ውላጅ ወያኔዎች ባይሆኑ ኖሮ ዛሬ በሳውዲዎች ወገኖቻችን ላይ የተሰራው ወንጀል አይፈፀምም ነበር። ሲጀመር ተቆርቋሪ መንግስት ባለበት፤ ለዛውም ሀያ ሶስት አመት መግዛት የቻለና መንግስቱን ያፀና መንግስት ባለበት አገር ዜጎቹ እራሳቸውን እዚህ አይነት ችግር ውስጥ ማግኘት አልነበረባቸውም። አንዴ ከገቡም ዘረኛ ውላጅ ወያኔዎች ባይሆኑ ስልጣን ላይ ያሉት በጣም፤ በጣም፤ በጣም በቀላሉ ይህን ግፍና ውርደት ማስቀረት ይቻል ነበር። ሰውዲ አረቢያ ውስጥ የሆነው በቀላሉ በርግጠኛነት  መከላከል ይቻል የነበረ ችግር ነው። የሰማነው አይነት ዎይታ በሌለበትና በሰከነ ሁኔታ በቀላሉ ወደ አገራቸው መመለስ ሲቻል ነው እነዚህ ጉዶች ቁጭ ብለው ሲያዩ የከረሙት። ዛሬ  የህዝብ ጩህትና ውግዘቱ ሲበዛ ተንደፋድፈውና አተረማምሰውት ይባስ ብለው ችግሩን ፎቶ መነሻና መታያ አድርገው ከውነውታል።

“ይቁረጥ!። ማንሿከክ አላውቅ ወይ በተፈጥሮዬ ማሽንክነት የለብኝም። ይቁረጥ ብያለው። ያለበለዚያ እኔ እቆርጥልሀለው”። ከረጅም ጊዜ በፊት ካየሁት ድራማ ሁሌም የማስታውሰው ትወና ነው።

ዛሬ በአለም ያሉ የደሀ ይሁን የሀብታም፤ አንባገነናዊ ይሁኑ ዲሞክራሲያዊ፤ አፍሪካዊ ይሁኑ ኢሲያዊ፤ ትናንት ነፃ የወጡም ይሁን የኛ አይነት የጠገበ ታሪክ ያላቸው አገራት የየትኛዎቹም አይነት መንግስታት ህዝበቸው በሌላ አገር መንግስታትና ህዝብ በዚህ ደረጃ ሰቆቃ እንዲፈፀምበት አይፈቅዱም። ሲፈፅም ማየትም የሚያስደስታቸው አይደሉም። ለሀያ ሶስት አመት አይደለም ለአንድ ቀንም የዜጎቻቸውን ያለ አግባብ መበደል አይተው ዝም የሚሉም በጭራሽ አንዳቸውም አይደሉም። በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ ያሉ መንግስታት በሙሉ የሚመሩት ህዝብ እራሱን የዚህ አይነት ችግር ውስጥ እንዳይገባ ያቅማቸውን የሚቻላቸውን ሁሉ የሚያደርጉ  ናቸው። ለማድረግ ቁርጠኛነቱና ፍላጎቱም ያላቸው ናቸው። ስለዚህም ይቁረጥ ብያለው።

ዛሬ በኛ ላይ እየሆነ ያለው ወገንታዊ የሆነ መንግስት ስለሌን ብቻ ነው። የምንሰማውን የወገን መገደል፤ መደፈር፤ ይውጡልን መባል መንጓጠጥ፤ ማበድ በአጠቃላይ በየአረብ አገራቱ በወገናችን ላይ የደረሰውን ሰቆቃ ሁሉ  ማስቀረት የሚቻልበት አንድ ሚሊዮን ቀላል የሆኑ መንገዶች ባሉበት የሚፈፅም ነው። ምን ያደርጋል የኛዎቹ መሪዎች ጋር ፍላጎቱ የለማ። ወገንታዊነት ሸቀጥ አይደለም። እሱቅ የማይሸጥ ሆነ። ስለዚህም ለምን? እኛ ኢትዮጵያዊያን ላይ ብሎ ለሚጠይቅ በቂ ከበቂ በላይ አጥጋቢ የሆነ ምክንያት ያለው ችግር ነው። ወደፊትም የሚገዙን ወያኔዎች እስከሆኑ የዚህ አይነት አገራዊ ውርደትና የዜጎች መጎዳት የሚቀጥል ነው።

ችግሩ ላይ የዜጎች ግንዛቤና’ የመንግስት አያያዝ እላይ ባየንበት ጠቅለል ያለ ሁኔታ ላይ እያለ ነው ኢሳት አገልግሎቱን የጀመረው። ኢሳት በዋናነት ህዝብን ስለችግሩ በማሳወቅ ከፍ ያለ ሚና ተጫውቷል። ላለፉት ሶስት አመት ተኩል ህዝብ ማወቅ መብቱ የሆነውን እውነት ይነግረው ጀመረ። የመንግሰት ደርሻ፤ ግዴለሽነትና ዜጎቹን ለመታደግ አለመፈለግ ያጋለጥ ገባ።  ወያኔዎች አያሳደዱና እያዋከቡ እነዚህ የመከራ አገር የከተታቸው ጋዜጠኞች እቦታው ሆነው የመከራውን ብዛት እውነቱን የማጋለጥ የጀግና ስራቸውን ቀጠሉበት፤ ወገንታዊ ሜዲያዎች ይህ የዜጎች ሰቆቃና መከራ ዋና አምዳቸው ሆነ። ምሁራን ፀሀፍት እንዲሁ በውጪም በአገር ውስጥም ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና ወገንታዊ የሆኑ ዜጎች ባገኙት አጋጣሚ ይናገሩበት ይፅፉበት ጀመረ። ችግሩ ሊደበቅ ከሚችለው ደረጃ አልፎ የውጪ ሜዲያዎች ሽፋን ማግኘት ጀመረ። እንደምናያው ተንተክትኮ ተንተክትኮ መገንፈል ጀመራል። እዚህ ላይ ያለማቀፉ የሴቶች ማህበር ያደረገው ያላሰለሰ ጥረት  እጅጉኑ የሚያስመሰግናቸው ነው።

ወያኔዎች ይህን አገራዊ ውርደት የችግሩን መጠንና የተጎጂ ዜጎችን ሰቆቃ ግዝፈትና በነሱ ምክንያት ይህ መከራ አንደመጣብን ህዝቡ ማወቁ እየጨመረ መሄዱን ሲገነዘቡ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ በሟቹ መለስ ዜናዊ የተደረሰ ‘ያዞ እንባ” የተሰኘ ድራማ መፍትሄ ነው ብለው መተወን ጀመሩ። ከሀያ ሁለት አመት በሗላ  መሆኑ ነው።ክንቅልፍ እንደባነነ ህፃን በገፍ ለመካራ ሂወት ስላጋዟችውና ስላሰደዷቸው ዜጎቻችን እንደማያውቁ ሆነው እንደ አዲስ ሊነግሩን ጀመሩ።  መፍትሄ ፈላጊዎች ችግሩ ላይ ተረቃቂዎች ሆነው ለመታየ እላይ እታች አሉ። ተሰብስበው አልቅሰው ሊያስምኑን ሁሉ ሞክረዋል። ይህ መራወጥ የገባው ድራማውን “ከአዞ እንባ” ወድ “ሀይሌ እንባ”  ቀይሮ ቁጭ ብሎ አየው።   መፍትሄ ብለው የሞከሩት ድራማ ያስገኘው ውጤት ህዝብ የበለጠ ስለችግሩ እንዲያውቅና መታየት በሚገባው መንገድ የገዘፈ ሀገራዊ ችግር አድርጎ እንዲያየው ማድረግ መቻሉ ብቻ ነው። አሁን ለረጅም ጊዜ ችላ ከመባሉ ብዛት ችግሩ ነቀርሳ ሆኗል። ለገዥዎቻችን መፍትሄውም ከጃቸው ወጥቷል። ህዝብ ብሄራዊ ውርደትና በያንዳንዱ ዜጋ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት አድርጎ ወስዶታል። ለወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው የቀራቸውና ማምለጫው መንገድ በጊዜ ማቄን ጨርቄን ሳይሉ መሸሽ ብቻ ነው እላለው።

ይህ ፅሁፍ ለፕሮፌሰር ተኮላ ሀጎስ  ባደባባይ የተሰጠ መልስም  ተደርጎ ይወሰደልኝ። ጊዜው አንዳንድ መያዝን ይሻል።  የሚቀናቀን ካልመጠ ተመችተውኝ ቀድሜ ይዣቸዋለው።   ወደፊትም በፃፉ ቁጥር መልስ እሰጣለው። የበዛው አንባቢ ዘረኝነት ፃያፍ የሰውን ልጅ ፍረድና አመለካከት ምን ያህል እንደሚያዛባ ያውቃል። ዘረኝነትን ግን እስከ ቦርቃቃ አፉ፤ አስከ ስድስት እግሩ፤ አስከ ጥፍራም እጆቹና እስከ ተንጨባረረ ፀጉሩ አውሬውን ማየት ከፈለጋችሁ የኚህን እውቅ ፕሮፌሰር ፅሁፎች አንብቡ። በቅርቡ አቦጊዳ ላይ የወጣላቸው ፅሁፋቸው አውሬውን በደንብ ልታዩበት የምትችሉበት ነው።

 

Pen

 

ለባለስልጣናት እንጸልያለን፤ ግፍን ግን አንታገስም ! ግርማ ካሳ

$
0
0

Muziky68@yahoo.com

triad candles croppedበቅርቡ በአቶ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ላይ ጠንካራ ትችት ያዘለ ጽሁፍ ለአንባቢያን አቅርቤ ነበር። አዉራምባ ታይምስ ጽሁፌን «What’s the hell is wrong with Haile Mariam Desalegn”  በሚል ርዕስ  ነበር ለአንባቢያኑ ያቀረበዉ። ይህ  ርዕስ ፣  የአዉራምባ ታይምስ ኤዲተር ምርጫ እንጂ የኔ እንዳልሆነ በቅድሚያ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ።

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ብዙዎች እንደ «እግዚአብሄር ሰው» ይቆጥሯቸዋል። በየቀኑ ጸሎት እንደሚያደርጉ፣ መጽሃፍ ቅዱስን እንደሚያነቡም ይናገራሉ። እርግጥ ነዉ፣ ሰዎች ጸሎት ሲያደርጉና መጽሃፍ ቅዱስ ሲያነቡ፣  መልካም ነዉ። ነገር ግን ጸሎት ማድረግና መጽሃፍ ቅዱስ ማንበብ፣ በራሱ የእግዚአብሄር ሰው ያሰኛል ብዬ አላስብም። ቄስ፣ ወንጌላዊ፣ ፓስታር፣ ጳጳስ ..መሆን የእግዚአብሄር ሰው አያሰኝም። መስቀል ይዞ መዞር፣ በያሬዳዊ ዜማ ቅኔ መዝረፍ፣ በልሳን መጸለይ ….የእግዚአብሄር ሰዉነት መመዘኛ አይደለም።

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የተባረኩ ሴት ልጆች አሏቸው። ልጆቻቸው፣ የሚኒስቴር ልጆች ሆነዉ እያሉ፣ ሳይኮሩ፣ ከሌሎች በላይ ለመሆን ሳይሞክሩ፣  በሚሄዱበት ቤተ ክርስቲያን፣ እሁድ ከአምልኮ/ቅዳሴ  በኋላ፣  ሻሂ እያፈሉ ምእመናንን እንደሚያስተናግዱ አንብቢያለሁ። በአባታቸው ስልጣን፣ በሶሻል ስታተሳቸው ሳይመኩ፣ እራሳቸዉን አዋርደዉ፣  ሌላዉን ማገለገል መቻላቸዉ፣ በርግጥ የልጅ ትልቅ መሆናቸውን ያሳያል። የእግዚአብሄር ሰዉነት መመዘኛ እንግህ ይሄ አይነቱ ትህትና የተሞላበት ተግባር ነዉ። (የአቶ ኃይለማሪያም ባለቤት ወ/ሮ ሮማንም፣ ከአንድ አመት በፊት ቀዳማዊ እመቤት ከነበሩት የሰማይና ምድር ያህል የሚራራቁ፣   እንደ ቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ዉብአንቺ ቢሻዉ፣ ትሁትና ሰው አክባሪ እንደሆኑ ይነግራል )

አንድ ጊዜ እንዲህ ሆነ። አንድ ሰው ከኢያሪኮ ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዝ ወንበዴዎች አገኙትና በሕይወትና  በሞት መሃከል እስኪሆን ድረስ ደብድበዉት ሄዱ። ሃዘኔታና ርህራሄ የሌላቸው፣ ሌሎች ሲሰቃዩና ሲጎዱ ምንም የማይመስላቸው፣ የሰው ልጅ ስብእናና ክብር እንደ መጫወጫ ካርታ የሆነባቸው፣ ሰዉን በዉሸት ክስ የሚያስሩ፣ እየተኮሱ የሚገድሉና የሚደበድቡ፣ በሰላማዉያን ላይ ሽብር በመንዛት፣ ሰዎች  በሰላም ወጥተዉ በሰላም እንዳይገቡ፣ የፈለጉትን እንዳይጽፉና እንዳይናገሩ፣ በአገራቸው እንደ ስደተኖች እንዲሆኑ የሚያደርጉ፣ እያስፈራሩ ሌላዉን የሚያሸማቅቁ፣ የዘመናችን «ወንበዴዎች» በአገራችን ኢትዮጵያ ብዙ አሉ። እንደዉም በስፋት በየሬዲዮና ቴሌቭዥኑ የምንሰማዉ እነርሱን ነዉ።

በመንገድ ዳር የወደቀውና የተደበደበው፣ የሚረዳው ፈልጎ እያቃሰተ ሳለ፣  ድንገት አንድ ቄስ/ፓስተር በመንገድ ዳር አለፉ። ካባ ለብሰዋል። በታላላቅ መንፈሳዊ ጉባኤዎች የእግዚአብሄርን ቃል የሚያስተምሩ፣ መጽሃፍ ቅዱስ የሚያነቡና ፣ የ«እግዚአብሄር ሰው» የሚባሉ ናቸው።  ነገር ግን የቆሰለዉን ሰው ባዩ ጊዜ እንዳላየ ሆኑ። መንገድ ቀይረው ፣ ለተገፋዉና ለተጎዳው እጃቸውን ሳይዘረጉ ጉዟቸውን ቀጠሉ። ትንሽ ቆይቶም አንድ ሌዋዊ (ዲያቆን)፣ ትንሹ የ«እግዚአብሄር ሰው»  መጣ። እርሱም እንደ ቄሱ እንዳላየ ሆነ አልፎ ሄደ።

ሳምራዊያን የሚባሉ ነበሩ። እግዚአብሄርን እንደማያውቁ ሐጢያተኞችና የረከሱ  ተደርገዉ የሚቆጠሩ።  ታዲያ አንድ ሳምራዊ፣  በወንበዴዎች ተደብድቦ የወደቀዉ ሰው ባለበት መንገድ አለፈ። ቁስለኛዉን ሲያይ ቆመ። ከበቅሎው ወረደ። ተጎነበሰ። ከአንገቱ ሰዉዬን ደግፎ፣ የያዘዉን ወይን ጠጭና ዘይት በሰዉዬዉ ቁስል ላይ አፈሰሰ። ሽሚዙን ቀደደና የሰዉዬዉን ቁስል አሸገ። ሰዉዬን ተሸክሞ በበቅሎው ላይ ጭኖ፣  እርሱ ግን በእግሩ፣  አብረው መንገድ ጀመሩ።  ቁስለኛዉን ወደ አንድ ሆቴል ቤት ገንዘብ ከፍሎ አሳረፈ። አስገራሚ ፍቅር ! አስገራሚ ሰብዓዊነት ! አስገራሚ ርህራሄ ! ይህ ታሪክ፣  ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣  የእግዚአብሄር ሰዉ፣  ምን ማለት እንደሆነ ለማስተማር የተናገረው ግሩም ታሪክ ነዉ። ቄሱ፣ ወይንም ዲያቆኑ ሳይሆኑ፣  «የእግዚአብሄር ሰዉ አይደለም» ተብሎ ይቆጠር የነበረው ሳምራዊዉ ነበር፣  በአምላክ ሚዛን የእግዚአብሄር ሰው የተባለው።

በመጽሃፍ ቅዱስ ፣ ኢሳያስ 1፡ 16 እንደተጻፈው፣ እግዚአብሄር ምን ያህል የፍትህ አምላክ እንደሆነ፣ ሲናገር «መባዎቻችሁንና ሰንበታችሁን፣ በጉባኤ መሰብሰባችሁን አልወደዉም። በደልንም የተቀደሰዉንም ጉባኤ አልታገስም። መባዎቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች። ሸክም ሆነዉብኛል። ልታገሳችሁ ደክሜያለሁ።  እጆቻችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፣ አይኔን ከእናንተ እሰዉራለሁ። ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም …. ፍርድን ፈልጉ። የተገፋዉን አድኑ። ለድሃ አደጉ ፍረዱለት፤  ስለመበለቲቱም ተሟገቱ። » ነበር ያለው። ከሚደረጉ ዉጫዊና ሃይማኖታዊ ስርአቶች በላይ፣ እግዚአብሄርን የሚያስደስተው፣  የሰዉ ልጆች ደህንነትና ስብእና ነዉ።   አስር ሺህ ቅዳሴዎችና መንፈሳዊ ጉባኤዎች ይልቅ ፣ አንድን ሰው ከወደቀበት ማንሳት፣ አንድን በግፍና በዉሸት የታሰረን ሰው ማስፈታት፣ አንድ የተገፋና የተጮቆነን ሰው ቀንበር መስበር፣ አንድን ሰዉ ማዳን፣  በጌታ ፊት የበለጠ ክብር አለው። የእግዚአብሄር ሰው መሆን ማለት፣  ለፍትህ መቆም ማለት ነዉ። የእግዚአብሄር ሰው መሆን ማለት  ሙግት መፍጠር (መታገል) ማለት ነዉ። ምን አይነት ሙግት ?  የተቀደሰ ፣ ስድብና ጥላቻ የሌለበት፣  ሰላማዊ የሆነ፣  ለፍትህ የሚደረግ ሙግት!

በአገራችን ኢትዮጵያ ያሉ፣ ልንታገልላቸው ወይንም ልንሟገትላቸው የሚገባ  «መበለቶች» ብዙ ናቸው። ገዢዎች ከሚፈልጉት ዉጭ በመናገራቸው፣ እዉነትንና እኩልነትን በመስበካቸው ፣ በዉሸት ክስ፣  «ሽብርተኞች» ተብለው በወህኒ የተወረወሩ፣ ፍርድና ፍትህ የተነፈጉ ሁሉ «መበለቶች» ናቸው።  ሙስሊም ሊሆኑ ይችላሉ፣  ከርስቲያኖች ሊሆኑ ይችላሉ! ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ወላይታ ሊሆኑ ይችላሉ! ጉዳዩ የሰብአዊነት እንጂ የሃይማኖት ወይንም የዘር አይደለም።

ለምሳሌ እነ እስክንደርን እንዉሰድ። በግለሰብ ደረጃ እስክንድር ነጋን እና አንዱዋለም አራጌን አውቃቸዋለሁ። ብዙ ጊዜ በአገራችን ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦችን በግል ተለዋውጠናል። ስለ ትጥቅ ትግል፣ ስለ ግንቦት ሰባት ወዘተረፈ ያላቸውን አመለካከት በሚገባ አውቃለሁ። የጻፉትን እና በአደባባይ የተናገሩትን ተከታትያለሁ። የነርሱን አገር ወዳድነትና ሰላማዊነት፣ በየትኛዉም ፍርድ ቤት ሆነ አደባባይ፣  እጆቼን መጽህፍ ቅዱስ ላይ ጭኔ የምመሰክረው ነዉ።  እግዚአብሄርን  የሚወዱ፣ ቤተሰባቸዉን የሚወዱ፣ በአገራችን እርቅና ሰላም እንዲመጣ የሚናፍቁ፣ ማንም የማያነቃንቃቸው የሰላም አርበኞች ናቸው።  እስክንድርና አንድዋለም እንዲሁም ሌሎች የሕሊና እሥረኞች የአገራችን «መበለቶች» ናቸው። እስክንደርና አንዱዋለም እንዲሁም ሌሎች፣ በመንገድ ዳር ወንበዴዎች እንደደበደቡት ሰዉዬ ናቸው።

እንግዲህ «መጽሃፍ ቅዱስን እናነባለን፤ እግዚአብሄርን እናምናለን. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንከተላለን» ካልን፣   እየመረጥን አይደለም እግዚአብሄርን የምንታዘዘው። ለተገፉ፣ ለወደቁ፣ በዉሸት ለታሰሩ፣ ፍትህ ለተነፈጉ፣  ወገኖቻችን መቆም መጀመር አለብን።  በጣም አሰምርበታለሁ። ለታሰሩ እስረኞች መቆም ክርስትና ነዉ !  ለፍትህ ለዜጎችን ነጻነት መቆም፣  መጽሃፍ ቅዱሳዊ ነዉ። የእግዚአብሄርን ቃል መታዘዝ ነዉ።

በአንጻሩ፣ ግፍ፣ ቀንበር፣ ጭቆና እያየን፣  ዝምታን ከመረጥን፣ የእግዚአብሄር ቃል እንደሚለዉ  መባዎቻችንና ሰንበታችሁን በጉባኤ መሰብሰባችንን እግዚአብሄር አይወደዉም። እጆቻችንን ወደ እርሱ ብንዘረጋ፣ አይኖቹን  ከእኛ ይሰዉራል።  ልመናንም ብናበዛ አይሰማንም።  ሌላዉ በግፍ ሲታሰር ዝም ማለት፣ ከራሳችን ጥቅምና ምቾት አልፈን አለመሄድ፣ የዘመኑ ጡንቸኞችን ቢያስደስትም፣ ጥቂት ፍርፋሬዎች ቢወረወርልንም፣  የዘላለም አምላክ እግዚአብሄርን  የማያስደስት  እርግማን ነዉ። ነዉር ነው።

አንዳንዶች የመንግስት ባለስልጣናት ላይ ተቃዉሞ ማንሳታችንን ተገቢ እንዳልሆነ ለማሳየት፣ ከመጽሃፍ ቅዱስ አንድ ጥቅስ ነጥለው በማውጣት ለማስተማር የሚሞክሩ፣ ቄስ/ፓስተር ተብዬ የአገዛዙ ካድሬዎች አሉ።  «ለባለስልጣን ጸልዩ፣ ታዘዙ» ተብሎ ስለተጻፈ «ፖለቲካ ዉስጥ ሳንገባ ፣ ታዘን መኖር ነው ያለብን» ይሉናል። አዎ ፣ በዚህ ምክንያት የአገሪቷን ሕግ እናከብራለን። ግብር በጊዜው እንከፍላለን። በትክክል የአገሪቷን ሕግ ከጣስን መቀጣታችን ተገቢ ነዉ እንላለን። ለአቶ ኃይለማሪያም ፣ ልቦና እንዲሰጣቸው፣ በልጆቻቸው ያለው የርህራሄና የፍቅር መንፈስ በርሳቸውም እንዲሰርጽ ፣ አብረዋቸው ያሉ የሰይጣን መልእክተኖችን ሳይሆን የእግዚአብሄርን መንፈስ ማዳመጥ እንዲጀምሩ፣ ሕዝብን ማስተዳደር የሚችሉበት ጥበብ  ጌታ እንዲሰጣቸው ሊጸለይላቸው ይገባል። እኛም እንጸልያለን።

ነገር ግን ባለስልጣናት ግፍ ሲፈጽሙ፣ ለነርሱ እንደምንጸልየዉ ሁሉ ፣ እነርሱን መሟገትንና መታገል  የግድ ነዉ። ነብዬ ናታን ንጉስ ዳዊት ስልጣኑን ተጠቅሞ የሰው ሚስት ደፍሮ፣ የደፈራትም ሴት ነፍሰ ጡር ስትሆን፣  ሐጢያቱን ለመደበቅ ባሏን ባስገደለ ጊዜ፣  ንጉሱን  ፊት ለፊት አወገዘ፣ ተቃወመ። «ለባለስልጣን ታዘዝ» ተብያለሁ ብሎ ዝም አላለም። ንጉስ ሄሮድስ አንቲጳስ፣ የወንድሙን ፊሊጵስ ሚስት ሄሮድያዳን ነጥቆ የራሱ በማድረግ ጸያፍ ተግባር በፈጸመ ጊዜ፣ መጥምቁ ዮሐንስ፣ በአደባባይ ነዉ «ንስሐ ግባ»  ብሎ ያወገዘዉ።  በዚህም ምክንያት ሄሮድስ የመጥምቁን አንገት ሁሉ አስቆርጧል።

የእምነት ሰው መሆን ማለት፣  ባርነትን መቀበል ማለት አይደለም። የእምነት ሰው መሆን ማለት አደርባይ መሆን አይደለም። የእምነት ሰው መሆን ማለት የፍትህ፣ የሰላምና  የነጻነት አርበኛ መሆን ማለት ነዉ። የእምነት ሰው መሆን ማለት እንደነ ነብዩ ናታን፣  ባለስልጣናት ስልጣናቸውን ተጠቅመዉ የሚፈጽሙትን ግፍ ማውገዝና መቃወም ማለት ነዉ። እነ ነብዩ ናታን እንዳደረጉት እኛም፣ ግፍን በምናወግዝበት ጊዜ፣ «እግዚአብሄርን እናምናለን»  የሚሉ ሊቀላቀሉን ይገባል እንጂ ዝም እንድንል ሊነግሩን አይገባም።

አቶ ኃይለማሪያምን  እንወዳቸዋለን፤ መልካም ሲሰሩ ፣ ደግፈናቸዋል፤ ወደፊትም እንደግፋቸዋለን። ነገር ግን ክፋታቸውን፣   አይተን ዝም አንልም። በሽብርተኝነት ስም ፍርድ ሲያዛቡ፣  በዜጎች ላይ ሲዝትኑ ዜጎችን ሲያስፈራሩ ዝም አንላቸዉም። «ባርነት ፣ ጭቆና፣ ግፍ፣ ዘረኝነት፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ .. በቃ ! »  ብለናል።  ግፍን አንታገስም። ጥቂቶች የሕዝቡን መብት ረግጠው እንዲቀጥሉ አንፈቅድላቸዉም። ይሄን እንሟገታለን፤ ይሄን እንታገላለን። ጆሮ ያለው ይስማ። ልብ ያለው ያስተውል። እግዚአብሄር ልቦናችንን በፍቅሩ፣ አይምሯችንን በጥበቡ ይሙላልን ! አገራችን ኢትዮጵያ እንዲሁም ኤርትራን ይባርከልን !

