መግቢያ
በመጀመሪያ ደረጃ ውድ አቶ ካሳሁን ነገዎ ታዋቂ ሰዎችን ወይም ምሁሮችን ለቃለ-መጠይቅ እያቀረበ አስተያየታቸውንና አመለካከታቸውን እንድናዳምጥና ትምህርት እንድንቀምስ የሚያደርገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው። በዚህም መሰረት በአ.አ በ23.12.2013 ዓ.ም ዶክተር ብርሃኑ ነጋን በቅርቡ ለዕትመትና ለንባብ ባበቃው፣ “ዲሞክራሲና ሁለንታዊ ልማት“ በተባለው መጽሀፉ ዙሪያ ምን ማለቱ እንደሆነ ለቃለ-መጠይቅ ጋብዞት አንዳንዶቻችን ለማዳመጥ ችለናል። የቃለ-መጠይቁን ምልልስ በጥሞና ላዳመጠ የዶክተር ብርሃኑ ነጋ መልስ ግልጽና ብዙም የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም።
የአንድን ህብረተሰብ ችግር የመረዳትና መፍትሄ የመፈለግ ጉዳይ (ከፈቃዱ በቀለ)
ኢትዮጵያዊነት የደሜ ዕምነት ሥነ- ሕይወት! –ከሥርጉተ ሥላሴ
ኢትዮጵያዊነት የፍጥረት ዓይነ – ህሊና ነው! እውነተኛ ሐሴትን የመፍጠር አቅሙ ሙሉዑ! ኪናዊ!
ከሥርጉተ ሥላሴ 31.12.2014
ውህዳዊ የደሜ ልዩ ጽጌያዊ ህልው ንጥረ ቅምረት፤ ውስጤን አስውቦና አሳምሮ፤ ደንግጎ እኔን ሰጠኝ።
ወደ ውስጤ ለመግባት ይለፍ የሚሰጠው በኢትዮጵያዊነት ዋና በር ብቻ ነው። የዕልፍኙ ዕድምተኝነት ፈቃድ የሚያገኘው ከዚህ ከነጠረ፤ ዓለምን ከፈጠረ ማንነት ላይ ሲነሳ ብቻ ይሆናል። እምነትህን ከልብ ስትቀበለው ሚስጢሩ ይገለጽልኃል፤ አቀባይህ መንፈስ ቅዱስ ነውና። ሚስጢሩ ሲገለጽልህ ደግሞ ውስጥህን ትተረጉመዋለህ። ውስጥህን የመተርጎም ዬጸጋህ ብቃት የማንነትህ ጌታ እንድትሆን ይዳኝኃል። ሚስጢሩን በውስጥ አደላድሎ በድል ላይ፤ በአሸናፊነት እስቀምጦ እኔን የገለጸኝ ደግሞ የደሜ ዕምነት ሥነ – ሕይወት አትዮጵያዊነት ብቻ ነው – ለሥርጉተ።
የውስጥ ውበቴ ጅረት የሚመነጨው ከዚህ ጥልቅና ምጥቅ፣ ረቂቅ ማህደረ – ገነት ውስጥ ፈለቀ። ኢትዮጵያዊነቴን ሳስብ ልክ ቅድስት ድንግል ማርያምን በመንፈሴ አደባባይ መንበር ላይ ሳስቀምጣት የሚሰማኝን መርኃዊ፣ ስህናዊ ሰናይ ያህል ይመግበኛል። ዜግነቴ የተፈጥሮ ህግ ጭብጥ ነውና።
የስደትን ሁለገብ ፈተና የሰበርኩበት ታላቁ መሳሪያ፤ ቋሚ ቅርሴ፤ የብቻዬ ውድ የጽናት ዋንጫ፤ የብርታት ቀንዲሌ፤ የአሸናፊነት ብርታቴ፤ የተፈሪነት እርስቴ፤ የትእግስቴ ቅዳሴ፤ በራስ የመተማማን ጉልበታም መንፈሴ መቅኑ ያለው ከመኖሬ ግንድ ከገናናው ኢትዮጵያዊነት ላይ ብቻ ነው። መሪዬ፤ የፖለቲካ ፓርቲዬ፤ የቅኔ ዘ-ጉባኤ ሊቀመንበሬ፤ የተስፋዬ ቀንድ፤ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። በፍላጎቴ ሙቅ ስሜት ውስጥ የዕለታዊ ገጠመኞቼ ስንኞች ሁሉ ዘኃቸው ከኢትዮጵያዊነት በታች ሲሆኑ ከእሱ በላይ ያለው ግን አንድዬ አማኑኤልና ድንግል እናቴ ብቻ። ምዕራፉ ተገልጦ ተገልጦ የማያልቀው ቀለማሙ ማንነቴ፣ አይጠገቤው ልዩ የመንፈስ የጸዳ አደባባዬ የተዋጣለት – ጉልቴ – ምልክቴ ኢትዮጵያዊነት።
ፍጥረታዊ ነገር ፈራሽም ፍሳሽም። የማይሞት መንፈስ ቢኖር ኢትዮጵያዊነት ብቻ። ምንም እንኳን ሀገር በቀልም ሆነ ጠጉረ ልውጥም ጠላት ባያበራላትም። ጠለል፣ ደለል የሌለው የተጣራ ዓለምዓቀፋዊ ስመጥር ማንነት ነው ኢትዮጵያዊነት። በህይወትህ የማትሸሸውና የማትሸሸገው ህብር፤ የውስጥ እኔነትህ ውበት ቢኖር፤ ህሊናህንና ኢትዮጵያዊነትን ብቻ … ፍቅሩ እርቦ – ሲሶ – ሳይሆን ውስጥን እንደ አሻው አሳምሮና አሳምኖ የሚገዛ ሙሉ ዕጅ ሰንደቃዊ ዐጤ – የማርያም መቀነት! አበጀህ የካምና የሴም መለሎ!
ህም! እም! ባላንጣው አይሎ ጦር የመዘዘበት የሰባት ሰማያት ሚስጢር። ባላንጣው እሱን ለማጥቃት ለዘመናት አልሞ የተነሳበት ግን ድል ያደረገ ቋሚ ቁርጠኛ የአርበኝነት ቤተ – ማዕዶት – የእኛ! የነፃነት ፍጽምና የትርጉም – መጸሐፍ። እያለ በቁሙ የጸደቀ ድንግል። ወጥ ማንነት። የልተቀዬጠ የውስጥ ሰላም ማግ። የጠላቱ ሆድ እቃው ሳይቀር ለፍልሚያ ያላባሩለት – የእኛ- ጹዕመ ልዑል። ግጥምጥም ያልሆነ። ሽብሽብ ያልሆነ። ሽምቅቅ ያልሆነ። ጭምትር ያልሆነ። ደቃቅ ያልሆነ። ኮረኮንች ያልሆነ። ቡላማ ያልሆነ …. ያልተቀረቀረ … ያልተጣበበ – ያልተጣበቀ – ያልተዋሰ – ያልተለጠፈ …. ያልተረተረ … ያልተጋደመ … ቀኙ ቀጥተኛው መንገድ፤ እሱን ቀዶ ጥገና ለማድረግ ማንም የማይችለው፣ በሙሉ ቀን የተፈጠረ የሥነ- ሕይወት ግጥም- ቋሚ አዛውንት – ንዑድ! ፈጣሪ አምላክ ለአማንያን የሁላችን ነው እንደ እራሱ አድርጎ የፈጠረን። የኢትዮጵያዊነት ውስጠት ደምና ሥጋ፤ ነፍስና እስትንፋስም …. ውህድ – በአምሳል።
ብሩህ ነበልባላዊ ላንቃ! የሚያበራ … ፍጹም ደማቅ … የሚያሞቅ ጃኖ፤ ነፍስን የሚታደግ የሰማያት ፍጹም ሽልማት፤ ቅመመ ብዙ – ልዩ ጣዕም፤ ሁሌ እንደ አሸት የሚኖር ያመረበት። እርጅና ከቶም ዝር የማይልበት – ሀመልማለ ህብሬ፤ የወስጠት – ሰላማዊ ዕንቁ – ለእኛ። ለወያኔና ለመሰሎቹ ግን አንጡራ ጠላት፤ ለባላንጣው የፋመ ረመጥ። የእኛ የርትህ – ክብረ – ዝናር፤ የእኛነታችን ልዕለ – ባለአደራ፤ የጥቁር ደም የግንባር ማህተም፤። ወርደ ሰፊ ማንነት፤ ደንበር ዬለሽ ሐርግ ነው ኢትዮጵያዊነት። በተጋድሎ ድል አብዝቶ የተቀለበ! የአሸናፊነት በትረ – ሰገነት! የነፃነት – ቅዱስ መንፈስ።
ዘንካታ! መጠነ ሰፊ ንጥር ሚስጢር፤ እራሱን ለመግለጽ ሆነ ለማብራራት የማይቸግረው የድህነት ፍጹም ኤዶማዊ ስጦታ። የዜግነታችን መለዮ ግርማ – ሞገሰ – ዘውዳችን! እውነትን ጸንሶ እውነት የተገላገለ። በእውነትም እውነትን አሳድጎ የቀመረ የተመረቀ። እውነትን ያነጠረ የሰብዕዊነት መረቅ። እውነትን ጃንደራባው በማድረጉ ዓለምን ከነሙሉ ዘሩ የፈጠረ የሥነ -ፍጥርት ድንቅ፤ ጥልቅ አልማዝ፤ የድንቅነሽ ክታብ፤ ለፍጥረታት ሁሉ ቅርንጫፍ ያልሆነ መሰረት – ኢትዮጵያዊነት። ግንድ!
የተፈጥሮ አጥር! ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ የጽናት ወተት ጠጥቶ ያደገ፤ በፈተና ተፈትኖ ታሽቶ፤ ተሰልቆ የፈለቀ ወርቅ- ኢትዮጵያዊነት። እኔን – ለእኔ፤ እርሰዎን – ለእርሰዎ እያነገጋረ ቀጥ ያለ ንጹህ ቡናማ ሐዲድ ዘርግቶ የሰራ አካላትን በመግዛት ፍቅር ሰጥቶ፣ ፍቅርን ተቀብሎ፣ ፍቅር ሆኖ፤ ፍቅርን አፄው ያደረገ ዓውራ መረኃ – ፅድቅ። ሐመረ – ሕይወት።
ልግለጽህ ወይንስ ትገልጠኝ?
ውስጤን ስታይ አባብለህ – ስትመስጠኝ
የእኔ በመሆንህ ሳጌጥብህ
ልኖርብህ በመንፈሴ ሳደላድልህ፤
ነፍሴ ታርጋለች፤ በሰናይ
ትሰግራለች ኤዶምን በፍሰኃ ልታይ፤
ትፈጥናለች ትሆናለች በአንተ ሐሤት አዳይ።
የትንፋሼ መቀነተ – ቃታ ….
እሱ በእሱ ያመረበት በድንቅነሽ ገበታ
ታደገኝ ሁሉን በገፍ ሰጥቶ – በአንድምታ፡፡
የውበት ማህደር! ቀለማም፤ የመስከረም አድዮ አባባ፤ የጸደይ ጽጌረዳ፤ የክረምት ፏፏቴ፤ የበልግ እሸት፤ የበጋ ጣና ዘገሊላ። እኔን ያጀራገደ፤ እርሰዎን ያዘናከተ፤ እኛን ያሞናሞነ፣ ሳቂተኛ – ፍልቅልቅ፤ ባለ ማጫ – ግራጫ፤ ባለ ካባ – ኩሩ፤ ባለ ጃኖ – ከሩቅ ጠሪ፤ ባላ ጭራ – ንጹህ፤ ባለ ከዘራ – ምርጥ ዘር – ዘርቶ ያበቀለ፤ ባላ እጀ ጠባብ – ዓዕማድ፤ በላ ጋሻ የቀደምት ሁለገብ አብነት፤ በላ ጎራዴ ጠላትን ጎራርዴ፤ ባለ ጦር የነፃነት – ሰቅ፤ ባለ ማህተም – የፍቅር ማህደር፤ አንበሳ – የቅኝ ግዛት ምኞትን ያከሰረ – ከሥሩ አምክኖ የአብነት ዘውድ በጥቁር መሬት የደፋ አዛዥ፤ ሁለመናው እርስ -በእርሳቸው በተያያዙ ባለ ቃልኪዳን ሴሎች ተመስጥረው የሚገኙበት የውበት ማዕዶት ኢትዮጵያዊነት። ጉልህ!
ሳተና! ጥሩ ሰብሳቢ፣ መልካም አደራጅ፤ ሸጋ አስተናባሪ፤ ውብ አድማጭ፤ የውስጥ አሳ – ሰጋር፤ ኣራት ዓይናማ፤ መንገዱን ያወቀ፤ ፍላጎቱን የተረዳ፤ እሩቅ አልሞ፤ የፊቱን በስልት ከውኖ፤ ነገን በቅጡ ለማሰናዳት የማይታክተው እንቅልፍ አልባ ታታሪ፤ ትናንትን በድርጊት ዘክሮ መነሻውን ለመድረሻው በመሆን መቻል ተፈጥሮ ድሮ – ኩሎ፤- ማጫ አማቶ፤ መልስና ቅልቅሉን በድል የሚቋጭ ስልጡን ማንነት – ኢትዮጵያዊነት – የታሪክ መምህር። ቀለማም ትውፊት!
ጌታ!
የማያመናታ
የማይማታ!
የማያ~~~~ ም ~~~~ ታታ!
ትብትብን የ ~~~~ ሚፈታ
ከጥበት – የሚያፋታ!
ለጠላቱ የማይሰጥ ፋታ።
ያልተዛናጋ፤ በማሌሊት ድንፋታ፤
የመንደርተኝነትን እንጥል የገፈተረረረረ
የቆረጠ … የተረተረ …. ያሳረረረረ
ንቆ ያሰወገደ የጎጥን ሽቅብታ!
አሰተዋይ፤
የአረንጋዴ ቢጫ ቀይ ሲሳይ
ውሉ ያለ፤ ከሰማዬ – ሰማይ።
ቆቅ! ዓራት ኣይናማ ሥነ – ጥበብ። የጊዜን ህግጋት ከመፈጠሩ በፊት ተቀብሎ የዋጠ፤ ቀደምትነትን – ያበቀለ። አስራሁለት አካላትን በአኃትዮሽ ለማንቀሳቀስ የፋታ ፖሊሲ ፈጽሞ ጠይቆ የማያውቅ – ዕውቅ ስንዱ። የሥነ መኖርን ዶግማ ከራሱ ጋር በፋቃዱ አዋህዶ ለነባቢተ ነፍስ ታላቅ ዩንቨርስቲ የከፈተ የመንፈስ መብራት። የማይተኛ፤ የማያንቀላፋ። የማያንጎላች የ24 ሰዓት ሙሉ አገልግሎት ለመስጠት ከአረንጓዴው ወርቃችን ጋር በሥራዓተ – ተክሊል የተገባ ንቁ፤ ብቁ – ዘብ አደር ኢትዮጵያዊነት። መዳፍ!
ማህደር! የማያልቅበት። የመልካም ነገሮች ሁሉ ሙዳይ። የጨዋነት ሞሰብወርቅ። የሆደ ሰፊነት ዋሻ። የትህትና ቀለበት። የቅንነት ማተብ፤ የእንግዳ ተቀባይነት ጎተራ። ሃዘን ተፍሰኃ የመጋራት ድሪ። የዕምነት ማህደር። የአክብሮት ተቋም፤ የይሉኝታ ማርዳ፤ የይቅርባይነት ፍትኃት – ኢትዮጵያዊነት የሰው ተፈጥሮ መንበር። መቅድም!
ወበራ! የሥራ ወዳድነት መንክር። በተፈጥሮው የተደራጀ። በኽረ – የአፍሪካ ልጅ፤ የድርጀት ፅንሰ ሃሳብ የፈለቀበት ማንነት። የፈትል፣ የስፊት፣ የእርሻ፣ የአረም፣ የጉልጓሎ፣ የአጨዳ ሙሽራ – ኢትዮጵያዊነት። ጥቁር አንበሳን አደራጅቶና መርቶ ለዓለም የሽምቅ ውጊያ ደንብና የአፈጻጸም ስልት በመቅረጽ ገጸ በረከት የሰጠ- ቀደምት፤ ያሰተማረ ብሩክ መንፈስ – ኢትዮጵያዊነት። የሰው ልጅ በህብረት ተረዳድቶ መኖርን ያስገነዘበ፤ የድርጅትን ጽንሰ ሃሳብ ድርጊት ላይ በማዋል ልዩ ዓርማው ያደረገ – ሰልጥኖ የተወለደ። ማህበራዊነትን በመበትን ሳይሆን ተፈጥሮውን መርምሮና አጥንቶ በተሰበሰበ መልኩ እንደ ባህሪው በተከታታይ የመራና ያሰተዳደረ ሊጋባ። ለማህበራዊ ኑሮ የዕድሜ ልክ የጉባኤ ሰብሳቢ። እንደ ማስረጃ … ሰንብቴው፣ ጽጌው፣ አድርሽኙ፣ ማህበሩ፣ እድሩ …ን፣ ሀሳብን በሃሳብ አታግሎ እምነታዊ ጉባኤዎችን በድምጽ ብልጫ የቋጨ መቅድመ – አብነት። እንደዬባህሬያቸው ከነሥነ – ምግባራቸው ወስዶ ማገናዘብ የቻለ – ችሎት። ንጋት!
ተመስገን! የኢኮኖሚስት ሙሑር ነው ኢትዮጵያዊነት። የባንክን ጽንሰ ሃሳብ በመጀመር እረገድ በቁቤ፤ እንዲሁም በወለድ ብድርን መስጠት በሚመለከት ቀዳሚ ነው። አዎና! የማራቶን አሸናፊ – ኢትዮጵያዊነት። …. ስለዚህ ዛሬ ዓለም በተለያዩ ሁኔታዎች እንዲህ ተደራጅታ በተመሳሳይ ፍላጎት ተዋህዳ ለመፈጠሯ ዘ – ኢትዮጵያዊነት ፋና ወጊ ነው። ኢትዮጵያዊነትን ፍተሻ ስናደርግለት የናሙና ተምሳሌነቱ የምህረት ዓውድ ነው። ኢትዮጵያዊነት ዓለምን በመፍጠር፤ በመቀመር እረገድ መነሻም መድረሻም ፌርማታ ነው። ግዴላችሁም እንስማማ …. ብዙ ያልተነኩ መዋለ ኃብታት ያሉት ዲታ፤ የምርምር ዕምቅ ጥሪቶች ባለቤት ነው – ኢትዮጵያዊነት። አንቱነት!
ማህጸን። ዕውቀት አድጎና ጎልምሶ በ21ኛውን ምዕተ ዓመት እንዲያሸበርቅ የረዳው መነሻ መሰረቱ የቀደምቱ በሀረግ በጽጌረዳ አባባ የተንቆተቆጡት፤ ከበሬና ከፍዬል ቆዳ ተፍቀው ከተሰሩት ብራና፤ በሸንበቆ የቀለማት የንድፍ ጠብታ የፈለቀ ነው። የዛሬው የአስትሮኖሚ የምርምር ማዕከል የትናንት የቤተክርስትያናት ሊቃውንት ጥልቅ የምርምር ውጤት ነው። ሊቃውነተ – አውሮፓውያን ዕውቅናቸው የተቀዳው የፈለቀው ከቀደምቱ ኢትዮጵያዊ ሥነ -ህሊና ጭማቂ ነው። ይህን ፈረንሳይ፤ ስፔን፤ ኢጣሊያን፤ ባቲካን፤ ጀርመን፤ ኢንግላንድ ካሉ ዩንቨርስቲዎች ማዕከላዊ ከሆኑ ዕወቅ ቤተ -መጸሐፍቶች ጎራ ይበልና ይፈተሽ፤ የሥልጣኔው ታቦት፣ የጥብቡ ማሳ፣ የዘመናት ቆጠራ፤ የሳይንስ መሰረት፤ የፍውሰት ብልኃት፤ የፊደሉ ግባዐት ይመሰክራሉ ይናገራሉ …. የሥነ – ጹሑፍ እድገታቸውም መሰረቱም ኢትዮጵያዊነት! …. ለሁለመና – ኢትዮጵያዊነት። አንጎል!
መዳህኒት! ዛሬ በዓለማችን በልማዳዊ ወይንም ባህላዊ መዳህኒት በቀደምትነት የሚጠሩት እነቻይና ናቸው …. ነገር ግን ዋገምትን፣ ሳማን፣ …. ሽፈራው ቅጠልን፣ እርድንና ጥቁር አዝሙድ ቅመማትን እሰቧቸው፤ ተልባንና ጤፍን አሰሷቸው፤ ነጭ ሽንኩርትንና ዝንጅብልን – ዱባን፣ ዳስሷቸው …. የባህር ማሽላ የጭራውን ሻይ፤ የአብሽን ሻይ … እሰቡት …. መቀንደብን አሳሉት …. ደመ ካሴን ወይንም አረግሬሳን፤ የምድር እንቧይን እሰቡት፤ እሬትን ላንቁሶን፤ ስሚዛንና እንዶድን፤ ወይራን ሁሉንም ዳስሱት የኢትዮጵያዊነትን ባይወሎጂስታዊነት ቀደምትነትን ያስነብባል፤ ይተረጉማል፤ ይመሰጥራል …. ስለሆነም የጤና ህክምና ባህላዊ ኮሌጅ መናገሻው ኢትዮጵያዊነት ነው …. ለሰው ልጅም ለእንሰሳትም … አስሮኖሚነትንም አክሎ …. ከዚህ ጋር ጸበሉ፣ ዕምንቱ፤ ፆም ጸሎቱ የተዘጋን የእነ አፄ ሰርጸ ድንግልን አንደበተ የመከፍት አቅሙ ወደር የለሽ ነው። በሌላ በኩል ዐፄ ልብነ ድንግል ለአስር አመት ሰላም በመሆኑ ግንባቸውን በጦር እዬወጉ አፍርሰው የተጠጉ ነዳያን አለቁ። ጦር እንዲታዘዝባቸውም ጫን* እጣን ለጣና ቂርቆሰ ጫን* ዕጣን ለደብረ ሊባኖስ ገዳም በመላክ ጦር አውርድለት ብላችሁ ጸልዩልኝ ሲሉ መልእክት ላኩ፤ የወደዱትና የለሙኑትን አሳዝዟል። የዋዛ!
ፈዋሽ
ዳሳሳሽ
አራሽ!
የቀደምትነት – ማሟሻ – መቋደሻ
የድርጊት አትረኖሰ- ማዳጎሻ
አሳሽ።
ቅድሳት – በስክነት
እርቀት – በፍልቅት
ምርቃት – በምጥቀት
እርገት በመሆን ጥምቀት።
ቅድመት … በዕምነት
በህግጋተ – ሥርዓት፤
የዶግማ – ቅምረት
- ድልነት
ብሥራተ – ኢትዮጵያዊነት
ሥርዬት። ምህረት። ድህነት።
ውቅራት! ዛሬ የውበት ማዕከል ሆኖ የዓለምን የመገናኛ አውታሮች ያጠበበው ትናንት ሃብትነቱ የኢትዮጵያዊነት ነበር። አሃ! ካለምንም ማጋነን ኢትዮጵያዊነት በዘርፉ ማሾ ነው። ለጌጥነትን ከእምነት ጋር አስተጋብሮ፤ በመስተዋደድና አስተፃምሮ ሥራ ላይ ያዋላ … አንቱ ነው ኢትዮጵያዊነት … ለጀግንት መለያ ጉትቻው፤ ለብሄረሰብ ባህሉ ክብሩ ጌጡ ለተብዕት ከቀደምቱ የተዛቀ ነው። የውበት ማዕከላት፤ እንሶስላው ጉርሽጡ አደሱ ድሪው ስንድዱ ድኮቱ – መራዊነት!
ዋው! ዛሬን እዩት አስተውላችሁ። የጸጉር ቆረጣን …. አፍሮ፤ ሹሩባ፤ ጋሜ፤ ቁንጮ፤ ታሬ፤ ቅምቅም፤ ሰርዴታ፤ ስርንቅ፤አለባሶ ሁሉም ቤቱ ከኢትዮጵያዊነት የተነሳ ነው። እራሱ ለዓለም አዲስ የሆነው የወንዶች ሹሩባ፤ የወንዶች ሎቲ የትናንት የጀግኖቻችን የአንበሶቻችን መለያ መታወቂያ ካርዳቸው ነበር …. እንዲንጠፍላቸው፤ እንዲጎዘጎዝላቸውና የትዳር ጓደኛቸውን ፈቃድ ለማግኘት ይለፍ የሚያገኙበት ደማቸው ነው። ስለዚህ ለኢትዮጵያዊነት የነበረ ተፈጥሮ፤ ለዓለም ግን በ20ኛውና 21ኛው መቶ ክፈለ ዘመን ብርቅዬ ሆኖበት ሲንደፋደፍ …. እናያለን። አቅጣጫ መሪነት!
እሰይ! ትናትን ከዛሬ ጋር የሚያጋባው የሀገር ሽማግሌውን ሥነ -ጹሑፍስ አተኩራችሁ እዩት። የላቀ ትውፊት። በራስ እንደራስ ሆኖ የተፈጠረ የውስጥ መስታውት። ባለቤትነቱ ኢትዮጵያዊነትን በከብር ያንቆጠቁጠዋል። ዝክረ ቤተ መዘክር ፊደላችን፤ ድርሳናት፤ ስንክሳራት፤ ወርቀ ዘወንጌል*፤ ድጓው፤ ፆመ ድጓው፤ ቅኔው፤ ገድላት፤ ታምራት …. መሰል መጸሐፍታት፤ ታሪከ ብራና፤ ቀለም ጠጭ ብዕር፤ ቀለምን የመፍጠር ሂደት፤ ተክለ ኢትዮጵያዊነትን ለምለም ዋርካ ያደርገዋል። የሥነ ቃል፤ የሰዋሰው ህጋግት፤ የቃላት እርባታና ፍሰትን የሥነ ጥብብ ፍጹም ጥልቅ ሚስጢር በቅንብር፤ በሚጨበጥና በሚዳሰስ ሁኔታ ተግባር ላይ የወለበት ውስጡ ኢትዮጵያዊነት ነው። ግጥም ስድ ቦዝ ገላጭ ተራኪ መንትያው …. የሥነ ሥዕልን አዛውንትነት ረቂቅነት፤ የሙያው ጥልቅነት ህይወትን ሲመክር፤ ስለ ትናንት በአደባባይ ሲመሰክር …. መለ አካላትን ሲያፍነሸንሽ፤ ሲዳስስ የሺ ዘመናት ቅኝት ድርና ማግ መሸቢያ ትዕይንት ነው። ውርስ!
የርትህ መክሊት! ተጠዬቅ! ጥብቅና፤ የውርርድ አነዛዝ ስልቶች፤ የዋርካ ችሎትና ሥርዓታት …ዋው! ነፍስን ይታደጋል ከሳሽ የተከሳሽን ገመና ዘረዘርኩ ብሎ ….
„በላ ልበልሃ!
ያጤ ሥራቱን የመሰረቱን
አልነገርም ሃሰቱን
ሁሌ እውነት እውነቱን።
ላምህ ብትወልድ ዛጎላ
ሚስትህ ብትልበስ ነጣላ
አንተ ብትውል እጥላ ….“
ተሰዳቢው ተሟጋች ምንም እንኮን አደባባይ የማያዘወትር፤ የኑሮ ደረጃው ዝቅ ያለ ቢሆንም ቅሉ ነገር አዋቂ ነበርና እንዲህ ሲል መለሰለት ….
„በላ ልበልሃ!
ላሜ ብትወልድ ዛጎላ
አውራውን አስመስል ብላ።
ሚስቴ በትለብስ ነጠላ፤ ቀን እስኪያለፍ ብላ
እኔ ብውል እጥላ፤ የአንተን ብጤ ነገረኛ ብጠላ …“
(ከተጠይቅ ከደራሲ አቶ ሺበሺ ለማ ገፅ 22 እስከ 23 “) መጽሐፍ የተወሰደ ነው። ስመ ጥሩው ጀርመናዊ ፕሮፌሰር ኢኖ ሊትማን ለዓለም ህዝብ ያላቸውን አስተያዬት፤ የጥበቡን እድገትና ብልጽግና እንዲሁም አድናቆታቸውን በተባ ብዕራቸው አሳውቀውበታል። ይህ የሚያሳዬን ኢትዮጵያዊነት ጠበቃ፤ ዳኛ፤ ጥሩ ተናጋሪ፤ ገጣሚ፤ ባለ ቅኔ፤ ጥሩ ተከላላካይ፤ የተዋጣላት አቃቢ ህግ በተፈጥሮ ብቻ – ለፍትህ ያደረ ስለመሆኑ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ሌላው ፈርኃ እግዚአብሄር የውስጥ ደንቡ ነው። ነጋስታቶቻችን ሁሉ ከትልማቸው በፊት አምላካቸውን ያማክራሉ። የህበረት ሱባኤ ይጠይቃሉ። በቅርባቸው ካሉት ሽማምነት ጋርም ይመክራሉ፤ እጅ ያነሰው ሃሳብን ተቀበለው ይፈጽማሉ። መንፈስ!
ታሪከ ነገሥት፤ መዋለ ነገሥት፤ ክብረ ነገሥት፤ ብዕለ ነገሥት፤ ፍትሃ ነገሥት፤ የገዳ ሥርዓት፤ የወንጀለኛና የፍትሃብሄር መቅጫና ሥርዓቱ ማንነቱ የጎለመሰበት ምንጮች ናቸው። እንኳን ሰው ግመልም ተፈጥሮውን ስላማወቁ አፋራዊ ህሊናችን በአርምሞና በተደሞ አመሳጥረውልናል። እንዲሁም በንጉሥ አምላክ …. ሲባል እንኳንስ የሰው ልጅ ነፋስን ቀጥ የሚያደርግ ጸጋ ነው ኢትዮጵያዊነት። ኢትዮጵያዊነት ባለ ሚዛንነቱንና ባላነቱን ለዓለም ህዝብ እርሾ የሆነ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያዊነት እራሱ ህግ ነው። የመኖር ተፍጥሯዊ ህገ – መንግሥት ይሉኃል ኢትዮጵያዊነት። ደልዳላ!
ቀዛፊ! ያለ ተቀናቃኝ እንዳሻው በደም ውስጥ የመንሸራሸር አቅሙ ከቶም መመጠን አይቻልም። የውስጥ አሳነቱ ቅዝፈቱ አስመችቶን እሱም ተመችቶ ነው። እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ጠላቱን ያሰግዳል። ተፈሪነቱን ያመሳክራል። አይበገሬነቱን ያውጃል ትናንትም ዛሬም። እስኪ ለአፍታ እውነተኛው ሰንደቅ ዓላማችን ቃኙት፤ ወይንም ስለ ኢትዮጵያዊነት የተዘመሩትን የተደረሱትን ዜማዎች ሁሉ በአርምሞ ቃኟቸው። አገኛችኋት ብልኃቱን? መጻፍ፤ መናገር፤ መተንተን ይችላልን? … ፈጽሞ አይቻልም። ይርባል …. ልበለው? … ይወራል ልበለው? በውስጥ ይወርባል …. ልበለው? የቱ ይሻላል? …. ያሸበሽባል … ይባል? መግለጫ የለኝም። …. ሲቃ – የፍሰኃ፤ ፍንደቃ – የፍካት፤ እልልታ – የድህነት …. ሆታ የናፍቆት ሁሉንም ነው …. እንኳን ተፈጠረ መርቁልኝ። ስስታም አትሁኑ ከፍ አድርጋችሁ ድምፃችሁን አጉልታችሁ ለዘለዓለም ኑርልን በሉልኝ …. የእርገተ ነፍስን ፈዋሽ ….. የብርኃናት ድርሰትን ኢትዮጵያዊነትን ….
ለስላሳ! ሸከራ አይደለም። ሲፈጠር ሞንሟና ነው ጤፍ እንጀራ በእርጎ። በአጠገባችሁ ሲሆን ልዩ ሙቀትን ይለግሳል። ስትንቀሳቀሱ ጉልበት ይጨምራል። ስታስቡት ይጠግናል። ስታነጋግሩት በተደሞ ያዳምጣል። ስትከፉ በቅርብ ሆኖ ተመክሮውን በማቅናት ያባብላችኋል። ስታኮርፉት መላሾ ሰጥቶ እቅፉን ያንተርሳችኋል። ፊት ስተነሱት ሐዋርያ ሆኖ እራሱን ዝቅ አድርጎ ያስተምራችኋል። ኢትዮጵያዊነት ጥበብ ነው። መሻገሪያ ስታጡ የአረንጓዴ መሰለላል፤ የቀይ ድልድይ፤ የቢጫ ሰገነት ያዘጋጅላችኋል። ትንፋሻችሁን መልሶ በፍቅር ዓይን ዓይናችሁን በማዬት ይስማችኋል። አስጠግቶ ሽጉጥ አድርጎ ይይዛችኋል። የውስጥ ጠረናችሁን ቀረብ ብሎ ይጠጠዋል። ትርቡታላችሁ። ትጠሙታላችሁ። ይወዳችኋልና። የእኩል ዓውደ ምህረት፣ ብሲል ከቀሊል የማይለይ፣ ታይቶ የማይጠገብ ማር ወላላ። ታጋሽ! ኢትዮጵያዊነት ሁሌ ለጋ ወተት ግን አደብ የገዛ ዕድሜ ጠገብ ተመክሮ ያለው ሊቅ ሙሑር ነው። እንደ ወጣትነቱ ያሸተ፤ እንደ ጎልማሳነቱ አስተዋይና ሆደ ሰፊ፤ እንደ አዛውንትነቱ ደግሞ መካር ዳኛ። ደማም – ሚዛን!
ፈጣን! ሲነሳ ወኔን ቀልቦ፤ ሲያስብ እልህን ሰንቆ፤ ሲታጋ ጀግንነትን አስቀድሞ፤ ሲንቀሳቀስ የተፈሪነት ሰራዊት አስታጥቆ፤ ለድል ሲባቃ አብሮነትን ከሽኖ፤ ሲመራ አኃታዊነትን አመክንዮ አድርጎ፤ አስራሁለት አካላትን ሲሰርጽ ነፃነትን አጎናጽፎ፤ በራሱ ጊዜ ተወዳጅነትን አፍልቆ ነፍስን የሚታደግ የልብ አምላክ ቅኔ ነው ኢትዮጵያዊነት። የእኛ ክብረት!
እልፍ ሰራዊት በእልፍ ብቃትና ተምክሮ አሰልፎ፤ ከራሱ ተርፎ የጥቁር ዓለም መወድስ የሆነ። የአፍሪካዊነት ልዩ ዝማሬ፤ የዓለም የነፃነት ታሪክ ሥልጡነ -ቀንዲል፤ የአርነት ሰንደቅ፤ ትናንት የነበረ፤ ዛሬም የሚኖር ነገን የቀደመ ህላዊ የድርጊት አባት፤ የመሆን መቻል አንባሳደር ነው ኢትዮጵያዊነት። ጌጥ!
ጉልላት! የታሪክ ቅድመ አያት። የመኖር አንባ። የሰው ልጆች መነሻ። የሥልጣኔ እንብርት፤ የአዶሊስ ዓውራ፤ የተግባር ልምድ አቮል ተቋም፤ የፓን አፊሪካኒዝም ጫጉላ፤ የጥቋቁር ፈርጦች እልፍኝ፤ ለጠላቱ የመያበገር፤ ለወዳጁ የአለኝታ ዋስትና ሳያወላውል የሚሰጥ ጸዓዳ – መቅደስ ነው ኢትዮጵያዊነት። አብነት!
መዝሙር! የመንፈስ ሐሤት መቋሚያ፤ የረቂቅነት ቅኔ ዘጉባኤ፤ መንፈስን የሚጋራ ድጓ፤ የሚያድን ድርሳን፤ የሚፈውስ ጸበል። የሚመርቅ አባወራ፤ የሚያጸድቅ ግብር ሰናይ፤ የሚዳኝ ባለ ሃቅ ሚዛን፤ የሚችል የትእግስት ማዕድ፤ የሚመከት የጥንካሬ አበው፤ አርቆ የሚያስብ የቅዱስ ወንጌል – የቁራን እልፍኝ ቅዱስ መንፈስ ነው ኢትዮጵያዊነት። ዬልብ!
ጤና አዳም! ጠረነ መልካም፤ ከሩቅ ወዙ የሚያሳሳ፤ መቃረቢያ ትንፋሹ ያመረ የሰመረ፤ የጥርስ መፋቂያ ዘመናዊ ኮልጌት ወይንም ጦር ማስቲካ የአፍ ማሟሻ የማያስፈልገው፤ ታጥቦ የፈጠረው ደንበር አልባ የስኬት ቁልፍ ነው ኢትዮጵያዊነት። ኢትዮጵያዊነት ሲሰላ ወይንም ሲታሰብ ውቅያኖስ የሆነው ተፈጥሮው ያፋጣል። ስለምን? ሁሉንም ልዘርዝር ቢባል የማይቻል በመሆኑ። ሁሉን የሚችል አምላክ አዶናይ ኢትዮጵያዊነትን መርቆ፣ አንጽቶ ስለፈጠረልን፣ የእኛም ስለአደረገው ጭምር እናመስግነው። ፈጣሪያችን ከእሱ ሳይለዬን ከአብረንታት ጋር ያኑረን። አሜን በሉ!
እኔ የአንተ – አንተም የእኔ
የፍቅር ጠመኔ
የናፍቆት ጠኔ
የሽውታ ህመሜ
አንተ የእኔ
እኮ! … ለምኔ?
…. ለመንፈሴ
ለሩሄ ፈውሴ።
ሥሜ
አነተዬ ደማሜ
ላወሳሳህ ደጋጋግሜ፤
ባገግም – ከቁስለቴ
በስደት ስለት ከተሰነጠረው መንፈሴ፤ ከከሰለው ቀለበቴ
አንተ የእኔ ንጹህ ስስቴ
የአድርሽኝ – መስታውቴ
እኮ አንተ አፈሬ የእኔ!
የውስጤ እውኔ~! ~~~!
ና! ወደ እኔ
ኑርልኝ – በእኔ
ሰብስቤ እኔን – በእኔ።
መፍታታት። ትንሽ … ይባልለት። ዋናው፤ አደኑ፣ ትግሉ፣ የእግር ጉዞው፤ ጉጉሱ፤ ፈረስ ግልቢያው፤ ሻምላዊ ትዕይንቱ፣ የገና – የገበጣ – ጨዋታው መሰረቱ ከፍጥረተ – ምንጩ ከኢትዮጵያዊነት ነው። ዛሬ ዓለምን እዬገዙ ያሉ የስፖርት እቅስቃሴዎች አብዛኞቹ ከእኛነት የተቀሰሙ ናቸው። በሌላ በኩል ዜግነት በመስጠት በኢንተግሬሽን በኩልም ፋና ነው ኢትዮጵያዊነት። የአጥቢያ ኮከብ! ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ትርጉምን መስጠሮ ለቀጣዩ ትውልድ ነገ ሰፊ የምርምር የሥራ መስክ ከፍቶ ይጠብቀዋል አንቱ ለማደረግ። ዓይነታ ማህተም!
ዝና … ዘና ያደርጋል … ገናው፣ እንቢልታው፣ ክራሩ፣ ከበሮው፣ ጽናጽሉ፣ ዋሽንቱ፣ ነጋሪቱ፣ የዝማሬ ያያሬድ ኖቶች ውዝዋዜውው፤ ሽብሽባው ምቱ – ስልቱ – ቅኔ ዘረፋው፣ ቅላጼው የ80 ብሄረሰቦች እሰቡት … ዲካ የለሽ።
ክውና!
ኢትዮጵያዊነት ጣዝማ ነውና ፍወሰቱን፤ ድህነቱን፤ ነገን ሳይሰጋ እንደ አማረበት ለመቀበል ዝግጁነቱና እርግጠኝነቱ በሙላት ነው። ኢትዮጵያዊነት ልብም ልካችንም ነው። አክብሮ – ያሰከበረን፤ ተወዶ – ያስወደደን፤ ነፃነት ቀልቦ በራስ የመተማማን ብቁ የመንፈስ ልዩ ዝናር የሸለመን ዘለዓለማዊ ማንነት ነው። ታውቆ ዕውቅናን ያለበሰን ጥንግ ድርባችን ነው ኢትዮጵያዊነት።
ሥጦታ! ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያን (አቶ ኦባንግ ሜቶን) አሰብኩት። ውስጡን ያደነ። ውስጡን ያሸነፈ፤ ለውስጡ ፈቅዶ ከጎሳ ቅኝነት እራሱን ነፃ ያወጣ፤ ሚስጢር የተገለጠለት ለዘመናችን ጥሩ ምልክት ነው። ስለሆነም የመንፈሴን ጭማቂ ለአዲስ የነጮች ዓመት ደስ ብሎኝ ሸለምኩት፤
ክብረቶቼ! አብረን ቆየን በውስጥነት። መልካም የነጮች አዲስ ዓመት። ደህና ሰንብቱልኝ – የኔዎቹ!
ማሳሰቢያ ሀ. የግጥም አፃፃፍ ፍሰቴ ከውስጤ ፈንገጥ ብሎ የተፈጠረ ስለሆነ እርእሶች በጉልህ የተፃፉት የተሰመረባቸው ናቸው። ቅርፃቸውም በመንፈሴ የተሳሉ በንድፍ የተቡ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች
ለ. ወርቀ ዘወንጌል አክሱምና ጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴ ብቻ ነው የሚገኙት።
ሐ. አቶ ኦባንግ ሜቶን እኔው ነኝ ወደ አምስት አመት ሆነኝ ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ የምለው። „አንተ“ ማለቴ ደግሞ እሱ የፈጠረልኝ ያሰናዳልኝ ቅን አያያዝ ነው – ነፃነት።
ሁሉን የረታ፤ ቅንነቱ – ጸድቆ – አሽቶ – አፍርቶ – አስብሎ ያኖረዋል – ኢትዮጵያዊነትን!
ኢትዮጵያ አምላክ አላት፤ ፈተናዋን ሁሉ የዶግ አመድ የሚያደርግ። ተመስገን!
መፍቻ ጫን። ጫን ማለት አስር ማድጋ ማለት ነው። አንድ ማድጋ ማለት ደግሞ 25 ኪሎ ማለት ነው። ሁለት ጫን ሃያ ማድጋ 500 ኪሎ ማለት ነው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
የማለዳ ወግ …አዲሱ 2014 አመት በዱባይ ፣ በባህሬንና በሳውዲ … ! (ነቢዩ ሲራክ)
ነቢዩ ሲራክ
* ዱባይ በአስደናቂ 400 ሽህ ርችቶች አለምን አስደመመች!
* እፁብ ድንቅ ርችቶች የአለምን ሪኮርድ ሰብረዋልም ተብሏል
* ሳውዲና ባህሬንን በሚያገናኘው ድልድይ ተጨናንቋል
* እኛም እያዘንን ለመደሰት በመሞከር ላይ ነን
ከአመታት በፊት 828 ሜትር እርዝመት ያለው የቡርጅ ከሊፋን ሰማይ ጠቀስ ህንጻ በመገንባት የአለምን ሪኮርድ የሰበሩት ኢምሬቶች ዛሬ በጀመርነው አዲሱ አመት 400 ሽህ እፁብ ድንቅ በህብረ ቀለማት ያሸበረቁ ርችቶች ወደ ሰማይ በማጎን በኮዌት ተይዞ የነበረው 77,282 የአለም ሪኮርድ በመስበር በአዲሱ 2014 አመት አዲስ ሪኮርድ ተቀዳጅታለች። በኢምሬት አንብርት በዱባይ ሚሊዮኖች ያየነው የሰማዩን ውብና ድንቅ ርችት ብቻ አልነበረም ። በመላ ከተማዋ በሚገኙት ሰማይ ጠቀስ ፎቆቿና መዝናኛ ቦታወች እየተነሱ በምድር ለምድር በመምዘግዘግ በሰው ሰራሽ ሃይቆችና በሚያምሩት ህንጻዎች ተስፈንጥረው የሚወጡት ዘመነኛ የሌዘር ህብረ ቀለማትን የተላበሱ ርችቶች እና መብራቶች በእርግጥም አረቧ ሃገር ኢምሬት የደረሰችበትን የእድገት ደረጃ በገሃድ የሚያሳይ ነበር ማለት ይቻላል። በዘንባባ ቅርጽ በተገነባውና የአለማችን ታዋቂ ሰዎች በከተሙበት የጀማርያህ የባህር ዳርቻዎችና በደሴቶች ፣ ብረት ቀልጦ እንደ ልብስ ጥበብ በአስደናቂ ስነ ህንጻ ጥበብ የሚታይባቸው ሰማይ ጠቀሱ ቡርጅ ከሊፋ እና የቡርጅ አል አረብ ህንጻዎችም ዛሬ የአለምን አይን አማልለው ማምሸታቸው እውነት ነው። በከተማዋ ዙሪያ ገብ በተሰሩት ህንጻና ሰው ሰራሽ ባህሮች እየተስፈነጠሩ ወደ ሰማይ የሚወረወሩት ፣ ወደ ጎን ፣ወደ ላይ ወደ ታች የሚተጣጠፉት መብራቶች ብቻ አልበሩም ። ውሃው በድቅድቁ ጨለማ ከመብራት ተዋህዶ አይንን ሲያማልል ሲፈስ ፣ ሲለው ዝም ጭጭ ሲል በአረብቸኛ ባህላዊ የካልጅ ዝማሬ ቅላጼ ታጅቦ መሆኑ የሰው ልጅን መዘመን ምጥቀቱን ሲያሳብቅ ውሃና ሌዘር ተወንጫፊ መብራቶች እጥፍ ዘርጋ ሲል ጉድ በዱባይ ያየነው በአዲሱ አመት ዛሬ ነበር ። ግዑዙ ፈሳሽ ውሃ በቧንቧ እየተፈናጠረ ከመብራት ጋር ተዋህዲ እንደ ግብጽ “ረጋሳዎች “ዳንሰኞች ሲያረገርግ መመልከት በእርግጥም “ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ ” አለ ያስብላል!
ከእኔ ቢጤው ደካማ ገቢ ካለው እስከ ናጠጠው ሃብታም አረቦች አዲሱን አመት ለመቀበል የኢምሬቷን እንብርት ዱባይን ከአፍ እስከ ደገፏ ጢቅ አድርገው ሞልተዋታል። ዱባይ የፈረንጆችን የዘመን መለወጫ ቀምታ ለራሷ አድርጋው ዛሬ አይተናል። እንዲህ አድርገው እንዲህ ሆነው አጅብ ተያሰኙን የዱባይ ስልጡን አረቦች ሰማይ ምድር ባህሯን በህብረ ቀለማት ርችቶች አድምቃ እና በባህላዊ የከልጅ ጣህመ ዜማ አዲስ ታሪክ ሲያስመዘግቡ የፈረንጆቹን ቴክኖሎጅን በገንዘባቸው ገዝተው ቢሆንም ዛሬ ከሸጡላት ስልጡን ሃገራት ደምቀው ፣ ተውበው ተአምርን ለአለም በማስመስከር “የአረቦች ኒዮርክ !” ተብላ በአረቦች የምትንቆለጳጰሰው ዱባይ አዲሱን አመት እንዲህ ጀመራዋለች !
በሳውዲየከተሙ ፣ ዱባይ መሄዱ ያልቀናቸው ወደ ጎረቤት ባህሬን እየጎረፉ ሲሆን ቀይ ባህርን ሰንጥቆ ሳውዲና ባህሬንን በሚያገናኘው በደማም በኩል የተዘረጋውን ድልድይ አጨናንቀውት ማምሸታቸውን የሳውዲ መገናኛ ብዙሃን ዘግበውታል ። ምክንያቱ ባህሬን ከሳውዲ በውበት ደምቃ አይደለም ! ብዙዎች ሳውዲ የሚከለከሉትን ዳንኪራ ቤትና ፈሳሿን ” ቅብአ ቅዱሷን!” እዚያ በነጻነት እየተጎነጩ ነፍሳቸውን የሚያስደስቱባት ባህሬን ብቸኛ አንጻራዊ ነጻነት የምታስተናግድ የቅርብ ጎረቤት ናትና ነው ብለን እንገምት:)
ብዙሃኑ ሃበሻም ባይሆን እኔ እና መሰሎቸ በየአቅጣጫው የወገንን ጭንቅ ፣ ስጋት ሮሮ እየሰማን ፣ ግማሽ ጎናችን ታሞ ግማሹን በአዲስ አመት ትፍስህት በተስፋ ለመቀበል እያዘንን ለመሳቅ በመሞከር ደመቅመቅ ብለን አዲሱን አመት ” እንኳን ደህና መጣህ !” ብለነዋን ! …ህይዎት እንዲህ ናት !
መልካም አዲስ አመት !
