Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ፖለቲካና ግለሰብ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም)

$
0
0

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

Prof. Mesfin

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

ለእኔ ፖሊቲካና የግለሰብ ጠባይ እንደውሃና ዘይት የማይደባለቁ ነገሮች ይመስሉኛል፤ አጼ ምኒልክ ‹‹አመልህን በጉያህ›› ያሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፤ ዘይትና ውሀ በባሕርያቸው የሚለዩትን ያህል ፖሊቲካና ግለሰብም የባሕርይ ልዩነት አላቸው ማለት ነው፤ የወያኔ መሪዎች ምንም ነገር የማይሰምርላቸው፣ ከመጀመሪያውኑ እነዚህን ሁለት የማይደባለቁ ባሕርዮች አደባልቀው በመንሣታቸው ነው፤ ፖሊቲካ ለማኅበረሰቡ መቆርቆር ነው፤ ለሕዝቡ መቆርቆር ነው፤ ለአገር መቆርቆር ነው፤ የፖሊቲካ መነሻም ይኸው መሆን አለበት፤ ዓላማውም የማኅበረሰቡ፣ የሕዝቡ ልማት እንጂ ጥፋት አይደለም፤ የነበረውንና ያለውን ማጥፋት የፖሊቲካ ዓላማ ሊሆን አይችልም።

የደርግ መንደር ምሥረታ የሕዝብ ዓላማ ነበረው፤ የዓላማው መሣሪያ ግን የሕዝብ ሳይሆን ወታደራዊ ጉልበት ነበር፤ በዚህም ምክንያት የሕዝብ ዓላማ ያለው ሥራ የሕዝብን ህልውና በሚፈታተን የጉልበት መንገድ መከተሉ ዓላማው እንዳይሳካ፣ ሕዝብና አገዛዙ ባላንጣዎች ሆኑ፤ ጥሩው ዓላማ በከሸፈ ጉልበተኛነት ሳይሳካ ቀረ፤ በመንደር ምሥረታው ዓላማ ደርግ ክፋት ወይም ቂም ቋጥሮ አልተነሣም፤ ስሕተቱ ከውትድርና ባሕርይ የመጣ ይመስለኛል፤

ማጥፋት ዓላማ ሲሆንና ጉልበት የማጥፋት መሣሪያ ሲሆን ፍጹም የተለየ ነው፤ማጥፋት የሚመጣው ከግል ጠብና ከግል ቂም ነው፤ የራሱን ወይም የአባቱን፣ ወይም የእናቱን ቂም በልቡ ቋጥሮ ፖሊቲካ ውስጥ የሚገባ ሰው ለጥፋት የተዘጋጀ ነው፤ ለጥፋት የተዘጋጀ ሰው ፖሊቲካ ውስጥ ሲገባ እሳት አደጋ መኪና ላይ ቆሞ ቤት እንደሚያቃጥል ሰው ነው፤ አታላይ ነው፤ ዓላማውንም የዓላማውንም መሣሪያ አያውቅም፤ የሚንቀሳቀሰው በጥላቻና በቂም ነው፤ ወይ የሕጻን ልጅ ወይም የተስፋ-ቢስ ደደብ ጠባይ ነው፤ እንዲህ ያለ ሰው ፖሊቲካ ውስጥ የሚገባውም በዚሁ በደደብነቱ ምክንያት ነው፤ የደደቡ ፖሊቲከኛ ሥራ የማያስወቅሰው ፖሊቲከኛውን ብቻ አይደለም፤ በዚያ ፖሊቲከኛ የሚመራው ሰው ሁሉ አብሮ የሚወቀስ ነው፤ እንዲያውም በፖሊቲከኛው እውቀትና ችሎታ ማጣት የተነሣ የሚደርሰው ስቃዩና መከራው፣ ችግሩና አበሳው በዚህ ዓይነቱ ፖሊቲከኛ ላይ አይደርስም፤ ሰቃዩንና መከራውን፣ ችጋሩንና አበሳውን የሚጋፈጠው በዚህ ዓይነቱ ፖሊቲከኛ የሚመራው ሕዝብ ነው፤ ሕዝብ መሪውን በትክክል መምረጥ ያለበትም ለዚህ ነው፤ ተንጋሎ የተፋ ለራሱ ከፋ የሚባለው ይደርሳል።

ዛሬ እያጎረሰ ምረጠኝ የሚለው ነገ ቆዳህን ልግፈፍ ይላል፤ እንደምንሰማው ወደቦሌ አካባቢ ‹መቀሌ› የሚባል የሰማይ-ጠቀስ ፎቆች መንደር አለ ይባላል፤ የዚህ መንደር ባለቤቶች የወያኔ ባለሥልጣኖች ለመጦሪያቸው የሠሩአቸው ናቸው ይባላል! በአንጻሩ እኔ የማውቀው አንድ ወያኔ አለ፤ በውጊያ ላይ በደረሰበት ጉዳት ይመስለኛል አንድ ዓይኑን ክፉኛ የታመመ ነው፤ ስለሚሸፍነው የጉዳቱን መጠን ባላውቅም ጉዳቱ ይሰማኛል፤ ሚስትና ሁለት ልጆች አሉት፤ ሚስቱ ጠዋት በጀርባዋ ከባድ ነገር አዝላ ልጆቿን ወደተማሪ ቤት ታደርሳለች፤ እንደምገምተው አንድ ቦታ ገበያ ዘርግታ የምትሸጠውን ትሸጣለች፤ ወደማታም እንደጠዋቱ ተጭና ወደቤትዋ ከልጆችዋ ጋር ትመለሳለች፤ የዚህ አንድ ጉዳተኛ ወያኔ ቤተሰብና የባለሰማይ-ጠቀስ ሕንጻ ባለቤቶች የሆኑት ወያኔዎች ኑሮ የሰማይና የመሬት ያህል የተራራቀ ነው፤ ለአንድ ዓላማ አብረው የተነሡ ሰዎች በሃያ ዓመታት ውስጥ ይህንን ያህል መራራቃቸው በጣም ያሳዝናል ብሎ ማለፉ አይበቃም፤ ደሀው ወያኔ ሕመሙንና ስቃዩን የምገነዘብበት መንገድ ባይኖረኝም አንድ ዓይኑን ማጣቱ ብቻ ጉዳቱን ያሳየኛል፤ እንግዲህ ባለሰማይ-ጠቀስ ወያኔዎችና ይህ ደሀ ወያኔ በጦርነት ላይ ያደረጉት አስተዋጽኦ በጉዳታቸው ቢመዘን የዚህ ደሀ ወያኔ እንደሚበልጥ አልጠራጠርም፤ ቢያንስ እንደአንዳንድ መሪዎቹ አልሸሸም፤ ታዲያ በምን ተበላልጠው እነሱ እዚያ ላይ እሱ እዚያ ታች ሆኑ? ይህንን አሳዛኝና አገርንና ሕዝብን የሚጎዳ ሁነት የሚያመጣው እሳት አደጋ መኪና ላይ ቆሞ ቤት እንደሚያቃጥለው ሰው ያሉ ፖሊቲከኞች-ነን-ባዮች የተዛባ ሚዛን ነው፤ በዚህ የተዛባ ሚዛን በየጦር ሜዳው አሞራ የበላቸው የታደሉ ናቸው፤ ተስፋቸው ትርጉም አጥቶ ሳያዩ፣ ውርደት ሳይሰማቸው፣ ችግርንና ግፍን ሳይቀምሱ ቀርተዋል፤ ለነገሩ ነው አንጂ እንኳን ወያኔ በሥልጣን ምኞት ከወገኑ ጋር የተዋጋውና ከኢጣልያ ወራሪ ጦር ጋርም የተዋጉት አርበኞችም ተመሳሳይ ዕድል ገጥሟቸው ነበር፤ ዛሬ ኢትዮጵያን ለክፉ ነገር የዳረጋት የእነዚህ ሰዎች ጡር ይመስለኛል።

የፖሊቲካ ተግባሮቻቸውን ከግል ጠባዮቻቸው እየለዩ የሚኖሩ ፖሊቲከኞች በአንዳንድ አገር አሉ ለማለት ይቻላል፤ ከአውሮፓ ስዊድንና ኖርዌይ፣ ስዊትዘርላንድ፣ ከእስያ ዛሬን እንጃ እንጂ በነኔህሩ ዘመን ህንድ የሚጠቀስ ነበር፤ በአብዛኞቹ አገሮች ግን ፖሊቲከኞቹ እንደየደረጃቸው ለሀምሳ፣ ለሠላሳ፣ ለሀያ፣ ለአሥር ሰዎች የሚበቃ የተሟላ ቤት ውስጥ አምስት መቶ ሰዎችን የሚያስተዳድር ደመወዝ እያገኙ የሚኖሩ ሲሆኑ ምግባቸው ግን አብዛኛውን ጊዜ የአንድ ሰው ይመስለኛል፤ የዚህ ትርጉሙ ምንድን ነው? ለፖሊቲከኞቹ መቀማጠል በላባቸው የሚከፍሉት ደሀዎች ናቸው፤ ከተፎካካሪዎቻቸው ተንኮል የሚጠብቋቸው ደሀዎች ወታደሮች ናቸው፤ ምርጫ ሲደርስ በነቂስ ወጥተው ፖሊቲከኞቹን የሚመርጧቸው ጦማቸውን የሚያድሩት ደሀዎች ናቸው፤ እነዚህም ጊዜያዊና ትንሽ የግል ጥቅምን ከዘላቂው የአገርና የሕዝብ ጥቅም መለየት ያልቻሉ የሕዝብ ክፍሎች ከተበላሹት ግለኛ ፖሊቲከኞች የማይለዩ ናቸው።

ወደፍሬ ነገሩ ልምጣና፤- በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ፖሊቲከኞች የሚወጡትና የሚወርዱት ለየትኛው ዓላማ ነው?

የበትረ መንግሥቱን ሥልጣን ከወያኔ ፈልቅቆ ለማውጣትና ለመያዝ?

በምክር ቤት ገብቶ የወያኔ አጫፋሪ በመሆን ደህና ደመወዝና ነጻ ቤት ለማግኘት?

ከውስጥ ሆኖ ወያኔን ለማጋለጥ?

የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖሊቲካ ቡድኖችን ሲደግፍ የፖሊቲካ ቡድኖቹን ዓላማዎች አጣርቶ በማወቅ መሆን አለበት፤ አለዚያ በሎሌነት እየኖሩ ጌታ መለወጥ ነው።


የግል ሚዲያው “በጸረ ሽብር ህግ” ሊበላ ይሆን? (አቶ ግርማ ሰይፉ)

$
0
0

አቶ ግርማ ሰይፉ

Girma-Seifu2

(አቶ ግርማ ሰይፉ

የመንግሰትን ቀጣይ እርምጃ የሚያሳዩ ተከታታይነት ያላቸው በግል ሚዲያዎች ላይ የሚደረጉ ዘመቻው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መልክቶች እየታዩ ነው። በቀጣይ ለሚቀርበው ዶክመንተሪ ተጋባዥ አንግዳ ሆኜ ለቆርጦ ቀጥሉ ኢቲቪ ቃለ ምልልስ እንደሰጣቸው ጥያቄዎቹ ደረስውኝ ተመልክቸዋለሁ። የጥያቄዎቹን ዝርዝር እንተወው እና ዓላማው ግን ባለፈው ከቀረበው ዘጋቢ ፊልም የተለየ ነገር የለውም። በነገራችን ላይ ባለፈው የቀረበውም ዘጋቢ ፊልም ላይ እንድሳተፍ ተጠይቄ እንደማይሆን ገልጨላቸው ነበር። ውሳኔዬ ትክክል መሆኑን ዘጋቢ ፊልሙን ካየሁ በኋላ ገብቶኛል።

የዘጋቢ ፊልሞቹ ዋና ግብ “የኢህአዴግን አብዮታዊ ዲሞክራሲን መንገድ አምነው ያልገበሩ የግል የሚዲያ ተቋማትን ለማጥፋት ጥርጊያ መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡” የግል ሚዲያውን ማጥፊያ መንገዶች ሁሉን አቀፍ ናቸው። በዋነኝነት ኤኮኖሚያዊ የሚባለው ሲሆን ይህም በምንም ሁኔታ ከመንግስት ወይም “ከልማታዊ ባለሀብቶች” ገንዘብ እንዳያገኙ ማድረግ ሲሆን ከአንባቢ የሚሰበሰቡትንም ገንዝብ ለእዕትመቱ ቀጣይነት እንዳይመች የሚቻለውን ቀዳዳ ሁሉ መዝጋት፤ ይህ የማይሳካ ቢሆን በአሰተዳደራዊ ዘርፍ እንዲወሰድ የተቀመጠው ፍርድ ቤትን በመጠቀም ጋዜጠኞችን ማስር ነው። ይህ በመጨረሻ የተቀመጠው አማራጭ የውጭ ሀይሎች የማይቀበሉትም ቢሆን መጠቀም ሲያስፈልግ መጠቀም ግድ ነው። ይህ ሃሳብ የኔ የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ አይደለም። አቶ መለስ ዜናው አዘጋጅተውት ኢህአዴግ የሚባለው ፓርቲ እንደ መርዕ ተቀብሎት አሁን በአቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የገዢነት ዘመንም የሚቀጥል የሟቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር የራዕይ ክፍል ነው። ይህን ራዕይ አላስቀጥልም ሚዲያ በዓለም ተቀባይነት ባለው መስፈርት አራተኛ መንግሰት እንዲሆን አደርጋለሁ ይሉናል ብለን ብንጠብቅም ሊሆን የቻለ ነገር የለም።

ለዚህም ማሳያው ባለፈው ሳምንት የቀረበው ዘጋቢ ፊልም ነው፡፡ ክሱም በቀጣይ ዝም ብሎ ተራ ክስ እንደማይሆን ምልክቶች መጥቀስ ይቻላል። ዜጎችን አሸባሪ በማለት ክስ በመመስረት ታዋቂ የሆኑት ግለሰብ በዋና ተዋናኝነት የቀረቡበት ሲሆን ይህ ዘጋቢ ፊልምም ለቀጣይ ለሚያዘጋጁት ክስ መንደርደሪያ ሊሆናቸው ይችላል። ስለዚህ በሽብርተኝነት የሚከሰሱ ሚዲያዎችና አምደኞች እንደሚኖሩ መጠበቅ ይኖርብናል። እዚህ አካባቢ እስክንድር፣ ርዕዮት፣ ውብሸት ሰለባ የሆኑለት የግል ሚዲያ ተሳትፎና ሃሳብን የመግልፅ ነፃነት መሆኑ መዘንጋት የለበትም። ሀቃቢ ህጉ ከሰጡት አሰተያየት ሳይሆን ስንት ሰው ከሰው ወህኒ የወረወሩበትን አዋጅ ሰም በትክክል መጥራት አለመቻላቸው ነው። ለነገሩ “የሽብር ህጉ” እያሉ ሲጠሩት ትክክለኛ የተፃፈ ስሙ ባይሆንም እውነተኛ ምግባሩን ግን መግለፁን አልዘነጋሁትም፡፡ በተደጋጋሚ “የሽብር ህጉ” እያሉ ሲጠሩት አዘጋጁ ጋዜጠኛም አውቆ መሆን ይኖርበታል ይህን ክፍል ማስተካከል ያልቻለው፡፡ የውስጥ አርበኝነት ይሆን ብለን ታዝበን ከማለፍ አንባቢም ልብ ካላለው ለማስታወስ ብዬ ነው። ይህ “የሽብር” ያሉትን ህግ መቼ እንደምንገላገለው ባናውቅም ግብሩ ግን አሸባሪነት መሆኑ ተገልፆልናል።

የብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ ቀደም ሲልም ከበላያቸው ለስሙ ኃለፊ የነበረ ቢሆንም በመሰሪያ ቤታቸው አድርጊ ፈጣሪ እንደ ነበሩ ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡ እርሳቸው ከሰጡት ውስጥ ድንቅ የሆነብኝ ግን 45 ሺ ታትሞ ሁለትና ሶሰት ሺ ነው የሚሸጠው የሚለው ክፍል ነው፡፡ ከዚህ ቀጣይ ያለው ነገር ግልፅ ነው፡፡ ክቡርነታቸው እንደነገሩን እነዚህ ጋዜጦች የሚደጉማቸው አንድ ኃይል አለ የሚል ነው፡፡ ይህ ሀይል ደግሞ ሀገሪቱን ለማተራመስ የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ አምደኛ ሆኜ እንኳን አንድ መፅሄት በነፃ እንደማልወስድ እግረ መንገዴን ብነግራቸው ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ ቅዳሜ ሳልገዛ ካመለጠኝ እሁድ ከገበያ ላይ እንደማላገኝው ልባቸው ያውቀዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለብሮድክሳት ባለስልጣኝ ሃላፊ ሁለት ሺ ኮፒ ለኢህአዴግ አባላትም እንደማይበቃ አልተረዱትም፡፡ በዚህ ክፍል አንባቢ እንዲረዳልኝ የምፈልገው አንድ እውነት ከሻቢያ፣ ከግብፅ፣ ከግንቦት ሰባት፣ ወይም አንድ የውጭ ሀይል የሚል ክስ ታሳቢ መደረጉ ነው፡፡ ክሱ ልክ መሆኑ አያስጨንቃቸውም ማንን ፈርተው ልክ እንዲሆን ይጨነቃሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ስንወያይ አንድ ወዳጄ ያለኝን ማንሳት ይጠቅማል፡፡ እነዚህ ሰዎች ቤተሰብ ዘመድ የሚባል የላቸውም ወይ? ይታዘበናል አይሉም ወይ? ነው ያለኝ፡፡ እኔም ደገምኩት አፈርኩ ለእናንተ ስል ብዬ፡፡

ለነገሩ እነዚህ ጋዜጦች በዚህን ያህል ዝቅተኛ ኮፒ የሚሸጡ ከሆነ መንግሰት የሚባል አካል ለምን ተሸበረ? ለምንስ ዘጋቢ ፊልም መስራ አሰፈለገው? ብለንም ልንጠይቅ እንገደዳለን፡፡ ሌላው ጥያቄ ደግሞ እነዚህ የውጭ የሚባሉ ሀይሎች የማይሸጥ ጋዜጣና መፅሔት ታትሞ ቢቀመጥ የሚያስቡተን ሀገር የመበተን ሴራ እንዴት ይሳካል ብለው ነው ድጋፋቸውን የሚቀጥሉት? ብለን ጠይቀን እንለፍ፡፡

ሌላው አስቂኝ ክስ ደግሞ “አሻጥረኛ አከፋፋዮች” የሚለው ነው፡፡ አቶ ሽመልስ ከማል አዲሰ ዘመን ከገበያ ልትወጣ የተቃረበችው በእነዚህ አሻጥረኛ አከፋፋዮች ሴራ እንደሆነ ምክር ቤት ቀርበው ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የኢዲስ ዘመንን ይዘት ማስተካከል ሲያቅታቸው የመጣላቸው ሰብብ አድርገን መውሰድ ያለብን አይመስለኝም፡፡ ዋናው ግብ አከፋፋዮችን በይፋ በማውገዝ ለቀጣይ እርምጃ ማዘጋጀት ነው፡፡ እነዚህ አከፋፋዮችን ማጥፋት ደግሞ የግል ሚዲያ ዕትመቶች ወደ ህዝብ እንዳይቀርብ ማድረጊያ ወሳኝ መንገድ ተብሎ እየታሰበ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የዚህ ክስ ተጋሪ የሆኑት አቶ እውነቱ በለጠ የኮሚኒኬሽን ሚኒሰቴር ዴህታ ናቸው፡፡ የአቶ ሽመልስን አሳበ በመጋራት በዘጋቢ ፊልሙ ላይ ተመሳሳይ ሃሳብ አንፀባርቀዋል፡፡ ሰለዚህ የመንግሰት ኮሚኒከሽን ሚኒሰትር መሰሪያ ቤት የግል ሚዲያውን የሚያሽከረክሩት ዋናኛ ሞተሮች “አሻጥረኛ አከፋፋዮች ናቸው የሚል ስምምነት ላይ መድረሱን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ከዚያስ …… ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡

እነዚህ ከላይ የተቀሰኳቸው ሁለት የመንግሰት ተቋማት በግብ ከመስማማታቸው ውጭ የሚያቀርቡት ሃሳብ ግን ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንደሆነ አይረዱትም፡፡ በእነዚህ ሁለት የመንግሰት ተቋማት ውስጥ የግል ሚዲያውን በማጥፋት ዙሪያ ስምምነት አለ፤ ሁለቱም በየፈርጃቸው ግን ሊወስዱ ያሰቡት መንገድ የተለያየ እና የሚቃረን ነው፡፡ የብሮድካስት ባለስልጣን ዕትመቶቹ አይሸጡም፤ እነዚህ ሚዲያዎች በውጭ ሀይል ድጋፍና ዕርዳት ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩት ይላል፡፡ የመንግሰት ኮምኒኬሽን መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ደግሞ እነዚህ የግል ሚዲያዎች በከፍተኛ ደረጃ እንዲታተሙ እና እንዲሰራጩ የሚያደርጉት አከፋፋዮች ናቸው፡፡ የመንግሰት ልሳን እንዳይሽጥ በማድረግ ጭምር እያሉን ነው፡፡

አቶ ብርሃኑ አዴሎ “በፀረ ሽብር አዋጅ” ዝግጅት ወቅት የነበራች የሞቀ እና ሰሜት የተሞላበት ተሳትፎ ታይቶ ለዘጋቢ ፊልም መቅረባቸው አንዱ ቢሆንም የሀቃቢ ህጉን በዘጋቢ ፊልም ላይ ያደረጉትን ንቁ ተሳትፎ ወስደን ጉዳዮን ስናየው በቀጣይ ክሱ “የሽብርተኝነት” እንደሚሆን መጠርጠር ብቻ ሳይሆን መዘጋጀትም ይኖርብናል፡፡ እግረ መንገዳቸው ግን አማረልኝ ብለው ያነሱትን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ቋሚ አምደኛ መሆን ትክክልም ተገቢም እንዳልሆነ ለማስረዳት የሄዱበት ርቀት ነው፡፡ ዝም ብሎ ለማስታወስ ያህል በአዲስ ነገር ጋዜጣ የኢህአዴግ አባል የሆነ ቋሚ አምደኛ ነበር፡፡ ይህ ጋዜጣ ግን በመንግሰት ጥርስ ተነክሶበት ከገበያ የወጣ፤ ምርጥ ልጆቹም የተሰደዱበት ነው፡፡ በአቶ ብርሃኑ አዴሎ አመክንዮ ከሄድን ኢህአዴግና አዲሰ ነገር ግንኙነት ነበራችው ልንል ነው? እኔ በምፅፍበጽ ፋክት መፅሄት ላይ አባል የሆኑኩበትን ፓርቲ እያብጠለጠሉ ይፅፋሉ፤ በግሌ የፖለቲካ አቋሜንም ሆነ ማህበራዊ ብሎም ኢኮኖሚያዊ ምልከታዬን አሰፍራለሁ አቶ ብርሃኑን ጨምሮ ብዙ እንባቢዎች እንዳሉኝ ከሚደርሰኝ መረጃ አውቃለሁ፡፡ ይህ እኔ አባል የሆኑኩበት ፓርቲና ሚዲያውን ምን ያገናኛቸዋል፡፡ አንድ እውነት ግን አለ፡፡ ይህውም የህዝብ ሚዲያዎች በኢህአዴግ ታግተው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ እኩይ አስተሳሰብ ማረጋቢያ የሆኑ ሲሆን የተገፉት ደግሞ አማራጭ አሳቦችን ለማቅረብ አሁን የግል ሚዲያዎች ምቹ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ብዙ ሚሊዮን ተመልካች እንዳለው እናውቃለን፡፡ እድሉን ብናገኝ ከ20 ሺ ኮፒ በላይ በሳምንት ከማይታተሙ መፅሄቶች ይልቅ ኢቲቪን እንመርጥ ነበር፡፡

የተዘረፈው የህዝብ ሚዲያ ለህዝብ ጥቅም የሚውልበት ቀን እሰኪደርስ ግንበተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንጠቀማለን፡፡ ይህ ምርጫ ሳይሆን ተገደን የገባንበትነው፡፡ የግሉ ሚዲያ ለጊዜው የተገፉትን መወከሉ ስህተት የለበትም፡፡ ይልቁንምሊበረታት የሚገባው ነው፡፡

ኢህአዴግ የህዝብ ውሳኔ የማይቀበል ፓርቲ እንደሆነ ዋነኛ ማሳያ ሊሆን የሚችለው አሁን በግል ሚዲያዎች ላይ የያዘው አቋም ነው፡፡ ያለምንም ጥርጥር አሁን በገበያ ላይ ያሉት ዕትመቶች በገበያ ላይ እንዲኖር የኑሮ ሸክሙን አቻችሎ በውድ ጋዜጣና መፅሄት የሚገዛ ህዝብ ነው፡፡ ይህ ህዝብ ደግሞ ለግል ሚዲያው የድጋፍ ድምፅ እየሰጠ መሆኑን መረዳት አለብን፡፡ የማይፈልገውን መፅሄት በገንዘቡ ገዝቶ ቤቱ የሚገባ ጅል አይደለም፡፡ አንዳንዱ መፅሄት ሲገዛ ለታሪክ ጭምር የሚቀመጥ ብሎ ነው፡፡ ኢህአዴግ በዚህ ጉልበቱ ይህን የህዝብ ድምፅ ሊያሸንፍለት የሚችል ሚዲያ ሊያዘጋጅ አልቻለም፡፡ ስለዚህ አሁን የያዘው መንገድ እነዚህን የህዝብ ድምፆች ለማፈን የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ነው፡፡ እነዚህ የህዝብ ድምፆች ደግሞ እንዲታፈኑ የተፈለገው ከቀጣይ ሁለት ሺ ሁለት ምርጫ ጋር ተዳምሮ ካደረበት ስጋት የሚመነጭ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ አሁን በቅርቡ የሚደረገው የደሞዝ ጭማሪ የግል ሚዲያዎችን ተገዢነት እንደሚጨምረው ይገመታል፡፡ ምክንያቱም ብዙ የመንግሰት ሰራተኞች ሊኖራቸው የሚፈልጉትን መፅሄት መግዛት ባለመቻላቸው በማንበብ ብቻ ተገድበው ነበር የሚል እምነት ስለአለኝ ነው፡፡

ቸር ይግጠመን

የተደራጁ ወንበዴዎች ለመፍጠር እየፈለጉ ያሉትን ብዥታ ለማጥራት (ዳንኤል ተፈራ)

$
0
0

ከዳንኤል ተፈራ

daniel tefera

(ዳንኤል ተፈራ

ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በጣም ወሳኝ የሆነ ስራ ሲሰራ ነበር፡፡ እሱም ውህደት ነው፡፡ የአንድነት/መኢአድ ውህደት ወሳኝና መሰረታዊ ድርድሮችን አልፎ የቅድመ ውህደት ፊርማው ከተቀመጠም ከወር በላይ ሆነው፡፡ከፊርማው በኋላ ውህደት አመቻች ኮሚቴ ተዋቅሮ በአጭር ጊዜ ነገሮችን መልክ ለማስያስ የቻለ ሲሆን ውህደቱም የሁለቱ መስራች የጉባዔ አባላት በተገኙበት ነሐሴ 3 እና 4 ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ታዲያ ከመስራች ጉባዔው አስቀድሞ ሁለቱ ፓርቲዎች በተናጠል ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት የውህዱን ፓርቲ ደንብና ፕሮግራም፤ ለውድድር የሚቀርብ እጩ ፕሬዘዳንት መምረጥ፣ አዲስ ስያሜ በመጠቆም እንዲሁም ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎችን በመስራት ይጠናቀቃል፡፡ በነገራችን ላይ የተናጠሉ ጉባዔ ስራውን የሚጀምረው አዲሱን የጋራ ደንብ በማፅደቅ ይሆናል፡፡ አጠቃላይ ውህደቱን ተቀበለው የሚባለው ደንብና ፕሮግራሙን ሲያፀድቅ ይሆናል፡፡

በአንድነት ፓርቲ በኩል በምክር ቤት ደረጃና በተለያዩ መዋቅሮቹ የሀሳብ ክርክር ማድረግ የተለመደ እንጅ ብርቅ አይደለም፡፡ የሃሳብ ክርክር ሲደረግ ‹‹ተባሉ፣ ምናምን›› እያሉ የሚጮሁት ከክርክሩ ትርፍ ለመሸመት የተሰለፉ ባእድ ሃይሎች እንጅ አንድነቶች አይደሉም፡፡ ነገዳቸው የሃሳብ ክርክር ከማውቀው ጎራ ስለሆነ የአንድነት አባላት የሃሳብ ፍጭት ሲያደርጉ ይደነግጣሉ፡፡ በአንድነት በኩል እጩ ፕሬዘዳንቶችን አስመልክቶም የተለመደው ክርክር ተደርጎ፤ እጩ ፕሬዘዳንቶቹ ወደ ጠቅላላ ጉባዔ ሄደው ከሦስቱ አንዱ እንዲመረጥ በዴሞክራሲያዊ መንገድ በድምፅ ተወሰነ፡፡ የቀረቡት እጩ ፕሬዘዳንቶች ከታወቁ በኋላም ደጋፊዎቻቸው እከሌ ቢመረጥ ይሻላል የሚል ሀሳብ የማቅረብ መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ እኔም እከሌ ቢመረጥ ፖለቲካውን የተሻለ ያንቀሳቅሰዋል የሚል መብት አለኝ፡፡ ይህንን መብት የሰጠኝ ማንም ሳይሆን አንድነት ነው፡፡

ሀቁ ይሄ ቢሆንም የአንድነት ወገን ያልሆኑ ስማቸውን የደበቁ ወሮበላ ተላላኪዎች ሶሻል ሚዲያውን በመጠቀም የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ ለማስፈፀም መንፈራገጣቸው አልቀረም፡፡ ዘመቻ ከተከፈተባቸው መካከል ደግሞ አንዱ እኔ መሆኔ ፈገግ ያሰኘኛል፡፡ ብዥታውን ማጥራት ያስፈለገኝም ለምን ስሜ ተጠቀሰ ብየ ሳይሆን የሀሰት ዘመቻውን አንድምታና ከየት አቅጣጫ እንደተሰነዘረ ለመጠቆም ነው፡፡ ዘመቻው የውሸት ስሞችን በመጠቀምና ማስጃ አልባ የተቀነባበሩ ስድቦችን በማዥጎድጎድ ብዥታ መፍጠር ነው፡፡ በተለይም ስርዓቱ ምንደኛ የሆኑ ተላላኪ ግለሰቦች ‹‹አሉላ እንደገና፣ ሰለሞን ሳልሳዊ፣ የፍቅር ቃልና አፄ ልብነድንግል›› የሚሉ የተልኮ ስሞችን በመጠቀም ውህደቱ ከመደረጉ በፊት ክፍፍል ለመፍጠር ኢህአዴጋዊ ተልዕኮ ተሰጥቷዋቸው እየባዘኑ ይገኛሉ፡፡ አንድነት አበቃለት እያሉ ስማቸውን ደብቀው እንደተራበ ቁራ ያንቋርራሉ፡፡ እነዚህን ከሙታን የሚለያቸው በድን ተንቀሳቃሽ መሆናቸው ነው፡፡ ህሊናቸውን የሸጡ ርካሽ ፍጡራን ናቸው፡፡

ዋናው ቁምነገር ዘመቻው ለምን ተከፈተ የሚለው ነው፡፡ የሚጠበቅም ነበር፡፡ ዘመቻው በተለይም በእኔና ጓዶቼ ላይ የተከፈተው ስለለውጥ፤ የተቃዋሚ ጎራውን የማይናድ መሰረት ስለማስያዝና የተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ስለተናገርን ብቻ ነው፡፡ ስለሰራን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ መስራትን ደግሞ የአንድነት ልጆች ይደግፉታል እንጂ አይቃወሙትም፡፡ የሚቃወመው ሃይል ‹‹ተቃዋሚው ማንሰራራት የለበትም፤ እግር ማውጣት የለበትም›› ብሎ የሚያምነው ኢህአዴግ ብቻ ነው፡፡ የስም ማጥፋት ዘመቻው በቀጣይ አመት የሚካሄደው ምርጫ ላይ የሚኖረንን ተሳትፎና ትግል አጋጣሚውን ተጠቅሞ የመምታት ነው፡፡ እነዚህ ከላይ የተቀስኳቸው የሀሰት ስም ተጠቃሚ ባንዳዎች ሀብታሙ አያሌው ላይ ተመሳሳይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተው ነበር፡፡ ስም በማጥፋት እንደማይበገር ሲያውቁ አሰሩት፡፡

አንድነት ካቀረባቸው ሦስት ጠንካራ እጩዎች መካከል የጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊው አንዱን ይመርጣል፡፡ ዋናው የሂደቱ ዴሞክራሲያዊ መሆን ነው፡፡ ኢንጅነር ግዛቸውና አቶ ትዕግስቱ ለአንድነት እዚህ መድረስ ያደረጉት ትልቅ አስተዋፅኦና የከፈሉት ዋጋ ሳይዘነጋ ነገር ግን አሁንም የእኔ እምነትና ፍላጎት ሀቅን መካድ ስለማይቻል ለአንድነት ፓርቲ አሁን ያለበት ከፍታ ላይ መድረስ በላይ ፈቃዱ ዋናው ስለሆነ፤ ትግሉን ወደ ህዝቡ ለማውረድና ከቢሮ ለማውጣት በነበረው ትንቅንቅ ላይ እውቀቱን፣ ገንዘቡንና ጊዜውን ያለ ምንም ስስት ሲሰጥ ስላስተዋልኩ፤ በላይ ፍቃዱ የሚታወቀው ሀሳብ በማመንጨትና ያ ሀሳብም ተግባራዊ እንዲሆን ሳይደክም በመስራት ስለሆነ፤ ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› የሚለው ወሳኝ ህዝባዊ ንቅናቄ ስያሜ በበላይ በኩል የቀረበ እንደነበር ስለማውቅ እንዲሁም በላይ ፈቃዱ ፓርቲያችን የማተሚያ ማሽን ሊኖረው ይገባል የሚል ሃሳብ በማቅረብና በመተግበር ውጤት ያሳየም በመሆኑና በአጠቃላይ የጀርባ ሞተር ሆኖ የቆየ ውድ የአንድነት ልጅ ነው ብየ ስለማምን ለበላይ ድጋፌን እሰጣለሁ፡፡

ታዲያ ይህ ግልፅ እምነቴ በድብቅ ስሞች ስም ለማጉደፍ በሚሯሯጡ በገዥው ፓርቲ ምልምሎች በኩል የተቀነባበረ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲከፈትብኝ አድርጓል፡፡ ልብ በሉ ‹‹ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው›› ነውና በወሬኞች ላለመፈታት እንጠንቀቅ፡፡ ስም አጥፊዎቹ የአንድነት ልጆች ቢሆኑ ኖሮ እንደዘረዘሩት የሀሰት ውንጀላ አንድ ቀን አናድርም ነበር፡፡ የውሸት ስም መጠቀም ሳያስፈልጋቸው ቢፈልጉ ፕሬዘዳንቱ ጋ አሊያም የምክር ቤት ሰብሳቢው ጋ በማምጣት ባቀረቡ ነበር፡፡ አድናቆቴ ከፍ ይል የነበረውም ይህንን ማድረግ ቢችሉ ነበር፡፡ አሁንም እስከነፃነት ትግሉን እንቀጥላለን፡፡

“በእኔ ስም አይሆነም!”ክፍል ሦስት (በልጅግ ዓሊ)

$
0
0

ብረሥላሴ ደስታ ( ካርሜሎ ክሪሼንቲ) የሚባል ጣላኒያዊ የሃገራችን ወዳጅ ወደ ደብረ ሊባኖስ ተጉዞ የጀግናውን የአበበ አረጋይን መቃብር ተመልክቶ የተሰማውን ሃዘን እንዲህ ብሎ አጫወተኝ።

 

gth“ስለ አበበ አረጋዊ ጀግንነት የሰማሁት ከአንድ በጦርነቱ ከነበረ ኢጣልያዊ  ሽማግሌ ነበር። ወደ ኢትዮጵያ ስጓዝ ለእኚህ ጀግና ለማስታወስ  የተሠሩ  ብዙ ሐውልቶች፣ ብዙ ሙዚየሞች እንደሚገጥመኝ ገምቼ ነበር።  ነገር ግን የገጠመኝ የእኚህ የጀግናችን መቃብር ደብረሊባኖስ ውስጥ ዳዋ በልቶት የሚንከባከበው አጥቶ ነው። በጣም አዘንኩ። በአካባቢው ያገኙትን በመጠቀም ለማጽዳት ሞከርኩ። ከተሳካልኝ በሕይወቴ ውስጥ የአበበ አረጋይን መቃብር በተሻለ ሁኔታና ከጎኑም ሰፋ ያለ ሙዚየም ባሠራ ደስ ይለኛል።”

 

ገብረሥላሴ(ካርሜሎ) እስከ አሁን ድረስ በልቡ ዕረፍት አላገኘም። ቀን ሲሞላለት ለእኚህ ጀግና ብዙ ማድረግ አስቧል። አዎ ዛሬ ብዙዎቻችን ላለፈ ታሪካችን አንጨነቅም። አዎ ብዙዎቻችን አዲስ በወያኔ በተፈጠረው የዘር ፓለቲካ አማካኝነት ሁሉን ነገር ከዘር አንጻር እንመለከተው ይሆናል። ዛሬ በፋሽሽት ኢጣሊያ ስለተጨፈጨፉት ዜጎቻችን መስማት ያዳግተን ይሆናል። ግን ደግሞ ቴዲ አፍሮ በዘፈኑ እንደገለጸው “የኋላው  ከሌለ የለም የፊቱ” ነውና፣ ወደድንም ጠላንም ለዛሬ ማንነታችን የፊቱ ታሪካችን ነጸብራቅ ነው። ብንክደውም ጥላችን ሆኖ ይከታተለናል።

 

ታሪካችን ለማጉደፍ፣ መስዋቱንም ለማዋረድ የሚደረገውን ጥረት ዛሬም በሰፊው እንደቀጠለ ነው። ይህንን ደባ ቆርጠን መታገል ይኖርብናል።  ዜጎቻችንን የጨፈጨፉ እነ ግራዚያኒ እንደ ጀግና ሲቆጠሩና ሃውልት ሲገነባላቸው ይህንን መቃወም ወደ ኋላ የማንልበት ተግባራችን መሆን አለበት።  ይህ በተለይ በፋሽሽት ኢጣሊያን የተሠራውን ግፍ ማጋለጥ  የዓለም አቀፍ ትብብር ለፍትህ(GLOBAL ALLIANCE FOR JUSTICE:  THE ETHIOPIAN CAUSE) http://www.globalallianceforethiopia.org  ብቻ የሚመስላቸው ትንሽ አይደሉም። አንዳንድ ድረ ገጾች ይህንን ከላይ የጠቀስኩትን ድርጅት የሚያወጣውን መግለጫ አልፈውም ስለ ፋሽሽት ኢጣሊያ፣ ስለ ቫቲካን ፋሽሽቶችን መተባበር የሚገልጽ ጽሁፍ በድረ ገጻቸው ልዩ ልዩ ምክንያት በመስጠት ላለማውጣት የወሰኑ አሉ። ይህ የሚያሳዝን ነው።  ቫቲካን ከፋሽሽት ወረራ ጊዜ ከሞሶሎኒ ማበርዋ የአደባባይ ምሥጢር ነው።  ስለ ቫቲካን ከፋሽስቶች ትብብር ለማወቅ ለምትፈልጉ ከላይ የጠቀስኩትን ድረ ገጽ ብትጎበኙ ጠቃሚ ነው።

 

የኢትዮጵያን አንድነት የሚቃወሙ ሁሉ የዳግማዊ ምንሊክን ሃውልት ለማፈረስ የሚያደርጉት ጥረት ጥንትም ይሁን አሁን እንደቀጠለ ነው። በፋሽሽት ወረራ ወቅት የቅኝ ግዛት ሚኒስተር የነበረው ሌሶና(Lessona) በሌሊት የዳግማዊ ምንሊክን ሐውልት ከቦታው አንስቶት እንደነበር የሚታወስ ነው። ይህ ግለሰብ ወደ አዲስ አበባ በባቡር ሲጓዝ በደጃዝማች ፍቅረ ማርያም ሥር የነበሩ አርበኞች አደጋ ጥለውበት ነበር። ይህ በጎን የምታዩት ፎቶ ይህንን የሚሳይ ሲሆን ኢያን ካምፕቤል(IAN CAMPBELL) የሚባል ጸሐፊ (The plot to kill Graziani – ገጽ 100) ከሚለው መጽሐፉ ላይ በሰፊው አትቶታል።

 

ዛሬም ቢሆን ይህንን የፋሽስቶች ዓላማ ተቀብለው ምንሊክን የሚቃወሙ ከሃውልቱ ጋር የሚጣሉ በየቦታው እናገኛለን። በእውን በምንሊክ ዘመን በደረሰባቸው ግፍ ከሆነ ሁኔታው በዛ ዘመን ካለው የዓለም ሥልጣኔ አንጻር ልንመለከተውና እውነተኛውን ሁኔታ ለታሪክ ማስቀመጥ ይኖርብን ይሆናል። ነገር ግን ብዙዎቹ በምንሊክ ዘመን ለደረሰባቸው ጭቆና ሳይሆን የኢትዮጵያን አንድነት ለማፍረስ ካላቸው ፍላጎት ወይም ለወቅታዊ ሥልጣን ቃረማ ምንሊክን ሲያወግዙ ይታያሉ። ጣሊያኖች በአደዋ ጦርነት ወቅት በደረሰባቸው ውርደት ምከንያት  ምንሊክን ቢጠሉ የሚገርም አይሆንም። የዘንድሮ የሃገራችን ዘረኞችም የምንሊክን የአደዋ ድል ያነሳ ሁሉ ጠላታችን ነው በማለት የሚያደርጉት ቅስቀሳ ለምን እንደሆነ የረባ ትንታኔ ሲሰጡ አይሰሙም።

በክፍል አንድና ሁለት እንደገለጽኩት በሃገራችን ያን ሁሉ ጭፍጨፋ ያካሄደው ፋሽሽቱ ግራዚያኒን ለማስታወስ በአሁኑ ወቅት አፊሌ ከተማ ውስጥ የተጀመረው ሃውልት የማነፅ እንቅስቃሴ መቃወም የሁላችንንም ትብብር ይጠይቃል። በክፍል አንድና ሁለት በአፊሌ የተሠራውን ሃውልት በሚመለከት የተነሳው ተቃውሞ ጁላይ 28 ላይ አፊሌ ከተማ ውስጥ የተሳካ ሰልፍ ተደርጓል። በአካባቢው የሚገኙ አምስት ከንቲባዎች የኢጣሊያንን ባንዲራ በማሸረጥ በቦታው ተገኝተው ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር። የፋሽሽቱ ግራዚያኒ ደጋፊ የሆነው የአፊሌ ከተማ ከንቲባ ይህ በግራዚያኒ ላይ የተነሳውን ተቃዉሞ በመቃወም “እዚህ የምትገኙት በሙሉ የአፊሌ ከተማ ነዋሪዎች አይደላችሁም“ በማለት ላቀረበው ተቃውሞ በሰልፉ ላይ የነበረ የአፊሌ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ “የአፊሌ ሕዝብ ከንቲባውን ፈርቶ እንደቀረ አስረድቷል“። በሰልፉ ላይ የዜጎቻችን ተሳትፎ የጎላ አልነበረም።

