Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ስደተኞችን እንደ መንግስት “የገቢ ርዕስ”ከማየት አባዜ ባሻገር –ከሙሼ ሰሙ

$
0
0

ከሙሼ ሰሙ

mushe semu በመጀመርያዎቹ ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶችን አስመልክቶ ባረቀቀው ደንብ አንቀጽ 18 ላይ ስደተኞችን ወይም መጤዎችን ስለማፈናቀል ድንጋጌ አውጥቶ ነበር፡፡ ድንጋጌው እንደሚያትተው ከሆነ መጠነ ሰፊ በሆነ ደረጃ፣ ያለማመዛዘን፣ ልዩነት ሳያደርግ ሃይል በታከለበት ሁኔታ መጤዎችንና ስደተኞችን ማፈናቀል በሰብአዊ ፍጡር ላይ እንደተሰራ ከባድ ወንጀል ተቆጥሮ አባል ሃገራት በድርጊቱ ፈጻሚ መንግስታት ላይ የጋራ አቋም እንዲወስዱ ስምምነታቸውን የሚጠይቅ ነበር፡፡

ይህ የተባበሩት መንግስታት ደንብ የሁሉንም ሃገራት ይሁንታ በተለያየ ምክንያት ማግኝት ባይችልም፤ በዓለማችን ላይ ስደተኛ የሌለው ሃገር ከቶም ሊገኝ ስለማይችል በመርህ ደረጃ ሁሉም መንግስታት የሚስማሙበት ጉዳይ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡ የዓለማችን የመጎጎዣ ስርዓት እጅግ በመቀልጠፉና በመዘመኑ፣ የጉዞ ውጣ ውረዳችን ከቀናት ወደ ሰዓታት በመቀነሱ፣ መረጃዎች በስፋትና በጥልቀት በመናኘታቸው ምክንያት ዓለማችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠባለች፡፡ በዚህም ምክንያት የተሻለ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ሕይወት ፍለጋ ቁጥራቸው ይብዛም ይነስ ዜጎቹ ለስደት የማይዳረጉበት ሃገር የለም፡፡ እንግሊዞች ሁለተኛ ሃገራችን ወደሚሏት አሜሪካ ተሰደው፣ ይሰራሉ፡፡ እስራኤሎች፣ የሳኡዲ አረቢያና የአውሮፓ ዜጎች ሳይቀሩ በየሃገሩ በመኖር ሕይወታቸውን ለማቃናት ብሎም ለሃገራቸው ለመትረፍና ከግፍና መከራ ለመሸሽ ይሰደዳሉ፡፡ ዛሬ ላይ ሲወሳ እውነት ሊመስል ባይችልም፤ አብዛኛዎቹ የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ነዋሪዎች ሕይወታቸውን የሚገፉት በስደተኛነት እንደነበረ እጅግ ቢርቅ ከአንድ ትውልድ የማይዘል ሃቅ መሆኑን መረዳት ያሻል፡፡
1604714_600436510028405_2111798139_n
መጠነ ሰፊ ማፈናቀል (Mass Deportation) በዓለምችን ላይ አዲስ ክስትት አይደለም፡፡ የሳሳንያው ስረወ መንግስትና የፐርዢያው ንጉስ ኮስራው/ሽራው/ 292,000 ባርያዎችንና ምርኮኞችን በጦርነት ካሸነፋት ሃገር አፈናቅሏል፡፡ አሜሪካኖች በየዓመቱ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የላቲን ዜግነት ያላቸውን ስደተኞች አስገዳጅነት በተቀላቀለበት መንገድ ወደ ትውልድ ሃገራቸው ታባርራለች፡፡ እስራኤሎች ቁጥር ስፍር የሌላቸው ፈለስጢናውያንን ከቤታቸውና ከቀያቸው ሲያፈናቅሉና ሲያሰድዱ ዘመናት ተቆጥሯል፡፡ እስከዛሬም ድረስ ፈለስጢናውያን ሃገር አልባ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡
በዓለም ታሪክ ከፈለስጢኖች ቀጥሎ በመጠነ ሰፊነቱና በአሰቃቂነቱ በተለይ ተጠቃሽ የሆነው ማሰደደና ማፈናቀል ቱርኮች በአርመኖች ላይ እ.ኤ.አ ከ1915 ጀምሮ በሶስት ተከታታይ ሂደት የፈጸሙት ማፈናቀል ነበር፡፡ በአንደኛው ዓለም ጦርነት ከጀርመንና ከኦስትሮ ሃንጌሪያውያን ጋር ያበረችው ኦቶማን ቱርክ እ.ኤ.አ በ1922 የደረሰባት አሳፋሪ ሽንፈትና ውድቀት ከአንድ ሚሊያን ለሚበልጡ አርመኖች ከቀያቸውና ከመንደራቸው ለመነቀልና ሃገር አላባ ሆነው የስደተኛ ሕይወት እንዲገፉ ምክንያት ሆኗል፡፡ በሃንጌሪ፣ በሎክስመበርግና በቤልጅየም የተፈጸሙ በርካታ ማሰደዶችና ማፈናቀሎች ሌሎች ተጠቃሽ ምሳሌዎች ናቸው፡፡

ሕጋዊ በሆነ መንገድም ሆነ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ አንድ ሃገር የሚገቡ መጤዎችንና ስደተኞችን ወደ መጡበት ሃገር ማሳደድ ወይም ማፈናቀል (Mass Deportation) የሉዓላዊ ሃገራት ወይም መንግስታት የማይገሰስ መብት ነው፡፡ ከሞራል ሙግት ውጭ ምክንያት ሊጠየቅበት የሚችል አይደለም፡፡ ይህንን ስንል ግን ዜጎቹ የተሰደዱበት ሃገር መንግስት በዜጎቹ መሳደድና መፈናቀል ምክንያት የተከሰተውንና የሚከሰተውን ኢኮኖሚያና ማህበራዊ ቀውስ አስመልክቶ ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ የለም ማለት አይደለም፡፡ አጠቃላይ የካሳ ጥያቄ አንዱ ነው፡፡ በተለይ ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ ቅድሚ የሚሰጠው ስደተኞቹ ከውርደትና ከመብት ረገጣ ከለላ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማምቻቸት አንዱ ሲሆን ሌላው ተሰዳጆቹ ሃብት ንብረታቸውን ሳይነጠቅ እንዲሰናበቱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው፡፡ ምክንያታዊ የሆነ መንግስት የዜጎቹ ውርደት የሃገር ውርደት መሆኑ ሊነገረው የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሃገር ያለ ዜጎቹ የሚዋረድበት ሌላ መገለጫ የለውም፡፡ ከዜጎች ውጭ ሃገር ማለት ድንጋይ፣ ተራራ ወይም መሬትና ወንዝ… ነው፡፡

በኢትዮጵያዊያን ስደተኖች ቁጥር ዙርያ ተጨባጭ መረጃ ማቅረብ ባይቻልም በዓለም ላይ በኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ምክንያቶች በየሃገሩ የተበተኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ቁጥራቸው በሚሊዮኖች እንደሚቆጠር ይነገራል፡፡ ምናልባትም
ኢትዮጵያዊ ስደተኛ የሌለበት ሃገር ማግኝት አዳጋች እንደሆነም በርካታ ለስራም በግል የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን ይናገራሉ፡፡ በተቃራኒው ግን ስደት እንደዚህ ርካሽ የሆነባት ኢትዮጵያ ደግሞ ለስደት የተዳረጉ ዜጎቿን እውቅና በመንሳት፣ ጥበቃናና ከለላ በመነፈገ አቻ የማይገኛላት ሃገር ነች፡፡ ዜጎቻችን ለስደት የዳረገው ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ወይም የሰብአዊ መብት ጥሰት መንስኤ የሆኑ መሪዎቻችን በስደተኛ ዜጎቻችን ላይ የሚደርሱ ግፎችን አይቶተው እንዳለዩ ሰምተው እንዳልሰሙ መሆን መገለጫቸው ነው፡፡ ጫጫታው ገፋ ሲል ደግሞ የእብድ ገላጋይ ይመስል በስደተኞቹ ላይ ስም እየለጠፉ ለጥቃት ማጋለጥ ከአንዴም ሁለቴ የታዘብነው ፈተና ነው፡፡

በገዢዎቻችን ታሪክ ስደተኞች በመካድ፣ ከለላና ድጋፍ በመንፈግ በተለይ ኢህአዴግን የሚደርስበት የለም፡፡ ኢህአዴግ ከሽግግሩ ጊዜ ጀምሮ በኤርትራ መሬት በጦርነቱ ተሸንፈው ወደ የመን፣ ሱዳን ሊቢያና የመሳሰሉት ሃገራት የተሰደዱ ኢትዮጵያዊን ወታደሮችን እውቅና በመንሳት በርካታ ግፍና መከራን እንዲቀበሉ አድርጓል፡፡ ከጦር ቀጠናቸው ውጭ ኤርትራን የማያውቁ በርካታ ወታደሮቻችን በኤርትራ በረሃዎች ላይ ሰብሳቢና ተመልካች ማጣታቸው ሳይንስ ከሰው ፍጠሩ ያልተወለዱ ይመስል የቂም በቀል መወጣጫ ሲሆኑ ኢህአዴግ “ሃይ፣ ጉዳዩ በዓለም አቀፍ ሕግን ስርዓት ይዳኝ” ማለት ስላልፈለገ ዜጎቻችን የትም ባክው ቀርተዋል፡፡ ይበልጥ የሚያስደንቀው ደግሞ ዜጎቻችን “ለወረራ የዘመቱ የደርግ ወታደሮች” ናቸው በማለት የእብድ ገላጋይ ዱላውን በማቀበሉ ወታደሮቹ አይከፍሉ ዋጋ እንዲከፍሉ መንስኤም ሆኖ ነበር፡፡ ዛሬ የተረሳ ቢመስለም በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ታሪክ በአስከፊነታቸው ከሚብጠለጠሉት አሳዛኝ ግፎች ባልተናነሰ ደረጃ ጠባሳውን ጥሎ ያለፈ ሂደት ነበር፡፡

ደርግ በሽብር እየታገዘ እንደ እርድ ከብት ከእርሻ መሬታቸውና ከየትምህርት ቤቱ ያነዳቸው የድሃ አርሶ አደርና የከተሜ ልጆች በኤርትራ መሬት ላይ ለሽንፈት መዳረጋቸው ሳያንሰቸው ተጨማሪ ግፍና መከራ ይቀበሉ ዘንድ ኢህአዴጎች ከሻቢያ ጋር ሊመሳጠርባቸውም ባልተገባ እንደነበር ዛሬ ላይ ድርጅቱ የሚስተው አይመስለኝም፡፡ ጥርሳቸው እየተነቀለ፣ ንብረታቸውን እያተዘረፉ እርቃናቸውን ወደ መጡበት እንዲመለሱ በመደረጋቸው ቁትር ስፍር የሌላቸው ዜጎች በየበርሃውና ጥሻው ውስጥ ወድቀው ቀርተዋል፡፡ በኮንቴይነር ውስጥ እየታሸጉ በባርነት ጉልበታቸውን የተበዘበዙ ወታደሮች ቁጥር ማንም ሊገምተው ከሚችለው በላይ እንደሆነ የሚዘነጋ አይደለም፡፡
saudi
ጊዜ ማለፉ እንደማቀር የሚውቁ አብው ሲተርቱ “ለሕሊናህ መፈረድ ቢያቅት ለጊዜ ፈረድ ይላሉ፡፡ ዛሬ ላይ ያ ሁሉ አልፎ ለደረሰው ውጥንቅጥ ሁሉ መንስኤ የነበሩት አዝማች የደርግ ባለስልጣናት “ይቅርታን አግኝተው” መጽሐፍ ለመድረስና በኢህአዴግ መድረኮች እያተጋበዙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ለመወያየትና ኢህአዴግን ለማማከር በቅተዋል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ እነዚህ ወጣቶች ባልቀሰቀሱትና ባልፈቀዱት ጦርነቱ ውስጥ ተማግደዋል፡፡ ብዙዎቹም ከሞት መንጋጋ ማምለጥ ቢችሉም “የደርግ ሰራዊት” ነበሩ በሚል ሰበብ ብቻ በዓለም አቀፍ ሕግ የተደነገገውንና ለጦር ምርኮኛ የሚገባውን ጥበቃና ከለላ ሳያገኙ በመቅረታቸው የቂም በቀል መወጣጫ ለመሆን ሆነዋል፡፡ ኢህአዴግ በወቅቱ ለሕሊናም ሆነ ለጊዜ ባለመፍረዱ ቢያንስ አዝማቾቻቸው በይቅርታ ሰበብ የተቋዳሱትን የእፎይታ ሕይወት እንኳን ለመቋደስ አልታደሉም፡፡ ከጥፋታቸውም ሆነ ከሕሊና ጸጸት ይድኑ ዘንድ እድል አላገኙም፡፡
ምክንያታቸው ሊዋጥልኝ ባይችልም ኢህአዴግን ለመከላከል ሲባል ብቻ ጉዳዮችን በቀላሉ ከማያጣፉት የኢህአዴግ ካድሬዎች የሚያነሱ ኢህአዴግ መንግስት አልነበረም የሚሉ መከራከርያዎች እንዳሉ እገምታለሁ፡፡ ችግሩ የሚነሳው ኢህአዴግ መንግስት ለመሆን መደላድሉን ያላመቻቸና እርካቡን ያልተቆናጠጠ በመሆኑ ነው አልነበረም፡፡ ችግሩ የርዕዮተ ዓለምና የአመለካከት ነው፡፡ ዛሬም የሳኡዲውን ሌሎችንም ስደተኞችን በሚመለከት ያለው ግንዛቤ ይህው ነው፡፡ ኢህአዴግ ፍላጎቱ ቢኖረው ኖሮ መንግስት መሆን ሆነ አለመሆኑ ሊገድበው ባልተገባ ነበር፡፡ ተደማጭነቱ ቢቀር እንኳ፤ ቢያንስ አቤቱታ በማሰማት ጉዳዩ እንዲታሰብብትና አጀንዳ እንዲሆን ግፊት ለማድረግ ከግለሰብ የላቀ አቅም ነበረው፡፡ ደርግ በትጥቅ ትግል ዘመን በሕዝቦች ላይ በሚያካሂደው ማሳደድ ምክንያት ቀላል የማይባል ህዝብን እየተቀበለና እያገዘ እጅግ አስከፊ ስደቶችንና ውጣ ውረዶችን ከሕዝብ ጋር ያሳለፈ ድርጅት ውሎ ሳይድር በዚህ ዓይነት ድርጊት ውስጥ እጁ ሲገኝ መመልከት ለትንታኔ የሚከብድ መሆኑ አጠራጣሪ አይደለም፡፡

በዚህ ጉዳይ የኢህአዴግ ሁነኛ ባሕሪ ለመደገም ተጨማሪ አስርት ዓመታትን መጠበቅ አላስፈለገም ነበር፡፡ “ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም” እንዲሉ በ1990 ዓ.ም ያልተጠበቀው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሲፈነዳ ነገሮች ይበልጥ ፍንትው ብለው ወጡ፡፡ የደርግ ወታደሮች በሚል ስም ገና ከጅምሩ ስደተኞችን ከለላ በመንፈግና እውቅና በመንሳት አዲስ ታሪክ ያሟሸው
ኢህአዴግ፣ በመቀጠል ሚናውን ከተመልካችነት ወደ ስደተኛ አባራሪነት (Mass Deportion) አሳድጎ ብቅ አለ፡፡ ለዝንተ ዓለም ኢትዮጵያ ውስጥ በመኖር ኢትዮጵያዊነታቸውን በሕግ የተቀዳጁ፤ ነገር ግን በደም ኤርትራዊ የነበሩ አባወራ፣ ሴት፣ ሕጻናት ወይም ሽማግሌ ሳይመርጥ በጅምላ በማፈስ እስር ቤት እያጎረ ሃብት ንብረታቸውን ለመሰብሰብ እንኳን በቂ ጊዜ ሳያገኙ ከኢትዮጵያ አባሯል፡፡ ኢህአዴግ በኤርትራዊያን ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሲፈጸም ሂደቱን ለመቀልበስም ያልቻለው ወይም ያልፈለገው በሌላ ምክንያት ሳይሆን እንደዚህ ዓይነት የማሳደድ ድርጊቶች በሌሎች ላይ ሲፈጸም ዝምታን የመረጠ ድርጅት በመሆኑ ነበር፡፡
ዛሬ ላይ ኢህአዴግ በስደተኞች ላይ የሚያሳየው ፍጹም የሆነ ቸልተኝነት መንስኤው ገጽታ ያበላሻሉ ከሚል ጥቅል ድምዳሜ እንደሚነሳ እገምታለሁ፡፡ በተለይ ደግሞ ወደ አረብ ሃገርት በድህነት ምክንያት ስራ ፍለጋ ለሚሰደዱ ዜጎች እውቅና መስጠት የልማት አጀንዳዬንና ያስመዘገብኩትን ኢኮኖሚያዊ እድገት ያጨልማል፣ በስራ ፈጠራና በልማት ተጠምጄ እያለሁ እነሱ በስደት በመጠመድ የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ገሃድ ያወጣሉ የሚል ድብቅ ( የማይነገር) ሰበብ ስላለው እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡ ኢህአዴግ ከነባራዊ ሁኔታው ተነስቶ ስደተኞቹ ከችግሩ ጥልቀትና ስፋት የተነሳ ከመሰደድ እንደማይቦዝኑ ያውቃል፡፡ በዚህም ምክንያት ድህነትን ከስሩ አድርቄዋለሁ ማለትና በድህንት ሰበብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተሰደዋል ማለት ለፕሮፓጋንዳ አያመችም፡፡ ያለው አማራጭ ስደተኞቹ በሚሊየን ቢቆጠሩም በሰላሳ ሺዎች እየገደቡ እንደ ሳኡዲዎቹ ጉዳዩ ገንፍሎ ገሃድ እስኪወጣ ድረስ እውቅና መንሳት ብቻ ነው፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ በተለይ በሳኡዲ አረቢያ፣ በኩዌትና በሊባኖስ በሌሎቹም ሃገራት የዜጎቻችን የአካል ክፍሎች (Organs) ባልሰለጠኑ የመንደር ሃኪሞች ስለት እየተሞሸለቀ ለቱጃር አረቦች ሲቸበቸቡ ኢህአዴግን ጨምሮ ሁላችንም ለመታዘብ ችለናል፡፡ ዜጎቻችን ከህንጻ ላይ እየተወረሩ ተነኳኩተው በቃሬዛ አሊያም ከተሸከርካሪ ወንበር ጋር ተቆራኝተው ያለ ካሳ አንደ አሮጌ እቃ ሲወረወሩ ተመልክተናል፡፡ በየመን፣ በሱማሌና በሊቢያ በረሃዎች ዜጎቻችን አይዋረዱ ውርደት ሲዋረዱና መሸሺያና መከለያ አጥተው ጦርነት ላይ እንደተማረኩ የዝሙት ባርያዎች (Sex Selave) በሰንሰለት እየታሰሩ የዝሙት ፍላጎት ማርኪያ ሆነዋል፡፡ ወንዶቹ በባርነት ሲያገለግሉ የተቀረጹ ዶክመንትሪ ፊልሞችን በዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት በጋራ ተመልክተናል፡፡ በደርግ ስርዓት ጦርነትና የመልካም አስተዳደር እጦት ፤ የተቃና የኢኮኖሚ ፖሊሲ አለመኖርን የመብት ረገጣ ባደረሱቡን ፈተና ምክንያት ሰቆቃችን፣ እርዛታችንና ልመናችን ዓለምን እንዳላሰለቸ ሁሉ ዛሬ ደግሞ ስደታችንና የስደተኝነት ታሪካችን መንግስታዊ ከለላና ድጋፍ በመነፈጉ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መጠቋቆሚያና መዘባበቻ እንድንሆን አድርጎናል፡፡

በዚህ መልኩ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሚደርሰው የተናጠል ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ተባብሶና ገዝፎ ጭካኔ ወደ ተሞላበት መጠነ ሰፊ ማፈናቀልና ማሰደደ ሲሸጋገር ኢህአዴግ የጉዳዩ ባለቤት መሆኑን መቀበል ባለመፈለጉ እራሱን በታዛቢነት አስቀምጦ መክረሙ ቀጣዩ አሳዛኝ ትዕይንት ነበር፡፡ ኢህአዴግ በተለይ በስደተኛች ጉዳይ ዘንድሮም እንዳልተሻሻለ የሚያረጋግጠው፤ በኤርትራ መሬት ላይ በስደት ሲባክኑ የነበሩ ወታደሮችን “ወራሪ የደርግ ወታደር” ማለቱ ለጥቃት በር የከፈተ መሆኑን ዘንግቶ፤ ዛሬ ላይ ደግሞ ከሳኡዲ በግፍ ለተፈናቀሉ ዜጎቻችንን ሌላ ተቀጻላ ስም ለመስጠት አለመቦዘኑ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ግፉ እንደተጀመረ ሰሞን እራሱን ከደሙ ንጹሕ ለማድረግ ያቀደ በመሆኑ “ሕገ ወጥ ስደተኞች” የሚል ተቀጽላ በመስጠት ለመከራቸውና ውጣ ወረዳቸው ጀርባውን መስጠቱ ይታወሳል፡፡

የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ስደተኞችን በመቀበሏ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣትን የኢትዮጵያ ሃገራችን ስደተኞች የእስልምና መሰረት በሆነችው በሳኡዲ አረቢያ አምባገንን ፖሊሶች፣ ደህንነትና ሰራዊት አማካኝነት በጠራራ ጸሃይና በዓለም አቀፍ መገናኝ ብዙሃን ካሜራ ፊት አስነዋሪ ድርጊት ፈጽመውብናል፡፡ ሰብአዊ ክባራችንን አዋርደዋል፡፡ ዜጎቻችንን ገድለዋል፡፡ ሴቶቻችንን ደፍረዋል፡፡ ሃገራዊ ክብራችንን ተፈታትነዋል፡፡ ይህ ሁሉ ድርጊት በሳኡዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ደጃፍ ስር መፈጸሙ ሌላ አሳፋሪ ጉዳይ ነው፡፡ ኢምባሲው በሩን ከፍቶ የዜጎቻችንን መከራ ለመቋደስ መድፈር ቢያቅተው አንኳን ብሶታቸወን ለመዳመጥ በሩን ገርበብ አድርጎ መታዘብ አልቻለም፡፡

ይልቁንም የኢምባሲው አባላት በዘመናዊ ፎቴ ላይ ተቀምጠው የዜጎቻችንን ግፉ በዲሽ እንደ ፊልም እየተመለከቱ መመሪያ ከመጠበቅ ያለፈ ሚና አልነበራቸውም፡፡ ኢምባሲው የስደተኞቹን ፓስፖርት ለማደስ የአባይ ቦንድ መዋጮ ካልከፈላችሁ በማለት ቁም ስቅል ሲያሳያቸው ከርሞ ከሰባት ወር ውጣ ውረድ በኃላ ፓስፓርታቸውን ሳያድስና ሕጋዊነታቸውን ሳያረጋግጥ በመቅረቱ ያ ሁሉ መዓት በዜጎቻችን ላይ ሊወርድ ችሏል፡፡ ይህ የተለመደው የኢህአዴግ ችግር መገለጫ በመሆኑ

ለዚህ የዜጎቻችን ፈተና የተጠየቀም ሆነ ኃላፊነት የወሰደ የለም፡፡ ሕዝባዊ ነኝ ለሚል ድርጅት በግብር ከፋይ ሕዝብ ወጭ ለሚያለግሉና ለሕዝብ ለማይቆሙ ጥቂት የኢምባሲ ሰራተኞችን ከላላ መሆኑና ከሕዝብ ቁጣ መሸሸጉ እንቆቅልሽ ከመሆን ሊዘል አይችልም፡፡

እርግጥ ነው የሳዑዲ መንግስት የስራ ፈቃድ የሌላቸውን ቀርቶ ፈቃድ ያላቸውን ስደተኞችም ቢሆኑ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ተገቢውን ካሳ ከፍሎና ንብረታቸውን እንዲሰበስቡ አደርጎ ባዘጋጀላቸው ትርንስፓርት ግፍና መንገላታት ሳይደርስባቸው ማሰናበት ይችላል፡፡ የሳኡዲ መንግስት ይህንን አድርጎ ቢሆን ኖሮ ጥያቂ ሊነሳበት ባልተገባ ነበር፡፡ ነገር ግን፤ ከላይ ለማንሳት እንደሞከርኩት የተፈጸመው ግፉ መስመሩን የሳተ እንደመሆኑ መጠን ኢህአዴግ ለስደተኞቹ ተቀጸላ ስም እየሰጠና ቁጥራቸውን እያወራረደ ለጥቃት ከማጋለጥና ከደሙ ንጹሕ ለመምስል ከመትጋት ይልቅ፤ በቂ ምክንያት ስለነበረው ቢያንስ ማፈናቀሉንና ማሰደዱን ማስቆም ባይችል እንኳ መፍትሔ ሊያገኙ በሚገባቸው በርካታ የዜጎነት ጉዳዮች ዙርያ ጥላ ከለላ በመሆኑ በሕጋዊ መድረኮች ሁሉ መሟገት ነበረበት የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ ለዚህም ቢያንስ ቢያንስ እነዚህን መሰረታዊ ጉዳዮች ማከናወን ነበረበት፡፡

የመጀመርያውና ወሳኙ ጉዳይ ለዜጎቹ እውቅና መስጠትና ለክብር ዘብ መቆም ነበር፡፡ ሳኡዲዎች በዚህ ደረጃ ዜጎቻችንን ሰብአዊ ክብራቸውን እንዳያዋርዱ ለመከላከል ኢህአዴግ ከሳኡዲ መንግሰት ጋር በማንኛውንም ጉዳይ ጋር ለመነጋገር ዝግጁነቱን ቀድሞ በመግለጽ በዜጎቹ ጉዳይ ሃላፊነት የሚሰማውና የዜጎቹን ክብር ለመታደግ ግዴታውንና ኃላፊነቱን የሚወጣ መንግስት መሆኑን ማረጋገጥ ነበረበት፡፡ ስደተኞቹ ለዚህ ሁሉ ጥቃት ለመጋለጥ የቻለሁትም ይህ ባለመሆኑና ባለቤት፣ ተጠሪም ሆነ ወቃሽ የሌላቸው ተደርገው በመወሰዳቸው እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ ስደተኞች ኑሮ ስለደላቸውና ስለተረፋቸው እንዳልተሰደዱ ይታወቃል፡፡ በርካታዎቹ መሬታቸው ምርት መስጠት አቅቶት በማረጡ ምክንያት ሌላ የሕይወት መንገድን የመረጡ ናቸው፡፡ ይህንንም የስደት ሕይወት ለማሳካት ሃብት ንብረታቸውን ሽጠው ወይም ተበድረውና ተለቅተው ጉዞ የጀመሩ ናቸው፡፡ ፊታቸውን ወደ ሃገር ቤት አዙረው ለመመለስም መጀመርያ እዳ መክፈል የሚችሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነበረባቸው፡፡ ቀጥሎም እዳቸውን መክፈል ቢችሉ ዳግም ወደ ችጋርና ሰቆቃ ሕይወት ላለመመለስ ትንሽም ብትሆን ጥሪት መቋጠር ነነበረባቸው፡፡ አብዛኛዎቹ ስደተኞቹ ይህንን ማቃናት ባለመቻላቸው ተይዘው ከመመለስ ይልቅ እራሳቸውን ከሕግ በመሰወር ለመደበቅና ለመሸሽ መሞከራቸው የግድ ነበር፡፡ ይህንን ውስብስብ ችግር ለሳኡዲ መንግሰት፣ የደህንነትና የፖሊስ ተቋማት ቀድሞ በማስረዳት በሕገ ወጥነት ተፈርጀው ግፍ እንዳይፈጸምባቸው መከላከል ይቻል ነበር ፡፡

ሁለተኛው አነሰም በዛ የጉልበታቸውን ዋጋ የማስከበር ጉዳይ ነው፡፡ በመጀመርያውንም ዜጎቻችን የተሰደዱት ሃብት ለማፋራት አቅደው በመሆኑ ሃብታቸውን የማሰባሰብ ጉዳይ ኢህአዴግ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነበር፡፡ እነዚህ ስደተኞች በሳኡዲ ኢኮኖሚ ውስጥ ርካሽ ጉልበታቸውን በመሸጥ ቀላል የማይባል አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው መገመት ይቻላል፡፡ በተለይ ደግሞ ማሰደዱ ሃይልና ግፍ የተቀላቀለበት በዘመቻ የተደረገ እንደመሆኑ መጠን ብዙዎቹ ያፈሯትን ጥሪት ለመሰብሰብና ደሞዛቸውን ለመቀበል እንኳን ፋታ አላገኙም፡፡ ስደተኞቹ ወደ ሃገር ተመልሰዋል፡፡ ሃብት ንብረታቸው ግን የትም ተዝረክርኮ ይገኛል፡፡ ሃብት ንብረታቸውን የማሰብሰብ ጉዳይ አሁንም ያልተፈታ ጥያቄ በመሆኑ ኢህአዴግ ዛሬም ላይ ሆኖ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ኢህአዴግ ዓለም አቀፍ ግፊትና ተጽእኖ ፈጣሪ ተቋማትንና መንግስታትን መሰረት በማድረግ የሳኡዲን መንግስት ወደ ድርድር መውሰድ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነም ጉዳይን ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት በመውሰድ ዜጎቻችን ተገቢውን ካሳ አንዲያገኙ ክስ በመመስረት ለዜጎቹ ጉዳይ ተጠሪና መንግስት መሆኑን በተግባር ማሳየት አለበት፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ለስደተኞቹ ከሚያስገኘው ጥቅም በላይ ወደፊት ሌሎች መንግስታት በኢትዮጵያዊያን ላይ እንዲዚህ ዓይነት ድፍረት የተሞላበት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እንዳይፈጽሙ ተመክሮ ይሰጣል የሚል እምነት አለኝ፡፡

የሳኡዲ ስደተኞቹ ወደ ሃገራቸው ከመመለሳቸው ውጭ እዚህ ግባ የሚባል ተጨባጭ ስራ እየተሰራ እንዳልሆነ ለመገመት አያዳግትም፡፡ የሳኡዲ ስደተኞች ሕይወት ምናልባትም ከነበሩበት በባሰ ሁኔታ አስቸጋሪ ነገር ላይ እንደወደቀ የሚያሳዩ በርካታ ጠቋሚ ምልክቶች እያታዩ ነው፡፡ በቁጥር ቀላል የማያባሉት ወደ ቀያቸው ከመመለስ ይልቅ በየመንደሩ በሚገኙ ዝቅተኛ መኝታ ቤቶች አስርና አስራ አምስት እየሆኑ በደቦ መኖር ጀምረዋል፡፡ ሴቶች እህቶቻችን በሂደት ለምን አይነት ሕይወት እያተዘጋጁ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ ወንዶቹ ዳግም በተለመደው መንገድ ወደ መጡበት ስደት ለመመለስ ጉልበትና አቅም እስኪፈጠር በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ ለመሰንበት ሲባልም ወደ አስከፊ ሕይወት ማዝገማቸው የሚገመት ጉዳይ ነው፡፡

ችግሩ ሁሉንም ዜጋ ያስቆጣና በአንድ ያስተባበረ ጸጸትን የፈጠረ እንደነበር የሚረሳ አይደለም፡፡እንደተለመደው ጸጸቱ ቁጣ ከመቀስቀስ ውጭ ወደ ተግባራዊ እርምጃ መለወጥ አልቻለም፡፡ አጋጣሚው የቁጭትና የዋይታ ከመሆን አልፎ ለምን እንደዚህ ዓይነት ፈተና ላይ ወደቅን የሚል መሰረታዊ ጥያቄም ሊወልድ አልቻለም፡፡ ቀጥሉም በጥሞና ለመነጋገርም ሆነ መፍትሔ ለማመንጨት መንስኤና መንገድ ሊዘረጋ አልቻለም፡፡ የዲያስፖራ ፖለቲከኞችም የፖለቲካ ትኩሳቱን በማጋል ለሰልፍ ከመገባበዝ ውጭ የስደተኞቹን ሕይወት በቀጣይ ከአደጋ ለመታደግ ምን መደረግ አለበት ለማለት አልቻሉም፡፡ ዲያስፖራዎች “ከደማቁ ሰልፋቸው” በኃላ ጥቂት መዋጮ አድርገው፣ ቁጣቸውን አብርደው፤ አጀንዳቸውን በእንጥልጥል እጀመሩት ጉዳና ላይ ጥለውት መደ ጉዳያቸው ተመልሰዋል፡፡ ታዋቂ ሙዚቀኞች፣ ግለሰቦች፣ ባለሃብቶች አርቲስቶች… የኢቲቪን መድረክ ሲያጨናንቁ እንዳልነበረ ሁላ የስደተኞቹን ጉዳይ በቀጣይ ምን መፍትሔ ሊቸሩት እንዳቀዱ ለማሳየት አልደፈሩም፡፡ በእርግጥ መንግስት የጉዳዩ ቀዳሚው ባለቤት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ መንግስት ፈተናውን ሊያልፍ አልቻለም፡፡ መንግሰት ፈተናውን ማለፍ ባለመቻሉ ዜጎቻችን አጋር የሌላቸውና ለዘለቄታው ከንቱና ተንከራታች ሆነው መቀረት አይገባቸውም፡፡
በአጠቃላይ ሂደቱ በአሳዛኝ መልኩ ቢጠናቀቅም፤ ከፍተኛ ትምህርት ሰጥቶ እንዳለፈ መረዳት ይቻላል፡፡ መንግስት የዜጎች ጉዳይ በሃገር ወስጥም ሆነ በወጭ ሃገር ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ የትኩረት አቅጣጫው በመጀመርያ መሆን ያለበት ዜጎች በሃገራቸው ተጠቃሚ የሚሆኑበትንና መብታቸው የሚከበርበትን የመልካም አስተዳደርና የኢኮኖሚ ስርዓት በመዘርጋት ከስደትትና ከውርደት መታደግ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ሁኔታ አጣብቂኝም ውስጥ ሆነው ልባቸው በሕጋዊም ሆነ በሌላ መንገድ ለመሰደደ የተዘጋጁ ዜጎች መኖራቸው ስለማይቀር የስደተኞች ጉዳይ በአለም አቀፍ ግንኙታችን ላይ የምንመዘንበት አንዱ መገለጫችን በመሆኑ ዜጎቻችን ተገቢው ጥበቃና ከለላ እንዲያገኙ ማድረግ ያሻል፡፡ መንግስት፣ኢምባሲዎችና ቆንስላዎች በስደት ላይ የሚገኙ ዜጎቻችንን የገቢ ርዕስ አድርጎ ከማየት መታቀብ አለባቸው፡፡


የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ –ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት የዳግማዊ አጼ ምኒልክ መቶኛ የሙት ዓመት በዚህ በያዝነው ዓመት (በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር) እየተከበረ ባለበት ወቅት ሙሉ ጊዜውን በመስጠት ንጉሱ የሰሩትን ታላቅ ስራ ሁሉ በማጣጣል እና ጥላሸት በመቀባት ዘመቻ ላይ በመጠመድ ታሪክ የማጠልሸት ድራማውን በመተወን ላይ ይገኛል፡፡ የታሪክ ማጠልሸት ዘመቻው በዋናነት እየተከናወነ ያለው ለገዥው አካል ቅርበት ባላቸው ታማኝ ሎሌዎች፣ የጥቅም ተጋሪዎች እና የእራሳቸው ስብዕና በሌላቸው አሻንጉሊቶች አማካይነት ነው፡፡ ገዥው አካል ሲያስነጥሰው መሃረብ ይዘው በሚቀርቡ አጎብዳጆቹ አማካይነት የጥላቻ መርዛማ ቃላትን፣ የሚቆጠቁጡ ባዶ ዲስኮሮችን እና እርባናየለሽ ምዕናባዊ ስዕል በአዕምሮው ላይ እየፈጠረ አጼ ምኒልክ የግዛት ማስፋፋት ጥማታቸውን ለማርካት ሲሉ በዜጎች ላይ የጭካኔ ተግባራትን እንደፈጸሙ በማስመሰል ለምንም የማይጠቅሙ እርባናየለሽ እና ተራ አሉባልታዎችን በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡
582717_198631520276500_222803186_n

የገዥው አካል ድንጉላ አገልጋዮች በማናቸውም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በመሰማራት ታሪካዊ ቅጥፈቶችን፣ አሳሳች ዘገባዎችን፣ የሀሰት ታሪክ ፈጠራዎችን፣ ሆን ተብሎ በሀሰት ላይ የተመሰረቱ መረጃዎችን እና ነጭ ውሸቶችን እንደ በቀቀን እየደጋገሙ በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡ የዕኩይ ዓላማው አራማጆች በታላቁ የኢትዮጵያ መሪ ላይ ግነታዊ ኩምክና በመስራት፣ በማዋረድ እና እውነተኛውን ስብዕናቸውን ጥላሸት በመቀባት የስሜት ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ውስጥ በመዘፈቅ ጌቶቻቸውን ለማስደሰት በታለመ ዕኩይ ምግባር ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ የታላቁ መሪ ነብስ ከስጋቸው ከተለየች ከአንድ መቶ ዓመታት የጊዜ ቆይታ በኋላ የተቀበረን ጉዳይ በማንሳት ታላቁን መሪ ሰይጣናዊ ስብዕና እንደነበራቸው ለማስመሰል በማሰብ የዕኩይ ምግባር ጎተራዎቹ የቻሉትን ያህል ጥረት ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት ከተለዩ ሁለት ዓመታት እንኳን ሳይሞላቸው የዕኩይ ምግባራት ቋቶቹ የኢትዮጵያ አዳኝ መልዓክ ሊያደርጓቸው ይፈልጋሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ በተከፈተው የገፍ ወይም የኃይል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ወይም ደግሞ የአጼ ምኒልክን የሙት መንፈስ ደጋግመው በማንሳት ፍጹም ጥላቻ እና የጥላቻ አመለካከት እንዲንሰራፋ በገዥው አካል ስልታዊ እና የተቀነባበረ ዘመቻ የማካሄድ አመክንዮ ለማንም ቢሆን ሊደንቅ አይገባም፡፡ ሀቁ አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡ የኸውም የምኒልክን ስም ጥላሸት በመቀባት (ሰይጣናዊ ስብዕና በመስጠት) በሚሽከረከር ጉዳይ ላይ ብቻ የሚቆም ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገር ግን በቅርቡ በህይወት የተለዩትን የገዥውን አካል የአለቆች ሁሉ አለቃ (Capo di tutti capi) አቶ መለስ ዜናዊን በመላዕክነት ቀብቶ ለማቅረብ የታቀደ ዕኩይ ምግባር ነው፡፡

ዳግማዊ ምኒልክን ጥላሸት የሚቀቡ ሙትመንፈሶች፣

minilikበዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ እየተካሄደ ያለው ከፍተኛ ጥላሸት የመቀባት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ያነጣጠረው የኢትዮጵያን ታሪክ በመፋቅ በአቶ መለስ ዜናዊ የመላዕክነት የህይወት ታሪክ (የመላዕክነት ትረካ) በመተካት የታላቋን ሀገር ትክክለኛ ታሪክ እንደገና ለመጻፍ፣ አዛብቶ ለመጻፍ፣ ገልብጦ ለመጻፍ፣ አወዛግቦ ለመጻፍ፣ በመቀባባት የሚያምር አስመስሎ ለማቅረብ እና እውነተኛውን ታሪክ ለማስወገድ በመደረግ ላይ ያለ ከንቱ ሙከራ ነው፡፡ የአጼ ምኒልክን ታሪክ በመሰረዝ የዘመናችን የ”አፍሪካ ታላቁ መሪ” በማለት የመለስ ዜናዊን ታሪክ ለመጻፍ ይፈልጋሉ፡፡ በሀሰት እምነት ላይ በመመስረት መለስ “አዲሱ የአፍሪካ መሪ ዝርያ“፣ መለስ “የዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስት ቀያሽ”፣ መለስ “በዓለም አቀፋዊ የሙቀት እና የአየር ጸባይ ለውጥ የአፍሪካ ጠበቃ”፣ መለስ “ከጂ-8 እና ጂ-20 መሪዎች ጋር በመሆን ክርናቸውን የሚያሳዩ አፍሪካዊ መሪ”፣ መለስ “የቻይና-አፍሪካ የትብብር መድረክ የቤጂንግ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጉባኤ ሊቀመንበር”፣ መለስ የሶማሌ ጅሃዲስቶች እና አሸባሪዎች አስወጋጅ”… ተብለው ከእውነተኛ ስብዕናቸው ውጭ በሆነ መልኩ እንዲመለክባቸው ይፍልጋሉ፡:

የታላቁን መሪ የዳግማዊ ምኒልክን ስብዕና ጥላሸት በመቀባት አቶ መለስን ቅብዓ መልዓክ (የተቀባ መልዓክ) ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡ ለመሆኑ አጼ ምኒልክን ጥላሸት የሚቀቧቸው ለምንድን ነው? ምክንያቱም አጼ ምኒልክ በአመራር ጥበባቸው እና በትግላቸው ግጭትን በመፍጠር ሲናቆሩ ከነበሩት ባላባቶች፣ ለስልጣን ብቻ ከሚቋምጡ ከተለያዩ አካባቢያዊ ንጉሶች፣ ከተለያዩ ልዕልቶች የቅምጥል የአገዛዝ ስርዓት፣ እና ከጎጣዊ ምስለኔዎች የተበታተነ አገዛዝ በማላቀቅ ዘመናዊቷን የአፍሪካ ብሄር ታላቋን ኢትዮጵያን በመመስረታቸው ብቻ ነው፡፡ የዕኩይ ምግባር አራማጆች አጼ ምኒልክን ጥላሸት ይቀቧቸዋል፣ ምክንያቱም ምኒልክ ታላቆቹን የአውሮፓ ኢምፔሪያሊስት ኃያላን በጦር ሜዳ ውሎ በማሸነፍ አንጸባራቂ ድል በመቀዳጀት የኢትዮጵያን ዘለቄታዊ ነጻነት ያጎናጸፉ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ያስከበሩ ጀግና መሪ በመሆናቸው ነው፡፡ ጥላሸት ይቀቧቸዋል ምክንያቱም ምኒልክ እውነተኛ የአፍሪካ መሪ በመሆናቸው ነው፡፡ የአጼ ምኒልክን ስም በማጥፋት እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ያበረከቱትን የውርስ ትሩፋታቸውን በማንቋሸሽ ለአቶ መለስ ክብር ለመስጠት እና ከእርሳቸው የሚገኘውን ውርስ ብጹዕ/ቅዱስ ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡

ገዥው አካል የአጼ ምኒልክን ታሪክ በእራሱ ታሪክ ለመተካት ይፈልጋል፡፡ አጼ ምኒልክ የባቡር ሀዲድ በመዘርጋት የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ነበሩ፡፡ ይህንን አንጸባራቂ ታሪክ በመለወጥ አቶ መለስ ረዥም፣ ቆንጆ እና ቀላል የባቡር ሀዲድ ሲስተም በኢትዮጵያ ለማምጣት የመጀመሪያው መሪ ነበሩ በማለት የታሪክ ባለቤትነት ሽሚያን ለማጎናጸፍ ይፈልጋሉ፡፡ አጼ ምኒልክ የስልክ እና የቴሌግራፍ አገልግሎትን በአፍሪካ አህጉር በማስተዋወቅ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ነበሩ፡፡ እ.ኤ.አ በ1889 አሌክሳንደር ግራህም ቤል “የድምጽ መነጋገሪያ መሳሪያ” የፓተንት ዕውቅና ካገኙበት 13 ዓመታት በኋላ እና በአጼ ምኒልክ ቤተመንግስት የመጀመሪያው የስልክ መስመር በተዘረጋበት ጊዜ በቴክኖሎጂው ሁኔታ ጭንቀት ውስጥ ገብተው የነበሩት የቤተክህነት ሰዎች ይህ የሰይጣን ስራ ነው በማለት ንጉሱ እንዲያስወግዱት በጠየቋቸው ጊዜ አጼ ምኒልክ ለቴክኖሎጂው ጠቀሜታ ካላቸው ጽኑ እምነት አኳያ ሳያስወግዱት ቀርተዋል፡፡ በአስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አጼ ምኒልክ አዲስ አበባን በምስራቅ ኢትዮጵያ ከምትገኘው የሀረር ከተማ ጋር የሚያገናኝ የስልክ መስመር በመዘርጋት መርቀው ከፈቱ፡፡ ያንን አንጸባራቂ ታሪክ ወደ ጎን በማለት የአሁኖቹ ገዥዎች በኢትዮጵያ ዘመናዊ የመገናኛ ቴክኖሎጂ ሲስተምን በኢትዮጵያ ያመጡ አቶ መለስ ዜናዊ እንደሆኑ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ እውነታው ግን በተገላቢጦሽ በአፍሪካ የስልክ እና የቴሌግራፍ መስመር በመዘርጋት ግንባርቀደም የነበረችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከአፍሪካ በመጥፎ የተንቀሳቃሽ ስልክ እና የኢንተርኔት አግልግሎት አጠቃቀም ሳቢያ በመጨረሻው እረድፍ ላይ ትገኛለች፡፡ ባለፈው ሳምንት የዎል ስትሪት መጽሄት/Wall Street Journal እንደዘገበው በኢትዮጵያ ውስጥ አርሶ አደሮች የተንቀሳቃሽ ስልኮች ቢይዙም “ችግሩ የግንኙነት መስመር ለማግኘት ብዙ ማይሎችን (ኪሎሜትሮችን)መጓዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡“ በማለት የችግሩን አሳሳቢነት አመላክቷል፡፡ ኢትዮጵያ በመጥፎ የኢንተርኔት አገልግሎት አጠቃቀም ከአፍሪካ ከመጨረሻዎቹ ሀገሮች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

