Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

„ ….. / –ምንአውቅልህ?“ –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

 

ከሥርጉተ ሥላሴ 10.06.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

እኔስ እላለሁ —- ጥበብ የተጠጋቸው ነፍስ ትኩስ መንፈስ ይዞ ነው መድረክ ላይ መወጣት ያለበት፤ በሰተቀር – ይበርዳል።

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

እም! “እንደው በማዬ ሞት ለዚህ ሕዝብ መሰ-ዋ ይገባል ? ይሄ ሕዝብ እኮ አይደለም”  እም! ታዲያ የኢትዮጵያ ህዝብ ካልሆነ ከቶ መደቡ እንሰሳ ይሆን? የኢትዮጵያ ህዝብ ለማለትም ድፈረት አጣሕ፤ ላኺ ይኑርህ … አትፍላም።

አቶ ወንድም እንዴት ሰነበትክ። አሁን አሁን አካሄድህን እዬለመድኩት ነው መሰለኝ በቀላሉ ፊደል መቁጠር የጀመርኩ ይመሰለኛል። ምን ፊደል ብቻ መልዕክተ ዮኋንስንም …  እማዬን ተወት አድርጋት። ቃተኛ እያበላች ማሳደጓ ይኽው ሆኗል ትርፏ፤ የአንተ ብቻ አይደለችም የእኛም ናትና ትረፍበት አታንሳት – አትጣላት። እንዲህ መላ ስታጣ፤ እንዲህ ሥራ ስታጣ እንዳትቃጠል ብሎ ይሆናል እምዬን መድህኒታዓለም ነይልኝ ያላት። ነፍሷን አርያመ – ገነት ያስገባልን። አሜን!

 „ሰው እንጂ ህዝብ አላጣሽም“ ይህ የመጸሐፍህ እርእስ ነው። በሌላ ጹሑፍ ደግሞ ይቺ ኢትዮጵያ ሀገራችን ሰው እንደሌላት ፍንትው ብሎ ታየኝ ።“ ብለህናል – ምንአውቅልህ።  ዛሬ ደግሞ „ለዚህ ህዝብ መሰዋት ይገባል“ ወስጠ – እንቆቆ እርእስህ ተስፋን በይ – ትጥቅ አስፈቺ –  አዛይ – በሽተኛና ድውይ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ህግንም አብዝቶ የተላለፈ። ፈጣሪውንም የተዳፈረ እራሱንም – የበለ። አሁን ከቀደመው የመጸሐፍህ እርእስ መነሳት ግድ ይለኛል። ሌሎች ጹሑፎችህንም በምልሰት በተገባው መልክ መቃኘት ዬግድ ይል ስለበረ – ተሂዶበታል። በተቃርኖ የተሰነጉ ጹሑፎችህን የቀደመውን ሳታነብ ሌላ ትጽፋለህ፤ መንፈሱ እንኳንስ ለሌላው ተዳራሽ ሊሆን አንተን እራስህን በቀሪነት – ያጣፋኃል። ማርፈድ የአባት ጭራሹን – የለህም።

ከመጸሐፍህ እርዕስህ ልነሳ – እኔን ሲገባኝ – ሀገር ማለት ምን ማለት ነው ለሚለው ወልኛ ጥያቄ  ሀገር ማለት ዓለምአቀፍ እውቅና ባለው ደንበር የተከለለ መሬት ማለት ነው። ህዝብስ? ህዝብ ማለት ደግሞ ዓለምዓቀፍ ዕውቅና ባለው መልካምድራዊ አቀማመጥ ውስጥ የሰፈረ – የሰዎች ማህበር ማለት ነው። ማህበረሰብ የሚለው ሥያሜም የመጣው ከዚህው ሥርወ – ግንድ ቃል ነው። ህዝብ የሚባለው የሰዎች ማህበር ከሆነ፤ ካለ ህዝብ ሰው፤ ካለሰው ህዝብ የለም። ካለ ህዝብ ሀገር ካለ ሀገር ህዝብም የለም። ይህ የእኔ የሥርጉተ ዕይታ ነው። ሰዎች የሚወጡት ከህዝብ ነው። ሰዎች አንድ ሁለት ተብለው ተቆጥረው ነው ህዝብ የሚሆኑት።  ስለዚህ የመጸሐፍህ እርእስ እኔን በተናጠል እያንዳንዱን እንደ ዜጋ ሁላችንም በጋራ መድረሻ አልባ ያደረገ ነበር። እኔም ልቅር፤ አንተም ቅር ቢያንስ እስር ቤት ያሉትን ለነፃነት፤ ለፍትህ፤ ለርትህ፤ ለመናገር – ለማሰብ – ለመጻፍ ነፃነት እሳት ውስጥ የሚርመጠመጡት ማገዶዎች ሰዎች አይደሉንም? ቢያንስ ለእንሱ እንኳን ምን አለበት የሰውነት ማዕረግ ብትሰጣቸው? የእኛን የምርቆችን ተዎው – በአንተ ግንፍል ቤት ወንጀለኞች ልንሆን እንችላለን። ከዚህ ሌላ „ እግዚአብሄርም አለ ሰውን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር“ /ዘፍ. ም.1ቁ.26/ ይህም ቃለ ህይወት አለ። በአንተ መንፈስ ውስጥ ሁሉም ተደርምሰዋል – መጥኔ!

ከገሃዱ ዓለም ወጥተን ወደ መንፈሳዊው ዓለም ስናስተውል ደግሞ  ቅዱሳን ደናግል ሌት ተቀን በጸሎት በሰጊድ በፆም በድዋ የሚተጉ የማናቸውም ቤተ አምልኮ ንዑዳን – ንጹኃን ከዬት ይሆን የመደብካቸው? እነሱስ ሰዎች አይደሉንም? „ሰው አጣሽ“ ስትል – አንተም ሰው ሆነህ እኮ ነው የጻፍከው – አይደለም? አንተም እራስህ እኮ የለህም – በዚህ እርእስህ አምክንዮ። ሰውስ ከሌላ ለማን ነው የተጻፈው? – ተደራሽ ሳይኖር መቼም እንዲህ እንገትህን ድፍት አድርገህ ስትኮልም አትከርምም …. ግን አንተ ለማንነህ? ለዚህ ነው እኔ የመጸሐፍህ እርእስህ ያልገባኝ ስለመሆኑ ጠቆም አድርጌህ ያልፍኩት „ከተስፋ“ ጋራ በነበረን ቆይታ፤ ተከራክሬበትምአለሁ፤