 

በዚህ የግራዚያኒን ሐውልት በመቃወም ተግባር ላይ በተለይ በኢጣሊያን የሚገኙ ዜጎቻችን ተሳትፏቸው የጎላ መሆን ቢገባውም በጣሊያን የዜጎቻችንን ኑሮ በኢጣሊያን የሚያፈናፍን ሆኖ አላገኘሁትም። ከኑሮ ትግል አልፈው ይህንን ዓይነት ትግል ለማካሄድ በጣም አስቸጋሪ ነው። እስቲ ስለኑሯቸው በጥቂቱ።

 

 

ክፍል አራት

የዜጎቻችን ኑሮ በሮማ

 

ጣሊያን ዋና ከተማ ሮማ  የዜጎቻችን ቁጥር ከመቼውም ባለይ  በዚህ ዓመት ከፍ ብሏል ። በሊቢያ የመንግሥት አለመኖር በፈጠረው ሁኔታ ምክንያት ከሰሃራ በርሃ የሚፈልሰው ወጣት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። የሰሃራ በረሃ ጉዞም ከዛም በሊቢያም ባህሩን አቋርጠው አውሮፓ እስኪደርሱ ያለው ጉዞ ከበፊቱ የበለጠ አደገኛ ሆኗል። በሶርያ የተፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነትም የልዩ ልዩ ዐረብ ሃገር ዜጎች ወደ አውሮፓ በሶርያውያን ስም ለመፍለስ ምክንያት ሆኗል። ይህ ጉዞ በሁለት ግንባር የሚካሔድ ነው። አንዱ ግንባር ከቱኒዚያ ሲሆን ፣ ሌላው ደግሞ ከሊቢያ ነው።

 

በሊቢያ ጋዳፊን በመቃወም የተነሳው የእርስ በእርስ ብጥብጥ ሊቢያ ውስጥ ሆነው ይጠብቁ የነበሩ ስደተኞችን ስቃይ ውስጥ ከቶ ነበር። እነዚህ ስደተኞች ጦርነቱን በመፍራት ወደ ቱኒዚያ ሸሽተው በሊቢያና በቱኒዚያ ድንበር አጠገብ በሚገኝ ራስ አጂዲር( Ras Ajdir) በሚባል ቦታ  ሾሴ መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ብዙ ወገኖቻችንን ነበሩ። ቱኒዚያ ውስጥ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውና በዓይኔ የተመለከትኩትን ስቃይ ለመግለጽ አዳጋች ነው። ሌሎች ሃገሮች  ዜጎቻችውን ሲወስዱ አፍሪካውያን እዛ በርሃ ውስጥ ነበር የቀሩት። ከእነዚህ ስደተኞች ውስጥ አንዳንዶቹ ተሳክቶላቸው ወደ ምዕራብ ሃገሮች ጥገኝነት ቢያገኙም ብዙዎቹ ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ክፍል ካለ አንዳች እርዳት በርሃ ውስጥ በትኗቸዋል። እነዚህ ዜጎቻችን ከቱኒዝ እንደገና ወደ ሊቢያ ተመልሰው አሳቃቂውን ጉዞ ለማድረግ ተገደዋል። በዚህ ጉዞ ብዙዎቹ ሕይወታቸው አልፎል።

 

 

አሁን ደግሞ እነዚሁን ወገኖቻችንን ከቱኒዚያ ወጥተው ወደ ሊቢያ ተመልሰው፣ አሰቃቂውን የባሕር ጉዞ አድርገው ሮም ደርሰው አግኝቻቸዋለሁ። ምንም እንኳን አውሮፓ መድረሳቸው የሚያስደስት ቢሆንም ኢጣሊያ ሮም የተሻለ ኑሮ ገጥሟቸዋል ማለት አይቻልም።  ከላምፓዱዛና ከሌሎቹ ደሴቶች ሕይወታቸው ተርፎ ጉዞአቸውን ወደ ሮም ያደረጉት ስደተኞች የሚገኙበት ሁኔታ ስመለከት የዜጎቻችን ስቃይ አውሮፓ ስለደረሱ ብቻ እንደማይቀረፍ ጎልቶ ይታያል። (ፎቶው አዲስ የመጡት ስደተኞች መተኛ አጥተው በየቦታው ተኝተው የሚያሳይ ነው።)

 

ከሊቢያ የመጡትን ስደተኞችና ስለሮማ  ስደተኞች ለመነጋገር ከተፈለገ ሦስት ቃላቶችን አንባቢያን ከአማርኛ መዘገበ ቃላት ውስጥ እንድትከቱልኝ እጠይቃለሁ።

1ኛ ፊሽ – - – ፊሽ ማለት በስደተኛው የአማርኛ አጠቃቀም ውስጥ ዐሻራ ማለት ነው።(ፊሽ አለብህ ወይ? ፣ ፊሽ ተደርግሃል ወይ ? ማለት ዐሻራ ተወስዶብሃል ወይ ? ዐሻራህን አንስተውታል ወይ ማለት ነው ። ቃሉ ከየት እንደመጣ ጠይቄ መረዳት አልቻልኩም። ዐሻራ የሚለው ቃል በማርጀት ፊሽ የሚለው በወጣቱ አካባቢ ተጠቃሚነቱ በዝቷል።

2ኛ ቤት ሰበራ – - -  ማለት የግል ወይም የመንግሥትን ቤት በጉልበት ፤ በሕዝብ ብዛት መውረር ማለት ነው። ( የቤት ችግር እዚህ ሮም ውስጥ ስላለ መክፈል የማይችሉ የብዙ ሃገር ዜጎች (ጣሊያኖችም ጭምር ) ባዶ ሆኖ የተዘጋ የመንግሥት ወይም የግል ቤትን በመውረር በሩን ሰብረው ገብቶ መውረርን የችግር መፍቻ ካደርጉ ሰንብተዋል።

3ኛ መጠረዝ – - -  ታስሮ ወደ መጡበት ቦታ መመለስ ( ለምሳሌ ወደ ጣሊያን ተጠረዘ – - – ወደ ጣሊያን እንዲመለስ ተደረገ።)

 

እነዚህ ሦስት ትርጉሞች ማወቅ ለዜጎቻችንን የሮማ ኑሮ አስፈላጊ ነው።  ሦስቱም ከስደተኞች በተለይ በቅርብ ከመጡት ጋር የተዋሃዱ ናቸው።

 

ባሕሩን አቋርጠው ወደ አውሮፓ የደረሱ ስደተኞች ፊሽ (ዐሻራ) ይነሳሉ። ይህ ፊሽ ሌላ የአውሮፓ ሃገር ቢሄዱ ከየት እንደመጡ ለማወቅ ይረዳል። የሌላ ሃገር ፊሽ የተገኘበት ሰው ፊሽ ወደሰጠበት ሀገር ይጠረዛል።  በአውሮፓውያን ሕግ ስደተኞቹ መጀመሪያ የደረሱበት የአውሮፓ ሃገር ነው ስደተኛነት መጠየቅ የሚቻለው። አንድ የአውሮፓ ሃገር ስደተኝነት የጠየቀ ግለሰብ ሌላ ሃገር ቢጠይቅ እንኳን ተቀባይነት ለማግኘት አይችልም። ሌሎች ምክንያቶች እስከሌሉ ድረስ።

 

ፊሽ የሌለበት ስደተኛ በጣም እድለኛ ነው። ሌላ አውሮፓ ሃገር ጥገኝነት መጠየቅ ይችላል። ይህ ግን ደግሞ ቀላል አይደለም ። መጀመሪያ ከጣሊያን ወጥቶ ሌላው ሃገር መድረስ አለበት። የሌላው ሃገር ጉዞ እስከሚሳካ እስከዚያ ጣሊያን ውስጥ መቆየት አለበት። ጥያቄው የት ነው የሚቆየው? ነው። ዘመድ ያለው ከዘመድ ተጠግቶ ይኖራል። የሌለው ግን መወደቂያ የለውም። ሮማ ውስጥ ግን የተሰበሩ ቤቶች ስላሉ እዚያ አካባቢ ሄዶ ጊዜያዊ መጠለያ ያገኛል።

 

 

በአሁን ጊዜ በጣሊያን ውስጥ በተለይ በሮማ ቤት መስበር በሰፊው በመካሄድ ላይ ነው። እንቅስቃሴውን የሚካሄደው በዓላማቸው ሕዝብ መኖሪያ አጥቶ ሕንጻዎች ክፍት ሆነው መቀመጣቸውን የሚቃወሙ ቡድኖች ናቸው። የቡድኑ አባሎች የግድ የቤት ችግር ላይኖርባቸው ይችላል። ግን ይህንን እንቅስቃሴ ይመራሉ። ይህ የሚደረገው በሚስጥር ነው። አንድ ቤት ባዶ መሆኑ ከታወቀ ይህንን የሚያቀነባብሩት የኮሚቴ አባላት ይወስኑና ችግር ያለባቸውንም ይሁን በተወረረው ቤት የሚኖሩትን በድብቅ ምስጢራዊ በሆነ መንገድ አዲስ በሚወረረው ሕንጻ አካባቢ እንዲሰበሰቡ ይጠራሉ። ከዛም አዲሱን ሕንጻ ሰብረው ቤቱን ገብተው ይወራሉ። በዚህ ሰዓት ቁጥሩ ብዙ የሆነ ሰው በመሰብስቡ ምክንያት ጠባቂዎችም ሆነ ፖሊስ ኃይል አይኖረውም። ሕጻን፣ ወጣት፣ አሮጊት ወይም ሽማግሌ ልዩነት ሳይኖረው በዚህ ወረራ ላይ ይሳተፋሉ። ከዚያም ያንን ቤት ተከፋፍለው ይይዛሉ። ነገሩ ረጋ ሲል ከሌሎች ከተወረሩ ቤቶች ለእርዳታ የመጡት ይመለሱና አዲሶቹ ተከፋፍለው ቤቱን ይይዛሉ። መንግሥት ዓመጹን በመፍራት ችግሩን ያበርዳል።

 

ሮም ውስጥ የተሰበሩ ቤቶች በብዛት ቢገኙም፣ ሙሉ በሙሉ በዜጎቻችንን ቁጥጥር ሥር ያሉ  ሁለት ሕንጻዎች አሉ። አንደኛው ኮለንቲና ሲባል ሁለተኛው አነኒና ይባላል። ሁለቱም ሕንጻዎች የአውሮፓም ሆነ የኢጣሊያን ሕግ አያስተዳድራቸውም። በተቋቋመ ኮሚቴ ነው የሚተዳደሩት። ሕንጻዎቹ ከውጭ ሲመለከቷቸው ውብ ናቸው። ውስጥ ግብቶ ማየት የሚያሰቅቅ ነው።

 

 

እነዚህ ሁለት ሕንጻዎች ሌሎች ከተሰበሩ ቤቶች ለየት የሚያደርጋቸው ከአስተባባሪው ኮሚቴ ነጻ ወጥተው ራሳቸውን በማስተዳደራቸው ነው። ይህ ማለት አስተባባሪው ኮሚቴ ለሌሎች ቤቶች ሰበራም ሆነ ለተቃውሞ ሰልፍ የእነዚህ የሁለቱን ነዋሪዎችን አይጠራቸውም፣ አያስገድዳቸውም። ይህ ማለት በቤት ሰበራ ኮሚቴ የሚተዳደሩት ሕንጻዎች ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞች እልክ አስጨራሽ የሆነ ትግል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። እነዚህ የኮሚቴ አባላት የሰዎችን መብት መከበር ዋና አላማቸው ስለሆነ በሚያደርጉት ትግል ላይ መሳተፍ ግዴታ ነው ። የእኔ ችግር ተፈትቷል ብሎ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ አይፈቀድም። የተደጋገመ ሰልፍ ላይ መገኘት ግዴታ ነው። ይህ ለዜጎቻችን ደግሞ የማይዋጥ ነው ። የእራስ ችግር ከተፈታ በኋላ ለሌሎች ችግር መታገል ደግሞ አለመደብንም። ስለዚህ ከዚህ የጋራ ትግል ወጥተው ብቻቸውን መኖር አማራጭ በመሆኑ ኮሚቴዎችን በማባረር ራሳቸውን ማስተዳደርን መርጠዋል። ከዚያም በተረፈ የሕንጻውን ሁኔታ በሚመለከት ራሳቸው ነዋሪዎቹ የመደራደር መብት አላቸው።

ኮለቲናና አነኒና በአሁኑ ወቅት በሰሃራ አድርገው፣ ያንን  ስቃይ የበዛበትን፣ ሞት የረከሰበት ጉዞ አጠናቀው ጣሊያን የደረሱትን ዜጎቻችንን በመቀበልና ማረፊያ በመሆን ይህ ነው የማይባል ትልቅ እርዳታ እያደረጉ ነው። እነዚህ ሕንጻዎች በአውሮፓ ደረጃ መፍረስ የሚገባቸው ቢሆኑንም በውስጡ ግን ብዙ ተዓምሮችን ለማየት ይቻላል። መጀመሪያ ሕንጻዎቹን የወረሩት ዛሬ በብዛት በዚህ ሕንጻ ውስጥ አይኖሩም። የያዙትን ክፍል ‚ ሸጠው ሄደዋል። የተሸጠለትም ደግሞ ከፋፍሎ አከራይቶታል። ክፍል ለመግዘት እስከ አስር ሽህ ኢሮ ሲደርስ፣ ለመከራየት ደግሞ በወር እስከ 200 ኢሮ  ይሆናል። ይህ መክፈል የማይችል አዲስ መጤ ደግሞ ከፎቁ ሥር ካለው የመኪና ማቆሚያ ፍራሽና ብርድልብስ ለምኖ ይተኛል። ይህንን ማመን ያዳግት ይሆናል። ግን ሐቅ ነው። መንገዱ ተሳክቶለት ወደ ሌላ የአውሮፓ ሃገር እስከሚሄድ በብርድ እየተጠበሰ ይቀመጣል። ምግብ ደግሞ እየተለመነ ይኖራል። በዚህ ቦታ የምንታዘበው ብዙ አሳፋሪ ተግባሮች አሉ። ቁማር፣ ስካር፣ ድብድብ የየዕለቱ ተግባሮች ናቸው።

 

ከኢጣሊያን ወደ ሌሎች ሃገሮችም ሆነ ፣ ከኢጣሊያን ሌሎች ቦታዎች ወደ ሮማ መሻጋጋሪያው በባቡር ነው የሚሆነው። ይህንን ጉዞ የሚቀነባብሩም ደላላዎች ባቡር ጣቢያ  አይጠፉም። ባቡር ጣቢያው ተርሚኒ ይባላል። እስቲ ትንሽ ስለ ተርሚኒ።

 

 

 

ክፍል አምስት

 

ተርሚኒ

 

ጣሊያ- ሮማ  ለመጎብኘትም ሆነ ጥገኝነት ለመጠየቅ የመጣ ዜጋችን ወደ ባቡር ጣቢው ጎራ ማለቱ አይቀርም። ባቡር ጣቢያው ተርሚኒ ይባላል። ቦታው ለሚዝናና ወይም ሰው ለሚጠብቅ በሚስማማ ሁኔታ የተሠራ ነው። ከትልቁ አዳራሽ ውስጥ አንድ ፎቅ ነገር አለ። እዛ ላይ ደግሞ አንድ ቡና ቤት ። ይህ ቡና ቤት ቻዎ ይባላል። ቀጠሮም ያለው ይሁን የሌለው እዛ ቡና ቤት ተቀምጦ ወደ ታች ገቢው እና ወጭውን ያነጣጥራል። ቻዎ ቡና ቤት ሁሉንም ለመቆጣጠር የሚያመች ገዢ ምድር ነው። ቡናውም ጥሩ ነው። አካባቢውም ያመቻል። የጠፋብዎትን ዜጋችንን ሁለት ቀን ከተመላለሱ ሊያገኙት  ይችላሉ። ቻዎ እንገናኝ የሮም የቀጠሮ ቦታ ነው።

 

አዲስ አባባል  – - -  ጣሊያን ውስጥ አንድ የአማርኛ አጠቃቀም አለ። በኋላ እንሰማማ የሚል ነው። ይህ ማለት በኋላ እንድዋወል፣እስከ በኋላ  ማለት ነው። ብዙ ጊዜ በስልክም ሆነ በአካል ሰዎች ሲሰነባበቱ ይህንን አባባል ይጠቀማሉ። በኋላ እንሰማማ ። በሌሎች የአውሮፓ ሃገሮች ያልሰማሁት አጠቃቀም ነው። ይህ አባባል ከኢጣልኛው (ci sentiamo dopo) ከሚለው አነጋገር የመጣ ነው እንደሆነ ተረድቻለሁ።

 

ሮምን የጎበኘ ዜጋችን ተርሚኒ ባቡር ጣቢያ ከሚገኘው ቻዎ ቡና ቤት ፎቁ ላይ ቁጭ ብሎ ጣፋጭ የጣሊያን ቡናውን እየጠጣ ወደ ታች ቁልቁል የሚተራመሰውን ሕዝብ እየተመለከተ ከጎን፣ ከጀርባ፣ ካጠገብ የሚሰማውን የተለያየ  ቋንቋ እየሰማ መደሰት የተለመደ ነው። ተርሚኒ ቻዎ ቡና ቤት ሮምን ለቀው ከወጡ በኋላም ቢሆን የማይለቅ ትዝታ አለው።

 

አዎ ቻዎ ልዩ ትዝታ አላት። የቆየ ዘናጭ፣ አዲስ የመጣ እንግዳ፣ የሲኞራ ቤት ሥራ ያደከማት ዜጋችን፣ ኪሱ ሳንቲም የሌለው ቀፋይ፣ ፓለቲከኛው፣ ጸረ ፓለቲካው፣ የቸኮለ ሠራተኛ፣ ሥራ አጥ፣ ሥራ ፈላጊ፣ ከሥራ እረፍት አግኝቶ መዝናናት የፈለገ፣ የተቀጣጠረ፣ ያልተቀጣጠረ፣ ሚስቱ ሠርታ የምታስተዳድረው ጎረምሳ፣ ሥራ ያደከመው፣ ከዛም አልፎ ተርፎ ከኤርትራ ማሰልጠኛ ጣቢያ ከሰዋ አምልጦ የመጣ አዲስ ባለሸበጥ ጫማ ጎረምሳ  . . .  ወዘተ ይሰበሰቡባታል።  ሁላችንም ከፎቁ ተደርድረን ከስር የምታልፈውን ዜጋችን ከዓይናችን እስከምትጠፋ የምንገላምጥበት ምርጥ ቦታ ነው። ቻዎ ቆይቶ የተገናኘ የሞቀ ሰላምታ፣ የደረት ለደረት ድለቃ የጎላበት፣ እንስት መተዋወቅ የፈለገም ሆነ ብቸኝነት ያጠቃትም ዜጋችንም ዘንጣ የምትታይበት ምርጥ ቦታ ነው። ቻዎ ከባዱ ቡና እስፕሬሶ የከበደን፣ ካፌ ሉንጎ አሜሩካኖ የምናዝበት፣ ጣፈጭ ኬክ (ኮርኔንቶ) በቡና ይዘን የምንዝናናበት ነው። ቻዎ ቡና ቤት የማይረሳ ትዝታ አለው።

 

ቀን ሞልቶ እስኪጻፍ ይደር እንጂ ቻዎና ደላላዎቻም ብዙ ታሪክ አላቸው። ለታዘበ ማን ምን እንደሆነ ቻዎ ለሳምንት ከተመላለሰ ይገለጽለታል። ቻዎና ደላሎቿ ብዙ ታዕምሮችን የሚፈጽሙበት ቦታ ነው። እዚሁ ተርሚኒ ቻዎ ቡና ቤት ተቀምጠው አዲስ የመጡትና የቆዩትን ዜጎቻችንን መለየት ይቻላል። በአለባበስ ፣ በአካሄድ ፣ ባነጋገር . . . ። በተለይ በሴቶች እህቶቻችንና በወንድሞቻችን መካከል ልዩነቱ የጎላ ነው። ብዙዎቹ እህቶቻችን ሰው ቤት ተቀጥረው የሚሠሩ በመሆናቸው ምክንያት ያችን በሳምንት አንድ ቀን የሆነች ዕረፍታቸውን በጸጉር ቤት፣ በሱቅ መዞር፣ ወዳጅን ማግኘት፣ ለዘመድ አዝማድ መደወል . . .  ለማብቃቃት ሲራወጡ ይታያሉ። ወንዶችም እንደ እህቶቸችን ባይሆንም ትንሽ ጥድፊያ አለባቸው። ግን በዛው ደግሞ ለብሶ፣ አማምሮ ቻዎ ቡና ቤት ውስጥ ቡናውን ሲጠጣ፣ አላፊ አግዳሚውን በዓይኑ ሲሸኝ የሚውል ደግሞ ትንሽ አይደለም። ይህንን ሽሙንሙን ጠጋ ብለው ቢጠይቁት ሚስቱ ሲኞራ ጋ የምትሰራ ሆና በሳምንት አንድ ቀን ወይም በየቀኑ ማታ ማታ የምትመጣ እንደሆነች ይነግርዎታል። የሚኖሩት በተሰበረ ቤት ውስጥ እንደሆነም አይደብቅዎትም። ዋናው የእሱ ስራ ቤቱ ለመስበር የተባበሩት ኮሚቴዎች በሚያዙትን ሰልፍ ላይ ቤተሰቡን ወክሎ መገኘት ብቻ እንደሆነ ይነግሮታል።

 

አዲስ መጤዎችንና የቆዩትን ለማወቅ በንግግር ለማወቅ ከፈለጉ ደግሞ ከባድ አይደለም። የቆዩት እንደ ጣሊያኖቹ እጃቸውን ሲወናጭፉ ያገኙቸዋል። አዳዲሶቹ ግን በዚህ ግርግር በባዛበት ትልቅ ከተማ ውስጥ፣ ነገ ምን እንደሚጠብቃቸው፣ ስለማያውቁ በጭንቀት ያዩት ሰው ሁሉ የሚያውቃቸው እየመሰላቸው ዓይናቸው ሲቅበዠበዥ ያገኙአቸዋል።

 

ሮማ በነበርኩበት ወቅት ተርሚኒ ቻዎ ጎራ ሳልል አላልፍም። ብዙ ጊዜ እዛ ቡና ቤት የሚደበሩ ዜጎቻችንን ተመሳሳይነት አላቸው። በተለይ አንድ ሁል ጊዜ የማላጣት አስቂኝ ዜጋችን ምን ጊዜም የማልረሳት ነች። ቻዎና ደላላዎቻ ጋር ትጠቃለላለች።

 

ይህቺ አስቂኝ ፍጡር ራሷ ላይ ያደረገችው ሰው ሰራሽ ጸጉር (ዊግ) እድሜዋን ከሚያሳብቀው ፊቷ ጋር ቅራኔ ውስጥ ገብቶ ጦርነት የገጠመ ይመስላል። የምታደርጋቸው ልብሶች  አሁንም ለእሷነቷ ማንነት የማይመጠን ነው። ከንፈሯ ላይ ያለው የከንፈር ቀለም ጀማሪ ቀለም ቀቢ የተማረበት ይመስላል። ጣትዎ ላይ የሳካችው ሰው ሰራሽ ጥፍር ከማማር አልፎ የቡቱ ቡቱቱን ጥፍር መስሏል። አብራቸው የምትቀመጠው ልጆችም ቢሆኑ ጫጩቷን ታቅፋ የተቀመጠች እናት ዶሮ ያስመስሏታል። የቆየች መሆኗን ግልጽ ነው። አዲስ በመጡትና ጣሊያንኛ በማይችሉ ዜጎቻቸን ላይ የጣሊያን ቃላት በመጠቀም ግራ ስታጋባቸው መታዘብ በቀላሉ ይቻላል።

 

አጠገብዋ የሚኮለኮሉት ወጣቶች ሁልጊዜ ይቀያየራሉ። ዛሬ ያሉት ከትንሽ ቀናት የሉም። እነርሱ ሲሄዱ ሌሎች ይመጣሉ። ወጣት ሴቶች ወጣት ወንዶች ይከቧታል። በጣም ቁልፍ አስፈላጊ ሰው እንደሆነች ሁኔታው የተከታተለ አያጣውም። ምኞቴ ምን እንደምታወራቸው መስማት ነበር። አንድ ሁለቴ ጠጋ ብል ንግግሯን አቋመች። የጋሜ( የደላላ) ጠባይ ስላየሁባት ፍላጎቴ ጨመረ። አንድ ቀን ብቻዎን አገኘኋት ጠጋ ብዬ በአማርኛ ሰላም አልኳት። በትግርኛ መለሰችልኝ። ትግርኛ እንደማልችል ነገርኳት። እዋይ ብላ በጣሊያንኛ ቀጠለች። መግባባት ጠፋ። ምንም ማድረግ አልተቻለም። ቻዎ ብላኝ ሄደች። ተስፋ አልቆረጥኩም። መከታተል ቀጠልኩ። ብዙም አልወሰደብኝም ምሥጢሩ ተገኘ። አዲስ የሚመጡት ልጆች ጉዳይ አስፈጻሚና ወደ ሌሎች ሃገሮች አሳፋሪ፣ ዘመድ ወዳጅ ገንዘብ ቢልክ ተቀብላ የምትሰጥ ጠንከር ያለ ሥራ እንዳላት ተረዳሁ። ሌላም ብዙ ብዙ ነገር ሥራዋ ያካትታል . . .  በእሷ የሚያለቅሱም፣ የሚደሰቱም አግኝቻለሁ። ደግነቷን የሚናገረው ከማዘር ቴሬዛ ሲያወዳድራት ፣ የጠላት ደግሞ መምህር ግርማ ሰሞኑን ሮማ ውስጥ አስወጡ ከሚባለው ሰይጣን ያመሳስላታል። የሥራ ጸባዩ ከሁለቱ መሃል አስቀምጧታል።

 

አዎ ሮምና ተርሚኒ ብዙ ትዝታዎች አላቸው። ሮም ተርሚኒ ፣ ተርሚኒ ሮም . . . .

 

እዚሁ ተርሚኒ ውስጥ በምመላለስበት ወቅት አንድ ከስዊድን የመጣ አንድ ግለስብ አገኘሁ። ይህ ግለሰብ ብቻዬን ስለተቀመጥኩ ቦታው እንዳልተያዘ ጠይቆኝ ተቀመጠ። በዚህ ጥያቄው ግለሰቡ ከውጭ እንደመጣ ጠረጠርኩ። ቻዎ ቡና ቤት ውስጥ ከታዘብኩት ጉዳይ አንዱ ሁሉም ባይሆኑም ብዙዎቹ ሰላም ብለው አጠገብህ ሲቀመጡ ስለቦታው መያዝ አይጠይቁም።  ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ

 

- የዚህ ነዋሪ ነህ? ብሎ ጥያቄውን አቀረበልኝ።

- አይደለሁም ብዬ መለስኩ።

- በቀጥታ ከየት መምጣቴን ሳይጠይቅ የመምህር ግርማን ተዐምር ለማየት ነው የመጣኸው? ብሎ የሰሞኑን ጣሊያንን ብቻ ሳይሆን አውሮፓን ያመሰውን ጉዳይ ጠየቀኝ።

- አይደለም አንተስ ? አልኩት ።

- ቆዳው የተላላጠውን እጁን(Psoriasis)እያሳየ ለዚህ ነው የመጣሁት። መምህር ግርማ ይህንን ያድናሉ የሚል ሰምቼ አለኝ።

-ታዲያ ያድኑኛል ብለህ ታምናለህ? ነበር ጥያቄዬ። በእውነቱ ባደረግነው ጭውውት ከበሽታው ለመዳን በመምህሩ ላይ  ያሳደረውን እምነት ተመልክቻለው። ለትንሽ ደቂቃ ቢሆን እግዜር እረድቶት ቢድን እንዴት የሚያስደስት ነበር።

 

ይህንን እውነተኛ ችግር ያለበትን ከተመለከትኩ በኋላ ከጀርመን ለዚሁ ጉዳይ የመጡ ብዙ አግኝቼ አነጋግሬ ነበር። ብዙዎቹ እውነተኛ በሽታ ሳይሆን የወሬ በሽታ ይዟቸው ነበር። ያንን ሁሉ ገንዘብ አጥፍተው ወሬ ለመቃረም መምጣታቸው ሳያስደንቀኝ አልቀረም። አዎ ለእነዚህ የወሬ በሸተኞች መምህር ግርማ መድሐኒት ቢያገኙ ኖሮ ስለ መምህር ግርማ ችሎታ የምስማው ታዕምር ግማሹም አይኖርም ነበር። በእውነት ከታመሙትና መፍትሄ ከሚፈልጉት ጋር የተጣላቻትን ጓደኛዋን በቡዳነት ለማሰደብ የሰፍር ሰው ሰብስባ፣ ቪዲዮ አስቀድታ ወደ መጣችበት ተፈውሳ የተመለሰች ሰው አጋጣሞኛል።

 

ጣሊያን በዜጎቻችን ችግር ተወጥራለች። ይህ ሳምንት ግን የታዕምር ነበር። በዚህም ሳምንት ሆነ በሌሎች በጣሊያን የግራዚያኒን ጉዳይ አንስቶ መወያየት ቢሞከር እንኳን አድማጭ አይገኝም። ተመልሶ ተመላልሶ ወደ መምህር ግርማ ታዕምር ይቀየራል።

 

ምን አልባት የአፊሌ ከተማ ከንቲባ ኢትዮጵያውያን ስለ ታሪካቸው ደንታ የላቸውም ያለው እውነት ይሆን?

 

 

ስለ ታሪካችን መከበር የሚታገሉ በሰላም ይክረሙ!

 

 

በልጅግ ዓሊ

beljig.ali@gmail.com

 

ሐምሌ – 2014 ሮማ

ገደል (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ 24.07.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ይድረስ ለአቶ አለማዬሁ አንበሴ ካሉበት።

እርእሱን የፈቀዳችሁት እናንተ ስለሆናችሁ እኔ ተጠያቄ አይደለሁም። ከርቤም ዝቅንቅም ይሁንላችሁ ብያለሁ የሰማዕቱ የዬኔ ሰው ገብሬ ሥጋ ጪስ …. ወይ ጠቅጥቁት ወይ ወደ ውስጣችሁ ይመልስላችሁ። ታሪክን ጥላሸት ማቅ አታልብሱት!

Gedel

ሰዉ ታሟል ወይ አዚም ተደርጎበታል – አላውቅም። ታዲያ ምን ልበል እንዲህ አራባና ቆቦ የሚያስረግጠው የጤናው ነውን? ወይስ ይህ አካል የሚባላው ነገር ሁሉ በወያኔ ተዘርፏልን? አሁን አሁንማ በጣም ጥርጣሬ የሚያስገቡኝ ብዙ ዕድምታዎች እዬተበራከቱ ነው። እኔ ነኝ ከእኔ ወዲያ ለነፃነት የሚለው የመጸሐፍ ቅዱስ ታሪክ የጦርነት ታሪክ መሆኑን ዘንግቶ „በጸሎት ብቻ ወያኔ ይወገዳል“ እያለ ትጥቅ ሲያስፈታ ታዩታላችሁ …. በሌላ በኩል ደግሞ ቢያንስ ልጆችን እናገናኝ አዋቂዎች በፖለቲካ ቢለያዩም ተብሎ መርህ የጣሰ በሳቢዮዎች ላይ አሸሼ ገዳሜ የሚል ብክነት ታያላችሁ፤ የዬኔ ሰው የገላው ጥብስ ሽታ ጠረን መንፈስ ውስጥ ተቀምጦ ሊነስት ሲጋባ እራስን በማሰናዳት በዕንባ ጥሪ ታድሞ ምን ተባላ ወይንም ኢሳት ምን አለ ከማለት እራስን ማሸነፍ ተስኖን – ሻታ!

ያቺ አንስት ባላቤትሽ መሳሪያ ደብቋል ተብላ ተወልዳ ባደገችበት – በኖረቸውበት ነፍሰጡሯ የባላቤቷን የመለያነት አካል በጥርሷ እንድትጎት መደረጓ እንደ ሰው እህል ቀምሶ ለማደር የሚያነገፈግፍ ግፍ መፈጸሙ የሰርግ ድንኳን ሆኖልን ይሆን? ያ ዓለም ሳያውቅ የመኖር መብቱን ተነፍጎ በግፈኞች ጽንሱ ህልፈት የተፈረደበት ደምና ሥጋ ተፈጥሯዊ  ዕንባም እንደ የምቾት ሽርሽር እያጣጣምነው ይሆን?  የጀግና የወ/አልጋነሽ ገብሩ ልጆች ወላጅ አልባ ሆነው ጎዳና ላይ መውጣታቸው ለእኛ ሞቅ ያለ 50 ክንድ ጋቢያችን ሆኖ ይሆን? የምወዳት ወይኔ ተቀጥቅጣ ጭንቅላቷ ተፍንክታ ስትሰፋ ካለመደንዘዣ ነበር ይህም ለእኛ ገነታችን ሆነን? በጡት ህመም በሽታ የምትሰቃዬው የርዕዮት የዬሰከንዱ ህመም ሞዝቦልድ አልጋችን ሆነልን? የውብሸት የኩላሊት ህመም ንጹህ አዬራችን ሆነን? የጀግናው አቶ አንዳርጋቸው ሁለተኛ ዬETV ጀርባ ያለው ያ መራር ያ ጥቁር ያ ሃሞት ያ ጎምዛዛ ያዳመጥነው የጣር ኡኡታ የወገኖቻችን የቀራኒዮ ድምጽ ሐሴታችን ሆኖ ይሆን እንዲህ የምናላግጠው? እንዲህ ዝምንምን የምንለው? እንዲህ ቅብጥብጥ የሚያደርገን? አላውቅም ብቻ … እም!

ለመሆኑ እንዴት አሉ አቶ አንበሴ ካሉበት። ጫታ ሰፍኗል በሃገሩን? ጫታ ነዎትን? እጅ ነሳን ለእርሰዎ – ለአካለዎት ብቻ። ለመንፈስዎ ግን አይደለም። ምክንያቱም መንፈሰዎት የገማ እንቁላልን ተዛመደኝ እያለ ጉዞ መጀመሩን ከጹሁፎዎት መንፈስ ስለ ተረዳን እኔና ብዕሬ – ያው ለነገርኩወት ለነገ አፈር ገላ ብቻ ለጥ ብለን መስገዱን መረጠን።

በአንድ ወቅትም እንዲህ ዓይነት ጠቃራ ነገር ነበር። ወራቱን አላስተውሰውም ብቻ ተዛነፍ መርዝን ያነገበ ጹሑፍ እርእሱን ብቻ አይቼ ለማንበብ አቅም አነሰኝ። እውነት ለመናገር ጤነኛው መንፈሴ አብዝቶ ተጸዬፈው። ከሩቁ ጠረኑ አይስቀርብም ነበር ይሸታል።  ለጎንደር ዘመን ዘለቅ የማንነት ንዑድ ብቃት ጥያቄ ይህ ዲዲት በቀል ጥንዙል አስተሳሰብ የማይምጥነው ስለነበረ። ዛሬም ገባ ብዬ ዘልቄ አላነበብኩትም። የማንበብ ግዴታም የለብኝም። ታሪክን አጋድሞ ያረደው እርእሱና መግቢያው በቂ ነበር።

እንዴት ነው „የቅማንትን“ ዓርማ ጋሼ ነጋ ፈርማሴው ላይ አላንጠለጠለ ሆኖ ይሆን ታላቁን የማንነት ዓርማ ከዚህ ከሚያቁስል የማንነት ክብር ገዳይ ፍላጎት ጋር ወስዳችሁ የቀረቀራችሁት? እናንተ አልማችሁ ለተነሳችሁበት የወያኔ የባንዳነት ፈል ሰንድቅዓላማችን አራንጓዴ ቢጫ ቀዩ ፈጽሞ አይመጥንም። በቃ እኮ ተሽንፋችኋል። በዜግነታችሁ ሳይሆን ሳንባችሁ የሚተነፍሰው በጎጥ መሽረፊት ነው – እፍረት! አፈርኩላችሁ!

ኢትዮጵያን ያህል ታላቅ ሐገር ያለው አንድ ህዝብ፤ ኢትዮጵያን ያህል ገናና ታሪክ ያለው ታላቅ ህዝብ፤ ኢትዮጵያን ያህል በወርቅ የተባ ትውፊት ያለው አንድ ታላቅ ህዝብ፤ ኢትዮጵያን ያህል ባላብዙ ህብረ ቀለም ባህል ያለው አንድ ታላቅ ህዝብ እያለ ከዚህ ማዕቀፍ ወጥቶ ጣሊያኖች፣ ቱርኮች፣ ፖርቹጊዞች፤ እንግሊዞች ባጠቃላይም የምዕራቡ ዓለም በሚፈልገው የውድቀት ረግረግ ውስጥ ገብቶ መዛገጥ ሳልፈጠር ከእናቴ ማህጸን ውሃ ሆኜ ቀርቼ በሆነ ያስብላል።

አሁን ቢዘህ ዘመን ያቺ ኩርማን የምታክለው – ከምክትል ወረዳ ያነሰቸው ጎንደር ዳር ድንበሯ ተጥሶ ለሱዳን ተሰጥቶ፤ በታላቋ ትግራይ ቅዠት እሰኪበቃው ወያኔ አንጡራ ሃብቷን ዘርፎ ትግራይ ለናሙና የተግባር የእድገት ት/ቤት ሆና በልማት አደገች ተብሎ የምንሰማው ዲስኩር ከዬት የተገኘ ይመስላችኋል? ከሰሊጥ – ከጥጥ ምርት ውጤት መሆኑን እያወቃችሁ፤ በመተማ በኩልም ተጎርዶ ለቤንሻጉል ተሰጥቶ በዘነዘናዋ ሆና በምታነባ ባዕት ይህም ተቀንቶባት ዛሬ እናንተ ደግሞ ሊቆረቁራችሁ – ሊያርመጠምጣችሁ – ሊያንገበግባችሁ – ሊያቃጥላችሁ የሚገባውን መሰረታዊ የሀገር ዳር  የሉዕላዊነት ድፍረት፣ የትውልድ ክስምት መሆን ሲገባው ሌላ ትውልድ ከቶውንም ይቅር የማይለው ነቀርሳ ለመትክል ከፍና ዝቅ ትላላችሁ። እፍረት!

አቬቶ ነጋ ፈርማሲ ለዚህ መርዝ ቡቃያ እኔ ነኝ ብሎ በግንባር መሰለፉ ያቺ ደግና ሩህሩህ ባለቤቱ አበጠርዬ ምን ልትል እንደምትችል አላወቅም። ምክንያቱ „ኢንተርናስዮናል የሰውዘር ይሆናል“ ብላ ከእኔ ጋር ዘምራለችና፤ እንዲህ ከዛቀጠ -ከሚያረግርግ መጠራቅቅ ገብታ ትቀረቀራለች ብዬ አላስብም። ብልህ መሆኗን ስለማውቅ አሁንም ጥረቷን ቀጥላ አቬቶ ነጋን ብታድነው እመርጣለሁ። ስለምን እኔ በግሌ ከባንዳነት ለይቼ አላዬውምና። እስከ መጨረሻውም ፊት ለፊት ወጥቼ እጋፈጠዋለሁ። እንዲህ በቀደምት አርበኞቻችን ታሪክ ላይ ተቀለዶ መኖር ሆነ ተከብሮ መኖር አይታሰብም።

የኢትዮጵያዊነት ፍረሰት የኢትዮጵያ ንደት፤ የትውልዱ ጥፋት መሰረቱ የወያኔ የጎሳ ማንፌስቶ ነውና። ይህን የሚደግፍ ይህን የሚያንቆለባብስ ሁሉ ለእኔ ባንዳ ነው። ወያኔ የሠራው የፈጠረው መርዝ እኮ ጊዜውን እዬጠበቀ እያዬነው ነው። የቀረ ምን ተቋም አለና? የፈራው አንድነታችን – ጥንካሬያችን  - ጉልበታችን ነው። የጥንካሬያችን የጉልበታችን የሃይላችን መሠረቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። ከዚህ ማዕቀፍ እስከአለን ድረስ ሁሉም አለን። ከዚህ ማዕቀፍ በትንሹ ፈቅ ስንል ደግሞ በራሳችን በውስጣችን ንደትን እናውጃለን። እንዲያውም ለወያኔ የኢትዮጵያዊነት አፍራሽ ዘመቻው እንደእናንተ ያሉ አጋፋሪዎች ናቸው የመጀመሪያ ረድፍ ተጠያቄዎች። ተግባባን? እሱ ብቻ አይደለም እጅግ በጣም ታሪክ ዘለቀ ትውፊት በሞዶሻ እዬከተከታችሁት ነው።

ጎንደር ሲፍረስ ጎጃም፤ ጎጃም ሲፍረስ ሽዋ፤ ሽዋ ሲፈርስ ወለጋ፤ ወለጋ ሲፈርስ ሐረር ወዘተ ነው …. የፍርስት ድምሩ ደግሞ እራስን ማጣት ነው። ካለአፈር ካለመኩሪያ ካላ መመኪያ። ካለ እናት … በረንዳ አዳሪነት።

እንዲህ የጫካ አራዊት በመንፈሳችሁ ላይ ሲጋልብ ፈቅዳችሁ ማስጋለባችሁ መንፈሳችሁ ከዬት ሊመደብ እንደሚችል ልባችሁን ለአራዊቱ አካልሸለማችሁት „ልብ ያለው ሸብን“ አዋህዱት።

እኛ ኢትዮጵውያን የወያኔ ማናቸውም ህጉ – ፖሊሲው – መርሁ – ፍላጎቱ – ህልሙን – ንክኪውን ሁሉ  በጣም ነው የምንጸዬፈው። የትግራይ ወያኔ ሃርነት ስርክራኪ ይቀርበናል ካላችሁ ቀጥሉበት። የቀደሙትን አያት ቅድማያታችሁን አጥንት በብረት ጫማ ቀጥቅጡት፤ ልጅ ያወጣላችሁ ከሆነ። ትውልድ ይተካላችሁ ከሆነ። ሀገር ቃሬዛ ላይ ሆና እናንተ „በ2007 የቅማንት ብሄረሰብ እራሱን ያስተዳድራል ብለን እናምናለን“  ትሉናላችሁ። ያሳፍራል። መጀመሪያ ሀገር ይኑራችሁ። ሀገራችሁ ተዋርዳ ሞቷን የምትጠብቅ፤ ሰኔልና ቹቻ የተዘጋጀላት፤ ክብርና ኩራቷ የተገፈፈ እርቃኗን ያለች ሀገር ናት። የመን ሀገር ሆና ነው የደፈረቻት። ሳዊዲ ሀገር ሆኖ የልጆቿን ደም አስፓልት ላይ አፍሶ የረገጠው። ሰንደቋን የተፋበት፤ ይህ  ለእናንት የሽርሽርሽር ጉዞ ሊሆን ይችላል።  ለእኔ ግን ደም የማምጥበት ዘመኔ ነው። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/32804

 

ለመሆኑ እንዴትና እንዴት አድርጋችሁ ነው ልታካልሉት የምትችሉት። ወገራ መግቢያ ጫፍ ላይ ያለውን ኮሶዬን፤ ጎንደር ድንበር ያለውን ወለቃን በምንና በምን ስሌት ነው ጭልጋ ካላው ጋር አካላችሁ ልትመሠርቱ ያሳባችሁት። ዕብን ናችሁ ልብል ከቶ? ተኝታችሁ ነው የምትሄዱትን? እንኳንም አለፉ እነዛ በዘመናቸው ተከብረው – ተወደው – ተጋብተው – አበልጅ ተናሰተው በአንዲት ኢትዮጵያ መንፈስ የኖሩት ግንዱ – ዋርካው ክቡር ካሰኝ አለማዬሁ። እንኳንም ይህን ጉዳችሁን ይህን ገመናችሁን ይህን ጃርት ያሰናዳላችሁን ጉዞ ሳያዩ አለፉ። ለነገሩ ቅኖች ስለሆኑ እንደ እኛው ዘመን ያሻከረው ልቦና ስላልነበራቸው ዕትብታቸው ከተቀበረው ማህበረሰብ ጋር ተመራርቀው ነው በሥጋ የተለዩት። አሁንም ነፍሳቸውን የሚወዱት ጥዋት ማታ ከደጁ የማይለዩት መዳህኒዓለም አባቴ አርያመ – ገነት ያስገባልን! አሜን።

አቬቶ ነጋን ደግሞ የነቀዘ ዘመኑን ተሸከሞ በቁሙ እያለ ፍርዱን አምላክ ይስጠው። ቀፎውን ያስቀረው። ድንቄም ሽልማት። እናውቀዋለን እኮ —- እጅግ የተከለከለውን ዬሙያውን ሥነምግባር ጥሶ ስንት ገመና ሲከዘን። „ጅብ ከማያውቁት ሀገር ሄዶ ቆርበት አንጥፉልኝ“ ይላል።

ዛሬ አቬቶ ነጋ ባልተፈጠራችሁበት፤ ባልኖራችሁበት፤ ገደል ላይ አንጠልጥሎ ታላቁን ክብራችሁን እንድታጡ የእኩይ ሙሴ ሆኗልና የእጁን ይስጠው። ለነገሩ እራሱን ለመግለጽ እንኳን አቅም ያልነበረው ሰው ነበር፤ እኔ ሳውቀው። ልጅ ሆኜም ወጣት ሆኜም ሳውቀው አንድ የረባ ቃል ሲተንፈስ ተስምቶ አያውቅም።

እርግጥ የሰጠ ቁመና እና ልዩ ግርማ ቢኖረውም የአደባባይ ሰውነቱ ከእሱ ይልቅ ባለቤቱ ወ/ሮ አበጠሩ አንቱ ነበረች። ሥነ ምግባሩ ግን እእ! የሚጎድለው ትልቅ ነገር ነበር። አንቱ ተብሎ የኖረውም በትዳሩ ነበር። ለማንኛውም በፃፋችሁት ላይ ከታች የጻፍኩት አስተያዬት እራህቤን ሊያስታግሰው ስላልቻለ፤ ሾልካችሁ ከምትቀሩ ወደ ራሳችሁ ትመለሱ ዘንድ ለመጻፍ ተገደድኩኝ። ምን ልትሆኑ እንደሚገባችሁ ደግሞ እኔ ሳልሆን  ያልባለቀው ደማችሁ ከእናንተ ጋር መሆኑን ካረጋገጣችሁ  ጠይቁት። ይነግራችኋል። እኔን የሚመራኝ ድንግሉ ደሜ ነው – እንደራሴ እንድሆንም ልዩ ጥበቃ ዘብ የሚያቆምልኝ – እሱ ነውና።

በቃችሁን! ጎጥ ላይ ተቀርቅራችሁ በኢትዮጵያ የነፃነት አርማ በሰንደቅዓላማችን አትነገዱ! ይህ ሰንደቅ የእናንተ ሊሆን ከቶም አይችልም። ዜግነታችን ኢትዮጵያዊ – ሀገራችን ኢትዮጵያ  ለሚሉት ብቻ የተሰጠ የሰማይ ሥጦታ ነው። መጀመሪያ ሥራ ላይ ያዋሉትም እቴጌ ምንትዋብ ነበሩ። ይህን ነው እናንተ ቤንዚን አርከፍክፋችሁ እያቃጠላችሁት ያላችሁት። ይህ ሰንደቅዓላማ የክብር መለያቸው ሊሆን እንዲገባ አሁንም ተኝታችሁ እሰቡት!