እ.ኤ.አ የ2013 ዓመት የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) መነሳሳት ሲገመገም፣
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 2013 “እ.ኤ.አ 2013 የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ ዓመት ይሆናል“ በማለት ትንበያ ሰጥቸ ነበር፡፡ እንዲህ ስልም ቃል ገብቸ ነበር፣ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ለፍትህና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚያደርጉትን ትግል ለመደገፍ እና ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ እንዲል የእራሴን ሙሉ አስተዋጽኦ እንደማደርግ እንዲሁም ትግሉ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር ወጣቱ ትውልድ እንዲነሳሳ ሳደፋፍር ነበር፡፡” በዚህም መሰረት ጀግኖቹ ወጣቶች ትግላቸውን ቀጥለው ከፍ ወዳለ ደረጃ ላይ አድርሰውታል፡፡ ለወጣቶቹ እንዲህ በማለትም ተማጽኘ ነበር፣ “ብዙዎቹን ወጣቶች፣ ለመድረስ፣ ለማስተማር እና የበለጠ ግንዛቤ እንዲያገኙ ጥረት አድርጉ፡፡” ከዚህ አንጻር ቃሌን ሙሉ በሙሉ በማክበር ስኬታማ ስራ በመሰራቱ የተሰማኝን ኩራት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ዴሴምበር 2013 በአሜሪካ በአርሊንግተን ከተማ ከሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከይልቃል ጌትነት ጋር በመገናኘቴ ታላቅ ደስታ እና ክብር የተሰማኝ ሲሆን ለወደፊትም ከኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) ጋር ያለኝን የትግል አጋርነት በጽናት እንደምቀጥል ቃል ገብቻለሁ፡፡
እ.ኤ.አ በዴሴምበር 2013 የአቦ-ጉማሬው (የወጣቱ እና የቀድሞው ትውልድ) ትውልድ በሰላማዊ ትግሉ ሂደት በንቃት ከሚሳተፈው ከኢትዮጵያ አቦሸማኔ ትውልድ ጋር ያለውን የትግል አጋርነት ይፋ አድርጓል፡፡ እንዲህ ብዬ ተናግሬም ነበር፣ “የአቦ-ጉማሬው ትውልድ አባል መሆኔ በኩራት እንድሞላ አድርጎኛል፡፡” በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬ ትውልድን “የመፍጠር” አስፈላጊነት ከምንም በላይ ተቀዳሚ ተግባር ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ በአፈጣጠሩ የጉማሬው (የቀድሞው ትውልድ) አባል ሲሆን በተግባራዊ ድርጊቱ ግን እንደ አቦሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) የሚያስብ፣ አቦሸማኔውን የሚመስል እና እንደ አቦሸማኔው ሁሉ የክንውን ድርጊቶችን የሚፈጽም የማህበረሰብ ክፍል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ የጉማሬውን (የቀድሞውን ትውልድ) ድክመቶች በሚገባ የተረዳ እና እነዚህን ግድፈቶች በማስወገድ የወጣቱን ትግል ወደ ላቀ የእድገት ምዕራፍ ለማሸጋገር በአንድ ዓላማ ለአንድ ዓላማ የሚሰራ የህብረተሰብ አካል ነው፡፡
የአቦ-ጉማሬው ትውልዶች ድልድይ ገንቢዎች ናቸው፡፡ ወጣቱን ከቀዳሚው ትውልድ የሚያገናኙ ጠንካራ የትውልድ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸውና፡፡ ህዝቦችን በዴሞክራሲ፣ በነጻነት እና በሰብአዊ መብት ጥበቃ የሚያስተሳስሩ ድልድዮችን ይገነባሉና፡፡ በትውልድ ቦታቸው እና አካባቢያቸው ተጠርንፈው የተያዙ ህዝቦችን የሚያገናኙ እና ጥልቅ የጎሳ ሸለቆዎችን ሰንጥቀው የሚያቋርጡ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸውና፡፡ በቋንቋ፣ በኃይማኖት እና በክልል ተነጣጥለው የተቀመጡ ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን ይገነባሉና፡፡ ደኃውን ከሀብታም የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸውና፡፡ ብሄራዊ ዕርቅ ለማውረድ እና የብሄራዊ አንድነትን ለማምጣት ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸውና፡፡ በአገር ቤት ውስጥ ያሉትን ወጣቶች በውጭ አገር ከሚኖሩት የዲያስፖራ ወጣቶች ጋር የሚያገናኙ ድልድዮችን ይገነባሉና፡፡
በእ.ኤ.አ 2013፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች የእራሳቸውን የኃይማኖት ጉዳይ እራሳቸው በሚፈልጉበት መልክ ማስተዳደር እንዲችሉ እና በእምነታቸው ላይ የሚካሄደውን የመንግስት ጣልቃገብነት በመቃወም በሰላማዊ ሰልፍ ብሶታቸውን በመግለጻቸው ብቻ በገዥው አካል ብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች ረበየለሽ እና ግዙፍ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ተካሂዶባቸዋል፣ በታጠቁ ኃይሎች በዘፈቀደ ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርገዋል፣ በየማጎሪያ እስር ቤቶችም እንዲጋዙ ተደርገዋል፡፡ ሀገር በቀል የእስልምና አክራሪዎች እና አሸባሪዎች “የኃይማኖት ጦርነት” በማወጅ በኢትዮጵያ ውስጥ የእስላም መንግስት ማቋቋም ይፈልጋሉ በሚል ሰበብ በህዝብ ዘንድ ለማጋለጥ በማሰብ ገዥው አካል “ጅሃዳዊ ሃራካት” (“የኃይማኖት ጦርነት እንቅስቃሴ“ የሚል ርዕስ በመስጠት ለአንድ ሰዓት የዘለቀ “ዘገባዊ ፊልም” አዘጋጅቶ በአየር ላይ አውሏል፡፡ ያ የሞራል ዝቅጠት የተንጸባረቀበት፣ ሆን ተብሎ ዜጎችን ለማጥቃት በማለም እና ለምንም የማይጠቅም እርባናየለሽ ዘገባዊ ፊልም ለህዝብ በማሳየት የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች በናይጀሪያ በመንቀሳቀስ በህዝብ ላይ ጅምላ ፍጅት በማድረስ ላይ የሚገኘው ቦኮ ሃራም የተባለው ጽንፈኛ እስላማዊ አክራሪ ድርጅት ተከታዮች እና የአልቃይዳ ታዛዦች እና አሸባሪዎች ናቸው በማለት ወጣቶቹን ከህዝብ ነጥሎ ለማሳየት የታለመ ነበር፡፡ ያንን አስቀያሚ እና መቅንየለሽ ዘገባዊ ፊልም በጣም አድርጌ እኮንነዋለሁ፡፡ ምክንያቱም “ውሸቶች ታጭቀውበታል፣ ዓይን ያወጡ ደረቅ ውሸቶች፣ የተወገዙ ውሸቶች እና ሞራለቢስ ቅጥፈቶች፡፡ ‘ጅሃዳዊ ሃራካት’ የእነዚህ የአራት ቀጥፈቶች ጥቅል አንድ መጠሪያ ስም ነው::”
በእ.ኤ.አ የ2013 የእኔን ልዩ ጀግኖች አክብሪያለሁ፡፡ ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ለጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ልዩ ክብር እሰጣለሁ፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሁለቱ ጋዜጠኞች በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ኢትዮጵያ በአምባገነኑ ገዥ አካል እየታሰሩ፣ እየተሰቃዩ፣ ከህግ አግባብ ውጭ ብይን እየተሰጠባቸው፣ እና የማስፈራሪያ ውርጅብኝ እየተፈጸመባቸው ለሚገኙት ወጣት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ቋሚ ተምሳሌት በመሆናቸው ነው፡፡ እነዚህ ጋዜጠኞች ለእኔ ልዩ ናቸው፣ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ በአሁኑ ጊዜ ከአምባገነኖች ጋር እተካሄደ ያለውን ትግል እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ለነጻነት የሚያደርጉትን ተጋድሎ የሚወክሉ የወጣቱ ቀንዲል በመሆናቸው ነው፡፡ እውነትን እና ትክክለኛውን መርህ ከመያዝ በስተቀር ሌላ ምንም ዓይነት የሚዋጉበት ነገር የላቸውም፡፡ ቅጥፈትን እና ውሸትን በእውነት ጎራዴ ድል ያደርጋሉ፡፡ ብዕርን ብቻ በመታጠቅ ተስፋ ማጣትን በተስፋ፣ ፍርሀትን በድፍረት፣ ቁጣን በምክንያታዊነት፣ እብሪትን በክብር፣ ድንቁርናን በዕውቀት፣ ታጋሽየለሽነትን በትዕግስት፣ ጭቆናን በትግል፣ ጥርጣሬን በመተማመን፣ እና ጭካኔን በሩህሩህነት ይዋጋሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ እነዚህ ጋዜጠኞች በስልጣን ላይ ላሉት እና ስልጣናቸውን ለታዕይታ ለሚያወሉ፣ ስልጣንን አላግባብ ለሚጠቀሙ፣ ስልጣናቸውን ከተሰጣቸው ስልጣን በላይ ለሚያውሉ እና ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በሙስና ለሚዘፈቁ ባለስልጣናት ትኩረት በመስጠት ፊት ለፊት በመግጠም እውነት እውነቱን እስከ አፍንጫቸው ድረስ ይነግሯቸዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ2013 በኢትዮጵያ ጥልቀት እና ስፋትን በመያዝ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን አስደንጋጩን ሙስና ዓለም ተመልክቷል፡፡ ሙስናው በየትኛውም ኢከኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዘርፍ ላይ ተንሰራፍቶ ይገኛል- በኮንስትራክሽን፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በመሬት፣ በጤና፣ በፍትህ፣ እና በትምህርት፡፡ በትምህርት ላይ የሚፈጸም ሙስና ምናልባትም በጣም የአውዳሚነት ባህሪ ይኖረዋል፣ ምክንያቱም በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ጠንከር ያለ አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚያስከትል ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ትምህርትን አስመልክቶ እንዲህ ብለዋል፣ “ትምህርት ዓለምን ለመለወጥ የምትጠቀምበት ጠንካራ መሳሪያ ነው፡፡“ በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል ግን ድንቁርና ለውጥን ለመከላከል እና በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጦ ለመኖር የሚያገለግል ጠንካራ መሳሪያ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ገዥው አካል የተሳሳተ መረጃ በመስጠት፣ የውሸት መረጃ በመጋት፣ የማሳሳቻ ለውጥ በማቅረብ፣ አቅጣጫቸውን የሳቱ ሀሳቦችን በማሰራጨት፣ ጊዜ ያለፈባቸውን መፈክሮች እና ካለፉት ዘመናት የመከኑ ቀኖናዎችን በመምዘዝ እና ለወጣቱ በማቅረብ የሀሰት የፕፓጋንዳ ዳቦ በማስገመጥ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያን ደንቆሮ ንጉሶች፣ ንግስቶች፣ ልዑላን እና ልዕልቶች የነገሱባት “የደንቆሮዎች ግዛት” እንድትሆን አድርገዋታል፡፡ የትምህርት ሙስና የወደፊቱን ወጣት ትውልድ እድል ይሰርቃል፡፡ እውቀትን ለማግኘት፣ ህይወታቸውን ለመለወጥ፣እና የአገራቸውን ዕጣፈንታ ለመወሰን የሚያገለግሏቸውን ዕድሎች በመዝጋት ለዘላለም የዕውቀት እና የምሁርነት ሽባ አድርጓቸው ይቀራል፡፡ ማልኮም ኤክስ በውል እንዳጤኑት፣ “ያለ ትምህርት በዚህች ዓለም ላይ የትም መሄድ አይቻልም” ብለዋል፡፡ በዚህ በወጥመድ በተያዘ እና ቁጥጥር ባለበት ዓለም እና ሙስና በተንሰራፋበት የትምህርት ስርዓት የኢትዮጵያ ወጣቶች የትም መሄድ ይችላሉን?
እ.ኤ.አ በዴሴምበር 2013 አጋማሽ የኢትዮጵያ ወጣቶች ቃልኪዳናቸውን አድሰዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ የኃይማኖት ነጻነት እንዲከበር፣ ሰብአዊ መብቶች እንዲጠበቁ እና የህገ መንግስት እና ህዝባዊ ተጠያቂነት መኖርን በመጠየቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በአገሪቱ ማዕከል በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡ በወጣቱ ስራ አጥነት፣ በዋጋ ግሽበት እና በተንሰራፋው ሙስና ላይ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ገዥውን አካል ጠይቋል፡፡ እኔ በዚህ ሁኔታ በጣም ተመስጫለሁ፡፡ “በኢትዮጵያ ወጣቶች ረዥሙ የነጻነት እና የክብር ጉዞ ተጀምሯል፡፡ በጣም ቆንጆ ነገር ነው፡፡ በጣም ቆንጆ ነገር ነው፣ ምክንያቱም ሰላማዊ ነው፡፡ በጣም ቆንጆ ነገር ነው፣ ምክንያቱም የአንዲት አገር ኢትዮጵያ ውድ ልጆች እርስ በእርሳቸው በመዋደድ እና በአገር ፍቅር ስሜት ሆ ብለው በአንድነት ሆነው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲህ እያሉ ሲጮሁ ነበር፣ “ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት ትዕግስት የለንም! ለውጥ እንፈልጋለን!”
በሰማያዊ የአቦሸማኔ (ወጣቱ ትውልድ) መነሳሳት ጊዜ የኢትዮጵያ ወጣት የህብረተሰብ ክፍል የለማ ምናባዊ አስተሳሰቡን በመጠቀም አዲስ ልዩ የሆነ ለውጥ በኢትዮጵያ ሀገሩ ለማምጣት እየተነሳ ነው በማለት የክርክር ጭብጤን ሳቀርብ ነበር፡፡ ወጣቶቹ አዲሲቷን የጀግኖች ሀገር የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ያልማሉ፡፡ በዘር ክፍፍል ላይ የተመሰረተችውን፣ በጎሳ አፍቅሮ የተዋቀረችውን፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነት እና አፍቅሮ ዘረኝነትን አካታ የተመሰረተችውን አሮጊቷን ኢትዮጵያ አይፈልጉም፡፡ የጾታ እኩልነት እንዲሰፍን ይፈልጋሉ፡፡ በድፍረትም እንዲህ በማለት እጠይቃለሁ፣ “ወጣቶቹ የራሳቸው የሆነች ኢትዮጵያ ለምን አትኖራቸውም? የእኛ የእራሳችን የሆነች ኢትዮጵያ አለችን፣ ወጣቶቹ የራሳቸው ኢትዮጵያ እንድትኖራቸው ጊዜው አሁን አይደለምን?”
እ.ኤ.አ በሳመር 2013 ፕሬዚዳንት ኦባማ አፍሪካን በጎበኙበት ጊዜ የኢትዮጵያን ወጣት የህብረተሰብ ክፍል በስፋት ለመድረስ ስል በማዘጋጃቸው ትችቶቼ ላይ ተጨማሪ ፈጠራ ለመጨመር በማሰብ ሁለት “ፍላሽ ድራማ” (ትያተር) ጭውውቶችን አካትቼ ነበር፡፡ በዚያ ጽሁፌ ላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ተዋሃኒዎች ኦባማ ለምን “ወደ አፍሪካ እንደመጡ” በእርግጠኝነት የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ የንግግራቸው ዳህራ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
…
ዱማ፡ አሃ! ኦባማ ወደ ትውልድ አሁጉሩ ወደ አፍሪካ ተመልሶ መጣ፣ ጥሩ ነው ሹዲ
ሹዲ፡ የለም፣ ከአፍሪካውያን ጋር ለመነጋገር ነው የመጣው
ዱማ፡ ለመነጋገር? ጣፋጭ ንግግር? ጠንካራ ንግግር? ትንሽ ንግግር? የሰላም ንግግር?
የጦርነት ንግግር? የሚተገበር ንግግር? ንግግር ብቻ? የስሜት ንግግር? ትርጉመቢስ ንግግር?
ርካሽ ንግግር? ገንዘብ ይናገራል… ንግግር፣ ንግግር፣ ንግግር…?
…
ከኦባማ የአፍሪካ ጉብኝት በኋላ ሁለቱ ወጣት ተዋሃኒዎች የእራሳቸውን ዳኝነት ሰጡ፣
…
ሹዲ፡ ኦባማ መጡ እና ሄዱ…
ዱማ፡ ኦባማ መጡ እና አዩ፣ ግን ምን አሸነፉ? አገኙ?
ሹዲ፡ ኦባማ መጡ፡፡ አዩ፡፡ ተመልሰው ሄዱ፡፡
በእ.ኤ.አ 2013 ፕሬዚዳንት ኦባማ “አፍሪካን ማጠናከር” በሚል ለጀመሩት ተነሳሽነት የአፍሪካን ወጣቶች ለማጠናከር የእራሴን ጠቃሚ ምክሮች ልለግሳቸው ሞክሬ ነበር፡፡ “አፍሪካን ከማጠናከራቸው” በፊት ወጣቱን እንዲያጠናክሩት፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ አፍሪካ የኃይል (ኤሌትርክ) ችግር እንዳለባት እንደሚያውቁ እና ለዚህ ችግር መወገድም አጋር እንደሚሆኑ የተናገሩትን ንግግር እኔም እስማማለሁ፡፡ አፍሪካ በኃይል ስልጣን ከሚባልጉ፣ በኃይል ስልጣናቸውን አላግባብ ከሚጠቀሙ፣ በኃይል ስልጣናቸውን እና ኃላፊነታቸውን ከሚያደበላልቁ እና በኃይል ስልጣናቸውን ትክክል በማስመሰል አላግባብ ከሚጠቀሙ ሌባ መሪዎች ፕሬዚዳንት ኦባማ በእርግጥም አፍሪካን ባለ ኃይሎች እያጠናከሩ ነው፡፡ ጥያቄው አፍሪካን ከማጠናከሩ ላይ አይደለም፣ ነገር ግን አሜሪካ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በእየዓመቱ በእርዳታ፣ በብድር እና በቴክኒክ እገዛ ሰበብ ኃያላን አምባገነን አፍሪካውያን ገዥዎች ኪስ እያጨቀች ኃይል የሌላቸውን የአፍረካ ህዝቦች እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል ከማወቁ ላይ ነው፡፡ ኦባማ አፍሪካውያንን ማጠናከር ከፈለጉ ተራ አፍሪካውያን ህዝቦችን ስልጣናቸውን አላግባብ ከሚጠቀሙ እና በስልጣን ከሚባልጉ አምባገነን ገዥዎች መዳፍ በመጠበቅ የማጠናከር ስራውን መጀመር ይችላሉ፡፡ የፖለቲካ ስልጣኑን ይዘው የወጣቱ እምቅ ኃይል ጎልቶ እንዳይወጣ እንቅፋት የሚሆኑበትን እንዲሁም ብዝበዛ እና ስልጣንን አላግባብ መጠቀምን በማስቆም የወጣቱን ኃይል ማጠናከር አለባቸው፡፡ በየዓመቱ የሚለገሰውን በቢሊዮን የሚቆጠር የዶላር ዕርዳታ የአፍሪካ የሌባአምባገነኖችን ኃይል በመቀነስ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠረውን የአፍሪካ ወጣቶችን ኃይል ማጠናከር ይኖርባቸዋል፡፡
አ.ኤ.አ በማርች 1963 የተካሄደውን የአሜሪካ የሲቪል መብቶች እንቅስቃሴን የመሩትን ወጣቶች 50ኛ ዓመት በዓል በዋሽንግተን ዲሲ አክብሪያለሁ፡፡ በ26 ዓመታቸው የአሜሪካንን የሲቪል መብቶች እንቅስቃሴ የጀመሩትን እና ፍቅር የነገሰበት ማህበረሰብን ለመመስረት ማርቲን ሉተር ኪንግ “በህብረተሰቡ ህይወት የይዘት ለውጥ እንዲሁም በኑሮው የመጠን ለውጥ“ በሚያመጡት ነገሮች ልዩ ትኩረት ሰጥተው ሲታገሉ ነበር፡፡ የማርቲን ሉተር “ፍቅር የነገሰበት ማህበረሰብ” ከዘረኝነት፣ ከድህነት እና ከጦረኝነት ነጻ የሆነ ማህበረሰብ ነው፡፡ ፍቅር እና ፍትህ የነገሰበት ማህበረሰብ በእትማማቾች እና በወንድማማቾች ፍቅር እና መተሳሰብ መርሆዎች ላይ በመመስረት ለህይወት ትርጉም የሚሰጥ ነው፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ ብለዋል፣ “የዘመናችን ዋና የፖለቲካ እና የሞራል ጥያቄዎች መልስ ሰላማዊ ትግል ነው፡ ጭቆናን እና ኃይልን በሰላማዊ መንገድ ለማስወገድ ጭቆንና እና ኃይልን አለመጠቀም የሰው ልጅ ፍላጎት መሆን አለበት፡፡ የሰው ልጅ በቀልን፣ ኃይልን እና አሉታዊ የአጻፋ ምላሽ የመስጠት መንገዶችን በማስወገድ በሰዎች መካከል ያሉትን ግጭቶች በሰላም መፍታት አለበት፡፡ እንግዲህ የዚህ ሁሉ መሰረቱ ፍቅር ነው፡፡” ሲሉ ማርቲን ሉተር ኪንግ ተናግረዋል::
እ.ኤ.አ በ2013 “የኢትዮጵያ ወጣቶች ህዳሴ” እውን እንዲሆን ጥሪ አቅርቢያለሁ፡፡ እንዲህ በማለት የክርክር ጭብጤን አቀርባለሁ፡፡ በኢትዮጵያ እውነተኛ “ተሀድሶ”, “እንደገና የመወለድ” ወይም “እንደገና የመፈጠር” ዓይነት ዕድል እንዲመጣ ከተፈለገ ሊመጣ የሚችለው በወጣቱ ደም፣ ላብ እና እንባ ብቻ እንጅ በአምባገነኖች ወይም በእነርሱ አፈቀላጤዎች ከሚፈበረክ የውሸት ፕሮፓጋንዳ አይደለም፡፡ ሀገሪቱን ወደ ኢኮኖሚ ተሀድሶ ለመምራት የጦሩ ጫፍ ኢትዮጵያውያን/ት ወጣቶች ናቸው:: ኢኮኖሚዉን የሚንቀሳቀሱት ኢትዮጵያውያን/ት ወጣት ኢንተርፕሪነሮች መሆን እንዳለባቸው፡፡ ወጣት ኢትዮጵያውያን/ት ምሁራን የዕውቀት ኃይል ሽግግርን በግንባርቀደምትነት መምራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ወጣት የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶች እና ኢንጅነሮች አገሪቱ እራሷን እንድትችል እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነቷም እንዲጎለብት ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ወጣት የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ወጣቶች የፍትህን ጎራዴ መታጠቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ወጣት የኢትዮጵያ መሪዎች ጠንካራ የማህበራዊ እና የፖለቲካ ለውጥ አራማጆች በመሆን የ21ኛው ክፍለ ዘመን የተከበረች እና ኩሩ ኢትየጵያን መመስረት አለባቸው፡፡
እ.ኤ.አ በ2013 በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወጣት ስደተኛ ሰራተኞች ለአስደንጋጭ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተዳርገዋል፡፡ የሳውዲ ፖሊሶች፣ የደህንነት ሰራተኞች እና ዘራፊዎች ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን በመንገድ ላይ በማደን የመደብደብ፣ የማሰቃየት እና አንዳንድ ጊዜም የመግደል ወንጀሎችን ፈጽመውባቸዋል፡፡ የሳውዲ ፖሊሶች ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ሲያሰቃዩ የሚያሳዬውን የቪዲዮ ክሊፕ መመልከት ለህሊና የሚሰቀጥጥ ነገር ነው፡፡ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች እና የደህንነት ኃይሎች ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን በየመንገዶች ላይ ሲያሳድዱ፣ ሲያጠቁ እና ሲገድሉ የሚያሳየው የቪዲዮ ክሊፕ ትርምስ በሰው ልጆች ዘር ላይ የተፈጸመ የሰብአዊ መብት ወንጀል ዋና ማረጋገጫ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል “የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር” “የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣኖች በህገወጥ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ ያሳለፉትን ውሳኔ እና ህገወጥ ኢትዮጵያውያንን/ትን ወደ ሀገራቸው በመመለሱ ፖሊሲ ላይ ኢትዮጵያ ያላትን አክብሮት ትገልጻለች፡፡” በማለት በሳውዲ አረቢያ ያለው ገዥ አካል በስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ለፈጸመው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንዲህ ሲሉም አክለዋል፣ “አገሮች በጦርነት ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ህገወጥ ናቸው የሚሏቸውን ዜጎች እንደዚህ ያለ ወደ አገራቸው የመመለስ ፈጣን እርምጃ ቢወስዱ ህዝብም ሊቀበለው እና ሊረዳው ይችላል፣ ሆኖም ግን በሰላማዊ ጊዜ እንደዚህ አይደረግም” በማለት የሳውዲ አረቢ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ የፈጸመውን ሁኔታ ገልጸዋል፡፡ በሌላ አገላለጽ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ሰራተኞች ለተፈጸሙባቸው የመብት እረገጣዎች እራሳቸውን ተጠያቂ ማድረግ አለባቸው ማለት ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለጥንቱን አባባል “የሚያጎርስህን እጅ በፍጹም አትንከስ” አዲስ ትርጉም ሰጥተውታል፡፡
የእኔን አፍሪካዊ ጀግና ታላቁን ኔልሰን ማንዴላን ደህና ይሁኑ ብዬ የምሰናበትበት ጊዜ ነበር፡፡ ኔልሰን ማንዴላን በፍጹም ላገኛቸው አልቻልኩም፣ ባገኛቸው እንዴት ደስ ባለኝ! ለማግኘት የምፈልገው ደግሞ በዓለም ላይ እጅግ ከተከበሩት ሰው ጋር ተገናኝቸ ነበር በማለት ለስሜቴ ክብር ለመስጠት አይደለም፣ ነገር ግን ለአፍሪካውያን ክብርን፣ ኩራትን እና ሞገስን ላጎናጸፉት እኒያን ጀግና ኔልሰን ማንዴላን በዚህ አጋጣሚ “አመሰግናለሁ” የምትለዋን ቃል በትህትና ለማቅረብ እንጅ፡፡
ኔልሰን ማንዴላ ድልድይ ቀያሽ ነበሩ፡፡ ዘርን፣ ጎሳን እና የህብረተሰብ መደብን የሚያገናኙ ድልድዮችን ገንብተዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እሳት አጥፊ ነበሩ፡፡ በዘር እና በጎሳ ጥላቻ ተቀጣጥሎ የነበረውን ቤት እሳት በማጥፋት በደቡብ አፍሪካውያን ዘንድ እውነት እና ዕርቅ እንዲሰፍን አድርገዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ መንገድ ቀያሽ ነበሩ፡፡ በረዥሙ ጉዞ ወደ ነጻነት የሚያደርሱ በስም “ደግነት” እና “ዕርቅ” የሚባሉ ሁለት መንገዶችን በመገንባት የተናገሩትን በተግባር አሳይተዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ የህንጻ ንድፍ ነዳፊ/architect ነበሩ፡፡ በአፓርታይድ አመድ ላይ በብዙሃን ዘር ዴሞክራሲ የተዋበውን ማማ ገንብተዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ የልዩ ተሰጥኦ ባለቤት ነበሩ፡፡ ከባርኔጣ ላይ ጥቁር እና ነጭ እርግቦችን በአንድ ጊዜ በመልቀቅ በነጻነታቸው ተንፈላስሰው እንዲበሩ አድርገዋል፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ለዘላለም የሚኖር የለውጥ ሐዋርያ ነበሩ፡፡ ጥላቻን በፍቅር፣ ፍርሃትን በወኔ፣ ጥርጣሬን በእምነት፣ ታጋሽየለሽነትን በትዕግስት፣ ቁጣን በመግባባት፣ ጥላቻን በስምምነት፣ እና ቅሌትን በክብር የሚለውጡ ነበሩ፡፡
የማንዴላን መልዕክት ለኢትዮጵያውያን/ት ወጣቶች አስተላልፌአለሁ፡፡ “ፍቅር የነገሰበትን የኢትዮጵያን ማህበረሰብ ለመመስረት ደግ ነገርን አድርጉ፣ ይቅርታን እና እርቅን አውርዱ፡፡ የስኬት ቃልኪዳን ባይኖርም ሞክሩ፣ ውድቀት እንዳለ ብታውቁም ሞክሩ፣ ጥርጣሬ ያለ እና እርግጠኝነት የጎደለ መሆኑን ብታውቁም ሞክሩ፡፡ ደክማችሁ እና መቀጠል የማትችሉ መሆኑን ብታውቅም እንኳ ሞክሩ፡፡ ተስፋ በማይኖርበት ጊዜም ሞክሩ፡፡ ዓላማችሁን ካሳካችሁህ በኋላም ቢሆን ሞክሩ፡፡ ማንዴላ እንደሞከሩት ሁሉ ሞክሩ፡፡”
እ.ኤ.አ በ2013 የሰማያዊ ፓርቲ አስረጅ ምስክርነት ሆኘ ቀርቢያለሁ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ሰማያዊ ፓርቲን የምደግፍበት ምክንያት ከወጣቶች፣ በወጣቶች፣ ለወጣቶች፣ የተቋቋመ የፖለቲካ ፓርቲ ስለሆነ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የአብዛኛውን የኢትዮጵያን ህብረተሰብ ፍላጎት እና ጥቅም ሊወክል የሚችል ፓርቲ ስለሆነ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝብ ከ35 ዓመት የዕድሜ ክልል በታች ያለው የህብረተሰብ ክፍል 70 በመቶውን ይሸፍናል፡፡
በአሁኑ ጊዜም የኢትዮጵያ ወጣቶች ለዴሞክራሲ፣ ለህግ ልዕልና፣ ለነጻነት እና ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ሲባል የደም፣ የላብ እና የእንባ መስዕዋትነት በመክፈል ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ምርጡ እና ብሩህ አዕምሮ ያለው ወጣት እየተቀጣ፣ ፍርደገምድል ፍርድ እየተበየነበት፣ እየታሰረ፣ እና ጸጥ እረጭ ብሎ እንዲገዛ እየተደረገ ነው፡፡ ከእነዚህ የወጣት ዝርዝር የመጀመሪያው እረድፍ ላይ የሚገኙት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ በቀለ ገርባ፣ አቡበካር አህመድ፣ ውብሸት ታዬ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ አህመዲን ጀቤል፣ አህመድ ሙስጣፋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ በቅርቡ ከህይወት የተለየው የኔሰው ገብሬ እና ሌሎች ለቁጥር የሚያታክቱ ትንታግ የኢትዮጵያ ወጣቶች ናቸው፡፡ “የሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄን” የኢትዮጵያ ወጣቶች ለእራሳቸው እና ለወደፊቱ ትውልድ የሚተላለፍ ህልማቸውን እና ሀሳቦቻቸውን የሚተገብር ድርጅታዊ ተቋም አድርጌ እወስወደዋለሁ፡፡ ዝምታውን ከዚህ በኋላ እናቁም እና “ከሰማያዊ ፓርቲ ንቅናቄ” ጎን በመሰለፍ ድጋፋችንን እንድንሰጥ ለሁሉም ህዝቦች ተማጽዕኖዬን አቀርባለሁ፡፡
የኢትዮጵያ ወጣቶች፡ ከተኛችሁበት እንቅልፍ በመንቃት እንደ አንበሳ በመነሳት እና እንደ አቦሸማኔ በመወርወር “ውዲቱን ኢትዮጵያ” ገንቡ፣
በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2013 የአቦሸማኔዎች ትውልድ ዓመት ዋና የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ያለፈው ከድንቁርና፣ ከጎሳ ጥላቻ፣ ከዘር አድልኦ እና ከጾታ ኢፍትሀዊነት የጸዳች “ውዲቷን ኢትዮጵያ” ተገንብታ የማየትን ህልም ወጣቶቹ በፍጹም በፍጹም እንዳያቆሙ የሚለው ነው፡፡ ዓመቱ የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች የስኬት ዓመት ነው ማለት እችላለሁ፣ ሆኖም ግን ስራዎቻቸው ገና ሙሉ በሙሉ አልተከናወኑም፡፡ ከፊታቸው ገና ረዥም እና አስቸጋሪ ጉዞ ይጠብቃቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ከመጨረሻው ግባቸው ከመድረሳቸው በፊት በጣም አደገኛ የሆኑ ሸለቆዎችን የማቋረጥ፣ ድንጋያማ እና ቀጥ ያሉ ተራራዎችን የመውጣት፣ እና ጎርፍ የሞላው ወንዞችን የመሻገር ተግባራትን ማለፍ ይጠብቃቸዋል፡፡ ጉዟቸውን በድፍረት እንዲቀጥሉ እማጸናለሁ፡፡ እ.ኤ.አ በ1819 የእንግሊዝ ሙሰኛ፣ ጨካኝ እና ቀጣይነት ያለው የአምባገነን አገዛዝ ጥቃትን በመቋቋም በሰላማዊ ትግሉ ሲፋለሙ ለነበሩ ወጣቶች ድጋፍ ይሆን ዘንድ ፔርሲ ባይሸ ሸሌይ የቋጠሯቸውን ስንኞች እንድያጣጥሙ እጋብዛቸዋለሁ፣
…
ታላቅ ስብሰባ ይደረግ፣
በታልቅ ግነዛቤ፣
በነጠሩ ቃላቶችም አውጁ፣
አምላክ ነጻ አድርጎ ፈጥሯችዋልና፣
…
አምባገነኖቹም ከደፈሩ፣
ከማሀላችሁ ታጥቀው በፈረሳቸው ይጋልቡ
ይውጉ ይቁረጡ ይጨፍጭፉ
እንደልባቸው ያርጉ፡፡
…
በታጠፉ እጆች እና አተኩረው በሚያዩ ዓይኖች፣
አለቅንጣት ፍርሃት አለመገረም፣
ሲገድሉ ሲያርዱ ልብ በሏቸው፣
ቁጣቸው እስኪበርድላቸው፡፡
…
ከዚያም ከእንቅልፋቸው እንደነቁ አንበሶች ተነሱ፣
በቁጥር የለሽ ብዛታቸሁ፣
በንቅልፍ የጣሉባችሁን የእስር ሰንሰለቶች እንደጤዛ አራግፏቸው፣
እናንተ ሺ ናቸሁ፣ እነርሱ ግን ጥቂት፡፡
…
የኢትዮጵያ ወጣቶች፡ እንደ አንበሶች ተነሱ! እንደ አቦሸማኔዎች ተሰንዘሩ!
ታህሳስ 22 ቀን 2006 ዓ.ም
ቴዲ አፍሮና የቢራው ፖለቲካ (ክንፉ አሰፋ)
ክንፉ አሰፋ
በጋዜጠኛ ስህተት የወጣች አንዲት ጽሁፍ ምክንያት 18 ሺህ ፊርማ በኢንተርኔት መሰበሰቡን ሰማን። ጽሁፉን ያሳተመው መጽሄት ስህተቱን አረመ። ይቅርታም ጠየቀ። ዘመቻው ግን እንደቀጠለ ነው። ቴዲ አፍሮ ይንን እንዳልተናገረ መግለጫ ቢሰጥም ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም። ከቶውንም አንድነታችንን የማይፈልጉ ምእራባውያን ጭምር ይህችን ምክንያት በመያዝ ጉዳዩን ማረገብ ጀመሩ። አንድ የዳች ጋዜጣ አጼ ምኒሊክን ከሂትለር ጋር አመሳስሎ በመጻፍ ጋዜጣውን በዚህ ሳምንት አሰራጭቷል! ያለ አንዳች መረጃ። “ለነጮች እጄን አልሰጥም!” ብሎ አድዋ ላይ ስላዋረዳቸው ምኒሊክን ለማንቋሸሽ ምንም መረጃ አያስፈልጋቸውም።
እልፍነሽ ቀኖ የተባለች የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ በአንድ ወቅት በለቀቀችው ነጠላ ዜማ ምክንያት ማእከላዊ እስር ቤት ታስራ ነበር። ምርመራውን የሚያካሂዱት ሰዎች በመጀመርያ የዘፈኑ ግጥም ወደ አማርኛ እንዲተረጎም አደረጉ። በግጥሙ ምንም አይነት የወንጀል ነገር ሲያጡ ግጥሙ “የህግ ትርጉም ይደረግለት” ሲሉ አዘዙ። የህግ ትርጉሙም ብዙ ስላላስኬዳቸው ለግጥሙ የፖለቲካ ትርጉም እንዲሰጠው አደረጉና ሙዚቀኛዋን “ጥፋተኛ ነሽ” ሲሉ ከሰሱ። የፖለቲካ ትርጉሙ “ይህን ያለችው እንዲህ ለማለት ነው…” ከማለት ተነስቶ አቀንቃኝዋ በልቧ አስባው ይሆናል የሚለውንም ያካተተ ነበር። በኢትዮጵያ “የፍትህ ሰዎች” የምናስበውንም ያውቁ ኖሯል።
የበደሌ ቢራ አድማ ጠሪዎች ቴዲ አፍሮ በልቡ ያሰበውን የማንበብ ሃይል እንዳላቸው አናውቅም። እሱ ግን የተባለውን ነገር እንዳልተናገረ ገልጾላቸዋል።
አጼ ምኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ያከሄዱት ጦርነት “ቅዱስ ጦርነት ነው” ወይንም “አይደለም” የሚለውን ሙግት ለግዜው ወደጎን እንተወው። ምክንያቱም የዚህ ውይይት ውጤጥ የኦሮሞ ህዝብ አሁን ላለበት ችግር የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም። የህሊና አይኖቹን ክፍት አድርጎ ለሚመለከት ሁሉ፤ የዛሬው የኦሮሞ ህዝብ ችግር የበዴሌ ቢራን ከመጠጣት እና ካለመጠጣት የላቀ ነው። ለነገሩ እንጂ 90 በመቶ የሚሆነው የኦሮሞ ህዝብ የሚተዳደረው በግብርና፤ ኑሮውም ከእጅ ወደ አፍ በመሆኑ የበደሌ ቢራን የመጠጣት አቅሙም ሆነ እድሉ የለውም። የዚህ ዘመቻ መሪ ተዋንያን የሆነው ጃዋር መሃመድ እንደነገረን ከሆነ ደግሞ 90 በመቶው የኦሮሞ ህዝብ የሙስሊም እምነት ተከታይ ነው። በሙስሊም አልኮል “ሃራም” ነው።
“እስር ቤቱ ሁሉ ኦሮምኛን ይናገራል!” ያለው ማን ነበር? አዎ! የስርዓቱ ቁንጮ የነበረው ስዬ አብርሃ ነው። ስዬ ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ከርቸሌ ታስረን የነበርን ጋዜጠኞች የእነ ኦቦ ባይራን ጉዳይ እያነሳን በኦነግ ስም በግፍ ለታሰሩት ስንጮህ የዝሆን ጆሮ ነበር የሰጠን። አቶ ስዬ አብርሃ አይኑ የተከፈተውና ጆሮው ኦሮምኛን መስማት የጀመረው እጆቹ የኋሊት ታስረው ቃሊቲ ሲወርድ ነበር። በእርግጥ ማየት ማመን ነው። ያየውንና የሰማውን በመመስከሩ ሊመሰገን ይገባዋል። ልብ በሉ። እስረኛው ሳይሆን እስር ቤቱ ነው ኦሮምኛ እየተናገረ ያለው።
ሂዩማን ራይትስ ዋች ሰሞኑን በለቀቀው ዘገባ፤ በኦሮሞ ወገናችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን አስከፊ ስቃይ በድምጽና በምስል ጭምር አሰራጭቷል። ይህንን ስቃይ ለማስቆም የፌስቡክ ታጋዮቹ ስንት ሺህ ፊርማ እንዳሰባሰቡ አልነገሩንም። የበዴሌ ቢራን የኦሮሞ ህዝብ እንዳይጠጣ በ24 ሰዓታት ውስጥ 18 ሺ ፊርማ ተሰብስቧል ብለውናል።
እርግጥ ነው። “ሰብአዊ መብት ይከበር!” የሚል ዘመቻ ከመጀመር ይልቅ “ቢራ አትጠጡ!” ማለቱ ቀላል ሊሆን ይችላል። በምእራቡ አለም የሚመረተውን ሄነከን ቢራ ራሳቸው እየተጎነጩ ይህንን ቀጭን ትእዛዝ ሲያስተላልፉ ግን በዚያ ትልቅ ህዝብ ላይ እያሾፉበት መሆኑን የዘነጉት ይመስላል።
የኦሮሞ ልሂቃን ግራ ያጋቡኛል። ይህን ስል ያለምክንያት አይደለም። በአባ ጅፋር ግዛት ተወልጄ በኦሮሞ ባህል ታንጼ ነው ያደግኩት። በደሙ ብቻ ‘ኦሮሞ ነኝ’ እያለ ከሚመጻደቀው ይልቅ የኦሮሞን ህዝብ ማንነት ጠንቅቄ አውቀዋለሁ። ቋንቋው፣ ባህሉና ስነልቦናው ውስጡ ሰርጎ ሳይገባ በደሙ ብቻ ራሱን እየለካ ከህልም እና ከቅዠት አለም ውስጥ ገብቶ የኋሊት ከሚራመደው በተሻለ መንገድ። … እናም አንድ የኦሮሞ ህዝብ አውቃለሁ። በቋንቋው፣ በባህሉና በታሪኩ የሚኮራ ህዝብ። ታታሪና ሰራተኛ ህዝብ። ከሌላው ጋር ተዋልዶና ተከባብሮ በፍቅር አብሮ የሚኖር ህዝብ። የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር በደም ተሳስሯል። ሃቁ ይህ ነው። ግና ፖለቲከኞቹ ከዚህ ህዝብ በሁለት ሺህ ማይልስ ርቀው በምእራቡ አለም በሚሰሩት ስራ ይህንን ትልቅ ህዝብ እጅግ ትንሽ የሚያደርግ መሆኑን ያስተዋሉት አይመስለኝም።
በቅርቡ ሳውዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ የጸመችውን ግፍ ለመቃወም በአለም ዙርያ ያለ ኢትዮጵያዊ በጋራ በሚጮህበት ወቅት አንድ እንግዳ ክስተት በኢንተርኔት ላይ ወጥቶ አየን። “ሳውዲ አረቢያ ኦሮሞን አትግደሉ፣ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ አይደለም፣ ኦሮሞ ወንጀለኛ አይደለም።” የሚል መፈክር የሚያሰሙ ሰዎች ለብቻቸው ሰልፍ ወጡ። እነዚህ ሰዎች የተሰለፉት “ኦሮሞን አትንኩ። ሌሎቹ ግን ወንጀለኞች ስለሆኑ ይገባቸዋል” የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነበር። መቼም ከማንም ሰብአዊ ፍጡር እንዲህ አይነት ኢ-ሰብአዊ አባባል አይጠበቅም። ድርጊታቸው ያሳፍራል። አንገትም ያስደፋል። ይህ አሳፋሪ ድርጊት እኔን እንዲህ ካሸማቀቀኝ፤ አፈር ስንፈጭ ያደግነው በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሮ የኦሮሞ ልጆች ቢያዩት ምን ሊሉ እንደሚችሉ በምናቤ እስል ነበር። በዚያ ትልቅ ሕዝብ ስም አደባባይ ወጥተው፣ ተግባራቸው ግን ማስተዋል የተሳነው ትንሽ ህዝብ ነበር። ያንን ኩሩ ህዝብ እንዲህ … እንዲህ እያሉ ሊያሳንሱት አየን።
እ.ኤ.አ. በ1998 ገደማ አቶ ዳዊት ዮሃንስ በሆላንድ ውስጥ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ከስብሰባው መሃል አንድ ሰው ከመቅጽበት ተነስቶ ‘ለኦቦ ነጋሶ ጊዳዳ የሚያደርሱልኝ ጥብቅ መልእክት አለኝ’ አለ። ስብሰባውን የሚመራው አቶ ዳዊት ዮሃንስም ሰውዬው ተነስቶ መልእክቱን እንዲናገር ፈቀደለት። ሰውየው ከመቀመጫው ተበሳ።
“ፊንፊኔ መሃል ላይ ያለው የምኒሊክ ሃውልት በአስቸኳይ እንዲነሳ ይንገሩልን!” አለ ፊቱን ቅጭም አድርጎ በኩራት እየተናገረ። በስብሰባው የነበርን ሰዎች ግን ለተናጋሪው አፈርን። ያሳፈረን ይህንን መልእክት ማስተላለፉ አልነበረም። ሰውየው ሊናገር ከመቀመጫው ሲነሳ ሌላ አንገብጋቢ ጉዳይ ያነሳል ብለን ገምተን ስለነበር እንጂ። ‘ሰዎች በዘራቸው (በኦሮሞንታቸው) ብቻ የሚታሰሩት፣ የሚሰቃዩትና የሚገደሉት እስከመቼ ነው?’ የሚል መልእክት ነበር የጠበቅነው። ምክንያቱም ወቅቱ በቁጥር 20 ሺህ የሚደርስ የኦሮሞ ተወላጆች የጦር ካምፕ እስረኛ እንዲሆን ካደረጉ በኋላ፤ የኦነግ መሪዎች በባሌ ሳይሆን በቦሌ እየተሸኙ የወጡበት ሰሞን ነበር። የኦነግ መሪዎች ከህወሃት ጋር በጋራ መስርተውት የነበረውን ቻርተር ረግጠው በመውጣታቸው ምክንያት ኦሮሞው ወገናችን የህይወት መስዋእትነት ጭምር ይከፍል የነበረበት ወቅት።
ዳዊት ዮሃንስም አግባብ ያለው ጥያቄ መሆኑን ከተናገረ በኋላ መልእክቱን ለርእሰ-ብሄሩ እንደሚያደርስ ቃል ገብቶ ሄደ። መልእክቱን ለዶ/ር ነጋሶ ያድርስ፤ አያድርስ የታወቀ ነገር የለም። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በዚያን ወቅት የሃገሪቱ ርዕሰ-ብሄር ነበሩ። እንኳንና የተባለውን መልእክት ሊያስፈጽሙ፤ እሳቸውም የዛ ስርዓት ሰለባ ሆነው አየን።
የአጼውን ሃውልት ግን ዛሬ በባቡር ሃዲድ ስራ ምክንያት ከነበረበት ስፍራ እንዲነሳ አድርገውታል።
የተዛባ ታሪክ ይዘን፣ ጥላቻን ብቻ በምናባችን አርግዘን የት እንደምንደርስ አላውቅም። አሁንም በመፍትሄው ላይ ሳይሆን በችግሮቹ ላይ ተወጥረናል። የምኒሊክ ሃውልት ተነሳም አልተነሳ እንደ እንስሳ ለሚታደነው የኦሮሞ ህዝብ ምን ፋይዳ አለው? “በእስር ያሉ ወገኖቼ ይፈቱ!” ለማለት እንኳን ሞራል ሳይኖረን አእምሯችንን በአፈ-ታሪክ ብቻ ወጥረን አንዲት ኢንች እንኳን ወደፊት መራመድ እንዳልቻልን ለምን አናስተውልም?