በሰላማዊ ትግልና ባህሪያቱ -ክፍል አራት (በአቶ ግርማ ሞገስ)

$
0
0

 

Girma Moges

አቶ ግርማ ሞገስ

በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርት (አንድነት) በሰላማዊ ትግልና ባህሪያቱ ክፍል አራት በአቶ ግርማ ሞገስ በስካይፕ የሚሰጠው ስልጠና ተጠናቋል። ዝርዝሩ ዝቅ ብሎ ቀርቧል።]

አምባገነኖች ስልጣን ላይ ለመቆየት ህጋዊነት፣ የህዝብ ድጋፍ እና ትብብር፣ የአገር ተፈጥሮ እና የኢኮኖሚ ሃብት ባለቤትነት የተባሉትን የፖለቲካ ኃይል ምንጮች መቆጣጠር አለባቸው። የፖለቲካ ኃይል ምንጮች የሚኖሩት ሰማይ ውስጥ ወይንም አምባገነኖች ደም ውስጥ ሳይሆን ባለቤታቸው ከሆነው ህዝብ ጋር እንደሆነ በስልጣና ክፍል ሶስት አጥንተናል። እርግጥ አምባገነኖች በእነዚህ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ላይ ያላቸውን ቁጥጥር የሚያገኙት ህዝብ ፈቅዶላቸው ወይንም ፈርቶዋቸው ወይንም የተወሰነው ህዝብ ፈቅዶላቸው የቀረው ህዝብ ደግሞ ፈርቷቸው ሊሆን ይችላል። ያም ሆነ ይኽ የእነዚህ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ባለቤት እራሱ ህዝብ እንደሆነ ግልጽ ነው። ለዚህም ነው የፖለቲካ ኃይል ምንጭ ማለትም የመንግስት ስልጣን ምንጭ ወይንም ባለቤት ህዝብ ነው የሚባለው። ህዝብ የፖለቲካ ነፃነቱን የሚነጠቀውም ይኽን የፖለቲካ (የመንግስት) ስልጣን ባለቤትነቱን በኃይል በአምባገነኖች ሲነጠቅ ነው። ነፃ ሆኖ የተወለደ የሰው ዘር ለምን ነፃነቱን ለጥቂት አምባገነን ገዢዎች አስረክቦ ካለነፃነት መገዛትን ይቀበላል? የሚለውን ጥንታዊ የፖለቲካ ፈላስፎች እና ተመራማሪዎች ጥያቄ አንስተን በክፍል ሶስት ማጥናታችን ይታወሳል።

 ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Download (PDF, 213KB)

 

በማንዴላ ሞት መንግሥቱን ከግፍ ለማንፃት? በልጅግ ዓሊ

$
0
0

በልጅግ ዓሊ

madiba2የማንዴላን ሕልፈተ ሕይወት ተመልክቶ በዓለም ደረጃ የሚያስደንቅ ሁኔታ ስናይ ሰነበትን። ማንዴላ የሠራውን መስራት ሳይሆን እሱ የታሰረበትን ዓላማ በተጻራሪ የሚተገብሩ ሁሉ በቀብሩ ላይ ለመገኘት ከተደበቁበት ብቅ ብቅ ማለታቸው የሚስደምም ነው።

በተለይ አንዳንዶቹ በተለያየ የመገናኛ ዘዴዎች ስለ ማንዴላ ጥሩ ምግባር ቃለ መጠይቅ የሰጡትን  ስናጤናቸው ብዙ የሚያስተዛዝብ ሁኔታዎችን እንገነዘባለን።  በሺህ መጽሐፍ፣ በሽህ ሬዲዩ ቢታገዙም በደም የወየበ ታሪካቸውን  የማይሰርዝላቸው ፋሽሽቶች ይህችን ወቅት ተጠቅመው ለሕዝብ ሃሳቢ ሆነው ለመታየት መራወጣቸው የሚገረም ነው። ይህንን ወቅት ለመጠቀም “እኔም ነበርኩበት“ የሚለው ፋሽሽቱ መንግሥቱ ኃይለማርያምም ሳይቀር ከዚምባዌ ድምጹን አስምቷል።

ታሪክ  እንደ ማንዴላ ያለውን ጀግናን ሲያከብር ቡከን ፋሽስትንም ሲኮንን ይኖራል። ይህንን መቀየር የሚችል ማንም አይኖርም። ማንዴላ እንዲህ የተወደደውን ያህል እነ ሒትለር፣ እነ ሙሶሎኒ ፣ እነ እስታሊን ደግሞ ሲኮነኑና ሲወገዙ ኖረዋል። ለወደፊቱም እንዲሁ። ታሪክ በሠሩት ግፍ ብዛት ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ ሲያወግዛቸው ይኖራል።

የማንዴላ ሞት ዜና በጎላበት ጀምበር በጀርመንም የናዚ ፋሽሽቶች መሪ ሒትለር ሲነሳ መሰንበቱ አንድ ሌላ አስገራሚ ክስተት ሆኗል። ትግሌ (ማይን ካንፍ ፣Mein Kampf )  ሒትለር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1923 በመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ምክንያት ታስሮ በነበረበት ወቅት የጻፈው መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ እንደ ናዚዎች ማኒፌሰቶ ሆኖ ይታያል። መጽሐፉ በአይሁዳውያን ላይ ጥላቻን የሚያስፋፋና ጀርመኖች ምስራቅ አውሮፓንን መውረር እንዳለባቸው የሚቀሰቅስ ነው። በጀርመን ሕግ በተደነገገው መሠረት ይህን መጽሐፍ መልሶ የማሳተም መብት እገዳ (copy right) በ2015 ዓ.ም ያልቃል። ስለሆነም ማንም የፈለገ አካል የማሳተም መብት ይኖረዋል።

ይህንን ድንጋጌ በሚመለከት ጀርመን ውስጥ የጦፈ ክርክር ሲከናወን ሰንብቷል። እንደተለመደው የናዚ ደጋፊዎች ሒትለር ሃገሩን ይወድ ነበር፣ ለሃገሩ ጥሩ ሰርቷል . . .  ወዘተ.  የሚል ለሒትለር በታሪክ ጥሩ ቦታ ለመስጠት እንቅልፍ አጥተው ሰንብተዋል። ደጋፊዎቹ መጽሐፉን እንደገና ለማሳተም ሲታገሉ በተቃራኒው የቆሙት ደግሞ በሒትለር የተፈጸመውን ግፍ እያነሱ እንደ ሒትለር ዓይነት በዓለም ውስጥ ዳግም እንዳይነሳ መጽሐፉ መልሶ መታተም እንዳይችል ሲታገሉ ተስተውሏል።

በጀርመን ሃገር ባይረን ተብሎ በሚጠራው ክፍለ ሃገር ግን በ2015 የሚልቀውን የማሳተም መብት በመጠቀም የሒትለር መጽሐፍ  እንደገና ለማሳተም የተደረገው ጥረት ከሽፏል። የባየር አስተዳዳሪዎች በሒትለር የተጨፈጨፉትን በማክበር መጽሐፉን እንደገና ማሳተም ኢ-ሰባዓዊነት ነው ሲሉ ወስነዋል።

http://www.bbc.co.uk/news/world-europe-25346140

የክፍለ ሃገሩ መንግሥት ብዙ በሒትለር የተጎዱ ቤተሰቦችን አነጋርግሮ ይህንን መጽሐፍ ማሳተም በቤተሰቦቹ ላይ ሕመምን መቀስቀስ እንደሚሆን አሳምኖ ማሳተምም ሆነ ማባዛትን እንደገና ከልክሏል። ይህ ውሳኔ ፋሽሽቶችን ለሚቃወሙ ጀርመኖች ትልቅ ድል ነው።

ይህ ዓይነት ትግል የሚደረገው በጀርመን ብቻ መሆን የለበትም። በእኛም ሃገር ይህ ዐይነቱ አመለካከት ሊዳብር ይገባል። ወያኔ ስልጣን ከወጣ በኋላ የተጀመረውን የጎጠኝነት ፖለቲካ ለመቃወም የተጀመረው ትግል የመንግሥቱ ኃይለማርያምን ወንጀል ለጊዜው ወደ ጎን አድርጎ ትግሉ በወያኔ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ቀጥሏል። ግን ይህ ሃገርን የማስቀደም ክቡር ዓላማ በመንግሥቱ ደጋፊዎች ሲጣስና የመንግሥቱን አረመኔነት ለማድበስብስ የሚደረገው ጥረት ብልጭ ድርግም ማለት ከጀመረ ሰነባብቷል።

የፋሽሽቱ ደጋፊዎች መሪያቸው ከወደቀ በኋላ ስለ መሪያቸው ትልቅነት ማውራት የተለመደ ባህሪያቸው መሆኑንም ታዝበናል። እዚሁ ጀርመን ውስጥ ሒትለር ሃገሩን ይወድ ነበር እንደሚሉት የፋሽሽት ደጋፎዎች ማለት ነው። የሒትለር ደጋፊዎች ለዚህም ድጋፋቸው የሚያቀርቡት ምክንያት ባንድ ወቅት ከየሃገሩ በሰበሰባቸው እስረኞች ያሰራው አውራ መንገድ (Autobahn) ሁል ጊዜ ይጠቀሳል። “ሒትለር ቢኖር ኖሮ ጀርመን የትና የት በደረስች ነበር“ በማለት  ዓመኔታ ለመሸመት ይጥራሉ።

እነዚህ የአስተሳሰብ-ደሃ ጀርመኖች በዴሞክራሲ ካገኙት የዓለም የኤኮኖሚ ትልቅነት ይልቅ የእነርሱ ዘር ትልቅነት ላይ የተመረኮዘው የሒትለር ዓላማ ታላቅነትን የሚያጎናጽፋቸው ይመስላቸዋል። ለዚህም የሒትለርን መሪ መፈክር አንግበው ሲጓዙ ይታያሉ። በአሁኑ ሰዓት ያለውን የዓለም ሥርዓትና ይህም ሥርዓት ለጀርመን ሕዝብ የሰጠውን ጥቅም የሚያውቀው የጀርመን ሕዝብ ሥርዓቱን በማናጋት ይህንን የተንደላቀቀ ኑሮውን ለማበላሸት የሚጥሩትን ወገኖች ዕድሉ እንዲሰጣቸው ብዙሃኑ የጀርመን ህዝብ ፍላጎት የለውም።

ፋሽሽቶችን ከፍ አድርጎ ለማሳየት የሚደረገው ጥረት በጀርመን ብቻ ሳይሆን በኢጣሊያም ይታያል። በቅርብ ጊዜ ግራዚያኒ ሐውልት ተሰርቶለታል። ሞሶሎኒንም እንደ ጀግና የሚቆጥሩ አልታጡም። በተለይ በፋሽሽቱ ሥርዓት ጥቅም ያገኙ የነበሩ ወገኖች የሌላው ሕብረተሰብ ቁስል አይሰማቸውም። ይልቁንም እንጨት ሊሰዱበት ይፈልጋሉ።

በእኛም ሃገር የሚስተዋለው ከዚህ የተለየ አይደለም። “መንግሥቱ ሃገር ወዳድ ነው “፣ “መንግሥቱ ቢኖር እንዲህ አይደረግም“፣ “መንግሥቱ ቆራጥ ነበር“. . . .  ሌላም ሌላም ብዙ ከሥርዓቱ ጥቅመኞች የምንሰማው ባዶ ጩኽት አለ። ቆራጥነቱንም በፍርጠጣው፤ ሃገር ወዳድነቱም የተማረ የሰው ኃይል እንዳይኖር በቀይ ሽብርና በሌሎቹ የግድያ ዘዴዎቹ አስመስክሯል። ወንጀሉ የመንገድ ላይ ስጦ ሆኖ የተመለከትነው ነው።  ለሃገራቸው አንድነትና ልዋላዊነት አጽማቸውን ሲከሰክሱ የነበሩ ጀግኖች በመንግሥቱ ነፍስ ገዳዮች ከሃዲ እየተባሉ ሲገደሉ፣ ፈሪ  ፈርጣጩ ቡከን ጀግና ተብሎ ሲወደስ መስማት ውርደትም ሃፍረትም ይሆናል። እነዚህ ጀግኖችን እየሰደቡ ይጽፉ የነበሩ አሁን ደግሞ በውጭ ሃገር የዚህ ፋሽሽት ቆዳ ለማዋደድ የሚደርጉት ጥረት የሚያሳፍር ነው። ለመሆኑ በዚህ ዓይነት ክህደት ይች ሃገር ከወያኔ ነጻ ትወጣለች ብለው ያስቡ ይሆን?

የመንግሥቱ ደጋፊዎች ሰሞኑን የኔልሰን ማንዴላን ሕልፈተ ሕይወት ምክንያት በማድረግ የሃገራችንን ፋሽሽት አረመኔው መንግሥቱን   ቃለ መጠይቅ በማድረግ ፋሽሽታዊ የሆነውን ገጽታውን እንደገና ለማደስ ጥረት አድርገዋል። ደጋፊዎቹ  ይህንን ቡከን ፋሽሽት ከሃገሩ አልፎ ለዓለም አቀፍ ጭቆና እንደታገለ ሊነግሩን ይፈልጋሉ። እነዚህ የመገናኛ ዘዴዎች መንግሥቱን ቃለ መጠይቅ በማድረግ በመንግሥቱ በግፍ የተገደሉትን ወገኖች መልሰው ለመግደል ይጥራሉ። በሕይዎት በተረፉትና የወላድ መኻን በሆኑት ወላጆች ቁስል ላይ ጨው እየነሰነሱ መሆናቸን እንዲገነዘቡ አስታዋሽ የሚሹ ይመስላሉ። እንደ ባየር ክፍለ ሀገር ጀርመኖች የሌሎች ሃዘን ሳይሰማቸው የዚህን አረመኔ ፋሽሽታዊ ገጽታ ለማሳመር ጥረት አድርገዋል። ይህ ደግሞ የሚያሳፍር እንጂ የሚያኮራ ድርጊት አይሆንም። ከማሳፈርም አልፎ  በመንግስቱ ኃይለማርያም የተገደሉትን ሰማዕታት መልሶ  እንደመግደል መግደል ይቆጠራል። በሃገር ላይ የተሰራ ወንጀልም ነው።

በቃለ መጠይቃቸው ላይ ማንዴላን የጦር ሥልት በማስተማር ትልቅ ጥረት ያደረጉትን እነ ጀኔራል ታደሰ ብሩን ለምን መንግሥቱ ራሱ እንደገደላቸው እንኳን ማንሳት አልፈለጉም። ሳያውቁት ቀርተው አይደለም ነገሩን ሳያነሱት የቀሩት። እንደተለመደው መጠየቅ የሚገባቸውን ሃቆች በመሸፈን የፋሽሽቱን ቆዳ የሌለውን መልክ እንዲኖረው ለማድረግ እንጂ።

http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-23515879

እነዚህ የሬዲዮ ጣቢያ ሃላፊዎች የመንግሥቱ ጉዳይ መነሳት ለጸረ ወያኔው ትግል ከፋፋይ መሆኑ አይታያቸውም። ከፋፋይ መሆኑም ቢያውቁም ከመንግሥቱ ይበልጥ ሃገር በወያኔ ብትፈርስ ድንታ እንደሌላቸው ነው ድርጊታቸው የሚያሳየን። የብዙሃኑ ጸረ ወያኔ ትግል  መንግሥቱን ሥልጣን ላይ ወይም ደጋፊዎቹን ስልጣን ላይ ለመመለስ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ትግላችን ዘረኝነትን አጥፍተን ዴሞክራሲን መገንባት መሆኑ  ያልገባቸው ካሉ ትልቅ ስህተት ላይ ወድቀዋል። በኢሠፓ አባልነታቸው እንደገና ወደ ስልጣን ተመልሰን እንወጣለን ብለው አስበው ከሆነ ተስፋ ሊቆርጡ ይገባል። ምንም ይሁን ምን ወደ ኋላ አንመለስም።

መንግሥቱ በሃገር መክዳት ለፍርድ መቅረብ እንጂ እንደ ጀግና በየቦታው ቃለ መጠይቅ እየተደረገለት የእሱ ቆዳ ተገልብጦ እንዲለበስ ጥረት መደረግ የለበትም። ከሃገር ሰርቆና ዘርፎ በፈረጠጠው ገንዘብ የሚገዛው የዕውቅና የሃገር ወዳድነት ጃኖም ሊኖር አይገባም። የወንጀለኛ ቆዳ እንጂ። ንፁህ ነን የሚሉ ካሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ራሳቸውን ከፋሽሽቱ በመነጠል ግልጽ የሆነ አቋማቸውን ሊያሰሙ ይገባል።

በተለይ በሕዝብ ገንዘብ የተቋቋመ እንደ ኢሳት ዓይነት የዜና ማሰራጫ በመንግሥቱ ግፍ የተሰራባቸው ሁሉ እርዳታቸውን የለገሱት መሆኑን አስተዳዳሪዎቹ ልብ ሊሉት ይገባል። እርዳታቸውን ለጠላታቸው ማስተዋወቂያ ሲያደርጉት ሊያጡት የሚችሉትን ድጋፍ መመዘን ብልዕነት ነው። ለምን ቢባል ጥያቄው የሞራል ጥያቄ ነውና!!  አሊያ ግን የኢሳትን ዓላማ ጥርጣሬ ውስጥ ይከተዋል።

http://ethsat.com/ESAT-Radio-player/archive/ESAT_Radio_Wed_11_Dec_2013.mp3

ለኢሳት ገንዘብ በማሰባሰብ ጥረት ያደረጉ “የሰበዓዊ መብት ታጋይ ነን” የሚሉ ደግሞ ይህ ድርጊታቸው ለሁሉም የሰው ዘር ሰብዓዊ መብት መከበር እንዳልቆሙ ያጋልጣቸዋል። ያገኙት ተሰሚነትም ፀሐይ እንደነካው በረዶ ሊቀልጥ ይችላል።

ይህንን አረመኔ ለፍርድ ይቅረብ ብለው ሲናገሩ ያልተሰሙ፣ በመንግሥቱ ስለተጨፈጨፉት ሲናገሩ ያልተደመጡ፣ ለፍትህ ያልቆሙ፤ ዛሬ ለዚህ አረመኔ መድረክ መስጠታቸው የሃገሪቱ ዜጎች ሁሉ በእኩል አይን እንደማያዩ ድርጊታቸው አጉልቶ ያሳየናል። ሌላው ቢቀር ማንዴላን በሚመለከት ባለውለታዎች ሲነሱ ጀኔራል ታደሰ ብሩም ሆነ ማንዴላን በብዙ የደገፉ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት ባለስልጣናት የአሟሟት ሁኔታም መጠቀስ ነበረበት። ታሪክ ግማሽ የለውምና ሙሉው የኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦ በዘገባው መካተት ነበረበት።

http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-23515879

ወያኔን አስወግደን ሃገራችንን ዴሞክራሲያዊት እናደርጋታለን ብለን የምናስብ ሁሉ ከደርግና ከመንግስቱ ኃይለማርያም ፋሽሽታዊ ወንጀል ራሳችንን ነጥለን መንግሥቱም ይሁን ወያኔን የህዝብ ጠላትነታቸውን አውቀን ካልሄድን ሃገራችንን ከወያኔ ጭቆና ነጻ የምናወጣበትን ቀን እናራዝመዋለን። ትግሉ ጥርት ብሎ ለዴሞክራሲ ካልሆነ በስተቀር ከሃገር በተሰረቀ ገንዘብ መልሰን ስልጣን እንወጣለን በሚል እቅድ መጓዝ በሃገሪቱ ውስጥ ሊነሳ የሚችለውን ችግር አለማጤን ይሆናል። ማንም ከድጡ ወደ ማጡ መሄድ የሚፈልግ አይኖርም።

መንግሥቱን ለቃለ መጠይቅ የጠሩ የሬዲዮ ጣቢያዎች ይህንን በማድረጋቸው ምን ያህል ከወያኔ ጋር የሚደረገውን ትግል እንደከፋፈሉ ካልተረዱ የሚያሳዝን ነው። በዚሁ አጋጣሚም የሕዝብ ድጋፍ እንደሚያጡ ሊረዱት ይገባል። ነጻ ፕረስ ሃላፊነት የጎደለው ፋሽሽቶችን ማመጻደቂያ ሊሆን አይገባምና ከዚህ መጥፎ ምግባር መቆጠብ አስተዋይነት ይመስለኛል።

ሂትለር፤ ጀኔራል ፍራንኮ፤ ሞሶሎኒ፤ መለስ ዜናዊ፤ መንግስቱ ኃይለማርያም፤ (በቁም የሞተ) ሁሉም ፋሽሽቶች ሞተዋል። ስማቸው ግን ከታሪክ ጠባሳ ገጾች አይፋቅም። ባንጻሩ ጋንዲ፤ ማንዴላ፤ ማርቲን ሉተር ኪንግና ሌሎቹም ጀግኖች ሞተዋል። ግን ሰማዕታት ናቸው። ታሪካቸውም በጀግንነት የወርቅ ቀለም ተጽፎ ትውልድ ሲወራረሰው ይኖራል። የሁለቱም ወገኖች ስም ከመቅበር በላይ ውሏል። ሆኖም የፋሽሽቶቹ የነ ሂትለር በፀረ-ህዝብነት፤ የነማንዴላ ግን በህዝባዊነት!!

በፋሽሽቶች ለተጨፈጨፉ ሁሉ የሚያስብ በሰላም ይክረም !

ታህሳስ 2006

Beljig.ali@gmail.com

 

 


አይ አበሻ! አበሻና ልመና፦ አንድ (መስፍን ወልደ-ማርያም)

$
0
0

መስፍን ወልደ ማርያም

ኅዳር 2006

Pro Mesfinበዓለም ሕዝቦች መሀከል ውድድር ቢደረግ ያለጥርጥር አበሻ አንደኛ ከሚወጣባቸው ነገሮች አንዱ ልመና ሳይሆን አይቀርም፤ ለአበሻ፣ ልመና የኑሮ ዘዴ ነው፤ እንዲያውም ከልመና ውጭ የሆነ ኢትዮጵያዊ ኑሮ የለም ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ ስለዚህም ልመና ባህላዊ ጥበብ ሆኖአል፤ አንዳንድ አላዋቂዎች፣ አንዳንድ አዋቂዎችም አንዳንዴ እየተሳሳቱ ልመናን እንደነውር ይገልጹታል፤ ልመና ነውር አይደለም፤ ለጨዋ ልጆችማ አንዳንድ አጥንትን የሚያበላሽ ሥራ ከመሥራት ለምኖ መብላት ክብር ነው፤ ይህ ባህላዊ ጥበብ ያልገባቸው የድሬ ዳዋ ለማኞች ብቻ ናቸው፤ እጃቸውን እየዘረጉ ‹‹እስቲ አሥር ብር ስጠኝ!›› ይላሉ! በጫት ሞቅ ሲላቸው መቶ ብር ይጠይቃሉ፤ የድሬ ዳዋ ልመና መሆኑ ነው!

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቄሶቹ ምንም ይስበኩ በተግባር እንደሚታየው ጽድቅ የሚገኘው በልመና ነው እንጂ በሥራ አይደለም፤ ሥራኮ ለአበሻ ከእርግማን የመጣ ነው፤ አበሻ አልተረገመ፤ ታዲያ ለምን ብሎ ይሥራ! አሁን እንደሚሰማውና እንደሚመስለኝ አገዛዙም እንደተቀበለው የቻይና ሰዎችም እንደመሰከሩለት ከሥራ ጋር ጠብ አለው፤ ደግሞስ ለምን ይሥራ! ለአንድ እንጀራ? ለተራበ አብልተው ለመጽደቅ የሚፈልጉ ስንትና ስንት ሰዎች አሉ፤ ስለዚህም ደግ ሰዎች መጽውተው እንዲጸድቁ በግድ ለማኞች ያስፈልጋሉ፤ ለመጽደቅም መለመን ያስፈልጋል፤ ጸሎት ልመና መሆኑን አትርሱ፤ ስለዚህም ዋናውና ከፍተኛው ልመና ወደእግዚአብሔር ነው፤ ብልጦቹ እግዚአብሔርን የሚለምኑት ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት ነው፤ አንድ ቀን ተነሥተው እግዚአብሔር ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት እንደሰጣቸው ያውጃሉ፤ አውጀውም በሕዝብ ራስ ላይ ይወጣሉ፤ በራሱ ላይ ወጥተውም ይጨፍራሉ፤ ሰውን ከመሬቱ፣ መሬቱን ከሰው መለየት ይሳናቸዋል፤ ሰውን ከመሬቱ፣ መሬቱን ከሰው ያጣላሉ፤ እግዚአብሔር ለእናንተ ብቻ እንዴት ሰጣችሁ? እግዚአብሔር እኛን ለምን ነፈገን? ብሎ የሚጠይቃቸውን እየደበደቡና እያቃጠሉ፣ እየገረፉና እያራቆቱ በዝምታ እንዲገዛ ያደርጉታል፤ አልበቃው ካለም አካሉን ለውሻ ሰጥተው ነፍሱን ወደእግዚአብሔር ይወረውራሉ፤ እግዚአብሔር እየቆጠረ የማይመዘግብ ይመስላቸዋል፤ የጠጠረ ጉልበታቸው ዓይኖቻቸውን አውሮ፣ ኅሊናቸውን አፍኖ እግዚአብሔር በዕዳ እንደሚይዛቸውና በጥጋባቸው ያደሉትን መከራና ስቃይ፣ የወረደውን እንባና ደም ከነወለዱ እንደሚያስከፍላቸው መገንዘብ ያቅታቸዋል።

እግዚአብሔር ፍርዱን እስቲሰጥ ድረስ ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት ተረክበናል የሚሉት የተለያዩ ስሞችን እየለጠፉ በተዋረድ የለማኞችን ሠራዊት ያደራጃሉ፤ ሕዝብ ሁሉ ከነዚህ የለማኞች ሠራዊት በአንዱ ውስጥ ለመግባት በፉክክር ይተላለቃል፤ ሠራዊቱ ውስጥ በመግባት የሚገኘው ጉርሻ ልጆቻቸውን እንኳን ከረሀብ የማያድን መሆኑን ሳይገነዘቡ መብታቸውን እያስረገጡ የሌሎችን መብት ለመርገጥ መሣሪያ ይሆናሉ፤ እነዚህ እንግዲህ ልመናን በማኅበረሰቡ ውስጥ ተክለው እየኮተኮቱ የሚያስፋፉት ናቸው፤ ልመናን ባህል የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው፤ ልመናን ታሪካችን ያደረጉት እነዚህና ከነሱ የቀደሙት ገዢዎቻችን ናቸው።

በእኛ ባህል የራበውን በማብላት ጽድቅ ይገኛል፤ ስለዚህም ለምኖ መብላት ይቻላል፤ ስለዚህም ሰዎች መጽውተው እንዲጸድቁ በግድ ለማኞች ያስፈልጋሉ፤ እንግዲህ ለምነው እየበሉ መኖር ከተቻለና እግዚአብሔርን በመለመን ጽድቅ ከተገኘ፣ የመሬቱንና የሰማዩን ጣጣ በልመና መገላገል ከተቻለ ታዲያ ሥራ ለምን ያስፈልጋል! ለነገሩስ ሥራ በእርግማን የመጣ ነው፤ ስለዚህ የተረገሙት ሲሠሩ ያልተረገሙ የሚመስላቸው ይለምኑ፤ ለሌላው ዓለም ልመና የችግር ምልክት ነው፤ ለአበሻ ግን ልመና የጽድቅ ምልክት ነው፤ የጨዋ ልጅ፣ ማለት በልመና በሰዎች ላይ ሥልጣንን ከአግዚአብሔር አግኝቻለሁ ብሎ የሚያምን፣ አይሠራም፤ ቀን ቢጥለውም የጨዋ ልጅ በእጁ ሠርቶ ከሚበላ ለምኖ ቢበላ ይሻለዋል፤ ሆድ የተፈጥሮ ነው፤ ረሀብም የዕለት ከዕለት የተፈጥሮ ግዳጅ ነው፤ ስለዚህም ለአበሻ የተፈጥሮን ሆድና የተፈጥሮን ረሀብ በልመና መወጣት የተፈጥሮን ሥርዓት መከተል መስሎ ይታየዋል።

ሌላ ቀርቶ ተማሪ ለምኖ ካልበላ ትምህርት አይገባውም፤ ለተማሪ ሲሆን ልመና አይባልም፤ ቀፈፋ ነው፤ አበሻ በልመና ምን ይህል እንደተራቀቀ የሚያመለክተው ለተለያዩ ልመናዎች የተለያዩ ስሞች ማውጣቱ ነው፤ እንደተባለው ተማሪ ሲለምን ቀፈፋ ነው፤ በዘመናዊ ቋንቋ የትምህርት ታክስ ነው፤ ምግብ የሚቀርብበትን ሰዓት እየጠበቀ ከተፍ የሚለው ቀላዋጭ ነው፤ አብዛኛውን ጊዜ ለቀላዋጭ ቀላል ሰበብ የሚሆነው ቀላውጦ የሚያገኘው ወሬ ነው፤ ሌላም የልመና ዓይነት አለ፤ እርጥባን ይባላል፤ — ደርቄአለሁና አርጥቡኝ ማለት ነው! ‹ላሊበላዎች› የሚባሉት ለምነን ካልበላን እንቆመጣለን በማለት ልመናን የኑሮ መሠረት አድርገውታል፤ ሌላም የልመና ዘር አለ፤ ደጅ መጥናት ይባላል፤ ደጅ መጥናት ማለት ብርዱን ችሎና እንቅልፉን አቋርጦ በሌሊት እየተነሡ በመኳንንቱና በመሳፍንቱ፣ በንጉሡ፣ በንጉሠ ነገሥቱ ደጃፍ ላይ አጥር ወይም ዛፍ እየተደገፉ የተፈለገውም ሰው ብቅ ሲል በመሬት ላይ በመነጠፍ እጅ በመንሣት ፊት ለማስወጋት ለመታወቅና ለሹመት ለመታጨት የሚጠቅም የልመና ዘዴ ነው፡፡ በአበሻ አገር ሁሉም ነገር በልመና ነው፤ ምግብ በልመና፣ ትምህርት በልመና፣ መሬት በልመና፣ … በልመና፣ ግብር የሚከፈለው በልመና ነው፤ ሥልጣን የሚገኘው በልመና ነው፤ ንጉሥነትም የሚገኘው በልመና ነው፤ ባጭሩ ኑሮ ማለት ልመና ነው፤ ልመና ማለት ኑሮ ነው ።

 

 

የማለዳ ወግ …ስደተኛው ዘፋኝ በሳውዲ በርሃ …(ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0

ነቢዩ ሲራክ

Bekah

   የእንጀራ ነገር ሆኖብኝ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ … እንደጨው ተበትነናልና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወገኖቸን በየሔድኩበት ከተማ ፣ እግር በጣለኝ የሳውዲ የቀለጡ በርሃዎች ወንድም እህቶቸን አገኛለሁ ። ላፍታም ቢሆን ጊዜ ሰጥቸ እየኑሩት ስላለው ኑሮ ፣ እየገፉት ስላለው ክፉም ደግ ተሞክሮ እጠይቃቸዋለሁ አንድም ሳይደብቁ የሆድ የሆዳቸውን ያጫውቱኛል …
እለተ ቅዳሜ በማለዳው ያቀናሁት በያንቦና በጅዳ መካከል በምትገኝ የዋዲ በርሃ ዙሪያ ነበር ። አየሩ ተቀያይሯል ፣ ከዚህ ቀደም ወደዚህ ቦታ ሳመራ እንደ እሳት ነበልባል የሚጋረፈው ሙቀት ዛሬ የለም ። ለስራ ወዳቀናሁበት በድቅድቁ በርሃ ላይ በተሰራው የድንጋይ መከስከሻ ፋብሪካ እንደደረስኩ አንድ መልከ መልካም ወንድም የግቢውን በር ከፍቶልኝ ለመግባት ወዴት መሄድ እንደምፈልግ ጠየቀኝ  ፣ ወጣቱ \ሃበሻ ለመሆኑ ቅንጣት ያህል አልተጠራጠርኩምና የሚጠይቀኝን ትቸ እኔው ጠየቅኩት “ሃበሻ ነህ! ” ነበር ያልኩ ። ይህን ስጠይቀው እንደ መሽኮርመም እና እንደመሳቅ እያለ “አዎ ሃበሻ ነኝ ፣ ኢትዮጵያዊ ! ” ሲል መለሰልኝ !  ብዙ ሃበሾች አላችሁ?  ስል ጥያቄየን ቀጠልኩ “አዎ አምስት ሃበሾች አለን! ” አለኝ ፈገግ እያለ … በአሻጋሪ መምጣቴን የሚጠብቀው የፋብሪካው ሃላፊ “አስገባው ፣ አስገባው! ” ሲል ፍልቅልቁ ወደ የት እንደምሄድ የጠየቀኝ ወንድም ተደናግጦ በወራጅ ብረት እንደነገሩ የተዘጋውን የግቢ ብረት አጥር ከፍቶልን እኔና የስራ ባልደረባ ረዳቴ የፊሊፒን ዜጋው ግላዲ ወደ ግቢው ገባን ፣ ወጣቱን ወንድም በመስኮት በኩል አንገቴን ወጣ አድርጌ ስራየን ከዋውኘ እንደማገኘው ቃል ገብቸለት ወደ ውስጥ ገባሁ  …

  unn2343     ሱዳኑ የፋብሪካ ሃላፊ ከድንጋዩ መፍጫ የቅርብ ርቀት ካለው ጋራጅ አጠገብ ከተሰራች ባለሁለትና ሶስት ዛኒጋባ ቆርቆሮ ቤት ወጥቶ ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጥቶ ተቀበለን ። ድንጋዩን እየከሰከሰ ጠጠር የሚያደርገው ፋብሪካ ነጭ አመድ ወደ ሰማይ እየተፋ የጓራል …ዲንጋው እየተፈጨ ጠጠር እየተሰራ መሆኑ ነው! የመንገድ መደልደያ ፣ የምንገድ መጥረጊያ እና የመንገድ ማለስለሻ ዳምጤ ከባባድ የኮንስትራክሽን መኪኖችን ጨምሮ ጥገና የሚያስፈልጋቸው መኪኖች ጋራጁን አጨናንቀውታል  … ከጋራጁ ጀርባ ደግሞ እኛ መመርመር ያከብን የተሽከርካሪ ጎማ መአት ተከምሯል። …አምስት የተባሉትን ሃበሾች አግኝቸ እስካዎጋቸው ቋምጫለሁ …የፊት የፊቱን እያስቀረብኩ ፊሊፒኑ አጋሬ ምን መስራት እንዳለበት አሳወቅኩት ፣ ስራውን አጣድፊ ግን በአግባቡ መርምሬ እንደጨረስኩት ሌሎች ሁለት ሃበሾች ሃበሻ ወንድማቸው መምጣቴን ሰምተው ኖሮ በፈገግታ እየተፍለቀለቁ መጥተው ሰላምታ ተለዋዎጥን …