እንደመሸ አይቀርም። ብቻችሁን እንደምትቀሩ ደግሞ እርግተኛ ነኝ። የጭልጋን ገበሬ አሳምሬ አውቀዋለሁ። አንድ ቀን ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ጮንጮቅ በወያኔ ጥቃት ደረሰባት ብሎ ዘገባ ሲያቀርብ ለአካባቢው ህዝብ የምትቆረቆሩ ከሆነ ስለምን ዝምታን መረጣችሁ? እዬተለጉ እንለጋለን የሚሉት ጨዋታ እራስን ለግቶ ከጫወታ ውጭ ያደርጋል። የቀደመው ቀለማሙ ማንነት ይብልጥ ውበት አላው ከዛሬው የጎጥ ባንዳ በሽተኝነት። እኔም ለጮጮንቅ ገበሬ ስል ነበር አባቴን የገበርኩት። አዎን ….. ቁስሌን ህመሜን ዛሬ ልናገረው። ዛሬም እናንተ ሽህ ካድሬ ብታሰልፉ ክልትምት ብላ ከዛች ደሳሳ ጎጆው ኑሮውና ኑራ ያደራጀቻቸው እሙሃይ በአንድ መስምር ንግግር አፈር ታስግጠው ነበር የሰነቃችሁትን ቁርሾችሁን። አለመገናኘታችን ብቻ ነው እንዲህ ሠርግና መልስ የሆነላችሁ። እያንዳንዷን አጥቢያ፤ እያንዳንዷ ዳገትና ቁልቁለት፤ እያንዳንዷ ጋራና ሸንተረር ሥርጉተ ታውቃታለች። የመጀመሪያው የገጠር ሴቶች ማህበር የተደራጀበት ጭልጋ ላይ ነበር። ለጭልጋ ህዝብ ኩራቱ – ኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ነው።

 

ወገኖቼ የጹሑፌ ታዳሚዎች አንድ የማውቀውን ታሪክ ላጫውታችሁ። ጎንደር ከቤተ መንግሥቱ ጀርባ ጡረታ ሰፍር የሚባል አለ። በውትድርና ቆይተው በጥሮታ ከሥራ ሲገለሉ ከዬትኛውም የሀገራችን ክልል የመጡ አባቶች ቤት ሰርተው ጎጆ ፈጥረው ልጆች ወልደው የሚያሳድጉበት ማህበራዊ ኑሮ ቁሞ በእግሩ የሚሄድበት ድንቅ ቦታ። በከፍተኛ አንድ በቀበሌ ሶስት ይገኛል። አንዲት ደህና ኑሮ የነበራት የቴሌ ኮምኒኬሽን ባልደረባ ወ/ሮ እልፏ ትባላላች ቢነኳት የምታድፍ የምትመስል አበባ የሆነች ሴት አንድ የአውራጎዳን ባልስልጣን ካልተሳሳትኩኝ ደጉን አቶ ካሳን አግብታ በአጥር በተከለለ ትልቅ ቢላ ጡሮታ ሰፈር ትኖር ነበር፤

ጎንደር ሰው ሲሞት ወይንም መርዶ ሲኖር ባህሉ እሰከ ሰባት ቀን ሁሉም እያዋጣ በእድር ሆነ በተደራጃ ቡድን  ነገር በሃዘንኑ አብሮ ሁሉ ይታደማል። ታዲያ እመቤቲቱ ሃዘን ሲኖር እንጀራዋንና ወጡን እያሳያዘች ለቤት ሠራተኛ ትልክ ነበር። ሁሉን እኩል የሚያደርገው አቶ ሞት ከቤቷ መጣ። ደህና ሰው የነበሩት ባለቤቷ አለፉ። በቀብሩ ሁሉ ተገኝቶ እንደ አባት አደሩ ቀበረ። ማታ ግን ሠራተኛ ያለው በሠራተኛ፤ የሌለው በልጁ፤ ልጅም የሌላው የጎረቤት ልጅ እዬለመነ እማ ወራዋ ያሰናዳችውን እንጀራውና ወጡ ብቻ እዬተላከ ድንኳኑን ብቻዋን አስታቀፏት። ማን ያስተናብረው ያ በዬቤቱ ለሰባት ቀን የሚላከውን እንጀራና ወጥ፤ ማንስ ይታደምበት? አምሮ የተሰራው ድንኳኑ እርቃኑን ውሎ ያድራል። ከዛ በኋላ እሜቴ እልፏ እዬወጣች ሃዘን ላይ መገኘቱን ማን ቀድሟት።

ይህን ያነሳሁት ያለምክንያት አይደለም ነጋ ፋርማሲ ይኖር የነበረው የዛሬን አላውቅም ጡሮታ ሰፈር ሲያልቅ ዳገቱ ላይ ነው። በላሊበላ መንገድ አፋፉ ላይ ነበር ቢላው፤ ስለዚህ የእኔ ጀግኖች ሰላምታ ንፈጉት። መላ የጎንደር ከተማ ነዋሪም ፈርማሲው አንዲት መዳህኒት አትግዙት።

ውዶቼ የጹሑፌ ታዳሚዎች ይህችን ፌስ ቡካችሁ ላይ ለጠፍ አድርጉና ቁጣችሁንና ኩርፊያችሁን አሳዩት። አበጠርዬ ማለትም ባለቤቱ ከእኛ ጋር ከሆነች አሷም አቋሟን አስተካክላ ከእናነተ ጋር ከሆነች እንደ አባት አደሩ እግሯን ተሰብራ ለረጅም ጊዜ ሆስፒታል ተኝታ በነበረች ጊዜ እናደርግ እንደነበረው አድርጉላት። ከነጋ ፈርማሲ ጋር ከሆነች እሷንም እከሉ። በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞን በተግባር መግለጽ። ከማህበራዊ ኑሮ ማግለል ነው ታሪክን ሊያድን የሚችለው መንገዱ። ከኢትዮጵያዊነት ከሉዕላዊነታችን የሚበልጥ የለምና። የጥንት የጥዋቱ የአርበኛው መንደር ጡረታ ሠፈር ይህንን ያደርገዋል። ልኩን አሳውቁት የጋሼ ነጋን እሺ – ክብረቶቼ!

በተረፈ ለድውያን ወገኖቼ ደግሞ እግዚአብሄር ይማራችሁ። ጸበል የሚያስፈልግ ከሆነም ተጠመቁ። ያችን በአንኮላ „ስላህ“ የምታስፈልግ ከሆነችም በአንኮላዋ  ጎንጨት እያደረጋችሁ መላልሳችሁ ምከሩ።  ገደሉን ስትወዱ ተድርምሶ እንዳይውጣችሁ ገደሉን ሩጡና ቅደሙት። ታታሪ መሆናችሁን፤ ብልህ መሆናችሁን፤ ሥልጡን መሆናችሁን በሚገባ አውቃለሁ ታዲያ ለገደል ከሆነ ግን ግደለት ይሆናል ወፋችሁ! ወፏን አድማጭ አይደላችሁ? ጠይቋት። ጉዟችሁ ወፍ አላወጣውም። በመላ ዓለም ተበትኖ ያለው ወገናችሁ ሁሉ ይህቺን የሃቅ ፈለፈል ካነበበ በኋላ ለባንዳ ትብብር መንፈሱን እንማይሸልም ልብ ልክ ነው። ተዛነፋችሁ ….. በጣም …. ምነው ጋድም መንገድ አሰኛችሁ //// የጤና!!!!?

 

ክውና ምን ነበር አሁን ራዲዮ ፕሮግራሜ እረፈት የበጋ ብለው ከርችመውታል። የሆነ ሆኖ የቆዩትን ገባ እያላችሁ ማደመጥ ካሰኛችሁ www.tsegaye.ethio.info or www.lora.ch.tsegaye or Radio Tsegaye በዚህ እንገኛለን። ውድድ – ክብር – ፍቅር አድርጌ ውስጤን ሸልሜ ስንብት። ቸር እንገናኝ!

 

ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረው ምስጥር ኢትዮጵያዊነት።

 

  • ስላህ በቅማንትኛ ጠላ ማለት ነው።

 

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ገንዘብ ሲናገር ህግ ዝም ይላል!!!

$
0
0

ከጋሻው መርጊያ

የሰው ልጅ ነጻ ሆኖ እንደተፈጠረ ታላቁ መጽሀፍ እንዲህ በማለት ይገልጻል፡፡‹‹በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፡፡ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ፤እንደገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ›› ገላትያ 5፤1፡፡ የዚህ ጥቅስ ጭብጥ ሰው ነጻ ሆኖ ይኖር ዘንድ ክርስቶስ ዋጋ ከፍሎለታል የሚል ነው፡፡እውነታው ይህ ቢሆንም ቅሉ እያደገ የመጣው ማህበራዊ ግንኙነቱ አንዱ በሌላው ላይ አለቃ የመሆንን ዝንባሌ አሳዬ፡፡ አለቅየውም በበታቹ ይፈራና ይሰገድለት ዘንድ ህግ የሚሉት መጨቆኛ አወጣ፡፡ ይህ ህግ እንደ ዛሬው ዘመን ህግ ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው የሚል ሳይሆን እንደ ጆርጅ ኦርዌል የእንስሳ እድር(animal farm) ገጸ ባህርያት ‹‹ሰው ሁሉ እኩል ነው አንዳንድ ሰው ግን የበለጠ እኩል ነው›› የሚል አይነት ነው፡፡ በዚህ የአሸናፊና ተሸናፊ መስተጋብር ውስጥ አሸናፊው በተሸናፊው ላይ ቀንበሩን እየጫነ እርሱ እንደሚፈልገው እየነዳ፤ሲያሻው አሽከር አድርጎ እየገዛው ካስፈለገውም ባሪያ አድርጎ ሲሸጠው እና ሲለውጠው እንደኖረ የሰው ልጅን የማህበራዊ እድገት የፈተሸ ሁሉ ያውቀዋል፡፡ ተፈጥሮ እንደ ጎልያድ ግዙፍ እንደምታርግ ሁሉ እንደ ዳዊት ልባምነትንም ታጎናጽፋለች፡፡ እንደ ጥንት ኢትዮጵያዊያን አትንኩኝ ባይነትን እንደምትሸልም ሁሉ እንደ ዘመን ተጋሪዎቸ ፍርሃትንም ታጎናጽፋለች፡፡ በዚህም የተፈጥሮ መሰናሰል ጉልበታሙ ገዥ በደካማው ተገዥ ላይ የግዛት ቀንበሩን ሲጭንበት እዚህ ዘመን ደረስን፡፡ ፈረሱ እስካልደነበረ ድረስ ጋላቢው አለመሰልቸቱን ማን ይዘነጋዋል፡፡ የታዘለ ልጅ የከተማውን ርቀት ሊረዳ አይችልም እንደ ማለት ይሆናል፡፡

በዚሁ የሰው ልጅ የአሽከርና ጌታ ግንኙነት ከላይ ያለው ተንደላቆ ይኖር ዘንድ የታችኛው ትክሻውን አደንድኖ፤ጉልበቱን አበርትቶ መሸከም ግድ ይለዋል፡፡ በነገራን ላይ አንዱ ገዥ ሌላው ተገዥ ለመሆን መስተጋብር መፍጠሩ እራሱ በሰውኛ እሳቤ ግርምትን ያጭራል፡፡ ለነገሩ የሚገዛለት እስካገኘ ድረስ ገዡ ምን ከዳው፡፡ መግዛት አይሰለች፡፡ ማዘዝ አቀበት(ዳገት) የለውም ይላሉ አባቶቻችን፡፡ ተገዥው እንደ እርሱው በአምሳሉ ለተፈጠረ ሰው አሽከር ለመሆን ሲወድ ማየት እና መገዛትንም እንደ ቁም ነገር በመውሰድ <<እኔ የእንትና አሽከር›› ብሎ ብሎ መፎከሩ ገራሚ ነው፡፡ ከራሱ አልፎ ‹‹ልጀ የእንትና አሽከር ነው›› ሲልም ሊኮፈስ ያምረዋል፡፡ በቆየው ዘመናቻን አባቶች ልጆቻቸውን ለነገስታት እሽከርነት ለመስጠት ይሽቀዳደሙ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ለነገሩ አሁን ላይ የእኔ ዘመን ተጋሪዎች ራሳችንን አሽከር ለማድረግ ስንደክም ሲታይ የአባቶቻችን ብዙም ላይደንቅ ይችላል፡፡ የሀገሬ ህዝብ በገዥና ተገዥ መስተጋብር በአለም አንደኛ ነው ብየ ብናገር ውሸታም የምባል አይመስለኝም፡፡ እነዚያ አትንኩኝ ባይ አባቶቻችን ለውጭ ጠላት ረመጥ ሆነው እንዳለበለቡት ሁሉ ለውስጥ መዥገሮች ግን ለስላሳ ነበሩ፡፡ ይህ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ባህላችን ጠርንፎ ይዞን አለም በስልጣኔ የት በደረሰበት በዚህ ዘመን እንኳን የተፈጥሮ ኡደት እስኪመስለን ድረስ መገዛትን አሜን ብለን እንቀበላለን፡፡

Azebbየኢህአዲግ መንግስት ሀገረ ኢትዮጵያን ዘውዱን ጭኖ ኮርቻውን አደላድሎ፤እርካቡን አስተካክሎ፤ይጓሙን ሸብቦ፤በአዞ አለንጋ ሾጥ እያደረገ ካሰገራት ይሄው ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ፡፡ በኢህአዲግ የስልጣን ዘመን የተወለዱት ወጣቶች ሳይቀር የስርዓቱ ቀንደኛ ተቃዋሚዎች እስኪሆኑ ድረስ ጉልበታሙ ስብስብ አሰራሩን ሊያሻሽል ፈቃደኛ አለመሆኑ የተገዥዎቹን ትዕግስት የስርዓቱንም ‹‹ስልጣን ሙጥኝ›› ለትዝብት ይዳርገዋል!!:: ይህን ክፉ ልማድ ዘወር ብሎ ለሚያየው የእኛን ትዕግስት ብቻ ሳይሆን የኢህአዲግን የሩብ ክፍለ ዘመን ስልጣን አለመጥገብም ይታዘብ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ስለ ኢህአዲግ ዘልዛላ የስልጣን እድሜ ከአንድ ወዳጀ ጋር እናወራለን፡፡ ይህ ወዳጀ እንዲህ ሲል በትዝብት መልክ ኢህአዲግን አሽሟጠጠልኝ፡፡ ኢህአዲግ ዲሞክራት ቢሆን እንኳ ለሩብ ክፍለ ዘመን ስልጣን ላይ ሙጥኝ ማለቱ በራሱ ወንጀል ነው፡፡ እስኪ አስበው ይላል ይህ ወዳጀ ኢህአዲግ ምኒልክ ቤተ-መንግስትን ከተፈናጠጠ ታላቋን አሜሪካን ስንት መሪዎች መሯት? የታሪክ ማጠንጠኛችን በኋላ ማርሽ አሽቀንጥረን ከተጓዝን ለዚህን ያክል ጊዜ እንዲህ ተበድለን ኑሯል ያስብላል፡፡ እዚህ ጋር የሚመሳሰል የአንድ ሰውዬ ታሪክ ትዝ አለኝ፡፡ በአዲስ መስመር እንመለስ፡፡

ሰውየው ባልንጀራው በጣም ይበድለዋል፡፡ ተበዳይም በደሉምን መሸከም ያቅተውና በባልንጀራው ላይ ክስ ለመመስረት ይወስናል፡፡ ተበዳይ ራቦል ጸሃፊ (ክስ አቀነባብሮ ጸሀፊ) ዘንድ ይሄድና በደሉን በዝርዝር አንድ በአንድ እየነገረ ያጽፈዋል፡፡ ክስ ጸሀፊውም እያንዳንዷን ጉዳይ በሚያምር ቋንቋ ክሽን አድርጎ ከጻፈለት በኋላ በንባብ እንዲያሰማው ይስማማሉ፡፡ ተበዳይም አንድ በአንድ ራሱ እየነገረ ያጻፈውን የክስ ዝርዝር በንባብ ሲሰማው ሲቅስቅ ብሎ ያለቅሳል፡፡ በሁኔታው የተደናገጠው ክስ ጸሃፊ ምን ሆኖ እንደሚያለቅስ የግል ተበዳይን ይጠይቀዋል፡፡ ከሳሽም(ተበዳይ) ‹‹ለካ ይህን ያክል ተበድዬ ኖሯል›› አለ ይባላል፡፡ ይህ ታሪክ ከኢትዮጵያውያን ጋር በቀጥታ ተመሰሳይነት አለው፡፡ በደላችንን ሳስታውስ ለካ ይህን ያክል ተበድለን ነበር እንድል ያደርገኛል፡፡ ዘመን ዘመነኛ ጨቋኞችን እያስነሳ በግፍ ላይ ግፍ ሲደራረብ እዚህ ደርሰናል፡፡ የግፉ ጽዋ በምድረ ኢትዮጵያ ሞልቶ ቢፈስም ፈውስ ማግኘት ግን አልቻልንም፡፡ የኢትዮጵያ እናቶች እንባ ጸባኦት ደርሶ የአምላክን ቁጣ መቀስቀስ አልቻለም፡፡ ዘመነኛው ጨቋኝ <<ብሶት ወለደኝ›› የሚለው ኢህአዲግ እርሱን ከወለደው በላይ የሆነ ብሶት አስረግዞናል፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ለክብራቸው ሲሉ መስዋዕት የሚሆኑ፤ለውዷ ሀገራቸው ሲሉ የግፍ ጽዋውን የሚጎነጩ፤በሰላማዊ ትግል ከሀገሪቱ እምብርት አዲስ አበባ እስከ ኢትዮጵያ ጫፍ የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ዱሩ ቤቴ ብለው ኢህአዲግ በሚያውቀው ቋንቋ ውረድ እንውረድ ብለን እናነጋግረዋለን የሚሉና ሽፍታው ህወሀት የተከተለውን የስልጣን መፈናጠጫ መንገድ የጀመሩ አልጠፉም፡፡ በአሁኑ እንቅስቃሴያቸው የሁለቱም ትግል ግን የኢህአዲግን መንበር በቀላሉ የሚነቀንቀው አይነት አይደለም፡፡ ዱሩ ቤተ ያሉት ይህን ያክል ዘመን አንድ ወረዳ እንኳን ነጻ ሳያወጡ ለኢህአዲግ የአፈና ስርዓት መጠናከር የራሳቸውን ድርሻ ከመወጣት ያለፈ ፋይዳ ሲኖራቸው አይታይም፡፡ ግንቦት ሰባት ካሰባሰበው ሽምቅ ተዋጊ ይልቅ ኢህአዲግ ግንቦት ሰባት ብሎ ቃሊቲ ያወረዳቸው ሰዎች በቁጥር ይልቃሉ፡፡ አሁን አሁን አመራሩም አልቀረለትም፡፡ ኦነግ ሚኒሶታ ሆኖ በጮኸ ቁጥር እስር ቤቱ ሁሉ በኦሮምኛ ተናጋሪ ይጥለቀለቃል፡፡ የድርጅቱ ጀማሪዎች እንኳን የማያስታውሱትና እስትንፋሱ ህቅ ብላ የጠፋችው አርበኞች ግንባር እንኳን ስንቱን የጎንደር ወጣት ለመግረፍ አገልግሏል፡፡ የሕወሀት የጡት አባት የሆነው ሻዕቢያ እንኳ ሳይቀር ‹‹የሻዕቢያ ተላላኪ ለሚል›› መወንጀያነት ታገለግላለች፡፡ ፈረንጆቹ አንድን ነገር ለማድረግ ወይም ላለማድረግ ከፈለግክ ሁሉም ነገር ምክንያት ነው እንደሚሉት አይነት፡፡ አካፋውን ለባልንጀራው ላለማዋስ የፈለገ ሰው እንዲህ አይነት ምክንያት ቢሰጥ እንደማለት ነው፡፡ አካፋየን አላውስህም ምክንያቱም ‹‹ነገ የቻይና ነጋዴዎች ከአሜሪካ ነጋዴዎች ጋር የምክክር ጉባኤ ስላላቸው›› አይነት ያልተገናኝቶ ምክንያት፡፡

በሌላ ረድፍ ብሶቱ ያንገሸገሻቸው ኢትዮጵያውያን በየአቅጣጫው የኢህአዲግ ግፍ እየተጋቱ ይገኛሉ፡፡ በየ ማጎሪያው ያለውን የግፉ ዘግናኝነት አይደለም ለመክፈል ለመስማት እንኳ ከባድ ያደርገዋል፡፡ ከፖለቲከኛ እስከ ጋዜጠኛ፤ከሀይማኖት መሪ እስከ ተማሪ ድረስ በየስርቻው የኢህአዲግን ዘግናኝ ጽዋ የሚቀምሱ ኢትዮጵያውያን እስር ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡ በጣም የሚያሳዝነውና እንደ ሀገር የሚያሽማቅው ደግሞ ወላጆቻቸውን በእስር ምክንያት ያጡ ህጻናት የሚማሩበት ደብተር እንኳ ሲቸግራቸው ማየት ነው፡፡ ለዚህም እንደ ማሳያ የምወስደው በአንድ ወቅት ከጓኞቸ ጋር በመሆን የተወሰኑ የሕሊና እስረኞችን ቤተሰቦች ለመጎብኘት ሙከራ አድርገን ነበር፡፡ የእነዚህ የህሊና እስረኞች ልጆች በሚያሳዝን አኳሃን ፍዝዝ ብለውና አመድ ውጧቸው ማየት እንዴት ያማል መሰላቹ፡፡ ያለ አባት እንዲያድጉ የተፈረደባቸው ህጻናት ነገ የሀገራችን መልካም ዜጋ የማፍራት ምኞታችንስ ምን ያክል ያሳካል፡፡ በአንድ ወቅት የአቶ አስገደ ልጆችን መታሰር ምክንያት አድርገው ፕሮፌሰር መስፍን በአንድ ጋዜጣ ላይ ከኦሪት ዘመን የባሰ ህግ ብለው ነበር፡፡ በኦሪት ዘመን እንኳን አባት ባጠፋ ልጅና ቤተሰብ አይጎዳም ነበር፡፡ ከኦሪት የባሰው ኢህአዲግ ግን እስክንድርን አስሮ ልጁ ናፍቆትን ማሳደጊያ ያሳጣዋል፡፡ ቤት ንብረቱን በመውረስ ጎዳና ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል፡፡ መቸም ይህን መረን የለቀቀ አምባገነንነት አንዳች የሚገታ ታኮ ካልተደረገለት የማያሳየን የግፍ አይነት አይኖርም፡፡

በአንድ ወቅት በእኔ ህግ መተላለፍ ሳይሆን በኢህአዲግ ፍርሀት ምክንያት ለሁለት ሳምንታት ያክል ታስሬ ነበር፡፡ በእነዚህ የእስር ቀናት ውስጥ ያዬሁትን አፈናና ለአቅመ ችሎት የማይደርስ ውሽልሽል ክስ በኮሜዲ ድራማ እንኳን ያጋጥመኛል ብየ አስቤው አላውቅም፡፡ ‹‹የታሸገ ውሃ እናስገባለን ብለው ጠይቀዋል›› የሚል ክስ እስከማቅረብና ዳኛውም እህ ብሎ በመስማት ለማጣሪያ ብሎ የሶስት ቀን ቀጠሮ ሲሰጥ ሳይ በእስር ቤቱ ግድግዳ ላይ ተጽፎ ያየሁትን ‹‹ገንዘብ ሲናገር ህግ ዝም ይላል›› አይነት አባባል እውን ሆነልኝ፡፡ እስከተከፈላቸው ድረስ ህሊና ለሚባለው ነገር ግድ የሌላቸው የጸጥታ አካላት፤ክፍያቸውን እንጅ ቃል የገቡለትን የዳኝነት ስነ-ምግባር የማያስታውሱ ጥቁር ጋዎን አጥላቂ ዳኞች፤ከሀገር ደህንነት ይልቅ የግለሰብን ስብዕና ለመጠበቅ ሲታትሩ የሚስተዋሉ ደህንነቶች ከምድረ ኢትዮጵያ ውጭ ከወዴት ማግኘት ይቻላል፡፡ ተቃዋሚነትን እንደ ጠላትና የሀገር ጠልሰም ፈርጆ የሚለፍፍ ስርዓት፤ከሀገር ልዕልና ይልቅ ስልጣን የሚያሳብደው መሪ፤ከሁለትዮሽ ጥቅም ይልቅ መጎናበስን የተከተለ የውጭ ግንኙነት እና ህልቆ መሳፍርት የሌለው ግፍ የሚፈጸምባትን ሀገሬን ለመታደግ ለምን ዝም አልን፡፡ ፈሪዎች ስለሆን ይሆን ወይስ ‹‹ገንዘብ ሲናገር ህግ ዝም ይላል›› የሚለው አባባል እኛንም ስለሚመለከት፡፡

ኢትዮጵያ ትቅደም!!!

የኣንድነትና መኢኣድ ውህደት ኣብነት ይሁን ለ ኦነግ፣ ሸንጎ፣ ግንቦት 7፣ ሰማያዊ፣ ሌሎችም፦

$
0
0

በወለየሱስ

የኣንድነት እና  መኢኣድ ውህደት ፍጹም ጽናት በተሞላበት ኣቓም ጸንተው እዚህ ደርሰዋል። በኢህኣዴግ ስር ሁኖ እዚህ መድረስ ምን ያህል ፈታኝ መሆኑን ተገንዝበን የሚገባውን ድጋፍ ለመስጠት የኛ ፈንታ መሆኑን ላስታውስ እወዳለሁ። ዛሬ 8/1/2014 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰነድ ዝግጅት፣ የጠቅላላ ጉባኤ ጠሪ፣ የሕዝብ ግንኝነት፣ የመድረክ ዝግጅት እና መስተንግዶ፣ የሕግና ጸጥታ እንዲሁም የፋይናንስ ንዑስ ከሚቴዎችን ማቋቋማቸው ገልጸዋል። ግን ኢህኣዴግ የህዝብ ገንዘብ ኣሰራጭቶ ሳይበታትናቸው ኣለንላችሁ የሚል ከኛ የተጠናከረ ድምጽ ማሰማት ይጠበቃል።

በግለሰቦቹ ለሚወሩት ጆሮ ኣንስጥ። እዚህ የደረሱት ድምጽ ኣግኝተው እንጂ በሩጫ ኣይደለም። ያጠፉት ጥፋት ካለ የድርጅታቸው ኣባላት ይቀይርዋቸው፣ ኣልያም ኢህኣዴግ ካወደቁት በኃላ ድምጽ ሳይሰጥ እንዲሸነፉ ማድረግ። መንግስቱ ሃይለማርያምም ድምጽ ይዞ ከመጣ ይምጣ ኢህኣዴግ ይወገድልን ከዛ በሽግግር ሂደት በድምጽ ማቅረት። ማን ከማን ንጹህ ሁኖ ነው እና እንዲህ ነበር እያልን የራሳችንን ደብቀን በሌሎች እንቅፋት እየሆን የኢህኣዴግን እድሜ የምናራዝም ያለነው።

በውጭ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተመሳሳይ ኣብሮ የመስራት ኣንድነት ማሳየት ኣለብን። ኣንድ ድርጅት ለብቻው የትም እንደማይደርስ ማመን ኣለበት፣ ቢሆን ከኦነግ የበለጠ ማን ነበር እና ግን ኢህኣዴግ እንደማያሳልፍ ተገንዝበን ኣንድነት መፍጠር ግን ኢህኣዴግን ያንበረክከዋል፣ ይበታትነዋል፣ ህዝብ ተስፋ ኣግኝቶ ሆ ይላል፣ ኣወንታዊ ስራ ለመስራት ይመቻል።

ኦነግ፣

ሸንጎ፣

ግንቦት 7፣

ሰማያዊ፣

ኣንድነት (የኣመሪካ)፣

የኣፋር ኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ኣንድነት ግንባር፣

ዴሞክራስያዊ ምንቅስቓስ ህዝቢ ትግራይ፣

የኢትዩጵያ ድርበር ጉዳይ ኮሚቴ፣

የኢትዮጵያ ሕዝብ ኣርበኞች ግንባር፣

ሌሎቻችሁ ተሰባሰቡና ህብረት ፍጠሩ።

በነጻ ኣገር ሕግ የመላይነት ባለበት፣ በጠሬቤዛ ዙርያ መስማማት ያልቻላችሁ እንዴት ነው 90 ሚልዮን ህዝብ ለመምራት የምትችሉ? የግል እውቀትና ልምድ ሊኖራችሁ ይችላል ግን ኣብሮ የመስራትና ኣገር የመምራት ብቃት ልምድ ግን ኣላየንም ወይስ እንደ ኢህኣዴግ ወደ ዘር ትውልዳችሁ ብቻ ነው ግባችሁ። እንዲህ ከሆነ ኢትዮጵያ እያላችሁ ኣታላይ ኣትሁኑ። ኢትዮጵያ ግዙፍ እና ጥልቀት ያለባት ህዝብ መጠርያው ኣታኮላሹት።

ለምን  በሃሳብ ተለያይተው የተገዳደሉትን ትምህርት ኣይሆነንም፤ መኢሶንና ኢህኣፓ፣ ኢህኣፓና ወያኔ፣ ሻእቢያና ጀብሃ፣ ኢድዮና ወያኔ፣ ኢህኣፓ በሁለት ሲከፈሉ፣ ቅንጅት ሲበታተኑ፣ ወዘተ ምን ነው ከስህተት ተምረን፣ ይቅር ተባብለን፣ በሕግ የሚጠየቅ ለዳኝነት ትተን፣ ኣወንታዊ ስራ ለመስራት ህዝባችንን ለማበልጸግ ኣናደርግም።

ትምክህቱን ተው እና የሃይማኖት ኣባት ወይም የጭንቅላት ሃኪም ማማከር ያስፈልጋል። ምርጫ 3007 ከመድረሱ በፊት፣ ኢህኣዴግ በኣንድነትና መኢኣድ ገብቶ ሳይበታትናቸው፣ በውጭ ያላቹሁ ተቃዋሚ ማእከላይ ኣመራር ተሎ ምስርታቹሁ የውጪዊን የዲፕሎማሲ ስራ መስራት እና ለሃገር ህዝብ ተስፋ ሆኖ መገኘት የምርጫ 97 ትርኢት ሊደገም ይችላል። ከዘር በሽታ ወጥተን ሃገራዊ ምንነት ኣስቀድመን የጣልያን ሽንፈት በባንዳዎች እንድገመው።

 

Comment

 

 

የጨረቃ ፈስ። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

የቀልዱ ጎጆ የድቡሽቱን ህልምን ይደረምሳል።
ሥርጉተ ሥላሴ 02.08.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ክፍል – አንድ።

አዬነው ሰማነው ጉዳችሁን። እንዲህ መንፈስን ማሰራችሁ አልበቃ ብሎ ደግሞ የኤሉሄ ስቃዩን ዓለም እንዲታደምበት ማደረጋችሁ አሳምሮ ገማናችሁን የአደባባይ ሲሳይ አደረገላችሁ —– ጅልነታችሁን ሆነ ጭቃነታችሁን ጫካ እያላችሁ „ማሌሊት ያሸንፋል እያላችሁ“ በአይነ ምድራችሁ የምትጽፉ ገለባዎች መሆናችሁን ስለምናውቅ „ለማያውቅሽ ታጠኝ“ እንላለን – ለእነ አይሁድ። አሪዎሶች!

አሁን በዚህ ሽርክት ዘገባችሁ አንዳርጋቸውን የመሰለ ዕንቁ የነፃነት ፈላስማ ሰብዕናውን ያዋረዳችሁ ሊመስላችሁ ይችል ይሆናል። ይህ ቅንጥብጣቢ ግርድፍ ቅንብር እራሳችሁን ማበሻ ጨርቅ ነው ያደረጋችሁ። አንድ የብዕር ወዳጄ „ወያኔ ለአቅመ አዳም ያልደረስ ድርጅት ነው“ ያለውን ስመረምረው እውነት ነው። አቅማችሁም አቅላችሁም አይፈቅድም። ኢትዮጵያን ያህል ታላቅ ሀገርና ህዝብን ለመምራት እንዴት ትችሉ?  ለነገሩ አቅማችሁን ስላወቃችሁም ነው ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥማችሁ ፈቅ ለማለት የተሳናችሁ። ሰሞኑን ደግሞ የቤት ሥራችሁ ሆኖ ለመቀዬር ካልተንደፋደፋችሁ። አይቻችሁ አለሁ እኮ በሴቶች ጉዳይ ጠንከር ያሉ ወቀሳዎች በ2014 ሲቀርቡ በ2012 እንቅልፍ መዳህኒት ወስዶ ለሽ ያለውን ዬጠ/ሚሩን ወንበር የሸንበቆ ድጋፍ በአምአሳላችሁ ስታወቅሩ ትዝ ሳይላችሁ በ2014 ም/ጠሚር ሴት ለዛውም መቅድም የሆነችውን ስትሉ ተደመጣችሁ። በማግሥቱ በዩንቨርስቲ ተማሪ ሴቶች ላይ፤ በጋዜጠኛ ሴቶች ላይ፤ በብሎገር ጦማርያን አንስት ላይ፤ በፓርቲ አመራር ሴቶች ላይ የለመዳችሁትን የአራዊትነት ተግባር ስትፈጽሙ ም/ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይሰማሉ እልም – እልም – እልም – እያሉ -

እውነት ህዝብን የመምራትና የማስተዳደር ኣቅማችሁ ወርደ ጠባብ ነው። ብናኝ ጸጋው የላችሁም። ከላይኛውም አልተሰጣችሁም። እኔ ከእናንተ ይልቅ „ኢህአድግ“ እያሉ የሚያንቀባርሯችሁን ሆነ „መንግሥት“ እያሉ የተነፋ ባዶ ትቦነታችሁን ለሚዘክሩ ሁሉ አዝንላቸዋለሁ። ምክንያቱም ጫካ በነበራችሁበት ጊዜም ሆነ በሰርጎገቦቻችሁ ባገኛችሁት ዱካ ውንብድናችሁን አሳምሬ ስለማውቅ፤ ተፈጥሯችሁ እስክትከስሙ ድረስ ሆነ ተቃጥላችሁ አመዳችሁ ቢቀበርም „መንግሥት“ „ኢህድግ“ ብዬ አልጠራችሁም። አይገባችሁማ!

ሽፍታ ናችሁ። ኪስም መንፈስም አውላቂ። ወንበዴ ናችሁ – ዘራፊ። „መንግሥት“ አይደላችሁም የማፍያ ቡድን ናችሁ። ስለዚህ መጀመሪያ በነጠረ ቋንቋ የነፃነት ትግሉ አቅም ባለው ጸዕዳ መንፈስ የሚገኘው ወገን፤ ድርጅት ሁሉ ግልጽ የሆነ መስምር ሊከተል ይገባዋል ባይ ነኝ። በተቆርቋሪነት በሚጻፉ – በሚዘገቡ – በሚዘከሩ ልዩ ዝግጅቶች ሁሉ ሊጠነቀቁበት እንደሚገባ አበክሬ በአጽህኖትና በአክብሮት አሳስባለሁ። ማናቸውም የመንፈስ ምርት አዬር ላይ ከመዋሉ በፊት ይፈተሽ ዘንድም በትሁት ሥነ – ምግባር እጠይቃለሁ። በህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የሚወጡ ፖስተሮች ሆኑ በራሪ ጹሑፎች ሁሉ የተገባውን የኤዲትንግ ተግባራቸውን በሚገባ ከጨረሱ በኋላ መሆን ይኖርበታል ለአደባባይ መብቃት ያለባቸው። እንዲያውም እንደ እኔ ማዕከላዊ የሆነ መስመር ቢኖር እመርጣለሁ። ስለምን? እኔ እራሴ የምቆስልበት ስለሆነ። ገንዘቤን – ጊዜዬን – ጉልበቴን እማፈስበት „የሽፍታ አስተዳደሩን ወያኔን እኩይ ኢ-ሰብዕዊ  ተግባርን ተቃውሜ ነው“ ስለዚህ እንደ ደላው ሰው ሁለመናዬን በሞስኮት መበተን አልሻምና። በማያተርፈኝ የግማሽ ጥገና ልስልስ ያለ ዬተቃውሞ ሰልፍና ስብሰባ መገኘት እራሴን የመግደል ያህል ይስማኛል። በዕንባንም መቀለድ።

„ኢህድግ“ ለማለት በእያንዳንዷ ሥነ – ሀገራዊ እንቅስቃሴ አባል ድርጅቶች መምክር መወሰን – ማጽደቅ ሲችሉ ነው። ይህ ደግሞ በወያኔ ቤት አይታሰብም። ለእንጉልቻው የተሰዬሙት ጠ/ሚር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በታሪካችን እኮ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ምርኩዝ የተዘጋጀላቸው፤ እራሳቸውን ችለው የማይቆሙ ሽባ ጠ/ሚር ብሎ ወያኔ እራሱ ሥም ሰጥቷቸዋል። ቦታው ያስገድድ ስለነበር ወንበር ጠባቂነት ነው የተሰጣቸው። ይሄው ማዕረግ መስሏቸው ፍንጭታቸውን ብልጭ እያደረጉ በዳዴ ይኳትናሉ። መጥኔ!

