ሪያድ ኢብራሂም/ከኖርዌይ
ከሰሞኑ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ የማንኛውም ሀገር ዜጎች ወደ ሃገራቸው በሃይል የመመለስ ስራ ተጠምዶዋል ። በመሆኑም ይህ ጉዳይ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ቤት በር የሚቆረቁር ዜና ሆኗል ። ወገኖቻችን እያዩት ያለውንም ፍዳ በአጫጭር ቪዲዮ ምስል ተቀርጸው በየማህበራዊ ድረገጾች የተለቀቁትን ተመልክተናል ። የምናየው ትእይንት አክሽን አሊያም ሆረር ፊልም አይደለም:: የወገኖቻችን የዕለት ተዕለት ትክክለኛ ስቃይ ነው ። ይህንንም ስቃይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደራሱ ስቃይ ሊሰማው፥ ሊቆረቆረው ና ሊያንገበግበንው ይገባል::ይህ ሁሉ ስቃይ፣ መከራ፣ ውርደት መቼም ቢሆን ደርሶም ፥ታይቶም አይታወቅም:: ከሁሉ በላይ የሚያስጨንቀው ስቃይና መከራ ለደረሰው ወገን እኔ አለሁ የሚል የመንግስት አካል ውይም ድርጅት አለመኖሩ ነው። አሁንም ቢሆን የወያኔ የጭቆና አገዛዝ መቋጫ እስካልተገኘለት ድረስ ይህ የወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የስደት ስቃይ ያበቃል ብሎ መገመትም ሆና ማሰብ አይቻልም። ስደት በሀገራችንም ከተጀመረ ትንሽ ቆየት ያለ ቢሆንም ግን ያሁኑ በወያኔ አገዛዝ ግን ከሁሉም በላይ መሰደድ ጣራ ላይ ደርሶዋል:: ወያኔ መንግስት መስሎ ሃገራችን ለማጥፋት፣ህዝባችንም ለማሳሰድ ሆን ብሎ አስቦበት እየሰራ፣ታሪክ ያለንን ፥ታሪክ አልባ ያደረገ፥የተከበርንን ያረከሰ፥ያልተሰደድንን ያሳደደ፥ለውጭ ሃገር ያልተገዛንን፥ እኛን መስሎ ወሮን የሚገዛ፥ አረመኔ የሃገር ጠላት የሆነ መንግስት ነው::
ግን እስኪ ቆም ብለንእኛ እናስብ ምክንያቱ ምን ይሆን ? ኢትዮጵያ ባላት አንጡራ ሃብት ከአጎራባች ሃገሮችዋ አንሳ ነው? አረ በፍጹም ! እኛ እኮ የቡና ፣ የወርቅ እንዲሁም የተለያዩ አዝርእቶች ያሉባት ሀገር ባለቤቶች ነን ። ህዘቦችዋ ከመጠን በላይ ሆነው እራሳቸውን በሃገራቸው ማኖር አቅቶአችው? አረ በፍጹም ! ኢትዮጵያ እኮ ከአፍሪካ በቆዳ ስፋቷ 10ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገር ናት ይህም ማለት ከኛ በቆዳ ስፋት እጅጉን ያነሱ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የኛን ያህል አይሰደዱም ።
በአንደኛ ደረጃ የሚያሰድደን ፦ የመልካም አስተዳደር እጦት ፣የሃገር ፍቅር ስሜትን በግድ መነጠቅ ፣ዜጋው በሀገሩ ላይ በፍርሃት እና በስጋት መኖሩ፣ በሃገሩ ላይ አንደሁለተኛ ዜጋ መታየቱ ፣ በሰው ሰራሽ የኢኮኖሚ ድቀት ምክንያት ህዝቡ እራሱን በአግባቡ ማሰተዳደር ባለመቻሉ ፣ ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬኣቸው በሀይል በመፈናቀላቸው፣ የእምነት ነጻነትን ማጣት እነዚህ ከዚህም አልፎ ወያኔ ሃገራችንን እያፈረሰ ሰለሚገኝ እና ለሃገረም ሆነ ለህዝብ የሚያስብ መንግስት ባለ መኖሩ ከዋናዎቹ በጥቂቱ ናቸው
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ፦ የወያኔ ስርዓቱ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ደባ በጥንቃቄ በመከታተል የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል ብለው ለሀገር እና ለህዝብ የሚታገሉ ኢትዮጵያውያ ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ና አባላት፣ ታዋቂ ና ሃገራዊ ስሜት ያላቸው ገለሰቦች ብሎም የሃይማኖት መሪዎች ና አባላት በሙሉ እስር፣ እንግልት፣ ድብደባ እና ሃገራቸውን ትተው እንዲወጡ እያደረገ፣ ህዝባችንን ሃገር አልባ እየሆነ ይገኛል::
