Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

አቶ አያሌው ጎበዜም የድል አጥቢያ አርበኛ እንደ ውሃ ላይ ኩበት እመሀል ላይ እንደዋለሉ የማይቀረውን ስንብታቸውን ተሰናበተዋል

$
0
0

ዳዊት መላኩ(ከጀርመን)

አያሌው ጎበዜ

አያሌው ጎበዜ

አቶ አያሌው ጎበዜም እንደምንም  የመምህርነት ስራቸውን ትተው የድል አጥቢያ አርበኛ በመሆን ገብተው ወይ ራሳቸውን ነፃ ሳያወጡ ወይ ህዝቡን በትክክል ሳያገለገሉ እንዲሁ እንደ ውሃ ላይ ኩበት  እመሀል ላይ እንደዋለሉ የማይቀረውን ስንብታቸውን ተሰናበተዋል፡፡ወያኔ እንደ ሸንኮራ ምጥጥ አድርጎ ተፋቸው፡፡እኔ እስከማውቃቸው አቶ አያሌው ከሌሎች የወያኔ ባለስልጣናት የሚለዮት በሙስና አለመጠርጠራቸው፤ብዙ ማውራት የማይወዱ ሲናገሩም ከባህል እና ከሞራል የማያፈነግጡ፤ለሚኖሩበት ማሀበረሰብ ክብር በመስጠት ሚስታቸው ሳይቀር አብረዋቸው ከሚኖሩት እድርተኞች እኩል መሳተፋቸው ነው፡፡ አቶ አያሌው እንደአባዱላ ገመዳ ብዙ ቤት ገንብተው ለትግሉ ስላስቸገረኝ ውሰዱልኝ ሲሉ አልተደመጡም፡፡እስካሁን ባለኝ መረጃ መሰረት አቶ አያሌው ባህርዳር ከተማ ውስጥ ቀበሌ 14 አካባቢ በማህበር ተደራጅተው በወሰዱት አንድ ቦታ ቤት እንደገነቡ ነው ፡፡ ዘመድ አዝማዳቸውን ስራ በማስገባት አይታሙም ፡፡የአቶ አያሌው ልጆች እንደ ሌሎች የባለስልጣን ልጆች አሜሪካ እና አውሮፓ ወይም አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ ውድ የግል ትምህርት ቤቶች አይደለም  የሚማሩት፡፡እንደማንኛውም ደሃ ቤተሰብ ባህርዳር ውስጥ ባሉ የመንግስት ትምህርቤቶች ያስተምሩ ነበር፡፡

አቶ አያሌው እንግዲህ እነዚህ መልካም ነገር ቢኖራቸውም የተሰጣቸውን መክሊት አባክነው የክልሉ ህዝብ በየቦታው ሲፈናቀል የክልሉ መሬት እንደዳቦ እየተሸነሸነ ሲታደል የተቀመጡባትን ወንበር ላለማጣት በዝምታ ማለፍን መርጠዋል፡፡ይህ ደግሞ በምንም መልኩ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ከሌባ ጋር አብሮ ስርቆት ሂዶ  በቅርብ ርቀት ሲሰርቁ እያዩ ዝም ማለት እና የሰረቀው አብሮኝ ያለው ሰው ነው አንጂ እኔ ነፃ ነኝ ቢሉ ከቅጣት አያመልጡም፡፡እንግዲህ እርሳቸው በስልጣን ላይ በቀዮበት ጊዜ ለጠፋው ሀይወት፤ለወደመው ንብረት፤ለተፈጠረው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድቀት የድርሻቸውን ይወስዳሉ፡፡

መቼም በዘመኔ ወያኔ ስራና ሰራተኛ ተገናኝተው ባይውቁም እንደአማራ ክልል  ባለስልጣናት በእውቀት ድርቅ የተጠቃ የለም፡፡”ሰው ሢታጣ ይመለመላል ጎባጣ” ነው ነገሩ፡፡ሰው ሲታጣ ማለቴ ለወያኔ በታማኝነት የሚያገለግል ማለቴ ነው፡፡አቶ አያሌውን የተኩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በርቀት ትምህርት በማኔጅመት የመጀመሪያ ዲግሪ ሲኖራቸው በ1998 ዓ.ም የብአዴን ቢሮ ውስጥ ይሰሩ ነበር፡፡የተኛው የተምህርት ዝግጅት ተዛምዶ የክልሉየግብርና ቢሮ ኃላፊ ሁነው እንዲሰሩ እንዳበቃቸው የሚያውቀው ወያኔ ብቻ ነው፡፡ይባስ ብሎ ክልሉን የመምራት ሀላፊነት ለሳቸው መስጠት ከምጡ ወደ ዳጡ ነው፡፡ አቶ ገዱን የአማራ ወጣቶች ከከፍተኛ ትምህርቶች ተመርቀው የፓሪቲ አባል ካልሆኑ ስራ እንዳይሰጣቸው በክልሉ ላሉ ሁሉም ዞኖች ትእዛዝ ሲያስተላልፉ በተቃራኒው አባል ለሆኑት ስልክ ብቻ በመደወል እንዲቀበሉዋቸው ያል ምንም ውድድር እና ማስታወቂ  በደብዳቤ ብቻ ሲመድቡ እንደነበር ይታወቃል፡፡በተለይ በ1998ዓ.ም የንግድ እና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት በወረዳዎች መከፈትን ተከትሎ በሁሉም ወረዳዎች የተመደቡ ፈላፊዎች በዚህ አይነት የተመደቡ ነበሩ፡፡አቶ ገዱ የክልል ፕሬዚዳንት ቀርቶ ለቀበሌ አመራርነት ሚያበቃ ስብእና እንደሌላቸው ሚያወቁዋቸው ሁሉ የሚስማሙበት ሀቅ ነው፡፡ግን ምን ይደረግ ወያኔ በሚመራው ሀገር ውስጥ ለሀገር የሚጠቅም ነገር በነፃነት መስራት ስለማይቻል አንዴ አዲሱ ለገሰ፤አንዴ ደመቀ መኮነን፤አንዴ ገዱ አንዳርጋቸው እተፈራረቁ በህዝቡ ትክሻ ላይ ያለከልካይ ይጫናሉ፡፡

በመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ የምናውቀው ደጉ አብረሀም የተወለደው ያደገው ከጣኦት አምላኪ ቤተሰብ ነበር፡፡  እግዚያብሔርም አብርሀምን “አብርሀም አብርሀም ውጣ !እኔ ወደማሳህም ወደዚያ ተራራ ሂድ አለው”፡፡አብርሀምም ቤተሰቡ የሚያመልከው ጣኦት አይን እያለው የማያይ ጆሮ እያለው የማይሰማ “ልክ እንደ ኢህአዴግ”  ነበርና ከፈጣሪው የመጣለትን ትእዛዝ ሳያመነታ ተቀበለው ፡፡በሀጢያት ከረከሰው አካባቢውም ተለይቶ ወጣ፡፡አብርሀም ያደረገው ከሚወደው ቤተሰቡ  በባእድ አምልኮ አብሮ ላለመኖር የግድ መለየት ነበረበት ተለያም፡፡ዛሬ በተለያዮ የስልጣን እርከን በወታደራዊም ሆነ በሲቪል ተቋማት ከወያኔ ጋር እየሰራችሁ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ልክ እንደ አብረሀም በደም ከተበከለው ፤ህዝብን አፍኖ በችግር እየገደለ ካለው ስርኣት ራሳችሁ ለይታችሁ ውጡ፡፡አብርሀም ቅድስናን የተቀዳጀው ከባእድ አምልኮው ተለይቶ ነው፡ለጊዜያዊ ሥልጣን ጥቅም ወዘተ ራሳችህን እስካሁን አስገዛችሁ፡፡መጀመሪያ እውነት አለ መስሎአችሁ ገብታችሁ ይሆናል፡፡ግን ወያኔ ጋ ቀርቦ ያላየ የለም ደረጃው ይለያ እንጂ ፡፡ አንድም እውነት የለም ሁሉም ነገር የውሸት የማስመሰል ነው፡፡ወያኔ ጣኦት ነው፡፡ህገ-መንግስቱ፤የመለስ ራዕይ፤የብሄር መብት፤እድገት እና ትርናስፎርሜሽኑ፤የሚወራው ዲሞክራሲ ሁሉም ባእድ አምልኮዎች ጣኦቶች ናቸው፡፡እውነታውን ታውቁታላችሁ፡፡ስለገባችሁበት ነው እንጂ ሁሉም የህወአትን እድሜ ማራዘሚያ ነው፡፡ማንም ከወያኔ ጋር ሁኖ ህሌናው ያመነበትን እንደማይሰራ እናንተም ታውቁታላችሁ፡፡ፍርድቤቶች የሚፈርዱት በህሌናቸው ነው?ጋዜጠኞች እየሰራችሁ ያላችሁት እውነታውን ነው? ወታደሩ  የገንዛ ወንድሙን፣እህቱን  በቆመጥ የሚቀጠቅጠው አምኖበት ነው?፤የሚስኪኑዋ እናትክን ቤት እላይዋ ላይ የምታፈርሰው ህሌናህ ፈቅዶ በችግር ለተቆራመደው ወገናችን መርዳት ስንችል ለምን ተጨማሪ እዳ እንሆንባቸዋለን፡፡ከወያኔ ፍርፋሪ መጠበቅ ለጣኦት የተሰዋ መብላት ነው፡፡ ነው?ከወያኔ አገልጋይነት ተለዩ!ከወያኔ መንደር ውጡ!


‘ነውጥ አልባ ትግል’ – ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ ስለ አዲሱ ጥናታዊ ፊልም ይናገራል – ሁሉም ሊያዩት የሚገባው

$
0
0

በአለም ዙርያ ተበታትነው ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከነ ጋንዲ ምን ይማራሉ? የሳውዲ አረቢያ መንግስት በዜጎቻችን ላይ እያደረሱ ያሉት ግፍና መከራን እንዴት መቋቋም ይቻላል? በሌሎችስ ላይ እንዳይደርስ እንዴት መከላከል ይቻላል? – ‘ነውጥ አልባ ትግል’ ለእነዚህና ሌሎች ተዛማች ጥያቄዎች ምላሽ አለው – ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ ስለዚሁ አዲስ ዶክመንታሪ ፊልም ይናገራል። አስተናጋጁ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ነው።

‘ነውጥ አልባ ትግል’ – ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ ስለ አዲሱ ጥናታዊ ፊልም ይናገራል – ሁሉም ሊያዩት የሚገባው

ባዶ ሳጥን። ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ   21.12.2013

ኢትዮጵያዊነት ለሄሮድስ መለስ በሽታቸው ነበረ። ደፍረን እንናገረው …..

ቀልዴን እንዳይመስላችሁ የእውነቴን ነው። ተረብ እንዳይመስላችሁ ነው የምር። ከልቤ ሙዳይ ያለችውን ሚስጢር ዘክዘክ አድርጌ ላጋራችሁ እንሆ ዛሬ ወደድኩ። የታደለቸው ኩኑ በ15.12.2013 የነገ የሰላም መዲና ሆነች። የአፓርታይድን ግብዕት ለመፈጸም ፍሬ አፍርታ ዘር አንዘርዝራ ጎታዋን በእኩልነት ሞላልታለችና እንደ ጎለጎታ ዎህ ብላ በልበ -ሙሉሉነት ሰከነች። እንሆ … ኩኑ ሰላማዊ ቅዱሳዊ እረፍት ለልጇና ለወዳጇ በክብር ሸለመች። ይጋባታል! ይህ የዓለም ፊኖሚናና አጀንዳ የሆነ የበኽረ አስራታት እናት ናትና ዬምርት ጎታዋ ተትረፈረፈ – በዕውቅና። አደናቆትም በአርቱ ማዕዘናት ተቸራት። ኩኑዬ ልበላት ትቆላመጥ አይደል? ቢያስፈልግም ዬወርቅ ቀለበት አስርቼ ላክ ነው የማደርግላት። የሰላም አባት የእረፍት ቦታ ለትውልዱ፤ የነገም የአፍሪካ ትውፊት። ማለት ቅርስና ውርስ የቅብብል አድባር በመሆን አፈሯ ከበረ – ተባረከ – ተመረቀ። የነፃነት ራህብተኞች ሁሉ ስብከቱን፤ ማህሌቱንና ቅኔውን ከቦታዋ በመሄድ ያጣጥማሉ … ከዛሬ ጀምሮ። ለማግስት ወደ ምስራቃዊዋ የኬፕ ገጠራማ ወደ ኩኑዬ ሚሊዮኖች ይተማሉ ….. ዕምነት – ፅናት – ቅንነት – ይበቃኛል – ቤዛነት – ፍቅር  የሰበለባት ደግ ሰፈር። ማህደረ – ዕሴት! ትልቅ የተግባር ሙዚዬም ይገነባባታል። ዩኒስኮም ይሄኔ አጭቶት ይሆናል። ጽድቅ።

መስታውቷ ኩኑ ተልዕኳውን በተግባር ትማ፤ ለትውልድ አደራን አቅልማ አስማምታ ዳረች። ትንሿ የደቡብ እፍሪካዊቷ መንደር ልክ እንደ ጎለጎታ ፍቅርን በአግልግሏ በአደራ አመሰጥራ ታሪክን በዕንቁ አንቆጥቁጣ አስቀመጠች። የታደለች! መርቋታ! የምን ዝም እዬበሉ እዬጠጡ። ኩኑ – ኩሩ ምህረትን ፈትላ ነገን በተዋበ ጃኖ አለበሰች። ሰላምን ጠርታ ቅንነትን ለድል አቀለመች። መታባበርን ጋብዛ ዓለምን በአንድ ቀለበት በኪዳን አዋውላ ጠመቀች። ፍላጋ አስምራ ለፍትኃት ናፍቆትን ታጠቀች። አማረባት!  አስተሳሰረች …. ኩኑ አስናች – አስቀችም። አንድ ቀን ሄጄ አያታለሁ። እኔም የድርሻዬን ሁለቱን መስኮቶቼ ከፋፍቼ እንዲተነፍሱ አደርጋለሁ። የነፃነት እምነቴንም ቆጣጥሬ ስቀበር አብሮኝ እንዲሆን እናዘዛለሁ …. ታደልኩ።

በመጤ እንደራሴ ሲባክኑ፤ ማንነታቸው አምልጧቸው እንደ ግዑዝ ሞትን ሳያስቡ ያለፉት ሄሮድስ መለስ በመላጣና በተጠ ገጠመኝ ሲወዛወዙ፤  ከተኮፈሱበት ወረድ ብለው በዓለም አደባባይ „ጊዜ ገቢረ ለእግዚአብሄር“ ሆነና በባተሌ ትንታግ፤ የዕንባም ሰማያዊ መልክተኛ፤ መክሊተኛም ግራማቸው ሸሽቶ በቅፅበት ከሰሉ። በጉልበታሙ ዬነፃነት ስንኛዊ ድምፅ ብቻ በርግገው ክብራቸው ለአፍታ ተኖ ተገፈፈ። ጥቂትም ሳይቆዩ ከል ዕንባ የተላኩ የመላእከ ሞት ወታደሮች መንፈሳቸውን በክርኒ ሰልቀው ለህልፈት ዳረጓቸውና ሥጋቸውም ሆነ መንፈሳቸው አፈር ሆነ። እሳቸውን አፋችነን ሞልተን ሞቱ ማለት እንችላለን። አፍር ሆኑ – በሐምሌ 7.2012። በሽታቸው ቀኑ የተሰበረበት፤ አሟሟታቸው ቀኑ የተጣፈበት፤ ቀብራቸው ደግሞ እሬሳ የሌለው ባዶ ሳጥን።  እንዲህ ዓይነት ታሪክ በዬትኛው ሀገር በዬትኛው መሪ ደርሶ ያውቃል?!  ይህ ብቻ በራሱ ቆሞ የሚመሰክረው አንድ የነጠረ ሃቅ አለው። ለኃጥ የወረደ ለፃድቅ ሆኖ ተወዳጁ የጋናው መሪም ወጨፎ ደረሳቸው። ቀን ጠበቃ ነው። ቀን ጥግ ነው። ቀን ለቀን ሰጥቶ ጥቃትን ያወጣል። የበቀል አምላክም እርግማኑን ካለይቅርታ ልኮ ዕንባን ይታደጋል። …. ሊቀ – ሊቃውንቱ አልፃፉትም እንጂ ታምሩስ ታምር ነበር። ለዓለም ህዝበ -ክርስትያን በብራናቸው ከተብው ማወጅ ነበረባቸው። እኛ የትናንትናውን ብቻ እናዘክራለን፤ የትናንት አምላክ ዛሬም አለ፣ የዛሬም አምላክ ነገም ይኖራል፣ በዘመናችን በዓይናችን ያዬነው ገድል ነበር …. እንደ ታምረ ማርያም … እንደ ገድለ ጊዮርጊስ ….

 

አወና! እኔ እላለሁ በቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ተቀበረ የተባለው የሄሮድስ መለስ አስከሬን ፈጽሞ የለበትም ባዶ ሳጥን ነው እላለሁ። ወያኔ ማለት እኮ ጉድጓድ ነው። መንፈሱና ሚስጢሩ የከተሙት ከሸሩ መቃብር፤ ከተንኮሉ ጎጆ ውስጥ ከዛ ነው። እንደምታውቁት ሄሮድስ መለስ ሀገር አልነበራቸውም። ብሄራዊ መዝሙርም አልነበራቸውም፤ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማም አልነበራቸውም፤ የእኔ የሚሉት የነጠረ ማንነት አልነበራቸውም፤ እሳቸው የእኛ – እኛም የእሳቸው አልነበርነም። ስለሆነም በድናቸው እንኳን መሬቷን እንዳይነካ ጎሳን የከዘነው መንፈሳቸው አይፈቅድላቸውም።  አምላካችንም ይህን አያደርገውም። ገዳዮዋን እንዴት … ተብሎ ነው እቴ … ምን በወጣት ጦቢት ተሸከሚ ተብላ የሚበዬንባት? ስለሆነም የመለስ በድን ቅድስተ ሥላሴ ላይ የለም ባይ ነኝ። ዬት ገባ? የቆዬ ሰው ይዬው …

 

በታመቀው ጥላቻ ከርፍቶ ለኑዛዜ ሳይበቁ መቅረታቸው ሆነ መታመማቸው ላይበቃ በመሞታቸው ፍንክች ሳንል ሳይሞቀን ወይም ደግሞ ሳይቀዘቅዘን ያሳለፍን ሚሊዮኖች ነበርን። የዓለም ሚዲያም ሆነ ህዝቡም እንዲሁ። የተከበሩ ማንዴላም የሀዘን መግለጫ የላኩ አይመስለኝም። የተከደነ ሚስጢር ይላችኋል ይህ ነው። ሄሮድስ መለስ ጠላት ጣሊያን ቢገዛ ሊያደርስ ከሚችለው በላይ ኢትዮጵያን በመከራ የጠበሱ፤ ኢትዮጵያዊነትን በጋለ ብረት ያቃጠሉ፤ ማንነትን አጋደመው ያረዱ፤ ዜግነታቻን ያለርህራሄ በቋሳ የቀቀሉ፤ ታሪክን አንጠልጥለው የሰቀሉ የበቀል አጋፋሪ ነበሩና ….  የተጠቀጠቀው የአርበኞቻችን አፅምም ይቅር አይልም – እኛም።

 

ሄሮድስ መለስ እንደ ጠላት የሚያዮትን ታሪካዊት ቀደምት ሀገር ኢትዮጵያን በድፍረትና በልበ ሙሉነት አንድም ቀን ኢትዮጵያ ሀገሬ፤ መኩሪያና መመኪያ፤ የምወዳችሁና የማከብራችሁ ህዝቦቼ ሳይሉ ሰንደቅዓላማችን እንደተጸዬፉት፤ ኢትዮጵያዊነትን ፊት እንደነሱት፤ ዜግነታቸው እንደ ቀፈፋቸው አለፉ። የነጠረው ውስጣችንም ቃር …  ቃር እንዳላቸው። ግን ከእናት ሀገር ጥሪት፣ ቅርስና ውርስ ሞጥጠው ከድቀት ተነስተው ለእርሳቸው፤ ለቤተሰባቸውና ለጋሼ ጃግሬዎቻቸው በምልዕት ዘርፈው ሳይበሉት ለአንድ ሰኔል፣ ለጥቂት ቹቻና ለስንዝር ገመድ ዲታነት ሳይወዱ ተገደው አደገደጉ …. ተመስገን!

 

ሄሮድስ መለሰን አወቂ ነበሩ የሚሉ የነፃነት ቤተኛ ጋዜጠኛዎችን ሳደምጥ እኔ ይገርመኛል። የእውቀት መለኪያ የክብር መሰረት ብሄራዊ መግለጫ ትራስ ሲኖረው ነው። እሳቸው በዚህ ህይወት አልኖሩበትም። ቅርፊትን ተማፅነው ልጥን ተማማነው በመንደር ትርምስ ሲቀብጡ ሲለጠጡ ተበጠሱ እውቀት ሆነ ለእኔ የህዝብ መሪነት ብቃት መለኪያው  ፍቅር ሰጥቶ ፍቅር ለመቀበል የመወሰን አቅም። የህዝብን አንጡራ የመንፈስ ኃብት በቅንነት ሸምቶ ለህዝብ ጠቀም ተግባር ማዋል። ዜግነቱን ግርማ ሞገሱ በማደረግ ከራሱ ባላይ ከፈጣሪው በታች አድርጎ መቀበል። ብሄራዊ ስሜቱ ወላፈኑ ከሩቅ ጠረኑ የሚጠራ ሲሆን፤ ወስጡን በውስጥ አጣጥሞ እኔነቱን የዋጠ። በራሱ የሚኮራ። ቅልውጥ የማያምረው እራሱን ለባእድ መንፈስ ጥገኛ ያለደረገ። ክህዝብ ቅምጥ ሃብት ትውፊትና ታሪክ ለመማር የፈቀደና የወሰነአንጡራ ጥሪቷና ሚስጢሯ የማያሰፍረው፤ ተፈሪነቷ አንገቱን የማያስደፈው። የማያነበብ ግን የሚነበብ። እውነት ለማናገር ኢትዮጵያ እኮ ባለቤት እረኛ የሌላት ሀገር እኮ ናት። እውቀት የሚባለውም ነገር ለዚህ የኃላፊነትን ብቃት በሰገደ መንፈስ ማስተናገድ የሚችል የላቀ ህሊና ይመስለኛል። ከዚህ አንፃር አቶ መለስ ነበራቸው ለሚባለው ዕውቀት እኔ እንደ ልዝ እንጨት ወይንም ማገዶ ነው የማዬው፤ ማፍረስ – መናድ ይህ እውቀት …?! የተተረተረ ውስጥ የነበራቸው የጎሳ መሪ አዋቂ ሲባሉ ያማል። እባካችሁ እንተዛዘን – የሀገሬ ጋዜጠኞች

 

ቀድሞ ነገር ዜጋ ያልሆነ ያልተቀበለውም፤ ዜግነቱን የናቃ የተሳለቀ … ያዋረደ እኮ ነው ኢትዮጵያዊነትን ሲመራ የነበረው። ኢትዮጵያዊነት ለሄሮድስ መለስ በሽታቸው ነበር – ንዳድ ወይንም ወባ። የሚያንደፈድፍ የሚያንዘፈዝፍ። ደፍረን እንናገረው። ውስጣቸው ከዚህ ቅዱስ መንፈስ በጣሙን የራቀ ጎሳ ላይ የጎደበ በድን። ሌላው ውስጤ ሲስቅበትም ሲያዝንበትም የነበረው መሰረታዊ ጉዳይ ደግሞ ከመንደር ጉርኖ ያለወጣ ስንኩል መንፈስ አህጉራዊ የሆነ ውክልና ሲሰጠው ነበር። ይህን ሳሳላ ውስጤ በግራሞት ተቆናጦ ይህን ልብጥ የመቋቋም አቅማችን ሳስቶ ያን ያህል ጊዜ እናታችን በመጤ እንደራሴ፤ በሚባዝን ባዕድ መንፈስ ተረግጣ መመራቷ የመንፈሴን ሰሌዳ እዬቆሰቆሰ ያቆሳስለው ነበር። ከዚህ አንፃር ነው እኔ ለጋዜጠኛ አበበ ገላው የላቅ ክብርና ዘመን የማይሽረው ልዩ ፍቅር ያለኝ። ጥቃቴን ስላወጣ። አቤ ተጋድሎውን በድል ቋጭቷል። ቀሪው የእኛ ጣጣ ነበር ተግባርን ቀልበን ማታ እንዲያበቃ ማደረግ ….

 

ከዚህ በተጨማሪም መንደር ላይ ያለ ፍልስፍና ለዘመኑ ደረጃውን ያልጠበቀ ወርደ ጠባብ ቅንጥብጣቢ የዘበጠ ግንዛቤ ነው። እውነት ቁመህ ተናገር ቢባል በ23 ዓመት ውስጥ አዋቂ መሪ ኢትዮጵያ እንዳልነበራት አሳምሮ በገለጸ። ስብከቱንም የምንምነት ናዳ በለቀቀበት። እኔ አይገባኝማ የሄሮድስ  መለስ የአዋቂነት እጀ ጠባብ። ስለዚህ ለእኔ ሄሮድስ መለስ ውስጥ ያለው የዕውቀት እንጥፍጣፊ በራሱ ጊዜ ተኖ ካለታሪክ ያስቀራቸው የተላጠ ነገር ነው – አሰር። ይልቅ ትውልድንና ታሪክን በመሻርና በመደምሰስ፤ እንዲሁም በማጥፋት ብቸኛው መሪ የነበሩት ሄሮድስ መለስ በቋሳ ተሞሽረው፤ በትዕቢት ተነፍተው፤ በማንአለብኝነት ተራራ ላይ ቁጢጥ እንደ አሉ ለሁሉ በእኩልነት ድልድል ወደ ሚሆንበት የንበት ጉዞ እንደ ተሉ መሄዳቸው የእጃቸውና ድርሻቸው ይመስለኛል። ጨዋን ህዝብን በማዋረድና በመናቅ፤ ህግ የሆነን ምልዕት በማንጓጠጥና በማጣጣል የሚታወቁት ሄሮድስ መለስ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ትናትን ገልበው፤ ዛሬን በጎጥ ዲዲቲ በመጋለብ ሀገርና ትውልድን አፈርሰው በድንገት ፈረሱ። የፈለሱ።

 

መራራው የሄሮድስ ዘመን ስጋትንና ሰቀቀን በባዕት በገፍ አምርቶ፤ ወርቅና ብር ተለይቶበት፤ የክትና የዘወትር ተበጅቶበት፤ የልጅ እና የእንጀራ ልጅነት ልዩነት ሰግሮበት፤ በማይገፋ ጥቋቁር የቀን ሌሊቶች፤ አዘውትረው ደም ባነቡ የሌሊት ድቅድቆች ወደ 21 ዓመት አካባቢ የአፍሪካን ቀንድ ፍርሰትን ዓውጆ፤ ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ እናት ሀገርን እንዳወጣ ቸብችቦ፤ የአባቶቻችንና የእናቶቻችነን የአርበኝነት አብነታዊ ውሎ ደመ ከልብ በማደረግ በአደራ ላይ ጦር የመዘዘ፤ ጥቃትን ያወጀ እኩይ አስተዳደር ነበር …. የጉዲት መሳ  …

 

ዘመኑ ለሚሊዮኖች የወስጥ ሰላም አመክኖ፤ በሀገሩ ዜጋ ባይታዋር ሆኖ፤ ተገፍትሮ በፍርኃት ተሰቅዞ፤ በልዩነት ተወግሮ፤ በጥርጣሬ ተቃብቶ፤ አሳሩን የባላበት የራህብና የፍዳ ነበር። በመለስ የተመለሰ ምንም ቅርስና ጥሪት የለንም። ይልቁንም ዕንባ በማምረትና በማከፋፈል ብቸኛው የህማማትና የምድራዊ የሲኦል ጊዜ ነበር። ዳር ድንበራችንም ለባዕድ በችሮታ የታጨበት … ጭጋጋማ … ጢሳማ ….

 

ስለሆነም ባዶ ሳጥኑ የተቀበረበት የቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል በራሱ ፍትኃት፤ ጥምቀተ – ትንሳኤ ያስፈልገዋል ባይ ነኝ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ በድፍረት። ጸበል መረት አለበት። በስሙ የተሰዬመው ባዶ ሳጥን፤ ፀላዬ ሰናይ የከተመበት ነውና። ባዶ ሳጥኑ ያረፈበት ቦታ እንኳንስ ሺዎች ሚሊዮኖች እንደ ደቡብ አፍሪካዊት የምህረት አባት፤ የይበቃኛል ልዑል ኔልሰን ያረፋባት ኩኑዬ ለዝክረ ነፃነት የሚተሙበት ሳይሆን ይልቁንም ነገ የሚወቀስበትና የሚነቀስበት ይሆናል። በዚህ ሥርዓት በተባባሪነትና በመሪነት የተሳተፉ ሁሉ አንገታቸውን የሚደፉበት ጠቀራማ። ከሀገር በላይ ምን ፍቅር – ምን ዕምነት – ምን ጌጥ – ምን መኖር – ምን ትምክህት – ምን ፍላጎት – ምን ህልም ምን ትዳር – አለና!? ማረራችን ከስሎ መንፈሳችን ወስጥ አመድ ሆኗል። ቁስለታችን ምግለቱ ውስጣችነን መድረሻ አልባ አድርጎታል። ወስጣችን ማረተ – በለዘ። የዘመኑ ታዳሚ ነንና …. አንሸሸው ነገር …. ተ – ቃ – ጠ – ል – ን!

 

ዘመነ ሄሮድስ መለስ አይዋ አብሮነት አዘውትሮ ደመር* (በቀጠሮ የሚካሄድ የወል የለቅሶ ቀን) የዋለበት ነበር፤ ሌላው ቀርቶ መርዙ በአንድ ቤተሰብ በእናትና በልጅ፤ በእህትና ወንድም፤ መሃከል ለነበረው እትብታዊ ፍቅር እንኳን ያላዘነ ፈጽሞም ያልራራ የዲያቢሎስ ዘመን ነበር። የፍቅር ተቋማት ተንደው፣ የልዩነት አረም የበቀለበት ዘመነ – ክህደት። ዘመነ – ፍልሰት። ዘመነ – ጥፋት። ፍደሰት። እኛነታችነን በጅራፍ የተቀጣበት ዘመን። የወዬበ ዘመን ነበር የሳጥናኤል መለስ ዘመን። ዛሬም አለቀቀም … ለነገም መለስ ብዙ የጥፋት ሴራዎችን ኮልኩለው አፍልተውና ዘርተው ነው ያለፉት …. አሜኬላ። መከራችን ማለቂያ መክተቻም የለውም።

 

ትውልዱ የችግራችን ሥሩን በመመርምር ጥናቱን በራሱ ላይ በውስጥነት ሰርቶ ቅንነትን ቢመገብ፤ ተግባርና ኃላፊነታችን ለመወጣት ቢያንስ የማሰብ አቅም ይኖረናል። እያንዳንዱ ዜጋ ሌላ ቦታ ሄዶ አይደለም የጥናት ተግባሩን መከወን ያለበት ከራሱ ይጀምርው። ውጭ ያለነው በልተን አድረን ሊሆን ይችላል። ግን የብዙ ነገሮች ተጠቂ ሆነናል። ቤታቻን ተቀምተናል። እናታችን ተዘቅዝቃ ከእነ-ተስፋዋ ተንጠልጥላላች። በትን ታግታለች። ወገኖቻችን በነፃነት ራህብና በእህል ውኃ እራብ እስኪበቃቸው እዬተወቁ ነው። ዛሬ የጠራው የትናንቱ ባህላችን የለም። አዲስ ቅይጥ ባህል እንጂ።  ግለኝነቱ ብቻ አይደለም መሬታችን እንደ እንሳሳ ለሚኖሩ መጤዎች ታድሏል። መኖር ጋብቻን ያመጣል። ጋብቻው ትውልድን ይፈጥራል። ነገ የእኛ አይደለም። ነገ የእኛ አንጡራ ጠረኑኑ እንዲፈልስ ሄሮድስ መለስ ረቂቅ ደባ ፈጽመዋል። የኛን ወዝ ተቀምተናል። ያ … መደበኛ የውስጥ ጠረን ተሰርቀናል። መከራው ያመረቀዘ ነው። ፍዳው የመገለ ነው። ስቃዩ የሚያርመጠምጥ ነው። ተስፋውም – የተሰቀዘ።

 

መሬቱ ለባዕድ በመሰጠቱ በኬሚካል እዬተቃጠለ ነው። አዬሩም የብክለት ታዳሚ ሆኗል። ስለሆነም ነገ ገና ከመምጣቱ አሯል። ሄሮድስ ያሰለጠናቸው በእግር ተተኪዎች በሀገር ውስጥና በውጭ መጠነ ሰፊ የመማር ልዩ ዕድል ስለነበራቸው በአረም የበቀለው የሄሮድስን የበቀል ዶክተሪን የጎጥ ፍልስፍና ለማግሥት ነቀረሳን ተክሏል። የአርበኝነት ታሪክ የነፃነት ታሪክ „የጀብደኝነት““ የሚሉ ማፈሪያ ተባዮችን አፍርቷል። ጥቁር አንበሳ እኮ የመጀመሪያው የተደራጀ የሽምቅ ውጊያ ሰንደቅ ነው። ዓለምን በድርጊት የመራም ያስተማረም ታላቁ ኢትዮጵያዊነት ነው። እንኳንስ ሌላው … ቅኝ ለማደረግ የተመኙት እንኳን የማይሉትን ነው የሄሮድስ አረማዊ ችግኞች ሲሉ የሚደመጡት።

 

ከ15 ቀን በፊት ቃሌ ሩም ነበርኩኝ። እንግሊዝ ሀገር የሚኖር “እምነት ወይንም ነጋድራስ ባይከዳኝ“ በሚባል የፓል ሥም የሚጠራ ወጣት በድፍረት ዓለምን ያስደመመውን ግሩሙን የተጋድሎ የነፃነት ታሪካችን ትቢያ በማልበስ ሎቱ ስብኃት ስለ ቃሉ „የጀብደኝነት“ ሲል በቦጅቧጇ የድምጽ ቃና ነበር እንደ መሪው እንደ ሄሮድስ በመታበይ የገለጸው። ስሰማ ተንዘፈዘፍኩ። በርቀትም የቤት ሥራችን ምን ያህል ውስብሰብ እንደ ሆነ ተልምኩት … ይህ ሰው ሀገራችነን አንድ ጊዜ ከዩጎዝላብያ፤ ሌላ ጊዜ ከአልባንያ ጋር ወስዶ እዬቀረቀር መርዙን ሲረጫጭ „ልጅ ሰለሞን“ በሚል የፓል ስም የሚጠራ ጥሩ ተናጋሪና ስለ አውሮፓ ሀገሮችም ጠንቅቆ ያነበበ የቤቱ አድሚን የተገባውን ቅጣት አስታጠቀው። መመከተም አልቻለም ነበር። በምን ስሌት ነው የሰው ልጅ መገኛ፤ የአፍሪካ አርማ ከነአልባንያ ከነኮዘቦ … ዬምታዳበለው … ዝብርቅ ባለ መንፈስ ሲላተም የሚመክት ወንድም በመኖሩ መርዙን ከጅራቱ ነቅሎ ለራሱ አወራረደለት። በዚህ መልክ ስንት ነፍስ ከማእዱ ወጥቶ ይሆን? „ትምህርት ዜግነት“ የወቅቱ የትኩረት አቅጣጫችን ሊሆን ይገባልም እላለሁ … ለነገም የሚመረቁበት ሙያ እንዲሆን ምኞቴ ነው። ያልተበከለ ማሳ፤ አረም ያልነከው መሬት የለነም …

 

በክርክር ወይንም በዲቤት ወቅት ስድብ ሳይሆን ፋይዳው፤ ነጥቦችን እንዲህ በፋክት አፋጦ፤ በእውነት መክቶ ሃሰትን ጠርቦ፤ በወጥ አምክንዮ ትራስነት በብልጫ አቅም መርዛዊ የሄሮድስን ሰደድ መመከት ያስፈልጋል። ለኢትዮጵያዊነት ሌላ የማማሳከሪያ ሰነድ ወይንም ሀገር፤ ሌላ የሪፈረንስ ሊንክ አያስፈልገንም። ባህረ መዝገቡ ማውጫ ሰነዱ እሱ እራሱን በራሱ ተርጉሞ ያመሳጠረ ነውና – ኢትዮጵያዊነት። ለነገሩ ማማሳጠር የተሰጣቸው ብቻ ልዩ መክሊት ነው። ያልተሰጠውን ከአረም የበቀለ ችግኝ በምን አቅሙ …. መንጠራራቱ በራሱ ይገርማል …

 

ወገኖቼ የመለስ ዶክተሪን መርዝ ዕዳው ከትውልዱ አቅም በላይ በመሆኑ በእጥፍ፤ በድርብ በፍቅርና በስምምነት ተግተን ብንሰለፍ እንኳን ያችን የትናንቷን ንፁህ ሀገር፤ ቅዱስ መንፈሷን ከእነ-ልቧ ለማግኘት ዳገቱ – ዳገት ነው። – ተራረውም የጨው ውሃን ያዘለ። እኛን የሚጠብቀን ድርሻ በእናቱ ማህፀን ዓይን ያልተፈጠረለትን፤ የዓይን ቦታውም ድምስስ የሆነውን ልጅ ሲወለድ ዓይናማ ማደረግ ነው።

 

የእኔ ጸጋዎች፤ የሀገሬ ልጆች …  በእናቱ ማህጸን የዓይን ቦታ ያልነበረውን በምን ታምርና በምን ረቂቅ ትንግርት ነው ዓይናማ ማደረግ የምንችለው?! በምን ጉልበትና የስበት ኃይል ነው ይህን ተልዕኮ ተውጥተን የተቀበልነውን የአደራ ጸጋ ቅብብሎሹን በመራረቅ ለቀጣዮ የምናስረክበው?! ልብ ብንለው የትውልዱ የፊት ለፊት ተግባር ይህን ያህል ጥልቅ ነው። ስለሆነም ዛሬ አዎን ዛሬ አደራ በላ ሳንሆን የውስጥ ለውጥ በማምጣት ቅንነትን ፈቃድ እንስጠው። በአውንታዊ ዕይታ መንፈሳችን እናናው። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ ይወለዳልና ያለንን ጥቅም ላይ ለመዋል ወታደራችን፤ ዘበኛችን፤ ጠበቃችን፤ አጋፋሪ ሊጋባችን መሪያችንም ቅንነትን እናድርግ በስተቀር ደርቀን እንቀራለን።

 

ከሄሮድስ የተረከብነው ባዶ ሳጥን ነው። … መንፈሱ የተሰደደ። እኛ ግን ሁሉ አለን። ሁሉንም ለመሆን እንፈቃቀድ … እንደ ዕዬምነታችንም ቃሉን ለድርጊታችን መሪነት እንፍቀድለት። …. መፍትሄው ያለው ከዛ ላይ ነው። …. ለእኔ ከፍቅር ይልቅ ቅንነት ይበልጥብኛል። ቅንነት ጥገት ነው። ጋቱ ሙሉዕ የሆነ። ቅንነት ካለ ምቀኝነት ይሰባራል። ቅንነት ካለ ፍቅር ለመስጠት ንፉግ አይኮንም። ቅንነት ካለ ጥላቻ ይሞታል። ቅንነት ካለ አቅማችን አቅደን ወደ ተግባር በመለወጥ  የአደራችን ባለቤት መሆን እንችላላን። ቅንነት የእስር ቤት ዳኛ ነው። ቅንነት ምህረተኛ በመሆኑም ንዑዳን ተግባራት ካለመሰናክል ገቢራዊ በማድረግ ፍሬዎች እንዳሻቸው ይፈነጥዛሉ …. ነገም ከዛሬ ይጀምራል። ፍሬም ከዘሩ ይበቅላል። የአሉታ ዕይታ ለአውንታ እጁን ይሰጣል ዳኛው ቅንነት ከሆነ …. መጠራጠር ለመተማማን ይሰግዳል … የጎሸው ይጣራል የከረረው ይለዝባል። ፍላጎታችን አንድ ከሆነ ኃብታችን አቅም እንዲኖረው እንፍቀድ ….

