Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ግልጽ ድብዳቤ ለፕሮፌሰር መስፈን ወልደማሪያም –ግርማ ካሳ

$
0
0

ግርማ ካሳ

Pro Mesfinየእግዚአብሄር ሰላምና ጸጋ ከርስዎ ጋር ይሁን። ከአጼ ኃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ፣ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ብዙ ያበረከቱ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ኖት። በተለይም ደርግ ሊወድቅ አካባቢ፣ ከነዶር ሰለሞን ተርፋ፣ ዶር ስብሀት ጋር ሆነዉ አቅርበዉት የነበረው የእርቅ ሰነድ መቼም የማልረሳው ነዉ። «ይቅር ለእግዚአብሄር» በሚል መንፈስ፣ ከኢሰፓና ከሽምቅ ተዋጊዎች ከተወከሉ፣ ከአገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች የተወጣጣ፣ የሽማግሌ መንግስት እንዲቋቋም ነበር ሃሳብዎት። መንግስቱ ኃይለማሪያም ፈርጥጦ ሊጠፋ ፣ «የአገር ጉዳይ የባልና የሚስት ጉዳያ አይደለም በይቅር ለእግዜር የሚፈታዉ» ብሎ፣ በአራት ሰዓቱ ባዶ ዲስኩር አደንቁሮን፣ ሃሳብዎትን ዉድቅ አደረገዉ እንጂ።

አሁንም ያኔ በርስዎ ዘንድ የነበረዉን የማስታረቅና የማቀራረብ መንፈስ ነዉ ማየት የምፈልገዉ። እንደሚያወቁት በምርጫ ዘጠና ሰባት፣ ቅንጅት ዉስጥ ነበሩ። ከዚያም በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራዉን የአንድነት ፓርቲን ተቀላቀሉ። መድረክ የሚባል ስብስብ ተፈጠረ። በመድርክ ዙሪያ አንዳንድ ልዩነቶች ጎልተዉ ወጡ። እርስዎም በወቅቱ «ዝም አንልም» ከዚያም «መርህ ይከበር» ከሚሉ ወገኖች ጋር በመሆን በአንድነት ፓርቲ አመርሮች ላይ ከፍተኛ ተቃዉሞ አሰሙ። (ዴሞክራሲያዊ መብቶትን ተጠቅመው) በተለይም በመድረክ ዙሪያ ከአንድነት ፓርቲ ጋር ያላችሁ ልዩነቱ መፍትሄ ሲያጣ፣ ሰማያዊ ፓርቲ የሚባል ድርጅት አቋቋማችሁ። ባልሳሳት እርስዎ የመጀመሪያው መሪ ሆኑ። ይኸው የርስዎ ድርጅት ሰማያዊ ፓርቲ፣ አገር ቤት ጥሩ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ድርጅቶች ከጥቂቶቹ መካከል አንዱ ሆኗል። ምንም እንኳን አሁን የድርጅቱ አመራር አባል ባይሆኑም፣ ትልቅ ተሰሚነት ያልዎት፣ የሰማያዊ ፓርቲ «አባት» መሆንዎ ግን የማይካድ ነዉ።

የአንድነት ፓርቲ፣ በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤዉን አድርጓል። የቃሊቲ ወዳጅዎ ኢንጂነር ግዛቸው፣ ሊቀመንበር ሆነዉ ሲመረጡ፣ 65% የሚሆኑ የአመራራ አባላቱ ከሰላሳ አምስት በታች የሆኑ ወጣቶች ሆኑ። ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ፣ ድርጅታቸዉ አንድነት፣ ከሰማያዊ፣ መኢአድ፣ አረና፣ ኤዴፓ ጋር ለመዋሃድ ፍላጎት እንዳለው፣ ለዚያም ተግቶ እንደሚሰራ ተናገሩ።

እንደሚያወቁት በሰማያዊና በአንድነት መካከል፣ ይሄ ነዉ የሚባል የጎላ የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነት የለም። ሁለቱም አሁን ያለዉ በዘር ላይ ብቻ የተመሰረተ ፌደራል አወቃቀር መቀየር አለበት ይላሉ። ሁለቱም ብሄረሰቦች ባህላቸውንና ቋንቋቸው የማስፋፋት መብት እንዳላቸው፣ ኢትዮጵያ ዉበቷ ብሄረሰቦቿ እንደሆኑ ያማናሉ። ሁለቱም «የብሄረሰብ ሆነ የቡድን መብቶች መከበር አላባቸው» ይላሉ። የቡድን(ብሄረሰብ) መብቶች ከግለሰብ መብት ጋር ከተጋጨ ቅድሚያ የሚሰጠው ለግለሰብ መብት እንደሆነ ሁለቱም ያረጋግጣሉ። በመሬት፣ በጸረ-ሽብርተኘነት ሕግ እንዲሁም በርካት ፖሊሲዎች ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም አላቸው።

እርግጥ ነዉ በአንድነትና በመድረክ ግንኙነት ዙሪያ የተንጠላጠሉ ችግሮች አሉ። ነገር ግን የአንድነት ፓርቲ በሶስት ወራት ጊዜ ዉስጥ የመድረክን ጉዳይ እልባት እንዲሰጠው ጠቅላላ ጉባዔው ወስኗል። ወይ የመድረክ አባል ድርጅቶች፣ ልዩነቶቻቸውን አጣበው፣ ዉህደት ይመሰርታሉ፤ አሊያም አንድነትና መድረክ ይለያያሉ። ስለዚህ ሰማያዊ ፓርቲ ከአንድነት ጋር የዉህደት ንግግር እንዳይጀመር ፣ መድረክ መሰናክል ሊሆን አይችልም።

እርስዎ እንዴት እንደሚያዩት አላውቅም፣ እኔ ግን የሰማያዊ ፓርቲና አንድነት መዋሃድ ድርጅቶቹን ብቻ ሳይሆን፣ ትግሉን ይጠቅማል ባይ ነኝ። በ2007 ዓ.ም የሚደረገዉ ብሄራዊ ምርጫ አንድ አመት አካባቢ ነዉ የቀረው። በ547 ወረዳዎች ተወዳዳሪዎችን ማሰለፍ የግድ ነዉ። አንድ ድርጅት ብቻ ሊሰራዉ አይችልም። የግድ አቅምና ጉልበትን ማስተባበር ያስፈልጋል። እርስዎም ይሄን ያጡታል ብዬ አላውቅም፤ የሰማያዊና አንድነት አብሮ አለመሆን የሚጠቅመው አገዝዙን ብቻ ነዉ ።

እንግዲህ እንደ አባት ሁሉን እየተቆጡና እየመከሩ፣ ዘንድሮም እንደ ከዚህ በፊቱ ቁም ነገር እንዲሰሩ እማጸንዎታለሁ። የፖለቲክ መሪዎች ከራሳቸው ስሜት አልፈዉ፣ ከድርጅታቸው በላይ የአገርንና የሕዝብን ጥቅም ማስቀደም እንዲችሉ፤ የትላንቱ ልዩነቶች ገመድ ሆነው እንዳይጠልፏቸው እንዲጠነቀቁ፣ ከግትርነት እንዲወጡ ፣ ይቅር ለእግዚአብሄር እንዲባባሉ ያስፈልጋል። ያላጠፋ የለም። ያልተሳሳተ የለም። እርስዎም ቢሆኑ፣ ሁላችንም ያጠፋነው ጥፋት አለ። ነገር ግን ትልቅ ሰው ከስህተቱ ይማራል። ትልቅ ሰው በትላንቱ ስህተቶቹ እግሮቹን አስሮ ወደፊት ከመጓዝ አይቆጠበም። ትልቅ ሰው ይቅር ይላል።

ከላይ እንዳልኩት የአንድነት ፓርቲ የዉህደት ጥሪ አቅርቧል። መኢአድና እና አራና ከአንድነት ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች እንደጀመሩ የሚገልጹ ዘገባዎችን አንብቢያለሁ። አቶ ልደቱ አያሌዉ ለአድምስ ጋዜጣ ጋር ከሰጡት ቃለ መልልስ አኳያ፣ ኤዴፓም ከነአንድነት ጋር አብሮ ለመሆን የመፈለግ አዝማሚያ ሳይኖረው እንደማይቀር አስባለሁ። የቀረዉ ሰማያዊ ነዉ። እንግዲህ የሰማያዊን ነገር ለርስዎ ጥዬዋለሁ። ያሳምኗቸዉና ያግባቧቸው ዘንድ እጠይቅዎታለሁ።

ምክርዎትን አልሰማ ብለው የተናጥል ጉዟቸዉን ከቀጠሉ ግን፣ ምንም ማድረግ አይቻልም፣ ምርጫዉ የነርሱ ይሆናል። ጉዳዩ የፌዝና የቀልድ፣ ወይንም የግልሰቦች ተክለ ሰውነት የመገንባት ሳይሆን፣ የአገር ሕልዉናና ደህነት ነዉ። ይሄንንም ጠንቅቆ የሚረዳው፣ በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ፣ ሁሉንም ያታዘባል። ትልቁ ነገር ቅንነት ነውና፣ እግዚአብሄር ለሁላችንም የቅንነትን እና የትህትናን መንፈስ ያላብሰን ! «እኔ ለምን ተነካዉ» ብለን የምንቆጣና የምንቀየም ሳይሆን ይቅር ባዮች ያድርገን !

እግዚአብሄር ያክብርልኝ።


2014፡ የኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ዓመት- ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

(ክፍል አንድ) 2014 የኢትዮጵያ የአቦ -ጉማሬው ትውልድ የሚነሳሳበት ዓመት፣

እ.ኤ.አ በ2013 በመጀመሪያው ሳምንት ባቀረብኩት ሳምንታዊው ትችቴ ዓመቱ “የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (የወጣቱ ትውልድ) ዓመት ይሆናል “የሚል ትንበያ ሰጥቼ ነበር፡፡ እንደትንበያውም ዓመቱ የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (ወጣቱ) ትውልድ ታላቅ የስኬት ዓመት ሆኖ ተጠናቅቋል፡፡

Alemayehu G. Mariam

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

2014 ደግሞ “የኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ዓመት ይሆናል” የሚል ትንበያ እሰጣለሁ፡፡  የአቦ-ጉማሬው ትውልድ በአፈጣጠሩ የጉማሬው (የቀድሞው ትውልድ) አባል ሲሆን በተግባራዊ እንቅስቃሴው ግን እንደ አቦሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) የሚያስብ፣ አቦሸማኔውን የሚመስል እና እንደ አቦሸማኔው ሁሉ የክንውን ድርጊቶችን የሚፈጽም የማህበረሰብ ክፍል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ለፍትህ እና ለነጻነት በሚደረገው የትግል ሂደት ላይ የጉማሬው (የቀድሞው ትውልድ) የሚያንጸባርቃቸውን ድክመቶች በሚገባ የተገነዘበ እና እነዚህን ግድፈቶች በማስወገድ የወጣቱን የትግል መንፈስ እና ወኔ ወደ ላቀ የእድገት ምዕራፍ ለማሸጋገር በአንድ ዓላማ ለአንድ ዓላማ ከአቦሸማኔው (የወጣቱ) ትውልድ ጎን በመሰለፍ የሚሰራ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ በአፈጣጠሩ ልዩ የሆነ የትውልድ ዝርያ ነው፡፡ ይህ ትውልድ በተፈጥሮው ድልድይ ቀያሽ እና በኃይል አሰላለፍ ላይ ያለውን ወቅታዊ እና ነባራዊ ሁኔታ በተገቢው መንገድ እያጠና ወጣቱን ትውልድ ለድል የሚያበቁ የኃይል ምንጮችን ቀጣይነት ባለው መልክ የሚፈበርክ የህብረተሰብ አካል ነው፡፡ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ወጣቱን ከቀዳሚው ትውልድ የሚያገናኙ ጠንካራ ትውልድ አገናኝ የትውልድ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ ደኃውን ከሀብታም የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ ህዝቦችን ከአምባገነናዊ ስርዓት ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚያሸጋግሩ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ በጎሳ የተለያዩ ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ “ክልላዊ ደሴቶች (የጎሳ መንደሮች ወይም ባንቱስታንስ)” ተብለው ተነጣጥለው የሚኖሩ ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ በቋንቋ፣ በኃይማኖት እና በክልል ተነጣጥለው የተቀመጡ ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው:: ባለመተማመን ሸለቆዎች፣ በእምነት ማጣት ጥልቅ  ገደሎችና   እና  በጥርጣሬ ጎርፍ ወንዞች ላይ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ ብሄራዊ ዕርቅ ለማውረድ እና የብሄራዊ አንድነትን ለማምጣት ህዝቦችን የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚነገነቡ ናቸው፡፡ በአገር ቤት ውስጥ ያሉትን ወጣቶች በውጭ አገር ከሚኖሩት የዲያስፖራ ወጣቶች ጋር የሚያገናኙ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ለመሻገር አስቸጋሪ በሆኑ የውኃ አካላት ላይ ድልድዮችን የሚገነቡ ናቸው፡፡

 

የኢትዮጵያ የአቦ-ሸማኔው ትውልድ አባላት ኃይል አባዥዎችም ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ዘለቄታ ያለው መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እንዲቻል የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት ከእራሳቸው እውቀት፣ ዘዴ እና ልምድ አኳያ በመቀመር የወጣቱን ኃይል፣ ፍቅር እና ጽኑ ዓላማ በአግባቡ ያለምንም ብክነት በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋሉ፡፡ በግትር የአምባገነኖች ተለዋዋጭ ባህሪያት ላይ የእራሳቸውን ፈጠራ በመጠቀም በወሳኝ ጉዳዮች ላይ የወጣቶች የለውጥ አራማጅነት የትግል መንፈስ ውጤታማ እና ስኬታማ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡

 

የአቦ -ጉማሬው ትውልድ አባል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል!

 

የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ትውልድ በአስፈሪ ዕጣ ፈንታ ውስጥ፣

 

በእኔ አስተያየት የኢትዮጵያ 21ኛው ክፍለ ዘመን ግንባርቀደም ችግር ሆኖ የሚቀርበው የኢትዮጵያ ወጣቶች ችግር ነው፡፡ በአሜሪካ የህዝብ ቆጠራ ቢሮ ትንበያ መሰረት ከ37 ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር አሁን ካለበት ደረጃ በሶስት እጥፍ በማደግ 278 ሚሊዮን በመሆን ኢትዮጵያን ከዓለም በህዝብ ብዛት ከአንድ እስከ አስር ደረጃ ከሚይዙ አገሮች ተርታ ውስጥ ምድብተኛ ያደርጋታል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕድገት ላለፉት አስርት ዓመታት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው የመጣው፡፡ እ.ኤ.አ በ1967 የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 23.5 ሚሊዮን ነበር፡፡ በ1990 ወደ 51 ሚሊዮን ያደገ ሲሆን በ2003 ደግሞ ቁጥሩ እየጨመረ በመምጣት 68 ሚሊዮን ደረሰ፡፡ በ2008 ይህ ቁጥር እየጨመረ በመምጣት ወደ 80 ሚሊዮን ከፍ አለ፡፡ በ2013 የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ከ94 ሚሊዮን በላይ እንደሚደርስ ተገምቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ 70 በመቶ (66 ሚሊዮን) የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ከ35 ዓመት በታች እንደሆነ ይገመታል፡፡ እ.ኤ.አ ከ1995 ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ ዓመታዊ አማካይ የዕድገት መጣኔ ከ3 በመቶ በላይ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡

 

ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ በማለት አመላክተዋል፣ “ልጆቻችን ታላቅ ኃብቶቻችን ናቸው፡፡ ልጆቻችን የወደፊት ተስፋዎቻችን ናቸው፡፡ የልጆቻችንን መብት የሚጥስ ማንም ቢሆን የህዝባችንን የትስስር ክር የሚበጥስ እና አገራችንን የሚያዳክም ነው፡፡“ ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች የአገሪቱ ታላቅ ኃብቶች ናቸው ብለን ካሰብን እና በአሁኑ ጊዜ በታላቅ አደጋ ውስጥ ይገኛሉ ከተባለ የሀገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታም በአደጋ ላይ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡ የኢትዮጵያ ታላቅ ኃብቶች ተረስተዋል፣ መብቶቻቸው ተደፍጥጠዋል፣ ወርቃማው ጊዚያቸው፣ ዕውቀታቸው፣ ጉልበታቸው እና ብሩህ አዕምሯቸው ለሀገር ጥቅም ሳይውል ቀርቷል፣ እንዲሁም ባክኗል፡፡ “ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሆነ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት የቅበላ መጣኔ (Enrollment Rate) ከሚያስመዘግቡ በዓለም ላይ ከሚገኙ አገሮች አንዷ ናት፡፡…የአፍሪካ የህዝብ እና የጤና ምርምር ማዕከል ባቀረበው ዘገባ መሰረት በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት እያሽቆለቆለ እና የክፍል ደጋሚ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣት፣ እንዲሁም በጾታ፣ በገጠር እና በከተማ መካከል የሚታየው ሰፊ ልዩነት የአገሪቱ ከባድ ፈተናዎች ሆነው ቀጥለዋል፡፡“ የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግባት፣ ወይም ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ስራ የማግኘት ዕድላቸው የመነመነ ሆኗል፡፡

 

እ.ኤ.አ በ2012 ዩኤስኤይድ/USAID በኢትዮጵያ ላይ ባደረገው ጥናት መሰረት “ኢትዮጵያ 50 በመቶ የከተማ ወጣቶች ስራ አጥ መጣኔ/Unemployment Rate በማስመዝገብ ከፍተኛ ደረጃ የያዘች መሆኗን እና 85 በመቶ ገደማ የሚሆነው ህዝብ በሚኖርበት የገጠር አካባቢ ያለው ወጣት ከፍተኛ በሆነ ስውር ስራ አጥነት/underemployment/disguised unemployment ውስጥ ተተብትቦ ይገኛል፡፡“ በማለት የጥናት ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በ2012 በዓለም አቀፍ የዕድገት ማዕከል/International Growth Center በተባለ ድርጅት በተደረገ የወጣት ስራ አጥነት ሌላ የጥናት ዘገባ መሰረት “የአሁኑ የኢትዮጵያ የ5 ዓመት የልማት ዕቅድ ማለትም እ.ኤ.አ ከ2010/11–2014/15 ድረስ በሚዘልቀው ገዥው አካል የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ/Growth and Transformation Plan እያለ በሚጠራው ዕቅድ ውስጥ የወጣቶች የስራአጥነት ጉዳይ አልተካተተም…“ ያ ጥናት “እ.ኤ.አ በ2011 38 በመቶ የሚሆነው ወጣት መደበኛ ባልሆነው የስራ ዘርፍ ተቀጥሮ የሚገኝ“ ሲሆን “ዝቅተኛ ተከፋይነት ያላቸው እና የምርት ጥራታቸውም ዝቅተኛ የሆኑ“ እንደነበሩ የጥናቱ ግኝት አመላክቷል፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ስራ አጥ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን ስራአጥ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን   ወደፊትም ተቀጣሪ የመሆን ዕድል የላቸውም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ወጣቶች ከትምህርት አደረጃጀቱ እና አሰጣጡ አንጻር የጥራት ጉድለት የሚንጸባረቅበት በመሆኑ መሰረታዊ የሙያ ክህሎት ያልጨበጡ በመሆናቸው ነው፡፡ ወጣቶቹ በስራ ላይ ለመቀጠር የሚችሉት በሰለጠኑባቸው እና ክህሎት በጨበጡባቸው የሙያ ዘርፎች በመንግስት ስር ያሉ ቀጣሪ መስሪያ ቤቶች ተቀጣሪዎችን በብቃታቸው እና በተወዳዳሪነታቸው መዝነው ሳይሆን አብዛኛውን ጊዜ ከገዥው አካል ጋር ካላቸው የፖለቲካ እና የማህበራዊ ግንኙነት ቅርርብ አንጻር የፓርቲ አባል በመሆን ብቻ ነው፡፡ ማንኛውም ወጣት ኢትዮጵያዊ በትክክል የእራሱን ጥረት አድርጎ የዩኒቨርስቲ ዲግሪ ከመያዝ ይልቅ የገዥውን ፓርቲ የአባልነት ካርድ መያዝ የበለጠ ዋጋ እንዳለው ይገነዘባል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መሬት የሌላቸው የገጠር ወጣቶች ወደ ከተማ ስራ ፍለጋ በገፍ በሚመጡበት ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን ከገጠር ወደ ከተማ ፍልሰት፣ ስራ አጥነት እና ተስፋ የማጣት ቀውስ የበለጠ እያወሳሰበው ይገኛል፡፡

 

የኢትዮጵያ ወጣቶች አጠቃላይ የአገሪቱን የማህበራዊ ችግር ቀውሶች ቀንበር የመሸከም ኃላፊነት ወድቆባቸዋል፡፡ እንደሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ጎል/GOAL ዘገባ ከሆነ በመንገዶች ላይ በመንከላወስ የሚኖሩ 150,000 ህጻናት ሲኖሩ ከእዚህ ውስጥ 60,000 የሚሆኑት የአገሪቱ ዋና ማዕከል በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ናቸው፡፡ ህጻናት ቤትአልባ የሚሆኑባቸው እና ወደ መንገድ የሚወጡባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በአማካይ 10 እና 11 ዓመት ዕድሜ ሲያስቆጥሩ ነው፡፡ ወጣቶች በኤችአይቪ ኤድስ እና በሌሎች በግብረስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች የመጠቃት ዕድላቸው እየጨመረ በመምጣት ላይ ይገኛል፡፡ የተሻለ ዕድል ማግኘት ያልቻሉት በርካታዎቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች በአደንዛዥ ዕጽ እና አልኮል እንዲሁም በዘሙት አዳሪነት እና በሌሎች የወንጀል ድርጊቶች ተዘፍቀው ይገኛሉ፡፡ ምንም ዓይነት የትምህርት ዕድል እና ስራ ያላገኙ የከተማ ወጣቶች ዕጣፈንታቸው ስራየለሽ፣ ቤትየለሽ፣ እረዳትየለሽ እና ተስፋየለሽ መሆን ብቻ ሆኗል፡፡

 

ከአስርት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል “የብሄራዊ ወጣቶች ፖሊሲ” ሰነድ አዘጋጀ እና “44 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ከፍጹም የድህነት ወለል በታች ነው“ በማለት መግለጫ ሰጠ፡፡ በዚህ ዓይነት የድህነት ሁኔታ ውስጥ ወጣቱ በከፍተኛ ሁኔታ ለጥቃቱ ተጋላጭ የሆነ የህብረተሰብ ክፍል ነው… ከስራ አጥ ወጣቱ አብዛኛውን የሚሸፍኑት ሴት ወጣቶች የመሆናቸው ሀቅ በአብዛኛው በሚባል መልኩ የችግሩ ሰለባ ወጣት ሴቶች መሆናቸውን ያመላክታል፡፡” በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ “የብሄራዊ ወጣቶች ፖሊሲ” ተብሎ የሚጠራው የድርጊት መርሀግብር ለገዥው አካል እና ለፓርቲው ደጋፊነት መመልመያ ሰነድነት ከማገልገል በዘለለ የፈየደው ነገር የለም፡፡ የዚህን ፖሊሲ የማስፈጸም ብቃት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ “መንግስት የመምራት፣ የማስተባበር፣ የማዋሀድ እና የመገንባት ኃላፊነት ተጥሎበታል” በማለት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ ሆኖም ግን የዓለም አቀፉ የዕድገት ማዕከል የጥናት ውጤት በግልጽ እንደሚያመለክተው ከ2010/11-2014/15 ድረስ ለአምስት ዓመታት በሚዘልቀው የአሁኑ የኢትዮጵያ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ቀጥታ የወጣቱን የስራ አጥነት የሚመለከት ጉዳይ አልተካተተም፡፡ “ብሄራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ሰነድ” በተግባር ላይ ያልዋሉ የብሄራዊ ወጣት ፖሊሲዎች ዓለም ዓቀፋዊ የመረጃ ቋት በመሆን ላለፉት አስርት ዓመታት በመደርደሪያ ላይ ተቀምጦ አቧራ በመጠጣት ላይ ይገኛል፡፡

 

የሁለት ትውልዶች ትረካ፣ በኢትዮጵያ የጉማሬው እና የአቦሸማኔው ትውልዶች ተቀራርቦ የመነጋገር አስፈላጊነት፣

 

አሁን በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር መሰረት ስንት ሰዓት ነው? በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የአቦ-ገማሬው ትውልድ ሰዓት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአቦሸማኔው እና የጉማሬው ትውልዶች ተቀራርበው ለመነጋገር እና ብሄራዊ ዕርቅ ለማውረድ ጥረት የሚያደርጉበት የመጨረሻው ሰዓት ነው፡፡ ጊዜው የኢትዮጵያ እረፍትየለሾቹ የአቦሸማኔው ትውልዶች እና ተራማጁ፣ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው እና አርቆ አሳቢነት የተላበሱት የጉማሬው ትውልዶች በአንድ መድረክ በአንድነት ተቀራርበው የሚያስቡበት እና በአንድነት ወሳኝ እርምጃ የሚወስዱበት ጊዜ ነው፡፡ አሁን ጊዜው 2014 ነው፡፡

 

ተቀራርቦ መነጋገር ስል በአቦሸማኔው እና በጉማሬው ትውልድ መካከል በግልጽ እና ግልጽ ባልሆኑ መድረኮች ሁሉ… ማለትም ከእራት ግብዣ አዳራሾች እስከ አካዳሚክ የጥናት ማዕከሎች፣ ከቤተክርስቲያኖች እና መስጊዶች እስከ ሲቪክ ድርጅቶች እና ማህበራት ድረስ የሚያካትት የንግግር እና የውይይት መድረኮችን ማለቴ ነው፡፡ የመነጋገሪያ አጀንዳዎቹ ያልተወሰኑ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን ዓላማዎች አንድ ዓይነት ናቸው፡፡ በአሮጌዎቹ ሀሳቦች ላይ ጥያቄዎችን ለማንሳት እና ጥሩዎችን ለማካተት አስፈላጊ ያልሆኑትን ደግሞ ለማስወገድ የንግግር መድረኮች ሊኖሩን ይገባል፡፡ አሮጌዎችን፣ ጠባብ አስተሳሰቦችን እና ለሰላም እና እድገት እንቅፋት የሚሆኑ አሉታዊ እንቅስቃሴዎችን ለመለወጥ የንግግር መድረኮች አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ስለፖለቲካ፣ መንግስት እና ህዝብ አዳዲስ ሀሳቦችን ለማመንጨት የንግግር መድረኮች አስፈፈላጊዎቻችን ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቀፍድደው ከያዙን የማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች በድል አድራጊነት ለመውጣት የንግግር መድረኮችን በማመቻቸት ገንቢ እና አዳዲስ የመፍተሄ ሀሳቦችን በማመንጨት የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ ላለመስማማትም ቢሆን በሰለጠነ እና በመከባበር ላይ በተመሰረተ አቀራረብ የንግግር መድረኮችን በማዘጋጀት ስምምነት ማድረግ ይቻላል፡፡ ስህተቶችን በማረም ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመምጣት እንዲቻል ተቀራርቦ መወያየት አስፈላጊ እንደሆነ እርስ በእራሳችን መተማመን አለብን፡፡ ይህንን ከባድ ኃላፊነት ለመሸከም እና ለማስተባበር የሚችለው “አዲሱ ትውልድ” ያስፈልገናል፡፡ ሀሳበ ሰፊዎቹ የአቦሸማኔው እና ተራማጅ የጉማሬው ትውልዶች የውይይቱን ሂደት ሊያፍጥኑልን ይችላሉ፡፡

 

የውይይቱ ዓላማ ያልሆነው የቱ ነው? እንዲካሄድ የሚፈለገው ውይይት አንዱ ሌላውን ጥላሸት ለመቀባት፣ ለመካሰስ እና አንዱ በሌላው ላይ ጣቶቹን ለመቀሰር አይደለም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ቀደም ሲል በተከናወኑ እና ባልተከናወኑ ድርጊቶች ላይ የሆድ ቁርጠት፣ የልብ ስብራት፣ ወይም ጥርስ መንከስ ድርጊቶችን ለማበረታታት አይደለም፡፡ የአቦ-ጉማሬው ትውልድ ኃላፊነት የያዘባቸው የንግግር መድረኮች ሁለት ዓላማዎችን ያካተቱ ናቸው፡፡ እነሱም 1ኛ) ዓለም አቀፋዊ ዕርቅ በማውረድ የንግግር ስራውን መጀመር እና 2ኛ) በአቦሸማኔው እና በጉማሬው ትውልዶች መካከል ባለው የስራ ክፍፍል እና ሚና መግባባት ላይ መድረስ ናቸው፡፡

 

“የቋንቋ” መግባባት ችግር ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፋዊ መግባባት ሊኖር አይችልም፡፡ በጸጥታ በሚናገሩት የኢትዮጵያ የጉማሬው ትውልድ አባላት እና በዚያ በማይሰማው ንግግር ከኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ ጋር የመግባባት ችግር አለ የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ ጥቂት ምሳሌዎችን እስቲ እንመልከት፡፡ ብዙዎቻችን የጉማሬው ትውልድ አባላት ስለለውጥ ስናነሳ የሚታየን ነገር በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኘውን ገዥ አካል ከስልጣን መንበር ላይ በማስወገድ እራሳችንን ከስልጣን ወንበር ላይ ፊጥ ማድረግ ነው፡፡ በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች መጥፎዎች ናቸው፣ እኛ ግን ጥሩዎች ነን፡፡ አይደለም እኛ የተሻልን ነን፣ በእርግጥም እኛ እጅግ የተሻልን ነን፡፡ በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ላይ ያሉት የጉማሬው ትውልድ አባላት እራሳቸውን ብቸኛ የለውጥ ሀዋርያ አድርገው ያስባሉ፡፡ እኛ የጉማሬው (የቀድሞው) ትውልድ አባላት ስለአመራር ጉዳይ ስናነሳ የአዲሱ ትውልድ አባላት የእኛን ትዕዛዞች ብቻ እንዲከተሉ እንፈልጋለን፣ ምክንያቱም እኛ ኃይል፣ ልምድ፣ ዘዴዎች እና/ወይም እውቀት ያለን አድርገን እንቆጥራለን፡፡ የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ የበግ መንጋ ሆነው እኛን የሚከተሉ ብቻ እንጅ እነርሱ መልካም ነገሮችን በውል የሚያጤኑ እና ወሳኝ ድርጊቶችን ሊፈጽሙ የሚችሉ ልዩ ችሎታ እና የአመራር ብቃት ያላቸው ወጣቾች እንዳሉ ለመቀበል በጣም እንቸገራለን፡፡ ወጣቶቹ ከእኛ በተለየ መልኩ የእራሳቸው ልዩ የሆነ እና የእራሳቸው ነጻነት እንዲኖራቸው እንፈልግም፡፡ በአጠቃላይ ወጣቱን አሳንሶ የማየት ባህል ተጠናውቶናል፡፡ ወጣቱ ኃይል ዝቅ ያለ ዳኝነት የመስጠት ወይም ነገሮችን በጥልቀት የመረዳት ችሎታ ስለሚያንሰው የእኛን የበግ ጠባቂነት ሚና ማግኘት እና እኛ የምንነግራቸውን ብቻ መከተል አለባቸው እያልን አስተያየት እንሰጣለን፡፡ “ልጆችመታየት አንጂ መደመጥ የለባቸውም”፣የሚሉ ጊዜ ባለፈባቸው የአረጁ እና የአፈጁ አባባሎች ወጣቶቹን ዝቅ አድርገን እንመለከታለን፣ እንዲህ እያልንም እንተርትባቸዋለን፣ “ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም“፡፡ የወጣቶቹን ሀሳቦች አናከብርም፣ ወይም ደግሞ ለየት ያለ ነገር ሲያቀርቡ እና የተሻሉ ነገሮችን ሲሰሩ እየተመለከትን አድናቆት አንቸራቸውም፣ ነገር ግን እነሱን ለመተቸት እና ለማውገዝ የሚቀድመን የለም፡፡

 

እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት ስለስልጣን ስንነጋገር ምንም ዓይነት ተጠያቂነት እና  ግልጽነት በሌለው መልኩ ስልጣንን እንድንይዝ እንገልጋለን፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው የጉማሬ ትውልድ ስልጣኑን የሚጠቀምበት ለመከፋፈል እና ለመግዛት ነው፣ ስልጣናቸውን በስልጣን ላይ ለመቆየት ከህግ አግባብ ውጭ ይጠቀሙበታል፣ ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ ምክንያቱም ማድረግ ይችላሉና፡፡ ከስልጣን ውጭ ያሉ የጉማሬው ትውልድ አባላት ስልጣን ማግኘትን ይፈልጋሉ ምክንያቱም የላቸውምና፣ ምክንያቱም ስልጣን በእራሱ ሁሉንም ነገር ነውና፡፡ የጉማሬው ትውልድ አባላት ስልጣን ያጡትን ወይም ስልጣን የሌላቸውን  ስልጣን እንዲያገኙ አያደርጉም፡፡ በኢትዮጵያ ያሉት ወጣቶች ምንም ዓይነት ስልጣን የሌላቸው እና ስልጣን አልባ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡ ይህም ማለት 70 በመቶ (66 ሚሊዮን) ያህሉን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚይዘው የህብረተሰብ ክፍል ስልጣን የለውም፡፡

 

የኢትዮጵያ የአቦሸማሜው ትውልድ በአቦ-ጉማሬው ትውልድ ላይ እምነት አጥቷል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ ያ እምነት ወደ መተማመን ሊመለስ የሚችለው በጋራ በመከባበር እና በመግባባት እንዲሁም በመተማመን እና በመቀራረብ ብቻ ነው፡፡ ወጣቶቹ ከእኛ ጋር እኩል እንደሆኑ እና እነሱን በአግባቡ በማስተናገድ መተማመን እና እርቀሰላምን ማውረድ ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ለሀገራቸው ያሏቸው ሀሳቦች እና  ራዕዮች ጠቀሜታቸው ከእኛ ሀሳቦች እና ራዕዮች ያላነሱ መሆናቸውን ሙሉ በሙሉ መቀበል አለብን፡፡ ከወጣቶቹ ጋር በእኩልነት በመከባበር እና ተቀራርቦ በመወያየት የጋራ ችግሮቻችንን መፍታት አለብን፡፡

 

የጉማሬዎቹ አስተምህሮ ለአቦሸማኔው ትውልድ፣

 

የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት ከእኛ ከጉማሬው ትውልድ አባላት ጋር ተቀራርበው መነጋገር ለእነሱ በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ነው ፡፡ ምሳሌ በማቅረብ የጉማሬው ትውልድ ትምህርት ማስተማር ይችላሉ፡፡ ከታላላቆቻቸው ስህተቶች ሊማሩ የማይችሉ ወጣቶች ተመሳሳዮቹን ስህተቶች ይደግማሉ፡፡ እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት ብዙ ስህተቶችን ሰርተናል፡፡ ሁለተኛው ትምህርት የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት የጉማሬውን ትውልድ አባላት ድክመቶች ማሸነፍ እና የእራሳቸውን አዲስ ጅምሮች መተግበር ነው፡፡ የጉማሬው ትውልድ ለአቦሸማኔው ትውልድ ሊያስተምሯቸው የሚችሏቸው ነገሮች የድፍረት ወኔን፣ መተማመንን፣ ለበጎ ነገር መስዕዋትነት መክፈልን፣ ታማኝነትን፣ መንፈሰ ጠንካራነትን፣ ችግሮችን በጽናት የመቋቋም ችሎታ የማዳበርን፣ ለውሳኔ ተገዥነትን፣ እና ችግሮችን በድል አድራጊነት እንዴት መውጣት እንደሚቻል ማስተማር ከብዙዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ “ክብር እና ሞገስ አጥተን” በታላቅ ችግር ላይ ነን፡፡ እነዚህን ክብር እና ሞገሶች ለመመለስ ግን በጋራ ሆነን መሞከር እና ለመተግበር መሞከር ነው፡፡ የአቦሸማኔ ትውልዶችን ከግትርነት፣ ከቁጣ፣ ከጥርጣሬ፣ ከታጋሽየለሽነት፣ ከሙስና፣ ካለመቻቻል፣ ስልጡን ያልሆነ አካሄድን ካለመከተል፣ ከፍርሀት፣ መጥፎ ነገር ከማድረግ፣ ከበቀልተኝነት እና እራስን ከማድነቅ በማለት በእርግጠኘነት የአቦሸማኔውን ትውልድ ለማስተማር ይቻላል፡፡ የአቦሸማኔውን ትውልድ ግልጽ የሆኑ ውይይቶችን በማድረግ በግል እና በህዝብ ህይወት ላይ የተጠያቂነት እና ግልጽኘነት የማስተማር ዘዴን በማሳየት የአቦሸማኔውን ትውልድ ማገዝ እንችላለን፡፡

 

የአቦሸማኔው አስተምህሮ ለጉማሬው ትውልድ፣

 

የአቦሸማኔው ትውልድ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ችግሮችን በሰላማዊ እና ኃይልን ባልተጠቀመ መልኩ ሰላማዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ ወጣቶቹ የሚማሩት እና የሚሰለጥኑት የጦር ተዋጊዎች እንዲሆኑ ብቻ ለማድረግ ብቻ አይደለም ነገር ግን የሰላም ጠበቃዎች እንዲሆኑ ጭምር እንጅ፡፡ ወጣቶቹ ጤናማ የህብረተሰብ ግንኙነቶችን የመፍጠር እና የጎሳ፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነትን እና የዘር ጥላቻን የማስወገድ ችሎታ አላቸው፡፡ ወጣቶቹ የህብረተሰብ ትብብሮችን፣ ፍቅርን፣ መግባባትን፣ ሰላምን፣ አንድነትን እና ተስፋን የሚፈጥሩ አስፈላጊ ጉዳዮች ሁሉ ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ ሁላችንም በሰላም፣ በእኩልነት እና ፍትህ በነገሰበት መልኩ የምንኖርባት “አዲሲቷን ኢትዮጵያ” ለመገንባት የሚያስችል ችሎታ እንዳላቸው ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ የአቦሸማኔው ትውልድ አባላት ከተፈቀደላቸው እና በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እውነተኛ ተባባሪ እና አጋር እንዲሆኑ ከተደረጉ ለውጥን የሚያመጡ የለውጥ ዘዋሪነት ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ መሆናቸውን ለጉማሬው ትውልድ ማስተማር ይችላሉ፡፡ ወጣቶቹን በጥሞና የምናዳምጣቸው ከሆነ እራሳችንን ከእራሳችን እንድንጠብቅ ሊያደርጉን ይችላሉ፡፡ ይኸንን ጉዳይ እናስብ! ወጣቶቹ ከጎሳ እስር ቤቶች ግድግዳዎች ሰብረን እንድንወጣ፣ ከምናባዊ ፍርሀቶች እንድንላቀቅ እና የሌሎቸን ሀሳቦች ያለመቀበል እና መጥፎ ሀሳቦች ዓይናችንን እንዳያይ ሸፍነው “አዲሲቷን ኢትዮጵያ” ከአድማሱ ባሻገር እንዳናይ አድርገውን የነበሩትን እንድናስወግድ ሊረዱን ይችላሉ፡፡

 

ኢትዮጵያውያን እንደ አገር እና እንደ ህዝብ ህልውናቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ከተፈለገ ያ ህልውና የሚወሰነው በፈጣሪነት፣ በአዕምሯዊ ሃይል እና ጥንካሬ፣ መንፈሰ ጽናት፣ መልካም አመለካከት እና  በወጣቶቹ መንፈሰ ጠንካራነት እና በሚከፍሉት መስዋዕትነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ያ ሁኔታ በወጣቶች ላይ ከባድ ሸክምን ይጥላል፡፡ ወጣቶቹ ያንን ከባድ ሸክም፣ ከባድ ስራ እና ታላቅ መስዋዕትነት በመክፈል የአንበሳውን ድርሻ መያዝ አለባቸው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያውያን እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ህልውናቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ከተፈለገ ያ የመቆየት ህልውና የሚወሰነው የቀድሞው ትውልድ አባላት ለአዲሱ ትውልድ አባላት ቀልጣፋ እና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ማድረግ ስንችል ነው፡፡ እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት የምንችለውን ነገር ሁሉ በማድረግ የአቦሸማኔዎቹ (ወጣት) ትውልድ እምነት እንዳያጡ እና ውድቀት እንዳይደርስባቸው ተጋድሎ ማደረግ ይጠበቅብናል፡፡ ወጣቶቹ ይህንን ሲያደርጉ ማበረታታት፣ ማገዝ እና ደጋግመው እንዲሰሩት ድጋፍ መስጠት ይኖርብናል፡፡ ትግሉ የፈለገውን ያህል ረዥም ጊዜ ቢወስድም ምንጊዜም ቢሆን ከወጣቶቹ ጎን መሰለፍ አለብን፡፡ ከወጣቶቹ ጋር መወያየት እና መነጋገር አለብን፡፡ ወጣቶቹን መደገፍ እና መውደድ ይኖርብናል፣ ወጣቶቹ በአዲሲቱ ኢትዮጵያ የፕሮጀክት የግንባታ መስክ ላይ ሆነው በጽናት እየሰሩ አስከቆዩ ድረስ ለእነሱ ውኃ ማቀበል እና ሌሎችንም ድጋፎች በደስታ በማድረግ መደገፍ ይኖርብናል፡፡

 

የኢትዮጵያ ወጣት ኃይል ምንም ማንም ሊያቆመው የማይችል ኃይል ነው፡፡ የኢትዮጵያን ተወርዋሪ የአቦሸማኔ ትውልድ ሊያቆመው የሚችል ምድራዊ ኃይል፣ እስካፍንጫው የታጠቀ አምባገነን ኃይል ሊያሸንፈው የሚችል ኃይል የለም፡፡ እኛ የቀድሞው ትውልድ አባላት ምንጊዜም ቢሆን የሚከተለውን የድሮ አባባል ልንከተል ይገባል፣ “ልታሸንፋቸው አለመቻልህን ካረጋገጥህ ተቀላቀላቸው፡፡“ የአቦሸማኔውን (የወጣቱን) ትውልድ በውይይት እንቀላቀል፡፡ ከእነርሱ ጋር ቀረብ በማለት እንወያይ፣ ምን ፍላጎት እንዳላቸውም እንጠይቃቸው፡፡ የእኛን ምክር የሚወዱ እና የሚፈልጉ ከሆነ ይህንን በለጋሽነት እና በነጸነት እንችራቸው፡፡ የእኛን ቴክኒካዊ እገዛ የሚፈልጉ ከሆነ ዕገዛውን እናድርግላቸው፡፡ የሞራል ድጋፋችንን የሚፈልጉ ከሆነ ለእነሱ እናደርግላቸው፡፡ የማቴሪያል ድጋፍ የሚፈልጉ ከሆነ ለእነርሱ የገንዘብ መዋጮ በማሰባሰብ ድጋፍ እናድርግ፡፡ ወጣቶቹ ታላቅ ሸክሞችን ከጫንቃቸው ላይ ለማውረድ፣ ድልድይ በሚገነቡበት ጊዜ፣ የመንገድ ጥገና በሚያካሄዱበት ጊዜ እና ተራሮችን በሚወጡበት ጊዜ በትህትና የተሞላን ውኃ አቀባያቸው ሆነን መቅረብ አለብን፡፡ ለወጣቶቻችን የኃይል ምንጮች መሆን አለብን!

 

(ክፍል ሁለት ይቀጥላል፡፡)

 

ታህሳስ 29 ቀን 2006 .

 

 

ጠቅላይ ምኒስትራችን ለደቡብ ሱዳን የተመኙትን ለኢትየጵያም ቢያደርጉት

$
0
0

ከታምራት ታረቀኝ

ደቡብ ሱዳን ግጭቱ ተባብሷል፣እልቂቱ ከፍቷል፣የተፈናቃዩ ቁጥር ጨምሯል፣ድርድሩ አልሰምር ብሏል፣ ጠቅላይ ሚኒስትራችንና ውጪ ጉዳይ ምኒስትራቸን ሥራ በዝቶባቸዋል፡፡
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ምክትላቸውን ከሥልጣን ማባረረረራቸውን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ግጭት እንበለው ጦርነት አንድም ኢትዮጵያ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በመሆኗ፣ሁለትም ወሰን ተጋሪ ቅርብ ጎረቤት ሀገር በመሆኗ ሶስትም ተመሳሳይ ጎሳዎች እዚህም እዛም ያሉ በመሆኑ አራትም አዲሲቷ በነዳጅ የከበረች ሀገር ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የሥራ ቦታ በመሆኗ ወዘተ ምክንያቶች የተቀሰቀሰው ግጭት ኢትዮጵያን በጣሙን ያሳስባታል፡፡ ይህም በመሆኑ ነው ሁለቱ ምኒስትሮች ፋታ ማጣታቸው፡፡
sudan south north sodan
ነገሩ ወደ ጎሳ ግጭት እንዳያመራ ያሰጋል፣

ውጪ ጉዳይ ምኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም 2006 ከጅምሩ ሥራ አብዝቶባቸዋል፡፡ሰውዲ አረቢያ ከሀገሬ ውጡ በማለት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈጸመችባቸው ኢትዮጵያዉያንን ጉዳይ ከጅምሩ ተገቢ ትኩረት ባይሰጠውም የዓለም የመገናኛ ብዙኋን በማስተጋባታቸውና ተቀዋሚዎችም በሀገር ወስጥም በተለያዩ ሀገራም ሰላማዊ ሰለፍ በመውታት ጭምር ሰወዲን በኢሰብአዊ ድርጊ ቷ እኛን መነንግስት ደግሞ በቸልተኝነቱ በማውገዛቸው መንገሥት በእቅድ ሳይሆን በግብታዊነት የገባበት ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ላይ ዋንኛ ባለድርሻ ሆነው የታዩት ዶ/ር ቴዎድሮስ ናቸው፡፡ስራው ደንገቴ ከመሆኑ በላይ የተመላሾቹ ቁጥር ከተገመተው አይደል ሊታሰብ ከሚችለው በላይ መሆኑ ደግሞ ሌላው ራስ ምታት ነበር፡፡

ይህ ሳይጠናቀቅና መልክ ሳይዝ በጎረቤት ደቡብ ሱዳን የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የመንግሥት ያለህ፣ከዕልቂት አድኑን፣ከጦርነት እሳት አውጡን የሚል የዜጎች ጩኸት በመሰማቱ በእንቅር ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኗል፡፡
በዚህ ውጥረት ወስጥ የሚገኙት ዶ/ር ቴዎድሮስ የደቡብ ሱዳን ግጭት ተባብሶ እልቂት ከመንገሱ በፊት ለግጭቱ ምክንያት የሆኑትን ፕሬዝዳንቱንና ም/ል ፕሬዝዳንቱን ወደ ድርድር ለማምጣት ከአዲስ አበባ ጁባ ተመላልሰዋል፡፡ነገሩ ተባብሶ ወደ ጎሳ ግጭት እንዳያመራ ያላቸውን ስጋትም ገልጸዋል፡፡
በጎሳ ላይ በተመሰረተ የሥልጣን ክፍፍል ከያዙት ሥልጣን አንዱ አባራሪ ሌላው ተባራሪ ሲሆን ጉዳዩ የሁለቱ ሰዎች ብቻ ሆኖ ሊቆም፣ በፖለቲካ መንገድ ብቻ ሊስተናገድ አይቻለውምና ወደ ጎሳ ግጭት ማምራት አይደለም ሲጀመርም በዛው መልክ ነው የሚነሳው፡፡ ሹመታቸው በጎሳቸው እንደመሆኑ ጸባቸውም ጎሳዊ ነው የሚሆነው፡፡ ስለሆነም አስፈሪው የጎሳ ግጭት መቼም የትምና በማንም እንዳይነሳ ዋናው መፍትሄ ከመነሻው ፖለቲካው በጎሰኝነት ዜማ የሚዘፈንበት እንዳይሆን ማድረግና የሥልጣን ክፍፍሉ ጎሳን መሰረት አድርጎ ታማኝ ከሆነ ዘበኛም ቢሆን ምኒስትር አድርገን እንሾማለን እየተባለ የሚፈጸም ሳይሆን በእውቀትና በብቃት ብሎም በሕዝብ መራጭነት ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡

ውጪ ጉዳይ ምኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ ደቡብ ሱዳን ተገኝተው የተመለከቱት ከአቻዎቻቸው ፖለቲከኞች ጋር ሲነጋገሩ የተገነዘቡት አሳስቧቸው ወደ ጎሳ ግጭት እንዳይሸጋገር መስጋታቸውና ይህንኑ በአደባባይ በይፋ መግለጻቸው ተክክል ቢሆንም እውነቱ የተከሰተላቸው በሰው ቤት ያውም ግጭት ተቀስቅሶ ደም ከፈሰሰ በኋላ መሆኑ ነው አጠያያቂው፡፡

እኛ ቤት፣ ከኢትዮጵያዊነት ጎሰኝነት ቀድሞ መጀመሪያ በየጎሳችሁ ተበታትናችሁ ከዛ በኋላ ኢትዮጵያን በመፈቃቀድ እንመሰርተንለን የሚል ቅዠት ተፈጥሮ፣ እንትንነቴን(ጎሳውን) የማታረጋግት ኢትዮጵያ ትበታትን እየተባለ ተፎክሮ በአንድ ሰሞን የፖለቲካ ስካር ወገን በወገኑ ላይ ጦር እንዲመዝ መደረጉ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ አንደ እየምነቱ ለፈጣሪው የሚገዛ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ የቀጠለ ጨዋነት የባህሪው መሆኑ እንጂ አንደ ፖለቲከኞቹ ፍላጎት ቢሆን ኢትዮጵያ በዛሬ መልኳ መታየት ባልቻለች ነበር፡፡
ኢትዮጵያዊነትን ማንም በምንም መንገድ ሊያጠፋው አይችልም፡፡ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም በ1986 ዓም ኢትዮጵያ ከየት ወዴት በሚል ርእስ በጻፉት መጽሀፍ ገጽ 32 ላይ «የኢትዮጵያ ታሪክ ሊያስተምረን እንደሚችለው ኢትዮጵያዊነት አንደ ላስቲክ ነው ሲስቡት ይሳባል፣ሲለቁት ይሰበሰባል ፣ ማለት ይሳብና ይሳሳል እንጂ አይበጠስም» ይላሉ፡፡ የጎሳ ፖለቲካ አቀንቃኞቹ ካልተሳካው ተግባራቸው ይህን መረዳታቸው ባያጠራጥርም አልሆንልህ አለኝ አጉራህ ጠናኝ ብለው ወደ ትክክለኛው መስመር መመለስን ሽንፈት አልያም ውርድደት ሆኖባቸው እንደ አጀማመራቸው ባይሆንም ዛሬም ጎሰኛነትን ከማቀንቀን አልተመለሱም፡፡

ለሥልጣን መሰረቱ ለሹመት መስፈርቱ የጎሳ ድልድል ሆኖ ማስፈጸሚው ደግሞ በስም ለኢህአዴግ በተግባር ለህውኃት ብሎም ለወሳኞቹ ባለሥልጣኖች ታማኝ ሆኖ መገኘት ሀኖ ያሟላሉ ተብሎ ታምኖባቸው የተሾሙ ወደ ህሊናቸው ሲመለሱ፣ ወይ ታማኝነታቸውን ሲያጓድሉ፣ አልያም እንደታሰቡት ሆነው ሳይገኙ ሲቀሩ በሙስና ወይንም በመተካካት ሰበብ ለእስር ሲዳረጉ ወይንም ሲገለሉ፣አለያም ከሥልጣን ዝቅ ሲደረጉ ድርጅታቸውም ሆነ ጎሳቸው ድምጽ አለማሰማታቸው የእርምጃውን ትክክለኛነት የጎሳ ሥልጣን ክፍፍሉን ጤናማነት የሚያረጋግጥ ተደርጎ ታስቦ ከሆነ ስህተት ነው፡፡
ድርጅቶቹ (ፓርቲዎቹ) ምንም አለማለታቸው አፈጣጠራቸውም ሆነ እድገታቸው ለዚህ የሚያበቃ ነጻነት የሌለቸው በመሆኑ ሲሆን ( የሁሉም ፈጣሪ ህውኃት ስለመሆኑ ፈጣሪውም ተፈጣሪውም በኩራት የሚናገሩት ነው) የጎሳቸው ዝምታ ደግሞ መጀመሪያም ውክልናቸውን አለመቀበሉ ሁለተኛም የሾማቸው አነሳቸው በሚል አይመለከተኝም ስሜት እንደሚሆን ይገመታል፡፡

ፕ/ር መድሀኔ ታደሰ በ1996 ዓም ከአንድ በሀገር ውስጥ ይታተም ከነበረ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ «ብሔረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር አለባቸው ስትል በርግጠኝነት ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር አለባቸው፤አሁን በክልል ይሄ ነው ችግሩ፡፡ ከዚህ በላይ ግን ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን ማስተዳደር ያልቻሉ ክልሎች ክልላቸውን እንኳን ቢያስተዳድሩ በቂ አይደለም፡በማዕከላዊ መንግሥት ጭምር በውሳኔ ሰጭነት ጭምር መሳተፍ ነበረባቸው፡፡ይህ በሌላበት ሁኔታ የብሔር ጭቆናን መሰረት ያደረገ ሥርዓት መሥርተህ ልትተገብረው ካልቻልክ ጭቆናውን በማባባስ የበለጠ ግጭት እንዲፈጠር ነው የሚያደርገው» በማለት የታሰበው በሚነገርለት ደረጃ እንኳን ተፈጻሚ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአስተዳደር ክልልን በጎሳ የሹመት ድልድልን በጎሳ፣የፖለቲካውን ቅኝት በጎሳ፣ ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን በጎሳ፣ ወዘተ መቃኘቱ የመጀመሪያው ችግር ሆኖ ይህንኑ በሚነገርለትና በህግ በተጻፈው አግባብ ተግባራዊ አለማድረግ ሁለተኛው ችግር ነው፡፡ በየቦታው በፖለቲካ ፓርቲ መሪነትም ሆነ በክልል አስተዳዳሪነት የሚቀመጡ ሰዎች አመኔታ የሚያጡት ብዙ የሚባልለትን እኩልነት በተጨባጭ ተግባራዊ ለማድረግ በአለመቻላቸውና እንወክለዋለን ከሚሉት ህብረተሰብ ይልቅ ታማኝነታቸውም አገልጋይነታቸውም ላስቀመጣቸው ሀይል መሆኑ ነው፡፡
ነብሳቸውን ይማረውና አቶ መለስ ሳይታሰብ በድንገት በሞት ሲለዩን አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ወደ ጎን ሊገፉ የማይቻልበት ቦታ ላይ በመገኘታቸው ምክንያት ሙሉው ሥልጣን ባይኖራቸውም የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ሲይዙ በህውኃት ሰፈር አሰረክባችሁ መጣችሁ በሚል ጥያቄ መነሳቱን ውስጥ አዋቂዎች በተለያዩ የመረጃ ማስተላለፊያ መንገዶች ገልጸውታል፡፡ በአቶ መለስ የሁለት አሥርት አመታት የሥልጣን ዘመን ያልነበረ የሶስት ምክትል ጠቅላይ ምኒስትሮች ሥልጣን የተፈጠረውም ይህንኑ የህውኃትን ጥያቄ ተከትሎ እንደሆነ ነው የተነገረ የተጻፈው፡፡
ሌሎቹ ድርጅቶች ነጻነታቸውን አረጋገጥው በየራሳቸው እግር መቆም ከቻሉ ተመሳሳይ ጥያቄ ሊያነሱ እንደሚችሉ አያጠያይቅም፡፡ ጥያቄውም ከፖለቲካዊነቱ ጎሰኛነቱ ስለሚያመዝን ለምላሽ ያስቸግራል፣ ውጪ ጉዳይ ምኒስትራችን በደቡብ ሱዳን እንዳይፈጠር ወደ ሰጉት የጎሳ ግጭትም ሊያመራ ይችላል፡፡ ዮሀንስ ገብረማሪያም የተባሉ ጸሀፊ በ1987 ዓም በጦቢያ መጽሔት ጎሰኞችና ጎሰኝነት ያሳፍራሉ ያስፈራሉ በማለት ባሰፈሩት ጽሁፍ «ጎሰኝነት ብዙውን ግዜ ሌሎች ጎሳዎች አደረሱብን የሚሉትን ይም ደርሶብናል ብለው የገመቱትን ጥቃት ለመመከት ወይም ደግሞ ሆን ብሎ ሌሎችን ለማጥቃት የሚውል የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ ነው፡» ብለዋል፡፡ ጎሰኝነትን በሚያቀነቅኑ ወገኖቸ የሚካሄድ ቅስቀሳን አደገኛነትም ሲገልጹ «ይህ ቅስቀሳ አውቆ አበዶችን ብቻ ሳይሆን መሰሪነቱን ያልተረዱ ብዙ የዋህ ተከታዮችን ሊያስገኝና ሊያሳስትም ይችላል» ይላሉ፡፡
ዛሬ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ገመድ ተሸብበው ፣በማሌ አደረጃጀት ተቆላልፈው፣ በአንድ ለአምስት ተጠርነፈው ህውሀት በቀደደላቸው ቦይ ቢፈሱም አንድ ቀን ግድቡን ጥሶ አልያም መስመሩን ለውጦ ሊፈስ እንደሚችል ያን ግዜ ደግሞ ለቁጥጥርም ለድርድርም እንደሚያዳግትና ከፍተኛ ጥፋት ሊያደርስ እንደሚችል ሌላው ቢቀር በደቡብ ሱዳን ከሚታየው መገንዘብ ይቻላል፡፡ ስለሆነም መሪዎቻችን የደቡብ ሱዳንን ችግር ለመፍታት እየሸመገሉ ከሂደቱ ለራሳቸውም ቢማሩ መልካም ነው፡፡ አስተዋይ ከጎረቤቱ ይማራልና፡፡
የተዳፈነው እሳት ተግለጦ ከተቀጣጠለ፣በድርጅታዊ ቅርጫት ያስገቡት አፈትልኮ ከወጣ ማጣፊያው እንደሚያጥር፣ ነገሩ እንደሚከርና መዘዙ ብዙ ነገር እንደሚመዝ የደቡብ ሱዳኑ ጉዳይ ቅርብና ግልጽ ማሳያ ነውና አንማርበት፡፡
ስለሆነም ዛሬ የጎሳ ፖለቲካ ደቡብ ሱዳን ላይ ስጋት መሆኑ የታያቸው ውጪ ጉዳይ ምኒስትራችን አንድ ቀን እኛም ቤት አደጋ ሊሆን እንደሚችል በማጤን ፖለቲካችንን ከጎሳ ሰገነት ላይ ለማውረድ ቢሰሩ ለርሳቸው ክብር ለሀገርና ለሕዝብም ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ማስገኘት ቻሉ ማለት ነበር፡፡

ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድርደር፣

ጠቅላይ ምኒስትራችን የወቅቱ የአፍረካ ህብረት ሊቀመንበር፣የቅርብ ጎረቤት ሀገር መሪ ወዘተ አንደመሆናቸው በደቡበ ሱዳን ግጭት አንደተቀሰቀሰ ፈጥነው ወደ ከቦታው በመድረስ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በተነጋገሩበት ወቅት መፍትሄው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድርድር መጀመር እንደሆነ መናገራቸውን ከዜና ማሰራጫዎች ሰምተናል፡፡ ሀሳቡ የቀረበው ጥይት ከተተኮሰ ደም ከፈሰሰና አቅም ከተፈተሸ በኋላ በመሆኑ ያለቅድመ ሁኔታ የሚለው የተወሰኑ የሀገሪቱን ቦታዎች በመቆጣጠር አቅሙን በፈተሸው አማጺ በኩል ተቀባይነት አላገኘም፡፡ እንደውም ያቀረባቸው ቅድመ ሁኔታዎች በመንግስት በኩል በጎ ምላሽ ሊያገኙ ባለመቻላቸው ከሁለቱም ወገን ተደራዳሪዎችን አዲስ አበባ ማምጣት ቢቻልም ይህ ጥሁፍ ወደ ዝግጅት ክፍሉ እስከተላከበት ቀን ድረስ በግንባር ማገናኘት አልተቻለም፡፡

