Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የአዲሱ ህውሀት መንግስት መጥፎ አጋጣሚ!! –ከኤርሚያስ ለገሠ

$
0
0

ከኤርሚያስ ለገሠ

1• ደስታ እና ሀዘን

ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ ስትነቃ አቅፎ ሊያነሳት በመቻሉ ደስ ይለኛል። እንኳን ለዚህ አበቃህም ማለት እፈልጋለሁ።
ermias copy
በሌላ በኩል ገዥው ቡድን በምክንያት እያሰረ በምክንያት የሚፈታበት ሁኔታ ለራሱ ስልጣን መቆያ ትክክል ቢሆንም ለኢትዬጲያ የፍትህ ስርአት ምን ያህል ንቀት እንዳለው የሚያሳይ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው። ሰዎች በህውሀት ላይ አደጋ ሲጋርጡ በፓለቲካ ውሳኔ ይታሰራሉ…ህውሀታዊ ምክንያት !። ገዥው ቡድን ላይ የተጋረጠው አደጋ በሌላ ጐን ሲያጋድል ደግሞ በእጁ ይዞ የሚያሰቃያቸውን ይፈታል…ህውሀታዊ የመፍታት ምክንያት!!

ሀብታሙ አያሌውና ድርጅቱ ” አንድነት” ህውሀትን በሰላማዊ ትግል ፈተና ውስጥ ለመክተት ስትራቴጂ ነድፈው ሰፊ እንቅስቃሴ ጀመሩ። የለውጥ ንፋስም በስሱ መንፈስ ጀመረ። እነ ሀብታሙ በአደባባይ ” እመኑኝ ኢህአዴግም ይወድቃል! ኢትዬጲያም ነጳ ትወጣለች!” በሚል መሪ መፈክር ገዥዎችን አስጨነቁ። የስርአቱን ባህሪያት በቅርብ የምናውቅ ሰዎች የእነ ሀብታሙ እድሜ አጭር እንደሚሆን አሳወቅን። ርግጥም ” ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም!” በሚል መርህ የሚመራው ገዥ ቡድን እነ ሀብታሙን የውሸት ክስ በማዘጋጀት ወደ ማእከላዊ ወረወረ። ” አንድነት” ፓርቲንም አፈረሰ። ኩሸቱን በመደጋገም የራሱን እውነት ፈጠረ። እነ ሱዛን ራይዝን “በ100%” ጦሽ ብለው እንዲስቁ አደረገ።

በሌላ በኩል ለውጥ በሁሉን አቀፍ ትግል ብቻ መምጣት እንዳለበት የሚያምኑ ኢትዬጲያውያን የለውጥ እንቅስቃሴውን በግላጭ ማቀጣጠል ጀመሩ። ምሁራን ዱር ቤቴ በማለት ወደ በረሀ ተመሙ። አዲስ ህልምና አዲስ አቅጣጫ ይዘው የነጳነት ትግሉን ዙር አከረሩት። እናቶች ከጣታቸው ቀለበት፣ ከአንገታቸው ሀብላቸውን እያወለቁ ትግሉን ወደማገዝ ተሸጋገሩ። የመኪናቸውን ቁልፍ ለአርበኞች አስረከቡ። በየቦታው አዳራሽ ሞልቶ እስኪፈስ ድረስ ” እኔ አርበኞች ግንቦት ሰባት ነኝ!”፣… ” እኔ አንዳርጋቸው፣ ብርሀኑ፣ ኤፍሬም፣ ንአምን… ነኝ!” የሚል ቃልኪዳን ከመግባት ባሻገር እስከ መቶ ሺህ ዶላር መዋጣት ተጀመረ። ይህን የለውጥ ስሜት በስማ ስማ ሳይሆን በአይኔ በብረቱ ተመልክቻለሁ። ቆም ብዬም ለማሰላሰል ሞክሬያለሁ።

እንደ እውነቱ ከሆነ ህውሀት ቆም ብሎ ለትክክለኛው መፍትሔ የማሰቢያው ግዜ ነበር። ይሁን እንጂ አፈጣጠሩ፣ ባህሪውና የበታችነት ስሜቱ ይህን ስለማይፈቅድለት ሌላ መፍትሔ ማሰብ ነበረበት። ከእነዚህም ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ባሉት አንዳርጋቸው ጵጌ ስም መጵሀፍ መጳፍና እንደ ሀብታሙ አያሌው ያሉትን የፓለቲካ እስረኞች መፍታት የሚጠቀሱ ናቸው። በበረከት ፀሀፊነት በአንዳርጋቸው ስም የሚወጣው መጵሀፍ ” የሶስት ምርጫዎች ወግ!” ( ስያሜው የእኔ ነው) ገና ባይወጣም በቅርብ ቀን እንደሚወጣ ይጠበቃል። ምርቃቱም ሸራተን አዲስ አንዳርጋቸው በሌለበት ይሆናል። …እነ ሀብታሙ አያሌውም ተፈተዋል።