የዘመኑ ገዥዎቻችን አጼ ምኒልክ የሴቶችን ጡት ቆርጠው የሚጥሉ ጨካኝ ንጉስ እንደሆኑ አድርገው ታሪክን አዛብተው ለመጻፍ ይፈልጋሉ፡፡ ጨካኝነት ከተነሳ ዘንድ ከአቶ መለስ ዜናዊ የበለጠ ጨካኝ እና አረመኔ ይኖራልን? አቶ መለስ እራሳቸው እ.ኤ.አ በ2005 በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ መጭበርበር ምክንያት ተቃውሟቸውን ለመግለጽ በወጡ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ለአነጣጥሮ ተኳሽ ጦራቸው ትዕዛዝ በመስጠት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲገደሉ አድርገዋል፡፡ ይህንን እልቂት አስመልክቶ በእራሳቸው በአቶ መለስ ልዩ ትዕዛዝ ጉዳዩን እንዲያጣራ የተሰየመው የአጣሪ ኮሚሽን ምርመራውን አካሂዶ ባቀረበው ዘገባ መሰረት በአቶ መለስ ቀጥታ ትዕዛዝ እና ቁጥጥር አማካይነት የፖሊስ እና የደህንነት ኃይሎች በዕቅድ ተይዞ እና ሆን ተብሎ ታስቦበት 193 ሰላማዊ ሰዎች እንዲገደሉ እና ሌሎች 763 ሰዎች ደግሞ ከባድ ቁስለኛ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ እ.ኤ.አ በ2004 አቶ መለስ እራሳቸው ለታጣቂዎቻቸው ትዕዛዝ በመስጠት በምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ 400 ሰላማዊ ዜጎች እንዲያልቁ አድርገዋል፡፡ ኦጋዴን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተካሄደውን የአየር ድብደባ እና መንደሮችን በማቃጠል የጥቃት ሰለባ ያደረገው ወንጀል የተፈጸመው በአቶ መለስ ስልጣን ልዩ ትዕዛዝ ነበር፡፡ በአቶ መለስ ትዕዛዝ በኦጋዴን ታጣቂ ኃይሎች ሴቶችን አስገድደው ደፍረዋል፣ መንደሮችን አቃጥለዋል፣ ህዝቡን በሽብር ቆፍን ውስጥ ለመሸበብ ሲባል “የመቀጣጫ ግድያዎችን” ማለትም በህዝብ ፊት በአደባባይ በስቅላት እንዲሁም ጭንቅላትን ቆርጦ የመጣል ወንጀሎች እንዲፈጸሙ ተደርጓል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሂዩማን ራይትስ ዎች ተሟጋች ዳይሬክተር/United Nations Advocacy Director for Human Rights Watch ስቴቭ ክራውሻው በኦጋዴን አካባቢ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል “ትንሿ ዳርፉር” በማለት አመሳስለው ገልጸውታል፡፡
ገዥዎቻችን አጼ ምኒልክን የኦሮሞ ህዝቦች ጠላት እንደሆኑ አድርገው ታሪክን በመበረዝ የታሪክ ድሪቶ አቀነባብረው እንደገና የጎደፈ ታሪክ ለመጻፍ ይታትራሉ፡፡ አቶ መለስ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ እሳቸው እና የዕኩይ ምግባር አጋሮቻቸው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እስከ አሁን ድረስ ያልተነገረውን እና ለመናገር የሚዘገንነውን በሰው ልጆች ላይ የፈጸሙትን ወንጀል ወደ ፍትህ አደባባይ በማቅረብ እንዲታይ ለማድረግ ከበቂ በላይ መረጃዎች አሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 ፍሪደም ሀውስ/Freedom House የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ባቀረበው ዘገባ መሰረት አቶ መለስ እና አገዛዛቸው በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሰፊ የሆነ የአድልኦ እና የጭቆና መረብ በመዘርጋት ተግባራት ላይ ተጠምደው ቆይተዋል፡፡ አቶ መለስ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን እንቅስቃሴ በመገደብ ብዛት ያላቸው ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የሚጠረጠሩ የድርጅቱን አባላት እና መሪዎችን ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስር በማዋል በማጎሪያ እስርቤት አስገብተው ሲያሰቃዩ ቆይተዋል፣ አሁንም በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2001 የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስልጣናቸውን ሲለቁ እንደተናገሩት “ወደ 25,000 የሚሆኑ የኦሮሞ ህዝቦች ከኦሮሞ ህዝቦች ነጻነት ግንባር ጋር በተያያዘ የገዥው አካል ክስ ምክንያት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች እና በአዲስ አበባ ከተማ እስር ቤቶች ታስረው በመማቀቅ ላይ ነበሩ፡፡” በማለት ይፋ አድርገዋል፡፡ የመለስ የትግል ጓድ እና የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ በሚያስገርም ሁኔታ እንደተመለከቱት “ቃሊቲ እስር ቤት ኦሮምኛ ይናገራል፣ በዚሁ ግቢ በአንድ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን በሚይዝ ካምፕ ውስጥ 99 በመቶ የሚሆኑት እስረኞች ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ አብዛኞቹ እስረኞች ደግሞ የታሰሩበት ምክንያት ምን እንደሆነ አያውቁም፣ ሆኖም ግን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተጠርጣሪ በመባል ዓመታትን በእስር ቤት በማስቆጠር ላይ ይገኛሉ፡፡“ በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Adwavictoryእ.ኤ.አ በ2006 ጂሃዲስቶች (አሸባሪዎች) የሶማሌን አገር ወረዋታል እና የሶማሌ መንግስት ጣልቃ ገብቸ ጂሃዲስቶችን እንዳስወጣለት “ጋብዞኛል” በሚል ተንኮልን ያዘለ ሰበብ ምክንያት አቶ መለስ በሶማሌ አገር ላይ ወረራ አካሂደዋል፡፡ አቶ መለስ በቴሌቪዥን ቀርበው እንዲህ ብለዋል፣ “የአገራችንን ሉዓዋላዊነት ለማስከበር እና በእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት እና በሌሎች ጸረ ኢትዮጵያ ኃይሎች በመታገዝ የሚያደርሷቸውን ተደጋጋሚ አደጋዎች ለመግታት ሲባል የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ወዳልፈለገው ጦርነት እንዲገባ ተገድዷል፡፡“ በተመሳሳይ መልኩ በዴሴምበር 27 2006 የአቶ መለስ ሰራዊት እና ታንኮች የሞቃዲሾን ከተማ ወረሩ፡፡ እ.ኤ.አ በኦገስት 2007 የአቶ መለስ ሰራዊት በሶማሌ ውስጥ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተገታ፣ በሰው ህይወት ላይ የደረሰው ኪሳራ አስደንጋጭ ነበር፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን የሶማሌ ዜጎች ህይወት የተቀጠፈ ሲሆን ከ870,000 በላይ የሚሆኑት ዜጎች ደግሞ ሞቃዲሾን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ በ2006 በሞቃዲሾ ከተማ ወደ 1.2 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን ህዝብ ነበር፡፡ ከአቶ መለስ የሶማሌ ወረራ በኋላ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች “ከአፍሪካ በጣም አስቀያሚ አስከፊ የሰብአዊ መብት ሁኔታ ያለበት“ በማለት የሶማሌን የሰብአዊ መብት አያያዝ በተጨባጭ ገልጸውታል፡፡

አጼ ምኒልክ ከአውሮፓውያን ወራሪ ኃይሎች ጋር የመከላከል ጦርነትን በማካሄድ በድል አድራጊነት ተወጥተዋል፡፡ አጼ ሚኒልክ የአውሮፓ ኃያል ከሚባል አገር ጋር ጦርነት በማድረግ በጦር ሜዳ ድል አድርገው ወራሪው ኃይል በመጣበት እግሩ ጓዙን ጠቅልሎ እንደ ውሻ ጅራቱን በእግሮቹ መካከል ወትፎ እንዲመለስ በማድረግ በአፍሪካ ታሪክ የመጀመሪያው መሪ መሆናቸው የሚካድ ጉዳይ አይደለም፡፡ አጼ ምኒልክ ወራሪውን የኢጣልያንን ጦር አምባላጌ እና መቀሌ ላይ ድል አድርገዋል፡፡ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ1896 አድዋ ላይ ወሳኙን ፍልሚያ በማድረግ የአድዋን ጦርነት በድል አድራጊነት ተወጥተዋል፡፡ “ኋላቀር አፍሪካውያን ጥቁሮች” ወታደሮች ኃያሉን የአውሮፓ ኢምፔሪያሊስት የጦር ኃይል ያሸንፋል የሚል እምነት በማንም አውሮፓዊ የተገመተ አልነበረም፡፡ አጼ ምኒልክ በዘመናዊ መሳሪያ ትጥቅ፣ በስልት እና በቁሳቁስ አቅርቦት በዘመኑ በጣም የተጎዱ መሪ ቢሆኑም ቅሉ የብሩህ አዕምሮ ባለቤት እና ወታደራዊ ስልት የሚያውቁ በመሆናቸው ውጊያውን በማካሄድ ጦርነቱን አሸንፈው በአንጸባራቂ ድል በመታጀብ የነጮችን የበላይነት እና አይበገሬነት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በማስወገድ ለጥቁር ህዝቦች በአጠቃላይ ለአፍሪካውያን ደግሞ በተለይ የኩራት ፈርጥ ለመሆን በቅተዋል፡፡ ብዙ የአውሮፓ ኃያላን አገሮች አጼ ምኒልክን በማታለል እና በማጭበርበር ከኢትዮጵያ ግዛት ቆርሰው በመውሰድ ኢትዮጵያን ቅኝ ተገዥ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1889 አጼ ምኒልክ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሚገኙ ግዛቶችን አስመልክቶ ከኢጣሊያ መንግስት ጋር የውጫሌ ስምምነትን አጸደቁ፡፡ በውል ስምምነት ሰነዱ የኢጣሊያንኛው ትርጉም ከኢትዮጵያ የአማርኛ ትርጉም ጋር የማይመሳሰል መሆኑን አጼ ምኒልክ እንደተገነዘቡ እና ኢትዮጵያ በኢጣሊያን ጠባቂነት የሚለውን ሀረግ ሲመለከቱ የውል ስምምነቱን በማውገዝ አፈረሱት፡፡

የገዥው አካል አፈቀላጤዎች አቶ መለስ ኢትዮጵያ የአህጉሩ ታላቅ አገር እንድትሆን ጥረት ያደረጉ እና የአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ መሪ እንደሆኑ በማድነቅ እና ስብዕናቸውን ከፍ ከፍ በማድረግ የአሁኑን የኢትዮጵያ ታሪክ ደልዘው በእርሳቸው ተተክቶ እንዲጻፍ ነው በመዋተት ላይ የሚገኙት፡፡ አቶ መለስ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ያስከበሩ መሪ እንደሆኑ አድርገው ለማሳየት ይፈልጋሉ፡፡ እውነታው ግን የተገላቢጦሹን ያመላክታል፡፡ እ.ኤ.አ ከ1998-1999 ድረስ የባድሜን የግዛት ወሰን ለማስከበር በተካሄደው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦርነት የአቶ መለስ ጦር የ80,000 ኢትዮጵያውያንን ህይወት ያለምንም ወታደራዊ ስልት በጭዳነት ለመስዋዕትነት ዳርጎ ወታደራዊ ድልን ተቀዳጅቶ ነበር፡፡ በወገኖቻችን የህይወት እና ንብረት መስዋዕትነት የተገኘውን ድል ሰራዊቱ ገና አጣጥሞ ሳይጠግብ የኢትዮጵያው መሪ አቶ መለስ ከመቅጽበት በመገለባበጥ ባድሜን በዓለም አቀፋዊ የስምምነት ውል በማስቀየድ ለኤርትራ መንግስት ቡራኬ ብለዋል፡፡ በምንም ዓይነት መልኩ በየትኛውም አገር አንድ ወታደራዊ ኃይል እጅግ ከባድ መስዋዕትነትን ከፍሎ ያገኘውን አንጸባራቂ ድል ለተሸናፊው ጠላቱ በፈቃደኝነት መልሶ የሰጠበት የጦርነት ታሪክ የለም፣ ተመዝግቦም አያውቅም፡፡ እ.ኤ.አ በ1991 ወታደራዊውን አምባገነን ደርግን በትጥቅ ትግል ካስወገዱ በኋላ በአሜሪካ መንግስት አደራዳሪነት የሽግግር ስምምነቱ በሚፈረምበት ወቅት እኒሁ የኢትዮጵያው መሪ አቶ መለስ በኤርትራ የወሰን ግዛት ዳርቻ ላይ የምትገኘውን ከቀይ ባህር ጋር በመግቢያ እና በመውጫነት ለኢትዮጵያ ህዝብ የባህር በር በመሆን አገልግሎት የምትሰጠውን የአሰብን ወደብ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንድትካለል የቀረበውን ሀሳብ አልቀበልም በማለት አሁንም በድጋሜ ለኤርትራ መንግስት ቡራኬ በመስጠት ይደልዎ ብለዋል፡፡ አቶ መለስ የኢትዮጵያን ግዛት ለባዕድ ኃይል በመስጠት ታላቋን አገር ወደብአልባ በማድረግ በፈጸሙት የአገር ክህደት ወንጀል ብቸኛው ተጠያቂ ናቸው፡፡ አሁንም ተከታታይነት ያለውን የትራጄዲ ድራማ በመቀጠል በሚስጥር በተደረጉ ስምምነቶች የይስሙላው ፓርላማ ለስሙ እንኳ መከረበት ሳይባል ምንም ሳይታሰብበት በጥድፊያ እኒሁ የኢትዮጵያው “መሪ” አሁንም የኢትዮጵያ አንጡራ ግዛት የሆነውን መሬት ለሱዳን መንግስት እንደ የገና ስጦታ የእጅ መንሻ ቡራኬ አድርገውታል፡፡ እኒሁ የኢትዮጵያው መሪ አቶ መለስ በድብቅ እና ታማኝነት በጎደለው መልኩ የአገሪቱን እጅግ በጣም ለም የሆነውን በሚሊዮኖች ሄክታር የሚቆጠር መሬት ዕዳቸውን እንኳ ውል ባለው መልክ ለመክፈል ለማይችሉ የአየር ባየር ጭልፊት ነጋዴዎች አሁንም ለእጅ መንሻ አቅርበዋል፡፡

አጼ ምኒልክ የኢትዮጵያን አንድነት በማጠናከር ዘመናዊ የመንግስት መዋቅር ዘርግተዋል፡፡ አቶ መለስ ግን ምዕናባዊ ዘመናዊነትን አምጥተዋል፡፡ አቶ መለስ ያለሐኪሞች እና መድኃኒት ሆስፒታል ገንብተዋል፡፡ በአንድ ወቅት ሐኪሞች አያስፈልጉንም በማለት በይፋ ተናግረዋል፡፡ ብቃት ያላቸው የዩኒቭርስቲ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች፣ መጻህፍት፣ ቤተ መጻህፍት፣ ወይም ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሳይኖር ዩኒቨርስቲዎችን ገንብተዋል፡፡ የመጸዳጃ ሲስተም የሌላቸውን ህንጻዎች ገንብተዋል፡፡ አጼ ምኒልክ ኢትዮጵያን የምዕራቡ ዓለም ስልጣኔ ትሩፋት ተቋዳሽ እንድትሆን አድርገዋል፡፡ አቶ መለስ “ልማታዊ መንግስት” የሚል እርባናየለሽ ህልዮት ከምስራቅ ኢስያ ሀገራት አምባገነኖች ኮርጀው በማምጣት ኢትዮጵያን ወደ ኋላ መልሰዋታል፡፡ እ.ኤ.አ በ1991 ስልጣን ከያዙ በኋላ አቶ መለስ ዘመናዊውን የኢትዮጵያ መንግስት አወቃቀር በማፈራረስ ወዲያውኑ አገሪቱን ክልል እየተባለ በሚጠራው ወይም የአፓርታይድ አይነት ባንቱስታንስ ወይም ክልሊስታንስ የተባለ የመከፋፈል ተልዕኮውን አጠናቀቀ፡፡ አቶ መለስ በሀሰት ላይ በመመስረት ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግበናል፣ እና “ኢትዮጵያ ነዳጅ ወደ ውጭ ከማይልኩ የሰብ ሰሀራ አፍሪካ አገሮች መካከል ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የምታስመዘግብ አገር ናት” በማለት በሸፍጥ ለማሳመን በመወትወት ላይ ይገኛሉ፡፡ እውነታው ግን ኢትዮጵያ በዓለም ከሚገኙ የመጨረሻዎቹ ደኃ አገሮች ከመጨረሻው በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ አገር መሆኗን “ኢትዮጵያ ለምንድን ነው ደኃ የሆነችው?” በማለት ቀደም ሲል ባዘጋጀሁት ትችቴ ላይ በግልጽ አስቀምጨዋለሁ፡፡

አጼ ምኒልክ የኢትዮጵያ “ህዳሴ” መሪ ነበሩ፡፡ አገራቸውን ለማጠናከር እና ዘመናዊ ለማድረግ ወሳኝ የሚባሉ እርምጃዎችን ወስደዋል፡፡ ለዘመናዊ ቴክኖሎጂ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለአገራቸው አዲስ ዓይነት የግንኙነት ስርዓት እንዲዘረጋ አድርገዋል፡፡ አጼ ምኒልክ አገራቸው ኢትዮጵያ የስልክ እና የቴሌግራፍ እንዲሁም ዘመናዊ የፖስታ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደትሆን አድርገዋል፡፡ አጼ ምኒልክ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ እንዲጀመር አድርገዋል፡፡ የመጀመሪያዋን በሞተር ኃይል የምትንቀሳቀስ አውቶሞቢል ወደ ሀገራቸው ያስገቡ አጼ ምኒልክ ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የማሪያ ቴሬዛ ገንዘብን የማይመች የገንዘብ መገበያያን በዚያን ዘመን በዓለም ገበያ ላይ በመገበያያነት አገልግሎት ስራ ላይ ይውሉ በነበሩ በመዳብ የወርቅ ቁራጭ የገንዘብ ሳንቲሞች በመተካት ዘመናዊ የገንዘብ ግብይትን በኢትዮጵያ አስጀምረዋል፡፡ አጼ ምኒልክ ከምንም ከማንም በላይ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ቅድሚያ ይሰጡ ነበር፡፡ አጼ ምኒልክ እ.ኤ.አ በ1894 ከጅቡቲ እስከ አዲስ አበባ የሚዘልቅ የባቡ ሀዲድ መስመር ለመዘርጋት ከፈረንሳይ መንግስት ጋር የስምምነት ውል ፈረሙ፡፡ በተመሳሳይ ዓመት የአውሮፓ ኃያላን አገሮች አፍሪካን እንደ ቅርጫ ስጋ የሚከፋፍለውን የአውሮፓ ቅኝገዥዎች የበርሊን ጉባኤን አካሄዱ፡፡ በዚያን ጊዜ ፈረንሳዮች የነበራቸውን ኃይል በመተማመን ከባቡር ሀዲዱ ጋር በተያያዘ መልኩ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመዳፈር ሲሞክሩ አገር ወዳዱ መሪ ፈረንሳዮችን ጭጭ እንዲሉ አድርገው በ1906 የአገራቸውን ሉዓላዊነት ካስጠበቁ በኋላ ነው ቀዝቀዝ ማለት የጀመሩት ሐዲዱም መሰራት የቀጠለው ፡፡ እንግዲህ እንዲህ የነበረውን አንጸባራቂ ታሪክ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል የውሸት የአቶ መለስን ትረካ በማጉላት የህዳሴው መሪ፣ በአፍሪካ ታሪክ እስከ አሁን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ የኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ ገንቢ፣ የድልድዮች ገንቢ፣ የመንገዶች እና የባቡር ሀዲዶች… በማለት ታሪክን አዛብቶ ሸውራራ ታሪክ ለመጻፍ እየተውተረተረነው ያለው፡፡

አጼ ምኒልክ የፊውዳል መንግስታት የበላይ የነበሩ መሪ ነበሩ፡፡ በወቅቱ በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ በነበረበት ጊዜ ማድረግ የሚፈልጉትን ማድረግ የሚችሉ አፍሪካዊ መሪ ነበሩ፡፡ በእግዚአብሄር በአላህ ፈቃድ አንዲት የተባበረች እና የተከበረች ኢትዮጵያን ለተተኪው ትውልድ አውርሰው አልፈዋል፡፡ የአቶ መለስ ጠንካራው የውርሳቸው ትሩፋት በአፍሪካ የመጀመሪያውን ፈላጭ ቆራጭ አምባገነናዊ አገዛዝ ማውረሳቸው ነው፡፡ በሁፊንግተን ፖስት ትችቴ/Huffington Post Commentary በግልጽ እንዳስቀመጥኩት “ዴሞክራሲ የህዝብ፣ በህዝብ፣ ለህዝብ የቆመ የመንግስት አስተዳደር ከሆነ የማፊያ አገዛዝ/thugocracy ደግሞ (የወሮ በላ) የሌቦች፣ ለሌቦች በሌቦች የቆመ የወሮ በላ መንግስት አስተዳደር ነው፡፡“ በግልጽ አባባል የማፊያ አገዛዝ የሚሽከረከረው በወሮበላ ሌቦች እና በዘራፊዎች ነው፡፡ በማፊያ የአገዛዝ ስርዓት የፖለቲካ ስልጣንን ሙዝዝ ብሎ መያዝ እና እንደ መዥገር መጣበቅ ዋናው ተግባሩ ሲሆን ገዥው አካል የህዝብን ገንዘብ በመዝረፍ እና ለብዙሀኑ ህዝብ ህልውና የቆሙትን መሰረታዊ አገልግሎቶች ውሱን ሀብቶች በመቀራመት ግላዊ ሀብትን ለማጋባስ ነው፡፡

የአቶ መለስ የማፊያ (የወሮ በላ) አገዛዝ በሰነድ ብቻ ተመዝግቦ የሚያዝ ሳይሆን በቀድሞው የመከላከያ የትግል ጓደኛቸው ጭምር የአይን ምስክርነት የተሰጠበት ጉዳይ ነው፡፡ ገና ከጫካ ትግል ሲጀምሩ አቶ መለስ እና የትግል ጓዶቻቸው የሌቦች አስተዳደራዊ ስርዓት ነበር የዘረጉት፡፡ እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት ለረሀብ ሰለባ ለወደቀው የትግራይ ህዝብ እርዳታ ተብሎ ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የተላከውን ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን ገንዘብ ከተሰጠበት ዓላማ ውጭ አማጺው ቡድን ለጦር መሳሪያ መግዣ እና እራሳቸውን ማበልጸጊያ አድርገውታል፡፡ በቅርብ እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት ከግማሽ በላይ የሚሆነው የአገሪቱ ኢኮኖሚ በአቶ መለስ ባለስልጣኖች፣ ደጋፊዎች፣ ሎሌዎች፣ ጓደኞች፣ የስራ ባልደረቦች እና ሌሎች ቁጥጥር ስር ተቀፍድዶ ይገኛል፡፡ ሙስናን በሚመለከት የዓለም ባንክ “ሙስናን በኢትዮጵያ መመርመር” በሚል ርዕስ የተወሰኑ አገሮችን ባናሙናነት ወስዶ በማጥናት ባወጣው ባለ500 ገጽ የግኝት ዘገባ መሰረት ሙስና እና የህዝብን ሀብት መዝረፍ በኢትዮጵያ ዋና መገለጫ ሆኗል በማለት ደምድሟል፡፡ ዘራፊነት አና ሙስና የአቶ መለስ የመጨረሻው ውርሳቸው ነው፡፡

አጼ ምኒልክን መጥላት ይወዳሉ፣

ጥላቻ የነብሳችን የመጨረሻው የበሽታ ምልክት ነው፡፡ ጥላቻ ኢምክንያታዊ ነው ወይም አመክንዮ የለውም፡፡ በጥላቻ ላይ የተጻፉ በርካታ ሳይንሳዊ ጽሁፎች እንደሚያመለክቱት በጥላቻ የተመረዙት ምንጊዜም ይጠላሉ ምክንያቱም ይፈራሉ፣ ደህንነት አይሰማቸውም፣ ምቀኞች ናቸው፣ ወይም ደግሞ እራሳቸውን ይጠላሉ ምክንያቱም የጥላቻቸው መነሻ እና መድረሻ እነዚሁ በጥላቻ የተሞሉት ግብዞች ናቸውና፡፡ ከሁሉም በላይ በጥላቻ የተሞሉት ወገኖች እራሳቸውን ይጠላሉ ምክንያቱም ብቁነት የጎደላቸው፣ ኃይልየለሽነት፣ ተስፋቢስነት፣ እና የእረዳትየለሽነት ስሜት የተጠናወታቸው ነው፡፡
ማንዴላ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ሰው በቆዳው ቀለም፣ ወይም ደግሞ በማንነቱ፣ ወይም በኃይማኖቱ ምክንያት ብቻ ማንም ማንንም ሊጠላ አልተወለደም፡፡ ሰዎች መጥላትን መማር አለባቸው፣“ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉትን የገዥው አካል ኃላፊዎች ሁኔታ በማስብበት ጊዜ በማንዴላ ፍልስፍናዊ ግምገማ ላይ አምነት ማጣት ይቃጣኛል፡፡ ማንዴላ እንዲህ በማለትም አክለዋል፣ “መጥላትን የሚማሩ ከሆነ ፍቅርን ሊማሩም ይችላሉ፣ ምክንያቱም ፍቅር ከተቃራኒው የበለጠ በሰው ልጅ ልብ ውስጥ የመስረጽ ተፈጥሯዊ ባህሪ አለውና፡፡“ ተቃራኒውን በተጨባጭ የሚያመላክቱ በርካታ መረጃዎች ቢኖሩም የማንዴላ መርሆዎች በስልጣን ላይ ባሉት ባለስልጣኖች ሁሉ ሊተገበሩ እንደሚችሉ ጽኑ እምነት አለኝ፡፡

በመርህ እና በተግባርም እንደሚታየው በጋንዲ መርሆዎች መሰረት ለመኖር ጥረት ማድረግ አለብን፣ “ኃጢያተኛውን ሳይሆን ኃጢያቱን እንጥላ፣“ በጥላቻ የተመረዙትን የምንጠላ ከሆነ የእነርሱ የመስታወት ነጸብራቅ እንሆናለን፣ እራሳችንም የምንጠላቸውን እንሆናለን፣ እንደ ሰው ስብዕና አቶ መለስን እና መሰሎቻቸውን የምንጠላ ከሆነ እነርሱኑ ሆን ማለት ነው፡፡ የምንጠላ ከሆነ ምግባራቸውን እንጅ እንደ ሰው እራሳቸውን መሆን የለበትም፡፡

ጥላቻ ጠንካራ ኃይል ነው፡፡ በናዚዝስቶች የተሰራጨው ጥላቻ አገሮችን በጠቅላላ እንዲጠፉ አድርጓል፡፡ በሩዋንዳ የተከሰተው ጥላቻ የሚሊዮኖችን ሩዋንዳውያን ህይወት ቀጥፏል፡፡ በዳርፉር የተቆሰቆሰው ጥላቻ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሱዳን ዜጎችን ህይወት አጥፍቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተከሰተው የኃይማኖት ጥላቻ በናይጄሪያ እና በመካከለኛው አፍሪካ ሬፑብሊክ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመሞት ላይ ይገኛሉ፡፡ በምንም ዓይነት መንገድ ወደ ጥላቻ መግባት የለብንም፡፡

በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት ህዝቦች እንዳሉ አምናለሁ፡፡ “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ውደድ“ የሚለውን ወርቃማ ህግ የሚከተሉ ህዝቦች አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ “የመዳብ ህግ” እያልኩ በምጠራው “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ጥላ“ እያሉ የሚኖሩ ህዝቦች አሉ፡፡ በጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የእራሳቸውን እረዳትየለሽነት፣ የደህንነት እጦት ስሜት፣ የጥፋተኝነት ስሜት እና በጥላቻቸው መሳሪያነት ድርጊቶችን በመለወጥ አሸናፊነትን የሚጎናጸፉ ይመስላቸዋል፡፡ ሌሎችን በመጥላት የራሳቸውን የበታችነት ስሜት እና የእራስን ዋጋ ዝቅ አድርጎ የማየት ችግራቸውን በማስወገድ እራሳቸውን ከፍ ያደረጉ ይመስላቸዋል፡፡ አጼ ምኒልክን የሚጠሉ ሰዎች በእርግጥ አይጠሏቸውም፣ እራሳቸውን የሚጠሉ እና ምኒልክን ለመሆን የሚያስቡ ምኒልክ የሚያደርጓቸውን ነገሮች ሁሉ ተምሳሌት ለማድረግ የሚጥሩ ናቸው፡፡

በአሁኑ ጌዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት ሁሉ አዝንላቸዋለሁ፡፡ በእርግጥ በጣም አዝንላቸዋለሁ፡፡ እነዚህ በጥላቻ የተሞሉት ወገኖች የኢትዮጵያን ታላላቅ መሪዎች እና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት በመቀባት በቅርቡ በህይወት የተለዩትን መሪያቸውን እና የሁለት አስርት ዓመታት ኃጢያታቸውን በማስሰረይ ብጹ የሚያደርጓቸው ይመስላቸዋል፡፡ የአጼ ምኒልክን እና የቀዳማዊ ኃይለስላሴን በጎ ተግባራት ጥላሸት በመቀባት የአቶ መለስን ስብዕና የሚገነቡ ይመስላቸዋል፡፡ የአጼ ምኒልክን ሐውልት ከህዝባዊ ቦታዎች በማራቅ እና የአቶ መለስን እርካሽ ወረቀት ፎቶግራፎች በየመንገዶች ላይ በመለጠፍ አቶ መለስን ወደ መልዓክነት ያቀረቧቸው ይመስላቸዋል፡፡ አቶ መለስ የአጼ ኃይለስላሴ ሀውልት ከንክሩማህ ቀጥሎ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳይቆም ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል፡፡ ሆኖም ግን ንክሩማህ እራሳቸው የአጼ ኃይለስላሴ ያልተጠቆጠበ ጥረት ባይኖር ኖሮ የአፍሪካ ድርጅት እውን መሆን አይችልም ነበር በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉት ባለስልጣኖች የጥላቻቸው ባህሪ እና አተገባበር ነጻብራቅ ረዘም ያለ ጊዜ የቆየ ቢሆንም ለዚህ ምክንያታዊ መግለጫ አላገኘሁለትም፡፡ ብዙ ሰዎች በፍርሀት እና በጭንቀት ላይ ያሉ ሰለ ወደፊት ምንይመጣል አያሉ ነው ምክንያቱም በቀጣይነት የሚከሰተው ሁኔታ የማይታወቅ እና ለመተንበይም አስቸጋሪ የሆነበት ሁኔታ ሰለሆነ ነው፡፡ ያለፈውን ጊዜ፣ የጥንት 19ኛውን ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ የሚፈሩትን ሰዎች በትክክል ለመረዳት አልችልም፡፡ በሞያዬ ካለኝ ልምድ አንጻር ያለፈውን ጊዜ የሚፈሩ እና የሚሸበሩ ወንጀለኞ ይሄዉም በፊት በፈፀሙት ወንጀል የሚያዙ ሰለሚመስላቸውና ሰለሚፈሩ ነው:: በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነኖች ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም የሰላማዊ ዜጎችን መብት የጣሱ እና የደፈጠጡበትን ወንጀል ለመደበቅ ሲሉ ጥላቻን በማራመድ እና ከፋፍሎ መግዛትን አጀንዳቸው አድርገው ይይዙታል ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ፡፡ በኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ ጎሳዎች ላይ ጥልቅ ጥላቻና እና ፍርሀትን በመፍጠር ለፈጸሟቸው እኩይ ተግባራት ተጠያቂ እንዳይሆኑ እና ኃላፊነትን እንዳይወስዱ የጥላቻ መንፈስን እንደ መርህ በመያዝ ያራምዳሉ፡፡ በህዝቦች መካከል ጥላቻን በመዝራትም በኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ተወጥረው ያሉትን ዜጎች ሀሳቦች ለማስቀየሻ ይጠቀሙበታል፡፡

በጥላቻ የተሞላን ሰው እንደ እራስህ ውደድ፣

ወርቃማው ህግ እንዲህ ይላል፣ “ጎረቤትህን እንደ እራስህ ውደድ፡፡“ እኔ ደግሞ እንዲህ እላለሁ፣ “የሚጠላህን እንደ እራስህ ውድ፡፡“ ከመጥላት ይልቅ መውድደ የተሻለ ነገር ነው፡፡ ጥላቻ ወርዋሪውን ተመልሶ እንደሚጎዳ ቦንብ ነው፡፡ መጀመሪያ ከሚወረውረው ሰው እጅ ይወጣል ተመልሶ ግን በጥላቻ የተሞላውን ሰው እራሱን ይጎዳዋል፡፡ የማንዴላን አባባል በመዋስ፣ ጥላቻ የነብስ መርዝ ነው፡፡ በጥላቻ የተሞሉት በሚጠሉበት ጊዜ መርዝን ይጠጣሉ እናም የሚጠሏቸው እንዲሞቱ ይጠብቃሉ፡፡ በስልጣን ላይ ያሉ ሁሉ ጥላቻን ማራመድ እንዳለባቸው ልዩ ምክር የሚሰጥ ለየት ያለ የፍልስፍና ዓይነትም አለ፡፡ ጥላቻ ሁልጊዜ የተጠላውን ሰው የተወደደ እና የተከበረ ስብዕና ያለው እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተቆናጥጠው ያሉ ወገኖች በዱሮዋ ደቡብ አፍሪካ ከነበሩት የአፓርታይድ መሰል የመንፈስ ጓዶቻቸው ትምህርቶችን ሊማሩ ይገባል፡፡ የአፓርታይድ ጌቶች የማንዴላን ስብዕና፣ አመራር እና ክብር ለበርካታ አስርት ዓመታት ለማዋረድ ፈለጉ፡፡ ማንዴላ አሸባሪ እና ኮሙኒስት ናቸው በማለት ማንኛውንም ዓይነት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፈቱባቸው፡፡ ይንንም ምክንያት በማድረግ ማንዴላ በእስር ቤት በቆዩባቸው ጊዚያት ሁሉ ምንም ዓይነት የፎቶግራፍ ምስላቸው እንዳይወጣ አደረጉ፡፡ ሆኖም ግን ያልታሰቡ አጋጣሚዎች ተከሰቱ፡፡ በሂደት ጊዜ እያለፈ እና የጸረ አፓርታይድ ንቅናቄው እየተጠናከረ ሲሄድ ማንዴላን አሳንሶ የማየት አባዚያቸው የማንዴላን የመላዕክነት ደረጃ ከፍ እያደረገ ወደ ዓለም አቀፋዊ ተምሳሌነት እንዲሸጋገሩ እገዛ አደረገላቸው፡፡ ከዚህ ሊወሰድ የሚችለው ታላቅ ቁምነገር የአጼ ምኒልክን እና የአጼ ኃይለስላሴን ስብዕና ዝቅ ለማድረግ ጥረት ባደረጉ ቁጥር እነዚህ መሪዎች በኢትዮጵያ የወጣቶች ትውልድ የአስተሳሰብ አድማስ ዘንድ የበለጠ ክብር እና ሞገስን እየተቀዳጁ ታዋቂ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ በእነዚህ መሪዎች ላይ የማያቋርጥ እና ዘለቄታዊ ያለው የማዋረድ ዘመቻ ባደረጉ ቁጥር የቀድሞው ትውልድ ጉዳዩን የበለጠ እንዲገመግመው እና አቋሙን እንዲያጠናክር ያደርገዋል፡፡

ፍቅር ከጥላቻ በላይ ዘልቆ መሄድን ይጠይቃል፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ማንዴላ በሰዎች እና በህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ፍቅር ያለውን የማይበገር የአሸናፊነት ኃይል፣ እንዲሁም ፍቅር በዘር፣ በጎሳ እና በኃይማኖት የተዘራን የጥላቻ ካንሰር የመፈወስ ችሎታ እንዳለው በግልጽ አስተምረውናል፡፡ ማንዴላ ለመጥላት እና በቀልን ለመፈጸም ምክንያት አላቸው፡፡ ለ27 ዓመታት የማንዴላ ስም የእስረኛ ቁጥር 46664 ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 1990 ጧት ከእስር ቤት ተለቅቀው ከእስር ቤቱ በር ሲወጡ ከሚሊዮን ዶላር ዋጋ በላይ የሚያወጣውን ፈገግታቸውን አሳይተዋል፡፡ ለ27 ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ነጥለው በእስር ቤት ውስጥ ባማቀቋቸው የአፓርታይድ ጌቶች ላይ ምንም ዓይነት የጥላቻ ስሜት አላሳዩም፡፡ ማንዴላ ታላቅ ትምህርት አስተምረውን አልፈዋል፣ እንዲህ በማለት፣ “እየተራመድኩ ወደ በሩ በምቃረብበት ጊዜ ይህ ሁኔታ ወደ ነጻነት እየመራኝ እንደሆነ አስብ ነበር፡፡ የበቀልተኝነት ስሜቴን እና ጥላቻዬን እዚያው እስር ቤት ጥዬው ካልወጣሁ እዚያው እስር ቤት እንዳለሁ እቆጥረዋለሁ፡፡“ በማለት የጥላቻን መጥፎነት በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ማንዴላ ፍጹም የጥላቻ እስረኛ አልነበሩም፡፡ እስረኛው የአፓርታይድ ጥላቻ ነበር፣ እናም አስረኞቹ የአፓርታይድ አለቆች እና ጌቶች ነበሩ፡፡ ማንዴላ ከእስር ቤት በመውጣት በጥላቻ ሰንሰለት ከአፓርታይድ ግንብ ጋር የታሰሩትን እውነተኞቹን የአፓርታይድ እስረኞች ከጥላቻ፣ ከፍርሀት፣ እና ከበቀልተኝነት ነጻ ለማውጣት ተንቀሳቅሰዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያሉት ገዥዎች በጥላቻቸው የሚቀጥሉ ከሆነ በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ የደረሰው ዕጣ ፈንታ የሚደርስባቸው መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ በአፓርታይድ የአገዛዝ ዘመን ጊዜ “ነጻዎቹ” ነጮች እውነተኛው የማይቀረው የብዙሀን አገዛዝ በሚመጣበት ጊዜ ለብዙ ጊዜ በጭቆና ቀንበር አስረው ሲያማቅቋቸው የነበሩት ጥቁር አፍሪካውያኖች ምን ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ ሌት እና ቀን ያሰላስሉ ነበር፡፡ በጥቁር አፍሪካውያን ላይ የነበራቸው ጥላቻ እንቅልፍየለሽ ሌሊቶችን ብቻ እንዲያሳልፉ አላደረጓቸውም፣ ሆኖም ግን ልቦቻቸው፣ አዕምሯቸው እና ነብሳቸው እንዲሁም ስብዕናዎቻቸውም ጭምር እንዲሰበሩ አደረጋቸው እንጅ፡፡ ሙት መንፈሶች አደረጓቸው፣ ነጻ ሆነው ባሏቸው ኃብቶቻቸው ለመደሰት ባለመቻል የቁም ሙት አደረጓቸው፣ እንዲሁም በኤሌክትሪክ እና በእስር ቤት የሽቦ አጥር ታጥረው የእራሳቸው ጎረቤቶች የእስር ቤት በሮች ሆኑባቸው፡፡ በእርግጥ በጦር ካምፕ የሚኖሩ ህዝቦች ሆኑ፡፡
ምንጊዜም የተሻለ መንገድ አለ፡፡ የጥላቻ ትችት ከማቅረባችን በፊት እውነተኛውን ነገር ለማወቅ የበለጠ ጽናት ሊኖረን ይገባል፡፡ ስለዳግማዊ አጼ ምኒልክ፣ ስለ አጼ ኃይለስላሴ፣ ስለ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እውነኛውን ነገር ማቅረብ ይኖርብናል፡፡ እነርሱን መጥላት ሳይሆን ከስህተቶቻቸው እንማር፣ እኛ በህይወት ያለነው የእነርሱን ስህተት መድገም የለብንም፡፡ ጥላሸት በመቀባት ላይ ላለመሰማራት ከእነርሱ ስህተት እንማር፣ ነገር ግን የእርቅን መንገድ በመፈለግ የእነርሱን ስህተቶች እናርም፡፡ ከኢትዮጵያ ወጣቱ ትውልድ ጋር ህብረት በመፍጠር ማንም ወንድ ወይም ሴት በማንነቱ/ቷ፣ በዘሩ/ሯ ሳይሆን ሰው በመሆኑ/ኗ፣ አፍሪካዊ/ት እና ኢትዮጵያዊ/ት በመሆናቸው ብቻ በመመልከት አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ ማንም ወንድ ወይም ሴት ባለው/ላት ስልጣን በመመካት ባልታጠቁ ዜጎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጦር እልቂት ሊያዝዝ/ልታዝዝ የማይችሉበት እና ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብም ሊወገድ የሚችልበት ነጻ ህሊናን በመፍጠር አዲሲቷን ፍቅር የነገሰባት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንነሳ፡፡ በእያንዳንዱ/ዷ ግለሰብ የጎሳ፣ የእምነት ወይም የቋንቋ ልዩነት ሳንፈጥር በአንድነት በመሆን የእያንዳንዱ/ዷ ዜጋ መብት እና ክብር የሚጠበቅበትን ህብረተሰብ ለመፍጠር እንነሳ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው የወደፊቱን ብሩህ ዘመን ለመፍጠር የምንችለው፡፡ ለብዙ ጊዜ በመቆየት በጊዜ ደመና ተሸፍኖ የደበዘዘውን ነገር ቆፍሮ በማውጣት እና ጥላሸት በመቀባት አይደለም ፍቅር የነገሰበትን የወደፊቱን ትውልድ መገንባት የምንችለው፡፡

በጥላቻ ንግግር አንዘን ወይም ደግሞ አንቆጣ፡፡ ምንም ዓይነት እርባና የለውም፡፡ ይልቁንም ጥላሸት የመቀባት ዘመቻውን በሰከነ መልክ እናጋልጥ፡፡ መላዕክ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ስህተት እና ውሸት መሆኑን እና የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት ለመቀበት እና ለመበረዝ የሚደረገውን መዋተት እናጋልጥ፡፡ ከጥላቻ አራማጆች ጋር በማበር እራሳችንን ወደ ጭቃ እና የሚያጣብቅ ቆሻሻ ውስጥ አንጣል፡፡ እንዲህ የሚሉትን የጆርጅ በርናርድ ሻውን ምክሮችን በፍጹም መርሳት የለብንም፣ “ከብዙ ጊዜ በፊት ከአሳማ ጋር ማጥ ዉስጥ ላለመታገል ትምህርት አግኝቻለሁ፣ ለመታገል ከሞከርክ ቆሻሻ ትሆናለህ፣ አሳማው ግን ማጡን የነብሱን ያህል ይወደዋል፡፡“ ጥላቻን ሙያ አርገው ከሚኖሩ ሰዎች ጋር የጥላቻ ቃላትን መለዋወጥ ከአሳማ ጋር በጭቃ ማጥ ውስጥ የነጻ ትግል ውድድርን እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
ጥላቻን ወደ ፍቅር መለወጥ
በጥላቻ መንፈስ የተሞሉት ወገኖች ይጥሉ እና ይዋሹ፡፡ ስለዚያ ጉዳይ የምናደርገው አንዳች ነገር የለም፡፡ በእራሳችን የሀይል ንፍቀ ክበብ ውስጥ ያለን ልዩ ችሎታ እራሳችንን ከጥላቻ ወደ ፍቅር ከመቀየር ላይ ነው፡፡ በእርግጥም አሉታዊ ኃይሎችን ወደ አዎንታዊ ኃይሎች የመቀየር ችሎታ አለን፡፡ ከጥላቻ ወደ ፍቅር ለመቀየር እንችላለን፣ ይህን የምናደርገው ግን ነገሩ ቀላል ስለሆነ አይደለም ይልቁንም የበለጠ ከባድ ስለሆነ እንጅ፡፡ ፍቅር በግለሰብ ደረጃም ይሁን፣ በሌሎችም ይሁን፣ በማህበረሰቡ ወይም በአጠቃላይ በህዝቡ ላይ ይሁን ለተግባራዊነቱ ታላቅ ስራ መስራትን ይጠይቃል፡፡
ከማህተመ ጋንዲ እና “እውነተኛው ኃይል”/Satyagraha ከሚሉት አቀራረባቸው እስቲ ትምህርት እንቅሰም፡፡ ጋንዲ እንዲህ በማለት ገለጻ አድርገዋል፣ “እውነት/satya ፍቅርን በማጎናጸፍ የመንፈስ ጽናትን ይወልዳል፣ እናም ከኃይል ጋር ተመሳሳይ በመሆን ያገለግላል፡፡“ ዓላማው በጥላቻ የተሞላው/ችው እንዳያስገድድ/እንዳታስገድድ በማድረግ ሀሳባቸውን ለማስለውጥ ነው፡፡ በተግባራዊነት ሁኔታው ስንመለከተው ዓላማው በጥላቻ የተሞላውን/ችውን ጥላቻ ማራመድ የእራሱን/ሷን ልብ፣ አዕምሮ እና ነብሳቸውን የሚጎዳቸው መሆኑን በማሳመን እንዲቀየሩ ለማድረግ ነው፡፡ ከማንኛውም ጉዳትን ከሚያመጡ ነገሮች ሁሉ የሚጠብቁን እራስን፣ ማህበረሰቡን እና አገርን መውደድ ነው፡፡ በጥላቻ ከተሞሉት ወገኖች ፍቅር የተሞሉ ወገኖችን ለማፍራት እውነተኛውን ኃይል/Satyagraha በተግባር እናውል፡፡

ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የምንማራቸው በርካታ ቁምነገሮች አሉ፣ እንዲህም በማለት ያስተምሩናል፣ “ጨለማን ጨለማ አያስወግደውም፣ ብርሃን ብቻ ነው ያንን ማድረግ የሚችለው፡፡ ጥላቻን ጥላቻ ሊያስወግደው አይችልም፣ ፍቅር ብቻ ነው ያንን ማድረግ የሚችል፡፡“ ብለዋል፡፡ እንዲህ በማለትም አስተምረዋል፣ “ይቅርታ የማድረግ ችሎታችንን ማሳደግና ማጠናከር ይኖርብናል፡፡ ይቅርታ የማያደርግ/የማታደርግ ሰው ለማፍቀር ኃይል የለውም/የላትም፡፡ በመጥፎነታችንም ላይ ጥሩ ነገሮችም አሉ፡፡ በመጥፎ ነገሮቻችን ላይም ጥሩ ነገሮች አሉ፡፡ ይህንን ሁኔታ ባወቅን ጊዜ ጠላቶቻችንን ከመጥላት በመጠኑም ቢሆን እንታቀባለን፡፡“ ይቅርታ አድራጊነት እና እርቅ ብቸኞች የጥላቻ ፈውስ እና መድኃኒቶች ናቸው፡፡