 

አንድ ሰው ብዙ ነው። መንፈሱና አካሉን ንፉግ ሳይሆን ለነፃነት ትግሉ ከለገሰ እንደአሰብነው እንሆናለን። እንደ ተፈጥሯችን እናመራለን። የጋዜጠኛ አበበ ገላው አንድ ስንኝ እኮ ነው ያን ያህል ጉልበት ኖሮት መተንፈሻ ቧንቧችን በመክፈት ጥቃትን አውጥቶ ለሄሮድስ መለስ ቅጣትን ያስታጠቀ። አቤ ችሎት – ጠበቃ – አቃቢ ህግ – ዳኛም ነው። ሚሊዮኖች የተገፉ ህዝቦች በአንድ ላይ ቢነሱ ወያኔ እኮ ምንም ነው። ጠርሙስ። ከባህር የወጣ አሳ። የተግባር ጥግና ከለላ የሌለው … ብን … ትን — ብትን ….. የሚል። ይ ቻ ላ ል ….. እንደ ገና እንረባረብበት እንችላለን።

 

በተን ብላ በቀረበችው የባዶ ሳጥን የብዕር ጠብታ ካበዛሁባችሁ ይቅርታችሁን እጠይቃለሁ። አቀናሁ። ሸምቱ። እንደገናም አቅኑልኝ። …. እንፈቃቀድ …. እንደማመጥ …. ህመሙ እንዲመረምረን ይለፍ እንስጠው። …. ስቃዩም ሥር ሰዶ መንፈሳችን እንዲንው በቂ የርስት ማሳ ህሊናችን ይሰጠው። …. ቆጥቆጥ ሲያደርገን ቆረጥ፤ ቆረጥ ስናደርግ በቃን እንወልዳለን። …. ጉልበተኛን አንባገነን እየተጋፉ መሄድ ደስ ይላል ~~~ የአሸናፊነትን ዋዜማ ነውና!

 

 

ኑሩልኝ እኔ ካለ እናንተ ምንም ነኝና ….. ትቢያ …

 

ኣራት ዓይናማው መንገዳችን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው!

እልፍ ነና እልፍነታችነን በተግባር እልፍ እናድርገው!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

sreate1

 

የተሳካ ትርጉም ያለው –እንቅስቃሴ በሲቢሊቲ ሩም። ሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ 22.12.2013

sreate1ዕለቱ ሰንበት የተቀደሰ የተወደደ በፈጣሪው የተመረጠ ነበር። በዲኔግዲ አማክኝነት ሸገር የዘገበው የታልቅ ሚስጢር ዕውነተኛ ቀን ነበር 08.12.2013። በዚህ ሰዓት ነበር አባ መላ /አቶ ብርኃኑ ዳምጤ/ የሩሙ ባላቤት እጅግ በተመሰጠና ተቆርቆሪነቱ በአዬለ ሁኔታ በዕለቱ ስልኩን ፈልጎ ቃላቸውን በጀሯችን ያደረሰን። ስደት ደስታን የሚገፍ ሲሆን ያን ቀን ግን እውነተኛ ደስታ ነበር የተሰማኝ ከደስታም በላይ ሐሴት። በወቅቱ „ኢትዮጵያዊነት የታላቁን የሰላም አባት የኔልሰን ማንዴላ ህይወት የታደገ ታላቅ ሚስጢር …. አነጠረ።“ በሚል አንድ መታጥፍ ቢጤ ጽፌ ዘኃበሻም ታድጎኝ ለንባብ በቅቶ ነበር አመስግናለሁም።

አባ መላ ጥሩ ተናጋሪ ነው። ንግግር ሥነ – ጥበብ ነው። ጸጋም ነው። ተሰጥዖ። ሥጦታውም የማዳህኒዓለም ቢሆንም በክህሎት፤ በስልጠና ሥነ ደንቦችን በማጥናት ማሳደግ የሚቻል ጉልበታም ፊኖሚና ነው። ንግግር አድማጭን ወደ ተፈለገው አቅጣጫ የሚመራ የተዋጣለት መሪ ነው። ጥሩ ንግግር … በእጅ ያለ ወርቅ ነው። ጥሩ ንግግር ገዢ መሬት ላይ አለ አጥቂ ሰራዊት ነው። ይህን ለመልካም ተግባር ካዋሉት ውስጥ ዕውቅ የዓለማችን ሰዎች ውስጥ ኪንግ ማርቲን ሉተር፤ ፕሬዚዳንት አብርኃም ሊንከን፤ ማህተመ ጋንዲን ትናት፤ ዛሬ ደግሞ ፓኪስታናዊዋ የ16 ዓመቷ ታዳጊ ወጣት የታለቢና ጥቃት ሰለባ ሆና ከሞት የተረፈቸው ማላለ ለምሳሌነት ብናነሳ … ለጥፋት ደግሞ ጀርማናዊ አዶልፍ ሂትለር – ለናኒዝም፤ ሞሶሎኒ – ለፋሺዝም ተግባራዊነት ህዝብን በምዕላት ያንቀሳቀሱበት ታላቅ መሳሪያ ነው።

እኔ የአባ መላን የንግግር ጸጋ የማዬው ከዚህ አንጻር ነው። አባ መላ የተዋጣለት ተናጋሪነቱ ብቻ ሳይሆን የድምጹ ቃና ሳቢነት፤ እንዲሁም ሳቁ እራሱ ውበት አለው። ጥሩ ተናጋሪ ልብን ገዝቶ፤ ግርቶ ወደ ተፈለገው አቅጣጫ የመምራት ሞገዱ ሆነ አቅሙ መጠነ ሰፊ ነው። የአባ መላ የመታገስ አቅም፤ ኦዲዬንስ እንደ ባህሪው ለማስተናገድ ያለው ስልት፤ ከተረብ ጋር ይመቻል። የነፃነት ጉዞም ምልክት ነው – ለእኔ። የተመቸንና ያልተመቸን ኃሳብ አንዱ ለሌላው ቢጎረብጠውም አለስልሶ እውነትን አሸናፊ የማደረግ ኃይሉ ዓምድ ነው። አንድ ጊዜ እንደ ዋዛ „ከአባይ በፊት ሽሮ ይገደብ“ ሲል አዳምጥኩት። ይህ ቅኔ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ ወፈር ያለ ሽሮ ሰርቶ ለመብላት እንኳን ያልተቻለበት የተፋቀ ዘመን ስለመሆኑ እዬሳቀ ግን መንፈስን ሰርስሮ የገባ ሥነ – ቃላዊ አገላላጽ ነበር። ይህ አገላለጽ ህሊናን በአግባቡ የማዘጋጀት ስበቱ እጅግ ጠንካራና ረቂቅ ነው።

የታላቁ ሚስጢር ባላቤትና ባለውለታ የሆኑትን ትክሊላችን ካፒቴን ሻንበል ጉታ ዲንቃን ህይወት ከኢትዮጵያዊነት ሚስጢራዊ ተፈጥሮ ጋራ ከፍ ብሎ ዕውቅና እንዲያገኝ የነበረው ፍላጎትና ጉጉት ውስጡን ገልጦ ያሳይ ነበር ንግግሩ። ያን ቀን አባ መላ ዓዋጅም ዓወጆ ነበር  ከእንግዲህ አለ … “ልጅ የምትወልዱ ቤተሰቦች ልጆቻችሁን ጉታ ዲንቃ እያላችሁ ጥሩ“ አለ። የዛሬ ሳምንት ደግሞ „ ኢትዮጵያዊነት መሪ አገኘ ጉታ ዲንቃን“ አለን።

የካፒቴን ጉታ ዲንቃ ህልም ደቡብ አፍሪካ ሄዶ የምህረት፤ የትግል፤ የጽናት፤ የይበቃኛል አባት ከሆኑት ከኔልሰን ማንዴላ ቀብር ላይ መገኘት ስለነበር። የማይቻለውን ቻለ። በአራት ቀን ውስጥ ከኢትዮጵውያን የሚሰበሰበወን ገንዘብ ሳይጠብቅ የራሱን ገንዘብ የትኬት ምግዣ ልኮ። የኢሳትን ቲም፤ አርቲስት ታማኝ በዬነን፤ አቶ ነዓምን ዘለቀን በመያዝ በንዑድ ቅንነት ተግባሩን ጀመረ። በሩሙ ታዳሚዎች በመተማመን። ያው በፍቅር ስለሚያስተናግድ ለፍቅሩ የሚቻለውን ዋጋ ለመክፈል የቻሉ፣ በወቅቱ መልዕክቱን ያደመጡ፣ እንደ አቅማቸው ተባበሩት። ሀገር ውስጥም ደቡብ አፍሪካም የነበረውን ትብትቡን ቢሮክራሲ በታታሪንት ተቋቁሞ የዛሬ ሳምንት ዕለተ ቅዳሜ 14.12.2013 ዘውዳችን ሻንበል ጉታ ዲንቃ አውሮፕላን ውስጥ እንዳሉ ሲነገረን ፈነጠዝን። ዛሬ እኛነታችን፤ ማንነታችን ፈተና ላይ ወድቆ፤ ባለቤት አጥቶ ወገኖቻችን በዬተሰደደበት እያታነቁ በሚገደሉበት ወቅት አጋጣሚው የሰማይ ገድል ነበር። ሊያመልጠን አይገባም ነበር። በተባረኩ ወገኖችም አጋጣሚው እነሆ አፈራ። ቀሪው የሎቢ ተግባር ተጠናክሮ ከተሰራበት የበለጠ ትርፋማ መሆን ይቻላል። ኢትዮጵያዊነት የተከበረ ሰንደቅ ስለመሆኑ የዓለም ሚዲያ እንደመሰክር ማደረግ ይቻላል።

የተከበሩ ሻንበል ጉታ ዲንቃ ደቡብ አፍሪካ ከደረሱበት እስከ ተመለሱበት ድረስም የደቡብ አፍሪካ ጥቁር አንባሶች የኢትዮጵያዊነት ዓርማ ናቸውና አደራቸውን በተግባር አቅልመው ኢትዮጵያዊነትን ከፍ አደረጉልን። እግዚአብሄር ይስጣችሁ። በ2013 የአፍሪካ የእግር ኳስ ዋንጫ ወቅት ኢሮ ስፖርት ደቡብ አፍሪካ ላይ ስለሚገኙት ኢትዮጵውያን ልክ እንደ ሀገሩ ዜጋ ነበር በክብር ሲገልጻቸው የነበረው። ያኮራሉና! ኢሮ ስፖርት ስለ ኢትዮጵውያን የዘገበው እጅግ ነፍስን የሚገዛ ነበረ። ዛሬም ታሪካዊ ኃላፊነተቸውን በብቃት ተወጡ ሁነኛዎቻችን መካታና መመኪያዎቻችን ናቸው። ጠቅላላ ቃለ ምልልሱ፤ ምን እንደ ተሳማቸው ምስጋናው ሁሉም አለ …. ያልነባራችሁ ሲቢሊቲ ሩም እንሆ …. የ22.12.2013 የካፒቴን ሻንበል ጉታ ዲንቃ ቃለ ምልልስ በሲብሊቲ ሩም … „ፓን አፍሪካኒሰት የዘመኑ“ ይላቸዋል አባ መላ። በ አስር እጣታችን እንፈርማለን …. ጧፋችን ….

ማጠቃለያ …. አረሙ ወያኔ የምታሴሩትን የልዩነት ትብትብ ኢትዮጵውያን ፈተን አንድ ቀን ኢትዮጵያ ወደ ነበረችበት ክብር ትመለሳላች። በዚህ መልክ በትግባር፣ በመደማመጥ፣ ከተጋን አትጠራጠሩ የቀን ጉዳይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አሁንም የታሪካችን ሚስጢር አካል የሆኑት የጄ/ታደሰ ብሩ ልጆች ቤተሰቦች ይኖራሉ። እነሱን አፈለልጎ የተገባውን ክብር መስጠት የተገባ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የማዲባ የቅርብ ጓደኛቸውና መምህራቸው የነበሩት ዛሬ ህመም ላይ ያሉት የኮ/ ፈቃደንም ጉዳይ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ራዲዮ ያደረገው ቃለ ምልልስ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎ ትውልዱ ታሪኩን በአግባቡ ይዘግበው ዘንድ ዝቅ ብዬ አሳስባለሁ። አክብሮታችን ፍለጋችን እኩል በተግባር ደምቆ መከናወን አለበት። ኢትዮጵያዊነትም ወደ ዘውዱ።

ዛሬ ደግሞ አባ መላ አዲስ ሃሳብ ይዞ መጥቷል ከትንሹ እንጀምር እያለን ነው። ወያኔ ለእርቅ ጠርቶ  እስርና ለበሸታ የዳረጋቸውን ጽኑ አቶ አበራ የማናአብ ከቤተሰባቸው ጋር አሜሪካን ሀገር የማቀላቀሉ የሎቢ ተግባር አብረን እንታደም ዘንድ አሳስቦናል። ወያኔ የሚጠላውን ስንፈጽም ወያኔን በቁሙ መግደል እንችላለን። ለነጻነት የአንድ ወጣት ዕድሜን ያሳለፉ፤ በሳንባ በሽታ የተጠቁ አካላችነን በአክብሮት ማገዝ በመርዳት ከጎን ተሰልፎ የድርሻን መወጣት ይገባል – ከትህትና ጋር። ቃለ ምልልሱ፤ ምን እንደ ተሳማቸው ምስጋናው ሁሉም አለ …. ያልነባራችሁ ሲቢሊቲ ሩም እንሆ …. የ22.12.2013 የካፒቴን ሻንበል ጉታ ዲንቃ ቃለ ምልልስ በሲብሊቲ ሩም … „ፓን አፍሪካኒሰት የዘመኑ“ ይላቸዋል አባ መላ። በ አስር እጣታችን እንፈርማለን …. ጧፋችን …. ልብል እኔ ደግሞ

 

ኢትዮጵያ ለዘለ ዓለም ትኑር!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ

 

የአማራ ዴ/ኃ/ን ለሱዳን ተላልፎ በተሰጠው መሬት ዙሪያ “ዳሩ ካልተጠበቀ መሃሉ ዳር ይሆናል” የሚል መግለጫ አወጣ

$
0
0

Amara Democratic Force
ጋዜጣዊ መግለጫ 

“ዳሩ ካልተጠበቀ መሃሉ ዳር ይሆናል”!!

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የተሰጠ መግለጫ

ታህሣሥ 10 ቀን 2006 ዓ.ም.

በዓለም ላይ እስከአሁን የተከሰቱ መንግሥታት (ቅኝ ገዥዎችን ጨምሮ) ጨቋኝ (አምባገነን)፣ በዝበዥ፣ ዘራፊ (በሙስና የተዘፈቀ) … ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። አሁን ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ እንዳለው የትግሬ ዘረኛ ቡድን የሚገዛትን ሀገርና ሕዝብ የሚጠላና ሀገሩንም ለማጥፋት 24 ሰዓት የሚሠራ መንግሥት ግን እስከ አሁን በታሪክ አልታየም። ወደፊትም ከወያኔ በስተቀር የሚገዛትን ሀገር፣ ታሪኳንና ሕዝቧን የሚጠላና ሆን ብሎ ለማጥፋትም ቀን – ተሌት የሚጥር መንግሥት በምድር ላይ ይከሰታል ብለን አናምንም። ይህ የትግሬ ዘረኛ ቡድን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን መጥላቱን የሚያሳይ የድርጊቱን ሥንክሣር መዘርዘር ቢቻልም፣ በአሁኑ ሰዓት የተከሰቱ ሁለት ታላላቅ ብሔራዊ ጉዳዮችን ብቻ እንኳ ብናይ ዘረኛው ቡድን ምን ያህል የሚገዛትን ሀገርና ሕዝቧን አምርሮ እንደሚጠላ ፍንትው አድርገው ያሳያሉ፦

  1. በሣዑዲ አረቢያ የወገኖቻችን ደም  በግፍ ሲፈስስ፣ እህቶቻችን ያለርህራሄ በቡድን ሲደፈሩ፣ በ21ኛው ክ/ዘመን በሰው ልጅ ላይ የፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ ኢሰብአዊ ግፍ ሲፈፀምባቸውና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ላይ ብሔራዊ ውርደት ሲደርስ የትግሬው ዘረኛ ቡድን “የሣዑዲ አረቢያ መንግሥት በሀገሩ ላይ ይህንን ማድረግ መብቱ ነው” ነበር ያለው።
  2. በዚህ ሰቅጣጭ ሐዘን ውስጥ ተውጠንና በስቃይ ላይ ያሉ ወገኖቻችንን ለመርዳት ላይ ታች በምንልበት ጊዜ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳው የትግሬው ዘረኛ ቡድን አባቶቻችን ደማቸውን በማፍሰስና አጥንታቸውን በመከስከስ ጠብቀው ያቆዩትን 1600 ኪ/ሜ ርዝመትና ከ20-60 ኪ/ሜ ወደ ኢትዮጵያ ጥልቆ የሚገባውን ከሱዳን የሚያዋስነውን ድንበራችንን በሕገወጥነት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ፈርሞ ለሱዳን አስረከበ። ምንም እንኳን በሚስጥር ሊይዘው ቢሞክርም የድንምበር ማካለሉ ከጥር ወር 2006 እስከ መስከረም 2007 ችካል በመቸከል እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) ይህንን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ የሚደረግ ሕገወጥ የድንበር ክለላ አጥብቆ መቃወምና ማውገዝ ብቻ ሳይሆን እንዳባቶቹ ደሙን አፍስሶና አጥንቱን ከስክሶ ታሪካዊ ድንበሩን ለማስከበር ቆርጦ ተነስቷል። ባንዳ የባንዳ ልጆች ከአባቶቻቸው የወረሱትን ሀገር የማጥፋትና የመሸጥ ውርስ ተግባራዊ ሲያደርጉ እኛ የአርበኛ ልጆች ነን የመንል ይህንን ደባ ዝም ብለን ብንመለከት ድንበር ላይ የተከሰከሰው የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይዎጋናል። በመሆኑም በአካባቢው ያላችሁ ታጋይ ኃይሎችና የገፈቱ ቀማሽ የሆንከው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በርስቱና በሚስቱ ያልሞተ ወንድ ልጅ ወንድ አይደለምና ወንድ ልጅ ነኝ ያልክ ሁሉ ተባበረን፣ ከዚህ በላይ የሞት ሞት የለምና።

አዴኃን ይህንን ድርጊት አምርሮ የሚቃወመው እንዲያው በጭፍኑ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ሕጋዊ የሆነ ድንበር አይኑራት ብሎ አይደለም። የድንበር ስምምነቱ ኢትዮጵያን ጎድቶ ሱዳንን የሚጠቅም፣ ከ110 ዓመታት በፊት የፈረሰና ሕጋዊ ያልሆነ ውልን መሠረት ያደረገ፣ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን ጥናትና ውትወታ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ  ሕዝብ ጀርባ በደባና በሕገወጥነት የተፈረመ ውል በመሆኑ እንጅ።

በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረገው የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴና ከዚያ በፊትም ጥናት ያደረጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሑራን እንደሚሉን ከሆነ ይህ ዛሬ የትግሬው ዘረኛ ቡድን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ለተፈራረመው ውል ዋቢ የሚያደርገው ውል በዳግማዊ አፄ ምኒልክና በጊዜው የሱዳን ቅኝ ገዥ በነበረችው እንግሊዝ መካከል የተፈረመው እ.አ.አ 1902 ነበር። አፄ ምኒልክ ይህንን ውል የፈረሙት በኃይል ተገድደውና በይዞታቸው ሥር የነበሩ ብዙ መሬቶችን ለቀው ነበር። በዓመቱ በ1903 የእንግሊዙ የጦር መኮንን ሻለቃ ጉዊን ድንበሩን ከስምምነቱ ውጭ ብቻውን ሄዶ ከመከለሉም በላይ አፄ ምኒልክ ተገድደውም ቢሆን የፈረሙትን ካርታ አዛብቶ ኢትዮጵያን እየጎዳ ችካል ቸከለ። ይህንንም ሻለቃ ጉዊን ከተሰጠው ሥልጣን በላይ ሄዶ መሥመሩን በማዛባት ከኢትዮጵያ መሬት እንደወሰደ በራሱ ሪፖረት ላይ በግልፅ ሳይደብቅ ጽፏል። እንግሊዞችም በ1902 የተፈረመበትን ካርታ ጥለው በችካሉ መሠረት በ1903 አዲስ ካርታ በመሥራት እነርሱ ከፈረሙበት በኋላ አፄ ምኒልክን ለማስፈረም ቢሞክሩም ከስምምነት ውጭ ለተቸከለው የጉዊን ክለላ ዕውቅና በመንፈግ ሳይፈርሙበት ቀርተዋል። የትግሬው ዘረኛ ቡድን አፄ ምኒልክ፣ አፄ ኃይለሥላሴና ደርግ የጉዊንን መሥመር ተቀብለዋል እያለ የሚያላዝነው ይህንን የመሰለውን ሐቅ በመካድ ነው። ይህንንም ዓይን ያወጣ የወያኔን ቅጥፈት አዴኃን ብቻ ሳይሆን ሰኞ 19 ኖቬምበር 2007 (እ.አ.አ.) ሱዳን ትሪቢዩን የተባለ ጋዜጣም “ድንበሩን አስመልክቶ የሱዳን መንግሥት ከቀደምት የኢትዮጵያ መንግሥታት ጋር የነበረው ግንኙነት ቀና አልነበረም። በድንበሩ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የመጀመሪያው ፈቃደኛ መንግሥት ገዥው የኢሕአዴግ መንግሥት ብቻ ነው” በማለት መሥክሮበታል።

ጥሪ፦     

ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራትም ጭምር፣ ይህ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ በሀገር ከሃዲው የትግሬ ዘረኛ ቡድ ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከወለጋና ከኢሊባቡር ክፍለ ሀገሮች ተቆርሶ ለሱዳን የሚሰጠው ለም መሬት የክፍለ ሀገራት ተወላጆቹ መሬት ብቻ አይደለም፤ የአንተም የኢትዮጵያዊው መሬት እንጅ። በመሆኑም አዴኃን ይህንን በባንዳ ልጆች የተጋረጥብንን ኢትዮጵያን የማጥፋት ታላቅ አደጋ ለመቀልበስ ስንል ያሉንን ጥቃቅን ልዩነቶች ወደጎን በመተው፣ ከምንጊዜውም በላይ እጅ ለእጅ ተያይዘንና ያለንን አቅም ሁሉ አስተባብረን በመነሳት የዜግነት ግዴታችን እንድንወጣ አስቸኳይ ጥሪውን ያስተላልፋል። “ዳሩ ክልተጠበቀ፣ መሀሉ ዳር ይሆናል” እንደሚባለው የትግሬውን ዘረኛ ቡድን በተባበረ ክንድ ዛሬውኑ ካላስወገድነው በስተቀር እናት ሀገራችን ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዕኩይ ተልዕኮው የድንበር መሬቶችን እየቆረሰ ለጎረቤት ሀገራት በመስጠት ብቻ ያቆማል ብሎ ማሰብ ፍፁም የዋህነት ነው።

ለመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ኃይልና የኢሕአዴግ ደጋፊዎች፣ እናንተ የምትደግፉት ሀገር አጥፊው የትግሬ ዘረኛ ቡድን አባቶቻችን ደረታቸውን ለጦር፣ እግራቸውን ለጠጠር ሰጥተው በደማቸው ያቆዩአትን ይህችን ጥንታዊትና ታሪካዊት ሀገራችንን እያጠፋት እንደሆነ ለእናነተ የተሠወረ አይደለም። ይህንን ሀገር የማጥፋት ወንጀል የሚፈፅመው ደግሞ እናንተን በመሣሪያነት በመጠቀም ስለሆነ ይህንን ተገንዝባችሁ አሁኑኑ ከሕዝባችንና አደጋውን ለመቀልበስ ከሚታገሉ ኃይሎች ጎን በመቆም ሀገራችሁን እንድትታደጉ ስናሳስብ፣ ጥሪያችን ችላ በማለት ለሀገር አጥፊው ቡድን ተባባሪነታችሁን ከቀጠላችሁበት ግን ታሪክና ሕዝብ ይቅር እንደማይላችሁ በጥብቅ ልናስጠነቅቃችሁ እንወዳለን።

ለብአዴን አባላት፦ “እሣት አመድ ይወልዳል” እንደተባለው ካልሆነ በስተቀር፣ አባቶቻችሁ ኢትዮጵያን ከሚያጠፋ ጠላት ጋር ተባብረው እናት ሀገራቸውን አላጠፉም፤ ይልቁንም ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው የታፈረችና አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለእናንተ አስረከቧችሁ እንጅ። እናንተ ግን የጀግኖች አባቶቻችሁ የባሕሪ ልጆች መሆን አቅቷችሁና አደራቸውን በልታችሁ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና አማራን ለማጥፋት ቆርጦ ለተነሳው የትግሬ ዘረኛ ቡድን አሽከር ሆናችሁ እናት ሀገራችሁንና ወገናችሁን እያጠፋችሁ ነው። “ለእንጀራየ፣ ለልጆቼና ለቤተሰቦቼ ስል ወይም ተገድጀ ነው ይህንን የማደርገው” የሚለው ውሃ የማይቋጥር ምክንያት እንደማያዋጣችሁ አውቃችሁ የጋራ ሀገራችንንና ወገናችንን ለመታደግ አብራችሁት እንደትቆሙ አዴኃን ከልብ የመነጨ የሀገር አድን ጥሪ ያቀርብላችኋል።

ወንድም ለሆነው የሱዳን ሕዝብ፦ የኢትዮጵያና የሱዳን ሕዝብ ለብዙ ሺህ ዘመናት ከአንድ ወንዝ ከተቀዳ ውሃ እየጠጣ፣ በመከባበር ላይ በተመሠረተና በመልካም ጉርብትና አንዱ ለሌላው የችግር ጊዜ ደራሽ ሆኖ የኖረ ወንድማማች ሕዝብ ነው። ነገር ግን ዛሬ የትግሬው ዘረኛ ቡድን በሀገር ውስጥ የሚገኙ ነገዶችን እርስ በእርሳቸው ከማናከስ አልፎ የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይም የአማራውን ነገድ ወንድም ከሆነው የሱዳን ሕዝብም ለማናከስ ቆርጦ የተነሳ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕውቅና ውጭ የተፈረመን የድንበር ስምምነት እንዳይቀበል በጥብቅ እናሳስባለን።

በመጨረሻም የዓለም ምንግሥታትና ዓለም – አቀፍ ሠላም ወዳድ ሕብረተሰብም የወያኔ ዘረኛ ቡድን ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ፈፅሞ እንደማይወክልና አሁን ከሱዳን መንግሥት ጋር በድብቅ የተፈራረመውንም የድንበር ስምምነት ንቅናቄያችን አዴኃን እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማያውቁት ተገንዝበው ስምምነቱ አሁንም ይሁን ወደፊት በሁለቱ ሀገራት ሕዝብ መካከል የሚፈጠረውን ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለስምምነቱ ዕውቅና እንዳይሰጡና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ይህንን ሤራ እንዲቃወሙ አዴኃን ጥሪውን ያስተላልፋል።

በደም የተረከብናትን ሀገር በደም እንጠብቃታለን!!

 

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ

የኢህአዴግ አዲሱ አሰላለፍ ፪ –ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

samora and azeb

በድህረ-መለስ ኢትዮጵያ የፖለቲካው ሥልጣን በስርዓቱ ልሂቃን መካከል ከሚደረገው የኃይል መተናነቅ አንጻር፣ ዛሬም ከመፈራረቅ ጣጣው የተላቀቀ የማይመስልባቸው ምልክቶች መታየታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአራት ወር በፊት በዚህ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ባቀረብኩት ፅሁፍ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ክፍፍል የትኛው ቡድን የበለጠ ጉልበት አግኝቶ በአሸናፊነት መውጣት እንደቻለ ከገለፅኩ በኋላ ፅሁፉን የቋጨሁት እንዲህ በማለት ነበር፡- ‹‹የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈልግም፡፡››

እነሆ በዚህ ፅሁፍ ደግሞ በቅርቡ በተጨባጭ የታዩትን አዳዲስ ኩነቶች እና ይህንኑ ተከትለው ሊመጡ ይችላሉ ብዬ የምገምታቸውን ‹የቢሆን ዕድሎች› (Scenarios) ለማየት እሞክራለሁ፡፡
ሰላም የራቀው-ኢህአዴግ
በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ዛሬም ድረስ ሙሉ በሙሉ የተረጋጋ ፖለቲካ አልሰፈነም፤ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ፣ ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችን ጠቅልሎ ይዞ በነበረው በቀድሞ ሊቀ-መንበሩ ህልፈት ሳቢያ የተፈጠረው የአመራር ክፍተት እና እርሱን ሊተካ የሚችል መሪ ማግኘት ባለመቻሉ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎችም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ከሕግ ይልቅ የጠመንጃ ኃይልና የግለሰብ አምባገነናዊነት በገነነበት ሀገር ‹የማይገመቱ ክስተቶች› (Unpredictable Event) ማምጣታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡

የሆነው ሆኖ በዚህ አጀንዳ ለመመልከት የምሞክረው ጉዳይ፣ በአሁኑ ጊዜ ሀገር እየመራ ያለው ኃይል ለሁለት የተከፈለ ቢሆንም፣ በአንፃራዊነት በጥምር የሚሰራ መሆኑን በማስረገጥ ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቡድኖች የጉልበት ምንጭም የታጠቀውን ኃይል በመቆጣጠር እና የፖለቲካውን ሥልጣን በመያዝ ላይ የተመሰረተ ነው፤ ይኸውም ሠራዊቱ እና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሙሉ በሙሉ በህወሓት ሰዎች ሲንቀሳቀሱ፣ ፖለቲካውን ደግሞ የብአዴን መሪዎች፣ ከተወሰኑ የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት ጋር ተባብረው መያዛቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች መኖራቸው ነው፡፡

የህወሓት ኃይል

ህወሓት የቀድሞው ፍፁማዊ የበላይነቱን ለመመለስ ዋና ችግር የሆነበት በውስጡ ለተፈጠረው መከፋፈል እስካሁን መፍትሄው ተለይቶ አለመታወቁ ነው፤ ከዚህ ቀደም በዚሁ መፅሄት፣ አንዱ ኃይል የተሻለ ጉልበት በማግኘቱ ሌላኛውን (እነአዜብ መስፍንን ጨምሮ አባይ ወልዱና ቴዎድሮስ ሀጎስን የመሳሰሉ ከፍተኛ ካድሬዎች የተሰባሰቡበትን) በመብለጥ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እንቅስቃሴያቸውን መገደቡ ተሳክቶለት እንደነበረ ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ ይህ ክፍፍል ምንም እንኳ እንደ 1993ቱ ከፓርቲ እስከ ማስወጣት የሚደርስ አለመሆኑ ቢታወቅም፣ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ጌታቸው አሰፋ የተሰለፉበት ቡድን ተፅእኖ ፈጣሪ ሆኖ መውጣት ችሏል፤ ይህም ሆኖ ውስጥ ውስጡን የሚገመደው ተንኮልም ሆነ ሽኩቻ ገና መቋጫ አለማግኘቱ ግልፅ ነው፡፡
በዚህ ፅሁፍ ጠመንጃ የታጠቀውን ክፍል ‹የህወሓት ኃይል› እያልኩ የምገልፀበት ዓብይ ምክንያት፣ በጄነራል ሳሞራ የኑስ ኤታ ማዦር ሹምነት የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት እና በማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጌታቸው አሰፋ ስር ያለው የደህንነት ኃይል ለሚደግፉት ቡድን መጠናከር እያበረከቱት ያለውን አስተዋፅኦ ከግምት በመክተት ነው፡፡ ሁለቱም ሰዎች ለመለስ ፍፁም ታማኝ የነበሩ ቢሆንም፣ ከህልፈቱ በኋላ እንደእርሱ ተጭኖ ሊቆጣጠራቸው የሚችል ጉልበታም ህወሓትን ጨምሮ በሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲ ውስጥ አለመኖሩ፣ በፖለቲካው ‹ቼዝ› የ‹ዘመነ መሳፍንቱ›ን ሚካኤል ስሁል አይነት ሚና እንዲጫወቱ አስችሏቸዋል፤ ሁለቱም ከስራቸው የነበሩትንና ‹ስልጣን ሊጋፉ ይችላሉ› ብለው የጠረጠሯቸውን ባልደረቦቻቸውን አስቀድሞ ገለል ማድረጉ ከሞላ ጎደል የተሳካላቸው ይመስለኛል፡፡
በተለይም ጌታቸው አሰፋ ከራሱ ወንበር አልፎ ከእነአዜብ መስፍንና አባይ ወልዱ ጋር በመተባበር አንድ ቀን በጠቅላላው የመንግስት የሥልጣን እርከን ላይ ‹ናቡቴ ሊሆን ይችላል› የሚል ስጋት ያሳደረበትን እና ‹መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድመው በእርሱ ቦታ ሊተካው ነበር› እየተባለ የሚነገርለትን የመረጃ ኃላፊ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና የሚወነጀልበትን መንገድ አመቻችቶ ለእስር ባይዳርገው ኖሮ ‹‹ለቁርስ ያሰቡንን…›› አይነት ታሪክ ራሱን መድገሙ አይቀሬ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡
ጄነራል ሳሞራ የኑስ በበኩሉ ተቀናቃኙ አድርጎ ይመለከታቸው የነበረው ሶስቱ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ ወልደስላሴ ‹ፍንቀላ መሳይ ነገር ሊሞክሩ ይችላሉ› ተብለው አይደለም፡፡ የእነርሱ የመጀመሪያው ችግር ከወታደራዊ ዲሲፕሊን በማፈንገጥ አለቃቸውን አለማክበራቸው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሳሞራ ‹በየትኛውም ምክንያት ከኃላፊነቴ ብነሳ የቆየ ፋይል አገላብጠው አደጋ ላይ ሊጥሉኝ ይችላሉ› በሚል ስለሚጠረጥራቸው ነው፡፡ እነዚህ መኮንኖች የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል ሰዓረ መኮንን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መልካም ግንኙነታቸው እንደቀድሞው እንዳልሆነ የሚነገረው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል አበባው ታደሰ እና የአየር ኃይሉ አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሞላ ኃይለማርያም ናቸው፡፡ እናም ሰዓረ እና አበባው በቀጥታ ሠራዊት ከሚያዙበት ቦታ ተነስተው በመከላከያ ሚኒስትር ውስጥ በቢሮ ስራ ላይ ሲመደቡ፣ ሞላም ከነበረበት ኃላፊነት አኳያ ብዙም ይመጥነዋል የማይባል የቢሮ ስራ ተሰጥቶታል፤ በእርሱም ቦታ ሜጀር ጄነራል አደም መሀመድ ተተክቷል፡፡ የሳሞራ እና የሞላ ልዩነት በመለስ ዘመንም በአደባባይ የሚታወቅ እንደነበረ ሰምቻለሁ፡፡
Samora (2)
ለጉዳዩ ቅርብ ከሆነ የመረጃ ምንጬ እንዳረጋገጥኩት የአስተዳደር ዘይቤውን በማኪያቬሊያዊ አስተሳሰብ (ከፋፍለህ ግዛ) የሚያሳልጠው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ለሞላ ትዕዛዝ የሚሰጠውም ሆነ ማንኛውንም ጉዳይ በተመለከተ የሚያነጋግረው የዕዝ ተዋረዱን ጠብቆ በኤታ ማዦሩ በኩል ሳይሆን፣ በቀጥታ በመገናኘት መሆኑ፣ አየር ኃይሉን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገነጠለ አስመስሎት ነበር፤ ይህ ሁኔታም በሁለቱ መኮንኖች መካከል ያለው ግንኙነት የሥልጣን ተዋረድን የጠበቀ እንዳይሆን በማሰናከሉ በጄነራሉ ላይ ደፍሮ የማይናገረው ቅሬታ ሊያሳድርበት ችሏል፤ ከመለስ ህልፈት በኋላም ሳሞራ ሂደቱን ለማስተካከል መሞከሩ፣ በየግምገማው ላይ እስከ መዘላለፍ አድርሷቸው ነበር (በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ እንደ ጦር ኃይሎች አዛዥነቱ፣ ከጄነራሎቹ ጋር መደበኛ /Official/ በሆነ መንገድ ትውውቅ አላደረገም፤ እነዚህ ሶስት ጄነራሎችም ለዚህ አይነቱ የአሰራር መፋለስ ጥፋተኛ የሚያደርጉት አለቃቸውን ሳሞራ የኑስን ነው፤ ከምንጮቼ እንደሰማሁት ከሆነም ከወራት በፊት ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኘበት ‹ጎልፍ ክለብ› በሚባለው የጄነራሎቹ መዝናኛ በተዘጋጀ ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ላይ ሳሞራ አንድ ጠረጴዛ ከበው ወደ
ተቀመጡት እነዚህ ጄነራሎች ጋ ሄዶ ‹ኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ላስተዋውቃችሁ› ማለቱን እና እነርሱም በጥያቄው ተበሳጭተው ቢሮ ያላቸው መሆኑን እና ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ መተዋወቅ እንደነበረባቸው በኃይለ ቃል መመለሳቸውን ነው)