አጼ ምኒሊክ ኢትዮጵያን ግዛት አንድነት ለማስፋፋት ባደረጉት ጦርነት ወንጀል ፈጽመው ከሆነ አጽማቸው ወጥቶ ለፍርድ ይቅረብ ነው የምትሉት? ወይንስ ይህ ትውልድ የዚያ ወንጀል ውርስ አለበት? ውርስ ካለበትስ ማን ነው ወራሹ? አማራው? ጉራጌው ወይንስ ኦሮሞው? እንደ ዘረኞች፣ ደም መለካት ካለብን እኚህ መሪ ከአማራም፣ ከኦሮሞም፣ ከጉራጌም ይወለዳሉ። ጠለቅ ብለን ከሄድን ደግሞ ራስ ጎበና ዳጬን በዚያ ስእል ውስጥ እናያለን። ምእራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያን በሃይል የያዙና ያስገበሩ የአጼው የጦር መሪ። ራስ ጎበናን ልንጠላቸው እንችል ይሆናል። ኦሮሞነታቸውን ግን ልንክደው አንችልም። የወንጀል ውርስ በተዋረድ (guilt by association) ውስጥ ከገባን የኦሮሞን ህዝብም በአእምሯችን ለፈጠርነው ወንጀል ወራሽ ልናደርገው ነው።
የቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” አልበም የሚያሞግሰው ኢትዮጵያን ከወራሪ ጠላት የታደጉትን ጀግኖች ነው። እነ ፊታውራሪ ሃብተጎርጊስ ዲነግዴን እና እነ ባልቻ አባ ነፍሶ። ቴዲ አፍሮ ለነዚህ ጀግኖች ባያቀነቅንላቸውም ከታሪክ መዝገብ ላይ ልንፍቃቸው አንችልም። የታሪክ ተመራማሪዎች ስለነዚህ ጀግኖች የጻፉት አፈ-ታሪክ ወይንም ድርሰት አይደለም። በጀግኖቹ የምንኮራው በዘራቸው ሳይሆን የሰሩት ገድል ነው። በ’ጥቁሩ ሰው’ የተመራው ይህ የጸረ-ቅኝ ግዛት ገድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው አፍሪካና ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ይህ ሊዋጥላችሁ የሚገባ እውነታ ነው። በዚያ ገድል የሚያፍሩ ካሉ የራሳቸው ጉዳይ። መላው የአፍሪካ ህዝብ ግን ይኮራበታል። የአለም ጥቁር ህዝብም ሲያስታውሳቸው ይኖራል።
ዘር እየቆጠርን ከሄድን ብዙ የሚጎረብጡ ነገሮችን ልናነሳ ነው። በግዛት ማስፋፋቱ ሂደት ግን አንድ ሃቅ አለ። ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ህልቀ መሳፍርት ኢትዮጵያዊ አልቋል። ይህ ደግሞ የድንበር መስፋፋት፤ እድገት እና ስልጣኔ ይዞት የሚመጣው ችግር እንጂ አንድን ህዝብ ለመጨረስ ጥናት ተደርጎ የተሰራ እንዳልሆነ ታሪኩን ከስር መሰረቱ ማየቱ ይበጃል። ችግሩ በእኛ ላይ ብቻ ሳይሆን በአያሌ ሃገሮች እንደተከሰተ የታሪክ መዛግብት ይነግሩናል። በ17ኛው ክፍለዘመን የተከሰተው የኢንዱስትሪ አብዮት ሳብያ እንኳን ከሁለተኛው የአለም ጦርነት የማይተናነስ እልቂት ነበር።
አጼ ምኒሊክን ከጀርመኑ ኦቶ ቮን ቢስማርክ ጋር የሚያመሳስሉ ምሁራንም አሉ። እርግጥ ነው ጀርመን አሁን የያዘችውን ግዛት ቅርጽ እንድትይዝ ያደረገው ፕሩሲያዊው ቢስማርክ ነው። ቢስማርክ የጀርመንን አንድ ታላቅ ኤምፓየር ለመፍጠር አንባገነን፣ ሃይለኛና ጦረኛ መሆን ነበረበት። ታዲያ ይህችን ሃያል ሃገር በመመስረቱ ጀርመኖች አልጠሉትም። ይልቁንም የጀግንነት ስያሜ ለግሰውታል። አያሌ የመታሰቢያ ሃውልቶችንም አቁመውለታል።
ቢስማርክ የህግ ምሁር ነበር። አጼ ምኒሊክ ግን መደበኛም ሆነ ዘመናዊ ትምህርት የተማሩ ሰው አልነበሩም። ከታሪክ እንደምንረዳው በአጼ ልብነድንግል ዘመነ መንግስት፤ የግራኝ አህመድ ወረራን ተከትሎ የነበረውን መከፋፈልና መተላለቅ ለማስቆም መሪዎች ተነሱ። ሃገርን አንድ የማድረጉን ትግል አጼ ዮሃንስ ጀመሩት፣ አጼ ቴዎድሮስ ቀጠሉበት ከዚያም እምዬ ምኒሊክ ተረከቡት።
አጼ ምኒሊክ ለአመታት በኦነግ ሰዎች ተወግዘዋል። ውግዘቱ አሁንም እታገልለታለው የሚሉትን ህዝብ ችግር ሲፈታው አለየንም። በ1991 ከህወሃት ጋር ጋብቻ ፈጽመው የምኒሊክ ቤተ-መንግስት ሲገቡ ይናገሩት የነበረውን ሁሉ ረሱት። ከቶውንም ያነሱት የነበረው የኦሮሞ ህዝብ የመብት ጉዳይ ሳይሆን የስልጣን ጥያቄ ለመሆኑን አረጋገጡልን። የሽግግር መንግስቱን ቻርተር ሲያጸድቁ “ኢትዮጵያዊ አይደለንም” የሚለውንም ሳያውቁ ዘንግተውት ነበር። ከገዢው ፓርቲ ጋር የጀመሩት ግዚያዊ ጋብቻ በፍቺ ሲጠናቅቅ የምኒሊክ ጠላትነት መፈክራቸውን እንደገና አነሱት።
የዘር ፖለቲካው ስካር ሞቅ ብሎ በነበረበት በዚያን ወቅት እንደቀልድ ይነገር የነበረ አንድ ቁም ነገር አለ። አንድ የምግብ ቤት በር ላይ በላቲን ፊደል “አማራ መግባት ክልክል ነው!” የሚል ጽሁፍ ሰፍሯል። የጽሁፉ ትርጉም ያልገባው አንድ የአማራ ተወላጅ ጎራ ብሎ ምግብ አዘዘ። አስተናጋጆቹ የሰውየው ድፍረት አስደነገጣቸው። ባለስልጣን ስለመሰላቸው አስተናገደዱት። ዳግም እንዳይመለስም እጥፍ ዋጋ አስከፈሉት። ሰውየው በድጋሚ ሲመጣ ሶስት እጥፍ አስከፈሉት። በሌላ ግዜ ከአምስት ጓደኞቹ ጋር መጥቶ ምግብ አዘዘ። ከተስተናገደ በኋላም አራት እጥፍ ቢል አቀረቡለት። በዚህ ግዜ ቲፕም ጨምሮ ሰጣቸው። የሆቴሉ ባለቤት በነጋታው “አማራ መግባት ክልክል ነው!” የሚለውን ጽሁፍ አንስቶ “ኦሮሞ መግባት ክልክል ነው!” በሚል ቀየረው።
በአሁኑ ዘመን ከበድ አለ እንጂ፣ ሰዎችን በጎሳ አደራጅቶ ከማሳደም የቀለለ ትግል የለም። ደም ከውሃ ይወፍራል እንዲሉ፤ ሰዎች በጋራ የሚጋሩትን ነገር እያነሱ ስነልቦናዊ ዘመቻ ማድረግ ስኬት ሊኖረው ይችላል። ዘለቄታ ግን አይኖረውም። የዘር ፖለቲካ ልክ እንደ ስካር ነው። ይሞቃል ከዚያም ይበርዳል። በርግጥ በሞቅታ ግዜ የሚፈጠረው አደጋ ቀላል ላይሆን ይችላል። እ.ኤ.አ. በ1993 በምስራቅና በምእራብ ኢትዮጵያ የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ለዚህ ዋቢ ነው። የኦነግ ልሂቃን የ19ኛውን ክፍለ ዘመን ጉዳይ እየደጋገሙ ያነሱልናል። በ21ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው እጅ የተፈጸመው ግድያ ግን በብሄራዊ ቴሌቭዥን ጭምር እንድናየው ተደርጓል። ነብሰ-ጡር ሴቶች በጩቤ ሆዳቸውን እየተሰነጠቁ ሲገደሉ አየን። ነብስ ያላወቁ ሕጻናትና የ90 አመት አዛውንት ጭምር ከተራራ ላይ እየተወረወሩ ሲጣሉም የአይን ምስክሮች ነን። እነዚህ ሰዎች የምናስታውሰው ይህን በመሰለ ወንጀል ብቻ አይደለም። ድርጊቱ የቂምና የቁርሾ አሻራ ጥሎ አልፏል።
ይህ ሁሉ በደል በዘመናችን ተፈጸመ። በዳዮቹ ግን አሁንም በቀልን አርግዘው ይጓዛሉ።
የበደሌ ቢራን አለመጠጣት የኦሮሞን ችግር የሚፈታ ከሆነ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ቢራውን መጠጣት ያቁም። የአኖሌን ሃውልት መሰራት ለኦሮሞ ህዝብ ፍትህ የሚያመጣ ከሆነ ደግሞ፤ ሃውልቱ በየከተማው ይገንባ። ግና ይህ ሃውልት ለመጭው ትውልድ ጥሎት የሚያልፈው ቂምና በቀልን እንጂ፤ ለሚታገሉለት ህዝብ የፍትህ ጥያቄ ዋስትናው ምን እንደሆነ ልንረዳው አልቻልንም። አሁን ያለው ትውልድ ያልፋል። ከዚህ ትውልድ በኋላ ለሚወለዱት ልጆች ጥለንላቸው የምናልፈው ቅርስ ጥላቻ፣ ቂም እና በቀል ብቻ ይሆናል።
ከዘመናችን ታላቅ ሰው ከኔልሰን ማንዴላ አንድ ነገር እንማር። ማንዴላ የደቡብ አፍሪካን ብቻ ሳይሆን የአለምን ፖለቲካ የለወጠ የፖለቲካ ነብይ ነው። ይህንን ሲያደርግ የፖለቲካ ፎርሙላ አልነበረውም። ክፉን ነገር በበጎ ለማሸነፍ ወሰነ። ጥላቻን በፍቅር ለወጠ። ልክ እንደ ክርስቶስ፣ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ብሎ በፍቅር አሸነፋቸው። ታሪክ ሰርቶ አለፈ። ስሙም ከመቃብር በላይ ለዘልአለሙ ይኖራል።
የከተማ አብዮት! –ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)
ከሩሲያውያኑ ቦልሼቪክና ሜንሼቪክ አንስቶ፣ የእኛዎቹ ኢህአፓና መኢሶን በፊት-አውራሪነት እስከ ተሳተፉበት ድረስ ያሉ በደም የጨቀዩ አብዮቶች በሙሉ በከተሞች የተካሄዱ ሲሆን፣ አብዛኛው አጋፋሪዎቻቸው ደግሞ ልሂቃኖች እንደነበሩ በጉዳዩ ዙሪያ የተፃፉ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ይሁንና እነዚህ አብዮቶች (የተሳኩትም ሆነ የከሸፉት) ሰላማዊውንና ህጋዊውን መንገድ የተከተሉ ባለመሆናቸው ዛሬም ይዘገንናሉ፤ ለወደፊቱም ባልተደገሙ ያሰኛሉ፡፡ ስለምን ቢሉ? ግድግዳው ላይ የተቸከቸከው ፅሁፍ እንዲህ የሚል ምላሽ ያስነብባልና፡- በጭቁን ሕዝብ ስም የብዙሀኑን ቤት አፍርሰዋል፤ ሀገርና ታሪክ ለመቀየር የማይሳናቸው አፍላ ወጣቶችን እርስ በእርስ አጫርሰዋል፤ ‹አንቱ› ሊባሉ የሚችሉ ምሁራንን በአንድ ጀንበር ወደ ትንታግ ነፍሰ-ገዳይነት ቀይረዋል፤ ክስረቱም ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ጠባሳ ሆኖ ዛሬ ላይ ደርሷል…
በርግጥም ያ ወቅት መደማመጥ፣ መነጋገር፣ መወያየት፣ መቻቻልን… የመሳሰሉ ምክንያታዊ እሴቶች ህቡዕ ገብተው፤ መጯጯኽ፣ መነቋቆር፣ መፈራረጅ፣ መገዳደል… የገነኑበት ነበር፤ ለዚህም ይመስለኛል ሀገር ሊረከብ የተዘጋጀ አንድ ትውልድ፣ በተኮረጀ ርዕዮተ-ዓለም፣ ባልጠራ ፕሮግራም እቅሉን ስቶ ‹ማርክስ እንደፃፈው›፣ ‹ሌኒን እንዳብራራው›፣ ‹ማኦ እንዳስተማረው›፣ ‹ሆጃ እንደመከረው›… በሚል ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ስቶ-በማሳት፣ ሀገር ምድሩን የጦር አውድማ አድርጎ ማለፉ የትላንት የቁጭት ትዝታ የሆነብን፡፡ በአናቱም ዛሬ ‹‹ነፃ አወጣናችሁ›› እያሉ ጃሎታ የሚመቱት የኢህአዴግ መሪዎች ከዚሁ ምንጭ የተቀዱ፣ ግና በቃላት ስንጠቃና በጎሳ ጠባብ አስተሳሰብ የተለዩ የትውልዱና የመንፈሱ ተጋሪ በመሆናቸው፣ የሁነቱ ‹ታሪክ›ነት ለተሰዉት እንጂ፣ ለእነርሱ ‹ሀገር እየመራንበት ነው› የሚሉበት ‹ፖለቲካ› ነውና፣ የነገይቷ የምንወዳት ኢትዮጵያችን መፃኢ ዕድል ገና ከእርስ በእርስ ግጭት ስጋት አለመላቀቁን ያመላክታል፡፡ በዚህ ፅሁፍም የምንዘመርለት የ‹አትነሳም ወይ?› ድምፅ አደገኛውን ስርዓት የመቀየሪያው ጊዜ አሁን በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ግን እነኢህአፓ ተቸንፈው የተሰናበቱበትም ሆነ ኢህአዴግ ድል አድርጎ የመጣበት መንገድ ለዘመኑ መልካም ተሞክሮ ሊሆን ይችላል እንደማለት አይደለም፤ ምክንያቱም በእኔ እምነት የእነርሱ ‹ፋኖ ተሰማራ…› ጊዜው በበየነበት ሙዚየምና የታሪክ ትምህርት ክፍል ውስጥ ብቻ ካልተገደበ ጉዳቱ በቀላሉ የሚጠገን ካለመሆኑም ባለፈ፣ የምንመኘውን ለውጥ ሊያመጣ አይችልምና ነው፡፡
የሆነው ሆኖ ለትውልዱ ክቡድ ጥያቄ ስኬታማነት መንገድ መሪ አብርሆት መሆን የሚችሉ የደም ግብር ያልጠየቁ፣ ፍፁም ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ በከተሞች ተካሂደው ሀገርና ህዝብ ያለ ብዙ ኪሳራ በአሸናፊነት የወጡባቸው በርካታ አብነታዊ አብዮቶች (እንደ አረቡ ፀደይም ሆነ እንደ አውሮፓውያኑ ጆርጂያና ዩክሬን ብርቱካናማ-አብዮቶች) መኖራቸው እውነት ነው፤ እንዲሁም በእነርሱ መንፈስ መቀደስ፣ በእነርሱ ፀበል መጠመቅ የአምባገነኑንና የበደለኛውን ሥርዓት እድሜ ለማሳጠር የሚያበረታ ኃይል ማስረፁ እውነት ነው፡፡
ከተማን እንደ ጠላት
የ‹ያ ትውልድ› የጠብ-መንጃ ትንቅንቅን በድል የተሻገረው ኢህአዴግ (ከልቡ አምኖበት ባይሆንም) ይህንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈለው በተለይም ለአርሶ አደሩ ጥቅም መሆኑን በአገኘው አጋጣሚ ሳይናገር አያልፍም፡፡ በግልባጩ ደግሞ የከተማ ነዋሪዎችን ‹ጠላት› አድርጎ በመፈረጅ ሲገነግን ተደጋግሞ ተስተውሏል፤ በርግጥ የዚህ መግፍኤ በብሔር እና በሀይማኖት የከፋፈለውን ሕዝብ፣ በመደብም ለያይቶ የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ ለማድረግ እና በየአምስት ዓመቱ በሚያካሄደው የይስሙላ ‹ምርጫ› ኮረጆ ገልብጦ ሲያበቃ የፈረደበት ምስኪን አርሶ አደር ‹መርጦኛል› ለሚለው የተለመደ ሰበቡ ‹ይጠቅመኛል› በሚል ለማመቻቸት ‹አዛኝ ቅቤ…› ተቆርቋሪ በመሆኑ ይመስለኛል፡፡ ይህም ሆኖ ድርጅቱ ይህንን የማጭበርበሪያ ስልት በደደቢት በረሃ ራሱ የቀመረው ነው ብሎ ለመከራከር የሚያስችል ገፊ ጭብጥ ይኖራል ብዬ አላስብም፤ ምክንያቱም በአንዳንድ የዓለማችን ሀገራት የፖለቲካውን ኃይል ከጨበጡ በኋላ በሕዝባቸው ላይ ነጋሪት ጎስመው ሞትን ከነዙ፣ ስቃይን ከረጩ እርኩሳን መሪዎች (ፓርቲዎች) ድርሳናት ቃል-በቃል የተገለበጠ መሆኑን የሚያስረግጡ (በስነ-አመክንዮ) የተቀኙ ማሳያዎች ማቅረብ ይቻላልና፤ እንደምሳሌም አንዱን በአዲስ መስመር እንምዘዘው፡-
የ‹ኬመር ሩዥ› መንገድ
በተለምዶ ‹ኬመር ሩዥ› (Khmer Rouge) በመባል የሚታወቀውና አክራሪ ኮምኒስታዊ የገበሬዎች ድርጅት እንደሆነ የሚነገርለት ‹‹Communist Party of Kampuchea /CPK/›› እ.ኤ.አ ከ1975-1979 ዓ.ም ድረስ፣ በወጣት የገበሬ ሠራዊት ታግዞ በካምቦዲያ መንግስታዊ ሥልጣን ተቆናጥጦ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ጨካኝና አፍቃሪ ቻይና የሆነው የፓርቲው ሊቀ-መንበር ፖል ፖትም (Pol Pot)፣ ማኦ ዜዱንግ ‹‹የሀገሬን ኢኮኖሚ ያሳድግልኛል›› በማለት ያረቀቀውንና በግብርና ላይ የሚያተኩረውን ‹‹Great Leap Forward›› ፕሮግራም፣ ‹‹Super Great Leap Forward›› በሚል ተቀጥላ እንደወረደ በመኮረጅ ‹‹ሙሉ የካምቦዲያን ሕዝብ ወደ ‹እርሻ መር-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ› (Agrarian Society) እቀይራለሁ›› ብሎ ያደረገው ሙከራ ወጪ-ኪሳራን ያወራረደው ሁለት ሚሊዮን ዜጎቹንለህልፈት በመዳረግ እንደ ነበር የታሪክ መፃህፍት ያትታሉ፡፡
ከሁሉም የከፋው ግን ፖል ፖትና ጓዶቹ ‹‹እውነተኛ ዜጋ ገበሬ ብቻ ነው›› በማለት የከተማ ነዋሪዎችን በጠላትነት ከፈረጁ በኋላ ‹‹ማህበረሰባችንን ለማንፃት›› በሚል የቁም-ቅዠት ምዕራባዊ አስተሳሰብ የተንፀባረቀበትን ማንኛውንም ጉዳይ፣ የከተማ ሕይወትን፣ ኃይማኖትን፣ ትምህርትን፣ አንድ ብርም ቢሆን በግል መያዝን… በአዋጅ ማገዳቸው ነበር፤ እንዲሁም ኢምባሴዎችን፣ ጋዜጣና ቴሌቪዥን ጣቢያን ዘግተዋል፤ በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎችን በማፈናቀል ወደ ገጠር አግዘው፣ በግዳጅ የእርሻ ሥራ ላይ አሰማርተዋል፤ ከዋና ከተማዋ ‹ፈኖሞ ፔንህ› (Phnom Penh) ብቻ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች ወደ ገጠር በእግር እንዲጓዙ በመገደዳቸው ሃያ ሺህ የሚሆኑት በጉዞ ላይ ወድቀው እንደወጡ ቀርተዋል፤ ገጠር የደረሱትንም ቢሆን ‹የግድያ ወረዳዎች› እያሉ በሚጠሯቸው የእርሻ ሥራ ላይ አሰማርተው ለአንድ ሰው በነፍስ ወከፍ በየሁለት ቀኑ አንዴ 180 ግራም ሩዝ ብቻ በመስጠት በረሀብ፣ በበሽታ፣ ብስቅየት እና በግድያ እንዲያልቁ አድርጓል፡፡ በመጨረሻም አገዛዙ በቬትናም ጣልቃ ገብነት እ.ኤ.አ በ1979 ዓ.ም በኃይል በመወገዱ፣ ፖል ፖት ከእነተከታዮቹ ሀገሩ ከታይላንድ ወደምትዋሰንበት ጠረፍ አካባቢ በመሸሽ፣ የትጥቅ ትግል እንደአዲስ ጀምሮ ለረዥም ዓመታት ከታገለ በኋላ፣ እ.ኤ.አ በ1997 ዓ.ም እርጅና ተጭኖት በህግ ቁጥጥር ስር በዋለ፣ በዓመቱ ከልብ ጋር በተያያዘ ህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል (በነገራችን ላይ ይህ ድርጅት የሽምቅ ውጊያ ከመጀመሩ በፊትም ሆነ በኋላ የተጠናከረበትን ምስጢራዊ መንገድ ጨምሮ የተከተለው ስልት
ከሞላ ጎደል ከኢህአፓና ህወሓት አፈጣጠር ትርክት ጋር ተመሳሳይነት አለው)
ኢህአዴግ እንደ ‹ኬመር ሩዥ›
ከሁለት አስርተ ዓመታት የሥልጣን ቆይታም በኋላ፣ የከተማ ነዋሪዎችን በጠላትነት ካሰፈረበት ጥቁር መዝገቡ ላይ መሰረዙ ያልሆነለት ኢህአዴግ ‹እንደ ኬመር ሩዥ ሁሉንም የጭካኔ ተግባራት በአደባባይ ፈፅሟል› ተብሎ ባይወነጀልም፣ ተመሳሳይ ስልቶችን በመኮረጅ በረቀቀ መንገድ አለዝቦ መተግበሩን ግን መካድ አይቻልም፡፡ እንዲሁም የሁለቱ ድርጅቶች ዋነኛ ልዩነት ወደ እንዲህ አይነቱ የጥላቻ ጠርዝ የተገፉበት ምክንያት ይመስለኛል፤ ይኸውም ፈላጭ ቆራጩ ፖል ፖት በከተሜው ላይ የከፋ ቂም የቋጠረበት መነሾ፣ ከገበሬ ቤተሰብ መገኘቱን ጨምሮ፣ ከአስተዳደጉ ጋር በሚያያዙ ‹ህመማቸው-ህመሜ› በሚል ሲባጎ የተቋጠረ ሲሆን፣ መለስና ጓዶቹ ደግሞ የሥልጣን ዕድሜያቸውን ለማራዘም በማስላት ብቻ መሆኑ ነው፤ መቼም መሬት የረገጠውን እውነታ ተመልክቶ የሀገሬ አርሶ አደር ከፕሮፓጋንዳ ፍጆታ በዘለለ፣ ከከተሜው የተለየ የመልካም አስተዳደርም ሆነ የመሰረተ-ልማት ተጠቃሚ አለመሆኑን መረዳቱ አዳጋች አይደለም፡፡
የሆነው ሆኖ የኢህአዴግ ‹ፀረ-ከተሜነት› እንዲህ በግላጭ አፍጥጦ የወጣው ከምርጫ 97 በኋላ ነው፤ በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትሩ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ፣ ድርጅቱ በከተሞች መሸነፉን ከገለፀ በኋላ፣ በገጠር ሙሉ በሙሉ ስለተሳካለት መንግስት ለመመስረት የሚያስችል የመራጭ ድምፅ ማግኘቱን አውጇል፤ ይህንንም ተከትሎ ግንባሩን ያልመረጡ የከተማ ነዋሪዎች በተቀነባበረ ሴራ የጥቃት ዒላማ መሆናቸውን የሚያመላክቱ በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ በተለይም በድህረ-ምርጫው ከተሜውን ዒላማ ያደረጉ በስራ ላይ የዋሉ አፋኝ ህጎች እና ፖሊሲዎችን ጨምሮ በደባ የተፈፀሙ መንግስታዊ ጥፋቶችን ዘርዘር አድርገን እንያቸው፡፡
መሬትን በተመለከተ የወጣውን የሊዝ አዋጅ በቀዳሚ ምሳሌነት እናንሳው፤ ፓርቲው በ1987 ዓ.ም ባፀደቀው ህገ-መንግስት የመሬት ፖሊሲውን አንዱ ዕማድ አድርጎ በማካተቱ፣ የመንግስት ጭሰኝነትን (Tenants of the state) በገጠሩ ክፍል ሲያሰፍን፣ የመሬት ከፊል ባለቤትነትን ደግሞ ለከተሞች እንዲፈቅድ አድርጎት ነበር፡፡ እናም የግል ይዞታን መሸጥ (መንግስት ለሚፈልጋቸው ‹‹ልማቶች››ም ሆነ በሊዝ ለመቸብቸብ ዜጎችን የማፈናቀል መብት ከማግኘቱ ውጪ) እስከ 97ቱ ድህረ-ምርጫ ድረስ ተፈቅዶ የዘለቀበት ሂደት፣ በዚህ የሊዝ አዋጅ በመሻሩ የተነሳ፣ ነዋሪው መሬት በመሸጥ ሊያገኝ ይችል የነበረው ገቢ ተጨምቆ ወደ መንግስት ካዝና እንዲሻገር ሆኗል፡፡ የዚህን አዋጅ ‹ፖለቲካዊ ንባብ› ውስጥ የምናገኘው ጭብጥ፣ በከፊልም ቢሆን መሬት ላይ የቆመውን የሀብት መሰረት በመናድ፣ የተቃውሞ ኃይሉ የድጋፍ መዕከል እንደሆነ ያመነውን የማህበረሰብ ክፍል ክፉኛ ማድቀቁን ስንረዳ ነው፡፡ አዋጁን እንለጥጠው ካልን ደግሞ ግንባሩ በገጠሩ ያነበረውን የዜጎች የመንግስት ጭሰኝነት በጠመዝማዛ መንገድ፣ በተለይም በአዲስ አበባ የመፈጸም ዕቅዱ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡
የኢህአዴግ ከተማንና ከተሜዎችን የመፍራት አባዜ ከጫካ ትግሉ ጋርም በረዥሙ የሚተሳሰር ነው፡፡ በወቅቱ በጥላቻ ከመተያየት አልፎ ደም የተቃባቸው ኢህአፓን መሰል ኃይሎች መሰረታቸው ከተሞች ላይ እንደነበረ ይታወቃል፤ በአናቱም በትግሉ መጠናቀቂያ ዋዜማ እና ማግስት ሊገዛለት ያልቻለው (ማማለሉ ያልተሳካለት) ልብ በተለይ የአዲስ አበቤዎችን ነበር፤ በ1980ዎቹ መጀመሪያም ፓርቲው አንገት ላይ ታንቆ ሊደፋው የነበረው ዋነኛ ጉዳይ፣ ብሔር ተኮር ስርዓቱ ህገ-መንግስታዊ ድጋፍ ሲያገኝና የብሄር ፖለቲካ ብቸኛው የድጋፍም የተቃውሞም ተዋስኦ እንዲሆን መደረጉ ነበር፡፡ ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት መንፈስ ከተገራው የአዲስ አበቤ ብሔር ዘለል ማንነት ጋር እንዲህ በፊት ለፊት መጋጨቱ፣ ከተማይቱን በወረራ የያዛት እስኪመስል ድረስ በጥላቻ እንዲዘምቱበት አነሳስቷል፡፡
ሁለተኛው ምዕራፍ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ የመጣው የአሰብ ወደብን ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንዲካለል የመፈለግ የከተሜዎቹ ግፊት ነው፡፡ ጦርነቱ ሲያበቃና የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ ሲገደዱ የነዋሪው ቁጣ ብርቱ እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ይህ እውነትም ሌላኛው ፓርቲውን ቂም ያስቋጠረ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡ በድህረ-ምርጫ 97 የፀደቀውና አፋኝነቱ በተግባር የተረጋገጠው የሲቪል ማህበረሰቡን የሚመለከተው አዋጅም ‹የብዙዎች ተቋማት ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የወጣ ነው› በማለት ከየአቅጣጫው ይነሳ የነበረውን የተቃውሞ ውግዘት አጣጥሎ፣ በሥራ ላይ ባዋለበት ዓመት በርካታ ተቋማትን ከማፈራረሱ አኳያ፣ መጀመሪያውንም ለእንዲህ አይነቱ ክፉ እርምጃ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ወደሚል ጥርዝ ይገፋል፡፡ በተጨማሪም ያለፉትን ሃያ ሁለት ዓመታት ሙሉ በአይኑ መዓት የሚያያቸው ምሁራን፣ የነፃው ፕሬስ አባላት እና
በየዘመኑ ከባድ ተግዳሮት የፈጠሩበት የተቃውሞ ስብስቦች ጠንካራ መሰረት በከተማይቱ ውስጥ መሆኑ ጥላቻ እና የጭካኔ እርምጃዎቹን አብዝቶታል፡፡
ሌላው አገዛዙ በከተሜዎች (በሸማቾች) ላይ ያለውን ስር የሰደደ ጥላቻ የሚያሳዩት፡- ከምርጫው በኋላ ጤናማ ያልሆነ የዋጋ ንረት በከፋ ደረጃ ማሻቀቡ፣ ፍትሃዊ ያልሆኑ የተለያዩ የግብር ህጎች በእንጀራ እና ሽንኩርት ቸርቻሪዎች ላይ ሳይቀር መተግበራቸው ነው፡፡ በተለይም ካለፉት ስምንት ዓመታት ወዲህ የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት ዋነኛ አባባሽ ኃይል የምግብ ዋጋ መናር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ የምግብ ዋጋ መናር በዋነኝነት ቋሚ ደሞዝ ተከፋዩ የከተማ ነዋሪው ተጎጂ መሆኑን የስርዓቱ ባለስልጣናትም ይቀበላሉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ከሁለት ወራት በፊት በ‹‹አዲስ ዘመን›› መፅሄት የተጠየቀው የፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ‹‹በ2006 ዓ.ም የሚጨመር ደሞዝ አይኖርም›› ከማለቱ ባለፈ ‹‹ነገ ይችን አገር ወደተሻለ የሚያደርስ በጎ መስዋዕትነት ነው›› ሲል በከተሜው መከራ ላይ አላግጧል፡፡ በርግጥ ይህ ሁሉ መዓት ከመውረዱ በፊት በ1998 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ራሱ አቶ መለስ በደቡብ ክልል ወደምትገኘው ይርጋለም ከተማ ድረስ ሄዶ የሙዝ አምራች አርሶ አደሮችን ሰብስቦ ካነጋገረ በኋላ፣ እንዲህ ለፍተው የሚያገኙትን ምርት ለከተሜው በርካሽ መሸጣቸው አግባብ አለመሆኑን ቀስቅሶ ዋጋውን በአራት እጥፍ እንዲጨምሩ በማድረጉ የተፈጠረው የገበያ እጥረት፣ ምንም እንኳ መልሶ አምራቾቹን ሰለባ ቢያደርግም፣ ኩነቱ የጠቅላይ ሚንስትሩን ቀጣይ ዕቅድ የሚያመላከት ነበር፡፡
በከተሞች ውስጥ እየተደረገ ያለው ‹‹የሰፈራ ፕሮግራም››ም (Urban Resettlement) አንዱ ሊነሳ የሚገባው ነጥብ ነው፡፡ በእርግጥ በዚህ ዕቅድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተሻለ የመኖሪያ ቤቶች ተጠቃሚ እንደሆኑ ማየት እንችል ይሆናል፡፡ ጥያቄው የሚነሳው ግን፣ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎችን ከሌሎች የፈረሱ የከተማዎቹ ክፍሎች ከሚመጡት ጋር በአንድ አዳብሎ በኮንዶሙኒየም ቤቶች አጥሮ የማስቀመጡ አንደምታ ላይ ነው፡፡ የዚህ ዕቅድ ክፉ ገፅ የሚገባን በረዥም የአብሮነት መስተጋብር (ሶስት መንግስታትን መሻገር የቻለ የአንድ አካባቢ ነዋሪነት) የተገነባው የጋርዮሽ ፖለቲካው አረዳድ እና የእርስ በእርስ ፍፁም መተማመን፣ 97ን ጨምሮ በተለያዩ ወቅቶች በተነሱ ተቃውሞዎች ወጥ ምላሽ እንዲሰጡ ማደፋፈሩን (አራት ኪሎን የመሳሰሉ አካባቢዎች) አስታውሰን፣ በመልሶ ማስፈሩ ደግሞ የአንዱን አካባቢ ነዋሪ በታትኖ ወደተለያዩ ሳይቶች መውሰዱን ስንመለከት ነው፤ ይህ መራራ እውነታም የገዥዎቻችን ጥላቻ ስር የሰደደ መሆኑን እና የአምባገነናዊ ስርዓቱን ዕድሜ ለማራዘም ያለመ እንደሆነ ይጠቁመናል፡፡
(ስርዓቱ በከተሜዎች ላይ የሰረፀበትን ጥልቅ የጥላቻ ፅንፍ እንዲህ ከተመለከትን፣ የከተማ አብዮት፣ ማኦኢዝም ከሚያዘው ከገጠር ከሚነሳው ብረታዊ ትግል ጋር ያለውን ልዩነት፣ በአረቡ ፀደይ ተሞክሮ በመንተራስ መፈተሹን፤ እንዲሁም የኢህአዴግ ግድፈቶች (Achilles’ heel) የከተማ አብዮትን ለማስነሳት ያላቸውን አስተዋፅኦ፣ በአደባባይ ሊያሰባስቡ የሚችሉ ጥያቄዎች ምን ቢሆኑ የተሻለ ነባራዊውን እውነት ያንፀባርቃሉ… የሚሉትን ጉዳዮች እና መንገዱን ስለሚመሩ የሚችሉትን መልከአ-ቡድኖች ማንነት ሳምንት እመለስበታለሁ)
ኣወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ –ከሄኖክ የሺጥላ
ኣወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ
ብቸኛው ልቤ ሰው በመውደዴ
ነው ያለው ኣረጋሃኝ ወራሽ ኣሁን እንደሱ ልፋትና ጥረት ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የት በደረሰ። ለነገሩ ይሄ ትውልድ የተሰራውን ሁሉ በመናድ : የተጣፈውን ሁሉ በመካድ ነው የሚታወቀው። እኔ እንኳ በዘመኔ ስንት ኣየሁ። ኣሁን ማን ይሙት ኣደይ ትርሃስ በፍራሽ መዋጥ ለሁለት ዕየከፈሉ ያጸኑት ሹሩባ የሚረሳ ሆኖ ነው “ቢዮንሴ ሄር ስታይለር ምናምን ምንምን በሚል ሰጋቱራ ሃገሩን ያጥለቀለቅነው።” እስኪ ኣሁን ምን ትውልድ ኣለ። ድሮ ቡና እንኩዋ እስከ ሶስተኛ ነበር የሚጠጣው፤ ኣሁን ግን ኢኮኖሚው በ ፲፩ ፐርሰንት ኣድጎ ቡና እንኩዋ የሚያቆመው ሰባተኛ ምናምን ላይ ነው። በውነት ፕሮፌሰር ኣልማርያም እንደሚሉት ይሄ ትውልድ ኣቦ ሸማኔ ሳይሆን ኣቦል ሸማኔ ነው። ኣያቶቻችን ለኣድዋ ጦርነት ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ሲሉ፤ መለከት: ጥሩንባ ሲነፉ ነው ታሪክ የሚነግረን። ዛሬ ግን የመለከት እና የእንቢልታ ሪሚክስ በየ ስርጣ ስርጡ ሺሻ መንፋት ሆኖዋል ግብራችን። የሰሞኑ መፈክር ኪንግ ኣብደላ ሼም ኦን ዩ፤ ሼም ሼም ሼም፤ ነበር ኣይደል፤ ምነው ሺሻው ተረሳ ታዲያ፤ ኣጎቶቻችን ባርነትና ውርደት ብቻ ሳይሆን ሱሰኝነቱንም ኣወረሱን።Ethiopian poet Henok Yeshitla
እንግሊዚኣዊው ጋዜጠኛና ጠሃፊ Grham Hancook The sign and the Seal (The Quest for The Lost Arc of the Covenant) በሚለው መጥሃፉ ላይ The Ethiopian slept a thousand years forgetting the world by whom they were forgotten by ይላል :: በነገራችን ላይ የላይኛውን የኣነባበብ ዘዬ (style ) ኣንድ ነገርን ኣስታወሰኝ :: ባንድ ወቅት በስድስት ኪሎ (university ) ያስተምሩ የነበሩ መምህር ስለ ጆነፍ ኬንዲ ሞት ለተማሪዎቻቸው ሲያስተምሩ (During the time and death of Jonneif Kennedy everybody was shocken) ኣሉ በዚህን ጊዜ ኣንድ የቅዱስ ዮሴፍ ተማሪ ሳቁን ለሞአቆጣጠር ሲታገል ያስተዋሉ እኝሁ መምህር በነገሩ በስጨት ይሉና “ምን ያስቅሃል ሾካካ!!!” ኣሉ ኣሉ። እንግዲህ ያዙልኝ ሾክን ሾካካ ከሚለው ነው የመጣው ማለት ነው። እሺ ይሁን ሾክንስ ከሾካካ ነው እንበል፤ ኣድርባይነት፤ ባንዳነት፤ ሆዳምነት፤ ታሪክ ሸቃይነት፤ እነዚህስ? ኣንድ ወዳጄን በጣም በስጨት ብዬ ኣረ ባክህ እኔ ኣልገባኝም ይሄ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መናቅ ከየት የመጣ ባህል ነው ስለው፤ ፈገግ ብሎ በርግጠኝነት ከቻይና ኣይደለም፤ ከቻይና ቢሆን ይህን ሁሉ ዘመን ኣብሮን ኣይቆይም ነበር፤ ማናልባት ከጣልያን ይሆን እንዴ ኣለኝ። ወይ ኢትዮጵይ፤ ልጆችሽ ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም የሚለውን ዘፈን በየስብሰባው እና ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ደጋግመው በማቀንቀናቸው ዘፈኑ ራሱ ሰልችቶት ልጆቼ ሃያ ሶስት ኣመት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ተዘፈንኩላችሁ በሉ ኣሁን ሌላ ዘፈን ፈልጉ፤ እናንተን እንዳየሁዋችሁ ከሆነ ፤ እኔን እንደ ልደት ዘፈን በሻማ ከባችሁ ከማልቀስ ውጪ ምንም የምታመጡ ኣይመስለኝም፤ እና ጡረታዬን ጠብቁልኝና እስኪ ደሞ ይቺ የቀረችው ጊዜዬን እፎይ ብዬ ልኑር ኣለ ኣሉታዲያ ምን ይዋጠን፤ ኣንቺም ዜሮ ዜሮ እንዳንል ዘፋኙ እንጀራው ላይ የቅንድብ ጠጉር ተገኝቶበት ገበያውን ገደለው፤ ምን ይበጀን፤ ምን ይሻለን። ከማቀንቀን ውጪ ሌላ ነገር ለማድረግ ዛሬም በቅጡ የተዘጋጁ ኣይመስልም፤ በየ ዝግጅቱ ላይ ኣበው ኣባቶቻችንን በ ፩ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ከማሰብ ውጪ ሰምሮላቸው የተሻለ ነገር ሲያደርጉ ዛሬም ኣናይም።
ወደ ግራሃም ሃንኩክ ልመለስ…ኣዎ “The Ethiopian Slept…. A 1000 years forgetting the world by whom they were forgotten by.”
(ይህንን ፈረንጅኛ በኣማርኛ ብናራምደው ወይም ወደ ኣማርኛ ብንቀዳው) ኢትዮጵያዊያኖች ኣለምን ረስተው ኣለምም እነሱን ረስታ ለሺ ኣመተታት ኣንቀላፉ)ማለት ይሆናል። ታዲያ የዚህን ሰውዬ ኣባባል የነብይ ግብር ለመስጠት ኢስቲመስል ድረስ ዛሬ ሃገሪቱ ኣልጋ በኣልጋ ሆናላች። ኣዎ ለኢሃዲግ መራዡ (ይቅርታ መራሹ መንግስት ኣልጋ ባልጋ) ከዚህ ካለሁበት ኣማሪካም ይሁን ከኣውሮጳና ከሩቅ ምስራቅ ሃገራት ለሳምንታት ተንፍሰው መምጣት ለሚፈልጉት ኣቦ ሸማኔዎችም ኣልጋ በኣልጋ። ኣንቺ ሃገር ያለው ዘፋኝ ማን ነበር። ማንስ ቢሆን ምን ዋጋ ኣለው።
ታላቁ የኢሃዲግ መንግስት ከሚከበርበትና ከሚወደስበት የቀለበት መንገድ በተጨማሪ (ግድቢ ኣደይ ሃዳስ (የእማማ ሃዳስ ግድብ) (ለመሃል ኣገር ሰው ይስማማ ዘንድ የህዳሴውን ግድብ እየተባለ የሚነገረውን ሳይጨምር…) ከሚታወቅበት ኣንዱ እንቅልፍን ያለ ገደብ መፍቀዱ ነው። በነገራችን ላይ ያባይ ቦንድ የብዙ ኣባወራዎችን ትዳር በማፍረሱ ያባይ ቦንብ የሚል ስም ሊሰጠው እንደሆነ ጥቃት ያደረሱትም ጥቃት የደረሰባቸውም እየተናገሩ ነው:: የዚህ ያባይ ቦንብ የሽብር ጥቃት ሰለባ የሆኑት ሰዋች እንደሚሉት ከሆነ ኣማሪካ ቢሆን disability ክሌም ኣርገን እንደ ኣካፋ ዝቆ በሚያነሳ ኣውቶብስ ፈልሰስ እያልን እንኖር ነበር፤ እኛ ግን ከጥቃታችን ሳናገግም፤ ተገድቦ የት ያደርሰናል ያልነው ኣባይ ጉሮሮዋችንን ገድቦ ይስረቀረቃል ብለዋል። ለነገሩ ኣባይ ኣፍ የለውም እንጂ ቢጠይቁት የደደቢት ድርዬዎች ሃንግ ኣረጉኝ ብሎ ለኣውሽና ቦርከና ይናገር ነበር። ምን ያረጋል ታዲያ ኣባይ እንኩዋን ኣፍ ማደሪያ የለውም። ኣባይ በስምሽ ስንት ታሪክ ተሰራ። ትገርሚያለሽ፤ በቃ ግንዱ ኣልበቃ ብሎሽ የዲያስቦራን ዶላር ትጠርጊ ጀመር፤ ለነገሩ ኣንቺ ምን ታረጊ፤ ሆዶ ነው ቁም ነገረኛ ያረገሽ እዚህ ዛሬ ከኛ ጋ ተቃውሞ ማታ ደሞ እትዮጵያ ደውሎ፤ እንዴት ነው ቦንዱ፤ ግድቡ እያለቀ ነው፤ ምን ይጠበቅብኛል ጌቶች የሚለው፤ ይሄ ሁለት ቢላ ህዝብ ኣባይዬ በናትህ በጣና ይሁንብህ፤ ይህንንማ ውስክስክ ላፍልኝ፤ መቅኖ ኣስቀረው፤ ኣላርፍ ያለ ዲያስፖራ ያባይ ቦንድ ይገዛል ኣሉ።
የጎጃም ገበሬ እንኩዋ ዛሬ ቦንድ ካልገዛህ ኣባይ ኣጠገብ ዋሽንት መንፋት ኣትችልም ሊባል እንደሆነ ሰምቼኣለሁ፤ ዋሽንቱስ ይሁን፤ ቢያንስ ውሃ ሽንት ይፍቀዱላቸው።
በኣባይ ቦንድ መሸወዳቸው የገባቸው ኣንዳንድ ግለሰቦች በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ሲናገሩ እንደሰማነው ከሆነ “ቦምብን በቦንድ ስም መንግስት ሲያስታጥቀን ዝም ብሎ የተመለከተው ሰማያዊ ፓርቲ ይጠየቅልን ብለዋል።” ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው መንግስትም ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ኣፍራሽ ድርጊቱ ካልተቆተበ ኣሸባሪ ተብሎ ከነግንቦት ሰባትና መሰል ድርጅቶች ተርታ ሊፈረጅ እንደሚችል ኣስምሮበት ኣልፉዋል ይልቁንም ሰማያዊ ፓርቲ በኣባይ ቦንድ እና በመሰል ጉዳዮች ዙሪያ ኣስተያየት ከመስጠት ታቅቦ፤ ልማታዊ ጉዳዮች ላይ ቢያተኩር በማለት የመንግስት ቃል ኣቀባይ የሆኑት ኣቶ ኣከሌ ተናግረዋል (ኣከሌ ያልኩበት ምክንያት ከመለስ ሞት ወዲህ ሰው ኣጥፊ ብቻ ሳይሆን ኣላፊና ጠፊ እንደህነ ስለተረዳሁ ነው)፤ ኣያይዘውም ሰማያዊ ስሙ ከኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ጋም የተያያዘ ስለሆነ፤ የህገ-መንገስት የበላይነት እና የእምነት እኩልነት በሰፈነበት ሃገር ፓርቲያቸው ኢሃዲግ እንዲህ ኣይነት መድሎ ስለማይቀበል፤ ሰማያዊ በሚለው ላይ ተቀጽላ ጨምሮ (ሰማያዊ ኣል ረካት) ብሎ እንዲያስተካክለው እናሳስባለን፤ ይህ ባይሆን ግን ፤ ህገ መንግስቱ በሚፈቀደው መሰረት፤ ህጋዊ እርምጃ እንደምንወስድ እናሳስባለን። በነገረችን ላይ ይሄ የኣሸባሪነት ህግ ከመጠን በላይ መናፈስ በጀመረበት ዘመን የልጅ ልጃቸውን ማየት የቻሉ ኣያት፤ ልጃቸው እማ ልጄን ማን ልበልው ብላ ለጠየቀቻቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ፤ ማንስ ብትይው ምን ዋጋ ኣለው፤ ገና ሳይወልድ እኮ ነው መንግስት ስም ያወጣለት፤ ስለዚህ ኣድጎ ግራ ከሚገባው ኣንድ ፊቱን ኣሸብር በይው ኣሉዋት። ኣረ እቴ፦
በነገራችን ላይ የጎጃም ገበሬ ነው ኣሉ፤ ስለ ኣዲሱ የኣደይ ሃዳስ ግድብ ወይም ህዳሴ ግድብ ከጋዜጠኛ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፤ እናንተ የኢትዮጵያን ባህልና ወግ ለመናድ ስትታገሉ፤ ኣባይ ደሞ የኣማራ ኣፈርን ሲንድ፤ ነው የማወቀው፤ እንግዲህ ዛሬ ኣባይ ከዚህ ጸያፍ ድርጊቱ ታቅቦ፤ እንደ ሴተኛ ኣዳሪ እዚህም እዚያም ከማስካካት እናንተ ባበጃችሁለት ቦይ ለመንዶልዶል መወሰኑ ጥሩ ጅምር ነው፤ ዋናው ቁም ነገር ግን መንግስት ከዚህ ግድብ ምን ይማራል ነው፤ ይህ የሺህ ኣመት ቦዘኔ፤ ጨርቄን ማቄን ሳይል፤ ጉዋዙን ጠቅሎ እዚሁ የተፈጠረበት ሃገር ለመስተር መሞከሩ፤ መንግስትን ምን ያስተምረዋል፤ የገዛ ሃገራቸውን ኣንጡራ ሃብት ለባ፤ኣዳን የሚቸበችቡ ኣሻጥረኞች ከዚህ ምን ይማራሉ ነው። ብሎ ኣስተያየቱን ሰትቶ ኣልፎዋል።
ሲታረስ ሳያምር ሲታጨድ ሳያምር
ዋራን ኣሳመረው የድንጋይ ቤት ክምር
ያለው ማን ነበር
ሲነገር ሳያምር ሲወራ ሳያምር
ደለል ሻኛ ሆነው የጭቃ ቤት ክምር
ብለን ለኣባይ መሳ ግጥም ገጥመን እንለፋ።
እና ስለ እንቅልፍ ተመልሰን እናውራ….