በተዘጋ አንደበት – በታሰረ መብት – በታፈነ ሃላፊነት ነው በስላቅ ፈገግታ እንዲያረግዱ የሚያደርገው  – ለወያኔ። ስለሆነም አባል ድርጅቶች ጉልቻነታቸው አንደበቱን ከፍቶ መብቱን ማስከብር ሲችል የወልዮሽ መጠሪያ ይገባል።

የሆነ ሆኖ የእስታሁኑ በምህረት ይታረቅና ቢያንስ ከእንግዲህ በድርብ ስለት እጥፍ የበቀል እርምጃ እያዬን – እዬሰማን ስለሆነ ቀጥ ባለ አቋም ለደጋፊ ወይንም ተባባሪ መንግሥታት ሀገራት መሪዎች ሁሉ ኢትዮጵያ በሽፍታ ቡድን እዬተመራች ያለች ስለመሆኗ ውስጣችን አምጦ እንዲወልደው የግድ መታገል አለብን። ወያኔ የተጠቀለለበትን ምስጣዊ ሸንኮፉን ወይንም ክንብንቡን መግፈፍ ያስፈልጋል! እራሱን መለመላውን ገላልጦ እርቃኑን ለህዝብ ዕይታና ፍርድ ማቅረብ የግንባሩ ተግባራችን መሠረታዊ አካል ሊሆን ይገባል።

እራሱ „ወያኔ መራሹ“ የሚለውም የሚያስኬድ አይመስለኝም።  አይመችም። በጣም አሻሚ ትርጉም አለው። ብጣቂ አዎንታዊ አምክንዮች አሉበት። ፍርፋሪ ብናኝ የኢትዮጵያዊነት ጠረን በሌለበት ሁኔታ „ኢትዮጵያን“ „ኢትዮጵያዊነትን“ ለመደርመስ የተሰበሰቡ ድርብ የባንዳ ባለሟሎች ስብስብ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በጠራ መሥመር ትወና ላይ እያለ ይህንን እውነት የምንሸፍንበት ካሊም የሚያስፈልግ በፍጹም አይመስለኝም። ወገኖቻችንም ይህንን ጠንቅቀው እንዲያውቁ ማድረግ አለብን። ጠላትን ሳያውቁ ጥይት መተኮስ ባሩድን ማክሸፍ ይሆናል። ይህ ደግም የመሸነፍ የመጀመሪያው መግቢያ በር ነው። ይህ ከወያኔ ጉያ ውስጥ ሆነው ራሳቸውን ቀብረው ላሉት ትሎች ሁሉ ማርካሻ መንገዳችን ነው። ጥዝጥዝ ያደርጋቸዋል። ያርመጠምጣቸዋል። እሾኾች የሚፈሩት ነገር ተለባብሳ የኖረችው ቅብ ሽሙንሙን ገማና ደፍረን ስንዘምትባት ያን ጊዜ የድልና የተስፋን ዕለት ቢያንስ ማለም ይቻላል —-

ሌላው „መንግሥት“ የሚለው ነው። መንግሥት ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲካዊ ፍልስፍናዊ ትንታኔውን ትቼ በተለምዶው ትርጓሜ ሲፈታ ለአንድ ህዝብ መንግሥት ማለት እኮ ከፈጣሪ በታች ያለ በፈጣሪው የተቀባ – የተፈቀደለት  ጠበቂ – እረኛ – ወላጅ – ተንከባካቢ – ተቆርቋሪ – የህዝብ ሎሌ – የህዝብ ፍቅር የመረጠው – መንፈስ የፈቀደው ማለት እኮ ነው። አስተውሉ ወገኖቼ የኔዎቹ ፉከራ አይደለም ከልባችሁ ሆናችሁ አዳምጡኝ ማለቴ ነው። ከፈጣሪ አምላክ በታች የጸጋ ስግደት ተፈቅዶና ተወዶ የሚሰገድለት ማለት ነው መንግሥት፤ የሚሰጠው አክብሮትም ከልብ ነው። ጨዋ የሆነ – ሥርዓት ያለው – ፈርሃ እግዚአብሄር ያለው – የህዝብ አገልጋይ – የህዝብ ብሶት ሰሚ – የህዝብ ዕንባ ጠባቂ  – የዜግነት ወታደር – የሀገር ወደር የለሽ ፍጹም አብነታዊ ተቆርቋሪ የልዐላዊነት ሰንደቅ ማለት ነው።

ታዲያ ይህ ዬአራዊት ቡድን በ21ኛው ምዕተ ዓመት ላይ የሰው ልጅን የማናቸውም ዓይነት መርዝ መፈተሻ – መሞከሪያ

እንደ ጥንቸል ሲያደርግ ቃሉ „መንግሥት ወይንም ወያኔ መራሹ“ የሚለውን ደፍሮ ለመናገር እውነት ይቻላልን? ይህ እኮ አሁን የምንሰማው የምናዬው ነገር ሁሉ ከጫካ ጀምሮ ወያኔ ጠላቴ ባላቸው፣ አቅም በነበራቸው፤ ይቀናቀኑኛል ብሎ በሰጋባቸው ወገኖቻችን ሁሉ ሲፈጸም የኖረ የጣር ድምጽ እኮ ሰሞኑን በይፋና በአደባባይ የሰማነው።

ዛሬም የኢትዮጵያ ህዝብ በሚከፍለው ግብር፣ በተሰበሰበው ገንዘብ ሽፍታ ተኮፍሶ ሚሊዮኖች ያለቁበት፤ የተደመሰሱበት ከጠላት እጅ የወደቁ ሥጋና ደሞቻችን ሁሉ እንደ ዘመነ ኦሾትዝ  ወያኔ ሲፈጸም የኖረ በደል – ግፍና ገመና እኮ ነው ያደመጠነው የስቃይ ሲቃ! ይህን እንደ ሰብዕዊ ፍጡር በተደሞ በውስጣችን ሆነን እንፈትሸው። በቀሌንሶ እስር ቤት ይፈስ የነበረው ደም የዚህ ጣር ጭብጥ ነው። እኛ በመናውቃቸው እንጦርጦስ ጉድጓዶችም ….

እጅግ የምትናፍቁኝ ወገኖቼ ዘመን ዋሾ አይደለም። ዘመን ቀጣፊ አይደለም። ዘመን እውነት ነው። ዘመን ዕንባውን እንዲህ እያፈሰሰ ዛሬ ማቄን ጨርቄን ለምንለው ሁሉ ቁርጣችን እንድናውቅ አፍጦ ፍረዱ እያለን ነው። የተከበሩ ዬአቶ አንዳርጋቸው የመከራ ሰከንዶች ሁሉ ሌላ ተጨማሪ የሃቅ ሰነዶችን እያብራራልን ነው። ሌላ ታካይ የቁረጡ ነጋሪት ጎሳሚ ሰቀቀኖችን ሁሉ የአዳባባይ ሲሳይ እያደረገ ነው። መከራን እያነበብን ነው።  ስለዚህ ወያኔን ሚዛን ላይ አስቀምጠን „መንግሥት“ ለማለት የሚያስችለው ምን አምክንዮ አለ? „መራሽ“ ለማለትስ? ይህም ቢሆን የሚሩት በሥሩ ያሉትስ አባል ድርጅቶች ቆራጣ ሥልጣን አላቸው ወይ? ድምፃቸውን ይሰማል ወይ? ይደመጣሉ ወይ? ካለሰጋት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት እርግጠኝነት አላቸው ወይ? ብለን የሂደቱን ሆድ ዕቃ ስንመረምረው ምላሹ ምንም ነው።

ስለዚህ ምንም ላይ ተቀምጠን ምንም ለሆነ ምላሽ፤ በነጠረ ስሙ፤ እሱ በማያፍርበት ስሙ፤ የሽፍታው ዬወያኔ ቡድን ማለት እንጥሽት ውሃውን የሚፈስና አከርካሪውንም የሚያደቅ ስለሚሆን ደፍረን ሚዲያ ላይ አደባባይ እናውለው። እኔ እህታችሁ እንዲህ እንዲህ ማንቆለባበስ አይነካካኝም። ብዕሬም፣ አንደበቴም፣ ካሜራዬም ይጸዬፋዋል። ቆርጫለሁ። ወያኔን ጫካ እያለ ሁሉ በሚገባ አውቀዋለሁ። አጋጣሚው ሲሰጠው ጥፍሩን ከርክሞ ከአጥፊነቱ ይመለስ ይሆን ብዬም ድምጼን አጥፍቼ አዳምጨዋለሁ። ያልተፈጠረበትን ከዬት ያመጣዋል – ወያኔ?

ሰውን ያህል በፖርሳ ጥቅልል አድርገህ የማትይዘውን ግዙፍ ዬፍጥረታት አውራን እኮ ነው በጠራራ ጸሐይ ዬሌላ ሀገርን  የድንበር ክልልና ሰንድቅዓላማ፤ ዬአዬር ወሰን እዬጣሰ የሚዘርፍ – ጭራቅ እኮ ነው። ይህንን ነው ለዓለም ህዝብ በተለያዩ በራሪ ጹሑፎችና ቋንቋዎች በዝርዘር ማስረዳት ያለብን። ከነተባባሪው፣ ከነአጃቢው፣ ከነአልባሹ ማጋለጥ ያለብን። ቀኑ አሁን ነው ዳታ አያስፈልግም። ከመሬት በታች በከርስ ውስጥ ስንት ዕንባ፣ ስንት እሮሮ ተዳፍኖ ይሆን?

እርግጥ ነው  „ኢህድግ/ወያኔ“ እንዲህ በቅንፍ አድርጋችሁ የምትጽፉ ወገኖቼንም  አያለሁ። ትናንት ስላልታያችሁ ወይንም ጫካ እያለ ለማታውቁት አብሮ የሰነበተ ነገር ነው። ዛሬስ? እኮ ዛሬስ? የነፃነት ትግሉ አባወራ ጭንቅላት አንገት በጠላት እጅ ወድቆ እዬታዬ፤ በዘመቻ የነፃነት አርበኞቻችን እዬታፈሱ በገፍ ወደ ወያኔ የፍል – የጋመ ዬበቀል ጉድጓድ እዬተወረወሩ፤ ቀንበጦቻችን አድምጠን ሳንጠግባቸው ወጣቶቻችን፤ እህቶቻችን፤ ዬዕምነት መሪዎቻችን፤ ዬብሄረሰብ፤  ዬእድሜ ዬእውቀት ደረጃ፤ ሳይኖር ኑሮና መኖር እዬተጣሱ ፍቅርና ራዕይ እዬተገረደሱ ገደብ አለቦሽ ግፍ የሚፈጸምባቸው መከራ አለዬንህም አልሰማንህም ማለት እንቸችለላን? የዘመኑ ታዳሚዎች ነን —-

ታዲያ ይህንን እያዬን እንዴት ይሳነን በነጠረ አይሁድ ስሙ ወያኔን ብለን ለመጥራት ////// የሴት እሰረኞች መከራ ደግሞ ብዕርም – አንደበትም – ህሊናም – ባህልም – ትውፊትም – ተመክሮም – ደፍሮ ለመናገር አይችሉትም። ተቀብሮ የሚቀር ሚስጥር ነው። ዘመንና ታሪክም አያወጡትም – እኛ ባልነበርንበትና ባልተፈጠርንበት ውስጥ ሃቁን ለህዝብ አደባባይ አውጥቶ መጻፍ አንችልምና! ለመዳህኒተአለም – ለአውደ ምህረቱ – ለመንበሩ ለመንገርም እንኳን አቅም ያንሳል። እንኳንስ ለሚዲያ ፍጆታ ለማዋል። ሃቅ በሆነ አገላለጽ የወያኔ መሰረተ ተፈጥሮው – ሰብዕናውም ከኢትዮጵያዊነት ጠረን ውጪ ነው — እንዲህ ልከውነው። ትግራይ አኮ ለእምነቱና ለባህሉ የበዛ አክራሪ ነው። እነዚህ ከዬት እንደመጡበት፤ ከዬት እንደፈሉበት አላውቅም። የኔዎቹ በክፍል ሁለት መልሰን እስንገናኝ ድረስ መሸቢያ ሰንበት – ውድድ!

 

  • የጨረቃ ፈስ —የጨረቃ ፈስ በልጅነቴ ነው የማውቀው። መልኩ አፈር ይመስላል። ቅርጹ ድንቡልቡል ነው። መተንፈሻ የለውም። ቆዳው ስስ ነው። ስትነኩት ትንቡክ ትንቡክ ይላል። ስታስተነፍሱት የተቃጠለ ዬአፈር ጢስ ብቻ ነው። ጠረኑም ሥም -የለሽ ነው። የወያኔ ዘመንም እንደዚሁ  ነው።  የወያኔ መረጃው ሆነ ፍጥረተ ነገሩ  የተቃጠለ የአፍር ጢስ ነው።

 

እምዬ ኢትዮጵያን ከዚህ መራራ ዘመን ፈጣሪ ይታደጋት! አሜን!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

Comment


ችግራችን ምንድነው? ከእውነት፣ ከነፃነትና ከህይወት ጋር መጣላታችን!

$
0
0

1.ለ6 ወር የታገደው “ሕገመንግስታዊ መብት”፤ 9 ወር ሞላው – ለአገር ገፅታ ሲባል

  • ወደ አረብ አገራት ለስራ መጓዝ ከታገደ ወዲህ ወደ የመን መሰደድ ተባብሷል
  • ባለፉት ሶስት ወራት ከ18ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የመን ገብተዋል
  • አምና በተመሳሳይ ወራት ወደ የመን የተሰደዱት ኢትዮጵያውያን 14ሺ ናቸው

2.በደቡብ ኦሞ በአመት 300 “እርጉም” ሕፃናት ይገደላሉ – ለብሔረሰብ ባህል ሲባል

  • በደቡብ ኦሞ ስለ ሐመር ድንቅ ባሕላዊ አኗኗር ምሁራንና ጋዜጠኞች ይነግሩናል
  • በባሕላዊ እምነት ሳቢያ የወላድ መካን የሆኑ እናት፤ ባህላችንን እጠላዋለሁ ይላሉ
  • የደቡብ ኦሞ ሸለቆ ላይ ያተኮረው የኤንቢሲ የቪዲዮ ዘገባ “የሞት ሸለቆ” ይሰኛል

3.በዋጋ ቁጥጥር የተነሳ የዳቦ ቤቶች ቁጥር እየተመናመነ ነው – ለህዝብ ጥቅም ሲባል

  • ለምሳሌ በሙዝ ላይ የተጫነው የዋጋ ቁጥጥር ሲሰረዝ የሙዝ ዋጋ አልጨመረም
  • ዳቦ ላይ የዋጋ ተመን ሲታወጅበት፣ የዋጋ ተመን ያልወጣለት አንባሻ ይበራከታል
  • የታክሲ እጥረቱንም ተመልከቱ። የዋጋ ተመን በደርግ ጊዜ ለአገሬው አልበጀም    

    6a6924426f0f5679ad76c145c71ab412_M  “ለስራ ወደ አረብ አገራት መጓዝ ለ6 ወር ታግዷል” የሚለውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ የሰማን ጊዜ፤ ብዙዎቻችን በግርምት “እኮ እንዴት?” ብለን አልጠየቅንም። እንደዘበት የተነገረንን መግለጫ እንደተራ ጉዳይ አደመጥነው። ይሄውና ዘጠኝ ወር አለፈው። እንግዲህ አስቡት።  የሌላ ሰው ኑሮና ንብረት እስካልነካን ድረስ፤ በግል ሕይወታችን ውስጥ ወዲህ ወዲያ ለመንቀሳቀስ፤ መንግስትን የምናስፈቅድበት አንዳችም ምክንያት የለም። ለዚህም ነው፤ በደርግ ዘመን “የመውጫ ቪዛ” በሚል ሲደረግ የነበረው ቁጥጥር ሙሉ ለሙሉ እንዲቀር የተደረገው። በአገር ውስጥ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስም ሆነ ከአገር ውጭ የመጓዝ መብት፤ “ተፈጥሯዊ የሰው ነፃነት” ነው። ለነገሩማ፤ በሕገመንግስት ውስጥም ከመሰረታዊ ነፃነቶች ተርታ በጥቁርና ነጭ በግልፅ ሰፍሯል። 
“ማንኛውም ኢትዮጵያዊ… በፈለገው ጊዜ ከአገር የመውጣት ነፃነት አለው” ይላል – አንቀፅ 32። እንግዲህ፤ ለነፃነት ወይም ለሕገመንግስት ክብር እንሰጣለን የምትሉ ሁሉ ይህንን አስተውሉ።
በፅሁፍ ላይ የሰፈረው አንቀፅ ቀላል አይደለም። መንግስት፤ መሰረታዊ መብቶችን በይፋ ማገድ የሚችለው፤ ለፓርላማ ቀርቦ በሚፀድቅ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” አማካኝነት ብቻ ነው። ለዚያውም ከፓርላማ አባላት መካከል 51 በመቶ ያህሉ ስለደገፉ ብቻ አይፀድቅም፤ ቢያንስ 67 በመቶዎቹ መደገፍ አለባቸው። ለዚያውም ከ6 ወር ላልበለጠ ጊዜ ብቻ ነው እገዳው የሚቆየው። ይህም ብቻ አይደለም። ስርዓት አልበኝነት ካልነገሰ ወይም የውጭ ወረራ ካላጋጠመ በቀር፤ አልያም አደገኛ ወረርሺኝና የተፈጥሮ አደጋ ካልተፈጠረ በቀር፤ መሰረታዊ መብቶችን ለማገድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማውጣት አይቻልም።

ይሄ ሁሉ የተባለለት መሰረታዊ የሰዎች መብት ነው፤ በአዋጅና በፓርላማ ሳይሆን፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ የታገደው። እገዳውን ለማራዘምማ፣ አዋጅ ይቅርና ብጣሽ መግለጫ ማውጣትም አላስፈለገም። ለመሆኑ፤ ተፈጥሯዊውና በሕገመንግስት የሰፈረውን “የመንቀሳቀስ ነፃነት” እንደ ተራ ነገር ያለገደብ ለመጣስ፤ ምን ምን ማመካኛዎች ቀርበዋል? ሁለት ማመካኛዎች ናቸው የቀረቡት። አንደኛ፤ “እናውቅላችኋለን” የሚል። ሁለተኛ ደግሞ፤ “የአገር ገፅታንና ክብርን እናስጠብቃለን” የሚል።  

የመጀመሪያውን ማመካኛ እንመልከት። በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ወጣት ኢትዮጵያዊያን በየአመቱ የሚሰደዱት፣ “ትክክለኛ መረጃ ስለሌላቸውና የስደትን አደጋ ስለማይገነዘቡ ነው” ሲባል እንሰማለን። ግን፤ ይሄ አባባል ሃሰት ነው። በሃረር በኩል ድንበር ለማቋረጥ ሲጓዙ ከተገኙት 700 ሰዎች መካከል ብዙዎቹ፣ ዘንድሮ ከሳዑዲ አረቢያ የተባረሩ ወጣቶች ናቸው። አደጋውን አያውቁም ልንል ነው?
በእርግጥ፤ የስደት ጉዞው ስንት ቀን እንደሚፈጅ እቅጩን አያውቁ ይሆናል። በጉዞ ላይ የሚገጥማቸው የውሃ ጥም፣ ዝርፊያ፣ እገታ… የቱን ያህል አደገኛ እንደሆነ በቁጥርና በመቶኛ አስልተው ለመግለፅ አይችሉም። ነገር ግን፤ ከሞላ ጎደል ሁሉም ስደተኞች በርካታ ፈተናዎች እንደሚገጥሟቸው ያውቃሉ። እንዲያውም ከሰማኒያ በመቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፤ ገና ከመነሻው ዋና ዋናዎቹን ፈተናዎች በዝርዝር ጠንቅቀው እንደሚያውቋቸው ዘንድሮ የተካሄደ ሰፊ የጥናት ሪፖርት ይገልፃል። ዩኤንኤችሲአር፣ አይኦሜ እና ሌሎች አለማቀፍ ተቋማት ያቋቋሙት ፅ/ቤት (RMMS) ነው ጥናቱን ያካሄደው። በሰኔ ወር ይፋ የተደረገው የጥናት ሪፖርት ላይ እንደተገለፀው፤ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በጉዞ ላይና ከዚያ በኋላ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በዝርዝር ከማወቅም በተጨማሪ ህይወታቸው ለአደጋ እንደሚዳረግ ይገነዘባሉ።  

ስለዚህ፤ “አያውቁም፤ መረጃ የላቸውም” የሚለው ማመካኛ፤ መሰረት የለሽ ውሸት ነው። ደግሞስ፤ የመረጃና የእውቀት ጉድለት ካለባቸው፤ መፍትሄው መረጃ በስፋት ማቅረብና ማሳወቅ እንጂ፤ “አትጓዙም” ብሎ በግድ መከልከልና ነፃነታቸውን መጣስ ምን አመጣው?     
ከዚሁ ጋር አብሮ የሚነሳ ሌላ ማመካኛ አለ – በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ወጣት ኢትዮጵያዊያን በየአመቱ የሚሰደዱት፣ “በደላሎች ስለሚታለሉ ነው” የሚል። ይሄም፤ መሰረት የለሽ ውሸት ነው። ካልተሰደድክ ብሎ የሚያስገድድ ደላላ የለም። ደግሞም፤ አዲሱን የጥናት ሪፖርት መመልከት ትችላላችሁ። በስደት ወደ የመን ለመጓዝ የወሰኑት በደላሎች አማካኝነት እንደሆነ ከተጠየቁ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መካከል፤ 98 በመቶ ያህሉ “አይደለም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በደላሎች ውትወታና ማታለያ ለስደት የተነሳሱት ወጣቶች፤ እጅግ ጥቂት ናቸው – ሁለት ከመቶ ብቻ።
እውነታው እንዲህ በግልፅ ቢታወቅም፤ ስለ ስደት በተወራ ቁጥር፣ እንደተለመደው “ስደተኞች መረጃ የላቸውም፤ ተጠያቂዎቹ ደላሎች ናቸው” የሚል ውንጀላ ከየአቅጣጫው እንደሚዥጎደጎድ አያጠራጥርም። ለምን? ለእውነታ ብዙም ክብር የለንም። ለነፃነትም ዋጋ ስለማንሰጥ፤ በመግለጫ ብቻ “የጉዞ እገዳ” እንጥላለን – “እናውቅላችኋለን” ወይም “የአገርን ገፅታ ታበላሻላችሁ” በሚል ማመካኛ።

ነገር ግን፤ በሕጋዊ መንገድ መጓዝ ቢታገድም፣ በዘፈቀደ መሰደድ መች ይቀራል? ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ከ18ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ገብተዋል። በዚህ ከቀጠለ፤ በአመት ከ90ሺ በላይ ይሆናል። አደጋውን አስቡት። ከ2000 ዓ.ም ወዲህ፣ ወደ የመን ሲጓዙ ሁለት ሺ ያህል ሰዎች መንገድ ላይ ሞተዋል።  በህጋዊ ምዝገባ ወደ አረብ አገራት የሚደረገው ጉዞ ስለታገደ፤ ያለ ቪዛ ወደ የመን የሚሰደዱ ሰዎች ሲበራከቱ በአመት ውስጥ ምን ያህሉ ሊሞቱ እንደሚችሉ አስቡት። በአማካይ ከ40 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን በጉዞ ላይ እንደሚሞቱ ልብ ማለት ያስፈልጋል – በአንድ አመት ውስጥ። “አገር” ወይም “የአገር ገፅታ” ለሚባል ጣኦት መስዋእት እያደረግናቸው እንደሆነ አስቡት። በህጋዊ ቪዛ ሲጓዙ ከነበሩት ውስጥ የዚህን ያህል ሰዎች አይሞቱም ነበር።
“እናውቅላችኋለን” ከምንል ይልቅ “አናውቅላችሁም” ብንል ይሻላቸው ነበር።  ምክንያቱም፣ በሺ የሚቆጠሩት ወጣቶች ያለ ቪዛ ለመጓዝ የመረጡበትን ምክንያት ሲጠየቁ፤ ህጋዊው ጉዞ በተንዛዛ ቢሮክራሲ ሳቢያ እንቅፋት ስለበዛበት ነው ብለዋል። ዘንድሮ ደግሞ ከነጭራሹ ታግዷል። ምን ይሄ ብቻ! ጭራሽ በድንበር በኩል ከአገር ልትወጡ ስትሞክሩ ተገኝታችኋል ተብለው እዚሁ አገራቸው ውስጥ የሚታሰሩ ወጣቶችን አይተናል። ወንጀላቸው ምንድነው? የትኛውን የወንጀል አንቀፅ ጥሰዋል? ማንን ጎድተዋል? ምንም!  
በአጠቃላይ ሲታይ፤ የኛ ችግር፣ የአገራችን ችግር በአጭሩ ሊገለፅ ይችላል – ለእውነታ ዋጋ አንሰጥም። ለነፃነትስ? ለህገመንግስትስ? ለሰው ሕይወትስ? ለሰው ምርጫና ጥረትስ? ለሰብአዊ ክብርስ ዋጋ እንሰጣለን? አንሰጥም። በዚህም ምክንያት፤ “እናውቅላችኋለን” በሚል ወይም “የአገር ገፅታ” በሚሉ ሰበቦች፤ የሰዎች ተፈጥሯዊ ነፃነትና ሕይወት ላይ እንጫወታለን።
“አይ፤ ለእውነታ፣ ለነፃነትና ለሕይወት ክብር እንሰጣለን” የሚሉ ሰዎች እንደሚኖሩ ይገባኛል። “እገዳው ተገቢ ባይሆንም፣ ቢያንስ ቢያንስ በቀጥታ የሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ያነጣጠረ የመብት ረገጣ አይደለም” የሚል መከራከሪያም ያቀርቡ ይሆናል። በቀጥታ የሰው ሕይወት ላይ ያነጣጠረ ሲሆንስ ደንታ ይኖረናል?
ኢትዮጵያዊቷ የደቡብ ኦሞ ተወላጅ ቡኮ ባልጉዳ ይመስክሩ። 

ሕፃናት ወደ ገደልና ወደ ወንዝ ይወረወራሉ
የ45 ዓመቷ ቡኮ ባልጉዳ የወላድ መካን ናቸው። ልጆቻቸውን በሞት የተነጠቁ እናት። የወለዱትን ህፃናት በአንዳች በሽታ ወይም በአንዳች አደጋ ማጣት ልብን ይሰብራል። በግድያ ሲሆን ግን፣ ለማሰብም ይከብዳል። እንደ ብዙዎቹ የደቡብ ኦሞ ሴቶች፣ ቡኮ ባልጉዳ ልጅ የወለዱ ጊዜ የደስታና የስጋት ስሜት ቢቀላቀልባቸው አይገርምም። የጎሳ መሪዎች መጥተው የህፃኑን አፍ ከፍተው ድዱን ያያሉ። ህፃኑ የመጀመሪያ ጥርሱን በላይኛው ድዱ ካበቀለ፤ ይዘውት ይሄዳሉ – “ሚንጊ” (እርጉም) ነው በሚል። “በጎሳችን ላይ መዓት የሚያመጣ እርጉም!” የተባለው  ሕፃን  ወደ ገደል፣ ወደ ወንዝ ይወረወራል። ይሄ ባህል ነው። ለዘመናት የዘለቀ ማይሞገት አይነኬ ባህል! “ለጎሳው” እና “ለባህሉ” ሲባል፤ ሰዎች መስዋእት ይሆናሉ። 

ቡኮ ባልጉዳ የመጀመሪያ ልጅ ከተገደለባቸው በኋላ እንደገና ወልደዋል። እንደገና “ሚንጊ ነው” በሚል ተገደለ። እንዲህ ሲወልዱና ሲገደልባቸው ነው የኖሩት። በሕይወት ዘመናቸው ስምንት ወንድ ልጆችንና ሰባት ሴት ልጆችን ወልደዋል። 15ቱም ሕፃናት “ሚንጊ ናቸው” ተብለው ተገድለዋል። የወላድ መካን ያደረጋቸውን ባህል እንደሚጠሉት ይናገራሉ – ቡኮ ባልጉዳ። ዴይሊ ሜይል እንዳለው፤ 300ሺ የሕዝብ ቁጥር በያዙት የሃመር እና የባኮ ማሕበረሰብ ውስጥ በየአመቱ 300 ሕፃናት፣ “ሚንጊ ናቸው” ተብለው እንደሚገደሉ ገልፀዋል። ይሄው የሚንጊ ባህል በመላ አገሪቱ የተለመደ ቢሆን ኖሮ፣ በየአመቱ ከመቶ ሺ በላይ ሕፃናት በተገደሉ ነበር።

አሰቃቂ ነው። ግን ስለ አሰቃቂነቱ ሲነገር ሰምተናል? ተፅፎ አንብበናል? 
ብዙውን ጊዜ የሚነገረንና የሚፃፍልን፤ ስለ ሐመር ወይም ስለ ደቡብ ኦሞ ድንቅ ባሕል ነው። እንዲያውም ብዙዎቹ ተናጋሪዎችና ፀሃፊዎች፤ በጋራ የተመካከሩና የተስማሙ፤ አልያም የታዘዙ ይመስል፤ ስለ ሚንጊ አይናገሩም፤ አይፅፉም። ግን የትዕዛዝ ወይም የምክክር ጉዳይ አይደለም። ለእውነታ፣ ለነፃነት፣ ለሰው ሕይወት እና ለሰብአዊ ክብር የላቀ ዋጋ ስለማንሰጥ ነው። በየአመቱ 300 ሕፃናት! ባሕልን ወይም ብሔር ብሔረሰብን በማክበር ስም ነው ይሄ ሁሉ የሚደረገው። ለዚያ ለዚያማ፤ በየአመቱ እንደ ቡኮ ባልጉዳ የመሳሰሉ የብሔረሰቡ ተወላጅ የሆኑና ልጆቻቸውን የሚነጠቁ 300 እናቶች እና 300 አባቶችስ? ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ ፀሐፊዎች … ለእውነታ፣ ለነፃነት፣ ለሰው ሕይወትና ክብር የማትቆሙ ከሆነ፣ ሥራችሁ ምንድነው? ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ለነፃነትና ለሰው ሕይወት የማትሟገቱ ከሆነ፣ አላማችሁ ምንድነው? እርስበርስ እየተጠላለፋችሁ ስልጣን መያዝ ብቻ!

ከዳቦ ወደ አንባሻ

በ2003 ዓ.ም ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ አዳዲስ የገንዘብ ኖቶችን በማሳተም ከፍተኛ የዋጋ ንረት የፈጠረው መንግስት፤ የዋጋ ንረቱን በነጋዴዎች ላይ በማሳበብ የዋጋ ቁጥጥርና የዋጋ ተመን እንዳወጣ ታስታውሳላችሁ።  ከመነሻው፤ የገበያ ጠቃሚነቱኮ፣ ሰዎች በፈቃደኝነት የሚያካሂዱት መሆኑ ነው። ለምንድነው መንግስት በሰዎች ንብረት ላይ አዛዥ ናዛዥ የሚሆነው? “ለህዝብ ጥቅም” ሲባል ነዋ። “ለድሃው ጥቅም” ታስቦ ነዋ። ለሰፊው ሕዝብና ለድሃው ሕብረተሰብ ይጠቅማል እስከተባለ ድረስ፤ የሰዎችን ነፃነት መጣስ ይቻላል። አያችሁ? ለነፃነት ያን ያህልም ክብር የለንም። የዋጋ ቁጥጥርና የዋጋ ተመን የታወጀ ጊዜ ተቃውሞ አሰምተናል እንዴ? ብዙዎቻችን ደግፈናል። መንግስት ከጥቂት ወራት በኋላ የዋጋ ተመኑን ለመሰረዝ የወሰነው፣ ኢኮኖሚውን ይብስ እያቃወሰ እንደሆነ በግልፅ መታየት ስለጀመረ ነው። ነገር ግን፤ ሁሉም የዋጋ ተመን አልተሰረዘም – ለምሳሌ የዳቦ።

እንግዲህ አስቡት። የዋጋ ቁጥጥርና ተመን፣ የሰዎችን ነፃነት የሚጋፋ ቢሆንም እንደግፈዋለን – ለነፃነት ዋጋ ስለማንሰጥ። የዋጋ ቁጥጥርና ተመን፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን የሚያበላሽ እንደሆነ በግልፅ ቢታይም እንደግፈዋለን – ለእውነታ ዋጋ ስለማንሰጥ። ቢያንስ ቢያንስ ለእውነታ ክብር ቢኖረንኮ፣ የዋጋ ተመን እንደማያዋጣ ተገንዝበን ተመኑ እንዲሰረዝ ማድረግ እንችል ነበር። እስቲ ይታያችሁ። በመንግስት የገንዘብ ህትመት ሳቢያ የዋጋ ንረት ሲከሰት፣ እንደሌላው ሸቀጥ የስንዴ ወይም የዱቄት ዋጋም ይጨምራል። ዳቦ ጋጋሪው ግን፤ ዋጋ መጨመር አትችልም ተብሏል። 

ይሄ ሊያስኬድ አይችልም። መንግስትም ይህንን ያውቃል። እናም፤ ዳቦ ቤቶች በድሮው ዋጋ የስንዴ ዱቄት እንዲያገኙ አደርጋለሁ አለ። አንደኛ ነገር፤ የመንግስት ቢሮክራት፣ “ምን አተርፋለሁ፣ ምን አገኛለሁ” ብሎ፣ በጊዜ ስንዴ ለማቅረብ ይተጋል? ከደሞዙ ውጭ ምንም አያገኝም። በጊዜ ስንዴ ባያቀርብ ኪሳራ አይደርስበትም። የወር ደሞዙ አይቀነስበትም። እናም፤ እንደምታዩት ዳቦ ቤቶች በየጊዜው የስንዴ እጥረት እየገጠማቸው ስራቸው ይስተጓጎላል። ነገር ግን፤ የስንዴ ዱቄት በፍጥነትና በድሮ ዋጋ ለዳቦ ቤቶች ቢቀርብላቸውም እንኳ ብዙም አያስኬድም። ዳቦ እያመረቱ በድሮው የዋጋ ተመን መሸጥ እንዴት ይሆናል? የቤት ኪራይ፣ የማገዶ፣ የትራንስፖርት… ብዙ ነገሮችኮ ዋጋቸው ጨምሯል። ለዚህም ነው፤ በየሰፈሩ ብቅ ብቅ ሲሉ የነበሩት ዳቦ ቤቶች እየተዳከሙና እየተዘጉ፣ ቀስ በቀስ የየከተማው የዳቦ ቤቶች ቁጥር ሲመናመን የምናየው። 

በዳቦ ምትክ፤ አሁን አሁን የአንባሻ ጋጋሪዎች ቁጥር እየተበራከተ መጥቷል። አንባሻ ላይ የዋጋ ቁጥጥር አይደረግማ። ግን፣ ውድ ነው። ምክንያቱም እንደዳቦ፣ አንባሻ በብዛት ማምረት አይቻልም። ለነገሩ፤ በብዛት ማምረት ቢቻል እንኳ ዋጋ የለውም። ያኔ፣ አንባሻ ላይም የዋጋ ቁጥጥር ይጀመርና እሱም ይዳከማላ።

የዋጋ ቁጥጥር ለሰዎች ኑሮ እንደማይበጅ በተደጋጋሚ አይተነዋል። የታክሲዎች ቁጥር የተመናመነውና የትራንስፖርት እጥረት የተባባሰው ለምን ሆነና! ለነገሩማ፤ በደርግ ዘመን በስፋት ተግባራዊ የተደረገው የዋጋ ቁጥጥር፣ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ከማቃወስና ድህነትን ከማባባስ ያለፈ ጥቅም አላስገኘም።

እንዲያም ሆኖ፤ የዋጋ ቁጥጥር ላይ ብዙም ቅሬታ የለንም። ለምን? እውነታውን ብናውቀውም፣ ነፃነትን የሚጥስ ቢሆንም፣ ኑሮን የሚረብሽ ቢሆንም፤ ለእውነታ፣ ለነፃነትና ለሕይወት ብዙም ክብር ስለሌለን የዋጋ ቁጥጥርን አንቃወምም።   

ምንጭ፥ -አዲስ አድማስ

ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግሉስ አይሞትም!

$
0
0

Free andargachew tsige LGየወያኔው መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን ጠልፎ በኢቲቪ ማስለፍለፉን እናወግዛለን!  በሀገራችን ኢትዮጵያ ምድር ለዴሞክራሲያዊ ሕዝባዊ ሥርዓት የሚደረገው መራራ ትግል ከፍተኛ መስዋዕትነትን የሚያስከፍል ለመሆኑ ላለፉት ፶ ዓመታት በእሥር ሥየል እየተፈጸመባቸው ካለፍርድ ለብዙ ዓመታት የተንገላቱ፤ መዳረሻቸው ጠፍቶ ደብዛቸው የሚጠፉትን፣ የተሰደዱትንና ጭካኔ  በሞላበት አኳኋን ግድያ የተፈጸመባቸውን ቤት ይቁጠራቸው ከማለት ባሻገር ቆጥረን ይህን ያህል ብለን የምንለካው አይሆንም። ባለፉት ፶ና ዓመታት ከሦሥት ሥርዓቶች ማለትም ከአፄው የባላበት ስርዓት፤ ከደርጉ ምርጥ መኮንኖች ወታደራዊ የፋሺሽቶች ሥርዓትና እነሆ ላለፉት ፳፫ ዓመታት ደግሞ በወያኔ አንጋፋ መሪነት ኢትዮጵያን ከሚጠሉ ጠባብ ብሔረተኞች ጋር እልህ አስጨራሽና አሁንም መስዋዕትነትን የሚያስከፍል ትግል እየተካሄደ ነው። ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተመሥርቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት እስኪሆን ድረስ ትግሉ ይቀጥላል። ትግሉም እስከቀጠለ ድረስ ደግሞ የሚከፈለውም መስዋዕትነት በዚያው መጠን እየጨመረ መሄዱ አይቀርም። የሰሞኑም በአንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የደረሰውንም ትግሉ የሚጠይቀን እያንዳንዳችን ልንጎነጨው የማንፈራው የመሥዋዕትነት መራራ ጽዋ መሆኑን ልንገነዘበው ይገባል። ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግሉ አይሞትም የሚባለውም ለዚሁ ነው።–[ሙሉውንለማንበብእዚህላይይጫኑ]—

ይድረስ ለኢትዮጵያውያን ይድረስ ለ”ክርስቶስ ደቀመዝሙር”

$
0
0

ሐምሌ 17/2006 “ይድረስ ለኢትዮጵያዊ” በሚል ርዕስ ኢትዮሚድያ ዶት ኮም የለጠፈውን ጽሑፍ አንብበናል [ይጫኑ]። የጽሑፉ ደራሲ “የክርስቶስ ደቀመዝሙር” ነኝ ብሎናል። ጽሑፉ ታሪክን ስነ መለኰትን ፖለቲካን ያካተተና ውስብስብ በመሆኑ በመሠረታዊ አሳቦቹ ላይ በቀር በያንዳንዱ ላይ ምላሽ ለመስጠት ጊዜውም ቦታውም አይፈቅድልንም። ምላሽ መስጠት ያስፈለገው ምናልባት ጽሑፉን የሚያነብቡ የሃይማኖት አስተምህሮ ብዙ ያልገባቸው በሚያነብቡት ክርስቲያናዊ ቋንቋ እንዳይወናበዱ ከመሥጋት ነው። “ደቀመዝሙሩ” ያነሳቸው አሳቦች ምንና ምንድናቸው? 1/ አገራችን የምትገኝበትን ሁኔታ፦ ጭከና የበዛበት፣ ማስተዋል የጠፋበት፣ ዘረኝነት የነገሠበት፣ ሰይጣን መንግሥትን ከበስተኋላ የሚያንቀሳቅስበት፣ የዘመኑ መጨረሻ የተቃረበበትና ሃሰተኛው መሲሕ ሊገለጥ ፍንጭ ያሳየበት ነው ሲል ሥሎልናል። ሃሰተኛውም መነሻው ከዐረብ ምድር ሳይሆን ከኢትዮጵያ ነው ብሎናል [ገጽ 9]። በዚህ መሠረት 2/ በአገራችን ለተከሰተው ችግር ምንጩ በተለይ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝና ጴንጤ/ፕሮቴስታንት ደጋፊዎቻቸው ናቸው። ስለዚህ፣ 3/ ከፍተኛ ትግል አለብን፤ ትግሉ እንዲሠምር ክርስቲያኑና እስላሙ አንድ መሆናቸውን መረዳት አለባቸው፤ 4/ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ የገባላት ተስፋ ስላለ የአገራችንን አስከፊ ሁኔታ ለመቀየርና የክርስቶስን ዳግም ምጽኣት ለማፋጠን እንነሳ የሚል ነው [ገጽ 10]። -—[ሙሉውንለማንበብእዚህላይይጫኑ]——

 

Comment

አርሲ እና ምኒልክ፡ ጠማማነት ለማቅናት ወይስ ቂመኝነት ለማጉላት?!