የሳሞራ የኑስ እና ሰዓረ መኮንን መነቋቆር ከትግሉ ዘመን ጀምሮ የመጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ሳሞራ ከማንም በላይ የሚፎካከረውም ሆነ መበለጥ የማይፈልገው በሟቹ ጄነራል ኃየሎም አርአያ እንደ ነበር የቀድሞ ጓዶቻቸው ያስታውሳሉ፤ ይህ ሁኔታ ዛሬም ድረስ በስራ ላይ ያሉ መኮንኖችን ‹የሳሞራ› ወይም ‹የኃየሎም ተከታይ› በማለት መከፋፈሉ በጓዶቻቸው እና በፓርቲው መሪዎች አካባቢ የሚታወቅ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለማዕረግ እድገት የተለየ የድጋፍ አስተያየት የሚያገኙት በዛን ዘመን ‹የሳሞራ ተከታይ› የሚባሉት እየተመረጡ እንደነበረ በወሬ ደረጃ ይናፈሳል (በነገራችን ላይ ጄነራል ሳሞራ ከጤንነት ጋር በተያያዘ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጡረታ ይሰናበታል በተባለበት ጉዳይ ላይ እያንገራገረ እንደሆነ ከመከላከያ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፤ እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ ‹ለእኔ በጎ አመለካከት የላቸውም› በሚል የሚጠራጠራቸው ጄነራሎች በሥራ ላይ እያሉ የእሱ ጡረታ መውጣት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ያደሩ የሙስና ካርዶች የሚመዘዙበትን ዕድል ያሰፋዋል የሚል ነው፤ በተለይም በግዙፍ የቢዝነስ ሥራዎች ላይ በታላቅ ተፎካካሪነት እየተሳተፈ የሚገኘው ‹መቴክ› ምንም እንኳ ማረጋገጫዎች ባይቀርቡበትም በመከላከያ ሥር ከነበረበት ዘመን እስከ 2002 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ከግዥዎች ጋር ተያይዘው የሚነሱ በርካታ የሙስና ሁኔታዎች በመኖራቸው ነው፡፡
መቴክ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ በአዋጅ የልማት ድርጅት እንዲሆን ቢደረግም፣ ዛሬም ዳይሬክተሩ የሠራዊቱ አባል ብርጋዴር ጄነራል ክንፈ ሲሆን፣ መከላከያ ደሞዝ የሚከፍላቸው ጥቂት የማይባሉ ሠራተኞችንም እንዳቀፈ ይታወቃል፡፡ እናም ሳሞራ ሃሳቡ ከተሳካለት ለጥቂት ተጨማሪ ዓመታት በሥልጣኑ ላይ ሲቀጥል፣ አሊያም ‹የወንድ በር› ለማግኘት በትግሉ ዘመን የእርሱ ሰልጣኝ እንደነበረ የሚነገርለትን እና በቅርቡ ብቸኛው ከሜጀር ወደ ሌፍተናት ጄነራል ማዕረግ ያደገው ዮሀንስ ገ/መስቀል እንዲተካው መንገድ ጠረጋውን ማመቻቸቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ ይመስለኛል)
samora
ይህም ሆኖ የተኮረኮርን ያህል የምንስቀው ጄነራል ሳሞራ የኑስ በቅርቡ ለታተመው ‹‹ህብረ ብሔር›› መፅሄት ሙስና ለሠራዊቱ አደገኛ መሆኑን እንዲህ በማለት መግለፁን ስናነብ ነው፡-
‹‹ሙስና ሠራዊቱን ሊያበላሸው ይችላል፡፡ ሙስና ፀረ-ልማት ነው፤ ሠራዊቱን ሊበትነው እና ሕዝባዊ ባህሪውን እንዲያጠፋ ሊያደርገው ይችላል፤ አንድ ሠራዊት ሠራዊት ነው የሚባለው እንደ ወታደር እንደ አንድ አካል ሲያስብ እንጂ ለግሉ ሲያስብ አይደለም፡፡ …በአጠቃላይ (ሠራዊቱ) በዚህ ነው የሚፈርሰው፡፡››
መቼም ጄነራሉ ይህንን የተናገረው እራሱን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ እንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰቦች በተንጣለለ ቪላ ቤት ውስጥ፣ የተቀማጠለ ኑሮ መኖራቸውን ረስቶት አይመስለኝም፤ ‹ይህ የተንዛዛ ወጪያቸውም የሚሸፈነው ከደሞዛቸው በሚያገኙት ገቢ ነው› ብሎ ቧልት መሳይ ክርክር ሊያመጣ አይችልም፡፡ ይሁንና እታች ያለው ጭቁን የኢትዮጵያ ሠራዊት ምንም እንኳ በአለቆቹ ‹ቴክሳስ›ነት ላይ ለመቆጣት ባይደፍርም፣ እንደማንኛውም ዜጋ ለኑሮ ውድነትና አስከፊ ድህነት የተጋለጠ መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡
የሆነው ሆኖ ተሰሚነታቸው እየተቀዛቀዘ የመጣው አቦይ ስብሃት ነጋ ከወራት በፊት ለ‹‹ውራይና›› መፅሔት ‹‹ህወሓት ትንሳኤ ያስፈልገዋል›› በማለት የሰጡትን ምክር ተከትሎ፣ ጄነራል ሳሞራ እና አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ከድርጅቱ ምክትል ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ጋር በመተባበር ህወሓትን ለማጠናከር እና በፖለቲካ ውስጥ የነበረውን የአንበሳውን ድርሻ ለማስከበር (ጉዳዩን ከለጠጥነው ደግሞ ‹ለማስመለስ›) እየሰሩ እንደሆነ ይነገራል (በነገራችን ላይ የሳሞራና ጌታቸው ተፅእኖ መጨመሩን ለመረዳት፣ መከላከያ ‹አገራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ለመከላከል› በሚል ‹እጅግ ጥብቅ ሚስጢር ብሎ የሰየማቸውን የሰው ኃይል ፕሮፋይል፣ የሒሳብ መዝገቦችና ሰነዶች እና የክፍያ ማስረጃዎች ለማንም አካል እንዳይገለፅ› የሚያስችለውን ስልጣን፣ ደህንነቱ ደግሞ በስራ ላይ የሚፈፅማቸው ማንኛውም ጉዳዮች ወደፊት በህግ እንዳይጠይቅ እስከ መከላከል የሚደርሰውን አዲስ የተዘጋጁትን አዋጆች ማንበቡ በቂ ነው፡፡ በርግጥ እነዚህ ባለሥልጣናት እንዲህ ባለ ተመሳሳይ መንገድ እንዲጓዙ ያስተሳሰራቸው አንዱ ጉዳይ ‹ህወሓት ተዳከመ፣ ተሸነፈ፣ አበቃለት…› የሚለው የካድሬውና ደጋፊው ቁጭት እንጂ ወትሮም መልካም ግንኙነት ኖሯቸው አይመስለኝም)

ለማንኛውም በጥቅሉ ሲታይ የህወሓት ትልቁ ችግር ተብሎ በአመራር አባላቱ የሚጠቀሰው ‹በዚህ ወቅት ወደፊት መምጣት የሚችሉ ጠንካራ ቴክኖክራቶችን አለማፍራቱ፣ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግለትን የታጠቀውን ኃይል ተጠቅሞ የፖለቲካ ልዩነቱን ጨፍልቆ በአሸናፊነት ይዞት መውጣት የሚችል መሪ እንዳይኖረው አደረገ› የሚል ነው፡፡ በርካታ የላይኛ እና የታችኛው ካድሬዎችም ‹ለእንዲህ አይነቱ ክፉ ጊዜ ድርጅቱ የሚያስፈልገው፣ በትግሉ ዘመን ልምድ ያካበተ ታጋይ ብቻ ነው› የሚል አቋም እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ስርዓቱ ከሚያራምደው ርዕዮተ-ዓለም ጋር ጠንካራ ትውውቅ ያሌለውን እና የትግሉን ዘመን በአሜሪካን ሀገር በማሳለፉ ‹የምዕራባውያን ድጋፍ አለው› ለሚባለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚሰጡት ዝቅተኛ አመለካከት መግፍኤም ይኸው ይመስለኛል፡፡
ለነገሩ እርሱም ቢሆን በጠንካራ ድርጅታዊ ዲሲፕሊን ካለመታነፁ እና መሰል ጉዳዮች ጋር በሚያያዙ ምክንያቶች ለትንፋሽ ጊዜ የማይሰጠውን የድርጅት ሊቀ-መንበርነትንም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የሚወራውን ያህል ይፈልገዋል ብሎ መደምደሙ አስቸጋሪ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ከዚህ ይልቅ በተፈጥሮ ከታደለው የተግባቢነት ባህሪው አኳያ እንደ ሕዝብ ግንኙነት የመሳሰለ ብዙም የማያጨናንቅ ሥራን ይመርጣል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከሰለጠነበት ሙያ ጋር የቀጥታ ተያያዥነት ያለውን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሚመራበት ዘመን፣ ከውጭ ሀገር በርካታ የተቋረጡ ፈንዶችን እንደገና ለማስለቀቅ መቻሉ እንደ ታላቅ ስኬት የሚወራለት፤ አልፎ ተርፎም ‹ወባን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት ብርቱ ትግል አደረገ› ተብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሳይቀር እስከ መሸለም የደረሰው እዚህ መስሪያ ቤት እያለ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

ትንቅንቅ

ትንቅንቅ


በሌላ በኩል ደግሞ በፓርቲውም ሆነ በመንግስት አስተዳደር ከህወሓት ሰዎች ትልቁን ስልጣን የያዘው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከምዕራባውያን ጋር የቆየ ቀረቤታ እንዳለው ሰምቻለሁ፤ እንደሚታወሰው ደብረፅዮን ከክፍፍሉ በፊት (የደህንነት መስሪያ ቤቱ እንዲህ እንደ ዛሬው እጅግ ዘመናዊ በሆነው የቻይና ቴክኖሎጂ ሳይጥለቀለቅ) ከነበረው ከፍተኛ የሥልጣን ቦታ ላይ ተነስቶ፣ ቁልቁል ወርዶ በሁመራ በአንድ ዞን እንዲሰራ የተመደበው (ሁላችንም ስንገምት እንደነበረው) የአንጃው አባል ወይም ደጋፊ ሆኖ አይደለም፤ ይልቁንም የእነስዬ-ተወልደ ቡድን በመባል የሚታወቀው (‹አፈንጋጩ› ኃይል) ደብረፅዮንን በሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ ወኪልነት የመክሰሱ ጉዳይ የድርጅቱን በርካታ አባላት ቀልብ በመሳቡ፣ መለስ ይህንን ተከትሎ ከሚመጣበት አደጋ ራሱን ለመከላከል የወሰደው እርምጃ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት እስከ 1998 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በሁመራና ራያ አካባቢዎች በዞን ደረጃ ለማገልገል ተገዷል፡፡ እናም እርሱን የምዕራቡ ዓለም ፊት-አውራሪ አሜሪካና ሸሪኮቿ ወዳጅ ነው የሚያስብለው በቀድሞ መስሪያ ቤቱ በኩል በነበረው ግንኙነት ይመስለኛል።

የፖለቲካውን መዘውር የጨበጠው ኃይል

የዚህ ቡድን አምበል እንደ ድርጅት ብአዴን ቢሆንም፣ በቋሚ ተሰላፊነት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ሙክታር ከድር እና ሬድዋን ሁሴን እንደሚገኙበት ይነገራል፤ ለብአዴን ‹በተሻለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ለመገኘቱ መደላድል ፈጥሮለታል› የሚለውን ሙግት ምክንያታዊ የሚያደርገው ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ በረከት ስምዖን፣ የኢህአዴግን የካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከል በዳይሬክተርነት የሚመራው አዲሱ ለገሰ፣ ደርቦ ይዞት የነበረውን የትምህርት ሚኒስትርነት ለሽፈራው ደሳለኝ በመልቀቅ፣ በአሁኑ ወቅት ሙሉ የስራ ጊዜውን በግንባሩ ፅ/ቤት የሚያውለው ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤው ካሳ ተክለብርሃን የያዙት ሥልጣን ያለውን የፖለቲካ አቅም መመዘኑ ይመስለኛል፡፡ በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥም ከሳሞራ አንድ እርከን ዝቅ ባለ ሥልጣን ከሌሎች ሁለት ጄነራሎች ጋር የሚገኘው አበባው ታደሰ እንደ ቀድሞው በዕዝ አዛዥነቱ (በቀጥታ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማንቀሳቀስ የሚችልበት) ላይ ቢሆን ኖሮ ጥንካሬውን የተሟላ ማድረጉ አይቀሬ እንደነበረ መገመት ይቻላል፡፡

ከዚህ ሌላ ለእነበረከት ቡድን ተጨማሪ የፖለቲካ ጉልበት እየሆናቸው ያለው የኃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ እና በአባዱላ ገመዳ አፈ-ጉባኤነት የሚመራው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው፡፡ አባዱላ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ለማቅረብም ሆነ ለመታዘዝ ፍቃደኛ ያልሆኑ አንዳንድ ባለስልጣናት፣ በውስጥ መስመር በሚተላለፍለት ‹ጥቅሻ› በምክር ቤቱ በኩል የሚመለከተው የቋሚ ኮሚቴ አባላት አስጠርቶ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚገመግምበት ስልት እየተገበረ ነው፡፡ በአናቱም ምን ጊዜም የሳምንቱን የሥራ መጨረሻ ቀን አርብን ጠብቆ የሚሰበሰበው የሚኒስትሮች ም/ቤትን ከሞላ ጎደል ይህ ቡድን እየጠቀመበት ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ሚኒስትሮቹ በሚገናኙበት አብዛኛውን ሰዓት ሳይግባቡ (በጭቅጭቅ) ማሳለፋቸው ይነገራል፤ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በአቶ መለስ ዘመን ም/ቤቱ የሚሰበሰበው የተለያዩ አጀንዳዎችን ለማቅረብ እና በቀረበው አጀንዳ ላይ ለመከራከር (ለመመካከር) ሳይሆን፣ መለስ ወስኖ የመጣበትን የሥራ ድርሻ ተቀብሎ ለመበተንና ሪፖርት ለመስማት የነበረው አሰራር፣ ዛሬ ተቀይሮ በርካታ የተነቃቁ ሚኒስትሮች የየራሳቸው ሃሳብ ተቀባይነት እንዲያገኝ (ለማንፀባረቅ) የሚታገሉበት መድረክ ወደ መሆን በመሸጋገሩ ነው፡፡ ይህም ሁናቴ ዋናውን የመንግስት ሥራ የመገምገም እና የማስፈፀም አቅምን ሳይቀር ከሚኒስትሮች ም/ቤት ወደ ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አሻግሮታል የሚያስብሉ ማሳያዎች አሉ፡፡ ይሁንና በዚህስብሰባ ላይም ቢሆን ደፈር ብሎ ከበረከት ስምዖን እና አባይ ፀሀዬ የተሻለ አዳዲስ ሃሳብ የሚያቀርብ ባለሥልጣን እንደሌለ ሰምቻለሁ (በነገራችን ላይ ምክንያቱን ባላውቅም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ› ተደርገው የተሾሙት በረከት ስምዖን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ኩማ ደመቅሳ እና ዶ/ር ካሱ ኢላላ የሥራ ቦታቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ሳይሆን መገናኛ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ላይ ነው፡፡ የተሰጣቸው ኃላፊነት ኃይለማርያምን በቅርብ እንዲያገኙ ከማስገደዱ እና በግልፅ ከሚታወቀው የአማካሪ አስፈላጊነት አኳያ ካየነው ግን ግራ የሚያጋባ ይመስለኛል)

አቶ አባይ ጸሐዬ

አቶ አባይ ጸሐዬ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ…

ኃይለማርያም ደሳለኝ ይህንን ቦታ ከያዘ በኋላ፣ ብዙዎች በስልጣኑ የማዘዝ አቅሙ ላይ አመኔታ እንደሌላቸው (አንጋፋ ታጋዮች እንደ ‹አሻንጉሊት› ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ) ደጋግመው መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ በግልባጩ ‹አፈንግጦ ለመውጣት መሞከሩ አይቀሬ ነው› የሚሉ ግምቶች ነበሩ፡፡ በርግጥ እነዚህ መላ-ምቶች ዛሬም ድረስ እልባት ባያገኙም፣ እዚህ ጋ ያልጠቀስኳቸው አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ያሳያቸው ወጣ ያሉ አቋሞቹን ሳስተውል ግን፣ አሁን ያለው አሰላለፍ (የአነበረከት እና አባዱላ ፖለቲካዊ መጠናከር) ለእርሱም የተረፈው ይመስለኛል፡፡ እንዲሁም ከቤንች ማጂ የተባረሩ አማርኛ ተናጋሪዎችን አስመልክቶ በድርጅቱ ውስጥ ባልተለመደ መልኩ ‹አጥፊዎቹ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ› ከማለት አንስቶ (በነገራችን ላይ በአማካሪ ብዛት እንዲከበብ ካደረገው ምክንያት አንዱ ጓዶቹ በዚህ ንግግሩ መበሳጨታቸው ነው) በቅርቡ ህወሓትን ለመሸምገል በተዘጋጀ መድረክ ላይ ‹ሁኔታዎች እንዲህ እየተካረሩ ከሄዱ ወደ ማሰሩ መግባታችን አይቀርም› በማለት ማስፈራራቱ እና በቴዎድሮስ አድህኖም የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ የመቆጣቱ ጉዳይ ድረስ የሚካተቱ እውነታዎች ሰውየው የራሱን መንገድ ለመከተል እየሞከረ መሆኑን ያሳያሉ ብዬ አስባለሁ፡፡

የሆነው ሆኖ እነዚህ ሁናቴዎች የፖለቲካውን ጉልበት ሙሉ በሙሉ በብአዴንና በተባባሪነት በጠቀስኳቸው የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት አካባቢ ቢያከማቻቸውም፣ በማንኛውም ሰዓት ያሻውን ማድረግ የሚችለው የታጠቀው ኃይል ደግሞ ከህወሓት ጎን እንደተሰለፈ ይገኛል፡፡ መጪውን ጊዜም አዲስ ክስተት እንድንጠብቅ ገፊ ምክንያት ይህ አይነቱ የኃይል አሰላለፍ ይመስለኛል፡፡

ምን እንጠብቅ?

ከረጅሙ የፓርቲ ፖለቲካና መንግስታዊ መንገራገጮች በኋላ፣ የሁለቱንም የኃይል መሰረቶች ጠቅልሎ በመዳፉ ሥር የከተተው መለስ ዜናዊ በሞተ ማግስት ‹የኃይል መገዳደሮች ሊከሰቱ ይችላሉ› የሚለው የብዙዎቹ ግምት ነበር፤ ከወራት በፊት አስነብቤ በነበረው ከላይ በተጠቀሰው ፅሁፍም ግምቶቹ እውን መሆን እንደ ጀመሩ ማሳያዎች ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ ራሳቸውን ያቧደኑት ኃይሎች ዋነኛ ግብ ከሥልጣን የሚነሱ ጥቅሞችና አነስተኛ የየራሳቸው ፓርቲ ፍላጎቶች የፈጠሩት በመሆኑ፣ እንደ ሟቹ ደመ-ቀዝቃዛ አምባገነን አይነት በጠንካራ መዳፍ ሥር የሚያሰባስባቸው ባለመገኘቱ በየጊዜው የኃይል መሸጋሸጎች ሊከሰቱ እንዲችሉ አድርጓቸዋል፤ አሁንም እየተስተዋለ ያለው ይኸው እውነታ ነው፡፡ በዚህ አውድ ላይ ቆመን ሊፈጠሩ የሚችሉ የቢሆን ሃሳቦችን ስናስቀምጥም በጠረጴዛው ላይ የምናገኘው ሁለት ዕድሎችን ይመስለኛል፡፡

የመጀመሪያ ሲናሪዮ የሚሆነው ከላይ የጠቀስኩት ቡድንተኝነት እንዳለ ሊቀጥል ይችላል የሚል ነው፤ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ባለኝ መረጃዎች መሰረት የፖለቲካውን መስመር የያዘው ቡድን መሪ አባላት፣ አሁን ያላቸውን መንግስታዊ ሥልጣን ጠብቀው መቆየትን መሰረታዊ መሰባሰቢያ አጀንዳ ማድረጋቸው ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሳሞራና ጌታቸው ጥምረት ህወሓትን ወደ ቀደመው ዘመኑ ለመመለስ ቢሻም፣ ሊሄድበት የሚችልበት መንገድ አደገኛ መሆኑ (ወታደራዊ ላዕላይ መዋቅሩንና የደህንነት ኃይሉን ከመያዙ አኳያ) ሁኔታዎችን ባሉበት ይዞ መቀጠልን በትርፍ-ኪሳራ ስሌት የተሻለ አማራጭ አድርጎ ይወስደዋል ብዬ አስባለሁ፡፡
ሁለተኛው የቢሆን ዕድል፣ ዳግመኛ የኃይል መሸጋሸግ ሊፈጠር መቻሉ ነው፤ ሰዎቹ ጥቅመኛ በመሆናቸው የቋንቋ ተናጋሪነት ልዩነቶቻቸውንና የኋላ የመቆራቆስ ታሪኮቻቸውን ተሻግረው፣ አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር ሌላ መልክ ያለው ስብስብ ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆናል፤ ይህ አይነቱ አዲስ የኃይል አሰላለፍም፣ ከቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በፊት በማይታወቀው ተሰዊና ሰዊ ሊጠናቀቅም ይችላል፡፡
በመጨረሻም ምንም ይፈጠር ምን፤ እኛን ሊያግባባን የሚገባው ጭብጥ፣ የትኛውም ቡድን በግንባሩ ውስጥ ቢነሳ፣ የማዕከላዊ መንግስቱን ህልውና ወደሚበታትን ሂደት መግባቱ ሊሰካለት አለመቻሉ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ መልኩ ሄዶ የሚጣሉበትን ጠረጴዛ መስበሩ ምን እንደሚያስከትል ያውቁታልና ወደዚህ ምዕራፍ እንደማይሻገሩ አምናለሁ፡፡ ይሁንና ከፓርቲው ዝግነት እና ከፖለቲከኞቹ አቋም የለሽነት አንፃር አሁንም ሆነ በቀጣይ ጊዜያት ከማንም ግምት ውጪ ያሉ ክስተቶች እንደ ደራሽ ውሃ ድንገት ሳይታሰብ ግንባሩን ሊያተራምሱት ይችላሉ ብሎ መገመቱ አግባብ ይመስለኛል፡፡

ኢትዮጵያ የጋራችን ኤርትራ የግላችን! “ከ 40 ግድብ አንድ የአሰብ ወደብ” –ከሰመረ አለሙ

$
0
0

ኤርትራዉያኖች ተበልጠዉ በኢትዮጵያ ተንደላቅቀዉ የሚኖሩበትን ሁኔታ ከተነጠቁ በሗላ እንደገና እጃቸዉ ለማስገባት በተለያየ ዘዴ ቢጠቀሙም ህዋአት እና ሻቢያ “እባብ ለባብ ይተያያል ካብ ለካብ” አይነት ሆነና ኤርትራዉያን የፈለጉትን ያህል ሳይሆንላቸዉ ቀርቶ እዚሀ ላይ ተደረሷል። የጸሀየ ግብአተ መሬት ፉከራ ከከሸፈ በሗላ ኤርትራዉያን ኢትዮጵያን ሊበትንልን ይችላል የሚሉትን ሀይል እና ዘዴ ቢበደሩም መላ ቢመቱም ቢያሰባስቡ እና ቢያሰለጥኑም፤ የኢትዮጵያ አንድነት ፍንክች ሳይል ቀርቶ እዚህ ላይ ይገኛል። የኤርትራ ምሁራን ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸዉ ተራ ወርደዉ የሚያስገምት ጽሁፍ ቢጽፉም፤ በቀይ ባህር ማተሚያ ቤት የእዉሸት ፋብሪካቸዉ ተረት መሰል የኢትዮጵያ ታሪክ ቢያሳትሙም፤ ቅጥፈት የተሞላዉ ወረቀት ቢጽፉም ድካማቸዉ ሁሉ ያለምንም ፍሬ ልፋት ብቻ ሁኖ ቀርቷል
ታድያ ለሁሉም ብልሀት አለዉ እንዲሉ ይህ ዘዴ ያለመስራቱን የተረዱ ኤርትራዉያን አቶ መለስንና ለኤርትራ ስስ ልብ ያላቸዉን የህወአት ባለስልጣኖች በመጠቀም ዛሬም ከዜጋዉ በላይ የኢትዮጵያን በረከት እየተጎናጸፉ ይገኛሉ። በተለይ ከአቦይ ስብሀት አለንላችሁ መግለጫ በሗላ ብዙ ኤርትራዉያን ባላቸዉ ንክኪ አማካኝነት በብዛት ወደ ሀገር ጎርፈዋል ከኢትዮጵያ ሳይባረሩ የቀሩትን ወገኖቻቸዉንና በዉጭ ሀገር በሚኖሩ ኤርትራዉያን አማካይነት የዉስጥ ለዉስጥ ግንኙነታቸዉን በማጠናከር ኢትዮጵያ ዉስጥ የቀድሞ ቦታቸዉን ይዘዋል።
በቅርቡ በወጣዉ ጽሁፍ ወደ 1700 የሚሆኑ የኤርትራ ተወላጆች ከኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በላይ ቅድሚያ ተሰጥቷቸዉ ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ጎርፈዋል ይህ አፊሲያላዊ ቁጥር ነዉ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ቁጥር እንዳላቸዉ እማኝነት ያላቸዉ ዜጎች በቁጭት ይገልጻሉ። እንግዲህ ልብ ይበሉ እንደ አይን ብሌን በምናያቸዉ የትምህርት ተቋማት ኢትዮጵያዊዉ ወጣት በጫት የቀን ህልም ሲያልም ትላንት ኢትዮጵያ ላይ የተኮሱ ዛሬም ለኢትዮጵያ ክብር እና ፍቅር የሌላቸዉ ኤርትራዉያን በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ሲማሩ በእጂጉ ያሳዝናል።እነሱ እንዲማሩ ሌላዉ ኢትዮጵያዊዉ ቦታዉን ለነሱ መልቀቅ አለበት ማለት ነዉ።
ethiopias-planned-renaissance-damይህ በትምህርት ዘርፍ የተገኘዉ መረጃ ነዉ። በንግድ፤እርሻ፤ፐሮፐርቲን በተመለከተ ከሀገሬዉ ነዋሪ በላይ እዛ ያሉትም ከኤርትራ፤ከአዉሮፓ እና አሚሪካ እየጎረፉም በከፍተኛ ሁኔታ በመጠቀም፤በመጠቃቀም፤ከባንክ በመበደር እና በማምታት ህገ ወጥ ጥቅም በማግኘት ላይ ይገኛሉ። ገንዘብ ማሸጋገር ዋናዉ አገር መጉጃቸዉ ነዉ በዚህም ሂደት ገንዘብ አገሩን እየለቀቀ በባህር ማዶ ባንክ እና በዉጭ ሀገር ኢንቨስትመንት ላይ ይዉላል። እነሱም በዚህ ህገ ወጥ ስራ አንድም ጠላታቸዉ ኢትዮጵያን ይጎዳሉ አንድም ትርፋቸዉን ያደልባሉ። በህጋዊ መንገድ ቀረጥ ከፍለዉ ከመስራት ይልቅ ህገወጥ የሆነዉ መንገድ ባያተርፋቸዉም ይመርጡታል።
የሚያሳዝነዉና አንጀት የሚያበግነዉ እኛዉ መሀል ስንት ቤት ሰርተሀል? ሰሞኑን ምን ልከሀል? ትንሺ ገንዘብ ሰጥተህ በትግራይ በኩል ዘመድህን አስመጣ እያሉ በድፍረት ሲያወሩ በጣም ልብ ይሰብራል። ይህች ሀገር መች ነዉ ለዜጎቿ የምትሆነዉ? መች ነዉ ዜጎቿን የምታከብረዉ? መች ነዉ ዜጋዉ ከእንደዚህ አይነት ጥቃት ድኖ ሀገሩ የእርሱ መሆኑን የሚረዳዉ ብዬ አንዳንዴ እራሴን እጠይቃለሁ። እንደዉም ደግሞ የድፍረት ድፍረት ከህዋአት ጭቆናም ነጻም የሚያወጡን እነሱ ሁነዉ ተገኝተዋል ጆሮ የማይሰማዉ የለ። የአለሙ ሚዲያ አምነስቲ ኢንትርናሽናልን ጨምሮ በወር 3000 ኤርትራዊ አገሩን ይለቃል ሲባል አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ከህዝቡ ፍቅር የተነሳ ያለ አጃቢ ነዉ የሚሄዱት ብለዉ ተቃዋሚዎቻችንን ሊያሳምኑን ይከጂላቸዋል ታዲያ ይህ ሁሉ ፍልሰት ነጻነት ፍለጋ ካልሆነ ፍለሰቱ አድቬንቸር ነዉ ማለት ነዉ ወይስ አቶ መለስ እንዳሉት ኤርትራዉያን እግር እንጂ አገር የላቸዉም የሚባለዉ አባባል እዉነት ሊሆን ነዉ?
በመሰረቱ አፍቃሪ ኢትዮጵያ ኤርትራዉያን ኢትዮጵያ ዉስጥ መኖራቸዉ ቅር የሚለኝ ሰዉ አይደለሁም ባለፈዉ ጽሁፌም እንደገለጽኩት ሀገሪቱ ዛሬ በስልጣን ላይ ቁጭ ብለዉ ከገደሏት በላይ ለሀገራቸዉ ኢትዮጵያም የሞቱ ታላላቅ የኤርትራ ተወላጆችንም ገልጫለሁ ምንም እንኳን ዛሬ በህይወት ባይኖሩም ለነሱ ያለኝ አድናቆትና ክብር ከጊዜዉ ጋር የሚደበዝዝ አይሆንም። እኔም የምኖረዉ በዉጭ ሀገር ነዉ ልዩነቱ እኔ ዛሬ የምኖርበትን ሀገር በክብር እና በፍቅር የማገለግል ነኝ በሀገሩ ተጠቃሚ ሁኜ ለሀገሩ ጥፋት የምመኝ አይደለሁም። ይህ ነዉ የእኔና የዘመኑ ኤርትራዉያን ልዩነት።
ዛሬ ሰዉ ምን ይለኛልም ቀርቶ ኤርትራዉያን በግላጭ ኢትዮጵያ የጋራችን ኤርትራ የግላችን፤ የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ የሚል ፌዝ የሚመስል ፌዝ ያልሆነ ቋንቋ በብዛት ሲጠቀሙ ይሰተዋላሉ። የሚገርመዉ ሀገር ዉስጥ ኑሮዉን ዘርግቶ የሚገኘዉ ኤርትራዊ ወይም ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ በፍልሰት የሚገባዉ ኤርትራዊ ስለ አሰብ ምን ታስባለህ ስለ ባድሜ ምን ታስባለህ ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ለማያዉቃት፤ ላልኖረባት ፤ ላልተጠቀመባት፤ ለተንገላታባት አገሩ ኤርትራ ነዉ።

ኤርትራዉያን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ሰፈር እንዴት ተንሸራተዉ እንደገቡ ግንዛቤ ቢያስፈልግ አንድም የህዋት ንክኪያቸዉን በመጠቀም፤ማንነታቸዉን በመለወጥ ሲሆን ሌላዉ ደግሞ በግንዛቤ የተጎዳዉን ኢትዮጵያዊ እየመረጡ በመጠቀም ነዉ። አንበሳዉ አለማየሁ መሰለንማ ማን ይደፍረዋል ተጠቃሚዉን ይጠቀምበታል እንጂ። እንግዲህ ወደፊት በስፋት ብመለስበትም ጀግና በጠፋበት ዘመን እንደ ቀድሞቹ ጀግኖች አያቶቹ በጠላት ሜዳ ተረማምዶ ግዳይ ጥሎ የቁርጥ ቀን ሲመጣ ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ አስመስክሮ ኢትዮጵያዉያን ሰፈር እንደገና የተሀድሶ መንፈስ ለሰጠዉ አለማየሁ መሰለ በያለንበት ዋንጫችንን እንድናነሳ በትህትና እጠይቃለሁ ገድሉም ከጊዜዉ ጋር ሊደበዝዝ አይገባም። በእዉነቱ አለማየሁ ያነን የመሰል ገድል ሲሰራ ዉቅያኖስ ጠልቆ ዉሀ ሳይነካዉ እንደወጣ ዋናተኛ ነዉ የምቆጥረዉ። ከጀብድ ስራዉ በላይ ደግሞ ንግግሩ የቀድሞዎቹ አንበሶች አያቶቹን መንፈስ የሚያንጸባርቅ ነበር። አለማየሁ በአንድ ቃለ መጠይቅ “ተስፋዬ ምንም እንኳን የሻቢያ ሰላይ ቢሆንም እኛም ከእሱ በላይ መስራት እንችላለን በሚል ጽኑ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ስራዬን ተያያዝኩት” ነበር ያለዉ። ቆፍጣናዉ አለማየሁ በእዉነት የዘመናችን በላይ ዘለቀ ቢባል ብዙም ማጋነን አይሆንም ሰዉ የሚለካዉ እንደየዘመኑ ነዉና።