  ሃበሻ ዝር በማይልበት በርሃ ያገኙኝን ወንድም እነርሱም ሊያስተናግዱ ሊያጫውቱኝ እንደቋመጡ አልጠፋኝም … በተንቀሳቃሽ ኮንቴነር በፋይዚት ግሩም ሆና የተሰራቸው ማረፊያ ቤት  ከጋራጁ የቅርብ ርቀር ትገኛለች ። አቧራ የጎረሰውን እጀን ሳልተጠብ በበርሃው ወዳገኘኋቸው ወንድሞች ማረፊያ ቤት አመራሁ … ረመድ ረመድ እያልኩ ከመድረሴ ወንድሞቸ በደስታ እየተፍለቀለቁ ግማሽ መንገድ ላይ ተቀበሉኝ ! ጠባቧ ቤት ማረፊያ ቤት ብቻ እንዳልሆነች ከበር የተደረደሩትን ጫማዎች ስመለከት ገባኝና ጫማየን አውልቄ “ቤት ለእንቦሳ! ” ብየ ዘው ብየ ገባሁ…  ቤቷ ጽድት ያለች ናት … ሶስት አልጋዎች ሶስቱን ማዕዘኖች ጥግ ይዘው ተዘርግተዋል ። የተቀበሉኝ ወንድሞቸ ሶስት ሲሆኑ ዘግየት ብሎ ሌላ ወንድም ገባ … አምስተኛው ወንድም የት እንዳለ ስጠይቅ እሱ ስራ ላይ እንደሆነ ገለጹልኝ። ሁላችንም የምናወራው ከአልጋዎች ላይ ተቀምጠን ነው ።  እንደገባኝ ከሆነ አልጋዎች ይተኛባቸዋል ብቻ ሳይሆን በመቀመጫነት ያገለግላሉ!  … ጫዎታችን ከመጀመራችን በፊት እጀን ለመታጠብ ውሃ ቢጤ ስጠይቅ ድምጹ ጎርነን ያለው “ሸዋንግዛው እባላለሁ!” ብሎ የተዋወቀኝ ወንድም በእጅ ከምትያዝ ማቀዝቀዣ ውሃ ይዞ ወደ ” በር ላይ ላስታጥብህ! ” ብሎ ግማሽ ጎኔን ከበሩ ወጣ አድርጌ እንደነገሩ ጣቶቸን ውሃ አስነካሁ ብል ይሻላል ፣ ብቻ ታጠብኩ !

  unnajgj6    ወጋችን  የጀመርነው በድፍኑ አበሻ ሁኘ እንጅ ማንነቴን የተረዳ ሰው የለም! ብዙ የህይወት ልምዳቸውንና ስለስራቸው ስለተመለከቱት የቴክኒክ ስራየ ፣ ሱዳኑ ሲጠራኝ ስለሰሙት የእንጀራ ስሜና ስለ አጠቃላይ የሳውዲ ህይወት እንዳንፈራራ ፣ እንዳንደባበቅ ፣ እንደ መተዋወቂያ አወራን … ጋዜጠኛ መሆኔን ትንፍሽ ሳልል “ራዲዮ ትሰማላችሁ ፣ ኢንተርኔት ፊስ ቡክ ትከታተላላችሁ? ” በማለት ደጋግሜ ጠየቅኳቸው!  አዎንታቸውን ገለጹልኝ ። ስሜን የእኔ ነው ሳልል ታውቁታላችሁ?  ስላቸው አዎንታቸውን በዝርዝር ገለጹልኝ!  ስገባ በር የከፈተልኝ እያሱና የቀሩት ሁለት ያህሉ በአካል የማያውቁት  ግን ማንቴስ ተብሎ የተዋወቃቸው “የነቢዩ “  የፊስ ቡክ ጓኞች እንደሆኑ በኩራት ገለጹልኝ :) አክለውም በቅርቡ የለቀቃቸውን የራዲዮ መጠይቆች እያነሱ የሚያውቁትን ሰው ስም ስላነሳሁላቸው በደስታ ብዙ አወሩኝ !  … እንዲህ ጥቂት ከቀጠልን በኋላ ግን እነርሱ እዚህ ስላደረሳቸው መንገድ መጠየቅ ጀመርኩ !  ሁሉም የሆነውን ሁሉ ሲያጫውቱኝ  ” አበባ ተሸልሜ በጭብጨባ የተሸኘሁ ዘፋኝ ነበርኩ !” ያለኝ  ድምጸ ጎርናናው የሸዋንግዛው ታሪክ ልቤን ነካው …  ብዙም ሳልቆይ ግን የእውነተኛው አለም  ማንነቴን ገላልጨ ለወንድሞቸ ሳጫውታቸው ነገሮች ተቀያየሩ!  … በጣም ተገረሙ !  ብዙ ተጫወትን … ለዛሬ እንዳላደክማችሁ በሚል በሳውዲ በርሃ ስላገኘሁት ዘፋኙ ወንድም ትኩረቴን ላድርግ  …

     ሸዋንግዛው እና ከቀሩት ጓደኞቹ ሃገር ቤት አይተዋወቁም ። ዳሩ ግን ድህነት ፣ የኑሮ ውድነት ፣ የማደግ የመመንደግ ፍላጎት በቁንጮዋ ነዳጅ አምራች ሀገር በሳውዲ በርሃ ላይ አገናኝቷቸዋል ! … ከሁሉም ወንድሞች ይልቅ ዘፋኙን ስደተኛ  ሸዋንግዛውን እዚህ ያደረሰ መንገድ ለማወቅ ጓጉቻለሁ !  እናም ላፍታ ከዘፋኙ ወንድም ጋር የሆድ የሆዳችን ላፍታ አወጋን … ሸዋንግዛው ንጉሱ ይባላል ፣ እድሜው በአርባወቹ  ውስጥ እንጅ ከዚያ አይዘልም! ዘፋኝ መሆኑን ካጫወተኝ ታሪክ አልፎ በበርሃው ሲያንጎራጉር ከተቀረጻቸው ድምጾች እና የተለቀቀውን ነጠላ ዜማ ሰምቸ ለመረዳት ጊዜ አልወሰደብኝም … “ዘመኑ የዘፋኝ ነው” በሚባልበት ዘመን ድምጸ መረዋውን  ዘፋኝ ወደ ሳውዲ ምን አመጣው ?  በሚል ባለጉዳዩ ስደተኛ ዘፋኝ ጠየቅኩት  … መልሶልኛል ….

    ሸዋንግዛው ንጉሴ በቀድሞው የአርሲ ክፍለ ከሃገር ሎዴ ኤዶሳ በሚባል አከቀባቢ በአንድ መንደር ተወለደ። የሙዚቃ ጥበብ ገና በብላቴና እድሜው የለከፈችው ሸዋንግዛው በሎዴ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቱን ሲከታተል ጥበብ አብራው አደገች ። ገና ከጅምሩ የጥበቡ ምሳሌ ከልብ የሚወደውን ክቡር ዶር ጥላሁን ገሰሰን ጥሩ ምሳሌ አድርጎ ገሰገሰ።  ሎዴ የትምህርይ ቤት ኪነት ለመመረጠረም ተሰጥኦ ያደለው ተርገብጋቢ ድምጽ ተሰጥኦና ፍላጎቱን ደገፈው ፣  የቀደሙትን ዜማ እያነሳሳ ሲለው የራሱን እየገጠመና እያንጎራጎረ ህይወት በፈለገችው መንገድ ትጓዝ ዘንድ ሸዋ ብርታት አገኘ። ብዙም ሳይቆይ ታዳጊው ሽዋንግዛው ከትምህት ቤት ወደ ወረዳ ኪነት ከፍ እያለ ሄደ … ከወርቁ ቢቂላ ( በኋላ ከሃይሌ ገ/ስላሴ ጋር አለም አቀፍ ሩጫን ይሮጥ ነበር) ታዳጊ እያለ የሙዚቃ ዝንባሌ ስለነበረው በአርሲ ሎዴ የወረዳ ኪነት አብረው እንደሰሩ ሸዋ ሩቅ ተጉዞ ዘርዘር ያለ ትዝታውን አዎጋኝ ። ሸዋ ብዙ ትዝታ አለው ። በአስደሳቹ ፈገግ ፣ በአሳዛኙ ትክዝ  እያለ አጫውቶኛል …

ታዳጊው ሸዋንግዛው በወረዳው ኪነት ቡድን  ተግቶ እየሰራ ባለበት ወቅትም ወደ ክፍለ ሃገር ኪነት ቡድን ለመምረጥ በተደረገ ውድድር ከወረዳ ወደ አርሲ ክፍለ ሃገር ቢመረጥም የወረዳው ሃላፊዎች በቅንነት “ልጃችን አሰልጥለን አንሰጥም !” በማለታቸው ወጣቱ በሙያው ርቆ የመሄድ ስሜቱ ተጎዳ !  እናም በብስጭት ወደ ውትድርና አለም ገባ ። ሸዋንግዛው ማንጎራጎሩን ባንድ በኩል በሌላ በኩል ሳይወድ በተጎዳ ስሜት ገፋፊነት የገባበትን የውትድርና ስልጠና ወሰደ። ቀን ቀንን ሲወልድ ግን ውትድርናው ወደ ጦር ሜዳ ሳይሆን ወደ አሳደገው የሙዚቃ ጥበብ ዶለው !  ሸዋ በብስጭት የተጎዳኘው የውትድርና ስልጠና እንደጨረሰ የባሌ ሸዌ የጦር እዝ ማዕከል የኪነት ቡድን አባል ለመሆን ጊዜ አልፈጀበትም ።

     በጦሩ የኪነት ቡድን በመስራት ላይ እንዳለ የደርግን ስርአት የሚታገለው የኢህአዴግ ጦር ወደ ከተማዎች እየገፋ ሲመጣ የኪነት ቡድኑ ወደ ሲዳሞ በመሄድ ሌላ ተጨማሪ የመከላከል ስልጠና እንዲያደርግ ሲታዘዝ ሸዋንግዛው  ከጓዶቹ ጋር ስልጠናውን ወሰደ። ከዚያም ድልድሉ ወደ ሞያሌ ሆነና ወደ ዚያው አመራ። በጭንቁ ቀን ያልተለየው የጥበብ አውሌ ተጭኖት ማንጎራጎሩን ስላላስቆመው እንቅስቃሴውን ያዩ የሰራዊቱ አባላት ሸዋንግዛው የደቡብ እዝ ኦርኬስትራ ቡድን እንዲቀላቀል ግፊት አድርገው እንዲመረጥ ቢያደርጉም አሁንም የጦር አዛዡ ” ሸዋግዛውን ወደ ደቡብ እዝ አልለቀውም! ” በማለታቸው እድሉ ተጨናገፈ። ይህም ሲሆን ዳግም እክል የገጠመው ዘፋኙ ወጣት ተስፋ አልቆረጠም። ሙዚቃው እንቢ ቢለው በልጅነት ወደ ሚወደው ሌላ ሙያ አጋደለ። ባለበት ብርጌድ የእግር ኳስ ብቃቱን አስመስክሮ እግር ኳስ መጫወቱን በደስታ ተቀላቀለ  ! በወቅቱ ኳሱም ተሳክቶለት ኮከብ ኳስ አግቢ በመሆን ተመርጦ እንደነበረ ሲያጫውተኝ ህይወት በትግል እንደምትፈተን አሸንፎም መውጣት ግዴታ እንደሆነ ሸዋንግዛው በፈገግታ እየገለጸልኝ ነበር ። ኢህአዴግ መላ ሃገሯን ሲቆጣጠር ጦሩ ፈረሰና ከሞያሌ ወደ ኬንያ የገባው ሸዋንግዛው እና የቀረው ስደተኛው በቀይ መስቀል ትብብር ወደ ሃገር ቤት ሲገባ ቤተሰቦቹን ከጠየቀ በኋላ ወደ  አዲስ አበባ ገባ…

  232 አዲስ አበባ ለአርሲው ተወላጁ ለሸዋንግዛው የተመቸች ነበረች። በተለይም በልጅነት የተለከፈባት የሙዚቃ ጥበብ ተሰጥኦውን  የሚያጎለብትበት ብቸኛ እድል አገኘ ። እናም በየምሺት ቤቶች “ከተፋ ቤቶች” ተሰማርቶ ምሽቱን እያደመቀ እና ራሱንና ቤተሰቦቹን በመርዳት መስራት ጀመረ ። ባለትዳር የሆነው ሸዋንግዛው በምሽት ስራው በአሁኑ ሰአት ታዋቂ ከሆኑ ዘፋኞች ጋር እኩል ድምጽ ማጉያን ተጋርቶ በጥበብ ተናኝቷል !

  ይህም ሁሉ ሆኖ ፣ ይህንን የከበደ መንገድ ተጉዶ ሸዋንግዛው ከልጅነት እስከ እውቀት ሙጥኝ ያላትን ጥበብ አዳብሮ የራሱን ወጥ ዘፈን ለማውጣት አቅሙ አልገደደውም። ያም ሆኖ ግን  በማይቆጣጠረው እክል ስራውን ለሃገር መናኘቱ አልሆንልህ እያለው መቸገሩ አልቀረም። ሸዋንግዛው እንዲህ እየሆነ ህይወትን ሲገፋ ለማደግ የሚያደርገው ግብግብ ባያሸበርከውም ሩጫው አልፎ አልፎ  እንዳደከመው ሳይደብቅ አጫውቶኛል።  የጥበብ አውሌ ብቻዋን ከተዘፈቀበት ድህነት ራሱን ቀና አላደረገችውም!  ይህ እንዳይሆን ፣ በሰው ሰራሽ ምክንያት በጥበብ ላይ የሚሰራ ደባ እየደሰቀው መፈናፈኛ እንዳሳጣው ሸዋንግዛው ይናገራል ! በተለይም “ከከተፋው” ዘፋኝነት ጎን ለጎን ብዙዎችን ዘፋኞች ያሳወቀውን ነጠላ ዜማ ግጥምና ዜማውን ራሱ ደርሶ ቢያወጣም ሃገር ስራውን እንዳያውቅለት ጫና ፈጣሪዎች አላገዙትምና ድንቅ የባህል ዘፈኑ ሳይደመጥለት እንደቀረ ዜማዋን እንድሰማት በመጋበዝ ሸዋ ብዙ አጫወተኝ።  በሙዚቀኞች መካከል ውስጥ ለውስጥ የሚሰራውን “የቲፎዞ ” ድጋፍ ፣ አንዳንድ የሃገር ቤት ጋዜጠኞች በተለይም  የኤፍ ኤም ራዲዮ ጋዜጠኞችን ድጋፍ ማጣቱ አውኮተ አሰናክሎታል። ሸዋ ባለሙያዎች ሙያቸውን በሙስ አርክሰው የሚሰሩትን በገደምዳሜም ቢሆን አጫውቶኛል። እኔም በሙስናው ዙሪያ ያለውን አበሳ ወገንተኛ ዘመም የቲፎዞ አካሄድ ግልጥልጥ አድርገው ካወሩት ጉዳዩ ብዙ እንደሆነ ከዚህ በፊት የማውቀውን ታሪክ ሸዋንግዛው አስታወሰኝ …

ሸዋን ሳውዲ አረቢያ ስላደረሰው መንገድ እና የወደፊት ህልሙ እንዲያጫውተኝ ጠይቄው እንዲህ አለኝ ” ነጠላ ዜማው አልሳካ ሲለኝ ድህነቱንና የኑሮ ውድነቱን ለማሸነፍ እንዳልቻልኩ የገባት ጅዳ የምትኖረው እህቴ በኮንትራት ስራ እንድመጣ አመቻቸችልኝ። ተሳክቶም ልክ የዛሬ 11 ወር ወደ ሳውዲ አረቢያ በኮንትራት ስራ መጣሁ ።  በዘፈን ብዙዎች ይሳላካላቸዋል ። እኔ የእድል ጉዳይ ሆኖ አልተሳካልኝም ። ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ። የመጣውን መቀበል እንጅ አላማርረውም። አሁን የምሰራው “ሮለር ” በሚባል የኮንስትራክሽን ተሽከርካሪ ላይ ነው። በሃገራችን ዳምጤ ይባላል። ዳምጤን እየነዳሁ በርሃውን ማቅናት ነው የአሁን ስራየ ። በቃ ! ህይዎት እዚህ አድርሶኛል! እንደኔ ሃሳብና ህልም ከሆነ እንደ ምንም የሁለት አመት ኮንትራቴን ጨርሸና ገንዘቤን ሰብስቤ እግዚአብሄር ብሎ የሙዚቃዋ አድባር ከጠራችኝ ወደ ሙዚቃው መመለስ ነው ሃሳቤ፣ ካልሆነ የማገኛትን ይዠ ቤተሰቤንና ራሴን እየረዳሁ በሃገሬ መኖር ነው የምፈልገው!  ለእስካሁኑ  እግዚአብሔር ይመስገን! ወደፊትም እሱ ያውቃል! ” በማለት ሸዋንግዛው መልሶልኛል…

    ሸዋንግዛው “ይሻላል እንደሁ! ” ብሎ በኮንትራት ከመጣ ቀን ጀምሮ ስራውን የበርሃውን ቃጠሎ ተቋቁሞ ከጓደኞቹ ጋር እየሰራ ቢሆንም በደመወዝ አከፋፈሉ ላይ ቅሬታ እንዳለውና ይህም ፈተና እንደሆነበት ገልጾልኛል።  ከሸዋንግዛው ጋር በነበረን ቆይታ በበርሃው ውሎ አዳር ስለሚለከታቸው በእረኝነት ተቀጥረው ስለሚገፉ ኢትዮጵያውያን ይዞታ ሲያጫውተኝ እንዲህ ነበር ያለኝ ” የእኛን ተወው ደህና ነው ፣ የእረኛ ወንድሞቻችን ህይወት ብታየው ያሳዝናል፣ ሃበሾችን ከሩቅ ታውቃቸዋለህ። ስናናግራቸው ደስተኛ እንዳልሆኑ ይገልጹልናል። ወደ ሃገር ቤት እንዳይመለሱ ከድህነትና ኑሮ ውድነቱ በተጨማሪ ያላቸውን ቅሪት አንጠፍጥፈው ተሰደዋልና ምን ይዘን እንግባ ?  ይሉሃል ! ምን ትላቸዋለህ? ያ ያ ስላለ እንጅ ከኢትዮጵያ መጥተህ በበርሃው ውሃ እየተጠማህ የመንጋ በግ ፣ ፍየልና ግመል እረኛ ሆነህ ኑሮን መግፋት ይከብዳል። ታለቅሳለህ! ” ሲል ፊቱን በሃዘን ክችም አድርጎ ዘፋኙ አዝኖ አሳዘነኝ …

    አዎ እኔም በአካል ተገኘቸ ያየሁትና ዛሬ በርሃ ላይ ባገኘሁት ዘፋኝ የተገለጸልኝ ህይወት በእርግጥም ያሳዝናል!  ያማል!  ማለቱ ብቻ ስሜትን የሚገልጸው አይሆንም …ብቻ በባለጸጋ አረቦች ሃገር ከአረቦቹ ጓዳ ፣ እስከ ደራው ከተማና በርሃው የእኛ ህይዎት ሲሰሙት ውለው ቢያድሩ ተነግሮ አያልቅምና በዚሁ ልግታው እና ወደ በርሃው ውሎ የመጨረሻ ምዕራፍ ላቅና…

    ከሸዋንግዛውና ከጓደኞቹ የነበረኝ አጭር ቆይታ ታላቅ የጽናትን እና ዥጉርጉሩን ህይዎት የተረዳሁበት መልካም አጋጣሚ ሆኗልና እዚያው ውየ ባድር ደስታየ በሆነ ነበር … ያ እንዳይሆን የእንጀራ እና የህይወት ጉዳይ አልፈቀደልኝም!  እናም መለያየት ግድ ሆነ  ! በሳውዲ ራብቅ በርሃ ላይ ያገኘሁትን ዘፋኙን ሸዋንግዛውንና  ጓኞቹን ስለያቸው በፍቅር ተሳስቀን እና ተቃቅፈን ተሳስመን ነበር …ደግሜ ልጎበኛቸው ቃል በመግባት …

     ሸዋንዳኝን ስለየው ያቀበለኝን ባንድ ወቅት ሰርቷት በህዝብ ጀሮ ያልደረሰችውን “ሸዋ ጥበብ ያውቃል! ” ነጠላ ዜማው እየኮመኮምኩ በርሃውን ለቅቄ ወደ ጅዳ መገስገስ ጀመርኩ  …

” ከወዲያ ከወዲህ ስታንገላታኝ
ይህች የመንዝ ልጅ አስራ ልትፈታኝ
ቃሌ አይታጠፍም የመጣው ቢመጣ
እንዳሻት ታድርገኝ አላበዛም ጣጣ ” ይለዋል  ሸዋ… በጥበቡ የሸዋን ጉብል የከበደ ፍቅር ሲገልጸው ….
የሙዚቃው የደመቅኩት ምንጃርኛውን ሞቅ ደመቅ ባለው ቅንብርና ዜማ የታጀበ ብቻ በመሆኑ አይደለም!  የሸዋ ግጥሞች መልዕክት አላቸው …

     የእንጀራ ነገር ሆኖብኝ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ … እንደ ጨው ተበትነናልና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወገኖቸን በየሔድኩበት ከተማ  ፣ በቀለጡ በርሃዎች እና መንደሮችም ወንድም እህቶቸን አገኛለሁ ! እንዲህ በማለዳ ወጌ ወጋወጉን ለተሞክሮ ሳካፍላችሁ ደግሞ ደስታ ይሰማኛል ! ህይዎት እንዲህ ይኖራል …

ሰላም

ነቢዩ ሲራክ

YeMaleda Weg

የኢትዮጲያ ሰላም በአንድነታችን ላይ ነው (ገብሬሉ ተስፋዬ)

$
0
0

   ገብሬሉ ተስፋዬ ኖርዌ

The shadow of a supporter of Ethiopia's Unity for Democracy and Justice party (UDJ) is seen through an Ethiopian flag during a demonstration in the capital Addis Ababa

               የሚያኮራ የሚያስደስት ኢትዮጲያዊ አንድነት ሰሞኑን በተደረጉት የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ አይተናል:: በሳውዲ አረቢያ እየተሰቃዩ ላሉት እህትና ወንድምቻችን ሀይማኖትና ዘርን ሳንለይ ያሳየነው የአንድነትና የቁጣ መንፈስ በጣም የሚያስደስት ነው:: ይሄ ያሳየነው አንድነት እና ቆራጥነት መቀጠል ሊኖርበት ይገባል:: ካልሆነ ግን የችግራችንን ሥር መንቀል አስችጋሪ ነው:: ሳውዲ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጲያዊያን ሲገደሉ፣ሲደበደቡ እና ሲደፈሩ በኢትዮጲያዊነታችው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል:: ይሄ አይነቱ ኢሰብሐዊ ጥቃቶች በሰፊው እየደረሰ ያለ ሲሆን አንድነታችንን አጠናክረን ወደ ፊት ካልተጓዝን በተለያየ ቦታና ሀገር ኢትዮጲያዊነት ሊደፈር ይችላል::

       በመጀመሪያ መግለፅ የምፈልገው የኢትዮጲያን ክብር እና ማንነት ያጠፋው ወያኔና አመራሩ ናችው:: ስለዚህ ሁል ጊዜ ለሚፈጠሩት ችግሮች ሆይ ብለን መነሳት ብቻ በቂ መፍቴ አይሆንም ዋናው የችግሩን መንሴ ወያኔን ማስወገድ ነው:: ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እህትና ወንድሞቻችን ተሰደዋል፣ተገድለዋል፣ተደፍረዋል ይሄ አዲስ ነገር አይደለም ሁላችንም ቢሆን እየሰማን እያየን የቆየነው ነገር ነው:: በአሁኑ ሰሀት በሳውዲ አረቢያ እየተደረገ ያለው ግፍ በዛ እንጂ በፊትም የነበረ ነው::የወያኔ አገዛዝ በሀገር ፍቅር ወይም በአንድነት ላይ የተመሰረተ አይደለም:: ይሄን በደንብ አድርጎ ለብዙ  አመታት አሳይቶናል:: የእናትና የአባቶቻችንን መሬት ለበአድ ሀገር ተወላጆች በመሸጥ፣መሀበረሰቡን በዘር እና በሀይማኖት በመከፋፈል፣እህትና ወንድሞቻችንን ለበአድ ሀገር አሳልፎ በመስጠት እና በመሳሰሉት ማየት ይቻላል::

 የአንድነታችን  መላላት መንሴወች እና መፍቴያችው ያልኩዋችውን ላብራራ

         አንደኛው እንደ ሰው እናም እንደ ኢትዮጲያዊ ለሚደርሱብን ኢሰብሀዊ ድርጊቶች አይሆንም፣አይደረግም የሚል ቆራጥ መንፈስ በውስጣችን መመንመኑ :: ይሄ ወደ ምን ያመራል ብንል ለገንዘብ እና ላአንዳንድ ጥቅማ  ጥቅሞች አገርን አሳልፎ ወደ መሸጥ:: ሰው እንደመሆናችን መጠን ቆም ብለን ልናስብ ይገባል  የወያኔ መንግስት የህዝብ  ጥርቅም መሆኑን:: ህዝብ ደግሞ የእያንዳንዱ ሰው ስብስብ ነው :: ስለዚህ እንደ ሰው ወያኔ ለሚያደርስብን ጥቃቶች አይሆንም ካልን ወያኔ የሚቀጥልበት ምንም ምክንያት አይኖርም:: ህዝብ የመረጠው መንግስት ደግሞ ለህዝቡ አንድነት የቆመ ነው::

   ሁለተኛው የወያኔ የአገዛዝ ስልት ነው:: በህዝብ ያልተመረጠ መንግስት(ወያኔ) ስልጣን ላይ ለመቆየት የተለያዩ  ጫናዊ የአገዛዝ ስልቶችን ይጠቀማል:: ከሁሉም የሚከፋው ዘርን ከዘር  እና ሀይምኖትን ከሀይማኖት  በማጣላት የህዝቡን አንድነት የሚበታትኑት ነው:: ለዚህም ምስክሩ ኢትዮጲያን ለቀው የሚሰደዱ ሰዎች የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ችግር ያላችው ብቻ አይደሉም ጥሩ የትምህርት ደረጃ እና ክፍያ ያላችውም ናችው::ይህ የሚያሳየው የደንነት እና የአንድነት ስሜታ በመሀበረሰቡ መመንመኑን ነው::መፍቴው ህዝብ የመረጠውን መንግስት ለማምጣት የበኩላችንን  አስተዋፆ ማድረግ:: ለምናደርጋችው ማንኛውም እንቅስቃሴወች ከማስተዋል ጋር ሊሆን ይገባዋል:: ሌላው እንደ አሜሪካ ካሉ ያደጉት ሀገራት በዘርም በቀለምም በሀይማኖት የማይገናኙ ህዝቦች እንዴት ለአንድ አላማ እንደቆሙ ትምህርት ከነርሱ በመውሰድ::

ሦስተኛው የኛ የሆኑ ችግሮችን ሌላ ሀገሮች መተው ችግራችንን ይፈቱልናል ብሎ መጠበቅ:: ይሄ እምነታችን ያመጣብን የራሱ የሆኑ ችግሮች አሉት፥ ከችግሮቹም አንዱ ያሀገራችንን ታሪክና ሚስጥራት አሳልፈን መስጥት:: ይሄ ደግሞ የተለያዩ የምእራብአዊ ሀገሮች በኢትዮጲያ ፖለቲካ እንደፈለጉት እጃችውን እንዲያስገቡና እንዲያሶጡ መንገድ ከፍቶላችዋል:: ይሄም ለአንድነታችን መላላት ትልቅ አስተዋጾ አለው::ለምሳሌ የጫካ ውስጥ ጎሾችን ብንወስድ በተናጠል ሳር በሚግጡበት ጊዜ በቀላሉ አውሬ ያጠቃችዋል ግን ሶስትም አራትም ሆነው ሲግጡ እራሳችውን በሁሉም አቅጣጫ ከአውሬ መከላከል ይችላሉ:: ስለዚህ መፍቴው ምንልያይበትን ነገር ከማየት አንድ የሚያደርገንን ነገር በማየት ችግራችን እርስ በእራስ በመወያየት መፍታት ነው::

አራተኛው ከታሪክ አለመማራችን ነው:: ኢትዮጲያ ባለ ብዙ ታሪክ ሀገር ስትሆን  የሚያስደስት ታሪክ እንዳላት ሁሉ የሚያስከፋም ታሪክ አላት:: ታሪካችንን በአግባቡ መርምረን አጥንተን ምንጓዝ ብንሆን ኖሮ አንዳይነት ችግሮች በተደጋጋሚ ባልመጡብን ነበር::መፍቴው የሰው አገርን ታሪክ ቀድሞ ከማወቅ ይልቅ የሀገራችንን ታሪክ አምብበን ተረድተን ተገንዝበን ለችግራችን ቀድመን መፍቴ ፈልገን መገኘት ይኖርብናል::

በኔ እምነት ከላይ የጠቀስኩዋችው አራት ነጥቦች ለአንድነታችን መላላት ቁልፍ ከሆኑ መሰረታዊ ችግሮች አንዳንዶቹ ናችው:: በአሁኑ ሰሀት ኢትዮጲያ እየሄደች ያለችበት ጎዳና አስከፊ እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው:: ስለዚህ እኛ ኢትዮጲያውያን ከምን ጊዜ በበለጠ ለአንድነታችን እናም ለሀገራችን  ሰላም የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ ያለብን ሰሀት አሁን ነው::

ፍቅር ለኢትዮጲያ እዝብ!