የዛሬው ደግሞ አለ ያልከው ህዝብ እስኪበቃህ ከተከትክው። ሽሽቱ ከማንነቱ ይሁን  የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ከማንነቱ የሚሸሸው? የሥነ – ፍጥረት አውራነቱ የት ሄዶ? ወቃኽው። ፈለጥከው። ይህ ትጥቅ አስፈቺ ጉራማይሌ ቅላፄህ ዬት ላይ ሊያደርስህ እንደሚችል አላውቅም። ማወቅም የግድ የለብኝም። ይህ ህዝብ ምን እንዲያደርግ ይሆን የምትፈልገው? ከዚህ በላይስ ምን ይሁን? እሱ የሚችለውን ሆኗል። የቀረው የእኔና የአንተ የቤት ሥራ ነው። „ፋናዬንም ተነሺ ልጂሽን ጋዜጠኛ ተመስገንን መመረቅ ትተሽ ለማይገባው ህዝብ ክብር ሰጥቷልና – ውቀሺው እዘኝበት፤ ሌሎቻችሁም አርፋችሁ ተቀመጡ“ እዬልክ ነው? ይህ ከዕንባ ጋር ግብግብህ ተናጠላዊ ሳይሆን ወላዊ ነው። የቀረህ ወንዙ ተራራው ሸንተረሩ ፋፏቴው የዱር አራዊቱ ስለሆኑ፤ እነሱም ወረፋቸውን ይጠብቃሉ፤ ለመሰለቅ – በአንተ ቡጢ።  በሌላ በኩል ለዕንባ ሲሉ በቤንዚን የተቃጠሉት የህዝብ አካል ሰዎች ናቸው፤ ሰማዕታቱም እንዲሁ ከህዝብ የወጡ ናቸው። በተለያዬ የሙያ ዘርፍ ያፈሩ ዜጎችም አሏት – ልዕልተ። „ሰውም አልነበራችሁም“ አልበቃ ብሎ „የተሰዋችሁት የደካማችሁት ሀገራችሁን በመልካም ያስጠራችሁት ዕሴት ለሌለው፤ ፋይዳ ቢስ ለሆነ ህዝብ ነው“። ይቅር ይበልህ – አምላካችን። ለእሱ ሲሉ የከሰሉ – በመከስል ላይ ያሉትንም ትሩፋት አልባ፤ ታሪክ አልባ አደረግካቸው። በእውነቱ ሄኖክሻ ኃላፊነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን የምልዕትን ሥነ ልቦና የተዳፈረ ሴረኛ ጹሑፍ ነው። ዳምጠው – ዳጠው ብዬ ሥም ላውጣልህ ይሆን?

የተጠቀምክባቸው አባባሎች እያሳሳቅክ „ሳቁበትም ህዝቡን“ እያልክ የደፋህበት የሾኽ አክሊል ሀገር ውስጥም ሆነ ውጪ በሚኖረው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሥርዬት የሚያስጠይቅህ ነው። ስለምን? ቀራንዮ ያወጀ ስለሆነ። „በግንቦት ሆይ“  ጹሑፍህ እልቂትን ተማጽነሃል። ና ውረድ ሥርዓት አልበኝነት ብለህ መሬት ደብድበሃል።  መቼ ነው አዲስ አበባ ላይ የወያኔ ባለስልጣን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ ሲባል የምንሰማው“ እኔ እንደማስበው በቆሰለው ስሜት ላይ ሙከራ (test) እዬሠራህ ነው። አዬህ ኰስሞቲክ፣ ሽቶ ወይንም ልብስ ይለካል – ይሞከራል። በችግርና በፈተና እንደሁም በሞት ላይ ግን ሙከራ (test) የለም። የአንድ ሰው ሞት ሥርዓትን አይለወጥም። ብቁ የህሊና መሰናዶ ነው ሊለወጥ የሚችል፤ ለተነሳበት ፍላጎቱ ለናሙናነት „ድምጻችን ይሰማን“ ማንሳት ይቻላል። በሚዲያው ዘርፍም ቢሆን የ2007 ምርጫ አስመልክቶ ሶስት ዘገባዎቹ የጋዜጠኛ ሳዲቅ የለማ – ህሊና በመቅረጽ በኩል ዓይነተኛ መንገድ ነው። „ሊደመጥ የሚገባው“ ብሎ ዘሃበሻ ለጥፎት ነበር። ሌሎችም በቀጥታ በሚተላለፉ ራዲዮናቸው ሊጠቀሙበት ይገባል። አስፈላጊ ግን ያልተተጋበት ዘርፍ ነውና። ሀገር የሚደርሱ ራዲዮኖች የህሊና ችግኞችን  በአጥቂነት ማፍላት ይኖርባቸዋል። ይህ ከሚሊዮን ፈንጂ በላይ ተዋጊ አደራጅና መሪ አቅጣጫ ነው። ወንድምአለም ስለ „ሰው ልጅ ተፈጥሮና ክብር“ እሰብ። የቂም ፖሊሲ ያለው አስተዳደር በአንድ ቀንጣ ባለስልጣን ነፍስ ምክንያት ለዛውም አዲስ አበባ ላይ ሚሊዮኖች ሰላማዊ ሰዎች ህጻናት ነፍሰጡሮች – መነኮሳት ያልቃሉ። ሰላማዊ ትግልም ፈጽሞ ዕድል አይኖረውም፤ ከዚህ እርምጃ በኋላ። አንድ ሰው ገድሎ መሮጥ ህግ የለውም – ጦሱ የደም ወንዝ ነው። ለነገሩ አንተ ምን አለበህ ያለኸው …. እ!

