“ገንዘብ አላችሁ” ምንጩን ለሌላ ልቀቁ ከጌታቸው ኃይሌ ፕሬዚዴንት ኦባማ አዲስ አበባ ላይ ለተሰበሰቡት የአፍሪካ መሪዎች ሰኞ ዕለት ሐምሌ 20 ቀን 2007 ዓመተ ምሕረት ንግግር እንዳደረገላቸው እናስታውሳለን። በንግግሩ ውስጥ ሥልጣን ለባለተራ የሚተው እንጅ እስከ ዕለተ ሞት የሚስገበገቡለት እንዳይደለ ለመሪዎቹ ሲያስታውሳቸው ገንዘብ እንደሆን አከማችታችኋል አላቸው። አፍሪካውያንን በሥልጣን ኮርቻ ላይ ለመንጠላጠል፥ ከተንጠላጠሉ በኋላም እዚያው ተጣብቆ ለመኖር የሚያጓጓቸው ገንዘብ ለመግፈፍ ብቻ ሊሆን አይችልም። ይህ አንዱ ነው እንጂ፥ ሁሉም አይደለም። ለምሳሌ፥ የደርግ ባለሥልጣኖች ለሥልጣኑ የተስገበገቡት ገንዘብ ለማካበት አይመስለኝም። ባለሥልጣን መሆን ስም ያስጠራል። አልባሌ ሆኖ ከመቅረት ያድናል። ሥልጣን ለኀይለ ማርያም ደሳለኝ የጠቀመው ይኸ ብቻ ይመስለኛል። በችሎታቸውና በሕዝብ ምርጫ የታላላቅ አገሮች መሪዎች ከሆኑ ጋር እኩል ይቆማል፤ አብሮ ይበላል። ከሰው ዓይንና ከሰው አፍ ላለመጥፋት ብዙ ሰዎች የቱን ያህል እንደሚጓጉለት በርሊን ከተማ ሄዶ ለሰፊ ሕዝብ በመታየት ራሱ መስክሯል። —–-[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]–—