$
0
0

ከማስተዋል ይኑረን

ለዚህ ጽሑፍ ምክንያት የሆነኝ አቶ ወርቁ ፈረደ ፋክት መጽሔት ቅጽ ሑለት ቁጥር አርባ ሰባት ላይ ግንቦት 2006 ዓ/ም “ምኒልክና አርሲ” በሚል ርእስ ያቀረቡት ጽሑፍ ነው፡፡ ይህ ጽሑፍ በኢትሚዲያ ድሕረ ገጽም ለንባብ ቀርቧል፡፡የጽሑፌ ዓላማ አቶ ወርቁ ፈረደን በመደገፍ ወይም በመቃወም ለመተቸት ሳይሆን እርሳቸውም፤ ጽሑፉን ያነበበ ሁሉም፤ ወይም በአጋጣሚ የእኔን ጽሑፍ የሚያነብ ሁሉ የዘር ግንድን ወይም ቋንቋን መሰረት ያደረገ ማንነትን ተንተርሶ ፍርድ እንዳይሰጥ በስብእናው ብቻ ለራሱ ፍርድ እንዲሰጥና እግዚአብሔር ከረዳን አስተውሎት እንዲኖረን ለማድረግ ነው፡፡ በአማርኛ ሥነ ቃል “ምንትስን ያየ በእሳት አይጫወትም” የሚል አባባል አለ፡፡ “ምንትስ” የሚለውን ቃል የተጠቀምኩት ወድጄ ሳይሆን ይትበሃሉ ከሰው ስም ጋር ግንኙነት ሰለአለው ለመጥቀስ ስላልፈለኩ ነው፡፡ አንባቢ በዚህ ረገድ ይረዳኛል/ይገነዘበኛል የሚል እምነት አለኝ፡፡

Minilikለወንድሜ ለአቶ ወርቁ ፈረደ (በእድሜ ተቀራራቢ ከሆንን) ወይም ለአባቴ አቶ ወርቁ ፈረደ (በእድሜ ስለ አባት ያክል የሚበልጡኝ ከሆነ) ወይም ለልጄ ለአቶ ወርቁ ፈረደ (ስለ አባት ያክል የምበልጠው ከሆነ) ላስታውሳቸው/ላስታውሰው የምፈልገው ነገር አለ፡፡ ይህ የማስታውሰቸው ጉዳይ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል (Genocide crime) ላይ የተሰሩትን ሁለት ፊልሞችን እንዲመለከቱልኝ ነው፡፡ እነዚህም Hotele Ruwanda እና Shake Hands with Devil ናቸው፡፡ ሁለተኛው ፊልም ታሪኩ በመጽሐፍ ታትሞ ከወጣ በኋላ “የተተወነ” ነው፡፡ ወዳጄ አድራሻቸውን ከሰጡኝ መጽሐፉን ላውሳቸውና እንዲያነቡ እድል ልሰጣቸው እችላለሁ፡፡ ያላነበቡ ከሆነ፡፡ ቢያነቡ በዘር ጉዳይ እንዲህ ያለ መከራከሪያ ጭብጥ ያቀርባሉ ብዬ ስለማልገምት ነው፡፡ እነዚህን ሁለት ፊልሞች ያየ ወይም መጽሐፉን ያነበበ በእግዚአብሔር መልክና አምሳልየተፈጠረ ሰው ይህን ዓይነት በአንደበት ለመግለጽ፤ በአእምሮ ለማስብ፤ በጽሑፍ ለማስፈር የሚያስቸግር፤ የሚያም፤ የሚቆረቁር፤ የሚያፈዝ፤ የሚያደነዝዝ፤ የሚያቆስል፤ የሚጠዘጥዝ ድርጊት ይፈጽማል ብሎ ለማስብ ያስቸግራል፤ እራስንም ሌላውን ሰው የተባለውን ፍጥረትም በዘመናችን ሁሉ እንድንጠራጠር ያደርጋል፡፡

አቶ ወርቁ ፈረደ ሌላም መጽሐፍ እንዲያነቡልኝ በእግዚአብሔር ስም ልለምናቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ የተጻፈው በቄስ ዴዝሞንድ ቱቱ ነው፡፡ ርእሱ፡- “The Future of Forgiveness” የሚል ሲሆን መጠኑም በጣም ትንሽ ስለሆነ አንድ ቀን ከሰዓት ቁጭ ብለው ቢያነቡት ጊዜ የሚወስድ አይደለም፡፡ ይህ መጽሐፍ ቄስ ዴዝሞንድ ቱቱ የደቡብ አፍሪካ የእርቅ ኮሚሺን ሊቀመንበር ሁነው በሰሩበት ጊዜ ከቀረቡላቸው እጅግ አሳዛኝ ነገሮች አንኳር አንኳሩን ሰው እንዲያውቀው መረጃ የሰጡበት ሲሆን መጽሐፉን የጀመሩበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከጢሞቲዎስ መልእክት የተወሰደ፤ እግዚአብሔር በፈቀደ ጊዜ ሁሉም እንደሚከናወን በሚያሳይ ጥቅስ ነው፡፡ ላስተዋለውና ላጤነው የደቡብ አፍሪካዎች መንገድ እንደ ኢትዮጵያ ላለ አገር ፈውስ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፡፡

አቶ ወርቁ ፈረደ ለጽሑፋቸው ማጣቃሻ ያደረጓቸውን መጽሐፎች ጠቅሰውልናል፡፡ እጅግ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ ጽሑፌ ከመረቀነ አእምሮ ሳይሆን ከደለበ እውቀት፤ ማስረጃ ካለው ምንጭ የተገኘ ነው ለማለት ነው፡፡ ዋቢ መጽሐፎች ምን ያክል ታማኝ ናቸው? የሚል ጥያቄ ከማንሳቴ በፊት በ1974 ዓ/ም ከብሪቲሽ ካውንስል ተውሼ ያነበብኩትን አንድ መጽሐፍ አስታወሰኝ፡፡ ጊዜው በመርዘሙ (ሰላሳ ሁለት አመት ስለሆነው) ጸሐፊውን ለማስታወስ ቢቸግረኝም ርአሱን ግን በደንብ አስታውሰዋለሁ፡፡ “The public Image of Casar” የሚል ሲሆን ወደ ዋናው ምንባብ ከመግባታችን በፊት መግቢያው ላይ፡- “When you study history study the historian, when you study the historian study the time in which that history is written” ይላል፡፡ ታሪክን ስታጠና ታሪክ ጸሐፊውን አጥናው፤ ታሪክ ጸሐፊውን ስታጠናው ታሪኩ
የተጻፈበትን ጊዜም አጥና እንደማለት ነው በግርድፉ ሲተረጎም፡፡ የትርጉም ባለሙያ የሆነ ከእኔ በተሻለ ሁኔታ አሳምሮ ሊተረጉመው/ ልትተረጉመው እንደሚችል/ እንደምትችል እገነዘባለሁ፡፡ ይህን ካልኩ በኋላ ወደ ዋናው ጉዳዬ ልምጣ፡፡

የጸሐፊው አቶ ወርቁ ፈረደ ጽሑፍ በእኔ እምነት ለአማራውም ለኦሮሞውም ቂም አስታዋሽና በቀል ቀስቃሽ ነው፡፡ ለዚህ ነው በቃለ አጋኖ የታጀበ የጥያቄ ምልክት በማድረግ ጠማማነትን ለማቅናት ወይስ ቂመኝነትን ለማጉላት?! የሚል ርእስ የመረጥኩት፡፡ በጥንቃቄ ጽሑፉን ለመረመረው ሰው ዋና ጭብጡ ምኒልክ አገር ለማቅናት አሬመኔ ጨካኝን፤ መንገድ አላስኬድ ያለን “ነውጠኛ” ለመግራት ሄዱ እንጂ ለሌላ ጉዳይ አይደለም፤ ተግባራቸው በሌላ አኋን ሊታይ አይገባውም የሚል እንድመታ ያለው ነው፡፡ ይህ አባባል በወንድሜ በአቶ ወርቁ ፈረደ የተጀመረ አይደለም፡፡ ጣሊያን አገራችንን
ኢትዮጵያን በእብሪተኝነት ስትወር በአለም መንግስታት መድረክ መሟገቻ ጭብጥ አድርጋ ያቀረበችው ምክንያት “ተግባሬ ወረራ ሳይሆን ይህን በጨለማ ውስጥ ያለ ሕዝብ “ለማሰልጠን” ነው::” የሚል ነው፡፡ የጣሊያን ጭብጥ አግባብ ነው በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ ለጣሊያን አልተገዛም፡፡ ለአገራችን በዱር በገደሉ በፈፋውና በሽነተረሩ እየወጣንና እየወረድን አልገዛም ባይነታችን ላልተቋረጠ አምስት አመት ትግል ካሳየን በኋላ ነጻነታችንን በትግላችንና በመስዋእትነታችን ደማችንን አፍስን፤ አጥንታችንን ከስክሰን፤ ስጋችንን ነስንሰን መልሰን አግኝተናል፡፡ ሃያላን መንግሥታት ሙግታችንን፤ የድረሱልን ጩኽታችንን ሰምተው ከጎናችን ለመቆም፤ ፍትሐዊ የሆነ ዳኝነት ለመስጠት የጀርመንና የጣሊያን ጊዜያዊ ሕብረት፤ የሞሶሎኒና የሒትለር እብደት ቢያሰጋቸውም እሳቱ ሲለበልባቸው ግን ሳይወዱ በግድ ከጎናችን ቆመዋል፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተባበሩት መንግሥታት መድረክ ያሰሙት ታሪካዊ የትንቢት ንግግርም ይህን በእሳት የመለብለባቸው ጉዳይ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ለእነርሱም የማይቀርላቸው መሆኑን ያረጋገጠ ነበር፡፡ ሲጠቃለል የአቶ ወርቁ ፈረደ ጽሁፍ አገር ለማቅናት፤ አረመኔን ለመግራት በሚል ሰበብ ያን ያክል ርቆ መሄድ ባላስፈለገ ነበር፡፡ ከውጭ ሲደርስብን እንቃወመው እርስ በርስ ሲሆን
እንቀበለው ካልተባለ በስተቀር፡፡ ግዳይ እየጣሉ ወንድነትን ማስመስከር በኦሮሞ ማሕበረሰብ ታሪክ ብቻ የተገደበ ተግባር አይደለም፡፡ ሕጻናት እየታረዱ ለመስዋእትነት የሚቀርቡበት ባህል እንደነበር ብሉይ ኪዳንን ጠንቅቆ ያነበበ ይረዳል፡፡ ሞሎክ ለተባለው “አምላክ” ህጻናት ይሰውለት ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ቢሆን ይህ ጉዳይ ይተገበር ነበር፡፡ አይደለም በዚያ በጨለማው ዘመን በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ አንዱ ክፍል (ከኦሮሞ ማሕበረሰብ ውጭ በሆነ አካባቢ) በውሃ ኃይል የሚንቀሳቀስ የእህል ወፍጮ አልሰራልኝ አለ ብሎ ሕጻን በማረድና ለሰይጣን መስዋእት በማቅረብ ለማስነሳት የተደረገን የወንጀል ድርጊት የፖሊስ ጋዜጣ በወቅቱ አስነብቦናል፡፡ ዝርዝሩን መረዳት ለፈለገ ፖሊስ ላይብረሪ በመሄድ ወይም ብሔራዊ ቤተ መዘክር (ወመዘክር) በመሄድ መረዳት ይቻላል፡፡ እኔ እራሴ የፎረንሲክ ምርመራ ዘርፍ የወንጀል ምረመራውን ያጣራሁትን የነፍስ ግድያ ወንጀል ምርመራ ልንገረዎት አቶ ወርቁ ፈረደ፡፡ ሰዎች እነማን ነበሩ ካሉ ከኦሮሞ ማሕበረሰብ ውጭ የሆኑ ሰዎች ናቸው (ዘር ወይም የሚናገሩትን ቋንቋ ያልገለጽኩት እኔም በዘር ፍረጃ እንዳልሰምጥ ስለፈራሁ ነው)፡፡ በቤታቸው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ገብስማ ዶሮ ይታረዳል፡፡ በአንድ ወቅት ሚስት ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ በአይሮፕላን በረራ ስትጓዝ አድራ ጠዋት አዲስ አበባ ትገባለች፡፡ የገባችው ወር በገባ የመጀመሪያው ቀን ጠዋት አስራ ሁለት ሰዓት ላይ ነው፡፡ እጅግ ደክሟት ስለነበር እንቅልፍ ስለአሸነፋት ዶሮውን ማረድና መስራት አልቻለችም፡፡ ለገዳይዋ ባለቤቷም ይህን ነግራው ነበር፡፡ ዶሮው በወር
መግቢያ ለምን እንደሚታረድ ግን እርሷ አታውቅም ነበር፡፡ እርሷ የምታውቀው ታርዶ ተሰርቶ መበላቱን ብቻ ነው፡፡

anoleከድካሟ ለመለቃቅ ተኝታለች፡፡ አጅሬ ባል ዶሮ ካልታረደ የቤት ጣጣ ምን ሊያደርስበት እንደሚችል የሚያውቀው ሲወርድ ሰዋረድ የመጣ እምነትና ስጋት ነበረው፡፡ ይህን በመፍራት የሦሥት አመት ልጁ ባለበት የልጁን እናት በዶሮው ምትክ አረዳት፡፡ ቤቱን ዘግቶባት ሕጸኑንን ከእናቱ አስከሬን ጋር እንዲሆን ትቶ ሄደ፡፡ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው ከወንድሙ ጋር በመሆን ነው፡፡ ለምርመራው ፍንጭ የሠጠን እቤት ተዘግቶበት ከእናቱ አስከሬን ጋር የተገኘው ድርጊቱን የተመለከተው ሕጻን ነበር፡፡ ሲጠቃለል በእያንዳንዱ ማሕበረሰብ ከልምድ ወይም ከግንዛቤ ሕጸጽ የሚመነጩ አስከፊና አሳዛኝ በሰብአዊ ፍጡር ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች እንዳሉ አነዚህ ተግባራዊ ምሳሌዎች ያስረዱናል፡፡ በኦሮሞው ማሕበረሰብ ብቻ ሳይሆን ዓለም ሁሉ ቢፈተሽ በብዙ ማሕበረሰብ ታሪክ ብዙ ነገሮችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ እነዚህ ከሰው ልጅ ኋላ ቀርነት፤ ከእውቀት ማጣት/ማነስ ለወንድነት ወይም ለጀግንነት መለኪያ የሆኑ ተገቢ ያልሆኑ በሰብአዊ ፍጡር ላይ የሚፈጸሙ ዘግናኝ ነገሮች የሚቀሩት አእምሮአችን የተቃኘበት ያለማወቅ ስፍራውን ለእውቀት ሲለቅ ነው፡፡ በመሆኑም አሁን እነዚያ ነገሮች ፍጹም የሉም ባይባልም አዘውትረው አይሰተዋሉም፡፡ ሰው በራሱ መጥፎ አይደለም፡፡ ዛሬ ጨካኝ የሆነው ሰው ነገ ርህሩህና አሳቢ ወገን ሊሆን ይችላል፡፡ ጊዜ መስታውቱ ይህን አሳይቶናል፤ እናያለንም፡፡ ሌላው በጽሑፈዎ ውስጥ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ የአኖሌ ሀውልት ጉዳይ ነው፡፡ የሀውልት ነገር ከተነሳ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያሉ ሀውልቶችን አንድናስብ ያደርገናል፡፡ በእኔ እምነት ሀውልት በማስታወሻነት የሚቆመው መልካም ነገርን ለማስታወስ ብቻ አይደለም፡፡ ለዚህ አስረጂ አለኝ፡፡ የምኒልክ ሀውልት እርሰዎ እንዳሉት ቢስማርክነታቸውን ለማስታወስ መሆን ይችላል፡፡ ከዚያም ያለፈ ለኢትየጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ሕዝብ ታሪካዊ ፋይዳ አለው፡፡ በጥቁሮችና በነጮች
መካከል በተደረገ ጦርነት ለመጀመሪያ ጊዜ በአመራራቸው ብስለት ነጭን ድል የነሱ ንጉስ ናቸው ምኒልክ፡፡ ለጥቁር ሕዝብ ትግል አይን የከፈቱና ወኔን ያቀጣጠሉ ናቸው፡፡ ምኒልክን በዚህ እንስታውሳቸዋለን፡፡ ይህ አንዱ ገጽታቸውና ሲወደስ ሲሞገስ የሚኖረው ነው፡፡ ሌላም ገጽታ አላቸው፡፡ ሰው ናቸውና ያለደካማ ጎን አልተፈጠሩም፡፡ ፍጹም እግዚአብሔር ብቻ ነውና፡፡

መሀል ስድስት ኪሎ ያለው የሰማእታት ሃውልት፤ አራዳ ጊዮርጊስ በታች ያለው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ደግሞ ግፈኞች በእኛ ላይ የፈጸሙትን በደል ያስታውሰናል፡፡ እንዴት ተባብረን ወራሪ ኃይልን እንዳሰወገድን የትግላችን ሕያው ምስክሮች ናቸው፡፡ የተፈጸመብንን ግፍና አልበገር ባይነታችንን የምናስታውስባቸው ናቸው፡፡ እንዚህ የጣሊያን የግፍ ጭፍጨፋ ማስታወሻ ሀውልቶች ጉዳዩ የውስጥ ጉዳይ ቢሆንና ከወገን በወገን ቢፈጸሙ ኖሮ በአገር ውስጥ ለተፈጸመ ግፍ አስታዋሽ አይሆኑም ነበር ማለት አይቻልም፡፡ የእነዚህ ሀውልቶች በማስታወሻነት መቆየት መጪውን ትውልድ የደረሰብንን በደል፤
ያደረግነውን ተጋድሎ ብቻ የሚያሳዩ ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለጣሊያን ሕዝቦች አዲስ ግንኙነት መሰረት ናቸው፡፡ ጣሊያን ኢትዮጵያ ይህን ሀውልት ሰራች ብላ ቂም አልያዘችም፤ እንደውም ጣሊያን በሰጥችው ካሳ የቆቃ ግድብ ተሰርቷል፡፡ አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያና የጣሊያን ግንኙነት በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ ለምን ቢባል ሞሶሎኒ ወይም ወኪሉ ግራዚያኒ ለፈጸመው የግፍ ሥራ የአሁኑ የጣሊያን ትውልድ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ ሀውልቶች የሚያሳዩት ከአልበገር ባይነትና ከመስዋእትነት ባሻገር ይቅር ባይነትን፤ አስተዋይነትን፤ ያ አሳፋሪና ዘግናኝ ነገር እንዳይደገም፤ ስህተት እንዳይፈጸም
አስተማሪነትን፤ ከዚህ በመነሳት መልካም የዓለም ማሕበረሰብ አብሮነትና ተምሳሌነትን ነው፡፡

የአኖሌ ሀውልት ለምን በዚህ መልክ አይታይም አቶ ወርቁ ፈረደ? የአኖሌን ሀውልት ከመስራት ለህዝቡ ለምን የመብራትና የውሃ አገልግሎት አቅርቦት አልተመቻቸልትም? በማለትና ጥያቁ በማቅረብ አቶ ወርቁ ፈረደ ለሀውልቱ የወጣው ወጪ ከንቱ እንደሆነ ነግረውናል፡፡ የምኒልክ፤ የአቡነ ጴጥሮስ፤ የሰማእታት ሀውልቶቸች ሲሰሩ የአዲስ አበባ ሕዝብ መብራትና ውሃ በበቂ ሁኔታ ነበረው? በቂ ት/ቤት፤ በቂ መኖሪያ ቤት ነበረው? ጉዳዩ “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” ካልሆነ የአኖሌ ሀውልት በአገራችን ዋና ከተማ በአዲስ አበባ ካሉት ከላይ ከፍ ብሎ ከጠቀስኳቸው ሀውልቶች የሚለይ አይደለም፡፡ መልካም ያልነበረውን የግንኙነት ታሪካችንን በማስታወስ ያ እንዳይደገም፤ በመተባበር፤ በመፈቃቀር፤ በመደጋገፍ፤ እንዴት ወደፊት አብረን መኖር እንዳለብን የሚያሳይ እንጂ በአያት ቅደመ አያት ለተፈጸመ ጉዳይ የዛሬው ትውልድ እዳ ከፋይ፤ ተበዳይም ካሳ ጠያቂ እንዲሆን አይደለም፡፡ ምናልባት ሀውልቱ ሲመረቅ የተደረጉ ንግግሮች፤ የተሰጡ አስተያየቶች የኦሮሞን ሕዝብ የሚወክሉ ተደርገው ተወስደው ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ መልክ ሊወሰዱ ግን አይገባም፡፡ መንግስታት ያልፋሉ ሕዝብ ግን አብሮነቱ ይቀጥላል፡፡ የአኖሌ ሃውልት መልካም ላልነበረው ግንኙነታችን ማስታወሻ፤ ለወዲፊት አብሮነታቸን ማስተማሪያ፤ ከስህተት መታቀቢያ እንጂ ቂም በቀል ቀስቃሽ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡ ለምን ቢባል የሰማእታት ሀውልት በኢትዮጵያና በጣሊያን መካከል ጦር አላማዘዘም፤ የጣሊያን ነጋዴ፤ ወይም ቱሪስት፤ ወይም ዲፕሎማት ኢትዮጵያ ሲመጣ አሉታዊ ተጽእኖ አልፈጠረም፡፡ ይልቁንስ አሁን በአቶ ወርቁ ፈረደ ስለ አኖሌ ሀውልት የቀረበው ጽሑፍ አሉታዊ ተጽእኖ አለው፡፡ ሊስተዋልና ሊታይ ይገባል ቂም ይቀሰቅሳል በሚለው ብቻ ሳይሆን በመልካም ጎኑ ተገቢ ያልነበረውን ግንኙነት እያስታወሰ ግንኙነታችን በእኩልነት ላይ እንዲመሰረት በማድረግ የጋራ ተጠቃሚ ያደርጋል ብለን ልንቀበለው ይገባል፡፡

ሦሥተኛው በአቶ ወርቁ ፈረደ ጽሑፍ ያለተመቸኝና ለአማራውም ለኦሮሞውም ቂም በቀል ቀስቃሽ ነው የምለው የቃላት አጠቃቀማቸው ነው፡፡ “ነውጠኛ”፤ “ገባር”፤ “መመጻደቅ” የመሳሰሉት ለጽሁፋቸው የሚመጥኑ ሆነው አላገኘኋቸውም፡፡ ነውጠኛ የሚለውን ቃል ለእንግሊዝኛው violent የሚል ቃል አቻ አድርገው ተጠቀመውበታል፡፡ አቶ ወርቁ ፈረደ እንደ ዋቢ የተጠቀሙበት ታሪክ ጸሐፊው የአርሲ ኦሮሞዎችን የውጊያ ችሎታ ፍጥነታቸውን ከጭልፊት፤ የፈረስ ውጊያ ችሎታቸውን ሁለት ሰው በአንድ ፈረስ ላይ በመሆን እንዴት በሃይለኝነት እንደሚዋጉ በመግለጽ ኃይለኛና ፈጣን ተዋጊዎች እንደነበሩ ሲገልጽ በጽሑፉ ወስጥ violent የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል ተጠቅሟል፡፡ ይህን ቃል የተጠቀመው የአርሲ ኦሮሞዎቸችን የውጊያ ጥበብ፤ ጀግንነታቸውን፤ ፍጥነታቸውንና ኃይለኛነታቸውን ለመግለጽ እንጂ ነውጠኛ ለማለት አይደለም፡፡ እረ ለመሆኑ የራሴን የግሌን አላስነካም በማለት የሚዋጋ ሰው እንዴት ነውጠኛ ይባላል? እንዲህማ ከሆነ አብዲሳ አጋ፤ አሉላ አባ ነጋ፤ ሞገስ አስገዶም፤ አብርሃም ደቦጭ፤ ዘርዓይ ደረስ ነውጠኛ ናቸው ማለት ነው? የአድዋው ድል የነውጠኞች ድል ነው ማለት ነው? “ገባር” እና “መመጻደቅ” የሚለው አገላለጽም በቀል ቀስቃሽ ሰውን ተንኳሽ ነው፡፡
ባይጠቀበሙት ይመረጥ ነበር፡፡

አቶ ወርቁ ፈረደ በገዳ ሥርዓት ውስጥ ሰው ያልገደለ ሥፍራ የለውም በማለት አትተዋል፡፡ እስካሁን ድረስ በታላላቅ ምሁራን ስለገዳ ሥርዓት ከተጻፉት መጽሐፎች አቶ ወርቁ ፈረደ ያነበቡት የተለየ ነው፡፡ እንደውም አይደለም ነፍሰ ገዳይ በሌላ የወንጅል ድርጊት የተቀጣ ወይም የተጠረጠረ ሰው በገዳ ሥርዓት ውስጥ ስፍራ የለውም፡፡ ለዚህ ነው በመግቢያዬ ላይ ከሰላሳ ሁለት አመት በፊት ስላነብብኩት መጽሐፍ የጠቀስኩለዎት፡፡ እነዚህ ታሪክ ጸሐፊዎች አንደኛው ወዶ ገብ ተዋጊ ሲሆን የተዋጋው ደግሞ ለአጼ ምኒልክ ነው፡፡ አጼውን ደግፎ ጦር ሜዳ ውሎ ግዳይ የጣለ (ምናልበትም ቅጥረኛ ተዋጊ
የሆነ) ከዚህ ውጭ ምን ይጽፋል ተብሎ ይጠበቃል? አቶ ወርቁ አንባቢ ይመስላሉ፤ ይሁን እንጂ በአንድ ጭብጥ ላይ በአንድ መጽሐፍ ንባብ ድምዳሜ ላይ የሚደርሱ ከሆነ ወጀብን መቋቋም ያቃታት ጀልባ እንዳይሆኑ እሰጋለሁ፡፡ አራተኛው ነጥብ በአቶ ወርቁ ፈረደ ጽሑፍ ላይ ሳላነሳ የማላልፈው የመስፋፋቱ ጭፍጨፋ ምክንያት በኦሮሞ የሚሰለቡ ሰዎችን ለመታደግ ነው መባሉና በጭፍጨፋው ጊዜ ኦሮሞዎች እናቶችንና ሕጻናትን ገደል ከተዋል መባሉ ነው፡፡ በአንኮበርና በአርሲ መካከል ሰፊ የሽዋ መሬት ዛሬም ሕያው ምስክር ሆኖ ይኖራል፡፡ አርሲዎች አንኮበር ወይም መንዝ፤ ሸንኮራ ወይም ቡልጋ ወይም ተጉለት ሂደው ሰልበው ነው የነፍስ አድን ጦርነት የታወጀው? ታሪክ በዚህ መልክ አልዘገበውም፡፡ አጼ ምኒልክም ከውጭ መንግስታት ጋር ስለመስፋፋታቸው የተጻጻፏቸው ደብዳቤዎች ይህን አያስረዱም፡፡ መስለብን ለመከላከል ሲባል ነው ምኒልክ ይህን እርምጃ የወሰዱት የሚለው ምክንያት ውሃ አይቋጥርም፡፡ ለምን ቢባል የወረራው ምክንያት መስፋፋት መሆኑ በግልጽ በራሳቸው በንጉሱ ታምኗልና፡፡ አቶ ወርቁ ፈረደ የምኒልክን ቢስማርክነት (አገር ፈጣሪነት፤ ግዛት አስፋፊነት) ከተቀበሉ ለምን የአርሲን መወረር ሰለባን ለመከላከል እንደሆነ አድርገው ምክንያት
ያቀርባሉ? ምክንያቶቸዎ እርስ በእርስ አይጣረሱም?

አንድ የሕዝብ ክፍል ሌላውን ሲወር ወራሪው ሴትና ሕጻን ይዞ ወረራ ሊሔድ የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡ ባይሆን ተወራሪው ሴቶችም ህጻናቶችም ሊኖሩት ስለሚችል ተጠቁብኝ ቢል ምክንያታዊ መሆን የቻላል፡፡ ተደርጎም ከሆነ እጅ መገንጠል ጡት መዘንጠል የደረሰበት ልቡ የቆሰለ አእምሮው በበደል ከሰከረ ተጎጂ እንዴት ማስተዋል የተመላበት የዘመናዊ ተዋጊ ጦር ተግባር ይጠበቃል? በአርሲው ወረራ ጊዜ ሴቶችና ሕጻናቶች ከወራሪው ወገን ያን አክል አለቁ ቢባል ጉዳዩ ወረራ መሆኑ የቀርና ሰፈራ ወይም ስደት ይሆናል ማለት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ለጥናተዎ መነሻ የሆነው መጽሐፍ ተአማኒነት ይጎድለዋል ማለት ነው፡፡

ሲጠቃለል አቶ ወርቁ ፈረደ ጽሑፈዎ ከገንቢነቱና ከአቀራራቢነቱ ይልቅ ለሁለቱም ወገን ለተሰለበውም ለተቆረጠውም ቁስል አመርቃዥ በመሆን ፍጻሜ የሌለው አዙሪት (Vicious Circle) ውስጥ እየገባን እንድንዳክር የሚያደርገን እንጂ የሚያቀራርበን አይደለም፡፡ ጽሑፉን ሲጽፉት በቁጭት የጻፉት እንጂ ጊዜ ወስደው አስበውበት የጻፉት አይመስልም፡፡ ጽሑፉን ሲጽፉት ከስነ አመክንዮ ይልቅ ስሜት የገዛዎት የመስላል፡፡ ክርስቶስ ለስጋው ሳያደላ እንደተሰቀለልኝ ባምንም “ክርስቶስ ለስጋው አደላ” እንደሚባለው የማድላትና የመቆጨት ነገር ይስተዋልበዎታል፡፡ ዘር በደም ቢሆን ኖሮ ወሎ ዛሬ
ኦሮሞ ነበር፤ ጎጃምም ጎንደርም በከፊል፡፡ እኔና እርሰዎ አሁን ካለንበት ህልዎት ሌላ መሆን ባንችልም ልጆቻችን፤ የልጅ ልጆቻችን ነገ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ አናውቅምና ይረጋጉና ጠማማነት ለማቅናት ወይስ ቂመኝነት ለማጉላት?! በሚለው ርእስ ላይ ያስቡ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ጸሐፊውን በኢሜል አድራሻው kahalilukas@gmail.com ማግኘት ይቻላል፡፡

ብሔራዊ መግባባት ወይስ አገራዊ ውድመት?

$
0
0

( ያዕቆብ ኃይለማርያም )

አንዳንድ እንደዘረኝነት፣ ጐሰኝነትና የሃይማኖት ጥላቻ ስለመሳሰሉ አጸያፊ ክስተቶችና ሕዝባዊ ግንኙነቶች ማንሳትና ስለእነርሱም መጻፍ የሚቀፍ ከመሆኑም በላይ፤ ያልሆነ ስም ሊያሰጥና በዘረኝነት ተጠቃሚ የሆኑ አካላትንም ሊያስከፋ ይችላል፡፡ ሆኖም ሳይመሽ አገርን ከውድቀት ለመታደግ እና ሕዝብን ከጥፋት አፋፍ ለመመለስ ሲባል፤ ከአገርና ከሕዝብ የሚበልጥ የለምና ይሉኝታን ዋጥ አድርጐ በፍርሃት ሳይገደቡ፣ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ሳይሽሞነሞኑ እነዚህን አገር በታኝ ክስተቶችን በአደባባይ አፍርጦ ለማውጣት ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ሰው መሆንም በቂ ነው፡፡
hqdefaultጥላቻና ገደብ የለሽ የአገር ሀብት ዝርፊያ በተለይም የዘር ጥላቻና ዘረኝነት በሩዋንዳ ያስከተለውን በቃላት ሊገለጽ የማይችል ዘግናኝ እልቂትና ጭካኔን ያየና፤ የእነዚያ አክራሪ የሁቱ ጐሣ አባላትና መሪዎቻቸውን ሰይጣናዊ ድርጊቶች በፍርድ ቤት ከስሶ ሁኔታውን በዝርዝርና በጥልቀት የተረዳ ኢትዮጵያዊ፤ የዘርና የጐሣ ጥላቻ ያስከተለውን እልቂትና የአገር ውድመት በአገሩ ላይ እንዳይከሰት፣ ምንም ቢያስከፍልም ሆነ ምናልባትም የቁራ ጩኸት ቢሆን እንኳን ‹‹ውርድ ከራሴ›› በማለት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊረዳው በሚችልበት ቋንቋ በግልጽ የማስረዳት ኃላፊነት አለበት፡፡ በሩዋንዳ ከሰላሳ ዓመታት በላይ ሲያመረቅዝ የቀዬው የዘር ጥላቻ ወደ እልቂት ሊያመራ እንደሚችል ገና ከጠዋቱ ያስጠነቀቁ ምሁራን ከፋፋይ ሽብር ነዢዎች ተብለው እንደተፈረጁ ሁሉ፤ አሁንም ይህ ማስጠንቀቂያ ተመሳሳይ ዘለፋ ያስከትል ይሆናል፡፡ ዋናው ነገር ግን በአገራችን ላይ እያንዣበበ ያለውን አደጋ ሕዝብና መንግሥት ይረዱት እንጂ፣ ሌላው ሁሉ ገብስ ነው፡፡
የዘር ጥላቻንና የጐሣ ግጭቶችን በጠቅላላው ጐሰኛነትንና ጐጠኛነትን፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ገና ድሮ ልናልፋቸው በተገባ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ እኮ፣ ከብዙ አገራት ቀድማ አገራዊ አንድነትና ሉዐላዊነት የተጐናጸፈች፣ ጥልቅ ታሪክና የራስዋ ፊደልና የዳበረ ባህል ያላት አገር ነች፡፡ ሕዝቡም ለብዙ ምዕተ ዓመታት ክፉውንና ደጉን እየተጋራ በነፃነት የኖረ ሲሆን፤ ትናንት የተፈጠሩ አገራት ዘረኝነትንና ጐጠኝነትን አልፈው ሄደው አገራዊ አንድነት ሲፈጥሩ፣ እኛ በብሔረሰቦች መብት ስም እንዴት በዘረኝነት ውስጥ እንደነጋገራለን? ኢሕአዴግ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ በመታወቂያ ካርድ እየለየ በጐሣ ወይንም በብሔር ከረጢት ውስጥ እንዲገባ ከመደንገጉ በፊት፣ ይህንን ዛሬ የተንሰራፋውን ጐሰኝነት ልናልፈው ተቃርበን ነበር፡፡ በነገራችን ላይ በሩዋንዳ የተካሄደውን ጭፍጨፋ ቀላል ካደረጉት ነገሮች አንዱ፣ ሕዝቡ በነቂስ ዘሩን ወይንም ብሔሩን የሚያመላክት መታወቂያ አውጥቶ እንዲይዝ መደረጉ ነበር፡፡ በኢትዮጵያም ይህ አላስፈላጊ የሆነ ዝርዝር ሁኔታ፣ ማለትም ብሔረሰብ በመታወቂያ ካርድ ላይ እንዲጠቀስ የመደረጉ ጥቅም ምን እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡
ጐሰኝነትንና ጐጠኝነትን ልናልፋቸው ተቃርበን እንደነበረ ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ከሰላሳ ዓመታት በፊት ዩኒቨርስቲ አካባቢ፣ አንድ ሰው ከኢትዮጵያዊነቱ ውጭ አማራ ይሁን ኦሮሞ፤ ጉራጌ ይሁን ከምባታ አይታወቅም ነበር፡፡ ቢታወቅም በጓደኛ አመራረጥ ላይ የብሔር ማንነት ምንም ተጽእኖ እንዳልነበረው በዩኒቨርስቲው ያለፉ ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ በጊዜው የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ኢዲዩ፣ ኢሠፓ፣ ወዘተ ሕብረ ብሔራዊ ድርጅቶች ሲሆኑ፤ ከሕወሓትና ከኦነግ ውጭ ጐሰኝነትን መሰረት ያደረገ ፓርቲ አልነበረም፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሊቀበሉት የሚገባ አንድ ሐቅ ግን አለ፡፡ ይኸውም ዛሬ የአንድ ጐሳ ወይንም ብሔር አባል ቋንቋውን የመናገርና የማበልጸግ፣ በባህሉ መኩራትና መተግበር፣ የውስጥ አስተዳደሩን ራሱ የመምራት መብት እንዳለው አጠያያቂ ያለመሆኑ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ሕግጋት እውቅና ያገኘ ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም እንዲህ ዓይነት ያልተገደበ መብት መገንጠልን እንደማይጨምር አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የተረዱት አይመስልም፡፡ የመገንጠል መብት መቼና በምን ሁኔታ ይፈቀዳል የሚለው ጥያቄ ሰፊ ርዕስ በመሆኑ በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን፡፡ የእነዚህ የብሔረሰብ መብቶች መከበር፣ ዘረኝነትን አጥፍተው ብሔራዊ አንድነትን ያዳብራሉ እንጂ አያዳክሙም፡፡
ወደ ዋናው ጉዳያችን እንግባ፡፡ በስውር ቋንቋ ሳንሸፋፍነው፣ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ሳናሽሞነሙነው ከተነጋገርን፤ በአገራችን የዘር ጥላቻ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየተንሰራፋና እየተስፋፋ መሄዱ፣ ሰው ሁሉ ያወቀው ጸሐይ የሞቀው እውነታ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ በእነዚህ 23 ዓመታት ውስጥ የዘረኝነት ክስተቶች የተገለጡባቸው ቦታዎችና ሁኔታዎች በጣም ብዙ ስለሆኑ፣ ለናሙና ያህል ጥቂቶችን ብቻ እንጥቀስ፡፡
በብሔር ወይንም በዘር ልዩነት ምክንያት ከሕይወት መጥፋት ጀምሮ ያሉ ግጭቶች ያልተከሰቱባቸው የአገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች ጥቂቶች ናቸው፡፡ አንድ ጐሳ ወይንም ብሔር ከሌላ ጐሳ ጋር ተጋጭቶ፤ ይህን ያህል ሰው ሞተ፣ ይህን ያህል ንብረት ወደመ የሚል ዜና ሰርክ እየሰማን ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት አንዳንድ ሃፍረተ ቢስ ኃላፊነት የጐደላቸው ኢትዮጵያውያን፣ በፌስ ቡክ አማካይነት የሩዋንዳ እልቂት በኢትዮጵያ መደገም አለበት የሚል አስደንጋጭ መልእክቶች እንደሚያስተላልፉ ሳንረዳ አንቀርም፡፡ ጨቅላ ሕፃን ይዛ የእለት ጉርስዋን የምትለምነው የእኔ ቢጤ እንኳን፣ ብሔሯን ከምትለምነው ሰው መደበቅ አለባት፡፡ አለበለዚያ ተለማኙ ሰውዬ የማይወደው ብሔር አባል መሆኗን ካወቀ፣ የዳቦ ሳንቲም መንፈግ ብቻም ሳይሆን ብሔሯን እየጠቀሰ ሊቀልድባት ይችላል፡፡
መንግሥት አለ ወይ እስኪባል ድረስ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን፣ የክልሉ ብሔር አባላት አይደላችሁምና ከክልሉ ወይንም ከወረዳው በዚህ ቀናት ውጡ እየተባለ፤ የአካባቢው ሕዝብ ማፈናቀሉን ቢቃወምም እንኳን፣ ባለስልጣናቱ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ሜዳ እንዲወድቁ አድርገዋቸዋል፡፡ በጊዜው በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በቁጣ በታጀበ ንግግራቸው፣ በቤኒሻንጉል አማርኛና ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ከኖሩበት ክልል ማፈናቀል ሕገ-ወጥ መሆኑን እና ጥብቅ እርምጃም በአስቸኳይ እንደሚወሰድ ገልጸው ነበር፡፡ አስገራሚው ነገር ደግሞ ተፈናቃዮቹ ወደ ቤት ንብረታቸው ካለመመለሳቸውና መንግስት ነገሩን ናቅ አድርጐ ከመተው ባሻገር፣ እንዲያውም ተጨማሪ ዜጐች እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፡፡ ‹‹አለማወቅ ደጉ›› ሆነና ነው እንጂ፤ በዓለም አቀፍ ወንጀለኝነት የሚታወቀው የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈጽሙና የፈጸሙ ባለስልጣናት ምን እንደሚጠብቃቸው ቢያውቁ እንቅልፍ በዓይናቸው ባልዞረ ነበር፡፡ ከሰባ አመታት በፊት ለፈጸሟቸው ዓለም አቀፍ ወንጀሎች የቀድሞ ናዚ ጀርመናውያን፤ ስፔን ውስጥ ተይዘው፣ በዚሁ በያዝነው ዓመት ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ የቀድሞው ዩጐዝላቪያ መሪ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ፊት የቆመው፣ ግድያ ቢኖርም ግን በዋናነት ሰርቦች ሙስሊሞችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅለው ካምፕ ውስጥ አጉረው በማሰቃየታቸው ነው፡፡
የዘር ጥላቻ የሰውን ሕሊና ከሚሰውሩ፣ የሰው ልጅ የመጨረሻ አውሬነት አፍጥጦ እንዲወጣ ከሚያደርጉ ክፉ ድርጊቶች አንዱ ነው፡፡ የዘር ጥላቻ ተደጋግሞ እንደታየው በዘር ማጥፋት ይደመደማል፡፡ ቦስኒያ ውስጥ ሰርብ ያልሆኑት ዜጐችን መጨፍጨፍ፣ ኦቶማኖች በአርመኖች ላይ ያደርሱት እልቂት፣ የጀርመን ናዚዎች በይሁዲዎች ላይ የፈጸሙት ግድያና ስቃይ፣ ሳዳም ሁሴን በኩርዶች ላይ ያካሄደው የዘር ምንጠራ፣ ፖል ፖት ያካሄደው ገደብ የለሽ ጭፍጭፋ፣ ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ የፈፀሙት እልቂት፤ በዘር ጥላቻ ላይ ተመስርተው ከተፈፀሙ ግድያዎችና ሰቆቃዎች ውስጥ ዋንኞቹ ናቸው፡፡ አሳዛኙ ነገር ዘረኛነት ከመሰረተው ስርዓት ተጠቃሚ ያልሆኑ የዚያ ዘር አባላትንም ለብቀላውና ለጥቃቱ ሰለባ ማድረጉ ነው፡፡
የዘር ጥላቻ ከወለዳቸው ዕልቂቶች መሀከል፣ እንስሳት እንኳን ሊፈጽሙት ከማይችሉት የጭካኔ ተግባራት የሚቆጠረው የሩዋንዳው የቱትሲዎች እልቂት ቀዳሚነቱን ሳይዝ አይቀርም፡፡ ሩዋንዳ የቤልጅየም ቅኝ ግዛት በነበረችበት ጊዜ፤ ቅኝ ገዢዎቹ አፍንጫ ሰልካካና ቁመተ ረጃጅምና ከኢትዮጵያ ፈልሰው እንደሄዱ የሚነገርላቸውን ከሕዝቡ 15% የሚሆኑትን ቱትሲዎች ወኪል በማድረግ፣ 85% በሆኑት መደበኛ አፍሪካዊ መልክ ባላቸው ሁቱዎች ላይ አነገሷቸው፡፡ የቱትሲዎችና የኢትዮጵያ ግንኙነት ከተነሳ፤ ከሃያ ሺህ በላይ ቱትሲዎች እግርና እጃቸውን ታስረው ወደአገራችሁ ኢትዮጵያ ግቡ ተብለው ወደሰሜን ከሚፈስ ቪክቶሪያ ኃይቅ ጋር ከሚቀላቀል ወንዝ ውስጥ መጨመራቸው ይታወቃል፡፡ ሥልጣን በመጠቀም የመንግሥቱን ቢሮክራሲ፣ ንግዱን፣ ትምህርቱን፣ የከብት እርባታውን በመጠቅለል ሁቱዎችን መብት አልባ ዜጐች አደረጓቸው፡፡
ቂም ቋጥረው የኖሩት ሁቱዎች፣ እ.ኤ.አ. በ1962 ዓ.ም. ሩዋንዳ ነፃ ስትወጣ የመንግሥቱን ሥልጣንና መዋቅራት፣ ቢሮክራሲውን፣ የትምህርቱና የንግድ ዘርፎችን በሙሉ ከመጠቅለል አልፈው፤ በቱትሲዎች ላይ የበቀል እርምጃ መውሰድ ጀመሩ፡፡ ቤት ንብረታቸውን ንግዳቸውን የተዘረፉት፣ ከቢሮክራሲው የተባረሩት ቱትሲዎች ደግሞ ወደኡጋንዳ ተሰደዱ፡፡ ወደኡጋንዳ የተሰደዱት ቱትሲዎች ተደራጅተው ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ በጦር ኃይል አማካኝነት ወደ አገራቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ ሲጀምሩ፤ ለዘመናት እያመረቀዘ የመጣው የዘር ጥላቻ፣ አገሪቷ ነፃ ከወጣች ከ32 ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ. በ1994 ዓ.ም. ፈንድቶ፣ መቶ በማይሞሉ ቀናት ውስጥ በሩዋንዳዎች ስሌት አንድ ሚልዮን ሶስት መቶ ሺህ ቱትሲዎችና ጥቂት ለዘብተኛ ሁቱዎች፤ ህፃን፣ አሮጊትም ሆነ ሽማግሌ ሳይባል በቆንጨራ ራሳቸውን ለሁለት በመበርቀስ ተጨፈጨፉ፡፡ በኢትዮጵያ ፋሽስቱ ደርግ እንዳደረገውም፣ አንዳንዶቹ የሚገደሉበትን ጥይት መግዛት መቻላቸውን እንደ አንድ ልዩና ጥሩ ዕድል ቆጥረውታል፡፡ የሩዋንዳ ሁቱ ጨፍጫፊዎች ተራ የመንደር ወይንም የገዢው ፓርቲ ዱርዬዎች (ኢንተራሃሞዌ) ብቻ ሳይሆኑ፤ የዘር ጥላቻ ምሁር ወይንም መሃይም ስለማይል የታወቁ ምሁራን እና ቄሶች ሳይቀሩ ተሳትፈዋል፡፡ በመሃል ኪጋሊ አንድ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ሁቱ ቄሶች ቱትሲ ቄሶችና ምዕመናንን የጨፈጨፉት የሬሳ ክምር፣ ዛሬም በቤተ-ክርስቲያኑ ውስጥ ይታያል፡፡ ቱትሲዎች ወደኡጋንዳ ሲሰደዱ የ6 ዓመት ሕፃን በነበረው በዛሬው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ መሪነት፣ በጦርነቱ አሸንፈው አገሪቱን ሲቆጣጠሩ፤ ቁጥራቸው የበዛ ሁቱዎች በተራቸው ተገድለዋል፡፡ የእነዚህ የሁለቱ ጐሳዎች መጨፋጨፍ የአገር ጥፋትንና የጅምላ እልቂትን ከመውለዱ ውጪ፤ በዘር ጥላቻ አሸናፊና ተሸናፊ እንደሌለ አመላካች ነው፡፡
ፈረንጆች፣ አንድ ክፉ ነገር አሸንፎ የሚወጣው በጥቂት ሰዎች ዝምታ ምክንያት ነው የሚል አባባል አላቸው፡፡ በዚህ ድሀ ሕዝብ ጫንቃ ተምረው፣ ኑሮአቸውን ካደላደሉ በኋላ አገር አማን ነው ብለው ዝምታን መርጠው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፤ ቢያንስ የሕሊና ወቀሳ እንደሚነዘንዛቸው ሊክዱ አይችሉም፡፡ በዚህ አደገኛ ጊዜ ዝምታ ወርቅ ሳይሆን ክህደት ነው፡፡ በሥልጣን ላይ የተቀመጡ ሰዎች ስልጣንና ቁሳዊ ጥቅሞች አይናቸውን ጋርዶት፣ ልሳናቸውን ዘግቶት እንደሆነ አይናቸውን መግለጥ ብቻ ሳይሆን ቢበለጥጡት ይበጃቸዋል፡፡ ምክንያቱም ይህች አገር በዘር ጥላቻና በሙስና ምክንያት ብትፈርስና የጅምላ እልቂት ቢከሰት፤ በመጀመርያ የገመዱ ሸምቀቆ የሚገባው በእነርሱ አንገት መሆኑን መዘንጋት የለባቸውምና፡፡
በአገራችን የዘር ጥላቻ በየእለቱ የምናየው ነገር መሆኑ፤ በዚህ ጥላቻ ምክንያትም አገራችን ወደገደል እያመራች መሆኑን አሌ የሚሉ መሪዎችም ሆኑ ምሁራን፤ አውሎ ነፋስ እየመጣ መሆኑንና ሊያደባያት እንደሚችል እያወቀች ራሷን አሸዋ ውስጥ በቀበረች ሰጐን ይመሰላሉ፡፡ ስለዚህ ዘረኝነት የሚያስከትለው አሸናፊና ተሸናፊ የሌለበት የጅምላ እልቂት እርቆ ሳይሄድ፣ መዋጋት ዛሬ እንጂ ለነገ የሚተው አይደለም፡፡ የዚህ ጸሐፊ አስተያየትና ግንዛቤ ስህተት ቢሆን ምንኛ በተደሰተ! ስህተት ባይሆንስ? አንዴ ካንሸራተተ መመለስ እንደማይችል ወይንም እጅግ በጣም አስቸጋሪ ለመሆኑ፤ በመፍረስ ላይ ያሉት እነሶርያ፣ የመሃከለኛው አፍሪቃ ሪፐብሊክና ደቡብ ሱዳን (ግብጽ እንኳን ሳትቀር) ሕያው ምስክሮች ናቸው፡፡
የችግራችን መፍትሔ ሁሉም ሊገባው በሚችልበት፣ በሁለት ቃላት ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ይህን ያህል የዘር ጥላቻ ተካርሮ ወደ ግጭት ባላመራባት ኢትዮጵያ ቀርቶ፤ በዚያ በጥቂት ቀናት ውስጥ በዓለም ተወዳዳሪ ያልተገኘለት እልቂት በተፈጸመባት ሩዋንዳ እንኳን፤ ዛሬ በሕዝቡ መሀከል እርቅ ወርዶ፣ ሩዋንዳ በአፍሪቃ የሰላምና የእኩልነት ተምሳሌት ለመሆን ችላለች፡፡ ዛሬ ሩዋንዳዊ እንጂ እገሌ ሁቱ ነው፣ እገሌ ቱትሲ ነው ማለት አጸያፊ ሆኗል፡፡ ስለዚህ፣ ምንም እንኳን መጪዎቹ ጊዜያት አስፈሪ ቢሆኑም ቅሉ፤ ብሔራዊ ዕርቅ በሚሉ ሁለት ቃላት፣ መፍትሔውን ማስቀመጥ ይቻላል፡፡
በአገራችን የኢሕአዴግ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝባዊ ድርጅቶች ፈቃደኝነት እስካለ ድረስ፣ በቀላሉ እርቅ ወርዶ፣ ለዘር ጥላቻ መንስኤ የሆኑ ነገሮች ታርመው፤ አገራችን ሰላም፣ ፍቅርና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ከመሆን ምንም የሚያግዳት ነገር አይኖርም፡፡ ብሔራዊ ዕርቅ ይውረድ ሲባል፣ “ማን ከማን ጋር ተጣልቷል?” ብሎ መቀለድ፤ በኋላ መሪር ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል፡፡ ብሔራዊ መግባባት እንዴት ይመጣል የሚለው፣ በአገሪቱ እኩልነት፣ ዴሞክራሲና ፍትሕ ያለመ በአገር ደረጃ የሚወሰን ሲሆን፤ ለመነሻነት ያህል ቀጥሎ በተዘረዘሩት መጀመር ይችላል፡፡

 

ሀ) ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲና የሃይማኖት መሪዎችና አባላት፤ በጠቅላላው ከፖለቲካና ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎችን በሙሉ መፍታት፤
ለ) የጸረ-ሽብርተኛ አዋጅ መሰረዝ፤ እና
ሐ) በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝባዊ ድርጅቶች አባላትና መሪዎችን በሽብርተኛነት የተፈረጁትንም አጠቃሎ የያዘ አንድ ጉባዔ በአዲስ አበባ ማካሄድ፤ የሚሉት መነሻ ሊሆኑን ይችላሉ ብዬ አምናለሁ፡፡
ይህ በሀገራችን ያለው ሁኔታም፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊረዳው የሚገባ በመሆኑ፣ ጽሑፉን ያነበበ ለሌላ ቢያስተላልፈው ግንዛቤ ለማስጨበት የሚረዳ ይመስለኛል፡፡

በዓሉ ግርማን ለመግደል ሴራ ያስፈልግ ነበር ወይ?