በዕንባ ዘመን ሌላ ዕንባ በግብታዊነት በሚወሰድ እርምጃ ማዬት አብዝቶ ናፈቀህ። አዬህ እጅግ የተቋጠሩ በደሎች ቂምን አርግዘው ቀን ይጠብቃሉ። እነዚህን የምጥ ቀን ጭንቀቶችን ለመታደግ ብዙ የህሊና ተግባራት መከወን አለባቸው። የእኛ ጭንቀት ይህ ነው።በሌላ በኩል ፓርቲዎችን ደራሽ የተቀናቃኝ ጥቃቶች – አይመራቸውም። ፓርቲዎች የሚመሩባቸው ቋሚ ሰነዶች አሏቸው። ሰነዶቹ ዕለታዊ ጋዜጦች አይደሉም፤ ወይንም የፕሮፓጋንዳ ምርቶች አይደሉም። በራሳቸው ተፈጥሮ እራሳቸውን የሚመሩ ሩቅና – ቅርብን ሀገራዊ ራዕይን የዋጡ ናቸው። አንድ ፓርቲ በተቃናቃኙ ጥቃት በደረሰበት ቁጥር ያዙኝ ልቀቀኝ ሊል አይገባውም። ይህ ከሆነ ብሄራዊ ራዕዩ በአውሎ የተናጠ ይሆናል። እርግጥ ነው የፓርቲ ሰነዶች መሠረታዊዎቹ ሊለወጡ ሊሻሻሉ ወይንም ሊቀዬሩ ይችላሉ – በአባላት ጠቅላላ ጉባኤ። የሚቀዬሩት የሚለወጡትና የሚሻሻሉት ግን በግብታዊነት በመሸና በነጋ ቁጥር አይደለም – ታቅዶ ነው። ወቅት ተደምጦ፤ ስሜት ተጠንቶ፤ ተጨባጩ ታይቶ ነው። የራሱ መርህ ሊመራው ያልቻለ ፓርቲ ከመፈጠሩ በፊት የከሰመ ነው። አንተ የፈለግኸው ይሄን ነበር፤ ለዛውም ከተማ ላይ – አንድ ሁለት የወያኔ ሃርነት ትግራይን ባለሥልጣናት ገድሎ እልፎችን ማቃጠል። – ይዘግንናል። ለነገሩ በመደበኛ ፕሮግራም አልተማራችሁም። ስለዚህ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ፤ ግንባር ወይንም ንቅናቄ ከደረጃው፤ ከፍላጎቱና ከመርኹ እርቃችሁ ትገኛላችሁ። ማወቅ ከተፈለገ ግን በማንበብም ከሥነ ምግባሩ ጋር መጋባት ይቻላል።

አንድ ፓርቲ ግንባር ወይንም ንቅናቄ ከሰነዶቹ የፈለቀ ዕቅድ ይኖረዋል። ዕቅዱ በሶስት ይከፈላል። የረጅም የአጭር የመከካለኛ ተብሎ። የመካከለኛው – የአጭር ጊዜውንና የረጅም ጊዜውን የሚያገናኝ ሊንክ ነው። ተግባሮቹ ተወራራሽነት – ተከታታይነት እንዲኖር የሚያደርገው የመካከለኛ ጊዜው ነው። አንድ ፓርቲ መርኃ ግብሩን ወይንም ዕቅዱን ሲነድፍ ከስልቱ ተነስቶ አቅሙን ለክቶ ነው። ደራሽ ችግሮች በአብዛኛው የግንኙነት መሥመርና የኢኮኖሚና የድርጅት ዘርፍ አቅም ላይ ያተኮሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ደራሽ ችግሮችን ለመፍታት ከዘላቂ መርሁ ጋር አይጣላም። ደራሽ ችግሮችም ፓርቲውን ሊመሩት አይገባም። ይህ ከሆነ ከመሰረታዊውና ከዘለቄታ ፍላጎቱ ውጪ ስለሚሆን በህዝብ ተቀባይነቱ – ይዘብጣል። የአንተ ፍላጎት ደግሞ እንዲህ እንዲሆን ነበር። የጽንሰ ሃሳብ ግንዛቤ ከፍላጎት ጋር ለማጣጣም ተመክሮችን ማድመጥ ያስፈልግ – ይመስለኛል፤ ተግባባን ወንድም ሄኖክሻ።

ሌላው ሰለ ሀገረ አሜሪካ የመነፀር ገብያ ስታነሳ ለሚያምንበት ነገር ሰልፍ ለመውጣት መፈክር ሳይሆን ጥቁር መነጽር ለመግዛት ከሰልፉ ቀደም ብሎ ሞል ( የገባያ አዳራሽ ) የሚሄድ ሕዝብ እኮ ነው”  የሚረዱት ወገን አላቸው – ጥንቃቄ ያተርፋል፤ ሌላም ፊት ለፊት ወጥተው የወያኔ ሃርነት ባለሥልጣናትን የተጋፈጡ፤ መግቢያ መውጫ የነሱ፤ ሰንደቅዓላማቸውን በክብር በወያኔ ኢንባሴ ላይ ያውለበለቡትን፤ ዬሬግን ህንጻ ገድል – ስንቱ ይነሳ አንበሳ ወገኖቻችን ዘለልካቸው። የዚህ ዓመቱ የአውሮፓው ኮሚሽን የደም ዕንባን የተጋራው ዘገባ በምንና በማን ልፋትና ጥረት የተገኘ ይመስልሃል? በአንተ ስሌት እነሱ ከሰው ተራ አይመደቡም – ይሆን?

„አድገሃል ሲሉት የጠዋት ጥላውን የሚያይ አይነት ቀበሮ ነው ።” “ቀበሮ” የኢትዮጵያ ብልህ ህዝብ በቀበሮ መሰልከው። ይህን ከምሰማ ብሞት ይሻለኛል። ይበቃዋል – በትዕቢተኞች የሚጠቀጠቀው – ተወው። ከእሱ ወረድ በል። ዕንባ የዕለት ጉርሱ የሆነ ሳይማር ያስተማረ፤ ታርዞ ያለበስ ህዝብ እንዲህ ከፍና ዝቅ በትዕቢት ታደርገዋለህ። ልክ መጠን አጣህ። ቀድሞ ነገር እንደ ጥበብ ሰውነትህ ከአክብሮተ – ህዝብ ሥነ ተመክሮ ብጣቂ ትንፋሽ አለህን?! „ሥነ – አክብሮት“ የዓለም መርህ ነው – ዛሬ። የኢትዮጵውያን ተፈጥሮም። „ደሞ በዛ ላይ ፈሪሃ እግዚያብሄር ያለኝ ምናምን ይልሃል። እንዴት አይነት የምነት ሰው ነውእንደ አዋዜ ደቆስከው። ፈርኃ እግዚአብሄርነትም – ተወነጀለ። ሃይማኖት ተዘለፈ – ተሳህለነ! ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል ይላል – ጎንደሬ። ከልክህ ጋር ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵውያን ካደግንበት – አስተዳደግ፣ ተፈጥሮ ከለገሰን ፍጹም ሞራል፤ ከህገ ወንጌልም ጋር እዬተላላፍክ ነው። መሃከነ!