ጠቅላይ ማኒስትራችን ከዚህ ሂደት ሁለት ነገሮችን ይገነዘባሉ ብለን አንገምት፡፡ አንድ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ድርድር ለደቡብ ሱዳን ብቻ ሳይሆን ለእኛም ሀገር ችግር መፍትሄ መሆኑን ቢያምኑበትና ለተግባራዊነቱ አቅማቸውም ነጻነታቸውም የሚፈቅደውን ቢያደርጉ፡፡ ሁለት በሥልጣን ላይ ያለ ሀይል ከተቀዋሚዎቹ ጋር ለመነጋገርም ሆነ ለመደራደር ሸብረክ የሚለው ብረት አንስተው ዱር ቤቴ ሲሉ ብረት ያነሱትም አቅማቸውን ከፈተሹና ነጻ መሬት መያዝ ከጀመሩ በኃላ መሆን እንደሌለበት አቶ ኃይለማሪያም እየሸመገሉ ቢማሩ በአጭሩ የሥልጣን ዘመናቸው የዘለዓለም ክብር የሚያቀዳጃቸው ተግባር ፈጸሙ ማለት ነበር፡፡
ክቡር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ስመ ሥልጣኑን በመሀላ ከተቀበሉ በኋላ ሀላፊነታቸው የቀድሞውን ጠቅላይ ምኒስትር የመለስን ሌጋሲ ማስቀጠል መሆኑን በመግለጻቸው ሰላማዊ ትግል ከመረጡት ጋር ለመነጋገርም ሆነ ኢህአዴግን ማነጋገር በሚገባው ቋንቋ ነው ከሚሉት ጋር ለመደራደር የሚቀርቡ ጥያቄዎችም ሆኑ የተሞከሩ ጅምሮች የማይታለፉ ቅድመ ሁኔታዎች እየቀረቡ ተሰናክለዋል፡፡ ትናንት ዛሬ እንዳልሆነ ሁሉ ነገም ዛሬ አይሆንምና ዛሬ የገፉት የንግግርም ሆነ የድርድር ጥያቄ ነገ ፈልገው ለምነው የማያገኙት ሊሆን ይችላልና ወዳጅ ሳይርቅ ጉልበት ሳይከዳ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ንግግርም ደርድርም መጀመር ለሁሉም ይጠቅማል፡፡

ይህ ጽሁፍ በኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ የታህሣሥ 30/2006 ላይ ወጥቷል።

የግንቦት 7 ወቅታዊ መልዕክት፡ “ከተገኙት አስከሬኖች ግድያው የቅርብ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል”

$
0
0

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው የክብርዘበኛ ጦር ካምፕ ውስጥ ማንነታቸው ያልታወቁ የ6 ዜጎች አስከሬን ለመንገድ ሥራ በተሠማሩ ቆፋሪዎች አማካኝነት መገኘቱ የሰሞኑ አሳዛኝ ዜና ነው።
ginbot 7
አንድ አይነት ቀለም ባላቸው ብርድ ልብሶች ተጠቅልለው ከተገኙ 6 አስከሬኖች የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰለባዎች ታስረውበት የነበረው የእጅ ሰንሰለታቸው እንኳ እንዳልወለቀና ከተቀሩት የአንዱ እጆች ደግሞ የፍጥኝ ወደ ኋላ እንደታሰሩ መገኘታችው ግድያው በቅርብ እንደተፈፀም አንዱ አስረጂ ነው።

በእንዲህ አይነት ጭካኔ የተገደሉ ዜጎች አስከሬን መገኘት በመንግሥት ተብየው አካል ካለመገለጹም በላይ ግቢውን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው 3ኛ ክፈለ ጦርም ሆነ በግብር ከፋይ ገንዘብ የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን እስከዛሬ አንድም ቃል መተንፈስ አለመፈለጋቸው ጉዳዩን እጅግ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን የሚያስገርምም አድርጎታል። ይባስ ተብሎም በመንገድ ሥራ ቁፋሮው የበለጠ አስከሬን ሊወጣ ይችላል በሚል ስጋት አካባቢው በፖሊስ እንዲታጠር ከተደረገ በኋላ ሥራውም እንዲቋረጥ ተደርጓል።

በፖለቲካ መስመር ልዩነት ምክንያት ደርግ ያለ ርህራሄ የጨፈጨፋቸውን ከመቃብር እያወጣ ዘመድ አዝማድ በማላቀስ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲዳክር የኖረ አገዛዝ በእንዲህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታና አጋጣሚ የተገኘውን የጅምላ አስከሬን አይቶ አንዳላየ ለማለፍ መሞከሩ ለምን ይሆን?

mekabir
አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ እንደሚያስታውሰው የክብር ዘበኛ ጦር ካምፕ በመባል የሚታወቀው የጃን ሜዳ 3ኛ ክፍለ ጦር ግቢ ድህረ ምርጫ 97 ወያኔ ለጅምላ እስር ቤትነት ከተጠቀመባቸው የማጎሪያ ቦታዎች አንዱ ነበር። ከዚያን ጊዜ በፊትና በኋላም ቢሆን ካምፑ በወያኔ ጠላትነት ተፈረጀ በጸጥታ ሠራተኞች ከታገቱ በኋላ አድራሻቸው እስከዛሬ ተሰውሮ ላሉ በርካቶች በምስጢር እስርቤትነት በማገልገል ላይ ከሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች አንዱ እንደሆ ይታወቃል።

ዘመድ አዝማዶቻቸው ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቋቸው ሳይመለሱ እንደወጡ የሚቀሩ በርካታ ዜጎች አሉ። በእንዲህ ሁኔታ ወጥተው ከቀሩ መካከል ከሰሞኑ የስድስቱ መቃብር በአጋጣሚ ተገኝቷል። የተገነዙበት ብርድ ልብስ ይነትብና ምንም ዓይነት ብልሽት ሳይደርስበት መገኝቱ ግዲያው በህወሃት ዘመነ መንግስት ስለመፈፀሙ ጥሩ ማስረጃ ነው። ለህወሃት ሰው መግደል ሥራ እንጂ ወንጀል አይደለም። በህወሃት ነፍሰ ገዳይ ይሞገሳል ይሾማል እንጂ አይወቀሰም አይጠየቅም። የስድስቱ ስዎች አስከሬን ሲገኝ መንግስትነኝ የሚለው ህወሃት አይቶ እንዳላየ መሆን ብቻ ሳይሆን ሌሎች አካላትም የሥፍራውን ሚስጢር እንዳያዩ ከልክሏል።በቁጥጥሩ ሥር ያሉ መገናኛ ብዙሃንም ዜናውን እንዳይናገሩ ታግደዋል። ህወሃት ከሚሰራቸው አስገራሚ ወንጀሎች መካከል አንዱይሄው ነው። ይሄ ግድያ በሌላ አካል ተፈፅሞ ቢሆን ኑሮ በረከት ስምዖንና እና ሺመልስ ከማል እየተፈራረቁ ያደነቁሩን ነበር።ይሄ የራሳቸው የእጅ ሥራነውና አይነገርም። የሄንንም የሚናገር እንደ ኢሳት ያለ ነፃ ሚዲያ ካለም ይታፈናል። አሸባሪም እየተባለ ይፈረጃል።

ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እነዚህ ዜጎች በህወሃት ተግድለው እንደተጣሉ ያምናል። ውሎ አድሮ እውነቱ እስከሚወጣ ድረስ ግን ዜጎች በሙሉ ይሄን ግድ በተመለከተ መረጃ የመሰብሰብና የማሰረጫት ሥራችውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እናሳስባለን። ይሄን ወንጀል የፈፀሙ አካላት መጠየቅ አለባቸው። የዜጎች ደም እንዲሁ በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም።

ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ጥቅም እንታገላለን የሚሉ የፖለቲካና የስቪክ ድርጅቶች እንዲሁም ለሰው ልጆች የሰብአዊ መብት የሚሟገቱ ሁሉ የተገኘው አስከሬን በአስቸኳይ ተመርምሮ ማንነታቸው ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲገለጽ፤ ተጨማሪ አስከሬን ሊገኝ ይችላል በሚልስጋት የመንገድ ቁፋሮውን ከሰዎች እይታውጪ ለማካሄድ እንዲቋረጥ የተደረገው ሥራ ለህዝብ እይታ ግልጽ በሆነመንገድ በአስቸኳይ እንዲጀመር የመጠየቅ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ግንቦት 7 ያሳስባል::
mekabir 1
በዚህአጋጣሚ ወያኔ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜጀምሮ በሱማሌ፣ በጋምቤላ፣ በአዋሳ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባና ሌሎች የአገራችን ክፍሎች በጠራራ ጸሃይ ካስጨፈጨፋቸው በተጨማሪ በፖለቲካ እምነታቸው ምክንያት ታግተው በየእሥርቤቱ የተወረወሩትንና ከታገቱበት ዕለት ጀምሮ እስከ ዛሬ የደረሱበት ያልታወቁ ወገኖቻችንን ዝርዝር በአስቸኳይ ያሳውቅ ብለን አንመክረውም።እኛ ግን ህወሃት የደበቀውን ወንጀል ሁሉ ህዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ያለምንም ማቅማማት ጠንክረን እየሰራን ነው። መንግስት ነኝ ብሎ በሥልጣን ላይ የሚወጣ ማንኛውም አካል የህዝብ አገልጋይ እንጂ ነፍሰገዳይ እንዳይሆን የጀመርነው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።

እንግዲህ ህወሃት በህዝባችንና በአገራችን ላይ የሚፈጽመውን ሰቆቃ ለማስቆም ግንቦት 7 የጀመረውን የነጻነት ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል እያስታወቅን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንዲህ በየቦታው ተገድሎ ከመጣል ራሱን ለመታደግ ሲል የነፃነቱ ትግል አካል እንዲሆን ጥሪያችንን አሁንም ደግመን እናቀርባለን::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

አዲስ ዓመት ለጋራ ራዕይ –በአበራ ሽፈራው /ጀርመን/

$
0
0

በአበራ ሽፈራው /ጀርመን/

በፈረንጆቹ ወይም እንደ ጎርጎርያን አቆጣጠር 2013 ዓ.ም  በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭው አለም ታላላቅ አሳዛኝና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ግጥመውን አልፏል፡: አንዳንዴም ይህ ዓመት ባልነበረ የሚያስብል ነበር :: እንኳን አለፈ ::

ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥ ብዙዎች ለእስር የተዳረጉበት፣ ፍርደገምድል ፍርዶች በፍርድ ቤቶች የታዩበት፣ የፖለቲካ እስረኞች በከፍተኛ ሁኔታ የተበራከቱበት፣ እስር ቤቶች በፖለቲካ አቋማቸውና አስተሳሰባቸው ብቻ በህወሓት ሰዎች አይን ውስጥ በገቡ የተሞሉበት ፣ የነጻው ፕሬስ ከመቼውም ጊዜ በላይ በህወሓቶች ጥቃት የደረሰበት ፣ የአማራ ተወላጆች በዘረኞችና ግልጽ በወጣ የዘር ጥቃት በሚፈጽሙ በህወሃቶች ባለሟሎች እቅድ ማፈናቀል የተደረገበት በዚህም ምክንያት ብዙዎች ለመከራና ለችግር የተዳረጉበት፣ አጥፊው የህወሓት ማኔፌስቶም አሁንም ትግበራውን ይቀጥላል ማኔፌስቶው ሳይሆን ምስጊን የቤንሻንጉልና ጉምዝ ሰዎች በትግበራ ዙሪያ እንደደቡቡ በተጠና መልኩ ማፈናቀሉን ባለማድረጋቸውና ህወሓቶችን በአደባባይ ያጋለጠ ድርጊት በመሆኑ ለቅጣት ተዳረጉ፣ አዛዡ አሳሪ ታዛዡ ታሳሪ ሆነና ድራማው ተጠናቀቀ በዚሁ ክፉ ዓመት : : በተለይም የሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሃይማኖት ነጻነት ትግልን በሃይል ለመጨፍለቅ ታስቦ ብዙዎች በአደባባይ የተገደሉበት፣ የታሰሩበትና እጅግ አስከፊ ግፍ የተፈጸመበት ዓመት ነበር በአገራችን ኢትዮጵያ::

ይኸው 2013 የህወሓት ዘረኛ ቡድን የአገሪቷን ወታደራዊ ኃይል ለመቀራመት በድርጊቱ ጠንሳሽና መሃንዲስ በነበረው መለስ ዜናዊ እቅድና ራዕይ መሰረት ሁሉንም ወታደራዊ ሃይል በህወሓቶች ለማስያዝና የአፈናውን ሥርዓት ለማጠናከር ሲባል በየትኛውም የአገሪቷ ዘመናት ባልታየ መልኩ ከፍተኛ የጀነራልነት ማዕረጎችና ሌሎች ወታደራዊ ሥልጣኖችን 99% በሚባል መልኩ የህወሓትን የበላይነት ለማረጋገጥና ስርዓት የለቀቀውን አገርን የመምራት አቅም ማጣት ለማስጠበቅ ሲባል ምንም ወታደራዊ አቅምና ትምህርት ለሌላቸው ሰዎች ብዛት ያለው የጀነራልነት ማዕረጎችን በመስጠት በአለምና በአገሪቷ  ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የሹመት ድግስ የተደገሰበት ዓመት በመሆን ተመዝግቧል ::

በዚሁ በ2013 የሰላማዊ ትግል አራማጅ ፓርቲዎች በአገር ውስጥ በተለይም የአንድነት ፓርቲ፣ የሰማያዊ ፓርቲና የመድረክ አመራሮችና አባሎቻቸው ለከፍተኛ ጥቃት የተጋለጡበት፣ በየምክንያቱ አባሎቻቸው ለእስር፣ ለድብደባና ለእስራት የተዳረጉበት ጊዜ በመሆን የሥርዓቱ አስቸጋሪነትን የተመለከትንበት ዓመት በመሆን አልፏል :: የተቃዋሚው ሃይል ከገዢው የማፍያ ቡድንም ጋር  ግልጽ የሆነ ትንቅንቅ ውስጥ የገባበትና የህወሓት ገዢ ቡድንም በከፍተኛ ትዝብት ላይ የወደቀበት ጊዜ በመሆን የተሰናበተን ዓመት ሲሆን በተቃዋሚው ላይ የደረሰው መከራ ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ የሆነበት  ዓመት ለመሆን በቅቷል ::

አገራችንና ህዝቦቿ በእነዚህ ሙሰኞችና በዝባዦች እጅ ከወደቀችበት ጊዜ ጀምሮ ፍጹም ባልታየ መልኩ ጥቂቶች እየበሉና እየጠጡ የሚኖሩባት ሌሎች ወይም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ለፍጹም የኑሮ ውድነት የተጋለጠበት ዓመት ከመሆኑም በላይ በኑሮው ውድነት ምክንያትም ህዝቡ ለከፍተኛ የኑሮ ምስቅልቅሎሽ ተዳርጎና ለከፍተኛ ስደትም በመዳረግ በልዩ ልዩ ቦታዎች የሚደርስበት የስደት መከራና ሞት ቀላል አልነበረምና አብዛኛው ህዝቡ ችግሩን ተጋፍጦ መፍትሄ የሚያመጣለት አጥቶ አምላክን በመማጸን ያሳለፈበት አመት በመሆን አልፏል :: ይሁንና ህወሓቶችና ባለሟሎቻቸው ግን በየምክንያቱ ጮማ እየቆረጡና ውስኪ እየተራጩ ዓመቱን ሲያሳልፉ መክረማቸውንና በተለያዩ አገራት ያሸሿቸው የገንዘብም መጠን ቀላል እንዳልሆነና ከሟቹ መሪያቸው ጀምሮ እስከ ትልልቅ ሹማምንቶቻቸው ድረስ የአገሪቷን ገንዘብ ለመበዝበዛቸው የውጭ ሚዲያዎችና እራሱ ኢቲቪ ሳይቀር ተገዶ “ሙሰኞች ነን” ለማለት የሞከሩበት አመት ሆኖ ተመዝግቧል :: ይሁንና ከዚሁ ከሙስና ጋር ተያይዞ ሙሰኛ ጋኖችን ሳይሆን ሙሰኛ ገንቦዎችን በመስበር ሲቀልዱ የታዩበት ዓመት ነበር :: ከዚህም የተረዳነው የጠገቡ ሙሰኞች ያልጠገቡ ሙሰኞችን ሲያጠቁ ተመለከትን ::

በዚሁ ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት ህወሓት በታሪክ አጋጣሚ ከሱዳን ጋር ባለው የጥፋት ቁርኝት አገርን ለባእዳን አሳልፎ በመስጠት የሚታወቀው ሥርዓት ከኢትዮጵያ ድንበር ሰፊውን ግዛትና ለም የሆነውን የአገሪቷን መሬት ለሱዳን ለመስጠት ውሎችን ለመፈራረምና ለዘመናት ደም እየተከፈለበት የኖረን የአገሪቷን መሬት አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀበትና ህወሓት ምን አልባትም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያስብ ቡድን እንኳን ሆኖ ቢገኝ በአገሪቷ ታሪክ በክህደት የሚጠየቅበትን ሁኔታ ያስመዘገበበት አመት ሆኖ ከመመዝገቡም በላይ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከአሰብና ከሌሎች በህወሓት ምክንያት ደም ካፋሰሱ የኢትዮጵያ ድንበሮች በተጨማሪ አሁን ደግሞ በዚህ ዘመን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አገርን ለመሸጥ ሲደራደሩ የከረሙበት ዓመት በመሆን ተመዝግቧል ::

የብዙዎች የኢትዮጵያ ሱማሌዎችና የአፋር ህዝቦች ደምም በህወሓት ወታደሮች የፈሰሰበትና ህወሓቶች በሌሎች ዓለም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ግፍ የፈጸሙበትን ማስረጃ የቀረበበት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውንና ማስፈጸማቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎች የተገኙበትና ያንንም ለማጠናከር ትልቅ ግልጽ ዘመቻ የተከፈተበት ዓመት በመሆን በአውሮፓዊቷ አገር በሲውዲን አገር እንቅስቃሴ የተጀመረበት ዓመት በመሆንና ከዚሁ ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮችን ለማጠናከር እንቅስቃሴ የተጀመረበት ዓመት በመሆንም ይታወሳል 2013 ::

“አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል ” እንዲሉ ዘረኛውና አንባገነኑ የህወሓት መሪ ለ21 ዓመታት ለብቻው ይዞት የነበረው የጭቆና ቀንበር ለዘለዓለም ወደዚች ምድር ላይመለስ በሞት በመሰናበቱ ምክንያት አገሪቷን ለከፍተኛ ችግርና አዳጋች ሁኔታ አጋልጧት እንደሄደና ህወሓትንም እርቃኑን አስቀርቶት ባዶ ቡድን መስርቶ የነበረ ለመሆኑ ማስረጃ መሆኑ እስኪታይ ድረስ ተተኪን ለመፍጠር እንኳን እንዳይቻል እያስፈራራ የፈጠረውና የገነባው ሥርዓት ለመሆኑ በግልጽ እስከሚታይ ድረስ በህወሃቶች መካከል ብቻ ሳይሆን በተለጣፊዎቹ የህወሃት ኢህአዴግ ፓርቲዎች ጭምር የዕርስ በርስ ትርምስ የተፈጠረበትና አገሪቷን የሚመሩ ግማሽ ደርዘን ሊጠጋ ትንሽ ቁጥር የቀረው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን በመያዝ የተመዘገበችም አገር በመሆንና ኢትዮጵያውያንን በማስገረም ያለፈ ዓመት ሆኖ አልፏል ይኸው 2013 ጉደኛ ዓመት ::

ይኸው 2013 በአባይ ግድብ ሰበብ ከመላው ኢትዮጵያና ከመላው ዓለም ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ኪስ የህወሓት ቀማኞች ገንዘብ የሰበሰቡበት፣ በግዳጅ የነጠቁበትና ገንዘባቸውን ለቀማኛ ቡድን ለመስጠት ያልፈለጉ በውጭው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የአባይን ግድብ እንዲገደብ ቢደግፉም በብዝበዛ፣ በሙስናና በመስረቅና የሃገርን ሃብት በውጭው ዓለም በሚገኙ ባንኮች በማስቀመጥ የሚታወቁትን የህወሓት የማፍያ ቡድንን ከአባይ በፊት ሰብዓዊ መብት እንዲያከብሩ በመጠየቅ፣ መለስና ሌሎች የህወሓት ሰዎች በውጭ ያከማቿቸው ገንዘቦች አንድ አባይን አይደለም ብዙ አባይን ይገነባሉና አውጡና በአገራችሁ አውሉት እያሉና ሌሎች ተመሳሳይነት ያላቸውን ሃሳቦች በማንሳትና በመቃወም በመላው ዓለም ህወሓት የቀለለበት ዓመት ነበር 2013 በእርግጥም ሕወሓት ቀድሞውንም ቢሆን በኢትዮጵያ ህዝብ ፊት የቀለለ ለመሆኑ እራሱ ህወሓትም ያውቀዋል ::

በዚሁ በ2013 በአገራችን በተለይም በጋምቤላ ክልል ሰፊ የመሬት መቀራመት የተፈጸመበትና ከፍተኛ ተቃውሞም በዚሁ ዙሪያ የተደረገበት ዓመት ከመሆኑም በላይ የጋምቤላ ነዋሪ ወገኖቻችንም በተወለዱበት፣ በአደጉበትና ተፈጥሮና ትውልድ ያስረከባቸውን መሬት በህወሓት ቀማኞች በአደባባይ በሃይል የተነጠቁበት ዓመት ነበር :: በሌሎች ክልሎች የገጠር ቦታዎች ብቻ ሳይሆን በከተማ ቦታዎችም ዙሪያ ግልጽ ቅሚያ የተፈጸመበትና ህወሓትን ተው የሚለው ጠፍቶ ያሻውን ያደረገበት ዓመት ነበር ::

የህወሓት አንዱ የመበዝበዣ ተቋም የሆነው የመከላከያ ሚንስቴር መስሪያ ቤትና ተያያዥ መምሪያዎችና የወታደራዊ መዋቅሮች በአገሪቷ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአንድ ዘር ስር መውደቁ የታወቀ ቢሆንም የአገሪቷ ሃብት በዚሁ ተቋም በነዚሁ በህወሓት ጀነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች እንደሚበዘበዝ ግልጽ እየሆነ ባለበትና ወቅትና ይህንንም ችግር ለማስቆም የተለያዩ አካላት ጥያቄ ማንሳት በጀመሩበት ወቅት ማንም ምንም አያመጣም ያሉ እስኪመስል ድረስ መከላከያ ኦዲት አይደረግም የሚል ሃሳብ መነሳቱና ጉዳዩ የህግ ከለላ እንዲያገኝ ለማድረግ ጥረት ማድረጋቸው የታየበትና ጉዳዩ በግልጽ እንደሚያሳየው ብዝበዛው በህግ እንዲደገፍ አዋጅ ያስነገሩበት ዓመትም ነበር በእርግጥም አይን ያወጣ ዝርፊያ ለመቀጠል ከፍተኛ መሰረት የተጣለበት ነበር ይህ ክፉ ዓመት:: አይ 2013 ጉደኛ ዓመት ::

የህዝቡን የፍትህና የነጻነትን ጥማት ይልቁንም ለመቀልበስና የህወሓትን ብዝበዛና ጭቆናን ለመቀጠል በታሰበ መልኩ “1 ለ 5″ የሚልን የአፈና መዋቅር ለመተግበር ከፍተኛ ርብርብ የተደረገበትም ዓመትም ነበር::

በሌላ በኩል  በዚሁ አስከፊ ሥርዓት ምክንያት በዓረቡ ዓለም ተበትነው የሚኖሩና በተለይም በሳውዲ አረቢያ በልዩ ልዩ መንገድ ወጥተው ተቀጥረው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በደረሰው ችግርና ሰቆቃ ምክንያት ብዙው ኢትዮጵያዊ በዓለም ህዝብ ፊት በዕንባ የተራጨበትና አምላክንም የተማጸነበት ዓመት ሆኖ ነበር :: በዚህ ምክንያት ብዙ ኢትዮጵያውያን ውስጣቸው ያዘነበት ዓመት ነበር::

 

ይህም ሆኖ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ህወሓትን ለመጋፈጥና በግልጽ መስዋዕትነት ለመክፈል የቆረጠበት፣ የሠላማዊ ትግል አራማጆችም ትግሉን በተለያዩ አቅጣጫዎች ያደረጉበትና የህወሓትን ማንነት በማሳወቅ ዕርቃኑን እንዲቀር ያደረጉበት ፣ የትጥቅ ትግል አራማጆችም ትግሉን በተለያየ አቅጣጫ በማድረግ ህወሓት ድንጋጤ ውስጥ እንዲገባና የሚይዘውና የሚጨብጠው እንዲያጣ በማድረግ ያደረጉት ትግልም ቀላል አልነበረም:: በዚህ ዙሪያ አርበኞች ግንባር፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦጋዴን ነጻነት ግንባርና ሌሎችም ያደረጉት የትጥቅ ትግልና ድል ቀላል አልነበረም:: ከዚህ በተጨማሪ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልም ትግሉን ወደፊት ለመውሰድ የጣለው መሰረት በህወሓት መንደር ትልቅ ድንጋጤን ከመፍጠሩም በላይ በህወሓት ላይ ከፈጠረው ጫና የተነሳ ህወሓት ሳይወድ በግዱ የንደራደር ጥያቄንም እንዲያቀርብ ያስገደደው ሁኔታ ገጥሞታል ::

 

እነዚህ ከላይ ያየናቸው ሁኔታዎችና ሌሎች አሁን ያልጠቀስናቸው ሰፊ የአገራችን ችግሮች በዚሁ በ2013 በመፈጠራቸው ዓመቱ እጅግ አሳዛኝና መራራ አመት ነበር ለማለት ያስችላል :: ለዚህ ሁሉ ችግር ትልቁ ተጠያቂም ህወሓት እራሱ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም  :: 2014 አዲሱ ዓመት ግን ለዓመታት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ ከሁሉም በላይ ደግሞ በሰብዓዊ ፍጥረት ላይ ይህ ዘረኛ ቡድን የሚፈጽመውን ግፍ ለማስቆም በጋራ የምንቆምበትና በአገራችን ሁላችንንም በእኩልነት፣ በፍትህ፣ በነጻነት፣ በህግ የበላይነት ሥር ሁላችንም በህግ ፊት እኩል ሆነን የምንኖርባትን አገር ለመመስረትና ለዚህም የህዝብና የአገር ራዕይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለራሱ ሲል አቅሙ በቻለ ሁሉ ትግሉን እንዲቀላቀልና ህወሓትን በመደምሰስ በጋራ ሁላችንንም የምትወድ አገር  ልንመሰርትበት የምንችልበትን መሠረት የምንጥልበት ዓመት ሊሆን  ይገባናል  እላለሁ :: ቸር ይግጠመን ::

comment pic

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን  ይባርክ !

 

እስክንደር ነጋ አሸባሪ ከተባለ ጆን ኬሪና አል ባራዴየም አሸባሪዎች ናቸው ማለት ነው –ግርማ ካሳ

$
0
0

ግርማ ካሳ

Eskinder-Negaኢቲቪ በቅርቡ አንድ በአንድ በኩል አሳዛኝ በሌላ በኩል አስቂኝ ዶኪሚንተሪ ለተመልካቾቹ አቅርቧል። በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል። ለዛሬ፣ የፌዴራል ከፍተኛ አቃቤ ሕግ የሆኑት፣ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ አንጋፋዉ ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋን በተመለለተ፣ በተናገሩት ላይ ጥቂት ሃሳቦችን ለመገልጽ እወዳለሁ። ሰዉዬ ስለ ሕግ፣ ስለ ሕገ መንግስቱ እየደጋገሙ አውርተዋል። ማንም ሕገ መንግስቱን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነትና ግዴታ እንዳለበት የገለጹት፣ አቃቤ ሕጉ፣ የአገሪቷ ሕግ ሲናድ ወንጀለኞችን ይዞ ለሕግ ከማቅረብ ወደኋላ እንደማይሉ አሳስበዋል። ማለፊያ ነዉ። ወንጀለኛ መያዝና መቀጣት አለበት። ሕግ መከበር አለበት። ይሄ ብዙ አያከራክረንም።

ነገር ግን «ሕግ፣ ሕግ» እየተባለን፣ ፍጹም ሕገ ወጥ የሆነ ተግባራት፣ ሕግ አስከባሪ ነን በሚሉ እየተፈጸመ መሆኑ ነዉ ብዙ እያከራከረን ያለው። ሕግ ሁላችንንም በእኩልነት የሚዳኝ መሆኑ ቀርቶ፣ ጥቂቶች እንደፈለጉ የሚገለባብጡት፣ የመጨቆኛ መሳሪያን በርት መሆኑ ነዉ እያሳሰብን ያለው። አቶ ብርሃኑ ስለ እስክንደር ነጋ ሲናገሩ የሚከተለዉን አሉ፡

«የእስክንድርንም ኬዝ ቢሆን፣ የ2004 አረብ ስፕሪንግ አይነት፣ ኢትዮያ ዉስጥ የአመጽ ጥሪ በማድረግ ከተንቀሳቀሱ ኃይሎች አንዱ እራሱ ነዉ። እርሱ በተለይም በየተኛዉ እርስ ላይ፣ በመጻፉ ምክንያት፣ አንድም ክስ አልቀረበበትም።የእስክንድር ጉዳይ ከፍሬደም ኦፍ ኤክስፕረሽን፣ ከመናገር ነጻነት ጋር፣ ከመናገር መብት ጋር የተያይዘ በፍጹም አይደለም። ቅድም እንዳልኩት፣ የአመጽ ጥሪ ማስተላለፉ ነዉ። የአምጽ ጥሪው ደግሞ የግንቦት ሰባት ተልእኮን ለማሳካት ነዉ። ከዚህ ጋር እስከ ፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ በጣም ሰፋ ይሉ ክርክሮችን በተደጋጋሚ አድርገናል።የአገሪቱ የመጨረሻ የሆነው ፌደራል ጠቅላ ፍርድ ቤት ፤ የጠፋተኝነት ዉሳኔ ሰጧል።»

በግብጽ የታየው፣ በኢትዮጵያም እንዲደገም እስክንደር ነጋ የሚፈልግ እንደነበረ ብዙም አያክራክረንም። በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በተደረገ ስብሰባ ላይ «እንችላለን! በሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች እንደሚቻል አይተናል። ኢትዮጵያ ከእነሱ ቢያንስ ቢያንስ አታንስም። ታሪክ እንስራ!» ያለዉና ኢቲቪ ቀንጥቦ ያወጣዉ አባባል ትክክለኛ አባባል ነው። እስክንደር ነጋ፣ ይሄን አልክዳእም። ሊክድም አይችልም።

«እስክንደር፣ በግብጽ የተከሰተዉ በኢትዮጵያ እንዲከሰት መፈለጉና በዚያ ዙሪያ መንቀሳቀሱ በምን መስፈርትና ሚዛን ነዉ ሽብርተኘንት ተደርጎ ሊወሰድ የሚችለው ? » በሚለው ላይ ነዉ የመጀመሪያ ክርክራችን። በግብጽ የነበረው እንቅስቃሴ ፍጹም ሰላማዊ የነበረ እንቅስቃሴ ነዉ። ከዚህ እንቅስቃሴ መሪዎች መካከል የነበሩ አንዱ ዶክርተር ሞሃመድ አል ባራዴ ይባላሉ። በተባበሩት መንግስታት የአለም አቀፍ ኑክሊያር ኤጀንሲ ሰብሳቢ ሆነው ለበርካታ አመት ያገለገሉ የተከበሩ ሰው ናቸው። እንደ ሳዳም ሁሴን የመሳሰሉ ሽብርተኛ መንግስታት ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች በማከማቸት ለአለም ስጋት እንዳይፈጥሩ የታገሉ የሰላም ሰዉ ናቸው። እኝህ ሰውና የሚመሪት ድርጅታቸው እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ2005 የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ሆነዋል። ታዲያ ሰላማዊ በሆነ መልኩ፣ አምባገነኑ የሙባረክ መንግስት ለሕዝብ ፍቃድ ተጠያቂ እንዲሆን፣ የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ፣ መታገላቸው እኝህ የሰላም የኖቤል ተሸላምዊ ሽብተኛ ያደርጋቸዋልን ?

ከሰባት ወራት በፊት ጆን ኬሪ፣ ሃርድ ቶክ ቢቢሲ ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተማሪዎች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተው ነበር። የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቴዎድሮስ አዳኖም በዚያ ነበሩ። ጆን ኬሪ ንግግራቸውን ሲጀመሩ የተናገሩትን ማንሳት እፈልጋለሁ። በግብጽ ስለነበረው ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ሽብርተኘንት ብሎ ስለሚጠራዉ፣ እንቅስቃሴ ሲናገሩ የሚከተለዉን ነበር ያሉት፡

«…the greatest concern has to be the lack of the fulfillment by governments in many countries, of the aspirations of people. Particularly the creation of jobs, and tሀ educational opportunities that are needed, for this modern world….In Egyopt, that was not a revolution that was moved by Islamism, or any ideology ….It was young people.. ..it was you ..people who came to the square , and twitted each other , texted each other , e-mail each other and brought people»

ጆን ኬሪ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ንደ ሽብርተኝነት የሚቆጥረዉን በግብጽ የታየውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንደ ትልቅ ምሳሌ አጉልተው ሲናገሩ፣ እስክንደር ነጋና ሌሎች ከተናገሩት አባባሎች ጋር የሚስማማ ንግግር ሲናገሩ፣ የሕወሃት/ኢሕአዴጉ ዶር ቴዎዶርስ ቁጭ ብለው ያዳምጡ ነበር። ታዲያ ጆን ኬሪ፣ የግብጽን እንቅስቃሰ እበነደገፋቸው፣ ወጣቶች ከግብጽ ወጣቶች እንዲማሩ በማባረታታቸው ችብርተኛ ሆኖን ? ሌላ ሌላም ምሳሌዎች ማቅረብ ይቻላል።

በግብጽ የታየዉ «አምባገነኖች» እምቢ የማለት ሰላማዊ እንቅስቃሴ የአለም አቀፍ ሕግን ያከበረ፣ በሰለጠነው አለም አድናቆትን ያተረፈ፣ የሕዝብ ጉልበት ታፎኖ እንጂ ከተነሳ ተአምር ሊያደርግ እንደሚቻል ያስተማረ ፣ ለአምባገነኖች ፍርሃትን የለቀቀ እንቅስቃሴ ነዉ። ሽብርተኝነት በፍጹም አይደለም።

እንግዲህ ሕወሃት/ኢሕአዴግ እስክንደርን ሽብርተኛ እያለ መጠራቱን ከቀጠለ ጂን ኬሪ፣ የስላም የኖቤል ተሸላሚ የሆኑትን ዶር መሃመድ አልባራዴን የመሳሰሉትን ሽብርተኛ እያለ እንደሆነ መቆጠር ይኖርበታል።

ሌላዉ ማንሳት የምፈልገው አቶ ብርሃኑ ከየት ዘለዉ እስክንደር ነጋን ከግንቦት ስባት ጋር እንዳገናኙት ነዉ። በግብጽ የነበረዉ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነዉ። ግንቦት ሰባት «የሰላም እንቅስቃሴ አይሰራም» ብሎ ነፍጥ ጨብጫለሁ ያለ ደርጅት ነዉ። እንዴት ተደረጎ ነዉ በግብጽ የታየዉን መደገፍ፣ የግንቦት ሰባት አባል የሚያሰኘው ? እዚህ ላይ ሕወሃት/ኢሕአዴጎች እራሳቸው ያስገመቱ ይመስለኛል። ምን አለ ባይቀልዱብን ?

በመጨረሻ በትክክለኛ መንገድ ክርክሮች ተደረገዉ በርካታ መረጃዎች ቀርበው፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ የጥፋተኛ ዉሳኔ እንደሰጠ በመግለጽ አቶ ብርሃኑ፣ የሕግ ስርዓት እንዳለ፣ ለማሳየት ሞክረዋል። እስክንደር ነጋ ቦምብ አላፈነዳም። ቤቱ ተበርብሮ አንድም ጥፋተኝነቱን የሚገልጽ መረጃ አልተገኘም። ወንጀሉ እንደ ጆን ኬሪ፣ ሞሃመድ አልባራዴ የግብጽ ሕዝባዊ እንቅስቃሴን መደገፉ ፣ በሕዝብ ጉልበት ኃይል መተማመኑ ነዉ። ወንጀሉ አገሩን መዉደዱ ነዉ።

«እክንድር ሽብርተኛ መሆኑን የሚያመለከት መረጃ አላየሁምና ልፈታው ነው» ባሉ ጊዜ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ አማረ አሞኜ ፣ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ተጠርተዉ መመሪያ እንደተሰጣቸው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አንድ ወቅት ዘግቦልን ነበር። ዳኛ አማረ፣ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው፣ ምንም እንኳን ጉዳዩን ሲያዳምጡ የነበሩ እርሳቸው ቢሆንም፣ ጉዳዪን ያላዳመጣ ሌላ ዳኛ (ወይንም ካድሬ) ተመድቦ ነዉ፣ የፖለቲካ ዉሳኔዉን በፍርድ ቤት ያነበበዉ። ሐቁ እንግዲህ ይሄ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ የሕግ ስርዓት የለም። የግብጽ አይነቱን እንቅስቃሴ፣ የሕዝቡ መነሳት ምን ጊዜም አምባገነኖችን የሚያስጨንቅ ስለሆነ፣ ክህደት፣ ሽብር፣ ወዘተረፈ እያሉ ማሰርና መግደል ልማዳቸው ነዉ። ነገር ግን ለጊዜ ያሸነፉ ሊመስላቸው ይችላል እንጂ ወዳቂዎች ናቸው። ይህ በነ እስክንደር ላይ የምናየው ድራማ አገዛዙ በራሱ የማይተማመን፣ የደነበረ መሆኑን ያሳየ ነው፡ በሚቆጣጠሩት ሜዲያ ጠዋትና ማታ መለፈፋቸውም የዉሸታቸውና የግፋቸውን መጠን አይቀንሰውም። ሕዝቡንም ማታለል አይችሉም። ሕዝቡ ያውቃል። ሕዝቡ እስክንደር ነጋ ማን እንደሆነ ያወቃል። እስክንደር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግና ነው። እርሱ ቃሊቲ የሚቆዩባቸው ቀናት በጨመሩ ቁጥር፣ እርሱ የበለጠ እየሸነፈ፣ እነርሱ ደግሞ እየመነመኑ ፣ ምናምንቴ እየሆኑ ነዉ። እርሱ በአለም አቀፍ መድረክ እየተከበረ፣ እነርሱ ደግሞ ሃፍረት እየተከናነቡ ነዉ።

ሻምበል ጉታ ዲንቃ፤ ጊዜውን ጠብቆ ይነጋል –ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

$
0
0

በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ሰውን እያፈረሰ፣ ማህበረሰብን እያፈረሰ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻዎችን በሚሠራበት ጊዜ፣ ከትናንት ወዲያ የሰዎችን ቤቶች አፍርሶ ትናንት የመኪና መንገድ ከሠራ በኋላ ዛሬ መንገዱን አፍርሶ የባቡር መንገድ እየተሠራ አዲስ አበባ በትራፊክ መጨናነቅ መኪና መንዳት አደገኛ በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ባለሥልጣኖች የሚሠሩት ጠፍቶአቸው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሚባለውን በአማካሪዎች ከሞሉት በኋላ ለሚኒስትሮችም አማካሪ መሾም በተጀመረበት ጊዜ፣ ዛሬ በሳኡዲ አረብያ ኢትዮጵያውያን እንደአደገኛ አውሬ እየታደኑ በሚደበደቡበት፣ በሚታሰሩበት፣ በሚደፈሩበትና በሚገደሉበት ጊዜ፣ ዛሬ በኬንያና በዩጋንዳ እንዲሁም በእሥራኤል ኢትዮጵያውያንን የማንገላታት ዝንባሌዎች በሚታዩበት ጊዜ፣ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከስዊድን እስከአውስትራልያ እየተሰበሰቡ በመጮህ ለማይሰሟቸው ሁሉ አቤቱታቸውን በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ዛሬ በተለያዩ አገሮች በኢትዮጵያውያን ላይ በሚፈጸመው ጥቃትና በደል፣ አለሁላችሁ የሚል መንግሥት በሌለበት ጊዜ —- ዛሬ ታሪካዊትዋ ኢትዮጵያ፣ ራሳቸውን የሚያከብሩና ኩራት ራታችን የሚሉት ኢትዮጵያውያን አልቀው ለሆድ በየሰው አገር መሰደድ ባህል በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያውያን ውርደት ደጋግሞ የነፍሱን ኡኡታ ባሰማበት ጊዜ በድንገት አንገታችንን ቀና አድርጎ ኩራታችንን ሊያስጎነጨን የሞከረ ሰው ተገኘ! ኢትዮጵያ ሁሌም የተአምር አገር ነች።
guta dinqa
በታላቁ ሰው በኔልሰን ማንዴላ እረፍት ምክንያት አንድ ተደብቆ የኖረ ክቡር ኢትዮጵያዊ ብቅ አለ፤ ማንዴላ ለሥልጠና በኢትዮጵያ በነበረበት ጊዜ ምናልባትም እንግሊዞች ማንዴላን ሊያስገድሉ ከጠባቂዎቹ አንዱ የነበረውን ወታደር በገንዘብ ገዝተው ዓላማቸውን ለመፈጸም አቅደው ነበር፤ ወታደሩ ገንዘቡን ከተቀበለ በኋላ ሀሳቡን ለውጦ ገንዘቡን ለአለቃው ሰጠ፤ ማንዴላ ከሞት ተረፈ፤ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊ ራሱንና አገሩን የሚያስከብር ሥራ ሲሠራ የሚኮሰኩሳቸው ባለሥልጣኖች ለእነሱ የማይተላለፍ ክብር በመሆኑ ተዳፍኖ እንዲኖር አደረጉት፤ እነሱ ሞተው ወይም ተሰድደው ሲያልቁ የተዳፈነው ምሥጢር ብቅ አለ፤ ባለሥልጣኖቹ ሸልመውት ይሆናል፤ ግን አላከበሩትም፤ ሻምበል ጉታን ያከበረው የማንዴላ ሞት ነው፤ የሚያሳዝነው ማንዴላ ይህንን የሱን ሕይወት ለማትረፍ ሁለት ሺህ ፓውንድ ያጣውን ኢትዮጵያዊ ወታደር ሳያውቀው መሞቱ ነው።

የኢትዮጵያ አርበኞች ታሪካቸው ተቀብሮ የቀረው እንዲህ እየሆነ ነው፤ ታዴዎስ ታንቱ ሥራዬ ብሎ የተረሱ አርበኞችን ከመቃብር እያወጣ ያስተዋውቀናል፤ በሌሎች አገሮች እንደዚህ ለአገር ትልቅ ፋይዳ ያለው ሥራ በአንድ ሰው በበጎ ፈቃድ የሚሠራ ሳይሆን ዋና የመንግሥት ተግባር ነው።

Pro Mesfinሻምበል ጉታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባይሆንም ራሱን ችሎ ለኔልሰን ማንዴላ መቃብር ደርሶአል፤ በአገር ደረጃ በሥልጣን ወንበሮቹ ላይ ለአገር የሚያስቡ ሰዎች አለመኖራቸውን ለማወቅ ግሩም ማስረጃ ነው፤ ለቀብር የሄደው ባለሥልጣን ሻምበል ጉታን ይዞ ቢሄድ ኖሮ ለራሱም ሆነ ለአገሩ ክብርና ጌጥ ይሆንለት ነበር፤ ለደቡብ አፍሪካ ሕዝብም ሆነ ለዓለም በመላ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር አልሸጥም-አልለወጥም ብሎ የኔልሰን ማንዴላን ሕይወት ማትረፉን በማስታወቅ አገሪቱን ያስከብር ነበር፤ የታፈነው ታሪክ አፈትልኮ ሲወጣ ከስደተኞች ጋር ተያይዞ መሆኑ ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የአደባባይ መክሸፍ የሚያሳይ ነው፤ ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ ተቀበለው፤ መንግሥት ያፈነውን ክብር ስደተኞች አጌጡበት!

ለእኔ አሁን አንድ ጥያቄ ይቀራል፤ ሻምበል ጉታ የአገሩን ክብር ከራሱ ጥቅም በላይ በማድረጉ፣ የተቀበለውን አደራ በመጠበቁ ቢያንስ ሁለት ሺህ ፓውንድ አጥቷል፤ እንዳጣ ሊቀር ነው? ቢያንስ የከፈለውን ሁለት ሺህ ፓውንድ ወይስ ያንን አሥር እጥፍ አድርገን እንከፍለዋለን? ሻምበል ጉታን የምናመሰግነው በርጥቡ ነው በደረቁ? እኛ ያለጥርጥር ኮርተንበታል፤ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን የሱን ክብር በመጋራት ራሳችንን አክብረናል፤ ሻምበል ጉታም በእኛ እንዲኮራና በእኛ እንዲከበር ማድረግ ያለብን ይመስለኛል፤ ስለዚህ ምን እናድርግ? ለራሱ ክብር፣ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ክብር ሲል የከፈለውን እስቲ ከወሬ ያለፈ ነገር እናስብና ለዚህ ጀግና የምንችለውን አድርገንለት እግዚአብሔር ዕድሜ ይስጥህ እንበለው።

ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ንባብ ነው –ለእኔ! ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 11.01.2014

sreateሰንበትን እንደ መክለፍት በእኛነት ዙሪያ ልል አሰብኩ። …  … አብሶ ሩሄን በትዝታ በሚያባክኑኝ ዬውስጥ – ለውስጥ የመንፈስ ሃዲዶች ዙሪያ ትንሽ ማለት ወደድኩ። የጹሑፉ ጥራት እስተዚህም ነው። ግን የሃሳቤ ፍሰት ማንነቴን ስለሚዳስስልኝ፤ ፍቅሬን – ትዝታዬን ይመግበኛል። ኢትዮጵያዊነት ንባብ ነው። ሲፈቀድልን ብቻ ማንበብ እንቻላለን። ኢትዮጵያዊነት ትርጉም ነው፤ ሲፈቀድልን ብቻ መተርጎም እንቻላለን። ኢትዮጵያዊነት ሚስጢር ነው ሲፈቀድልን ብቻ ነው፤ ቁልፉን መክፈት የሚችለው። ኢትዮጵያዊነት የመኖር ሕይወት ነው ሲፈቅድልን መታደስ ይቻላል፤ ለዛውም አምሮብን። ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ነው፤ ሲሰጠን ብቻ ዓይናችን ይከፈታል …. በስተቀር ዲዳ ሃሳብ ማስተናገድ ዕጣችን ይሆናል። ይህ ደግሞ ቅርስ አልባ ባዶነት፤ እርሾ አልባ ዘርየለሽ መሆን ነው። አያድርስ!

 

ኢትዮጵያዊነት ፍጹም ተወዳዳሪነት የማይገኝለት ተናፋቂ ማንነት ነው። ናፍቆቱ ውስጥን እንደ አሻው ገዝቶ አፍርህን በህሊናህ ስትቃኘው ፍውሰትን ያድልኃል፤ው ደግሞ ውበቱ ይቆጣጠርኃል። ስትፈቅድለት ትድናለህ። እሺ ስትለው ትፈወሳለህ፤ በስተቀር ግን ጉጉ ማንጉግ የሆነ አንካሳ መንፈስ ይጨፍርብኃል …፤ እስኪበቃው ያጨቀይኃል። አሸንፈውና ውጣ! … አሸናፊነትን ዋጥ አድርገውና ውስጥህን አሳምርብት …. ጌጥ ይጣላልን?

 

እንጀራን ስትወደው፤ ሽሮ ሰፍ ሲያደርግህ፤ ቁርጡ ሲታይህ፤ ቆሎው ሰፍ ሲያደርግ፤ ምቸት አብሹ ውል ሲልህ፤ ክትፎው ሲመጣብህ ሚጥሚጣዋን ስትዳስሳት፤ ቆጮን ስታላምጠው፤ ጭኮውን ቀረብ አድርገህ ስታሸተው፤ ዳቦው በእንሰት ወይንም በኮባ ተደፍቶ ከነክብሩ በሞገስ  በቁንዶ በርበሪ ለምለም ዝንጣፊ ወይንም ጉዝጓዝ ተሽሞንሙኖ ሲታይህ፤ አንባሻው ሲሸትህ፤ ንፍሮው ሽው ሲልህ፤ ዝግኑ – ጥብሱ – ቅቅሉ – ጎረድ  ጎረዱ፤ ዝልቦው፤ ቦዘናው፤ ገንፎው ቅንጨው፤ ጨጨብሳው፤  ፍርፍሩ ሲያሰኝህ ዕወቀው ይህ ስሜት ውስጥህን ገዝቶ አንተነትህን የሰጠህ ስለመሆኑ። በጣም በእርግጠኝነት  ከዚህ ፈጽሞ አታመልጥምና ውበቱን አጊጥበት! ….

…. አንተን አሳምሮ የሚገልጸህ ተራጓሚህ መሆንህን አትዝለለው፤ እርቀህ የማትርቀው ወስጥህ ነውና – አድምጠው።

ቄጤማው ለሽ ብሎ … ረከቦቱ ተኮፍሶ፤ ጭሱ ትጉልል – ትጉልል እያለ ሀገር ምድሩን ሲያካልለው፤ ማዕዛው የእጣኑ ዝንቅንቁ ጨስጨስ ሲል፤ ፍንጃሉ ወይንም ስኒው ላይ የፈረስ ጭራ መስሎ ቆረር ሲል፤ ጤናዳሙ ጣል ብሎ ወይ በወተት ወይ እንዲሁ፤ ጨው ሆነ ማጣፈጫ ታክሎበት ፉት ፉት – ትኩስ ትኩሱን፤ ዳበስ አድርገው – ሁንለት።  የቡና ቁርሱ በቀለምሽሽ ተሽሞንሙኖ ቀረብ ሲል ቸርፈስ፤  ዘንጣፌ ሚጢሚጣዋ በተን ብላበት፤ ወይ ዳቦዋ … በህብረት  በአብሮነት  ሰምሮ ከልብህ ከት ብለህ ስትስቅ – ስትተራራብ … ያ ነው ፎሎቄው አንተነትህን የሰጠህ ኢትዮጵያዊነት። ይህን ዘለህ ወይንም ጨፍልቀህ ልትሄድ ብትል አይሆንም —  አትችልም በፍጹም፤ እባክህን አትግደርደር። አንተ ማለት የዚህ ውጤት ጭማቂ ነህ።  ማንነትህ የተቀዳው ከዚህ ማርን ከሚያዘንብ ባህል ነው። እዚህ ላይ ያለው ንባብ ልዩ ነው … ይጣፍጣል፤ መንፈስን በሽብሸባ ዘና ያደርጋል፤ በዜማ ይቃኛል። ግን ትጉህ አንባቢ ይሻል – ስትታደል ይገለጽላኃል በስተቀር …. አንተን እራስህን ተላልፈኸዋል …. ተመለስ! የተፈጥሮ መስተውትህን ድጠህ አትስበረው። ይህ ቅልቅል ግን ውህድ ውብ ቅመም ቁንጅናህ እንዲሆን …. አብስለው።

 

ዋው! ስንቱ ይዘርዘር …. የንብ አውራ በመሰለ ሽንጣም ሞሰብ፤ ሌማት፤ ጥራር፤ ሰብሰብ ብለህ ስተታድም፤ ስትጎራራስ፤ በሞቴ አፈር ስሆን፣ ይህችን ይሀችን ብቻ!ች በእኔ ሞት ወይንም በእከሌ ወይንም በእከሊት ሞት እየተባልክ በአፍ በእፍህ ፍቅርን ተጥቅልሎ ስትጎርስ ዬት እንደተቀዳህ ሹክ ይልኃል፤ ጣዕሙን ኑርበት – ለራስህ ብትል። አድምጠው አንተን እራስህን አግኝተህ አንገትህን ቀና አድርገህ እዬው፤ የነፃነት ቅኔ ዘጉባኤ በራስ መተማማን ስሜት እንዲፈነድቅ የረዳህ አንትን በአንተነትህ የፈጠረህ ቅዱስ መንፈስ ነው። የራስህም ጌታ እንድትሆን …. ያደርግኃል። አስተውል እባክህን? … ምንጩ ይህ ነው የማንነትህ ፈርጥ። ስታከበረው ማን እንደ አንተ ጌታ! ውስጥህ የባዕድ ሽፍትንት እንደይጨፍርበት ካልፈቀድክ፤ አንተ ዬዛ የጥቁር አንበሳ ደም ትውፊት ስለመሆንህ አሳምሮ ይነገርኃል – ያስተምርኃል። የዚህ ልዑቅ ንጥር አካል ቤተኛ – ተጋሪ መሆንህ ተሰጥቶኃልና እንኳን ደስ አለህ። …. እንዳይሾልክብህ ግን ጠብቀው!

 

… ያደክበት፣ ያ … ሜዳማ መስክ? ወይንም ያ … ጋራ ሸንተረሩ – ጅረቱ – ፋፏፈቴው የእነ-ባሮ፤ ፤ ዬእነ -አንገረብ የእነ-ጣና የእነ-አባይ፤ የእነ-መረብ፤ የእነ-ቀኃ፤ የቢሸፍቱ ሐይቅ ወዘተ የሌሎችንም ዋናና ገባር ወንዞች፤ ሐይቆች፤ጠረን – ስበት ከልብ ሆነህ መርምረው፤ እዬተራጨህ ትጫወትበት የነበረው ንፁህ አዬር በቅንነት ቅዘፈው፣ ሂድበትበት፤ ዋኝበት፤ ተፈጥሮህ የተቀመረበት የአንት ጸጋ ነው፤ ወስጥህን አሳምርበት፤ የአንተ ልዩ መለያ የተቀረጸበት መንፈስ ነው። በልጅነት ጊዜ ሰኞ ማክሰኞው፤ ቅልሞሹ፤ ገበጣው፤ ድብብቆሹ፤  በማዕድ ጥያቄ ተጠይቆ ላልመለሰ መሸነፉን እድምተኛው ሲወስንበት ፍርዱን ተቀብሎ ተሸናፊው የማይበላውን እንዲባላ በድምጽ ብልጫ ሲወሰንበት፤ ወርርዱ፤ ያ ውድና ደግ የልጅነት ዘመንህ የሰጠህ – የለገሰህ – የሸለመህ ረቂቅ ፍቅርን ካሰብከው በመንፈስህ እንዲሸራሸር ከፈቀድክለት እሱ ነው ተነስቶ የማይጠገብ ኢትዮጵያዊነት ማለት … አትረሳውም አይደል? ወደ ዛ … አዎንታዊ ዕውነት የህሊና ዓይን ላከው … ትበራለህ!

 

የምንጩን ውኃ ገለጥ – ገለጥ አድርገህ ፎልፎል የሚለውን ጎንበስ ብለህ ጠጥተህ ስትራካ እሱ ነው የአንተነትህ ቅኝት – እሺ! ተከታይህም ተራው ሲደርስ ትራፊ ነው ሳይል ተጎንብሶ ጥሙን ሲያረካ አንተ የተቀዳህበት ማንነት እሱ ነው ወርቅ ጸጋ ተመቸው! በቆሬ – በግሬራ – ወተቱ ከዛው ታልቦ ትኩሱን በርከክ ብለህ ስትጎነጭ አቤት ፍሰኃው! ይህ ለውስጥህ በገፍ ማንነትህ ያበቀለ መክሊትህ ነውና አጣጥመው! እርጎውን በፋጋ ጎንበስ ብለህ ውስጥህ ራስ ስታደርግበት፤ እርጎው በጉርና ተገፍቶ ቅቤው ሲወጣ፤ ትኩሷና አናትህን ረጠብ ስታደርግህ ነጮቹ ያልደረሱበት ሳውና ይሉኃል ይህ ነው።

 

ይህ ማንነት ተቀድቶ ያማያልቅ የኤዶም ገንት ነው … ግን ሚስጢር የመተርጎም ብቃቱ ካለህ፤ ከላይ … ከላይ የማታነበንብ ከሆንክ ብቻ …. ይህ መንፈስ ነው ማንነትህ የጸደቀበት – የበቀለበት – ያፈራበት። አትለፈው —-  ነገ ውስጡን አታገኘውማና ጠንቀቅ ነዋ!  አንተ ከሸፍትክበት እሱም ጀርባውን መስጠቱ አይቀሬ ነው – በጊዜ! …. በአንኮላው – በዋንጫው – በብርሌው ጥሩው ገፈታውን እፍ እፍ ብለህ ለቀቅ ስታደርገው፤ በተኃዋን በብርሌ ቆረር እያደረክ ወደ ሰራዊቶችህ ስትልከው፤ ቡቡኙምንም ጥምህን ሲያባርር ረጠብ የሚያደርግህ ያ ውስጥነት ህይውት እስበው፤ ፍቀድና ….  ዘና አድርገህ አጣጥመው … አስላው …. ቁጠረው ….  ሥፍር ቁጥር የሌለው ሐሤት ታገኝበታለህ። ያ ሐሤትህ የተጸነሰበት ጀግናው ማንነትህ፤ የነጠረው የአንተነትህ ጮማ ነው ….

 

ቁምጣዋን፤ ቦላሌዋን፤ ሽርጡን፤ ሳንጃውን – ኮልቱን – አልቢኑን – ግልቢያውን – ዋናውን ጉዞውን – ሁሉንም ከልብህ ሆነህ እሰባቸው፤ በምልሰት ጊዜ ሰጥተህ አጫውታቸው፤ ይሰጥህ የነበረውን ደስታ ምልሰት አድርገልት፤ ያ ነው ውዱ ዕሴትህ፤  ሙሉ ወርዱ፤ ሽብሽብዎ በመቀነት ሸብ ሲል፤ ጃኖው ቀለማሙ ህይወት፤ ጥልፋማ ማንነትህ የተወለደበት ውስጥህ ነው …. ከመንፈሰህ ጋር ስለመሆንህም አረጋግጥ …. ጤናማነትን ይሸልምኃል።

 

እርገት። ኢትዮጵያዊነት ጥሪኝ አለው። ኢትዮጵያዊነት ሥራዓትን ፈጥሮ ጨዋነትን ያበቀለ፤ መቻቻልን ውጦ በውስጡ ያጸደቀ፤ ትእግስትን ተቀበሎ ውስጥን የሚዳኝ የፍቅር ቤት ነው። እያንዳንዱ የአመጋገብ፤ የአኗኗር፤ የዕምነት፤ የወግና የልምድ ሞራሉ ልራቅህ ቢባል የማይቻል፤ መስጥረን፤ ተሸሽገን፤ ተቆራኝተን እዬኖርን ግን ቅብ ሽፍትነት ብታቆለባባስ ትርፉ ትዝብት ብቻ ነው ውጤቱም ባዶነት።

 

ምስጋናዬ ከልብ ነው። ኑሩልኝ የኔዎቼ።

 

ወስጤን ከሽኖ ጌጠኛ ያደረገው፤ የውበቴ ማርዳ፤ የመንፈሴ ዘውድ፤ ኢትዮጵያዊነት ይኑር ለዘለዓለም!

ፈተናን ከመፈጠሩ በፊት አሸንፎ የተፈጠረ ማንነት – ኢትዮጵያዊነት!