ኢትዮጵያ ጥንታዊ እና ገናና አገር ነች በዚህ በረጂም ዘመኗ ረጅም ስርን ተክላለች በረጂም ዘመኗም ብዙ ጠቃሚ እዉቀቶችን፤እምነቶችን፤መረጃዎችን ለዜጎቿ እና ለአለም አበርክታለች ከዚህ እና ከሌላም ስንነሳ ኢትዮጵያ እንደሀገር ኢትዮጵያዉያንም እንደተከበረ ዜጋ በቀጣይነት መኖር አለባቸዉ። ኢትዮጵያ ትላንት በግርግር እንደተፈጠረች ሁሉ አንዳንድ ብሄረተኞች አንድም የበታችነት መንፈስ በተጠናወታቸዉ በሌላም በባእድ ሀይሎች እየተገፉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን ለመፈታተን የሚያደርጉት ጥረት ያለ ይሉኝታ ሊመከት ይገባል እላለሁ።
እንግዲህ እንዲህ ያለዉን አልፎ ሂያጅ የግርግር መንፈስ ሳይበግረዉ በእዉቀቱ ስዩም እንዳለዉ ወጣቱ ኢትዮጵያ አገሩን ከአባቶቹ በበለጠ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ማድረስ ይገባዋል እላለሁ። ዛሬ እንዲህ አደርግልሀለሁ እንዲህ ብናደርግ የምድር መንግስተ ሰማያት እንኖራለን በሚል ቀቢጸ ተስፋ የሰፈሮቻቸዉን ልጆች እያማለሉ ኢትዮጵያዊነት ላይ ወገኖችን የሚያስኮርፉ ነገ ሀሳባቸዉ ተሟልቶ እነሱ ኢትዮጵያን ቢከፋፈሉ እንደ ደሀ አጥር ሁሉም እየጣሳቸዉ ይሄዳል እንጂ እነሱም ተጠቃሚ እንደማይሆኑ በልምምጥ ሳይሆን በድፍረት ሊነገራቸዉ ይገባል። ፍቅርን የሚያዉቅ ጀግና ብቻ ነዉ እነሱ ግን ፍቅርን ልምምጥ ያደርጉታል። እነሱን ትልቅ ያደረገ እንዲህ የማኩረፍ ነጻነት ሁሉ የሰጣቸዉ ኢትዮጵያዊነት ነዉ። በአንድ ወቅት ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሐይሌ የዘረኞች እብሪት ሲበዛ አይተዉ ለአንዱ ዘረኛ በሰጡት መልስ ምንሊክ ባይሰበስቡህ እራስህን አንዱ የጎረቤት አገር ታገኝዉ ነበር ያሉት ዛሬም በባዶ ሜዳ ለሚያብዱ ነገር ለጠፋባቸዉ ዘረኞች በግልጽ ሊነገር ይገባል እላለሁ። እነዚህ የምንሊክን ታላቅ ስራ የማያዉቁ ደካሞች ምንሊክ ባይሰበስቧቸዉ ስማቸዉ ሌንጮ/ሀጎስ/ጫላ/ለማ… ከመሆን ይልቅ ሪካርዶ/ሮበርት/ዴቢድ ሲሆን ሀይማኖትም በልካቸዉ ይሰፋላቸዉ ነበር። የሚያሳዝነዉ የፕሮፌሰሩ ጽሁፍ ከግማሽ ቀን በላይ በድረ ገጾች ላይ አልዋለም ምክንያቱም የታወቀ ነበር።
እዚህ ላይ ላልፈዉ የማልፈልገዉ ስለ ታላቁ የኦሮሞ ህዝብ በኢሳይያስ ታግተዉ ጻፉ በሚባሉ ዘረኞች በነ አስመሮም ለገሰና 12ኛ ክፍል ባልጨረሰ መሀይም ተጽፎ ለንባብ ሲበቃ ማየት በእጅጉ ያሳዝናል ዛሬ በኢትዮጵያ ምስረታ በኢትዮጵያ ስነጥበብ በኢትዮጵያ አስተዳደር የኦሮሞ አሻራ ያላረፈበት አንድም ነገር አይገኝም። በሀገር እና ከሀገር ዉጭ ታላላቅ የኦሮሞ ጠቢባን ባሉበት አለም ስለ ኦሮሞ ህዝብ ታላቅነት፤በደል፤ጭቆና ከኤርትራ ኤክስፖርት ሲደረግ ከምንም በላይ የሚያሳፍረዉና የሚያዋርደዉ የኦሮሞን ህዝብ እንጂ ሌላዉን አይሆንም። የኦሮሞ ህዝብ ሞግዚት የሚያስፈልገዉም አይደለም የኦሮሞ ህዘብ በደሉን እና ጥቅሙን በሚገባ ያገናዝባል የኦሮሞ ህዝብ ህመም ከአማራዉ፤ጉራጌዉ፤ወላይታዉ…. በላይ እነ አስመሮም ለገሰንና ተስፋዬ ገ/አብን ለምን እንዳመማቸዉ ነገሩ ግልጽ ነዉ እነሱን ያቃታቸዉን ሀይል እነሱ እንዲሞክሩላቸዉ ታስቦ ነዉ ታዲያ ኦሮሞ ይህን አጣ? የምን ንቀት ነዉ? ከኦሮሞ እና አማራዉ የተወለደ 10 ሚሊዮን ህዝብ ከመኖሩም በላይ የአንዱን ደም አጥርቶ አንተ ከዚህ ነህ አንተ ከዚያ ነህ የሚያሰኝ ሁኔታም አይኖርም። አሁንም የኦሮሞን ህዝብ አታላግጡበት አርፋችሁ ቁጭ በሉ ሊባሉ ይገባል። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ምነዉ ተስፋዬ ገ/አብ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ሆነ ያሉት እነ አስመሮም ለገሰን አፍ አዘግቶ እዛዉ እስር ቤታቸዉ ሊያስቀምጣቸዉ በቻለ ነበር ታድያ እነሱ ለክብር ስላልተፈጠሩ በተቻላቸዉ መጠን ቶሎ ትርፍ ያመጣልናል ብለዉ የሚሉትን ብቻ መሞከር ስለሆነ ሊማሩ አይችሉም። እንደ እዉነቱ ከሆነ በዛሬዉ አለማችን ከማንም በላይ በባርነት ቀምበር ስር ያለ ህዝብ ቢኖር ኤርተራዊ በመሆኑ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ካማራቸዉ እዛዉ በእስር ቤት የሚኖረዉ ህዝባቸዉንና እራሳቸዉን ነጻ እንዲያወጡ ይጠየቃሉ ለዛም ካልታደሉ ተራ የኢሳይያስ ካድሬ መሆናቸዉ ቀርቶ በክብር እንዲቀመጡ እናሳስባለን 90 ሚሊዮን ህዝብን መናቅ የጤንነት አይመስልም።
ለማጠቃለል በስልጣን ላይ የተቀመጡት ህዋቶች በአቶ መለስ ምንጠራ አክራሪ ትግሬዎች ተነስተዉ በአብዛኛዉ ኤርትራ እና አፍቃሪ ኤርትራዉያን ቦታዉን በመያዛቸዉ የትግራይ ወንድሞቻችን ነገ ከሚመጣዉ ጥፋት እራሳቸዉን ለመከለከል ከወገናቸዉ ጋር ሰልፍ እንዲቆሙ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። ትላንት የትግራይ ወንድሞቻችንን ነፃ ለማዉጣት፤ የትግራይ ክልል ባድሜ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ድምበሮች እንዲከበሩ በዛ የፈሰሰዉ ደም ከንቱ ሁኖ ቀርቷል። ባድሜም ለኤርትራ ሊመለስ ዉስጥ ለዉስጥ ዲፕሎማሲዉ ተጧጡፏል ኤርትራዉያንም ያለምንም ችግር በኢትዮጵያ የቀድሞ ቦታቸዉን በመያዝ ላይ ናቸዉ። ትላንት የትግራይ ህጻናትን በቦምብ የፈጀ ሀይል ዛሬ ለትግራይ ህዝብ ወዳጂ የሚያደርገዉ ምንም ነገር ሊኖር አይችልም ህዝቡም አስተዳደሩም ትላንት የነበረ ነዉና። የኢትዮጵያም ህዘብ በችግሩ ጊዜ የችግሩ ተካፋይ ካልሆናችሁ የችግራችሁ ጊዜ ብቻ ድረሱልን ብትሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግነቱና እርዳታዉ ቀጣይነት ሊኖረዉ ስለማይችል ካሁኑ ማሰብ አግባብ ነዉ እላለሁ።

እንግዲህ በእነ ገበየሁ ባልቻ፤በላይ ዘለቀ፤በላይ ቃለአብ፤ኡመር ሰመታን፤ታከለ ገ/ሀዋያት፤አብዲሳ አጋ በነ አፈወርቅ ወ/ሰማያት እና ዛሬ ደግሞ እንደ ጎሹ ወልዴን

አለማየሁ መሰለን የመሰሉ ጀግኖቻችን ባሉበት አገር ወገን ዉርድተን መቀበል በእጂጉ ይከብደዋል። እንግዲህ የተኛዉ ወገን ነቃ ብሎ እንዲጠበቅ መሰሪዎችም እንዲጠነቀቁ ያህል ነዉ እንጂ ምን ያልተጻፈ አለ ሰሚ፤ አንባቢና አገናዛቢ ከተገኘ። ይህችን ጽሁፍ ከከተብኩ በሗላ በህዋትና በሻቢያ መሀከል በራቸዉን ዘግተዉ ኢትዮጵያንን አግልለዉ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሁሉ በተዋራጅነት የሚያስቀምጥ አንዳንድ ድርድሮችን በማድረግ ላይ እንደሆኑ ጠቋሚ ጽሁፎች በብዛት ተሰራጭተዋል። ኤርትራ ኢትዮጵያ ኮሚቴም የሚባል የማወናበጃ ስብስብም በየቦታዉ እንደ አሸን ብቅ በቅ እያለ ነዉ። ብዙ ለግላጋ የኢትዮጵያ ህጻናት ያለቁበት የትግራይ ከልል ባድሜም በተዋራጂነት ለኢሳይያስ አፈወርቅ በእጅ መንሻነት ህዋአት ሊያስረክበዉ እንደሆነ ይገመታል። እንግዲህ ይህንና ሌላዉን አጠቃለን ስንመለከተዉ ኳሷ ያለችዉ የትግራይ ወንድሞቻችንን ክልል ስለ ሆነ ወደ ወገናቸዉ ተጠግተዉ የሚጠበቅባቸዉን ግዴታ እንዲወጡ አሳስባለሁ ለራሳቸዉም ጥቅም ሲባል። ከላይ እንደገለጽኩት የህጻናት ትምህርት ቤት በቦምብ ያጋየ ለትግራይ ህዝብ ወደፊት ወዳጂ ይሆናል የሚል እምነት ስለሌለኝ ከህዋአት ዉጭ ማሰብ እንዲችሉ በድጋሚ አሳስባለሁ።
እስከዛዉ በቸር ይግጠመን ሰመረ አለሙ ነኝ ከባህር ማዶ መልካም የፈረንጂ ገና
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ሴቶች ጥሩ ነገር አላቸው ጊዜ እሲኪሰጣቸው ድረስ ጠብቀው ይይዙት ዘንድ እለምናቸዋለሁ።

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ 21.12.2013

በሴቶች ስሜት ውስጥ መሆንና በስሜቱ ውስጥ ሴቶችን ሆኖ ማሰብ ከባድ ነው።

sreate1እኔን ተብድሬው አላውቅም። እኔንም ተውሼው አላውቅም። እኔንም ሸቅጬው አላውቅም። እኔንም መስዬው ሳልሆን ሆኘው ስለምጽፈው በስሜቴ ውስጥ ያሉ ነገሮች ሁሉ በአብዛኞቹ ሴት እህቶቼ ስሜት ውስጥ እንደሚኖር አስባለሁ። የድምፄ ምት ከማህጸኔ ይነሳል። የመንፈሴ ትንፋሽ ደግሞ የልቤን ክናድ ይንተራሳል። መንፈሴ ሰግሮ ሁነኛ ማረፊያ ወይንም ድልዳል ሲያጣ ትካዜ ሲዋኝበት የኖረ ቢሆንም፤ አሁን ከዘሃበሻ ጋር መታደሙ የመገለው ስቃይ ተግ ብሎለት ህምሙም ታግሶ፤ በስክነትና በቅደም ተከተል ማሰብና ከረመጥ ላይ የበቀለውን ጸጋ ማቆለማመጥ ጀመርኩኝ። ስለሆነም እኔ ራህብ ላይ ሆኜ ሌላ ራህብተኛ ለማስናገድ አቅሜን በሙሉ ቀን መርቆ የሰጠኝ አምላኬ፤ ምክንያት ፈጥሮ የመተንፈሻ ቀዳዳ ለፈቀደለኝ የዘሃበሻ ድህረ ገጽ ምስጋናዬን በሐሴት ጠልፌ ተቀበሉኝ በማለት እነሆ ጀመርኩኝ …

ሴቶች የመኖር ቋንቋ ናቸው። የኑሮ አይደለም። ኑሮ ቅርንጫፍ መኖር ግንድ። ውድ ወገኖቼ አጠቃላይ የነፃነት ትግሉን የአቅም ግንባታ፣ ጥበቃ፣ ያለውን ሃብት በቋሚነት ማዝለቅ እንዲሁም ስምሪት በተመለከተ ያላችሁበት በመሆኑ እሱን ተወት አድርጌ በዚህ ዙሪያ አንስት እህቶቻችሁ ያላቸውን ልዩ መክሊት አትኩሮት ብትሰጡት ሁሉም አካባቢ ያሉ ክፍተቶችን እንዴት ሊያበጅና ሊያሳምርም እንደሚችል በአላቸው  ዙሪያ  ትንሽ ነገር ለማለት ፈለግሁ። 

 

ሀ.       ሴቶች ችግርን ለመፍታት ቁርጠኝነት ጠረናቸው ነው።

 

የሴቶች ተፈጥሮ መግለጫ ከሆኑት መሰረታዊ ጉዳዮች እንብርቱ ሴቶች ችግርን የማይፈሩ ደፋሮች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ችግሩን ለመፍታት ቁርጠኝነትን በአጽህኖት የተካኑ ከመሆናቸው ላይ ነው። እንዲያውም ሴቶች ወስነው ችግር ወደ አለበት ፈጥነው የሚገሰግሱ መሆናቸው የተፈጥሯቸውን ብቃት ያመሳክራል። ስለዚህ ሴቶች ማናቸውንም ችግር ከቤት እስከ አደባባይ ያለውን ሁሉ አሳር ዳፍረው ከመፍቻው ቁልፍ ጋር መፍትሄ የሚያስገኙ ድንቆች ናቸው። የፈለገ ዓይነት፣ በፈለገ ሁኔታ፣ በፈገ መጠን፣ በፈለገ ጊዜ፣ በፈለገ ግንኙነት፣ በፈለገ ልኬታ፣ ችግር በቅሎ ይጠብቃቸው አብዛኞቹ እንደ አመጣጡ መክተው፣ መንገዱን ጠርገው ለጥ ያለ አስፓልት በማድረግ፤ ወጣ ገቡን የሚታድጉ የመፍትሄ ማሃንዲሶች ናቸው። አቅርቧቸውና ፈትኗቸው ወኔው ካላችሁ ….

 

ለዚህ ማገናዘቢያ ይሆን ዘንድ …. እኔ በተመስጦ የኩርድሽ ሴቶች የጫካ ትግል እከታተላለሁ። ወንዶች ከተማ ሆነው የሎቢ ተግባር ይሰራሉ፤ ሴቶች ጫካ ሆነው የጀግንነት ግሩም ድርጊት ይከውናሉ። ጦር አዛዧ ሴት፤ የግንኙነት ኃላፊዋ ሴት፤ የሎጅስቲክስ ስምሪት አስተዳዳሪዋ ሴት፣ የጓድ መሪዋ ሴት፣ አዝማች ሴት … ወዘተ  ከትንግርት በላይ ነው። ጥንካሬያቸው፣ ብርታታቸው፣ ትብብራቸው፣ ጽናታቸው፣ የጫካ ህይወት ፍቅራቸው ንዑድ ነው። አምላኬን የምለምነው እንዲህ እንደ ጨው ዘር የተበተነውን ለእነሱ ቅንነት ሲል እንኳን በጉልበተኞች የተወሰደባቸውን መሬት አግኘተው ለሀገራቸው እንዲበቁ ነው። የአርበኝነት ውሏቸው ሰው መሆንን ይመረምራልና። ዓላማችውን አሳክቶ፤ አርበኛነታቸውን ለፍሬ አብቅቶ መሬት አልባነት ትሞ እማዊ የተግባር ሰውነት ምን ያህል ፍሬ ስለመሆኑ በ21ኛው ምዕተ – ዓመት በዓለም ዓቀፍ ዕውቅናውን እንዲያስጌጥ የዘወትር ፀሎቴ ነው።

 

ለ.       ሴቶች ስልት ተፈጥሯቸው ነው።

 

የሴቶች የአያያዝ ጥበብ በስልት ነው። ስልቱ ደግሞ ሩቅ ዓላማን ሰንቆ የቅርብ ፍላጎትን ሳይዘል አስማምቶ፣ አስመችቶም የመከወን ጠንካራ አቅም አላቸው። አሁን የቅርብ ምሳሌ ባነሳ በሳውዲ ላይ የተፈጠረው ችግር ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት መረባረቡን ሴቶች ከልብ ያምኑበታል። ነገር ግን ይህ የመከራ ዘመን የሚመክንበት ጉዳይ ላይ በርትቶ መስራትን ያሰምሩበታል። ለዚህም ዕድሉ ቢኖራቸው ቅደም ተከተል ሰጥተው የአቅም ክፍፍሉን አሳምረው ይቀይሱታል እንጂ ሳቢያዎች በሚፈጥሩት ውጤቶች ላይ ብቻ ጊዜያቸው እንዲላ አይፈቅዱም። በፍጹም። ነገም ሌላ ችግር በባሰ እንደሚበቅል ጠንቅቀው ያውቁታል። ስለሆነም አትኩሮታቸው በሳቢያ ላይ የሚያጠነጥን ብቻ ሳይሆን ይልቁንም በምክንያት ውጤቶች ላይ የተሳላ ነው። ተግባባን?

የችግሩ መፈልፈያ ከምንጩ መድረቅ አለበት። መነቀል አለበት – የሥራዓት መሰረታዊ ለውጥ ላይ አብዝቶ ከተሰራበት አብዛኞቹ የዛሬ ችግሮቻችን በሂደት በራሱ ጊዜ ያስተካከለዋልን።

ሐ.      የሴቶች ቀድሞ የመተንበይ አቅም ዓይነታ ነው።

 

አንድ ጊዜ በ90ዎቹ አጋማሽ ውጭ ሀገር አንድ የሥራ ባልደረባዬ፤ አለቃችን ሳይኖር አለቃዬም ነበር ለነገሩ  አዛውንት ጋዜጠኛ ታዋቂ በድንገት ሞቶ ቀብሩ ላይ ነበርኩኝ። አስከሬኑ ተቃጥሎ በትንሽ ነገር መያዙን አላስተዋልኩትም ነበር። እኔ እምጠብቀው ሳጥን ስለነበረ ከአጠገቤ ላላው ባልደረባዬ የተግባር መምህሬም ነው፤ መቼ ነው አስከሬኑ የሚመጣው? ስል ጠዬኩት ሂደቱን አጫወተኝ። ባለቤቱ የውጭ ዜጋ እንደ ሆነች እንደ እምነቷ፣ ቦታም ገንዘብም ለመቆጠብ እሬሳው እንዲቃጠል መወሰኗን አብራርልኝ። ይህን አሰቃቂ  ትዕይንት ስሰማም፣ ሳይም የመጀመሪያ ቀኔ ስለነበር አካባቢው እራሱ ቀፈፈኝ። ከአጠገቤ ደግሞ አንዲት አበባ የመሰለች ውብ ሴት እጅግ አምርራ ታለቅሳላች። ወደ እሷ ዞር አልኩኝና ጠጋ ብዬ እንድትታገስ ነገርኳት። ከዛ ምን እንዳለችኝ ታውቃላችሁ“ለራሴ ነው የማለቅሰው“ እንዴት? ስል ጓጉቼ ጠዬኳት። ለዛውም ሰው ፈቅዶ ካልነገረኝ ስለምንም ነገር መጠዬቅ አልወድም።

 

… ብቻ ጠዬኳት „ እኔ ተሰደድኩ፤ የስደቱን ፈተና ስላልቻልኩት የውጭ ዜጋ አገባሁ፤ ወለድኩኝ። አዬሽ አይደል መመለሻ የለኝም፤ አስከሬኔም የሀገሬ አፈር አያገኝም – በሁለት ምክንያት። ቀድሜ ብሞት ባለቤቴ የሚያደርገው ይህንኑ ነው። እንደ ባህሉ ያቃጥለዋል። ልጆቼም በዚህ ውስጥ ስለሚያድጉ ያፀድቁለታል አለችኝ“ ምንም እንኳን ሁሉም ጋብቻ ላይ ይህ ባይደርስም ዛሬ ላይ ሆኜ የትናት ትንበያዋን፤ ያ ሁለቱ የተፈጥሮ መስኮቶቿ ተከፈተው ገድቡን ጥሶ ሙላቱን ይለቀው የነበረው ፍላሎት ዛሬ ላይ በምልሰት ስቃኘው ሚስጢሩ ተገለጠልኝ። ሴቶች ነገን የማየት አቅማቸው ብጡል* (ጥንካሬው የደመቀ ልዩ) ነውና። ይህን ዘመን በድርብ ስመዝነው ደግሞ አይደለም ውጪ ሀገር … ሀገር ውስጥም መሰሉ ሊፈጸም እንደሚችል ምልክቶች ይጠቋቁማሉ። አስፓልቶች የኢትዮጵያ መሬት አይመስሉም፤ የገጠር መንደሮችም እንዲሁ …. ተወራላች ሀገራችን …. ውርርሱ የመሬት ብቻ ሳይሆን የዕምነት አፈጻጸም የተጋደመ ባህልም … እንዳይሆን ስጋቴ ነው።

 

… በዛው የቀብር ሥርዓት ያቺ ፔርሙስ በምትመስል ሰፋ ባለች ጎድጓዳ ማህል እጅ ላይ ተቀምጣ የነበረችው አዬኋት። አፈሩ ጫረጫር ተባለላትና እንደ ሀገሬው ባህል ወጉ ደራሳት። መሬቷ አንድ ስንዝር ብትሆን ነው። ያን ዕለት ከጎኔ ላላው ለማከብረው የቅርብ አለቃዬ ጠጋ አልኩና እኔ ደግሞ „በሰው እጅ የሞተ ይመስለኛል አልኩት።“ በጣም ፍጥነት የተሞላበት ነገር ነበር የተመለከቱት። እሱም “እናንተ ሴቶች መቅደም ተፈጥሯችሁ ነው። አብረን በኖርንባቸው ወቅቶች የታወቀ ምንም ዓይነት በሽታ አልነበረውም። ሁልጊዜም የህክምና ቁጥጥር ያደርጋል። ባለቤቱን ስለሁኔታው ደውዬ ስጠይቃት በመረጋጋትና  በአሸናፊነት መንፈስ ነበር ያጫወተችኝ። አሁን አንቺ ይህን ስትይ ግን የተሰወረ ግን ልንድርስበት ያልቻልነው ነገር አለበት ብዬ አስባለሁ። ለዚህም ይሆናል ብቻዋን ወሰዳ እንዲቃጠል ካስደረገች በኋላ የቀብር ሥርዓት ላይ ብቻ እንድንገኝ የነገረችን“ አለኝ። ከዚህ ላይ እኔ ትንቢተኛ ነኝ ለማለት አይደለም። ሴቶች ደራሽ ችግሮችን በተለያዬ አቅጣጫ እንደሚያዩት ለማጠዬቅ እንጂ …

 

ወገኖቼ … ሴቶች ንደ ወረደ የሚያስተናግዱት ምንም ነገር የለም በፍጹም። ይበልቱታል። የበለቱትን ክፍል ሰጥተው ይደለድሉታል። የደለደሉትን ንክኪና ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ ከአገናኙ በኋላ ይፈታትሹታል በዬ አቅጣጫው፣ በዬዞኑ። ፍተሻው ጠንከር ያለ የራ ፊድ ባክ ወይንም ምላሽ ይሰጣቸዋል። ያ ፊድ ባክ ወይንም ምላሽ ዕርገታቸውን ያሳካላቸዋል …. እህታችሁን፤ የትዳር አጋራችሁን፤ እናታችሁን ለናሙና ወስዳችሁ መመዘን ይቻል ይመስለኛል።

 

መ.      ሴቶች በተፈጥሯቸው የተደራጁ ናቸው።

 

በሙያዬ አደራጅም ስለነበርኩ ብዙ ሳልጓዝ ብዕሬ በተወሰነ ጉዳይ ላይ ብቻ እንድታጠነጥን እለምናታለሁ። የሴቶች የመደራጀት ሂደት ከዬት የሚጀምር ይመስላችኋል። ከማህል? ከጠርዝ? ከማዕዘን? ከቀኝ – ከግራ – ከፊት – ከበስተኋላ? የሴቶች መደራጀት የሚጀመርው ከመንፈሳቸው አስኳል ነው። እንቅስቃሴያቸው „ሀን“ ዘሎ „ለን“ አይጀምርም – በፍጹም። እራሳቸውን አደራጅተው ነው የሚኖሩት። የሴቶችን እንቅስቃሴ የሚመራው በተደራጀ፣ በተሰናዳና በተከወነ መንፈስ ነው። ስለዚህ ከመደራጀት የሚገኘው ዕሴት ሁሉ ተጠቃሚ ናቸው። በዓለም የመጀመሪያው የድርጅትን ዋጋ አውቆ ጥቅም ላይ የዋለ ፍጥረት ቢኖር ሴቶች ናቸው። በሴቶች ህይወት ውስጥ ምን ያልተዳረጀ ነገር አለና? ስለሆነም አቅማቸውን በሥርዓት መርተው ለአቀዱት ዓላማ ጥቅም ላይ በአግባቡ ያውሉታል /ኢንቤስት/ ያድረጉታል …. ኃይላቸው ብክነት የለበትም። የፍሬ ነገሩ ኩላሊት ያለው ተዚህ ላይ ነው። ኃይላቸው ጥግና መጠለያ ምንጊዜም አለው። አሁን በዚህ የነፃነት ትግል የሚባክነውን ገንዘብ? ጊዜ? የሰው ኃይል ቁጭ ብዬ ሳዬው የነፃነት ራህብተኛ ነንኝና እስላላሁ … እንደ እኔ ሚሊዮኖችም …. አቅም እኮ አድመጭ ያጣ ቅምጥ ሃብት ነው። ለነፃነት ትግሉ ግን ጆሮም የለም ጊዜም በኩርማን ተቆንጥጣ … ለዛው ከተገኘ … በጠብታ ….

 

ሠ.       የድምጽ እንቁጢ የሴቶች መክሊት።

 

ሰሞኑን አንድ ሁለት መጣጥፍ ላይ ስለ ድምጽ አንስቻለሁ። ተወቅሸበታለሁም። እሱን በደስታ አስተናግጄ … በሰለጠነው አለም እኮ ድምጽ የሚሰለጥኑበት ሙያ ነው። ድምጽ ከምንም ነገር በላይ ቀልብን የመግዛት ሙሉ አቅም አለው። አዎን እኔ ሥርጉተ የውብ ድምጽ ቃና ፍቀረኛ ነኝ። አውዳለሁም። ነፃነት መጋፋት ኃጢያትም ወንጀልም ነው። በነፃነት ሀገር ነፃነቴን ማንም እንዲነጥቀኝ አልፈቅድም። ስለሆነም ነው የታሰረውን እዬተጋልኩ ተስፋ ሳልቆርጥ በተገኘው አጋጣሚ የምተነፍሰው። የተሰበረ ሞተር ወይንም ኮሳሳ ወይንም የሩጫ ፍልሚያ የሚጋብዝ ፋታ ነሽ ወይንም የታፈነ …. ለታላቁ የነፃነት ጉዞ አልመኝለትም። ምን በወጣው ….? በራሱ የሚተማማን፤ እውነትን የተንተራሰ፤ ለህግ የበላይነት የቆረጠ ዓለምን የሚየስደምም ኢትዮጵያዊነትን የሚታደግ ባለ ግርማ ሞገስ ድምጽ ናፍቆቴ ነው … እንዲመራኝ።

አሁን ወደ ቀደመው ነገር እንደ አቨው ….ካለ ዓመት የማትመጣው ብሄራዊ አበባችን እንቁጣጣሽ። እንቁጢ ተናፋቂ ናት። እንቁጢ ተስፋ ድውለቷ ነው። እንቁጢ አዲስነት ቅልጥሟ ነው። እንቁጢ ፍቅር ብርንዷዋ ነው። ታጥቦ የፈጠራት፣ ተናፍቃ ትመጣላች ሳትጠገብ ደግሞ ሽው …. እሷን ባደረገኝ።

የሴቶች ድምጽም እንቁጢ ነው። ድምፃቸው በደመቀ – በለሰለሰ – በሰከነ  – ልዩ ቃና የጣፈጠ ነው። ደወሉ የመንፈስ ድህነት ነው። ምቱ … የተዘጋ ይከፍታል። የታመመ ይፈውሳል። ተስፋን ላጣ በገፍ ተስፋን ይቸራል። የደከመን ያበረታታል። የጎበጠን ያቃናል። መፍቻ ያጠን ያፍታታል። ምን የማይሆነው አለ? የሴቶች ድሪያማ ውብ የርህራሄ፣ የቸርነት፣ አበረታች ለስላሳ ቀለማም ቅላፄ ይጠጣል።  ይጎረሳል። ይዋራረዳል። ያግራል። ያፍለቀልቃል። ያጽናናልም …. ይብቃ አይደል ወራጅ አለ በሉኝ።

ለማንኛውም ይህ ሃብት ግን ከቁጥር የማይገባ … ከፋይዳ የተዘለለ፤ ከመርኃ – ግብር የተፋቀ የተረሳ ጸጋ ነው። ዘንቦ ተባርቆ የሚዲያ የራዲዮ ሆነ የቴሌቪዥን ሰራተኛ ካልተሆነ ምክንት አብዝቶ የሚጨፍርበት አንጡራ ሃብት። በዬትኛውም ቤታ የአሸናፊነት መንገዱ ሁሉንም አካባቢ ዳስሶ በታቀደና በተደራጀ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ኢትዮጵያዊነትን መታደግ ሲቻል … ፀጋው ውሃ ሲሄድበት የከረመ አለት ሆኖ ኤሉሄ አሉሄ ይላል …. ሞገዳማ ተንቀሳቃሽ ድምጽ የአጥቂነት ትጥቅ፤ የአሳማኝነት በትረ ሞገድ ነበር ላወቀበት ግን እንዴት? የታነቀ እውነት ….

 

ረ.      እናትነት።

 

ይህ እንግዲህ ለተባዕት የተከለከለው መንገድ የራሳችን ብቸኛው አንጡራ ሃብት ነው። ተቀናቃኝን በራሱ ጊዜ የመከተ። በፌክም ከማስመሰል በስተቀር መሆን የማይቻልበት ለሴቶች ብቻ የሰማዩ ዳኛ መርቆ የሰጠን የጸጋዎች እጬጌ ነው።  እናትነት የድርብርብ ፍቅር ክታብ። እናትነት በልቡ ውስጥ ልብ። የእናትነት ነገር ሲነሳ ወላዊና አውንታዊ እድምታ ላይ እንደርሳለን። እናትነት ሚስትነት ነው። የጡት ባህረ መዝገብ ሲገለጥ እናትነትን ከነክብሩ ይመጣል። ፍቅር ይከተላል። እናትነትን ሚስጢር የሚለው ቃል ሊገልጸው የሚችለው አይመስለኝም። የተከደነ ታምር ወይንስ የገድላት ቅዱስ መጸሐፍ ልበለው። እናትነት አይደለም ለሰው ልጆች እንሰሳ ላይ እንኳን ሲታይ ታምሩን የሰው ልጅ በጥበቡ ሁሉ ያልደረሰብት መክሊት ነው። እናትንት በተን ግን ጠቅላል ያሉ ሰንደቃዊ ቃሎችን ወይንም ኃብታቱ …

አለሁነት …. መቅድምነት …ቤተሰባዊነት … ታማኝነት … ተሳታፊነት …ቅርብነት … እቅፍነት …ተከታታይነት … አራራቢነት … አቀናባሪነት …ቀጥተኝነት … ዕንባመነት …ማራኪነት … ቻይነት … መሪነት … ሃላፊነትን በፈቃድ መውሰድ … ርህርህና … ስብዕዊነት … ሚዛናዊነት … ፍቅር … ቅንነት … አዎንታዊነት … አርቆ አሳቢነት … መምህርነት … ማህበራዊነት … ታማኝነት … ግልጽነት … ቀጥተኛነት … አድናቂነት … አክባሪነት … ተንከባካቢነት …. ኪዳንነት …. ለችግር ቀድሞ ደራሽንት … አጉራሽነት … አጽናኝነት … እውነትነት … ፈጣንነት … ባለሙያነት …. መሪነት …  አስተዳዳሪነት … መስዋዕትነትን ፈቅዶና ቆርጦ ተቀባይነት … አደራጅነት … አስተባባሪነት … ተጠያቂነት … ለጋስነት … ቸርንት …. አድማጭነት … አዛኝነት … ፈቃደኝነት … ቀዳሚነት … ኑሮነት …. ሁለመናነት … የሁሉዬነት …. መሆንነት … ሎሌነት …። በጣም በእርግጠኝነት እናት ለልጇ፣ ለትዳሯ፣ ለወገኗ፣ ለኃላፊነቷ ሁሉ ሎሌ ናት።

እያንዳንዱ ሥነ ተፈጥሯዊ ገፀ ባህሪ ደግሞ የራሱ ጭብጥና አምክንዮ አለው። እንደ እራሱ የመኖር ነፃነትና ከሌሎች ጋርም በመፈቃቀድ የሚያስተሳስረው ወርቃዊ ሃዲድም አለው። ድንበርና ወሰንም። ይህ ተፈጥሯዊ የገነት ህይወት ያለው የጸጋ ጅረት የራሱም ሥነ ምግባር፣ የራሱ አርትና ጣዕም አለው። ዬራሱ ዜማና ቃና አለው። የራሱ ማንነትና መግለጫ አለው። የራሱ አናትና ልብ አለው። የራሱ ፋይዳና ዕሴት አለው … የራሱ መተዳደሪያ ደንብና ሰነድም አለው። ይህ ሁሉ ተዝቆ የማያልቅ ጥሪትና እምቅ ቋሚ ሃብት ተዘሎ ይታቀደላል ሁል ጊዜ ግን ታቱ ዥግራ …

 

ሰ.      ሴቶች ብልህነት ወስጣቸው ነው።

የሴቶች ጸጋ ልጥፍ አይደለም። ከውስጣቸው በመሆን ያታተመ እንጂ። ሴቶች እጅግ ሲባዛ ብልሆች ናቸው።  በእያንዳንዱ የዓለም ታዋቂ ወንድ በሉት፤ ጀግና – ሳይንቲስት በሉት፤ ተመራማሪ በሉት፤ ተወዳጅ መሪ፤ በስተጀርባ አንዲት ብልህ ሴት በቅርበት አለች። አብዛኛውን ጊዜ የትዳር አጋራቸውን የሰሙ፤ ያዳመጡ፤ የተከበሩ መሪዎች ሆኑ፤ ለሽልማት የሚበቁ የስኬት ቁልፋቸው በእጃቸው መኖሩን ይቀበሉና ያረጋጋጡ ። እርማጃቸውን አንድ ብለው ከመጀመራቸው በፊት። የሁሉም ነገር መፍቻ ስልትና ብልሃት የመዳፋቸው እርስና እርት ሆኗልና እንኳንም ደስ አላቸው። የንጉሦች ንጉሥ የአፄ ቴውድሮስ ጠቅላላ ታሪክ በዛ መልክ የተጠናቀቀው እቴጌ ምንትዋብ በሞት ስለተለዮዋቸው ብቻ ነበር እንጅ እቴጌ በህይወት እያሉማ ድል በድል እዬተነባባረ የአሸነፊነትም የመሪነቱ እርክን አንቱ ነበር። እስከ እስራኤል ድረሰም ነበር ምኞታቸው።

እቴጌ ጋር የዐጤው መንፈሳቸው በድል ሰረገላ ላይ ያሸበሽብ ነበር። እቴጌ ለንጉሡ መዳህኒት ነበሩ ….  በብልህነት ሴቶች ተዝቆ የማያልቅ ፍጹም ልዩ ሥጦታ ነው ያላቸው። ደግሞም ስልታቸውን ተክትሎ ለሚጓዝ ህልሙ ቅርብ ነው። ድሉም ከፊት ለፊቱ ….

እስቲ ጠይቁልኝ እርቃ ሳትሄድ

እቴጌ ተዋበች ሚስትናት ገረድ

እጅግ „ሥራ አዋቂ“ ትናንትና ሞተች

መዳህኒቱን „ምሳ“ ታበላኝ ነበረች።

/ምዕራፍ 19 ከዐፄ ቴውድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ መጸሐፍ የተወሰደ።/  እጅግ „ሥራ አዋቂ“ ይህ ኃይለ ቃል የሴቶች ሥነ – ተፍጥሮ ተግባር ስለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ዕውቀታዊ – አንስታዊ ውስጥንም አሳምሮ ይገልጠዋል። ሴቶች ለቧልት ጊዜ የላቸውምና። ሁለተኛው „ምሳ“ ታበለኛለች የሚለው ሰምና ወርቅ ነው። ሰሙ የማዕከላዊ የምግብ ክፈለ ጊዜን ማዕደኝነት ሲገልጽ፤ ወርቁ ሁለት ጥንድ ትርጉምን ይዟል። አንደኛው ቀደም ባለው ጊዜም ሆነ አሁን በገጠሩ ሀገረ-ሰብዕዊ መዳህኒቶች ከተክል ሥር ወይንም ከዕፅ ተቆፍሮ የሚገኝ ስለመሆኑ፤ ዶሱ ወይንም መጠኑ በጣት ተለክቶ እንደ ዕድሜው መሰጠቱን ይገልፃል። ስለዚህ ዐፄ ቴወድሮስ ህምም ሲሰማቸው ፈርማሲያቸው፣ ሃኪማቸው ከቤታቸው ነበሩ – እመቤት እቴጌ ምንትዋብ። ሌላው የወርቁ መጠነ ሰፊ ክፍለ አካል በዘመናችን ቁብ ያልተሰጠው ፍሬ ዘር ወይንም ነገረ ሚስጢር ግን ዐፄ ቴውድሮስ በንግሥና ዘመናቸውም ሆነ ሃሳባቸውን ሲወጥኑት ከልጅ ካሳነት ዘመናቸው ጀምሮ አስተዳደራዊ ብቃታቸው  ከእቴጌ ይቀዳ እንደነበር ለማጠዬቅ ነው።

በሌላ በኩል የአልጋቸው ጽኑ ጠባቂ የፕሮቶኮል ሹማቸው አማካሪያቸው እቴጌ መሆናቸውን ያመሳጥርልናል። ከዚህ ላይ የጉዳዩን ኩላሊት ከልብ ስንፈታትሽው ደግሞ ቀደምት ንጉሦቻችን የሴቶችን ተፈጥራዊ ልክ የማይወጣለት ብቃት ለመዳህኒትነት፣ ለችግር መፍቻነት፤ ለጭንቅ መበተኛነት፣ በአግባቡ ጥቅም ላይ ያዋሉና በዚህም ፈውስና ድህነት ማግኘታቸውን ቁልጭ አድርጉ ያስተምረናል ….

ከዚህ ጋር በተያያዘ የደህንነት እና የልጅነት ሚስጢርን በእናትነት ፀጋ ጎልምሶ የምናዬው ክፍል ደግሞ እቴጌ ሲሞቱ  …. የነበረውን አብረን እንመልከት።

እቴጌ ለባለቤታቸው አድልተው ወደ ትዳራቸው ፍላጎታቸው ቢመዝንም፤ እንደ ቤተሰባዊ ጸጋቸው በሴት ልጅነታቸውም አባታቸው በነበሩበት የግዞት ዘመን ሁሉ ከጎናቸው ነበሩ፤ ትዳራቸውን ሳያስከፉ በጥንቃቄ የልጅነት ድርሻቸውን በስውር ተወጥተዋል። ሊደረግላቸው የሚገባውን ተግባር ሁሉ አድርገዋል። እጥፍ ጸጋ። ሴት ልጅና ወንድ ልጅ ለወላጆቹ እኩል ተግባር ላይ አይገኙም። በቤተሰብ አያያዝና ክህሎትም ቢሆን  እኩል የመሆን አቅም የላቸውም - ፈጽሞ ። ለዚህ ነበር ራስ ዐሊ ልጃቸውን ሞት ሲነጥቅባቸው …. እንዲህ ብለው ቅኔውን የዘረፉት …. የጎደለ ሞይነት – ሁለመናነት … ሁሉዬ ሴት!

 

ጠጅ አማረኝ ስላት ማሩን ትሰዳለች (ለተጠማ ሆነ ለአምሮት ደራሽነት)

ራበኝም ስላት እኽሉን ታስጭናለች (ለራህብ ፈጥኖ ደራሽነት)

በረደኝም ስላት ሸማ ትሰዳለች      (ለታረዘ አልባሽነት)

ሌባዬ ተይዛ ባልጋ ትሄዳለች        (የድህንነት ጥበቅ ተግባር በስውርና በጥበብ)

የት አባቷን ዐውቃ ታሳዝነኛለች    (ችግርን ተጋሪ ሲርቅ ረመጥ ስለመሆኑ)

የጣቴን ቀለበት አንተ አድርገው ካሳ (ኪዳንህን ጠብቅ አደራ፤ ጽና!)