„ሰው“ ለሚለው ፍጡር ቃልና ፍቺ የለውም። አምላክ በአምሳሉ እንደ እሱ ቀድሶ የፈጠረው ሆኖ ሳለ አንተ ደግሞ – ቀደድከው። እግዜሩ ይይልህ። ድሮ ድሮ ሰርግ ላይ ይዘፈን የነበረ ዘፈን ( እርግጠኛ አይደለሁም አሁንም ድረስ ይዘፈን ከሆነ ) የዚህን ሕዝብ ሁኔታ ( ስነ ልቦናዊ ቁምጥና እና አቀማመጥ ለማለት ነው ) የሚያሳይ ይመስለኛል እየበሉ እየጠጡ ዝም ! አዎ እያሳሰሩ እያስገደሉ ዝም ከተባለ የዚህ ሕዝብ ሁነኛ መገለጫ ነው !” የቆዳ ህመም ለአንተ የውርዴት መለኪያ ነው።የኢትዮጵያ ህዝብ ሥነ ልቦናው አካለ ጎደሎ ነው”  ማለትህ ነው። ስለቃሉ ሎቱ ስብሃትት፤  ዘለልክተወጠርክ – ልትበጠስ ይሆን?! ምንአውቅልህ።

እንዴት አንድ ሙሉ ህዝብ “ቆማጣ ዝርያ” ይባል? ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መራራውን የነፃነት ትግል መስመር በሚሊዮን ዝብርቆችህ እንደሰኘህ እንዲህ ትለጋዋለህ – ትነስተዋለህ ቁም ተሰቀል ትለዋለህ። ግን የጤናህ ነው? ቢያንስ አንተ ከምትጽፈውና አቋም ከያዝክባቸው ስሜቶች ጋር እንኳን የመቆዬት፤ የመስማማት አቅም በእጅጉ እያነሰህ ነው። እንቆቅልሽ –

ወንድም ገጣሚ ሄኖክ የሺጥላ “የቻለ ፓርላማ ያልቻለ ፓልቶክ  ጹሑፍህን እንደ ሥጋ ቀረመት ከህትምቱ በኋላ ቆራርጬ በዬቤቱ አደራጀሁት። የፖለቲካ፤ የቂም፤ የስብዕዊነት፤ የሥነ ጥበብ ቤተኝነት – ሥነምግባር፤ ወጣትነት፤ ሚዲያ – ፤ ምን አለፋህ ተብትበትሀ – ተብትበህት – ተብትበህ ላይና ታች፤ እግርና እራስ አድርገህ በዝንቅ የጻፍከውን አፍታትቼ በመደብ መደቡ ካሰናዳሁት በኋላ፤ ፎቶኽን – ዓይንህን ከውስጥ አስተዋልኩት። ዓይን ዬነፍስ – ዬመንፈስ መስኮት ነውና። ከዚህ በኋላ ነበር  በሰብዕዊነትና ሥነ ጥበብ እንዲሁም በሚዲያ ዙሪያ ብቻ ያለውን መንፈስ ጊዜ ወስጄ ለማስተናገድ ዬሞከርኩት። እንጂ አውሎ ያሳድር ነበር።

… ያልቻለ ፓልቶክ”  እኔ ቤተ – መቻል ልበለው ሆደ ሰፊዎች ብቻ ተግባር ላይ የሚገኙበት የእልፎች ቤተ – ሀገር፤ ቤተ  ናፍቆት፤ ቤተ – ኃላፊነት፤ ቤተ መተሳሰብ – መተዛዘን – መረዳዳት ነው። ስንት ተግባር እንደ ከወነ፤ ስንት መርሃ ግብሮችን ከግብ እንዳደረሰ፤ ስንት የነፃነት ስብሰባዎችን – ሰላማዊ ሰልፎችን በኃላፊነት እንደመራ፤ ስንት ፊርማዎችን በእኔነት እንዳሰባሰበ፤ ስንት ደብዳቤዎች በሰብዕ መርህ እንደ ጻፈ፤ ስንት ቃለምልስ ክፍለ ጊዜን እንዳስተናገደ የዕንባ ቅርብነቱን ብራናው አይበቃውም። “አደራ” በሚባል ራዲዮ ዝግጅቱም ክፍተት ለነበራቸው ወቅቶች ድልድይ ሆኖ አገልግሏል … ለአንተ ሁሉም ባዶ ምንም ነው። ምንአውቅልህ።

ከሁሉ በላይ እንዴት ቆጥቋጣ እንደሆንክ የተረዳሁበት ምስጋና ሃሳቡን ላፈለቁት ሌላ ምስጋና ያንን ሃሳብ ላላባከኑት ! ( ለሰረቁት አላልኩም !)”  ከጹሕፍ ሥር ከአስተያዬት ሰጪዎችህ “ሲያልቅ አያምር” የሚል ነበር – በእውነት ይገልጥሃል። አንድ ለዛ መንፈስ እኔው ልከል – አሰር። ከዬትም ይምጣ እንደ ጥበብ ሰውነትህ በአዎንታዊ ይሁን በአሉታዊ አስተያዬት ሰጪዎችህን አድምጥ። ትህርት ቤቶች ናቸው – አንባብያን። የሳትከው የተለለፍከውን ያሳዩሃል – ባትሪም ናቸው።

ለማንኛውም ከምስጋና አቅም እንኳን ሃብትህን – ሰብልህን አክብሮ መንፈስህን ላላቀው፤ መንበር ላይ ላስቀመጠህ፤ የሥነ ግጥም ሙያተኞች ዬሁሉ ቁንጮ አንበል ላደረገኽ መንፈስ አራት ፊደል መጸፍ ተሳነህ። ማነን ለማስደት ማነን ለማስከፋት እንደሆነ አንተው  እራስህ ታውቀዋለህ። ሌላው ደግሞ አንተ በበላህሰቦች እጅ የወደቀን አርበኛ መንፈስ እንኳን እረፍት የማትሰጥ ወጣት ቂመኛ ነህ። “ ተጨባበጡተደባደቡ፤ አማራን መጸሐፍ በመጻፍ ካሳ ያቀረቡትእንደዛ አብሮህ የነበረ ሥጋህና ጨርቅህን ልንካ እንደጸድቅ ብለህ አብረህ እንዳልተሰለፍክ በአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የወያኔ ሃርነት ትግራይ እና ሰንዕ የመን፤ ከፈጸሙት ጭካኔ ከቶ የአንተው የበቀል ብቅልና ጠላ ምን ይለይ ይሆን? መከረኛውን አማራን ለማስነሳትም – አኮበኮብክ።