ከዘመናችን ታላቅ ቀልድ አዋቂ ከቻርለስ ቻፕሊን እንኳ ትምህርት መቅሰም ይኖርብናል፡፡ እንዲህም ይለናል፣ “የሰው ልጅ ጥላቻ ያልፋል፣ እና አምባገነኖችም ይሞታሉ፣ እናም ከህዝቦች የነጠቁት ስልጣን ተመልሶ በህዝቡ እጅ ይገባል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጅ ሟች እስከሆነ ድረስ ነጻነት ከናካቴው ሊጠፋ አይችልም፡፡“ ነጻነት በጥላቻ ከተሞሉት የሰው ዘሮች ሁሉ የበለጠ እድሜ አለው፡፡ በጎሳ ማንነት መፈረጅን እርግፍ አድርገን እንተው እና ሰው በመሆናችን ብቻ በኢትዮጵያዊነታችን እና በአፍሪካዊነታችን እንኩራ፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉ የማስተላለፈው መልዕክት፣

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ሆነው ጥላቻን ለሚያራግቡት አጭር መልዕክት አለኝ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የምትቆሰቁሱት የዘር እና የጎሳ ጥላቻ ፍላጻ በአንድ ወቅት ተመልሶ እራሳችሁ ላይ ይሰካል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአጼ ምኒልክን ክብር እና ዝና ለማንቋሸሽ በታለመ ዕኩይ ምግባር ጡት ቆራጭ አረመኔ ነበሩ በማለት በመሳለቅ እና በማፌዝ ላይ ትገኛላችሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አጼ ምኒልክን እንዲጠሉ የሚሰበክላቸው ሰዎች ነገ ደግሞ አቶ መለስን እንዲጠሉ የማይሰበክበት ምክንያት አይኖርም፡፡ የእናንተ ታላቁ ባለራዕይ መሪ አቶ መለስ በኦጋዴን፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ቦታዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ በፈጸሟቸው የጅምላ እልቂቶች ሳቢያ በድንጋይ እና በእብነበረድ በተቀረጹ ሃውልቶች ላይ ሆነው ሁለተኛው ሮዶልፍ ግራዛኒ በመባል የሚታወሱበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡ ዛሬ ጓደኞች ብላችሁ የያዛችኋቸው ሰዎች ነገ ቀንደኛ ጠላቶቻችሁ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ዛሬ የእናንተ ጠላቶች አድርጋችሁ ጥላሸት የምትቀቧቸው ሰዎች ነገ ጽዋው ሞልቶ እጣ ፈንታችሁ ደርሶ የዘራችሁትን የምታጭዱበት ጊዜ ሲመጣ የእናንተ ጓደኞች ሆነው ይቀርባሉ፡፡

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ መልዓክ ወይም ጭራቅ አልነበሩም፡፡ ሰይጣን ወይም ደግሞ እግዚአብሄርም አልነበሩም፡፡ የተቀሩት የአፍሪካ አገሮች በኃአውሮፓ ኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ሲቆራረሱ፣ መጫወቻ ሲሆኑ፣ ሲነሱ ሲጣሉ፣ ሲበጠሱ ሲቀጠሉ፣ ሲሸጡ እና ሲለወጡ እንዲሁም ሲጋዙ በነበረበት ጊዜ አጼ ምኒልክ ደግሞ ኢትዮጵያን ሲያጠናክሩ እና ሲያዘምኑ የነበሩ የተከበሩ አፍሪካዊ ንጉስ ነበሩ፡፡ ዳግማዊ አጼ ምኒሊክ በአንድ መለኪያ ብች ይገምገሙ፣ በእውነት! የታሪክ ሰዎች እውነታውን መናገር አለባቸው፣ እና ሁሉንም እውነታዎች፣ ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን ስለምኒልክ ያለውን እውነታ ብቻ፡፡ ለአጼ ምኒልክ 100ኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ ሲባል እ.ኤ.አ በ1909 በኒዮርክ ታይምስ ባሮን ዲ ጃርልስበርግ የተባለ የቤልጄም አሳሽ ለዳግማዊ አጼ ምኒልክ ምስክርነት ለጋዜጣው ቃል በመስጠት የተዘገበውን በከፊል ምስከርነት እውነታ መረጃ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡፡ ይህ ታሪካዊ የምስክርነት መረጃ ዳግማዊ አጼ ምኒልክን ከሰሯቸው ስራዎች አንጻር በትክክለኛው የታሪክ ሚዛን ላይ በማስቀመጥ እንዲገመገሙ ያስችላል የሚል ጽኑ እምነት አለ፡፡

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የዘውድ ስልጣኑን ለመቆናጠጥ ትግል ማድረግ ከጀመሩበት ከ20 ዓመታት በኋላ አቢሲኒያን ከከፊል የኋላቀርነት አገዛዝ በማውጣት ወደ አውሮፓውያን የንጉሳዊ ህገመንግስት የአገዛዝ ስርዓት ምሳሌነት አሸጋግረዋታል… እራሳቸውን ነጻ እና በእራስ የሚተማመኑ አድርገው የሚቆጥሩት ዘ እምነገደ የይሁዳ አንበሳ ስዩመ እግዚአብሔር የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ የኢጣሊያንን የቅኝ ግዛትነት ፍላጎት አምባ ጋሪማ ላይ ጦርነት ገጥመው በአሸናፊነት እንዳንኮታኮቱት… አጼ ምኒልክ ከአጼ ዮሀንስ ህልፈተ ህይወት በኋላ እ.ኤ.አ ኖቬምበር 4 1889 የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሆነው ሲሰየሙ የአቢሲኒያን መንግስት ከመሰረቱት የአካባቢያዊ መንግስታት በሙሉ ቅቡልነት አልነበራቸውም፡፡ ከብዙ ድካም እና ትግል በኋላ ነው እነዚህን የአካባቢ ገዥዎች እና ንጉስነታቸውን አንቀበልም ያሉትን አማጺ ገዥዎች በማሳመን እና በኃይል በማንበርከክ በመጨረሻ ስኬታማ ለመሆን የበቁት… ከዚያ በኋላ የአጼ ምኒልክ ዋና ዓላማ የነበረው የአውሮፓን ስልጣኔ ወደ አገራቸው ማስገባት ነበር፡፡ ንጉሱ የፊውዳሉን ህግ በማፈራረስ በእርግጥም በግዛታቸው እስከ አሁንም ድረስ ጨርሶ እንዳልጠፋ እና ባሮችን ነጻ በማውጣት የባሪያ ንግድን በማጥፋት በግዛታቸው በሙሉ ከክፍያ ነጻ የሆነ የትምህርት ስርዓትን ዘርግተዋል፡፡ በዚህም መሰረት እንደማንኛውም የአውሮፓ ሀገር ሁሉ በቀጣዮቹ ትውልዶች ትምህርት በመላ የአቢሲኒያ ግዛት ውስጥ የሚስፋፋ ይሆናል፡፡

ምኒልክ በመላ አፍሪካ በስልጣን ላይ ካሉ መሪዎች ሁሉ ልዩ ባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡ እንደ የዲፕሎማሲ ሰው፣ እንደ ገንዘብ ኃላፊ፣ እንደ ወታደር ከሌሎች ወንድማዊ ንጉሶች የቅርበ መረጃዎችን በመውሰድ በእራሳቸው አካሄድ እንደሚመስላቸው የሚተረጉሙ ንጉስ ናቸው፡፡ እንደ ወታደር እና እንደ የዲፕሎማሲ ሰው የኢጣሊያኖችን በአቢሲኒያ መሸነፍ ለንጉሱ እንደ መልካም አጋጣሚ ምን ያህል ጠቃሚ የሆኑ ንጉስ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡ በቅርብ ዓመታት ደግሞ የገንዘብ ብልህ ጥንቁቅ አያያዝ ምኒልክን ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ስለገንዘብ እንደ ወጣትም፣ የዙፋን ስልጣናቸውን ከመያዛቸው እና በዙፋኑ ላይ ከተቀመጡም በኋላ በፓሪስ የስቶክ ገበያ ትንበያን/Paris Bourse ላይ ተሳትፎ ማድረጋቸው መልካም ተፈጥሯዊ ችሎታ ያላቸው መሆኑን ያመላክታል፡፡ እነዚህ ጠቃሚ ትንበያዎች የነበሩ ሲሆን ምኒልክ የዙፋን ስልጣኑን ከያዙ በኋላ ለመቋረጥ ችለዋል… የገንዘብ አሰራር ስርዓታቸውን በማስፋት እስከ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ድረስ በማስፋት በአሜሪካ የባቡር ሀዲድ ካምፓኒዎች ላይ ትልቅ የድርሻ ባለቤት ለመሆን በቅተዋል፡፡ ከአሜሪካ የሴኪዩሪቲ ሰርቲፊኬቶች እና ከፈረንሳይ እና ከቤልጄም ባለሀብቶች ጋር ከ25 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ መዋዕለ ንዋይ በስራ ላይ እንዲውል አድርገው ነበር፡፡
በጣም የሚያስገርመው የአቢሲኒያው ደብዛዛ ንጉስ በሁሉም ነገሮች ላይ ያላቸው ሁለገብ እውቀት ነው፡፡ በጣም ምጡቅ የቋንቋ ችሎታ የነበራቸው ሲሆኑ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛ እና ጣሊያንኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ለመንግስታዊ ስራቸው ሙሉ ጊዜ ሰጥተው የሚሰሩ ሲሆን በአውሮፓ የሚዘጋጁ ጽሁፎችንም የመከታተል ዕድል ስላላቸው እና በትኩረት ስለሚከታተሉ አዲስ መጽሀፍ በወጣ ቁጥር ስለደራሲው ሲጠየቅ አዲስ አይሆኑም፡፡ ባዲሳባ ቤተመንግስት በሰዎቻቸው በሚታወቁበት መጽሀፍትን በማሰባሰብ ስራቸው እውቅና እንዲሰጣቸው ሲባል በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ በተገኙበት ዕለት በቤተ መጻህፍታቸው ከ20 ሺህ ያላነሱ ጥራዞች መገኘታቸው ልዩ ኩራት እንዲሰማቸው አድርጓል፡፡ የምኒልክ መጻህፍትን የማሰባሰብ የትርፍ ጊዜ ስራ በጥንት የአፍሪካ እና የኢስያ ስልጣኔዎች ዘመንም የሚደረግ ነበር፡፡

በአጼ ምኒልክ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ከሚያደርጉት ወገኖች ጋር የማቀርበው መደራደርያ ፣

በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ስለማሰራጨት ጉዳይ የማቀርበው መደራደርያ አለኝ ፡
በአጼ ምኒልክ ስብዕና ላይ የምታደርጓቸውን ውሸቶችና ቅጥፈቶች የምታቆሙ ከሆነ እኔም ስለአቶ መለስ የምናገራቸውን እውነቶችመናገር አቆማለሁ!
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም

የመረጃና የሃሳብ ነፃነትን ለጋራ ጥቅም እናውለው! –ቃልኪዳን ከኖርዌ

$
0
0

kalkidanቃልኪዳን ካሳሁን /ከኖርዌ

ሀገሪቱ እየገነባች ያለው ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የፈጣን ልማት ባለቤት አላደረጋትም። ባለፉት ሺ ዓመታት በኢትዮጵያ ያልነበረ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንድንጀምርና በጋራ እንድናሳድግ እድል አልፈጠረም። ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከመለያየትና ከፀረ እኩልነት አስተሳሰብ ወጥተው መከባበር፣ መደጋገፍና በልዩነት ውስጥ አንድ ሀገር መገንባት እንዲጀምሩ አላገዘም።

Read full Story in PDF

“የአንድነት ፓርቲ የመጪው ጊዜ ፈተና”–የመልስ መልስ ለአቶ ግርማ ካሳ እና ለመሰሎቻቸው –ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

$
0
0

“የአንድነት ፓርቲ የመጪው ጊዜ ፈተና” በሚል ርዕስ ለጻፍኩት ጽሁፍ ስለሰጡት ምላሽ ከልብ አመሰግናለሁ። ሀሳቦችን በጨዋ መንገድ ማንሸራሸር ለእድገት ይጠቅማልና ሁላችንም ይልመድብን እላለሁ። ስለአንድነት ፓርቲ ተቆርቋሪ ሆነው የሰጡት መልስ ብዙም እንዳላረካኝ ስገልጽልዎ በከፍተኛ አክብሮት ነው። ማንም ጤናኛ ሰው በአገር ውስጥ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲመጣ ይፈልጋል። አንድነት ፓርቲ በዚህ እምነት የሚያደርገውን ትግልም አደንቃለሁ። ይሁን እንጅ የትግል ፍሬ መለኪያው ሂደት ሳይሆን ውጤት ነውና አንድነት ፓርቲ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሊሄዱበት ባሰቡት መንገድ ከተጓዘ፣ ውጤታማ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም። እርስዎ በዚህ አስተያየት አልተስማሙም። አለመስማማትዎን ሁለት ቁምነገሮችን በማንሳት ለማሳየት ሞክረዋል፤ እኔም በእነዚህ ነጥቦች ላይ ተመስርቼ የመልስ መልስ አቀርባለሁ።

አንደኛ፤ አንድነት ፓርቲ፣ የአገሪቱ የህግ አካል የሆነውን ፣ የምርጫ ስነምግባር መመሪያው እስካሁን አለመፈረሙ ስህተት ነበር፣ አሁንም ፈርሞ ከኢህአዴግ ጋር መነጋገር አለበት የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል። የስነምግባር መመሪያውን ፈርመው ለድርድር ተቀምጠው የነበሩት የቀድሞው የመኢአድ ሊቀመንበር ኢ/ር ሃይሉ ሻውል በመጽሀፋቸው የተናገሩት ሰነዱን መፈረም ያዋጣል አያዋጣም የሚለውን ለማየት ይረዳናልና ልጥቀስ፤-

Hailu Shwel ” ከኢህአዴግ ጋር ያደረግነውን ድርድር በተመለከተ አንዳንዱ ‘ ወደሰለጠነ ፖለቲካ ልንገባ ይሆን?’ ብሎ በደህና ሁኔታ ያየው ወገን ነበር። ሌላው ወገን ግን ‘እንዴት ያሰረውን ሰው ሄዶ እጅ ይጨብጣል’ የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምቷል። የ2002ቱን የምርጫ ስነምግባር ሰነዱን ስንፈርም ተቃውሞ እንደሚኖር ሳናውቅ ቀርተን አይደለም። ፊርማው ብቻውን ለእኛ ደስታን የሚሰጠንም ሆኖ አልነበረም።ሌላኛው አማራጭና አስተሳሰብ ግን ግብዝነትናን የሚያጠናክርና የሰላም ሂደትን የሚገታ ይሆናል የሚል ግምት መያዛችን አንዱ ምክንያታችን ነው። በወቅቱ እኛ ሰነድ መፈረማችን ለህዝብ ምን ፋይዳ አለው የሚለውንም በአግባቡ አይተነዋል። እኛ ያሰብነው ወረቀት ቢሮ ውስጥ ይፈረማል፣ ያልቃል የሚል ነበር። እነሱ ግን አምባሳደሮች ጋብዘው፣ ሚዲያዎችን ጠርተው የተለየ ዝግጅት አደረጉ። ነገሩን ለዓለም ለማሳወቅ መፈለጋቸው ለሁሉም ግልጽ ሆነ። በዚያን ወቅት እኛ የማናውቀው ውጥረት ነበረባቸው የሚል የዘገየ ግምት ተከሰተልኝ ። እኔ እንደሚመስለኝ የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች የመታዘብ ይሁንታ የሰጡት ያ ስምምነት ስለተፈረመ ይመስላል። መኢአድ ሰነዱን የፈረምንበት ዋናው ምክንያት ግን የ500 ስቃይ ላይ የነበሩ እስረኞችና የቤተሰቦቻቸው ሰቆቃ አሰቃይቶን ነው። እኔን በተመለከተ ኢህአዴግ ወደ እኛ አስገባነው ብሎ ቢያስወራም አልሰመረለትም።”

(ህይወቴና የፖለቲካ እርምጃየ፣ ሃይሉ ሻውል፣ ገጽ139)።

አቶ ግርማ እዚህ ላይ አራት ነጥቦችን ላንሳ። አንደኛው፣ አቶ ሃይሉ እንዳሉት የስነምግባር መመሪያው ለኢህአዴግ አለማቀፍ ተቀባይነትን ለማሰጠት ጠቅሟል። ቢያንስ የምርጫ ታዛቢ እንዲላክ አድርጓል። የታዛቢው የመጨረሻ ሪፖርት ባያምርም። ሁለተኛ አቶ ሃይሉ 500 ሰዎችን ከእስር ለማስፈታት ብለው እንጅ ሙሉ በሙሉ አምነውበት ሰነዱን አለመፈረማቸውን ገልጸዋል። ልብ ይበሉ አቶ ግርማ! ከ80 ሚሊዮን እስረኞች የተፈቱት 500 ዎቹ ብቻ ናቸው። 80 ሚሊዮኑ ህዝብ ከእስር እንዲፈታ ስንት የምርጫ ስነምግባር ፊርማዎችን መፈረም ይኖርብን ይሆን? ሶስተኛ ፣ መኢአድ ፊርማውን መፈረሙ ህዝቡ እንዲከፋፈል አድርጎታል። አንድነትስ ተመሳሳይ ነገር አይሰራም ብለው ያስባሉ? የሚከፋፈለውን ህዝብ አንድ ለማድረግ እርስዎ የህዝብ ግንኙነት ስራ ለመስራት ተዘጋጅተዋል? አይርሱ ፖለቲካ 50 በመቶው ገጽታ ( image) ነው። አራተኛ፣ ኢህአዴግ የፊርማውን ስነስርአት ለራሱ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ተጠቅሞበታል። በድብቅ ይፈረማል የተባለውን ፊርማ ለአደባባይ አብቅቶታል። በአንድነት ላይስ እንዲህ እንደማይደረግ ምን ዋስትና አለ? በህዝቡ ላይ የሚፈጥረውን አሉታዊ ስሜትስ እንዴት ነው መቋቋም የሚቻለው?

ኢ/ር ሃይሉ ሻውል አያበቁም፣ ይቀጥላሉ ” በሌላ በኩል ከህዝቡ ወገን ደግሞ ” ሃይሉ ከዳን” የሚልም ነበር። ውጪ አገር ያሉትማ በኢንተርኔት ላይ ፎቶግራፌን እያገላበጡ እኔ ለቀድሞው ጠ/ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ እጅ እንደምነሳ አስመስለው ሲዘልፉኝ ከርመዋል።… የሰነዱ መፈረም ለ2002 ምርጫ ዝግጅት ለእኛ አባላት ትንሽ ፋታ ሰጥቷል። ገጠር ሲታገሉ የሰነበቱት እሳት ውስጥ ነበሩ፤ ከፊርማው በሁዋላ ለአጭር ቀናት ቢሆንም በመጠኑ ማስፈራራት ጋብ አለ።” ይሄ ፊርማውን በመፈረም የተገኘ ጥሩ ዜና ነው አቶ ግርማ። ግን ይቀጥል ይሆን ? እንመልከተው፦ ” ምርጫው እየተቃረበ ሲመጣ ግን ሁሉም ነገር ተረሳና ኢህአዴግ የተለመደ ጭቆናውን ማስፋፋት ተያያዘው… መኢአድ ከ2002 ምርጫ ጋር ተያይዞ ከኢህአዴግ ጋር የስነምግባር ደንቡን ከፈረመ በሁዋላ በኢህአዴግ በኩል የተገቡ ቃሎች ባለመተግበራቸው ከጋራ መድረኩ ራሱን አግልሏል። ኢህአዴግ ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር እንዲሆን ፈለገ። በመድረኩም እንነጋገር ብለን የምንጠይቀውን አጀንዳ አይቀበሉትም። የሄ ከሆነ የጋራ ስምምነት የምክክር አይደለም ብለን ተውነው። ስንመለከተው ኢህአዴግ ትእዛዝ የሚያስተላልፍበት መድረክ ስለሆነ ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ግንባታ ጸር እንጂ ጠቃሚ አለመሆኑን በገሀድ ታየ። ገዢው ፓርቲ በዚህ በጋራ መድረክ አባልነት የቀጠሩትን ፓርቲዎች ደመወዝ መሰል ድጎማ እየከፈለ በቁጥጥር ይዟቸው ቀጥሎአል።በ2002 የስነምግባር ደንቡን ብንፈርምም የእኛ አባሎች ላይ የሚደርሰው ወከባና እንግልት ከዚያ በሁዋላ እየቀጠለ መጣ…” ይሉና አቶ ሀይሉ ይቀጥላሉ…
አቶ ግርማ ካሳ እንግዲህ አንድነትንም ወደዚህ የአራዊቶች ጉባኤ ( ፋቡላ) በመክተት ፓርቲውን በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ሊያደርጉት እና ደሞዝ ሊያሰፍሩለት ያስባሉ ማለት ነው። ለአንድነት ፓርቲ ታጋዮች ካለኝ ከበሬታ አንጻር ፓርቲው በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር እንዲሆን አልመኝም። ወርሃዊ ደሞዝ እንዲሰፈርለትም አልሻም።ምክንያቱም እንዲህ አይነቱ አካሄድ ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል የሚገድል ነውና ።

መድረክም አንድነትም ፊርማውን እስከዛሬ ባለመፈረማቸው የረባ ውጤት አላገኙ ይሆናል፤ ነገር ግን ” No to cheating!” በማለታቸው ከመኢአድ የተሻለ ክብር እና ድጋፍ አግኝተው እንደነበር አንዘነጋውም።

andu_udjሁለተኛው መከራከሪያዎ አቶ አንዱዓለምንና ናትናኤልን በተመለከተ የሰጠሁትን አስተያየት ተንተርሶ የቀረበ ነው። እኔ አንድነቶችን ከመከፋፈል ማዳን እንጅ፣ እነሱን የመከፋፈል አላማ የለኝም፣ በፍጹም!። ይሄን ስጽፍም ፓርቲውን ከመከፋፈል ለማዳን እንጅ ለሌላ አላማ አይደለም። ወ/ት ብርቱካን እስር ቤት ከገባች በሁዋላ ፓርቲዋ ( አመራሩ) ረስቷት ነበር። እንዴያውም አንዳንዶች “እንኳን ታሰረች” ሳይሉ ሁሉ አልቀረም። ያን ጊዜ ማን ነበር ለብርቱካን አብዝቶ የጮኸው? ዲያስፖራው እና በተለይ ኢሳት አልነበሩምን? የካናዳው ልጅ ተክሌ ” ብርቱካኔ ብረሳሽ ቀኜ ይርሳሽ” ብሎ ዜማ ያወጣላት አምስተርዳም የኢሳት ስቱዲዮ ውስጥ ሆኖ ነው። በወቅቱ የነበሩ ባልደረቦቼ ብርቱካንን በተመለከተ ብዙ ዝግጅቶችን ይሰሩ ነበር። ምንም እንኳ ኢሳት እዚህ ውስጥ እንዲገባ ባልሻም፣ “የኢሳቱ ባልደረባ” እያሉ ስለጻፉና በተዘዋዋሪም እኔ የጻፍኩትን የኢሳት አቋም አድርገው ለማሳየት ስለሞከሩ ትንሽም ብትሆን እውነቱን ለመናገር ይጠቅማል ብየ ስላሰብኩ ነው ኢሳትን መጥቀሴ። ( በነገራችን ላይ ኢሳት የግል አስተያየቴን እንዳልጽፍ እያደረገኝ ነው፣ በግሌ የምጽፈውን አንባቢዎች ” የኢሳት አቋም አድርገው ይወስዱብኝ ይሆን” እያልኩ በመስጋት፣ መጻፍ እየፈለኩ አልጽፍም፤ ለሀሳብ ነጻነት በሚታገል ድርጅት ውስጥ የምሰራ ሰው፣ በዚሁ ድርጅት መልሼ መታፈኔ ይገርመኛል፤ ያፈነኝ ግን ድርጅቱ ሳይሆን፣ ሰዎች ከድርጅቱ ጋር ያያይዙብኝ ይሆን የሚለው ፍርሀት ነው።)

አንዱዓለምና ናትናኤል የብርቱካን እጣ እንዲገጥማቸው አልሻም። በፓርቲው ሸውራራ አካሄድ ስነልቦናቸው እንዲጎዳም አልፈልግም፤ የስነምግባር ደንቡን መፈረም አንዱዓለምን እና ናትናኤልን ከእስር እንደያማያስፈታ አስረግጬ መናገር እችላለሁ። እነሱን የማያስፈታ ሰነድ ደግሞ ጥንቅር ብሎ ይቅር። አንዱዓለምና ናትናኤል በመረሳታቸው እጅግ ያንገበግበኛል። የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉና የገንዘብ መዋጮ የመሰብሰቡ ስራ እንኳ ቆሟል። ይሄ አልበቃ ብሎ በደንብ ባልተጠና የፖለቲካ አካሄድ ስነልቦናቸው ሲጎዳ አይቶ በሁዋላ ከመጸጸት አሁን የሚመስለንን መናገሩ ይጠቅማል እንጅ አይጎዳም።
እነ አንዱዓለም ያልመከሩበት ፖሊሲ በምንም ታዕምር ተግባራዊ መሆን የለበትም! አንዱዓለም የታሰረው ሮቢን አይላንድ አይደለም! ማማከር ይችላል። አንዱዓለም ” አይቃወምም ፣ ይስማማል” በሚል የሚቀርበው መከራከሪያ ብዙ መንገድ አይወስድም።

አንዱአያም አራጌ ” ያልተሄደበት መንገድ” በሚለው መጽሀፉ በገጽ 58 ላይ ስለ አምባገነኖች ባህሪ የጠቀሰው ትክክለኛ ነው እላለሁ ” የአለም ታሪክ እንደሚያሳየው አምባገነኖች በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸው ለቀው አያውቁም። እንደውም እነርሱ ስልጣን ከለቀቁ ሀገር እንደሚበታተን፣ ህዝብ እንደሚጨራረሽ የማስፈራሪያ ፕሮፓጋንዳ ይነዛሉ። ፈርተው ያስፈራሉ። ይሄ ባህሪያቸው መሆኑን መረዳትና ያለመዘናጋት መታገል ያስፈልጋል… ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሁን ያለውን አገዛዝ ለህዝብ ፈቃድ እንዲገዛ የግድ ማለት ያስፍልጋል።”

እኔ ነገ ስለሚሆነው ነገር ነው የምጽፈው፣ ትክክል መሆንና አለመሆኔን ለማየት ትንሽ ጊዜ መጠበቁ የሚሻል ይመስለኛል። ተሳስቼም ከሆነ ያን ጊዜ ሂሳቤን አወራርዳለሁ። ( በነገራችን ላይ አንድ ጊዜም እንዲሁ ሰማያዊ ፓርቲ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዱን በመቃወሜና ቀኑን እንዲቀይረው በመጠየቄ ብዙ ትችቶችን አስተናግጃለሁ፤ በሁዋላ ፓርቲው ( የእኔን ምክር ሰምቶ ይሁን አይሁን አላውቅም) ቀኑን ቀየረው፤ ለወረደብኝ ትችት ግን ሂሳቡን ያወራረደልኝ ሰው አልነበረም፤ ሲጽፉብኝ የነበሩ የማውቃቸው ሰዎች ሳይቀር ድምጻቸውን አጠፉ። እኔ ከተሳሳትኩ ሂሳቤን እንደማወራርድ ቃል እገባለሁ፣ ለመመጻደቅ ሳይሆን ለእድገት ይጠቅማል ብየ ስለማምን ነው።)

ቴዲ አፍሮ የቅኔ ዕንቡጥ –ለእናቱ ልዩ ዓርማ ነው!

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 16.01.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

“የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል እግዚአብሄር፤ ግን አካሄዱን ያቃናለታል“ (ምሳሌ ምዕራፍ 16 ቁጥር 9 )

የሀገሬን ክብር አዝልቀህ – ልታደምቅ
ታጥቀህ ተነስተኃል – አንተ የቅኝት ብርቅ፤
ራዕይ — አብነት።
እማን ከፍ አድርገህ ልታሸልማተኝ ጌጥ
ዕውቅናዋ ፈክቶ ዓለምን ልትመስጥ።
ተግተህ ትሠራለህ – አንተ የቅኔ ዕንቡጥ፤
የነፃነት ቃና – የትውልዳችን – ፈርጥ!

ባልባለቀው መንፈሴ – ቴዴ አፍሮ የተስፋዬ ፀሐይ ነው። ማህተም አለበት!
teddy afro
ዋና በር … ከሳቢያ ጥረት ምክንያታዊ፤ ከሳቢያ ተኮር ድካምም ምክንያታዊ ተግባራት የድል ዋዜማ ናቸው። ምክንያቱም የችግሩን ምንጭ ከሥሩ የሚያደርቀው በምክንያታዊና መሬት በረገጠ ተግባር ብቻ ጨለማው ነግቶ፤ የምሥራች ለነፃነት የመሸለም ስበታቸው ሆነ አስገዳጅነታቸው ጉልበታም ናቸው። የሚያስቀሩት ፍርፋሪ ስለማይኖርም ዘላቂ ድህነት ያስገኛሉ። የመፍትሄ መንገድ ጠራጊ የችግሩን ሳቢያ ማወቁ ሳይሆን ይልቁንም ምክንያቱን በሚገባ በልቶ ያማያዳግም መለስ ከመስጠቱ ላይ ነው። ምክንያት ተኮር የምርምር ተግባር በሸታውን ያገኛል። ህመሙን ከሥሩም ይነቅላል። ሳቢያ ተኮር እርጃዎች አቅመቢስ በመሆናቸው፤ ዋስትና የማይሰጡ ማስታገሻ ናቸው፤ አዘናጊ ልፈስፍስ ዝልቦ መንገዶች ናቸው!

ምልሰት፣ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2008፤ በኢትዮ – አፍሪካዊው የቅኔው ልዑል በብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ሥም በሰዬምኩት ማህበራዊ ድህረ ገጽ፤ እንዲሁም በጸጋዬ ድምጽ ራድዮ ፕሮግራሜ ቃሊቲ ውስጥ ለነበረው ታናሼ „ሥምን መላዕክ ያወጣዋል“ በሚል አንድ መጣጥፍ መጻፌን ብቻ ሳይሆን በድምፄም ማቅረቤን አስታውሳለሁ። ልቤ ውስጥ የገባ የቅኔ ቀንበጥ ነበርና ቴዲ አፍሮ። ስለ ወጣቱ ከያኒ – ገጣሚ – ዜመኛ – ድምጽ ቃና፤ እንዲሁም የአቀራረብ ብቃት- በዛ ጹሑፌ ላይ ሥራዎቹ ተተርጓሚነታቸው (interpretable) እንዲሁም ተዋራራሽነታቸውን በስፋት ነበር የገለጽኩት።

የድርሻዬን ይባልለት – ስለ ይፈልቃል ገና!

ዛሬም ደግሞ ትንሽዬ የግል ዕይታዬን ለማለት ትክሻዬን ለሚወርደው ዱላ አስመችቼ ለመቀበል ቆረጥኩና እንዲህ ልል ነው። በዚህ ፈታኛ ወቅት መቆስቋሻ የሚያስፈልግበት ሳይሆን ገብቶ መርመጥመጥም ይጥማል። ፈተና ተፈልጎ የማይገኝ ከተገኘ ግን አንጥሮ የሚያሳምር ሜሮን ነው። አባቶቻችን ፈተናቸው ሲዘገይ ወይንም ፈተና ቸልም ብሎ ሲረሳቸው ሁለት ሶስት ሱባኤ ይይዛሉ። እኔው የእነሱ ህይውት ኑሮኝ በመንፈሳዊ ዘርፍ ብጣቂ ዘር ባይኖረኝም። በገኃዱ ዓለም ግን እኔም ፈተና ሥልጡን አድርጎ ቀርፆኛል። ተላምጄዋለሁ። ከጋሼ ጸጋዬ ፍቅር መንጭቶ በውሰድኩት የድህረ ገጽ ስያሜ ብርትዬም ታስራ በነበረችበት ውቅት ተግቼ በብዕር ብቻ ሳይሆን በተገኘው አጋጣሜ ሁሉ መፋለሜ፤ እኔን ቢደቁሰኝም፤ ክሱ ሀገር ምድሩን ቢያዳርስም እኔኑ ቢያደቃኝም፤ የወረደው ማዕት …. ግን ኃይልና ብርታት ሰጥቶት ከዛ በኋላ የተከደኑ ብዙ ሲሳዮችን እንድከውን አምላኬ ረዳኝ። ቀን ሲወጣ ታላቋ ኢትዮጵያ ትንቆጠቆጥበታለች። አዎን! እኔ በምኖርበት ሀገር ኢትዮጵያ የምትባል ታላቅ ሀገር ጸጋዬ የሚባል የኢትዮ አፍሪካዊ ፈላስፋ ዕውቅናቸው ሙሉዑ እንዲሆን ሆኗል። የኦነግን ተልዕኮ ለማሳካት ሆነ በቅዱስ ወንጌል ሰባኪ ተብዬ ክስ ተመስርቶብኝ ነበር። ለዛውም ለአንስት ባልተሰጠኝ ጸጋ ብከሰስም አሸነፍኩ። ተመስገን። እድሜ ለሚሹንግ ዩንቨርስቲ ታላቅ ሚዛናዊ ኢትዮጵያዊ ሙሑር። ብዕራቸው ከእሥር አስለቀቀን በጋራ ….. ሰላምም አሰፉን። ምስክርነታቸው አንጀት አርስ ነበርና። አለን ሚዲያዎቼ እና እኔ እንደ አመረብን። ፈቃዱን ለሰጠኝ ለራዲዮ ፕሮግራሙ ቲም የተሰጠው አጥጋቢ ጥሁፍም በእጄ ላይ ይገኛል።

እግዚአብሄር ይመስገን የ21ኛው ምዕተ ዓመት ታላቅ ሥራ የሆነውን የደራሲ አቶ ምስብእክ ወርቁን „ዴርቶ ጋዳን“ ረቂቅ ወጥ ሥራ ጭብጥ ሳስብ፤ የቴዲን በጋሼ ጸጋዬ ዙሪያ የሰራቸውን ድንቅ ጽጌረዳዊ ተግባር በመንፈሴ ደም ሳዘዋውር፤ የመንፈስ ቋሚ ትውፊታችን በዕድሜ ተከታዮቼ እንዲህ ፋፍቶ ሳልሞት ቆሜ በህይወት በማዬቴ እግዜአብሄር ይመስገን። አሜን! የኔ ታናሾችን እግዚአብሄር ያኑልርኝ። ደሜ ቋንቋ ቢኖረው የሚናገረው ቋንቋ ጸጋዬ በሆነ ነበር – ተግባባን?! እኔ ጋሼ ጸጋዬን እማውቀው ኢትዮጵያዊ ሆኖ እናቱን – ሰንደቁ ሲያደርግ ነው። ክብራችንም ነው። ጉልህ የቋንቋ ሊቅም።

አሁን ወደ ተነሳሁበት ወጣቱ የተወቀሰበትን „ጥቁሩን ሰው“ ለእኔ የሰጠኝን ንጹህ ትርጉም ለሌሎች ወገኖቼ ለምን አልሰጣቸውም ብዬ አላዝንም። ውበት እንደ አካባቢው ስለሚተረጎም። እኔ በሚታዬኝ፣ ለእኔ በሚሰማኝ ውስጥ እነሱ ላይኖሩ ይቻላሉ – ለእኔ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ሥጦታ ነው። ለትውልዱ በጣምራ ገለጻ አንገት ነው። ባለዜማዎችን ለዘመኑ ሊመራ የሚችል ምልክትም ነው። ይህ ወጣት የከወናቸውን ተግባራት በማስተዋል ሆነን ስናነባቸው አሱም ሆኑ ሥራዎቹም አርማችን ናቸው። ባለመታደል ሆኖ እንጂ። ከዚህ ሌላ እኔ የወጣቶች አደራጅ ስለነበርኩኝ ስሜታቸው በጣም ቅርቤ ነው። „የልጅ ነገር አንዱ ፍሬ አንዱ ጥሬ ሆኖ“ ነው እንጂ በዚህ ዙሪያ መሬት ዬያዘ ሰፊ ጥናት ከወጣቶቹ ጋር ሰርተን ነበር። ከእጄ ቢኖር እንዴት ወርቅ በነበረ። በሌላ በኩልም ወጣትነት ሁላችን ያለፍንበትም ነው።
ለማንኛውም ወጣት አትሁን ማለትም የፈጣሪን ታላቅ ተፈጥሮዊ ዶግማ ሆነ ሥልጣን መጋፋት ይመስለኛል። በዚህ አፍላ ዘመን ስንት ቦታ ይደረሳል። ወጣትነት ሳተናነት ነው ….. በእኔ ስሜት ማዕቀፍ ውስጥ ያለው የነፃነት ትርጉም፤ የማንነቴ ጣዝማ በመሆኑ የውስጤ ፍጹም ገዢ ነው። ነፃነት ማንነት ላለው እኔነቴ አንጎሉም ነውና። ማናቸውም የገኃዱ ዓለምን የኑሮ ስንክሳሮች የማያቸው ሆነ የምመዝናቸው እኔን ከሰጠኝ ብሄራዊ ነፃነት በታች እንጂ በላይ ከቶም ሊሆን አይችልምና። ከዚህ አንጻር ቴዲ አፍሮ ለትውልዱ ጥበብ ነው። አጀንዳዎቹ ኢትዮጵያና ነፃነቷ ስለሆነ – የሥርጉተም።

ስለሆነም „የጥቁሩ ሰው“ ፊልም በሙዚቃ የተቀነባበረ ብቻ ሳይሆን እኔ ሳዬው፤ እውነትም ለመናገር፤ ፊልሙ በዛ ዘመን የተሰራ ነው የመሰለኝ። ማለት ትዕይንቱ ጦርነቱ እዬተካሄደ የተቀረጸ ዓይነት ነው። ጭብጡና የጭብጡ ማዕከላዊ ተልኮዎ በሥርዓተ ተክሊል በፍጹም ሁኔታ በተፈጥሯዊ አኃታዊነት የተጋቡ ናቸው። በጣም የተዋጣለት ታላቅ ተግባር ሆኖ ነው ያዬሁት። ከዚህ ባለፈ ድሉ ሙሴውን – የህዝብ ስለመሆኑም አባወራ ጀግኖቻችን በነቂስ አውጥቶ ነው የተቃኘው ስለሆነ ይህ ወጣት በቀደመው፤ በዛሬው ወይንስ በሚመጣው በዬትኛው ዘመን የተፈጠረ ነው በማለት በልቤ ውስጥ ባለችው ሙዳይ ወስጥ እጅግ መስጥሬ አስቀመጥኩት። መብቴ ነው። እኔ እንደዚህ ላሉ ወጣት ጀግኖቼ አብዝቼ እሳሳላቸዋለሁ፤ ሰብስቤ በማህጸኔ ውስጥ ባስቀምጣቸውም እወዳለሁ፤ ዓለም ቀናተኛ ስለሆነች እንዳትነጠቀኝ ስለምሰጋ

teddy afroየወጣቱን ንጥር ተግባር ብቁ ከሚያደርጉት መሰረታዊ ነገሮች ግጥሞቹ ጥልቅ መሆናቸው ነው። ትናንትን ከዛሬ፤ ዛሬን ከነገ በነብይነት ማያያዣ ፈጥሮ ያወራርሳቸዋል። ጥበብ ማለት ይህ ነው። ግጥምጥሞሽ ያልሆነ። እርግጥ ነው በግልብ ካዬናቸው ጊዜያዊ ደስታ ወይንም የማንደግፈው ከሆነም ጠብ አጫሪነ ስሜትን ቀስቅሶ ሊያበሳጨን ይችላል። አብሶ ከመልዕክቱና ሰብሉ ሊያለማ ከፈለገው ማዕከላዊ ማሳ ካልተነሳን እንደ መደዴ የቃላት ድርደር አድርገን ልንመከተው እንችላለን። የመልዕክቱ ውስጥ ንዑድ መንፈስ ነፃነት ነፃነት ነፃነት፤ ተፈሪነት ተፈሪነት፤ ገናናነት ገናናነት፤ ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያዊነት – አፍሪካዊነት ነው – የዓለም አብነት ኢትዮጵያ! ይህ ነው ውስጣችነን የወያኔ ሸፍጥ ካላሸፈተው …..
እያንዳንዱን ስንኝ በተን አድርገን በቁሙ ሳናነብ ውስጡን በቅንነትና በአዎንታዊነት ስንፈትሸው ቃሎችን ከስንኙ ሐረግ ነጥለን በመልካቸው ስናይ ደግሞ ቀለማችን አጉልቶ፤ እኛነታችን አብርቶ፤ ፍቅርን እንደ ታቦት ከብክቦ፤ ሩቅ ተጉዞ ሰላምን በናፍቆት ይጠራና ውስጣችን አስተቃቅፎ፤ ነገን በተስፋ ቀይሶ ይመከረናል፤ ያስተምረናል። ይፈትሸናል። ፍላጎታችን ኮትኩቶ የአቅጣጫውን ቅዬሳ ናሙና ከመንፈሳችን ሰርበዬር ውስጥ በሳቢነት ይቀርጸዋል። …..

እንዲሁም „ጥቁሩ ሰው“ በሀገራችን የነበረውን፤ አሁን ያለውን የሥነ ጥብብ እድገት ሥልጣኔም ቁልጭ አድርጎ ያሳዬናል። „ይህ የትውልድ ክፍተት አለበት፤ ወጥ ሥራዎች ተራቆቱ፤ የቀደሙት የሙዚቃ ስንኞች ቃናቸው ከዕውነተኛው ወይንም ከጋህዱ ዓለም ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ነበሩ። መሬት ያያዙ ነበሩ፤ ስለሆነም ወስጥን የመግዛት አቅም – ኃይልና – ስበት ነበራቸው። የዛሬዎቹ ግን ቤታቸው እንኳን አይመታም፤ ሥር አልሰደዱም“ … ወዘተ
… ለሚሉት ዕውነት ለመናገር የአርቲስት ቴዲ አፍሮ የመንፈስ ምርት ጥያቄያቸውን ሁሉ በአግባቡ የመለሰ ይመስለኛል። ደግሜም እላለሁ … እኔ አሁን ለተፈጠሩት ወጣቶች እጅግ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት አለኝ። በስለው ነው የተወለዱት ማለት እችላለሁ። መድረክ ሲያገኙ የማዬው ብቃት ከቶውንም ሊለካ የማይችል የመንፈስ ሐሴት ይሰጠኛል። ለዛውም በዚህ ሙጃ ሥርዓት፤ በዘመነ ወያኔ ተወልደውና አድገው … ሞት ያልተዋጀበት አንድም የኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ተቋም በሌለበት …. ይህን ጥሰው የወጡ የዘመኑ ጥቁር አንበሶች ናቸው – ለእኔ።

ንጽጽር፤
የብዙ ታዋቂ ዓለምዓቀፍ ባንዶችን ኮነሰርትን አብዝቼ እከታተላለሁ። የወጣቱ የፈጠራ ብቃት እኔ ነኝ ካለ ባንድ ጋር ሊመጥን የሚችል በቂ አቅም እንዳለው ነው ያዬሁበት። የቴዴ ሥራዎች መነሻ እሩቅ አይደለሙ። ከእናቱ ጓዳ፤ ከተጨባጩ ጭብጥ ስለሆነ፤ ስሜትን የመሳብ ችሎታው ብቻ ሳይሆን ስሜትን ተቆጣጥሮ የማቆዬት ጉልበቱም አንቱ ነው። ሁሉን ነገር፣ ሁሉን አካባቢ በቅኑና በትሁት መንፈስ ይዳስሳል። አንዱ የግጥም ዜማ በራሱ አንድ መጸሐፍ ይወጣዋል። ይህ ለኢትዮጵያ የሥነ – ግጥም ሆነ ሙዚቃ ነገ አዲስ አቅጣጫ ነው። ለማግሥትም ብቁ እርሾ!

ሌላው ቅኝቱ ራሱ መሰራቱ፤ ፍሬዘሩ ከውስጡ መፍለቁ፤ ከዚህም በላፈ የስንኙን ፍሰት ሳይጎዳ እንደ ራሱ ውስጠት አድርጎ፤ ጤናቸውን ጠብቆ፣ ሴላቸው ሆነ ደም ሥራቸው ሳይጎዳ፤ ኦርጋናቸው ሳይነደል እንደ ተፍጥሯቸው ስለሚቀርበው ይህ ደግሞ የወጣቱ ልዩ መለያ ጸጋው ነው። /ጀርመኖች አውስጌቦልሼ ታለንት/ ከሰው ዘር የተለዬ መክሊት እንደ ማለት። በዬሙያው እንዲህ ያሉ ሁለት አንጎል ያላቸው ይፈጠራሉና። በዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊነት በጠላትነት ተፈርጆ፤ በፖሊሲ ደረጃ ወያኔ ተግቶ እዬሰራ፤ በዘመኑ ተፍጠሮ ግን፤ የወያኔን ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ ፖሊሲ የቀደመ፤ የበለጠ ሥራ ነው። አንድ የፖለቲካ ድርጅት ረጅም ዓመት ከደከመበት የቴዲ ስንኞች የበለጠ ያፈሩና አርበኞች ናቸው። ለኢትዮጵያዊነትም ዘብ አደርም ናቸው። ሥነ ጥበብ ወተቱ የአድማጭ የሰላ እርምት ነውና ወጣቱ እርማቶችን በጸጋ ተቀብሎ ማስተናገድ ከቻለ አንድ ትውልድ የመፍጠር አቅሙ አንቱ እንደሚሆንም አልጠራጠርም።

የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ያን የመሰሉ ሥራዎቹን፤ ትውልድ የማይተካው ያ …. ዕንቁው ጋሼ ወጋዬሁ እሸቱ ነበር የሚተውንለት – የሚያነብለት። መዳህኒተዓለም አባታችን ንጉሥ ዳዊትን „እንደ ልቤ“ አለው ለጋሼ ጸጋዬም እንደ ልቤ ነበረው ጋሼ ወጋዬሁ። ዕድለኛ ነበር። እንደ ውስጡ ሆኖ፣ ከውስጡ የተቀመጠ ለእሱ ጸጋ ብሎ አምላኩ የመረቀለት ጋሼ ወጋዬሁ ነበር። ትውናው እንደ እራሱ ውስጥ አድርጎም ያቀርብለት ነበር። የጋሼ ጸጋዬ ስሜቱ መንትዮሽ በአህትዮሽ እንደ ነበር ይሰማኛል። መቼም እንዲህ ዓይነት አጋጣሚ በሺ ዘመናት አንድ ጊዜ ወይንም ሁለት ጊዜ ነው የሚከሰተው። ከዚህ አንፃር ውስጡን ከእነተፈጥሮው ማቅረብ መቻሉ ለቴዴ ዕድለኛነቱን ድርብ ያደርገዋል። በስሜቱ የፍልጎት ልብ ውስጥ እሱ እራሱ በመንፈስም በአካልም አለና። ተቀድቶ የማያልቀው ውበቱም ይህ ነው። ወጣቱ ከያኒ የጻፈውን እራሱ ያቀርበዋል …. እራሱ አቀናብሮ እራሱ ያስጌጠዋል። አደራጅቶ፤ ውስጡን የሚገልጽለት ሌላ ሰው ቢያስፈልገው ኖሮ ከባድ ነበር። ግን እድሉና ምርቃቱ ወፍ አወጣቸው። ስለሆነም ተ — ጠ – በ – በ – በ – ት።

የሰማይ የላቀ ስጦታ!