በኔማ ጣት ገብቶ አስጨነቀኝሳ (የሃዘኑ ቋያ ረመጥ ልኬታ አለመኖሩን) ያመላክተናል

( ከዐፄ ቴወድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከተክለ ጻድቅ መኩሪያ መጽሐፍ ገጽ 20) የተወሰደ

ሴት ልጅ – እናት፤ እህት – ጓደኛ – አክስት –  ስትሆን ሚስጢሩ ሆነ ትርጉሙ ጣና ዘገሊላ ነው ….. ዛሬስ አቶ ወንዶች ይህን የማመሳጥር አቅም አላችሁን?

 

ሸ.      ሴቶች የተረጋጋ መንፈስ።

 

ይህ የሴቶች ተፈጥሮ ተግባር ላይ የሚውለው በትዳራቸው፤ በእናትና ልጅ ዙሪያ ወይንም በስብዕዊነት ዙሪያ አይደለም። ስለምን? በዚህ ዙሪያ ለሚመጡ ሰቀቀኖች ሴቶች ስሜታቸው ስስ ነውና። ነገር ግን ኃላፊነትን በሚጠይቁ የመወሰንን የመቁረጥ ሂደቶች፤ ሂደቶችን ተከትለው በሚመጡ አጣብቂኝ ፈተናዎች ዙሪያ ሴቶች የሰከነና መሬት ያዬዘ የተረጋጋ መንፈስ አላቸው። በመጀመሪያ ነገር ጉዞውን ሲጀምሩትም በአመዛኙ ይመጣል ብለው ካላሙት ችግር ውስጥ ያፈነገጠ አይሆንም። ስለሆነም በታቀደ እንቅስቃሴ ውስጥ የተጠበቀን ፈተና ለማስተናገድ ሴቶች ተረጋጋግተው የማስተናገድ ሆነ የመራመድ አቅማቸው ማገርፒላር ነው። በተፈጥሮ ሊቅነት። … ሥጦታው በትምህርት በተመክሮ ሲታክልበት እንዲሁም የተከበረ ተደማጭነት ሲያገኙ … መስፈርቱን ሆነ ዕሴቱን ለመለካት አይችልም … ዝልቅ ነዋ!

 

ቀ.      ማስተዋል ሴቶችን ይገልጣቸዋል።

 

ሴቶች አጋጣሚዎች የሚመራቸው ፍጥረቶች አይደሉም። ወይንም ሴቶች አጋጣሚን ተጠልለው አያቅዱም። መርኃ ግብራቸው እራሱን የቻለ እና ግብታዊነት የማይመራው በመሆኑ አትኩሮታቸው በጭብጡ ማዕክላዊ ዙሪያ ስለሚሆን ለግቦች ቅርብት ሆነ ለውጤቶች አስተማማኝ ግብዕት ናቸው። የሴቶች የፍላጎት ትልም ለወጀብ ሆነ ለአውሎ የተጋለጠ አይደለም  … እሳተ ጎመራን የመቋቋም ብቃቱ መካች ነው።

 

በ.      የሴቶች ነፃነት ናፈቂነት፤

 

ይህ የሴቶች በኽረ ህልም ነው። ምክንያቱም ውስጣቸውን ጠንቅቀው ስለሚያውቁት ድርሻቸውን ለመወጣት ተድቦልቡሎ ግን ተስውሮ የሚፈታታናቸውን የትምክህት ቲወሪ የሚመክት ነፃነት ይሻሉ። ለዚህ ነፃነትም ትርጉም ያለው፣ ድርጊተኝነትን በማስቀድም በግንባር ቀደምትነት ይጋፈጣሉ። እርግጥ ዘመንና ጊዜ የሚጠበቁ ነገሮች እንዳሉ ቢገነዘቡም፤ አጋጣሚዎችን ሳይዘሉ የምልክት ደወል መደወላቸውን ግን አያቋርጡም። ከናፍቆታቸው ጋርም ለመገናኘት ተግባር እንደሚያሸንፍ ስለሚያምኑ ድምጻቸውን አጠፍተው ከድርጊት ጋር ይባትላሉ – ይመስናሉ … በታሪክ ጊዜ የሌላቸው ቢዚ ፍጥረቶች ቢኖሩ ሴቶች ናቸው። በሁሉም ቦታ በተጫነ ጉልበታም ትምክህት ሥር ወድቀው፤ ግን ተሳትፏቸውን በትጋት ይወጣሉ። ፈተናው ሲጠናባቸው ሲስፈልግዞር ወይንም ለቀቀ አድርገው ግን ቀዳዳ ፈልገው ይተጋሉ። እንግሊዘኛው ስለሚገልጽልኝ ሙሉ ፓኬታቸው ትንታግ ነው – ። ለዚህም ነው ዕርሴ መጠበቅን ጽላቱ በማድርግ ሴቶች ጥሩ ነገር አላቸው ጊዜ እሲኪሰጣቸው ድረስ ጠብቀው ይይዙት ዘንድ  እለምናቸዋለሁ ያልኩት።

 

ጠቅለል ይበል …

 

የተፈጥሮ ውብ ዘላቂ ጥሎሽ የሴቶች ብቃት ነው። ዝም ብዬ ቁጭ እልና ሴቶችን ፊት ለፊቴ አስቀምጬ ሁለመናቸውን እፈትሸዋለሁ። እንደ ሰርጀሪ ነገር …  ሁለመናቸውን አስተውለዋለሁ። እያንዳንዱን ቅመማዊ ተፈጥሮ እዬነጠልኩም አናግረዋለሁ። ሁለመናቸውን እዬተነተንኩም እመካበታለሁ። ሁለመናቸውን እያፍታታሁ እጽናናባቸዋለሁ። ሁለማናቸውን እያስተዋልኩ አደንቃቸዋለሁ። ሁለመናቸው እዬዳሰስኩ እበረታታባቸዋለሁ – እውዳቸዋለሁም። ሁለማናቸውን በዓይኔ ወስጥ አስቀምጬ መንፈሴ እንዲደለው ፈቅጄ ነገን አልመበታለሁ። ቀደም ባለው ጊዜ „ እረኛ ምን አለ“ ይባል ነበር። አሁን ሰሞኑን የኢትዮጵያዊነት ስሜትን ፍላጎትን ሳወጣና ሳወርድ ከአንድ ጥቅል ፍላጎት ላይ ደረስኩ“ጣይቱ“ የሚለው አዲሱ  የአንስት ወላዊ፣ ትንቢታዊ፣ ፍላጎታዊ፣ ፈቃዳዊ፣ ጠያቂያዊ … ዜማ … እርገቱ በታዳጊ ወጣት የተስፋ ጠቅላይ ሚ/ር ቃለ ምልስልስ ሲጠናቀቅ ጨዋው ህዝባችን፤ ፈረኃ እግዚአብሄር ያለው ህዝባችን፤ ለእምነቱ ዶግማና ቅኖና ሞቱን የሚመርጠው ህዝባችን አንድ ነገር መንፈስ ቅዱስ እንደ አቀበለው ልብ አልኩኝ …. እንኩይ ….. የናፈቀው የሰከነ ፖለቲካዊ አመራር ከአንስት ነውና …

 

ከዚህ ጋር በተያያዘ ደግሞ መራኂት አርቲስት አለምጸኃይ ወዳጆ „የጣይቱን የሥነ – ጥበብ ማዕከል“ አሜሪካን ላይ አደራጅታ ጥበብን ተጠዬቅ ስትል፤ ቀድሞ የታያት ወርቅ እንደነባራትም ተገለጠልኝ። …. እሷም እኮ አለች … የጀመሪያው የተውኔት ባላሙያዎች ማህበር ብሄራዊ ሊቀመንበር … አስታዋሽ አርቲስት ታማኝ ባጠገቧ በመኖሩ ምክንያትም ቢሆን ኢሳት ይመስገን ተዚህ ላይ። … በሶስተኛ ጉባዔው ላይ ገላጭ አድርጓት አይቻለሁ፤ ግን ይህ በቂ አይደለም … ማስታወሱ መልካም ሆኖ ግን ሩቅ መጓዝ፤ ትብትቡን ፈቶ ቅኔዊ ውስጧን በቋሚነት ጥቅም ላይ መዋል ይገባል … ስብሰባ እኔ የምተረጉመው ገብያ በማለት ነው።

 

እናቴ ስትነግረኝ በልጅነቷ ጓደኛ ታበዛ ነበርና መሞታቸውን አውቀው፣ ሰኔልና ቹቻ አዘጋጅተው፣ ልጆቻቸውን መርቀውና ተሰነባተው ጸሎት ቤታቸው በሰላም ያረፉት ሊቀ – ሊቃውንቱ አያቷ መላክ ብርኃን ልሳንወርቅ ኃይለ ሥላሴ ቤተሰብ „ገብያነሽ“ ያላትን ስም አስቀሩት። ስለምን ገብያ ተሎ ይፈታል። ልጄ ዕድሜዋ ተግባሯም አጭር ይሆናል በማለት ሌላ ድንቅ ስም አወጡላት። አሁንም ሰው ወዳጅ ስለሆነች ተከባ ተከብራም አለች በባዕቷ። ምን ለማለት ነው እጅግ የፍቅሯን ንጥር ቅቤ ጠጥቶ ባደገው የልቤ ሙዳይ ውስጥ ብቸኛ ቦታ የሰጣት መራኂት ዓለምጸኃይ ወዳጆ … ቶሎ ለሚፈታ ጉባዔ ብቻ አትታጭ ዘለግ – ዘለቅትርጉም ላላው ተሳትፎ፤  አቅሙ ጉልበታም ለሆነ የኃላፊነት ቦታም ትታሰብ እንላለን … እንጮኃለን …. ተፈጥሮ እንዲያምርበት ማጣፈጫ አምላክ ፈጠረለት ሴትን

 

ሉሲ የ21ኛው ምዕተ ዓመት የሰው ልጅ ምንጭ ሆነች … ሳይንስም የኢትዮጵያዊነትን ሚስጥር ሳይነቅፍ ከሃቅ ጋር እርቀ ሰላም አወረደ። አመሳጠረ። ታዲያ ድንቅነሽ ማለት እኮ ሴት ናት … ተዚህ ማዕከል ይኮንና በኩነኔ ተፈርጆ ገሃንም የተወረወረው የሴቶች ብቃት ባሊህ ይባል እንላላን። የተከረቸመው በርም ይነቅነቅ እንላላን ///  እኔና የተከበረችው ብዕሬ – መንፈሴም ይታከል ….  ከዓውደ ምህረቱ ሆኖ  እንቢልታውን እያስነካ ውስጡን ላከ … ለጆሮ ….

 

ለነበረን የመደማማጥ ሸጋ ጊዜ ኢትዮጵያዊ ዘንካታ ምስጋና አቅርቤ ለዛሬ ልሰናበት። ቸር ያሰንብተን፤ ቸር ያሰማን አምላካችን አሜን።

 

ሴቶች የድርጊት ጀግኖች ናቸው!!!!!

የሴቶች ተሳትፎ በማለት የሰከረ ሳይሆን መሆንን የሰነቀ ነው!!!!

 

ይቅርታ በትህትና አክብሮትም ታክሎበት አንዳንድ ቦታ ላይ እንግሊዘኛውን ቃል ወስጃለሁ፤ ውስጤ አቅም አንሶት አይደለም ፍላጎቴን የበለጠ አስረግጦ የሚገልጸው እንግሊዘኛው ሲሆንብኝ ነበር … ትንሽ ዲቃላ ነገር የሆኑት ገለፃዎቼ …

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 


ጥቁር ነኝ … ነገር ግን ውብ ነኝ

$
0
0

ሙሉጌታ አሻግሬ

mulugetaashagre@yahoo.com
ማህበር እየደገሰች ዘመድ የምትሰበስበዋ አክስቴ ‘አገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው’ ትላለች። ይህን አባባል ለአክስቴ መስጠቴ አይደለም ሙስና እንዳይሆንብኝ። ህዝቡ ሁሉ እንደዛ ይላል። አክስቴ ምን ታድርግ መስመርና አብዮት የተባሉ ሰው ሰራሽ ጭራቆች ወንድሞቿን በልተውባታል። ይህ አባባል በፖለቲካ ምክንያት እሳት እና ጭድ የሆኑ ቀሪ ዘመዶቿ የተለመደውን ንትርክ እንዳይጀምሩ የምትጠቀምበት ዘዴ ነው። እኔ ግን ስተረጉመው ‘ዝምድና የጋራ ነው ፖለቲካ የግል ነው’ ማለቷ ነበር። በአክስቴ እምነት ፖለቲካ ጥሩ አይደለም። ሞት ያስከትላል።
ግን ሃይማኖትና ፖለቲካ እውነት ለየቅል ናቸው? ይህን አስተያየት ለመፃፍ ያነሳሳኝ ሰሞኑን አንድ ወዳጄ ጀባ ያለኝ የስብከት ሊንክ ነው።

ምንም እንኳን እንደአባባሉ ሃይማኖት የግል አገር የጋራ ቢሆንም የወያኔ ገዥ ቡድን አገርም የእነርሱ፤ ሃይማኖትም የእነርሱ እንደሆነ ህቅ እስኪለን ድረስ አሳይተውናል።
የእስለምና መሪዎች ሹመት በቀበሌ ምርጫ ካልሆነ ምኑን ሃይማኖት ሆነው ሊሉን ዳርዳር ያሉ የወያኔ ካድሬዎችን ታዝበናል። ማንን ፈርተው እንደተዉት ባይታወቅም ‘የመጅሊስ ተመራጮች ምርጫ ቦርድ መመዝገብ አለባቸው’ የሚል የደደቢት ቀጭን ትዕዛዝ ይተላለፋል ብዬም ጠብቄ ነበር። ኦርቶዶክሱንም ቢሆን ያልተመቻቸውን ሽረው፣ የተመቻቸውን ሾመው ፣ ኽረ ወግ እየተናደ ነው ብለው ቅሬታ ያሰሙ አባቶችን ደብድበውና አስደብድበው ሲኖዶሱ የእነሱን መስመር የሚከተል እንዲሆን ሰርተዋል። በአደባባይ በመውጣት ሚዲያ በመጠቀምም የኦርቶዶክስን አከርካሪ ሰብረናል ብለዋል። ስለዚህ ፖለቲካ ከእኛ በላይ ለአሳር ያሉት የወያኔ ገዥ ቡድን አባላት ይህን ካደረጉ እና ከተናገሩ፤ የእኔ የተራው ዜጋ ሁለት መስመር አስተያየት ሃይማኖት እና ፖለቲካን እንደማታቀላቅል እጅግ እርግጠኛ ነኝ።
ስብከቱ ከአንድ ሰዓት በላይ ነው። ትዕግስቴ አፍንጫዬ ላይ እንደሆነ የሚያውቀው ወዳጄ ግን አዳራ ጨርሰህ እንድትሰማው ብሎ መክሮኝ ነበር፤ አይገርምም አንዴ አይደለም ደግሜ ሰማሁት። በዚህ አስተያየት ውስጥ የሃይማኖት ክፍሉን ለሃይማኖቱ ተከታዮች በመተው ወቅታዊ የአገሪቱን ችግር የተመለከተውን ብቻ ለማሳየት እሞክራለሁ። የሰባኪውንም ማንነትም ሆነ የሃይማኖትን ጉዳዮች ሳልነካካ ማለት ነው። የወዳጄም ትልቁ ፍላጎት ይህ ነው።
ሰባኪው ይናገራል። በጥንቱ መፅሐፍ ቅዱስ እያጣቀሰ የኢትዮጵያን የዛሬ መከራ እና ችግር ይተረትረዋል። ወጣትነት፣ ስደት፣ ሙስና ፣ አድልዎ፣ ተጠያቂነት ምንም አልቀረውም። ሰባኪው የቤተክርስትያኗን አንደበት የሸበበውን በረዶ ሰብሮታል። ልክ ‘ICE Breaker’ እንደሚባለው ማለት ነው። ይህ መጀመሪያው ነው፤ አምናለሁ በርካቶች ሊከተሉ እንደሚችሉ እርግጠኛ ነኝ። አሸባሪ ተብሎ ክስ ካልተመዘዘበት በቀር። ግን ደጋግሞ ‘መናገር ካለብኝ እናገራለሁ፣ አልፈራም ’ ይላል ሰባኪው።
ወያኔ ድሮም በሃይማኖት ጣልቃ የመግባት ምስጢር መንግስተ ሰማያት አሊያም ጀነት የመግባት ፍላጎት አሳስቦት አይደለም። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ያውቀዋል። ኢትዮጵያዊው በሃይማኖቱ ስነምግባርን ብቻ ሳይሆን መስዋዕትነትም የተማረ ህዝብ ነው። ስለዚህ ወያኔ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ትላልቅ የሚባሉ ሃይማኖቶችን ወደራሱ መንገድ መጠምዘዝ ነበረበት። ህዝቡ የሃይማኖት አባቶችን ፣ የእምነት ተቋማቱን ያዳምጣል። ከልቡ። ስለዚህ ወያኔ በዚያ በኩል ሊመጣ የሚችለውን ‘የስልጣን አደጋ’ ለመከላከል የዘየደው ዘዴ የሃይማኖት ቁንጮዎችን ማወየን አሊያም መቆጣጠር ነበር።
እንደስብከቱ ግን ሃይማኖትን በአግባቡ ለማምለክ አገርና ማንነት ያስፈልጋል የሚል ግልጽ መልዕክት ተላልፏል። አትዝረፉ። ኽረ ሙስና ይብቃ።ተጠያቂነት ወዴት ነሽ? እያለ ሰባኪው ይጠይቃል። በቃ፣ በቃ፣ ይበቃል። ይላል ሰባኪው። ወያኔዎች በዚህ መልኩ ከተረዱት ትምህርት ይወስዳሉ። እራሳቸውንም ከጥፋት መልሰው ህዝቡን ማዳመጥ ይጀምራሉ። ይህን መልዕክት የትምክህተኞች እና ያለፈ ስርዓት ናፋቂዎች ነው ብለው የተለመደውን ነጠላ ዜማ ከለቀቁ ግን ከእግራቸው ስር ያለው መሬት እየተሰነጠቀ መሆኑን ለመረዳት እንደረፈደባቸው ያሳያል።
ህዝቡ በሃይማኖት በኩል ማጉረምረም ከጀመረ …. ኦሮማይ።
ጥቁር ነኝ … ነገር ግን ውብ ነኝ
ሰባኪው በክሊፑ ከ18፡00 እስከ 19፡15 ስደትን እየነገረን ለሚደርሰው ግፍ እና ኢሰብዓዊ ድርጊት ተጠያቂ የለም ይለናል። ከ 28፡33 እስከ 29፡35 ስለ ኢትዮጵያውያኖች ጀግኖች፤ ስላልተዘመረላቸው የኢትዮጵያ እንቁ ጀግኖች ይጠይቃል። ይናገራል። የእኛ ጀግኖች ብዙ እንደሰሩ ግን እንደተደበቁ ያስታውሰናል።
ከ42፡20 ጀምሮ ስለ ኢትዮጵያ ጥቁር ህዝብ ማንነት ይናገራል።የኦርቶዶክስን አከርካሪ መስበር ኢትዮጵያን ለመስበር መሞከር እንደሆነ በማስረጃ ይተነትናል። ቤተክርስቲያኗ ትምህርት ቤት፣ የህክምና ቤት፣ የፍርድ ቤት እንደነበረች ይነግረናል። አከርካሪዋ መሰበር ሳይሆን መመስገን ይገባታል ይለናል።
ከ46፡50 ጀምሮ ስለ ሞራል፣ ስለ አገር ተረካቢነት ይጠይቃል። ሙስና ከቤተመንግስት እስከ ቤተክህነት መንደሯን በስፋት እንደሰራች በግልጽ ይነግረናል። ህዝቡን እርስ በእርስ የማበላላት ፕሮግራም የኢትዮጵያን የወደፊት ማንነት ጥያቄ ውስጥ እንዳስገባ በመጠየቅ፤ መብላት እና መበላላት መወገድ አለበት ይላል። አጽንኦት በመስጠት።
ከ58፡30 ጀምሮ ሰባኪው ወደማንነታችን እንመለስ ይለናል። ወደ እውነት እንምጣ ይለናል።እምቢ፣ እምቢ እንበል ይለናል፤ ኢትዮጵያውያኖች ነንና። ኢትዮጵያውያኖች ነንና ነውር የሆነውን ትተን ወደክብራችን እንመለስ ይለናል።
ከ 1፡00፡50 ጀምሮ ስለነፃነት አባቶች ፣ ከባርነት ላወጡን አርበኞች ክብርና ምስጋናውን ያቀርባል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ኢኮኖሚያችን ሲያድግ የህዝቡ ኑሮ ለምን አሽቆለቆለ?

$
0
0

Question-Markላለፉት 8 እና ዘጠኝ ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሁለት አሃዝ አያደገ ነው ሲባል እንሰማለን፤  የእድገት ፍጥነቱ  ላይ የሚነሱ በርካታ ጥያቄውች  ቢኖሩም መንግስት  የመንገድ ግንባታ ፣ የኃይል ማመንጫ ግንባታወችን እና መሰል ነገሮችን  በመጥቀስ እድገት እንዳለ አስረግጦ ይከራከራል::  በሌላ በኩል የኢኮኖሚ እድገቱ ተመዘገበ በሚባልባቸው ዓመታት በዋጋ ንረት የህዝቡ ኑሮ ከጊዜ ወደጊዜ እያሽቆለቆለ  እንደሆነ በግልፅ የሚታይ ነገር ነው:: ታዲያ  የኢኮኖሚ እድገት አለ በተባለባቸው ዓመታት የህዝቡ ኑሮ ለምን አሽቆለቆለ? ይህን ጥያቄ ከ 7 ዓመት በፊት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ  ተጠይቀው የሰጡት መልስ የዋጋ ንረቱን የኢኮኖሚ እድገቱ እራሱ የፈጠረው ጉዳይ ነው ነገር ግን ቀስ በቀስ እድገቱ ሲቀጥል ራሱ እድገቱ ችግሩን ይፈታዋል ብለው ነበር፤ ነገር ግን ከሰባት ዓመት በዃላም እንኩአን ሊሻሻል  የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየባሰበት ሂዷል::  ችግሩ የተለያዩ  ምንጮች ቢኖሩትም በዋናነት በ 2 ከፍሎ ማየት ይቻላል::

፩. የኢኮኖሚ እድገቱ ምንጭ

፪. የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅር

የኢኮኖሚ እድገት ማለት በአጭሩ ኢኮኖሚዉ ዉስጥ ተጨማሪ ሀብት መፍጠር ማለት ነው::  በመጀምሪያ ላለፉት 8  እና ዘጠኝ ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ  የተፈጠሩት ተጨማሪ ሀብቶች ምንድን ናቸው ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል ፤  በአብዛኛዉ ሀገሪቱ ዉስጥ የተፈጠሩት ሀብቶች ከመንገድ ፣ ከሕንፃ እና ከ ከኃይል ማመንጫ ከግንባታ ጋር የተያያዙ ናቸው:: በመቀጠልም የዚህ ሀብት የገንዝብ ምንጭ ምንድን ነው ብሎ ማየት ያስፈልጋል፤ የገንዘቡ ምንጭ በዋናነት ከብድር እና እርዳታ የተገኘ ሀብት ነው ፣ በተለይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ 1998 ዓም ጀምሮ በሶማሊያ በመጀመሪያ የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት በመቀጠልም የአልሻባብ እንቅስቃሴ መጠናከር ለኢትዮጵያ ትልቅ ሲሳይ ይዞ ነው የመጣው:: በሶማሊያ ያለዉን ሁኔታ  ለመቆጣጠር ምዕራባዉያኑ የሚያደርጉትን ጥረት በመደገፍ  በዋና አጋርነት የተሰለፈችዉ ኢትዮጵያ ላለፉት ስምንት ዓመታት በየዓመቱ በቢልየን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ በእርዳታ መልክ ከምዕራብ ሃገራት እንድታገኝ አድርጓታል:: ይህም ማለት ሀገሪቱ ዉስጥ የጎላ  የኢኮኖሚያዊ መዋቅር ፣ የአሰራር ስርዓት  እና የቴክኖሎጅ ለውጥ ሳይኖር ከፍተኛ ገንዘብ ወደኢኮኖሚው ፈሰስ እንዲሆን አድርጓል:: በሌላ አገላለፅ  የቆየው የሀገሪቱ  ኢኮኖሚ የጎላ የምርት ጭማሪ ሳይኖረው ከዉጭ የተገኘ ብድር እና እርዳታ ኢኮኖሚዉ ዉስጥ ተጨመረ እና የኢኮኖሚዉ መጠን አደገ ማለት ነው::  ስለዚህ የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ እና የሀገሪቱን ተወዳዳሪነት ሊያሻሽል የሚችል የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ የጎላ  ለዉጥ ሳይታይ ለመሠረት ልማት ኢኮኖሚዉ ዉስጥ ፈሰስ የተደረገው ገንዝብ የገንዘብ አቅርቦትን (Money Supply) በመጨመር እና  የአገልግሎት ዘርፉ ( Service sector) ከሌሎቹ የኢኮኖሚ ዘርፎች ተነጥሎ እንዲለጠጥ እንዲሁም ዋጋ እንዲንር በማድረግ አብዛኛዉን ሕዝብ ለችግር አጋለጠ ::

ከብድር እና እርዳታ የተገኘው ገንዘብ መሰረተ ልማት ላይ ሲዉል ከላይ የተገለፀው ችግር ቢኖርበትም በአንፃሩ የመሰረተ ልማት መስፋፋት የማምረቻ ወጭ ( cost of production) እንዲቀንስ በማድረግ የሚያስገኘው ጥቅም አለ ፤ በተጨማሪም ገንዘብ ገንዘብን ይፈጥራል “ money creats money” በሚለው የኢኮኖምክስ  መርህ መሰረት ኢኮኖሚዉ ዉስጥ የተረጨው ገንዘብ በአብዛኛዉ አገልግሎት ዘርፉ ላይ የፈጠረው ተጨማሪ ሀብት አለ:: ነገር ግን ይህ የተፈጠረ ተጨማሪ ሀብት በጠንካራ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅር ስላልተመራ ወደጥቂት ሰወች እጅ እንዲገባ ሁኗል::  ሃብቱ እጃቸው የገባ ሰወችም የኢኮኖሚዉን መዋቅር ሊለዉጡ የሚችሉ እንደኢንዱስትሪ አይነት ዘርፎች ላይ ከመሰማራት ይልቅ ከሙሰኛ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለዉን የከተማ ቦታ በኢንቨስትመንት እና በሊዝ ስም በመዉሰድ ህንፃ በመገንባት እየተለጠጠ ላለው የአገልግሎት ዘርፍ በማከራየት በአቁአራጭ ከፍተኛ ገቢ ለመሰብሰብ ተጠቀሙበት::

በሌላ በኩል የሀገሪቱ የመሬት አስተዳደር ስርዓት በሙስና የተጨማለቀ እና ወጥ ስላሆነና አዳዲስ ብቅ ለሚሉ ባለሀብቶች መሬት ማግኘት ከባድ ስለሆነ ሀገሪቱ አሁን ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ወሳኝ ሀብት (strategic resource) የሆነዉን የከተማ ቦታ ቀድመው የያዙ ባለሀብቶች የገቢያ ዉድድሩን ሚዛናዊ እንዳይሆን በማድረግ አዲስ የሚፈጠሩ ተወዳዳሪያቸውን በቀላሉ ከገቢያ ያስወጣሉ:: በተጨማሪም እንደነዚህ አይነቶቹ  ባለሀብቶች በአብዛኛው የፖለቲካዉ እና የግዥዉ ፓርቲ ጥገኛ ስለሆኑ የሚጠበቅባቸዉን ያክል  ግብር እና ታክስ አይከፍሉም:: ሥራቸዉን ስለሚያውቁም በሀገሪቱ በረጅም ጊዜ ሊከሰት ይችላል ብለው የሚፈሩትን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ስለሚሰጉ የሚያገኙትን ትርፍ ወደዉጭ ያሽሻሉ ፤ በጎን ሙሰኛ ባለስልጣናትም የሚዘርፉትን ገንዘብ ከሀገር ያሸሻሉ:: ከዚህ ላይ ፋይናንሽያል ትራንስፓረንሲ ኳሊሽን  ያወጣዉንና ኢትዮጵያ በህገወጥ የገንዘብ ፍሰት (illicit financial flow) በፈረንጆቹ ከ 2000 እስከ 2009 ያጣችዉን 11. 7 ቢልየን ዶላር ልብ ይሏል::

ለማጠቃለል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኖ እንዲያድግ ከተፈለገ ከላይ የተጠቀሱት  የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ መዋቅር ድክመቶች መስተካከል የሚገባቸዉ ሲሆን ፤ በዉጭ ብድር እና እርዳታ ላይ መንጠልጠሉን ቀንሶ ከሀገር ቤት በፍትሃዊነት ከሚሰበሰብ ግብር ሊሆን ይገባል:: ከዉጭ የሚገኘዉን ሀብትም  በብዛት መሰረተ ልማት ላይ ብቻ ማዋሉ የሚያስከትለዉን ችግር ጥልቅ ጥናት በማካሄድ  መመርመር እና  ገንዘቡ ከመሰረተ ልማቱ ጎን ለጎን የኢንዱስትሪው እና የእርሻዉን ዘርፍ መዋቅር ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርስ ለማስቻልም መሰራት አለበት:: ከሁሉም በላይ ግን የኢኮኖሚ ነቀርሳ የሆነዉን ሙስና ለማስወገድ ከአንድ ፓርቲ የበላይነት ወደ መድብለ ፓርቲ ስርዓት መሸጋገር እንዲሁም ተጠያቂነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ እንደገለልተኛ ፍርድ ቤቶች ፣ የግል መገናኛ ብዙሃን  የመሳሰሉትን ተቋማት መፍጠር ያስፈልጋል:: ይህ ካልሆነ ግን ሀገሪቱ ሽህ ጊዜ ብታድግ የኢኮኖሚውን ፍሬ ጥቂቶች እየበሉ የአብዛኛዉ ሕዝብ  ኑሮ ማሽቆልቆሉ ይቀጥላል::

 

 

 

የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ጉዳይ ለወያኔ እጅ መስጠት ወይም ነጻ የመዉጣት ትግል ነዉ፤ ምዕመናን በድምጽ የማሸነፍ ሙሉ መብት አላቸዉ

$
0
0

ከአጥቃዉ ቦጋለ

የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ጉዳይ ለወያኔ እጅ መስጠት ወይም ነጻ የመዉጣት ትግል ነዉ። ምዕመናን በድምጽ የማሸነፍ  ሙሉ መብት አላቸዉ። በድምጽ ያሸነፈ ብቻ ይረከባል፦ይህ መብት የእንግሊዝ አገር ዲሞክራሲ  ነዉና፤ ግን ሰዉ ያልዘራዉን ማጨድ አይችልም።

londonየለንደን የደብረ ጽዮን ቅድስት ማሪያም በሁለቱም ጎን ከወያኔ ጋር እከከን ልከክህ እያሉ የዉጩን ህጋይዊ ሲኖዶስ ሙሉ በሙሉ በመርሳት ብሎም ለማዳከም በቃወም  በርከት ያሉት ዉስጥ ዉስጡን የወያኔ የልማት አጋር ሁነዉ የቆዩ ናቸዉ። አንዱ ለተፈጠረዉ ችግር ምክንያት ይህ ሳይሆን አይቀርም። ወያኔ የሚሰራዉን ግፍ ጥቂት ምዕመናን ከተቃዋሚዉ ጎን ያሉ አባላት ቢያወግዙም  በልማት አጋሮች  አስተባባሪነት አብዛናወቹ ህዝበ ክርስቲያን  ወያኔ የሚሰራዉን ግፍ ጀሮ ዳባ ልበስ ብሎ ቆይተዋል።አሁን በአንድነት የቆሙት አባላት እንኳ ቀኖና ተጥሶ በመሳሪያ አፈሙዝ ግፍ የተፈጸመባቸዉን ስደተኛ የኦርቶዶክስ አባት በጽሁፋቸዉ እንኳ ማንሳት አይፈልጉም፤ ይህ የትቢት ይሁን የጎጥ ወይም የሃይማኖት ልዩነት ግልጽ አይደለም፤ ግፍን ከማዉገዝ ገለልተኛ የሆነ ትዉልድ የለምና። ወያኔም ይህ የደለላቸዉን ብዙ የወዳጆቹን  አቋም  በገንዘብ በዉስጥ መሰሪ ካድሬወችን አሰማራ ፤የልማት ተዋናኞችም ደስተኛ ሆኖ፤ አሁን ግን ደረቅ ችሆት ይጮሃሉ። ዛሬም የወያኔ የድብቅ ነጋዴዎች  መንታ መንግድ ላይ መሆናቸዉ ጥርጥር የለዉም፤ ስለወያኔ ወንጀለኛነት በአንድ ድምጽ ሲያወግዙ አይሰማም፤ የሚሰድቡ ካድሬዉን ካህን ብቻ ነዉ፣ አህያዉን ፈርቶ ዳዉላዉን ይላሉ ይህ ነዉና። ይልቅስ አባላት ጸረ ወያኔ አቋም ይዘዉ ወንጀለኛ መንግስት ከቤተ ክርስቲያናችን እጁን  ያንሳ ማለት መቻል አለባቸዉ። የተሰደዱ አባቶች የወያኔን በደል እንዲመሰክሩ ከምዕመናኑ ፊት ባይርቁ ጥሩ ነዉ።። ወያኔ ነብስ አጥፊና  የሃይማኖት አባቶችን አሳዳጅ እንደሆነ በመረጃ አስረግጠዉ ካድሬወችንና ኢምባሲዉን ያዉግዙ፤ ይክሰሱ።ግፉ እየተፈጸመ ያለዉ በኦርቶዶክስ የሃይማኖት ዕምነት ተከታይ ክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ዉስጥ በሁሉም ዘርግ በዕምነት መገደል, መታሰር ለስደት መዳረግ መኖሩን በመረጃነት አቅርቡ። የአቡነ መርቆሪወስና የሌሎች አባተች ቀኖና ተጥሶ በወያኔ ግፍ  ጭካኔ የተሞላት ድርጊት ተሣደዉ መሰቃየታቸዉን ሳትሸማቀቁ በመረጃነት ጥቀሱ፤  የሃይማኖት ጉዳይ በመሀል ሰፋሪነት ፍጹም ሊሆን አይችልም። በሃይማኖት  ዋናዉ ቁም ነገሩ የቤተ ክርስቲያን ህንጻ በብዙ ሚሊዮን መገንባት  ብቻ ሳይሆን  ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከአንድ አምላክ በታች  ሁልጊዜም እራስ አላት ብሎ መጽናት እዉነተኛ መንገድ ነዉ። በተለይ የኛ ቤተ ክርስቲያን ብትሰደድም ገለልተኛ ሁና አታዉቅምl። ወደፊትም በአስቸኳይ ወያኔን ማስወግድ ገዘገየ ከተሰደዱ ህጋዊ አባቶች ጋር የጽድቅ ጉዟችን መቀጠል  የሃይማኖት ግዴታችን ነዉ።  ሌላዉ መንገድ ለእግዚአብሔሩ ቀርቶ ለአለማዊ የአንድነት ኑሮ አላመቸም፤  ይልቅስ የወያኔ ጅቦች  በቀዳዳዉ ይገባሉ በሚል ፍራቻ እርስ በእርስ እየተጠራጠርን ለፍርድ አናስቸግር። የዉስጥና የዉስጭ ሲኖዶስ እስቲታረቁ ከሆነ የምንጠብቀዉ እንደዚህ አይነት የሃይማኖት እምነት የለም። ኢትዮጵያ ያለዉ መንግስት ሃይማኖትን ተቆጣጥሮ ኢትዮጵያዉያንን እያሳደደ ከሆነ  ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስና ሌሎች አባቶች ጭምር እየተሳደዱ ነዉ። ይህንን በደልም ከመጥቀስ ወደኋላ አትበሉ፤ ግፍን በመረጃ ማቅረብ እኮ የአባ መርቆሪዮስ ደጋፊ አያሰኝምl፤ እኒህ የኦርቶዶክሳዊያን አባት  ለሁላችንም ሃያ አራት ሰዓት በመጸለይ ላይ እንደሆኑ አትዘንጉ፤ አስታዉሷቸዉ፤ ከህንጻዉ ይበልጣሉና።

