Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር «ኦሮሞዉን» ጎድቷል

$
0
0

- አማኑኤል ዘሰላም

የኢትዮጵያ ፈዴራል ሕገ መንግስት አንቀጽ 46 «ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ የማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት ነዉ» ይላል። አንቀጽ 47 ደግሞ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሩፑብሊክ አባላት የሆኑቱን ክልሎች ይዘረዝራቸዋል። እነርሱም የትግራይ፣ የአፋር ፣ የአማራ፣ የሱማሌ፣ የቤኔሻንጉል/ጉሙዝ፣ የደቡብ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች እና የሃረሪ ሕዝብ ክልሎች ናቸው።

የዚህን የፌደራል ክልልን በተመለከተ በክልሎች እየታዩ ያሉትን አንዳንድ ሁኔታዎች ለማሳየት እንሞክራለን። ከትልቁ ክልል ኦሮሚያ እንጀምር።

ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ ሃያ ዞኖች አሉ። ሶስቱ «ልዩ ዞኖች» ይባላሉ። ናዝሬት/አዳማን ያካተተ፣ የአዳም ልዩ ዞን፣ ጂማን ያካተተው፣ የጂማ ልዩ ዞን እና የቡራዮ ልዩ ዞን ናቸው። በነዚህ ዞኖች የመጀመሪያ ቋንቋቸው አፋን ኦሮሞ የሆኑቱ ቁጥራቸው ከ45 በመቶ በታች ነዉ። በአዳማ 26%፣ በጂማ 39% እና በቡራዮ 44% ናቸው።
Oromia
በአሥራ ሶስቱ ሌሎች የኦሮሚያ ዞኖች አፋን ኦሮሞ የመጀመሪያ ቋንቋቸው የሆኑ ከ90 % በታች ናቸው። እነዚህም ምስራቅ ሸዋ ( 69%)፣ ጉጂ (77%) ፣ አርሲ ( 81%)፣ ሰሜን ሸዋ ( 82%)፣ ደቡብ ምስራቅ ሸዋ (84%)፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ (85%) ፣ ምእራብ አርሲ (87%)፣ ምስራቅ ወለጋ (88%) ፣ ምእራብ ሃረርጌ (89 %)፣ ኢሊባቡር (90%) ፣ ጂማ – የጅማ ከተማ አካባቢ ( 90%)፣ ባሌ (90%)፣ ቦረና (90%) ናቸው። እንግዲህ ከሃያ የኦሮሚያ ዞኖች፣ በአሥራ ስድስቱ፣ ምን ያህል አፋን ኦሮሞ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያን በስፋት እንዳሉ እያየን ነዉ። በአራት የኦሮሚያ ዞኖች፣ በአፋን ኦሮሞ አፋቸዉን የፈቱ፣ ከዘጣና ሶስት በመቶ በላይ ናቸው። እነርሱም ምእራብ ወለጋ (97%) ፣ ምእራብ ሸዋ (93%)፣ ምስራቅ ሃረርጌ፣ (94%)፣ ቀለም ወለጋ ( 94%) ናቸው።

አሁን በሥራ ላይ እየተተገበረ ያለው የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ 33 «በክልሉ ዉስጥ ነዋሪ የሆኑና የክልሉን የሥራ ቋንቋ የሚያውቅ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በማንኛዉም የክልሉ መንግስታዊ ወይም ሕዝባዊ ሥራ ተመርጦ ወይም ተቀጥሮ የመስራት መብት አለዉ።» ይላል። አንቀጽ 5 ደግሞ « ኦሮምኛ የክልሉ መንግስት የሥራ ቋንቋ ይሆናል። የሚጻፈዉም በላቲን ፊደል ነው» ይላል።

74% የአዳማ፣ 61% የጂማ ከተማ ፣ 56% የቡራዩ ዞን፣ 31% የምስራቅ ሸዋ ዞን፣ 23% የጉጂ ዞን ፣ 25% የሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን፣ 23% የምእራብ አርሲ ዞን … ነዋሪዎች የመጀመሪያ ቋንቋቸው አፋን ኦሮሞ ባላመሆኑ፣ አፋን ኦሮሞ ካልተማሩ በቀር፣ የመመረጥ፣ በኦሮሚያ ክልል የመስራት መብት የላቸውም። ይህም አማርኛና ሌሎች ቋንቋዎች የሚናገሩ፣ በኦሮምያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን እንደ ሁለተኛና ሶስተኛ ዜጋ እንዲቆጠሩ የሚያደርግ ነዉ። በብሄረሰብ መብት ስም የግልሰበ መብት እየተረገጠ ነዉ።

«ኦሮሚያ ፈርስት» የሚል እንቅስቃሴን የሚመራው ጃዋር ሞሃመድ፣ አንድ ወቅት «Ethiopians Out from Oromia» የሚል መፈክር ያሰማበትን ቪዲዮ ተመልክቻለሁ። ጃዋር በአጭሩ አነጋገር፣ ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ብቻ እንደሆነችና ሌሎች «ኦሮሞ» ያልሆኑ፣ በኦሮሚያ ዉስጥ እንግዶች፣ ኦሮሞዎች ሲፈቅዱላቸው ብቻ ሊኖሩ የሚችሉ እንደሆኑ ነው የነገረን። ይህ የጃዋር አባባል፣ ብዙዎችን እንዳስገረመ ተመልክቻለሁ። ነገር ግን አንድ የዘነጋነው ነገር ቢኖር፣ ይህ የጃዋር አባባል ፣ ጃዋር የፈጠረዉ ሳይሆን በኦሮሚያ በአሁኑ ሕግ መንግስት፣ በሰነድ የተቀመጠ እንደሆነ ነዉ።ይህ አይነቱን ዘረኛ የጃዋር አባባል፣ የኦሮሚያ ክልል «ሕግ» ይደግፈዋል።

የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ ስምንትን ይመልከቱ። «የኦሮሞ ሕዝብ የክልሉ የበላይ ስልጣን ባለቤት ሲሆን ..» ሲል የኦሮሚያ ባለቤት «ኦሮሞው» ብቻ እንደሆነ ነው የተቀመጠው።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ፖሊሲን ካየን ደግሞ፣ አዲስ አበባ አካባቢ ያሉ እንደ አዳማ/ናዝሬት ያሉ ቦታዎች ሕዝቡ ተቃዉሞ ስላስነሳ፣ በዚያ ተማሪዎች አማርኛም ከአፋን አፋን ኦሮሞ ጎን ለጎን እንዲማሩ ከመደረጉ በስተቀር፣ በኦሮሚያ የሚኖሩ ተማሪዎች አማርኛ እንዲማሩ አይደረግም። አማርኛ ማንበብና መጻፍ አይችሉም።

አንድ የግል ባለሃብት ከአዲስ አበባ ሄዶ አንድ ኩባንያ በአንድ የኦሮሚያ ከተማ ይመሰርታል። ሰራተኞች ቀጥሮ ያሰራል። ሰራተኞቹ ስራቸዉን በተመለከተ፣ ሪፖርት ማቅርብ ሲጠበቅባቸው ሪፖርት ሳያቀርቡ ይቀራሉ። አለቃቸው ያስጠራቸዉና ይጠይቃቸዋል። ሪፖርታቸውን በቃል ያቀርቡለታል። «እሺ በፋይል እንዲቀመጥ በጽሁፍ አምጡልኝ» ሲላቸው፣ ማንገራገር ጀመሩ። «ጌታዬ እኛ አማርኛ መጻፍ አንችልም። በቁቤ እንጻፈዉና ከፈለጉ ያስተርጉሙት፤ ወይም እኛ አስተርጉመን እንመጣለን» ይሉታል። ሰዎዬዉ ባንድ በኩል በጣም ተናደደ፣ በሌላ በኩል አዘነ። ቢዝነስ ነዉና፣ ለስራው ብቃት ከሌላቸው ሰራተኞቹ መባረር አለባቸው።

አማርኛን የመጥላት የኦህደድ እና ኦነግ ፖለቲካ ፣ ዜጎች አፋን ኦሮሞን ያዉም በቁቤ ብቻ እንዲማሩ በማድረግ፣ ትልቅ የኢኮኖሚ ጉዳት በ«ኦሮሞዎች» በትግራይ ከአንደኛ ክፍል ጀመሮ ከትግሪኛ ጎን አማርኛ እንዲማሩ ይደረጋል።

የኦሕደድ ባለስልጣናት እነ አባ ዱላ ገመዳ፣ ኩማ ደመቅሳ የመሳሰሉት ልጆቻቸዉን የሚያስተምሩት በአዲስ አበባ ሃሪፍ ተምህርት ቤቶች ነዉ። ሃብታም የሆኑና አቅሙ ያላቸው ልጆቻቸውን ወደ አዲስ አበባ እየላኩ ያስተምራሉ። ለምን ቁቤ ብቻ ተምረው ልጆቻቸው የትም እንደማይደርሱ ስለሚያወቁ።

የግል ኢንቨስተሮች የሥራ ቋንቋቸው በኦሮሚያም ሳይቀር በብዛት አማርኛ ነዉ። በናዝሬት፣ በጂማ በመሳሰሉት ቦታዎች ሂዱ፣ የንግድ ተቋማት፣ የግል መስሪያቤቶች .. የሚጠቀሙት አማርኛን ነዉ። ከክልል መንግስት ጋር አንዳንድ ደብዳቤዎች መላላክ ካስፈለገ ፣ የክልሉን የአፋን ኦሮሞ ብቻ ፖሊስ ሕግን ለማክበር ፣ ተርጓሚ ይቀጥራሉ።

በኢትዮጵያ ካሉ 9 ክልሎች በአራቱ (አማራዉ፣ ደቡብ፣ ጋምቤላና ቤኔሻንጉል ጉሙዝ) ክልሎች፣ እንዲሁም በአገሪቷ መዲና አዲስ አበባ፣ በድሬደዋ የሥራ ቋንቋ አማርኛ ነው። የፌደራልም ቋንቋ አማርኛ ነዉ።

በመሆኑም ኦሮሚያ ያለው የቁቤ ትዉልድ፣ በፌደራል መንግስት ዉስጥ ተቀጥሮ የመስራት አቅሙ ዜሮ ነዉ። እንደ ባህር ዳር፣ አዋሳ፣ ድሬደዋ፣ አዲስ አበባ በመሳሰሉ ታላላቅ ከተሞች ለመኖርና ለመስራት፣ ለመቀጠር በጣም ይቸገራል። በአጭሩ በኢኮኖሚ እንያድጉና እንዳይሻሻሉ ትልቅ ማነቆ ነው እየሆነባቸው ያለዉ ይህ የኦሮሚያ ክልል አሰራር። በሌሎቹ ክልል ካሉ ጋር ሲወዳደሩ ወደኋላ ቀርተዋል። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የኦነግ መሪዎች ልጆቻቸው በበርሊን ሚኒሴቶች …በመሳሰሉ ቦታዎች ናቸዉ። አማርኛም ባያወቁ፣ እንግሊዘኛ እስካወቁ ድረስ ችግር አያጋጥማቸዉም። የኦህደድ መሪዎች ልጆቻቸውን ሃሪፍ ትምህርት ቤቶች ነዉ በአዲስ አበባ የሚያተምሩት። ድሃዉና ምስኪኑ የኦርሚያ ተማሪ ግን፣ አጥር ታጥሮበት፣ በአጉል የኦሮሞ ብሄረተኘንት ስም እንዲተበተብ ተደርጎ ጉዳት እየደረሰብት ነዉ።

ይህ በኦሮሚያ የሚኖረው ወገናችን በኢኮኖሚ፣ በትምህርት ፖሊሲ ረገድ እየደረሰበት ካለው ግፍ በተጨማሪም፣ ኦነግ እየተባሉ በሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን እየታሰሩና እየተሰቃዩ ናቸው። ሕወሃት/ኢሃዴግ በአንድ በኩል እነሌንጮን ቀንደኛ ኦነጎችን እያባበለ፣ በሌላ በኩል የነሌኝቾ ደጋፊ ናችሁ እያሉ ሰላማዊ ዜጎችን ያስራል።

ታዲያ መፍትሄዊ ምንድን ነዉ ? አራት መፍትሄዎች አሉ፡

1. ኢትዮጵያዉያን አፋቸዉን በየትኛው ቋንቋ ነዉ የፈቱት የሚለዉን ጥያቄ ብንጠይቅ ፣ በአንደኝነት የሚቀመጠዉ ኦሮምኛ ነዉ። በበርካታ ዞኖች ከዘጠና በመቶ በላይ ኦሮምኛ የሚነገርባቸው ቦታዎች አሉ። 33.8 % የሚሆነው ሕዝባችን አንደኛ ቋንቋዉ አፋን ኦሮሞ ነዉ። 29.36% የሚሆነው ህዝብ አማርኛ አንደኛ ቋንቋዉ ነዉ። ሁለቱ ቋንቋዎች እንደ አንደኛ ቋንቋ የሚናገሩ 63.2% ይደርሳሉ። በመሆኑም ኦሮሞኛ ከአማርኛ ጎን የፌደራል ቋንቋ ቢሆን ትልቅ ጥቅም ይኖረዋል።

2. በሁሉም ክልሎችና ወረዳዎች፣ በአካባቢዉ ከሚነገረው ቋንቋ ጎን ለጎን፣ ተማሪዎች አማርኛ እንዲማሩ መደረግ አለበት። አማርኛ እንደ አንደኛ ቋንቋ 29.3% የሚሆነው ሕዝብ ይናገረዋል። እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ደግሞ፣ ከ30፣ 40 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ሊናገረው ይችላል ብዬ አስባለሁ።በመሆኑም አማርኛ ማወቅ ጥቅም አለው። ቋንቋ በአጠቃላይ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። አማርኛን መማር ኦሮሞኛን አይጎዳም። የኦሮሞ መሪ ነን የሚሉ ፖለቲከኞች፣ ለራሳቸው ልጆች እንዳሰቡት፣ ለተቀረዉም የኦሮሞ ልጅ ሊያስቡ ይገባል ባይ ነኝ።

3. የኦሮሚያ ክልል መንግስት አማርኛን ከኦሮሞኛ ጎን የሥራ ቋንቋ ማድረግ አለበት። ኦሮሞኛ የማይናገር በክልሉ አስተዳደር ዉስጥ የመስራት መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። በኦሮሚያ 95% ነዋሪዉ ኦሮሞኛ የሚናገር ቢሆን፣ እሺ አንድ ነገር ነዉ። ግን ከ 15% በመቶ በላይ ሕዝብ አንደኛ ቋንቋም ኦሮሞኛ ባልሆነበት፣ «አፋን ኦሮሞ ብቻ ወይንም ሞት» ማለት ትልቅ ስህተት ነዉ። በክልሉ ዋና ከተማ አዳማ/ናዝሬት እንኳን ፣ አንድ አራተኛ ሕዝብ ብቻ ነው ኦሮሞኛ የሚናገረው።

4. ናዝሬት/አዳም እና ጂማ የመሳሰሉ እንደ አዲስ አበባና ድሬደዋ፣ ለጊዜዉ ቻርተር ከተማ ቢሆኑ መልካም ነዉ። (ለዘለኬታዉ፣ ለሁሉም በሚበጅ፣ የተለያዩ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባና በተጠና መልኩ ፣ፌደራል አወቃቀሩ እንደገና በአዲስ የሚዋቀርበትን ሁኔታ በመፈለግ ለብዙ ችግሮች መፍቴሄ ማግኘት ይቻላል)

ከላይ የዘረዘርኳቸዉ አሃዞች በኦፊሴል ከተመዘገበዉ የኢትይጵፕያ ሕዝብ ቆጠራ ሪፖርት ነዉ። በሚቀጥለው ጊዜ የቤኔሻንጉል ጉምዝ እና ሃረሪ ክልሎችን እንመለከታለን።


[የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] የፍርድ ቤቱ ውሎ ይህን ይመስል ነበር –ከቤዛ ለኩሉ ሰንበት ት/ቤት ሕዝብ ግንኙነት

$
0
0

debereselam Minnesota
ከሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የቤዛ ኩሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ለሕዝብ ያወጣው መረጃ ለዘ-ሐበሻ ደርሷል። የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሕዝብ ግንኙነት ያሰራጨው ዜና እንደወረደ ይኸው፦

የቤተክርስቲያን ውሎ በጲላጦስ አደባባይ

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን

ዛሬ ቤተክርስቲያናችን በጲላጦስ አደባባይ ላይ እንደምትቆም ስላወቃቸሁ ግማሾቻችሁ በአካል በመገኘት፤ አብዛኞቻችሁ ድግሞ ካላችሁበት ቦታ “እለት እለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሃሳብ ነው” እንዳለ ቅዱሱ ሐዋርያ (ቆሮ ፲፩፡፳፰) ( በፀሎትና እንባ ቀኑን ለቤተክርስቲያን ድል የሆን ዘንድ ፀልያችኋል አልቅሳችኋል።

የእግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን ውሳኔው ይህን ይመስል ነበር……
፬ቱ የቦርድ አባላት (አቶ ጥበቡ፤ ቀስስ አዲስ፤ ወ/ሮ ደብረ ወርቅና አቶ አዳም) የቤተክርስቲያን አስተዳደሩን የከሰሱት በነዚህ ነጥቦች ዙሪያ ነበር…
1- – የሕዝቡን ውሳኔ አንቀበልም አሉ
2-ያለ ሊቀ መንበርና ም/ሊመንበር ፍቃድ ያደረጉት የ January 23, 2014 ስብሰባ ሕጋዊ አይደለም
3- አቶ ጥበቡን ከሊቀመንበርነት አወረዱ
እነሱ ዳኛዋ እንድትወስን የፈለጉት….
1- በ ጃንወሪ 23 የተጠራው የቦርድ ስብሰባ ኢ-ሕጋዊ አይደለም ዳኛዋ እንድትል
2- ምንም አይነት ስብሰባ እስከ ፌብ 23 ቦርዱ እንዳያደርግ፡ ለጊዜው እንዲታገድ (Temporary injunction)
3- ፍራቻቸው– ብር ያዘዋውርሉ፡

ይህንን ሁሉ ክስ ዳኛዋ ከአዳመጠች በኋላ ያቀረቡትን ሁሉ ክስ ውድቅ አድርጋለች። ስለዚህ በ ጃንዋሪ 23 የተደረገውን የቦርድ ስበሰባ ሕጋዊነቱን ዳኛዋ አስድቃለች። ነገር ግን እንደ መተዳደሪያ ደንቡ መሠረት (by law) ጠቅላላ ጉባዔ ሲጠራ የአቶ ጥበቡን ከሥልጣን መውረድና የአቶ ይመርን ሊቀመንበርነት ጠቅላላ ጉባዔው ያፀድቃል። እሰከዛ ድረስ አቶ ይመር ሕጋዊው ሊቀመንበር ናቸው። አቶ ጥበቡ በቦርድ ስብሰባ መሳተፍ አይችሉም። ባንኩኑም ቦርዱ unfreeze አድርጎ መደበኛ አገልግሎቱን ይቀጥላል።
-የ፬ቱ ካሳሾች ጠበቃ፤ ቀሲስ አዲስ ወደፊት የሚጠራውን ስብሰባ እንዲመራ ጥያቄ (recommendation) አቅርበዋል። ቦርዱም ለስብሰባ ሲቀመጥ ይወያይበታል።
የፌብ 23 ጠቅላላ ጉባዔ ይኑር አይኑር ወይንም ወደፊት ይራዘም የሚወስኑት ቦርዱ ነው እንጂ አቶ ጥበቡ በቦርድ ስብሰባ ምንም ተሳትፎ ከአሁን በኋላ አይኖራቸውም።
- March 10 2014 የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተይዟል

እንግዲህ ቅድስት ቤተክርስቲያን በራሷ ልጆች ተጎትታ በዛሬው አማኑኤል ቀን (ጥር 28. 2006 ዓ/ም) የፍርድ ቤት ውሎዋ በአጭሩ ይህን ይመስል ነበር።
በእግዚአብሔርም ክብርም ተስፋ እንመካለን። የህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ እንመካለን በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። (ሮሜ ፭፡፪-፭)

ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥
2ቆላስይስ 3፡23

ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ

$
0
0

- ግርማ ካሳ

ከበደ ካሳ የሚባሉ አፍቃሪ ኢሕአዴግ ግለሰብ “አንዳንድ ሰዎች «ብሄር ..?» ተብለው ሲጠየቁ «ኢትዮጵያዊ!!!…» እያሉ የሚመልሱት፣ የራሳቸዉን ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አድርገው ያስቀመጡና በራሳቸው ማንነት የሌሎቹን ለመጨፍለቅ የሚያልሙ – የቅዠት ታንኳ ቀዛፊዎች ናቸው…. ተዛብታችሁ ሌላንም ለማዛባት ለምትፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ብሄር አይደልም። ኢትዮጵያ ሃገር እንጂ የአንድ ሕብረተሰብ ክፍል መለያ አይደለም።” የሚል አባባል ፌስቡክ ላይ ለጥፈው አነበብኩ።
በአንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ሕገ መንግስቱ እንዲህ ይላል ፡
UDJ - Ethiopia
“በዚህ ሕገ መንግስት ዉስጥ «ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸዉን ባህርይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነዉ። ሰፋ ያላ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልዉና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛዉ በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው»

እንግዲህ እዚህ ላይ እናስተዉል። ለብሄር የተሰጠው ትርጉምና ለብሄረሰብ የተሰጠው ትርጉም አንድ አይነት ነዉ። በአጭሩ ብሄር ማለት ብሄረሰብ ማለት ነዉ በሕገ መንግስቱ መሰረት።

ብሄር በእንግሊዘኛ ኔሽንስ ማለት ነዉ። «ዩናይትድ ኔሽንስ» ስንል የተባበሩት መንግስታት (የተባባሩት አገሮች ማለታችን ነዉ) ። እንደሚገባኝ ኢትዮጵያ እንጂ፣ ኦሮሞ፣ ወይንም፣ ትግሬ ወይንም ወላይታ የተባበሩት መንግስታት አባል አይደሉም።
«ብሄር» የሚለዉን ቃል የመጀመሪያ አመጣጥ ስንመለከት ፣ ከግእዝ የተወሰደ እንደሆነ እንረዳለን። ትርጉሙም በግእዝ አገር ማለት ነዉ።

ስለዚህ ኢሕአዴግን እና ኦነግ በሕገ መንግስቱ ብሄር የሚለዉን ቃል ያኔ የወሸቁት፣ ኢትዮጵያን እንደ አንዲት አገር ሳይሆን የተለያዩ የአገሮች ስብሰብ እንደሆነች ለማሳየት፣ በፈለጉ ጊዜ ደግሞ ከኢትዮጵያ ለመለየት አማራጭ እንዲኖራቸው ከመፈለግ የተነሳ ነዉ።
ፕሮፌሰር ተኮላ ሃጎስ ደግሞ ብሄር ብሄረሰብና ሕዝብ የሚለውን ለምን ሕገ መንግስቱ ዉስጥ እንደገባም ሲጽፉ የሚከተለዉን ነበር ያሉት፡

“The phrase “the nations, nationalities and peoples” thus found in the Ethiopian Constitution is a legacy from the writings of immature and juvenile diatribe of badly educated and socially disfranchised and radicalized students of Haile Selassie I University of the 1970s. It is the ersatz voice of Meles Zenawi forcing himself through the 1995 Constitution on the People of Ethiopia his narrow and ignoramus ideas on the history of Ethiopia and the process of nation building”

ስለዚህ «ብሄርህ ምንድን ነዉ ?» ተብሎ አንድ ሰው ሲጠየቅ «ኢትዮጵያዊነት» ብሎ ከመለሰ፣ በትክክለኛዉ የግእዝ አተርጓጎም እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ብሄር የሚለው ቃል ያለው አጠቃቀም አንጻር፣ ትክክለኛ መልስ ነዉ።
«ብሄረሰብህስ ምንድን ነዉ ? » የሚል ጥያቄ ቢነሳስ ?

አንድ መርሳት የሌለብን ነገር አለ። አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የተደባለቀ ነዉ። ሰሜን ጎንደና ሰሜን ወሎ ከሄዳችሁ ትግሪኛ ተናጋሪዉና አማርኛ ተናጋሪዉ ተደበላልቋል። ኦሮሚያ ዉስጥ በሸዋ፣ በሰሜን እና በምስራቅ ወለጋ..፣ አማራዉ ክልል ደግሞ በወሎ ፣ ኦሮሞኛ ተናጋሪው ከአማርኛ ተናጋሪው ተደባልቋል። በምስራቅ ሃረርጌና በባሌ ደግሞ ሶማሌዉና ኦሮሞዉ የተደባለቀበትም ሁኔታ አለ። በደቡብ ክልል ከሄድን፣ ወላይታዉ ከሲዳማው፣ ከንባታዉ ከሃዲያዉ …ሁሉም ተበራርዟል። ስለዚህ በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የብዙ ብሄረሰቦች ድብልቅ ናቸው። በመሆኑም «ብሄረሰብህ ምንድን ነዉ?» ተብለው ሲጠየቁ እዚም እዚያም በመሆናቸው፣ ለመመለስ ይቸግራቸዋል። ስለዚህ በአጭሩ በብሄረሰባቸው ወይንም ዘራቸው ሳይሆን በኢትዮጵያዊነታቸው መለየትን ይመርጣሉ። ከነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነኝ።
አቶ ከበደ፣ ኢትዮጵያዊያን፣ ብሄራችን ኢትዮጵያዊነት ነው ማለታቸው፣ የሌሎችን ማንነት ለመጨፍለቅ እንደመሞከር አድርገውም ወስደዉታል። አንድ ሰው «ኦሮሞ ነኝ፣ ትግሬ ነኝ ወዘተረፈ » የማለት መብቱ ከተከበረለት፣ ሌላው «አይ እኔ በዘሬ መለየት አልፈልግም፣ በኢትዮጵያዊነቴ ነዉ መለየት የምፈልገው » ካለ የርሱስ መብት ለምን አይከበርለትም ? ኦሮሞ፣ ወይም ትግሬ ፣ ወይም አማራ ያለመባል መብቱ መጠበቅ የለበትምን?

በኢሕአዴግ መንግስት፣ ይሄ መሰረታዊ መብት እየተጠበቀ አይደለም። እያንዳንዱ ዜጋ፣ እነርሱ ብሄር ብሄረሰብ የሚሉት አንዱ የዘር ሳጥን ዉስጥ መግባት አለበት። ያ ካልሆነ መታወቂያ እንኳ ማግኘት አይቻልም።

እንግዲህ ይሄንን ነዉ የምንቃወመው። «ለአገራችን የሚያዋጣዉ ዘር ላይ ማተኮር ሳይሆን፣ሥራ ላይ ማተኮር ነዉ። መመዘን ያለብን በዘራችን ሳይሆን በስራችን መሆን አለበት» እያልን ነዉ።
አፋን ኦሮሞ፣ ትግሪኛ፣ ጉራጌኛ፣ ሃምባሻ፣ ቆጮ ….በተለያዩ የአገራችን ግዛቶች ያሉ የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችን ፣ ምግቦች …ሁሉም «ኢትዮጵያዊነት» ናቸው። ሁሉም የኢትዮጵያ መገለጫዎች ናቸው። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ አይደለችም። የተለያዩ ባህሎችን ፣ ቋንቋዎች፣ በአጭሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች ያሉባት አገር ናት። ቢራቢሮዎችና አበባዎች የተለያዩ ቀለማቶቻቸው ዉበታቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ዉበቷ ብሄረሰቦቿ ናቸው።

ግርማ ጌታቸዉ ካሳ
ዘብሄረ ኢትዮጵያ ( የዶር ፍቅሬ ቶሎሳን አባባል ልዋስና)

የብዕር ዕጢ –መናጢ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 07.02.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

Cry  ethiopiaዛሬ ልተርብ ሳይሆን ከልብ ሆነን በጎርባጣ መንገዶች ሊያስጉዙን የሚሽቱትን ፈንጋጣ ስሜቶች ከልብ ሆነን ባትኩሮት እንመረምር ዘንድ ፈለግሁኝ። ብላሽ – ዬቀለም ብዕር …. ሲባዛ መንፈስን ይበጥሳል ሲያንሰ ይሸረሽራል። ለመሆኑ ማንና ምን እንዲመራን እንፍቅዳለን? ናፍቆታችንስ ምንድን ነው?!
ህም! ቀዶ ጥገና ማድረግ ሽው አለኝ። ዖዬ! በምኞት ቀረ እንጂ የወጣልኝ የባይወሎጂና የኬሚስትሪ ትጉህ ተማሪ ነበርኩኝ። ያ .. ቢቀር ደግሞ ቢያንስ በደም ውስጥ የመርዝ መስኖ ቦይ ለከፈተ ባለ ዕጢ ብዕረ- በዝውውሩ ላይ ማዕቀብ ጥሎ ወደ ሆስፒታል ጎራ በማደረግ የተበከለውን ደም አጣርቶ በንጡህ ደም መተካት ግድ ይላል። የትውልዱ ንጹህ መንፈስ እጅ የሚያነሳ ወደርየለሽ ቅዱስ መንፈስ ሆኖ፤ የባለ ዕጢዋ ግን በካይ ሆነብን። ስለሆነም ግራ ቀኙን በንጽጽር በማቅረብ ለስሜታችንና ለፍላጎታችን የራቀውን ገፍቶ፤ የቀረበውን ማጣጣም ሸጋ ነው። ለነገሩ ባለ ዕጢዋ ብዕር ድሃ አይደለችም ምን አጥታ ዲታ ናት። መልክ ጥፉም አይደለችም ደም- ግቡ ናት። ነገር ግን ጣል ጣል የምታደርጋቸው ማላታይሎች ነገ ከመምጥቱ ቀድማ ችግር ጠሪ በመሆኑ ትፈተሽ፤ ትበርበር ተብሎ ብይን ተላላፈባት — እንዲህ ከወደ ሲዊዘርላንድ …..