 

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


የአሰብ ጉዳይ:- “ጦርነት ፈርተን ግን ሀገራችንን አሳልፈን አንሰጥም”–ከአብርሃ ደስታ

$
0
0

 

ገና በጠዋቱ “ዓሰብን ማስመለስ አለብን የምትለው እንዴት ነው? ወደ አላስፈላጊ ጦርነትና ደም ማፋሰስ ልታስገቡን ፈለጋቹ?” የሚል አስተያየት አዘል ጥያቄ አገኘሁ።
asab port
መጀመርያ ወደ ጭንቅላታችን መምጣት ያለበት ጉዳይ ‘የዓሰብ ወደብ የማነው?’ የሚል ነው። ዓሰብ የኢትዮጵያ ልአላዊ ግዛት (ንብረት) ስለመሆኑ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ሕጋዊ (በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት) ማረጋገጫዎች አሉን። ዓሰብ የኛ ስለመሆኑ የሚያጠራጥር ምንም ምክንያት የለም። ማስረጃዎቹ (ማረጋገጫዎቹ) እዚሁ ፌስቡክ ላይ ባልፅፋቸውም በወደቡ ባለቤትነታችን ጥርጣሬ አይግባቹ። ስለዚህ ጥያቂያችን ፍትሐብሄር ነው።

ሁለተኛ ጉዳይ ዓሰብ የኛ ቢሆንም አሁን ያለው ግን በኤርትራ ቁጥጥር ስር ነው። ንብረት ሃብታችን ተነጥቀናል ማለት ነው። ጥያቄው መሆን ያለበት ‘ዓሰብ ወደብ ለኢትዮጵያ ያስፈልጋል?’ የሚል ነው። መልሱ: ‘አዎ! ያስፈልጋታል’ ነው። የባህር በሯን የተነጠቀች ብቸኛዋ ትልቅ ሀገር ኢትዮጵያ ናት። በአሁኑ ግዜ የባህር በር የአንድ ሀገር የህልውና በር ነው። የህልውና በሩ መዘጋት የለበትም። ስለዚህ ኢትዮጵያ ንብረቷ (ወደቧ) የማስመለስ መብትም ታሪካዊ ግዴታም አለባት።

 

ሦስተኛ ‘እንዴት ነው ወደቡን ማስመለስ የምንችለው?’ የሚል ጥያቄ ማየት ተገቢ ነው። ምክንያቱም ዓሰብ የኢትዮጵያ ቢሆንም በመሪዎቻችን ሐላፊነት የጎደለው ዉሳኔ ምክንያት ለኤርትራ ተሰጥቶ ይገኛል። ‘ወደባችን አለ አግባብ ለኤርትራ በመሰጠቱ ምክንያት ዓሰብን የማስመለስ ጉዳይ ከባድ ሊያደርገው ይችላል’ የሚል ሐሳብ ቢነሳ አግባብነት አለው። ጦርነትም ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ሊቀቅ ይችላል።

ግን ማትኮር ያለብን ስለ ጦርነት አይደለም፤ ስለ ዓሰብ ንብረትነት እንጂ። ዓሰብ የኛ መሆኑ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማረጋገጥ (ማሳመን) ይኖርብናል። በዓሰብ ጉዳይ ፅኑ አቋም ይዘን የኢትዮጵያም የኤርትራም ህዝብ እንዲገነዘበው መጣር አለብን። የዓለም ህዝብ ይሁን መንግስትታት ይደግፉናል። ምክንያቱም የባለቤትነት መከራከርያ ነጥባችን ጠንካራ ነው። የዓለም አቀፍ ሕግም ይደግፈናል። ዓሰብ የኢትዮጵያ ስለ መሆኑ የሚመሰክግሩ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችም አሉ።

አራተኛ ዓሰብ የኛ መሆኑ ቢናረጋግጥና ለዓለም መንግስታትና ማህበረሰብ ቢናሳውቅ እንኳ እንዴት ዓሰብን መመለስ እንችላለን? የኤርትራ መንግስትኮ ፍቃደኛ አይሆንም፣ ጦርነት ሊነሳ ይችላል … ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች መነሳታቸው አይቀርም። ግን ችግር የለውም። ዓሰብ የኛ መሆኑ ካረጋገጥን ‘ንብረታችን መልስልን’ ብለን የመጠየቅ መብት አለን። የኤርትራ መንግስት ፍቃደኛ ላይሆን ይችላል። ጦርነትም ሊከፍት ይችላል።

እኛ ጦርነት አንፈልግም። ሕጋዊ ንብረታችን (ወደባችን) በሰለማዊ መንገድ እንዲሰጠን ነው የምንጠይቀው። አዎ! ጦርነት አንፈልግም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ግን ጦርነት ከፍተን በሃይል የሌላ ሀገርና ህዝብ ንብረት አንወርም ማለት እንጂ ጦርነት ፈርተን ልአላዊ ግዛታችን (ሃብታችን) ለሌሎች ሃይሎች አሳልፈን እንሰጣለን ማለት አይደለም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ጦርነት እንፈራለን ማለት አይደለም። አዎ! ጦርነት ስለማንፈልግ ሌሎች ህዝቦችን አንወርም። ጦርነት ፈርተን ግን እናት ሀገራችን አናስደፍርም።

ጦርነት ስለማንፈልግ ዓሰብን በሰለማዊ መንገድ የምንረከብበት መንገድ እናመቻቻለን። የኤርትራ መንግስት ጦርነት ሊከፍትብን ይችላል ብለን ግን ሃብት ንብረታችን ከመጠየቅ ወደኋላ አንልም። ጦርነት ተፈርቶኮ የሀገር ግዛት አሳልፎ አይሰጥም። ጦርነት ተፈርቶኮ ልአላዊ ግዛትን ከማስከበር ወደኋላ አይባልም። በባድመ ጉዳይ ጦርነት ዉስጥ የገባነው ጦርነት ስለምንፈልግ ሳይሆን ልአላዊ ግዛታችን የማስከበር፣ ሀገራችን ከወራሪዎች የመከላከል ሀገራዊ ግዴታ ስላለብን ነው። ጦርነት ፈርተን እጃችንና እግራችን አጣጥፈን የባድመን መሬት ለሻዕቢያ ወራሪዎች አሳልፈን አልሰጠንም።

(በኋላ በፖለቲካዊ ዉሳኔ፣ በመሪዎቻችን ግድየለሽነት ምክንያት ባድመን መስዋእት ከፍለን በደም አስመልሰን ሲናበቃ በእስክርቢቶ ለወራሪዎች ተላልፎ ተሰጠ እንጂ። በጦርነት የተመለሰ ንብረት በድርድር ሲከሽፍ በታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ነው። የባድመ ጉዳይ …!)

ምንም እንኳ ጦርነት ባንፈልግም ሃብት ንብረታችን ግን አሳልፈን አንሰጥም። ጦርነት መስዋእት ይጠይቃል። ግን ለሀገራችን መስዋእት ብንከፍል ችግሩ ምንድነው? ለሀገራችንኮ መሞት አለብን። በምንክያት መስዋእት መሆን እንቻላለን። ደግሞኮ ኢህአዴጎች የዓሰብን ጉዳይ ስናነሳባቸው ‘ጦርነት ናፋቂዎች’ ይሉናል። እኔ ግን ለሀገር መስዋእት ብንከፍል ጉዳት የለውም ባይ ነኝ። እንኳንም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ለሶማሊያም እየሞትን ነው። ይቅርታ ለሶማሊያም እየሞትን አይደለንም። ምክንያቱ ላልታወቀ ጉዳይ ነው በሶማሊያ እየሞትን ያለነው። ወታደሮቻችን በሀገረ ሶማሊያ እየሞቱ ያሉ ለምን ዓላማ ነው? ዜጎቻችን ዓላማው ለማይታወቅ ጉዳይ በሶማሊያ ከሚሞቱ ለሀገራችን ቢሞቱ አይሻልም ነበር? ኢህአዴጎች ‘ጦርነት ጥሩ አይደለም’ ይሉናል። ጦርነት ጥሩ አለመሆኑ ቢያውቁ ኑሮ ለምን በሶማሊያ ያሉ ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው አያስገቡም?

አዎ! ጦርነት ጥሩ አይደለም። በተቻለ መጠን ጦርነትን ማስወገድ አለብን። ጦርነት ፈርተን ግን ሀገራችንን አሳልፈን አንሰጥም።

አሜን!

ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች? (ግርማ ሞገስ)

$
0
0

ግርማ ሞገስ

Girma Moges

አቶ ግርማ ሞገስ

ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የአገር ተወላጅ እና የውጭ አገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በስልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሃቅ ነው። ይኽ እንዴት ሊሆን ቻለ? ረጅሙን የነፃነት ዘመን በስልጣኔ ወደፊት ለመራመድ ለምን አልተጠቀመችበትም ኢትዮጵያ? ምን ስትሰራ ነበር? የሚሉት የቁጭት ጥያቄዎች የሁላችንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ናቸው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው አነሳሽነት አውሮፓውያን ጎብኚዎችን እና ሚሲዮናውያንን እየተከተሉ ከአገራቸው ወጥተው የፖለቲካ ሳይንስ፣ የህክምና፣ የምህንድስና፣ የኢኮኖሚ፣ የመንገድ ስራ … --ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ—

 

 

አባጣለው ገብሬና ጓደኞቹ፦(ጌታቸው ከሰሜን አሜሪካ)

$
0
0

(ጌታቸው ከሰሜን አሜሪካ)

ዓመተ ምህረቱንና ወሩን ለጊዜው አላስታውስውም።ድርጊቱ የተፈጸመ ሰሞን ወሬው በየአቅጣጫው በሰፊው ይወራ ነበር።ጉዳዩ ግን የሀገር ድንበር ጉዳይ ነበር።ቦታው ምዕራብ ጎንደር አርማጭሆ ወረዳ ከሱዳን ጋር በሚያዋስነው ሰበካ(አጥቢያ) ወዲ ከውሊ ፈሸካ ከምትባል ቀበሌ የሱዳን ጦር ካምፕ አደረገ የሚል ወሬ የሰሙ ትውልዳቸው እዛው አርማጭሆና ጠገዴ የሆኑ አራት ሰዎች(ገብሬ ተወልደመድህን፤ድረስ ዓይናለም፤አወቀ ዋናሁንና ሌላ አንድ ሰው) መሬቱ የኢትዮጵያ ነው ።የሱዳን ጦር ለምን እዚህ መጥቶ ሠፈር በሚለው ጉዳይ ተቆጥተው ጦሩን መግጠምና ካምፑን ማቃጠል አለብን የሚል አቋም ላይ ደርሰው ተኩስ ከፈቱ።እንዳሉትም የሱዳንን ጦር ሠራዊት ክፉኛ ጎድተው ካምፑን አቃጥለው ክቡር መስዕዋትነት ከፍለው የሀገራቸውን ድንበር አስከብረው አልፈዋል።ሲባል እንደሰማሁት አባጣለው ገብሬ የተመታው ነብሱ ባልወጣች አንድ የሱዳን ቁስለኛ ጦር ሠራዊት እንደሆነና አባጣለውም የታባትክ እንዲህ ነው የምናደርግ እያለ ሲንጎራደድ እንደሆነ ይነገራል።እነዚህ ትልቅ ታሪክ ሰርተው ያለፉ ኢትዮጵያውያንን ታሪክ እንዲዘክራቸው ይደረግ እያልኩ ከዚህ ባሻገር ይህ የሰሜን ምዕራብ ጎንደር ወሰን ለይስሙላ ካልሆነ በስተቀር መንግሥት ድንበር ጠባቂ ጦር ሠራዊት መድቦ የሚያስጠብቀው ሳይሆን በአካባቢው በሚኖሩት ተወላጆች የጎበዝ አለቃ እየተሾመ በሕዝብና በሕዝብ የግል ብረት ተጠብቆና ተከብሮ መኖሩ የትናንት ትዝታችን ሲሆን ያን ዛሬ ላይ ሆነን ስናስበው ነገሮች ተገላብጠው እናገኛቸዋለን።

 

የዛሬዎቹ ገዥዎች በዱር በነበሩበት ወቅት ከሱዳን ለተደረገላቸው ትብብር የኢትዮጵያ ሀብት የሆነውንና ባጥንትና በደም ተከብሮ የኖረውን ለም መሬት ለሱዳን መስጠት ማለት በሕዝብ ላይ ያላቸውን ንቀትና ኢትዮጵያ ጥቂቶች እንዳሻቸው የሚያደርጓት ብቻ መሆኑ ሳይሆን ትናንት ኢትዮጵያ ከመሐዲስቶች (ድርቡሽ) ጋር ስትዋጋ ንጉሧን አጼ ዮሐንስንና ሌሎች ልጆቿን የገበረችበትን መሬት አስልፎ ለጠላት መስጠት ማለት ገዥዎቻችን ምን ያህል ለትውልድ ፤ለሀገርና ለታሪክ የሚያስብ ጭንቅላት ያልፈጠረላቸው እነሱን ብቻ የሚያስቡ አራዊቶች መሆናቸውን እንድንገነዘብ የሚያደርግ ነው።መሬቱ የኢትዮጵያ ሀብት ነው።በመሬቱ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይመክርበት ኢትዮጵያና ሱዳንን የሚያካልለው ድንበር ድንበሩን በሚያውቁ ሰዎችና የታሪክ ተመራማሪ የሆኑ ሰዎች ሳይሳተፉበት ህወሃቶች ደፍርሰው ባደሩ ቁጥር የመሬት ስጦታ ማበርከት ሸክማቸውን የሚያቀልላቸው መስሎ ቢታያቸውም አንዲት ስንዝር መሬትም ብትሆን ለማንም የመስጠት መብቱ በፍጹም የላቸውም።አዎ! ጦሩ ፤ፖሊሱ ፤ ደህንነቱ በእጃቸው እንዳለ እናውቃለን።የአሰብና ከኤርትራ ጋር ደም ያፋሰሰው ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ሌላ ጠብ አጫሪ የሆነ መሰሪ ተንኮል መጎንጎን መታጠፊያውን የተበላሸ ያደርገዋል። እንደ ኃይል የሚመኩበትና ደረታቸውን ያሳበጠው መከላከያውም ሆነ ደህንነቱ ነገ ይናዳሉ።ይህ የማይቀር ነገር ነው።ደርግን ይወድቃል ብሎ ያሰበ አልነበረም ነገር ግን በአፍሪቃ ቀንድ ወደር ያልነበረው ግዙፍ ጦር ፈረሰ።ህወሃትንና ደርግን ለንጥጥር አቅርበን ስንመለከትም በገዳይነታቸው አንድ ቢሆኑም በሀገር ጉዳይ ደርግ ዋዛ አልነበረም። በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ደርግ በህዝብ ዘንድ ይሁንታ ነበረው።ህወሃት ከሕዝብ ተነጥሎ ቆሞ በየአመቱ የሀገር ጥፋትን ለምን እንደሚያውጅ በውል ሊመረመረ የሚገባው ጉዳይ ነው።

 

ህወሃት ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት በትክክል ሱዳን ትጠቀምበታለች ብሎ አስቦ እንዳልሆነና ሱዳኖች ግብር እየከፈሉ ለከብት ግጦሽ ይጥቀሙበት የነበረ የኢትዮጵያ መሬት እንጅ የሱዳን ይዞታ አለመሆኑን ያውቃሉ።የሚያውቀ ከሆነ ለምን መሬታችን አሳልፈው ይሰጣሉ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ይህ ግልጽ ነው የህዋሃትን አጀንዳ ምንድን ነው ብሎ ማየት በቂ ነው። ሱዳን ያላትን ኃይል በሙሉ የተሰጣትን መሬት ለሚያለሙ ጥበቃ መመደብ አለባት ወይም ህወሃት የራሱን መከላከያ ኃይል መመደብ አለበት።ይህ ካልሆነ ገና ኢትዮጵያ ይገባኛል የምትለው መሬት ከሱዳን ሳይመለስ ሌላ ወሰን ዘላ እንድትገባ ማድረግ አካባቢውን ሰላም ለማሳጣትና ደም ለማፋሰስ ካልሆነ መሬትህ ይወሰድብሃል የተባለውን የአካባቢ ሕዝብ ከማንም በላይ ህወሃት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በውጤቱ ማንም ትርፍ እንደማያገኝና በህወሃት ላይ የተጀመረውን የተቃዋሚ ኃይሎች ሥርነቀል የሥርዓት ለውጥ ትግልም ሊያዘናጋ እንደማይችል መገንዘብ ይኖርባቸዋል። በርግጥ እንደዚህ ላለው ቀን የሚሆኑትን ውድ የሀገር ልጆች አስቀድመው ገድለዋቸዋል፤ አስድደዋቸዋል ወይም በሌላ ምክንያት በዚህ ክፉ ቀን ለሕዝብ እንዳይደርሱ ተደርጓል። ይሁን እንጅ «እሳት ከነበረበት ረመጥ አይጠፋም ይባላልንና» ጀግናው የሽንፋ ሕዝብ ፤የመተማ የቋራና የአዳኝ አገር የጫቆ ሕዝብ ፤የወልቃይት የጠለምት የጠገዴና የአርማጭሆ ጀግና ሕዝብ ዛሬም እንደትናንቱ አባቶቹ የሚከፈለውን ከፍሎ ድንበሩን እንደሚያስከብር እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል።እንደዚሁም የሌላው አካባቢ ኢትዮጵያዊ የጥቃቱ ዒላማ የሆነው የራሱን የጎበዝ አለቆች እየመረጠ በመተባበር ድንበሩን ማስከበር ይኖርበታል። በተናጠል እየገጠመ የጥቃቱ ሰለባ መሆን አይገባውም የሚገጥመው ከሱዳን ብቻ ሳይሆን ከህወሃትም ጋር ስለሆነ «አንድነቱን አጠንክሮ መዋጋት አለበት በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊም አቅሙ በሚፈቅደው መጠን ሕዝቡን ማገዝና ከተቻለም እዛው ተገኝቶ የሕዝቡን ሞት መሞት ክብር ስለሆነ ታሪክ ሊሰራ ይገባዋል እዚህ ሆኖ ማቅራራቱ በቂ አይደለም። ህወሃትን በሚፈልገው ቋንቋ ማናገር ስንችል ነው ሀገርና ሕዝብን የምናድነው;» ከባዶ እየተነሱ ሚንስትር ለመሆን መሮጥና ፈርም ከተባለው ላይ እየፈረሙ ታሪክን ማበላሸት  ሳይሆን ለተተኪ ትውልድ ለሀገር ለሕዝብ ማሰብ ይገባል።ያሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር ያለፈውን ጠቅላይ ሚንስትር ውዝፍ ሥራዎች ለመጨረስ ከሆነ ቦታውን ይዞት ያለው ባዶ ቀፎ ከመሆን አይዘልም ። መለስ ሀገርን አጥፍቶ የረጅም ዓመት የቤት ሥራ ጥሎልን ሄዷል።አሁን ያለው ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሌላ ሰው ነው ታሪክ መስራት መቻል ያለበት አሁን ነው።ሥልጣኑን መጠቀም ያለበት በል እያሉ ከኋላው ተቀምጠው ለሚጋልቡት ሳይሆን ለራሱ ፤ለቤተሰቦቹ ለሀገር ለህዝብ በተለይም ለተተኪው ትውልድ አስቦ መሥራት ይኖርበታል። በተለይ ጠቅላይ ሚንስትር  ኃይለማሪያም ደሳለኝ  ሥርዓቱን በማራመድ እንደማንኛውም ተጠያቂ ቢሆንም ጎልተው እንደወጡት የህወሃት ነብሰ ገዳዮች የሚታደን አይመስለኝም እነሱ የደረሱበት ልድረስ ብሎ የሚሮጥ ከሆነ ግን ፍርሃትን እንዳዘለ ውለህ ግባ ሳይባል ከጨዋታው ይወጣል። መመርመር ያለበትም ይህ የመሬት ስጦታ ውል የድሮ ህወሃት አጀንዳ  ኢትዮጵያን ለመበታተንና ወደ መጨረሻም «ታላቋን ትግራይ ትግርኝት ሪፐብሊክ » ለመመሥረት በነበረው ወቅት ስለሆነ ወደ ፊት ከእጁ ያለውን ክብር የሚያሰጥና በሕዝብ ዘንድ እምነት እንዲጣልበት የሚያደርግ ተግባር መፈጸም ያለበት ይመስለኛል። ሕዝቡን ለማጭበርበር ጡረታ ወጥተዋል የተባሉት ዛሬም በቁልፍ ጉዳዮች ላይ እጃቸውን እንደሚያስገቡና ውሳኔ እንደሚሰጡ መዘናጋት የለብንም  ለማንኛውም እነሱም ሆኑ አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት የህወሃት ገዥዎች በጎ ነገር እንዳይታያቸውና እንዳያስቡ የሚገፋቸው ችግር ብዙ ነው።ለምሳሌ ይህ ዛሬ የተነሳሁበት ሃሳብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት የሆነውን መሬት ለሱዳን አሳልፎ መስጠት የሀገርን ልዓላዊነት የሚነካና የተዳፈረ ተግባር ነው፤ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል እርስ በርሱ እንዲጋጭ አድርገዋል፤ገድለዋል ፤አስረዋል፤አስድደዋል፤አፈናቅለዋል፤የኢትዮጵያዊ ዘግነት መብቱን ገፈዋል፤ሀብት ንብረቱን ዘርፈዋል…ወዘተ ይህ ወንጀል ነው።ይህ የሕሊና እርፈት ይነሳቸዋል በውስጣቸው ሰላም እንዲያጡ ያደርጋቸዋል ይታመሳሉ።በሰላም ጊዜ ከሕዝብ ጋር እንዳይኖሩ የሚያደርግ ተግባር ስለፈጸሙ ከሕዝብ መነጠላቸውን ስለሚያውቁ ሕዝብና ሀገርን በማወክ ሥራ ላይ ብቻ የተጠመዱ ናቸው።ስለዚህ አዲሶችና ወጣቶች ወደ ሥልጣን ገበታው ብቅ ያሉትን በህወሃት ስብስብ ውስጥ ለመታቀፍ የሚያስችል ወንጀል እንዲፈጽሙ ያደርጓቸዋል። ልክ አይደለም ይህ መሆን የለበትም የሚሉትን ደግሞ ደብዛቸው እንዲጠፋ ይደረጋሉ። ጠቅለል አድርገን ስንመለከት የህወሃት አመጣጥና ወደፊትም ግዞው ይህ ነው የሚሆነው። የበሉበትን መሶብ የሚደፉ የእናት ጡት ነካሽ ይሏል ይህ ነው።

 

የኢትዮጵያ የቦርደር ኮሚቴ(በውጭ የሚንቀሳቀሰውን የሕዝቡን የኢትዮጵያ የቦርደር ጉዳይ ኮሚቴ ማለቴ ነው) በተደጋጋሚ የሚያወጣቸውን መግለጫዎች ፤በራዲዮ የሚደረጉ ቃለ-ምልልሶች ተከታትያለሁ ለገዥው ቡድን የተላከ እንደሚሆንም አምናለሁ።አንዲት የምትጣል ነገር የላትም የኢትዮጵያና የሱዳኑን ድንበርም ከማንም በተሻለ ስለማውቀው የቦርደር ኮሚቴውን ማመስገንና እንዲበራቱ ማድረግና የምናውቀው ማስረጃ ካለን እንድንሰጣቸውና ከጎናቸው እንደንቆም እየጠየቅሁ ገዥው መደብ አሁንም ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ አቋሙን እንዲመረምርና ውሳኔውን እንዲያነሳ ወደ ግጭቱ ሳንገባ መፍትሄ እንዲሰጡበት ማስጠንቀቅ እወዳለሁ።እሳቱ ከተጫረ በኋላ ሰማይ መሬቱን ማየት ፍሬ አይኖረውም። ምናልባት ይህን ስል ይህ ሰው እብድ መሆን አለበት እንደምትሉኝ ይገባኛል። በጣም ጤናማ ሰው ነኝ። ህወሃትና እኔ ስለምንተዋወቅ በገዳዳሙ ምን እያልኳቸው እንደሆነ ግጥም አድርገው ያውቁታል  ለአይን ጤና።

 

በመጨረሻ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር እንጅነር ይልቃል ጌትነት በዋሽንግተን ዲሲ በጠሩት ስብሰባ የታደሙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ ስለድርጅቱ ምንነት ሌሎችም ጉዳዮች ካዳመጡ በኋላ አንዳንድ ጥያቄዎች ተነስተው ነበር ሁሉም ጥያቄዎች በተገቢው ተመልሰዋል ብየ አምናለሁ።አንዱና ሁሉም የተቃዋሚ ኃይሎች ሆነ እኛም ልንመልሰው ያልቻልነው ጥያቄ የአንድነት ጥያቄ ነው። ጥያቄው ለእንጅነሩ ቀርቦ ነበር እንጅነሩ ወጣት ነው የሚገርመው ነገር ግን ያለው ፈሪሃ እግዚአብሔርና ትግስቱ ትህትናውና ለወገኖቹ ያለው አክብሮት ምንኛ የላቀ እንደሆነ በአንክሮ ተመልክቸዋለሁ። ስለጥያቄው ሲመልስ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ስለ አንድነት ግንባታ የሄዱበትን ርቀትና ወደፊትም በአንድነት ግንባታ ጉዳይ የድርጅቱን ራእይ በግልጽ አስቀምጦ አንድ ቦንብ የሆነ ጥያቄ ግን ለሁላችንም በተራው ጠይቆናል። ኃይለኛ ጥያቄ ነው። ሰማያዊ ፓርቲ ሆነ ሌሎች የተቃዋሚ ኃይሎች በአፋኙ የህወሃት አምባገነናዊ ሥርዓት እየተዋከቡ ፤እየታሰሩና እየተደበደቡ በዱላ እንደ እባብ ራስ እራሳቸውን እየተቀጠቀጡ አንድነት ለመፍጠር ያንጎላቹ ቢመስሉም አልተኙም እንደማለት ነው።ሁሉም ሥርአቱን እየተጋፈጡ በጋራ ለመስራትና ወደ አንድነት ለመምጣት የሚያደርጉትን ጥረት ገልጾ ነገር ግን እኛ እንዲህ ባለ ሁኔታ ላይ እንገኛለን። በዚህ በውጭው ዓለም ዴሞክራሲ በሰፈነበት አገር በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት ለምን አንድነት የፈጠረ «የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ» አልፈጠራችሁም? የሚል ጥያቄ ነበር ለቤቱ የጠየቀው።«የሽ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ» እንደሚባለው እስኪ በራሳችን ላይ እንፍረድና ከጥቂቶችና በጣት ከሚቆጠሩት በስተቀር ሰላም እንዲፈጠር አንድነት እንዲገነባ የሚያደርጉ አጀንዳዎች ዙሪያ ተነጋግረን እናውቃለን? መቼ? በቴሌ ኮንፈረንስና ፓልቶክ እንደምትሉኝ ገባኝ እሱ አይደለም። በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብሎ ሰጥቶ በመቀበል፤ አንተ ትብስ አንቺ በመባባል ኢትዮጵያዊ ባህል በተላበሰ መልኩ ተከባብረን ተመካክረን ሳንፎካከር ትግሬው አማራውን ሳይዘረጥጥ ኦሮሞው ጉራጌውን ሳይነቅፍ ሁሉን አቀፍ መድረክ ፈጥረን ለእኛም ሆነ ለተተኪው ትውልድ ታሪክ ለምን አንሠራም? እንጅነሩ ጥሩ የቤት ሥራ ሰጥቶናል እስቲ ስንቶቻችን እንደጎበዝ ተማሪ የእንጅነሩን ጥያቄ መልሰን እንደምንመጣ እንይ። በተለይ ጋዜጠኞች ፤ኢሳት እንዲሁም ሌሎች የፖለቲካ አክቲቪስቶች በዚህ ዙሪያ ዳሰሳ ብታደርጉ መልካም ነው እላላለሁ።

 

 

ኢትዮጵያ ልዓላዊነቷ ተከብሮ ለዘላዓለም ትኑር!!!

 

ጨርሰን ሳናልቅ ህወሃት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አያስረክብም!!

Pen(ጌታቸው ከሰሜን አሜሪካ)

መሰረታዊ ግንዛቤ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ! (ዘነበ በቀለ)

$
0
0

   ዘነበ በቀለ

music-notesሙዚቃዊ ፍልስፍና እንቆቅልሹ የሚፈታው ህዝባዊ በሆነው መሰረታዊ ግንዛቤ ላይ ተመርኩዞ ነው። ህዝባዊ ግንዛቤ ስንል ደግሞ ሙዚቃው የሚሰጠውን ስሜትም ሆነ መልዕክት የገባውና አሰራሩን የተረዳው ክፍል ወሳኝ መሆኑን ለመጠቆም ነው።

የኢትዮጵያ ሙዚቃ ማለት በብዙ ዘመናት የህዝቡ አብሮ የመኖር ስልት መሰረትነት የተገነባ የጋራ ግንዛቤን የፈጠረ የባህሎችን ልዩነት አቀናብሮ የያዘ አንድ ወጥ ቅርስ የሆነ ማለት ነው። እነዚህን የቅርርብ ሁኔታዎች ለመገንዘብ ሶስት መሰረታዊ የሆኑ የዜማ መዋቅሮችን መመልከት የተገባ ነው። እነዚህም

1ኛ/ የዜማ ስልት

2ኛ/ ሪትም/ምት

3ኛ/ ቋንቋ

ሲሆኑ ከመመርመሪያቹ መንገዶች መሃል ዋነኞቹ ናቸው።

 

የዜማ ስልት ስንል ሙዚቃው የተገነባበትን መሰላል/ስኬል ማለታችን ነው።

ሪትሙ ደግሞ በየአካባቢው የአኗኗር ዘይቤ ላይ ተመርኩዞ በረገዳ፣ በዘፈን፣

በእስክስታ፣ በጭፈራ የሚተረጎም መሆኑን የሚገልፅ ነው።

ቋንቋውም ቢሆን እንደየአካባቢው የአነጋገር ፈሊጥ የሚታይ በመሆኑ ለምሳሌ ያህል – በጎንደር አማርኛና በጎጃም አማርኛ፣ በሸዋ አማርኛና በወሎ አማርኛ መሃል ልዩነት አለ። በኤርትራ ትግሪኛና በትግራይ ትግሪኛ መሀል ልዩነት አለ። ይህ ሁኔታ በዜማው ላይ ተፅዕኖ አለው’ የዜማው ስሪት ደግሞ ጭፈራውን ይወስነዋል።  ለምሳሌም የሸዋው ኦሮሞ ጎፈር አጥልቆ ረገዳ ሲጫወት ይስተዋላል። የወሎ ኦሮሞ ግን ጭፈራውን  በእስክስታ አጅቦ ነው የሚያቀርበው። የወለጋና የጂማ ኦሮሞ በጭፈራው ላይ እጅን ማርገብገቡ ተመሳሳይ ቢያደርጋቸውም ያርሲ ኦሮሞ አንገትን ማሽከርከር ይጠቀማል። በሁሉም ዘንድ የዜማ ባህሪያቸውና ሪትሙ የተለያየ ነው። ስለዚህም መለኪያው ሁሉንም ነጥቦች የዳሰሰ መሆን ይገባዋል እንጂ! የኦሮሞ ባህላዊ ሙዚቃ አንድ አይነት ነው ከማለት ይልቅ ኢትዮጵያዊ ትርጉም ያለው ለመሆኑ የበርካታ ባህሎችን ተመሳሳይ አሰራር መገምገም ያስፈልጋል።

 

የወያኔ ፖለቲካ የተቀነበበው በነገድ ማንነት ዙሪያ በመሆኑ ሙዚቃን በተለይም ኢትዮጵያዊ ፀባይ ያለውን ክፍል ለመተርጎም በርካታ ችግሮች ሲደነቀሩ ይስተዋላል። የሙዚቃን ምንነት በራሳቸው ፍላጎት ላይ ተመርኩዘው የሚተረጉሙ ግለሰቦች መኖራቸው ተገቢውን ግንዛቤ ያልጨበጡ አድማጮችን ለመፍጠር ምክንያት ሆኗል። በመሆኑም የሙዚቃ ግንዛቤ ፈሩን የለቀቀ ማንኛውንም ነገር በምርታማነት/ሽቀላ ስሌት ውስጥ ያስገባ በመሆኑ፣ የሙዚቃ ሰዎች በስራቸው ላይ ከጥራት ይልቅ ብዛትን እየመረጡ  በመምጣታቸው መካለስና መደለዝ፣ መደባለቅና መዋዋጥ፣ በተለይም በስታይል/ አሰራር ዘይቤው/ እንዲጨፈለቅ አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆናቸው ይስተዋላል። በዚህም ምክንያት ከላይ የተጠቀሱትን ማገናዘቢያ ነጥቦች ያላሟሉ ሙዚቃዊ ስራዎችን በተናጠል በማቅረብ፣ በቋንቋ ላይ ብቻ የተመረኮዘ ግምገማን በመሰንዘር ይኸ ሙዚቃ የእከሌ ጎሳ/ነገድ ባህል ነው ብሎ መደምደም ፈሊጥ ሆኗል። ይሁን እንጂ! የየነገዱን አኗኗር ከቋንቋው ውጭ ተመልክቶ መገምገም አስፈላጊ ነው። ከሙዚቃው ጥበብ ባህርይ የወጣ ግምገማ ለሙዚቃው ምንነት ጠቃሚ አይሆንም።

 

የሙዚቃ አሰራር በተለያዩ መልኮች በህዝብ ውስጥ መተላለፉ ሀቅ ነው። በጉርብትና፣ ገበያ፣ ጦርነት፣ ራድዮ ማሰራጫ ወዘተ. ዋና ዋና የመተላለፊያ መንገዶቹ ናቸው። በመሆኑም

የኢትዮጵያ ህዝብ ባህል በነዚህ ሁሉ መልኮች የመተላለፍ ዕድል ስለገጠመው አንድ ወጥ የሆነ ሙዚቃዊ መሰረት ይዞ እንዲወጣ ዕድል አግኝቷል። ይህም የአምስት ድምፅ መሰላል ተከታይ መሆኑ አንዱና ዋናው ነው። በጣም ጥቂት የሆኑ ባህላዊ ሙዚቃዎች ከዚህ ባነሰ /ቶናል ሬንጅ/ ወይም የድምፅ ገደብ ውስጥ ያሉና በኦሮምኛ እንጉርጉሮ ሙዚቃ ውስጥ ከሚታየው ሄክሳቶኒክ/ ወይም ስድስት ድምፅ መሰላል እንዲሁም በአደሬ ክሮማቲክ ታይፕ/ የግማሽ ድምፅ ግንባታ ያለው ሙዚቃ መሰላል ውጭ፣ አብዛኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ማለትም የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የትግሬ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ ወዘተ. የነገድ ሙዚቃዎች በአምስቱ መሰላል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በመሆኑም አንድ አይነት ሳይኮሎጂካል ሜክአፕ/ ፈጥረዋል።

 

የአምስቱ መሰላል ቶን የፈጠረው ሜላንኮሊክ ጠባይ የአድማጩን ሙዚቃዊ ግንዛቤ በመወሰኑና አንዳንድ ሁኔታዎችን ተመርኩዞ የሀዘን ስሜት የሚፈጥር በመሆኑ በተለይ እንዳሁኑ አይነት ህዝብ ያዘነበት የተከዘበት ዘመን ሲከሰት ለቅሶንና ሙሾን በመድረስ የሙዚቃውን አጠቃላይ ግንዛቤ ለውጦ እንባ አባሹ እንዲበራከት የሙዚቃው ይዘት  አንድወጥ ትርጉም ብቻ እንዲይዝ የሚያደርጉ ሙያተኞች ምክንያቶች ይሆናሉ። ሙዚቃ ደስታና ሀዘን የሚገለፁበት ጥበብ ብቻ አይደለም። ትምህርትንም ማስተላለፊያ እንደመሆኑ ሁሉ ፖለቲካም ጓዙን ጠቅልሎ በጥበቡ ታዛ ስር እንደሚጠለል ታሪክ መስክሮልናል።  ትክክለኛ ሁኔታዎች ከተለዋወጡ አጉል ቦታ የሚደነቀረው አሰራር ብዙ ትርጉሞችን ያዛባል። ለምሳሌ የቀረርቶ ዜማን  ያለቦታው መደባለቅ “ሳይገድሉ ጎፈሬ…” የሚሉት አይነት ትርጉምን የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ ወቅታዊ የሆነ የመነሳሳት ስሜት ፈጣሪ የነበረውን የጦርነት ሙዚቃ ማዕረጉን ቀንሶ ለዳንስ እንዲውል ያደርገዋል።

 

የኢትዮጵያ ሙዚቃ በጊዜው ያልተዋዋጡ የተለያዩ የአካባቢ ባህሎችን ልዩ አሰራር የሚያከብርና በጋራ የሚታዩ ሙዚቃዊ እሴቶችንም አቅፎ የሚጓዝ የህዝብ ባህል ነው። የኢትዮጵያ ሙዚቃ በእንጉርጉሮና በዘፈን በመዝሙርና በመንፈሳዊ ዜማ መንገዶች መካከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ በመረዳት የሚጓዝ መሆኑ መታወቅ ይገባዋል።

 

ቸር ይግጠመን!!

ከአምባገነን ባሻገር-የተወሳሰቡ ነገሮችን የመረዳት አስፈላጊነትና የነፃነት ጥያቄ ! ከፈቃዱ በቀለ

$
0
0

የነፃነት ጥያቄ !    ከፈቃዱ በቀለ

መግቢያ

ከረዠም ዐመታት ጀምሮ ትግላችን የአምባገነን አገዛዝ በሚለው ላይ ያተኮረ ነው። ባለፉት 22 ዐመታት፣መጀመሪያ

በመለሰዜናዊ፣ ከአንድ ዐመት ወዲህ ደግሞ በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራው አንድ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ የአገራችንን

አምባገነንህልውና ወሳኝ በመሆን ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በማፈን፣ ቁልፍ ቁልፍ የሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎችን በመቆጣጠርና፣ ጥቂቱ ብቻ እንዲበለጽግ በማድረግ፣ ገበሬውን ከእርሻው እያፈናቀለ መሬቱን በመንጠቅና አልሚ ነን ለሚሉ ነገር ግን ዕውነተኛ የሆነ ሀብረተሰብአዊ ሀብትን ለመፍጠር ለማይችሉና አካባቢን ለሚያወድሙ የውጭ ቱጃሮች በማከራየት፣ በዚያው መጠንም ድህነትን በማስፋፋት እንዳለ በየጊዜው ይጻፋል። በእኛ አገር ስላለው አምባገነናዊ አገዛዝ ብቻ ሳይሆን፣በብዙ የአፍሪካ አገሮች ከ20ና ከሰላሳ ዐመታት በላይ ስልጣንን የሙጥኝ ያሉ አገዛዞች አምባገነኖች እየተባሉና፣ ለዲሞክራሲያዊ መብቶች አለመኖርና ለሰብአዊ መብት ረገጣ ተጠያቂዎች እንደሆኑ ይነገራል። ሰሞኑን የተያዘው ፈሊጥ ደግሞ እነዚህ አምባገነን መሪዎች የግዴታ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው አስፈላጊውን ቅጣት ማግኘት አለባቸው የሚል ነው። ይኸኛው ውትወታ ትንሽ ዕውነት ቢኖረውምና እስከተወሰነ ደረጃም ድረስ መደገፍ ያለበት ቢሆንም የጥቂቶች በዓለም ፍርድቤት በሚባለው ፊት መቅረብ አፍሪካ ለገባችበትና አሁንም ላለችበት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና እሴታዊ ቀውስ ብቻውን እንደ በቂ መፍትሄ ሆኖ ሊቀርብ እንደማይችል ግልጽ ነው።  የነሱ ትክክለኛውን ፍርድ አግኝቶ ለረዠም ዐመታት እስርቤት ውስጥ እንዲማቅቁ ማድረግ የአፍሪካን ህዝብ ነፃ እንደማያወጣውና በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሰፋ ያለ የውስጥ ኢኮኖሚ መገንባት እንዳማያስችለው ሰፊ ምርምርና ጥናት ያካሄዱ ምሁራን ይናገራሉ።  በነዚህ

አመለካከትና ትንተና መሰረት ቀድሞም ሆነ ዛሬ አምባገነኖችና ወንጀለኞች እየተባሉ የሚከሰሱ የአፍሪካ ገዢዎች በየአገሮቻቸው ለደረሰውና ለሚደርሰው ሰቆቃና የኢኮኖሚ ኋላ-ቀርነት ብቻቸውን ተጠያቂ መሆን እንደማይችሉ ነው። ነገሩን ከአንድ ወገን ብቻ ማየቱ ለዕውነተኛ ነፃነት የሚደረገውን ትግል እንደሚያጨናግፍና የአፍሪካን ጥገኝነትና በኢኮኖሚ ኋላ-ቀርነት እንደሚያራዝመው በመተንተን አመኔታ ያለው ማረጋገጫ ይሰጣሉ። ስለዚህም ይላሉ እነዚህ ኃይሎች፣ ቀድሞም ሆነ ዛሬ በአፍሪካ ምድር ውስጥ በስልጣን ላይ የተቀመጡትና የተቆናጠጡ ገዢዎች በምዕራቡ ዓለም፣ በተለይም በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና በእንግሊዝ የስለላ ድርጅት በተቀነባበረ ስትራቴጂያዊ ክንውን እንደሆነ ያመለክታሉ። እንዲያውም ይላሉ እነዚህ ኃይሎች፣ ቀድሞም ሆነ ዛሬ ለአፍሪካ ኋላ-ቀርነትና የዲሞክራሲ አለመኖር ዋናው ተጠያቂ ኃይል የአሜሪካንና የእንግሊዝ ኢምፔሪያሊዝም ናቸው። በመሆኑም ሁለቱም የኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ብቻ ሳይሆኑ ጠቅላላው የምዕራቡ ዓለምና የነጭ ኦሊጋሪኪ መደብ በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በአፍሪካ ውስጥ የዕውነተኛ ዲሞክራሲ አጋዦች ሊሆኑ እንደማይችሉ ሰፋ ያለ ትንተናና ኢምፔሪካል ማስረጃ ያቀርባሉ።  ስለዚህም፣ አምባገነን እየተባሉ በሚጠሩት የአፍሪካ መሪዎችና በኢምፔሪያሊስት መሀከል ያለው የተቆላለፍ ግኑኝነት ሲበጠስ ብቻ ነው ዕውነተኛ ነፃነትን መቀዳጀት የሚቻለው ብለው ይነግሩናል። አምባገነን አገዛዞች እያሉ በየጊዜው መለፍለፉና መወትወቱ አውቆም ሆነ ሳያውቁ በኢምፔሪያሊስቶች ጉያ ስር ለመውደቅና እነሱን ተገን አድርጎ ስልጣን ላይ ቁጥጥ ብሎ የነሱን ፖሊሲ ተግባራዊ ከማድረግና ጥቅማቸውን ከማስጠበቅ ውጭ በፍጹም ለመታየት እንደማይችል ያመለክታሉ። በዚያውም መጠንም የጭቆናው ዘመንና ድህነቱ፣ በረቀቀ መልክ ደግሞ አምባገነንነቱ እንደሚራዘም የዕቅጩን ይነግሩናል።

 

ይህ ዐይነቱ ግልጽ አመለካከትና በብዙ ኢምፔሪካል ጥናት የተደገፈ ትንተናና ማስረጃ እያለ፣ እንዲሁም ደግሞ እንኳን ለተማረ ሰው ቀርቶ ላልተማረም ሰው ግልጽ የሆነ ቀጥተኛ በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የሚካሄድ ወረራና ዲሞክራሲያዊ ያልሆኑ ኃይሎችን ስልጣን ላይ እንዲወጡ በማድረግ ዕውነተኛ ዕድገት እንዳይመጣ በሚካሄድበት ዘመን ለምንድ ነው ዝም ብሎ ቁንጽል የሆነ አስተሳሰብ በማስተጋባት አምባገነኖች ብቻ ይጠየቁ እየተባለ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦቾን ማሳሳቱ? በየጊዜው ስለአምባገነን አገዛዝ የሚጽፉ የፖለቲካ ተንታኞች የነገሩን ውስብስብነት ማየት ለምን ተሳናቸው? ወደ ኋላ በመሄድ የታሪክን ሂደትና የህብረተሰቦችን ዕድገት ውጣ ውረድ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተዘረጋውና ከተቀነባበረው ሁኔታ ጋር በማቀናጀት ሰፊ ትንተና ለመስጠት ምን የሚያግዳችው ነገር አለ? በእርግጥስ በዚህ ዐይነቱ አተናተናቸውና ውትወታቸው ለህዝባችንና ለተቀረው የአፍሪካ ህዝብ ውሸቱን ከዕውነቱ ነጥሎ በማሳየት የስልጣኔና የዕውነተኛ ነፃነት አጋዠ የሆኑ ይመስላቸዋል ወይ? የአጻጻፍ ስልታቸውና አመለካከታቸው በአንዳች ፍልስፍናና ሳይንስ ላይ የተመሰረተ ነው? ወይስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚናፈሰው ሁኔታ ጋር በማገናዘብ የሚቀርብ ሀተታ ነው ወይ?  ይህ ዐይነቱ አመለካከት ከምን እንደመነጨ ጠጋ ብሎ መመልከቱ ጠቃሚ ይመስለኛል። በየሳምንቱ ቦምባስቲክ በሆኑ ቃላቶች እየተሸፈነ የሚቀርበው ሀተታ ለምን የዕውነተኛ ነፃነትና ስልጣኔ አጋዠ መሆን እንደማይችል ጠጋ ብለን መመልከት አለብን። በተጨማሪም ከዚህ ዐይነቱ ሳይንሰ-አልባ የሆነ ትንተና እስካልተላቀቅን ድረስና፣ ይህንን ትክክለኛ ነው ብለን የምናራግብና የምናሰራጭ ከሆነ ወደድንም ጠላንም የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘውን ዕውነተኛውን ስልጣኔና ነፃነት እንዳያገኝ አስተዋፅዖ እናበርክታለን ማለት ነው፤ ሳናውቀውም እያበረክትንና፣ ራስን ችሎና ተከብሮ ለመኖር የሚያስቸለውን በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ  የኢኮኖሚ ግንባታ እንዲጨናገፍ  ማድረጋችን የማይቀር ነው።

 

 

 

 

ትክክለኛ የሆነ የሳይንሳዊ ግንዛቤ እጦት የሚፈጥረው የአመለካከት ችግር !

         ለአብዛኞቻችን ግልጽ ያልሆኑ መሰረታዊ ችግሮች አሉ። አንዳንዶቻቸን በእንግሊዘኛም ሆነ በአማርኛ አንድ ጽሁፍ አዘጋጅተን እንዲነበብለን ለድህረ-ገጾችም ሆነ ለመጽሄቶቸ እንዲወጣልን ወይም እንዲታተምልን በምንልክበት ጊዜ ከሳይንሳዊ ምርምርና ከኢምፔሪካል ጥናት ጋር የተያያዘ መሆኑና አለመሆኑ በግልጽ አይታወቅም። የፍልስፍናችንም መሰረት ምን እንደሆነ ግልጽ አይደለም። ዕምነታችንም ወይም የምናስተጋባው መልዕክት የሰውን አስተሳሰብ  በመቅረጽና ለአንድ ዓላማ ለመታገል ያለው ችሎታ እንዲዳብር ለማድረግ የምንፈልገውና የምንጽፈው ጽሁፍ አስተዋጽዖው የቱን ያህል መሰረት ይጣል አይጣል፣ ተቀባይነትን አግኝቶ በዚያው ላይ መስፋፋትና ክሪቲካል ትንተና ተጨምሮብት ይዳብር አይዳብር ጉዳያችን አይደለም። እንዲያው በደፈናው ካለምንም ፍልስፍናዊ ዕምነት፣ ሳይንሳዊ የአጻጻፍ ዘዴና የተወሳሰበ ኢምፔሪካል አመለካከት፣ `እኔ የማምነው በዚህ መልክ ነው፣  ከተቀበልክ ተቀበል ካለበለዚያም ተው` በሚለው አካሄድ የምንጽፈው ሀተታ አንዳችም ፍሬያማ ውጤት ላይ ሊያደርሰን አይችልም። እንዲያውም ጥራትን ከመስጠትና በፕሪንስፕልና በዓላማ ላይ ተመርኩዘን እንድንታገል ከማድረግ ይልቅ ውዝንብር ነዢ እየሆነ መጥቷል። ይህ ዐይነቱ ከሳይንስ ውጭ የሆነና፣  በግልጽ ከሚታዩ፣ ግን ደግሞ እንደተራ ወይም ኖርማል ነገር ሆኖ የሚወሰድ አጻጻፍ ባሻገር የማይታይና የማይተነተን አመለካከት ለሳይንስና ለተክኖሎጂ ዕድገት፣ እንዲያም ሲል ለዕውነተኛ የህዝቦች ነጻነት የማያመች፣ አንድ ህዝብ ዕውነትን ከውሸት ለይቶ ማየት የማይችልበት በመሆኑ የውስጥም ሆነ የውጭ ኃይሎች በፀረ-ዕድገትና በፀረ-ዲሞክራሲ አገዛዛቸው እንዲገፉበት የሚያደርግ ነው።

 

በጥንት የአውሮፓ የፍልስፍናና የሳይንስ ትግል ዓለም ውስጥ ነገሮችን በጥቁርና በነጭ እየፃፉ የማየትና፣ አንድን ሁኔታ እንደኖርማል አድርጎ የመውሰድ ባህል የለም።ሁሉም ነገር በዲያሌክቲክ መነጽር መታየትና ለፈተና መቅረብ አለበት። ስለዚህም ስለአንድ ነገር በሚጻፍበት ጊዜ ከቦታና ከጊዜ በሻገር፣ በአንድ ወቅት ውስጥ ተዋናይ የሆኑ ኃይሎች ምን ዐይነት ርዕይና ፍልስፍና እንደሚያራምዱና፣ ሚናቸውንም መረዳቱ ለምናደርገው የነፃነት ትግል ወሳኝ ሚናን ይጫወታል። የየአንዳንዱን ግለሰብም ሆነ ድርጅት አመለካከትና ብቃት እንዲሁም ሚና ለመረዳትም የምንችለው  በየኤፖኩ የተለወጡትን ውስብስብ ርዕዮተ-ዓለማዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችና፣ የበላይነትንና ተፆዕኖን(Sphere of Influence) ማስፋፋት በትንታኔያቸን ውስጥ አካተን መጻፍ የቻልን እንደሆን ብቻ ነው።  ከዚህ ስንነሳ በየአገሮች ውስጥ በምድር ላይ የሚታዩ የተበላሹ ሁኔታዎች፣ ድህነት፣ መዝረክረክ፣ የከተማዎች አገነባብ ዕቅድ አለመኖርና ውበት ማጣት፣ የጥቂቱ በሀብት መናጠጥና መባለግ… ወዘተ. የብቃት ዕጦት ውጤቶች ብቻ ሳይሆኑ፣ የሳይንሳዊ ግንዛቤ እጦትና በአንድ የተወሰነ አመለካከት መሰልጠን የሚፈጥራቸው ሁኔታዎች ናቸው።

 

በታሪክ ውስጥ ለዕውነተኛ ነፃነት ትግል ሲደረግ፣ በመጀመሪያ ደረጃ በአንድ ወቅት ስልጣንን የጨበጡ ኃይሎች የተበላሸ ወይም ደግሞ ህዝብን የሚበታትንና ወደ ድህነት የሚገፉ ፖለቲካዎች ለምን እንደሚከተሉ ዋናው የምርምር ዘዴ ነበር። ስለሆነም ትግሉ በግልጽ የሚታዩ ነገሮችን ከማይታዩ ነጥሎ በማውጣት በማይታየው ላይ ማነጻጸርና ወደ ውጭ አውጥቶ በመጻፍ ህዝብን ማሰተማርና አንድ ሀዝብ ለትክክለኛው የነፃነት ትግል እንዲነሳ ማድረግ ተቀዳሚው ተግባር ነበር። ስለሆነም በጊዜው የነበረው ትግል በስልጣን ላይ የነበሩትንና በጦርነት መንፈስ የሰከሩ ኃይሎችን አዕምሮ መመርመሪያው ዘዴ በስልጣን ላይ ያሉትን ኃይሎች የዕውቀት መሰረትና የሞራል ብቃት መመርመር ነበር። ከዚህም በመነሳት እነዚህ ኃይሎች ድርጊታቸውን በትክክል ይገነዘቡ አይገነዘቡ እንደሆን፣ ድርጊታቸው በተከታታይ ትውልድና በጠቅላላው ህብረተሰብ ስርዓት ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ጠንቅ በደንብ መረዳት መቻላቸውንና አለመቻላቸውን መመርመርና፣ ይህንንም በመመርኮዝ ትግል ማካሄድ ነበር። ትግሉ በቀጥታ እነሱን ማስወገዱ ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን፣ የሚመሩበትንም ጠቅላላ ፍልስፍናና ፖሊሲ በመመርመር እሱን በመዋጋት ዕውነተኛ የጭንቅላት ተሃድሶን ሊያመጣና አንድን ህዝብ ፈጣሪ ሊያደርግ በሚችል ፍልስፍናና ላይ መረባረብ ነበር። ይህም ማለት ትግሉ በአንድ ነጠላ ነገር ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን በጠቅላላው ሁኔታ ላይ የሚያነጻጽር ሲሆን፣ መምጣት ያለበትም ለውጥ ጠቅላላውን ሁኔታ ቀስ በቀስ እንዲለወጥ የሚያደርግና  በጸና መሰረት ላይ ሊቆም የሚችልና ዘላቂነት ያለው አገር መገንባት ነው። በዚያውም መጠን ሰላምና ዕኩልነትን ለማስፈን ነው።

 

በሌላ ወገን ግን የጥንቱ ሁኔታ እንደዛሬው የተወሳሰበና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዘረጋ ፖለቲካዊ፣ ሚሊታሪያዊና ኢኮኖሚያዊ አወቃቀር ስላልነበረና፣ በሺህ ድሮችም ከውስጡ ሁኔታ ጋር ያልተሳሰረ ስልነበር ትግሉ ንጹህ በንጹህ ብሄራዊ ነበር። እንደዛሬው አንድ ወይም ሁለት ኃያል መንግስታት በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን፣ በሚሊታሪና በኢኮኖሚ እንዲሁም በርዕዮተ-ዓለም አይለው በመሄድ የዓለምን ህዝብ ዕድል የሚወስኑበት ሁኔታ ስላልነበር ትግሉን ለማካሄድ በጣም ቀላል ነበር። ፍልሚያው ወደ ውስጥ ያተኮረና ግልጽም ነበር። አሁን ያለንበት የታሪክ ወቅት ግን እንደ ጥንቱ ግልጽ ስላይደለ ለነፃነት የሚደረገው ትግል እዝጅግ አስቸጋሪ ነው። ከሁለት መቶ ዐመት ጀምሮ የዓለምን ህዝቦች ዕድል ወሳኝ በመሆን አይሎ የወጣው የካፒታሊዝም ኢኮኖሚያዊ ክንውን ወይም ስልተ-ምርትና፣ በ19ኛው ክፍለ-ዘመን ደግሞ ወደ ሞኖፖሊዝምነትና ከዚያም ወደ ኢምፔሪያሊዝምነት የተለወጠው ፓለቲካዊ፣ ሚሊታሪያዊ፣ ርዕዮተ-ዓለማዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ክንዋኔዎችን የሚያካትተው በአንድ አገር ውስጥ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን የዓለምን ህዝብ ሁሉ ዕድል ወሳኝ በመሆን ለነፃነት የሚደረገው ትግል እጅግ እየተወሳሰበ መጥቷል። በተለይም እ.አ ከ1945 ወዲህ የተፈጠረው አዲስ የኃይል አሰላለፍ የብዙ አፍሪካ መንግስታትንና የላቲንና የአሽያን አገሮች የመንግስት አወቃቀር ጥንካሬና ድክመት ሊወስን ችሏል።

 

ስለሆነም በተለይም ባለፉት 60 ዐመታት በአገራችን ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የርዕዮተ-ዓለም ውዥንብር በመፈጠር ትግሉ በኮሙኒስቶችና የሊበራል ዲሞክራሲን መንፈስ በሚያስተጋቡና የህግ የበላይነት እያሉ በሚጮሁ መንግስታትና ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች አስመስሎታል። ይህ ዐይነቱ አካሄድ ሁላችንም በእንደዚህ ዐይነቱ በተወናበደ ርዕዮተ-ዓለም ውስጥ ገብተን እንድንዋኝ በማድረግ፣ የዕውነተኛውን ፍልስፍናና የነፃነት መንገድ በመሳት ወደድንም ጠላንም የአንድን አገር ነባራዊ ሁኔታና የተወሳሰበውን ዓለም ሁኔታ እንዳንገነዘብ በማድረግ ወደ ግብግብ እንድናመራ አድርጎናል። እ.አ ከ1989 ዓ.ም ወዲህ ደግሞ ዓለም ወደ አንድ መንደር እያመራች ነው ከተባለና የአሜሪካንን የነፃ ገበያና የነፃ ንግድ መርሆ ማራገብ ከተጀመረ ወዲህ የዓለም ህዝብ አመለካከት የባሰውኑ ተዘበራረቀ እንጂ ጥራት አግኝቶ በየአገሮችም ውስጥ ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰላምና ብልጽግና ሲሰፍኑና ሲዳብሩ አይታይም። እንደምናየው ዓለም በግሎባላይዜሽን ውስጥ ተጠቃለለች፣ ርዕዮተ-ዓለም የሚባልም ነገረ ጠፋ፣ ከእንግዲህ ወዲያ የሚኖረው ግጭት የባህል ግጭት ነው ከተባለ ወዲህ የዓለም ህዝብ ሲረጋጋና ሰላማዊ ኑሮ ሲገነባ አይታይም። ግሎባላይዜሽን አዲስ መዘዝ ይዞ በመምጣት እንደሸበርተኝነት የመሳሰሉት ዓለም አቀፋዊ ክስተቶች በመሆን መንፈሳዊ መረጋጋት እንዳይኖር ተደርጓል። ከዚህም ስንነሳ ብዙ ነገሮች ስለተምታቱ ሀቁን ከውሸቱ መለየት የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። በመሆኑም እኛም ራሳችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተስፋፋው የየአገሮችን ህይወት የሚያበላሸው ኢምፔሪሲስታዊ አመለካከት ሰለባ በመሆን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንድንወድቅ ተገደናል።

 

ከዚህ ስንነሳ በአብዛኛው ለድህረ-ገጾችም ሆነ ለመጽሄቶችና ለጋዜጦች ጽሁፍ የሚያቀርቡ ምሁራን ዘንድ የዓለምን ፖለቲካ አወቃቀርና፣ በአፍሪካና በአሜሪካን፣ እንዲሁም በተቀረው ኢምፔሪያሊስት አገር ያለውን ትስስር በደንብ ዘርዝሮ ለማቅረብ ምንም ጥረት አይደረግም። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ በየአገሮች ውስጥ ያለውን ወይም የሰፈነውን ህብረተሰብአዊ አወቃቀር፣ የማቴሪያል ሁኔታና የስነልቦና ባህርይ የመረዳት ችግር አለ። ስለሆነም ብዙዎቻችን ሁኔታዎችን በተሳሳተ መልክ ስለምናነብና በተሳሳተ የአሰራር ስልት ስለምንጠቀም  ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን። እንደሚታወቀው በተፈጥሮ ሳይንስም ሆነ በህብረተሰብ ሳይንስ ውስጥ ግልጽ የሆኑ ሳይንሳዊና ኢምፔሪካል የአሰራር ስልቶች አሉ። ችግሮችን ለመረዳት የሚያገለግሉና የተደራረቡ ችግሮችም እንዴት ቀስ በቀስ መፈታት እንደሚችሉ የሚያሳዩ። ስለሆነም ሳይንሳዊ የአሰራር ስልትንና አንዳች ዐይነት የሆነን ፍልስፍናዊ አመለካከት መሰረት ያላደረገ አቀራረብ የችግሩን መሰረት እንድንረዳ ከማድረግ ይልቅ እያሳሳተንና ውዥንብር እየነዛብን ነው። በተለይም ስለ አፍሪካ አምባገነኖችና ሚናቸው በየጊዜው የሚቀርበው የፖለቲካ ሀተታ ብዙ ግድፈቶች ይታይበታል። የአፍሪካን ህዝብ ዕድል ወሳኞች እነዚህ አምባገነን እየተባሉ የሚጠሩ አገዛዞች እንደሆኑ ተደርገው ነው እንጂ፣  በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደረግባቸውን የሚሊታሪ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጣልቃ-ገብነትና ጭነት ከቁጥር ውስጥ በማስገባት አይደለም ለሌላው ለማስተማር ጥረት የሚደረገው። በተወሰነ የአስተሳሰብ መነፅር በመመልከትና በመመራት የነገሮችን ሂደትና ዕድገት ለመገንዘብ ወደ ኋላ ትንሽ ተጉዞ ከመመርመርና፣ የአፍሪካን የህብረተሰብ ዕድገት ከአውሮፓው የህብረተሰብ አካሄድ ጋር እያነፃፀሩ(Comparative Studies)  የአፍሪካን አገሮች ችግር ከማጥናት ይልቅ አንድ ውሳኔ ላይ በመድረስ በየአገሮች ውስጥ ለደረሰውና ለሚደርሰው በደልና ድህነት ተጠያቂዎቹ አምባገነኖች ብቻ እንደሆኑ እንከሳቸዋለን። በዚህም ምክንያት የተነሳ ለዕውነተኛ ነፃነት የሚደረገውን ትግል እያዛነፍን ነው። እንደ ዕውነቱ ከሆነ  በዓለም አቀፍ ደረጃ ለዕውነተኛ ነፃነት፣ ለዕኩልነትና በአገሮች መሀከል በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግኑኝነት እንዲፈጠር የሚደረገውን ትግል ጠጋ ብሎ ለተመለከተ ወይም ለተከታተለ ሰው የሚገነዘበው ነገር ለእኛ ነፃነትና ዕድገት የሚታገሉንን እኛው ሳንሆን ከራሱ ከካፒታሊዝም አብራክ ስር የፈለቁ አንዳንድ የተገለጸላቸው ምሁራን ናቸው። የሚገርመውም ነገር እዚህ ላይ ነው። እኛው ተበዳዮችና ተበዝባዦች ቁጭት ይዞን በትጋት እያጠናንና እየተባበርን፣ እንዲሁም ሃሳብ ለሃሳብ እየተለዋወጥን በጋራ ለዕውነተኛ ነፃነት ከመታገል ይልቅ አንገታችንን ደፍተንና በመሸማቀቅ ከዋናው ችግር ለመሸሽ እንሞክራለን።ይህ ዐይነቱ መሸማምቀቅና ቁንጽል አስተሳሰብ፣ እንዲሁም ኢ-ሳይንሳዊ አመለካከት እንዴት ሊስፋፋና በጽሁፍ መልክ ሊስተጋባ ቻለ?