አወ ለፍርድ ቤት በመጨረሻ ጉዳዩ ቢቀርብ ከኛ በበለጠ የኛን ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መዋቅር ቁልጭ አድርገዉ ፍርድ ቤቶች ያዉቃልና ሌሎች ቤተ ክርስቲያናትም  ከእምነታችን አስተዳደር ዉጭ ገለልተኛ ነን እያላችሁ  የምትዝናኑ ችግሩ በራችሁን ላይ በአጭር ጊዜ ያንኳካል በእዉነት ስለ ዕዉነት አስቡበት። ለመሆኑ በአሁኑ ሰዓት አገር እየጠፋ ከምኑ ገለል እደምትሉ የሚጨበጥ ቁም  ነገር ጠፍቷል። ጉዳዩ በጽዮን  ብቻ አያበቃም፤ የሃይማኖት ቤታችን ወደ ንግድ ተቋም የመሸጋገር አደጋ እዬገጠመዉ ነዉ፤ እግዚአብሔር ወደ እዉነቱ ቦታችን ይመልሰን። ሌላዉ የዚህ ዓለም መንግስታዊ ፍርድ ቤት በህዝብ ድምጽ ያምናልና ለወያኔ ጊዚያዊ  የልማት ተጠቃሚ የሆናችሁ ወያኔን ካዱትና ድምጻችሁን ስጡ። የለደን ደብረ ጽዮን አባላት ብዙ ምሁራን እና የቤተ ክርስቲያን ሊቃዉንት እያሉበት  ግን በልማት ስምና ጎንደሬ ፓትራሪክ አቡነ መርቆሪዮስ ለመቃዉም ሲባል  የገለልተኛ ከበሮ አታድምቁ  ሲሆን የተበደለዉ ሁሉ ተባብሮ ማሸነፍ ፤ካልሆነም ገለል ከማለት በዓላማ ጸንቶ አወዳደቅን ማሳመር ተገቢ ነዉ። ወያኔም  ይህን የወላዋይ አቋም ይዘዉ መክረማቸዉን አስተዉሎ ጭራቸዉን በመያዝ  ፊታቸዉን መልሰዉ ወያኔ ገዳይ ነዉ ፤ጠላትም ነዉ ብለዉ መናገር እንዳይችሉ አደረገ። ምርጫዉ የኛ ነዉ፤ ለፍትህ ፤ ለሃይማኖት መቆም ወይስ ሁለት ባላ ላይ ለመቆም ወያኔ መንደር የተሰራዉን  ከንቱ የልማት ቤት በህልም እያዩ ወያኔ የጠለፋ ገመድ ታስሮ ባርነትን መምረጥ ፤ የቆጡን አወርድ ብሎ የ…..ማለት እንዲህ ነዉ። ሁሉም አባላት  ማለትም አብዛኛዉ ከተስማሙ መፍትሄዉ ቀላል ነዉ በአንድ ድምጽ የሚሰራዉን ግፍ ስናወግዝ ያኔ የወያኔ አደራጆች /ጠርናፊወች ጓዛቸዉን ጠቅለዉ ይሄዳሉ። በአሜሪካ ሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድሃኒአለም የሆነዉ እንደዚህ ነዉ፤ የወያኔ ጠርናፊወች በስድስት ወራት 700 አባላትን አስመዝግበዉ በድምጽ ለማሸነፍ  በጉባኤ ሲቀመጡ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን ነብር ዝንጉርጉርነቱን አይቀይርምና  አብዛኛዉ አባላቱ አቋማቸዉን አንድ አድርገዉ ወያኔ በመካድ  ኢትዮጵያ ዉስጥም ሆነ በየአለማቱ ወያኔ ሲሰራ የቆየዉን የሃያ ሁለት ዓመታት ግፍ አስረግጠዉ በመንገር፤  ከወያኔ ስር የምንወድቀዉ ምን አዲስ የሃይማኖትም  ወይም የህዝብ ነጻነት ተገኘ በማለት  ከሆዳሞች በቀር አብዛኛዉ ምዕመናን በጸረ ወያኔ አቋሙ ወስዶ  መድሃኒአለምን እጅ መንሻ ከመሆን አዳነ።  የለንደን ጽዮን ምዕመናን ትኩረታችሁ በቻሪቲ ጉዳይ ብቻ አታድርጉ ከዉስጣችሁ የመሸጉትን የልማት አባዉራወች በመነጸር እዩ ፤ በደም የተጨማለቁ በመዋለ ንዋይ የሰከሩ ወያኔወች ገለልተኛነት የወያኔ መሸጋገሪያ መንግድ አድርገዉ የተጠቀሙ ካድሬዎች ከዬቤተ ክርስቲያን ተመንጥረዉ ያለ እሉኝታ መባረር አለባቸዉ። በሚኒሶታ የተሰገሰጉት ንፍቀ ወያኔወች የወደፍቲ እጣ ይህ ነዉ። አሁን  ቢወድቁም ሙቶ የመፈራገጥ የወያኔ ባህሪያቸዉ አይጠፋምና  ምዕመናኑ ጠንቅቆ ስለሚያቃቸዉ በሚቀጥለዉ ምርጫ ከሚኒሶታ መድሃኒዓለም ግቢ ጨርሶ እንደሚያስወጣቸዉ እርግጠና ነኝ። ዘረኛዉ ወያኔ በለደን አካባቢ መሽጎ የሚተበትበዉ የሴራ ገመድ በአጭር ቀን ይበጣጠሳል። ምዕመናኑ በአንድነት መቆም ብቻ ሳይሆን የችግሩ ዋና ምንጭ የሆነዉን ወያኔን በማጋለጥ l ማለትም የሚያካህደዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራዉ፤ በኦሮሞዉ, በጋምቤላዉ፤ በአፋሩ ሁሊንም ብሔሮች በመክፋፈልና በማጋጨት በዘረፋ ላይ መሰማራቱን መላዉን ኢትዮጵያዉያን የዕምነት ነጻነት መንፈጉን በአ,ደባባይ ተናገሩ። የወያኔዉን ተላላኪ ካህን ብቻ ማዉገዙ ፋይዳ የለዉም፤ አህያዉን ፈርቶ ዳዉላዉን ነዉና፤ ወደቁንጮዉ አነጣጥሩ። የሰዉ ዘር አጥፊና የሃይማኖት አባቶቻችን በማሳደድ ላይ እንዳለ ለለንደን ህዝብና ለእንግሊዝ መንግስት  አስረዱ። የወያኔ መንግስት ተባባሪ እነማን እንደሆኑ አጋልጣችሁ ከስርዓቱ ጋር ተጠያቂ መሆናቸዉን አስተምሩ፤ ከዉስጣችሁ ገና በህዝብ መብት ጉዳይ በወያኔን ጠላትነት ጉዳይ የጠራ  አቋም ያልያዙ ያሉ ይመስለኛል፤ ሁላችሁን ማለቴ አይደለም፤ ገለልተኛ ነን፤ ብዙ ገንዘብ አዉተን ህንጻ ገንብተናል ማለት ብቻ በቂ አይመስለኝም፤ ይህ በሃይማኖት ቤት ብዙ አይስተናገድም። ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ በግፍ የተሰቃዩ አባት መሆናቸዉን ጭራሹን  አትርሱ፤ ከቀኖናም ሆነ ከሃይማኖት አንጻር መሰረታችሁ መስመሩን መዉጣት የለበትም፤ አባ መርቆሪዮስን ወያኔ በመሳሪያ ማዉረዱን ታዉቃላችሁ። እናንተን ግን በልማት ስም ወያኔ ሊያዋርዳችሁ በአንድ ለአምስት ጥርነፋዉ በገለልተኛ መርሆ ገብቶ ህገ ቤተ ክርስቲያን እያፈረሰ ነዉ። በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ  መፍትሄ የሚገኘዉ  የእዉነቱን በመናገር እንጂ ንብረቱን ለመቆጣጠር የሚደረገዉ የሽቅድድም እሩጫ የአምላክ መልካም ፈቃድ አይጨመርበትም። አወ ወያኔ ባወጣዉ የጎጥ መስፈርት  አቡነ መርቆሪዮስ ጎንደር ክፍለ ሃገር የተወለዱ ናቸዉ፤ ሃቁ ግን ወያኔ ሊቀ ጳጳሱ ትግሬ ቢሆኑ  አያባራቸዉም።  ይኸዉ አሁንም ደግሞ ደጋግሞ የሚሾመዉ የትግሬ ፓትራሪክ፤ የትግሬ ጀኔራል ነዉ። በእርግጥ ይህ ስልቱ ትግሬዉን ከሌላዉ ህዝብ እያራራቀ የስልጣን ዘመኑን አስረዝሞ ለመዝረፍ ነዉ። ሃቀኛ የትግራይ ልጆች አሁንም በወያኔ እዬተገደሉ እዬተሳደዱ ነዉ፤ ዉሎ አድሮ የትግራይ ህዝብ በቃ ይላቸዋል፤ አዎ ብዙ ገንጣይ ወያኔን ታገሉት ግን አፍኖ አዳከማቸዉ፤ የዕራያ ህዝብ ዛሬ ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ነዉ፤ የተንቤን ህዝብ ከተረሳ ዓመታት አልፈዋል። ኢትዮጵያን ቆራርሶ ወያኔ ለባዕድ አግር በመስጠት ያዋረዳት እየከነከነዉ ቆሽቱ ያረረዉ  የትግራይ ህዝብ ከመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሁኖ  ወደክብሯ ለመመለስ ትግሉን ቀጥሏል። አየ ጉድ ጽሁፌን የወያኔ የዘር ጣጣ ጠልፎ ወሰደብኝና ብዙ ተናገርኩ፤ በሉ የጀመርኩትን ልጨርስ። አባ መርቆርዮስ ጎንደር ቢወለዱም እዉነተኛ ኢትዮጵያዊ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ/ክ  አባት ናቸዉ፤ በእርሳቸዉ የደረሰዉ ስቃይና መከራ እየረሳን  ማህበረ ቤተ ክርስቲያን ማጠናከር ወይም ባለቤት መሆን እግዚአብሔርም ሆነ ቀኖና አይደግፈንም። ሁላችን ሁሉን ህግ የሚጥሰዉን ወያኔን  ዘረኛ፤ ነብሰ ገዳይ፤  ዘራፊ ነዉ ብለን፤ ትግሬዉ፤ ኣማራዉ፤ ኦሮሞዉ፤ ሃድያዉ፤ ማለትም መላዉ ኢትዮጵያዊያን በዉጭ የዘረጋዉን የዘር መረብ በአንድነት መበጣጠስ አለብን። ችግሩ  በአሜሪካም እንዳንዣበበ ነዉ ። የዋሽንግተን የማሪያም  ቤተ ክርስቲያን እጣ ፈንታም  ተመሳሳይ ነዉ። እጀ እረጅሙ ወያኔ ለስላ ከመደበዉ 40MILLION ዶላር ብዙዉን ይህችን ትልቅ ካቴድራል አንቆ ለመያዝ የተጠቀመበት ነዉ። የልማት ሚሊዬነሮች በመቶ ሺህ በሚቆጠር ገንዘብ እዬደለሉ  ከካህናት ጋር እየተጋሩ ወያኔ መስመሩን  አንድ በአምስት በማደራጀት መርሆ ዘርግቶ በልማት ባላንባራሶቹ አማካይነት ዘርጥጦ ለመጣል ትልቅ ምሽግ ይዞ  60 ሚሊዮን የሚገመት  ንብረት በመጨረሻ የወያኔ ጦር ሜዳ ይሆናል። ቢያንስ በአቡነ መርቆርዮስ ማለትም በስደደተኛ አባቶች አስመዝግበዉ ቢቆዩ መልካም ነበር። ችግሩ ግን ከወያኔ ጋር በልማት የተቆራኙ ብዙ ሃብታሞች  ስላሉ  ከወያኔ ስዉር ሰንሰለት ነጻ የሚሆኑበት መንግድ እየጠበበ ሳይመጣ አይቀርም፤ በአቋራጭ እግዚአብሔር ከወያኔ እንደሚገላግለን  ግን ሙሉ ተስፋ አለኝ። ማሪያምን ከሆዳሞች ሽያጭ ያድናት። በሉ ሃይማኖታችሁንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መሳሪያችሁ አድርጉ፤ ስደተኛ አባቶቻችሁን አትርሱ፤ አባ መርቆርዮስም አይባርኩን፤ አባ ማትያስምም አንፈልግም እንዲያዉ ከንቱ ምክንያት አልባ ህዝቡን ኦርቶዶክሳዊ ባልሆነ መንገድ አታድክሙት። የግፍ አገዛዝ በቃ በሉ፤ በከንቱ ዳር ዳርና የገለልተኛ ማሃል ሰፋሪነት  በሃይማኖት መሪነታቸዉ ብቻ የተሰቃዩ አባቶችን ከመርሳት ደረጃ አያደርስም።  ለህዝብ መብትና ለቤ/ክ የአስተዳደር ነጻነት ታገሉ፤ የአንድነት መድሃኒታችን የጎጠኛነት መርዝን ይነቀል። እግዚአብሔር ለዕዉነትl ለፍቅር ለቆሙ ሁሉ ዘወትር አይለይምና ለሃይማኖታችሁና ለአገራችሁ ያላችሁን አቋም  ከስጋዊ ኑሮና ከባለጸጋነት  በላይ አድርጉ፤ እግዚአብሄር ሁሌ ከተበደሉ ጎን አይለይማና ሰይጣኑን ወያንን የሚያሸንፍ ሃይል ይስጣችሁ።

መልካ ገና እና የምዕራቡ ጥሩ አመት ያድርግልን

አጥቃዉ ቦጋለ

ወስብሃት ለእግዚአብሔር

ቴዲ አፍሮ እና ጥሬ ጨዋዎች

$
0
0

teddy 2
ሁኔ አቢሲኒያዊ - ፒተርቦሮው ዩ.ኬ

ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) በብዙዎች ሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ትልቅ ስፍራየሚሰጠው ወጣት ከያኒ ነው፤ በሙዚቃዎቹ በሚያነሳው ሀገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ታሪካዊና ወቅታዊ ጉዳዮች የተነሳ የብዙዎችን ቀልብ ለመግዛት የቻለ ይመስለኛል፡፡ የእርሱን ታላቅነት መግለፅ የዚህ ጹሑፍ ዓላማ፣ ጥያቄም፣ የማወቅም ፍላጎት አይደለም፡፡
ይልቁንም ለዚህ አጭር መጣጥፍ መነሻ የሆነኝ ከሰሞኑ በአንዳንድ ጥቃቅን እና አነስተኛ ካድሬዎች እንዲሁም መንግስትን ለምን እንደሚቃወሙ እንኩአን በማያውቁት እንደ እነ ጃዋር መሀመድ የመሳሰሉ ሰሞንኛ ትችታቸውን በመሰንዘራቸውን ምክንያት እኔም የተሰማኝን ልጨምር በሚል ነው፡፡
እንደምናውቀው ቴዎድሮስ ካሣሁን በዚህች የሙዚቃ ህይወቱ ከዛቻ እስከመታሰር ድረስ የደረሰ መሆኑ እሙን ነው ይህም የደረሰበት የተለየ ሰው ስለሆነ ነው
ቴዲ ሺህ ዘመናት ስልጣኔያችንና ታሪካችን፣ ጥበባችን በፍቅር፣ ፍቅራችን በጥበብ የተገመደበት ውሉ ከየት ተጀምሮ የት እንደተቋረጠ ታሪክንእንጠይቅ ዘንድ እንዲህ ሲል በቅኔው ተመራምሮ ያመራምረናል፡-
ብራናው ይነበብ ተዘርግቶ ባትሮኖሱ ላይ፣
የእነ ፋሲለደስ የእነ ተዋናይ፣
የት ጋር እንደሆነ ይታይ የእኛ ጥበብ መሰረቱ…፡፡
እናም እስቲ ታሪክ ይታይ፣ ይመርመር፣ ዘመናትን ያስረጁና የተሻገሩ ብራናዎቻችን ይውጡ፣የሺህ ዘመን የሃይማኖት፣ የጥበብ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔና የፍልስፍና ድርሳኖቻንን ይታዩይመርመሩ… በአክሱም ስልጣኔ፣ በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ትንግርት፣ በጎንደርበእነ ፋሲለደስ የስልጣኔ አየር ዝናዋ የናኘላት፣ እነዛ ፍቅርን በጥበብ አስውበው በቅኔያቸውናበማኅሌታቸው ሰማይ ሰማያትን ሰንጥቀው በመንፈሳቸው ጸባዖት የደረሱ፣ በፍቅር ጧፍ የነደዱበማሕሌታዩ ያሬድ መንፈስ የተነሱ እንደ ተዋናይ ያሉ የቅኔ የጥበብ ጉልላቶች እንደ አጥቢያኮከብ በደመቁባት ምድር ዛሬን ፍቅር የተራብን፣ ጥበብን የተራቆትን፣ ስለ ፍቅር የደከመንምንድነው ምክንያቱ የሚል ይመስለኛል ቴዲ…፡፡
ቴዲ በሙዚቃው ለታሪክ ያለውን ስሱነትና (sensitivity) እውቀትም (Indigenous Knowledge)አሳይቶናል፡፡ ተዋናይን ስንቶቻችን እናውቀዋለን ተብለን ብንጠየቅ የሚያስተዛዝበን ሳይሆንይቀራል፡፡ በተለይ ደግሞ ለዘመናችን ትውልድ ለአፉም ለልቡም ቅርቦቹ እነ አርሴናል፣ቼልሲ፣ ሜሲ፣ ሮናልዶ፣ እነ ፊፍቲ ሴንት እነ ቢዮንሴ፣ ወዘተ… የባሕር ማዶዎቹ ዝነኞች ናቸውእንጂ እነ ተዋናይን እነ ቅዱስ ያሬድን፣ እነ አጼ ፋሲልን ሊያስባቸው ወኔው ያለውአይመስልም፣ ኅሊናውንም ይደክመዋል እናስ እንዴት፣ ምን ሲደረግስ ሊያስባቸው ይችላል የኔትውልድ፡፡ በቅኔው የተራቀቀና በመንፈሳዊ እውቀቱ አንቱ ስለተባለው ስለ ተዋናይለመስማትም ሆነ ለማወቅ የታሪክ መዛግብትን ማገላበጥ ግድ ይላል፡፡ አሊያም ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች እግር ስር ቁጭ ማለት ያስፈልግ ይመስለኛል፡፡
ቴዲ በየትኛው መንገድ የሀገሩንና የቤተ ክርስቲያኑን የጥበብ እና የሥልጣኔ ከዋክብቶችንሊያውቅ እንደቻለ ባይነገረንም የትናንትናዎቹን የሀገራችንን ባለውለታዎችና የዘመንፈርጦች ማንነት ለማወቅ እና እንዲሁም ታሪኩን ለመመርመር ግን የተጋና የሰላ አእምሮእንደተቸረው/እንዳለው የግጥሞቹ መልእክቶች ይነግሩናል፡፡ እናም ከታሪካችንናከስልጣኔያችን መሰረት ከአክሱም ተነስቶ በጊዜና በታሪክ ሃዲድ ላይ አሳፍሮን በትላንትታሪካችን ውስጥ ራሳችንን እንድንመረምር፤ ራሳችንን እንድናይ ይወተውተናል፡፡ ለዚህደግሞ ምክንያቱ ይለናል ቴዲ ስለ ፍቅር ዜማው ውብ የግጥሞቹ ስንኞች፡-
. . .የኋለው ከሌለ የለም የፊቱ፣
ሳይራመድ በታሪክ ምንጣፍ፣
ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ፡፡
በማለት ከታሪካችን ጋር እጅ ለእጅ በምናብ ሊያጨባብጠንና ሊያስተያየን ይፈልጋል፤ እናምያለ ትላንት ዛሬ የለም፣ ያለ ዛሬ ደግሞ ነገ አይታሰብም በሚል የመጣንበትና የተጓዝንበትንአኩሪና አሳፋሪ የታሪካችንን ምእራፍ ለማገላበጥ ለደከምን ለእራሱ እና ለእኛ ትልቅ ቁም ነገርያለው ምክር ያስተላልፋል፡፡ ይህ የከያኒው የግጥም ስንኝ የሮማውን ታላቅ የሕግ ሊቅ፣ፈላስፋና አስተማሪ የሆነውን የሲስሮን አባባል አስታወሰኝ፡- ‹‹ከመወለዳችን በፊት ያለውንታሪክ ካላወቅን ዕድሜ ልካችንን ሕጻን ሆነን እንቀራለን፡፡›› ታሪካችንን ለመመርመር እናከታሪካችን ለመማር የደከምን እኛ ዛሬም እንደ አዲስ ሰናፈርስ ስንጀምር ከመጀመር ሀ ሁሳንወጣ እንደ ህጻን ባለህበት እረገጥ የሆንበትና ታሪክን እንድንደግም የተፈረደብን ምስጢሩምን ይሆን በማለት ታሪክ ጠያቂ፣ የታሪክ ወዳጅ፣ ከታሪክ የምንማር እንድንሆን ያተጋናል፡፡
ከምንኮራበት ታሪካችንና ስልጣኔያችን ባልተናነሰ አንገት የሚያስደፋ ስማችንና ማንንታችንበዓለም ፊት በቀየረብን በበርካታ የራብ፣ የእርስ በርስ ጦርነትና መበላላት ታሪክ ዘመናትንውስጥ አልፈናል፡፡ እናም የመጣንበት መንገዱ ረጅም ዘመናቶቻችንም መከራ ሰቆቃና ዋይታ የነገሰባቸው ናቸው ሲል የትናንቱን ታሪክ ለመድገም የተፈረደብን ይመስል ታሪክ ደጋሚዎች እንድንሆን የሆንበትን እውነታ መመርመርና ማየት እንችል ዘንድ ትልቅ ጥያቄያጭርብናል፡፡ ዛሬም እግራችን መሄድ ተስኖት ቆመናል
የእርሱ ደጋፊዎች እንዳሉ ሁሉ የእርሱ ተቃዋሚዎች መኖራቸው ተፈጥሮአዊ ነው ነገር ግን በአሉባልታ የቴዲን ስራዎች ጥላሸት ለመቀባት የሚደረግ ትግል ወይ ቅናት ነው አልያም ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው እንደሚባለው ይሆናል፡፡
ለእምዬ ምንሊክ ያላቸው ጥላቻ ሰሞኑን ተቀስቅሶባቸው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ከርመዋል አስገራሚው ነገር ምንሊክን ለመሳደብ ቴዲን ሰበብ ማድረጋቸው ነው ሌላው ደግሞ መረጃውን እኔ ለቅቄዋለው ብሎ ማንም ኃለፊነቱን እሰከዚች ሰዐት ድረስ ሳይወስድ እነርሱ ቴዲን እና ምንሊክን መዝለፍ የየእለት ተግባራቸው አድርገውታል፡፡
ምንሊክን ህዝቡ እምዬ ብሎታል ቴዲን ደግሞ የዘመናችን የሙዚቃው ንጉስ ብሎ ሰይሞታል
ደበበ ሰይፉ ጥሬ ጨው በሚለው ግጥሙ እንዲህ ነበር ለነፈዞች የገጠመው

ጥሬ ጨው – ደበበ ሰይፉ
————
መስለውኝ ነበረ ፣
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች ፣
ለካ እነሱ ናቸው ፣
ጥሬ ጨው..ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች ፣
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ-
መታሸት-መቀየጥ
ገና እሚቀራቸው ፣
“እኔ የለሁበትም !”
ዘወትር ቋንቋቸው ።

ለማንኛውም እኔም እንደ ደበበ ሰይፉ ሰሞንኛ የቴዲ ተቺዎችን ጥሬ ጨው ብዬ ሰይሜያቸዋለው፡

 

አንድነትና የሚሊየንም ድምጽ ለነጻነት ንቅናቄ –አማኑኤል ዘሰላም

$
0
0

amanuelzeselam@gmail.com
ታህሳስ 15 ቀን 2006 ዓ.ም
 

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር፣ አቶ ይልቃል ጌትነት፣ በዉጭ አገር የሥራ ጉብኘት እያደረጉ እንደሆነ በስፋት እየተዘገበ ነዉ። ታዲያ «ስለ ሰማያዊ ብዙ እየሰማን፣ የአንድነት ፓርቲ ድምጽ ግን ምነዉ ጠፋ። የሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነትስ ወዴት ገባ ?» ብለን የምንጠይቅ ልንኖር እንደምንችል አስባለሁ። በዚህም ረገድ በአንድነት ፓርቲ ዙሪያ አንዳንድ ሃሳቦች ለአንባቢያን ለማካፈል እሞክራለሁ።

በቅድሚያ አንድ መረዳት ያለብን ነገር አለ። የአንድነት ፓርቲና እና ሰማያዊ ፓርቲ፣ ሁለቱም ተመሳሳይ የፖለቲካ ፕሮግራም ቢኖራቸውም ፣ ሁለቱም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለዉጥ ለማምጣት ቢታገሉም፣ የአሰራር ልዩነቶች አሏቸው። የአንድነት ፓርቲ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የትግሉ አካል እንደሆነ ቢያውቅም፣ መሰለፍ ብቻ በራሱ ምንም ሊያደርግ እንደማይችል ጠንቅቆ የተረዳ ደርጅት ነዉ። በዚህም ምክንያት ግብታዊ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ከማድረግ ብዙ ይቆጠባል። ሰልፎችም ሆነ ማናቸዉም አይነት ሰላማዊ እንቅስቅሴዎች ተጠንተዉ፣ በጥንቃቄና ዉጤት በሚያመጣ መልኩ መደረግ አለባቸው ብሎ ያማናል። ካለፈው የቅንጀት ስህተቶች ብዙ የተማረ ነው።

በመሆኑም ሰልፍ አልተደረገም ማለት እንቅስቃሴ የለም ማለት አይደለም። የአንድነት ፓርቲ በአሁኑ ወቅት እያደረጋቸው ያላቸዉን አራት በጣም አስፈላጊና መሰረታዊ ጉዳዮች እንዳካፍል ይፈቀድልኝ፡

1. አንድነት፣ ከሰኔ እስከ መስክረም የተደረገዉን የሚሊየኖችም ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴዎች፣ እንዲሁም የፓርቲዉ ጠቅላላ ስራዎች፣ ወደ ኋላ ተመልሶ ግምገማ እያደረገ ነዉ። «የቱ መስተካከል አለበት ? የቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ? ..»እየተባለ ፣ ጠቃሚ ትምህርቶችን ለማሰባሰብ እየተሞከረ ነዉ። ዝም ብሎ መሮጥ አይደለም። ቆም ብሎም ማሰብና እራስን መመርመር፣ ካለፉትን ተግባራት መማር ያስፈልጋል።

2. ፓርቲው በቅርቡ የአመራር አባላትን ይመርጣል። አብዛኞቹ አገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ ያሉ ድርጅቶች አንድ መሪ ነው ለዝንተ አለም የሚመራቸው። የአንድነት ፓርቲን መጀመሪያ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ከዚያም ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ፣ ከዚያም ዶር ነጋሶ ጊዳዳ መርተዋል። አሁን ደግሞ ዶር ነጋሶን ለመተካት ሶስት እጩዎች የምረጡኝ ዘመቻ ላይ ናቸው። እነርሱም የፓርላማ አባል የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ ቀድሞ ፓርቲዉን ሲመሩ የነበሩትና በበርካታ አባላት እንደገና እንዲወዳደሩ ግፊት እንደተደረገባቸው የሚነገረዉ፣ አንጋፋው ኢንጂነር ግዛቸው እንዲሁም ኮንሴንሰን ቢልድ በማድረግና በአስተዋይነታቸው የሚታወቁት፣ በአሁኑ ወቅት ፓርቲዉን በፋይናንስ ሃላፊነት የሚመሩት፣ አቶ ተክሌ በቀለ ናቸው።ይህ በአንድነት ዉስጥ እየተደረገ ያለው ፉክክር ፣ በማንም የአገራችን ድርጅቶች ያልታየ ዴሞክራሲያዊ  ፉክክር ነዉ።

3. እርግጥ ነዉ ከአሁን ለአሁን ሕብረት ያስፈልጋል ተብሎ፣ ወደ ኋላ ከሚጎትትና ስራን ከማያሰራ ድርጅት ጋር ሕብረት አይፈጠርም። ሕብረት ሲፈጠር ለዉጤት መሆን አለበት። በዚህም ረገድ አንድነት ከዚህ በፊት አካል ከሆናቸው እንደነ መድረክ ካሉ ስብስቦች ጋር ያለዉን ግንኙነት እየፈተሸ ነዉ። በአንጻሩም ደግሞ ፓርቲውን ሆነ ትግሉ ወደፊት እንዲሄድ ሊረዱ የሚችሉ ፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ፣ የላይ ላይ ትብብር ሳይሆን የዉህደት እንቅስቃሴ እያደረገ ነዉ። ከዚህ በፊት እንደ ብርሃን ፓርቲ ያሉ ድርጅቶች ከአንድነት ጋር መዋሃዳቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ አንድነት ፓርቲ ከአንጋፋዉ መኢአድና በአሁኑ ወቅት አስደሳች እንቅስቅሴ በሜዳ ላይ አያደረገ ካለው ከአረና ጋር ለመዋሃድ ትልቅ ሥራ እየሰራ ነዉ።

4. ሰላማዊ ሰልፍ ሆነ ሌላም ሌላም እንቅስቅሴዎች እንዲሁ በግብታዊነት አይሰሩም። ጥናት፣ ጥንቃቄ፣ ዝግጅት ያስፈልጋል። የስሜት ትግል የትም አያደርሰም። ትግሉ የሰከነ፣ የበሰለና ዉጤት የሚያመጣ መሆን አለበት። የአንድነት ፓርቲ የሚሊየነም ድምጽ ለነጻነት በሚል ስም የጀመረው እንቅስቃሴ ክፍል ሁለት፣ ከአመራር አባላት ምርጫ በኋላ፣ ይታወጃል። ይህ እንቅስቃሴ አዲስ አበባ ዉስጥ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን፣ በመላ አገሩቷ ያተኮረ፣ ትግሉን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚወስድ እንቅስቃሴ ይሆናል። ለዚህም እንዲረዳ አባላት በሰላማዊ ትግል ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎች እየወሰዱ ናቸው።

እንግዲህ አገር ዉስጥና ከአገር ውጭ ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እላለሁ። በአገራችን ሙስና የመስፋፋቱ፣ ዘረኝነት የመብዛቱ፣ የሕግ ስርዓት ያለመኖሩ፣ የኑሮ ዉድነቱ፣ የሰባአዊ መብት ረገጣዉ ፣ ኢትዮጵያ ለብዙሃኑ ሲኦል፣ ከገዢው ፓርቲ ጋር ግንኙነት ስላላቸው ብቻ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ሚሊየንር ለሆኑት ለጥቂቶች ገነት ለመሆኗ ምክንያቱ የፖለቲካዉ ችግር ነው። የፖለቲካ ችግርን ለማስተካከል ደግሞ የፖለቲክ ትግል ይጠይቃል። የአንድነት ፓርቲ ይህ ለሰላምና ለፍትህ የሚደረገዉን የፖለቲክ ትግል ለመምራት እየሰራ ነዉ።

የአንድነት ፓርቲ ከሁለት ወራት በፊት ባደረጋቸው አገረ ሰፊ፣ የሚሊየም ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴዎች፣ በአዲስ አበባ፣ በመቀሌ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በደሴ፣ በጂንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በወላይታ ሶዳ፣ በባሌ/ሮቢ ፣ በፍቼና በአዳማ ሰላማዊ ሰልፎች አድርጓል። በመቀሌ ሰልፉ ሊደረግ አንድ ቀን ሲቀረዉ የሕወሃት ባለስልጣናት «እንኳን አንድነት፣ ቅንጅትም መቀሌን አልደፈረም»በሚል የቅስቀሳ መኪናዎችን እና ማይክሮፎኖችን በማገታቸውና የአመራር አባላትን በማሰራቸው፣ ከአሥር አምስት ቀናት ቅስቀሳ በኋላ ሰልፉ ሊሰረዝ ችሏል። በባሌ/ሮቢ፣ ኦሕድዶች ሰልፉ ከመደረጉ አንድ ቀን በፊት፣ «ሰልፉን ካደረጋቸው ከፍተኛ ደም መፋሰስ ይሆናል» የሚል ዛቻ በመሰንዘራቸው ፣ ሕዝብን አደጋ ላይ ላለመጣል ሲባል፣ ሰልፉ ሳይደረግ ቀርቷል።

የአንድነት ፓርቲ በአዋሳ፣ በጋምቤላ፣ በወሊሶ፣ በድርደዋና በአሳሳም ሰልፎች ለማድረግ እቅድ ነበረዉ። ነገር ግን በገንዘብ ማነስ ምክንያት እነዚህ ከተሞች ሰልፍ ማድረግ እንዳልተቻለ ነው።

አሁንም ፓርቲዉ የተቻለዉን ለማድረግ የወሰነነ የቆረጠ ቢሆንም፣ ፓርቲዉ የሕዝብ ድጋፍ ከሌለዉ ሊያደርግ የሚችለው የተወሰነ ነዉ። በተለይም የገንዘብ አቅም ላይ ትልቅ ትኩረት መስጠት እፈልጋለሁ። እንዲሁ ለዉጥ ስለተመኘን ለዉጥ አይመጣም። አገር ቤት ያሉ ኢትዮጵያዉያን በጓዳና በሹክሹክታ ብሳታችንን መግለጽ ማቆም ይኖርብናል። ትግሉ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊን ተሳትፎ ይጠይቃል። ጠንካራ ፓርቲ ሲመጣ መቀላቀሉ ሳይሆን፣ አሁን ያሉትን፣  እንድ አንድነት ፓርቲ አይነቶችን ጠንካራ እንዲሆኑ ማድረጉ ይበጃል።

ዉጭ አገር ያለነው ፣ ምን እንኳን የመገደል፣ የመታሰር፣ የመዋከብ አደጋ ባያገኝንም፣ ቢያንስ ስራችን እና አፋችን መገናኘት ያለባቸው ይመስለኛል። «አገር ቤት ካሉት ድርጅቶች ለዉጥ ለምን አያመጡም» ብለን መናገርና መጠየቅ ሳይሆን፣ ለዉጥ እንዲያመጡ የነርሱ አካል ሆን ድጋፋችንን መስጠት ይጠበቅበናል። ሕዝቡ ካልተነሳና ካልተነቃነቀ በምን ሁኔታ ለዉጥ ሊመጣ አይችልም። ህዝቡ እንዲነሳ ሕዝቡ መሃከል ሆኖ ትልቅ ድርጅታዊ ሥራ መስራት ያሰልጋል። ይህን አይነት ድርጅታዊ ሥራ ለመስራት፣ ሕይወታቸው ለዚህ ሥራ አላልፈው ከሰጡ አገር ቤት ካሉ ጀግኖች ጎን መቆም ይኖርብናል።

እንግዲህ ለሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴ ክፍል ሁለት ከወዲሁ ሁላችንም እንዘጋጅ። ፓርቲዉን በገንዘባችን እንደግፍ። በገንዘብ ለመርዳትና ከሚሊዮኖች አንዱ ለመሆን የሚፈልጉ ከሆነ የሚከተለዉን ድህረ ገጽ ይጎብኙ !

http://www.andinet.org/

 

comment pic

 

 

ትንሽ ስለጃዋር መሀመድ _ ከዓለማየሁ መሀመድ

$
0
0

ሁለት ነገሮችን ላንሳ።

1.  የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል መሬት አንቀጥቅጥ ሆኖ ለሁለት ዓመት ገደማ ዘልቋል። በዚህ ትግል ውስጥ በሀገር ቤት ከስርዓቱ ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው ደም ህይወታቸውን ገብረው ትግሉ በማይናወጥ ጽናት ላይ እንዲቆም ያደረጉት ብዙሃኑ ሙስሊሞች ዋጋቸው በክብር መዝገብ ላይ ምንጊዜም ወርቃማ በሆነ ቀለም ተመዝግቦ ይቀመጣል። ከእነሱ ባሻገር በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትግሉ መሬት ይዞ  በሰከነ መልኩ እንዲጓዝ ያደረጉት አስተዋጽኦም የሚዘነጋ አይደለም። ጃዋር በዚህ ውስጥ ስሙ ሲጠቀስ ነበር። የሙስሊሞች ትግል ላይ ትንሽም ብትሆን አሻራው አርፎበታል። ያኔ ነው። በፊት። አሁንስ?

2.  የኦሮሞ ህዝብ ጭቆና ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተለየ ነው- አይደለም -የሚለው ክርክር ለጊዜው ይቆይና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ለ40 ዓመታት ሲያቀነቅነው የነበረውና ውጤት ሳይኖረው ዘመናት የቆየው ትግሉ አሁን ‘’የኦሮሞን ህዝብ ትግል በኢትዮጵያ ጥላ ስር’’ የሚለው ሀሳብ አሸንፎ ሲወጣ ጃዋር ብቅ አለ። መጀመሪያ ላይ በሳል በሆኑ፡ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ፡ የሰውን ልጅ በአንድ መነጽር የሚመለከቱ የሚመስሉ ሀሳቦች በጃዋር አፍ ውስጥ ይዋኙ ነበር። ይህም በተቀረው ኢትዮጵያውያን ዘንድም ጃዋር ምናልባት ያረጀውን የኦነግ ጠባብ ብሄርተኝነት ከመቃብር አስቀመጦ የኦሮሞን ህዝብ ከዕውነተኛ ድል የሚያቀርብ አዲስ መንገድ ይጀምራል የሚል ብጣቂ ተስፋ ውስጣቸው የነበሩ ጥቂቶች አልነበሩም። ከመነሻውም የተጠራጠሩት፡ የተደበቀው ማንነቱ አንድ ቀን ይወጣል ብለው በጥርጣሬ ሲመለከተቱት የነበሩት ቁጥራቸው የትየለሌ ነበር። ሆኖም እኔም ሆንክ ጥቂቶች ጃዋርን እንደ አብሪ ኮከብ መመልከታችን አልቀረም። አሁንስ?

ጃዋር አሁን አይሰማም። መስማት የሚፈልገው የፈለገውን ብቻ ነው። በየአዳራሹ የሚሰማው ጭብጨባ ሰርቆታል። ቀልቡ አሁን ከሚኒሶታ እስከ ለንደን በተዘረጋው የ’ኦሮሞ ፈርስት’ ቅልጥ ያለ የወቅቱ ነጠላ ዜማ ላይ ሆኑዋል።

1. የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል በእፎይታ ጊዜ ላይ ቢሆንም የጃዋር ‘ኦሮሞ ፈርስት’ በይፋ ከታወጀችና ‘ሜንጫ’ዋ በሚኒሶታ መድረክ ከተስተጋባች በኋላ የሙስሊሞች ትግል ላይ መጠነኛ ተጽእኖ መፈጠሩ አልቀረም። የሙስሊሙን ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል አድርገው የተሰለፉ ወገኖች በጥቂቱ ማፈግፈጋቸው በመጠኑ ይታያል። ሜንጫ የሚለውን ቃል ጃዋር ሚኒሶታ ላይ ካፈነዳት ወዲህ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ እንኳን ውዥንብር ተፈጥሯል። እናም የሟችዋ ሚካያ በሃይሉ ዜማን ልዋሰው- “ሸማመተው”::  ህወሀት ሸመተ:: ትግሉ እንዲደበዝዝ ቀን ከሌት ይመኝ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ- ሸማመተው!!