Read Full Story in PDF/ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

[የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሕዝብ ግንኙነት ቅጥፈት ሲጋለጥ

$
0
0

ከመ/ር ሰናይ ገ/ህይወትና ቴዎድሮስ

በቅድሚያ ዘሀበሻ ድረ ገጽ ሁለቱንም ወገኖች ህሳባቸውን ለማደመጥ የምታደርገውን ጥረት አደንቃለሁ። ሆኖም ግን ሃገር ቤት ካለው ሲኖዶስ ጋር እንዲቀላቀል ከሚፈልገው ወገን የሚሰጠውን ሃሰተኛ ዘገባ ዘሀበሻ ለሚዛናዊነት በሚል በቀጥታ ከማስተናገድ ይልቅ ቆም ብላ ብታስብበት መልካም ነው እላለሁ። ዛሬ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ትናንት በዚሁ ድረገጽ ላይ የታተመውን የቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በኢሜይል እና በተለያዩ ዘዴዎች የበተነውን መግለጫ ይመለከታል። ዘገባው እጅግ ሃሰት እንደሆነና ሁሉም ነገር በፍርድ ቤት ውድቅ እንደሆነ የዘገበበትን ቅጥፈት ለማጋለጥ ነው ወደዚህ ብቅ ያልኩት።

ከአንድ የሰንበት ትምህርት ቤት አባል ወይም መሪ ነኝ ከሚል ሰው የማይጠበቅ ቅጥፈት ተፈጽሟል። ይህም እግዚአብሔርን ያሳዝናል። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ዶክመትን እንደሚከተለው አያይዣለሁ፤ አንባቢዎች እንደሚፈርዱም ይህ ያሳያል።
order for trial (1)_Page_1
ልብ ብላችሁ ካነበባችሁት በመጨረሻው መስመር ላይ “ከማርች 10 በፊት የሚስማሙ ከሆነ” ይላል። ይህ ማለት የሚጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ነው። ይህን ደግሞ ዘሀበሻም ቀድሞ ዘግቦታል። የሰንበት ትምህርት ቤቱ እንዳወራው ቅጥፈት ፍርድ ቤቱ በጽሁፍ ባወጣው ትዕዛዝ ላይ ስለ ቦርዱ፣ ስለገንዘቡ፣ ወዘተ… የሚያወራው የለም። የእግዚአብሄርን ስም እየጠሩ ቅጥፈት ያሳፍራል።

እኔን የገረመኝ ቤተክርስቲያኑን በተመለከተ ይህን የመሰለ ሃሰተኛ ወሬ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ሲያሰራጭ ደብረሰላምን የሚመራው ማን ነው? የሚለውን ጥያቄ ውስጥ ይከታል።

ውድ ወገኖች፤ እውነቱ ይኸው ነውና በቀጣዩ የአጠቃላይ ጉባኤ ላይ በመገኘት ለውሳኔ እንዘጋጅ። ቤተክርስቲያናችንን የምናድነው ያኔ ነው።

ተጨማሪ አስተያየት ቴዎድሮስ ከተባሉ የቤተክርስቲያኑ አባል የተሰጠ ይከተላል

የሜኖሶታ: ደብረሰላም: መድሀኒአለም: ቤተክርስቲያንን: የውስጥ: ችግር: ለመፍታት: በ02/05/2014 የነበረው: የፍርድ: ቤት: ውሎ: እና በዳኛዋ: የተሰጠ: ያልተዛባ: ውሳኔ: እንደሚከተለው: ነው።

በመጀመሪያ: ከላይ: በተጠቀሰው: ቀን: የአቶ: ጥበቡ: እና: አቶ: ጥበቡን: አወረድኩ: የሚለው: ቦርድ: በጠበቆቻቸው: አማካኝነት: ጉዳያቸውን: አቅርበው: በተከበረው: ፍርድ: ቤት: የተከራከሩ: ሲሆን፣ የተከበሩት: ዳኛ: ነገሩን: ከነመረጃቸው: ካዩ: ቡሃላ: የሚከተለውን: አጠቃላይ: መመሪያ: ለሁለቱም: ወገን: ጠበቆች: ሰጥተዋል።
1፣ አጠቃላይ: የአባላት: ስብሰባ: ለ02/23/2014 እንዲደረግ (ይህ: የተወሰነው: አቶ: ጥበቡ: ባቀረቡት: የ 355: የአባላት: ግልፅ: እና: እውነተኛ: ፊርማ: ነው።)

2፣ በ 02/23/2014: በሚደረገው: አጠቃላይ: የአባላት: ስብሰባ: ጊዜ: አባላቱ: ማድረግ: የሚፈልገውን: ማንኛውንም: አይነት: አጀንዳ: አንስቶ: የማፅደቅና: የመጣል: ፍፁም: ሙሉና: ያልተገደበ: መብት: አለው።

3፣ ምክትል: ሊቀመንበሩ: ለጊዜው: የሚሰሩ: ስራዎችን: ያከናውናል።

4፣ የባንክ: አካውንቱ: ከመደበኛ: ክፍያዎች: ውጪ: መጠቀም: ወይም: ማንቀሳቀስ: ፈፅሞ: አይቻልም።

5፣ ይህ: ጉዳይ: በአጠቃላይ: ስብሰባው: ካልተፈታ: የተከበሩት: ዳኛ: በ 03/02/2014: ነገሩን: አይተው: የፍርድ: ሂደቱ: ይቀጥላል: ማለት: ነው።

እነዚህ: ናቸው : እንግዲህ: አጠቃላይ: ውሳኔዎቹ።
ማንኛውም: ሰው: እነዚህን: የዳኛ: መመሪያዎች: ከሁለቱም: ጠበቆች: ማግኘት: ይችላል። በጣም: የሚገርመው: ይህ: የተከበሩት: ዳኛ: ውሳኔ: በኢትዮጽያ: ሲኖዶስ: ይሁን: የሚሉትን: ጠበቃ: እና: ደንበኞቿን: ለምን :እንደሚያስፈራቸውና: እንደሚያስደነግጣቸው: አይገባንም። በተለይ: ለምን: አጠቃላይ: ስብሰባን: እንደጦር: እንደሚፈሩት: ሲታይ: በጣም: ይገርማል።
ይህ: አሜሪካ: ነው። ማንም: የማንንም: መብት: የሚገድብበት: መብት: የለውም። በተጨማሪም: የሜኖሶታ: መድሀኒያለም: ቤተክርስቲያን: የህዝብ: እንጂ: የጥቂት: ሰዎች: አይደለም። እናም፣ እንደራሳችሁ: የግል: ቤትና: ንብረት: መቁጠራችሁን: ትታችሁ: የህዝቡን: ድምፅ: ያለምንም: ቅድመሁኔታ: በፍፁም: ትህትናና: አክብሮት: ስሙ።
debereselam Minnesota

የቤተ መንግስት ዙሪያ መፈክሮች!

$
0
0

ከቤታቸው ሽፈራው

ድሮ በቤተ መንግስት ዙሪያ ሳልፍ የሆነ ነገር ይጫጫነኝ ነበር፡፡ በቃ! ቤተ መንግስቱ አንዳች ጣኦት የሚመለክበት፣ አሊያም ባዕድ ነገር የሞላው አድርጌ ስለምቆጥረው በአካባቢው ማለፍ ይከብደኝ ነበር፡፡ አሁን ግን ቤተ መንግስቱ አጥር ላይ የተሰቀሉት ጽሁፎች ይህን ድባብ በትንሹም ቢሆን ቀይረውልኛል፡፡ እነዚህ መፈክሮች ሁሌም ያስፈግጉኛል!
meles fun
የአቶ መለስ ሞት ከተነገረ በኋላ እንደ ማንኛውም የአዲስ አበባ ነዋሪ ቤተ መንግስት የመግባት እድል ባገኝም ለመግባት ደስተኛ አልነበርኩም፡፡ አንድ ቀን እንደምንም ደፍሬ በለቅሶ ስም ይህን የምጠላውን ቤተ መንግስት ለመጎብኘት ወንድሜን ሳማክረው ‹‹መለስን ያልሰራውን ሰራ እያሉ የሚዘሉ የሚፈርጡትን ካድሬዎች ስናይ ሳቃችን ያመልጠናል፡፡ ይቅርብን!›› የሚል ጠቃሚ ምክር ስለለገሰኝ ቤተ መንግስቱን ሳላየው ቀርቻለሁ፡፡

በእርግጥ ቤተ መንግስት ውስጥ ለማስመሰል ሲዘሉ የነበሩትን ካድሬዎች በኢቲቪ መስኮትም አይቼ ሆዴን ጨብጩ ስቄያለሁ፡፡ የፈረንሳይ ልጆች ደግሞ ይህን የካድሬዎች የለበጣ ለቅሶ ‹‹አሸባሪ በለኝ፣ አንድ ለአምስት ጠርንፈኝ፣ የምርጫ ኮረጆ ልገልብጥልህ፣ ትምክተኝ ብለህ ስደበኝ፣ ተንበርካኪ በለኝ፣ ልማታዊ በለኝ፣ በይቅርታ አስፈርመኝ፣…….›› እያሉ በሽሙጥ ሲያለቅሱ እንደልባችን እየሳቅን የምንታደምበትን ቤተ መንግስት (ፈረንሳይ) መረጥን!

ቤተ መንግስት ባንገባም ስለ አቶ መለስ የሚባሉትን ነገሮች ከአልቃሾቹ እኩል በኢቲቪና ጎዳና ላይ እንከታተላለን፣ እናነባለን፡፡ በዚህ ረገድ ቤተ መንግስቱ ዙሪያ የተሰቀሉት መፈክሮች ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ በተለይ የመጀመሪያው ሰሞን ላይ እነዚህን ጽሁፎች ስመለከት በሚቀፈኝ መንገድ እንደ እብድ ገጥጨበታለሁ፡፡ በርካቶችም ልክ እንደ እኔ ሲስቁ ተመልክቻለሁ፡፡

ከአራት ኪሎ በኩል በሚገኘው የቤተ መንግስቱ ጫፍ ላይ ‹‹ጀግና አይሞትም!›› የሚል መፈክር ከአቶ መለስ ፎቶ ጋር ተሰቅሏል፡፡ ይህኔ ከአርጀንቲና ቮልቪያ፣ ከዛም ኩባ፣ ከደቡብ አሜሪካ ወደ አፍሪካዋ ኮንጎ በጎሳ፣ ዘውግ፣ ሀይማኖት፣ ቀለም የማይመሳሰሉትን ዜጎች ከጭቆና ለማውጣት የባዘነውን ‹‹ቼ››ን አሰብኩት፡፡ ሁችሚኒ፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ ቴዎድሮስ፣ በላይ፣ አቢቹ፣ አሉላ፣ አብዲሳ አጋ…….ህዝብን በጎሳና ዘውግ ሳይከፋፍሉ መሞታቸውን አስታወስኩ! ታዲያ የትኛው ጀግና ነው የማይሞተው? ነው የጀግና ትርጉም ተቀየረ? እያልኩ በማሰላሰል ላይ እያለሁ ሁለተኛውን መፈክር ተመለከትኩ፡፡

‹‹ዓለም ያጣችው ምርጥ መሪ!›› የሚል ነው፡፡ ዓለም ቤተ መንግሰቱ ነው? አዜብ መስፍን ናቸው? ቻይና ነች? እያልኩ ከራሴ ጋር ስቀልድ የመጀመሪያውን መፈክር በሙሉ ድምጽ የሻረ ሌላ መፈክር ተሰቅሎ አየሁ፡፡ ይህኛው ጉደኛ መፈክር ‹‹የጀግና እረፍቱ ሞቱ ነው!›› ይላል፡፡

ይህ ለሌላ ሰው ነው እንዳልል የአቶ መለስ ፎቶ ተለጥፎበታል፡፡ አዎ! ለመጀመሪያ ጊዜ ያንን በዓድ መንገድ ረዥም ሳቅ ሳቅኩበት፡፡ በቤተ መንግስቱ አስቂኝ መፈክሮች መሰረት 20ና 30 ሜትር ውስጥ ዘላለማዊ የነበረ ‹‹ጀግና›› ለእርፍት ወደ ሰማይ ቤት ያመራል፡፡ በዛን ሰሞን ወይዘሮ አዜብ መስፍን ቤተ መንግስቱን የራሳቸው ንብረት አድርገው ‹‹እዩት የእኛን ቤት፣ ይህ ነው የእኛ ቤት፣….›› እያሉ ሲያስጎበኙ በጣት የሚቆጠሩ ሰከን ያሉ ካድሬዎች ሳይቀሩ ‹‹እኒህ ሴትዮ ጭራሹን ባሰባቸው›› ብለው አሽሟጥጠዋል፡፡ እኔም ምን አልባት እነዚህ ጽሁፎች በአዜብ መስፍን ትዕዛዝ የተሰቀሉ ቢሆኑስ? የሚል ሀሳብ መጣብኝ፡፡ ደግሞ ‹‹ቤቴ ነው!›› ከሚሉት ቤተ መንግስት አጥር ድረስ ይቅርና ሳውዲና ስይዘርላንድ ድረስም በአገሪቱ ገንዘብ የሚያንጋጉዋቸው ታማኞች እንዳሏቸው አውቃለሁ፡፡ ከወይዘሮ አዜብ ጋር ቤተ መንግስቱ ውስጥ ሲያለቅሱ የነበሩትን ግራ አጋቢ ካድሬዎች አስታወስኩ! ግራ የተጋቡ ካድሬዎች በበዙበት መፈክሮቹም የትየለሌ ናቸው!

አንዳንዶቹ ከጎኑ ደግሞ ምን አልባትም አቶ መለስ አምስትና ስድስት አመታቸው የተነሱት ፎቶ ግራፍ አብሮ ተለጥፏል፡፡ አቶ መለስ በአምስትና ስድስት አመታቸው ጀምረው ነው ኢትዮጵያን ሲመሩ የኖሩት ከሚል እሳቤ የመጣ መሆን አለበት፡፡ ይህኛው ደግሞ ከሀይማኖት አባትነታቸው ይልቅ ካድሬነታቸው ከሚያመዝነው ‹‹የሀይማኖት አባቶች›› የተበረከተ ይሆናል፡፡ ልክ እየሱስ ክርስቶስ ልጅ ሆኖም ጌታ እንደነበረው ማለት ነው፡፡

አሁን የቤተ መንግስቱን አጥር እያጋመስን ነው፡፡ ሌላ መፈክር! ‹‹አንተ ብትሞትም ራዕይህ ይቀጥላል!››፡፡ ይህኛው እረፍትም ሆነ ዘላለማዊነት የለውም፡፡ በእነዚህ መፈክሮች ተቃርኖ ሳቄን ሳላባራ ማዶ ላይ በላቸው ግርማ ከአንዲት አሮጊት፣ ሸገር ብሎ ደግሞ ከወት ጋር ተንጋሎ እየሳቀ ተመለከትኩት፡፡ እነዚህ መፈክሮች አይደለም አንተን? ሌላ ቀን ግርማቸው በደረቁ ነው የሚስቀው፤ ቤተ መንግስት ፊት ለፊት ያለው ግርማቸው ግን ሁሌም ከምር ይንፈረፈራል! እኔም ተክዤ፣ ተናድጄ፣ ደክሞኝ ውዬም ቢሆን የምስቀው ቤተ መንግስት ስደርስ ነው፡፡
የገረመኝ የኃይሌ ጉዳይ ነው፡፡ ብዙዎቹ በሚስቁበት ጎዳና ሁሌም አረቄውን ከፊቴ አጋድሞ ይሮጣል፡፡ ከፊቱ ላብም ይሁን እንባ ብቻ የሆነ ነገር ይታየኛል፡፡ እምባ መሆን አለበት፡፡ የመፈክሮቹን ተቃርኖ የተመለከተማ (በአረቄ) ስካር የተጻፉ ስለነሆናቸው ቢጠረጥር አይፈረድበትም፡፡ መጠርጠር ነው!

እውን ሻዐቢያ እና ህወሀት ተጣልተዋልን?

$
0
0

(ሁኔ አቢሲኒያዊ)

ማማ እና የሾላ ወተት ሁለቱም ወተት ናቸው የሚለያቸው ነገር ቢኖር ማማ ማማ መባሉ ሲሆን ሾላ ደግሞ ሾላ መባሉ ነው እንደዚሁ ህወሀት እና ሻዐቢያም የስም እንጂ የይዘትም ሆነ የአላማ ልዩነት የሌላቸው ጸረ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ፀረ ኢትዮጵዊ መሆናቸው ሀቅ እና ምስጢር ያልሆነ ነው ይልቁንስ በዚህች አነስተኛ ጦማር ማሳየት የፈለኩት ሻዐቢያን አምነው የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለመቀየር ከኢሳያስ ጋር ስለተወዳጁ ወገኖቻችን ጉዳይ ነው።
isayas afewerki
ምርጫ 2002 በተቃረበበት ወቅት በኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ቀረበ የተባለው እና በፊታውራሪ ህወሀቶች ጭምር ድጋፍ ተሰጥቶት ነበረ የተባለው የስልጣን እንልቀቅ ጥያቄ ውድቅ የተደረገው እኛ ስልጣን ከለቀቅን ሻዐቢያ በእጅ አዙር ሀገሪቷን ሊመራት ስለሚችል ስልጣን መልቀቃችን ሊታሰብ የማይችል ነው ሲሉ በተላላኪ ጋዜጠኞቻቸው በኩል አስነገሩ ብዙሀኑ ምስኪን የግል ጋዜጦችም ይህንን ጉዳይ አንስተው ከሁሉም ጆሮ እንዲዳረስ አደረጉ፡፡ ይህ ሁኔታ ወያኔ ኢህአዴግን በሁለት መንገድ ተጠቃሚ አደረገው እነርሱም፡-

1. ሻዐቢያ እውነትም ፀረ ኢትዮጵያዊ ነው ኢህአዴግ ከወደቀ ደግሞ ሻዐቢያ ኢትዮጵያን ይቆጣጠራል የሚለው አስተሳሰብ ውስጥ ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊ ጥልቅ ብሎ እንዲገባ ያስቻለ ሲሆን

2. በሌላ በኩል ዲያስፖራ ላይ የመሸጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እነ ኦነግ ከኢሳያስ ጋር ተለጥፈው ለምን ውጤታማ ሳይሆኑ ቀሩ እንኳን ብለው ሳያጤኑ ሻዐቢያ የወያነ ጠላት ስለሆነ ለእኛ እና ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ብቸኛው ኢትዮጵያን ነጻ የማውጫ መንገድ አስመራ ላይ መክተም ነው ብለው አውጀው የማይታመነውን ኢሳያስን አምነው አስመራ ከተሙ፡፡

እነዚህ ሁለት ከላይ የጠከስኳቸው ሁለት አብይት ጉዳዮች ወያኔን ተጠቃሚ ያደረጉ እንዲሁም የኢትዮጵያን ፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲዳከሙ ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች ነበሩ፡፡

– እውን ህወሀት እና ሻዐቢያ ተጣልተዋል ወይስ ጥላቸው ለሚዲያ እና ለህዝቡ ጆሮ ብቻ ነው?
- ኤርትራ የከተሙ ፓርቲዎችስ ስለምን ውጤታማ አልሆኑም?
- እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ እስኪ በቅድሚያ ይህንን ሀሳብ በአዕምሯችን እናሰላስለው
- ሻዐቢያ አሰብ የራሱ እንዲሁም የኤርትራ ንብረት እንደሆነ ያምናል
- ህወሀትም አሰብ የኤርትራዊያን ንብረት እና ሀብት ነው ብሎ ያምናል

በተቃራኒው ብዙዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሰብ የኢትዮጵያ ነው አልፎም ተርፎ የኤርትራን መገንጠል የማይደግፉ ናቸው ታድያ የኛ ፓርቲዎች እንደምን ብለው ነው ኢሳያስን አምነው አስመራ ላይ የከተሙት እውን ኢሳያስስ አሰብ የኢትዮጵያ ናት ብለው የሚሰብኩት ተቃዋሚዎች ይሻሉታል ወይስ ኤርትራ ነጻ ሀገር ነች አሰብም የኤርትራ ነች የሚለው ወያኔ?

ህወሀት እና ሻዐቢያ በስልጣን ላይ ለመቆየት የማይገድሉት ሰው የማይቆፍሩት መሬት የለም በኤርትራ ሪፈረንደም ወቅት እስካሁን ትርጉሙ ሊገባኝ ባልቻለ መልኩ የመለስ ዜናዊ እናት ኢትዮጵያ ሬድዮ ላይ ቀርባ ኤርትራዊያን ነጻ ሀገር ስለሆኑ እንኳን ደስ ያላቹህ ያሉ ሲሆን ነጻነቱም እንደሚገባቸው ተናግረዋል ነገር ግን ከአመታት በኋላ እነዚሁ የህወሀት ባለስልጣናት እናቶቻቸውን ሁሉ ያስደሰተውን መልካ ግኑኝነት ወደኋላ ብለው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተፈጠረ ተባለ እና ከ 78000 በላይ ወጣት ኢትዮጵያዊያን እንዲፈጁ ተደረገ ይህም ጠንካራ የነበረውን የኢትዮጵያ ወጣት እሳት ውስጥ የማገደ ብሎም የቀረው ጠንካራ ወጣት እንዲሰደድ ምክንያት የፈጠረ ሴራ ነበር በጦርነቱ መሀል መሪዎቻችን ምን ያደርጉ እንደነበር በቅርቡ ዊኪሊክስ ላይ ካየነው በኋላ ጦርነቱ የድንበር ሳይሆን ወጣት የማስፈጃ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡
በአንድ ወቅት መሳሳት ልማዱ የሆነው ስብሀት ነጋ አዳልጦት በብሄራዊ ቲያትር የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች እጅግ የሚዋደዱ እና ወንድማማች ህዝቦች ናቸው ካለ በኋላ ኤርትራን የሚወር አንድ ሀገር ቢመጣ ቀድመን ጦራችንን ከኤርትራ ወንድሞቻችን ጋር እናሰልፋለን በማለት መናገሩን ለሚያስታውስ ግለሰብ ግን ህወሀት እና ሻአቢያ ተጣልተዋል የሚለው ብሂል እውነታነቱ ለኢቲቪ ተመልካች እንጂ ማሰብ ለሚችል ሰው መራር ቀልድ ነው የሚሆነው፡፡

ከሰሞኑ ደግሞ በኤርትራ የሚገኙ የት.ብ.ዴ.ን አባላት ነጻ እናወጣዋለን ያሉትን የትግራይ ህዝብ ነጻ ከማውጣት ይልቅ ወታደሮቻቸው አስመራ ውስጥ ኬላ ጠባቂ እንደሆነ በማህበራዊ ድህረ ገጾች አነበብኩ የተጠበኩት ነገር ስለሆነ ባይገርመኝም የወያኔን እድሜ እያራዘመን እንደሆነ ሲገባኝ ግን አዘንኩኝ በነገራችን ላይ የኤርትራ ተቃዋሚዎችንም ሰብስቦ በመያዝ ረድፍ ህወሀትም ለሻዐቢያ ውለታ እየሰራ እንደሆነ ጠጋ ብሎ የሻዐቢያ ተቃዋሚዎችን ያነጋገረ ግለሰብ የሚረዳው ሀቅ ነው፡፡

ስለ ሻአቢያ ደህንነት ከህወሀት በላይ የሚጨነቅ ሊኖር ይችላል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው ሻዐቢያ ማለት ለህወሀት ዘብ ነው ህወሀት ለሻዐቢያም እንደዛው እናም ከሻዐቢያ ጋር በመወዳጀት ወያኔን እንጥላለን ሀገራችንንም ነፃ እናወጣለን ማለት ሞኝነት ስለሆነ ቆም ብለን አካሄዳችንን ማሳመር ይኖርብናል፡፡

ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ

ኢትዮጵያዊነት –”የለህም ይሉኛል፤ እውነት የለሁም ወይ?”

$
0
0

ከመስፍን ነጋሽ (ጋዜጠኛ)
(የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ)

(ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ)

(ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ)

ከማንነት ጋራ የተያያዙ ጥያቄዎች፣ ሙግቶች፣ በተቃራኒውም አስቀያሚ ሐሳብ አልባ ስድድቦች ሰሞኑን በርከትከት ብለዋል። ጥያቄዎቹና ሙግቶቹ መኖራቸውን አጥብቄ እደግፈዋለሁ። በእኔ እይታ አብዛኞቹ ምልልሶች ወይም ሙግቶች በመሠረቱ አዲስ ጭብጥም ሆነ መከራከሪያ አላቀረቡም። ቢሆንም የነበረውንም ቢሆን በአግባቡ በተደጋጋሚ እያነሱ ሐሳብ መለዋወጡ ጠቃሚ ነው፤ ሙከራው ቢያንስ እርስ በርስ መተዋወቅን ይጨምራል፤ አልፎም አዲስ ሐሳቦችን ለማፍለቅ እድል ይሰጣል።

የማነ ናግሽ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት የለም፤ ያለው በብሔረሰብ ላይ የተመሰረተ ማንነት ብቻ ነው የሚለውን ሐሳብ በትግሪኛ ጽፎት ተመልክቼ ነበር። ኃላም ራሱ ወደ አማርኛ እንደመለሰው ይህን ጽሑፍ ወደማጠናቀቁ ስቃረብ ተመልክቻለሁ። በመሠረቱ ሐሳቡ አዲስ አይደለም። በየማነ አስተያየት መነሻነት ሌሎችም አመለካከታቸውን አካፍለዋል፤ ጥቂቶቹን በሚገባ አንብቤያለሁ። በሒደቱ የታየው ጉዳዩን ከመመርመር ይልቅ ተናጋሪውን የማጥቃት ስልት ጠቃሚ ስላልሆነ ወደዚያ አንመለሰም። በሐሳቡ ላይ ግን አስተያየቴን ላካፍል።

1. ስለማንነት እንደመነሻ

ሁልጊዜም ከጥንቱና ከስሩ መጀመር ጠቃሚ ቢሆንም ጽሑፌን ወደ መጽሐፍ ምእራፍነት እንዳይቀይረው በመስጋት፣ ከዚያ በላይ ደግሞ አንባቢዎቼ ስለማንነት እና ስለፖለቲካው መሠረታዊ ጉዳዮች ያውቃሉ ከሚል እምነት ስለማንነት ወደመዘርዘር አልገባም። በምትኩ ለክርክሬ የሚሆኑኝን መነሻዎች ብቻ እጠቅሳለሁ። አምስት ጭብጦች ላስይዝ፤
Map ethiopia
1.1. አንድ ሰው ብዙ አይነት ማንነቶች ሊኖሩት ይችላሉ፤ ይኖሩታልም። አንድ ማንነት በጉልህ የሚታየው ከሌላው ጋራ ሲነጻጸር እንደመሆኑ መጠን፣ አንድ ሰው ማንነቱን የሚገልጽበት መንገድ እንደሁኔታው ይለያያል። ጥያቄው ሃይማኖትን ሲከተል፣ ሃይማኖታዊ ማንነቱን ያስቀድማል እንደማለት። እዚህ የምናነሰው ግን ቋንቋን ጨምሮ ከተመሳሳይ ባህል፣ ታሪክ እና ስነልቦና ጋራ ስለተቆራኘው ማንነት ነው። የማንነት ፖለቲካ በአገራችን በዋናነት የሚወከለውም በዚሁ ነው። ለውይይታችን እንዲረዳ በብሔረሰባዊ እና በአገራዊ ማንነት ላይ ብቻ እናተኩር።

1.2.ማንነት (ብሔረሰባዊም ይሁን አገራዊ) ማኅበረሰብ ሠራሽ ነው፤ ተፈጥሯዊ አይደለም። ማንነት ከቤተሰብ፣ ከማኅበረሰብና ከትምህርት ቤት የምንማረው ነው። ስለዚህም ባለበት አይረጋም፤ መጠነኑና ፍጥነቱ ቢለያየም ይለወጣል።

1.3.ማንነት በአጋጣሚ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ በመወለድ እና/ወይም በማደግ፣ አለዚያም በተጽእኖ ሊገኝ ወይም ሊለወጥ ይችላል። ይህ ብቻ ግን አይደለም። ማንነት በምርጫም ሊገኝ ይችላል፤ አንድ ሰው በፍላጎቱ የአንድ ማንነት አካል ሊሆን ይችላል፤ ምን ያህል ይሳካለታል የሚለውን የሚወስኑ ብዙ ከእርሱ ውጭ የሆኑ ሁኔታዎች ቢኖሩም። አንዳንድ ማኅበረሰቦችና ማንነቶች ከሌላው የበለጠ አዲስ መጤን የመቀበልና የማዋሐድ ጠባይ አላቸውና።

1.4. አንድ ማንነት ከቀላል ጀምሮ ወደ ውስብስብና ብዙ እንደሚያድግ ሁሉ፣ ማንነቶች ሊወራረሱ፣ አልፎም ማንነቶች ተደባልቀው/ተዋሕደው ”አዲስ/የተለየ” ማንነት ሊፈጥሩም ይችላሉ።
1.5. በማንኛውም መንገድ መስተጋብር የመፍጠር እድል ያገኙ ማንነቶች የተለያዩ እሴቶቻቸውን ይለዋወጣሉ፣ ይዋዋሳሉ፣ ያዳቅላሉ። እንዳለ የሚያስጠብቁት የማንነታቸው አካል መኖሩ እንደማይቀርም እሙን ነው። ስለዚህም ንጹህ የሚባል ማንነት አይኖርም። ንጹሕ የሚባል ማንነት ካለ ያ ማንነት በላቦራቶር የተፈጠረና እስካሁንም ወደምንኖርባት የሰው ዓለም ያልመጣ ማንነት ነው።

ከዚህ የሚከተለው ክርክሬ ቢያንስ በእነዚህ አምስት መንደርደሪያዎች ላይ የተመሠረተ ይሆናል። እነዚህን መነሻዎች ይዘን ወደ ጥያቄው እንመለስ። እውነት ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም?