( ” የሶስት ምርጫዎች ወግ” በተመለከተ ” የነጳነት ትግሉና ስድስት የህውሀት ማደናገሪያ ነጥቦች” በሚለው ሀሳብ ውስጥ አካትቼ በዳላስ ቴክሳስ በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ አቅርቤ ነበር። ብዙዎች እንዲለጠፍ ስለጠየቁኝ በሌላ ክፍል እንደምመለስበት ተስፋ አደርጋለሁ።)

2• ” መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል”

አዲሱ የህውሀት መንግስት ሁለተኛው መጥፎ አጋጣሚ በኢትዬጲያ ሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ነው። እነዚህ ለሀይማኖታቸው ነጳነት የሚታገሉ ታጋዬች የያዙት አቋም ገዥው ቡድንን ወደ ከፍተኛ ፈተና ጐትቶ ወስዶታል። ይህን ለማለት ያስደፈረኝ ያለምክንያት አይደለም። ከልምድ በመነሳት እንጂ!

የዛሬ ሰባት አመት በዚህ አካባቢ የአዲስ አመት መምጫ በድርቡም የኢትዬጲያ ሚሊኒየም መግቢያ ነበር። በመላው ኢትዬጲያ በተለይም በከተሞች የቅንጅት መሪዎች ካልተፈቱ ” በሚሊኒየም ምንም የለም!” የሚሉ መፈክሮች ተስተጋቡ። ሁኔታዎች አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር (” ታላቁ መሪ” ባለማለቴ እቴጌን ከወዲሁ ይቅርታ እየጠየኩ) መውጫ መንገድ ፈለገ። “የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መጠቀም” የሚል የውስጠ ድርጅት ሰነድ እንዲዘጋጅ አደረገ። ይህ ሰነድ የታሰሩ ተቃዋሚዎችን በይቅርታ የመፍታት ፋይዳውን የሚተነትን ነበር። በዚህ ጵሁፍ ህዝቡ የይቱልን ጥያቄ ያለማቋረጥ እያነሳ ያለው ከአርቆ አስተዋይነት የመነጨ እንደሆነ ዘረዘረ። ህዝቡ ይፈቱልን የሚል ጥያቄ እያነሳ ያለው ” እኔው መርጬ ለዚህ አደረስኳቸው” ከሚል የህሊና ፀፀት እንደሆነ ተገለፀ። በመሆኑም ታሳሪዎችን በይቅርታ መፍታት ህዝቡን ከፀፀት የማውጣት ሁኔታ ስለሚፈጥር መንግስት የሚፈታበት ሁኔታ ማማተር እንዳለበት በሰፊው ተነገረ።

ታሳሪዎች የይቅርታ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የፍርዱ ሂደት እንዲፋጠን ተደረገ። በአስቂኝና ባዶ ማስረጃ ታሳሪዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲወሰን አደረገ። ( በነገራችን ላይ በመስካሪነት የቀረቡት የቀበሌ ካድሬዎች የነበሩት እነ አበባ ሽመልስ ከማል ልምምድ የሚያደርግላቸው በኢህአዴግ ቢሮ ነበር) ። የፍርድ ውሳኔውን አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እስከ እድሜ ይፍታህ አምዘገዘገው። ይህ ውሳኔ ታሳሪዎችና ቤተሰባቸው ተደናግጠው ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት ይገባሉ የሚል ታሳቢን የወሰደ ነበር። በወቅቱ በታሳሪዎች መስመር ያለውን ተጵእኖ በቀጥታ ከራሳቸው መስማት የምችልበት እድል ባይኖርም በአንዳንድ የቅንጅት አመራሮች እና ቤተሰባቸው ዘንድ ተጵእኖ እንዳሳደረ ሰምቻለሁ። በሌላም በኩል እንደ አንዱአለም አራጌ ያሉ አመራሮች ውሳኔውን ከመቄብ ባለመቁጠር ይቅርታ ለመጠየቅ እንዳስቸገሩ በተባራሪ ሰምተናል።

ዞሮ ዞሮ ህውሀት የገባበት አጣብቂኝ የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መፍትሔ ሊያገኝ ቻለ። ይህን አስመልክቶ አቶ በረከት በጳፈውና የህውሀትን ገድል በሚያሳየው መጵሀፋ ገጵ 233 ላይ እንደሚከተለው አስፍሮ እንመለከታለን፣

” …የፍርድ ሂደቱ ነጳ መሆን በግልፅ መታየቱና መንግስት የቅንጅት መሪዎች የተከሰሱባቸውን ወንጀሎች ከበቂ በላይ በማስረጃ አቅርቦ በማረጋገጡ ህብረተሰቡ የሰዎቹን ጥፋተኝነት በጥያቄ ውስጥ የሚጥልበት አልነበረም። በመሆኑም መንግስት በህዝቡ የቀረበው የይፈቱ ጥያቄ ፣ ማንኛውም ህዝብ በአርቆ አስተዋይነቱ የሚያደርገው… እኔ መርጬ ለእስር አበቃኃቸው ከሚል የህሊና ፀፀት ነጳ ለመውጣት በመፈለግ ያቀረበው ጥያቄ እንደሆነ ተገንዝቧል። ለዚህ አይነቱ የህዝብ ጥያቄ በጐ ምላሽ መስጠት ምንግዜም ቢሆን ግዴታው እንደሆነ የሚገነዘበው መንግስት፣ ጥያቄው የህግ የበላይነት ለድርድር ሳያቀርብ ሊመለስ እንደሚችል አምኗል። እናም በአንድ በኩል የህግ የበላይነትን እያስከበረ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝብን የይፈቱ ጥያቄ ለማስተናገድ የሚችልበትን ሁኔታ ማማተር ነበረበት። በዚህ አኳኃን ነው የኢትዬጲያ ሚሌኒየም ራሱን እንደ መልካም አጋጣሚ የከሰተው” ይለናል።