“አና ጐሜዝ አሁንም ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ይቆረቆራሉ” –አቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)

$
0
0

ከአቶ አስራት ጣሴ (የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ)

ከአና ጐሜዝ ጋር ከአንድ ሠዓት ተኩል ለማያንስ ጊዜ ነው የቆየነው፡፡ የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ከእኛ ጋ የተገናኙት ገለፃ ለማድረግ አስበው ሣይሆን የእኛን አስተያየት ለመስማት ነበር፡፡ ውይይቱ፣ ኢትዮጵያ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን እና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነበር፡፡ በወቅቱ ከሞላ ጐደል ተደጋጋፊ እንጂ የሚቃረኑ ሀሣቦች አልተነሱም፡፡ በእኔ በኩል፣ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል በከፍተኛ ችግርና አደጋ ላይ እንደሚገኝ፣ ኢትዮጵያም መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደሆነች፣ ከፊታችን አሳዛኝና አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ ሰላማዊ ትግሉን አስመልክቶ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታዎች እያሣየ መሆኑን ገልጫለሁ፡፡
Ana Gomez
“ሰላማዊ ትግል” የሚለው “ሰላማዊ እንቅልፍ” የሚል ደረጃ ላይ ለመድረሱ ዋነኛ ምክንያቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትከሻቸውን ታስረው ለመንቀሣቀስ ያለመቻላቸው ነው፡፡ የህዝባዊ ስብሰባዎች እና የሰላማዊ ሰልፎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ መታገድ፣ የአዳራሽ መከልከል፣ ልሳናችንን እንዳናሳትም መታገድን ጨምሮ በርካታ ሕገ መንግስታዊ ጥሰቶች እየተፈጸሙብን ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ሕገ መንግስቱን እየጣሱ ነው እየገዙን ያሉት፡፡ ሕገ መንግስቱ እየተተገበረ ነው የሚያስብል ሁኔታ የለም፡፡ ከድጡ ወደ ማጡ እየገባ ነው ያለው፡፡ ነገሮች ተባብሰዋል፡፡
የስልጣን ኃይል ሚዛኑ በማን እጅ ላይ ይገኛል ብሎ መጠየቅ እስኪያስፈልግ ድረስ ሁሉም ነገር ተወሳስቧል፡፡ በሚኒስትር ደረጃ የተቀመጡት ሲቪሎቹ ናቸው ወይስ ከጀርባ የሚያስተዳድሩን አሉ? ሂደቱ ሀገሪቱን ወዳልተፈለገ ቀውስ ሊወስዳት የሚችል ትልቅ አደጋ ነው፡፡
ከአና ጎሜዝ ጋ በተተወያየንበት ወቅት የተቃዋሚ ፓርቲ አንድ ተወካይ ብቻ በፓርላማ እንደሚገኝን ተናግሬያለሁ፡፡ አስቀድመውም ያውቁታል፡፡ በ1997 ዓ.ም. የተቀማውን ድምጽ ትተን 180 የሚሆኑ ተቃዋሚዎች በፓርላማው መቀመጫ ነበራቸው፡፡ አሁን ግን ወደ አንድ ወርዷል፡፡
ኤልሳቤት ሃይኒ የተባለች የቢቢሲ ጋዜጠኛ ያነሣችውን ጥናት ለአና ጎሜዝ አሳይቻቸው ነበር፡፡ አንድ ፓርቲ በምርጫ ከ51-59 ፐርሰንት አግኝቶ ካሸነፈ ታላቅ ድል ነው፡፡ ከ60-69 አምጥቶ ካሸነፈ “ዝረራ” የሚባል ውጤት ነው፡፡ ከ70-79 አምጥቶ ካሸነፈ ደግሞ የሕዝቡን ጥያቄዎች የመለሰ ፓርቲ ነው፡፡ ከ80-89 የሚያገኝ ፓርቲ ግን የሚፈራ፣ አምባገነን፣ ጉልበተኛ ፓርቲ ነው፡፡ ከ90-99 ፐርሰንት ከተገኘ ደግሞ ምርጫ አልተካሄደም ማለት ነው ይላል፡- ጥናቱ፡፡ በኛ ሀገር ይኸው “99” አልፎ ዜኀር ነጥብ ስድስት ሁሉ ተጨምሮበታል፡፡ ስለዚህ ይሄ በግልፅ የሚያሣየው ፍፁም የዴሞክራሲ ስርዓት መጣሱን ነው፡፡ ምህዳሩ ተዘግቷል፡፡ ተደፍኗል፡፡

አስራት ጣሴ

አስራት ጣሴ

የተቃዋሚ ፓርቲዎች በየጊዜው የምናቀርባቸው የውይይት እና የእንደራደር ጥያቄዎች ከስልጣን ጋር ግንኙነት የላቸውም፡፡ ሀገራዊ አጀንዳዎች ናቸው፡፡ ብሔራዊ ውይይት፣ ብሔራዊ ንግግር ይከፈት ብለን ደጋግመን ብንጠይቃቸው ባለሥልጣናቱ አሁንም ያሾፋሉ፡፡ “የምርጫ ስነምግባር ደንብ” ፈርሙ እንባላለን፡፡ እንኳን “የምርጫ ስነምግባር ደንብ” ይቅርና የማንወደውን፣ እየተጐዳንበት ያለውን “የፀረ ሽብር አዋጅ” ተቀብለን ነው የምንተዳደረው፡፡ ምክንያቱም በሕግ የተደነገገ ነው፡፡ እንዴት ተደርጐ ነው “የምርጫና ስነምግባር ህግ” በምክር ቤት ጸድቆ በነጋሪት ጋዜጣ በወጣ ህግ ለይ ዳግም ፈርሙ የምንባለው? የሚል ሀሳብም አንስቻለሁ፡፡
መንግስት “ፀረ ሽብር” አዋጁን የማጥቂያ መሣሪያ አድርጎታል፡፡ ሽብርተኝነት የአውሮፓም፣ የአሜሪካም ከፍተኛ ስጋት በመሆኑ የፀረ ሽብር ህግ አውጥተዋል፡፡ ወደ እኛ ሃገር መለስ ስንል የፀረ ሽብር ሕጉ የወጣው ሽብርተኞችን ለመቅጣት ብቻ ሳይሆን፣ ሰላማዊና ሕጋዊ ፓርቲዎችን ጭምር ለማጥቃት ነው፡፡
ሽብርተኝነትን በማንኛውም መልኩ፣ በየትኛውም ገፅታው እንቃወመዋለን፡፡ ሽብርተኝነት ምን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ በአፍጋኒስታን፣ በፓኪስታን፣ በኢራቅ፣ በናይጄሪያ /ቦኮ ሀራም/ እናውቀዋለን፡፡ እዚህም በሕዝብ፣ በህፃናት፣ በእርጉዝ ሴቶች፣ በሽማግሌዎች፣ በወጣቶች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት እናውቀዋለን፤ እንቃወማለንም፡፡ ኢትዮጵያውያን በባህላችን፣ በአስተዳደጋችን፣ በኃይማኖታችን፣ በእምነታችን… ለሽብርተኞች የተጋለጠ ስነ ልቦና የለንም፡፡ “ሽብርተኝነት” ይምጣብን የሚል ልመና ካልተያዘ በቀር ኢትዮጵያዊ ሽብርተኝነት የለብንም፡፡ የ“ጸረ ሽብር” አዋጁ በሽብርተኝነት ከፈረጃቸው ፓርቲዎች መካከል… ለአብነት ግንቦት 7፣ ዋና መቀመጫው በአሜሪካና አውሮፓ ከተማዎች ነው፡፡ ይሄ እንቆቅልሽ ይሆናል፡፡ አወሮፓውያን ከተማዎቻቸውን ለአሸባሪዎች ምሽግነት መርጠዋል ማለት ይሆን?
ሌላ እንቆቅልሽም አለ፡፡ ስርዓቱ “ሽብርተኛ” ብሎ ያሰራቸው ሰዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶችን እና ክብሮችን እያገኙ ነው፡፡ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙ፣ አንዱአለም አራጌ… ወዘተ በፀረ ሽብር አዋጁ ነው የታሰሩት፡፡ በ”ሽብርተኝነት” የተፈረጁት ግን በአሜሪካና፣ አውሮፓ ከተማዎች እንደፈለጋቸው እየተዘዋወሩ ነው፡፡ አውሮፓና አሜሪካ ሽብርተኞችን እየደገፉ ነው ማለት ነው?
የፖለቲካ ምህዳሩ ከድጡ ወደ ማጡ እየገባ ነው፡፡ የሕዝብን ችግር፣ እሮሮ በሳዑዲ አረቢያ በዜጐቻችን ላይ የሚደርሰው እልቂት፣ የስራ አጥነት፣ በስታቲስቲክስ ማሣየት ይቻላል፡፡ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ የኑሮ ውድነት፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የሙስና መንገስ፣ የስርዓቱ መገለጫ ሆኗል፡፡ እነዚህ ጉዳዮች የአውሮፓ ህብረትን ትኩረትና ዕይታ ሊስቡ ይገባል፡፡ ይሄን የምንለው ግን ትግሉን ታገሉልን ለማለት አይደለም፡፡ ትግሉ የራሣችን ነው፡፡ ትግሉ የኢትዮጵያውያን ትግል ነው፡፡ ነገር ግን እናንተም ደግሞ ባላችሁ ደረጃ፣ ባላችሁ የግንኙነት መስመር፣ የሚደረገውን ነገር ለማድረግ ጥረታችሁን ቀጥሉ ብለናቸዋል፡፡ የተወሰነ ድጋፍ ካልተደረገ ወደፊት ሊመጣ የሚችለው ችግር ሁላችንንም ጉዳት ላይ የሚጥል ነው፡፡ ጉዳቱ ስርዓቱን የሚመሩት ሰዎችንም ጭምር የሚምር አይደለም፡፡
አና ጐሜዝ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ያላቸው ግንዛቤና የመቆርቆር አቅም አሁንም ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተረድቻለሁ፡፡ በውይይቱ ወቅት እንኳ ከሌላ የአውሮፓ ፓርላም አባል ጋር ያለመስማማት ሁኔታን አይቼባታለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብና፣ ኢትዮጵያ ልታከብራቸው ከሚገቡ በዓለም ላይ ከፍተኛ የፖለቲካ ስብዕና ካላቸው ሰዎች መካከል አንዷና ትልቋ አና ጐሜዝ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ ጐሜዝ የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርብ ይከታተላሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ያላቸው ተቆርቋሪነት ከ1997 ዓ.ም. ከነበረው የበለጠ ነው፡፡ የሰጧቸው ቃለ ምልልሶች ዛሬም ለኢትዮጵያ ሽንጣቸውን ገትረው እንደሚከታተሉ ያመላክታሉ፡፡
በውይይቱ ወቅት “እኔ እኮ ዛሬ ኢትዮጵያ ለመግባት የቻልኩት አቶ መለስ በሕይወት ባለመኖራቸው ነው፡፡ በሕይወት ቢኖሩ እዚህ ሀገር አልገባም” ነበር ያሉን፡፡ ከፍተኛ ጥንካሬና ተቆርቋሪነት ነው ያየሁባቸው፤ ውይይታችን የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞችን ጭምር የሚመለከት ነበር፡፡
የአውሮፓ ፓርላማ ልዑካን ቡድን ኃላፊ በስብሰባው ላይ አልተገኘችም፡፡ እና ምክትሏ ሆና ነው ስብሰባውን የመራችው፡፡ “ኃላፊዋ በአሁኑ ሰዓት እዚህ ስብሰባ ላይ ያልተገኘችው ቃሊቲ እስረኞችን ለመጠየቅ ሄዳ ነው” ብላን ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ተወካዮች መጥተው፣ ጠ/ሚኒስትሩ ከፈቀዱ በኋላ “ቃሊቲ” ሄደው ተከልክለው ሣይገቡ ነው የተመለሱት፡፡ እርሷም በዛው እለት በዚህ ጉዳይ ተበሣጭታ ወደ ሃገሯ ተመልሣ ለምክትሏ ስለሁኔታው ገልጻላት ነበር፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የእስረኞቹን ጉዳይ በበቂ ለማስረዳት ሞክሯል፡፡
የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያላቸው እውቀት አናሳ ነው፡፡ የሚያውቁት ጥቂቱን ነው፡፡ ግንዛቤ አላቸው ከተባለ ደግሞ ብዙ ትክክል ያልሆነ መረጃዎችን የያዘ ነው፡፡ ለምሣሌ ሀገሪቱ በልማት እየተራመደች መሆኗን፣ ኢትዮጵያ የአውሮፓ የፀረ ሽብር ከፍተኛ አጋር መሆኗን፣ የአፍሪካ መዲና መሆኗን… ይሄም የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ እንሚያሣይ የሚገልፁ አሉ፡፡ የአና ጐሜዝን ሩብ ያህሉን የማያውቁ አሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ከኛ ለመስማት ስለነበር ፍላጐታቸው የሚያውቁትን ለኛ ለመናገር አስፈላጊ አድርገው ላይመለከቱት ይችላሉ፡፡ በውይይቱ ወቅት ሁሉም ጊዜ ሰጥተው በጥሩ ሁኔታ ነው ያዳመጡን፡፡ በትኩረት ያነሱት ግን በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን መብዛት ነው፡፡

ቴዲ Vs ምኒልክ፡ ስለ ጥቁር ሰው ወይንስ ስለ ጥቁር ገበያ? –ከታምራት ነገራ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ቴዲ አፍሮ ዳግማዊ ምኒልክን አስመልክቶ ለዕንቁ መጽሄት የሰጠውን ቃለ መጠይቅ ተከትሎ ሱናሚ ሊባል የሚቻል ንትርክ ስለ ቴዲ እና ስለ ዳግማዊ ምኒሊክ በሶሻል ሚዲያ ተናፍአል፡፡ ሰሞኑ ደግሞ የዳግመዊ ምኒልክ ያረፉበት መቶኛ ዓመት የሚታሰብበት መሆኑ ለሱናሚው ትልቅ ድምቀት ሰጥቶታል፡፡
ቴዲ አፍሮ ጥቁር ሰው ከሚለው አልበሙ ወዲህ ስለዳግማዊ ምኒልክ በተለያዩ ቦታዎች ተናግሯል፡፡ እኔን ግን ከቴዲ አፍሮም ፣ ከዳግማዊ ምኒሊክም፣ ከጥቁር ሰው አልበምም በእጅጉ የሳበኝ የዳግማዊ ምኒልክ ተዋስዖ (Discourse) ነው፡፡ በተለይም ተዋስዖው እየተካሄደ ያለበት ገበያ በእጅጉ ስቦኛል፡፡ አንድን ተዋስዖ ስናስተውል የተዋስዖውን በርካታ ክፍሎች ለያይተን ልናይ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ የአንድን ተዋስዖ ይዘት የሚያጠና ሰው በተዋስዖው ውስጥ ጎልተው በተደጋጋሚ የሚታዩ ሐሳቦች፣ ቃላት፣ እና ዝንባሌዎች ያጠናል፡፡ በተያያዥነትም በተዋስዖው ዙሪያ ወሳኝ የሚባሉትን መልዕክት አስተላላፊ ምርቶች ለምሳሌ ዘፈኖች፣ ፊልሞች፣ አልበሞች፣ መጽሐፍትን፣ መፈክሮች፣ እና ፖስተሮች ሊያጠና ይችላል፡፡ በተዋስዖው ዙሪያ ያሉ ተዋናዮች ላይ ማተኮር የሚፈልግ ሰው ደግሞ ተዋስዖውን የሚያንቀሳቅሱትን የሐሳብ አመንጭ እና አከፋፋይ ጋዜጠኞች፤መጽሄቶች፤ ፀሐፍት፤ ምሁራን ፤አርቲስቶች ዙሪያ ጥናቱን ያተኩረል፡፡ ልክ እንደዚሁ አንድ ሰው አንድ ተዋስዖ የሚካሄድበትን ገበያ አተኩሮ ማየት ይችላል፡፡
Teddy afro minilik
ገበያ የሚለውን ቃል የምጠቀመው በተዋስዖው ውስጥ ያለውን ትርፍ ወይንም ኪሳራ ብቻ ለማሳየት ሳይሆን ተዋዖውን በሚያካሂዱት ግለሰቦች፣ ተቋማት፣ ቡድኖች እና ሐሳቦች መካከል የሚደረገውን ግብይት የሚካሄድበትን ሥርዓት (System) ለማመላከት ነው፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ ወቅታዊው፣ ትልቁ፣ እና እውነተኛው ጥያቄ ቴዲ፣ ጃዋር፣ በቀለ፣ ጫልቱ፣ እና አብደላ ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ምን አለ? ምን አለች? ምን አሉ? አይደለም፡፡ ስለ ዳግማዊ ምኒልክ በክፉም ኾነ በደጉ መናገር እስከ ዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ እንዴት ሱናሚ ማስነሳሳት ቻለ ? ስለ ዳግማዊ ምኒልክ እገሌ ገለመሌ ቢል ስለለምን ይኼን ያህል ያወዛግበናል? ይኼ ለእኔ ትልቁ እና ዋነኛው ጥያቄ ነው፡፡ ሱቅ በደረቴዎች የዳግማዊ ምኒልክ አድናቂዎችም ኾኑ ተቺዎች ስለ ዳግማዊ ምኒልክ የሚያስደስታቸውን፣ የሚያምኑበትን፣ እንደውም ሕይወታቸውን እስከሚሰጡለት ድረስ የሚያምኑትን ነገር እየተናገሩ፣ እያደረጉ እንደኾነ ሊወተውቱን ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በዳግማዊ ምኒሊክ አድናቂዎችም ሆነ አውጋዦች መካከል በሚደረገው ምልልስ ከመሳተፍ በመጠኑም ራቅ እና ከፍ ብለን ለማየት ከሞከርን ግን የዳግማዊ ምኒልክን አድናቂዎችም ኾነ ተቺዎችን የሚያስተዳድረውን ገበያ ለማየት እንችላለን፡፡ የዳግማዊ ምኒልክ ደጋፊዎችም ኾነ ተቺዎች በዳግማዊ ምኒልክ ተዋስዖ ዙሪያ ያላቸውን ሐሳብ በተገኘው አጋጣሚ እና ሥፍራ ከማስተላለፋቸው አልፈው በዳግማዊ ምኒልክ ዙሪያ አለኝ የሚሉትን ዕውቀት እና ግንዛቤ እንዴት እንደ ጨበጡት፣ ማን እንደሰጣቸው፣ ከየት እንዳገኙት፣ እና እንዴት እንደ ቀረበላቸው የሚኖራቸው ግንዛቤ እጅግ ውሱን ነው፡፡ አንድ ባለሱቅ በሱቁ ውስጥ ስላለው እቃ እና ዋጋ መጠነኛ ግንዛቤ ይኖረዋል ሊኖረውም ይገባል፡፡
ከዛ ባለፈ ግን አገሪቷን ወይንም ዓለምን ስለሚያንቀሳቅሰው የገበያ ሥርዓት፣ የገበያ መርህ፣ የገበያ ተቋማት፣ እና የገበያ ሕግጋት ኃይል ያለው ግንዛቤ እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ ጩኸት፣ ትርምስ፣ምሥጢር፣ ግርግር፣ ፍርሀት… ዳግማዊ ምኒልክ እና ሥርወ መንግሥታቸው በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ካላቸው ሰፊ ተጽዕኖ ተነስተን ከተወያየን እስከ ዛሬ አይደለም ገና ለሚቀጥሉት ብዙ መቶ ዓመታት የማንግባባቸው በርካታ ነጥቦች ይኖራሉ፡፡ ለእኔ አሳሳቢው ጉዳይ ስለዳግማዊ ምኒልክ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ አይደለም፡፡ አሳሳቢው ጉዳይ ለምን በውይይቱ መካከል ስክነት፣ እርጋታ፣ ዕውቀት፣ እና እውነት ጠፍተው በሥፍራቸው ጩኸት፣ ትርምስ፣ እና ድንቁር እንደ ምን ነገሡ ነው፡፡ እንደ እኔ እምነት በዳግማዊ ምኒልክ ዙሪያ የሚደረገው ተዋስዖ ከስክነት ትርምስ እንዲበዛው፣ በምክንያት ከሚናገሩ ሰዎች ጯኂዎች መድረክ እንዲያገኙ፣ አዋቂዎች ከአላዋቂዎች እንዳይለዩ፣ እውነት የያዙ ፈርተው ሐሰተኞች እንዲዳፈሩ ነገር ዓለሙ በአጠቃላይ ትርምስ እንዲበዛበት ሆን ተብሎ እተደረገ ነው፡፡
minilikበዚህ አጋጣሚ ርዕሰ ጉዳዩ የምኒልክ ተዋስዖ ስለኾነ እንደ ምሳሌ ልጠቀመው ብዬ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ብሔራዊ እና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ስላለው ማንኛውም ተዋስዖ በእርጋታ፣ በአመክንዮ እና በዕውቀት መናገር አይቻልም፡፡ ይህ ትርምስ የተፈጠረው ደግሞ በአብዛኛው ኾን ተብሎ በተገነባ የተዋስዖ ገበያ ሥርዓት እንጂ ዝም ብሎ በአጋጣሚ ከሰማይ ዱብ ያለ ክስተት አይደለም፡፡ የዳግማዊ ምኒልክን ተዋስዖ በምናየው እጅግ አጨቃጫቂ በኾነ መልኩ በመላው አገሪቷ እንዲተዋወቅ የተማሪዎች ንቅናቄ እና የሕወሃት መንግሥት ዋነኛውን ሚና ተጫውቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በዳግማዊ ምኒልክ ዙሪያም ኾነ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ብሔርተኝነት ዙሪያ የምንሰማቸውን በርካታ ሀሳቦች ጥንስሳቸው በ1966ቱ የተማሪዎች ንቅናቄ ነው፡፡ በተማሪዎች የተነሱትን አንዳንድ ሐሳቦች ለምሳሌ መሬት ላራሹ የደርግ መንግሥት በከፊል ተግባራዊ ተደጓል፡፡ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል እና ሌሎች መሰል ሐሳቦችን ግን እንኳን ሊተገብር መኖራቸውንም እንኳ በአግባቡ ሳይናገር ዘመኑን ጨረሰ፡፡ በ1983ዓ.ም ሕወሃት ሥልጣን እንደያዘም ሻዕቢያን እና ኦነግን በግራ እና በቀኝ አስከትሎ በተማሪዎች ንቅናቄ የተጠነሰሱ በርካታ ሐሳቦችን በመላው አገሪቷ አወጃቸው፡፡ የፈለገውን ሕግ አደረገ ያልፈለገውን ችላ አለ፡፡ ሌዋታን፤ የገበያው ጌታ ማንኛውም መንግሥት በሚያስተዳድረው አገር ላይ በሚካሄደው ተዋስዖ ላይ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ ኢትዮጵያን ለማስተዳደር የታደለ ማንም ግለሰብ እና ቡድን ደግሞ በኢትዮጵያ ተዋስዖ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ በእጅጉ ኃያል ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ኋይት ኃውስን ለመቆናጠጥ እድል የቀናው ፓርቲ በአሜሪካ ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ተዋስዖውን ሊያነቃንቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን አሜሪካንን የሚገዛው ፓርቲ በአሜሪካ ተዋስዖ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው ፓርቲ በኢትዮጵያ ተዋስዖ ላይ ከሚኖረው ተጽዕኖ ጋር ሲነጻፀር አቅሙ እጅጉን ውሱን ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፓርቲ ዋይት ኃውስን ያዘ ማለት ኮንግረስ በእጁ ነው ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ በፖሊሲ እና በጀት መሰል ጉዳዮች ላይ ያለው ተጽዕኖ ይወሰናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ተዋስዖን በመቅረጽ፣ በማዳበር፣ እና በማከፋፈል ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ሚዲያ፣ የሕትመት ቤቶች፣ እና መሰል ተቋማት በዋይት ኃውስ እጅ ውስጥ አይደሉም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንድ ቡድን በድንገት ተነስቶ ወዲያውኑ የአገሪቷን ተዋስዖ ወደ ፈቀደው ርዕዮተ ዓለም (Ideological) ዝንባሌ መንዳት እንዳይችል የሚያደርጉት ዘልማዶች እና ሕግጋቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ የአሜሪካን ዶላር እና ሳንቲሞች ላይ የሕያው ፕሬዝዳንት ምሥል እንዳይቀረጽ ህግ አለ፡፡ ይህ ሕግ እንደ አሁኑ በይፋ ሕግ ሆኖ ከመጽደቁ በፊት የሕያው ፕሬዝዳንት ምሥል በዶላር ላይ እንዳይቀረጽ ያልተጻፈ ስምምነት ነበር፡፡ የኛ ብር መልኩ ስንቴ ተለዋወጠ? እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት ማንበብ እና መፃፍን የመሰለ ዝቅተኛው የተዋስዖ መሳተፊያ ክህሎት ጭራሹኑ በሌለበት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ገደብ የሌለው ሥልጣን በእጁ ላይ የወደቀ ቡድን በአገሪቷ ተዋስዖ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ልክ የለውም፡፡
በዚህ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚኖረው ጉልበትም የተዋስዖውን ይዘት ከመቆጣጠርም አልፎ ተዋስዖው የሚካሄድበትን ገበያ ሕግጋት እንደ ፈለገው መቆጣጠር እንዲችል አቅም ይሰጠዋል፡፡ ሕወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በዳግማዊ ምኒልክ ዙሪያ የለኮሰውን ተዋስዖ ለአጃንዳ አጠር ሎሌዎች በሊዝ አኮናትሮ ገበያውን በጌታነት ከላይ ሆኖ እየዘወረው ነው፡፡ በአንድ አገር የተዋስዖ ገበያ ላይ እጅግ ተፈላጊው ግብ እውነትን ማግኘት ነው፡፡ እውነት በአንድ ጉዳይ ላይ የሚኖረንን የመረጃ ትክክለኝነት እና ሐሰትነት ላይ ብቻ የተገደበ ግንዛቤ አለመኾንኑ፤ በተዋስዖ ትንታኔ ውስጥ በአብዛኛው እውነት ስንል ከመረጃው ትክክለኝነት እና ስህተትነት ባሻገር ያሉ ሐሳቦችንም ይዳስሳል፡፡ በተዋስዖ ትንታኔ ውስጥ እውነት የተዋስዖው ተሳታፊዎች በመረጃው ላይ የሚኖረቸውን ትርጓሜ፤ በትርጓሜው ላይ ያላቸውንም ስምነት ሊያካትት ይችላል፡፡ ዳግማዊ ምኒልክ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ዘመቱ የሚለውን አረፍተ ነገር እንውሰድ፡፡ ይህኑ አረፍተ ነገር አንድ የዳግማዊ ምኒልክ ነገር ሲነሳ ሆዱን ባር ባር የሚለው ወዳጃችን ብድግ ብሎ ዘመቻው ከእግዚአብሄር ለኢትዮጵያ የተሰጠ ቅዱስ ስጦታ ነው ብሎ ይህንኑ አረፍተ ነገር ሊተረጉመው ይችላል፡፡ የዳግማዊ ምኒልክ ነገር ሲነሳ የሚያንገሸግሸው ሌላኛው ወዳጃችን ደግሞ ብድግ ይልና ዘመቻው የተካሄደው ዳግማዊ ምኒልክ አያቶቼን እንዲያጠፏቸው በሰይጣን ስለታዘዙ ነው ብሎ ትርጓሜውን ይሰጠናል፡፡ እነዚህም ሆኑ ሌሎች በርካታ ትርጓሜዎች በዳግማዊ ምኒልክ ተዋስዖ ዙሪያ ይኖራሉ፡፡ እያንዳንዱ ቡድን የራሱን ትርጓሜ ይዞ ወደ ገበያው ይመጣል፡፡ ትርጓሜ ሊሸጥ፣ ትርጓሜ ሊገዛ፡፡ ሕወሃት ግን ገበያው ውስጥ ትርጓሜ ይዞ ከመቅረብ የተዋስዖ ቸርቻሪነት ከወጣ ሰነበተ፡፡
tedy afro new
እጅግ የሚያዋጣው የገበያውን ሥርዐት እና መዋቅር መቆጣጠር እንደ ሆነ ስለገባው ችርቻሮውን ለጉልቶች ሰጥቶ ኪራይ ይሰበስባል፡፡ ሕወሃት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የተዋስዖ ገበያ በነጻ ገበያ መርህ እንዲመራ ፈጽሞ አይፈልግም፡፡ ይልቁኑ የተዋስዖው ገበያ የሚያስተዳደረው ሻጭንም ሆነ ሸማችን በሚያደናብረው የጥቁር ገበያ መርህ ነው፡፡ በነጻ ገበያ መርኾዎች የሚንቀሳቀስ የተዋስዖ ገበያማ እውነትን ያገኛታል፡፡ እውነትን ያገኛት እርሱ ደግሞ አርነት ይወጣል፡፡ ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት በገበያው ካሉን እልፍ አዕላፍ የምኒሊክ ትርጓሜዎች በተደጋጋሚ ጮክ ብለው የሚሰሙት ሁለቱ ጽንፈኞች ብቻ ናቸው፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ የተዋስዖ ገበያ የሚመራበት ሥርዐት የገበያው ተሳታፊዎች ወደግራም ሄዱ ወደቀኝ ወደ አንድ ትርጓሜ እንዲሰባሰቡ፤ በዚያ ትርጓሜ ዙሪያም አዲስ እውነት ቀርጸው የጋራ አገር እንዲገነቡ የሚፈልግ የገበያ ሥርዓት አይደለም፡፡ ሕወሀት ምን ዐይነት ሚዲያ፤ በምን ያህል መጠን እንደሚኖር ይወስናል፡፡ ያለማንም ሀይ ባይነት የትምህርት ሥርዐቱን ወደ ፈለገው የትርጓሜ አቅጣጫ ያሳልጣል፡፡ የአደባባዮች፣ የመንገዶች፣ የሀውልቶች፣ አስፈላጊ ከኾነ ደግሞ የከተሞችን ስም እርሱ ወደፈለገው የተዋስዖ ትርክት እንዲያፈገፍጉ በማድረግ ገበያውን እንዳፈተተው ያቆማል፣ ይበትንማል፡፡ የብሔራዊ መዝሙር፣ የባንዲራ፣ የብሔር ብሔረሰብ ክብረበዓላት ይቀርጻል፣ ያውጃል፣ ይበጅታል፣ ያስፈጽማል፡፡ የአየር በአየር ነጋዴዎች ለጥቂት ደቂቃ አገሪቷ ውስጥ ያሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከፓርቲው ገለልተኛ ቢሆኑ፤ ነፃ ሚዲያ በብዛት እና በጥራት ቢስፋፋ፤ የትምህርት ሥርዓቱ የሚቀረጸው አሁን ከሚታየው ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት በተለየ መልኩ ቢኾን ኖሮ ምን አይነት የተዋስዖ ገበያ በኢትዮጵያ እንደሚኖር ለመገመት አያዳግትም ፡፡ በምናባዊቷ ኢትዮጵያም እንኳን ስለዳግማዊ ምኒልክም ኾነ ስለጨለንቆ ሙሉ በሙሉ አንስማማም፡፡ ነገር ግን ውይይቱን የሚያስተናብሩት የጥቁሩ ገበያ የአየር በአየር ነጋዴዎች ፤ ውይይቱንም የሚመሩት ለጥቁር ገበያው የተመረቱ አልበሞች፣ መጽሐፎች፣ ድግሶች እና ሰልፎች አይሆኑም፤ የውይይቱ ይዘትም ልክ 1983 ዓ.ም እንደ ነበረው እጅ እጅ አይልም ነበር፡፡ ያልጨረቱ ሀልዮቶች፣ ያልነፈሰባቸው ትችቶች፣ አዳዲስ ዘርፎች በየጊዜው እየበቀሉ እያደጉ ስለዳግማዊ ምኒሊክም ሆነ ስለ ኢትዮጵያ የሚደመጡት ትንታኔዎች እና ትርጓሜዎች ለተዋስዖው ሞገስ ይሆኑት ነበር፡፡ የገበያው የበላይ ጠባቂ ሕወሃት እጅጉን የሚጠነቀቀው ስምምነት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በየትኛውም ተዋስዖ ላይ የሰከኑ አስታራቂዎችን ሳይሆን ስምምነት ላይ ለመድረስ ይቅር እና ለመደማመጥ የማይችሉትን ያበረታታል፡፡
በዚህ ድቅድቅ ጭለማ ውስጥም ሁሉም በእውር ድንብር ይተራመሳል፡፡ ጥቂት ትንሽ ሻል ያሉ አራዶች በየጥጋጥጋቸው ርዕስ እና ትርጓሜ እየመረጡ ቢጫ ሰው ፣ ሰማያዊ ዶሮ፣ ሲያዴ ፈረስት፣ እና ሚያዚያ 9 ምናምን የሚል የአየር በአየር ቡቲክ ይከፍታሉ፡፡ ከዚህም ከዚያም የለቃቀሙትን የትርጓሜ ሰልባጅ አዲስ ልብስ አስመስለው ይሸጣሉ፡፡ እነዚህ የአየር በአየር ነጋዴዎችም የገበያውን ሕግ አይቀይሩም፡፡ አንዳንዶቹ እንደውም የገበያው መሰረታዊ ሕግ ከተቀየረ ሕልውናቸው አደጋ ላይ እንደሚኾን ስለሚገነዘቡ ከጥቁር ገበያነት ወደ ነጻ ገበያነት እንዲለወጥም አይፈልጉም፡፡ ገበያውን እንዴት አድርጌ ነው የምጠቀልለው ብለው ሁሉ የሚገዛው ትርጓሜ ለማምጣትም አፈልጉም፡፡ የአየር በአየር ነጋዴዎች ናቸው እና ቶሎ ቶሎ ከግርግሩ አትርፈው ሽል እና ሽብልል ከማለት ውጪ ገበያውን ሙሉ ለሙሉ ለመማረክ ወገቡም የላቸውም፡፡ To be fair ለሕወሀት ሳይሆን ለእውነት ‘ፌር’ ለመሆን የኢትዮጵያ ተዋስዖ ገበያ የጥቁር ገበያን መርህ መከተል የጀመረው ግንቦት 20/1983 አይደለም፡፡ ከሕወሀትም በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የትርጓሜ ገበያው በገዢው ቡድን ተፅዕኖ መሆኑ አይካድም፡፡ የወቅቱ ትክክለኛ መረዳት ተዋስዖው የጥቁር ገበያ ሥርዐት መኾኑን ማስተዋል ይገባል፡፡ እንዴት ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ትርጓሜዎች በሰላም ሊንሸራሸሩ የሚችሉት ? በእርጋታ እና በስክነት የሚንቀሳቀስ የተዋስዖ ገበያ ሥርዐት መመስረቻ ቁልፎቹ ምንድን ናቸው ? በባህሎቻችን እና በቋንቋችን ውስጥ ምን ያህል ሀብት ምን ያህል ድህነትስ አለ ? አሁንም ስለጥቁር ሰው ማሰብ ይፈልጋሉ ? I don’t .