ወያኔ ና የወያኔ አጃቢ ኣካላት የተለያየ ድርጅታዊ ፖሊሲ ይኑራቸው እንጂ ሃገርን ለማፍረስ ና የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ከማስከበር ውጭ ሌላ ምንም የህዝብ ና የሃገር ፍቅር የሌላቸውም ግዑዛን የማያስቡ ከእንስሳት ምንም የማይለዩ የሃገር ና የህዝብ ሸክም ሰለሆኑ በእነዚህ ግዑዛን አካላት ላይ አስተያት መስጠት በራሱ ለማይናገር ና ለማያስብ እንስሳ እንደ ሰው ቆጥሮ እውቅና መስጥት በመሆኑ ግዑዙን አካል ፈንቅሎ መጣል እንዳለብ ምንም ጥርጥር የለለው መንገድ ነው::
ስለዚህ የውያኔን መንግስት መጣል አለብን ብሎ ከመታግል ሌላ አማራጭ የለም :: መሰደድ መፍትሄ አደለም:: ተሰደንም ባደባባይ ለአዓለም ህዝብ መዋረዳችን እየታየ ይገኛል:: ከዚህ በላይ ሌላ የምንሰደድበት ቦታ፣ ሃገር ፣ጊዜ ና ሰዓት የለንም:: አሁን ለሁሉም ግልጽ መሆን ያለበት ነገር ቢኖር እንደ ሚከተለው ይሆናል::
- Ø ወያኔን ማስወገድ አለብኝ ብሎ እያንዳንዱ ግለሰብም ሆና ድርጅት ማሰብ መጀመር ብሎም ከሃገር ውስጥም ፣ ውጭም ያለ ማነኛውም ዜጋ ወደ ማስወገድ ተግባራዊ ስራ መግባት አለብን::
- ሁሉ ተቃዋሚ ፓርቲ እርስ በርስ ከመቃወም ወያኔን ማሰወገድ እና ሃገራችንን ከማጥ ወጥመድ ውስጥ ማዳን ፣ እንደ ሃገር እንድትቀጥል ማደረግ መቻል::
- ወያኔን ለማስወገድ በጦር መሳርያ የሚፋለሙ ድርጅቶችን ማበረታታት ከማነኛውም ዜጋ ብሎም በወያኔ ስር ላሉ የጉዑዙ አካል የድጋፍ ድርጅቶችም ከወያኔ ጋር ሃገርን ለማጥፋት ከመስራት ሃገርን ወደ ማዳን መሸጋገር አለባቸው::
- Ø ማነኛውም የሜድያ አወታር ለህዝብ ና ለሃገር፥ ኢትዮጵያኖች መከራ ፣ስቃይ ና ሞት ሲደርስባቸው ካልሆነ ለ 22 አመታት ለ85 ሚልዮን ህዝብ ውሸት ከማውራትን ማቆም ፥ከህዝብ ጎን መቆም ሜድያ ለወያኔ ሳይሆን ለ85 ሚልዮን መሆን አለበት::
- ከመሰደድ ና ከመሞት እንድሰደድ እና እንድሞት፥ እንድስቃይ፥ ለአለም ውርድት ከመሆን ወያኔን ታግሎ መጣል፥ ያሃገርን ክብር ማስከበር አለብኝ የሚል ወጣት ና ዜጋ መፈጠር፥ መወለድ አለበት::
እስካሁን በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው የስደት እንግልት የእለት ተእለት ዜና ከሆነ ሰነባብቶኣል ከየዜና አውታሮች እንደምንሰማው ገሚሱ በበረሃ እንደቅጠል ሲረግፍ፣ገሚሱ ባህር ሲውጠው፣ ገሚሱ የሰውነት ክፍሉን በየበረሃው ሲነጠቅ፣ ገሚሱ በየአረብ ሀገሩ የአሰሪዎቻቸው ተጠቂ ሲሆኑ እያየነው ያለ እውነት ነው። መንግስትን በአንድ በቤተሰብ ብንመስለው ፦አንድ ቤተሰብ ልጆቹን የሚበትነው የቤተሰቡ ሃላፊዎች ቤተሰቡን በአግባቡ ማስተዳደር ሲያቅታቸው ነው ።ስለሆነም ትልቁ በሀገራችንም ችግር የአስተዳዳሪ ማጣት ነው ። ስለዚህም የሚበጀንን አስተዳዳሪ ማበጀት እያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነት ነው ።ሃገሪቱዋ የሁላችንም እንደመሆኑዋ መጠን ሁሉም ዜጋ የራሱን ሃላፊነት መወጣት እንዳለበት ግልጽ ነው ። አንዱ ነጻ አውጭ ሌላው ነጻ ወጭ መሆኑ የትም የማያደርስ የትግል ስልት ነው ። ምክንያቱም የያዝነው ትግል የሁላችንም የጋራ ርብርብ ይፈልጋል ። ካልሆነ ግን ሁሌም የግፍ ቀንበር እንደተሸከምን ለቀጣዩ ትውልድ ስርዓቱን ማስረከባችን አይቀሬ ነው።
የሃገርን ና የህዝባችንን መከራ መጋራት፥ ሃገር እና ህዝብን ማዳን የሁሉም ዜጋ የግዲታ ውዴታ ነው!!!