Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

በኢትዮጵያ በፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን ፓስተሮች እና ዘማሪዎች አማካኝነት በግልጽ እየተፈጸመ ያለ የዝሙት ጅሀዳዊ ሐረካት ኑዛዜ

$
0
0

“ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ኤፌ 5:11-12

ቢንያም መንገሻ September 13,2015

የእግዚያብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ለእውነተኛ ክርስቲያኖች የየእለት እለት የህይወት አኗኗር የኑሮ ዘይቤ እንዲተዳደሩበት እና እንደተጻፈው ህግ እንዲኖሩበት ከእግዚያብሔር ዘንድ የተሰጠ ታላቅ የህግ እና ስርአት ያለው የዘላለም ህይወት የሚገኝበት መጽሐፍ ነው:: ይሁን እንጂ ዛሬዛሬ አያሌ የፕሮቴስታንት የቤተ እምነት አስተማሪዎች ( ሽማግሌዎች ፣ ፓስተሮች እና ነቢያቶች) እንዲሁም የተቋሙ ባለቤቶች በግልጽ ቃሉን በህገ ወጥ መልኩ አስጸያፊ ለሆነው ለስጋዊ ፍጆታቸው ሲጠቀሙበት ማየት ዛሬዛሬ እንደ አንድ የጸጋ ስጦታ ተደርጎ ተቆጥሮላቸዋል:: በዚህ ባለንበት በመጨረሻ የዘመን ፍጻሜ በኢትዮጵያ ያሉ የፕሮቴስታንት አገልጋዮች በአብዛኛዎቹ ማለት ይቻላል ስለመጨረሻው ዘመን ፍጻሜ መቅረብን አስመልክቶ ለምልክት እንዲሆን ከእግዚያብሔር ዘንድ ከተሰጡት እና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፉት የትንቢት ቃሎች ብዙዎቹ የተፈጸሙ ሲሆን ቀሪዎቹም በመፈጸም ላይ ናቸው:: ብዙዎቹ የትንቢት ቃሎች የሚፈጸሙት ደግሞ በእግዚያብሔር ስም እና የእግዚያብሔር ስም በሚጠራበት ቤት ውስጥ መሆኑ ደግሞ የዘላለም ህይወትን የሚገኝበትን የክርስቲያኖችን ፈተና እጅግ አክብዶታል:: ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመኑ መጨረሻ እንደአሸን ፈልተው በስሙ የሚያስተምሩትን ሀሰተኛ አስተማሪዎች፣እረኞች እና ነቢያቶችን እንድንጠነቀቅ ብዙ ግዜ አበክሮ አስጠንቅቆናል:: “እንዳትስቱ ተጠንቀቁ፤ ብዙዎች። እኔ ነኝ፥ ዘመኑም ቀርቦአል እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ እነርሱን ተከትላችሁ አትሂዱ።” ሉቃ 21:8
rp_pastor-getenet-tekeste-zemari-sa.jpg
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው ዘመን በስሙ ስለሚገለጡ ሀሰተኛ ከዲያብሎስ ወገን የሆኑ አስተማሪዎች፣እረኞች እና ነቢያቶችን የምናውቃቸው በፍሬያቸው ማለትም ተገልጦ በሚታይ ህይወታቸው እና ስራቸው እንደሆነ የእግዚያብሔር ቃል እንዲህ በማለት ያስተምረናል:: “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?” ማቴ 7:17_17“ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።” ዮሐ3:19:21