እኔ የእግር ኳስ ፍቅረኛ ነኝ። እጅግ በጣም እግር ኳስን እወዳለሁ። አሁን ዬይድነቃቸው ልጆች ለእፍሪካ ዋንጫ በ2013 እ.ኤአ. ሲታደሙ ሰፊ የሆነ አትኩሮት ነበረኝ። ኢሮ ስፖርት ሀገራችን እንዴት ከፍ እዬደረገ ሲገልጸው እንደ ነበረ ማመን እስኪያቅት ድረስ እጅግ እጅግ ድንቅ ነበር። ያን ጊዜ አጋጣሚው ረድቶ ሀገሬ ኢትዮጵያ ከፍ አለች። ታሪኳ፤ የህዝቧ ባህል፤ ወግ ልምዷ፤ የነፃነት ገድሏ ሁሉ ተዘከረ። ኢትዮጵያን የኢሮ ስፖርት ፕሮግራም አቅራቢዎች ሆኑ አዘጋጆች ውስጣችን አሳምረው ነበር ኪናዊ አድርጎ ያነበቡን – ቀለማም አድርገው ነበር የኳሉን። ለእኔ ፈውስ ነበር። ዳንኩኝ!
መቼም ትውልዱ አዲሱ ማለቴ ነው በብዙ ፈታና ውስጥ ሆኖ፤ ግን ድንቅ ነገር ያሳዬናልና ከዓለም ዋንጫ ዝርዝር ውስጥ ዬኛዎቹ ሲገቡ ደስታዬ ወደር አልበረው። ታዲያ የመጨረሻ ማጣሪያው ከናይጀሪያ ጋር ሲሆን ግን አልተመቸኝም ነበር። አሳምሬ ናይጀሪያዎችን አውቃቸዋለሁና። የሆነ ሆኖ የኔዎቹ ማጣሪያ ሳያልፉ ሲቀሩ ዕንባ አውጥቼ ነበር ያለቀስኩት። የእውነት። እናት ሀገሬ፣ የመንፈስ ተክሊሌ፤ እምዬ ኢትዮጵያ – እንጀራዬ የመላ ዓለምን የእግር ኳስ ጨዋታን አለመገኘቷ አስከፋኝ። ልክ እንደ መጻፍ፤ መጸሐፍ ማንበብ ድንቡልቡሏንም ስለምወድ ብራዚል ላይ እመቤት ኢትዮጵያ ስትደምቅ ናፈቆኝ ግን ሳይሆን ሲቀር በጣም ተጎዳሁ። የኢትዮጵያ ጎል ጠበቂ ገና አልተወለደምና።

እግዚአብሄር ይመስገን … ሁልጊዜም የማምናበት ነገር፤ ኢትዮጵያ አምላክ አላትና ዕንቡጡ ቅኔ አህጉርን ወክሎ በ2014 የዓለም ዋንጫ ብራዚል ላይ መገኘት በራሱ ክብር ነው። የሰማይ የላቀ ሥጦታ ነው። ልዩ ምርቃት ነው። የሥነ ጥበብ ቤተኛ ታዳሚዎች ሁሉ ልንደሰትብት የሚገባው መሪ ድል ነው። ቅኔኛው ቴዲ አፍሮ እንደ አባቶቹ እንደነ የቅኔው ልዑል ብላቴ ጸጋዬ ገ/መድህን መንገድ ተከትሎ፤ የአፍሪካ ነገር መስመሩ ነበርና፤ ፈልጎ የተነሳለት ድንቅ ራዕይ ከሀገሩ አልፎ አህጉሩንም ሊወክል ነው። እግዚአብሄር ደግ አምላክ ነው እንሆ አደረገለትም። ጉዞው አቅጣጫው እጅግ አጓጊ ነው።

ፅኑ ዕይታ!

እናት ሀገር ኢትዮጵያ ስትከብር፣ ስትደምቅ፤ ከፍ ስትል፣ ዜግነት ሲያበራ፣ እንደ ትናንቱ ኢትዮጵያ አፍሪካን በሥነ ጥበብ ጎራ ዳግም ልትመራ ስትመረጥ፤ ለመልካም ነገር ስትታጭ፤ ልዩ ፍጹም ልዩ ትርጉም ነው – ዕጹብ ድንቅ። ፍካታዊ ገጸ በረከት ነው። አበባዊ ረድኤት ነው። ለዚህ ተግባር ስኬታማነት እንደ ሰው የተገባን እናድርግ እንጂ፤ ትዕዛዙ ከመዳህኒተዓለም አባቴ ስለሆነ ሳንኩን ሁሉ አሸንፎ ሚሊዮን ፈን ያፈራል። አብሶ ጀርመኖች የሥነ – ጥበብ አክባሪና አፍቃሪ በመሆናቸው ለሽልማት ያጩታል። ጠብቁ። ቴዲን የቆዬ ሰው ይዬው። አፍሪካዊ ቪቫ ይሆናል። ዕውቅናውን አሳምረው ይሰጡታል። ሰፊ የሆነ በር ተክፍቶለታል። በሰውኛ ሥልጣን በሩን መዝጋት አይቻልም። „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላል ጎንደሬ ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነውና!
ጀርመን በሥነ ጥበብ ጉዳይ 13ኛው ፕላኔት ነው – ለእኔ። ፍጹም የተለዩ ናቸው። በደንበር – በክልልል – በቀለም በምንም ነገር አይደለም የጥበብን ልዩ ጸጋ የሚለኩት፤ በመንፈስ ቅዱስ ንዑድ ስሜት እንጂ። የሰማይ ጸጋን ለመተርጎም ሆነ ለማመሳጠር ተስጥቷቸዋል። ይህ ቀን እኔ ስመኘው ነበር። አንድ ዝግጅት ለጀርመን ህዝብ ቢኖረው በማለት። የለመኑትን የማይነሳ አምላክ ከጀርመን አልፎ ዓለም ሊታደምበት እንሆ ፈጣሪ አምላክ ወሰነ። ተመስገን!
እኔ በግሌ በፈጣሪዬ ስለማምን፤ ደግሞም የሥነ ጥብብ ሰውነት ሥጦታው የሰማይ ስለሆነ ጥበቃው ሰማያዊ ነው። በድንግልና ውስጡን ሆኖ ስለሚጫወተው ሥነ ጥበብን ያምርበታልና ሰጪው አጥር ቅጥር ይሆንለታል።

አዎን! ቀኑ እስኪደርስ ድረስ በጥንቃቄ፣ በፆም በጸሎት፣ ከብዙ ነገር ታቅቦ፣ ለዚህ ማዕረግ ካበቃው ከአምላኩ ጋር ቴዴ መሆን እንዳለበት እንደ ታላቅ እህታዊ አስተያየቴን አካፍለዋለሁ፤ ህይወቱ ያላችሁ ደግሞ እንደ ዕምነታችሁ በጸሎት ትደግፉት፣ ትረዱት ዘንድ በትሁት መንፈስ እጠይቃችኋለሁ። ከፀሎት በላይ ጠበቂ የለምና። ከጸሎት በላይ ዘበኛ የለምና። ምክንያቱም ያቺ መከራዋና ፍዳዋ የጠናባት ልዕልት ኢትዮጵያ፣ ልጆቿን አብልታ ማሳደር ያቃታት እናት ሀገር፤ ሚሊዮን የነገ ፍሬዎች ጉርሻ አጥተው በጠኔ የሚረግፉባት አምላኳ አረሳትምና እንሆ ከፍ ሊያደርጋት ማቀዱ ዬምልዓት ዕንባ ካሳ ነው። ለአምላካችንም ለቅዱስ እግዚአብሄር ከእኛ የሚፈልገውን ምስጋናችን ሳናቋርጥ እንግለጽለት። በዚህ ዘመን አንድ ታዊቂ፤ ተደማጭ ለዛውም ወጣት ማፍራት ነገን ያበራልና።
የአይቮሪው ዓለምዓቀፍ ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫወች ዝሆኑ ድሮግባን፤ የዩክራይን ሁለት ወንድማማቹች የጀርመን ዓለም ዓቀፍ ቦክሰኞች ወስጥ ታናሹ ለዩክሬን ፍትኃዊ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሲገኝ የዓለም ሚዲያ እንዴት ያረብርባል መሰላችሁ፤ የኛ ግን ትዕቢተኛው የሳውዲ መንግሥት የታላቅ ሀገርን ክብር ጠቅጥቆ ልጇቿን እንደ እንሰሳ አስፓልት ላይ እንደዛ ሲያርድ አንድ ለዕንባችን ዕውቅና የሚያሰጥ ታዋቂ፤ ተደማጭ፤ ዓለም ጆሮውን የሰጠው ዋቢ አልነበረንም። ነገ ግን ይኖረናል ….. ለዚህ ፈታናውን ተጋርቶ መረባረብ የግንባር ተልዕኳችን ነው። ጦርነቱ ተክፍቷል በድል ማጠናቀቅ አለብን! ማቄን ጨርቄን የለም! ለተደራጀ መሬት ለያዘ ተግባር እያንዳንዳችን በግል ሁላችንም በጋራ እንትጋ! ኢትዮጵያ ናት ፊት ለፊት ቁማ እሳት ውስጥ እዬተርመጠመጠች ያለችው። በኪነጥበቡ ይህ ዕውቅና ሲመጣ ደግሞ ግንባር መሆን!

በተረፈ ትምክህት ጎርፍ ነው፤ አድማም ጤዛ ነው። በሥነ ጥበብ ላይ ተደራጅቶ ጦርነት መክፈትም ወስጥን መፋቅ ነው። ፍቅር ግን የጸደቀ ፍሬ ነው። ኢትዮጵያዊነት የሚያሳፍር ሳይሆን የሚያኮራ፣ ተለምኖም የማይገኝ ምርጥ ዘርነት ነው። ውስጣችን የነጠረ ወርቅ ነው። ድህነታችን፣ የህዝብ መበደል፣ መንገላታት ደግሞ የሥርዓታት እንጂ እናት አንዱን ልጅ የክት ሌላውን የዘወትር፤ አንዱን አብልታ ሌላውን አስርባ በፍጹም አታውቅም። የወተት ጡት ጋቶቻ ለሁላችንም እኩል ማጥባትን አዘውትረው ይሻሉ …. ህግጋቶቿ ናቸውና። እቅፏም ለሁላችን ሳይዛነፍ በእኩልንት ነው። ማዕዷም እኩል ለሁላችንም ነው። ስለሆነም በእናት ሀገራችን ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ሁሉ መቆስቆሻ ሳንፈልግ ሁላችንም እኩል መማገድ በእጅጉ ያስፈለገናል። ፈተና መጥቷል – ማለፍን ይጠይቃል_! እናት ኢትዮጵያ የበደለችው አንድም ሰው የለም!

ክወና! …

ኢትዮጵያን የፈጠራት አምላኳ ምንጊዜም ስለማይረሳት እሷን ለማጠቃት የተነሱት ሁሉ የዶግ አመድ ይሆናሉ። በእኛ እድሜ እንኳን ሱማሌ፤ ኤርትራ፤ ግብጽ፤ አሁን ደግሞ ሱዳን ይታመሳሉ። አምላኳ ቀናተኛ ነውና። በ2012 እ.ኣ.አ. የአሳ ግማቱ ከአናቱ እንዲሉ እጬጌውን ከመንበራቸው፤ የጎጥ አፄውንም ደግሞ ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ለኑዛዜ ሳያበቃ ነበር ያነሳቸው። ይህ ምርታማ መሬት፤ ለምለም አካባቢ፤ ሃብታምነት የሚባለውም ቢሆን አባታችን ከተከፋ ትል ከሰማይ ሊያዘንብበት ይችላል። እናስተዋል! —- ጉዳቱ ደግሞ የጋራ ነው እንደ ሰው ለምናስበው – ለእኛ።
እንኳንስ በተፈጥሮ ኤኪኖሚዋ ጥገኛ ለሆነ፤ ያልጠመጣጠነ ኤኮኖሚዊ ዕድገት ለሚገርፋት ኢትዮጵያ ቀርቶ የሰማይን ቁጣ እንጃፓን፣ ሱናሜም ማስቆም አልቻሉም። ይልቅ እንደ ሰው አስበን በዛ ቦታ ማን ይኖራል? ህፃናትን፣ አቅመ -ደካሞችን፤ ህሙማን፤ ነፍሰጡር ሴቶችን፤ እንሳሰት ሳይቀሩ ሊታስብላቸው ይገባል። ቀይ ቀበሮ እኔን ይገልጸኛል። ሶፍ ኡመር ዋሻ እኔን ያብራራኛል። ልዩ የሚባሉ አብዛኞቹ ሌላ ዓለም የማይገኙ አዕዋፋት ኢትዮጵያ ብቻ ነው የሚገኙት፤ ሁሉንም የሰማዩ ቁጣ ውስጣችን አብሮ እንዳያጭደው አደብ ገዝተን ወደ ፈጣሪያችን እንመለስ!
… ለሰው አይደለም። ወደ ፈጣሪያችን ቀልባችን መልሰን እራሳችን አዋርደን፤ ይቅርታ አምላካችን እንጠይቅ …. ኢትዮጵያ ሶስት አፄዎቿ ዓለም በቃኝ ብለው ገዳምን የመረጡ ንዑዳን የፈጠረች ቅድስት ሀገር ናት። ዘጠኙ ቅዱሳን ከተፈጠሩባት ሀገር አስበልጠው የመረጧት ሀገር ናት። ነብዩም ለጆቻቸው የተመኩባት ተምሳሌት ሀገር ናት።

የማከብራችሁ ወገኖቼ …. እጅግም የምናፍቃችሁ ደሞቼ … መንጠራራት መልካም ባይሆንም፤ ሰው ባላው ነገር ወይንም በቀጣይ ፍላጎቶቹ ዙሪያ አብዝቶ ሊንጠራራ ወይንም ሊመካ ይችላል። በተማመነበት ጉዳይ። በክርስቶ ወይንም በአላህ ሥልጣን መንጣራራት ግን ዕጣው ትውልድን ያሳርራል – ያርሳልም። ቅጣቱን የሚያቆም ምድራዊ ኃይልም አይኖርም፤ አባ ጳውሎስን አተረፈ ተዋህዶ? ወይንስ ቲፒ.ኤል.ኤፍ ሄሮድስ መለስን ታደገ? ገዳማት ታረሱ …. ቁጣውም ነደደ!
ፍቅር ተንበርክኮ እንሆ ይለምናል። አሁንም ህዝባችን በፍቅር ይጋባል፣ ይዋለዳል፣ አብልጅነት ይናሳል፣ ይጎራበታል፣ ጡት ይጣባል፤ ጓደኝነት ይገጥማል፣ ማህበሩን ዝክሩን አብሮ ይጠጣል፤ ሀዘን ተፍሰኃውን ፈቅዶና ደስ ብሎት ይጋራል፤ ይረዳዳል፤ ይህን የደም ግንኙት መበጠስ አይቻልም … ሰውኛ አይደለምና ….. በቁጭት ምክንያት ምላሽ ለመስጠት ፍላታችን ለማስታጋስ ስንል በምንሰነዝራቸው ቃሎች ከእልህና ከግብታዊነት ጸድተን እንስከን። ማስተማር የሚቻለው የሚወረወረውን ናዳ መልሶ በመልቀቅ ሳይሆን፤ ጨዋነታችን በለገሰን አርምሞ፤ በተደሞ፤ በትግሥትና በሆደ ሰፊነት ወያኔ ያዘጋጀውን ሴራ ማክሸፍ ስንችል ብቻ ይሆናል ብጡልነት። የዚህ ሁሉ ትርምስ ተዋናዩ ወያኔ ነው። ይህ አውሬ ያዘጋጀው መርዝ ወገኖቻችን አልተረዱትም። ዕውነተኛውን ነገር ወስጣችን ፈቅዶ ይቀበል ዘንድ እግዚአብሄር ይርዳን። ትጉኃን ቀጥሉ የሃቅ ምስክር መረጃዎችን በሚዛን ቀልቡን። አትናቁ ወይንም አቅልላችሁ አትዩትት። የተደራጀ ፈተና ነው። ፈተናው የሚረታው ደግሞ በበለጠ በተደራጀ ሥልጡንና ብልህ ተግባር ብቻ ነው።
ቀኑ እዬናፈቀኝ – የሰንደቄ ዜማ …
ህብር ስንኞችህ ማንነት ሊያለማ።
አፍሪካዊነቴ ሊደምቅም – ሊያበራ
በፈጠራ ዓውራ! ….
ዛሬ ለትናንቱ፤ ትናንትም ለነገ – አድዮ አጎመራ፤
ሉሲ ከፍ ትላላች በመንፈስ – በማማ
በፍውሰትህ – ጣዝማ …..።
እናት ታጌጣለች ….. በሞገስህ ግርማ፤
ታሪክ ይዘከራል – በወጣቱ ዓርማ!
ዓለም ይታደማል በመረዋ እማማ!
ህበረ – ቀለማቱ፤ — የቁንጅና ዋና!
አማንህ – ሊያዘመር ….
እሙ – ልትቀምር
የታጠቀ ዕውነት ብቃት ሊመሰክር፤
ያ …. የደግ ታሪክ ገር፤ መቅድምን ሊመራ
የዘማናት ሂደት …. ትውፊት ሊያነባብር
ዋዜማን – ሊያዘመር …. ብቃት አጎመራ!

ማሰሰቢያ።
• ግጥሞቹ 13.01.2014 00.17 (እ.ኤ.አ) ተጻፉ።
• ጎልተው የተጻፉት ፊደላት ጠብቀው እንዲነበቡ የሻትኳቸው ናቸው።
• የግጥሞቹ – ዕርእሶቹ ጎልተው የተጻፉት የተሰመረባቸው ቃሎች ናቸው። ነፃነት ታወጀላቸው ከፈለጉት ቦታ ላይ ሆኑ፤
• ፎቶው ከቴዲ አፍሮ የግል ድህረ ገጹ የተወሰደ ነው።
መፍቻ።
ዋና ሁለቱንም ትርጉም ይዞ ነው የታደመው። ለሁለተኛው ግጥሜ እርእስም ነው።
• ላልቶ ሲነበብ አብይ፣ ኣናት፣ አለቃ፣ መሪ፤ አስተዳደሪ፤ ሰብሳቢ፤ አዛዥ፤ ሙሴ፣ እረኛ፣ ተጠሪ፣ እርእሰ ጉዳይ እንደ ማለት … ሁሎችም እንደ አረፍተ- ነገሩ ፍሰት ይተረጉሙታል። ለእኔ ግጥም ሙሴ የሚለው ግጥሙ ነው።
• ሁለተኛው ጠብቆ ሲነበብ ደግሞ የአሳን ተፈጥሮዊ የኑሮ ልማድን የሚከተል ይሆናል። … የሰው ልጅ በእህልና በመጠጥ ብቻ አይኖርም። ህሊናው መስኖ ይፈልጋል። መስኖው ደግሞ ሥነ ጥበብ ነው። ሥነ ጥበብ ጥሩ ዋናተኛ ነው። ዋናው በውጭ ሳይሆን ውስጥን የሚቀድስ የሚፈውስ፤ የሚጠግን፤ የሚያጽናና፤ የሚያጸና፤ የውበት ውበት፤ የጌጥ ጌጥ ነው። ልዩነት በአንድነት አንድነት በልዩነት አኃቲነት በመፈቃቀድ የሚያበቅል – የሚያጸድቅም ነው … በዚህ ሂደት ህልም ህልም ነው ነገሩ የሚመስለው የዓለም ብቸኛ ፍቅረኛ በሆነው የእግር ኳስ ትንሳኤ የኢትዮጵያ ሥነ – ጥበብ በበትሩ አሳላፊ በውስጥነት ሊዋኝ ነው …. ያ … የዓለም ሚዲያ ሰልፉ፤ ያ … የዓለም ዕውቅ ሰዎች ታዳሚነት ውስተት እኛነት መስፍን ሆኖ ሊሰነቅ፤ እሰቡት ….. ውህድነት። በአንድ ለጋ ሊጋባ …. ይህ የምልዓት መንፈስ በሐሤት ኢትዮጵያን በዕዝነ – ህሊናን ሲዳስሳት … የቅዝፈቱን ቅኔ ዘጉባኤን የዳጎሰ ድምር ነው ዋና ያልኩት ….
• ጣዝማ …. ከተለመደው ውጪ የሚገኝ የተፈጥሮ የማይረጋ ማር። ለጤና እጅግ መዳህኒት የሆነ። አብዛኛውን ጊዜ የሚገኘው በቆላማ የሀገራችን ቦታዎች ነው። ቀለሙም ትንሽ ደመቅ ያለ ነው።
• አድዮ ማንም ሀገር ብሄራዊ አበባ የለውም። ኢትዮጵያ ግን አላት። መንገድ ጠራጊዋ የተስፋ አበባ አድዮ የአዲስ ዓመት ዋዜማ! የሰንደቅዓላማችን ማዕከላዊ ቀለም ከዚህ ተፈጥሮ ጋር የተሳሰረ ይመስለኛል – በኪዳን። በ5ኛው መጸሐፌ ላይ „በፊደል“ የልጆች የግጥም መድብል የተሰራበት ነው፤ እንደዚህ ለዬት ያሉ ተፈጥሯችነን ከፊደል ላይ ዘርዘር አድርጌ ጽፌዋለሁ። በነገራችን ላይ የፊደል የፊት ሽፋን ከዓለም የሚለዬን፤ እንደ ውስጣችን የተፈጠረው ድንቁ የፊደል ገበታችን ሲሆን ከሌሎቹ መጸሐፍቶቼ በበለጠ በነጮች ተወዳጅም የሆነው እሱ ነው። ይወዱታል … በጣም። ቋንቋው አማርኛ ግን ተማረኩለት … ሌላ ቀን በዚህ ዙሪያ እመጣላሁ … አሁን ደግሞ የአፈሙዙ አቅጣጫ በእሱ ዙሪያ ስለሆነ ….
መንፈሶቼ – ታዳሚዎቼ! የፍቅር ማዕድ በመከባባር አብሮ አቆዬን ፤ለተሰጠኝ በቂ ጊዜ ምስጋናዬን በቅኑ ውስጠት – እንሆ!
ፈጣሪ አምላካችን የተበተነን ልቦናን ስበስቦ፤ እናታችን ከፍ ትል ዘንድ የጀመረውን ይጨርስ።
ልብ ይስጠን – ለሁላችን! የምንችለበትም ጽናትም! አሜን

ጨረስኩ — ንጹህ አዬርም አገኘሁ – ዱላውን የምችልበት!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

የአንድነት ተልእኮና የፋሲል የኔአለም ጫፍ የቆመ እይታ

$
0
0

ዳንኤል ተፈራ

Daniel-Tefera አንድነት ፓርቲ በተሳካ ሁኔታ ጠቅላላ ጉባኤውን ፈጽሞ በበርካታ ወጣቶች የተገነባውን ካቢኔ ይፋ ካደረገ በኋላ ጥቂት ሳምንታት አለፉ፡፡ በነዚህ ጥቂት ሳምንታትም ትግሉን በማያዳግም ሁኔታ የህዝብ አድርጎ የሚፈለገውን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን ለማድረግ ቀን ከሌሊት መስራት ይገባል የሚል እቅድ አንግቦ ደፋ ቀና በማለት ላይ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለን ግን የግል አስተያየት በማለት የኢሳቱ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም “የአንድነት ፓርቲ የመጭው ጊዜ ፈተና›› በሚል የፃፈውን ያልታሰበበት ጽሁፍ አነበብኩ፡፡

በቅድሚያ ጽሁፉን አንብቤ ሳበቃ ለምን መልስ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ እንዳገኘሁት መግለጽ ይገባኛል፡፡ ፋሲል ማስተላለፍ የፈለገው ‹‹አንድ ጫፍ ብቻ›› የረገጠ መልእክት የተዛነፉ ሃሳቦች የተላለፈበት፣ ከግለሰብ ጥላቻ በመነሳት ፓርቲውን ፈተና ውስጥ ያለ በማስመሰልና ዋጋ እየከፈሉ ያሉትን ውድ አባሎቻችንን በግብአትነት በመጠቀም ክፍፍል ለመፍጠር የፈለገ በመሆኑ ነው፡፡ ወይም ፀሀፊው ‹‹ሁለት የከረሩ ጫፎች ብቻ ያስፈልጋሉ›› ከሚል አይነት አመለካከት ላይ ቆሞ ከመፃፍ የመነጨ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያቴ በአምባገነኑ ስርዓት ተጠፍንገው ከተያዙ የብሮድካስት ሚዲያዎች ውጭ አማራጭ አልባ ለሆነው ህዝብ በአማራጭነት ለቀረበው ኢሳት ካለኝ አክብሮት ነው፡፡ ምክንያቱም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም የኢሳት ባልደረባ እና ኃላፊነት ያለበት ሰው በመሆኑ፡፡

ፋሲል በጠቅላላ ጉባኤው በከፍተኛ ድምጽ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው የተመረጡት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ቃለ-ምልልስ ካደረጉት ውስጥ ‹‹ከኢህአዴግ ጋር ገንቢ ግንኙነት (Contractive engagement) እንዲኖረን እንፈልጋለን. . .›› የሚለው ለሱ ሃሳብ የሚመቸውን ቆንጥሮ በማውጣት ከልደቱ አያሌው ‹‹ሦስተኛ መንገድ›› ካለው ወይም ‹‹ መሀል ላይ መቆም›› ብሎ ከተረጎመው ሃሳብ ጋር ለማያያዝ ሞክሯል፡፡ ስህተቱ እዚህ ላይ ይጀምራል፡፡ አንድነት ሊበራል አስተሳሰብ የሚያራምድ በመሆኑ የግለሰቦች መብት በቅድሚያ መረጋገጥ አለበት ብሎ ያምናል፤ በስትራቴጂው እንዳስቀመጠውም የኢህአዴግ አይነት ብሔር (የቡድን) መብትን ማክረር ወይም የዚህ ተቃራኒ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት ላይ ብቻ ቆሞ ሌሎችን አለማዳመጥ ዴሞክራሲያዊ አይደለም ይላል፡፡ ሁሉም ባልተሸራረፈ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ ያለምንም ጣልቃ ገብነት የመደራጀት መብታቸው መከበር አለት፡፡ ስለዚህ ጥያቄው ጫፍ የመቆም ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመፍጠር ነው፡፡
UDJ
ስለዚህ አንድነት እንደ ሊበራል ፓርቲ ከገዢው ፓርቲ ጋር መደራደር ይገባል፡፡ መደራደር፣ ሰጥቶ መቀበል እንደነውር መታየት የለበትም ብሎ አስቀምጧል፡፡ ኢ/ር ግዛቸውም በቃለ ምልልሱ ያስቀመጡት ይህንን ነው፡፡ መደራደር የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ ሥራ ነው፡፡ መደራደር ዘመናዊ አስተሳሰብም ነው፡፡ አሁንም እየታገልን ያለው ችግራችንን በጠረጴዛ ዙሪያ እንፍታ፣ ሆደ ሰፊ እንሁን፣ ጠርዝ ከያዘና ከፍረጃ ፖለቲካ እንላቀቅ በማለት ነው፡፡ አቶ ፋሲል ‹‹መሀል ላይ መቆም›› ያለው እንደዚህ አይነቱን ሃሳብ ነው፡፡ እንጅ ራሱ ፀሀፊው አንድነትም ሆነ አመራሩ ተንበርክኮ እንዳልሆነ፣ እንደ አንድነት ዋጋ የከፈለና እየከፈለ ያለ ፓርቲ እንደሌለ የሚያውቅ ይመስለኛል፡፡

ጠርዝ ላይ የቆመ ሃሳብ አለማራመድ ወላዋይ አያሰኝም፡፡ አንድነት መሀል መንገድ የሚለው የብሔረሰብ አክራሪነትም ሆነ የህብረ ብሔር አክራሪነት አይጠይቅምም ከሚል ነው፡፡ ሁለቱን የሚያቀራርብ የመሀል መንገድ መኖር አለበት እንደማለት፡፡ እንደዚህ ማሰብም ጤናማ ነው፡፡ መብትም ነው፡፡ ሁላችንም ሃሳብ የምናቀርበው ለሀገር ይጠቅማል የምንለውን ነው፡፡ አሸናፊው ሃሳብም በህዝብ ዘንድ ቅቡል ይሆናል፡፡

ጋዜጠኛ ፋሲል ግን ለኢ/ር ግዛቸው ካለው የግል ጥላቻ ይመስለኛል ጥቂት ነገር ቆንጥሮ ‹‹ፍርሃት ነው›› ለማለት ይሞክራል፡፡ በውጭ ሀገር እየኖሩ መታገል፣ ትግሉን መደገፍ እንደሚችል አምናለሁ፡፡ ለፋሲል ግን አንድ ጥያቄ መጠየቅ እፈልጋለሁ፡፡ የሚፈራ ሰው መቀመጫው የት ነው? እንደሚመስለኝ ወይ የኢኮኖሚ ጥያቄ ካልሆነ በስተቀር ፀሀፊው ከሀገር የወጣው ሀገሩን ስለሚጠላ ሳይሆን ሥርዓቱን ስለፈራ ነው፡፡ ሥርዓቱን ፈርቶ በተሰደደ ሰውና ከሥርዓቱ ጋር ፊት ለፊት ግብግብ እየፈጠረ ያለ ሰው መካከል ትልቅ የሞራል ልዩነት አለ፡፡ ስለዚህ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ፍርሃትን የተረጎመበት መንገድ ድንጋዩ ተመልሶ ወደ እርሱ እንዲያርፍ የሚያደርግ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ከሀገር ወጥቶ ትግሉን መደገፍ ትክክል ቢሆንም ፖለቲካውን ለመምራት መሞከርም ሌላ ትልቅ ስህተት ይሆናል፡፡ እንዲህ ሲባል እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት የአቅማችንን እያደረግን ያለን ሰዎች መተቸት የለብንም ብዬ አላምንም፡፡ በመሳደበና በመተቸት መካከል ግን ትልቅ ልዩነት እንዳለ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
ሌላው ማንሳት የምፈልገው ጋዜጠኛ ፋሲል የአንዱዓለምንና ናትናኤልን ስም በመጥቀስ ጫፍ ላይ የቆመ ሃሳብ የሚያራምዱ አድርጎ መግለፁም ስህተት ነው፡፡ አንዱዓለምም ሆነ ናትናኤል ፋሲል የጠቀሰውን አይነት ሃሳብ የሚያራምዱ አይደሉም፡፡ ሆነውም አያውቁም፡፡ በተለይም የአንዱዓለምን ሃሳብ ለመረዳት መጽሀፉን ማንበብ ተገቢ ነው፡፡ ወጣቱ ፖለቲከኛ በሆደ ሠፊነት ‹‹ ኧረ የመቻቻል ያለህ፣ ኧረ የድርድር ያለህ፣ ኧረ የመደማመጥ ያለህ . . .›› በማለት አንድ ጫፍ ላይ ቆሞ ማክረር እንደማይጠቅም ገልጿል፡፡ ለአዲሱ አመራርም እውቅናና ድጋፍ ሰጥቷል፣ ደስተኛም ነው፡፡ ይሄን የምለው አንዱዓለም ለገና በዓል በአካል አግኝቼ ሃሳቡን ለረዥም የማዳመጥ እድል ስለገጠመኝ ነው፡፡

በመጨረሻ ግን ስለ ኢሳት ማንሳት እፈልጋለሁ፡፡ ኢሳት ለኢትዮጵያውያን በአማራጭነት ብቅ ያለ ትልቅ ሚዲያ ነው፡፡ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ያለውን አበርክትቷል ማድነቅ እፈልጋለሁ፡፡ እኔም በተለያየ ጊዜ በዚሁ ሚዲያ ላይ የተለያዩ ሃሳቦችን ሰጥቼ አውቃለሁ፤ ወደ ፊትም እድሉን ባገኘሁ ቁጥር እሰጣለሁ፡፡ የተለያዩ አማራጭ ሃሳቦችን በተደራጀ ነፃ ሚዲያ ማግኘት የተራበው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳያዝን የኢሳት ጋዜጠኞችን የኢዲቶሪያል ቦርድ አባላት በእጅጉ ሊየስቡበት ይገባል፡፡ ማንኛውም ሚዲያ ከአድሎ አሠራር ነፃ መሆን አለበት፡፡ በዚህ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ጋዜጠኞቹ ግን የግል አመለካከታቸውንና እምነታቸውን በማስቀደም አንድን ድርጅት ለማጥቃት የሚሄዱበትን መንገድ መፈተሽ ጠቃሚ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ፋሲል በአንድነትና አመራሩ ላይ የሰነዘረው የተዛባ አስተሳሰብ “በግል አስተያየት ስም” የቀረበ ቢሆንም ግለሰብ አንድ ትልቅ ፓርቲ ላይ ሲጽፍ መውሰድ የሚገባውን ጥንቃቄ አላደረገም፡፡ ስለዚህ ብዙ ተሳሳተ፡፡ ለማንኛውም ሁሌም ከጥላቻ የሚነሳ ሃሳብ ለህዝብም አይጠቅምም በማለት ላጠቃልል፡፡

“ብጥብጥና ሁከት” የህወሃት የተለመደ አባባል: “መንግስት ሆይ ህዝቦችህ ይወዱሃል የምንልህ እኛ ነን እንጂ እነሱስ ሞትህን ይመኛሉ”

$
0
0

ናትናኤል ካብቲመር ኦስሎ ኖርዌይ 5 ጥር 2006

መቼም በኢትዮጲያ ብጥብጥና ሁከት የሚባለውን አባባል የማያቅ አለ ለማለት ያሰቸግራል። ምክንያቱም የመብትና የፍትህ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር የህወሃት መንግስት “ ብጥብጥና ሁከት ሊያሰነሱ ሲሉ” ማለቱ የተለመደ ነው። ምንም አይነት መብትን የተመለክቱ ጥያቄዎች በድርጅት ወይም በግለሰብ በተነሱ ቁጥር “ብጥብጥና ሁከት” ሊያስነሱ ሲሉ ይባልና እስር ቤት ይወረወራሉ። እዚህጋ በርካታ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ነገር ይታያል። በኢትዮጲያ መብት ማለት ምንድነው? አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን የመብት ጥያቄዎቹን ለመንግስት እንዴት ነው ማቅረብ ያለበት? ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ግን አንድ መራራ እውነት አለ እሱም መብት ማለት በኢትዮጲያ መንግስት መጥኖና ለክቶ ለራሱ በሚስማማ መልኩ ለማህበረሰቡ መብቶች ብሎ የተዋቸው ናቸው። መብት ሲባል በወያኔ ካድሬ አመለካከት ያው ሁሌ ንፅፅሩ ከዛ ከፈረደበት ደርግ ነው “በደርግ ጊዜ ሰአት እላፊ ነበር አሁን ግን የለም” ፣ “በደርግ ጊዜ ብሄራዊ ውትድርና ነበር አሁን ግን የለም” ስለዚህ ወያኔ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነው እንባላለን።
semayawi
ብጥብጥና ሁከት ምን ማለት እንደሆነ ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን ነገር ግን በአሁኑ ሰኣት በየእስር ቤቱ እየማቀቁ የሚገኙት ወጣቶች የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ነው እንጂ በጥብጠው እንዳልሆን ለማንም ግልፅ ነው። ደሞ ሌሎች አባባሎች አሉ “የተወሰኑ” ፣ “አንዳንድ” የሚባሉ ለምሳሌ ባለፈው ምስኪኖቹ የኢትዮጲያ መምህራን ደሞዝን አስመልክቶ ላነሱት ጨዋነት የተሞላው የመብት ጥያቄ ሟቹ አቶ መለስ “አንዳንድ ብቃት ያነሳቸው መምህራን ብጥብጥና ሁከት ሊያስነሱ ሲሉ” ብለው በአነስተኛ ገቢ በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩትን ምስኪን የኢትዮጲያ መምህራን በሃዘን አንገታቸውን አስደፏቸው። እብሪት ከተሞላው ስድብና ማስፈራሪያ ውጪ ላነሱት ጥያቄ በአግባቡ እንኳን ማብራሪያ አልተሰጣቸውም።

የኢትዮጲያ ሙስሊም ማህበረሰብም ከህፃን እስከ ሽማግሌ እምነታቸውን አስመልክቶ ላነሱት ጨዋ የመብት ጥያቄ “አንዳንድ ብጥብጥና ሁከት ፈጣሪዎች” እየተባለ ይዘገባል። ባለፈው የብራዚል ማህበረሰብ ላነሳው የመብት ጥያቄ ፕሬዝዳንቷ ዲልማ ሩሴፍ የተናገሩት ንግግር እጅግ ያስቀናል “መብታችሁን ለማስከበር በመነሳታቹ ኮራሁባቹ” ነበር ያሏቸው። አንድ ነገር እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው በወያኔ አገዛዝ ይህንን በፍፁም አንሰማም። ለምን? የኢትዮጲያ ህዝብ በጥባጭ ስለሆነ? ወይም መንግስትን አጉል ጥያቄ ስለሚጠይቅ? አይደለም። ህወሃት ራሱ የሰራውና እየሰራ ያለው ኢሰባዊ የሆን ግፍና የመብት ረገጣ ስለሚያስበረግገው ሰው ሲሰብሰብ አይወድም። እጅግ በሚያስገርም መልኩ በቅርቡ የሳውዲ መንግስት በኢትዮጲያዊያን ላይ ያደረሰውን አስከፊ ግፍና የመብት ረገጣ ለመቃወም የወጣውን ህዝብ እንኳን “ብጥብጥና ሁከት” ሊያስነሱ ተብሎ እየተደበደቡ ተበተኑ። ኧረ ሌላም ብዙ አይተናል።
ነፃና ዲሞክራሲያዊ መንግስትማ የህዝቡን የመብት ጥያቄ እንዴት እንደሚመልስ እናያለን። እንደውም የኢትዮጲያ ህዝብ ሲበዛ የዋህ ነው ባለፈው ውጥንቅጡ በወጣውና መላቅጡ በጠፋው የኢትዮጲያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ የተነሳ ተሰደው በሳውዲ ሲሰቃዩ ቆይተው ወደሃገራቸው ከተመለሱት ስደተኞችጋ አንድ ሁለት ፎቶ ስለተነሱ ብቻ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን የሚያደንቁም ተነስተው ነበር። ምን ስላደረጉ? ምንም። እንደው ህዝባችን ትንሽ ሲያረጉለት ወዲያው ለምስጋና አንገቱን ስለሚያጎነብስ ነው እንጂ። ይህን የመሰለ የዋህ ምስኪን ህዝብ በዘርፈብዙ ችግር ሲሰቃይ ማየት እጅግ ያበሳጫል።
ለምሳሌ የመብት ጥያቄ ማንሳት “ብጥብጥ” መባሉ ቀርቶ ለማንኛውም ኢትዮጲያዊ ተፈቀደ እንበልና ምስኪኑ የኢትዮጲያ ህዝብም “ኧረ ተው ከዚህ ሀገር ንቀለኝ” እያለ አማልክትን ከማስቸገር መብቱን ለማስከበር ቢነሳ ምን ያህሉ የሃገራችን ህዝብ የመብት ጥያቄ እንደሚያነሳ ሁላችንም መገመት አያቅተንም።
Muslim Etiopia 1
አንዳንዴ ሳስበው መንግስት ዝም ሲባል የተወደደ ይመስለዋል መሰለኝ ምናልባትም አንዳንድ አገልግሎት ሰጪ ቦታ የሚሰሩ ካድሬዎች የህዝቡን ሮሮ ትተው “ህዝቡ ለመንግስት ፍቅር አለው” ብለው ሪፖርት ስለሚያቀርቡ ይሆናል። እውነታው ቢገለፅ ግን ሪፖርታቸው የሚሆነው “መንግስት ሆይ ህዝቦችህ ይወዱሃል የምንልህ እኛ ነን እንጂ እነሱስ ሞትህን ይመኛሉ” ነበር።

ታስታውሱ እንደሆን አቶ መለስ “ይህ ማዕበል” ብለው አለወትሮአቸው ድምፃቸውን ሞቅ አርገው የተናገሩት መንግስታቸው የተወደደ መስሏቸው ነበር ወዲያው በነጋታው መልሱን አገኙት እንጂ። ግን እንዴት እንደዛ አሰቡ? በትክክል ቁጥሩን የማያውቁትን ህዝብ ፣ መንግስት በስርአቱ መዝግቦ ያልያዘውን ህዝብ ፣ በኑሮ ውድነት ፣ በነፃነት እጦት እያሰቃዩት ያለውን ህዝብ እንዴት ይወደኛል ብለው አሰቡ። ያስገርማል።

ወደዋናው ሃሳቤ ስመለስ ማንኛውም የሰው ልጅ መብቱን መጠየቅ ማስከበር አለበት ማንኛውም ኢትዮጲያዊም እንድዚሁ። ይህን ስል ግን የግድ መስቀል አደባባይ መሰብሰብ ላይቻል ይችላል ቢሆን ጥሩ ነበር ነገር ግን ሁሉም ኢትዮጲያዊ በሚኖርበት ፣ በሚሰራበት ፣ በሚማርበት ፣ አገልግሎት በሚያገኝበት ቦታ መብቱን ማስከበር አለበት። ባገኘው አጋጣሚ እምቢ ማለት አለበት።

ግራ እና ቀኝ ጠፋን –ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0

ታኅሣሥ 2006

Pro Mesfinበአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው፤ ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ አጠቃላይ ነጻነት ሲመጣ ወንጀለኛነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የጽሑፍ ቁጥጥር ሲነሣ ጸሐፊዎች ይበዛሉ፤ ትምህርት በተስፋፈበትና ማንም እንደፈለገ ለመጻፍና ለማሳተም ችሎታውም ዕድሉም በማይገኝበት፣ ሳያበጥርና ሳይሰልቅ አሰር-ገሰሩን ጽፎ በአደባባይ የሚወጣውን ጥምብ-እርኩሱን አውጥተው ሁለተኛ እንዳይለምደው የሚያደርጉ የታወቁና የሰላ አእምሮና ብዕር ያላቸው አርታእያንና ሐያስያን (ገምጋሚዎች) ባሉበት ብዕሩን የሚያባልግ ጸሐፊ አይወጣም፤ ይህ ሁሉ ባልተሟላበት እንደኛ ባለ አገር ውስጥ ብዕርን ማባለግ እንደመብት ወይም እንደነጻነት እየታየ ነው፡፡

በአደባባይ የሚጽፉ ሰዎች ሁለት ነገሮችን ለይተው መገንዘብና ለሌሎችም ሲየያስተላልፉ ለይተው ማስተላለፍ አለባቸው፤ አንዱ የሆነና የተረጋገጠ ሁነት ነው፤ይህንን ሳይበርዙና ሳይከልሱ እንዳለና እንደተገኘ ማስተላለፍ ግዴታ ነው፤ ሁለተኛው የራስ አስተያየት ነው፤ የጠራውንና የነጣውን አውነት ከጎደፈ የግል አስተያየት ጋር አጋብቶ ማቅረብ ወይ አለማወቅ ነው፤ አውቀው ከሆነም ለማታለል ከመሞከር የሚቆጠር ነው፤ በአለንበት ዘመን አብዛኛውን ጊዜ የምናየው ፊደሎቹን ማወቅ እንደሙሉ እውቀት ይቆጠራል፤ ወይም በሌላ አነጋገር ፊደልን ማወቅ የመጻፍ ችሎታን ይሆናል፤ ይህ ትልቅ ስሕተት ነው፤ ፊደሎችን ማወቅ ትልቅና መሠረታዊ የእውቀት ጎዳና ላይ መግባት ነው፤ ጎዳናው ግን በጣም ረጅም ነው፤ በእውቀት ጎዳና ላይ መግባት የእውቀት ባለቤት ከመሆን ጋር እንዳይደባለቅ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በአገራችን ፊደልን ማወቅ ሌላም አደጋ አለው፤ ፊደልን ማወቅ ከሥልጣን ጋር ሲጋባ የሚያስከትለውን ውድቀት ከአንዴም ሁለቴ አይተናል፤ እያየንም ነው፤ ስለዚህም ፊደል ኃላፊነትን ያመጣል፤ አለዚያ በአለፉት ሠላሳ ዓመታት ያየነው ውድቀት እየተከበረ ይቀጥላል፡፡

መጻፍ እንደመናገር ሊቆጠር ይቻላል፤ሆኖም በመጻፍና በመናገር መሀከል ትልቅ ልዩነት አለ፤ በንግግር ላይ ከሰዎች በሚቀርበው ጥያቄም ሆነ ተቃውሞ እንዲህ ማለቴ ነው ብሎ የተናገሩትን እዚያው ለማረምና ለማስተካከል ይቻላል፤ በተጻፈ ነገር ላይ እንዲህ ዓይነቱ ወዲያው የመታረም ዕድል የለም፤ ስለዚህም ለመጻፍ በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ማለት ነው፤ ከላይ እንደተገለጸው ፊደልና ሥልጣን ሲጋቡ ሰንደቅ ዓላማው ጨርቅ ነው ከማለትም ሊያልፍ ይችላል፤ ለምሳሌ የደርግን የትርፍ ቤቶች አዋጅ ብንመለከተው ‹‹ትርፍ ቤት›› ሲል ትርፍን እንተወውና ‹‹ቤት›› ለሚለው ትክክለኛ ትርጉም አልሰጠም፤ ስለዚህም በጭራሮ የተያያዘ ምንም ‹‹ቤት›› የሚያሰኘው (መኝታ ቤት፣ ወጥ ቤት፣ መታጠቢያ ቤት፣ … የሌለው) በሃምሳ ሳንቲም የሚከራይ ነገር ‹‹ቤት›› ተብሎ በሺህ ብር ከሚከራይ ቤት ጋር ተወረሰ! ያፈረ የለም እንጂ አሳፋሪ ነው!

