ዳዊት መላኩ
እንደሁልጊዜው እያሰረ እና እየገደለ ለዘላለም ስልጣን ላይ በአንባገነንነት መኖር የሚፈልገው ዘረኛ ነፍሰ ገዳይ ቡድን በተለመደው መልኩ የባህርዳር ነዋሪዎችን አካል ጉዳተኞች እና በእድሜ የገፉ አሮጊት እናቶችን ጨምሮ አሰቃቂ ድብደባ ሲፈጽም አምስት ንጹሀን ዜጎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡መቼም ለመዘርዘር እስኪታክተን ድረስ በዚህ ህዝብ ላይ ያልተፈጸመ የወንጀል አይነት የለም፡፡ በጅምላ በሶማሌ ክልል የተፈጸመውን ግድያ እና የአሰከሬን ሁኔታ በዘር ልክፍት የተጠመዱት ነፍሰ-ገዳዮች በግፍ ለተገደሉት አሰከሬን እንዴት በእግራቸው ይረጋግጡት እንደነበር በኢሳት ቴሌቭዥን ያየነው ሁሌም ከአይናችን የማይጠፋ ምስል እና የስርዓቱን ሰይጣናዊነት ቁልጪ አድርጎ አሳይቶናል፡፡በጋምቤላ ፣ በአፋር በኦሮሚያ፣ በደቡብ እንዲሁም በእስልምና እምነት ተከታዮች የተወሰደው የግፍ ግድያ እና የጀምላ እስራት በስርዓቱ ምሬት ምን ያህል የታመቀ ብሶት እንዳለ የሚያሳይ ነው፡፡
በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ስብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ የተከለከሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮቻቸው በጅምላ እየታሰሩ እና እየተደበደቡ ባለበት ሁኔታ የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች በሀይል ለመጨፍለቅ የሚደረገውን ጥረት ሕዝቡ በራሱ ብሶቱን መቆጣጠር ከማይችልበት ደረጃ አድርሶታል፡፡ታህሳስ 19 ቀን 2014 እ.ኤ.አ የእስልምና እምነት ተከታዮች በአዲስአበባ በኑር መስጊድ እና የክርስትና እምነት ተከታዮች በባህርዳር በተመሳሳይ ቀን ያለማንም አነሳሸነት ያካሄዱት ተቀውሞ ለዚህ ማሳያ ከበቂ በላይ ናቸው፡፡አባቶች ሲተርቱ “ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ” ይላሉ፡፡ካለፈው መማር ያልቻለው የወያኔ አገዛዝ በግድያ እና በእስራት እንባገነንነትን ለማስቀጠል ይፈልጋል፡፡የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ እንኩዋን ለጊዜው ወደጎን ትተን የሀገራችንን ያለፉት አራት አስር አመታት ወደ ኋላ ዘወር ብሎ መቃኘት በቂ ነው፡፡በንጉሱ ጊዜ የታየውን የለውጥ ነፋስ ዘውዳዊ አገዛዙ በማናኛውም መልኩ ማስቆም አልቻለም፡፡በደርግ ጊዜ የነፈሰውም የለውጥ ነፋስ በአንድ ቀን 12 ከፍተኛ የጦር መኮነኖችን እና የበታች አመራሮችን በመረሸን ለውጡን ማስቆም እንዳልተቻለ በቂ ማስረጃዎች ቢሆኑም አይናቸውን የሸፈነው ግብዝነታቸው እና የዘር ልክፍታቸው ከዚህ ወጣ ብለው እንዲያስቡ እና ቆም በለው አካሄዳቸውን እንዲመረምሩ አላደረጋቸውም፡፡ዛሬም በእብሪት እና በማንአለብኝነት ተወጥረዋል፡፡