እናላችሁ መተኛት ለሚፈልግ ከምግብና መጠጥ ሌላ ሁሉም ይሞዋላለታል። እንኩዋን ሰዉ ዛፍ እንኩዋ እንቅልፍ ለምዱዋል። መወዛወዝ የል፤ ቅርንጫፍ ማፋጨት የለ፤ ዘነበ ኣልዘነብ የለ፤ ከሰው ጉንጭ ውስጥ ገብቶ ለጥ። ማ ወንድ ነው የዘንድሮን ዛፍ የሚቀሰቅሰው። ስሙስ ቢሆን ኣሱም እንደ ቢዮንሴ ሄር ስታይለር …ተቀይሮ። ድሮ ኣባቶቻችን ሰለ ዛፍ ሲያወሩ፤ ዝግባ፤ ዋንዛ፤ ቀርቀሮ፤ ጥድ፤ የባህር ዛፍ፤ ወይራ፤ ኣር ስንቱ፤ የዘንድሮ ዛፍ ለስለስ ያለ ስም ነው ያለው፤ ለስለስ ያለ እጅም ነው የሚይዘው። የዘንድሮ ዛፍ ምንጣፍ ተነጥፎለት ነው ቤት የሚገባው እንጂ በኣህያ ጀርባ ተጭኖም ኣይደል። ከትግራይ ውጭ በኣራቱም ማእዘናት ይበላል፤ ኣወዳይ ወይም በፈረንጅኛው (I will die) ገለምሶ፤ በለጬ ፤ ጉራጌ ገለመኔ ነው ስሙ። የዚህ የእንቅልፋም ትውልድ ቀርቀሮና ዝግባ። ይሄ ትውልድ በእውነትም እንቅልፋም ነው።
ደጉ መንግስቴ በክርስትና ስሙ (የዘመናት ብሶት የወረሰው፤ ወይም የወረረው) (በዳቦ ስሙ ባለ ራእዩ መንግስቴ)… የኣቡነ ጴጥሮስን ሃውልት ኣፍርሶ (ነቅሎ)፤ ቁልቁል ሲንደረደር በተኛበት ቤቱ የፈረሰበት ሰው ነው ኣሉ እንዴ ይሄ ባቡር ሳይገባ ገጭቶ የጨረሰን ሲገባ ምን ልንሆን ነው ኣለ ኣሉ። ሲገባማ ምን ችግር ኣለው፤ ያባልነት መታወቂያ ከያዝክ እንቅልፍህን ትራንሰፈር ታደርገው ዘንድ በርህ ላይ ቆሜ እየጠበቑ ነው የሚል ኣይመስልሕም።
ባለ ራአይ ስል…. የቀድሞ የሳውዝ ኣፍሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ኔልሰን ማንዴላን የቀብር ስነ ስርኣት በተሌቪዥን ሲከታተል የነበረ ኣንድ ታጋይ (በሃደግ)ለማንዴላ እንደኛ ባለ ሯዩ መሪ የጎዳና ተዳዳሪዎችና ሴተኛ ኣዳሪዎች ያላለቁሱለት ለምንድን ነው ኣለ ኣሉ። ስላልወለዳቸው እናም ስላላገባቸው ልበልህ። ምን ልበል እኛ በህግ የተመዘገበ፤ ህገ መንግሱ የሚያውቃት ልጃቸው ቢሊየነሩዋን ሰማኸል መለስን ነበር፤ ታዲያ ጆቢራው ሲሞት ባንዴ (ባሌ ባሌ፥ ኣባቴ ኣባቴ ባዩ መብዛቱ) ድሮም ሾፌርና የእንትን ወንድ ይሉ ነበር ዘመዶቼ::
ማን ነበር ሎዚች ጦላ ሎጦሞቆ ሴት ሙተኛት ነበር ያለው። ኣይ ሃገር፤ ቡና ቤት ኣረጉሽ፤ ኣይ ትውልድ ቁመን ኣየንሽ።
ሲታረስ ሳያምር ሲታጨድ ሳያምር
ዋራን ኣሳመረው የድንጋይ ቤት ክምር
ያለው ማን ነበር
ሲፈጥረው ሳያምር
ሲገለው ሳያምር
ክፋት ግብር ሆነው የደደቢት ንስር።
ብዬ ለኣባባ መልስ እኔ ወዲ ሃድጊው በጎዳ ልጆች ስም ግጥም ባበረክትስ።
ቸር ይግጠመን
ኢትዮጵያ የብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ማቋቋም የሚያስፈልጋት ጊዜ ላይ ናት (ገለታው ዘለቀ)
ገለታው ዘለቀ
ባለፉት ጥቂት ተከታታይ ጽሁፎች ላይ እንደተወያየነው በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ውስጥ መግባት ኢትዮጵያን እንደገና ለማነጽ ኣማራጭ መፍትሄ ይሆናል። ታዲያ በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ላሉብን ውስብስብ ሁለንተናዊ ችግሮች ሁሉ መፍትሄ ይሆናል ማለት ሳይሆን ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሊፈቱ የሚገባቸውን ባህላዊ ማህበራዊ ችግሮች መስመር በማስያዝ በሂደት እየተፈቱ እንዲሄዱ ከማድረጉም በላይ ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት ደግሞ ቀጥተኛ ያልሆነ ኣስተዋጾ ስላለው ነው። በችግር ኣፈታት ጊዜ ከሚመጡት መፍትሄዎች መካከል የትኛውን ብናስቀድም ነው ሌላውን ችግርም ኣብሮ ሊፈታልን የሚችለው ብለንም እንጠይቃለንና በዚህ ረገድ በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ውስጥ መግባት ሌሎች መጋቢና ተለጣጣቂ ችግሮችን ለመፍታት ይጠቅማል ከሚል ነው።
ባለፉት ዘመናችን ያሉብንን ሃገራዊ ችግሮች ሁሉ ስንዘረዝር ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ምናምን እያልን ለያይተን እንዘርዝራቸው እንጂ ሁሉንም ችግሮች ለመፍታት የምንሄድበት መንገድ ግን ፖለቲካዊ ይዘት ባለው መንገድ ነው። ፖለቲካዊ ችግሮቻችንን ፖለቲካዊ ይዘት ባለው መንገድ፣ ማህበራዊውን ደግሞ ማህበራዊ በሆነ መንገድ፣ ኢኮኖሚውንና ሌሎቹንም እንደ ተፈጥሯቸው ከመፍታት ይልቅ ለሁሉም ችግር ፖለቲካን የችግር መፍቻ ቁልፍ ኣድርገን መውሰዳችንና የፖለቲካው ጣልቃ ገብነት በማየሉ ችግሮቻችን መፍትሄ ሳያገኙ እንዲቆዩ ያደረገ ይመስላል። ለማህበራዊ ችግሮቻችን ሁሉ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ ባህላዊና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዩችን ከባህርያቸው ኣንጻር ለመፍታት ብንጥር ችግሮቻችን ኣሁን ያሉትን ያህል ኣይበዙም ነበር። በኣሁኑ ሰዓት ፖለቲካው ማህበራዊውን ህይወታችንን የነካበት ምክንያት የማያገባው ውስጥ ገብቶ በመገኘቱ ነው።
በዛሬው ውይይታችን የምናነሳው ጉዳይ በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ስንል ኣንድ ቁልፍ ቃል በዚህ የመወያያ ርእስ ውስጥ ይሰመርበታል። ይህም ስምምነት የሚለው ነው። ስምምነት ስንል ወይም እንዴት ኣድርገን ነው ወደ ስምምነት የምንመጣው ስንል በዚህ ኣገባብ ሶስት ጉዳዩችን ይዳስሳል።
1. ያለፈውን ታሪካችንን እንዴት ኣድርገን ነው ወደ ስምምነት የምንመጣው? ታሪካዊ ግድፈቶችን እንዴት እንፍታቸው? እንዴትስ እንያቸው? በሚለው ዙሪያ ያጠነጥናል::
2. ችግሮቻችን ታሪካዊ ብቻ ሳይሆኑ ኣሁን ድረስ ስላሉ እነዚህን ችግሮች እንዴት እንያቸው? እንዴትስ እንዳይቀጥሉ ማድረግ እንችላለን? የሚለውን ይይዛል
3. ሁላችን የምንፈልጋትን የወደፊት ኢትዮጵያን እንዴት ኣድርገን ነው በጋራ ጥሩ መሰረት ጥለን መጻኢ እድሏን የምናበጀው? የሚለውንም ይይዛል።
እንግዲህ በነዚህ ከፍ ብለን በዘረዘርናቸው ኣሳቦች ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ ያስፈልጋል ስንል በምን መንገድ ነው የምንወያየውና የምንስማማው? የትና በማን ኣማካኝነት ይፈጸማል? የሚሉ በጣም ተግባር የናፈቃቸው ጥያቄዎች መነሳታቸው ኣይቀርም። ምክንያቱም ሃገራችን ውስጥ ላሉት ችግሮች የመፍትሄ ኣሳብ ኣይደለም የጠፋው:: በየጊዜው በቡድንም በግልም ጠቃሚና የሃገርን ችግር ሊያቃልል የሚችል ኣሳብ ይመጣል:: ነገር ግን እነዚህን የመፍትሄ ኣሳቦች የሚያደራጅና መልክ የሚያስይዝ ባለመኖሩ እንዲሁ ኣንዱን እያነሳን ኣንዱን እየጣልን እንኖራለን።
በዛሬው ውይይታችን ስምምነት የሚለውን ኣሳብ እንዴት ልናመጣው እንደምንችል ተግባራዊ ሃሳቦችን እናነሳለን። እንግዲህ ወደ ነጥባችን እንውረድና ስምምነትን ልናመጣበት ከምንችልባቸው ዘዴዎች ኣንዱ የብሄራዊ እርቅ ኮሚሽንን ኣቋቁሞ በመስራት ነው። ይህ ኮሚሽን ኣሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ቢደግፈውና ኣብሮ ቢሳተፍ እሰየው ካልሆነም ግን ከመንግስት እውቅና ውጭ መቋቋም ይችላል። መንግስት ደገፈው ኣልደገፈው የሚያመጣው ችግር ኣይኖርም። በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ሁዋላ እንወያያለን። ለኣሁኑ ስለ ብሄራዊ እርቅ መሰረታዊ ጉዳዮችን ኣንስተን እንወያይ።
ስለ ብሄራዊ እርቅ ምንነትና ይዘት እንዲሁም ኣፈጻጸም ስንወያይ ብሄራዊ እርቅን የምናየው ባለፈው በተወያየንበት በስምምነት ላይ በተመሰረተ የባህል ውህደት ጽንሰ ሃሳብ ማእቀፍ (framework) ውስጥ ነው።
የብሄራዊእርቅምንነት ይዘትና ኣፈጻጸም
ከሁሉ ኣስቀድመን ብሄራዊ እርቅ የሚባለው ጽንሰ ሃሳብ በኢትዮጵያ ሁኔታ ምን ማለት እንደሆነ ልንበይነው ይገባል። ብሄራዊ እርቅ በኣለማችን ታሪክ ውስጥ በብዙ ኣገሮች የተፈጸመ ሲሆን የእርቁ ትርጓሜና ኣፈጻጸም እንዲሁም ግቦች ሁሉ ሊለያዩ ይችላሉ። እኛ ኢትዮጵያዊያን ወደ ብሄራዊ እርቅ ለመግባት መጀመሪያ ብሄራዊ እርቅ በኢትዮጵያ ሁኔታ (context) ምን ማለት እንደሆነ በሚገባ ካልተረዳን ብሄራዊ እርቁ ግቡን ላይመታ ይችላል። በመሆኑም ብሄራዊ እርቅ ማለት ምን ማለት ነው? የሚለውን ጉዳይ ኣንስተን በሚገባ እንወያይ። ሃሳባችንን ለማፋፋት ብሄራዊ እርቅን ከኣንዳንድ ሃገሮች ታሪክ ኣንጻር በመጀመሪያ እንመልከት። ለምሳሌ ያህል በኣውስትራሊያ ውስጥ የብሄራዊ እርቅ ጉዳይ ተነስቷል። እንደሚታወቀው ከታላቋ ብሪታኒያ የኣስራ ስምንተኛው ክፍለዘመን ሰፈራ ፕሮግራም በፊት ኣውስትራሊያ በነባር(indiginious) ህዝቦች የተያዘች ኣገር እንደነበረች ይታወቃል። በሰፈራው ጊዜ በነባሮቹ ህዝቦች ላይ የመፈናቀል፣ የማንገላታት ወንጀሎች ተፈጽመዋል። ዛሬ የኣውስትራሊያ መንግስት ያን የተፈጸመ ታሪካዊ ስህተት ኣመርቅዞ እንዳይቆይ የወሰደው ርምጃ ብሄራዊ እርቅ ማድረግ ሲሆን ከ 1998 ዓ.ም ጀምሮ መንግስት የብሄራዊ እርቅ ወይም (National sorry day) ኣውጆ በየዓመቱ እየታሰበ ይገኛል። የዚህ የይቅርታ ቀን ኣዋጅ የሚያሳየው ነገር ላለፉት ስህተቶች ሃላፊነት የሚወስድ ኣካል መገኘቱንና የነበረውን ግፍ እውቅና መስጠት መቻላቸውን ለወደፊቱም እንደዚያ ኣይነት ግፍ እንዳይፈጸም ዋስትና መስጠታቸውን ነው። የኣውስትራሊያ ችግር እንደኛ በሶስት መንገድ ላይታይ ይችላል። ይቅርታው ግን ለስንት ኣመት እንደሚደረግ ኣይታወቅም። ዋናው ግን በነባሩ ህዝብ ዘንድ የነፍስ ጽዳት ለማምጣት የታሰበ በመሆኑ ብሄራዊ እርቁ ለኣውስትራሊያውያን ከፍተኛ ጠቀሜታ ኣለው። የነበረውን ታሪካዊ ችግር እውቅና ሰጥቶ ይቅርታ ማወጁ የኣውስትራሊያን ህዝብና መንግስት ልበሰፊነትና ኣርቆ ኣሳቢነት ያሳያል። ነባር ህዝቦችም በዚህ የሚረኩ ይመስለኛል። ከዛ ውጭ ኣፈታሪክ እንደሚናገረው ራሳቸው ነባር ህዝቦችም ከሌላ ክፍለ ዓለም መጥተው የሰፈሩ ናቸው። ዋናው ጥያቄያቸው በሰፈራው ወቅት የነበረው ግፍና በደል ሲሆን እነሆ ዛሬ ተባብረው ዴሞክራሲያዊ መንግስት በመመስረታቸው ታሪክን ወደ ሁዋላ ኣይቶ ለችግሮች እውቅና ለመስጠት ችለዋል።
ደቡብ ኣፍሪካን ደግሞ እንይ። በደቡብ ኣፍሪካም እንደዚሁ ታሪካዊ የሆነ ብሄራዊ እርቅ የተካሄደባት ኣገር ስትሆን ከኣፓርታይድ ኣገዛዝ ለመላቀቅም ሆነ ከተላቀቀች በሁዋላ ደቡብ ኣፍሪካን በከፍተኛ የመንፈስ ልእልና ሲመራ የነበረው የብሄራዊ እርቅ ስሜት ነው። በደቡብ ኣፍሪካ ብሄራዊ እርቅ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱት መካከል Nelson Mandela ኣውራ ናቸው። በኔልሰን ማንዴላ የተመራው ደቡብ ኣፍሪካን እንደገና የማነጽ ስራ ሲጀመር ኣገሪቱ ያለፈችበትን መራራ ችግር ለመፍታት የተጠቀመችው ዘዴ በሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ (Restorative justice) እና ቀስ እያለ በሚያድግ ዴሞክራሲ ቁስልን ማከምና የወደፊቷን የሁሉም የምትሆንን ደቡብ ኣፍሪካን መገንባት ይመስላል።
ደቡብ ኣፍሪካ ከኣፓርታይድ እንደተላቀቀች ወደ ሪትሪቢዩቲቭ ጀስቲስ (Retributive juctice) ኣተኩራ ቢሆን ምናልባትም ውጤታማ ኣትሆንም ነበር። ዋናው ጉዳይ ግን ደቡብ ኣፍሪካ ውስጥ የኣፓርታይድ ገዢዎች ለነበረው ችግር ሃላፊነት የመውሰድና ብሄራዊ እርቅን በሪስቶሬቲቭ ጀስቲስና በዝግ እያለ በሚያድግ ዴሞክራሲ ለመፍታት ፈቃደኛ በመሆናቸው የጥፋትና የሞት መላእክን ከደቡብ ኣፍሪካ ሊያባርሩት ችለዋል። ታላቁ የብሄራዊ እርቅ መሪ ኔልሰን ማንዴላም በዚህ ረገድ የተጫወቱት ሚና ታሪክ ሁሌ ሲዘክረው ይኖራል።
የሩዋንዳን ጉዳይም እናንሳ። ሩዋንዳ በዚህኛው ክፍለ ዘመን የዓለምን ህዝብ ያስደነገጠ ወንጀልን ካስተናገደች በሁዋላ ወንጀሉ ጋብ ሲል የወደፊት ኣቅጣጫዋ ግራ ያጋባት ኣገር ነበረች። ለኣንድ መቶ ቀናት በየቀኑ ስምንት ሺህ ሰዎች፣ በየሰዓቱ ከሶስ መቶ ሰላሳ ሰዎች በላይ ያለቁባት ሃገር የወደፊት እጣ ፈንታዋን ለማሰብ በርግጥም እጅግ ከባድ ስራ ነበር። በርግጥ ሩዋንዳ ያ ወንጀል ጋብ ሲል ለወደፊት እጣፈንታዋ ወዲያው ኣዋጭ መስመር መስሎ የታያት ብሄራዊ እርቅ ማውረድ ቢሆንም ብሄራዊ እርቁ በሩዋንዳ ሁኔታ ምን መልክ ይያዝ? በምን መልኩ ይፈጸም? የሚሉት ጥያቄዎች ግን በጣም ሊከብዷት የሚችሉ ጉዳዩች ነበሩ። በኣንዳንዶች ዘንድ ኣጥብቆ ይቀነቀን የነበረው ጉዳይ ብሄራዊ እርቁ በሪትሪቢዩቲቭ ጀስቲስ ኣማካኝነት ሊፈጸም ይገባዋል የሚል ነበር። ሁላችን እንደምናውቀው ሪትሪቢዩቲቭ ጀስቲስ ማለት ለወንጀለኛው ተገቢውን ቅጣት በመስጠት የተበዳይን ነፍስ ማጽዳት ወይም ማርካት ማለት ሲሆን ሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ ደግሞ የሚያተኩረው ወንጀለኛውን በመቅጣት ላይ ሳይሆን ተበዳዩን በመካስ ላይ ያተኮረ የፍትህና የእርቅ ማውረጃ ዘዴ ነው። ታዲያ ኣንዳንድ ሩዋንዳዊያን ሪትሪቢዩቲቭ ጀስቲስ ነው ፈውስ የሚያመጣልን ሲሉ በርግጥ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ሳያገኙ ኣልቀሩም። ምክንያቱም ወንጀሉ የተፈጸመው በኣጭር ጊዜ በመሆኑ፣ ወንጀሉ ግድያ በመሆኑ፣ ገዳይና የሟች ቤተሰብ ጎረቤት በመሆናቸው፣ ኣሰቃቂ ወንጀል በመሆኑ ሪትሪቢዮቲቭ ጀስቲስ ተገቢነው እንዲሉ የገፋፋቸው ይመስላል። ይሁን እንጂ በኣንድ መቶ ቀናት ላለቀው ስምንት መቶ ሺህ ህዝብ ገዳዩችና ለገዳዩቹ ተባባሪዎች ፍርድ ለመስጠት ሩዋንዳ ኣቅም ኣልነበራትም። ሩዋንዳ በዚያን ወቅት ላለቁት ስምንት መቶ ሺህ ቱትሲዎችና ለዘብተኞች ወደ ኣንድ መቶ ሺህ ወንጀለኞችን ለፍርድ ኣቅርባ መቅጣት ከፈለገች ኣጠቃላይ የፍርዱ ሂደት ወደ ኣንድ መቶ ኣመት ይፈጅባት ነበር የሚሉ ወገኖች ኣሉ። ሪስቶረቲቭ ጀስቲስን ተጠቅማ ችግሯን ለመፍታት ብትሞክር ደግሞ ገዳይና ሟች ጎረቤታም በመሆናቸው፣ የሟች ደም ገና ስላልደረቀ በርግጥ የሃገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ሌላ ችግር ውስጥ መውደቁ ሌላ ኣሳብን ያመጣባት ትመስላለች። ሩዋንዳ የነበረችበት መስቀለኛ መንገድ ኣስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የጣላት በመሆኑ ሁለቱንም የፍትህ ኣሰጣጥ ዘዴዎች ኣደባልቃ እንድትሄድ ሳያስገድዳት ኣልቀረም። በመሆኑም ባህላዊ የጋካካ ፍርድ ቤቶችን በማቋቋም የተወሰነውን ችግር በዚህ በሪትሪቢዩቲቭ ጀስቲስ የተወሰነውን ደግሞ ዝግ እያለ በሚያድግ ዴሞክራሲና በሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ ይፈታል እያለች እየደለለች ማርገብ ችላለች። ከሁሉ በላይ ግን ሩዋንዳ ወደ ዘጠና በመቶ የሚሆነው ህዝብ ክርስቲያን በመሆኑና ኣብያተ ክርስቲያናት የሚሰብኩት የይቅርታና የምህረት ትምህርት የሩዋንዳን ችግር በሪስቶሬቲቭ ፍትህ ለመፍታት ከፍተኛ ኣስተዋጾ ሳያደርግ ኣልቀረም። በኣጠቃላይ የሩዋንዳ ችግር ውስብስብና ኣስቸጋሪ በመሆኑ ሁለቱም የፍትህ ኣሰጣጥ ዘዴዎች ተግባር ላይ የዋሉ ይመስላሉ።
ለኣብነት በየሃገሩ የተፈጸመውን ወንጀል እያነሳን የተወያየነው ችግር በየቤቱ ኣለ፣ ይሁን እንጂ ሁሉም ሃገር ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረገ ነው ኣገር የቆመው ለማለት ነው። ወደኛው ኣገር እንመለስና ብሄራዊ እርቅ በኢትዮጵያ ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት።
በኢትዮጵያ ውስጥ ሊኖር የሚችለውን የብሄራዊ እርቅ ይዘት ለማየት መጀመሪያ ስለ ኣለፈው ታሪካዊ ግድፈቶች ማንሳት ተገቢ ነው። ከፍ ሲል እንዳልነው በኣውስትራሊያ ውስጥ ለነበረው ግፍ ሃላፊነት የሚወስድ እውቅና የሚሰጥ ኣካል ተገኝቱዋል። ወደኛ ሃገር ስንመጣ ላለፉት በደሎች እውቅና ለመስጠትም ሆነ ኣንድ ኣካል ለጥፋቱ ሃላፊነት ለመውሰድ የምንችልበት ሁኔታ ጠፍቷል። ይህ የሆነበት ምክንያት ሁሉም የባህል ቡድን በየፊናው ባለፉት ስርዓቶች ተጎድቻለሁ ባይ በመሆኑ ነው።
በኣጼ ምኒልክ ጊዜ የጠፉ ጥፋቶች ካሉ ለነዚያ ጥፋቶች የኣማራውን ህዝብ ሃላፊነት ውሰድና ይቅርታ በል የሚል ኣካል ቢነሳ ኣማራው ለራሱ ተበድያለሁ ባይ ነው። በፊውዳሉ ስርዓት በጭሰኝነት፣ በባርነት መከራየን ኣይቻለሁ:: በወቅቱ የተጠቀሙት ጥቂት ፊውዳሎች ናቸው:: ተውኝ እባካችሁ ይላል። በኣጼ ሃይለስላሴ ዘመንም ቢሆን የወሎ ርሃብ ሲመጣ ሃይለስላሴ ዓለም እንዳይሰማ ኣድርገው በዚያ ደረጃ ጨክነው ኣስጨርሰውኝ የለም ወይ? ደርግ ኣማራ ነው ካላችሁ ደግሞ የጎንደርንና የወሎን ወላድ እምባ ኣታዩም ወይ? ወዘተ. እያለ እያነባ ባለፉት ስርዓቶች የተጎዳውን ይቆጥራል። ኦሮሞው በበኩሉ በዚህኛውም ባለፈውም መንግስት ተነጥየ ተጎዳሁ፣ ባህሌ፣ ማንነቴ ተጎዳ ብሎ እያነባ ይናገራል፣ ትግሬው በበኩሉ ባለፈውም ሆነ ኣሁን የተመቸኝ ነገር የለም፣ የውስጥ ችግሬን እኔ ነኝ የማውቀው ተለይቼ ተበድያለሁ እያለ ያነባል፣ የደቡብ ህዝቡ ተበድያለሁ የኔን መከራ ማን ባየው እያለ እያነባ ይናገራል፣ ሱማሌው የኔ መከራ መቼ ነው የሚያቆመው? መከራየን እያየሁ ነው እያለ ያነባል። ጋምቤላው፣ ኣፋሩ ሁሉም በተናጠልም በቡድንም ተጎድቻለሁ እያለ ያነባል። ታዲያ እንዲህ በሆነባት ኣገር ብሄራዊ እርቅ ምን መልክ ይኖረዋል የሚለው ጥያቄ ላይ ነው መወያየት ያለብን።
በመጀመሪያ ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን ያለፉ ታሪካዊ ችግሮች ኣጥንተን መፍትሄ ለመስጠት የታሪክ ተዓማኒነትም ችግር ኣለብን። በተለይ በኣሁነ ወቅት ፖለቲካው ከፋፍሎ የመግዛት ዘዴን የሚጠቀም በመሆኑ ኣንዳንድ በፈጠራ የሚጻፉ ታሪኮች ያለፈውን ታሪካችንን በሚገባ ኣይተን ብሄራዊ እርቅ ለማምጣት እንቅፋት ነው። የሆነ ሆኖ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ላለፈውም ሆነ ኣሁን ላለው ግፍና በደል ኣንድ ቡድን እንደ ቡድን ሃላፊነት ወስዶ ይቅርታ የሚልበት ሁኔታ የለም። በደቡብ ኣፍሪካም ሆነ በኣውስትራሊያ ወይም በሌሎች ኣገሮች እንደተፈጠረው ኣይነት ሃላፊነት ወስዶ የቡድኖችን እንባ የሚያብስ ጠፋ። በመሆኑም የኢትዮጵያ ምሁራን በዚህ ኣስቸጋሪ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ብሄራዊ እርቅ ማለት ምን ማለት እንደሆነና ሁላችንን የሚፈውስ ኣሳብ በግድ ኣምጠው ሊወልዱ ይገባል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳየው ቡድኖች እንደቡድንም በጅምላም ባለፈው ጊዜ ለደረሰባቸው በደል ሁሉ ያለፈውንና ኣሁን ያለውን ስርዓት የታሪክ ተጠያቂ ማድረጉ ኣንዱ የስምምነቱ ኣሳብ ወለል ቢሆን መልካም ነው። ይሁን እንጂ ላለፉት ችግሮቻችን ቡድኖች እንደ ቡድን ተጎዳሁ የሚሉት ካለ ለዚያ ቡድን ጉዳት እውቅና መስጠት ኣንዱ የስምምነቱ ኣካል ሊሆን ይገባል። ኣንድ ቡድን ተጎዳሁ ተጎድቼ ነበር ሲል የለም ያንተ ጉዳት ትንሽ ነው የኔ ይበልጣል ማለቱ ብሄራዊ ፈውስን ኣያመጣም።ሰው ህመሙን የሚያውቀው ራሱ ነው። በመሆኑም ቡድኖች የተጎዳነው ኣለ ሲሉ ማዳመጥና ሃዘንን መጋራት ለችግር እውቅና መስጠት ነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ መሰረቱ። ኦሮሞው ኣጼ ምኒሊክ ጎድተውኛል ካለ ሌላው ብሄር ልክ ኣይደለም ኣልጎዱህም ማለቱ ለብሄራዊ እርቁ ኣይጠቅመንም። ኣንዱ ዜጋ ኣጼ ምኒሊክ ካጠፉት ጥፋት ይልቅ የሰሩት ጀብዱ በተለይም ኢትዮጵያን ከውጭ ወራሪ ለመመከት ያደረጉት ተጋድሎ ከበለጠበት ቢወዳቸው ቢፎክርላቸው ሌላው ኢትዮጵያዊ መበሳጨትና ጥል ውስጥ መግባት የለበትም። ኣንድ መሪ ለኣንዱ ኢትዮጵያዊ ተወዶ ለሌላው የሚጠላ ቢሆንም ከዚህ ልዩነታችን ጋር ኣብረን መኖር እንችላለን። ኢትዮጵያዊ ለመሆን ሁሉ ሰው ኣጼ ምኒሊክን መውደድ ኣለበት ማለት ኣይደላም።ፕሬዚደንት ኦባማንና ፕሬዚደንት ቡሽን የሚወድም የሚጠላም በሰላም እንደሚኖረው እኛም ከልዩነት ጋር መኖርን መልመድ ያስፈልገናል።
ኣሁን እኛ ጋር ያለው የኮሙኒኬሽን ችግር ይመስላል። የኮሙኒኬሽን ችግሮች ምንጫቸው የእውነት መዛነፍ (distortion of truth) እንዲሁም የማንነት ፖለቲካ ውጤቶች ስለሆኑ ለነዚህ ችግሮች ራስን ሰለባ ኣለማድረግ ነው።በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ ዋናው መሰረት እርስ በርስ መረዳዳት(understanding eachother) ነው ማለት ነው። ያለፈውን ህመማችንን በመደማመጥ ነው ልንፈታው የምንችለው። ችግራችንን ስንገልጥ የለም ያንተ ቁስል ትንሽ ነው የኔ ነው ትልቁና ኣንተ ስለ ብሶትህ ኣታንሳ ኣይባልም። ቢሆን ቢሆን ራስን ከውጭ ወደ ውስጥ ከውስጥ ወደ ውጭ የማየት ልብ ቢኖረን እሱ ነው ያለፈውንና ኣሁን ድረስ የቀጠለውን ችግራችንን የሚፈታው። በኣሁኑ ሰዓት እኔ ኦሮሞ መሆኔ ቀርቶ ትግራይ ሆኘ ብፈጠር ምን ይሰማኝ ነበር? ምን እሆን ነበር? ብሎ ቢያስብ በኣንጻሩ የትግራይ ህዝብ ኦሮሞው ኣማራው ተለይቼ ተጎዳሁ ሲል በኣሁኑ ሰዓት እኔ ኦሮሞ ሆኘ ተፈጥሬ ቢሆን ምን ይሰማኝ ነበር? የሚል ከፍ ያለ መረዳት (understanding eachother’s pain and understanding each other’s feelings) በተለይ በሌሂቁ በኩል ቢታይ ነው የብሄራዊ እርቁ መሰረቱ የሚጠብቀው። ኣንድ ሰው ጉዳቴ ከፍተኛ ነው ሲል የለም ያንተ ትንሽ ነው የኔ ነው ትልቁ ጉዳት ወደ ማለት ማዘንበላችን የኮሙኒኬሽን ችግር ያመጣብናል። እውነቱን እንነጋግር ከተባለ እኛ ኢትዮጵያዊያን ያለፈውን ችግር በብሄራዊ ይቅርታ ለመዝጋት የገጠመን ችግር ይሄው የኮሙኒኬሽን ችግር ነው። ያለመደማመጥና ህመምን ለመካፈል መድረክ ማጣት ትልቅ ችግሮች ሆነዋል። ሌላው ደግሞ ቅድም እንዳልኩት ያለፈውን ችግራችንን በብሄራዊ እርቅ ለመፍታት የነበሩትን በደሎች ወደ መድረክ ኣምጥቶ እውነትን ለመግለጥ ኣሁን ያለው መንግስት ታሪክን ስላቆራፈደውና ብርታትንም ሆነ ድካምን ከቡድን ማንነት ጋር እንድናያይዝ የሚገፋ ነገር በመኖሩ በከፍተኛ ሁኔታ እውነትን የማግኘትና የመዋጥ ችግር ይገጥመናል። በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያን ኣዳዲስ በሚወለዱ ታሪኮች ሳንደነብር ከስሜት በላይ ሆነን እርስ በርስ በመረዳዳትና ኣለ ለተባለው ችግር እውቅና በመስጠት ነገሩን ማርገብ ይጠበቅብናል።ከሁሉ በላይ ግን ኢትዮጵያ ያለፈውን ችግር ልታይበት የምትችልበት ኣንድ ሌላ ትልቅ ነገር የዛሬው ይዞታዋ ነው። በፊት የነበሩ ማህበራዊና ፓለቲካዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ኣሁን ድረስ እየተንከባለሉ መጥተው ስለሚገኙ ኣሁን ያለውን በቡድኖች መካከል ያለውን ክፍተት በሪስቶሬቲቭ ፍትህ ልትፈታው ይገባታል። በትምህርት፣ በፖለቲካ ተሳትፎ በባህልና በቋንቋ ኣካባቢ ያለውን ችግር ኢትዩጵያ ለመፍታት ስምምነት ውስጥ መግባት ኣለባት። ይህ ስምምነት ነው ኣንዱ የብሄራዊ እርቁ ይዘት። ሪስቶሬቲቭ ፍትህ ስንል በማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ይሁን ከፍ ሲል በገለጽናቸው ሁኔታዎች የተጎዱ ኣካባቢዎችን በኣፌርማቲቭ ኣክሽን ዘዴዎች ለመፍታት ስምምነት ላይ መጀመሪያ መድረስ ኣለብን። ይህ የብሄራዊ እርቁ ሰነድ የሚይዘው ኣንዱ ጉዳይ መሆን ኣለበት።
በመሆኑም ኢትዮጵያ በስምምነቱዋ ወቅት የምታካትታቸው ጉዳዩች በግልጽ መጀመሪያ መቀመጥ ኣለባቸው። ቡድኖች እንደ ቡድን ሁሉም ተበድለዋልና ብሄራዊ እርቁ ሁሉንም ሊክስ የሚችልና ኮሙኒኬሽንን የሚያዳብር መሆን ኣለበት። በዓለማችን የሚነሱ ጦርነቶች ኣብዛኛዎቹ ማለት ይቻላል ምክንያታዊነት ያላቸው ኣይደሉም ኣብዛኛዎቹ ከኮሙኒኬሽን ችግር ጋር የተያያዙ ናቸው። ኣንዳንዴ ቡድኖች የተጣሉበትን ሁኔታ በውል ሳያውቁት ብዙ ይዋጉና ብዙ ሰው ካለቀ በሁዋላ ይታረቃሉ። የሚገርመው ሲታረቁና ስሜታቸው ሲረጋ የከፈሉት ዋጋ እንዲሁ ሜዳ ላይ ሆኖ የሚያገኙበት ጊዜ ይኖራል። በመሆኑም ብሄራዊ እርቁ በቡድኖች መካከል ያለን ኮሙኒኬሽን ለማስተካከል መላ ሊወልድ ይገባዋል።
ከፍ ሲል እንዳልነው ብሄራዊ እርቅ በኢትዮጵያ የሚኖረው መልክ ሁሉንም በመካስ ላይ ሁሉንም ችግሮች እውቅና በመስጠት ላይ የተመሰረተ መሆን ይኖርበታል። በተለይ ያለፈውን ችግራችንን ለመፍታት ችግሩ ከኮሙኒኬሽንና ከስሜት ሃያልነት ጋር የተያያዘ በመሆኑ በረጋና በሰከነ መንፈስ ዜጎች ያለፈውን ችጋራቸውን በጋራ እውቅና ሰጥተው ሲንከባለል ለመጣው ችግር ደግሞ ኣፈርማቲቭ ኣክሽንስና ሌሎች የርስበርስ የመካካሻ ዘዴ ተጠቅመው ፈውስን ማውረድ ኣለባቸው። እንዲህ ስናደርግ ብሄራዊ እርቁ ሁለቱን ርምጃዎች የሚራመድ ሲሆን ሌላ ሶስተኛ ጉዳይ ደግሞ በውስጡ ሊያቅፍ ይገባዋል :: ይህ ሌላው የእርቁ ፓኬጅ የሚይዘው ደግሞ ኣዲሲቷን ኢትዮጵያን እንደገና ለማነጽ እንዴት ኣብረን እንውጣ? እንዴት የጋራ ቤታችንን ኣብረን እናጥብቅ የሚለውን ያካትታል:: በመሰረቱ ይሄ ጉዳይ ቀላልም ከባድም ነው። ቀላል የሆነበት መንገድ በኣብዛኛው ፖለቲከኛና ሌሂቅ ዘንድ ቅንነቱ ካለ መፍትሄው ቀላል ስለሆነ ሲሆን ጠማምነቱ ካለ ደግሞ ፈተና ነው።
በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ብሄራዊ እርቅን በኢትዮጵያ የሚያየው እንደዚህ ነው። በዚህ ጽንሰ ሃሳብ መሰረት ብሄራዊ እርቁ ሪስቶሬቲቭ ጀስቲስን መሰረት ያደረገና በሚያድግ ዴሞክራሲ ችግሮችን ሊፈታ የሚችል ስምምነት ማለት ነው። ይህ ማለት ግን ሪትሪቢዩቲቭ ጀስቲስ ቦታ የለውም ማለት ኣይደለም። በኣሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ሙስናና ከፍተኛ ወንጀል እየፈጸሙ ያሉ ሰዎች ይህንን ኣሳባችንን እያዩ እንደ ጅልነት ኣይተው ከስልጣን እስኪወርዱ በግፋቸው እንዲቀጥሉ በር ኣይከፍትም።
የብሄራዊ እርቅ ሰነዱ እንደነዚህ ኣይነት ሰዎችን በቡድን እያየ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ወደ ፍርድ ሊያመጣቸው መቻሉ ኣያጠያይቅም። እንደ ቡድን እንደ ሃገር ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻችንን ዝግ እያለ ሊሰራጭ በሚችል የሪዲስትሪቢዩሽን ዘዴ ተመጣጣኝ እድገት ለማምጣት መስማማት፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎን ከባህላዊ ውህደት ስምምነት ኣንጻር ኣይቶ ከብሄር ፖለቲካ ኣውጥቶ በኣንድ ብሄራዊ ማንነት ስር ለመገንባት መስማማት፣ ዋና የሃገሪቱን ቋንቋዎችን ቁጥር መጨመር ኣጠቃላይ ፈውስን ለማምጣት ይጠቅማል።
ኢትዮጵያ ሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ ላይ እንድታተኩር የሚያደርጋት ለዘላቂ ሰላምና ልማት ኣንድነት የሚረዳት ሲሆን ይህ የፍትህ ኣሰጣጥ ዘዴ በኢትዮጵያ ቡድኖች ዘንድ የተባረከና የሚበረታታ ነው። የኦሮሞ ስርዓትን ብናይ ለሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ ትልቅ ቦታ ኣለው። ይቅር ማለትን፣ በዳዩን ከመቅጣት ይልቅ ተበዳዩን መካስን ያበረታታል። ኣማራው ኣካባቢ ያለውን የሽምግልና ስርዓት ስናይ በኣብዛኛው ሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ የሚበረታታበት ሁኔታ ኣለ። በደቡብ፣ በምስራቅ በተለይም በሶማሌ ክልል ይህ የፍትህ ስርዓት ከፍተኛ ተጽእኖ ኣለው።
የሃይማኖት ዳራችንም ቢሆን ወደ መቶ ፐርሰንት የሚጠጋው ህዝብ ሃይማኖተኛ በሆነበት ኣገርም ይህ የፍትህ ስርዓት ሊሸከመው የሚችል በተፈጥሮው የተደራጀ ተቋም በመኖሩ ተመራጭ እንዲሆን ያደርገዋል።
ሌላው ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ባለፈው ጊዜ በግድ በሆነ ኣሲምሌሽን ጠፉ የሚባሉ ባህሎች ካሉ እነሱን የማስመለስ (Restoration and revival) ስራ ለመስራት መስማማቱ ነው ኣንዱ የእርቁ ሰንድ የሚይዘው ጉዳይ። የጠፉና በመጥፋት ላይ ያሉ ጠቃሚ ባህሎች ካሉና ቡድኖች የሚቆጩባቸው ከሆነ የማስመለስ ፖሊሲ ኣውጥቶ ቡድኖችን ሁሉ ተባብሮ ለመካስ ኪዳን መግባት። ቡድኖች ኣጣናቸው የሚሉዋቸውን በሙሉ ለማስመለስ ባይቻልም ኣብዛኛውን በመመለስ የቡድኖችን ልብ ማሳረፍ ይቻላል።
ሌላው የብሄራዊ እርቁ ሰነድ ሊይዘው የሚገባው ጉዳይ ለወደፊቱዋ ኢትዮጵያ የሚሆን ኣስተዳደራዊ ባህልን የመገንባት ስምምነት ሲሆን ይህም ዴሞክራሲ ነው። ቡድኖች በመጀመሪያ ዴሞክራሲ ከኣሁን በሁዋላ ያስተዳድረን መንግስታት ቢቀያየሩም ዴሞክራሲ ግን የጋራ ባህላችን ይሁን የሚል ስምምነት ውስጥ ሊገቡ ይገባል። ይህ ኣስተዳደራዊ ባህል የጋራ የሁላቸው በመሆኑ ወደፊት ለህይወታቸው መሪ ይሆናል ማለት ነው።
ሌላው መሰመር ያለበትና የስምምነቱ ኣንዱ ኣካል ሊሆን የሚገባው ለመልካም ታሪኮቻችንም እውቅና መስጠት ነው። ኢትዮጵያን የመከራ ቤት ብቻ ኣድርጎ ከማየት የኣፍሪካ መቀመጫ ያደረጋትን የነጻነት ታጋይነቱዋን ማስታወስና ለነዚህ ታሪኮቻችን ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ኣስተዋጾ በማድረጋቸው እውቅና ሊሰጡት ይገባል። ይህ ኣይነቱ ስሜት ሚዛናዊ የሆነ ስሜትን ከመፍጠሩም በላይ ኣገር ኣለን ስንል የምንመካባቸው ብዙ ኣኩሪ ታሪኮች እንዳሉንም ስለሚያደርግ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ የስምምነታቸን ሰነድ ኣንዱ ሊይዘው የሚገባው ነገር የማትከፋፈል ኢትዮጵያን ለትውልድ ማሳለፍ ነው። መንግስት መጥቶ መንግስት ሲሄድ ቋሚ ዶግማ የሆነ ስምምነት ሆኖ ሊቀመጥ የሚገባው ጉዳይ ነው። የወደፊቷን ኢትዮጵያን እንደገና ማነጽ ማለት ይሄው ነው።
ማጠቃለያ
በቅርቡ ከኔልሰን ማንዴላ ሞት ጋር በተያያዘ ዓለም ያሳየችውን ስሜት ስናይ ያስደንቃል።በኔልሰን ማንዴላ ሞት ምክንያት የዛሬይቱ ዓለማችን በሚያስደንቅ መልኩ መነቃነቋ፣ ያ ሁሉ መሪ ወደ ደቡብ ኣፍሪካ መጉረፉ የሚያሳየው የሃያ ኣንደኛዋ ክፍለ ዘመን ዓለም ለብሄራዊ እርቅና ይቅርታ የሰጠችውን ታላቅ ክብርና ቦታ ነው።ኢትዮጵያዊያንም ከዚህ የምንማረው ኣለ:: ኢትዮጵያ ብህዙ በመሆኑዋ ይህ ተፈጥሮዋ በስምምነት ላይ የተመሰረተች ኣገር እንድትሆን ያስገድዳታል:: በመሆኑም በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ያስፈልገናል የምንለው ኣንዱ መነሻ ይሄ ነው። እንዴት ወደ ስምምነት እንገባለን? በምን መንገድ ነው ወደዚያ መስመር የምንገባው? ተግባራዊ ሂደቱ ምንድነው? ካልን ኣንዱ መንገድ ብሄራዊ እርቅ ማምጣት ነው። ከፍ ሲል እንዳልነው ብሄራዊ እርቅ ማለት በኢትዮጵያ ኣንዱ በዳይ ሌላው ካሳ የሚሰጥ ሳይሆን ርስበርስ የሚረዳዱበትና ሁሉም የሚካሱበት የእርቅ ኣሳብ ነው። በዋናነት ብሄራዊ እርቁ ያለፈውን ችግር መፍታት ኣሁን የዘለቀውን ችግር ማቆም ሆኖ ከሁሉ በላይ ግን ኢትዮጵያን እንደገና ለማነጽ የስምምነት ነጥቦችን ኣውጥቶ በነዚያ ስምምነቶች ዙሪያ መስማማት ነው። እነዚህ የስምምነት ኣጀንዳዎች የሃገሪቱ ዶግማዎች ይሆኑና ዘላለማዊ ኪዳን ይሆናሉ። ይህ ኪዳን ከህገ መንግስቷም በላይ ሆኖ የሚኖር ይሆናል።። ህገ መንግስት የሚያረቁ መንግስታትም ከነዚህ ዶግማዎች ኣንጻር ህጎችን ሊያወጡ ይገባል። ይህ የእርቅ ሰነድ በሃይማኖት መሪዎች፣ በባህል መሪዎች በፖለቲካ ፓርቲዎችና በሲቪክ ማህበራት ዘንድ ሁሉ የሚቀመጥ የሚከበር ትልቅ ኪዳን መሆን ኣለበት።ኢትዮጵያ በእንደዚህ ኣይነት ለየት ባለ ቅርጽ ብትተዳደርስ? ከህገ-መንግስቷም በላይ ሌላ ዶግማ የሆነ ኣዲስ ኪዳን ቢኖራት ጥሩ ኣይሆንም ?