እንዲህ ዓይነቱ ችግር ከየት የሚመጣ ነው? አንድ አጠቃላይ የአስተሳሰብ ችግር አለ፤ ለየት ያለውን ከጅምላው፣ ግዙፉን ከረቂቁ፣ አንዱን ከብዙው ያለጥንቃቄ ማደባለቅ በአማርኛ በጣም የተለመደ እየሆነ ነው፤ የአስተሳሰብ ችግር ነው፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ (አበሻና ሆድ የሚለው ጽሑፍ ባሕር ተሻግሮ የአበሻን ነገር-ዓለም ትቶ የተጠበሰ ውሻ (ሆት ዶግ) የሚበላውንም አስቀየመውና ሌሎች ስለአበሻ የጻፍኋቸውን ተውኩት እንጂ አበሻና መናገር የሚለው በተለይ ለባሕር ማዶው ዘሎ-ጥልቅ ተስማሚው ነበር፤) በማናቸውም ነገር ላይ ለመቀባጠር በጣም ኃይለኛ ምኞት አለው፤ አንዱ ያስተሳሰብ ችግር ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፤ ሳያስቡና ሳይጨነቁ አፍ እንዳመጣ ከመናገር ልማድ ጋር የተያያዘ ነው፤ አሁን ደግሞ የጎሠኛነት ሥርዓት ካመጣብን ጣጣ ዋኖቹ የአስተሳሰብ ችግሮች እነዚህ ናቸው፤ የቡድን መብትን መሠረታዊ አድርጎ የግለሰብን መብት ጨፍልቆ የተነሣው የወያኔ የጎሣ ሥርዓት ከሃያ ዓመታት በኋላ በስንት ጥረት የደረሰበት አሁንም የተዛባ ድምዳሜ የቡድን መብትንና የግለሰብ መብትን ጎን ለጎን አቁሞ እኩል ናቸው ማለትን ነው፤ ለውጡ የተጣራ ባይሆንም ሃያ ዓመታት መፍጀቱ የወያኔን የመማር ፍጥነት የሚያመለክት ነው፤ የሥልጣን ጉልበትና የሥልጣን ምኞት ተጽእኖ እንደአንድነት ያለውንም የፖሊቲካ ፓርቲ ፐሮግራሙን እንዲለውጥና የግለሰቦችንና የቡድን መብቶች በአንድ ደረጃ ላይ እንዲያስቀምጥ ተደርጎአል፤ ከቡድን ውስጥ ግለሰቦች ሁሉ ሙልጭ ብለው ሲወጡ ስለቡድን መብት የሚያወራ ምን እንደሚባል እንጃ! ከቀኝ ወደግራ የዞረ? ወይስ ከግራ ወደቀኝ? ወይስ … ቀኝ ፖሊቲካ ባዶ ከረጢት ይዞ ይቀራል።

በተደጋጋሚ እንዳየሁት ለግለሰብ መብቶች የቆመ ቀኝ-ዘመም፣ ለቡድን መብቶች የቆመ ግራ-ዘመም የሚባል ይመስላል ይህ ስሕተት ነው።

ቀደም ሲል የታወቀው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ እኔን ቀኝ-ዘመም እያለ ጽፎ ሳይ ይህ ሰው በአውነት አንድ መዝገበ ቃላት ማየት አቅቶት ነው? ወይስ እኔን በተለየ ዓይን ለማየት ከመፈለግ የተነሣ ነው? ወይስ የሲአይኤውን መልክተኛ ፖል ሄንዜን ሰምቶ ነው? የሱ ጎሣ አባል መሆንንና አለመሆንን እኔ የምመርጠውና የምወስነው አይደለም፤ ታምራት በኢትዮጵያዊነት ወይም በዜግነት ዓይን ሊመለከተኝ አለመቻሉም የእኔ ጥፋት አይደለም፤ ሁሉም ቢቀር በሰውነት ደረጃ ሊያየኝ ይችል ነበር፤ ይህንንም አልቻለም፤ እንግዲህ ወይ እኔ ሰው አልሆንኩለትም፤ ወይ እሱ ወደሰውነት ደረጃ አልደረሰም፤ በታምራት ነገራ ቀኝ-ግራ መጋባት እንደኔው ጥርጣሬ ውስጥ ገብቶ የነበረው ክፍሉ ሁሴን ወደጥናት ተመልሶ የታምራትን ስሕተት አረጋገጠ፤ እኔም እንዲሁ አደረግሁና የታምራት ነገራን ግራ መጋባት አረጋገጥሁ፤ ታምራት ነገራ የጎሣ ቀኝ ገብቶት ግራ ፖሊቲካ ቀኝ ሆኖበታል! ቀኝ-ግራ ፖሊቲካ በጎሣ አባልነት የሚገኝ ወይም የሚታጣ ይመስለዋል፤ ዘር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ሀብትና ሌላ ማናቸውንም ነገር ከቁም-ነገር ሳይቆጥሩ ለማንም ሰው በሰውነቱ ብቻ ማግኘት የሚገባውን መብት እንዲያገኝ ቆሞ መከራከር ለታምራት እንግዳ ነገር ይመስለኛል፤ ገና እሱ ሳይወለድ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቲያትር በተደረገ ስብሰባ ላይ ለምን የኢትዮጵያ ራድዮ በኦሮምኛ አይናገርም? በማለት ጌታቸው ኃይሌ ጋር ሆነን የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሰዎችን ሞግተን ነበር፤ ይህ ለታምራት የቀኝ ፖሊቲካ ነው፤ የሱ ጎሣ-ዘመም ፖሊቲካ ግራ መሆኑ ነው! ጎሠኛነት ምን ጊዜም የትም ቦታ እንደግራ ፖሊቲካ ተፈርጆ አያውቅም።

አሁን ደግሞ ሰሎሞን አብርሃም ይህንኑ የታምራት ነገራን ስሕተት ለመድገም የዳዳው ስለመሰለኝ በዝምታ ለማለፍ አልፈለግሁም፤ ሰሎሞን (liberalism) የሚለውን የአንግሊዝኛ ቃል በባሕርዩ የሌለበትን ትርጉም ሊሰጠው ይዳዳዋል፤ ሰሎሞን አብርሃም ሊጽፍበት የተነሣው ጉዳይ በእኔ ግምት በጣም ወቅታዊና አስፈላጊ ነው፤ ነገር ግን የግል ስሜትን ከሁነት ጋር፣ ያልተጣራ የተውሶ ሀሳብን (‹‹ፊዩዳሊዝም፣ ሊበራሊዝም››…) ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር በማያያዝ አስተሳሰቡን ያጎደፈው ይመስለኛል፤ ያነሣው ጉዳይ በተለይም እንደሱ ላለ ፖሊቲከኛ ከስሜተኛነትና ከወገንተኛነት የጸዳ ቢያደርገው (‹‹ወግ አጥባቂ፣ቀኝ አክራሪ›› ..)፣ወይም ደግሞ ያልተጣራ (‹‹የሊበራል ዴሞክራሲን ርዕዮተ ዓለም የሚከተሉ ይመስላሉ፤›› እያለ በጎን ከሚጎሽም የጸዳውን እውነት ፊት ለፊት እያቀረበ ድካማቸውን ቢተነትን የሚጠቅም ይሆን ነበር።

ግራና ቀኝ ፖሊቲካ የሚባለውን ከጎሣ ፖሊቲካ ጋር ለማገናኘት የሚፈልጉ ሰዎች ወጣቶችን ወደአስከፊ ስሕተት እንዳይመሩ መጠንቀቅ ያለባቸው ይመስለኛል፤ የጎሣ ሥርዓትን የሚቃወሙትን ወገኖች በሌላ መንገድ ለመቋቋም ቢሞክሩ የተሻለ ነው፤ በጎሣ ክፍፍል ማመን ሌላው ቀርቶ በሰውነት ደረጃ ለመሰለፍም ያስቸግራል፤ ለማናቸውም የጎሣ ፖሊቲካን ከግራ ፖሊቲካ ማዛመዱ እሳትና ውሀ ነው።


ምርጫ እና የስርዓት ለውጥ

$
0
0

ሙሉጌታ አሻግሬ
mulugetaashagre@yahoo.com

አገራት ዘመናዊ የተባለውን የመንግስት አስተዳደር መተግበር ከጀመሩበት ግዜ አንስቶ እስከዚህኛው ዘመን ድረስ የተለያዩ የመንግስት አወቃቀርና ርዕዮተ ዓለም ተስተናግደዋል። ሰዎች መለኮታዊ እምነታቸውን ወደጎን አድርገው ከማኦ እስከ ማርክስ ከሌኒን እስከ ካስትሮ ‘ማርክሲዝም ያነበቡና የተገበሩ ብፁዓን ናቸው’ ብለው የችግርን ጥግ እስኪገነዘቡ ድረስ ነጉደዋል። ዓለማችን በሶሻሊዝም ስትናጥ፤ ኮምኒዝምም የዓለማችንን ህዝቦች ሁሉ እኩል አደርጋለሁ ብሎ በተነሳ ሰባ ምናምን ዕድሜው ተንኮታኩቷል። ምዕራባውያን ምስራቆችን በኢኮኖሚ ብልጫ ማርከዋቸዋል። የምስራቅ አውሮፓ አገራት ከምዕራብያውያኑ በኢኮኖሚ አቅማቸው እጅግ ዘቅጠው ተገኝተዋል።
election
ይሁን እንጂ አሁንም የዚህ ርዕዮተዓለም አራማጆች በአንድ ወይም በሌላ መልኩ እዚህም እዚያም ይታያሉ። የቻይናው ዘመናዊ ‘ልማታዊ መንግስት’ አወቃቀር ለዚህ አባባል አንዱ ማሳያ ነው። አሁን በአገራችን ያለው መንግስት ትላልቆቹ ‘ተሰሚ’ ባለስልጣናት የማሌሊት ደቀመዛሙርት ነበሩ። አሁንም በውስጣቸ እንደዛው ሊሆኑ ይችላሉ…ማን ያውቃል። ለዚህም ይሆናል ኢትዮጵያ የቻይናን ጠረን እየያዘች የመጣችው። የቻይና አካሄድ የአፍሪካ አምባገነን ባለስልጣናትን በወንበራቸው ለማቆየት ፍቱን መንገድ ነው። “ከዳቦ በኋላ ዲሞክራሲ”። አጭር እና ግልጽ አምባገነናዊ አካሄድ። ስለዚህ የመጨረሻው ሰው ዳቦ እስኪያገኝ ድረስ ዴሞክራሲ አላስፈላጊ ትሆናለች። ይህች አካሄድ በአገራችን መንግስት ይፋ ዕውቅና የተሰጣት ግዜ… አዲዮስ መድብለ ፓርቲ ስርዓት በኢትዮጵያ።

በሌላ በኩል ‘ ዲሞክራሲ ዘመናዊነት ነው’ ብለው የተነሱት ምዕራባውያን፤ ሃሳብን የመግለፅና የመንግስትን በህዝቦች በጎ ፍቃድ የመመረጥ ሁኔታን ጠቅልለው ለህዝባቸው በመስጠት ህዝቡ የዚህ ዕድል (መብት) ተጠቃሚ እንዲሆን አድርገውታል። ይሁን እንጂ እንደ ኮሚኒስቶቹ የጎላ የኢኮኖሚ ችግር ባይታይም በዲሞክራቶች በኩልም የኢኮኖሚው ሁኔታ ኮለል ብሎ እየፈሰሰ ነበር ለማለት ያስቸግራል። ዓለማችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተዘፈቀችበት የኢኮኖሚ መውሸልሸል ምክንያትም ሃብት በተወሰኑ ቡድኖች እጅ እየተጠቀለለች መግባቷና የመንግስታት (የመስተዳድሩ) ኢኮኖሚውን የመቆጣጠር አቅም መልፈስፈስ ውጤት ነው የሚሉ ወገኖች አሉ። ይህ አስተያየት ትክክል ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም ስርዓቱ ሃብትን ማዕከል በማድረግ ስለተገነባ ኢኮኖሚው ጡንቻ አውጥቶ የመንግስታትን የመወሰን አቅም ሲፈታተነው ታይቷል።

ከዚህ በተቃራኒ ጠንካራ ኢኮኖሚ በራሱ አገራትን እንደ አገር ሊያቆም እንደሚችል በተለያዩ አገራት በተከሰቱ ሁኔታዎች ታዝበናል። ከጥቂት ዓመታት በፊት ቤልጄየም ያለመንግስት ከአንድ ዓመት በላይ ቆይታለች። በዚህ ግዜ ውስጥ ሁሉ ይህ ነው የሚባል ችግር ሳይከሰት ዜጎች በነባር ህጎች ሲተዳደሩና ባለሃብቱም የታክስ ግዴታውን ሲወጣ ተስተውሏል። አንዳንድ ግለሰቦች የዚህ ውጤት ምክንያት የህግ የበላይነት በአገሩ በመስፈኑ ነው ብለው ቢከራከሩም የኢኮኖሚው ጥንካሬ በራሱ ትልቁ የወሳኝነት ድርሻ ነበረው። በእርግጥ የተዘረጋው አስተዳደራዊ ስርዓት(System) ጉልህ ድርሻ ነበረው። በኔዘርላንድም የተከሰተው ተመሳሳይ ሁኔታ ነበር። የመንግስት ካቢኔ አባላት ተኮራርፈው ምክር ቤታቸውን ከአንዴም ሁለቴ ዘግተው ፓርላማውን የልጆች እቃ እቃ ጨዋታ ባስመሰሉበት ግዜ ሁሉ የአገሩ ዜጎች ይህ ትርምስ እና ጫጫታ ትዝ ሳይላቸው የዕለት ተዕለት ድርጊታቸውን ሲያከናውኑ ታይተዋል። ዲሞክራሲና ኢኮኖሚ ከተባበሩ አይቀር እንዲህ ነው።

ስለዚህ በአግባቡ የተገራ ኢኮኖሚ የዜጎችን ሰላምና አኗኗር ለማቃናት ብቻ ሳይሆን ለአገር ህልውናም የራሱ አስተዋፅኦ አለው ማለት ነው።

ወደ አገራችን ይህን ሁኔታ ስንወስደው ያለመታደል ሁኖ ኢትዮጵያ ባዶ እጇን እያጨበጨበች ትገኛለች። ኢኮኖሚው የለ፣ ዲሞክራሲው የለ።

ኢትዮጵያችን ከተገነባችበት የነፃነትና የተጋድሎ ታሪክ ባሻገር ነፃነታችን ዳቦ እንዲሆንና አገራችን ዘመናዊ የመንግስት አወቃቀር እንዲኖራት ሁሉም ቅን አሳቢ ዜጋ ይመኛል። ዘመናዊነት ዘመናዊ ቁሶችን መጠቀምና ዘመን አመጣሽ ሁኔታዎችን መከተል ብቻ አይደለም። ዘመናዊነት ማለት መግባባት፤ ዘመናዊነት ማለት መቻቻል፤ ዘመናዊነት ማለት እርስ በእርስ መቀባበል፤ ዘመናዊነት ማለት ሃሳብን የመግለጽ ሁኔታ መመቻቸት፤ ዘመናዊነት ማለት የሕግ የበላይነት፤ ዘመናዊነት ማለት ህዝቦች በመረጡትና በፈቀዱት አካል መወከልና አገር እንድተዳደር ማድረግ ነው። በዚህ ዓለምአቀፋዊ የኢኮኖሚና ማህበረሰባዊ ትስስር (Globalization) ስርዓት ውስጥ ለመኖር የሌሎችን በጎ ልምድ መውሰዱ ብልህነት ነው። ካልሆነ ግን ያለንበትን ደረጃ አሻሽለን ቁልቁል እናድጋለን። ስለዚህ በአንጻራዊ ሁኔታም ቢሆን የተሻሉ የሚባሉትን አገራት የኢኮኖሚና መንግስት አስተዳደር ስርዓት ከኢትዮጵያ ባህልና አኗኗር ጋር አስታርቆ መተግበሩ እጅግ አስፈላጊ ነው።

አገራችን ንጉሣዊ ስርዓትን በሰፊው አስተናግዳለች። ከዚያም ሶሻሊዝምን ብሎም ያለፈው ስርዓት ዕድሜ ጥንፋፊ ላይ ቅይጥ ኢኮኖሚ ጭልጭል ብላ አልፋለች። በዚህኛውም መንግስት ‘ዲሞክራሲያዊ’ (እንዳትታዘቡኝ) ስርዓት እየተከተለች ነው።

በጄ!!! ዲሞክራሲውን ተቀብለን ስርዓቱን ለመገንባት ሰማይ እየቧጠጥን ይኼው ሃያ ሦስት ዓመት እንደምንም አለፈ። በ1997 አገር ጉድ ብሎ ፤ ህዝብ ተጨንቆ፤ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ልትወለድ የምጥ ሂደት ውስጥ ገባን። ዲሞክራሲ ለጥቂት እውን ሳትሆን ጨነገፈች። ‘ዲሞክራቶቹ’ መግደል ጀመሩ። ዲሞክራሲ ናፋቂዎች ታሰሩ፤ ተገደሉ። ሌሎች የሚዜ አገልግሎት ለመስጠት ፓርላማ ገቡ። ለአምስት ዓመት በዘለቀው የመሣቂያ መሣለቂያ ድራማ እንደ ችሎታቸው ተውነው፤ ህዝቡ ዲሞክራሲ ይዘውልን ይመጣሉ ብሎ ደጅ ደጁን እያየ ሲጠብቅ ከፓርላማ ተሰናበቱ። አራት ነጥብ።
ቀጠለች አብዮታዊ ዴሞክራሲ። ምረጡ አስመርጡ ። ሃሳባችሁን ስጡ ተናገሩ ተባለ። እጅግ የተሳካ ምርጫ ተደርጎ ታሪካዊዋ አብዮታዊ ዲሞክራሲ 99.96% የፓርላማ ወንበር አግኝታ ኑሮ ቀጠለ።

አሁንም በቅርቡ ምርጫ አለ። ህዝቡ ጥያቄ አለው፤ ነፃነትና ፍትህ። ልማትና ዕድገት። እኩልነትና ሰላም። ይኽን ጥያቄ እንመልሳለን ያሉት ሰላማዊ የትግል ስልት የሚከተሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ጓዛቸውን እየሸከፉ ነው። በምርጫ ሊወዳደሩ። መንግስትም የ ’ ይቻላል’ አረንጓዴ መብራት አሳይቷቸዋል። ለእነዚህ ድርጅቶች ጥያቄው የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው።

የመጀመርያው ጥያቄ፣ የመጪው ምርጫ ዓላማ ምንድን ነው?

ህዝቡ የአጃቢነት ስራ የሚሰሩ ግለሰቦችን በፓርላማ ማየት አይፈልግም። ፓርላማ ገብቶ የአምስት ዓመት የስራ ኮንትራት የሚፈልግ የሰላማዊ ትግል አራማጅ አባል ካለ፤ በህዝቡ ስም ከመነገድ በየትኛውም የመንግስት ይሁን ሌላ ድርጅት መቀጠር ቢሞክር መልካም ነው። ለፓርላማ የሚደረገው ሩጫ ውጤት ለህዝቡ የሚታይና የሚጨበጥ ለውጥ ማምጣት አለበት። ካለፉት የፓርላማ ኳኳታዎች እንደታዘብነው፤ ድምፀ ተዓቅቦ በማድረግ ይሁን ድጋፍ ባለመስጠት አንዲት ነገር ስትለወጥ አሊያም ስትስተካከል አላየንም። ለውጥ ለማምጣት ደግሞ ፓርላማ ገብቶ በቃላት ጉሽሚያ የነፃ ትግል ማድረግ የትም እንደማያደርስ በደማቁ አይተነዋል።

የመንግስትን ኪሳራነትና ድክመት ዲያስፖራው ሳይቀባባና ሳይፈራ እንደ ጉድ ያጎነዋል። “የተከበሩ” “ክቡርነትዎ” ምናምን ሳይል አካፋን አካፋ ይለዋል። ጉድለትን መናገር ለውጥ የሚያመጣ ቢሆን፤ የህዝቡን ጥያቄ እያሽጎደጎደ በየዕለቱ በሚጮኽው ዲያስፖራ ብቻ ኢትዮጵያ ውስጥ ከዛሬ ስንት ዓመት በፊት ዲሞክራሲ በነገሰች። የመንግስት ተቃዋሚ ነን የሚሉት ፓርላማ ቁጭ ብለው የሚያሽሞነሙኑትን ጥያቄ ገዥው መንግስት እጅግ ቀድሞ ከዲያስፖራው እርቃኑን ይነገረዋል። ስለዚህ ይህ ችግር “በክቡርነትዎ ታጅቦ ሲቀርብ የፓርላማው ስራ እንደተለመደው የፕሮቶኮል አገልግሎት ይሆናል ማለት ነው። የፓርላማ መግባት ዋነኛ ግብ በስማ በለው “የተከበሩ” ለማለት ሳይሆን የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ብቻ ነው። የህዝቡ ጥያቄ ምላሽ ደግሞ በተግባር መሆን አለበት። ዳቦ እና ነፃነት ከቃላትነት ወርደው የሚዳሰሱ መሆን አለባቸው። የመንግስትን አሰራር አቃቂር በማውጣትና በቃላት መጎንተል ዳቦ አልሆነም። የህሊና እስረኞችንም ነፃ አላወጣም። በዚህ ሂደት ውስጥ አንድም ግዜ ቢሆን ገዥው መንግስት ለማከናወን ያቀደው ተግባር ተከልሶ አሊያም ተሰርዞ አያውቅም።

ስለዚህ። ስለዚህ ህዝቡ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ለውጥ የሚመጣው ደግሞ በ50+ የፓርላማ ጨዋታ ብቻ ነው። ይህን በኢትዮጵያ ፓርላማ ስንተረጉመው በፓርላማው ካሉት 547 መቀመጫዎች ቢያንስ 274 መቀመጫዎች (ሁሉም ተመራጮች አምስቱን ዓመት በሰላም ካጠናቀቁ) ያስፈልጋል። በመሆኑም የሰላማዊ ትግል አቀንቃኞች ይህን ያህል መቀመጫ ማግኘት ግድ ይሆንባቸዋል። የወንበሯ ቁጥር ከዚህ ዝቅ ካለች የተለመደው አጃቢነት በመሳቂያ መሣለቂያነት ይቀጥላል። ስለዚህ አጃቢነት መብቃት አለበት።
ሁለተኛው ጥያቄ፣ የሰላማዊ ትግል ሰልፈኞች ድል ለማድረግ ምን ያህል ዝግጁ ናቸው?

የፓርቲዎቻችንና ድርጅቶች ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ናት። ሁሉም ሰላማውያን የሰፈሩት ከከተሜው ጋር ነው። አገሪቱ ደግሞ 85% ህዝብ አለኝ የምትለው ከከተማው ውጭ ነው። ስለዚህ የፓርላማው ወንበር ያለው ከተማ ላይ አይደለም። ወንበር ከድሃው ገበሬ ጋር ነው ያለችው። ከህዝቡ የወንበር አደራ ለመቀበል መታመን ያስፈልጋል። ህዝባችንስ ደግሞ ለማያውቀው ሰው እንዴት ወንበሩን በአደራ ይሰጣል ? ለዚያውም ለአምስት ዓመት። ስለዚህ እንሂድ ፤ እንውረድ። የደፈረሰውን ጠጥተን፤ ጢስ አይናችንን እየወጋን የድሃውን ወገን ክፉ እና ደግ እንካፈል። የሃዘን እንጉርጉሮውን ቅኔ እንፍታ።
የእኛ ነጭ ሸሚዝ በከረቫት መታነቁ በጠኔ ለሚመታው፤ በበሽታ ለሚማቅቀው፤ ለታረዘው ላልተማረው ወገን ምኑም አይደለም። ምናልባት የበላይነታችንን ለማሳየት ካልተጠቀምንበት በስተቀር። ነገርግን አገሪቷን እንደ አገር ለማቆም ደም እና ላቡን ለማፍሰስ የማይሰለቸው ወገን የእኛ ነጭ መልበስና ማማር መሠረት ነው። አገር ስትወረር ደሙን የሚያፈስ ድሃው ገበሬ ነው። ሃገርህ አይደለም ተብሎ የሚፈናቀለው ይሄው ወገን ነው። ረሃብና ድርቅ ሲመታው የሚረግፈው ይሄው ድሃ ዜጋ ነው። እኛ ነጭ ከሻኛ እያማረጥን እንድንበላ አፈር ምሶ አፈር ሆኖ የሚለፋው ይህ ድሃ ገበሬ ነው። ስለዚህ እሱን ሳንይዝ ሰላማዊ ታጋዮች ሆነን ከተማ ውስጥ ተሞሽረን በአምስት ዓመት ውስጥ ሁለት ቀን ሄደን ምረጠን ስንለው ይታዘበናል። መቼም ቋንቋውን ስለምንናገር፤ ብንወዛም መልኩን ስለምንመስል የአንድ አገር ህዝብ እንደሆንን ከመገመት ውጭ ችግሬን ይገነዘባሉ ፤ መፍትሄ ያመጣሉ ብሎ አያምንም። ህዝባችን እንዲያውቀን አብዛኛው ኑሯችን ከእሱው ጋር ይሁን።

ፓርቲዎችና ድርጅቶች በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት እንዳላቸው ይናገራሉ። የእነዚህ ጽህፈት ቤቶች ስራ ምን እንደሆነና ምን እንደሰሩ የሚያሳይ ሪፖርት ለህዝብ የቀረበበት ግዜ የለም። አንዳንዶቹ በራቸው በወር አንዴ ይከፈት ይሆናል። የበዙት ደግሞ የሸረሪት ትዕይንት ማሳያ ሆነው ይከርማሉ። የተወሰኑት ደግሞ የፊት በሩ ተቆልፎ በስተጀርባው የግለሰብ መኖሪያም እንደሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ምን እየሰራን ነው የህዝቡን ጥያቄ እንመልሳለን የምንለው? በቃ ከታገልን የእውነት እናድርገው። ከተማ ላይ ተከማችተን በፓርላማ ናፍቆት ከምንቆዝም ፤ ህዝቡን ተጠግተን ኑሮውን እንኑር።

ስለዚህ የፓርላማ ወንበር የምታልሙ ድርጅቶች ተባብራችሁም፤ ተዛዝላችሁም ቢያንስ 274 ወንበር ማምጣት አለባችሁ። ሰሞኑን እንደተሰማው ከሆነ አዳዲስ ድርጅቶች ልምድ ለማግኘት እንዲችሉ ፓርላማ ቢገቡ የተሻለ ነው የሚል አንዲት ቀልድ ተለቃለች። የምን ልምድ እንደሆነ ግልፅ አይደለም። የፓርላማ ወንበር ምን ያህል እንደሚመች? አፈጉባዔው ስንት ግዜ እንደሚያስፈራራና መነጋገሪያውን ስንት ግዜ እንደሚያጠፋብን? ወይስ የፓርላማው በር ላይ ጫማ እና ቀበቶ እያወለቁ የሚደረገው ቅጥ አንባሩ የጠፋውን ፍተሻ መለማመድ?
የኢትዮጵያ ህዝብ ሲጀመር ሰው ነው። ከዚያም የአገሩ ዜጋ። መለማመጃ አይደለም። ስለዚህ ለፓርላማ እንሮጣለን የምትሉ ወገኖች የተለመደውን የሚዜ አገልግሎት ላለመስጠት እርግጠኞች መሆን ያስፈልጋችኋል። ከዚህ በዘለለ ፓርላማ በመግባት በገዥው ስርዓት የሚዘጋጀውን ድራማ በአጃቢ ተወናይነት በመተወን የምታተርፉት መሳቂያና መሳለቂያ መሆን ብቻ ሳይሆን የህዝቡንም ችግር ለአምስት ዓመት ማራዘም ነው። በጥልቀት አስቡበት።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ክህደት ከአናት ሲጀምር:- በቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ

$
0
0

እውነት ቤት ሥትሰራ …
ውሸት ላግዝ ካለች
ሚስማር ካቀበለች
ጭቃ ካራገጠች
ቤቱም አልተሰራ … እውነትም አልኖረች ።
… እንደዚያ ነው በባቢሎን ዘመን ።

የአንዱ ቋንቋ ከአንደኛው ይዘበራረቃል ….. መግባባትና መረዳዳት ብርቅ ይሆናል ። በጠራ አማርኛ የተጣፈውን በጉግማንጉግኛ በመተርጐም ከውስጡ የሚፈልጉትን ብቻ አለፍ አለፍ እያሉ ያነቡታል ። እናም የራሳቸውን ትርጉም ይሰጡታል ። ፍየል ወድያ ….. ቅዝምዝምም ወዲህ ይሆናል ።
ከቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት መካከል ጥቂት አዛውንቶች ታሪክን ደልዘው በወያኒኛ አዲስ ታሪክ ስለ አየር ኃይሉ እንዲፅፉ በህውሃት እየተጠየቁ ነው ። እነዚህ ባለ ብዙ አኩሪ ታሪክ ባለቤት አዛውንቶች መንታ መንገድ ላይ ቆመዋል ። በዓለም ዙርያ ተበትነው ያሉት የቀድሞው አየር ኃይል አባላት ሃሳባቸውን እንዲደግፉና የእርዳታ እጃቸውንም እንዲዘረጉ ለማግባባት እየሞከሩ ነው ። እኛም የቀድሞው የአየር ኃይል አባላት እንዲህ አልን ……….
ethiopian airforce
“ የአየር ኃይልን ታሪክ ለትውልድ ለማስቀረት የምታደርጉት ጥረት በጐና የሚደገፍ ምግባር ነው በርቱ ፤ ነገር ግን የገዢው ፓርቲ ሞግዚትነት አያስፈልጋችሁም ። በተጨማሪም በተፅዕኖ ስር ሆናችሁ ሚዛናዊነት የሚጐድለውና የተደለዘ ታሪክ ለትውልድ እንዳታቆዩ ሥጋት ቢጤ አለችን ።
(ያም ቢሆን መፅሃፉን ካነበብን በኋላ የምንታዘበው ይሆናል … አያጣላም ።) የአየር ኃይል ቬተራን አሶሴሽንን እናቋቁማለን የምትሉትን በተመለከተ ግን ወራጅ አለ ። እጅግ ከስጋት በላይ የሆኑ ጥያቄዎች አሉን ። “ የቀድሞው አየር ኃይል ቬተራን አሶሴሽን ” እያላችሁን ከሆነ ግን እንግባባለን ።
የሚለውን ጥቅል ሃሳብ በመልዕክታችን ብንሰድላቸው በጉግማንጉግኛ በመተርጐም እኛ ፖለቲካ አንነካካም …. ፖለቲካንና ኰረንቲን በሩቁ ነው ብለናል ይሉናል ከአዲስ አባ ደብዳቤ እየፃፉ ። እነሱ ለካ የአሁኑን የህውሃትን መንደርተኛ አየር ኃይል ነው ቬተራን እያሉ የሚያንቆለጳጵሱት ። በህውሃት ሰማይ ስር ጉድ ሳይሰማ አያድርም አይደል !

እኛ ድፍን የአየር ኃይል ተቋም ላይ ስለተፈፀመ ክህደት ስናወራ …. እነሱ አንድ ግለሰብ አገርንና ህዝብን ለከዳ ስርዓት ስለሚመሰርተው ዕድርና የተዝካር ግርግር ሊያስረዱን ይሞክራሉ ። እኛ እኰ የቆማችሁበት አፈር ሥር ነፍሱ ያልወጣች የምታጣጥር የገዛ ጓደኛችሁ ነፍስ አለች ነው የምንላቸው ።
መጀመሪያ ባለንጀራችሁን ነፃ አውጡት ፤ እናንተም በጐን በሾርኔ ሳይሆን በአደባባይ በህግ ነፃ ውጡ ምክንያቱም እንደ ዶሮዋ ገመዳችሁ ረዘመላችሁ እንጂ ፈፅሞ አልተለቀቃችሁም እያልን ነው ።

ህውሃት እንደሆነ በሰው ተጠቅሞና አዋርዶ እንደሚያባርር የአደባባይ ሚስጢር ነው ። ደግሞም ይህ ይጠፋችኋል ብለን አንሞግትም ፤ ….. የመሰንበት ጉጉት ህሊናን ፈፅሞ ካልተቆጣጠረ በቀር ። አየር ኃይል ለአገር አንድነት የተፋለመ ጀግና እንጂ ጨፍጫፊ ያለመሆኑን በአደባባይ ስትመሰክሩና በህግ
ስታስነግሩ ….. የአየር ኃይል ተቋም እንደ ተቋም ነፃ ሲወጣ …. እርቅ ሲወርድ ፣ አገርን ከጠላት በመከላከላቸው ብቻ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኞች በአደባባይ ነፃ ሲወጡ …. ያን ጊዜ ሁላችንም በአንድነት ነፃ እንወጣለን ። ያለበለዚያ ግን ትውልድም አገርም ላይ ይቅር የማይባል ክህደት ትፈፅማላችሁ እያልን ነው ያለነው ፤ በጠራ አገርኛ ቋንቋ ።

የቬተራን አሶሴሽንን በመወከል ያገባኛል ብለው ከአዲስ አበባ መልዕክት የሰደዱልን ሰው በፍፁም ሃሳባችንና ሥጋታችንን በትክክል የተገነዘቡ አይመስሉም ወይንም ዛሬ ኢትዮጵያ በምትባለው አገር ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የሚከታተሉም መሆናቸውን እንድንጠራጠር እያደረገን ነው ። ድንገት ዘንድሮ ጆሮዋቸውም ዓይናቸውም የተከፈተላቸው ይመስል በቃል ያጠኑትንና ስለ አየር ኃይሉ የሚገምቱትን በጐ ፍላጐት ለመተግበር የተነሱ ይመስላል ።

የህውሃት አስተዳደር አዛውንት የአየር ኃይሉን አባላት በማምሻ እድሜያቸው ታሪክን ደልዘው የእራሱን የተንጋደደና የተንሸዋረረ ታሪክ እንዲፅፉለት እየተጠቀመባቸውና ከጠራ ታሪካቸው አንስቶ ከራሱ ቆሻሻና ስውር ፍላጐት ሥር እያንደባልላቸው ያለ ይመስላል ። አየር ኃይሉ በአዋጅ ሙሉ ለሙሉ ከስራ ውጪ በተደረገበት ዘመን ላይ ፤ ጨፍጫፊ ተብሎም ቅፅል ስም ወጥቶለት ወደ ከርቸሌ መጋዙንና በመንደርተኛ ፓይለቶች እየተተካ መሆነኑን ትንፍሽ እንዳይሉ በዚሁ በምሽት እድሜያቸው እየተደለሉ ናቸው ። እንዲያውም ሙዝየም እስከ መክፈት የዘለቀ ህልምም እንዳላቸው እየጠቀሱ ነው ። አገር ቢኖረንማ ኖሮ ለትውልድ የሚቀር ፣ ታሪክን የሚዘክር ሙዝየም ማቆም እንዴት የተባረከ ህልም ነበር ? ነገር ግን አገርም ዜግነትም በተዋረዱበትና እድሜያቸውን ሙሉ ለአገር አገልግሎት ያበረከቱ አንጋፎች እንደ አሮጌ ቁና በውርደት እንዲኖሩ በአደባባይና በአዋጅ ባይበየን ኖሮ ፣ ትውልድም በበጐ መሰረት ላይ ቀጥሎ ቢሆን ኖሮ …. ሁሉም አላማ በጐና ለአገርም ሆነ ለትውልድ የሚጠቅሙ ይሆኑ ነበር ።

እንግዲያውስ እነዚህ በህውሃት እየተደለሉ ያሉት የአየር ኃይሉ ነባር አዛውንቶች እርማቸውን ያውጡ ። ህውሃት አገሪቷን ከተቆጣጠረ ወዲህ ያለውን አየር ኃይል ተብዬ እንጂ የቀድሞውን ታሪክ ምናምኒት አሻራ እንኳ አያገኙም ። አጠቃላይ ሰፈሩና ቢሮዎቹም ጭምር በአይጥ መንጋ እንደተመታ ባድማ ዶክመንቶች ተፈርፍረው ድምጥማጣቸው መጥፋቱን አይጠራጠሩ ። የአየር ኃይሉን የታሪክ አሻራ ሊያስረዱ የሚችሉ የተለያዩ አውሮፕላኖችን ማናምኒት ሳያስቀር አቧራቸውን እያራገፈ የህውሃቱ አበበ ተ/ኃይማኖት (ጆቤ) እዚህ ግባ በማይባል ዋጋ መቸብቸቡን እንዴት ሳይነግራቸው እንደቀረ ይገርመናል ? ይህ ቀበኛ ሽፍታ ለጌጥና ለታሪክ በአየር ኃይሉ ጠ/መምሪያ ፊት ለፊት እንኳ ተቀምጣ የነበረችውን ገብሬ ቦላሌን ሳይቀር አንጠፍጥፎ መሸጡን ለምን ደበቃቸው ? ታሪክ በመስራት አገራችንን ያስከበረችውን ኤፍ-5 አውሮፕላንንስ አንዲት ሳያስቀር መቸብቸቡንስ ?

በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር የሚመራውን የአሁኑን ሥርዓት አያውቁትም እንበል ወይስ የክፋትና የብቀላ ምግባሩን ሁሉ ትተው በጐ ተክለ ሰውነት ሊገነቡለት እየሞከሩ ይሆን ? ታዲያ ይህንን እየሰሩ እንዴት ፖለቲካ አንነካካም ይሉናል ? በእነርሱው አመራር ስር የተገነባው የአየር ኃይል ሰራዊት እኰ በጅምላ ጨፍጫፊና ወንጀለኛ ተብሎ እድሜውን ሙሉ ከአቀናው መስሪያ ቤት በውርደት ተባሮ ቤተሰቡ ተበትኖ በረሃብና በችጋር እንዲያልቅ ተፈርዶበታል ! እውነተኛዎቹ የአየር ኃይሉ አርበኞች ድፍን 22 ዓመታት ሙሉ ተሸማቀውና አንገታቸውን ደፍተው መሃል ደ/ዘ ውስጥ (በቀለ ሞላ ሆቴል ፊት ለፊት) በጠጠርና በቆርኪ ዳማና ቼዝ ሲጫወቱ የአዛውንቶቻችን መንግስት የት ነበር ? ለዚህ ሁሉ ግፍና በደል ተጠያቂው ማነው ? እነዚህንና ሌሎች በደሎችን እንዴት ነው የሚያስታርቁት ? በምንስ መመዘኛ ቀበኛ ሽፍታ የመሰረት ድንጋይ እንዲያነጥፍላቸው ያደርጋሉ …. ! ከረገጡት ምድር ስር
የባልንጀሮቻቸው የምትቃትት ነፍስ ምን ትላቸው ይሆን ? ፖለቲካ … ፖለቲካ …. ለምን እንደሚሉን አልገባንም ። ፖለቲካ ምንድነው ?

ለዘመነኖቹ የመንግስት ባለስልጣናት ማደር ? ለስብሰባ ሲጠሩ ፈጥኖ ሸገር ላይ መከሰት ? ወይስ ሲመሩት የነበረውን ሰራዊት አስማርኰና ክዶ ለትግራዩ የነፃነት (ተገንጣይ) ግንባር በፈቃደኝነት መገበር ? እኛ ፖለቲከኞች እያሉን የሚያበሻቅጡን ከአገር በግፍ ተገፍታሪ ስደተኞች በሰላም ተከባብረንና ተዛዝነን ድፍን 20 ዓመታትን እንዳሳለፍን በአለፈው የበጋ ወቅት በዋሽንግተን ከተማ ተገኝተው መታዘባቸውን እናውቃለን ። አየር ኃይል ማለት ለኛ መታወቂያችን ፣ ማንነታችንና ዜግነታችንም ጭምር ነው ። በህብረት ተደጋግፈን እንኖራለን ፤ የተቸገረን እንረዳለን ፣ የታመመን እናስታምማለን … እንጠይቃለን ፣ እስከወዲያኛው የሚሰናበተንንም በኃዘን እንሸኛለን ።

ጀግኖቻችንን ከተጣሉበት እያስታወስንና እያነሳን እናከብራቹኋለን እንላለን ። በየዓመቱም የአየር ኃይል ቀን በማለት በህብረት ዩኒፎርማችንን ለብሰን ባንዲራችንን ከፍ አድርገን እያውለበለብን ኢትዮጵያ ሃገሬን እንዘምራለን ….. ። ይህንን ባንዲራና ዝማሬ የአሁኑ መንግስት አይወደውም ። በዘር ከፋፍሎ እኛ እና እነርሱ ፣ የቀድሞውና የአሁኑ ፣ ጨፍጫፊና ዲሞክራቲክ በማለት እየለያየ አጥፍቶናል ። አሁን ደግሞ እዚሁ ያለንበት አገር ድረስ ክንዱን እያረዘመ መካከላችን ሊገባ እየተቅበዘበዘ እንደሆነ ይገባናል ። እባካችሁን አዛውንቶቻችን ለዚህ መንደርተኛ ስርዓት ክርንና ጅማት እየሆናችሁ ህውሃት ጣቱን እቤታችን ድረስ እንዲያረዝም እየረዳችሁ መካከላችን እንዲገባ አታድርጉ ፤ በማህበራችንም በኩል አትምጡ ።

በግል እኰ መፅሃፍ አይደለም ኤግዚቢሽንም መክፈት ትችላላችሁ ። አሁን እየመጣችሁበት ያለው መንገድ ግን የሁሉንም ምክር ፣ የብዙሃንን ይሁኝታ ይጠይቃል ። እናንተ ደግሞ እዚያው አገር ቤት ያሉትን እውነተኞቹን አርበኞች አንድ በአንድ ሲያልቁ ጠብቃችሁ ፣ በህይወት የተረፉትንም ንቃችሁና ገፍትራችሁ ቀበኛ የሃገር ጠላት የሆኑትን ቱባ የህውሃት ባለስልጣናትን በጀርባችሁ አዝለችሁ አትላንቲክን በማቆራረጥ ልታነታርኩን ትሞክራላችሁ። ለምን ድምፃችሁን አጥፍታችሁ ታሪክ መፃፍም ሆነ ዕድር ማቋቋም አልመረጣችሁም ? በማህበራችን በኩል ለመምጣት ለምን መረጣችሁ …. ? በብዙሃን ስደተኛና በውርደት ተባራሪ ስም በየሸራተኑ ከበሮ መደለቁንስ ምን አመጣው ?