በአገራችን የብሔረሰብ ማንነት አለ፤ ራሱን የዚህ ወይም የዚያኛው ብሔረሰብ አባል አድርጎ የሚመለከት ሰውም አለ። ይሄ ለክርክር የሚቀርብ፣ ያልተረጋገጠ ጉዳይ አይደለም። ይህኛው ቡድን ”ብሔርሰብ ነው ወይስ ዘውጌ ወይስ ጎሳ?” የሚለው ጥያቄ ላነሳነው ክርክር አስፈላጊ አይደለም። ለአሁኑ፣ ቁም ነገሩ፣ የራሳችን ባህላዊና ታሪካዊ ማንነት አለን የሚሉና ያላቸው ብድኖች መኖራቸው ነው። ስለዚህ ”እኔ የእገሌ ብሔረሰብ አባል ነኝ፤ የዚያኛው አይደለሁም፤ ማንነቴም አገው፣ ትግራዋይ፣ ጉሙዝ፣ ኦሮሞ፣ አማራ…ነው” የሚሉ ሰዎች አሉ። መኖራቸው እውነት ነው፤ በአግባቡ ከተያዘም ጸጋ ነው። አሁን የቀረበው ጥያቄ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት እነዚህ ብሔረሰባዊ ማንነቶች ብቻ ናቸውን የሚል ነው። ወይም፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት የለምን? እርግጥ የአንድ ማንነት ታጋሪዎች ነን የሚሉ ሰዎች እስካሉ ድረስ ስለማንነቱ ለማረጋገጥ ሌላ ምርመራ ማድረግ የግድ አይደለም ብሎ የሚከራከር ይኖር ይሆናል። በዚህ ስሌት፣ ”ኢትዮጵያዊ ማንነት አለን” የሚሉ ሰዎች መኖራቸው ብቻውን በቂ ማስረጃ በሆነ ነበር። ቢሆንም ተጨማሪ ሐሳቦችን መለዋወጡ አይጎዳም።

2. ኢትዮጵያዊ/አገራዊ ማንነት የለም የሚሉ ሰዎች ቢያንስ አራት ስሕቶችን ይፈጽማሉ።

2.1. ከፍ ሲል የጠቀስኩትን የማንነቶችን መወራረስ፣ አልፎም የአዲስ ማንነቶች መፈጠር አይቀበሉም። ይህ ማለት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ብሔረሰቦች (የፖለቲካ ማኅበረሰቡ አባል የሆኑት ወደውም ይሁን ተገደው) በታሪክ ባካሔዱት መስተጋብር የሁሉም ”ቅልቅል” የሆነ (ምናልባትም የሆኑ) አዲስ ማንነቶች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ አይቀበሉም ማለት ነው። አዳዲስ ማንነቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ ብለው ካመኑ ክርክራችን በአገራችን አዲስ ማንነቶች ስለመፈጠራቸው እና ስለተፈጠረው/ስለተፈጠሩት አዲስ ማንነቶች ስያሜ ይሆናል ማለት ነው። በእኔ እምነት፣ በረጅሙና በውስብስቡ የአገረ ኢትዮጵያ መስተጋብር አዳዲስ ማንነቶች ተፈጥረዋል። (ይህ ማለት የብሔረሰብ ማንነቶች ጠፍተዋል ማለት አይደለም፤ እርግጥ ባሉበት አንዳችም ሳይለወጡ ቀጥለዋል – ንጽሕ የሚለው ቁልምጫ ትርጉሙ እርሱ ይመስላል- ማለትም ቢያንስ ፖለቲካዊ የዋህነት ይሆናል።) ከተፈጠሩት ”አዲስ/የተለዩ” ማንነቶች አንዱና ዋናው ብዙዎቻችን ”ኢትዮጵዊነት” የምንለው ማንነት ነው። ስለዚህ ማንነት አይነቶች ወይም አረዳዶች ወደ ኋላ አነሳለሁ፤ የችግሩ መነሻ ”ኢትዮጵያዊነት” የሚለው ስያሜ ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም መስጠቱ ሊሆን ይችላልና።

2.2. ተከታዩ ስህተት አንድ ሰው ከአንድ በላይ ማንነት ሊኖረው አይችልም፣ አንዱን ማንነት ሲቀበል ሌላውን መተው አለበት፣ ወይም የቀደመ ማንነቱን ከአዲስ ማንነት ጋራ ማዳበል ወይም ማዋሐድ አይችልም ከሚል የተሳሳተ አመለካከት የሚመነጭ ነው። ይህ በንድፈ ሐሳብም ሆነ በተግባር የተሳሳተ ነው። አሁን ያለችውን ኢትዮጵያ ተጨባጭ እውነታም መረዳት ይጎድለዋል። ዛሬ፣ ራሳቸውን በብሔረሰባዊም በአገራዊ ማንነታቸውም የሚገልጹ በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሰዎች አሉ። ልብ በሉ፣ ለእነዚህ ሰዎች ኢትጵያዊነት ዜግነት ብቻ አይደለም፣ ማንነትም ጭምር ነው። ራስን በብሔረሰብ ማንነት ብቻ ሳይሆን በሃይማኖት ማንነትም ደርቦ መግልጽ እንደሚቻለው፣ ኢትዮጵያዊነትን ተጨማሪ ማንነት ማድረግ እውነት የማይሆንበት ምክንያት አይታየኝም። ብሔረሰባዊም አገራዊም ማንነት ያለቸው ሰዎች ስለመኖራቸው ማረጋገጥ ከባድ አልመሰለኝም። አገራዊ ማንነት የለንም የሚሉ ሰዎችን የግድ ይኑራችሁ ብዬ አልከራከርም። ዝርዝሩ ሌላ ውይይት ይፈልጋልና ልተወው።

2.3. ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም የሚሉት ሰዎች የሚሰሩት ሌላው ስሕተት ከፍትሕ ጋራ የተያያዘ ነው። እነርሱ ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ”ማንነታችንን ሳታከብር ኖራለች፣ እውቅና ተነፍገን ኖረናል፣ ይህም ሊለወጥ ይገባል” ብለው ይከራከራሉ። ተገቢና እውነት ያለው የፍትሕ ጥያቄ ነውና ከልቤ እደግፈዋለሁ። ይህን እነርሱ የሚጠይቁትን ፍትሕ ግን ለሌሎች፣ ዛሬ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት አለን ለሚሉትን ወገኖቻቸው እየከለከሉ ነው። አሁንም ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ማንነት ወደ ኋላ አነሳለሁ።

2.4. እነዚህ ሰዎች ከሚሰጡት ማብራሪያ የምንረዳው ሌላው ጭብጥ እውነተኛው/ደንበኛው ማንነት በብሔረሰብ ላይ የተመሰረተው ነው የሚል ነው። እነርሱ ባወጡት የማንነቶች ደረጃ መሠረት፣ ከብሔረሰባዊ ማንነት ውጭ ያሉት ማንነቶች አንድም ውሸት ናቸው አለዚያም ጠንካራ አይደሉም። ብሔረሳባዊ ማንነት ከሌሎቹ ማንነቶች ቀዳሚነት እንዳለው ይሰብካሉ። ይህንን ለፖለቲካ መቀስቀሻነት የሚጠቀሙት ሰዎች ዓላማ የተሰወረ አይደለም። ሐሳቡ ግን በግማሽ እውነት ላይ የተመሰረተ ስንኩል መከራከሪያ ነው። ግለሰቦችና ቡድኖች የሚያስቀድሙት የማንነት መለያ የሚወሰነው በኖሩበትና ባሉበት ታሪካዊ ሁኔታ እንጂ አስቀድሞ በወጣ የማንነቶች ደረጃ አይደለም። ከሌላው ማንነቱ በፊት በሃይማኖታዊ ማንነቱ ራሱን የሚገልጽ ሰው/ቡድን ይኖራል፤ ለሌላው ደግሞ ብሔረሰባዊ አለዚያም አገራዊ ማንነቱን ቀድሞ ይሰማው ይሆናል። ሁሉም የማኀበረሰባቸው ታሪክ ውጤቶች ናቸው። አንዱ ከሌላው የበለጠ ትክክል አይደለም፤ እንደ ግለሰቡ እና ቡድኑ ሊለያይና ሊለዋወጥ የሚችልም ነው። ይህ አመለካከት አንዳንድ ጊዜ ብሔረሰባዊ ማንነታቸውን የማያስቀድሙ ሰዎችን ”የማንነት ችግር” እንዳለባቸው ወይም እየዋሹ እንደሆነ የመክሰስ ድፍረት ተላብሶ የሚታይበት ጊዜም አለ።

3. ኢትዮጵያዊነቶች?

እንደማንኛውም ማንነት ኢትዮጵያዊነትም ብዙ ገጽታዎች አሉት። በታራካዊ ሂደቶችም ብዙ ተለውጧል፤ ገና ይለወጣልም። ኢትዮጵያዊ ማንነት ብዙ ገጽታዎች አሉት ወይም ብዙ አይነት ኢትዮጵያዊ ማንነቶች አሉ ብሎ መነሳት ይቻላል። ለዚህ ጽሑፍ አግባብነት አላቸው ያልኳቸውን ሦስት የኢትዮጵያዊ ማንነት አረዳዶች ብቻ ላስቀምጥ።፡ይህን የማደርገው፣ ኢትዮጵያዊ የምንለው ማንነት ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም እየሰጠ አለመግባባት ፈርሮ እንደሆነ በሚል መነሻ ነው። ለመግባባት ሲባል ለማንነቶቹ ሌላ ስያሜም መስጠት እንችል ነበር፣ ለጊዜው ይቆየን።

3.1. አንደኛው ኢትዮጵያዊ ማንነት ራሱን የሁሉም የአገራችን ብሔረሰቦች አካል አድርጎ ይመለከታል፤ ለአንዱ የተለየ ቅርበት አይሰማውም። እነዚህ ሰዎች ምክንያቱ ምንም ይሁን፣ ራሳቸውን የዚህ ወይም የዚያኛው አንድ ብሔረሰብ አባል አድርገው አይቆጥሩም። የዚህ ማንነት ባለቤት የሆነው ኢትዮጵያዊ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ነገር እኩል ተጋሪ ባለቤት እንደሆነ ያምናል። ብሔረሰባዊ ማንነትን ያከብራል። ብሔረሰባዊ ማንነትን ተገዳዳሪው አድርጎ አይፈራውም። ይህ ማንነት ድንገት ከሰማይ ወርዶ የሁሉም አካል ነኝ የሚል፣ ባለቤት አልባ ማንነት አይደለም። በአብዛኛው በተለይ በከተሞች አካባቢ ያደጉ (ለረጅም ጊዜ የኖሩ) ሰዎች የዚህ ማንነት ተጋሪዎች ናቸው። ባህላዊና ስነልቦናዊ ማንነታቸውን የቀረጸው ያለፉበት ታሪክ ነው፤ ፖለቲካው፣ ጦርነቱ፣ የሕዝብ እንቅስቃሴውና መስተጋብሩ፣ ትምህርቱ፣ የከተሜ ኑሮ…። ለእነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያዊነት ዜግነት ብቻ ሳይሆን ማንነትም ጭምር ነው። ቁጥር የበለጠ ትርጉም የሚሰጣቸው ሰዎች ካሉ፣ የዚህ ማንነት ባለቤቶች ቢያንስ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ስለመሆናቸው አልጠራጠርም። (እኔም ራሴን ያገኘሁት እና መሆንም የመረጥኩት እዚህ ውስጥ ነው።)

3.2. ሁለተኛው ኢትዮጵዊነት የአንድ ብሔረሰብ ማንነት ያለው፣ ነገር ግን በተጨማሪም ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው ነው። በብሔረሰብ ማንነቱ የብሔረሰቡ የሆነውን ሁሉ ይጋራል፤ እዚያ ግን አያቆምም፤ በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ከሎሎች ኢትዮጵያዊ ማንነት ካላቸው ጋራ የሚጋራው ሌላም ብዙ ነገር አለ። ይህ ሰው የሚረዳው ኢትዮጵያዊ ማንነቱ፣ ብሔረሰባዊ ማንነቱን እንዲተው የሚጠይቅ አይደለም። ይህ ማንነት፣ ከከተሞች መስፋፋት፣ ከትምህርትና ከመንግሥት ቢሮክራሲ ዝርጋታ ጋራ እያደገ እንደመጣ እገምታለሁ። አሁንም የዚህ ቡድን አባላት ቁጥር ከአገሪቱ ሕዝብ ከግማሽ በላይ እንደሚሆን አልጠረጥርም። ይህ ባይሆን አገሪቱ ህልውናዋ ባከተመ ነበር ከሚል መነሻ።

3.3. ሦስተኛው ኢትዮጵያዊነት፣ ብሔረሰባዊ ማንነትን የሚክድ ወይም ለማጥፋት የሚፈልግ ተጻራሪ ማንነት አድርጎ የሚመለከት አረዳድ ነው። ከታሪክ አንጻር በከፊል እውነት ነው። ለዚህ አረዳድ፣ ኢትዮጵያዊነት ማለት የክርስቲያን ሰሜን ኢትዮጵያ ባህልና ማንነት ነው። እንደ ጉዳዩ አቅራቢ ይህ ኢትዮጵያዊነት የአማራ ባህልና ማንነት ብቻ ተደርጎ የሚቀርብበት አጋጣሚም አይጠፋም። ለዚህ አመለካከት አስፈላጊው ጭብጥ ግን፣ ”ኢትዮጵያዊ” ማንነት ቀድሞም ይሁን አሁን ሌሎች ባህላዊ ማንነቶችን ለመደፍጠጥ ያሰፈሰፈ ማንነት ተደርጎ መታየቱ ነው። ይህ መሠረተ ቢስ ስጋት ነው ብዬ እንዳልደመድም እነርሱ ”ኢትዮጵያዊነት” ከሚሉት ውጭ ያለ አገራዊም ሆነ ብሔረሰባዊ ማንነት እንዲጠፋ አዋጅ ማወጅ የሚቃጣቸው ሰዎች አሉ። ማለት የምችለው፣ የእኔ ኢትዮጵያዊነት ከዚህ ይለያል። ይህ የኢትዮጵያዊ ማንነት አረዳድ የብሔረሰብ ማንነቶችን የማያከብር፣ ስለመኖራቸውም ሙሉ እውቅና የማይሰጥ ነው። ይህ ኢትዮጵያዊነት ብሔረሳባዊ ማንነቶችን በጥርጣሬ ይመለከታል፣ የአገራዊ መተሳሰር ጠላቶች አድርጎ ይፈርጃል፣ ማንነቶቹን ማዳከምም ይፈልጋል። የዚህ ማንነት አቀንቃኞች በአብዛኛው በአማራ ልሒቃን መካከል የሚገኙ ጥቂቶች ናቸው። እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያዊ ማንነት በዚህ ገጽታው ብቻ ሲወከል ይስተዋላል።

ህወሓት/ኢሕአዴግ በስልጣን ዘመኑ የመጀመሪያ አስር ዓመታት ሆን ብሎ ሁሉንም ኢትዮጵያዊነቶች በጅምላ እንዲጠሉ ብዙ ሰርቷል። ሌሎቹ ብሔረሰብ ተኮር ፓርቲዎችም ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ስትራቴጂ ተከትለዋል። ስጋታቸው ግልጽ ነው፤ የብሔረሰባቸው አባላት ኢትዮጵያዊ ማንነትን ከደረቡ የደጋፊ መጠናቸው ሊቀንስ ይችላል። በውጤቱም፣ ዛሬ፣ ”ኢትዮጵያዊ ማንነት” ሲባል በብዙ የአደባባይ ሰዎች ዘንድ አስቀድሞ የሚጠቀሰው ይህ ሦስተኛው አመለካከት ብቻ ሆኗል። የፖለቲካ ልሒቃኑ ኢትዮጵያዊነትን በቀዳሚዎቹ ሁለት መልኮቹ የሌለ በማስመሰልም፣ ሦስተኛውን ግን በማጉላት፣ የማንነቱን ባለቤቶች በጅምላ ጥፋተኞችና ተጠርጣሪዎች አስመስለው ያቀርቧቸዋል። ይህ ስህተት ብቻ ሳይሆን ሸፍጥም ነው። የሸፍጥነቱ ስላቅ ወደዜኒቱ የደረሰው፣ እነመለስ ደርሶ የሁለተኛው ዓይነት/አረዳድ ኢትዮጵያዊነት (3.2) አራማጆች ሆነው፣ ባንዲራ መስቀልና ስለሺህ ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ መስበክ ሲጀምሩ ነበር። ሌላው በጣም የሚገርመኝ ነገር፣ የመጀመሪያው ዓይነት ኢትዮጵያዊ ማንነት ያላቸው ዜጎች መኖራቸውን ገዢው ፓርቲ ጭምር ዛሬም ድረስ እውቅና ለመስጠት መፍራታቸው ነው።

ብሔረሰባዊ ማንነትን የፖለቲካቸው ማቀጣጠያ አድርገው መጠቀም የሚፈልጉ ልሒቃን፣ እንዲሁም ከማንነት ፖለቲካና የውድድር ስሜት የሚመጣው ስሜተ-ስሱነት የሚያስከትለውን ሚዛን የመሳት አደጋ ቀድመው ያልጠረጠሩ ሰዎች፣ በአገራችን ውስጥ ያሉት ብሔረሰባዊ ማንነቶች ብቻ ናቸው ይላሉ። ይግረማችሁ በማለትም፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም ይላሉ።

ማንኛውም ማንነት እና ከእርሱ ጋራ ተያይዘው የሚመጡ ስሜቶች (የኩራት-ሃፍረት፣ የበላይ-የበታችነት፣ የአሸናፊ-ተሸናፊነት፣ የጊዜው የእኛ ነው-አይደለም፣ የተስፋ-ስጋት ወዘተ) መኖራቸውን ማስቀረት ባይቻልም መጠናቸውን ሲያልፉ ከፍተኛ አደጋን ይጋብዛሉ። አደጋው ሐልዮታዊ ብቻ ሳይሆን ማኅበረሰባዊም ነው። በሐልዮት ደረጃ፣ አሁን እንደምናየው፣ ”ያለሁት እኔ ነኝ እንጂ አንተ አይደለም” እስካማስባል ያደርሳል። አገራችንም ሆነች ዓለማችን በዚህ መሰሉ ሚዛኑን የሳተ የማንነት ስሜት ብዙ ዋጋ ስለመክፈላቸው ታሪክ ብዙ ያስነብበናል። አገራዊ ማንነት ሲጦዝ ሌላውን አገር በእብሪት ወደ መውረር ስካር ያመራል፤ በቆዳ ቀለም መኩራት (የሚያኮራ ከሆነ) ከዚያ አልፎ የበላይነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሆኖ ሲወሰድ ወደ አፓርታይድ ያደርሳል፤ በብሔረሰባዊ ማንነት ኮርቶ ራስን ማስተዳደርና ባህልን ማዳበር ከዚያ አልፎ የሌላውን (በተለይ ተፎካካሪ ተደርጎ የሚቆጠረውን) ማንነት መኖርና አለመኖር (በሐልዮትም ይሁን በአካል) ለመወሰን ወደሚያስችል ስልጣንነት ሲቀየር የመጠፋፋት በር ማንኳኳቱን ልብ እላለሁ፤ እሰጋለሁም።

ማንኛውም ብሔረተኝነት በጋራ ታሪክና መጻኢ እጣ ሚዛን መገደብ አለበት። ይህ ካልሆነ፣ ገደብ አልባ በራስ የመተማመን እና የእርግጠኝነት ስሜት ይፈጥራል። ትህትናንና መተሳሰብን ከግለሰብ ልብ፣ ከቡድን የጋራ ስነልቦና ያጠፋል። ይህ ስሜት በግለሰብም በቡድንም ደረጃ ሊንጸባረቅ ይችላል።

ኢትዮጵያዊ ማንነት አለ። ኢትዮጵያዊ ማንነት የሚለው አገላለጽ የሚወክለው መጥፎ የታሪክ አሻራም አለ። የመጥፎው አሻራ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያዊነት አረዳድ በሒደት እየተዳከመ መሔዱ ግልጽ ነው። ምኞቴም ነው። ሌሎቹ ሁለቱ አይነት ኢትዮጵያዊ ማንነቶች ግን የታሪካችን ተጨባጭና በጎ ውጤቶች አድርጌ አያቸዋለሁ። ምንልባትም መጻኢው የኢትዮጵያ መልካም እጣም ያለእነርሱ እውን የሚሆን አይመስለኝም። ራሴንና መሰሎቼን እንዴት ከነገው መልካም ቀን አውጤቼ ልመለከት እችላለሁ? እንዴትስ፣ ”እንኳን የነገው አካል ልትሆን፣ ዛሬም የለህም” ስባልስ ዝም እላለሁ?! ኢትዮጵያዊነት አለ። የለም ስለተባለም አይጠፋም። እኔ አለሁ።

* መስፍን ይህ ጽሁፍ በፌስቡክ ሰሌዳው ላይ ያቀረበው ነው። ጽሁፉን በፌስቡ ለማየት እዚህ ይጫኑ


ሕወሓት ከመለስ ጋር አብሮ ተቀብሯል –ክፍል 2

$
0
0

Bereket Simon weeping with his wife over Meles Zenawi's death
ከነፃነት አድማሱ
dalul@gmail.com

የሰው ልጅን ነፃነት የማይገባው ነፃ አውጪ!!

በትግራይ የህወሓት እኩይ ተግባር በቅርብ የተከታተሉት አንድ የሽሬ እንዳስላሴ አዛውንት እንዲህ በማለት በምሬት ይገልፁታል። “ደርግ ሰው ገድሎ በአደባባይ ይፎክር ነበር። ዛሬ ህወሓት ግን ሰው ገድሎ ልቅሶ ይደርሳል” ሲሉ የድርጅቱን እርኩስነት፣ አስከፊነትና የሰብኣዊ ፍጡር ባላንጣነት ካለፈው የደርግ አገዛዝ ጋር በማነፃፀር ቁጭታቸውን በትካዜ ሲናገሩ አጋጥሞኛል። የዛሬው ፅሑፌም ካለፈው ክፍል አንድ የቀጠለ ነው። በክፍል አንድ የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎችም በኋላ በዝርዝር ለማስቀመጥ እሞክራለሁ። ለዛሬ ግን ቀደም ብዬ በክፍል አንድ የጀመርኩትን “አደናግረህ፣ አስፈራርተህ፣ አሸብረህ፣ ወገን ከወገኑ ጋር አናቁረህና ለያይተህ ግዛ” የሚለውን የህወሓት የደደቢት የደንቆሮ ፍልስፍናና መፈክር በሚመለከት አጭር ማጠቃሊያ በማከል ፅሑፌን እቋጫለሁ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አሜሪካውያን ባለስልጣኖችን ያጃጃለ አለማቀፍ አራዳ፤ በብርሃኑ አስረስ መጽሐፍ መነሻነት

$
0
0

ከክፍሉ ሁሴን

penራሱን ካልናቀ እና ጣል ጣል ካላደረገ በቀር ማንኛውም ጎልማሳ የተካበተ፣ሊወሳ እና በታሪክ ሊዘከር የሚችል የሕይወት ልምድ አለው።አንዳንዶች እንዲያውም የራሳቸውን ግለ ሕይወት ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ የአንድን ማህበረሰብ ታሪክ በእጅጉ ሊመለከት ከሚችል ሁነት ጋር ባጋጣሚ ይገናኙና የታሪክ ሁነቱ አካል ወይም ማዕከል እስከመሆን ይደርሳሉ።የሚያሳዝነው በኛይቱ አገር ይህንን አውቀን ማስታወሻ በመያዝ ለሚቀጥለው ትውልድ ትምህርት እንዲሆን ትውስታችንን በጽሁፍ የምናበረክት እጅግ ጥቂቶች ነን።ለዚህም ነው በቅርቡ ያነበብኩትን የ “ማን ይናገር የነበረ–የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ”ን መጽሐፍ ደራሲ አቶ ብርሃኑ አስረስን ለማድነቅ፤ከማድነቅም አልፎ በመጽሐፋቸው የተነሱት አንዳንድ የታሪክ ሁነቶች እኔንም በትውስታ ብልጭታ (flashback )ወደኋላ ስለወሰዱኝ ይህንኑ በማነሳሳት ሌሎች ልክ እንደ አቶ ብርሃኑ አስረስ የተካበተ ልምድ ያላቸው እንዲሁም አገራችንን በሚመለከት የታሪክ ሁነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተሳተፉ እንዲጽፉ ለመጎንተልም ጭምር ነው።እርግጥ ባሁኑ ወቅት የግለ ሕይወት ታሪክ (Autobiography )መጽሐፍ ትንሳኤ የሆነ እስኪመስል ድረስ ታዋቂም፤ እጅግም ታዋቂ ያልሆኑ ግን ባንድ የታሪክ ክስተት የተሳተፉ ሰዎች የጻፏቸው መጽሐፍት በብዛት እየታተሙልን በማንበብ ላይ እንገኛለን።በዚህ አይነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (አአዩ) ፕሬስ ከታተሙት መጽሓፍት ይህን እንድጭር የጎነተለኝ የአቶ ብርሃኑ መጽሐፍ አንዱ ነውና ዩኒቨርሲቲውንም በዚህ አጋጣሚ ይበል ይበል ማለት ተገቢ ይመስለኛል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ/PDF

ምኒልክን ብትወቅሱ ማንነታችሁን ትረሱ –ከኃይሌ ላሬቦ (ባለ 51 ገጽ ሰፊ ትንታኔ)