መቼም ይሄ ተግባር የናፈቀው ህሊናችን ጥያቄ ማንሳቱ ኣይቀርም። ይህ ብሄራዊ እርቅ የሚባለው ነገር መቼ ነው መካሄድ ያለበት? ተዋንያኑስ እነማን ይሆናሉ? የሚል ተግባራዊ ጉዳዮች ይመጣሉ። በኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ ማለት የተጣሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መታረቅ፣ ወይም ውህደት ማድረግ ማለት ኣይደለም። በርግጥ የነዚህ ፓርቲዎች ውህደትና ስምምነት ለብሄራዊ እርቁ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ኣለው። ኣሁን የምናወራውን ሰፊ ኪዳን ለመፈጸም ነው። ዓለምን የሚያስደምም ስምምነት ተስማምተን ኢትዮጵያን እንደገና ልናቆም ነው። ተዋንያን የሚሆኑት የተለያዩ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ቡድኖች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ባህላዊ ቡድኖች ዜጎች ሁሉ ናቸው። ከኣለማቀፉ ማህበረሰብም ታዛቢ ኣስገብታ ይህንን ስምምነቱዋን ለኣለም ማሳየት ኣለባት። ከዚያ በሁዋላ ኢትዮጵያ ታላቅ ድግስ ደግሳ ያን የተስማማችበትን ቀን ዘወትር የምታከብረው የኢትዮጵያ ዳግም ምስረታ (Foundation day) ቀን ብላ ያን ቀን ዘወትር በየዓመቱ ታከብረዋለች።ይሄ መሆን የሚችል ነው።
ኢትዮጵያ ይህን የእርቅ ኪዳን የምትገባው ኣሁን ያለው መንግስት ወደ እርቅ ከመጣ ብቻ ኣይደለም። ይህ መንግስት ለዚህ እርቅ ሁኔታዎችን ቢያመቻችና ኣብሮ ቢሳተፍ ታሪክ ያመሰግነዋል። ነገር ግን በነውጥም ሆነ በጠመንጃ ይህ መንግስት ከወደቀ በሁዋላም ኢትዮጵያ የግድ ወደዚህ ኪዳን ውስጥ መግባት ስላለባት ከወዲሁ መዘጋጀት ያስፈልጋል። ባለፈው ታሪካችን የጠፋው ይሄ ነው። ለውጦች ሲመጡ ብሄራዊ እርቅ ሳይደረግ ኣሸናፊው ተሽናፊውን እየረገመ የተሻልኩ ነኝ እያለ ስለመጣን ብሄራዊ ችግሮቻችን እየባሱ መጥተዋል። ኣሁን ግን በየትኛውም ሁኔታ ቢሆን ኢትዮጵያ በዚህ የእርቅ ኣሳብ ውስጥ ማለፍ ኣለባት። ይሄ የግድ ነው።የብሄራዊ እርቁን የሚመራውና የእርቅ ኣሳቦችን የሚያመጣውን ኮሚሽን ኣገር ወዳድ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ሚዲያዎችና ኮሚኒቲዎች ከፊታቸው ያለውን የልዩነት ተራራ በጎን በኩል ዞረው ኣልፈው ይህን ሰነድ የሚያዘጋጁና መላ የሚፈጥሩ ኣካላትን ሊፈጥሩ ይገባል።ይሄ ሰው የሚሰራው ኢትዮጵያዊያን ልንሸከመው የምችለው ሃላፊነት ነው። ኣሁን ባለው የፖለቲካ ኣሰላለፍ ኢትዮጵያ የጎደላት ይሄ ነው። ኣልፎ ኣልፎ የተለያዩ ፓርቲዎችን ኣገናኝቶ በማነጋገር የእርቅ ኣሳብን ለማዳበር የሚሰራ የለም ማለት ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ በየጊዜው የሚመጡ ለችግራችን የሚሆኑ የመፍትሄ ኣሳቦችን የሚያጠናና የሚያደራጅ ባለመኖሩ ወርቅ የሆኑ ኣሳቦች ሁሉ ባከኑ። ለዚህም ኣንድ ጠርናፊ እውነትን የሚያፈላልግ የእርቅ ኣሳቦችን የሚያዳብር ተቋም ያስፈልገናልና በዚህ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትኩረት ሰጥቶ መላ ሊለው መስሎኝ ነው።
እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ቸር እንሰንብት
geletawzeleke@gmail.com
ያለፉት ስህተቶች ትምህርት እንጂ ማነቆ አይሁኑ –ግርማ ካሳ
ግርማ ካሳ
እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር፣ ኖቬምበር 17 ቀን 1996 ነበር። በሰርቢያ (የቀድሞ ዩጎስላቪያ) ፣ የክልል ምርጫ ይደረጋል። በቩክ ድራስኮቪች የሚመራዉ SPO ፣ በቬስና ፔሲች የሚመራዉ GSS እና ሌሎች ድርጅቶች በአንድ ላይ ሆነው አብላጫ ድምጽ ያገኛሉ። ነገር ግን በወቅቱ የነበሩ አምባገነን ባለስልጣናት፣ እነ ስሎቦዳን ሚሎሶቪች አጭበረበሩ። ከኖቬምበር 17 1996 እስከ ፌቡሩያሪ 11 1997 ድረስ፣ «ያጄድኖ» የሚል፣ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች በስፋት ተደረጉ። ባለስልጣናቱ፣ የሕዝቡ ሰላማዊ ተቃዉሞ አይሎ መምጣቱን ሲያዩ አፈገፈጉ። የተቃዋሚዎች ስብስብ በክልል ምርጫዉ ያገኙትን ምርጫ፣ ተቀበሉ። ሊበራል ዴሞክራቱ ዞራን ጂንጂች የአገሪቷ መዲና የቤል ግሬድ ከንቲባ ሆኑ።
ብዙም አልቆየም፣ በተቃዋሚዎች መካከል ችግር መታየት ጀመረ። በቩክ ድራስኮቪች የሚመራዉ ፓርቲና በዞራን ጂንጂች በሚመራዉ ፓርቲ መካከል ልዩነቶች ተፈጠሩ። መካረር መጣ። የሕዝብን ጥያቄ አንግቦ በጋራ መቆም ተሳናቸው። በአደባባይ መወጋገዝ ጀመሩ። በአመቱ አገራዊ የፕሬዘዳንት ምርጫ ሲደረግ የሚሎሶቪች የሶሻሊስት ፓርቲ በቀላሉ ስልጣኑን ጨበጠ። የተለፋበት፣ የተደከመበት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ከሸፈ። አምባገነኖች አሸነፉ። በሕዝብ ትግል የተገኙ ዉጤት እንደገና ተቀለበሱ። ዞራን ጂንጂችም ከናካቴዉ ከተመረጡበት የቤልግሬድ ከንቲባነት ተነሱ።
በ1998 በየክልሉ ተማሪዎች «ኦትፖር» ( በሰርቢያን ቋንቋ እምቢተኝነት) በሚል ስም ከታች ወደ ላይ የሆነ እንቅስቃሴ ጀመሩ። የተከፋፈሉ የፖለቲካ ደርጅቶች በአንድ ላይ እንደገና ተሰባሰቡ። ካለፉት ስህተቶች በመማር፣ ፍጹም ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለሚቀጥለው ምርጫ መዘጋጀት ጀመሩ። ከፍተኛ ጫና እየተደረገም ዝግጅቱ ተጧጧፈ። የገዥዉ ፓርቲ ደጋፊዎችን የመሳብ ሥራ በስፋት ተሰራ። በዚህም ምክንያት በርካታ የገዢዉ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተቃዋሚዎችን መቀላቀል ጀመሩ። ኢቫን ስታምቦሊች ፣ የሚሎሶቪች አጋር የነበሩ ፖለቲከኛ ፣ ተቃዋሚዎች በመቀላቀላቸውም በሚሎሶቪሽ የደህንነት ሰራተኞች ታፍነው ተገደሉ።
ሴፕቴምበር 2000 ዓ.ም ምርጫ ተደረገ። የሚሎሶቪች ምርጫ ቦርድ፣ አሁንም የተጭበረበረ የምርጫ ዉጤት ይፋ አደረገ። ያንን አስከትሎ ኦክቶቦር 2000 ዓ.ም ፣ ትልቅ ተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ። ምርጫ ቦርድ የምርጫዉን ዉጤት ወደ ነበረበት እንዲመልስ ተገደደ። የተቃዋሚዎች እጩ የሆኑት ኮስቶኒሳ እንዳሸነፉ ተገለጸ። የሚሎሶቪች ስልጣን ፍጻሜ ሆነ። የሰርቢያ ሕዝብ የማይቀለበስ ድል ተቀዳጀ።
ይሄንን ያለ ምክንያት አይደለም ያመጣሁት። በሰርቢያ፣ በመጀመሪያዉ ምርጫ የተከሰተው፣ በኢትዮጵያም በምርጫ ዘጠና ሰባት ከተከሰተው ብዙ የሚለይ አይደለም። ያኔ በቅንጅት ጊዜ የሕዝብ ጉልበት አያሎ የወጣበት ወቅት ነበር። ነገር ግን በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠሩ ልዩነቶች፣ በቀላሉ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ስልጣን ላይ ለመቆየት ቻለ። (በገዢው ፓርቲ የደረሰው ወከባ፣ ግድያ፣ እሥር፣ እንግልትን ጫና ቢኖርም፣ በዋናነት የተቃዋሚዎች ችግር ነው አገዛዙን ያቆየው ብዬ ነዉ የማምነው)
ሰርቦች ጠመንጃ አላነሱም። ሰርቦች ለዉጥ ማምጣት አይቻልም ብለው አላወጁም። ሰርቦች ተስፋ አልቆረጡም። እኛ ኢትዮጵያዉያን ግን ተስፋ ቆረጥን። ፎጣችንን መሬት ላይ ጥለን፣ አምባገነንነትን አሜን ብሎ የመቀበል አዝማሚያ አሳየን። «ተቃዋሚዎች አይረቡም። ያኔ ደግፈናቸው ጉድ አላደረጉንም እንዴ ? አርፎ መቀመጥ ይሻላል፣ ሰላማዊ ትግል አይሰራም ….» የሚሉ ጨለምተኛና የሽንፈት አባባሎችን ማሰማት ጀመርን።
የገዢዉ ፓርቲ ሰዎችም፣ ስልጣን ላይ ለመቆት የሚያስችላቸው፣ ይሄዉ የተቃዋሚዎች መከፋፈልና የሕዝቡም ተስፋ መቁረጥ ስለነበረ፣ በሚቆጣጠሯቸው ሜዲያዎች፣ ሕዝቡ በተቃዋሚዎች ላይ የበለጠ ተስፋ እንዲቆርጥ፣ ከፍተኛና ሲስቴማቲክ፣ ተቃዋሚዎች የማጥላላትን የማሳነስ ዘመቻቸዉን አፋፋሙ። ጠንካራ የሚሏቸውን የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች ያለ ርህራሄ አሰሩ። ብርቱካን ሚደቅሳን አሰቃይተውና ሰባብረው (ለስድስት ወራት ሁለት ሜትር በሁለት ሜትር ጨለማ ቤት ዉስጥ እንዳስቀመጧት) ለስደት ዳረጓት። «እነርሱን ያየህ ተቀጣ» በሚል፣ በአንዱዋለም አራጌ፣ በእስክንደር ነጋ፣ በርዪት አለሙ፣ በዉብሸት ታዬ፣ በበቀለ ገርባ እንዲሁም በሌሎች ..ሰላማዊ ወገኖቻችን ላይ፣ በተራ የዉሸት ሽብር ክስ፣ ኢፍትሃዊነትና ኢሰብአዊነት የተሞላበት ግፍ መፈጸማቸዉን ቀጠሉ። በሕዝቡ አይምሮ ዉስጥ፣ እነርሱን ማንም ሊነካቸው የማይችሉ፣ ግዙፎች (ኢንቪሲብል) እንደሆኑ ለመሳል መሞከርና፣ ሕዝቡ እርስ በርስ ተፈራርቶ እንዳይደራጅ፣ እንዳይነጋገር፣ እንዳይተማመን፣ በዘር፣ በኃይማኖት በጥቅም እንዲከፋፈል፣ ማድረጉን ተያያዙት።
ነገር ግን ኢትዮጵያዉያን መንቃት ያለብን ይመስለኛል። ከሰርቦች መማር ያለብን ይመስለኛል። አምባገነኖች ኃይለኛ የሆኑ ይመስላሉ እንጂ ሁልጊዜ ባዶ መሆናቸዉን መረዳት አለብን። ሕወሃት/ኢሕአዴግ የሕዝብ ድጋፍ የሌለው፣ በሙስና የተዘፈቀ፣ ለሕዝብና ለዜጎች ከበሬታ የማያሳይ፣ ዜጎችን ሽብርተኞች እያለ የሚያሸብር፣ የበሰበሰ ድርጅት እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነዉ።
እንግዲህ «ትላንት ወድቀናል ብለን፣ የትናንቱ ጠባሳችንን እያየን ወደፊት ከመራመድ መቆጠብ የለብንም» እላለሁ። ከስህተቶቻችን ተምረን፣ ያለፈው ታሪካችን በአይምሯችን እየፈጠረ ካለው ጎታች ጫና ተላቀን፣ ይሄንን ዘረኛና አምባገነን ስርዓት ለመቀየር በቁርጠኝነት መነሳት የግድ ነዉ። ቁልፉ በእጃችን ነዉ። በርግጥ ለዉጥ ማምጣት እንችላለን። ጥያቄው «ፍላጎቱ አለን ወይ?» የሚል ነዉ።
እያንዳንዳች ወደ ራሳችን እንመልከት። እራሳችንን እንጠይቅ። «እስከመቼ ነዉ፣ በአገራችን እንደ ባይተዋር ፈርተን እና አንገታችንን ደፍተን የምንቀመጠው ?» ማለት እንጀመር። በየወረዳችን፣ በየአካባቢያችን፣ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ድርጅቶችን እንቀላቀል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ ጠንካራና አገር ሰፊ የኢትዮጵያዊትነትና የሰለጠነ ፖለቲካ የሚያራምድ ድርጅት ነዉ። በመቀሌ፣ አርባ ምንጭ፣ ጂንካ፣ አዳማ ፣ አሶሶ …በአገርቷ ክፍሎች ሁሉ ብትሄዱ አንድነት በዚያ አለ። አንድነትን እንቀላቀል። አንድነትን እንደግፍ። የሰማያዊ ፓርቲ ፣ መኢአድ፣ ኤዴፓ፣ አረና ..ሁሉም በፊናቸው የሕዝብን ጥያቄ እያሰተጋቡ ነው። እንቀላቀላቸው። እንደግፋቸው። ልዩነቶቻቸውንም አጣበው ፣ የበለጠ ኃይልና ጉልበት ኖሯቸው ሰላማዊ፣ የኢትዮጵያዊነት የሰለጠነን የፖለቲካ ትግል ይመሩ ዘንድ፣ እንዲሰባሰቡ፣ እንዲዋሃዱ እናበረታታቸው።
ፈረንጆች ኒው ዪር ሬዞሉሽን (የአዲስ አመት ዉሳኔ) ይሉታል። እንግዲህ፣ በዚህ የ2014 አዲስ አመት፣ የሁላችንም ምኞት፣ ጥረትና ዉሳኔ፣ በአገራችን መልካም ለዉጥ እንዲመጣ፣ የድርሻችንን በሃሳብ፣ በገንዘብ፣ በጸሎት ለማገዝ ይሁን። የሌሎች ሕመምና ስቃይ ይሰማን። ዝምታን በቃ እንበል። እግዚአብሄር አምላክም ረድኤቱን ያብዛልን!
የለንደን ማርያም ቤ/ክ ጉዳይ፡ የሃሰተ መአትን በመርጨት እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚጥሩ ካህናትን አሁንም ማርያም እያጋለጠቻቸው ትገኛለች
ቀን፡ 03/01/2014
በክህነት ካባ ተሸፍኖ እግዚአብሔን ሳይፈሩና ሰውን ሳያፍሩ የሃሰተ መአትን በሕዝበ ክርስቲያን ውስጥ በመርጨት እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚጥሩ ካህናትን አሁንም ማርያም እያጋለጠቻቸው ትገኛለች።
አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ።እንደነዚህ ካሉት ራቅ።1ኛ ጤሞቲ.6፤4-6።
የቤተ ክርስቲያን አባላት፤ ካህናቱንና ምእመናኑን ወክለው ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንን በበላይነት እንዲያስተዳድሩ ሕዝብ መርጦ ሰይሟቸው የነበሩት 3 ካህናት፤ 4 ምእመናንና 1 የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች የአገልግሎት ጊዜአቸውን ጨርሰው ለረጅም ጊዜ በኃላፊነት ላይ በመቆየታቸውና ከዛም ጋር ተያይዞ ብዙ የአስተዳደር ችግሮች በመከሰታቸው ምክንያት በ23 September 2012 ሁላችንም በገዛ ፍቃዳችን ከሥልጣናችን ለቀናል በማለት ለሕዝብ ይፋ አደረጉ።
ከዛም በመቀጠል አዲስ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ምርጫ ይካሄዳል ሲባል የካህናቱ ተወካዮች በተለይም አባ ግርማ ከበደ ሥላጣናቸውን ዘለዓለማዊ ለማድረግ ሲሉ አዲስ ምርጫ የሚካሄደው በሕዝቡ ፍላጎትና ውሳኔ ሳይሆን እኛ ባልነውና በሚመቸን መንገድ ብቻ ነው በማለታቸው ከፍተኛ ሁከት ተፈጠረ።
በዚህ ጊዜ ይህንን ሁከትና መከፋፈል መቋቋም ያቃታቸው 4ቱ የምእመናን ተወካዮች ቃላቸውን በመጠበቅ ሥራቸውን ሙሉ በሙሉ አቆመው እቤታቸው ቀሩ።
ይህ በሆነበት ወቅት አባ ግርማን ጨምሮ ሦስቱ ካህናት በምእመኑ መልቀቅ ተደስተው ሥልጣኑን ሁሉ የግላቸው በማድረግ የማይፈልጓቸውን የቤተ ክርስቲያኑን አባላት ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳትደርሱ በማለት በደብዳቤ ማገድና ማባረር በመጀመራቸው ቤተ ክርስቲያንን እስከማዘጋት የሚደርስ ሁከትና ረብሻ አስነሱ።
ከዛም በመቀጠል የቤተ ክርስቲያኑ መሰሶ፤ ጣሪያና ግድግዳ የሆኑትን አባላቱን ለማሸነፍ የሚችሉበትን ኃይል ለማግኘት ሲሉ የመረጣቸውንና የወከላቸውን ሕዝብ ከድተው ቤተ ክርስቲያኗ የሃገረ ስብከቱ ናት፤ ንብረቷም የቅዱስ ሲኖዶስ ነው የሚል ማጭበርበሪያን በመጠቀም የመንግሥት ተወካይ የሆኑ ጳጳሳትንና የኤምባሲ ባለሥልጣናትን ተጠቅመው ቤተ ክርስቲያኗን ከአባላቷ ነጥቀው በመውሰድ እጅ መንሺያና መሾሚያ መሸለሚያ ሊያደርጓት ጣሩ፤ ሆኖም ግን አባላት ባደረጉት ጠንካራ ትግልና በእግዚአብሔር ተራዳኢነት አንዱም ተንኮላቸውና ክህደታቸው ውጤት ሳያስገኝላቸው መክኖ ቀረ።
ከዛም በመቀጠል ቤተ ክርስቲያኗ የምትገኝበትን ሃገር አጠቃላይ ሕግና በተለይም ቤተ ክርስቲያኗ የተመዘገበችበትን የቻሪ ሕግ መከተልን አሻፈረኝ በማለት በማታለልና በመዋሸት የቤተ ክርስቲያንን ንብረት ከአባላቷ መንጠቅ እንችላለን በማለት የሃገርንም ሆነ የሕዝብ ንብረትን ሲዘርፉ ይሉኝታም ሆነ ሃፍረት ካልፈጠረባቸው የዘመናችን የቀን ጅቦች ጋር በመመሳጠር በቤተ ክርስቲያኑ አባላት ላይ የጥቃት ዘመቻ ከፍተው አሁንም በአባላቱ ጥንካሬና በእግዚአብሔር ተራዳኢነት የተኮል መረባቸው ሁሉ እንዳይሰራ ተደረገ፡፡
በመጨረሻ የቻሪቲ ኮሚሽን ጉዳዩን በመረዳት ምንም እንኳ ከሥልጣን አንለቅም ብለው ሥልጣንን የሙጥኝ ብለው ሕዝብንና ቤተ ክርስቲያንን የሁከት መድረክ ያደረጉት 4 የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት (Trustees) ውስጥ አንድም ሥለ ምእመኑ የሚከራከርና ምእመኑን የሚወክል አባል ባይኖርም ከዚህ እነሱ የሙጥኝ ካሉት ሥልጣን እንደ ሰንኮፍ አውጥቶ በመጣል ቤተ ክርስቲያኗን እና አባላቷን ከፈጠሩባት ሕመም ለማዳን ያለው አማራጭ አዲስ ምርጫ ማካሄድ መሆኑን በመረዳት ባለ አደራዎች (Trustees) ነን ብላችሁ ከሆነ የምትንገታገቱት ኃላፊነት የሚሰማው ሥራ መሥራት አለባቸሁ በሚል በንፈስ መብታቸውን ለማስከበርና ቤተ ክርስቲያናቸውንና ሃይማኖታቸውን ጠብቀው ለማኖር ሕጋዊ መንገድ ይዘው ከሚታገሉ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ተወካዮችና የሕግ ጠበቃቸው ጋር ግንኙነት በመፍጠር ከቤተ ክርስቲያን መከፈት ጀምሮ አዲስ ምርጫ ስለሚካሄድበት ሁኔታ ታዛቢ ባለበትና፤ በፊርማ በሚረጋገጥ የውል ሰነድ መሰረት ስምምነትና መግባባት ላይ እንዲደርሱ ቀነ ገደብ ወስኖ መመሪያ ሰጣቸው።
ቻሪቲ ኮሚሽን ይህንን መመሪያ ሲያወጣ ግን እነሱ ብቻ ናቸው ትረስቲዎች ብሎ መወሰኑ ሳይሆን ማን ትረስቲ እንደሆነ የሚወስነው ፍርድ ቤት ነው በማለት ከችግሩ ለመውጣት ግን መፍትሔው ሁሉም ወገን የተስማማበት ምርጫ ማካሄድ ነው የሚለውን አበክሮ በመግለጽ ነበር።
ይህንንም ቻሪቲ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ በተራ ቁጥር 5 ላይ እንደሚከተለው በማለት ያብራራዋል።
“As part of our regulatory case we considered the question of who are the validly appointed trustees of the charity. This is a matter to which only the Courts can provide a definitive answer because the question centers on interpreting the governing document of the charity, which is under the jurisdiction of the Courts.”
ይህንን የመሰለ መመሪያና ማብራሪያ ቻሪቲ ኮሚሽን ለሁለቱም ወገን የሕግ ጠበቆች ልኮ እያለ የእውነትና የፍትሕ መንገድ ሁሉ ጨለማ መስሎ የሚታያቸው አባ ግርማና ተከታዮቻቸው ግን በተለመደው የቅጥፈት ተግባራቸው መሠረት ከመመሪያው ውስጥ ቻሪቲ ኮሚሽን ትረስቲዎች ናችሁ ብሎ ተቀብሎናል የሚል የተሳሳተ ትርጉም በማውጣት ከአሁን በኋላ የምንፈልገውን የፈላጭ ቆራጭነት ድርጊት ሁሉ የመፈጸም መብት ተሰጥቶናል የሚል አዋጅ አሰሙ።
ከዛም በመቀጠል
1. ረብሻና ሁከት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተከሰተ በHealth & Safety ችግር ምክንያት ተዘጋ ብለው ለ9 ወር ያሸጉትን ቤተ ክርስቲያን የኛ ሥልጣን ተረጋግጦልናልና የቤተ ክርስቲያን አባላት ቢፈልጉ ገብተው ይጫረሱ በሚል የአረመኔነት መንፈስ ቤተ ክርስቲያኑ በ29/12/2013 እንከፍታለን የሚል ማስታወቂያ አሰራጩ።
3. ከቄሱ የጳጳሱ እንዲሉ አቡነ እንጦስ የሚባሉ በኢትዮጵያ መንግሥት የዲፕሎማሲ ፓስፖርት የሚንቀሳቀሱና መንበራቸው በሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሆነ፡ ራሷን ችላ ስትተድደር ከኖረችው ከንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው በሥላሴ ቤተ ክርስቲያንና በገብረኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ቤተ ክርስቲያኑን እንድከፍት ቻሪቲ ኮሚሽን ስለፈቀደልኝና ከቅዱስ ሲኖዶስም ስለታዘዝሁ እኔ አቅመ ደካማ ነኝና በ29/12/13 እሑድ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ድረሥ ሁላችሁም መጥታችሁ እንድትረዱኝ በማለት ስብከት፤ ቅስቀሳና ጥሪ አደረጉ። ከዛም በማያያዝ ከለንደን ውጪ ያሉ ተንቀሳቃሽ አብያተ ክርስቲያናት የመጓጓዣ ኮች ተልኮላቸው በነጻ በመጓጓዝ ማርያም ቤተ ክርስቲያን መጥተው የእነ አባ እንጦስ ሠራዊት ሆነው እንዲዘምቱ መርሃ ግብር ተዘጋጀ።
አቡነ እንጦስ ከአሁን በፊትም እንኳንስ ብጹዕ ከተባለ ጳጳስ ቀርቶ ከማንኛውም የእግዚአብሔር አማኝ ሰው በማይጠበቅ ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት የሚጸልዩበት ቦታ ድረሥ በመምጣት ሰላም አወርዳለሁ በማለት እኔ የሁለታችሁም አባት ነኝ፤ ለአንዳችሁም አላደላም በማለት እውነተኛ አባት መንፈሳዊ አባት መሆናቸውን ለማሳየት ጥረው ነበር። የሚገርመው ግን ይህንን የቅጥፈት ቃል የሚናገሩት በሌላ በኩል ከቤተ ክርስቲያኗ አባላት ጋር ለውነት ቆመው የእውነት ሥራን በመስራት ላይ ያሉትን ቄስ ብርሃኑን ከቤተ ክርስቲያኑ አባላት ጎራ ወጥተህ ከኔ ጎን ተሰልፈህ አባላቱ እንዲበተኑ ካላደረግህ አሳርህን አሳይሃለሁ በማለት በስማቸው እየፈረሙ የሚልኩትን ከአንድም ሁለት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤና ከአባ ግርማ ጎን ቆመው ቀን ከሌሊት እንደሚሰሩ እግዚአብሔር ቀርቶ አባላትም የሚያቁት የአደባባይ ምሥጢር ስለነበር እኝህ ጳጳስ እንኳንስ ሰውን እግዚአብሔርንም አታልላለው ብለው በማሰብ የሚያደርጉት ጥረት በእጅጉ የሚያሳዝንና የሚያሳዝን ነበር።
ይህ አልበቃ ብሏቸው ነው ዛሬ ደግሞ ሌላ በሬ ወለደ ሃሰት ለሕዝበ ክርስቲያኑ የሚነግሩት። አቡነ እንጦስ ቻሪቲ ኮሚሽን ቤተ ክርስቲያን እንድከፍት ፈቅዶልኛል ያሉት ቻሪቲ ኮሚሽን ግን የእሳቸው ጣልቃ መግባት ተገቢ ያልሆነ መሰናክል ነው በማለት የገለጸው ባጭሩ እንደሚከተለው ነበር።
“We have pointed out that a role of the Archbishop of the Diocese of North West Europe is neither appropriate nor desirable for the trustees to create unnecessary barriers to an inclusive election process.”
በሌላ በኩል ደግሞ አቡነ እንጦስ ይህንን የሃሰት መረጃ መሠረት በማድረግ ለጸሎትና ለቅዳሴ የተሰበሰበውን ሕዝበ ክርስቲያን እኔ አቅመ ደካማ ነኝና መጥታችሁ እርዱኝ ማለታቸው የቤተ ክርስቲያኑን በር ለመክፈት የሚፈነቅል ድንጋይና የሚጎተት ገመድ ኖሮ ጉልበት አስፈልጎ ሳይሆን በብዛት መጥታችሁ በቤተ ክርስቲያኑ አባላት ላይ በመዝመት ቤተ ክርስቲያኗን እንድወርስ እርዱኝ ማለታቸው ነበር።
በዚህ ድርጊታቸው እኚህ ጳጳስ ምን ያህል እግዚአብሔርን ሳይፈሩና ሰውን ሳያፍሩ ውሸትን ከመንዛት አልፈው ዓላማቸውን ለማሳካት ሲሉ አንዱን ክርስቲያን በሌላው ላይ አዝምቶ ማፋጀት የማያሳስባቸውና የማይጸጽታቸው ሰው እንደሆኑ መረዳት ይቻላል።
4. ከዚሁ ጋራ አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው፤ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሥልጣናት፤ የወያኔ የደህንነት ሰዎች፤ የሃገረ ስብከቱና የሥላሴ ሹማምንቶች ጋር በመሆን ለአካባቢው ፖሊስ ሥለ ቤተ ክርስቲያኑ አባላት የሃሰት መረጃንና ማስፈራሪያ በማቅረብ የፖሊስ ኃይል በተጋነነው መረጃ ላይ በመመርኮዝ ከፍተኛ የደም መፋሰስና መበጣበጥ ሊመጣ ነው ብሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ልዩ የፖሊስ ኃይል እንዲያሰማራ አስደረጉ።
5. አባ ግርማና ተከታዮቻቸው የሚደገፉት እጅግ ጥቂት በሆኑ አባላት በመሆኑና 90% የሚሆነው የቤተ ክርስቲያኑ አባላት አንባ ገነናዊና ክርስቲያናዊ ያልሆነውን ድርጊታቸውን የሚቃወምና የሚኮንን በመሆኑ፤ ቤተ ክርስቲያኑ ሲከፈት የወያኔ መንግሥት ደጋፊ የሆኑ የሥላሴና የገብረኤል ቤተ ክርስቲያን አባላት በተለይም የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አባላት ከነካህናቱና የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት (Trustees) ሳይቀሩ በዘመቻ መልክ መጥተው የቤተ ክርስቲያኑን አባላት በቁጥር በመብለጥ እንዲያጠቁላቸውና እንዲያባርሩላቸው በማሰብ የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን የቅዳሴ አገልግሎት በመጨረስ ተጓጉዘው እስኪደርሱላቸው ጊዜ እንደሚወስድ በማሰብ የቤተ ክርስቲያኑን መከፈቻ ሰዓት ከጠዋቱ 5 ሰዓት (1100) እንዲሆን አደረጉ።
የቤተ ክርስቲያኑ በሕገወጥ መንገድ መከፈት ከተረጋገጠ በኋላ የተፈጠሩ ክስተቶች።
1. የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ቤተ ክርስቲያናቸው ከተዘጋችባቸው ጀምሮ ላለፉት 9 ወራት በብርድ፤ በዝናብና በቸነፈር ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ሳያስተጓጉሉ በየዕለተ ሰንበቱ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል ጀምሮ ቤተ ክርስቲያናቸው በመድረስ በቅጥር ግቢ ውስጥ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ጸሎትም ሆነ ሥርዓተ ቅዳሴ ያካሂዱ ሥለ ነበር በ29/12/13 በዛው መሠረት እቤተ ክርስቲያናቸው ቅጥር ግቢ ሲደርሱ አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው ከወያኔ ወኪሎችና ደጋፊዎች በሚያገኙት የገንዘብ ፈሰስ በመጠቀም ከፍተኛ ክፍያ የሚጠይቁ ከ10 ያላነሱ Private Security ቀጥረው በማቆም አባላቱ ወደ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገቡባቸውን በሮች በሰንሰለት በመቆለፉ እንዲከለከሉ አደረጉ። ይህ የተደረገበት ምክንያትም አባላቱ የሌሎች ቤተ ክርስቲያን አባላት የራሳቸውን አገልግሎት ጨርሰው ተጓጉዘው ማርያም ቤተ ክርስቲያን እስኪደርሱና የአባ ግርማ ጎራ በሰው ኃይል እስኪጠናከር ጊዜ ለመግዛትና ከዚህም በተጨማሪ አባላቱ ለምን ማምለኪያና መጸለያ ቦታችንን እንከለከላለን ብለው አንባ ጓሮ እንዲፈጥሩና ይህ ሁኔታ ሲፈጠርም ፖሊስ ጠርቶ አባላትን ለማስያዝና ለማስወንጀል ነበር።
2. በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያኗን ከመመሥረት ጀምሮ ለደረሰችበት ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ ለማብቃት ላለፉት 40 ዓመታት በጽናት ቆመው ሃብትና ጉልበታቸውን በማፍሰስ፤ የለፉ የደከሙና ያገለገሉ ካህናትና ምእመናን ከ1 ዓመት ህፃን ጀምሮ እስከ 80 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አዛውንቶች፤ አቅመ ደካሞችና ህመምተኞች ሳይቀሩ በከፋው የክረምት ብርድና ቁር እየተጠበሱ አውራ ጎዳና አስፋልት ጫፍ ላይ በመኮልኮል ከሦስት ሰዓታት የበለጠ ቢሰቃዩም የደረሰባቸውን በደል ሁሉ በጽናትና በትዕግሥት በማለፍ ከፓሊስ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር በመጨረሻ በፖሊስ ውሳኔና መመሪያ መሠረት የቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ በር ተከፍቶላቸው ሊገቡ ችለዋል።
3. እነዚህ በቁጥር ከ320 በላይ የሚሆኑ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ካህናትና ምእመናን ወደ ቅጥር ግቢው ሲገቡ አባ ግርማና ተከታዮቻቸው ተቻኩለው የቤተ ክርስቲያኑን ዋናና ትልቅ በር ብርግድ አድርገው ቢከፍቱም አባላቱ ግን የተከፈተው ቤተ ክርስቲያን መዝጊያ በር እንጂ የሰዎች በር እንደተዘጋና እንደተቆለፈ በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አባላት ላይ ቂምን ቋጥረው፤ ክርስቲያኑን ህብረተሰብ እርስ በእርሱ አጋጭተው በዛ መሃል ለመኖር ቀንና ሌሊት የዲያብሎስን ሥራ ከሚሰሩ ካህናት ጋር ሆዶ ሻክሮ ጥላቻን አዝሎ እርቅ ሳይወርድና ሰላም ሳይሰፍን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ መቀደስም ሆነ ማስቀደስ በእግዚአብሔር ማላገጥ ነው በሚል ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መግባትን ትተው ወደ ተለመደው የመቀደሻ ሥፍራቸው እየተዥጎደጎዱ ገቡ። ከዛም በመቀጥል ምንም ምንም ሳይሉ የዕለቱን ጸሎታቸውንና ሥርዓተ ቅዳሴ ማካሄድ ጀመሩ።
4. አባ ግርማና ተከታዮቻቸው፤ ከሥላሴ ቤተ ክርስቲያንና ከወያኔ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን ከሌላ ቤተ ክርስቲያናትና ከለንደን ውጪ ያስመጧቸውን የወያኔ ደጋፊዎች በማግተለትል ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እንዲገቡ አደረጉ፤ እነዚህ አዋጅ ተነግሮና ነጋሪት ተጎስሞ የመጡ የወያኔ ደጋፊዎች ግን ሲበዙ ቢውሉ በቁጥር ከ120 የሚበልጡ አልነበሩም።
5. አቡነ እንጦስና የሃገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የተባለው መጋቢ ተወልደና ሌሎች የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ሹማምንቶች የቤተ ክርስቲያኗ አባላት በአንጡራ ገንዛባቸው ገዝተው ባቆሙት የቪካሬጅ ህንፃ ውስጥ ሌሊቱን ተደብቀው በማንጋት በጓሮ በር አድርገው ከሕዝብ ተሸሽገው እንደ ሌባ በጓሮ በር ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ገቡ።
6. አባ ግርማና ተከታዮቻቸው ከቤተ ክርስቲያኑ መከፈት ጋር ያቀዱት ዕቅድና ያዘጋጁት ነገር ቢኖር በተቀደሰው የእግዚአብሔር ቤት፤ በጽላት ፊት ሕዝበ ክርስቲያንን ለማጋጨትና በሚነሳው ሁከት የቤተ ክርስቲያኑ አባላትን ወንጀለኛ አድርጎ በፓሊስ ለማስያዝ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በየ ጥጉ ካሜራና የድምጽ መቅጃ መሣሪያ አዘጋጅተው ልክ ወጥመድ ውስጥ እንደሚገባ አውሬ አባላትን መጠበቅ ነበር። እነሱ አባላትን ለማጥቃት ወጥመድ ቢያዘጋጁም በዛ ወጥመድ ውስጥ የሚገቡት ግን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ተጠርተው በማያገባቸው የሌላ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ እንዲገቡ የተደረጉት ክርስቲያኖች ጭምር ሊሆኑ እንደሚችሉ ግን የእነ አባ ግርማ ጭንቅላት ታሳቢ እንደማያደርገው የታወቀ ነበር፤ ለዚህም ማረጋገጫው ከአሁን በፊት ወጣቶችን ከየቦታው ሰብስበው አባላትን ለጸብ እንዲያነሳሱና እንዲያስወነጅሉ፤ በመስደብና በድብቅ በመማታት እነሱ መልሰው እንዲመቷችሁ አድርጉ ብለው አሰማርተዋቸው አምስት ወጣቶች ሲታሰሩና ሲወነጀሉ እነ አባ ግርማን የተሰማቸው አንዳችም ፀፀት አልነበረም።
ይህንን ሁሉ ያገናዘቡትና አርቀው ያዩት የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ቻሪቲ ኮሚሽን የሰጠው ሕጋዊና መመሪያ ተጥሶ ከአባላት ተወካዮችና ጠበቆች ጋር ፍጠሩ የተባሉትን line of communication ተግባራዊ ሳያደርጉ እነ አባ ግርማ ለሚፈጽሙት ሕገ ወጥ የተንኮል ተግባር ሰለባ ላለመሆንና ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በራሳቸውም ላይ ሆነ በሌሎች ክርስቲያን ወገኖቻቸው ላይ የሚደርሰውን ያልተገባ ነበር ለማስቀረት ሲሉ እነሱ እውጪ በብርድ እየተጠበሱ የሌላ ቤተ ክርስቲያን አባላት ቤተ ክርስቲያናቸውን ወረው ሲይዙ እያዩ ያቺን ቀን በታላቅ ትዕግሥትና ብልህነት አሳልፈዋታል፤ ነገም ቀን አለና የነገው ቀን ደግሞ ምን እንደሚሆን የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
በመጨረሻም አባ ግርማ ከበደም ሆኑ ቄስ ዳዊት አበበና ቄስ አባተ ጎበና ሕዝብ አምኖና መርጦ የሰጣቸውን ጊዚያዊ ኃላፊነት ዘለዓለማዊ ለማድረግ ሲሉና የራሳቸውን ዓላማ ለማሳካት ሲሉ አንድ ሆኖ በኖረው ሕዝበ ክርስቲያን መካከል የሃሰት ክምር በመሥራት ሕዝብ እርስ በእርሱ እንዲከፋፈልና በጥላቻ እንዲተያይ ከማድረግ አልፈው የቤተ ክርስቲያኑን ውስጣዊ የአስተዳደር ችግር ወደ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት በማዛመት በሚያገኙት ድጋፍ የአባላትን መብት ለመጣስ የሚያደርጉት ጥረት በመጨረሻ በሕግ የሚያስጠይቃቸውና ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ፍርዳቸውን ከማግኘት እንደማይድኑ ማመንና መረዳት ያስፈልጋል።
ውድ የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮችና በ29/12/2013 በቤተ ክርስቲያናችሁ በመገኘት ቤተ ክርስቲያናችሁንና ሃይማኖታችሁን ለመጠበቅና መብታችሁን ለማስከበር በታላቅ ትዕግሥትና ችሎታ ዕለተ ቀኑ በሰላም እንዲያልፍ በማደረጋችሁ እግዚአብሔርም የሚወደው ሰላምና ትዕግሥትን ነውና የማያልቅበት አምላክ በረከቱን አብዝቶ ይሰጣችሁ! ያሰባችሁትን ሁሉ ያሳካላችሁ!!
ወደ ፊትም እንዲሁ በየ ዕለተ እሑዱና በአስፈላጊው ጊዜ ሁሉ ወደ ቤተ ክርስቲያናችሁ በመምጣት በዚህ የሕግ የበላይነት በሰፈነበትና የሰው ልጅ ነጻነት በተረጋገጠበት ሃገር የሃሰት ተግባርን፤ ተንኮልንና አንባ ገነንነትን በሕጋዊ መንገድ በመዋጋት ለቤተ ክርስቲያናችሁ፤ ለሃይማኖታችሁና ለመብታችሁ መከበር በጽናት በመቆም ሃሰትን በእውነት በማሸነፍ ሃይማኖታችሁንና ቤተ ክርስቲያናችሁን በመጠበቅ ለትውልድ የሚተላለፍ ስራ ታከናውኑ ዘንድ የእውነት አምላክና የእውነት መንገድ በሆነው በጌታችን በመድሐኒታችን በእየሱስ ክርስቶስ ሥም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር! አሜን!!
ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያንን ከነጣቂዎች እናድን!!
የጃዋር ተቃርኖዎች፡ ባለመንጫው መቼ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳል?
በጌታቸው ሺፈራው
የዛሬን አያድርገውና ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ ጃዋር መሃመድ በበርካቶች በተለይም በዲያስፖራው ዘንድ ተቀባይነት ነበረው፡፡ ጃዋር በተለያዩ ጊዜያት ሶማሊያና የኢትዮጵያ ሁኔታ ከሚሰጠው ትንተና ባሻገር ባገኛቸው አጋጣሚዎች ሁሉ የኢህአዴግን አስተዳደር ሲቃወም ተስተውሏል፡፡ ለአብነት ያህል በአንድ ወቅት ከቀድሞው የኮሚኒኬሽን ሚኒስተር አቶ በረከት ስሞኦን ጋር አልጀዚራ ቴሊቪዥን ላይ ቀርቦ ለኢትዮጵያውያንን ጠበቃ ሆኖ መከራከሩ አይዘነጋም፡፡ ይህ የጃዋር ጥረት ከኦሮሞ ብሄርተኝነትንና የፖለቲካ ተንታኝነት አልፎ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሚል ክብር አጎናጸፈው፡፡ ጃዋር ራሱም ከጠባብ ብሄርተኝነት ይልቅ በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ውስጥ አብሮ መስራት እንደሚያስፈልግ መክሯል፡፡ ለአብነት ያህል የብአዴን ጀኔራሎች ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ ተለቅመው በታሰሩበት ወቅት ለአማርኛ ተናገሪ ኢትዮጵያውያን ተከራክሯል፡፡ እነዚህ ህዝቦች ላይ የሚደርሰውን በደል ለማስቆምም ኢትዮጵያውያን በአንድነት መስራት እንዳለባቸው መክሯል፡፡ በወቅቱ ‹‹Ethiopia: General Tadesse and General Asaminew›› በሚል መጣጥፉ ኢትዮጵያውያን በየ ብሄራቸው ከመታጠር ይልቅ አንድ መሆን እንዳለባቸው ለማሳሰብ ታዋቂውን ጸረ ናዚ አባባል ተቅሶ እንዲህ መክሯል፡፡ ‹‹መጀመሪያ በኮሚኒስቶቹ ላይ መጡ፡፡ አልተናገርኩም፡፡ ምክንያቱም ኮሚኒስት አልነበርኩም፡፡ በመቀጠልም በማህበራቱ ላይ መጡ፡፡ አልተናገርኩም፡፡ ምክንያቱም ማህበራቱ ውስጥ አልነበርኩም፡፡ ከዚያም በቤተ እስራኤላዊያን ላይ መጡ፡፡ አልተናገርኩም፡፡ ምክንያቱም ቤተ እስራኤላዊ አልነበርኩም፡፡ ከዚያም በእኔ ላይ መጡ፡፡ (አሁን) ለእኔ የሚናገርልኝ ማንም አልቀረም፡፡›› ብሎ ኢትዮጵያውያንን አስጠንቅቆ ነበር፡፡
‹‹በኢትዮጵያውያን መካከል ጥላቻን እየዘራ ለምዕተ አመት ስልጣኑን እያራዘመ የቆየውን አምባገነንነት መበጠስ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ የተረጋጋ አገርና ዴሞክራሲ ለመመስረት ያስችል ዘንድ አንዱን ቡድን ከሌላው ቡድን እያጋጨ የመኖርን አዙሪት መበጠስ ይኖርብናል፡፡ ዜጎቻችን በሰላምና በተድላ ይኖሩ ዘንድ በአገራችን የህግ የበላይነት መስፈን ይኖርበታል፡፡›› ሲልም ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከብሄር ድንበር ወጥቶ ለኢትዮጵያውያን መቆሙን እምነት ተጥሎበት ነበር፡፡ በወቅቱ በአማራነታቸው ታሰሩ ያላቸውንም ‹‹የፖለቲካ እስረኞቻችንን በዚህ በዓል ሰሞን እናስታውሳቸው፡፡ ገቢያችን የሚፈቀድልን ደግሞ ለሚወዱት (ለቤተሰቦቻቸው) እጃችንን መዘርጋት ይገባናል›› ሲል በኢትዮጵያውነት መንፈስ ጽፏል፡፡ በእርግጥ እነዚህን ተግባራት በሚያከናውንባቸው ጊዜያት ጃዋር በብሄር ጉዳይ ሰፊ እንቅስቃሴ ያደርግ እንደነበር ይታወቃል፡፡ አሁን ግን ጃዋር ባልታወቀ ምክንያት አቋሙን ቀያይሮ የማይታረቁ ተቃርኖዎች ውስጥ እየገባ ይገኛል፡፡
እንደገና ጠባብ ብሄርተኝነት (ተቃርኖ.1)
የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ በብዛት፣ በኢኮኖሚ፣ በባህልና በሌሎች ወሳኝ ጉዳዮች ትልቁን ቦታ የሚይዝና የሚያበረክት ህዝብ ነው፡፡ ይህን ጃዋርም በተደጋጋሚ ሲሟገትበት ተስተውላል፡፡ ኦነግ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለውን ህዝብ ‹‹መገንጠል›› በሚል የአናሳ ጥያቄ ውስጥ አፍኖ ማግኘት የነበረበትን ስልጣንና ክብር አሳጥቶታል፡፡ ጃዋርም ኦነግ ለኦሮሚያ ህዝብ የሚገባውን እንዳልሰራና ህዝብም ተገቢውን ስልጣን አለማግኘቱን ባገኛቸው መድረኮች ይገልጻል፡፡ ከዚህም ባሻገር ጃዋር በሌሎች ብሄሮች ላይ ተፈጸመ የሚለውን ችግር ‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያ አገራችን፣ ወንድሞቻችን›› በሚል በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ሲታገል ቆይቷል፡፡ አንድ ሆነን ብሄርን የሚያጋጨውን ስርዓት እናስወግድ፤ በራሳችን ብቻ ታጥረን ሌሎቹ ላይ የሚደርሰውን ችግር ዝም ብለን በማየታችን ችግሩ የሚደርሰው ‹‹እኛው›› ላይ ነው ብሎም ታዋቂውን ጸረ ናዚ አባባል ጠቅሶ መክሯል፡፡ በዚህ ሰናይ አቋሙም በተለያዩ ወቅቶች እንደ አንድነት ያሉ ህብረ ብሄር የአገር ውስጥ ፓርቲዎችና የዲያስፖራው አካላትም እየተጋበዘ ኢትዮጵያውያን በጋራ ችግራቸውን መቅረፍ እንዳለባቸው ትንታኔውንና አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ ይህም ይበልጡን በኢትጵያውያን ዘንድ እንዲታወቅና ትልቅ ክብር እንዲያገኝ አድርጎታል፡፡
ሆኖም ህዝብን ተጠቃሚ ባለማድረጉ የሚተቸው ኦነግ በተሸነፈበት በአሁኑ ወቅት ብሄር ዘለል ትግል ጀምሮ የነበረው ጃዋርም እንደገና ወደ ኦነጋዊ ጠባብ ብሄርተኝነት ተመልሷል፡፡ በተለይ በቅርቡ ‹‹እኔ በቅድሚያ ኦሮሞነቴን ነው የማስቀደመው›› ብሎ አገራችን፣ ወንድሞቻችን እያለ ሲያነሳው ከነበረው ይልቅ ከኦሮሞ ጉዳይ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጻል፡፡ ምንም እንኳ ይህ የአቋም ለውጥ በጃዋር ያልተጀመረ ቢሆንም ‹‹አንዱን ብሄር ከሌላኛው ብሄር›› በማጋጨት ላይ ተመስርቷ ብሎ ይቀወመው ወደነበረው ያረጀ ያፈጀ ፖለቲካ መመለሱ ትልቅ ቦታ ይሰጡት በነበሩት ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል፡፡
ከኦሮሞነት ወደ ሙስሊም ኦሮሞነት (ተቃርኖ.2)
ጃዋር በኢትዮጵያውነት ማዕቀፍ ከሌሎች ጋር ጀምሮት የነበረውን ትግል ትቶ ‹‹ቅድሚያ›› ለኦሮሞ ማለቱ ያልተጠበቀ ቢሆንም መብቱ ነው ማለት ይቻል ይሆናል፡፡ በዚህ መንሸራተቱ አለመቆሙ ግን ተቃርኖውን ይበልጡን አጠናክሮታል፡ በተለይ አልጀዚራው ‹‹ስትሪም›› በኋላ ጃዋር ከኦሮሞም ወረድ ብሎ ለኦሮሞ ሙስሊም ቅድሚያ እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡ በአንድ መድረክ ባስተላለፈው መልዕክት እሱ የተወለደበት አካባቢ ‹‹99 በመቶው›› ሙስሊም በመሆኑ ቀና ብሎ ለመሄድ የሚሞክር ክርስቲያን ኦሮሞ አንገቱን በሜንጫ እንደሚቆረጥ በኩራት ተናግሯል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ማዕቀፍ አምባገነንነትን መዋጋት አለብን ብሎ ጸረ ናዚውን አባባል ጠቅሶ ሲያስተምር የነበረው ጃዋር ወደ ኦሮም ማዕቀፍ መውረዱ ሳይበቃ አሁን ደግሞ ከኦሮሞነትም ወደ እምነት አጥብቦታል፡፡ ‹‹የተወለድኩበት አካባቢ አንገትክት ቀና ያደረክ ክርስቲያን ኦሮሞ አንገትክን በሜንጫ ትቆረጣለህ›› የሚል ‹‹ጃሃዲስት›› መልዕክት አስተላልፏል፡፡ በዚህም ጃዋር ‹‹የኦሮሞ መብት›› ይከበር ሲል የሙስሊም ኦሮሞዎች መሆኑ እንደሆነ አሳብቆበታል፡፡ ምክንያቱም ሙስሊም ኦሮሞዎች ክርሲቲያን ኦሮሞዎች አንገታቸውን ቀና አድርገው ሲሄዱ ሙስሊሞች በሜንጫ እንዲጨፈጭፏቸው እየሰበከ ለክርስቲያን ለኦሮሞ መብት መቆም ስለማይችል ነው፡፡
……ወደ ኢትዮጵያዊ ሙስሊምነት (የማይታረወቅ ተቃርኖ.3)
ስለ ሌሎች ብሄሮች ችግር፣ ስለ ሁሉም ኢትዮጵያዊነት ሰብአዊ መብት አብረን እንስራ በሚል ወደ ኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ እየገሰገሰ የነበረው ጃዋር ወደ ኦሮሞነት ከዚያም ለክርስቲያን ኦሮሞዎች ርህራሄ የሌለው ሙስሊም ኦሮሞነት ተንደርድሯል፡፡ በዚሁ አቋሙ ሳይወጣ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ለመሆንም ይጥራል፡፡ ኦሮሚያ ውስጥ ያሉት ክርስቲያኖች በሙስሊሙ አንገታቸው እንዲቀላ የሚያበረታታው ጃዋር የጎንደርና የአክሱም ሙስሊሞች ከኦሮሞ ሙስሊሞች ጋር አብረው እንዲሰሩ ሊመክር ሞክሯል፡፡ ከኢትዮጵያውነት ወደ ኦሮሞና ከዚያም ሲጠብ ወደ ኦሮሞ ሙስሊምነት የወረደው ጃዋር የብሄርን ድንበር ጥሶ የእምነት አንድነት ለመፍጠር ሲፍጨረጨር የማይታረቅ ሌላ ተቃርኖ ውስጥ መግባቱን የተረዳ አይመስልም፡፡
የዚህ ተቃርኖ በሁለት መንገድ የሚታይ ነው፡፡ አንደኛው ወደ ጠባብ የኦሮሞ ሙስሊምነት የተንደረደረው ጃዋር በብሄር ለማይመስሉት የትግራይና አማራ ሙስሊሞች መጨነቁ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ እምነትና ብሄር አብረው የማይሄዱና የሚጋጩ ማንነቶች መሆናቸው ነው፡፡ የብሄር ደንበር የማይወስነው የእምነት ማንነት መገንባት ከተፈለገ ‹‹እኔ ቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ፣ አማራ፣ ጉራጌ…›› ማለት አያስፈልገውም፡፡ ቅድሚያ ሙስሊም አሊያም ክርስቲያን መሆን ነው የሚችለው፡፡ ይህ ከሆነ ጃዋር በቅርቡ ‹‹እኔ ቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ›› ያለው ማንነቱ ያበቃለታል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ብሄርና እምነት በአገር ማዕቀፍ ሲታዩ የማይጣጣሙ ማንነቶች በመሆናቸው ነው፡፡ ጃዋር መጀመሪያ ሙስሊም ልሁን ካለ አርሲ ውስጥ ከሚገኘው ክርስቲያን ኦሮሞ ይልቅ አክሱምና ጎንደር ከሚገኙት ሙስሊሞች ጋር ዝምድና ይኖረዋል፡፡ በዚህ ወቅት ማንነቱ ኢትዮጵያዊ ነው የሚሆነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም! ሙስሊም ኦሮሞ ነኝ ብሎ ከክርስቲያን ኦሮሞው ይልቅ ሌላውን ሙስሊም ሊያስቀድም አይችልም፡፡ ‹‹ቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ!›› ካለ ደግሞ ቀድሞ የሚመጣው የጎንደርና የአክሱሙ ሙስሊም ሳይሆን ኦሮሚያ ውስጥ ያለው ክርስቲያንና ዋቄ ፈታ ኦሮሞ ነው፡፡ ጃዋር ግን በሁለቱ መካከል ሲምታታ ቆይቷል፡፡
ጃዋር ከዚህም ባሻገር ኦሮሞ ማለት ሙስሊም ማለት ነው በሚል ሌላ የተምታታ ትርጓሜ ውስጥም ገብቷል፡፡ ኦነግና አንዳንዴ የዚሁን ተሸናፊ ፓርቲ አቋም የሚይዘው ጃዋር ኦሮሚያ ምድር ላይ አልደረሱም የሚሏቸው እነ አጼ ዮሃንስና አጼ ቴዎድሮስ በሰሜን ኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ አደረሱ ብሎ የሚያምነውን ጥቃት ኦሮሞን ለመጉዳት መሆኑን ሲገልጽ መታረቅ ወደማይችለው የተቃርኖ አዙሪት ውስጥ አስገብቶታል፡፡ በአንድ ወቅት ሌላኛው ሲጎዳ ዝም ማለት የለብንም በሚል ጸረ ናዚውን አባባል ተቅሶ ሲመክር የነበረው ጃዋር አሁን ወደ ብሄር ከዚያም ወደ እምነት ናዚያዊነት እየወረደ ነው፡፡
ከኦነግነት ወደ ‹‹ጎበናነት›› (ተቃርኖ 4)
ያኔ እንዲህ ሳይምታታበት ጃዋር ኦህዴድን ኦሮሞን የሚያስገዙ አዲሶቹ ‹‹ጎበናዎች›› ብሎ ይተች እንደነበር ይታወቃል፡፡ ያኔ ‹‹ከጎበናዎቹ›› ይልቅ ከእነ አንድነት ጋር በመስራት የበኩሉን አስተዋጽኦም አድርጓል፡፡ እያቆየ ግን ጃዋር ከኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች እየሸሸ አሁን አብሯቸው እየሰራ ከሚገኘው ኢህአዴጎች ጎን መሸጎጥ ጀምሯል፡፡ ጃዋር ‹‹እኔ መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ›› ከሚለው አንስቶ ከህወሓት ጋር እንዲተባበር ያስገደዱት የተለያዩ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አንዱና የመጀመሪያው እሱ ‹‹ቀኝ ጽንፍ›› ብሎ የሚጠራቸው ፓርቲዎች ከሌሎቹ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ነው፡፡ ጃዋርና አቶ ቡልቻ ይበልጡን መጥበብ የጀመሩት አንድነት አብሮት መሄድ ካልቻለው መድረክ ይልቅ ከሌሎች ህብረ ብሄራዊ ፓርቲዎች ጋር ትብብር ለመፍጠር ፍላጎት እንዳለው በተነገረበት ማግስት ነው፡፡ ሰማያዊና አንድነት በሰላማዊ ሰልፍና በሌሎች መንገዶች ጠንከር ያለ የፖለቲካ እንቅስቀሴ ሲያደርጉ ደግሞ እነ ጃዋር ‹‹የጠላቴ ጠላት›› ብልሹ ፖለቲካ ውስጥ ገቡ፡፡
ዶ/ር መረራ ጉዲያ በአዲሱ መጽሃፋቸው እንደሚገልጹት 97 ላይ ቅንጅት ጠንካራ እንቅስቀሴ ሲያደርግ ህወሓትም ሆነ ኦህዴድ ‹‹የጸረ ነፍጠኛ›› ግንባር ለቋቋም ጥሪ አድርገውላቸው ነበር፡፡ ዶክተሩ ‹‹አልፈልግም!›› ብለው ባይመልሷቸው እሳቸውም በነ ጃዋር ‹‹አዲስ ጎበና›› ሆነውት አርፈው ነበር፡፡ ይህ ለደ/ር መረራ የቀረበ ጥሪ አንድነትና ሰማያዊ ሲጠናከሩ፣ አሊያም ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ኦህዴድ እራሱን ሊያጠናክር፣ ወይንም የዲያስፖራውን ጫና ለመቀነስ ጃዋርና የእነ ለንጮው ኦነግም ‹የጸረ ነፍጠኛው›› ጥሪ ደርሷቸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም የእነ ለንጮ ለታው ኦነግ በ2007 ዓ/ም ምርጫ ለመድረስ እየተሰናዳ እንደሆነ እየተወራ ነው፡፡ ኦነግ ለ‹‹ጸረ ነፍጠኛ›› ትግሉ ያመቸው ዘንድ አገር ውስጥ የራሱን ጠባብ ሚዲያዎች ማቋቋም ጀምሯል፡፡ ለአብነት ያህል ከወራት በፊት ‹‹ሰፉ›› የተባለች በኦሮምኛና አማርኛ የምትታተም መጽሄት ገበያ ላይ አውሏል፡፡ ለዚህም የተደራዳሪዎቹ የኦህዴድም ሆነ ህወሓት ይሁንታ እንደሚያስፈልግ አጠያያቂ አይደለም፡፡ የመጽሄቷ ዋና አላማም ስለ አሁኑ ዘመን ጭቆናም ሆነ በደል ሳይሆን ‹‹አማራ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሰውን በደል ማጋለጥ ነው››፡፡ ይህ እንግዲህ የድርድሩም ሆነ የኦነግ ስልት አንዱ አካል መሆኑ ነው፡፡ ህወሓትና ኦነግ የሚስማሙበት አላማ!