እንግዲያውስ ለሁለተኛ ጊዜ ምክር እንለግስ ……….
ሰው ባለቀ እድሜው ላይ ለኑዛዜ ይመቻቻል ….. እውነትን ተናግሬ ካልሞትኩ ብሎ ከህሊናው ጋር ትንቅንቅና እልክ ይጋባል ….. እውነቱን አፍርጦ በመሸበት ያድራል … እንጂ ለዳግም ምርኰ እራሱን አሳልፎ አይሰጥም ። በዚህ እድሜ እኰ ግጥም ብሎ ከሞላ የውስኪ ባንኰኒ ላይ የምንጭ ውሃ ካልሆነ ንክች አላደርግም .. ፣ ከተትረፈረፈ ጮማና ቁርጥ መሃል ቲማቲምና ቅጠላ ቅጠል ካልሆነ ምናምኒት አልቀምስም እየተባለ የሚኖርበት እድሜ ነው ፣ ብዙ የሚያጓጓ ህይወት የለም ። ታዲያ ምንድነው በዚህ በኪኒኒ ተደግፎ በሚኬድበት የምሽት እድሜ ላይ ሆኖ ውሃና ዘይትን ለመቀላቀል መሞከር ? በዚህ ምግባር ትውልድ አይደለም ከአብራክህ የወጣ ልጅ ይጠየፍሃል ።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
ታዛቢዎች በህብረት !
ከቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በያሉበት ።

PDF created with pdfFactory trial version www.pdffactory.com

በሃይማኖት ጭቆና ስም የሚረጩ አደገኛ መርዞች –ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

(የግል አስተያየት)

አራተኛውን የኢቲቪ “ጥናታዊ ፊልም” አየሁት፤ ዝቅ ሲል ለምርጫ ቅስቀሳ፣ ከፍ ሲል ደግሞ ከፋፍሎ ለመግዛት ተብሎ የተዘጋጀ ይመስለኛል። ፊልሙ ኢህአዴግንና የቀድሞ ስርዓቶችን ያነጻጽራል፤ ማንም ነፍስ ያለው ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ጭቆና አልነበረም ብሎ አይክድም፤ ልዩነቱ የሚጀመረው “ጨቋኙ ማን ነው? ተጨቋኙስ?” የሚለውን ለመመለስ ሲሞከር ነው። በእኔ እይታ ጨቋኞቹ የኦርቶዶክስ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ መንግስታት ብቻ እንደነበሩ ተደርጎ የሚቀርበው አስተያየት ስህተት ነው፣ ተጨቋኞቹ ከኦርቶዶክስ ውጭ ያሉ ሃይማኖቶች ብቻ እንደነበሩ ተደርጎ የሚቀርበውም አስተያየት በታሪክ ያልተደገፈ፣ የስህተት ትምህርት ነው ። ታሪካችን እንደሚነግረን ከ66ቱ አብዮት በፊት፣ ሁሉም ስልጣን የያዙ ሃይሎች ስልጣናቸውን ለማቆየት ወይም ግዛታቸውን ለማደራጀት እነሱ የሚደግፉትን ሃይማኖት በሌላው ላይ ለመጫን ሙከራ አድርገዋል። የአጼ ሃይለስላሴ መንግስት የመጀመሪያውን የጽሁፍ ህገመንግስት ስላረቀቀና በህገመንግስቱ ላይ “ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት” የመንግስት ሃይማኖት መሆኑን በይፋ ስላወጀ ዛሬ እንደ ትልቅ ግኝት ተጋኖ ይቀርባል እንጅ፣ ከዚያ በፊት የነበሩት ገዢዎች ኦርቶዶክስን ብቻ ሳይሆን፣ካቶሊክንና እስልምናን የመንግስት ሃይማኖት ለማድረግ ሞክረዋል። ክርስትናን በይፋ ከተቀበለው ከመጀመሪያው ንጉስ ኢዛና ጀምሮ እስከ አክሱም ስርወ-መንግስት ውድቀት ድረስ ኦሮቶዶክስ ሃይማኖት የመንግስት ድጋፍ ነበራት፤ ዮዲት መጣችና ስርዓቱን ለማፍረስ ሞከረች። ቀደም ብሎ ክርስትናን የማያውቁት አገዎች፣ ክርስትናን ከአክሱሞች ስለተቀበሉ፣ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ያለምንም ችግር የመንግስት ሃይማኖት ሆኖ ቀጠለ። ይኩኖ አምላክ ከዛግዌዎች ስልጣኑን ከቀማበት እስከ ግራኝ አህመድ ዘመቻ ድረስ ኦሮቶዶክስ አሁንም የመንግስት ሃይማኖት ሆና ቆይታለች። ይሁን እንጅ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑት ነገስታት ከኦሮቶዶክስ ውጭ ያሉ ሃይማኖቶችን ብቻ ሳይሆን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ሆነው፣ የአስተምህሮ ልዩነት የነበራቸውን ሳይቀር፣ ሃይማኖታቸውን በነጻነት እንዳያስፋፉ ያግዱ ነበር። የደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ታሪክ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው። ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን እስከመጨረሻው ኦርቶዶክሶች ነበሩ፣ከሙስሊሙ ወይም ከቤተ-እስራኤላውያን ባላነሰ መልኩ ወከባ ደርሶባቸዋል።
muslim and christian
ግራኝ አህመድ ዘመቻውን ወደ ሰሜን ባስፋፋበት ወቅት ደግሞ ቀድም ብሎ ክርስቲያን የነበሩት ዜጎች እስልምናን በግድ እንዲቀበሉ ተደርጓል። ግራኝ ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ ቆይቲ ቢሆን ኖሮ እስልምና የመንግስት ሃይማኖት የመሆን እድሉ ሰፊ ነበር። ግራኝ በስልጣን ላይ በነበረባቸው አመታት እስልምና ዋና የአገሪቱ ሃይማኖት ነበር። ግራኝን ለመውጋት የመጣው የፖርቱጋል ጦር በበኩሉ አንዱ አላማው የካቶሊክ ሃይማኖት በኢትዮጵያ ማስፋፋት ነበር። ገልውዲዎስ ፈቃደኛ ቢሆን ኖሮ ካቶሊክ የመንግስት ሃይማኖት የመሆን እድሉ ሰፊ ነበር፤ አጼ ሱስንዮስ ሲነግሱ ግን ካቶሊክ የመንግስት ሃይማኖት ሆነ ። ኦርቶዶክስ የሆኑትም ያልሆኑትም እኩል ሃይማኖታቸውን እንዲለውጡ ተገደዱ። ካቶሊክ ለአጭር ጊዜም ቢሆን የመንግስት ሃይማኖት ሆነ፣ በዚህም የተነሳ ብዙ ደም ፈሰሰ። አጼ ፋሲል ሲነግሱ ደግሞ ኦርቶዶክስ ተመልሳ ከበሬታ አገኘት- “አጼ ፋሲል ነገሱ፣ ሃይማኖትን መለሱ” ተባሉ። ይሁን እንጅ በእርሳቸውም ጊዜ “ሁለት ልደት ፣ ሶስት ልደት፣ ቅባት ፣ ተዋህዶ” በሚሉ የአስተምህሮ ልዩነቶች ኦርቶዶክስ ትናወጥ ጀመር። ከዚያ በሁዋላ በመጡ መንግስታት ቅባቶች ሲያሸንፉ ተዋህዶዎች ተሳደዱ፣ ተዋህዶዎች ሲያሸንፉ ደግሞ ቅባቶች ተሳደዱ። በዘመነ መሳፍንት ጊዜ ደግሞ ለ90 ዓመታት ገደማ ማእከላዊ መንግስት የሚባልም ነገር ስላልነበር፣ የመንግስት ሃይማኖት የሚባል ነገር አልነበረም፣ መንግስት ነበር ከተባለም የይስሙላ ነበር። ከዚያ በሁዋላ የመጡት አጼ ቴዎድሮስ በኦርቶዶክስ ውስጥ የአስተዳደር“ ተሃድሶ” ለማካሄድ ሞከሩ። አብዛኞቹ አማካሪዎቻቸው ፣ ፈረንጆቹ ማለቴ ነው፣ ፕሮቴስታንቶች ነበሩ። ንጉሱ የኦርቶዶክስ ተከታይ ቢሆኑም ሃይማኖቱን ለማስፋፋት ወይም ሌላው ሰው ሃይማኖቱን እንዲቀይር ሲያስገድዱ አልታየም፤ ከኦርቶዶክስ ጋር የነበራቸው ግንኙነት መበላሸት ለውድቀታቸው አንዱ ምክንያት ሆኗል፣ ታሪክ አስተማሪዎቻችን እንደነገሩን ንጉሱ የፕሮቴስታንቱ ትምህርት እየጣማቸው ሄዶ ነበር። ከዚያ በሁዋላ የመጡት አጼ ዮሃንስ አራተኛ ደግሞ አጥባቂ ኦርቶዶክሳዊ ነበሩ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በይፋ የመንግስት ሃይማኖት እንዲሆን ቦሩ ሜዳ ላይ ደንግገዋል። ሙስሊሙ ሃይማኖቱን እንዲቀይር አስገድደዋል፤ ከተዋህዶ ውጭ ያሉት፣ በተለይ ቅባቶች በጎጃም ( ምስራቅ ጎጃም) አካባቢ ተጠልለው እንዲቀሩ አድርገዋል። ለእርሳቸው ሃይማኖት ትልቅ ቦታ ነበረው።

እርሳቸውን የተኩዋቸው አጼ ሚኒሊክ ኦርቶዶክስ ቢሆኑም፣ ቀደም ብሎ ሃይማኖት የነበራቸው ሰዎች ፣ በተለይ ሙስሊሞች፣ ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ሲያስገድዱ እምብዛም አይታይም፤ ሃይማኖት የላቸውም ተብለው የሚታሰቡት ወይም ከኦርቶዶክስና እስልምና ውጭ ያሉት ግን ኦርቶዶክስን እንዲቀበሉ ተጽእኖ ይደረግባቸው ነበር። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን የመንግስታቸው ሃይማኖት ነበር፡፡ ከእርሳቸው በሁዋላ የመጡት ልጅ እያሱ፣ኦርቶዶክስን የሚወዱ ሰው አልነበሩም፣ ከስልጣን የወረዱትም የመንግስትን ሃይማኖት እስልምና ለማድረግ አስበዋል በሚል ተዶልቶባቸው ነው፤ በእርሳቸው ዘመን፣ ጊዜው አጭር ቢሆንም ከኦርቶዶክሶች ይልቅ ሙስሊሞች የተሻለ ተቀባይነት ነበራቸው፤ በእርግጥ አባታቸውም ቀደም ብሎ ሙስሊም የነበሩ ናቸው። ልጅ እያሱ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ ቆይተው ቢሆን ኖሮ፣ እስልምና የመንግስት ሃይማኖት እንኳን ባይሆን፣ እንደ ኦርቶዶክስ እኩል የመንግስት ሃይማኖት የመሆን እደል ይኖረው ነበር ብየ አስባለሁ።

አጼ ሃይለስላሴ ከእያሱ ውድቀት ተምረው ኦርቶዶክስ ተዋህዶን መንግስታዊ ሃይማኖት ሆኗል ብለው በህገመንግስት ደነገጉ፤ እርሳቸውን ዘመናዊውን ትምህርት ያስተሟሩዋቸው ሰው ካቶሊክ ነበሩ። አጼ ሃለስላሴ “ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት፣ የመንግስት ሃይማኖት ነው” ቢሉም፣ ሙስሊም በሙሉ በአንድ ጊዜ ኦርቶዶክስ እንዲሆን አላዘዙም፣ በሙስሊሙ፣ በካቶሊኩና በሌላው ሃይማኖት ተከታይ ላይ አስተዳደራዊ ተጽኖዎች አልነበሩም፣ የመንግስት አድልዎ አልነበረም ማለት ግን አይደለም ። ኮሎኔል መንግስቱ ሃየለ-ማርያም መጡና “እግዚአብሄር የሚባል የለም” ብለው ሙስሊሙንም ክርስቲያኑንም ኩምሽሽ አደረጉት፤ ሙስሊሙ የአሁኑ ይባስ አለ፣ ክርስቲያኑም፣ እግዞዎ አለ። ሙስሊሞች “አላህ በኖረና በተጨቆንን ፣ ኦርቶዶክሶች ደግሞ “እግዚአብሄር በኖረና መንግስታዊ ሃይማኖት መሆኑ በቀረብን” ሳይሉ የቀሩ አይመስለኛም ። መንግስቱ በሁሉም ሃይማኖት ላይ ሳያዳላ ነው የተነሳው፤ ያም ሆኖ ግን ጓድ መንግስቱ ሰዎች በአንድ ጀንበር ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ አላስገደዱም፤ የሚከተለውን ያውቁ ነበርና። ፕሮቴስታንትን በተመለከተም ኮሎኔል መንግስቱ፣ ፕሮቴስታንት ስለሆነ ብቻ፣ የተለየ አሉታዊ ተጽእኖ አላደረጉበትም፤ እርሳቸው ፕሮቴስታንት እንዲስፋፋ ያልፈቀዱት ሌላ ራስ ምታት ላለመጨመር ነው፣ ራሳቸውን ለማዞር ኦርቶዶክስና እስልምና በቂዎች ነበሩ። መንግስቱ ኮሚኒዝምን ትተው የምእራባውያንን ዲሞክራሲ ቢከተሉ ኖሮ፣ ፕሮቴስታንት ሃይማኖት እንደልቡ እንዲንቀሳቀስ ይፈቀድለት ነበር።

በኢህአዴግ ጊዜ ደግሞ ፣ ሙሉ መብትን የማይጠይቁ ሃይማኖቶች እስካልተነሱ ድረስ፣ ማንም የፈለገውን ሃይማኖት መከተል ይችላል። ሙሉ መብትን የሚጠይቁ ሃይማኖቶች ከመጡ ግን በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው መቀመቅ ይወርዳሉ።

እንግዲህ ሳጠቃልለው፣ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን እና ሃይማኖቱን ይከተሉ የነበሩ ነገስታትን ብቻ ጨቋኝ አድርጎ ማቅርብ ስህተት ነው። የኦርቶዶክስም ሆነ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ገዢዎች፣ ሃይማኖታቸውን በሃይል ለማስፋፋት ጥረት አድርገዋል፤ ገዢዎቹ እነሱ ከሚከተሉት ሀይማኖት ውጭ ያሉትን ዜጎች ብቻ ሳይሆን በአንድ ሃይማኖት ስር እንኳ ሆነው የተለየ አስተምህሮ ይከተሉ የነበሩትን ሳይቀር አሳደዋል። ኦርቶዶክስን ጨቋኝ ፤ ሙስሊሙንም ተጨቋኝ አድርጎ ለማሳየት የሚደረገው ሙከራ እጅግ አደገኛ ነው። ገዢው ፓርቲ ራሱን ለአንዱ የመስቀል ጦረኛ፣ ለሌላው ጂሃዲስት እያደረገ ለማቅረብ የሚያደርገው ሙከራ ከራሱ አልፎ ለአገር እንዳይተርፍ ፣ከአሁኑ እረፍ ሊባል ይገባዋል።

ዴሞክራሲ ከማን ይጠበቃል??

$
0
0

ከነብዩ አለማየሁ /ኦስሎ ኖርዌይ
ዴሞክራሲን ለማምጣት እርስ በእርስ መደማመጥና ሃሳብን በነፃ ማንሸራሸርን ይጠይቃል ይሄ ዋና መሰረታዊ ነገር ንው።
እስቲ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ እንዳስ በኢትዮዽያ የህውሀት መንግሥት አመጣጡ እንደኔ ዓመለካከት ጥቂት የትግራይ ገበሬ ልጆች በኤርትራ የሻብያ እንቅስቃሴ በማየት ለምን እኛስ ሀገራችንን ትግራይን ነፃ አናወጣም ብለው ነፍጥ ይዘው ጫካ ገቡ በጊዜው የደርግ መንግስት በብዙ ሀገር ወዳድ ኢትዮዽያዊያን የተቀጣጠለውን ዘውዳዊውን ስርኣት አስወግዶ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲውተረተር የእንዚህ ጥቂት የዘረኝነት ዐባዜ የተፀናወታቸው ጥቂቶች ኣላማቸውን ለማሳካት ኣመቺ ጊዜ ተፈጠረላቸው በተጨማሪም በወቅቱ ሿብያ በኤርትራ በኩል ያድርገው የነበረው ጦርነት የደርግን አትኩሮት በተሻለ መልኩ መሳቡ ተመቻቸው በሶማልያ በኩል የሚካሄድውም ጦርንት ሌላው ምቹ ኣጋጣሚን ፈጥሮላቸው ነበር።
tplf
እነዚህም የትግራይ ልጆች በዙ ተባዙ በትግራይም ጫካዎች ውስጥ ተሰባሰቡ ነገር ግን በህልምም ይሁን በውን በኢትዮዽያ ዴሞክራሲን ለማስፈን የህግ የበላይነትን ለማስከበር ኣላማ አልነበራቸውም በጭራሽ ኣላማቸው ኣንድ ና ኣንድ ነበር የትግራይ ህዝብ ነፃ ኣውቺ ነበሩ ከእነርሱ ዴሞክራሲን መጠበቅ የማይታስ ነው።

የእውነቱ ሌላው እይታ በትግራይ ጫካ የበዙት የቀድሞው ታጋዮች የደርግ መዳከም ምቹ አጋጣሚ ፈጠረላቸው ተከዜን ተሻገሩ ያኔ ኢትዮጵያን መቆጣጠር እንደሚችሉ ሁኛ ሰው ከወደ UN ሹክ ኣላቸው ያኔማ ለኣማራው ፥ ለኦሮሞው ፥ ለቤሄሩ ሁሉ ተወካይ ፈላልገው ካገኙ ቡሃላ ሰተት ብለም ገቡ ።

በስልጣን ለመቆየት አንዱን ብሄር ከሌላው ማጋጨቱን ተያያዙት ከዚያም እነርሱ የተዋደቁለትን ዐላማ ማራመድ ጀመሩ የሃገሪቱን ዋና ዋና ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታነት በማዘዋወር ሰበብ ወሰዱ ትልቅ የቢዝነስ ኢምፓየር አቋቋሙ ለኢትዮዽያ ህዝብም የይስሙላ ህገ መንግስት ጣል ተደረገለት እንርሱ ቀጠሉ መሠሎቻቸውን አምጥተው በመሀበር ቤት ስም ና በኮንዶሚኒየም ስም ከተሙ።
hailemariam and samora
ኢትዮጵያ ያሉ ጥቂት ጋዜጦችና ፓርቲዎች ዴሞክራሲን እንፈልጋለ ሲሉ እሺ ይታሰብበታል በማልት ስራቸውን ቀጠሉ የሃገሪቱዋን መሬት ለበዓድ ሸጡ ተከታዮቻቸውን በሃገር ውስጥና በውጪ ልከው አስተማሩ ኣላማቸውን የሚያሰናክልና ከእንርሱ ሃሳብ ውጪ የሆነውን ሁሉ ኣሰሩ ዓልያም ከሀገር አስወጥተው ለስደት ዳረጉት ዋናውን ዓላማቸውን ኣልሳቱም የራሳቸውን ሰዎች ኑሮ ማሻሻልና በኢትዮዽያ የበላይ ሆኖ መታየት። እኛም ኧረ ዴሞክራሲ ኧረ ነፃነት ኣልን ወይ ዴሞክራሲ ዓንዳንዶቹ እንዳውም ዴሞክራሲ ከፈለጋችሁ ጫካ ግቡ ማለት ጀመሩ በዚ መሃል ባዘጋጁት ምርጫ በተገኘች ትንሽ ክፍተት ያኔ የኢትዮዽያ ህዝብ እንድሚጠላቸው ግልብጥ ብሎ ውጥቶ ኣሳያቸው ከዚያም ገድለውም ኣስረውም ገርፈውም ቢሆን ካረጋጉ ቡሃላ በውንም ይሁን በህልም ይህ ኣይነቱ ስተት ዳግመኛ እንደማይደገም ቃል ገብተው እስከ መጨረሻው ጭላንጭሉን አዳፈኑት።

ሀይልማርያም ጠቅላይሚንስትር ሆነ ያኔ ከጀርባ ሆነው ኢኮኖሚውን ፥ መከላከያውን ፥ ደህንነቱንና ውጪጉዳዪን ህውሀቶች በመቆጣጠር እኛ ዴሞክራሲያዊነን በህጉ መሰረት የስልጣን ርክክብ ዓደረግን ኣሉን ታድያ እውነት ከነኚህ የምንሻውን ዴሞክራሲ የሠፈንባት እኩልነትና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ኢትዮዽያን ከህወሓት መጠበቅ የዋሀneት ነው ። ካለን ተሞክሮ እናም እንደኔ ሃሳብ ስልኛ ነፃነት ከኛ ሌላ ሊጮህልን የሚችል የለምና ልዩነታችንን አቻችለን ሁላችንም በትግላችን እንፅና።

ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአስተዳደር ቦርድ ኃላፊነትና የሥራ ድርሻ የኅዝብን/የምዕመናንን ውሳኔ በሙሉ ማስፈጸም ነው!!!

$
0
0

ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአስተዳደር ቦርድ ኃላፊነትና የሥራ ድርሻ የኅዝብን/የምዕመናንን ውሳኔ በሙሉ ማስፈጸም ነው!!!

01/19/2014

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ፤ አሜን።

በምእመናን ተመርጠው ቃል የገቡ አንዳንድ የአስተዳደር ቦርድ አባላት ባለፈው ዲሴምበር 15 ቀን 2013 ዓ.ም የቤተከርስቲያናችን ጠቅላላ ጉባዔ ቤተከርስቲያናችን በአባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየትና መወጋገዝ እስኪያበቃና አንድ እስኪሆኑ ድረስ ለ20 ዓመታት ስትመራበት የነበረው የገለልተኝነት አስተዳደር እንዲቀጥል በማለት በከፍተኛ አብላጫ ድምጽ የወሰነውን ውሳኔ አንቀበለውም አናስፈጽምም በማለት ላይ ይገኛሉ። ይህም የተመረጡበትን አላማ አለማወቅና ኅዝብንም የመናቅ አካሔድ ነው። በምእመናን የተመረጡት የራሳቸውን ፍላጎትና አላማ ለማስፈጸም ሳይሆን የህዝቡን ውሳኔና ድምጽ በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ ነው።
deb
የቤተክርስቲያናችን መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 5 ክፍል 3 ‘ሀ’ በግልጽ እንደሚደነግገው ‘‘ የቦርዱ አጠቃላይ ኃላፊነት ጠቅላላ ጉባኤው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በሙሉ በሥራ ላይ ማዋል ይሆናል’’ ይላል። በተጨማሪም በአንቀጽ 4 ‘ሸ’ ላይ ‘‘ በጠቅላላ ጉባዔ የሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተግባራዊ ይሆናሉ’’ ካለ በኋላ የቦርዱን ሊቀመንበር የሥራ ኃላፊነትና ተግባር በዘረዘረበት አንቀጽ 6 ክፍል 3 ‘ሀ’ ላይም ‘ሊቀመንበሩ የጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔዎችን በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል።’ በማልት በማያሻማ ሁኔታ በኅዝብ ድምጽ የተመረጡ የቦርድ አባላትን ኃላፊነትና ተልዕኮ ደንግጎ ይገኛል።

ቤተክርስቲያናችን ደብረሰላም መድኃኔዓለም የምትተዳደረው በሕግና በሥርዐት ነው። በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 1 ክፍል 3 ውስጥ እንደሰፈረው አስተዳደርን በተመለከተ ቤተክርስቲያኗ የምትመራው በሚኔሶታ የቤተክርስቲያናት ማቋቋሚያ ሕግ መሠረት ነው። ግልጋሎትም የምትሰጠው በአሜሪካ የአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት ከታክስ ነጻ የሚያደርገውን መመሪያ 501c(3)ን ተከትላ ሲሆን ከእነኝህ ሕግጋት መውጣት ወይንም ባልተጻፈና ስቴቱም ሆነ ፌደራል መንግሥቱ በማያውቁት ሕግና አሠራር መመራይ ቅጣቱ ከባድ ነው። ከዚህ አኳያ የቤተክርስቲያናችን የኅዝብ ተመራጭ የቦርድ አባላትም ሆኑ ካህናት እንዲሁም ምእመናን ባጠቃላይ ቤተክርስቲያናችን የምተደዳደርበትን የውስጥ ደንብና ሕግጋት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ሕጎችን ማወቅና ከእነርሱም ጋር የማይጋጭ አካሔድን መከተል ይጠበቅባቸዋል። ይህን ባለማወቅ ከሕግና ሥርዓት ውጪ በሆነ አካሔ በሚደረግ እንቅስቃሴ ምክንያት በግል ሕይወትና ታሪክ እንዲሁም የሕብረትሰባችንን መልካም ስም በማጉደፍ የሚደርሰው ጉዳት ቀላል ሊሆን እንደማይችል ከወዲሁ አበክሮ ሊታሰብበት ይገባል። ሕግን አለማወቅ ከቅጣት አያድንምና!

በምንኖርበት አገር ሰው ሁሉ በማናቸውም ሁኔታ ድምጹን የመስጠትና ያለምስጠት፣ የመደገፍና ያለመደገፍ መብት ያለው ሲሆን፤ ትክክል አይደለም ብሎ ያመነበትን ጉዳይ ደግሞ ሕግን ብቻ ተከትሎ አቤቱታውን ማቅረብና በፍርድቤትም ሆነ በሚመለከትው አካል ብይን የማግኘት መብት አለው። ከዚህ ተጻራሪ በሆነ ሕገ-ወጥ አካሔድ በመሔድ ግን ማናቸውንም ፍላጎት ወይንም አላማን ማስፈጸም ግን በፍጹም አይቻልም። ምክንያቱም በተለምዶ እንደሚባለውና በርግጥም እንደምናየው THIS IS AMERICA! ስለሆነ ነው።

ምናልባት ከውጪ ሆነው ግፋ በለው እያሉ የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት ለማናጋት እየሰሩ ያሉ የወያኔ ፖለቲካ ጉዳይ አስፈጻሚዎችና ሆድ አደር ጋሻ ጃግሬዎች በተለያዩ አካባቢዎች እንዳደረጉት ቤተክርስቲያናችንን የማዘጋትና አገልግሎቷን የማቋረጥ አላማ የሚሳካላቸው መስሏቸው ከሆነ ፈጽሞ ተሳስተዋል።

ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም እውነተኛው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትና ሥርዓት ብቻ የሚፈጸምባት ቦታ እንጂ የዘረኝነት አቀንቃኞች መፈንጫ ከቶውንም አትሆንም!

በኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ በፖለቲካ ጣልቃገብነት(በወያኔ ቀጥተኛ ጣልቃገብነት) በአባቶች መካከል የተፈጠረውን መለያየት በምንም መሸፋፈንና መቀባባት አይቻልም። ይህ መከፋፈል የመጣው በኃይማኖት ላይ የተለያየ አቋም ስላለ አይደልም። የቤተክርስቲያንን መዋቅራዊ አሰራር ባለማወቅ የተከሰተም አይደለም። ወይንም የአባቶች ጳጳሳትን ክብርና ድርሻ ካለማወቅ የመጣ አይደለም። በውጪ አገርም አገር ቤት የሌለው ነፃነት ስለተገኘ አይደለም። የቤተክርስቲያን ቀኖናና ነፃነት በፖለቲከኞች መጣሱን፣ የአገር ሉአላዊነት መገሠሡንና የኅዝብ መብት መገፈፉን ተከትሎ እንጂ! ስለሆነም በማጭበርበርና ሕገወጥ አካሔድ በመከተል የሚመጣ ለውጥ ስለሌለ አርፎ መቀመጥ ይበጃል እንላለን።

እጅጉን ከሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ለዚሁ የጥፋት ተልእኮ ወያኔ ያሰማራቸው የቤተክርስቲያንን እና የህዝብን ገንዘብ ዘርፈው ሳለ በወንጄል የሚፈለጉ ሰው ስለመልካሚቷ ቤተክርስቲያናችን የሐሰትና የጥላቻ ስብከታቸውን ማሰማታቸው ነው። አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንዲሉ በዘረፉት የኅዝብ ገንዘብ ምክንያት በወንጀል ስለሚፈለጉ ወደ አገር ቤት ለመሔድና በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንኳን ለመገኘት የማይችሉ ሰው በዓለም ላይ የተናኘ ኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት እየሰጠች ያለችን ቤተክርስቲያን መሳደባቸው ከማሳዘንም አልፎ ያስገርማል። ይቅርታ አባ ዘካርያስ ሚኔሶታ የሚዘረፍ ቤተክርስቲያንም ሆነ ገንዘቡንና ንብረቱን አሳልፎ የሚሰጥ ምእመንም የለም!!!

እኚህ ሰው ላለፉት 5 ዓመታት በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አልተገኙም። እንደቤተክርስቲያ ሕግ ግን ከሁለት ጊዜ በላይ መቅረት አይቻልም። እርሱም በፈቃድና በበቂ ምክንያት ብቻ ነው። የቀድሞው አባ ጳውሎስ ከወንጀል ክስ ለማሸሽ ሲሉ በቅጡ መናገር እንኳን የማይችሉትን ሰው በአሜሪካ መድበው በውጪው ዓለም ብዙ መስራት የሚጠበቅባትን ቤተክርስቲያን እያዘቀጧት ይገኛሉ። ገንዘብና ንብረታቸውንም አናዘርፍም ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይዘልፋሉ። ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ሞተናል ካሉ በኋላ ለአለማዊ ፖለቲከኞች ተገዝተው ቅድስቲቱን አገርና ንጽሕት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ከሚያጥፋ ኃይል ጋር ሆነው ፍርድን ለራሳቸው ያከማቻሉ። እግዚአብሔር ልብ ይስጣቸው።

በመጨረሻም የሚኔሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ምእመናን ዛሬም እንደትናንቱ ቤተክርስቲያናችንን ከውስጥና ከውጪ አፍራሽ ቡድኖችና ግለሰቦች ነቅተን እንጠብቅ።
ለሰላምና ለአንድነት የቆሙ ምእመናን።

በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!

$
0
0

By BERHANE ASSEBE

Dccc
ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብቷ የታደለች ፣መልካም የአየር ፀባይ ያላት፣ህዝቦቿ የራሳችን አኩሪባህልና ወግያለን፣የራሳችን መልካም መልክዓ ምድራዊና አሰፋፈር ያለን በጋራ ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት በየትኛውም ዘመን ሉአላዊነቷ ያልተደፈረ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት። በተለያየ ወቅት የተፈጥሮ ሃብቷን ለመቀራመትና ሉአላዊነቷን ለመዳፈር የሞከሩ ሃገራት ሁሉ፣በውድ ልጆቿ የተባበረ ክንድ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ኢትዮጵያን ዳግም እንዳይመኟት የተባረሩበትና የኢትዮጵያን አይበገሬነት በአፍሪካም ሆነ በአለም መድረክ ያስመሰከረች፣ አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ በማቆየት በአለም ታሪካዊ ስፍራ ያላት፣ በቀደምት ውድ ልጆቿ የደም መስዋዕትነት ሀገራችን ሉአላዊነቷ ሳይደፈር ለብዙ ሺ አመታት ቆይታለች።
በአሁኑ ስዓት ኢህአዴግ/ህወሃት ለግልና ለግዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲል የኢትዮጵያን አንድነት በማደብዘዝ እንሆ በእኛ ዘመን ለዘመናትተደፍሮ የማያውቀውን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት የኢትዮጵያ የሉአላዊነት ባለቤት የሆኑት ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሳይወያዩበትና ሳያፀድቁት በጓሮ በር የኢትዮጵያን መሬት ለባዕድ ሃገር/ሱዳን ቆርሶ ለመስጠት ሽርጉዱን ተያይዞታል። ከአመታት በፊት በምዕራቡ የሃገራችን ክፍል /ድንበር በኩል/ በመሸራረፍ ለም የሰሊጥ ምርት የሚሰጥ መሬት ለሱዳን ሲሰጥ ዝም በማለታችን እንሆ ዛሬ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚጋፋ ፣ የኢትዮጵያን ቅርጽ የሚያጠፋ ረጅም ርዝመት ያለው ለም መሬት ለሱዳን ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ሰማን ።

ዛሬ ላይ ሆነን ይህንን መሰሪ ተግባር አንድነታችንን አጠናክረን መግታት ካልቻልን ነገ ደግሞ በሌላኛው የኢትዮጵያ ጫፍ በኩል የኢትዮጵያ መሬትተቆርሶ ለሌሎች አጎራባች ሀገራት ላይሰጥ ምን ዋስትና አለን ?
አያቶቻችንና አባቶቻችን ደማቸውን ገብረው ፣አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቡንን የሀገር ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ የእኛ የአሁኑ ትውልድ የታሪክ ግዴታ ነው። ይህን የታሪክ ግዴታችንን ሳንወጣ/ችል በማለት/ በመሰሪው የህወሃት/ ኢህአዴግ አመራር የሃገራችን ሉአላዊነት እየተሸራረፈ ለባዕድ ሀገራት ሲሰጥ በምን አገባኝ ስሜትዝም ብለን ብንመለከት በ– ዚ–ያ ዘመን ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀ የውጭ ጠላትጋር የሀገሬን ሉአላዊነት አላስደፍርም በማለት በዱላ፣ በጦርና ጋሻ፣ ዘመናዊ ባልሆነ የጦር መሳሪያ ፣በባዶ እግራቸው በመዝመት ደማቸውን አፍስሰው ፣ አጥንታቸውን ከስክሰው የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ሳያስደፍሩ ያስረከቡን የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይወጋናል።

«የኢትዮጵያ ድንበሮች በኢትዮጵያውያን ደም የራሱ፣ በኢትዮጵያውያን አጥንት የተገነቡ ሲሆኑ ድንበሮቻችንን ለማስከበር ከሁልቆ መሣፍርት፣ ተራ ዜጐች አንስቶ እስከ አንድ ታላቅ ንጉሠ ነገሥት አጼ ዮሐንስ አንገታቸው ሰጥተዋል፡፡ በዶጋሊ፣ በጉራዓ፣ በጉንዲት፣ በመተማ፣ በአድዋ፣ በወልወል በቅርብ ጊዜያት ደግሞ በሶማሊያና በኤርትራ የፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም የሌላውን ግዛት በመቋመጥ ሳይሆን ድንበሬን አላስነካም በሚል ነበር፡፡ እንደዛሬው መኪና ወይንም ባቡር ባልኖረበት የቀደምት ኢትዮጵያውያን ከመሃል አገር ተነስተው በእግር ለወራት በረሃውን አቋርጠው፣ ተራራውን ወጥተው፣ ንዳዱን ተቋቁመው፣ ወባውን ደፍረው ከሙስታሂል እስከ ጋምቤላ፣ ከራስ ካሣር እስከ ሞያሌ ዘልቀው ድንበሩን ሰፍረው ኢትዮጵያን ለዚህ ትውልድ አስረክበው ሄዱ፡፡ ይህ ተረካቢ ትውልድ የተረከበውን መሬት ሳይቀነስ ለቀጣዩ ትውልድ ያስተላልፋል ይሆን—-«ከያዕቆብ ኃይለማሪያም/20 July 2008/።
ይህ ትውልድ ከአባቶቹ የወረሰውን አደራ ጠብቆ የሀገሩን ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ በማስከበር ለመጭው ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት መሆኑን ለአፍታ መዘንጋት የለበትም ። ህወሃት/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ህዝብ እውቅና ውጭ በሚስጥር የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት ዳር ድንበራችንን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የተደረገውን የውል ስምምነት የፖለቲካ ልዩነት፣ ብሄር፣ ሃይማኖት፣አመለካከት ሳይለያየን የፖለቲካፓርቲዎች ፣ ድርጅቶች፣ ሲቪክስማህበራትና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በጋራ ተንቀሳቅሰን አሁኑኑ ማስቆም ካልቻልን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ከማስደፈርም አልፎ እስከ ወዳኛው ትውልድ ድረስ ብጥብጥና ትርምስን የሚያወርስ ስውር ደባ ነው።
በመሆኑም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት በመጋፋት ለም መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ የሚሰጠውን ስምምነት አገር ወዳድ የሆንን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በጋራ በመንቀሳቀስ በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም! በሚል መርህ ተግባብተን ይህንን እኩይ ተግባር ለማስቆም ግዜ ሳንወስድ በያለንበት ፈጥነን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል።
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ ሀገር አሳልፎ የመስጠት ታሪክ አልወረስንም!

የውስጤ ብቁ ዳኛ!

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

አምቄ ብይዘውም ጠብታወቼ ዘመን አመጣሹን ብራና አራሱት
አይቀርም ደግሞ ደረሰ …. ጥር 21 የሚሉት ….
ለብር አንባር – የካቴና እራት የዶለተ – ጨጎጎት ….
የዓይናማዋ የመከራ ቀን አከባበር የልደት።
reeyot alemu
ወጣትነት ውበት የሚሆነው ቀድሞ ማለም፤ ቀድሞ መሆን ሲቻል ብቻ ነው። ወርቅ በእሳት እንደሚነጥረው እንሆ በዬጊዜያቱ የነፃነት ደቀ መዝሙራት የሆኑት የኢትዮጵያ ወጣቶች ማገዶ ሆነው ይነዳሉ፤ ይፈልቃሉ ወጣትነታቸውን በመሰዋት — በሐዋርያነት። እነሱ አራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡበት ሚስጢር ኢትዮጵያዊነት ነው – ትኩስ ሁልጊዜም ቋያ ነው። የእናቱ ነገር አይሆንለትም። ገላጫቸው ብሄራዊነት ነው፤ ማንነት ላላው ጌጣማ ዜግነት የሚከፈል ታላቅ ዋጋ፤ አብይ ጉዳይ፤ እራስን ፈቅዶ ለበለኃሰብ የሰጠ የፍጽምና ገድል። ወጣቶቹ የሚከፍሉት ምክንያታዊ ግብር የአደራ ዕዳ ነው። ወጣት የሀገሩን ክብር ረዘም አድርጎ የሚያይ ድንቅ የማህበረስ አካል ነው። እግዚአብሄር ይስጥልን የእኛ መብራቶች። ለሰማዕታትም በአርያመ – ገነት ያኑርልን አባታችን ክርስቶስ። አሜን!

ጥር ጣና ዘገሊላ – የእናት ክብር ብቸኛው ጊዜው ሳይደርስ ታዕምር የተገለጸበት ሚስጢራዊ ወርኽ ነው። ወጣትና የእኩልነት መምህር፤ ዓላማውን ያወቀች፤ መንገዷን ጠንቅቃ የተረዳች፤ የምልዕትን አንጡራ የህልውና ፍላጎትን አስመችታ በልቧ ጽላት በቋሚነት ያነጸች የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ልደት እ.ኤአ. ጥር 21.20014 በነፃነት ፈላጊ ቤተሰቦች በውስጥነት ደምቆ ይከበራል። በቃሊቲ እስር ቤት በአጋዚ የጭካኔ መጋዘን ግን ይከበራል ከምል ይልቅ በቋሳ ይቀጠቀጣል፤ በግፍ ይቀጣል፤ በበቀል ይጨቀጨቃል ብል ይሻላል። አህህህ …

ክብርት እህታችን … በወፈ በላ ታጥራ፤ በጉልበተኞች ታፍና፤ እዬተገላመጠች፤ በክፉ ዓይን እዬተገፈተረች የሚከበር ጥቁር ዕለት። አስኪ ይሁን ትኑርልን። … ትሰንብትልን። እርግጥ ነው ይህ ጥንካሬ የሴቶችን የብቃት ልኬታ ሙሉ አቅም በእጅጉ ያጎላዋል – ነገ ደግሞ ካልዘለልነው።
በ2005 ዓ.ም የዘሃበሻ ማህበራዊ ድህረ ገጽ ድንቅ ሰው ተብላ በህዝብ ድምጽ የደመቀቸው፤ በተመሳሳይ ዓመት ማለት በ2013 እ.ኤአ. ዬዓለምዓቀፍ ሽልማት ያገኘችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ የ2006 ዓዲስ ዓመትን በወያኔ ቀደመት አቀንቃኝ በኮ/ሌ ኃይማኖት የሚደርስባትን ዙሪያ ገብ ፈተና አሻም ብላ፤ በራህብ አድማ ነበር የተቀበለችው። ከወላጅ እናቷ በስተቀር ከዕምነት አባቷ ጀምሮ የቤተሰብ ጥዬቃ ማዕቀብም ተጥሎባት እንደ ነበር ይታወሳል።
የእኩልነት ህሊናችን! ለወያኔ ቀለጦና ተውሳክ ፍላጎት እስር ቤት ሆና የምትጋተራዋ ቀንበጥ፤ በራስ የመተማመን ስሜቷ ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ነው፤ ድፍረቷም ሙሴ ነው፤ ስለሆነም ወጣቷ ጋዜጠኛ ነገሮችን ከተለያዬ አቅጣጫ ተመልክታ የምትሰጠው አፋጣኝ ውሰኔና የምተወስደው ቁርጠኛ እርምጃ ለተለዬ ተልዕኮ ፈጣሪ አምላካችን መምረጡን ያመላክታል። ከልብ ካስተዋልነው። የምትመክታቸውን የፈተና ትብትቦች ሁሉ በዘርፍ በዘርፍ ለይተን ስንመረምራቸው አባታችን መዳህኒተአለም ለዚህ ታላቅ ኃላፊነት እንደመረጣትም ይተረጉምልናል። የህሊናዋን መስኮት ቧ አድርጎ ከፍቶ የብርሃኑ ተጠቃሚ እንድንሆንም ፈቅዶልናል። አዬን ሰማን … በታናሻችን …. ድንቅ ነገር። ከድንቅ ፍሬ ሲገኝ ዘሩን ማብቀል ደግሞ የእኛ ተግባር ይመስለኛል።
አህትዓለም! እንኳንም አደረሰሽ የእኔ የነፃነት አረበኛ! አንበሲት! ግንባር ቀደምት ቅንነት – የውስጤ ብቁ ቀጥተኛ ዳኛ! እንኳንም በመከራ ተከበሽ ይህን ቀን ለማዬት አበቃሽ – አንቺ ቀለሜ! እመቤቴ ….. ዘመኑን በመከራ፣ እኩልነትሽን በአሳር በከዘነው፤ የአፍላ ዕድሜሽን የወጣትነትሽ ውበት ፈተና በስፋት በሚናኝበት፤ አፍ ባላው መቃብር ሆነሽ፤ በሰንሰለት ታስረሽ እኩልነትሽን በነጠረ አስተምህሮ በኪዳን አከበርሽው። እግዚአብሄር ይስጥልን አንቺ የጽናት ልዩ አድማጭ።

እንቺ …. ትርጉም
የማንነት ንቁ ዓለም!
መሆንን በመቻል ይሁንተኛነት፤
ቀደምሽለት ….
አንችኑ እራስሺን ማግደሽ …. በሐሤት – በቀሉን – አዋዋጥሽበት፤
አዳራን – ልታበሪ
ዘመንን – ልትገሪ
ነገን ልታስተምሪ! ውብ ድሪ …. የእናት ጠበቃ – የነፃነት ቃና ዘማሪ!

አንቺ ፋና! … ፈተናው በጸጋ ተቀብልሽ፤ መንፈስሽን በቋሚ ብርታት ገርተሽ፤ ወጣትነትሽን ለእኛ ሸልመሽ። አንቺ በጨለማ አሳርሽን – ፍዳ – መከራሽን – ታያለሽ። በጽኑ በሽታ እዬተሰቃዬሽም እንሆ ለእኛ አንችን – ውስጥሽን በልግሥና ታድያለሽ። አንቺ የዕልፍ ትውልዳዊ ድርሻ ቀዳሚ …. ችግርን በፈቃድሽ ተቀብለሽ የምትቀልጪ የአንስት አብነት፤ የወጣትነት ልዩ ጉልላት፤ ማን እንደ አንቺ? …. – ሁሉንም ታግሰሽ ተሸከምሽ።

ውዴ! ታመሽ ባጠገብሽ ማንም ሳይኖር፣ አረመኔው ወያኔ እያለሽ ሞት የፈረደብሽ የዛሬም፤ የነገም የነፃነት ወጋገን…. አይዞሽ! … እናትዬ አምላካችን ፈተና ከሰጣቸው ጋር ነውና ብርታቱ ተስፋሽ፤ ቅዱስ መንፈሱ ደግሞ ጠባቂሽ ይሆናል። ቀን ደግሞ ለቀን ይሰጥና ቋሰኞችን እዬደነ ይቀጣል። ይህን ያደርጋል የፈጠረሽ አምላክ። ለቅኖች ቅርብ ነውና የመሃፀን ምር ሀዘንም ፈሶ አይቀርም … እንዲህ እንደ ዋዛ ወጣትነትሽን ለነፃነት አርበኝነት ወደሽ ማስበለታሽ ከንቱ አይሆንም። አንድ ቀን አዎን አንድ ቀን … ምላሹ ጣፋጭ ይሆናል። የመከራሽ ዋጋ ታሪክን ይፈጥራል – ይሰራልም። ታሪክ ያደምጣል – ትውፊት በአስር እጣቱ ፈርሞ ይቀበላል። የሴቶች የወጣቶች ዝክረ ገድል የህዝብ አንጡራ ሃብት ይሆናል።

ውስጥሽ ፍሬ – ዘር
ትንፋሽሽ – የነፃነት ሃር፤
ርዕዮት የነገ መንበር!
አንቺ የእኛ ….
አንቺ ብርቱ የአርነት ጽኑ ዘበኛ፤
የፍቅር ማዕድ ሁነኛ!

ይህቺ ፍቅር! ትንሽ ብልህ ብላቴና! በዚህ ዕድሜ፤ ከእሳት ከውሃ በሚባልበት ወቅት ላይ ወጣትነቷ የሚያዛትን ሥነ – ሕግጋት ተላልፋ በቃኝን በድርጊት ቀድማ፤ በአርያነት እንሆ ትመራናለች የመሆን እሸት። ወጣትነቷን ይፈሩታል፤ ሴትነቷንም እንዲሁ። ለዚህም ነው የእግር ብረት ቤተኛ እንድትሆን የተፈረደባት። በፈንጅ ወረዳ ተከባ ስለ እውነት መሰከረች፤ ስለሃቅ ሰበከች፤ ስለ ነፃነት አወጀች፤ ረመጡን ፈቅዳ በመቀበል ስለ ነገ ብሩህ ቀን ተግባርን ቀለበች፤ ስለ አዲስ የፍትህ ሥርዓት ነገረች – „ጠንክራቸሁ ታገሉ“ ብላም ጥብቅ መልዕክት ላካች – ጋዜጠኛና …. መምህርት ርዕዮት ዓለሙ።
እኛስ ወገኖቼ … ካለንበት ወይንስ ብጣቂ ፈቀቅ አልን ይሆን? እንፈታተሽ – ከህሊናችን ጋር …. ለፊርማ አንኳን ተለምነን ነው። የእኛ ተግባር የሎቢ ሆኖ፤ አትራፊነቱም የወርቅ ክምችት ሆኖ ግን አንተጋም። ነጮቹ አይደለም የብዙኃን ሰብሰብ ያለ ድምጽ ቀርቶ ለአንድ ሰው ብጣቂ አረፍተ ነገር እንኳን ክብር አላቸው። እባካችሁ እንበርታ፤ ቋሚ ተግባራትንም ተከታታይነት ባለው ሁኔታ እንፈጽም። አንድ ሰሞን ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ አናድርገው፤ የወያኔ የካቴና ኑሮ እዬባሰ፤ እዬከፋ ከመሄድ እኮ ለዘብ አላለም ….