በዛሬ ግዜ በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ተቋማቶች ውስጥ የሚገኙ አገልጋዮች በአብዛኛዎቹ ለበጎ ነገር ምንም አይነት ፍቅር ሳይኖራቸው ለክፉ ነገር ግን ፍቅራቸውን ሲያየው ዲያብሎስ እራሱ እንኳ በእጅጉን ይቀናባቸዋል:: ዛሬ ዛሬ በግልጽ የፕሮቴስታንት አስተማሪዎች፣እረኞች እና ነቢያቶች ዋና መታወቂያቸው (ፍሬያቸው) ልቅ የዝሙት እርኩሰት፣ ያለመጠን ገንዘብን መውደድ ፣ ለበጎ ነገር እርስ በእርስ መጠላላት ፣ ውሸት ፣ እብሪት ፣ ቅናት ፣ አድመኝነት ከአለማውያን በላይ እየተንሰፈሰፉ አለምን የመውደድ ፍቅር በእጅጉን በግልጽ በየእለት እለት የስብከት ስጋ አገልግሎታቸው እና ህይወታቸው የሚታይ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ በጸያፍ የዝሙት ፣ የስርቆት ፣ የስካር ቅጥ ያጣ አለመኛ የሆኑ አስተማሪዎች ፣ እረኞች እና ነቢያቶች ጸያፍ የሀጢያት እርኩሰት ስራቸው ጸሐይ ላይ ሲወጣባቸው ደግሞ ጉድ በሚያስብል ፍቅራቸው በእግዚያብሔር ፊት ወድቀው ንስሀ ከመግባት ይልቅ ለስማቸው እና ለክብራቸው በመቆርቆርና ሰውእንዳይሰማ በማለት ከአዲስ አበባ እስከ ዋሽንግተን እንዲሁም ካናዳ ድረስ ሁሉም በተገለጠው ጸያፍ ሀጢያታቸው ላይ የተገለጠውን ህፍረተ ስጋቸውን ለመሸፈን ደራርበው “ብሉኮ” እና “ብርድ ልብስ” ሲያለብሱት ይታያል:: የእዚያብሔር ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም እንደነዚህ አይነቶች ስላሉት አስተማሪዎች ፣ እረኞች እና ነቢያቶች በትንቢት ቃሉ እንዲህ በማለት ያስተምረናል:: “እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና። ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና። እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።” 2ቆሮ11:13_15

“ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።” 2ጢሞ3:1-5“ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል። ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።” 2ጴጥ2:1-3“እነዚህም ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እያስተማሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ፥ አፋቸውን መዝጋት ይገባል።” ቲቶ 1:11“ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።” 1ጴጥ2:11-12“ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ኤፌ 5:11-12

ዛሬዛሬ ማንም ፓስተር እና ነቢይ መሆን የፈለገ ሰው ከጫት ላይ ተነስቶ የቃመውን ጫት በጉንጩ እንደያዘ የእግዚያብሔርን መንግስት ቃልን ማስተማር ፣ እረኛ እና ነቢይ መሆን ይችላል:: ዛሬዛሬ ማንም ፓስተር እና ነቢይ መሆን የፈለገ ሰው ከሚጠጣው አስካሪ የአልኮል መጥጥ ላይ ተነስቶ የሚጨልጥበትን ብርጭቆ እንደያዘ የእግዚያብሔርን መንግስት ቃልን ማስተማር ፣ እረኛ እና ነቢይ መሆን ይችላል:: ዛሬዛሬ ማንም ፓስተር እና ነቢይ መሆን የፈለገ ሰው ከዝሙት አልጋ ላይ ተነስቶ የሚዘሙትበትን ኮንዶም በኪሱ እንደያዘ የእግዚያብሔርን መንግስት ቃልን ማስተማር ፣ እረኛ እና ነቢይ መሆን ይችላል:: ዛሬዛሬ በኢትዮጵያ ፕሮቴስታንት ቤተእምነት ውስጥ አብዛኛዎቹ አስተማሪዎች የሚያስተምሩት ሳይማሩ ነው:: አብዛኛዎቹ እረኞች እረኛ የሆኑት የራሳቸውን ቤተሰቦች መጠበቅ አቅቷቸው በትነው ነው:: አብዛኛዎቹ ዘማሪዎች የሚዘምሩት የዝማሬ ጸጋ ከእግዚያብሔር ዘንድ ተሰጥቶዋቸው ሳይሆን ድምጸ መርዋ ስለሆኑ እና በገንዘብም ረገድ ስለሚያዋጣ እና ጥሩ ገቢ ስለሆነ በሰዎች ተመስክሮላቸው እና ተመክረው ጭምር ነው:: አብዛኛዎቹ ሰባኪዎች የሚሰብኩት የእግዚያብሔርን ቃል አውቀውት እና ተረድተውት ሳይሆን ወሬ ማውራት ስለቻሉ ብቻ ነው:: ለዚህም አብዛኞቹ ሰባኪዎች ከሰበኩ ቡኋላ ነው መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡት:: አብዛኛው ምእመና ሞቅ ተደርጎ በተሰበከው ስብከት የሞቀ “ሀሌሉያ!” እና “ኢየሱስ ጌታ ነው!” ብሎ በስሜት የሚጮኅውና የሚዘለው እንዲሁም እቃ የሚሰብረው የእግዚያብሔርን ቃል የመጽሐፍ ቅዱስን አውቀውት እና ተረድተውት ሳይሆን እንዲያው ካለምንም ማስረጃ በሉ ስለተባሉ ብቻ ነው:: ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በትንቢት ቃሉ እግዚያብሔር ህዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሰ ጠፋ (የገሀነም እሳት ማገዶ ሆኑ) ይለናል:: “ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። እንደ ብዛታቸው መጠን ኃጢአት ሠሩብኝ፤ እኔም ክብራቸውን ወደ ነውር እለውጣለሁ።” ትንቢተ ሆሴ 4:6-7 “ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው! በዓይናቸው ጥበበኞች በነፍሳቸውም አስተዋዮች ለሆኑ ወዮላቸው! የወይን ጠጅ ለመጠጣት ኃያላን የሚያሰክረውንም ለማደባለቅ ጨካኞች ለሆኑ፤ በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፥ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው!” ኢሳ 5:20_23