$
0
0

( ከተስፋዬ ተሰማ)

በቅርቡ በኢትዮ ሚዲያ የታዋቂው ጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ አሳዛኝ ህልፈት/አሟሟት በተመለከተ “በዓሉ ግርማን የበሉት ጅቦች አልጮህ አሉ” በሚል ርእስ አንድ ጽሑፍ ቀርቦ ነበር። ይሄ ጽሁፍ የቀረበው በማን፣ በየትኛው የስነፅሁፍ ወይም የጋዜጠኝነት መስፈርት ተመዝኖ እንደሆነ ባይታወቅም “ድንቅ ጽሁፍ” የሚል ክብር ተሰጥቶታል። ይህን ጽሁፍ የፃፈው አበራ ለማ ይባላል። ጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ በተገደለበት ዘመን በአንድ መስሪያ ቤት ህዝብ ግንኙነት ውስጥ ይሰራ የነበረ ነው።

አበራ ያቀረበውን ጽሁፍ ሳነበው ታዋቂው የህግ ባለሙያ አቶ አለማየሁ ዘመድኩን (አሌክስ) እየደጋገመ የሚነግረኝ ቀልድ ለበስ ቁምነገር ትዝ አለኝ፤ አሌክስ ለፍትህ የቆመ እውነተኛ ሰው ብቻ ሳይሆን ትልልቅ ቁምነገሮችን ለዛ ባለው ቀልድ የመግለጽ ችሎታም ያለው ሰው ነው። አሌክስና እኔ ብዙ ጊዜ ሻይ እየጠጣን ስለሃገራችንና ስለዓለም ሁኔታ የምናወራቸው የጋራ ወዳጆች አሉን። ሁለቱም ጋዜጠኞች ናቸው። አንደኛው ብዙ ነገር የሚያውቅ፣ በምክንያት የሚያምን፣ሃሳቡን በጥሩ ሁኔታ የሚገልጽ ነው። ሌላው ደግሞ ስሜታዊና አሰልቺ ነው። አሌክስ የሁለቱን ሰዎች ልዩነት ለዛ ባለው ቀልድ ለመግለጽ እንዲህ ይለኛል፤ «ስማ ምናለበት ጋዜጠኝነት እንደወታደርነት አስር አለቃ፣ ጄኔራል..የሚባል የማዕረግ ስም ቢኖረው?.አሁን እነዚህ ሰዎች ሁለቱም ጋዜጠኛ ይባላሉ?» ይለኛል፤
bealu girma 1
ጋዜጠኛ አበራ የፃፈው ፅሁፍ 16 ገጽ ያለው፣ በአራት ዋና ዋና ክፍል ተከፍሎ የሚታይ ነው። ፅሁፉን በአጭሩ፣ በጨዋነትና በቅንነት ስንፈትሸው ሶስት መልክቶችን በአንድነት የያዘ ይመስላል። በስነፅሁፍ አንድ ፀሐፊ በፅሁፉ ሊነግረን ከሚፈልገው መልክት ውጭ ሌሎች ተጨማሪና ዋና መልክቶች ሲኖሩት ፅሁፉ(intentional fallacy) አለው ይባላል። የአበራ ለማ ጽሁፍ የመጀመሪያ መልእክቱ ታዋቂው ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ የተገደለው የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኰ/ል መንግስቱ ሃ/ማርያም፣ በወቅቱ የነበሩ ከፍተኛ የደርግ ባለስልጣናት፣ ማንነታቸውን ግልጽ ያላደረገልን በዓሉን የሚጠሉ ሰዎች፣ ጥቅም የሚፈለጉ የበዓሉ ጓደኞች፣ የስራ ባልደረቦችና (በጊዜው የማስታወቂያ ሚ/ር መስሪያ ቤት ባለስልጣኖች የነበሩ) ሰዎች በመተባበር በተለየ ሴራ ነው። እኔ ይህን ሴራ ደርሼበታለሁ ነው።

ሁለተኛው መልእክቱ ደግሞ የበዓሉ አሟሟት ግልጽ እንዲሆን የደርግ ባለስልጣናት (በሱ አጠራር ትልልቆቹ ጅቦችና ጓደኞቹ፤ የስራ ባልደረቦቹ አሁንም በሱ አጠራር ትንንሾቹ ጅቦች በዓሉ እንዴት እንደተገደለ፣ ለምን እንደተገደለ፣ ማን እንደገደለውና ማን እንዳስገደለው ለኢትዮጵያ ህዝብና ለበዓሉ ቤተሰቦች ምስጢሩን የመናገር ታሪካዊ ግዴታ አለባቸው፤ እኛም እየጠበቅናቸው ነው የሚል ትእዛዝ አዘል ጥያቄና የአንድ ወገን ክስ ነው። የመጨረሻው ምናልባትም የዚህ ጽሁፍ ዋናው መልክት ጋዜጠኛ አበራ በተለያዩ ምክንያቶች ከቀድሞ የማስታወቂያ ሚ/ር አለቆቹና ከተወሰኑት ደራሲያን ጋር ያለውን ግጭት በቂም ደረጃ ይዞ፣ አሊያም ባለው የፖለቲካ አቋም በኢህአዴግ ውስጥ ያለውን ታማኝነት ለማሳየት እነሙልጌታ ሉሌን መስዋእት አድርጐ በኢህዴግ ለመሰዋት የበዓሉን ስም አስታኰ ስማቸውን ለማጥፋት የፃፈው ጽሁፍ ይመስላል።

በእርግጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ምክንያትና ያለበቂ ምክንያት የፍትህን አደባባይ እየታሰሩ፣ እየተገረፉና እየተገደሉ እንዲሁም አገዳደላቸው ምስጢር እንደሆነ ቀሮቷል። እንዳለመታደል ሆኖ ይህ አሳዝኝ ድርጊት አሁንም በኛ ዘመን ቀጥሏል። በደረግ ዘመን የአምባገነኖቹና ነፍስገዳዩቹ ሰለባ ከሆኑት ንፁሃን ዜጎች ውስጥ አንዳንዶቹ ለሃገራቸው ብዙ የደከሙና ሽልማት የሚገባቸው ነበሩ።በህይወት ቢኖሩ ለሃገራቸው ብዙ የሚጠቅሙ ነበሩ። በጣም የምንወደውና የምናደንቀው ታዋቂው ጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማም ያለበቂ ምክንያት በግፍ ከተገደሉት የሀገራችን ታላላቅ ሰዎች አንዱ ነው። የደራሲ በዓሉ ግርማ ጉዳይ የቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳይ ነው። በዓሉ ግርማን የሚያክል በኢትዮጵያ ጋዜጠኛነትና ስነጽሁፍ ታላቅ ቦታ የነበረው ሰው እንደዋዛ ወጥቶ መቅረቱ ወይም ያለበቂ ምክንያት መገደሉ የሁላችንም ሃዘንና የልብ ስብራት ነው። የዚህን ታላቅ ሰው የአገዳደል ምስጢር ማወቅና ለማወቅ ጥረት ማድረግ መቀጠል ያለበት በመሆኑ ሁሉም ወገን ሃላፊነት እንዳለበት እሙን ነው።

በዓሉ ግርማ ከሞተ ከ30 አመት በኋላ የተፃፈው የጋዜጠኛ አበራ ለማ ጽሁፍ አሳዛኙን የበዓሉ ግርማን አሟሟት ምስጢር የሚፈታ ሳይሆን ነገሩን የበለጠ የሚያወሳስበውና አንባቢውን ግራ የሚያጋባ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።በአሉ ግርማ የተገደለው በሴራ ነው ብሎ ቃላቶችን እየቆራረጠና እየቀጠለ ሊያሳየን የሚፈልገው ነገር ምክንያታዊ ያለሆነና እውነትነት የሌለው ሁላችንም ከምናውቀው ወፍ በረር አሉባልታና ወሬ ያለፈ አዲስ ነገር የለውም። አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል እንደሚባለው አንድ ሰው ሲናገር/ሲጽፍ የተናጋሪው ወይም የፃሀፊውን ማንነት ከፅሁፉ በቀላሉ መረዳት ይቻላል። አበራ ለማ ይህን ጽሁፍ ሲፅፍ የበዓሉ ግርማ አሳዛኝ የአሟሟት ምስጢር አሳዝኖትና አሳስቦት መሆኑን እንድንጠራጠር የሚያደርጉ ጭብጦች ግን አሉ።

በዓሉ ግርማ ያለበቂ ምክንያት መሞቱ ያሳዝነኛል፣ የሚል ሰው ሌሎች ንጹሃን ሰዎችን ያለበቂ ማስረጃ “የበዓሉ ገዳዮች” እያሉ መወንጀልም አግባብ አይደለም። ከወንጀሎች ሁሉ ወንጀል- ወንጀለኛ ያልሆነን ሰው “ወንጀለኛ” ማለት ነው! የበዓሉን ስም እየጠቀሱ “የበዓሉ ጠበቃ ነኝ” በማለት የበዓሉን ጉዳይ አስታኮ የግል ቂም መወጣጫና የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈፀሚያ ለማድረግ መሞከር – በዓሉን እንደገና የመግደል ያክል ነው። በዚህ ቅኝት የተፃፉ ፅሁፎች በህዝቡ ውስጥ ሲሰራጩ የበዓሉን የአሟሟት ምስጢር የበለጠ ውሉን እያጠፋውና እያወሳሰበው ይመጣል የሚል ስጋት አለኝ። በዓሉ ግርማን በተመለከተ እስከአሁን ያልተመለሱ ጥያቄዎች ስላሉ እነሱ እስኪመለሱና የበዓሉ ግርማ መጨረሻ እስኪታወቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚችለውን ማድረግ አለበት። ይሄ ጥረት እንዲሳካ ከተፈለገ ከምንም አይነት ፖለቲካ ጋር ንክኪ የሌላቸው፣ ነፃና ገለልተኛ ሰዎች በተለይም የሀገራችንን ታሪካዊና ወቅታዊ ሁኔታ በትክክል የሚረዱ፣ ከቂምና ጥላቻ ነፃ የሆኑ ወጣት ምሁራኖች ማሳተፍ ያስፈልጋል። እዚህ ላይ ሁላችንም ልንረዳው የሚገባ አንድ ቁም ነገር ያለ ይመስለኛል።

እንደ አንድ መጠነኛ የስነጽሁፍ ግንዛቤ ያለው ተራ ዜጋ የጋዜጠኛ አበራን ያለፈ ታሪክ፣ የግለሰቡን ባህርይ፣ ድሮ የነበረውንና አሁን እያራመደ ያለውን የፖለቲካ አቋምና እንቅስቃሴ፣ ይህን ጽሁፍ ለምን አላማና ማን ልኮት ፃፈው የሚለውን የሰውዬው የግል ታሪክ ላይ ብዙ ጊዜ ሳላጠፋ የጽሁፉን ይዘት ብቻ ሚዛን ላይ አስቀምጬ ለማየት ሞከርኩ። ይኸው ጽሁፍ እንኳን እውነተኛውን የበዓሉ ግርማን አሟሟት ሊነግረን እራሱ በውሸት ስማቸውን ሊያጠፋቸው የፈለጋቸውንም ሰዎች ሰሩት የሚለውን የውሸት ወንጀል ሴራም በግልጽ የሚያሳይ አይደለም። ፅሀፊው ይህን ትልቅ አጀንዳ ያለውን ጽሁፍ ሲጽፍ በቂ ዝግጅት አላደረገም፣ አለኝ የሚለውን እውነት የሚያጠናክርለትም የተለየ ማስረጃ የለውም። የአበራ ጽሁፍ በልብወለድም ይሁን በኢልብወለድ መሰረታዊ የጽሁፍ ሚዛን ሲመዘን ደረጃውን ያልጠበቀ ተራ የፕሮፖጋንዳ ጽሁፍ ነው። ጽሁፉ በእውነተኛ መረጃ ድርቅ የተመታ በመሆኑ እንደ አጭር ልብወለድ መለካቱ የተሻለ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። የሚያሳዝነው ነገር ፅሁፍ እንደ ልብወለድ ቢወሰድ እንኳ ደካማ ከሚባሉት የልቦለድ ፅሁፎች የሚመደብ ነው፡:

ይሄ በዓሉን ለመግደል የተጠነሰሰ ሴራ የሚባለው ነገር ግልጽ ሆኖ ያልተቀመጠ እርስ በርሱ የሚጋጭ ነው። ለመሆኑ በአሉ ግርማን ለመግደል ይሄ ሁሉ ባለስልጣን የሚሳተፍበት ሴራ አስፈላጊ ነበር ወይ? ሴራው ቢኖርስ ይሄን ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት የተሳተፉበትን ሴራ ተራው ጋዜጠኛ አበራ ለማ ለማውቅ እድሉና አጋጣሚው ነበረው ወይ? አበራ የሌሎች ሰዎችን ማስረጃ በመውሰድ እሱ ከሚያውቀው ነገር ጋር በማገናኘት መረጃ ትንተና ነው የሰጠው ቢባል እንኳ ለመሆኑ አበራ እንደምንጭ የተጠቀመበት መረጃ ምን ያክል እውነተኛ ነው? ይህን ያገኘውን መረጃ አበራ በትክክል ለመተርጎማና ለመትንተን ችሎታውና ፍላጎቱ አለው ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀርም። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ብዙ የሚጠየቁ ጥያቄዎች፣ ብዙ ያልተመለሱ ነገሮች አሉት።

በኔ ግምት አንድ ቅን ዜጋ ይህን ጽሁፍ ሲያነብ መጀመሪያ አበራን የሚጠይቀው ጥያቄ “ለመሆኑ በደርግ ዘመን አንድ ደራሲ ለመግደል ይህ ያክል የተቀነባበረ ሴራ አስፈላጊ ነበር እንዴ?.” የሚል ነው። ጋዜጠኛ አበራ የደርግ ስርአትን ጠንቅቀው የሚያውቁ ንጹሃን ዜጎችን ያለምንም ምክንያት ያለምንም ሴራና አድማ በቀላሉ የመግደል ዘመቻው ውስጥ ተሳታፊ ስለነበሩ ጥያቄውን በቀላሉ ይመልሱታል። በነገራችን ላይ ጋዜጠኛ አበራ የቀይ ሽብር ነፍሰ ገዳዮች ጉዳይ የያዙት ልዩ አቃቤ ህግ ግርማ ዋቅጅራ ክስ ውስጥ እነማህደር የተባሉትን ወጣቶች በማስገደል ስማቸው በ27ኛ ተርታ ተመዝግቦአል። ከኢህአፓ መስራች አንዱ የሆኑትም ክፍሉ ታደሰ ደግሞ በመጽሃፋቸው ላይ አበራ ለማ ማስታወቂያ ሚ/ር አካባቢ በ07 ቀበሌ ቀንደኛ ነፍሰ ገዳይ እንደነበሩ ጠቅሰዋቸዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የብዙ ወጣቶችን ደም የጠጣው የእርገጤ መድበው የቅርብ ጓደኛ እንደነበሩም የሚያውቋቸው ሁሉ ስለሚናገሩ በደርግ ጊዜ እንኳን እነኰ/ል መንግስቱ እነ አበራ እንኳን የሰዎችን ነፍስ በቀላሉ ማጥፋት የሚችሉበት ዘመን ስለነበረ የጋዜጠኛ/ደራሲ በዓሉ ግርማም ህይወት እንዲሁ በቀላሉ መቀጠፉን ለማሰብ አስቸጋሪ አይደለም።

ሌላው ይህን ጽሁፍ ተራ ውሸት የሚያደርገውና አጠቃላይ የጽሁፉን ይዘት የሚያናጋው በዓሉ ግርማ የተገደለው በተቀነባበረ ሴራ ነው ብሎ ሊነግረን የሚፈልገው ሃሳብ በግልጽ የተቀመጠ አለመሆኑ ነው፤ “ሴራውን” በጥንቃቄ ስንመረምረው ሁለት አይነት ይመስላል፤ በሴራው ውስጥ ማን ከማን ጋር ተባብሮ እንዳቀነባበረው በግልጽ አላስቀመጠውም። በጥንቃቄ ስላልዋሸ ሴራዎቹ የተለያዩና እርስ በርስ የሚቃረኑ ሆነውበታል። አንደኛው ሴራ መንግስቱ የተሳተፉበት ሆኖ ምንጩ ከላይ ይመስላል፤ አበራ በአጽሁፉ ገጽ 7 ላይ « ሊቀመንበር መንግስቱ በዘመነ ስልጣናቸው እነበዓሉ ግርማን ለማሰውገድ እነሙልጌታ ሉሌን ተጠቅመው» በዛው ገጽ ላይ በዓሉ ግርማ ለማጥፋት ከነኰ/ል መንግስቱ ጋር ከመሰጠሩ ጓደኞቹ ጋር ሙልጌታ ሉሌ አንዱ እንደሆነ በዚህ መጽሀፍ ገጽ 59 ላይ ይስተዋላል» ይለናል።

ሁለተኛው ሴራ የደርግ ባለስልጣኖች በዓሉን ለማስገደል ኰ/ል መንግስቱን ለማሳመን ያደረጉት ይመስላል። የዚህ ሴራ ምንጩ ከስር ይመስላል። በአላማም ሆነ በአቀናባሪዎቹ ማንነት ከአንደኛው ሴራ የተለየ ነው።ሁለተኛው ሴራ በአበራ ፅሁፍ ላይ እንደዚህ ተቀምጣል። « ኦሮማይ ብዙ በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎችን ስለሚነካካ ብዙ ሰዎችን አስቆጥቷል….እንደተለመደው ሊያጠፉት የሚፈልጉ ሰዎች ተሰባሰቡና መከሩ፤ ሁሉም በየተራ መንግስቱ ጋር እየሄዱ አሉታዊ የሆኑ ነገሮችን እንዲነግሩት ተደርጐ በዓሉን የማጥፋቱ ሴራ ተቀነባበረ» ይሄ ሴራ መንግስቱን ብቻ ሳይሆን ጓደኞቹንም ለማሳመን ጥረት ተደርጓል፣ “የቅርብ ጓደኞቹን አሳመኑና” ይህ ሴራ የደርግ ባለስልጣናት መንግስቱን ለማሳመን በራሳቸው በመንግስቱ ላይ የተጠነሰሰ ሴራ ነው። ለበዓሉ ቅርብ የሆኑና ጓደኞቹን ጭምር አሳመኑና ሁሉም በየተራ መንግስቱ ጋር እየሄዱ ስለበዓሉ አሉታዊ የሆኑ ነገሮችን እንዲነግሩት ተደርጐ በዓሉን የማጥፋቱ ሴራ ተቀነባበረ፤ ኦሮማይ ማለት አለቀለት፣ አበቃለት ማለት እኮ ነው እያሉ መንግስቱን ጠመዘዙት፣ መንጌ ይህን አይወድም» እዚህ ላይ የሴራው ጠንሳሾች የደርግ ባለስልጣኖች ናቸው፤ አላማው መንግስቱን መጠምዘዝ ነው፤ በዚህ ሃሳብ መንግስቱ ስሜታዊ እንጂ ሴረኛ አይደሉም።
ስለ በአሉ ግርማ አሟሟት ከነገርከን ከነዚህ እርስ በርስ ከሚቃረኑ ሁለት ሴራዎች የትኛውን አምነን እንቀበልህ? የመጀመሪያውን ማለትም በመንግስቱና በጋዜጠኛ ሙልጌታ ሉሌ መካክል የተደረገውን? ወይስ በመጽሀፉ በተናደዱት የደርግ ባለስጣናት መካከል የተደረገውን ሁለተኛውን ሴራ? ለወደፊቱ እንዲህ አይነት ከባድ ውሸት ስትዋሽ ሰዎች ሊነቁብኝ ይችላሉ ብለህ መጠንቀቅ ጥሩ ነው። ለግዜው የመጀመሪያውን ሴራ ትክክል ነው ብለን እንውሰደው፤ ምክንያቱም ከመጀመሪያው ሴራ ተነስተህ የራስህ የሆነ ሌላ ሰዎችን የሚወነጅል ተከታታይ ታሪክ በጽሁፉ ውስጥ ስለጨመርክ።
ኰ/ል መንግስቱና ታዋቂው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በአሉን ለማጥፋት በመንግስቱ አማካይነት ሴራ ተጠነሰሰ። መንግሥቱ በአሉን ማጥፋት ሲያቅታቸው ለሙልጌታ በአሉን እንድገድል ከረዳኸኝ የበአሉን ስልጣን እሰጥሃለሁ አሉት፤ ሙልጌታ የበአሉን ቦታ ይመኝ ስለነበር በሴራው ውስጥ (ለመንግስቱ ምን እንድሚረዳቸው ግልጽ አይደለም) ተሳተፈ፤ በኋላ መንግስቱ በአሉን ካስወገዱ በኋላ ለሙልጌታ የገቡትን ቃል ሳይፈጽሙ ቀሩ፤ በዚህ ምክንያት ሙልጌታ ሉሌ ቂም ይዞ ነበር፤ ኢህዴግ ሲገባ “አጥፍቶ መጥፋት” የሚል መጽሃፍ ፃፈባቸው፤ በዚህ ምክንያት በአሉን ለመግደል ያሴሩት ሰዎች ተጣሉ የሚል ለማመን የሚያስቸግር ቅዠት የሚመስል መላምት ቃላት በመቀጣጠልና በመቆራረጥ ሊፈጥር ይፈልጋል።
ለመሆኑ ኰ/ል መንግስቱ በአሉ ግርማን ለምን መግደል አስፈለጋቸው? በመጽሃፉ ውስጥ ስለ እርሳቸው ጥሩ ነገር ነው የጻፈው። እሺ መግደል ፈለጉ የሚለውን እንመን። በአሉን ለመግደል ኰ/ል መንግስቱ ከሌሎች ሰዎች ጋር ሴራ ማድረግ ለምን ያስፈልጋቸዋል? ሴራ ማድረግ ቢያስፈልጋቸው በሴራው ውስጥ እነሙሉጌታ ሉሌ ምን ይጠቅሟቸዋል? የሚሾሙት ራሳችው፣ የሚሽሩት ራሳቸው፣ የሚገድሉት ራሳቸው ሆነው ለመሆኑ መንግስቱ ሃ/ማርያም በአሉን ለማጥፋትና ሙልጌታ ሉሌን ለመሾም ምን ሴራና ምስጢር ያስፈልጋቸዋል? ይሄ አላግባብ የመንግስቱን መረን አልባ ስልጣን ማኰራመትና በአሉንና ጋዜጠኛ ሙልጌታን ስልጣን መለጠጥ ይመስለኛል። አበራ ይህን የመንግስቱንና ሙልጌታን ሴራ አገኘሁት የሚለው በአንድ ምንጭ ዙሪያ ጥምጥም ሄዶ ነው። ከቀድሞ አንድ የደርግ ባለስልጣናት ጋር ቃለመጠይቅ አድርጋለች የሚላት በእሱ አጠራር “መርማሪ ፀሐፊ” ገነት አየለ ናት። ጓድ ቁጥር 53 የሚል ኮድ ተሰጥቶታል። ስለዚህ ሰው ኋላ እመለስበታለሁ፡፤

ለጊዜው ይሄ ጓድ ቁጥር 53 እውነተኛ ሰው ነው (ፈለቀ ገድለጊዮርጊስ ነው) የተናገረውም እሱ ነው ብለን ብንቀበለው ይሄን ሃሳብ እንደተለመደው እርስ በርሱ ይጋጭል። መንግስቱ ሃ/ማርያም 17 ዓመት ሙሉ ብቻቸውን የፈለጉትን እየገደሉ፣ የፈለጉትን እየሾሙ፣ ያሻቸውን እያደረጉ የኖሩ ፈላጭ ቆራጭ መሪ ከነስማቸው “ቆራጡ መሪ” አንድ በአሉን ለማስወገድ ያውም ሌሎቹ የደርግ ባለስልጣናት ፍላጐት ተጨምሮበት ሴራ ውስጥ ገቡ በሴራው ምንም ጥቅም የሌላቸውን ግለሰቦች ሴራ ውስጥ አስገቡ ነው የሚለን። ይህን ሴራ አለ ብሎ ማሰቡ በተለይ ደግሞ ከዚህ ሴራ ተነስቶ በመንግስቱና ጋዜጠኛ ሙልጌታ መካከል ከበአሉ ሞት በኋላ መካካድና ጭቅጭቅ ተፈጠረ ብሎ ሌላ ሴራ ከአየር ላይ ዘግኖ ማምጣቱ ሞኝነት ነው፤ ይህን ሃሳብ ሰው ያምንልኛል ብሎ ማሰቡ እብደት ነው።

በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሰራዊት የሚያዙ፣ የጥይትን እርሳስ እንደመፃፊያ እርሳስ የሚጠቀሙ ታላላቅ የጦር ጄኔራሎችን በአንድ ቁራጭ ወረቀት አዘው በአንድ ጀንበር የሚያስፈጁት ኰ/ል መንግስቱ ሃ/ማርያም በአሉ ግርማን ለማስገደል ከነሙልጌታ ሉሌ ጋር በማሴር ጊዜ ሲያጠፉ ነበር የሚል ታሪክ ጽፎ ማቅረብ የአንባቢውን ጊዜ ማጥፋት ይመስለኛል። በነገራችን ላይ “መርማሪዋ” ጋዜጠኛ ለሁለተኛ ጊዜ ባሳተመችው መጽሃፍ ላይ መንግስቱን ስለሙልጌታ ሉሌ አንስታባቸው ነበር፤ « እኔ ከርሱ ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፤ ከሱም ጋር ምሳ የበለሁበት ጊዜ የለም፤ ሾምነው ምን እንደሚፈልግ አላውቅም» ነው ያሉት።እና ገነት በመጀመሪያው መጽሃፍ ስለ ሁለቱ ሰዎች የነገረችንን በሁለተኛውም መጽሃፍ ኰ/ል መንግስቱ ያፈርሱታል። በርግጥ ታዋቂው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ “አጥፍቶ መጥፋት” የሚል መፅሀፍ ጽፎ መንግስቱን በስልጣን ዘመን ያጠፉትን ጥፋት በዛ ልዩ የጽሁፍ ችሎታው በማስቀመጡ ደስተኛ እንዳልነበሩ ይታወቃል። ይሄን ቅሬታ ወስዶ ከበአሉ ሞት ጋር በማገናኘት ሴራ መፍጠር የአበራን ሴረኛነት ነው የሚያሳየን።

ከኰ/ል መንግስቱና ከጋዜጠኛ ሙልጌታ ሉሌ ሴራ ሳልወጣና ወደ ሌላ ሃሳብ ሳልሄድ የአበራ የፈጠራ ሴራ አንድ ነገር ልበል፤ ጓድ ቁጥር 53 ይኑር አይኑር የማይታወቀው የደርግ “ቱባ” ባለስልጣን የሰውን ፍላጐት የማንበብ ልዩ የነብይነት ፀጋውን ተጠቅሞ ይሁን እራሱ ጋዜጠኛ ሙልጌታ ሉሌ ነገሮት እንደሆነ ሳይገልጽልን ጋዜጠኛ ሙልጌታ ሉሌ ለምን የበአሉ ማስገደል ሴራ ውስጥ እንደገባ የሚያሳይ በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ አንባቢ እንዲያስብ ተደርጐ የተሳለ አንድ አረፍተ ነገር አለ። “የበአሉን ቦታ ይመኝ እንደነበረ አውቃለሁ” በአበራ ጽሁፍ ገጽ 6 ላይ በገነት መፅሃፍ ገጽ 59 ላይ ይገኛል።
የአበራ ለማ ዋና አጀንዳ ታዋቂወን ጋዜጠኛ ሙልጌታ ሉሌን የበአሉ ግርማ ሞት ላይ እጁ እንዳለ በማስመሰል ያለ የሌለ እውቀቱንና አረፈተ ነገር የመቀጣጠልና የመቆራረጥ ጥበቡን ይጠቀማል። እንዳለመታደል ሆኖ ዓ/ነገርን ቆራርጦና ቀጣጥሎ ሊነገረን የፈለገው ሙልጌታ ሴራ ውስጥ የነበረው የበአሉን ቦታ ፈልጐ ነው የሚለውን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ ውሸት የሚያደርግ እርስ በርሱ የሚቃረን ሌላ መረጃ አስቀምጧአል።

አበራ በጽሁፉ መጀመሪያ በዓሉ የሞተበትን ቀን የካቲት 24 1976 ዓ.ም ነው፤ በ3ኛው ገፅ የመጨረሻው አንቀጽ ላይ ኰ/ል መንግስቱ በዓሉ ግርማ በመጽሃፉ ምክንያት ከስራ እንደተባረረ ይነግሩናል። በአሉን ከስራ ያሰናበቱት ቀን ኰ/ል መንግስቱ እንዲህ አሉት “ባለህበት የሃላፊነት ቦታ የምትቆይበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም” ብለው ጳጉሜ 5 ላይ ከስራ አሰናብተውታል። በሌላ አገላለጽ በዓሉ በመፅሃፉ ምክንያት ከመገደሉ ከ6ወር በፊት ከስራ ተባሮአል፤ የኔ ጥያቄ ሙልጌታ ሉሌ ከስራ ከተባረረ 6ወር ያለፈውን ጓደኛውን ቦታ ለመያዝ ጓደኛውን አስገደለው የሚል ነገር መናገር ለሰው ምን ትርጉም ይሰጣል?
አበራ የበአሉ አሟሟት ሴራ (የተነሳበትን ሃሳብ) ያጠናክርልኛል ብሎ በዋና የመረጃ ምንጭነት የሚጠቅሳቸው ሶስት ሴቶችን ነው። አንደኛ- የጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝን፣ የበዓሉን ሴት ልጅ ወ/ሮ መስከረም እንዲሁም ስለበዓሉ ጉዳይ ከወ/ሮ መስከረም ኢሜል ውጭ ሁለቱ ጽሁፎች አገር ሁሉ የሚያውቃቸውና 10 አመት ያለፋቸው ታሪኮች ናቸው። የወ/ሮ መስከረም ኢሜልም ስለበዓሉ አሟሟት ፍንጭ አይሰጥም። ጋዜጠኛ አበራ ለማ ከበዓሉ ግርማ ቤተሰቦች ጋር የተለየ ቅርበት ስላለው ያገኘው መረጃ አስመስሎ ያቀረበው የመጀመሪያው ማስረጃ የደራሲ በዓሉ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝ በዓሉ ስለመጥፋቱ ደራሲ አስፋው ዳምጤ ያውቃል ብለው በኢህአዴግ ዘመን ለጠቅላይ አቃቤ ህግ ያቀረቡትና ውድቅ የተደረገው ክስ ነው። ሌላው ጋዜጠኛ አበራ ለማ “መርማሪ ፀሃፊ” እያለ የሚያደንቃት ገነት አየለ የመንግስቱ ሃ/ማርያም ትዝታዎች ብላ ያወጣችው መፅሃፍ ላይ ስለበዓሉ የተጠየቁ ጥያቄዎችንና መልሶችን መስረት አድርጐ ነው (በዚህ መፅሀፍ ገፅ59 ላይ የተጠቀሰው ቁጥር53 የሚባል የፈጠራ ሰው በውል ይኑር አይኑር ያለየለት የፈጠራ ሰው የሚመስል ሰው የተናገረው ነገር የሃሳቡ ማጠናከሪያ መሆኑ ነው)
ፀሀፊ ገነት አየለ የበዓሉ ግርማን አሟሟት በተመለከተ ሶስት የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣኖችን አግኝታ 5 ጥያቄዎችን ብቻ ጠይቃለች። አራቱ ጥያቄዎች « በዓሉ ማን ገደለው?» የሚል ተመሳሳይ ጥያቄ ሲሆን አንዱ ደግሞ በጋዜጠኛ አበራ አገላለጽ “መርማሪዋ ጋዜጠኛ” ኰሎኔል መንግስቱን “አፋጠጠቻቸው” የተባለለት “በዓሉ መፅሃፍ እንዲጽፍ አዘውታል?” የሚለው ነበር። አበራ የዚህን ጥያቄና እነኰ/ል መንግስቱ የሰጡትን መልስ መሰረት አድርጐ ነው በዋነኛነት ጽሁፉን የሚጽፈው። መርማሪ የተባለችው ጋዜጠኛ ሶስት የደርግ ባለስልጣኖችን አግኝታ የበዓሉን ግድያ ምስጢር እስከወዲያኛው የሚፈቱ መቶ ጥያቄዎችን መጠየቅ ሲገባት አንድ ጥያቄ ብቻ ሰንዝራ እድሉ እንዲያመልጥ ማድረጓ ያሳዝናል።

መቸም ገነት አየለ በተፈጠረላት አጋጣሚ የደርግ ባለስልጣናትን ስለበዓሉ ጉዳይ መጠየቋ የሚደነቅ ቢሆንም ነገር ግን መርማሪ ጋዜጠኛ (ኢንቬስቲጌቲቭ ጆርናሊስት) የሚለው ስም የሚበዛባትና ጨርሶ ያልነካቸው መሆኑ ሳልገልጽ አላልፍም። አንድ መርማሪ ፀሃፊ ስለሚጠይቀው ነገር በሚገባ የተዘጋጀ፣ የውስጥ መረጃ ያለው መሆን አለበት። መርማሪ ጋዜጠኛ የተባለችው ገነት ግን ምንም አይነት መረጃ እንደሌላት የሚያስታውቀው በአበራ ጽሁፍ ገፅ 3 እንዲሁም በገነት መጽሀፍ ገጽ212 ላይ ያነሳችውን ጥያቄ ስናይ ነው። « ስለዚህ እርስዎ ቀይ ኮከብን በተመለከተ በዓሉ ግርማን መፅሀፍ ፃፍ ብለውታል የሚባለው እውነት ነዋ?» ይላል። ከዚህ ይልቅ “ የበዓሉ መፅሀፍ ኦሮማይ ከመታተሙ በፊት አንብበው እንዲታተም ፈቅደውለት ነበር ወይ?” ተብሎ ጥያቄው ቢቀርብ ኖሮ እንቆቅልሹ ይፈታ ነበር። ለነገሩ ወ/ሮ ገነት ያችኑ ጥያቄ ጠይቃ ተጠያቂው አላስፈላጊ ነገር እንዲያወሩ እድል መስጠት እንጂ- ተከታታይ ጥያቄ (ፎሎው ኦፍ ኮዌስችን) አላቀረበችም። በመሆኑም ጋዜጠኛ አበራ የጋዜጠኛ ገነትን ተልካሻ ጥያቄ መሰረት አድርጐ እጅግ ደፋር ድምዳሜ ላይ መድረሱ አሳፋሪ ነው።

ጋዜጠኛ አበራ ለማ የፅሁፉ ዋና አጀንዳ አድርጐ የተነሳው ገነት አየለ አግኝታ ጠየቀችው ከሚባለው ከሶስቱ የደርግ ባለስልጣኖች አንዱ የሆነውና ስሙ ያልተጠቀሰው “ጓድ ቁጥር 53” የሚባለው ግለሰብ ነው። ይሄ ጓድ ቁጥር 53 በእውን በገሃዱ አለም ያለ ሰው ነው..ወይስ የገነት የፈጠራ ውጤት?..የሚል ጥያቄ ለማንሳት የግድ ጋዜጠኛ ገነት አየለን መሆን አያስፈልግም። ሰውየው እንደተባለው እውነተኛና ያለ ሰው ነው ከተባለ “የበዓሉ ግርማን አሟሟት አውቃለሁ፣ እነሙልጌታ ሉሌ አሉበት” እያለ የሰው ስም እያጠፋ በአንፃሩ የራሱን ስም መደበቁ በጭራሽ ተቀባይነት የለውም። ትክክልም አይደለም። ለበዓሉም፣ ለሚከሰስትም ሰዎች፣ ለደራሲ በዓሉ ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያ ህዝብ ሲል አውቃለሁ የሚለውን አደባባይ ወጥቶ ይናገር። ( ለነገሩ ጓድ ቀጥር 53 ስለበዓሉ አሟሟት አውቃለሁ የሚለውን ነገር ለመናገር ድፍረት አግኝቶ ከወጣ በገነት አየለ መጽሀፍ ገጽ 59 ላይ የቀባጠረው ብዙ ነገር ስላለ ለሱ ጥያቄ መልስ ሊያዘጋጅ ይገባዋል) በህግም ቢሆን ገድሎአል ብሎ የከሰሰው ሰው እንጂ ገድለሃል የተባለው ሰው አለመግደሉን የሚያሳይ ማስረጃ ማምጣት አይጠበቅበትም። ስለዚህ በአሉን የበሉት ጅቦች ሳይሆን በአሉን የበሉትን ጅቦች አውቃለሁ የሚለው ሰው የግድ ወጥቶ መናገር አለበት።

የጋዜጠኛ አበራን ጽሁፍ በዓሉ ግርማን ለማስገደል በኰ/ል መንግስቱ ሃ/ማርያምና በሌሎች ታላላቅ የደርግ ባለስልጣኖች እንዲሁም የበዓሉ የቅርብ ጓደኞች፣ ጋዜጠኞችና የማስታወቂያ ሚ/ር ባለስልጣኖች መካከል የተደረገውን ሴራ ሊነግረን ይሞክራል። ከላይ በገለጽኩት መንገድ ህዝብ የሚያውቃቸውን መረጃዎችንና የመረጃ ምንጮችን መሰረት አድርጐ እንደ አዲስ ክስተት ሊነገረን ይሞክራል። ታዋቂው አልበርት አንስታይን “እብደት ማለት አንድን ተመሳሳይ ነገር እየደጋገሙ፣ እያደረጉ የተለየ ውጤት/ አዲስ ነገር መጠበቅ ነው” ይላል። በርግጥ ይሄ ምሳሌ የሚመለከተው በቅንነት – ስህተት ለሚሰሩ የዋሆች እንጂ ለጋዜጠኛ አበራ ለማ አይነቱ ሆን ብሎ ለሚያጠፋ ወይም የተለየ ተልእኮ ላለው ሰው አይደለም። አበራ አምነን እንድንቀበለው የሚፈለገው ሴራ በእውነት ላይ ያልተመሰረተ፣ ለአመታት ሲወሩ ከነበሩት ነገሮች የተለየ አዲስ ነገር የሌለው፣ የመረጃ ምንጮቹ ያልተቀየሩና በስነፅሁፍ ሚዛን ተራ የሚባል ነው። ይሄ ጽሁፍ ለበዓሉ ግርማ ታዝኖና ታስቦም የተፃፈ አይደለም። ብዙ ተራ ስድቦች የሚበዙበት ነው። ሆን ተብሎ በዓሉ ግርማን “አስገደሉ” የሚላቸውን ሰዎች ብቻ ሳይሆን የራሱን የበዓሉን ስም ጥላሸት ለመቀባትና ህዝቡን ለማሳሳት (ግራ ለማጋባት) በተፈጠሩ የውሸት ታሪኮች የታጨቀና የተንሻፈፉ መላምቶች የሚበዙበት፣ በጣም አደገኛ የክርክር ግድፈቶች ያሉት፣ አሰልቺ ቃላቶችና አረፍተ ነገሮች የሚበዙበት፣ ግማሽ እውነቶች በተደጋጋሚ የሚጠቀም ተራ የፕሮፖጋንዳ ፅሁፍ ነው።

በመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኩት የጋዜጠኛ አበራ ጽሁፍ አራት ክፍሎች አሉት። የመጀመሪያው ገጽ በበአሉ ሞት እጁ አለበት የሚለውን ደራሲ አስፋው ዳምጤ ይከሳል። ከገጽ2 እስከ 5 ደግሞ “ታላላቅ” ጅቦች የሚላቸውን የደርግ ባለስልጣናት ይከሳል። ከገፅ 5 እስከ 9 ታዋቂውንና አዋቂውን ጋዜጠኛና የብእር አርበኛ የሙልጌታን ሉሌ ስም ያጠፋል። ከገጽ 10 በኋላ ደግሞ “የማስታወቂያና መርሀ ብሄር ሚ/ር ካነሳን ዘንዳ ወደኋላ ዘመን ተመልሰን የጓዳ ምስጢር ሰነድ መፈተሽ የግድ ሊለን ነው” ብሎ በደርግ ዘመን ብቻ ሳይሆን በአጼ ሃ/ስላሴ ዘመን ሁሉ የተከበረውን ታዋቂውን ጋዜጠኛ የገዳሙ አብርሃን ስም ጥላሸት ለመቀባት ይፈለጋል።

በርግጥ አበራ ለማ ይሄ ምኞቱ ብዙ የተሳካለት አይመስልም። አንድ ስለ ኢትዮጵያ መጠነኛ ግንዛቤ ያለው ሰው የአበራን ጽሁፍ ሲያነብ የነዚህን ሰዎች ጥፋት ሳይሆን የአበራ ለማን አጭበርባሪነት ውሸታምነት በተራ ምክንያት ሰዎችን ለማታለል የሚሞክር አላዋቂ ሰውነት ግልጽ አድርጐ ያሳያል። ይሄ ጽሁፍ እንኳን ወንጀለኛ ናቸው ያላቸውን ሰዎች ይቅርና እየታገልኩለት ነው የሚለውን የደራሲ በአሉ ግርማን ገጽታ የሚያበላሽ ሰላማዊውና ተወዳጁ በአሉ ግርማን ባለብዙ ጠላት የሚያደርግ ጽሁፍ ነው።

ስለ በአሉ ግርማ አሟሟት አጣራች የሚላትን ገነት አየለን ቃለምልልስ ዋቢ አድርጐ የሚነሳው የአበራ ለማ ጽሁፍ በአሉ ግርማን የደህንነት ሰራተኛ ያደርግዋል። አበራ ገነት ስለ በአሉ ቃለመጠይቅ ካደረገችላቸው ሰዎች አንዱ የቀድሞ የደህንነት ዋና ሰው ተስፋዬ ወ/ስላሴ ናቸው ይላል፤ በአበራ ጽሁፍ በአሉ ግርማ ከስራ ባልደረቦቹ ጋር ችግር እንዳለበት ተስፋዬ ወ/ስላሴ ጠቁመውኛል ብሎ ተስፋዬ ወ/ስላሴ ስለበአሉ ለገነት ነግሮት የሚለውን ሀሳብ በራሱ በአበራ ፅሁፍ ገጽ 5 ላይ እንዲህ አስቀምጦታል፤

« በዓሉ መቼም በዚህ መጽሀፉ ብቻ ሳይሆን በሌላ በሌላም..ከእኛ ጋር በመስራቱም ሁሉ ብዙ ሰዎች ጠምደውታል…የስራ ባልደረቦቹም ቅርበት በመፍጠሩ ጥላቻ አላቸው» ይልና እንደአበራ አባባል ይህን ሃሳብ የተጠቀመበት በአሉ ከስራ ባልደረቦቹ ጋር ችግር አለበት ለማለት እንዲመቸው ነበር፤ ጽሁፉ ግን በአሉ ግርማ የደህንነት ሰው ነበር ነው የሚለን። በርግጥ አበራ ቃላት የመቆራረጥና የመቀጠል የሞኝ ዘዴውን በመጠቀም ከዚህብ አረፍተ ነገር “ ቅርበት በመፍጠሩ ጥላቻ አላቸው” የሚለውን በሚቀጥለው ገጽ ቆርጦ ወስዶ የበአሉን ጓደኞች ሊወነጅልበት ነበር። በአሉን ብዙ ጠላት አለው የደህንነት ሰው ነው ብቻ ሳይሆን የሚለው በመጽሃፉ የሚያውቃቸውን ሰዎች ገፅባህርይ አድርጐ መሳደብ የሚወድ ሰው ነው ይለናል፡፤

“በአሉ ግርማ በ1972 ዓ.ም ባሳተመው “የቀይ ኮከብ ጥሪ” ታሪካዊ ልብ ወለድ መጽሃፍ ላይ ከዋናው ሚ/ር እስከ ተራ ሪፖርተሮች ያሉትን የማ/ሚ/ር ሰራተኞች በገፀ ባህርይነት እየተጠቀመባቸው ደህና አድርጐ ተሳልቆባቸዋል። ከነዚህ በገፀ ባህርይነት ከተሳለቀባቸው መካከል ገዳሙ አብርሃ ነው” ይለናል። በሱ ቤት ስለበአሉ ደህና ነገር ማውራቱ ነው፤ ለሌላ አንባቢ የሚሰጠው ትርጉም በ1972 የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ላይ ተሳለቀ፣ በ1974 መጽሃፉ ላይ ደግሞ ስለደርግ ባለስልጣናት ሲሳለቅ አደገኛ ወጥመድ ውስጥ ገባ የሚል ትርጉም ነው የሚሰጠው።
በአሉን በማስገደል ሴራ ላይ እጁ አለበት ብሎ በመጀመሪያው ገፅ ላይ ያቀረበው አስፋው ዳምጤን በተመለከተ ብዙ ውሸቶች የተንሻፈፉ መላ ምቶች፣ የአንድ ወገን እውነቶች ይበዙበታል። በነገራችን ላይ ስለአስፋው ዳምጤ ወንጀለኛነት አበራ የፃፈው አበራ የጋዜጠኞች ማህበር ሊቀመንበር ለመሆን ፈልጐ እሱና ማሞ ውድነህ ስለተቃወሙት ነው ይባላል፣ ለጊዜው እኔም እንደሱ አሉሽ..አሉሽን ትቼ ወደዋናው ይዘት ላይ ብቻ ላተኩር።

አበራ ስለአስፋው ዳምጤ ወንጀለኛነት የሚጠቅሰው ማስረጃ የበአሉ ግርማ ባለቤት በኢህዴግ ዘመን በአሉ በሞተበት ቀን አስፋው ደውሎለት ነበር፤ በአሉም ከቤት ወጥቶ የቀረው አስፋው ጋር ልሂድ ብሎ ነው፤ ብለው ለአቃቤ ህግ ያመለከቱትና ውድቅ የሆነ ክስ መሰረት አድርጐ ነው፤ ስለበአሉ አሟሟት የተለየ ሴራ አለ እስከተባለ ድረስ ያንኑ ነገር ነው ደግመን የምንጠይቀው ለመሆኑ በደርግ ዘመን ደርጐች በአሉን መግደል ከፈለጉ አስፋው ዳምጤን ከቤት ይዘህልን ውጣ ይሉታል ወይ? ይዘህ ውጣ ቢባል መልሱ ምን ነበር የሚሆነው? ግምቴ ስህተት ሊሆን ይችላል፤ ግን እንደኔ ግምት በዛ ዘመን ደርጐች በአሉን ከፈለጉት ራስህ ና ቢሉት በአሉ እንቢ አይልም፤እንኳን እሱ ባለቤቱም ይዘውት ይምጡ ቢሉዋቸው የተለየ መልስ ያላቸው አይመስለኝም፤ በተለይ አበራ በአሉን ይዘህ ና ብለው እነመንግስቱ ቢያዙት ገና እነሱ ጋር ሳይደርስ እራሱ ገድሎት ሬሳውን ይዞ የሚመጣ ነው የሚመስለኝ፤
አበራ የወ/ሮ አልማዝን ክስ መሰረት አድርጐ የራሱን ሴራ የሚያጠናክርበትና አስፋው ዳምጤን የሚከስበት ታሪክ ይፈጥራል፤ አንደኛ አስፋው ዳምጤ በአሉ ከሞተ በኋላ በዚያው ጠፋ፣ እባሉም ቤት ሄዶ አያውቅም፣ ስልክም ደውሎ አያውቅም ይሄ የሆነው ደግሞ የጥፋተኝነት ስሜት ስለሚሰማው ነው፤ ለማለት የመፅሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ይጠቅሳል። ለዚህ የውሸት ክስ አሁንም አስፋው ዳምጤን በቅርብ ከሚያውቁ ሰው የሰማሁት ወ/ሮ አልማዝና ደራሲ አስፋው ዳምጤ በበአሉ ጉዳይ ተገናኝተው አውርተዋል፤ በመሃላቸው የተፈጠረ ቅሬታ አለ፤ እሱን ደግሞ አስፋው ዳምጤ እንደ አበራ ለማ ስላልሆኑ እውነቱን እንደ ጥላሁን ገሰሰ ሆድ ይፍጀው ብለው ዝም የሚሉ ይመስለኛል፤ ህዝብ ይወቀው ብለው የራሳቸውን እውነት ቢያወሩ ጥሩ ነው፤

ሌላው አበራ ለማ አስፋው ዳምጤን ወንጀለኛ ነው ብለን እንድናምን በገጽ 2 የመጀመሪያው አንቀጽ ላይ “በአሉ ግርማ እንደወጣ በቀረበት ሰሞን ከገንዘብ ሚ/ር ቋሚ ተጠሪነት ስራው ተባሮ…በድንገት የኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ በደርግ ተሾመ” ይልና ይሄ ሴራ አስፋው በአሉን አስገድሎ ተሾመ ነው መልክቱ፤ ይሄ ደግሞ ግማሽ ውነት ይባላል፤ አስፋው ዳምጤ ከደርግ ዝመን በፊት ከታወቀው ካምብሪጅ ዩኒቭርሲቲ የኢኮኖሚክስ ማስተርስ የነበረው በደርግ ጊዜ ልክ እንደ ጓደኛው እንደበአሉ ግርማ የገንዘብ ሚ/ር ቋሚ ተጠሪ (ሚኒስትር) የነበረ፣ ደርግ ጋር ስላልተጣጣመ ስራ የለቀቀ ሰው በአሉን አስገድሎ እዚህ ግባ የማትባል ድርጅት ም/ስራ አስኪያጅ ሆነ ነውየምትለን አቶ አበራ? ሰው ባታፍር እንኳ ፈጣሪን ፍራ::

አበራ በጽሁፉ ውስጥ ከገጽ 2-5 ገነት አየለ ከደርግ ባለስልጣናት ጋር ያደረገችውን ቃለመጠይቅና የነሱ መልስ ነው፤ ከላይ እንደጠቀስኩት ገነት አየለ በአሉን በተመለከተ በቂ ጥያቄ ስላልጠየቀች ከዛ ተነስቶ ምንም ማለት ባይቻልም በኔ አመለካከት አበራ በሚነግረን ሴራ መንግስቱና ሙልጌታ ሉሌ አሲረውም ይሁን ታናናሾቹ የደርግ ባለስልጣኖች ነገር እየሸረቡ እናዶዋቸው በአሉን ከገደሉ በህግ ባይቻል በታሪክ ተጠያቂ ናቸው፤ መንግስቱ ብ ዙ ሰው ገድለዋልና በአሉንም ገድለውታል ወይም እጃቸው አለበት ብሎ ካለጥፋታቸው መክሰስ አስፈላጊ አይመስለኝም፤፡

በአሉ ግርማ ተገደለ ተብሎ በደርግ ባለስልጣናት ዙሪያ እንደዘበት የሚወራው እውነት አሁን አበራ ወይም ገነት እንደምትነግረን አይነት አይደለም፤ ሌላ የተለየ ታሪክ ነው፤ እጃቸው አለበት የሚባሉትም ሰዎች ሌሎች ናቸው፤ የበአሉ ጉዳይ የቤተሰቡና የጓደኞቹ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ስለሆነ ሁላችንንም ይመለከተናል፤ አሁን ሁሉም ነገር አልፎ ታሪክ ሆኗል፤ ግን እውነተኛው ታሪክ ለኛና ለልጆቻችን ግልጽ ቢሆን የዘወትር ምኞታችን ነው፤ ስለበአሉ አገዳደል ትክክለኛው መረጃ ያላችሁ ባለስልጣኖች፣ ግለሰቦች ይህን በመስራት ታሪካዊ ግዴታችሁን ልትወጡ ይገባል።
በነገራችን ላይ ጓድ ቁጥር 53 የገነት መፅሀፍ በገጽ 59 በአበራ ጽሁፍ ገጽ 6 ላይ የተጠቀሰ በነአበራ አገላለጽ የደርግ ባለስልጣን ነው ይባላል፤ አንባቢዎች ጊዜ ካላችሁ አንድ ገጽ ብቻ ስለሆነች አንብቧት፤ በጣም የሚገርመው ለማመን የሚያስቸግሩ ሃሳቦች አሉት፣ እና ከዚህ ሰው ንግግር ተነስቶ ሰውን ወንጀለኛ ማለት በጣም ያሳዝናል።ጓድ ቁጥር 53 በኔ እይታ የበአሉ ግርማና የሙልጌት ሉሌ አለቃ ሳይሆን የነፍስ አባት ይመስላል፤ እነሱ የማይነግሩት ነገር የለም በዛ ላይ አይምሮ የሚያነብ ተሰጥኦም አለው።

ገና በጽሁፉ መጀመሪያ ጓድ ቁጥር 53 እንዲህ ይላል« መንግስቱ በአሉ ግርማን ቀይ ኮከብ መጽሀፍ እንዲጽፍ ይጠይቀዋል፤ ራሱ ፃፍ ማለቱን ማንም ሰው አያውቅም» ማንም ሰው ካላወቀ ጓድ ቁጥር 53 እንዴት አወቀ? « መንግስቱ ከሲዳሞ ጉብኝት ሲመለስ ኦሮማይን እያነበበ ነው የመጣው» ይለናል፤ መንግስቱ ደግሞ በአበራ ፅሁፍ ገጽ 3 ላይ “መጽሃፉን ማታ ማታ ነው ያነበብኩት 1 ሳምንት ፈጀበኝ” ይላሉ፤ ጓድ ቁጥር 53 “እንደተለመደው ሊያጠፉት የሚፈልጉ ሰዎች ተሰበሰቡና መከሩ፣ ለበአሉ ቅርብ የሆኑ ጓደኞቹ ጭምር አሳመኑ” እንደተለመደው ሊያጠፉት የሚፈልጉት እነማን ናቸው?

“ሙልጌታ ሉሌ ለደህንነት ይሰራል” ደህንነት የምስጢር ስራ ነው፤ “የበአሉን ቦታ ይመኝ እንደነበረ አውቃለሁ” ይህን ነገር ያወቀው በዛ የሰውን አይምሮ በማንበብ ችሎታው ተጠቅሞ ነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል፤ የጓድ ቁጥር 53 ሌላ አስቂኝ ነገር ይነግረናል፤ መንግስቱ በአሉን ለመግደል ከሙልጌታ ጋር ሊያሴሩ ሲፈልጉ ሙልጌታን በቀጥታ ማግኘት ሲችሉ፤ሽመልስ ለጓድ ቁጥር 53 ፣ ጓድ ቁጥር 53 ለሙልጌታ ነገሩት ይለናል፤ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌን ጠርቶ ማሴርፈለገ በቀጥታ ደውሎ መጥራት ሲቻል ይሄ ሁሉ መዞር ለምን አስፈለገ? ገድ ቁጥር 53 ሌላ የሚቀባጥረው ነገር አለው ፤ ሙልጌታ ሉሌ መንግስቱ ጋር ሄዶ በአሉን ለመግደል በምስጢር ካሴሩ በኋላ ጓድ ቁጥር 53ን ፈልገው እኔና መንግስቱ በአሉን ለመግደል አሴርን ሊሉት ፈለጉ ጓድ ቁጥር 53 ምንም ነገር ሳይሰማ አእምሮው የማንበብ ችሎታውን በመጠቀም የሁለቱን ሰዎች ምስጢር ስለደረሰበት ለራሱ ለበአሉ ንገረው አልኩት ይለናል።

ጓድ ቁጥር 53 ምን ያህል ሞኝ ናቸው ሙልጌታን ያህል የአለምን የኢትዮጵያን ፖለቲካና ኢኮኖሚ ታሪክ ጠንቅቆ የሚያውቅ ምሁር በቀን አንድ መጽሃፍ የሚያነብ ፈላስፋ በ50 አመት የጋዜጠኛነት ሙያ ብዙ የኖረ ሰው ሰው ለመግደል ከመንግስቱ ጋር አሲሮ ለአለቃው/ለነፍስ አባቱ ሊነግረው ፈለገ፣ ነፍስ አባቱ ግን የነብይነት ችሎታውን ተጠቅሞ ይህንን ሴራ ቀድሞ አውቆ አልሰማ አለ፤ ጓድ ቁጥር 53 ፈለቀ ገ/ጊዮርጊስ ይሁን ከነብያቶቹ አንዱ መጥቶ እርሱን ለህዝብ መግልጽ ያለበት ይመስለኛል።

ጓድ ቁጥር 53 የራሱን ስም ደብቆ እየቀባጠረ የሰው ስም ካጠፋ በኋላ ስሙ የጠፋው ሰው ወጥቶ ይናገር እንኳን ሙልጌታ ሉሌ ሌላም ሞኝ ሰው የሚቀበለው አይደለም፤ ሙልጌታ ሉሌ ለውነት የቆመ፣ ከማያለቀው እውቀቱ ትውልዱን የሚያስተምር፣ የህዝብ አስተማሪ፣ የኢህዴግን መንግስት ገና ከመጀመሪያው በጽኑ የሚቃወምና የሚታገል የብዕር አርበኛ ነው። በአፄ ምኒልክ ዘመን ጋዜጠኛ የነበሩ ደስታ ምትኬን ጨምሮ እስከአሁኖቹ በዘመናችን ጋዜጠኞች እንደአርአያ የሚታይ ሰው ወያኔን የሚቃወምና የተጣመሙ የሃገራችን ታሪኮችን ጻፍክ ተብሎ ስሙን ማጥፋቱ ትክክል ነው ብዬ አላምንም። ሙልጌታ ሉሌ አሁንም ይጽፋል፣ አሁንም ትውልዱን ስለምንወዳት ኢትዮጵያ ያስተምራል፣ ስለ ዲሞክራሲ ይሰብካል፤ ስለ ጀግንነት ይናገራል። ትልቁን ሰው ማዋረድ ትንሹን ትልቅ አያደርገውም።

ጸጋዬ ገ/መድህንና ሙልጌታ ሉሌ በአንድ አካባቢ ያደጉ ብቻ ሳይሆን የአንድ ዘመን ሰዎች ናቸው። ከሙያቸው ጋር በተገናኘ አላስፈላጊ እስጥ አገባ አጋጥሟቸው ነበር። ሁለቱም ለተነሱባቸው ሰዎች የሰጧቸው ምላሾች ተመሳሳይና ሁል ጊዜ የሚጠቀሱ ናቸው። ጸጋዬ ገ/መድህን የሆኑ ሰዎች ተነስተውንብሃል በየጋዜጣው ስምህን ያጠፉታል፣ ለምን መልስ አትሰጥም ተብሎ ተጠየቀ። ጽጋዬም እነዚህ ሰዎች የትልቅ ሰው እግር ይዘው ሽቅብ መሳብ የሚሹ ናቸው፡ እኔ ደግሞ ለነኚህ ግልገሎች እግሬን አለሰጥም አለ፡፤ ሙልጌታ ሉሌም በጣም የምትወደውን የቅርብ ጓደኛህን በአሉ ግርንማን በማስገደል ሴራ ውስጥ አለህበት ብለው ሰዎች ስምህን ያጠፉታል፤ ለምን መልስ አትሰጣቸውም ተብሎ ሲጠየቅ እንዲህ ሲል መለሰ፣ በድሮ ጊዜ አንድ ሰው መኪና እየነዱ ሲሄዱ መንገድ ላይ ሰው ገጩ የገጩት ሰው ትንሽ ጠቆር ያለ በዛን ጊዜ አጠራር “ባርያ” ስለነበረ እኔ ከሱ ጋር አልነጋገርም፣ ጌታውን ጥሩልኝ አሉ። እኔም ስለዚህ ነገር መልስ ል፤እመስጠት ወይ ጓድ ቁጥር 53 ራሱን ገልጦ ይምጣ፣ ካልሆነም አበራን የላኩት ጌቶች ይታወቁና ለነሱ መልስ እሰጣለሁ አለ።
ጋዜጠኛ አበራ ከገጽ 10 ጀምሮ እስከ ጽሁፉ መጨረሻ ገጽ 16 ድረስ የፃፈው እሱ ጋዜጠና ሆኖ በሰራበት ዘመን በማ/ሚ/ር ውስጥ የነበሩ የጓዳ ምስጢሮችን የሚላቸውን ነው፤ “የማ/ሚ/ር መስሪያ ቤት ካነሳን ወደ ኋላ ተመልሰን የጓዳ ምስጢር ሰነድ መፈተሽ የግድ ነው” ይለናል፤ በዚህም መሰረት አበራ በዚህ መስሪያ ቤት ይሰሩ የነበሩ ጋዜጠኞችን በራሱ አይን እያየ እራሱንና የሚወዳቸውን ሰዎች የሚያወድስበትን የድሮ አለቆቹን የሚሰድብበት ክፍል ነው፤ ይሄ ጽሁፍ ከበአሉ አሟሟት ጋር ምንም አይነት ቀጥተኛ ግንኙነት አልነበረውም። በአሉ በወቅቱ በስራው ደስተኛ አልነበረም። ከስራ ባልደረቦቹ ጋርም ጥሩ ግንኙነት አልነበረውም ይለናል። አበራና በአሉ አንድም ቀን ተገናኝተው ሻይ ጠጥተው እንደሚያውቁ አልነገረንም። በአሉም በስራዬ ችግር አለብኝ ብሎ ለአበራ አልነገረውም፤ የተገናኙት ከ2 ጊዜ አይበልጥም፤ እሱንም በአሉ የስራ መመሪያ ሊሰጠው ቢሮ ጠርቶት፤
በዚህ በመጨረሻው የአበራ የፕሮፖጋንዳ ጽሁፍ ውስጥ ውና የጥቃት ሰለባ የነበሩት ጋዜጠኛ ገዳሙ አብርሃ ናቸው። ብዙ በሙያው የለፋና ሰውዬውን የሚያውቁ ሰዎች እንደሚሉት የኢትዮጵያ ታሪክ በትክክለኛ ሰዎች ሲፃፍ ገዳሙ አብርሃ በጋዜጠኛነት ሙያ አንቱ ከተባሉት ተርታ ይመደባሉ። ወዳጄ አለማየሁ እንደሚለው ጋዜጠኛነት እንደወታደር ማእረግ ቢኖረው ባለ 4 ኮከብ ጄኔራል የሚባል ስልጣን ሊሰጣቸው የሚገባ በኢትዮጵያ ጋዜጠኛነት ሙያ ከፍተኛ አስተዋፆኦ ያደረጉ ያገር ባለውለታ እንደነበሩ ከታሪካቸው፣ ከሰሩት ስራ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል።

ገዳሙ ዛሬ በህይወት የሉም። አሁን አበራ ስለሚከሳቸው ክስ ከመቃብር ተነስተው መልስ አይሰጡትም። ለነገሩ በህይወት ቢኖሩም መልስ የሚሰጡት አይመስለኝም። አበራ ገዳሙን የለየላቸው ሻእቢያ ናቸው ይለናል፤ ገዳሙ ፀረ አንድነት አቋም ስለነበራቸው ሌሎች ኢትዮፕያዊ ጋዜጠኞችን ያሰቃዩ ነበር፣ ገዳሙ በበአሉ ስልጣን የሚቀኑ ሰው ነበሩ፣ ይለናል። እውነታው ግን ገዳሙ ጥርት ያሉ ኢትዮጵያዊ እንኳን ኤርትራን ከሚያስገነጥለው ሻእቢያ ይቅርና ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌላቸው ነፃ ጋዜጠኛ ገዳሙ ጋዜጠኛነትና ፖለቲካ ተለያይተው መታየት አለባቸው የሚል ትክክለኛ የጋዜጠኛነት አቋም ላይ የተመሰረቱ፣ በሌሎች ጋዜጠኞችም እንደ ሞዴል የሚታዩ ነበሩ።

አበራ የገዳሙን ስም ለማጥፋት ለምን ፈለገ? ብለን ከጠየቅን መልሱ አንድና አንድ ነው፤ በራሱ በአበራ ጽሁፍ ውስጥ በተለያየ ቦታ ይታያል ገጽ 10 ላይ “ገዳሙ አብርሃ የዚህን ጽሁፍ አቅራቢና የጐበዞቹን አገር ወዳድ ባልደረቦቹን ፎቶግራፍ በማስለጠፍ ወደ ኢትዮጵያ ራዲዮ ግቢ እንዳንገባ ያከናወኑት ህገወጥ ተግባር” እነዚህ ጋዜጠኞች በገዳሙ ትእዛዝ ከስራ እንደተባረሩ ሁላችንም እንስማማለን፤ ለምን ተባረሩ ለሚለው መልስ ግን ይለያየናል፤ አበራ እንደሚለው እነአበራ የተባረሩት አገር ወዳድ ስለሆኑ፣ ገዳሙ ደግሞ ሻእቢያ ስለሆኑ ነው፣ ገዳሙን የሚያውቁ ሰዎች የሚሉት ደግሞ ገዳሙ እነዚህን ሰዎች ያባረረው መኢሶን የሚባል በወቅቱ ከደርግ ጋር ይሰራ የነበረ ድርጅት አባል ነበሩ፣ የድርጅታቸውም አባል የአራት ኪሎ ወጣቶችን የጨረሰው ግርማ የሱ ተራ ደርሶ ደርግ ሲገድለው አንደኛው የነአበራ ጓድ የግርም፣አን መሞት በዜና አልናገርም አለ በዚያ ምክንያት ገዳሙ ስራህን ስላልሰራህ ብለው ከስራ አባረሩት፤ የሱ ፓርቲ አባላት በሰውየው መባረር ሲጮሁ ጀግናው ገዳሙ ፖለቲካና ጋዜጠኛነት አብሮ አይሄድም ብለው ሁሉንም አባረሯቸው፣ አበራ ሁልጊዜ እንደሚያደርገው ይህን ታላቅ ውነት ዘለለው።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ አንድ የተለመደ ነገር አለ፤ የአንድን ሰው ሃሳብ ሃሳቡን መቃወም ሲያቅትህ ሰውዬውን ሌላ ሳጥን ውስጥ ማስገባት፣ ገዳሙ የወሰዱትን እርምጃ ማስተባበል ስላልተቻለ ወይም የሰውዬውን ችሎታና ስራ ማጣጣል ሳይቻል ሲቀር ከሰውዬው ሃሳብ ይልቅ የሰውዬውን ማንነት መምታት ነው። በነገራችን ላይ በሃ/ስላሴና በደርግ ዘመን በኢትዮጵያ 24% የመንግስት ሰራተኛና የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የኤርትራ ተወላጆች ነበሩ። ጥቂቶቹ ኢትዮጵያዊ ናቸው ብለን ስናስብ እነሱ ኤርትራዊ ሆነው ቢያሳዝኑንም ብዙዎቹ የኤርትራ ተወላጆች ከማንም የበለጠ ኢትዮጵያዊነት የሚሰማቸው በኢትዮፕያ ብዙ የሰሩና ዋግ አየከፈሉ ናቸው። አልበርት አንሰታይን በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፤ ጥሩ ከሰራሁ አሜሪካኖቹ አሜሪካዊ ነው ይሉኛል፣ እነሱ የማይፈለጉትን ካደርጁ አሜሪካኖቹ ጀርመናዊ ነው ይሉኛል፣ ጀርመኖቹ አይሁድ ነው ይሉኛል..እንደሚለው ታላቁን የኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ገዳሙን ሻእቢያ ማለት ትክክል አይደለም።

አበራ ለማ በጅብ የጀመሩትን ታሪክ እኔ በውሻ ልጨርሰው፤ ጀግናው አሉላ አባነጋ በዶጋሊ ጦርነት ወራሪውን ጠላት ድል በማድረግና 500 የጣሊያን ወታደሮች በመግደላቸው ብዙ ጣሊያኖች ተናደው እንደነበረ ይታወቃል። ከነዛ መሀል አንዱ በጣም የተናደደ ጣሊያን ውሻውን አሉላ ብሎ ጠራት፤ ውሻ ከለታት አንድ ቀን ኢትዮጵያዊው የጣሊያን አሽከር ውሻዋን ጫካ ወስዶ ገደላት፣ ጣሊያኑ ውሻዋን ሲጠራት አትመጣም፤ ጣሊያኑ አሽከሩን ጠርቶ ውሻዋ የት ደረሰች?. ብሎ ሲጠይቀው ስሟ ከብዷት ሞተች አለው ይባላል።
እኔም የአበራ ለማ ፅሁፍ ድንቅ መባሉ አበራ በጽሁፉ ዋና ምንጭ የተጠቀመባት ገነት አየለ “መርማሪ ፀሐፊ” መባሏ፣ ለዚህ ሁሉ አላስፈላጊ ውዝግብ ምክንያት የሆነው የነገነት አየለ የፈጠራ ሰው ጓድ ቁጥር 53 “ቱባ የደርግ ባለስልጣን ” መባሉ ከሁሉ ደግሞ ራሱ አበራ ለማ ጋዜጠኛ መባሉ እንደውሻዋ የተሸከሙት ስም እንደከበዳቸው አሳይቶኛል።

የጨረቃ ፈስ –ክፍል ሁለት። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

የቀልዱ ጎጆ የድቡሽቱን ህልምን ይደረምሳል።

ሥርጉተ ሥላሴ 05.08.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

 

እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ባለፈው ሳምንት ክፍል አንድን እንዲህ ነበር ያሳርግሁት።

„… ታዲያ ይህንን እያዬን እንዴት ይሳነን በነጠረ አይሁድ ስሙ ወያኔን ብለን ለመጥራት ////// የሴት እሰረኞች መከራ ደግሞ ብዕርም – አንደበትም – ህሊናም – ባህልም – ትውፊትም – ተመክሮም – ደፍሮ ለመናገር አይችሉትም። ተቀብሮ የሚቀር ሚስጥር ነው። ዘመንና ታሪክም አያወጡትም – እኛ ባልነበርንበትና ባልተፈጠርንበት ውስጥ ሃቁን ለህዝብ አደባባይ አውጥቶ መጻፍ አንችልምና! ለመዳህኒተአለም – ለአውደ ምህረቱ – ለመንበሩ ለመንገርም እንኳን አቅም ያንሳል። እንኳንስ ለሚዲያ ፍጆታ ለማዋል። ሃቅ በሆነ አገላለጽ የወያኔ መሰረተ ተፈጥሮው – ሰብዕናውም ከኢትዮጵያዊነት ጠረን ውጪ ነው — እንዲህ ልከውነው። ትግራይ አኮ ለእምነቱና ለባህሉ የበዛ አክራሪ ነው። እነዚህ ከዬት እንደመጡበት፤ ከዬት እንደፈሉ አላውቅም።“

ክፍል ሁለት።

ንጹህ ልብ፣ ቅን ህሊና ያላቸው ወገኖቼ ከልብ ሆነው ይከታተሉኝ ዘንድ በትህትና ዝቅ ብዬ ጠዬቅኩኝ – እኔ ሎሌያቸው ሥርጉተ ሥላሴ ተዚህ ተጭምቷ – ሲዊዝዬ።

  1. መጓጓዣ – እንደ በር። ለመነሻ ትንሽ ነገር ልበል። ዬአንድ የፖለቲካ ድርጅት መሠረቱ ዬሚያምንበት ዓላማው ነው። ዓላማውን ለማስፈጸም የሚችሉ የፈቀዱና የወደዱ ከማህበረሰቡ የተወሰኑት ብቻ አባላትም ይኖሩታል። የአባላቱ ኃላፊነት የአፈጻጸም ድርሻ በግልና በጋራ ይሆናል። አንድ የፓርቲ አባል በአባልነት ብቻ ወይንም አባልነቱንም አመራር አካልነቱንም አክሎ ድርሻ ሊኖረው ይችላል። ጥምር ኃላፊነት እንደ ማለት። እንዴት?

ሀ.        እንደ አንድ አባል ወርሃዊ የፓርቲውን ክፍያ ከመክፈል ጀምሮ የፓርቲውን መሰረታዊ ሰነዶች ማለትም ደንቡን፤ ፕሮግራሙንና የውስጥ መመሪያ የመፈጸም ግዴታ ይኖርበታል። በስብሰባ የመገኘት፤ ድምጽ የመስጠት መብትም፡

ለ.        እንደ አካልነቱ ደግሞ እነዚህን የፓርቲ መሰረታዊ ሰነዶችን ማለትም ፕሮግራሙና ደንቡን ከሁለቱ የሚመነጨውን ዬአፈጻጻም የውስጥ መመሪያውን በተጨማሪም ዓላማውን ወደ ተግባር ለማሸጋገር የሚያስችሉትን የሥራ ንድፎች – ትልሞች  እንደ ተሰጠው ዬእርከኑ ደረጃ ይከታታላል – ይቆጣጠራል። የሥራ ንድፉ ወይንም ትልሙ በሦስት ክፈለ ጊዚያት ይመዳባሉ። ይብራራ –  የረጅምና የአጭር፤ እንዲሁም ሁለቱን የሚያገናኘው በዘመንኛው ቋንቋ link የመከካለኛ ጊዜው ይሆናል። (ረጅም 5- 10 መካከለኛ 1 – 3 አጭር ከሳምንት እስከ አንድ አመት ሊሆን ይችላል)

መነሻዬ ሁለተኛው የወያኔ የቪዲዮ የትነት ድራማ ነው። ቋራርጦ- ለብዶ – ጥፎ – ለጋግቦ በስለላ ተግባር የለመደበት ድውይ ያቀነባባረውን ሁለተኛ የቪዲዮ ምስል ፍላጎት በተመለከተ የተከበሩ ዶር ብርሃኑ ነጋ የግንቦት 7 ሊቀመንበር  ከኢሳትት ጋር በነበራቸው ቆይታ ማብራሪያ ሰጥተውበታል። ማበራሪያው –  የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በድርጅቱ ውስጥ ከነበራቸው የንቅናቄው የግልና የጋራ ሃላፊነት አንጻር ነበር።

1.1      የፓርቲ አካላት እርከን።

አንድ የፓርቲ አካል ትልቁ ዬአመራር አካሉ ጉባኤው ሲሆን ጉባኤው እስኪሰበሰብ ድረስ የጉባኤውን ውሳኔ የሚከውነው ደግሞ ማዕከላዊ ኮሚቴው ሁለተኛውን ደረጃ ይይዛል። ማዕክላዊ ኮሚቴው በተወሰነ ጊዜ ብቻ ስለሚሰበሰብ ማናቸውንም የውሳኔዎቹን ዕለታዊ ተግባራት ኃላፊነቱን የሚሰጠው ለሥራአስፈጻሚ ኮሜቴው ይሆናል። ሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴው እንደ ኮሚቴ በጋራ የሚከውናቸው ተጠያቂ የሚሆንባቸው መስኮች ሲኖሩት ሰፊው የፓርቲው ተልዕኮ የሚከወነው ግን በመምሪያዎች ነው። አንድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የራሱን መምሪያ በግል ሃላፊነቱ የወሉን ድርሻ በሥራ አስፈጻሚ አባልነቱ ይከውናል። የጠቅላላ የፓርቲው መርኃ ህይወት መርሁ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ይሆናል። ስለዚህም ነው የተከበሩ አቶ አንደዳርጋቸው ጽጌን የድርሻ ሰሌዳና የወያኔ ህልም የግንቦትን ጸሐፊ በመያዝ እንደ ጦር የሚፈራውን የግንቦት 7 ሙሉ መረጃ ለማግኘት የማይችል መሆኑን ያብራሩት። በተሰጣቸው የሃላፊነት ማዕቀፍ ውስጥ ብቻ ለዛውም ንቅናቄው በህቡ ስለሚሰራ ሌላም ይፋዊ ነገሮች በአፈጻጻም ሥርዓቶች የተቆለፉ ስለመሆናቸው በአጽህኖት ሊቀመንበሩ የገለጹት። በፓርቲ ህይወት ውስጥ ለቆዬና ለሠራ ሰው ግልጽ ነው።

አሁን እኔ ከዚህ የፓርቲ አደረጃጀትና መርህና ፓርቲውን ከሚመራው ብቸኛ መርሁ ከዴሞክራሲያዊ ማዕክላዊነት ወጣ ያለ እይታ ስላለኝ ነው የግድ ማብራሪያ መስጠት ያስፈለገኝ። ወያኔ ያነጣጠረው ሥምን የማጉደፍ፤ የታማኝትነትን ጥሪት ግድፈትን ቀፍሮ  የፈራውን መጠነ ሰፊ ተቀባይነትን የአረም ፈል ሊያፈላበት ስለፈለገ ይህን በብዕር ቦንብ ድቅቅ ማድረግ እንዲህ አሰኘኝ። አክርክራውንና አተርፍበታለሁ ብሎ ያሰፈሰፈበተን መናኛ ዲስኩሩን አፈር ማስጋጥ ግድ ይላል።

የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እንደ አንድ ኢትዮጵያን የፍትህ ሀገር እንድትሆን ረሃብተኛ ዜጋ ስንመለከታቸው እጅግ ጥልቅ የሆኑ እርስ በእርሳቸው በፋክትና በእውነት ዘለበታማ መስዋዕትነት የከበሩ ሥነ – ምግባር ያላቸው፤ በተግባር የበቁ ዜጋ መሆናቸውን እንመለከትበታለን።

  1.         ምስክርነት

እኔ አጋጣሚ ሰጥቶኝ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን ሁለት ጊዜ መደረክ ላይ አገኘኋቸው። በሙያዬ ሲኔዬር የፖለቲካ ፓርቲ አደራጅ ስለነበርኩኝ ሁለቱንም አጋጣሚዎቼን በግልብ አላለፍኳቸውም ነበር። ውስጣቸውን ጊዜ ወስጄ ነበር ያጠናሁት። መጀመሪያ ያዬኋቸው በጤነኛው ጊዜ ሚያዚያ 29.2006 ሲዊዘርላንድ ጄኔባ ዩነቨርስቲ የሲዊዝ ቅንጅት መሥራች ጉባኤ ላይ እሳቸው „የቅንጅትን መንፈስ ዕያነቡ ሲገልጹ“ እኔ ደግሞ „በጸረ ወንበዴ ትግል የመደራጀት አስፈላጊነትና ድርሻ“ በሚል እርእስ ጊዜ ተሰጥቶኝ አፍ ካለው መቃብር ወጥቼ እንዲህ ካሉትን ታላቅ ሰው ጋር አብሬ ታዳሚ በመሆን ነበር። እንዲሁም በዕለቱ „በጎሳ አስተዳደር የጤና ፖሊሲ ዕጣ ፋንታ የስርጭት ዝበት ያስከተለውን መዘዝ በመረጃ በተደገፈ“ የተከበሩ ዶር አሰፋ ነጋሽ በሰጡበት መድረክ ነበር የተገናኘው። ከስበሰባው በኋላ ስልክም ኢሜልም አላስፈለገኝም። ሀገሬ ኢትዮጵያ ውጭ ሀገር ያላትን ንጡር ሃብት ግን አዬሁበት።

ለሁለተኛ ጊዜ የተገናኘነው ከሦስት ዓመት በኋላ ነበር። በ2009 የካቲት ወር ላይ ነበር። እሳቸው ጄኔባ ዩንቨርስቲ ላይ መድረክ ላይ በገላጭነት አብሬያቸው የነበርኩት መሆኔን ያወቁ አይመስለኝም። ሥሜንም ሆነ ዬኃላፊነት ድርሻዬን አልተናገርኩም። ለግንቦት 7  አውሮፓ አቀፍ መሥራች ናሙናዊ ስብሰባ እሳቸው በገላጭነት ከለንደን እኔ ደግሞ በሰብሳቢነት ከሲዊዘርላንድ ደግመን ፍራንክፍርት አማይን ጀርመን ላይ ተገናኘን። አሁንም አድራሻ ኢሜል አላስፈለገኘም።

ብቻ — በወጣትነቴ ሰፊ እድል አገኝቼ ሊተረጎም የማይችል ብቃት፤ ጥልቅ ተመክሮ፤ ሰፊ እውቀት ካላቸው ወገኖቼ ጋር የሠራሁ ስለነበር ውጭ ሀገር ደግሞ እንዲህ ዓይነት ውስጡ የተደራጀ – መንፈሱ ድርጅት የሆነ የተረጋጋ ሰው በማዬቴ „ተስፋን“ ጸነስኩኝ። በጣም በማስተዋል በልቤ ሙዳይ ወስጥ አስመጠቀኳቸው። ከነዚህ ሁለት ቀናት ውጪ በስልክም በኢሜልም አለተገናኘሁም። ግን መንፈሴን ሸልሜያቸው ኖርኩኝ።

ስለ አቶ አንዳርጋቸውን ጽጌ የመንፈስ ሃብታት 1+1= 2  ወይንም  2×2= 4 ብሎ ሰብዕናቸውንም ሆነ ውስጣቸውን፤ በውስጣቸው ያለውን የማያልቅ ጥሪት፣ ንጹህ ቅን ራዕይ በቀመር መግለጽ የሚቻል አይመስለኝም። ሥራ ነበሩ። በውስጣቸው እራሳቸው ተደላድለው ነበሩ። ራዕያቸው በህዋሳቸው ውስጥ ጽላት ነበር። ኢትዮጵያዊነትን የሚተረጉሙ አመክንዮዎች የሰበለባቸው ነበሩ። የንግግር ሥነ -ጥበብ ሥነ -ምግባርም ከልቡ የተቀበላቸው ልሳነ – ርትዑ ነበሩ። ይልቅ ከ2013 ቃለ ምልልሳቸው feedback ዬቋሰኛው በተቀናቃኝነትን ለመታገል ይመጣል ብለው የሚያስቡትና የሚጠራጠሩት ነገር አለነበረም እኔ ሳያቸው። ስለሆነም እኔ በግሌ ብዙ የሚረብሹኝ ሁኔታዎች ነበሩ። የፖለቲካ ሰው ጠርጣራ መሆን አለበት። ቢሆንስ? ብሎ በህይወቱ ዙሪያ ላሉት ነገሮች አለመመችትን መከብከብ አለበት። አገላለፄ ድፍን ሊሆን ይችላል በሞቴ ፍቀዱለት  —

ካናዳ የሚኖር እጅግ የምወደው ዘመን እንዳይቀማኝ የምሳሳለት ልዩ የሆነ ጓደኛ አለኝ። እኔን በብዙ ነገር ይበልጠኛል። ቀደም ብዬ ስለእሳቸው ስነግረው በአትኩሮት ያዳምጠኛል። ምንም አስተያዬት ግን አይሰጠኝም ነበር። አሁን ይህ ድርጊት ሲፈጸም የሰጡትን የቀደመት ቪዲዮ አይቶ ሥርጉቴ ከምትነግሪኝ በላይ እውነት ሆኖ አገኘሁት አለኝ። የምርም ነው ከልቡ ያዘነው። እንደምታዝኚ አውቄ ነው ዬደወልኩልሽም አለኝ። መተካካት ይኖራል አንዳርጋቸውን መተካት ግን ፈጽሞ አይቻልም። የዘመን ዘለቅ ብቃት እርስተኛ ነውና!