መንፈስሽ ሲያማትር
ነፃነት ሊመትር …..
ሆንሽለተኝ ማገር።

የእኔ ውስጥ!…. የእኔ እናት አንቺ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን አሥራት ….
ለህግ የበላይነት፤ ለሰብዕዊ መብት መከበር፤ ለተስተካከለ ሚዛናዊ አስተዳደር፤ እኩልነትን ለሁላችን ልትመግብ የምትችል እናት ኢትዮጵያን ለማግኘት፤ ከቶም በማይቻልበት ሁኔታ፤ ፊት ለፊት ተጋፍጠሽ የምትከፍይው መስዋዕትነት ለትውልዱ ታላቅ ክበረ ወሰን ነው። ዓለምንም አስተምሯል። እስር ቤት እንኳን፤ በዛች በተጣበቀች የድቅድቅ ዛኒጋባ እንኳን፤ ይህም ተቀንቶበት አዬሩ እንዲታውክ በውስጥም በውጭም ሙጃው ወያኔ የሚያደርስብሽ ተጽዕኖ የበቀል አምላክ ቸል ሳይለው በእጥፍ ድርብ ዋጋቸውን እንደሚሰጣቸው በፈጣሪዬ እተመመናሉሁ! ዕንባ ፈሶ አይቀርም፤ ዋጋ ያስከፍላል በእጥፍ ድርብ።

ጌጤ! … አንቺ የነገን ቀና መንገድ አላሚ — የዕውነት ፍሬ እግዚአብሄር አምላክ መከራውን ሁሉ የምትታገሺበት ጉልበትና አቅም ይሰጥሽ ዘንድ አዘውትሬ ለአምላኬ፤ ለፈጣሪያ ሳልቦዝን አቀርባለሁ። ድንግልም አትተውሽም እናት ትደባብስሽአለች። አቅሜ ይህ ብቻ ነውና። አሁንም አይዞሽ! በርችልን የእኛ የነፃነት ራህብተኛ፤ የርትህ ናፋቂ፤ የእኩልነት አስተማሪ – የሰማይ ሲሳይ!
ክውና
አንቺ የእኔ ለጋ፤ እጅግ የምሳሳልሽ ታናሼ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ … እንዲህ የተግባር ጋት ሙሉዑ ሆኖ መስካሪ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ክብር ነው። በዚህ ዘመን ኢትዮጵያን ከገደለ፤ ዳር ደንበሯን ካስደፈረ፤ ትውልዱን ከተበቀለ፤ ታሪክን ከደለዘ፤ ነገን ሳይመጣ አስቀድሞ ለማሰረር ታጥቆ ከተነሳ፤ እልፎችን በማንአለብኝነት ከቀጠቀጠ አረም ድርጅት ከወያኔ – ፓሊሲ ጋር – ግብረ አበር ሳትሆኝ፤ ነገር ግን የነፃነት መዝሙር፤ የአርነት ዜማ መሆንሽ ኩራት ነሽና ጽናቱን ፈጣሪ አምላካችን ጨምሮ በገፍ ይሥጥልኝ። አሜን! የተመረጥሽው ለዚህ ነው። ይህ ጸጋሽ ነው። አምላክሽ የመረቀልሽ – ሻማነት! እኛም ታድለናል ለሞት የቆረጣች ታናሽ እህት ስለ አገኘን። ከሁሉም ነገር መማርን ከፈቀድንለት መማር እንችላላን። ባለውለታችን ነሽ። የሀገራችን ሆኖ የመገኘት ሰንደቅዓለማም።
በተጨማሪም ድንቁ ነገር የቤተሰቦችሽ ብርቱነት ናሙናነት ነው። የነፃነት ትርጉም የገባቸው ወላጅ አባትሽም በጣም ብዙ ርቀው አሰተማሩን። አጋጣሚው በብዕር ካገናኘን ዘንዳ ዝቅ ብዬ ምስጋናዬን አቀርብላቸዋለሁ። አምላካችን እኛን የፈጠረበት ምክንያት እንድናመሰግነው ነውና አንቺን ለሰጡን እንዲሁም በቅርብ ሆነው ሁሉንም ፈተና ለሚጋሩት ለተከበሩት መላ ቤተሰቦችሽም እግዚአብሄር ይስጥልን እላለሁ። ለወላጅ በዚህ ቀንበጥ ዕድሜ ከሙሽርነት – እስር ቤት ፍሬን ማዬት ከባድ ነው – እጅግ። እነሱም አብረው እዬደቀቁ ነውና ብርታቱን ይስጥልኝ አምላኬ። አሜን!

የማከብራችሁ ታዳሚዎቼ ቀለማሙ የብዕር ቆይታ ከአድማስ ባሻገር አብሮ በፍቅር አቆዬን። ፈቅዳችሁ ለሰጣችሁኝ ቅኑ ጊዜ ዘንካታውን ኢትዮጵያዊ ምስጋና በአክብሮት እንሆ – የኔዎቹ! እናንተን ያኑርልኝ።

ሴቶች የድርጊት ጀግኖች ናቸው!
ሴቶች የመሆን መቻል ጉልህ ምልክት ናቸው!

ማሳሰቢያ …
* እናንተ ድንቅ የሀገሬ ልጆች በዘመን አመጣሹ ፌስ ቡክና ሌሎችም አካውንት ያላችሁ የእንኳን አደረሸሽ ሻማ ትለዋወጡ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ። ከዋዜማው ጀምራችሁ …. በእጃችን ባለ፤ ማድረግ በምንችለው አጋርነታችን አዳንቆታችን ምስጋናችን እንገልጽላት ዘንድ አሳስባለሁ። አብሶ ሴቶች ቅን ወንድሞቻችንም በዬቤታችን ሻማ እናበራለት ዘንድም እጠዬቃለሁ በጥር 21. 20014 … እንዳትረሱ አደራ! ፍቅራችሁን በፊርማችሁም ግለጹ …. አመሰግናችኋለሁ።
Facebook – just click here to share the petition on Facebook.
Here’s the link:

http://www.change.org/petitions/free-reeyot-alemu-imprisoned-award-winning-ethiopian-journalist-with-breast-tumour?share_id=tzbOCsHCEK&utm_campaign=signature_receipt&utm_medium=email&utm_source=share_petition

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


“ወደው አይስቁ”ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።
የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ። “የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። … የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።…”
በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። “የባሰ አታምጣ!” ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል። የሚናገሩትን አያውቁትም። የማየውቁትን ነገር ሁሉ ይናገራሉ። እነሱ የሚናገሩትን ደግሞ በምኒሊክ ቤተ-መንግስት ያሉ ሰዎቻቸው በተግባር ይፈጽሙላቸዋል።
ተናጋሪው የእለቱ የክብር እንግዳ መሆኑ ነው። በጉዳዩ ላይ ብዙ ጥናት እንዳደረገም አስቀድሞ ገለጻ ተደርጓል። ሰዎቹ የወንዶች ብልት መቆረጥን የፈጠራ ታሪክ ያነሱት ያለምክንያት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ጡትን በአደባባይ ያቆሙ እብዶች፣ የወንድ ብልትን አያቆሙም ማለት አንችልም። “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም!” ይላል የሃገሬ ሰው። ስለ አኖሌ የፈጠራ ውጤት በያዝነው አዲስ አመት አውርተን ሳንጨርስ፤ ይኸው የባሰ ነገር እየመጣ ነው። ምኒሊክ የወንድ ብልትምም ቆርጠዋል ነው እያሉን ያሉት – ጨዋታቸውን ሲያራዝሙት። አጼ ሚኒሊክ ለካ የጉጂ ኦሮሞ ኖረዋል። ትንሽ ቆይተው ጉጂዎች የወንድ ብልት መቁረጥ የተማሩት ከምኒሊክ ነው ይሉናል። እዚህ ላይ ሰዎቹ እየቀለዱ ብቻ አይደለም። እየቀለዱብንም ነው። ወዳጆቼ ግን አሁንም ሙድ ይዘዋል።…
በነዚህ ቀልደኞች ዘና እንል ይሆናል። አንድ የዘነጋነው ነገር አለ። የሴት ልጅ ጡት በአደባባይ ሃውልት የተሰራለት በእኛ ምድር ላይ ብቻ ነው። ይኸውም በእኛ ዘመን። ሴት ልጅ በሃገራችን ትከበራለች። የውስጥ አካልዋ እንዲህ በአደባባይ ላይ ሲውል ክብርዋን ይቀንሰዋል። የሴትን ልጅ ጡት በአደባባይ ላይ አውለው፤ ህጻናትና አዋቂው እንዲመለከተው ማድረግ በባህላችንም እጅግ ነውር ነገር ነው።
“ምሁሩ” የታሪክ ተንታኝ ንግግሩን በዚህ አላበቃም። ማብራራቱን እንደቀጠለ ነው። “…ይህንን ታሪክ ለማወቅ የታሪክ መጽሃፍ ማንበብ አይጠበቅባችሁም። በኢንሳይክሎፔዲያ ላይም ግዜያችሁን አታባክኑ። በቀላሉ ጉግል አደርጉና ታገኙታላችሁ… ” አለ። ጉግል ስናደርግ ይህንኑ መረጃ በራሱ ድረ-ገጽ ላይ ልናገኘው እንችል ይሆናል።
አጼ ምኒሊክ አምስት ሚሊዮን ጡት ቆርጠዋል ሲሉን ግን፤ ስሌቱ ላይ የቤት ስራቸውን በደንብ የሰሩት አይመስልም። በአጼ ምኒሊክ ዘመን አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ቁጥሩ ስምንት ሚሊዮን ነበር። የአምስቱ ሚሊየን ህዝብ ጡት ከተቆረጠ፣ በዘመኑ ወንዶቹም ጡት እንደነበራቸው ያመላክታል። ግን ያንን ሁሉ ጡት እንዴት ሊቆርጡት እንደቻሉ ተናጋሪው አላብራሩም። ስልጣኔን ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት አጼ ምኒሊክ በመጀመሪያ ያደረጉት የጡት መቁረጫ ማሽን ማስገባት መሆኑን ከጉግል ላይ በቅርቡ ሊገኝ ይችላል።
ጉግል፣ ጉግል፣ጉግል፣ጉግል፣…… እያለ መነጋገርያውን ለቆ ወረደ – የምኒሊክን አዲስ ታሪክ የሚያስተምረው።
“ሉሲ ኦሮሞ ናት። ጎንደርም ከኦሮሞ ላይ የተቀማች ሃገር እንደሆነች ጥናት አድርገን ጨርሰናል።… ይህንንም በቅርቡ ይፋ በሚሆነው ጥናት ታገኙታላችሁ… ።” የሚል ሌላ ተናጋሪ መድረኩን ይዞ ሲናገር ከማርስ የመጣ ፍጡር ነበር የመሰለን።
ጨርቁን ጥሎ እርቃኑን መንገድ ለመንገድ የሚሄድ፤ ወይንም ደግሞ እጅና እግሩ በሰንሰለት የታሰሩ ሰው ስናይ፤ በተለምዶ ይህ ሰው አብዷል እንላለን – ውጭውን ብቻ አይተን። ጥሩ ልብስ ለብሰው በስነልቦና እና በአእምሮ መታወክ የሚሰቃዩ እጅግ ብዙ እብዶች እንዳሉ ብዙውን ግዜ እንዘነጋለን። እንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች በቀን ቅዠት የሚሰቃዩ፣ የስነምግባርና የሞራል እስረኞች በመሆናቸው አእምሯቸው ይታወካል። በእውናቸው ይሁን በህልማቸው የአጼ ምኒሊክ ጣእረ ሞት እየመጣ እንቅልፍ እንደነሳቸው ግልጽ ነው።
ፓልቶክን ከሰባት አመታት በኋላ መስማቴ ነው። ይህን ትልቅ መድረክ፣ አንዳንዶች ታሪክ ሰርተውበታል። ሌሎች ታሪክ ሲያወሩበት ሰንብተዋል። እነሆ ዛሬ ደግሞ ታሪክ የሚያጎድፉ ጉዶች ይዘውታል። ከሰባት አመታት በኋላ የኛ ፓልቶክ ሽቅብ ሳይሆን ቁልቁል አድጎ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ቢገርመኝም፤ በአንጻሩ ግን እንደ አዝናኝም እየሆነ መምጣቱን አልጠላሁትም።
እንደሰማነው የፓልቶክ ርእሱ ላለፉት ሶስት ሳምንታት አልተቀየረም። የዛሬውም መነጋገርያ ርእስ ዳግማዊ ምኒሊክ ናቸው። እኚህ መሪ ካለፉ እነሆ መቶ አመት ሆናቸው። “የሞኝ ለቅሶ፣ መልሶ መላልሶ!” እንዲሉ አንዳንዶቹ ቀኑን ሙሉ ስለ አጼ ምኒሊክ አውርተው ሌሊቱንም ይመለሱበታል። ዛሬ ግን ወሬውም፣ ስድቡም ያለቀባቸው ይመስላል። ዛሬ ስለጀኖሳይድ እያወሩ አይደለም። ይልቁንም ጀኖሳይድ እያወሩ ነበር። ወንጀሉን ራሳቸው በቃል እየፈጸሙት…።
ሌላኛው ተናጋሪ ተራውን ጠብቆ መነጋገርያውን ያዘ። የተለመደውን የአጼ ምኒሊክን አጽም ከመቃብር እየጠራ ካወገዘ በኋላ፤ እንዲህ ሲል ተናገረ። “…አበበ ቢቂላን በባዶ እግሩ እንዲሮጥ አድርገው ታላቅ በደል ፈጽመውበታል።”
መቼም ወደው አይስቁ። እንዲህ አይነቶቹ ሰዎች እንኳ አይፈረድባቸውም። ገና ሃገር ሲለቅቁ የለቀቁ ስለሆኑ ለክርክርም አይመቹም። “አበበ ቢቂላ በሮም እና በቶክዮ ላይ የሮጠው በአጼ ምኒሊክ ዘመን ነው።” ብሎ ከሚከራከር ሰው ጋር ሙግት መግጠም እብደት ይሆናል።
“የቁቤ ትውልድ ነን።” የሚል ሌላ ታናጋሪ ደግሞ መጣ። ይሄኛው ደግሞ የቆሪጥ መንፈስ የሰፈረበት ሳይሆን አይቀርም። የሚያወራው ሁሉ ስለ መቁረጥ ብቻ ነው። ሚኒሊክ ጡት፣ እጅ፣ ቆለጥ፣ እግር፣ ጥፍር… ቆርጠዋል አለን። እንደታናጋሪው ከሆነ እኚህ መሪ ያልቆረጡት ብልት የለም። ሃገር ማስተዳደሩን ትተው አስራ ሁለቱንም የሰውነት አካል ሲበልቱ ኖሯል!
አርፍደው የሚገቡት ተሳዳቢዎች ከአፋቸው የሚወጣውን ጸያፍ ስድብ ለመድገም ይዘገንናል። በ”ምሁሮቻቸው” ገለጻ መሃል እንደ አዝማች ጣልቃ እየገቡ በአማራው ህዝብ ላይ ይወርዱበታል። በዚህ ሁሉ መሃል ትንሽ የገረመኝ አንድ ክስተት ነበር። የክፍሉ መሪ በስድድቡ መሃል ገብቶ በኦሮምኛ እንዲህ ሲል ተናገረ።
“ጀሪን ወል አኛተኑ። ማይኪ ኢቲ ኬኒ። ኑ ሂንደጌኛ”።
ወደ አማርኛው በግርድፉ ሲመለስ፣ “ማይኩን ስጣቸው። እነሱ እርስበርስ ይባሉ። እኛ እንሰማለን።” እንደማለት ነው። ዋናው ጨዋታ እዚህ ላይ ኖሯል። ምክንያቱም ይህንን ውግዘት እና ውርጅብኝ ሜንጫዎቹ ያለምክንያት በዚህ ሰዓት አላነሱትም። ነብሳቸውን ይማርና አፄ ምኒሊክ ካረፉ 100 አመት አለፈ። የሙት አመታቸው መከበር ከጀመረ ደግሞ 70 አመት ሆነው። ይህንን ወቅት ጠብቆ በአማራ እና በክርስትና እምነት ላይ ለመዝመት የሚደረገው ሙከራ፣ ግብታዊ ሳይሆን በጥናት የተደረገ ስለመሆኑ ያመላክተናል። ግርግር በመፍጠር እና ዜጎችን እርስበርስ በማባላት፣ ትንሽ የፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት የሚፈጸም የፖለቲካ ዝሙት መሆኑ ነው።
ልብ በሉ! የዚህ የሜንጫ ዘመቻ መሪዎች ኦሮሞዎች አይደሉም። አብዛኞቹ በግማሽ ከሌላ ዘር የሚወለዱ ናቸው። በእምነታቸውም ሆነ በዘራቸው የተቀላቀሉ ሰዎች ብዙውን ግዜ የማንነት ቀውስ ውስጥ ይገባሉ።
ስድስት ሚሊየን አይሁዶችን የፈጀው አዶልፍ ሂትለር ግማሽ አይሁድ እንደነበር አንዘንጋ።

ከቃሊቲና ቂሊንጦ እስር ቤቶች በላይ የሚያንጸባርቁ ከዋክብት –ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ) [ጋዜጠኛ]

$
0
0

(ይህ ጽሁፍ የርዕዮት አለሙ የልደት በአል በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት; ከውጭ አገር ንግግር እንዳደርግ በተጋበዝኩበት ወቅት… የስራ ባልደረቦቼን እስክንድር, ውብሸት እና ርዕዮትን በማሰብ የተዘጋጀ ነው)

ይህ ሳምንት የታላቁ ማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በመላ አሜሪካ የሚከበርበት ነው:: በአሜሪካ ከክርስቶስ ልደት ቀጥሎ ስራ እና ትምህርት ቤት ተዘግቶ ልደቱ የሚከበርለት አንድ ሰው ቢኖር ማርቲን ሉተር ኪንግ ብቻ መሆኑን ልብ ይበሉ:: የማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በሚከበርበት ወቅት በህይወት ዘመኑ ለጥቁር ህዝብ ነጻነት ያደረገው አስተዋፅኦ ይታወሳል:: በህይወት በነበረበት ወቅት ለሰው ልጅ እኩልነት ተሟግቷል; የነጻነት ቀንዲልን ለኩሷል:: ሆኖም እኩልነት እና ነጻነትን ሳያጣጥም በበርሚንግሃም እስር ቤት ተጥሎ ፍዳውን እንዲቆጥር ተፈርዶበት ነበር:: በመጨረሻም የሰውን ልጅ ክብር እና ነጻነት በማይደግፉ ሰዎች ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል – መልካም ስራዎቹ ግን አላለፉም::
reyot alemu
ዛሬም በአገራችን ስለፍትህ, ስለነጻነት የሰበኩና የደሰኮሩ; የጻፉና የመሰከሩ… ለሃቅ ቆመው፣ ግፍ የተሰራባቸው፣ ከአገር የተሰደዱና የወጡ፤ በግፍ ሰንሰለት ለጨለማ እስር የተዳረጉ ወገኖቻችን ብዙ ናቸው:: እስክንድር፣ ውብሸት፣ ርእዮት፣ አንዷለም እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን በሰብአዊነት መሰረት ላይ ስላነጹ እና ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ መጨረሻቸው እስር እና እንግልት ሆኗል::

እንደ እውነቱ ከሆነ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ… ብሎም የህዝብ ልሳን ሆኖ ለህዝብ የቤዛነት ዋጋ መክፈል የሚያስከብር እንጂ የሚያሳስር አልነበረም:: በመሆኑም ለነጻ ፕሬስ መክፈል የሚገባቸውን ዋጋ ከመጠን አሳልፈው የከፈሉት፤ ርዕዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ እና ውብሸት ታዬ… ሶስቱም ከአገራቸው አልፈው በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝተዋል:: በአለም አቀፍ ደረጃም በልዩ ልዩ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች ማህበራትና ተቅውውማት ለሽልማት ታጭተው አሸናፊ ሆነዋል::
የ’ነዚህ የስራ ባልደረቦቼ ብዕር… ህዝብን ሳይሆን የተወሰኑ ወገኖችን አሸብሮ ሊሆን ይችላል:: እነርዕዮት አለሙ በዚህ አይነት ሰበብ አስባብ በቃሊቲ እና በቂሊንጦ እስር ቤት ታግተው፤ ነጻነታቸውን አጥተውና ህክምና ተነፍገው ይታሰሩ እንጂ፤ ለእውነት የቆሙ ወገኖች ግን ለመልካም ስራቸው ሽልማትን አልነፈጓቸውም::

ማርቲን ሉተር ኪንግ በበርሚንግሃም እስር ቤት ታስሮ ቢማቅቅም የአሜሪካም ሆነ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አልዘነጋውም:: ቆይቶም ቢሆን የአለም አቀፉ ኖቤል ተሸላሚ እስከመሆን ደርሷል:: ዛሬ በእስር ላይ የሚገኙት የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች የኖቤል ተሸላሚ ባይሆኑም አለም ግን አልረሳቸውም:: ከታሰሩበት የጨለማ ወህኒ ቤት ጀርባ፤ ከብረት ፍርግርግ እና ከግድግዳዎቹ ባሻገር በመቶዎች፣ በሺዎች እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እነዚህን ጋዜጠኞች በመልካም ስራቸው ያስታውሷቸዋል; ይዘክሯቸዋል:: ስለሆነም የጻድቃን ሞት፤ የሰማዕትነት ጽድቅ ተደርጎ እንደሚቆጠረው ሁሉ… የነ እስክንድር፣ ውብሸትና ርዕዮት እስር፤ ከቶውኑ ዋጋ ቢስ እና ፍሬ አልባ ሊሆን አይችልም::

ኢትዮጵያ ውስጥ በነበርኩበት ወቅት በፕሬስ ጉዳይ ተደጋጋሚ የሆነ እስር ደርሶብኛል:: በ’ነዚህ የእስር እና እንግልት ጊዜያት ግን… ከጨለማው እስር ቤት ማዶ ለምን እንደታሰርኩ የሚረዱ ሺዎች በመኖራቸው ሁልጊዜ እጽናና ነበር:: በተደጋጋሚ እስር ቤት እየመጣ የሚጠይቀኝ እና የዋስ መብቴን አስጠብቆ ከእስር እንድወጣ ያደርገኝ የነበረው ወላጅ አባቴ፤ “የታሰርከው ሰርቀህ ወይም ሌላ ወንጀል ሰርተህ ሳይሆን፤ እውነትን ስለተናገርክ ነው:: ስለዚህ አንገትህን ቀና ልታደርግ እንጂ ልትሸማቀቅ አይገባህም::” የሚል አጽናኝ ቃል ሁሌ ይነግረኝ ነበር:: ዛሬ አባቴ በህይወት የለም:: ቃሉ እና ምክሩ ግን አብሮኝ አለ:: በእስር ላይ ለሚገኙ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ “አንገታችሁን ቀና አድርጉ!” የሚለውን መልዕክት አጋራቸዋለሁ::

ዛሬ በጋዜጠኞቻችን ላይ የተለያዩ ክሶች ተመስርቶባቸው መታሰራቸው ሳያንስ; ከታሰሩም በኋላ በሃሰት ሊወነጅሏቸው የሚሹ ብዙ ግራ ዘመም ሰዎች መኖራቸውን ታዝበናል:: በአሜሪካ ከፍተኛ የአየር ሽፋን አግኝቶ ዲሞክራቶችን በመሳደብ የሚታወቀው ራሽ ሊምቦ የተባለ ጋዜጠኛ በቅርቡ ኔልሰን ማንዴላ በሞት ሲለዩ… “ብታምኑም ባታምኑም ኔልሰን ማንዴላ አሸባሪ ነበሩ::” ብሎ ሰፊ ሙግት ፈጥሮ ነበር:: ይህ አባባሉ ለኛ እና ለሌሎች አፍሪቃውያን ሊገርመን ይችል ይሆናል:: ነገር ግን የራሳቸው አመዛዛኝ ህሊና ያልፈጠረባቸውና ይህን ሰው በጭፍን የሚከተሉት ሰዎች “አዎ ማንዴላ አሸባሪ ነበሩ” ብለው ቢሉ ሊገርመን አይገባም::

ዛሬም ባገራችን በተመሳሳይ መልኩ የነርዕዮት አለሙን መልካም ስም ጥላሸት ለመቀባት እላይ ታች የሚሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ… እኛ ግን እንላለን:: “ወንጀል አልሰራችሁምና አንገታችሁን ቀና አድርጉ!” ስማችሁ ከቃሊቲና ከቂሊንጦ እስር ቤቶች በላይ፤ በጠራው ሰማይ ላይ ያንጸባርቃል፤ ቃለ ሃቃቹህ በአየር ናኝቶ… ኢትዮጵያዊያን ባሉበት ሁሉ በመላው አለም ላይ ተሰራጭቷል::

የማርቲን ሉተር ኪንግ ልደት ሲከበር መልካም ስራዎቹ እንደሚወደሱ ሁሉ፤ ዛሬም ሆነ ወደፊት የነርእዮት አለሙ ልደት ሲከበር መልካም ስራዎቻቸው በተደጋጋሚ ይነሳሉ ይዘከራሉ:: ዛሬ ማንዴላን አሸባሪ ብለው የሚከሱ ሰዎች እንደመኖራቸው መጠን; በተመሳሳይ መልኩ ለነርእዮት አለሙ ተመሳሳይ ስም የሰጡና ያሰጡ… ለመስጠት እና ለማሰጠት የሚጥሩ ሰዎች አሉ:: እኛ ግን የተለኮሱ ሻማዎች ይዘን ልደት ስናከብር; የብርሃናችን ጮራ፤ ሌሎች የፈጠሩትን የጨለማ ድባብ ሰንጥቆ… አንዳች ብርሃን እንደሚፈነጥቅላቸው በማመን ነው:: ዛሬ የርዕዮት አለሙን የልደት ቀን ስናከብር፤ ያለፍትህ የታሰሩትን ፍትህ የሚፈልጉትን፤ ነጻነት የተጠሙትን ነፍሶች በማሰብ ጭምር ነው::
መልካም ልደት – ርዕዮት!

የሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ጉዳይ፡ ሰሞነኛ ክራሞት

$
0
0

saudi ethiopian boy
ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

ከመሰንበቻው …

በጅዳና በሪያድ መጠለያዎች …

* ባለፉት ቀናትም እንደ ክራሞቴ እኔን ጨምሮ የሳውዲ መንግስትና የእኛ መንግስት ተወካዮች “እጃችሁን ሰጥታችሁ ወደ ሃገር ለመግባት እጅ ስጡ ፣ ወደ ሃገር ግቡ! ” ስንል ወትውተን ወደ መጠለያ ያስገባናቸው በርካታዎች በጅዳ ሽሜሲ መጠለያ እና በሪያድ እስር ቤቶች ሮሯቸውን እየደወሉ ገልጸውልኛል። እኒሁ በመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ ነገር ግን የመኖሪያ ፈቃዳቸው የተበላሸባቸው ፣ ከአሰሪዎቻቸው ጋር የማይሰሩ እና በኮንትራት ሰራ መጥተው የሳውዲው የስደት ኑሮ ያላማራቸው “ወደ ሃገር እንግባ ብለን እጅ ሰጥተን ተሰቃየን “ብለውኛል ።እኒሁ ቁጥራው በውል ማረጋገጥ ያልቻልኩት ወገኖች ወደ ሃገር ለመግባት ቢፈልጉም በሳውዲም ሆነ በኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በኩል መፍትሔ የሚሰጣቸው አጥተው ከወር በዘለቀ ጊዜ እንግልት እንደደረሰባቸው በምሬት ያስረዳሉ!

ለመናገር የሚከብደው አሰቃቂ ወንጀል ..

* ከትናነት በስቲያ ረቡዕ ማታ በስጨትጨት ያደረገኝን ወሬ ሹክ ያለኝ አንድ ከበድ ያለ መረጃ ሲደርሰው ብቻ “ሃሎ ” የሚለኝ ወዳጀ ነበር። አንድ የ7 አመት ታዳጊ በገዛ አባቱ የተፈጸመበት አሰቃቂ ወንጀል አሳፋሪ ነው ብቻ ተብሎ አይታለፍም ። ብቻ በዚህም ተብሎ በዚያ ጉዳዩን ወደ ፖሊስ ለማድረስ በተደረገው ርብርብ ወዳጆቸ ያደረጉት ትብበር ያኮራ ነበር ። ረቡዕ እኩለ ሌሊት መረጃው ደረሰኝ ። ሃሙስ በማለዳውም ጉዳዩን ቆንስል ሙንትሃ ሲነገራቸው የሆኑትንና የመስሪያ ቤታቸው ወንጀለኛውን ሱዳናዊ ባለጌ አባት ወደ ፍርድ ለማቅረብ ለፖሊስ ደብዳቤ በመጻፉ ረገድ ያልተለመደ ቀልጣፋ ትብብርንም ደንቆኝ አመስግኛለሁ! ከባለጉዳዩዋ ኢትዮጵያዊ ልበ ደንዳ እናት ጎን በመሆን ወዳጀ ” ሸሁና” ዘንድሮ በምትሰራውን መልካም ስራ የማውቃት አንዲት ወዳጀ የሰሩት አኩሪ ትብብርም አኩርቶኛል። ወገን ለወገን እንዲህ ሲደጋገፍ ፣ ሰብዕና ሲደፈር በህጻናት ላይ አስነዋሪ ወንጀል ሲፈጸም እንዲህ ተግቶ ለወገን አለኝታ የሚሆኑ ጥቂት ለሆዳቸው ብቻ ያላደሩ ለህሊናቸው የሚሰሩ በጣም ጥቂት ወገኖችን ማየት በእርግጥም ያስደስታል። ከቀትር በኋላ እናት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ ክስ ስታቀርብ የገጠማት ቢያናድድም አይገርምም! የሆነው እየቆየሁ ሳስበው ግን ” ወዴት እየሄድን ነው! ” ስል ራሴን እንድጠይቅ አድርጎኝ ፣ አስደምሞኝ አመሸ .. !. ክሱን ተቀባይ ወታደር ” በልጀ ላይ በደል ፈጸመ !” ብላ ፍትህን ፈልጋ የሄደች እናት ባሏ ከሰራው ወንጀል ክብደት አንጻር የሚከተለውን ፍርድ ሃይለኛነት በመግለጽ ክስ አቅራቢዋን “በባልሽ ላይ ይህንን ከባድ ክስ ከመመስረትሽ በፊት አስቢበት !” ብሎ ህግ አስከባሪው እናት ከሁለት ቀን በኋላ አስባ ክሷን ለመመስረት እንድትመጣ መክሮ እንደመለሳት ሰማሁ ! ትናነት ሃሙስ …! ወቸ ጉድ … አልኩ የምለው ባጣ … ተናድጀ !

የውጭ ጉዳይ ሃላፊዎች ሽኝትና በጅዳ ቆንስል የጊዜያዊ ሰራተኞች ስንብት

* ከሁለት ወራት ወዲህ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተልከው በሪያድ እና በጅዳ መጠለያዎች ድጋፍ ሲያደርጉ የከረሙ ዲፕሎማቶች ወደ ሃገር ቤት መመለስ ጀምረዋል ። ችግሩ አለቀ እንዴ ? በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተልከው መጡ የተባሉትስ ሁሉ ቢቀር ለምን የነዋሪውን ሮሮ ሰብስበው ሳይሰሙት ሄዱ? በማለት ብዙዎች ጠይቀናል ። መልስ ግን የለም ! ስብሰባ ሲነሳ በወገን ችግር ሰብስቡን እያልን የምንለውን ጩኸት ባይሰሙትም የጉራጌ ልማት ማህበር አመታዊ ሪፖርት ሊያቀርብ በጠራው ስብሰባ አንድ በቅርቡ የሚሸኙ ልዑክ ከሪያድ መጥተው ከስብሰባው ተካፋይ እንደሚሆኑ በሹክሹክታ ተሰምቷል ። በጉራጌ ማህበሩ ስብሰባ የጨነቀውን ወገን ሮሮ ተሰምቶ ምክክር ቢደረግበትም አይከፋም ። ወዳጆቻችን የጉራጌ ተወላጆች “ነዋሪው ሰብስቡን !” ሲል አልሰማ ያሉትን ሃላፊዎችን በነዋሪውን ጉዳይ ዙሪያ ለማነጋገሩ ብርታቱን ይስጣቸው ብለን እንጸልይ !

የጅዳ ቆንስልም በተመላሽ ወገኖችን ሽኝት ለማሳለጥ በጊዜያዊነት ተቀጥረው የነበሩ በማስታወቂያ ተነግሮ የተቀጠሩ አልነበሩም ። በዋናነት በኢህአዴግ ድርጅት ፣ በማህበራታና ለመንግስት ቅርበት ባላቸው ግለሰቦች ጠቋሚነት ተቀጥረው በቆንስሉ ስር ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞችን ቆንስሉ ማሰናበቱን እየሰማን እያየን ነው! ለመንግስት እና ለቆንስላው ከባባድ ሃ ፊዎች ካላቸው ቅርበት ብቻ ሳይሆን በኢህአዴግ ድርጅት አባልነት ፣ ደጋፊነት እና ተሰሚነት ባላቸው ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጠቋሚነት በጅዳ ቆንስል ተቀጥረው የነበሩት ወገኖች በስራቸው ያሳዩት ትምክህት ቢያናድድም አንዳንዶች በዚያ ክፉ ቀን ለወገን ያደረጉት ትብብር የሚመሰገን እንደ ነበር መናገር እወዳለሁ! ይህ የግል አስታያየቴ ነው!

ሹክሹክታው ሁሉ ከሹክሹክታ ያለፈ በጭብጥ መረጃ የተደገፈ ለመሆኑ አንድታምኑኝ አልማጸናችሁም ! መረጃ የማቀብላችሁ የመረጃ ክፍተቱን ለመዝጋትና ስለ እውነት ነውና እመኑኝ ! በቃ ! ሌላ የምለው የለም!

ሰላም

ይድረስ ለጓድ መንግሥቱ ኃ/ማርያም

$
0
0

ከወልደ ቴዎፍሎስ (ኦታዋ፡ ካናዳ)
tewoflos2013@gmail.com
“የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”
ትንቢተ ኢዩኤል 2፡32፤ ሮሜ 10፡13.

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት እና የደርግ ሊቀመንበር ጓድ መንግሥቱ ኃ/ማርያም፡ ባሉበት በሐራሬ ዝምቧብዌ ለጤናዎ እንደምን ከረሙ? መቼም “ጓድ” ብዬ ስጠራዎ ደስታ እንጂ ቅሬት እንደማይሰማዎ እርግጠኛ ነኝ፤ ይህን መጠሪያ ስለሚወዱት፡ የትግል አጋርዎችዎን ብቻ ሳይሆን ውድ ባለቤትዎንም “ጓድ” ብለው ለመጥራት ወደኋላ አላሉምና (ትግላችን፤ “ምስጋና” ገጽ ፭)።
mengistu hailemariam
“ትግላችን፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ” የተሰኘው መጽሐፍዎ ለህትመት ከበቃ ዓመት ከመንፈቅ ቢሆነውም፡ ሰሞኑን እጄ ገብቶ አነበብኩት። እኔ ያነበብኩት ለአምስተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ በሐምሌ ወር 2004 ዓ.ም. የታተመውን ሲሆን፡ መጽሐፉ ብዙ ጥያቄዎችን ቢፈጥርብኝም ርዕሴ እንደሚያመለክተው በመረጥኩት ጉዳይ ላይ ብቻ ይህን አጭር ጦማር ልጽፍልዎ ወደድሁ።

የተወለድኩት እርስዎ እና መሰሎችዎ በኢትዮጵያ የፊውዳሉን ሥርዓት በገረሰሳችሁበት ዓመት ነው። ስለዚህ በዕድሜ አሳምረው አባቴ መሆን ይችላሉ። እንዲያውም ከመጽሐፍዎ ስለእርስዎ ዕድሜ እንደተረዳሁት ከወላጅ አባቴ በ5 ዓመት ይበልጣሉ። “ውሃ ሽቅብ አይፈስም” እንዲሉ ኢትዮጵያዊው ጨዋ ባህላችን እንዳስተማረን ልጆች በአባቶቻቸው ላይ ሂስ (ነቀፋ) መሰንዘር ባይችሉም፡ እንደ አንድ የ72 ዓመት (ካልተሳሳትኩ) ኢትዮጵያዊ አዛውንት እርስዎን በማክበር፡ ከይቅርታ ጋር መጠነኛ ምክር ልለግስዎ ወደድሁ። መቼም “በአብዮቱ ፍንዳታ ወቅት የተወለደ ልጅ እንዴት እኔን ይመክራል?”፤ “ወይኔ መንግሥቱ ተደፈርኩ!” በማለት ዘራፍ እንደማይሉ ተስፋ አደርጋለሁ። ይህን አነስተኛ ጦማር ለተለያዩ ድህረ ገጾች ለመላክ ስላሰብኩም፡ መጣጥፌን አንብበው በጽሑፍ መልስ ቢሰጡኝ ደስ ይለኛል።
ይህ ጦማር የመጽሐፍዎ አጠቃላይ ቅኝት (Book Review) ወይም ግምገማ ስላልሆነ፡ በመጽሐፉ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ አስተያየት አልሰጥም። ነገር ግን ወደፊት በሚያዘጋጇቸው ተከታታይ ቅጾች ላይ ያካትቷቸው ዘንድ፡ የተወሰኑ ነጥቦችን ልጠቁም፤
- እስካሁን ድረስ የብዙ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ የሆነው፡ 60ዎቹ የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘግናኝ በሆነ መልኩ ያለፍርድ የተገደሉበትን ሁኔታ መጽሐፍዎ በዝርዝር አይዳስስም። አንባቢዎችዎን ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ ከሌ/ጄነራል አማን ሚካኤል አንዶም አሟሟት ጋር በማያያዝ ይህን ዐቢይ ጉዳይ በአንድ ፓራግራፍ ብቻ ነው ያለፉት (ትግላችን፡ ገጽ 219)።

- ስለ ብ/ጄነራል ተፈሪ ባንቲ ግድያ በመጽሐፍዎ ምንም ነገር አልነገሩንም። ገጽ 253 ላይ ግን፡ ስለ እኚሁ ጄነራል ማንነት በቅጽ 2 እንደሚጽፉ ስላሳወቁን ይህን በተስፋ እንጠብቃለን።

- ስለ አፄ ኃይለሥላሴ እና ስለ ሌ/ኮሎኔል አጥናፉ አባተ አሟሟት (ግድያ) የተረኩት ትረካ፡ በወቅቱ በሕይወት የነበሩ እና እውነታውን የሚያውቁ ኢትዮጵያውያንን ቀርቶ ከአብዮቱ ፍንዳታ በኋላ የተወለድኩትን እና ስለወቅቱ ቀውጢ ሁኔታ ምንም የማላውቀውን እኔን እንኳ አላሳመነኝም። በመካከላችሁ በነበረው የሥልጣን ፉክክር ምክንያት ኮሎኔል አጥናፉን ከጄነራል ተፈሪ ባንቲ ጋር የእርስዎ ከሳሽ (ገጽ 246) እንዲሁም መስከረም 13/1969 ዓ.ም. የተሞከረብዎ ግድያ “ፈጣሪ፤ መሪ እና ተጠርጣሪ” (ገጽ 250) አድርገው ያስቡ ስለነበር፡ ኮሎኔል አጥናፉ በተወሰደባቸው አብዮታዊ እርምጃ የእርስዎ እጅ ወይም ግፊት የለበትም ብሎ ማሰብ ጥበብ የጎደለው የዋህነት ይመስለኛል። የአፄ ኃይለሥላሴ እና የጄነራል ተፈሪ ባንቲ ህልፈተ ሕይወት ጉዳይም እንዲሁ።

ሞት ይርሳኝ፡ የተነሳሁበትን ጉዳይ ረሳሁት እንዴ? አይ አልረሳሁትም፤ ጥቆማዬ አላልቅ ብሎኝ ነው እንጂ። ከላይ ያነሳኋቸውን ነጥቦች አብዛኞቹ የመጽሐፍዎ አንባቢዎች ይጋሩታል ብዬ አስባለሁ። አሁን ደግሞ የጦማሬ ርዕስ ወደሚያጠነጥንበት ጉዳይ ከመግባቴ በፊት በቅጽ 2 መጽሐፍዎ እንዲመልሱልኝ የምፈልጋቸውን የግሌን ጥያቄዎች ላቅርብ፤

- እርስዎ እና ባልደረቦችዎ የተከተላችሁት የኮሚኒስት ሥርዓት፡ በእግዚአብሔር ሕልውና በማያምኑ ሰዎች (atheists) የሚመራ ስለሆነ አንድ ሰፊ ሕዝብን ለማስተዳደር የሕዝቡን የእምነት ተቋማት በመቆጣጠር ላይ ያተኩራል። ይህ አባባል የራሽያ ኮሚኒስት ሥርዓት በራሽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፤ እርስዎ የመሩት ተመሳሳይ ሥርዓት ደግሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ባደረሷቸው ተጽዕኖዎች ይረጋገጣል። ታዲያ በቅጽ 1 መጽሐፍዎ፡ ደርግ የኢትዮጵያ መኩሪያ ከሆነችው ከጥንታዊቷ እና የአገሪቱ ብሔራዊት ቤተክርስቲያን ተብላ ልትጠራ ከሚገባት (ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን) ጋር ስለነበረው ግንኙነት ምንም ነገር ያልነገሩን ለምንድን ነው?
- በወቅቱ የነበሩት የቤተክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን በመጽሐፍዎ ያነሷቸው በአፄ ኃይለሥላሴ ጸሎተ ፍትሐት ጉዳይ ላይ ብቻ ነው (ገጽ 271)። እባክዎን የተከበሩ ኮሎኔል መንግሥቱ፡ በሞቴ ልበልዎና ፓትርያርክ ቴዎፍሎስን ማን እንደገደላቸው በክፍል 2 መጽሐፍዎ ይንገሩን።
- አያይዘው ደግሞ፡ ከፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ግድያ በኋላ እርሳቸውን የተኳቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ-ሃይማኖት እንዴት እንደተሾሙ በዚሁ በቅጽ 2 ቢያብራሩልን ምስጋናዬ የላቀ ነው። መቼም ጓድ ሊቀመንበር፡ “እኔ ስለ ቤተክርስቲያኒቱ ፓትርያርኮች የማውቀው ነገር የለም” የሚሉ ከሆነ፡ አኔም ሆንኩ ሌሎች አንባቢዎች በጣም ነው የምንታዘብዎ።

ቅጽ አንድን ሳነብ፡ ከ50 እና ከ30 ዓመታት በፊት የተፈጸሙ ነገሮችን በዝርዝር የማስታወስ ችሎታዎን በጣም አድንቄያለሁ። እርስዎ የ20 ዓመት ወጣት መኰንን ሳሉ ስለገጠምዎት ጉዳዮችም ሆነ የፊውዳሉን ሥርዓት በገረሰሳችሁበት ጊዜ (ያኔ እርስዎ የ34 ዓመት ጎልማሳ ነበሩ) ስለተፈጠሩ ሁኔታዎች ያወጉን በሚገርም መልኩ ጠለቅ ካሉ መረጃዎች ጋር ነው። ጉዳዮቹ የተፈጸሙባቸውን ቦታዎች ከረጅም ዓመታት በኋላ እንኳን ቢሆን በፍጹም አልረሱም፤ በአካባቢዎ የነበሩትን ጓዶች ደግሞ፡ ከነማዕረጋቸው እና የአባት ስሞቻቸው ጭምር ላፍታ እንኳ አልዘነጓቸውም። ታዲያ በተፈጥሮ ስለተለገሱት ንቃተ ኅሊናም ሆነ የማስታወስ ከፍተኛ ችሎታ “የፍጥረታት ፈጣሪ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን” ብል በአባባሌ አይስማሙም?

መቼም የ72 ዓመት አረጋዊ ሆነው “የምን እግዚአብሔር አመጣህብኝ?” እንደማይሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ተስፋ እና ምኞት አይከለከልም፡ አይደል? “ኢትዮጵያ ትቅደም” የምትለዋን መፈክር በጥቁር ሰሌዳ ላይ ለደርጉ አባላት ከጻፉበት ጊዜ ጀምሮ፡ እንደ ታላቁ ኢታዮጵያዊ ጀግና አፄ ቴዎድሮስ እስከመጨረሻዋ ጥይት ሳይዋጉ ወደ ሐራሬ እስከኮበለሉበት ግንቦት 1983 ዓ.ም. ድረስ የእግዚአብሔርን ስም በስህተት እንኳ ሲጠሩ አልሰማንም። እኔ እና የእኔ ትውልድ ያደግነው የሚያንባርቅ እና እሳት የሚተፋ የሚመስል ድምጽዎን በሬድዮ እየሰማን ሲሆን፡ ክርስትናን በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተቀበለች የታላቂቱ ኢትዮጵያ ርዕሰ-ብሔር እንደመሆንዎ የልዑል እግዚአብሔርን ስም በንግግርዎ መሀል ሲጠቅሱ ለመስማት አልታደልንም። የዚህ ምክንያቱ፡ ለቆሙለት የማርክሲስት ሌኒኒስት ርዕዮት (አመለካከት) ታማኝ ለመሆን ብለው ነው ወይስ ስለ ሀልዎተ እግዚአብሔር “እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” (መዝሙረ ዳዊት 67፡31) ከተባለላት ከኢትዮጵያችን የተማሩት ምንም ነገር ስላልነበር?

ወላጅ አባትዎ አቶ ኃ/ማርያም (ይቅርታ ሌላ የማዕረግ ስም ካላቸው) ስለፈጣሪ ምንም ነገር ሳይነግርዎ ነው ያሳደጉዎት ብዬ ላስብ አልችልም። ለመሆኑ እርስዎ በልጅነትዎ ፊደል ሲቆጥሩም ሆነ ቄስ ትምህርት ቤት ገብተው ዳዊት ሲደግሙ (እንደደገሙ በመገመት ነው) የተማሩት የዳዊት መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ምን እንደሚል አስበው ያውቃሉ? ወይስ ይኸው የዳዊት መዝሙር “ይብል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር – ሰነፍ በልቡ ‘እግዚአብሔር የለም’ ይላል” ስለሚል (መዝ ፲፫፡ ፩) በልብዎ ‘እግዚአብሔር የለም’ እያሉ አድገው፡ ወታደራዊ ሳይንስ በሚማሩበት ጊዜ ይህን አመለካከትዎን አጸኑት? የደርግ ቁንጮ ለመሆን በቅተው “ጓድ ሊቀመንበር” ከተባሉ በኋላ ደግሞ በእግዚአብሔር መኖር እንደማያምኑ በተግባር አሳዩን። ይህንን የምለው፡ ሌላውን እንተወውና “እግዚአብሔር ያያል፤ ኃያሉ አምላክ ይፈርድብኛል” ብሎ የሚያስብ አንድ ግለሰብ፡ ቢያንስ ንፁህ ደም በግፍ ከማፍሰስ ይቆጠባል ብዬ ስለማምን ነው። ሌ/ኮሎኔል አጥናፉ አባተ እውነት በሆነው፡ ግን ለሞት ባበቃቸው ንግግራቸው እንዳሉት፡ እርስዎ እና መሰሎችዎ “ከአገራችን ባህል፤ [ሃ]ይማኖትና ታሪክ ጋር ፈፅሞ የማይገጥምና የማይስማማ የሶሻሊስት ሥርዓት እንከተላለን [ብላችሁ] አገሪቱን የጦርነት አውድማ [አደረጋችኋት]” (ትግላችን፡ ገጽ 254)። ተቆጡ እንዴ ጓድ ሊቀመንበር? ምን ይደረግ እንግዲህ፤ “እውነቱ ሲነገር ይጎዳል” ይባል የለ?