እንግዲህ ከዚህ ልምድ በመነሳት የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጣቸው። ውሳኔውን መሰረት በማድረግ እስከ ሀያ አመት የሚደርስ እስራት ተፈረደባቸው። ይህ ለመጥራት የሚዘገንን ቁጥር የተበየነበት ምክንያት ታሳሪዎችን ለማስደንገጥ እና ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት እንዲገቡ ታስቦ እንደሆነ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። አንድ ግጥም አቅርበሀል የተባለ ወጣት የተፈረደበትን አመት ለተመለከተ ደግሞ በህውሀት የተጠነሰሰውን ሴራ ለመገንዘብ የእነሱን ያክል ማሰብ ከቻለ በቂው ይሆናል።

ይሁን እንጂ ይህ “የይቅርታ ይደረግልን” ሴራ ቅንጅት ላይ እንደሰራው በሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎቹ ላይ የሚሰራ አይደለም። ሲጀመር የመጀመሪያዉ ፓለቲካዊ፣ የአሁኑ ደግሞ ሀይማኖታዊ ነጳነትን በግንባር ቀደምትነት ያስቀመጠ በመሆኑ በባህሪ የተለያዩ ናቸው። ርግጥ ፓለቲካዊ መብቶች ባልተከበረበት ሀይማኖታዊ መብቶች ይከበራሉ ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ቢሆንም። ከዚህም በተጨማሪ የሀይማኖታዊ ነጳነታዊ ጥያቄዎች ለድርድር የመቅረብ እድላቸው እጅግ ጠባብ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው።

ከላይ የተቀመጠውን ከግምት በመውሰድ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴው አባላት አጥፍተናል እና ይቅርታ ይደረግልን የሚሉ ከሆነ እስከዛሬ ያነሷቸው ሶስት ጥያቄዎች ( ለጊዜው የማውቃቸው) ትክክል አልነበሩም፣ አሊያም ምላሽ አግኝተዋል የሚል እንድምታ ይኖረዋል። ይህም የህውሀትን ድል አድራጊነት ከማረጋገጥ ባሻገር የኢትዬጲያ ሙስሊሞችን የሶስት አመት ትግል ውሀ ይቸልስበታል። ወደ ኃላ የመመለስና በቀላሉ የመክሰም እድል ያጋጥመዋል። የኮሚቴዎቹ አባላት ይህን በመገንዘብ ይመስላል አስደንጋጩ ብይን ሲሠጣቸው ያለምንም መደናገጥ የትግል ጵናታቸውን ለማሳየት የቻሉት። ቤተሰቦቻቸውም ቢሆን የኮሚቴው አባላት እየከፈሉ ያሉት መስዋእትነት ለሀይማኖታቸው ነጳነት መሆኑን በመገንዘብ ከጐናቸው የቆሙት።

ስለዚህ እነዚህ የኮሚቴ አባላት እንደ ቡድን የይቅርታ ጥያቄ ያቀርባሉ ብሎ ማሰብ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደመውጣት ይሆናል። በግለሰብ ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች የይቅርታ ሂደት ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ቢሆንም። ይህ አማራጭ ዝግ ሆነ ማለት ህውሀት መራሹ አዲሱ መንግስት ዝም ብሎ ይቀመጣል ማለት አይደለም። በሁኔታዎች አስገዳጅነት ያለ ይቅርታ ጥያቄ ምህረት የማድረግ ግን ደግሞ በፍርድ ቤት እንዲወሰን ያደረገውን የህዝብ እንቅስቃሴ ገደብ ያለማንሳት ሊኖር ይችላል። ይህም ኮሚቴዎቹን በአይነ ቁራኛ በመከታተል የቁም እስረኛ ወደ ማድረግ መሸጋገር ይሆናል። ይህም ቢሆን ለገዥው ቡድን የሚያመጣለት አንዳችም ፓለቲካዊ ትርፍ አይኖረውም።

ግራም ነፈሰ ቀኝ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የአላማ ጵናት ለአዲሱ የህውሀት መራሹ መንግስት የእግር እሳት እንደሆነ ይቀጥላል። የኢትዬጲያ ሙስሊሞች የነጳነት ትግልም በኢትዬጲያ ታሪክ ውስጥ የሚኖረውን የላቀ ደረጃ እንደጠበቀ ይኖራል!…”መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል” ይሉሀል ይህ ነው!!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>