2.  ከምንጊዜውም በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነቱን ለማሳየት፡ በጋራ ወደ ምር ነጻነት ለመምጣት እጅ ለእጅ እየተያያዘ ያለበት ወቅት ላይ እነጃዋር የኦሮሞ ብሄርተኝነትን ወደ ጠባቡ ጽንፍ ወስደውት ዘራፍ ማለት መጀመራቸው በተወሰነ ደረጃ ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ከሰማይ የወረደ አዱኛ ሆነለት:: አሁንም ሚካያ ትላለች -“ሸማመተው” – ህወሀት ሸመተ::

እነ ጃዋር እየተናገሩ ነው:: ‘ኦሮሞ  ፈርስት’-‘ ማይ ካንትሪ ኢዝ ኦሮሚያ’ ::  የህወሀት የፌስቡክና ትዊተር ሰራዊቶች ስማቸውን በኦሮምኛ ለማድረግ ከብርሃን ነበር የፈጠኑት:: እናም ‘ኦሮሞ  ፈርስት’  መፈክራቸው ሆኖ አጼ ሚኒሊክ ላይ እርግማናቸውን ውእግዝ ከማርዮሱን እያዘነቡት ነው።

ጭብጨባው ቀልጧል። ነጠላ ዜማው ሰማይ ምድሩን አድምቆታል፡፡ እነጃዋር በህወሀት ነጠላ ዜማ ዳንሱን እያቀለጡት ነው። የሚሰማ ጆሮ የላቸውም። ልባቸው ሸፍቷል። አውቀው ይሁን ሳያውቁት ከህወሀት መንደር ዘልቀው የልፊያ ፖለቲካውን ተያይዘውታል። ጭብጨባ ክፉ ነው። ላላወቀበት ስካር ነው።

ሰሞኑን ከጨፌ ኦሮሚያ አንድ መረጃ ደርሶኛል። ሳይላመጥ አይቀርብም በሚል ለጊዜው ይዤዋለሁ። እነጃዋርን የተመለከተ ነው። ምናልባት መረጃውን በማስረጃ ማስደገፍ ከቻልኩኝ በድብቅ የተፈጸመውን የእነጃዋርንና ህወሀትን ጋብቻ ይፋ አደርጋለሁ።

እስከዚያው ጩኧቱን እየሰማን እንቆይ። መልካም ጋብቻ የምንልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።

comment pic

ሰላማዊ ትግል እና ባህሪያቱ: ስልጠና ክፍል አምስት፥ ከ1924 – 2002 በኢትዮጵያ የተደረጉ ምርጫዎች ግምገማ –በግርማ ሞገስ

$
0
0

በግርማ ሞገስ
ቅዳሜ ታህሳስ 12 ቀን 2006 ዓ.ም.

Girma Moges

ግርማ ሞገስ

የስልጠና ክፍል አምስት ግብ በዐፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት (1924-1967)፣ በደርግ ዘመነ መንግስት (ከ1967 – 1983)፣  (3ኛ) በህውሃት/ኢህአዴግ ዘመነ መንግስት (1983 – 2002) የተደረጉትን ምርጫዎች በአጭር በአጭሩ መጎብኘት እና  መገምገም ነው። ምርጫ 97 ግን በርከት ያሉ ትምህርቶች በመለገሱ ሰፋ አድርገን እንጎበኘዋለን።
ምስጋና፥ ይኽን ግምገማ ሳዘጋጅ ከሌሎች መረጃ ምንጮች በተጨማሪ “ግንቦት 7” በሚል ርዕስ ክፍሉ ታደሰ ስለ ምርጫ 97  ዝግጅት፣ ሂደት እና አፈጻጸም የጻፈውን መጽሐፍ አና “ነፃነት እና ዳኝነት” በሚል ርዕስ ስየ አብርሃ ከጻፈው መጽሐፍ ውስጥ  ስለምርጫ 97 አንስቶ ምክሮች የሚለግስበትን ጠቃሚ ምዕራፍ ተጠቅሜያለሁ። እንዲሁም የታሪክ ባለሙያዎቹን የባህሩ  ዘውዴን እና የተክለ ፃድቅ መኩሪያን መጽሐፍቶች ተጠቅሜያለሁ። ለሁሉም ምስጋናዬ ገደብ የለውም።   – ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ–


እኛና እነሱ/ ዝቅ እንበል/ በጌዲዮን ከኖርዎይ

$
0
0

እኛና እነሱ/ ዝቅ እንበል/

ጌዲዮን ከኖርዎይ

Norway

በአለም ላይ ካሉ ሃገሮች ውስጥ ስልጣን የሌለበት ሃገር ቢኖር ወይም ባለስልጣኑ ህዝብ የሆነበት ሃገር ቢኖር ሳላጋንን ኖርዎይ የምትባለው ሃገር ናት ማለት እችላለሁ፥፥ በግልፅ ህዝቡ የሚፈልገውን፥ ያስተዳድረኝ እገዛለታለሁ ብሎ አምኖ ድምፁን የሚሰጥለት መሪ፥፥ መሪውም ከልቡ እራሱን ዝቅ አርጎ ለሃገሩ፥ ለወገኑ የሚሰራበት ሃገር፥፣ ህገመንግስቱ ወይም በኖርዌጅያኑ አጠራር /GrunnLov/ ለሁሉም እኩል የሚሰራና ተፈፃሚ የሚሆን፥፥

በቃ ዋናው ነገር ህገመንግስቱን አትንካ ነው፥፥
አስታውሳለሁ በአንድ ወቅት የአለም መንግስታት ተባብረው ቢንላዲንን ለመደብደብ ብለው አፍጋኒስታንን በሚደበድቡበት ወቅት የኖርዎይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተለያየ የስራ ጉዳይ በሚል በብዛት ወደ አፍጋኒስታን ይመላለሱ ነበርና እዛም ሲመላለሱ በአፍጋኒስታኖቹ ባህል ስጦታ የተለመሰ ነገር በመሆኑ ለካ አቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርዬ አንድ ምንጣፍ በስጦታ አጊንተው ሲመለሱ ስጦታው ወደድ ያለ ሆኖ እያለ ለኖርዌጂያን ግብር ስብሳቢ ቢሮ ወይንም /tax Administration/ ማስመዝገብ ሲገባቸው ዘንግተውት በኖርዎይ ትልቅ መነጋገሪያ ርእስ ሆኖ ሚዲያዎች ቁም ስቅላቸውን ሲያበሉአቸው ነበር፥ እንዲሁም ባንድ ወቅት የትራንስፖርት ሚኒስትርዋ በአንድ ወቅት አነስተኛ መርከብ ለመመረቅ ተጋብዘው በሄዱበት ወቅት ከአንድ ባለሃብት የእጅ ሰንሰለት የወርቅ በስጦታ አጊንተው እሳቸውም ዋጋው ውድ መሆኑን በለመረዳት ይመስላል ሳያስመዘግቡ በመቅረታቸው ሚዲያዎች ነገሩን ይደርሱበትና ካራገቡት በኋላ ታክስ አስቆርጠውባቸዋል ሚኒስቴርዋም ስጦታውን በመቀበላቸው እንደተፀፀቱ ለህዝባቸው ተናግረዋል፥፥
አሁን ግን ይህችን አጭር ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ከዚሁ ከኖርዎይ ሳልወጣ በዚህ በፈረንጆች ገና ዋዜማ በኖርዎይ ውስጥ ተሆነውን በሃገራችን ህልም ሳይሆን ቅዠት ወደሆነብኝ ነገር ልውሰዳችሁ፥፥
ከሶስት ወር በፊት በሴፕቴምበር 2013 በኖርዎይ በተደረገው የጠቅላይ ሚኒስቴር ምርጫ ተሸንፈው ስለጣናቸውን ያስረከቡት በኖርዎይ ምናልባትም ቁጥር አንድ ተወዳጅ ናቸው የሚባልላቸው የንስ ስቶልተንበርግ እንደውም ለምርጫው ጊዜ ታክሲ ሾፌር ሆነው ቅስቀሳ ሲያረጉ በነበረበት ጊዜ በኢሳት፥ በቢቢሲ የተዘገበላቸውhttp://ethsat.com/video/esat-kignet-taxi-shofieru-prime-minister/ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስቴር ለአሁኑ ገና በአል ዋዜማ ስራ ከለቀቁ በኋላ የመጀመርያ ስራቸው ያረጉት የገና ዛፍ መሸጥ ነበር፥፥
ዜናውን ሳየው ብዙም አልደነገጥኩም፥ ግን ቅናት አደረብኝ እንደውም ተስፋ ነው የቆረጥኩት፥፥
ሰውዬው እንዳልኩት በአንድ ወቅት በተለይ ኢኮኖሚ ክራይስስ ተብሎ አውሮፓውያኑ እየተጨናነቁ በነበረበት ወቅት ሃገራቸውን በብቃት ችግሩ ባጠገቧም ሳይደርስ ስላሳለፉት የሃገሪቷ ቁጥር አንድ ተወዳጅ ሰው ከንጉሱም በላይ ተብሎ ሚዲያ ላይ ወቶ እንደነበር አስታውሳለሁ፥ ሃብታም ናቸው፥ እውቀት አላቸው በነገራችን ላይ አባታቸውም የኖርዎይ ጠቅላይሚኒስቴር ሆነው አገልግለዋል፥፥ ብቻ ለማጠቃለል ያህል ሰዎቹ ከራሳቸው በላይ የሚያስቀድሙት ብዙ ነገር ዓላቸው፥ ህዝባቸው፥ ሃገራቸው፥ አላማቸው፥ ግባቸው፥ ሌላም ሌላም
እንግዲህ እስካሁን ስለ እነሱ ነው ያወራሁት ግን እኛስ?

እኛ ማን ነን?
ለምንድነው የምንታገለው?
ለማን ነው የምንታገለው?
ምንድነው አላማችንና ግባችን?
ወደኛ ሲመጣ ይህ ጥያቄ ለሁላችን በግለሰብ ደረጃ መልስ ሊያገኝ የሚገባው ጥያቄ ይመስለኛል፥፥
ዝቅ እንበል!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ልጓሙን የበጠሰው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የስድብ ፈረስ ዳኛቸው ቢያድግልኝ

$
0
0

በ ዳኛቸው ቢያድግልኝ

ፕሮፌሰሩ በጽሁፎቻቸው እንዲህ ብለውናል

“…በዓለም ሕዝቦች መሀከል ውድድር ቢደረግ ያለጥርጥር አበሻ አንደኛ ከሚወጣባቸው ነገሮች አንዱ ልመና ሳይሆን አይቀርም፤ ለአበሻ፣ ልመና የኑሮ ዘዴ ነው……” http://www.goolgule.com/abesha-and-begging-1/

“…አዳም አበሻ ሳይሆን አይቀርም፤ ሁሉንም ነገር ብላ ከተከለከለው በቀር ብሎ ያስቀመጠው ይመስላል፤ በላባችሁ ወዝ ብሉ ተብለው አዳምና ሔዋን መረገማቸውን አበሻ ገና አልሰማም፤ አበሻ የተፈጠረው ገነት ውስጥ ቁጭ ብለህ ያለውን ሁሉ ብላ በተባለበት ጊዜ ነው፤ እግዚአብሄር አበሻን ሁሉንም ብላ ሲለው ምናልባትም በጆሮው ጭራሽ አታስብ ብሎት ይሆናል …….” (ሰረዝ የተጨመረ)

እስከናካቴው “ሆድ” የሚባል ቃል ከአበሻ ቋንቋ ፈጽሞ ቢሰረዝ ቋንቋው ብቻ ሳይሆን አበሻም ጉድ ይፈላበታል። አዕምሮ ፣ ሕሊና የሚባሉትን ቃላት አበሻ አያውቃቸውም፤ ተግባራቸውንም ሁሉ ለሆድ ሰጥቶታል። (ሰረዝ የተጨመረ) http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9015

 

ልጻፍ ልተው… ምናልባት… እንዲያው ምናልባት በዚሁ የሚያበቁ ከሆኑ አይቶ እንዳላየ ማለፍ ይሻል ይሆናል ስል ልጓሙን የበጠሰው የስድብ ፈረሳቸው በማንአለብኝነት ጋለበብን። ባእዳን አበሽ እያሉና እየሰደቡ ይገድሉናል። የራሳቸው ታሪክ በረሀብ ቸነፈርና ስደት የተሞላ እንዳልሆነ ሁሉ በመዝገበቃላታቸው ውስጥ ኢትዮጵያን የረሀብ ምልክት አድረገው የሚያዋርዱን በርካታዎች ናቸው። ፕሮፌሰሩ በአንድ ወቅት ሲሉ እንደሰማሁዋቸው ወያኔዎች ከዱር ወደከተማ ሲገቡ ህዝቡን ፈሪ ለማድረግና የሚያከብረው ምልክት ለማሳጣት በየቀዬው በህብረተሰቡ ዘንድ የሚከበሩትን እያፈላለጉ በአደባባይ ፂማቸውን ይዘው በመጎተት ያዋርዱዋቸው ነበር። ይህን መሰሉ የወያኔዎች ተግባር በሚያሳዝን ሁኔታ በፕሮፌሰሩም ላይ በተደጋጋሚ ደርሶባቸዋል። የወያኔዎች ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን የማዋረድ ዘመቻ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ታዲያ ይህ ባለበት ሁኔታ የእውቀት ጣርያ ላይ ደርሰዋል የሚባሉት አዛውንቱ ፕሮፌሰር መስፍንም በአሮጌና ያለአግባብ በተደረደረ ምሳሌ ይህን መከራ የበዛበትን ህዝባችንን በሚሸነቁጥ የጅምላ ስድብ መቀጥቀጣቸው ግር የሚያሰኝ ሆነብኝ። ይህ ወቅትና ሁኔታን ያላገናዘበ መፍትሄ የመጠቆም፣ የማስተማር አቅምም የሌለው ኢትዮጵያዊነትን የሚያዋርድ ጅምላ ስድብና ሽሙጥ በተከታታይ ሲወርድብን አይቶ እንዳላየ ማለፉ ክብራችንን ለማጉደፍና ለማዋረድ ኢትዮጵያችንን ለማንቋሸሽ ለሚተጉት ዱላ ማቀበል ይሆናል። እናም ይህ ጥያቄ ይከነክነኝ ገባ። እውን አበሻ ሥራ ጠል፣ ለማኝና ሆዳም ነውን? በምን ጥናት በማንስ ትንታኔ?

 
እድሜአቸውን ሙሉ ሀገራችንን አገልግለዋል ሲባል መስማቴ ብቻ ሳይሆን በባህላችን አዛውንት ይከበራልና ክብራቸውን የሚያጎድፍ ትችት ማቅረብ አልፈልግም። ቢሆንም ታድያ የሰሞኑ ማቆሚያ ያጣው የስድብ ጅራፍ ዘላቂ ጉዳቱ ከፍተኛ ነውና አክብሮቴን ሳላጎድል እባክዎን የስድብ ፈረስዎን ልጓም ያዝ አድርጉልን እላለሁ።
በሀገራችን አዋቂ ነን የሚሉ ሰዎች ከነሱ የተለየ ሃሳብ ይዞ የሚመጣን ተወያይቶ የተሻለውን ሃሳብ ከመደገፍ ይልቅ ለየት ያለ ሃሳብ ያቀረበውን አንገት የሚያስደፋ የስድብ ናዳ ማውረድ ይቀላቸዋል። ይህንን በመፍራት አዋቂዎቹ ግዙፍ ስህተት ሲፈጽሙ በዝምታ ማለፍ ለሌላ ስህተት በር መክፈት ይሆናል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ጽሁፍን በይዞታው ሳይሆን በጸሃፊው ማንነት እየመዘኑ ጸሀፊው በግልጽ ያስቀመጠውን ሃሳብ ወደጎን ትተው ያልተባለውን መልካም ሃሳብ ፍለጋ እየማሰኑ የራሳቸውን ትርጓሜ ይሰጣሉ። ሰአሊ በስህተት የረጨውን ቀለም “አብስትራክት” ነው ብለው በምናባቸው ውብ ስዕል እንደሚሰሩት አይነት ከስድብ ጀርባ ሙገሳ መፈለጉ ከንቱ ነው።

 
የፕሮፌሰር ተከታታይ ጽሁፎች የተጻፉት ኢትዮጵያን በስፋት በማያውቅ ሰው፣ ሀሳብን ለህዝብ ለማቅረብ ምን አይነት ጥንቃቄ የተመላበት የምርምር ጥበብ አስፈላጊ እንደሆነ በማያውቅ ሰው ቢሆን፣ ሀሳብን የማስፈር ዓላማና ግብን መረዳት በማይችል የእውቀት አድማሱ ያልሰፋ፣ በሌሎች ሀገራት የሚኖሩ ሰዎችን አኗኗር በተመለከተ ምንም ግንዛቤ በሌለው ሰው ወይም እንዲያው ለፌዘኛ የመሸታ ቤት ቀልድ ሲባል ለተወሰኑ ታዳሚዎች የቀረበ ቢሆን ምንም ትኩረት መስጠት ባላስፈለገ ነበር። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ግን አለምን ተዘዋውረው የጎበኙና ያልኖሩበትን ዘመንና ያልጎበኙትን አገር ህዝብ አኗኗር በምርምርና በንባብ ጠንቅቀው የተረዱ እድሜ የጠገቡ ምሁር ናቸውና በምንም ጥናታዊ መረጃ ባልተደገፈ መንገድ የአንድን ጥንታዊና ታሪካዊ ሀገር ሕዝብ በዚህ መልኩ ማሳነስና ከሌላ ፕላኔት የመጣ ሰንካላ ፍጡር ማስመሰል እድሜያቸውንና እውቀታቸውን አይመጥነውም። የአንድ ሀገር 90 ሚሊየን ሕዝብ በአንድ ቅንፍ ውስጥ “አበሻ” ብለው ከተው እንኳን የሰው ልጅ ቀርቶ ማንኛውም ማህበራዊ እንስሳ የሚያደርገውን ተሳስቦ፣ ተዛዝኖ፣ ተካፍሎ መኖርን በዚህ መልክ አሳንሶ ኢትዮጵያዊነትን ማዋረድ ታላቅ ስህተት ነው።

 

ኢትዮጵያዊነትን እያዋረዱ አገር አልባ ሊያደርጉን አዲስ ታሪክ ሊጽፉልን ያሰፈሰፉ ጠላቶች አራት ኪሎ በተቀመጡበት ሰዓት፤ ከልመና ግርድና ይሻላል ብለው የፕሮፌሰሩ የልጅ ልጆች በመላው አለም ተበትነው ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ቢያልፍልን ብለው በሰው ሀገር እየተደፈሩ፣ እየተዋረዱ በሚዳክሩበት በዚህ ዘመን፣ በርካታ እናቶች አራስ ልጆቻቸውን ታቅፈው ትንሽ ሳንቲም ለማግኘት በየመንገዱ ዳር ጥቂት የተቀቀለ ድንችና ንፍሮ ለመሸጥ ጸሀይና ብርድ ሲፈራረቅባቸው ውሎ በሚመሽበት ዘመን፣ ደካማ እናቶች ወገባቸው እስኪጎብጥ ቅጠልና ጭራጭሮ ተሸክመው የእለት ጉርሳቸውን በሚያገኙበት ሀገር፣ ተራራ የሚያክል ሸቀጥ በጭንቅላታቸው ተሸክመው የሚሮጡ ወገኖች በሚርመሰመሱበት ሀገር፣ ህጻን አዛውንቱ ትንሽ ባገኝ ብሎ ሊስትሮና ማስቲካ ነጋዴ በሆነበት ሀገር ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያውያን ሥራ-ጠል ሆዳምና ለማኝ መሆናችንን አስረግጠው ሲነግሩን መስማት እጅጉን ያማል።
 

ሀገር በሞታቸው ያቆዩልን ተዋርደው አጽማቸው ከመቃብር ሀውልታቸው ከቆመበት እየፈረሰ ባለበት፣ የኢትዮጵያን ገጽታ ማቆሸሽ የመንግስት ፖሊሲ በሆነበትና ግፈኞችና ጎጠኞች ሰው በሀገሩ ሰርቶ ሰው መሆን እንዳይችል በየማዕዘናቱ እየበተኑት ባሉበት የመከራ ጊዜ የኛው የተማሩ አዛውንት ዋናው ተሳዳቢ መሆናቸው ያሳዝናል። አብረን ስለበላን ሆዳም፣ ተቸግሬአለሁ ብሎ ድጋፍ ለጠየቀ ወገን ስለለገስን ኅሊና ቢሶች አሉን። ሰውን ከመዝረፍ መለመንን ስለመረጠ ፈሪና ጅል፣ ስላመነ ሞኝና ተላላ አድርጎ መመልከት ነውር ነው። ይህ መተዛዘንና ተካፍሎ መብላት ቀለም ያልቆጠረው ኢትዮጵያዊ ያቆመውን መሰረትና ያቆየውን ባህላዊ እሴት ልናከብረውና ልንከባከበው ይገባል። በተከታታይ በፕሮፌሰሩ የተጻፉት ጽሁፎች የሚደመድሙት አበሻ ስራ ጠል መሆኑን፣ ሆዳምነቱንና፣ ለማኝነቱን ነው። በሚቀጥለው ጽሁፋቸው ደግሞ ሌላም ሊያስከብሩን የሚገባቸውን ባህሪያችንን ልናፍርባቸው የሚገቡ አጉል ገጽታዎች አድርገው ይጽፉልን ይሆናል። ይህ ወይ እራስን ከፍ ከፍ ለማድረግ ሌላውን ዝቅ ዝቅ ማድረግ በመፈለግ አለዚያም ተስፋ የቆረጠ ሰው አገርን በጅምላው ሊያስነውር የሚያደርገው ድርጊት ይመስላል።
 

ለመሆኑ ፕሮፌሰሩ ሆድ መውደድን እንዴት ይገልጹታል? ምግብ መውደድ፣ መውደድ ብቻ አይደለም አጣፍጦና አስውቦ መብላት አንደምንስ ያስወቅሳል? በውጪው አለም የምግብ ስራ ጥበብ ምንኛ የተከበረ ሙያ መሆኑን፣ ቴሌቪዥኑ በሙሉ በምግብ ስራ ፕሮግራም መጨናነቁንና የምግብ ስራ ጥበብ መጻህፍት ጸሀፊዎች ምንኛ የተከበሩ መሆናቸውን እንዴት ዘነጉት? ምግብ እኮ የህልውና መሰረት ነው በአካል ለመዳበር፣ አእምሮን ለማጎልበት፣ የማስታወስና የማሰብ አቅምን ከፍ ለማድረግ የታመቀውን የተፈጥሮ አቅም ለማውጣት የሚያግዝ ነው። በጣም የሚገርመው ደግሞ ቢወደውም ጥቅሙን ቢረዳውም እንኳ አልሚ ምግብ አግኝቶ ሳይሆን በተገኘው ምግብ ሆዱን ሞልቶ የሚያድር እንኳን በሌለበት ሀገር ውስጥ ለሚገኝ ሕዝብ በረሀቡ ላይ ሆዳም የሚል የስድብ ምርቃት ማከሉ አሳዛኝ ነገር ነው። ምክርም ይሁን ግልጽ ዓላማ የሌላቸው ጽሁፎች መጻፉ ግቡ ኢትዮጵያን ለሚያዋርዱት ‘ምሁራዊ’ ድጋፍ መስጠት ብቻ ይመስለኛል።

 
በምግብ አብዝቶ መብላትና ሲያመነዥጉ በመዋል የሚታወቁት የሌሎች አገሮች ዜጎች ናቸው። ይህንን የማያውቅ ከመንደሩ አለፍ ብሎ የማየት እድል ያልገጠመው ሰው እንጂ እንደ ፕሮፌሰር አውሮፓ ኤዥያና ሰሜን አሜሪካን ያሰሰ ሊሆን አይችልም። ለዚያውም ባንድ ወገን ሆዳምና አይነቱና ብዛቱ ወደር የማይገኝለት ምግብ ስለመብላቱ የሚነገርለት ሕዝብ በሌላው የፕሮፌሰሩ ፅሁፍ ለማኝነቱንና አምላክ ደድብ ያለው ሥራ-ጠልነቱ ይበሰርለታል። አንዱን ፅሁፋቸውን ከሌላኛው ማገናኛ ድልድዩ ምን ይሆን ያሰኛል። ለማኝ እኮ አጣጥሞና አማርጦ ለመብላት ያልታደለ ምርጫ አጥ ነው። ሥራ ጠልቶና ለምኖ አማርጦ መብላት ከተቻለማ ኢትዮጵያችን መና ከሰማይ የሚዘንብባት ሁናለች ማለት ነው።

 
ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላው በገበታ ዙሪያ የሚሰባሰበው ለመብላት ምክንያት በመፈለግ አይደለም፤ ምግቡ የመገናኛው ማጣፈጫ እንጂ። ሰርግም ሆነ መልስ፣ ልደትም ሆነ ተዝካር፣ ፋሲካም ሆነ እንቁጣጣሽ በጋራ ገበታ መቀመጥ መሰረታዊ ምክንያቶቹ ማህበራዊ ግንኙነቶች ናቸው። የሰው ልጅ ማህበራዊ እንስሳ ነው። አብሮነቱን ካላዳበረ ተነጣጥሎ ይሞታልና የትኛውም ማህበረሰብ በየትኛውም የዓለም ጫፍ ቢኖር በራሱ መንገድ ይሰባሰባል። አብሮ ያድናል፣ ተጋግዞ ያርሳል፣ ፈረቃ ገብቶ ያመርታል። ያንን ውበት ለመስጠትና አብሮነቱን ለማሳመር ደግሞ በጋራ ገበታ ይቁዋደሳል። ታዲያ ለምንድን ነው ኢትዮጵያውያን አብረው መብላታቸው ልዩ እንከን ተደርጎ የሚቀርበው? እንዲያውም ኢትዮጵያውያንን ሰብስቦ የያዘው ጠንካራ ድር ቢኖር እንዲህ ያለው በደስታና በሀዘን አብሮ መሆኑ ነው። አብሮ ያቆመን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ባህላዊ እሴት እንደ ሁዋላ ቀርነትና ሆዳምነት ሲቆጠር ስቆ ማለፉ የሚያስከትለውን እራስን የማዋረድን ጣጣ ልብ ያለማለት ነው። ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የቆዩ በአብዛኛው ከሀይማኖት ጋር የተገናኙ አሰባሳቢና አገናኝ በዐላት አሏቸው። በለጸጉ የሚባሉት አገሮች ደግሞ ከሀይማኖታዊ በአላት በተጨማሪ ለንግድ የሚመቹ አዳዲስ በዐላት እየፈጠሩ አብሮነታቸውን የሚያጠናክሩበትን መንገድ ፈጥረዋል። የእናት ቀን፣ የአባት ቀን፣ የፍቅር ቀን፣ የምስጋና ቀን እያሉ አብረው ይበላሉ ይጠጣሉ። ስለዚህም ኢትዮጵያውያንን አብረው በመብላታቸው ሆዳም የሚላቸው በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ትንሽም ቢሆን ጥናት ያላደረገ ብቻ ነው።

 

ከዚህ ቀደም እንደ ጻፍኩት ኢትዮጵያውያንን ‘አበሻ’ ባልል እመርጣለሁ ምክንያቱም ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ለማሳነስ በርካቶች አበሻ የሚል ስያሜ ላይ በመንጠልጠል መጥፎና ደካማ የሆነውን ነገር ሲያጎሉ ማየት እየበዛ ነው። ‘አበሽ’ የሚለውን የንቀት መሰል አጠራር የሚጠቀሙትም እነማን እንደሆኑ እናውቃለንና ኢትዮጵያ እያልኩ እቀጥላለሁ። እናም ክቡር ፕሮፌሰር የአለም ሕዝብ ከእንቅልፉ ተነስቶ ማዛጋት ሲጀምር ነቃ የሚያደርገውን ቡና…. ፓስታና ማኮሮኒ እያማረጠ የሚበላበትን ስንዴ…. ‘ግሉቲን’ ሆዱን እየነፋው ፊቱን እያዠጎረጎረ የሚያስቸግረውን ሕዝብ ጤናማ የሆነ እሹኝ ፈትጉኝ የማይለውን ጤፍ ጠገብ ሲል ደግሞ የበላውን የሚያወራርድበትን ጥሙን የሚያስታግስበትን ገብስ ለአለም ያበረከተው “ሰነፍ፣ ሆዳምና ለማኝ” እየተባለ የሚዘለፈው የኢትዮጵያ ገበሬ ነው። የሀገሬ ገበሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ የሚተጋ ጠዋት ያሟሸውን አፉን ማታ ባገኛት እፍኝ እህል እየዘጋ የሚኖር ነው። ይህ ደግሞ ከሰማንያ በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን ይወክላል። ይህ ወገንዎ ክብር እንጂ ስድብ፣ ሙገሳ እንጂ ውርደት አይገባውም። በምንም መልኩ ኢትዮጵያውያንን እርሶንም ጨምሮ እግዜር በጆሮአችንን አታስቡ ብሎ መርጦ አላደደበንም። ያንን ስድብ ተቀብለው የሚኖሩ ደደቦች ካሉ ምህረቱን ያውርድላቸው። ሀገራችንን ለማጥፋት የሚያዋርዱን በቂ ጠላቶች አሉንና እራሳችንን በማዋረድ ለጠላት ስራውን አናቅልለት።

 
ኢትዮጵያውያንን ከሀገራቸው ውጪ የሚያሳዩትን የስራ ፍላጎትና መነሳሳት ለመመልከት እድል ላገኙ ሁሉ ኢትዮጵያውያን ሀገሬውንም ሆነ ሌሎቹን መጤዎች በልጠው ሲተጉና ውጤትም ሲያመጡ እንጂ ሰነፍ በመሆን ከሌላው አንሰው አያዩም። ስለዚህ በጅምላ ኢትዮጵያውያንን ስራጠል ሰነፍ አድርጎ መኮነኑ ውሃ አያነሳም። ኢትዮጵያውያን ስራጠል ከሆኑ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ስለምን ወደ አረብ አገር ሊሄዱ ቻሉ? ለልመና ነበር? ለመሆኑ ኢትዮጵያውያን በተሰደዱባቸው ሀገራት በአውሮፓና አሜሪካ በአፍሪካ ሀገራትም እንኳን የሚታወቁት በስራ አይደለምን? ባዶ እጃቸውን ከሀገር ወጥተው አዲስ ሀገር ውስጥ ኑሮ መስርተው ከብረው ለመኖር የቻሉት በአስማት ነውን? ስለዚህ ፕሮፌሰሩ እነዚህ በአንዲት ጀንበር ዘርፈው የከበሩ ነጣቂዎችን መንግስት ብለው መንግስት አንደተቀበለው ቻይና እንዳረጋገጠው ብለው ስንፍናችንን ሲደመድሙ የፌዘኛ እንጂ ምሁራዊ ትችት አይመስልም። አንድን በይሉኝታና በፈሪሃ እግዚአብሄር (አምላክ) የሚኖርን ሕዝብ አዕምሮና ሕሊና ቢስ የሚል ሰው እውን ሕሊናና አእምሮ አለው ብሎ መገመትስ ይቻላልን?
ኢትዮጵያውያንስ እንዴት ሁኖ ነው በሆዳቸው ነው የሚታወቁት የተባለው? ኢትዮጵያውያን ተጋብዘው ድግስ እንኳን ሲሄዱ “ቤታቸው ምግብ የለም እንዴ” ላለመባል እቤታቸው በልተው የሚሄዱ ናቸው። ነፃ ምግብ አለ ሲባሉ ለሳምንት የሚበቃ ቀለብ በሆዳቸው ለመጫን የሚዳዳቸው ሌሎች አንጂ ኢትዮጵያውያን አይደሉም። ኢትዮጵያዊውማ ከሆዴ ይልቅ ክብሬ በማለት እርቦትም አሁን በላሁ ነው የሚለው።

 
ሰዎች ይህንን ስራ ከምሰራ ለምኜ እበላለሁ የሚሉበት ዘመንም ከነበረ በትንሹ ግማሽ ምዕተ አመትን አሳልፏል። ይህም ክስ እውነት እንኩዋን ቢሆን ኢትዮጵያውያንን ለይቶ ከንቱና ርካሽ የሚያደርግበት ምንም ሚዛን የለም። በየትኛውም የአለም ክፍል ቢሆን በአንድ ወቅት የተናቀ ስራ ነበር። ዛሬም ቢሆን ይህን ከምሰራ ዌልፌር ምን አለኝ ብሎ እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ ስንት ፈረንጅ በየሀገሩ አለ። ሌላም አንድ እውነት አለ፣ ሰዎች ከልምዳቸው ውጪ የሚመጣን ነገር የመቀበል ፍላጎታቸው ውሱን ነው። ለምሳሌ ከብት አርቢዎች እርሻን በንቀት ይመለከታሉ። አንዳንድ ከብት አርቢዎች ለምን እነደዚህ ያለ ስራ አትሰሩም የሚባል ከአካባቢው ሁኔታ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ሲቀርብላቸው የኛ ዘሮች ይህንን አይሰሩም ይህን የሚሰሩት ሌሎች ናቸው ይላሉ። አንጥረኞች፣ አዝማሪዎች፣ ነጋዴዎች ሁሉም የለመደውን ስራ አጥብቆ መያዝ የኢትዮጵያውያን ብቻ ባህሪይ አይደለም። እንዲያም ሆኖ ኢንጅነሮች፣ የሙዚቃ ጠበብቶች፣ ዶክተሮች የመንግስት ተጡዋሪ ላለመሆንና ለቤተሰባቸው የተሻለ ህይወት ለመስጠት ስራ ሳይንቁ ከጠዋት እስከማታ መኪና በመጠበቅ፣ ታክሲ በመንዳት፣ ዘበኛ በመሆን፣ ጽዳት ሰራተኛ በመሆን ይዳክራሉ። እንዴት ነው ይህን ህዝብ ስራጠል አድርጎ መኮነን የተቻለው?

 
በሀገራችን ያለጥናትና በቂ መረጃ በምሁሩ ምክር የሰው ንብረት መውረስና ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ጥፋት በስመ ሶሻሊዝም በተፈጸመበት ጊዜ የተመለከትነው አንድ እውነት አለ። ሁለት ስራ መስራት አድሃሪነት ነበር ገንዘብ መያዝና ፈጠራ ወንጀል ነበር። ሶሻሊዝምን ያመጣውና መስራትንና መክበርን ወንጀል ያደረገው ተማርኩ ያለው ወገን የመረጠው የሶሻሊዝም መንገድ ነበር። እንዲያም ሆኖ በአዋጅ ሰዎች ድህነትን እንዲቀበሉ በተደረገበት ጊዜ እንደ አቅምቲ ከበርቴ ተብለው ሀብት ንብረታቸው እየተዘረፈ ሰዎች ወደ እስርቤት በተጋዙበት ጊዜ አዲስ አበባ የተከፈቱ ምግብ ቤቶች (ኢድዩ ቤቶች)፣ ባልትና ቤቶች ሁሉ ሕዝባችን ችግሩን ለማሸነፍ ምን ያህል የሚፍጨረጨር እንደነበረ የሚያስመሰክር ታሪካዊ ወቅት ነበር። እነዚያ “እመቤቶችና ወይዛዝርቶች” ሆቴል ቤት ከፍቼ ለማንም ከማስተናግድ ልመና እመርጣለሁ አላሉም።

 
ኢትዮጵያውያኖች ለማኞች መሆናችንን ፕሮፌሰር በተለያየ ምሳሌም አስቀምጠዋል። መንግስትን መጠየቅን፣ ሰውን መማለድን (ድርድርን)፣ ትህትናንና ሰላማዊነትን ፕሮፌሰር በልመናነት መድበውታል። እውነታው ግን እነኚህ ባህሪያት አስተዋይነትንና ህግ አክባሪነትን ነው የሚያመለክቱት። ሁሉንም በጉልበት የሚያስፈጽም ማህበረሰብ በሰላም መኖርም አይችልም። በርካታ ታጋዮች የኔ መንገድ ብቻ ነው ትክክል በማለት የተለየ አመለካከት ባሳየው ላይ ተከታታይ በደልን በመፈጸማቸው ሰዉ ክፉኛ እንዲሸማቀቅ ተደርጎአል። ነገርግን ሕዝቡ የለማኝ ባህሪ ተጠናውቶታል ብሎ መደምደም ከባድ ስህተት ነው። ፕሮፌሰር ደግሞ ሰላማዊ ትግል ብቻ የሚሉ እንደመሆናቸው መጠን ዘራፍ ብሎ ለዱላ ከመጋበዝ ይልቅ መንግስትን በጥሞና መማለድን የሚደግፉ ኢንጂ እንዴት የሚኮንኑ ሊሆኑ ይቻላቸዋል?