በእርግጥ ወደ አገር ውስጥ የሚመለሱት የኦነግ አመራሮች ብቻ አይደሉም፡፡ ጃዋር ሊመለስ እንደሚችልም አንዳንድ ጭምጭምታዎች እየተሰሙ ነው፡፡ ኢህአዴግ ከሌሎቹ ተቀናቃኞቹ ይልቅ ለጃዋር ርህራሄ ማሰየቱን ማሳየቱ አንድ ፍንጭ ነው፡፡ እነ አቡበክር፣ እስክንድር፣ ርዕዮት…. በእጃቸው ምንም ሳይገኝ፣ በፍጹም ሰላማዊነታቸው ‹‹አሸባሪ›› ተብለው ሲፈረድባቸውና ፊልም ሲሰራባቸው የሜንጫ ጀብድን ሲያስተምር የታየው ጃዋር ምንም አልተባለም፡፡ ከእሱ ይልቅ ኮፈሌ ውስጥ ለበቅ የያዙ ወጣቶችን ከቦኮሃራም፣ ከታሊባንና አልቃይዳ ጋር እያመሳሰሉ ‹‹አሸባሪዎች›› ብለው ፊልም ሰርተውባቸዋል፡፡
ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ደግሞ ኤሊያስ ክፍሌ ስለ ኤሌክትሪክ ገመድ ማቋረጥ ያወራው ‹‹የአሸባሪዎች ማንነት ማሳያ!›› ተደርጎ ሊቀርብ ነው፡፡ በምን መመዘኛ የኤሌክትሪክ መስመር መቁረጥ የሰው አንገት በሜንጫ ከመቁረጥ በልጦ ‹‹ሽብር›› ሊሆን ይችላል? የጃዋርን ‹‹ጀብድ›› እነ ዶ/ር መረራ፣ ዶ/ር ብርሃኑ፣ የኢሳት ጋዜጠኞች፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ….አውርተውት ቢሆን ኖሮ ስንት ፊልም ይሰራበት ነበር? ኢህአዴግ ይህንን የጃዋር ጀብድ አሁን ባይጠቀምበትም መቼም አይጠቀምበትም ማለት አይደለም፡፡ ሌሎች እሱ ከእኛ በላይ የሚያውቃቸውንም ሚስጥሮች እንደተደራደረባቸው ሁሉ ወደ አብሯቸው እየሰራ እንዳያፈነግጥም በልጓምነት ይጠቀሙበታል፡፡ እግረ መንገዱን በርካታ ‹‹ፋኦሎችን›› ያሰሩታል፡፡
በእርግጥ ጃዋር በፖለቲካው ከስሮ ወደ አገር ቤት የገባ የመጀመሪያው ሰው አይደለም፡፡ በርካቶቹ ከእሱ በላይ ‹‹ጀግና›› ተብለው ከህወሓት/ኢህአዴግ ብብት ተሸጉጠዋል፡፡ እነ ሰለሞን ተካልኝ ኤርትራ በርሃ ድረስ ሄደው ‹‹በለው!›› እንዳላሉ ተመልሰው ‹‹ይቀጥል!›› ብለዋል፡፡ ሙዚቀኞች፣ ጋዜጠኞች ፖለቲከኞች፣ የእምነት ‹‹አባቶች›› ብቻ በርካቶች እየከሰሩ ተመልሰዋል፡፡ ሲወናበድ የኖረው ጃዋር ተደራድሮ ቢመለስ የሚገርም አይደለም፡፡
ኢትዮጵያ ለጃዋር አገሩ ናትና መመለሱን የሚጠላ የለም፡፡ ችግሩ በዚህ ስርዓት ምርጫ እንደሌለ ሲናገር እንዳልቆየ ለምርጫ ሊመለስ መሆኑ መነገሩ ነው፡፡ ለኦሮሞ ህዝብ ባለመቆማቸው ኦህዴዶችን ‹‹ጎበናዎች›› እንዳላለ ከህወሓት፣ ብአዴንና ደኢህዴን ስር የሴቶች፣ የትራንስፖርት……ሚኒስቴር ስር ለመስራት ከፈቀደ ነው፡፡
አይ ስብሐት ነጋ –ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ታኅሣሥ 2006
በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ሥልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሐት ነጋ ብቻ ነው፤ እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊ ነጻነት ያለው ግለሰብ ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ በዚህ ግለሰብ ላይ የማደንቃቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፤ በሉዓላዊነቱ የተጎናጸፈውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል፤ ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም፤ ስብሐት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም፤ ሁለተኛ በሉዓላዊነቱ ያለውን ሙሉ ነጻነት በሙሉ ልብ ይጠቀምበታል፤ ናስ በላይ ከበደ እንዳለው ‹‹የቅብጠት መዘላበድ›› ሊሆን ይችላል፤ ስብሐት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም፤ ዋናው ነገር መናገሩ ነው።
በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጋዜጠኛነት ተማሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ሁለት ሰዎች ጽፈው አይቻለሁ፤ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ በፋክት ላይ፣ ናስ በላይ አበበ በኢትዮ-ምኅዳር ላይ፤ ሁለቱም ሰዎች አልወደዱለትም ማለት ያንሳል፤ የሚወዱለትና የሚያጨበጭቡለት መኖራቸውም ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ነገር ግን ስብሐት ነጋም ሆነ ደጋፊዎቹ አደባባይ ወጥተው ለመከራከር አይችሉም፤ ናስ በላይ አበበ እንደሚነግረን ‹‹አቶ ስብሐት ነጋ የውጭ ሰው እንዳይገባ ከተማሪዎቹ ጋር ተደራድረው ነበር የመጡት፤ ስለሆነም ነበር ከፍተኛ ጥበቃ አልፈን የገባነው፤›› ብቻውን ተናግሮ በጭብጨባ የሚሸኝበት መድረክ በመፈለጉ በከባድ ጥያቄም ቢሆን የሚያጣድፉት ሰዎች እንዳይኖሩ ማረጋገጡ በተማሪዎቹም ቢሆን ውሎ አድሮ ትዝብት ላይ ይጥለዋል።
ዶር. በድሉ ዋቅጂራ ስለስብሐት ነጋ ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ በሚል በጻፈው ላይ ዶር. ዳኛቸውን እንደሚከተለው ይጠቅሳል፤ ‹‹ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት፤ በቃ በአጭሩ (ኢትዮጵያዊ ሆኖ) ኢትዮጵያዊ አለመሆን ነው፤›› በቅንፍ ውስጥ ያለው የኔ ነው፤ ልክ ነው፤ አንድ ግለሰብ በማናቸውም ምክንያት ከኢትዮጵያዊነት ቢወድቅ ኢትዮጵያዊነቱ የከሸፈ ነው ለማለት ይቻላል፤ ነገር ግን ከኢትዮጵያዊነት መውደቅንና ኢትዮጵያዊነትን መጣልን ለይተን ማየት ያስፈልጋል፤ አንድ ሰው በማናቸውም ምክንያት ከፍተኛውን የኢትዮጰያዊነት ባሕርይና ግዴታ መሸከም አቅቶት ቢወድቅ ለዚያ ሰው ኢትዮጵያዊነቱ ከሸፈ፤ ለስብሐት ነጋና ለጓደኞቹ ከከሸፈባቸው የቆየ ይመስለኛል፤ ከራሱ አልፎ የሌሎችን ኢትዮጵያዊነት ለማክሸፍ የሚሞክር ደሞ ከመክሸፍ አልፎአል፤ ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት የከሸፈ ኢትዮጵያዊነት ነው ማለት ነው።
ስብሐት ነጋ ዋና ዓላማው በሙሉ ነጻነት የመጣለትን እንደመጣለት መናገር ነው፤ ምሳሌዎችን እንጥቀስ፤– ሀ) ‹‹ከኢትዮጵያ ሕዝብ በላይ የኤርትራ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት አለው፤›› ስብሐት ነጋ ስለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ስለኤርትራ ሕዝብ፣ ስለኢትዮጵያዊነት ያለው እውቀት የሚባል ነገር እንዲህ ያለው መዘባረቅ ነው፤ ስብሐት ነጋ ጨረቃ ከጸሐይ የበለጠ ትሞቃለች ቢልም አይደንቀኝም፤ አልከራከረውም፤ ስብሐት ነጋም ብቻውን መናገር እንጂ መከራከር አይፈልግም፤ ለ) ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኤርትራ ሕዝብ የበለጠ የኤርትራን መሬት ይፈልጋል፤›› እንደምሳሌ ያነሣው አሰብን ነው፤ ባድመን አላነሣም! እሱና ጓደኞቹ የኢትዮጵያን ወጣቶች በከሸፈ ጦርነት ውስጥ የማገዱት ባድመ ለሚባል መንደር ነው እንጂ አሰብ ለሚባል ወደብ አልነበረም፤ በዚያን ጊዜ ጦርነቱን በመቃወም ድምጼን ያሰማሁት ኢትዮጵያዊ ወይም ኤርትራዊ ሆኜ አልነበረም፤ ሰው ሆኜ ነው፤ ዛሬ ስብሐት ነጋ ሲዘላብድ ኢትዮጵያዊነት የማይታይበትን ያህል ኤርትራዊነትም አይታይበትም፤ በዚህም ጉዳይ ላይ መከራከር አይፈልግም፤ ሐ) ‹‹ለማንኛውም ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ መከልከላቸው የማውቀው ብዙ ነገር የለኝም፤ ይከልከሉም አልልም፤ አይከልከሉም አልልም፤ መብታቸው ነው፤›› ይህ መዘላበድ ካልሆነ ምንድን ነው? ምን ቁም-ነገር ይዞ ነው ይህንን የተናገረው? የገለባ ክምር ውስጥ አንድ ፍሬ መፈለግ ይቀላል።
አንድ ሌላ የስብሐት ነጋ ዘዴ (ዘዴ ካልነው!) ጉዳዩን በሚገባ ሳያጣራ እንደመጣለት ይናገርና ‹‹አላውቅም›› ይላል! የማያውቀውን መዘባረቅ ግን ይችላል፤ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የምን ፓርቲ እንደሆነ አይታወቅም፤ የእስላም ፓርቲ ነው?›› ስብሐት ነጋ እውቀትን የሚሻ ቢሆን ለፓርቲዎች እውቅናን የሚሰጠውን መሥሪያ ቤት ያውቀዋል፤ ለምን ብሎ ይጠይቅ? ለምን ብሎ እውነቱን በማወቅ ይታሰር? ትክክለኛ መረጃ ባለማወቅ እንደልብ የመናገርን ነጻነት ይገድባልና ‹‹አላውቅም›› ማለት ለመዘላበድ ይጠቅማል፤ ምንም እንኳን የሰላዮች ሠራዊት እንዳለው ብናውቅም ስለእስላሞችና ስለሰማያዊ ፓርቲ የተናገረውን እንደፖሊቲካ ከወሰደው ደረጃውን ከማሳየት አያልፍም፤ ሰማያዊ ፓርቲን በሁሉም ዘንድ ለማስጠላት የሚከተለውን ይላል፤ ‹‹እስላሞች ወንድሞቻችን የሚሉት ደግሞ የት ያውቁናል? ሲቀጠቅጡን የነበሩ፤ ተራ ሕዝቡም አይወዳቸውም፤›› የጤፍ ቅንጣት የምታህል የማሰብ ተግባር ቢኖርበት ስብሐት የተናገረው ያልተጠረነፉትን እስላሞች በሙሉ የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊ የሚያደርግ መሆኑን መረዳት ይችል ነበር።
ስብሐት ነጋ አንድ መቶ ሃያ ዓመታት ያህል ወደኋላ ቢሄድ ኤርትራ የሚባል አገር አያገኝም፤ በዚያ መሬት ያሉ ሰዎች ላላቸው ወይም ለሌላቸው የኢትዮጵያዊነት ስሜት የስብሐት ነጋን ምስክርነት እንደማይፈልጉ በጣም እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል፤ ለሌሎቻችን ኢትዮጵያዊነትም ቢሆን የስብሐት ነጋ ምስክርነት አያሻንም፤ አሰብን አንሥቶ ብዙ ወጣቶች ያለቁበትን ባድመን ሳያነሣ መቅረቱ በአንድ በኩል፣ አሰብንም ሆነ ባድመን ከሚፈልጉ ወገኖች መሀል እሱ መውጣቱን በጣም ግልጽ አደረገ፤ ወዴት እንደገባ ግን ገና አልነገረንም!!!
አልጋ ወራሹ ማነው?
የአንድ ወጣት እድሜ አስቆጥሯል፤ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ህወሃት/ኢህአዴግ መግዛት ከጀመረ። በብሄርና በሃይማኖት እኩልነት ስም ህብረተሰቡን በመከፋፈል ለሃያ ሶስት አመታት ስልጣኑ ላይ ከመቆየቱም በላይ፤ ጥቂቶቹ የቡድኑ አባላትና ደጋፊቆቻቸው በጉቦ በዘረፋና ለም መሬት በመሽጠት ጭምር ሲከብሩ፤ ብዙሃኑ ሕዝብ ግን ኑሮው ከእለት እለት እያሽቆለቆለበት ሲሄድ፤ አገዛዙ ግን በአሥራ ምናምን ከመቶ አድገሃል እያለ ሕዝቡን ሊያታልለው ይሞክራልል።
በአሳ መበላት፤ በዘራፉዎች መደብደብና መዘረፍ ከዚያም አልፎ ተገድሎ የሆድ እቃው መቸብቸብ እንዳለ እያወቀ ባለሁበት ሁኜ ከሚሞት እድሌን ልሞክር በማለት ክፍት በሆነለት መንገድ ከአጋሪቷ የሚሸሸው ህዝብ ቁጥር ከፍተኛ ነው ። ከዚህ ሁሉ መከራና ስቃይ ተርፈው ወደ “ተፈለገበት አገር” የሚደርሱ ወገኖቻችን እዚያም ከደረሱ በኋላ የሚደርስባቸው ስቃይና እንግልት ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም። ለዚህም በአለም ደቻሳ በሊባኖስ፤ በሸዋዬ ሞላ በሊቢያ፤ እንዲሁም ካሜራና የድምጽ መቅረጫ ያላገኛቸው በሺዎች በሚቆጠሩ፡ ወገኖቻችን የደረሰባቸውና ዛሬም በሳውዲና እንዲሁም በደቡብሱዳ እየደረስባቸው ያለው መከራና ስቃይ በቂ ምስክርነው። በእንቅርት ላይ ጆሮደግፍ እንዲሉ ሊወክላቸው የሚገባው መንግስት ህገወጥ ስደተኖች ናቸው ብሎ ተሳልቆባቸዋል።
ከላይ እንደገለጽኩት የገዢው ቡድን ህብረተሰቡን በመከፋፈልና ያለውን ሃይል በመጠቀም ጭምር እስካሁን ስልጣን ላይ ለመቆየት በቅቶአል፡:
የዛሬው ሁኔታ ባለ መልኩ ለዘላልም ስለማይቆይ ሁሉም ነገር ያልፋልና እነሱ ሲያልፉ (በጡረታም ሆነ በደከመን ወይም በዘረፋው በቃን ሲገለሉ) ልጆቻቸውን ለመተካት ሽርጉዱ ከተጀመረ አመታት ተቆጥረዋል። መተካካት ይሉታል በነሱ ቋንቋ ።
የመተካካቱ ጉዳይ ተግባራዊ ለማድረግ የመጀመሪያ እርምጃ ተተኪዎችን በአምሳያቸው ማሰልጠን ስለሆነ ለዝህም ለጆቻቸውን በውጭ ሃገር በጥሩ ትምህርት ቤቶች (በአብዛኛው ለዚሁ ጉዳይ) አስተምረዋል እያስተማሩም ነው:: በአንድ ውቅት ይህንኑ የታዘበው ጋዜጠኛ ተመስግን ደሳልኝ እንድህ ብሎ ጽፎ ነበር፡
“በእርግጥ እናንተ ሲደክማችሁ ብላቴና ልጆቻችሁን ለመተካት አስባችሁ ከሆነ የክፍለ ዘመኑ አስቂኝ ቀልድ ነው። ያውም እንዲህ የሚል..ብሶት ከወለዳቸው ወደ ደም የወለዳቸው የሚደረግ መተካካት…በሰም እና አጥንት ቆጠራ ለስልጣን መብቃት ወይም በአባት እግር ልጅን መተካት። ይህ ከሆነ መቼም በነካ እጃችሁ የመሬት ፖሊሲያችሁንም ወደ … ርስተ ጉልት … ሲስተም መቀየር የሚኖርባችሁ የመስለኛል።”
ገዢው ቡድን እንኳንስ ለሚያስቅ ለሚያስለቅስ ያውም የደም እምባ ተግባር ግድ የለለው መሆኑን ላለፉት ሁለት አስርት አመታት ሲያሳየን የሰነበተ በመሆኑ ከተሳካለት ለሳቃችን ብዙም ደንታ የለውም። የመሬት ስሪቱንም በተመለከተ ዛሬም የመሪት ባለቤት ማን ሆኖ ነው።የገዢው ቡድን ነው ገንዘብ ሲያጥረው በእንቨስትመንት ስም መሬቶችን እየቸበቸበ ያለው።ያውም ነዋሪዎችን ከቄዬያቸው በማፈናቅል።
ሃገርን የሚያህል ነገር ለማስተዳደር አነሰም በዛ በተመሳሳይ ሁኔታ በተግባር መፈተንን የግድ ይላል። ይህንን ስል መልካም አስተዳድርን ማለቴ ሳይሆን በስልጣን ላይ እንዳለው ቡድን ለራስ በሚያመች ሁኔታ መግዛትና ህዝቡን መቆጣጠር መቻል ማለቴ ነው። የህወሃት አባላት ይህንን በረሃ በነበሩበት ወቅት ተለማምድው ነው ቤተ-መንግስቱን የተቆጣጠሩት። ስለዚህም ለተተኪዎቻቸው የሙከራ ሜዳ ማስፈለጉ አልቀረም:: አገር ውስጥ መዋቅሩን እነሱ ስለዘረጉት ተተኪዎቻቸውን (ወራሾቹን) ለማሰልጠን ላያስችግር ይችላል። በዝህ የስለላ መዋቅራቸው (አንድ ለአምስት) ህዝቡን ለግዜውም ቢሆን ጠፍሮ ስለያዙት ስጋታቸው ሌላ ቦታ ነው። ለገዢው ቡድን የራስ ምታት የሆነውና ለወደፊትም ለወራሾቻቸው (ለማውረስ ከበቁ) ጭምር መሆኑ የሚቀጥለው የዳያስፖራው ክፍል ስለሆነ፤ ይህንን ክፍል ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ቀጥሎ፤ ዛሬ ወራሾቻቸው ከሆኑ ዳያስፖራውን መቆጣጠር ከቻሉ የተሳካ ውርስ ሊሆንላቸው ስለሚችል ይህንኑ የተያያዙ ይመስላል። ለዚህም ያለፈው ሰሞን የሳውዲ ተቃውሞ ሰልፍ ሁኔታና የነሱ ቀደም ቀደም ማለት በቂ ምስክር ነው።
ተመስገን ጽሁፉን በመቀጠል
“ከአባት አመራርም ወደ ልጆች አመራር ልታሸጋግሩን መዘጋጀታችሁም ምን አልባት የምትመሩትን ህዝብ አለማወቅ እንዳይመስልባችሁ ብትጠነቀቁ መልካም ነው። ምን አልባት የምትነጥፍው ጥገት ታልባ የተገኘውን ማውረስ እንጂ ሃገርና ህዝብን ለማውረስ መሞከር የመጨረሻ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል ።” ብሎ ነበር
እነርሱ ለምክር የሚሆን ጆሮ ያላቸው አይመስልም። ስልጣናቸውን ተጠቅመው ሀብት አፍርተዋል። የቀራቸው ለስም መጠሪያ የሚያገለግል ዶክቶሬት መሸመት ስለሆነ ይህንኑን ከሰሞኑን የአለም ረከርድ ባሻሻለ ሁኔታ ተያይዘውታል። ስልጣኑን ለልጆቻቸው ካወረሱ በኋላ በጡረተኛ ኑሯቸው ዶክተር እገለ ተባብለው ኑሯቸውን ለመግፋት።
ዳያስፖራው
የተቃዋሚው/የአማራጩ ክፍል ግን ገዚው ቡድን ካጠመደለት የክፍፍል ወጥመድ ብዙም ያመለጠ ሳይመስል 23 አመት አስቆጠረ::
የሃገር ቤቱን የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴን በተመለከተ በዘርም ሆነ በብሄራዊ ደረጃ የተደራጁ ፓርቲዎች እንደ አሸን የፈሉበ ወቅት ከመሆኑ ባሻገር ሀዝቡን በማሳተፍም ሆነ ጫና በመፍጠር ገዢውን ቡድን በህዝባዊ ምርጫ ለመለወጥ አለመቻላቸው እንዳለ ሆኖ ብዙዎቹ በሰላማዊም ሆነ በሌላ አማራጭ ለሥርዓት ለውጥ ትግላቸውን ቀጥለዋል:: ለትግሉ እስካሁን ውጤታማ አለመሆን ምክንያታዊ ሃተታውን ግን ሃገር ቤት ላሉት ገምጋሚዎች ብተው መልካም ነው።
የዳያስፖራው ተሳትፎ ግን ልዩ መልክና ሚና አለው:: በተለያዩ ምክንያቶች ከነበረበት አገር ለቆ ወደ ሌላ አገር ለተወሰነም ሆነ ላልተወሰነ ጊዜ እየኖረ ያለ ሰው/ማኅበረሰብ ቀድሞ ለነበረበት አገር ሰዎች ‹ዳያስፖራ› ይባላል (dispersed; Diaspora /የፈለሰ፤ ፈላሻ ፡፡ ባጭሩ ይህ የዳያስፖራ ትርጉም ሲሆን ይህ የህብረተሰብ ክፍል ለትውልድ አገሩ (Home land) በፖለቲካው በኢኮኖሚውና በማህበራዊ ኑሮ ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።
አፋኝ የሆኑ አምባገነናዊ መንግስታት ባሉባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉት ሃገሮች ሚዲያ በገዢዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ ለነሱ ፕሮፖጋንዳ መሳሪያነት ብቻ በሚያገልግልበት ዳያስፖራው የራሱን ዘዴ በመጠቀም መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ መረጃዎችን ለህዝብ ለማድረስ አቅም አለው። በተለይም በአሁን የመረጃ ቴክኖሎጂ ክፍለ-ዘመን፤ ማህበራዊ የመረጃ ልውውጦሽ በተስፋፋበት ስራውን ያቃልለታል። ሀገር ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ በገንዘብ በመደጎም አንጻርም የተሻለ አቅም ያለው ማህበረሰብ ነው።በ እንግድነትም ሆነ በቋሚነት በሚኖርበት ሁለተኛ አገሩ ባሉት መግስታት አማካይነት በትውልድ አገሩ አገዛዝ ላይ ጫና በማስፈጠርም ሚና ይጫወታል። ለዝህም ሃገራችንን በተመለከተ ምርጫ 97ትን አስከትሎ ገዚው ቡድን በህዝብ ስም የሚሰበስበውን እርዳታ በተመለከተና የ2006 የኢትዮጵያ ዴሞክራሲና ተጠያቂነት ድንጋጌ ህገ-ረቂቅ (H.R.5680 (Bill) known as The Ethiopia Freedom, Democracy and Human Rights Advancement Act of 2006) በምሳሌነት የሚጠቀስነው። ለቅንጅትም ስኬታማነት ዳያስፖራው ጉልህ ሚና ተጫውቷል። በተሟላ የ97 አይነቱ መንፈስ ጥንካሬ ባይሆንም የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ለትግሉ ወደፊት መራምድ ተጽ እኖ ማሳደሩን እንደቀጠለ ነው። በጥቅሉ ዳያስፖራው ለትውልድ ሃገሩ (Home land ) ለሚደረገው ለውጥ የሚጫወተው ሚና የጎላ ቢሆንም፤ ወሳኝነት የለውም፡፡ ወሳኙ ህዝቡ ነው፤ ችግሩንና ብሶቱን እየኖረ ያለው እሱ ነውና።
በአንጻሩም ሁሉም የዳያስፖራው ማህበረ ሰብ አባል ለትውልድ አገሩ እኩል ይቆረቆራል ወይም ይሳተፋል ማለት አይደልም።ሁሉም ከህወሃት/ኢህአዴግ ከከፋፍለህ ግዛ ዘይቤ የጸዳ ነው ማለትም አይደለም። እንዲያም ከሀገር ውስጥ ይልቅ መከፋፈል በጉልህ የሚታይበትና የሚተገበርበት በዳያስፖራው ሳይሆን አይቀርም። በዘር በሃይማኖት እንዳለ ሆኖ አልፎ አልፎ በተመሣሣይ እምነትና ዘር መንደርን ጨምሮ ክፍፍል ይንጸባረቃል። የክፍፍል ወረርሺኝ ባህር ተሻግሮ እዚህ ካለንበት ሲያተራምሰን ማየቱ እጅግ ያሳዝናል:: ይህም በበኩሉ ከመተማመን መጠራጠርን፡ ከመከባበር መናናቅን፡ ከጋራነት ግለኝነትን ካንድነት መከፋፈልን አስፍኗል። አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ይህንን የሚያራምዱ ጥቂት የማይባሉ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ በበኩሉ ትግሉን ያከብደዋል ያራዝመዋልም።
በርግጥ በግል አነሳሽነት ብዙ መስራት ቢቻልም ለአስትማማኝና ዘላቂ ውጤት ግን በጋራ መስራት አማራጭ የለውም። ለዚህም ነው የድርጅትና የመሪዎች አስፈላጊነትና ወሳኝነት። ከላይ በጠቀስኩት ምክንያት አብሮ መስራት በማይቻልበት ወቅት ሰዎች የራሳቸውን ድርጅት ለመመስረት ይወስናሉ::
በርግጥ ይህ ለትግሉ ቀጣይነት አማራጭ ከመፈልግ የመነጨ ቢሆንም የድርጅት ጋጋታ ለብቻው መፍትሄ ልሆን አይችልም። ትግላችን የሚለካው ሃገር ውስጥም ሆነ ውጭ ባሉት የድርጅቶች ብዛት ቢሆን ኖሮ ለህዝባችን ያሰብነውን መልካም አስተዳደር እውን ባደረግን ነበር።
የድርጅት መብዛት ውድድሩን ያሰፋና የተወሰኑት ጠንክረው አሸናፊ ሆነው የወጣሉ ብለው የሚከራከሩ አልጠፉም። በሃገራችን የተፈጠሩት ድርጅቶች ግልጽ በሆነ የፖለቲካ ስርአት ላይ ሳይሆን ብሄርን መስረት ያደረጉ በመሆኑ ለፉክክር የማያመቹ ናቸው ያ ከሌለ ፉክክር ደግሞ አንዱ አሸናፊ ሆኖ መውጣቱ አይኖርም ማለት ነው። ስለዝህም መሬት ላይ ያለው እውነታ የሚያሳየው በሚያመቸው መልኩ የድርጅቶች አብሮ መስራት የግድ ይላል። የሰው ሃይልና ሃብት/ገንዘብ አንድ ላይ በማምጣት ያሉት ድርጅቶች እንዲጎለብቱና ትግሉን በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ይረዳል።
ብዙዎች የዲያስፖራው ማህበርሰብ አባላት፤ አቶ ሃይለማርያም የገዚው ቡድን መሪ ሆኖ ሲተኩ ከቅን አመለካከት የተነሳ፤ መሰረታዊ ባይሆንም ለውጥ ይኖራል፡ በይቅር መባባል ህዝባችንን ወደ ተሻለ አቅጣጫ መምራት ይቻላልና ጊዜ እንስጣቸው ብለው ነበር ። ያ ሳይሆን ቀረ። አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ ምንም እንኳን የተለወጠ ነገር ባይኖርም የማንዴላን ህልፈት በማስታከክ ለእውነትና ለእርቅ (truth and reconciliation) በድጋሜ ጥሪ እየቀረበ ነው።
የበደልንን ይቅር ብሎ አብሮ ለመስራት መፍትሄ መፈለግ ለሁሉም ይበጃል። ተበዳዩ ህዝብ ነውና እሱኑ ይቅርታ ጠይቆ እሱኑ ለማገልገል አብሮ መስራት ብልህነት ነው። የቂም ፖለቲካ የትም አያደርስምና። ችግሩ ግን እርቅ የሁሉንም በጎገ ፍቃደኝነት ይጠይቃል። በምኞት ብቻ የሚሆን አይደለም። ከምኞትም አልፎ አስገዳጅ ሆኔታዎች መፈጠር የግድ ይላል። የደቡብ አፍሪካን ስንመለከትም የአለም አቀፍ መንግስታት ጫና፣ መገለልና አለም አቀፍ ፖለቲካ አሰላለፍ በመለወጡ ጭምር እንጂ ዘረኛው የነጮች መግስት ከምንም ተነስቶ አይደለም ማንዴላንና ፓርቲያቸውን የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስን ነጻ ያደረጋቸው።
ህወሃት/ኢህአዴግ ከጥንስሡ ጀምሮ እያካሄደ ያለው የቂም ፖለቲካ ነው። ብዙ አመታት ወደኋላ ሄዶ እንድህ ነበርን/ነበራችሁ፡ ተደረግን/ተደረጋችሁ እያለ ለስልጣን መቆያ ከመጠቀም ባሻገር እየተጓዘበት ያለው መንገድ የትም እንደማያድርስ አውቆ፤ አንዴም ቆምብሎ አስቦ አብሮ የመድራትን ፍንጭ ያሳየበት ወቅት የለም።
የተቃዋሚው ክፍል ጫና ማሳደር ካልቻለ እርቅ ምኞት ሆኖ የቀራል። በርግጥ ገዢዎቻችን ቢያውቁበት ኖሮ፤ ፕ/ት ኦባማ እንዳሉት በፍቃደኝነት ህዝቡን ነጻ ቢያወጡ፤ እነሱ ጭምር ነበር ነጻ የሚወጡት:: ጊዜያቸው ሲደርስ መውደቃቸው ላይቀር። ያኔ ግን ለይቅርታ ጊዜው የመሸ ይሆናል።
ከዳያስፖራውም ክፍል ለሆዱ ያደረና ከህዝቡ ይልቅ ህገር ቤት የቀለሰ ጎጆ የሚያሳስበው፤ ቤተሰቡን ሰብስቦ ለቀሪው ዘመዱ ላልሆነው የማይጨነቅ “ገለልተኛ ነኝ” ባይ፤ እኔ ፖለቲካ አልወድም ከሚለው አልፎ ፤የመቶ አመት ታሪክ እየጠቀሰ ተበድለን ነበር ፤ በተቃራኒው “ለዘመናት የነበረህን ቦታ ዛሬ ተቀማህ” እያለ ጢቂቶችን የሚያስጨበጭብ…. .ወዘተ አውቆም ሆነ ሳያውቅ የገዢውን ቡድን እድሜ የሚያራዝም በተቃዋሚው ጎራ ነኝ ባይ ቁጥሩ ቀላል አይደለም። የገዚው ቡድን አንደኛውን “ጠባብ” ሌላኛውን ደግሞ “ነውጠኛው ዳያስፖራ” ብሎ የጠራቸዋል። ለትግብርቱ ግን ቀዳሚው እርሱ ነው። ሁለቱም ቃላት ብዙውን ግዜ ያለቦታቸው ጥቅም ላይ ስለሚውሉ ባይመቹኝም ከላይ የተጠቀሱትን በተመለከተ ግን ሃቁን ያንጸባርቃሉ።
ጥሩም ሆነ መጥፎው፤ ክፉም ሆነ ደግ ያለፉት የኢትዮጵያ ታሪኮች ወደድንም ጠላን የጋራ ታሪኮቻችን ናቸው። ያለፈወን ታሪካችንን መዝግበን የምናቆየውና የምናስታውሰው መጥፎውን ላለመድገምና ጥሩውን ደግሞ ያለንበት ዘመን የሚፈቅድ ከሆነ ለማስቀጠል አሊያም በጥሩነቱ ለማስታወስ እንጂ ለቂም በቀል መጠቀሚያነት ለማዋል አይደለም። እዚህ ላይ በማንኛውም ህብረተብ በአብዛኛው ያለፉት ታሪካዊ ስህተቶች በስህተትነታቸው የሚታወቁት ከብዙ ጊዜ በኋላ እንጂ በወቅቱ ተጫባጭ ሆኔታ እንደ ስህተት ተደርገው አይቆጠሩም። ከነዚህ ስህተቱች ያመለጠና ፍጹም የሆነ የአለም ታሪክም የለም።
ህዝባችን የሚፈልገው የዛሬው ጎስቋላ ኑሮው የሚሻሻልበት፤ ነጻ አየር ተንፍሶ በመኖር የተሻላች ሃገር ለመጪው ትውልድ የሚያስተላልፍበትን ሁኔታ የሚያመቻችለትን እንጂ ብዙ አመታት ወደኋላ ሄዶ በታሪክ ያሳለፈውን ኑሮ እንዲኖር ወይም ከዛሬው መከራና ስቃይ በተጭማሪ ያሳለፈው ችግር እያስታወሱት ለጊዚያዊ የፖሊቲካ አላማቸው መጠቀሚያ የሚያደርጉትን የአዞ እንባ የሚያነቡለትን አይደለም።
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ ተደራጅቶ እንደታወቁት የአይሁዶች የኩባና የአይርላንድ ዳያስፖራ ድርጅቶች ደረጃ ለመድረስ ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም፤ ያላቸውን ሃይልና ገንዘብ አንድ ላይ በማምጣት ልዩነትን አቻችሎ፤ ከመጠላልፍ መደጋገፍን፤ ከግትርነት ሰጥቶ መቀበልን በማስቀደም፡ ሁሉንም እኔ አውቃለህና ተከተለኝ እኔ ብቻ ልናገርና አንተ አድምጠኝ፡ ፍጹም ነኝና እኔን ለማረም አትሞክር የመሳሰሉትም ግብዝነትን ትተን፤ በተቃራኒውም የሚሰራ ሰው እንደሚሳሳት በመዘንጋት አሊያም ሆን ተብሎ ትግሉን ለማደናቀፍ የምንሰነዘረውን ቅጥ ያጣ ገንቢ ያልሆነ ትችትን፤ እንደ ጭቃ አንስቶ መለጠፍን አቁመን ለዋና ግባችን (የስርአት ለውጥ) አብረን ከሰራን፤ በየምንኖርበትርበት ሃገር የውጭ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖን በማሳደርና ህገር ውስጥ ለሚደረገው ትግል የተሟላ ድጋፍ በመስጠት ገዢው ቡድን ቢያንስ ወደ ክብ ጠረጴዛ እንዲመጣ ማድረግ ይቻላል። ያለ ጫና ከህወሃት/ኢህአዴግ እርቅ መጠበቅ ከየዋህነትም አልፎ ጅልነት ነው።
አላህ ኢትዮጵያን ከነ ህዝቦቿ ይባርካት
ባህር ከማል
ለአስተያየት bahirk@hotmail.com
ዋቢ:
• ይድረስ ለኢህአዴግ አመራር አባላት ልጆቻችሁ ቻይና ምን
እየሰሩ ነው? ተመስገን ደሳለኝ ከፍትህ ገዜጣ የተወሰደ
• The Role of Diasporas in Peace, Democracy and Development in the Horn of Africa Ulf Johansson Dahre (ed.)
• Diasporas and democratization in the post communist World Maria Koinova
ጃዋርና መንጋዎቹ –ዓለማየሁ መሀመድ (4)
ምጥን መረጃ (ሀ)
አባ ሜንጫ ሰሞኑን ያልረገጠው ደጅ፡ ያላንኳኳው በር የለም። ቦይኮት በደሌን ከማወጁ ቀደም ብሎ በጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ዶይቼ ቬሌ የአማርኛ ፕሮግራም አንድ የውይይት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ነበረ። በዚህ ውይይት ላይ ሶስት እንግዶች በአጼ ሚኒሊክ ዙሪያ ይሟገታሉ። አንጋፋው የኦሮሞ ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አንደኛው ተሳታፊ ነበሩ። ለእኚህ ጉምቱ ፖለቲከኛ የነበረኝ ትልቅ ግምት ተሸርሽሮ አፈር ከድሜ አሽቀንጥሬ የጣልኩት በዶይቼቬሌው ውይይት ላይ ነው። ጃዋርና እሳቸው በእድሜና በአገላለጽ ካልሆነ በቀር ፈጽሞ የሚለያዩበት ነገር አጣሁባቸው። በእስተርጅና መዘባረቅ በእርግጥ በእሳቸው አልተጀመረም። በእሳቸውም የሚቆም አይሆንም። ለኢትዮጵያችን እንደአባት የምመለከታቸው፡ ወጠጤ ፖለቲከኞች ሽምጥ ቢጋልቡ እንኳን የሚመልሱ፡ የሚያስታርቁ ብዬ ተስፋ ከጣልኩባቸው አዛውንት አንዱ አቶ ቡልቻ ነበሩ። ሰው ሲረክስ ለነገ እንደማይል የተረዳሁትም በእሳቸው ነው። ቀለሉብኝ። ከወርቅነት በአንድ ጊዜ የቆርቆሮን ዋጋ እንኳን ልሰጣቸው ከበደኝ።
ለማንኛውም የዶይቸቬሌው ውይይት አቶ ቡልቻ የዘረኝነት በሽታ የተጠናወታቸው፡ እንደ ወጠጤዎቹ አባ ሜንጫ በተረት ተረት ሀገር ለማመስ ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸውን ነበር ያጋለጣቸው። ከታሪክ ጋር ተላተሙ። አሻሮ ይዘው ከቆሎ ጋር ሞገቱ። አፈታሪክ ሰንቀው ከታሪክ ምሁር ጋር ቀረቡ።ከዚያም የሆነው ሆነ። በውይይቱ አቶ ቡልቻ በዝረራ ተሸነፉ። በቅጽበት ከሰፊው የፖለቲካ ስብዕናቸው ወርደው፡ ወደ ጎሳ መንደር ጓዛቸውን ጠቅልለው ገቡ። አቶ ቡልቻ የእድሜአቸውን መሆን አቃታቸው። በጠባብነት ጽኑ ህመም እንደሚሰቃዩ ተረጋገጠ። እናም በዜሮ ወጡ።
ይሄኔ በራሱ ጊዜ የኦሮሞ መሪነትን አክሊል የደፋው አባ ሜንጫ(ጃዋር) ከኒውዮርክ ተወነጨፈ። ለጀርመን ሬዲዮ የአማርኛ ፕሮግራም ክፍል ደብዳቤ ሰደደ። መንጋዎቹን አስፈርሞ፡ በዕለቱ ውይይቱን የሚመራው ጋዜጠኛ ‘’የሚኒሊክ የልጅ ልጅ ልጅ ነው፡ ሆን ብሎ; ያልተዘጋጁትን አቶ ቡልቻን በማቅረብ የኦሮሞን መብት አልከሰከሰው; ስለዚህ ጋዜጠኛው ከስራ ይታገድልን’’ የሚል ደብዳቤ ጽፎ ለሬዲዮ ጣባያው ሃላፊዎች ላከ። መቼም ልቡ ተራራ ነው። መንጠራራት ያውቅበታል።ባዶ ሜዳ ተወጠረ። ከማጠሩ ደግሞ መወጠሩ።
የጀርመን ሬዲዮ ሃላፊዎች ደብዳቤው ሲደርሳቸው ጉዳዩን የተረዱት በተቃራኒው ነው። ለካንስ እንደዚህ ያለ ሞጋች ውይይት ማዘጋጀት ይቻላል? የሚለው ነው ለጀርመኖቹ ጎልቶ የታያቸው። እናም ጋዜጠኛውን በርታ አሉት። አቶ ቡልቻ የተዘረሩት ስላልተዘጋጁ አልነበረም። ይዘው የቀረቡት አፈታሪክ ስለሆነ እንጂ። ተረት ተረት። እነጃዋር የወረወሩት ሰይፍ ዶለዶመ።
ምጥን መረጃ(ለ)
የአኖሌ ፈጣሪ; የሻዕቢያ ሴራ አስፈጻሚ; በስደተኛ ስም ስለላና ጸረ ኢትዮጵያ መርዙን በየሄደበት የሚተፋው ተስፋዬ ገብረአብ ሰሞኑን ድምጹን ያጠፋ የመሰላቸው ካሉ ተሳስተዋል። የቦይ ኮት በደሌ ዘመቻ ስውር አስፈጻሚ ስለመሆኑ የሚያሳዩ መረጃዎች ደርሰውኛል። ተስፋዬ ሆላንድ የሚገኝ አንድ ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ይዞት የወጣውንና ሚኒሊክን ጡት ቆራጭ አድርጎ ያቀረበበትን ዘገባ በሙሉ መረጃውን ያቀበለው ተስፋዬ ነው። ጃዋርና ተስፋዬ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ጋብቻ መፈጸማቸው የተረጋገጠበት አንዱ ማሳያ የተስፋዬ ለሆላንዱ ጋዜጣ የተንሸዋረረ መረጃ መስጠቱ ነው። ጃዋር ከስንቱ ተጋብቶ እንደሚዘልቅ እኔጃ! ኢትዮጵያ የምትጠፋ ከሆነ ከአጋንንት ጋርም ይወዳጃል። ለማንኛውም የሆላንዱ ጋዜጣ የተሰጠውን መረጃ ሳያላምጥ እንዳለ ዘርግፎታል። የሌላኛውን ወገን ሀሳብና አቋም ሳያካትት ጋዜጣው ታሪካዊ ስህተት ሰርቷል። በቀጣይ ኢትዮጵያውያን እዚህ ጋዜጣ ላይ ጫና ፈጥረው ይቅርታ እንዲጠይቅና በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያወጣ ማድረግ አለባቸው። ተስፋዬ ለውለታው የኦሮሞ ፈርስት መድረኮች ላይ እየተጋበዘ ነው።
ወደ ጉዳዬ ተመለስኩ
የጤሰው አቧራ በእርግጥ ሰከን እያለ ነው። የተቀሰቀሰው የጥላቻ ዘመቻ በረድ እያለ ነው። ጃዋራውያን በሌላ ሃይል ጣልቃ ገብነት የመጣን ውሳኔ ቀምተው በአስረሽ መቺው ለቀናት ቆይተዋል። ጃዋርና መንጋዎቹ ዳቦ ሳይቆረስ ስም ላወጡት የጥላቻ ዘመቻቸው(የቁቤ ትውልድ) ከወያኔ ባገኙት ቀጥተኛ ድጋፍ ያዙኝ ልቀቁኝ ብለው ከሰነበቱ በኋላ አሁን ጥርሳቸውን እየሞረዱ ነው። ከጥላቻ በቀር መልካም ነገር ለማሰብ ያልታደለውን አእምሮአቸውን እያስጨነቁት ነው። ማጥፋት እንጂ ማልማት ሲጀምርም ያልፈጠረላቸውን እጆቻቸውን ከፌስቡክ መንደር ለማያልፈው ጫጫታቸው እያሰናዷቸው ነው። የጭብጨባ ስካሩ ያለቀቀው አባ ሜንጫ(ጃዋር) ከታላላቁቹ የትምህርት ተቋማት ስታንፈርድና ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲዎች ያገኛቸውን ምጡቅ እውቀቶች ትራሱ ስር ወሽቆ መንጋውን ለሌላ ዙር የጥላቻ ዘመቻ ሊያሰማራ እየተዘጋጀበት ነው። መቼም ፈጣሪ የልቡን አውቆት ለእባብ እግር ነሳው ነው የሚባለው? የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ወደ ሰማይ ቀዘነ ብሎ የነገረኝ ማን ነው?
