ሳሙኤል አሊ ከ- ኖርዌይ
ህግ በታሰረበት አገር ሰለ ህግ ማውራት ቀልድ ሊሆን ይችላ ይሆናል። ነገር ግን ትግልን የሚወልደው ወይም ታጋይን የሚያበዛው የህግ የበላይነት ሲጠፋ ነው። ህግ ባልተከበረባት አገር ዜጎች ሁል ግዜም ሰቆቃ ውስጥ እንደሆኑ ማሰብ አለብን። ህግ እራሱ ሰለታሰረ ፍርድ ቤቶች የቧልት ቤት ሆነዋል።
የፖለቲካ እስረኞች ጋዜጠኞች ጦማሪያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አሸባሪ በሚል ታርጋ ወደ እስር ቤት ተወርውረው የመከራና የሰቆቃ ግዜአቶችን ሲያሳልፉ ምን ባደረጉት ወንጀል ነው የሚል በሁሉም ልብ ውስጥ ጥያቄ መጫሩ አይቀሬ ነው። ታዲያ የሚፈለገው እኮ እርሱ ነው እነዚህ ሰወች እኮ ለኛ ትልቅ የትምህርት ተቋም መምህሮቻችን ናቸው። የወያኔን ስርአት ቁልጭ አድርገው ያሳዩን በነዚህ በእውነተኛ ብዕረኞችና ፖለቲከኞች ነውና ። ኢትዮጵያዊው ሁሉ ጎበዝ ተማሪ ሆኖ የታሰረውን ህግ ማስፈታት የሚችል እንደ መምህሮቻችን ቆራጥና ጀግና የሚሆን ትውልድ እነደ ሰደድ እሳት ውስጥ ውስጡን ሊቀጣጠል ይገባል። ጊዜው በኢትዮጵያ የታሰረውን ህግ በማስፈታት ነጻና እውነተኛ ፍታዊ ስረአትን መዘርጋት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል እንጂ፡ ህግ አሳሪን አስወግደን በምትኩ ሌላ ህግ ጨፍላቂ ለመተካት አለመሆኑ ይታወቅ።
ምርጫ በቀረበ ቁጥር ጭንቅ ጥብብ የሚለው ወያኔ አሉ አሉ የተባሉትን ፖለቲከኞች እና ፀሐፍትን፤ ጋዜጠኞችን፤ ለቅሞ ማሰር የተለመደ ተግባሩ ነው። ምክንያቱም በክፍተኛ ሁኔታ ሕዝቡን ሊያነሳሱት ይችላሉ በማለት እና ሕዝቡንም መሪወቻቹህ እና ጋዜጠኞቻቹህ ታስረዋል እናተም አንዳች ነገር አደርጋለው ካልቹህ ካለችሁበት ተለቃቅማቹህ እነሱ የገቡበት ትገባላቹህ የሚል መልእክት ማስተላለፊያ መንገድ ነው። ሰለዚህ የኢትዮጵያ ህግ ቀድሞ ስለታሰረ የህግ ከለላ ማግኘት አይችሉም።
ታዲያ እኛ እንሱ ሲታሰሩ እሪ ብሎ ማልቀስና መጮህ ሲፈቱ ደግሞ እልል ብሎ መዘመር ነው እኔዴ ስራችን? ይሄ አይደለም የኛ ኢትዮጵያን ስራ ሊሆን የሚገባው ስታስሩ ለምን? ሲፈቱስ በምን የህግ አግባብ ተፈቱ? ብሎ የመጠየቅ ሃላፊነት አለብን። እዚህ ጋር ሊሰመርበት የሚገባው አሳሪውም ማን ነው? ፈቺውስ ማን ነው? አሳሪውም ፈቺውም በህግ ሊጠየቁ ይገባል ለምንስ አሰርካቸው ለምንስ ፈታሃቸው?