 

በኛ በኢትዮጵያውያኖች ዘንድ ያለው ዋናው ችግር በየጊዜው ጥያቄ ያለመጠየቅና፣ አንድ ቦታ ላይ ቆሞ በመገረምም ሆነ በማዘን አንድ ነገር ሲከሰት ሁኔታው ለምን በዚህ መልክ ሊከሰት ቻለ? ብሎ የነገሮችን መነሻና ርስ በርስ መያያዝ በዲያሌክቲካልና በሚታፊዚካል መነጽር ለመመርመር ያለመቻል ዋናው ምክንያት ይመስለኛል። ይህንን ቁንጽል አስተሳሰብና የነገሮችን ዕድገትና ውስብስበነት ለመረዳት ያለመቻል ደግሞ በራሱ በቂ ምክንያት አለው።

 

ለምሳሌ የኢትዮጵያን የትምህርት ስርዓትና ካሪኩለሙን ስንመለከት ክሪቲካል በሆነ መልክ የተዘጋጀ አይደለም። ሳይንሳዊና ክሪቲካል አመለካከት እንዲዳብር የተዘጋጁ የመማሪያ መጽሀፎችና አስተማሪዎችም ስለሌሉ ተማሪዎች ጨርሰው ሲወጡ የሚያስቡና የነገሮችን ሂደት ክሪቲካል በሆነ መልክ ከመመልከት ይልቅ አንድን ነገር በጥቁርና በነጭ በመሳል የአንድን ነገር ሁኔታና ዕድገት ለመረዳት በጣም ይቸግራቸዋል። ከዚህም የተነሳ አብዛኛዎቹ አቀራረቦችና ትንተናዎች ሎጂክን ያዘሉ አይደሉም። ስለሆነም ለነፃነት እታገላለሁ የሚለውን ሰው አቋምና ፍልስፍና ለመረዳት በጣም አአስቸጋሪ ነው። እንደዚሁ ዐይነቱ አስተሳሰብና አመለካከት የሚንፀባረቀው በአገር ቤት ብቻ ሳይሆን በውጭ አገርም የመማር ዕድል ባገኘውም ላይ ይታያል። ወደ ውጭ ለመማር ዕድል ያገኘው አብዛኛው በኒዎ-ክላሲካልና በኒዎ-ሊበራል አስተሳሰብ ክልል ውስጥ ወይም ደግሞ በኢምፔሪሲስት አስተሳሰብ ክልል ውስጥ ስለሚሽከረከርና፣ በዚህ አስተሳሰብ ስለሚታነጽ የሚኖርበትንና የዓለምን የፖለቲካ አወቃቀርና አካሄድ የመረዳት ችግር አለበት ብል የምሳሳት አይመስለኝም። ለምን እንደሆን አላውቅም አብዛኛው ተማሪ ቶሎ ብሎ የኒዎ-ክላሲካል አስተሳሰብ ያላቸው ፕሮፊሰሮች ጋር ስለሚወድቅና በነሱ አስተሳሰብ ስለሚጠመድ የዓለምንም ኢኮኖሚ አወቃቀርና በተለያዩ አገሮች ያለውን የተዛባ ዕድገትና እጅግ አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ለመረዳት ያዳግተዋል።  ሌላው ምክንያት ደግሞ፣ በውጭ አገር የሚኖረው አብዛኛው ተማሪም ሆነ ምሁር ሰፋ ያለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ባለበት አካባቢ ስለማይውልና ከሌላውም የመማር ዕድል ስለማያገኝ በአስተሳሰቡ ውስን ይሆናል። ተገልሎም ስለሚኖር የመወያየትንና የመከራከር፣ እንዲሁም ሃሳቡን በድፍረት የመግለጽ ችግር ይታይበታል።  ሌላው ደግሞ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም እንደ አሸን የፈለፈለው ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ውስጥ እየተመለመለ ስለሚገባና ቲክኖክራሲያዊ የአሰራር ልምድ ስለሚያካብት የዓለምንም ሆነ የየአገሩን ተጨባጭ ሁኔታ የማንበብ ችግር አለበት። በስራ ዓለም ላይ በሚቆይበትም ጊዜ ከተለያዩ የስራ ባልደረቦች ጋር ስለሚገናኛና ልዩ ዐይነት የፍጆታ አጠቃቀምና አነጋገር ባህርይ ስለሚለምድ ሁለንታዊና ክሪቲካል የሆነ አስተሳሰብና አመለካከት ሊያዳብር አይችልም። በዚህም የተነሳ ዕውነተኛ የሰብአዊነት ባህርይና ርዕይ ማዳበር ስለማይችል ስልጣን ላይ በሚወጣበት ጊዜ በዓለም ላይ የተስፋፋውን የብዝበዛና የጭቆና ስርዓት የሚያጠናክር ይሆናል። ለስልጣኔም ጠንቅ ይሆናል። የተገለጸለት አስተሳሰብ ከማዳበር ይልቅ ፊዩዳላዊውንና የአሜሪካን ኤምፔሪያሊዝምን የአመጽ አስተሳሰብ በማጣመር ወደ ጨቋኝነትና ታዛዥነት፣ እንዲያም ሲል ህዝብን ወደ መናቅ ያመራል። በዓለም የአገዛዝ የጭቆና ሂራርኪ ውስጥም ስለሚካተትና የምዕራቡ የተሳሳተ እሴት ዋና አቀንቃኝና አራማጅ ነው ተብሎ ሰለሚታይ በዚህ እየተደሰተና ውስብስብ ስምምነት ውስጥ እየገባ ድህነትን የሚያስፋፋና ብሄራዊ ነፃነት የሚገፍና የሚያስገፍፍ ይሆናል። በዚህም መልከ የረቀቀ የህዝብን ነፃነት የሚገፍ አምባገነናዊነት ይስፋፋል። በዚህም ምክንያት ያለበትን አገር የኑሮ ሁኔታ፣ የዕውቀት ጉዳይ፣ የኃይል አሰላለፍና የምርት ግኑኝነት፣ እንዲሁም ይህንን ለማጠናከር የሚወሰደውን ርዕዮተ-ዓለማዊ ሰበካ ለመመርመር የሚያስችለው ዕውቀት ስለማይኖረው ዕውነተኛ ሀብትን አፍሪና ስልጣኔን አምጭ አይሆንም ማለት ነው። አውቃለሁ የሚለው ደግሞ በቆንጆ ቃላቶችና `በተወሳሰበ` የአጻጻፍ ስልት በመጠቀም የነገሮችን ሂደት እንዳንረዳ በማድረግ አመለካከታችንን ያዛንፍል። ይህ አቀራረቤ ተራ ውንጀላ ሳይሆን ከብዙ ምርምርና ግንዛቤ በኋላ የደረስኩበት ድምዳሜ ነው። በኛ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለውን የተሳሳተ ግንዛቤ- በምዕራቡ ማስ ሚዲያ በተሳሳተ መልክ ፕሮፖጋንዳ ስለሚነዛና አብዛኛውም በስራ ስለሚጠመድ ይህ ዐይነቱ የተዛባ አመለካከትና ዕምነት የኛ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ነ- ለመረዳት ታች ያለውን የተሳሳተ የታሪክን ሂደት የማንበብ ችግር መጥቀሱ አቀራረቤን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል ብዬ እገምታለሁ።

 

ለምሳሌ በጣም ጥቂቶች ካልሆን በስተቀር ወደ ኋላ መለስ ብለን በካፒታሊዝም ዕድገትና መስፋፋት ውስጥ የተደረጉትን ውጣ ውረድ ሁኔታዎችንና ወንጀሎችን የምንጠይቅ በጣም ጥቂቶች ብቻ ነን። ለምሳሌ የጦርነትን ታሪክ ስንመረምር አብዛኛው ጦርነት የተካሄደው በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ ነው። የመቶ ዐመት፣ የሰላሳ ዐመት፣ የሰባት ዐመትና ከዚያ በኋላ ደግሞ ትናንሽ ጦርነቶች የተካሄዱት በምዕራቡ የካፒታሊስት ምድር ነው። እጅግ በአሰቃቂ መልክ ሴቶች እንደጭራቅ እየታዩ ይቃጠሉ የነበረው በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ፣ ያውም ሬናሳንስ፣ ፕሮቴስታንቲዝምና ኢንላይተንሜንት የተባሉ ጭንቅላትን የሚያድሱና ሰው ሰው መሆኑን እንዲገነዘብ የሚያደርጉ የአውሮፓ ህዝብ ከፊዩዳሉ ስርዓት እየተላቀቀ ወደ ካፒታሊዝም በሚሸጋገርበት ዘመን ነበር። ካፒታሊዝም እንደህብረተሰብ ስርዓት ተቀባይነት እያገኘ ከመጣም ወዲህ ህጻናት ሁሉ ሳይቀሩ ወደ ስራ ዓለም በመሰማራት የሚሰቃዩበት ዘመን ኮሙኒዝም ሳይሆን ካፒታሊዝም ነበር። ካፒታሊዝም ወደ ሞኖፖሊዝምነት ከተለወጠ በኋላ የመጀመሪያው ዓለም ጦርነት የተቀሰቀሰውና ለብዙ ሚሊዮን ህዝቦች ዕልቂት ተጠያቂ የሆነው የመጀመሪያው ዓለም ጦርነት የተቀሰቀሰው በካፒታሊስት አገር ነው። የሁለተኛው ዓለም ጦርነትም እንደዚህ በካፒታሊስት አገር ሲቀሰቀስ ወደ ሃምሳ ሚሊዮን የሚጠጉ ህዝቦች ህይወታቸው እንዳጡ ይታወቃል። ታሪኮች፣ ባህሎችና ከተማዎች ወድመዋል። እንደዚሁም ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ ይሁዲዎች የተቃጠሉት፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ቆዳቸው እንዲገፈፍ የተደረገውና በየቦታው የተገደሉት በሰለጠነው የካፒታሊስት ስርዓት ያውም በ20ኛው ክፍለ-ዘመን ነው። የጦርነቱም ዋናው አራጋቢዎች የጀርመን ፋሺዝም ብቻ ሳይሆን ስርዓቱም እንደነበርና፣ ይህም ደግሞ በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና በእንግሊዝ ሲደገፍ ዋናው ዓላማው በጊዜው በተቀናቃኝነት የወጣችውንና ሌላ ስርዓት በመመስረት ላይ የነበረችውን ሶቭየት ህብረትን ለመደምሰስና ሀብቷን ለመቆጣጠር ነበር። ስሌቱ ግን ስላልሰራ ሂትለር ጠላቶቼ ናቸው የሚላቸውን ሁሉ በቦምብ መደብደብ ጀመረ። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ጦርነት የካፒታሊዝም አንደኛው አካል ነው። በሰላም ሊያገኛቸው የማይችላቸውን መሬትም ሆነ የጥሬ ሀብት የግዴታ በጦርነት አማካይነት አገኛለሁ ብሎ ስለሚያምን ደካማ አገሮችን ይወራል። የሚፎካከሩትን ደግሞ በተለያዩ መንገዶች ለመዳካም ይጥራል። ይህ ካላዋጣው ደግሞ ወደ ጦርነት ውስጥ የሚገቡበትን ዘዴ በመፍጠር እንዲወጠሩ ያደርጋል። በዚህ መልክ ጦርነቶችን በየቦታው በመቀስቀስ ለብዙ ሚሊዮን ህዝቦች መሞት ምክንያት ይሆናል። ከ1950 ዓ.ም ጀምሮ  ደግሞ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች እየተባሉ በሚጠሩት አገሮች ውስጥ የተካሄዱትና ዛሬም የሚካሄዱትንም ጦርነቶች ስንመለከት፣ በመጀመሪያ በቀጥታ ወረራ፣ ቀጥሎ ደግሞ የውክልና ጦርነት(Proxy War) በማስፋፋት ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ባህርይ እንዲይዝ ያደረገው በተለይም የአሜሪካን ኢምፔርያሊዝም እንደሆነ ራሳቸው የሲአይኤ የቀድሞ ሰራተኞች ሳይቀሩ ያረጋግጣሉ። ብዙ አሜሪካዊያን የሊትሬቸርና የፖለቲካ ተንታኞች በሰፊው ዘግበዋል።

 

ሀቁ ይህ ከሆነ ታዲያ በኛ ምሁራን በምንባል ኢትዮጵያኖች ዘንድ ለምን የአስተሳሰብ ግድፈት ይታያል? ነገሩ ቀላል ነው። ላይ እንዳልኩት ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብለን የምንመረምርበት መሳሪያ ዲያሌክቲክና ሜታፊዚክሳዊ አመለካከት አይደሉም። ይህም ማለት የነገሮችን ሂደት ወይም ሁኔታ በተወሰነ የክስተት (Empiricism) መነጽር ብቻ ነው የምንመለከተው። ስለሆነም የአንድን ነገር ሁኔታ ወደ ውስጥ ገብቶና ውስብስብ ሁኔታዎችን መርምሮ አንዳች ውጤት ላይ ከመድረስ ይልቅ ቶሎ ብለን አንድ መደምደሚያ ላይ በመድረስ ለስልጣኔም ሆነ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የማያመች የወገናዊ ስሜት እንወስዳለን። በቂ ኢንፎርሜሽን ሳይኖረንና ሁኔታዎችን ከብዙ አቅጣጫ ሳንመረምር እጅግ የሚያሳስትና ጭንቅላትን የሚያደነዝዝ ሀተታ ነገር በመሰጠት ለዕውነተኛ ነጻነት የሚደረገው ትግል ተልከስክሶ እንዲቀር እናደርጋለን፤ እያደረግንም ነው። በዚህም ምክንያት የአንድን ችግር ዋና ምንጭ ለመረዳት ባለመቻላችን ትግላችንን ውስብስብ እያደረግነውና የአገራችንንም ዕድል እያበላሸነው ነው። ከዚህ ዐይነቱ ኤምፔሪሲስታዊ አመለካከት እስካለተላቀቅን ድረስና፣ ተራ የጋዜጣ ዐይነት ሪፖርት በማቅረብ ውንጀላን በአንድ ግለሰብ ወይም አገዛዝ ላይ ብቻ የምንለጥፍ ከሆነ የምንፈልገውን ነፃነት ማግኘት አንችልም። ይህ ማለት ግን አንድ ግለሰብም ሆነ አገዛዝ የችግር ምንጭ ሊሆኑ አይችሉም ማለት አይደለም። ጥያቄው ለምን የተስተካከለ ዕድገትና ዲሞክራሲያዊ አገዛዝ ሊያመጡና ሊያሰፍኑ አልቻሉም? ብሎ በምሁራዊ መነፅር መመርመር የምሁራን ኃላፊነት ነው። የለም አምባገነኖች ስለሆኑ ነው የተስተካከለ ዕድገት እንዳይኖር የሚያደርጉትና ጭቆናንም የሚያሰፍኑት የሚለው በምንም ዐይነት እንደዋና ምክንያት ሆኖ ሊተነተን አይችልም። ለምንድነው አምባገነን ለመሆን የቻሉት የሚለውንም መመርመሩ የግዴታ ችግሩን የመረዳት አንድ አካል መሆን አለበት። በሌላ አነጋገር ማንም ሰው በአፈጣጠሩ አምባገነናዊ ሆኖ ስለማይፈጠር የዕውነተኛ ምሁራን የምርምር ዘዴ አምባገነን እየተባሉ የሚወነጀሉትን ግለሰቦችና አገዛዞች የተወለዱበትን የህብረተሰብ ሁኔታ፣ የአደጉበትንና የተማሩትን ትምህርት፣ ከዚያም በኋላ በፖለቲካ ዓለም ውስጥ ሲገቡ ከተለያዩ ኃይሎች ጋር የሚፈጥሩትን ትስስርና የሚያስተጋቡትንና የሚጽፉትን ጽሁፍ ጠጋ ብሎ መመርመር ያስፈልጋል። ይህ ዐይነቱ የምርምር ዘዴ የተጠጋጋ መልስ ሊሰጠን ይችላል።

 

ሌላው በእኛ ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ በተለይም በድህረ-ገጾችና ለመጽሔቶች ወይም ለጋዜጦች አርቲክሎች ጽፈን እንዲወጣልን የምንልክ ምን ዐይነት ርዕይ ወይም ርዕዮተ-ዓለም እንዳለንና እንደምናስተጋባ በፍጹም ግልጽ አይደለም። እንደሚባለው ዕሴተ-አልባ ሳይንስ (Value free science) ወይም ዕሴተ-አልባ የስነ-ጽሁፍ አጻጻፍ ስልት የለም። ጋዜጠኞች እንኳ በዚህ በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ በርዕዮተ-ዓለም በመከፋፈል ነው የዚህን ወይም የዚያኛውን መደብ ጥቅም ለማስጠበቅ ደፋ ቀና የሚሉት። በተቻለ መጠን ያለው ስርዓት አማራጭ እንደሌለው ለማሳመን በሚሞክሩና ስርዓቱ በዚህ ሊቀጥል አይችልም፣ የግዴታ እዚህና እዚያ ቦታ የጥገና ለውጥ ያስፈልገዋል ብለው የሚታገሉ፣ ወይም ደግሞ ሌሎች ጥቂቶች ስርዓቱ እንዳለ መለወጥ አለበት እያሉ አስተያየት የሚሰጡም አሉ። የካፒታሊዝምን ጠቅላላ ዕድገት ከፍልስፍናና ከንጹህ የተፈጥሮ ሳይንስ አንጻር የሚመረምሩና በዚህ ዐይነት ካፒታሊስታዊ የጥሬ-ሀብት ጨራሽ የምርት አደረጃጀት ስልት የሰው ልጅና ተፈጥሮ ወደፊት ተቻችለው ሊኖሩ እንደማይችሉ ነገሩ የግዴታ መታረም እንዳለበት ግሩም ግሩም የሆነ የምርምር ጥናት የሚያቀርቡም አሉ። አንዳንዶቹ እንዲያውም አልፈው በመሄድ ለዚህ ዐይነቱ በማያቋርጥ የምርት ሂደተና የፍጆታ አጠቃቀም ዋናው ተጠያቂው በተወሰኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተመራማሪዎች በኒውተንና በዴካ ተፈጥሮን እንደበድን ተደርጎ የተወሰደው የሳይንስ አመለካከት በመስፋፋቱና ስር እየሰደደ በመምጣቱም ነው የሚሉም አሉ። በሬነ ዲካ ዕምነት በመንፈስና በሰውነት መሀከል ልዩነት ሲኖር፣ መንፈስ ህይወት ሲኖረው ሰውነት ግን በድን ነው። ተፈጥሮም እንደዚሁ በድን ነች የሚል ነው።  በተጨማሪም ወደ አንድ ነገር ለመድረስና ሳይንሳዊ መልክ ለመስጠት ነገሮችን እየሰበጣጠሩና በሚጠቅመው ነጠላ ነገር ላይ ማተኮሩ የምንፈልገውን ውጤት ይሰጠናል ይላል። ስለሆነም ይላሉ ክሪቲካል አመለካከት ያላቸው ፈላስፋዎች፣ ይህ ዐይነቱ ፍልስፍና በመስፋፋቱና በነጠላ ነገሮች ላይ ማትኮር፣ እንዲሁም ደግሞ በነገሮች መሀከል ያለውን የተወሳሰበ ቅንጅትና መደጋገፍ አለመረዳትና ይህንን ሳይንሳዊ መሰረት አለማድረግ፣ ካፒታሊዝም ሳይንስንና ቴክኖሎጂን የችግር መፍቺያና የኑሮ ማቃለያ ከማድረግ ይልቅ ወደ ንጹህ ትርፍ ማትረፊያ መሳሪያና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ-ሃሳብ ውስጥ እንዲያተኩር ስላደረገው ሰውና ተፈጥሮ ወደ ተራ ተበዝባዥነት ተለውጠዋል ይላሉ። በካፒታሊዝም የቴክኖሎጂ ምጥቀት የተነሳ ቴክኖሎጂ የችግር መፍቻ መሆኑ ቀርቶ በኢኮኖሚ ቁጥጥር ውስጥ በመውደቁ የሰው ልጅ የቲክኖሎጂ ተገዢ እንዲሆንና እንዲሰቃይ ተደርጓል። ይህንን በሚመለከት ጎተ ፋውስት ሁለት(Faust II) በሚለው ልበ-ወለድ የቲያትር ድርሰቱ ውስጥ በሚገባ አስቀምጦታል። የሰው ልጅም ፍላጎት ከማምረትና ፍጆታን ከመጠቀም ባሻገር መታየት የለበትም። ይህም ማለት በዚህ መንፈስ የሰለጠነው የሰው ልጅ ሌሎች የሰውን ልጅ ባህርዮች፣ ማለትም አርቆ አሳቢነት፣ ርህሩህነት፣ ሰብአዊነት፣ ሰነምግባራዊነትና ማህበራዊነት እንዲያጣና ወደ ንጹህ ኢኮኖሚያዊ መሳሪያነት በመለወጥ እየተፈራራ እንዲኖር ተገዷል። ገንዘብም የግኑኝነት መለኪያ እንደመሆኑ መጠን፣ ባለው ውስጣዊ `የሳይኮሎጂካል ኃይል` የሰውን መንፈስ በመቆጣጠር የሰው ልጅ ራሱን እንዲሸጥና ለሌላው ደንታ እንዳይኖረው ወደ ማድረግ ተቃርቧል። ይህ ወረቀት የሚመሰለውና ውስጥዊ ዋጋ(Intrinsic Value) የሌለው ወይም በምንም ነገር ያልተደገፈው የሰውን መንፈስ በመቆጣጠር አጭበርባሪዎችን፣ ጦረኞችንና አገር ሻጮችን በማፍራት እያንዳንዱ ዜጋ በራሱ አገር እየሰራ እንዳይኖር አግዷል። በተለይም የአሜሪካን ዶላር ዓለም አቀፋዊ የመገበያያና የሀብት ማከማቺያ መሳሪያ ከሆነ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ የፈጠረው መንፈሳዊ ኃይል የሰውን ልጅ የርስ በርስ ግኑኝነትና የየአገሮችን የስልጣኔ መሰረትና ራስ እያመረቱ ራስን መመገብ የሚለው መሰረታዊ መመሪያ እንዲወድም በማድረግ በብዙ ሚሊያርድ የሚቆጠር ህዝብ በድህነት ዓለም ውስጥ እንዲኖር ተገዷል። የአመራረትን ስልት ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው የፖለቲካ ስርዓቱ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እያጣ እንደመጣና በገዚዎችና በተገዚዎች መሀከል ያለው ግኑኝነት ከምንጊዜውም በላይ እየራቀ እንደመጣ እየተነተኑ ያስተምራሉ። በቴሌቪዠንም እየወጡ ይከራከራሉ። ራሳቸው ወግ-አጥባቂ ነን የሚሉ ሳይቀሩ የድሮ እሴት ያለው የአኗኗር ስልት መምጣት አለበት እያሉ የራሳቸውን የድሮ አቋም በጥያቄ ውስጥ እያስቀመጡት ነው። ከዚህ ስንነሳ የኛ የኢትዮጵያውያን ምሁራኖች አቋም ግራ የሚያገባ ነው የሚመስለኝ። እንደሚባለው እያንዳንዱ ነገር ስም አለው። ስርዓትም እንደዚሁ። ስለሆነም ለምን እንደምንታገል ግልጽ የሆነ አቋም ቢኖረንና ለሱ እንደጠበቃ ብንቆም የትግሉ መስመር መጥራት ብቻ ሳይሆን፣ ውስብስብ የሆነው ትግላችንም መልክ በመያዝ ኃይል ከመጨረስ ተቆጥበን ቶሎ ወደ ድል ማምራት እንችላለን።

 

ያም ሆነ ይህ በየሳምንቱ አምባገነን እያሉ የሚወተውቱት ምሁራን በቀላሉ ልንወጣው የማንችለው የችግሩን ምንጭ ያለመረዳት ችግር ውስጥ እየከተቱን ነው። በየሳምንቱ ከየአቅጣጫው በዚህ መልክ የሚቀርበው ትንተና ልክ እንደ ድረግ ጭንቅላታችን ውስጥ በመተከል አምባገነን ካለወረደ እያለን በመወትወት ለሌላና ለሳይንሳዊ ትንተና በር በመዝጋት ያለንን የተመሰቃቀለና የተወሳሰበ ችግር ለሌላ መቶ ዐመት እንዲተላለፍ እያደረግን ነው። ህዝባችንም ዘለዓለሙን ድህነትና ስቃይ ከእግዚአብሄር የተላከበት መጥፎ ዕድሉ አድርጎ በመውሰድ እጁን አጣጥፎ እንዲቀመጥ በማድረግ የውጭ ኃይል በተለያየ መልክ አገሩን ሲወርና ባህሉንና ታሪኩን ሲያበላሽ እንዲመለከት በማድረግ የታሪክ ወንጀል በመስራት ላይ ነን ብል የምሳሳት አይመስለኝም።

የፅንሰ-ሃሳብን አመጣጥና ትርጉም የመረዳት አስፈላጊነት !

 

         በታሪክ ውስጥ ብቅ ብቅ ያሉና አንድን ነገር ወይም ስርዓትን መግለጫ ፅንሰ-ሃሳቦች ዝም ብለው በጥራዝ ነጠቅ ወይም በአክራሪዎች የሚወረወሩ ሳይሆኑ፣ ከፍተኛ ዕውቀት በነበራቸውና በአላቸው የሰውን ልጅ ስልጣኔ በትክከለኛ መነፅር በሚመለከቱ ምሁራን ነበር። የፅንሰ-ሃሳቦችም አፈላለቅ በየታሪክ ኤፖኩ የነበሩትን አደገኛ፣ ለሰላምና ተቻችሎ ለመኖር የማያመቹ አገዛዞችን መግለጫዎች ነበሩ። ለምሳሌ ኢምፔሪያል ወይም ኢምፔሪያሊስት የሚለውን ፅንሰ-ሃሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙት ፕላቶና ቱካይዳይደስ(Thucydides) ሲሆኑ፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛውና በአራተኛው ክፍለ-ዘመን የነበረውን ከጦርነትና ከህዝቦች ዕልቂት ጋር የተያያዘ የጥቂት ገዢዎችን ብልግናና ቅጥ ያጣ ስረዓት መግለጫ ነበር።በሁለቱም ፈላስፋዎችና የታሪክ አዋቂዎች ዕምነት የዚያን ጊዜው የአቴኑ የመስፋፋትና ሌሎች ነፃ አገሮችን በራስ ተፅዕኖ ስር ማድረግ ዋናው ምንጩና ምክንያቱ ስግብግብነትና(Greed= pleonexia) ሶፊስታዊ የተሳሳተ ዕውቀት መሆኑን ያብራራሉ። በላቲን ቋንቋ ደግሞ ኢምፔሪያሊዝም ማለት መስፋፋትና ተፅዕኖን በሌሎች ህዝቦች ላይ ማሳደርና የመጨረሻ ላይም በቁጥጥር ስር ማዋል ማለት ነው። በተለይም በአራተኛው ክፍለ-ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት አቴን በእነፕሬክሊን አገዛዝ ወቅት ኃያል በነበረችበት ዘመን በስፓርታና በሌሎች ደካማ በነበሩ ግዛቶች ላይ ታደርስ የነበረውን ወረራና አሰቃቂ ድርጊት እነ ፕላቶን ይገልጹ የነበረው አገዛዙ ስነ-ምግባር የጎደለውና፣ በእኩልነት መርሆችና የሌሎችን ግዛቶች በማክበር ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ስላልነበር ይህ ዐይነቱ ወረራ ኢምፔሪያሊስት ነው እያሉ ነበር። በፕላቶንና በተከታዮቹ ዕምነት ይህ ዐይነቱ የሌሎችን መብት በእኩልነት መኖር አለማክበር ከውስጡ በእኩልነትና በዲሞክራሲያዊ አገዛዝ ላይ ካልተገነባ አገዛዝ ጋር በማያያዝ ነው። በሌላ ወገን ደግሞ እነ ፕሬክሊን በጊዜው የነበረውን ኃያልነታቸውንና ወራሪነታቸውን ይገልጹ የነበረው አቴን ከሌሎች የበለጠችና ለዚህም የተባረከች ስለነበረች በሌሎች ላይ የበላይነቷን የማስፈንና የእነሱን ዕድል የመወሰን መብት አላት ብለው ነበር የሚከራከሩት። ዛሬም በሞራል ውድቀት የበሰበሰው የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ስንትና ስንት ሺህ ህዝቦችን እየገደለና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦችንም ለመጨረስ የሚያስችለው መሳሪያ እየሰራ ከሌሎች አገሮች  በሞራል የምበልጥና የሰውን ልጅም ዕድል እኔ በምፈልገው መልክና ርዕይ ነው መቀረጽና መከተል አለበት እያለ የሚሰብከውና መንፈሳችንን የሚያጠበው ከእነ ፕሬክሊን በመማርና፣ እንዲሁም ደግሞ  የዓለምን ታሪክና የተለያዩ ህዝቦችን የባህል ዕድገትና ልዩነት መኖር አስፈላጊነት ባለመረዳት ነው። የራሱን ቤት ሳያጸዳና ወደ 40 ሚሊዮን የሚጠጋ አሜሪካዊ አንድ ሰው በቀን መኖር ካለበት የኑሮ ደረጃ እየኖረና የህክምናም ዕድል እንዳያገኝ በተደረገበት አገር እኔ ነኝ የሞራልና የስልጣኔ መመዘኛ ነኝ ማለት የስልጣኔንና የሞራልን ትርጉም በአፍጢሙ ደፍቶ የሰውን ልጅ ዕድገት ከዚህ አንፃር እንደማየትና ተግባራዊ ለማድረገም እንደመሞከር ይቆጠራል። ወደ ግሪኩ ስልጣኔም ስንመጣ፣  ይህ ዐይነቱ ኢምፔሪያሊስታዊ ፖለቲካና አመለካከት በእነ ፕሬክሊን ስልጣን ዘመን ተቀባይነት ያገኘውና የውጭ ፖሊሲ መመሪያም ሊሆን የበቃው በስልጣን አካባቢ የነበሩ ሰዎች ሶፊስታዊ አመለካከት በነበራቸው፣ እኩልነትን በሚቃወሙና ኦሊጋርኪያዊ አገዛዝን በሚሰብኩና በሚያስተጋቡ ፖለቲከኞች ስለተከበበ ነበር። በሶፊስቶች አመለካከት ማንኛውም ከአንድ አገዛዝ የፈለቀ ህግ ወይም መመሪያ እንደደንብ መወሰድና ማንኛውም ሰው ተግባራዊ ማድረግ ያለበት ነው። ፍልስፍናም ለሰው ልጅ አያስፈልገውም። አንድ አገዛዝ የሚለው ሁሉ ትክክል ስለሚሆን ማንኛውም ዜጋ እሱን መቀበል አለበት።  ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላም አዲሱ የአሜሪካን ኦሊጋርኪ መደብ የእነ ፕሬክሊንን የተዛባ አመለካከት እንዳለ በመውሰድ ከአገሩ አልፎ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት እንዲያገኝ አደረገ። ይህንን  ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ  ግሎባላይዜሽንና የነፃ ንግድን የዕድገት መሰረቶችና አጋዦች አድርጎ በመስበክ የዓለምን ህዝብ ማሳመን ቻለ። ዕውቀት፣ ንቃተ-ህሊና፣ በልዩ ልዩ ነገሮች የሚገለጽ የባህል ዕድገት፣ ሳይንስና ቲክኖሎጂ ሳይሆኑ ለአንድ ህዝብ ወይም አገር የሚያስፈልጉት፣ ንግድና ትርፍ ናቸው በማለት የሰው ልጅ የኑሮ ፍልስፍናና አመለካከቱ በእነዚህ ዙሪያ ብቻ እንዲሽከረከሩ ማድረግ ቻለ። ከዚህ ስንነሳ እነ ፕላቶንም ሆነ ሌሎች በኢምፔሪያሊዝም ዙርያ ምርምር ያደረጉ ምሁራን፣ ኢምፔሪያሊዝም የሚለውን ጽንሰ-ሃሳብ የተጠቀሙትና የሚጠቀሙት አንድን ተስፋፊ አገር ለመስደብ ሳይሆን ተስፋፊነቱንና ወራሪ ባህርይውን ለመግለጽ ነው። ስለሆንም ጽንሰ-ሃሳቡ ሳይንሳዊና ከአንድ ሁኔታ ጋር የሚገናኝ ነው።

 

ይህ ዐይነቱ ሌሎችን አገሮች መውረርና ስልጣኔያቸውን ማፍረስ በሮማውያን አገዛዝ ዘመንም የተስፋፋና፣ ለግሪክና ለግብጽ ስልጣኔ መፈራረስ፣ እንዲሁም ደግሞ በኋላ ላይ የጨለማው ዘመን ለተባለውና ፊዩዳሊዝም ለሚባለው እጅግ ወደ ኋላ የቀረ አገዛዝ በሩን እንደከፈተና ሁኔታውን እንዳመቻቸ የታሪክ ጸሀፊዎች በመረቃ መልክ ያስረዳሉ። የሮማውያንን አምፔሪያሊስታዊ መስፋፋት ልዩ የሚያደርገው በያዙበት ቦታ ሁሉ የአስተዳደር መዋቅራቸውን አንድ ወጥ ማድረግ ነበር። ይሁንና ግን ፖሊሲያቸው ሌላውን ከማስገበርና ለነሱ ተገዥ ከማደረግ የራቀ ፖሊሲ አልነበረም። ይህም ዐይነቱ በስልጣን መባልግና በተወሰነ ርዕዮተ-ዓለም ታውሮ ይህንን ብቻ ተቀበል፣ ይህንን ካልተቀበልክ ድምጥማጥህን አጠፋሃለው የሚለው አባባልና ተግባር በአውሮፓ ምድር ውስጥ የተስፋፋና ለብዙ ሚሊዮን ህዝቦች ዕልቂት ተጠያቂ እንደሆነ የታሪክ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ። እንዲያውም ብዙ የታሪክ ማስረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ከሆነ የሰው ልጅ የኑሮ ሁኔታ ሳይንስና ታሪክን በትክክል በተረጎሙና በተረዱ ምሁራን ቢመራ ኖሮ የሰው ልጅ ስቃይ በቀነሰ ነበር እያሉ ነው በደንብ የሚያብራሩት። ይህም ባለመሆኑ በአውሮፓ ምድር ውስጥ አሰቃቂ አገዛዝ መስፈን የቻለው ሃይማኖትን ወደ ሞራል ኮድነት ሳይሆን ወደ ንጹህ ርዕዮተ-ዓለምነት በመቀየርና የስልጣን መሳሪያ በማድረግ የሰውን ልጅ የስቃይ ኑሮ ለማራዘም በተነሱ ጥቂት ኃይሎች አማካይነት ነው። በካቶሊኮችና በፕሮፕቴስታንቶች ለሰላሳ ዐመት ያህል የተካሄደው የርስበርስ ጦርነት ዋናው መነሻው ሃይማኖት ሳይሆን የስልጣን ሽኩቻና ስልጣኔን ከመቀናቀን ጋር የተያያዘ እንደሆነ የታሪክ ዘጋቢዎች በደንብ ያስረዳሉ።

 

በዚህ ዘመን ኢምፔሪያሊዝም የሚለው ፅንሰ-ሃሳብ በደንብ ባይስፋፋም፣  የኋላ ኋላ በ17ኛውና በ18ኛው ክፍለ-ዘመን የነፃ ንግድ የሚለው መርህ ሲስፋፋ ዋና ዓላማው ኢምፔሪያሊስታዊ እንደነበር ግልጽ ነው። ከነፃ ንግድ ጋር የተያያዘው የኢምፔሪያሊዝም አገላለጽ ግን ከነፕላቶኑ የሚለይበት በቀጥታ የሌሎችን አገሮች ዕድገት ከመቀናቀንና፣ ደካማ አገሮችን ወደ ተራ ተበዝባዥነትና ጥሬ አምራችነት ጋር ከመቀየሩና ተገዢዎች እንዲሆኑ ከማድረግ ጋር የተያዘ በመሆኑ ነው።

ለካፒታሊዝም ማደግና መስፋፋት ከ17ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ በአውሮፓው ምድር ውስጥ ተቀባይነት ያገኘው

የህብረ-ብሄር ምስረታ ነው። ከ30ኛው ዐመት ጦርነት በኋላ ተቀባይነት ያገኘው የህብረ-ብሄር ምስረታ በጊዜው ብቅ ያሉትን

የፍጹም ሞናርኪዎች  ወደ ውስጥ የውስጥ ገበያን ማዳበር አስገደዳቸው። የአንድ አገር ጥንካሬ የሚመዘነው በጦርነት ብቻ ሳይሆን የግዴታ ጠንካራና ርስ በርሱ የተሳሰረ ኢኮኖሚ ሲገነባ ብቻ ነው የሚለው አስተሳሰብ በምዕራብ አውሮፓ የፍጹም ሞናርኪዎች የአገዛዝ ዘመን ተቀባይነትን አገኘ። ስለሆነም ወደ ውስጥ ሰፋ ያለና ጠንካራ ኢኮኖሚ ገንብቶ ወደ ውጭ ደግሞ መወዳደር መሰረታዊ የፍጹም ሞናርኪዎች ፖለቲካ ነበር። ይህ ዐይነቱ ወደ ውስጥ ያተኮረ ሰፋ ያለ የኢኮኖሚ ግንባታ ለከበርቴው መደብ ማየል ሁኔታውን ሲያመቻች፣ የፍጹም ሞናርኪዎች ደግሞ የውጭ ፖሊሲያቸውን የበለጠ በአመጽ ላይ እንዲመሰረትና ደካማ አገሮችንም ለመውረርና ተገዢያቸው የሚያደርግ ሆነ። ከአስራስምንተኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻና ከአስራዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ አፍሪካን ለመቃረም በአውሮፓ ኃያላን መንግስታት መሀከል የሚደረግ ፍጥጫና ሽቅድምድሞሽ ዋናው የዓለም አቀፍ የፖሊታክ ቅየሳ ሆነ። ይህ ዐይነቱ አካሄድ አጠቃላይ ለሆነ ኢምፔሪያሊስታዊ ወረራና ብዝበዛ በሩን ከፈተ። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ ካፒታሊዝም ዓለም አቀፋዊ የሆነ ሚሊታራዊ መልክ በመያዝ በብዙ አገሮች መሳሪያዎችም መሰራጨት ጀመሩ። በዚህ ዐይነቱ የወረራ ፖለቲካና ቅኝ ገዢዎችን በቁጥጥር ስር ማድረግ የተነሳ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ዋናው መሳሪያ በማድረግ ቀደም ብለው የማይታወቁ ዛሬ አፍጠው አግጠው የወጡና ብዙ የአፍሪካ አገሮችን የሚያተራምሱ የጎሳ ቦድኖች እንደአሸን ፈለቁ። ድሮ ርስ በርሱ ይጋባና በንግድ አማካይነት ይገናኝና ራሱን የሌላው አካል አድርጎ ይቆጥር የነበረ፣ የባሪያ አጋዛዝ፣ የቅኝ አገዛዝ፣ ቀጥሎ ደግሞ በአዲሱ ዓለም አቀፋዊ የስራ ክፍፍልና በተቀነባበረ ድህነትን ፈልፋይ በሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጎሰኝነት በማቆጥቆጥና ሁሉም በጎሳው መስክ በመመሸግና ከሌላው የተለየሁ ነኝ ብሎ በማመን ወደ ማያልቅ ጦርነት አመራ። አዲሱ ኢምፔሪያሊዝም ከላይ የሱን ጥቅም አስጠባቂና ተጎታች(Vasal) አገዛዝ በማስቀመጥና ህዝቡን በመከፋፈልና በጦርነት በመጥመድ ሀብትን በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሊዘርፍ የሚችልበትን መንገድ ዘረጋ። እዚህ ላይ መያዝ ያለበት ዘረኝነትና ፋሺዝም በካፒታሊስት ስርዓት ውስጥ የተፈጠሩና የስርዓቱ አንድ አካል የሆኑ ናቸው። ይህም የሚያሳየው ካፒታሊዝም እንደስርዓት በቅራኔዎች የተወጠረ መሆኑንና እንደሚባለው ሙሉ በሙሉ የሊበራል ዲሞክራሲ መሰረተ-ሃሳቦች የሰፈነበት ስርዓአት አይደለም ማለት ነው።

 

ለአብዛኛዎቻችን በሊበራል ዲሞክራሲ ለምናምንና፣ የሰውን ልጅ ዕድገት በዚህ ክልል ውስጥ ብቻ በማገናዘብ ለምንተነትንና ለማሳመን ለምንሞክር፣ በመሰረቱ ሊበራል ዲሞክራሲ እየተባለ የሚወደሰው የምዕራቡ ዲሞክራሲ መሰረቱ ካፒታሊዝም እንደሆነ ግንዛቤ ውስጥ የገባ አይመስልም። በአብዛኛዎቻችን ዕምነት ሊበራል ዲሞክራሲ እንጂ ካፒታሊዝም የሚባል ስርዓት የለም። ከዚህ ስንነሳ በብዞዎቻችን ዘንድ ያለው አመለካከት የሊበራል ዲሞክራሲን በሚያራምዱ አገሮች ውስጥ እኩልነት የሰፈነ ስለሆነ ማንኛውም ዜጋ በማንኛውም መስክ በመሳተፍ የኑሮውም ሆነ የፖለቲካና የማህበራዊ ደረጃውን ሊያሳድግ ይችላል የሚል ዕምነት አለ። በሌላ ወገን ግን ሊበራል ዲሞክራሲን እንደስርዓት መውሰድና ሌላውን ለማሳመን መሞከር ሳይንሳዊ አቀራረብ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን እጅግ አደገኛ አመለካከት እንደሆነ ብዙ ጥናቶች ያመለክታሉ። እነዚህ ክሪቲካል አመለካከት አላቸው በሚባሉ ምሁራን ትንተና መሰረት የሊበራል ዲሞክራሲን እንደ ስርዓት መውሰድና እኩልነት የሰፈነበት ነው ብሎ ሌላውን ለማሳመን መሞከር የካፒታሊዝምን ውስጣዊ ህጎች አለመረዳት ብቻ ሳይሆን፣ በገሀድ የሚታየውን የሀብት ቁጥጥርና ክፍፍል መዛባት፣ የፖለቲካና የመንግስትን በጥቂት ቡድኖች ስር መውደቅን መካድና ለተሻለ የዲሞክራሲ ሪፎርሞች የሚደረገውን ትግል ለማዘናጋት እንደመሞከር ነው ብለው ይናገራሉ።

 

ነገሩን ይበልጥ ለመረዳት ኢምፔሪያሊዝም በሚለው ፅንሰ-ሃሳብ ላይ ትንሽ እንቆይ።  ቢያንስ በቅኝ ግዛት ዘመን የነበረውንና በብዙ የአፍሪካ አገሮች ተግባራዊ የሆነውን የብዝበዛና የፀረ-ዕድገት የኢምፔርያሊስት ፓሊሲና ፕሮጀክት የሚክድ የለም ብዬ አምናለሁ። ከ16ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የባሪያ ንግድን ማስፋፋት፣ ቀጥሎ ደግሞ በ19ኛው ክፍለ-ዘመን ፖርቱጋል፣ ስፔይን ፈረንሳይና እንግሊዝ ተራ በተራ አፍሪካን ሲወሩና የግዛታቸው ተቀጥያ ሲያደርጉ ዋና ዓላማቸው ጥሬ-ሀብትን መበዝበዝና ወደ ምዕራብ አውሮፓ እንዳለ እያጋዙ ማምጣት ሲሆን፣ በዚያው መጠን ደግሞ በአፍሪካ አገሮች ውስጥ ምንም ዐይነት ህዝቦችን የሚጠቅም ዕድገት እንዳይመጣ ማገድ ነበር። ስለሆነም የአፍሪካ ገበሬና ነጋዴ ከለመደው ሰራና የስራ ክፍፍል እየተፈናቀለ ለምዕራብ አውሮፓ የጥሬ-ሀብት አምራች እንዲሆን ተገደደ። በዚህም ምክንያትና በተመሰረቱት የጭቆና አገዛዞች ምክንያት ወደ ውስጥ የስራ ክፍፍል እንዳይዳብርና ከተማዎችም እንዳያድጉ ሆኑ። ይኸኛው የስራ ክፍፍል ፕሮጀክትና የአፍሪካ አገሮችን ወደ ጥሬ-ሀብት አምራችነት መለወጥና ተበዝባዥ ማድረግ በተለይም የእንግሊዝ ካፒታሊዝም እያደገ ከመጣና ሌሎችን አገሮች ተበዝባዥ ማድረግ ያስፈልጋል የሚለው መሰበክ ከጀመረ ከ18ኛው ክፍለ-ዘመን ወዲህ ነው። እነ አዳም ስሚዝና እነ ሪካርዶ በቲዎሪ ደረጃ ያስቀመጡት ዓለም አቀፋዊ የስራ-ክፍፍል በመጀመሪያ ደረጃ የግዴታ በአመጽ በመደገፍ ተግባራዊ እንዲሆን መደረግ ተጀመረ።

 

እንምደሚታወቀው ከአስራስምንተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የሊበራል ዲሞክራሲ ስርዓት ሳይሆን በካፒታሊዝም ሎጂክ ላይ የተመሰረተ፣ ግን ደግሞ ለይስሙላ ያህል የተለያየ አመለካከት ያላቸውን ኃይሎች ሊያሳትፍ የሚችል የፓርሊሜንታሪ ዲሞክራሲ መቋቋም አስፈላጊ ሆነ። የፓርሊሜንታሪ ዲሞክራሲ መስፋፋት በጊዜው የነበረውን የኃይል አሰላለፍ ለውጥ የሚያመለክት ሲሆን፣ በሌላ ወገን ደግሞ የካፒታሊዝምን  አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ፕሮጀክት የሚያረጋግጥ አማራጭ የሌለው አንድ ወጥ ኢኮኖሚዊ የአመራረት ሆኖ የተወሰደበት ነው። የካፒታሊዝምንም ከተራ የሸቀጣ ሸቀጥ ምርት አንስቶ ወደ ተወሳሰበ የምርት ሂደትና፣ ከዚያም በኋላ ቀስ በቀስ ትናንሽ አምራች ኃይሎችን እያፈራረሰና ወይንም ደግሞ በራሱ ቁጥጥር ስር እያደረገ መምጣትና ወደ ኦሊጎፖሊስቲና ወደ ሞኖፖሊዝምነት መለወጥና ከባንኮች ጋር መዋሃድ ለተመለከተ መገንዘብ የሚችለው፣ እንደዚህ ዐይነቱ ኢኮኖሚያዊ የአመራረት ዘዴ በአንድ ክልል ብቻ ተወስኖ መቅረት እንደማይችል ነው። ይህም ማለት ከ18ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ካፒታሊዝም ውስጣዊ-ኃይል እያገኛና እየተስፋፋ በመምጣት ከአገር አቀፍ ደረጃ በማለፍ ዓለም አቀፋዊ ባህርይ መውሰድ እንደጀመረ ነው። ስለዚህም ገበያን ብቻ ሳይሆን ለዕድገትና ለመስፋፋት የሚያስፈልገውን የጥሬ-ሀብት ለማግኘት የግዴታ ሌሎች አገሮችን አይ በጦርነት፣ ከተቻለ ደግሞ  አዳዲስ መስበኪያ ዘዴዎችን እየፈጠረ በቁጥጥሩ ስር ማዋል አለበት። ከዚህ ስንነሳ ማርክስ እንደሚነግረን ሳይሆን፣ ካፒታሊዝም ሁሉንም አገሮች በሱ አምሳል በመቅረጽ በየአገሮች ውስጥ የተስተካከለ ዕድገት ማምጣት እንደማይችል ነው። ካፒታሊዝም በአገርም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባልተስተካከለ መልክ ብቻ ነው መስፋፋት የሚችለው።

 

ስለሆነም  በቅኝ ግዛት የተገነቡትን ወደቦችና ከተማዎች በደንብ ለተመለከተ፣ በጊዜው የኢምፔሪያሊስት ፕሮጀክት እነዚህን አገሮች ለማበልጸግና ዲሞክራሲን ለማስፈን ሳይሆን ብዝበዛን ለማጠናከርና፣ በከፈፍለህ ግዛ ፖሊሲ አማካይነት ጥቂቱን እየጠቀሙ አብዛኛው ደሃና ተራ ሰራተኛ ተበዝባዠ እንዲሆን ማድረግ ነው። ይህ ዐይነቱ አቀራረብ በእነሮዛ ሉክሰምበርግ በበቂው የተተነተነና ኋላም ላይ በሌሎች ክሪቲካል አመለካከት ባላቸው ምሁራን ተቀባይነት ያገኘ ሳይንሳዊ አመለካከት ነው። ይህም ማለት ኢምፔሪያሊዝም በየጊዜው ገፅታውን የሚለዋውጥና እንደየሁኔታው፣ ሳያመቸው በወረራ፣ ሲያመቸው ደግሞ አዳዲስ ዘዴዎችን በመፍጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተስተካከለ ዕድገት(Uneven Development)  እንዲስፋፋ የሚያደርግ መሆኑን ነው። ለምሳሌ በአብዛኛው የምዕራብ አውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ከሞላ ጎደል የተሰተካከለ ወይም ተመሳሳይ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የውስጥ ገበያ ሲኖር፣ በአፍሪካና በላቲን አሜሪካ ተመሳሳይ ዕድገት ሊኖር ያልቻለው ዋናው ምክንያት ኢምፔሪያሊዝም እነዚህን አገሮች ዕንቅፋት ስለሆነባቸው ነው። ዕድገታቸውን የሚያጨናግፍ ልዩ ልዩ ዘዴዎችን በየጊዜው ስለሚፈጥር ነው።

 

በዚህ መልክ ካፒታሊዝም ዓለም አቀፋዊ ባህርይ እየወሰደ ሲመጣ የጥሬ-ሀብት ዘረፋን በልዩ መልኩ በቁጥጥር ስር ለማዋል ዓለም አቀፋዊ የስራ ክፍፍል የሚለው ከተግባር ጀምሮ በቲዎሪ ደረጃም በየትምህርት ቤቱ ወይም በየዩኒቨርሲቲዎች የሚሰበክበት መሳሪያ ሆነ። እያንዳንዱ አገር በመጀመሪያ የራሱን የውስጥ ገበያ በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት አለበት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ማዳበር ያስፈልገዋል በሚለው ፈንታ፣ በዓለም አቀፍ የስራ ክፍፍል ውስጥ ቢሳተፍና በሩንም  ለዓለም አቀፋዊ ኩባንያዎች ቢከፍት ዕድገትን ሊጎናጸፍ ይችላል የሚለው ትጥቅ አስፈቺ ቲዎሪ በመስፋፋቱ ለኢምፔሪያሊዝም ቀዳዳ መግቢያ አመቺ ሁኔታ ፈጠረለት። እያንዳንዱ አገር በዚህ ዐይነቱ የስራ ክፍፍል ውስጥም በመካተቱ እንደ ተፈጥሮ ሀብት ዐይነቱና አቅራቢነቱ በዚያው ተወስኖ በመቅረት የየአገሮች ዕድል በእንደዚህ ዐይነቱ ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት ውስጥ በመካተቱ ዕድገቱ የተኮላሸ ሆነ። ምርታዊ ክንውንና የፍጆታ አጠቃቀም ዓለም አቀፋዊ ባህርይ በመውሰድ የስራ መስክ ዕድል ማግኘትና ገቢ አግኝቶ ፍጆታን ገዝቶ መጠቀም የማይችለው ሁሉ በእንደዚህ ዐይነቱ የስራ ክፍፍል ውስጥ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችል መሰለው።

 

ይህ ዐይነቱ ዓለም አቀፋዊ የኢምፔሪያሊስት ፕሮጀክት ከላይ በተዘረዘረው ጥንታዊ ወይም ክላሲካል መንገድ ብቻ የሚሰራ ሳይሆን የየአገሮችን ዕድል ለመወሰንና በዚያው ባሉበት ብቻ ረግተው እንዲቀሩ ሰፊና የተወሳሰብ ኔት-ወርክ ዘርግቷል። በዙሪክ/ስዊዘርላንድ መቀመጫውን ያደረገው የሂሳብና የፊዚክስ ተመራማሪዎች ቡድን ከረዠም ጊዜ ጥናትና ምርምር በኋላ ያገኘው ውጤት በአሁኑ ጊዜ የዓለምን ኢኮኖሚ የሚቆጣጠሩ 147 የሚሆኑ ትላልቅ የኢንዱስትሪ፣ የባንኮችና የኢንሹራን ኩባንያዎች እንዳሉ ነው። በኒዚህ ስር የሚተዳደሩ ሌላ  ከ40,000 በላይ የሚሆኑ ኩባንያዎች እንዳሉና፣ 147ቱ ትላልቅ ኩባንያዎች ከ40% በላይ የሚሆነውን ኔት-ወርክ ይቆጣጠራሉ። ከዚህም በላይ እነዚህ 147 ትላልቅ ኩባንያዎች ሜዲያዎችን፣ ፖለቲካን፣ ቲንክ-ታንክ ግሩፖችን፣ መንግስት-ነክ ያልሆኑ የዕርዳታ ሰጭ ድርጅቶችንና ልዩ ልዩ መንግስታዊ ኢንስቲቱሽኖችን በመቆጣጠር የሶስተኛውን ዓለም ዕድገት ብቻ ሳይሆን በካፒታሊስት አግሮች የኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ ተፅዕኖ በማሳደር የሀብት ክፍፍል በምን መልክ መዳረስ እንዳለበት ይወስናሉ። በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታትን፣ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትን፣ የዓለም ባንክንና የዓለም የንግድ ድርጅትን በመቆጣጠር በሶስተኛው ዓለም አገሮች ምን ዐይነት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ መሆን እንዳለበትና ዕድገቱም ምን መምሰል እንዳለበት ይወስናሉ። እንደምናየው የኢኮኖሚው ፖሊሲ በየአገሮች ውስጥ ለነሱ የሚያጎበድድ አዲስ ቡችላ መፍጠርና በአንድ በኩል ሀብት ወደ ካፒታሊስት አገሮች እንዲፈስ ማድረግ፣ በሌላ ወገን ደግሞ ድህነቱ ስር እንዲሰድ ማድረግና ዘለዓለማዊ ተመፅዋች ማድረግ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ትላልቅ የአሜሪካንና የእንግሊዝ ባንኮች የክሬዲት ካርዶችን፣ ማስተር ካርድ፣ ቪዛ ካርድና ይህንን የመሳሰሉትን በመቆጣጠር በቀጥታ ሀብት ከልዩ ልዩ አገሮች ወደ ካፒታሊስት አገሮች እንዲፈስ ያደርጋሉ። የወደፊቱ ትልቁ ፕሮጀክት ደግሞ የወረቀት ገንዘብን እንዳለ አጥፍቶ በኤሌክትሮንኪስ ገንዘብ(RFID=Radio Frequency Identification) መተካትና የዓለምን ሀብት ብቻ ሳይሆን የዓለምንም ህዝብና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር አደገኛ ናቸው የሚላቸውና የሚጠረጥራቸውን ማስወገድ ነው ። ይህ ቺፕ ገንዘብ የየሰውን መለያ ቁጥር፣ የስራ ህይወት ታሪክ፣ ትምህርት፣ ሃይማኖት፣ ጎሳና ሌሎችም የወንጀለኛ ሪኮርዶችን የሚይዝ ነው። ከዚህም ባሻገር የሶስተኛው ዓለም አገሮችን እየደለሉና እየመከሩ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል እንዲሆኑ ማድረግና በነፃ ንግድ ስም ገበያቸውን ልቅ እንዲያደርጉ ማስገደድ የየአገሩ ገበያዎች ሙሉ በሙሉ በትላልቅ የአሜሪካንና የአውሮፓ የዘር ፋብሪካዎችና የእርሻ ኩባንያዎች ቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ የማምረት ኃይላቸውን ማዳከም ነው። በዚያውም መጠንም በላቦራቶሪ ውስጥ የተዳቀለ የእህል ዘር (Genetically Modified Seed) በማስገባት ለብዙ ሺህ ዐመታት ያካበቷቸውን የእርሻና የእህል ዘር እንዲያጡ በማድረግ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ ማድረግ ነው። ይህ ዐይነቱ ዓለምን አንድ ወጥ የማድረጉ አካሄድ የተፈጥሮን ህግ የሚፃረርና ለሰው ልጅ ጤንነት ጠንቅ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሰላም የሚያናጋውና ረሃብንም ሊያስከትል የሚችል ነው። በዚህ መልክ በአገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም አምባገነናዊ አገዛዝ በመስፈን የዓለም ህዝብ መብት በሙሉ ይገፈፋል ማለት ነው።

 

ይህም የሚያመለክተው የካፒታሊስት አገር መንግስታት የእነዚህ ትላልቅ ኩባንያዎች ተጠሪዎችና ስራ-አስፈጻሚዎች እንጂ የህዝቦቻቸው ወኪሎች እንዳልሆኑ ነው። የተለያየ ስም እየያዙ በየአራት ዐመቱ የሚመረጡ፣ ዲሞክራቶች፣ ሊበራሎች፣ የክርስቲያን ዴሞክራቶችና ሶሻል ዴሞክራቶች ወይም ሶሻሊስቶች ሙሉ በሙሉ የሚያገለግሉትና የሚያስጠብቁት በየአገራቸው የሰፈነውን የሚሊታሪ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስና የፋይናንስ ድርጅቶችን ጥቅም ነው። ሰለሆነም የተለያየ ስም ይዘው ስልጣን ላይ የሚወጡ ፓርቲዎች በውጭ ፖሊሲያቸው ተመሳሳይ ናቸው። ያላቸውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚን የሚሊታሪ ኃይል ተገን በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጦርነትን የሚያስፋፍ እንጂ የሰላምና የዕኩልነት አፍቃሪዎችና አስከባሪዎች አይደሉም። በየአገሩ ውስጥ አዳዲስ ሰፊውን ህዝብ ይጠቅማሉ የሚባሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ከመጀመሪያዎኑ ተቃውሞ የሚገጥማቸው-ለምሳሌ በአሜሪካን ኦባማኬር የሚባለው ጥገናዊ ለውጥ- የትላልቅ ኩባንያዎችን ትርፍ ይጋራሉ ተብለው ስለሚገመቱ ብቻ ሳይሆን፣ የዝቅተኛው ህብረተሰብ ክፍል የኢኮኖሚ ስታተስ በዚያው መቅረት አለበት ከሚለው ኋላ-ቀር አስተሳሰብም በመነሳት ነው። እዚህ ላይ ግን የኦባ አስተደዳር ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈልገው ፖሊሲ በሙሉ ከኒዎ-ሊበራሊዝም አስተሳሰብ የጸዳ ነው ማለት አይደለም። የኦባማ አስተዳደርና የፖሊሲ አማካሪዎችን ለተመለከተ ከዎል-ስትሪት ጋር የጠበቀ ግኑኝነት የነበራቸውና ያላቸው ሲሆን፣ ቀውሱን ለመግታት በሚል በዝቅተኛ ወለድ አማካይነት ለዎል-ስትሪት ሰዎች ነበር ገንዘቡን የሚያስተላልፉት። በዚህም ምክንያት የተነሳ የስቶክ ገበያውና ክፍያው(Share) እያደገ ሲመጣና ሀብታሙ የበለጠ ሀብታም ሲሆን፣ ኢንዱስትሪዎች ግን ወደ 15 ሚሊዮን ለሚጠጋ የስራ አጥ የስራ መስክ ሊከፍቱ በፍጹም አልቻሉም። ለዚህም ነው እስከዛሬ ድረስ ቀውሱ በመጠኑም ቢሆን ሊፈታ ያልቻለው። ይህ ብቻ ሳይሆን አሜሪካንን በተጨባጭ የሚገዛው የሚሊታሪ ኢንዱስትሪው ኮምፕሌክስና ከሱ ጋር የተሳሰሩ ወደ አስራስምንት የሚጠጉ የስለላ ድርጅቶች ናቸው። ይህ ዐይነቱ የአገዛዝ አወቃቀር ከአሜሪካን አልፎ ዓለምን ለመቆጣጠርና ዓለም አቀፋዊ አገዛዝ ለማስፈን የሚያስችል ኔት-ወርክ ዘርግቷል።  የኤንሴአ(NSA) ሁኔታን ስንመለከት ይህንን ነው የሚያረጋግጠው። በአሁኑ ወቅት ኳንተም ኮምፒዩተር የሚባል በመስራት ዓለምን እንዳለ ለመቆጣጠር በመዘጋጀት ላይ ነው። ይህንን ስንመለከት እኛ ለባራክ ኦባማ የምንጽፈው የልመና ደብዳቤና ጩኸት ተደማጭነት ማግኘት ያልቻለውና የማይችለው፣ በጠቅላላው የአሜሪካን አገዛዝ ነፃ ንግድን የሚያራምድና፣ ይህም ነፃ ንግድ የአሜሪካንን ኮርፖሬሽኖች የሚጠቅም በመሆኑ በኛ አገር ዲሞክራሲያዊ ለውጥና ዕድገት መምጣት ከዚህ ዐይነቱ የነፃ ንግድ መንፈስ ጋር ስለማይጣጣሙ ነው።  ዓለምን በሱ ቁጥጥር ስር ከማምጣት ህልምና ስትራቴጂ ጋር በፍጹም የሚሄዱ አይደለም።  ባለፉት 60 ዐመታት እንደተረጋገጠው አሜሪካን በአገሮች ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ያስፈልጋል ሲል የሱን ጥቅም የሚጻረሩ አገዛዞችን ለማስወገድና በሱ የጥቅም ክልል ውስጥ ለማምጣት እንጂ በአንድ አገር ውስጥ ዕውነተኛና ህዝባዊ ዲሞክራሲ ተግባራዊ እንዲሆን ስለሚፈልግ አይደለም።

 

 

ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ የተፈጠረው አዲስ ሁኔታ !