ወያኔ በብሔር ብሔረሰቦች መንገድ ይብቃህ ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ትሆናለች (ደመቀ በሪሁን -ከኢትዮጵያ)

ሰዉ በዘሩ ሳይሆን በስራዉ ይመዘን –ግርማ ካሳ

$
0
0

ግርማ ካሳ
Muziky68@yahoo.com

 

በፌስቡክ የሚጽፋቸውን እየሰበሰቡ አንዳንድ ድህረ ገጾች ያስነብቡናል። በመቀሌ ነዉ የሚኖረዉ። ወጣት ነዉ። አብርሃ ደስታ ይባላል። የሚያምንበትን ከመናገርና ከመጻፍ ወደ ኋላ አይልም። በቅርቡ ከጻፋቸው አስተያየቶች አንዱ፣ ልቤን ማረከው። እኔም በዚያ ላይ ጨመር ለማድረግ ፈለኩ።

«ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩል ናቸው ብለን ከተነሳን ሁሉንም ብሄራቸውን ግምት ዉስጥ ሳናስገባ (ምክንያቱም ሁሉም እኩል ናቸው ብለናልና) በኢትዮጵያዊነታቸው እንመዝናቸው። ለማንኛውም ጉዳይ (ለስራ፣ ለስልጣን …) በትምህርት ደረጃቸው ወይ ብቃታቸው ወይ ሌላ፣ ለሁሉም በእኩል ሊያገለግል በሚችል መስፈርት እንመዝናቸው። ሁላችን እኩል ከሆንን፣  አንድ ሰው ለመመዘን ጉራጌነቱን፣ ኦሮሞነቱን፣ ትግራዋይነቱን፣ አማራነቱን፣ ዓፋርነቱን፣ ሶማሌነቱን፣ ጋምቤላነቱን … ማስታወስ አያስፈልገንም። ማንነቱ የራሱ ነው። በኢትዮጵያዊነቱ መመዘን መቻል በቂ ነው።» ነበር ያለው ወጣቱ።

«አቶ መለስ ታመዋል፣ ሞተዋል» እየተባለ በሚወራበት ወቅት፣  ማን ሊተካቸው እንደሚችል፣ ከሕወሃት/ኢሕአዴጎች ጋር ቅርበት ካለው አንድ ወዳጄ ጋር  የተነጋገርኩትን ላካፍላችሁ። «ላለፉት ሃያ አመታት ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበረዉ ትግሬ ስለነበረ አሁን ከሌላ ብሄር ብሄረሰብ መሆን አለበት» አለኝ። «ይሄማ አይሆንም። መስፈርቱ መሆን ያለበት፣  ዘር ሳይሆን ብቃት ነዉ» አልኩኝ። ትግሬም ቢሆኑ፣ አቶ አርከበ እቁባይ፣ መለስን ቢተኩ መልካም ሊሆን እንደሚችል ገለጽኩ ። «ለምን ?» ቢባል፣  አዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩ ጊዜ መልካም የሰሩ ተወዳጅ ስለነበሩ።  መቼም አቶ አርከበ እቁባይን፣ በሌሎች ነገሮች ሊወቀሱ ቢችሉም፣ አዲስ አበባ  ከንቲባ የነበሩ ጊዜ «ጥሩ አልሰሩም ነበር» የሚሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ብዙ ይኖራሉ ብዬ አላስብም። ታዲያ በተግባር መልካም ያደረገ ሰው፣ ከአንድ ዘር ስለሆነ አገር እንዳይመራ ለምን ይከለከላል ?  ሰው መመዘን ያለበት በዘሩ ሳይሆን በስራዉ መሆን የለበትም ወይ ?

እርግጥ ነዉ ሕወሃት/ኢሕአዴጎች ዘረኛ በመሆናቸው ፣ ጠዋትና ማታ የሚለፍፉት የዘር ፖለቲካን በመሆኑ፣ እኛንም በመጠኑም ቢሆን በክለዉናል። እኛም እንደነርሱ «ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ …» መባባል እየለመድን ነዉ። «ለሃያ አመት ትግሬ ገዝቶ፣ እንዴት ከአሁን በኋላ ትግሬ ይገዛል ? » የምንልም አለን። መልካም ከሰራ፣ ሕዝብን ካከበረ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ፣ ሳይሰርቅ፣ ሳያጭበረብር በሕዝብ ከተመረጠ፣ ኢትዮጵያዊ እስከሆነ ድረስ ማንም ለምን መቶ አመት አይገዛም !!!! ዘሩ ምን እንደሆነ በማይታወቀዉ  በመንግስቱ ኃይለማሪያም ዘመንና በትግሬዉ/ኤርትራዊዉ መለስ ዜናዊ ዘመን ፣ የሕዝቡ ጥያቄ ዳቦና መብት ነበር። በወላይታዉ ሃይለማሪያምም ዘመን አሁንም ጥያቄዉ ዳቦና መብት ነዉ። የገዚዎች ዘር ቢለዋወጥም፣ የሕዝቡ ጥያቄ አልተለወጠም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎትና ጥያቄ «ማን ነው ስልጣን ላይ ያለው ? » የሚል ሳይሆን «ስልጣን ላይ ያለው ምን እየሰራ ነዉ ? » የሚል ነዉ።

ገዢዎቻችን ሁሉንም ነገር የሚያሰሉትንና የሚያሰቡት በዘር ሂሳብ ስለሆነ፣ በብቃት ሳይሆን በዘር ላይ ተመስርተዉ የስልጣን ድልድል አደረጉ። አቶ ኃይለማርያምን ጠ/ሚኒስቴር፣  ሌሎች ዘሮችን ለማስደሰት ደግሞ፣ ከሕገ መንግስቱ ዉጭ፣ በርካታ ጠቅላይ ሚኒስቴሮች መደቡ። አንዱን ለአማራ፣ አንዱን ለትግሬ፣ አንዱን ለኦሮሞ ሰጡ። የካቢኔ ድልድልም ሲደረግ፣ ክርክሩ «የኔ ዘር ብዙ አላገኘም.. ወዘተረፈ» የሚል ነበር። ብቃት ሳይኖራቸው ከአንድ ዘር በመሆናቸዉ ብቻ ሃላፊነት እየተሰጣቸው፣ ሕዝብን በስራቸው የሚበድሉ በዙ።

ዜጎች በመታወቂያቸው ላይ፣ ወደዱም ጠሉም ዘራቸውን መጻፍ አለባቸው። ኦሮሞ ወይ ትግሬ ወይ አማራ ካላሉ መታወቂያ አያገኙም። ኢትዮጵያ ኤምባሲ ባሉ ፎርሞች ላይ ዘር መጠቀስ አለበት። እኔ በዘሬ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቴ ነዉ መታወቅ የምፈልገዉ፤ ዘሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ» የሚል ካለ አንዳች የዜግኘት መብት አይሰጠዉም። እንድ ዉጭ አገር ሰው ነዉ የሚቆጠረው። ከዘር ዉጭ አሁን ምን አለ ከዚህ የኋላ ቀር  ጎጣዊ አመለካከት ነጻ ብንወጣ ? ምን አለ አብርሃ ደስታ  እንዳለው፣  በስራችን ብንመዘን ?

በነገራችን ላይ አብርሃ ደስታ፣ በቅርቡ ከአንድነት ጋር ለመዋሃድ ጥያቄ ያቀረበዉ  የአራና ትግራይ አመራር አባል ነዉ። ከጥቂት አመታት በፊት ደግሞ፣  የቀድሞ የአራና ሊቀመንበር ፣ የተከበሩ አቶ አስራት ገብሩ የተናገሩት ግሩም አባባልም ነበር። ከአምስት ሺሆች በላይ በተሰበሰቡበት የመቀሌ ስብሰባ፣  አንድ ጥያቄ በአንድ የሕወሃት ካድሬ ተጠየቁ። «እንዴት ከትግራይ ጠላቶች ጋር ትሰራላችሁ ? » የሚል። አሳፋሪ፣ ዘረኛ ጥያቄ !!!! የአቶ ገብሩ መልስ ቀጥተኛና ግልጽ ነበር። «ማንም ኢትዮጵያዊ ለማንም ጠላት አይደለም። ትግራይ የትግሬዎች ብቻ ሳይሆን የአማራዉ፣ የኦሮሞው የሁሉም ናት፡፡ ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ብቻ ሳትሆን የትግሬዉ የጉራጌዉ የሁሉም ናት። ማንም ኢትዮጵያዊ በየትኛዉም የአገሪቷ ግዛት የመኖር መብት አለው» የሚል የሚያረካ መልስ ነበር የመለሱት።

 

ከቀድሞ የአረና አመራር አቶ ገብሩ፣ ከአሁኑ ደግሞ አቶ አብርሃ ደስታ አባባሎች የምንማረው ፣ የሰለጠነ የኢትዮጵያዊነትን ፖለቲካ ነዉ። ሕወሃት/ኢሕአዴግ የሚያራምደው የዘር ፖለቲካ ምን ያህል የከሰረ መሆኑን በግልጽ ያጋለጠ ነዉ። አረናዎች፣ በትግራይ እንደነበሩት ጀግኖቻችን (ራስ አሉላ፣ አጼ ዮሐንስ ) የኢትዮጵያዊነት አርበኞች፣  በኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ቀዳሚ ሆነው የተሰለፉ መሆናቸዉን እያስመሰከሩ ነዉ።

 

እዚህ ላይ አንድ ነገር አንርሳ። ይህ አሁን በሕወሃት/ኢሕአዴግ አማካኝነት በአገራችን ላይ የተዘረጋዉ ፣ በዘር ላይ የተመሰረተው፣ የኋላ ቀር ፖለቲካ፣ ይህ አሁን ዜጎችን ትግሬ፣ አማራ ብሎ የመለየትና የመከፋፈል  አባዜ፣ መሰረቱ ትግራይ አይደለም። በአንድ በኩል ከሞስኮ፣ ከማርክሲስቶች፣ ከነስታሊን ኮርጀዉ፣ እነ ዋለልኝ መኮንን ያመጡት፣ አንድ ወቅት ኢሕአፓዎችም ሲያራግቡት የነበረዉ፣  አጉልና እንግዳ ፍልስፍና ሲሆን፣ በሌላ በኩል አንዳንድ ክርስቲያን ተብዬ፣ ጸረ-ወንጌልና ጸረ-ፍቅር የሆኑ ሚሲዮናዉያን (በተለይም በምእራብ ኢትዮጵያ)፣ የላካቸው መንግስት ኢትዮጵያን ግኝ ለመግዛት እንዲመቸው ሆን ብለው፣  ሕዝቡን ለመከፋፈል የረጩት መርዝ ነዉ። እነ መለስና ስብሃት ነጋም ከዚያ ወስደው ነዉ፣ በትግራይና  በተቀረዉ ኢትዮጵያዊ ላይ መርዘኛና ዘረኛ ስርዓትን የጫኑት። እንጂ መሰረቱ ከትግራይ የሆነው ኢትዮጵያዊነት ነው !!!!!

 

ቃሊቲ እሥር ቤት የነበሩ ጊዜ ፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ስለትግሬዎች የጻፉት አንድ ጽሁፍ ነበር። አንድ የቀድሞ ተማሪያቸው፣ ደርግ እንደወደቀ ትግራይ ሄዶ የታዘበዉንና  ያካፈላቸዉን ነበር የጻፉት። ሕወሃት በአደባባይ፣  የሕወሃት እንጂ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ እንዳይውለበለብ  አግዶ ነበር። «ኢትዮጵያዊነት» እንደ ሐጢያት ይቆጠር ነበር። ኢትዮጵያዊነት ወደዚያ ተጥሎ፣ ዋናዉን ስፍራ የያዘዉ «ትግሬነት፣ ኦሮሞነት፣ ጉራጌነት..»  ነበር። ነገር ግን ሕዝቡ በአደባባይ ቢከለከልም፣  በቤቱ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ይሰቅል ነበር። «ምንም እንኳን ሕወሃት ቢያስፈራራንም ኢትዮጵያን ከልባችን የሚወስዳት የለም። የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ልባችን ዉስጥ ናት። ቤታችን ዉስጥ ናት» እያሉ ፣ የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ከማንም በበለጠ እንጂ ባልተናነሰ መልኩ ያንጸባርቁ ነበር። በርግጥ ትግራይ ዉስጥ ከጥንት ጀምሮ፣ የነበረዉ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ጠፍቶ ወይንም መንምኖ አያውቅም፤ እንደዉም የበለጠ ጠነከረ እንጂ።

 

ለማጠቃለል አንድ ነጥብ ልጨመር። አገራችን ዉስጥ ያሉ የተለያዩ ቋንቋዎች ፣ የተለያዩ ባህሎች ኢትዮጵያዊነት ናቸው። የኢትዮጵያ የተለያዩ ጅማቶች ናቸው። አፋን ኦሮሞ፣ ትግሪኛ፣ ጉራጌኛ  እንዲስፋፋ ማድረግ ኢትዮጵያዊነትን ማጠናከር  ነዉ።  እናቴ ጅጅጋ ተወልዳ ሃረር ያደገች ናት። ሶማሌኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ አማርኛ እኩል ትናገራለች። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣  አማርኛ ያስተማሩኝ አንድ መምህር ነበሩ። ጉራጌኛ፣ ትግሪኛ፣ አፋን ኦሮሞና አማርኛ አቀላጥፈው ይናገሩ ነበር። ሲዳማዎች በብዛት በሚኖሩባት ይርጋለም ከተማ፣  ከወላይታ ቤተሰቦች ነዉ የተወለደችው። በደርግ ጊዜ አስመራ መካነ ሕይወት ሆስፒታል ለብዙ አመታት ሰርታለች። ሲዳምኛ፣ ወላይተኛ፣ አማርኛና ትግሪኛ ትናገራለች። አያስደስተም። ቋንቋ ጠቃሚ ነዉ። ቋንቋ መግባቢያ ነዉ። ብዙ ቋንቋ ባወቅን ቁጥር እነጠቀማለን እንጂ አንጎዳም። ቋንቋ የልዩነት ምክንያት ሊሆን አይችልም።

 

ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት ስል «የብሄረሰቦች ቋንቋ ይደጉ፣ የብሄረሰቦች ባህል ይስፋፋና ይዳብር» ማለቴ ነዉ። «አፋን ኦሮሞ ፣ ትግሪኛ፣ ጉራጌኛ …. የኦሮሞዎች ፣ ትግሬዎች ፣ ጉራጌዎች  ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዲ ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎች፤ የኢትዮጵያ ሃብቶች ናቸው» ማለቴ ነዉ። እንደ አንድ ሕዝብ ተያይዘን፣  የተለያዩ ቋንቋዎቻችንና፣ ባህሎቻችን እናዳብራለን። የኢትዮጵያ ዉበቷ ብሄረሰቦቿ ናቸውና !!!!!!!

 

ግርማ ካሳPen

 

 

 

 

 

 


የፍርሃት ባህልን እያነገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፤(ያሬድ ኃይለማርያም)

$
0
0

አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት ወደ ኋላ
(ክፍል ሁለታ)

ያሬድ ኃይለማርያም
ከብራስልስ    
ታኅሣሥ 9፣ 2006

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት በኢትዮጵያዊያን ላይ እያሰፈነ ስላለው የፍርሃት ባህል ቀደም ሲል ባሰራጨሁት የዚህ ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ባለሙያዎች በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ለፍርሃት ባህል መስፈን መንሰዔዎች ያሏቸውን ነጥቦች ዘርዝሬ ነበር። በክፍል አንድ ጽሑፌ መግቢያ ላይ እንደገለጽኩት ምንም እንኳን ፍርሃት የግለሰቦች ባህሪ መገለጫዎች መካከል አንዱ ቢሆንም የዚህ ጽሑፍ ትኩረት በወል የምንጋራቸውና በማኅበረሰብ ደረጃም በሚንጸባረቁት የፍርሃት ምልክቶች ላይ ብቻ ያተኮረ ነው። በመሆኑም በዚህ ክፍል ውስጥ የህሊና እና የአካል ቁስልን ባስከተሉ ትላንቶች ውስጥ ማለፍ የሚፈጥረውን የፍርሃት ቆፈንና የሚያስከትለውን መዘዝ በመቃኘት ፅሑፌን ልደምድም።

በአለማችን ታሪክ ከሰው ልጅ አዕምሮ ተፍቀው የማይወጡና እጅግ አሰቃቂ በመሆናቸው ሲታወሱ የሚኖሩ በርካታ ጦርነቶችና የእርስ በርስ እልቂቶች ተከስተዋል። የመጀመሪያውና የሁለተኛው የአለም ጦርነቶች፣ የኦሽዊትዝ ጭፍጨፋ፣ የአፓርታይድ የግፍ አገዛዝ፣ የሩዋንዳው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ እንዲሁም በተለያዩ የአፍሪቃ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ውስጥ የተከሰቱትና የሚሊዪኖችን ሕይወት የቀጠፉት እልቂቶች በዋነኝነት ተጠቃሾች ናቸው። እነኚህ በክፉ ክስተትነታቸው በታሪክ የሚወሱት አጋጣሚዎች ካስከተሉት እልቆ መሳፍርት የሌለው ሰብአዊ ቀውስ እና የንብረት ውድመት ባሻገር ከትውልድ ትውልድ የሚወራረስ ትምህርትንም አስተምረው አልፈዋል። በተለይም የምዕራቡ አለም በራሱም ሆነ በርቀት በሌሎች ላይም የተፈጸሙትን እነዚህን መሰል መጥፎ ክስተቶች በአግባቡ በመመርመር፣ መረጃዎችን ሰብስቦና አደራጅቶ በማስቀመጥ፣ በመጽሐፍ ከትቦና እና በፊልም ቀርጾ በማኖር ቀጣዩ ትውልድ እነኚህን መሰል አደጋዎችን ከሚያስከትሉ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ፣ ኃይማኖታዊና ኢኮኖሚያው ቀውሶችና ቅራኔዎች እራሱን በማራቅ ችግሮችን እጅግ በሰለጠነና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲፈታ ማድረግ ችለዋል። ዛሬ ላይ ያለው ትውልዳቸውም እነ ናዚ እና ሌሎች አንባገነኖች በታሪካቸው ውስጥ ያደረሱትን ሰቆቃና ግፍ እያሰብ የሚሸማቀቅ ወይም በፍርሃት የሚርድ ሳይሆን ታሪክን በታሪክነቱ ትቶ ሙሉ አቅሙንና ጊዜውን ከሳይንስና ተክኖሎጂ ጋር አዋህዶ በዚህ ምድር ላይ ያሻውን ሁሉ ለማድረግ የሚያስችል አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል።

ወደ አገራችን ስንመለስ ኢትዮጵያም ዛሬ ያለችበትን ጂዮግራፊያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ሌሎች ገጽታዎች ለመላበስ ያበቋት እጅግ በርካታ ክፉ እና በጎ ተበለው የሚጠቀሱ የታሪክ ክስተቶችን አስተናግዳለች። ምንም እንኳን ከላይ ከተጠቀሱት የአለማችን አሰቃቂ ታሪኮች ጋር ባይወዳደርም አገራችንም ከውጭ ወራሪዎች በተሰነዘረባት ጥቃትም ሆነ በልጆቿ መካከል በተከሰቱ የእርስ በእርስ ግጭቶች በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ውድ ልጆቿን አጥታለች። ድህነትን ጠራርጎ ሊያስወግድ ይችል ከነበረው አቅም በላይ በብዙ እጥፍ የሚገመት አንጡራ ሃብቷን በጦርነቶች፣ በግጭቶችና በዘራፊዎች ተነጥቃለች። ይህ እና ሌሎች በርካታ ምክንያቶችም ተደራርበው አገሪቱን ከድሃም ድሃ ተብለው ከሚጠቀሱት አገሮች ተርታ አሰልፈዋታል። እንግዲህ ትልቁ ጥያቄ እኛስ እንደ ሌላው ዓለም ሕዝብ አገራችን ካለፈችበት የረዥም ዘመን ታሪክ እና በየወቅቱ ከተከሰቱ መጥፎና በጎ የታሪክ ክስተቶች ምን ተማርን? ተምረንስ ለዛሬ እኛነታችን ምን አተረፍን? በአያቶቻችን እና በእኛ መካከል በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እና በፖለቲካ ተክለ አቋማችንም ሆነ አመለካከታችን ዙሪያ ለውጦች አሉ ወይ? ለውጣችን ቁልቁል ወይስ ካለፉት ወገኖቻችን የህይወት ተመክሮ ትምህርት ወስደን የደረስንበት የላቀ የአስተሳሰብና የኑሮ ደረጃ አለ? የታሪክ መዛግብቶቻችንስ ያለፉ ነገስታቶችን እና የጦር አበጋዞቻቸውን ከማወደስና ገድላቸውን ከመተረክ ባለፈ በቀጣዩ ትውልድ ሕይወት የጎላ ሚና ሊኖራቸ በሚችል መልኩ ተዘጋጅተዋል ወይ? ወይስ ‘እኔ የገሌ ዘር’ እያለ እንዲያዜምና በአያቶቹ ገድል እንዲያቅራራ ብቻ ተደርገው ነው የተዘከሩት? እንደ እኔ እምነት ከምዕራቡ አለም እኛንና ብዙዎች የአፍሪቃ አገራትን ከሚለዩን ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ ከነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የሚመነጩ ይመስለኛል።

የዛሬ መቶ እና ሁለት መቶ አመት በፊት የተፈጠሩ የታሪክ ክስተቶችን ፍጹም በተዛባ መልኩ እያጣቀስን ልክ የእኛ የልፋት ውጤት አስመስለን እስኪያልበን የምንፎክርና የምንጨፍር እኛ ነን። ታሪክን እና ጀግኖችን ማወደስ ተገቢ ቢሆንም የኛን ድርሻ እነሱን በማወደስ ብቻ ስንገታው አደጋ ላይ ይጥለናል። እንደ አያቶቻችን ታሪክን መስራት ሲያቅተን ታሪክ ሰሪዎችን በማውሳትና በዜማና በግጥም ማወደስ ብቻ ብንኮፈስ የዛሬውን ማንነታችንን አይሸፍነውም። ይህ በአያቶቻችን ታሪክ ውስጥ ተደብቀን ‘በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ’ እያሉ ማዜም፣ መፎከር፣ ማቅራራትና ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ዛሬ ከተጣቡን የድህነት፣ የፖለቲካ ጭቆና እና ማኅበራዊ ቀውስ የማያስጥለን እና ነፃ የማያወጣን እሰከ ሆነ ድረስ ኩራታችን ከድንፋታ አያልፍም። አገሬን እወዳልሁ፣ በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ እያሉ ባንዲራ ለብሶ ማቅራራት በተግባር ካልታገዘ የውሸት ወይም ባዶ ኩራት (false pride) ነው የሚሆነው። እውነተኛ ኩራት የሚመነጨው ከራስ ነው፤ የራስን ማንነትን በማወቅና በመቀበል ላይ የሚመሰረት ነው። ማንነትን አምኖ መቀበል አቅማችንንም አብረን እንድፈትሽ ይረዳል። የዛሬ ባዶነታችንን በአያቶቻችን የታሪክ ገድል እንድንሞላ ወደሚያስገድድ የሞራል ክስረት ውስጥም እንዳንገባ ይረዳናል። የዛሬ ውርደታችንን በአድዋ ድል እና በሌሎች የአያቶቻችን ተጋድሎዎች በተገኙ ስኬቶችን ልንሸፍነው ከመጣር ይልቅ ታሪክ እንድንሰራ ብርታት ይሆነናል።