ዛሬ የፈታቸውን ነገ አለማሰሩ ምን ዋስትና አለ? ዛሬ ነጻ ናቸው የተባሉት ነገ ወንጀለኛ ናቹሁ ተብለው አለመያዛቸው ምንስ ማረጋገጫ አለ? ወያኔ ሲጨንቀው ማሰር ሲጠበው ሊፈታ የሚችልበትን ህግ ማን ሰጠው ይህ ሁሉ ዘግናኝ ስህተቶች እየተፈጸሙ ያሉት እራሱ ህግ እሰር ላይ ስለሆነ ነው።
እንጠይቃለን፦
1 ህግ (ፍርድ ቤቱ) ይፈታልን ነጻ ይሁንልን።
2 ያለወንጀላቸው አሸባሪ ተብለው ንጹሃን የኢትዮጵያ ልጆች በእስር መማቀቃቸው ይታወቃል ስለዚህ እነዚህ ንጹሐን ወደ እስር ያስገባቸው አካል በአስቸካይ ለፍርድ ይቅረብልን።
3 ያለ በቂ ማስረጃ ታስረው ቆይተው አሁን ላይ ነጻ ናቹህ ብሎ የለቀቃቸው አካል የደረሰባቸውን የሞራል፤ የጊዜ ፤ የስነ ልቦና ጉዳት፤ ሳይመለከት ነጻ ናቹህ ብሎ አሳሪወችን ለፍርድ ሳያቀርብ የፈታው አካል ለፍርድ ይቅረብልን።
4 በነዚህ ንጹሃን ኢትዮጵያን ላይ የተሰራው ግፍ በነሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ እየተፈጸመ ያለ ጉዳይ ስለሆነ ያለምክንያት ከተያዙበት ጊዜና ሰዓት ጀምሮ ሰለደረሰባቸው የሞራልና እና እንዲሁም ያለአግባብ በእስር ስላባከኑት ጊዜ ተገቢውን ካሳ እንዲከፈላቸው እንጠይቃለን።
5 ሌሎች ንጹሃን ኢትዮጵያን በወያኔ ጉጅሌ የፈጠራ አኬል ዳማ ድርሰት የታሰሩት በአፋጣኝ ተፈተው ተገቢውን ካሳ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን።
ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነው። ወያኔ ከአሁን በሃላ በአንተ ስራ ማንም አይታለልም የካንጋሮ ፍርድ ቤትህንም ማንም ኢትዮጵያዊ አያምነውም የምንታገለው የታሰረው ህግ እስከሚፈታ ድረስ ነው እንጂ በፈጠራ ድርሰት ያሰርካቸው ብቻ እስኪፈቱ አይደለም። የምንታገለው ህግን ያሰሩትን እና ሕዝብን የሚያሰቃዩበትን ህግን አስፈትተን ህዝባችን ነጻ አደርገን ህግ አሳሪ እና ሕዝብ ጨቋኝ የነበሩትን ለፍርድ ለማቅረብ ነው። አገራችን ነጻ እስከምትሆን ድረስ ነጻ የሆነውን ህዝባችንን ልታሰቃዩ ትችሉ ይሆናል፡ አሳሪ እና ገዳይ እንዲሁም አረመኔ የሆነው ወያኔን አስወግደን የሁላችን አገር እስከምናደርጋት ድረስ ልታስሩን ልትገድሉን ትችሉ ይሆናል፡ በደል ጭቆና እስራት እንግልት ግድያ የመብት ጥሰት ሲበዛ ሰው ፈሪ ይሆናል ብላቹሁ አስባቹ ከሆነ በወያኔ አእምሮአችሁ ማለትም በጠባብ እና እውቀት በሌለው ማሰቢያቹህ የተጨቆነ ሕዝብ የሚባላ አብዮት እንደሆነ የምታዩበት ጊዜ ቅርብ ነው። ህዝብ አብዮት ነው አብዮት የሚመጣው የተጨቆኑ ህብረተሰብ ለለውጥ የሚነሳበት አንባገነኖች የሚያለቅሱበት የማይጠፋ እሳተ ገሞራ ነው ይሄም ሕዝባዊ አብዮት አንባገነኖችን የሚያጠፋ እሳት ነው።
ጋዜጠኞች እንዲሁም ፖለቲከኞች እንዲሁም ፀሃፊያኖች በመፈታታችሁ ደስተኛ ነኝ። አሁን ግን ትግሉ ኢትዮጵያን ለማስፈታት ነውና ትግሉን ሁሉም በአንድነት ተቀላቀሉ ኢትዮጵያዊ ሁል ጊዜ አሸናፊ ነው።
ድል ለሰፊውየኢትዮጵያ ሕዝብ
ሞት ለዘረኛው ወያኔ ይሁን
ሳሙኤል አሊ ከ-ኖርዌይ
Email samilost89@yahoo.com