         እንደሚታወቀው ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም በአሸናፊነት የወጣበት ወቅት ነው። ከ1944 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን የወርቅ ክምችትና የውስጥ ሰፊ ገበያና የኢንዱስትሪ መሰረት ተገን በማድረግ ለሱ በሚስማማው መልክ የዓለምን ገበያ ያዋቀረበት ሁኔታ ነበር። በዚህም መሰረት እንደ እነ የዓለም አቀፍ የገንዝብ ድርጅት፣ የዓለም ባንክና የዓለም የንግድ ድርጅት ይህንን አዲሱን የአሜሪካን ዓለም አቀፋዊ የኢምፔሪያሊስት ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግና ተቀጥያ መንግስታትን ለማፍራት የተቋቋሙ ድርጅቶች ናቸው። በዚያው መጠንም እነዚህ ዓለም አቀፋዊ ባህርይ ያላቸው የሚመስሉ ድርጅቶች በዕድገት ስም እያሳበቡ በምሁር ደረጃ ያልበለጸጉ አገሮችን እንዲያሳስቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመንደፍ በብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ከውስጥ ዕድገት እንዳይመጣ እገዳ የሚያደርጉ ድርጅቶች ሆነው የወጡበት ወቅት ነው። በተጨማሪም፣ በተዘዋዋሪና ግልጽ ባልሆነ መልክ የዕድገትን ፖሊሲ ለማጨናገፍ በማይቻልበት አገሮች ውስጥ የግዴታ የመንግስት ግልበጣ ሙከራ በማድረግ ፋሺሽታዊ መንግስታትን በማቋቋም ጠቅላላውን የዕድገት ፕሮጀክት ማክሸፍ ሌላው የአሜሪካን ኢምፔርያሊዝም ፕሮጀክት ነበር። ከኢራን እስከ ቺሌ የተደረጉትን የመንግስት ግልበጣዎች ለተመለከተና በህዝብ የተመረጡ ፕሬዚደንቶችን ማስገደል ዋና ዓላማው በሶሻሊዝም ስም በማሳበብ በየአገሮች ውስጥ ህዝቡን የሚጠቅም የተስተካከለ ዕድገት እንዳይመጣ ማገድ ነበር። በዚያው መጠንም የኢንዱስትሪ ከበርቴ መደብ ብቅ እንዳይልና ተወዳዳሪ እንዳይሆን ማደናቀፍ ነበር። ከብራዚል እስከቺሌና አርጀንቲና ድረስ በ60ኛው መጨረሻና በ70ኛው ዓ.ም ያለቁትንና የተገደሉትን ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ስንመለከት አብዛኛዎች የዕውነተኛ ዲሞክራሲ ናፋቂና ለሚድል ክላስ ማበብ የሚያመቹ ነበሩ። በሌላ አነጋገር ሶሾሊዝምን የሰው ልጅ ነፃነት ዋናው ጠላት አድርጎ በማቅረብ በመንግስታት የተደገፉና የሚደገፉ የኢንዱስትሪ ፖለቲካ እንዳይካሄድ ማደናቀፍ ዋና ዓላማው ሶሻሊዝምን መዋጋት ሳይሆን በሶስተኛው ዓለም አገሮች ካፒታሊስታዊ ዕድገት እንዳይመጣና ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ነፃነትን እንዳይቀዳጁ ማድረግ ነበር። ለምሳሌ የምዕራብ አውሮፓንንም ሆነ የአሜሪካንን የካፒታሊዝምን ዕድገት ታሪክና ሂደት ስንመለከት የኢኮኖሚ ፖሊሲያችው ዋናው መሰረት መርካንትሊዝም ወይም በመንግስት የተደገፈ ሁለንታዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነበር።

 

ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው?  የካፒታሊዝምን የዕድገት ታሪክ በደንብ ላጠና የእነ አዳም ስሚዙ የረቀቀው እጅ(Invisible Hand) ተግባራዊ ሊሆን የቻለው በመጀመሪያውኑ ቀደም ብለው ለዚህ የሚያመቹ የባህልና የህብረተሰብአዊ ለውጥና አመለካከት ስለተካሄዱ ነው። በአውሮፓ ምድር ውስጥ የግለሰብ ተሳትፎና ሚና ቀስ እያለ እያደገ  የመጣው በመጀመሪያ በሬናሳንስ አማካይነት ሲሆን፣ ይህ ስላልበቃ የግዴታ የሃይማኖት ክፍፍል እንዲደረግ በማድረግ ፕሮቴስታንቲዝም ለአስተሳሰብ መዳበር አመቺ ሁኔታን ፈጠረ። ለምሳሌ የማክስ ዌበርን የካፒታሊዝም መንፈስና የፕሮቴስታንቲዝምን ስነ-ምግባር የሚለውን ግሩም ስራ ስናነብ የምንረዳው ፕሮቲስታንቲዝም በበኩሉ የቱን ያህል ለካፒታሊዝም ዕድገት አመቺ ሁኔታን እንደፈጠረ እንገነዘባለን። ከዚህም ባሻገር የፕሮቴስታንት ስነ-ምግባር ቀስ በቀስ ተግባራዊ መሆን ለካፒታሊዝም ሙሉ በሙሉ በአሸናፊነት መውጣት በቂ ስላልነበር በ17ኛው ክፍለ-ዘመን የግዴታ የኢንላይተንሜንት አብዮት ማካሄድ አስፈለገ። የሞናርኪስቶች የዲስፖቲዝም አገዛዝ ዘመን ፈተና ውስጥ የወደቀበትና የሪፑብሊክ ምስረታ መንገዱ የተቀደደበት ዘመን ነው። ከዚህም ጊዜ ጀምሮ ማለት ይችላል የዲስፖቲዝም አገዛዝ እየተዳከመ ሲመጣና የከበርቴው አገዛዝ ቦታውን ሲወስድ ግለሰብአዊ አስተሳሰብና ድርጊት ህብረተሰብአዊ ተቀባይነት እያገኙ መምጣት ቻሉ። ይህም ማለት ግለሰብአዊነት ከሰው ልጅ ጋር አብሮ የተወለደና ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ያለ ሳይሆን፣ በአንድ የታሪክ ወቅት በተከሰተ ሁለንታዊ የአስተሳሰብና የባህል፣ እንዲሁም የኢኮኖሚ አወቃቀር ለውጥ የተነሳ የተፈጠረ ድርጊት ነው ማለት ይቻላል። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ በተለይም የተፈጥሮ ሳይንስ የበለጠ የመፈናፈኛ ዕድል እያገኘ በመምጣቱ ለካፒታሊዝም ዕድገት መሰረት ጣለ። ይህም ሆኖ የግዴታ የመንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ ገብቶ የማኑፋክቱር አብዮት እንዲካሄድ ማድረግና የውስጥ ገበያ እንዲስፋፋ መንገዱን ማዘጋጀት የየመንግስታቱ ዋና ፖሊሲ ነበር። ይህም የሚያመለክተው ግለሰብአዊነትና ግለሰብአዊ ነፃነት ወደ ተግባር ሊለወጡ የሚችሉት የግዴታ የባህል ለውጥ ሲካሄድ ብቻና ግለሰቦች ራሴ ጥሬ ግሬ ሀብትም ማግኘት እችላለሁ የሚለውን ሲረዱ ብቻ እንድሆነ የአውሮፓው የህብረተሰብና የኢኮኖሚ ዕድገት ታሪክ ያረጋግጣል። ከባህልና ከህብረተሰብአዊ ለውጥ በፊት የግለሰብ ድርጊቶች በታሪክ ውስጥ አልታዩም። ወይም ደግሞ በተራ አዋጅ የሚሆኑ አይደሉም።  በአንፃሩ ግን ወደ ሶስተኛው ዓለም ወደሚባሉት አገሮች ስንመጣ በመንግስት የሚደገፉ ወይንም የሚወሰዱ ዕርምጃዎች ሁሉ ከሶሻሊዝም ጋር አየተገናኙ ዘመቻ ይካሄድባቸዋል፤ መንግስታቱ በዚያው ሲገፉበት ደግሞ የመንግስት ግልበጣ ሙከራ ይደረግባቸዋል። በአንዳንድ አገሮችም ፕሪዚደንቶች ይገደላሉ። ለዚህም ዋናው ምክንያት ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት ሶሻሊዝምንም ለመዋጋት ሳይሆን የሶስተኛው ዓለም አገሮች፣ በተለይም ላቲን አሜሪካና አፍሪካ አውሮፓውያን የሄዱበትን የዕድገት ፈለግ ወይንም የመሰላል መወጣጫ ዘዴ መከተል የለባቸውም፤ ባሉበት ቀጭጨው መቅረት አለባቸው ከሚለው አደገኛ አመለካከትና የሰውን ልጅ እኩልነት ከሚፃረር አስተሳሰብ በመነሳት ነው።

 

ወደ አፍሪካ ስንመጣ ከቅኝ አገዛዝ  ተላቀው የፖለቲካ ነፃነት የተቀዳጁ አገሮች በሙሉ ከባድ ፈተና ውስጥ ወድቀው ነበር። በመጀመሪያ ደረጃ የወረሱት ኢንስቲቱሽንና የመንግስታት አወቃቀር የቅኝ ግዛት አስተዳዳሪዎች ያዋቀሯቸውና ለብዝበዛ የሚያመቹ ነበሩ። በሌላ አነጋገር ለውስጥ የኢኮኖሚና የህብረተሰብ ዕድገት የሚያመቹ አልነበሩም። በሁለተኛ ደረጃ፣ ብዙ አገሮች ከፍተኛ የሆነ የምሁር ክፍተት ነበራቸው። አሁንም በሌላ አነጋገር ከውጭ የሚመጣውን ማንኛውንም የኢኮኖሚ ፖሊሲና ርዕዮተ-ዓለም ለመመርመርና ለየአገሩ ተስማሚ ሊሆን የሚችል የኢኮኖሚና የሶሻል ፖሊሲ የሚነድፍ ሰፋ ያለ የምሁር ኃይል አልነበራቸውም። በሶስተኛ ደረጃ፣ አብዛኛዎቹ አገሮች ወደ ውስጥ የተሰፋፋ የስራ ክፍፍልና የውስጥ ገበያ አልነበራቸውም። በዚህም ምክንያት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙት ዓለም አቀፋዊ ኢንስቲቱሽኖችና የዓለም ገበያ የአፍሪካን ዕድገት ወሳኞች ነበሩ። አሁንም ናቸው። ስለሆኑም ሁሉም አገሮች ተመሳሳይ የሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንዲከተሉ ተገደዱ። የህዝቦቻቸውን መሰረታዊ ፍላጎት እያሟሉ ቀስ እያሉ ከማደግ ይልቅ በተወሰኑ የፍጆታ ምርቶች ላይ ያተኮረ የምትክ ኢንዱስትሪ ተከላ(Import-Substitution Industrialization) ኢምፔርያሊስታዊ ፕሮጀክት በመከተል ዕድገታቸው እንዲሰናከል ወይም እንዲጨናገፍ ሆነ። የባህልና የትምህርት ለውጥም ስላልተካሄደ ሰፋ ያለ ዕድገት ማምጣት አልተቻለም። ከዚህ በሻገር በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር የነበሩ አገሮች እስካሁን ድረስ ነፃ የሆነ የራሳቸው የገንዘብ ፖሊሲ እንዳይኖራቸው ተደረገ። የውጭ ከረንሲያቸው በመጀመሪያ ደረጃ ከፍራንክ ጋር፣ አሁን ደግሞ ከኦይሮ ጋር በመያያዙ የገንዘብ ፖሊሲያቸውን እንደያስፈላጊነቱ ሊለዋውጡ እንዳይችሉ ተደረጉ። ይህ ብቻ ሳይሆን በፈረንሳይ ቁጥጥር ስር የነበሩ ወደ አስራአራት የሚጠጉ አገሮች ነፃነታቸውን ተቀዳጁ ከተባለ በኋላ ከውጭ ንግድ የሚያገኙትን የውጭ ገንዘብ 60% የሚሆነውን የፈረንሳይ ማዕከላዊ ባንክ ውስጥ ነው ማስቀመጥ ያለባቸው። በውጭ የተከማቸውን የወርቅና የውጭ ምንዛሪ መጠንም የማወቅ መብት የላቸውም። እነዚህ አገሮች አሁንም በቅኝ ግዛት ቁጥጥር ውስጥ እንዳሉ ሆነው ነው የሚታዩት።  በዚህ መልክ ዕድገታቸው እንዲጨናገፍና ዕውነተኛ ነፃነት እንዳያገኙ ሆኑ። ይህም የሚያመለክተው የአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች አምባገነንነት ከውጭ ከመጣውና በአገዛዞች ላይ ከተጫነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ በዚህ ዐይነቱ ጭቆናዊ አገዛዝ ፈረንሳይና ሌሎችም ኢምፔሪያሊስት አገሮች በቀጥታ እንዳሉበት ነው። የአምባገነንነትና የጭቆናው አገዛዝ፣ እንዲሁም የፀረ-ዕድገት ፖሊሲው አንድ አካል ናቸው ማለት ነው።

 

ወደ የመንግስታቱ የመኪና አወቃቀር ስንመጣ፣ ከሲቪል ቢሮክራሲው አንስቶ እስከ ጸጥታ ኃይሉ፣ ፖሊስና ወታደር ድረስ አንዳንዶች በአሜሪካን ርዕዮተ-ዓለም ሲሰለጥኑ፣ የተቀሩት ደግሞ በእንግሊዝና በፈረንሳይ የሚሊታሪ ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ቁጥጥር ስር ያሉ እንጂ በነፃ በየአገሮች መሪዎች የየአገሩን ሁኔታ በሚመለከት ረገድ የተደራጁ አይደሉም። በዚህም ምክንያት በስድሳኛውና በሰባኛው፣ አልፎ አልፎም በሰማኒያኛው ዐመተ ምህረቶች የተካሄዱት ወደ ስድሳ የሚጠጉ የመንግስት ግልበጣዎች በሙሉ በፈረንሳይ፣ በእንግሊዝና በአሜሪካን የተካሄዱ ናቸው። የየመንስታቱም አምባገነናዊ ባህርይ ላይ ከገለጽኩትና ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ከተቀናጀው የዓለም ኢኮኖሚ፣ የፓለቲካና የሚሊታሪ ሁኔታ ጋር የሚያያዝ እንጂ የአፍሪካ መሪዎች በአፈጣጠራቸው አምባገነን ስለሆኑ አይደለም። በሌላ አነጋገር ከውስጥ ህብረተሰብአዊ ለውጥ ባለመካሄዱና ኢንስቱቲሽናዊም ግንባታ ስለሌለ ስልጣን ላይ ቁጥጥ ያሉ መሪዎች ቀድሞ የተገነባውን የሚሊታሪና የፀጥታ መሰረት በመጠቀም ስልጣናቸውን ለማጠናከር ይገደዳሉ። ከውስጥ ለውጥ ለማምጣት የሚያስቡ ከሆነ ደግሞ የግልበጣ መኩራ ይደርግባቸዋል፤ ወይም ይገደላሉ። ለምሳሌ ሳንካራ ለውጥ አመጣለሁ፣ የአገሩንም ሀብት እቆጣጠራለሁ ስላለ ነው ለፈረንሳይ ታማኝ በሆነው በአገሩ ሰው እንዲገደል የተደረገው። እነ ፕሬዚደንት ንክሩማ፣ ፓትሪስ ሉቡምባና ፕሬዚደንት ኦቦቴ ከስልጣን እንዲወገዱና እንዲገደሉ የተደረገው በሲአይኤ፣ በእንግሊዙ የስለላ ድርጅትና በሞሳድ አማካይነት ነው። ዛሬም ያለው ሁኔታ የሚያረጋግጠው አብዛኛዎቹ የአፍሪካ መንግስታት በምዕራቡ የስለላ ድርጅት የተተበተቡና የሚሰለጥኑትም በምዕራቡ፣ በተለይም በአሜሪካኑ የሚሊታሪ አሰለጣጠን ዘዴ ነው። በተለይም አሁን ከቻይና ጋር ባለው የጥሬ ሀብት እሽቅድምድሞሽ የተነሳ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም አፍሪኮም የሚባል የወራሪ ጦር በማደራጀት ከ 53 የአፍሪካ መንግስታት ጋር የጦር ግኑኝነት ተፈራርሟል። ብዙ የአፍሪካ መኮንኖችም አሜሪካን ድረስ እየሄዱ ይሰለጥናሉ። ከዚህ ባሻገር ኮለኔል ጋዳፊ ከሞቱ በኋላ መንገዱ ክፍት ስለሆነ በማሊ የተነሳውን የቱዋሬግ ኖማዶችንና የእስላሞችን ጥምር ግፊት ለመግታትና አልቃይዳን ለመዋጋት በሚል የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ኒጄር ውስጥ የጦር ካምፕ በማቋቋም ከዚያ በመነሳት ጠቅላላውን አፍሪካን በራሱ ቁጥጥር ስር ለማድረግ እየጣረ ነው። ከአንዳንድ የድሮ የኢትዮጵያ ኦፊሰሮች ለእነኦባማ `ምክር` ከመለገሱ በፊት፣ ሲአይኤና ሌሎች ወደ 17 የሚጠጉ የስለላ ድርጅቶች ለአሜሪካን አጠቃላይ ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት አስፈላጊውን የቤት ስራ ሰርተውለታል። ስለዚህም ፕሬዚደንት ኦባማ ከኢትዮጵያውን `የዲሞክራሲ ጠበቃ ባዮች ነን` ምክር የሚያስፈልገው አይመስለኝም። በየአገሮችም ውስጥ ባስፈለገው ጊዜ ብጥብጥ ለማንሳት ይችል ዘንድ የስለላና የስልጠና መረቦችን ዘርግቷል።

 

በዚህ መልክ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም በጥንታዊው  የኢምፔርያሊዝም የወረራ ስልት ብቻ ሳይመካ በየአገሮች ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ይችል ዘንድ ሁለንታዊና የረቀቀ እንዲሁም የተወሳሰበ ኔት-ወርክ ለመዘርጋት በቅቷል። አፍሪካ በምንም ዐይነት የማደግና ራሷን የመቻል ዕድል እንዳይኖራት ለማድረግ የተቻለውን ሁሉ አዘጋጅቷል። ከዚህ ዐይነቱ የስግብግብነት ባህርይው በመነሳት ነው  ከረዠም ጊዜ አንስቶ ሲአይኤ አንዳንድ ሊቢያዎችን በማሰልጠን ጊዜውን ጠብቆ በሊቢያው ኮለኔል ሙአመር ጋዳፊ ላይ ህዝቡ እንዲነሳ ያደረገውና፣ ፕሬዚደንቱም እልክ የተጋቡት። እንደሚታወቀው ፕሬዚደንት ጋዳፊ የአፍሪካን አንድነት ለማጠናከር በፖለቲካም ሆነ በኢኮኖሚ ድጋፍ ይሰጡ እንደነበር ይታወቃል። የራሳቸውን አንዳንድ ምኞትና ስህተት ወደ ጎን ትተን- ከባህል የመጣ ችግር- አፍሪካ ራሷን እንድትችል በወርቅ የሚደገፍ፣ ዲናር-ወርቅ የሚባል የውጭ ገንዝብ ወይም ከረንሲ ተግባራዊ ለማድረግ ሽር ጉድ ይሉ እንደነበር ይታወቃል። የሚሸጡትንም ዘይት በአሜሪካን ዶላር ሳይሆን በኦይሮ እንዲከፈል ዕቅድ ነበራቸው። ከዚህ በላይ ኮለኔል ጋዳፊ የመጀመሪያውን የአፍሪካ የሳቴላይት ግኑኝነት እንዲቋቋም ከፍተኛውን ወጭ በብድር መልክ የለገሱ ነበሩ። እ.አ በ1992 ዓ.ም 45 የአፍሪካ አገሮች ከአውሮፓ ጥገኝነት ለመላቀቅ ሲሉ የሳቴላይት ኩባንያ ያቋቁማሉ። ፋይናንስ ለማድረግ እ.አ እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ ከአውሮፓው አንድነት ጋር ይደራደራሉ። የአውሮፓው አንድነት እምቢ ይላል። በዚህን ጊዜ ፕሬዚደንት ጋዳፊ $ 300 ሚሊዮን ብድር ይሰጣሉ። የአፍሪካ የዕድገት ባንክና የምዕራብ አፍሪካ ባንክ $50ና $27 ሚሊዮን ያክሉበታል። በተጨማሪም ራሺያና ቻይና ርዳታ ይለጉሷቸዋል። በዚህም ርዳታ አማካይነት አፍሪካ በታሪኳ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የራሷን ነፃ የግኑኝነት ሳተላይት ማቋቋም ትችላለች። ከዚህ በተረፈ ሙአመር ጋዳፊ ሰፋ ያለ የባቡር ሀዲድ ለመዘርጋትና የአፍሪካ የውስጥ ገበያ እንዲቋቋም ምኞትና ዕቅድ ነበራቸው።ይህ ጉዳይና የአፍሪካን ከረንሲ ተግባራዊ ለማድረግ ማቀድ በአሜሪካንና በአውሮፓ እንደክፉ ነገር ይታይ ስለነበር የግዴታ ኮለኔሉ መወገድ ነበረባቸው። ስለሆነም ይህንን የኮለኔል ጋዳፊን ህልምና ዕቅድ ለማጨናገፍ ጊዜ ይጠብቁ ነበር፤ መንገድም ያመቻቹ ነበር።

 

ወደ ውስጥ ፖለቲካቸው ስንመጣ እንደሚባለውና እንደሚነፍሰው የሊቢያ ህዝብ በችግር ውስጥ የሚኖር አልነበረም። በእርግጥ አንድ አገዛዝ ነበር። የምዕራቡ ዐይነት ዲሞክራሲም አልነበረም። ይሁንና ሰፊው የሊቢያ ህዝብ የዘይት ውጤቱ ተጠቃሚ ነበር። በመጀመሪያ ደረጃ ኮለኔል ጋዳፊ ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት ማንበብና መጻፍ የሚችለው ህዝብ 25% ብቻ ነበር። በአሁኑ ጊዜ 83% ነው። 2ኛ) መብራት በነጻ ነው፤ 3ኝ) ማንኛውም ዜጋ ብድር ካለወለድ የማግኘት መብት አለው። 4ኛ)እያንዳንዱ ሊቢያዊ በነጻ ቤት ይሰጠዋል። 5ኛ) አዲስ ለሚጋቡና ቤተሰብ ለመመስረት ለሚፈልጉ በነጻ $ 50 ሺህ ይሰጣቸዋል። 6ኛ) ማንኛውም ሊቢያዊ ትምህርት በነጻ ነው የሚማረው። ውጭ የሚማር፣ በተለይም የህክምና ትምህርት ለመማር የሚፈልግ በየወሩ $2, 500 ይሰጠዋል።7ኛ) ለማረስ የሚፈልግ መሬት፣ የገበሬ ቤት፣ የእርሻ መሳሪያና ዘር በነጻ ይሰጠዋል። 8ኛ) አንድ ሊቢያዊ አዲስ መኪና ለመግዛት ሲፈልግ መንግስት 50% በነጻ ይሸፍንለታል። 9ኛ)አንድ ሌትር ቤንዚን 0.14$ ነው የሚያወጣው። 10ኛ) አንድ ሰው ትምህርቱን ጨርሶ በሙያው ቶሎ ስራ ካላገኘ፣ እስኪያገኝ ድረስ የአገሪቱ አማካይ የወር ደሞዝ ይከፈለዋል። ጋዳፊ እስከሞቱ ድረስ ሊቢያ ምንም የውጭ ዕዳ አልነበረባትም። እንዲያውም በምዕራብ ባንክ ውስጥ ከ$150 ቢሊዮን በላይ በህዝቡ ስም ተቀምጧል። ሀቁ ይህ ከሆነ ለምንድነው በሰውየው ላይ እንደዚህ ዐይነቱ ዘመቻ የተካሄደው? ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩትና በብዙ ማስረጃዎችም እንደተረጋገጠው የአፍሪካን ዕድገት ለማኮላሸት እንደዚህ ዐይነቱ መሪ መወገድ ነበረባቸው። አገሪቱ ውስጥ ዛሬ እንደምናየው ኬኦስ መፈጠር አለበት። ግርግር ለሌባ ይመቻል እንዲሉ፣ በዚህ ዐይነት ሁኔታ የሰሜን አትላንቲክ የሚባለው የወራሪዎች ጦር የመዝረፍ ዕድል ያገኛል። በዚህ ብቻ ሳያበቃ ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ ከተገደሉና አዲስ መንግስት ከተቋቋመ ወዲህ፣ አዲሱ መንግስት ውጭ የተቀመጠውን ገንዘብ እንዳያገኝ ታግዶበታል። በዚህም ምክንያት የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ተንጠልጥለው እንዳሉ ናቸው። ከዚህም በላይ በተለይም ከውጭ የሚመጡ ዕቃዎች ወደ ሊቢያ እንዳይገቡ የሰሜን አትላንቲክ ጦር መርከቦች እንዳይተላለፉ  የባህር ዕገዳ አድርጓል። ውጭ አገር ከዚህ ቀደም ከጋዳፊ መንግስት ስኮላር ሺፕ እየተከፈለው እንዲማር የተደረገው አሁን በችግር ላይ እንደሚገኝ አዲሱ የሊቢያ መንግስት አስታውቋል። ዲሞክራሲና ነፃነት ማለት እንደዚህ ነው። ይህንን ዐይነቱን ዐይን ያወጣ ጣልቃ-ገብነት የኛዎቹም ጋዜጠኞችና ታጋዮች አምባገነኑ ተወገዱ፣ ተገደሉ በማለት ተደስተዋል። በጣም የሚያሳዝን ድርጊት ከማለት በስተቀር ሌላ የምለው ነገር የለም። አብዛኛዎቻችን ሰፋና ጠለቅ ያለ ኢንፎርሜሽን ሳይኖረን ከፍተኛ ስህተትና ወንጀል እንሰራለን፤ እየሰራንም ነው። ይህም የሚያመለክተውና የሚያረጋግጠው የምዕራቡ ማስ ሚዲያ በሚሰጠው የተሳሳተ ኢንፎርሜሽን ብቻ ስለምንመካና ከዚህ በመነሳት የዓለምን ሁኔታ በተሳሳተ መልክ ስለምናነብ ሚዛን ያለው ፍርድ ለመስጠት ተስኖናል። የራሳችንን ፍርድ ለመስጠት ከሁሉም አቅጣጫ ኢንፎርሜሽኖችና መሰረታዊ ሃሳቦችን ለመሰብሰብና ለማወዳደር ፍላጎት ያለን አይመስለኝም። እንደዚህ ዐይነት ኢትዮጵያኖች ስልጣን ቢይዙ ምን ዐይነት ኢትዮጵያን እንደምናይ ዕድሜውን ይስጠን ከማለት በስተቀር ሌላ የምለው ነገር የለኝም።

 

ወደ አገራችንም ስንመጣ የአፄ ኃይለስላሴ የመንግስት የሲቪልና የሚሊታሪ ቢሮክራሲ በእንግሊዝና በአሜሪካን እስከተወሰነ ደረጃም በእስራኤሎች የሰለጠነ ስለነበር በአጠቃላይ ሲታይ አገዛዙ ህዝባዊና ብሄራዊ ባህርይ አልነበረውም። በመሆኑም ለዕድገት የሚያመች አልነበረም። እንዲያውም ዕድገትን የሚያጨናግፍ ከመሆኑ የተነሳ ለዲሞክራሲ መብቶች የሚታገሉ ኃይሎችን ማፈኛና መግደያ መሳሪያ ነበር። አብዮቱ ከፈነዳ በኋላ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊፈጠር የቻለው አንደኛውና ዋናው ምክንያት ይህ በውጭ ኃይል የሰለጠነ ቢሮክራሲ ከውስጥ ሆኖ ለውጥን አፋኝና የኢምፔሪያሊዝምን ፕሮጀክት ተግባራዊ ስለሚያደርግ ነበር። በጠቅላላው ወታደሩ በአሜሪካን ርዕዮተ-ዓለም የሰለጠነ ስለነበር የሶሻሊዝምን ርዕዮተ-ዓለም ለጊዜው የተቀበለ ቢያስመስለውም ወደ ጭፍጨፋና ወደ ጦርነት ያመራው ፊዩዳላዊና በጭንቅላቱ ውስጥ የተቀረጸው የአሜሪካን የሚሊታሪ የጭፍጨፋ ርዕዮተ-ዓለም ስላየለበት ነው። ይህንን በርዕዮተ-ዓለም መጨፈንና ወደ መጥፎ ተግባር መሰማራት በሳይኮሎጂ ቲዎሪ መነጽርና በፍልስፍና መመርመር ይቻላል። ለምን የቀድሞው ርዕዮተ-ዓለም እንደሚያይልና ኢሰብአዊነት ዋናው ተግባሩ እንደሆነ ማረጋገጥ ይቻላል። ከዚህ ስንነሳ ማርክሲዝምና ሶሻሊዝም ናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ለደረሰው የርስ በርስ ጦርነትና ለብዙ ወጣቶች መሞት ተጠያቂው ነው የሚለው ቦታ ሊኖረው በፍጹም አይችልም። እንደዚህ የምንል ከሆነ በክርስትና ሃማኖት ስም በማዕከለኛውና ከዚያ በኋላ ዘመን በብዙ መቶ ሺሆች የሚጠጉ ህዝቦች አልቅዋል። በቁርአንም ስም በቡዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ተገድሏል፤ እየተገደለም ነው። ስለዚህ መጽሀፍ ቅዱስና ቁርአን ወይም ክርስቶስና ነቢዩ መሀመድ ናቸው ለዚህ ሁሉ ህዝብ ተጠያቂዎቹ ብለን ልንደመድም ነው ማለት ነው።

 

ያም ሆነ፣ ይህ ትላንትም ሆነ ዛሬ በተቀሩት የአፍሪካ አገሮችም ሆነ በአገራችንም ምድር የተፈጠረውን አምባገነናዊና ፀረ-ዕድገት ሁኔታ በምንመረምርበት ጊዜ ሁኔታውን ከአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም አገሮችን በሱ ቁጥጥር ስር አምጥቶ ከማሸትና ዕድገታቸውን ከማጨናገፍ ስትራቴጂ ውጭ ነጥሎ ማየት እጅግ አደገኛ አመለካከት ነው። ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የተስፋፋውንም ዓለም አቀፋዊ የትምህርት ሁኔታ፣ በተለይም የሶሻል ሳይንስንና የኢኮኖሚክስን ትምህርት ሁኔታ ስንመረምር ዕውነቱን ከውሸት መለየት እንዳይቻልና ክሪቲካል አስተሳሰብ አዳብሮ ዕውነተኛ ህብረተሰብአዊና አንድን አገር እንደ አገር እንዳትገነባ የተደረገበት ዋናው ምክንያት የውስጡ ከውጭው ኃይል ጋር በመያያዙና በመቆላለፉ  ነው። ለምሳሌ ከሁለት መቶ ዐመት በፊት የነበሩትን የትምህርት ዐይነቶች ስንመለከት አብዛኛው በቋንቋ፣ በፊሎሶፊ፣ በሊትሬቸርና በተፈጥሮ ሳይንስ ላይ የተመሰረተ ስለነበር ለዕድገት የሚያመች ነበር። በዚህም ምክንያት በብዙ የምዕራብ አውሮፓ አገሮች ቀደም ብሎ ከተካሄደው ለውጥ ጋር ተያይዞ አዲስ ኢኮኖሚያዊና ህብረተሰብአዊ ዕድገት ለመቀየስ ከባድ አልነበረም። ወደ አገራችን ስንመጣ ግን በኢምፔሪያሊዝም ስር የተቀናጀው ዕድገትን አጨናጋፊ የሆነው የሶሻል ሳይንስ ትምህርት ጭንቅላታችንን እንድንከፍትና ራሳችንን ተገንዝበን ህብረተሰብአዊ ለውጥ ለማምጣት አላስቻለንም። ይህ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም አገሮችን የማደንቆር ፕሮጀክት፣ ውስጥ ካለው የፊዩዳል ባህልና የኢኮኖሚ አወቃቀር ጋር በመጣመር የሰብአዊነት ባህል ከማዳበርና ዕድገት አጋዠ ከመሆን ይልቅ በተለይም በሚሊታሪውና በሲቪል የመንግስት አወቃቀር ውስጥ ለፋሽሽታዊ ድርጊት የሚያመቹ ሁኔታዎችን ፈጠረ። ወደ ተማረውም ስንመጣ ከጥቂቱ በስተቀር አብዛኛው የተማረው የለውጥ አጋዠ መሆን ያልቻለውና ሰፋ ላለ በሁሉም መልክ ሊገለጽ የሚችል እንስቃሴ ውስጥ ሊሳተፍም ሆነ ራሱም ጀማሪ መሆን ያልቻለው የነበረውና የተዘጋጀው፣ እንዲሁም የተማረው ትምህርት ውስጠ-ኃይሉን ውስን ስላደረጉበት ነው። ምኞቱና ድርጊቱም በአሜሪካን ናፍቆትነትና የበላይነት የሚገለጽ እንጂ ብሄራዊ ባህርይ ሊወስድና ሊያዳብር የቻለ አልነበረም። የብሄረተኝነት ወይም የአገርወዳድነት ስሜት አልነበረውም።  ይህ ማለት ግን አውቆ አገሩን በመጥላት ያደረገው ነገር ሳይሆን ከንቃተ-ህሊና ማነስ የጎደለ ስለሆነ ብቻ ነው። ሳይንቲስቱ ተመራማሪና ፈላስፋው ላይብኒዝ እንዳለው „እየተማርኩና እያወቁ በሂድኩ ቁጥር አገሬንና ህዝቤን እወዳለሁ“ እንዳለው፣  የኛው የስድሳዎቹ ዘመን የተወሰነው አዲስ ትውልድ የላይብኒዝን አንድ ሶስተኛ የሆነ ዕድል እንኳ ማግኘት ስላልቻለ ታሪክን ሊሰራ አልቻለም።  ስለዚህም የየካቲቱ አበዮት ሲፈነዳ ብዙ ግልጽነት ያለው ነገር መስራትና ሁኔታዎችን ማቃናት ያልተቻለው እነዚህ ሁሉ ነገሮች በመደራረባቸው ነው። በአጭሩ የአሜሪካን ዓለም አቀፋዊ አገሮችን የማደኽየት ፕሮጀክት ሁኔታውን ስላጨለመብን በቀላሉም ወደትርምስና ወደ ብጥብጥ ገባን። ራሱም ያሰለጠናቸውን ሰዎች ወደ ትግሉ ውስጥ በመክተት ለዕልቂቱ ተጠያቂ ሆነ። በግድያ ውስጥ እንዲሰማሩ በማድረግ ብዙ ምሁርና ወጣት ህይወቱ እንዲቀነጠስ ተደረገ። ዛሬም ያለብን ችግር አገር ወዳድ ስሜትን ከሳይንስና ከፍልስፍና ጋር ለማዋሃድ ወይም እነሱን መሰረት አድርገን ለመታገል ስላልቻልን ብዙ ነገሮች ተምታተው ይገኛሉ። ሁሉም በኢትዮጵያዊነት ስም የሚምልበት ጊዜ ስለሆነ ዕውነቱን ከውሸት በመለየትና በዕውቀት መነፅር በመመልከት መልክ ለማሲያዝ አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል።

 

ከዚህ ስንነሳ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም አገሮችን በማዳከምና ወደ ርስ በርስ ጦርነት እንዲመሩ ማድረግ እስካሁን ድረስ ሊቆይ የቻለው በብዙ ምክንያቶች የተነሳ ነው። እንደሚታወቀው በዓለም ታሪክ ውስጥ የተነሱና የተስፋፉ፣ እንዲሁም ለብዙ ሚሊዮን ህዝቦች ዕልቂት ምክንያት የሆኑ ኢምፓየሮች በራሳቸው ብልግናና ኩራት የመጨረሻ መጨረሻ ሊወድሙ ችለዋል። የቀድሞዎች ኢምፔሪያሊስት ኃይሎች፣ ፐርሺያ፣ አቴን፣ ሮማውያንና የብሪትሽ ኢምፓየሮች እንደዛሬው የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የታደሉ አልነበሩም። ከብሪትሹ በስተቀር የተቀሩት በውስጥ ኢኮኖሚያቸው ደካማና ወደ ውጭ ደግሞ እንደዛሬው የሰውን ጭንቅላት የሚሸፍን የተወሳሰበ ርዕዮተ-ዓለም ስላልነበራቸው ሊቆዩ አልቻሉም። አሜሪካንን ልዩ የሚያደርገው በተለይም፣ ከ1973/74 ዓ.ም የኢኮኖሚ ቀውስ በኋላ ዶላር ከወርቅ ጋር መላቀቁ ትልቅ መፈናፈኛ ሰጥቶታል። ከዘይት ሺያጭ የሚተርፈውና ሪሳይክልድ የሚሆነው የአሜሪካን ዶላር የግዴታ የጦር መሳሪያውን በየጊዜው እንዲያሻሽል አግዞታል። በዚህ ላይ ደግሞ የቻይና በዶላር መትረፍረፍና የአሜሪካንን ስቴት ቦንድ መግዛት ተጨማሪ መፈናፈኛ ሊሰጠው ችሏል። የአሚሪካን ዶላር የዓለም ንግድ መገበያያ መሆን ሌላው ምክንያት ሲሆን፣ አሜሪካን አንድን አገር ለመደብደብ ወይም ለመውረር በሚነሳበት ጊዜ ሊያሰልፋቸው የሚችሉ ኃይሎች አሉ። በተለያዩ አገሮች ያሉት ቫሳል የሚመስሉ አገዛዞች ለአሜሪካን እንደ ኢምፓየር መቆየትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ነፃነትን እንዲያፍን አስችሎታል። ይህ ሁኔታ ግን ዘላቂነት አይኖረውም። የመጨረሻ መጨረሻ የመከስከሱ ጉዳይ የማይቀር የታሪክ ግዴታ ነው።

 

የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲ አምባገነንነትን የማጠናከር ኃይል!

 

በእኛ ታጋይ ነን በምንለው ኢትዮጵያኖች ዘንድ ያለው ችግር የአንድን ፅንሰ-ሃሳብ አመጣጥ ሁኔታና በየትኛው የህብረተሰብ ግኑኝነት ውስጥ መፍለቁና መዳበር እንዲሁም ዓለም አቀፋዊነት ባህርይ መያዝ እንደቻለ አለመረዳት ነው። ከዚህ ስንነሳ አንድን ፅንሰ-ሃሳብ ከራስ አመለካከት ጋር የማይስማማ ከሆነ አለመቀበል ስልታችን ሆኗል። ስለሆነም ለትምህርት የተዘጋጀውን መማሪያና ከውጭ የመጣውን አስተሳሰብ ከአገር ሁኔታ ጋር ይስማማ አይስማማ፣ ዕድገት ያምጣ አያምጣ፣ ህብረተሰብአዊ ስምምነት ይፍጠር አይፍጠር፣ በጠቅላላው ለህብረተሰብአዊ ለውጥ ያለውን ብቃትና ኃይል ሳንመረምር ዝም ብሎ መቀበልና በወጣቱ ጭንቅላት ውስጥ እንደ አንዳች ቫይረስ በማስፋፋት ተለክፎ እንዲቀር ማድረግ ሌላው ችግራችን ነው። የማይስማማንን አመለካከት ደግሞ የአንድን ህብረተሰብ ችግር በደንብ ለመረዳትና መፍትሄም ለመፈለግ ቢያስችልም እሱን ማንቋሸሽ ወይም ደግሞ ላለመቀበል ያለን ፍላጎት ከፍ ያለ ነው።

 

የኒዎ-ሊበራሊዝም ተቀዳሚና መሰረት የሆነውን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ኒዎ-ክላሲካል፣ በብዙዎቻችን ዘንድ ሚክሮና ማክሮ ኢኮኖሚክስ በመባል የሚታወቀውን ለተመለከተ፣ ቲዎሪው በ1880 ዓ.ም ሲፈልቅ ዋና ዓላማውም በጊዜው የነበረውን የማርክሲዝምን የፖለቲካ ኢኮኖሚ ፍልስፍና ለመዋጋት ነበር። መሰረተ-ሃሳቡም የአንድ ህብረተሰብ ችግር ዕውነተኛ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ምርትን ማሳደግ ሳይሆን የሰውን ልጅ አርቆ-አሳቢነት(Rationality) ዋናው የምርምሩ ስትራቴጂ በማድረግ ተጠቃሚነትና አትራፊነትን ከፍ ለማድረግ የሚቻልበትን ሁኔታ መፈለግ ነበር። ማለትም የሰው ልጅ አስተሳሰብ ወደ ንጹህ ተጠቃሚነትና አትራፊነት በመቀነስ በማቲማቲካል ሞዴል መጠናቀርና መቀየስ አለበት። በዚህም መሰረት እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱ ዕድል ወሳኝና የራሱን ገቢ እንደፈለገው የሚወሰንና የሚያወጣ ነው በማለት ከተጨባጩ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም አስተሳሰብ ማስፋፋት የኒዎ-ክላሲካል ኢኮኖሚክስቶች ዋናው የቅስቀሳ ፖሊሲ መሰረት ሆነ። በኒዎ-ክላሲካል ኢኮኖሚስቶች ዕምነት በኢኮኖሚ ውስጥ የሚታዩ ቀውሶችም ከውጭ በሚመጣ ግፊት እንጂ  ከስርዓቱ የሚወለዱ አይደለም። ስለሆነም ይህ ዐይነቱ የውጭ ግፊት ሲነሳ ወይም ሲቀንስ ኢኮኖሚው ወደ ሚዛናዊነት ያመራል። በጠያቂና በአቅራቢዎች መሀከል ያለው ግኑኝነት ይስተካከል ይላል። ይህ ዐይነቱ የኢኮኖሚክስ ትምህርት የፈለቀው የፊዚክስን የመካኒካልና ስታቲስት ቲዎሪ በወሰዱና እንደመመሪያቸው ባደረጉ ምሁሮች ነው። በነሱ ዕምነትም ማንኛውም ኢኮኖሚያዊ ምርትና ግኑኝነት የመጨረሻ መጨረሻ ወደ ተስተካከለ ሁኔታ ይመጣል። በኢኮኖሚ ውስጥ የመፈራረስ፣ ራስን የማደስና ከዚያም በመነሳት ለውጥና መተሳሰር የለም። የሹምፔተር ኢኮኖሚና የዳርዊን ኢቮሉሺነሪ ቲዎሪ ግን ይህንን የኒዎ-ክላሲካል ኢኮኖሚስቶች ስታቲክ ወይም ቋሚ ቲዎሪ አይቀበሉም። በድርጊትም እንደታየውና እንደምናየው የካፒታሊስት ኢኮኖሚ ውስጥ-ኃይሉ ከፍ ያለና በቅራኔዎችም የተጠመደ ስለሆነ የአረጁ ቴክኖሎጂዎችን በመጋፋት ለአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና ፈጠራዎች በሩን ይከፍታል። እርስ በርሱም የተቆላለፈ ስለሆነ ኢኮኖሚያዊ ክንውኑ እንደ ደም ዝውውር ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ግን ከቀውስ ነፃ ነው ማለት አይደለም።

 

የኔዎ-ሊበራል ርዕዮተ-ዓለም ከዚህ ለየት የሚያደርገው ወደ መንግስታት ፖሊሲም መለወጡ ነው። በዚህም መሰረት በአንድ አገር ውስጥ የሚከሰቱ መዛባቶች፣ በውጭ ንግድ፣ በስራ-አጥ፣ በዋጋ ግሽበትና በከረንሲ ከፍና ዝቅ ማለት፣ እነዚህ መዛባቶች ከክስተት ጋር የተያያዙ እንጂ የስርዓቱ ውስጣዊ ባህርዮች አይደሉም የሚል ነው። በዚህ ዐይነት የመዛባት ሁኔታ መንግስታት በኢኮኖሚ ፖሊሲ ውስጥ ጣልቃ መግባት የለባቸውም። ማድረግ ያለባቸው የተቅዋም መዛባት የሚሏቸውን፣ የሰራተኛውን ደሞዝ ህጋዊ መሰረቱን አላቆ የግዴታ ንጹህ በንጹህ በገበያ ህግ እንዲተዳደር ማድረግ፣ በዚያውም መጠን የካፒታሊስቶችን ኃይል ማጠናከር፣ ገንዘብ ወደነሱ የሚፈስበትን መንገድ ማመቻቸት፣ ለትምህርት፣ ለጤናና ለሌሎች የሶሻል መስኮች የሚወጡትን መቀነስና ምርታማ ወደ ሆኑ መስኮች ማሸጋሸግ፣ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ የህዝብ ሀብቶችን እንዳለ መሸጥ፣… ወዘተ. ወዘተ. የሚሉ ናቸው። ይህ ዐይነቱ የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ በ1930ዎቹ ውስጥ በቲዎሪ ድረጃ ሲስፋፋ፣ ከ1973/74 የኢኮኖሚ ቀውስ በኋላ ነፍስ እንዲዘራ በማድረግ፣ ተግባራዊ መሆን የጀመረው ግን ከ1979 ዓ.ም በእንግሊዝ አገርና ቀጥሎም በአሜሪካን ነው። ከዚህን ጊዜ ጀምሮ ካፒታልና ካፒታሊዝም ሙሉ በሙሉ ዓለም አቀፋዊ ባህርይ እንዲወስዱና የዓለም ማህበረሰብም በሙሉ የኒዎ-ሊበራል የገበያን ኢኮኖሚ ተግባራዊ ማድረግ አለበት የሚባለው ይደመደማል። ለአፍሪካ አገሮች ደግሞ በዋሽንግተን ስምምነት(The Washington Consensus)  መሰረት ለነሱ የሚስማማ የተቋም ፖሊሲ(Structural Adjustment Progarm) በቀኝ ወይም አክራሪ ኢኮኖሚስቶች እንደ ዊሊያምሰንና ሚልተን ፍሪድማን በመሳሰሉት የኖቭል ዋጋ ተሸላሚዎች ይረቃል። ይህ ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ይደመደማል። የአፍሪካ መንግስታት እንደፕሮጀክት መወሰድ እንዳለባቸው ይረጋገጣል።

 

ከ1980ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ ይህ  የተቅዋም ፖሊሲ በጋና፣ በናይጄሪያና በሌሎች ከሰሃራ በታች በሚገኙ አገሮች ውስጥ ተራ በተራ ተግባራዊ ይሆናል። እነዚህ የኒዎ-ሊበራሊዝምን አጀንዳ ወይም የተቅዋም ፖሊሲ የሚባለውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ ያደረጉ አገሮች በሙሉ ገበያቸውን ወደ ውስጥ ከማሳደግና ከማስፋፋት ይልቅ ወደ ውጭ እንዲያተኩሩ ይገደዳሉ። የገበያን ፖሊሲ ተግባራዊ ያደርጋሉ። የተቅዋም ቀውስንም(Structural Crises) ይቀርፋል የተባለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በብዙ ጥናቶች እንደተረጋገጠውና ራሱም የተባበሩት መንግስታት የንግድና የዕድገት ኮሚሽን(UNCTAD) በጥናቱ እንዳረጋገጠው፣ የኒዎ-ሊበራል የተቅዋም ፖሊሲን በአፍሪካ ምድር ውስጥ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ወዲህ ብዙ ኢንዱስትሪዎች እንደፈራረሱና ልዩ ዐይነት ቀውስም መከሰት እንደቻለ ነው። በዚህም ምክንያት የተነሳ በቁጥር እየጨመረ የመጣውን የስራ ፈላጊ ህዝብ የስራ ዕድል መስጠት ያልተቻለበት ሁኔታና ልዩ ዐይነት ህብረተሰብአዊና ማህበረሰብአዊ ቀውስ እንደተፈጠረ ይህ ጥናትና ሌሎች ጥናቶችም በሰፊው ዘግበዋል።

 

በአንጻሩ ግን ይህ ዐይነቱ የኒዎ-ሊበራል ፕሮጀክት አዲስ አምራች ሳይሆን ተጠቃሚ የሆነ የህብረተሰብ ክፍል እንዲፈጠር በማድረግ ለከበርቴ መደብ ማደግ መንገዱ እንዲዘጋ አድርጓል። በዚያው መጠንም ይህ አዲስ የምዕራቡን የፍጆታ ዕቃ እየገዛ የሚጠቀም የህብረተሰብ ክፍል ሀብት አካባች ከመሆን አልፎ ከመንግስት መኪና ጋር በመቆላለፍ ልዩ ዐይነት ህብረተሰብአዊ ጭቆና እንዲዘረጋ ማድረግ ችሏል።ኮሙኒዝም የሚባለው አስፈሪው ስርዓት ከተገረሰሰና ግሎባልይዜሽን ብዙ ደሀ አገሮችን በቁጥጥሩ ስር እያዋለ መምጣት ከጀመረ ወዲህ ብዙ የአፍሪካ አገሮች ወደ ዲሞክራሲና ወደ ነፃነት ሲያመሩ በፍጹም አልታዩም። ተግባራዊ የሆነው የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲ አብዛኛዎችን አገዛዞች የመንግስቱን መኪና የበለጠ ጨቋኝ በማድረግና ሀብታቸውን በጦር መሳሪያ ላይ በማፍሰስ የህዝቡን ነፃነት እየገፈፉ በመምጣት ላይ እንደሆኑ ሁኔታዎች ያረጋግጣሉ። ይህም ማለት ብዙ የአፍሪካ መንግስታት ኢኮኖሚውና ህብረተሰቡ ከሚችለው በላይ ለመንግስቱ መኪና ሀብት በማፍሰስ የተዛባ ሁኔታን እንዲፈጥሩ አድርጓቸዋል። አሁን ደግሞ አፍሪካ ውስጥ እየተስፋፋ ነው የሚባለው የአልቃይዳ ሴል ብዙዎችን ስላሳሰባቸው አትኩሮአቸው ይበልጥ አሸባሪዎችን ለመዋጋት በሚል እዚያ ላይ ማትኮር እንጂ የተስተካከለና ጤናማ ኢኮኖሚ መገንባት አይደለም። የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ራሱ የፈለፈለውንና ያደራጀውን አልቃይዳ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስፋፋትና መንግስታትን በማስፈራራት ቀስ በቀስ አትክሮአቸው እንዲለወጥና ድርጊታቸውም ወደ ጦርነት እንዲያመራ ሊገደዱ በቅተዋል።

 

ቀደም ብሎም ሆነ ዛሬ ቀንደኛ የአልቃይዳ መሪዎች ከአሜሪካኑና ከሌሎች የስለላ ድርጅቶች ጋር የሚሰሩ ሲሆን፣ ሲሪያ፣ ኢራክና ሊቢያ የሚካሄዱት ጦርነቶች ሆን ተብለው የተቀሰቀሱና መንግስታቱን በውጥረት በመያዝ እንደ አገር እንዲወድሙ ማድረግ ነው። በዚህ ዐይነቱ እርኩስ ስራ ሳውዲዎች ሲኖሩበት፣ የየአገሩ መንግስታት በሶሻልና በኢኮኖሚ መሳሪያዎች ሊፈቷቸው ያልቻሏቸውን ሰፊ ማህበራዊ ችግሮች በመጠቀም በየቦታው አክራሪዎችን በመመልመል በየአገሮች ውስጥ የሃይማኖት ጦርነት እንዲመጣ እየቀሰቀሱ ነው። ይህ ጉዳይ ወደኛም አገር ሊመጣ የሚችልና ለዚህ የተዘጋጁ ወጣት አክራሪዎችም እንዳሉ ይታወቃል። ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ ከዚህ ቀደም የፖለቲካ አክቲቪስት የነበሩ ከመቅጽበት ተገልበጠው አክራሪነትን ማራመድ ጀምረዋል። የተሌቪዥን ጣብያቸውንና እንቅስቃሴያቸውን፣ እንዲሁም በየጊዜው የሚሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ ስንመለከት ከበስተጀርባቸው በሃሳብም ሆነ በገንዘብ የሚደግፏቸው ኃይሎች እንዳሉ መጠራጠር ይቻላል። የእነዚህ ወጣት አክራሪዎች ዋና ዓላማ በግልጽ ባይታወቅም አንድ ነገር ማለት የሚቻለው በዚህ ድርጊታቸውና ቅስቀሳቸው ከገፉበት በአገራችን ውስጥ በቀላሉ ሊገታ የማይችል ህብረተሰብአዊ ውዝግብ ሊፈጥሩ ይችላሉ።   እንደዚህ ባለ ሁኔታ ውስጥ በቂ ዝግጅትና ጥንቃቄ የማያደርግ አገርና አገዛዝ፣ እንዲሁም ደግሞ የታሪክ ኃላፊነትን ሳይሆን የስልጣን ስግብግብነትን የሚያስቀድምና ሁሉንም ነገር በራሱ ቁጥጥር ስር አድርጎ ህብረተሰቡን የሚያሽና የሚያዋካብ፣ ባላሰበው መልክ አገሩን የዚህ ዐይነቱ ዕርኩስ ድርጊት ሰለባ በማድረግ አገራችን በዘለዓለም ትርምስ ውስጥ እንድትኖር ያስገድዳታል። ይህ ሁኔታ በአንድ በኩል የባሰውኑ ለአክራሪዎች አመቺ ሁኔታዎችን ሲፈጥርላቸው፣ በሌላ ወገን ደግሞ አክራሪዎችን ለመዋጋት በሚል የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የስለላ ድርጅቱን ያጠናክራል። በዚህ መልክ በአገራችንም ሆነ በተቀሩት የአፍሪካ አገሮች የሚሊታሪና የስለላ ተቋም ውስጥ ሰርጎ በመግባት የባሰውኑ አምባገነናዊ ስርዓትና ጭቆና እንዲሰፍን ለማድረግ ይችላል ማለት ነው።

 

ስለሆነም በብዙ የአፍሪካ አገሮች በተለያየ መልክ የሚገለጽ የሰውን መብት መርገጥና መግፈፍ ተግባራዊ ሲሆን፣ ህዝቦቹም በአገራችው ውስጥ ሁለተኛ ዜጋ ይሆናሉ።  ባህላቸውን፣ እሴታቸውን፣ ታሪካቸውን፣ የመንፈስ ነፃነታቸውን፣ እንደ ሰው ሰርቶ መኖርና ቤተሰብ መመስረትና የማስተዳደር አቅማቸውን፣ ባጭሩ ማንነታቸው ተገፎ ታሪክ እንዳይሰሩ ይታገዳሉ። ዛሬ በግልጽ እንደምናየው አብዛኛው የአፍሪካ ህዝብ መሬቱን መነጠቁና የጥሬ ሀብቱ መዘረፉ የዚህ ዐይነቱ በረቀቀ መንገድ በሚካሄድ የአገዛዞች በዓለም አቀፍ የሂራርኪ አገዛዝ ውስጥ መውደቅና የአገርነት ነፃነታቸውን የማጣት ውጤት ነው ። የክርስቲያን ዲሞክራሲ እሴት አለኝ፣ የህግ የበላይነትን አከብራለሁ፣  ለዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊበራል ዲሞክራሲን የማስፋፋ ነኝ የሚለው የምዕራቡ ካፒታሊዝም፣ በተለይም የአሜሪካን ካፒታሊዝም በዚህ መልክ አገሮችን በልዩ ዐይነት የህብረተሰብ፣ የማህበረሰብና የባህል፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የሚሊታሪ ቀውስ ውስጥ በመክተት በተለይም ወጣቶችና ታዳጊው ትውልድ አዲስ ህይወት እንዳይቀምሱና ፈጣሪ እንዳይሆኑ ለማገድ በቅቷል። ኑሮአቸው የጨለመና፣ በየአገሮቻቸውም ዕድል ማግኘት ስለማይችሉ ባህርን እያቋረጡ ወደ ውጭ አገር እንዲሰደዱ ተደርገዋል፤ አየተደረጉም ነው። በመርከብ ላይ እያሉ ህይወታቸን የሚያጡ ደግሞ ቁጥራቸው በየጊዜው እየጨመረ እንደመጣ ነው የምናየውና ዜናውን የምንሰማው።

 

ከዚህ ስንነሳ በብዙዎቻችን አምባገነን እየተባሉ በአንዳንድ መሪዎች ላይ የሚለጠፈው ቅጽል ታሪካዊ ሂደቶችን ያላከተተ፣ የዓለም አቀፋዊውን ሁኔታ ያለገናዘበና በጥናቱ ውስጥ ያልጨመረ፣ ነፃነትን የሚያጎናጽፍ ሳይሆን ብዙ ነገሮችን በግልጽ እንዳናይ ከማድረግ አልፎ የዝንተ-ዓለማችንን በውጭ ኃይል እየተሽመደመድን እንድንቀር የሚያደርግ ነው። ይህ ዐይነቱ ሀተታና  የተቆነጸለ ግንዛቤ ደግሞ ዕውነተኛውን የክርስትና ሃይማኖትን የፍልስፍና መሰረተ ሃሳብ የሚቃወም ነው። በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሰው ልጅ በእግዜአብሄር አምሳል እንደተፈጠረና የራሱንም ዕድል ወሳኝ እንደሆነ ያብራራል።  አንዱ ለሌላው ጠላት ሳይሆን ወዳጁ፣ አደጋ ሲደርስበት የሚደርስለትና ችግሩን የሚጋራው መሆን አለበት ነው የሚለው። ፍልስፍናም ከዚህ የተለየ መልዕክት የለውም። የሰው ልጅ ፈጣሪና አድራጊ ነው። በማሰብ ኃይሉ ቆንጆ ቆንጆ ነገሮችን በመፍጠር ኑሮውን ያሻሽላል፤ በዚያውም የተረጋጋ ህብረተሰብ ይፈጥራል ይላል። በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የሚመራው ግሎባል ካፒታሊዝም ግን ይህንን በመጻረር የእያንዳንዱን ዕድል እኔው ነኝ ወሳኝ ይላል። ከዚህም በመነሳት ጥቅሜን ያስጠብቃሉ ከሚላቸው የሰይጣን ኃይሎች ጋር በመሰለፍና በመተባበር፣ እንዲሁም እነሱን በማስታጠቅና በመምከር የድህነቱንና የጭቆናውን ዘመን ያራዝምብናል። እያንዳንዱ ዜጋ ርስ በርሱ በመፈራራት እንዲኖር በማድረግ በዘለዓለማዊ ጦርነት ውስጥ እንዲኖር አድርጓል። የዛሬው በአፍሪካ ውስጥ ጎልብቶ የሚታየው አምባገነናዊ ስርዓት የሚባለው፣ የባሪያ ንግድ፣ የቅኝ-ግዛት፣ የእጅ አዙር ቅኝ-ግዛት አስተዳደርና፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዋቀረው ድህነትን ፈልፋይ የሆነው የግሎባል ካፒታሊዝም ውጤት ነው። ከዚህ ውጭ ማሰብ ፀረ-ታሪክና ፀረ-ሳይንሳዊ አቀራረብ ነው።

 

የወያኔ አገዛዝና የአምባገነንነት ሂደት !