በሌላ በኩል የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ያሳቀፉንን የዘረኝነት መርዝ እያራባን በታሪክ ተፈጽመዋል የተባሉ አንዳንድ ክስተቶችን እየመነዘርን ‘ያንተ ቅም ቅም አያትህ የእኔን ቅም ቅም አይታቶች በድሎ ነበር፤ ስለዚህ በቅም ቅም አያቶቼ ላይ ያንተ ዘሮች ላደረሱት በደል ኃላፊነቱን አንተ ትወስዳለህ እያልን ድርጊቱን ዛሬ ላይ እንደተፈጠረ በመቁጠር የምንጋጭና ለመነጣጠል እንቅልፍ አጥተን የምናድርም አለን። እራስን እንደተበዳይ ሌላውን የኅብረተሰብ ክፍል እንደ በዳይ በመቁጥርና የተዛባን ታሪክ በመተንተን ለዛሬው በዘረኝነት መርዝ ለተለወሰው የፖለቲካ አጀንዳቸው ማሳኪያነት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ካፈር የሚለውሱ ኢትዮጵያዊያኖችም (እነሱ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ቢሉም) ልብ ሊገዙ ይገባል። በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ጎሣዎች በገዛ አገራቸው እኩል መብትና ጥቅም እንዲረጋገጥላቸውና የሁሉም አገር እንድትሆን ከመጣር ይልቅ በዘረኝነት ስሜት ውስጥ ተወጥሮ ኢትዮጵያዊነትን መካድና ከራስ ጎሣ ውጭ ያለውን የኅብረተሰብ ክፍል እንደ ጠላት መቁጠር መዘዙ ብዙ ነው። ይህን ለመረዳት ብዙ ምርምር አያስፈልገውም። በቅርባችን ካለችው ከሩዋንዳ ትምህርት መውሰድ ይቻላል። ይህን የዘረኝነት እሳት እየተቀባበሉ የፖለቲካ መታገያቸው ያደረጉ ኃይሎችም ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ በስሙ የሚነግዱበት ሕዝብ ሊያወግዛቸው ይገባል።

እርቀን ሳንሄድ የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን እንኳን ብንፈትሽ ዛሬ ለምንገኝባቸው እጅግ ውስብስብ እና ፈታኝ ችግሮች መንስዔ የሆኑትን ነገሮች በቀላሉ ልንገነዘብ እንችላለን። የችግሮቻችንን ምንጮች እና ያስከተሉብንን መዘዝ በቅጡ መረዳት ከቻልን ከተዘፈቅንበት አረንቋ ውስጥ ለመውጣት ጊዜ ላይወስድብ ይችላል። መወጣጫውም ላይርቀን ይችላል። ትልቁ ጥያቄ ችግሮቻችንን ከመዘርዘር ባለፈ ምንስዔዎቻቸውንም በቅጡ ተረድተነዋል ወይ? እንደ አንድ አገር ሕዝብ በችግሮቻችን እና በችግሮቹ ምንጭ ዙሪያ የጠራ የጋራ ግንዛቤ አለን ወይ? በፖለቲካ እና በሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስንደራጅስ ከነዚህ ግንዛቤዎች ተነስተን ነው ወይ? የጋራ የሆኑ ችግሮች ሰዎችን ያስባስባሉ፣ ለድርጅቶች መፈጠርም መንስዔ ይሆናሉ፣ ችግሮቹንም ለመቋቋም እና ለማስወገድ “ከአንድ ብርቱ …” እንደሚባለው ኃይልን ይፈጥራሉ። ይሁንና ስብስቡ ወይም የተደራጀው ኃይል ፊት ለፊት ከተጋረጡት ችግሮች ጋር ከመፋለም ባለፈ በድጋሚ እንዳይከሰቱ ምንጮቻቸውን ለማድረቅ የሚያስችል እይታ ከሌለው እና አቅሙንም በዚያ ደረጃ ካላሳደገ ይህ አይነቱ ማኅበረሰብ ሁሌም ለተመሳሳይ አደጋዎች የተጋለጥ ነው። የችግሩን መንሰዔ አጥንቶ ምንጩን ለማንጠፍ ከሚያወጣው ጉልበት፣ ገንዘብና ጊዜ የበለጠ አዳዲስ ችግሮች በተከሰቱ ቁጥር ከተኛበት እየባነነ ተነስቶ ችግሮቹን ለመቋቋም የሚያስችሉ ድርጅቶችን ለመፍጠርና ለማፍረስ የሚያወጣው ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት እጅግ የላቀ ነው። በእንዲህ አይነት ማኅበረሰብ ውስጥ ጠንካራ የሆኑና ልምድ ያካበቱ ድርጅቶችን መፍጠር አይቻልም። ብዙዎቹ ድርጅቶች ሳይጎረምሱ፣ ሳይጎለምሱ እና ሳያረጁ በጨቅላነታቸው ይሞታሉ ወይም ደንዝዘው ስማቸውን ብቻ ይዘው ይቀራሉ። ይህ አይነቱ ማህበረሰብ አውራ የሚሆኑና በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉም የፖለቲካ፣ የኃይማኖት እና የማኅበራዊ ህይወት መሪዎችን የመፍጠር አቅም የለውም፤ አይፈጥርምም፤ በራሳቸው ጥረት ቢፈጠሩም ጎልተው እንዲታዩ እድሉን አይሰጥም። ትላንት ያነገሳቸውን በማግስቱ አፈር ከድሜ ሲደባልቃቸው ምንም አመክንዮ አይፈልግም። ሲያከብርም፣ ሲሾምም፣ ሲያዋርድም ሆነ ሲኮንን በስሜት ነው። በተለይም እንደኛ በብዙ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ተተብትቦ ግራ ለተጋባ ማኅበረሰብ ልምድና በእውቀት የጎለበቱና የሕዝብ አመኔታን ያገኙ ባለ ዕራይ ድርጅቶችና ግለሰቦች መኖር እጅግ ወሳኝ ነው።

የፖለቲካም ሆነ ሌሎች ልዩነቶቻችንን የምንይዝበት መንገድ ሊፈተሽ ይገባዋል። የቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ማብቂያን ተከትሎ የፈረሰውና ጀርመንን ለሁለት ከፍሏት የነበረው ግንብ ሲናድ ምስራቅና ምዕራቡን ወደ አንድ አገር ከመለወጥ ባለፈ መላው አውሮፓን አንድ ያደረገ ክስተትን ፈጥሯል። የሰብአዊ መብቶች እና የዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሳቦች የልዩነት ማጦዣ ምክንያቶች ከመሆን ወጥተው ጀርመንን ብቻ ሳይሆን አውሮፓን ያዋሃዱ ተጨባጭ እውነታዎችን ፈጥረዋል። ይህን ተከትሎም ከታሪክ ለመማር ዝግጁ በሆኑ በበርካታ የአለማችን አገራት በመሬት የተገነቡም ሆነ በሰዎች አዕምሮ ውስጥ የተካቡ የልዩነት ግንቦች ሁሉ ፈርሰው ዜጎች ለጋራ ራዕይ በጋራ የመቆም ጽናትን አሳይተዋል። ሕዝባቸውንም ነጻ አውጥተዋል። ሌሎች እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ አገሮች (አብላጫዎቹ የአፍሪቃ አገራት) የልዩነቶቻቸውን ግንቦች አጠንክረውና አዳዲስ ግንቦችን በአይምሯቸው ውስጥም ገንብተው የተሰበጣጠረና የሚፈራራ የኅብረተሰብ ክፍልን በመፍጠር ጉዞዋቸውን ቀጥለዋል። የጎሣ ግንቦች፣ የሥልጣን ግንቦች፣ የኃይማኖት ልዩነት ግንቦች፣ የድሃና የሃብታም ግንቦች፣ የጨቋንና የተጭቋኝ ግንቦች፣ ሌሎች ማኅበረሰቡን በአንድ ላይ እንዳይቆም እና ድህነትና አንባገነንነትን አሽቀንጥሮ እንዳይጥል አቅም የሚያሳጡ በርካታ የልዩነት ግንቦች ተገንብተዋል።

ድርጅቶችን እና መሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን እየፈጠርንና መልሰን እየደፈጠጥን የመጣንበትን የ50 ዓመታት የፖለቲካ ጉዞ ወደ ኋላ መለስ ብለን ብንቃኝ ይህንን እውነታ ያረጋግጥልናል። ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ለቁጥር የሚታክቱ የፖለቲካ፣ የሙያና በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮሩ ድርጅቶች ተፈጥረው ብዙዎች ካለሙበት ሳይደርሱ ከስመዋል። ጥቂቶችም ባልሞት ባይ ተጋዳይነት በመኖርና ባለመኖር መካከል ሆነው ቀጥለዋል። በከሰሙትም እግር ሌሎች በርካቶች ተተክተው በተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ ወድቀው የኅብረተሰቡን ቀልብ ለመሳብ ደፋ ቀና ሲሉ ይስተዋላል። እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው በዚህ ዘመን ውስጥ ብቅ ብለው በከሰሙትም፣ ተውተርትረው ቆይተው በተዳከሙትም፣ አዳዲስ ስም እየያዙ በተፈጠሩትም ድርጅቶች ውስጥ ዋነኛ ተዋናዮቹና የድርጅቶቹ ፈጣሪዎችም ሆኑ አጥፊዎቹ አንድ አይነት ሰዎች መሆናቸው ነው። ትላንት በአንድ ድርጅት ጥላ ስር ሆነው ሌሎችን እንደ ጠላት ይፈርጁ የነበሩ ሰዎች ዛሬ የብዙ ድርጅቶች ፈጣሪዎች ሆነዋል። ትላንት በጠላትነት የሚፈራረጁ ድርጅቶች አባል የነበሩ ሰዎች ቂማቸውን እንዳረገዙ ዛሬ በአንድ ድርጅት ጥላ ሥር የተሰባሰቡበትንም ሁኔታ እናያለን። በድርጅቶቹ መካከል እጅግ ጠባብ የሆኑ የርዕዮታለም ልዩነቶች ከመኖራቸው ውጭ አብዛኛዎቹ የመጨረሻ ግባቸው አንድ እና አንድ ነው። ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ የሕግ ልዕልና የተረጋገጠባት፣ ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት እና ድህነትን ያሸነፈች ኢትዮጵያን ማየት፣ መፍጠር ነው። በነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የሚለያዩ ድርጅቶች ያሉ አይመስለኝም፤ ሊኖርም አይችልም። ልዩነቱ እነዚህ ግቦች ላይ ለመድረስ ድርጅቶቹ በሚከተሉት አቅጣጫና መንገድ ቅየሳ ላይ ነው።

በዚህ የ50 ዓመት ጉዞ ውስጥ በሽብር መንፈስና በነውጥ ተግባራት የተሞላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በድርጅቶች መካከል እርስ በርስ አለመተማመንንና መካካድን ፈጥሯል። ይህም አለመግባባቶቹ ከጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት አልፈው እልቂትን አስከትለዋል። በዚያም የተነሳ አገሪቷ በፍርሃት እንድትዋጥና ሕዝቧም በስጋት እንዲኖር፤ የፍርሃት ባህልም እንዲጎለብት ከፍ ያለ ሚና ተጫውቷል። ዛሬ በእያንዳንዳችን አዕምሮ ውስጥ በርካታ የልዩነት ግንቦች ተፈጥረዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በሲቪክ ማኅበራት፣ በኃይማኖት ተቋማት፣ በማኅበረሰብ ድርጅቶች መካከልም የበርሊን ግንብ አይነት ግዙፍ የልዩነት ግንቦች ተፈጥረዋል። የዛሬዎቹ ኃይሎች ከገዢው ፓርቲ በስተቀር በትጥቅ የተደራጁ ስላልሆኑ ነው እንጂ ለመጠፋፋት ቅርብ ናቸው። ትልቁና እያንዳንዳችን እራሳችንን ልንጠይቅ የሚገባን፤ እነዚህን ግንቦች ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዴት ንደን እና በላያቸው ላይ ተረማምደን ልብ ለልብ እንዋሃዳልን? እንዴት እንደ አንድ ሕዝብ የጋራ ዕራይ፣ የጋራ መዝሙር፣ የጋራ ህልም፣ የጋራ መፈክር፣ የጋራ መድረክና የጋራ አገር እንፈጥራለን? እንዴት ከቂም፣ ከበቀልና ከቁርሾ ሽረን ከታይታና ከቧልት ፖለቲካ ወደ እውነተኛ የፖለቲካ ሕይወት እንመለሳለን?

ለማጠቃለል ያህል በእኔ እምነት ከተተበተብንበት ውስብስብ ችግሮችና ከተጫነን የፍርሃት ድባብ ለመላቀቅ፤ አልፎም ጤናማ የሆነ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ሥርዓት ባለቤት የሆነ ማኅበረሰብ ለመፍጠር የሚከተሉት ተግዳሮቶች ቢቀድሙ ይበጃል እላለሁ::

-       ዛሬ ለፖለቲካ ንትርክና  እርስ በርስ መፈራራት እንደ ምክንያት የሚነሱት የታሪካችን ክፍሎች ከፖለቲካ፣ ከኃይማኖት እና ከሌሎች ወገንተኝነት ነጻ በሆኑ ምሁራን በአግባቡ የሚጠኑበት ማዕከል ቢኖረን። የመወዛገቢያ ነጥብ የሆኑትም ታሪካዊ ኩነቶችን በአግባቡ ቢጠኑ እና በተለያዩ መንገዶችም ተደግፈው ለማስተማሪያነት ቢውሉ በድንቁርና ላይ ከተመሰረቱት ታሪክ ጠቀስ የሆኑና በጥላቻ መንፈስ የተሞሉ ክርክሮች ወጥተን እውቀትን በዋጁ ውይይቶች ላይ እናተኩራልን።

-       የሩቁን ለታሪክ ምሁራን እንተወና ባለፉት አምሣ ዓመታት ከ1960 ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ በፖለቲካ ትግል ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑ ኃይሎች ዛሬም በአገሪቷ የለት ተዕለት የፖለቲካ ህይወት ውስጥ በግራና በቀኝ ሆነው እና በመቶ ድርጅቶች ጉያ ውስጥ መሽገው በአገሪቷና በድሃው ሕዝብ እጣፈንታ ላይ ወሳኞች ሆነው ቀጥለዋል። በተለይም ‘ያ ትውልድ’ በሚል የሚታወቀው የኅብረተሰብ ክፍል ከልጅነት እስከ አዋቂነት ክቡር ሕይወቱን፣ ጊዜውን፣ ገንዘቡን እና እውቀቱን ያለምንም ስስት የዛችን አገር እጣ ፈንታ ለማቅናት መስዋዕትነት ሲከፍል ቆይቷል፤ ዛሬም ዋነኛ ተዋናይና አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ቀጥሏል። ይህ ትውልድ ትላንትናም ሆነ ዛሬ በገዢና በነጻ አውጪዎቻች ቡድኖች ተፈራርጆ እርስ በርሱ ተጨራርሷል፣ ቂምና ቁርሾም ተጋብቷል፣ ተሰዷል አሰድዷል። ዛሬም በልቡ ቂም ይዞና በቀልን አርግዞ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ መሽጎ የጎሪጥ ይተያያል። ባገኘው አጋጣሚም ሆሉ ይናቆራል። ‘ቂም ተይዞ ጉዞ’ እንዲሉ ትላንት በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ሆነው በጠላትነት ይፈራረጁና ሊገዳደሉ ይፍላለጉ የነበሩ ሰዎች ይህን ሸክማቸውን በንስሃ እና በይቅር ባይነት ከላያቸው ላይ ሳያራግፉ ውስጥ ውስጡን እየተብሰከሰኩና እየተፈራሩ ገሚሶቹ በልጅነታቸው በቆረቡባቸው ድርጅቶች እየማሉ ቀሪዎቹም ዘመኑ በወለዳቸው አዳዲስ ድርጅቶች ውስጥ ሆነው የለበጣ ውህደት እየመሰረቱ በዋዜማው ይፈረካከሳሉ። እንደ እኔ እምነት ከዚህ የእርስ በርስ መፈራረጅ፣ መፈራራትና የቆየ ቂምና ጥላቻ ሳንሽር የምንክበው ካብ ሁሉ የእምቧ ካብ ነው የሚሆነው። እየሆነ ያለውም ይሄው ነው። ከዚህ አዙሪት ወጥተንና ከቂም ተላቀን የጋራ ራዕይ እንዲኖረን እያንዳንዱ ግለሰብ እራሱን ለይቅርታ ማዘጋጀት አለበት። ከልብ የበደላቸውን ይቅርታ ለመጠየቅና ይቅርታ ለመቀበል። ከድርጅታዊ ወገንተኝነትም እራሱን ነጻ አውጥቶ በሱና በድርጅቱ ላይ የተፈጸመውን በደል ብቻ ሳይሆን እሱም ጠላት ብሎ በፈረጃቸው ሰዎችና ድርጅቶች ላይ ያደረሰውን ግፍና በደል ለመናዘዝና ለደረሰውም ሁሉ አቀፍ ጥፋት ድርሻቸውን በድፍረት በማንሳት የተጠታቂነት ባህልን ‘ሀ’ ብለው ሊጀምር ይገባዋል።

-       ይህ ሁኔታም የደረሰውን የጉዳት መጠን በቅጡ እንድናውቅ ከማድረጉም ባሻገር እርስ በርስ የመወነጃጀሉን ታሪክ እንድንገታውና ልባችንንም በፖለቲካ ንስሃ አንጽተን የሚነገርለትን ያህል የተሳካ ባይሆንም እንኳ ልክ እንደ ደቡብ አፍሪቃው ‘በእውነት’ ላይ ወደ ተመሰረተ የእርቅ እና የሰላም መድረክ እንድቀርብ እድል ይፈጥርልናል።

-       የልጆቹን እርስ በርስ መጨራረስ እየተመለከት ፓለቲካ እንዲህ ከሆነ አርፎ መቀመጥ ይበጃል፤ እርም የፖለቲካ ነገር በሚል አይምሮውን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶ የለት ጉርሱን ብቻ እየቃረመ የአገሩን የፖለቲካ እጣፈንታ ለእዝጌሩ ትቶ ደግ ቀንና መልካም አስተዳደርን እንደመና ከሰማይ እንዲወርድለት የሚጠባበቀውም የኅብረተሰብ ክፍል አይኑን ይገልጣል፤ ከመጠፋፋት ወደ ሰለጠነ የውይይት ባህል በሚሻገረው የፓለቲካ ኃይልም ላይ እምነት ያሳድራል፤ እራሱንም ከፍርሃት ነጻ አውጥቶ በሙሉ ልብ በአገሩ ጉዳይ ባለቤት ይሆናል።

-       ስለዚህም የገዢው ኃይል ወያኔ ካለበት ጥልቅ ፍርሃት እና የሥልጣን ጥም የተነሳ ለእንዲህ ያለው ለውጥም ሆነ የሰላምና የእርቅ ጎዳና ገና ዝግጁ ባይሆንም የተቀሩት የፖለቲካ ሃይሎች መንገዱን በመጀመር ለዘመናት በመካከላቸው የቆየውን ቁርሾና ቂም ከአዕምሯቸው በማውጣት ከልብ የመነጨ እርቅ በማድረግ የልዩነት ግንቦችን ማፈራረስ ይጠበቅባቸውል። የሰላም፣ የእርቅ እና የእውነት አፈላላፉ ጉባዔ ያስፈልገናል።

በእውነት ላይ ተመስርተው ተቃዋሚዎች በቅል ልቦና ከታረቁ አብረው ከሠሩ በኢትዮጵያዊና በኢትዮጵያዊያን ላይ ለዘመናት እንደ መዥገር ተጣብቀው ደማችንን የሚመጡትን፣ ክብራችንን ገፈው እርቃን ያስቀሩንን፤ ድኅነት፣ እርዛት፣ አንባገነናዊ ሥርዓትና ጭቆና፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ ጦርነትና የእርስ በርስ ግጭቶች፣ ድንቁርና፣ ጨለምተኝነት፣ ፍርሃት፣ ሙስና እና ጥላቻን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅለን መጣል እንችላለን። ቅን ልቦና ይኑረን! ለዘመናት የተጫነንን ሸክማችንንም እናራግፍ። ያኔ ለፍቅር በፍቅር፣ ለሰላም በሰላም፣ ለነጻነት በነጻነት፣ ለአንድነታችን በአንድነት የምንሰራበትና ታሪክ ዘካሪ ብቻ ሳንሆን ታሪክ ሰሪ የምንሆንበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም።

 

ቸር እንሰንብት!

comment picያሬድ ኃይለማርያም
ከብራስልስ

http://humanrightsinethiopia.wordpress.com/     

የታሪክ ክህደት በማንዴላ የስንብት ፆሎት ላይ ሲደገም!! (አንተነህ ሽፈራው)

$
0
0

አንተነህ ሽፈራው – ታህሳስ 9/2006 ዓ.ም/Dec 18, 2013
comment picበኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት አገሮች ሁለንተናዊ ከፍተኛ ድጋፍ የወያኔ የጎጠኝነት ወታደራዊ ክንድ በመፈርጠሙና በኋላም በመንገድ መሪነት የወሎን፣ የጎንደርንና የጎጃምን ሕዝብ ትጥቅ ያለ ብዙ ወጣ ውረድ በማስፈታት ባገለገሉ በነ ታምራት ላይኔ ተዋናኝነት ወያኔ መላ አገሪቷን በግንቦት 1983 ዓ.ም በዚሁ ወታደራዊ ክንዱ መውረር መቻሉን ተከትሎ በተፈጠረው አዲስ ዓይነት የጎሣ/የቋንቋ/ ፖለቲካ አደረጃጀት እነ ሆድ- ባምላኩ ወዲያው ለዚሁ የወያኔ የጎሣ/የቋንቋ/ ፖለቲካ አደረጃጀት ሴራ ሰለባ በመሆን የጋራ ኢትዮጵያዊ ቤታችንን ለማፍረስ ከመሞከር አልፎ እርቆ በመሄድ ወያኔ በጠላትነት/በኢትዮጵያዊነት የፈረጀውን የሕብረተስብ ክፍል ለያቶ በመግደልና በማፈናቀል በታሪክ፣ በትውልድና በሕግ ፊት የሚያስጠይቅ ተደጋጋሚ ወንጀል እየፈጸሙ መሆናቸውን ላለፉት 23 ረጅም የመከራ ዓመታት በግልፅ እያየን ነው:: –- ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ—-

Download (PDF, 565KB)

የቀበጠ ቀን፤ የአቅል ማጥ –ዳጥ፤ –በስንጥቅ። (ከሥርጉተ ሥላሴ )

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 19.12.2013
ገርሞኝ! … ሲያንስ …. መገረም …. ም …. እም! ህም!
ጠ/ር ኃይለማርያም ደስአለኝ ያላግጠሉ …
 

sreate1ወይ መዳህኒተ – ዓለም አባቴ … እንዴትና እንዴት ነው ነገሩ? የዓለም ህዝብ በደቡብ አፍሪካ ህዝባዊ አደባባይ የማህሪ ተምሳሌት የሆኑትን የሰላም ልዑቁን ኔልሰን ማንዴላን አክብሮታዊ ዝክረ በተምስጦ ጉባዔ ከወነ። 60000 ነፍስ በአካል ስቴዲዮም ላይ፤  በቴሌቪዥንና በራዲዮ ደግሞ ቪሊዮኖች ታደሙ። ከ100 ሀገሮች በላይ መሪዎቻቸውን ሆነ ውክል አካላቸውን ልከው ሀገሮች ማዕደኛ ሆኑ። በዕለቱ ዬይበቃኛሉን ልዑል የኔልሰንን በተግባር የተባውን፤ በድርጊት የፈለቀውን የህይወት ዘመናት በምልሰት በመቃኘት ሰላም ወዳድ ቤተሰብ ሁሉ ዕንባውን ሲራጭ፤ ልብ በሚናካ ስሜት ውስጡን ሲጋራ፤ የኢትዮጵያ ቴሊቪዥን ኢቲቪ ግን በሁለት ደቂቃ የውክልና ተራ ሪፖርት አጠናቆ የወጣቶች፤ ህብረ – ትርዒት እያለ ሲደልቅ ኢትዮጵያ የዓለም፤ የአፍሪካ አካልነቷ እስኪያጠራጥር ድረስ የቀበጠ ቀን የአቅል ስንጥቅ በዳጥ ሲተራመስ አዬን፤ ሰማን። ትዝብት ነው። ኢቲቪ ከሰረ …

 

… ውሎ አድሮ  ግን የለበጣ ጨዋታ ተጀማመረ፤ የሃዘን ቀናት ተባለ፤ አለፍ ተብሎም አፍር ለማልበስ በ15.12.2013 ጠ/ሚር ኃይለማርያም ዓይናቸውን በጥሬጬው አሽተው ኩኑ ላይ ተገኙ። በትርጉም ማቃናት ስለማይቻል ገጠመኙን በሰባራ ገሉ፤ ልብጥ የሄሮድስ መለስ ሌጋሲ ተብሎ ቢወራረድ ይሻል ይመስለኛል – ሸንጣራ። ከዚህም በተጨማሪ የወያኔ ደጋፊዎችም ዓለም ለታላቁ የነፃነት አባት የሰጠውን ልዩ አክብሮታዊ ዕውቅና ሲያጣጥሉና ሲያወራጫቸው ነበር የሰነባበተው …. የተበደሉ። …. በቅናት አረሩ – ደበኑ – ትክን ብለውም ተኮመታተሩ ….. የእነሱ መለመላ እንዴት እንደተሰናበቱ ያውቁታልና ….

 

እንደሚታወቀው በቀደምቶቹ ደጋጎች፤ በተግባር አዛውንታት መሪዎቻችን ኢትዮጵያ በፓን አፍረካኒስትነት እንቅስቃሴ፤ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት በዛሬው ህብረት ምስረታ፤ በተባበሩት ዓለምዐቀፍ ድርጅት፤ በስፖርት አህጉራዊና ዓለምዓቀፍ ፌድሬሽኖች፤ በዓለም ዐቀፍ የውርስ ቅርስ ቤተኝነትም ሳይቀር በሁሉም ትርጉም ያለው ተግባርን የከወነች አንቱ ሆና፤ አስተውሉ አንቱ ሆና፤ በዘመነ ዱድማ ወያኔ ግን ጭራ መሆኗ ሲገርመኝ ውሎ አደረ ….. ያን ቀን ዓለምን የአስከፋ የዕንባ ቀን ሆኖ ህብረት ትርዒቱ በአፍሪካ መዲና አዲስ አባባ ላይ ቅልጥ ቅብጥ ሲል ማዬት ለትውልደ ኢትዮጵውያን ሃሞት ነበር። እነዚህ ጉዶች እኮ ሁለመናችን ነው ፍቅፍቅ እያደረጉት ነው ያሉት ….

 

ህም! … ኢትዮጵያ ሀገራችን የነፃነት ትርጉም ያገባት ቀደምት አብነታዊት ሀገር በመሆኗ፤ ለመላ አፍሪካ የነፃነት ትግል የደም ጋን ልብ ነበረች። ኢትዮጵያ ለአህጉራችን ለአፍሪካ አርነታዊ እንቅስቃሴ መሪና ረኛም ነበረች። ኢትዮጵያ ነፃነትን የታረቡ ነፍሳትን በእቅፏ ውስጥ በማድረግ ከእቅሟ በላይ የመስዋዕትነቱን ቀንበር የተሸከመች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ነፃ ሀገር ነበረች። ኢትዮጵያ ያን ፈታኝ ኃላፊነት ወዳና ፈቅዳ በመውሰድ ከቅኝ ገዢዎች ዴፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ ሳይቆስል ወይንም ሳንክ ሳይፈጠር፤ ግን በጥበብና በብልህነት መስጥራ አህጉሯን ከቅኝ ግዛትና ከአፓርታይድ ሰላባ የታደገች ልዩ ቅዱስ መንፈስ ነበረች። ውለታው ማገርነት፤ ምሰሶነት ለጥቁር አርማነት፤ ዓዕምድነቷ ለሰብዕዊ መብት መከበር ቀደምትነት – ለህጉራችን ለአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለዛሬዎቹ ዓለምዓቀፉ ሰብዕዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች ሁለመና ብሩህ ተስፋን የዛራና ያዘመረ ነበር። በዛ ደግ ዘመን ኢትዮጵያ ሥራቸውን አቃለለችላቸው፤ ሸክማቸውን አራገፈችላቸው ለአምንስቲ በሉት ለቀይ መስቀል። ህማማቸውን ቀድማ ፈወሰችላቸው። ትናንት ። መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ ለእኛ ፍቅር እራሱን ሰጠ። ኢትዮጵያ ለአፍሪካዊነት ክብር እራሷን የሰጠች የነፃነት መዳህኒት ሀገር ነበረች …. ዛሬን ተውት … እሷም ህማማት ላይ ናትና ….