$
0
0

minilik
የኔልሶን ማንደላን ለቅሶና ቀብር ሳይ በጣም ተገረምሁ ብቻ ሳይሆን እፍሪቃዊ መሆኑ ራሱ አኰራኝ። ከዚህም ተነሥቼ፣ታሪክን ወደኋላ መለስ ብዬ በኅሊናዬ መስተዋት ቃኝቼ ሳበቃ፣ ጊዜው እንደዛሬ ሁኖ ቢያመችለት ኖሮ፣ እንደሳቸው ሊለቀስ የሚገባ ሰው በአፍሪቃ ምድር ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅምን ብዬ ራሴን በራሴ ደጋግሜ ጠየቅሁ። ማንዴላ የሚደነቁት፣ በቀለሙ በመጀነንና፥ በዘመናዊ መሣርያው በመተማመን፣ በበላይነት ረግጬው ልግዛው ብሎ፣ ለብዙ ዘመናት በሥልጣን ላይ ሁኖ ያሠቃይ የነበረውን ጨቋኙን የነጮች ግዛት ከነሥርዐቱ አሸንፈው፣ ለሀገራቸው ጥቊር ሕዝብ የድል ዋንጫ አጐናፅፈው፣ ነፃነቱንና ክብሩን ስለመለሱለት ነው። ግፈኞቹን የድሮ ጠላቶቻቸውንም እንደመበቀል ፈንታ በፍቅር ያዟቸው። ሁሉም የደቡብ አፍሪቃ ዜጋ በጐሣና በዘር፤ በሃይማኖትና በቀለም ሳይለያይና ሳይከፋፈል፣ ታዲያ በመቻቻል፣ ባንድነትና በፍቅር ተቀራርቦ እንዳንድ ሀገር ሕዝብ እንዲኖር አደረጉ። ለኻያ ሰባት ዓመታት በእስራት ራሳቸውን በመሠዋት፣ ጠላታቸውን በማሸነፍ፣ ራሳቸውንና ሀገራቸውን ያኰሩ ደግና ብልህ መሪ፣ ሰውን በማንነቱና በእምነቱ ሳይሆን በሙያውና በችሎታው የሚፈርጁ፤ ጠላትን እንኳ የሚራሩና የሚወዱ ሰው ነበሩ። ይኸንን በዐይነ ኅሊናዬ መላልሼ ካሰላሰልሁ በኋላ፣ የዓለምን ታሪክ ደግሞ ቃኝቼ ሳበቃ አንድ እጅግ በጣም ታላቅ ሰው አገኘሁ። አፄ ምኒልክ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ/PDF

የማለዳ ወግ …በጅዳ አለም የኢትዮጵያውያን አቀፍ ት/ቤት ከትምህርት ጥራት እስከ ባለሙያው ፈተና

$
0
0

ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ
Saudi arabia ethiopian school
ባሳለፍነው ሃሙስ የወላጅ መምህራን ስብሰባ ላይ ስለጅዳው አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ትምህርት ቤት አስተዳደር ፍትሃዊነት የቅጥር ሂደት እና በትምህርት ጥራቱ ዙሪያ ላይ አንድ በኢኮኖሚክስ ትምህት በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀ ወጣት የሰላ ሂስ አቀረበ። በቀረበው የወጣቱ የዩኒቨርስቲ መምህር ስደተኛ ስራ ፈላጊ አስተያየት ድጋፍና ተቃውሞ ቤቱን በየተራ ናጠው ። በትምህት ጥራት አለመኖር የሚስማማው ወላጅ በጭብጨባ ድጋፉን ሲገልጽ የትምህርት ጥራቱን አንድ ከኢትዮጵያ ትምህርት ቤት የ12 ኛ ክፍል ተማሪ ጋር በእንግሊዝኛ ትምህርት እውቀታቸው የኤርትራ ኢንባሲ የ7ኛ ክፍል ተማሪ እንደሚልቅ በንጽጽር ማቅረቡ የተከፉ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ፖርቲ አባላትና ደጋፊዎች ውግዘት አስከተለበት ። አንዲት የወላጅ መምህራን ህብረቱ አባል ለትምህርት ጥራቱ ንጽጽር “ኤርትራ” የምትባለውን ሃገር ከአፉ ያወጣውን ወጣት ምሁር በአደባባይ ወጥተው ወረፉት። የወላጆችና መምህራን በሆነው ስብሰባ ለምን ይሳተፋል ሲሉም ከስብሰባው እንዲዎጣ ሲሉ በድፍረት እስከመናገር ደርሰው ብዙሃን ተሰብሳቢውን አሳፈሩ :(

ግማሽ ሌሊት በዘለቀው ስብሰባ የሚጨበጥ መፍትሔ ሳይያዝ ተበተነ ። ስብሰባው አብቅቶ ወደ የቤታችን ለመሔድ ከግቢው እንደወጣን ከአዳራሹና ከኮሚኒቲው ግቢ ውጭ ” የተከበሩት ” የድርጅት ሰዎች ወጣቱን ከበው ሲያዋክቡት ደረስኩ ። ምክንያቱን መጠየቅ አላስፈለገኝምና ግርግሩን በአርምሞ መታዘብ ጀመርኩ። ወጣቱን ከመካከል አድርገው ሲያዋክቡት ቁልጭ ቁልጭ እያለ ለሚሰነዘርበት ትችት መልስ ለመስጠት ይሞክራል ። እነሱ ይዝታሉ ፣ ያንቋሽሹታል። ” የትምህርት ንጽጽሩን በተጨባጭ ካየው እውነታ ጋር የመናገር ነውርነቱ ምኑ ላይ ነው? ” የሚሉት በአንጻሩ የባለጊዜወችን ቁጣ በመቃወም በእሰጣ ገባው መካከል ለወጣቱ ድጋፋቸውን መግለጽ ሲጀምሩ ክርክሩ ሜዳ ላይ ለአፍታም ቢሆን ተፋፋመ ። አፍ የፈታበት ትግርኛ ቋንቋ አፉን ያዝ እያደረገው መልስ የሚሰጠውን ወጣት ምሁርን በራስ መተማመን ስመለከት የመቀሌው አብርሃ ደስታ ትዝ አለኝ። ልዩነቱ አብርሃ መቀሌ ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ስርአት አልበኝነትን የሚቃወም ሆኖ ሳለ ይህኛው ወጣት የሚሞግተው ፖለቲከኛ ሆኖ ስለፖለቲካና ኢ ፍትሃዊ አስተዳደር እያወራ አለመሆኑ ነው። ወጣቱ በ3000 ታዳጊዎች የትምህርት ማዕከል ላይ የሚታየውን የአስተዳደር ኢ ፍትሃዊነትና የትምህርት ጥራት አለመኖር በድፍረት በመናገሩ በወንዙ ልጆች ዘንድ ” አይንህን ላፈር ” አስብሎ በእርጉም አስፈርጆታል ። ግርግሩ በረድ ሲል ወጣቱ ወደ ቤቱ ለመሄድ ከአንድ ወዳጀ ጋር የሚያደርሳቸው ሲያፈላልጉ አየኋቸውና እግረ መንገዴን ላድርሳቸው ጠራኋቸው። ወጣቱ ኢኮኖሚስትና “አላጠፋም አትንኩት! ” ሲል ይሞግትለት የነበረው ወዳጀ ከእኔው ጋር ተሳፍረው መጓዝ ጀመርን … እናም ከሰላምታ በኋላ እኔ እንደለመደብኝ መጠየቅ እሱም መመለስ ያዘ …

ገና ልጅ እግር ነው ። እድሜው ከሃያዎቹ አያልፍም። በ1990 ዎቹ ከትግራይ ክልል ተነስቶ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ዘመነኛውን የኢኮኖሚክስ አስተዳደር ትምህርት ለስድስት አመታት ተከታትሎ በማዕረግ ተመርቋል ። ከ2000 ዓም ወዲህ በትምህርቱ የላቀ ውጤት በማምጣቱም እዚያው አዳማ ለስድስት አመታት ዩኒቨርሲቲ አስተምሯል ። በሃገር ቤት የኑሮ ውድነት ጣራ ነክቶ አልመቸህ ቢለው ባንድ ክፉ ቀን ከስራ ባልደረቦቹ ጋር ወደ ውጭ ሃገር ሄደው በስደት የተሻለ ገቢ አግኝተው በሚሰሩት ሁኔታ ዙሪያ ተመካከረ። “በሳውዲ በኩል ወደ ሌላ አውሮፖ ሃገር መውጣት ይቻላል!” የሚባል መረጃ ለእርሱና ለጓደኞቹ ስለደረሳቸው በአሳር በመከራ ያጠራቀሟትን ጥሪት በመሰባሰብ ቪዛ ገዝተው ከአመት በፊት ወደ ሳውዲ ጅዳ ከተፍ አሉ።

… ሳውዲ አረቢያ ግን እነሱ እንዳሰቧት ሆናም ሆነ ወደ አውሮፖ የሚደረገው ስደት የቀለለ አለመሆኑን የአረቦቹን ኑሮ በተቀላቀሉ ቅጽበት ማገናዘብ ቻሉ ። በቃ እሱና ጓደኞቹ ሳውዲን እንዳሰቡት አላገኟትምና ብዙ ሳይቆዩ በጅዳ የተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ስራ ፍለጋ ጀመሩ … በሰው በሰው በጅዳ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ” የመምህራን እጥረት አለ !” ሲባል ሰምተው ከአንድ ጓደኛው ጋር ወደ ትምህርት ቤቱ አስተዳደር በመሄድ የትምህርት መረጃቸውን አቀረቡ። ምንም እንኳን ትምህር ቤቱ ካላቸው ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ አንጻር ባይመጥናቸውም እንደ ዜጋ ዝቅ ብለው ለመስራት እና ለዚህ ትውልድ እውቀታቸውን ለማካፈል እድል አገኘን ብለው ያቀረቡት አቤቱታ ግን በትምህርት ቤቱ አስተዳደር በኩል ለውድድር ቀርበው ግልጋሎት መስጠት የሚችሉበት እድል የተነፈጋቸው መሆኑን ወጣቱ አጫወተኝ ! ይህ ወጣት ምሁር አክሎ እንዳጫወተኝ ከሁሉም የሚያስገርመው የ11 ኛ እና የ12 ኛ ተማሪዎችን በኢኮኖሚክስ ያልተመረቀ መምህር ታዳጊዎቹን በሚያስተምርበት ትምህርት ቤት እንዴት በሙያው የተካንን ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዩኒቨርሲቲ የማስተማር ብቃት ያለው ዜጋ ዝቅ ብየ ላስተምር ሲል እንዴት እድሉን ይነፈጋል ? ሲል የሚያጠይቀው ወጣት የትምህርት መረጃዎችን ተቀብሎ ማወዳደር መጠየቅና ተገቢውን ለታዳጊዎች የሚጠቅም እርምጃ መውሰድ ሲገባ ” ስትፈለጉ እንጠራችኋል! ” በሚል መልስ መሸንገላቸውን በስሜት ገልጾልኛል!

“በዜጎች ላይ አንቀልድ ፣ በነገ የሃገሪቱ ተስፋዎች ልንቀልድባቸው አይገባም ” ሲል ስሜትን በሚነካ መንገድ የገለጸልኝ ይህ ወንድም በአሁኑ ሰአት የተለያዩ ተማሪዎችን በየቤታቸው እየሄደ በማስተማር ትምህርት ቤቱ ሊከፍለው ከሚችለው ገንዘብ በላይ ገቢ እንዳለው የገለጸልኝ ሲሆን ያም ሆኑ ትምህርት ቤቱ ለመደገፍ ይቻል ዘንድ ባለው ትርፍ ጊዜ መምህራን እንዴት ራሳቸውን ብቁ አድርገው ማስተማር እንዳለባቸው የተለያዩ ትምህርት ማጎልመሻ ስልጠናዎችን በነጻ ለመስጠት ከጓደኞቹ ጋር ጥያቄ ቢያቀርብም ትምህርት ቤቱም ሆነ ለባለቤት ተብየው ለጅዳ ኮሚኒቲ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት እንዳላገኘ በቁጭት አጫውቶኛል። እስኪ እሰበው ” ዜጎችን እንደግፍ ስንል ለምን እድሉ አይሰጠንም ? ” በማለት ያጠይቃል ! ወጣቱ እውነት አለው !

3000 ታዳጊዎች የምናስተምርበት ትምህርት ቤት ባልረባባ ምክንያት በአደጋ ላይ እንዳለ በስብሰባው በግልጽ ተመልክቷል። የመምህራንን እጥረትን መሰረት አደረገ የሚባለው የትምህርት ጥራት እያደረ ማሽቆልቆል በስብሰባው በአደባባይ በወላጅ እና መምህራን ህብረቱ ፣ በስብሰባው ተሳታፊ ወላጆች እና በመምህራን በግልጽ ተነግሮናል። ይህ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ እያለ ለትምህርት ጥራቱ ማሽቆልቆል የመምህራን እጥረት ምክንያት በሆነበት የትምህርት ማዕከል የላቀ እውቀት ያላቸው አቤቱታ ወገኖች አቤቱታ ለምን ተፈነገለ ? የ11ኛ እና የ12 ኛ ክፍል ወሳኝ ክፍሎች ለምን አዋቂ ሳይጠፋ እውቀቱ በሌላቸው መምህራን እንዲማሩ ማድረግ ለምን አስፈለገ ? በዚህ መሰል አስተዳደር የሚመራው ትምህርት ቤት የትምህርተ ጥራቱን አስጠብቆ ልጆቻችን ወደ ተሻለ የእውቀት ጎዳና ያደርሳቸዋል ብሎ ማሰብስ እንዴት ይቻላል? ለዚህ ጥያቄ መልስ መስጠት ያለባቸው ወጣቱን በመረጃ በአደባባይ መሞገት ያልቻሉት ወገኖች እና አጫፋሪዎቻቸው ቢሆኑ ደስ ይለኛል ። ኤርትራ የምትለው ሃገር ስለተነሳች ያንገበገባቸው ወገኖች ንጽጽሩ ከሱዳን አለያም ከፖኪስታን ተማሪዎች ጋር ቢሆን እንዲህ ያንገበግባቸው ነበርን ? ጉዳዩን በቅንነት ማሰብ ከቻሉ ኤርትራን የምትለውን ቃል ትተው የትምህርት ጥራት የለም ለሚለው የወጣቱና የብዙሃን ወላጅ አስተያየት ለምን በአደባባይ ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም ? ለነገሩ ይህንን ለማድረግ ሞራል የላቸውምና አልፈርድባቸውም ። እኔም ቢያንስ ከዚህ ተነስቸ ይህንን ደረቅ እውነት ለመገምገም የተለየ ክህሎት ይጠይቃል ብየ ስለማላምን በማለዳ ወጌ ተነፈስኩት …
ቸር ያሰማን
ነቢዩ ሲራክ

አንድ ቁምነገር፤ የብሄራዊ ቋንቋ ያለህ…!!! –ከአቤ ቶኪቻው

$
0
0

በነገራችን ላይ ብሄራዊ ቋንቋ የሚባል ነገር የለንምኮ… አማርኛ ለረጅም ጊዚያት የሀገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ ሆኖ አግልግሏል። አሁን ግን አማርኛ በአማራ ክልል እና በፊደራል አስተዳደሮች (አዲስ አበባ እና ድሬደዋ እንዲሁም ይሁንልን ባሉ አንዳንድ ከልሎች) ብቻ ተውስኖ ይኖር ዘንድ ተፈርዶበታል። ሁሉም ክልሎች ውስጥ የሚኖሩ ተማሪዎች በገዛ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይማራሉ። እንዲሁም እንደየ ክልሎቹ ሁኔታ ‘የፌደራሉን’ ቋንቋ (አማርኛ) ከተወሰነ ክፍል በኋላ መማር ይጀምራሉ። (የፌደራል ቋንቋ ስል የፌደራል ፖሊስ ቋንቋ ማለቴ አይደለም ካነሳናቸው አይቀር ግን የእነርሱ ቋንቋ ራሱ መቀየር እንዳለበት ጠቁሞ ማልፉ መልካም ነው እስከመቼ ድረስ ቆመጥ እና ክላሽ ለመግባቢያ ቋንቋ ይጠቀማሉ… ) ሃሃ… ብለን ወደ ቁምነገራችን ስናሳልጥ፤

school
በግሌ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማራቸውን አሳምሬ እደግፈዋለሁ። በአፍ መፍቻ ቋንቋ አለመማር አቀበቱ ብዙ ነው። ለምሳሌ፤ አንድ በጉራግኛ አፉን የፈታ ልጅ በሳይንስ ትምህርት ክፍለ ጊዜ በቅጡ በማይርዳው ቋንቋ የእጅ መታጠብ ጥቅም ቢነገረው ቋንቋውን ለምዶ መምህሩ ምን እያለው እንደሆነ እስኪገባው ድርስ ፊቱን ሳይታጠብ ወደ ትምህርት ቤት ሊመጣ ነው ማለት ነው። ስለዚህ በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማርን ድሮ አርስናልን እድግፍ ከነበረው በላይ የምደግፈው ነገር ነው። (እኔ የምለው አርሴ ገሰገሰች…. አሁንም ድጋፌን ለጅምርላት ወይስ አርፌ ሲቲዬን አይዞሽ… ልብል…)

ያም ሆኖ ግን ኢትዮጰያን የመሰለች ሀገር፤ እንዴት ብሔራዊ ቋንቋ አይኖራትም… ይሄን ጊዜ አንስተኛ እና ጥቃቅን የኢህአዴግዬ ካድሬዎች “ኢትዮጵያ የሚባል ብሄር ስለሌለ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ አያስፈልጋትም” ሊሉ እንደሚችሉ ይጠረጠራል ተጠርጥሮ ታድያ እንዴት ዝም ይባላል…

አሁን ‘በስራ’ ላይ የሚግኘው የኢትዮጵያ ህግ መንግስት፤ አንቅጽ አራት ላይ የኢትዮጰያ ብሄራዊ መዝሙር፤ በሚለው ርዕስ ስር “የኢትዮጰያ ብሔራዊ መዝሙር የህገ መንግስቱን ዓላማዎችና የኢትዮጵያ ሕዘቦች በዴሞክራሲ ስርዓት አብረው ለመኖር ያላቸውን እምነት፤ እንዲሁም የወደፊት የጋራ ዕድላቸውን የሚያንፀባርቅ ሆኖ በሕግ ይወሰናል።” ይላል። ይህም ሕግ መንግስቱ ራሱ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት መኖሩን ያመለክታል ማለት ነው። ስለዚህ ኢህአዴግ መስተፋቅር እና መስተ ነዋይ ያስነካቻችሁ በሙሉ “ኢትዮጵያዊ ብሄርትኝነት የለም” ስትሉ ከህገ መንግስቱ ጋር እየተላተማችሁ እንድሆነ ታውቁት ዘንድ ይሁን፤ (መላተም ብርቃችን አይደለም ካላችሁንም እንግዲህ በቴስታ በሉትና የግንባራችሁን ታገኛላችሁ!)

ሀገር በብሔራዊ መዝሙር ብቻ አትኖርም በብሄራዊ ቋንቋም እንጂ… ብለን በአዲስ መስመር ስንቅጥል፤

አሁንም ህግ መንግስቱን ስናየው፤ አንቅጽ አምስት ላይ ስለ ቋንቋ ሲደነግግ፤ “ማናችውም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በእኩልነት የመንግሥት እውቅና ይኖራችዋል” ይላል… እስይ የኔ አንበሳ ብለን ስንወርድው፤ በዚሁ አንቅጽ ቁጥር ሁለት ላይ “አማርኛ የፌድራሉ ቋንቋ ይሆናል” ይላል። እዚህ ላይ ነው እንግዲህ የምንቀውጠው፤ (አራዳ “ቀወጠው” ብሎ ሲል፤ አጥብቆ ተከራከረ አለቀም እምቢኝ አለ፣ በጉዳዩ ላይ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ተጨቃጨቀ። የሚል ትርጉሜ ይይዛል።)

“አማርኛ የፌደራሉ የስራ ቋንቋ ይሆናል” ሲል የደነገግውን ሕገ መንግስት አፍ ካለው ይናገር ዘንድ ከሌለውም በተወካይ በኩል እንዲመልስልኝ ሁለት ጥያቄዎችን እጠይቀዋለሁ፤ አንደኛው አማርኛ ብቻውን ምን እዳ አለበት እና ለብቻው የፌደራሉ ቋንቋ ይሆናል… የሚለው ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ፤ ብሄራዊ መግባቢያ ቋንቋችንስ ምንድን ነው… የሚል ይሆናል።

እንደ ሀገር የሚያስትሳስርን የሚያግባባን ሁለትስ፣ ሶስትስ ቋንቋ ቢኖርን የሚጎዳው ማነው… በባቢሎን ዘመን ስራ ፈቶች እግዜርን ላይ ለመድርስ ግንብ ሲገነቡ የልባቸውን ክፋት ያየው አምላክ ቋንቋቸውን ደበላልቀው የሚል ሃይማኖታዊ ትምህርት ሰምቼ አውቃለሁ፤ ታድያ መንግስታችን በልባችን ምንም ክፋት የሌለብንን ዜጎቹን በቅጡ ተግባብተን በቅጡ ተባብረን ትልቅ ሀገር ብንገንባ ምን ይጎድልበታልና ብሔራዊ ቋንቋ አሳጣን…. (የጥያቄ ምልክት በብዛት)

እናም፤ ጆሮ ያለው ይስማ አንድ የሚያደርጉን ቋንቋዎች ያስፍልጉናል። ሶስት እና አራት ቋንቋዎቸን ብብሔራዊ ቋንቋ ደርጃ የሚጠቅሙ ሀግሮች ተጠቀሙ እንጂ አልተጎዱበትም። ስለዚህ እየተግባባን እንድንገነባ ዛሬውኑ ብሔራዊ ቋንቋዎቻችንን አሳውቁን እና አስትምሩን፤ የዚህ ቁምነገር ፀሀፊ፤ አንጅት ላይ ጠብ በሚሉ አጥጋቢ ምክንያቶች፤ ቢያንስ አማርኛ እና ኦሮምኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ሆነው ግልጋሎት መስጥት እንዲጅምሩ በብርቱ ይውተውታል።

ተቃዋሚዎች ሰምታችኋል!

“ጥቁሩ ሰው” –የጥቁር ሕዝብ አባት – (ከስንሻው ተገኝ)

$
0
0
minilik                                  
   አንድ ዘመን ሥርዓተ መንግስቱ በመቆየትም ሆነ አባላቱ የአሥራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን የተረት ዓለም ሰዎች ስለ መሰሉን- ሁሉም ነገር ስለገለማን አዲስ ሥርዓት፣ አዲስ መሪ፣ አዲስ ዘመን መናፈቅ ይዘን ነበር። ሰዓሊ ሁሉ፣ ደራሲ ሁሉ፣ ጸሐፌ -ተውኔት ሁሉ እጁን የሚያሟሸው በቴዎድሮስ ሥዕል፣ ተውኔትና ታሪክ ሆነ። ብርሃኑ ዘሪሁን- የቴዎድሮስ እንባ -(መጽሐፍ) ከዚያ በፊት ደጃዝማች ግርማቸው ተክለሐዋርያት- ቴዎድሮስ (ተውኔት) አቤ ጉበኛ – አንድ ለእናቱ (ታሪካዊ ልቦለድ) ጸጋዬ ገብረ መድኅን – ቴዎድሮስ (ተውኔት)…ሥዩም ወልዴ -ሥዕል..ታደሰ ወ.አ….ቅርጻቅርጽ እና የሥነ ጥበባት ትምህርት ቤት ሥስት አራተኛ ተማሪዎች..የቴዎድሮስ ሥዕል ግጥም -ቅኔ- ሥዕል አለፈላት።
ከአሮጌና ከገለማ ሥርዓት ነፃ የሚያወጣ አመጸኛና አመጻ የሚመራ ጀግና ስንፈልግ ባጀንና ቴዎድሮስን አገኘን። ከመቶ አመት በኋላ ነው ቴዎድሮስ የተፈለገው። በአጤው ሥርዓት በአንዳንድ ደራስያንና የዘመን ታሪክን በውዳሴና በነቀፋ በሚያቀርቡ ግለሰቦች ዘንድ እንደጭራቅ ይቆጠር የነበረው መይሳው ካሣ በለውጥ መሪነት የተፈለገበት መሪ ነበር። አብዮታዊው መሪ ጓድ መንግሥቱ እንኳ፥ “ቴዎድሮስ” (ምናልባትም ዳግማዊ ቴዎድሮስ) እኔ ነኝ። የዚህን ሕዝብ አብዮት እንድመራም ከሙታን የተጠራሁ ነኝ” እስከ ማለት ደርሰው ነበር። በቴዎድሮስ መንገድ አልተጓዘም እንጂ። በተረተኞች፣ በተረበኞችና በዋልጌዎች፣ በጐታቾችና በክፍፍል በኖሩ ዘንድ ተወዳጅ ያልሆነው ሕልመኛው ቴዎድሮስ በእርግጥ ከዘመኑ አርቆና አልቆ የሚያይ ስለሆነ ከወቅቱ ደባትርና ከመሳሰሉት ጋር ስምምነት አልነበረውም።
የአገር አመራር በተበላሸና ሕዝቡ የሚያምነው መንግስት ባጣበት፣ ብሔራዊ አንድነቱና ዳርድንበር አስከባሪ በሚሻበት ሰዓት ከመሐሉ የወጣ የጐበዝ አለቃ ሲያደንቅ ይገኛል። እንዲያ ካልሆነ ደግሞ ከአባት መሪዎቹ መካከል ያደነቀውን፣ የሚያደንቀውናና የሚያከብረውን መናፈቅ ይጀምራል። ባያውቀውም። ዛሬን ያስቡአል። አገር እንደ አቃቂ በሰቃ (ኮሎናልቤ) ከስኩት ፍርክስክሱ በወጣበት፣ ሕዝብ እንዲከፋፈልና እንዲጨራረስ ማናቸውም ዓይነት ሴራ በሚጐነጐንበትና መቀበሪያ ሳይቀር “እናገኝ ይሆን” የሚል ስጋት በተጫጫነን ሰዓት “የአንድነትን ጌታ” የአገሪቱን እውነተኛ አባት መናፈቅ ያለ ነው። እነዚህማ ሸጡን። እነዚህማ ለወጡን። መሬቱን ጋጡት። ከትውልዱ አባልነት መብታችን አንዲቱንም አላከበሩልንም። የአንድነትን አባት፣ የዘላለም ኩራታችን ምንጭ፣ ሁሉንም አበሻ በእኩልነት የመራውን ጀግና እንድንናፍቅ ጊዜው አስገድዶአል። ምኒልክን! ይኸ ደግሞ ከመካከላችን እንደ ምኒልክ ያሉ የአንድነት እምነት አራማጆች እስኪንቀሳቀሱ ድረስ ነው።
ነፃነት አንድን ሕዝብ ወደፊትና ወደላይ የሚያንደረድር (የሚወስድ) ኅይል ይሻል። ስለዚህ እውነተኛና ከዚህ በኋላ የሚመሩን (ከዘመኑ ቀድሞ እንደ ተወለደው ምኒልክ) ሰዎችም ወደፊት ብቻ ሳይሆን ወደ “ላይም” ሊመሩን የተዘጋጁ ናቸው። እነዚህ ቆነጃጅት አልተወለዱም አይባልም። እንዲያውም አይተናቸዋል። ዳስሰናቸዋል። ዓለምም አውቆአቸዋል። እኛ ግን ከጥቃት፣ ከእሥራት፣ ከእንግልት…ከመከራ አላዳናቸውም፥ እስክንድርን፣ አንዱዓለምን፣ በቀለን…ካድናቸው። ለወያኔ ወረወርናቸው ለአውሬ። አገርን የሚያድን መሪ ብቻ አይደለም። ዋናው ሕዝቡ ነው። በአድዋ ወሳኙን የመሪነት ሚና የያዘው ምኒልክ ነበር። የተዋጋው ሕዝቡ ነበር። ሕዝባችን ቅንና ጀግና መሪ፣ መሪውም ታማኝና ቆራጥ ሕዝብ ያገኘበት አንድ ወቅት ይኸ ነው።
በአንጻሩ በአመራር የጊዜ ማኅፀን ውስጥ ያሉት ወይም ቢወለዱም በአመራር ጉልምስና ዘመን ላይ የሚገኙት “መልካካም የኢትዮጵያ ልጆች” ወደ አገር አዳኝነቱ መንበር ሲመጡ የሚገጥማቸው ፈተና የትየለሌ ነው። ሁላችሁም አስቡት። የተሸጠ አገርና መሬት የማስመለስ ግዴታ ሊሸከሙ ነው። የተከፋፈለ የሕዝብ ይዞታ ሊያስተካክሉ ነው። የኢኮኖሚውን ሥርዓት መስመር ሊያስይዙት ነው። “ወደ ላይ መምራት” ባልሁት የአመራር ፈርጅ ደግሞ የሚጠብቃቸው ከዚህ ሁሉ በላይ ነው። በታላላቅ ዲታዎችና መንግሥታት ትእዛዝና መሪነት ሥር የወደቀችውን አገር ዜጐችዋ ባለሥልጣናት ይሆኑ ዘንድ መንገዱን መጥረግ አለ። የሕዝብን ነፃነት፣ መብትና ሕዝቡ በአገሪቱ ላይ ያለውን ሉዓላዊነት ማወቅና ማክበር አንዱ ነው። የሕብረተሰቡን መንፈሳዊና ባሕላዊ መብቶች ማረጋገጥና የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ማስወገድ፣ የጽሑፍና አሳብን በነፃ የመግለጥ ተፈጥሮአዊ መብቶቹን መንከባከብ፣ ፍትሕና ርትእ በራሳቸው ጐዳና ከመጓዝ እንዳይታወኩ ማድረግ ማለት ነው። ዝርዝሩ በዚህ ይቀጥላል። በመሰረቱ ደግሞ ታሪክ ስትቆፍሩ ብትውሉ አገር የሸጠ፥ የአገር መሬት የቸበቸበ መሪ ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም። በውጭ ምስጢር ባንክ የተቀመጠውን ገንዘብ ቁልፍ መለስ ለሚስቱ ካልሰጣት እሱም በሞቱ ከስሮአል። እኛም ያንን ለማስተካከል ብዙ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። የእሱን ወንጀል።
ጆርጅ ኦርዌል በ1984 መጽሐፉ በአምባገነኖች አገዛዝና ዘመን “እውነት ውሸት፣ ማይምነት እውቀት፣ ጥላቻ ፍቅር..ይሆናል” ይላል። ስለዚህ የወያኔን ባሕርያት የምንረዳው ዛሬ አይደለም። አብረን ኖረን የመንግስት ጠባያት ያልሆኑ- መሆንም የማይገባቸውን ስርቆትን፣ ተራ ውንብድናን፣ ቅጥፈትን፣ የጅምላ ግድያን፣ ፀረ ሃይማኖት አቋምን፣ የመብት ረገጣን…በየዓይነቱ እንደ ቡልኮ ተከናንቦ አይተነዋል። አንዳንድ ፀረ ሕዝብ ተግባራት ከየት መጡ ሳይባል እንኳ “የእሱ ሥራዎች ናቸው” ማለት ቀላል ሆኖአል። ትግርኛ ተናጋሪ ወገኖቼ ፀላዔ ሰናይ ይሉአቸዋል። አንዳችም በጐነት ያልተፈጠረባቸው ለማለት ነው። የሰሞኑን ደንባራ ፖለቲካ ለአብነት ማውሳት ለተነሳንበት ጉዳይ ብርሃን ይፈነጥቃል ባይ ነኝ።
በቅጥፈት የተካነው ሰውየ ከተለያቸው ወዲህ ወያኔዎች ያንኑ የተለመደ ውሸት ከመደጋገም በቀር ሌላ መፍጠር፣ በሌላ ስልት ማወናበድ አልሆንላቸው ብሎአል። ውሸት እንደ ቅርስ በነገሠበት አምባቸው ደግሞ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ያላትና ያፈራችው መንፈሳዊና ስጋዊ ቅርስ ሁሉ አንደኛ መጥፋት አለበት፣ ዳግመኛም- አገሪቱ ካልጠፋች..ታሪክዋ ከዛሬ ተጀመረ መባል አለበት። ታሪክ ከእነሱ አልነሳ ሲላቸው አሁንም ያለፈውን በጐ ታሪክ፣ አኩሪ ባሕልና ጀግንነት፣ የአንድነት ጥበቃ መንፈስ…እንደ ቀላል ነገር ለመግደል ወጥተዋል።
    ውሸታቸው ባያልቅም እውነት መናገር እንጀምር
ለዚህ ሥርዓት ማንኛውም ያለፈ ታሪክ፣ ታላላቅ ጀግኖች፣ ዳር ድንበር…የረከሰና የተናቀ፣ መለወጥና መደምሰስም አለበት። ሁላችሁም ለወያኔ ዓላማና ዛቻ፣ ቅጥፈትና ፀረ አንድነት እንግዳ አንዳለመሆናችሁ የሟቹንም ዛቻና አቋም ታስታውሳላችሁ። ስለ ሰንደቅ ዓላማ ምን አለ? ስለ አገሪቱ አንድነት ምን አለ? ምንስ ፈጸመ? ተከታዮቹስ ምን እያሉና ምን እያደረጉ ናቸው? በአጭሩ የሚነገረው ውሸት፣ የፈጠራ ታሪክና ከፋፋይ ፕሮፖጋንዳ አልቆ እናርፈዋለን ብለን ስናስብ ከቶውንም ወፍጮው ይበልጥ እየፈጨ ስለሆነ በውሸቱ መካከል ስለእነሱም እውነቱን መናገር መጀመር ያለብን ይመስለኛል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትሩማን “ሪፐብሊካኖች ስለእኛ ውሸት መናገርን ካላቆሙ ስለእነሱ ያለንን እውነት መናገር መጀመር ያለብን ይመስለኛል” ብለው ነበር።
ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ጥቂት ከመናገሬ በፊት ስለ መለስ ጥቂት-እጅግ ጥቂት ለማለት እወድዳለሁ። የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሲዘልፍ..ዋና ዓላማው የኢዮጵያን ስም መለወጥ ነበር። ስለዚህ ለብዙ ዓመታት ኢትዮጵያን በስም ከመጥራት ይልቅ “አገሪቱ” ነበር የሚለው። ሥልጣን ሲጥመውና አገሪቱም የማትፈርስ (በቀላሉ) ስትመስለው “ኢትዮጵያ” ማለት ይዞ ነበር።
ቀደም ሲል ጆርጅ ኦርዌልን ያነሣሁበት ምክንያት “ውሸት እውነት” የሚሆንበትን ትክክለኛ አጋጣሚ መከሰት በሚመለተው ነው። እንደሚባለው በአምባገነን መንግሥት ሥር የመጀመርያው ጥቃት የሚደርሰው “በእውነት” ላይ ነው። በሕዝባዊ እውነት ላይ! በታሪኩ ላይ ነው። በጀግኖቹ ላይ ነው። ስለዚህ በአገር የተገኘው ቀጣፊ ሁሉ ዛሬ በፕሮፓጋንዳው ሰፈር፣ በአራት ኪሎ ቤተ መንግስትና በየክልሎቹ አመራር አምባ የተሰባሰቡት የሥነ አእምሮ ጠቢባን (pathological liars) የሚሉአቸው የሚታዘንላቸው ሕመምተኞች፣ እውነትን የሚፈሩ፣ እውነት ሲነገር የሚደነግጡ፣ እውነት ሲወጣ የሚረበሹ ናቸው። ስለዚህ “አንድነት” በተፈተነበትና የአገር ሽያጭ በደራበት ሰዓት አንዱ ማወናበጃ ስልት ያው ምኒልክን በወንጀል መክሰስ ነው። “አምስት ሚሊዮን ኦሮሞ ገደለ” ነው አዲሱ አማርኛ። ለመሆኑ በምኒልክ ጊዜ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከ5 ሚሊዮን ይበልጥ ነበር? ከዚህ ውስጥ የኦሮሞው ቁጥር ስንት ነበር? ለመሆኑ ምኒልክ ማነው? ምን ሰራ? ሕዝብን ከጫጫታው (ከዘመኑ) ለማዳን መሞከር አለብን ወይስ ታሪክ ነፃ ያወጣዋል በሚል አደብ እንግዛ?
       “ ጥቁሩ ሰው” – እንደ ሰው