         ስለወያኔ አመሰራረት፣ አነሳሰና ማደግ ሙሉ በሙሉ የተሟላ ኢንፎርሜሽን የለንም። ማለት የሚቻለው በኋላ መለሰ ዜናዊ ብሎ ስሙን የለወጠውና ለፕሬዚደትነት፣ ቀጥሎም ለጠቅላይ ሚኒስተርነት የበቃው ዊንጌት ትምህርት ቤት በነበረበት ጊዜ በእንግሊዞች ይመከርና ይሰበክ እንደነበር፣ የብሄረሰብን ጥያቄ ዋናው አጀንዳው እንዲያደርግ ምክር ይሰጠው እንደነበር ሁኔታውን በቅርብ የተከታተሉ ይናገራሉ። ራሱ ውስጥ ከነበረው የዝቅተኛና የአማራ ጥላቻ ስሜት ጋር ተደምሮ ይህንን የተደበቀ ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ ከሰይጣን ሁሉ ጋር መተባበር ነበረበት። ከመጀመሪያውኑ ግን በዚህ ዐይነቱ ፕሮጀክት ወደ እንቅስቃሴው ውስጥ ከመግባቱ በፊት የማርክሲዝምን ሌኒንዝምን ካባ አጥልቆ ቀስ በቀስ ስልጣን ላይ በሚወጣበት ጊዜ የኢምፔሪያሊስት ፕሮጀክቱን፣ ወይም ኢትዮጵያን የማዳከሙን ስትራቴጂውን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ግልጽ ነበር።

 

በግልጽ እንደሚታወቀው መለስ ዜናዊ ጦር ሜዳ ውስጥ በነበረበት ወቅት ፓውል ሂንዘ ከሚባለው በስድሳኛውና በሰባኛው ዓ.ም በቱርክና በአንዳንድ የደቡብ አውሮፓ አገሮች ኮሙኒስቶችንና የግራ አዝማሚያ ያላቸውን ኃይሎች ወይም አአገዛዞች ለማዳከም የሲአይኤን የህቡዕ ጦር ከሚገነቡትና የውስጥ ለውስጥ ከሚያደራጁት ጋር የጠበቀ ግኑኝነት እንደነበረው ነው። እንደሚታወቀው ፓውል ሂንዘ ፖፕ ጆን ፓውልን ለማስገደል ሁኔታውን ያቀነባበረው እሱ እንደነበር መረጃዎች ያረጋግጣሉ። በተለይም ዳንኤለ ጋንሰር ግላዲዮ ወይም የሰሜን አትላንቲክ የህቡ የጎሬላ ጦር በሚለው መጽሀፉ ውስጥ በዝርዝር ጽፏል። መለሰ ዜናዊ ከፓውል ሂንዘ ጋር ብቻ ሳይሆን ጋይሊ ስሚዝ ከምትባለው የሲአይኤ የአፍሪካ ተወካይ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት እንደነበረው ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ። ጋይሊ ስሚዝ ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ የሲአይኤ ተወካይና የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምን ጥቅም ለማስጠበቅ በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ጋ የምትንቀሳቀስና ይህንን ርኩስ ስራዋን ተግባራዊ የሚያደርጉ የነፃ አውጭ ድርጅቶችን የምትረዳና፣ በተለይም መሪዎቻቸውን በህቡዕ የምትመለምልና የምታሰለጥን፣ አሜሪካንም ድረስ ሄደው ልዩ ስልጠና እንዲሰጣቸው የምታደርግ የነበረች ሴት ነች። በኋላም በፕሬዚደንት ክሊንተን የስልጣን ዘመን ልዩ ቦታ ተሰጥቷት ጠዋት ጠዋት ለፕሬዚደንቱ ኋይት ሀውስ እየገባች በምስራቅ አፍሪካ ስለሚካሄደው እንቅስቃሴ አጫጭር መግለጫዎች የምትሰጥ ነበረች። ይህንን ርኩስ ተግባሯን ዕውን ለማድረግ ከመለሰ ዜናዊ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት በመፍጠር ወደ ስልጣን እንዲመጣ ካበቁት ሰዎች አንዷ ነበረች። እንደሚታወቀው መለስ ዜናዊ ጦር ሜዳ በነበረበት ጊዜ ለተወሰኑ ጊዜያት ተሰውሮ እንደነበር ይታወቃል። ምናልባትም በዚህ ወቅት ልዩ ስልጠና ለማግኘት በድብቅ አሜሪካን የሲአይኤ ካምፕ ጋ ሄዶ ይሆናል። ለዚህም ነው ካጋሜ፣ ሙሰቬኒና መለሰ ዜናዊ አዲሶች ተስፋ የሚጣልባቸው ወጣት ዲሞክራቶች ተብለው በዚያን ጊዜ የአሜሪካን ፕሬዚደንት በነበሩት ቢል ክሊንተን ይወደሱ የነበረውና ቀደም ብለውም በተወሳሰበ መንገድ ወደ ስልጣን ላይ እንዲወጡ የተደረገው።

 

አንዳንዶች የሱ የትግል ጓዶች መለሰ ዜናዊን ማርክሲትና፣ ማርክሲዝምን ሌኒንዝምን እንዳነበበ ይናገራሉ። ከዚህም የተነሳ እነሱ ብቻ ሳይሆኑ የምዕራቡም ሜዲያ፣ ኮትኳቶቹ ሁሉ ሳይቀሩ በአንድ ወቅት ማርክሲስት እንደነበር ይነግሩናል። ጥያቄው ግን እሱ ማርክሲዝምን ማንበቡና አለማንበቡ ሳይሆን፣ በመጀመሪያ ደረጃ የቱን ያህል ተረድቶታል? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው። በሁለተኛ ደረጃ፣ ትርጉሞችን ነው ወይም ኦሪጂናል መጽሀፎችን ነው ያነበበው?   በሶስተኛ ደረጃ፣ የኢትዮጵያን የህብረተሰብ ታሪክና የዕድገት ደረጃዎች ገብቶታል ወይ? መመርመር ያለበት ጉዳይ ነው። በአራተኛ ደረጃ፣ መነሳት ያለበት ጥያቄ፣ የወጣለት ማርክሲስት-ሌኒሲስት ከሆነ ለምን የሰውን ልጅ ዕድገትና ዕኩልነት ከሚጠላው ከሲአይኤ ጉያ ስር መወደቅ ተገደደ?  በአምስተኛ ደረጃ፣ ማርክሲዝምን ሌኒንዝምን አምኖት ነው የተቀበለው ወይስ ለስልጣን መወጣጫ? እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች በዝርዝር መመመለስና መተንተን ያለባቸው ሲሆኑ፣ ማርክሲዝምን ያነበበ ሁሉ ማርክሲስት ይሆናል ማለት አይደለም። እዚህ በከበርቴው ህብረተሰብ ውስጥ ካፒታሊስቶች ሳይቀሩ እስከ የተለያዩ የፓርቲዎች አመራሮች ድረስና የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚስቶች በተለይም ዳስ ካፒታልን አብጠርጥረው ያውቃሉ። በማርክስም ትክክለኛ ትንታኔ ጥርጣሬ የላቸውም። ይሁንና ግን ክርስት ዲሞክራቶች እንደ ክርስት ዲሞክራትነታቸው፣ ካፒታሊስቶችም እንደካፒታሊስትነታቸው ይሰራሉ፤ በዕምነታቸውም ይቀጥላሉ። በውሸት ግን ያልሆኑትን ሆኛለህ እያሉ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ 180 ዲግሪ ተለውጠው ሌላ አቋም ሲወስዱ አይታይም። ስለዚህም ስለ መለስ ማርክሲስትነት ስናወራ ብዙ መመርመርና መጠየቅ ያለብን ጉዳዮች አሉ። በተለይም ደግሞ ከአንድ እጅግ ወደ ኋላ-ከቀረ ህብረተሰብ የወጣ ታጋይ ነኝ ባይ ማርክሲዝምንም ቢያነብ ብዙም ልንጠብቅ የምንችለው ነገር የለም። እንደሚባለው አንድ ሰው መጽሀፍ ብቻ ስላነበበ ሳይሆን ጭንቅላቱ በመጥፎም ሆነ በጥሩ ነገር መቀረጽ የሚችለው፣ በተለይም ለአስተሳሰቡና ለአመለካከቱ ያደገበት ህብረተሰብአዊ አወቃቀርና የማቴሪያል ሁኔታዎች ወሳኝ ናቸው። ማርክስ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢወለድና ቢያድግ ኖሮ ዳስ ካፒታልን መጻፍ ባልቻለ ነበር። ይህም ማለት የአንድን ሰው አስተሳሰብ በመቅረጽ፣ በረቀቀ መልክ ለማሰብና ንቃተ-ህሊናው አድጎ ህብረተሰብአዊ ኃላፊነት ይሰማው ዘንድ በዚያው ህብረተሰብ ውስጥ የተዘረጉት የማቴሪያል ሁኔታዎች ወሳኝ ሚናን ይጫወታሉ። ይህ ሁኔታ በሌለበት ደግሞ የሰዎች አስተሳሰብ በጣም ውስን ይሆናሉ ማለት ነው። አሁንም ማክስ ዌበር ስለሰው ልጅ የአስተሳሰብ መቀረጽ(Rationalization Process) ሲያትት ከላይ የተቀመጠውን ቁም ነገር በማስመር ነው። ኖርበርት ኤሊያስም የስልጣኔ ክንውን(The Civilization Process) በሚለው ግሩም መጽሀፉ ውስጥ የማክስ ዌበርን አመለካከትና የአተናተን ዘዴ ይጋራል።

 

ከዚህ ባሻገር የአንድን ግለሰብ የፖለቲካ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን የድርጅቱንም አወቃቀርና ርዕዮተ-ዓለም ጠጋ ብሎ መመልከት ያስፈልጋል። አንዳንዶች ድርጅቱ ጥብቅ በሆነ የማርክሲስት ሌኒንስት የአደረጃጀት ህግ የተደራጀና፣ ከላይ ወደ ታች ትዕዛዝን ተቀብሎ የሚያስፈጽም ነው ይላሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርክሲዝም ሌኒንዝም ስም ይንቀሳቀሱ የነበሩ ድርጅቶች ከሞላ ጎደል ሴንትራላይዝድ የሆነ ተቋም ቢኖራቸውም ይህ ማለት ግን ይህ ዐይነቱ አደረጃጀት ተፈጥሮአዊ ወይም ማርክስ ቲዎሪውን ሲያዳብር ማንኛውም ድርጅት አንድ ወጥ በሆነ መልክ መዋቀር አለበት ያለበት ቦታ የለም። በነገራችን ላይ በብዙ ቢሮክራሲያዊ አደረጃጀቶች፣ የሚሊታሪንም ጨምሮ ሊኖር የሚችለው ሂራርኪያዊ አደረጃጀት ነው። ስለዚህ አንድ ድርጅት በማርክሲዝም ሌኒንዝም ስለሚመራ ነው ሴንትራላይዝድ የሆነ የአደረጃጀት ስልት የሚከተለው ብሎ መደምደም አይቻልም፤ ትክክልም አይደለም። ከላይ እንዳልኩት ለአንድ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ መኖርና አለመኖር፣ ወይም ማዳበርና አለማዳበር ሊወሰን የሚችለው በተወለደበት፣ ባደገበት ሁኔታና በቀሰመው የትምህርት ዐይነት ሁኔታ ነው። በተጨማሪም በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ሰፋ ያለ ህብረተሰብአዊና ምሁራዊ እንቅስቃሴዎች መዳበር ለአንድ ሰው የማሰብ ኃይልና ዲሞክራት መሆን ይረዱታል። ሰፋ ያለ ምሁራዊ እንቅስቃሴና ክርክር በሌለበት ህብረተሰብ ውስጥ ደግሞ ትንሽ ተማርኩ የሚለው አወቅሁኝ በማለት ወደ አምባገነንነት ማዘንበሉና ዕድገትን የመቀናቀን ኃይሉ ከፍ ሊል ይችላል።

 

ስለሆነም የወያኔ ወይም የህወአት አደረጃጀትና አስተሳሰብ ከዚህ ውጭ ሊወጣ አይችልም። ይህ ሁኔታና፣ በተለይም ደግሞ ራሱ ትግሬ በኢንዱስትሪ ዕድገት፣ በባህልና በምሁራዊ እንቅስቃሴ እጅግ ወደ ኋላ ቀሩ ከሚባሉት ክፍለ-ሀገሮች ውስጥ አንዱ በመሆኑ ካለምንም ጥርጥር የድርጅቱን ካድሬዎችና አመራሩን ሙሉ በሙሉ በጥላቻና በንቀት ላይ እንዲደራጁና በዚህም እንዲገፉበት ሆነዋል። ከዚህም በላይ በድርጅት ውስጥ ምንም ዐይነት የሃሳብ መንሸራሸርና ምሁራዊ ውይይት ስላልነበር-ብዙ ነፃ አውጭ ነኝ የሚሉ ድርጅቶች ያለባቸው ችግር- የግዴታ አንድ ወጥ አመለካከትና ወደ ፊት የመግፋት ባህርይ ይዘው መውጣት ችለዋል። ስለዚህም ነው ስልጣን ከያዙ በኋላ አመራሩ በተለይም በኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ የተከተለውን መስመር አንስተው መወያየት ያልቻሉት። ምናልባት ኒዎ-ሊበራሊዝምና የማርክሲዝም የኢኮኖሚ አስተሳሰብ አንድ መስሏቸው ይሆናል። ከዚህ ስነሳ ድርጅቱ የኋላ ኋላ አምባገነን እየሆነ ቢመጣምና ሙሉ በሙሉ በኢምፔሪያሊዝም ጉያ ስር ቢወድቅ የሚገርም አይደለም።

 

ያም ሆነ ይህ የወያኔና የእነ መለስ ዜናዊ ስልጣን አወጣጥ በደንብ የተቀነባበረና የተጠና፣ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ብዙ ኃይሎች የተሳተፉበት ነገር ነው። 1ኛ)  አገር ቤት ተራማጅ በሚለው መሀከል የተፈጠረው ሽኩቻና መገዳደል ለነሱ የመደራጀት መፈናፈኛ ሊሰጣቸው ችሏል። 2ኛ) ራሳቸው በአንዳንድ ብሄራዊ ባህርይ አለን በሚሉ ድርጅቶች ውስጥ  የታቀፉ ስለነበር ድርጅቶችን ከውስጥ ማዳከም ችለዋል። ከዚህም በመነሳት በነጭ-ሽብር ቀይ ሽብር ትርምስ ውስጥ በመካፈል ለብዙ ታጋዮች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆነዋል። 3ኛ) ራሳቸው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ አካል ስለሆኑ ጠላትን ከወዳጅ መለየት የሚያስቸግርበት ወቅት ነበር። በተለይም በሚሊታሪውና በሲቪል ቢሮክራሲው ውስጥ ይሰሩ ስለነበር ኢንፎርሜሽን በማቀበል ይተባበሩና የደርግን ውስጣዊ ኃይል ያዳክሙ ነበር። 4ኛ) በተለይም ሲአይኤ በሚሊታሪውና በጸጥታው ውስጥ የዘረጋው መስመርና የኢትዮጵያ ወታደር እንዲዳከም ማድረግና፣ የኋላ ኋላ ደግሞ ተራው ወታደርና ኦፊሰሮች ካለምንም አመራር መቅረትና መበታተትን በቀላሉ ስልጣን ላይ እንዲወጡ አድርጓቸዋል። 5ኛ) በአካባቢው አገሮች ያለው አመቺ የመግቢያና የመውጫ መንገድ፣ የኤርትራ ነጻ አውጭ ድርጅት ነኝ ከሚለው ያገኙት የነበረው ዕርዳታና፣ በተጨማሪም ኢትዮጵያን ከሚጠላው ከአረብ አገሮች የሚፈስላቸው ዕርዳታና፣ ወደ ውጭም በነፃ አውጭ ድርጅት ስም የዘረጉት የዲፕሎማሲ ግኑኝነት፣ እነዚህ ሁሉ በአንድነት ተደምረው ስልጣን ላይ ለመውጣትና ፀረ-ብሄራዊና ፀረ-ኢትዮጵያ ድርጊታቸውን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችሉ አግዞአቸዋል። ትግላቸው በሙሉ ፀረ-ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው የጥቁርን የነፃነት ፍላጎት የሚጻረርና፣ ኢትዮጵያም ብዙ የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ አገዛዝ ነፃ እንዲወጡ ያደረገችውን አስተዋጽዖና መንፈስ ሙሉ በሙሉ የሚቀናቀን፣ ፀረ-ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ፀረ-ጥቁር ትግልና የስልጣን አወጣጥ ነው ብሎ መደምደም ይቻላል። ከዚህ በላይ ደግሞ ትግላቸውን የጀመሩት በኢትዮጵያ ምድር አብዮት ፈንድቶ ሞቅ ሞቅ በሚልበት ወቅትና፣ ህዝባችን ከሁሉም አቅጣጫ ትብብር በሚፈልግበት ወቅት ነበር። ከዚህም ስንነሳ ትግላቸው ፀረ-አብዮትና ፀረ-ህዝብ፣ ፀረ-ዕድገት ነበር ማለት ይቻላል። በጠቅላላው በጥቁር ህዝብ ላይ የተሰነዘረ የነጭ ኦሊጋርኪን ኢምፔሪያሊስታዊ ዓላማና ህልም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ነው።

 

ስለሆነም መለሰ ዜናዊና ቡድኑ ስልጣን ሲጨብጡ መከተል ያለባቸው ፖሊሲ ከመጀመሪያውኑ በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የተደነገገ ነበር። 1ኛ) የአገሪቱን የተቀረውን ጦር እንዳለ መበታተን፣ 2ኛ) በደርግ ጊዜ የተቋቋመውንና ብዙ የተወሳሰቡ የጦር መሳሪያዎችን የሚሰራውንና የሚያመርተውን፣እንዲሁም ለወደፊቱም የአገሪቱ ዕድገት ሊያገለግል ይችላል የተባለውን የጦር መሳሪያ ፋብሪካ ማውደም፣- መለሰ ዜናዊ ለምን አፈራረሳችሁት ተብሎ ሲጠየቅ ማንኪያ፣ ሹካና ድስት ይሰራበታል፣ ኢትዮጵያ እንደዚህ ዐይነት ነገር አያስፈልጋትም እያለ ነው ያሾፍ የነበረው- 3ኛ) የአገሪቱን የዘር ባንክ ለአሜሪካ አሳልፎ መስጠትና አገራችን ከአሜሪካን በሚመጣ የእህል ዘር ጥገኛ እንድትሆን ማድረግ፣ 4ኛ) አገሪቱን በክልል ደረጃ በማደራጀት የብሄረሰብ ስሜት ዳብሮ የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲወድም ማድረግ፣ ባጭሩ የኢትዮጵያን ናሺናሊዝም ስሜት መጥፋት አለበት፣ 5ኛ)  የአማርኛን ቋንቋ  እንዲዳከም ማድረግና ብዙ ቋንቋዎች ፊደል ተቀርጾላቸው ህዝቡ በአንድ ቋንቋ እንዳይግባባ ማድረግና፣ 6ኛ) በኒዎ-ሊበራሊዝም ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በማውጣት ንጹህ የገበያን ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ናቸው። በዚህም መሰረት የአገሪቱ ገበያ ለውጭ ንግድ ክፍት መሆን አለበት። በዚህ መልክ የአገራችን ገበያ በውጭ ሸቀጣ ሸቀጥ ሲወረር፣ በዚያው መጠንም የማምረት ኃይሉ ይዳከማል። ጥገኝነት ይጠናከራል፤ ድህነት በመስፋፋትም ህዝቡ አቅመ-ቢስ ይሆናል።

 

የመለሰ ዜናዊ ቡድን ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ የተከተለውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ደግሞ እንመልከት። ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲና በተለይም ደግሞ የመዋቅር ማስተካከያ ፕሮግራም(Structural Adjustment Programm SAPs) በነፃ ገበያና በነፃ ንግድ አሳቦ ለካፒታሊስት አገሮች መግቢያ ቀዳዳ መክፈትና የማምረት ኃይልን ማዳከም ሲሆን፣ ከዚህ ባሻገር ወደ ውስጥ ያልተስተካከለ ሀብት በመፍጠርና የተወሰነን የህብረተሰብ ክፍል በማደለብ ከውጭው ዓለም ጋር ተቆላልፎ ድህነትን ማጠናከርና ማስፋፋት ነው።

 

ዝርዝር የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሳሪዎችን ከመመልከታችን በፊት የተቅዋም ማስተካከያ ፕሮግራም(Structural Adjustment Programm) የሚለውን ጽንሰ-ሃስብ ትርጉም እንመርምር። ጽንሰ-ሃሳቡ የአንድን ህብረተሰብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ህሊናዊ አወቃቀሮች የመረዳት ችሎታ አለው ? ወይስ ዝም ብሎ የተወረወረ ነው? በእንግሊዘኛው ስትራክቸር የሚለውን ስንተረጉም የአንድን ነገር ህይወት ያለውንም ሆነ የሌለን ውስጣዊ አቀራረጽና ውስጣዊ አገነባብ መግለጫ ነው። የአንድን ነገር ውስጣዊም ሆነ የውጭውን ሎጂካዊና ስነ-ስርዓት ባለው  መልክ መገንባቱን ወይም መዋቀሩን የሚገልጽ ነው። ይሁንና ግን ይኸኛው አተረጓጎም የማይለወጥ(Static) ሲሆን ወደ ህብረተሰብ ስንመጣ ግን የስትራክቸር አጠቃቀም ውስጠ-ኃይልን(Dynamism) መኖር ያመለክታል። ስለሆነም ስለስትራክቸር በምናወራበት ጊዜ በቀጥታ በሚታየው ላይ ብቻ ሳይሆን ወደ ማይታየውም ወደ ውስጥ ገባ ብሎ መመርመር ያስፈልጋል። ይህንን በኢኮኖሚ ላይ ለመመርመሪያ ስንጠቀምበት የአንድ አገር ኢኮኖሚ አወቃቀር ምን ይመስላል? በምን ዐይነት ህጎችስ ይተዳደራል? አንድ ኢኮኖሚያዊ አወቃቀር በግልጽ ከምናየው ሌላ ኢኮኖሚው የሚገዛበት ውስጣዊ ህጎች አሉት ወይ? የሚለውንም መመርመር ያስፈልጋል። በዚህም መሰረት በአጠቃላይም ሆነ በተናጠል የኢኮኖሚ መስኮችን በመመርመር በአዲስ መልክ የሚዋቀሩበትን ሁኔታ ማጥናትና ማቀድ፣ እንዲሁም ሰፋ ያለ የኢኮኖሚ ተቋም እንዲዘረጋና የህዝቡ የማምረት ኃይል በማደግ ፍላጎቱን በማሟላት የተሳሰረ ኢኮኖሚ ለመገንባት ነው። የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክን የተቅዋም ፖሊስ ጥናትና ምክር ስንመረምር ግን ጥናቱ ዓለም ሁሉ አንድ ዐይነት መልክ አላት ብሎ ስለሚነሳ የሚሰጠውም ምክር ተራ የፖሊሲ መሳሪያዎችን ተግባራዊ እንድናደርግ እንጂ የአንድን ህብረተሰብ ችግር ከሁሉም አቅጣጫ በመመርመር መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ አይደለም። ማስተካከል ወይም አድጀስትሜንት የሚለውንም ፅንሰ-ሃሳብ ስንመለከትም ምኑ ከምን ጋር ነው የሚስተካከለው? የሚለውን ጥያቄ በምናቀርብበት ጊዜ በፍጹም መልስ አናገኝም። የውስጡ ከውስቱ ሁኔታ ጋ? ወይስ የውስጡ ከውጭው ጋ?  ነገሩን ጠጋ ብለን ስንመረመር መስተካከል ወይም አድጀስትሜንት የሚለው የአንድ አገር ኢኮኖሚ ለውጭው ዓለም በሚስማማ መልክ መቀናጅት አለበት የሚል እንጂ ወደ ውስጥ መሰረታዊ ለውጥ ይምጣ ማለቱ እንዳልሆነ መረዳት ይቻላል። በዚህ ዐይነቱ የፅንሰ-ሃሳብ ጨዋታ ዝም ብለን  በጭፍናችን እንድንነዳና ገደል ውስጥ እንድንወረወር ተደርገናል። ይህ ዐይነቱ አቀራረብ ወይም ምክር የዓለም አቀፍ የገንዘብ ችግር ብቻ ሳይሆን እኛው ራሳችን ነገሩ ያገባናል የምንል ሰዎች ጥያቄ ስለማንጠይቅ ብቻ ሳይሆን፣ ስለማናወጣና ስለማናወርድ ከውጭ የሚመጣውን ሃሳብ ዝም ብለን የእግዚአብሄር ቃል ይመስል ተግባራዊ እንድናደርግ ተገደናል። በብዙዎቻችንም ዕምነት ፈረንጅ የሚያመጣው ነገር ሁሉ ትክክል ነው የሚል ዕምነት ስላለን ወይም ከበስተጀርባው በርዕዮተ-ዓለም የተሸፈነና ተንኮልን ያዘለ ነው ብለን ስለማንገምት ዝም ብለን በመቀበልና ተግባራዊ በማድረግ አጠቃላይ የሆነ ህብረተሰብአዊ ቀውስ እንዲፈጠር ለማድረግ በቅተናል። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ህብረተሰብአችን በቀላሉ ሊወጣው የማይችለው በብዙ ነገሮች የሚገለጽ ቀውስ ውስጥ እንዲወድቅ አድርገናል። በአገራችን ተግባራዊ የሆነው የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲና ግሎባላይዜሽን ሰተት ብሎ ገብቶ ህብረተሰብአችን በቀላሉ ሊወጣው የማይችለው ቀውስ ውስጥ መክተት በወያኔ ብቻ የሚሳበብ አይደለም። ራሱ ተቃዋሚ ነኝ የሚለውና ምሁሩ ዝም ብለው ማየታቸውና እንደዚህ ዐይነት ፖሊሲ ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ ለመመርመርና ለመዋጋት ያለመቻልም ጭምር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

 

የኢኮኖሚውን ፖሊሲ መሳሪያ ደግሞ አንድ በአንድ እየተነተነ ለተመለከተ በምንም ዐይነት ወደ ውስጥ ሰፋ ላለ ገበያ መዳበር፣ ለቴክኖሎጂና ለሳይንስ መበልጸግ፣ ለህብረ-ብሄር ምስረታና ማጠናከሪያ፣ እንዲሁም ለማህበራዊና ለምሁራዊ እንቅስቃሴ መዳበርና መጠንከር የሚያግዝ አይደለም። የኢኮኖሚው ፖሊሲ ከሌሎች ነገሮች ተነጥሎ መወሰዱ ራሱ ፀረ-ሳይንስና ፀረ-ፍልስፍና ነው። በተለይም ገና በእግሩ ለመቆም በሚንደፋደፍ አገር ላይ እንደዚህ ዐይነቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚያመጣው አሉታዊ ውጤት ዛሬ እንደምናየው ዐይነት ነው። መዝረክረክን፣ ድህነትን፣ ብሄራዊ ውርደትን፣ ልዩ ልዩ ዐይነት የብልግና ስራዎች መስፋፋትን፣ በሽታን፣ የኢንዱስትሪ ዕድገት መዳከምንና ሀብት ለመፍጠር አለመቻል፣ ከተማዎች መፈራረስና፣ ጠቅላላው ህዝብ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጎ የተወሰነው እንዲሰደድ ማድረግ፣ የመጨረሻ መጨረሻም የውጭ ኃይሎች ተገዢ መሆንና ህብረተሰብአዊ ውርደትን መቀበል ነው።

 

ኢኮኖሚ ለሚገባው በተለይም የኢኮኖሚ መሳሪያዎችን ጠጋ ብሎ መመልከት ያስፈጋል። እንደሚታወቀው ኢኮኖሚ ራሱ እንደባዮሎጂካል ክንዋኔና ነው።ከታች ወደ ላይ እየተኮተኮተ የሚያድግ እንጂ በአወቅሁኝ ባይነት ከላይ ወደታች የተወሰኑ የፖሊሲ መሳሪያዎችን በመጫን ሊስተካከል የሚችል ነገር አይደለም። ይህንን በደንብ ለመረዳት የገንዘብን ወይም ከረንሲን ዝቅ አድርጎ መተመን(Devaluation) ሎጂካዊና ሳይንሳዊ ያልሆነ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትን የኢኮኖሚ ስሌት እንመልከት። በዓለም አቀፍ የገንዘብና በጠቅላላው የኒዎ-ክላሲካል ወይም ኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚስቶች ዕምነት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ከረንሲዎች ኢኮኖሚው ከሚፈቅደው በላይ ከፍ ብለው የተተመኑ ስለሆነ እነዚህ አገሮች ወደ ውጭ የሚሸጡትን ምርት እንደልብ ለመሽጥ አይችሉም። ስለዚህም ያላቸው አማራጭ ከረንሲያቸውን ከዶላር ጋር ሲነፃፀር ዝቅ(Devalue) ማድረግ አለባቸው። በዚህ መልክ ምርታቸውን በብዛት መሸጥ ይችላሉ ይሉናል። ይህ ዐይነቱ ስሌት ግን በተለይም የእርሻንም ሆነ ሌሎች የጥሬ-ሀብት ውጤቶችን ለዓለም ገበያ ለሚያቀርቡ አገሮች በፍጹም ሊሰራ አይችልም። በመጀመሪያ ደረጃ፣ የዓለም ገበያ ሊገዛ የሚችለው በሚፈልገው መጠን ብቻ ነው። ይህ ማለት አንድ አገር ገንዘቧን ዝቅ ስለ አደረገች የፈለገችውን ያህል ትሸጣለች ማለት አይደለም። የዚህ ዐይነቱ የውጭ ከረንሲ ዝቅ ማለት በቴክኖሎጂ መጥቀው ለሚገኙ አገሮችና ዕቃዎቻቸውም በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተፈላጊነት ያለውን አገሮች ብቻ ነው ሊጠቅም የሚችለው። ሁለተኛ፣ የቡናም ሆነ የሌሎች ጥሬ-ሀብቶች ዋጋ በአገር ውስጥ የምርት ሂደት በዋጋና በሺያጭ ስሌት ተተምኖ የሚመረትና የሚሸጥ ሳይሆን የዓለም ገበያ፣ በተለይም የቡናን ገበያ በሚቆጣጠሩ ጥቂት ካርቴሎች የሚወሰን ነው። ሶስተኛ፣ የቡና ገበያ አስተማማኝ ስላልሆነ ዋጋው በየጊዜው ከፍና ዝቅ ይላል። በዚህም ምክንያት ከረንሲያዋን ዝቅ ያደረገች አገር ለማካካስ ስትል ብዙ ቡና በዝቅተኛ ዋጋ ወደ ውጭ መሸጥ አለባት ማለት ነው። የኢትዮጵያ ብር ዝቅ እንዲደረግ ከተደረገ ወዲህ  በተለይም ቡናን አልፎ አልፎ በብዛት መላክ ቢቻልም የውጭ ንግድ ሚዛኑ ግን በከፍተኛ ደረጃ እንደተናጋ እንመለከታለን። ወደ ውስጥ ደግሞ በተለይም ከውጭ የመለዋወጫ ዕቃና ሌሎች ምርቶችን አምጥቶ በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ለሚሸጠው ነጋዴ አንድ ዶላር ለመግዛት ብዙ የኢትዮጵያ ብር ማምጣት ስላለበት፣ ይህ ሁኔታ በግሽበት ላይና በምርት ክንዋኔ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይኖረዋል። በሌላ አነጋገር የማምረቻ ዋጋን በማስወደድ በተጠቃሚው ላይ ጉዳት ያደርሳል። ብዙ የውጭ መለዋወጫ ዕቃዎች ወይም ማሺኖች መግዛት የማይችለው የምርት እንቅስቃሴውን እንዲያዳክም ይደረጋል። የምርት እንቅስቃሴም ሲዳከም የተወሰነው ሰራተኛ መባረሩ ብቻ ሳይሆን በተወሰነ ካፓሲቲ እንዲያመርት የሚገደደው አምራች ምርቱን በውድ ዋጋ እንዲሸጥ ይገደዳል። ምክንያቱም በዚህ ዐይነቱ የከረንሲ ፖሊሲ የተወሰነው ካፓሲቲ እንደማያመርት ስለሚደረግ ቋሚ ዋጋው(Fixed Cost) እንዳለ ስለሚቀር በእየአንዳንዱ ምርት ላይ ይህ ዋጋ በሚካፈልበት ጊዜ የግዴታ የሚሸጠውን ምርት እንዲወደድ ያደርገዋል።

 

ከኢኮኖሚክ ሳይንስ ወይም ከካፒታሊስት የኢኮኖሚ ዕድገት አንጻር ስንመለከተው በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች የገንዘብ ኢኮኖሚ በደንብ ያልተስፋፋባቸውና የምርትም እንቅስቃሴ በጣም ደካማ ስለሆነ እንዲያውም የገበያን ኢኮኖሚ ዕድገት ከማገዝ ይልቅ የተቃራኒውን ነው የሚያደርገው። ስለገንዘብ ዕድገትና ተግባራዊነት፣ እንዲሁም ዛሬ ስላለበት ደረጃ ሚልተን ፍሪድማን ሳይሆን ማርክስ ነው በዳስ ከፒታል የመጀመሪያው ቅጹ ውስጥ በሰፊውና ሎጂካል በሆነ መልክ ያቀረበው። ስለዚህም የገንዘብን ዕድገትና ውስጣዊ ወይም ህብረተሰብአዊ ኃይል ሁለንታዊ ከሆነ ከካፒታሊስት ስልተ-ምርትና ዕድገት ተነጥሎ ሊታይ በፍጹም አይችልም። የገንዘብን ዕድገትና ምንነት መረዳት የሚቻለው በኒዎ-ሊበራል ወይም ኒዎ-ክላሲካል መነጽር ወይም ቲዎሪ ሳይሆን ካፒታሊዝምን እንደ ስልተምርትና እንደ ሸቀጥ አምራች ኃይል ወስደን ስንመለከትና መተንተን ስንችል ብቻ ነው። ከዚህ ስንነሳ ለምሳሌ በካፒታሊስት ኢኮኖሚ ውስጥ ገንዘብን ከፍና ዝቅ ማድረግ አያስፈልግም። አውቶማቲክ ዲቫሊዬሺን የሚባል ነገር አለ። ወደ ውስጥ ኢኮኖሚው መጠናከርና መዳከም፣ ወደ ውጭ በሚላከው የዕቃ ዐይነትና ብዛት፣ በካፒታል እንቅስቃሴና እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ አልፎ አልፎ በሚታይ ፖለቲካዊ ቀውስ እንደዶላር፣ ኦይሮና ዬንስ  የመሳሰሉት ከፍና ዝቅ ይላሉ። በሌላ አነጋገር በገበያ ህግ መሰረት በጠያቂና በአቅራቢ መሀከል የነዚህ አገር ከረንሲዎች ከፍ ወይም ዝቅ ሊል ይችላል። በመንግስት ጣልቃ-ገብነት ወይም በማዕከላዊ ባንክ የከራንሲን ዋጋ ከፍና ዝቅ ማድረግ አያስፈልግም። በሌላ ወገን ግን ለምሳሌ ብዙ ዶላር በገበያው ውስጥ ካለና በሁለት ወይም በሶስት ከረንሲዎች መሀከል መዛባት ከተፈጠረ፣ ዶላር ወይም ሌላ ከረንሲ ዋጋው የባሰውኑ ዝቅ እንዳይል ማዕከላዊ ባንኮች የተትረፈረፈውን ገንዘብ በመግዛት እንዲረጋጋ ያደርጋሉ።

 

ያም ሆነ ይህ እንደኛ ባለው አገር የውጭውን ገንዘብ  መቀነስና ከሌሎች ፖሊሲዎች ጋር አጣምሮ ተግባራዊ ማድረግ፣ በዚህም አማካይነት የገበያ ኢኮኖሚ ሊዳብር ይችላል የሚለው አስተሳሰብ ከካፒታሊስት የኢኮኖሚ ዕድገትና ሎጂክ አንፃር ስንመረምረው ሊሰራ የሚችል አይደለም። ህብረተሰብን ከማዘበራረቅና ችግሮችን በመደራረብ የህበረተሰቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዳይፈቱ ከማድረግ በስተቀር ኢትዮጵያ ለነበረችበትና ዛሬም ላለችበት የተወሳሰበ ቀውስ እንደ ፍቱን መሳሪያ ሆኖ ሊሰራ አይችልም። ይህ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የፖሊሲ መሳሪያዎችን፣ ማለትም የመንግስት ሀብቶችን መሸጥና ወደ ግል-ሀብትነት እንዲዛወሩ ማድረግ፣ እንዲሁም የውጭውን ንግድ ነፃ ማድረግ ወይም ሊበራላይዜሽን ስንመለከት በፍጹም የገበያን ወይም የካፒታሊስት ኢኮኖሚን እንድንገነባ የሚረዱን አይደሉም። በታሪክም አልታየም። እንደዚህ ዐይነት ፖሊሲዎች ከላይ እንዳልኩትና በኛም ሆነ በሌሎች አገሮች እንደተረጋገጠው ጥቂት ግለሰቦችን ወይንም የመንግስትን መኪና የሚቆጣጠሩትን በተለያየ ዘዴ ሀብት እንዲያካብቱና እንዲደልቡ በማድረግ ዕድገት እንዳይመጣ የሚያግዱ ናችው።            የወያኔ ካድሬዎችና ደጋፊዎቹ  ምንም ሳይሰሩ ሀብታም መሆን እንደቻሉ እንመለከታለን። ስልጣን ላይ ያለው ቡድን ኃይሉን ተገን በማድረግና ባንኮችን በማስገደድ ለካድሬዎቹ ብድር እንዲሰጡ በማድረግ፣ ጥቂት ሰዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የናጠጡ ሀብታሞች ሊሆኑ በቅተዋል። እነዚህ በካፒታሊስት ሎጂክ ያልተኮተኮቱ ግለሰቦችና ቡድኖች ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ሳይሆኑ ከውጭ የሚመጣ ፍጆታ ተጠቃሚዎች በመሆንና በአገልግሎት መስኩ በመሰማራት ወደ ውስጥ የምርት እንቅስቃሴ እንዳይዳብርና ስራ ለሚፈልገው የስራ መስክ እንዳይፈጠር አድርገዋል። ይህ ዐይነቱ ልዩ ዐይነት የፍጆታ አጠቃቀምና ሀብታም መሆን በህዝቡ ላይ ኢኮኖሚያዊ አምባገነንነት እንዲጫንበትና ተፈጥሮአዊ መብቱን እንዲያጣ ሊያደርገው በቅቷል። በዚህም መልክም አገሪቱ የቆሻሻ መጣያ በመሆንና ኢኮሎጂያዊ መዛባት በመፈጠር ህብረተሰቡ፣ በፖለቲካና የሚሊታሪ አምባገነንነት፣ኢኮኖሚያዊ አምባገንነትና የባህል ድቀት ተጨምሮበት ከብዙ አቅጣጫዎች እንዲወጠር በመደረጉ ለበሽታ እንዲዳረግ ሆኗል።

ከብዙ የአፍሪካ አገሮች ልምድና በአገራችንም ተግባራዊ የሆነውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስንመለከት፣ የፖሊሲው ዋና ዓላማም የውስጥ ገበያን ማዳከም፣ ዕውነተኛ በካፒታሊዝም ሎጂክ ላይ የተመሰረተ የገበያ ውድድር እንዳይኖር ማገድ፣ አጠቃላይ የሆነ የምርት እንቅስቃሴ እንዲዳከም ማድረግ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዳይዳብር መንገዱን መዝጋት፣ በአንድ አገር ውስጥ ለገበያ ኢኮኖሚ የሚያገለግሉ ከተማዎችና መንደሮች በስነስርዓትና ውበት ባለው መልክ እንዳይገነቡ ማድረግ፣ ባጭሩ የተስተካከለ ዕድገት እንዳይመጣ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው። ከማዕከለኛና ከረዢም ጊዜ አንፃር ደግሞ ህዝባዊ መተሳሰር እንዳይኖር ማድረግ፣ ህበረተሰብአዊ እሴቶች ተበጣጥሰው አንዱ ሌላውን እየፈራ እንዲኖር ማድረግ፣ አንድ አገር ታሪክ የሚሰራበት መሆኑ ቀርቶ በተወሳሰበ ሰንሰለት ከውጭው ኃይል ጋር የተሳሰሩ ማፊያዊ ቡድኖች የሚፈልቁበትና ህብረተሰቡን የሚያከረባብቱበት ሁኔታ መፍጠር ነው። የሰውም የርስ በርስ ግኑኝነት በገንዘብ አማካይነት ስለሚሰላ፣ በተለይም ምሁራዊ የሆነ ክርክር በሌለበት አገርና የገንዘብን ሚና ባልተገነዘበ ማህበረሰብ ውስጥ ገንዘብ ራሱ ህብረተሰቡን የሚያጠፋ ኃይል ይሆናል። ዛሬ በኢትዮጵያ ምድርና በውጭውም አገር ባለው ኢትዮጵያዊ ዘንድ በገንዘብ መካካድ የተነሳ የተፈጠረውን አደገኛ ሁኔታ ስንመለከት የአገራችን ዕድገት የተወሰነ ታሪካዊና ህብረተሰብአዊ ሎጂክን ተከትሎ እንዳልተጓዘ እንመለከታለን። በተለይም እዚህ ውጭ አገር ሆነው ለፍተው ጥረው ገንዝብ አጠራቅመው ቤት እንዲሰራላቸው ለዘመዶቻቸው፣ በተለይም ለወንድሞቻቸውና ለእህቶቻቸው ሲልኩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ አገራቸው ሲመለሱና ቤት  እንዳልተሰራላቸው ሲመለከቱ ተደናግጠው የሚመለሱ ጥቂት አይደሉም። ገንዘብ የሚላክለትና አደራም የሚጣልበት ሰርቶ ያላገኘው ገንዝብ እጁ ላይ ሲወድቅለት የቱን ያህል ተለፍቶ እንደተገኘ ስለማይረዳው ገንዘቡን ለምግብና ለሌሎች ቁሳቁስ ነገሮች ይጠቀምበታል እንጂ እስቲ ለመዋዕለ-ነዋይ ላውለውና እኔም ተጠቅሜ ገንዘብ የላከልኝን ልጥቀመው ብሎ አያስብም። በዚህ ረገድ በነፃ ገበያ ስም የተካሄደው  የፖሊሲ ለውጥና ተግባሩ ኢኮኖሚውን ከማድቀቁ አልፎ የህዝቡን ሞራልና ስነ-ምግባር እንዲሁም ርስ በርስ አለመተማመን በከፍተኛ ደረጃ እንዳበላሸውና እንዳናጋው የአገራችንን ተጨበጫ ሁኔታ በቅርቡ የተከታተለ ሊገነዘበው ይችላል።

 

በዚህ ዐይነቱ የተቅዋም መስተካከያ ፖሊሲ አማካይነት ጥገኝነትና፣ በተዘዋዋሪ ደግሞ በቀጥታ ጥምር አምባገነንነት ሊሰፍን ችሏል። የኢኮኖሚው ፖሊሲ ዕውነተኛ ሀብትን ለመፍጠር ስለማያስችልና የአንድን አገር ጥገኝነት ስለማይቀንስ በገንዘብ ቅነሳው አማካይነትና በጠቅላላው ፖሊሲ ግድፈት የተነሳ አንድ አገር በዕዳ መተብተቧ ብቻ ሳይሆን የውጭ ንግዷ ስለሚዛባ በየጊዜው ልዩ ልዩ ግን ደግሞ ተመሳሳይ የሆኑ አንጀት አጥብቅ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ እንድታደርግ ትገደዳለች። ምክንያቱም የዓለም የገንዘብ ድርጅት በየጊዜው ብድር ሊሰጥ የሚፈልገው አንድ አገር የድርጅቱንና የዓለም ኮሙኒቲ የሚባለውን ትዕዛዝ የተቀበለች እንደሆን ብቻ ስለሆነ ነው። በዚህ መልክ የአንድ አገር ህዝብ ዕድል ወደድንም ጠላንም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተቀነባበረ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የተነሳ የረቀቀ ዓለም አቀፋዊ የአምባገነን ስርዓት እንዲሰፍንበት ይሆናል። አገዛዙ ብቻ ሳይሆን ሌላውም ተቃዋሚ ነኝ የሚለው ኃይል ከዚህ ሌላ አማራጭ የሌለው ስለሚመስለው አንድ ጊዜ የተዋቀረውንና ስር የሰደደውን አስከፊ ስርዓት ሊያስተካከል አይችልም። ሳይወድ በግድ በድሮ መልኩ በመቀጠል ችግሩን ውስብስብ ያደርገዋል። ድህነትና መጎሳቆል የአንድ ህዝብ ዕጣው ይሆናሉ ማለት ነው። ስለዚህም ነው የአገራችን ኢኮኖሚ አድጓል ቢባልም ከዐመት ወደ ዐመት የህዝቡ ኑሮ እየተበላሸና፣ ድህነትና መጎሳቆል፣ እንዲሁም ደግሞ አገር እየጣሉ መሄድ እንደባህል ሊወሰዱ የተቻለበት።

 

እንደሚታወቀው ቀደም ብለው በሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ሆነ በእኛ አገር ተግባራዊ የሆነው የተቅዋም ማስተካከያ ፖሊሲ(Structural Adjustment Program) በጥገናዊ ለውጥ ስም ተሳቦ ወይም ሪፎርም ያመጣል ተብሎ ነው። ለመሆኑ በአንድ አገር ጥገናዊ ለውጥ ለምንድን ነው የሚያስፈልገው? ጥገናዊ ለውጥስ ሲባል ምን ማለት ነው? በመሰረቱ በአንድ አገር ውስጥ የኢኮኖሚ ወይም የፖለቲካና የሶሻል ሪፎርሞች ያስፈልጋሉ ሲባል ቀደም ብሎ የነበረው ስርዓት በደንብ ስለማይሰራና ለሰፊው ህዝብ አስፈላጊውን መሰረታዊም ሆነ ለኢኮኖሚ ግንባታ የሚያስፈልጉ ቅድመ-ሁኔታዎችን ማሟላት ስለማይችልና ለድህነትና ለኢኮኖሚ ዕድገት አንቅፋት ሆኗል ተብሎ ስልሚገመት ወይም ስለሚታመን ነው። ስለሆነም ከሱ በተሻለና ውስጠ-ኃይሉ(Dyanamism) ከፍ ባለና፣ ከማዕከለኛም ሆነ ከረዢም ጊዜ አንፃር የሰፊውን ህዝብ ፍላጎት በማሟላት ኢኮኖሚው አድጎ አንድ አገር በአስተማማኛ መሰረት ላይ ልትቆም ትችላለች በማለት ነው። ይህ መሆኑ ቀርቶ ግን በሪፎርም ስም ተግባራዊ የሚሆን ፖሊሲ የተቃራኒውን የሚያደርግ ከሆነ ይህ ዐይነቱ ጥገናዊ-ለውጥ ሳይሆን ስለኢኮኖሚና ስለህብረት ሳይንስ የማይገባቸውን ህዝቦች ለማታላል ሆን ብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚቀነባበርና አንድን ህዝብ ወደ ድህነት የሚገፈትር አደገኛ ሴራ ወይም የሰይጣን ስራ ነው ማለት ይቻላል። ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት የኒዎ-ሊበራል የተቅዋም ማስተካከያ ፖሊሲ ተግባራዊ በሆነባቸው አገሮች በሙሉና በአገራችንም ሁኔታዎች በሙሉ ቀድሞ ከነበረው ሁኔታ ጋር ሲነፃጸሩ እየተበላሹ እንደመጡ ብዙ ጥናቶች ያሳያሉ። እንደዚህ ዐይነት የኢኮኖሚ ፖሊሲ በኢኮኖሚው ላይ ብቻ ሳይሆን አሉታዊ ተፅዕኖና ክስተት ያሳደረውና ያሰፈነው፣ በአጠቃላይ ሲታይ በህብረተሰቡ ውስጥ ከፍተኛ የባህል ቀውስ በማስከተል በቀላሉ ሊወገድ የማይችል መዘዝ ተክሏል። ለምሳሌ የአገራችንን ሁኔታ ብቻ ስንመለከት በደርግም ሆነ በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ ህዝቡ ደሀ ቢሆንም የተስፋፋ የቆሻሻ መኖሪያ ቦታና(Slums) በመቶ ሺህ የሚቆጠር ወጣት መንገድ ላይ እያደረ ምግቡን ከቆሻሻ ቦታ እየለቀመ የበላበት ጊዜ አይታወቅም።  በወያኔ ዘመን ግን ይህ ዐይነቱ የተቅዋም ፖሊሲ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ወደህ የድህነቱ መጠን ብቻ ሳይሆን በቆሻሻ ቦታዎች የሚኖረውና  የቆሻሻ መኖሪያ መንደሮች እየተስፋፉ እንደመጡ እንመለከታለን። ይህ ብቻ ሳይሆን በወያኔ የአገዛዝ ስር ግብረ ሰዶማዊነትና የወጣት ሴቶች በየመንገዱ እየቆሙ ሰውነታቸውን መሸጥ እየተለመደና የህብረተሰብአችንም አንድ አካል እየሆነ መጥቷል ማለት ይቻላል። ይህ ዐይነቱ አጸያፊ ድርጊት በአፄ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ የአገዛዝ ዘመን የሚታወቅ አልነበረም፤ ወይም በዚህ መልክ መረን የለቀቀና ህዝቡ የሚያውቀው ነገር አልነበረም። ይህ አጸያፊ ድርጊት እየተስፋፋ በመምጣቱ የህብረተሰባችንን እሴትና ባህል በከፍተኛ ደረጃ ሊያናጋው በቅቷል። ከዚህ ስነንሳ በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ የዓለም ባንክና የዓለም አቀፍ ኮሙኒቲ በሚባለው በደካማ አገሮች ላይ የሚጫነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጥገናዊ-ለውጥ ሳይሆን በመሰረቱ ድህነትን ፈልፋይና አንድን ህዝብ አቅመ-ቢስ አድርጎ ነፃነቱን በማሳጣት ባህሉንም በማውደም በውዥንብር ዓለም ውስጥ እንዲኖር ማድረግ ነው። በድህነተና በውዥንብር ዓለም ውስጥ የሚኖር ህዝብ ደግሞ ራሱንም ለመከላከል ሆነ ሳይንስና ቴክኖሎጂን በማዳበር የስልጣኔ ባለቤት ሊሆን በፍጹም አይችልም።

 

የወያኔ አገዛዝ የሲቪል መንግስት ወይስ ወታደራዊ አምባገነን !

 

        በአብዛኛዎች የአፍሪካ አገሮች ያለውን ሁኔታ ስንመለከት  በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካው፣ በፀጥታውና በሚሊታሪው መሀከል ግልጽ የሆነ ልዩነትና የስራ ክፍፍል የለም። ከላይ ለማሳየት እንደፈለጉት የብዙ አፍሪካ አገሮች የህብረተሰብ አወቃቀር በቅኝና በእጅ አዙር አገዛዝ ስር ስለተመሰቃቀለና ዕድገቱም ስለተበላሸ ብዙ ነገሮች ተመሰጣጥረው ይገኛሉ። እንደ ምዕራቡ የካፒታሊስት ስርዓት ግልጽ የሆነ የፖለቲካ አወቃቀር፣ የመንግስት አመሰራረትና ሚና፣ እንዲሁም መንግስት ከኢኮኖሚው ጋር የሚኖረው ግኑኝነትና የሚከተለው ፖሊሲ ግልጽ አይደለም። በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገዛዞች በቅኝ አገዛዝ ዘመን ከተተከሉት ኢንስቲቱሽኖች ባለመላቀቃቸውና በውጭ ተፅዕኖ ስርም ስለወደቁ የመንግስት መኪናዎቻቸው ወደ አምባገነንነት እንዲቀየሩ ሆነዋል።

 

ይህ ብቻ ሳይሆን ለብዙ የአፍሪካ አገዛዞች ወደ አምባገነንነት ማምራትና የውጭ ተገዢ መሆን በመሰረቱ ሰፋ ካለ ዕውቀትና ምሁራዊ እንቅስቃሴ ዕጦት ወይም አለመኖር ጋር የተያያዘ ነው። የተወሳሰበና በሁሉም መልክ የሚገለጽ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ማለትም፣ በሊትሬቸር፣ በፍልስፍና፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ፣ በአርክቴክቸርና ውበት ባላቸው ከተማዎች የሚታይ ነገር ስለሌለ አገዛዞች አምባገነን የመሆን ኃይላቸው ከፍ ይላል። ከላይ የተዘረዘሩት ነገሮች አለመኖር ለውጭ ኃይሎችም በማመቸት በየአገሩ እየገቡ እንደፈለጉት መፈትፈትና አገዛዙን ማሳሳት ይችላሉ። በዚህም መሰረት የአገሬው ህዝብ በራሱ አገዛዝ ብቻ ሳይሆን በውጭ ኃይሎችም ይናቃል። በአገሩ የሚናቅ ህዝብ ደግሞ ውጭ አገርም በሚሄድበት ጊዜ ሊዝናና ግለሰብአዊ ነፃነት ሊሰማው በፍጹም አይችልም።

ወደ ኢትዮጵያም ስንመጣ፣ ምንም እንኳ አገራችን በቅኝ ግዛት ስር ባትተዳደርም እ.አ ከ1945 ዓ.ም በኋላ በተፈጠረው ዓለም አቀፋዊ የአገዛዝ አወቃቀር ሎጂክ ውስጥ እንድትካተት በመደረጓ ሰፊው ህዝብ ተፈጥሮአዊ መብቱ እንዲገፈፍ ሆኗል። ይህ ዐይነቱ ቢሮክራሲያዊ አወቃቀር በደርግ ዘመን እንዳለ ሲወሰድ፣  የወያኔ አገዛዝም ቀስ በቀስ እያለ ትንሽ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን በማጥፋት የሚሊታሪውን፣ የፀጥታውንና የመንግስቱን ቢሮክራሲ በመቆጣጠር፣ ሲቪል የሚመስል በእርግጥ ደግሞ የሚሊታሪ አምባገነን መንግስት ለማዋቀር ችሏል።የሚሊታሪ ርዕዮተ-ዓለሙንና የአሰራር ስልቱን እንዳለ ወስዷል። ይህንን ማድረግ የቻለው ደግሞ ከአሜሪካንና ከእንግሊዝ ኢምፔሪያሊዝም ጋር የጠበቀ ግኑኝነት በመመስረትና በፀረ-አሸባሪነት ካምፕ ውስጥ እንዲጠቃለል በመደረጉ ነው።

 

ለወያኔ ይበልጥ መጠናክር ደግሞ የምርጫ 97 ዓ.ም  ውጤት የራሱን ሚና እንደተጫወተ የሚታወቅ ሲሆን፣ ራሱ ወያኔና ጠቅላላው የኢምፔርያሊስቱ ካምፕ በዚህ በመደናገጡ የግዴታ ወያኔ የበለጠ ሚሊታራይዝድ አንዲሆንና በአሜሪካን የወረራና የጦር ሎጂክ ስር ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። ከመጀመሪያው የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦር አንስቶ ሱማሌን እስከመውረር ድረስና በአልሻባብ በሚባለው የእስላም አክራሪ ላይ እንዲዘምት ማድረግ ወያኔን የበለጠ በዚህ ዐይነቱ የጦርነት ሎጂክ ውስጥ ለመክተትና አካባቢውን ዘለዓለማዊ የጦርነት አውድማ ከማድረግ ጋር የተያያዘ ነው። በዚህም መሰረት ወያኔ ጦሩንና የስለላ መዋቅሩን የበለጠ ዘመናዊ በማድረግ ተጠናክሮ አንዲወጣ አድርጎታል። ይህ ዐይነቱ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ተንታኞች ግልጽ ያልሆነ የመንግስቱን መኪና የበለጠ ሚሊታራይዝ ማድረግና አምባገነንነትን ማስፋፋት ከአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ብዙ ደካማ አገሮችን የሱ ተቀጥያ መንግስታት(Vasal States)  ከማድረግ ስትራቴጂ ጋር የተያያዘ ለመሆኑ መታወቅ አለበት።

 

በተለይም በእ.አ ከ1989 ዓ.ም ወዲህ የተፈጠረው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታና የምዕራቡ ዓለም በተለይም የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ባልጠበቀው መልክ የቻይና ተጠናክሮ መውጣትና መጪው ኃያል መንግስት መሆን የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም በተለይም በአፍሪካ ምድር ውስጥ የሚከተለውን ስትራተጂ በአዲስ መልክ እንዲያዋቅር አስገድዶታል።  ስለሆነም አፍሪኮም የተባለ ወራሪ ጦር በማቋቋምና በእስላም አክራሪዎች ስም በማሳበብ ጦርነትን በአፍሪካ ምድር ውስጥ ማስፋፋት ሲሆን፣ በዚያውም መሰረት የተለያዩ የአፍሪካ መንግስታትን ኦፊሰሮች ማስልጠንና በዚህ የጦርነት ሎጂክ ውስጥ እንዲካተቱ ማድረጉ ለወያኔም ሆነ ለሌሎች የአፍሪካ አገዛዞች እንዲጠናከሩ ዕድሉን ሰጥቷቸዋል።  በዚህም መሰረት በጂቡቲ ትልቅ የጦር ካምፕ ሲኖረው፣ ኒጀርና ኢትዮጵያ ውስጥ የሰው አልባ የጦር ካምፕ በማቋቋም ከዚያ እየተነሳ አሸባሪዎችን ለመደብደብ አስችሎታል። በመሆኑም  ቁጥራቸው የማይታወቁ በተለይም ሱማሌ ውስጥ ብዙ ሽማግሌዎች፣ ሴቶችና ህፃናት እንደተገደሉና በየጊዜውም ንጹህ ዜጋዎች እንደሚገደሉ ይታወቃል። በዚህም መልክ ኦባማ ስልጣን ከያዘ ወዲህ አሸባሪዎች ያልሆኑ ከአምስት ሺህ  በላይ የሚቆጠሩ ንጹህ ዜጋዎች በሱማሌ፣ በፓኪስታንና በየመን ተግድለዋል።

ከዚህ ስንነሳና የወያኔን ዕድገትና ዛሬ በሚሊታሪና በጸጥታ ኃይል መጠናከርን ስንመለከት ብዙ ማስረጃዎች እንደሚያረጋግጡት- ሁሉም ሳይንሳዊ ጥናቶች እንጂ ኮንስፓይረሲ ቲዎሪዎች አይደሉም- የወያኔን የመኖርና የኢትዮጵያን ህዝቦች ነፃነት ረግጦና የአገሪቱን ድህነት የበለጠ ጥልቀት እንዲኖረው ማድረግ  ከአሜሪካን የረዥም ጊዜ ስትራቴጅና ደካማ አገሮችን በሱ ተፅዕኖ ስር ለማዋል ካወጣው ዕቅድ ጋር በጥብቅ የተያያዘ ነው። የዛሬው የወያኔ አገዛዝ በፍጹም ነፃ የሆነና የራሱን ነፃ የውጭ ፖለቲካ የሚከተል አይደለም። በአጭሩ የአሜሪካን መንግስት ስራ አስፈጻሚ ነው ማለት ይቻላል። የኢትዮጵያ ህዝብም የነፃነት ጥያቄ የመፈታቱና ያለመፈታቱ ጉዳይ ከዚህ አንፃር ነው መታየትና መተለም ያለበት።

 

ስለዚህም በአብዛኛዎች የኢትዮጵያ የፖለቲካ ተንታኞች አልፎ አልፎ የሚቀርበው የፖለቲካ ሀተታ ህዝብን ለማዘናጋትና ትግሉ እንዲጨናገፍ ከማድረግ በስተቀር ሀቁን የሚነግረን አይደለም። ለምሳሌ የዓለም አቀፍን የፖለቲካ፣ የሚሊታሪና የኢኮኖሚ አወቃቀር የሚተነትኑና በድህረ-ገጾች የሚቀርቡ ጽሁፎች እያሉ፣ የኢትዮጵያውያን ድህረ-ገጾችና አዘጋጆች ከነዚያ ትምህርት በመቅሰም ለምን ክሪቲካል የሆኑ ጽሁፎች እንዲቀርቡ ጥረት አያደርጉም? በአብዛኛዎቹ ሚዲያዎች ላይ ለምን በአገራችን ውስጥ ጣልቃ የሚገቡትንና ህብረተሰብአችንን የሚያዘበራርቁትን ጠጋ ብለው በመመልከትና በማጥናት ጽሁፎች እያቀረቡ እንድንወያይባቸው አያደርጉም? እስከዛሬ በሚካሄደው እምብዛም ክሪቲካል አመለካከት ባልያዘ አቀራረብ የኢትዮጵያን ህዝብ መጥቀም ይቻላል ወይ? በእርግጥስ በዚህ መልክ ለዕውነተኛ ነፃነት መታገልና ጠንካራ አገር መገንባት ይቻላል ወይ ? በሽታውን የደበቀ መድሀኒት አይገኝለትም እንደሚባለው ዛሬ በመሀከላችን ያለው አላስፈላጊ ጨዋነትና የፖለቲካ ትንተና አቀራረብ የኢትዮጵያን ህዝብ ሰቆቃ ያራዝመዋል እንጂ ሊጠቅመው አይችልም። እንደዚህ ስል ግን ግልጽ የሆነ ፀረ-ኢምፔያሊስት ትግል እናካሂድ ማለቴ አይደለም። ክሪቲካል የሆነ ጥበብ የተሞላበት አቀራረብንም ከተጠቀምን የብዙ የዋህ ሰዎችን ጭንቅላት በማንቃት ለዲሞክራሲና ለነፃነት የሚደረገውን ትግል መስመር ልናሲዘውና ልናፋጥነውም እንችላለን። እንደሚታወቀው አንድ ሰው ሲያመው በሽታው ከመጠናከሩ በፊት እንዲፈወስ ወይም እንዲሻለው ከፈለገ ቶሎ ብሎ ወደ ሀኪም ቤት መሄድ አለበት፤ የሀኪሙንም ምክር መስማት አለበት። በዚህ  መልክ ብቻ ነው ከበሽታው ሊገላገል ወይም ሊፈወስ የሚችለው።

 

 

አምባገነንነትና የነፃነት ጥያቄ !

