ለጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ምላሽ
ከቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲ፡ሲ 7/7/15
አቶ ደምስ በለጠ “ጋዜጠኛ ሔኖክ ሰማእግዜር ላይ የተደረገውን ወከባ አወግዛለሁ!” በሚለው ጽሁፋቸው ሃሳብ በነጻ ስለመግለጥ፡የዓለም አቀፍ ህግጋትን ጠቅሰው፡የአማሪካ ዜግነትም ለዜጋው የሚደነግገውን መብት አስገንዝበዋል።በዚሁ ባአማሪካ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣል።ጠብ ዱላ ፍጽም የለም ማለት አይቻልም።አፍሪካዊ አሜሪካውያን የሆኑት ወይም ጥቁሮች በየከተማው በግፍ የተገደሉ ወገኖቻቸው ስም ጠርተው ይጮሃሉ። በሰላማዊ ሰልፍ ስሜት ይቀሰቀሳል።ከቁጥጥርም ይወጣል። በቅርቡ የወጣ ፊልም “ሴልማ” የተሰኘ ትዝ ይለኛል። እኔም የየካቲት 66 ትወልድ ስለሆንኩ ከልምድ ከትዝታ ነው ግንዛቤ የምወስደው። የኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት ሊቃወሙ የወጡ ወጣቶች በሔኖክ ሰማእግዜር ጉዳይ ጩኅታቸው ተቀሙ እላለሁ። የአላማቸውን ግዝፈት ከሔኖክ ኢምትነት ጋር እንዲመዘን ፈቀዱ።ስሜት ዋጣቸው።ተንኩሶም ይሆናል ሔኖክ አናውቅም። ብቻ የሳት እራት ሆንዋል።ቪኦኤ ችግር እንዳለበት በግልጽ እያወቀ ለምን መደበው? ምን ተንኮል ነው? እራስዎ አቶ ደምስ አበበ ገላው እንደሞገተው አንስተዋል። ሔኖክ ሰማእግዜር ሆን ተብሎ የቀረበ የሳት እራት ነው። ሰልፈኞቹ አላሰቡትም።ብሽቀት፡እልህ ምሬት። ስሜት አቸንፏቸው ነበር እላለሁ።ልምድ ሊያርመው የሚችል ስተት ነው።
የነበረውን ሰልፍ ሰልፈኛው በልቡ አምቆ የያዘውን ሳናነሳ ህግና ደብን ብቻ መጥቀስ “አታውቁም ላስተምራችሁ” ወደሚል የእብሪት ጎዳና ይወስዳል።እንደምገምተው ሰልፈኛው ንዴቱ በፕሬዚዳንት ኦባማ ላይም ይመሰለኛል።እንዳቶ ደምስ ዜጎች የሆኑ ሁለቴ መርጠዋቸው ተከድተዋል።ፕሬዚዳንቱ ህወሃት ጋር አዲሳባ መሄዴ ነው በማለታቸው። በግሌ ለአካባቢው ሰላም ለኢትዮጵያ ይፈይዳሉ የምለው የለም። ሰልፈኛው ይህን ምክኛት ያደረገ ትኩሳት ያጣዋል? ሔኖክ የሳት እራት ሆንዋል። ምነው ባልሆነ! ስለተመስገን ደሳለኝ፡ስለ እስክንድር ነጋ፡ስለ ርዕዮት፡በግፍ ተይዘው የሚሰቃዩትን ትተን እንደማንኛችን እንጀራ በወጡን ስለሚዚቅ ሔኖክ እንዲወራ ሆነ። ይህ ልጅነት ነው። የፖለቲካ ትግል ውጣ ውረዱ ብዙ ነው። ከስተት ይማሯል። “እኔ በበኩሌ ጨቋኞችን አንስቼ ሌላ ጨቋኞች ትከሻየ ላይ የምጭንበት ምክንያት ስለሌለ ትግሉ ባፍንጫየ ይውጣ።” ብለዋል አቶ ደምስ። መቸስ አፍንጫ ግም ነገርም ይወጣበታል። አቶ ደምስ በለጠ ጨቋኙን ከትከሻቸው የማውጣት የማውረድ ችሎታ አለኝ ብለዋል። ወጣት ታጋዮቹን ዘዴ ቀይሱ።በህብረት፡ክስተት ተማሩ እላቸዋለሁ።የሽምግልና ምክሬ ይህ ነው። በተረፈ የካቲት 66 ውስጤ ያለው ትግል የወንድሞቸ ደም ስላለበት የአካሌ ክፋይ ነው ከውስጤ አይወጣም። “ባፍንጫየ ይውጣ።” በፍጹም አልልም፤ ወያኔ ሆዳም ሳይሰናበት። አቶ ደምስ ዛሬ እኮ የህወሃትን የመጨረሻ ምእራፍ እያነበብን ነው። መለስ ሲሞት ህወሃት እኮ አብቅቷል። ትግሉ ባፍንጫዎ መውጣቱን መብት ካሉት እሱም ይከበራል። ዝም ማለትም ብልህ ምርጫ ነው።