ስለሆነም በምንም ታምር እኛ እያለን የአንዳርጋቸውን ታሪክን ማክሰል ሽፍታው ወያኔ አይችልም። ቁመን እንመሰክራለን። ሥራችን ነው። ትናንት ጠላቶቻችን ታሪካችን ጻፉ እንዳስፈለጋቸው አድርገው። ዘቅዝቀውም አንጠልጥለውም። ዛሬ ግን እልፎች አሏት ልዕልት ኢትዮጵያ። አውሮፓን የመሠረተው የቀደምት ህዋ ድረስ የዘለቀው የቤተክርስትያናት የሊቃናት ገድላት መጸሐፍታት – የትርጓሜ ዕድማታዎች የአመራር ብቃትና ጥበባት ናቸው። የሳይንቲስትነታቸው ምንጭ እናት ኢትዮጵያ ናት።

እኔ እንደማስበው አርበኛ አንዳርጋቸው በጠና ቢታመሙ ስለህመማቸው ሳይሆን በታመሙበት ወቅት ስለሚጓደለው የተሰጣቸው ኃላፊነት መስተጓጎል ይሆናል የበለጠ በሽታቸውን የሚጠነክራባቸው። አብዝቶ በመሥራትና በመልፋት ድካምን ንቆ ትጋትን ማበልጸግ ተፈጥሯቸው ነው ብዬ አምናለሁ። ሌላው በእሳቸው ላይ ዬያሁትና የተገነዘብኩት እንዲሁም ጊዜ ወስጄ ያዳመጥኩት አንድ ነገር አለ። መንፈሳቸውን ለሚሸከመው አካላቸው እረፍት መንሳታቸው ነው። ይህም ብቻ አይደለም አብረዋቸው ለሚሠሩትም ሊደክማቸው ይችል ይሆን ብለውም አያስቡም ነበር ብዬም አስባለሁ። እሳቸው የሚያስቡት የሥራውን ቅልጥፍና ከጥራት ጋር ማዬትን ብቻ ነበር።

ስለዚህ አሁን ጫናን በቀለበት ወዶና ፈቅዶ አግብቶት የኖረው መንፈሳቸው ከጠላት እጅ ሲገባ አካላቸውም ጋር መያያዝ አልቻለም። ተለያይተው ነው የኖሩት ብዬ አስባለሁ። ያን ያህል ጎደሎን ለመሙላት፤ የገቡትን ቃል ዕውን ለማደረግ ሲባትሉ በመንፈሳቸው ላይ ለምሳሌ … 500 ኪሎ ቢጭኑ ቢያንስ ይህን መሸከም እንዲችል አካላቸው ስለሚያሰፈልገው እረፍት፣ አንክብካቤ የተመጠጠነ ጥንቃቄ ሩቡን እንኳን ሊያደርጉ ያልቻሉ ፍጹም የቅንነት ናሙና ሰው ነበሩ። ያስቀመጡት የመንፈስ ጥሪት ቢኖርም ችግር ቢገጥም ሊቋቋም የሚችል ለሥጋቸው፤ መንፈሳቸውን ለሚሸከመው ለአካላቸው ጥሪት አልነበራቸውም። ሥጋቸውን ረስተውት ነው የኖሩት። ሥጋቸው ደግሞ እንደ እኛ የሰው እንጂ ማሽን አልነበረም። ለዚህም ነው በቀጥታ ቪዲዮውን ስታዩት የእኛን ውስጥ ዬሚደበድብ መጎሳቆል የምናዬው። ይህን አምክንዮ ይህን ክስተት የሥነ ልቦና ባለሙያዎች በሚገባ ሊተርጉሙት ይችላሉ ብዬ አስባለሁ። አብሶ የግንቦት ልጆች ይህ ውስጥን በሲባጎ የሚሰረስ ጭብጥ ተክቶ የመገኘትን አቅምን አምጠው መውለድ ያለባቸው ይመስለኛል።

3.      ጸጸት።

ስክነታቸው – እርገታቸው – በተሰጣቸው ጊዜ መንፈስን ይዞ የማቆዬት ብቻ ሳይሆን እንዳይረሱ የማድርግ አቅማቸው ወደር የለሽ ነበር። ስለሆነም እኔ በግሌ ሀዘኔ ጥልቅ ነው። መከፋቴም አጥንቴን ሰንጥቆታል። አመለጡን። እንደ ሰው ልብ ኖሮን እግዚአብሄር ይስጥልን ሳንል። የነፃነት – የርትህ – የፍትህ  – ታጋይነታቸውን ሳናከብረው – አፈሰስነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ከልቡ ሆኖ፤ ከመንፈሱ ሆኖ ዳግም መልሶ በነበሩበት አቅም ለማያገኛቸው ታላቅ የቁርጥ ቀን ልጁ ፍቅሩን ያለውን አክብሮትና አድናቆቱን እንደወርቅ ያፍልቀው ዘንድ በተመስጦበአንክሮ – በትህትና እጠይቃለሁ። ኃላፊነትን ወስዶ ለምልዕት ዕንባ እንዳሉት ሆነ መገኘት መቻል ሥጦታው የአባታችን የመዳህኒዓለም ነው። ይህን ማክበር ደግሞ የአምንያን ግዴታ ነው። መተከያ የለሹን ልጁን የኢትዮጵያ ህዝብ አበክሮ በጸሎት ጥበቃውን ሊያደርግለትም ይገባል ባይ ነኝ።

  1. የተቃጠለ ዬአፈር ጢስ ድራማ።

ከጨረቃ ፈስ ስለ „ኢትዮጵያዊነት“ የምናገኘው አዎንታዊ መረጃ ፈጽሞ የለም። መጠበቅም የለብንም። የከሰለ ያረረ ድራማ። የተኮማተረ – የጠወለገ - የነፈሰበት - የወደቀ- ጊዜው ያለፈበት፤ ተንተርሰውት ያደሩት ኩፍትርትር ያለ አንቀልባ መረጃ ነው ከሰላይ ዞገኛ ምርጦች ዘጋቢዎቻቸው የምናዳምጠው። ለዚህ ስሌት ነው የዘር በሽተኛው የጎጡ መርዝ ያሰከረው ብኩናቸው ወደ ሀገረ ኢትዮጵያ የተመለሰው። የጎረበጠው – ያነገበገበው – ያርመጠመጠው ግንቦት 7 እና ኢሳት ነበሩ። ብዕሩም – ካሜራዉም ለጥፋት እንሆ ይኳትናሉ። ልሳኑን ተዘግቷል። ሳቁን አውጥቶ መሳቅ እንኳን አይችልም። አሜኬላ ተግባሩ ሰብዕዊ ነፃነቱን ደፍኖታል። ቀና ብሎ ከቶም አይሄድም። የአሉላ ዕንባ ፍል ነውና ይገርፈዋል። የዬኋንስም ደም ያቃጥለዋል። ባንዳነት ቅንቅን ነው = ዘነዘና የሚያስቀር። ባንዳነት ነቀዝ ነው – ቀፎ የሚያስቀር። ባንዳነት ዛሬን እያስካደ ነገን ደርምሶ የሚጠብቅ ዕብቅ የራቁትነትነት ጉዞ ነው። ባንዳ ሆኖ ከመኖር ጭንጋፍ ሆኖ አፈር ውስጥ ማደግ በእጅጉ ይበልጣል። ቀን ያልፋል። ክፉ ተግባር ግን ህሊናን አስሮ እንጦርጦስ ይልካል። በምንም መልኩ ቢሆን ሸርና ደባ አንገታቸውን ቀና አድርገው ዋቢ ሊሆኑ አይቸሉም። የጥግ እርብራብም አያዘጋጁም። ይልቅ ናዳና – ንደት – መደርመስን አስከለትለው  ቀንን ይጠብቃሉ።

ወያኔና ግብረ አበሮቹ ዛሬ ያሸነፉን – የቀጡን ሊመስላቸው ይችል ይሆናል። የበደሉ ረመጥ ልቦናችን ውስጥ ኃይልና አቅም ፈጥሮ በዬደቂቃው ከእናት ሃገራችን ፍዳና መከራ ጋር እንድንቆራኝ ያደርጉናል እንጂ የነቃው መንፈሳችን ሊበርደው ከቶውንም አይችልም።

ያ — ዬመከራ ጩኽት የወንበዴው ወጀብ ከሰላማዊ ትግላቸው ያደናቀፋቸው የአርበኞቻችን ዬአብርሃም፤ የሃብታሙ፤ የዳንኤል፣ የሺበሺ  ጩኽት እንደሆን እንረዳለን። የእነሱ ክስ ዬተያያዘው ከማን ጋር እንደሆነ የሚያብራራልን አንበደርም። ቀና ሲሉ ቀንበጦች መንፈሳቸው – ህሊናቸውና ተስፋቸው በግፍ እንዲፈልስ ወያኔ ያደረጋል። ቀደም ባለው ጊዜም የዬካቲቱ የዕህል ዘረፈ ዘመቻው በመጀመሪያ ጥቃቱን የሚሰነዝረው ት/ቤት በማፈረስ ጥቁር ሰሌዳን በማቀጠል ነበር። ስለምን? ወያኔ አዲስ ኢትዮጵያዊ ትውልድን የማዬት ህልም ፈጽሞ ስላልነበረው።

ወመኔው ወያኔ የቀደሙትን ታሪክ ጠገብ አዋቂ ባለግራጫዎችንም ሳይራራ አፍኖ በገደል ለቋል። ቅርሶቻችንም ቢሆኑ ከባንዳው የወያኔ ጥቃት አላመለጡም። የዘረፈውን ዘርፎ፣ የተቀሩትን ነዲድ እሳት ተሸሽጎ በመለቀቅ አቃጥሎ አውድሟቸዋል። ቅዱስ ሥፍራዎችን፣ በፈጣሪ የተመረጡ ቦታዎችን፤ የማህበረ ምዕመኑን መንፈስ ማረፊያ መጽናኛወችን ገዳማት ሆነ መስኪዶችን በትዕቢት ተደፍሯል። ትውልድን መንቀል፤ የቦታዎችን ሥም መደለዝ ወይንም መሰረዝ የተፈጠረበት ባንዳዊ ዶክትሪኑ ነው። ቀጣዩን ትውልድም በዘመቻ አጨዷል። የባድመ ጦርነት ግቡ ያ ነበር። በቀሉ በሁለት የተሳለ አፍ ኢትዮጵያን በላት – ፈጃት።

  1. መቋጫ

ወገኖቼ ውድ ግፉዐን – እኔ እላለሁ ሁሉም ሰው በውስጡ ለመኖር ውስጡን ለእናት ሀገሩ የዕንባ ምጥ መፍቀድ ያስፈልገዋል። ሃብት ቢፈራ፤ ልጅ ቢወለድ፤ ትዳሩ ቢጎመራ፤ ቢማሩት – ቢመራመሩት ሀገር ከሌላ ግንጥል ጌጥ ግማሽ ሹሩባ ነው። ሀገር ማለት ነፍስ ያለው ህይወት ማለት ነው። ባህል ማለት መንፈስ ያለው ኑሮ ማለት ነው። ትውፊት ማለት ትናንት ያለው ነገ ማለት ነው። እምነት ማለት ድግሞ የተስፋ እልፍኝ ማለት ነው። ሁሉም ግን በሽፍታው ወያኔ ተቀጠቀጡ። መጠጊያ ብትን አፈር ለማኝ ሆኑ። የኔዎቹ  የምጥ ጊዜ ነው – የውቂ ደብልቂው አይደለም።

በዘመነ ሂትለር ኦሾትዝ በሚባል የፖላንድ ሀገር ሰው በላ ቦታ የሞት ተረኛ አይሁዶች ተራቸው እስኪደርስ ድረስ ወገኖቻቸውን በመርዝ በናዚ ወታደሮች ተገደው ጨረሱ – እያዩ ለመቀጣጫ። የዛሪዎቹ ኢትዮጵያዊ ናዚዎች ግን ለሆዳቸው ሲሉ ነው የናዚው የወያኔ ግብረ አበር ሆነው ወገኖቻቸውን የሚቀጠቅጡ – የሚያርዱ – የሚደፍሩ – የሚያቃጣሉ – በመርዝ መንፈሳቸውን የሚያቃጥሉት። ዬአርበኛ አንዳርጋቸው ገጽ ተቆርጦ ስንብቶ የተቀቀለ ጎመን ይመስል ነበር። ይህ ግፍ ወዮ! ነው የነነዌን ቁጣ ይልካል። አምላኩን የጠዬቀ የዕንባ ምጥ ዬማዕት ሞገዱን ያዘንባል። ወዮ! ከናዚ ወያኔ ጋር ያበረ – የተባባረ ….. በአንድም በሌላም ቅጣቱ ቀኑን ጠብቆ ይጠጣታል። ሲሆን ከፍልሰታ ግድፍት በፊት አንድ ታምር እናይ —-

ወገኖቼ ጨዋዎቹ፤ ለህሊናችሁ ዬምታድሩት – ጀግኖቻችን ቢሞቱም – አይሞቱም፤ ጀግኖቻችን ታሪካቸውና ገድላቸው ለምለም ነው። መከራቸውን ቆመው ጨርሰዎታልና በቁማቸው የጸደቁ የገነት ፍሬዎች ናቸው። ተጋድሏቸው እጥፍ ትውልድን ይገነባል። ስለሆነም ከሽፍታው ወያኔ ጋር በጀግኖቻችን ፍልቅ የተግባር ማንነት ማናቸውም ዘርፈ ብዙ ፍሬዎች መደራደር የለብንም። ቅራፊ መንፈሳችን ለናዚ መረጃ ማወስ አይኖርብንም። ነገን ያለመው ማንነት አለው። ድንቅ ኢትዮጵያን የናፈቀው የአርበኛው መንፈስ አይሞትም፤ አይድክምም፤ አያንቀላፋም። በእጥፍ ተባዝቶ – በእጥፍ ተራብቶ እሱ በፈቀደ ቀን እሱ ባለለት ምኞትና ተስፋ ዕውን ይሆናሉ። እንበርታ!

የኔዎቹ በዚህ እርእስ ዙሪያ የነበረኝ ቆይታ እንዲህ ተከወነ። የመሰጠርኳት ውበታማ እርእስ ደግሞ አለችኝ።  ከልፋጩ ሁለተኛ የቪዲዮ መረጃ ጋር የቀሩኝ ጥቂት ነገሮችን ስላሉኝ ተመላሽ ነኝ። ማለት ርእሱ ሌላ ጭብጡ ግን ከቀደሙት ሁለት ክፍሎች ጋር የሚወራረስ መሰል ቁምነገሮችን ይዤ እስክመጣ ድረስ ደህና ሁኑልኝ። ውድድድ ….

6. ተግባር – እጣታችሁን እባካችሁ  ከተግባር ጋር አቆራኙት። ፍጥነት …. እሺ

http://ecadforum.com/2014/07/31/urgent-campaign-to-call-fax-white-house/

 

 

  • ማሳሰቢያ ለቤተሰብ – ወያኔ ውሰዱ የፈለግሁት አገኝቻለሁ ቢል። ከርክክቡ በፊት ደማቸው ለማዕከላዊው የለንደን የባይወለጂ ሥነ – ምርምር ማዕከል መላክ አለበት። እዚህ ቦታ ሠራተኛ ሲቀጠር እንኳን ከደህነነት ዋና መ/ቤት መረጃ ያለገኜ አይቀጠረም። የሰው ሥነ – ተፈጥሮና ሳይንስ የሚፋጠጡበት ጥብቅ ቦታ ስለሆነ። ስለዚህ ውስጣቸውን አውልቆ ከሆነ ወያኔ በእጥፍ ድርብ ዕዳውን መክፈል ስላለበት ቅድመ ሁኔታው  በአግባቡ በጥንቃቄ መታደም አለበት።
  • የጨረቃ ፈስ —የጨረቃ ፈስ በልጅኔቴ ነው የመውቀው። መልኩ አፈር ይመስላለ። ቅርጹ ድንቡልቡል ነው። መተንፈሻ የለውም።ስትነከት ትንቡክ ትንቡክ ይላል። የፈር የተቃጠለ አፈር ጢስ ጢስ ብቻ ነው ውስጡ የወያኔ ዘመንም እንደዚሁ  ነው። እራሱ ከመክፈታችሁ በፊት ስትንኩት ትንቡክ ትንብዩክ ነው ሚለው ጠረኑ ደግሞ ስምየለሽ ነው። በቃ ወያኔ ማለት ሁለመናው የተቃጠለ የአፈር ጢስ ነው። ዘር የማያበቀለ የመከነ እሮ!

 

ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር ኢትዮጵያዊነት!

 

እኔው ሥርጉተ ሥላሴ – ለጀግኖቼ ቤተ –  ብቃት ቀናዕይ ነኝ!

 

ፆመ ፍለሰቲትን ለጀግናቻችን ሱባኤ እንያዝበት አደራ -  ህይወቱ ያላችሁ።

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

Comment

 

 


An act of Boycott (እቀባ የማድረግ ርምጃ) በአሸባሪነት ያስቀጣ ይሆን?

$
0
0

ጌታቸው ፏፏቴ

Boycottየ21ኛው ክፍለ ዘመን ፋሽስቶች የኢትዮጵያን ሕዝብ በኃይል አንበርክኮ ለመግዛት የመንግሥትን የሥልጣን ቦታ ከያዙ አንድ መቶ ሺ ስምንት መቶ ቀኖች(100800) ሆነዋል።በእነዚህ ቀኖች ውስጥ ታዲያ በእያንዳንዷ መንደር አንድ ሰው ይገደላል፤አንድ ሰው ይታሰራል፤አንድ ሰው ታፍኖ ደብዛው ይጠፋል፤የብዙ ሰዎች ሀብት ይዘረፋል፤ ብዙ ሰዎች ኮቴ ኮቴያቸውን እየተቀጠቀጡ አገር ጥለው እንዲወጡ ይደረጋል፤ብዙ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ይደበደባሉ፤ብዙ ሰዎች አካለ ጎደሎ እንዲሆኑ ይደረጋል፤ብዙ ሰዎች በርሃብ ይቀጣሉ፤ብዙ ሰዎች ህክምና እንዳያገኙ ይከለከላሉ፤የብዙ ሰዎች ጉዳይ ፍትህ ሳያገኝ ያድራል፤በሕግ ዓምላክ የሚባልበት ቦታ ሳይኖር ነው እነዚህ ቀኖች የነጐዱት።

ይህን እኩይ ድርጊት የሚፈጽመው ደግሞ የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ታሪክ አልዋጥህ ያላቸው፤ካንዴም ሁለት ጊዜ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስደፈር ሞክረው አልሳካ ያላቸው የምእራቡ አለምና የመካከለኛው ምሥራቅ ዐረብ ቱጃሮች ቅጥረኛ የነበሩ የባንዳ ልጆች ስብስብ ነው።የዚህ መረጃ ወይም ይህን ጉዳይ ጭብጥ ለማድረግ ሩቅ መሄድ የሚያስፈልገው አይደለም።ታሪክን አገላብጦ ማንበብ ነው።ዛሬም ቢሆን ይህን እኩይ በጥላቻ የበቀለና ያደገ ቅጥረኛ ድርጅት እንደ ተሰባሪ ዕቃ ተንከባክበው የያዙትና ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርጉት እነዚህ የኢትዮጵያ ጠላት አገሮች ናቸው።ይህን የመሰለ ድጋፍ ባይቸርለት ኖሮ ህወሃት በኢትዮጵያ ምድር አንድ ቀን እንኳን ማደር ባልቻለ ነበር።

መሬት በሰው ልጅ ሙት አካል ስትጫንና የንጹሓን ደም እንደ ውሃ ሲጎርፍ ከዚህ በፊት በኢትዮ-ሶማሌ፤በኢትዮ-ኤርትራ፤በሱዳን መሐዲስቶች፤በግብጽ፤እንግሊዝ፤ቱርክ፤ጣሊያን እንዲሁም እንደ ህወሃት አገር በቀል የሆኑ የግራኝ መሀመድና ዮዩዲት ጉዲት ወረራ ሲካሄድ መከሰቱን ከታሪክ የተማርነውና በአይናችንም ያየነው እውነታ ነው።የቅርብ ጊዜውን የደርግን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ስናነሳም ጥቃቱ የተሰነዘረውና ኢላማው ያደረገው አቅም የሌለውንና ያልተደራጀውን ድኻ አርሶ አደርና ሰርቶ የሚበላ ከተሜ ነበር።

እነዚህን ዘመናዊ ፋሽስቶች የተለየ የሚያደርጋቸው “የምንፈልገው የኢትዮጵያን ህዝብ ሳይሆን  ያፈራውን ሀብትና መሬቱን ብቻ ነው”ብለው የተነሱና በሰው ልጅ ላይ በሚደርስ አሰቃቂ ድርጊት የሚደሰቱ መሆን ነው።መሬቱን ሸጠዋል፤ለተባባሪ የጎረቤት አገሮች በነፃ ሰጥተዋል፤የሀገርና የሕዝብ ንብረት ዘርፈዋል፤ትውልደ ኢትዮጵያውያንንም እንደ ጎመን እየመተሩ ቀጥለዋል።ጊዜው ደርሷል መሰለኝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ጭራሹን እንደ አበደ ውሻ ያክለፈልፋቸው ጀምሯል።አንድ አበአዊ አነጋገር አለ »ካልጠገቡ አይዘሉ ካልዘለሉ አይሰበሩ«እንዲሉ ጠገቡ ዝላይም አበዙ የቀረው መሰበርና መሰባበር ነው።ይህን ሁሉ ያመጣው የህዝብና የሀገር ሀብት ተዘርፎ፤ በሀገር ስም የሚለመን የውጭ እርዳታና ከበጎ ለጋሽ አገሮች የሚሰጥ ድጎማ ወደ ህወሃት ካዝና በመግባቱ ነው።

የተተኪውን ትውልድ ተስፋ የሚያጨልም ሴራም እየተካሄደ ነው።የፊተኞቹ ገዥዎቻችን ያሸከሙን የውጭ ብድር ወገብ አጉብጦ እያለ የዛሬዎቹ አይቶ አያውቁ ብሔራዊ ሞራል የሌላቸው ማህይማን ስብስቦች ደግሞ ብድርንና እርዳታን መደበኛ ተግባራቸው በማድረግ ቀጣዩ ትውልድ ከፍሎ የማይዘልቀው እዳ እየከመሩለት ነው።በብድርም ይምጣ እርዳታ መልክ ለሀገር ልማትና ለውስጥ ጉዳይ ውሎ ቢሆን እሰየው ለቁምነገር ውሏል ይባል ነበር።ይህ ግን ገንዘቡ ከመጣበት አገር ተመልሶ በግለሰቦች አካውንት ገብቶ ወደ ግል ሀብትነት መቀየሩ ነው ጉዳዩን የተለየ የሚያደርገው።

አንዳቸውም ሥራቸው አልቆ ለሕዝብ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ የሚል ዜና ሰምቸ ባላውቅም ህዝቡን ለማደናገርና ወደ መብት ጥያቄ እንዳይሄድ ለማድረግ በርካታ ፕሮጀክቶች መወጠናቸውን ግን እሰማለሁ። በኢትዮጵያ ስም ከውጭ የሚገኘው ድጎማ ብቻውን የአባይን ግድብ ማስጨረስ ይችላል። ወይም በቅርቡ እንደሰማነው 488 የመንግሥት ቤቶች ለ23 ዓመታት ያህል አንዲት ቀይ ሳንቲም ገቢ ሳያስገኙ የትግራይ ወንበዴዎች በነፃ የኖሩበት ሂሳብ ቢወራረድ የስኳሩንም የአባይንም ጉዳይ ማስፈፀም በቻለ ነበር። ዳሩ ግን ሁኔታው ሌላ ነው ሕዝብን እያዘናጉና እያጭበረበሩ ለመኖር በሌላ መንገድ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው ማጠንጠኛው።

በነገራችን ላይ አዲሱ ለገሰ አንድ ወቅት በድሬ-ቱቢ ሲናገር ከወንድሙ ጋር በመሆን አባቱን ትጥቅ አስፈታነው ሲል ሰምታችሁ ከሆነ አባቱን ማዋረዱ ሳይሆን የታየው ሀቀኛ አብዮታዊ መሆኑን ነው።እኔ ስከማውቀው ድረስ ደግሞ አዲሱ ወላዋይና አድር ባይ አስመሳይም ነው።የ488 የመንግሥት ቤቶች የወንበዴዎች መኖሪያ መሆኑን ካጋለጡት መሀል አንዷ እንወይ ገብረመድኅን ስትሆን እንዲህ እንደ ዛሬው ብርጫው ሰፊ ባልነበረበት ወቅት እንወይ የአዲሱ ለገሰ ሚስት ነው የነበረች።ታዲያ ጀግናችን አዲሱ ለገሰ የጋሊቲ ሰፈር ልጅ እንወይን ከሥራ አስባረረ፤በዱላም አስደበደበ ታዲያ ይህ ሰው ነው ወይስ አውሬ?እንወይ ለአዲሱ በጣም የምትልቅበት እንጅ የምታንሰው አይደለችም።አዲሱ አሁን ደግሞ ህወሃት የግንባሩን አባላት ገለል በሉ ብሎ ብቻውን መሰብሰብ ሲጀምርና ሌሎችን ከጨዋታ ውጭ ሲያደርግ የአዲሱ ለገሰ ምርጫ ምን ሊሆን ይችል ይሆን?

ወደተነሳሁበት ሳልገባ ብዙ ነገር ነካካሁ እንደምናውቀው ማንኛውም መንግሥት ሲሄድ ሌላ መንግሥት ይተካል።በዚህ ሰአት አዲሱ መንግሥት በመንግሥት ይዞታ ሥር የነበሩ የመንግሥት የተባሉ ተቋማትን ፤ገንዘብን፤ሌሎች የጦር ኃይልን ፤የአየር መንገድን፤የትራንስፖርት አገልግሎትን፤ሕንፃዎችን ከሂያጁ መንግሥት ይረከባል ወይም በኢትዮጵያችን እንደተለመደው በኃይል ይወርሳል።የአሁኑ ሁኔታ ግን በጣም የረቀቀና በአይነቱ የተለየ ነው የጭነትም ሆነ የሕዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ሰጭ ተቀሟት፤ራሱ አየር መንገድና የጦርና የፖሊስ ኃይልን ስንመለከት በአንድ ጎሳ የሚመሩና የህወሃት አገልግሎ ሰጭ ናቸው።ጉኡዝ የሆነውን ሕንፃም ይዘውት ባይሄዱም የመጨረሻዋ ቀን ስትደርስ እንደሚያፈርሱት ይታወቃል።

አንድ በወር 4.000.00 ዶላር ገቢ ሊያስገኝ የሚችልን ሕንፃ አንድ የህወሃት አባል የሆነ ሰው ለ23 ዓመታት አንዲት ቀይ ሳንቲም ሳይከፍል መኖር ሲባል በ488 ሕንፃዎች ኢትዮጵያ ልታገኝ ይገባት የነበረውን ገቢ ማሳጣት ማለት እንደ-እኔ ድምጹ በማይሰማ መሣሪያ ኢትዮጵያን መግደል ነው።ይህ አሀዝ ለጊዜው ይቅርብ እንጅ የእነዚህ እኩያን ተግባር ወደ መሀል ገባ ብሎ ሲታይማ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን ዓለምን የሚያስደምም ነው የሚሆነው።

«በሬ በስድብ አይታረስም»እንዲሉ ህወሃትን በሰላማዊ ሰልፍ፤በስድብና በጥላቻ ብቻ እንደማንጥለው አውቀን ጥጋቡ ከልኩ አልፎ ዝላይ ስለጀመረ ዘሎ እንዲሰባበር ማድረግ የኛ ፋንታ ነው።በብድር በልገሳ ከውጭ የሚገኝ ገንዘብና ቁሳቁስ፤በሀገር ውስጥ የመንግሥት የነበረና ከሕዝብም የተዘረፈ ገንዘብና ሀብት በህወሃት እጅ ገብቶ ስለሚገኝ ሕዝብ በዚህ ላይ ዘመቻውን ማጧጧፍ ይገባዋል።ዘመቻው ግን የተደራጀና መሪ ያለው መሆን አለበት።መሪ የሌለው ዘመቻ ውጤቱ መጥፎ ሁኔታዎችን ሊያስከትል ስለሚችል የተቃዋሚ ኃይሎች ኃላፊነቱን መውሰድ አለባቸው።በቅርቡ ድምጻችን ይሰማ በማለት ህወሃትን እያርበደበዱት የሚገኙት እስላም ወገኖቻችን ያደረጉትን የ24 ሰአት የቴሌፎን አለመደወል እቀባ እንደ አንድ አብነት ወስደን በሚከተሉት የህወሃት ተቋማት ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ እቀባ ማድረግ ከቻልን የህወሃት ጥጋብ በመጠኑም ቢሆን ሊተነፍስ ይችላል ብየ አስባለሁ።

1/ገንዘብ መላክ፦አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አነሰም በዛ የሰውነቱ ክፋይ ለሆኑ ወገኖቹ ወደ ሀገር ቤት ገንዘብ ይልካል ይህ የሚላከው ገንዘብ ደግሞ የህወሃት ወደ ሆነው ባንክ ሄዶ ይገባል በዚህ ምክንያት የህወሃትን የገንዘብ(የዶላር) እጥረት ቀረፍንለት ማለት ነው።በሌላ መንገድ ሳናስበው ህወሃትን እያጠናከርን እንደሆነና ሀገር ከሚያፈርስና ህዝብ ከሚጨፈጭፍ ፀረ-ሕዝብ ድርጅት ጋር ተባብረናል ማለት ነው የሚሆነው።ስለዚህ የህወሃትን ባንኮች ለይቶ ማወቅና በነዚህ ባንኮች ገንዘብ አለመላክና አለማስቀመጥ አንዱ ይሆናል።

2/ድሮ የመንግሥት የነበሩ የጭነትና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ሥራ እንዲቆም በማድረግ ቦታውን ህወሃት ተክቶ እየሠራበት ይገኛል።የሌሎች የግል ባለሀብቶችን የትራንስፖርት አገልግሎት መጠቀም መቻልና ህወሃትን ከመተባበር መቆጠብ።

3/አቅሙ የተመናመነ ቢሆንም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ህወሃት ገቢ በሚያገኝባቸው ተቋማት ለምሳሌ እንደ ዳሽን ቢራ የመሳሰሉትን ህዝቡ ይገለገልባቸዋል ይህ ደግሞ በተዛዋሪ የፀረ-ሕዝብ ካምፕን ማጠናከር ነው የሚሆነው ስለዚህ በዚህ ዙሪያ ርምጃ(አቋም) መውሰድ ያስፈልጋል።

4/ሆቴሎች፤ሬስቱራንቶች፤ቡና ቤቶች፤ምግብ ቤቶች፤ግሮሰሪዎች በህወሃት እጅ እንደወደቁ ይታወቃል እነዚህን በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ አገር ህዝቡ ዘር እንዳይልባቸው ቢደረግና የሌሎችን አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን ምርት ብንጠቀም ወገንን እረዳን እኛንም ጠቀምን ማለት ነው አልጠግብ ባዮችንና ስግብግቦችን ደግሞ ትምህርት እንዲሆናቸው አደረግን ማለት ነው።

5/በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ትብብርን መንፈግ፤ደህንነት፤ፖሊስና የአጋዚ ሠራዊት አባላትን ስምና የኃላፊነት ደረጃ ማወቅ፤የሚሠሩትን ዘግናኝ ተግባር ዘግቦ በፌስ ቡክና በሌሎች ድረ-ገጾች እንዲነበብ ማድረግ፤አንድ ግለሰብ ላይ ጥቃት ሲሰነዘር ሌሎቻችን ጩኸት ማሰማትና ማደናገጥ ላልሰማው ማሰማት…ወዘተ ተግባራት ገቢራዊ ለማድረግ የተቃዋሚ ኃይሎች የሚከተሉት መንገድ ሊሆን ይገባል ብየ አምናለሁ።

በመጨረሻም ከአንዳርጋቸውና ከሌሎችም እንደተመለከትነው የውጭ አገር ዜግነት አለኝ ብሎ መዘናጋት ከንቱነት ነው።ለአሜሪካም ሆነ እንግሊዝና ሌሎች አገሮች የሚቀርበው አቤቱታና ሰላማዊ ሰልፍም ለጊዜው ስሜትን ለማብረድ ካልሆነ የሚገኝበት ተስፋ የለም።አቀናባሪውና ከኋላ ሆኖ አይዞህ ባዩ ማን ሆነና? ይልቁንስ አንድ ሕዝቡም ሆነ የተቃዋሚ ኃይሎች እጅግ ጠቃሚ መሆኑን እያወቅን ነገር ግን በተግባር የማንፈጽመው ጉዳይ «ህወሃት አጥብቆ የሚፈራውንና የሚጠላውን አንድነት መፍጠር አለመቻል ነው»ይህ ደግሞ ኃላፊነት የጎደለው በሀገርና በህዝብ ላይ ያለንን ደካማ አስተሳሰብ አጉልቶ የሚያሳይ ነው።አመንም አላመን ህወሃት በሚሄድበት መንገድ እየሄድን እንደሆነ ልንቀበለው ይገባል።አሁን በቅርቡ ብቻ ህወሃት የግንባሩ አባላትን እያገለለ የሚሄድበትን መንገድ እንኳ ተገንዝቦ መቀስቀሻ ነጥብ አለማድረግ ትልቅ ድክመት ነው ብየ አምናለሁ።

ቸር ይግጠመን፦ ጌታቸው ፏፏቴ

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ከ1986-2006 ዓ/ም (ሚሊዬን ዘ አማኑኤል) »

$
0
0

dd

ከሚሊዬን ዘ አማኑኤል

በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ባለፈው 20 አመታት 365 መንግስታዊ ድርጅቶች ወደ ግል ዘርፍ ተዛውረዋል!!!  እስከ 1986 ዓም ድረስ ወደግል ከተዛወሩ የልማት ድርጅቶች 3.3
ቢሊዩን ብር ተገኝቶል:: ከ1997 ዓ/ም እስከ 2006 ዓ/ም ድረስ ደግሞ 15 ቢሊዩን ብር ተገኝቶል፡፡ በድምሩ 18.3 ቢሊዩን ብር መገኘቱን የተሰበሰበው ገቢ ግን 4 ቢሊዩን ብር ብቻ መሆኑን
እስረድተዋል፡ [ሙሉውንለማንበብእዚህላይይጫኑ]

የኢፈርትና ሜድሮክ የቢዝነስ (ሞኖፖሊ) ምፓየር በኢትዬጵያ (ሚሊዩን ዘ አማኑኤል)

$
0
0

ddከሚሊዩን ዘ አማኑኤል የኢትዬጵያ ኢኮኖሚ በሁለት ትልልቅ የቢዝነስ ሞኖፖሊዎች ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡ Aንደኛው በህወሃት የፖለቲካ ድርጅት የሃብት ቁጥጥር ስር የሚገኘው በስጦታ የተላለፈ ሃብት ለትግራይ መልሶ ማቆቆም The Endowment Fund For The Rehabilitation of Tigrai (EFFORT) የሚባል ሲሆን የዚህም የሃብት ምንጭ ህወሃት በሽፍትነት ለአስራ ሰባት ዓመታት ከኢትዬጵያ ህዝብ የዘረፈው ሃብት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ (ሜድሮክ) ሞሃመድ ዓለም ዓቀፍ የእድገትና ጥናት ድርጅት ካንፓኒዎች Mohamed International Development Research Organization  Companies (MIDROC) —– [ሙሉውንለማንበብእዚህላይይጫኑ]—    

የሚዲያ አፈና ትግሉን ያጠናክረወል እንጂ አያቀጭጨውም ! (ከይድነቃቸው ከበደ)

$
0
0
(ይድነቃቸው)

(ይድነቃቸው)

ተሰባስቦ መቃወም እንዲሁም መደገፍ፣ አንድ ሰው የሚመስለውን ሃሳብ በፈለገው መንገድ መግለፅ፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ መንግስትን የመተቸት፣ በራስ ፍቃድ የመናገረ እና ያለመናገር ፣ በዓልንና አይማኖትን መከተልና ማስፋፋት እንዲሁም ህግ ለሁሉም የሚሰራስ ለመሆኑ መረጋገጥ እና የመሳሰሉት ሁሉ ተግባራዊ የሚሆነው ተአቅቦ ያልተደረገበት የመናገርና የመረጃ መብት ልውውጥ ተግባሪዊ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ሰው በመናገሩ አና በመፃፉ ብቻ ለእስር እና ለስደት የሚዳረግበት አገር በዋነኝነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዶናት፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በኢትዮጵያ ህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገመንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆይገኛል፡፡
ይሁንእንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አልፎ ተርፎ በአስተሳሰብ ወይም በአመለካከት ላይ ተፅኖ እስከመፍጠር ተደርሶኦል ፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ለህግም ሆነ ለሞራል ተቃራኒ እንደመሆኑ መጠን የፈጀውን ፈጅቶ ወደ ነበረበት መመለሱ የማይቀር ሃቅ ነው፡፡በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለህዝቡ ተገቢውን መረጃ እያስተላለፉ ያሉ የእትመት ውጤቶችን ከገቢያ ለማውጣትና ፈርጆ ለመክሰስ እየተደረገ ያለው ዝግጅት ሌላው ማሳያ ነው፡፡ ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣ በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ በሁለተኝነት ደረጃ ላይ ትገኛለች ፡፡ መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ለእስር የሚዳረግበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡
በዲሞክራሳዊ ሥርዓተ ዜጎች የሚኖሩት ግልፅ በሆነ የሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡ የትኛውም አይነት ሃሳብ ከማንም ሊመጣ ይችላል ቁም ነገሩ መሆን ያለበት የሚመጣው ሃሳብ የሚመከተው በምንድነው የሚለው ነው፡፡ ለነፃ ንግግር ችግር የተሻለው መንገድ የበለጠ ነፃ ንግግር ነው፤ አሳብን በመግለፅ መብት ላይ የሚደረግ ማናቸውም ተፅእኖ ሲውልሲያድር በእያንዳንዱ ግለሰብ የመናገር መብት ላይ ስጋት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ለዚህም ነው ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ነው ለማለት የሚያስደፍረው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ማንም ሰው በስጋት ውስጥ መኖርን ስለማይፈልግ ነው፡፡
በመሆኑም በአገራችን እየከሰመ ያለው ሃሳብን በነፃ የመግልፅ እና መረጃ የማግኘት መብት በገዥው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረት ወደመሆን ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ የፈለጉትን መስማት እና ማዳመጥ እንዲሁም በፈለጉት የመገናኛ ብዙሃን መንገድ ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን ማግኘት ግለሰብ ከሆነ እንደግለሰቡ፣ ተቋም እንደተቋም እንዲሁም ፓርቲ እንደ ፓርቲ የመምረጥ የራስ መብት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ የዲሞክራሲ መገለጫ ባህሪ ነው፡፡
ሌላው እና አሳሳቢ ሊሆን የሚገባው ሰው የመረጠውን መስማትና ማዳመጥ እንዲሁም ማንበብ መብቱ እንደጠጠበቀ ሆኖ ግለሰብ ወይም ተቋም ሃሳቡን እንዴት የመግለፅ መብት እና ግዴታ አለበት የሚለው ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ተቋም ወይም ግለሰብ ሃሳብን ወይም መረጃን በማንኛውም መንገድ የመገልፅ ሙሉ መበት በህግ የተጠበቀ ነው ፡፡ እንዲኹም የዚህ መብት ተቃራኒ የሆኑ ማናቸውም ነገሮች ተቀባይነት እንደሌላቸው በህገመንግስቱ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በማናቸውም የመገናኛ ብዙሃንሃ ሳብን መግለፅ እና መረጃን መስጠጥ በራሱ ወንጀል ወይም ጥፋት አይደለም ይህ የሆነው ደግሞ መብት ከመሆኑ አንፃር ነው፡፡ በመሆኑም በኢዲስ ጉዳይ፣ ፋክት፣ ሎሚ፣ .እንቁ እና ጃኖ መፅሔት ላይ መንግሰት ክስ የመሠረተበት ዋንኛ ምክንያት ሃሳብን የመገለፅ እና የሚዲያ ነፃነት በማፈን የለየለት አምባገነናዊ ስርዓት በአገራችን በማስፈን ስልጣንን ለማረዘም የተደረገ መፍጨርጨር ነው፡፡ የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ እና ለዲሞክራሲ ማበብ የሚደረገው ጥረት በይበልጥ እጅ ለእጅ ተያይዘን እስከድል ጫፍ የምንደርስበት እንጂ ወደኋላ የማንል መሆኑ ወያኔ ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡
ይድነቃቸው ከበደ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

የሳዑዲ ዓረቢያ ንጉስ አብዱላህና ሽህ ሞሃመድ አላ አሙዲ (ከሚሊዬን ዘ አማኑኤል)

$
0
0

ddከሚሊዬን ዘ አማኑኤል የሳዑዲ ዓረቢያ ንጉስ አብዱላህ አነሳሽነት የተጀመረው የሳውዲ የግብርና ዘርፍ መርሃ ግብር መሬት በሚሸጡ ደሃ አገራቶች መንግስታት ላይ በማተኮር፤ በባህር ማዶ አገራት የሚገኙትን ለም መሬቶች በሳዑዲ መንግስት ስም በሸያጭና ወለድዑግድ የመሬት ይዞታ/ንብረትን በግዥ’ በኮንትራት ‘በሊዝ ባለቤትነት በመያዝ Aስፈላጊውን የመዋኢለ ንዋይ ፍሰት/ ኢንቨስትመንት/ በማድረግ የግብርናውን ምርት ወደ ሳዑዲ በመላክ ህዝቡን መመገብ የሚል ነው፡፡ —--[ሙሉውንለማንበብእዚህላይይጫኑ]—–  

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>