 

        በአብዛኛዎቻችን ዘንድ እስካሁን ድረስ ያለው ዕምነትና ተቀባይነትም ያገኘው፣ በአገራችን ምድር ለነፃነት ዕጦት ዋናው ተጠያቂው የዛሬው የወያኔ አገዛዝ እንደሆነ ነው። ስለሆነም ይህ አገዛዝ ከወረደ ወዲያውኑ ነፃነታችንን እንቀዳጃለን የሚል ዕምነት በሁላችንም ጭንቅላት ውስጥ ሰፍኗል። ይሁንና ግን በአለፉት 22 ዐመታት ይህ አገዛዝ የአዋቀራቸው የሚሊታሪና የፀጥታ ኃይሎች፣ እነዚህን ተጠቅሞ የሰፊውን ህዝብ ነፃነት መግፈፍና ውስጥ ለውስጥም የማይስማሙትን ማሰርና እንዲያም ሲል መግድል፣ እነዚህ ሁሉ ዝም ብለው ካለምንም የርዕዮተ-ዓለም መሰረት የሚካሄዱ ሳይሆኑ በውጭው ኃይል ከውስጡ ጋር በማበርና በማጣናከር በህዝባችን ላይ የተጫኑ አደገኛ የመጨቆኛ መሳሪያዎች ናቸው። የወያኔ የመንግስት መኪና፣ የሚሊታሪው፣ የፀጥታውና የፖሊሱ አወቃቀር ካለውጭ ዕርዳታና ምክር እንዲሁም ስልጠና በራሱ ኃይል የተደራጀ ነው የሚል ሰው ካለ በዓለም አቀፍ ደረጃ ምን እንደሚካሄድ አያውቅም ማለት ነው። ስለዚህም ለነፃነት የሚደረገው ትግል ብዙ የማይታሰቡ ጥያቄዎችን ይዞ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን፣ በአንድ አገዛዝ መገርሰስ ወይም መወገድ ብቻ አንድ ህዝብ ነፃነቱን ሊቀዳጅ እንደማይችል ከብዙ አገሮች ታሪክ የምንማረው ሀቅ ነው።

በተለይም ያለፈውን የሰላሳና አርባ ዐመታት የህዝቦችን የነፃነት ትግልና ጥም ስንመለከትና ስናጠና በአብዛኛው የሶስተኛው ዓለም አገሮች የህዝብ ነፃነት ተግባራዊ ሊሆን ያልቻለው የመንግስትና የመንግስት መኪናዎች ጥያቄ በገቢው ሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ በሆነ መንገድ ስላልተፈቱና ለመፈታትም ስላልቻሉ ነው። አንደሚታወቀው  በዓለም አቀፍ ደረጃ ካፒታሊዝም ከተስፋፋና የበላይነትን ከተቀዳጀ ወዲህ ጭቆናዊ አገዛዝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋና አብዛኛዎቹ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ሚሊታራይዝድ በመሆን በዓለም አቀፍ የጭቆናና የአፈና ሰንሰለት ውስጥ ተዋቅረዋል፤ ተዋህደዋልም። የጥሬ-ሀብት ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ይህንን የተትረፈረፈ ጥሬ ሀብታቸውን እያወጡ በስርዓት ለመጠቀምና ህዝቦቻቸውን ከድህነት በማላቀቅ ስነ-ስርዓት ያለው ኑሮ ለመገንባትና ህዝቦቻቸውን ለማስከበር ያልቻሉት ከላይ በተዘረዘረው የሚሊታሪና የስለላ የጭቆና ሰንሰለት ውስጥ ስለተካተቱና በአሜሪካንና በተቀረው የምዕራቡ ካፒታሊዝም የብዝበዛ ሎጂክ ውስጥ ተቀነባብረው ሀብታቸውን በስርዓት እንዳይጠቀሙ ስለተደረጉ ነው።

ስለሆነም በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች የተዋቀረው የመንግስት መኪና በመሰረቱ የህዝቦች አለኝታና የሀብት ፈጣሪ መሳሪያ ወይንም መንገዱን የሚቀይስ ሳይሆን ድህነትን ፈልፋይ በመደረጉና፣ እያንዳንዱ አገዛዝ የራሱን ህዝብ ከውሻ በታች አድርጎ እንዲያይ በመደረጉም ነው። በሳይንስና በአንዳች ፍልስፍና ያልተዋቀሩ የመንግስታት መኪናዎች፣ ስነ-ምግባርና ሞራል የጎደላቸው፣ ማህበራዊ፣ ህብረተሰባዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ኃላፊነት እንዳይሰማቸው በመደረጉ ወደ ተራ ታዛዥነት ተቀይረዋል። ወደ አገራችንም ስንመጣ የመንግስቱ መኪና አወቃቀር ከተቀሩት የአፍሪካ አገሮች እምብዛም አይለይም። ስለሆነም አንድ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ የሚችለው ይህ ዐይነቱ እንደሰንሰለት የተያያዘ የጭቆና አገዛዝ ለዕውነተኛ ነፃነት እጦት ዋናው ምክንያት እንደሆነና የድህነትንም አፍላቂና የተስተካከለ ዕድገት እንዳይኖር የሚያግድ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ሲገባ ብቻ ለነፃነት የሚደረገው ትግል የተቃና ይሆናል። በሌላ አነጋገር፣ ለዕውነተኛ ነፃነት እታገላለሁ የሚል ሁሉ የመንግስታችንና የአብዛኛዎችን የአፍሪካ አገዛዞች አወቃቀር በሚገባ መገንዘብና እስካሁን በተካሄደው መንገድ ወደ ዕውነተኛው ነፃነት ማምራት እንደማይቻል መረዳት ይኖርበታል።። እንዲያው በምርጫ ብቻ ወይም ደግሞ በውጭ ኃይል ታግዤ ስልጣን ቢያዝ የነፃነት ጥያቄም ሊመለስ ይችላል የሚለው እስከዚህም ከሳይንስ ጋር የማይጣጣም አደገኛ ግምት ብቻ ሳይሆን ፣ በተዘዋዋሪ የባርነቱ ዘመን እንዲቀጥል እንደማድረግ ይቆጠራል። በተጨማሪም ሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ መሰረት የሌለውም የሰላም ወይም የዕርቅ እንዲሁም የጦር ትግል እንደመፍትሄ ሊወሰዱ አይችሉም። ከዚህ ስንነሳ ይህ ከውጭው ጋር የተያያዘው ሰንሰለትና በውጭ ኃይል የተጫነብንና፣ አላፈናፍነን ያለንን ኃይል ከላያችን ላይ ማስወገድ እስካልቻልን ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን ይቀዳጃል ማለት ዘበት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ርዕዮተ-ዓለማዊ መሰረቱንና አሳሳች አቀራረቡንም መረዳትና መመርመር የነፃነት ትግሉ አንድ አካል ሆኖ መታየት አለበት።

 

በፖለቲካ ትግል ውስጥም ዕውነተኛ ነፃነት ሌላን አገር በመለማመጥና አድኑኝ እያሉ ደብዳቤ በመጻፍና በመወትወት የሚገኝም እንዳይደለ መገንዘብ ያስፈልጋል። ዕውነተኛ ብሄራዊ-ነፃነትና ጠንካራ አገር መገንባት በልምምጥ የሚሆኑ ነገሮች አይደሉም። ዕውነተኛ ነፃነት የሚገኘው በሁሉም አቅጣኛ በሚካሄድ፣ በተለይም ደግሞ በዕውቀት ደረጃ በሚገለጽ ትግል ብቻ ነው ኃያልነትና መከበር የሚገኘው። ለምሳሌ ራሺያ ከ1989 ዓ.ም ወዲህ ትርምስምሱ በዚያው ቀጥሎ ቢሆንና አሜሪካኖች ስልጣን ላይ ያወጧቸው ወጣት ኃይሎች በዚያው ቢቆዩ ኖሮ ራሺያ ተመልሳ ነፃነቷን መቀዳጀት ባልቻለች ነበር። ለራሺያ ህዝብ ፕሬዚደንት ፑቲንን የመሰለ ሰው ስለጣለላትና፣ ህዝቡ በታሪክ ሂደት ውስጥም ከተቀዳጀው ዕውቀት ጋር ተደምሮ ዛሬ ራሺያ የተወሳሰቡ መሳሪያዎችን በመስራት ለመፈራትና ለመከበር ችላለች። በምዕራቡ ራሺያን ለመክበብና ለማዳከም የተደረገውና የሚደረገው ጥረት በየጊዜው እየከሸፈ ነው። ይሁንና ግልጽ ባልሆነ መንገድ አሸባሪዎች  አልፈው አልፈው ጥቃት በማድረስ የራሺያን ሁኔታ ማወዛገብ ጀምረዋል። አንዳንዶች እንደሚሉት ከሆነ በዚህ ዐይነቱ የአሸባሪዎች ድርጊት  ውስጥ የምዕራቡ እጅ እንዳለበት ነው። በተለይም ደግሞ ለሊበራል ዲሞክራሲና ለህግ የበላይነት ቆመናል የሚሉና በተሳሳተ ኢንፎርሜሽን የተወናበዱ ኃይሎችን በምክርም ሆነ በገንዘብ በመርዳት ምዕራቡ፣ በተለይም አሜሪካን ራሺያን ለማዳከምና በራሱ ተፆዕኖ ስር አድርጎ የተትረፈረውን ጥሬ-ሀብቷን ለመዝረፍ የማያደርገው ጥረት ይህ ነው አይባልም። ይሁንና ራሺያኖች እንደኛ ተላሎችና ደካሞች አይደሉም። ባላቸው ዕውቀትና የዲፕሎማሲና ፖለቲካዊ ጥበብ የምዕራቡን ተንኮል መቋቋም ይችላሉ። በተወሳሰበ የጦር መሳሪያቸውም ማስፈራራት ይችላሉ። ቻይናም ቢሆን ከ1950 ዓ.ም ጀምሮ ቀስ በቀስ እየተጠናከረች የመጣችውና ዛሬ ሁለተኛዋ ኃያል መንግስት መሆን የቻለችው በመለማመጥ አይደለም። የታሪክን ሂደት በመረዳትና፣ ዕውነተኛ ነፃነት ሊገኝ የሚችለው በውጭ ቁጥጥር ስር እስከወደቁ ድረስ አለመሆኑን በመገንዘብ ነው። ስለዚህም ለነፃነት የሚደረገው ትግል በቁንጽል አስተሳሰብ የሚካሄድ አይደለም።

 

በኛ ምሁራንና ተቃዋሚ ነኝ በሚለው ዘንድ ያለው ችግር ለችግራችን ዋናው መፍትሄ ሊበራል ዲሞክራሲና ነፃ ገበያ ብቻ ነው ተብሎ በመወሰዱ የዓለምን ሁኔታ በየዋህነት መነጽር እንድንመለከትና፣ ትግላችንንን በተወሰነ አቅጣጫ ብቻ እንድናተኩር በመደረጉም ነው። የዓለም ገበያና ፖለቲካ መወዳደሪያ መድረኮች መሆናቸው ለብዙዎቻቸን ግልጽ አይደሉም። ወደድንም ጠላንም የዓለም ገበያ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ጥቂት ሞኖፖሊስቶች የሚቆጣጠሩት ሲሆን፣ የምዕራቡ መንግስታት በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችና ድርጅቶች የሞኖፖሊስቶችን ጥቅም የሚያስጠብቁ ናቸው። ያለው ሂራርኪያዊና ዓለም አቀፋዊ የኢንስቲቱሽን አወቃቀር በዚህ ሎጂክ መሰረት ነው የተዋቀረው። ስለዚህም ስለ አምባገነንነትና አምባገነንነትን ስለመታገል ስናወራ ዛሬ ከምናደርገው ትግል ባሻገር የነገሩን ውስብስብነት ጠለቅ ብለን ማየት አለብን። በዚህ መልክ ብቻ ነው ለዕውነተኛ ነፃነት ለሚደረገው ትግል የየበኩላችንን አስተዋፅዖ ማድረግ የምንችለው።

 

ይህ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን ሊቀዳጅ የሚችለውና፣ አገራችንም እንደ አገር መከበር የምትችለው የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት ስትሆን ብቻ ነው። አንድ ህዝብ ለመኖርና እስከተወሰነ ደረጃም ድረስ ተፈጥሮን በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ በየጊዜው እየተሻሻለ የሚያድግ ቴክኖሎጂ የሚያስፈልገው ብቻ ሳይሆን፣ ከውጭው ዓለም የሚመጣበትን ግፊት ሊቋቋም የሚችለው በቴክኖሎጂም ዕድገት አማካይነት ነው። እንደሚታወቀው አንድ ሁኔታ በተዓምር እስካልተፈጠረ ድረስ በተለያዩ አገሮች መሀከል ፍጥቻ መኖሩና፣ አንደኛው ሌላውን የሱ ተገዢ በማድረግ ነፃነቱን እንደሚወስን ይታወቃል። የኛ አለመገዛት ወይንም የዕውነተኛ ነፃነት መቀዳጀት ሊወሰን የሚችለው ማንኛውንም ዐይነት መሳሪያ መስራት የምንችል እስከሆን ድረስ ብቻ ነው። ወደዚያ ለመድረስ ግን በመጀመሪያ ደረጃ ቀስ በቀስ ቀላል የሆኑ የኢኮኖሚ ችግሮችን፣ የምግብን፣ የንጹህ ውሃን፣ የቤትን፣ የህክምናንና የትምህርትን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት መቻል አለብን። ጎን ለጎንም ስርዓት ባለው መልክ ቴክኖሎጂዎችን መፍጠርና ማምረት መቻል አለብን። ለዚህ ደግሞ ዋናው ቁልፉ ከዕውቀት ባሻገር ፍላጎትና የአገር ወዳድ ስሜትነት ሲሆኑ፣ ለአንድ ዓላማ ለመታገል ጠንካራ መንግስታዊና ህዝባዊ አደረጃጀት ወሳኝ ሚናን ይጫወታሉ። የአንድ አገር የመንግስት መኪና ለውጭ ኃይሎች ክፍት ከሆነና ውስጥ ሆነው የማያሰሩ ኃይሎች ኢንፎርሚሽን በማቀበል የአገራቸው ዕድገት ጠላት እስከሆኑ ድረስ ስለ ዕድገትና ስለመከበር በፍጹም ማውራት አይቻልም። ስለዚህም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከሁለት ነገሮች አንዱን መምረጥ መቻል አለበት። ወይ የኢትዮጵያ ህዝብ አገልጋይ፣ ካሊያም ደግሞ የውጭ ኃይል። በሁለት ቢላ መብላት እንደማይቻል ሁሉ፣ ከሁለት አንዱን መምረጥ የግዴታ ነው። በዚህ መልክ ኢትዮጵያዊነትን ካስቀደምንና ዕውቀትንና ቴክኖሎጂን እየኮረጅንና እየሰረቅን ወደ አገራችን ማስገባት ከቻልን የታሪክ ሚናችንን ተወጣን ማለት ነው።

 

ከዚህ ስንነሳ ማንኛውም ለነፃነት እታገላለሁ የሚል ኃይል ሁሉ አሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፈነው አደገኛ የአገዛዝ መዋቅርና የጦርነት አካሄድ እንዴት አድርጎ ለኢትዮጵያ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነት እንደሚያመጣለት ማሳየት መቻል አለበት። ይህ ብቻ ሳይሆን አሁን በዓለም ላይ በሰፈነው የጎሎባል ካፒታሊስት የኢኮኖሚ ስርዓትና ብዙ አገሮች የነፃ ንግድንና የገበያን ኢኮኖሚ መርሆአቸው ባደረጉበት ወቅትና ተግባራዊ በሚያደርጉበት ሁኔታ ውስጥ እንዴ ተደርጎ አንድ ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነቱን መቀዳጀት እንደሚችል እያብራሩ ማሳየት ያስፈልጋል።

 

ስለሆነም የላይኛው ጥያቄ  የፖለቲካን፣ የኢኮኖሚንና የማህበራዊ ነፃነት ወይም ዕኩልነት ጥያቄን እንድናብራራና፣ እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች እንዴትስ ተራ በተራ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ማሳየት ያስፈልጋል። ቀደም ብዬ ለማሳየት እንደሞከርኩት የአንድ ህዝብ የፖለቲካ ነፃነት ህልም ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው በምርጫ ብቻ  ወይም ተወካይነትን በማግኘትና በሱ አማካይነት መልስ ይገኛል ብሎ በመጠባበቅ አይደለም። ዕውነተኛ የፖለቲካ ነፃነት ከምርጫ ተሻግሮ የሚሄድና የህዝቡን በፖለቲካ ክንዋኔ ውስጥ መሳተፍንና፣ ለዚህ ደግሞ የንቃተ-ህሊናን ማደግንና መደራጀትን ይጠይቃል። የአንድ አገር ህዝብ፣ ቢያንስ የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል የየፓርቲዎችን ፕሮግራምና ሃሳብ ሊረዳና ሊቆጣጠራቸውም የሚችለው የፓርቲዎችን  ፕሮግራምና ርዕይ የመረዳት ዕውቀት ሲኖረው ብቻ ነው። ካለበለዚያ  ማንኛውም ግለሰብ ወይም ፓርቲ ነኝ የሚል ይህንን ወይም ያኛውን ነገር እየያዘ በመነሳት እንደዚህ አደርጋለሁ በማለት ህዝብን የሚደልልበት ሁኔታ በመፍጠር ህዝቡ ዕውነተኛ የፖለቲካ ነፃነት እንዳይጎናጸፍ ያደርጋል።

 

ያለፉትን የአርባ ዐመት የፖለቲካ ትግልና ለዚህ ተብሎ የተደረገውን መስዋዕትነት በምንመረምርበት ጊዜ ቀድሞም ሆነ ዛሬ ስለ ፖለቲካ ያለን አስተሳሰብ እጅግ የተሳሳተ ይመስለኛል። በመጀመሪያ የፖለቲካ አስተሳሰባችን ከፍልስፍናና ከሳይንስ ውጭ ተነጥሎ ስለታየና በዚህም ላይ የተመሰረተ ስላልነበር ያነጣጠረው ስልጣንን ለመያዝ ብቻ ነበር። በዚህም ምክንያት የተነሳ ፖለቲካ የሚባለው ጽንሰ-ሃሳብ ግልጽነትና ህዝባዊነት ያለው ግዙፍ የሃሳብ መንቀሳቀሻ መድረክ መሆኑ ቀርቶ ወደ ምስጢራዊነትና ወደ ህቡዕነት ተለወጠ። ህቡዕነትና ምስጢራዊነት ደግሞ የግዴታ ለተንኮልና ለሽወዳ በራቸውን ክፍት አደረጉ። ፖለቲካ ተንኮል ወደ መስራትና መሸወድ፣ እንዲያም ሲል ቶሎ ብሎ የጠረጠሩትን ማጥፋት ተቀንሶ እንዲታይ ተደረገ። ይህ ዐይነቱ የትግል ዘዴ ደግሞ የግዴታ ነፃነትን የሚያፍንና በከፋፍለህ ግዛ ላይ የተመሰረተ ስለነበር የመጨረሻ መጨረሻ ወደ መጠራጠርና ወደ ርስ በርስ መጨራረስ አመራ። በሁለተኛ ደረጃ፣ ለፖለቲካ ለውጥ እንታገላለን ይሉ የነበሩትና ዛሬም ያሉት ኃይሎች ለፖለቲካ ለውጥ የሚደረገው ትግል ከፍተኛ ንቃተ-ህሊናንና የጭንቅላት ጂምናስቲክን እንደሚጠይቅ በፍጹም የተረዱ አልነበሩም፤ ዛሬም አይደሉም። በታላላቅ ፈላስፋዎች ከፕላቶን እስከ አሪስቶተለስ፣ ከኩዛኑስ እስከ ላይብኒዝና፣ ሺለርና ካንት ድረስ ያሉትን የፖለቲካ ፈላስፋዎች ስራዎች ስንመለከት አጻጻፋቸው በሙሉ የሰውን አእምሮና መንፈስ በመረዳት ዙሪያ የሚሽከረከር ነበር። በነሱም ዕምነት የሰው ልጅ ችገር የግዴታ ከጭንቅላት በደንብ አለመታነፅ ወይም ከንቃተ-ህሊና ማነስ ጋር የተያያዘ ነው። ከፍተኛ ንቃተ-ህሊና በሌለበት ህብረተሰብ ውስጥ የፖለቲካ ትግል ብሎ መጀመር፣ ወይም ደግሞ ዕውቀትን ሳያካትቱ በዚያው መቀጠል የህብረተሰብንና የተፈጥሮን ህግ እንደ  መጣስ ይቆጠራል፤ በነሱ ላይም ዘመቻ ማድረግ ነው። ምክንያቱም ህብረተሰብም ሆነ ተፈጥሮ የረሳቸው የሆኑ ውስጣዊ ህጎች ስላሏቸው፣ የሚካሄደው ትግል ቀስ ተብሎና ከታች ወደ ላይ መሆን ስላለበት ነው። ስለሆነም አንድን ህብረተሰብ ነፃ አወጣለሁ ብሎ ሲታሰብ ከመጀመሪያውኑ ትግሉን ለመጀመር የሚፈልገው ራሱን ነፃ ማውጣት አለበት። በየጊዜው ወደ ውስጥ ጭንቅላቱን በማየት የሚሰራቸውን ስራዎች መመርመር የሚችል መሆን አለበት። በዚህ መልክ ብቻ ታሪካዊ ተልዕኮውን ሊወጣ ይችላል።

 

ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሂደትና የፓርቲዎች አደረጃጀት ስንመለከት ትላንትም ሆነ ዛሬ በሳይንስና በፍልስፍና ዙሪያ የሚሸከረከርና እነዚህን መሰረት ያደረገ አይደለም። እንደ ትላንትናው ዛሬም ቡዳናዊ ስሜት አይሎ ይገኛል። እንደ ትላንትናው ዛሬም ስለ ፖለቲካ የማያውቅና የማይገባው ወይም ለማወቅ ጥረት የማያደርግ የፖለቲካ ትግሉ ውስጥ እየገባ የሰውን ልብ ያደርቃል። ከመጠየቅ ይልቅ አውቃለሁ በማለት ፍጥጫ ይጀምራል። ምንም ዝግጅትና በህይወቱም ለፖለቲካ ትግል አስተዋፅዖ ሳያደርግ ፓርቲ ወደ መመስረት ያመራል። እንደሚታወቀው ለፖለቲካ ትግል ሲካሄድ አንድ ሰው ከአረጀና ከአፈጀ በኋላ አይደለም ስለ ፖለቲካ ትግል ማሰብና ማውራት እንዲሁም ገብቶ መሳተፍ ያለበት። ለፖለቲካ ለውጥ እታገላለሁ የሚል በ 15 እስከ 20 ዐመት ባለው ዕድሜው ውስጥ መጀመር ሲገባው፣ በመጀመሪያ ከፖለቲካ ጋር ከመተዋወቁ በፊት ከፍልስፍናና ከሳይንስ ወይም ከሊትሬቸር ጋር መተዋወቅ አለበት። በዚህ ከጀመረ ጭንቅላቱ ክፍት እየሆነና ህብረተሰብና ተፈጥሮን በመረዳት የሌላውንም አስተሳሰብ ለመቀበል ዝግጁ ይሆናል። ከአመጽ ይልቅ ውይይትንና ክርክርን ያሰቀድማል። ለኩርፊያና ለመቀየም ቦታ አይሰጣቸውም። እራሱንም የተፈጥሮና የህብረተሰቡ አካል አድርጎ በመቁጠር ለዕውነተኛ ህዝባዊ ነፃነትና ዕድገት ይታገላል። የብዙዎችን የአውሮፓ የጥንት የፖለቲካ ሰዎች ባዮግራፊ ስናነብ ይህንን ነው መገንዘብ የምንችለው። ዛሬም ቢሆን የብዙ አውሮፓ ፓርቲዎች አባል፣ ቢያንስ ባለሁበት አገር ለፖለቲካ እንታገላለን የሚሉ ቀደም ብለው ነው የሚጀምሩትና አባል የሆኑበትን ፓርቲ ፍልስፍናና ፕሮግራም በደንብ አብጠርጥረው የሚያውቁት። ለዚህም ነው ባለፉት 60 ዐመታት ተከታታይነት ያለው የፖለቲካ ስራ መስራት የተቻለው።

 

በኛ አገር ግን በጣም ጥቂቱ ካልሆነ በስተቀር አብዛኛዎቻችን ከአረጀንና ከገረጀፍን፣ ወይንም ደግሞ በወጣትነታችን ዘመን ጭንቅላታችንን የሚያበላሹ ብዙ ውትብትብ ነገሮች ሰርገው ከገቡ በኋላ ነው ስለ ፖለቲካ ትግል የጀመርነውና ዛሬም የምናካሄደው። ቀድሞ የነበረብን ችግር የታወቀ ቢሆንም፣- የህብረተሰባችን የዕውቀት ደረጃ ዝቅ ማለት- ከአርባ ዐመት የፖለቲካ ትግል በኋላ ብዙም የተማርን አይመስለኝም። አሁንም ቂም በቀለኝነት፣ ኩርፊያ፣ ተንኮልና የማያስፈልግ ምስጢራዊነት፣ ሃሳብን በግልጽ አውጥቶ አለመናገርና አለመከራከር፣ አውቃለሁ ባይነት… ወዘተ. መለያችን በመሆን ስራ አላሰራ እያሉን ነው። በዚህ ላይ ደግሞ በፍልስፍናቸውና በርዕያቸው ላይ ሳይሆን በግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ስድብ እየወረደ የፖለቲካ አየሩን እየመረዘው ነው። ፖለቲካ ህበረተሰብአዊ ነፃነትን የሚያጎናጽፍ ከመሆኑ ይልቅ የመነታረኪያ መሳሪያ እየሆነ መጥቷል ብል የምሳሳት አይመስለኝም።

 

ስለሆነም ስለፖለቲካ ነፃነት  እታገላለሁ የሚል ትልቅ ህብረተሰብአዊ ኃላፊነትን እንደሚሸከም ተገንዝቦ በመጀመሪያ የጭንቅላት ስራ መስራት እንዳለበት መረዳት አለበት። የአንድ አገር ህዝብ ዕድልና ብሄራዊ ነፃነት በፖለቲካ ዙሪያ የሚሽከረከር ሰለሆነና በሱም ስለሚመካ ከፖለቲካ ግንዛቤ እጦት የሚሰራ ስህተት አንድን ህብረተሰብ እያወዛገበ ይኖራል።አንድ ህብረተሰብ ታሪክ የሚሰራበት መሆኑ ቀርቶ ቡድናዊ ስሜት በመዳበር ህብረተሰቡ የሚፈልገው የዕድገት ስራ እንዳይሰራ ያግዳል።

 

ይህ በራሱ ደግሞ ወደ ኢኮኖሚ ነፃነት ወይም የኢኮኖሚ ዕኩልነት(Economic Justice) ወደ ሚለው ያመራናል። እንደሚታወቀው በአገራችን ምድር በአለፉት 22 ዐመታት አዲስ ዐይነት ህብረተሰብአዊ የኢኮኖሚ ግኑኝነት (Production Relationship)ተፈጥሮአል። ይህ በአገራችን ምድር የተተከለው አዲሱ የኢኮኖሚ ስርዓት ከውጭው ዓለም ጋር በሺህ ድሮች ተሳስሮ ለኢኮኖሚ ዕድገት እንቅፋት ሆኗል። ድህነትን ፈልፋይ ሆኗል። ዕውነተኛ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ህብረተሰብአዊ ሀብት እንዳይፈጠር ዕገዳ አድርጓል። ከዚህ ጋር ተያይዞ አገሪቱ በሯን ክፍት በማድረጓ የሊበራላይዜሽንና የግሎባላይዜሽን ሰለባ በመሆን የቆሻሻ መጣያ ሆናለች። ዛሬ ህዝባችን እጅግ አሳፋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚኖረው። በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ የወያኔ አገዛዝና የፖሊሲ አውጭዎቹ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን ከስምንት ዐመት በፊት አመልክተዋል። እስካሁን ድረስ በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ የሚባለው፣ የነፃ ንግድን አራማጅ ድርጅት ውስጥ በአባልነት ከገባች ወደ እስር ቤት ውስጥ እንደተወረወረችና፣ የህዝባችንም የነፃነት ፍላጎት መልስ እንዳያገኝ በሩ ሁሉ ይዘጋበታል ማለት ነው። ኢትዮጵያ የንግድ ድርጅቱ አባል ከሆነች የአሜሪካን ዓለም አቀፋዊ ኩባንያዎችና የዘር አምራች ድርጅቶች መጨፈሪያ በመሆን ህዝባችን ዕውነተኛ ነፃነቱን እንዲገፈፍ ይደረጋል። አገራችን የአሜሪካ የስጋ፣ የእንቁላል፣ የዘርና ልዩ ልዩ ለዕድገት የማያመቹ ቆሻሻ መጣያ ስትሆን፣ በዚያውም መጠን የህዝባችን የማምረት ኃይል ይዳከማል። የምናልመው በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ሰፋ ያለ ብሄራዊ የውስጥ ገበያን መገንባቱ እንደ ውሃ ሽታ ይሆናል ማለት ነው። በዚህ መሰረት ኢኮኖሚያዊ ነፃነታችንን ማጣታችን ብቻ ሳይሆን፣ ብሄራዊ ነጻነታችንም ይገፈፋል። ስለሆነም ለነፃነት ትግል ሲደረግ ይህ ዐይነቱ የኢኮኖሚ አወቃቀርና የምርት ግኑኝነት መስተካከልና ሰፊው ህዝብም የመሬት ባለቤት ሊሆን የሚችልበትና ቤትም ሰርቶ ተዝናንቶ ሊኖርበት የሚችልበት ሁኔታ መፈጠር አለበት።

 

እንደሚታወቀው ወያኔ በዓለም የገንዘብ ድርጅትና በዓለም ባንክ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ኮሚኒቲው እየተባለ በሚጠራው እየተመከረና እየታገዘ ተግባራዊ ያደረገውና የሚያደርገው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ብሄራዊ ባህርይ የሌለውና ሰፋ ላለ፣ እርስ በርሱ የተሳሰረ የኢኮኖሚ ግንባታ አመቺ ያልሆነ ነው። ሰፋ ባለ የማኑፋክቱር፣ በምርምርና በዕድገት፣ እንዲሁም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ ያልተመሰረተ ስለሆነ እየሰፋ ሊመጣና አገሪቱን ሊያዳርስ የቻለ አይደለም። በየክልሎቹና በየከተማዎች እንዲሁም በየመንደሩ ዘመናዊ ኢንስቲቱሽን ባለመዘረጋቱ የአገሪቱን የተትረፈረፈ ሀብት ለማንቀሳቀስና ዕድገትን አምጥቶ ሰፊውን ህዝብ ከድህነት ማላቀቅ አልተቻለም። ስለሆነም ይህ ዐይነቱ የተዝረከረክ አካሄድ ከቀጠለ ድህነቱ ጥልቀት ማግኘቱ ብቻ ሳይሆን አገራችን እንደ ህብረ-ብሄር ልትታይ በፍጽም አትችልም። ከዚህ አደጋ ለመላቀቅ የግዴታ ሁለንታዊ(Holistic) የሆነ ሰፊውን ህዝብና የአገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት የአካተተ የዕድገት ፈለግ መከተሉ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው። የአገራችንን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማህበራዊ ችግር ልንቀርፍ የምንችለው በኒዎ-ክላሲካል ወይም በኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ሞዴል ሳይሆን በጥንታዊው የሬናሳንስ የኢኮኖሚ ሞዴል ብቻ ነው። ከአገዛዞች መቀየር በኋላ በየአገሮች በእነ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አቀነባባሪነት የሚወጡትና ተግባራዊ የሚሆኑት ፖሊሲዎች በሙሉ የቴክኖክራቶች ጫወታዎች እንጂ በምድር ላይ የሚታየውን የህዝቦችን ችግር መፍታት እንዳልቻሉ ነው የምናየው። በታሪክ ውስጥም ቴክኖክራሲያዊ የኢኮኖሚ ሞዴል የአንድን አገር ህዝብ ችግር የፈታበት ቦታና ጊዜ የለም። ቴክኖክራቶች ስለቁጥር እንጂ ስለ ሰው ልጅና ስለስልጣኔ ብዙም ስለማይገባቸው ተግባራዊ የሚያደርጉት ፖሊሲ በሙሉ ችግሩን ውስብስብ ያደርገዋል እንጂ በፍጹም ሊፈታው አይችልም። በተጨማሪም የአገራችን የተወሳሰበ ችግር በአንድ ትልቅ ፕሮጀክትና ወይም ደግሞ እዚህና እዚያ በሚተከሉ ትናንሽ ፕሮጀክቶች ሊፈታ እንደማይችል መገንዘብ ያስፈልጋል። ኢኮኖሚያዊ ክንውን ከህብረ-ብሄር ግንባታ ጋር እስካልተያያዘ ድረስ ትርጉም ሊኖረው በፍጽም አይችልም። ስለሆነም ሰፊውን ህዝብ ያስቀደመና ለሁሉም የሚያመች ቆንጆ አገር ለመገንባት ከዚህ ከተክኖክራሲያዊ ሞዴል ባሻገር ማየትና ማለም ያስፈልጋል። በዚህ መልክ ብቻ ወደ ተፈለገው ዕውነተኛው ነፃነት ማምራት ይቻላል። የተከበረችና የምትፈራ አገርም  መገንባት ይቻላል።

 

ስለሆነም አምባገነንነትን እቃወማለሁ፣ ነፃነትን አመጣለሁ ለሱም ጠበቃ የቆምኩ ነኝ የሚል ኃይል ሁሉ ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተስፋፋው የተዛባ ስርዓትና ለብዙ ህዝቦችም ነጻነት ጠንቅ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ እንዴት ዕውነተኛ ነፃነት ሊመጣ እንደሚችልና ተግባራዊም እንደሚሆን ማስረዳት ያስፈልጋል። ይህንን ሳያሳዩና ሳያስተምሩ ነፃነት ነፃነት አየተባለ የሚደረገው ውትወታና ህዝብን ማደናበር ወደ ዕውነተኛው ነፃነት በፍጹም ሊያመራን አይችልም። ትግላችን ውስብስብ ስልሆነ ብዙ ጥያቄዎች በሳይንስ፣ በፍልስፍናና በቲዎሪ ደረጃ መብራራትና መልስ ማግኘት አለባቸው። ይህ ሲሆን ብቻ ለዕውነተኛ ነፃነት የቆመው ኃይል ማን እንደሆነ መታወቁ ብቻ ሳይሆን፣ የነፃነት ትግላችንም የተቃና ይሆናል ማለት ነው። መልካም ንባብ!!

 

ፈቃዱ በቀለ

fekadubekele@gmx.de 

ማሳሰቢያ፣  የዚህ ጽሁፍ መልዕክት ያለንበትን የተወሳሰበ የዓለም ሁኔታ ለማሳየት ብቻ ነው።የዚህ ጽሁፍ ሌላውና

                መሰረታዊው ዓላማ የተወሳሰበውን ዓለም ሁኔታ እስካልተረዳን ድረስ ወይም ለመረዳት የማንፈልግ እስከሆነ

             ድረስ ለነፃነት የሚደረገው ትግል የተሟላ ሊሆን አይችልም።  ጽሁፉ ማንንም ለማወናበድ የቀረበ ወይም ደግሞ

             አንድን ርዕዮተ-ዓለም ለማስፋፋት የታቀደና ወይም በጥላቻ ላይ ተመርኩዞ የቀረበ ሆኖ መወሰድ የለበትም።

             በማስረጃ የተደገፈ ነው። ሁለተኛ፣ ይህ ዐይነቱ ጽሁፍ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሮችና የኢንቬስቲጋቲቭ

             ጋዜጠኞች ስራ ነው። ስለሆነም ወደ ፊት የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሮች እንደዚህ ዐይነቱንም ሁኔታ እያተቱ

             ቢያቀርቡ ብዙ ሃሳቦችን ማንሸራሸር ይቻላል። ሶስተኛ፣ ይህ ዐይነቱ አቀራረብ በጣም አድካሚ ስለሆነ ተግባሩን

             ለፖለቲካ ሳይንስ ምሁሮች አስተላልፋለሁ። ብዙ ነገሮችን እየተከፋፈልን ብንሰራ ድካምን ማቃለሉ ብቻ ሳይሆን

             እንደሚታወቀው የስራ ክፍፍል ጥራትንም ያመጣል። እያንዳንዱ በችሎታው ላይ ቢያተኩር ለኢንፎርሜሽን

             መለዋወጥ በጣም ያመቻል። አራተኛ፣ የዚህ ጽሁፍ መልዕክት እስካሁን ባደረግነው የትግል ዘዴ ለመቀጠል

             እንደማንችል ለማሳሰብም ነው። ርስ በራሳችን እየተባላን አገራችንን ከማጥፋት ይልቅ በከፍተኛ የንቃተ-ህሊና

             በመታገዘና በመሰባሰብ በጋራ እንድንታገል ነው። ስለዚህም ራሳችንም የጠላት መሳሪያ ላለመሆን ለማሳሰብ ብቻ

             ነው። የኛ አጉል መናቆርና መበላላት፣ ወይም እንደጠላት መተያየት የመጨረሻ መጨረሻ ለጠላት የሚያበጀውና

             አገራችንን የሚያወድም ነው። የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲና የሃይማኖት ሰለባ ከመሆን መጠንቀቅ አለብን። የነፃነቱ

             ቁልፍ  በራሳችን ውስጥ ያለ ሲሆን፣  መቀዳጀትም የምንችለው ራሳችንን መልሰን መላልሰን በመጠየቅ ብቻ

             ነው።

የህወሓት መፈክር፡ ‘የአማራ የበላይነት ይውደም!’ (በአብርሃ ደስታ)

$
0
0

Abrha Desta

በአብርሃ ደስታ

ግርማይ ገብሩ የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የአሁን የቪኦኤ (VOA) ዘጋቢና ደራሲ ነው። ዓላማዬ ስለ ግርማይ ገብሩ ለመፃፍ አይደለም፤ ግርማይ በፌስቡክ ገፁ ስላሰፈረው መረጃ ለመዋስ እንጂ። መረጃው ከዚህ በፊትም አውቀው ነበር። ግን ለማስረጃ ያህል ግርማይን ልጥቀስ: ምክንያቱም ግርማይ የህወሓት ታጋይ ነበርና።

ግርማይ በ1969 ዓም የህወሓት (ተሓህት) ሦስቱ መፈክሮች ሲጠቅስ የመጀመርያውና ዋነኛው አድርጎ የፃፈው “አፄነት፣ መስፍንነትና የአማራ የበላይነት ይወድማሉ” ይላል።
በትግርኛ “ካብ ጭርሖታት ህወሓት 1969 ዓም: ሃፀይነት፣ መስፍንነትን ናይ አምሓራ ዕብለላን ዓነውቲ እዮም!” ይላል። ግርማይ ገብሩ አልተሳሳተም። ከህወሓቶች ጋር የማልስማማበት ግን ነጥብ አለኝ።

እርግጥ ነው። እኔም አፄነትና መስፍንነትን እንደ ስርዓት አልቀበልም። ምክንያቱም አፄነትና መስፍንነት (እንደ ስርዓት) ላሁኗ ኢትዮጵያ አይመጥኑም። የአፄነትና መስፍንነት ስርዓት በኢትዮጵያ ታሪክ እዚ ግባ የሚባል ለውጥ አላመጣም። ስለዚህ እኛ የሚያስፈልገን ዘመናዊ (ከዘመኑ ንቃተ ህሊናችን ጋር አብሮ የሚሄድ) የህዝብ አስተዳደር (ዴሞክራሲ) እንጂ ንጉስነት (የሰው ገዢነት) አይደለም። የምንፈልገው የሕግ የበላይነት እንጂ የንጉስ የበላይነት አይደለም።

ግን አፄነትና መስፍንነት እንደ ስርዓት ባልቀበለውም የንጉሳውያን ቤተሰቦችና መሳፍንቶች መጥፋት አለባቸው ብዬ ግን አላምንም። እኔ ብሆን እነኚህ የንጉስ ቤተሰቦችና መሳፍንት ቁልፍ የመንግስት ስልጣን አልሰጣቸውም ነበር። በሀገራቸው በሰላም እንዲኖሩ ግን እፈቅድላቸው ነበር። ምክንያቱም እንደማንኛውም ሰው ዜጎች ናቸው፤ ለሀገራቸው በተቻላቸው መጠን አስትዋፅዖ አድርገዋል። ስለዚህ ንጉሳዊ ቤተሰብና መሳፍንት ስለሆኑ ብቻ መጥፋት አለባቸው ብዬ አልፈርድም። እንደ ጠላትም አላያቸውም፣ እንደ ዜጎች እንጂ።

ህወሓት ግን በመፈክር ደረጃ በጠላትነት ፈረጃቸው። በተግባርም አጠፋቸው፣ ገደላቸው። በንጉሳዊ ቤተሰብና መስፍንነት ዝንባሌዎች ሰበብ ብዙ የተምቤን፣ ዓጋመ፣ እንደርታ፣ ዓድዋ፣ ሽረ፣ አክሱም ወዘተ መሳፍንቶች እንዲጠፉ ተደረገ። ‘ትግራይ ከመሳፍንቶች ነፃ ወጣች’ ተባለ። እውነታው ግን ‘ትግራይ ተገደለች’ መባል ነበረበት። መሳፍንቶች ከስልጣን ማውረድ እየተቻለ መግደል ምን አመጣው (ህወሓቶች ከስልጣን ማውረድ እየተቻለ መግደል ለምን ያስፈልጋል)?

ባጠቃላይ መሳፍንቶቹ ሲወድሙ ትግራይ ወደመች። አሁን በትግራይ የተቃውሞ መንፈሱ የተዳከመው በመስፍንነት ሰበብ ብዙ ብቁ ሰው ስለተፈጀብን ነው የሚል እምነት አለኝ። በህወሓት የተገደሉብንን ያህን በሌላ ስርዓት አልተገደሉብንም። ስለዚህ መሳፍንቶች ከስልጣን በማውረድ (መሳፍንቶችን ሳይሆን መስፍናዊ ስርዓቱ) ከህወሓቶች ጋር እስማማለሁ። መስፍናዊ ስርዓቱ ለማጥፋት መሳፍንቶቹ ማጥፋት ከሚል የህወሓት መፈክር ወይ መርህ ግን አልስማማም።

ሌላውና መሰረታዊ የህወሓት ችግር “የአማራ የበላይነት ይውደም!” የሚል መፈክር ነው። እኔም ብሆን የማንም ሰው ወይ ብሄር ወይ ሌላ አካል የበላይነት አልቀበለም። የቴድሮስ ወይ ዮሃንስ ወይ ምኒሊክ ወይ ኃይለስላሴ ወይ መንግስቱ ወይ መለስ ወይ ኃይለማርያም ወይ አማራ ህዝብ ወይ ትግራይ ህዝብ ወይ ኦሮሞ ህዝብ ወይ ሌላ … የበላይነት አልቀበልም። እኔ የምቀበለው የበላይነት ‘የሕግ የበላይነት’ ብቻ ነው። የሌላ የማንም የበላይነት አልቀበልም።

እንደ ፖለቲካ ድርጅት አንድን ህዝብ ዒላማ አድርጎ መነሳት ግን ስህተት ብቻ ሳይሆን በሽታ ነው። ህወሓት (ተሓህት) የአማራን ህዝብ ዒላማ አድርጎ ሲነሳ፣ ሌሎች የህወሓት ተቃዋሚዎች ደግሞ በህወሓት ምክንያት የትግራይን ህዝብ ዒላማ ሲያደርጉ ዉጤቱ ምን ይሆናል? አንድን ህዝብ ከሌላ ህዝብ ጋር የማጣላት ስትራተጂ የፖለቲካ ዕብደት ነው። ህዝብና ገዢው መደብ አለመለያየት (አንድ እንደሆኑ አድርጎ ማሰብ) የፖለቲካ እውቀት ማነስ ዉጤት ነው። ስርዓቱ መቃወምና መታገል እየተቻለ ህዝብን ዒላማ አድርጎ በህዝቦች ላይ መተማመን እንዳይኖር መትጋትና በህዝቦች መካከል ጥላቻ እንዲነግስ መስራት ጠባብነት ነው።

አንድን ህዝብ የበላይነት ሊይዝ አይችልም። አንድን ቡድን ግን በአንድን ህዝብ ስም በመነገድ ሌሎችን ሊበድል ይችላል። የሰው የበላይነት (በህዝቦች ላይ) ሊተገብር ይችላል። ህዝብ እንደ ህዝብ ግን ሌላውን ህዝብ ሊበድል አይችልም። ህወሓት የትግራይን ህዝብ እንደሚወክል ይነግረናል። የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ እያለ ሌሎች ህዝቦች (የትግራይን ጨምሮ) ይበድላል። ሌሎች ህዝቦች (የትግራይ ዉጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን) ደግሞ በህወሓት ስርዓት ሲበደሉ በትግራይ ህዝብ የተበደሉ አድርገው ያስባሉ። ግን ስህተት ነው። መታረም አለበት። የትግራይ ህዝብ ለራሱ በህወሓት አገዛዝ የሚበደል ነውና።

“የአማራ የበላይነት” የሚባለው የህወሓት በሽታ እስካሁን ፈውስ አላገኘም። በመርህ ደረጃ ህዝብን ዒላማ አድርጎ ህዝብን ለመታገል መነሳት ስህተት ነው ብያለሁ። በፖለቲካ ህዝብን ዒላማ አይደረግም። ምክንያቱም የፖለቲካ ዓላማ ህዝብን ማገልገል እንጂ ህዝብን መጨቆን አይደለም። ስለዚህ ህዝብን የመበደል ዓላማ መያዝም መተግበርም የህሊና ወንጀል ነው። ህወሓቶች ይህን በሽታ (“የአማራ የበላይነት” መፈክር) አልተዋቸውም። አሁንም “ፀረ አማራ” እንቅስቃሴዎች አሉ። የህወሓት የአሁኑ ስትራተጂ “እኛ ከስልጣን የምንወርድ ከሆነ ከአማራ ጋር አብረን አንቀጥልም” የሚል ገንጣይ አስተሳሰብ እያራመዱ ይገኛሉ። “እኔ ከሌለሁ ሠርዶ አይብቀል …” ዓይነት ስትራተጂ መሆኑ ነው። በጣም የሚገርመው ነገር ፀረ ብአዴንም መነሳታቸው ነው። ለነሱ ከስልጣን ከሚወርዱ ኢትዮጵያ ብትበታተንና ትግራይን አስገንጥለው ትግራይን እየጨቆኑ ቢገዙ ይመርጣሉ።

ግን ይህን “አማራ” የሚባል ህዝብ መቼ ይሆን የበላይነት ይዞ ሌሎች ህዝቦችን የበደለው? አንድን ህዝብ እንዴት ሌላውን ህዝብ ይበድላል? ህዝብ ህዝብን ሊበድል አይችልም። ምክንያቱም አንድን ህዝብ ሌላውን ህዝብ መበደል ከጀመረ (ከቻለ) ህዝብ መሆኑ ቀርቶ ገዢ መደብ (elite) ሁነዋል ማለት ነው። ገዢ መደብ ከሆነ ደግሞ ህዝብ አይደለም። ገዢ መደብ ስርዓት ነው። ህዝብና ስርዓት ደግሞ ይለያያሉ።

ምናልባት የህዝብ የበላይነት አለ የምንለው ህዝብን የሚያስተዳደር (የሚገዛ) ስርዓት ከህዝቡ የወጣ ሲሆን ይሆን? ይህም አሳማኝ አይደለም። ምክንያቱም ገዢ ሁሌ ከህዝቡ ነው የሚወጣው (የቅኝ ግዛት ካልሆነ በስተቀየር)፤ ገዢ ከህዝቡ እንጂ ከማርስ አይመጣም። የኢትዮጵያ መሪ ከኢትዮጵያ ህዝብ ይወጣል። በኢትዮጵያ ብዙ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አሉ። ስርዓቱ ከሁሉም ህዝቦች ሰዎች ይኖሩታል። መሪ ግን አንድ ነው የሚሆነው። ያ አንድ ሰው (መሪው) ከአንድ ብሄር ሊሆን ይችላል። ያ አንድ ሰው ስልጣኑ ተጠቅሞ ሌሎች ህዝቦችን ሊበደል (ወይ ሊጠቅም) ይችላል። ሰውየው የፈጠረው ስርዓት ለህዝቡ ቢጎዳም ቢጠምም ከስርዓቱ ይገናኛል እንጂ መሪው ከመጣበት ብሄር ጋር አይገናኝም። ስለዚህ ገዢዎች የሚወክሉት የፈጠሩትን ስርዓት እንጂ የመጡበትን ብሄር አይደለም።

የደርግ ስርዓት ሲበድለን፣ “አማራ በድሎናል” ይሉናል። የኃይለስላሴ ስርዓት ሲበድለን “አማራ በድሎናል” ይሉናል። የምኒሊክ ስርዓት ሲበድለን “አማራ በድሎናል” አሉን። የህወሓት ስርዓት ሲበድለንስ ማን በደለን ሊሉን ነው? የትግራይ ህዝብ? አይሆንም። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ የትግራይን ህዝብ ይበድላል? አንድን ህዝብ ራሱን ይበድላል? በደል ሁሉ ወደ አማራ ህዝብ ለምን? ስርዓትና ህዝብ ማገናኘት የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል።

ግን እስቲ ይሁን፤ መሪዎች የመጡበትን ብሄር ይወክላሉ እንበል (ስህተት ቢሆንም)። እነሱ (መሪዎቹ) ሲበድሉ የመጡበት ብሄር በበዳይነት ተፈርጆ እንደ ጠላት ይቆጠር እንበል። የአማራ ህዝብ መቼ ይሆን በመሪዎቹ አድርጎ ሌሎች ህዝቦችን የገዛ (የበደለ)? ያለፉ ጨቋኝ ስርዓቶች አማራ ነበሩ ያለው ማነው? አማርኛ የተናገረ ሁሉ አማራ አይደለም። እስቲ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ መሪዎች እንመልከት።

ብዙ ግዜ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው ከአፄ ቴድሮስ ነው (ወይም ከዚሁ እንጀምር! ምክንያቱም ከአፄ ቴድሮስ በፊት ኢትዮጵያ በመሳፍንቶች ነበር የምትተዳደረው። በዘመነ መሳፍንት መሳፍንቶች የራሳቸውን ህዝብ (ብሄር) ይገዙና ይበድሉ ነበር)። “አማራ” ተብሎ ከተሰየመው አከባቢ የሚወለድ ገዢ ቴድሮስ ነው። አፄ ቴድሮስ ኢትዮጵያ አንድ ለማድረግ በዛን ግዜ የነበሩ መሳፍንቶች ተዋጉ። አፄ ቴድሮስ ዉግያው የጀመሩት በአማራ መሳፍንቶች (የጎጃም፣ ወሎና ጎንደር) ነበር። ቴድሮስ “ከአማራ ስለመጣሁ፣ አማራ ስለምወክል፣ የአማራ መሳፍንቶች ማጥፋት የለብኝም” አላሉም። (ህወሓት ለትግራይ መሳፍንቶች እንዳደረገው ሁሉ)። ስለዚህ አፄ ቴድሮስ አማራን ወክለው ሌላው ኢትዮጵያዊ አልበደሉም (ከበደሉም ለሁሉም ነው)። ስለዚህ “በአማራ ህዝብ ተገዛን” የሚለው ክስ “በአፄ ቴድሮስ ተገዛን” የሚል እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

የአማራ ተወላጅ የሆነ የኢትዮጵያ ገዢ ቴድሮስ ብቻ ነው ብዬ አስባለሁ (ጉዳዩ ለታሪክ ተመራማሪዎች ልተወው እንዳልሳሳት፤ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ)። ዮሃንስ አማራ አልነበረም፣ ምኒሊክ አማራ አልነበረም፣ ኃይለስላሴ አማራ አልነበረም፣ መንግስቱ አማራ አልነበረም፣ መለስ አማራ አልነበረም፣ ኃይለማርያም አማራ አይደለም። ማነው አማራ?

ምናልባት “የአማራ ገዢዎች” የምንለው ግለሰቦቹ (ንጉሶቹና መሪዎቹ) ሳይሆን ስርዓቱ ነው ካልን ያው ስርዓቱማ ከሁሉም ህዝቦች ተወካዮች አሉበት። አማራ ለብቻው ገዥ ነበር ማለት አንችልም። ምናልባት ገዢዎቹ አማርኛ ስለሚናገሩ ነው ካልን ደግሞ አማርኛ የተናገረ ሁሉ አማራ አይደለም። አቶ መለስም አማርኛ ይናገር ነበር። አፄ ዮሃንስም አማርኛ ይናገሩ ነበር (አማርኛ የኢትዮጵያ ኦፊሽየላዊ የስራ ቋንቋ እንዲሆን የወሰኑት አፄ ዮሃንስ ናቸው የሚል መረጃ አለኝ፤ ‘መረጃ’ እንጂ ‘ማስረጃ’ አላልኩም)።

የአማራ ህዝብ እንደ ማንኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በኢትዮጵያ ገዢዎች ሲሰቃይ የነበረ ነው። ባልበላበት በልተሃል፣ ባልገዛበት ገዝተሃል ሲባል ይገርማል፤ ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ። የትግራይ ህዝብ ሳይበላ በልተሃል፣ ሳይገዛ ገዝተሃል ይባላል፤ ህወሓት በበላው፣ ህወሓት በገዛው። ህወሓት ትግርኛ ተናጋሪ ስለሆነ ከትግራይ ህዝብ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም (በፖለቲካ መልኩ)። ያለፉ ገዢዎች አማርኛ ስለሚናገሩ ከአማራ ህዝብ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም። ህዝብ ሌላ ገዢ ሌላ።

ባጭሩ ፀረ ህዝብ አቋም መያዝ ተገቢ አይደለም (ለማንኛውም ህዝብ)። ሰው የፈለገውን የፖለቲካ አመለካከት መያዝ ይችላል። “የቀድሞ ስርዓት አባላት …” ምናምን እያልን አንፈርጅ። የህወሓት አባላት ለሌሎች ሰዎች የቀድሞ ስርዓት አባላት፣ ናፋቂዎች ወዘተ እያላቹ ስትፈርጁ እናንተም ራሳችሁ ከህወሓት ስርዓት በኋላ “የቀድሞ ስርዓት አባላት ..” ምናምን እየተባላቹ ስማቹ ይጠፋል፣ የፈለጋችሁን የፖለቲካ ፓርቲ አባል የመሆን መብታቹ ይገደባል። አሁን በሌሎች ላይ የምትፈፅሙትን ስም የማጥፋት ተግባር በናንተ (በራሳቹ) ይፈፀማል።

ስለዚህ እናስተውል። ከጥላቻ ፍቅር ይሻለናል። ጥላቻ ይውደም። አሜን!

It is so!!!