 

ይህን ለሚያውቅ ዘርና ግንድ፤ የዛሬው ታሪክን በሁሉም መስክ ትቢያ ለማልበስ ወያኔ ለሚያደረገውን የታቀደ ደባ ለሚመዝን ህሊና፤ የሽፍታውን እስተዳደር የቋሳ ዓላማ ሆድ እቃ መፈተሽ፤ ሌላ ማገናዘቢያ ሳይስፈልገው ብዙም ሳይደክም ጠንቅቆ ማወቅ ይችላል። ለአደባባዩ የሃዘን ቀን ሀገራችን በባይታውርነት ብቻውን ተንጠልጥላ ተነጥላ ቀረች። ይሁን ተብሎ … ያው እንድትሰረዝ፤ ክብሯም እንዲቀበር፤ ተፈሪነቷም ማቅ እንዲለብስ ተፈርዶባታልና ብጣቂ አትኩሮት ሳይሰጥ የዓለም ሀገሮች ሁሉ በቂ ሽፋን በመስጠት የጥቁር ዕንቁ የስንብት ሳምንታትን በተደሞና በአርምሞ በአኃቲ ድምጽ ከወነ። የአፍሪካ የነፃነት ዓርማዋ ውክል አካል ደግሞ ክብሯን ለመሸጥና ለመለወጥ ሱዳን ላይ አታሞ ሲደልቁ ነበር። ዳር ድንበሯን በስጦታ ለመለገስ ሱዳን ላይ ጠብ እርግፍ ይሉ ነበር ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደስአለኝ። ከእሳቸው የተጠጋ ቅብዐ የማረት ጉድ – ሥጦ። አቅምና ችሎታው የኢትዮጵያዊነት ሚስጢር ለመተርጎም በፍጹም ሁኔታ አለመጠኑን ከዚህ በላይ ማስረጃ ማቅረብ የሚቻል አይመስለኝም። የሰሞናቱ ሂደት ማንነታችን እንድናመሳጥር ግድ ይለን ስለነበር በትዝብት ሁኔታውን ስንከታታል ደግሞ አይታፈር …. ቀብር ላይ እገኛለሁ ብለው ዱቅ! …. የቀበጠ ቀን አቅሉ ሲሰነጠቅ፤ …. ማጥ ዳጥ  … በወያኔ ሽቦ ቱቦ፤

 

አሁን በሞቴ ወያኔ መራሹ አስተዳደር በምን ሞራሉ ነው በነፃነት አባት ቀብር ላይ ተገኝቶ ስለ ነፃነት የሚሰብከው። ማላገጥ ነው። የዛሬው ማንዴላ እኮ በአሸባሪነት የክስ መዝገብ የሚታወቁት የትግል መስመር እኮ ነው የኛዎቹ እነ በቀለ፤ እነ እስክንድር፤ እነ ውብሸት፤ እነ አንዷዓለም እነ በላይነሽ እነ ርዕዮት ቁጥር የለሽና ስምዬለሽ ሺዎች በካቴና የሚታመስቡት …። አሁን እነሱን በእግር ብረት የቆለፈ አንደበት በምን ሞራል? በምን አቅም? በምን ስሌት? በምን ሜትር? በምን አንደበት? በምን ህሊና? ነው በሰላም – በፍቅር – በነፃነት ወዳድ ህዝብ መሃከል መናገር የሚችለው? …. ይችላል? የቀበጠ ቀን አቅሉ ሲሰነጠቅ በዳጥ ሲያምጥ!

 

በወ/ሮ /ት ባርባራ የተመራው የአውሮፓ ኮሚሽን እስረኞችን ለማዬት እንኳን ሳይፈቀደለት ተስፋውን ምች አስመትቶ የሸኘ ደኛ አስተዳደር እንዴት ብሎ ነው አፉን ሞልቶ  „ …. አፍሪካ ከማንዴላ ብዙ አግኝታለች። የማንዴላ ህይወት በትግል ውጣ ውረድ የተሞላ ቢሆንም አርያነታቸው የነፃነት የፍትህ የእኩልነትና ነው። የማንዴላን የፍትህና የነፃነት ትግል ከምንም በላይ ደግሞ የሰብዕዊ ክብርን በመጎናጸፍ በክፋት ላይ ያሸናፊነት ተስፋን መፈንጠቅ እንደምንችል ተረድተናል። በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ከዚህ ታላቅ ሰው ሥራዎችን ለመማር በማቻላችን እራሳችንን እድለኛ አድርገን ልንቆጠር ይገባናል።“  በ15.12.2013 ከሰላም እናት ኩኑ ላይ ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደስአለኝ ያደረጉት የለበጣ፤ የማስመሰል፤ የማላገጥ ግልብ፤ እራስን የመዋስና የመበደር ገላጭ ዲስኩር – ተግባር የመከነበት። ማንነታቸው የሾለከባቸው፤ ውስጣቸው እሳቸውን ትቶ ረግረግ የሰመጠባቸው …. ። እራፊ አልባ ሩጫ … መጋጋጫ ….

ለመሆኑ ሰውዬው ከነፍሳቸው ወይንስ ደመ ነፍሳቸውን የትኛው ይሆን ዕጣ ክፍላቸው?! በሺህ የሚቆጠሩ የነፃነት ወገኖችን ያፈነ – ያሳደደ – የገፋ – ያሰረ – የገደለ፤ ህፃናትን፤ ቤተ አምልኮዎችን እስከ መሪዎቻቸው፤ አውደ ምህረቶችን እስከ ቅርሶቻቸው በማንአለብኝነት ያጠቃ። ምህረት ያልሰጠ ውርዴ  በምን ዓይነት  ወኔ ነው ለዛውም እንደ ድህነቷ ጎለጎታ የሰላም ምህረት ወላድ በሆነቸው ኩኑ መንደር አንደበቱን ከፍቶ አንድ ቃል መተንፈ የሚቻለው?  ቃር!

 

…. ድፍረት ነው! የምር ድፍረት … „በክፋት ላይ የአሸናፊነት ተስፋን መፈንጠቅ“ ይሉናል ጠ/ሚሩ ምን? ወያኔ እኮ ፍጥረቱ ክፋትና በቀልን የሰነቀ። የጎጥ ድርጅት – መርዝ። „ለመማር በመቻላችን“ ድንቄም … … ኪኪኪ … መሳቂያ   ምንድን ነው እነሱ ከተከበሩት የምህረት አባት የተማሩት … ማፈን? ማሳደድ? ማራድ? ማፍለስ? መግለል? መግደል? መብትን መፍለጥ?ልነትን በግፍ መተርተር?  እኮ! ምንድን ነው? እኮ!  ቀለም ፆታ፤ ዕድሜ፤ ወሰን ሳይለዬው ከሰማይ እስከ ምድር በሶስት ተፈጥሯዊ ጅረቶች ዕንባ ከዘነበላቸው ደግና ማህሪ የሰላም አባት ምንድን ነው የቀሰሙት? ለገዳያቸው ምህረትን በገፍ የቸሩ … የመሆን ለጋስ – የወንጌል አርበኛ እኮ ናቸው ማዲባ!   ይህ ሮ ወያኔ የሚሉት ሙጃ ስለምን? ትንሽ የሚመዝንበት ተፈጥሮ አባቴ መዳህኒተ ዓለም እንደ ነፈገው ግራ ያጋባል …. ለመሆኑ አቶ ኃይለማርያም ቃሉን „ነፃነት፤ ፍትህ፤ እኩልነት“ ያውቁታልን? የመንፈሳቸው እድገት ለእኔ ለሥርጉተ ከእንግዲህ ልጅ ላይ ያለ ይመስለኛል … ለነገሩ እሳቸው በፈቃዳቸው ነፃነታቸውን በጠራራ ፀሐይ የሸጡ – የጥገኝነት ሹመኛ፤ ዬት የሚያውቁትን …. በሶስት ምርኩዝ የሚተክዙ ብን …. ምስል።

 

መቼም የአረብ ሥነ – ጹሑፍ ምርጥ ሆኖ ለዛው ግን ያለ ነው – የውበት ፍልሰት የሚዋኝበት። ስለምን? ይሉኝታ ስለነጠፈበት። የወያኔው መራሹ ጠ/ሚር ቃናቸው የተላመጠ አገዳ ነው የሆነው፤ ይሉኝታው የተጣበቀ። ሰብዕዊ መብት በኢትዮጵያ ቀራኒዮ ላይ ሆኖ እሳቸው ግን በቅዠት ይዋዥቃሉ፤ ለመሆኑ ሰውዬው እያሉኑ ወይንስ …. እዬለሉ …. እንዲህ የጠቆረ ኪኖ በዬጊዜው ጎብኙ እያሉ ልባቸነን የሚያፈሱት …. የቋሳ ዳንኪረኛ!

 

ልሰብስበው … ጥምልምሉና ጥውልውሉ ንግግር ገመናን በአደባባይ ማወጁ አንገት የሚያስደፋ በመሆኑ እፍረትን ለሸመቱት ጠቅላይ ሚ/ር ወጣ ገቡ ብቃት አዳለጠው – ኩኑ ላይ። አይሆኑ ሆኖም እንኩትኩት ብሎ ኩኑ ላይ ደቀቀ። ከራባቱም ብላሽ ገበርዲኑም ከንቱነት ዘፈነበት።

 

ጌጦቼ … ቆይታችን ህመምን የነካካ ቢሆንም ፈቅዳችሁ መንፈሳችሁን ለሸለማችሁኝ አንባቢዎቼ ሁሉ ለጥ ብዬ በትህትና ምስጋና አቀረብኩ። መልካም ሰንበት።

 

አረም የጨፈረበት መንፈስ ሲቀበር ተባይ የለማበት ውስጥ ይጋለጣል።

 

 

አግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 

 

በህወሓት/ወያኔ መቃብር ላይ ብቻ ኢትዮጵያ በሰላምና በብልጽግና ትኖራለች!

$
0
0

አበራ ሽፈራው/ ከጀርመን/

comment picየኢትዮጵያ ህዝብ ማናቸውም መብቶቹ ተነፍጎ የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ ላይ እንገኛለን:: የህዝቡ የሰብዓዊ መብቶችበየትኛውም ዓለም በማይገኝ መልኩ ይጨፈለቃል ለዚህ ያበቃን ደግሞ ትልቁ ምክንያት የህወሓት/ወያኔን የወንበዴነት ጭካኔ ለመጋፈጥ ያለመፈለጋችን ወይም የጭካኔያቸውን መጠን የሚቋቋም ትግል ባለመኖሩና መስዋዕትነትን ለመክፈል ባለመቁረጣችን የመጣብን መከራ እንጂ ህወሓት/ወያኔ ምንም ስለሆነ አይደለም::  የተቃራነውን ጎራ የልብ ትርታ የተረዳው ህወሓት/ወያኔ ሲፈልገው ይገድላል፣ያስራል፣ ያዋክባል፣መሬትንና ንብረትን በሠበብ አስባቡ ይነጥቃል፣ ከስራ ያባርራል፣ የትምህርትና ሌሎች መብቶችን ገፎ ለመከራ ይዳርጋል ካልሆነም ከአገር ማሳደድን እንደትልቅ አማራጭ ተያይዞታል::

በኢትዮጵያ የመኖር መብት እንዳለንና አገራችን መሆኑን እያወቀ መብቶቻችንን የነፈገን ህወሓት/ወያኔ በማን አለብኝነት መቀጠላቸውን ይሁን ብለን ተቀብለን እኛም መስማማታችን ለዛሬው የባሰበት ችግር አድርጎናል:: እነሱ አገራችን አይደለችም ብለው በሚበዘብዟት አገር ላይ ተንደላቀው እየኖሩ ኢትዮጵያ አገሬ የሚሏት እየተዋከቡ ለችግርና ለመከራ መዳረጋችን እጅግ ያሳዝናል:: አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ለውጥ ልታመጣ የምትችለው ህወሓት/ወያኔ ይዞት ከተነሳው  አገርን የማጥፋት እኩይ ተግባሩና አስተሳሰቦቹ ጋር ወደመቃብር ሲወርድ ብቻ ነው :: ህዝቡም ጨክኖ ለዚህ እውነት ሲነሳ ብቻ ነው::

ከመቼውም ጊዜያት በላይ ህዝባችንና አገራችን ለከፍተኛ ውርደት የተጋለጥንበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል:: በሃገራችን መኖር አልቻልንም፣ በሃገራችን ጉዳይ ላይ መወሰን አልቻልንም ፣በሃገራችን ላይ የበይ ተመልካች ሆነን እንገኛለን፣ በህወሓት/ወያኔ ቀኝ ገዥነት ህዝባችንና አገራችን ለከፍተኛ ብዝበዛ ተጋልጠናል፣ በከፍተኛ ሁኔታ በታጠቁ የህወሓት/ወያኔ በዝባዞች ቁጥጥር ውስጥ ወድቀናል፣ ከፍተኛ ህዝብ ከረሃብ አልፎ ለከፍተኛ ጠኔ ተጋልጦ ይገኛል፣ ይህ አልበቃ ብሎ የአገሪቷ ህዝብ ወደ ውጭ ወጥቶ እንኳን እንዳይሰራ ለከፍተኛ ውርደት ተዳርጎ ማንም እንደፈለገው የሚያደርገውና ተከላካይ የሌለው በዓለማችን ላይ የሚገኝ ህዝብ ለመሆን በቅተናል::

ህዝቡ በአገር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጦ ማንም እንደፈለግ የሚጫወትበት ህዝብ ከመሆኑም በላይ በየትኛውም ነገሩ ላይ ሃይማኖታዊ ጉዳዮቹን ጨምሮ በፈለገው መልኩ እንዳያከናውን መደረጉ ይታወቃል:: ከዚህም አልፎ ደግሞ የአገሪቷ መሬት በተለያዩ ጊዜያት ለተለይዩ ጎረቤት አገራትና ሃይሎች በመስጠትና በማካለል ትልቅ የታሪክ ውርደት ገጥሞናል:: ኢትዮጵያ መቼም ባልታየ መልኩ ለትልቅ ችግር ተጋልጣለች:: ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ትልቅ መስዋእትነትን የሚጠይቅ ትግል ከፊታችን ተጋርጦብናል ይኸውም በህወሓት መቃብር ላይ አገራችንን እንደገና ለማከም የሚያስገድድ ሁኔታ ገጥሞናል:: የህዝብ መብት ጉዳይ ሲነሳ ግድያ፣እስራትና ሞት ሆኗል እጣችን የአገሪቷን ወሰን ለማስጠበቅ የተወሰደው እርምጃም ምንም ባለመሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያ መሬቷንና የግዛት ክልሎቿን እየተነተቀጭ ትገናለች::

በአባቶቻችን ተከብረው የነበሩ ድንበሮችን አሳልፎ ለመስጠት ዛሬ ለሱዳንና ለኤርትራም ጭምር እንደፈለገ የሚደራደረው ህወሓት/ወያኔ ገና ያልጨረሳቸው ኢትዮጵያን የማጥፋት አላማዎቹ አላለቁም እና እንዲሁም ቀደምት ወራሪዎቻችን  የፈለጉትን መሬት አባቶቻችን በትግላቸው ያቆዩትን አገር በባንዳዎች በእጅ አዙር ለማግኘት እየጣሩ መሆኑና ለዚህም ተፈጻሚነት ደግሞ የህወሓት/ወያኔ የባንዳ ቡድን ሃላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑን ስንመለከት ያሳዝናል::

የእነዚህ ባንዳዎች አስተሳሰባቸው እና ድርጊታቸው በኢትዮጵያ ላይ መቀጠሉ እንዲያበቃ ዛሬ በህብረት ሆ ብለን መነሳት ካልቻልን ተግባራቸውም ከመፈጸም ሊያቆሙ የሚችሉ አይደሉም :: ህወሓት/ወያኔን ለማሸነፍ ሰዎች የተለያዩ የትግል አማራጮች አዋጭ ናቸው ብለው ባሰቡበት መንገድ ሊሄዱ ይችላሉ፣ ይሁንና አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ግን ህወሓት/ወያኔን በሰላማዊ ትግል እናሸንፋለን ለሚሉ ትግሉ ተገቢ ውጤት እንዲያመጣ ከተፈለገ ትግሉን ማቀጣጠልና በአጭር ጊዜ ወደውጤት እንዲመጣ ማድረግ ወይም ትግሉን ትቶ መውጣት ሌላኛው አማራጭ ይሆናል :: ምክንያቱም ህወሓት/ወያኔ በናንተ ስም የኢትዮጵያን ህዝብ እያታለለና ብልጭ ድርግም በሚለው የሰላማዊ ትግል ውስጥ አማራጭ እየመሰላችሁ እየገባችሁ የህዝቡን ተስፋ ሟሟጠጥና ከትግል ማራቅ በፍጹም አዋጭ የትግል ሥልት እንዳልሆነ ሁላችንንም እንረዳለን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ ህወሓት/ወያኔ በአገሪቷ ታሪክ ውስጥ የፈጠራቸው ዘርን ከማጥፋት ጀምሮ እስከግለሰቦችና ቡድኖች ጭምር ለወሰዳቸው ግፎች  የሚፈለግ ቡድን ከመሆኑም በላይ በትግራይ ህዝብ ሳይቀር በተለያዩ ቡድኖችና ግለሰቦች የሚፈለጉ ሰዎች ስብስብ በመሆኑ ሰላማዊ ሽግግርን ይፈልጋሉ ብሎ ማሰብ በፍጹም የሚታሰብ አይደለምና ነው::

ለዚህም ምስክር ይሆን ዘንድ በቅርቡ በራያ በተደረገው ስብሰባ ለአቶ አብርሃ አንድ ተሰብሳቢ ያቀረቡላቸውን ጥያቄ መስማት ብቻ ይበቃል እሱም ህወሃት የሽፍታ ቡድን መሆኑን እና ከእነሱ የሚያላቅቋቸው መሆኑን በጥያቄ መልክ ማቅረባቸውን “ሽፍታ” ማለት ደግሞ ምን ማለት እንደሆነ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ የሚታወቅ በመሆኑ ነው::

 

ይህ ብቻ አይደለም በተለያዩ ጊዜያት አገርን በመክዳትና የአገሪቷንና የህዝቦቿን ጥቅሞች አሳልፎ በመስጠትም የሚፈለጉ ከመሆናቸውም በላይ በሠብዓዊ መብት ረገጣ በኩል አሁን ህወሓት/ወያኔን የሚመሩ ሃይሎች በአገራችን ውስጥ የተፈጸሙ የጅምላ ጭፍጨፋዎችን በማቀድ፣ በመተግበርና በማስተግበር በከፍተኛ ሁኔታ በአገር ውስጥና በውጭ ሃገራት የህግ አካላት እንደሚፈለጉ ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆናቸውም ጭምር ነው::

ስለሆነም ይህ ችግራቸው ሊያመጣባቸው የሚችለውን አደጋ በማየት አገሪቷን ለመከላከል ሳይሆን ይህንን የራሳቸውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችላቸውን ሁሉ ለማድረግ እንደቆረጡና ይህንን ችግራቸውን ሊያቃልልላቸው የሚችልን ካልሆነም ጊዜ ሊያራዝምላቸው የሚችልን ሁኔታን ለመፍጠር ሲባል ማናቸውንም የአገሪቷን ጥቅሞች አሳልፈው ለመስጠት መቁረጣቸውን በቀላሉ መረዳት እንችላለን፣ በምንም መለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆኑ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ከሚወስዱት አረመኔያዊ እርምጃ ልንመለከታቸው እንችላለን::

 

ከሁሉም በላይ ህወሓት/ወያኔ በተለያዩ ሰዓት የሚቀብራቸው በአንድ ወቅትና ወይም በተለያዩ ጊዜያት ሊፈነዱ የሚችሉ እምቅ ችግሮች በአገራችን ህዝቦች መካከል የፈጠራቸው እንዳሉ ሆነው አሁን ደግሞ ከጎረቤት አገራት በተለይም ከሱዳን ጋር ድንበር ለማካለል በሚል በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ተጠንሥሶ የነበረውና አብሮት ያልተቀበረው አስተሳሰቡ ዛሬ በቀሪዎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሊተገበር ከፍ ዝቅ እያሉ ያሉበት ጊዜ በመሆኑና በሌላ በኩል ከህወሓት/ወያኔ ማንነትና ይዞት ከተነሳው ዓላማው አንጻር ህወሓት/ወያኔ ሲፈልግ ኢትዮጵያዊ ይሆናል ሳይፈልግ ደግሞ ታላቋ ትግራይ ይሆናል  ስለሆነም ለመሆኑ የማንን መሬት ነው ህወሓት/ወያኔ የሚደራደርበት ? ህዝቦች ለተወሰነ ጊዜ ሊጨቆኑ ይችሉ ይሆናል ሁል ግዜ ግን እየተጨቆኑ ይኖራሉ ማለት ግን እንዳልሆነ አውቆ መረዳት ያልፈለገው ህወሓት/ወያኔ እራሱ ላይ ትልቅ ችግርን ሊያመጣ መቃረቡን በትክክል መገመት ይቻላል::

ህወሓት/ወያኔ በምንም መለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆነና ኢትዮጵያዊነት ምኑም እንዳልሆነ የራሱ ታሪክ ያሳየናል:: ለዚህም ማስረጃ ለታላቋ ትግራይ ሲሆን አሰብ ይካለላል ለኢትዮጵያ ሲሆን አሰብ የኤርትራ ይሆናል ፣ ለህወሓት/ወያኔ ሲሆን ህገመንግስት ይጣሳል ለህዝብ ጥቅም ሲሆን ይኸው ህገመንግስት እንደፈለገ ይተረጎማል፣ የኢትዮጵያውያን ደም በሳውዲ ሲፈስ ህገወጥ ያሰኛል ለዚሁ ሰብዓዊ ግፍ ካሳን ከሳውዲ መጥየቅ ሲግባ 360 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት እቅዶች ለሳውዲዎች ያሸልማል፣ በኢትዮጵያ ላይ የመበታተን አደጋ ስትፈጥር የነበረችው ሱዳን በአምላክ እጅ መልሷን አግኝታ ስትበታተንና ደረቅ መሬቷን ስትታቀፍ ለህወሓት በታታኝ ቡድን ላደረገችው አስተዋጾ ከ1200 ኪ. ሜ በላይ በሚሸፍን መሬት ላይ እስከ 50 ኪ.ሜ ወደ ውስጥ የሚገባን መሬት ለመስጠት ሲሆን ሽንጡን ገትሮ ህወሓት/ወያኔ ሲንቀሳቀስ ምን ይባላል ? ህዝብን የሚያሸብርና ሽብርተኛ እራሱ ህወሓት/ወያኔ ሆኖ ሳለ የህዝብ ወገኖች የሆኑ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ታጋዮች ምንም ትጥቅ ሳይኖራቸው በሽብርተኝነት እየተፈረጁ በየዕስር ቤቶች የሚንገላቱ ለመሆን በቅተዋል::

በአጠቃላይ ህወሓት/ወያኔ የኢትዮጵያዊነት መለኪያም ሆነ ተግባር የሌላቸው ህይሎች ስብስብ የሆነና በኢትዮጵያውያን ደምና ላብ የራሳቸውን የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነት ጥማት ለማርካት በቋመጡ  ሃይሎች የተዋቀረ ቡድን በመሆኑና ይህንን የማፍያ ቡድንን እኩይ ተግባርን ለማገዝ በነዚሁ ዘረኞች በተዋቀረ ሠራዊት እየታገዙ አገራችንን ይዘው ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናልና አገራችንን ለማዳን መቁረጥ ይኖርብናል:: ማንም ሊረዳን አይችልም ትግላችን ወደፊት ሲገፋ ግን ብዙዎች አቋማቸውን አስተካከለው ከኢትዮጵያውያን ጋር ይወግናሉ:: ምክንያቱም አገራችን በህወሓት/ወያኔዎች የባንዳ ሃይሎች ብቻ ሳይሆን በታሪካዊ ጠላቶችችንም እጅ ስር በመውደቃችንም ጭምር ነውና ::

ህወሓት/ወያኔ በወልቃይት ጥገዴ ህዝብ ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሰላም የተጠናቀቀ መስሎት ከሆነ ተሳስቷል:: የወልቃይት ጠግዴ ህዝብ፣ የሲዳሞ ህዝብ፣ የጋምቤላ ህዝብም ሆነ ሌሎች የህወሓት/ወያኔ የጅምላ ጭፍጨፋ ተጠቂዎች ሁሉ እንዳልተሸነፉ መታወቅ ይኖርበታል በእርግጥ መከራቸው ሁሌም የሚያደማ ቢሆንም :: ይልቁንም ህወሓት/ወያኔ አሁንም ሆነ ለወደፊትም ቢሆን በህዝብና በታሪክ ፊት በፍርድ ፊት ሊሆን የቀረበበት ጊዜ ነው:: ህወሓት/ወያኔ የሚቀብራቸው ፈንጂዎች ምን አልባትም በመጀመሪያ የሚያጠፉት እራሱን ህወሓትን/ወያኔን እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ:: ምክንያቱም ለህዝቦች መከፋፈልና እልቂት የቀበራቸው ፈንጂዎች አቅጣጫቸውን ወደ እራሱ  ወደ ህወሓት/ወያኔ እያደረጉ በመሆኑም ጭምር ነው:: ህወሓት/ወያኔና ባለሟሎቹ የኢህአዴግን ስም ተከናንበውና ተሸፋፍነው በህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ደባ ለማስቆም በሚደረገው ትግል ውስጥ ተሳትፎአችንን እናጠናክር በህወሓት/ወያኔ መቃብርም ላይ አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ እንመስርት:: ካልሆነ ህወሓት/ወያኔ አገሪቷን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊበታትናት መቁረጡን ከድርጊቱ መመልከት እንችላለን:: ቸር ይግጠመን::

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

 

http://aberashiferaw.wordpress.com/

የህወሃት አፓርታይድ አገዛዝና የተቃዋሚ ኃይሎች !! (በጌታቸው)

$
0
0

በጌታቸው   

«ጅብ እንደ አገሩ ይጮሃል» እንዲሉ ዘፋኝ ስለሀገር ስለራሱ ውስጣዊ ስሜት ስለ ፍቅረኛው ስለቤተሰቡ ስለጓደኞቹና ስለሚታየው ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታ ይዘፍናል።ፖለቲከኛውም ስለ ወቅቱ ስለአለፈው የፖለቲካ ጉዳይ ስለሥልጣን ማጣትና ስልጣን መያዝ፤ ስለጨካኝ አገዛዝ ስለፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ይተርካል። ሁሉም እንደ ሙያውና አሰላለፉ ያለፈውንና የሚመጣውን ይተነብያል። እኔም ካለፈው የተመለከትኩትንና አሁን እጅ ላይ ያለውን ሁኔታ ስመለከት ወደ ፊት ምን ይመጣ ይሆን በማለት የራሴንና የሀገሬን የኢትዮጵያ ተስፋ  በሚመለከት ሀሳቤን ብሰነዝርስ ብየ አሰብኩ።