ሌላው ቀርቶ ቀደም ሲል ገንቢ ሂስ ያቀርቡ የነበሩት ወገኖች እንኳን ያ ጥቃት ሲፈጸም እንደ እሳት ነበር ያረመጠመጣቸው። ተደፈርን ነው ያሉት። እልህና ቁጣ ሲቃ ነበር የተናነቃቸው። ሰው በመሆናቸው ከስንት ነገር እንደታቀቡ መንፈሳቸውን – አይቻለሁ። በአጋጣሚ አመሰግናቸዋለሁ። ለእርድ አብረው ያልተሰለፉ ወዳጅና ጠላታቸውን የተረዱ፤ ወቅትና ጊዜን ማንበብ የቻሉ፤ ብቻ ሳይሆኑ የህሊናቸው ጌታም ስለሆኑ። አንተ ግን ቁፋሮ። ለነገሩ አንተም ብለህ ነበር – ነገር ግን ባልነበርክብት ውስጥ እራስህን ዛሬ ገለጥከው።  ስለ አውሌ ወቅሰህ ጽፈሃል በሌላ ጹሑፍ ደግሞ ይቅርታ ጠይቀህበታል። ይህም ብቻ አይደለም አንተም “ ቅንጅትን ማን እንዳፈረሰው መጸሐፍ እንጽፋለን” ብለሃል። ጻፈው …. እንይህ – አቅም ካለበት ቦታ ስላለ ያስታጥቃህል – በቃኝ እስክትልም ይግትሃል። የሞትና – የመኖር፤ በባርነት የመዝለቅና ነፃነትን ዬማግኘት – ዬማዬት ጉዳይ ነውና …. በቂም የተሰራ ነፃነት መጥፊያችን እንጂ መዳኛችን አለመሆኑን ስለምናወቅ መጋፈጥን – አንፈቅዳለን። ከፈጣሪ በታች ከህዝብ በላይም ክብርም የለም።

የአንተ ነገር ሲሄዱ ማደር ነው “ የምወደው ኢሳት” ትለንና ደግሞ “ሌቦች” ቀሙት ትለናለህ። የምክር አገልግሎትም መክፈትህን ነገረህናል “ … እንመክራለን” መሪ ሆነህ ሰዎችም የትግል አቅጣጫቸውን በሚመለከት በሳል ምክር የሚጠይቁህ አንተን እንደሆነ በቀደመው ጹሑፍ አንብቢያለሁ። ለመሆኑ የትኛው ፎቅ ላይ ነው ቢሮህ? ቢያንስ መግባት ባይቻል አሻቅቤ እንዳዬው ብትነግረኝ። ስግደትም ካስፈለገ ለጥ እንድልልሕ – በጸጋ ስግደትም እንዳንቆጠቁጥህ። ወይንም ፍርፋሬ ወንበር እንድማጠንህ —–

አዬህ ልጅ ሄኖክ – ገጣሚ፤ ሃሳብ ማፍለቅ ቤት የማፈረስ ያህል ቀላል ነው። ቁምነገሩ ቤትን መሥራት መቻል ነው። ሃሳብን አቁሞ እንዲሄድ ብቻ ሳይሆን እኛ የምንፍራውን ኃላፊነት መቀበል በራሱ ድንቅ ቅኔ ነበርአቃለኽ “የሃሳብ ሌቦች¡” ስትል ተሳደብክ – ተሳለቅክበት። በነገራችን ላይ እራሱ ታሪኩና አንተ አትተዋወቁም። መፈንቅለ መንግሥቱና ዬኢሳት ምስረታ ሰሞናቱ ጋር ሰፊ የልዩነት ጊዜ ነበረው። ሌላም ልከልልህ የካቲት 2009 ፍራንክፈርት ላይ በነበረው አውሮፓ አቀፍ የግንቦት ሰባት የማስተዋወቂያ ድንቅ ስብሰባ ላይ ጉዳዩ ተነስቶ ነበር። ይህም ብቻ አይደለም ስብሰባውን የተቀረጸው የተደረጃ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ለመጀመር ከጀርመኑ ZDF የቴሌቪዢን ዝግጅት ጋራ የተነጋገረ፤ ጋዜጠኞችን – የካሜራ ባለሙያዎችን የሚያሰባበሰብ አንድ ግብረሃይል ነበር። በአቶ ተፈሪ የሚመራ። የተሟላ መሳሪያም ነበራቸው። ተከታታይ የቴሌ ኮንፍረንስም አድርገዋል። እኔን እራሴን እንድሳተፍ ጠይቀውኝ ነበር። ያን ጊዜ የጸጋዬ ድህረ ገጽ ቦርዱ በሙሉ ሃይሉ ይሠራ ስለነበረ፤ እንዲሁም የራዲዮ ፕሮግራሙም ስለነበር አልተሳተፍኩም እንጂ። ከዛም በፊት አሜሪካን ሀገር የነአርቲስት ታማኝ በዬነ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ስለነበረ ግብረሃይሉ ከእነሱ ጋርም በመደበኛ ውይይት ያደርግ እንደ ነበር አውቃለሁ። ተመክሮውን ለመጠቀም ይተጋም ነበር። እንዲያውም ያን ዕለት በነበረው ስብሰባ ላይ አንተ ያጣጣልከው የፓልቶክ ተግባር ድንቅነት፤ እንዲሁም የቴሌቪዥን ፕሮግራም በመጀመር ረገድ አትኩሮት የሳቡ ጉዳዮቻችን ነበሩ። ውጥን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ግብረኃይሉ ከአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋርም ቃለምልልስ አድርጎ ነበር።