በቅጽ አንድ መጽሐፍዎ የኢትዮጵያን የቀድሞ አፄዎች ለአገሪቱ ካከናወኗቸው ዐበይት ተግባራት አንፃር ያወዳድሯቸው ነበር። አፄ ቴዎድሮስ የመሳፍንቱን “ከፋፍለህ ግዛ” ሥርዓት አስወግደው አንዲት ኢትዮጵያን ለመመሥረት ባደረጉት ጥረት ማንም እንደማይስተካከላቸው፤ የአፄ ዮሐንስን መንፈሳዊ መሪነት፤ አፄ ምኒልክ ትምህርትን እና አንዳንድ ሳይንሳዊ ውጤቶችን ወደ አገሪቱ በማስገባት የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ መሐንዲስ ቢሆኑም የባሪያ ንግድን እና የገበሬውን ጭቆና ማስወገድ ስላለመቻላቸው፤ አፄ ኃይለሥላሴ ቀድመዋቸው ከነበሩት ነገሥታት በተለየ መልኩ የትምህርት እድል ስለገጠማቸው፡ ታላላቅ የፖለቲካ እመርታ የተሰኙ ሥራዎችን እንዳከናወኑ እና የእርሳቸው ዘመን ከደረሰበት የ እድገት ደረጃ አንፃር እርሳቸውን ከቀደምቶቻቸው አፄዎች ጋር ማወዳደር እንደማይቻል አስረድተውናል።

እስኪ እኔ ደግሞ በርእሴ ጉዳይ ላይ ብቻ እርስዎን ከመጨረሻው የዘውድ አገዛዝ መሪ (አፄ ኃይለሥላሴ) ጋር ለማወዳደር ልሞክር። አፄ ኃይለሥላሴ፡ እግዚአብሔርን የሚያውቁ እና የሚያምኑ መሪ እንደነበሩ ወደሌላ ዝርዝር ሳልገባ ከእርስዎ መጽሐፍ በመጥቀስ ብቻ ማረጋገጥ ይቻላል። ከዙፋናቸው ካወረዳችኋቸው በኋላ ወደ ማረፊያ ክፍል ተወስደው፡ እርስዎ “የጎደለ ነገር ካለ ለማሟላት ዝግጁ ነን” ሲሏቸው “ምንም አይደል፤ እግዚአብሔር እንደፈቀደ እንኖራለን” እንዳሉ ነግረውናል (ትግላችን፡ ገጽ 189)። ይህ ሁሉ ለደህንነታቸው እንደተረገ ሲነገሯቸውም፡ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት ባንጸባረቀ መልኩ “ለደህንነታችንም የሚያውቀው ሁሉን የሚችለው አንድ አምላክ ብቻ ነው” በማለት መለሱ (ትግላችን፡ ገጽ 189)። በዚሁ ገጽ ላይ ከክብራቸው በተዋረዱባት በዚያች ቀን መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው እንደነበርም ዘግበዋል። ከዚህ በመነሳት አፄ ኃይለሥላሴ እንደ ታላላቆቹ የአሜሪካ መሪዎች (አብርሐም ሊንከን እና ሩስቬልት) መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነቡ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ለሰው ዘር ያስተላለፈውን መልዕክት ከያዘው ከታላቁ የሕይወት መጽሐፍ ጋር የሚተዋወቁ መሪ እንደነበሩ ለመረዳት ይቻላል።

እርስዎ ግን 17ቱን የመሪነት ዘመንዎ በጦርነት ተወጥረው ስላሳለፉ እና ደግሞም ጊዜ ቢኖርዎት እንኳ ለማንበብ የሚመርጡት የኮሚኒዝም ፍልስፍና መጻሕፍትን ስለሆነ ቅዱሱን መጽሐፍ ያነበቡ አይመስለኝም። በግንቦት ወር 1983 ዓ.ም. አስቀድመው በተዋዋሉበት መንገድ ወደ ዝምቧብዌ ካመለጡ በኋላ ላለፉት 22 ዓመታት በፍጥረታት ፈጣሪ በሕያው እግዚአብሔር ላይ ያለዎት እምነት ምን እንደሆነ አይታወቅም። “ትግላችን…” የተሰኘው መጽሐፍዎ ግን በባዕድ አገር ሁሉንም ነገር በሰከነ መንፈስ ማሰብ በሚችሉበት ሁኔታ እየኖሩ እንኳን፡ የእምነት ሰው ወደመሆን እንዳልተቀየሩ በመጠኑም ቢሆን ያመለክታል። መጽሐፉን ከጥግ እስከ ጥግ ያነበበ ማንኛውም አንባቢ፡ አብዮታዊው እና ተራማጁ ጓድ መንግሥቱ በስደት አገርም ቢሆን ምንም አይነት የዓላማ እና የአመለካከት ለውጥ እንዳላደረጉ ይገነዘባል።

መጽሐፍዎ “አብዮት፤ አድኃሪ፤ ጭሰኛ፤ ጉልተኛ፤ ከበርቴ፤ ምንደኛ፤ ገንጣይ፤ አስገንጣይ፤ ወያኔ፤ ባንዳ፤ ሠራዊት፤ ብርጌድ፤ ጦርነት፤ እዝ፤ ጠገግ፤ ሜካናይዝድ ጦር ወዘተ.” በሚሉ አብዮታዊ እና ወታደራዊ ቃላት የተመላ ሲሆን፡ “እምነት፤ ተስፋ፤ ፍቅር፤ ይቅርታ፤ ምሕረት፤ ቸርነት፤ በጎነት” የተሰኙት ውብ ቃላት መጽሐፍዎ ውስጥ በመብራት ቢፈለጉ እንኳ ለማግኘት ያዳግታል። አማኝ ወደ መሆን እንዳልተቀየሩ ከሚጠቁሙት አገላለጾች መካከል፡ ገጽ 55 ላይ ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን “የምድር ገነት” እያለ ይጠራት እንደነበር ገልጸው፡ በዚህ አጠራር ላይ ያለዎትን አመለካከት “ገነት የሚባል ነገር ካለ…” በማለት አሳይተዋል። ምናልባት መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ጊዜ ቢኖርዎት ኖሮ፡ ሙሶሎኒ ምድረ ኢትዮጵያን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመጀመሪያው መጽሐፍ (ኦሪት ዘፍጥረት 2፡8) “የኤደን ገነት” ተብሎ ከተጠቀሰው ቦታ ጋር እንዳነጻጸራት መግለጽ ይችሉ ነበር። ደግሞም ይኸው መጽሐፍ “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል” (ኦ. ዘፍ 2፡13) ስለሚል የሙሶሎኒ ስያሜ ትርጉም ሊገባዎ ይችል ነበር። በሙሶሎኒ ስያሜ ላይ ከሰጡት አስተያየት የተረዳሁት ነገር ቢኖር፡ ገነት፤ ሲኦል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት (መንግሥተ ሰማያት) የሚባሉ ነገሮች እንዳሉ አለማመንዎን ነው።

በእግዚአብሔር ህልውና እና ለሰው ዘሮች ባለው ጥባቆቱ (መግቦቱ) እስካሁን ድረስ እንደማያምኑ የተረዳሁበት ሌላው የመጽሐፍዎ ክፍል ደግሞ፡ መስከረም 13/1969 ዓ.ም. ከተደረገብዎ የግድያ ሙከራ የተረፉበትን ምክንያት ሲያስረዱ፡ “ያንን ሁሉ ጥይት ሲያፈስብን እኛን ሊፈጀን ያልቻለው፡ አንደኛ የላንድሮቨሩ ተጠባባቂ ጎማ ከኋላ ከበሩ ጋር ተያይዞ የተቀመጠ በመሆኑ ስለተከላከለልን፤ ሁለተኛ አሉሚኒየም የሆነ ወፍራም የመኪናው ገላና እንዲሁም የመኪናው የኋላ መቀመጫ ጥቅልል ሽቦዎችና ስፖንጆቹ ጥይቶቹን ውጠው እየቀነሱና እያበ[ረ]ዱልን ነው” የሚለው ነው (ትግላችን፡ 7ጽ 248)። ይህ ሁሉ ዝባዝንኬ ውስጥ ከመግባት “እግዚአብሔር አትርፎን ነው” ቢሉ ምን ነበረበት? እዚህ ላይ መልስ ከሰጡኝ፡ እንዲመልሱልኝ የምፈልገውን አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ልጠይቅዎ፤ እርስዎም ሆኑ ባልደረቦችዎ የደርግ አባላት በሀልዎተ እግዚአብሔር የማታምኑ የሶሻሊዝም ፖለቲካዊ ርዕዮት ተከታዮች ሆናችሁ ሳለ፡ ላለመከዳዳት በገባችሁት ቃለ መሐላ ውስጥ ለምንድን ነው “በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ” የሚል ዐረፍተ ነገር የጨመራችሁት? (ትግላችን፡ ገጽ 171)።

የተከበሩ ኮሎኔል መንግሥቱ፡ ይቅርታው እና ምሕረቱ የበዛ ቸሩ እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሐ ስለሰጠዎ፡ በብዙ ጥይቶች መካከል አልፈው፤ ምድራዊ ፍርድንም አምልጠው እስካሁን በሕይወት ይገኛሉ። በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በዘር ማጥፋት ወንጀል ከስሶ ስለፈረደብዎ፡ በመሪነት ዘመንዎ የሠሩትን ሁሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ እያማከሩ የሠሩ ይመስል ፍርዱን በሕዝቡ ላይ የተፈረደ ነው በሚል መንፈስ፡ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘር አጥፊና የጦር ወንጀለኛ ተብሎ መፈረጁን በመስማቴ ለታሪክና ለሕዝቡ የተተወውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ እኔ እራሴ ለመጻፍ ተገደድኩ” ብለውናል (ትግላችን፡ ገጽ 5)። ፍርዱ አበሳጭቶዎት 500 ገጾችን የያዘ መጽሐፍ ስለጻፉ፡ እርስዎ ላይ ያደረሰውን አዎንታዊ ተጽዕኖ እረዳለሁ። ነገር ግን በሰከነ እና በተረጋጋ መንፈስ ማሰብ በሚችሉበት የኑሮ ሁኔታ እና የዕድሜ ክልል ውስጥ ሆነው ሳለ፡ በመሪነት ዘመንዎ በፍጹም ስህተት ሰርቻለሁ ብለው አያምኑም። በመጽሐፍዎ የመጸጸትም ሆነ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ የመጠይቅን ዝንባሌ አንድም ቦታ አላሳዩም። አቋምዎ አሁንም ‘አብዮት ልጇን ስለምትበላ የአብዮቱ ተጻራሪዎች እርምጃ ተወሰደባቸው (ተወገዱ)፤ እንዲሁም በወቅታዊው አጣብቂኝ እና አስገዳጅ ሁኔታዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት እና ዕድገት ስንል አስፈላጊ ውሳኔዎችን ወሰንን’ የሚል ይመስላል።

ከሞት በኋላ ሕይወት (ያውም ዘለዓለማዊ) እንዳለ የሚያምኑ ከሆነ ግን፤ የኢትዮጵያ የቀድሞ መሪዎች ጽዋቸው ሞልቶ በሞት እንደተጠሩ፡ እርስዎም አንድ ቀን ይጠሩና ነፍስዎ ወደ ፈጣሪዋ ልዑል እግዚአብሔር ትመለሳለች (መጽሐፈ መክብብ 12፡7)። “የእግዚአብሔር እስትንፋስ” በመባል የሚታወቀው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳን “ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን” (2 ቆሮንቶስ 5፡10)። የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ የሆነው ጌታም ለፍርድ ዳግም እንደሚመጣ እና ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው እንደሚከፍለው ነግሮናል (ራዕየ ዮሐንስ 22፡12)። በእግዚአብሔር የተወሰነልዎ የዕድሜ ገደብ አብቅቶ በአካለ ነፍስ በክርስቶስ ዙፋን ፊት ቆመው በሕይወት ዘመንዎ ስለሰሩት ነገር ሁሉ ከመጠየቅዎ በፊት፡ ቃሉ “ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ፤ ንስሐ ግባ፤ ያለበለዚያ ፈጥኜ እመጣብሀለሁ” (ራዕየ ዮሐንስ 2፡5) ይላልና ዛሬውኑ ከሕሊናዎ ጋር ተማክረው ወደ እግዚአብሔር ልብዎን ይመልሱ። “አባታችን ሆይ…” ብለን እንድንጠራው የፈቀደልን መሐሪው አምላክ፡ ልጆቹ በ11ኛው ሰዓት (የዕድሜያቸው መገባደጃ) ላይም ቢሆን በንስሐ ቢመለሱ በፍቅር ይቀበላቸዋልና “አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ” ይበሉት (መዝሙረ ዳዊት 50፡1)።

በምሕረቱ ባለጸጋ የሆነው እውነተኛው አምላክ፡ የእርሱን ምሕረት እና ይቅርታን ለማግኘት ከፈለግን መጀመሪያ ከወገኖቻችን ጋር ይቅር መባባል እንዳለብን ነገሮናልና (የማቴዎስ ወንጌል 5፡24፤ የማርቆስ ወንጌል 11፡25-26) በሥልጣን ዘመንዎ ለወታደሮችዎ ባስተላለፏቸው ቀጫጭን ትዕዛዞች አማካኝነት ልጆቻቸውን ወይም ወላጆቻቸውን በሞት በመቅጠፍ ለዓመታት ደም ዕንባ ያስነቧቸውን ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ በግልጽ ይቅርታ ይጠይቁ። አለበለዚያ እውነተኛው ዳኛ እግዚአብሔር፡ ለመጀመሪያው ነፍሰ ገዳይ ለቃየን እንደነገረው አሁንም “የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል” ይላል (ኦ. ዘፍጥረት 4፡10)። ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን የቃሉን መልእክታት በማስተዋል፡ የትዕቢት መንፈስ ቢጫንዎት እንኳ እንደምንም ይቃወሙት እና በትህትና ራስዎን ከኃያሉ አምላክ የጸጋ ዙፋን ሥር ይጣሉ። ምሕረቱን ይለምኑ፤ ቅዱስ የሆነውን ስሙንም ዘወትር ይጥሩት፡ መጽሐፍ እንደሚል “የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል[ና]።”

የኛ ነገር፡ የተሸነፈ ርእዮተአገርና ገፊ ፖለቲካ፤ (ተክለሚካሄል አበበ )

$
0
0

ስለመጪው ሶስተኛ ሪፐብሊክ፤ ካለፈው የቀጠለ፤ ሀ
Tekele ትንሽ ወደኁዋላ፤ እንደ መግቢያ
1. ግንቦት፤ 2003/2011፤ በቶሮንቶ ከተማ፤ ጃዋርና ኦባንግ፤ አሎ አይደሂስና (ሸጋ የአፋር ሰው ነው) አበበ በለው በእንግድነት የተገኙበትን ሕዝባዊ ስብሰባ ተንተርሼ፤ አንድ ወርቅ የሆነ ጽሁፍ ጽፌ ነበር፡፡ ጽሁፉን ያላነበባችሁ ብታነቡት፤ ያነበባችሁትም ብትደግሙት አይቆጫችሁም፡፡ ጽሁፉ ይቀጥላል ብዬ ጊዜ ጠፋና ቀጣዩን ክፍል ሳላቀርብ ቀጠልኩ፡፡ ስለኦባንግ ገጠመኝ ተርኬ፤ ስለጃዋር ጀምሬ ነበር ያቆምኩት፡፡ አሁን መቀጠሉ ወቅታዊ መስሎ ታየኝ፡፡ ከስብሰባው በፊት ይመስለኛል ስለወቅታዊና መሰረታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ስናወራ፤ ተራው ህዝብ ለገዢ መደቦች ስራ ተጠያቂ ባሆንም፤ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ግን፤ ተራው የአማራ ህዝብ፤ ገዢው መደብ የፈጠረውን ርእዮተአገር በገቢርም በነቢብም ተቀብሎ ኖሮበታል፤ በብዙ ስፍራዎችም ይሄንን ርእዮተ-አገር ተጠቅሞ ሌሎችን ጨቁኖበታልም፤ ብሎ ለማስረዳት ሞከረ፡፡ ምሳሌ ሰጠ፡፡ ነገሩ ከአመታት በፊት የሆነ፤ የተለመደ ሁሉም ወይም ብዙዎቹ ኦሮሞዎች እለት ተእለት የሚጋጥማቸው ቢሆንም፤ ነጥባችንን ለማስረዳት ይጠቅማልና እጠቅሰዋለሁ፡፡ እነሆ አጋጣሚው፡፡

ጃዋር መሀመድ
2. ጃዋር የገጠር ልጅ ነው፤ ከላይ በጠቀስኩት ጽሁፍ ላይ ራሱ እንዳለው፡፡ የዛሬ አስራምናምን አመት፤ ከቤተሰቦቹ ተለይቶ ከተማ ቤት ተከራቶ ትምህረቱን የሚከታተለው ታዳጊው ወጣት፤ ጃዋር ሲራጅ መሀመድ፤ አንድ ቀን አምሽቶ ዝናብ እየደበደበው ይመስለኛል ወደተከራው ቤት ይመጣል፡፡ አከራዩ ደግ አማራ ሴት፤ ለጃዋር ምግብ ሰጥታ፤ እሳት አንድዳ እያሞቀችዉ፤ ከላዩ ላይ ጋቢ ደርባ “ለምን እስኪመሽ ቆየህ አሁን ከመንገድ አንድ ጋላ ቢያገኝህና አንገትህን ቢልሀስ” አለችው፡፡ የዚህን ልጅ ስሜትና ምላሽ ለመረዳት ኦሮሞ መሆን አያስፈልግም፡፡ ራስን በሱ ቦታ ማስቀመጥና ነገሩን የራስን ጎራ ያለስስት በመተቸት ፈቃደኝነት ማሰላሰል እንጂ፡፡

3. ልክ ጅሁርና ጋይንት፤ ቢቸናና አንኮበር እንደምትኖር አንዲት አማራ ኢትዮጵያዊት፤ ይህቺ ሴት ክፋት እንደሌላትና የንግግሩዋን ፖለቲካዊ አንድምታ፤ በዚህ ልጅ ቀጣይ ማንነት ውስጥ የሚኖረውንም ፋይዳ እንደማታውቅ አሳምሮ መገመት ይቻላል፡፡ ይሄንን አጋጣሚ የነገረን ጃዋር ግን የሚለው፤ ይህቺ የዋህ ሴት የኢትዮጵያ ገዢ መደብ አካላት ያሰራጩትንና ለገዢ መሳሪያነት የተጠቀሙበትን የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍልን ዝቅ የማድረግ አመለካከት፤ ሳታውቀው ከነፍሱዋ አዋህዳዋለች ነው፡፡ ስለዚህም፤ በቀጥታ ይሄንን የተወሰነ ብሄርን ዝቅ የማድረግ ባህል በመፍጠርና በመቅረጽ ባትጠየቅም፤ የዚህ ባህል በረከት ተቁዋዳሽ በመሆንና አውቃም ሳታውቅም ይሄንን ባህል እድሜ በመስጠት ተሳታፊ ነች ሲል ተከራከረ፡፡ በላይኛው ጽሁፍ ላይ ሰፈርኩትን የኦባንግን ገጠመኝ ጨምረን ካየነው፤ የጃዋር መከራከሪያ ስሜት ይሰጣል፡፡

ገረሱ ቱፋ፤

4. የላይኛው የጃዋር ገጠመኝ ቀሽም ሊመስል ይችላል፡፡ ከሰደበኝ መልሶ የነገረኝ እንዳልባል እንጂ፤ የገረሱ ቱፋ የከረሩ ምሳሌዎች ደግሞ አሉ፡፡ አንዱን ልጥቀስ፡፡ ኦሮሞው ወዳጄ ገረሱ ቱፋም፤ እንዲሁ ልጅ ሆኖ ሳለ፤ ጾም መሆኑን ረሳና፤ ወተት ጠጣ፡፡ እናቱ ወደንስሀ አባታቸው ላኩት፡፡ ቄሱ ቃል በቃል ምን ብለው እንደመለሱለትና ልቡን እንዳደሙት የነገረኝን በደንብ አላስታውሰውም፡፡ ብቻ፤ “ኤድያ ደግሞ፤ የጋላ ጹዋሚ ብሎ ነገር የለም” ብለው መለሱለት፡፡ “ለጋላ ንስሀ አባት ዲያቆን መች አነሰው” አይነት የሚለውን፤ የተለመደውን ክብረ-ነክ ተረት የሚያጠናክርና የሚያናንቅ መልስ ነው፡፡ በወቅቱ ገረሱ የሱ ጣፋት መስሎት ነበር፡፡ ነፍስ እያወቀ ሲመጣ ግን የሱ ጥፋት ሳይሆን ልክ እንደጃዋር ቀላቢ፤ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ፤ በቄሱ ውስጥ የተተከለውን የሱን ብሄር ዝቅ የሚያደርግ ገዢው መደብ የፈጠረው ንቀትና ጥላቻ ተገለጸለት፡፡ ከአመታት በሁዋላ፤ እነሆ በገረሱ ነፍስ ውስጥ አብሮ የሚኖርና ዘወትር ቄሱ ስለወጡበት ህብረተሰብ ሲያስብና እኛ ጋር ክርክር በገጠመ ቁጥር ትዝ የሚለው መርዝ አጋጣሚ ሆነ፡፡ እንደውም ኢትዮጵያ ስትባል፤ የኚህን ቄስ ጋቢ የደረበች የአማሮች ፈጠራ መስላ ታየችው፡፡

jawar5. ይሄ ሁሉም ሆኖ፤ ጃዋር እንደውም ኢትዮጵያ ኦሮሞነትን የሚያንጸባርቅ ቀለም ከቀባናት፤ አንድ ነን ወይም ልንሆን እንችላለን የሚለውን ሀሳብ ይቀበል ነበር፡፡ የኛን ቄስ ንግግር ፖለቲካዊ አንድምታ ከተደራ በሁዋላ ለቀብር ካልሆነ ቤተክርስቲያን ደርሶ የማያውቀው ገረሱ ግን፤ የኢትዮጵያ አንድነት የሚባል ነገር አገባውም፡፡ አንድ አይደለንም ባይ ነው፡፡ ከሆንም፤ አንድነታችን የጎደፈ አንድነት ሆኖ ነው የሚታየው፡፡

6. ብዙ እላይ ከጠቀስኩዋቸው የከፉ ምሳሌዎችን ማንሳት ይሻላል፡፡ ግን እነዚህ የኦሮሞም ይሁን ሌሎች ብሄርተኞች የሚያነሱዋቸውን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ክሶች በንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችና ማስራጀዎች ለማስረዳት መሞከር፤ የክሱን ስፋትና ጥልቀት ማሳነስ ይመስለኛል፡፡ ማውራቱ ነገሩን ያቀለዋል፡፡ ያንን ስሜትና እውነታ መኖር ግን ከሕመም በላይ ነው፡፡ በዚህ አገባብ ውስጥ ነው ያለፉት ሶስት ወራት የነጃዋር ንትርክ የተጀመረው፡፡

7. እነዚህን ምሳሌዎች ያነሳሁዋቸው፤ አንደኛ፤ በዚህ ሰሞን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ዝልዘላችንን ተቆጣጥረውት የቆዩትን ከአኖሎ ሀውልት እስከ በደሌ ኮንሰርት፤ ከምኒሊክ ቅድስና እስከ ጃዋር ትንተና ያሉትን ጉዳዮች ስንመለከት፤ በተወሰነ መልኩ የነዚህን ሰዎች ስሜት ለመረዳት የነዚህን ሰዎች አመለካከት የለወጡ ወይንም ያዳበሩ አጋጣሚዎችን መስማት ራሳችንንና የምንደግፈውን ርእዮተአገረ ለመደገፍ ከመሽቀዳደም ይልቅ የሰዎቹን ክስ በትእግስት ወደማድመጥ ሊወስደን ይችላል በሚል እምነት ነው፡፡ ሁለተኛ፤ የጃዋርና የገረሱ ፖለቲካዊ ማንነት የተወለደውና የተሞረደው ከንደዚህ አይነት ፖለቲካዊና ማሀበራዊ ክስተቶች ነውና እነጃዋር የሚሉትን መስማትም መገምገምም ያለብን በዚህ ማእቀፍ ውስጥ እንደሆነ ለማሳየትና፤ በዚያ አይነት ጉዞ ውስጥ ያደጉና የነቁ ወጣቶች ኢትዮጵዊነት ለምን እንደሚያስጸይፋቸው ሲናገሩ፤ በተስኪያን እንደገባች ውሻ ከማባረር፤ እንደግለሰብም ይሁን እንደተቁዋም፤ እነዚህን ልጆች ጸረ-ኢትዮጵያ አድርገን ከመፈረጃችን በፊት፤ ህመማቸውን ለማድመጥና ለማከም መጣር ይገባል፡፡ ኢህአዴግ ወደቆ እንድትኖር የምንፈልጋት ኢትዮጵያም፤ እነዚህን ህመሞች ለማስታመም የሚችል ህገመንግስታዊ፤ ስነልቡናዊና ፖለቲካዊ ዝግጅት ከሌላት፤ የተቃውሞ ፖለቲካችን በርግጥም የመፍትሄ ሳይሆን፤ የማውገዝ ብቻ ይሆናል፡፡ የዛሬው ጽሁፌ ስለዚህ ፖለቲካዊ ህክምናና ብናደርግ ስለሚበጁን ነገሮች መንገድ ለመጠቆም ነው፡፡ በዚህኛው ክፍል ጠቅላላ ነገሮች ይነሳሉ፡፡ በሚቀጥለው ክፍል ደግሞ መፍትሄዎች ይጠቆማሉ፡፡

መጀመሪያ አፍሪካዊ ወይስ ኢትዮጵያዊ?

8. ባለፈው ሰሞን፤ አልጀዚራ ላይ በቀጥታ ስርጭት ይመስለኛል፤ ጃዋር ፖለቲካዊ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከተውን ጥያቄ ተጠየቀ፡፡ “መጀመሪያ ኦሮሞ ነህ፤ ኢትዮጵዊ?” የሚል፡፡ የሚቀጥለው ምሳሌ መቶ በመቶ ላይመሳሰል ይችላል፡፡ የተወሰነ መመሳሰል ግን አለው፡፡ አንድ ሰላሳ አመት ካናዳ ወይም አሜሪካ ውስጥ የኖረ ኢትዮጵያ፤ ወይንም እነዚህ አገር ውስጥ የተወለደ ናይጄሪዊ ይህንን ጥያቄ ቢጠየቅና፤ መጀመሪያ ናይጄሪያዊ ነኝ ብሎ ቢናገር፤ አሜሪካኖችን ወይንም ካናዳዎችን የሚያስቆጣ አይመስለኝም፡፡ ጃዋር ከኢትዮጵ በፊት መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ብሎ ሲናገር ግን ብዙዎች አኮረፉ፡፡ ንትርክ ተጀመረ፡፡ የነቁና የበቁ የሚመስሉ የአንድነት አቀንቃኞች ራሱ ተቆጡ፡፡ አሁን በእመብርሀን ይሄ ምኑ ያበሳጫል? በዚህ መደንገጥም መቆጣትም የለብንም፡፡ ማድረግ ካለብን መጠየቅ ብቻ ነው፡፡ ችግሩ፤ እንድንሸመድድ እንጂ፤ እንድንጠይቅ በሚያበረታታ ባህል ውስጥ አላደግንምና፤ ከመጠየቅ ይልቅ፤ ልጁን ወደመዘልዘሉ ዘለልን፡፡

9. አንደኛ፤ ከአገሬ በፊት ብሄሬን ነኝ የሚለው መልስ እንደየአመለካከታችን ትክክል ሊሆን ይችላል፡፡ በርግጥም ሰው ከአገሩ በፊት ብሄሩን ነው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነህ አፍሪካዊ ቢባልና መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ቢመልስ፤ ምንም ብዙ ቁጣ የሚቀሰቅስ አይመስለኝም፡፡ ያ ባይሆንም እንኩዋን፤ እንዲህ አይነት ጥያቄዎች አንድ ወጥ የሆነ ሳንሳዊ መልስ ስለሌላቸው፤ ሰዎች አጣብቂኝ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ ሲጠየቁ፤ ብዙ ሳያወጡ ሳያወርዱ እንዲህ አይነት መልስ ቢመልሱ፤ ሲሆን ሲሆን መልሳቸውን መቀበል፤ ያለበለዚያም የመልሳቸውን መሰረት ለመረዳት መሞከር እንጂ፤ ግፋ ካለም መልሳቸው ለምን ስህተት እንደሆነ ለመጠቆም መሞከር እንጂ፤ በመልሳቸው ማውገዝ አግባብ አይደለም፡፡ ለጃዋር የተሰጠው ተቃውሞ ደግሞ በብዛት የመጣው የአሜሪካና ካናዳ እንዲሁም የአውሮፓ ፓስፖርታቸውን ተሸክመው መጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ነን ብለው ከሚናገሩ ሰዎች አንደበት መሆኑን ስናይ፤ አንዳንድ ግዜ ሚዛናችን ምን ህል የተዛባ ነው ያሰኛል፡፡

ጃዋር ሚናገረውን ያውቃል፤ ያለውንስ ለምን አለ?

10. በመሰረቱ፤ ይህ ልጅ መቼም ሰው ነውና አንዳንድ ግዜ አግባብ ያልሆነ ነገር ቢያመልጠውም፤ የሚሰራውንም የሚናገረውንም ያውቃል፡፡ ከላይ በጠቀስኩት ጽሁፍ ኦባንግ ሜቶ እንዳለው፤ “በኢትዮጵያዊነታችን ያጣነው ነገር ስላለ ብቻ ኢትዮጵያዊነታችን ይሰረዛል ማለት አይደለም”። ጃዋር፤ ልክ እንደ ኤርትራ እዚያ አካባቢ ኦሮሞ ወይንም ኦሮሚያ የሚባል መንግስት እስካልተመሰረተ ድረስ፤ ቢወድም ባይወድም፤ ጥንትም አሁንም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ያውቀዋል፡፡ ኤርትራ ተፈጥራም እንኩዋን፤ ኤርትራዊነትና ኢትዮጵያዊነት በሁለቱ አገሮች መካከል እንደሚሰመር ድንበር ይቀላል ማለት አይደለም፡፡ ጥምር ዜግነት የሚሉትን ጽንሰሀሳብም ማስታወስ አይጎዳም፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆንም ሙሉ በሙሉ የስራችንና የምርጫችን ውጤት ሳይሆን፤ የትውልድና የሕግ ጉዳይ ነው፡፡ ጃዋር እስከቅርብ አመታት ድረስ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ይዞ እንደሚዞር እገምታለሁ፡፡ ልጁ እያለ ያለው ግን፤ ህግና አለማቀፍ ፖለቲካ አስገድዶኝ ኢትዮጵዊ ብሆንም፤ ፖለቲካዊ ነፍሴ ኢትዮጵያዊ አይደለም ነው፡፡

11. ነፍስ እንደዜግነት በህግ አትገደድም፡፡ ነፍስ ዜግነቱዋን ወይም ማንነትዋን ትመርጣለች እንጂ፡፡ ነፍሱ ማንነትዋን መረጠች፡፡ የኛ ስራ መሆን ያለበት፤ መናደድ ወይም ማበድ ሳይሆን፤ መጀመሪያ ማብረድ፤ ልክ አሁን እኔ እንደማደርገው፤ ከዚያ መጠየቅ ነው፡፡ ይሄ ልጅ ለምን እንደዚያ አለ፡፡ ኢትዮጵያዊ ነው ብለን፤ በየሬድዮና ቴሌቪዥናችን ስንሰቅለው፤ በየስብሰባና በየመድረካችን ስናቀርበው፤ ድንገት ተነስቶ እንዴት እንዲህ ጉድ አረገን፡፡ ብዙዎቻችን ግን አልጠየቅንም፡፡ ፈረድን እንጂ፡፡ አትፍረድ ይፈረድብሀል የሚል ብሂል ባነገበ ሀይማኖት ክርስትና የተነሳን ሁሉ ፈረድን፡፡

እንደሚመስለኝ፤ እኔ እንደማስበው፤

12. ጃዋር፤ ያንን የቴሌቪዥን ውይይት የሚከታተል ሁለት ትልልቅ ቡድን እንዳለ ያውቃል፡፡ አንደኛው በተለምዶ የአንድነት ሀይል የሚባለው፤ ሁለተኛው የነጻነት ወይንም የኦሮሞ ብሄርተኛ ሀይል፡፡ ሌሎች ሶስተኛም አራተኛም ቡድኖች ኖራሉ፡፡ ያለውን ፖለቲካዊ ራእይ በተደጋጋሚ የፈነጠቀው ጃዋር፤ ዞሮ ዞሮ የአንድነቱ ሀይል በጥርጣሬ እንደሚያየው ወይንም የብሄር ማንነቱን ጨፍልቆ እንጂ እሱ በሚፈልገው መልኩ እንደማይቀበለው በተለያየ አጋጣሚ አስተውሎዋል፡፡ ስለዚህ በሱ ቦታ ላለ፤ ከላይ በአንቀጽ 2፣ 3፣ እና አራት በጠቀስናቸው የእለት ተእለት ፖለቲካዊና ማህበራዊ ክስተቶች ውስጥ ላደገና ለሚኖር ኢትዮጵያዊ፤ እንደዚያ ባለ ፍጥነትን በሚጠይቅ አጣብቂኝ ውስጥ የሚሰጠው መልስ መጻኢ የፖለቲካ እድሉ ላይ እንደሚያጠላበት ያውቃል፡፡ ስለዚህ፤ መጀመሪ ኦሮሞ ነኝ አለ፡፡ በተወሰነ መልኩም ኢትዮጵያዊነት እንደተጫነበት ጠቀሰ፡፡

13. አስቀድመን ጃዋር ላይ የጫንበት ማንነት ወይንም ዜግነትና ለተጠየቀው ጥያቄ እኛ ያዘጋጀልነት መልስ ከሌለ በስተቀር፤ የሚሰማውን ማንነትና ውስጡ የሚቀበለውን ዜግነት የሚያውቀው እሱ እንጂ፤ እኛ አይደለንም፡፡ ስለዚህም በወቅቱ ብሄርን ማስቀደሙ ምክንያታዊ ውሳኔ ነው፡፡ ፖለቲካዊ ብልሀትም ነው፡፡ በርግጥም በሁዋላ የተከተለውን እሱንና አመለካከቱን የማሳደድ ዘመቻና ውግዘት ለተመለከተ፤ የጃዋር መልስ ትክክል ነበር ያሰኛል፡፡ ምክንያቱም እኝ የቀረጽንለት ኢትዮጵያ ለሱ ስሜት መፈናፈኛ የሌላት ሆና ተገኝታለችና፡፡ ጃዋር የቆየ የኢትዮጵያውን ልሂቃን፤ ”የኛ መንገድ ብቸኛውና አማራጭ የሌለው ምርጥ መንገድ ነው፤ ከኛ እውቅናና መንገድ ውጪ የሚጉዋዝ ውጉዝ ይደምሰስ”፤ የሚል ትውልድ ያጫረሰና፤ እነፍቅረስላሴ ወግደረስ ከ20 አመታት እስርም በሁዋላ ያልለወጡት፤ ችኮ ፖለቲካዊ ስነልቡና ሰለባ ነው የሆነው፡፡ እንደውም፤ ለጃዋር፤ እኛ ከቀረጽንለት ኢትዮጵያ ይልቅ፤ ኢህአዴግ የፈተለለት ኢትዮጵያ የተሻለች ብትመስለው አይገርመኝም፡፡

የብሄር ፖለቲካን፤ በከፊል መቀበል ነው፤

14. እነዚህ ወጣቶችም ሆኑ የፖለቲካ ንስሀ አባቶቻቸው፤ በዚህ በአልጀዚራ ላይ የሰማነውን አይነት፤ ኢትዮጵዊነትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ፤ ለኛ ለመቀበል የሚያስቸግረን ንግግር ሲናገሩ፤ የቆሰለውና እንዲህ ወዳለው ስሜት ውስጥ የሰነቀራቸውን ፖለቲካዊ ሕመም በማከም ፈንታ፤ እንደጠላት የሚፈርጅ አካሄዳችንና ራሳችንን የኢትዮጵያ አንድነት ጋሻዣግሬዎች አድርጎ የመሾም ባህላችንን ነው፤ እነዚህን ሰዎች ወደጽንፈንነት የሚመራቸው፡፡ ያ ደግሞ ለኛም ለኢትዮጵያም አይበጅም፡፡ በዚህ ረገድ ይሄን ያህል አመት በኢህአዴግ መበለጣችን ሁሌም ይገርመኛል፡፡ ምክንያቱም፤ ኢህአዴግ ለነጃዋር፤ የአንድነቱ ሀይል ለመቀበል የሚያዳግተውን፤ ኦሮሚያ የሚባል ክልል/ካርታ፤ ሙሉ ነጻነት ባይኖረውም በራሱ ቁዋንቁዋ የሚተዳደር መንግስት ሰጥቶዋቸዋልና፡፡ ስለዚህ ከአንድነት ሀይሉ ውግዘት ጋር ሲወዳደር ብቻ ሳይሆን፤ ራሱን ችሎም፤ ኢህአዴግ ለብሄር ፖለቲከኞች የሰጠው ፖለቲካዊ ገጸ-በረከት፤ ልብ የሚማርክ ነው፡፡

15. የዚህ የብሄር ፖለቲካ ርእዮተአገር እንደአዲስ በመጣበት ሰዓት ለብዙዎቻችን አዲስና አስደንጋጭ ነበርና ባንቀበለው አይገርመኝም፡፡ እኔና ተስፋዬ ”ጋላው”፤ ስለሺና ወዲ ትግሬው በብሄር ሳይሆን በሰፈር፤ በቁዋንቁዋ ሳይሆን በክፍል፤ በሀይማኖት ሳይሆን፤ በእድሜ ተከፋፍለን ኩዋስ ስንጠልዝ፤ ሴት ስናባርር፤ ጠላ ስንገለብጥ፤ ድግስ ስናሳድድ ነበርና ድንገት የመጣው፤ በርግጥም የብሄር ፖለቲካ አስደንጋጭ ነበር፡፡ ከ22 አመታት ሽንፈት በሁዋላም ግን ራሳችንንና አስተሳሰባችንን አሸናፊ ሆኖ ከወጣው የብሄር ፖለቲካ ጋር ማጣጣም አለመቻላችን ግራ ነው የገባኝ፡፡ ለዚህም ነው፤ የብሄርተኞችን ቁስል በማከክና በማከም ረገድ ኢህአዴግ በልጦናል፡፡ እኛ እንደውም ቁስሉን የምናክም ሳሆን የምናመረቅዝ ሆነናል፡፡

16. ኢህአዴግ ለነሱ አስቦም ይሁን ለራሱ የፖለቲካ ጥቅም፤ የብሄርን ፖለቲካ በሚገባ ተጠቅሞበታል፡፡ 22 አመታት ያለብዙ ፈተና መርቶበታል፡፡ ስለዚህም እነሌንጮ ለታ እነሌንጮ ባቲ እንኩዋን፤ እንደገና ወደሁዋላ የኢህአዴግን አስተዳደር ተቀብለው ለመኖር እያኮቦኮቡ ነው፡፡ ምክንቱም ኢህአዴግ ጠላት ቢሆንም፤ በሌላ በኩል ከተሰለፈው ወደሁዋላ ሊጎትተን ይፈልጋል ብለው ከሚፈሩት የአንድነት ሀይል የተሻለ ጠላት እንደሆነ ያውቁታልና፡፡ ስለዚህ ይሄንን ጎሳን ወይንም ብሄርን መሰረት ያደረገ ፖለቲካዊ መሳሪያ ይዞ፤ ኢህአዴግ ሌላ 20 አመት ቢገዛም አይገርመኝም፡፡

17. እንደፖለቲካዊ ስበስብ፤ ሙሉ በሙሉ የኢህአዴግን የብሄር ፖለቲካ ባንቀበለውም እንኩዋን፤ ኢህአዴግ ክፉ መንግስት እንደሆነ ቢያውቁም፤ በተወሰነ መልኩ በፊት ያልነበረንን መብት አስከብሮልናል ብለው፤ የኢህአዴግን የብሄር ፖለቲካ ተቀብለው ኢህአዴግን በሀይለኛው የሚደግፉትን ቡድኖች የሚማርክ አማራጭ ማቅረብ አልቻልንም፡፡ እንደግንቦት ሰባት ያሉ በንጽጽር የተሸሉና የሰለጠኑ አባላት ያሉበት ድርጅት እንኩዋን፤ ብዙውን እንዲህ ያለውን ፖለቲካዊ ጉዳይ፤ ”ህዝቡ ይወስናል”፤ የሚል የስንፍናና የሽሽት አንቀጽ ሰንቅረው፤ በጎን ሸውደው አልፈውታል፡፡ በዚህ የፖለቲካ ድርጅቶቻችን፤ እንኩዋን የሚያሸንፍ፤ የሚያሰልፍም አማራጭ ርእዮተ-አገር ባልቀየሱበት ሁኔታ ነው፤ ይባስ ብለን፤ በተወሰነ መልኩም ከኛ ጋር ለመስራት የሚጥሩትን ጃዋሮች አመናጭቀን የምንገፋው፡፡ የዚህኛው ገፊ ፖለቲካ መጨረሻ፤ ልጆቹ ልክ እንደ ሌንጮ ለታ ወደጠላት ጎራ እንዲገቡ መገፋፋት ያለበለዚም ሌላ የፈተና ግንባር እንዲፈጥሩ ማበረታታት ነው የሚሆነው፡፡

18. ባንድ በኩል የሌንጮን ወደኢትዮጵያ የመመለስ ውሳኔ፤ ድፍረትና ብልሀት የተሞላበት ውሳኔ ነው ብዬ ባደንቅም፤ በሌላ በኩል ግን የሌንጮ ወደኢትዮጵያ የመመለስ ውሳኔ የአንድነቱን ሀይል ፖለቲካዊ ችኮነትና ውድቀትም ያሳያል፡፡ ሌንጮስ እድሜውም እየገፋ ነውና እንደጎልማሳነት ዘመኑ ብዙ ላያስቸግረን ይችላል፡፡ መጪውን ዘመን የሚዳኙትን፤ እነጃዋር መሀመድን፤ እነገረሱ ቱፋን ግን በትእግስት ልናስተናግዳቸው ሲገባ፤ ሌንጮን መማረክ የተሳነን፤ በኛ ብሶ፤ ደግሞ ይሄንንም ልጅ፤ ጃዋርን ገፋነው፡፡ ከገፋነው በሁዋላ፤ ምንስ ቢል፤ ምንስ ቢያደርግ፤ ምን ይደንቃል፡፡ ከሲያትል እስከ ለንደን፤ ከቶሮንቶ እስከ እስከ ሚኒያፖሊስ ቀድሞም የድርጅት ድክመት ይዞት እንጂ፤ በቁዋፍ የነበረውን የኦሮሞ ብሄርተኛ፤ ለዘብተኛ የነበረውን ሁሉ፤ ኦሮሞ ይቅደም እያለ ሰበሰበው፡፡ እርግጠኛ ነኝ፤ ጃዋር በህልሙም በእውኑም ያላሰበውን ፖለቲካዊ መድረክ ፈጠርንለት፡፡ ገፊ ፖለቲካችን እኛኑ ሳይፈጀን፤ ይሄንን ገፊ የፖለቲካ ቅኝታችንን መለወጥ አለብን፡፡

ሶስት ሀይሎች፤ አንድነት፤ ነጻነት እና ኢህአዴግ

19. እንደሚመስለኝ፤ ይህ ልጅ፤ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ በዋንኛነት፤ ሶስት አገራዊ ሀይሎች የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ ለመለወጥ ትግል እንደገጠሙ ገምቶዋል፡፡ አንደኛው አህአዴግና አጋሮቹ፤ ሁለተኛው በተለምዶ የአንድነት ሀይል የሚባለው ቡድን፤ ሶስተኛው ደግሞ የነጻነት ሀይሎች ወይንም የዘውግ ብሄርተኞች የሚባሉት ናቸው፡፡ እንደሚመስለኝ የጃዋር ጠቅላላ ስሌት የሀይል ሚዛኑን ወደኦሮሞ ብሄርተኞች መድፋት ነው፡፡ ኢህአዴግ ኖሮም ይሁን ኢህአዴግ ወድቆ የምትቀጥለው ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ አወሳሰን ላይ፤ ቀደም ሲል ኦሮሞ፤ በድምስሱ ደግሞ እስላም ኦሮሞው የአንበሳውን ድርሻ እንዲይዝ ፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ በተለምዶ የአንድነት ሀይል እየተባለ የሚጠራው ሀይል በተዘረረበት ወይንም እርስበርሱ በተከፋፈለበትና በአንድነት ለመስራት በየወንዙ እየተማማለ መሀላውን በየጋራው በሚያፈርስበት ሰዓት፤ ሲሆን ሲሆን ኦሮሞውን አንድ አድርጎ፤ አንድም ባይሆን አጠናክሮ መያዝ፤ በቀጣይዋ ኢትዮጵያ ውስጥ የይል ሚዛኑንን ወደነርሱ እንዲሆን ያሰፋዋል ብሎ ያምናል፡፡

20. ስለዚህ ጃዋር መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ሲል፤ ይሄንን ኦሮሞን እንደአንድ ሀይል አጠናክሮ መጉዋዝ፤ መጪዋን ኢትዮጵያን ለመቅረጽ ያስችለናል ከሚል ስሌት ተነስቶ ይመስለኛል፡፡ ምክንቱም፤ ይሄ ልጅ ዞሮ ዞሮ፤ አማራ ወይንም አምሀራይዝድ ሌሎች የበዙበት የአንድነቱ ሀይል በቀላሉ እንደማይቀበለው ያውቀዋል፡፡ ትግሉን እንደከዳ፤ ከአማራ ጋር እንዳበረ እየተከሰሰም ቢሆን፤ ይህ ልጅ አምስት ስድስት አመት፤ ከአንድነት ሀይሉ ጋር አብሮ በልቶ ጠጥቶ፤ ተከራክሮና ተደራድሮ አየው፡፡ አንድነት ጭፍለቃ ነው የሆነበት፡፡ መፈናፈኛ አሳጣው፡፡ ስለዚህ፤ ጃዋር ተገኑን፤ ወይም ኮንስቲቲወንሲውን መምረጡ ነው መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ ያሰኘው፡፡ በሌላ አነጋገር፤ አማሮችና ትግሬዎች እየተፈራረቁ ይህቺን አገር መርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ እኛ እንምራ ነው ነገሩ፡፡ በትግሬ ታኮ ወይንም በአማራ ጥላ ስር ሳይሆን፤ በራሳችን መታወቂያ፡፡ አገሪቱን መምራት ካልቻልንም፤ ቢያንስ የራሳችንን እጣ ፈንታ እንወስን ነው፡፡ የኛ ምላሽ ….

ይቀጥላል፤
ተክለሚካኤል አበበ፤ ጥር፤ 2006/2014፡፡ ተረንቶ፤ ካናዳ፤

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>