“እነዚህን አስተምርና ምከር። ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን፥ በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።” 1 ጢሞ 6:3-5 “ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ። ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ። አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።” 1 ጢሞ 6:6-11

ዛሬ አብዛኞቻችን በእግዚያብሔር አይን ስንታይ አስጸያፊ በሆነ የሀጢያት እርኩሰት ውስጥ ተዘፍቀናል:: ለዚህም ደግሞ እንደ ዋና ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው እራሳቸውን በራሳቸው እና በኮሚቴ እርስ በእርስ የተሿሿሙት እና የተመራረጡት የፕሮቴስታንት የቤተ እምነት ባለቤቶች (ሽማግሌዎች ፣ ፓስተሮች እና ነቢያቶች) በግፍ እና በድፍረት ያለማንም ከልካይ በሀጢያት እርኩሰት ውስጥ በግልጽ ሲጨፍሩ እና ሲኖሩ ማየት እና መስማት ዛሬዛሬ በቤተ እምነቱ አማኝ ዘንድ የተለመደ የአምልኮ ህይወት ነው:: ለዚህም አገልጋዮች በክፉዋ የ“ኤልዛቤል” እርኩስ የዲያብሎስ መንፈስ ተይዘው የሚያስተምሩት እና በህይወታቸው የሚገልጡት ፍሬ መራራ ስለሆነ የእነሱም ተማሪዎች (ምእመናዎችም) ልዩ ልዩ የሀጢያት እርኩሰቶችን በግልጽ ተለማምደውት በተገለጠ ህይወታቸው ሲኖሩት ማየት አሁን አሁን በፕሮቴስታንት ቤተእምነት የሀጢያት እርኩሰት በተለይም “ዝሙት” እንደ ጸጋ ስጦታ የሚታይበት ዘመን ላይ መድረሳችን ያመላክታል:: የእግዚያብሔር ቃልም እንደነዚህ አይነት አገልጋዮችን እንደዚህ በማለት በትንቢታዊ ቃሉ ያስጠነቅቀናል::

“ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን እብድነት አገደ። ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውኃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው። ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፥ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ። ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው። አርነት ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና።በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል። አውቀዋት ከተሰጣቸው ከቅድስት ትእዛዝ ከሚመለሱ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት በተሻላቸው ነበርና። ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ። የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።”2 ጴጥ 2:16-22