ይህን ስል በአዲስ ተሃድሶ ሃሳቡን ላሳደጉት ሆነ በታታሪነት ለተገበሩት ወገኖቼም እንደ አንተ በስላቅ – በአሽሙር ተዥጎርጉሮ ሳይሆን ከግልጹና ከእውነት ፈላጊው መንፈሴ የተቀዳ አክብሮቴንና ምስጋናዬን አቀርብላቸዋለሁ። PROUD! ለመሆኑ አረብ ሀገር፤ አፍሪካ ላይ ክርትት ለሚሉ ወገኖች የሚያስባስብ ፤ በረሃ ላይ ወልደው የበግ ሽንት እዬጠጡ ለሚታረሱት እህቶቻችን የሚደርስ፤ ስንፖንሰር የሚያደርግ ፋውንዴሽን አቅም ያለው አካል ተፈጥሮ፤ ኃላፊነቱን ወስዶ ሁለመና በመሆን ቢታደግልን ትጠላለህን? አይመስለኝም። ከሆነስ ሁለመናዋ በታሰረች ሀገር ኢትዮጵያ ላይ ህዝቡ የመረጃ ነፃነቱን እንዲገኝ ሃላፊነቱን ወስዶ በተደራጀ፤ በተማከለ፤ በጥንካሬ በተከታታይነትና በታታሪነት መከወን አንቱ ያሰኛል እንጂ እንዲህ ውርዴት ሊሸለም ባልተገባ በነበረ „ሃሳቡን ሰረቁት¡“ ልንገርህ  ፍቀት – ሌላውን ከመፋቁ በፊት እራሱን ነው የሚያጠፋው። እኛ እኮ ተደማጭነት ያለው፤ የህዝብን ቀልብ የሚስብ፤ ዕንባን የሚጋራ ቋሚና ቀጣይ የሆነ አንደበት አልበረነም። ይህን ስል መሰረት በመሆን አስተዋፆ ያደረጉትን ሳልዘል። ግን እንደ ኢሳት ጉልበታም፤ ተደማጭነት ያለውና ተፈቃሪ፤ ተፎካካሪ ሚዲያ አልነበረንም። ዕለት ከእለት እድገቱ እራሱ የተስፋ አዝመራ ነው። እሱን እንኳን ተስፋዬ ለማለት አልደፈርክም። …. ቀን የካብከውን ማታ ስትንድ ታድራለህ። አዬህ እኛ ዬረባ ማይክራፎን ያልነበረን፤ ዬስብሰባዎችን ሂደት የገላጩን እንጂ የተሳታፊውን ለማድመጥ የማይችልበት ሁኔታ ላይ ነበርን። ጉልህ ፍላጎት ግን ስስ አቅም ነበረን። መረጃን ተወዎው የስሚ – ስሚ ዘንቦ ተባርቆ በዓመት ትንሽ ነገር ቢገኝ ነበር ዛሬ ግን … ዲታ አድርጎናል። አፋችን ሞልተን መናገር ብቻ ሳይሆን ምንጭ ስላለን አቤት! ማለት ችለናል። አዬህ ሄኖክሻ – ሚዲያ – ነፍስ ነው። ሚዲያ ቅዱስ መንፈስ ነው። ሚዲያ ሰው ነው። ሚዲያ ተፈጥሮ ነው። ሚዲያ ድል ነው። ሚዲያ ነገ ነው። ሚዲያ ተስፋ ነው። ሚዲያ ሃዲድ – ግንኙነት – ሥልጣኔ ነው። በዚህ የጫቅላነት ዕድሜው አፍሪካን ማሰተማር ብቻ ሳይሆን የፓን አፍሪካኒስትነት መንፈስም እዬወለደ ነው። የተወለደውን ላሳደገ፤ ለከበከበ፤ ለመራ፤ አሉኽልህ ላላ ልዑቅ መንፈስ እኔስ እላለሁ ይባረክ! መንገዱን ለምለም አምላክ ያድርግለት – አሜን። ከዚህም ሌላ ሚስጢሩን የገለጠለት አምላኬም ይመስግን አሜን። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል“ /ምሳሌ 16 ቁ 9/

ከዚህም ሌላ የተገፉ ጋዜጠኞች መጠለያ አግኝተዋል። ይህ የመሃያ ጉዳይ አይደለም። ከሙያ ተነጥሎ መኖር አፍ ባለው መቃብር የመኖር ያህል ነው። የአቅሙን አይደለም ከአቅሙ በላይ ወዘተረፈ ፍላጎታችን በትእግስትና በመቻል እያስተናገደ ይገኛል „ሃሳቡን የሰረቀው¡  ያልከው አልታበዬም – የእኔ ብቻ ይሁን አላለም። እለተመካም። እንደ አንተ „ስጥ – ስጥ“ ይለኛል ብሎ በሰጠው አልተቆረቆረበትም። የበላችሁትን ትፉት ብሎ – አላፈጠጠም። አልወቀሰም –  አልነቀሰም። ሁሉን ተሸክሞ በመቻል ላይ ይገኛል። ከዚህ ሌላ ህሊናቸው የሚያይ አንቱ ጋዜጠኞችን – ሸልሞናል። እያንዳንዳቸው በራሳቸው ተፈጥሮና ጸጋ ቀለማም አድርጎታል -ፍላጎታችነን። ሊተኩ የማይችሉ ሆደ ሰፊ ባለሙያዎችንም – አበርክቶናል። በትርፍ ሰዓታቸው የተጉትም ቢሆኑ ልዩ ጌጦቻችን ናቸው – እግዚአብሄር ይስጥልኝ። „ድረስልኝ ኢሳት“ ይላል ወገነህ – ወገኔ፤ ለዚህ መብቃቱም መታደል ነው።

እምነት የመንገድ ጠጠር አይደለም። እምነት ለማንም አይሰጥም – ኢሳት ግን መታመንን አግኝቷል። በአብዛኛው ክንዴ – ጥላዬ – ጋሻዬ ተብሏል።  „ሃሳቡን የሰረቁት ¡  ያን ቅዱስ መንፈስ ቁሞ ቀር አልደረጉትም – አፍርቷል። ዓለምአቀፍ ዕውቅናውም – ብሩኽ ነው። ተቀባይነቱም በዓለምአቀፉ ማህበረሰብ የዚያኑ ያህል – ደማቅ ነው። ስለዚህ ይሄ ሕዝብ እኮ ከራሱ በላይ ፍርሃቱን የሚያምን ነው ይህ አገላላጽህ የእንቧይ ካብ ያደርገዋል የኢትዮጵያ ህዝብ ፍርሃቱን ሳይሆን ተግባርን የሚያምን፤ በአምላኩ ተስፋ የሚያደርግ የነጠር ዕንቁ ሥነምግባር ባለቤት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ሃይማኖትም አለውመለያውም ነው።እንዴ! ይሄ ሕዝብ እኮ መብቱን በአደባባይ በሳቅ እና በስላቅ ሲቀሙት ቦርሳውን እንደጣለ ሰው መሬት መሬት እያየ እኮ ነው ወደ ቤቱ የገባው ! ይሄ ሕዝብ እኮ ዘንድሮን ለማምለጥ ስለ ትናንትና የሚያወራ ነው” –  ለመሆኑ የት ነበርክ? አልሞተም? አልተደበደበም? አልታሰረም? አልተቃጠለም? አልደማም? በዚህ ሁሉ አፈና ማህል ሆኖ እንኳን  –