ታሪክ የበጐነት ምስክር – ወይም ለበጐነት የሚያደላ እማኝ ብቻ አይደለም። የአጥፊዎችን ጥፋት፣ የከሐዲዎችን አሳፋሪ ተግባር፣ የአምባገነኖችን ክፋትና ኢሰብአዊ አገዛዝ ጭምር ዘግቦ ለትውልድ ያስተላልፋል። ይሁንና ታሪክ የማያውቁ አዋቂዎች በመምሰል፣ አዳዲስ ድርሰት በመጻፍ ከሐቅ ግድግዳ ጋር የሚላተሙ፣ በባሕርያቸው ፀላዔ -ሰናይና የእውነት ጠላትነት ያላቸው ደካማ ፍጡራን መድረክ ሲደላደልላቸው የሚያዥጐደጉዱት ቅጥፈት መታለፍ እንደማይገባው እየተከሰተልን መጥቶአል። እስካሁን ግን “ለቅጥፈት ማስተባበያ” ወይም ማስተካከያ አያስፈልገውን በሚልና ውሎ አድሮ ሐቅ ይረታል በሚል እምነት ቅጥፈት ቅጥፈትን፣ ፈጠራና ድንፋታ ራሱን ሲፈጥርና እንደአሜባ ሲራባ በቸልታ ያለፍናቸው ጉዳዮች ሞልተዋል። ከሁሉም ከሁሉም አንድን ኅብረተሰብ የሚያቃጥለው የታሪኩና የጀግንነቱ መታወቂያ ሰነዶች፣ ግለሰብ ጀግኖችና ብሔራዊ መከበሪያ ሐውልቶቹና ቅሪቶቹ መደፈር ነው። በዚህ ረገድ ብዙ ተደፈርን። በዓለም አቀፍ ደረጃ የ”ታላቅ መሪነት”ን ደረጃ የተቀዳጁትን፣ ጠላት ሳይቀር የሰገደላቸውን መሪዎቻችንን ሳይቀር ዛሬ የራሳችን ልጆች በእነዚህ ላቅ ያሉ ሰዎች ላይ ሲያቅራሩ ስንሰማ እንቅልፍ መንሳቱ አልቀረም።
የወያኔ ቀዳሚ ሰልፍና ፍልስፍና ሕዝብን መከፋፈልና አገሪቱንም ማፍረስ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠራጥረው ይከራከሩን የነበሩ ሰዎች ዛሬ ከግንዛቤ በመነሳትራሳቸው “አገር እየጠፋ” መሆኑን እያረዱን ነው። በወያኔዎች በኩል ደግሞ የአገሪቱንም ሲሳይ እያፈሱ መልሰው አገሪቱን ለማጥፋት ማናቸውንም ሴራ እየፈፀሙ ናቸው። የትሮትስኪ ታሪክ መዝጋቢና የሩሲያን አብዮት ክሽን አድርጐ ያቀረበው አይዛክ ዶቸር ስለ ሩሲያ አብዮት መሪዎች ሲጽፍ እነዚህ ሰዎች የማያውቁትንና ሊያውቁ ያልቻሉትንአገር ተረከቡ። ወይም በእጃቸው አስገቡ። ቀጥሎም የሚያምኑበትን አቃጠሉት። አቃጥለውም ሰገዱለት” ይለናል። አዎን ወያኔዎች ጥገትዋን አልበው እየጠጡ፣ አርደውሊበሉአትም ፈለጉ” ለማለት ይቻላል። በተአምር በእጃቸው የገባችውን አገር ማዳን የብዝበዛቸውና የዘረፋቸው ዋስትና በሆነ ነበር። ይልቁን እዚህ ከደረሱ በኋላ እንኳ የዚህንአገር አንድነት ማዳን ቢሞክሩ ቢያንስ ልጆቻቸው አገር አለን እንዲሉ ባስቻላቸው ነበር። ይልቁንም ኦሮሞዎች ነን የሚሉ በዕድሜም፣ በግንዛቤና በአእምሮ ያልበሰሉ ልጆችን በመመልመል የሚያንጫጩብን እነዚሁ አገር በእጃቸው የወደቀ ሰዎች ናቸው። ምኒልክን ለመወንጀል የክሱን ነጥብ ሁሉ ከየት አገኙት?

እውን እነዚህ ጨርቋ ሕፃናት – የጨርቋ አእምሮ ውጤት የሆነ ፕሮፓጋንዳ በጩኸትና ሰላላ መላላ በሆነ ልሳን ሲያስተጋቡ የዚህ አገር ዋልታና ወጋግራ የሆነው ኦሮሞውኅብረተሰብ ምንኛ እንደሚያፍርባቸው ትገነዘባላችሁ?

ለመሆኑ ከኢትዮጵያ ታሪክ ባለቤትነትና ክብር ሊነጥለን የሚችል ማነው? ጃዋር? አያት ቅድመ አያቶቻችን ደምናአጥንት የሰጡአት አገርኮ ናት! የወያኔ የመስዋዕት ጠቦቶች ለሆኑት እነዚህ ኅፍረተ ቢሶሽስ የኦሮሞን ውክልና ማን ሰጣቸው? ስለማያውቁት፣ ስላላወቁትና ሊያውቁትምስላልፈለጉት ሕዝብ በድፍረት መናገርን ከየት አመጡት? እነዚህ ልጆች “ወገኔ ነው” የሚሉትን ኦሮሞውን ኢትዮጵያዊ ከሌሎች (ለምሳሌም አማራው) ብሔሮች ጋርበማጋጨት ሊያመጡ የሚችሉትን ትርፍ ሊነግሩን ይችሉ ይሆን? ወይ ልክፍት!

ከሶቪየት ኀብረት ኤምፓየር መፍረስ በኋላ አንዳንድ የአሜሪካ የፖለቲካ ፈላስፎች እንደ ሶስተኛ አገር የሚታዩ የኅብረተሰብ ጽናትና ሰላም ያላቸው አገሮች በተቻለ መጠንተሸንሽነው ብዙ አገሮች እንዲወጣቸው ሰፋፊ ጽሑፎችን በገበያ አውለዋል። ከእነዚህም መካከል መለስ ዶላር ያፈስስለት የነበረው የሐርቫርዱ ሳሙኤል ሐንቲንግተን ይገኛል። ከዚያም ሌላ አንዳንድ የሲአይኤ ቅጥረኞች ጽሑፎችየጥናቱ መደብር አሉ። ዩጐዝላቪያ የዚህ ፍልስፍና “ጊኒፒግ” ናት። ከ1991 ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያየምትታመሰው በዚሁ ረቂቅ የጥፋት አውሎ ነፋስ መሆኑን አንዘንጋው። እነሆ እንደ ጃዋር ያሉ አለማወቃቸውን እንደ እውቀት፣ ጮኾ መናገርን እንደ ሐቅ፣ የፈለጉትን ጥጃየአምልኮ ጸጋ በመቁጠር አየረ አየራቱን ሲያተረማምሱት ከእንግዲህስ “ተመከር! ተሳስተሃል! በአገር፣ በሕዝብና በታሪክ ላይ ያመጽህ ባለጌ ነህ” ማለት የሚገባ ይመስለኛል።ልድገመውና “በአባቴ ሙስሊምና ኦሮሞ፣ በእናቴ ክርስቲያንና አማራ ነኝ” በማለት ጅምሩን በማይጠቅመው መደምደሚያ ያበላሸዋል። ጃዋር መሐመድ። ሙስሊም፣ ክርስቲያን፣ አማራ፣ ኦሮሞ! ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ምን ይሁን?

ጐበዝ በዚህ ዓይነቱ ጊዜ ከየጉድጓዱ ብዙ አይጦች ሊወጡ ይችላሉ። አትደነቁ። አንዳንዶቹ የመታወቅ አባዜ (የእንክብካቤ እጦት አባዜ…ዘተ) የተከሰተባቸውና “እገሌ”ለመባል የሚጣባ ሕመም ተሸካሚዎች ናቸው። አንዳንዶቹ ቀጥታ ራሳቸውን ለማያውቁት ተልእኮ በመስዋዕትነት ለመሰጠት በምንዳ የተገዙ ናቸው። ለዚህ ዓይነቱ ተልእኮየተመደበ በጀት ስላለ ሰው ከተገኘ ገዥ አለ። ሕሊና ለሌለው፣ ለሚሸጥ ወይም ለሚያከራይ ዘወትር ክፍት ቦታ አለ። እነ እንቶኔ በዚህ የሕመም ዘርፍ ላይ በመሆናቸውሊታዘንላቸው እንጂ ሊታዘንባቸው አይገባም። ቀደም ሲል የተጠቀሰውን ጉብል አንድ ጊዜ በአንድ የቨርጂኒያ አዳራሽ ትልቅ ስብሰባ ላይ አይቼዋለሁ። እዚያ ስብሰባ ላይ ወደዘጠኝ መቶ የሚጠጉ ሰዎች ነበሩ። ይሁንና እስኪታወቅ ሳይሆን እስክንሰለቸው ድረስ የባጡንም የቆጡንም ሲናገር ቆይቶ “እዚህ ሥፍራ ኦሮሞና ሙስሊም ለምንአልተጋበዘም?” ይላል። መቸም “ከእናንተ መካከል ኦሮሞ የሆናችሁ ተነሱ! ሙስሊም የሆናችሁ ተነሱ!” አይባልም። ይኸ ደግሞ ከቅን አእምሮ የመነጨ ነው አይባልም።የሌሎቹንም “ዋልጌ ጭንቅላት” ባለዶላሩ ዋሐቢ፣ የሽብሩ ልጆች እነ…..በማናቸውም ሂሣብ ሊገዙአቸው አይፈልጉም አይባልም። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እስከተዋጉላቸው ድረስ።

አንዳንድ የዋሐን ወገኖቼ የእነዚህን በጥላቻ የተፀነሱ፣ በጥላቻ የተወለዱና የጥላቻን መርዝ በመካከላችን የሚዘሩ ሰዎችን ተጽእኖ እስከ መፍራት ደርሰዋል። ኦሮሞውኅብረተሰብ እንዳይቀበላቸው ነው? ያፍርባቸዋል። ከአገር እድር ያስወጣቸዋል። ስለዚህ በሶሻል ኔትወርኩ ረገድ ኅላፊነት የወሰዱ ሁሉ ለኦሮሞ ወገኖቻችን የመናገር ዕድል(በሰፊው) መክፈት አለባቸው። በአንድ በኩል ደግሞ ታሪክ የሚያቆሽሹትና ወደ ኋላ እየተመለከቱ የሚናገሩት እነዚህ ወገኖች ርስበርሳችን ስለጀግንነት፣ ስለታሪክ፣ ስለታላቋኢትዮጵያ ማንነትና ምንነት….እንድንነጋገር ዕድል እያስገኙልን ይመስለኛል።