እውነተኛ ክርስትያን ማንም ቢሰብከው እና ቢያስተምረው ትምህርቱ እውነት እንደሆነ ከእግዚያብሔር ቃል ጋር እየመረመረ ያመሳክራል እንጂ ስለተሰበከ ብቻ እውነት ነው ብሎ አይቀበልም:: የእግዚያብሔርም ቃል ሁሉንም የምንማራቸውን ትምህርቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ በማስተያየት መመርመር እንዳለብን አብክሮ ያስጠነቅቀናል:: “ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።” 1ዮሐ4:1 “እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና። ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።” ሐዋ 17:11 “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትሰሙ፤ ከንቱነትን ያስተምሩአችኋል፤ ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ ልባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ።” ኤር 23:16 “ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤ ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን።” 1 ቆሮ 11:31-32 “በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ::” 2 ቆሮ 13:5

ለመግቢያ ከላይ በሰፊው እንደጠቀስኩት ስለ ፕሮቴስታንት የቤተ እምነት ባለቤቶች (ሽማግሌዎች ፣ ፓስተሮች እና ነቢያቶች) ጸያፍ የድፍረት ሀጢያት እርኩሰት የተገለጠ ህይወታቸውን መነሻ በማድረግ ይህን የዛሬውን መልእክቴን እንድጽፍ ካነሳሳኝ አንዱ እና ዋናው ነገር ከአንድ ሳምንት በፊት በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ አብዛኛዎቻችን ያነበብነው አንድ ዜና ነበር ያም ዜና ዘማሪ ተከስተ ጌትነት ወደ መደበኛው ስራው መመለሱን የሚናገር ዜና ሲሆን እኔ በግሌ እንደክርስቲያን ነገሩ በጣም አሳዝኖኛል:: ያዘንኩበትም አንዱ እና ዋናው ነገር ዘማሪ ተከስተ ወደ መደበኛው ስራው መመለሱ ሳይሆን እንዲመለስ የተደረገበት የአሰራር ሂደት ፍጹም አጋንንታዊ አሰራር መሆኑን ደግሞ ስረዳው እጅግ እጅግ ድርጊቱ ዘግንኖኛል:: እንደነዚህ ካሉት ሰዎች ጋር ምግብ እንኳን እንዳንበላ እንዲውም ከእነርሱም እንድንርቅ እንድንፈርድባቸውም እንኳ የእግዚያብሔር ቃል አበክሮ ያዘናል:: “ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ በመልእክቴ ጻፍሁላችሁ። በጠቅላላው የዚህን ዓለም ሴሰኞችን፥ ወይም ገንዘብን የሚመኙትን ነጣቂዎችንም፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩትን አላልሁም፤ ይህስ ቢሆን ከዓለም ልትወጡ ይገባችሁ ነበር። አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደነዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ። በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ መፍረድ ምን አግዶኝ? በውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን? በውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።” 1 ቆሮ 5:9-13

የእግዚያብሔር ቃል ሲናገር የሰው ሚስት የሚነካ አይምሮ የጎደለው ነው ይላል:: “ወደ ሰው ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፤ የሚነካትም ሁሉ ሳይቀጣ አይቀርም። ሌባ በተራበ ጊዜ ነፍሱን ሊያጠግብ ቢሰርቅ ሰዎች አይንቁትም፤ ቢያዝም ሰባት እጥፍ ይከፍላል፥ በቤቱም ያለውን ሁሉ ይሰጣል። ከሴት ጋር የሚያመነዝር ግን አእምሮው የጐደለ ነው፤ እንዲሁም የሚያደርግ ነፍሱን ያጠፋል። ቍስልንና ውርደትን ያገኛል፥ ስድቡም አይደመሰስም። ቅንዓት ለሰው የቍጣ ትኵሳት ነውና፥ በበቀል ቀን አይራራለትምና። እርሱም ምንም ካሣ አይቀበልም፥ ስጦታም ብታበዛለት አይታረቅም።” ምሳ 6:29-35