http://ethsat.com/video/esat-breaking-news-protesters-clash-with-police-april-22-2015/  22.04.2015 ይህን የቅርብ ስለሆነ እንጂ ተዘርዝሮም ተጽፎም የማያልቅ ነው። የሀገር አንበሳ የውጪ እሬሳ ሌባ  ቀደም ሲልም ዓለምን ያስተማረ – ቀልብ የሳበ „ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል“ ከዚህ በላይ ምንድን ነው የምትፈለገው?! የሚመችህን ፓርቲ አደራጅተህ በመረጥከጠው ስልት የድርሻህን መወጣት ትችላለህ፤ ሁኖልህም መሰሉን የቴሌቪዢን ፕሮግራም ብትጀመር ጀግና እንጂ “የሃሳብ ሌባ¡” አትባልም።  ስለዚህ መንገዱም መስመሩም መጀመር ነው፤ ልብ ያለው። ለነገሩ ግንቦት ሆይ ብለህ በጻፍከው ጹሑፍ ላይ የድርጅት ጽንሰ ሃሳብ የመግባቢያ ያህል እንኳን አንደሌለህ ተገንዝቤያለሁ። ቀደም ብዬም እንደገለጽኩልህ አንድ ፓርቲ ሲደራጅ የሚያጸድቃቸው ሰነዶችን ድንገተኛ አደጋ በገጠማቸው ቁጥር በግብታዊነት ሰራርዞ እንደ ሰከረ በቅሎ ይበርግግ ነበር ያልከን። ለነገሩ ባልኖርክበት ህይወት ነበር – የዳከርከው። ዘግዬት ብዬ ልኬው ብሆን ባላደራርባቸው፤ የመልስ ጹሑፌ ወጥቶ ቢሆን ኖሮ ልክ ያስይዝህ ነበር። ፓርቲ እንቅስቃሴ፤ ግንባር የቡና ተርቲም አይደለም። ፈተና ህይወቱ ነው። ዬተደራጀውም ለዚህ ነው። ፈተናዎቹን በስልትና በብልሃት ከሥራቸው – ለመፍታት። መሪው ዘላቂ ዓላማው እንጂ ድንገተኛ ችግሮቹ ጋላቢ ስሜቶች አይደሉም – ለፓርቲ። ይህ ውልቅልቅ ያለውን፤ ወለምታ የሚበዛበትን ፍላጎትህን ለማሳካት አንተ በህይወት እያለህ በዚህ ወጣት ዕድሜህ ጀምረው። ሌላው የዓለም ዕውቅ የሰላም አርበኞችን እንደ ማሀተመ ጋንዲ እንደ ማርቲን ሉተር ከተከበሩ ኢንጂነር ይልቃል ጋር ስታስማማ ቢያንስ – በልፋት የተገኘውን የሙያ ደረጃ አትርገጠው „ …. እሱ ከሆነ እኔም እንደ ብርሃኑ ነጋ የምርጫ ካርዳቹን ቅደዱት በሚለው ሃሳብ ላይ እስማማለሁ።  የቆሎ ጓደኛ። በዚህ መንፈስ አንተን እራስህንም – ዘልፈኽዋል። ስለምን? ለአንተ ውስጣቸውን ያበረከቱ ንጹኃን ሚዛናቸውን እንዲጠይቁ – ስለሚገደዱ። አዬህ አቶ ወንድም ታላቅ – ይከበራል። ይህ እኛን በልዩ ሁኔታ የሚገልጽ ንጹሕ ሃብታችን ነው። ትውልዱ መነሳት ያለበት ከትናንት በጎ እና ጠቃሚ ከሆኑ የአብሮነት ሥነ – ምግባሮች መሆን ይኖርበታል። በኢትዮጵውያን ዘንድ ታላቅን አንጠልጥሎ መጥራት እጅግ ጸያፍና ነውር ነው። አሳዳጊንም – ያስወቅሳል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44090ለዚህ ሕዝብ መሰዋት ይገባል -„

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37017„ግንቦት ሆይ“

http://www.ethioreference.com/archives/1510 „ስለ አንዳርጋቸው ሳስብ“

http://ethiocenter.blogspot.ch/2015/04/blog-post_22.html „የምትሞትለት ሰው ከሌለህ አንተ ሞተሃል“

http://ecadforum.com/Amharic/archives/14727/ „የይቅርታ ደብዳቤ ለጃዋር መሐመድ“

በነዚህ ሊንኮች ለናሙና የለቀምኳቸው ሥነ – ጉዳዮች የተቃርኖ ቤተኛ የሆኑ የራስህን ዕይታዎች፤ በራስህ ውስጥ እንኳን አድራሻ ቢስ ያደረካቸውን ሥነ – ፍላጎቶችህን ጥቂት ጉዳዮችን ብቻ ነጥዬ በሰንጠረዥ ሰርቸዋለሁ። አንድ ጹሑፍ ፖስት ከተደረገ በኋላ ሌላ ከመላክ በፊት – የቀደመውን ደጋግሞ በምልሰት ማንበብ፤ መቃኘት – ያስፈልጋል። አብሶ አቋምን በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ ብክል – ዝልት – ጡዘት ወይንም ንዝረት ያላቸው ስሜቶችን መመርመር በእጅጉ ያስፈልጋል። እንጡሩብ እንዝለል የሚሉ ወጠጤ ስሜቶችን በስክነትና በመስተዋል ማሰስ ተገቢ ነው። ስንበቴ አብይ ጉዳዮችን አበክሮ በተደሞ ገልፆ ይሆናል። ይኸውም – ብልጹጉን እኛነታችነን ዒላማህ አታደርገው – እኛንም በማንአለብኝነት አትቀማን! ስንብት – ይህ ጹሑፍ የመጨረሻዬ ነው። ሄኖክሻ ወደ ውስጥህ ብትመለስና ክፉና ደጉን ለመለዬት እራስህን ብተመክር ደስ ይለኛል። ድንግል ትጠብቅህ። ከቻልክ በትህትና እማሳስብህ –  መዝሙረ ዳዊትን – ምሳሌን የሰለሞንን ጥበብ እንዲሁም መጸሐፈ ሲራክን ከልብ አንብብ – ይጠቅምሃል። እንዳትሰበርም – ይታደግኃል። ከውስጥ እንዳትወጣም – ይፈውሥኃል። ደህና ሰንብት።

 

„     መቼም በደንብ እንደምታውቀው እኔ ” ወያኔ ባሩድ አሽትተን እንጂ ፣ እርግብ አሳይተን እናሸንፈዋለን ማለት ዘበት የሚመስለኝ ሰው ነኝ ” እንዴት ሸለምጥማጥን እርግብ ሆነህ ትቀርበዋለህ ?