ወደለላው ትችቴ ሳላልፍ ግልጽ እንዲሆን ልድገመው።ሄኖክ ዝንቡ እሽ መባል አልነበረበትም። ቢሳደብ ቢማታ እንኳን ትዕግስት የሚጠበቀው ክሰላማዊ ሰልፈኞቹ ነወ።
አሁን ወደ ሁለተኛው የምላሼ ክፍል ልሂድ። አቶ ደምስ በለጠ ሔኖክ ሰማእግዜርን አንስተው አልቆሙም።በግራበቀኝ ተቌሞችን የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችን ተችተዋል። የሚካሄደው ትግል አርቢት ይመስላሉ:: ቢጫ ካርዶች ሰጥተዋል። አንድ ባንድ እንመልከት። እንዲህ ብለዋል።
“ኢሳት ወያኔ ሃሳቤን በነጻነት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዳላስተላልፍ ከለከለኝ ብሎ የሚከስ ሚዲያ ነው።
የኢሳት አባላት በምን የሞራል የበላይነት ነው ጋዜጠኛውን ሄኖክ ሰማእግዜርን ያን ያህል ወከባ ሊያደርሱበት የቻሉት ?”
ኢሳት ምን አገባው ? የደምስ በለጠ ክስ ጭብጡ የት ነው ? ሰልፉን ያደራጀው የመራው ኢሳት ነኝ አላለም። ሰልፉን አደራጀሁ መራሁት የሚለው የዲሲ ወጣቶች ግብረሃይል ነው። አቶ ደምስ በስተት ይሆን ወይስ እሶም እንደህወሃት የኢሳት ስሙ ሲነሳ ያንገሸግሽዎታል? ኢሳትን ሲከሱ ያቀረቡት ማስረጃ ሰልፈኞቹ የኢሳት ቲ ሸርት ለብሰው ነበር ነው። የስፖርት ፌዴሬሽን ባዘጋጀው በዓል ከኢሳት በብዛት ቲ ሸርት ሰዎች ገዝተዋል። ወንጀለኛ መሆናቸው ነው? አዝናለሁ ለሔኖክ መብት የምክራከረውን ያህል ለኢሳትም እቆማለሁ። ኢሳት በጥቅል ለሁላችንም ህወሃት ጨርሶ እንዳያፍነን እምቢኝ የምንልበት ተቋም በመሆኑ። አቶ ደምስ ኢሳት ዛሬ የሚያስተዳድሩት ሰዎችም ታዛቢዎችም እንደሚያስተውሉት የህዝብ ንብረት አለኝታ ነው።ስለዚህ አይድከሙ። ወያኔም ታክቷል።
አለፍ ብለው ደግሞ ስለአንዱ የሳምንት መጨረሻ የራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ መበደል ያወሳሉ። ስለ አበበ በለው። እዚህ በሰፊው ማቅረብ ከገዘፈው ያገራችን ችግር ይልቅ በአንድ የሳምንት መጨረሻ ቱሪናፋ ላይ ማተኮር ይሆናል። የጠቀሱት ኢንተርቪው (እነ ልኡል ቀስቅስንና እነጋዜጠኛ ክንፉ አስፋን )እንዳቀረበ ያደረግከው ደግ አይደለም። አንዱን ወገን ብቻ ይዞ አይቀርቡም ተብሎ ተተችቷል። “አበበ በለው ራሱ ባይልክልኝም ጉዳዩን አስመልክቶ ለነአምን ዘለቀና ለብርሃኑ ነጋ የጻፈው ደብዳቤ ደርሶኛል በጎንዮሽ።” ብለዋል አቶ ደምስ። ይህ አርበኞች ግንቦት 7ን ሊጎሽሙ ውስጥ ውስጡን የሚሰሩ ያስመስልዎታል። አርበኞች ግንቦት 7 ጋር ምን አጋፋዎት ?ለኢትዮጵያ የሚቆረቆሩ ከሆነ ለህወሃትና በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ በሚገቡ ላይ ይበርቱ::
በመጨረሻ “በአጠቃላይ የሰዎችን የማይሻርና የማይገሰስ መብት የማክበር ልምድ ይኑረን።” ብለዋል:: አሚን። አላህ ጤናዎን ይስጥዎት።
The post ሔኖክ ሰማእግዜር በገዛ እጁ የሳት እራት ሆነ appeared first on Zehabesha Amharic.