   ጥቁሩ ሰው – ለጥቁር ሕዝቦች
Adwavictoryጀርመኖች በኦቶፎን ብዝማርክ፣ ጣልያኖች በጁሴፔ ጋሪባልዲ፣ ፈረንሳዮች በናፖሊዮን ቦናፓርቲ፣ በዣንዣክ ሩሶ፣ በዣን ደ አርህ፣ አሜሪካኖች በጆርጅ ዋሽንግተን፣ አብርሃም ሊንከን…..እንግሊዞች በዊልያም ዘኮንከረር፣ በዊንስተን ቸርችል፣..ይኰሩም ይኩራሩም ይሆናል። የእነዚህን ሰዎች ጀብዱ ስንሰማ፣ በትምህርት ቤቶች ዝናቸውን ስናወሳና ስናጠናቸው ስለኖርን የራሳችን ሰዎች እስኪመስሉን ድረስ በልባችን ጽላት ላይ ታትመዋል። ሰዎቹ በየዘመናቸው ለአገሮቻቸው ባበረከቱአቸው አስተዋጽዎችና የተለዩ አገልግሎቶች የየአገራቸው “አባቶች” እስከ መባል ደርሰዋል። በፖለቲካና በወታደራዊ መስክ ብቻ ሳይሆን እነዚህ አገሮች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም አያሌ አገሮች ለአለም ጸጋ በሆኑ ልጆቻቸው አማካይነት በኪነ ጥበባት፣ በሳይንስ፣ በሥነ ጥበባትና በኬንያ (ቴክኖሎጂ) ባርከውናል። ልጆቻቸውን ተጋርተናል።
እንደገና ጀርመኖች በሒትለር፣ ጣልያኖች በሙሶሊኒ፣ ካምቦድያውያን በፓልፓት፣ ኡጋንዳውያን በኢዲአሚን፣ወዘተ እጅግ እንደሚያዝኑና እንደሚሸማቀቁ ይሰማኛል። እኛም የዚች አገር ጐስቋሎች  ኢትዮጵያውያን በሃያ አንደኛው ምዕት ዓመት መለስ የሚሉት እኩይ ነፍስ ለኢትዮጵያ የዛሬው ትውልድ በመስጠታችን ጭብጥ ልናክል ነው። ሞተ ከተባለ ወዲህ እንኳ አገር እየሰጠ፣ አረብና ሕንድ እያነገሰብን፣ ምውት መንፈሱ እንዳሸበረን ነው። ሁላችንም የዓለም ዜጎች ይቺን የጋራ መሬት እኩል እንደምንባረክባት ሁሉ ጀግንነታቸው ያሞቀን የሃያኛው ክፍለ ዘመን ግዙፋን ባለታሪኮች ነበሩ። ጀኔራል ድዋይት አይዘንሐወርን፣ ጀኔራል ጆርጅ ፓተንን፣ ፊልድ ማርሻል ሞንትጐመሪን…እንደራሳችን እንጋራለን የሚል እምነት አለኝ። “እነዚህ ሰዎች ምነው ኢትዮጵያውያን ቢሆኑ ኑሮ” ብዬ በቁጭት አልናገርም። የአንዲት ምድር (ራችን) ልጆች በመሆናቸው ብቻ እንደራሳችን ጀግኖች- የሁላችንንም እምነት በተግባር ያዋሉ፣ የሁላችንንም ጦርነቶች ተዋግተው ያሸነፉ ስለሆኑ “የሁላችንም” እናደርጋቸዋለን። እንደ ምኒልክ ያሉ – እንደ ጐበና ያሉ- እንደ አሉላ ያሉ- እንደ አበበ አረጋይና በላይ ዘለቀ ያሉ ጀግኖች አባቶች ያሉት አገር ልጆች በመሆናችን እኛም ለዓለም ባበረከትናቸው ጀግኖቻችን ኩራት ይሰማናል። በምኒልክ የተመራው የኢትዮጵያ ሠራዊት በአንዲት ጀንበር የአንድ አውሮፓ ኅይል ካንኮታኰተ በኋላ በማግሥቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስፒ መንግሥት (በኢጣክያ ሕዝብ እንደጐርፍ መውጣት ምክንያት) ከሥልጣን ከመወገዱም በላይ በናፖሊ ከተማ የነበረውን የንጉሡን (አምቤርቶ) አልጋ ወራሽ ሕዝቡ በትከሻው ተሸክሞ “ታላቁ ምኒልክና የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለዘላለም ይኑሩ ብለህ ጩኽ” በማለት ቀኑን በሙሉ በዚህ መልክ ሲያንባርቅ እንዲውል አድርገውታል። በማግሥቱ የወጡ የኢጣልያ ጋዜጦች ኢጣሊያ ራስዋ እንደተማረከች አድርገው ጽፈዋል። ምኒልክ!
አንዳንድ የጦርነት ዘገባዎችን፣ መጻሕፍትንና ታሪኮችን ለተከታተሉ ጀግኖች የሠራዊት አዛዦች ድል ካደረጉ በኋላ “ጠላት ነው” በማለት አይንቁትም። ወይም በእጄ ገብቶአል ብለው አይበቀሉትም። እንዲያውም በ”ተቃራኒ መስክ” የተሰለፈውን በክብር ያስተናግዱታል። በጦር መሪነታቸው እጅግ የተደነቁና በመሠረቱ በተቃራኒ ዐውድ ተሰልፈው ታሪክ የሰሩ ጄኔራል መኰንኖችን ላስታውስ እወዳለሁ። በአሜሪካ የሲቪል ጦርነት የኮንፌደሬሽኑ ጦር አዛዥ ሮበርት ሊ በአሜሪካ ሕዝብ ዘንድ ከሜጀር ጄኔራል ጆርጅ ማክሊላን የበለጠ ይታወቃል። በየከተማው መንገዶች ተሰይመውለታል። የጦር ምሽጐች በስሙ ተጠርተዋል። ከስለጠነው ዓለም ሌላም ማስረጃ ለማምጣት ይቻላል።
የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ከሚያውቃቸው ታላላቅ ጄኔራሎች መካከል ሒትለር በሰሜን አፍሪካ በዋና አዛዥነት ያሰለፈው ፊልድ ማርሻል አርዊን ሮሜል (የበረሃው ተኩላ) በምዕራብም ሆነ በምሥራቅ- በአክሲስ ፓወርስም ሆነ በአላይድ ፎርስስ እጅግ የተደነቀ ነው። በመሠረቱ ለጀግና ሠራዊት ባላንጣው የተከበረ ነው። በሬሳው አይጫወትም። ወይም ወያኔዎች በኢትዮጵያ ሠራዊት ሬሳና የደከመ አካል ላይ ቆመው እንደ ፈነደቁትና እንደሸለሉት ሳይሆን የሰብአዊነት ክብርና መገመቻ ጠላትን እንደአግባቡ ማድነቅ መቻልም ነው። ለተፋላሚ ክብር መስጠትና እንክብካቤ ማድረግ ነው። እነዚህ ሰነፎች ገዥዎቻችን ምንኛ ደካሞች እንደሆኑ አያችሁት?
ከአገራችንምኮ ለዚህ ክርስቲያናዊ አርአያነትና የሰለጠነ ወታደራዊ ባሕል ምሳሌ አንቸገርም። አድዋ ላይ በአንድ ጀምበር በርከት ያሉ ጄኔራል መኰንኖችን ድባቅ የመታውና ያንኑ ያህል የማረከው እምዬ ምኒልክ በእጃቸው የገቡትን ምርኮኞች ማለፊያ ምግብ እየሰሩ (ፓስታ፣ ሞኮሮኒ ወዘተ) በደንብ ከመመገብ ባሻገር ራሳቸውና ደገኛይቱ ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ እንደ ሐኪም ቁስል መጥረግ፣ ፋሻ ማሠርና የመሳሰሉትን የሕክምና አገልግሎቶች ጐንበስ በማለት ፈጽመዋል። ጦርነቱ እንዳለቀ ምሽት ላይ በየድንኳኑ እየተዘዋወሩ “ገደልን ብላችሁ እንዴት እንዲህ ያለ ፍከራና ሽለላ ታደርጋላችሁ?” በማለት ኅዘናቸውን እስከ መግለጥ ደረሰዋል። (አንቶኒ ሞክለር ኅይለስላሴስ ዋር በሚለው መጽሐፉ በመጀመሪያው እትም እንደ መግቢያ አድርጐ ገልጦታል።
በሌላው ታሪካቸው እንደ ተገለጠው አጤ ምኒልክ ከንጉስ ተክለሃይማኖት (ራስ አዳል ይባሉ ከነበሩት) ጋር እምባቦ ላይ ሲዋጉ የጐጃሙ ገዥ ቆስለው ሲማረኩ ራሳቸው ከመሬት ተቀምጠው ቆስሉን በጨውና በአልኮል እየጠረጉ እንዳስታመሙአቸው ይታወቃል። በኋላ ደግሞ አጤ ዮሐንስ ያለ የሌለ ጦራቸውን አስከትተው ጐጃምን ወርረው፣ ሥፍር ቁጥር የሌለውን ሕዝብ ዓይን በጋለ ብረት አቃጥለው፣ ሠራዊታቸው ቤት እየዘረፈ፣ በወንዱ  ፊት ሚስቱን እየደፈረና ጐተራ እያራገፈ በጠቅላላው ንጉሰ ነገሥቱ እያዩ ሲያቃጥሉ አጤ ምኒልክ “እባክዎ ጃንሆይ ከንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ጋር ተጋጨሁ ብለው ሕዝብዎን አይጨርሱት” በማለት እንደተማጸኑአቸው የተጻፈ ታሪክ ሞልቶአል። እንዲያም ቢሆን የትናንት የአገሪቱን መሪዎች ለመወንጀል አልሻም።
ወደ ሃምሳ ዓመት የሚገመት ሙያዬ ከብዙ ሰዎች ጋር አገናኝቶኛል። እንደ ደጃች ኅይለ ሥላሴ ጉግሳ ካሉ ከሐዲዎች- እንደ ራስ መስፍን ካሉ አርበኞች- እንደ ጋዜጠኛ (ከንቲባ) ደስታ ምትኬ ካሉ በየአድዋው ጦርነት ላይ ከዋሉ የታሪክ ምስክሮች፣ እንደ ፊታውራሪ ተክለሃዋርያት ካሉ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ አንስቶ አገሪቱን ከፊውዳል ሥርዓት ለመጠራረግና የፖለቲካውን ሥርዓት ግልብጥብጡን ለማውጣት ከደከሙ ምሁራንና መሪዎች ጋር ትከሻ ለትከሻ ባልተሻሽም አጠገባቸው ተቀምጨ ያልነበርሁበትን ዘመን ልኖረው ሞክሬአለሁ። የሁሉም የጋራ ምስክርነት (የጀግናውም የባንዳውም) ኢትዮጵያ እንደ ምኒልክ ያለ መሪ ታድላ አታውቅም። እግዚአብሔር ይመስገን፤ ጻድቁ ዮሐንስ በጐ አእምሮ የወለደው ነው።
አዎን የዚህ መጣጥፍ አጀማመሬ አውሮፓውያንና አሜሪካውያን (ሌሎችም ሕዝቦች) የሚኮሩባቸው መሪዎችና በመሰረቱም የሚያፍሩባቸው አምባገነኖችም ሊኖሩባቸው እንደሚችል ላመለክት ሞክሬአለሁ። እንዲያውም አገር በችግር ማጥ ውስጥ ስትገባ ልባቸውን፣ ጭንቅላታቸውንና እጃቸውን አስተባብረው ሕዝብን በአንድ ጐራ አሰልፈው ከታላቅ ውጤት ላይ ያደረሱት እንዲህ ያሉ መሪዎች የየአገሮቻቸው አባቶች እስከ መባል ደርሰዋል። ጆርጅ ዋሽንግተንን አላነሣሁምን? የመቶዎች ባሪያዎች ባለቤት ቢሆን እንኳ ሁሉም አሜሪካዊ የአገሪቱ አባት ይለዋል። በዚሁ ልክ የኢትዮጵያን ታሪክ የመረመሩ የውጭ አገር የታሪክ ስዎችና ኢትዮጵያውያን ምሁራን ሁሉ አጤ ምኒልክንና አሳዳጊ አባታቸው አጤ ቴዎድሮስን የኢትዮጵያ አባቶች ይሉአቸዋል። ለከፈሉት የሞት ዋጋ፣ ለተሸከሙት የኢትዮጵያ ግዙፍ ተራራ፣…ይኸ የሚበዛባቸው ክብር አይደለም። ሁለቱ ሰዎች (ባይሆን ጣይቱን እንጨምራለን) ይህን ክብር ካልተቀዳጁ ማን ሊቀዳጅ ነው? ጣይቱን እናታችን ብንል ምንኛ ደስ ባለኝ!
ያለፈው ወር የእምዬ ምኒልክ መቶኛ ሙት ዓመት ነበር። አሸናፊዎች ሁሉንም እንደ ፈለጋቸው በሚያደርጉበት፣ በብር በወርቁ በሚያዙበት፣ ታሪክ ድርሰት ሆኖ በማረሻ በሚጻፍበት፣ የአገር ዳር ድንበር ያለ ጠባቂ በሚቀርበት፣ ጀግኖች የወደቁለት አንድነት መጫወቻ በሆነበት፣ ዜጐች እየተነቀሉ ነጩ፣ ብጫው፣ ጠይሙ…የባዕድ አገር ነጋዴ የሚምነሸነሽበት መሬት ጥንቡን በጣለበት ዘመን ላይ፣ መንግስት ሌባ፣ ሌባም መንግሥት በሆነበት ወቅት-እንደ መገኘታችን ብዙ ብዙ -የለም፤ ሁሉም በጐ አገራዊ ባሕል ትርጉም ባጣበት ሰዓት በሕዝብ ዘንድ ያለው ሐቅ ሁሉ ተጠቂ መሆኑ አንድና ሁለት የለውም። እነሆ ከሃያ ሦስት ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ታሪክ ተለውጦ ስለኢትዮጵያ አንድነትና ታሪክ የቆመው ሕዝብና ተቃዋሚ ኅይሎች ከሐዲ ሲባሉ…ወርቁም ሚዛኑም እንዳልነበረ ሆኖአል። ስለዚህ በምኒልክና በጣይቱ ላይ የሚወርደውን የፕሮፓጋንዳ መዓት፣ የፈጠራ ድርሰትና ልብ ወለድ ድርሳን ስታስቡት ለመሆኑ ከወያኔ አምባ የተጠበቀው ሌላ ንግርት ምን ነበር? በግልጽ የኢትዮጵያን አንድነት ተቋቁመው ከዚህ ደረጃ ያደረሱት ግለሰቦች በረከት፣ ስብሐት ነጋ፣ ዐባይ ጸሐይና ግልገል ወያኔዎችና እንደ ወያኔ የማሰብ በሽታ ከሸመቱ ግለሰቦች ምን ይጠበቅ ነበር? የኢትዮጵያን አንድነት አባቶችና ጠባቂዎች እንዲያወድሱ ነበር? ቀደም ሲል እንዳልሁት ታሪካችንን በጽሞና እንድንመረምር ዕድል የሰጡን ይመስለኛልና በበጐነት እንጠቀምበት።
ቀደም ሲል ስማቸውን ያነሣኋቸውን ጋሪባልዲንና ቢዝማርክን ለምክንያት ነበር የጠቀስሁአቸው። ጋሪባልዲ ኢጣልያንን ለማዋሐድ፣ ቢዝማርክ ተበታትና የቆየችውን ጀርመንን አሰባስቦ አንድ አገር (ኔሽን) ለማድረግ ሲወጡና ሲወርዱ የነበሩበት ሰዓት (በዘመነ ጓድነት) አንድ ነው። አፍሪካዊው መሪ (ጥቁር ሰው) ምኒልክ በተመሣሣይ ጥሪ በታሪክ መድረክ ላይ የታየውም በዚሁ የታሪክ ወቅት ነው። በዚህ ታሪካዊ ወቅት ምን ተፈጠረ? በዘመናት ውስጥ ተሸርሽራና ተበጣጥሳ የቆየችውን ኢትዮጵያ ዳር ድንበር አንድ አደረጉ። ሰበሰቡአቸው። በእነዚህ ተግባራት ብቻ ዓለም ካደነቃቸው ከነጋሪባልዲ ጋር ታሪክን ሊሻሙ የሚገባቸው ምኒልክ ዛሬ በወያኔና አንዳንድ አጫፋሪዎች ምን እየተባሉ ነው? አንዱና ጥሩ ውሸት መፍጠር ያልቻሉት ፀረ አንድነቶች የጡት ቆረጣ ወንጀል ነው። ይኸ ከየት የመጣ ነው? ለመሆኑ ወንጀሉስ የት ነው የተፈጠረው? ትክክለኛም ሆነ አልሆነ መልስ የመስጠቱን ዕዳ የሚሸከሙት ወያኔና ሁሉም ፀረ አንድነት የሚያቀነቅንበት ዜማ የሚጫወቱት ናቸው።
በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ሴቶችን ጡት ስለማስቆረጥ የተፈጠረው አጉል ነጥብ ከአማራው (ማለትም ከክርስቲያን) ባሕልና እምነት ጋር ጨርሶ የሚሄድ አይደለም። በአንጻሩ ለጋብቻና ለመሳሰለው ዕድሜና እጆቹ እርፍ ለመጨበጥ የደረሰ ኦሮሞ ገበሬ ሚስት ሊያገባ የሚችለው አማራ በመስለብ መሆኑን እንኳ ለመስማት ፈልጌ አላውቅም። በእውነቱ ግን ወንጀሉ በየዘመኑ ለሚፈጠር ኦሮሞ ሁሉ እንዲቆየው አልሻም። በዚሁ ዓይነት አጤ ዮሐንስ ወሎንና ጐጃምን “ፈጅተውታል፣ አቃጥለውታል” በሚል የዛሬና የወደፊቱ ጐጃሜና ወሎየ ሁሉ ትግሬንና አጤ ዮሐንስን እንዲጠላ አላደፋፍርም። በውነቱ ደግሞ ዘወትር የምናወድሰው ታሪካችን አላስፈላጊና አሳፋሪ ጓዝም አለው። ቀደም ሲል ያነሳናቸው የኢጣልያንና የጀርመን የዛሬ ትውልዶች የየራሳቸው አንካሳ ታሪክ አላቸው። እኛ ላይ ሲደርስ ነው ከተደረገውና ከተፈጸመው ሁሉ በላይ የታሪክ ድሪቶና ቡትቶ ያየነው።
 ኢትዮጵያዊነት አረጀ?
ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና የዚችን አገር ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብታት፣ ዜግነትንና እሴትን የሚጸየፍ አንድ ምስኪን ልጅ በአልጀዚራ ሲናገር ብዙ ኢትዮጵያውያን ሰምተውታል። የጋናው ኒክሩማህ፣ የኬንያው ኬኒያታ የኮትዲቮሩ ሑፌትቧኘ፣ የማላዊው ካሙዙባንዳ…በጆርጅ ፓድሞን መሪነት..ወደ አንድ የለንደን የስብሰባ አዳራሽ (በ1953 እ.አ.አ) የገቡበት ሁኔታ ትዝ ይለኛል። አዳራሹ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆአል። እነዚህ በኋላ የአፍሪካ ታላላቅ መሪዎች የሆኑ የዚያን ዘመን የነፃነት ታጋዮች አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የሆነውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለቡ ወደ አዳራሹ ሲገቡ የነበረበትን የክብር ሰልፍ ሳስብ በቦታው ለመገኘት እንደ ታደለ ሰው ዛሬ የልቤ ኩራት ወደር ያጣል! የጃንሆይ አጤ ኅይለሥላሴን ምስል በኮታቸው ክሳድ ላይ ያደረጉት እነ ንክሩማህ ሁኔታ ወለል ብሎ ይታየኛል። አዳራሹ በአእምሮዬ ይመጣል። ኢትዮጵያዊነትና “ኢትዮጵያዊ ነኝ” የዓለም ጭቁን ሕዝቦችና በተለይም የጥቁር ሕዝብ ኩራት እንደሆነ እነ ጃዋር ሰምተው ያውቃሉ? ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ “ኢትዮጵያ” ምን ትርጉም እንደምትሰጥ ለመሆኑ እነዚህ ይቺን አገር ካላፈራረስን እንሞታለን የሚሉ ሰዎች በመጠኑስ ቢሆን ያውቁ ኖሮአልን? “ኢትዮጵያዊነት” ከተራ ስያሜና ከአንድ ተራ አገር መጠሪያ በላይ መሆኑን ያውቁ ኖሮአልን?  ለእነዚህ ሕዝቦች ዞሮ መግቢያና መመኪያ …መንፈሳዊ ቤታቸውና ምስለ-ገነት የመሆንዋን ሐቅ ምን ያህል ሰምተዋል? የማርከስ ጋርቪን ፍልስፍና ያውቁታልን? ዛሬ ዛሬ ደግሞ እግዚአብሔር (ያህዌ ኤሎሒም) ለአዳምና ለሔዋን የፈጠረላቸው ገነት በአንደኛዋ የኢትዮጵያ ክፍል የመሆንዋ ግልጽነት አማራውን፣ ኦሮሞውን፣ ትግሬውን፣ ከምባታውን፣ ሐድያውን…ለሁሉም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት ተጨማሪ ኩራት በሆነ ነበር። (ከላይ የነካካኋቸውን ነጥቦች በይበልጥ ለማወቅ ማርከስ ገርቪንና ዱቢድ ሜሬዲትን ያነብቡአል።) በነገራችን ላይ ማርከስ ገርቪና ራስ መኮንን ይባል የነበረው ጃሜይካዊ ጓደናው በጃንሆይ ቅሬታ ያደረባቸው እነሱ ካሰናዱአቸው 3ሺ ዓለም አቀፍ ተጋዳዮች ይልቅ በእንግሊዝ ጦር በመጠቀማቸው መሆኑ ይነገራል።
jawar
በኢትዮጵያዊነት ማፈር እንደ አልጀዚራው ጉብል ባሉ የሐቅ ማይማን እየተነገረ ነው። ያ ጉብል – ጃዋር ደግሞ በሌላ ጊዜ በመቅለስለስ መልክ “ እኔ በአባቴ ኦሮሞና ሙስሊም፣ በእናቴ አማራና ክርስቲያን ነኝ።” ሲል አድምጨዋለሁ። የልጅነት ተማሪዬ ሌንጮ ለታ የደረሰበትን አጉል አጋጣሚ ያስታውሰኛል። የኦነጉ መሪ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ልብ ሲዘዋወር በነበረባቸው ወራት በጣም የተከበሩ አባቶች ወደ ነበሩበት ወደ ጅባትና ሜጫ ሄዶ ነበር። ያ አካባቢ እጅግ አስተዋይ የሆኑት ፊታውራሪ አባዶዮ ሠርገኛ ጤፍ አስመጥተው “ከዚህ መካከል ነጩንና ጥቁሩን ለይልኝ” ብለው ጥላቻንና ጠላትነትን ያወገሁበት አካባቢ ነው። ታዲያ ሌንጮ “አማሮች ያገኙን እንደእነዚህ እንስሳት ከብቶች አድርገውን ነው” ብሎ ሲጀምር “ልጆቻችንና ወንድሞቻችን..አንተ የምትላቸው አማሮች ናቸው። እኛም አማሮች፣ አማሮችም ኦሮሞዎች ናቸው።” ብለው በማስጠንቀቂያ ሸኝተውታል። የሮይተርን ቀጥታ ምስክርነት ለመጥራት እችላለሁ። ታዲያ ጃዋር እንደ ነገረን፣ ኦሮሞም ነው። አማራም ነው። ሙስሊምም ነው ክርስቲያንም ነው። ኢትዮጵያዊ ካልተባለ ምን ሊሆን ፈለገ? ቅጥ አምባሩ የጠፋበት አይደለም ትላላችሁ?
እነዚህን ሰዎች ሳስብ ኢሳይያስና መለስን አስባለሁ። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የሚለውን ድሪቶ የለጠፈባቸው ኢሳይያስ አፈወርቂ ነው። ወይም ኦነግን ጠፍጥፎ የሰራው እሱ ሲሆን “ኦሮሚያ” የሚለውን በታሪክም በተረትም የማይታወቅ የሕልም ዓለም ክልል ስያሜ ደግሞ በዳቦ ስምነት ያሸከማቸው አስመሮም ለገሰ የተባለው የእኛው ዩኒቨርሲቲ ውጤት ነው። በነገራችን ላይ የአስመሮም ለገሰ የገዳሥርዓት መጽሐፍ እስኪወጣ ድረስ ኦሮሚያ የሚባል ቃል አላውቅም ነበር። እንደ ነገሩ ደግሞ መጽሐፍ አገላባጭ ሰው ነኝ፥ እላለሁ።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ-ይልቁንም መንግሥታዊው መድረክና አጀንዳ የፀረ አንድነቱ አቋም ማራገቢያ እንደ መሆኑ አገሪቱን ወደ ማፍረስ እየረሸጋገሩም ይመስላል። ለሱዳን፣ ለሳዑዲ፣ ለሕንድ፣ ለቻይና፣ ለፓኪስታንና ዶላር ላለው ሁሉ ተከፋፍሎ የተረፈውን ማለቴ ነው። ከዚህ መሠረትነት በመነሳት የሺህ ዘመናት ሥልጣኔ የነበረው የኦሮሚያ በአማሮች ተወርሮ “ኢትዮጵያ” የተፈጠረችው ከአንድ መቶ ዓመታት ወዲህ በዚያ መንግስት ፍራሽ ላይ ነው እየተባልን ነው። የዜጐች፣ የታሪክ ተመራማሪዎች ዝምታ ለተረትና ለቧልት መፈጠር፣ ለልብ ወለድ ታሪክ መፈብረክ አስተዋጽዖ አድርጐአል። ኦሮሞው ኅብረተሰብ (በብዙዎች አካባቢዎች- ለምሳሌ በወሎ ወዘተ ጋላ ማለት ስድብ ሳይሆን የተከበረና ትርጉሙም ትልቅ ማለት ነው) የዚህ አገር ታሪክ ተጋሪ፣ ፈጣሪና በግንባር ቀደምም እንደ አገሪቱ ዳር ድንበር ተከላካይና መከታ ሆኖ የቆየ ነው። አንዲት የምኒልክ ስንኝ በማስታወሻነት ከእናንተ ጋር ባቆይስ? እነሆ!
“ጐበና ጐበና ጐበና የኔ
የጦር ንጉሥ አንተ ያገር ንጉሥ እኔ” አዳዲሱ ድርሳናቸው ከዚህ ሐቅ ጋር የሚጋጭባቸው ደራስያን “አዳዲስ ታሪክ የመጻፍን የአሸናፊዎች አንበሶችን ሚና” ይዘዋል። እኛም ማፈሪያዎች እነሱም ማፈሪያዎች ነን። ይህን እንቀበል!
   ስለ ጥቁሩ ሰው
 ወደ ሌላ ከመሻገሬ በፊት ከምኒልክ የተለያዩ ጠቅላይ ገዢዎች መካከል ዋነኞቹ (ሦስቱ) ስለ አገርና ስለ ምኒልክ የነበራቸውን ቁምነገሮች ለማንሳት እወድዳለሁ፤
“ምኒልክ ትንሽዋን ወላይታ ወስዶ ትልቂቱ ኢትዮጵያን ሰጠኝ። በእውነት ምኒልክ የእኔም የኢትዮጵያም አባት ነው። – ካዎ ጦና ጋጋ – የመላው ወላይታ ርእሰ መሳፍንት ልጅ እያሱ ቀድሞ ኩምሳ ሞረዳ ይባሉ የነበሩትን የደጃች ገብረእግዚአብሔር ሞረዳን ልጅ ለማግባት ጥያቄ ሲያቀርቡላቸው – “ ምነው! ምነው ጌታዬ! እኔና እርስዎ ኮ ወንድማማች ነን። እኔ በመንፈስ ከአጤ ምኒልክ ተወልጃለሁ (አበልጅ) ስለዚህ እርስዎና እኔ ወንድማማች ነን። የእኔን ልጅ ሊያገቡ አይችሉም። ( አንዳንድ የወለጋ አረጋውያን በዚህ ላይ ሲጨምሩ ሰምቻለሁ። ተጨማሪው ቃል “ሲሆን ባል ሲመጣለት አባት ሆነው የሚለመኑ፣ ቆመው የሚድሩ መሆን ይገባዎታል”)
የደጃዝማች አባ ጅፋር አባ ጆብር (የከፋው ገዥ) ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ዘወትር ይሹሙኝ እያለ ደጅ ይጠናቸው ነበር ይባላል። እንዲያውም አንድ ቀን እጅግ አምርሮ “ለመሆኑ እነዚህ ለሹመት ያበቁአቸው ሰዎች ከእኔ ይቀርቡዎታልን? ለእኔ አንድ የሹመት ቦታ አጥተው ነው?” ይላቸዋል።
  አባ ጅፋር በተለመደው ስል አነጋገራቸው “የሕዝብ አደራን በተመለከተ ምኒልክ እጄን ይዞ ነው የነገረኝ። ያ ባይሆን ኖሮ እኔ እዚህ አልገኝም ነበር። ምኒልክ እጁን ይዞ “ሹመት የሕዝብ ነው- ሹመት ሺህ ሞት ነው” ብሎናል። ወንድሜ! ወደ ሥልጣን የገቡት እንዴት በነፃነት እንውጣ እያሉ ይጨነቃሉ። ይህንን የማያውቁ ደግሞ እየዘለሉ መግባት ይመኛሉ። እንድታውቅልኝ የምመኘው ከዓለም መንግስታት እኩል ያደረገን ምኒልክ አደራ ከባድ መሆኑን ነው።”
በነገራችን ላይ አጤ ምኒልክ ዘወትር ምሳና ራት ሲበሉ አብረዋቸው ማዕድ የሚቀርቡ (ሁል ጊዜ) ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ፣ ደጃዝማች ወልደሚካኤል ጉዲሳ (የአጤ ኅይለሥላሴ አያት)፣ ፊታውራሪ ቱሉ፣ አፈ ንጉሥ በዳኔና ብላታ አቲከም ነበሩ።
 በአንድ ነጥብ እንለያይ። አጤ ምኒልክ በአንድነት አሰባሳቢነትና ተበታትና የቆየች አገራቸውን ወደ አንድ ኅብረት በማምጣት ረገድ የየአካባቢው መሪዎችን ትብብር በግድን በውድም ተቀዳጅተዋል። ስለዚህም በወለጋ ደጃዝማች  ገብረ እግዚአብሔር፣ በከፋ ደጃዝማች አባጅፋር፣ በወላይታ ካዎ ጦና ጋጋ አካባቢያቸውን ይዘው፣ የውስጥ አስተዳደራቸውን አደራጅተው ሕዝቡን ይመሩ ነበር። ይሁንና በአርሲ በኩል ለጊዜው ሕዝብ የሚቀበለው ጐላ ያለ ተወላጅ በመታጣቱ አጐታቸው ራስ ዳርጌ ተመደቡ። ራስ ዳርጌ ደግሞ እጅግ ሃይማኖተኛ፣ ሕዝቡን በርኅራኄ የሚመለከቱ የአባትነት ተቀባይነት የነበራቸው ስለሆኑ አንዳች ዓይነት ግፍ ለመፈጸም ባሕርያቸው የማይፈቅድላቸው ሰው ነበሩ። እንግዲህ “አጤ ምኒልክ ጡት አስቆረጡ” የሚባለው አነጋገር አርሲ ውስጥ መሆኑ ነው። ማንም እንደሚገምተው ጡት የመቁረጥ የአረመኔ ተግባር የአማራ ባሕርይም የክርስቲያን ሕዝብም ተግባር አይደለም። በአንጻሩ እነ አባ ባሕርይና ሌሎችም ሥፍር ቁጥር የሌላቸው የታሪክ ጸሐፊዎችም ለአካለ መጠን የደረሰ አንድ ኦሮሞ ጐልማሳ ከማግባቱ በፊት ብልት እስከ መስለብ፣ ጡት እስከ መቁረጥ የደረሰ “ጀብድ” መቁጠር መቻል አለበት፥ ይሉናል። ይኸም የትናንት ታሪክ ነው።
ለማንኛውም ተረት እየፈጠሩ ታሪክ፣ ድርሳን እየጻፉ በሕዝብ ዴሞክራሲ ስም ወደ ኋላ እየሄዱ የአገር ጊዜና ዕድሜ ከማባከን ይልቅ ጥላቻን ቀብረን፣ ፍቅርንና አንድነትን አንግበን ሰላም የተጠማችውን አገር ወደ ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ማሸጋገር አይበጅም ኖሮአል? ዓለም እየታዘበን አይደለምን? ምን ይሁን ነው የምንለው?
 በሕብረተሰብ ትክክለኛ አመራር ባሕርይ መንጸባረቅ ያለበት አንድ ክስተት “የነገው ከዛሬው” የተሻለ፣ ብሩሕ፣ አሰባሳቢ፣ እኩልነት የዳበረበት፣ ነፃነት የከበረበት መሆን አለበት። ያለፈው ጓዝና ጉዝጓዝ እንደ ጸሐይ ማብራት የሚገባውን “ነገ”ን በጨለማማ ገጽታው ሊያደበዝዘው አይገባም። ከትናንትና ከዛሬው ይልቅ “በነገው” ተስፋና አለኝታ መጣል ይገባናል። እንዲያም ቢባል ከትናንቱ ብሔራዊ ውርስና ቅርስ -ከትናንቱ የእድገትና የአንድነት መሠረት መካከል- ምኑም ማናምኑም በዛሬና በነገው ቀጣይ ታሪካችን ውስጥ ሥፍራ ሊኖረው አይገባም አይባልም። ታሪካችንም ሆነ የነገው “ጸጋችን” ምንም ዓይነት ተቀባይነት አይኖረውም አይባል። አያቱንና አባቱን የማያውቅ ትውልድ በፈንታው ለነገው ትውልድ አባትነትና አያትነት አይሰማውም። አዎን የምንኰራባቸው አባቶችና እናቶች አያቶችና ቅም አያቶች ያሉንን ያህል አሳፋሪዎች፣ ፈሪዎችና ደካሞች፣ መልቲዎችና ሰነፎች የሆኑ ዜጐችም ነበሩብን። አሉብንም።
እነዚህን ማወቁ-ታሪካችንን ጠንቅቀን መረዳቱ፣ ጀግንነትን ለማደስና ከቶውንም ያንን አዳብረን የዓለም “ጨው” እስከምንባል ድረስ ለመጓዝ ዓለማቀፋዊነት መሠረት ይሆነናል። አፍሪካውያን ብቻ ሳይሆን፣ ጥቁር ዓለምንም ብቻ ሳይሆን- የዓለምን ነፃነት ወዳጅና አክባሪ ሕዝቦች ሁሉ የሚያደንቁት “ምኒልክ” ከዚች አገር የጐን አጥንት የተከፈለ ነው። አንድን አገር ታላቅና ገናና፣ የተከበረችና የታፈረች የሚያደርጉአት ሕዝብዋ ሲሆኑ ለዚያ ሁሉ ታሪካዊ ሥፍራ ተቀዳጅነት የሚያስፈልጉ መሪዎች ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ በመሪነት የተነሡትን ልዩ ልዩ ነገሥታትና የዛሬዎችንም አምላክ ለቅጣት የሰጠንን ጨምሮ- ለኢትዮጵያ አንዳች ክብር ያመጣውን ዋነኛ ሰው ለማግኘት ብዙ ማሰስ አስፈላጊ አይደለም። የዶክተር ሥርግው ሀብለ ሥላሴን “አጤ ምኒልክ” ማንበብ የአሰሳው ፍጻሜ ሊሆን ይችላል። ደራሲው በዚህ መጽሐፍ ከሳባ ንግስት አንስቶ እስከ ቀዳማዊ ኅይለሥላሴ ድረስ ይዘልቃል። ለዚህ አገር ታዋቂነት- ይልቁንም ዳር ድንበርዋንና ነፃነትዋን በማስከበር ረገድ ድንቅ አስተዋጽዖ ያደረጉ፣ በመንፈሳዊና ቁሳዊ ሥልጣኔ ታስደመሙ መሪዎችን ታሪክ ለላንቲካ ያቀርባል። ከሙሉው- ከዚያ ሁሉ ጀግናም ሆነ ሰነፍ መሪ መሐል አንድ ሰው ነጥሮ ይወጣል። በፀረ አንድነት ኅይልነት ጸንቶ ያለው ወያኔ ይንጨርጨር እንጂ- ወያኔና ሻዕቢያ የፈጠሩአቸው ትንንሽ ጩዋሒዎች ይንጨርጨሩ እንጂ ሰውዬው ወጣቱ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን “ጥቁሩ ሰው” የሚለው ነው።
ይቺ አገር በነፃነት የተፀነሱ፣ በነፃነት ያደጉና ድሀም ቢሆኑ በነፃነት የሚራመዱ ዜጐች እናት ናት። ያቺ አገርና ሕዝብዋ ከምን ጊዜውም በላይ ያልተጠናቀቀ ብሔራዊ ዕዳ፣ ለትውልዶች የሚጠቅም ቅርስ ለማቆየት በጥድፊያ ላይ ያሉ ወገኖች እናት ናት። እዚህ መሬት ማሕፀን ውስጥ የተከበሩ ጀግኖች ተኝተዋል። በዚች ዛሬ የታሪክ መጫወቻ በሆነች አገር ማኅፀን ውስጥ ታላላቅ ጀብዱ ፈፅመው ያንቀላፉ፣ በልዩ ልዩ ሙያና በፍልስፍናም ጭምር ልቀው ያላቁን ታላላቅ ነፍሳት የእናት አገራቸው እቅፍ ሞቆአቸው ተኝተዋል። ዓምደ ጽዮን፣ ያሬድ፣ በካፋ፣ ቴዎድሮስ፣ ዮሐንስ፣ ምኒልክ፣ ሀብተ ጊዮርጊስ፣ አሉላ፣ አብዲሳ አጋ፣ በላይ ዘለቀ፣…የተኙባትና እረፍት ላይ ስላሉም መሬቲቱ በጥንቃቄ መረገጥ ያለባት ናት። እነሱን ያህል ለመሥራት ያልቻልን ሰነፎች እንደ መሆናችን ቆምብለን ራሳችንን መርገምም የሚገባን ነን። ይኽ ሁሉ የወያኔ ልዑካን ጫጫታ አያሳፍርም? ይኸ ድምፅ ከየት መጣ? ወሮበሎች አያሰኝንምን? ስድ አደግ ማለት- የእምነት ድህነት ማለት- የሕሊና ባዶነት ማለት- የአቋም ምስኪንነት ማለት ምን ማለት ነው? ይኸው በአደባባይ እየታየ ነው።
(በዚህ ጉዳይ ላይ እመለስበታለሁ) 

የሃገራችን ወጣት በዘመነ ወያኔ “በጨረፍታ”

$
0
0

በናትናኤል ካብቲመር (ኦስሎ ኖርዌይ) የካቲት 4 2006

ሁላችንም እንደምናውቀው ከግዜ ወደ ግዜ አሰቃቂነቱ እየጎላ የመጣው የሃገራችን ወጣት የስደት ጉዳይና ለዚህም ዋነኛ መነሾ ስለሆነው በሃገር ውስጥ የሚኖረው የኢትዮጲያ ወጣት ማህበረሰብ እጅግ የከበደ የኑሮ ሁኔታ በጨረፍታ አንዳንድ ነገር ለማለት አሰብኩ።

(ናትናኤል ካፕትይመር)

(ናትናኤል ካፕትይመር)


ለምንድነው ደሃ የሆንነው? ለምንስ ነው ደሃ ሆነን የምንቀጥለው? ለምንስ ነው ወጣቱ በሃገሩ ሰርቶ የመኖር ተስፋው መንምኖ ለህይወት አስጊ የሆነውን ስደት እየመረጠ ያለው? ተብለው ለሚነሱት ጥያቄዎች በርካታ መልሶች ሊነሱ ይችላሉ ነገር ግን ከሚነሱት መልሶች ሁላችንንም የሚያስማማውና ሚዛን የሚደፋው “የዜጎችን መብት አክብሮ የሚያስከብር እንዲሁም መሰረታዊነት ያለው የሃገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ሚዛናዊና ወጥ የሆን የኢኮኖሚ ስርዓት የሚገነባ ሁነኛ መንግስት ማጣታችን ነው” የሚለው ነው። በርካታ የሃገራችን ምሁራንም ሆነ በሞያው የበቃ ልምድ ያላቸው ግለሰቦች በሃገራቸው የኢኮኖሚ ስርዓት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ሃሳቦችን የሚያመነጩበት መድረክ እንዳይኖር የሚያደርግ ሌት ተቀን የስልጣን ዘመኑን ለማስረዘም ሲል ብቻ የኔ የሚላቸውን ግለሰቦች ከስልጣን ስልጣን እያቀያየረ የሚሾም ጎጠኛ ስርዓት እንደ እርግማን ተጭኖብናል። በዛው ፓርላማ ተብዬ እንኳን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ተቃራኒ ሃሳብ እንዳይስተናገድበት ከላይ እስከታች ለሆነው ላልሆነው እጅ ሲያወጡና ሲያጨበጭቡ በሚውሉ የህዝብ ተወካዮች ነን ባይ አስገራሚ ግለሰቦች ሞልተውታል።