በእርግጥ ማስረጃዎቹ እስከአሁን ከእጄ አልገቡም:: እየጠበኳቸው ነው። ለመዘግየቱ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ለነገሩ ወያኔ እኔ ማስረጃዎቹን እየጠበኳቸው እያለ ሊያግዘኝ ነው መሰለኝ በይፋ ጋብቻቸውን አብስሯል። መቼም አመስግኜ የማላውቀውን ወያኔን ዛሬ ላመስግነው ይሆን? ደግ ነው። አንዳንዴም እውነት ታምልጣችሁ እንጂ!
የሄኒከን ኮንሰርቱን የመሰረዝ ውሳኔ የመጣው ከወያኔ መንደር በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ስለመሆኑ በእርግጥ ጃዋራውያን ያጡታል ብዬ አላስብም። አልጠብቅምም። ለራሳቸው እያጨበጨቡ፡ ውስኪ እየተራጩ መሆናቸው በአደባባይ እያሳዩት ያለው ጩኧት ቢሆንም በውስጣቸው ፡ በልባቸው ግን ወያኔን እያመሰገኑ ተላላኪውን ኦህዴድን ያኑርልን እያሉ መሆናቸውን መቼም ልብና ኩላሊት መመርመር የሚችለው ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው:: እነሱ ለራሳቸው ከካዱ ማለቴ ነው። ለማንኛው ወያኔ በኦህዴድ አማካኝነት ለሄኒከን ኩባንያ ማስፈራሪያ ሰጥቷል። የጸጥታ ዋስትና የከለከለው ወያኔ በጃዋርና መንጋዎቹ ጫጫታ ያልተንበረከከውን ሄኒከንን በመጨረሻም እጁን ጠምዝዞ ኮንሰርቱን እንዲሰርዝ አድርጎታል። የእነጃዋርና ወያኔ ጋብቻን ያሳበቀው ይኧው የኮንሰርት መሰረዝ የባረቀበት ይመስላል። ጃዋራውያን የሌላን ውሳኔ መንትፈው መጨፈራቸው ብዙም ርቀት ያልወሰዳቸው ለምን ይሆን? ከማጥቃት ወደ መከላከል በፍጥነት ተገልብጠው ‘’ድሉ የእኛ ነው;; ማንትስ ይመስክር; የአኖሌ አጥንት እሾክ ሆኖ ይውጋን’’ ዓይነት መሃላ እያዥጎደጎዱ ያሉት ማን ሞግቶአቸው ነው?
እግር ጥሎኝ ከፓልቶክ መንደር ባለፈው ሳምንት ጎራ ብዬ ነበር። የጃዋር መንጋዎች ‘’ጄኖሳይድ’’ ብለው ፓልቶክ ከፍተው ይንጫጫሉ። እንደ ቢንቢ ጆሮ ላይ ይጮሃሉ። የጡሉትን የአማርኛ ቋንቋ እያቀላጠፉት ሚኒሊክን ይረግማሉ። ቴዲን ይዘልፋሉ። አማራው ላይ የስድብ ናዳ ያወርዳሉ። የገረሙኝ ሁለት ነገሮች። አንደኛ ጄኖሳይድ ብለው የጫጫታ መድረክ መክፈታቸው ነው። ካልጠፋ ስም ምናለ ይህቺ የኤርትራዊው ተስፋዬ ገብረአብ የብእር ጭማቂ በሆነችው የፈረደባት ‘’አኖሌ’’ ስም እንኳን ቢጠሩት? ወይም ‘’ጡት’’ ቢሉት?
ሌላው እድሜው ለአቅመ መናገር ያልደረሰ ሁሉ ማይክ እየጨበጡ ቋንቋ መለማመጃ፡ አፍ መፍቺያ ያደረገው አጼ ሚኒሊክ ላይ መሆኑ ነው። ይገርማል። አንድ ዓይነት ሰዎች። መንጋዎች። እንደ ሳሙና ፋብሪካ አንድ ዓይነት ምርቶች። ከንቱ።
ታዲያ ከዚያ ከጄኖሳይ ፓልቶክ ክፍል ለደቂቃዎች ቆይቼ ነበር። ድንገት የፓልቶክ ክፍሉ መሪ ብቅ አለና ‘’ኦቦ አባዱላ ገመዳ እዚህ ክፍል እንዳሉ እናውቃለን;; ጀግናው ወንድማችን! እናመሰግናለን;; እባካችሁ ለዚህ ወንድማችን ምስጋና እናቅርብለት;; አባዱላ –ገለቶማ!!’’ የፓልቶክ ክፍሉ መሪ በሞቅታ ይሁን በቴዲ ኮንሰርት መሰረዝ- ደስታ አስክሮት አይታወቅም እንደ ህጻን እየቦረቀ ምስጋናውን አዥጎደጎደጎደው። መንጋው ተከትሎ ለአባዱላ ገመዳ አበባ አበረከተለት። የፓልቶኩ ሎቢ ለአባዱላ በተበረከተ አበባ ተሽቆጠቆጠ። ጃዋር የለም። ስሙ አይጠራም። ቦይ ኮት በደሌ ዘመቻ አይነሳም። ኮንሰርቱ እንዲሰረዝ ያደረገው አካል ተመሰገነ። ተወደሰ። ‘’አባዱላ –ገለቶማ’’። በስውር ወያኔ የምስጋና መዓት ሸመተ። ለካንስ ምድረ የወያኔና ኦህዴድ ሹማምንት ነው በጄኖሳይድ ፓልቶክ ክፍል የሚርመሰመሰው?!
ታዲያ እነ ጃዋር ለምን ውስኪ ይራጫሉ? መንጋዎቹ ለምንስ መለኪያ ያጋጫሉ? ቺርስን ምን አመጣው? ኮንሰርቱ እንደሚሰረዝ ቀድሜ አውቄ ነበርና ጃዋር ዳንኪራ ሊመታ እንደሚመጣ ገምቼ ነበር። የሄኒከንን ውሳኔ ይፋ መሆን ተከትሎ ጃዋርና መንጋዎቹ ድል አደረግን ብለው ሰማይ ምድሩን ሊቀውጡት እንደሚችሉ ጠብቄ ነበር። የሆነውም የገመትኩት; የጠበኩት ነው። የህንድ ፊልም ቀሽም ነው የሚባለው የሚጠበቅ የሚገመት ቀጥሎ ስለሚሆን ነው። እነጃዋር እንደ ህንድ ፊልም ቀሽም ሆነው ብቅ አሉ። ዋንጫውን ለራሳቸው ሸለሙ። ለራሳቸው አጨበጨቡ። ራሳቸውን አወደሱ።አሞገሱ። አባ ሜንጫ ደግሞ አበጠ። ትልሿ ልቡ ተራራ አክላ ልትፈነዳ ደረሰች። ተንጠራራ። ተወጠረ። ከማጠሩ መወጠሩ።
የወያኔ የፌስ ቡክ ሰራዊት
ዳንኤል ብርሃኔ የሚባል አንድ ከፌስ ቡክ መንደር የማይጠፋ፡ ተከፋይ የወያኔ የፌስቡክ ሰራዊት ጠርናፊን የማያውቅ ያለ አይመስለኝም። ስለዚህ የወያኔ ጃንደረባ ብዙም የማውቀው ነገር የለም። በጫት ሱስ የሚስተካከለው እንደሌለ ሳር ቅጠሉ የሚመሰክሩለት፡ እነበረከት ስምኦን ምን እያሰቡ እንዳለ ለማወቅ ይሄን ጃንደረባ መከታተል ብቻ እንደሚበቃ የነገሩኝ ወዳጆቼ ናቸው። የፌስ ቡክ ሰራዊት ተዘጋጅቶለታል። ከወያኔ የመረጃና የደህንነት መስሪያ ቤት ሚስጢራዊ መዋቅር ተዘርግቶለታል። በጀት ተመድቦለታል። ስራ የፈቱ፡ በየዩኒቨርሲቲው ዓመታት ቢቆዩ የማይመረቁ ጆሮ በመጥባት ጆሮአቸውን ያሳበጡ አማተር ካድሬዎችን በስሩ አድርጎ በማህበራዊ መድረኮች ላይ ከዘመተ ሰነባብቷል።
ዳንኤል ጭፍን ነው። ዓይኑን በጨው አጥቦ ጥቁሩን ነጭ ነው ይላል። ሀፍረት፡ ይሉኝታ፡ ዕውነት፡ ሀቅ ሲያልፉም አይነካኩትም። ወያኔን ቀለም እየቀባ በየፌስ ቡኩ ግድግዳ ይርመሰመሳል። አጀንዳ ሲሰጠው ፌስቡክ፡ ቲውተርና ብሎጉ ላይ ይዘረግፋል። አጨብጫቢዎቹና አማተር ካድሬዎቹ ያጅቡታል። ወያኔን ቆንጆ ነው እያለ ይዘላብዳል። ሁል ጊዜም ያበሳጨኝ የነበረው የዳንኤል መርመጥመጥ ሳይሆን እሱ በቸከቸከ ቁጥር የሚሟገቱት የሚላፉት ናቸው።
ዳንኤል የሰሞንኛው የእነጃዋርና መንጋዎቹ ጩኧት የወያኔ የመደናበር ውጤት የመዘዘው የመጨረሻው ካርድ መሆኑን በይፋ አሳይቷል። ዳንኤልና ጃዋር ተስማምተው አንድ አጀንዳ ቀርጸው ተነስተዋል። ዳንኤል የጃዋር አለቃ ሊሆን ይችላል። ኦህዴድ የወያኔ አለቃ መሆን እንዴት ይቻለዋል? እናም ጃዋር ከኒው ዮርክ፡ ዳንኤል ከድሬዳዋ ተመሳሳይ እሳት መትፋት ጀመሩ። ዳንኤል ሌላም ተረት ተረት ጀባ ብሎናል። ጃዋር ሚኒሊክን ጡት ቆራጭ አድርጎ ይጮሃል። መንጋዎቹን ያስጠናል። ዳንኤል ደግሞ ሚኒሊክ ወደትግራይ ሰራዊታቸውን ሲያሰማሩ የትግራይ ወንዶችን ቆለጥ ይቆርጡ ነበር አለና አረፈው። የባሰ አታምጣ ነው መቼም። ትግራይ ላይ የቆለጥ ሀውልት እንዳያቆሙና በሳቅ እንዳያፈነዱን??!!!
መንጋዎቹ
የኦሮሞ ወንድሞቼና እህቶቼ በእርግጥ ሁሉም ከጃዋር ጋር እያበዱ ነው ማለት አይቻልም። የጃዋር ስካር ወላፈኑ የደረሳቸው፡ የሰሙትን ሳያላምጡ በስሜት ብቻ ተደፋፍረው ሞቅታ ውስጥ ገብተው ድንኪራውን እያቀለጡት ላሉት ጃዋራውያን የማሰቢያ ጊዜ ሊሰጣቸው ይገባል ባይ ነኝ። ጃዋር ሲለቀልቅ ተንጋግቶ ማጫፈር ጃዋርን አሳበጠው እንጂ የኦሮሞን ህዝብ ትግል ስንዝር እንኳን ፈቅ አላደረገውም። በጃዋር ፌስ ቡክ ላይ እያደፈጡ ለሚውሉ የኦሮሞ ወንድሞቼና እህቶቼ ከመንጋው ወጥተው ማሰብና ሰከን ማለት እንዳለባቸው ብመክራቸው ደስ ባለኝ። በዘር ማሰብ የደካማነት ሁሉ መጨረሻው ነው። አንድ ሰው አቅም ሲያጣ ሮጦ የሚወሸቀው በዘር ስብስብ ውስጥ ነው። መዳንም መሞትም በጅምላ አይደለም። በሰማይም በምድርም ለፍርድ የምንቀርበው በግል እንጂ በዘር ስብስብ አይደለም። የጃዋር መንጋዎች ሰከን በሉ። ከስካር ውጡ። ሃንግቨር ላይ ያላችሁም በቶሎ ተላቀቁ።
ማጠቃለያ
ወያኔ ኦህዴድን አሰማርቷል።የመጨረሻውን ካርድ ስቧል። ተስፋዬ ገብረአብ ስራውን እየሰራ ነው። ጃዋር እናት ድርጅቱን ለማዳን የሞት ሽረት ትግል ላይ ነው። ኦህዴድን(ወያኔን)። የቦይ ኮት በደሌ ዘመቻና የሰሞኑ ጫጫታ የወያኔ ስሌት መሆኑን ያላመነ ካለ እሱ አውቆ የተኛ ነው። ቢቀሰቅሱትም አይሰማም። በታሪክ መጽሀፍት ውስጥ ተደብቆ የመቶ ዓመት ክስተትን በሸውራራው እያነሱ ዛሬን በጨለማ መጋረድና የነገን ተስፋ ማጠልሸት የ21ኛው ክፍለዘመን ጭንቅላት አይደለም። ጃዋር ከንቱ ነው። በእድልም በጥረትም ለማይገኙት ከሚከብዱት ከታላላቆቹ የትምህርት ተቋማት ዕውቀት ሸምቶ እሱ ዘር ቆጠራ ውስጥ ጭልጥ ብሎ በመግባት የህዝብ እልቂት የሚጋብዝ መሆኑ ከማንም በላይ ለተማረባቸው ዩኒቨርሲዎች ውርደት ነው። ድንጋይ 40 ዓመትም ውሃ ውስጥ ቢቆይ መዋኘት አይችልም። ዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎቻቸውን አይከታተሉም ማለት ነው? ሰው መቀየር እንደማይችሉ ፍንጭ የሰጠበት ይሆን የጃዋር ሁኔታ?ሽልም ካለ ይገፋል ቦርጭም ከሆነ ይጠፋል። የእነጃዋር ዳንኪራ ከአንድ ሰሞን ግርግር እንደማያልፍ ይታወቃል። ይኧው እየከሰመ ነው። ወያኔ ለጊዜው እፎይታን አግኝቶ ሊሆን ይችላል። እነጃዋር አዲስ አበባ ገብተው የጨፌ ኦሮሚያን ስልጣን የሚቆጣጠሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። የኦሮሞና የሌላው ኢትዮጵያዊ ትግል ግን ፈር ይዟል። እነጃዋር የወያኔ ነፍስ ለማስቀጠል ያደረጉት መፍጨርጨር ብዙም ርቀት አልወሰዳቸውም። ከዚህ በኋላ ምናልባት የቀናት ጉዳይ እንጂ ጫጫታው እስከመኖሩም ይጠፋል።
ቸር እንሰንብት
አቶ አያሌው ጎበዜ ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንትነታቸው ለምን ተነሱ?
ከአቡዛብር ተገኝ
ፋክት መፅሄት (በታህሳስ 2006፣ ቁጥር 26 እትሙ) የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ አያሌው ጎበዜ በምን ምክንያት ከስልጣን እንደ ተነሱ ያሰፈራቸውን መላምቶች አንብቤያለሁ፡፡ ብዙዎቹ በግምትና በይሆናል ላይ የተመሰረቱ ከመሆናቸውም በላይ ለግለሰቡ ከፕሬዝዳንትነት መነሳት በዋና ምክንያትነት ሊመደቡ የሚችሉ አይደሉም፡፡ ለዚህም ነው ለመፃፍ መነሳቴ፡፡
አቶ አያሌው ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንትነት የተነሱበት ዋና ምክንያት ምንድነው?
ከዜናው ሀሳብ በመነሳት በአንድምታ የምንረዳው እውነታ ስላለ፣ በኢቲቪ ከቀረበው የአቶ አያሌው ዱላ የማቀበል ዜና ልጀምር፡- በኢቲቪ ዜና መሰረት አቶ አያሌው ጎበዜ ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንትነት ስልጣናቸው የተነሱት በፍቃዳቸው ነው፤ “በቃኝ፣ ዱላውን ላቀብል” ብለው፡፡ እንኳንስ ከክልል ፕሬዝዳንትነት ስልጣን ላይ ይቅርና ከተራው የሹመት ስልጣን (ለምሳሌ ምክትል ቢሮ ሀላፊ፣ ከዚያም ዝቅ ሲል “ፕሮሰስ ኦውነር”) ላይ በራሱ ፈቃድ “ልውረድ” ያለን የፖለቲካ ተሿሚ፣ ኢህአዴግ “‘በቃኝ’ ካልክማ እሰዬ” ብሎ ቶሎ የመልቀቅ ልምድ የለውም፤ ኢህአዴግ እንደ ገብስ ቆሎ ሳያሽ የማውረድ ባህል የለውም፡፡ ኢህአዴግ፣ አፍ አውጥቶ “ሹሙኝ-ሹሙኝ” ያለን ወይም በጣም “በሚያስበላ” ሁኔታ እንዲሾም የቋመጠን ሰው የስልጣን መንበሩ የማያቀምሰውን ያህል፣ “ስልጣን በቃኝ” ያለን አባል፣ ተንደርድሮ አያወርድም – ለዚያውም የክልል ፕሬዝዳንት ያህልን ሰው፣ ለዚያውም አስቸኳይ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ ጠርቶ፡፡
ስለሆነም ኢቲቪ አቶ አያሌው ጎበዜ በራሳቸው ፈቃድ “የመተካካት መርሁ በ’ኔም ላይ ይተግበርልኝ” ብለው ከፕሬዝዳንትነታቸው ስለመልቀቃቸው የነገረን ዜና ታእማኒነት የሌለው፣ የተለመደ የኢህአዴግ ድራማ ለመሆኑ አንድ ማሳያ ነው፡፡ ሌላው ማሳያ ግለሰቡ አስቸኳይ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ ከስልጣን በለለቁበት እለት፣ ሙሉ አምባሳደር ሆነው የመሾማቸው “ትንግርት” ነው፡፡ የአማራው ክልል የምክር ቤት አስቸኳይ መደበኛ ስብሰባ የተጠራው፣ በአቶ አያሌው የቀረበውን “የመተካካት መርሁ በ’ኔም ላይ ይተግበርልኝ” ጥያቄ አዳምጦ ካመነበት ከፕሬዝዳንትነታቸው ሊያነሳቸው፣ ካላመነበት ደግሞ ጥያቄውን ውድቅ ሊያደርግ ነው፡፡ ወይም ደግሞ ጥያቄያቸውን በመሰረታዊ ሀሳብነት ተቀብሎ ከፕሬዝዳንትነታቸው የሚያነሳበትን ወቅት ግን የተወሰነ ጊዜ ሊያራዝም ይችላል፡፡
ከአምባሳደርነት ሹመታቸው የምንረዳው ግን ሁሉም ነገር ቀድሞ ያለቀ መሆኑን ነው፡፡ ግለሰቡ መነሳታቸውም፣ መሾማቸውም ያለቀ ነገር ነበር፡፡ መቼም ምክር ቤት ተብዬው የመወሰን ሙሉ ቀርቶ እንጥፍጣፊ ስልጣን እንኳን ቢኖረው፣ በአምባሳደርነት የተሾመን ግለሰብ ከፕሬዝዳንትነት ስለማውረድ፣ አለማውረድ ጉዳይ እንዲወያይ ባልተደረገ ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር አቶ አያሌ ጎበዜ ከፕሬዝዳንትነታቸው እንዲነሱ ለምክር ቤቱ ሀሳባቸውን ካቀረቡበት እለት በፊት አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡ ስለሆነም ቢያንስ በዚያች እለት ግለሰቡ ሁለት ጥምር ስልጣን በትከሻቸው ላይ ነበር – የአማራ ክልል ፕሬዝዳንትም፣ በቱርክ የኢትዮጵያ ሙሉ አምባሳደርም ነበሩ፡፡ ስለዚህም የአማራው ክልል ም/ቤት አስቸኳይ መደበኛ ስብሰባ ተጠርቶ ሲወያይ የነበረው፣ ቀድሞውኑ ከፕሬዝዳንትነቱ በተነሳና አምባሳደር ሆኖ በተሸመ ግለሰብ (አቶ አያሌው) ጉዳይ ላይ ነበር፡፡ (የኢህአዴግ ድራማ እንዴት ደስ ይላል¡)
ድራማው ግን በዚህ አያበቃም፡፡ አቶ አያሌው ለምን ከፕሬዝዳንትነታቸው እንዲነሱ ተደረገ? ፋክት መፅሄት ከተወሰኑ መላምቶች አንፃር በማየት ስለግለሰቡ አነሳስ ምክንያት ለማቅረብ ሞክራለች፡፡ ሆኖም አንዳንዶቹ መላምቶች የተሳሳቱና እጅግ የተጋነኑ ስለሆነ፣ እኔ ለክልሉ ባለስልጣናት ካለኝ ቅርበት አንፃር የተወሰኑት ላይ ማስተካካያ ለመስጠትና ለግለሰቡ ከስልጣን መነሳት ዋናውን ምክንያት ለመጠቆም እፈልጋለሁ፡፡
አቶ አያሌው ከስልጣን የተነሱት ለሱዳን ከተሰጠ የወሰን አካባቢ ቦታ ጋር የተያያዘ መሆኑን አንዳንድ ሰዎች ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በፊትም አቶ አያሌው “አልፈርምም አለ” ተብሎ መናፈሱ ይታወቃል፡፡ ይህ ግን ስህተት ነው፡፡ አቶ አያሌ በዙሪያቸው ያሰባሰቧቸው የወንዝ ልጆች በስፋት የለቀቁት ተራ ፕሮፓጋናዳ ነው፡፡ አንደኛ መለስን እንኳንስ “የቁርጥ ቀን ልጅ” በሚፈለግበት እንዲህ ባለው ሁኔታ ቀርቶ፣ ቀላል በሚባሉት ጉዳዮችም “ይህን እኔ አልሰራም” የሚል ባለስልጣን ኢትዮጵያ አልነበራትም (ያማ ቢሆን ኖሮ፣ የተሸከምነው መከራ በግማሽ እንኳን በቀነሰልን ነበር)፡፡ እንዲያውም አቶ መለስ በአንድ ወቅት አቶ አያሌውን “አንተ የማትጠቅም፣ የማትጎዳም ነህ” ብለው በመተቸታቸው በድርጅቱ ትልልቆቹ አባላት ውስጥ ዜናው በስፋት ተናፍሶ ነበር፡፡ ባጭሩ አቶ አያሌው “እምቢ” የማለት ወኔው የላቸውም፡፡ (በሱዳኑ ፊርማ ላይ አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሳተፉ የተደረገው፣ ሙስሊም ስለሆኑ/ኢስላማዊ ዳራ ስላላቸው የሱዳኖችን ስነልቦና “ለመግዛት” ኢህአዴግ የቀየሰው ስልት ከመሆን አይዘልም፣ ወደ አንዳንድ አረብ አገራት ዲፕሎማቶችን ሲመድብ ተመሳሳይ መንገድ ስለሚከተል፡፡)
እና አቶ አያሌው ለምን ከፕሬዝዳንትነታቸው እንዲነሱ ተደረገ? የአቶ አያሌው ከፕሬዝዳንትነት መነሳት ለብዙዎች ድንገታዊ ሊመስል ይችላል፤ አንደኛ አቶ አያሌው “የመተካካት መርሁ በ’ኔም ላይ ይተግበርልኝ” ብለው እንዲጠይቁና ይቺው ቃላቸውም ሳትጨመር-ሳትቀነስ በኢቲቪ እንድትተላለፍ ተደርጓል፡፡ ሁለተኛ “ከስልጣን አውርዱኝ” ጥያቆያቸውን ያየው ም/ቤት ጉዳዩን የተወያየበት በ“አስቸኳይ መደበኛ ስብሰባ” ነው፡፡ ሆኖም ግን ሀቁ ሌላነው፡፡ (እነዚህ ግርግሮች ሌላው የድራማው አካል ናቸው)፡፡
አቶ አያሌውን ከፕሬዝዳንትነት የስልጣን ኮርቻ የማንሳቱ እቅድ የተዘረጋው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር (አቶ መለስ) በነበሩበት ወቅት ነው፡፡ አቶ መለስ በመሩትና ባህር ዳር ላይ በተካሄደ የኢህአዴግ ስብሰባ ላይ አቶ አያሌ ተገምግመዋል፡፡ በዋናነት የቀረበባቸውና የተቀበሉት ክስም በክልሉ ባሉ የተለያዩ የስልጣን/የሹመት እርከኖች ላይ የራሳቸውን አካባቢ ሰዎች እጅግ በተደራጀ መንገድ ማሰባሰባቸው ነው፡፡ አንዳንዶች ሂደቱን “ጎጃማይዜሽን” ይሉታል፤ ሌሎች ደግሞ “ማርቆሳይዜሽን” በማለት ይጠሩታል፡፡
አቶ አያሌው ሹመት የሚሰጡበት ቀመር በጣም ግልፅ ነው፡፡ እሳቸው ከመጡበት ከደብረ ማርቆስና አካባቢው የተማረ ከተገኘ ያለ ምንም ጥርጥር ይሾማል፡፡ ማርቆሴ እያለ ሌላ ሰው በምንም ሁኔታ አይሾምም፡፡ ማርቆሴ ከጠፋ፣ የአቶ አያሌው ሁለተኛው የሹመት ቀመር ስራ ላይ ይውላል፤ ጎጃሜ የሆነ ሰው ተፈልጎ ይሾማል፡፡ ማርቆሴ ሁሉ ጎጃሜ ቢሆንም፣ ጎጃሜ ሁሉ ግን ማርቆሴ አይደለም፡፡ ሆኖም ማርቆሴ ያልሆነ ጎጃሜን መሾም፣ ጎንደሬን፣ ወሎዬን ወይም የሰሜን ሸዋ ሰው ከመሾም እጅግ የተሻለ ነው፤ ምክንያቱም ጎንደሬም፣ የሸዋ ሰውም ሆነ ወሎዬ መቼም ቢሆን ጎጃሜ አይደለምና፡፡ ይህ የአቶ አያሌው የሹመት ቀመር ከስልጣን በሚወርዲት ላይም ስራ ላይ ይውላል፤ ባብዛኛው ከስልጣን የሚወርድ ተሿሚ ማርቆሴ ወይም ጎጃሜ አይደለም፤ ባጋጣሚ ነገሩ ከፍቶ ከስልጣን ከተነሳም ወይ የተሻለ ቦታ ይሰጠዋል፤ ካልሆነም በያዘው ደረጃና ደመወዝ የአቶ አያሌው አማካሪ ሆኖ ይሾማል (ፉገራ በሚወዱ ካድሬዎች አነጋገር Recycle Bin ውስጥ ይገባል፡፡ ይህ ማለት እንደ ገና የሚሾምበት ጊዜ አለ ማለት ነው፤ አቶ አያሌው ማዘናጋት የሚገባቸውን ካዘናጉ በኋላ፡፡ የቀመሩን ዘረኝነት (racist) ልብ ይሏል፡፡)
ይህም በመሆኑ አሁን በአማራ ክልል ርእሰ ከተማ -በባህር ዳር- ብዙዎቹን የመንግስት ተቋማት የሚመሩት ባለስልጣኖችና ምክትሎቻቸው፣ ዝቅ ሲልም የምክትሎቹ ምክትሎች (ፕሮሰስ ኦውነር፣ መምሪያ ሀላፊ፣ ወዘተ) በዚህ የአቶ አያሌው የሹመት አሰጣጥ ቀመር ወደ ስልጣን የመጡ ናቸው፡፡ ይህ የአቶ አያሌ የሹመት ቀመር በቀጥታ በማይመሩት በባህር ዩኒቨርስቲ ጭምር ስራ ላይ እየዋለ እንደ ሆነ ይነገራል፤ ዩኒቨርስቲው በፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሚመራና ያሉት መምህራንም ከአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች የተገኙ ሆነው እያለ፤ የፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና ዲን ስልጣን (ወረድ ሲልም ከፕሮግራም ሀላፊ) በአብዛኛው በመጀመሪያ ደረጃ በማርቆሴዎች፣ ከዚያም በጎጃሜዎች “ቡድን” እንዲያዝ ተደርጓል፡፡ የአቶ አያሌው የጎጠኝነትና የዘረኝነት እጅ ይሄን ያህል ረጅም ነው፡፡
ይህ ድርጊታቸው ማለትም ክልሉን የጎጠኞች አምባ ማድረጋቸው አቶ አያሌውን ክፉኛ አስገምግሟቸዋል – በአቶ መለስና በሌሎቹም የኢህአዴግ ቁንጮ አባላት፡፡ ሆኖም አቶ መለስ በሀይል የወቀሷቸውን፣ የሰደቧቸውን፣ ያንቋሸሿቸውን ያህል አቶ አያሌውን ሮጥ ብለው ከስልጥን ማንሳት አልሆነላቸውም፡፡ በአቶ አያሌው ድርጊት “የበገኑትን” ያህል የይስሙላውን የአማራ ክልል ም/ቤት አስቸኳይ መደበኛ ስብሰባ አስጠርተው ግለሰቡን ከፕሬዝዳንትነታቸው በማስወረድ “የትምህን ግባ” ማለት አልቻሉም፡፡ ያን የመሰለ ባለ ራእይ መሪ ይህን ማድረግ ለምን ተሳነው?
ምክንያቱ ግልፅ ነው፡፡ አቶ አያሌው ዙሪያቸውን ያሰለፉት የጎጥ ሀይል ቀላል አይደለም፡፡ ከላይኛው የክልል ካቢኔ ጀምሮ፣ የቢሮ ሀላፊዎች፣ ምክትሎቻቸው፣ ከምክትሎቹ ስር ያሉ ሌሎች ሀላፊዎች ከ95 በመቶ በላይ ከፍ ሲል የተገለፀውን የአቶ አያሌውን የሹመት ቀመር ተከትለው የመጡ ናቸው፡፡ (እዚህ ላይ ከምክትል ቢሮ ሀላፊዎች በታች ባለ የስልጣን ሹመት ላይ አቶ አያሌ ቀጥተኛ ሚና የላቸውም፡፡ ሆኖም በሹመት ቀመራቸው ያመጧቸውን የራሳቸውን የወንዝ ልጆች በሳቸው ቀመር እንዲመሩ ማድረግ አይሳናቸውም፤ አድርገውታልም፤ ተገምግመውበታልም፡፡)
ስለሆነም አቶ አያሌውን በድንገት እንደ ሙጀሌ ፍንቅል ማድረግ አደጋ እንዳለው ኢህአዴግ አመነበት፡፡ እዚያ ክልል ላይ የሰፈረውን አብዛኛውን ባለስልጣን አስኮርፎ ክልሉን መምራት (እንደፈለጉ ማሽከርከር) እንደማይቻል ኢህአዴግ ልብ አለ፡፡ ምናልባት ቅሬታው ስር ሰዶ በተለይም ደብረ ማርቆስ ወደሚገኘው ህዝብ ሊደርስና ያልተፈለገ መነሳነሳት/ብጥብጥ ሊያስከትል እንደሚችል እነመለስ ሰጉ፡፡ ስለሆነም ግለሰቡን በረጅም ጊዜ ለማውረድ መስራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆነ፡፡
እናም በክልሉ መስተዳድር መዋቅር ውስጥ የሌለ አደረጃጀት ኢህአዴግ ፈጠረና ከፕሬዝዳንቱ ሰር ሁለት ምክትሎች እንዲኖሩ ተደረገ፡፡ ሁለቱ ምክትሎችም በአቶ አያሌው ዙሪያ ካሰፈሰፉት የጎጥ ቡድኖች ውጭ እንዲሆኑ ተደረገ፤ አቶ አህመድ አብተውና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች ሆነው ተሸሙ፤ ሁለቱም ከወሎ፡፡ ስለሆነም አቶ አያሌው የነበራቸው ያሹትን የማድረግ ስልጣን በእጅጉ ተገድበ፤ ባጭሩ ተንሳፈፉ፡፡
የተዘረጋውን ጠንካራ የማርቆሴ መዋቅርና የአቶ አያሌውን ተፅእኖ የማዳከሙ ስራ እንደ ተሳካ ሲታወቅ የይስሙላው የአማራ ክልል ም/ቤት ተጠራ፤ የይስሙላውን የአቶ አያሌው ዱላ ላቀብል የሚል ምክንያት አዳመጠ፤ አፅድቅ የተባለውን አፀደቀ፡፡ በቃ- የሆነው ይኼው ነው፡፡
በነገራችን ላይ ኢቲቪ በአንድ የዜና ስርጭት ላይ፣ የአቶ አያሌውን ከስልጣን መውረድ “ካረዳ” በኋላ፣ ወዲያው በማስከተል በሙሉ አምባሳደርነት መሾማቸውን “ማብሰሩ” ሰውዬው ከፕሬዝዳንትነት በመነሳቱ ቅር የሚላቸውን መገኖች (የማርቆሴ ቡድን) ስሜት ለማከም መሆኑን ልብ ይሏል፤ ኢህአዴግ እንዲህ ነው መፍራት ሲጀምር ልክ የለውም፣ መድፈር ሲያበዛ ልክ እንደሌለው ሁሉ፡፡
ሌላው ለአቶ አያሌው ከስልጣን መሳነት እንደ ተጨማሪ ምክንያት ሊቀርብ የሚችለው፣ የምስራቅ ጎጃም በተለይም በሞጣ የአዲስ አበባ መንገድ አቅጣጫ ያለው ህዝብ ተደጋጋሚ ቅሬታና አቤቱታ ነው፡፡ የአዲስአበባ-ሞጣ-ባህር ዳር የጠጠር መንገድ በአስፋልት እንዲሰራ የአካባቢው ህዝብ ለዘመናት ጠያቄ ሲያቅርብ ኖሯል፡፡ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር – አቶ መለስ – ለህዝቡ ቃል የገቡ ቢሆነም እስካሁን ድረስ የመንገድ ስራው ሊጀመር አልቻለም፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋናው ተጠያቂ፣ የአካባቢው ህዝብ እንደሚናገረው፣ አቶ አያሌው ናቸው፤ “አቶ አያሌው በስልጣን እያለ የኛ መንገድ አይሰራም” በማለት ቅሬታቸውን በምሬት ይናገራሉ፡፡ በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉ ወጥተዋል፡፡ ግን አቶ አያሌው ለምን ችክ ብለው መንገድ ግንባታውን ያሰናክላሉ?
የአካባቢው ተወላጅ ምሁራን እንደሚሉት የሞጣው መንገድ መሰራት ከአዲስ አበባ-ባህር ዳር ያለውን ርቀት ቢያንስ በ70 ኪሎ ሜትር ስለሚያሳጥረው፣ በነባሩ መስመር ማለትም በቡሬ በኩል ባሉት ከተሞች ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅኖ ይኖረዋል፤ ያለ ጥርጥር ብዙዎቹ ተሸከርካሪዎች በሞጣው መስመር ስለሚሄዱ የቡሬ መስመር ነጋዴዎች በተለይም ሆቴሎች ገቢ ትርጉም ባለው ሁኔታ ማሽቆልቆሉ አይቀሬ ነው፡፡ ደብረ ማርቆስ ያለችው ደግሞ በዚሁ የቡሬ መስመር ነው፡፡ አቶ አያሌው ደግሞ ከዚህች አካባቢ ምሁራን ብቻ ሳይሆን ከከተማዋ ጋር ያላቸው ፍቅር ወደር የለውም፡፡ እናም ለጎጣቸው ሲሉ የጎረቤታቸውን ጎጥ መልማት ሲከላከሉ ነው የኖሩት፡፡
እና ኢህአዴግ እኒህን ሰው ከስልጣን ማንሳት ይነሰው?
የሰላማዊ ትግል እድገታችን –ግርማ ሞገስ
የዚህ ጽሑፍ ግብ የሰላማዊ ትግል እድገት ከኢትዮጵያ ውጭ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጋቸውን እድገቶች ታሪክ ማጥናት ነው።
(ሀ) ከኢትዮጵያ ውጭ፥
(1) ከክርስቶስ መወለድ ቀደም ብሎ
ጥንታዊ ሮማውያን ከክርስቶስ ልደት 509 አመቶች ግድም ቀደም ብሎ የነበረውን ፍጹም አምባገነናዊ የዙፋን አገዛዝ አፍርሰው ረፓብሊክ የፖለቲካ ስርዓት መሰረቱ። ይህ አዲስ ህብረተሰብ ፓትሪሳን (Patrician) እና ፕሌቢያን (Plebeian) በሚባሉ ሁለት መደቦች የተከፈለ ነበር። ፓትሪሳን የሚባለው መደብ በቀድሞው ንጉሳዊ ስርዓት የነገስታት እና የባላባት ዝርያዎችን የነበሩትን ያካተተ የገዢዎች መደብ ነበር። ፕሌቢያን (Plebeian) የተባለው መደብ አናጺውን፣ ብረታ ብረት አቅላጩን፣ መንገድ እና ህንጻ ሰራተኛውን፣ አራሹን፣ ነጋዴውን፣ ምግብ አብሳዩን፣ በወታደርነት አገልጋዩን እና የመሳሰለውን የህብረተሰብ ክፍል ያካተተ መደብ ነበር። -–ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ–-
ዴሞክራሲያ ጋዜጣ (PDF)፡ ያልተቋረጠ ትግል፤ ያልተቆጠበ መሥዋዕት
መሠረትን በሕዝብ ፍቅርና በሃገር ጥቅም ላይ አድርጎ የሚታገል ድርጅት፤ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ያልተቆጠበ ትግልና ያልተቆጠበ መሥዋዕት ከመክፈል የተለየ ባህርይና ድርጊት አይኖረውም።
ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ዘመንን ለማሰር (በልጅግ ዓሊ)
ይህን 77 እስሩት በገመድ፣
ወደ 78 እንዳይረማመድ።
ይህች አነስተኛ ስንኝ የሰማኋት እንደ ሃገራቸን አቆጣጠር በ1978 ዓ.ም ላይ ነበር። መቼም የማይረሳ የለም አሥረኛው የአብዮት በዓልም ተረሳ። ያኔ እነ “ጓድ መንግሥቱ“ ድርቁን ደብቀው አሥረኛውን የሥልጣን ዘመናቸውን ለማክበር ውስኪ በመርከብ ያስገቡበትና የተራጩበት ዘመን ነበር። ያኔ እነ “ብጻይ መለስ“ በድርቁ ስም በተገኘው ገንዘብ ጠብመንጃ የገዙበት ዘመን ነበር። የማይረሳ የለም በዚያ ዘመን በድርቅ ያለቀው ወገናችንም ተረሳ። የሕዝብ ገንዘብ ለውስኪና ለጠብመንጃ ያዋሉት ትንሽ ቆይተው ስልጣን ተቀያየሩ። 1977 ማሰር አቅቶን 1983 ከድጡ ወደ ማጡ አነጎደን።
በደርግ ዘመን የደረሰውን ድርቅ ለመከላከል በሰሜን የሚኖሩትን ዜጎቻችንን(ከሰሜን እየታፈሱ የመጡት ዜጎቻችን በድርቁ ምክንያት ይሁን በሌላ ወደፊት አዋቂዎች ይጽፉት ይሆናል) ወደ ምዕራብ ማስፈር ተጀምሮ ነበር። ማስፈሩ ሁለት መልክ ነበረው። ሠፈራ የሚባለው ሰው ባልሰፈረበት አካባቢ ወስዶ ማስፈር ሲሆን ስግሰጋ የሚባለው ደግሞ በሕዝብ ቁጥር የሳሱትን ወረዳዎች በሰፋሪዎች መሰግሰግ ነበር። ሠፈራና ስግሰጋ የራሱ የሆነ በሰፊው የሚተረክለት ታሪክ አለው።
ከሰሜን ኢትዮጵያ ለሠፈራና ለስግሰጋ ወደ ኢሉባቡር የመጡ አንድ ሽማግሌ ገበሬ ነበሩ ይህችን ከላይ የሰፈረችውን ስንኝ ለመጀመሪያ ጊዜ የነገሩኝ። ይህች ስንኝ ሁለት ትርጉም ይዛለች። አንደኛው 1978 ከ 1977 ይብሳልና አይሸጋገር የሚል ሲሆን ሁለተኛው 1977 ያየነው ችግር ወደ 1978 እንዳያልፍ የሚል ነው። ሽማግሌው እንዳስረዱኝ የመጀመሪው ነው ትክክሉ። ከጊዜ በኋላም አንድ የምቀርበው የወረኢሉ ሰው ስለነ መንግሥቴ ደፋር ፣ ስለነ ብሩኬ ስንጫወት ይህችን ግጥም አስተወሰኝና ማስታወሻ ላይ ጽፌ ይዣት ቆይቼ ለዛሬው መነሻ ሆነችኝ። (መንግሥቴ ደፋርና ብሩኬ በወረኢሉና ሰሜን ሸዋ ሃገር ያንቀጠቀጡ “ሽፍቶች“ ነበሩ። ቀን ሲሞላ የሚጻፍ ታላቅ ታሪክ አላቸው።)
ድርቅ ከሳይንስ በተቃረነ መልኩ በአገራቸን ሁል ጊዜ ዱብ እዳ ነው የሚሆነው። 1966 የደረሰውም ይሁን 1977 የተደገመው ድርቅ እንደው ሳንሰማው ነው በድንገት ያየነው። የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ 80ኛ ዓመት በተከበረ ማግሥት ድርቅ “ሳይታሰብ“ መጣ። ደርግም ሕዝብ ሲራብ የንጉሡ ባለሥልጣናት ኬክ ይበሉ ነበር በማለት ቅስቀሳ አድርጎ ነበር ወደ ስልጣን የመጣው። ደርግ ይባስ ብሎ የአሥረኛውን አብዮት በዓል እስከሚያልፍ ድርቁን ደብቆ፣ በዓሉ ባለቀ ማግስት ድርቅ እንደ ዱብ እዳ፤ እንደ ተምች ከሰማይ እንደወደቀ ነገረን። በ1966 ዓ.ም. እንደ ሃገራችን አቆጣጠር የደረሰው ድርቅ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ 60ዎቹን ባለሥልጣናት የገደለው መንግሥቱ በእሱ ዘመን ለተደበቀው ድርቅ ራሱን ሳይገድል መቅረቱ ፍትህ አልባነት ነው ማለት ይቻል ይሆን?