ዘማሪ ተከስተ ጌትነት ይህንን ቃል በደንብ አብጠርጥሮ ያውቀዋል ብዬ አምናለሁ:: እርሱንም ከዘማሪ ወደ ዘመኑ ፓስተርነት በእድገት የሾሙት ኮሚቴዎችም የፓስተርነቱ የሹመት የፊርማ ቀለም ሳይደርቅ በለጋ በእንጭጩ በተሾመ በአራት ወሩ የሰውን ሚስት በተደጋጋሚ በማርከስ እና አጭበርብሮ የሰውን ገንዘብ እንደወሰደ ተመስክሮበት የቀረበበትን ክስ አሻፈረኝ አልቀበልም ብሎ የእርሱ ቢጤ የሀጢያት እርኩሰት ተባባሪዎቹ በሰሜን አሜርካ እና በኢትዮጵያ የሚኖሩ የፕሮቴስታንት የቤተ እምነት ባለቤቶች (ሽማግሌዎች ፣ ፓስተሮች እና ነቢያቶች) ፓስተር ተከስተ ይህንን በኢየሱስ ስም! አያደርግም! ፣ አይሰራም! እንዲሁም ቅራ ቅንቦ የሆነ የዲያብሎስ ማጣቀሻ ጥቅስ በመምዘዝ “የወንድሞች ከሳሽ ተጥሏል” በማለት ሊከላከሉለት ሲሞክሩ ተበዳይ እግዚያብሔር እና ህጋዊ የልጆቹ እናት ሚስቱ የተነወረችበት ወንድም መላኩ የሺዳኜ ግን በማስረጃ የተረጋገጠ ማስረጃ አለን እናንተ እንቢ ካላችሁ እንግዲህ ፍርዱን ወደ አለም ፍርድ ቤት ወስጄዋለሁ:: በሚባልበት ግዜ በእግዚያብሔር ፊት የንስሀ ይቅርታ ሳይሆን በሰው ዘንድ ስም እና ክብር ለመጠበቅ ሲባል ብቻ የእርቅ የሩጫ ሂደት እንደተሰራ ሁላችንም የምናውቀው የቅርብ ግዜ እውነተኛ ታሪክ ትዝታችን ነው:: ከዚያም ዘማሪ ተከስተን እርሱን ፓስተር ያደረጉት የእርሱ ቢጤ የሙያ አጋር ጓደኞቹ የቤተክርስትያን ፓለቲካቸውን ተከስተ ከማንኛውም አገልግሎት ለረዥም ግዜ ታግዷል:: በማለት መግለጫ ያወጡ ሲሆን መግለጫውን ባወጡ ስድስት ወር እንኳ ሳይሞላቸው ፓስተር ተከስተ ከአንድ አመት በላይ በእግዚያብሔር ፊት ወድቆ ንስሀ ስለገባ ወደ ቀድሞው አገልግሎቱ ተምልሷል:: ሀሌሉያ! የሚል ሰበር ዜና አበሰሩን:: በጣም ሰቅጣጭ ግፍ ነው:: በእግዚያብሔር ስም እየተሰራ ያለው:: ለዚህም ደግሞ የእግዚያብሔር ቃል ለእውነተኛ ክርስትያን ለወገኔ ይጠቅማል ብላችሁ አንዳች እንዳታደርጉ ብሎ ያዘናል:: “ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።” ፊሊ 2:3-5 “እናንተ ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ፥ ያውም ወንድሞቻችሁን። ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” 1 ቆሮ 6:8_10የእግዚያብሔርም ቃል ሲናገር እንዲህ ይላል:: “ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።” 1ኛ ዮሐ 1

Tekeste and sami

ዛሬዛሬ እውነተኛ ክርስትያኖች ከምንግዜውም በላይ በቤተክርስትያን ውስጥ የሚፈጠሩትን የተገለጡ እርኩሰቶች በሙሉ ስጋን የለበሰን ሰዎችን ሳይፈሩ ሀጢያቱን መግለጥ እና ስለእግዚያብሔር ቃል ቅንአት ብቻ ስንል አስጸያፊ አገልጋዮችን እኩይ ምግባራቸውን አይሆንም ማለት አለብን:: “ደመና ከምዕራብ ሲወጣ ባያችሁ ጊዜ፥ ወዲያው። ዝናብ ይመጣል ትላላችሁ፥ እንዲሁም ይሆናል፤ በአዜብም ነፋስ ሲነፍስ። ትኩሳት ይሆናል ትላላችሁ፥ ይሆንማል። እናንት ግብዞች፥ የምድሩንና የሰማዩን ፊት ልትመረምሩ ታውቃላችሁ፥ ነገር ግን ይህን ዘመን የማትመረምሩ እንዴት ነው? ራሳችሁ ደግሞ ጽድቅን የማትፈርዱ ስለ ምን ነው?” ሉቃ 12:54_57 “ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ኤፌ 5:11-12