የመረጃ ነፃነት ?…

$
0
0
(ይድነቃቸው)

(ይድነቃቸው)

ይድነቃቸው ከበደ

‹‹ ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል ? ›› በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል ፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል፡፡ እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል ‹‹ እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ ? ››አላቸው ፡፡ እነሱም መለሱለት፡፡ ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ 9ቁ 18 ላይ ይገኛል ፡፡

መረጃ አይናቅም አይደነቅም ማለት እንዲህ ነው፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ሰዎች ስለሱ ምን እንዳሉ ብቻ ሳይሆን ምን እያሰብ እንደነበር የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ግን መጠየቅ እና መመለስ አሳብን መግለፅ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶ እንደሰው በምድር በተመላለሰበት ወቅት መረጃ ይጠይቅ የነበረው እሱም ስለራሱ መረጃ ይሰጥ የነበረው፡፡ እርግጥ ነው ክርስቶስ ይህን ሲጠይቅ የራሱ ምክንያት አለው፡፡
በመሆኑም ሃሳብ መግለፅ ተፍጥራዊ መብት ነው ወደሚለው ዓለም አቀፍ ስምምነት በመደረሱ የመናገር ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት የዲሞክራሲ ዋና የድም ስር ነው የተባለው፡፡ ስለዚህም ተሰባስቦ መቃወም እንዲሁም መደገፍ ፣ አንድ ሰው የሚመስለውን ሃሳብ በፈለገው መንገድ መግለፅ፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ መንግስትን የመተቸት፣ በራስ ፍቃድ የመናገረ እና ያለመናገር ፣ በዓልንና አይማኖትን መከተልና ማስፋፋት እንዲሁም ህግ ለሁሉም የሚሰራ ስለመሆኑ መረጋገጥ እና የመሳሰሉት ሁሉ ተግባራዊ የሚሆነው ተአቅቦ ያልተደረገበት የመናገርና የመረጃ መብት ልውውጥ ተግባሪዊ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
ለመደርደሪያነት የዚህን ያኸል ከተባለ ወደ ዋናው ጉዳይ አስፈቅደን ሳይሆን ፈቅደን እንገባለን፡፡ ያነሳነው አሳብ ‹‹ መረጃ ›› እንደመሆኑ መጠን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ተፍጥሯዊ መብታችን በፈለግነውና በፈቀድነው መንገድ እንገልፃለን፡፡ እኛ ስል ለመረጃ ነፃነት የቆምነው ሁላችንም ማለቴ ነው፡፡
ሰው በመናገሩ አና በመፃፉ ብቻ ለእስር እና ለስደት የሚዳረግበት አገር በዋነኝነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዶ ናት፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በኢትዮጵያ ህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገ መንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብ ላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆ ይገኛል፡፡

Free mediaይሁን እንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አልፎ ተርፎ በአስተሳሰብ ወይም በአመለካከት ላይ ተፅኖ እስከመፍጠር ተደርሶኦል ፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ለህግም ሆነ ለሞራል ተቃራኒ እንደመሆኑ መጠን የፈጀውን ፈጅቶ ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ሃቅ ነው፡፡ ነፃ አሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል አሉ ? ያሉት ጋዜጦች እና መፅሔቶች እየደረሰባቸው ያለው ማስፈራሪያና ዛቻ ደረጃው ምን ያኸል ደርሶአል የሚለውን መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በቅርቡ በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ አክራሪነትና ፅፈኝነት የሚያበረታቱና የሚያሰራጩ በማለት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለህዝቡ ተገቢውን መረጃ እያስተላለፉ ያሉ የእትመት ውጤቶችን ከገቢያ ለማውጣትና ፈርጆ ለመክሰስ እየተደረገ ያለው ዝግጅት ሌላው ማሳያ ነው፡፡ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በሁለተኝነት ደረጃ ላይ ትገኛለች ፡፡መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ለእስር የሚዳረግበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡

በዲሞክራሳዊ ሥርዓተ ዜጎች የሚኖሩት ግልፅ በሆነ የሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡ የትኛውም አይነት ሃሳብ ከማንም ሊመጣ ይችላል ቁም ነገሩ መሆን ያለበት የሚመጣው ሃሳብ የሚመከተው በምንድነው የሚለው ነው፡፡ ለነፃ ንግግር ችግር የተሻለው መንገድ የበለጠ ነፃ ንግግር ነው፤ በመናገር መብት ላይ የሚደረግ ማናቸውም ተፅእኖ ሲውል ሲያድር በእያንዳንዱ ግለሰብ የመናገር መብት ላይ ስጋት ሊያስከትል ይችላል፡፡ለዚህም ነው ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ነው ለማለት የሚያስደፍረው፡፡ምክንያቱ ደግሞ ማንም ሰው በስጋት ውስጥ መኖርን ስለማይፈልግ ነው፡፡
በመሆኑም በአገራችን እየከሰመ ያለው ሃሳብን በነፃ የመግልፅ እና መረጃ የማግኘት መብት በገዥው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረት ወደመሆን ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ለዚህም እንደማሳያ ከሰሞኑ የህዝብ ሳይሆን የገዥው መንግስት አንደበት በሆነው በኢቲቪ በተላለፈው የዘጋቢ ፊልም ግለሰቦችም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲ ለኢሳት መረጃ ከመስጠት እንዲቆጠቡ ምክር መሰል ማስጠንቀቂያ ተላልፏል፡፡

ለዚህም እንደምክንያት የቀረበው ኢሳት የተባለው የመገናኛ ብዙሃን በሽብርተኛ ድርጅት የሚደገፍ ነው የሚል ምክንያት ነው፡፡ ኢቲቪ በኢህአዴግ እንደሚደገፍ ሁሉ ኢሳት በማንም ሊደገፍ ይችላል፤ ቁም ነገር ሆኖ መታየት ያለበት ኢቲቪ ሆነም ኢሳት የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድነው ፡፡ በተጨማሪ መልዕክቱ ለህግም ሆነ ለሞራል ምን ያኸል ተቃራኒ ነው የሚለውን ነው፡፡ በተጨማሪ ኢቲቪ እንዲሁም ኢሳት በህግ መደመጥ እንዲሁም መሰማት የተከለከሉ የመገናኛ ብዙሃን ናቸው ወይ ተብሎ መጠየቅና መልስ ሊሰጥባቸው የሚገባ አሳቦች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ወደ መልሱ ስናመራ ኢቲቪ እንዲሁም ኢሳት በህግ የተከለኩ አይደሉም ዋንኛው እና አስፈላጊው ነገር ይሄ ነው ሌላው የህጉ ደጋፊ ሃሳብ ነው፡፡

በመሆኑም ከዚህ በኋላ የህግ ጉዳይ ሳይሆን የፍላጎት ምርጫ ነው የሚሆነው፡፡ የፈለጉትን መስማት እና ማዳመጥ እንዲሁም በፈለጉት የመገናኛ ብዙሃን መንገድ ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን ማግኘት ግለሰብ ከሆነ እንደግለሰቡ፣ ተቋም እንደተቋም እንዲሁም ፓርቲ እንደ ፓርቲ የመምረጥ የራስ መብት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከኢቲቪ ኢሳት ከአዲስ ዘመን አዲስ አድማስ የዝወትር ፍላጎታቸው ለሆነ እንዲሁም በተመሳሳይ ከኢሳት ኢቲቪ ከአዲስ አድማስ አዲስ ዘመን ለመረጡ ምርጫቸውን ማክበረ ነው፡፡
ሌላው እና አሳሳቢ ሊሆን የሚገባው ሰው የመረጠውን መስማትና ማዳመጥ እንዲሁም ማንበብ መብቱ እንደጠጠበቀ ሆኖ ግለሰበ ወይም ተቋም ሃሳቡን እንዴት የመግለፅ መብት እና ግዴታ አለበት የሚለው ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ተቋም ወይም ግለሰብ ሃሳብን ወይም መረጃን በማንኛውም መንገድ የመገልፅ ሙሉ መበት በህግ የተጠበቀ ነው ፡፡እንዲኹም የዚህ መብት ተቃራኒ የሆኑ ማናቸውም ነገሮች ተቀባይነት እንደሌላቸው በህገመንግስቱ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በኢሳት ሆነ በማናቸውም የመገናኛ ብዙሃን ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን መስጠጥ በራሱ ወንጀል ወይም ጥፋት አይደለም ይህ የሆነው ደግሞ መብት ከመሆኑ አንፃር ነው፡፡
eskinder
ከዚህ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ሃሳብን በመግለፅ እና መረጃን በመስጠት ዙሪያ ግዴታ ሊያመጣ የሚችለው ምንድነው የሚለው ነው፡፡ ግለሰቡ ወይንም ተቋሙ በግልፅ በህግ የተከለከለ መረጃ ወይም ሃሳብ የገለፀ እንደሆነ ግዴታው ተጠያቂነትን ስለሚያመጣ በህጉ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ይህ የህግ ተጠያቂነት አዱላዊነት የሌለበት ለሁሉም በሁሉም ቦታ እኩል የሚሰራ ነው፡፡ ይህም ማለት በህግ የሚያስጠይቅ ንግግር በኢሳትም ሆነ በኢቲቪ እንዲሁም በቢቢሲ ያደረግ በህግ ከመጠየቅ ንግግር ያደረገበት የብዙሃን መገኛኛ ሊታደገው አይችልም እንደማለት ነው፡፡
በመሆኑም በኢሳት ሃሳብን መግለፅ እንዲሁም መረጃ መስጠት አልፈልግም ማለት መብት ነው፡፡ ነገር ግን በኢሳት አሳባችሁን አትግለፁ መረጃም አትስጡ ማለት ከፍላጎት የመነጨ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን የለየለት የእብሪት ተግባር ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ አሰፋሪ ምኞት እና ተግባር የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ተምሮ ያለመለወጥ ልክፍትም ጭምር ነው! በተለይ በመንግስት ደረጃ ሲታሰብ እጅግ በጣም ያሳፍራል፡፡


የአንድነት ፓርቲ የመጪው ጊዜ ፈተና –ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

$
0
0

የግል አስተያየት

“አዲሱ” የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ግዛቸው ሺፈራው ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ስለመጪው የፖለቲካ እርምጃቸው እንዲህ ይላሉ ፦
” ከኢሕአዴግ ጋር ገንቢ ግንኙነት (Constructive Engagement) እንዲኖረን እፈልጋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ፖለቲካ ማብቃት አለበት፡፡ ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎችን የሚያያቸው እንደ ጠላት ከዚያም አልፎ እንደ ሽብርተኛ ነው. . . በእኛም በኩል ኢሕአዴግን የምናየው እንደ አውሬ ነው፡፡ ምናልባት የሠራውን ሥራ ሁሉ ዋጋ (Credit) ያለመስጠት አለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖለቲካችን ኢሕአዴግን መቃወም ብቻ ሆኖአል፡፡ ያ መቆም አለበት፡፡ ትልቁ ኳስ ያለው ኢሕአዴግ ዘንድ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ ወደፊት በማደርገው እንቅስቃሴ ገንቢ ግንኙነት አድርገን ያለውን የፖለቲካ ምኅዳር ለሁላችንም እኩል ማድረግ አለበት፡፡”
GizachewShiferaw
ይህ መንገድ፣ ካልተሳሳትኩ ” ሶስተኛው መንገድ” ( The Third Way) የሚባለውና አቶ ልደቱ አያሌው የ1997 ምርጫ አጣብቂኝ በገባበት ወቅት አምጥተው የደነጎሩት፣ በሌላ አነጋገር “መሀል ላይ መቆም” የሚባለው የፖለቲካ አካሄድ ነው። አሪስቶትል “መሀል ላይ መቆምን” ወርቃማ የፖለቲካ አካሄድ ነው ይለዋል ( The Golden mean- ) ። መሀል ላይ ቆመው የሚታገሉ ፖለቲከኞች ጫፍ እና ጫፍ ከቆሙት የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ሳይጋጩ ፣ ሁለቱንም መስሎ በመኖር ወይም ከሁለቱም ጫፎች የተወሰኑትን አስተሳሰቦች በመውሰድ የራስ አድርጎ በመታገል ያምናሉ ። “የመሃል ፖለቲካ” ምን ያክል ርቀት እንደሚወስድ በዚህ ዙሪያ የተሰሩ ትምህርታዊ ጥናቶችን ባላነብም፣ ሀሳቡን ሲያራምዱ የነበሩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተንም ሆኑ የቀድሞው የእንግሊዝ ጠ/ሚ ቶኒ ብሊየር ብዙ ርቀት እንዳልሄዱበት የሁለቱንም መጽሃፎች አንብቤ ተረድቻለሁ ። ዛሬም ቢሆን ዲሞክራቶችና ሪፑብሊካኖች ዳር እና ዳር ቆመው የአሜሪካን ፖለቲካ ይዘውሩታል፣ በእንግሊዝም ሌበርና ኮንሰርቫቲቮች ዳር እና ዳር ቆመው ይተያያሉ።

“መሃል ላይ የቆሙ” ፖለቲከኞች የራሳቸው የሆነ የፖለቲካ ፕሮግራም የላቸውም ተብሎ ስለሚታሰብ፣ ብዙውን ጊዜ በወላዋይነት ይከሰሳሉ፣ በምርጫ ጊዜ ድል የሚቀናቸውም አልፎ አልፎ ነው። ዲሞክራሲ በሆኑ አገሮች “መሀለኞች” የመመረጥ እድል የሚያገኙት ህዝቡ ጫፍና ጫፍ በቆሙ ፖለቲከኞች መሰላቸት ሲጀምር ብቻ ነው ፤ አምባገነንነት በሰፈነባቸው አገሮች ደግሞ መሀል ላይ የሚቆሙ ፖለቲከኞች ፈሪዎች ተደርገው ስለሚቆጠሩ ብዙም አይወደዱም። መሀል ሰፋሪዎች መሀል ላይ የሚቆሙት ከመንግስት የሚወርደውን ዱላ ስለሚፈሩ ነው ተብሎ ይታማሉ። አቶ ልደቱ አያሌው በ97ቱ ምርጫ “መሀል ላይ የመቆምን” ፖለቲካ ማራመድ ሲጀምሩ ደጋፊዎቻቸው በሁለት ምክንያቶች አልተቀበሉዋቸውም ነበር ፤ አንደኛው ምክንያት ምርጫውን ያሸነፉት “ዳር” ላይ ቆመው ባራመዱት የፖለቲካ አቋም እንጅ በሁዋላ ላይ ባመጡት “የመሀል ፖለቲካ” አስተሳሰብ ስላልነበረ፣ ደጋፊዎቻቸው አዲሱን ባህሪ ለመቀበል አልቻሉም ። አቶ ልደቱ የጨዋታውን ስልት ወደ ምርጫ ከመግባታቸው ቀደም ብሎ ቢያስታውቁ ኖሮ ሁዋላ ላይ የደረሰባቸውን አይነት ውግዘት አይደርስባቸውም ነበር፣ በምርጫውም ላያሸነፉ ይችሉ ነበር።

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ አቶ ልደቱ የጨዋታውን ህግ የቀየሩት በደህንነት ሃይሎች ብዙ እንግልትና ማስፈራሪያ ከደረሳቸው በሁዋላ በመሆኑ የአቋም ለውጡ ከፍርሃት ጋር ተያይዞባቸዋል። ጀግንነትን የሚያወድሰው የኢትዮጵያ ህዝብ ከመንገዱ ትንሽ ሸርተት ያለን ሰው በወላዋይነትና በፈሪነት ፈርጆ ይጠለዋል ።

ኢ/ር ግዛቸውም የመሀሉን ቦታ ይዘው እንደሚታገሉ አስታውቀዋል። እዚህ ላይ ሁለት ነጥቦችን እናንሳ። አንድነት ፓርቲ ከኢህአዴግ ጋር መልካም ግንኙነት ከማድረጉ በፊት በቅድሚያ በኢህአዴግ በኩል የሚቀርበውን ቅደመ ሁኔታ መቀበል አለበት፣ ያም ቅደመ ሁኔታ “የምርጫ ስነምግባር መመሪያ” ውን መፈረም ነው። መድረክና አንድነት ይህን መመሪያ አንፈርምም ብለው ላለፉት 6 ዓመታት በአቋማቸው ጸንተው ቆይተዋል። በ2002 ምርጫ ወቅት ኢ/ር ሀይሉ ሻውል ይህን መመሪያ በመፈረማቸው ከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ የደረሰባቸው ይመስለኛል፤ በወቅቱ አቶ ሃይሉ ፊርማውን የፈረሙት “ድጋሜ እንዳይታሰሩ ፈርተው ነው፣ ከፍተኛ ሀብት ያፈሰሱበትን ቢዝነስ እንዳይቀሙ በመስጋት ነው” እየተባሉ ይታሙ ነበር፤ ኢንጂነር ሃይሉ በገደምዳሜም ቢሆን፣ የአማካኙዋን ቦታ ይዘው ለመታገል ፈልገው ነበር። ኢ/ር ግዛቸውም ይህንን “የስነምግባር መመሪያ” ካልፈረሙ ከኢህአዴግ ጋር ቁጭ ብለው እንደማይነጋገሩ ያውቃሉ። ላለፉት 5 አመታት የስነ ምግባር መመሪያውን “አልፈርምም” ብሎ ጠንካራ አቋም ያራመደ ድርጅት፣ በአዲሱ አመራር አቋሙን እንደገና ለመፈተሽ ያሰበ ይመስላል። ፓርቲው መመሪያውን አልፈርምም በሚለው አቋሙ ከጸና ግን አዲሱ ሊቀመንበር ከኢህአዴግ ጋር ገንቢ ግንኙነት ለመመስረት የሚቸገሩ ይመስለኛል፣ ሌላ መንገድ አዘጋጅተው ከሆነ አላውቅም።
Andualem Aragie
ኢ/ር ግዛቸው በመሀል መንገድ ለመጓዝ ከመረጡ ከእርሳቸው በፊት በዚሁ መንገድ ተጉዘው የተሰባበሩ ፖለቲከኞች እጣ ፋንታ እንደሚገጥማቸው ለመናገር ነብይ መሆንን አይጠይቅም ፤ የፓርቲው ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቁም አያጠራጥርም። የያዙት አላማ ለበጎም ይሁን ለክፉ፣ አዲሱ መንገዳቸው ከፍርሀት ጋር ሊያያዝባቸው እንደሚችል ጥርጥር የለውም። ለዚህ ማጠናከሪያ የሚሆኑ ምክንያቶች ደግሞ አሉ። ሊቀመንበሩ ቀደም ብሎ፣ ከሌሎች የቅንጅት መሪዎች ጋር ታስረው በነበረበት ጊዜ የፈረሙት የይቅርታ ሰነድ አለ። ሊቀመንበሩ ገዢውን ፓርቲ የሚያስከፋ ነገር ከተናገሩ ይህ ፋይል በማንኛውም ጊዜ እንደሚመዝባቸው ይታወቃል፤ እንደ አንዱዓለም አራጌ የታሰሩበትን ገመድ ለመበጠስና ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት ምን ያክል ተዘጋጅተዋል የሚለውን ለመመለስ እቸገራለሁ፣ ከምርጫ 2002 ልምድ እንዳየሁት ግን የእስር ገመዳቸውን ለመበጠስ መዘጋጀታቸውን እጠራጠራለሁ። እንዲያውም የመሀሉን መንገድ አማራጭ ” የታሰሩበትን ገመድ ሳይበጥሱ፣ በገመዱም አጥብቀው ሳይታሰሩ ለመጓዝ ከመፈለግ የመጣ” ይመስለኛል። ፓርቲው ቀድሞውንም በረጅም ገመድ የታሰረን ሰው በመሪነት መምረጥ አልነበረትም፣ ከመረጠም ገመዱን ለመበጠስ የተዘጋጀ መሆን አለበት።
UDJ
የሊቀመንበሩ አካሄድ በእስር ላይ በሚገኙት አንዱለአም አራጌና ናትናኤል መኮንን ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም፤ አንዱዓለም ከሚታወቅባቸው ባህሪዎች አንዱ በአቋሙ የሚጸናና ላመነበት ነገር ህይወቱን ለመስጠት የተዘጋጀ ሰው መሆኑ ነው፤ ደስ ሲለው ወዲህ፣ ደስ ሳይለው ወዲያ የሚረግጥ ሰው አይደለም። ፓርቲው ለስድስት አመታት የተጓዘበትን መንገድ ቀይሮ መሀል ላይ ለመቆም ከወሰነ ፣ አቋማቸውን ለማሳወቅ እድል በማያገኙት አንዱአለምና ናትናኤል ላይ የስነልቦና ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም። አዲሱ መሪ ይህን ያሰቡት አይመስለኝም፣ ካሰቡበትም የእነ አንዱአለምን ሁኔታ ከግምት ያስገቡ አይመስለኝም፣ ከግምት ውስጥ አስገብተውት ከሆነም ፣ አንድ ነገር አስበዋል ማለት ነው። ለማንኛውም መጪው ጊዜ ለአንድነት ፓርቲ ፈተና የሚሆንበት ይመስለኛል።

“የህዝባዊ አንድነትና ኃይል የወያኔ ሕወሐት ማጥፊያ መድሃኒት”

$
0
0

ከሮባ ጳዉሎስ

ካለመታደል ሀገራችን ዛሬም ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በልማትና በእድገት ጎዳና የምትራመድ ሀገር አልሆነችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ ዓቢይ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው የህዝብን ይሁንታን ያገኘ፡ ህዝብን በእኩልነት የሚዳኝ፡ ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት አለመመስረቱ፡ አገርና ህዝብ የሚተዳደሩበት ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አለመኖሩ ነው። እስከዛሬ በተጨባጭ እንደታየው በ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈራረቁበት ገዥዎቹ በየበኩላቸው አንዱ ከሌላው የሚለዩባቸው ባህርያት ቢኖራቸውም ሁሉንም ግን አንድ የሚያስመስሏቸው ባህርያትም አሏቸው። እነሱም ሁሉም በኃይል ሥልጣን መያዛቸው፡ አምባገነንነታቸው፡ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማራመዳቸው፡ በህዝብ መካከል የጋራ መተማመንና ከበሬታን ለመፍጠር፡ ሁሉም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቱ ለማስፈን አለመቻላቸው ደግሞ ዛሬ ለሁሉም በግልጥ እየታየ ያለ ነው። በዚህም የተነሳ በሀገራችን ለብሔራዊ ክብርና ነፃነት፡ ለዲሞክራሲ፡ ለማህበራዊ ፍትህ፡ ለሰላምና ለእኩልነት የሚታገሉ ኃይሎች የሰላማዊ ለውጥ በሮች ስለተዘጉባቸው የአ መፅን ጎዳና እንዲከተሉ የሚጋብዝ በር ተቀዶ ይገኛል።
tplf-rotten-apple-245x300
በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት ንእዲፈጠር፡ ሕዝቡም አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ አግኝቶ ያለስጋት ለመኖር እንዲችል፡ የዳኝነት ተቋሞች ነፃ ሆነው የሚሠሩበት፡ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ሁኔታ እንዲፈጠርና፡ ህዝቡም በህግና ሥርዓት መኖር ላይ እምነት እንዲያድርበት ለማድረግ እንዲቻል፡ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ኃይሎች በተናጠልም ሆነ በኅብረት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል። ሆኖም እስከዛሬ የተደረጉት ጥረቶችን ሁሉ በማምከን ወያኔ የሰላምና የእርቅ መሰናከል ከመሆኑም ባሻገር በንፁሃን ዜጎች ደም ሰላምን አጠልሽቶታል። ወያኔ ስለ ሰላምና እርቅ ሊሰማም ሊነጋገርም እማይችልበት የደም ስካር ላይ ደርሷል።

ብአዴን ቢመጣ ኦህዴድ ቢመጣ ደህዴን ቢመጣ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ጠንከር ያለ ለለውጥ የተዘጋጀ – አስከ ሞት የቆረጠ -ጠቅላይ ሚኒስተር ስልጣን አገኘ ማለት የህወሃት የበላይነት እና ፈላጭ ቆራጭነት ፍላጎት ፈተና ይገጥመዋል ማለት ስለሆነ! ህወህት የበላይነቱን ለማሰጠበቅ የፈጠራቸው የመንግስት ስልጣን አደረጃጀት አና ተቋማት ዛሬም በሙሉ ሃይላቸው አሉ። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት ሳይዳከም ለውጥ አይመጣም። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት መሰረቱ ደሞ ከምንም በላይ ወታደራዊ ሃይሉ ላይ የተመሰረተ አንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በደህነንት ቢሮ ያሉትን የህወሃት አመራሮች ከታች ያሉት ማዳክም የሚችሉበትን አጋጣሚ አና ሁኔታ ተጠቅመው አስካላዳከሙት ደረስ የህወሃት የስልጣን የበላይነት ትርጉም ባለው ሁኔታ እክል ሊገጥመው አይችልም።

ሌላ ሌላውን ትተን መሰረታዊ የሆነ ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ ያስፈልጋል፣ የፍትህ ስርዕቱ የፍትህ ስርእት መመስልም መሆንም አለበት፣ የነጻው ፕሬስና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ህዳሴ አንመራለን አየተባለ በመካከለኛው ዘመን አና ከዛ በፊት ከነበረው አንደነበረው በሰይፍ አና በሰደፍ መያዝ የለበትም። አነኚህ ወሳኝ ርምጃዎች በአዝጋሚ ለውጥ ይመጣሉ ብየ አላስብም። የአዝጋሚ ለውጥ ዲስኩር (ፍላጎት ካለ ፍላጎትም) ጭራሽ ወደማይቀልበስ የባርነት ዓለም አና ዘመን የመውሰጃ ከፓለቲካ ዘዴ ሊሆን ይችላል። ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓለቲካ መሪዎች ዘብጥያ ሲጣሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፈጠሩትን ዓይነት ጫና መፍጠር ስላልተቻለ አንኳን መሰረታዊ የፕሬስ ነጻነት አና በነጻነት ያለገደብ የመደራጀት መብት የሚከበርበት ፍንጭ ሊገኝ ቀርቶ የታሰሩትን ጋዜጠኞች አና የፓለቲካ መሪዎች ማስፈታት አንኳን አልተቻለም። ጭራሽ መብታቸው ተረግጦ ያላግባብ አስር ቤት የተጣሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ድረስ “አሸባሪ” አየተባሉ አየተፌዘባቸው ነው ያለው። አቶ ኃይለማርያምም ፌዙን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ አያስተጋቡት ነው።

hailemariam and samoraከበቀለበት የተጋጋበት አንዲሉ የ”በሳሉ መሪ ራዕይ” ዜማ ከህወሃት አባላት በእህት ድርጂቶች የፓለቲካ አላዋቂዎች አና መሪዎች ይበልጥ ተዜመ! በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም ተሰማ። ችግሩ የለውጥ ጥያቄ ማድበስበሻ ሆኖ ለረዢም ጊዜ ሊቆይ አይችልም። በውሽት ላይ የተመሰረተ ፐሮፓጋንዳ ስር ሊይዝ አይችልም።አንዴት ይሄን ማየት አቃታቸው?!የሕዝባችን መከራና ሰቆቃ እየከፋ ሄደ። የተጨቆነዉ ሕዝብ ተነሳስቶ ለመብቱ ሲታገል ጨቋኝ መንግሥታት ለዉጥ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፤ ካለዚያ በተባበረዉ የሕዝብ ኃይል ተንኮታኩተዉ ይወድቃሉ። የታገለዉ ለዉጥ ያመጣል፤ ያልታገለዉ ቁጭ ብሎ በባርነት ሲገዛ ይኖራል፤ ቁጭም ባለበት ይሞታል ማለት ነው። የለዉጥ ባለቤት ሁሌ ሕዝብ መሆን አለበት። ህዝቡ ትግሉን በሚገባ እንዲያቀናጅ የትግል መሪ ይፈልጋል። ስለዚህ የተቃዋሚ የፖሊቲካ መሪዎች ታላቅ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል። ያገራችንን ጭብጥ ሁኔታ ስንመረምር ግን በሁለቱም በኩል ታላላቅና ተደጋጋሚ ድክመቶች ታይተዋል። አምባገነን መንግሥታት ለዘለዓለም ካልገዛን ሲሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ኅብረታቸዉን ማጠናከር ስላልቻሉ የጨቋኝ መንግሥታትን ዘመናት ሲያራዝሙ ቆይተዋል።ወያኔ/ኢሕአደግ ለዘለዓለም ሊገዛ አይችልም፤ ለሁሉም ጊዜ አለዉና።ትግሉ ይበልጥ መፋፋም፡ ይበልጥ መጨስ፡ መጋጋም፡ መንደድ ይጠበቅበታል። ትግሉን ለማፈንና አቅጣጫውን ለማሳት የወያኔ መንጋ እየተሯሯጠ ነው። በውጭ ያለውንም የሕዝብና የድርጅቶችን ተቃውሞ ቢቻለው ለማዳፈን፡ ካልሆነለት ደግሞ ለማዳከም፡ በአሁኑ ወቅት የወያኔ ከፋፋይ ቡድን በየቦታው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ እያየን ነው። ይህ ቡድንም፡ ምሁር ነን፡ አስታራቂ ነን፡ ሽማግሌ ነን ወይም ታጋይ ነን በሚሉ መሰሪዎችም እየተደገፈ ነው። የሕዝብ ክንድ ይላላ፡ ይደክም ዘንድ፡ በከፋፋይ ሴራ የተሰማሩትን ነቅቶ መጠበቅ፡ ትግሉን መከላከል ብቻ ሳይሆን ወያኔ ለባሾችን፡ ሰላዮችን ሳንፈራ እየመነጠርን ማጋለጥ ይኖርብናል። ዘረኛው ቡድንና ጭፍሮቹ የሕዝቡን ትግል ለመከፋፈል ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጣሩ ናቸውና። ሕዝብ አንድነቱን ጠብቆ፡ የወያኔን ቡድን ለአንዴም ለሁሌም ለማስወገድ አስፈላጊውን መስዋእ ትነት እየከፈለ ባለበት ወቅት የፖለቲካ ድርጅቶችን እገዛና አመራር ይጠይቃል። የሕዝብ አሸናፊነት አጠራጣሪ ባይሆንም፡ አሸናፊ ለመሆን ግን መታገል መቅደም እንዳለበት ምን ጊዜም መረሳት የለበትም። ለዚህ መሠረቱ ግን ከራስ ጋር እየታረቁ፡ ከወገን ጋር እየተስማሙ በጋራ ዓላማና ብሔራዊ እጅንዳ ዙሪያ ተሰባስቦ በጋራ መታገል ብቻ ነው። በዓለም ታላቅ ዝና ያተረፉት የግ/ቀ/ኃ/ሥና በአፍሪቃ አህጉር መሬትን ያንቀጠቀጠዉ የደርግ መንግሥት ቀናቸዉ ሲደርስ እንዴት እንደመነመኑና እንደከሰሙ መዘርዘር አይኖርብኝም፤ በታሪክ ፊት ተቀምጧልና። በሩቁም በእነ አሜሪካ ለረዥም ዓመታት ሲረዱና ሲደገፉ በነበሩት በእነ ሞቡቱ፤ የሻህ ንጉሥ፤ ሆስኒ ሙባረክ፤ ወዘተ ላይ በመጨረሻ የደረሰዉን ዉርደት መገንዘብ ያስፈልጋል። ተቃዋሚ የፖሊቲካ ድርጅቶች ነን የሚሉትና በተግባር ግን የጭቆናን ዘመን የሚያራዝሙ በሙሉ ካለፉት ስህተቶች ገና ሊማሩ አልቻሉም፤ ・ድር ቢያብር እንበሳ ያስር・ የተባለዉን ቅዱስ አሳብ ደጋግመዉ መናቃቸዉ ያስተዛዝባል። ቁርጥ ያለ አቋም ያስፈልጋል፤ ከዛፍ ዛፍ መዝለል ዬትም አያደርስም። ለጊዜያዊ ጥቅማ ጥቅሞች በርካሽ መገዛትና አገርን መሸጥ በሰማይም በምድርም ያስጠይቃል። ቀኑ ሲደርስ ራቆታችንን ወደምድር እነደመጣን ሁሉ ራቆታችንን ወደዚያዉ እነደምንመለስ አንርሳ!!!

ነገርግን በህብረት ለሀገር ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ዘላለማዊ የትዉልድና የሀገር ክብር ነዉ!!!

ይድረስ ለጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም፡ ማስረሻ ላይ የተፈፀመው በእርስዎ የበኩር ልጅ ዮሐና ላይ ቢፈፀም ምን ይሰማዎታል?

$
0
0

ይድረስ ለአቶኃይለማርያም ደሳለኝ እና ለኢህአዴግ አመራሮች!

ብስራት ወልደሚካኤል
afrosonb@gmail.com,
addismediab@gmail.com

በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ፤ ምንም እንኳ እናንተ ብዙውን ሰላም እየነሳችሁ ብታስቸግሩም፡፡ ዛሬ ግን እስኪ በእናንተ እና በቤተሰባችሁ ላይ እንዳይፈፀም የምትፈልጉትን በሌላው ላይ ስላደረጋችሁት ከብዙው አንዲት እውነት ብቻ አንስቼ ልጠይቃችሁ ወደድሁ፡፡ የጥያቄው መልስ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለህሊናችሁ፣ እናንተ በምትመሩት አስከፊ፣ አፋኝ እና ጨቋኝ ስርዓት ሰለባ ለሆኑ እንዲሁም አሁንም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተለመደውን እኩይ ተግባር ለምትፈፅሙባቸውና ለቤተሰቦቻችሁ ይሆን ዘንድም አበክሬ እጠይቃለሁ፡፡
hailemariam and Yohana hailemariam
ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እርስዎ ተወልደው ባደጉበት የደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ቦለሶ ሶሬ ወረዳ መዲና በሆነችው አረካ ከተማን መቼም የሚረሷት አይመስለኝም፡፡ እርስዎ አሁን የደረሱበት የይምሰልም ይሁን ተግባር የጠቅላይሚኒስትርነት በትረ ስልጣን ከመጨበጦ በፊት እዛው አረካ ከተማ አካባቢ እንደ አብዛኛው የሀገራችን ህዝብ በግብርና እርሻ ሙያ ዕየተዳደሩ ነው እንበል፡፡ ታዲያ በዚህ ሙያ ሳሉ ልክ አሁን እንዳሉት ባለትዳር እና የ3 ልጆች አባት ሆነው፤ እርስዎ በሚመሩት ኢህአዴግም ይሁን 24 ሰዓት በምትኮንኑት ደርግ ስርዓት አርዓያ “ሞዴል” አርሶ አደር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተብለው የትውልደ ቀዬዎትን ወክለው በደቡብ ክልል መንግስት ቢሸለሙ ምን ይሰማዎታል? ያው ደስታ እንደሚሉኝ አልጠራጠርም፡፡

አለበለዚያም ገበሬ ሆኜ አላውቅም ካሉም፤ ያኔ አርባምንጭ የውሃ ቴክኖሎጂ ተቋም (የአሁኑ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተመረቁበት ሲቪል ምህንድስና(Civil Engineering) አሊያም ከፊንላንድ በተመረቁበት የአካባቢ ንፅህና ምህንድስና(Sanitory Enegineering) እስተማሩና እያስተዳደሩ ሞዴል መምህር ተብለው በወቅቱ ገዥ ስርዓት ቁንጮዎች ቢሸለሙ ምን ይሰማዎታል? አሁንም ያው ደስታ ነው እንጂ ሀዘን ሊሉኝ አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ማንም ሰው በሙያው ጥሮ ግሮ ላበረከተው አስተዋፅዖ እና ለሌሎች መልካም አርዓያ በመሆኑ የሚጠላ አይኖርምና፡፡ ይሄንን ምሳሌ ለራስዎ መቀበል ካልቻሉም ከቤተሰብዎ እጅግ መልካም ነው ብለው አብልጠው የሚወዱት ወንድምዎ ካሉም በእርስዎ ምትክ እርሳቸውን ተክተው እርስዎን በታዛቢነት ያስቀምጡ፤ ስሜቶንም ያሰላሱ፣ ይግለፁ፡፡

በሙያዎ ለብዙ ዓመታት ሰርተው ለሌሎች አርዓያ ተብለው ሽልማት፣ እውቅና እና ሙገሳ ከተሽጎደጎደልዎ 3 ወር ሳይሞላ፤ ከትዳር አጋርዎ ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ እና የበኩር ልጅዎን ተማሪ ዮሐና ኃይለማርያምን ጨምረው ከሌሎች ልጆቾ ጋር አምላኬ በሰላም አሳድረኝ ብለው ተቃቅፈው ተኝተው በሸለሞት አካል አሸባሪ ተብለው ሌሊት በቤትዎና በቤተሰብዎ ላይ በ 16 “የፀረ-ሽብር” ግብረ ኃይል የጥይት እሩመታ ሲሰሙስ ምን ይሰማዎታል? አሁን ልክ እንደቅድሙ ደስታ ሊሉኝ አይችሉም፡፡ በዚህ ብቻ ሳያበቃ እርስዎን በቤተሰብዎ ፊት በሸለሞት አካል በ 16 ግብረ ኃይል ሽፍታ ነው ተብለው በክብር አርፈው ከተኙበት ቤት በሚተኮሱ የጥይት ናዳዎች በቤተሰብዎ ፊት ህይወትዎ እስከወዲያኛው ቢያልፍ እና እንደው ግማሽ ነብስ የለም እንጂ በከፊል ድርጊቱን ቢታዘቡት ምን ይላሉ; ከእርስዎ በተጨማሪ ለፍተው ጥረው ግረው ያቆሟት ቤት፣ ያፈሯቸው ላሞች ፣በጎችና በሬዎች በማያውቁት ነገር የጥይት ናዳ ሲያርፍባቸውስ; ከላይ በተጠቀሱት ሳያበቃ ግብረ ኃይሉ አሁን የሰው ህክምና ሳይንስ የምታጠናው የበኩር ልጅዎ ተማሪ ዮሐና ሌሊቱን ገና በ8 ዓመቷ ከእቅፎ ተኝታ እርስዎ ሲገደሉ እርሷ የምትፅፍበት፣ አሊያም በትርፍ ጊዜዋ ከብቶች የምታግድበት ወይንም እንደሌሎች ህፃናት ከአቻዎቿ ጋር ለመጫወት የምትጠቀምበት የቀኝ እጇ ሙሉ ለሙሉ በጥይት ቢቆረጥስ ምን ይሰማዎታል? በዚህም ደስታ እንደማይሉኝ ግልፅ ነው፡፡ ልክ በውጊያ አውድማ እንዳለ ወታደር ከወላጆቿ እቅፍ ሳለች ቀኝ እጇ የተቆረጠችው ልጅ ስታድግስ ምን ይሰማት ይሆን? ፍርዱን ህሊና ላለው ሁሉ ልተወው፡፡

ልክ እንደ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሌሎች የኢህአዴግ አመራሮች እና አባላት ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ቢፈፀም ምን ይሰማችኋል; እናንተም ደስታ እንደማትሉኝ አልጠራጠርም፡፡ ይህንን ሁሉ የጠቀስኩት በማንም የሰው ሰብኣዊ የሰው ልጅ ላይ እንዲህ ዓይነት ዘግናኝ ድርጊት እንዲፈፀም ፈልጌ ይደለም፤ ይሄንንም አቶ ኃይለማርያምም ሆኑ ሌሎች ግብር አበሮእዎ በቅን ልቦና እንድትረዱልኝ እሻለሁ፡፡

ክቡርነትዎ፤ ከላይ ብእርስዎ የጠቀስኩት ምሳሌ በሌላ ኢትዮጵያዊ ላይ በእናንተ ስርዓት አመራር የተፈፀመ እውነተኛ ድርጊት መሆኑንን ከዚህ እንደሚከተለው በአጭሩ ልነግሮት እወዳለሁ፡፡

ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ አረቦር ቀበሌ ልዩ ቦታው ደቀፉቀር በሚባል ስፍራ ከሌሊቱ 12 ሰዓት ከነ መላው ቤተሰቦቻቸው አምላኬ በሰላም አሳድረኝ ብለው የተኙ፤በእነ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስርዓት ሞዴል አርሶ አድር ተብለው የተሸለሙ ታታሪ ገበሬ አቶ ማስረሻ ጥላሁን በ 16 የፀረ ሽብር ግብረኃይል በተተኮሱ የጥይት ናዳዎች እዛው እቤታቸው ህይወታቸው አልፏል፡፡ የሚያሳዝነው ለግድያ የተላከው ግብረ ኃይል አቶ ማስረሻን ከገደሉ በኋላም በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ተከታታይ የጥይት ናዳ በማውረድ ቤታቸውን የጥይት ጌጥ ሲያደርጉት ጥረው ግረው ያፈሯቸው ከብቶችንም ከመግደል እና ከማቁሰል አልቦዘኑም ነበር፡፡

የሚገርመው እንዴት የአንድ ሰው መኖሪያ ቤት የቀድሞ የአድዋ ወይም ባድመ፣…የውጊያ ስፍራ ሊመስል እንደቻለ ግልፅ አይደለም፡፡

ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ እጅግ የሚዘገንነው እና የሚያሳዝነው በተመሳሳይ ሰዓት የአቶ ማስረሻ ጥላሁን የ 8 ዓመት ልጅ ስለእናት ማስረሻ እዛው በሞት ከተነጠቀው ወላጅ አባቷ እና በፀረ ሽብር ግብረኃይል ከተሸበሩ ምስኪን ቤተሰቦቿ እቅፍ ሆና ሲነጋ ጥቅምት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ከአቻዎቿ ጋር ትምህርት ቤት ስለመሄድ እና ስለመጫወት ስታልም ብዙ ስራዎችን የምትሰራበት ቀኝ እጇ በግብረ ኃይሉ ጥይት ሙሉ ለሙሉ ተቆርጧል፡፡

አቶ ኃይለማርያም በእርስዎ እና በግብር አበርዎ የሚመራው ኢህአዴግ ሞዴል አርሶ አደር ያላችኋቸውን አቶ ማስረሻ ጥላሁንን በ 16 “የፀረ ሽብር” ግብረ ኃይል ለማስገደል በወረዳውና በዞኑ አመራሮች ሽፍታ ነው የሚል ለባለቤታቸውና በህይወት ለተረፉ ልጆቻቸው መልስ ተሰጥቶ ፍትህ እንጦርጦስ ገብቷል፤ ቀድሞም ቢሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ኢህአዴግ እስካለ ፍትህ እና ርትዕ ከማግኘት ሰማይ ቤት ደርሶ መመለስ የቀለለ ይመስል ሰው ተስፋ ቢቆርጥም፤ ለወጉም ቢሆን ፍርድ ቤት መኳተኑ አልቀረም፡፡ ነገር ግን እሮጣ ያልጠገበች፣ክፉና ደጉን የማታውቅና ቂም በቀል የሌለባት፣ ዓለማችንንም ይሁን ሀገራችንን ኸረ እንደውም አካባቢዋን በቅጡ ለይታ የማታውቅ የ 8 ዓመቷ ህፃን ስለእናት ማስረሻ ጥላሁንን ምን ብላችሁ ይን እጇ እንዲቆረጥ የተደረገው? ነው ወይስ ይህቺን ህፃንም ሽፍታ ነች ልትሉን ነው? ኸ…ረ…ረ..የፍትህ ያለህ፣…የህፃን ልጅ ያለህ፣…ቢያንስ ሰብዓዊነት እንኳ እንዴት ይሳናችኋል?

እስኪ አቶ ኃይለማርያም ስለእናት ማስረሻ ላይ የተፈፀመው በእርስዎ የበኩር ልጅ ዮሐና ኃይለማርያም ላይ ቢፈፀም ምን ይሰማዎታል? ስለ እናንተ ልጆች እንደምታስቡ ሁሉ ስለሌሎች ህፃናት ያላችሁ አስተሳሰብና አመለካከት ወይም ግንዛቤ የት ድረስ ነው? ዛሬ በዚህ ግፈኛ ስርዓት ቀኝ እጇ የተቆረጠው ስለእናት ማስረሻ ነገ እንደማንኛውም ልጅ አራሷን፣ ቤተሰቧን፣ ሀገሯን ብሎም የዓለምን ማኀበረሰብ ልታገለግል ምትችል፣ ብዙ ተስፋ የሰነቀች ነች፡፡

አሁን ግን ገና የ !ኛ ክፍል ትምህርቷን በጀመረች አንድ ወር ከአስር ቀን የመመህሮቿን የፊደል አጣጣል ትዕዛዝ የምትቀበልበት ቀኝ እጇ ገና ከጅምሩ ተቆርጧል፡፡ በዚህም ምክንያት ሰኞ ማክሰኞ እያለች ትምህርቷን መከታተል ሲገባት ፍትህ አጥታ ከምትኖርበት ዳባት ወረዳ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ከዚያም የአማራ ክልል ፍትህ ፅፈት ቤት እስከ ህፃናት ጉዳይ በጥይት ናዳዎች ከተረፉ ቤተሰቦቿ ጋር ፍትህን ፍለጋ እየተንከራተተች ትገኛለች፡፡

በአንፃሩ ደግሞ የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ልጅ ዮሐና ኃይለማርያም በተደላደለ ሰላም፣ ጤናና እና ሁኔታ የህክምና ትምህርት ትከታተላለች፣ የብአዴኑ ሊቀመንበር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ልጆችም የተሻለ ትምህርት ቤት ከዚሁ ደህ ህዝብ በሚገኝ ገንዘብ ይማራሉ፣ የአቶ በረከት ስምዖንን ፣ የዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የአቶ ሙክታር ከድር፣ የነ ሀሰን ሽፋ፣ የነ ጌታቸው አሰፋ ፣ የነ አያሌው ጎበዜ፣ የነ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የነ ግዛቱ አብዩ እና የሌሎች የኢህአዴግ ሹማምንት ልጆች በህዝብ ሃብት ተንደላቀው በተመቻቸ ሁኔታ ይማራሉ፡፡ የዳባት ወረዳ ነዋሪዋ ህፃን ስለ እናት ማስረሻ ደግሞ ለትምህርት ባልተመቻቸ ሁኑታ እንኳ የጀመረችውን ትምህርት እንዳትማር ቀወላጅ አባቷን በግፍ ከማጣቷ በተጨማሪ ቀኝ እጇን ተቆርጣ ፍትህን ፍለጋ ትኳትናለች፡፡

ታዲያ ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ሌሎች የኢህአዴግ ሹማምንት ሆይ፤ የምትመሩት ስርዓት በህፃናት ስም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ረብጣ ዶላሮችን እንደሚያገኝ የምትዘነጉት አይመስለኝም፡፡ ይሁን እንጂ በህፃናቱ ስም የሚመጣው እርዳታ ቢያንስ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል ባይችል እንኳ ለምን አንዲትን ህፃን በፀረ-ሽብር ግብረኃይል በጥይት ለማስመታት ዋለ? በዚህች ህፃን ልጅ እና ወላጅ አባቷን ጨምሮ በቤተሰቦቿ ላይ የተፈፀመው ግፍ የት ድረስ ያስኬዳችኋል? ይህችን ደብዳቤ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ይህቺ ደብዳቤ ደረሳችሁ ሌሎች የኢህአዴግ አመራሮች ፤ ስለ ህፃናት ልጆቻችሁ፣ ስለ እናቶቻችሁ ፣ ስለሚስቶቻችሁ እና ስለራሳችሁ ብላችሁ የዚህቺን ህፃን እና ቤተሰቦች ጊዜ ሳትሰጡ ፍትህን ፍለጋ እየደከሙ ነውና ፍትህን ይሻሉ፡፡

እነ አቶ ኃለማርም ደሳለኝ የእውነት ከልብ አዝናችሁና እና ተሰነምቷችሁ ፍትህን መስጠት ከቻላችሁ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ብዙ በምታወሩበት ኢቴቪና በሌሎች መድረኮች ሌሎች አመራሮችም ሆኑ ህዝብ እንዲማሩበት ጭምሩ ተገቢው ፍርድ በግልፅ በአደባባይ ሊሰጥ ይገባል፡፡ እዚህ ላይ የሴቶች እና ህፃነት ጉዳይ ቢሮዎች፣ አቃቤ ህግ፣ ጠበቆች ፣የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ሌሎች የሚመለከታችሁ አካላት የድርሻችሁን ትወጡ ዘንድ ተግባሩ የት አለ? ስል መልሳችሁን በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

ታህሣሥ 2006 ዓ.ም. ተፃፈ

አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

አንድነት ፓርቲን በተመለከተ መልስ ለኢሳቱ ፋሲል የኔአለም –ከግርማ ካሳ

$
0
0

የኢሳት ባልደረባ አቶ ፋሲል የኔአለም «የአንድነት ፓርቲ የመጪው ጊዜ ፈተና» በሚል ርእስ የጻፉትን ዘሃበሻ ድህረ ገጽ ላይ አነበብኩ። አቶ ፋሲል ጽሁፉን ያቀረቡት እንደ ግል አስተያየት እንደመሆኑ፣ ኢሳትን በዚህ ዉስጥ ጣልቃ አላስገባም። የአንድነት ፓርቲ አዲሱ ሊቀመንበር፣ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ፣ አገር ዉስጥ ለሚታተመዉ ሪፖርተር ጋዜጣ ከሰጡት ቃለ ምልልስ፣ የሚከተለዉን በመጥቀስ ነበር አቶ ፋሲል ጹሁፋቸውን የጀመሩት

«ከኢሕአዴግ ጋር ገንቢ ግንኙነት እንዲኖረን እፈልጋለሁ። ኢትዮጵያ ዉስጥ የጥላቻ ፖለቲካ ማብቃት አለበት። ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎችን የሚያያቸው እንደ ጠላት ከዚያም አልፎ እንደሽብርተኛ ነዉ። በእኛም በኩል ኢሕአዴግን የምናየው እንደ አዉሬ ነዉ። ምናልባትም የሰራዉን ሥራ ሁሉ ዋጋ ያለመስጠት አለ። አንዳንድ ጊዜ ፖለቲካችን ኢሕአዴግን መቃወም ብቻ ሆኗል። ያ መቆም አለበት። ትልቁ ኳስ ያለው ኢሕአዴግ ዘንድ ነዉ። እኔ በበኩሌ ወደፊት በማደርገዉ እንቅስቃሴ ገንቢ ግንኙነት አድርገን ያለዉን የፖለቲካ ምህዳር ለሁላችንም አኩል መሆን አለበት» በማለት ነበር።

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም


«ይህ መንገድ (ኢንጂነር ግዛቸው በሪፖእርት የታናገሩት) ፣ ካልተሳሳትኩ ሶስተኛ መንገድ የሚባለዉና አቶ ልደቱ አያሌው የ1997 ምርጫ አጣብቂኝ በገባበት ወቅት አምጥተው የደነጎሩት፣ በሌላ አነጋገር መሃል ላይ መቆም የሚባለው የፖለቲካ አካሄድ ነዉ» ሲሉ የጻፉት አቶ ፋሲል፣ ከአገዛዙ ጋር እርቅና ሰላም ለመፍጠር ፍቃደኝነት መኖሩ፣ በአንዱዋለም አራጌና በናትናኤል መኮንን ላይ ተጽእኖ ሊያሳደር እንደሚችል ፣ የአንድነት ፓርቲም አደጋ ላይ እንደሚጥል የሚያመላክቱ ሃሳቦችን ለማሳየት የሞከሩ ይመስላል። የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤም፣ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉን ሊቀመንበር አድርጎ በመምረጡ፣ ትክክል እንዳልሰራም አቶ ፋሲል ጠቆም ሳያደርጉንም አላለፉም።

እዚህ ጽሁፍ ላይ ስለ ኢንጂነር ግዛቸው ብዙ መጻፍ አልፈልግም። ኢንጂነሩን ከማንም በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቃቸዋል። አብዛኞቹ ወጣቶች በሆኑበት ፣ ከክልሎች ሁሉ በተወጣጡ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት የተመረጡም ናቸው። በዲሞክራሲ የማምን እንደመሆኔም፣ አገር ቤት፣ ፊት ለፊት አፈናን እየተጋፈጡ ያሉ፣ የአንድነት ፓርቲ አባላት «እነዚህ ናቸው የሚመሩን !» ብለው የመረጡትን እደግፋለሁ። እቀበላለሁም።

አሁን ግን ኢንጂነሩ ለሪፖርተር ሰጡ በተባሉት ሃሳቦች ላይ፣ አንዳንድ አስተያየቶችን እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ። አንድነት ፓርቲ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀመሮ፣ የአንድነት ፓርቲ፣ ከገዢዉ ፓርቲ ጋር፣ ችግሮችን በሰላምና በዉይይት ለመፍታት ሁልጊዜ ፍላጎት እንደነበረዉ፣ የአንድነትን እንቅስቃሴ በቅርበት የሚከታተሉትና በሚገባ የሚያውቁት ነዉ። ገዢው ፓርቲ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን እያስቀመጠ፣ ለዉይይት ፍቃደኛ አልሆነም እንጂ፣ አንድነት ሁልጊዜ ለዉይይት በሩን የከፈተ፣ ሰላማዊ ድርጅት ነዉ። ኢንጂነር ግዛቸው፣ የተናገሩት አዲስ አባባል አይደለም። አቶ ፋሲልንም ለምን እንዳስቆጣ አልገባኝም። የቀድሞ ሊቀመናብርት፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን፣ ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ጠይቆ መረዳትም ይቻላል። (በነገራችን ላይ ኢንጂነር ግዛቸውን ከልደቱ አይሌው ፣ አንድነትን ከኢዴፓ ጋር የማገናኘቱ ነገር ትንሽ አስቆኛል። አቶ ልደቱ በቅርቡ በአዲስ አድማስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ዙሪያና ስለ ኤዴፓ ሶስተኛ መንገድ ወደፊት በሰፊዉ እመለስበታለሁ)

አቶ አንዱዋለምን በተመለከተ አንድ ነገር ላንሳ። ይህ ወጣት የዴሞክራሲ ታጋይ፣ የሰላም ሰው ነዉ። ብሄራዊ እርቅ በአገራችን እንዲመጣ የሚፈልግና የሚመኝ ነዉ። ኢንጂነር ግዛቸው የተናገሩትን እርሱም ቢሆን ይናገረዉ ነበር። አንዱዋለም ለአላማው የጸና ሰው እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን። ነገር ግን ለአላማ መጽናት ማለት በጥላቻ መሞላት ማለት አይደለም። የገዢዉን ፓርቲ ተግባራት እንጂ አንዱዋለም የሚጠላው፣ አሳሪዎቹን እንደ ጠላት የሚያይ አይደለም። ልብ ገዝተው ወደ ቀናዉ መንገድ ከመጡ ከምንም በላይ የሚያስደስተው ያ ነዉ። ለዚህም ነዉ ቀድሞ የሕወሃት ከፍተኛ አመራር የነበሩ እንደ አቶ ስዬ ያሉ ወገኖች፣ ወደ አንድነት እንዲመጡ ትልቅ አስተዋጾ ካደረጉ ወገኖች መካከል አንዱ የነበረዉ። አንዱዋለም፣ ሰላምና እርቅ እንደማይፈልግና ግትር እንደሆነ ተደረጎ መቅረቡ ትልቅ ስህተት ከመሆኑም ባሻገር፣ ዜጎች አንዱዋለም አራጌ ያልሆነዉ እንደሆነ አድርጎ እንዲያስቡ የሚያደርግ ጎጂ አቀራረብ ነዉ።

GizachewShiferawየአንድነት መሪዎች ከአንዱዋለም ጋር በቅርበት ይገናኛሉ። በአንድነት ዉስጥ ያለዉን ሁኔታም አንዱዋለም ያውቃል። እሥር ቤት ባሉ፣ በነአንዱዋለም እና በዉጭ ባሉት አንድነቶች መካከል ልዩነት የለም። አቶ ፋሲል የሚያስታወሱ ከሆነ ፣ በአዲስ አበባ፣ በቀበና አንድነት፣ በጠራዉ በመቶ ሺሆች በተገኙበት ሰልፍ ላይ፣ ከእሥር ቤት የመጡ የነአንዱዋለም ደብዳቤዎች ተነበዉ ነበር። የመንፈሰና የአላማ አንድነት በአንድነቶች ዉስጥ እንዳለ የሚያሳይ ነዉ። ለዚህ ነዉ አቶ ፋሲል አንዱን የአንድነት አባል በአንድ ወገን፣ ሌላዉን በሌላ ወገን ማቅረባቸው ብዙ ያላስደሰተኝ።

ለሰላምና ለእርቅ በር መክፈት፣ ገዢውን ፓርቲ ለማነጋገር መፈለግ፣ ፍርሃት አይደለም፤ የሰለጠነ የፍቅር ፖለቲካ እንጂ። ስለፍርሃት ማወቅ ከተፈለገ፣ ያገር ቤቱን ትግል ሸሽተው፣ በዉጭ «ዘራፍ» የሚሉ፣ በእነ አቶ ፋሲልም ይደገፋሉ የሚባሉ፣ የአንዳንድ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን ማነጋገሩ መልካም ሊሆን ይችላል። ኢንጂነር ግዛቸው እዚያው አገዛዙ አፍንጫ ሥር ሆነው እየታገሉ ያሉ ናቸው። ዉጭ ሆነን እርሳቸውን «ፈሪ» ማለት፣ ትንሽ የሚያስተዛዝብ መሰለኝ።

የአንድነት ፓርቲ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራቶች በሶስት መስክ፣ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ዝግጅት ላይ እንዳለ በአንድነት ራዲዮ ኢንጂነር ግዛቸው ለማስረዳት ሞከረዋል። የመጀመሪያው የተበታተኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን አሰባብሶ ጠንካራ ተቃዋሚ መመስረት ነዉ። የሕዝቡ ጥያቄ «ተባበሩ ወይንም ተሰባባበሩ» የሚል ነዉ። የህዝብን ጥያቄም አክብሮ፣ በዚህም ረገድ ንግግሮች ከአረና ትግራይና እና ከመኢአድ ጋር እየተደረጉ ናቸው። ውይይቱ ተሳክቶ መልካም ዜና እንሰማለት የሚል ተስፋ አለኝ።

ሁለተኛዉ ወደ ሕዝቡ ወርዶ የፖለቲካ ሥራ መስራት ነዉ። ከሰኔ 2005 እስከ መስከረም 2006 ዓ.ም ተደረጎ በነበረዉ የሚሊየሞች ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴ ወቅት፣ በደሴ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በመቀሌ፣ በአዲስ አበባ፣ በአዳም፣ በፍቼ፣ በባሌ/ሮቢ. በወላይታ ሶዳ፣ በአርባ ምንጭ ፣ በጂንካ …ሰላማዊ ሰልፎች ተደርገዋል። ሕዝቡ ድረስ ተኪዶ፣ በየበሩ እየተንኳኳ፣ ወረቀቶች እየታደሉ ሕዝቡ ለመብቱና ለነጻነቱ እንዲነሳ የመቀስቀስ ሥራ ተሰርቷል። ያኔ የተደረገዉ አይነት እንቅስቃሴ፣ በስፋት ፣ በተጠናከረ መልኩ፣ የሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ክፍል ሁለት፣ ሶስት በሚል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነዉ።

በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ፣ አገዛዙ ፍቃደኛ ከሆነ፣ ያሉትን የፖለቲካ ችግሮች በሰላምና በዉይይት መፍታት ነዉ። ኢንጂነር ግዛቸው «ኢሕአዴግ ፍቃደኛ ካልሆነ፣ እጆቻችንን አጣምረን እንቀመጣለን» አላሉም። የአንድነት ፓርቲም ከአገዛዙ መመሪያ የሚቀበል ድርጅት አይደለም። የትም ቦታ ቢኬድ፣ ችግሮችን በሰላም መፍታት ከተቻለ፣ ጭንቅላት ያለው ሰው ሁሉ፣ የሚመርጠው መንገድ ያ ነዉ። እንጂነሩ ግልጽ አድርገዉታል። «ኳሷ ኢሕአዴግ ሜዳ ላይ ናት» ነዉ ያሉት። ኢሕአዴግ በሩን ከዘጋ፣ ለውይይት ፍቃደኛ ካልሆነ፣ የታሰሩ የሕሊና እሥረኞችን ካልፈታ፣ ትግሉ አይቋረጥም። ነጻነቱን እና መብቱን ሕዝቡ በልመና የሚያገኘው አይደለም። ታግሎ እንጂ።

አቶ ፋሲል ስለ ምርጫ ስነ-ምግባር ኮድም አንስተዋል። የምርጫ ስነምግባር ኮዱን ካልፈረሙ ኢሕአዴግ ሊያነጋግራቸው እንደማይፈልግ የገለጹት አቶ ፋሲል፣ ኮዱን አንድነት መፈረም እንደሚኖርበትም ይናገራሉ። እዚህ ላይ ትክክል ናቸው። ገዢዉ ፓርቲ ከነአቦነግ ጋር ያለምንም ችግር ሲደራደር፣ ከነአንድነተኖች ጋር ግን የምርጫ ስነ ምግባር መግባር ኮዱን ፈርሙ የሚል ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ በሩን መዝጋቱን እናውቃለን።የምርጫ ስነ መግባር ኮዱን አንድነት ከፈረመ ደግሞ፣ እንደ ፈሪና ደካም ተቆጥሮ፣ የአንድነት ተቀባይነቱ እንደሚያሽቆለቁል አቶ ፋሲል ለመግለጽ ሞክረዋል። በዚህ ከርሳቸው ጋር ልዩነት አለኝ።

ጋዜጠኛ ፋሲል ምን ያህል ስለ ምርጫ ስነ-ምግባር ኮዱ ፣ እውቀት እንዳላቸው፣ ምን ያህልም እንዳነበቡት አላዉቅም። ኮዱ የአገሪቷ ሕግ ሆኖ የወጣ፣ አንድነትም ሆነ አገር ዉስጥ ያሉ ድርጅቶች ሁሉ የሚቀበሉት ነዉ። በኮዱ ያሉ አንቀጾች ከአንድነት መርሆዎችና እሴቶች ጋር የሚቃረኑ አይደሉም። በመርህ ደረጃ፣ በኮዱ በተካተቱት፣ ያኔም የአንድነት ፓርቲ ችግር አለነበረዉም። በኮዱ ዙሪያ የተነሱ ዉዝግቦች፣ የስነ ምግባር ኮዱ መጥፎ ሆኖ ሳይሆን፣ በሌሎች ተጨማሪ ሁለት ሰነዶች ላይ ለምን ንግግር አልተደረገም በሚል ነበር። ሕግ ሆኖ የወጣው የስነ ምግባር ኮዱ፣ የምርጫ ተወዳዳሪዎች ምን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የሚተነትን ነዉ። የምርጫ አስፈጻሚዉን (ምርጫ ቦርድ) እንዲሁም የምርጫ ታዛቢዎች ሊያደርጉት ስለሚገባዉ የሚተነትኑ ሌሎች ሁለት ሰነዶች ነበሩ። በነርሱ ላይም ስምምነት ለምን አልተደረገም የሚል ነበር ክርክሩ።

UDJአንድነት ያኔ በመድረክ ዉስጥ ሆኖ ነበር የሚደራደረዉ። መድረኩ፣ «ሶስቱንም ሰነዶች ተወያይተን በሶስቱም ላይ መፈረም ነው ያለብን» የሚል አቋም ያዘ። ከዚህም የተነሳ እራሱን ከድርድር አወጣ። ያ ዉሳኔ በኔ ግምት ስህተት ነበር። አንድነት የያኔዉን የመድረክ ስህተት መድገም ያለበትም አይመስለኝም። አንዱን ሰነድ ፈርሞ፤ በሌሎቹ ሁለት ላይ በሂደት መነጋገር ይቻላል ነበር እኮ። የአንድነት ፓርቲ በሕግ የወጣዉን እና የሚቀበለዉን የምርጫ ስነ-ምግባር ኮድ ቢፈርም፣ ከዚያም የተነሳ ከአገዛዙ ጋር የዉይይትን በር ማስከፈት ቢችል፣ ትልቅ ሥራ ነበር የሚሰራዉ። አንዳንዴ በትንሹም በትልቁም ማክረር ጥሩ አይመስለኝም። ከዋናዎቹና አብየት ከሆኑ ፕሮግራሞቻችን ጋር እስካልተጋጨ ድረስ፣ በሌሎች ማናቸዉም ጉዳዮች ዘንድ ፈረንጆች እንደሚሉት ፍሌክሲቢሊቲ ሊኖረን ይገባል።

በመጨረሻ ይሄን ብዬ ላጠቃል። የአንድነት ፓርቲ ይኸው ከተመሰረተ ጀምሮ ሶስት ጠቅላላ ጉባኤዎችን አድርጓል። በሶስቱ የተለያዩ ሊቀመናብርት ነዉ የተመረጡት። የግድ ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ መደረግ የለበትም፤ በማናቸዉም ጊዜ ብሄራዊ ምክር ቤቱ ኢንጂነር ግዛቸውን ከሃላፊነታቸው ሊያነሳ ይችላል። ፓርቲዉን በትክክል የማይመሩ ከሆነ፣ አብዛኛዉ የአንድነት አባል ሳይደግፍ፣ ድርጅቱን በአንድ አቅጣጫ ሊወስዱት አይችሉም። ተጠያቂ ናቸውና። በመሆኑም «ከአሁን ለአሁን እንዲህ ይሆናል» የሚል መሰረት የሌለው ዉዥንብሩ ዉስጥ ባንገባ ጥሩ ነዉ። አንድ ሰው ገና ሥራ ሳይጀምር ወደ ትችት መሮጡ አግባብነት ያለውም አይመስለኝም። የአንድነት ፓርቲ ላይ ከወዲሁ ከማሟረት፣ ከዳር ሆኖ ጠጠር ከመወርወር ፣ ፓርቲዉ አገር ቤት የሚያደርጋቸውን እንቅስቅሴዎች መደገፍ ፣ ፓርቲው ሥራዉን የማይሰራ ከሆነ ደግም፣ እንደደገፍነዉም ያኔ መተቸት የአባት ነዉ።

እንግዲህ እነዚህ ጥያቄዎች ለአቶ ፋሲልም ሆነ ለተቀረዉ ኢትዮጵያ መጠየቅ እፈልጋለሁ። በኢትዮጵያ ሕዝብ ጉልበት እና አቅም እንተማመናለን ወይ ? የኢትዮጵያን ሕዝብ ከላይ እስከ ታች ማደራጀቱ ዋና የፖለቲካ ተግባር ነዉ እንላለን ወይ ? በአዲስ አበባ እና ክልሎች ሰላማዊ ሰልፎች፣ ህዝባዊ ስብሰባዎች በስፋት እንዲደረጉ፣ ህዝቡ በራሱ እንዲተማመን የማድረግ ሥራ፣ እንዲሰራ፣ በ547 ወረዳዎች ጊዜና ጉልበታቸውን ሰጥተው፣ ለመታሰር፣ ለመገደል ዝግጁ የሆኑ፣ ሕዝቡን የሚያደራጁ ታጋዮች በስፋት እንዲሰማሩ፣ ሕዝቡ ያነባቸው ዘንድ ፣ ጋዜጦች፣ የቅሰቀሳ ወረቀቶች በስፋት እንዲሰራጩ እንፈልጋለን ወይ? መልሳችን አዎን ከሆነ፣ ታዲያ የዚህ ጥረት አካል መሆን አይጠበቅብንም?

በሃገር እንግሊዝም ሆነ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሁሉ

$
0
0

london
ከርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ይህ መልዕክታችን ይድረሳችሁ።

በእንግሊዝ ሃገር የምትገኘውን የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ከስደተኛው ሕዝብ ነጥቆ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ሥር ለማዋል የኢትዮጵያው መንግሥት (ወያኔ /ኢህአዲግ) እና ለንደን የሚገኘው ኤንባሲው ለአባ ግርማ ከበደና ለአቡነ እንጦስ ሙሉ ድጋፍና ትብብር እያደረገ ቀንና ሌሊት አብረው በመሥራት ላይ መሆናቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታተመው ዜና ቤተ ክርስቲያን የተባለ መጽሔት ይፋ አደረገ።

(ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>