በአጭሩ ለማስቀመጥ በዘውዳዊ አገዛዝ የመጨረሻ ዘመን አካባቢ  በነበረው ቀርፋፋ የፖለቲካ አያያዝ ምክንያት ተሸፍነው ሊታለፉ የማይችሉ በርከት ያሉ የሀገር ችግሮች በአደባባይ ላይ መውጣታቸው የግድ ሆነና ንጉሠ ነገሥቱንና ካቢኔያቸውን ከሥልጣን ገበታ ጠራርጎ የሚጥለው ሕዝባዊ ንቅናቄ በ1966ዓ/ም ወርሃ የካቲት ከዳር እስከዳር አስተጋባ። አንዳንድ ድርጅቶች ከዚያ በፊት ተደራጅተን ነበር ይበሉ እንጅ የሕዝቡን ትግል አደራጅቶ የሚመራውና ወደሚፈለገው ግብ እንዲጓዝ ለማድረግ ባለመቻሉ አንዳቸውም የሕዝብ ጥያቄዎች ሳይመለሱ ያልታሰበ ኃይል ወደ ሥልጣን ገበታው ብቅ አለ።ገብቶንም ይሁን ሳይገባን የመጣውን አዲስ ገዥ መደብ ተቃወምን ደገፍን ሥልጣን ያማራቸው ደርግ ብቻውን ጠቅልሎ ይዞ አላካፍልም አለ በለስ ሳይቀናቸው ሲቀር ወደ አመፃዊ ትግል ገቡ አልተሳካም። ቀስ ብለው በጓዳ የገቡትም ወደ ደርጉ አዳራሽ ብቅ ቢሉና ሰነድ መሸጥ ቢጀምሩም ያችን ሥልጣን ደርግ ሊያቀምስ አልቻለም።ደርግ ግራ ተጋብቶ ነበር ቢባል ስህተት እንደማይሆን የሚያሳዩ ሁኔታዎች ነበሩ፦ ደርግን ወደ ሥልጣን ያመጣው የዝቅተኛው የወታደራዊ መኮንኖች ውስጣዊ ትግል ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ የተቀጣጠለው የሕዝብ አሻፈረኝ ባይነት ሆኖ ሳለ እነዚህን ጥያቄዎች ወደጎን በማድረግ ሥልጣኑን የማመቻቸት ትኩሳቱ ላይ ተጠመደ። ሌላው በሁሉም በር መግባት የሚቻልበት ቤት ሲገኝ የተነሳውን የተለያየ ምክንያት ያዘለና ተልዕኮ ያለውን ፖለቲካዊ ተቃውሞ ወይም ራሱን ደርግን ተቃውመው የተደራጁትን ድርጅቶች ጥያቄ በፖለቲካዊ አግባብ ሊፈታ ባለመቻሉ የተቃዋሚው ኃይል እየበረከተ ሄደ። የተቃዋሚ ኃይሎች በሦስት መስመር የተሰለፉ ሆነው አንዳንዴ እርስ በርሳቸው እየተባሉ ደርግ የተወሰነ እፎይታ ያግኝ እንጅ ከአካባቢ አገሮች ወረራ ጋር ተዳምሮ 17ቱ የደርግ የሥልጣን ዘመን ሕዝብን የሀገርን ኢኮኖሚ ያወደመና መጨረሻው የከፋ አወዳደቅ የወደቀ ደርግ ነበር። ሻእቢያ ለመገንጠል እንደ ነዳጅ የሚያገለግለውን ህወሃትን በማጠናከር አሳደገ ፤ ህወሃት ደግሞ በሻእቢያ ሰርጎ ገቦች እየታጀበ ከጌታው ሻእቢያ የሚወርድለትን ትእዛዝ ለማቀላጠፍና ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ታማኞችን በመመልመል ማደራጀቱን ቀጠለ።እንደሚታወቀው ኢህአፓ በኤርትራ ጉዳይ ግልጽ አቋም ሳይኖረው የዘለቀው በኢሳይያስ አፈወርቂ ማስፈራራት ብቻ አልነበረም።በራሱ በኢህአፓ ውስጥ የፖሊትና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና የአመራሩን ሚና ይጫወቱ የነበሩት ኤርትራውያንና ትግራውያን እንደነበሩ ግልጽ ነው።አሁንም ኢህአፓ ነባር አባሎቹን አሰባስቦ የተወሰነ ድንጋይ እንኳን እንዳይወረውር ገትተው የያዙት እነዚሁ የኤርትራና ትግራይ ትውልድ ያላቸው የሻእቢያን ይሁን የህወሃትን ዓላማ ለማሳካት በስመ ታጋይ ኢህአፓ ውስጥ በመግባት ኢህአፓን የበተኑ የኢትዮጵያ አንድነት ሊንኮላሽና የመገንጠሉ ፍላጎት ግቡን ሊመታ የሚችለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖትና አማራው ሲመቱ ነው በሚል ዓላማ ላይ አነጣጥረው የተነሱ እንደነበሩ መረጃ የሚያስፈልገው አይመስለኝም። ክፍሉ ታደሰ «ያትውልድ በሚል የጻፈውን ማንበብ ከቻላችሁ መረጃ አንድ ይኖራችኋል። መረጃ ሁለት የሪጅን ሦስት(የበለሳው ግንባር)ኢህአፓን ከድቶ ትግራይ ገብቶ በህወሃት ስር ሊወድቅና አሁን የደረሰውን «የቢሔራዊ ውርደት» እንዲሁም ጠቅላላ ሀገራዊ ቀውስ የፈጠረው የኢህዴንን ደባ መመልከት በቂ ነው። ኢህዴን ኢህአፓን እንዲበተን አስተዋጽኦ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን 1/የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ኦህዴድን)፤ 2/ድሮ የስምጥ ሸለቆ አሁን የደቡብ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ደሕዴድ)ና 3/የወታደራዊ መኮንኖች ድርጅት ተብሎ የተደራጀና ቶሎ ብለው ያፈረሱትን የጌታውን የህወሃት ዱላ ፈርቶ እነዚህን ድርጅቶች ለማቋቋም በቤት ሥራ ተጠምዶ ከዚህ ያደረሰ ስንኩልና ቅጥረኛ ድርጅት ሲሆን አሁን ደግሞ (ብአዴን)ብሔራዊ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በማለት ሰፊውን የአማራ ሕዝብ አፍነው የሚገዙ ትውልደ ኤርትራና ትግራይ የሆኑ የአማራውን ሕዝብ ለስደት፤ድህነትና እልቂት ዳርገውት ይገኛሉ።ሰፊው የአማራ ሕዝብ የሌላውን ዛር እየተላበሰ ግንባር ቀደም ለሀገሩ ድንበር መከበር መስዕዋትነት ከመክፈሉ ያለፈ የየትኛውም ሥርዓት ተጠቃሚ እንዳልነበረ በጠላትነት ፈርጀው መጠነ ሰፊ ጥቃት የሰነዘሩበት ድርጅቶች ጠንቅቀው ያውቁታል።ነገር ግን ፀረ ህዝብ ዓላማቸውን ለማሳካት እንዳይችሉ ቀድሞ የሚነሳውና በግንባር ቀደምትነት የሚፋለማቸው ስለሆነ እንፍጀውን አውጀውበታል እየፈጁትም ነው።ለምሳሌ ከአማራው ነገድ ሕዝብ የበቀለው አንዱዓለም አራጌ አንዲት ቅንጣት ታክል ስህተት ፈጽሞ አይደለም የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት የተፈረደበት አንዱዓለም እውነት ነው የተናገረውም እውነትን ነው። እውነትን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ባለመዋሸቱ ታስሯል።ግድ የለም ይታሰር ነገ ይፈታል።ዳሩ ግን በዓለም ከፍ ያለ ዝና ያተረፈችውን ኢትዮጵያ ሀገራችን ለማዋረድ ፤ለመበተን ፤ሀብቷን ለመዝረፍ ትውልዷን ማምከን እንዴት ተወሰነ? በሳውዝ አፍሪካ የተካሄደውን የነጮች በጥቁር ላይ ለዚያውም በራሳቸው ሀገር የአፓርታይድ አገዛዝ «በዓለም ደረጃ ታላቅ ዝና ያተረፉት የነጻነት አርበኛ ኔክሰን ማንዴላን ዜና ረፍት» ምክንያት በማድረግ ዓለም አቀፍ ሜዲያዎች በምስል እያስደገፉ ያቀረቡትን የክቡሩን ሰው የሕይወት ታሪክ ስመለከት በሀገራችን ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ የሆኑ መንፈሳዊና ብሔራዊ ሞራል የሌላቸው ሀሳበ ኩድኩድና ድኻዎች(ጥቁር ጣሊያኖች )በራሳቸው ሕዝብ ላይ የሚያደርሱትን ልክ የለሽ ጨካኝና አረመኔያዊ አገዛዝ ከሳውዝ አፍሪካው ጋር እንዳነጻጽረው ገፋፋኝና ወደ ተነሳሁበት ነጥብ ተመልሸ አሁን የመንግሥታዊ መዋቅሩን የያዘውና በጫካ ሕግ እየገዛ ያለውን ድርጅት ሁለት ካዝና ያለው ተቋም በሚመለከት ጊዜየን ሳላባክን በመደምደም ወደ የተቃዋሚ ኃይሎች በመጠኑ የሚሰማኝን ለማካፈል የሚከተለውን ማስነበብ እወዳለሁ።

ህወሃትን ፦ 1/መንግሥት ማለት አልችልም 2/ ወያኔም አልልም(ኢህአዴግም)ማለት አልችልም መሆን የሚችልበት ወይም በዚህ ስም ለመጥራት አንዱንም ነጥብ ወይም መስፈርት አሟልቶ ስለማይገኝ። ወያኔ የሚለው ከግእዙ ትርጓሜ ሲወሰድ አበየ-አመጸ- እምብኝ አለ ስለሚል ማንም የሚጠቀምበት እንጅ በቅጥረኝነት ለተሰለፈ ቡድን መጠሪያ አይሆንም። ምናልባት የአቶ ተክሌ የሻው የትግራይ ወያኔዎች የሚለው ይመቸኛል።መንግሥት ለማለት የሚከብድበት ምክንያት ይህ ቡድን ተግባሩ የማፊያ እንጅ መንግሥታዊ ባህሪ የለውም በዚህ ቡድን ውስጥ የተሰባሰቡትን ስንመለከትም እዚህ ግቡ የባይባሉ ስነምግባር የሌላቸውና በደም የሰከሩ ሰሞነኞች ስለሆኑ በተለመደው ህወሃት እያልኩ እጠራቸዋለሁ።ኢህአዴግ ለማለት ደግሞ አይቻልም ግንባሩ ወይም ስብስቡ ህወሃት ቁጭ ብድግ ሲያስብለው ቁጭ ብድግ የሚልን ስብስብ ግንባር ብሎ ቢጠራውም በዚህ ስሙ መጥራት አግባብ ሊኖረው አይችልም።

ህወሃት ዘራፊ ድርጅት ነው። በተለያዩ ስሞች እየተጠራ ከዚህ የደረሰው ህወሃት ኢትዮጵያንና አማራን ማጥፋት ብሎ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ የግል፤ የድርጅትና የመንግሥት ተቋሞችን በመዝረፍ የተሰማራ ለመሆኑ አሁንም በዚሁ መንገድ መቀጠሉን ራሱ ተቋሙ ሳያፍር የሚገልፀው ጉዳይ ስለሆነ በዚህ እንተማመንና የሀገር የሆኑ ታላላቅ ተቋሞችን ለትውልድ እንዳይተላለፉ ማውደም ድልድዮችን ግንቦችን ታሪካዊ ቅርሶችን ማፈራረስ ለምሳሌ የዋልድባ ገዳም የመሰሉትን በዶዘር ገብቶ ማረስ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የማይጠበቅ ምግባረ ብልሹ የሆነ ተግባር ነው። የመንግሥት መዋቅርን የተቆጣጠረ ድርጅት አሁንም በዚያ መጥፎና የትግራይን ሕዝብ አልፎ ለሌላውም እልቂት ምክንያት የሆነውን የደደቢቱን ስሙ አለመቀየሩ፤ የገብረሕዮት አክሲዮን ወጋገን ባንክ፤ ጉና የንግድ ድርጅት፤ኤፈርት፤የምናምንቴ ትራንስፖርት …ወዘተ ብሎ የሚጠራቸው ተቋማቅት  የመዝረፊያ ተቋሞች ናቸው።በነዚህ ተቋሞች አማካኝነት የሚዘረፈው የሀገር ሀብት ለሀገር እድገት የሚውል አይደለም።አንድ ምሳሌ እንውሰድና እንመልከት የህወሃቱ ጉና የንግድ ድርጅት ማሽላ ፤ሰሊጥና ጥጥ ይገዛል እንበል የሀገር ባለሀብቶችም እንዲሁ ማሽላ ፤ ሰሊጥና ጥጥ ይገዛሉ።ነገር ግን ይህ የግዥ ወቅት ከመድረሱ በፊት ከላይ እስከ ታች ባለው የህወሃት መዋቅር መመሪያ ተላልፎ ካድሬው የግል ባለሀብቶችን በትዕዛዝ በማገድ ጉና የንግድ ድርጅት ያለ ተወዳዳሪ በሚፈልገው ዋጋ ምርቱን የሚገዛበት ሁኔታ ይመቻቻል።በሥራው የሚሳተፉትም የድርጅቱ አባላት ብቻ ናቸው።ይህ አይነቱ የንግድ ድርጅት በተመሳሳይ በአማራ ክልል አምባሰል ሲኖር በደቡብና በኦሮሞ ክልልም ለጊዜው ስማቸውን ባልይዘውም በዚህ መንገድ በንግድ ሥራ የተደራጁ ተቋሞች አሉ።የሕዝብና የጭነት ማመላለሻ አገልግሎ፤ባንኮች፤በመካናይዝድ የሚያርሱ የእርሻ ድርጅቶች፤በሕዝብ ስም ለድርጅቱ ከውጭና ከሀገር ውስጥ እርዳታ የሚሰበስቡ እንደ ጥረትና ኤፈርት እንደ አልማ የመሰሉ የልማት ማህበር የሚባሉ ሕዝብን ያደኸዩ የመዝረፊያ ተቋሞች ሀገሪቱን ከጫፍ እስከ ጫፍ ጥፍረው ይዘው የሀገር ሀብት ይዘርፋሉ።የሚገርመው ነገር እነዚህ ተቋሞች ከፍተኛ ካፒታል ያላቸው ሲሆን ለሀገር እድገትና ግንባታ የሚውል «የገቢ ግብርና ታክስ የማይከፍሉ »መሆኑና ተዘርፎም ይሁን ተነግዶ የተገኘው ገንዘብ ጥቂቶች ተከፋፍለው የሚጠቀሙበት መሆኑ ነው።»

ህወሃት፦መሞት የሚፈልግ ነገር ግን የሚገድለው ያጣ ድርጅት ነው።ይህ ድርጅት ሥልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ በኃይል የሚተማመንና ጦር በማደራጀት ሕዝቡን አስገድዶ ለመግዛት ወይም በብጥብጥ ሀገር እያመሰ ለመኖር ያሰበ መሪዎቹ በደም የሰከሩና በውስጣቸው ሰላምን ያጡ ሲባንኑ የሚኖሩ ለመሆናቸው እያንዳንዷን የወንጀል ድርጊት አፈጻጸም ወስደን ብንመለከት ያን ተግባር ለመፈጸም የሚያስገድደው ምክንያት ከሕዝብ የተነጠለ ተስፋ ያጣ በውስጡ መተማመን የሌለውና ለመስንበት ሲባል ተመሳሳይ በወንጀል ተግባር የተጨማለቁ ኃላፊዎች ያሉበት ሲሆን ለጥቅሙ ሲል የታጠቀውን የመከላከያ ኃይል ተማምነው የሚኖሩ ናቸው።ለዚህም ነው በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ በየጊዜው የመቀያየር በጡረታና በመሳሰሉት ምክንያቶች ማግለል ኦሮሞውንና አማራውንም በጥርጣሬ ማየት ማሰርና ማባረር የሚስተዋለው

ሀወሃት፦አንድነትን አጥብቆ የሚጠላ በዘረኝነት የተበከለ ድርጅት ነው።አንድ ለአምስት አደረጃጀትን መነሻ አድርገን ብንወስድና 99.6 ድምጽ አግኝቼ ተመርጫለሁ የሚለው ኃይል ውሸቱን እንዴት እንደሚፈበርከው በግልጽ ያሳያል።99.6 ድምጽ ያገኘ ድርጅት በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያገኘ ማለት ነው።አንድ ለአምስት ማለት ደግሞ ከሕዝብ የተነጠለና ሕዝቡን የማያምን የሕዝቡን የየእለት ከእለት እንቅስቃሴን ለመከታተል አንድ ሰው አራቱን በመከታተል ሪፖርት የሚያደርግበት መንገድ ነው ሁለት በጣም የማይቀራረቡና የሚጋጩ ሁኔታዎች። ስለዚህ ድርጅቱ የሕዝብ ድምጽ ሌባ መሆኑን ራሱ የተቀበለ ለመሆኑ ይሰመርበታል።በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ ሀገር ህወሃት በርከት ያለ ገንዘብ በመመደብ እንደ ሽመልስ ከማል የመሰሉ አፈጮሌዎችንና ጮማ ምላስሞችን በማሰማራት የእቁብ ፤ የእድር ፤የሰንበቴ፤የሚካኤል የጊዮርጊስ ወዘተ… እና የመረዳጃ ፤የልማት ማህበራትን ፤ድርጅቶችን፤በቤተክርስቲያትን  በተቃዋሚ ኃይሎች ውስጥ፤በእስልምና ሃይማኖትና በማንኛውም የሕዝብ ስብስብ ውስጥ በመግባት የተጋቡ የአማራ ወንድና የትግሬ ሴትን እስከ ማፋታት የሚሄድ የስለላ መዋቅር ያለው ፀረ-ሕዝብ ድርጅት ሲሆን ዛሬ ሌላ ነገ ሌላ የሚቀላብደው በችግር ውስጥ የሚገኝ ጸረ-ሰላም በመሆኑ ነው።

ህወሃት፦ህወሃት መንፈሳዊ ሞራል  ብሔራዊ ወኔ የሌለው ቅጥረኛ ድርጅት ነው።በኢትዮጵያ የተለያየ እምነት የሚከትሉ እስልምና እና ክርስትና እምነታቸው የሆኑ ለረጅም ጊዜ በመከባበርና በመተባበር ሲኖሩ ይህ ድርጅት ደርግን ከተካበት ቀን ጀምሮ ሌት ከቀን አንዱን በአንዱ ላይ ለማናከስ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም።ሊሳካለት ግን አልቻለም።የቻለው ወይም የተሳካለት ቢኖር የእስልምና ሃይማኖት መሪዎቹን ማሰር ካድሬ እስላሞችን በመሪነት መሾምና የሀገር ቤቱን ሲኖዶስ ደግሞ ህወሃታዊ ሲኖዶስ እንዲሆን ማድረግ ነው።ዛሬ በውጭ ቀላልና ዋና የገቢ ምንጭ ሆኖ የሚገኘው ህወሃት በቀጥታ ወደ ውጭ የሚልካቸውን የሰንበት ተማሪዎችን ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የለቀቁና ካድሬዎቹን ካባ እያለበሰ ቄስ ናቸው በማለት የአማራ ፤የኦሮሞ፤የትግሬ የሌላም የሌላም ቤተክርስቲያን በየመንደሩ በመክፈት ሕዝቡን ማራራቅና ቅሬኔ ውስጥ ማስገባትን ዋና ተግባሩ አድርጎ ይዞታል፤በወርሃዊ መዋጮና በሙዳይ ገንዘብ ሀብታም የቤተክርስቲያን መሪ መፍጠርና የማይሰሩ የሰበካ ጉባኤዎችን በማስመረጥ የህወሃትን መዋቅር ማጠናከር አንዱ ስልት ሆኗል።የሚገርመው ግን ጽላቱ የት እንደሚገኝ ነው።አንዳንዱ ከግሪክ ነው ይላል ሌላው ከኢትዮጵያ ነው ይላል።ሞቀም ፈላም ተጠያቂው ግን አስፈጻሚው ህወሃት ይሆናል ማለት ነው።በሌላው መልኩ ህወሃትን ስንመለከት ትግራይን ገንጥሎ ከኤርትራ ከአፋር ከአማራ ሰሜን ወሎና ሰሜን ጎንደርን ቆርሶ በመውሰድ ታላቋን የትግራይ ሪፐብሊክ መመስረት እንደነበርና አሁንም ሕዝባዊ ኃይሉ እየገፋ ከሄደ የኢሳይያስን ቡድን ገፍቶ የሚጥል ሴራ በመሸረብ ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚኖሩ ኤርትራውያን በበላይነት የሚመሩት መንግሥት ለመመሥረት የማይቦዝን ሲሆን የአሰብን ወደብ አልቀበልም ያለበት ምክንያትም በኤርትራ እጅ እንዲቆይ ማድረግ ከዚህ አንፃር ሊታይ የሚችል መሆኑ፤ ኤርትራን ያስገነጠለበት አጀንዳም ባካፕ ወይም የኋላ ደጀን በማድረግ ኢትዮጵያን እስከሚያፈራርሱ ጊዜ ለመግዛት ሊጠቀሙ የሄዱበት መንገድ መሆኑን እኛ ኢትዮጵያ ሀገራችን የምንል ጉዳዩን ከተለያየ አንግል ለጥጠን ልናይ ይገባናል፤ የኢትዮጵያን ለም መሬት ኢትዮጵያውያንን በማፈናቀል ለውጭ ከበርቴዎች በነፃ የቸረ፤ ሰፊና ለም መሬት ከኢትዮጵያ ሳልፎ ለሱዳን የሰጠ የኢትዮጵያን ዳርድንበርና ሉዓላዊነት ያስደፈረ ከሃዲ ድርጅት ነው።በነዚህና በመሳሰሉት ምክንያቶች ህወሃት አንድም ቀን ቢሆን ማደር የማይገባው በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ኑና ግጠሙኝ በማለት ጉድጓዱን ቆፍሮ ቀባሪ እየጠበቀ አጥፍቶ ሊጠፋ የተዘጋጀና እንደ እንሰሳ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ያለ ጀግና በሀገር ጠፍቶ 22ኛውን ዓመት አሳልፎ 23ኛውን አመት እየተሻገረ ያለ ሀገርን ያጠፋ የዐረብና የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈጻሚ ቅጥረኛ ድርጅት ነው።

በመጨረሻም ህወሃት መሬት ለሱዳን መስጠት ለምን ተገደደ የሚለውን ስንመለከት 1ኛ/ ሱዳን ለህወሃት ሆነ ለሻእብያ ትልቅ ባለውለታ ነች ወይም አሁንም ሆነ በደርግ ወቅት ከደደቢት የበለጠ ምሽግ ሆና ማገልገሏ ግልጽ ነው።2ኛ/ ህወሃትን የሚቃወሙ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶችን በሱዳን አማካኝነት ከሱዳን ምድር ጽ/ቤታቸው እንዲዘጋ ንብረታቸው እንዲበረበር፤ከሱዳን እንዲወጡ በማድረግ የሱዳን መንግሥት ከፍተኛውን ድርሻ ተወጥቷል።ለዚህም ነው የመሬት ጉርሻ ለሱዳን እንዲሰጡ የተገደዱበት ይኸም ቀደም ሲል ቃል የተገባበት እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው። የሚገርመው ግን ከኔ ከራሴ ጀምሮ የሱዳንና የኢትዮጵያን ድንበር አበጥሮ የማያውቅ ይኖራል ብየ አላስብም ራሱ ህወሃት ያውቀዋል።የህወሃት ዓላማ ግን ሱዳን ከኢትዮጵያ የወሰደችውን መሬት ልትጠቀምበት ትችላለች ብለው አምነውበት ሳይሆን በሁለቱ አገር ሕዝቦች መካከል የሚኖረውን የወንድማማችነትና የወዳጅነት ግንኙነት ለማደፍረስ የታሰበ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ እንዲሻክርና እንዳይኖር በብጥብጥ ለማኖር የተጠመደ ፈንጅ ነው።

ወደ የተቃዋሚ ኃይሎች ስመጣ የተቃዋሚ ኃይሎችን በሁለት ከፍየ አያቸዋለሁ፦

1ኛ/ ሥርዓቱን በሰላማዊ መንገድ በመታገል በዴሞክራሲያዊ ምርጫ አሸንፈን የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት፤ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጎች በእኩልነት ተከባብረው እንዲኖሩ የሚያደርግ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሥርዓት ለመገንባት የተነሱ ናቸው። መነሻቸው ወይም ዓላማቸው በጣም የሚደገፍና ቅን አስተሳሰብ ነው። ችግሮች ድርጅቶች ህወሃትን በሚገባ አውቀው እንደ ባህሪው ክፋት ተንኮሎችን በጣጥሶ መሄድ የሚያስችለውን መንገድ አልተጠቀሙበትም። ይኸውም መጀመሪያ አንድ ጠንካራ ሕብረ ብሔራዊ ድርጅት መገንባት አለመቻላቸው ሲሆን ሁለተኛ የተንበሸበሸ ብዛት ሳይሆን ጥራት ያላቸው ጥቂት ድርጅቶች ቢኖሩ መልካም ነበር።ይህም አልሆነም ባሉበት ደረጃም ሆነው ገና ከመጀመሪያው መደራጀትን ሲመርጡ ህወሃት ሰርጎ እንዳይገባ የተጠነቀቁ አይደሉም።ይህ በሀገር ቤት ይሁን በውጭ አገር ያሉትን የሚያጠቃልል ነው።ይህን ለማለት ያስገደደኝ የህወሃትን ጠብ አጫሪነትና ሰርጎ ገብነት በተለያዩ ደረጃዎች በመመልከቴ በድርጅቶች ውስጥ የሚፈጠሩትን የመከፋፈልና የሚያጋጥሙ ችግሮችን ተገንዝቦ አስፈላጊውን መፍትሄ መስጠት ባለመቻላቸው የህውሃት እጅ ገብቶበታል እንድል ያስገድደኛል። በሕቡ አደረጃጀት ምን ያህል ርቀው እንደሄዱ ባላውቅም አንድ ለአምስት የተደራጀ የስለላ መዋቅር ዘርግቶ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ የልብ ትርታ አዳምጣለሁ ብሎ የሀገር ሀብት ዘርፎ የተደራጀን ቡድን መሰናክል ለመበጠስ ሕቡ አደረጃጀት አስፈላጊ በመሆኑ ነው። ሁሉም ድርጅቶች ፕሮግራማቸውን ለህዝብ ለማስተዋወቅ ፤ አባልና ደጋፊ ለማፍራት ያጋጠማቸውን የካድሬ ፤ የደህንነት፤ የመከላከያና የፖሊስ ወከባ ሁላችንም ሳንገነዘበው አልቀረንም ለዚህ ችግር ሕቡ አደረጃጀት አስፈላጊ ነው ብየ አስባለሁ። በተረፈ አንድነት ሊፈጥሩ አለመቻላቸውና በተናጠል ትግሉን ለመቀጠል የሚሄዱበትን መንገድ እርስ በራሳቸው የሚያደርጉትን መጠላለፍ ሳልደግፍ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በህዝብ ላይ የሚደርሰውን ግድያ፤ እስራትና አፈና ፤ ድብደባ ፤የንብረት ዘረፋ፤ማፈናቀል…ወዘተ ለህዝብ ጀሮ እንዲደርስ በማድረግ የሚሄዱበት መንገድ ጎሽ የሚያስብል ሆኖ አግኝቼዋለሁ ቀጥሉበት ።

2ኛ/ ህወሃትን በቋንቋው እናናግረዋለን እንጅ በሰላማዊ ትግል ሥልጣን ሊያስረክብ አይችልም ብለው በትጥቅ ህወሃትን ለማንበርከክ የተሰለፉ የተቃዋሚ ኃይሎችን ሞራል በእጅጉ እያደነቅሁ ነገር ግን እነዚህ ኃይሎችም ቢሆን ከፍ ብየ እንደገለጽኩት ከህወሃት ሰርጎ ገብነት ነፃ ለመሆናቸው፤ እርስ በርስ ከመጠላለፍ የወጡ ለመሆናቸውና በጋራ አንድ ግንባር ፈጥረው ለመታገል ያላቸውን እምነትና ቁርጠኝነት ለማመን እርግጠኛ አይደለሁም። አንዳንዶቹ ከተመሠረቱ ህወሃት በጥቂት ዓመታት የሚበልጣቸው ሲሆን ቀደም ብለው የትጥቅ ትግሉን የጀመሩ ሲሆን በነዚህ ኃይሎች ነፃ የወጣ ምድር አለ ሲባል ሰምቼ አላውቅም። ምናልባት ለድርጅታዊ ጠቀሜታና ደህንነት ተብሎ ከሆነ መልካም ነው። አንዳንዶቹ ማፈግፈጊያ ያደረጉት የኤርትራን ምድር ሲሆን በበኩሌ ይህ የግሌ አስተያየት ነው የኢሳይያስን መንግሥት በማመንና ከሱ ድጋፍ በማግኘት ህወሃትን ታግየ እጥላለሁ ብሎ ማሰብ« ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል »ብሎ እንደማሰብ ነው ብየ አስባለሁ። ለምን ቢባል ወደ ኋላ እንመለስና ኢሳይያስ አፈርቂ በኢትዮጵያ ላይ ያለው አመለካከት ከዚያ በፊት በታጋይ ድርጅቶች ላይ ከህወሃት ጎን በመሆን ያደረገው ጭፍጨፋና የነበረው አቋም ሲታይ ጊዜን ማባከን ወይም በህወሃት መንገድ እየሄዱ ነው የሚመስለው። ሻእብያ ህወሃትን ቃል አስገብቶ እንደፈረስ ይጋልበው እንደነበር መዘንጋት የለብንም። ለምሳሌ ምን ያህል እርግጠኛ እንደሆነ ሙሴን ባላምነውም ሰበር ዜና በማለት ያቀረበውን ስንመለከት የኤርትራና ህወሃት ጀኔራሎችና ባለሥልጣናት በሳውዲዓረቢያ ስብሰባ ማካሄዳቸው ተግልጿል። በዚህ ከተግባቡ ምናልባት ኢሳይያስን በማስወገድ አፍቃሪ ህወሃት ኃይል በኤርታራ አደራጅቶ ትግራይና ኤርትራን በጋራ በማድረግ እንዲሁም ከአፋርና አማራ ክልል በእቅድ የተቀመጠውን መሬት አካሎ የመለስ ዜናዊ «ራእይ»ን ተግባራዊ ለማድረግ ከመሆን ሊያልፍ ይችላል ወይ? ይህ ከሆነስ የኤርትራን ምድር ደጀን ያደረጉ በትጥቅ ትግል የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? በበኩሌ ነፍጥ ያነሱ ኃይሎች መጀመሪያ ሳይረፍድ ግንባር መፍጠር አለባቸው።ሁለተኛ የተከፈለው ይከፈል የኤርትራን ምድር ለቀው ኢትዮጵያ   ውስጥ ነጻ መሬት መያዝ ወይም የጎሬላ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ ግድ ይላቸዋል። ከዚህ ባለፈ ግን አማራጩ የራሳቸው ቢሆንም በአፈና ላይ ለሚገኘው ሕዝብ ደርሶ ከአፈና ለማውጣት ጊዜ የሚገድል ሆኖ ነው የሚታየኝ። ከፍ ብየ እንደገለጽኩት ህወሃት ጥጋቡ መረን በመዝለሉ ሞትን እየናፈቀ ያለ የሰላማዊ ትግልን በር እንዳይከፈት አጥብቆ የዘጋ ተቃዋሚዎችን ትንሽም ቅንጣት ያህል ሊያከብርና በሀገር ጉዳይ በጋራ ሊመክር የማይችል እብሪተኛ ድርጅት በመሆኑ በትጥቅ ትግል ማስተንፈስ ከተቻለ ልክ የማይገባበት ምክንያት አይኖርምና ለሀገርና ለህዝብ ብላችሁ ትግስት አስጨራሹን የትግል ጎዳና ከጀመራችሁ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ሕዝቡንና ሀገሩን ስለሚወድ የተቻለውን ሁሉ ድጋፉን እንደማይነፍጋችሁ እርግጠኛ ሆኘ ልነግራችሁ  እወዳለሁ። የተቻለውም በድጋፍ ብቻ ሳይገታ ትግሉንም ሊቀላቀል እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ።

ለዛሬ ያለኝን በዚህ ጨርሻለሁ በቼር ይግጠመን።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላአለም ትኑር!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

ሞት ለህወሃት!!!

 

ጌታቸው   Pen

 

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>