Cry Ethiopia1 የወያኔ መንግስት እንደምንም ተብሎ በተገኘችው ቀዳዳ አንፃራዊ የሆን አማራጭ ሃሳብ ሲቀርብለት የሃሳብ አመንጪውን አካል ዘርና ማንነት በክፉ እየመነዘረ ሰርቶ የሚያሰራና በመጠኑም ቢሆን ሊያስተማምን የሚችል የኢኮኖሚ ስርዓት ተፈጥሮ ወጣቱ ተረጋግቶ ሃገሩ ላይ የሚኖርበትን እድል እያጨለመ የመብት ጥያቄዎችን እያፈነ ወጣቱን ለአስከፊው ስደት እየዳረገው ይገኛል።

ከዚህ ሁሉ እጅግ የሚያመው ደግሞ ለህይወት አስጊ መሆኑና ምንም አይነት የህይወት ዋስትና እንደሌለበት መዓት ግዜ የሚለፈፍለት የአረብ ሃገራት ስደት ያ ሁሉ ስቃይና ህይወትን የሚያሳጣ መከራ በተሰደዱ ዜጎች ላይ በተጨባጭ እየታየ አሁንም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሲጎርፉ ይታያል። ወጣቱም ሃገሩ ላይ ከመኖር ይልቅ ከሞት የማይሻል የስደት አማራጭ ያስደፈረው ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ህዝብን አስተዳድራለሁ ብሎ በስልጣን የተደላደለው የወያኔ መንግስት ነው።

ያደጉ ሃገሮች መንግስታት አብዛኛውን ግዜያቸውን የሚያጠፉት የሃገራቸውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት ፣ ለሰራተኛው የሚከፈለው የደሞዝ ክፍያና ዝቅተኛ የክፍያ እርከን ላለው የኑሮ ሁኔታ የሚያስኖርና በቂ ስለመሆኑ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል አስተማማኝ የሆን የጤና ሽፋን መቅረቡን ለማረጋገጥ ነው። እንደው ዘለን እነሱን እንሁን ለማለት አይቃጣኝም ነገር ግን የመፍትሄ ሁሉ መጀመሪያ ችግሩን መለየት ስለሆነ ችግሩ አገዛዙ የፈጠረብን መላ ቅጡ የጠፋ የኢኮኖሚ ስርዓት መሆኑን ለመጠቆም ነው። ከዚሁ ጋር አያይዤ አንባቢያንን አንድ ነገር እንዲያስተውሉ የምጠይቀው የሃገራችን አነስተኛው የደሞዝ መጠን ስንት መሆኑን ፣ መጠኑን የሚያውቅ ካለም ከወቅቱ የኑሮ ሁኔታጋ እንዴት እንደሚጣጣም እንዲያሰላስሉ ነው።

የህወሃት መንግስት ባለስልጣናት ግን ስር ስለሰደደው የስራ አጥነትና ተያይዞ ስለሚመጣው የህይወት መመሰቃቀል ሲጠየቁ “ወጣቱ ስራ ፈጣሪ መሆን አለበት” የሚል መሰረት አልባ ለንግግር የቀለለ ለመተግበር ግን እጅግ የከበድ ብሂል እየተቀባበሉ ያስተጋባሉ።
ከወራት በፊት አቶ ቴውድሮስ አድሃኖም በአንድ የህክምና ዶክተሮች ምረቃ በዓል ላይ ተገኝተው ለተመራቂዎቹ ሃገራቸውን በፍፁም ጥለው እንዳይሄዱ ሲደሰኩሩ ነበር። እውነታው ሁሉም ግድ ሆኖበት እንጂ ማን ሃገሩን ጥሎ መሄድ ይፈልጋል ነው። በዘመነ ወያኔ እየተንሰራፋ ያለው በትዕቢት የተሞላ የመብት ረገጣ ፣ መረን የለቀቀ የኑሮ ልዩነት ፣ ልጓም ያጣው የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት እንዲሁም የስርአቱን ተጠቃሚዎችን እንጂ የማህበረሰቡን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበው የኢኮኖሚ ስርዓት የሃገራችንን ወጣቶች የወደፊት የኑሮ ተስፋና እድል ምን ያህል ጥያቄ ውስጥ እንዳስገባው ለዚህም የተቀመጠ መሬት የወረደ መፍትሄ እንደሌለ የምናውቀው ገሃድ የወጣ ሃቅ ነው።

ethiopian young የተገኘው ስራ ተሰርቶ እንኳን ኑሮን ለማሸነፍ እንደ አማራጭ የሚታየው የቁጠባ ባህልም ባልተረጋጋውና ጠንካራ መሰረት በሌለው የኢኮኖሚ ስርዓት ምክንያት በሚፈጠረው መላ በሌለው የምንዛሬና የዋጋ ከመጠን ያለፈ ግሽበት ሳቢያ ከጨዋታ ውጪ ሆኗል። ማህበረሰቡ ለአመታት ቆሎ ቆርጥሞ የቆጠበው ገንዘብ ዋጋ እያጣበት ኑሮውን ለእለት ብቻ ካረገው ሰነባብቷል። ወጣቱም ከዛችው ከአነስተኛ ደሞዙ ቆጥቦ የወደፊት ኑሮውን እንዲሁም ቤተሰብ እንዳይመሰርት ይኸው ችግር እንቅፋት ሆኖበታል።

የስርዓቱ አመራሮችና ባለስልጣናትም የደሃውን ህዝብ ገንዘብ በአግባቡ ስራ ላይ ከማዋል ይልቅ ለግል ጥቅማቸው ወደ ውጪ ሃገራት ማሸሸት ስራዬ ብለው ይዘውታል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ነፍሰ ጡር ሚስቶቻቸውን ሳይቀር ምዕራባዊ ሃገራት ላይ እየወሰዱ ማስወለድ መጀመራቸው በግልፅ የሚታይ በሃገር ላይ ተስፋ የማጣት አሳፋሪ ስነ ምግባር የተለመደ ሆኗል። ሃገር እንመራለን እያሉ ነገር ግን ወጣቱ ሃገራዊ ስሜቱ እንዲዳብርና ሃገሩ ላይ ተስፋ እንዲኖረው ምሳሌ የመሆንን ሃላፊነት አሽቀንጥረው በመጣል በሃገር የመኩራትን ስሜት እንደሁዋላቀርነት ሲቆጥሩት ማየት እጅግ ያሳዝናል።
መልካም አስተዳደር ከሚፈጥራቸው መልካም እንድምታዎች አንዱ ይኸው በሃገር ላይ ተስፋ ማሳደርን ከሁሉም ሃገርን ማስቀደምን ነው። መልካም አስተዳደር ሰርቶ ያሰራል እንዲሁም የዜጋው ጉዳት ይቆረቁረዋል። ነገር ግን የሃገራችን ጉዳይ የተገላቢጦሽ ነው “መልካም አስተዳደር መስርተናል” የሚሉት ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ጭምር አካላቸው እንጂ መንፈሳቸው ሃገራቸው ላይ የለም። የወያኔ ስርዓት ለአመታት እያምታታና የተለያዩ ምክንያቶች እየደረደረ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች እንዲሁም በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የሃገራችን ወጣቶች ስደትና ተያያዥ እንግልቶች የተድበሰበሰ ሰበብ ሲሰጥ ቆይቷል። አሁን ግን ወጣቱ የችግሩ ዋና መንስኤ የመንግስት ተብየው ብልሹ አስተዳደርና መሆኑን ተረድቶ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት መታገል አለበት።

አሁንም ቢሆን የወያኔ ስርዓት ካልተወገደ ህዝባችን መቸገሩን ወጣቱም ውድ ሃገሩን እየተወ መሰደዱን አያቋርጥም። የወያኔን ስርአት መወገድ ለችግራችን ሁሉ የመፍትሄ ጅማሮ ቁልፍ እርምጃ ነው።


አስገራሚው የሳውዲው “ኮራጅ ”አባት ምክር እና የኢትዮጵያ ሰርከስ መስራች በሳውዲው ስደት

$
0
0

ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

አስገራሚው የሳውዲው “ኮራጅ ” አባት ምክር

ethiopian athelete

ነገሩ እንዲህ ነው …ከ20 ዓመት በፊት ሳውዲው ወጣት ራሱን ለሁለተኛ ደረጃ ፈተና ከማዘጋጀት ይልቅ በረቀቀ መንገድ ለፈተናው መልስ የሚሆነውን ማጭበርበሪያ የመልስ ወረቀት አዘጋጅቶ ለፈተና ይቀርባል። ፈተናውን በረቀቀ መንገድ አጭበረብሮ ሰርቶታልና ፈተናውን በተገቢ ውጤት አልፎ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለማለፍ በቃ ! ከዚያም በታዋቂው ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ተከታትሎ ይመረቃል። ይህ ሁሉ አልፎ ስራ ይዞ እና ጎጆ ቀልሶ ለወግ ለማዕረግ በቃ ! ከጎጆም አልፎ የሰመረው ህይወቱ የልጆች አባት እስከ መሆን ታደለ !

በያዝነው ሳምንት የድሮው ተማሪና የዛሬው አባወራ ጆሮውን ያልተለመደና የማያውቀው ህመም ያሰቃየው ገባ ። ወደ ሃኪም ቤት ጎራ በማለት ምርመራ ሲያደርግ ለህምሙ ዋና ምክንያት በጀሮው ውስጥ ቁራጭ ወረቀት እንደሆነ የሚያስረዳው አስገራሚው ውጤት ተነገረው … አረጋዊው አባት በወጣትነት እድሜው ተግቶ በማጥናት ለፈተና ቀርቦ ማለፍ ሲገባው አስነዋሪ የማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙን እያስታወሰ አልተደሰተም ፣ አዘነ እንጅ ! ዛሬ ለማጭበርበሩ የተጠቀመበትን ወረቀት በጀሮው እንዴት ሊያስገባው እንደቻለ ማመን ቢያዳግትም ከ20 አመታት በፊት ለኩረጃ እና ለማጭበርብር የተጠቀመበት ወረቀት በቀዶ ጥገና ከጀሮው እንዲወጣ መደረጉ አስገራሚውን ዜና እየተቀባበሉ እየዘገቡ ካሉት የአረብ መገናኛ ብዙሃን ለመረዳት ችያለሁ … !

ከሁሉም የሚያስገርም የሚያስደስተው በሰራው ስራ የሚያፍር እንጅ የማይኮራው አባት ልጆቹንና ወጣቶችን ሲመክር “ልጆቸ ሆይ ፈተና ለማለፍ አታጭበርብሩ! ” ማለቱ ተጠቅሷል ። የትናንቱ ተማሪ የዛሬው አባወራ ሳውዲው አባት በሰራው ስራ ተጸጽቶ ቀሪውን ለመምከር ወደ አደባባይ መውጣቱ ቢያስደስተኝ በዝንቅ መረጃየ ስር መረጃውን ላካፍላችሁ ፈቀድኩ !

ሳውዲውን አባት መልካም ምክር ካነሳሁ አይቀር ሰሞነኛ የማለዳ ወጌ እንግዳ ለማድረግ ስለፈቀድኩት አንድ ከ20 አመት በፊት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባንድ ወቅት አንቱ የተባለ ስም ስለነበረው ብርቱ ወንድም ላጫውታችሁ … አብደላ አህመድ ኦመር ይባላል ። ቀዳሚው የኢትዮጵያን ሰርከስ መስራች ነው ። በስራው ቻይናን ጨምሮ በርካታ ሃገራትን ጎብኝቷል … ብርቱ ስፖርተኛ ከመሆን ባለፈ አንድን ሙያ ልያዝ ብሎ ከተነሳ በፍጥነት ክህሎትን የማዳበር ልዩ ተፈጥሮ ያለው ወንድም እንደሆነ ሰምቻለሁ ! ዛሬ በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ነገር ቢኖር ብዙሃን ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ሰርከስ መስራች ማን እንደሆነና የት እንዳለ የሚያውቁ አይመስለኝም ! … ብርቱው የቀድሞው ስፖርተኛ እና የሰርከሱ መስራች አብደላ ግን ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ትዳር መስርቶ እና ልጆች ወላልዶ በስደት ህይዎትን በመግፋት ላይ ነው ።

አብደላን ሳላውቀው… ላውቀው!

መልከ መልካምና ደልዳላ ተክለ ቁመና ካለው ወንድም ጋር ለአመታት ልጆቸን በማስተምርበት በጅዳ የኢትዮጵያውያን አለም አቀፍ ትምህርት ቤት እንተያያለን ፣ ግን አንተዋወቅም ። በአንድ ወቅት ከአንድ ወዳጀ ጋር የትምህርት መለቀቂያ ሰአት ደርሶ ልጆቻችን ስንጠባበቅ አብደላ ሰላምታ አቅርቦልን አለፈ … አብደላን አንድ ወዳጀ ያውቀው ነበርና እንዲህ አለኝ … ” ለመሆኑ ይህን ሰው ማን እንደሆነ ታውቀዋለህ? ” ሲል ጠየቀኝ አረ አላውቀውም ስል መለስኩለት … ” አየህ ሳውዲ ያልያዘችው ፣ ያላቀፈችው ሃበሻ አይነት የለም፣ አንተ ደግሞ የሩቅ የሩቁን ፣ በበርሃ የምታገኘው ዘፋኝና ግፉዕ ተምር ለቃሚ ግመል ጠባቂ እህቶችን እንጅ እንዲህ በቅርብ ያለውን አየታይህም ” ሲል የመሰለውን አስተያየት ሲሰነዝር እንደ መቀለድ እያለ በፈገግታ ተሞልቶ ነበር እና እኔም እንደመሳቅ አልኩ ! ወዳጀ ወጉን ቀጠለ …

abdela ” አንደላን በትንሹ ከአስራ አምስት አመት በላይ አውቀዋለሁ። ስፖርተኛ ፣ አስማተኛ ፣ የስነ ጽሁፍ ክህሎትን የተካነ በሁሉም የሙያ መስክ የምታገኘው ሰው ነው። ዛሬ እንዲህ አንገቱን ደፍቶ ፣ ሰውነቱ ገዝፎ ስታየው የዋዛ አይምሰልህ (ፈገግ ብሎ) ፣ ከበርካታ አመታት በፊት ታዋቂው የአካል እንቅስቃሴ አሰልጣኝ ግርማ ቸሩ ለአመታት በአሰልጣኝነት ይሰራባቸው ከነበሩ በወቅቱ ታዋቂ ቱጃር በነበሩት የሸህ አልዙማን ስራ ተሰናብቶ ሳውዲን ሲለቅ የተተካው ፈርጣማው ጎልማሳ አብደላ ነበር ። ከዚያም የባለጸጎቹን ቤተሰቦች በአካል እንቅስቃሴ አሰልጣኝነት እና በልዩ ጥበቃ ለአመታት በመስራት ያልዞረበት ሃገር የለም ። በአዕምሮው በሳል ፣ በአካል ፈርጣማ ስፖርተኛ ነው ። አየህ ነቢዩ በሳውዲ ስደት የታቀፈው ግፉአን እህቶችና ወንድሞች ብቻ አይደሉም። እንዲህ አይነት ባለሙያም ሳውዲ ውስጥ ይኖራል። ታሪኩን ለመናገር ፈቃደኛ ከሆነ ለቀረው ትውልድ አስተማሪ ነውና አንድ ቀን አስተዋውቅህና እንዲያጫውትህ አደርጋለሁ! ” አለኝ ። … አብደላን ሊያገናኘኝ ከአንድ አመት በፊት እንዲህ ቃል የገባልኝ ቅን አሳቢ ወንድም ግን ዛሬ ከአካባቢው የለም … ኑሮው ቢከብደው ቤተሰቦቹን ይዞ እና ጥሪቱን አጠረቃቅሞ የአቅሙን ያህል ለመስራት ሃገር ቤት ገብቷል … ካንድም ሁለት ሶስት ጊዜ በፊስ ቡኩ መስመር ብንገናኝም ሃገር ገብቶ የሚይዝ የሚጨብጠው እንዳጣ መረጃ የሚያቀብለኝን ወንድም” አብደላን አገናኘኝ?” ብየ ማስቸገሩ ከብዶኝ መክረሙ እውነት ነው! መቸም ዘንድሮ መንገድና ፊስ ቡክ የማያገናኘው የለም ፣ የኢትዮጵያውን ሰርከስ መስራች በቀጭኑ የስልክ መስመር በሌላ ጉዳይ አግኝቸው ስናወጋ ማንነቱን ሲያጫውተኝ ማመን አልቻልኩም ። ፎቶዎችን ፣ ሰነዶችን በመረጃ ማስረጃነት ሲያጋራኝ ግን የማይታመነውን አጋጣሚ ለማመን ተገደድኩ ! ከወንድም አብደላ ጋር ልንገናኝ ቀጠሮ ይዘናል ። … በቀይ ባህር ዳርቻዎች ከቤተሰቦቻችን ጋር ተገናኝተን ፣ ልጆቻችን ሲጨዋወቱ ነፋሻውን የባህር አየር እየማግን የኢትዮጵያ ሰርከስ መስራቹን የአብደላን ዠንጉርጉር ህይወት እኔ እየጠየቅኩ እሱ በትዝታ እየነጎደ እስኪያወራኝ ቸኩያለሁ …
መልካም ቀን
ነቢዩ ሲራክ / የካቲት 2006 ዓም

የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ መልዕክት ከዝዋይ ማረሚያ ቤት፡ ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ!

$
0
0

በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት

webshet taye
‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡

ይሁንና በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1906 ከታተመው የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102 ላይ ነው፡፡ የዛሬ 108 ዓመት አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!… ይህ ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤ ለምን? ቢሉ ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ‹ጠበቅ ያለ እርምጃ፣ የማያዳግም እርምጃ፣ የማስወገድ እርምጃ፣…› ወዘተ የሞሉ ከሕግ መርሕዎች ሳይሆን ከጥላቻ ፖለቲካ የሚመነጩ ፀያፍ አነጋገሮችን በሕዝብ የመገናኛ ዘዴዎች ሲተላለፉ እየሰማን እየታዘብን ነው፡፡ ቃል በቃል ‹ቀይ ሽብር ይፋፋም› ብሎ ማወጅ የቀራቸው የሕግም የግብረገብም ሚዛን ያልወጣላቸው ቀረርቶች በተለይ በእስር ቤት የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን እየሰበሰቡን ይገኛሉ፡፡

በኢ.ቴ.ቪ. የአብዮታዊ እርምጃ ፕሮግራሞች በቀረቡ ማግስት አሁን በዝርዝር ብለው የብዙ ቤተሰቦችን ስሜት ሊያሸማቅቁ የሚችሉ ሰቆቃና እንግልቶች በአስደማሚ ስልት ተቀናብረው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ እስኪ የተወሰኑትን እንይ፡፡ ማንኛውም ታሳሪ ቤተሰብ በቅርብ ሊጎበኘው በሚችለው እስር ቤት ይታሰር የሚለው ሕግ የተሻረው በእኛ ላይ ነው፡፡ ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት› ማለት ናት፡፡ ቤተሰብ ያን ያህል የበርሃ ጉዞ አቋርጦ የእኛዋ ሳይቤሪያ ሲደርስ በአድካሚና ግብረ-ገብ በጎደለው ፍተሻ መከራውን ማየቱ አንሶ ጆሮ ግንዱ ላይ በቆሙ የቤተሰብ አገናኞች ቤተሰባዊ ገመናውን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ሕፃናት ልጆች ወላጆቻቸው አንድ ላይ ሆነው ናፍቆታቸውን መወጣት አይችሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖሊሶቹ ሲዘናጉልን ልጆቻችንን አቅፈን እንስማለን፡፡ ይህ ከሆነ ቁጣና ዘለፋው ምንም አይደለም፡፡ ግን በሁኔታው ሕፃናቱ ክፉኛ ይበረግጋሉ፣ የእኛ ስጋት ይጋባባቸዋል፤ በዚህም መንፈሳቸው እርብሽብሽ ብሎ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፡፡

ሁኔታው በዚህ አያበቃም፡፡ ምንም እንኳን የመጠየቂያ ሰዓቱ በግልፅ የተቀመጠ ቢሆን ከቤተሰቦቻችን ጋር ገና መነጋገር ስንጀምር ‹‹በቃ… ቶሎ ጨርሱ›› የሚባልባቸው ጊዜዎች ብዙ ናቸው፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው የእስር ቤት ማኅበራዊ ጉዳዮችን ማለትም ለሳሙና፣ ለምግብ ማጣፈጫ፣ ለሻይ ለቡና፣ ለውስጥ አልባሳት፣ ለውኃ ማከሚያ/ውኃ አጋር/ ወዘተ፤ ገንዘብ የሚያስፈልገን ቢሆንም እና እንደሚያስፈልጉ ቢታወቅም ጉዳዩ ለይቶለት የማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ መበቀል ሆኗልና ለአንድ ወር ከአንድ መቶ ብር በላይ መጠቀም እንዳንችል የተከለከልን የመሆኑ አሳፋሪ ሐቅ ነው፡፡ ይህ እየተፈፀመ ያለው ደግሞ ዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለመግለጽ በሚከብድ ሁኔታ ሰብኣዊ ክብራችንን የማዋረድ ሙከራዎች እየተፈፀሙ ነው፡፡

በአገራችን ላይ እኔ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን የጨረስኩት ዝዋይ በመሆኑ ብዙ ወዳጅ ዘመዶቼ በእዚህ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ለአካባቢው ነዋሪዎች በሳምንት እንዲጠይቁን የተፈቀደላቸው አንድ ቀን /ረቡዕ/ ብቻ ሲሆን ‹‹የት ነው የምታውቁት? እንዴት አወቃችሁት? ምንድን ነው የሚያመላልሳችሁ?›› በሚሉትና በሌሎችም ጥያቄዎች ተደናግጠው መምጣቱን እርግፍ አድርገው ትተውታል፡፡

ሀገሩ ሞቃታማ ነውና በዚያ ላይ በእያንዳንዱ ቤት እስከ 150 ሰው ይታሰርበታል፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ እስረኛው የቱንም ያህል ፅዳቱን ለመጠበቅ ቢሞክርም የተባዩ መርመስመስ የእነ ትኋን እንዲህ መራባት፤ ለማሰብ እንኳን ይዘገንናል፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ገላን ሲቆፍሩ ማደር ነው፡፡ ሊናገሩት ይከብዳል፣ አንባቢንም ቅር ያሰኛል፤ ግን ይህ የፊልም ትረካ ሳይሆን በእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ላይ ሆን ተብሎ እየተፈፀመ ያለ ደባ ነው፡፡ […] ግን የባሰ አታምጣ ማለት ነው!

ግን የባሰ ነገር አለ፡፡ አፈር ቅጠል የማይል ምግብ ይቀርብናል፡፡ ‹በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ› ከፍተኛ የውኃ እጥረት /ዝዋይ ሀይቅ አናት ላይ ተቀምጠን/ አለ፡፡ የእስር እስር እንዲሉ ጄኔራል መኮንኖቹን ጨምሮ አብዛኛዎቹ አባሪዎቻቸውና ሌሎች ሌሎች የተወሰንን እስረኞች የምንገኘው በልዩ ቅጣት ጭለማ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ እንደምንም ለመቋቋም ጥረት ማድረግ ይቻል ይሆናል፡፡ አዲሱ ስልት ግን መዘዙ በጣም አደገኛ በመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፣ እያንዳንዱ ሃይማኖት ያለው፣ ፈርሐ እግዚአብሔር ያለው፣ እያንዳንዱ የመሠረታዊ ሰብኣዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበር የሚያሳስበው እያንዳንዱ ሰው የሆነ ሰው ሁሉ ሊያውቀው ይገባል ስንል ድምፃችንን እናሰማለን፤ በሕክምና ንፍገት ወደሞት እየተገፋን ነው፡፡

ከወር በፊት ገደማ ወጣቱ የአንድነት ፓርቲ አባል ናትናኤል መኮንን ለሕክምና በሪፈር ወደ ቃሊቲ ተልኮ የነበረ ቢሆንም፣ የዛኑ ዕለት ሕክምናውን ተነፍጎ ከሌሊቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ እስካሁን በሕመሙ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ የኢብአፓ ሊቀመንበር የነበረው ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር እንደዚሁ ለተጨማሪ ሕክምና ሪፈር ተብሎ ሲጠባበቅ ከቆየ በኋላ ዘዴው ተፈፃሚ ሆነበት እጁን አጣጥፎ ተቀምጧል፡፡ ከሕመሙ ጋር በተያያዘ በአካሉ ላይ አሳሳቢ ሁኔታ እየታየበት ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ገልጬው የነበረው የእኔ የኩላሊት ሕመም አሁን ለመቀመጥም፣ ለመንቀሳቀስ እያወከኝ የሚገኝ ሲሆን፣ እኔን ከቃሊቲ ዝዋይ ለማምጣት የተደረገው የተቀናጀ መረብ ሩብ ያህሉን ለሰብኣዊነት አውለውት ቢሆን ኖሮ እኔም ፋታ፣ እነሱም እርካታ ባገኙ ነበር፡፡ ሕመም ካልታከመ መጨረሻው ሞት ነው፡፡ የሞቱም ሰዎች አሉ!

የጄኔራል መኮንኖቹ አባሪዎች የነበሩት ኮረኔል ተስፋዬ ኃይሉ እና ኢንጂነር ክፍሌ ስንሻው፣ በዶክተር መረራ በሚመራው ኦሕኮ ፓርቲ አባል የነበሩት አሕመድ ነጃሺ፣ በጭለማ ቤት የከረመው ተስፋሀን ጨመዳ፣ የቤንሻንጉሉ አዛውንት ወዘተ ተገቢውን ሕክምና በማጣት ሕይወታቸውን ያጡ የእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ እንዴት ሕክምና ይከለከላል!? ግፍና ጭቆና ተቃውመው ደማቸውን ያፈሰሱና አጥንታቸውን የከሰከሱ ታጋዮችን በሥልጣን ማግስት ከፍርድ በመለስ በየእስር ቤቱ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቸው በሕክምና እጦት ሲረግፉ በእርካታ ማርመምን ከየት ተማሩት!? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ምን ይላል!? ሰው የሆኑ ሰዎች ሁሉ ከቶ ምን ይላሉ!?