እንደ እውነቱ የእግዚያብሔር ቃል እንደሚያስረዳን በአሁን ግዜ በእግዚያብሔር ስም የተመሰረቱት አዛኛዎቹ በሰሜን አሜርካ እና በኢትዮጵያ የሚኖሩ የፕሮቴስታንት የቤተ እምነት ባለቤቶች (ሽማግሌዎች ፣ ፓስተሮች እና ነቢያቶች) እነሱም ምእመናውም ወደ እውነተኛው የእግዚያብሔር መንገድ ካልተመለሱ ፍጻሜያቸው የገሀነም እሳት ማገዶ መሆን ብቻ ነው:: “እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።” ማቴ 23:13 “ስለ ምን። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ ትሉኛላችሁ፥ የምለውንም አታደርጉም?” ሉቃ 6:46 “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።” ዮሐ 14:15 “ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው።” ምሳ 16:25 ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን? ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?” 1 ጴጥ 4:17-18

የዚህ መልእክት ዋና አላማ ሀጢያተኞች ላይ ጣታችንን ለመቀሰር ወይም ለመውቀስ አሊያም ድንጋይ ለመወርወርም አይደለም:: ማንም ሀጢያት የሰራን ሰውን ከክፉ ስራው እንዲመለስ እንድናስጠነቅቅ የእግዚያብሔር ቃል አበክሮ ስለሚያዘን ብቻ ነው::“እኔ ኃጢአተኛውን። በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ አንተም ባታስጠነቅቀው ነፍሱም እንድትድን ከክፉ መንገዱ ይመለስ ዘንድ ለኃጢአተኛው አስጠንቅቀህ ባትነግረው፥ ያ ኃጢአተኛ በኃጢአት ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። ነገር ግን አንተ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቅ እርሱም ከኃጢአቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል፥ አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል። ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱም ዕንቅፋትን ሳደርግ፥ እርሱ ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል ያደረጋትም ጽድቅ ነገር አትታሰብለትም፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። ነገር ግን ኃጢአት እንዳይሠራ ጻድቁን ብታስጠነቅቅ እርሱም ኃጢአት ባይሠራ፥ ተጠንቅቆአልና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤ አንተም ነፍስህን አድነሃል።” ሕዝ 3:18-21 “የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።” 2ቆሮ2:17

“ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።” 1ጴጥ2:11-12“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ። በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።” ያቆ4:8-10“ወንድሞች ሆይ፥ እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።” 1 ተሰ 5:14

እርስዎ እውነተኛ ክርስትያን ነኝ ብለው ያምናሉን? እንግዲያውስ ካመኑ በእግዚያብሔር ስም የሚነግዱትን ሸቃጭ አስጸያፊ የሀይማኖት ነጋዴዎችን ልክ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚያብሔር ቃል ቅናት ሲሉ ብቻ የትኛውንም ስጋ ለባሽ ሰውን ሳይፈሩ እና ሳያመቻምቹ የራሶትን ጅራፍ አዘጋጅተው በእግዚያብሔር ስም የሚነግዱትን ነጋዴዎች ከስፍራቸው ያባርሩ:: ይህንን በማድረግዎ በፍርድ ግዜ ከተጠያቂነት ፍርድ ነጻ ይሆናሉ:: “በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥ ርግብ ሻጪዎችንም። ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም። የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ።” ዮሐ 2:14_17

እኛም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ “ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ” ብለናል::

ማራናታ!!!

“ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኃጢአት የሚሰሩትን በሁሉ ፊት ገሥጻቸው። አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ መዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።” 1 ጢሞ 5:20-21


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>