 

የመጽዋችና የተመጽዋች ግንኙነት ያለው ደግሞ በኢትዮጵያ ብቻ አይደለም። ምክንያቱም ያለውና የሌለው በየሀገሩ ነው ያለው። ያለው ደግሞ ለተቸገረው መቸርን የማያውቅ ከሆነ በሰላም ወጥቶ መግባትም አይቻልም። ከመለመን ይልቅ በጉልበት ቀምተው የሚወስዱ ነጣቂዎች የበረከቱበት ሀገር ይሻላል የምንል ካለን የማሰብ አቅማችን ተናግቶአል ማለት ነው። ኢትዮጵያውያን ካላቸው ላይ ቀንሰው ለሌላው መስጠታቸው የስነምግባርና የሞራል ባለጸጋ መሆናቸውን ያመለክታል እንጂ ልመናን የሚያበረታቱ ሰነፍ ማምረቻዎች አያሰኛቸውም። ጧሪ ያጡ አዛውንቶች፣ የአካል ጉዳተኞችና ህመምተኞች በመሆናቸው ስራ ማግኘት የማይችሉና ጤነኛም ሆነው ስራ ማግኘት ያልቻሉ መለመን ሊገደዱ ይችላሉ። ይህ ሰነፍ አያስብላቸውም። ባደጉት ሀገራትም የ ‘ዌልፌር/ድጎማ’ አሰራር አላቸውና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የተለያዩ እርዳታዎችን ይለግሳሉ። ይህ መንግስታዊ ድጋፍ በሌለባት ኢትዮጵያ ወገን ወገኑን መርዳቱ አስፈላጊና የሚደነቅ እንጂ የሚያስወቅስ አይደለም። ኢትዮጵያውያን ይህንን የመረዳዳት ባህል ባያሳድጉ ኖሮ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በተበተነ ጊዜ መሳርያውን ተሸክሞ ሰለ እግዚአብሄር ውሀ ስጡኝ ብሎ ባልጠየቀ ነበር። ተደራጅቶ መዝረፍ ሲችል ወርቅ ቤት ተደግፎ የሚለምን በዲሲፕሊን የታነጸ ጦር ኢትዮጵያ ብቻ በመኖሩ ጨዋና ህግ አክባሪ ያደረገንን ባህል ልናመሰግን ይገባል። ከዚህም ባሻገር ‘ልመና’ የሌለበት አገር የለም። አሜሪካም ሆነ አውሮፓ ወይም ኤዥያ በውበቱ ከሚያፈዝ ህንጻ ስር ቆቡን ዘርግቶም የሚለምን ሆነ ፕሮፌሰር እንደጠቅሱት የድሬዳዋ ለማኝ ብር ስጠኝ እያለ እንደማዘዝ የሚያደርገው ለማኝ ሞልቶዋል።

 
ልመናና ጸሎት ተመሳሳይ ትርጉም ከተሰጣቸው ደግሞ ሁሉም አገሮች ውስጥ ጸሎት አለና ልመናው አለምን አስጨንቆአል ማለት ነው። ድርድርም ልመና ከተባለ በትህትና የቀረቡ ጥያቄዎች ሁሉ ልመና ይደረጋሉና ጨዋነት እንደክፉ ባህሪ ሊታይ ነው ማለት ነው። ላሊበላነትም የልመና መስክ ሆኖ ተተችቷል። ነገር ግን ዘፋኝ ሲዲ አሳትሞ ለገበያ ሲያቀርብ ለማኝ አንለውም። አዝማሪዎችና ላሊበላዎች ደግሞ ዛሬ ላለው ኪነታዊ ጥበብ መሰረቶች ናቸው። ስለምን የቀድሞውን ነገር ሁዋላ ቀርና እርባና ቢስ እንደምናደርግ አይገባኝም።
የቆሎ ተማሪ በልመና ስለተለከፈ አይደለም የሚቀፍፈው። የሀገሬ ባላገርም የትምህርትን አስፈላገነት ስለተረዳ ካለችው ቆንጥሮ ያካፍላቸዋል። ፕሮፌሰርም ሲማሩ የተሰጣቸው መማርያ፣ የጠጡት ወተትና ልብሳቸውን ያጠቡበት ሳሙና እንደ ቆሎ ተማሪዎች ሰለ ማርያም ብለው ቆዳ ለብሰው ቀፈፋ ባይዞሩም ያው ከንጉሱና ከህዝቡ ቀፈፋ ነበር። እኛ ካልቻልንበት ያልቻልነውን በመጠቆም ማሻሻል እንጂ ያለፈው ትውልድ በቻለውና ባወቀበት መንገድ ሰርቶ ያቆመልንን አገር ማዋረድ ወንጀል ነው።

 
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የቆመችው ባሉን ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶቻችን ነው። የድሮውን አሳድጎ ዘመናዊ ማድረግ ወይም የተኮረጀውን ከሀገር አስማምቶ ጥቅም ላይ ማዋል ስላቃተን የነበረውን ስንወነጅል ልንኖር አይገባም። አገርን በጅምላ ስንወነጅል ራሳችን የምናበረክተውን እንገምግም። ራስን እያዋረዱ ክብር መሻት ሞኝነት ነው። ከልመና ለመውጣትና ገበና ለመሸፈን አስፈላጊ የሆኑ ተቋማት እንዲፈጠሩ ማበረታት ያሉትንም ማጠናከር እንጂ ወገን በሀዘኔታ ካለችው ላይ ስለሰጠ የተቸገረም ስለለመነ ማውገዙና በሽሙጥ መውገር ምን ይረባናል? ማንም በእርግጠኛነት ሊናገር የሚችለው ኢትዮጵያውያን ለማኝ፣ ሆዳምና ሥራ-ጠል ሳይሆኑ ዘመናትን የሚሻገር ባህልን ያሳደጉ ሲቸገሩ ተረዳድተው ሲመቻቸው አብረው ተደስተው የሚያኖራቸውን ባህል ያቆዩ ታታሪ ሰራተኞችና የሚረዳዱ መሆናቸውን ነው። የእውቀት መነጽራችን ይህንን ላላስመለከተን መቃወምና መንቀፍ ብቻ የእውቀት ምልክት የሚመስለን ህዝብን ከመስደቡ ብንታቀብና የማስተዋል አቅማችንን ብናዳብረው ይበጃል።

 
ሀገር አዋራጅ መሰረተቢስና ውልየለሽ ጅምላ ስድብን እውነት ነው ብሎ መቀበል ተቀብሎም ስድቡ ይገባናል በማለት እየተቀባበሉ መሰዳደብ ትክክል አይደለም። ስለዚህም በተከበሩ ፕሮፌሰር ስለተጻፈ ብቻ እንደታላቅ ግኝት በየሚዲያው ማሰራጨቱም “ሞኝን አንዴ ስደበው እራሱን ሲሰድብ ይኖራል” የሚለውን ብሂል በተግባር ማዋል ይሆናል። ኢትዮጵያንና በልጆቿ እየተሸረሸረ ያለውን ኢትዮጵያዊነትን እናድን ዘንድ እንትጋ።

 
comment_stage_5biyadegelgne@hotmail.com

 

 

እኔ ጃዋርን ብሆን ኖሮ ከዓለማየሁ መሀመድ(2)

$
0
0

ከዓለማየሁ መሀመድ(2)

በትላንቱ ጽሁፌ ጃዋርና ህወሀት የፈጸሙትን ለጊዜው መረጃው ብቻ ስላለኝ ያጋብቻ ጉዳይ አንስቼ በቀጠሮ ነበር የተለያየነው። ማስረጃው በቅርቡ እጄ እንደገባ ሰማንያ ተፈራርመው የሰሞኑን የፌስቡክ ግርግር እንዴት እንደገቡ ይፋ አደርጋለሁ። እስከዚያው ታገሰኙ።

ለአሁን ጃዋርን ብሆን አማረኝ

አዎ! ጃዋርን ብሆን ይሄን ጊዜ እነዚህን ነገሮች አደርጋለሁ

1. የኬንያና የህወሀት መንግስታት ተስማምተው የኦሮሞ ልጆችን እያደኑ ነው። ሰሞኑን ከወደ ኬኒያ እንደሚሰማው ከ 500 በላይ የወያኔን መንግስት ሸሽተው ኬኒያ የተጠለሉ ኦሮሞዎችን ኬኒያ አሳልፋ እየሰጠች ነው። በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ስም ኦሮሞች ተለቅመው ለወያኔ መንግስት እየተሰጡ ነው። ይህ ዘመቻ አሁንም ቀጥሏል። እናም እኔ ጃዋርን ብሆን ኬኒያ እያደረገች ያለችው ድርጊት ዓለም ዓቀፉን የስደተኞች መርህ የሚጣረስ በመሆኑ ለመንግስታቱ ድርጅት፡ ለዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት፡ ለኬኒያ ፓርላማ እና ለሌሎች ድርጅቶችና መንግስታት አቤቱታ እንዲቀርብ አስተባብራለሁ። ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ ባለመሆኑ ያለኝን ማህበራዊ ቦታና ተቀባይነት ተጠቅሜ፡ ሰፊ የቅስቀሳ ስራ በማከናወን ኬኒያ ላይ ጫና እንዲፈጠር አደርጋለሁ።

2. በምስራቅ ሀረርጌ ከሶማሌ ክልል ድንበርተኛ በሆኑ ወረዳዎች ላለፉት ሶስት ዓመታት በልዩ የሶማሌ ክልል ታጣቂዎች እየተፈጸመ ያለው መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰሞኑን ተባብሶ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። የሶማሌ ልዩ ሃይሎች የኦሮሞ ሴቶች እየደፈሩ፡ናቸው። ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በተለያዩ አጎራባች አከባቢዎች የተሰደዱት ወገኖች ቁጥር ከፍተኛ ነው። የሚበሉት ያጡ ህጻናት እየረገፉ ናቸው። እናም እኔ ጃዋርን ብሆን ተመሳሳይ የቅስቀሳ ዘመቻ በመክፈት ጉዳዩ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሰሚ እንዲያገኝና ወገኖቼ ከስቃይ እንዲድኑ የሚቻለኝን አደርጋለሁ። የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮች እንዲዘጋጅ እየቀሰቀስኩ ገንዘብ አሰባስቤ ለእነዚያ እየረገፉ ላሉት ህጻናት፡ መሄጃ መድረሻ ላጡት ወገኖቼ እደርስላቸው ነበር።

3. የወያኔ እስር ቤቶች በኦሮሞዎች ተጥለቅልቋል። በቅርቡ ኢንጅነር ተስፋሁንን ጨምሮ በርካታ ኦሮሞዎች በወያኔ የጭካኔ ተግባር በእስር ቤት እያሉ ህይወታቸውን አጥተዋል። ከሰሞኑ ሁለቱ የኦሮሞ መብት ታጋዮች አቶ በቀለ ገርባና አቶ ኦልባና ሌሊሳ በአንድ ዓይነት ህመም እየተሰቃዩ ነው። ህክምና ተነፍገው በከፍተኛ ስቃይ ላይ እንዳሉ ተሰምቷል። እናም እኔ ጃዋርን ብሆን ለእነ አምንስቲ ኢንተርናሽናል፡ ሂውማን ራይትስ ዎች እና ተጽእኖ ለሚፈጥሩ አካላት ጉዳዩን በማሳወቅ እስረኞቹን ከሞት እታደጋለሁ። ገንዘብ እንዲሰባሰብ በማድረግ ለእስረኞቹ ቤተሰቦች እርዳታ እንዲደረግ እቀሰቅሳለሁ።

ሌላም…. ሌላም…..

ግን ጃዋርን አይደለሁም። ባለኝ አቅም ጥረት እያደረኩ መሆኔን ግን መግለጽ እፈልጋለሁ። ጃዋር ካለው ማህበረሰባዊ ተቀባይነት አንጻር ከእኔ የተሻለ ውጤት ሊያስመዘግብ ይችላል ከሚል መነሻነት ነው ጃዋርን መሆን ያማረኝ።

ጃዋር ጆሮው ላይ የሚያቃጭለው የሙታን ድምጽ ነው። በዓይነ ህሊናው የሚሽከረከረው የሙት መንፈስ ነው። እየተላፋ ያለው ከማይጨበጥ ከማይዳሰሰው ጋር ነው። በህይወት ስላሉት ከንፈር እንኳን መምጠጪያ ጊዜ አላገኘም። ጠዋት ተነስቶ እስኪመሽ በኮምፒውተሩ ቂጥ ስር ተወሽቆ ኦሮሞ ፈርስት እያለ ማላዘኑ ተመችቶታል። የኬኒያዎቹ ኦሮሞዎችን ስቃይ የሚሰማበት ጆሮ የለውም። ለምስራቅ ሀረርጌዎቹ ህጻናት ሲቃ ጊዜም ሊሰጥ አልፈቀደም። በየእስር ቤቱ ለሚሰቃዩ የኦሮሞ ልጆች የሚያዝን ልቦና አልሰጠውም። ጸሀይ ወጥታ እስክትጠልቅ ከታሪክ ተራራ ጋር ይላፋል። ይቸከችካል። መሰሎቹ ጃስ ሲሉት ደስ ይለውና አሁንም ይቸከችካል። ሙቀቱ ተመችቶታል። ጭብጨባው ልቡን ላይ የትዕቢት ተራራ ቆልሎለታል። ድሮውንስ የኦሮሞ ህዝብ ስቃይ ለሱ የግል ዝና መሸመቺያ እንጂ መቼ መቆርቆር ከአጠገቡ ደርሳ?

ለማንኛውም በቅርቡ የጃዋርንና የህወሃትን ጋብቻ የተመለከተውን ማስረጃ ይዤ እመለሳለሁ። ለዘነጋችሁ; ጃዋር የወያኔ አሻንጉሊት የሆነው ኦህዴድ ልጅ ነው። ውለታ አለበት። ለአቅመ ፖለቲካ እንዲደርስ ያበቃውን ኦህዴድን(ህወሀትን) ቢረሳ አምላክም ደስ አይለውም። ወደፊት የማካፍላችሁ ዕውነትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው።

በመጨረሻም ለፈርስቶች መልካም የጩኧት ጊዜ። ሙቀቱ ሲለቃችሁ እንገናኝ።

comment pic

እኔ ኣላውቅም ፈራሁ ጁሃር (ሄኖክ የሺጥላ)

$
0
0

የበደሌ ቢራ ፋብሪካ ከአዲስ አበባ 483 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ኢሉ-ኣባ-ቦራ ( Eloo The father of Holstein Friesian) ኢልባቡር ከተማ በሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ስኩውር ሜትር ይዞታ ላይ ስራውን እንደ ኣውሮጳውያን ኣቆጣጠር በ 1993 ማከናወን የጀመረ ትልቅ የቢራ ማምረቻ ድርጅት ነው።

ኢሊባቡር መልካም ምድራዊ ኣቀማመጡም ሆነ ምድራዊ ልምላሜው፥ እንደ በቆሎ ፤ ገብስ፤ ጤፍ፤ የቅባት እሎች፤ ማር፤ ከነ ቦራ ደሞ ወተት፤ ቅቤ እና ወዘተ የሚዘራባት፤ የሚታጨድባት፤ የሚቆረጥባት፤ የሚታለብባት ሃገር እንድትሆን ኣድርጉዋታል።

Henok-Yeshitela-150x150

Poet Henok-Yeshitela

ኢሊባቡርን የጽሁፌ መንደርደሪያ አደረኩ እንጂ ዋናው ነጥቤ እሱ አይደለም። ዛሬ መናገር ወይም መጻፍ የፈለኩት ቴዲ አፍሮ በቅርቡ በመላው ኢትዮጵያ የሙዚቃ ዝግጅቱን እንዲያሳይ ወኪል የሆነውን የበደሌ ቢራን ያለመጠጣት አድማ ( boycotting) በመላው ኢትዮጵያ ይደረግ ዘንድ አንዳንድ ግለሰቦች የጀመሩትን ነገር ሰምቼ፤ ለምን በደሌን፤ ለምን ቴድን የሚል ጥያቄ ለሚጠይቁ፤ መልስ የሚመስለኝን ለመተየብ፤ ከተቻለም ለማሳየት መመኮር በመሻቴ ነው ።

ቴዲ አፍሮ በቅርቡ በ ጋዜጣ ላይ ስለ አድዋ ድል በሰጠው አስተያየት የተቆጡ፤ የተቀየሙ ግለሰቦች፤ ቴዲ አፍሮ ጥቁር ሰው ብሎ ንጉስ ሚኒሊክን፤ ከዛም በላይ አድዋ ድልን በመዘከሩ የተበሳጩ የህብረተሰብ አካሎች፤ ቴዲ አፍሮ ከዚህ ቀደም ጃ ያስተሰርያል ብሎ በመዝፈኑ ቂም የቁዋጠሩ ሰዎች፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በሊግ ኦፍ ኔሽን በ 1936 የኢጣልያንን የተለከለ የኬሚካል መሳሪያ መጠቀምን በመቃወማቸው፤ ኢትዮጵያን የ ዩናትድ ኔሽን ኣባል በማድረጋቸው፤ ቅራኔዎችን አብርደው ያፍሪካን ህብረት በመመስረታቸው፤ ለነዚህ ጉልህ አስተዋጾዎቻቸው በመዝፈኑ፤ ለነዚህ ለተጠቀሱት መልካም ስራቸው መታሰቢያ የጭንቅላቱ ውጤት የሆነውን ሙዚቃ በማበርከቱ፤ ቴዲ አፍሮ ፤ አቀንቃኝ ና አዝማሪ ፤ ገጣሚና ስዓሊ፤ ሃያሲና ደራሲ፤ ጸሃፊ ተውኔቱና ብላታው፤ አፉን በለጎመበት ዘመን፤ በብእሩ የታሪክ ጋሻ፤ በግጥሙ ለቆሰለ ታሪክ ማገገሚያ፤ በዘፈኖቹ ( ከ ማሊ ሱፊዎች ባልተናነሰ መልኩ) የነብስን ክር እየተጫነ ያላስለቀሰው፤ ያላስተከዘው፤ ሰው እንደሌለ የገባቸው ሰዎች፤ በይበልጥም የአድዋ ድል፤ የጥቁር አንበሳዎች ድል መሆኑን ያሳየበት በመሆኑ እና ይህም የሚያማቸው ሰዎች፤ ዛሬ በደሌ ቢራ ቴዲ አፍሮን ስፖንሰር ስላደረገ፤ በደሌ ቢራን ያለመጠጣት አድማ ጠርተዋል። አሁን ቴዲ አፍሮን አብዶ በረንዳ ( የጫት ማከፋፈያ በረንዳ ነው) ቢሆን ስፖንሰር ያረገው ምን ሊሉ ነበር።። ባረገው እና የተከታዮቻቸውን መልስ ባየን። አንድ ጊዜ ቆይ ጠብቁኝ ሳቄ መጣብኝ ያለው ተናጋሪ ማን ነበር።

አዲሱ የቴዲ አፍሮ አልበም ( ጥቁር ሰው) የብዙዎቹን ኢትዮጵያዊያኖች ድምጽ ያስገኘለትን ያህል፤ ንጉስ ሚኒሊክ በድሎናል፤ ጡታችንን ቆርጦዋል፤ ወዘተ ወዘተርፈ ለሚሉት ደሞ፤ ከሚኒሊክ መፈጠር፤ ከታሪክ አንቅጽነቱና አኩሪ ገድሉ ጋር የጀመሩትን እጹብ ጸብ ውሃ የሚደፋበት በመሆኑ፤ ጠላት ሊያፈራበት እንደሚችል መገመት ብዙም አይዳግትም። እናም እነዚህ ሰዎች ቀደም ብዬ እንደ ጠቀስኩት፤ በደሌ ቢራን ያለመጠጣት አድማ እናድርግ እያሉ ነው። ልክ ናቸው፤ ህዝብ በጥላቻም በቢራም ሰክሮ እንዴት ይሆናል፤ ባንዱ ብቻ ይበቃልና።

በነገራችን ላይ ይህንን አድማ ለማስመታት ከሚራወጡት እና ከሚሯሯጡት ሰዎች መሃከል አንዱ ጁሃር መሀመድ መሆኑን ሰምቼ አፍሬ ጥፍሬ ውስጥ ልገባ ነበር። ባንድ ወቅት ይሄ ወጣት ፖለቲከኛ ስለ ራሱ ሲናገር “እኔ እናቴ መንዜና የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነች አባቴ ደሞ ኦሮሞና ሙስሊም ነው ፤ ታዲያ ከኔ በላይ ኢትፖጵያዊነትን የሚወክል ምንነት ኣለ ወይ” ብሎ ነበር። መልሱ ሊሆን ይሚችለው ጁሃርዬ በውነትም የለም፤ እንዳንተው አቶ መለስም እኮ የተላቀቀ ነገርን ማጣበቅ የሚችል (ኡሁ የሆነ) (UHU…glue) ደም ነበራቸው፤ ግን ደሙ ሳይሆን የደሙ ባህሪ ነው ወሳኙ ነገር። የተሸከምነው ደም ሳይሆን በውስጣችን ያፋፋነው ስብዕና ነው ማንነት ፤ ማንነት ስራ ነው እንጂ አንተ እንዳልከው የ-ኢ-ተጎራባች ዘር ደም ውህደት (ኬሚስትሪ ውጤት አይደለም)፤ ክርስቶስ ( ኤሳው… ኣለይሁ ሰላም) በ-በረት ተወለደ ብለን እናምናለን፤ ግን እንደ ሰብኣዊ ፍጡር በ-በረት መወለዱ ሳይሆን ሰው ሆኖ ሲኖር ያደረገውን ነገር ነው የምናስበው፤ ስለ ነብዩ ሙሃመድ (ሰ.አ.ወ) ኣንድ ሙስሊም ሲያስብ ስለ ዘራቸው ሳይሆን ስለ ስራቸው ነው የሚያስበው ብዬ አስባለሁ ።

ባንድ ወቅት ይሄው ሰው፤ ፹ ከ ፻ የሚሆነው የሃገሬ እስላም ኦሮሞ ነው፤ እናም የኦሮሞ ህዝብን ኢምፓወር ማድረግ፤ እስልምናን ኢምፓወር እንደማረግ ነው አለን፤ ለመስማት አይደል የተፈጠርነው እናም ሰማነው፤ ባሜጃ አለን ዝም ብለን ሰማነው፤ ቀጥሎም ኢትዮጵያ አውቶ ኦፍ ኦሮሚያ አለን እሱንም ሰማነው። በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ኣውት ኣፍ ኦሮሚያን ወደ ፈርንጅኛ ስቀዳው ( the child give birth of her mother) ኣይመስላችሁም ? ለመተርጎም የተገደድኩት የመጀመሪያው ራሱ እንግሊዘኛ መሆኑን ስለተጠራጠርኩ ነው። ለነገሩ ስታንፈርድና ኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ እኮ መፈክር አያስተምሩም።

እና ዛሬ በደሌ መጣ እና ወንድሜ ጁሃር ሰማኒያ ከመቶ ካለው ሃሳብ ጋ ግንባር ለግንባር ተጋጨ ( head on collusion) እናም ሁለት የሚጋጩ ነገሮችን እንግዲህ እናስተውላልን።

፩) መቼም ፹ ከመቶው እስላም ኦሮሞ ነው ብለኽን፤ አንተም በዘር ብቻ ሳይሆን በእምነትም ጭምር ጠበኽ፤ ኣልገባኝም ታዲያ እንዴት ነው፤ እነማን ቦይ ኮት እንዲያረጉልኽ ነው ጥሪውን ያቀረብከው፤ ፳ ፐርሰንቱ እስላም ያልሆነው ኦሮሞ ? ደሞ ከ ፹ ከመቶ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ውስጥም ቢሆን አዲስ የበደሌ አድመኛ ማግኘት ይቸግራል ብዬ አስባለሁ፤ ምክኒያቱም እነሱ ላንተ ሲሉ ሳይሆኑ ለዲናቸው ሲሉ ድሮም እንዲህ አይነቱን ነገር ይነኩት ነበር ብዬ አላስብም፤ በፍጽም አያደርጉትም፤ ታዲያ የማይጠጡ ሰዎችን ነው አድማ የጠራነው፤ ወይስ ሙሉ የኢትዮጵያዊነት ማሳያ ምሳሌ እንድትሆን ያደረገችህ የመንዜዋ እናትህን ዘመዶች፤ እኔ ኣላውቅም ፈራሁ ሄኖክ ነው ያለኝ የልጅነት ጉዋደኛዬ፤ ባንድ ትልቅ የውሃ ጉድጉዋድ ውስጥ እንሹለክ ስለው። እኔ አላውቅም ፈራሁ ጁሃር።

ዛሬ ጀርመን ያላትን ቅርጽ እንድትጠብቅ ወይም እንዲኖራት ያደረገው ኦቶ ቮን ቢስ ማርክ፤ የደም ትግል ውጤት ነው። ታዲያ ጀርመኖች በ ቢስ ማርክ ተናደው ፒሊሲነርን ( የጀርመን ታዋቂ ቢራ ነው) ቦይ ኮት እናርግ አላሉሉም። በፈረንሳይ እንዲህ የሚባል ታሪክ አለ፤ በአሜሪካም፤ ኣረ ሆመር በጥንታዊያኖቹ የግሪክ ዘመን ስለነበረው ጦርነትም ጽፎዋል፤ ስለ ስርኣቱ፤ ስለ አገማምኖን እና የወንድሙ መንግስት፤ ስለ ሄለናዊው ስርዓት፤ ከዚያም በሁዋላ እነ ዳንቴ ስለ ጻፉት ስለ ዲቫይን ኮሜዲ፤ ፍሬድሪክ ዊልሃልም ኒቺ ስለተራቀቀበት የማህበረሰብ ስነ ልቦና፤ እነ አልበርት ካሙ ስለጻፉለት የፈረንሳይ ማህበረስብ እና በየስራቶቹ ውስጥ ስለ ነበርው ፍዳ፤ እነ ልዮ ቶሎስቶይ በሰላ ብእራቸው ስለዘገቡት የሩሲያ የጭቆና ቦለቲካ፤ እነ ፓብሎ ፒካሶ ጉሬንሽያ ብለው ስለገለጹት የስፔን ከተማ ስለ ስንቱ ለዚህ ለወጣቱ ፖለቲከኛ እንንገረው እስኪ ባክህ ጁሃርዬ ገረፍ ገረፍ አርጋቸው (በቃ እንደውም ለዚህ ክረምት ለፐርሰናል ዲቨሎፕመንት…ትመለከታቸው ዘንድ እጠይቅሃለሁ (ማሳሰቢያ በኣብዛኛው በአማራ ጻሀፊ አይደልም የተጻፉት ቢሆኑም ደሞ ኣነተ ሃምሳ ፐርሰንት አማራ አይደለህ እንዴ፤ የምሬን እኮ ነው)

በታሪክ ላይ ጥላሸት መቀባት በፍጹም ለማንም አይሳካም፤ ወደድንም ጠላንም፤ ጠቅልለን የምንጎርሰውን እንጀራ የፈጠሩት አባቶቻችን ናቸው፤ ለሆዳችን ያለን ቅርበት ለታሪካችንም ይኑረን። ቴዲ እንዳለው ክፉውን በክፉ ለመመለስ ማሰብ ሌላ ክፉነት ነው። ሁለቱ ደሞች እንደ ደም ይሰሩ፤ ያስቡ ዘንድ ሰው እንሁን።

ሄኖክ የሺጥላ

 

 

‘ሞረሽ ወገኔ’ ለተሰኘው ቡድን ሊቀመንበርና አቋማቸውን ለሚጋሩ ወገኖች በሙሉ

$
0
0

ከያህያ ጀማል

እንደሚታወቀው የዳግማዊ ምኒልክን 100ኛ የሙት ኣመት ለመዘከር በበደሌ ቢራ ስፖንሰርነት ቴዲ ኣፍሮ ሊያቀርብ ያቀደውን የሙዚቃ ኮንሰርት በጽኑ በማውገዝ ያገር ቤቱም ሆነ ዳያስፖራው የኦሮሞ ወገን እንዲሁም ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ የኦሮሞ ወዳጆች መጠነ ሰፊ የተቃውሞ ዘመቻ ላይ ይገኛሉ። እስካሁን ይህ ጽሁፍ በሚዘጋጅበት ሰኣት እንኩዋን #BoycottBedele በሚል ርእስ በማህበራዊ ሚድያዎች ላይ የተያዘው ዘመቻ 40,000 ገደማ የሚሆኑ ግለሰቦችን ኣሳትፏል። የተሳትፎው ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ በመሄድ በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚድያ ኣጠቃቀም ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዟል። ይሄም ዝም ብሎ ጩሄት ሳይሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ወገኖች ትኩረት ስቦ የተሳሳተውን ኣቅዋማቸውን መልሰው እንዲያስተካክሉ ተጽእኖ ሲያሳርፍባቸው እየታየ ነው።
Bedele Beer

የሞረሽ ሊቀመንበርና የሊቀመንበሩን ኣቁዋም የምትጋሩ ወገኖች ሆይ! የኦሮሞ ህዝብ ምኒልክን የሚያወግዝበት ምክንያት ከናንተ የተሰወረ ኣይደለምና ያንን በማብራራት የኣንባቢዎችን ጊዜ ማባከን ኣልፈልግም። ምኒልክ ለናንተ ጀግናችሁ ሊሆን ይችላል። ለኛ ለኦሮሞና ለኣብዛኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ግን ምኒልክ ኣፍሪቃዊ ሂትለር ነው ቢባል ማጋነን ኣይሆንም። ስለሆነም እኛ ኦሮሞዎችና እንደኛ ሁሉ የምኒልክ ጭፍጨፋ ሰለባ የሆኑ የደቡብ ብሄር ብሄረሰብና ህዝቦች ኣፄውን በጨካኝነቱ ስናስብ እናንተ ግን በጀግንነቱ እየዘከራችሁ ነው። ኣንዱና ትልቁ መለያያ ነጥባችንም ይሄው ለየቅል የሆነው የታሪክ መስተዋታችን ነው።

ስለ ኣመለካከታችን ልዩነት ይህን ያህል ካልኩ ዘንዳ ይቺን መልእክት ለመጫጫር ወዳነሳሳኝ ፍሬ ጉዳይ ልዝለቅ። በህብር ሬድዮ ጋባዥነት የሞረሹ ሊቀመንበር የተናገሩትን ፍሬ ጉዳይ በጥንቃቄ ኣድምጫለሁ። ሊቀመንበሩ ሲናገሩ የኦሮሞ ህዝብ በተለይም ወጣቱ ትውልድ የያዘውን ብሄርተኛ ኣቁዋም ለማጥላላት የተቻላቸውን ያህል ሞክረዋል። ‘የኦሮሞ ምሁራን የሚደልቁት ከበሮ በሻዕቢያና ወያኔ የተቀነባበረ አማራና ኦሮሞን ለማጋጨት የተወጠነ ልቦለድ ነው።’ ሲሉ ያለሃፍረት ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ ይህንን ሲናገሩ ኦሮሞና ኣማራ እንዳይጋጭ በጣም የተጨነቁ መስለው ለመቅረብ ቢደክሙም ኣልተሳካላቸውም። ሁለቱ ብሂሮች እንዳይጋጩ የሚመኝ ቅን ልቦና ቢኖራቸው ኖሮ የኦሮሞ ምሁራን ያነሱትን የጸረ ምኒልክ ተቃውሞ ‘ከበሮ መደለቅ፣ ልቦለድ…’ እያሉ ከማጥላላት ይቆጠቡ ነበር።

የዚህ መልእክት ትልቁ ኣላማ ግን የግጭት ጉዳይ ኣይደለም። ሊቀመንበሩ የተናገሩት ‘የኦሮሞ ምሁራን የሚደልቁት ከበሮ በሻእብያና ወያኔ የተቀነባበረ…’ የሚለው ነጥብ ላይ ያተኮረ መሆኑን ላሰምርበት እወዳለሁ። የግለሰቡ መልእክት እምብዛም ውሃ መቁዋጠር የማይችል ቢሆንም ኣባባላቸው ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ኣጋጣሚዎች ኣንዳንድ የኣማራ ልህቃን ሲያስተጋቡት ከኖሩት መሰል ኣስተያየት ጋር ስለሚገጣጠም ተንቆ መታለፍ የሌለበት ሆኖ ኣገኘሁት። የኦሮሞን ህዝብ የጭቆና በቃኝ ድምጽ ለማጥላላት ሲባል ከድምጹ በስተጀርባ ያለው እገሌ ነው የሚል በንቀት የተጠናወተ ኣቁዋም ሲራመድ የሞረሹ ሊቀመንበር የመጀመሪያው ኣይደሉም ማለቴ ነው። ኦሮሞ እንደብዙሃንነቱ ተደራጅቶ ሃይል መሆን የመቻሉን ሎጂካዊ እውነታ ኣምነው መቀበል የማይሆንላቸው ወገኖች መኖራቸውን እናውቃለን። እንደነዚህ ወገኖች እምነት ከሆነ የኦሮሞ ተወላጆች ይህን ያህል በሚያስድነግጥ ቁጥር ተደራጅተው ማህበራዊ ሚድያን በመጠቀም የሚቃወሙትን በመቃወም ወይም የሚደግፉትን በመደገፍ ጎላ ያለ ድምፃቸውን ለፈለጉት ኣካል ማሰማት ኣይችሉም። ኦሮሞዎች ይህን ለማድረግ የግድ የሆነ ሌላ ኦሮሞ ያልሆነ ሃይል ከበስተጀርባቸው መኖር ኣለበት። በተለይም እንዲህ ያለውን የኣማራውን ፅንፈኛ ወገን የማያስደስቱ መሰል እንቅስቃሴዎች የወያኔ እገዛ ሳይታከልባቸው በኦሮሞ ብቻ ተከናውነው ሊሰምሩ ኣይችሉም የሚለው ኣስተሳሰብ ወይም ማስመሰያ የሚያስተላልፈው መልእክት ቢኖር ኣንድና ኣንድ ብቻ ነው። የኦሮሞን ህዝብ መናቅ። ኦሮሞ በጭራሽ ብቻውን ቆሞ እንዲህ ያለ ታሪክ መስራት የማይችል ኣስመስሎ ለማሳመን የሚደረግ ጥረት ነው። እንዲህ ያለው ኣቀራረብ ኣንዳንዴ ከኣስገራሚነቱ ኣልፎ ኣስቂኝ ነው። ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ የኣማራው ጽንፈኛ ወገኖች ይባስ ብለው ጭራሽ የኦሮሞ ህዝብ የባህል፣ የቁዋንቁዋና ራሱን በራሱ የማስተዳደር ጥያቄ ከወያኔ የተኮረጀ ኣስመስለው እስከማቅረብ የሄዱበት ኣጋጣሚ ብዙ ነው። እንደዚህ ያሉ ሰዎች ማንን ለማታለል እንደከጀሉ ግልጽ ኣይደለም።

moreshminilikመሪም ሆነ መሰል ኣቁዋም የሚያራምዱ ወገኖች ከኦሮሞ ህዝብ ጋር እንደ ኣዲስ መተዋወቅ ያስፈልጋቸዋል። ወያኔን በወያኔነቱ፣ ራሱን ችሎ በሌላ ኣገር መሪነት የሚታወቀውን ሻእቢያም በጎሮበት ማንነቱ ለይተው በማወቅ ሃራምባና ቆቦን ከመደበላለቅ ተቆጥበው በተለይም በኦሮሞ ህዝብ ጉዳይ ላይ የሚጠቀሟቸውን ቃላት በጥንቃቄ መምረጥ ይጠቅማቸዋል። የኦሮሞን ህዝብ ለመናቅ ሲባል የህዝቡን ጥያቄ ከወያኔ ወይም ከሌላ ሃይል ጋር ለጥፎ መዘባረቅ ኣጉል ከመጃጃል ያለፈ ምንም የፖለቲካ ፋይዳ ኣያስገኝም።

የሞረሹ ሰውና መሰሎቻችሁ ሆይ!
ከመቶ ኣመታት በፊት በህይወት የነበረው የናንተ ጀግና ምኒልክ ኣንድ ብሎ ያስተማራችሁ ነገር ቢኖር ኦሮሞን በኦሮሞነቱ መናቅ ነው። ምኒልክ በዘመኑ ኦሮሞን ሊንቅ የቻለው ከኣውሮፓ በተገኙ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ተመክቶ ሰራዊቱንም እነዚህን ዘመናዊ መሳሪያዎች እሳክፍንጫው በማስታጠቅ ጦርና ጎራዴ ብቻ የያዘውን የኦሮሞውና ሌላውም መከታ ኣልባ ወገኔን በጭካኔ ጨፍጭፎ ማስገበር በመቻሉ ነው። ዛሬ ላይ ያለው የኣማራ ትውልድ ጽንፈኛ ወገን ግን እንዲህ ያለውን ከኣባቶቹ የወረሰውን ትምክህታዊ ንቀት እንዳለ ለማስቀጠል ሲንደፋደፍ ይገርመኛል። ኦሮሞን መናቅ ትላንት ባህላቸው ያደረጉ ወገኖች የወግ ነገር ሆኖባቸው ዛሬም የንቀት ባህላቸውን እንዳለ ማስቀጠሉ ኣጸፋው ኣደገኛ ይሆናል። ሁላችንም 21ኛውን ክፍለ ዘመን ኣብሬን እየኖርነው መሆኑ የተረሳ ይመስላል። ናቂው ወገን 21ኛ ክፍለ ዘመን ላይ ሆኖ ተናቂው ደግሞ 19ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ተገድቦ የሁዋሊዮሽ የቀረ እስኪመስል ድረስ ከኣማራው ጽንፈኛ ወገን ዘንድ የምናስተውለው ኦሮሞ ላይ ያነጣጠረ ስልተ-ብዙ ንቀት የጤና ኣይደለም።

የሞረሹ ሰውም ሆኑ መሰሎቻቸው ማወቅ ያለባቸው ኣንድ ሃቅ ኣለ። የኦሮሞ ህዝብ የማንም ድጋፍ ሳያስፈልገው ራሱን ችሎ ይበጀኛል ያለውን የትግል ጎዳና ቀይሶ በመገስገስ ላይ የሚገኝ ንቁ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ህዝብ ነው። የብሄር መብቱን ለማስከበር የሚያነሳው ጥያቄ የ50 ኣመት እድሜ ያለው ጥያቄ መሆኑ ከህሊናችሁ የተሰወረ ባይሆንም ገና ትላንት ስልጣን ከጨበጠው ወያኔ ጋር ኣስተሳስራችሁ ለማቅረብ መድከማችሁ ምናልባት ከፍራቻ የመነጨ ሊሆን ይችላል። ፍራቻን ደግሞ በዚህ መልኩ መዳፈር ተጨማሪ ኣስፈሪ መዘዞችን ከማስከተል የዘለለ ጥቅም ኣያስገኝላችሁም። ወያኔ እንደሆን ላለፉት 23 ኣመታት በጋራ ስናወግዘው የኖርን ኣምባገነን ሃይል መሆኑን እስከመዘንጋት ሄዳችሁኣል። ኣንድ ስልጣን ላይ ያለ ኣምባገነን ሃይል መብቴ ታፈኔ ብሎ ከሚታገል ተቃዋሚ ወገን ጋር ኣንድ ላይ የሚደመርበት ምንም ኣይነት ሎጂክ ኣይኖርም።

ይሁን እንጂ ከወያኔ ጋር የሚያመሳስለን ጉዳይ ሲኖር በስመ ጠላትነት ብቻ ኣይናችንን ጨፍነን ወደ ተቃራኒው ኣቅጣጫ በመነዳት ጥቅማችንን ኣሳልፈን የምንሰጥ ጅሎች ኣይደለንም። ከኣማራው ለዘብተኛ የፖለቲካ ሃይል ጋርም እንዲሁ። ማንኛውም ወገን የጋራ ጥቅማችንን በሚያስጠብቅ ጎዳና ላይ ከተቀላቀለን ታሪክን ለታሪክ ትተን ለመጻኢ እድላችን ኣብሬን የማንገሰግስበት ምክንያት ኣይኖርም። እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም የራሱን ፍላጎት በሃይልና በብልጣብልጥነት እኛ ላይ ለመጫን ያደባ ሃይል ካለ ግን እሱ የነጋበት ጅብ መሆኑን ላስታውሰው እወዳለሁ። ኣረቦች ሲተርቱ ‘ውሾቹ ይጮሃሉ ግመሎቹም ይገሰግሳሉ’ እንደሚሉት ሁሉ ትግላችንም በኣጉል ጩሄቶች ተደናብሮ ከግስጋሴው የሚገታ ኣይደለም።

ቸር እንሰንብት!

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>