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

(ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታተመው ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ የተወሰደ)

አለምነው መኮንን: ኃላፊነት የጎደለው ኃላፊ

$
0
0

alemenew mekonn
ነጋ ዓለማየሁ
alemayehu@hotmail.com
ሰሞኑን የአማራ ክልል ባለሥልጣን ነቻው የተባሉ ሰው በአማራው ሕዝብ ላይ የጀምላ ስድብ ሲሳደቡ ተደምጠዋል። ሰውየውን ስሙንም ሰምቼው አላውቅም። እንዲህ አይነቱን ሰው አንቱ ማለትም የሚገባ አልመሰለኝም። ሀገሪቱን የሚመራው መንግሥት ከየት አምጥቶ እንዳስቀመጠው እራሱ ነው የሚያውቀው።

በሕዝብ ተመርጨ ሥልጣን ይዣለሁ የሚል መንግሥት ባለሥልጣን የመረጠውን ሕዝብ አይደለም አንድን ግለሰብም ቢሆን በመሳደብ ጸያፍ አነጋገር አይናገርም። ይህ ሰው የክልሉ መንግሥት ሁለተኛ ባለሥልጣን ነው ተብሏል። ሥልጣኑን ሕግን ለማስከበር እንደማይጠቀምበት እያረጋገጠ ነው። የፈለገውን እየተናገረ፣ መረጠኝ የሚለውን ሕዝብ እያዋረደና “ለሀጫም” በማለት እየተሳደበ በስልጣኑ ከቆየ መንግሥት የሕግ የበላይነትን እንደማያከብር ብቸኛ ማረጋገጫ ነው። ለሕግ የበላይነት ቆሜአለሁ የሚል ከሆነ ተሳዳቢው ባለሥልጣን ካለበት ሥልጣን እንዲነሳ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ለሕግም ሊያቀርበው ይገባል። ስለእኩልነት እያወሩ አንደኛውን ወገን በማቆሸሽ ያሰቡትን ማምጣት አይቻልም።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በሳንሆዜ ከተማ ለወራት የታቀደው የወያኔ የማጭበርበር ሴራ በሚያሳፍር መልኩ ተጠናቀቀ

$
0
0

እራሱን የአባይ ግድብ ካዉንስል ብሎ የሚጠራው የወያኔ ስርጎ ገቦች እና የባንዳወች ቡድን ለወራት ለወያኔ ቱባ ባለስልጣናት እጅ መንሻ የሚሆን ገንዘብ የማግኛ ዘዴ ላይ መዶለት እንደጀመረ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን ወዲያውኑ ውጥኑን ስላወቅን በመሃከላቸው ሰርጎ በመግባት እያንዳንዶን እቅዳቸውን ስንከታተል ቆይተናል። የሴራው ዋንኛ የባንዳነት ሚና ተጫዋቾች ቀድሞውንም ለወራሪው የኢጣልያ ጦር እንቁላል አቀባይ ከነበሩ ቤተስብ የበቀሉ መሆናቸውን ስንረዳ ደግሞ ልባችን በሃዘን ደምቶል።በጣሊያን ወረራ ዘመን ድልድይና ህንጻ በመሰራቱ ወራሪው ጦር ይግዛን ያላለውን እና ነጻነቱን ያስቀዳመውን ህዝባችን ዛሬ የወያኔ ደናቁርት ካድሬዎች በህዝብ ጠኔ የትላልቅ ህንጻ ባለቤት እና የባለዘመናዊ ተሽከርካሪ ባለቤት መሆናችው ያደባባይ ሚስጥር ሆኖ ሳለ፤ ላለፉት ሃያሶስት አመታት የህዝባችን ኑሮ ከድጡ ወደማጡ ማምራቱ እየታወቀ ‘’ልማታዊ’’ የሚል ጭምብል ለብሰው ለማደናገር መሞከራቸውን ከጅምሩ በቁጭት ተከታትለናል።
ሴራው ወደ ተግባር የሚለወጥበት እለት እንደደረስም በከተማው የምንኖር ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖት፤ቋንቋ እና የብሄር ልዩነት ሳይከፋፍለን የእምነት እዳ የሆነውን እና በቃልኪዳን የወረስነውን ስንደቃችንን በማንገብ በቦታው ተገኝተን ካሃዲዎችን ተቃውመናል። ካአባይ በፈት ስብአዊ መብትን መገደብ ይገደብ ፤ ወያኔ ከፋፋይ ነው ፤ ወያኔ ህዝባዊ ውክልና የለውም፤ አላግባብ የታስሩ የሃይማኖት እና የፖለቲካ እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ፤ ሌሎችንም መፈክሮች በማሰማት እና መዝሙሮችን በመዘመር የተነቃቃ እና የሚያስደንቅ ወኔ የተላበስ ጨዋነታችን አሳይተናል።
በሃገር ወዳዱ ተቃዋሚ ወኔ ልባቸው የራደው የወያኔ ጀሌዎች ባለ አራት ስኮድ የፖሊስ ሃይል እና ከአስር በላይ የግል ጸጥታ ስራተኞች በማስመጣት ግቢውን ለማጠር ቢሞክሩም ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን የተላበሰው ተቃዋሚ ሃገር ወዳድ ለጸጥታ ሰራተኞች ህግ አክባረነቱን በማሳየት መብቱን ግን ሳይነጠቅ ድምጹን አሰምቶል። ተቃወሞውን ከሰአት በሆላ በስምንት ሰአት ግድም የጀመረው ሃገር ወዳድ እስክ ምሽቱ ሁለት ስአት በቦታው የተገኘ ሲሆን ጨለማን ተገን አድርገው ከገቡ ባንዳዎች በተጨማሪ በወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚነት የሚታወቁ ክሃዲወች ፤ ስለ ወያኔ አንጻራዊ ግልጽነት የሌላቸው ወይንም ከወያኔ ህልፈት በፊት ድርሻቸውን መውስድ የሚፈልጉ ባእዳን ተደምረው ከ40-50 ያልበለጡ ሰዎች ተገኝተውበታል።
አዳራሹ ባዶ የመኪና ማቆሚያው ባዶ ሆኖባቸው የተርበተበቱት የወያኔ ጀሌዎች ኑልን ኑልን እያሉ የተማጥኖ ስልክ ጥሪ ሰያደርጉም ተደምጠዋል። ማየት ማመን ነው እንዲሉ በቦታው የተገኙ ሃገር ዎዳዶች ለእማኝነት ያነሶቸው ፎቶግራፎች ይህን እውነታ ፍንትው አድርገው ያሳያሉ። የወያኔው አይጋ ፎረም እና ትግራይ ኦን ላይን በፎቶሾፕ ኪሳራቸውን ለመደበቅ ቢሞክሩም እውነታው ፍጹም ሌላ ነው። እንደሚታወቀው በወያኔ አገዛዝ ጋዜጠኞች አሸባሪ በመባል ዘብጥያ ወርደዋል፤ የሃይማኖት አባቶች ሞት እና ሰደት እጣ ፈንታቸው ሆኖል፤ ገዳማት ተደፍረዋል፤ዜጎቸ በራሳቸው ሃገር ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ሃብት እና ንብረት የማፍራት መብታቸውን ተነፍገዋል፡ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ እናቶቸ እና እህቶቸ የሚያመክን መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዲቀንስ ተደርጉዋል። እስር ቤቶች በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በተለይም በኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ተጨናንቋል፤ የኑሮ ውድነቱ እማይቀመስ ሆኖል፤ በምርጫ የተሸነፈው ወያኔ በጠራራ ጸሃይ ያልታጠቁ ህጻናትን በአደስ አበባ እና በሌሎች ክተሞች በግፍ ፈጅቷል። የእስልምና ጉዳይ አፈላላጊ ወገኖችን በአሸባሪነት ከሱዋል፤ በመሃከለኛው ምስራቅ ወጣት ሴት እህቶቻችን ለዘመናዊ ባርነት በመዳረግ በታሪካችን ታይቶ እማይታወቅ ውርደት እና የሰነልቦና ጠባሳ ጥሎብናል። በጋምቤላ ዜጎችን በማፈናቀል እና የውጪ ጉቦ ሰጭዎች ለም ቦታ እንዲይዙ አድርጎል፤ በኦጋዴን ግድያው አስገድዶ መድፈሩ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቱ እንደቀጠለ ነው፤ አልፎ ተርፎም የሃገራችን ድንበር ለሱዳን በእጅ መንሻነት ተሰጥቷል። ዛሬ ታድያ ምኑ ተቀየረና ነው ይህ ጎጠኛ ቡድን ጋር መተቃቀፍ ያስፈለገው?
በመጨረሻም በዚህ የባንዳወች ሴራ ኢትዮጵያውያን ግራ እንዳይጋቡ እና ሰልፋችውን ከወገኖቻቸው ጋር እነዲያደርጉ የጥሪ ወረቀቶቻችን ላወጣችሁልን ድህረገጾች እና በቦታው ተገኝታችሁ ድምጻችሁን ላሰማችሁ ወገኖቻችን በሙሉ ልባዊ ምስጋናችን እየገለጽን ትግላችን ይቀጥላል ወያኔም ያለጥርጥር በህዝባዊ ትግል ይገረሰሳል እንላለን። ተቃዋሞችን ልማትን ሳይሆን በልማት ስም የሚደረገውን ሙስና እና ኢፍትሃዊ የሆነ የአስተዳደር በደል መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል።
ኢትዮጵያ ለዘላላም ትኑር!!!
የሳንሆዜ ሀገር ወዳዶች ግብረሃይል::

የጤፍ ምርትን ለውጭ ገበያ ! ይቁም ሊባል የሚገባ ፤

$
0
0

አሰግድ ኣረጋ
(ኮለምበስ – ኦሃዮ)

ሰሞኑን ስለጤፍ ምርታችን የባዕዳኑ ብዙሃን መገናኛ አጀብ እያሉን ነው፤ ለዘመናት የተደበቀው የዘሩ ገመና መጋለጡን እየነገሩን ነው፤ ስለያዘው ንጥረ ነገር፣ ስለጤናማነቱ፣ በምዕራቡ ገበያ ስለመፈለጉ፣ ከሁለም በላይ ስለ ውጭ ምንዛሪ ምንጭነቱ። ምግብነቱ ተትረፍርፎ የኢትዮጵያ ህዝብ ማስቀመጫ – ቦታ ያጣ ይመስል፣ የወንዙ ልጆች ጭምር ፣ ጤፍ-የጤፍ ዘር፣ እንጀራ ፣ ብሰኩት፣ ኬክ ሆኖ ምግብ በዝቶበት ለሚቀናጣው ለውጭ ገበያ እንዲነጉድ ከምዕራባውያኑ ጋር አብረን ከበሮ እየደለቅን ነው፤ አደብ ልንገዛ ይገባል።
ባለሙያዎቹ ወቅታዊና በቂ መረጃ እሰካላስጨበጡን ድረስ፣ በዚህ ፁሁፍ አቅራቢ ዕምነት፣ ምርታማነቱ ባለህበት እርገጥ የሆነውንና – በደሃው ገበሬ ማሳ ዛሬም ሆነ የዛሬ 100 ዓመት በሄክታር ከዘጠኝ ኩንታል ያልዘለለውን ፣ ተገቢ የምርምርና ጥናት እገዛ በዙሪያዉ ያላንዣበበውን ይህን ብቸኛ የኢትዮጵያ ልጅ – ጤፍ ፣ አሁን ባለበት ደረጃ ለዉጭ ገበያ በውጭ ምንዛሪ ምንጭነት በሰፊው ለማቅረብ የተያዘው እንቅስቃሴ የምርቱንም ሆነ የህብረተስቡን የኑሮ ዕውነታ ያላገናዝበ ፣ከፈረሱ ኮርቻው ዓይነት ነው። በምርቱ ህልውናና በሸማቹ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ያልተፈለገ ጦርነት ክተት የማለት ያህል ነው። በመንግስት በኩል ቆም ተብሎ እነደገና ሊፈተሽ የሚገባ አብይ ብሔራዊ ጉዳይ ነው።
ጤፋችን በመሰረቱ የማንነታችን መግለጫ፣ ረሃብን ተዋጊ – ብሄራዊ ጦራችን ነው፤ ድንበር አስከባሪያችን ነዉ። “የዕለት እንጀራችንን አታሳጣን” እያልን ለፈጣሪ ቢያንስ በቀን አንዴ፣ ከሆነልንም ሶስቴ የምንጸልይለት የጤናችን ምሰሶ ነው፤ ከሚያመጣው ዶላር ይልቅ የሚያስታግሰው የሚሊዮን ረሃብተኛ ሆድ ሚዛን የደፋ ነው፤ በየሶስትና አራት ዓመቱ አንገት አስደፊና ብሄራዊ ውርደት የሆነውን የልመና እጅ ከመዘርጋት የሚያድን ነው። ለእኛ ለዜጎቿ ምርቱ ከቡናና ከወርቃችንም በላይ ነው፤የሱስ ማርኪያ ወይም ሠርግና በዓል እየተጠበቀ ብቅ የሚል ማጌጫ አይደለም፤ ሳይተርፈን ቡናና ወርቅ ለውጭ ገበያ ብንልክ በሕብረተሰባችን ማህበራዊ ህይወት ውስጥ የሚያመጣው ቀውስ የለም፣የሚበጅ እንጂ። ሳይተርፈን የጤፍ ዘርን በጥሬውም ሆነ በእንጀራ ለውጭ ገበያ መስደድ ግን ሀገራዊ ጥቃት ነው። እኛነታችንን ሳያስከብር ከሀገር እንዳይወጣ፣ ለባዕዳን ሲሳያ እንዳይሆን በያለንበት ዘብ ልንቆምለት ያስፈልጋል፤ የመስኩ ባለሙያዎች ከምርምር ጣቢያችው ወደ ህብረተስቡ መድረክ ወጣ ብለው ስለ ጤፍ
teff3
ልዩ ባህርይ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ሊነግሩንና ጥብቅና ሊቆሙ ይገባል፤ የጤፍ ምርት ያለበትን የምርታማነት ደረጃ ሊተነትኑልን ፣ ለውጭ ምንዛሪ የመዋልን ብሄራዊ ጠቀሜታና ጉዳት ግንዛቤ ሊያስጨብጡን ያሻል፤ብሄራዊ ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት ከመከላከሉ ላይ ኢትዮጵያዊ ሃይላችንን ማሳረፉ ላለውና ለመጪው ትውልድ ባለውለታ ያደርገናል።
በመሰረቱ ፣ የጤፍ ዘርን ህለውና የተፈታተነ የክተት ጥሪ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፤ በደርግ ዘመነ መንግስት የገበሬው የጤፍ ማሳ ምርታማነታቸው ከፍ ባሉ አዝዕርቶች እንዲተካ የሚያደርግና በመንግስት የተደገፈ “ጥናት” ቀርቦ ለአፈጻጸሙ በተወሰኑ የሀገሪቱ ክልሎች ሸብ-ረብ ተብሎ ነበር። ጥናቱ ምርታማዎቹ በቆሎ፣ ስነዴና ድንች ምርታማ ያልሆነውን የጤፍ ዘር ቢተኩ፣ የሀገሪቱን ዓመታዊ የምርት እጥርት ከመሸፈን አለፈው ለመጪው አመት የሚሻገር ምርት ለማከመቸት እንደሚቻል ያስረገጠ ነበር። ተግባራዊነቱ ከአንድ ዓመት አልተሻገረም። በይዘቱ ከዛሬው ጥሪ ቢለይም በገበሬው ኑሮና በጤፍ ህልውና ላይ ጥሎት የነበረው አደጋ ተመሳሳይ ተፅእኖ ነበረው። ውሳኔውንም ሆነ አፈጻፀሙን የተቃወሙ ጥቂት ወገኖች ነበሩ፤ መድረኩም ወቅቱም ባለመፍቀዱ አልተደመጡም። ውሳኔው ከማዕከል ወጥቶ ወደ ገጠሩ – ከገበሬው ማሳ አመራ፤ ገበሬው ጤፉን ወደ ጓዳው መልሶ፣ እንደታዘዘው ማሳውን በምርታማዎቹ በቆሎና ድንች አርመሰመሰው። መሰብሰብ ከሚችለው በላይ ማረስ ልምዱም ባህሉም ያልነበረው ገበሬ አቅሙና ጎተራው የሚችለውን ያህል ሰብስቦ የቀረውን ከማሳው ላይ ተወው፤ ወድሞ ቀረ። በጎተራ ያከማቸው ስንዴም በነቀዝ ተጠቃ፤ በቆሎና ድንች የከተሜውን ገበያ ቢያጥለቀልቀውም ዋጋው በመውደቁ ገበሬውን ከኪሳራ ዳረገው፤በአርሲና ባሌ በሰፊው የታረሰው የመንግስት እርሻ ምርትም ለተመሳሳይ አደጋ ተጋለጠ፤ አቅምን ያላገናዘበ ውሳኔ፣ በበቂ ጊዜ፣ ገንዘብ ባለሙያ ያልተደገፈ ምርትና ምርታማነትን የማሳደጉ ዘመቻ አባዜ፣ ለሌላ አስከፊ ችግር ገበሬውንም፣ ሸማቹንም መንግስትንም ጭምር አጋልጦ አለፈ።
ከስህተት ያለመማር ባህል የተፀናወታቸው ገዥዎቻችን በመጪው የዕቅድ አመትም መሰረታዊ ችግሩን ባልፈታና ስሙን ብቻ በቀየረ እቅድ እንዲቀጥል ተቃጥቶ ነበር፤ በዚህ ጊዜ ጥቂት ቆራጥ የሆኑ የጤፍ ምርት ተመራማሪዎች ድምጸ-አልባ የነበረውን የገበሬውን ድምጽ ከፍ አርገው በማስተጋባታቸውና በቁጥር ከሁለት ያልበለጡ የጊዜው ባለስልጣናትን ግንዛቤ ሊያገኙ በመቻላቸው፣ ከገበሬው ጉያ ተደብቆ የሰነበተው የጤፍ ዘር በግላጭ ወጥቶ ከማሳው ሊመለስ በቃ። ዛሬ ኢትዮጵያናችን እነዚያን የመሰሉ ለገንዘብና ለግል ስልጣን ያላደሩ ተመራማሪዎቿንና የመንግስት ሃላፊዎቿን በባትሪ የምትፈልግበት ወቅት ላይ ነች። አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የዚህ ፁሁፍ አቅራቢ ለማረጋገጥ መረጃ ባይኖረውም፣ በዚያን ወቅት በጤፍ ዘርና ምርታማነት ጥናትና ምርምር ዙሪያ ከተሰለፉት ሳይንቲስቶቻችን መሀከል እነ ዶ/ር ሰይፉ ከተማና ባልደረቦቻቸው ለአብነት የሚጠቀሱ የሀገሪቱ ባለውለታ ናቸው። ዶ/ር ሰይፉ የጤፍ ዘር ለዘመናት አላነዳች የቴክኖሎጂና የመንግስት ድጋፍ የመቆየት ሚስጥርን አበክሮ የሚገልጽ የምርምር ስራ (Tef ፤ Eragrostis tef , 1993) ለተነባቢነት አብቅተዋል፤ በዚያ ጥናታዊ ስራቸው ገበሬዉን ጭምር እማኝ በማድረግ እንደነገሩን፣ የጤፍ ዘር ከማንኛውም ምርት በተሻለ ድርቅንም ሆነ ከባድ ዝናብን የመቋቋም ልዩ ባህርይ የገበሬውን ቀልብ የሳበ ነው።
ጤፍ በምግብነቱ እንዲህ እንደዛሬው የሀብታሙ አልነበረም፤ ደሀው ችግር ሲጋፈጠው እየደበቀ፣ እየቆጠበ የሚበላው ሳር ነበረ። የዘሩን ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ደሀውም ሀብታሙም ገበሬ በእጅጉ ከተረዱት በሗላ ከትውልድ ትውልድ እየተቀባበሉት እዚህ
ለመድረስ በቅቷል። በተዘራበት ማሳ እንደ ስንዴና በቆሎ በዝናም እጥረትም ሆነ ብዛት ወድሞ አይቀርም፤ ገበሬውን አመድ አፋሽ አያደርግም፤ የጠበቀውን ያህል ባያገኝም ለዘር ያህል አያሳጣውም። በጎተራ ሲከማች እንደተቀሩት ምርቶች በነቀዝ አይደፈርም፣ ጭዱ የእንስሳቱ ተወዳጅ ምግብ፣ የጎጆው ግድግዳ ማገር መመረጊያ ነው። በገቢ ምንጭነቱም አንጀት አራሽ ነው። የጤፍ ዘር የሸማቹም ልዩ ወዳጅ ነው፤ በረከት ያለው እህል ነው፤ ግማሽ ኩንታል ጤፍ ከወፍጮ ቤት ወስዶ ሙሉ ኩንታል ዱቄት ተሸክሞ የሚመለስበት ነው፤ ለዚህም ነው ሸማቹ የዋጋ ውድነቱን አጠብቆ የሚያማርር። በምግብነቱም ቢሆን ተወዳጅና ሁለገብ ነው፤ ችግር ከመጣ አለማባያ፣ አለዚያም በወተት ተምጎ ፣ በሚጥምጣ ተረምዶ ይበላል። ማባያዎቹ ሳይደመሩ የጤፍ ዘር በራሱ አይነታቸውና መጠናቸው የተለያዩ በርካታ ለሰውነታችን ጤና ግንባታ የሚረዱ ንጥረነገሮችን(ፕሮቲን፣ አይረን፣ ካልስየም፤ ፋይበር እና የተለያዩ ቫይታሚኖችን) አዝሎ የሚገኝ ነው። ዜናው ከምዕራቡ ዓለም የወሬ ማሰራጫ ጣቢያ ካልመጣ ጆሯችን አልሰማ ብሎ እንጂ፣ አዲስ አይደለም። የደብረዘይቱ የግብርና ምርምር ሳይንቲስቶቻችን የዛሬ 25 ዓመት አስረግጠው ነግረውን ነበር። ኢትዮጵያውያኑ ተመራማሪዎች ይህን የጤፍ ዘር ባላቸው ውስን አቅም ምርታማ ለማደረግ ጥረታቸው የመቀጠሉ ተቀዳሚ ምክንያት ለምዕራባውያን የጤፍ ብስኩትና ትኩስ እንጀራ ለመሸጥ አልነበረም፤ አይደለመም። ዋና ግባቸው በሚሊዮን የሚቆጠረው የሀገሪቱ ጤፍ አምራች ገበሬ ለዘመናት ከያዘው አድካሚ አሰራር ተላቆና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ሆኖ ምርቱን በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለበላተኛው እንዲያቀርብ ማስቻል ነው። በሀገር ውስጥ ምርቱን የማስተዋወቅ ስራ ሳይሆን፣ ምርቱ የያዘው ንጥረ-ነገር ምን ያህል ለጤናችን አስፈላጊ እንደሆነ አግባብ በላቸው ተቋማት በኩል ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መስጠት ነው።
በጥናታዊ ጹሁፋቸው፣ የጤፍ ተመራማሪው ዶ/ር ሰይፉ እንደሚነግሩን፣ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በጤፍ ምርቱ ላይ ያተኮረ ሳይንሳዊ ምርምር የተጀመረው እንደ አውሮጳ አቆጣጠር በ 1950 ዎቹ መጨረሻ ግድም ሲሆን፣ የመጀማሪያው ኢትዮጵያዊው የጤፍ ሳይንቲስት ዶ/ር መላክ-ሃይለ መንገሻ ይባላሉ። እኒህ ሙሁር ስለጤፍ ዘር ባህሪ ጥናትና ምርምር ከማድረግ ጀምሮ በግብርና ኮሌጆችና የእርሻ ምርምር ጣቢያዎች ተገቢውን ትኩረት አግኝቶ ምርምሩ እንዲቀጥል በማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል። በመቀጠለም ሌላው ሳይንቲስት ዶ/ር ታረቀ በርሄ የተሰኙ በጤፍ ምርት ምርምር ሂደት ግኝቱ እጅግ አስቸጋሪ የሆነውንና በምርታማነቱ ልዩ ሚና የሚጫወተውን የጤፍ ባህርይ (The Pollination Habit of Tef) ግኝት በተጨባጭ በማሳየት በሙያ አጋሮቻቸው አድናቆትን ያተረፉ የመስኩ ባልደረባ ናቸው። በእነዚህ ግኝቶች ላይ በመንተራሰ ዶ/ር ሰይፉና ባልደረቦቻቸው በደብረዘይት የግብርና ምርምር ማዕከል በጀመሩት የናሙና እርሻ፣ በሄክታር 8 እና 9 ኩንታል ላይ የቆመው የጤፍ ምርት ከ 20 ኩንታል በላይ ለማምረት የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ሊያስመዘግቡ በቅተዋል። ይህ ድንቅና ተስፋ ፈንጣቂ ውጤት፣ ዛሬ ስለደረሰበት ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የዚህ ፁሁፍ አቅራቢ ምቹ ሁኔታ ባይኖረውም ፣ ከተጨባጩ የሀገሪቱ ሁኔታ መገንዘብ እንደሚቻለው የምርታማንቱ ማነቆ አሁንም ድረስ እነዳልተፈታ ነው፤ በአብዛኛው ገበሬ ማሳ ላይ የጤፍ ምርትና ምርታማነት ባለህበት እርገጥ ላይ ነው። በየክልሉ በደብቅና በገሀድ የረሀብ አለንጋ እየተቀጣ ያለው ህብረተሰብም በእማኝነቱ የሚያወለዳ አይደለም።
በሌላ በኩል – የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት – የጤፍ ምርት ከሀገር ውጭም በአሜሪካ፣በካናዳ፣ በአውሮጳ፣ በአውስትራሊያና በአፍሪካም ጭምር ለማብቀል ጥረቱ ተይዟል፤ በኢትዮጵያ አየርና አፈር የሚበቅለውን የጤፍ ዘር ሊተካ ባይችልም፣ ለጤፍ ምርታችን የሚበጁ ሁለት እገዛዎችን ለማድረግ ዕደሉ የሰፋ ነው። የመጀመሪያው፣ የጤፍን ምርታማነት ለማሳደግ ከበቃ፣ ለግብርናቸው የተጠቀሙበትን ቴክኖሎጂ በጥንቃቄ አጢኖ ለሀገራችን ጤፍ ምርታማነት በአጋዥነት ለማሰለፍ መቻሉ ነው። ሁለተኛው፣ የሀገሪቱን የምግብ ፍላጎት ሳያሟላ፣ ባልተመጣጠነ ዋጋ ከደሃው ገበሬ ተዘርፎና ከበላተኛው አፍ ተነጠቆ ወደ ውጭ በቀላሉ እየወጣ ያለውን ጤፍ ጊዚያዊ እፎይታ ለማሰጠት አቅሙ መኖሩ ነው። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጥቂት ባለጊዜ ባለስልጣናትንና ነጋዴዎችን ኪስ ከመሙላት ባለፈ ብሔራዊ ፋይዳ እነደሌለው በይፋ የሚነገረለት ይህ የሀገሪቱ ጤፍ፣ ለውጭ ገበያ እንዳይውል ጥሪ የመደረጉ አንዱም መልዕክት የሀገር ቤቱን ጤፍ ለሃገር ፤የውጭውን ለውጭ የሚል ነው። በዋና ዋና ያሜሪካ ከተሞች ነዋሪ የሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ወዳጆቻቸው ከሀገር ቤት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጭምር ተጭኖ የሚመጣውን ትኩስ እንጀራና ጥሬ ጤፍ ሸማቹ እንዳይገዛ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው፤ በተሳታፊ ነጋዼዎችም ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ግፊት እያደረጉ ነው፤ ምላሹ ግን አጥጋቢ ሆኖ አይታይም። ምዕራባውያኑ ጤፍን እንደ ጣሊያኑ ፒሳ እስከሚለምዱት ድረስ እኛ በውጭው አለም ነዋሪ የሆንን ዜጎቿ የፈረጠመ ክንድ አለን፤ ከደሀው አፍ ተነጥቆ ማዕዳችንን እያጣበበ ያለውን የኢትዮጵያ እንጀራ – የጤፍ ዘር – ለማስቆም ትግሉን መቀላቀል ይጠበቅብናል፤ የይቁም ጥሪውም ቅዱስ ጥሪ በመሆኑ፤ ከጎናቸው ልንቆም ያስፈልጋል።
ጤናማውን ኦርጋኒክ ጤፍ ወደ ባዕድ ሃገር ሰደን በኬሚካል ያበደውንና ለበሽታ መራቢያነት ምቹ የሆነውን የባዕድ እህል ወደ ሀገር ከማስገባት ፣ ወይም የጤፍን ኦርጋኒካዊ ይዘት ለሚያቃውሱ ባዕዳን ነጋዴዎችና ሳይንቲስቶቻቸው አጋልጠን ከመስጠት፤ ልንድን የምንችለው፣ ዜጎቿ በአንድ ሆነን ለምርቱ ደህንነትና ምርታማነት ዘብ ስንቆም ብቻ ነው።ሀገሪቱ ወጣት የጤፍ ሳይንቲስቶች በጥራትና በብዛት እንድታፈራ ፣ የምርምርና ጥናት ዘርፉ ሀገራዊና አለም ዓቀፋዊ ትኩረት እንዲያገኝና፤ በቂ የመዋዕለ ነዋይ ፈሰስ ለዘርፉ እንዲደረግለት የሚደረጉ ተከታታይ ጥረቶች ለጤፍ ምርታችን አይነተኛ ለውጥ መምጣት መሠረት የሚጥሉ ብቻ ሳይሆኑ፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር አንገቷን ቀና አድርጋ እንድትሄድ የሚያስቸላት ነው። ይህን ለመሆን ካበቃን፣ ከክረሰቶስ ልደት በፊት ጀምሮ የገበሬው ችግር ደራሽና አለኝታ ሆኖ እዛሬ ድረስ እስተንፋሱ የቆየው የጤፍ ዘራችን፣ ምርታማነቱ ከፍ ብሎና ከጥቂቶች ማዕድ ወጥቶ በተመጣጣኝ ዋጋ በሚሊዮን ህዘብ ማዕድ በመደበኛም ሆነ በአማራጭ ምግብነት የምናስተናግድበት ይሆናል። ከተጠነከረም፣ ሀገሪቱ ለጤፍ ምርት በሚውል መጠነ-ሰፊ መሬት የታደለች በመሆኗ፤ ዛሬ ከኢትዮጵያ አይውጣ እያልን የምንጮህለት ጤፍ – ያኔ ለውጭ ገበያ ጭምር በመዋል- ቡናና ወርቃችን ተደምረው ከሚያገቡት የውጭ ምንዛሪ በተሻለ ገቢ አስገኚና የሀገሪቱ የልማት ገንቢ ሆኖ እንደሚቀጠል ተስፋችን በእጅጉ የፀና ነው።

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>