ህወአት ያጠለቀው የሀሰት ካባ እየተቀደደ ገመናውን ፍንትው አድርጎ እያሳየን ነው፡፡ቀደም ሲል በነ ገብረ-መድህን አርኣያ ፣አብረሃ ደስታ እንዲሁም በሌሎች የተጀመረው ስርዓቱን የመተቸት እና ትግሬነትን ከህወአታዊነት በመነጠል በኢትዮጵያዊነት ከሌሎች ጋር አብሮ ለመታገል የተጀመሩ ለውጦች የሚበረታቱ ናቸው፡፡ በ19/12/2014 ለልምምድ የተሰጣቸውን MI-35 የውጊያ ሄሊኮፕተርን ይዘው ስርዓቱን ከዱት የአየር ሀይል አባላት የዘር ግድግዳን ጥሰው ከፍተኛ ሚስጢር የሚጠይቀውን አኩሪ ገድል ፈጽመዋል፡፡እነዚህ ጀግኖች ባስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲህ ያለ ውሳኔ መወሰናቸው ሰራዊቱ ምን ያህል በስርዓቱ እንደተማረሩ ያሳያል፡፡ህወአት የተንጠለጠለባቸው ሁለቱ ባላዎች ሰራዊቱ እና የትግራይ ህዝብን ስውር ደባውን ሲያስፈጽማበው የነበሩት ዛሬ ከጎኑ እየተለዩ ነው፡፡ ህወአት የቆመበት መሬት እንደከዳው በየጊዝው ስርዓቱን ትተው የሚጠፉት የሰራዊ አባላት እና ከተቀዋሚ ጎራ የሚሰለፉት የትግራይ ተወላጆች ቁጥር መበራከት እንደማሳያ ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡
ህወአቶች እንዲህ በታመቀ እሳተ-ገሞራ ላይ ቆመው እንደዚህ ቀደሙ የህዝቡን ትኩረት ለማስቀየር ዛሬም በተለመደው መልኩ ለማታለል ይሞክራሉ፡፡በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ታሪክ የማይረሳው ግድያ ፈጽሞ የህዝቡን ትኩረት ለማስቀየር ጊምቢ በሚገኙ አማራዎች ላይ ዘራፊዎችን አሰማርቶ ቤታቸው እንዲቃጠል እና በርካቶች እንዲገደሉ አድርገው የዘር ግጭት ለማሰነሳት እና እነሱም አስታራቂ ለመምሰል ሲሞክሩ አይተናቸዋል ፡፡ጋምቤል ውስጥ ከ500 በላይ አማራዎች ተገድለው የሌሎችም ህይወት በስጋት ተውጦ ባለበት ሰዓት በ12 የሰዊድን ዜጎች ላይ የግድያ ሙከራ ተካሄደባቸው ሚል አስቂኝ የለማጅ ተውኔት ለመድረክ አብቅቷል፡፡በተመሳሳይ መልኩ ስርዓቱን ከድተው ስለተሰወሩት የአየር ሃይል አባላት እና በባህዳር ስለተገደሉት ንጹሀን ዜጎች የተለያዩ አለም አቀፍ ሜዲያዎች እየዘገቡ ባለበት ሰዓት አለምአፉን ማህበረሰብ ለማወናበድ ያለመ የተለመደውን ትርዓት ሰርቶ በ23/12/2014 የአንድ እንግሊዛዊን ነፍስ በመቅተፍ ለመድረክ አብቅቷል፡፡ከወያኔ ተፈጥፘዊ ባህሪ በመረዳት በዚህ እንግሊዛዊ ጎብኚ ላይ የተወሰደውን ግድያ ለመገመት አያዳግትም፡፡ ቀደም ሲል በአፋር ክልክ ላይ የነበሩ ጎብኚዎች በተመሳሳይ ሁኔታ በዚህ መልኩ የተቀነባበረ ድራማ ሰለባ መሆናቸው እና የቀሩትን በሀገር ሽማግሌዎች አደራዳሪነት አሰመልስኩላችሁ ሲል ገመናውን ለመሸፈን ሲሞክር ተስተውላል፡፡ እዚህ ላይ ኦጋዴን ክልል ሲዘግቡ በነበሩ ሁለት ሰዊድናዊ ጋዜጠኞች ላይ የተወሰደውን እርምጃ ማስታወሱ ግድ ይሏል፡፡
ለምን ወያኔ የውጪ ዜጎችን ታርጌት ያድርጋል ?በሽበርተኝነት ስም ከአሜሪካ እና ከምዕራብ ሀገራት የሚሰጠውን እርዳታ እና ብድር ዘላቂነት ለማስጠበቅ እና በሀገሪቱ የሽብር አደጋ እንደተጋረጠ ለማስመሰል እንዲረዳው ያለመ ነው፡፡ሰሞኑን እንግሊዛዊው ላይ የተወሰደውም እርምጃ ከዚህ የዘለለ አይሆም፡፡አንድም የነጻነት ታጋዩ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እስራት አስመልክቶ እንግሊዝ ዜጋዋን እንድታስፈታ የሚደረገውን ጥረት ጥላ ለማጥላት ምናልባትም ግድያው በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ የተናደዱ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች የወሰዱት እርምጃ ሊሆን ይችላል የሚል የማደናገሪ ፈጠራ ማሰራጨት እና እሱን ተከትሎ እንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸውን በተመለከተ የያዘችውን አቋም ማስቀየር ፤ቀደም ብላ ስትሰጥ የነበረውን ድጋፍ እና ብድር ማስቀጠል፡፡ሌላውን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሀሰት ፕሮፖጋናዳ ለቀጣዩ ምርጫ የገንዘብ ድጋፍ የለማግኘት ለልመና በር ለማናኩኳት አፍ መክፈቻ ተጨባጭ የሚመስል ምክንያት ለመፍጠር ያለመ ሊሆን ይችላል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ በእንግዳ ተቀባይነቱ የሚታወቅ እና በግድያ የማያምን መሆኑን ማንም ያውቀዋል፡፡በቂም በቀል ቢያምን በሚያዝያ ወር አንቦ ላይ የኦሮሞ ተማሪዎን በጠራራ ጸሀይ ሲገደሉ፤ሶማሌ ክልል ንጽሀንን እንደቄጠማ አስከሬናበውን ሜዳ ላይ ሲነሰንሱት፤ጅማ ላይ ወጣቱን መኖሪያ ቤቱ ገብተው በግፍ ገድለውት ሲሄዱ፤በ1997ዓ.ም 200 የሚጠጉ ዜጎች በግፍ ሲገደሉ፤አኙዋኮች ጭዳ ሲሆኑ፤ዛሬም በባህርዳር የነገ ተስፋ የሆኑ ህጻነት ባዶ እጃቸውን ወጥተው ግንባራቸውን በጥይት ሲነደሉ ባለደማቸውን ገድለው ያሳዩት ነበር፡፡መግደል እንኩዋን ባይችሉ የድመትን ያክል ሳይጭሩት አይቀሩም ነበር፡፡ግን ሰላምን ህዝብ ስለፈለገው ብቻ ሰላም የማያውቁት ወያኔዎች የህዝቡን አስተዋይነት ከፍራት ከመቁጠር ያለፈ ፋይዳ አለው ብለው አያስቡም፡፡ሞት በመጣ ቁጥር መጮህ መፍትሄ አደለም፡፡ከዚህ ላይ አንድ የለቅሶ እንጉርጉሮ ማስታወስ ግድ ይሏል፡፡
ወይ ሰውና ጫጩት አሞራ እና ሞት፣
ሲመጣ መንጫጫት ሲሄድ መረሳት፡፡
መሞት ካለቀረልን በተናጠል ከምንጠቃ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሊገድለን የመጣ ጠላታችንን መከላከል እና ከተቻለም ወደ አጻፋዊ እርምጃ ካለተሸጋገርን ወያኔ ነገም ሌላ የሞት ድግስ ከመደገስ አይቆጠብም ፡፡በዚህ ገዳይ ስርኣት ስር ሁናችሁ ህዝባችሁን እየገደላችሁ ያላችሁ የመከላከያ ፣የደህንነት እና የፖሊስ አባላት ከከበባቸሁ የፍርሀት ካባ ወጥታችሁ ከሚገደለው፤ ከሚሞተው ወገናችሁ ጎን በመቆም ሊመጣ ከሚችለው ህዝባዊ እልቂት ካልታደጋችሁት በስተቀር ህዝቡ ከሚችለው በላይ ታግሷችኋል፡፡በዚህ አጋጣሚ ከስርዓቱ እየተለዩ ራሳቸውን ነጻ በማውጣት ከነጻነት ሀይሎች ጎን የተቀላቀሉትን እና በቅርቡ ኤም.አይ.35 ሄሊኮፐተርን ይዘው ስርዓቱን የከዱት የአየር አባላት እውነተኛ ጀግኖች ናቸው፡፡ተገቢውን እርምጃ በተገቢው ሰዓት ወስደዋል፡፡ ሌላውም የሰራዊቱ፣የፖሊስ፣የደህንነት እንዲሁም በተለያዩ እርከን ያላችሁ ዜጎች የጀግኖችን አርአያቸውን በመከተል የጀመርነው ትግል በማፋጠን ተስፋችንን እውን እናድርገው፡፡ወያኔ የቆመበት መሬት እየከዳው በመንገዳገድ ላይ በመሆኑ ወደ ገደሉ አፋፍ እንዳይመለስ አድርጎ ለመጣል ሁላችንም በተቻለ መጠን ልዩነታችንን ወደጎን ትትን በዋናው ጠላታችንን ላይ እናተኩር፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!