በዛ ዘመን ካለ መንግሥቱ አመራር ምንም ነገር የሚሆን አልነበረምና በዓሉ ካለቀ በኋላ ሁላችንም ስለድርቁ ተነግሮን ዝግጅት እንድናደርግ ታዘዝን። ከግብርና ሚኒስቴር እስከ ታች እስከ ወረዳ ድረስ ከግብርና ጋር ግንኙነት ያለን በሙሉ ክተቱ ተባልን። የኢሠፓ አባላት መሪዎቻችን ሆነው እኛ የእርሻ ኤክስፐርቶቹ ተመሪ ሆነን ሥራውን ጀመርን። ቀርፋፋዋ ኢሊባቡር ከአዝጋሚነት ወጥታ እንቅስቃሴ በእንቅስቃሴ ሆነች። በየመሥሪያ ቤቱ ያሉ መኪናዎች ከእኛ ተወስደው ለኢሠፓዎቹ መጓጓዣ ሆኑ። እኛ ወደ ሞተር ባይስክልና ወደ ትራክተር ተዘዋወርን።
በዚያ ወቅት ኢሊባቡር ነበርኩና እኔም ለዚህ “ሳይታሰብ በድንገት“ ከሰማይ የመጣብንን እዳ ለመቋቋም በየቦታው መራወጥ ጀመርን። በጋምቤላ ለሰፋሪዎች ቦታ መዘጋጀት ጀመረ። በሌላ በኩል ደግሞ በሕዝብ ቁጥር የሳሱ የገበሬ ማህበራት ውስጥ ከሰፋሪዎቹ ውስጥ እየተወሰዱ ይሰገሰጉ ጀመር። እኔ ጎሬ አካባቢ በሚገኝ ወረዳ ለሚሰገሰጉት ገበሬዎች ጎጆ ለመስራት ተመደብኩ። ዛሬ ያገኘሁት ትንሽ የየቀኑን ሁኔታ የምዘግብበት ማስታወሻ አንዲት ጎሬ ለምትኖር አንዲት ወይዘሪት የተጻፈ ደብደቤ ላይ የደብዳቤውን ብዙው ዝባዝብኬ ተቀንሶለት እንዲህ የሚል የተጠቀሰ ጉዳይ ይገኝበታል። ።
ውዷ
ጓጆ ቤት መሥራት ቀርቶ ጎጆ ቤት ውስጥ አድሬ አላውቅም። ይህ የምሰራው ጎጆ (ጎጆ ከተባለ) የሚገርም ነው። ከላይ ሳር ጣል ተደርጎ ይከደንና ግንድግዳው በዘንባባ ይሸፈናል። የኛን አዛዥ አላፊ ካድሬዎችን ለመሆኑ ይህ የምንሰራው ቤት ከምን ይከላከላል? ብዬ ጠይቄ ነበር። የተሰጠኝ መልስ ለጊዜው ማረፊያ ካገኙ ሰፋሪዎቹ ሲመጡ ያሻሽሉታል የሚል ነበር። በድርቅ የተጎዳ ሰው እውን ቤት መስራት ይችል ይሆን? የሚገርም ነው። ለማንኛውም ሥራውን እያጣደፍነው ነው። ስራው አልቆ ጎሬ ለመምጣት ቸኩያለሁ።
ይላል። በዛ ወቅት የነበረውን ጥድፊያ አጉልቶ ነው። ከሁሉ የሚገርመው በትንሽ ቀን ያንን ሁሉ ሕዝብ ማጓጓዝ እንዴት አስከፊ ነበር። በችኮላውና በሕዝብ ብዛቱ ምክንያት ከአንድ አውቶቡስ ውስጥ የነበሩ ቤተሰቦች በምደባ ይለያዩና አንዱ ጎሬ ሌላው ጋምቤላ ይደርሰው ነበር። ማንም ጥንቃቄ የሚያደርግ አልነበረም። ብዙ ቤተሰቦች ሳይገኛኑ ይቀሩ ነበር። ልጆች በረሃብም ይሆን በጉዞው አድካሚነት ይረግፉ ነበር። ይህንን ያልተጠና ሰፈራ የመንግሥቱ መመሪያ ነውና ማንም ባለሥልጣን፣ ማንም የእርሻ ኤክስፐርት ሊቃወም አልሞከረም።
ሰፋሪዎቹ መጥተው በሰራው ቤት ከተመደቡ በኋላ እየተመላለስኩ እጠይቃቸው ነበር። ይህንን ግዜ ነው አንድ ሽማግሌ ስለዚህ አባባል ያጫወቱኝ። አዎ ገበሬዎቹ ነገሩ ገብቷቸው ኑሮ በ1978 ከ 1977 እንደሚብስ ገምተው ነበር።
የፈረንጆቹ ዓመት ከ2013 ወደ 2014 ሲቀየር የተመኘሁት ይህንን ግጥም ነበር። የሃገራችንን ጉዳይ በጥሞና ሳስበው፣ በየቀኑ እየባሰ የሄደውን የወያኔን ግፍ ስንገምተው፣ የደሃውና የሃብታሙ ልዩነት እየገፋ መምጣቱን ስመለከተው፣ ችግርን በመሸሽ በየበርሃው በየባሕሩ የሚያልቀው ወጣት ዜጎችቻን ቁጥር መጨመርን ሳሰላው፣ በእየእስር ቤቱ የሚማቁትን ዜጎቻችንን ሳስታውሳቸው፣ ለሃያ ዓመት በነጃዋር፣ በነ ተሰፋዬ ግብረ አብ፣ በእነ ብርሃኑ ዳምጤ መሰሎቹ የተዘራው የዘር ፖለቲካ ስሞኑን የደረሰበትን ደረጃ በጣም ያሳስበኛል።
ሃገራችን አንድነቷን ጠብቃ የመኖሩዋ ሁኔታ ጥርጣሬ ውስጥ ሲገባ፣ ጠንካራ የሆነ ተቃዋሚ ለመፍጠር ያለውን ችግር ስንገመግመው፣ በትግሉ ውስጥ ተስፋ የሚሰጥ ሁኔታ ሳጣበት 2014 ከ 2013፣ የሚብስ መሆኑን ስንረዳው ያኔ እንደ ገበሬዎቹ፡ -
ይህን 13ትን እሰሩት በገመድ
ወደ 14ቱ እንዳይረማመድ ።
ለማለት ተገደድኩ።
የሃገራችንን ሁኔታ ልብ ብለን ስንመከተው ይህ ዘመን ከመቼውን ጊዜ ይበልጥ የሚያስፈራ ሆኖ ይታሰበኛል። በተለይ 2013 መጨረሻ ላይ የተመለከትነው ሁኔታ ስንገመግመው፣ በተለይ እነዚህ በዘር የተለከፉ አጋንቶችን እዚህ ማን አደረሳቸው የሚለውን ስንመለከተው፣ በወያኔ ቀጥሎ ራሳችንን እንድንገመግም ይጠይቀናል። ሞኝ ብቻ ነው ቤቱ ሲቃጠል የሚስቀው። ለሚቃጠለው ቤቱ ቤንዚል የሚያቀብለው። ሞኝ ብቻ ነው ፎቅንና ጥልፍልፍ መንገድን ተመልክቶ እየፈረሰ ያለውን የሃገሩን አንድነት የሚዘነጋው። ሞኝ ብቻ ነው ሃገርን ለሚፈርሱ መድረክ እየሰጠ ሃገሩን የሚያፈርሰው። የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ የሚለው በሃገር አይሰራም።
የዘር ፖለቲካ የደረሰበትን ደረጃ ያልተረዱ ብዙ ናቸው። ክምር ፎቅ፣ ጥልፍፍ መንገድ፣ ዳንኪራ መደለቂያ ቡና ቤት ብቻ ለሃገር አንድነት የሚበቃ የሚመስላቸው የዋሆች እየበዙ ነው። ዛሬ በድሎት የሚንደላቀቁ ዘመናዮች በየጥጉ በረሃብና በበሽታ የሚልቁት ዜጎቻችንን እንዳያዩ የየክለቡ አብለጭላጭ መብራት ዓይናቸውን ሽብቧቸዋል። በዓለም ታሪክ በቅርብ እንኳን ስንት የሚያምሩ ፎቆች በዘር ክፍፍል እንደፈረሱ የማይረዱ አሉ።ትንሽ ዘርን ተመርኩዛ የምትንሳ ሁኔታ የእርስ በእርስ መተላለቅን እንደምታስከትል፣ የተከመሩ ፎቆችም ሆነ ፣ጥልፍለፍ መንገዶች በቀናት ሊፈርሱ እንደሚችሉ ያልተረዱ የዋሆች የአንድነት ኃይሎችን እየተዋጉ ጭንብል ላጠለቁ ዘረኞች መድረክ ፣ እውቅና እየሰጡ እንዳሉ ሊረዱት ይገባል።
ከወያኔ ተፋተናል ያሉን ሁሉ መለያየታቸው መልካም ነው። ለምን ከወያኔ እንደተፋቱ አሳማኝ ምክንያት ሳያቀርቡ ሰው እንደጠፋ በየቦታው የፖለቲካ ተንታኝ . . . የኮሚቴ አባል . . . የመድረክ የክብር እንግዳ፣ . . . ወዘተ. እያደረጉ መካብ በተሰፋዬ ገብረአብም ይሁን በጃዋር የከሸፈ ነው። ነገም በብርሃኑ ዳምጤ ቢደገም የሚያስደንቅ አይደለም። ከወያኔ ወጥተው ተቃዋሚ ሆንን ሲሉ ወያኔ ውስጥ ሆነው የሠሩትን ጥፋት ለሕዝብ እንኳን ይቅርታ እንዲጠይቁ አይደረግም። ብቻ የሰሞኑን ፖለቲካችንን ይደግፉልን እንጂ በሃገር ላይ የሚያመጡትን ጥፋት አይታየንም።
ለሃገራቸው የሠሩ፣ የሞቱ እየተወገዙ፣ ሃገራቸውን የገደሉ ወደፊትም ሊገድሉ የተዘጋጁ ትላንት የወያኔ አሽከር የነበሩ፣ አሁን ተቃዋሚ ነን የሚሉ እነ ጃዋር፣ እነ ብርሃኑ ዳምጤ (ደቡር) ጀግና ተብለው እየተዘፈነላቸው ነው። ሲሞቅ ኦ.ፒ. ዲ. ኦ.(OPDO) ሲቀዘቅዝ ተቃዋሚ፣ ትላንት የወያኔን ቀንደኛ ደጋፊ ሥልጣን ሲከለከል ተቃዋሚ መሆን የዘመኑ የፖለቲካ ገጽታ ነው።
እንደነ ጃዋር አይነት የዘር ፖለቲከኞች አቋም በቀየሩ ቁጥር አብረን ዳንኪራ የምንረግጠው ምን እንባል? አንድ ሰሞን ፓልቶኩም ፣ ራዲዮኑም ጃዋር ፣ ጃዋርና ሲልና የፖለቲካ ተንታኝ የሚል አዲስ ስም ተሰጥቶት በባልና ሚስት ጥል ላይ እንኳን ሳይቀር(እንደ ቀልድ ውሰዷት) ሃሳብ እንዲሰጥ ሲጠየቅ እንዴት ያላገባ ሰው የትዳር ሊቅ ሊባል ይቻላል የሚል ተቃውሞዬን አቅርቤ ነበር። ይኸው ዛሬ ጃዋርን ተቀምጠቀው የሰቀሉ ካስቀመጡበት ቆመው ማውረድ አቃታቸው። ሕዝብን የሚከፋፍለውን ጥያቄ ይዞ ለኢትዮጵያ የሚመኝላትን የእርስ በእርስ ጦርነቱን ይቀሰቅስ ጀመር። ጃዋር ትንሽ ሲፍቁት ኦፒዲኦ(OPDO)፣ በጣም ከፋቁት ወያኔ(TPLF) መሆኑን አጥተነው ነው። አይመስለኝም ለሰሞነኛ ፖለቲካ ከጠቀመን ስለሃገራቸን ግድ ስለማይኖረን ይመስለኛል።
እነ ጃዋር እኛን የሞቀው ላይ የምንጣደውን ሲፈለጉ ደጋፊያቸው አድርገው ያጫጩናል፣ ሲደብራቸው ደግሞ የዘር ፖለቲካቸውን አምጥተው ያምሱናል። ዛሬ ወያኔ ፣ ነገ ተቃዋሚ ፣ ተነገ ወዲያ ደግሞ ተመልሰው ወያኔ እንደፈለጉ መሆን ይችላሉ። በተቃዋሚው መድረክ ላይ ከወያኔ ለተመለሱት ሁሉ እግራቸው ሥር እንድንነጠፍ የሚፈልጉ ብዙ ናቸው።
እድሜ “ለነጻ ሜዲያ ጋዜጠኞች“፣ እድሜ ለኛ በሞቀበት ለምንጣደው፣ ሃገራችንን ሊበትኗት ሲራወጡ አብረን ልንበትናት እየሮጥን ነው። እንግዲህ ፍላጎታችን ይህ ከሆነ አሁን የምናየው ደስ ሊለን ይገባል። ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ስንት አንጋፋ አሮሞዎች እያሉ ይህ ስንዝሮ ፖለቲከኛ ጃዋር ይጋበዛል። ስለ እስልምና ስንት የተማሩ የበሰሉ ሊቀ ሊቃውንቶች እያሉ ጃዋር ሁሉም ቦታ የሃይማኖት ተንታኝ ሆኖ ይቀርባል። ጥፋቱ ጃዋር ጋር አይደለም ጥፋቱ ለሃገራቸን አንድነት እንዋጋለን ብለን ግን ለክፍፍል በምንሰራው ላይ ነው። እነ ጃዋር በኛው መድረክ፣ በኛው ገንዘብ አላማቸውን ሲስፈጽሙ እንደሞኝ የሚቃጠለውን ቤታችንን እያየን እንስቃለን። በነጻ ፕረስ ስም እውቅና እንሰጣለን።
ትላንት የወያኔ ደጋፊ ሆኖ ዛሬ ከወያኔ ተጣላሁ ካለን ምራን ብለን እግሩ ሥር እንነጠፋለን። ይህ ደግሞ ለምዶብናል። 1997 ምርጫ ዋና የወያኔ አቀንቃኝ የነበረውና የነ ሽብሬን መገደል ትክክል ነው ብሎ ሲያቀነቅን የነበረው፣ አሁን በግል ጥቅም ምክንያት ከወያኔ የተጣላው ብርሃኑ ዳምጤ (ደቡር፣ አባ መላ) ዛሬ በየሃገሩ የክብር እንግዳ፣ በመገናኛ ዘዴው ተንታኝ ከሆነ ሰነበተ። ለአንዲት የሰሙኑ የፖለቲካ ጥቅም ሲባል ብርሃኑ ደቡርን እላይ የሰቀላችሁት በኋላ እንደለመደው ሲክዳችሁ ስትንጫጩ መስማታችን አይቀርም። ትንቢት እንዳይመስላችሁ ደቡርን በደንብ አድርገን እናቀውቀዋለን። ቆዳችሁን ገፎ ይሸጠዋል፣ ደቡር ሃገሩን አይደለም እናቱንም ቢሆን ይደልላል። አታውቁት እንደሆን መርካቶ ላይ ሄዳችሁ የተሰራውን ግፍ ጠይቁ። እንኳን የቀይ ሽብሩን ፣ እነ ሽብሬን ረስተን የለም እንዴ !! ምን ይደንቃል።
እድሜ ለኛ ብጻይ ብርሃኑ ዳምጤ ከወያኔ ጋር የምናደርገውን ትግል ይምሩልን ብለን . . . ሁሉንም እናስረክበው . . . እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ ብርሃኑ ዳምጤ ደቡር ይክደናል። ከዛም አሁን ከሰማይ ሰማየት የሰቀልነው እንደ ድመት እግሩ ስር እናለቅሳለን። ብርሃኑ ደቡር ቆዳችንን ገፎ ሥጋችንን ለአሞራ ይበትነዋል። በጨረታው አይገደድም ለበለጠው ይሸጠናል። ኢሕአፓ ነው ፣ ግንቦት 7 ነው ፣ መኢአድ ነው . . . እያለ እንደፈለገ ይከፍለናል። ምን እንሆናል ለመሸጥ የተዘጋጀን በጎች አይደለንም እንዴ? በሉ የዘመኑ ፖለቲከኞች ከጃዋር ፣ ከብርሃኑ ዳምጤ ጥፋት መፈለግ ትታችሁ ከነቴዲ አፍሮ ጥፈት ፈልጉ። መቼም፣ የምታሸንፉት አይደለም የምታጠቁ ወያኔን ከመቃወም ቴዲን መስደብ ይሻላል። ጃዋርን ከመቃወም ቴዲን መስደብ ለዝሙት ቱሪስቶች ፣ ለዘመኑ ኢንቨስተሮች ፣ የደደቦች ሸንጎ አባሎች የሚሻል ነው ።
2013 ተቀይሮ 2014 ሲገባ ተስፋ የሚሰጥ ራዕይ ያለው ፖለቲካ እያከተመ እንጂ እያበበ መሆኑ አይታይም። ጠብ አጫሪ፣ እኔ እኔ በሚል የተቃኘ የግለሰቦች ፍላጎት የሕዝብን ራዕይ ሸፍኖ ጎልቶ ወጥቶ ስንመለከት የዴሞክራሲ ትግል የመጨረሻው ቀን ርቆ ይታየናል። ከነገ ደህና የሚጠብቅ ትንሽ ነው።
ዓመትን ማሰር ቢቻል የምናስራቸው ዓመታት ብዙ ይሆኑ ነበር። ከዛ በፊት ግን ሕዝብ ለክፍፍል የሚጠሩ ምክንያቶችና እነዚህ አጀንዳዎች ለግል ጥቅማቸው ከፍ የሚደርጉ ፖለቲከኞች ከፖለቲካው መድረክ ሊሸበቡ ይገባል። እነ ተስፋዬ ግብረ እባብ፣ እነ ጃዋር ፣ እነ ብርሃኑ ዳምጤ . . . ነገም ብዙዎች ይመጣሉ። ተቃዋሚ መሆናቸውን መከልከል አይገባም ምሩን ማለት ግን ደደብነት ነው።
ወያኔዎች ሃገራችንን ለማፍረስ የማይጠቀሙበት መንገድ የለም። በማካከላችን አንቀላፊዎች(Sleepers) ያስቀምጡብናል። ቀኑ ሲደርስ ያነቋቸዋል። ሰሞኑን በእነ ጃዋር ያየነው ይህንን ነው። እነ ጀዋር ሲነቃባቸው ሌሎች ይላካሉ። እኛም ምሩን ብለን እንቀበላቸዋለን። ለወራት ካመሱን በኋላ ያደረሱትን ጉዳት አድርሰው ተልዕኳቸው ተፈጽሟልና ይሸሸጋሉ። ሌሎች በምትካቸው ይመደቡልናል . . . እንዲህ እንዲህ እያልን ዓመት እንቆጥራለን . . .። መቼ ይሆን እያየን አለማየታችንን የምንገነዘበው? መቼ ይሆን ከተኛንበት የቁም እንቅልፍ የምንነቃው? መቼ ነው ሰው ነኝ ወይስ በሰው ምስል የቆምኩ “ሰው“ ብለን ራሳችንን የምንመረመረው። ብልህን አንዴ ያሞኙታል፤ ሞኝን ግን ዘንተለት እንዲሉ ነውና ከእንቅልፋችን እንንቃ።
በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት ስለ ሃገራችን አንድነት የሚያስቡ ሁሉ በሰላም ይክረሙ!
ለንደን ታህሳስ 2006
የጨቅላዎች ሁካታ ! ከቴዎድሮስ ሐይሌ
ከቴዎድሮስ ሐይሌ (tadyha@gmail.com)
ምንሊክ መጓዙን የምትጠይቁኝ፤
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ።
ካለፉት ሳምንታት ወዲህ የማንነት ቀውስ ዋግ እንደመታው አገዳ ያኮሰሳቸው የበታችነት ስነልቦናቸውን ታሪክ በማፍረስና ጀግኖችን በመዝለፍ የሚጠገን የመሰላቸው አንዳንድ ተማርን ነን ባይ ደካሞች ዛሬን በድቅድቅ የባርነት ጨለማ አሳራቸውን እያዩ ፤ በራሳቸው ላይ የተጫነውን የአገዛዝ የጭቆና ቀንበር ለማንሳት ብርቱ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ወደኋላ ተጉዘው የነጻነትን ብርሃን ፤ የዘመናዊነትን ጎዳና፤ የአንድነትን መሠረት ከወረሪና ከተስፋፊ ቅኝ ገዠ አውሮፓውያን በብርቱ ታግለው የክብርን አክሊል፤ የኩራትን መንፈስ ያወረሱንን ደጋጎቹን አባቶች የሚያንጓጥጥ ከስደት ፤ ከረሃብና ፤ ከውርደት በዚህ ዘመን እንኳ ለራሱ መቀዳጀት ያልቻለ ደካማና ልፍስፍስ ህብረተሰብ ጀግኖች አባቶቻችንን ለመዝለፍ ሲንጠራራ ይበልጥ እየተዋረደ መሆኑን እንኳ አለመረዳቱ የሚያሳዝን ከመሆን አልፎ የዛችን ታላቅ ሃገር ኢትዮጽያዊ ዜጋ መጻዊ ሕላዌ ፈተና የሚደቅን በሌሎች ሃገሮች የታየው አይነት የእርስ በእርስ መተላለቅን የሚጋብዝ አደገኛ አካሄድ የጥቂት ጨቅላዎች ሁካታ ነው --–ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ–-
Share and Enjoy
ሕዝባዊ ብሶት –የከተማ አብዮት? –ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)
የኢህአዴግ ግድፈቶች
ፈረንጅኛው ‘Achilles Heels’ በሚል ስያሜ የሚገልፃቸው እና አማርኛው ደካማ ጎኖች ብሎ የሚሰይማቸው የስርዓቱ ታላላቅ ግድፈቶች ከዕለት ዕለት ራሳቸውን ማብዛታቸው ፍፃሜው የሚተነበይ አድርገውታል፤ ይኸውም ብሔር ተኮር ጥያቄዎች አለመመለሳቸው፣ ውጤት አልባው የገጠር ፖሊሲ፣ የድህረ-ደርግ የዴሞክራሲ ሽግግሩ መክሸፍ (ከፖለቲካ፣ ከሰብዓዊ እና ሀሳብን በነፃነት ከመግለፅ አንፃር)፣ የኢኮኖሚ እድገት አለመኖር፣ ድህነት ከቀድሞውም በበረታ መልኩ መስፋፋቱ፣ የትምህርት ፖሊሲው ክስረት፣ የስራ-አጥ ቁጥር አለቅጥ ማሻቀብ፣ የራስ አስተዳደር (Self-adminstration) ሙሉ ለሙሉ አለመተግበር (ከስልጤ እስከ ቁጫ ያሉ የማንነት ጥያቄዎች መቆሚያ ማጣታቸው)፣ የመሬት ፖሊሲው የአርሶ አደሩን የነፍስ ወከፍ የይዘት መጠን ከአንድ ሄክታር ማሳነሱ፣ የከተሞች ስራ-አጥነት በወጣት ከተሜ የተማሩ ልጆች ላይ መብዛቱ፣ በልማታዊ መንግስት ትግበራ እና በብሄር ፌደራሊዝም መሀከል የማይታረቁ ቅራኔዎች መኖራቸው፣ ከተሜነት እየተስፋፋ ሲመጣ በብሔር ፖለቲካ ሞት ላይ ግለሰባዊነት እንደሚነግስና ኢህአዴግም ይህንን ተቃርኖ ተከትሎ የርዕዮተ-ዓለም መሸጋሸግ ማድረግ የማይችል መሆኑ እና መሰል ተቋማዊ ክስረቶች በቀጣይ ሊያርማቸው የማይቻለው ታላላቅ ግድፈቶች በመሆናቸው እንደተለመደው ውጤቱ ቀድሞ የሚታወቀውን የይስሙላ ምርጫ ከመጠበቅ ይልቅ የአደባባይ ተቃውሞን ለማማተር ሥረ-ምክንያት ሊሆን መቻሉ አጠራጣሪ (አከራካሪ) አይደለም፡፡
ጉዳዩን በሚገባ ለማስረገጥ ከኢህአዴግ አጠቃላይ ህልውናዊ ባህሪ አኳያ ከላይ ከጠቀስኳቸው ነጥቦች ሊፈታቸው የማይቻላቸው ‹ብሎኖች› መሀከል ሶስቱን (ዋነኞቹ ናቸው ከሚል አረዳድ) በጨረፍታ በአዲስ መስመር እንያቸው፡፡
ያ ሁሉ ነጋሪት የተጎሰመለት የድህረ-ደርግ የዲሞክራሲ ሽግግር ‹ተስፋ› ሙሉ በሙሉ ሞት የታወጀበት አሁን በምንጠራው የ97ቱ ምርጫ ማግስት ነበር፡፡ ይህንንም ተከትሎ አቶ መለስ ‹ልማታዊ መንግስት› የሚል ሀልዮት ይዞ ብቅ ማለቱ ይታወሳል፤ በወቅቱ (1998 ዓ.ም ይመስለኛል) በማንችስተር ዩንቨርስቲ በመገኘት ቀጣዩ የስርዓቱ ማዋቀሪያ ምሶሶ አድርጎ ሃሳቡን ያብራራው የምርጫ ፖለቲካ፣ የሰብዓዊ መብቶችን እና መሰል ዲሞክራሲያዊ ዕሴቶችን ጨፍልቆ ‹በአብዮታዊ› መንገድ ልማት ማምጣትን ቀዳሚ ግቡ እንደሚያደርገው በመፎከር ጭምር ነበር፤ ይሁንና ፅንሰ-ሃሳቡን በቅርበት ስንመለከተው፣ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ አውድ፤ በተለይም ስርዓቱ ካነበረው ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝም ጋር በማይታረቁ ቅራኔዎች መሞላቱን ለመረዳት አያዳግትም፡፡
ለዚህ ክርክር ማስረገጫ ይሆን ዘንድም ከተቃርኖዎቹ ውስጥ ሁለት ነጥቦችን ብቻ እናንሳ፤ የመጀመሪያው ልማታዊ መንግስት ‹የዜጎች የክሂል ልቀትን በመንተራስ ብቻ የተሳለጠ ቢሮክራሲን መገንባትና ተቋማዊነትን ማጎልበት ያስፈልጋል› ከሚለው መደምደሚያ አንፃር ነው፤ በርግጥ ይህ ሃሳብ ስኬታማነቱ የታየው በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራት ውስጥ ቢሆንም፣ በሙያ ብቻ ስርዓቱ ሲዋቀር ግን የተለየ የቡድን ጥቅሞችን ለማስፈፀም እንደማይመች ተግባራዊ ተሞክሮዎቹ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ አኳያም የገዥው ፓርቲ የፌደራሊዝም ቅርፅ በግልባጩ የብሔር ማንነቶችን ተቀዳሚና ብቸኛ ተቋማዊነትን መገንቢያ አማራጭ ማድረጉ ከተጠቀሰው የልማታዊ መንግስት ጭብጥ ጋር በቀጥታ ያላትመዋል፡፡ እናም ከላይ እስከታች ያለው የስልጣን አወቃቀሩ የላቀ ክሂልን ረግጦ የብሔር ተዋፅኦን ለመጠበቅ በማለም ብቻ የተወሰነ ስርዓታዊ መልክ መያዙን ስንመለከት፣ ገዥዎቻችን ሀልዮቱን ለመተግበር ሲንቀሳቀሱ በሁለት ምርጫዎች ቅርቃር ውስጥ እንዲወድቁ መገደዳቸው የማይቀር ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን፤ እነርሱም የፌደራሊዝሙን ቅርፅ ወደ መልከአ-ምድራዊ (Geographical) መቀየር፣ አሊያም ‹‹ልማታዊ መንግስት ነን›› የሚለውን አሰልቺ ፕሮፓጋንዳ አራግፎ መጣል የሚሉ ናቸው፡፡ ይህንን ደግሞ ኢህአዴግ
ከግትረኛነት ባህሪው አንፃር ይቀበለዋል ተብሎ አለመጠበቁ አንዱ ህልውናዊ ግድፈቱ ያደርገዋል፡፡
ሌላው ተጣራሽ ርዕሰ-ጉዳይ በስልጣን ኢ-ማዕከላዊነትና በማዕከላዊ መንግስት መጠናከር መካከል ያለው ነው፤ በሁለት አስርታቱ ስርዓታዊ ሙከራ፣ የበዛው ከወረቀት ላይ ባይዘልም፣ በጥቂቱም ቢሆን ኢ-ማዕከላዊ ለማድረግ ስለመጣሩ የምናውቀው እውነት ነው፡፡ ይሁንና የልማታዊ መንግስት ፅንሰ-ሀሳብ ማዕከላዊ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ አጠቃላይ የስልጣን ገፆችን ጠቅልሎ እንዲይዝ ያስገድደዋል፡፡ ይህንንም ስልጣን በማከፋፈል ላይ የሚመሰረት ግጭት ህልውናዊ ድክመቱ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡
ሁለተኛው አስረጂ ጭብጥ የብሔር ማንነትን ዘላለማዊ የስርዓት መልክ ማድረጉ፣ ከከተሜነትና የከተሞች መስፋፋት ጋር አብሮ እየገነገነ ከሚመጣው ግለሰብኝነት (የግለሰብ መብትን ማስቀደም) ጋር ሊኖረው የሚችለው ግጭት ነው፡፡ በስነ-ማህበረሰብና ፖለቲካል ኢኮኖሚ አስተምህሮቶች መሰረት (በዋናነት በምዕራባዊ ሥልጣኔ)፣ የከተሜነት ዕድገት መገለጫ ኢህአዴግ ቀን-ከሌሊት እንደሚለፍፈው የፎቆች መደርደርና የመንገድ መስፋፋት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ከተሜነት ማለት ከጋርዮሽ ማንነት እየተላቀቁ በመምጣት የግል የሆኑ አለማዊ ዕይታዎችን በማጎልበት፣ በመረጡት ማንነትን መተርጎሚያ ፈር ከሚተሳሰሩ ዜጎች ጋር ህብረት መፍጠር የሚለው አንድምታ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም በፆታ፣ በሙያ፣ በኃይማኖት አሊያም በተመረጠ ርዕዮተ-ዓለም ስር ምክንያተኝነትን ብቻ በመንተራስ ‹መደራጀት› የከተሜነት ቀዳሚ መለዮ ነውና፡፡ ይህንን ድምዳሜ በተለይም በአዲስ አበቤዎች ዘንድ እየመጣ ካለው የከተሜነት ባህሪ እና ከብሔር ፖለቲካው ጋር ስናስተያየው ‹‹የማይታረቀው ቅራኔ›› (በካርል ማርክስ አባባል) እነበረከት ስምዖን ፊት ይቆማል፡፡ ኢህአዴግ ይህ ተፈጥሮአዊ የማህበረሰብ ዕድገት እንኳ እንደሚገታው አለማሰቡ ከህልውናዊ ግድፈቶቹ አንዱ አድርገን ልንቆጥረው እንገደዳለን፡፡
ርዕሰ-ጉዳያችንን ለመጠቅለል የምጠቅሰው የመጨረሻው ማሳያ፣ ስርዓቱ የተነሳበትን የራስ ዕድል በራስ በመወሰን መብት ላይ ትገበራው የሚያሳየውን ሀሳዊነት ነው፤ ወታደራዊው ደርግ ይከተለው የነበረው ‹አሀዳዊ አስተዳደር›፣ ቋንቋን መሰረት ባደረገው ፌዴራሊዝም ከተተካ በኋላ ስለ ጉዳዩ ያጠኑ ምሁራኖች ‹‹የስልጤ ሞዴል›› እያሉ የሚጠሩትን ይህንን ጭብጥ፣ ግንባሩ እየመረጠ መስጠቱን የሚዘክሩ በዜጎች ደም የተፃፉ የዳጎሱ ታሪኮች ያረጋግጡልናል፡፡ እንደ ምሳሌም የሲዳማንና ሰሞኑን እየታዘብን ያለውን የቁጫን የማንነት ጥያቄዎች ብቻ መጥቀስ በቂ ይመስለኛል፤ ሲዳማ በሀገሪቱ ሕገ-መንግስት መሰረት ክልል ለመሆን የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ሁሉ ቢያሟላም የተሰጠው ምላሽ ለዓመታት ሞትና እስርን በጥያቄው አራማጆች ላይ እንደ ሐምሌ ዝናብ መዘርገፍ ሲሆን፣ ከሲዳማ ቁጥር በታች ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ደግሞ በክልል ደረጃ የመዋቀር መብታቸው ሲከበር ተመልክተናል፡፡ ይህንንም የተዛነፈ የመብት ትግበራን በመሰረታዊ የስርዓቱ ክሽፈትነት ልንቆጥረው እንደምንችል ይሰማኛል፡፡ የተቃውሞ መድረኩን ከውስጥም ከውጭም የሞሉት ኃይሎች ዋነኛ ጥያቄም፣ የብሔራችን መብት አልተከበረም የሚለው መሆኑ (በመጠኑ ላይ ባንስማማም፣ ቡድኖቹ ከየብሔራቸው ደጋፊ እንዳላቸው አይካድምና) ስርዓታዊ ሽንፈቱን ያበዛዋል፡፡ በአናቱም በስልጤው ሞዴል ግፊት ወደ አደባባይ የመጡት የወለኔና የቁጫ የማንነት ጥያቄዎች የሚጠቁሙት አንዳች ነገር ቢኖር፣ የስርዓቱ ቁንጮዎች የተጠቀሰውን ስታሊኒስታዊ የራስ ዕድል በራስ የመወሰን ጉዳይ በሕገ-መንግስታቸው ውስጥ ሲከቱት፣ ኢትዮጵያን በመሰለ ባለብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ዜጎች ሀገር ጥያቄው ማቆሚያ እንደማይኖረው አለማሰባቸውን ነው፡፡
በእነዚህ የኢህአዴግ ታላለቅ ግድፈቶች ህላዊነት ከተስማማን የለውጥ መንገዱንም አንስቶ መነጋገሩ የግድ አስፈላጊ ነውና ወደዚያው እንለፍ፡፡
የከተማ አብዮት ሲባል…
በዚህ ተጠይቅ የምናየው አማራጭ የለውጥ መንገድ ያለንበት ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የሚበይነውን ሰላማዊ የከተማ አብዮት ብቻ ሳይሆን፣ ረዥም ዓመታትን ወደ ኋላ ተጉዘን በአማራጭነት ይተገበሩ የነበሩትንም ጭምር ነው፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያችን ዛሬም ከተቃውሞ ስብስቡ መካከል ሁለቱንም ስልት የሚያቀነቅኑ የፖለቲካ ድርጅቶች መኖራቸው እውነት ነውና፡፡
ምንም እንኳ ጥያቄያቸው፣ አመሰራረታቸው እና የሚከተሉት ርዕዮተ-ዓለም ፍፁም የተለያየ ቢሆንም፣ ከኦነግ እስከ ኦብነግ፤ ከአርበኞች ግንባር እስከ ግንቦት ሰባት (ሁሉን አቀፍ የሚሉት ስልት እንደተጠበቀ ሆኖ) ድረስ የሚጠቀሱ ድርጅቶች ከከተማ አብዮት የ‹ማኦኢዝም›ን (ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ጦርነት ላይ የሚያተኩር) የትግል ስልት እንደ ብቸኛ አማራጭ መውሰዳቸው የታወቀ ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ተቃውሞ መነሾ የሆነው ራሱ ኢህአዴግም ወደ ስልጣን የመጣበት መንገድ ሳይቀነስ ሳይጨመር ይኸው እንደነበረም አይዘነጋም፡፡
በኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ መቀንቀን ከተጀመረበት 1960ዎቹ አጋማሽ አንስቶ የተመሰረቱ ግራ ዘመም ድርጅቶች በሙሉ ‹‹መንፈሳዊ አባት›› አድርገው የሚወስዱት የማኦ ዚዱንግ (Mao Zedong) የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ (CCP) ለጥቂት ዓመታትም ቢሆን አራምዶት የነበረው የትግል ስልት ከከተማ ወደ ገጠር የሚነሳ እንደነበረ ይታወሳል፤ ይሁንና ሲሲፒ እ.ኤ.አ. በ1927 ዓ.ም. የፀደይ ወራት በሻንጋይ ሼክ (Chiang Kai-shek) ከሚመራው ‹‹Kuomintang›› (KMT)፣ የደረሰበትን ከባድ ወታደራዊ ጡጫ መቋቋም ተስኖት ከጠንካራ መሰረቶቹ ሻንጋይ እና ክንቶን (ዛሬ ስሟ ‹ጉዋንዡ› /Guangzhou/ በሚል ተቀይሯል) ከተሞች ወደ ገጠር ማፈግፈጉን ድርሳናቱ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በኋላም የእነ ማኦ ድርጅት ‹የሠራተኛ መደብ› የሚል አጀንዳውን አርቆ ሰቅሎ፣ እንደ አዲስ በገበሬ ሰራዊት በመዋቀር የትጥቅ ትግልን ከገጠር የመጀመር ጠቀሜታ ሰባኪ ብሎም የገበሬ አምባገንነት አቀንቃኝ ሆኖ ብቅ ማለቱን ከታሪክ ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡ በነገራችን ላይ ሲሲፒ የስልት ለውጥ ከማድረጉ በፊት ከ11 ሺ ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍነውን ‹‹ረጅሙ-ጉዞ››ን (Long march) በፅናት መጨረሱ የዓላማ ፅናቱን ያሳያል፡፡
እነ ማኦ ለመስማት ከሚዘገንነው መስዋዕትነት በኋላ ለሥልጣን የበቁት ድርጅታቸው በተመሰረተ በሃያ ስምንተኛ አመት (እ.ኤ.አ. በ1949 ዓ.ም) ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት የሚኖሩ ሕዝቦች ‹ጭቆናን ለማስወገድ› በሚል ‹ግራ ዘመም› ድርጅት መስርተው በእምቢተኝነት ሲያምፁ፣ ማኦኢዝም የትግል ስልት የሚበይነውን በገበሬዎች በተደራጀ ሰራዊት ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ሽምቅ ውጊያን እንደሁነኛ አማራጭ መከተላቸውን ታሪክ ይነግረናል፡፡ በአናቱም የማኦ አስተምህሮ ‹በገበሬ አብዮት› የሚመሰረትን የ‹እርሻ መር ኢኮኖሚ ማህበረሰብ› (Agrarian society) መፍጠርን እና የከተሞችን ፖለቲካል ኢኮኖሚ በማፈራረስ የገበሬውን ሁለንተናዊ ከፍታ ማረጋገጥ ላይ ማተኮሩ በዚህ መንገድ ወደ ሥልጣን የወጡ ገዥዎቻችንን ባህሪ ለመዳኘት ይረዳናል፡፡
እነሆም በዚህ ትውልድ መቀመጫቸውን በሀገራችን የጠረፍ ከተሞች አሊያም በአውሮፓና አሜሪካ ያደረጉ ብረት ያነሱ ድርጅቶች ከላይ በተጠቀሰው የታሪክ ንባብ ከተመዘኑ፣ አንድም የመረጡት የትግል ስልት ዘመኑን የሚዋጅ ነው ብሎ ለመቀበል ያዳግታል፤ ሁለትም በለስ ቀንቷቸው ያሰቡት መሳካት ቢችል እንኳ፣ በእንዲህ አይነት መልኩ ባንክ ዘርፈው፣ መሰረተ ልማቶችን አውድመው፣ ንፁህን ዜጎችን ለህልፈት ዳርገው፣ የቅርብ ጓደኞቻቸውን ሰውተውና ጠብ-መንጃ ተሸክመው ወደ ቤተ-መንግስት የሚመጡበት መንገድ፣ ከዓመታት በፊት መለስና ጓዶቹ ‹ታግለናል፣ ሞተናል፣ ደምተናል… እናም ምርጥ ምርጡ ለእኛና ለቤተሰቦቻችን ብቻ› በሚል ድምዳሜ ካዘጋጁት ‹መፅሀፍ› አንድ ገፅ ገንጥለው ‹‹የሞትንም እኛ፤ ያለንም እኛ…›› ወደሚል የአምባገነኖች ጠርዝ መገፋታቸው አይቀሬ ይመስለኛል፡፡
በተጨማሪም ‹‹ጨቋኝ ጨቋኝን ሊተካው ይችላል›› እንዲል አርስቶትል ኢህአዴግ ለአስራ ሰባት ዓመታት በዱር-በገደል ወጥቶና ወርዶ፣ አስከፊ መስዋዕትነትን ከፍሎ፣ አራት ኪሎ ከደረሰ በኋላ፣ ያነበረው ስርዓት ካመፀበት የመንግስቱ ኃይለማርያም አስተዳደር ጋር ያለው ልዩነት የስም ብቻ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ይህ ሁኔታም ነው በብረት የታጠረ፣ ደም አፋሳሽና የተናጥል አሸናፊነትን በሚያውጅ ስብከት ላይ ብቻ የተገነባው የትግል ትርጓሜ ዛሬም እንደአዲስ የመከለሱ ዜና በስጋት ያነጠበን፡፡ በርግጥም የጭቆናን ሸክም ከትከሻ ለማውረድ ሲባል የተካሄዱ መራራ ትግሎች ውጤታቸው ጨቋኞችን መቀያየር መሆኑና የትንቅንቁ ወራቶች መርዘም ያስከተሉት ኪሳራዎች ከዘመኔ ቀድሞ የነበረውን የማኦን መንገድ የታሪክ መዛግብት ላይ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር በመገደብ ለአማራጭነት እንኳ እንዳይበቃ አድርገውታል፡፡ የዚያን ዘመን የጨቋኞች አገዛዝ ውርስን ለመከተል ወቅቱ አመቺ አለመሆኑንና የሥልጣን ወንበርን ለጊዜውም ለማሰንበት ዘመን-ወለዱን አመቻማች አምባገነንትን መጠመቅ ማስፈለጉም የትግሉ ስያሜ በድጋሚ ለብይን እንዲቀርብ ተጨማሪ ኃይል ሆኗል፡፡ ርዕዮተ-ዓለማዊ ልዩነቶች እስኪዘነጉ ድረስ መጥበባቸው፣ ክስተቶች ከአንድ ሀገር ድንበር መዝለላቸው እንዲሁም ወቅታዊዎቹ የለውጥ ስኬቶች በጋራ የቀድሞውን የአብዮት መስመር በጥርጣሬ እንድንመለከተው ፈርደውበታል፡፡ ዛሬ ላይ አብዮት ቃሉ ብቻ እስኪቀር ድረስ ተነቅሎ ነባር የመዳረሻ መንገዶቹ ፈራርሰዋል፤ በፍርስራሹ ላይም አዲስ ትርጓሜ ተቸክችኮበታል፡፡
እነዚህና መሰል ሁነቶች የለውጡን መንገድ ለመቃረም ፊታችንን ወደ አውሮፓውያኖቹ የ‹ብርቱካናማ› እና የ‹ፅጌረዳ› አሊያም ወደ አረቡ የ‹ፀደይ› አብዮት እንመልስ ዘንድ ያስገድዱናል፡፡ ይህ ግን እነ ሌኒን ያራምዱትና ይመክሩት ከነበረው በከተሞች ውስጥ ከሚደረገው የትጥቅ ትግል ፍፁም የተለይ ይመስለኛል፡፡ በርግጥም እንዲህ አይነቱ አማራጭ በ1966ቱ አብዮት ማግስት በራሳችን ሰዎች ተሞክሮ ከመክሸፉም በላይ ሀገሪቱን ወደ ቀለም ሽብር ከቷት መቼም ሊተካ የማይችል ዋጋ ማስከፈሉ ሁሌም በቁጭት የምናስበው ታሪካችን ነው፡፡ እናም ለእኔ ትውልድ የለውጥ ጥያቄ ከሰላማዊው የከተማ አብዮት ውጪ ያሉ አማራጮች ከጠቀሜታቸው ይልቅ ጥፋታቸው አመዝኖ ነው የሚታየኝ፡፡ በተለይም ነባሩን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል (የ‹ጦር አርበኝነት›ን በ‹ሲቪል ጀግንነት›) ለመቀየርም ሆነ፣ ከእርስ በርስ እልቂት፣ ከደም መፋሰስ፣ ከደካማው ኢኮኖሚ መንኮታኮት፣ ካለመረጋጋት… ለመታደግ ብቸኛ መፍትሄ ይኸው ነው፡፡ በተጨማሪም ከከተማ መነሳቱ ለአገዛዙ ምሰሶ፤ ለሀገሪቱ ደግሞ ስጋት የሆኑትን የሃይማኖት እና ብሔር (ቋንቋ) ልዩነቶችን ተሻግሮ፣ በአንድ ሀገር በእኩል ማንነት ላይ የሚያሰባስብ ኃይል ይፈጥራል ብዬ አስባለሁ፡፡
በነገራችን ላይ ለእንዲህ አይነቱ አደገኛ ስጋት መቃረባችንን የሚያሳየው በይበልጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተቃውሞ ስብስቡ አካባቢ የሚሰማው ከሀገር ይልቅ የትውልድ መንደርን የማስቀደም ድምፅ ነው፡፡ ይሁንና ይህ መንገድ የትም ሊያደርስ ካለመቻሉም በላይ ላለፉት ሃያ ዓመታት የጭቆና ቀንበርን ትከሻችን ላይ እንዲከርር አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ እናም ወደ ተናፋቂው የነፃነት ምኩራብ ሊያደርሰን የሚችለው ድምዳሜ ስርዓቱ ትግራይን ከኦሮሚያ፣ ወይም ከአማራ… የበላይ አድርጎ ያስተዳድራል ለሚሉ ከፋፋይ አሉባልታዎች ጆሮ መንፈግ ብቻ ነው፤ የአንዳንድ ብሔር ተኮር ድርጅት አፈ-ቀላጤዎችም ንጉሳዊውን ዘመን የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወኪል ለማስመሰል መሞከራቸውም ሆነ ህወሓት የተሰኘው የማፍያ ቡድን የሚፈፅመውን ግፋአዊ አገዛዝ በየትኛውም መስፈርት ከትግራይ ህዝብ ጋር ለማያያዝ የሚያደርጉትን ጥረት ማክሸፉ ከአብዮቱ ቅድመ ዝግጅቶች አንዱ ይመስለኛል፡፡
የሆነው ሆኖ ‹አብዮት የራት ግብዣ አይደለም› እንዲል ማኦ፣ አሁን እየተናገርንለት ያለው ሰላማዊው የከተማ ተቃውሞ የጠብ-መንጃውን ያህል ባይሆንም እንኳ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀሬ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ በየትኛውም ሀገር ያሉ አምባገነን ገዥዎች በሕዝባዊ እምቢተኝነት አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎቻቸውን ወደ ቤተ-መንግስታቸው እንዲገቡ ሲፈቅዱ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡
እንዲያውም በግልባጩ በጦር ሠራዊትና በደህንነት ኃይል ለማስፈራራት ሲሞክሩ፣ ከተቃዋሚዎቻቸው የተወሰኑትን በመቀጣጫነት በጥይት ሲያስደበድቡ፣ አስተባባሪዎቹን ሲያስሩ፣ የአገዛዛቸውን የብረት መዳፍ ይበልጥ ሲያጠነክሩ… ይስተዋላሉ፡፡ ይሁንና ይህ አይነቱ የጭካኔ እርምጃ አምባገነኖችን ከአብዮቱ ወላፈን ሊታደጋቸው አለመቻሉን ማረጋገጥ ካስፈለገ ቱኒዝያ ጥሩ ማሳያ ትመስለኛለች፡፡ አደባባዩን ከማማተር አስቀድሞ ግን አብዮቱ መያዝ ስለሚገባው ባህርያት ጥቂት ነጥቦችን ማንሳት ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡
የለውጡ መስመር አንዱ መለዮ መሆን የሚኖርበት የትኞቹንም ጨቋኝ ህጎችን በአደባባይ መጣስ ነው፤ እዚህ ቦታ ለመሰለፍ ጠይቀን ተከለከልን፤ ደጋፊዎቻችንን እንዳንሰበስብ አዳራሽ አጣን… እና መሰል ቀልዶችን በመተው አዋጆቹን (እንደ ፀረ-ሽብር እና የፕሬስ አዋጅ ውስጥ ያደፈጡ ቀፍዳጅ አንቀፆችን) በግላጭ በመጣስ በገፍ ወደዘብጥያ ለመውረድ መወሰን የአብዮቱ ዋና አካሄድ መሆን የሚኖርበት ይመስለኛል (በዚህ አውድ አንድ የቢሆን ምሳሌ እናንሳ፤ አሁን ካሉት ህጋዊ ፓርቲዎች መካከል አንዱ በአንድ ክፉ ቀን የፓርቲው የህጋዊነት ማረጋገጫ በሎሌው የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ቢሰረዝና እኛም አማራጭ አካሄዶችን ስለማሰላሰላቸው ብንጠይቅ፣ ‹‹ጨዋታው ፈረሰ…›› ብለው ወደየቤታቸው ገብተው ይቀመጡ ይሆናል ከሚለው ውጪ የምናገኘው ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል?)
ሌላኛው ነጥብ ቡድናዊ መሰባሰቢያ መስፈርቶችን ይመለከታል፤ በአረቡ ፀደይ እንዳስተዋልነው (ስለአረቡ ዓለም አብዮት ባህሪያት ከፍትህ ጋዜጣ እስከ ፋክት መፅሄት ድረስ በተደጋጋሚ ሊብራራ ተሞክሯልና እዚህ መድገም አያስፈልግም) የፆታን፣ የኃይማኖትን፣ የመደብን፣ የአንድ ርዕዮተ-ዓለምን አሊያም የብሄር ልዩነቶችን በመሻገር ሁለንተናዊ የዜግነት ነፃነቶችን መሻትን ብቻ ማዕከል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሁለንተናዊ የዜግነት ነፃነቶች ሲባል ደግሞ የኃይማኖት፣ የፖለቲካና የሲቪል መብቶች መከበር ማለት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የትኞቹንም የቡድንም ሆነ ግለሰብ ተኮር ጥያቄዎች ይህንን ነፃነት በማስከበር ትግል ውስጥ ማስመለስ እንደሚቻል መታወቁ የአብዮቱን መሪ ቡድኖች መልከዓ-ባህሪ በዜግነት ላይ ብቻ እንዲቆም ያደርገዋል፤ ይህ ክንውንም፣ በአንድ በኩል የስርዓቱን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ሲያከሽፍ፣ በሌላ በኩል የተሻለች ሀገር ለማቆም የማይነቃነቅ ጠንካራ መሰረት ይጥላል (በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደም ፋክትን ጨምሮ በአራቱም የህትመት ውጤቶች ያነሳኋቸው የፈራ ይመለስ፣ ሞት የማይፈሩ ወጣቶች፣ ለምን ትፈራለህ? የታህሪር ናፍቆት፣ የዘገየው አብዮት፣ የግፉአን ዕድሜ ምን ያህል ይረዝማል? አደባባዩ ምን ያህል ይርቃል? የመሳሰሉት ቀዳሚ ድምፆች በዚህ አይነቱ ሰላማዊ የከተማ
አብዮት የሚበየኑ መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል)
የአብዮቱ ግቦች…
በጥቅሉ እዚህ ድረስ ስንነጋገርበት የነበረው የከተማ አብዮት እንደ ሊቢያ ወይም ሶርያ ለእርስ በእርስ እልቂት የሚዳርግ ደም አፋሳሽ አለመሆኑ ግልፅ ይመስለኛል፡፡ በዚህ አውድ ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባው አንኳር ጉዳይ የአረቡን መነቃቃት ተከትሎ በሞሮኮ፣ የመን እና ኳታር እንደታየው አይነት፣ ከስር ነቀል ለውጥ ይልቅ የፖለቲካ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ የአምባገነኑን አገዛዝ እጅ መጠምዘዙ ላይ ነው፤ ይህ ይሆን ዘንድም የሚከተሉት ጥያቄዎች ወደ አደባባይ መሰባሰብ የሚያስችሉን የጋራ አጀንዳ (የአብዮቱ ግቦች) ቢሆኑ ለስርዓቱ ‹‹የወንድ በር››፤ ለምንወዳት ሀገራችን ደግሞ የተስፋውን መንገድ ጠራጊ የሚሆኑ ይመስለኛል፡፡
ከፊታችን ያለው የ2007ቱ አምስተኛ ዙር አገር አቀፍ ምርጫ ከመደረጉ በፊት፣ ያን ጊዜ የ97ቱ ቅንጅት ፓርላማ ለመግባት በቅድመ ሁኔታነት አንስቷቸው የነበሩትን ከፊል ጥያቄዎች ጨምሮ ሌሎችም በዚህ ፅሁፍ የተካተቱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣቸው ዘንድ ከሥራ ማቆማ አድም አንስቶ ከአገዛዙ ጋር አለመተባበርን የሚያካትትና ለውጡ እስኪመጣ በተከታታይ (በብሔር አግላይ ያልሆነ) መሬት አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ መሰል እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ራስን ማዘጋጀት ይጠይቃል፤ ጥያቄዎቹም የሚከተሉት ናቸው፡-
1/ ሁሉንም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር መፍታት፤
2/ እስከ ዛሬ ድረስ በሀገር ጥቅም ላይ ለተፈፀመው ጥፋትም ሆነ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ለደረሰው ጅምላ ጭፍጨፋ፣ እስር፣ እንግልት፣ አካል መጉደል እና ስደት ኃላፊነት ወስዶ በአደባባይ ይቅርታ መጠየቅ (ካሳ የሚገባቸውን መካስ)፣ ለብሔራዊ ዕርቅ መደላድል መፍጠር፤
3/ አፋኝ የሆኑትን የፀረ-ሽብር፣ የፕሬስ፣ የመያዶች እና የፖለቲካ ማሻሻያ አዋጆችን መሻር፤
4/ ዜጎች በሚያምኑበት የፖለቲካ አስተሳሰብ የመደራጀት መብታቸውን ያለአንዳች ገደብ መልቀቅ፤
5/ ከሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በእኩል ደረጃ መወያየትና መደራደር፤
6/ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ነፃና ገለልተኛ መሆኑን በሚያረጋግጥ ሁኔታ እንደገና ማቋቋምና የአቅም ብቃቱን መገንባት፤
7/ ፍትሐዊ የመንግስት ሚዲያ አጠቃቀም እንዲኖርና የግል የኤሌክትሮኒክስም ሆነ የህትመት ሚዲያዎች ያለ ከልካይ እንዲኖሩ መፍቀድ፤
8/ የፍ/ቤትን እና የሌሎች የፍትህ አካላትን ነፃነት ማረጋገጥ፤
9/ የፖሊስ፣ የመከላከያና የደህንነት ተቋማት ከፖለቲካ ገለልተኛ እንዲሆኑ ማድረግ፤
10/ ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች ተፈፃሚ የሚያደርግ ለየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት የማይወግን ነፃ የሆነ አካል ማቋቋም የሚሉት
ጥያቄዎች የመንደርደሪያ ነጥብ መሆን የሚችሉ ይመስለኛል፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com
January 5, 2014