?ወደ አብይ ጥያቄዬ ስመጣ ስለ ትግሉ ሳስብ ሆድ ይብሰኛል ፣ መቼ ይሆን ጦርነቱ የሚጀመረው እያልኩ ከራሴ ጋ አወራለሁ ፣ በይበልጥ በግንቦት ሰባት ስም የተገደሉ ፣ የታሰሩ ፣ ከስራ የተፈናቀሉትን ሰዎች ሳስብ ፣ በጣም የዘገየህ ይመስለኛል ፣ ይሄ የኔ ብቻ ጥያቄ እና መብሰልሰል እንዳይመስልህ ፣ ያው እኔ ስለማልፈራ ነው ጥያቄውን የጠየቅኩት እንጂ አሁን አሁን የብዙ ወዳጆቼ ጥያቄ እየሆነ ነው ። መቼ ነው አዲስ አበባ ላይ የወያኔ ባለስልጣን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ ሲባል የምንሰማው ? መቼ ነው የወያኔ ባለስልጣኖች ሲንማ-ራስ መቃም የሚያቆሙት ፣ መቼ ነው ከህዝብ ጋ መተራመስ የሚያቆሙት ፣ መቼ ነው ቀን የግንቦት ሰባትን አባላት እና ሌሎች ንጹሃን ሰዎችን ማዕከላዊ ወፌ ላላ ሲገርፍ የዋለ የ ወያኔ ባለስልጣን ማታ አንገቱ ተቆርጦ የምናየው ? መቼ ነው ? የክርስቶስ ዳግም መምጣት እንኩዋ እንዳንተ ውጊያ መጀመር በዙም አልጉዋ-ጉዋ-ንኝም !“

 

 

 

 

„   እስከ መጨረሻው መጀመሪያ ድረስ በመታገል አምናለሁ ። የናንተ መንገድ ዛሬ የናንተ ብቻ ነው ፣ ነገ በምትወሱነት አካሄድ ወይ የናንተ ብቻ ሆኖ ይቀራል ወይም ደሞ ወደ ሕዝብ የኛነት ይቀየራል ።”

 

“ … ለ አንዳርጋቸው ጽጌ ሳስብ ዛሬ መተኛት አልቻልኩም። ከእንቅልፌ ተነሳሁ፣ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፣ ተመልሼ በማልቀሴ ተናደድኩ።ለማን ነው የማለቅሰው፣ ለአንዳርጋቸው ወይስ ና ተከተለኝ ሲለኝ ላልተከተልኩት እኔ ? ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሰአታት በፊት የተናገሩት ነገር ትዝ አለኝ ።”ይሄ የአንዳርጋቸው ጽጌ ለወያኔ ተላልፎ መሰጠት አንገት አያሰብርም ያሉት” ከዚያ ደሞ “Don’t get mad get evil ” ያሉት። እኔ ግን ሁሉንም መሆን ነው የምፈልገው። ቀጥዬም አንዳርጋቸውን እኔ መተካት አልችልምን ስል ራሴን ጠየቅኩ ( ልብ ዓርጉ መሆን አላልኩም መተካት ነው ያልኩት ፣ በግብር ማለት ነው ) ። ውስጤም መለሰለኝ ” ትችላለህ አታመንታ እንጂ አለኝ”

 

 

” ….. የተማሩት ሀገራቸውን ሊያገለግሉ ፣ እውቀታቸውን ሊያካፍሉ በየትምህርት ተቋማቱ ገቡ ፣ የቻሉት ቤተ- መንግስት ድረስ ዘለቁ ፣ ከያኔው ጠቅላይ ሚንስትር ጋ ተጨባበጡ ፣ ብርጭቆ አጋጩ ፣ አብረው ለመስራት ተስማሙ ፣ እንደውም አንዳንዶች እንደ ቀብድ አማራን የሚኮንን መጽሐፍ ጻፉ ። ….”
 

 

 

 

“ …. በነገራችን ላይ ቀኑን ጠብቀን ” ቅንጅትን ማን አፈረሰው !” የሚል ጽሑፍ እናወጣለን ። በይበልጥ የኔ ብርሃነ መዋ እና የሌሎች የዛሬ ጀግኖቻችን አስተዋጾ ምን እንደነበር እናትታለን ። ምክንያቱም የስራ ልምድ () ማንነትን በደንብ ስለሚገልጥ ።”

 

 

„የምትሞትለት ሰው ከሌለህ አንተ ሞተሃል“

 

“ይሄ ሕዝብ እኮ ዘንድሮን ለማምለጥ ስለ ትናንትና የሚያወራ ነው ( አኖሌ አንዱ ምሳሌ ነው !)። ሌላ ብዙ ምሳሌዎች መጥቀስ እንችላለን ።”

“ ለዚህ ሕዝብ እንኳን ሕይወቴን እንቅልፌን አልሰዋም ነበር ያለው እንዳለ ጌታ ! ምርጥ ጸሐፊ ! … አይ እማዬ ” ልጄ አትቃጠል ይሄ ሕዝብ በልጅነትህ የነገርኩህ ሕዝብ አይደለም እኔም ተሳስቼ አሳስቼህ ነው !” ነው ያልሽኝ አንድ ቀን ! አይ እማዬ”

 

የኔዎቹ መሸቢያ – ሰሞናት። እግዚአብሄር ይስጥልኝ ውዴና ጌጤ ዘሃበሻም።

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

The post „ ….. / – ምንአውቅልህ?“ – ከሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>